Author Archive

የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች

Sunday, October 7th, 2012

እንደሚታወቀው ሁሉ ከሁለት ዓመት በፊት የቤተ ክርስቲያኗ ሕንጻ ግዢ ክፍያ ሳይጠናቀቅና በተለይም ከፍተኛ የሕግ ክፍተቶችን በመያዝ የቤተ ክርስቲያኗን ሰላም በማናጋት ብጥብጥን ለማስነሳት ምክንያት ሆኖ የነበረው፤ በሥራ ላይ ያለው የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ስለነበር፤ ይህ ቤተ ክርስቲያኗ የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ የማያካትት እና ሌላ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ማስመረጥ የማያስችል የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ሳይሻሻልና ሳይለወጥ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ፤ የሰበካ አስተዳደር ጉባኤውና የልዩ ልዩ ኮሚቴዎች የአገልግሎት ዘመን መጠናቀቂያው ጊዜ ደረሰ። .. [ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ]

የምናውቀው ህወሀት ዘመን ላይመለስ አክትሟል

Monday, September 3rd, 2012

በፍስሀ አሸቱ (ዶ/ር)

[read in PDF]

ጊዜ የማያሳየን ነገር የለም፤ ትግስት ካለና አምላክ ከፈቀደ ደሞ የማይሆን ነገር የለም። እስኪ ራሳችንን ወደሗላ መለስ ብለን ሥድስት ወራት በምናባችን እንመለስና ጊዜን የሗልዮሽ እንቃኘዉ። በዚያን ግዜ እኔ ለዉጥ በምን ያክል ቅበጽነትና ሁኔታ ሊመጣ እንደሚችል አናዉቅም፤ ሰርገኛ መጣ ብለን ከምንሯሯጥ ተሰባስበን ለማናቸዉም አጋጣሚ እንዘጋጅ ብዬ ስናገር በርካቶች ሰዉዬዉ አበደ እንዴ ሲሉ ነበር። አንዳንዶቹ አስጠንቁሏል ሲሉ፤ ሌሎቹ ደሞ የሚያዉቀዉ ነገር አለ እያሉ በትንታኔ ዉድ ጊዜን አሳለፍን። ወደፊት ሄደን ዛሬ ላይ ቆም ብለን ያለፉትን ስድስት ወራት ስንመለከት ለማመን የሚያስቸግሩ ስንት ታአምሮች አየን። እኛ ስንዳክር አምላክ ግን ስራዉን ሰራና ታምራቱን አሳየን። እስኪ ስንቶቻችን ነን መለስ ለዚህ ይበቃል ብለን ቅንጣት እንኳን ጥርጣሬ የነበረን? የአቡነ ጳዉሎስና አጠቃላይ የሃገሪቱ ጉዳይስ? ሁሉም ነገር ፈጽሞ የማይታመንና እምነት ካለ የማይሆን ነገር እንደሌለ በተጨባጭ ያየንበት የበረከት ወቅትን አሳልፈናል። የዚህ ጽሁፌ አላማ ስለህልፈተ መለስ ወይንም አሁን እየታየ ስላለዉ ቴያትር ግለሰባዊ ትንተና ለመስጠት አይደለም። በአንጻሩ ግን ከጊዜዉ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ስለመጪዉ ሁኔታ እንደ አንድ ዜጋ ሚሰማኝን ለወገኖቼ ለማካፈል ነዉ።

ሁላችንም ሰሞኑን እየተከሰተ ካለዉ ሁኔታ በዉስጣችን እጅግ ብዙ የምናብሰለስላቸዉ ጥያቄዎች እንደሚኖሩ አያጠራጥርም። ለኔ ግን ወሳኙ ነገር ሰሞኑን እየተከሰተ ያለዉ ድራማ አይደለም። ወሳኙና ዋናዉ የሚያሳስበኝ እንዲያዉም የሚያንገበግበኝ ጥያቄ ግን የወደፊቱ ጥያቄ ነዉ። በዚሁ አጋጣሚ አንድ የፈረንጆች አባባል ታወሰኝ ይህም፡ ትንንሽ ሰዎች ስሌሌሎች ሰዎች ያስባሉ፤ መካከለኛ ሰዎች ስለ ክስተቶች ያወራሉ፤ ታላላቅ ሰዎች ግን ስለ ሃሳቦችና መርሆች፡ብሎም ስለወደፊቱ ያስባሉ ይላል። ስለራሴ ለመናገር ሳይሆን ሁላችንም በዚህ ግዜ ታላቅ ሆነን ስለወደፊቱ በማሰብና በመዘጋጀት በዚህ አምላክ በፈጠረልን ታላቅ አጋጣሚ እንድንጠቀምና ከዚህ በፊት እንዳደረኩት ሁሉ በድጋሚ ወገኖቼን ለመማጸን ወይም ለመለመን ነዉ። ከዚህ አንጻር በኔ እምነት በዚህ ግዜ ሁላችንም ከዚህ አለም ስለተለዩት ግለሰብ ወይም እየተሰራ ስላለዉ ቲያትራዊ ክስተት ሳይሆን ዋናዉ ጭንቀታችን የወደፊቱ መሆን እንዳለበት በአጽንኦት ማስረገጥ እሻለሁኝ። በኔ በእምነት አሁኑ ወቅት ሀገራችንና ሁላችንም በታላቅ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንገኛለን። የአንድ ታሪካዊ ምእራፍ ተዘግቶ የሌላ ታሪካዊ ምእራፍ ተከፍቷል። አበዉ የፈሰሰ ዉሃ አይታፈስም እንዳሉት ስላለፈዉ ታሪክ ብናወራ ምንም ማድረግ አንችልም። ፋይዳም አይኖረዉም። በጥሩነቱም ሆነ በመጥፎነቱ የራሱን እንደምታ ትቶ አልፏል።

አሁን ቢበዛም ቢያንስም ጨዋታዉ አዲስ ሆኗል። ለምን እንደሆን ወይም ከየት እንደመጣ ባላዉቀዉም እኔ በዉስጤ የሚሰማኝ በጣም ብዙ መልካም ነገሮች በሀገራችን እንደሚከሰቱ ነዉ። በኔ እምነት እንዲሁም በተለያዩ ሁኔታዎች የተተነበየዉ ኢትዮጵያ እጆትዋን ወደ አምላኳ ትዘረጋለች የሚባለዉ ግዜ እዉን እንደሚሁን ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለኝም። የሀገራችን ቅን ልጆች የሚነሱበት ግዜ ደርሷል። ክፋት፤ ምቀኝነት፤ ተንኮልና፤ ራስ ወዳድነት፤ በእዉነተኛ ሀገርወዳድ፤ ቅን ልጆችዋ ትግል የማይቀረዉ ታላቅ ሀገር የምንገነባበት ለዉጥ መምጣቱ አይቀሬ ነዉ። እመኑኝ በኢትዮጵያ የክፉዎች ዘመን እየጨለመ ነዉ። ለዉጥም የማይቀር ተፈጥሯዊ ሂደት ነዉ። እኛ ባንፈልገዉም አምላክ ምን ሊሰራ እንደሚችል በተጨባጭ አይተነዋል። ተሰጥቶ የማያልቀዉም ታምራቱና በረከቱ ወደፊትም ያለገደብ ይፈስልናል።

ይህንን እዉነታ በጭፍን አለመኖሩን ለማያምኑ፤ አምላክን ለማይፈሩ የዚህ ስርአት አራማጆች ግን አንድ መልክት አለኝ። ምንም ስርአት ዘላለማዊ አይደለም፤ ዘላለማዊ መንግስት የአምላክ ብቻ መሆኑንና ከዚያ በታች ግን ሁሉም ስርአት ለህይወታዊ ኡደት ህግ ተገዢ እንደሆነ ነዉ። ይህም ተፈጥሯዊ ሂደት ነዉ። ከዚህ አኳያ በኔ እምነት አሁን ያለዉ ስርአት በአራት ስነ ልቦናዊ ደረጃዎች ዉስጥ እንደሚያልፍ እጠብቃለሁኝ። እነዚህም በዝርዝር ሲቀመጡ፡

1. የሃዘን ጊዜ (grief phase)
2. የግርግር ግዜ (confusion phase)
3. የማጠናከርያ ጊዜ (consolidation phase)
4. የመምከኛ ጊዜ (decay phase) ናቸዉ።

የሀዘን ግዜን በተመለከተ ባሁኑ ሰአት ስርአቱ ምንም እንኳን አቶ መለስን ከድርጅት አኳያ ተለይተዉ አይታዩም እያለ ቢገዘትም ተወደደም ተጠላም ለአንድ ድርጅት፤ ሃያ አመትን ያስቆጠረ መሪ (figurehead) ለስርአቱ አይኑ፤ እፍንጫዉ፤ ጆሮዉ፡ ስሙ፤ ሀልዉናዉ፤ ባጠቃላይ ሁሉም ነገሩ፤ ከዚህም በላይ ለድርጅቱ ጭንቅላቱ በአጭሩ እናቱ፤ አባቱ፤ እንዲያዉም አሳነስኩት እንጂ አምላኩ ነበሩ። እንደማንኛዉም አባቱንና እናቱን የህልዉናዉን፤ ምልክት ብሎም የሚያመልከዉን እንዳጣ ስርአት ያዝናል፤ በተለይም ከታች ላሉ የስርአቱ አቀንቃኞች ሀዘኑ ታላቅ ነዉ የሚሆነዉ። ምክንያቱም የሁለንተናቸዉ መሰረት ተናግቷልና። አምላካቸዉና ጣኦታቸዉን አጥተዋልና። እንዲያዉ ስገምተዉ የሚያለቅሱት፤ በሲቃ የሚያነቡትም ስላለፉት መሪያቸዉ ሳይሆን ስለራሳቸዉ፤ ስለሰሩት ሃጢያታቸዉ፤ ብቻቸዉን በመቅረታቸዉ፤ ቀኑ ስለጨለመባቸዉ ይመስለኛል። ይህም ተፈጠሯዊ ስለቦናዊ ሂደት ስለሆነ ሊደንቀን የማይገባ ጉዳይ ነዉ። ከታች ያሉት ተራ ጀሌዎቻቸዉ በዚህ ሁኔታ ሲያሳልፉ መሪዎቻቸዉ ደሞ አንድ እንደሆኑ፤ ተሰፋ እንዳለ፤ አመራሩ በሁኔታዎች ላይ ቁጥጥር እንዳለዉ ለማሳየት የሚቻለዉን ሁሉ ድራማዊ ትወና እያከናወኑ የገኛሉ። ለህልዉናቸዉ ሲሉ ይህንን ቲያትር ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።

መቼም ግዜ ባለበት ቆሞ አይቀርምና ቀብሩም ያልፋል ታላቁም ድራማ ያበቃል። አለባብሰዉ ቢያርሱ እንደተባለዉም ጊዜያዊዉ ድራማ ሲያበቃ ሁሉም ስለወደፊቱ ማሰብ መጨነቅ መጀመሩ የሰዉ ጥቅማዊና ተፈጥሮያዊ ባህሪ ኑዉና ይህንኑ መጠየቁ አይቀሬ ይሆናል። ማንም ጨቋኝ መሪ ሁሌም እንደሚያደርገዉ ተቀናቃኝ ባጠገቡ እንዲኖር አይፈልግምና እኒሁ መሪም ግልጽ የሆነ ተተኪ ባለማዘጋጀታቸዉ በመሪ ነኝ ባዮች መካከል ሽኩቻዉ መጀመሩ አይቀሬ ነዉ። በእርግጥ አሁን የድራማዉ አካል በሆነ ሁኔታ ም/ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል። ግን ይህ ሂደት ተፈጥሯዊ ብሎም ህገ ማንግስታዊ ባለመሆኑ፤ እንደ ኢህአዴግ ላለ በአንድ ወገን ፈላጭ ቆራጭነት ሲመራ ለነበረ ድርጅት ህልዉናችዉን፤ ማንነትቸዉና ሚስጥራቸዉን፤ አሳልፈዉ፤ ለማያምኑት ግለሰብ፤ ብሎም ሌላ ብሄረሰብ፡ ሲብስ ደሞ ከነሱ ጋር መከራና ፍዳ ሳይቀምስ፡ ለመጣ ሰዉ በመስጠት እየተመሩ ይቀጥላሉ ብዬ ለማሰብ እጅግ ይከብደኛል። እርሳቸዉም እንደ ሰዉነታቸዉ ከዚያም እንደምሁርነታቸዉ ብሎም አማኝ ነኝ ባይነታቸዉ፤ ወንበር አሟሟቂ፤ ትእዛዝ ተቀባይ፤ ተላላኪ፤ ሆነዉ የመቀጠላቸዉ አዝማሚያ እጅግ የራቀ ይመሰለኛል።

ይህ ይሆናል ተብሎ ቢገመት እንኳን ሌላዉ ጥያቄ ማነዉ ከጀርባስ ሆኖ ትዛዙን ሚሰጠዉ? መቼም ጠ/ሚኒስትርነት እጅግ ዉስብስብ ስራ ይመስለኛል። እንኳን ሀገር ይቅርና ድርጅት መርተን የምናዉቅ ሰዎች የአመራር ሃላፊነት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ እናዉቀዋለን። በእያንዳንዷ ደቂቃ ዉሳኔ መስጠት በሚያስፈልግበት ሁኔታና በተለይም እንደሀገራችን በሀገር ዉስጥ፤ በአካባቢያዊና፤ አለማቀፋዊ ዉጥንቅጥ ዉስጥ ላለች ሀገር በዚህ ግዜ አጣብቂኝ ዉስጥ መሆናቸዉ እኔ መቼም መጥኔ ለሳቸዉ እላለሁኝ። ከዚህ አንጻር በኔ ግምት በሚፈጠረዉ ዉጥረት አንዱ ጉልበተኛ ከበታች ያለዉን ሀይል በማንቀሳቀስ ያሸንፍና እርሳቸዉን በመጠምዘዝ በፈቃዳቸዉ አልያም በሃይል እንዲወገዱ ያደርጋል። ሌላዉ አማራጭ ደሞ ምንም እኔ ባይመስለኝም፤ እርሳቸዉ የደቡብ ፕሬዝዳንት በነበሩነት ግዜ ያካበቱትን ልምዳቸዉን ተጠቅመዉና ባለፉት ሁለት አመታት ወደ ስልጣን ጠጋ ጠጋ በማለታቸዉ የአቶ መለስን ያክል የስልጣን ጥማት ተፈጥሮባቸዉ ከሆነና በዚህ ግዜ ጎጠኛ የሆኑትን አንዳንዶቹን የህወሀት ተበዳይ መሪዎች ማማለል ከቻሉ፤ ለተወሰነም ጊዜ በስልጣን ሊቆዩ ይችላሉ። በኔ እምነት ግን ይህ ጉዞ ግፋ ቢል በፊታችን ካለዉ ምርጫ ሊያልፍ የሚችል አይመስለኝም። ምክንያቱም ህወሀት ስልጣን ልጓሙን አሳልፎ ለሌሎች አምኖ ይሰጣል ብዬ ለመቀበል በጣም ያዳግተኛልና።

ሌላዉ መገንዘብ ያለብን መቼም መለስ ብልጥ እንደሆኑና በሽታቸዉም ለሁለት አመታት ያዉቁት ስለነበር ምንም ዝግጅት ሳያደርጉ አልፈዋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ይመስለኛል። ቁልፉ ግን የዚህ የዝግጅት ሂደት ባለመጠናቀቁ በሂደቱ ዉስጥ ቅሬታ የነበራቸዉ ወገኖችም የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ነዉ የሚሆነዉ። ነገሩን ለማጠቃለል ያክል ስርአቱ ከለቅሶ ጊዜ በሗላ የግርግር የትርምስ የዉድድር ጊዜ ዉስጥ መግባቱ ሳይታለም ተፈታ ጉዳይ ነዉ። ፈረንጆቹ እንደሚሉት በፖለቲካ ቀመሩ (equation) ላይ በርካታ ዉስብስብ ግብአቶች (variables) ጭንቅላታቸዉ መዞሩ አይቀሬ ነዉ። ለዚህም የመስለኛል አንዳንዶች ምእረብያዉአን ሳይቀሩ አሁን ማንግስት የለም ብለዉ እየተጨነቁና ከጥቅማቸዉ አንጻር ሁኔታዎችን በቁጥጥራቸዉ ስር ለማዋል ሚፍጨረጨሩት። ይህም ጊዜ ላገራችን እጅግ ወሳኝና ፈታኝ በተለይም አጋጣሚዉን መጠቀም ለሚሹት ተቃዋሚ ሀይሎች ወሳኝ ጊዜ የሚሆነዉ። በዚህ የፖለቲካ ጡዘት ዉስጥም ህዝቡና ተቃዋሚዎች መግለጫ ከማዉጣት ያለፈ ቁልፍ ሚና መጫወት ይጠበቅብናል። የሃይል ሚዛኑንና የፖለቲካ ጨዋታዉን ወደ ሚፈለገዉ አቅጣጫ ለመቀየር በሳል ሆን የመሪነት (proactive) ድርሻ መወጣት አለብን።

ይህ ከላይ ተዘረዘሩት ሂደቶች ፈረንጆቹ እንደሚሉት አቧራዉ ከረገበ በሗላ (after the dust settles down) የመረጋጊያ ዘመን ይመጣል። የዚህም ዘመን ባህርይ ባሸናፊዉ ወገን ማንነት ይወሰናል። አምላክ የጀመረልንን እኛ መጨረስ ካቃተን ጽንፈኛዉና ጨቋኙ ወገን አሸንፎ ህዋት ከአሁኑ በበለጠ ሁኔታ ፋሽሽታዊ ሆኖ ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን ተረጋግቶ ይወጣል – አምላክ ይህንን አያሳየን። በአንጻሩ ግን ህዝቡና ተቃዋሚዋች ነጻነትን ከልባችን የምንፈልጋት ከሆነና ይህንን አምላካችን የከፈተልንን ለመጨረስ ቆርጠን ከተነሳን ዉጤቱ ዉብ ይሆናል። የታላቅ ሀገር የታላቅ ዘመን ምእራፍ ይከፈታል።

አንድ ነገር በእርግጠኝነት የምናገረዉ ግን ህወሀት ከዚህ በሗላ በፍጹም የቀድሞ ህወሀት እንደማይሆን ነዉ። ጽንፈኛዉ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቢወጣ እንኳን በዉስጡ በሚፈጠረዉ የአንጃዎች ሽኩቻ እንዲሁም ከህዝቡና ከተቃዋሚዎች በሚደርስበት እንግልት ብዙም መዝለቅ እንደማይችል አልጠራጠርም። መለስ ምስጋና ይግባቸዉና የስልጣን ገብጋባነታቸዉ ከፍተኛ ክፍተትን ፈጥሮልናል። ለዘመናት የገነቡትን የጭቆና ድርጅታቸዉን በስስታምነታቸዉና በሞታቸዉ እንዳይሆን አድርገዉ በትነዉታል። ህወሀትም በዚህ ሂደት ያረጃል፤ ይጃጃል የማይቀረዉን ተፈጥሮአዊ ሞት ይሞታል። አልያም የብልህነትንና የአርቆ አስተዋይነትን መንገድ መርጦ እራሱን ቀይሮ ከጊዜዉ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር አመሳስሎ (adapt አድግጎ) የቀጥላል። እኔ እናንተን ብሆን የሁለተኛዉን መንገድ መርጬ ራሴን አስተካክዬ ለአምላክና ለህዝብ ፍላጎት ተገዝቼ የድርጅቴንና የአባሎቼን ህልዉና አረጋግጩ እቀጥላለሁኝ። ይህንንም መንገድ ለመምረጥ ኳሷ በሜዳቸሁ ነች። በአንፃሩ አማራጩን አይታችሁታል፤ ህዝብ አቅም ቢያንሰዉ፤ አምላክ ከጎኑ ነዉ። እርሱ ምን ሊያመጣ እንደሚችል በተግባር አሳይቷችሗል፤ ከእርሱ ጋር መዋጋቱን ከመረጣችሁ ግፉበት መንገዱን ጨርቅ ያርግላችሁ። እኔ ግን እንደ ፀሃይ ብርሃን ፈክቶ የሚታየኝን ሃቅ ልንገራችሁ፤ የቅኖችና፤ አምላክን የሚፈሩ፤ ኢትዮጵያዉያን ዘመን ቀርቧል፤ ይፈቀማልም፤ በትንቢቱም መረሰት ኢትዮጵያ ሀገራችን እጆችዋን ወደ አምላኳ ትዘረጋለች፤ ታላቅም ሀገር ትሆናለች። እኛም በሱ ተስፋ አለን። እንደሚሆንም ስለምንተማመን ሁሌም አሸናፊዋች ነን። አሜን።

ጋዜጠኛው አዲሱ አበበና አስገራሚው ቃለመጠይቅ

Tuesday, August 28th, 2012

ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ለርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች ሁሉ

Friday, August 24th, 2012

የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትና ወዳጆች፤ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያና በህዝቧ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና ሰቆቃ የምትቃወሙና ከሃገራችሁና ከህዝባችሁ ጎን የተሰለፋችሁ መላ ኢትዮጵያውያን ሁሉ።

የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ግርማ ከበደ በህይወት የሌሉትን አባ ጳውሎስን የፊታችን እሑድ (26/08/12) ወደ ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሊያመጧቸው ነው።

አባ ጳውሎስንና ክርስቲያናዊ ያልሆነውን ሥራቸውን በማውገዝ ጠንካራና እውነተኛ አቋም በመውሰድ በመላው ዓለም በሚገኘው ኢትዮጵያዊ ዘንድ የምትታወቀው የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ግርማ ከበደ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን አባ ጳውሎስን ብጹዕ ብለው በማወደስ የክብር ፍትሐት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ እንደሚፈጸምላቸው በይፋ አሳወቁ!!

በተለይ ከ6 ዓመት ጀምሮ አባ ጳውሎስን እውቅና የማትሰጠውና አባ ጳውሎስን በማውገዝ እንደ ፓትርያርክ ስማቸውን ብጹዕ ወቅዱስ ብላ ላለመጥራት አቋም ወስዳ አቋሟንም ኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስና ለዓለም ሁሉ ጭምር ያሳወቀችው የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ግርማ ከበደ በ19/08/2012 እሑድ ዕለት ከቅዳሴ በኋላ በህይወት የሌሉትን አባ ጳውሎስን ብጹዕ ወቅዱስ በሚል ስማቸውን በማወደስና በክብር በመጥራት ቤተ ክርስቲያኗ በሚቀጥለው እሑድ ማለትም በ26/08/2012 ለአባ ጳውሎስ የክብር ፍትሐት እንደምትፈጽም ለተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን ሲያሳውቁ፡

በቤተ ክርስቲያኗ የአስተዳደር ሕግና ደንብ መሠረት በህዝብ የተወከለውን የሰበካ አስተዳደሩንም ሆነ የጥምር ጉባኤ ተብሎ የሚጠራውን ከፍተኛውን የቤተ ክርስቲያኗን የውሳኔ ሰጪ አካል ሳያስፈቅዱና ሳያማክሩ ህዝብንም ሆነ ህዝብ የመረጣቸውን የኮሚቴ አባላት በመናቅ ሕግና ደንብን ጥሰው በራሳቸው ስልጣንና ውሳኔ በህዝበ ክርስቲያኑ የተወሰደውን አቋም ሁሉ በመሻር ፍጹም እብሪት በተሞላበት ሁኔታ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ይህንን የአባ ግርማን ድንገተኛ ማስታወቂያ ካዳመጠው ሕዝበ ክርስቲያን ውስጥ አንዳንዱ በየዋህነት መንፈስ መቸም ምንም ሆነ ምን ሰው ከሞተ ሞተ ነው በሚል በቸልተኝነት እንደሚያልፉት ቢገመትም፤ በሌላ በኩል ግን በአሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያኗንና ያፈራቸውን ንብረት ለመቆጣጠር በቋመጡ አካላት የሚካሄደውን ደባ አባ ግርማ የሚፈጽሙትን መጠነ ሰፊ ተንኮልና ቅጥፈት ለሚከታተሉና ለሚረዱ የሰሜን አሜሪካው አባ መላኩ ለጵጵስና ሹመትና ለፈላጭ ቆራጭነት ስልጣን ሲሉ የፈጸሙትን ክህደትና የፈጸሙትን ወንጀል ዛሬ አባ ግርማ በለንደን ሕዝበ ክርቲያን ላይ ሊደግሙት ከመጋረጃው በስተጀርባ ሥራቸውን ሲሰሩ መኖራቸውን በይፋ ያረጋገጡበት ዕለት መሆኑን በግልጽ የተረዱበት ዕለት ነበር።

አባ ግርማ ከበደ ይህንን የድፍረትና የንቀት ድርጊት የፈጸሙት በድንገት ተነሳስተው ሳይሆን በህይወት ዘመናቸው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንንና ገዳማትን ሳይቀር በመከፋፈልና በመነጣጠል በህዝብም ሆነ በሃገርና በሃይማኖት ላይ ከፍተኛ በደል የፈጸሙት አባ ጳውሎስ ህይወታቸውም ካለፈ በኋላ ፍትሓት ይደረግላቸው አይደረግላቸው በሚል ደግሞ ልክ በህይወት ዘመናቸው እንደተደረገው ሁሉ በሕዝበ ክርስቲያኑ መሃል ክፍፍልና ብጥብጥ ሲነሳ አባ ግርማ ባቀዱት መሠረት የደንቡ መጽደቅ እንዲከሽፍና እሳቸውም የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት ካርታ ፈራሚነታቸውን እንደያዙ ወደ ወያኔ ጎራ በመጠጋት በምላሹ የጵጵስና ሹመታቸውን በማግኘት የሁሉም የበላይና ፈላጭ ቆራጭ በመሆን ተደላድለው ለመኖር እንደሆነ ግልጽ መሆን ይኖርበታል።

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ እየጎላ የመጣው የአባ ግርማ ከበደ ክርስቲያናዊ ያልሆነ ተግባር ክፉ መንፈስን በመላበስ የዋህና ለሃይማኖቱ ሟች የሆነውን ህዝብ በመሃሉ ልዩ ልዩ የሃሰት ወሬ እያናፈሱ ጨርሶ እውነትነት የሌለውን መረጃ በማሰራጨት ካህን፤ ምእመንና ሰንበት ት/ቤት በሚል እርስ በርሱ በመከፋፈል አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ በማድረግ ህብረቱን አጥቶ ጠንካራ ውሳኔ የማያሳልፍ ስንኩል እያደረጉት በሌላ በኩል ግን ዓላማቸውን ለማሳካት ይረዳኛል ከሚሉት የወያኔ ቡድን ጋር ራሳቸውን በማቆራኘት በወሬ ያሰከሩትን የካህንም ሆነ የሰንበት ት/ቤትና የምእመናን ቡድን ለተነሱለት ግላዊ ዓላማ የሚጠቅማቸውን ተግባር ብቻ እንዲከናውንላቸው ሲያደርጉት ቆይተዋል።

እዚህ ላይ ጉዳዩ የሞተ ሰው ይጸለይለት? ወይስ አይጸለይለት በሚል አይደለም፤ ጸሎት ለጸላዩም ሆነ ለሚጸለይለት በጎ እንጂ ከቶ ክፉ ነገር ሊሆን አይችልም። ሆኖም ግን ዛሬ ፍትሐት እንዲደረግላቸው አባ ግርማ በቤተ ክርስቲያኗ አውደ ምሕረት ላይ ብጹዕነታቸው ብለው የጠሯቸው አባ ጳውሎስ በሃገሪቱ አጠቃላይና በተለይም ደግሞ በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ ከቶ ምን የፈጸሙ ነበሩ?

በአሁኑ ወቅትስ እኚህ ህወታቸው ያለፈን ሰው አምጥቶ የክብር ፍትሐት ማድረግ ማንን ያስደስታል? ማንን ያሳዝናል? ማንንስ ያስቆጣል?

እንደሚታወቀው ሁሉ በዘር በጎሳና በመንደር ልጅነት ተመርጠው ፍጹም ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክ ስልጣን ላይ እንዲወጡ የተደረጉት አባ ጳውሎስ፤ ስልጣን ላይ ላለው አገዛዝ የቅርብ ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ቤተ ክርስቲያንን በዘርና በጎሳ ከመከፋፈል አልፈው በአገዛዙ የመንግሥት መዋቅር እንደተደረገው ሁሉ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ያሉት ቁልፍ ቦታዎች ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ጎሳና ከዛም ወርደው በመንደር ልጅነት የበላይነትና አዛዥነት እንዲያዝ ያደረጉ ናቸው።

አባ ጳውሎስ በስልጣን ዘመናቸው ከፈጸሟቸው በደሎችና ድርጊቶች ውስጥ፡

· ባህታዊ መነኩሴ በአደባባይ አስገድለዋል፤

· በልደታ መድሐኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ካህናት ቆባቸው እየወለቀ እንዲደበደቡና እንዲገረፉ አድርገዋል፤

· በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የአባ ጳውሎስን አለ አግባብ ስልጣንን መጠቀም፤ ሙስናና የመሳሰሉትን ሕገ ወጥነታቸውን ያጋለጡ ጳጳሳት የያዙትን የእውነት ሥራ ለማሰናከል በየመኖሪያ ቤታቸው የደህንነት ሰዎች እየተላኩ እንዲደበድቧቸውና እንዲያስፈራሯቸው አድርገዋል፤ ከዚህም ጥቃት ሳያገግሙ ህይወታቸው ያለፈ ጳጳሳት እንዳሉ ይታወቃል፤

· የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናን በመጣስ ገና በህይወት እያሉ ምስላቸውን የያዘ ሃውልት በማሰራት፤ ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር እንዲያርሙና ሃውልቱም እንዲፈርስ በቅዱስ ሲኖዶስ ሲወሰንባቸው ውሳኔውን አልቀበልም በማለት እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ሕግን በመጣስ በእንቢተኝነት ኖረዋል።

· የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቅ የሆኑት አለቃ አያሌው በህይወት ዘመናቸው አባ ጳውሎስ የሚፈጽሙትን ከሃይማኖት የወጣ ተግባር በመኮነናቸው ሲሞቱ መቀበሪያ እንዲከለከሉ በማድረግ የሞተ ሬሳን ተበቅለዋል።

· በቅርቡ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ በአጠቃላይ ለሃገሪቱ ታላቅ ታሪካዊ፤ መንፈሳዊና ቅዱስ ቦታ የሆነውን የዋልድባን ገዳም አገዛዙ ቤተ ክርስቲያንን በማፍረስና መነኮሳትን በማሳደድ ለስኳር ፋብሪካ ማስፋፊያነት ለማዋል ሲል በቤተ ክርስቲያና ላይና በመነኮሳቱ ላይ የሚደርስርውን ሰቆቅና በደል በጸጋ በመቀበል መነኩሴዎችን ሳይቀር በጎሳና በዘር ክፋፍለው ከፍተኛ በደልና ጥፋት እንዲደረስ አድርገዋል፤

· የአሰቦትና የዙቃላ ገዳሞች ሲቃጠሉም ሆነ ክርስቲያኖች ከነ ቤተ ክርስቲያናቸው ሲቃጠሉና ሲታረዱ አባ ጳውሎስ በዝምታ ተመልክተዋል።

· ከአገዛዙ ነፍሰ በላ ወታደሮች ሸሽተው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተጠለሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለገዳዮች አሳልፈው ሰጥተዋል፤

· በ1997 ዓ/ም ከቅንጅት መመረጥ ጋር ተያይዞ ምንም ከማያውቅ የሰባት ዓመት ህጻን ልጅ ጀምሮ የ10 ልጆች እናት ያሉበትን ወንድ፤ ሴት፤ ልጅ አዋቂ ሳይል 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን አገዛዙ ሲገድል አባ ጳውሎስ ግድያውን ማውገዝ ሲጠበቅባቸው ይባስ ብለው ለነዚህ የሞቱ ዜጎች ምንም ዓይነት ጸሎትና ፍትሐት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳይደረግ ጥብቅ መመሪያ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በማስተላለፍ አገዛዙ ከፈጸመው ያላነሰ በክርስትና ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ግፍ ፈጽመዋል።

· አገዛዙ ለገዳላቸው ዜጎች ጸሎት አይደረግ የሚለው የአባ ጳውሎስ መመሪያና ትዕዛዝ ከኢትዮጵያም ድንበር አቋርጦ ወጥቶ በውጪ ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በወኪሎቻቸው አማካኝነት ተግባራዊ እንዲያደርጉት ተሞክሮ በተለይ የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት በህብረት በመነሳት መመሪያውን በመቃወም በግፍ ለተገደሉት የኢትዮጵያ ልጆች ጸሎት በማድረግ የእውነተኛ ክርስቲያን ሥራ ለሰራ ተችሏል።

· ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከ6 ዓመት በፊት በወሰደችው አቋማ ምክንያት ከማንም ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ ነጻ በመውጣት ፈጣሪ አምላክን ብቻ በመከተል እሱ መድሐኒአለም ረድቷት ባካሄደችው ከፍተኛ እንቅስቃሰ በጥቂት አመታት ውስጥ አባሎቿ በዝተውና ተጠናክረው የከፍተኛ ንብረት ባለቤት ለመሆን በመብቃቷ ይህንን የቤተ ክርስቲያኗን ዕድገት የተመለከቱት አባ ጳውሎስ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ከእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ልትገዛ ነው የሚል ወሬ እንደሰሙ ለእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ኦፊሻል ደብዳቤ በመጻፍ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን ህንጻ እንዳይሸጡላቸው ከፍተኛ ተቃውሞ አቅርበው ለመበቀል ጥረዋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህንን ሁሉ ሁኔታ አይቶና ገምቶ በአባ ጳውሎስ ላይ የወሰደውን አቋም ነው አባ ግርማ ከበደ ዛሬ ህዝብን ንቀውና ተዳፍረው የሕዝብን አቋምና ውሳኔ በራሳቸው ስልጣን ለማፍረስ የሚሞክሩት። ታዲያ ሕዝበ ክርስቲያን ዛሬ ለቤተ ክርስቲያንህና ለመብትህ ያልቆምክ መች ልትቆም ነው?

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ

Tuesday, August 7th, 2012

ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንቅስቃሴ በወያኔና አላሙዲ ላይ እያደረሰ ያለው ክስረት

Monday, August 6th, 2012

የኢኮኖሚ ማዕቀብ ግብረሃይል

[Read in PDF]

ከሃገራቸው ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሆነው የህዝብን ብሶት እንዳያሰሙና ወያኔን በማስወገድ ትግል በቀጥታ እንዳይሳተፉ ለማድረግ አገዛዙ የማይሸርበው ተንኮል የለም። የወያኔ ህልውና መሰረት በማንኛውም መንገድ ህዝቡንና ተቃዋሚውን መከፋፈል በመሆኑ እስትንፋሱ እስካለ ድረስ ስልቱን በመቀያየር መሞከሩ አይቀርም።

በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌደሬሽን አመራርን በመያዝ ተልእኮውን ለማስለወጥ ያደደረገው ጥረት በህዝብ ወገኖች ትግል መክሸፉ ይታወቃል። ከዚያም 29ኛውን የአንጋፋው ስፖርት ፌደሬሽን የዳላስ ዝግጅት ለማሰናከልና የህዝብ ወገኖችን ለመነጣጠል AESA ONE የሚባል ምንደኛ ቡድን በሼህ አላሙዲን ገንዘብ በመመስረት፤ በዋሽንግተን ዲሲ “ፌስቲቫል አዘጋጅቻለሁ” ብሎ ነበር። ይህ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ የተረጨበት የሆድአደሮች ዝግጅት ግን በኢትዮጵያውያን አገር ወዳዶች ጠንካራ ተቃውሞና እቀባ ብኩን ሆኖ ቀርቷል። ይህ ታሪካዊ ድርጊት ወያኔንና አጋፋሪዎቹን የውርደት ማቅ ከማልበሱ በተጨማሪ፤ ግልፅ በሆነ የተግባር አላማ ስር በአንድነት ለተሰለፈ ወገን ያሰበውን ለማሳካት የሚያግደው ሃይል አለመኖሩን አሳይቷል።

በመሆኑም የኢኮኖሚ ማዕቀብ ግብረሃይል BOYCOTT-TPLF Task Force ይህን በወያኔ ደጀንነት በአላሙዲና ጥቂት ሆድ-አደሮቹ የተቀነባበረውን ESFNA የማፍረስና ኢትዮጵያውያንን የመከፋፈል ሴራ በግንባርና በቁርጠኝነት ላከሸፉ ወገኖች፧ በተለይም በዲሲና አካባቢው ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለውን ከፍተኛ አክብሮትና አድናቆት ይገልፃል። ከዚሁ ባልተናነሰ አለኝታችን ESFNA ነው! አንከፋፈልም! በማለት ወደዳላስ በመትመም 29ኛው የስፖርት ክብረ-በዓል ከመቼውም በበለጠ ኢትዮጵያዊነት እንዲደምቅ ላደረጉ ሁሉ አድናቆታችን ከፍተኛ ነው።

ውድ ወገኖች!

በነፃ መገናኛ ብዙሃን ህብረት የተመሰረተው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ግብረሃይል BOYCOTT-TPLF ግብረሃይል ዋና አላማ በወያኔና በሸሪኮቹ የንግድ ተቋማት ላይ ማእቀብ በመጣል ለህልውናው መራዘም አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የውጭ ምንዛሪ ምንጮችን ማድረቅ መሆኑን ማስታወስ እንፈልጋለን። ስለሆነም የማያባራውን የወያኔ ከፋፋይ እንቅስቃሴ ነቅተን እየጠበቅን በሚከተሉት የማእቀብ እቅዶች ላይ በየአካባቢያችን ተደራጅተን እንድንረባረብ እንጠይቃለን።

1ኛ. ፀረ-አላሙዲን ESFNAን የማፍረስ ሙከራና የዲሲው ዝግጅት ቢከሽፍም በዘርፉ የሚካሄደው ትግል ግን አልተጠናቀቀም። በተለይም የዲሲውን ዝግጅት አላማ ቢነግሯቸውና ቢመክሯቸውም አልቀበልም በማለት በአዘጋጅነት፧ በአዝማሪነትና በመሳሪያ ተጫዋችነት፤ እንዲሁም በንግድ ዘርፍ የእለት ትርፍ አገኛለሁ በሚል የተባበሩትን ሁሉ በያሉበት ኢላማ አድርገን ማግለልና ከንግድ ድርጅታቸው ጋር የነበርንን ግንኙነት ማቋረጥ ስለሚገባ ሃገር-ወዳድ
ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከሃዲዎችን አበጥሮ በመለየት በያሉበት የማግለል እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን።

2ኛ. ብሄራዊ ኩራታችን አድርገን እንመካበት የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ የወያኔና አጋሮቹ ጥገት ሆኗል። አስተዳደሩ በወያኔ ከፍተኛ ሹማምንት ተይዞ ዘረፋና ሙስና ነግሶበታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንጡራ ገቢ አንድም አገዛዙን ለማጠናከርያ፥ ሁለትም ሹማምንቱ ከባህር ማዶ ለከፈቱት የባንክ ሂሳብ ማደለቢያ እየሆነ ይገኛል። ለኢትዮጵያ ህዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ስሙ ብቻ ሆኗል።

ስለዚህም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለመብረርና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም የወያኔን ከፍተኛ የገቢ ምንጩን እንድናደርቅ የኢኮኖሙ ማዕቀብ ግብረሃይል በኢትዮጵያና በህዝብዋ ስም ጥሪ ያደርጋል። አንድ ሰውም ቢሆን ለውጥ ማምጣት ይችላልና በግልና በጋራ በምንወስደው እርምጃ ወያኔን በአጭር ጊዜ አዳክመን ውድቀቱን እንደምናፋጥን እርግጠኛ እንሁን።

የኢኮኖሚ ማዕቀብ ግብረሃይል
Email: boycott.tplf@gmail.com
Tel: 703 828 4821

ህገ -መንግስታዊ ቀዉስ በኢትዮጲያ

Wednesday, August 1st, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ለአሜሪካ ድምጽ በቅርቡ በስጠሁት ቃለ ምልልስ ላይ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት መሰረት ጠቅላይ ሚኒሰተሩ በህመም፤ በእክል በሞት በአካለ ጉዳት በተለያዩ ሰበቦቸ በሰራው ላይ መገኘት ባይችል የስልጣን ዝውውሩ አንደት ይሆናል የሚል ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር ነበር። መልስ የሰጠሁት ብዙዎችን አሰግረምዋል፤ አሰደነግጦአል። ባጭሩ በኢትዮጲያ ሕገ መንግስት ስለ ስልጣን ዘውውር በግልጥ ያስቀመጠው ድነጋጌ ምንም የለም።

በማንኛውም ምክንያት ጠ/ሚኒሰትሩ ተግባራችውን መወጣት ቢያዳግታቸው፤ስልጣኑ ለምክትል ጠ/ሚኒስትር ይትላለፋል ይላሉ ተቃዋሚ ድርጅቶችም:: ይህ ግን በምንም መንገድ በሕገ መንገስቱ ላይ የተጠቀሰ ጉዳይ አይደለም። ስለዚህም ሕገ መንግስቱን ደጋግሞ መመልክት ያስፈልጋል።

በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ላይ የምክትል ጠ/ሚኒስትር ቢሮ በተደጋጋሚ 4 ጊዘ ይነሳል። ከነዚህ ሶሰቱ በአንቀጽ 75 አንዱ በአንቀጽ 76 ሲሆን ይህም የካወንሰል አባለንቱን የሚያሳይ ሲሆን ብ76 ላይ ደግሞ ስለ ተገባሩና ሃላፊነቱ የሚያስርዳው ነው። ዲፒዩቲ ጠ/ሚሩ ሀ) በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚስጥውን ተግባር ያክናውናል። ለ) ጠ/ሚሩ በማይኖርብት ውቅት ትከቶ ይሰራል። ምክትል ጠ/ሚኒስትር ተጠሪነቱ ለጠ/ሚሩ ነው የሚሉ ናቸው::

በአንቀጽ 75 ስር ምክትል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ስሪት ነው አንጂ ተግባሩና ሃላፊነቱ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠለት አየደለም። አንደ ጠ/ሚኒሰተሩ በተወካዮቸ ም/በት ወይም በፓርቲው የተመረጠ አለያም አበላጫ ወንበር በያዘው በጥምር ፓርቲው የተመረጠም አይደለም። ይልቁንም ምክትል ጠ/ሚኒስትር በጠ/ሚ የተመደበና የጠቅላይ ሚኒስትሩነ ፍላጎት የሚያሙዋላ የፖለቲካ ሹመኛ ባለስልጣን ነው። ማንኛውም ስልጣኑ ክጥ/ሚኒስትሩ የተቸረው አንጂ በሕገ መንግስቱ የተደገፈ አይደለም። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመደብልትነ ስራዎቸ ያከናውናል አንጂ በራሱ ተነሳሽነት የሚያከናውነው በሕገ መንግስቱ የተሰጠው አንዳችም ተግባር የለውም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ባስኝውና ሲምስለው ብቻ የሚሰጥው ስራ ነው ስራው የሚባለው። ምክትል ጠ/ሚኒስትር በማንኛውም ውቅት ጠ/ሚኒሰትሩ ሊያባርረውና በቦታው ሊተካ ይችላል። በደፈናው ምክትል ጠ/ሚኒስትር ባዶ የሕገ መንግስት ገንቦ ሊባል ይችላል። ከማንኛውመ ሕገ መንግስታዊ ስልጣን የተገለለ ማሰምሰያ፤ ማሳሳቻ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስራው ተመለስም አለትመለሰ የምክትል ጠ/ሚኒስትር የቢሮ ሃላፊነትና ተግባር በጥንቃቀ መመርምር ተገቢ ነው። በዚሀም ኢትዮጵያ ያጋጠማትነ ሕገ መንግስታዊ ቀውስ መመርመርና መርዳት ተገቢ ነው። ምክትል ጠ/ሚኒስትር በሕገመንግስቱ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተወካይ ነው ቢልም አቀማምጡና ትርጉሙ ለተውካዮቸ ምክር ቤት አባላት ለአምስት አመታት የሕዝብ ውክልና ተሰጥቶአችው ይምረጣሉ አንደሚለው ይዘት ያለው አይደለም።

ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ አንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተወካይነቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚሰጠው መመርያ መሰረት ወክሎ ሊገኝ ይችላል።አንደ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተወካይንቱ ግን ሕገ መንግስታዊ አውቅና የለውምና ከመታዘዝ ውጪ ምንም ሊያድርግ አይችልም። ለምሳለ ዲፒዩቲው አንደተወካይነቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩነ ቦታ የመያዝ፤የጦር ሃይሎች አዛዥ ይሚኒስትሮች ምክር በት ሰበሳቢ ሆኖ በምንም መልኩ ሊስየም አይችልም። በሰበብ አስባቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦታ ባዶ ቢሆነ ተገባራትን ለማከናወን ሕግመንግስታዊ አውቅናና ድጋፍ ስለሌለው መመረያ ሊሰጥ ውሳነ ሊያስተላልፍ፤ ሹመት ሊስጥ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ አይችልም። በአጠቃላይ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ በሕገመንግስቱ ተደግፎ በራሱ ሀሊና አየተምራ ሊያከናውን የሚቸልው አንዳችመ ተግባር የለውም፤ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተላላኪ አእለያመ ጉዳይ ፈጻሚ ብቻ ነው።

በአንቀጽ 72-75 ላይ ያለው የሚያስርዳው፤ የየምክትል ጠ/ሚኒስትር ቢሮ አምሰራረት ለይስሙላ በመሆኑ አንዲያው ለነገሩ ተብሎ መሆኑን ባግባቡ ያሳያል። ሕዝቡ ተተኪ አለ ጠቅ/ሚኒስትሩ በማይኖርበት ወቅት የምክትል ጠ/ሚኒስትር ይተካል በሚል ለማሳመን አንጂ በተጨባጩ ግን ለየምክትል ጠ/ሚኒስትር የተሰጠው ነገር ቢኖር ቢሮና ስም ብቻ ነው። የምክትል ጠ/ሚኒስትር የተፈጠረው በሕገ መንግስት ጨረርና፤ንፋስ ባመጣው ጠረነ ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ በሕግ መንግስት ቀውስ ውስጥ ነች?

አሁን የኢትዮጵያ ችግር የተፈጠረው የአመራር ክፍተት ብቻ ሳይሆን፤ዘላቂነት ያለው የሕገ መንግስታዊ ችግርም ነው። አመራሩን ለመተካተ አለመቻልና ሕገ መንግስቱ ሲነደፍና ተግባር ላይ ሲውል ያልታሰበበት አለያም ሆን ተብሎ የተፈጠረ ክፍተት በመሆኑ በሃገሪቱ ላይ ብጥብጥና የፖልቲካ ቀውስ መፍጠርያ ነው የሚሆነው። በማንኛውም ሃገር አመሪካንንም ጨምሮ፤ ባብዛኛዎቹ የሃገራት ሕገመንግስት ፕረዝዳነቱ ሰራቸውን ማከናወን ቢሳናችው ካላንዳች ውጣ ውረድ ማን ሊተካ እንደሚገባ በሕገ መንገሰቱ ላይ በግልጥ በመቀመጡ በምንም ሰበብ ቦታው ክፍት አይሆነም ውዝግብም አያስከትልም። በአመሪካመ ቢሆን ፕሬዘዳንቱ በአክል ቢሮአቸው መግባት ቢሳናቸው ምክትላቸው ቦታችውን ይዘው ይሰራሉ ሲመልሱም ምክትሉ ወደቦታችው ይሄዳሉ። ይህም በሕግ መንግስቱ ላይ በማያሻማ መልኩ ሰፍሮአል።

በቅርቡ በሰሜን ኮርያ ለማየት እንደቻልነው ምንም እንኩዋን የሽግግሩ ስሪት የተለየና ከአባት ወደ ልጅ የሚተላልፍ ቢሆንም ይሀውም ቢሆን በሕገ መንግስቱ ላይ ተደንግጎ በዚያ ነው የሚመራው። ታዲያ ለምንድን ነው በኢትዮጵያ ሕግ መንግስት ላይ የስልጣን ሽግግርን በተመለከተ በግልጥ መንገድ ያልተቀመጠው? በተለይም የምክትል ጠ/ሚኒስትር ስልጣን በተመለከተ የሕገ መንግስት አወቃቀሩ ላይ የተሰራው ተንኮል:: ይህ ግድፈት ጨርሶ ተቀባይነት የሌለወ ደባ ነው ሊባል ይቻላል። አወቃቀሩ፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አስከ መቸውም በምንም ምክንያት ከስልጣን መንበሩ ላይ የማይነቃነቅ፤ አንዳችም ሁነታ ከስልጣኑ ገለል የማያድረገው ልዩ ስብእና ያለው አእንደሆነና ተተኪም አእንደማያስፈልገው ተደርጎ ነው በ1995 አርቃቂዎች ሕገ መንግስቱ የተሰራውና ነው የምክትል ጠ/ሚኒስትር ሁንይታ ባለበት መንገድ ያስቀመጡት። ይህ የግብር ይውጣ አስራር መቸም ይሁን መቸ ከትውልድ ወቀሳ አያድንም። በስህትተም የተደረገ ነው ማለትም አይቻልም።

ምክንያታዊ ግምገማ ሲድረግም ውጤቱ አርቃቂዎቹ የምክትል ጠ/ሚኒስትር ጥርስ የሌለው አንበሳ፤አቅመ ቢስ ደካማ ስራ አጥ ቁጭ በሉ አድርገው በመሾም ጠ/ሚኒስትሩ በምንም መልኩ ስጋት አእንዳይስማው በጥንቃቄ ነው ያስቀመጡት። በአጨሩ ሰማይ አይየታርሰ …… አንዲሉ። ለመሸፈን የተሞከረውም ጠ/ሚሩ የአንድ ብሄር ተወላጅ ከሆነ የምክትል ጠ/ሚኒስትር የሌላ ብሔር መሆን አለብት የሚለውን መመርያ ለመሸፋፈን የትደረገ ሴራ ነው። ይህ የብሄር የስልጣን ክፍፍል በትክክለኛው መልኩ ቢተገበር ደግሞ ምናለባት ጠ/ሚኒስትሩ በአንዳቸ አጋጣሚ ስራውን ማከናወን ቢያዳግተውና ሸግግሩ በደንቡና በህጋዊ ሂደቱ ቢፈጽም በጠ/ሚኒስትሩ ዙርያ የተሰባሰቡተን የስልጣን ጠባቂዎች ፎሪ ስለሚያስውጣችው ይህንን ለማስወግድ ሲሉ ነው አሁን ባለበት መልኩ ያስቀምጡት። ካልሆነማ የምክትል ጠ/ሚኒስትሩን በደንቡ መሰረት የሚተካው ከሆነ የጠቀላይ ሚኒስትሩ ተተኪ የምክትል ጠ/ሚኒስትር ደጋፊዎቹ የጠ/ሚኒስትሩን ቦታ ሲይዙ የጠቀላይ ሚኒስትሩ ደጋፊዎች መና መሆናቸው ነው። በዚህም እጣ ፈንታችው ቦታውን በተካው በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስር መሆኑ ስለሆነ ይህንን ነው አስቀድመው የተዋጉት።

ያም ሆኖ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ሰዎችም ቢሆኑ ቀጣዩን የምክትል ጠ/ሚኒስትር ከሌላ በሕዝብ ብዛት አነስተኛ ከሆነ ወገን ለማስመረጥ ከቻሉ ጥቅማቸውን ማስጠበቅ አይሳናቸውም። ይህ አካሄድ ደግሞ ጥቅም አለው። የቀድሞው ባለስልጣናት አሁንም የሕዝብ ፍቅር አላችው፤ስልጣናቸውም አልትነካም መልካምነታቸው ተረጋገጠ ያስብልላችዋል።በዚህም ቀድሞ የነበራቸውን ሁንይታ እንደነበረ አድርገው ጥቅማቸውን በማስጥብቅ ይቀጥላሉ። ቦታውን የያዘውም የምክትል ጠ/ሚኒስትር ዲፒዩቲ ስልጣኑን በራሱ እሳብይ ሊጠቀምበት አያስችሉትም። ያልፈውን ጠ/ሚኒስትር ፍላጎትና እምነት፤ ሃሳብና ህልም ተግባራዊ ለማድርግ መንገዱ ክፍት ይሆንላቸዋል። አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የጦሩና ቀድሞ በነበረው የጠ/ሚኒስትር አወቃቀር የተካተቱት የሲቪክ ማህበራትም የቢሮክራሲውም ድጋፍ ስልማየኖረው ሂደቱ ሁሉ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ነው የሚሆነው።በዚህም ዲፒዩቲወ ምንም ተግባር የሌልው አሻነጉሊት ከመሆን አያልፍም።

በአንቀጽ 75 በአፍሪካ የሕገ መንገሰተ አቀራረጽ ታሪክ ከፍተኛ የፖለቲካ ክስርት ተብሎ ሊዘገብ ይችላል።አሁን ባለው ሁኔታ ጠ/ ሚኒስትሩ ወደ ስራው መመለስ ካዳገተውና ሸግግሩ እንቅፋተ ብዙ ሆኖ ከተገኘ ሌሎቸ የስልጣን ተጋሪዎች አዲስ ምርጫ አንዲካህይድ ሊጠይቁ ይቸላሉ፤ የጠ/ሚኒስትሩ ከባቢዎች ደግሞ ይህ አንዳይከናወን በርካታ እንቅፋቶች በመፍጠርና በመሃልም አለመግባባት እንዲከሰት ያደርጋሉ። ምናልባትም በሃገርና ከውጭም ችግር በመፍጠር ሃግሪቱ አደጋ ላይ ነች በማልትና ለሌላ ተንኮላቸው ጊዜ ለመግዛት ሲሉ የአሰቸኩዋይ ጊዜ አዋጅም ሊያውጁ ይችላሉ። ወይም የጠ/ ሚኒስትሩን ሁኔታ በመሽፋፈንመ ሊቀጥሉበት ይችላሉ። ካለያም ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ ጊዜያዊ መፍትሄ ለማግኝትና በሕገ መንግስቱ መሰረት አለያም በምርጫ ሸግግር እንዲከናወን ሲሉም የውጭ መንግስታትን ጣልቃ ገብነት ይሹ ይሆናል። ቀላሉና ጥሩው ምንገድ ደግሞ ይሄው ብቻ ነው። የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ተቃዋሚዎቸነ ችግሩን አብረን በሰላማዊና በሰከነ የሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሃገርም ለሕዝብም የሚብጅውን እናድርግ በማለት አንድ ላይ ለመቆም መወሰን።

ከተቁዋሚዎች ጋር ሰላም መፍጠር የሚያሳፍር ወይም ጉዳት ያለው ነገር አይደለም። በኬንያም በዝንባብዌም የታየ ጉዳይ ነው። እጅግ አስቸጋሪ በሆነው ወቅት እንኩዋን በደቡብ አፍሪካ ሆኖአል። በ2009 ኬንያ እጅጉን በተካርሩ ፓርቲዎች መሃል ጥምር መንግስት ማቁዋቁዋም ችለዋል።ለጥቀውም 67 በመቶ የሕዝብ ድጋፍ ያገኘውን ሕግ መንግስት ለማጽደቅ በቅተዋል። በ2008 ፕሬዜዳንት ሙጋቤና ተቃዋሚው ጠ/ሚኒስትር ሞርጋን ሲቫንጋሪ ባለፈው ሳምንት አዲሱን ሕገ መንግስት ፓርላማው እንዲያጸድቅ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ሁለቱም ሃግሮቸ ወደ ድይሞክራሲ አምባ በሙሉው ሁኔታ ለመቀላቀል ገና ቢሆኑም ትክክለኛውን መንገድ ግን ይዘዋል። በተለያየ መልኩ በብሩንዲ በጊኒ በማዳጋስካር ተሞከሮአል።

ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ ሕገመንግስታዊ ሽግግር

የምክትል ጠ/ሚኒስትር ጉዳይ አኢትዮጵያን ለገጠማት የሕገ መንግስት ጉዳይ አጫሪ ሆነ እንጂ ችግሩ ከዚያ ያለፈ ነው። አብዛኛዎቻችን በሕገ መንግስት ላይ እሳቤ ያለን የአኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በምክትል ጠ/ሚኒስትር ቢሮና ስልጣን አመዳደብ ላይና ሌሎችንም ያሉበትን በርካታ ሕጸፆቸና ችግር በሚገባ እንረዳለን። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዲክታተርንትም ቢሆን በግምት ሳይሆን በተጭባጭ እውንነቱ ገሃድ የወጣ ሃቅ ነው።ይህም ከተለያዩ ተግባራትና አካሄድ፤ ክጠ/ሚንስትሩ ድርጊትም ተረጋግጦል። ማናኛውም ስልጣን ባንድ ሰው ስር መሆኑም የዚሁ የፈላጨ ቆራጭነት ባህሪ ነው። የዲክታትርነት መገለጫው፤ምላት ስልጣንን አንቆ መያዝ ሲሆን፤ ይህ ደግሞ በ1995ቱ በተፈጠርው ሕገ መንግስት አንቀጽ 74 ላይ ተቀምጦአል። አንቀጽ 72-75 እንደሚገልጸው ደግሞ የሃገሪቱ ቁንጮ ባለስልጣን በመሆኑ የሀገሪቱ ስልጣናት ሁሉ በጠ/ሚሩና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ስር ናቸው ይላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም፤የሀገሪቱ የበላይ ቁንጮ ባለስልጣን ነው፤የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ፤የጦር ሀይሎቸ ጠቅላይ አዛዥ ነው። ጠ/ሚኒስትሩ ለሚኒስትሮች ምክር ቤትም ሆነ ለማንም ያለበት የተጠያቂነት ግዴታ ከቁጥር የሚገባ አይደለም:: እንዲያውም ጠ/ሚሩ በሃገሪቱ ላይ ያለውን ስልጣን በሙሉ ጠቅልሎ ይዞታል። በሁሉም የስልጣን እርክኖቸ ላየ አዛዠ በመሆኑ ማንኛችውንም መዋቅሮች ባሰኝው ወቅት ሊያፈርሳቸው፤ስማቸውን ሊለውጥ ይችላል። ከሚኒስትሮችም በኩል ያልተስማማውን ሊያነሳ፤ዳኞችን ሊመርጥ ሊሽረ ሊሾም የሚችል ሲሆን በአኢትዮጵያ ሕገ መንግስት መሰረት ለማንም ተጠያቂም አይደለም። የጠ/ሚሩ ቃለ አእሰትንፋስ የሓገሪቱ ሕግ ነው። ምንም እንኩዋን አባባሉ ቢከብድም፤ጠ/ሚኒስትሩ ገደብ የለሸ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ነው።

የአፍሪካ መሪዎች ሕይወትና ሕልፈት

ሁሉም ፈላጭ ቆራጭ ግዢዎች ሕይውታቸው ዘላለማዊ ነው ብለው ያምናሉ። ዘላለማዊ ሆኖ የሚኖረው ግን እነሱ ሳይሆኑ በሕይወት ዘመናችው የፈጸሙት ግፍና በደል ብቻ ነው። የአፍሪካ መሪዎች በስልጣን ኮርቻቸው ላይ በሚኖሩበት ዘመናት ሃገራቸውንም ሕዝቡንም ሳይፈሩ እግዚአብሐርንም ከቁብ ሳይቆጥሩ ይኖራሉ። እራሳቸውን ጀግኖችና አምላክ አድርገው አስቀምጠዋል። በዚህም ያምናሉ። ሁሉንም ግን አይደሉም ሃላፊ ጠፊ ናቸው። ይታመማሉ፤ ይሰቃያሉ ልክ ሲቀጠቅጡት ሲያስሩት ሲያንገላቱት ሲያስድዱት አንደንበረው ሕዝብ። ሕዝቡን ታምው ጤናማነታቸውን፤ ሲሞቱም ነፍሳችው እንዳለ ተደርጎ ይታወጅላቸዋል። የቶጎው ፕረዘዳንት አኢያደማ ለበርካታ አመታት ባደረብት የልብ ህመም ተሰቃየቶ መሞቱ ትደብቆ በበድኑ ሲገዛ ሰንብቶ በመጨረሻው በድንገት ላይ መሞቱ ታወጀ። ከሕዝብ ተደብቆ የነበረው እውንት ቀኑን ጠብቆ አደባባይ ወጣ። የጋቦኑ ዲከታተር ኦማር ቦነጎ፤የናይጀርያው ኡማሩ ያር አዱዋ፤የጊኒ ቢሳዋው ባቻይ ሳንሃ፤የማላዊው ቢንጉ ዋ ሙሀታሪካ ሁሉም መታመማችው በድብቅ ተይዞ፤ በሃግር ውስጥ ህክምና በማይድን ክፉ ደዌ ተይዘው ሳሉ ደህና ናቸው እየተባለላችው ሁኔታው ተስፋ ሲያስቆርጥ ለመሞት ወደ ሃገር ገብትወ ደህና ናችው የተባለላቸው ሞቱ ይባልላቸዋል። ከሕዝብ የተደበቀው በሸታ በሞታቸው ተተክቶ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል።

ባለፈው ሳምንት ያረፉት የጋናው ፕረዚዳንት አታ ሚልስ ከሌሎቹ የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎች ሁኔታው ይለያል። ለበርካታ ወራተ ሕዝቡ ስለሕመማችወ ያውቅ ነበር። በቦታቸው ለምክትላቸው ድራማኒ ማሃሚ ተተኪነትን በመስጠት እሳችው በማይችሉብት ሁሉ ወክለዋቸው አንዲገኙ አደርገው በይፋ አሳውቅው ነበር። ምንም እንኩዋን ምርጫውን በጠበበ ውጤተ ቢያሸንፉም በሕዝብ ዘንድ በአጭር ጊዜ ተወዳጅነትን አእትርፈው ነበር።ይህን አይነቱ መሪ ነው በለሎቸም የአፍሪካ ሃገሮች ሊኖርና የአፍሪካ መሪዎችም እንደምሳሌ ወስደው ሊከተሉተ የሚገባ።በጋናም ጎዳናዎች ሆነ በአካባቢው ባሉ የምእራብ አፍሪካ ጎዳናዎች ሕዝብ ከዳረ እስከዳር ጋናዊያን በያሉበት ቅስማቸው ተሰበሮ አይኖቻቸው በእንባ ታጥቡ። የተለቪዥን ጣቢያው የጋና ሕዝብ “የሰላም ንጉስ” ብሎ ስለስይማችው መሪ የሞት ዘገባ ገና አውርቶ ሳይጨርስ ነበር የጋና ሕዘብ ማልቀስ የጀመረው።ጋንዲ በአፍሪካ ስለሚገኙት ዲክታተሮች አስቅደመው ነበር የተናገሩት። “ነፍሰ ገዳዮቸና ጨካኘ አርመኔ ገዢዎቸ ለጊዘው የማይደፈሩ ቢመስላቸውም፤ መውድቃቸው ግን አይቀሬ ነው። ሁል ጊዘም ይወድቃሉ።ስልዚህ ሁል ጊዜ ተገንዘቡ::

ኢተዮጵያ አሁን ከገባችብተ የሕገ መንግስት ዝቅጠት መውጫ መንገድ አለ። ነልሰን ማንደላ ይህን መንታ መንገድ በደቡብ አፍሪካ “ይቅር ባይነትና መልካምነት””ብለው ቀይሰውታል። ሁላቸንም በዚያ መንገድ ለመጉዋዝ መዘጋጀት ይኖርብናል። ለብሐራዊ ውይይት ወቅቱ አሁን ነው።

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

የሸንጎው ራዕይ

Wednesday, August 1st, 2012

ከአገሬ አዲስ
ሃምሌ 24-2004 ዓ.ም.(01-08-2012)

ከሦሥት ወራት በፊት በይፋ የተቋቋመውን ሸንጎ ለመመሥረት ከሁለት ዓመት በፊት ጥሪ ያደረገው የጥቂት ግለሰቦች ስብስብ አገሪቱ የምተገኝበትን በማጤን ወደየት አቅጣጫ እንምትጓዝ፣አሁን የተፈጠረውን ሁኔታ በቅድሚያ በመገመት መደረግ የሚገባውን ብሔራዊ ተግባር ተንብይቶ ነበር።

ኢትዮጵያን ለገጠማትና ሊገጥማት ለሚችለው ችግር መፍትሔው በጋራ ታግሎ ዴሞክራቲክ ሥርዓት እንዲሰፍን ፣በአገሪቱ ሰማይ ላይ የተንጠለጠለው የመበታተን አደጋ እንዲቀለበስ፣የሕዝቦቿ ልዑላዊነት፣የግዛቷ አንድነትና ሰብዓዊ መብት የተከበረባት፣የሕግ የበላይነት የሰፈነባት አገር መፍጠር ሲቻል እንደሆነ በማመን፣ እነዚህን አብይ ጉዳዮች ዓላማው አድርጎ ለተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፣የሲቪክ ማህበራትና ግለሰቦች በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርግ ቆይቶ ጥቂቶች ጥሪውን ሰምተውና አክብረው ሸንጎውን ለማቋቋም ችለዋል።

ጥሪው ቡሁሉም ዘንድ ቀና አመለካከትና ሰሚ አግኝቶ ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ወቅት ጠንካራ የተቃዋሚ ጎራ ተፈጥሮ በተገኘ ነበር፤አሁን በየአቅጣጫው የሚደረገው ጥሪና እሩጫ ባላስፈለገም ነበር።ከጥሪ ወደ ተግባር ተሻግሮ ትግሉን የሚመራ ሃይል ፈጥሮ በሕዝቡ መካከል ተገኝቶ ታግሎ ማታገል በተቻለ ነበር።

አሁንም ቢሆን ምንም እንኳን የዘገዬ ቢመስልም ካለፈው ቸልተኝነት፣ግላዊና ቡድናዊ ፍላጎት፣የሥልጣን ሽኩቻ እስርቤት ወጥቶ ጠንካራ የጋራ ግንባር ፈጥሮ በአገር አድኑ የትግል ጎራ መሰለፍ አማራጭ የሌለው ብሔራዊ ግዴታ ነው።ከአሁን በዃላ ጨርቄን ማቄን ማለት ጊዜው ያለፈበት ሰበብ ነው።ተቀባይም የለውም።

ለኢትዮጵያ አገራችን አንድነትና እድገት፣የምናስብ ከሆነ፣ለዲሞክራቲክ ሥርዓት መስፈን የቆምን ከሆነ፣ለሕግ የበላይነትና ለሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የምንታገል ከሆነ፣ሸንጎው በቀየሰው ጎዳና ውስጥ ተቀላቅሎ የጋራ ትግሉን በጋራ አመራር መቀጠል ተገቢና ወቅታዊ ሕዝቡም ከተቃዋሚው ጎራ የሚጠብቀው ብሔራዊ ግዳጅ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበውና መልስ ሊሰጥበት ይገባል።

በአሁኑ ወቅት የጠ/ሚኒስትሩ የመለስ ዜናዊን የጤና ሁኔታ ተከትሎ በሚሰማው ወሬ ላይ አተኩሮ መወናበድና የትግሉ መጨረሻ አድርጎ ማየት ስህተት ነው።በገዢው ቡድን ውስጥ አንዳንድ ተለዋዋጭ ነገር መፍጠሩ ባይቀርም መሠረታዊ የሆነ ለውጥ እንደማይመጣ ጠንቅቆ ማወቅ ተገቢ ነው።መለስ ኖረ አልኖረ ትግላችን በአገራችን ዘለቄታ ያለው የሥርዓት ለውጥ እስኪመጣ ድረስ መቀጠል አለበት።አንዱ ወያኔ በሌላው ወያኔ ወይም አጫፋሪ ግለሰብ ቢለወጥ ወይም በጥገና ለውጥ ከተቃዋሚ ጎራ መካከል አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ሁኔታ ቢፈጠር፣አጃቢ ሆኖ ለመሥራት ይህን ሁኔታ አሰፍስፈው የሚጠብቁ ሃይሎች ቢኖሩ በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ መታለልና ትጥቅን መፍታት አይገባም።ግራም ነፈሰ ቀኝ ከአጠቃላዩ የትግል መስመርና አቅጣጫ ላለመውጣት ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።በሁኔታዎች መቀያየር ልንገዛና ትግላችንን ማርገብ አይኖርብንም።የዓላማ ጥራትና ጥንካሬ እንዲኖረን ያስፈልጋል። ዓላማችንም ዘረኛና እብሪተኛው የህወሃት/ኢሕአዴግ መንግሥት እንዲወገድና በምትኩ ሕዝባዊ ሥርዓት እንዲመሰረት ነው፤ከቀውስ ተርፎና አገግሞ አገዛዙን እንዲቀጥል መንከባከብና ድጋፍ መስጠት ወይም በተመሳሳይ ሌላ ድርጅት ተተክቶ የግፍና ዘረኛ ስርዓት እንዲቀጥል አይደለም።

በተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ስም የሚንቀሳቀሱት የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ሲቪክ ማህበራት፣የወጣት፣የሴቶች፣የሙያ፣የሃይማኖት ተቋማት እርስ በርሳቸው የሚያደርጉትን ንትርክና ሽኩቻና የተናጠል ጩኸት አቁመው በአገር አድን ትግሉ ለመሳተፍ በአንድነት ግንባር ምስረታው ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ በአደገኛ መንገድ ውስጥ ገብታ በምትዋልለው ኢትዮጵያ አገራችን ስም ጥሪ አደርጋለሁ።

አሁን በሸንጎው አነሳሽነት በመታየትና በመሰማት ላይ ያለው የአንድነት ግንባሩ ምሥረታ ጥረት ፍሬያማ ሆኖ አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዲደርስ በተለይ በውጭ አገር የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ለዚህ ሁሉን አቀፍ ለሆነው ግንባር ምሥረታ ያልተቀላቀሉት ድርጅቶች እንዲቀላቀሉ ጫናና ግፊ እንዲያደርግ፣እምቢ ያሉትንም እንዲያጋልጥና ድጋፍ እንዲነፍጋቸው፣በተጨማሪም ለሚፈጠረው የጋራ ግንባር የሃሳብ፣ የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፉን እንዲያደርግለት በትህትና እጠይቃለሁ።

ምናልባት በአገራችን የፖለቲካ ለውጥ የሚመጣ ከሆነና የተቃዋሚውን ጎራ የሚጋብዝ ሁኔታ ከተፈጠረ

በቅድሚያ

የዲሞክራቲክ መብቶች ማለትም የመናገር፣የመጻፍ፣የመሰብሰብ፣የመሰለፍ መብቶች ያለምንም ገደብ መከበራቸውን ማረጋገጥ፣የዜና አውታሮች ነጻነትና ለሁሉም እኩል አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ፣

የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ሁኔታ በነጻ መለቀቅና ለደረሰባቸው ጉዳት ካሳ እንዲያገኙ ማረጋገጥ

የምርጫ ቦርድና ፓርላማ ፈርሶ በአዲስ መልክ በሽግግሩ ቅርጽ እንዲቋቋም የሚያስችል ስምምነት ማድረግ፣

የአገሪቱ ሕገመንግሥት እንደገና እንዲታይና በሕዝቡ ተሳትፎ እንዲረቅ መስማማት፣

የአገሪቱ የጦር ሃይል የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አገልጋይ ከመሆን ተላቆ በብሔራዊ መከላከያ ተግባር ላይ እንዲያተኩር ማደራጀት፣አመራሩንም ሚዛናዊ በሆነ መልክ ማስተካከል፣

የሥርዓቱ ደህንነት ጠባቂ የሆነው የስለላ ተቋም መፍረስና የሕዝቡን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ በማስከበሩ ተግባር ላይ እንዲሰማራ በሚያስችለው መንገድ ማደራጀት፣

በሕዝቡና በአገሪቱ ላይ በደል የፈጸሙ በቁጥጥር ሥር ውለው ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚያስችል ውል ማድረግ፣ሥልጣንን ተገን አድርገው በዘረፉ ሃብት ያከማቹት እንዲወረሱና ለፈጸሙት ጥፋት ተገቢ ቅጣት እንዲያገኙ የሚያስችል አሠራርና አስቸኳይ ሕግ የሚወጣበትን ማመቻቸት።

ከዚህ በላይ የተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ለውጥ ይመጣል ብሎ ተንደርድሮ ከወያኔ ጉያ መግባት አንገትን ለገመድ አሳልፎ መስጠት ይሆናል።ከቅንጅትና ከሌሎቹ ተመክሮ መቅሰም ተገቢ ነው።

ይህ በግለሰብ ደረጃ ያቀረብኩትን ሃሳብ እንደመንደርደሪያ ወስዶ ለማሻሻልና ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም እንዲረባረብበት እጠይቃለሁ።

የመለስ መንፈስ (ክንፉ አሰፋ)

Monday, July 23rd, 2012

ከክንፉ አሰፋ

የሞዛምቢኩ መሪ የነበሩት ጀነራል ሳሞራ ማሼል በአውሮፕላን አደጋ በ1986 (እ.ኤ.አ) በሞቱ ጊዜ ወዳጃቸው ኮ/ል መንግስቱ በአደባባይ ወጥተው፤ “ሳሞራ አልሞተም! ሳሞራ በመካከላችን አለ!” ብለው ሲናገሩ ትዝ ይለኛል። አለም አቀፍ ሜዲያው የሚለው ሌላ – እሳቸው የሚነግሩን ሌላ። ነገሩ በለጋነት አስተሳሰብ ግራ ያጋባል። ኮሎኔሉ የሚናገሩት እንዳሁኑ ጥሬ ውሸት ሳይሆን፤ የሳሞራን በመንፈስ አለመለየት መሆኑ ቆይቶ ነበር የገባኝ።

እነ በረከት ስምኦን መለስ ይመጣል ነው የሚሉን። በመንፈስ ሳይሆን በአካል። ልክ እንደ አስፈሪ (ሆረር) ፊልም ላይ የምናየው ጣዕረ-ሞት አይነት። ብዙዎች ይህንን የበረከት የፖለቲካ ቅኔ “ከጥቂት የእረፍት ጊዜ በኋላ የመለስ ስርዓት ተመልሶ ይመጣል። ” በሚለው መተርጎማቸው ታዲያ አያስደንቅም።

ከሶስት ወር በፊት – በያዝነው አመት – ደግሞ ዶክተሮችና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የማላዊው ፕሬዚዳንት ቢንጉዋ ሙታሪካን መሞት እየተናገሩ፤ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ግን በመንግስት ሜድያ ብቅ ብለው “ቢንጉዋ አልሞተም ደቡብ አፍሪካ ህክምና ላይ ነው።” ይሉ ነበር።

የሙታሪካ ወራሾች የመሪያቸው ሞት በእጅጉ ረብሿቸው ኖሮ፤ በመጀመርያ መሪያቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ሲናገሩ ሰነበቱ፣ ቀተል አድርገው ትንሽ እንደነታመ፣ ከዚያ እያገገመ ነው፣ እያሉ … ትንሽም ቢሆን ግዜ ከገዙ በኋላ ምእራቡ አለም ሊያጋልጣቸው ሆነና እውነቱን መናገሩን ነበር የመረጡት። እዚህ ላይ የአንባገነኖችን የባህሪ ተመሳሳይነት እናያለን።

የፕሬዚዳንት ሙታሪካ ሞት በእጅጉ ያሳሰበው ሃገሬውን ሳይሆን የአሜሪካ መንገስትን እንደነበር ዘ-ኒው-ዮርክ-ታይምስ አስነብቧል። ፕሬዚዳንት ቢንጉዋ ሙታሪካ እንደ መለስ እጅግ ክብርን በሚነካ ሁኔታ ባይሆንም የምእራቡ አለም ጉዳይ አስፈጻሚ ተላላኪ ነበሩ። (የኋላ ኋላ ዊኪ ሊክ ይፋ ያደረገውን መረጃ አቅብለዋል ያሏቸውን የእንግሊዝን አምባሳደር ከማላዊ ሲያባርሩ ከምእራቡ አለም መቃቃራቸው አልቀረም) የአቶ መለስ ማምለጥም ከነበረከት በበለጠ ምእራቡን ያስጨነቀ ለመሆኑ ከሚደረገው ድብብቆሽ መረዳትይቻላል።

በአቶ መለስ ስርዓት መፍረስ ሊከሰት የሚችለው የሃይል አሰላለፍ እና ሊመጣ የሚችለው አዲስ የፖለቲካ አቅጣጫ ምእራብያውያኑንም ማስጋቱ አልቀረም። በተለይ ስር ነቀል ለውጥ ቢመጣና ብሄራዊ ስሜት ያለው መንግስት ቢመሰረት ኢትዮጵያ የአሜሪካ አጀንዳ አራማጅ ልትሆን እንደምትችል ምእራባውያኑ ይሰጋሉ። መለስም ቢሆኑ ለውጩ አለም በአለም አቀፉ መድረክም ብቻቸውን ጎልተው ወጥተው ከስዎቻቸውም መሃል አንድ እንኳ በላምባዲና ተፈልጎ እንዳይገኝ ማድረጋቸው ለዚህ ስጋት አስተዋጽኦ አድርጓል።

ዊኪ ሊክስ እንዳስነበበው አቶ መለስ የምእራቡ አለም ፍጹም ታዛዥ እና ጥሩ አሽከር ሆነው አገልግለዋል። በተለይ አስቸጋሪውን የሶማሊያ (አል-ሻባብ) እና የአሜሪካ ጦርነት አቶ መለስ ተዋግተውላቸዋል። በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ውድ ህይወታቸውን እየከፈሉበት ያለው ይህ ጦርነት ሙሉ በሙሉ የሚታዘዘው ከአቶ መለስ እንደሆነ ራሳቸው ፓርላማቸው መስክረዋል። በጦርነቱ ስንት ወታደር እንዳለቀ ፓርላማው የማወቅ መብት እንደሌለው በድፍረትና በንቀት ሲናገሩ አቶ መለስን የተቃወማቸው እንኳን አልነበረም።

ይህንን በእንዲሁ እንተወውና ወደ እነ በረከት ህዝብን በመዋሸት የማታለሉ ዘዴ እንሂድ።

እ.ኤ.አ. በ1913 ዓ.ም. ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ ከዚህ አለም ከሞት ሲለዩ፤ ልጅ እያሱ የንጉሰ ነገስቱን ቦታ መያዛቸው ይፋ አልተደረገም ነበር። በወቅቱ የካቢኔው ሚኒስትር የአጼውን መሞት ለሶስት አመታት ያህል ሆን ብሎ ደብቆት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ይነግሩናል። የአጼ ምኒሊክ ካቢኔ ሚኒስትሮች ይህንን ያደረጉበት ምክንያት የንጉሱ ሞት ዜና ከተሰማ በሃገሪቱ የርስበርስ ብጥብጥ እና አለመረጋጋትን ሊያመጣ ይችላል የሚል ስጋት ስላደረባቸው ይሁን እንጂ ውስጥ ውስጡን የልጅ እያሱ አልጋ ወራሽነትን በሙሉ ድምጽ ተቀብለውት እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል።

ወራሾቻቸው ለመደበቅ ይጣሩ እንጂ፣ አጼ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት እንደተለዩ የሚያረጋግጡ መረጃዎች አሁን ይፋ ሆነዋል። የሚገርመው አቶ መለስ የሚቃወሟቸው ወገኖች ላይ ከህግ ውጭ ግድያ አልፈው የሞት ቅጣት ሲያስወስኑ ሰንብተው እሳቸው ሞት ከተፈረደባቸው ወገኖች መቅደማቸው ነው።

ይህንንም ክስተት ተከትሎ የመጣው የአገዛዙ ሃይሎች የስልጣን ሽኩቻ እና የሃገሪቱ የሃይል ሚዛን አስላለፍ -በተለይ የህወሃት ቁንጮዎች የሚኒሊክ ዘመኑን ታክቲክ ለመጠቀም ደፋ ቀና ሲሉ የወቅቱ ሁኔታ ከአጼ ሚኒሊክ ዘመን ፈጽሞ የተለየ መሆኑን ያገናዘቡት አይመስልም። በመጀመርያ ያለንበት ሃያ አንደኛው ክፍለዘመን የመረጃ ዘመን በመሆኑ ያውም ፍጹም ከቁጥጥር ውጪ የሆነው የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሁሉንም ነገር እንደ አጉሊ መነጽር እያሳዩ ባሉበት ባሁኑ ወቅት ለረጅም ጊዜ ህዝብን እየዋሹ መቆየት እንደማይቻልም አልተረዱትም።

በሁለተኛ ደረጃ የአጼ ሚኒሊክ ካቢኔ ቢያንስ ልጅ እያሱ ዙፋኑን እንዲረከብ በሙሉ ድምጽ ተስማምቶ ወስኖ ነበር። ካቢኔው በወቅቱ ይሰጋ የነበረው በውስጥ የሚነሳ የስልጣን ሽኩቻ ላይ ሳይሆን ይልቁንም ከውጭ ሊመጣ በሚችል ሃይል ሳቢያ ሃገሪቱ አለመረጋጋት ውስጥ እንዳትገባ በማሰብ ለመሆኑ ከተግባሩ በግልጽ እናያለን።

የነስብሃት እና በረከት ግን ግልጽ የሆነ የርስበርስ ግጭት እና የስልጣን ሽሚያ ለመሆኑ ከአነጋገረቸው ብቻ ይታያልእናያለን። ስብሃት ነጋ ከምኑም ስለተገለሉ መረጃውም ያላቸው እናያለን።

“የአቶ መለስ ዜናዊ እረፍት በህወሃት ፖለቲካ ላይ ለውጥ አያመጣም!” ብለው ሊነግሩንም ሞክረዋል። ይህንን የሚያምኑ ካሉ የዋሆች ናቸው። ላለፉት 20 አመታት ኢትዮጵያ በአንድ ግለሰብ አገዛዝ ስር ለመውደቋ ምንም መረጃ መጥቀስ አያስፈልግም። መለስ ሀገሪቷን በህግ ሳይሆን ይልቁንም በአዋጅ ነበር ሲያስተዳደር የነበረው።

ለነጻ ፕሬስ አዋጅ፣ ለቤትና ንብረት አዋጅ፣ ለ “ሙስና” አዋጅ፣ ለ “ሽብር” አዋጅ፣ ለእርዳታ ድርጅቶች አዋጅ፣….ወዘተ። ይህ ደግሞ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውንና ለዘመናት ይሰራ የነበረውን የወንጀልም ሆን የፍታብሄር ህግ እንዲሁም የራሱ ፓርላማ ያጸደቀውን ህገ-መንግስት ለመጣስ ምቹ ዘዴ ሆኖ አገልግሏል። ሃገሪቱ በህግ ሳይሆን በአዋጅ መተዳደር ስትጅምር ነው ፍትህ የሞተው።

በአንባገነን ስርዓት ውስጥ የግለሰብ ሚና ወሳኝ ብቻ አይደለም። በእንደዚህ አይነቱ ስርዓት መሪውንና ድርጅቱን መለየት አይቻልም። ግለሰቡ ሲሞት ድርጅ ወዲያው ሲከስም እናያለን። የጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር ትልቁ ምሳሌያችን ነው። ሂትለር በሰዎች ውስጥ የፈጠረው የናዚ መርዝ ስር የሰደደ ቢሆንም በህልውናው ማብቂያ ናዚ የሚለው ስርዓት አበቃ። የሮማኒያው ኒኮላይ ቻውቼስኮ፣ የካምቦዲያው ካሜሩዥ መሪ ፖል ፖት… ሲወድቁ የበሰበሰው ፓርቲያቸው ሲጠፋ አይተናል። ላለፉት 26 አመታት በጦር ሄሊኮፕተር ጭምር ሲታገል የነበረው ታሚል ታይገር አማጺ ሃይል – ከሲሪላንካ ምድር የጠፋው በ2009 (እ.ኤ.አ) መሪው ቬሉ ፒላይ ሲገደል ነበር። ከቬሉ ፒላይ ሞት በኋላ ታሚል ታይገር ዛሬ ዜና ሳይሆን ታሪክ ሆኖ ቀረ።

አንባገነኖች የመንግስት ስልጣን ብቻ ሳይሆን ቴክኖክራቱም ቢሮክራሲውንም በአንድ ሰው ትእዛዝ ነው የሚንቀሳቀሱት። ይህ ባይሆን ስርዓቱ እንደ ስርዓት ይቀጥል ነበር። ቤልጂየም በፓርቲዎች አለመስማማት ጥምር ካቢኔው ወድቆ ከ 400 ቀናት በላይ ያለመንግስት እየተዳደረች ነው። ሆላንድም በተመሳሳይ ምክንያት ካቢኔው ለሶስተኛ ጊዜ ፈርሷል። እነዚህ ሀገሮች በግለሰብ ሳይሆን በስርዓት ስለሚመሩ አንድ ሰው ሞቶ አይደለም መላው ካቢኔ ፈርሶ ያለአንዳች ግርግር ይተዳደራሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የአቶ መለስ ዜና እረፍት ፓርቲውን ይሰነጣጥቀዋል ብለው የሚያምኑ የህወሃት ባለስልጣናት ህዝቡን ለማደናገርና በውስጣቸው ምንም ችግር እንደሌለ ለማስመሰል ሲናገሩ ይሰማሉ።

አቶ መለስ ሲመሩት የነበረው ስርዓት ከበሰበሰ ስንብቷል። ይህንን ከባድሜ ጦርነት ባኋላ የህወሃት አመራር ለሁለት ሲከፈል እና የነአቶ መለስ ጎራ አሸናፊ ሆኖ በወጣበት ማግስት ከራሳቸው ከአቶ መለስ አንደበት የሰማነው ነው። “ህወሃት በስብሷል!” ነበር ያሉት አቶ መለስ ዜናዊ። ይህንን የበሰበሰ ፓርቲ እየመሩ ያለፉ አስር አመታትን ሊዘልቁ እንደማይችሉም ግልጽ ነው። እነ ስዬ አብርሃን ገፖለቲካው ምእዋር ካስወገዱ በኋላ ካቢኔያቸውን መበወዝ ነበረባቸው። የተቃቃሩ የህወሃት ቡድኖችን በባትሪ እየፈለጉ፣ አንዱ ሌላዉን እንዲጠራጠር፣ እርስ በርስ መተማመን እንዲጠፋ፣ በተጠና መልኩ በየምኒስትሩ ቢሮ ሾሟቸው። በአለም አቀፉም መድረክ ከራሳቸው ውጭ አንድ የህወሃት ሰው እንዲመጣም እንዲታይም አላደረጉም።

የአቶ መለስ ወራሾች በየመገናኛ ብዙሃኑ እየወጡ የሚቃረኑ አስተያየቶች መስጠጣቸው ራሱ በውስጣቸው ያለውን ችግር አጉልቶ ያሳያል። የስልጣን ትግሉ ጀምሯል። ይህ ሊያሳስበን አይገባም።

ከሁሉም በላይ ሊያሳስበን የሚገባው ሃገሪቱ በችግር ላይ መሆንዋ ነው። ለአስርተ አመታት የታፈንና እንደ እሳተ ገሞራ ሊፈነዳ የታመቀ እሳት እንዳለ ይታያል። በሙስሊም ወገኖቻችን የተጀመረው አመጽ የዚህ ሱናሚ ነጸብራቅ ይመስላል። በመኖር እና ባለመኖር መሃከል ያለው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአመጽ ቋፍ ላይ ይገኛል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ፈተና ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች እውነት ለሃገርና ለህዝብ ደህንነት መቆማቸውን የሚያሳዩበት ፈታኝ ወቅት ነው።

ይህ ችግር በፖለቲካ ፓርቲዎች ጫንቃ ላይ ብቻ መተውም ተገቢ አይደለም። የዲሞክራሲ ሃይሎች፣ ተቃዋሚና የሲቭክ ድርጅቶች ተሰባስበው ሁሉንም አንድ በሚያደርግ የጋራ ጉዳይ ላይ ተወያይተው ስምምነት ላይ መድረስ ያላባቸው ወቅት አሁን ነው።

አገርን የማዳን ስምምነት።

አሁን ስለ ስልጣን፣ ስለፓርቲ ፕሮግራም ስለ ዲሞክራሲ ወዘተ የምናወራበት ወቅት አይደለም። የመለስ መንፈስ እነ በረከትን አንድ ቢያደርጋቸው ባያደርጋቸውም ለላው ወገን ግን ስለ ህብረት እና አንድነት ለጋራ አላማ መነጋገር አስፈላጊነት ያለበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያገባናል የሚሉ ሃይሎች ይህንን ካላደረጉ መጭው ዘመን ካለፈው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ለአያዳግትም።

በፍጥነት እንሰብሰብ (አክሎግ ቢራራ)

Sunday, July 22nd, 2012

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

በቁጥር ሰባት የደመደምኩት፤ አገርን ከአስከፊ አደጋ ለመከላከል ከተፈለገ፤ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰው ርህራሄ ከሌለው፤ ዘርፎ ለዘራፊ ዳራጊ ከሆነ የዘረኛ ስርአት አላቆ ለፍትሃዊ አማራጭ የሚቨጁ አገር አቀፍ ተቋሞችን መገንባት ያስፈልጋል። አለበለዚያ፤ አገራችን ሁልጊዜ ያልተረጋጋ ች ሆና ትቆያለች፤ ህዝቧም በድህነት አለንጋ ሲገረፍ፤ ወጣቱ ሲስደድ ይኖራል። መፍትሄው በእጃችን ነው። ይህን አስፈላጊ ለውጥ ለማድረግ የባህል፤ በመጀመሪያ፤ ያስተሳሰብ፤ የአሰራር፤ የአደረጃጀትና የአመራር ለውጥ መጀመር አለበት (Paradigm shift in thinking, organization and leadership)። ለፍትሃዊ ለውጥ የሚደረግ ጉዞ የማንኛውም አገራዊ የሆነ ተቃዋሚ ግለሰብ፤ የማንኛውም ማህበራዊና የፖለቲካ ድርጂት፤ የማንኛውም ብሄር፤ የማንኛውም ሃይማኖት ተከታይ፤ ወዘተ አላማ መሆን ይኖርበታል። የውጭ ጠላቶች፤ የውስጥ ደጋፊወች ባጠመዱልን “የከፋፍለህ ግዛው ክልል” ወጥመድ ከቆየን አሰቃቂውን የህወሓት/ኢሃዴግ አገዛዝ ለመለወጥ አንችልም። እነ “አቦይ ስብሃት” የሚናገሩት ፕሮፓጋንዳ ይቀጥላል።

የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ከሞት አፋፍ ያደረሰ ህመም (Critical illness and condition) በቅርብ የሚያውቁ ታዛቢወች እንደሚሉት ከሆነ፤ በህይወት መቆየታቸው ያጠራጥራል። ቢቆዩም፤ ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያን ሊገዙ/ሊመሩ አይችሉም። ስለሆነም፤ ተተኪ መሪ ወይንም መሪዎች መሰየማቸው አይቀርም። የገነቡት አገዛዝ ይቀጥላል። ለዚህ ሽግግር ከጀርባ ሆኖ ድጋፍ የሚሰጠው የአሜሪካ መንግስት ነው። ህወሓት/ኢሃዴግ፤ የአሜሪካ መንግስት፤ ኢንቬስተሮችና ሌሎች ደጋፊወች የመለስ አገዛዝ እንዲቀጥል ይፈልጋሉ። መረጋጋት (Stability)ተደጋጋፊ ጥቅም ስላለው።

በሌላው አንጻር ሲታይ ግን፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብና በአፍሪካ ቀንድ ያንዣበበውን የአልካይዳ ሆነ ሌላ አደጋ በዘላቂነት ለመከላከል፤ ብዙ ቢሊየን ዶላር ለሚያፈሰው የአሜሪካ መንግስት፤ ዘላቂና አስተማማኝ ጥቅም ሊያስገኝ የሚችለው አገዛዝ የህወሓት/ኢሃዴግ መንግስት አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ያውቃል፤ የአሜሪክ መንግስት የኢትዮጵያ ሕዝብን ፍላጎት ቸል ብሎታል። ዘላቂነትና ፍትሃዊ የሆነ አገዛዝና እድገት እውን የሚሆነው፤ በህዝብ የተደገፈ፤ በህግ የበላይነት የተመሰረተ፤ ፍትሃዊነቱ የተረጋገጠ፤ ተቋሞቹ አገራዊ የሆኑ፤ መንግስቱ፤ አስተዳደሩ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አገልጋይ የሆነ፤ ባጭሩ፤ ለህዝብ ተወካይ የሆነ አገዛዝ (Governance) ሲገነባ ብቻ ነው። ይህን ለማድረግ፤ ህወሓት/ኢሃዴግ መፍርስ አለበት። ይህን አማራጭ የማቀርብና የመደራደር ተግባርና ሃላፊነት የተቃዋሚው ክፍል እንጂ፤ የህወሓት ወይንም የአሜሪካ መንግስት አይደለም። ስለሆነም፤ ለአንድ አገራዊና ህዝባዊ ስር ነቀል እንቅስቃሴ ካሰብን፤ በመቻቻል ተነስተን በስራ የምናሳይበት ወቅት አሁን ነው። መግለጫ ማውጣት በቂ አይደለም። በመጀመሪያ እድሎች በፍጥነት እያመለጡን መሆኑን መቀበል አለብን።

በ July 17, 2012, Thomas Mountain የተባለ አስመራ የሚኖር ጋዜጠኛ ስለ መለስ ዜናዊ መንግስት “መፈራረስ” (Crumble) ና ሰለ ኢትዮጵያ መጥፋት የደረሰበት ድምዳሜ ሊሆን/ላይሆን ይችላል። እኔ ኢትዮጵያ ትጠፋለች ብየ አልቀበልም። እሱ መሆኑ አይቀርም ባይ ነው። አስመራ ተቀምጦ ይህን ቢል አያስገርምም። የኢትዮጵያ በዘር ተከፋፍሎ የመጥፋት ሴራ የተጠነሰሰው በውጭ ጠላቶቿና በኤርትርያ ተገንጣይ ቡድኖች ነው።  አሁንም መጥፋቷን ስራ ላይ ለማዋል የተዘጋጁ እንዳሉ አንጠራጠር። እ.አ.አ.በ 1993 መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ “ከመቶ አመታት አይበልጥም፤ ከዚህ የተለየ ነው ብለው የሚቃዡ ግለሰቦች የሚያወሩት ልብ ወለድ ነው” ያሉት ከሚያደንቁት ኢሳያስ አፈወርቂና ከሌሎች ጸረ ኢትዮጵያ ከሆኑ ግለሰቦችና ግንባሮች የተማሩትን ነው። ህወሓት የተጸነሰው በዚህ መሰረታዊ ፍልስፍና ነው። ስለሆነም፤ አደጋው አሁንም እያንዣበበ ነው። አገርን ለመታደግ የምንፈልግ ግለሰቦችና ድርጂቶች ይህን የሚያንዣብብ አደጋ በጥልቅ ካላየን፤ ለዚህ አማራጭ ለመስጠት ብቁ ሁነን ካልደረስን፤ ታሪክ የሚወቅሰው ኢሳይያስን ወይንም መለስን ሳይሆን እኛን ነው። እነሱ አላማቸውን ያውቃሉ፤ እኛ አላማ ቢስ ሁነን እንታያለን። ይህ ሁኔታ በፍጥነት መለወጥ አለበት።

ለኢትዮጵያና  ለመላው ሕዝቧ እንቁም/እንናግር፤

አሜሪካኖች በአሁኑ ወቅት የመለስን መታመም በማጤን፤ አድራጊ ፈጣሪ (Power brokers) ሁነው አማራጮችን ለእኛ በምስጢር ሲደራደሩልን፤ አገር አቀፍ የሆነው የተቃዋሚ ድምጽ የት ሄደ ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ነው። እኛስ አገራችን ለማስቀደም ምን እየሰራን ነው? ተባብረን ድምጽ እያሰማን ነው? ለምድን ነው አነድ አገር አቀፍ የሆነ፤ ሁሉንም የሚያካትት/የሚያነጋግር፤ በኢትዮጵያ አንድነት፤ በመላው ሕዝቧ እኩልነትና ሉአላዊነት፤ በሰብአዊ መብቶችና ክብር፤ በነጻነት፤ በፍትህ-ርትህ፤ በህግ የበላይነት፤ በነጻ ምርጫ፤ ወዘተ መስፈርቶች የሚመራ አለም አቀፍ ስብሰባ (a Grand National Coalition) አሁን ለማድረግ የማንነሳው ብለን መጠየቅ አለብን። አገራችን ከአደጋ ለማዳን ከፈለግን፤ የምንቃወመውን የጭቆና አገዛዝ ለመለወጥ ፍላጎት ካለን፤ ይህ ታላቅ ጥምረት (Grand Coalition)፤ ሽግግር ምን እንደሚመስል አገር ቤት ካሉ አገር አቀፍ ከሆኑ ተቃዋሚ ድርጂቶች ጋር በመወያየት አግቫቭ ያላቸውን አማራጮች መቅረጽ ይኖርባቸዋል። ሽግግሩ ወደ ዘላቂ መፍትሄ ሊመራ የሚችለው፤ ኢትዮጵያን ከአደጋ ለማዳን፤ አብሮ በመቻቻል ለመኖር፤ ፍትሃዊ ስርአት ለመገንባት የሚፈልጉ ሁሉ ሲካተቱና ሲሳተፉ ነው። ህወሓት/ኢሃዴግ ተካፋይ እንዲሆን ያልተቆጠበ ጥረት መደረግ የሚኖርብት ይህን አላማ  በማጤን ነው።

በእኔ ግምት፤ ህወሓትና እሃዴግ ውስጥ እርቅን፤ መቻቻልን የሚፈልጉ አሉ፤ እነዚህን መሳብ፤ ማነጋገር፤ መቅረብ ጥበብ ነው። የበላይ አዛዡ ህወሓት(ትግሬ) ቢሆንም፤ የአገራችን የጦር ሃይል ከሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጣ ነው። ተራው ሰራዊት ለሃገር እንዲያስብ ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው። የውጭ መንግስታት፤ በተለይ፤ የአሜሪካ መንግስት ይህን የእርቅ፤ የመመካከር፤ አማራጭ ለመቀበል የሚገደድበት ምክንያት እንዳለ በተደጋጋሚ አሳይቻለሁ።

ይህን አላማ እውን ለማድረግ መጠየቅ ያለብን ጉዳይ “ኢትዮጵያዊያን፤ ነገሮች ከመበላሸታቸው፤ ሁኔታወች ከቁጥጥር ውጭ ከመድረሳቸው በፊት አማራጮችን በጋራ ተወያይተው፤ በጋራ ለማቅርብ የሚችሉት” ቀን መቸ ነው፤ የሚጎተቱስ በምን ምክንያት ነው የሚለውን ጥያቄ በማቅረብ ነው። የተማረው፤ አገር ወዳዱ፤ በመድብለ ፓርቲ፤ ወዘተ የሚያምን ሁሉ መሰብሰብ፤ መነጋገር፤ መመካከር፤ አማራጮችን ማቅርብ ያለበት ያለመሰብሰብ/ያለመተባበር አደጋን በማየት ነው፡፡ የምእራብ አገሮች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ወዘተ ሊያከብሩን የሚችሉት ብቃት ያለን መሆኑን፤ ሃላፊነት የሚሰማን መሆኑን በተግባር ስናስመሰክር ብቻ ነው። ወሬ ስለተወራ ብቃት አይደለም፤ ስራ ስለተሰራ ብቻ ነው። የሃገራችን ሕዝብ ዋና ጥሪ መመለስ ብቃት ያሳያል። ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ አለሁ የማለት ጥያቄ ፋታ እነደማይሰጥ መገንዝብ የብቃት መለኪያ ነው።

አሁንም ክፍፍል እየጎዳን ነው፤

መጠንቀቅ ያለብን ግን እኛ ተበታትነን፤ ኢትዮጵያን ካለባት አደጋ ልናድን አንችልም። አማራጭ ለመስጥት አንችልም። ኢትዮጵያ ከፈራረሰች ዋጋ ከፋዩ አንድ ብሄር፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ መደብ ወዘተ አይሆንም። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከባድ ዋጋ ይከፍላል። የመገንጠል፤ የእርስ በእርስ ጦርነትን ጉዳት ባለፉት አስርት አመታት አይተናል። የባህር በር ማጣት ያመጣውን ጉዳት ብቻ ማየት ይበቃል። ችግሩን ሳጤነው የምፈራው አበይት ነገር፤ የማናየው/ የምናየው ተደጋጋሚ ድክመት አለ። አሁንም ወርቃማ የሆኑ፤ አገርን ከክፋ አደጋ ለማዳን፤ የነጻነትና የመልካም አስተዳደር ድልድይ ለመዘርጋት የሚያስችሉ፤ ተጨባጭ ሁኔታወች የፈጠሩት እድሎች እያመለጡን ነው። እስካሁን ልንጠቀምባቸው አልቻልነም። የተማረው የሰው ሃይላችን አያል ቢሆንም፤ የሃገራችንና የወገኖቻችን እድል የሚወስኑት ምእራባዊያንና የእነርሱ ደጋፊ የሆኑ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ለምን? በመከፋፈላችን። ስለሆነም፤ የእኛ መኖር፤ የእኛ መማር፤ የእኛ ድርጂት ማቋቋም ለኢትይጵያና ስብጥር (Diverse) ሕዝቧ ትርጉሙ ምንድን ነው ብለን መጠየቅና መልስ መስጠት ተገቢ ነው።

አገራዊ የሆነ፤ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊነት በሩ ክፍት የሆነ አገር አቀፍና ከብሄር በላይ የተደራጀ የፖለቲካ ተቋም በህወሓት መዳከሙ፤ በብልሃት፤ በጥበብ፤ በአርቆ አሳቢነት፤ በመቻቻል፤ መለኪያውች የሚዳኝ አመራር አለመኖሩ አደጋውን አባብሶታል። የነጻነት ጉዞውን ገትቶታል። ለዚህ ነው፤ አሜሪካኖች ለእኛ እየወሰኑ ያሉት። መኖራችን ያልተቀበሉት ስለተከፋፈልን ብቻ ነው። ማውንቴን የተባልው ጋዜጠኛ ይህን ድክመት ስላየ፤ ኢትዮጵያ ትበታተናለች ብሎ  በእኛ አገር እጣ ላይ ደመደመ። ቴሬንስ ላየንስም በቅርቡ ያወጣው ዘገባ ይህን ያለመረጋጋት አደጋ ያመለክታል። አንዳንዶቻችን፤ ጋዜጠኛው አስመራ ሆኖ ህወሓትን ስለሚቃወም ጉዳቱን አልተረዳነም። የተቃዋሚው ክፍል መበታተኑ፤ በብሄር የተደራጁና የታጠቁ ክፍሎች “አላማችን መገንጠል ነው” ማለታቸው ለህወሓት አመራርና ለአሜሪካ መንግስት ሚና ፋታ ሰጥቷል። የአሜሪካ መንግስት (የውጭ ጉዳይና የስለላ ድርጂቶች ልኡካን በመጠቀም) ከመቸውም ጊዜ የበለጠ በኢትዮጵያ  የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ውሳኔወችን የሚሰጥበት ምክንያት የመፈራረስ አደጋውን ስላየ፤ የአካባቢውን አደጋ ስለመዘነ፤ተቃዋሚው ክፍል መከፋፈሉንና በአንድ አገራዊ አጀንዳ አለመቆሙን ስለተገነዘበ ነው።

አሜሪካ የወሰደው እርምጃ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደህንነት፤ ለሃገራችን አንድነትና ጥንካሬ አስቦ ሳይሆን፤ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን አደጋ ለመከላከል፤ የአሜሪካን ጥቅም ለማስከበር፤ ለዚህ ታማኛ የሆኑ መሪወችን ለመመልመል ነው። እኛ በአንድ ላይ ሁነን ድምጽ ብናሰማ፤ ቢያንስ ሽግግሩን ለማሻሻል እንችላለን የሚል ግምት አለኝ።

ይህን አደገኛ ሁኔታ እያየን፤ አሁንም የምንዳኘው፤ ጊዜ ባለፈበት የግለሰብ፤ የራስ ቡድን አደረጃጀትና አመራር ነው። ትኩረታችን ተቃዋሚው ክፍል ምን አማራጭ አዘጋጅቷል በሚለው ተፈላጊ ቁም ነገር ላይ ሳይሆን፤ በህወሓት መሪ ላይ የደረሰውን ህመም በሚመለከት ሁኗል። ብንወድም፤ ባንወድም፤ ብንቀበልም ባንቀበልም፤ ማውንቴን አስመራ ሆኖ ቢበይን/ባይበይንም፤ የህወሓት አመራር ራሱን ስለመተካካት (Succession) እቅድ ካወጣ ቆይቷል። በተቃዋሚው ክፍል ያለውን ሁኔታ ስናይ ግን እንኳን ከዚህ ደረጃ ለመድረስ (ተተኪ ለማዘጋጀት ቀርቶ)፤ አሁንም እርስ በእርሱ ለመተማመን፤ ለመፈላለግ፤ በዙር ጠረጴዛ ተቀምጦ ስለ ሃገር፤ ሰለወገን ለመነጋገር አልቻለም። ህወሓት ያዘጋጀው የመተካካት አማራጭ የሚገዛው ለአንድ አላማ ብቻ ነው። ተተኪወች የሚመረጡት በታማኝነት፤ በስርአቱ ጠባቂነት፤ በአሜሪካ ጥቅም አገልጋይነት፤ በጥቅም፤ ተብሎ  እንጂ የነጻነት ለውጥ ሃዋርያት በመሆናቸው አይደለም። ሊሆንም አይችልም። አንዳንድ ተመልካቾች የሚሉት፤ ተተኪወቹ የባሰ “ተኩላ፤ የባሰ በዝባዥ፤ የባሰ ጨቋኝ” ወዘተ ይሆናሉ የሚል ነው። ሌሎች ደግሞ፤ የተሻለ ሁኔታ ይፈጠራል ይላሉ። ሊሆኑ፤ ላይሆኑ ይችላሉ። ዋናው መነጋገሪያ መሆን ያለበት የመለስ ተተኪ የህወሓት አባላት ምን ያደርጉ ይሆን  የሚለው፤ በምንም ልንቆጣጠረው የማንችለው ጉዳይ አይደለም። እኛ ማድረግ ያለብን ከመለስ ባሻገር አይተን የተቃዋሚው እምቅ ሃይል (Potential Force) አሁን ምን መስራት ይገባዋል የሚለውን አንገብጋቢ አገራዊ/ወገናዊ ጥሪ ነው።

የተዳፈነ እሳት ሲቀጣጠል፤

በአሁኑ ወቅት፤ ለግለሰብና ለህብረተሰብ ደህንነት፤ ለሰባዊ መብቶች፤ ለሃይማኖት መብት፤ ለነጻነት፤ ለፍትህ-ርትእ፤ ለህግ የበላይነት በተከታታይ የሚታገለው ተራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። በዚህ ዲሞክራሳዊ የሆነ የህዝብ ትግል ድምጻቸውና አቋማቸው የማይሰማው በውጭና በአገር ውስጥ የሚገኙ የማህበራዊና የፖለቲካ ተቃዋሚ አካሎች ናቸው ለማለት ይቻላል። ህወሓት አያሰራን አለ የሚለው እውነት ቢሆንም፤ ዘላቂ መልስ አይደለም። የሶሪያ ህዝብ በብዙ ሽህ እየሞተ መንግስቱን ከመገልብጥ አፋፍ ላይ የደረሰው በፍርሃት አይደለም። ለነጻነት ባለው ድፍረትና ህብረት ነው። የሚያበረታታው፤ የሃገራችን ህብረተሰብ ከፖለቲካ መሪወች መቅደሙ ብቻ አይደለም። የእስልምና ሃይማኖት መሪወችና አባላት ለመብታቸው ሲታገሉ፤ የክርስቲያን አባቶች በየገዳሙ ሲነሱ አብሮ የሚታገለው ወጣቱ፤ ሴቱ፤ አባቱ፤ እናቱ፤ ከተሜውና ገጠሬው፤ ወዘተ መሆኑ ጭምር ነው። የሃይማኖት ክፍሎች አገራዊ እንቅስቃሴ መጀመራቸው፤ ለነጻነት አብረው መታገላቸው፤ በያቅጣጫው መተባበራቸው ፤ ለሃገርና ለነጻነት ያለው ፍላጎትና ትግል የማይገታ መሆኑን አስምሮበታል። እምቁ ሃይል መንቀሳቀስ ጀምሯል፤ ምልክቶቹ ሁሉ የካቲትን፤ ምርጫ ዘጠና ሰባትን ይመስላሉ። ሕዝቡ አስተዋይ በመሆኑ፤ የሚያስበው ከመለስ ባሻገር ነው ለማለት የሚያስደፍሩ ምልክቶች አሉ። ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንካሬ ጎን ነው። የኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ይህን አይቀበሉም።

ከመለስ ባሻገር እንይ፤

የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ አንድ መሪ ብቻውን አገር ለመግዛት፤ ወይንም ድርጂት ለማስተዳደር አይችልም የሚለውን ተመክሮ ካለፈው ታሪኩ ተምሯል። አምባ ገነን ቢሆንም፤ መሪው ውጤት ለመቀዳጀት የሚችለው ደጋፊወችን መርጦ የስራና የጥቅም ተካፋይ በማድረግ ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ማን፤ ምን እንደሆነ በሚገባ ያውቃል። ስለሆነም፤ ከጠቅላይ ሚንስትር መለስ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ስርአቱ የፈጠረው ጠንካራ በጥቅም ላይ የተመሰረተ ድርጂትና ደጋፊወች የሉትም ብሎ አንደማሰብ ይሆናል የሚል ግምት እንደሌለው አልጠራጠርም። ህዝቡ፤ መለስ ዜናዊ ቢኖሩ ባይኖሩ፤ ስርአቱ ይቀጥላል ብሎ ያምናል። ለእኛም፤ ስርአቱ የፈጠራቸውን መተኪያወችና ተቋሞች መገንዝብ ለትንተናና አማራጭ ለመቅረጽ ይረዳናል። መተካካትን ስናይ፤ ግለሰብ ቢታመም፤ እነደማንኛውም ህያው ከዚህ አለም ቢያርፍ፤ ገዥው ፓርቲና የፈጠረው መንግስት እንዲቆዩ በቂ ዝግጂት አድርጓል። አሜሪካኖችም የህወሓት ሽግግር የረጋ እንዲሆን በማሰብ እየረዱት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል። ስለዚህ፤ ህወሓት “የዳበሳ ጉዞ” ሳይሆን፤ በእቅድ የሚመራ ስልት እየተከተለ ነው። የህወሓት/ኢሃዴግ ተጠቃሚወች፤ ያገኙትን ስልጣንና የኢኮኖሚ ጥቅም ከመጠበቅ ወደኋላ አይመለሱም።

ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በውስጥ የሚነጋገርበት፤ “በዳበሳ ጉዞ” የሚመራው የተቃዋሚው ክፍል ብቻ ነው የሚለውን ነው። ህዝቡ የቅንጂት መሪወች ያደረጉትን ስህተት የረሳው አይመስልም። ቶማስ ማውንቴንና ሌሎች በጀምላው እነደሚሉት፤ ስርአቱ እንደ እምቧይ ካቭ ይናዳል ማለት ዘበት ነው። ሆኖም፤ አምባ ገነን አመራርና አንድ መሪ የበላይ የሆነበት አገዛዝ መሪው ሲታመም ወይንም ሲሞት ይሸበራል፤ ይብረከረካል። እንዳየነውና እንደምንሰማው፤ አንዳንዱም አውጭኝ ይላል። ብዙወቹ፤ አስቀድመው ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ልከዋል፤ ሃቭት አሽሽተዋል፤ ቤት ገዝተዋል። እንደሚሰማው ከሆነ፤ ፈሪወች አገር ይለቃሉ፤ ገንዝብ ያሸሻሉ። ሁሉም ይሸሻል ማለት ዘበት ነው። ዋና ተጠቃሚወችና ተቋሞች ይቆያሉ። በተለይም፤ የስለላና የመከላከያ ተቋሞች መሪ የስርአቱ ደጋፊወች/ጠባቂወች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ውጭ በስደት ከምንኖረው የበለጠ ያውቀዋል።

የኤርትርያ ተወላጆች እንዴት ተመረጡ?

የመተካካትን አስፈላጊነት፤ የጠቅላ ሚኒስትሩ ህመም አስጊ መሆኑ ሲታወቅ፤ የህወሓት የስለላና የመከላከያ የበላይ ባለስልጣኖች ያደረጉት ይገልጸዋል። አሁን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሩት፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ ታማኝ የህብረምጣኔ አማካሪ፤ አቶ ነዋይ ገብረአብና የውጭ ጉዳይ ዋና የበላይ አቶ ብርሃኔ ገብረክርስቶስ–ሁለቱም የኤርትርያ ተወላጆች–የተደገፉት በመከላከያና ስለላ ድርጅቶች የበላዮች ነው ተብሎ አዲስ አበባ በሰፊው ይወራል። አሜሪካኖች እንዳሉበትም ይነገራል። ይህ የመተካካት ስልት ለህወሓት አደገኛ ሁኔታ እንደፈጠረና አነደሚፈጥር መገመት ይቻላል።በህወሓት ውስጥና በኢሃዴግ ውስጥ ፉክክር መፍጠሩ የማይቀር ነው። አገር ወዳድ በሆኑ የትግራይ ተወላጆችና በኤርትርያ ምርጦች መካከል የሚኖረው ፉክቻ መታየቱ አይቀርም። ሆኖም፤ ለጊዜው፤ የህወሓት የመተካካት መልክ በሽግግሩ የተከታታይነትን፤ የዘላቂነትን  ምኞትና አስፈላጊነት ያንጸባርቃል። የአሁኑ አወቃቅር የሚያሳየው ችሎታ ሳይሆን፤ ለህወሓትታማኝ መሆን ቁልፍ መሆኑን ነው።

ታዲይ “ምን ይደረግ” የሚለው ዝንኛው የሌኒን መሰረተ ሃሳብ የሚያገለግለው እዚህ ላይ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በተከታታይ ሲጠይቀው የቆየ ጥያቄ አሁንም መልስ አላገኝም– ህዝቡ ለመብቱ ሲነሳ ተቃዋሚው ክፍልስ ምን ይሰራል? ምን ይጠብቃል?

ታላቁን ክፍተት እንሙላው፤

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መታመማቸው አከራካሪ አይደለም። የእግዚአብሄር ፍጥረት መሆናቸውን አንርሳ። ፈላጭ፤ ቆራጭ፤ በሰላሚዊ ግለሰቦች ላይ ፈራጂ፤ ሰውን አዋራጂ፤ አማራውን “አህያ ነህ” ባይ፤ ሰንደቅ አላማችን “ጨርቅ ነው” ባይ፤ “ሌብነት ጀግንነት ነው” ባይ፤ ከተፈጥሮ አደጋ ሊያድናቸው አይችልም። መልአክ ስላልሆኑ፤ ዘላለማዊ ሊሆኑ አይችሉም። ብዙ ተመልካቾች የሚመኙት በህይወት እንዳሉ የገነቡት አሰቃቂ ስርአት ተገርስሦ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን ተጎናጽፎ እርሳቸውንና የቅርብ ግብረ አበሮቻቸውን ለህግ እንዲያቀርባቸው፤ እንዲፋረዳቸው ነው።

ይህ እንዳለ ሆኖ፤ በተደጋጋሚ ለማቅረብ የምፈልገው ዋና ነጥብ አለ። ይህም፤ ዛሬ እንደትላንቱ፤ አገራዊና ሁሉን አቀፍ የሆነ የተቃዋሚ ድርጂት አለመኖሩ፤ ለሽግግር የሚያበቃ፤ ትሁት፤ አገር ወዳድ፤ የማያዳላ፤ ትጉህ፤ አቻቻይ፤ ሚዛናዊ፤ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ያገባዋል ባይ፤ የኢትዮጵያና የአለም ህዝብ ብቁነቱን የሚቀበለው፤ ለመደራድር ድፍረትና ትጋት፤ ጥልቀትና አስተዋይነት ያለው አመራር አለመኖሩ ትልቅ ክፍተት ነው (Immense vacuum in national political organization and wise and seasoned leadership)። የኢትዮጵያን ሕዝብ እንቅልፍ የነሳው ነው ለማለት ያስደፍራል።

ለዚህ ክፍተት በአስቸኳይ መልስ ለመስጠት ካልቻልን ታሪክ የሚወቅሰው ህወሓትን ብቻ ሳይሆን (በእርሱ ላይ ታሪክ ሲፈርድ ቆየቷል፤ ወደፊትም ይፈርዳል)፤ የተቃዋሚውን ዘርፍ ጭመር ነው። ራስን ከመውደድ፤ ጉረኛ ከመሆን፤ ከመከፋፈል፤ ከመጠላለፍ፤ ከሃገር በላይ ለስምና ለግል ዝና ከማጎብደድ፤ ለስልጣን ተገዥ ከመሆን የሚመጣውን ጉድ ወደጎን ትቶ ከሌላው ላይ ጉድ አለብህ ሲሉ ከመኖር የሚታየው ሁኔታ ሃላፊነት መጉደሉን ነው። የህዝብ ጥያቄ ሃላፊነት ከጎደለው፤ አይጠቅምም፤ አያስተማምንም፤ ለውጣ አያመጣም። የዚህ አይነቱ ባህርይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት አያሟላም። ባለፈው እንዳየነው፤ የህዝብን፤ በተለይም የወጣቱን ተስፋ ይበርዘዋል። እነ አንዷለም አራጌ፤ እነ እስክንድር ነጋ፤ ሌሎች፤ ባልፈጸሙት ወንጀል የውሸት ምስክር እየቀርበ፤ ለሃገራቸው መኖር አለመኖር፤ ለመላው ህዝብ ሰብአዊ መብት መከበር፤ ለነጻነት፤ ለሰው ክብር፤ ለፍትህ-ርትእ በመቆማቸው ብቻ ሲወነጀሉ እያየን፤ ይህን አስጨናቂ የአገራዊ ድርጂት አስፈላጊነት፤ የአመራር ክፍተት ለመዝጋት አሁን አለመነሳታችን በህዝብ እያስጠየቅን ነው። ለሃገርና ለመላው ህዝብ “የቆምኩ ነኝ” የሚል ብቸኛ (Opposition groups that operate in silos) ተቃዋሚ ሁሉ እውነተኛ ገጹን ማሳየት ያለበት ልዩነቶችን ወደጎን ትቶ ለአንድ ሃገራዊ አላማ፤ ለነጻነት፤ ለእኩለንት፤ ለህዝብ የበላይነት፤ ለመድብለ ፓርቲ ስርአት፤ ተባብሮ መስራት ነገ ሳይሆን፤ አሁን በተግባር ማሳየት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ይህ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ደጋግሞ የሚለው፤ እስካሁን የተጓዝነው “የጨለማ” ፖለቲካ ጉዞ የትም አላደረሰንም። በመለያዩታችን የሃገራችን የባህር በር ተዘግቷል። ጥገኛ ሆነናል። ህወሓት በምስጢር ተዋውሎ ከአንድ ሽህ ስድስት መቶ ስኩየር ኪሎሜትር በላይ የሚሆን ለም መሬት፤ ወንዞች፤ ተራራውች፤ የማእድን ሃብት ምንጮችን ለሰሜን ሱዳን አስረክቧል። የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተራበ፤ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ለም መሬት ለውጭ መንግስታት፤ ድርጂቶችና ምርጥ የትግራይ ተወላጆች አዛውሯል። የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በገፍ እንዲሰደድ አድርጓል። በገፍ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እነደሸቀጥ የሚላኩት እህቶቻችን ለመብታቸው የቆመላቸው መንግስት የለም። የህወሓት አባላት የሰው ንግዱ ተጠቃሚወች መሆናቸውን ህዝቡ ያውቃል። ህወሓት/ኢሃዴግ፤ በአማራ፤ በኦሮሞ፤ በአዋሽ ሸለቆ፤ በሶማሌ፤ በአፋር ወዘተ ህዝብ ላይ ኢሰብአዊ በደል ፈጽሟል። በአማራው ህብረተሰብ ላይ ሲጸነስ የጀመረውን የብሄር ማጽዳትና መቀነስ አላማ አሁንም እያካሄደው ነው። በጎንደር በሁለት የአማራ ብሄረሰብ አባላት በሆኑ ወንድ ወጣቶች ላይ ህወሓት የፈጸመው የሚዘገንን ድርጊት ማንም ሊረሳው አይችልም። የሟቾችን አጽም ለመቀጣጫ ብሎ በመንገድ መጎተት ከኢሰባዊነት በላይ የሆነ አረመኔያዊ ወንጀል ነው። በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደዚህ ያለ ዘግናኝ ድርጊት የሚካሄድባት ኢትዮጵያ በ July 17, 2012, Economist, “Zenawi’s Police State” ብሎ የሰየመው መንግስት የሚያካሂደው የመለስ ዜናዊ የጭቆና መንግስት ውጤት ነው። የአምባገነን አመራር መልክ ይህን ይመስላል።

“ነገ በእኔም ይደርሳል”፤

እኛ ብዙ ጉድና ግፍ እያየን ችግሩ ነገ በያንዳንዳችን ላይ እንደሚደርስ አልተረዳነውም። የሁለቱ ጎንደሬወች ሬሳ በአደቫቫይ በመሬት ሲጎተት፤ የተጎተተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭምር መሆኑን የተገነዘብነው ጥቂቶች ነን ለማለት ይቻላል። ክብሩ የተገፈፈው፤ የተዋረደው የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነው። የሚያሳየው ሰቆቃ፤ በምንም ለሰው ክብር ደንታ የሌለው፤ አዋራጂ የመንግስት ስርአት እንዳለ ነው። ይህ ስርአት፤ ማንኛውም ፍትህ ፈላጊ ግለሰብ ዋጋ እንደሚከፍል ደጋግሞ አሳይቷል። ታዲያ፤ እንደዚህ የመሰለውን የሰው ክብር ገፋፊ መንግስት ሊያቆየው የቻለው የራሱ ጥንካሬ ብቻ አይደለም። የተቃዋሚው ክፍል መበታተን፤ የእኛ ቸልተኝነት፤ የእኛ በረባ ባልረባው መከፋፈል፤ የእኛ መናናቅ፤ የእኛ በዘር መደራጀት፤ በብሄር የተደራጁ እንቅስቃሴወች አሁንም እንገነጠላለን፤ አብረን ለመኖር፤ አብረን አዲስ ለሁሉም የሚቨጅ ስርአት አንገነባም ማለታቸው ወዘተ እየጎዳንና የህወሓትን አገዛዝ እድሜ እያራዘመው ነው። የተከፋፈለ ቤት የጠላት መግቢያ በር እንደሚከፍት ሁሉ፤ የእኛም መከፋፈል፤ በመነጣጠል እያስመታን ነው። አደጋው ህወሓት እየለየ ሲመታን በተመልካችነት፤ “ከእኔ አልደረሰም” በሚል የሞኝ አስተሳሰብ ደጋግመን መቀበል ልማዳችን ስለሆነብን ነው። አገራዊ ድርጂትና አመራር ለዚህ ሰቆቃ መልስ ሊሰጥ በቻለ ነበር።

የኢትዮጵያና የመላው ሕዝቧ ጥልቀት ያለው ችግር (Intractable problems)፤ በውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ጠላቶችም የተደገፈ ነው። ጠላቶቻችን እርስ በእርሳችን አናክሰው ሊያጠፉን ባዘጋጁልን ወጥመድ ውስጥ የመውደቅ እድላችን የሚያሳየው የራሳችን ከመከፋፈል የመጣ ድክመትን ነው። በውስጥ፤ ሌላው ቀርቶ ህወሓት ቁመንለታል ለሚለው ለትግራይ ህብረተሰብ አልሆነም፤ ሊሆንም አይችልም። ይህ ህብረተሰብ፤ በኢትዮጵያዊነቱ የኮራ፤ ከሌሎች እህቶቹና ወንድሞቹ ጋር አብሮ ተሰለፎ የውጭ ጠላትን የመከተ፤ የባህር በሩን ያስከበረ፤ በሃይማኖቱ የጸና፤ አብሮ መኖርን ከዘረኝነት በላይ የመረጠ ነው። የኦሮሞ ህብረተስብም እንደዚሁ ነው። ለመላው የትግራይ ህዝብ ደንታ የሌለው የማፍያ ቡድን በዘረፋ፤ በመስረቅ፤ በመበዝበዝ፤ በማፈን፤ በመግደል፤ በማሳደድ፤ በመዋሸት፤ ለማዋረድ ሲል የሰውን አጽም በመንገድ በመጎተት ሃይሉን የሚያሳይ፤ ገንዝብና ሌላ ሃብት በማሸሽ የሚያምን ቡድን ነው። ስርአቱ ካልተለወጠ ሰቆቃው ይቀጥላል።

ይድነቃችሁ ብሎ፤ ለሃገራቸው የሚያስቡ፤ ችሎታና ብቃት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን እንደሌሉ አድርጎ፤ ምርጥ የኤርትራ ዘር ያለባቸውን ታዛዦች መርጦ ለወቅቱ ተተኪ ሲያደርግ ሌላውን እንደማያምን፤ እንደማያከብር የሚያሳይ አገዝዝ መሆኑን አስመስክሯል። ይህ ተራ የዘረፋ ቡድን ማንኛውንም ለመብቱ፤ ለሰላም፤ ለነጻነት፤ ለፍትህ የቆመ ሁሉ እንደጠላት ይቆጥረዋል።

እንሰብሰብ፤ እንተባበር፤

ለዚህም ጭምር ነው፤ አሁን መሰብሰብ፤ አብሮ መስራት፤ ከብሄር በላይ ማሰብ፤ በአንድ ድምጽ፤ ለአለም ህዝብ አቅዋም ማሳየት፤ አገር ቤት ካሉ አገራዊ ከሆኑ ተቃዋሚ ስብስቦች ጋር ኩታ ገጠም መሆን የሚያስፈልገው። ይህን ካላደረግን፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢታመሙም፤ ባይታመሙም፤ ሌላም አደጋ ቢደርስባቸው፤ ባይደርስባቸው ያለው አሰቃቂ ስርአት በተጠቃሚወች ይተካል። ያለው የበላይ ተጠቃሚ ባለስልጣን ቡድን “ጂብ” ይመስላል ብንል፤ መጭው/ተተኪው ደግሞ አንበሳና ነብር ሆኖ ያገኘውን ሃይልና ጥቅም በበለጠ ያስጠብቃል ለማለት የሚያስችል ሁኔታ አለ። የተከፋፈለ ተቃዋሚ እስካለ ድረስ የመለስ ዜናዊ ፍልስፍና በሌላ መልኩ ይቀጥላል።

የምእራብ አገሮች፤ በተለይ አሜሪካ፤ እንደ ሕንድና ሳውዲ አረቢያ ያሉ የመሬት ነጣቂወች፤ ስርአቱ እንዲቀጥል የተቻላቸውን ድጋፍ ይሰጣሉ። እነሱ የማያዩት፤ እኛ መግፋት ያለብን፤ የምእራብ መንግስታትን ማሳመን ያለብን፤ የህዝቡ እንቅስቃሴ በምንም የማይገታ መሆኑን ነው። ይህን ማለት በቂ ሊሆን አይችልም። እድሉን የመጠቀም ምርጫው የተቃዋሚው ክፍል  መሆኑን ያለ ይሉኝታ መግፋት  አገራዊ ጥሪ መሆኑን ተቀብሎ  “ተባበሩ፤ አትከፋፍሉን” ማለት የሞራል ግዴታ ነው።  ለዚህ፤ ታላቅ አገራዊ፤ ሁሉን አቀፍ ስብስባ በፍጥነት አካሂዶ ያሉትን ገንቢ አማራጮች ተወያይቶ በጋራ ማቅረብ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው።

ቃሌ የመወያያ ክፍል 5 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጁላይ 28 ቀን ለውይይት ጋበዘ

Sunday, July 22nd, 2012

(ዘ-ሐበሻ) በፓልቶክ ውስጥ ካሉት በርከት ያሉት የመወያያ ክፍሎች መካከል አንዱና ግንባር ቀደሙ የሆነው ቃሌ የመወያያ ክፍል 5 የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጁላይ 28 ቀን 2012 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለማወያየት መጋበዙን ለዘ-ሐበሻ በላኩት ጥሪ አስታወቁ። የጥሪውን ሙሉ ቃል እንደሚከተለው አቅርበናል።

July 21, 2012

ለተከበራችሁ፡

የጥምረት ለነጻነት ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ

የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት

መሪዎችና አባሎች፤

ጉዳዩ፤ ቃሌ (የብርቱካን መዴቅሳ) የፖለቲካ መወያያ ክፍል ዉስጥ በጁላይ 28 ቀን 2012. ኤም ኢስተርን ታይም ወይንም በ20 ሴንትራል ዩሮፒያን ታይም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ላይ አስተያየታችሁን እንድትሰጡ በክብር ተጋብዛችሗል።

የቃሌ ታዳሚዎች ስለ ኢትዮጲያ ፖሌቲካ ዉይይት የጋበዟችሁ ለጁላይ 28 ቀን 2012 ቢሆንም፣ ሌሎች እህት ክፍሎች፤ ከረንት አፌይርስ፣ አበራሽ በርታ፣ አሉላ አባነጋና ለሌሎቹም ዉይይቱን መከታተል ለሚፈልጉ ለማሰማት ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል የሚመጡትን የተወካዮቻችሁን ስም የሚገልጽ የኢሜል መልስ ይህ ኢሜል ወደመጣበት አድራሻ ከጁላይ 26 ቀን 2012 በፊት በመላክ እንድትተባበሩን እየጠየቅን፣ ተወካይ ለመላክ የማትችሉ ከሆነ ደግሞ ከጁላይ 26 ቀን 2012 በፊት በኢሜል እንድትገልጹልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

በመጀመሪያ ቃሌ (የብርቱካን መዴቅሳ)፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መወያያ ክፍል ዓላማ ጸረ-ወያኔ አቋም ያለን ኢትየጵያዉያን እንዴት ፍትሕ፣ የግለሰብ ነጻነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማምጣት በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ እንድንወያይ ማድረግ ነዉ። ለዚህም የክፍሉ አድሚኖች በዚሁ ዓለማ የሚያምኑና የተለያየ የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊዎችና እንዲሁም ደግሞ የምንም ድርጅት መስመር ተከታዮች ያልሆኑም ይገኙበታል።

ለክፍሉ ታዳሚዎች፣ የወያኔን ፖለቲካ ማራመድ ከሚጥሩት በስተቀር፣ ዉይይቱ ላይ ሃሳባቸዉን በነጻ እንዲገልጹ መድረኩ ክፍት ነዉ። ቃሌ እንደዉይይት መድረክ የማንም የፖለቲካ ድርጅት ፕሮፓጋንዳ አይካሄድበትም። በተቃዋሚና በጸረ-ወያኔ ፖለቲካ የሚታወቅ የፖለቲካ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ወይንም የድርጅት መሪ አይዘለፍበትም።

በኢትዮጵያ ዉስጥ ስላለዉ ፖለቲካ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያዉያን ለዉይይት በሚቀርቡት የዉይይት ርእሶች ላይ የግራም ሆነ የቀኝ አመለካከት ይኑራቸዉ፣ ወይንም ደግሞ ይሄንን ድርጅት አልደግፍም በማለታቸዉ ከዉይይት አይታቀቡም። ከዉይይት የሚታቀቡት በዘለፋ፣ በስም ማጥፋት እንዲሁም ከተያዘዉ የዉይይት ርእስ እየወጡ ሲያስቸግሩ ብቻ ነዉ። የመሳተፍ መብታቸዉ ለአጭር ጊዜ ብቻ ይወሰድባቸዋል። የቃሌ አድሚኖችና ታዳሚዎች በአማካይ ቀን ለዉይይት እሰከ 110 ሲደርሱ፣ ለየት ባሉ ቀናት ደግሞ ከ250 በላይም በመሆን ሁለተኛ ክፍል እሰከመክፈትም የሚደረስበት ጊዜ አለ። እንደ ጁላይ 28 ቀን 2012 ባለዉ ሰፊ ዝግጅት ወቅት ደግሞ አህት ክፍሎች ከረንት አፌርስ፣ አበራሽ በርታ፣ አሉላ አባነጋና ሌሎቹም ዉይይቱን እንዲያሰተላልፉ ሲደረግ የታዳሚዉ ብዛት ከ800 በላይ ይሆናል ብለን እንገምታለን። ይህ እንግዲህ ቃሌን በሩቁ ለምታዉቁ ባጭሩ ግልጽ እንዲሆንላችሁ ለማድረግ ነዉ።

በዚህ ባሳለፍናቸዉ ጥቂት ወራት ኢትዮጵያዉያን ባገር ዉስጥና ከኢትዮጵያ ዉጭ በዲሞክራሲና በፍትሕ ዙሪያ በሚከተሉት ተግባራዊና ፖሌቲካዊ ሂደት ዉስጥ በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዙ ይገኛሉ፤

• በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በኦጋዴንና በበጌምድር ሕዝቡ ለነጻነቱ በተለያየ መንገድ እየተናነቀና እይተዋደቀ ነዉ።

• ሙሰሊም ዜጎቻችን ለእምነት ነጻነታቸዉ በየሳምንቱ ድምጻቸዉን በማሰማት እየታሰሩና እየተገደሉ ይገኛሉ።

• መምሕራን፣ ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም ሰላማዊ ታጋዮች የነጻነት ያለህ በማለታቸዉ ከስራ በመባረርና በሽብርተኛነት እስከእድሜልክ እስራት እየተበየነባቸዉ ናቸዉ።

• አቶ መለስ ዜናዊ አንዴ ታመዋል፣ አንዴ እረፍት ሄደዋል በሚል ሊተኳቸዉ የሚችሉትንም የሕወአት/ኢሕአዴግ መሪዎች ስም በተለያየ መንገድ በማስወራት ሕወአት በአንድ በኩል የአቶ መለሰን መገለል በሌላ በኩል ሌሎች የሚተኳቸዉ መሆኑን ቀስ በቀስ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲቀበለዉ በማለማመድ ላይ ይገኛል።

• በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ የሰላማዊ ትግል የሚያካሂዱ የፖሌቲካ ድርጅት መሪዎች ደግሞ ጊዜዉ የሚጠይቀዉ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ የአገር ማዳን ስብስብ ማድረግ አለባቸዉ እያሉ ነዉ።

• በዉጭ አገር ያሉ የኢትዮጵያ ፖሌቲካ ድርጅቶችና ኢትዮጵያዉያን፣ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በወያኔ ላይ በሚወሰደዉ ፖለቲካዊ እርምጃ ሁሉ ትብብር እያሳዩ ነዉ። የፖሌቲካ ድርጅቶች የጋራ ግንባሮች ተፈጥረዋል፣ የሽግግር ምክር ቤትም ተመስርቷል። የኢትዮጵያ ዲያስፖራም የፖሌቲካ ድርጅቶች ተሰባስበዉ ስለኢትየጵያ መነገጋር ያለባቸዉ ጊዜዉ አሁን በሚል በየመድረኩ ሲነጋገር ይሰማል።

ከየድርጅቶቻችሁ በጁላይ 28 ቀን 2012 ቃሌ የመወያያ ክፍል የምትልኳቸዉ ተወካዮች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሶሰት አበይት ጉዳዮች ላይ የድርጅቶቻችሁን እምነትና አስተያየት እንዲያካፍሉን በከፍተኛ ጉጉት እንጠብቃለን፤

1. የሃገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ አየር ምን ይመስላል? ሕወአት/ኢሕአዴግ ከመለስ በዃላ እመርታዊ ተሃድሶ ሊያመጣ ይችል ይሆን?

2. በተቃዋሚ ጎራ ያሉ የፖሌቲካ ቡድኖች መሰባሰብና ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ መነጋገር አያስፈልግም? ተሰባስቦ ስለሀገር መወያየት አያስፈልግም ከተባለ ደግሞ ምክንያቱ ምን ይሆን? ተሰባስቦ መነጋገር ካሰፈለገ ደግሞ የዚህ ተሰባስቦ መወያየት ጥቅሙ ምንድን ነዉ?

3. የመለስን መገለል ተከትሎ፣ የምእራብ አገሮች በፖለቲካ ስልጣን ዙሪያ እናደራድራችሁ ቢሉ፣ ሊሆን የሚችለዉ ምንድን ነዉ? የፖለቲካ ቡድኖች ወይንም ግንባሮች በተናጠል የሚደራደሩበት ሁኔታ ሊኖር ይችል ይሆን? በተናጠል የሚደራደሩ ከሆነ ደግሞ ከሕዝቡ የነጻነትና የፍትሕ ጥያቄ ጋር እንዴት ሊያያዝ ይችላል?

ዉይይቱ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ያለበት ሆኖም መጠየቅ ያለባቸዉ ጥያቄዎች ከታዳሚዉ በአክብሮት ስለሚጠየቁ ተወካዮቻችሁ ተገቢዉን መልስ ባለመሰልቸት እንደሚሰጡ እንተማመናለን።

ከአክብሮት ጋር

ቃሌ የኢትዮጵያ ፖለቲካ መወያያ ክፍል አድሚኖችና ታዳሚዎች

ፍትህ ጋዜጣ እንዳትሰራጭ ታገደች

Saturday, July 21st, 2012

(ፍትህ – ተመስገን ደሳለኝ) በትላ ንትናው ዕለት ለስርጭት መብቃት የነበረባት ፍትህ የጠቅላይ ሚንስትሩን መታተም ተከትሎ በተፈጠረው የስልጣን ትግል እያሸነፈ በመጣው አክራሪ ሀይል ተስተጓጉላ የነበረ ቢሆንም በማግስቱ እንድትታተም ተፈቅዷል ተብሎ ታተመች፡፡ ትላንት ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይም ሙሉ በሙሉ ታትማም አለቀች፡፡ ነገር ግን አንባቢያን እጅ ልትደርስ አልቻለችም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ (በዛው ኃይል ትዕዛዛ ይመስለኛል) በአቃቢ ህግ ብርሃኑ ወንድምአገኝ ‹‹ለሀገር ደህንንት የሚያሰጋ ዘገባ በጋዜጣው ላይ መታተሙ መረጃ ስለደረሰን እንዲታገድ ወስነናል›› በሚል የተፈረመ የዕግድ ደብዳቤ ማተሚያ ቤቱ እንደደረሰው ገለፀልን፡፡ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ሰዓት 30 ሺህ የፍትህ ጋዜጣ እትም በብርሃና ሰላም ማተሚያ ቤት ተቆልፎበት ይገኛል፡፡

…እንዴት ነው ነገሩ? ‹‹ትሻልን ፈትቼ ትብስን አገባሁ›› እየሆነ ነው? ይህ ሁኔታ ወደስልጣን እየመጣ ያለው ሀይል የባሰ እንደሆነ ምልክት እያሳየስ ይሆን? ለማንኛውም መጨረሻውን አይተን የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን፡፡

(ማተሚያ ቤቱ ለጋዜጣው ዝግጅት ክፍል የላከውን ደብዳቤ ከስር ይመልከቱ)

ይህች ምድር የሁላችንም ናትና በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር አለብን

Thursday, July 19th, 2012

ይህች ምድር የሁላችንም ናትና በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር አለብን::

By Haile Mulu Dated: Sunday, 08 July 2012 00:00

አቶ ተሻለ ሰብሮ፣ የኢራፓ ፕሬዚዳንት

ምርጫ 97ን ተከትሎ በኅብረተሰቡ ዘንድ የተፈጠረውን ከፖለቲካ የመሸሽ ሁኔታ ለማስተካከልና ተስፋ የቆረጠውን ሕዝብ ተስፋ የማለምለም ራዕይ ሰንቆ መቋቋሙን የሚናገረው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ የተመሠረተበትን ሦስተኛ ዓመት በቅርቡ አክብሯል፡፡

የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል የሆነው ኢራፓ ሰሞኑን ለገዢው ፓርቲና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የብሔራዊ መግባባት ጥሪ አቅርቧል፡፡ አቶ ተሻለ ሰብሮ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ፓርቲው ባቀረበው የብሔራዊ መግባባት ጥሪና በሌሎች ተያያዥ አገራዊ ጉዳዮች ኃይሌ ሙሉ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ኢራፓ ብሔራዊ መግባባት ያስፈልጋል የሚል ሐሳብ ይዞ መጥቷል፡፡ ብሔራዊ መግባባት ማለት ምን ማለት ነው? እንዴት ነው የሚገለጸው?

አቶ ተሻለ፡- በእንግሊዝኛው ብዙ ስያሜዎች አሉት፡፡ ‹‹National Reconciliation›› ይባላል፡፡ ‹‹National Dialogue›› ይባላል፡፡ ‹‹National Debate›› ይባላል፡፡ ብዙ ስሞች አሉት፡፡ የዚያን ቀጥተኛ ትርጉም ለመናገር ፈልገን አይደለም፡፡ በመሠረቱ ዓላማችን በሰላማዊ ትግል የተሻለችና የተሻሻለች ጠንካራ ኢትዮጵያን መመሥረት ከሆነ ከብሔራዊ መግባባት የተሻለ አማራጭ የለም፡፡ ወደድንም ጠላንም ወቅቱ የሚጠይቀን ይህንን ብቻ ነው፡፡

ብሔራዊ መግባባት ስንል ተራ እርቅ አይደለም፡፡ ተራ ሽምግልና አይደለም፡፡
ከዚህ ቀደም ብዙ ፓርቲዎች፣ ብዙ ግለሰቦችና ብዙ ጋዜጠኞች ብሔራዊ እርቅ ይደረግ ሲሉ ሰምተናል፡፡ ትክክል ናቸው፡፡ ነገር ግን ያ የመጨረሻ ምዕራፍ ነው፡፡ ከብሔራዊ እርቅ አስቀድሞ የኢትዮጵያ አጀንዳ በሚመለከታቸው አካላት መካከል ብሔራዊ ውይይት መጀመር አለበት፡፡ ብሔራዊ ውይይት ወደ ብሔራዊ መግባባት፣ ብሔራዊ መግባባት ደግሞ ወደ ብሔራዊ እርቅ ይመራንና ይደመደማል፡፡ የፖለቲካ ሰዎች፣ መሪዎች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ግለሰቦችና የፕሬስ ሰዎች አንዱ በሌላው ላይ ሳይጠቁም፣ ጠርዝና ጠርዝ ይዞ የቃላት የጥላቻ ፖለቲካ ከማራመድ ባለፈ ተቀራርበው በአገሪቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት ማካሄድ አለባቸው፡፡ ክርክር ማካሄድ አለባቸው፡፡ ያ ወደ ብሔራዊ መግባባት ይወስደንና በሁሉም በአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ አካል ተፈጥሮ ብሔራዊ እርቅ የሚቀርጽ ሥራ ይሠራል፡፡

ሪፖርተር፡- ብሔራዊ መግባባትን አልፎ በቀጥታ ወደ ብሔራዊ እርቅ መግባት አይቻልም?

አቶ ተሻለ፡- አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ለብሔራዊ መግባባትም ሆነ ለብሔራዊ እርቅ የሚመች ሁኔታ አለ ወይ? ብለን መጠየቅ ይገባናል፡፡ ጊዜው እያለፈብን ነው፡፡ እንዲያውም የእኛ ስጋት 11ኛው ሰዓት ላይ ደርሰናል የሚል ነው፡፡ ዕድሎች እያመለጡን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- አሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ደርሰናል ለማለት ያስደፈረዎት ምክንያት ምንድን ነው?

አቶ ተሻለ፡- አሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ምን ሊመጣ እንደሚችል ማየት አለብን፡፡ የአገራችን ነባራዊ ሁኔታዎች ምን ይመስላሉ ብሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡ የፖለቲካ ቋንቋ አለ፡፡ ለምሳሌ ገዥው ፓርቲ አባላቱን ይገመግማቸዋል፡፡ በመስመር ውስጥ ናቸው አይደሉም? ተልዕኳቸውን ይወጣሉ አይወጡም? ብሎ ይገመግማል፡፡ እኛ ደግሞ በአገራችን ጉዳይ ላይ ኢሕአዴግ እንደ አንድ ባለቤትና ባለጉዳይ ሆኖ ሌሎች የፖለቲካ ሽኩቻዎችን ትተን ዜጐች፣ ምሁራን፣ የፕሬስ ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የውስጥ ተጨባጭ ሁኔታ መገምገም አለብን፡፡ ለምሳሌ በሃይማኖት ጥያቄዎች፣ በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ፣ በዲሞክራሲ ጥያቄዎች፣ በኢንቨስትመንትና በአገር ልማት አካሄድና በመሳሰሉት አንኳር አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወደ አንድ መግባባት መድረስ እንዳለበት የሚያሳዩ ጠቋሚ ምልክቶች አሉ፡፡ አዎ ልማት ይካሄዳል፡፡ ግን ልማቱ የሌሎችን ዜጐች ዲሞክራሲያዊ መብት የሚነካ ነው ወይስ አይደለም? ብለን መነጋገር አለብን፡፡ ልማቱን እንደግፋለን፡፡ ይህንን ልማት አብዛኛው ዜጋ የእኔ ነው ብሎ መቀበል አለበት፡፡ ዜጋው ዲሞክራሲያዊ መብቱና ተሳትፎው ሲረጋገጥለት ነው ልማቱ የእኔ ነው ብሎ የሚጠብቀውና የሚንከባከበው፡፡ ደርግ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግድቦች ገድቦ ነበር፡፡ ደርግ በወደቀ በሰዓታት ልዩነት እነኛ ግድቦች ፈርሰዋል፡፡ ለምሳሌ ሀዲያ ውስጥ አንድ ቦታ ላይ ለምንም አገልግሎት በማይውል መሬት ላይ ልማት ይካሄድ ሲባል ሕዝቡ አልሳተፍም አለ፡፡ ደርግ ሲወድቅ በብዙ ሚሊዮኖች ወጪ የተገነባው ግድብ ፈረሰ፡፡ ጨለምተኛ ሆኜ ክፉ ነገር … (CONTINUED)

CLICK ON THIS SENTENCE TO READ THE REST OF THIS INTERVIEW BEFORE FORMING YOUR OPINION SO THAT YOU ARE FULLY INFORMED ABOUT TESHALE SEBRO’S PERSPECTIVE AND INSIGHT INTO ETHIOPIA.

EDITORS NOTE: The information from this point forward is not in any way affiliated with Teshale Sebro. The information below is the view of the Brown Condor staff and editorial board and should not be taken as a continuation of Teshale Sebros’ message of the “Power of Reconciliation”.

HEBRET Circle

Petition Obama to Stop Supporting Meles Zenawi & TPLF

[click logo to sign change.org petition]

Those of you who are comfortable with putting your name behind the cause of seeing Meles Government fall, please sign the petition. This is not just to attempt to make a change. This is about standing together with your fellow Ethiopians in Solidarity. If we can’t sign a petition that takes a minute, what other change do we expect to make in our country or in our lives. If you believe that Meles TPLF regime should remain in power, please disregard this message.

CREDIT Circle

Organizer

Selam Ashenafi Mentire

[click to view profile]

Tsion Tesfaye

[click to view profile]

Click on either picture above and ask Selam or Tsion about their petition drive. We as Ethiopians cannot get things to change if we do not organize and petition the US government for relief and justice for our home Ethiopia.

ያንዱ ጥቃት ለሌላው ውጋት ሊሆን ይገባል

Wednesday, July 18th, 2012

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ መግለጫ

በሀገራችን ላለፉት 21 ዓመታት የተንሰራፋው የህወሓት /ኢህአዴግ አገዛዝ የሕዝቡን አጠቃላይ ኑሮ ወደ አዘቅት የከተተው አልበቃ ብሎ አሁንም በከፋፍለህ ግዛው ስልት የጭቆና አገዛዙን አጠናክሮ ለመቀጠል እየተፍጨረጨረ ነው።

ህወሓት/ኢህአዴግ በትረ መንግስቱን እንደጨበጠ የሃገሪቱን መከላከያ ሃይልና የደህንነት ዘርፍ እንዳለ በማፍረስና በብቸኛነት የሚቆጣጠረውን ጦር ቦታውን እንዲይዝ በማድረግ ያለተከላካይ የቀረውን ሕዝብ ሲያሸብር ቆይቷል፤ አሁንም ያሸብራል፣ ያስራል፣ ያፈናቅላል፡ ንብረቱን ይወርሳል ሲሻውም ይገድላል። ይህንኑ ሲፈጽም እጅግ በጣም በተሰላና በተጠና የመከፋፈል ዘዴ በመጠቀም አንዱን በአንዱ ላይ በማስመታት ነው።

በዚህ ሂደት ለአመታት የዘለቀው የዚህ አምባገነን አገዛዝ የአሁኑ ተረኛ ተጠቂዎች ደግሞ የሀገሪቱ ሙስሊም ዜጎች ሆነዋል። ለአለፉት በርካታ ወራት በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ሲቀርቡ የነበሩ የመብት ጥያቄዎችን በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ባለፈው ሳምንት የተለያዩ የአምልኮ ቦታቸውን በመድፈር አገዛዙ ጥቃት አድርሷል። በአዲስ አበባ የአወልያ መስጂድ ለሰደቃ ዝግጅት በተሰበሰቡ ምእመናን ላይ የግቢ በር ሰብሮ በመግባት የፈጠረው ሸብር የአገዛዙን ማናአለብኝነት የሚያመለክት መሆኑ ግልጽ ነው ። የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች የጠየቁት መሰረታዊ የእምነት ነጻነታቸው እንዲከበርና የሀይማኖቱን መሪዎች ያለምንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት፣ በራሳቸው መምረጥ እንዲችሉ ሆኖ እያለ አገዛዙ ፖሊሱንና ነጭ ለባሾችን አዝምቶ መብታቸውን በሰላም የጠየቁትን ዜጎች በሀገር ላይ ደባ እንደፈጸሙ በማስመሰል ጭካኔ የተሞላበት ጉዳት አድርሷል። ምግብ በማብሰል የተሰማሩትን በሌሊት ከቦ አስለቃሽ ጋዝ በመርጨት ምእመናኑን ደብድቧል፣ አሰቃይቷል፣ አቁስሏል፣ ገድሏል፣ አስሯል።

አገዛዙ የሕዝብን ድምጽ ለማፈንና መሰረታዊ የስብዓዊ መብትን ለመግፈፍ የሚያደርጋቸውን ይህንን እና መስል የሽብር እርምጃዎቹን የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አጥብቆ ያወግዛል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታሰሩትንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ሕዝቡ የተባበረ ትግል እንዲያደርግ ይጠይቃል።

ሸንጎው ለመሰረታዊ የስብዓዊ መብቱ መከበር ትግል ከሚያደርገው ከህዝበ ሙስሊሙ ጎን መቆሙንም ያረጋግጣል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋር ትግል ሸንጎ በአሁኑ ወቅት ለሰላማዊ ለውጥ፡ ለፍትህና ለዴሞክራሲ እውን መሆን ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ባሰሙና ብእራቸውን ለሰብአዊ መብት መከበር፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ እውን መሆን ባነሱ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች መታሰርን እና የተጣለባቸውን ህገወጥ ብይን በጥብቅ ይቃወማል። በአስቸካይ ያለምንን ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱም ይታገላል።

ከዚህም በተጨማሪ በልማትና በተለያየ ፖለቲካዊ ስበቦች ዜጎችን ከሚኖሩበት ቦታ የማፈናቀሉ ተግባር በአስቸካይ እንዲቆም፣ የአምልኮ ቦታዎች የሆኑት የገዳማትና አድባራት ብሎም መስጂዶች ይዞታ እንዲከበር አጥብቆ ይታገላል።

በአንድ በኩል፣ በአስከፊው ጭቆና እየተንገፈገፈ ያለው ሕዝባችን አልገዛም ባይነቱን እያጠናከረ መምጣቱ፣ በሌላ በኩል የስርዓቱ ቁንጮ የመለስ ዜናዊ መታመምና ይህም ሁኔታ በአምባገነኑ ቡድን መካከል የፈጠረው የስልጣን ሽኩቻና የውስጥ መናጋት መጀመር፣ የአገዛዙን ወደ ከርሰ መቃብሩ የመውረዱን ሁኔታ እያፋጠነው መሆኑ የማይታበል ነው። ይህ ሁኔታ ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ፣ ሕዝቡን የማረጋጋታና አቅጣጫ የማስያዝን ሀላፊነት የሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አጥብቆ የሚጠይቀው ነው። ትግሉ በተናጠል ሳይሆን የተቃዋሚው ጎራ ህብረትን፣ ትግስትንና መመካከርን ብሎም በአንድነት ህዝብን ማስተባበርን የሚጠይቅበት ወሳኝ የታሪክ ምእራፍ ላይ ደርሷል። በመሆኑም ሸንጎው ሁሉም ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ትግላቸውን አስተባብረው በአንድ ላይ በመቆም የሕዝቡን ትግል ያስተባብሩ ዘንድ ጥሪ ያቀርባል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ህዝቡ በሃይማኖት፣ በብሄረሰብ፣ በጾታ …ወዘተ ሳይከፋፈል በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በአንድ ላይ በመነሳት አስከፊውን አገዛዝ ገርስሶ በምትኩ የህግ የበላይነት የሚረጋገጥበት፣ ዜጎች መሠረታዊ የስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸው በተግባር የሚውልበት፣ የሕዝብ ልዑአላዊነት እውን የሚሆንበት ስርዓትን ለመመስረት ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የሽግግር ሂደትን ለመጀመር በአንድነት እንዲቆም ጥሪ ያደርጋል።

የመከላከያ ሠረዊቱና የጸጥታ ኃይሉ ከኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ጎን እንዲቆም፣ በዜጎች ላይ የጥቃት እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብና የሀገሪቱን ዳር ድንበር በማስከበር ላይ እንዲያተኩር ሸንጎው ጥሪ ያደርጋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የአንዱ ጥቃት የሌላው ውጋት ሆኖ ሊሰማው ይገባል እንላለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

ዕውነትና ንጋት እያደር ይጠራል (የሽግግር ምክርቤት)

Wednesday, July 18th, 2012

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ም/ቤት የወጣ መግጫ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ም/ቤት ያወጣዉን የአቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት የመለየት ዜና በተመለከተ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የገዢዉ ስርአት እንዲያረጋግጥ በፈጠረዉ ጫና መሰረት 24 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የስርአቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ እንደታመመ አምኗል። አቶ መለስ እንዳልታመመ ላለፉት በርካታ ሳምንታት ሲክድ የነበረዉ ስርአት አሁን ደሞ በመጠነኛ ህመም ላይ እንደሆነ ገልጾልናል። ለነገሩ 21 አመታት ሲዋሽ ለነበረ ስርአት መልሳቸዉ ባያስደንቅም አሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ዝም ብሎ የሚያዳምጥበት ዘመን እንዳከተመ እናረጋግጥላቸዋለን። የሽግግር ም/ቤቱም አሁንም ስርአቱ በተጨባጭ በሶስተኛ ወገን የአቶ መለስን በሕይወት መኖር ለሕዝቡ እስካላረጋገጠ ድረስ አኛም ከራሳችን የታመኑ ም/ንጮች ያገኘነዉን የአቶ መለስን በህይወት ያለመኖር የሚያረጋግጥ መሆኑንና በኛም በኩል ከሃገር ደህንነት አኳያ እዉነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ጥያቄያችንን በህዝባችን ስም መጠየቃችንን እንቀጥላለን። ለኢትዮጵያ ህዝብ የምናስተላፈዉ መልእክት ሀገራችን ያለችበትን አስጨናቂ ሁኔታ በመገምገም በሀገር ደረጃ መደረግ ስለሚገባዉ ዝግጅት ባለዘጠኝ ነጥብ መግለጫ ማዉጣታችንን እያስታወስን በዚህ ወሳኝ ግዜ እዉነተኛ ህዝባዊ የሆነ መንግስት በድል እስኪመሰረት ድረስ ሀገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ የተፈለገዉን መስእዋትነት እንዲከፍል ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የ ሽግግር ም/ቤት አመራር

እሪ! እንበል ለኢትዮጵያ

Tuesday, July 17th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ለመናገር ነጻነት

የቆየውን አበባል ለማስታወስ፤‹‹በማንኛውም ሕብረተ ሰብ ውስጥ እጅጉን አስፈላጊ የሆኑ ሁለት ጉዳዮች ይገኛሉ፡፡ የመጀመርያው በነጻነት መናገር ሲሆን ሌላውን ግን አላስታውሰውም›› ይባላል::

በነጻነት መናገር የሁሉም የሰብአዊ መብቶች መሰረት ነው፡፡ በኔ ግምት፤የህብረተሰቡ ሃሳብን የመናገርን ነጻነት የሚሰጠው ዋጋ፤ ያ ሕብረተሰብ ነጻ መሆን አለመሆኑን የሚያረጋግጥበት መንገድ ነው፡፡ ግለሰቦች ያሻቸውን ለመናገር ፍርሃት ካደረባቸው፤ እንደህሊናቸው ፈቃድ ማሰብ፤ መጻፍ አለያም መንግስትን በመፍራት ከፈጠራ ተግባራቸው ከተገደቡ፤ ሊደርስባቸው በሚችል ማስፈራሪያና ዛቻ ወከባና እስር በመፍራት ያሰቡትን ማድረግ ካልቻሉ፤ያ ህብረተሰብ ነጻነቱን የተሰለበ ይሆናል:: ሃሳብን በነጻነት የማንሸራሸር መብት በአሜሪካን ሪፓብሊክ አመሰራረት ላይ ግዙፍ ቦታ ሊኖረው ስለተገባ፤ አሜሪካን የመሰረቱት ጨርሶ ሊነካ፤ ሊቀለበስና ልዩ ትርጉም ሊሰጠው የማይችል መሰረቱ የጸና ሕገ መንግስታዊ ድጋፍና ከለላ አደረጉለት፡፡ በዚህም ላይ በመመስረትና በእንግሊዝኛው ቋንቋ አማራጭ ትርጉም እንዳይኖረው በማድረግ ‹‹ኮንግሬስ በምንም መልኩ ቢሆን የመናገር ነጻነትን በሚጥስ መልኩ፤ወይም የፕሬስን መብት የሚገድብ ማንኛውንም ሕግ ሊያወጣ አይችልም›› በማለት ደምድመው አስከመጡት፡፡

በማንኛውም ሕብረተሰብ ውስጥ የመናገር ነጻነትን ለማክበርና ለመጠበቅ የሚያስፈልጉበት በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ የመናገር ነጻነት በሌለበት ሰዎች እንደተወተፈ ጠርሙስ ናቸው፡፡ግንኙነት የላቸውም፤ሃሳባቸውን ማንሸራሸር አይችሉም፤ስለፖለቲካ ያላቸውን አመለካከት፤ስለምንግስትና መንግስት ስለሚያወጣቸው ፖሊሲዎች ስሜታቸውንና ሃሳባቸውን መሰንዘር አይችሉም፡፡ መሪዎችና ገዢዎች ላይ ሂስ መሰንዘር አለያም ተጠያቂ ማድረግም አይቻልም ምክንያቱም ሃሳብን በነጻ መግለጽ ወንጀል በመሆኑ ነው፡፡ ለጥበባዊ፤ለቋንቋ እድገት ወይም ለበሰለ አስተሳሰብ ማንሸራሸሪያ በጣም ውስን ቦታ በመኖሩ በሕብረተሰቡ ውስጥ ስላሉት ከፍተኛ ጉዳዮች ለማንሳትና ለመወያየት ያለው ቦታ ጠባብ ይሆናል፡፡ በአጭሩ፤የመናገር ነጻነት በሌለበት፤ ‹‹እድገት ይሰነከላል፤የህብረተሰብ ሁኔታ መሻሻል ባለህበት ሂድ ይሆንና ብቸናው የእውነት መንገድ የገዚዎች ቅጥፈት ወደ እውነትነት ይለወጣል፡፡

የማያጠያይቀውን የመናገር መብት በተመለከተ ለመጻፍ አይደለም አነሳሴ፡፡ ወይም የመንግስታትን የመናገር መብት መጣስ ለመወንጀልም አይደለም የዛሬው አላማዬ፡፡ በርካታ አንባቢዎቼ የመናገር ነጻነትን መብትና ሌሎችም ሰብአዊ መብቶች በተመለከተ በምንም መልኩ ሊተካ የማይችል የመከራከርና ተግባራዊ የሚደረግበትን ሁሉ ለማረጋገጥ እንደምሟገት አበክረው ያውቁልኛል፡፡ በ2010 ፈላጭ ቆራጩ አምባገነን የግፍ ገዢ መለስ ዜናዊ፤በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ለማናግር በመጣበት ወቅት፤የሱንም የመናገር መብቱ እንዲከበር ተሟግቼላታለሁ፡፡ በዚህም ከወዳጅ ጓደኞች የሰላ ወቀሳና ሂስ ደርሶብኛል፡፡ ሆኖም ግን ምንም ያህል መለስ ዜናዊን በእኩይ ባሕሪው ብወቅስና ብኮንነውም፤ስለተግባሩ አስተያየት የሚሰጡትን ሁሉ እንደጠላት በመመልከት ለስቃይና ለእንግልት ቢዳርግም፤ሃገሪቱን ወደአዘቅት እንደሚጥል ባውቅና ያንንም ብቃወመውም፤በሃገሪቱ ያሉትን መገናኛዎች ሁሉ አፍኖ ቢይዝም፤የአሜሪካን ድምጽንና ነጻውን የሳታላይት ቴሌቪዥን ቢያግድና እኔም ብኮንነው፤በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተገኝቶ ንግግር የማድረግ የነጻነት መብቱን ግን እጠብቅለታለሁ፡፡ አዎንና መለስ ዜናዊ ጋዜጠኞችን ለእስር በመዳረግ በአፍሪካ ሁለተኛው ደረጃ ላይ ያለው እኩዩ አረመኔው መለስ ዜናዊ በነጻ ሃሳቡን የመነግለጽ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ባለፈው ጃንዋሪ ላይ የጁንታው መሪ የፈላጭ ቆራጩ መንግስቱ ሃይለማርያም መጽሃፍ የኮፒ ራይትን ህግጋት በጣሰ መልኩ ኮፒ ሲደረግና በየድህረገጹ ላይ ሲለጠፍና መንግስቱ ነፍሰ ገዳይ በመሆኑ፤ ሕዝብን ለመከራና ለሰቆቃ የዳረገ በመሆኑ፤ ያለአንዳች ርህራሄ ሕዝብን የጨፈጨፈ በመሆኑና ላደረሰው በደልና ለፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ዋጋገውን አልከፈለምና ከዚህ መጽኃፉ ሽያጭ ጥቅም ሊያገኝ አይገባውም ሲባል ያን ጊዜም ቢሆን፤ ምንም ያህል እብለትና ቅጥፈት የተሞላበት መጵሃፍ ቢሆም ሃሳብን የመግጽ መብቱ ሊጠበቅለት እንደሚገባ ተናገሬያለሁ፡፡

የእነዚህን ሁለት አረመኔ የጥፋት መንትዮች ጨካኝ ውጉዝ ከመአርዮስ ገዢዎች ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብታቸውን ስሞግትላቸው፤ በይበልጥ የሞገትኩት ግን አማራጭ የሌለውን የማንኛውን ሰብአዊ ፍጡር ሃሳብን በነጻ ለመግለጽ መብት ነው የቆምኩት፡፡ በነጻ የመናገር መብት፤በነጻ የመናገርም ያለመናገርም የሁለቱም መብት ማለት ነው፡፡የሌሎችንም ለማዳመጥና በሌሎችም ለመደመጥ ወይ አለማዳመጥና አለመደመጥ መብት ነው፡፡ ይህ የያንዳንዱ ግለሰብ ምርጫ ነው፡፡ በሃሳብ ከማልስማማቸውም ሰዎች ጋር መነጋገርንና ሃሳበቸውን ማድመጥ ባህሪዬ ነው፡፡ በሃሳብ ልዩነት ላይ ቆመን መደማመጥ ግዴታ ነው፡፡ ያንድን ሰው ሃሳብ ለመቃወምም ሆነ ለመደገፍ ማድመጥ ያስፈልጋል:: በሃሳብ ለመስማማትም ላለመስማማትም መወስን የምችለው የሌላውን ሃሳብ ሰምቼ እንነጂ በጭፍን መወሰን ያስቸግራል፡፡ በሃሳባቸው ካልተስማማሁ ምክንያቱን አብጠርጥሬ ማወቅና ማሳወቅም ይገባኛል፡፡ የሌሎችን ሃሳብ ውድቅ ከማደረግ በፊት ማድመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ የማንንም ሃሳብ ስቃወም ምክንያቱን ቁልጭ ባለ መልኩ አስቀምጬና አስረድቼ ነው፡፡ ስምምነትም ላይ ሆነ መለያየት ላይ ለመድረስ ሃሳብን ማድመጥ አስፈላጊ ነው ካልሆነ በጭፍኑ የሚደረግ ተቃውሞ ምክንያተ ቢስ ሊያደርገን ይችላልና፡፡

ከዚህ ባልተናነሰ መልኩ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ሊከበር የሚገባበት ሌላም ምክንያት አለ፡፡ የራሴ የመደምደሚያ ሃሳብ ላይ ለመድረስ እንደመፈለጌ ሁላ፤ሌሎችም ወደራሳቸው መደምደሚያ ሃሳብ እንዲደርሱ ፍላጎትና ፈቃደኝነት አለኝ፡፡ መንግስቱንና መለስን የሚደግፉን የሚያምኑባቸውም አሉ፡፡እነዚህ ተባባሪዎቻቸው፤ ያለምንም ጥያቄ የመሪዎቻቸውን ሃሳብ የማድመጥ መብት አላቸው፡፡ ሌሎችችንም እውነታቸውንም ሆነ ቅጥፈታቸውን ያለማዳመጥ መብት አለን፡፡ አድምጠናቸው ሌላ አሳማኝ አማራጭም ሆነ ሂስ ልናቀርብላቸው ልንመርጥም እንችላለን፡፡ ነጻ የመናገር መብት፤በ‹‹እውነት›› ላይ ማንም የሞኖፖል መብት ሊኖረው እንደሚችል አልተደነገገም፡፡ ሁሉም ፍጡሮች እኩል መፈጠራቸውንና በህይወትም ላይ ያልተዛባ ሰብአዊ ጉዳዮች አሉት በሚለው የማያልፉና የማይሞቱ ዘልዓለማዊ እውነታዎች እንዳሉ ብገነዘብም፤መሪዎች ስልጣናቸውን የሚያገኙትም ከሚያስተዳድሩት ሕብረተሰብ ነጻነትና ፍካጎት የሚወጣ እንደሆነ እገነዘባለሁ፡፡

ማንም ቢሆን ሞራላዊ የበላይነትን በመቀዳጀት፤በሚሊዮን የሚቀጠሩ ዜጎችን በመጨፍቸፍ ለስላጥን ከበቃው ላይ በመውሰድ መልሰው ለመጨፍጨፍ ቂም በቀል መሰለፍ እንደማይገባቸው አምናለሁ፡፡ተቃዋሚ ሃሳብ ያላቸውን በማፈን የነጻ ሃሳብን የመግለጽ መብት ደጋፊ ነኝ ማለት አይችልም፡፡ ‹‹የምንቃወማቸውን አካላት ሃሳብ ለማድመጥ ፍቃደኝነት ከጎደለን በነጻ የንግግር መብትም ጨርሶ አናምንም ማለት ነው››ይላል ኖአም ቾምስኪ፡፡ እንዲያውም የምንቃወማቸው አካላት ግልባጭ እንሆናለን፡፡

መናገርም መጻፍም የተነፈጉ

ከላይ የተነሱት መከራከሪያዎች ሁሉ ምክንያታቸው የመናገር ገደብ የተጣለባቸውን ወይም በራሳቸው እራሳቸውን የገደቡትን በይፋ እንዲናገሩና እንዲጽፉም ለማነሳሳት ነው፡፡ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊ ያለሆኑት ምሁራን ሁሉ፤ የኢትዮጵያን ሕብረተሰብ በተያየ መንገድ ሲያጠኑ የቆዩ አሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ ምሁራን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ጉዳይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመተንፈስም ለመጻፍም አልፈለጉም ወይም አልደፈሩም፡፡በሃገር ውስጥ ያሉት ምሁራን ግን በገዢው መደብ እስር እንግልት፤ ከስራ መባረር፤ ወደ እስር መጣልን በመፍራትና በመሸሽ ከመጻፍ ተቆጥበዋል፡፡ ከርቀት በሚሰነዘር የሳንሱር ፍራቻም ሳቢያ የዲያስፖራውም ምሁሮች አይጽፉም፡፡አሁን በስልጣን ካለው የአመለካከት ፍልስፍና አለያም የአመለካከት ልዩነት አንስተው ቢጽፉ ዘለፋና ውርጅብኝ ይደርስብናል በሚል ስጋት ዝም ብለው ተመልካች ሆነዋል፡፡ ፖለቲካውየተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩ ጣጣ ይከተላቸዋል፤በማንኛውም የፖለቲካ ስብሰባ ላይ ተቃውሞ ቢያነሱና ሙግት ለመግጠም ቢሞክሩ፤አለያም ስህተቱን አንስተው ትክክለኛውን መንገድ ቢጠቁሙ በበነገታው ስማቸው ጭቃ ለጭቃ ሲጎተትና ክብራቸው ሲደፈር ይታያቸውና ይተዉታል፡፡ በዚህና በመሳሰሉት ሰበቦች ስለ ኢትዮጵያ ለዘመናት ጥናት ያካሄዱና እውቀቱና ችሎቱ የተረፋቸው ምሁራን ከጉዳዩ ጨርሰው እራሳቸውን በማግለል ተመልካችነትንና አድማጭነትን መርጠዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያን ሲያጠኑና ስለ ኢትዮጵያ እውቀት ያዳበሩት ሁሉ አሁን ጊዜያዊው ጥሪ አስፈላጊነታቸውን ይጣራል፡፡ለዝምታና ለተመልካችነት፤ለምን አገባኝና፤ ጊዜው ሲመጣ ማለትን ትተው አሁን ነው በራሳቸው ላይ የጣሉትን የዴሞክራሲ ገደብ ወዲያ ጥለው አሁን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝና ከጥቂቶች የሰቆቃ ዘመን መገላገያውን በሰላማዊ መንገድ ለማምጣት መሰለፍ ያለባቸው፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ በመስቀልኛው መንገድ ላይ ቆማለች፡፡ የለውጥ ምልክቱም ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው፡፡የነጻነትና የዴሞክራሲ ማለዳ ጸሃይም ፈላጭ ቆራጭነትንና ማን አለብኝነትን በዚህ ጸሃይ ቀልጠው ሊጠፉ ነው፡፡ የግፈኛ ገዢዎችም መኩራራትና ድንፋታ የመጨረሻው ጠርዝ ላይ ደርሶ በመንገዳገድ ላይ ነው፡፡ የትዮጵያውያን ፈላጭ ቆራጭ ጨካኝ ፈላጭ ግፈኛ ገዢዎች የመፈንደቂያ ዘመን ወደማክተሙ ነው፡፡ የነጻነት ጎዳናዎች ሁሉ በመዝጋት ሊያፍኑና አሁንም መልሰው ለመግዛት ተስፋ በማድረግ ይንደፋደፋሉ፡፡ አሁን የነጻነት ፈላጊው ሕዝብ የነጻነት ሙዚቃ እየጮኸባቸው ነው፡፡ አሁን የጋንዲ መልእክት እየተሰማቸው ነው– “ግፈኞችና ነፍሰገዳዮች ነበሩ፤ለጊዜው የማይደፈሩ ቢመስሉም ውለው አድረው ግን አይወድቁ ውድቀት ወድቀው አይቀሉ ቅሌት እንደሚከናነቡ የተረጋገጠ ነው›› እስቲ ደጋግማችሁ አስቡት::

በመጨረሻው ሰአት ላይ እነዚህ አረመኔ የሕዝብ ጠላቶች ሲጨንቃቸውና ግራ ሲገባቸው የመጨረሻውን መሳሪያቸውን ሊመዙ መጣራቸው አይቀርም፡፡የመቸረሻው ማጣፊያው ሲያጥርባቸው በየቦታው እሳት መጫር፤ ንዳድ ማስነሳታቸው አይቀርም: እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል እንዲሉ፡፡እዚህ ላይ ግን እሳትና ንዳድ ለይቶ እንደማያቀጥል ነው፡፡ይህን አድርግ ይህን እሰር፤ይህን ፍጠር ሊሉት እንደማይችሉ መገንዘብ ይሳናቸዋል፡፡ ያገኘውን ሁሉ እያቃጠለና እያጠፋ እንደሚጓዝም አላወቁም፡፡

እነዚህ ሁሉ ለሕዝቡ ተስፋ የሰነቁ ቀናት ናቸው፡፡ በጭፍን ጨካኝ አረመኔ ገዢዎች የመጨረሻ የጥፋት ፍንጣቂ ጠርዝ ላይ የነጻነት ተስፋ ብርሃን ሲፈነጥቅ ያታያልና፡፡ የዴሞክራሲ፤ የሰብአዊ መብት፤የሕግ የበላይነት የብርሃን ጨረር ወደሕዝቡ አቅጣጫ ያበራል፡፡ ሕዝቦች አረመኔ ገዢዎችን መፍሪያ ዘመኑ አብቅቷል:: አረመኔ ገዢዎች በተራቸው ሕዝብን መፍራት ይጀምራሉ፡፡ ሕዝቡ ምን ያደርገን ይሆን የሚለው ፍርሃት ወጥሮ ይይዛቸዋል፡፡ ሕዘቡም ተቆጥቷል፤ ተርቧል፡፡ ቁጣ ሲፈላ ደግሞ ወደ ጭካኔ ጥላቻ፤እና ምሬት ይዞራል፡፡ ርሃብ ደግሞ ሰውነት ማቅጨጭና ማደከም ብቻ ሳይሆን ሕሊናንም ያስታል፡፡ የተራበ ሰው ቁጡ ነው፡፡ጨቋኝ ገዢዎችም በፍርሃት የሚርዱት ይህን የመጨረሻውን የጨዋታ ሂደት በማንበብ ነው፡፡

ወቅቱ የለውጥነት ነው፡፡ በዚህ ፈታኝ ወቅት የኢትዮጵያ ምሁራን በጎን ቆሞ ተመልካችነትን ሊይዙ ጨርሶ አይገባቸውም፡፡‹‹የበጋ ወታደሮችና የጸሃይ መውጫ ጀግኖች›› (የድል አጥብያ አርበኞች) ሊሆኑ አይችሉም፡፡ የነጻነት፤የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት አድናቂዎችም ሊሆኑ አይገባቸውም፡፡ ቶማስ ፔይን እንዳለው፡አሁን ጀምሮ ከጨቋኝ ገዢዎች ጋር የሚደረገው ትግል አካል ሊሆኑ የግድ ነው እንጂ ኋላ ላይ የስልጣን ተጋሪ ለመሆን ሩጫ ውስጥ ሊፈናጠጡ አይገባም፡፡ከሕዝቡ ጋር አሁን መሰለፍ እንጂ ሲረፍድ ተቀላቅሎ በህዝቡ ላይ መቆም አይችሉም፡፡

የኢትዮጵያ ምሁራን እውቀታቸውንና ልምዳቸውን የሰውን የጭካኔ አገዛዝ ብቻ ሳይሆን፤የረሃብን፤የበሽታን፤የመሃይምነትን፤የድህነትን፤ጭለማና እጦት ለማስወገድም ለጥሩና ከትግሉ ጎራ ሆነው ሊንቀሳቀሱ ተገቢ ነው፡፡ ጭቆናና ግላዊ የበላይነት በሁሉም መልኩ ሊገታ ይገባል፡፡ የችጋርንና የድርቅን ዱካ ማጥፋት የእርሻ ምሁራን ተግባር ነው፡፡የ ኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት በሁሉም መልኩ የወረደና ያዘቀጠ ሆኖ ሕዝቡን ሁሉ አስመርሯል፡፡ ይህን የበሰበሰና የአዘቀጠ የትምህርት ስርአት ምሁራን በመለወጥ የሕዝቡን ተስፋ ሊያለመልሙት የግድ ነው፡፡ በተለያየ የጤንነት አቅጣጫ ኢትዮጵያ አናሳ ሁኔታ ያላት ናት፡፡ ሕክምናን ከሚተገብሩት ባለሙያዎች ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የህክምና ባለሙያዎች በቺካጎ ያሉት ቁጥር በብዙ ይበልጣል፡፡በዲያስፖራው ያሉ የህክምና ባለሙያዎችስ ተሰባስበው በሃገራችንና በሕዝቡ ላይ በሽታ የሚያደርሰውን ሰቆቃ ሊታገሉትስ አይገባም? በሁሉም መስክ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን በሃጋራችን ያለውን ችግር በየሙያ ዘርፋቸው በመሰለፍ ታገሉትና ድራሹን ሊያጠፉትስ አይገባም? ስለዚህም ሁላችንም በአንድ ጎራ ተሰልፈን ይህን ጭቆናና ግፍ በሁሉም መስክ ለመታገልና ሃገራችንና ሕዘቡንም ነጻ ለማውጣት እንነሳ!

በየሙያ መስኩ መጻፍና መናገር የጉዞው መጀመርያ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ምሁራንና ባለሙያዎች ሕዝባዊ ምሁራበንና ባለሙያዎች እንዲሆኑ አብክሬ እለምናለሁ፡፡ ኢንተርኔት በህብረተሰቡ መሃል ብቻ ፤በጉልበተኛ ገዢዎች መሃል ብቻ ሳይሆን በምሁራንና እውቀት በራቃቸውም መሃል ሁሉንም እኩል የሚያሰልፍ እየሆነ ነው፡፡ ምሁራኑ የእውቀት ባለቤቶችና የግጭት የጥላቻ የትእግስት አልባነት ጠንሳሾች ሁለቱም ወገኖች የህዝብን ልብ በማግኘት አስተሳሰቡን የመቀየር እኩል መብት አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ምሁራን በመሰባሰብ የጠበበውን የእውቀት ድልድይ በማስፋት ህብረትን በማጠንከርና አንድነትን በማስተግበር ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ከፈላጭ ቆራጭ ገዚዎች ስርአት ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የምትሸጋገርበትን መንገድ መቀየስና ሕዝቡንም መምራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጆርጅ በርናርድ ሾው የተባለው ምሁር እንዳለው ‹‹ከአሳማዎች ጋር ትግል አትግጠም ያጠነቡሃል፤ እነሱ ግን ያን ያፈቅሩታል››ማንም ህልምን ፈርቶ ሳይተኛ እደማያድር ሁሉ፤ሊደርስብኝ ይችላል ብሎ ከሚፈራው አንዳንድ አስተያየቶች ወይም ያላዋቂ ሳሚ ግለሰባዊነትን አፍቃሪዎች አፍ ፍራቻና ሽሽት ማድረግ ከሚገባውና ነው ብሎ ከሚያምንበት አስተሳሰቡ ተቆጥቦ ሕዝባዊ ተሳትፎውን ሊገታ አይገባውም፡፡በሁሉም አቅጣጫ የኢትዮጵያ ምሁራንና የሙያ በላቤቶች ይህን የወቅቱን ፈታኝ ጥያቄ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

የመለስ ህመም፣ ታክቲክ እና መፃኢ እጣ ፈንታ – ፍትሕ ጋዜጣ

Saturday, July 14th, 2012

ተመስገን ደሳለኝ | ፍትሕ ጋዜጣ

ሰሞኑን አዲስ አበባ በወሬ መጋኛ ተመታለች። ወሬው በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በተለይም በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ጉድ እየተራገበ ነው- የ57 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በጠና መታመም። ህመማቸውንም ተከትሎ ቤልጂየም ለህክምና መሄዳቸው እና ከፍተኛ ሊባል የሚችል ክብደት የመቀነሳቸውም ወሬ እንዲሁ የመጋኛ ያህል ነው።

በእርግጥ የጉብዝናውን ወራት የዱር ፍሬ እየበላ በረሃ የታገለ ቀርቶ በቤተመንግስት ያደገ ‹‹ልዑል››ም ቢሆን የዚህን ያህል አመት በስልጣን መቆየቱ (ሌላ ምክንያት እንኳ ባይኖር) በጤናው ላይ አንዳች ጉዳት ማስከተሉ አይቀሬ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ችግርም ይህ ነው። ሌላ አይደለም። በበርካታ አምባገነን መሪዎች ላይ የታየ ማለቴ ነው፡፡

ምናልባትም የጠቅላይ ሚንስትሩን መታመም ተከትሎ በሀገሪቱ ውጥረት የነገሰበት ምክንያት የስርዓቱ ዴሞክራሲያዊ ያለመሆንም ነው። ምክንያቱም ዴሞክራሲያዊ በሆኑ ሀገራት የፕሬዚዳንቱ ወይም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤንነት አደጋ ላይ ከወደቀ እያንዳንዱ የህክምና ሁኔታ እና ሰውዬው ያለበት ደረጃ ለሁሉም ሚዲያዎች ይፋ ስለሚሆን ለአሉባልታ የሚጋለጥበት ክፍተት አይኖርም። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታመሙ ጀምሮ ‹‹ከፍተኛ የጤና መታወክ ገጠማቸው››፣ ‹‹ሕይወታቸው አልፏል››፣ ‹‹ሙሉ በሙሉ ተሽሏቸዋል›› የሚሉ እርስ በእርስ የሚጣረሱ ወሬዎችን እየሰማን ያለነው። ይህ ሁኔታ ወደታች ብቻ ሳይሆን ወደላይም ላሉት ግልፅ አይደለም። ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሰው ‹‹ከዚህ በኋላ ወደ ስራቸው አይመለሱም፡፡ ጉዳቱ ከፍተኛ ስለሆነ ሀኪም ለረጅም ጊዜ ከስራ ካልተገለሉ ለህይወታቸው አስጊ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ነግሮአቸዋል›› ሲሉኝ፤ ሌላኛው የፍትህ ምንጭ ደግሞ የዚህን ተቃራኒ ይናገራሉ። የእኚህ መረጃ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ ማገገማቸውን የሚያረጋግጥ እና በመኖሪያ ቤታቸው ስብሰባም እያካሄዱ እንደሆነ የሚገልፅ ነው። ‹‹ይህ የሆነው›› ይላሉ ምንጫችን ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩን በደንብ ካለማወቅ ነው። ምክንያቱም የህወሓት አመራሮች አብዛኛውን ጊዜ ይታመማሉ። ህመም የማያጠቃቸው አቶ መለስ እና አቶ ስዬን ብቻ ነው። ሆኖም እነዚህ ሰዎች ሲታመሙ ጉዳታቸው ‹ሞቶ የመነሳት› ያህል ነው። የአቶ መለስም የሰሞኑ ሁኔታ የዚሁ አይነት ሲሆን፣ ሰውዬው ወደ ስራቸው ለመመለስ እየተዘጋጁ ነው። የሰውነታቸው መጎዳትም የህመሙ ብርታት ሳይሆን የህክምናው ባህሪ (Treatment) የሚፈጥረው ተጽዕኖ ነው›› ሲሉ ወሬውን አጣጥለውታል።

የሆነ ሆኖ መለስ ከወትሮ በተለየ መልኩ ከፍተኛ ሊባል የሚችል የጤና መታወክ እንደደረሰባቸው እርግጥ ነው። በዚህም ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀዋል፤ የፓርቲያቸው አመራርም ከሚገባው በላይ አሳስቦታል፤ ከስር ያለው ካድሬም የተረጋገጠ መረጃ ባይኖረውም በደፈናው መደናገጡ የሚጠበቅ ነው፡፡ ‹‹ሌሎች›› ኢትዮጵያውያን (ይህ አገላለፅ ከ1983 ዓ.ም በኋላ የመጣ ነው) ደግሞ እንደ ልብ አንጠልጣይ ሲኒማ ክስተቱን በተመልካችነት እየተሳተፉበት ነው፡፡ ሁኔታው የአፄ ምንሊክን የመጨረሻ ዘመን ያስታውሳል፡፡ (ሰውየው ሀገሪቱን ለሁለት አስርት ዓመታት ቀጥቅጠው የገዙ ቢሆንም ‹‹እግዜር ይማሮት›› ማለት ባህላዊ ወጋችን ይመስለኛል፡፡ ለማንኛው እግዜር ይማራቸው) ጉዳዩ ግን ይህ አይደለም። ጉዳዩ የጤንነታቸው ሁኔታ እየተባባሰ ከሄደ ወይም የከፋ ከሆነ ‹‹በማን ይተካሉ?›› የሚለው ነው፡፡ ይህ አሳሳቢ ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው ዜጋ ለዓመታት በሀገሩ ጉዳይ ባይተዋር የተደረገ ቢሆንም በእንዲህ አይነት ቀውጢ ጊዜ መጨነቁ አይቀሬ ነው፡፡ እናም ከዚህ ተነስተን ‹‹ቀጣይ የሀገሪቱ ዕጣ ፈንታ›› ምን ሊሆን እንደሚችል ለመወያየት ያህል ሁኔታውን ከአስተዳደር ዘይቤአቸው ጋር እያነፃፀርን እንፈትሽ።

መነሻ አንድ

የፀረ-ደርግ ትግሉን በበላይነት የመራው ህወሓት ከምስረታው ጀምሮ ለሁለት እስከተከፈለበት 1993 ዓ.ም. ድረስ ይመራ የነበረው በ“Collective leadership” (በጋርዮሽ አመራር) እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በዛም ዘመን ‹‹ግለሰብን ማምለክ›› ከግምገማም አልፎ በተፃፈ ህግ እስከመቀጣት የሚያደርስ ጥፋት ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ‹‹ውድብ (ድርጅት) ወስናለች›› የምትለው አገላለፅም የህወሓት ቀኖና ነበር ማለት ይችላል- እስከ 1993 ዓ.ም። በትግሉ ዘመን ሌላው ቀርቶ ከዩኒቨርሲቲ በወጡት ምሁራን እና እርሻቸውን ትተው በረሃ በገቡት አርሶ አደሮች መካከል የሚታይ ልዩነት እንዳይኖር ህወሓት አጥብቆ ይቆጣጠር እንደነበር የኋላ ታሪኩ ይነግረናል። ሆኖም አሁን ያ ዘመን አልፎአል። ያ ህግም የኦሪት ህግ ሆኖአል። ምክንያቱ ደግሞ ዛሬ ግለሰብን ‹‹ማምለክ›› የህወሓት መለያ በመሆኑ ነው።

መነሻ ሁለት

‹‹ህወሓት››ን የመሰለ አክራሪ ብሔርተኛ እና ኮሚኒስት ድርጅት ውስጣዊ አደጋ ሲገጥመው የቆመበት የፖለቲካ ባህልም ሆነ መተዳደሪያ ደንብ መናዱ ከሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ተሞክሮ ስንነሳ የሚጠበቅ ነው። ልዩነቱ የናዳው ጉዳት ላይ ነው፡፡ ከዚህ አኳያም በ93ቱ ክፍፍል ህወሓት በአደገኛ ሁኔታ የቆሰለ (የተጎዳ) ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ወደ አንድ ሰው መዳፍ ጓዙን ጠቅልሎ የገባው ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ነውና። ህወሓትን ለተከታተለም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም እንዲሁ ‹‹ያ አንድ ሰው›› መሆናቸው የሚጠበቅ ነው።

የማይካደው ነገር በ1981 ዓ.ም አቶ መለስ ዜናዊ የድርጅቱ ሊቀመንበር ተደርገው የተመረጡት ከህወሓትም ሆነ ከኢህአዴግ የአመራር አባላት በርዕዮት አለም ትንተና የተሻሉ እና የተራቀቁ በመሆናቸው ነው፡፡ በአናቱም የብልህነትን ፀጋ ተላብሰዋል፡፡ ከአለፉት ስርዓት እና ከኒኮሎ ማኪያቬሊም የገነጠሏቸውን ‹‹ገፆች›› በማሻሻል የራሳቸው ማድረግ ችለዋል። ይህ በወንበሩ ዙሪያ ሊያደፍጡ ይችሉ የነበሩትን ‹‹እሾሆች›› ለመንቀል ጠቃሚ ቢሆንም-ጉዳትም አለው፡፡ በተለይ ‹‹ተተኪ›› እንዳይኖር ከማድረግ አኳያ ማለቴ ነው፡፡ ለምሳሌ ‹‹አጼ ኃይለሥላሴ ‹‹ፀሐዩ ንጉስ›› በሚል መወደስ ወደ መለኮታዊነት ለመቀየር ሩብ ሲቀራቸው ነው ድንገት ‹‹የምርጥ መኮንኖች›› የወታደር ‹‹ጫማ›› የደረሰባቸው፡፡ አፄው ‹‹ፀሐዩ ንጉስ›› ሲባሉ ሊመሰጠር የተፈለገው ግልፅ ነው፡፡ ፀሐይ ለአለም ብቸኛዋ የብርሃን ምንጭ እንደሆነችው ሁሉ አፄውም የኢትዮጵያ መተኪያ የሌላቸው እና ተፎካካሪ የማይገጥማቸው የብርሃን ምንጭ ናቸው የሚል የግለሰብ አምልኮ ጣሪያን ማመልከት ነው፡፡

በእርግጥ አፄው ‹‹ፀሐዩ…›› ይባሉ ዘንድ ዙሪያቸው በ‹‹ከዋክብት›› እንዳይከበብ ከሀገርኛው የፖለቲካ ባህል እና ከማኪያቬሊ ስልት ተደባልቆ በተቀመረ ‹‹ፎርሙላ›› የቻሉትን ያህል ጥረዋል። ለዚህም ነው ከጣሊያን መባረር በኋላ መንግስታቸውን፣ ከአርበኛ ይልቅ ለጠላት ባደሩ ግለሰቦች ያዋቀሩት። የዚህ ምክንያት ደግሞ ህዝቡ ‹‹ንጉሱ ከሌሉ እነዚህ ባንዳዎች ሀገሪቱን መልሰው ለጣሊያን አሳልፈው ይሰጧታል›› በሚል ስጋት መዋጡ አይቀሬ በመሆኑ ለንጉሱ ስልጣን ቀናኢ ይሆናል የሚል ነው። ማኪያቬሊም ይህን ይመክራል ‹‹ችግር (ጉድለት) ያለበትን እየመረጥክ ሹም››፤ አፄውም መለስም ይስማሙበታል። (በነገራችን ላይ አጼ ኃይለሥላሴም የኒኮሎ ማኪያቬሊ ቀንደኛ ተከታይ ነበሩ) እናም አፄው ብቸኛው ፀሐይ ይሆኑ ዘንድ ብዙ ፀሐዮችን አጨለሙ። የዚህ ውጤትም ነው የ66ቱ አብዮት ፈንድቶ ‹‹ደርግ›› ፊቱን ወደ ቤተ-መንግስቱ በመለሰ ጊዜ ከልዑላኑም ከሹመኞቹም አማራጭ ‹‹ፀሀይ›› እንዳይገኝ ያደረገው፡፡ በወቅቱ ደርግ አማራጭ በማጣቱ ደራሲ አዲስ አለማየሁን ሳይቀር ‹‹ጠቅላይሚንስትር›› ይሆኑ ዘንድ እስከመጠየቅ የደረሰበት ሁኔታ ነበር፡፡…ይህ ከሆነ ከ38 ዓመት በኋላ ደግሞ ‹‹መለስ ከሌለ ሀገሪቱ ትበታተናለች›› የሚል ስጋት በእያንዳንዳችን ልቦና እንዲያድር መደረጉን ተከትሎ ‹‹የሚተካቸው ሰው›› አሳሳቢ ሆኗል። በእርግጥ በተለይም በግንባሩ የታችኛው ካድሬ ውስጥ ያለው ሁኔታ ፈረንሳይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ከገጠማት ችግር ጋር የሚመሳሰል ነው። በወቅቱ የ1789 ዓ.ም. አብዮትን ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጣው Robespierre (ሮብስፒር) እ.ኤ.አ በ1794 ሲገደል፣ ጦረኛው Napoleon Bonaparte ስልጣን ላይ ወጣ። ናፖሊዮንም የፈረንሳይ አጎራባች ሀገራትን በመውረሩ በእንግሊዝ መሪነት የተባበሩት ሀገራት አሸንፈውና ከስልጣን አውርደው በኤልባ ደሴት ባሰሩት ጊዜም ሆነ ህይወቱ ካለፈ በኋላ በርካታ ፈረንሳዊያን ‹‹ናፖሊዮን አይሞትም!›› በሚል ተስፋ ተመልሶ እንደሚመጣ ይጠብቁ ነበር።

በኢህአዴግ ካድሬ ውስጥ ያለውም አስተሳሰብ የዚህ ግልባጭ ይመስላል፡ ፡ ‹‹መለስ አይሞትም!›› እናም ከዚህ አኳያ አንዳች ነገር ቢፈጠር ከአመራሩ ውጭ ያለው ካድሬ ለመቀበል የተዘጋጀ አይመስልም። ይህ ደግሞ ሌላ የዶግ አምድ ሊፈጥር መቻሉ አያጠራጥርም፡፡ (ለዚህም ነው ሁለቱም ተወራራሽ የአገዛዝ ባህሪያት አላቸው እያልኩ ያለሁት)

ሁለቱም ከፊታቸው ሊቆም የሚችል ‹‹ተገዳዳሪ›› በተነሳ ጊዜ በአደባባይ እየተቹ ወይም እያስተቹ ያሸማቅቁታል፡ ፡ አንገቱን እንዲሰብር ያደርጉታል። ለምሳሌ እውቁ የማራቶን ጀግና አበበ ቢቂላ የዚህ አይነቱ ፖለቲካ ሰለባ ነው፡፡ አቤ በሁለት ኦሎምፒክ ማሸነፉን ተከትሎ አለም አቀፍ ዝናን አገኘ። ይህን ጊዜም የምዕራብ ሀገራት ሚዲያ ኢትዮጵያን ሲያነሱ ‹‹የአፄ ኃይለሥላሴ ሀገር…›› የሚሉበትን ተቀጽላ ‹‹የአበበ ቢቂላ ሀገር…›› በሚለው ቀየሩት። በሁኔታው የተከፉት ንጉሱም ሌላ ‹‹ፀሐይ›› እየወጣ እንደሆነ አልተሰወራቸውም፡፡ ስለዚህም አትሌቱን በአደባባይ (በሚዲያ) መተቸቱን አጀንዳ አደረጉት፡፡ እናም ከዕለታት በአንዱ ቀን ‹‹…እጅግም መታበይ ደግ አይደለም። የዚህ ሁሉ ፈቃጅ እግዚአብሔር መሆኑን አስታውስ›› አሉና አጣጣሉት። …በአንድ ወቅት ታጋይ አርከበ እቁባይ የአዲስ አበባ ከንቲባ ነበሩ። በዘመነ ከንቲባነታቸውም ከተማዋን ካንቀላፋችበት ‹‹የሚቀሰቅስ›› የሚመስል ነገር ለማድረግ ሞከሩ። በዚህም የከተማው ዕድገት በሚያሳስበው ነዋሪ ዘንድ የአርከበ ስም ተደጋግሞ ይነሳ ጀመር። ይህ ከአቶ መለስ የሚሰወር አይደለም። ከእነዚህም ‹‹የአርከበ መብቂያ›› ወራት በአንደኛው ቀን አቶ አርከበ የኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ለመቀስቀስ በአርአያነት ራሳቸው ተመረመሩ። ተመርምረው ሲያበቁም ደማቸው ለናሙና ሲወሰድ የሚያሳይ ምስል በትልቅ ቢልቦርድ ተሰርቶ በከተማው እምብርት እንዲሰቀል አደረጉ። ይህ በሆነ ማግስትም የአርከበን ምስል የያዘው ግዙፉ ቢልቦርድ ‹‹መኪና ገጨው›› ተብሎ ወደቀ፡ ፡ ከወደቀም በኋላ እንደፈረሰው የሌኒን ሀውልት ከቦታው ተነስቶ ተወረወረ። ይህ ብቻም አይደለም፣ ራሳቸው አቶ መለስ ምርመራ ማድረጋቸውን አስመልክቶ ከጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹ተመርምሬአለሁ። ነገር ግን ለገበያ አላቀረብኩትም›› አሉና በዘወርዋራ ለአቶ አርከበ ‹‹ልታይ ልታይ ማለት ደግ አይደለም›› የሚል መልዕክት አስተላለፉ።

ሌላ ተመሳስሎ ልጥቀስ። አፄው በበርካታ ቦታዎች ስልጣን የሚሰጡት (ከባንዳ በተጨማሪም) በጨካኝነታቸው እና በስግብግብነታቸው ለታወቁ መኳንንቶች እንደሆነ ይነገራል። ምክንያታቸው ደግሞ እነዚህ መኳንንቶች በጨካኝ አስተዳደራቸው ህዝቡን ያስለቅሳሉ፣ ያማርራሉ፡፡ ይህ አካሄድ በመጨረሻ ጉዳዩ ወደ እሳቸው ሲደርስ ትንሽ መፍትሄ ለመስጠት እና መጠነኛ ማስተካከያ ለማድረግ እንዲያመቻቸው ነው። ይህን ጊዜም ህዝቡ ‹‹ንጉሡ እኮ ሩህሩህ እና ቅን አባት ናቸው። ጨካኞቹ መኳንንቶቹ ናቸው›› ሲል ቁጣውን ከስርአቱ ወደ አስፈፃሚው ያወርዳል። እንዲሁም ከንጉሱ ውጭ አማራጭ እንደሌለው ያስባል፡፡ የንጉሡም ፍላጐት ይህ ነው፡፡ ምህረት እና መልካም አስተዳደር የሚፈልቀው ከእኔ ብቻ ነው የማለት። የአቶ መለስ የአለፉት የአስራ አንድ ዓመታት ጉዞም ይህንኑ ነው የሚተርክልን፡፡

ሌላ አይደለም፡፡ ይህ አይነቱን ስልት አምባገነን ገዥዎች ብቻ ሳይሆኑ ‹‹ሆሊውድ››ም ይጠቀምበታል። ሆሊውድ በሚያዘጋጃቸው በርካታ ፊልሞች ላይ የመሪ ገፀ-ባህሪዋን ቁንጅና ለማጉላት በመልከ ጥፉ አክተሮች አጅቦ ያሳየናል። አይኖች ሁሉ፣ ጆሮዎች ሁሉ ወደ ዋናዋ አክትር እንዲያተኩር፡፡ ይህ ቴክኒክ ከፊልም ወደ ፖለቲካ ሲገለበጥ ደግሞ ተቀባይነት የሌላቸው እና የአቅም ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ወደ ስልጣን እንዲወጡ የሚደረግበት ስልት ሆኖ እናገኘዋለን። የጠቅላይ ሚኒስትሩን ‹‹ፀሐይነት›› ይበልጥ ለማድመቅ ማለት ነው፡፡ በአናቱም ባለስልጣናቶቻቸው ከኢትዮጵያውያን ስነ ልቦና በተቃራኒ እንዲቆሙ የሚያደርጉ ጨዋታዎችን አብዝተን እንድንመለከት የተደረግንበት ጊዜ አንድና ሁለት ብቻ ተብሎ የሚቆጠር አይደለም። ለምሳሌ ለተደጋጋሚ ጊዜ ባለስልጣኖች የተሳተፉበት የእግር ኳስ ውድድር ተደርጓል። በውድድሩ ላይ ግን አንድም ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አልተሳተፉም። ይህ የሆነው ከፀጥታ ጉዳይ እና ካለመመቸት ጋር ተያይዞ ብቻ አይደለም። ሆን ተብሎ ነው። አቶ መለስ የኢትዮጵያውያንን ስነ ልቦና ያውቁታል። ሀበሻ ሱሪውን አውልቆ ኳስ የሚራግጥ ባለስልጣን ላይ እምነት ጥሎ እንደመሪ እንደማይከተልም ጠንቅቀው ያውቁታል። ለዚህም ነው እነ አቶ አባዱላ ገመዳ እና ሌሎች ባለስልጣናቶች እንዲያ እንዲሆኑ የሚደረገው። ከዚህ በተጨማሪም የስልጣን መሠረታቸው እንዳይናጋ ከብቃት ይልቅ ታማኝነትን እንደ መስፈሪያ ይጠቀሙበታል። ለምሳሌ አጼው ‹‹ጋብቻ››ን ዋና የፖለቲካ መጠበቂያ ያደርጉት ነበር። ይህ አካሄድም ከንጉሡ የዘር ማንዘር ጋር የተጋባ ባለስልጣን ሁሉ ከ‹‹አማቹ›› ውጪ የሚቀርበው ስለማይኖር የንጉሱን ስልጣን መጠበቅ የህልውና ጉዳይ ይሆንበታል። የ‹‹ጋብቻ ፖለቲካ›› አቶ መለስ ጋ ሲደርስ ደግሞ ‹‹በአውራጃ ትስስር›› እና ‹‹በታማኝነት›› ተለውጦ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ አይነት የፖለቲካ ጨዋታ ለዓመታት ታሽቶ ያለፈው የአቶ መለስ መንግስት ከአቶ መለስ ጤንነት ጋር በተያየዘ አደጋ ተጋረጦበታል፡፡ የሰሞኑ ‹‹አራት ኪሎ›› ባልተለመደ የፖለቲካ ትኩሳት መጋልም የዚህ ምክንያት ነው፡ ፡ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጥርጣሬ ሲታይ የነበረው የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹‹የመተካካት ፖሊስ››ም ከጊዜው በፊት የደረሰ ይመስላል፡፡ በጠና መታመማቸውን ተከትሎ ማለቴ ነው፡፡ በእርግጥ ሀገሪቱ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የታነፀች ብትሆን ኖሮ በእንዲህ አይነት ጊዜ ‹‹ወንበሩን›› ለመያዝ በሚፈልጉ ተፎካካሪዎች መሀከል ውጥረት አይፈጠርም ነበር፡፡ ምክንያቱም ጠቅላይ ሚንስትሩ ህይወታቸው ቢያልፍ ወይም ከባድ የጤና መታወክ

ቢገጥማቸው የሚተካቸው ሰው ማን እንደሆነ አስቀድሞውን ‹‹በሚተገበር›› ህግ በግልፅ ተደንግጓል፡፡ የኢትዮጵያ ግን ከዚህ ይለያል፡፡ ጉዳዩን ይበልጥ ግልፅ ስናደርገው ከአገልግሎት ዘመናቸው በፊት ጠቅላይ ሚንስትሩ በድንገተኛ ሁኔታ ከስልጣን ቢነሱ እሳቸውን ለመተካት የህግ ድጋፍ ያላቸው ‹‹የምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ሹመት›› በማይተገበር ህግ የታነፀ የፖለቲካ ጫወታ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እናም የወንበሩ ይገባኛል ጥያቄ ከሀገሪቱ ህግ ይልቅ የፖለቲካ ጉልበት በማሰባሰብ ወደ ሚደረግ ‹‹ስልጣን የመነጣጠቅ ትግል›› ያመዝናል ማለት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ፉክክሩም ሄዶ ሄዶ አንድ አሸናፊ ሊያወጣ ስለማይችል ‹‹የስልጣን ክፍተት›› (Power Vacuum) መፍጠሩ አይቀርም፡፡ እንዲሁም ከአቶ መለስ ዜናዊ ‹‹የአንድ ሰው አስተዳደር›› ዝቅ ስንል ፓርቲያቸው ከውስጡ ለመነጨ አደጋ ተጋልጦ እናገኘዋለን። ምክንያቱም የተወሰኑ ኢህአዴግ አመራር አባላት ግንባሩ አሁን ባለበት ሁኔታ ደስተኛ አይደሉምና። ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ሰው የነገሩኝ በቀጣዮቹ ወራት ድርጅቱ የመሰንጠቅ አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በቢሮአቸው ያለመገኘት ጋር ተጋምዶ በፖለቲካው ላይ አዲስ ምዕራፍ ሊከፈት የሚችልበት ዕድል መፍጠሩ አይቀሬ ነው። ከዚህ አንፃርም ጥቂት የቢሆን ስሌቶችን (Scenarios) ብናይ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡

የግንባሩ አባል ፓርቲዎች ፍላጎት

ግንባሩ የአራት ብሄርን ማዕከል ያደረጉ ፓርቲዎች ጥምረት ከመሆኑ አኳያ ከላይ ያየናቸው አደጋዎች በቀረቡት ጊዜ ነጥሮ የሚወጣው በግርግሩ የተናጥል ፓርቲን ተጠቃሚ የማድረግ ፍላጎት ነው። በተለይ ደግሞ አብላጫ ቁጥር ያለውን ብሔር እንወክላለን የሚሉት ኦህዴድ እና ብአዴን በዚህ አይነቱ ‹‹ሽሚያ›› ዕድሜ ጠገብ ቅራኔዎች እና መገፋቶችን እያነሳሱ ዋነኞቹ ተሳታፊዎች ሆነው በአዲስ ‹‹አቁማዳ›› ብቅ ሊሉ ይችላሉ። እዚህ ጋር ምንአልባት የህወሓት ነባር ሰዎች ከሚጠብቃቸው ፉክክር ለማሸነፍ አዲስ ነገር ሊያመጡ ይችላል። እስከዛሬ የነበረውን የብሔር ኮታ ስልጣን የመከፋፈል አሰራርን ‹‹ብቃትን መሀከል ያደረገ›› በሚል ቀይረው ማለቴ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ዞሮ ዞሮ በሚኒስትር ማዕረግ በተመደቡበት ቦታ የተሻለ እየሰሩ ነው ተብሎ የሚታሰቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የህወሓት ቀጣዩ ‹‹ጆከር›› ሊሆኑ ይችላሉ። ረጅም ጊዜ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የሰሩት ብርሃነ ክርስቶስም ሌላኛው ‹‹ጆከር›› ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚህ ሌላ ደግሞ በቅራኔ ወይም ቁስል በመነካካት ላይ የተመሰረተ ጨዋታን ከጀመሩ አቶ መለስና ጓደኞቻቸው ያስተዋወቁት የብሄር ፖለቲካን በከፍተኛ ግፊት ያጠናክረዋል። የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው ሌሎች ብሄሮችን ጨቁኗል የሚለው የፖለቲካው አተናተን፣ ይህም በተለየ መልኩ የተነገራቸው በራሱ በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ልሂቃን “በታሪክ የተፈፀሙ” የሚሏቸውን ጭቆናዎች ለማወራረድ ‹‹አሁን ጊዜው የኦሮሞ ነው›› የሚል ባንዲራ ይዘው ወደ ስልጣን መተጋገሉ ሊመጡ ይችላሉ።

እንዲሁም ምንም እንኳን የቀድሞ ጥንካሬው የከዳው ቢሆንም ደርግን ለመጣል በተደረገው ትግል ‹‹የአንበሳውን ድርሻ›› የሚይዘው ህወሓት ‹‹የአቶ መለስ ብቸኛ ወራሽ›› ለመሆን የሚያደርገው ትግልም በቀላል የሚታይ ላይሆን ይችላል።

ከዚህ ባለፈ ብዙም የ‹‹ፖለቲካ ጉልበት›› የሌለው ወይም የ‹‹ፖለቲካውን ሻጥር›› ከህወሓት እና ብአዴን እኩል ሊያዳውረው የማይችለው ‹‹ደኢህዴን››፣ መሪዎቹን እና ወሳኝ ካድሬዎቹን ከጎናቸው ለማሰለፍ ሶስቱም ድርጅቶች ከሚያደርጉት ትንቅንቅ ባለፈ ‹‹በራሱ ለመቆም›› የሚያደርገው ትግል ላይኖር ይችላል። ደኢህዴን በዋናነት በራሱ ሊቆም የማይችልበት ዋናው ምክንያት ፓርቲው በትግሉ ዘመን ያልነበረ መሆኑና፤ አብዛኛው የፓርቲው አመራር በፓርቲው ካድሬ ድጋፍ ሳይሆን በአቶ መለስ ምርጫ ወደ ላይ የወጣ በመሆኑ ነው። ስለዚህም ከአቶ መለስ ‹‹አደገኛ የጤና መታወክ ጀርባ›› የሚኖረው የግንባሩ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች ደጋግመው የሚነግሩን ደግሞ በግንባር ደረጃ በተለያዩ ፓርቲዎች በተመሰረተ ድርጅት ውስጥ የዚህ አይነቱ ውጥረት ፈንቅሎ ሲወጣ ድርጅቱ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ሙሉ በሙሉ ሊከፋፍል ወይም ሊፈርስ የሚችልበትን ዕድል እንደሚያሰፋው ነው።

የሸዋ ፖለቲካ

አፄ ምንሊክ ከሞቱ በኋላ ስልጣናቸውን ወደራሳቸው ‹‹ሰዎች›› ለመሳብ በሹማምንቱ (በእቴጌ ጣይቱ በንጉስ ሚካኤል አሊ እና በእነ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ) መካከል የሶስትዮሽ ፉክክር እንደነበር ያለፈው ዘመን ትርክት ይናገራል፡፡ የታሪክ ተመራማሪዎች እንዲህ አይነቱን በጥሎ ማለፍ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ጨዋታ በተለምዶ ‹‹የሸዋ ፖለቲካ›› ይሉታል።

በዚህ ዘመንም በስርዓቱ ላይ ‹‹የሸዋ ፖለቲካ›› መከሰቱ አይቀሬ እንደሆነ የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይም አብዛኛው ሚኒስትሮችን፣ እንዲሁም ወሳኝ የብአዴን እና የኦህዴድ ካድሬዎችን ከጎናቸው ሊያሰልፉ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡት አቶ በረከት ስምኦን ከተገዳዳሪዎቹ አንዱ ሊሆኑ ይችላሉ። በረከት ስምዖን (በወሬ ደረጃ እየተነገረ ያለውን) ‹‹ዶ/ር ቴዎድሮስ አደህኖም አቶ መለስን ተክተው እየሰሩ ነው›› የሚለውን ንግርት ላይቀበሉት ይችላሉ። ዶ/ሩ ለግንባሩ የድል አጥቢያ አርበኛ መሆናቸውን ‹‹በማደማመቅ›› በአናቱም የራሳቸውን የትግል ታሪክ በማግነን ‹‹የመስራች ታጋይነት መብቴን አስከብራለሁ›› ሊሉ ይችላሉ፡፡ (ዶ/ሩ የአቶ መለስ ተተኪ እንደማይሆኑ አንድ ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ ሰው ነግረውኛል። በዚህ ወቅትም ብዙ ስራዎችን እየሰሩ ያሉት ዶ/ሩ ሳይሆኑ ከመንግሥት ስራ በጡረታ የተገለሉት አቶ አዲሱ ለገሠ እንደሆኑ ይነገራል)

በተለምዶ ‹‹የእነ ተወልደ ቡድን›› የሚባለውም (ከህወሓት በ1993 ዓ.ም. የወጣው አመራር) በዚሁ አጋጣሚ ‹‹አላዛር›› ለመሆን የሚሞክርበት እድል አለ። ይህ ከሁለት አንፃር ነው የሚታየው። የመጀመሪያው በራሳቸው በአቶ መለስ ፍላጐት ‹‹ህወሓትን ለማዳን›› በሚል ጥቅሻ የቀድሞውን ቅያሜ ‹‹ይቅር ለፖለቲካ›› በማለት ህወሓትን ለማዳን በጋራ ሊሰለፉ መቻላቸው ሲሆን፤ ሁለተኛው ግን ቡድኑ በተናጠል በተለይም ስዬ አብርሃ፣ ገብሩ አስራአት፣ አረጋሽ አዳነ… ከህወሓት ከወጡ በኋላ ከተቃዋሚዎች ጋር አብረው መስራታቸው የተሻለ የተደማጭነት እድል ሊፈጥርላቸው የመቻሉን አጋጣሚ በማስላት ዕድላቸውን መሞከራቸው የሚጠበቅ ነው። ምንአልባት ይህ ቡድን ነባር ታጋዮችን እና ከኢህአዴግ ጋር ባለመግባባት በጡረታ የተገለሉትን አቶ ተፈራ ዋልዋን ሊያካትት ከቻለም የብአዴንን ድጋፍ ከአቶ በረከት ሊነጥቅ የሚችልበትተጨማሪ የዕድል ቁጥር አለው።

አባይ ፀሐዬ፣ ስዩም መስፍን፣ አርከበ ዕቁባይን የመሳሰሉ አንጋፋ አመራሮችም ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ‹‹ልሞክረው›› ሊሉ የሚችሉበት አጋጣሚም ሌላኛው የጫረታው ተሳታፊ ያደርጋቸዋል። እነዚህ የቀድሞ የህወሓት ነፋስ-አባቶች በ1997ቱ ምርጫ ቅንጅትን እናሳንስበታለን በሚል ሊጠቀሙበት የሞከሩትን ‹‹ትግራይን ከሌሎች ጥቃት የማዳን›› መሰል መፈክሮችን ተሸክመው መሰባሰብ ከጀመሩ፣ ወንበሩን ለመያዝ የሚደረገውን ፍትጊያ እጅግ አደገኛ መዘዝ ወደሚያስከትል ‹‹ጫወታ›› ሊቀይሩት የሚችሉበት ዕድል ይሰፋል።

እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱት (ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ህወሓት እና ግለሰቦቹ) ‹‹በሸዋ ፖለቲካ›› ስልት ሙሉ በሙሉ ወደ ፉክክር ከገቡ በሀገሪቱ ያለመረጋጋት እና የእርስ በእርስ ግጭት ሊከሰት የሚችልበትን ቀዳዳ ያሰፋዋል። ይህ ትንተና ነው፡፡ ሆኖም አደጋውን ለመከላከል ሁለት አማራጭ የአለ ይመስለኛል።

አማራጭ አንድ

ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ባሉበት ደረጃ ለሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ እስረኞች እና ስደተኞች ምህረት አድርገው የታሰሩትን መፍታት፣ የተሰደዱትም ወደሃገራቸው እንዲገቡ መፍቀድ፡፡ እናም አንድም ጊዜ ከወቀሳ አምልጦ የማያውቀውን ምርጫ ቦርድ በትነው በቅንነት እና በታማኝነት በሚሰሩ ሰዎች እንደአዲስ ማወቀር። የፓርላማውንም የስራ ዘመን ክረምቱን እንዳይዘጋ በማድረግ ለዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ እንዳይጎለብት ‹‹አፋኝ›› የሆኑትን (የፀረ-ሽብር፣ የመያድ፣ የፕሬስ…) አዋጆች እና ሕጎች እንዲሽሩ በማድረግ፣ የምርጫውን ጊዜ ሳይጠብቁ ሁሉንም ወገን የሚያሳምን ምርጫ እንዲደረግ ማመቻቸት አደጋውን በቀላሉ ከማሰወገዱም አልፎ ገዥውም ተቃዋሚውም፣ ሌላውም ኢትዮጵያዊ የሚወዳትን ሀገር ወደአዲስ የታሪክ ምዕራፍ ያሸጋግራል። ነገር ግን በአቶ መለስ ቦታ ከላይ የጠቀስኳቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ወይም ዶ/ር ቴውድሮስ አድህኖም ወደ ስልጣን እንዲመጡ ከተደረገ በአሮጌ አቁማዳ አዲስ ወይን ከመተካት ውጭ ለውጥ የለውም፡፡ እንዲያውም በግልባጩ ህዝባዊ አመፅ ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡

ምንም እንኳ አቶ መለስ ከወራት በፊት የአረብ ዓለም አብዮትን አስመልክተው ለ“Pan-African magazine” በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ “Ethiopia and much of the Sub-Sharan Africa already had its own African spring back in the 1980’s and the Arabs are latecomers to the game” (ኢትዮጵያ እና አብዛኛው ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ጣጣቸውን የጨረሱት አስቀድመው በ1980ዎቹ ነው። አረቦቹ ግን ለጨዋታው አርፋጆች ናቸው) ሲሉ እኛ ለአብዮት እንግዳ አይደለንም፡ ፡ ከእነርሱ እንቀድማለን የሚል አንድምታ ባለው መልኩ የነገሩት፡፡ ለመጽሔቱ የነገሩት መተማመኛ የሚገለበጥበት እድል እንደሚኖር የተንታኞች ግምት አለ። ምክንያቱ ደግሞ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጐች ከቀን ወደቀን ቁጥራቸው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑ ነው። እናም እንዲህ አይነት ኩነቶችን ተከትለው የሚመጡ የመንግስት የመዳከም ምክንያቶች ‹‹ለውጥ ፈላጊውን›› የህብረተሰብ ክፍል ወደአደባባይ መግፋታቸው አይቀሬ ነው።

አማራጭ ሁለት-የታንታዊ መንገድ

የግብፅ አብዮትን ተከትሎ ስልጣን በወታደራዊው ጂንታ እንዲገባ ካደረጉት ውስጥ ዋነኛ ሠው ናቸው-Field Marshal Mohamed Hussein Tantawi (ፊልድ ማርሻል መሀመድ ሁሴን ታንታዊ)፡፡ ታንታዊ ግብፃውያን በታህሪር አደባባይ መሰባሰባቸውን ተከትሎ ከሌሎች 18 ወታደራዊ ኦፊሰሮች ጋር በመሆን የወታደራዊውን ከፍተኛ ምክር ቤት (SCAF) መስርተው፤ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክን ለፍርድ በማቅረብ (በፖለቲከኞቹ አነጋገር ‹‹ለአብዮቱ በመሰዋት››) ግብፅን ያረጋጉበት ጥበብ ነው-‹‹የታንታዊ መንገድ››

ምንአልባት ከላይ ባየነው ድንገቴ ፉክክር የተነሳ ሀገሪቱ በፖለቲካ ውጥረት ወደ አልታሰበ ግጭት ብትገባ የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል ሰራዊትም ከታንታዊ መፃሀፍ ‹‹አንድ ገፅ›› ሊገነጥል ከቻለ ለሀገሪቱ መፃኢ ዕድል የተሻለ መደላድል ሊፈጥር ይችላል። በግብፅ የመጣው ለውጥ (ምንም እንኳን አሁንም ወታደራዊው ሀይል በተወሰነ መልኩ ከመጋረጃው ጀርባ ያደፈጠበት ሁኔታ ቢኖርም) ከቀድሞ መንግስት አስተዳደር በእጅጉ የተሻለ ነው። የፖለቲካ ተንታኞች አሁን ያለውን አይነት የታንታዊ መንግስት ጥቂት የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን መልሶ ሌሎቹን መሰረታዊ የፖለቲካና የሲቪል መብቶችን የሚጨፈልቅን መሪ ‹‹Benevolent Dictator›› (ደግ አምባገነን) ሲሉ ይጠሩታል፡፡

ከዚህ ባለፈም የካውንስሉ አባል የሆኑት ሜጀር ጄኔራል መሀመድ ሰዒድ አል-አሰር ባለፈው ሳምንት ለታተመው ‹‹Time›› መጽሔት እሳቸውና ጓደኞቻቸው ለአብዮቱ ስላደረጉት አስተዋጾ ሲናገሩ “We have done the best we can for our country. We saved the revolution” (ለሀገራችን የቻልነውን ያህል የተሻለ አድርገናል። አብዮቱንም ታድገነዋል) ምንአልባት ይሄ ገፅ ከነታንታዊ በአማርኛ ቢገነጠል ሀገር ሊታደግ ይችል ይሆናል፡፡

ለስርዓት ለውጥ ዝግጅት ወሳኝ ምዕራፍ ተከፍቷል

Saturday, July 14th, 2012

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት የተሰጠ መግለጫ

ሐምሌ 6 ቀን 2004 ዓ.ም

[በPDF ለማንብብ እዚህ ላይ ይጫኑ]

ዘረኛውና ጨቋኙ የህወሓት አገዛዝ በሃገራችንና በህዝባችን ላይ እየፈጸማቸው ያለው ህዝብ የማሰቃየት፤ የማሰር፤ የመግደል፤ ከቀየ የማፈናቀል፤ ጋዜጠኞችን ማሰር፤ የመናገር፤ የመሰብሰብና የመቃወም ነጻነትን ማፈን፤ ታሪካዊ የሃይማኖት ተቋማትን ማፈራረስ፤ የስርዓቱን ካድሬዎች በሃይማኖት አመራር ላይ መመደብ፤ ህዝቡን በሀይማኖትና በዘር በማከፋፈል ማጋጨት፤ እህቶቻችንን በአረብ ሀገሮች ለባርነት መሸጥ፤ ሌሎችም እጅግ በርካታ በደሎች የቀጠሉ ሲሆን፥ በቅርቡ ደግሞ የአምባገነኑ ስርአት ቁንጮ የአቶ መለስ ዜናዊን የጤና መታወክ ተከትሎ እየደረሱን ያሉ መረጃዎች የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወዴት አቅጣጫ እየተጓዘ እንደሆነ ግልጽ አለመሆኑን እያለመለከቱን ነው። ከዚህም አንጻር ለሀገራችን ይህ ወቅት በአንድ በኩል እጅግ ፈታኝ ሲሆን፥ በሌላ በኩል ደግሞ መልካም አጋጣሚዎች ሊፈጥር ይችላል ብለን እናምናለን።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ም/ቤትም ከሚደርሱት መረጃዎች በመነሳትና የሁኔታዎችን አሳሳቢነት በመገንዘብ፤ ከዚያም በላይ የሽግግር ም/ቤቱ የተመሰረተበትን ሰላማዊና የኢትዮጵያን አንድነትንና ሉአላዊነት፤ የዜጎችዋን መብት የሚያስጠብቅ የሽግግር ሂደት የማመቻቸትን ተልእኮ በተመለከተ ይህንን ወቅታዊ መግለጫ አውጥቷል።

  1. በአምባገነኑ አቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁከት ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ በመላው ሀገሪቱ አለመረጋጋት ሊከሰት እንደሚችል ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ፤
  2. በስልጣን ሽኩቻ ምክንያት ሊከሰት የሚችለው አለመረጋጋት የራሱ የሆነ አሉታዊ ወይንም አወንታዊ ውጤቶችን ሊያመጣ ስለሚችል መላው ህበረተሰብ ለውጡ ዘወትር ሲመኘው የኖረውን ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ያመጣ ዘንድ እንዲታገል፤
  3. ተቃዋሚ ሀይሎች ሁሉ በአስቸኳይ ተሰባስበንና ተመካክረን፤ ሃገራችንና ህዝባችንን የሚታደግ አማራጭ እቅድ በመንደፍ፤ ሃይላችንን አስተባብረን ሁሉን አቀፍ የሽግግር ስርአት እንዲፈጠር የሚጠበቅብንን ሀገራዊ ሀላፊነት እንድንወጣ፤
  4. የመከላከያ ሃይሉም የኢትዮጵያን ሉአላዊነትን በማስከበር ሚና ላይ በማተኮር ከህዝብ ጎን በመቆም የህዝብ ወገናዊነቱን እንዲያሳይ፤
  5. ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ሳይሆን ለራሳቸዉ የስልጣን ጥም፤ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለውጭ ሃይሎች በተገዙ ቡድኖች እጅ የሀገሪቱ ሕልውና አደጋ ላይ እንዳይወድቅና መንግስታዊ ስልጣን በጸረ-ኢትዮጵያ ሀይሎች እጅ እንዳይወድቅ ሁሉም ሀገር ወዳድ ነቅቶ እንዲጠብቅ፤
  6. ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ህዝቡን በዘርና በሃይማኖት በመከፋፈል አላስፈላጊ ወደሆነ ግጭት ለመውሰድ የሚጥሩትን አፍራሽ ሀይሎች ህዝቡ በቆራጥነት በመታገል የሀገሩን ሉአላዊነትና የህዝቡን አንድነት እንዲያስጠብቅ፤
  7. በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያን እንወክላለን የሚሉ አምባሳደሮች ለአምባገነኖች ተገዥ ከመሆን እንዲታቀቡና ከህዝቡ ጎን በመቆም የህዝብ ወገናዊነታቸውን እንዲያሳዩ፤
  8. የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ሁኔታዎች ሳይባባሱ የተፈጠረውን የሽግግር ሂደት በመደገፍ  ድርሻቸውን እንዲወጡ፤
  9. በስማቸው የሚነገደው ነገር ግን የስርአቱ ተጠቃሚ ያልሆኑት አብዛኛው የትግራይ ህዝብ በዚሁ አጋጣሚ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ጎን በመቆም የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥቅም የሚያስከብር ስርዓት እንዲመጣ የትግል አጋርነታቸውን በተግባር እንዲያረጋግጡ፤

የሽግግር ም/ቤቱ አመራር ጠቅላላው ጉባኤ በሰጠው ሃላፊነት መሰረት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መወሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች በአፋጣኝ ምክክር ለመጀመር ያስችል ዘንድ ለሁሉም ተቃዋሚ ሃይሎች የትብብር ጥሪ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ያቀርባል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አመራር

በአቶ መለስ የሚሸበሩት የአዲስ አበባ ጎዳናዎች

Wednesday, July 11th, 2012

ከመ/ር ቀለሙ ሁነኛው | ፍኖተ-ነጻነት

ዛሬ ካለው የአለማችን ተጨባጭ ሁኔታ የየትኛውም አገር መሪዎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ የሚደረገው ጥበቃ እጅግ የጠነከረ ነው፡፡ ተራ ሰው በነበሩ ጊዜ እንዳሻቸው በህዝብ መሀከል የሚንቀሳቀሱ ሁሉ የሥልጣን ማማው ላይ ሲወጡ ዙሪያገባቸው በጦር መሣሪያ ይከበባል፡ በሚያልፉባቸው መንገዶች ወፍ እንኳን ዝር አትልም፡፡ በተለይ በሚመሩት ህዝብ የሚጠሉ መሪዎች ከሆኑማ ሽርጉዱ አይጣል ነው፡፡ ጠባቂዎቻቸው መርዝ እንደበላች ውሻ ሲክለፈለጉ ይታያል፡፡ በእርግጥ በህዝባቸው ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ዴሞክራት መሪዎች እንደልብ መንቀሳቀስ ቢችሉም ለደህንነታቸውና ለአገሪቱ ክብር ሲባል ተገቢው ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡ የሚደረግላቸው ጥበቃ ግን የህዝብን የየዕለት ኑሮ የሚያስተጓጉልና በሽብር የሚንጥ አይደለም፡፡ ሕዝቡ ራሱ በነፃነት የመረጣቸው በመሆኑ የሚመሩትን ሕዝብ አይፈሩም፡፡

የሚመሩትን ሕዝብ የሚፈሩ መሪዎች ግን ዕድሜ ልካቸውን በሥጋት ይኖራሉ፡፡ ለህዝብ የመጡ ሳይሆኑ በህዝብ ላይ የወጡ አምባገነኖች ናቸው፡፡ ዜጎች አይደለም በአካል ሊያዩዋቸው
ድምፃቸውን እንኳን መስማት አይፈልጉም፡፡ በተለይም በ21ኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪካ መርገም ሆነው የተነሱት መሪዎች በሚመሩት ህዝብ ዘንድ የማይታመኑና እነሱም የሚመሩትን
ህዝብ የማያምኑ ህዝባቸውን በዴሞክራሲና በፍቅር ሳይሆን በጠብመንጃ አፈሙዝ መግዛት የሚቀናቸው ናቸው፡፡ ለዜጎች ህይወት ግድ የላቸውም፡፡ ደም በማፍሰስና በማፋሰስ ይረካሉ፡፡ የሕዝቦቻቸው መጎሳቆል ጉዳያቸው አይደለም፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ የዚህ እኩይ ዕጣ ፈንታ ተጋሪ ናት፡፡ በየዘመናቱ የተነሱት መሪዎቿ በጠብመንጃ እንጂ፣ መቼም ቢሆን በህዝብ ድምጽ ተመርጠው ሥልጣን ላይ አልወጡም፡፡ ኢትዮጵያውያን እስከ አሁን ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ አልታደልንም፡፡ ዛሬም የምዕራቡን ዓለም ዴሞክራሲ ለመቀላወጥ ተገደናል፡፡ ያለፈውም ሆነ የዛሬው ትውልድ በመሪዎቹ ላይ እንዳቄመ፣ መሪዎቹም በህዝቡ መሀከል በነፃነት ለመንቀሳቀስ እንደሰጉ እስከ የት እንደምን ዘልቅ ግራ ቢያጋባም የነፃነት መሻታችንን እውን ለማድረግ በጽናት መታገልን ይጠይቀናል፡፡

አፄ ኃይለ ሥላሴ በግማሽ ምዕተ ዓመት የንግስና ዘመናቸው ከኮሎኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ዜናዊ በተሻለ መልኩ በህዝብ መሀከል በነፃነት ይንቀሳቀሱ ነበር፡፡ ይህን ስል ንጉሱ ዴሞክራት መሪ ሆነው ሳይሆን “ሥዩመ-እግዚአብሄር” በሚል የማስፈራሪያ ንጉሱ ከእ/ር ዘንድ እንደ ዳዊትና ሰለሞን ለመሪነት የተቀቡ ተደርጎ ስለሚሰበክ ህዝቡ ካደረበት ፈሪሀ እግዚአብሄር የተነሳ ንጉሱ ሲወጡና ሲገቡ እንኳን ሊተናኮላቸው ቀና ብሎ ለማየት ይፈራል፡፡ ንጉሱም የህዝቡን የውስጥ ስሜት ስለሚያውቁ እንደልባቸው ይወጣሉ ይገባሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የ1966 አብዮት ንጉሱን ከሥልጣን
ሲያሽቀነጥራቸው ህዝቡ መሬት ትንቀጠቀጣለች በሚል ይጠባበቅ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ይሁን እንጂ እንኳንስ መሬት ልትንቀጠቀጥ ንፋስም ሽው አላለ፡፡

የዘመነ ወታደራዊው ደርግ ፊታውራሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን በስበብ አስባቡ ካስወገዱ በኋላ “ቆራጡ መሪያችን” የሚል ካባ ደርበው ብቅ አሉ፡፡ በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ፓርቲዎች (ህቡዕ ድርጅቶች) የመስመርና የአላማ ልዩነት ሳቢያ በእነ ኢህአፓ ጅምላ ጭፍጨፋ እሳቸውም በላንድሮቨር መኪና አዲስ አበባ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ በጥይት መቁሰላቸው ይታወቃል፡፡ ከዚያ በኋላ የሚደረግላቸው ጥበቃ እንደ ብረት እየጠነከረ መጣ፡፡ አገሪቱን በአንድ ፓርቲ አገዛዝ ሥር ጠቅልለውና ሥልጣናቸው እጥፍ ድርብ ሆኖ እያለ የሚመሩትን ህዝብ አጥብቀው ስለሚፈሩ የጥበቃ አጀባቸው ጠንካራ ነበር፡፡ በቤተ መንግሥት ጠባቂዎቻቸው ላይ ፍፁም እምነት ነበራቸው፡፡ ኮሎኔሉ ምንም እንኳን ጨቋኝና የለየላቸው አምባገነን ቢሆኑም በውስጣቸው የሚንቦገቦገው የኢትዮጵያዊነት ስሜትና የሀገር ፍቅር ፅናታቸው ዛሬም ቢሆን በጨቆኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ ውስጥ እንዲታወሱ አድርጓቸዋል፡፡ “እናት ሀገር ወይም ሞት” የሚለው መፈክራቸው መለያቸው ነበር፡፡ በየጊዜው በሚያደርጓቸው ረጃጅም ንግግሮች መሀከል “እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ . . .” ማለት ይቀናቸው ነበር- ኮሎኔሉ፡፡ አምባገነንነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ለነገሩ ለ17 ዓመታት ከሻዕቢያና ከህወሓት ጋር ያደረጉት ጦርነት ኤርትራን ያለማስገንጠል ትንቅንቅም እንደ ነበር አይካድም፡፡

ኢትዮጵያ ከኮሎኔል መንግስቱ እጅ ተነጥቃ ለአቶ መለስ ዜናዊ ከተቸረች ይኸው ድፍን 21 ዓመት ተቆጠረ አቶ መለስም ኮሎኔሉን በ4 ዓመታት ብልጫ እየመሩ ነው፡፡ 21 ቁጥር ማሊያ ለብሰው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ክለብ አጥቂ በመሆን ይጫወታሉ፣ ሲያሻቸውም ግብ ጠባቂ በመሆን ከመሀል ሜዳ ኳሷን አፈፍ በማድረግ ፋዎል ይፈፅማሉ፡፡ በአጠቃላይ ሀገሪቱን በራሳቸው ፖለቲካ እያተራመሷት ይገኛሉ፡፡ በ1994 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር ባደረጉት ውይይት አንድ ምሁር አቶ መለስን “ኳሷ በእግርዎ ስር ናት ሲፈልጉ ይጠልዟታል፣ ሲያሻዎትም ጎል ያገቧታል . . .” ሲል የተናገራቸው በእርግጥም እውነት ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ኢትዮጵያን እንደ ነጠላ ወረቀት የሚያጥፉና የሚዘረጉ አንድ እና አንድ እሳቸው ብቻ ናቸው ያልገባው አንድ ሰው ካለ የሃያ አንድ አመቷን ኢትዮጵያን አያውቃትም ማለት ነው፡፡

በተለይም ከምርጫ 97 በኋላ የአቶ መለስ ተክለ-ስብዕና በመላው አገሪቱ እየገዘፈ እንዲመጣ በተለያየ መጠን የህዝብ ግንኙነት ስራ በመሰራት ላይ ነው፡፡ እንደ መከለሻ ቅመም በየሥፍራው
እየተገኙ የሚያደርጉት ዲስኩርና በጥቂት የህብረተሰብ ክፍሎች አንገት ላይ በሚያጠልቁት ሜዳሊያ የራሳቸውን ሰብዕና እንዲሰቅል ታስቧል፡፡ ፎቶግራፋቸው “ብልህ መሪ፣ አስተዋይ መሪ፣ የአፍሪካ ጠበቃ፣ አባይን የደፈረ መሪ፣ ምርጥ ነውና ምረጡት . . .” በሚሉ ‹‹አማላይ›› ቃላት ተዥጎርጉሮ በየአደባባዩ መሰቀል ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ እሳቸው ግን ከህዝቡ ልብ ውስጥ ውልቅ ብለው የወጡት ዛሬ አይደለም፡፡ ለዚህም ማረጋገጫው የምርጫ 97 የህዝብ ድምጽ ነው፡፡ የዴሞክራት መሪዎች መገለጫ በየአደባባዩ የሚሰቀለው ፎቶ ግራፋቸው ሳይሆን በሕዝብ ልብ ውስጥ መስረጋቸው ነው፡፡

አቶ መለስ “99.6% ህዝብ መርጦናል” ቢሉም ሕዝብ ወድዶ እንደመረጠው መሪ በህዝብ መሀከል ለደቂቃ እንኳን ለመንቀሳቀስ አይደፍሩም፡፡ ከቤተመንግስት ወጥተው እንደ ልብ ለመንቀሳቀስ
ድፍረቱም ሆነ ሞራሉ የላቸውም፡፡ አቶ መለስ ከአገር ሲወጡም ሆነ አዲስ አበባ ውስጥ ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ይናወጣሉ፡፡ የፖሊስ ሞተሮችና መኪናዎች አዲስ አበባን በጡሩምባ ጩኽት ያተራምሷታል፡፡ የፌደራል ፖሊሶች አገር አማን ነው ብለው የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን እያዋከቡ በየሥርቻው ሲወሸቁ አሊያም ከአስፋልቱ ርቀው ፊታቸውን እንዲያዞሩ ሲያስገድዱ ይስተዋላል፡፡ ላለፉት 21 ዓመታት የአዲስ አበባ ህዝብ በተለይም ከቤተ መንግስት እስከ ቦሌ አየር መንገድ የሚንቀሳቀሱ ዜጎችና አሽከርካሪዎች ይህንን ሰላማዊ መሰል ሽብር በማስተናገድ ተሰላችተዋል፡፡

ውድ አንባቢያን ሃሳቤን የሚያጠናክሩ ገጠመኞችን ላንሳላችሁ፡፡ አንዱ ገጠመኝ የራሴ ነው፡፡ ወሩን በትክክል ባላስታውሰውም ሁኔታው የተከሰተው ከዛሬ 13 ዓመት በፊት ነው፡፡ ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ቦሌ መንገድ በሚገኘው ፊላሚንጎ ሬስቶራንት በረንዳ ላይ ሻይ ቡና እያልን ስንጫወት ድንገት አካባቢው በፖሊስ ተተራመሰ፡፡ መኪናዎችም ሆኑ እግረኛው መግቢያ እስከሚያጡ ተጯጯሁ፡፡ እኔና ጓደኞቼም የተፈጠረውን ነገር ሳናውቅ በጥፊና በእርግጫ ተብለን እግሬ አውጭኝ አልን፡፡ ነገሮች ከተረጋጉ በኋላ ስንሰማ አቶ መለስ ከውጭ ስለገቡ መሆኑን ተረዳን፡፡ ሰሞኑን አንድ በዕድሜ የገፋ ሰው እንደ እኔው የገጠማቸውን አጫወቱኝ፡፡ ቦሌ አካባቢ ቆይተው መኪናቸውን እያሽከረከሩ ወደ መስቀል አደባባይ ሲጓዙ ድንገተኛ ግርግር ይገጥማቸዋል፡፡ ፌደራል ፖሊሶችና ትራፊክ በቁጣ
ያንቧርቁባቸውና “መኪናህን ይዘህ ከአስፓልት ውጣ” ሲሉ ያዟቸዋል፡፡ ግራ ቀኙን ሲያዩ ከአስፖልት ለመውጣት የሚያስችል አማራጭ ስላልነበራቸው “ወዴት ልሂድ?” ሲሉ በመደናገጥ ይጠይቃሉ፡፡ “ስትፈልግ ገደል ግባ!” በማለት ከደነፋባቸው በኋላ ከኋላና ከፊት መኪናቸውን እየገፉ ከመስመር አውጥተው የሆነ ገደላማ ሥፍራ ላይ ከነመኪናቸው ይወሽቁቸዋል፡፡ ወዲያው ግርግሩ
እንዳለፈ እነዚሁ ፖሊሶች “አሁን መሄድ ይችላሉ” ሲሏቸው መኪናዋን ለማንቀሳቀስ ተቸገሩ፡፡ ፖሊሶቹ ከኋላ እየገፉ ረድተዋቸው አስፋልት ከወጡ በኋላ በመደመም ስሜት ውስጥ ሆነው
“ለመሆኑ ይሄ ሁሉ ማዋከብ ምን ስለተፈጠረ ነው?” በማለት ይጠይቃሉ፡፡ አንዱ ፖሊስ ወደ ጆሮአቸው ተጠግቶ “ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ከውጭ እየገቡ ስለነበር ነው” እንዳላቸው አጫወቱኝ፡፡ እውነት ነው ህዝብ የመረጠው መሪ የሚመራውን ሕዝብ አይፈራም፡፡ በህዝቡ ላይ ሙሉ እምነት ሊኖረው ይገባል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ለዚህ ክብር አልታደልንም፡፡

ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ስድስተኛ ጉባዔውን አካሄደ

Wednesday, July 11th, 2012

የኢትዮጵያዊ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ዴሞክራሲያዊ) ከሰኔ ፳፫ እስከ ሰኔ ፳፯ ፪ ሺህ ፬ ዓ. ም (June 30 to July 4, 2012) ድረስ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ አባላቱ የተሳተፉበት ስድስተኛ ጉባዔውን አካሂዶ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ።

ጉባዔው የድርጅቱን የአመራር ምክር ቤት እና የአባላት መብት አስጠባቂ ኮሚሽንን የሥራ ዘገባዎች አዳምጦ ከመረመረ በኋላ አጽድቋል። የኢትዮጵያን እና የዓለምአቀፍ ሁኔታዎችን ጉባዔው በጥልቅ ከመረመረ በኋላም፣ የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ ቡድን የግፍ አገዛዙን በአፈናና በሽብር ደግፎ ለማቆየት ከምንም ጊዜ በላይ በከፋ መልኩ በሀገሪቱ ዜጎች ላይ አሰቃቂ ግፍ እየፈጸመ እንዳለ ግንዛቤ ወስዷል። የመጻፍ፣ የመናገር፣ የመደራጀት፣ ሰላማዊ ሠልፍ የመውጣትና ሌሎች መሠረታዊ የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች የተገደቡበት፣ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ ግድያና እስራት፣ ማንገላታትና ማሰቃየት፣ ማፈናቀልና ማሰደድ የአገዛዙ የየዕለት ተግባራት የሆኑበት፣ በሙስና በተጨማለቀና ብልሹ በሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሳቢያ ዜጎች ለከፍተኛ ሥራ አጥነትና ለችጋር የተጋለጡበት፣ ገበሬው ከእርሻ መሬቱ በልማት ስም የሚፈናቀልበት፣ የሀገሪቱ ለም መሬቶች ለውጭ ከበርቴዎች የሚቸበቸቡበት፣ የሀገሪቱ ድንበር እየተቆረሰ በስጦታ መልክ ለጎረቤት ሀገር የሚሰጥበት አስከፊ ሁኔታ ላይ ሀገሪቱ መውደቋን ጉባዔው በከፍተኛ ቁጭት አስተውሏል። ጉባዔው እነዚህንና ሌሎች ተዛማጅ ሁኔታዎችን ከመረመረ በኋላ አሁን በሀገራችን ላይ የተንሰራፋው የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ የአፈናና የጭቆና አገዛዝ በፖለቲካ፤ በኤኮኖሚና በማኅበራዊ ዘርፎች በሕዝባችን ላይ ያደረሰውንና እያደረሰ ያለውን በደል በጥብቅ አውግዟል። በሚከተሉት ዓበይት ወቅታዊ ጉዳዮችም ላይ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ጉባዔው አገዛዙ በተቃዋሚ ኃይል መሪዎችና አባላት፤ በጋዜጠኞችና በንፁሃን ዜጎች ላይ በሽብርተኛነት ስም እየወሰደ ያለውን የመብት አፈና፣ እሥራትና እንግልት እያወገዘ፣ የታሠሩትን ሁሉ ለማስፈታትና የግፍ ሰንሰለቱን ለመበጠስ ትግሉን አስተባብሮና አጠንክሮ ለመታገል ወስኗል።
ከግንቦት ፱ ቀን እስከ ግንቦት ፲፪ ቀን ፪ ሺህ ፬ ዓ. ም (May 18 – May 21, 2012) ድረስ በኦታዋ ከተማ (ካናዳ) የተቃዋሚ ኃይሎች ጉባዔ ተካሂዶ ለተመሠረተው ሸንጎ ሙሉ ድጋፉን ሰጥቷል። የኅብረት ትግሉንም የበለጠ ለማጠናከር እንዲቻል አዲስ የተመረጠው የድርጅቱ አመራር አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ መመሪያ ሰጥቷል።
የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ የእስልምና ሃይማኖትን የውስጥ አስተዳደር ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጣልቃገብነት ጉባዔው እያወገዘ፤ የሃይማኖቱ ተከታዮች ለመብታቸው መከበር የሚያደርጉትን ትግል ደግፏል።
በልማት ስም ታሪካዊ ገዳማትን ለማፍረስና መናንያንን መጠጊያ ለማሳጣት እየተደረገ ያለውን ሀገር አጥፊ እርምጃ ጉባዔው አውግዟል። በተጨማሪም በስደት ላይ ያለው ሕጋዊ ሲኖዶስ በዋሽንግቶን ዲሲ ተሰብስቦ ይህንን በተመለከተ ያስተላለፈውን ውሳኔ ጉባዔው አድንቆ ሙሉ ድጋፉንም ሰጥቷል።
ኢሕአፓ ለሁለት ከተከፈለ በኋላ ኢሕአፓ (ዴሞክራሲያዊ) ድርጅቱን መልሶ ለማዋሃድ በአምስተኛው ጉባዔ ላይ አንድ አቀራራቢ አካል አቋቁሞ ሲሠራ እንደቆየ ይታወሳል፤ ይህ አቀራራቢ ኮሚቴ ያቀረበውን ዘገባ ጉባዔው ከመረመረ በኋላ አካሉ የጀመረው ሥራ እንዲቀጥል ወስኗል።
ጉባዔው የድርጅቱን የፖለቲካ ፕሮግራምና የውስጥ መተዳደሪያ ሰነዶቹን በጥልቀት ከመረመረ በኋላ አስፈላጊ ማሻሻያዎችን አድርጓል።
ጉባዔው ለሚቀጥለው የሥራ ዘመን የሚያገለግሉ የድርጅቱን የአመራር ምክር ቤት አባላትን እና የአባላት መብት አስጠባቂ ኮሚሽን አባላትን መርጧል።

በመጨረሻም ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነውን የግፍ ቀንበር አሽቀንጥሮ ለመጣል ሁሉም የተቃዋሚ ኃይሎች ያላቸውን ጥቃቅን ልዩነት ወደ ጎን በመተው የተባበረ ትግል እንዲያደርጉ ጉባዔው አጽንዖት በመስጠት ጥሪ አድርጓል። በተለይም ባለፉት አራት አሥርተ-ዓመታት በሀገራችን የተካሄዱትን የፓለቲካ ትግሎች ታሪክ ጉባዔው ከመረመረ በኋላ በተለያዩ የፓለቲካ ድርጅቶችና ኃይሎች ውስጥ የተፈጠረውን የፓለቲካ ልዩነት በአግባቡ ለመያዝ አለመቻሉ ሀገራችንን ለመታደግ በሚደረገው የጋራ የፓለቲካ ትግል ደንቃራ መሆኑንና ለአምባገነኖች መፈራረቅ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረ ጉባዔው ተገንዝቧል። ሀገራችንን ለማዳን፤ ፍትህ እንዲሰፍን፤ ዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት እንዲከበሩ በአሁኑ ሰዓት ለሕዝባችን ፍትህና ዴሞክራሲ ለማምጣት ከሚታገሉ ኃይሎች ጋር ለመተባበር ጉባዔው ቃል ገብቷል። በተጨማሪም የዓላማና የፕሮግራም ተመሳሳይነትና አንድነት ካላቸው ድርጅቶች ጋር ከኅብረትም ዘለቅ ብሎ እንዲሄድ ጉባዔው ወስኖአል። የጉባዔው ተሳታፊዎችም እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩት ውሳኔዎች ለማሳካት ቃልኪዳናቸውን በማደስ ጉባዔው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ሀገራችንን ለማዳን እንተባበር!
ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘላለም ትኑር!

(Phone: 301-578-4466; Fax: 301-449-8363; Email Address: eprp-democratic@eprp-ihapa.com)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ምስረታ ጉባኤ አጭር ዘገባ

Tuesday, July 10th, 2012

ከአሰፋ ገብረማርያም ተሰማ

ከሁሉ አስቀድሜ የማክበር ሰላምታዬን ከ<እሳቱ ከተማ ወቁማሩ አውድማ>Las Vegas በትህትና አቀርባለሁ። ከሰኔ 24-26 ቀን 2004 አ.ም(July 1-3/12) በሰሜን አሜሪካ በቴክሳስ ዋና ከተማ
በዳላስ(Dallas,TX )በተደረገው<የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት ምስረታ ጉባኤ>ላይ በታዛቢነት እንድገኝ የላስ ቬጋስ ቻፕተር(Chapter-የአካባቢ ምክር ቤት) በጋበዘኝ መሰረት፤የጉባኤውን ሂደትና አፈፃፀም ሶስት ቀን ሙሉ በአንክሮና በጥሞና ተከታትያለሁ።ስለሆነም ይህን አጭር ዘገባ በትህትና አቀርባለሁ።

በጉባኤው ወቅት ያሰማሁትን ንግግርና ግጥም ከማቅረቤ በፊት፤ የምክር ቤቱን አላማና ግብ፧አወቃቀር፧ ምክር ቤቱን ማቋቋም ያስፈለገበትን ምክንያትና በምክር ቤቱ ጠንሳሽና ዋና ፀሃፊ በዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ላይ የተሰነዘረውን ቅሬታና ስሞታ በቅድሚያ በጣም በአጭሩ መግለፁ ተገቢ ይመስለኛል።የተቀረውን ከምክር ቤቱ ድረገፅ etntc.org ማግኘት ይቻላል።

የምክር ቤቱ ዋና አላማና ግብ፧ በኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት፤ በህግ የበላይነትና በዴሞክራሲ የሚያምኑ የዲያስፖራው ኢትዮጵያውያን በራስ አነሳሽነትና ፈቃደኝነት በቅድሚያ በቻፕተር ተደራጅተው፤ በዋናው የጋራ ምክር ቤታቸው አማካይነት በአገር ቤትና በውጭ አገር ከሚገኙ ተመሳሳይና ተቀራራቢ አላማና ግብ ካላቸው የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች እንዲሁም የህዝብ መገናኛ ተቋሞች ጋር በመተባበርና የሰፊው ህዝብ ትግል አጋር በመሆን ፤በስልጣን ላይ ያለውን ዘረኛና ጨቋኝ አገዛዝ አስወግዶ የሽግግር መንግስት የሚቋቋምበትን ስልትና ስርአት ለማመቻቸትና ለመቀየስ ነው። የመስራች ጉባኤውን ጋዜጣዊ መግለጫ (Press Release) Etiopian Review እና Ethiomedia ላይ ይመለከቷል በተጨማሪ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት-Ethiopian National Transition Council (ENTC) ከታች (ከgrass root) ወደ ላይ የተዋቀረ ዴሞክራሳዊና ህዝባዊ ውክልና ያለው የሲቪክ ድርጅት ነው። ይሄውም በስድስት ወር ጊዜ ብቻ በአሜሪካ፧ በአውሮፓና በአፍሪካ ከተቋቋሙት ከአርባ ከሚበልጡ ቻፕተሮች (የአካባቢ ምክር ቤቶች) የተላኩ ተወካዮች (delegates) የተሳተፉበት፤ በርከት ያሉ ወንዶች ወጣቶችና በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም የሴቶች ተወካዮች ንቁ ተሳትፎ ያሳዩበት፤ አንዳንድ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች የቀድሞና አዳዲስ አባላት በግል የተካፈሉበት፤ በእድሜ እንደኔ ጠና ያሉ በተወካይነትና በታዛቢነት የተገኙበት፤ በተለይም በቅርቡ በካናዳ ዋና ከተማ በኦቶዋ ከተመሰረተው <የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ> ሁለት ከፍተኛ የአመራር አባላት፦ የሸንጎው ም/ሊቀመንበር ወዳጄ ፕሮፌሰር አቻምየለህ ደበላና አቶ ነገሬ አዲስ ጠቃሚ ንግግርና ገንቢ አስተያየት የሰጡበት፤ በተለመደው ድርጅታዊ አሰራር ሳይሆን በግልፅ ውይይትና ክርክር፧ በጋራ በወል ስምምነት (consensus) ወይም በድምፅ ብልጫ ማንኛውም ውሳኔ የተላለፈበት ጉባኤ ነበር። ከዚህም በላይ የዋና ፀሃፊውም ሆነ የሌላ ተመራጭ የሰራ ዘመን አንድ አመት ብቻ እንዲሆንና ለሌላ አንድ አመት ከፈለገና ከተመረጠ ሊያገለግል እንደሚችል ተወስኗል። ይህም በድርጅቱ ውስጥ አምባገነንት እንዳይኖርና ሌላ አባልም የሃላፊነት ድርሻውን እንዲወጣ ያስችላል።

<ቀደም ብለው የተቋቋሙ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች ስላሉ ENTC አስፈላጊ አይደለም! የተጀመረውን ትግል የሚያቀዘቅዝና የሚያደናቅፍ ነው!> ለተሰኘው አስተያየት ደግሞ የበኩሌ አጭር መልስ፤ <በዳላስ የተደረገው
የENTC ምስረታ ጉባኤ አስፈላጊነቱን በሚገባ አረጋግጦአል ነው!>ሆኖም ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠቱ አይከፋምና እነሆ! በአሁኑ ወቅት በልዩ ልዩ ምክንያት ቀደም ብለው በተቋቋሙ የሲቪክና ፖለቲካ ድርጅቶች ያልታቀፉ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተለይም ወጣቶች ስላሉ፤ ENTC ከሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የላቀ አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል። በተለይም በቅርቡ ከተቋቋመው <የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ> ጋር የቅርብ ትብብርና ምክክር እንደሚኖረው ይታመናል።

በዋና ፀሃፊው በዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ላይ በቅንነትና በመሰሪነት ከጉባኤው በፊት የተሰነዘረው ቅሬታና ስሞታ መሰረተቢስ መሆኑን በጉባኤው ወቅት ለመገንዘብ ችያለሁ። ዝርዝር ገለፃ ውስጥ ባልገባም! ወያኔ የላካቸው መሆኑ ጭምር ተወርቶ ነበር! በጉባኤው ወቅት ጉልህ ተሳትፎ ያደረጉት፤ በወያኔና በሼህ አላሙዲን የተወነጀሉትና የተከሰሱት አቶ ኤልያስ ክፍሌ ያሉበት ENTC የወያኔ መሳሪያ እንዳልሆነና እደማይሆን በበኩሌ በፅኑ አምናለሁ!

የዶ/ር ፍስሃን ዳራ (background) ባላውቅም፤ በላስ ቬጋስ ቻፕተር ምስረታ ላይ በሰጡት ገለፃ፧ ከESAT ጋር ባደረጉት ውይይትና በጉባኤው ወቅት በነበራቸው አስተያየት፤ ግልፅ፧ ሃቀኛና ትሁት፤ ከፍተኛ የሃገር ፍቅር ያላቸውና አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል በገንዘባቸው ብቻ ሳይሆን በህይወታቸው ጭምር የቆረጡ ተግባራዊና ሃይማኖተኛ ምሁር መሆናቸውን ለመገንዘብ ችያለሁ በበኩሌ። ከዚህም በቀር በጉባኤው መዝጊያ ላይ አንዳንድ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተለይም <የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ> ሊቀ-መንበር ወጣቱ አቶ ማስረሻ ጥላሁን በስሜትና በሲቃ ያደረገው ንግግር የዶ/ር ፍስሃን ሃቀኛ ኢትዮጵያዊነት፤አገር ወዳድነትና የወገን ተቆርቋሪነት ሊያረጋግጥልኝ ችሏል። በተረፈ ዋና ፀሃፊው በተደጋጋሚ በአፅንኦት እንዳሉት ማንነታቸውን < ጊዜና ታሪክ ይመሰክራል!> ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ ወይም የገቡበትን ድርጅት ብቻ የሙጥኝ ብሎ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከማካሄድ ልንቆጠብ ይገባናል እላለሁ።

የአበውንም ዘመን የማይሽራቸውን ምሳሌያዊ ንግግሮች (Proverbs) ማስታወሱና ማጤኑ ተገቢ ነው!ከብዙዎቹ መካከል የስም ማጥፋትን በተመለከተ አበው < ጎረቤትህን ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ፤አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል! >ሲሉ፤ተባብሮና ተጋግዞ የጋራ ጠላትን ለማሸነፍ ደግሞ < ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!> ብለዋል። ስለዚህ ተባብረንና ተጋግዘን የኢትዮጵያን ጠላት እናስወግድ!

አገር ሲጠፋና ሲፈራርስ ገለልተኛ፧ ተመልካችና ከንፈር መጣጭ፧ የወሬ አናፋሽና አራጋቢ መሆን፤ ከዘረኛውና ከአምባገነኑ ከወያኔ መንግስት ደጋፊነት ተለይቶ አይታይምና አገር ወዳድና ተቆርቋሪ የሆን ሁሉ፤ በምናምንበት
የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ አባልና ደጋፊ በመሆን የኢትዮጵያዊነት ብሄራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ወቅቱ አሁን ነው!ይህን ያለመፈፀም የግልና የቤተ ሰብን ታሪክ ያጎድፋል! ብሄራዊ ግዴታችንንም ለመወጣት ENTC ከአመቺ መድረኮች አንዱ ነው!

ውድ አንባቢዎቼ! አስተያየታችሁን በE-mail: assefagmt@gmail.com ብትመይሉልኝ ከወዲሁ ከልብ አመሰግናለሁ። በግእዝ ፊደል ትየባ ገና ተለማማጅ በመሆኔ፤ እንደ ጥራጥሬ ለቃሚ ዶሮ ሆህያት መለቃቀሙ ስለሰለቸኝና ስለደከመኝ ከይቅርታ ጋር አጭር ዘገባዬን እዚህ ላይ ላብቃና ንግግሩንና ግጥሙን ነገ ተነገ ወዲያ አቀርባለሁ። አመሰግናለሁ! በቸር ይግጠመን !

ጃንደረባ ሎሌ በጌታው ብልት ይፎክራል

Tuesday, July 10th, 2012

ከቴዎድሮስ ሐይሌ

ገንዘብን መውደድ የጥፋት ሁሉ ስር ነው አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ስቃይ ራሳቸውን ወጉ።” (2 ጢሞ. 6፡6)

AESAONE is a legally registered non-profit organization based on a non-political, non-ethnic and non-religious platform. We remain sports and culturally focused. Our mission is to embrace ALL Ethiopians using sports and culture as a vehicle. We have organized concerts and cultural events throughout the week. We, again, invite each and every one of you to join us at the annual AESAONE soccer tournament.

በሃገራችን መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ አበው እንዲሉ ባህልና ወጋችን ሆኖ ፈሪውን ደምመላሽ በታኙን አንዳርጋቸው ክፉውን ለገሰ አስቀያሚዋን ዉቢት የሚቀመስ ጥሬ በሌለበት የተወለደውን ሐብታሙ አለያም ሺህበሺ እያልን ብቻ የባህሪ የተፈጥሮና የሃብት ጉድለታችንን በስም እየጠገንን በተስፈኝነት የስም ስንቅ ችግራችንን እያቀለልን ዘመናት ተሻግረናል በእርግጥ እንደህብረተሰብ ጠቀሜታው የጎላ እንጂ ጉዳት ያለው ነው ሊባል የሚያስችል አይመስለኝም።ይህን አይነቱ ባህል ሌሎች ሕዝቦች የሚጋሩት እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ በከሃዲነቱ ስሙ ጎልቶ የሚታወቀው ይሁዳ የስሙ ትርጓሜ በእብራይስጥ ቋንቋ ታማኝ አገልጋይ ማለት እንደሆነ የሚስጥርና አንድምታ ሊቃውንት ያስተምራሉ ። እንግዲህ የዚህ መልካም ስም ባለቤት የሆነው ይሁዳ የእጁን ታምራት የቃሉን ትምህርት የሰማይ መና የተመገበውን አዳፋ እግሩን በቅዱስ እጁ ያጠበውን የጌታውን እጅ ሊነክስ የበላበትን ወጭት ሊሰብር ያነሳሳው የዚህ ዓለም የጥፋት ስር የተባለው ገንዘብ በመውደዱ ለሰላሳ ዲናር አምላኩን ለሞት አሳልፎ እንደሰጠ ስንማረው ያደግነውና የምናውቀው ቢሆንም ባለማስተዋል ዛሬም በይሁዳ መንገድ የሚጓዙትን የገዛ ወንድሞቻችንን አይተን እንዳንስት ለማስታወስና አንዳንዶቻችንም ጥቂት ለጥቅም ብለው ወገን ሲከዱ ሃገር ሲያዋርዱ በምናያቸው ይሁዳውያን የተነሳ ራሳችንን እስክንጠላ ከአንድ ሃገር ማሕፀን በመፈጠራችን ራሳችንን ስንረግም ለምንገኘው ጥሩ ምሳሌ ይሆናል።

ተገንጣዩ AESAONE ነኝ የሚለው ከበርቴ ሰራሽ የአድርባይ መንጋ ወጉ እንዳይቀርበት አላማዬ በሚለው ከላይ በእንግሊዝኛው የቀረበውን አይነት በልኩ ያልተሰፋ ቀሚስ አጥልቆ ሠው ያወቀውን ፀሐይ የሞቀውን የአደባባይ ሚስጥር አይታወቅ ይመስል ከፖለቲካ ገለልተኝነቱን ከጎሳ አመለካከት መጽዳቱን ሊያሳምን ይሞክራል ፤ ለመሆኑ የስፖንሰሩ ፖለቲካዊ አቋም ከፖለቲካ ያለፈና የኢትዮጽያን ሕዝብ ደም የሚመጡትን እንደ በረከት ስምዖን ያሉትን እንደማንቆርቆሪያ እያንጠለጠለ ውጭ ወስዶ የሚያሳክምና ከመሸታ ቤት ቱማታነት ያላለፈውን የባልቴቶች ወግ የሆነውን መጽሃፍ ሲያሳትም የንብ ባንዲራ ለብሶ አራዊቱንና ሰው በላውን የወያኔ ቡድን ሲያስተዋውቅ አዲሱ የኳስ ቡድን አያውቅምን ከዘበኛው እስከ ዋና አማካሪው በአንድ ጎሳ ሰዎች የተከበበ የኢትዮጽያን ሕዝብ አፈናቅሎ በሚያርሰው መሬት ወገን እየተራበ ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ የሃገሪቱን ሃብት ያለ ገደብ እየተጠቀመ ያለ ግለሰብ በለገሰው ገንዘብ ገለልተኛ ነኝ ብሎ መዋሸት ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ነው።

እኔ በእውነቱ የሼኩም ሁኔታ ያሳዝነኛል አላህ በረከት ያበዛለት በህይወት ዘመኑ በልቶት አይደለም ቆጥሮ የማይጨርሰው ሐብት እያለው ከበረከቱ መረገሙ እየተረፈን እንኳ ከዓለም ሃብታሞች መካከል በባለጸጋነቱ የሃገራችን ተወላጅ ወንድማችን በመሆኑ እኛም ስንኮራበት ምን አለ ውሎውን ከጭፍራና ከምስለኔ ጋር ባያደርግ ለሃገር ፍቅር ከሆነ ያለ ምንም የወሽካታ መንጋ ሚሊዮኖችን ከጎኑ በተሰለፍን ነበር። ጥቂት ወንድሞቹን በጥቅም ቢያንበረክክም ቆሎ በልቶ እስቴኪኒ የሚይዝ ኩራት እራት ከሚል ጅንን ማህበረሰብ የፈለቅን ታሪካችንን ያልዘነጋን ዜጎች እልፍ አእለፍ በመሆናችን ይህን አይነቱ የአደግዳጊነት ባህል ለመቀበል አንችልም ።ቅዱስ ቁራን “ስታጣ ታጋሽ ስታገኝ ለጋስ ሁን!” ሲል ይመክራል ስለዚህም ያለው ይሰጣል የሌለው ይቀበላል ይህ ደግሞ የነበረ ያለና የሚኖር መንፈሳዊና ሰብዓዊ ዑደት ነው። ያለው የአመለካከት ባሪያዎችን ሊያሰማራ ቢችልም ይህን ማድረግ ለጌታውም ሆነ ለሎሌው የሞራል ክስረት እንጂ ክብርም ትርፍም የለውም ስለዚህም የተከበሩ ሼክ አላሙዲ የኔ ብጤው በሃገሩ የመኖር ነጻነት አጥቶ የኮበለለ ዜጋ ብርጭቆ አጥቦ በሚያገኘው ገንዘብ ፈጣሪውን አመስግኖ በሰላምና በነጻነት በመኖሩ ተረጋግቶ የሰው እጅ ሳያይ በሚኖርበት ሃገር ያውም የተሻለ ኑሮ እያላቸው ክብራቸውንን አድፋፍተው ወገናቸውን ክደው የተፉትን ልሰው ጫማዎት ስር የሚርመጠመጡት ጃንደረባ ሎሌዎች ከትቢያ ያላነሱ ከህዝብ ጋር እንዳይታረቁ እንቅፋት የሚሆኑ ከወዳጆ ከወያኔም የባሱ በመሆናቸው ከዚህ አፍራሽ ድርጊት ቢቆጠቡ መልካም ነው መጽሃፉም የቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ይላልና ሰልፎን ከሽፍቶች ሳይሆን ከህዝብ ያድርጉት!

አበው ሠይጣን ገንዘቡን ያስቀድምና ገመዱን ሲያሰስከትል አይታይም ይላሉ ነገሩንም ሲያጠናክሩ ይሁዳ ጌታውን በሰላሳ ዲናር አሳልፎ ከሰጠ በኋላ የተከፈለው ገንዘብ እርካታና ደስታ ሊገዛበት ይቅርና እጁ ገብቶ ሳይውል ሳያድር የፀፀት ማቅ አልብሶት ዕምነቱን ያሰጣው ፀጋውን ያስገፈፈው ያ የጓጓለት ገንዘብ ለባለቤቶቹ መልሶ ማቆና ታንቆ ራሱን እንደገደለና በጣለውም ገንዘብ መታሰቢ ይሆን ዘንድ ፈሪሳውያን የደም መሬት አኬል ዳማ የሚባል ርስት እንደገዙለት ታሪኩ ያትታል። ይሁዳ የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ይህን ታሪክ ፈጽሞ ቢያልፍም ዛሬ አለመታደል ሆኖ ሃዋረያቶች ከተሰውላት ጻድቃንና ሰማዕታት የተጋደሉላት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሳይቀር በውስጧ የመሸጉ በጥቅመ ሰናዖር የናወዙ ንዋይ አሳዳጆችና መንጋቸውን ለገንዘብ የሚሸጡ አደራ በላ ካህናት ሳይቀር ( እንደ አባ መላኩ ፤ አባ ምላጭ) አይነቱ ጭምር በክፉ አርዓያነት ትውልዱ የምግባር መስመሩን እንዲስት በተናገሩበት ጸንተው መገኘት በዋሉበት ማደርን ትተው በአደባባይ የተናገሩትን ዘንግተው በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ይዘው ሲገኙ ታዲያ እንዴት ትውልድ ለእውነት ዘብ ይቁም ማን ተምሳሌት ይሁነው አንዳንዴ በእውነት በተራው ዜጋ መፍረድ ይቸግረኛል።

ያም ሆኖ በሃገሩ የመኖር ነጻነት አጥቶ የተሰደደ ማህበረሰብ ቢችል ሃገሩና ወገኑ የተጫነውን የድህነትና የጭቆና ቀንበር አራግፎ የተሻለ ስረዓት ሊፈጥር የበኩሉን አስተዋጽዖ ሊያበረክት ባይችል ከገዳዮቿ ላያብር ዝምታን ሊመርጥ በተገባ ነበር። አለመታደል ሆኖ በተለይ በአሜሪካ የሚኖረው የኛው ወገን እነ ማርቲን ሉተርና የጥቁር መብት ታጋዮች ምስጋና ይድረሳቸውና በነሱ ሞት በመጣው ነጻነት ተጠቃሚ ሆኖ ያጣውን የሆድና የነጻነት በረከት በሌሎች መቃብር ላይ የሚያጣጥመው የኑሮ በረከት አንሶት በልቶ ማደር የህይወት ሸክም በሆነበት እናት ሃገር ባለው የአካላችን ቁራጭ የአጥንታችን ፍላጭ በሆነው በገዛ ወገናችን መከራ ላይ ለመዘበት በመከራው ልናተርፍ በስቃዩ ልንነግድ ምን መንፈስ አነሳሳን በእርግጥ ሰው ሰርቶ በሚበለጽግበት ሃገር ሆነን እንደ ምንዱባን ቀን ካነሳው ከበርቴ ሽርፍራፊ ሳንቲም ይመረን አረ ጎበዝ ቆም ብለን እናስብ ፤ ቢቸግረን እንኳ በፉድ እስታንፕ ማርና ወተት የሚቀልበን የአሜሪካ መንግስት እያለ እንዴት የደም ገንዘብ እንፈልጋለን።

ከላይ ከመግቢያው እንደሰፈረው የሃሰት የአላማ ሽፋን በአንድ የዋህ ከበርቴ ገንዘብ ተቋቁሞ አባታችን አዳምንና እናታችን ሔዋንን ከገነት እንዲባረሩ መልዕክተኛ የሆነውን ጥንት ጠላታችን እባብን በባህሪ የሚመሳሰው የወያኔው የጥፋት ሃይል በህዝብ መሃል ፍቅር እንዳይነግስ አንድነት እንዳይበረታ ሴራ በመጎንጎን መንድም መንድሙን እንዲጠላ ቅራኔን በማስፋፋት በጋብቻ በጉርብትና በፍቅርና በአንድነት የኖረውን ህዝብ ለመበታተን በተዘዋዋሪ የእርጉም ኣለማው ማስፈጸሚያ ለማድረግ ራሳቸውን የከበርቴ ጃንደረባ ባደረጉ የአመለካከት ስልቦችን በማስፎከር በተንበርካኪዎችና በነጉርሻ ብርቁ ምስለኔዎች ጀርባ ተረማምዶ የጥፋት ነጋሪቱን ለመጎሰም የተደረገው ሰጣናዊ ውጥን ከመነሻው የከሸፈ ቢሆንም የወያኔ ተፈጥሮው የእባብ ነውና እንደለመደው አቧራውን ቅሞ በሌላ ዙር የጥፋት ተግባር እንዳይሰማራ የተነቃቃው ሕዝባዊ ሃይል ትግሉን በበለጠ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

እኛስ ለነጻነት ምን እንሰራለን? (አክሎግ ቢራራ)

Saturday, July 7th, 2012

ከዶ/ር አክሎግ ቢራራ

በቁጥር ስድስት ለማስረዳት የሞከርኩት፤ የህወሓትን ተደጋጋሚ መራራ በደል በሚገባ ለማሳየት፤ ስርአቱ በቀጥታ፤ ጠባብ ዘረኝነትን፤ የገዥ ፓርቲን፤ መንግስትንና ጠቅላላ የመንግስት አስተዳደርን ከአንድ ላይ ቆላልፎ፤ (Total merger of ethnicity, political party, government and state) ወገናዊና አድሏዊ በሆነ መንገድ፤ የበላይነት ፍጹምነት መቀዳጀቱን ነው።በመሆኑም፤ ለይስሙላ ዳኛና ፍርድ ቤት፤ ህገ መንግስትና አስተዳደር አለ ቢባልም፤ ግለሰቦችና ተቋሞች የሚያስፈጽሙት የበላይ የፖለቲካ ውሳኔን ብቻ ነው። ለዚህ የቅርብ ማስረጃው፤ በአንዷለም አራጌና ሌሎች ሃያ ሁለት ሰላማዊ፤ አገር ወዳድ፤ ለነጻነትና፤ ለህዝብ እኩልነት፤ ታጋይ በሆኑ ኢትዮጵያዊያን ላይ ሰኔ ሃያ ሁለት፤ ሁለት ሽህ አራት አመተምህረት፤ የተደረገው አሰቃቂ የእድሜ ልክ እስራት ብያኔ ነው። ታዛቢወች ገና ይህ ፍርድ ከመሰጠቱ አስቀድመው የፖለቲካ ውሳኔ እንዳይሆን አሳሰበው ነበር። ለማስመሰል ብቻ፤ ፍርድ ቤት ቀረቡ እንጂ፤ የተባለውና የተፈራው እንደተፈጸመ የጠቆመው፤ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በተደጋጋሚ፤ የእነዚህን ግፋቸው፤ በደላቸው፤ ወንጀላቸው፤ ለስብአዊ መብትና የሰው ክብር፤ ለነጻነትና እኩልነት መቆም እንጂ፤ ሌላ ወንጀል እንዳልሰሩ፤ በማንም እንዳልተገዙ፤ አሽባሪ እንዳልነበሩ፤ እያወቁ ለተዘጋጀላቸው የማይቅር፤ የፖለቲካ ውሳኔ አጋልጠዋቸው ነበር። ከፍርዱ በኋላ፤ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ የሰሰብአዊ መብቶች ድርጂትና ሌሎች ያስታወቁት ተቃውሞ ህወሓት ለእውነተኛ ፍርድ፤ ለህግ የበላይነት፤ ለግለሰብ መብትና ነጻነት እንዳልቆመ ነው። የጸረ ሽብርትኝነት ህግ ያወጣው ማንንም ተቃዋሚ ለማሰር፤ ለማሳደድ፤ ዘመድ አዝማዱን መድረሻ ለማሳጣት፤ ፍርሃት ፍጹም እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡ በተዳጋጋሚ የምናየውም ህወሓት የፖለቲካ ውሳኔ ካደረገ በኋላ፤ ህጋዊ ለማስመሰል ብቻ፤ ግለሰቦችን ለፍርድ ያቀርባል። ምስክሮችን ይጠቁማል፤ ያዘጋጃል፤ ውሸት ተናገሩ ይላል። ያዘዘው ከስራ ላይ ይውላል። እንደዚህ ባለ ቅድመ ሁኔታ፤ ያልተዛባ ፍርድ ሊኖር አይችልም።

ዳኛው፤ የስርአቱ አገልጋይ የሆኑት አቶ እንደሻው አዳነ የተሰጣቸውን የፖለቲካ ትዛዝ ከስራ ላይ ማዋል እንጂ የህግን የበላይነት ይዘው ለእውነተኛ፤ ለሚዛናዊ ፍርድ፤ ለፍትህ መቆም አልነበረም። ቢቆሙ ኖሮ ያስደንቅ ነበር። የተመለመሉበት፤ የተማሩበት፤ የሚኖሩበት፤የገቢያቸውና ድጎማው ይዘት፤ የወደፊት እድላቸው ሁኔታ በሙሉ የሚወሰነው ለህወሓት ባላቸው ታማኝነት እንጂ፤ በሕዝብ ያለ አድሎ አገልጋይነት፤ በህግ፡ የበላይነት፤ በህሊና ንጹህነት አይደለም። ስለሆነም፤ የተቋምና ግልሰቦች ነጻነት በሌለበት አገር ፍትሀ ይኖራል ብሎ ራስን መደለል ተጨማሪ ማስረጃ አይሻም። ደጋግመን አይተነዋል። ወደፊትም ይሆናል። የሚሻለውስ፤ ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደ ጎን ትቶ ዘላቂነት ባለው መልክ ለፍትህ፤ ለእኩልነት፤ ለህግ የበላይነት አብሮ መነሳት ብቻ ነው።

ፈራጁ ሳይሆን የተፈረደበት ታሪክ ሰራ፤

አብሮ ለመስራት፤ አቶ አንዷለም አራጌ ለታሪክ ያስመዘገበውን ማየቱና እኛስ ምን እንሰራለን ብሎ መጠየቁ ጠቃሚ ነው። ቢያንስ ህሊናን ይቀሰቅሳል፡፡ “እኔስ ማን ነኝ? ምን እሰራለሁ? ነግ በኔ አይደለም? እስከ መቸ ነው ለልዩነት፤ ለቡድን፤ ለግለሰብነት፤ ለጉራ፤ የምገዛው” ብለን በያለንበት ሁሉ ብንነሳ የፍርድ ጨለማ ለሆነችው አገራችን ተስፋ ልንሰጥ እንችላለን። በግፍ ለታሰሩ፤ ለተሰደዱ፤ ለሚሰደዱ፤ ለሚታገሉ፤ ወገኖቻችን አርአያ ልንሆን እንችላለን። የፍርድ መጓደልን በማየት፤ እኛ ይህን በደል ስንቀበል አንኖርም ለሚለው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር አገር ውስጥ በሆዱ ለሸፈተ ወገን ሁሉ፤ በተለይ ተቆርቋሪ ለሆነው ወጣት ትውልድ ያስቆጣል:: የተቃዋሚውን ቁጥር ያበዛል እንጂ አይቀንስም። ህወሓት ቢወድም ባይወድም ከአምሳ በመቶ በላይ የሆነው፤ ወጣቱ ትውልድ ለነጻነት፤ ለፍትህ፤ለእኩልነት፤ ለራስ መቻል፤ ለህግ የበላይነት፤ መታገሉ እያደገ፤ እየሰፋ ይሄዳል። አቶ አንዷለም የዚህ አዲስ ትውልድ አባልና ድምጽ ነው። በእስር ቤት ህይወቱን እንዲያሳልፍ መደረጉ፤ ያቀረበልንን ሃሳብ አይቀብረውም። እንዲያውም፤ ህያው ያደርገዋል። ህውሓት፤ ሰውን ማሰር፤ መግደል፤ ማሳደድ ይችላል። የሃሳቡን ስርጭት ግን ማንም ሃይል ሊያግደው አይችልም። አርቆ ላሰበው ከጠበንጃ ሃይል ይልቅ ለገንቢ ለውጥ፤ ለሃሳብ ጥራት፤ ለአስተዋይነት፤ የሚያበረታታ ድጋፍና አቅጣጫ ለመስጠት፤ ለመተባበር፤ ታግሎ ሌላውን ለማታገል መቆም አሸናፊ መሆኑ አይቅርም። የቱኒሲያ፤ የሊቢያ፤ የየመን፤ የግብጽና አሁን የሶሪያ ህዝቦች የሚያደርጉት ትግል ከዚህ መንፈስ የተነሳ ነው። ለመነሳት የቀሰቀሷቸው ነባር ሁኔታወች ከኢትዮጵያ ብዙም አይለዩም። በእነዚህ አገሮች፤ በተለያየ ወቅት ግለሰቦች የተናገሩትና የሚናገሩት፤ የታሰሩትና የተገደሉት ከኢትዮጵያ ታጋዮች አይለይም። ባናውቅበት ነው እንጂ፤ ለፍትህ-ርትእ፤ ለነጻነት፤ ለዲሞክራሳዊ ለውጥ በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን ሰጥተዋል፤ ታስረዋል፤ ተሰደዋል።

ኢትዮጵያዊ አመራር ከአስኳል ሲቀጭ፤

“እኔ ለራሴ፤ ለልጆቸና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ ዲሞክራሲና ነጻነት እነደሚገባን በማወቅ አቅሜ በፈቀደው መጠን ታግያለሁ። ይህን በማድረጌ በማንም ላይ በክፋት አልተነሳሁም፤ ይህን በማድረጌ ህግ ጥሸ አላውቅም፤ ይህን በማድረጌ በድሃዋ አገሬ ጥቅም ላይ አልተነሳሁም፤ ይህን በማድረጌ ፈጣሪየን፤ የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ፤ ህሊናየን፤ የሚያሳዝን አንዳች ነገር ፈጽሚያለሁ ብየ አላምንም። …እኔን፤ ከዚህ ያቆመኝ፤ የነጻነት ናፍቆት ነው” ብሎ አንዷለም ለአለም ህዝብ ያቀርበው፤ መላው የሃገራችን ህዝብ የሚጋራው፤ ተከታታይ ትውልድ ሲጠቅሰው የሚኖረው፤ የኔልሰን ማንዴላ፤ የማርቲን ሉዘር ኪንግ አባባል የሚሆነው። ፈራጆቹ የህወሓት ገዦች፤ እንደሱ አያስቡም። ለማሰብም ፈቃደኛ አይደሉም። ለእነርሱ፤ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለሃገር አንድነት፤ ለመላው ህዝብ የተሻሻለ ኑሮ የመኖር መብት የቆመ ሁሉ፤ “ጠላት” ነው። ክፋት፤ ምቀኝነት፤ ውሸት፤ ዘራፊነት፤ ደማቸው የሆነ፤ በድሃ አገር የራሳቸውን ጥቅም ከህዝብ ጥቅም በላይ አሳዳጆች ናቸው ለማለት የሚያቨቃ ብዙ ማስረጃ አለ።

ሌላው ቀርቶ፤ ቁመንለታል ለሚሉት ነጻነቱንና ክብሩን ላጣ የትግራይ ህብረተሰብ የማይረሳ በደል እንዲሸከም አድርገውታል። በስሙ ጥቂት ግለሰቦች፤ ቤተሰቦቻቸው፤ ምርጥና ታማኝ ወዳጆቻቸው ሃቭት እያካበቱ፤ አድሏዊ በሆነ መንገድ ከይሉንታ በላይ በብዙ ቢሊየን ብር የሚገመት መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ ለትግራይ ህዝብ አለንልህ እያሉ፤ ከሌላው ህብረተስብ ጋር በሰላም፤ በፍቅር፤ በመከባበር፤ በመተሳሰብ፤ የሚኖረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል እንዲጠላ እያደረጉት ነው። እኛ ለሃገርና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የቆምን ሁሉ፤ በትግራይ ህብረተሰብ የሚደረገውን ሽንገላ ለተንኮል እንጂ ለዘላቂ እድገት አለመሆኑን መገንዝብ አለብን። በአድሎ የተገነባ እድገት ይቆይ እንጂ፤ ማጠያየቁ እንደማይቅር ከሌሎች አገሮች ልምድ አይተናል፤ እያየን ነው። የትግራይ ተቃዋሚወችም፤ ይህን ህዝብ ከህዝብ የሚለያይ ዘዴ ያለመቆጠብ ማውገዝ፤ ከሌሎች ኢትይጵያዊያን እህቶችና ወንድምቻቸው ጋር እጅ ለእጂ ተያይዘው መቃወም ታሪካዊ ግዴታቸው ነው። የእኛ ብሄር፤ የኔ ብሄር፤ የኔ ሃይማኖት፤ የኔ ቡድን ወዘተ፤ እያልን ከቆየን የምንደግፈው የህወሓትን ስርአት መሆኑ አያጠራጥርም። መነሳት ያለብን፤ ኢትዮጵያና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለበት ጭቆና፤ ካለበት አደጋ፤ ካለበት ዝርፊያ ነጻ መውጣት የሁላችንም ሃላፊነት ብለን ነው። ይህ አዲስ፤ ልሁሉም የሚቨጅ፤ ብሩህ ምእራፍ ይከፍትልናል።

የህወሓት የበላይ አዛዦች የሚጠቀሙበት ዘዴ ከመለያየት የባሰ ነው። በተለይ አማራውን “ጨቋኝ፤ ነፍጠኛ፤ ብዝብዥ”እያሉ ማሳደድ፤ መግደል፤ ካለበት ማስወጣት፤ ሃብት/ጥሪት/ትምህርት/ጤና/ስራ እንዳይኖረው ማድረግ። ከዚያም፤ አፋሩን፤ ኦሮሞውን፤ ሶማሌውን፤ ጉራጌውን፤ አኟዋኩን፤ ወዘተ፤ በየተራ፤ ማሳደድ፤ ባልሰራው ወንጀል በሽብርተኝነት መክሰስ፤ መወንጀልና ማሰር ነው። የፖለቲካ ስልጣንን ትተን በኢኮኖሚው ያለውን ሁኔታ ስናይ፤ የዚህ አሰቃቂ አገዛዝ ተጠቃሚወች፤ ምርጥና ታማኝ የሆኑ ጥቂት ግለሰቦች፤ ቤተሰቦች፤ ለዚህ ሆነ ተብሎ የተቋቋሙ ድርጂቶች ናቸው። በኢኰኖሚው በኩል ታምራዊ እድገት አለ ተብሎ ህዝብ “ዳቦውስ የታል” በሚባልባት ኢትዮጵያ፤ የውሸት ምስክር ፈልጎ ዋሽተህ ተናገር ማለት ቀላል ነው። ከፍርሃቱ ሌላ፤ ድሃው ሰው በልቶ ማደር ስላለበት በትንሽ ገንዝብ ይገዛል። ውሸት፤ ሙስና፤ ስርቆት በጦፈበት፤ ህግ በሌለበት አገር የፍርድ ችሎት በአግባቡ ይካሄዳል ብሎ ለአለም ህዝብ መናገር ለህሊና ይቀፋል። በአጠቃላይ ሲታይ ግን ምንም ሊያስገርመን አይችልም። በፖለቲካ መነጽር አይቶ፤ የውሽት ምስክር ጠርቶ፤ የፖለቲካ ፍርድ መስጠት የአብዮታዊ ዲሞክራሲ እሴት ነው። እድገት አለ እያሉ በተራ ህዝብ ላይ መቀለድ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስልት ነው። ስለዚህ ጎጅ ስርአት ከዚህ በፊት ብዙ ማስረጃወች አቅርቢያለሁ። ለማጠናከር አንድ ምሳሌ እሰጣለሁ።

የህወሓት የበላይ መሪወች ውሸትን፤ ትውልድ ጎጅ ተግባርን፤ ታሪክ መከለስን፤ ታላላቅ የኢትዮጵያ መሪወች ማዋረድን፤ ሙስናን፤ ስርቆትን፤ ግለስብና ብሄር ማዋረድን፤ እንደ እውቅት፤ እንደ ብልጠት፤ እንደ ዘመናዊ አመራር ስልት ያዩታል። የህሊና ገደብ የላቸውም። ከባህላችን የቀሰሙት፤ “ህሊናስ ለምን ይጠቅማል፤ ሰውስ ምን ይላል፤ ትዝብትስ፤ ታሪክስ፤ እውነትስ ምን ይመዘግባል” የሚሉ እሴቶች ለነሱ፤ ዋጋ የላቸውም፤ ባዶ ናቸው። በተደጋጋሚ፤ አስድናቂ የእርሻ ምርት አለ ብሎ ህወሓት አለምን ለማሳሳት የሚያደርገውን ውሸት፤ የአለም ባንክ ባለሙያወች “ታምራዊ የእርሻ እድገት የለም” ብለው ያስቀመጡትን፤ ጭብጥ ለማድረግ ከኢትዮጵያ የሚመጡ ግለሰቦችን ተራ በተራ አነጋገገርኩ። እነሱ፡ ከችግሩ ጋር አብረው ስለሚኖሩ የሚናገሩት እውነት ነው። በተጨማሪም፤ ማሰረጃወችን ሁሉ፤ እንደገና አየሁ። በአማራ ክልል፤ የህወሓት ካድሬወች የበላይ ትእዛዝ በማክበር አንድ ድሃና አፈ ጮሌ ወጣት ገበሬ ይመርጣሉ። አምስት መቶ ብር ጉርሻ ይሰጠዋል። ለጋዜጠኞች፤ ምንና አንዴት እንደሚናገር ያዘጋጁታል፡፡ መሬቱ የበሬ ግንባር የምታህል፤ ማደሪያ ቤቱ የጭቃ፤ ለስሙ መቶ ብር የሌለው፤ ጎተራ ቀርቶ ከእጅ ወደ አፍ የሚኖር ወጣት፤ አፈጮሌ ገበሬ፤ ወደ አዲስ አበባ ሄዶ “ ታታሪ፤ አዲስ ሃብታም ገበሬ፤ እህል አቅራቢ፤ ሚሊየነር” ተብሎ በጠቅላይ ሚንስትሩ ይሸለማል፡፡ ከተነገረው በላይ እንዴት ሃብታም እንደሆነ፤ መንግስት እንዴት እንደረዳው፤ የቤተሰቡ ህይወት እንዴት እንደተለወጠ፤ ለጋዜጠኞች ሁሉ ያስረዳል። ለማስተባበል የሚችል አማራጭ ስለሌለ የህወሓት ማስረጃ ሰጭ፤ እንደ ህያው ምስክር ቀረበ። ተመሳሳይ የሆኑ ምስክሮች ከልዩ፤ ልዩ ክልሎች ተመርጠው የዚህ አይነት “ተአምራዊ የእርሻ ውጤት” ዘገቫ አቅርበዋል።

የጎንደሩ ወጣት ገበሬ፤ እንደገና ትንሽ ድጎማ ተሰጥቶት፤ ወደ መጣበት ይመለሳል። ታዛቢወች፡ ለምን ዋሸህ፤ “የንብ ቀፎወች ከየት አምጥተህ አለኝ አልክ” እያሉ ጠየቁት። ሚሽቱና ልጆቹ፤ “ሚሊዮን ብር ደብቀህ ካስቀመጥክ አሁን ስጠን” ሲሉት “አይኑ ፍጥጥ አለ” ይባላል። ወጣቱን ገበሬ ያሳፈረው፤ በመጭው የእርሻ ወቅት (farming cycle) የሚዘራው አጥቶ ወደ አንድ ዘመዱ ሂዶ “እባክህ፤ የምዘራው ስጠኝ፤ ወይንም አበድረኝ” ማለቱ ነው። የገጠር ሚሊየኔሮች ታሪክ ይህን ይመስላል። አንድ የህወሓት ደጋፊ ስለዚህ እመርታዊ የገጠር እድገት ከእኔ ጋር በ ጀርመን ድምጽ ሲከራከሩ “የገጠሩ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማያውቅ እድገትና የኑሮ መሻሻል ተጎንጽፏል” ያሉት ትዝ ይለኛል። እንደዚህ ያለ እድገት ካለ “ኢትዮጵያ ለምን የምግብ ጥገኛ ሆነች፤ ህንዶችን፤ ቻይኒሶችን፤ ሳውዲወችን ጋብዞ ለም መሬትና ወንዝ መስጠት ለምን አስፈለገ? ቢል ጌትስ ‘የኢትዮጵያ ሕዝብ በተደጋጋሚ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው ተቀዳሚ አገር ነው’ ብለው ለምን ተናገሩ?” ብየ ስጠይቃቸው አጥጋቢ መልስ ለመስጠት አልቻሉም። የደመደሙት ግን “መሪወችን በመጥላት እድገቱን መካድ አይቻልም” ነው። ፖሊሲው ግድፈት ካለበት የማጋለጥ ሃላፊነት እንዳለብን ሊቀበሉ አልቻሉም። የህወሓት ባለስልጣኖች፤ ራሳቸው ዋሽተው ድሃውንም በመደጎም እንዲዋሽ ያስገድዱታል።ለህሊናው እንዳይገዛ፤ ይበክሉታል። ለሃፍረት ይዳርጉታል። ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው ዋሽቶ ራሱንና ቤተሰቡን መመግብ የተለመደ የሆነው ለዚህ ነው። ሌላም ህይወት አዳሽ አማራጭ የለም።ፍርዱ፤ በድሃው ሳይሆን፤ አውቅልሃለሁ በሚለው የህወሓት አመራር፤ በተለይ፤ በከፍተኛ ባለስልጣኖች ላይ ነው። አመራሩ መዋሽት ባህሉ ከሆነ፤ መላው ህብረተሰብ ይበከላል፤ ወጣቱ ትውልድ አርአያ አይኖረውም።

ስለ አመራር ድክመት፤ ውርደት፤ የማላልፈው ሌላ ምሳሌ አለ። በአገራችን ሌብነትና ሙስና ጡፏል። ግድያ ጡፏል። መሰደድ ጡፋል። ወጣት ሴቶችን እንደ እቃ ወደ አረብ አገሮች፤ በተለይም፤ ወደ ሳውዲ አራቢያ መላክ ጡፏል። በቅርቡ ከአዲስ አበባ የመጡ አዛውንትና ባለቤታቸው ቦሌ ያዩትን ኢንዲህ ብለዋል። “የምንሰማው ብዙ ወጣት ሴቶች ወደ አረብ አገሮች እንደሚላኩ ነበር። ቁጭ ብለው አውሮፕላን ይጠብቁ የነበሩት ስላስገረመኝ፤ አንድ ወዻጀን የት ነው የሚሄዱ፤ ስንት ናቸው አልኩት። በቀን ቢያንስ ሶስት አውሮፕላን ጭኖ ይሄዳል። ቢያንስ ሰቫት መቶ፤ ብዙ ጊዜ አንድ ሽህ ብሎ ነገረኛ አሉ።” ከሰላሳ እስከ ሰላሳ ስድስት ሽህ የሚሆኑ ወጣት ሴቶች፤ ህወሓት ፈቃድ በሰጣቸው ድርጂቶች አማካይነት እንደ ሸቀጥ ይላካሉ ማለት ነው። ታምራዊ እድገት ካለ የኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች፤ የትውልድ ተኪወች፤ የወደፊት እናቶች፤ አስተማሪወች፤ ሃኪሞች ወዘተ እንዴት እነደ ተራ ሸቀጥ ለውጭ ምንዛሬ ተብሎ ይላካሉ? እድገታዊው መንግስት ለምን በሃገራቸው ሌሎች አማራጮች አያቀርብም፤ አያመቻችም፤ሁኔታውን አይፈጥርም? ለመሆኑ፤ እየተመረጡ የሚላኩት ከየት ነው? ለዚህም፤ ከህወሓት እውነተኛ መልስ አናገኝም።

ዛሬ፤ መዋሽት ዕውነት ሁኗል። ስርቆትና ሙስና የኢኮኖሚ አስተዳደር ብልሽት መጸብራቅ ነው። የማንም አገር መሪ ለመናገር ቀርቶ የማያስበውን፤ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ደጋግመው ብለውታል። ስለስርቆት መስፋፋትና ስለ መንግስት ሃላፊነት ሲጠየቁ የመለሱት አንድ አስደናቅና አሳፋሪ፤ ማስረጃ ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ “መስረቅ ጀግንነት ነው፤ ክፉው መያዝ ነው” ብለው የተናገሩት የሃያ አንድ አመታት ገዥ ምን ማለታቸው ነው ብለን እንጠይቅ? መልሳቸው ከሚያስተዳድሩት ስርአት ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ነው። የምርጫ ዘጠና ሰባትን የህዝብ ድምጽ በአመጽ ሲሰርዙ ምርጫን “መስረቅ” ትክክል መሆኑን አስምረውበታል። “ጀግንነት” መሆኑ ነው። ህወሓት ባለፈው ምርጫ “መቶ በመቶ አሸነፍኩ” ሲል ጀግንነትን ማሳየቱ ነው። ብዙ ሽህ ቶን ቡና ተሰርቆ ሲጠፋ እያዩ አንዳላዩ ማለፍ የሰረቁት ደፋርና “ጀግኖች” መሆናቸውን፤ ከተጠቃሚወች መካከል የህወሓትና የመንግስት ተባባሪውች “ጀግኖች” እንዳሉበት አመልካች ነው። በአመት ቢያንስ ከሶስት ቢሊየን ዶላር በላይ ከሃገር የሚወጣውን ገንዘብ የሚያሸሹ፤ ደፋር፤ አይን አውጣ፤ “ጀግኖች” ናቸው ማለት ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ስርቆትን እንደ ጀግንነት ካዩት ህወሓትና ደጋፊወቹ ሁሉ፤ ዘረፋን፤ ማሰርን፤ መግደልን፤ ማሳደድን፤ ፍርሃት መፍጠርን፤ እየመረጡ ዘር ማጥፋትን፤ እንደ ጀግንነት ያዩታል ማለት ነው። አንዱ ባህሪይ ከሌላው ሊለይ አይችልም። መዝረፍ ሆነ፤ ዘርፎ ለዘራፊ መዳረግ ጀግንነት ነው የሚል ከገዡ አለቆች ቁንጮ የመጣ ስርአት በይፋ ክሌሎች አገሮች የበለጠ፤ የሚሰራው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ዛሬ መስረቅ፤ የውሸት ምስክር ጠርቶ በውሸት ክስ ማሰር፤ ሙስና፤ ገንዘብ ማሸሽ “ጀግንነት” ነው ማለት ነው። ስልጣኑ ከፍተኛ የሆነ ግለሰብ ወይንም ቤተሰብ ሌባ በምንም ሊያዝ አይችልም። ህጉ አይመለከተውም (Total immunity):: ቢያዝም ባይያዝም፤ ሰው ቢያየውም፤ ባያየው፤ ስርአቱን ተጠቅሞ የሰረቀ “ጀግና” ነው ማለት ነው። ስለሆነም፤ የስርአቱ አመራርና ጠቅላላው ስርአት፤ የሞራል ውድቅት (morally decadent) አለበት ማለት ነው። የሞራል ውድቅት በሚያሳይ ስርአት ፍርድ ፍትሃዊ ሊሆን አይችልም፡፡ እድገት ፍትሃዊ ሊሆን አይችልም። ማንም ስርአቱን የሚቃወም ግለሰብ በውሸት ተከሶ፤ በውሸት ምስክር፤ በውሸተኛ ዳኛ፤ የሚፈረድበት ለዚህ ነው።

አቶ አንዷለም እንዲህ ብሏል። “ከሳሾች እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ጽዋ በጸጋ ከመጠጣት ውጭ ባልፈጸምኩት ወንጀል ማቅለያ የመጠየቅን አማራጭ ህሊናየ ስላልተወልኝ (ስላልፈቀደ) አዝናለሁ።”ይህ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ባልፈጸመው ወንጀል ተከሶ፤ የእስራት ዘመንህ እንዲቀነስ ከፈለግህ “ወንጀል ፈጽሚያለሁ፤ የመንግስትን ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለህ ለምን፤ ተማጸን ብሎ ያስገደደው ስርአት ሁል ጊዜ የሚፈልገው እራስን ዝቅ አድርጎ/አዋርዶ፤ የመለስ ዜናዊይን ፍጹማዊነት፤ የበላይነት መቀበልን ነው። የሚለየው ይህ ነው። አንዷለም አራጌ እራሱን፤ ቤተሰቡን፤ አገሩን፤ ባህሉን አላዋረደም። ለጥቅም ሲል ህሊናውን፤ እምነቱን አልቸረቸረም።“አማራጩን” አልቀበልም ብሏል። ለሃገር፤ ለወገን፤ ለእውነት፤ ለታሪክ፤ ለፍትህ፤ ለነጻነት የቆመ ግለሰብና መሪ የሚያሳየው እሴት ይህን ይመስላል። ብንቀበልም፤ ባንቀበልም፤ ኢትዮጵያና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚያስፈልጉት፤ የሚፈልጉት ጠባብ ብሄርተኛ ድርጂትና አመራር ሳይሆን፤ ሆደ-ሰፊ፤ ሁለ-አቀፍ፤ እውነተኛ ዲሞክራሳዊ፤ ብቃት ያለው ኢትዮጵያዊ ድርጂትና ኢትዮጵያዊ አመራር ነው። መንግስቱ ሃይለማሪያምን ተክቶ፤ መለስ ዜናዊን፤ እሳቸውን ተክቶ ሌላ ትእቢተኛ፤ ወገኛ፤ አምባ ገነን አመራር ሊሆን አይችልም። አንዷለም አራጌ፤ እስክንድር ነጋና ሌሎች የሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወጣት፤ ብቃት፤ ተስፋ ሰጭ ፤ እምቅ መሪወች (a new generation of Ethiopian leaders with potential) የሚታሰሩት፤ የሚሳደዱት፤ በሌሎበትም ጭምር “በቃኝና የሞት ፍርድ” የሚፈረድባቸው አዲስ እሴት፤ አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ የፖሊሲ አቅጣጫ (ጸረ ዘረኝነት፤ ጸረ አምባገነናዊነት) ይዘው ሰለተነሱ ነው።

የኢትዮጵያዊ ድርጂትና አመራር ቁልፍነት፤

የኔ ትውልድ የአገራዊ ድርጅትና ጥቨቫዊ አመራር (Responsive country wide political organization and wise and far-sighted leadership) አስፈላጊነትን ሁኔታወች ካለፉ በኋላ በከፊልም ቢሆን፤ እያወቀ የመጣ ይመስለኛል። ችግሩ ብዙ ቢሆንም፤ ያለ ኢትዮጵያዊ ድርጂት፤ ያለ አዋቂ፤ ጥበበኛና ሁሉን አገልጋይ አመራር ለውጥ ለማምጣት አይቻልም። ያልፈታነው፤ እኛ ሃሁ የቆጠርን ኢትዮጵያዊያን አመራርን ያየነው፤ የምናየው “እኔ፤ ለኔ፤ ለቡድኔ፤ ለፓርቲየ፤ ለብሄሬ፤ ለመንደሬ” ከሚል መነጸር ነበር፤ አሁንም የግለኝነት ተገዦች ነን ለማለት ይቻላል። ይህ ዘመን ያለፈበት የአመራር ዘይቤ፤ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን በምንም አይሰራም። በተልይ፡ ህወሓት ባመጣው “የከፋፍለህ ግዛው” ስርአት፤ ቡድናዊነት የትም አያደርሰንም። የህዝብ ጥያቄን ሊመልስ አይችልም። በብዛት እየጨመረ የሄደውን ወጣት ትውልድ ፍላጎት፤ ምኞት፤ ተስፋ አያሟላም። ከሰላ ሽህ በላይ በአመት አገራቸውን ለቀው በሳውዲ አረቢያ ክብራቸው ለሚገፈፈው ወጣት እህቶቻችን ሰቆቃ መልስ አይሰጥም። መልስ ሊሰጥ የሚችለው አንዷለም፤ እስክንድርና ሌሎች ወጣት የሃሳብ መሪወች የሚሉትና የቆሙበት፤ የታሰሩበት ነው። ማለትም፤ ከአገራዊ ድርጂትና ጥቨቫዊ አመራር የሚፈለገው፤ ለአንድ አገር፤ ለአንድ ህዝብ ሉአላዊነት፤ ለፍትህ፤ ለእኩልነት፤ ለነጻነት፤ ለመቻቻል፤ ለሰው ክብር፤ ለተጠያቂነትና ሃላፊነት፤ ለዘላቂና ፍትሃዊ እድገት ያለመሰልቸት ታግሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አዛዥ እንዲሆን ተግቶ መስራትን ነው። ልንክደው የማንችለው ሃቅ አለ። አገር ክሌለ፤ ትግል ትርጉም የለውም። ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነትና እኩልነት ካልቆምን፤ ከህወሓት ልንለይ አንችልም።

ፍትህን-እርትን የተለየ የሚያደርገው እመርታዊ ለውጥ እናያለን። ይህም የወጣቱ ቁጥር እያደገ መሄድ ነው። የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ፤ የወጣቱ ብዛት ያድጋል። ፍላጎቱ ይለወጣል። ለውጡን የማይረዳ ድርጂትና አመራር ይህን ሃይል ሊሰበስበው፤ ልቀሰቅሰው፤ ሊመራው አይችልም። ደጋግሜ የአስተሳሰብ ለውጥ (Dramatic change in the paradigm of thinking) ያስፈልጋል የምለው ለዚህ ነው።

ክፍል ስምንት ያለፈውን የፖሊቲካ አመራር ታሪካችን በአጭሩ እቅርቮ፤ የአገራዊ ድርጂትና ዘመናዊ አመራርን አስፈላጊነት፤ ጠቃሚነት፤ ወሳኝነት፤ ከወጣቱ ትውልድ ምኞትና ተስፋ ጋር አያይዞ ይዳሥሳል።

ኳስና ቅሪላ፤ ሆድና ሕሊና

Friday, July 6th, 2012

ከቴድሮስ ሐይሌ

‘’መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው፥ መጨረሻቸው ጥፋት ነው ።’’ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፥19

ዋሽቶ ለመኖር ልቤ አይችልም ከቶ፤
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ።
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም፤
ይህን ለማግኘት ብዬ እኔ አላጣም ሰላም ።
…ሕሊና ሲያጣ ሰላም ወርቅ አልማዝ ሞልቶ ፤
ሳይተኙ መኖር ሊኖር ከራስ ተጣልቶ ፤
አስኮንኛት ነብሴን እኔ አልሞላም ኪሴን!!!

በሙያው የህዝብ ልጅነትን ከእድሜው በላይ መከበርን በሚሊዮኖች መፈቀርን በህፃን በአዛውንቱ መወደስን የተቸረው ብላቴናው የሙዚቃው ኮከብ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከዚህ በላይ የቀረበውን ስንኝ ያዘለውን አስተማሪ መንፈሳዊና መካሪ በሆነው በዚህ ዘፈኑ ላይ በሐሰት ከሚገኝ ገንዘብ ይልቅ የሕሊና ሰላም ምንኛ የተሻለ እንደሆነ ያሳየበት ከቤተመንግስቱ እስከ ቤተክህነቱ በንዋይ ፍቅር የእውነትን ዋጋ በሚያቃልሉበት ሃብት ሞልቶ የተተትረፈለት ከበርቴ ከረሐብተኛ ሕዝብ መከራ ላይ የበለጠ ትርፍ ለማጋበስ ከማፍያና ወንጀለኛ አገዛዝ ጋር ተባብሮ ወገኑን ሲያስጨቁን የሚታይበትን ‘’ምን አይነት ዘመን ነው የተገላቢጦሽ አህያ ወደ እርሻ ውሻ ወደ ግጦሽ ‘’ አበው እንዲሉ የኛ የኢትጽያውያን ሁኔታ እንደምሳሌው እየሆነ ያ የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ በሚል ከባድ የቃልኪዳንን አክባሪ ከነበረ ማሕበረሰብ የፈለቀ ወገን….. ይህን ጽሁፍ በPDF ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የአላሙዲ አሽከሮች በዲሲ ባዘጋጁት የወያኔ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን እንዳይሳተፉ የቀረበ ጥሪ

Tuesday, July 3rd, 2012

የአላሙዲ አሽከሮች በዋሽንግተን ዲሲ ባዘጋጁት የወያኔ ፌስቲቫል ላይ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዳይሳተፉ የቀረበ ጥሪ

[PDF]

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ ዝግጅት በዳላስ ቴክሳስ ከጁላይ 1 – 7፥ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሄሪቴጅ በዋሽንግተን ዲሲ ከጁላይ 27 – 29 ይካሄዳሉ። እነዚህን የኢትዮጵያውያን ዝግጅቶች ለማፍረስ ወያኔያዊ ተልዕኮ ያላቸውና በገንዘብ የተገዙ ግለሰቦች ያደረጉት ሙከራ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ተልእኮአቸው ከሽፎ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) የበለጠ ተጠናክሮ፥ ራሱን ከወያኔ ካድሬዎችና ከአላሙዲ አሽከሮች አጽድቶ እየወጣ ይገኛል።

ሆኖም የአላሙዲ አሽከሮች ዛሬም ቢሆን እርኩስ ተልእኮዋቸውን ለመወጣት ከመሞከር አልታቀቡም። በአንጋፋዉ ESFNA ስም ላይ (ONE) በመቀጠል ድርጅቱን ለመከፋፈልና ህብረተሰባችን ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠር የሞከሩት እኩይ ተግባር ፍርድቤት ቀርበው እንዲታቀቡ ተደርጓል።

በዚህም ሳያበቃ፣ ሆዳደሮቹ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የስፖርት ማሕበር አንድ (AESAONE) በሚል ስያሜ በዋሽንግተን ዲሲ ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 7 ድረስ የስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጃለሁ ብለው ተነስተዋል። ይህ ዝግጅት በዳላስ ከሚካሄደዉ የESFNA ታላቅ የስፖርትና የባሕል ፌስቲቫል ዝግጅት ቀናት ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን በማድረግ ያሰራጩት የእነሱን መሰሪ ተልእኮ በግልጽ የሚያስረዳ ነው።

ይህ የእነዚህ ጥቂት ሆድ አደሮች ጥርቅም ከአላሙዲ በሚቸራቸዉ ገንዘብ ከርሳቸውን ከመሙላት ባሻገር፤ ከነርሱና ከአላሙዲ ጀርባ የወያኔ አገዛዝ እንዳለበትና ዓላማውም ኢትዮጵያውያንን የመከፋፈል አጀንዳ ቅጥያ መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

ውድ ወገኖች!

በመስጠም ላይ ያለ ሰው፣ አድኖ ላያድነዉ አረፋም ቢሆን ይጨብጣል እንዲሉ፣ አንዴ በአባይ ስም፣ አሁን ደግሞ በስፖርት ሽፋን የተገመደው ተንኮል ለወያኔ የእግር እሳት የሆነበትን ዳያስፖራ ለማወናበድ የታለመ ነው። ታዲያ ይህን እየተካሄደ ያለውን ሴራ እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ለማክሸፍ ሃገርወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ እንሰለፍ።

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተመሰረተዉ Boycott TPLF ግብረሃይል ይህን በስፖርት ሽፋን ኢትዮጵያውያንን ለማወናበድና ለመከፋፈል የተዶለተውን ሴራ በጋራ እንድናከሽፍ ጥሪውን ያቀርባል።

በዋሽንግተን ዲሲ የወያኔ መልእክተኞች ትላንት ተቋቋምን ብለው ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥተው አዘጋጀን የሚሉትን ፌስቲቫል ሀገርወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዳትተባበሩ ጥሪ እናደርጋለን። በሚሊዮን ዶላር የተከራዩት ስታዲዮም የሰዓት እላፊ የታወጀበት መንደር ሆኖ ጭር እንዲል እንድናደርገው እንጠይቃለን።

በአንጻሩ ወደ ዳላስ ቴክሳስ በማምራት ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 7 ቀን 2012 ድረስ በሚካሄደው የሁላችንም መገናኛ፣ መዝናኛና የኢትዮጵያዊነት መግለጫ በሆነው 29ኛው በESFNA ፌስቲቫል ላይ በመሳተፍ በዓሉን የደመቀ እንድናደርገው እናሳስባለን።

የወያኔ ሴራ በየፈርጁ ይከሽፋል!
Boycott TPLF ግብረሃይል

Email: boycott.tplf@gmail.com
Tel: 703 828 4821

የንፁሃን ደም እንደፈሰሰ አይቀርም፤ አምባገነን ወያኔዎችም ከተጠያቂነት አያመልጡም!

Tuesday, July 3rd, 2012

ከአሰግድ ታመነ

የጥንት ታሪክ ነው። በሩስያ ውስጥ በጭካኔውና በአይለኝነቱ የሚታወቅ ጄኔራል ነበር። ታዲያ አንድ ህፃን በግቢው ሲያልፍ የጄኔራሉ ድንክ ውሻ ስትጫወት ያያታል ድንጋይም አንስቶ ሲወረውር የውሻዋን እግር ይሰብራታል። ጄኔራሉም ከስራ ሲምለስ ውሻው ስታነክስ በማየቱ ጠባቂዎችቹን ጠርቶ ማን እንደሰበራት በከፍተኛ ቁጣና ጩኸት ጠየቃቸው።
በአካባቢው ያለ አንድ ህፃን ነው ጌታዬ ድንጋይ ወርውሮ የሰበራት ይሉታል።
በሉ ይኽን ህፃን በፍጥነት ከእናቱ ጋር አምጡልኝ ይላል ጄኔራሉ በቁጣ።
ጠባቂዎቹም እንደታዘዙት ያመጧቸውና በጄኔራሉ ፊት ያቆሟቸዋል ህፃኑ በእናቱ እቅፍ ውስጥ ልመደበቅ የሚሞክር ይምስላል ደንግጠዋል ስል ጭካኔው በደንብ ያውቃሉና።

ልጁን እንድታወርደው የተነገራት የህፃኑ እናት እባክህ ጌታዬ ህፃን ልጅ ነው ምንም አያቅም የዛሬን ብቻ ማርልኝ ብላ ብትማፅነውም ከእጅዋ ላይ መንጭቆ ህፃኑን ካወረደ በኻላ ልጁን በሚያስፈራ ድምፅ ከዚህ ሩጥ ይልዋል::
ያ ቲኒሽ ልጅ ምክንያቱ ሳይገባው የሚያሳዝን አይኑን ወደ እናቱ አንዴ ደሞ ወደ ጄኔራሉ ቢያቁለጨልጭም የሚረዳው በማጣቱ በዝያች እግሩ መሮጥ እንደ ጀመረ አዳኝ ውሾች ይለቅበትና ብዙም ሳይሔድ ዘነጣጥለው ይበሉታል።

ታድያ ይህ ጨካኝ ጄኔራል በህዝቡ ላይ የሚፈፅመው ግፍ ይበረታና በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን ይወገዳል የተበደሉ ሰዎች እስር ቤት ሄደው ለምን እንዲህ እደረግክ ብለው ሲጠይቁት ስይጣን አሳስቶኝ ነው አለ ይባላል።

በ21 ዐመት የመለሰ ዜናዊ አገዛዝ ያላየነው ግፍና መከራ የለም ብዙ ህፃናት በየትምህርት ቤታቸው ደጃፍ ላይ ተገለዋል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በኦሮሚያ በአማራ በደቡብ በኦጋዴንና በ ጋምቤላ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋዎች በዚሁ የወያኔ መሪ መለሰ ዜናዊ ትህዛዝ ተፈፅመዋል።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር የነበረው ታምራት ላይኔ ስላደረሰው ግፍና ጭካኔ ከእስር ቤት ከወጣ በዋላ ሲጠየቅ ያለው ነገር ቢኖር ያኔ ሐይማኖት የለኝማ ነበር ሰይጣን አሳስቶኝ ነው የሚል መልህክት ያለው የይቅርታ አጠያየቅ መንገድ ነው የተጠቀመው። በሱ ትህዛዝ ግን በግፍ የሞቱት ሰዎች ደም በየሄደበት ይክተለዋል ጊዜው ይረዝማል እንጂ ለፍርድ መቅረቡ የማይቀር ሀቅ ነው።

የወያኔው መሪ አቶ መለሰ ዜናዊ በጠና ታመዋል በ G-8 ስብሰባ ላይ በጋዜጠኛ አበበ ገላው በደረሰባቸው ውርደት የተነሳ ከአንድ ወር በላይ በሚድያ ያልታዩት አቶ መለስ በደረሰባቸው እመም ለህክምና ቤልጂየም ብራስልስ ቆይተው በ G-20 ስብስባ ሜክሲኮ ላይ የፊት ገፃቸውና ሙሉ ስውነታቸው መሳሳት በጠና መታመማቸውን አሳብቆባቸዋል:: ከክሳታቸው ከመገርጣታቸው የተነሳ እኔ ሳያቸው በእውነቱ እድሜ ማራዘሚያ የሚወስዱ ነው የመሰሉኝ ።ታድያ እኚ ወንበዴ የሰይጣን ጆሮ ይስማውና ቢሞቱስ ኢትዮጵያ ትበታተናለች ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስታል እንዲያውም ሊለያየን ሊበታትነን የጣረውን በፅበል የማይወታው ሴይጣን ተገላገልነው ማለት አይደለም።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ ዘረኛና አንባገነን መሪ ብዙ ፍዳውን አይትዋል ብዙ ተሰቃይታል ባብዛኞቻችንም ሐገራችንን ጥለን በስደት እየተሰቃየን ነው። መብታችንን በመጠየቃችን ብቻ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረናል ታስረናል አሸባሪ ተብለናል ብዙዎችም ተገለዋል። ታዲያ ይህ አንባገነን የወያኔ መሪ መለሰ ዜናዊ ህመሙ ፅንቶ ወይም በሕዝብ ትግል ስልጣኑን ቢለቅና ስለፈፅማቸው ግፍና መከራ ለምንስ እንደ ፈፅማቸው ቢጠየቅ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው ሳይል ይቀራል ነገር ግን የትኛውም ምክንያት እነዚ ወንበዴዎችን ከነመርያቸው ከተጠያቂነትና ከፍርድ ሊያመልቱ አይችሉም ። ወይ የጋዳፊ ካልሆነም የሙባረክ እጣ እንደሚገጥማቸው እነሱም የሚያቱት አይመስለኝም ታዲያ ያኔ ስይጣን አሳስቶኝ ነው ሀይማኖት ስላልነበረኝ ነው….. ምናምን የሚል ምክንያት ከተጠያቂነት አያድናቸውምና።

ወያኔ መውደቂያው ስለተቃረበ እንዳበደ ውሻ እየተቅበዘበዘ ነው

Tuesday, July 3rd, 2012

ከ አሰግድ ታመነ
የወያኔ መሪ መለሰ ዜናዊ በዘረፋ የተባበሩዋቸው ዘሮቻቸው ለግል ጥቅማቸውና ለሆዳቸው ሲሉ ህዝባቸውን ለባርነት አሳልፈው የሸጡ የሌላ ብሄር ተወላጆች ስለራሳቸው ጥቅም እንጂ ስለ ኢትዮጰያ ሕዝብና ብሄራዊ ጥቅም ምንም ግድ የሌላቸው መሆናቸውን እስካሁን የሰሩት እኩይ ተግባር በቂ መረጃ ነው:: ላለፉት 21 አመታትም የህዝብን ይሁንታ ሳያገኙ በጠመንጃ ሀይልና ወያኔ ኢትዮጵያን ካልገዛ ሀገሪቱዋ ትከፋፈላለች በሚል ማስፈራሪያ የስልጣንና የውንብድና እድሜያቸውን ከራሳቸው ጥቅምና ስልጣን ጋር እንደ ሰአት ቦምብ አስተሳስረው ኢትዮጵያን ፍፁም ወደሆነ አምባገነን ስርአት አዘቅት ውስጥ ከተዋታል። የወያኔንና የሎሌዎቹን የውንብድና የህዝብና የሀገር ሀብት ዘረፋ እድሜ ለማራዘም እያሉ ኢትዮጵያዊያንን በተለያዩ ምክንያቶች በመከፋፈልና እርስ በእርሳቸው እንዲበጣበጡ ሲያደርጉ ቆይተዋል። እስካሁን ወያኔ በስልጣን ላይ የቆየው በፈጠረው ህዝብን በብሄር: በሀይማኖት: በቋንቋ: በጎጥ: በአናናር ዘይቤው: ከቀድሞ ስርአቶች ጋር በነበራቸው ትስስር ወዘተ መከፋፈልን በመፍጠር በጋራ ተባብረው ከወያኔ የበለጠ ሀይል እንዳይፈጥሩ በማድረግ ነበረ::

የህንንም የመከፋፈል ሴራ ተጠቅሞ ወያኔ በስልጣን ላይ መቆየት የሚያስችለውን ድርጅትም ሆነ አባላትን መመስረትና ማሰባሰብ አልቻለም:: ለዚህም ትልቁ ምስክሮቹ እራሱ ወያኔ የበሰበሰ የገማ ምናምን እያለ እስካሁን ድረስ ያካሄዳቸው ድርጅታዊና አቁዋማዊ ተሀድሶዎች; የአባላቶችና የደጋፊዎች በጥቅም የመተሳሰር; የህዝብና የሀገር ሀብት ዘረፋና ሙስናና ብልሹ አሰራር ናቸው:: አሁን ወያኔ ልክ እንደሱ በብሄር ደረጃ ከተደራጁ ፓርቲዎች ጋር እንኩዋን የመፎካከር አቅም የለውም ስለዚህ እያደረገው ያለው ተቃዋሚዎች ከወያኔ ያነሰ ድርጅታዊ አቅም እንዲኖራቸው ማድረግ ነው ለዚህም እኩይ ተግባሩ እያደረገ ያለው ህዝቡን በትንንሽ ቡድኖች እንዲደራጁና ከወያኔ ያነሱ እንዲሆኑ ማድረግ ነው:: የወያኔ ቡድኖችን የመከፋፈል ተግባሩ ሰሞኑን በሙስሊም ማህበረሰብ ላይ አነጣጥሮዋል::

በአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር ጉዳይ የተለኮሰው የሙስሊሞች ተቃውሞ በአዲስ አበባ በደሴ በከሚሴና በአሳሳ እየተቀጣጠለ እዚህ ደርስዋል። መረጃዎች እንደ ሚያሳዩት ከሆነ ሙስሊም ምእመናን በአወሊያ ትምህርት ቤት ና በአንዋር መስኪድ በየሳምንቱ ዓርብ የሚያደርጉት ተቃውሞ ወራትን አስቆጥሯል። ከዓርብ የጁምአ ስግደት ጋራ ተያይዞ በሚደረገው በዚህ የተቃውሞ ስብስብ ጎልተው የወጡት ተቃውሞዎች “የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቱን” (መጅሊሱን) አመራርና አሠራር እንዲሁም የመንግሥትን ጣልቃ ገብነትን የሚመለከቱ ናቸው። ተሰብሳቢዎቹ “አባይ ይገደባል፣ መጅሊስ ይወገዳል” የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ መሰንበታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል። “መጅሊስ አይወክለንም” “መሪዎቻችንን መንግሥት ሳይሆን ራሳችን እንምረጥ” የሚሉ ጥያቄ አዘል መፈክሮችም በስፋት ያሰሙ ሲሆን ተቃውማቸውንም በዚምታ አፋቸውን በ ፕላስተር በ መለጠፍ የገለጡበት ሁኔታም ነበር። በዚህም ተቃውሞ ፍርዶስን ጨምሮ ስድስት ሙስሊም ምእመናን ተገለዋል በርካቶች እስርና ድብደባ ደርሶባቸዋል።

ሌላው የተቃውሞ ምንጭ መንግሥት በሙስሊሙ ላይ “አህበሽ” የሚባለውን አስተምህሮ ለመጫን ያደርገዋል በተባለው ጫና ላይ ያነጣጠረ ነው። ከወራት በፊት መንግሥት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች “አሕበሽ” የተባለውን አስተምህሮ እንዲቀበሉ ጫና ለማድረግ መጀመሩና ይህም በርካታ የሃይማኖቱን ተከታዮችና ሌሎችንም ታዛቢዎች ማስቆጣቱ ይታወሳል።
‎ በአዲስ አበባ may 16 ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ በአማራ ክልል በላሊበላ የሚገኙ የሙሉ ወንጌል አማኞች ለአምልኮ የሚገለገሉበት ቤት ካለፍርድ ቤት ታሸገ ዜና አስነብቧል። በዚህም ወያኔ ፊቱን ወደ ፕሮቴስታንት በማዞር የአምልኮ ቦታቸውን ማሸግ ሌላ አጣብቂኝ ውስጥ ክቶታል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በኩል ደሞ ወያኔ በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል በሚገኘው ታላቁ የዋልድባ ገዳም አካባቢ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ፣ የፓርክ ይዞታ፣ እንዲሁም የመንገድ ጥርጊያ እሰራለሁ በሚል ሰበብ የዋልድባ ገዳም ይዞታን የተለያዩ ከባድና ቀላል የእርሻ መሳሪያዎችን በመጠቀም አጽመ ቅዱሳንን በማፍለስ፣ ቦታውንም በዶዘር በማረስ መጠነ ሰፊ የሆነ የጥፋት ዘማቻ ከጀመረ ውሎ አድሯል፤ ቦታው የመድኃኒዓለም ስም የሚወደስበት የሚሰለስበት ቅዱስ ቦታ ነው ያሉ ገዳማውያኑም ምህመናንም አቤቱታቸውን ቢያሰሙም ተቀባይነት ባለማግኝታቸው ከጎንደር ሕዝብና ከምሕመናን ጋር ጥርስ እንዳናከሰውና እንደ ተፋጠጡ እስካሁን አሉ ።
በእውነቱ ከሆነ ከወያኔ የተረፈን ነገር ቢኖር
1- አለመተማመን
2- ታሪክ መበረዝ
3- አባቶችን መስደብ
4- ደመኝነት
5- ዘረኝነት
6- መሬታችንን በመሸጥ በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ መሆን
በዚህም ምክንያት በየጊዜው ለድርቅና ረሀብ ለግጭትና ለመከራ ሲዳርጉን ህነዚህ የወያኔ መሪ ታሪካችንን እያጠፉ ከብሔር ብሔር ከጎሳ ጎሳ ከሃይማኖት ሃይማኖት እያጋጨ የትግራይን ሕዳሴ በማፋጠን ላይ ይገኛሉ፡፡
በመላው አገራችን እየተፈፀመ ላለውና ቀደም ሲል ለተፈፀሙት ኢሰብዓዊ ተግባር እዲሁም ታላቅዋ ትግራይ ለመመስረት እያደረሱ ያሉት ሌላውን በዘር የማጨፋጨፍ እንቅስቃሴ ከአቶ መለስ ጀምሮ ራሱን “በነጻአውጪ ግምባር” ስም ሰይሞ ኢትዮጵያን እየገዛ ያለውን ህወሃት/ኢህአዴግን፣ እንዲሁም በተዋረድ እስከታች ድረስ ትዕዛዝ ፈጻሚ የሆኑትን ሁሉ በቀጥታ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፡፡

አርቲስቶችና ነጋዴዎች በአላሙዲን AESAONE ዲሲ ፌስቲቫል ላይ እንዳይሳተፉ እንጠይቃለን

Thursday, June 28th, 2012

[Read in PDF]

የመለስ ዜናዊ አምባገነናዊ አገዛዝ አንጋፋዉን በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን ለማፍረስ የአላሙዲንን ገንዘብ ተጠቅሞ ህሊናቸውን በሸጡ ሆድአደር ወኪሎቹ አማካይነት የሰላም የሆነውን የስፖርት መድረክ በተለመደ የከፋፍለህ-ግዛ ፖሊሲው መጠቀሚያ ለማድረግ በስም አመሳስሎ ሊያደናግር ቢሞክርም በፍትህ አደባባይ ከተረታ በኋላ “AESAONE” የሚል ስም አውጥቶ እኩይ ዓላማውን ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በአላሙዲ አማካይነት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ዓላማቸውን ለማሳካት በገንዘብ እናሸንፋቸዋለን ያሉዋቸውን አርቲስቶች የበዓሉ አድማቂ እንዲሆኑ እና ለተሳታፊነትም በተለያዩ ግዛት ለሚገኙት የወያኔ ደጋፊዎች የጥሪ ዘመቻ ይዘዋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከላይ እስከ ታች በህወሃት ሰዎች ተይዞ ድርጅቱን የአፍሪካ መኩሪያ ያሰኙትን ዕውቀትና ልምድ ያላቸውንና በሙያቸው ከአገር አልፈው በዓለም ዕውቅና ያተረፉ ኢትዮጵያውያን ፓይለቶችን፣ የበረራ አስተማሪዎችን፣ ቴክኒሽያኖችን እና የማኔጅመንት ሰዎችን በማሳደድ የሽያጭ ስራውን ጭምር ለሕንድ እየሰጠ የበርካታ አገር ዜጎችን በከፍተኛ ገንዘብ እየቀጠረ ለህወሓት ሰዎች ግልፅ መጠቀሚያ ሆኗል። በውጭ ጭምር ለህወሃት ሰዎች የፓርቲ ድግስ የነፃ የትኬት ቶምቦላ መስጠቱ ሳያንስ አሁንም የወያኔውን የዲሲው ፌስቲቫል በስፖንሰርነት በመሰለፍ ከአገር ውስጥ ካድሬዎችንና ለበዓሉ ይመጣሉ ለሚባሉ ሁሉ የነፃ ትኬት እየሰጠ የስርዓቱ ወገንተኛና ግልፅ መገልገያ መሆኑን አረጋግጧል።

በዚህ በስፖርት ስም በሚካሄድ ዲያስፖራን የማከፋፈያ ፌስቲቫል ላይ የወገናቸው መከራ የሚታሰባቸው፣ ዛሬ አገራችን የገባችበት ኢኮኖሚያዊ አዘቅትን የተገነዘቡት በተለያዩ ንግድ የተሰማሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ አርቲስቶችና ነጋዴዎች ባይሳተፉም ጥቂቶች ግን እንደሚሳተፉ ለማወቅ ችለናል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች በወያኔው ፌስቲቫል ላይ ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን።

ይህን የወያኔን የከፋፋይ ሴራ የሚቃወም ጥሪ ባለመቀበል በዝግጅቱ ላይ የሚሳተፉትን አርቲስቶችና ነጋዴዎችን እያወገዝን ህብረተሰቡ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ካገራቸውና ነፃነታቸው ይልቅ ሆዳቸውን ያስቀደሙትን ለይቶ ሊያጋልጣቸው ይገባል።

በወያኔ ሆድ አደሮች ሽንገላ ባለመደናገር ክብራችን ከሆዳችን ይበልጣል! ከወገኖቻችን ገዳዮች ጋር አናብርም! በማለት በወያኔው ፌስቲቫል ላይ ሀገረ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዳትገኙ እናሳስባለን።

በወያኔው ፌስቲቫል ላይ መሳተፍ ማለት ዛሬ በጋምቤላ የአዶልፍ ሂትለርን የግፍ ተግባር በሚያስታውስ መልኩ ንፁሃንን ገሎ ሬሳቸውን በቤንዚን ያቃጠለውን፣ ዜጎችን በገዛ አገራቸው ዘራቸውን እየቆጠረ አማራ ይውጣ ሲል ከጉራ ፈርዳ በ70 ሺህ የሚቆጠሩትን ያፈናቀለውን፣ ፋሽስት ኢጣሊያ እንዳደረገው በጎንደር ንፁሃንን ገድሎ ሬሳቸውን መንገድ ለመንገድ በመኪና ለጎተተው፣ የታሪክና የሀይማኖት ቅርሳችንን ዋልድባን በልማት ስም የሚያፈርሰውን፣ የዕምነት ነጻነታችን ይከበር ያሉ ሙስሊም ወገኖቻችንን በአርሲ አሳሳ በመስጊድ ዉስጥ የገደለና የሙስሊሙን ህብረተሰብ ህጋዊ ጥያቄ ወደ ጎን አድርጎ አሸባሪ ሲል ስም የለጠፈውን፣ ጋዜጠኞችን፣ ነፃ አሳቢ ዜጎችንንና ተቃዋሚዎችን አስሮ የሚያሰቃየውን፣ ኦሮሞነትን ወንጀል አድርጎ እስር ቤቶችን በኦሮሞ ወገኖቻችን እያጣበበ ያለውን በኦጋዴን በወልቃይት፣ በአፋር ወገኖቻችን ላይ በጅምላ ግድያና በዘር ማጥፋት ወንጀሉ የገፋበትን በአጠቃላይ የስርዓቱን የመብት ረገጣና የአገር ሀብት ዝርፊያ መደገፍ ነው ብለን እናምናለን።

ስለዚህ አርቲስቶችም ሆኑ ነጋዴዎች እንደነፃነት ወዳድ ወገኖቻችን ሁሉ የወያኔውን የዋሽንግተን ዲሲ ከፋፋይ ፌስቲቫል አንሳተፍም በማለት በገንዘብ ማንንም ባሪያ አድርገን እንገዛለን ላሉት እብሪተኞች ትምህርት ልንሰጣቸዉ ይገባል ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Boycott TPLF Task Force
boycott.tplf@gmail.com
Tel: 202 656 5117

አላሙዲ ያዘጋጀው የወያኔ ፌስቲቫልን ለማክሸፍ የተጠራ ሰልፍ – እሁድ 5 PM

Thursday, June 28th, 2012

ለሆዳቸዉ ያደሩ የአላሙዲ አሽከሮች AESAONE በሚል ስም ዋሽንግተን ዲሲ ያዘጋጁትን የወያኔ ፌስቲቫል ለመቃወም በተዘጋጀዉ ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያነ ሁሉ እንድትገኙ እንጠይቃለን።

ሕጻናት በርሃብ ከሚቆሉባት ሃገራችን የተፈጥሮ ሃብትዋ በወያኔና አላሙዲ ሽርክና እየተበዘበዘ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ለዋልጌዎችና ሆድአደሮች ያስረሽ-ምቺዉ ፌስቲቫል እየባከነ ነዉ። የዚህ ፌስቲቫል ዓላማ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈልና በገንዘብ ሃይል ለዘረኛዉ ወያኔ የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ድጋፍ ለመግዛት ነዉ።

በRFK Stadium በተዘጋጀው የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ በመገኘት እነማ የኢትዮጵያን ሕዝብ መከራና ስቃይ ችላ በማለት ለሆዳቸው እንዳደሩና ስብእናቸዉን ለገንዘብ እንደሸጡ ለይተዉ ይወቋቸዉ።

ቀን፡ እሁድ July 1, 2012.
ሰዓት፡ 5፡00 PM
ቦታ፡ RFK Stadium, Washington DC.

የአንዱአለም አራጌ የዛሬው የፍ/ቤት ውሎ የመጨረሻ ንግግር

Wednesday, June 27th, 2012

ያሳለፍነው ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰብአዊ ክብሩና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የታገለበት ዘመን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ባለቤት ለመሆን እስካሁን አልታደለም፡፡ እኔም በተፈጠርኩበት በዚህ ዘመን ለራሴ፣ ለልጆቼና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ዴሞክራሲና ነፃነት እንደሚገባን በማመን አቅሜ በፈቀደው መጠን ታግያለሁ፡፡ ይኼን በማድረጌ በማንም ላይ በክፋት አልተነሳሁም፤ ይኼን በማድረጌ ህግ ጥሼ አላውቅም፤ ይኼን በማድረጌ በደሃዋ ሃገሬ ጥቅም ላይ አልተነሳሁም፤ ይሄን በማድረጌ ፈጣሪዬን፣ የኢትዮጵያን ህዝብም ሆነ ህሊናዬን የሚያሳዝን አንዳች ነገር ፈፅሜያለሁ ብዬ አላምንም፡፡ ፍፁም ሰላም ይሰማኛል፡፡ እኔን እዚህ ያቆመኝ የነፃነት ናፍቆት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችም ፍትህን ለምኜ ስነፈግ ይኼ የመጀርያዬ አይደለም፡፡ ከሳሾቼ እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ፅዋ በፀጋ ከመጠጣት ውጪ ባልፈረፀምኩት ወንጀል ማቅለያ የመጠየቅን አማራጭ ህሊናዬ ስላልተወልኝ አዝናለሁ፡፡

የሽግግር ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ከጁላይ 1 እስከ 3 ባሉት ቀናት በዳላስ ከተማ ይካሄዳል

Tuesday, June 26th, 2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ከጁላይ 1 እስከ 3 ባሉት ቀናት በዳላስ ከተማ ይካሄዳል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት እንደ ድርጅት የተቋቋመው ከጥቂት ወራት በፊት ሲሆን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ከዳር ቆመው ሲቆጩ የነበሩትን ኢትዮጵውያንን፤ ከአሜሪካ፤ ከካናዳ፤ ከአውሮፓ፤ ከአፍሪካ፤ ከሰላሳ በላይ ባሉ የአካባቢ ቻፕተሮች አሰባስቦ ለማደራጀት ችሏል። ይህ ድርጅት የሚከተሉትን ዋና ዋና አላማዎች ግንባር ቀደም ያደረገ ነው፤

  • ባገራችን ጉዳይ ላይ በድርጅት ዙሪያም ሆነ በግለሰብ ያለመሰልቸት የሚታገሉትን ወገኖችን፤ እንዲሁም በምንም ምክንያት ተገፍቶ በአገሩ ጉዳይ ላይ እንዳይሳተፍ የተገደደውንና ነገር ግን የኢትዮጵያ ስቃይ የሚያንገበግበውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአንድ መርህ ዙሪያ ማሰባሰብ – ይህም መርህ ኢትዮጵያ ባስቸኳይ የስረዓት ለውጥ እንደሚያስፈልጋት በማመንና የሚተካው ስራዓትም የቀድሞ ስህተቶችን መድገሚያ ሳይሆን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የኢትዮጵያውያን ነጻነት የሚረጋገጥበት እንዲሆን ማስቻል
  • በመላው አለም የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን ከላይ ለተገለፀው ግብ መሳካት ሃይላችንን አስተባብረን የምንታገልበትን ስልት በተቀናጀና ዲሞክሪያሲያዊ በሆነ መንገድ መምራት
  • ስርአቱ ሲገረሰስ የሽግግሩን ሂደት ፈር የያዘና የኢትዮጵያን ህዝብ እውነተኛ የስልጣን ባለቤትነት የሚያረጋገጥ እንዲሆን ማስተባበር፤ ለዚህም ህዝባዊ ውይይቶችና ቅድመ ዝግጅቶች ከአሁኑ መጀመር
  • ከእንግዲህ ወዲያ በአገራችን ስልጣን ለህዝብ አገልጋዮች እንጂ ለጨቋኞች እንደማይውል አረጋግጠን ወደየምንወደው ስራዎቻችን መሰማራት

በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ከመቼውም በላይ በአደጋ ላይ ያለች በመሆኑ የእያንዳንዱ አገር ወዳድ ዜጋ ተሳትፎ ወሳኝነት ይኖረዋል። ኢትዮጵያ ከመቼውም በተለየ ድምጽ ለልጆችዋ የአድኑኝ ድምጽ እያሰማች ነው። ከዳር ቆመን ዜና በመከታተልና በየቤታችን በመወያየትና በመተቸት ብዙ ፋይዳ እንደማይኖር ተገንዝበን የተነጠቅነውን የመኖር መብት ለማስመለስ ለተግባር የምንነሳበት ጊዜ ይሆናል። ከዚህ በኋላ ምንም ሰበብ አይኖረንም – ታሪክ የመስሪያ ጊዜ አሁን ነው!!

ይህ ታላቅ መስራች ጉባአኤ የሚካሄደው ከጁላይ 1 – 3 በዳላስ ማርዮት ሆቴል ይሆናል።

አድራሻ፡
Dallas/Addison Marriott Court Yard Quorum
14901 DALLAS PARKWAY
Dallas TX, 75254

በይበልጥ ለመረዳት በድህረ ገፃችን WWW.ETNTC.ORG
በስልክ ቁጥር፡ 202-735-4262
በኢሜይል፡ entc.pr@gmail.com ልታገኙን ትችላላችሁ።

ኢትዮጵያን በተባበረ ድምፃችንንና ትግላችን ከአደጋ እናድናታለን! እግዚአብሔር አገራችንንና ህዝባችንን ይባርክ!

ብላቴን ጌታ ሎሬንዞ ታዕዛዝና ኢትዮጵያዊነት

Saturday, June 23rd, 2012

ፕ/ር ዳንኤል ክንዴ

ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ነፃነትና ዕድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ብዙ የኤርትራ ተወላጆች ነበሩ፣ አሁንም አሉ። ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል ከፍተኛውን ቦታ ይዘው የሚገኙት ብላቴን ጌታ ሎሬንዞ ታዕዛዝ ናቸው። ብላቴን ጌታ ማለት የንጉሥ ዋና ጉዳይ ፈጻሚ ማለት ነው።

እኝህ ሰውዬ የት ነበር የተወለዱት? ኤርትራ የኢጣሊያን ቅኝ ግዛት በነበረችበት ወቅት እንዴት ብለው ነው ከአገራቸው ሊወጡ የቻሉት? በጊዜው ጀኔቫ በነበረው የዓለም መንግሥታት ማኅበር ውስጥ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እንዴት ሊሆኑ ቻሉ? ከጦርነቱ በኋላስ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዴት ሊሆኑ ቻሉ? ለኢትዮጵያ ብዙ ሥራ ይሠራሉ ተብሎ ይታሰብ በነበረበት ወቅት እኝህ ታላቅ ሰው ገና በወጣትነት ዘመናቸው በተወለዱ በ46ኛው ዓመታቸው ስዊድን ላይ ሞቱ። ስለአሟሟታቸው ብዙ ነገር ይወራል፤ ዕውነቱ ግን የት ላይ ነው? … ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በዋሽንግተን – ጁን 24

Saturday, June 23rd, 2012

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ መግለጫ

Monday, June 11th, 2012

ከሃያ ሁለት ወራት ዝግጅት በኋላ፣ ከግንቦት 10 ቀን እስከ ግንቦት 13 ቀን 2004 ዓ.ም. (ሜይ 2012) ድረስ በካናዳ ዋና ከተማ በኦታዋ የተካሄደው ሁሉን አቀፍ የአንድነት ግንባር ምሥረታ ጉባኤ፣የልዩ ልዩ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ሲቪክ ማህበራትና ግለሰቦች ተሳትፈውበት በደረሱበት ስምምነት መሰረት “የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ” መመስረቱ የሚታወስ ነው። የሸንጎው አመራር ምክር ቤት ሥራውን በመጀመር የመጀመሪያውን መደበኛ ስብሰባ በግንቦት 20 ቀን 2004 .ም.(28-05-2012) አካሂዷል። በዚህ ስብሰባው የተለያዩ የሥራ ዘርፎችን የዘረጋ ሲሆን በእያንዳንዱ የሥራ ዘርፍ ውስጥ ገብተው የሚያገለግሉትን አባላት መድቧል። የስራ መመሪያዎችንም ሰጥቷል። በሀገራችን ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እንደገና ከዳሰሰ በኋላም አንዳንድ ውሳኔዎችን ወስኗል። … ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የምግብ ዋስትና አለም አቀፍ ስብሰባ፤ ጠቃሚነቱ ለኢትዮጵያዊያን ነውን?

Friday, June 8th, 2012

ክፍል፡ አራት

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

ዛሬ፡ ሃገራችን፡ ኢትዮጵያ፤ የምትታወቅበት፡ አበይት፡ መለኪያ፡ የነጻነት፡ መዲና፤ የመላው፡ ጥቁር፡ ህዝቦች፡ የነጻነት፡ መኩሪያ፤ የአፍሪካ፡ አንድነት፡ ማህበር፡ ዋና፡ መናገሻ፤ የክርስቲያንና፡ የእስልምና፡ ተከታዮች፡ በሰላም፡ መኖሪያ፡ ሳይሆን፡ ህወሓት፡ ሆነ፡ ብሎ፡ በዘር፡ የከፋፈላት፤ የህግ፡ የበላይነት፡ የሌለባት፤ከአስር፡ እስከ፡ አስራ-ሶስት፡ ሚሊዮን፡ የሚሆኑ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ በለጋስ፡ ሃብታም አገሮች፡ የሚመገቡባት፡ መሆኗ፤ ለም፡ መሬቷና፡ ወንዞቿ፡ በልማት፡ ስም፡ በሳንቲም፡ የሚሸጡባት፤ እስከ፡ ዘጠና-ዘጠኝ፡ አመታት፤ ለውጭ፡ መንግስታትና፡ ሃብታሞች፤ ለተወሰኑ፡ ታማኝ፡ የሆኑ፡የትግራይ፡ ተወላጆች፤ የሚቸረቸሩባት፡ አገር፡ መሆኗ፡ ነው። ህወሓትና፡ ደጋፊወቹ፡ ይህን፡ ሃቅ፡ ይክዳሉ። እንዲያውም፡ የገጠር፡ እኮኖሚው፡ አስደናቂ፡ መዋቅራዊ፡ ለውጥ፡ አሳይቷል፤ የገጠር፡ ሚሊየነሮች፡ ተፈጥረዋል፡ ይላሉ። እነሱ፡ በሚሉትና፡ በአብዛኛው፡ ህዝብ፡ ያለው፡ አመለካከት፡ ሊገናኝ፡ አልቻለም። የህወሓት፡ ባለስልጣኖች፤ “በሬ፡ ወለደ፡ ብሎው፡” እኛን፡ ብቻ፡ ሳይሆን፡ አለምን፡ ለማሳመን፡ ይሞክራሉ። ለታዛቢወች፡ አስደናቂ፡የሆነው፡ ህወሓት፡ አመኔታ፡ የሌላቸውን፡ ማስረጃወች፡ እንደ፡ እውነት፡ ማቅረቡ፡ ሳይሆን፡ ሌሎቻን፡ ማመናችን፡ ነው። ለምሳሌ፡ እድገቱ፡ ፍትሃዊ፡ ነው፡ ሲሉን፤ ዲሞክራሲ፡ አለ፡ ሲሉን፤ እርሃቭ፡ የለም፡ ሲሉን፡ ያለ፡ ጥያቂ፡ እንቀበላለን። ድሃው፡ ህዝብ፡ የሚያየውን፡ እኛ፡ አናይም። ድህነት፡ እየጠፋ፡ ነው፡ ሲሉን፡ እንቀበላለን። ድህነት፡ ከጠፋ፡ ለምን፡ እንሰደዳደለን፡ ብለን፡ አንጠይቅም። አገራችን፡ ከምርጫ፡ ዘጠና፡ ሰባት፡ በኋላ፡ አስራ፡ አንድ፡ በመቶ፡ አድጋለች፡ ከተባለ፡ ይህ፡ እድገት፡ የአብዛኛውን፡ ህዝብ፡ ኑሮ፡ እንዴት፡ አለወጠውም፡ ብለን፡ ስንጠይቅ፡ ህወሓትና፡ ደጋፊወቹ፡ ለውጦታል፡ ይላሉ። እኛም፡ ይህ፡ እውነት፡ እንደሆነ፡ የብልጭልጭ፡ እድገቱን (ቪላ፣ ህንጻ፤ መንገድ፡ ወዘተ፡ መሰራቱን) እንደ፡ ፍትሃዊ፡ ልማት፡ ማየታችን፡ ቀጥሏል። ለዚህ፡ ነው፤ ዛሬ፡ በኢትዮጵያ፡ ውሸቱንና፡ እውነቱን፡ ለመለየት፡ አይቻልም፡ ለማለት፡ የሚያስደፍረው።

እድገቱ፡ ማንን፡ ጠቀመ? ማን፡ ሃብት፡ እያካበተ፡ ነው?

የእድገቱ፡ ውጤት፡ ለማን፡ ጠቃሚ፤ ለማን፡ ጎጂ፤ መሆኑን፡ ለማየት፡ የተራውን፡ ህዝብ፡ ኑሮ፡ ማየቱ፡ ብቻ፡ ይበቃል። የዋጋ፡ ግፍሸት፡ ጥሩ፡ ኑሮ፡ ይኖሩ፡ የነበሩትን፤ ወደ፡ ድህነት፡ እየመራ፡ ነው። ሌላው፡ የዛሬይቱ፡ ኢትዮጵያ፡ መገለጫ፡ ፍትህ፤ ነጻነት፤ የህግ፡ የበላይነት፤ የህዝብ፡ ድምጽና፡ ተሳትፎ፡ የሌለባት፤ በአንድ፡ ጠባብና፡ ትምክህተኛ፡ የንኡስ፡ ብሄርተኛ፡ የበላይነት፡ የሚመራ፡ ፓርቲ፡ የሚገዛት፤ ለሃያ፡ አንድ፡ አመታት፡ ጠቅላይ፡ ሚኒስትሯ፡ መለስ፡ ዜናዊ፡ የተባሉ፡ አምባ፡ ገነን፡ እንደ፡ ቤታቸው፡ የሚያዙባት፡ አገር፡ መሆኗ፡ ነው። የችግሩ፡ እምብርት፡ ይህ፡ ነው። መለስ፤ ይህንም፡ እንደ፡ ሌለ፡ ይነግሩናል። የማይቀበሉት፤ ኢትዮጵያ፡ እድገት፡ እየታየ፡ ድህነት፡ የሚሰፋባት፤ የእርሻ፡ እድገት፡ አለ፡ እየተባለ፤ እርሃቭ፡ በጥልቀት፡ የሚታይባት፡ አገር፡ መሆኗን፡ ነው። ሌላም፡ የማይቀበሉት፡ አበይት፡ ጉዳይ፡ አለ። የህወሓት፡ መንግስት፡ በተከታታይ፡ ምርጫን፡ በግድም፡ ሆነ፡ በውድ፡ አሸንፋለሁ፡ ብሎ፡ ሲነሳ፡ በኢኮኖሚው፡ በኩል፡ ውጤት፡ ማሳዩት፡ እንዳለበት፡ የተገነዘበው፡ ከምርጫ፡ ዘጠና፡ ሰባት፡ በኋላ፡ መሆኑን፡ የሚያሳዩ፡ ማስረጃወች፡ አንዳፈር፡ ናችው። ክዚያ፡ በፊት፡ በመዋእለ፡ ንዋይ፡ መልክ፡ በብዙ፡ ቢሊየን፡ ብር፡ የፈሰሰው፡ ክልል፡ አንድ፤ ትግራይ፡ ነበር። ይህ፡ የማያዋጣ፡ መሆኑን፡ የተረዳው፡ አመራር፡ መሰረተ፡ ልማት፡ ያሰፋፋው፡ ከምርጫ፡ ዘጠና፡ ሰባት፡ በኋላ፡ ነው። የዚህን፡ አዲስ፡ አቅጣጫ፡ ጥቅም፡ ቢያንስ፡ ከሁለት፡ ጎኖች፡ እንየው። አንዱ፡ ስልጣንን፡ ለማቆየት። ሌላው፡ ሃቭትን፡ አገር፡ አቀፍ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ ለገዡ፡ ፓርቲና፡ ለደጋፊወች፡ ለማስፋፋት፡ ነው። ይህ፡ ደግሞ፡ ለይስሙላም፡ ቢሆን፡ ሌሎችን፡ ማቀፍ፡ ነበረበት። ከታቀፉት፡ መካከል፡ በግልጽ፡ የሚታየው፡ የውጭ፡ ባለ፡ ሃብቶችና፡ ምርጥ፤ ታማኝ፤ የትግራይ፡ አዲስ፡ ሃብታሞች፡ አገር፡ አቀፍ፡ ሚና፡ ማግኘታቸው፤ ከመንግስት፡ ጥበቃ፡ መጎናጸፋቸው፡ ነው። የጥቅም፡ ሰንሰለት፡ እየጠነከረ፡ የሄደው፡ ለዚህ፡ ነው።ይህ፡ ሰንሰለት፤ ህወሓት፡ በሚፈልገው፡ ደርጃ፡ የሚያስተጋቡ፡ ተጠቃሚወችን፡ አስፍፍቷል። ይህ፡ የመሰረተ፡ ልማት፡ መስፋፋት፡ ግን፡ መዋቅራዊ፡ ለውጥ፡ አላመጣም። ግብርናን፡ እንይ።

የእርሻ፡ እድገት፡ አስደናቂ፡ ነው፡ በሚባልባት፡ ኢትዮጵያ፤ ባለፈው፡ አመት፡ ህወሓት፤ ስምንት፡ ሚሊዮን፡ ቶን፡ እህል፡ ሸምቷል። ህወሓትና፡ ደጋፊወች፡ ይህን፡ የሽመታ፡ ጥገኝነት፤ ይክዳሉ፤ ወይንም፡ መግለጫ፡ ይሰጡበታል። የሚሉት፤ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ እድገትንና፡ ዲሞክራሲን፡ ከተጎናጸፈ፡ ቆይቷል፡ ነው። ቢያንስ፤ እየተጎናጸፈ፡ ነው። አቅርቦት፡ ከፍላጎት፡(supply and demand) ጋር፡ የማይስማሙት፡ ህዝብ፡ እየጨመረ፤ ፍሎጎት፡ እያደገ፡ ስለሄደ፡ ነው፡ ይላሉ። መለስ፡ ክፍተቱንና፡ የዋጋ፡ ግፍሸትን፡ የእድገት፡ ምልክት፡ ነው፡ ይላሉ። በእድግትና፡ የውጭ፡ እርዳታ፡ ሲታይ፤ ኢትዮጵያ፡ በአመት፡ አራት፡ ቢሊየን፡ ዶላር፡ ታገኛለች። ስለሆነም፤ በመሰረተ፡ ልማትና፡ በፍጆት፡ ላይ፡ የፈሰሰው፡ መዋእለ፡ ንዋይ፡ የተመሰረተ፡ እድገት፡ መኖሩ፡ አያስደንቅም፤ ባይኖር፡ ያስደንቅ፡ ነበር። ቁም፡ ነገሩ፤ የእድገቱ፡ ውጤት፡ የሚያሳየው፡ ፍትሃዊ፤ ተሳትፏዊ፡ አለምሆኑን፡ ነው። የቁጥጥር፡ ፖለቲካው፡ የቁጥጥር፡ ኢኮኖሚን፡ ወልዷል፡ ለማለት፡ ይቻላል። የተወለደው፡ የምጣኔ፡ ሃብት፡ የሚያደላው፡ ለፈጠረው፡ ህወሓትና፡ ለደጋፊወቹ፡ ስለሆነ፡ ፍትሃዊ፡ ለመሆን፡ አይችልም። አብዛኛው፡ የእርዳታ፡ ገንዘብ፡ ይሰረቃል፤ ከሃገር፡ ህገወጥ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ ይወጣል። Global Financial Integrity እንዳሳየው፡ በ2000-2008: ብቻ፡ 12 ቢሊዮን፡ ዶላር፡ ተሰርቋል። ቢያንስ፡ በአመት፡ ሶስት፡ ቢሊየን፡ ዶላር፡ ከአገር፡ ይውጣል። በንጥር፡ (Net inflow) ሲታይ፤ እርዳታውና፡ ወደ፡ ውጭ፡ የሚላከው፡ የእቃ፡ ገቪ፡ በሙሉ፡ ይሰረቃል፡ ማለት፡ ነው። ስርቆቱና፡ ሙስናው፡ ቢኖር፡ ባይኖር፤ እርዳታ፡ ያለ፡ ህዝብ፡ ተሳትፎ፤ ያለ፡ ቁጥጥር፤ ያለ፡ ሕግ፡ አገርን፡ ለማልማት፡ አይችልም። ቢችል፡ ኖሮ፤ የአለም፡ ለጋሽ፡ አገሮች፡መለማመጃ፡ የሆነች፡ ኢትዮጵያ፡ አሁን፡ እንደ፡ ምስራቅ፡ ኤዥያ፡ ድንቅ፡ አገሮች፡ መሆን፡ በቻለች፡ ነበር። የሚታየው፡ ሃቅ፡ ግን፤ የውጭ፡ እርዳታ፡ ሙስናን፤ ስርቆትን፤ የሃብት፡ ሽሽትን፤ ኪራይ፡ ሰብሳቢነትን፤ የሃብት፡ ክምችን (concentration of incomes and assets)፤ ጥገኝነትን፡ አጠንክሯል። ተከታታይ፡ ሙስና፤ ስርቆት፤ አድሎ፤ ጥገኝነት፡ የእድገት፡ ምልክት፡ አይደለም። ከጥቅሙ፡ ጉዳቱ፡ ያመዝናል፡፡በኢኮኖሚው፡ በኩል፡ ሲታይ፤ የመለስ፡ መንግስት፡ ያመጣው፡በደል፡ ሙስና፤ ኪራይ፡ ሰብሳቢነት፤ ስርቆት፤ጥገኝነት፤ የመንግስትን፡ ሃብት፡ ወደ፡ ፓርቲው፡ ባለስልጣኖች፡ ምርጥ፡ ግለሰቦች፡ ማዘዋወር፤ ነው። ይህን፡ የአገዛዝ፡ በደል፡ አብዛኛው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ያውቀዋል። እድገት፡ አለ፡ ብለው፤ የሚያመሰግኑት፡ ተጠቃሚወች፡ ናችው። ለጋስ፡ የሆኑ፡ የውጭ፡ መንግስታትና፤ አበዳሪ፡ ድርጂቶችም፡ እድገት፡ አለ፡ ብለው፡ ሲናገሩ፡ ማስረጃውን፡ የሚያገኙት፡ ክህወሓት፡ ነው። ተጠቃሚወች፡ በመሆናችው፤ ለጠፋው፡ ገንዘብ፡ ተጠያቂ፡ እንዳይሆኑ፤ ታክስ፡ የሚከፍለው፡ ህዝባቸው፡ እርዳታ፡ ጥቅም፡ አለው፡ ብሎ፡ እንዲቀበል፡ ጭምር፡ ሙከራ፡ በማድረግ፡ ነው። የቱኒሲያና፡ የግብጽ፡ አመጽ፡ በተካሄደበት፡ ወቅት፡ አለም፡ ባንክና፡ አይ፡ ኤም፡ ኤፍ፡ በእነዚህ፡ አገሮች፡ እድገት፡ አለ፡ ይሉ፡ ነበር። ፍትሃዊ፡ እድገት፡ ቢኖር፡ ኖሮ፡ የብዙ፡ ሰላማዊ፡ ሰወች፡ ህይወት፡ የተሰዋበት፡ ለውጥ፡ ባላስፈለገ፡ ነበር። ለዚህ፡ ነው፤ ዛሬ፡ በአበዳሪ/ለጋስ፡ አገሮችና፡ በኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ መካከል፡ ያለው፡ የአመለካከት፡ ልዩነት፡ ሰማይና፡ ምድር፡ የሆነው። የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ አበዳሪወችን፡ የሚያያቸው፡ ልክ፡ ገዡውን፡ ፓርቲ፡ እንደሚያየው፡ ነው። በሁለቱም፡ ላይ፡ እምነት፡ የለውም። Human Rights Watch: ያወጣውን፡ ዘገባ፡ ማየት፡ ይበቃል። እርዳታ፡ አቅምን፡ ካልገነባ፤ ሰብ አዊ፡ ክብርን፡ ካላስተጋባ፤ ራስን፡ ካላስቻለ፤ አገራዊ፡ እድገትን፡ ጭብጥ፡ ካላስደረገ፡ ጥቅሙ፡ የት፡ ላይ፡ ነው?

የውጭ፡ መንግስታት፡ ሆኑ፡ አበዳሪወች፡ የሚመሩት፡ በራሳቸው፡ ጥቅም፤ ለራሳቸው፡ ጥቅም፡ እንጂ፡ ለኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ሰላም፤ አቅም-ግንባታ፤ ነጻነት፤ ፍትህ-ርትእ፤ ሉአላዊነት፤ ሁለ-አቀፍ፡ ልማት፡ አይደለም። ለዚህ፡ነው፡ የአሜሪካው፡ ፕሬዘደንት፤ ባራክ፡ ኦባማ፡ መለስ፡ ዜናዊይ፡ የሚሰሩትን፡ ጥፋት፡ እያወቁ፡ የስምንቱ፡ ሃብታም፡ አገሮች፡ ስብሰባ፡ ተካፋይ፡ አድርገው፡ ከኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ያላገኙትን፡ ማእረግ፡ ሰጥተው፡ በዋሽንግተንና፡ በካምፕ፡ ዴቪድ፡ እንዲገኙ፡ የጋበዟቸው። ይህ፡ ክብር፡ ከሶስቱ፤ የጋና፤ ታንዛኒያና፡ ቶጎ፡ መሪወች፡ ጋር፡ ሲነጻጸር፡ የመለስ፡ ዜናዊ፡ መሳተፍ፡ ለምእራብ፡ አገሮች፤ በተለይ፡ ለአሜሪካ፡ መንግስት፤ መለስ፡ በአፍሪካ፡ ቀንድ፡ ጠቃሚነታቸውን፡ የሚያሳይ፡ እንጂ፡ ለኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ታዛዥ፡ መሆናቸውን፡ ገላጭ፡ የማይሆነው። ከጋናው፡ ፕሬዘደንት፡ ሚልስ፡ ጋር፡ አይወዳደሩም። ጋና፡ የህዝብ፡ ድምጽ፡ የተከበረባት፤ ኢትዮጵያ፡ አንድ፡ ንኡስ፡ ብሄርተኛ፡ ቡድን፡ የሚገዛት፡ ናት። ይህ፡ ቡድን፡ የፖለቲካ፡ ስልጣን፡ ተጠቅሞ፡ የአገሪቱን፡ ወሳኝ፡ የኢኮኖሚ፡ ክፍሎች፡ (Pillars of the national economy)፤ በሙሉ፡ በቁጥጥር፡ ይዟል። ይቨቃኛል፡ የሚል፡ መንፈስ፡ የለውም። ይህ፡ ከቀጠለ፤ ማን፡ ሃብታም፤ ማን፡ ድሃ፤ ማን፡ ገዥ፤ ማን፡ ተገዥ፤ ማን፡ ስደተኛ፤ ማን፡ አዲስ፡ ተጠቃሚ፡ እንደሚሆን፡ ለመተመን፡ አያስቸግርም። የዘር፡ ማጥፋትን፡ ዘመቻ፡ የማየው፡ ከዚህም፡ አንጻር፡ ነው። ህወሓት፤ የቻይናን፤ የደቡብ፡ ኮሪያን፤ የታይዋንን፤ የቪየትናምን፡ አይነት፡እድገታዊ፡ አመራር፡ (developmental state model)፤ እከተላለሁ፡ ሲል፡ ለእራሱ፡ ሃይል፤ ሃብት፡ ክምችት፤ ቁጥጥር፡ እንጂ፡ ለመላው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ህይወት፡ መለወጫ፡ አይደለም። በልማት፡ ስም፡ ስልጣንን፤ የበላይነትን፡ ለማረጋገጥ፡ እንጂ፡ አገራዊና፡ ፍትያዊ፡ እድገት፡ ለማራመድ፡ አይደለም። እድገታዊ፡ መንግስት፡ ነኝ፡ ሲል፤ የእንዚህን፡ አገሮች፡ ልዩነት፡ ሳያሳይ፡ ነው። ለምሳሌ፡ እነዚህ፡ አገሮች፡ በአምባ፡ ገነኖች፡ በተገዙበት፡ ወቅት፡ እንኳን፤ ተቋሞቻቸው፡ ሆነ፡ መሪወቻቸው፡ አገር፡ ወዳድ፤ ታሪክ፡ ወዳድ፤ ባህል፡ አክባሪ፤ መላ፡ ህዝብ፡ አቀፍ፡ ነበሩ። የግል፡ ክፍሉ፡ ለሁሉም፡ በር፡ ከፋች፡ እንጂ፡ አድሏዊ፡ አልነበረም። በዘርኝነት፡ የታነጽው፡ የህወሓት፡ ስርአት፡ ከማንም፡ አገር፡ ጋር፡ ሊነጻጸር፡ የማይችለው፡ ለዚህ፡ ነው። ዘረኝነትና፡ አድሏዊይነት፤ ብቻ፡ መለያው፡ ሆኗል። ዘረኝነት፡ እድልን፡ አያሰፋም፤ እንዲያውም፡ ያጠባል።

መለስ፡ “ለእድገት፡ ዲሞክራሲ፡ አያስፈልግም፡” ይላሉ። እውነት፡ አይደለም።

መድቭለ፡ ፓርቲ፡ ያላቸው፡ የአፍሪካ፡ አገሮች፡ ፈጣን፡ ፍትሃዊ፡ እድገት፡ እንደሚያሳዩ፡ ማስረጃ፡ አለ። ናይጀሪያ፤ ደቡብ፡ አፍሪካ፤ ጋና፤ ማሊ፤ ኒጀር፤ ቤኒን፤ ሴኔጋል፤ ሲየራ፡ ሊኦን፤ የመካከለኛው፡ አፍሪካ፤ ሞዛምቢክ፤ ታንዛኒያ፤ ቦትስዋና፤ ናሚቢያ፤ ሞሪሽየስ፤ ኬፕ፡ ቬርዲ፤ ሌሶቶ፤ ኮሞሮስና፡ ሴየሽልስ፡ ዲሞክራሳዊ፡ መንግስታት፡ አሏቸው። የእነዚህ፡ አገሮች፡ መካከለኛ፡ የነፍስ፡ ወከፍ፡ ገቪ፤ በአመት፡ US$4,000፤ የሞሪሽየስ፤ ቦትስዋና፤ ሴየሸልስ፤ በአመት፡ የነፍስ፡ ወከፍ፡ ገቪ፡ US$10,000 በላይ፡ መሆኑን፡ IMF: መዝግቦታል። በጠቅላላው፡ ሲታይ፤ ሃያ፡ ስድስት፡ የአፍሪካ፡ አገሮች፡ የነፍስ፡ ወከፍ፡ ገቪያቸው፡ በአመት፡ ከUS$1,000 እስከ፡ US$3, 999: ነው። በአንጻሩ፤ የእርዳታ፡ ተቀዳሚ፡ የሆነችው፡ ኢትዮጵያ፡ የነፍስ፡ ወከፍ፡ ገቪ፡ አሁንም፡ የአፍሪካ፡ መጨረሻ፡ ከሆኑ፡ አገሮች፡ መካከል፡ ነው፤ በአመት፡ US$350. ዝቅተኛ፡ ገቪ፡ ካላቸው፡ ለመድረስ፡ ምን፡ ተአምር፡ ማድረግ፡ እንዳለባት፡ ማስረጃው፡ ያሳያል። ፍትሃዊ፤ በህግ፡ የሚዳኝ፤ መላው፡ ህዝብ፡ የሚሳተፍበት፤ ስርአት፡ ቢመሰረት፡ አልፋ፡ ለመሄድ፡ ትችላለች፡ ለማለት፡ እደፍራለሁ። የተሳትፎ፤ ፍትሃዊ፤ ዲሞክራሳዊ፡ ስርአት፡ የሚያስፈልግ፡ ለመሆኑ፡ የአፍሪካ፡ አገሮች፡ ጥሩ፡ አራያ፡ ናቸው። የአሜሪካ፡ መንግስት፡ እነዚህን፡ ከዲሞክራሲ፡ ስርአት፡ የሚገኙ፡ ጥቅሞች፡ ያውቃል።

ፕሬዘደንት፡ ኦባማ፡ መለስ፡ ዜናዊይን፡ በአሁኑ፡ ወቅት፡ ለታላቅ፡ ስብሰባ፡ የጋበዙበትን፡ ምክንያት፡ ከሌላው፡ ጊዜ፡ ለየት፡ የሚያደርገው፡ አቢይ፡ ጉዳይ፡ የምግብ፡ ዋስትና : (food security) ፡ ውይይት፤ መሆኑ፡ ነው። ችግሩ፤ አርእስቱ፡ አይደለም። ጠቅላይ፡ ሚኒስትሩ፡ስለ፡ ምግብ፡ ዋስትና፡ ኢትዮጵያን፡ ለመወከል፤ በየቀኑ፡ ለሚራቡት፤ በኑሮ፡ ውድነትና፡ የምግብ፡ ዋጋ፡ ግፍሸት፡ ለሚሰቃዩት፡ ወገኖቻችን፡ ድምጽ፡ ለመስጠት፡ ብቃት፡ የሌላቸው፡ መሆኑ፡ ነው። እስከ፡ አሁን፡ ያሳዩት፡ ተግባር፡ድሃውን፡ ህዝብ፡ ለቁጥጥር፡ እንጂ፡ ለብቃት፡ ሲያዘጋጁት፡ አያሳይም። ለወጣቱ፡ ትውልድ፡ በሃገሩ፡ ጥሩ፡ እድል፡ ሲከፍቱለት፡ አይታይም። ትምህርት፡ ቤት፡ ማስፋፋት፡ አስፈላጊ፡ መሆኑ፡ አያከራክርም። ትምህርት፡ ወደ፡ ስራ፡ ካላሸጋገረ፤ ብቃት፡ ካላሳየ፤ ጥራት፡ ከሌለው፡ በፍጥነት፡ ካደጉ፡ አገሮች፡ ጋር፡ ሊወዳደር፡ አይችልም። የህወሓት፡ ትምህርት፡ ወጣቱን፡ ትውልድ፡ ለስደት፡ እየዳረገው፡ ነው። የማሰብ፤ የመንቀሳቀስ፤ እንደልብ፡ ሃብት፤ ጥሪት፡ የመያዝ፡ መንገዶችን፡ ዘግቶበታል። ማንም፡ ኢትዮጵያዊ፡ ለመብቱ፡ ሲነሳ፡ እያሰሩት፤ እያሳደዱት፡ነው። ኦባማ፡ የቁጥጥር፡ መንግስት፡ የአምባገነነት፡ መለኪያ፡ መሆኑን፡ ያውቃሉ። የኢትዮጵያን፡ አምባገነን፡ መንግስት፡ ከግብጽ፤ ከሊቢያ፤ ከየመን፤ ከቱኒሲያ፤ ከሶሪያ፤ ከዝምባብዌ፡ የሚለይ፡ መለኪያ፡ ሊኖር፡አይችልም። ያለው፡ የጭካኔ፤ የመለየት፤ የአድሎ፡ መጠን፡ ለኢትዮጵያ፡ ብቻ፡ ሳይሆን፡ ለአፍሪካ፡ ቀንድ፡ አደጋ፡ እንደሚያመጣ፡ የአሜሪካ፡ ተቋሞች፡ አስምረውበታል። የአሜሪካ፡ የውጭ፡ ጉዳይ፡ መስሪያ፡ ቤት፡ በእየአመቱ፡ ያወጣው፡ ዘገቫ መለስ፡ ዜናዊይን፡ በአለም፡ ፍርድ፡ ቤት፤ እንደ፡ ላይብሪያው፡ ታይሎር፤ እንደ፡ ሱዳኑ፡ ባሽር፤ እንደ፡ ግብጹ፡ ሙባረክ (በቅርቡ፡ የእድሜልክ፡ እስራት፡ በሃገራቸው፡ የተፈረደባቸው) ወዘተ፡ ለማቅረቭ፡ የሚያስችሉ፡ “ወንጀሎች” እንዳሉ፡ ያውቃሉ። መለስ፡ እንደነዚህ፡ አምባገነኖች፡ በሰላማዊ፡ ህዝብ፡ ላይ፡ በተከታታይ፡ ወንጀል፡ የፈጸሙ፡ መሆናቸውንና፡ ተጠያቂነት፡ እንዳለባቸው፡ አያጠራጥርም። በቀጥታ፡ አንድም፡ ወንጀል፡ አልፈጸምኩም፡ ለማለት፡ አይችሉም። ከጀርቫ፡ ሆነው፡ እርሳቸው፡ ያልገቡብት፤ እርሳቸው፡ ትእዛዝ፡ ያልሰጡበት፡ አቢይ፡ ነገር፡ ከስራ፡ ላይ፡ እንደማይውል፡ ኦባማ፡ ያውቃሉ። እነዚህን፡ የወንጀል፡ መሰረቶች፡ የሚሆኑ፡ ጥቂት፡ ምሳሌወች፡ በመስጠት፡ ልለፍና፡ ወደ፡ ዋናው፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ ትንተናየ፡ ልሂድ።

ኪራይ፡ ፈላጊውና፡ ሰብሳቢው፡ ማነው?

ጠቅላይ፡ ሚንስትር፡ መለስ፡ ሃያ፡ አንድ፡ አመታት፡ የመሩት፡ የአንድ፡ አናሳ፡ ብሄርተኛ፡ ቡድን፡ መንግስት፡ በእርሻ-ላይ፡ የተመሰረተ፡ እድገት፡ የአብዛኛውን፡ የድሃ፡ ህዝብ፡ ኑሮ፡ አላሻሻለም። የአሜሪካ፡ መንግስት፡ ይህን፡ ያውቃል። መለስ፡ እድገታዊ፡ መንግስት፡ ብለው፡ የሚጠሩት፡ ስርአት፡ የፖለቲካ፡ ሆነ፡ የመዋእለ፡ ንዋይ፡ የበላይነትን፡ ከያዘ፡ መቆየቱን፡ ፕሬዘደንት፡ ኦባማ፡ያውቃሉ። ምሳሌወችን፡ ላቅርብ።

የኢትዮጵያ፡ ኢኮኖሚ፡ እንደ፡ ሌላው፡ አመራር፡ በምስጢር፡ የሚሰራ፡ ነው። የገበያው፡ ስርአት፡ ግልጽነት፡ የለውም። በህግ፡ አይተዳደርም። በኮንትሮባንድ፡ የሚንቀሳቀሰው፡ ዘርፍ፡ በህግ፡ ከሚንቀሳቀሰው፡ ያላነሰ፡ ወይንም፡ አመዛኝ፡ እየሆነ፡ ነው። ተቋሞችን፡ ከመንግስት፡ ቁጥጥር፡ ስር፡ አናውጣ፡ በሚል፡ ዘይቬ፡ ህወሓት፡ ስልጣን፡ ከያዘበት፡ ጀምሮ፡ እስካሁን፡ ቀስ፡ በቀስ፡ የሃገሪቱን፡ የምርትና፡ የአገልግሎት፡ ዘርፎች፡ ወደ፡ ፓርቲውና፡ ምርጥ፡ ባለስልጣኖች፤ የትግራይ፡ ታማኞች፤ ሌሎች፡ ተባባሪወች፡ አስተላልፏል፤ እያስተላለፈ፡ ነው። በሚያስገርም፡ ሁኔታ፤ ምንም፡ በስማቸውና፡ በስራቸው፡ ካፒታል፡ የሌላቸው፡ ግለሰቦች፡ ነጥረው፡ ሃብታም፡ የሆኑበት፡ ምስጢር፡ ከዚህ፡ የመነጨ፡ ነው። የፖለቲካ፡ ስልጣን፡ ለግል፡ ሃቭት፡ ማጠራቀሚያ፡ ከሆነባቸው፡ በእጂ፡ ከሚቆጠሩ፡ አገሮች፡ መካከል፡ ኢትይጵያ፡ ከፍተኛ፡ ደረጃ፡ ይዛ፡ ትገኛለች። የህወሓት፡ ባለስልጣኖች፡ ይህን፡ ታሪክ፡ የመዘገቨው፡ ዘረፋ፡ የሚያካሂዱት፡ በሚስት፡ ስም፤ በልጂ፡ ስም፤ በዘመድ፡ ስም፤ በወዳጂ፡ ስም፤ በድርጂት፡ ሰም፤ በውጭ፡ ኢንቬስተሮች፡ ስም፡ ነው። አገር፡ ውስጥ፡ የሚፈሰውን፡ መዋእለ፡ ንዋይ፡ ብቻ፡ ማየት፡ አይቨቃም። በዱባይ፤ በደቡብ፡ አፍሪካ፤ በምእራብ፡ አፍሪካ፤ በአሜሪካ፤ በደቡብ፡ ሱዳን፡ ወዘተ፡ የሚፈሰው፤ የሚሸሸው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ሃቭት፡ ሰፊ፡ ነው። ምርምርና፡ ክትትል፡ ይፈልጋል። ይህ፡ የካፒታል፡ ማዘዋወር፡ ዘመቻ፡ የሚደረገው፡ በዘዴና፡ በምስጢር፡ ነው። ባጭሩ፤ የፖለቲካ፡ የበላይነት፤ ስልጣንና፡ ቁጥጥር፡ ለኪራይ፡ ሰብሳቢነት፡ አመችቷል። የመንግስት፡ የነበሩ፡ አትራፊ፡ የምርት፤ የአገልግሎት፡ ድርጂቶች፡ ለግለሰቦች፤ ለከፍተኛ፡ ባለስልጣኖች፡ ሲተላለፉ (Transfer of real resources from Ethiopian society to TPLF core and supporters)፤ ኪሳራውን፡ የሚሸከመው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ነው። ትርፉን፡ የሚያገኙት፡ የህወሓት፡ ባለስልጣኖችና፡ ታማኝ፡ ግለሰቦች፡ እንደሚሆኑ፡ አያጠራጥርም። በቅርቭ፡ የተገኙ፡ ማስረጃወችን፡ እንይ።

1. የጣይቱ፡ ሆቴል፤ ያለ፡ ምንም፡ ወጭ (ካፒታል) ከህዝ፡ ሃብተነት፡ ወደ፡ ምርጥ/ታማኝ፡ ግለሰብ፡ ተሸጋገሯል፡

2. የጉለሌ፡ የሳሙና፡ ፋብሪካ፤ ከመንግስት፡ ሃያ፡ ሚሊዮን፡ ብድር፡ በመጠቀም፡ ፋብሪካው፡ ከኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ወደ፡ ግለሰብ፡ ተሸጋገረ። ይህ፡ ፋብሪካ፡ በአመት፡ ሃያ፡ ሚሊዮን፡ ብር፡ ትርፍ፡ ያስገኝ፡ ነበር። ትርፍ፡ የሚያስገኝ፡ ተቋም፡ ለግል፡ ተጠቃሚ፡ ለምን፡ እንደተሰጠ፡ ምስጢር፡ ሊሆን፡ አይችልም፡

3. የጉለሌ፡ ልብስ፡ ስፌት፡ ፋብሪካ፤ አስራ፡ ሰባት፡ ሽህ፡ ካሪሜትር፡ የሆነው፡ በአንድ፡ ነጥቭ፡ አንድ፡ ሚልዮን፡ ብር፡ ተመን፡ ለታማኝ፡ ግለሰብ፡ ተሽጦ፡ ከኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ወደ፡ ህወሓት፡ ባለስልጣኖች/ግለሰቭ፡ ያለ፡ ውድድር፡ ተዘዋውሯል፡

4. ታሪክ፡ ያለው፡ የባህር፡ ዳር፡ ጊዮን፡ ሆቴል፤ ለእንድ፡ ህወሓት፡ ደጋፌ፤ ታማኝ፡ ግለሰብ፡ ተዘዋውሯል፡

5. የጎንደር፡ ጎሃ፡ ሆቴል፤ በሳንቲም፡ ሂሳቭ፡ አንድ፡ በውጭ፡ ለጥቂት፡ ወራት፡ ለቆየ፡ ካፒታል፡ ለሌለው፤ ታማኝ፡ ለሆነ፡ የትግራይ፡ ግለሰቭ፤ እንደ፡ ስጦታ፡ ተዘዋውሯል። ሌሎች፡ ሊወዳደሩ፡ ቀርቶ፡ አልተጋበዙም።

6. በቻይና፡ ኢንቬስተሮች፡ የተደገፉ፡ የሲሚንቶ፡ ፋብሪካወች (ሞጆ)፤ የጫማ፡ ፋብሪካ፤ ሌሎች፡ ከኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ሃብተነት፡ ወደ፡ ህወሃት፡ ባለስልጣኖች/ደጋፊወች/ታማኞች፡ ተዘዋውረዋል። ህወሃት፡ ይህን፡ ሲያደርግ፡ በመንግስትነት፡ ስልጣኑ፡ ተጠቅሞ፤ የመንግስትን፡ ሃብት፡ ወደ፡ ግለሰብ፡ ማዘዋወር፡ ለእድገት፡ ይጠቅማል፡ በሚል፡ ዘዴ፡ ነው። በገቨያ፡ ውድድር፡ ስም፡ የሃብት፡ ክምችትን፡ አጠናከረ። ኢትዮጵያን፡ እያዳከመ፡ ሃብትን፤ ጥሪትን፡ ወደ፡ ራሱና፡ ደጋፊወቹ፡ አዛወረ፡ ማለት፡ ነው።

7. የደንበል፡ ሕንጻ፤ የሚያወጣው፡ በግምት፡ ከሰቫ፡ እስከ፡ ሰማኒያ፡ ሚልዮን፡ ብር፡ ሲሆን፡ ገዡ፡ ግለሰብ፡ (ከህወሓት፡ ጋር፡ የቀረቨ፡ ግንኙነት፡ ያላቸው፡) ህንጻውን፡ መያዣ፡ አድርገው፡ (collateral) ከመንግስት፡ ካዝና፡ ከሁለት፡ መቶ፡ አምሳ፤ እስከ፡ ሶስት፡ መቶ፡ አምሳ፡ ሚሊዮን፡ ብር፡ አገኙ። ገንዘቩ፡ የት፡ እንደደረሰ፡ አይታወቅም። ሁነኛ፡ ግለሰቦች፡ የነገሩኝ፤ ይህ፡ ገንዘቭ፡ በጥቁር፡ ገበያ፡ ወደ፡ ውጭ፡ ምንዛሬ፡ ተለውጦ፡ ከሃገር፡ ወጥቷል። የጥቁር፡ ገበያ፡ የደመቀበት፡ መርካቶ፡ በአሁኑ፡ ወቅት፡ በቀን፡ ብዙ፡ ሚልዮን፡ ብር፡ ወደ፡ ዶላር፡ ይለወጥበታል። የተለወጠው፡ አገር፡ አይቀርም። አብዛኛወቹ፡ ለዋጮች፡ ገንዘብ፡ በሚልዮን፡ የሚቆጥሩ፡ የህወሓት፡ ባለስልጣኖች፤ የቅርቭ፡ ቤተሰቦች፤ ወዳጆች፤ ታማኞች፡ ናቸው። ሕጉ፤ ደንቡ፡ አይመለከታቸውም። እነዚህ፡ የሚስና፤ የስርቆት፤ የአድሎ፤ የዘረፋ፤ የህገ፡ ወጥነት፡ ማስረጃ፡ ናቸው።

8. ህንጻወች፤ ቪላወች፤ ኮንዶሚኒየም፤ የግል፡ ቤቶች፡ በአሜሪካ፤ በዱባይ፡ ወዘተ፡ መሰራታቸው፤ ዛሬ፡ ከፍተኛ፡ ባለስልጣኖች፤ ታማኝ፡ ግለሰቦች፤ የፓርቲው፡ ሃላፊወች፡ ስልጣንና፡ የረቀቀ፡ ግንኙነት፡ በመጠቀም፤ ኢምባሲወችን፡ ለግል፡ አገልግሎት፡ በማዋል፡ በብዙ፡ ሚሊዮን፤ ዶላር፡ የኪራይ/መኖሪያ፤ ማረፊያ፤ የልጅና. የቤተሰብ፤ የወዳጅ፡ መገልገያ፤ የኪራይ፡ መሰብሰቢያ፡ እያደረጉበት፡ ነው። ገንዝብ፡ ሲሸሽ፡ የሚጎዳው፡ ድሃውና፡ የወደፊቱ፡ ትውልድ፡ ነው። በኢትዮጵያ፡ አየር፡ መንገድ፡ የሚጓጓዘው፡ የምግብ፤ ሌላ፤ እቃ፡ በአመት፡ ብዙ፡ ሚሊዮን፡ ዶላር፡ ትርፍ፡ እንደሚያስገኝ፡ ይገመታል። በአብዣኛው፡ ተጠቃሚወቹ፡ የህወሓት፡ ባለስልጣኖች፤ ታማኞች፤ ደጋፊወች፡ ናቸው። እቃ፡ ከቀርጥ፡ ውጭ፡ ለማጓጓዝ፤ ቤቶችን፡ ሆነ፡ ሌላ፡ የጥሬ፡ ሃብት፡ ለማቋቋም፡ የፖለቲካ፡ ስልጣን፤ ግንኙነት፤ ገንዘብ፡ ቁልፍ፡ ናቸው። ገንዘቡ፡ የሚመጣው፡ ከኢትዮጵያ፡ ድሃ፡ ህዝብ፤ ካገሪቱ፡ ባንኮች፤ ወዘተ፡ ነው። የኢትዮጵያ፡ ብር፡ በጥቁር፡ ገበያ፤ በሌላ፡ ማስተላለፊያ፤ እየተለወጠ፡ ወደ፡ ውጭ፡ የሚጎርፈው፡ ለዚህ፡ አመልካች፡ መረጃ፡ ነው። ስልቱ፡ በሚስት፤ በልጂ፤ በቅርቭ፡ ዘመድ፤ በሰራተኛ፤ በወዳጅ፤በኤምባሲ፡ ሰራተኞች፤ በፈረንጆች፡ ስራ፡ ላይ፡ የዋለ፡ ነው።

ጠቅላይ፡ ሚንስትር፡ መለስ፡ በመንግስት፡ ውስጥ፡ “ሌቦች፡ አሉ፤ እናውቃቸዋለን.” ብለው፡ ይናገራሉ።ኪራይ፡ ሰብሳቢወች፡ የህወሓት፡ መሪወች፡ አይደሉም፤ ትግራዮች፤ አይደለም፤ እኔ፡ ወይንም፡ ባለቤቴ፡ አይደለንም፡ ይላሉ። ችግሩ፤ ክህደቱ፡ እውነቱን፡ ሊሸፍነው፡ አይችልም። የመንግስት፡ ሌቦች፡ እንዳሉ፡ ካወቁ (ማወቃቸው፡ አያጠራጥርም)፤ የፖሊቲካ፡ ስልጣንና፡ ሙስና፤ ብልግና፤ ገንዝቭ፡ ማሸሽ፡ የተያያዙ፡ መሆናቸውን፡ ያውቃሉ፤ ማን፡ ሌባ፡ እንደሆነ፡ ያውቃሉ። ሕጉም፤ ፍርዱም፤ ፍርድ፡ ቤቱም፤እስር፡ ቤቱም፡ በእጃቸው፡ ነው። ለምን፡ የመንግስት፡ ሌቦችን፡ ለፍርድ፡ አያቀርቡም፡ ብለን፡ መጠየቅ፡ መብታችን፡ የሚሆነው፡ ለዚህ፡ ነው። እንቅጩ፤ ከማንም፡ በላይ፡ የስልጣን፡ ተጠቃሚው፡ የህወሓት፡ ከፍተኛ፡ ባለስልጣኖች፤ ቤተሰቦች፤ ከፍተኛ፡ የጦር፡ መክኖንኖች፤ ታማኛ፡ የትግራይና፡ ሌሎች፡ ግለሰቦች፡ መሆናቸውን፡ ተራው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ያውቀዋል። ጠቅላይ፡ ሚንስትሩም፡ እንደሚያውቁ፡ አልጠራጠርም። እነደ-ጠቅላይ፡ ሚንስትሩ፤ ይህን፡ ማስረጃ፡ የሚሰጡኝ፡ ግለሰቦች፡ የሚኖሩት፡ ኢትዮጵያ፡ ነው። ሁኔታው፡ ሰለዘገነናቸው፤ ባይሆን፡ ለታሪክ፡ ይጻፍ፤ በማለት፡ በየጊዜው፡ የሚሰጡኝ፡ ማስረጃ፡ ነው።

9. የከተማና፡ የገጠር፡ ለም፡ መሬት፡ አሰረጫጨት፤ ኪራይ፡ አልሰበሰብም፡ የሚለው፡ እድገታዊው፡ ህወሓት፡ ቢፈቅድም፤ ባይፈቅድም፡ ከደሙ፡ ንጹህ፡ ለመሆን፡ አይችልም። ለዚህ፡ ጥሩ፡ ማስረጀው፡ የከተማና፡ ለም፡ የገጠር፡ መሬት፡ ስርጭት/ቅርሚት፤ አስተዳደር፡ ነው። መሬት፡ የሃብት፡ ማከማቻ፡ መሰረት፡ ነው። በቦሌ፤ በዱከም፤ በቡራዩ፤ በሰንዳፋ፤ በሱሉልታ፤ በናዝሬት፤ በደብረዘይትና፡ በሌሎች፡ የአዲስ፡ አበባ፡ ዙሪያ፡ ያለውን፡ የመሬት፡ ስርጭት፤ ማን፡ ምን፡ እንደያዘ፡ በገሃድ፡ ያሳያል። በክልል፡ እርእሰ፡ ከተማወችም፡ ያለው፡ አጠቃቅም፡ ይህን፡ ይመስላል። ታላላቅ፡ የፓርቲውና፡ የመንግስት፡ ባለስልጣኖች፤ ከፍተኛ፡ የጦር፡ መኮንኖች፤ ታማኝ፡ ግለሰቦች፤ የባለስልጣን፡ ሚስቶች፤ (በተለይ፡ ምርጥ/ታማኝ፡ የሆኑ፡ የትግራይ፡ ብሄረሰብ፡ አባላት) ከሶስት፡ እስከ፡ አስር፡ ቁልፍ፡ ቦታወች፡ ተመርተርው፡ የ ራሳቸው፡ አድርገዋል፤ ታላላቅ፡ ፎቆች፡ ሰርተዋል። በዋሽንግቶን፡ የህወሓት፡ አምባሳዶር፡ “የህንጻ፡ ባለጸጋ፡ ናቸው፡” የሚል፡ ማስረጃ፡አንድ፡ ግለሰብ፡ በቅርቩ፡ አሳይቶኛል። እሳቸውም፡ ሆኑ፡ ሌሎች፡ ህንጻ፡ በማስያዝ፡ ከመንግስት፡ ባንኮች፡ ብዙ፡ ሚሊዮን፡ ብር፡ አግኝተዋል።

ባለስልጣኖች፡ ህንጻ፡ ሲሰሩ፡ በራሳቸው፡ ገንዝብ፡ አይደለም። ገንዘቡን፡ ከየት፡ያመጡታል? ከሰቫ፤ እስከ፡ ሰማኒያ፡ ሚልዮን፡ ብር፤ ለጀኔራሎች፡ ታላላቅ፡ ፎቆች፡ እስክ፡ ዘጠና፡ ሚልዮን፡ ብር፡ የሚፈጀው፡ ገንዘብ፡ የሚገኘው፡ ከመንግስት፡ ባንኮች፡ ነው። የመንግስት፡ ካዝና፡ የፓርቲ፤ የግል፡ጥቅም፡ ማካቨቻ፡ የሆነባት፡ አገር፡ ኢትዮጵያ፡ ብቻ፡ ናት፡ ለማለት፡ የሚያስደፍረው፡ ለዚህ፡ ነው። ባንኮች፡ እነደሚታለቡ፡ ላሞች፡ ሁነዋል። ሁኔታው፤ ስልጣንና፡ ዋስትና፤ ብድር፡ የማግኘት፡ አቅም፤ የሃቭት፡ ክምችት፡ የተቆላለፉ፡ መሆናቸውን፡ ይጠቁማል። የከፍተኛ፡ ፎቆችና፡ ህንጻወች፡ ባለቤቶች፡ ተራ፤ ወይንም፡ ከስልጣን፡ ጋር፡ ያልተቆራኙ፡ ኢትዮጵያን፡ አይደሉም። ሊሆኑ፡ አይችልም። እነሱ፡ ድምጽ፤ ስልጣን፤ የላቸውም፤ የበይ፡ ተመልካቾች፡ ናቸው።

10. የኮንትሮባድ፡ ንግድ፡ ለኪራይ፡ ፈላጊወች፡ መሳሪያ፡ ሲሆን፤ በህግ፡ የማይተዳደር፡ ስርአት፡ ከቁጥጥር፡ መውጣቱ፡ አያስገርምም። የሚያስደነግጠውና፡ የሚያበሳጨው፡ የመንግስት፡ ሰራዊት፡ መኪናወች፡የኮንትሮባንድ፡ ንግድ፡ ማንቀሳቅሻ፡ መሆናቸው፡ ነው።ማንም፡ አይፈትሻቸውም፤ ማንም፡ አይቆጣጠራቸውም፤ ኬላ፡ እንደልብ፡ ያልፋሉ። በብዙ፡ መቶ፡ ሚሊዮን፡ የሚታሰብ፡ ሸቀጥ፡ ከህግ፡ ውጭ፡ ያዘዋውራሉ፤ ከሃገር፡ ያወጣሉ፤ “የጦር፡ መሳሪያ፡ ይነግዳሉ፤” ትርፍ፡ ለግል፡ ያከማቻሉ። የስልጣን፡ ብልግና፡ ማለት፡ ይህም፡ ነው። ስርአቱን፡ ስለሚያገለግሉ፡ መንግስት፡ ሊቆጣጠራቸው፡ አይችልም።

የግብር (ቫት) አድሏዊነት፡

11. የሃገር፡ ውስጥ፡ ገቢ፤ ይህን፡ ተቋም፡ ሙሉ፤ በሙሉ፡ የሚመራው፡ የህወሓት፡ ታማኝ፡ የሆኑ፡ የትግራይ፡ ተወላጂ፡ ባለስልጣኖች፡ ብቻ፡ ናቸው። ግንኙነታቸው፡ በቀጥታ፡ ከጠቅላይ፡ ሚኒስትሩ፤ ከፓርቲው፤ ከጠቅላይ፡ ሚኒስትሩ፡ ባለቤት፤ ከስለላ፡ ድርጂቱ፡ ጋር፡ ነው። የኢኮኖሚ፡ የበላይነትን፡ ለመያዝ፤ የአገር፡ ውስጥ፡ ገቢን፤ መቆጣጠር፡ አስፈላጊ፡ ነው፡ ብሎ፡ የተነሳው፡ ህወሓት፡ ይህን፡ ድርጂት፡ አንደ፡ አይን፡ ብሌን፡ ያየዋል፤ ይቆጣጠረዋል። ለምን? አቸናፊውን፡ ይመርጣል፤ መገለል፡ ያለበትን፡ በእርቂቅ፡ ያባርራል፤ ይጎዳል፤ መድረሻ፡ ያሳጣል፤ ያደክማል። የሚያተኩርበትን፡ ብናይ፡ ጎጂነቱን፡ እንረዳለን። አብዛኛው፡ ዘመናዊ፡ የኢትዮጵያ፡ ኢኮኖሚ፡ የሚሽከረከረው፡ በዝቅተኛ፡ ነጋዴወች፡ ነው። ሴቶች፤ አናቶች፡ ይተዳደሩበታል። ከአስራ- አምስት፡ በመቶ፡ በላይ፡ ቀረጥ (Value added tax)፤ የሚደነገገው፡ በእነዚህ፡ ላይ፡ ነው። ለመጠጥ፤ ለቡና፤ ለሻሂ፤ ለዳቦ፤ የሚከፈለውን፡ ስናይ፡ ጎጅነቱን፡ ለመረዳት፡ ይቻላል። ማነጻጸር፡ የሚገባን፤ የህወሓት፡ ጥሪት፤ ከቀረጥ፡ ነጻ፡ የሆኑትን፤ እንደ፡ ኤፎርት፤ በኮንትሮባንድ፡ የሚሰሩትን፡ የመከላከያና፡ የስለላ፡ ድርጂቶች፤ በህግ፡ ያልታወቁ፡ ሌሎች፡ ድርጂቶችን፡ ነው። ባት፡ የማይከፍሉበት፡ ምክንያት፡ ለምንድን፡ ነው፡ ብሎ፡ ለመጠየቅ፡ የማይችለው፡ ህብረተሰብ፤ “ወይ፡ ጉድ” አያለ፡ ሁኒታውን፡ ተቀብሎታል። ቀረጥ፡ እንዳይከፍሉ፡ የተደረገው፡ ከስርአቱ፡ ጋር፡ የጥቅም፡ ግንኙነት፡ ስላላቸው፡ ብቻ፡ ነው፡ ለማለት፡ እንገደዳለን። በሃገር፡ አቀፍ፡ ደረጃ፡ ሲታይ፤ ዋናው፡ የንግድ፡ ስራ፡ በሙሉ፡ ለፖለቲካ፡ ባለስልጣኖችና፤ ታማኞች፡ ተዳርጓል። ዝቅተኛ፡ ነጋዴወች፡ ከፍተኛ፡ ግቭር፡ እንዲከፍሉ፡ ሲገደዱ፤ አቅማቸው፡ ስለማይፈቅድ፤ ቀስ፤ በቀስ፡ ስራቸውን፡ ይዘጋሉ። ሃብት፡ ያላቸው፤ አገር፡ ወዳድ፡ የሆኑ፤ ሲብስባቸው፡ አገር፡ ለቀው፡ ይወጣሉ። የህወሓት፡ ዋና፡ አላማ፡ የፖለቲካ፡ ስልጣኑን፡ ተጠቅሞ፤ የንግዱን፤ ቁልፍ፡ የሆነውን፡ የማምረቻ፡ ክፍል፤ ባንክ፤ መገናኛ፤ ማጓጓዣ፡ ሙሉ፤ በሙሉ፤ የህወሓት፡ የበላይ፡ ባልሰልጣኖች፤ ታማኝ፡ የትግራይ፡ ተወላጆች፤ ተባባሪ፡ የሆኑ፤ የውጭ፡ ባለሃብቶች፡ እንዲይዙት፡ ማድረግ፡ ነው። የማይፈለገው፡ የኢትዮጵያ፡ ስብጥር፡(diverse)፤ ህዝብ፡ የበላይነት፡ አንዳይኖረው፤ አንዳይወዳደር፤ ለማድረግ፡ ነው። የበላይነት፡ ከተረጋገጠ፤ ህወሓት፡ በተከታታይ፤ ለብዙ. አመታት፤ ወይንም፡ ከትውልድ፡ ወደ፡ ትውልድ፡ ለመግዛት፡ ይችላል፡ የሚለውን፡ ግምት፡ መሰረትና፡ ድልድይ፡ ለማመቻቸት፡ ነው፡፡ ችግሩ፤ የመስራት፤ ሃብት፡ የመያዝ፤ የመንቀሳቅስ፤ የተፈጥሮ፡ ሃቭት ፍትሃዊ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ የማግኘት፡ እድል፡ ክሌለ፡ ዘላቂነትና፡ በእኩለነት፡ የተመሰረተ፡እድገት፡ ሊኖር፡ አይችልም። የዛሬ፡ ተጠቃሚወች፡ የነገ፡ ኢላማወች፡ ሊሆኑ፡ ይችላል። ኢኮኖሚው፡ እንደ፡ ቦትስዋና፡ ሊሆን፡ አይችልም። የነፍስ፡ወከፍ፡ ገቪ፡ አያድግም፤ ድህነት፡ አይጠፋም።

12. የለም፡ መሬት፡ አያያዝ፤ የዘመናዊ፡ ግብርናውን፡ ክፍል፤ እንደ፡ ሌላው፤ ህወሓትና፡ ታማኞች፡ በኢትዮጵያዊያን፡ ስም፡ እየተቀራማቱት፡ ነው። ለውጭ፡ አገር፡ ታዛቢወች፤ የሚሉት፤ አብዛኛውን፡ ለም፡ መሬት፡ የተመሩት፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ናቸው፡፡ ይህ፡ ከእውነቱ፡ የራቀ፡ መሆኑን፤ (Oakland Institute, Human Rights Watch, the Guardian, Survival International, Desalegn Rahamato, etc)፤ ማስረጃ፡ አቅርቨውበታል። ለውስጥ፡ ኢንቬስተሮች፡ ተሰጠ፡ የሚባለው፡ ሰባ፡ አምስት‹ በመቶው፡ ለምርጥ፡ የትግራይ፡ ተወላጆች፤ ለከፍተኛ፤ የጦር፡ መኮንኖች፤ ለፓርቲው፡ ከፍተኛ፡ ሃላፊወች፡ የተሰጠውን፡ ነው። ሌሎች፡ ኢትዮጵያዊያን፡ የሉብትም፤ ወይንም፡ አያገቫቸውም፡ እንደማለት፡ ነው። የአድሎውን፡ ጨካኝነት፡ ያመለክታል። ሌላው፤ ግልጽነት፡ በሌለባት፡ አገር፤ የፓርቲው፡ ባለስልጣኖች፤ ታማኝ፡ የትግራይ፡ ተወላጆች፤ የህንድን፤ የፓኪስታንን፤ የሳውዲ፡ አራቢያን፤ ወዘተ፤ ኢንቬስተሮች፡ በውስጥ፡ ድርድር፡ ተካፋይ፡ እንዲሆኑ፡ አድርጓል። ይህ፡ የጥቅም፡ ውል፡ የኢትዮጵያን፡ ከበርቴወች፤ ዝቅተኛ፡ አምራቾች፤ ወጣቶች፡ ወደ፡ ጎን፡ እየተወ፤ ኢትዮጵያዊያን፡ በአገራቸው፡ ለም፡ መሬትና፡ ወንዝ፡ ተእጠቃሚ፡ እንዳይሆኑ፡ እያደረጋቸው፡ ነው። የመሬት፡ ነጠቃውን፡ በተናጥል፡ አላየውም። ከንግዱ፤ ከዘመናዊ፡ ምርቱና፡ ማጓጓዣው፤ ወዘተ፡ አጣምረን፡ ማየት፡ ይኖርብናል። አንዱ፡ ሌላውን፡ ይደግፋል።

በፍጥነት፡ ያደጉ፡ አገሮች፡ ታሪክ፡ የሚያስተምረን፤ እኔ፤ በአይኔ፡ ያየሁት፤ የታይዋን፤ የደቡብ፡ ኮሪያ፤ የኢንዶኔዝያ፤ የቻይናና፡ የህንድ፡ እድገት፡ ከኢትዮጵያ፡ በጣም፡ ይለያል። እንዚህ፡ አገሮች፡ የሃገር፡ ውስጥ፡ ታዳጊ፡ የኢኮኖሚ፤ የአገልግሎት፤ የንግድ፡ ክፍሎችን፡ ከውጭ፡ አገር፡ አትራፊወች፡ ተንከባክበው፡ እንዲጎለምሱ፡ አድርገዋል። ህወሓት፡ ሌላ፡ ቀርቶ፤ የቻይና፡ አትራፊወች፡ በችርቻሮ፡ ተግባር፡ ገብተው፡ ኢትዮጵያዊያንን፡ እየጎዱ፡ ያያቸዋል፤ ፈቅዶላቸዋል። የምስራቅ፡ ኤዥያ፡ አገሮች፡ የማይፈቅዱትን፤ የሞባይል፡ ስርጭት፤ የምግብ፡ አቅርቦት፤ የንግድ፡ ወዘተ፤ ተግባሮች፤ ህወሓት፡ ፈቅዶ፡ ኢትዮጵያዊያንን፡ እየጎዳ፡ ነው። አንባቢው፡ እንዲገነዘቭ፡ የምሻው፡ መልክት፡ ይህ፡ ነው። ሃላፊነት፡ የሚሰማው፡ መንግስትና፡ አመራር፡ ኑ፡ ብሎ፡ የውጭ፡ ኢንቬስተሮችን፡ ወደ፡ ሃገሩ፡ የሚያስገባው፡ የሃገሩ፡ ህዝብ፡ ለመስራት፡ የማይችለውን፡ እንዲሰሩ፤ አቅም፡ ገንብተው፡ ቶሎ፡ እንዲወጡ፡ ብቻ፡ ነው። የሃገሪቱን፡ አምራቾች፤ ነጋዴወች፤ ለመፍጠር፤ ለማምረት፤ የሚችሉ፡ ኢትዮጵያዊያንን፡ እንዲተኩ፡ አይደለም። በእርሻም፡ በኩል፤ ታናናሽ፡ ገበሬወች፡ ሆኑ፡ ፍላጎትና፤ ችሎታ፡ ያላቸው፡ ኢትዮጵያዊያን፡ መሬቱን፤ ወንዙን፤ ምርቱን፤ ገበያውን፡ እንዲቆጣጠሩት፡ የማድረግ፡ የማእክላዊ፡ መንግስት፡ ሚና፤ ተግባር፤ ነው፤ ሃላፊነት፤ አለበት፤ ተጠያቅነት፡ አለበት። ህወሓት፡ የሚያደርገው፡ ከዚህ፡ የራቀ፤ የኪራይ-ሰብሳቢነት፤ የትርፍ፡ አመቻችነት፡ ተግባር፡ ሆኖ፡ ይታያል። ለዚህ፡ ነው፤ የህወሓት፡ እድገት፡ ፍትሃዊ፡ ለመሆን፡ የማይችለው። አብዮታዊ፡ ዲሞክራሲ፡ በምንም፡ ፍትሃዊ፡ ለመሆን፡ አይችልም። ለዚህ፡ ነው፤ ጠቅላይ፡ ሚኒስትር፡ መለስ፡ መላውን፡ የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ ለመወከል፤ የሞራል፡ ብቃት፡ የላቸውም፡ ለማለት፡ የሚቻለው።

ከሁሉም፡ በላይ፤ “እድገታዊው”፡ የህወሓት፡ አስተዳደር፡ ያበለጸገው፡ እራሱን፤ ታማኝ፡ የትግራይ፡ አዲስ፡ ከበርቴወችን፤ ከፍተኛ፡ የጦር፡ መሪወችን፤ ለይስሙላ፡ ሌሎች፡ ደጋፊወችን፡ መሆኑን፡ ፕሬዘደንት፡ ኦባማ፤ ያውቃሉ። በአሁኑ፡ ወቅት፤ አገራችን፡ “ዘርፎ፡ ለዘራፊ፡” ተዳርጋለች፡ ቢባል፡ ከሃቁ፡ የራቀ፡ አይሆንም። የኢትዮጵያን፡ ስብጥር፡ ህዝብ፡ የሚያንጸባርቅ፡ አገር፡ ወለድ፡ ከበርቴ፡ ገና፡ መሰረት፡ መያዝ፡ ያልቻለው፡ አመራሩ፡ አገራዊ፡ ሳይሆን፡ ወገናዊና፤ ጠባብ፡ ዘረኛ፤ ኪራይ፡ ሰብሳቢወችን፡ የሰበሰበ፤ በመሆኑ፡ ነው። የአለም፡ ባንክ፡ ዘገባ፡ እንደሚያሳየው፡ የግል፡ ክፍሉ፡ በህወሓትና፡ ደጋፊ፡ ተቋሞች፤ በወጭ፡ ከበርቴወች፡ ታንቋል። ይህን፡ የአሜሪካ፡ ባለስልጣኖች፡ ያውቃሉ። ደንቡ፤ ህጉ፤ አስተዳደሩ፡ አድሏዊ፡ ከሆነ፡ አገር፡ ወለድ፡ ከበርቴ፡ በስፋት፡ ሊፈጠር፡ አይችልም። እንደ፡ ቦትስዋና፤ ኒይጀሪያ፤ ጋና፡ መካከለኛ፡ መደብ፡ ሊስፋፋ፡ አይችልም። የኮሪያ፤ ጃፓን፤ ቬትናም፤ እድገት፡ ጎዳናወች፤ የሚያሳዩት፤ አድሎ፡ የሌለበት፡ አገራዊ፡ እኮኖሚ፡ ለሁሉም፤ እድል፡ ከፋች፡ መሆኑንን፡ ነው። ለሴቶች፤ ለወጣቶች፡ እድል፡ ይከፍታል። በጋና፤ ሴኔጋል፤ ታንዛኒያ፡ የሚታየው፡ አገር፡ ወለድ፡ እድገት፡ ኢትዮጵያን፡ እንደሚለያት፡ አሳይቻለሁ። ህወሓት፡ አዲስ፡ የግል፡ ሃብታሞች፡ ተፈጥረዋል፡ የሚለው፡ የተወሰኑ፤ የተመረጡ፡ አብዛኛወቹ፡ የትግራይ፡ ብሄረሰብ፡ አባላት፡ መሆናቸውን፡ የኦባማ፡መንግስት፡ ያውቃል። በኢትዮጵያ፡ የተዛባ፤ ትግሬአዊ፤ በሆነው፤ የመከላከያ፡ እዝ፡ ላይ፡ የአሜሪካ፡ መንግስት፡ ተወካይ፡ ጀኔቫ፡ ያደረጉትን፤ ወቀሳ፡ ኦባማ፤ ክሊንቶን፡ አያውቁትም፡ የሚል፡ ታዛቪ፡ አላገኘሁም።

መለስና፡ ደጋፊወቻቸው፡ እንደሚሉት፡ ከሆነ፡ የዚህ፡ አንዱ፡ የተዛብ፡ የእድገት፡ ውጤት፡ የገጠር፡ ሚሊየኖርችን፡ ማምረቱ፡ ነው። ከምሳሌ፡ ውጭ፡ ግን፤ እነዚህን፡ የገጠር፡ ሃብታሞች፡ ፈልጌ፤ የት፡ እነደሚኖሩ፤የተ፡ እንደሚገኙ፡ ተመራምሬ፡ ልደርስባቸው፡ አልቻልኩም። ምን፡ አልባት፡ ጨረቃ፡ ላይ፡ ይሆኑ? የአሜሪካ፡ ተራድኦ፡ ድርጂት፡ የእርሻ፡ ምርት፡ አለማደጉን፡ ያውቃል። አብዛኛው፡ የምግብ፡ መደጎሚያ፡ የሚጎርፈው፡ከአሜሪካ፡ መንግስት፡ ነው። የአለም፡ ባንክ፡ የውስጥ፡ ዘገባ፤ “Poverty and well-being in Ethiopia: the role of agriculture agency” ያሳየው፡ መለስ፡ ከሚሉት፡ የገጠር፡ ልማትና፡ የምርት፡ እድገት፡ ይጻረራል። የገጠሩ፡ ህዝብ፡ የሚተዳደርብት፡ መሬት፡ ባለቤት፡ ካለመሆኑም፡ በላይ፤ መሬት፤ ምርጥ፡ ዘር፤ ብድር፤ ማዳበሪያ፤ ሌላም፡ የአገልግሎት፡ ግብአት፡(input): ለማግኘት፡ የገዡ፡ ፓርቲ፡ ታዛዥ፡ መሆን፡ አለበት። የአሜሪካ፡ መንግስት፡ ይህንም፡ ያውቃል። የሰብአዊ፡ መብት፡ ድርጂቶች፤ በተለይ፤ (Human Rights Watch): እንዳረጋገጡት፡ ህወሓት፡ የውጭ፡ እርዳታ፡ የሚያዳርሰው፡ በታማኝነት፡ መለኪያ፡ እንጂ፡ ያለ፡ አድሎ፡ የህዝብን፡ ችግር፡ ለመፍታት፤ የግል፡ ክፍሉን፡ አገራዊ፡ ለማድረግ፤ አቅምን፡ ለማጎልመስ፤ ድህነትን፡ በሙሉ፡ ለማጥፋት፤ አለመሆኑንም፡ ያውቃሉ። የግል፡ ክፍሉ፡ ያለምንም፡ አድሎና፤ ተጽእኖ፡ ካላደገ፡ ዘላቂነት፤ ፍትሃዊነት፤ ያለው፡ እድገት፡ አይኖርም። መዋቅሩ፡ አይለወጥም። ስደት፡ ይቀጥላል።

የሀወሓት፡ መሪ፡ እንደሚሉት፡ ከሆነ፡ ኢትዮጵያ፡ የእርሻ፡ ምርቷን፡ በሚያኮራ፡ ደረጃ፤ አሳድጋለች። የአለም፡ ባንክ፡ ባለሙያወች፡ እንደሚሉት፡ ከሆነ፡ ግን፡ “ኢትዮጵያ፡ በእርሻ፡ ምርት፡ አስደናቂ፡ እድገት፡ አሳይታለች፡ የሚለው፡ የመንግስት፡ ወሬ፡” በምንም፡ ማስረጃ፡ የተደገግፈ፡ አይደለም። የፈጠራ፡ ወሬ፡ ነው፡ ማለት፡ ነው። በፈጠራ፡ ወሬ፡ ህወሃትን፡ የሚወዳደር፡ አመራር፡ የትም፡ አይገኝም። አለም፡ ባንክ፡ እንደሚለው፤ በገጠር፡ በብዙ፡ ሚሊዮን፡ የሚቆጠሩ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ መሬት፡ አልባ፡ ናቸው። ያላቸውም፡ የተበላ፤ የተቦረቦረ፤ የተቆራረጠ፤ ከእጂ፡ ወደአፍ፡ የሚሆን፡ መሬት፡ ነው። በገጠር፤ ብዙ፡ ሰወች፡ ይራባሉ። ከስምንት፤ እስከ፡ አስራ-ሶስት፡ ሚሊዮን፡ የሚሆኑት፡ በውጭ፡ የምግብ፡ ድጎማ፡ ይኖራሉ። የሚያሳዝነው፤ ደጓሚወቹ፡ አቅምን፡ በመገንባት፡ ፋንታ፡ ጥግኝነትን፡ የመረጡ፡ ይመስላል። በቅርቡ፡ ቢል፡ ጌትስ፡ “የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ከየትኛውም፡ አገር፡ የበለጠ፡ የምግብ፡ እርዳታ፡ ያስፈልገዋል” ያሉት፡ የማያሻማ፡ ድምዳሜ፡ የመንግስቱን፡ ውሸት፡ አጋልጦታል። በተከታታይ፡ በአመት፡ ከ አስራ-አንድ፡ በመቶ፡ ባላነሰ፡ አድጋለች፤ አሁንም፤ እያደገች፡ ነው፡ የሚለውም፡ የመንግስት፡ ፕሮፓጋንዳ፡ ከዚህ፡ አንጻር፡ መታየት፡ ይኖርበታል። እድገት፡ መኖሩ፡ ባያከራክርም፡ እድገቱ፡ የአብዛኛውን፡ ህይወት፡ እንዳለወጠው፡ ማስረጃው፡ ብዙ፡ ነው። ያለፈው፡ አመት፡ የተባበሩት፡ መንግስታት፡ የህብረተሰብ፡ እድገት፡ መለኪያ፡ (Human Development Index 2011)፤ ኢትዮጵያን፡ ከመቶ፡ ሰማንያ፡ አገሮች፡ መቶ፡ ሰቫ፡ አምስተኛ፡ ያደረጋት፡ ለዚህ፡ ነው። ህወሓት፡ ሲፈልግ፡ እየመረጠ፡ አለም፡ ባንክ፤ የተባበሩር፡ መንግስታት፡ የእድገት፡ ድርጂት፡ እድገታችን፡ አመሰገኑ፡ ሲል፡ የሚፈልገውን፡ ዘገቫ፡ መርጦ፤ የማይፈልገውን፡ ትቶ፡ ዋናውን፡ የእድገት፡ መለኪያ፡ እንደሌለ፡ አድርጎ፡ ነው። በማስረጃ፡ መዋሽት፡ የህወሓት፡ ልዩ፡ ተሰጦ፡ ሁኗል፡ ለማለት፡ የሚያስደፍረው፡ ለዚህ፡ ነው። ተደጋግሞ፡ ከተነገረ፡ ውሸት፡ እውነት፡ ይሆናል፡ የሚል፡ ግምት፡ አለው።

እውነቱን፡ በግልጽ፡ እናስቀምጠው። እድገታዊ፡ የሚባለው፡ የህወሓት፡ መንግስት፡ የሚመራብት፡ ስርአት፡ የአንድ፡ አናሳ፡ ዘር፡ ፓርቲን፡ የበላይነት፡ ብቻ፡ የሚያንጸባርቅ፡ ነው። ስለሆነም፤ የታወቁት፡ ተመራማሪ፡ ደሳለኝ፡ ራሃማቶ፡ አንዳሉት፡ ከህወሓት፡ ውጭ፡ ያሉ፡ ሁሉ፡ በእድገት፡ ላይ፡ የመናገር፤ ሃሳብ፡ የማቅረብ፤ የመሳተፍ፤ የመተቸት፤ መብት፡ የላቸውም። መለስ፤ እነዚህን፡ “ኪራይ፡ ሰብሳቢ፡ ስለሆኑ፤ አልሚ”፡ ለመባል፡ የሞራል፡ ብቃት፡ የላቸውም፡ ብለው፡ ደንግገዋል። ኪራይ፡ ሰብሳቢ፡ ማን፡ እንደሆነ፡ በማስረጃ፡ ገልጨዋለሁ። ወደፊትም፡ በማስረጃ፡ የተደገፈ፡ ትንተና፡ አቀርባለሁ። የመለስ፡ ድንጋጌ፡ አገር፡ ወለድ፤ ኢትዮጵያዊ፡ የሆኑ፡ ሁሉ፡ የመፍጠር፤ የማምረት፤ የመንቀሳቀስ፤ የመወዳደር፤ ሃብት፡ አግኝተው፤ አገራቸውን፡ የማልማት፡ ሚና፡ እንዳይጫወቱ፤ የሃብታምና፡ መካከለኛ፡ መደቭ፡ ለመፍጠር፡ እንዳይችሉ፤ ማነቆ፡ ሁኗል። በስልጣን፡ ላይ፡ የመቆየት፡ ጉዳቱ፡ አንዱ፡ መልክ፡ ይህ፡ ነው። መለስ፡ እንደደነገጉት፤ ተቃዋሚወች፤ እድገቱ፡ “ፍትሃዊ፡ አይደለም፤ ሙስናን፡ ያጠናክራል፤ ሰው፡ በሃገሩ፡ ሰርቶ፡ እንዲኖር፡ አያበረታታም”፤ እድገት፡ አለ፤ ግን፡ ዳቦ፡ የለም” ለማለት፡ አይችሉም። ይህን፡ ካሉ፡ ምርጫቸው፡ ወይ፡ ከርቸሌ፤ ወይ፡ ስደት፡ ይሆናል። ተስፋ፡ የቆረጡ፤ በስር አቱ፡ እምነት፡ ስለሌላቸው፡ አማራጭ፡ ሁኖ፡ የሚያዩት፤ ከሃገር፡ መሸሽ፤ ሃቭትን፡ ማሸሽ፤ ወዘተ፡ ሆኗል። ጠቅላይ፡ሚንስትር፡ መለስ፡ እድገታዊ፡ መንግስት፡ ብሎው፡ የሚጠሩት፡ ወሳኝ፡ አመራር፡ ጥቅሙ፡ ለአንድ፡ ቡድን፡ መሆኑን፡ የሚያጠነክረው፡ ተወዳዳሪ፡ አለመፈቀዱ፤ የመንጋር፡ መብት፡ አለመኖሩ፤ እውነቱን፡ መናገር፡ አለመቻሉ፡ ወዘተ፤ነው። የህዝብ፡ ጠበቃና፡ ተወዳዳሪ፡ ቢኖር፤ የቻይና፡ የእድገት፡ ስርአት፡ ያስከተላቸውን፡ አስቃቂ፡ ውጤቶች፡ ማሳየትና፡ የኢትዮጵያን፡ የእድገት፡ መስመር፡ ማረም፡ በተቻለ፡ ነበር።

ለምሳሌ፤ የአካባቢው፡ ውድቅት (massive environmental degradation and social dislocation that threatens sustainability)፤ እያደገ፡ የሄደው፡ በሃብታምና፡ድሃ መካከል፡ ያለው፡ የገቢና፡ የኑሮ፡ ልዩነት፤ የሙስና፡ ስፋትና፡ ጥልቀት፤ የወጣቱ፡ ትውልድ፡ በመሪወች፡ ላይ፡ ያለው፡ አመኔታ፡ እየተናደ፡ መሄድ፤ መልካም፡ የሆኑ፡ የባህል፡ እሴቶች፡ መጥፋት፤ ስርቆት፡ እነደብልጠት፡ ስራ፡ ላይ፡ መዋል፡ ከጥያቄ፡ ላይ፡ ይወድቁና፡ ይታረሙ፡ ነበር። መለስ፤ አመራራቸውን፤ የልማት፡ መሰረታቸውን፡ ጥያቄ፡ ውስጥ፡ የሚያስገባ፡ ትችት፡ ሁሉ፡ አይፈቅዱም። ቢፈቅዱና፡ የእራሳቸውን፡ ህገ፡ መንግስት፡ ስራ፡ ላይ፡ ቢያውሉ፡ ተስፋ፡ይኖር፡ ነበር። እርሳቸውም፡ ሆኑ፡ ደጋፊወቻቸው፤ ፖሊሲያቸውን፡ ከእራሳቸው፡ መለየት፡ አልቻሉም። ተቀናቃይ፡ ሁሉ፡ ጠላታቸው፡ አድርገው፡ ስለሚያዩ። ደጋፊወቻቸውም፡ ጥያቄ፡ አቅራቢወችን፡ “ግለሰብ፡ (መለስን፡ ማላታቸው፡ ነው)፡ ስለጠላችሁ፡ እንጂ፡ ፍትሃዊ፡ እድገት፡ ስለሌለ፡ አይደልም፡” ብለው፡ በጭፍን፡ የሚከራከሩት፡ በዚህ፡ መነጸር፡ ስለሚያዩት፡ ነው።በዛሬይቱ፡ ኢትዮጵያ፡ ሰውንና፡ የመንግስት፡ አመራርን፡ ለመለየት፡ አይፈቀድም። እውንትና፡ ውሸት፡ መለየት፡ሃጢያት፡ ሁኗል።

በቅርቡ፡ አዲስ፡ አበባ፡ በተካሄደው፡ አለም፡ አቀፍ፡ የኢኮኖሚ፡ ስብሰባ፡ ላይ፡ አንድ፡የቻይና፡ ባለስልጣን፡ ለመለስ፡ የተናገሩት፡ የሚከተለው፡ ነው። “ተማሩ፤ በጭፍን፡ ቻይና፤ ቻይና፡ አትበሉ። ችግሮችን፡ ተገንዝባችሁ፡ ሌላ፡ ውብ (beautiful) አማራጭ፡ ተከተሉ።” ለመለስ፡ ይህ፡ ምክር፡ ዋጋ፡ የለውም። በኢትዮጵያዊነታቸውና፡ በመላው፡ ኢትዮጵያዊያን፡ የመስራት፤ የመፍጠር፤ የማደግ፡ ችሎታ፡ የሚያምኑ፡ አይመስልም። በለውጥ፡ አያምኑም። በቃኝን፡ አይቀበሉም። ስኅተት፡ ሰራሁ፡ ብለው፡ ለመናገር፡ አይችሉም። እንዲያውም፤ ሌላውን፡ ማንበርከክ፤ ሰብነቱን፡ መግፈፍ፡ ይቀድማቸዋል። ፈላጭ፤ ቆራጭ፡ መሆናቸውን፡ ከዚህ፡ ልንማር፡ እንችላለን። ስለዚህ፤ ካለፈው፡ ስህተት፡ ለመማር፡ የማይችሉ፤ ለህዝብ፡ ንቀት፡ ያላቸው፤ የሌለውን፡ ፍትሃዊ፡ እድገት፡ አለ፡ የሚሉ፤ ህዝብ፡ እየተራበ፡ አልተራበም፡ የሚሉ፤ ወዘተ፤ ጠባብ፡ ብሄርተኛ፡ መሪ፡ በአለም፡ መሪወች፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ ውይይት፡ ላይ፡ ለመገኘት፡ የሞራል፡ ብቃት፡ ሊኖራችው፡ አይችልም። በሃያ፡ አንድ፡ አመታት፡ ያላሳዩትን፡ የእርሻ፡ ምርት፡ ውጤት፡ መለስ፡ እንዴትና፡ በምን፡ ተአምር፡ በሚቀጥሉት፡ አምስት፡ አመታት፡ ለኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ እንደሚያጎናጽፉት፡ ለእኔ፡ እንቆቅልሽ፡ ነው። ሌላው፤ የአንድ፡ አገር፡ መሪ፡ ከሃገሩ፡ ህዝብ፡ የበለጠ፡ የውጭ፡ ለጋሾችን፤ ሃብታሞችን (donors and investors): ሲያቀርብ፡ በእራሱ፡ ህዝብ፡ አይተማመንም፡ ማለት፡ ነው።

በህዝብ፡ የመስራት፤ የመፍጠር፤ የማምረት፡ ሃይል፡ የሚያምን፡ መሪ፤ የሃሩን፡ አምራች፡ ገበሬ፡ አቅም፡ ይገናባል፡ እንጂ፡ ሳውዲ፡ ስታር፤ ካሩቱሪ፤ አርሰው፡ ይመግቡኛል፡ ብሎ፤ በውጭ፡ የትርፍ፡ አምራቾች፡ አይመካም፤ አገሩን፡ ዘርፎ ለዘራፊ፡ አይዳርግም። ለዚህም፡ ጭምር፡ ነው፡ ሁኔታው፡ ከቀጠለ፡ ድሃው፡ ሆነ፡ መካከለኛ፡ መደብ፤ አገር፡ ወለድ፡ ከበርቴ፡ ሆነ፡ የተማረው፡ የስራ፡ እድል፡ የሌለው፡ ወጣት፡ መብቱን፡ የሚያስከብርበት፡ መንገድ፡ መፈለግ፡አለበት፡ ለማለት፡ መድፈር፡ ያለብን። እኛ፡ ካልበርታን፡ ማንም፡ የውጭ፡ ሃይል፡ መብታችን፤ ነጻነታችን፤ ክብራችን፡ ሊያጎናጽፈን፡ አይችልም። ክብራችን፡ ለመጎናጸፍ፡ የምንችለው፡ “የልዩንት፡ ኮፍያ/ባርኔጣ፡” አንግቨን፡ ሳይሆን፡ ተቻችለን፤ ተከባብረን፤ ለአንድ፡ አገር፤ ለአንድ፡ ህዝብ፤ ለአንድ፡ አላማ፡ በአንድነት፡ ስንቆም፡ ብቻ፡ ነው። አብረን፡ ከቆምን፡ ኢትዮጵያ፡ ሃብታምና፡ ዘመናዊ፡ እንደምትሆን፡ አልጠራጠርም።

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪዎች በወያኔ ላይ የኢኮኖሚ ማእቀብ ጥሪ አቅርቡ

Tuesday, June 5th, 2012

ያዳምጡ

የነጻ ፕሬሱ ታጋይ ንጉሴ ጋማ በክብር ተቀበረ

Tuesday, June 5th, 2012

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የዋልድባ ገዳምን በተመለክተ የሂዩስተን ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ምዕምናን የአቋም መግለጫ

Monday, June 4th, 2012

ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰው ልጆች ደኅንነትና ዘላለማዊ ሕይወት የምናገኝበትን ቅዱስ ወንጌል መሠረቱን ሳትለቅ በማስተማር ሁለት ሺህ ዓመታትን አስቆጥራለች። በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ታማኝ ኣገልጋዮቿ በከፈሉት መስዋዕትነት ዕምነቷን፣ ሥርዓቷንና ትዉፊቷን ጠብቃ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ጽላት(ታቦተ ሕግ) አክብራና አስከብራ ለአኛ ትውልድ ለማድረስ በቅታለች። እኛም ይህን ከቀደምት አበው የደረሰንን የሃይማኖት አደራ ከማናቸውም በላይ አስበልጠንና አስቀድመን፤ ጠብቀንና አስጠብቀን ለቀጣዩ ትዉልድ የማስረከብ መንፈሳዊ ግዴታ እንዳለብን ለአፍታም አንዘነጋዉም።

ቤተ ክርስቲያናችን በረጅም ጊዜ ታሪኴ አያሌ ፈተናዎችንና ውጣ ውረዶች ቢገጥሟትም ሁሉንም አንደየአመጣጣቸው ተቌቁማ በፆምና ፀሎት ኃይል በመድኃኔዓለም ድጋፍ በድል አድራጊነት እንደተወጣችው የታሪክ መዛግብት ፍንትው አድርገው የሚያስነብቡን ሐቅ ነው።

በዘመናችን በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በያቅጣጫው የሚሰነዘሩትን ጥቃቶች እያስተዋልን በዝምታ ለመመልከት የሚያስችል ህሊና አይኖረንም። ከብዙ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል በአሰቦት ገዳም በሚኖሩ መነኮሳት ላይ የተደረገው ጭፍጨፋ፣ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት ላይ የተካሄደው የመዝረፍና የማቃጠል ተግባር፣ በዓለ ጥምቀትን የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላት በሰላም እና በድምቀት አንዳይከበሩ ማወክ፣የቅዱስ ሲኖዶስም ሆነ ሌሎች ታላላቅ የመንፈሳዊ ጉባዔዎች እንዳይሰምሩ የመከፋፈልና የመበታተን ሤራዎች፣ አንደ ዝቌላን በመሳሰሉ ቅዱስ ገዳማት ላይ የአሣት ቌያ መልቀቅ ወዘተ..፣ ይጠቀሳሉ።

በተለየ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከቤተ ክርስቲያናችን ታላላቅ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ በሆነው የዋልድባ ገዳም ላይ በልማት ሥራ ሽፋን አየተካሄደ ያለዉን አፍራሽና አሣፋሪ ተግባር በተመለከተ ሀገር ቤት ከሚገኙት ዘመዶቻችን በቀጥታ ከሚደርሱን መረጃና፤ በተለያዩ የዜና አውታሮችም ክሚቀርቡት ትንታኔዎች በጥሞና እንደተገነዘብነው በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከፈተ ታላቅ ሤራና ጥቃት ነው።

የዋልድባ ገዳም ቅዱሳን አበው መነኮሳትና መነኮሳይያት ረሀቡንና ጥማቱን፣ ብርዱንና ሀሩሩን ታግሠው፣ የሀገርን ቅርስና ሀብት ጠብቀው፣ ለሀገር ሰላም ፣ ፍቅርና ዕድገት ያልተቌረጠ ፀሎት የሚያደርጉበት ቅዱስ ሥፍራ ነው።

የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዱት ዋልድባ የአብረንታንት ገዳም በንጉስ አል አልዓሜዳ ዘመነ መንግሥት በ484 ዓ፡ም ተመሠረተ። ገዳሙን በማስፋፋትና በማደራጀት ረገድ በአፄ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግሥት በ 1319 ዓ፡ም አቡነ ሣሙኤል ታላቅ አስተዋፆ ሲኖራቸው፣ ከዚያም ከደብረ ሊባኖስ የሄዱ አባቶች “ በገዳም እንኖራለን፣እህል አይገባንም” በማለት በመወሰናቸው የጣመ የላመ የማይቀመስበት የሞቀ የደመቀ የማይለበስበት ሲሆን ቌርፍ ወይም ሙዝ በጨው ተቀቅሎ በመመገብ ብቻ እንዲኖር የተወሰነበት ገዳም ነው።

የዋልድባ ገዳም ከአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት (1426-1460 ዓ፡ም) ጀምሮ በአራት ጅረቶች መካከል እንዲሆንና ገዥ እንዳይገባ አራሽ እንዳይሰማራበት የተወሰነ ሥፍራ ነው። በዚሁ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ሽሬ እንዳሥላሴ እና በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ ክልል በሚገኙ ሦስቱ የዋልድባ ገዳማት በአጠቃላይ ከ3000 ያላነሱ መነኮሳትና መነኮሳይያት የሚገኙበት ቅዱስ ሥፍራ ሲሆን አስከ 50 ዓመት ድረስ በአርምሞ ተወስነው/ከሰው ተነጋግረው የማያውቁ/ ቅዱሳን አባቶች በዘመናችን ሣይቀር የሚገኙበት ነው።

ይህን የመሰለ ለዘመናት የተከበረና የተቀደሰ ሥፍራ ነው እንግዲህ የወቅቱ መንግሥት የስኴር ፋብሪካ አቌቁማለሁ በሚል ገዳሙን አቌርጦ የሚፈሰውን የዛሬማን ወንዝ ለመገደብ በሚካሄደው ቁፋሮ የቅዱሣን አባቶች ዐፅም ያረፈበት በግሬደርና በሌሎችም መሣሪያዎች ኃይል እየታረሰና እየፈለሰ መሆኑን ስንሰማ ልባችን ይደማል። ሰላምና ፀጥታ ነግሶበት ተከብሮ የነበረ ሥፍራ ዛሬ ግን የዓለማውያን መናኸሪያ፣የነጋድያንና የሕዝብ መሥፈሪያ፣የመኪና መሽከርከሪያ መደረጉ ማኅበረ መነኮሳቱ ያዘኑበትና በፅኑ እየተቃወሙት መሆኑን በተለያዩ የዜና ማሠራጫዎች ካቀረቡት ዘገባዎች ተረድተናል።

ከላይ ከብዙ በጥቂቱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት ላይ ከፍተኛ ጥቃት መድረሱን በወቅቱም መፍትሔ ሳይገኝላቸው እየተባበሱ መምጣታቸው የእምነቱ ተክታዮች የሆንነዉን እጅግ አሳስቦናል።በተለይም መንግሥት የሚለው መንግሥት የቤተ ክርስቲያንን ይዞታና መብት በመጠበቅ ለሌሎች ጭምር አርአያ መሆን ሲገባው ጉዳዩን ቸል በማለቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከታሪክ ተጠያቂነት አያመልጥም።የሕዝብን ድምፅ አለመስማት ፣የቤተ ክርስቲያንንም አቤቱታ አለመቀበል ትዕግሥትን የሚፈታተን፣ መፍትሔ ካልተሰጠውም ዉሎ አድሮ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ በመሄድ አገርን የሚጎዳ ፡ ታሪክንም የሚያበላሽ ክስተት ከመሆኑ በፊት አስቸኴይ ርምጃ ይወሰድ ዘንድ አበክረን እያሳሰብን የሚከተሉት ጥያቄዎች ባፋጣኝ ተገቢው ምላሽ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያውያን ሁሉ መንፈሳዊ ሀብትና የተቀደሰ ሥፍራ የሆነው የዋልድባ ገዳም ክልል በማንም እንዳይደፈርና በልማት ሰበብ የተጀመረው እንቅስቃሴ እንዲቆምልን፣
በዋልድባ ገዳምና በዙሪያውም በሚገኙት አብያተ ቤት ክርስቲያናት የሚደርሰው ዝርፊያና ምዝበራ እንዲቆም መንግስት ለገዳማውያኑም ሆነ ለቅርሶቹ ተገቢዉን ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደርግልን፣
የዋልድባ ገዳም መነኮሳት በዝርዝር ላቀረቡት አቤቱታ ተገቢና በጎ ምላሽ እንዲሰጣቸው፣
በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙት ገዳማትና አድባራት የሀገር ሀብትና ቅዱስ ቦታዎች ስለሆኑ በማንም እንዳይደፈሩ መንግሥት አስተማማኝ ማረጋገጫ እንዲሰጥ፣ጥበቃም አንዲያደርግላቸው።
የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስጠበቅ በሚንቀሳቀሱ አባቶችና ክርስቲያኖች ላይ በመንግሥት ኃይሎች የሚደረገው ዛቻና እንግልት አንዲቆም እንጠይቃለን።
የመንግሥት የዜና ማሰራጫዎች በኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት አንዲሁም ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰዉን ጉዳት አንዳያፍኑና በግልፅ እንዲዘግቡ እንጠይቃለን።

እግዚአብሔር አገራችንን ኢትዮጵያንና ጥንታዊ ገዳማችንን ይጠብቅልን። አሜን።

ኢትዮጵያ፡- ምግብ ለችጋርና ለማሰብ!

Monday, June 4th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

በቅርቡ በዋሽንግቶን ዲሲ በጂ8 አባላት በተካሄደው፤የምግብ ዋስትና ስብሰባ ላይ በዋሽንግቶን ነዋሪ የሆነው ቆፍጣና ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በአዳራሹ መሃል ለመሃል ቆሞ ለፈላጭ ቆራጩ ጨካኝ ገዢ መለስ ዜናዊ “ነጣነትለተነፈገው ምግብ ትርጉም አልባ ነው” በማለት ሕዝባዊ ጩኸት አሰምቶ ነበር። እና የአበበ አስተያየት ልክ ነው?

ፕሬዜዳንት ኦባማ በዋሽብግቶን ዲሲ፤በሜይ 18 በተካሄደው የምግብ ዋስትና ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ስላለው ሁኔታ ለማወያየት የጋናን፤የታንዛንያን፤የቤኒንን ፕረዚደንቶች እና መለስ ዜናዊን በጋበዙበት ወቅት፤ቁምነገር ያለው ውጤት ያመጣል ብለው ያሰቡት በጣም ጥቂት: ነበሩ። በሰሚቱ ላይ ከዋይት ሃዉስ በተ መንግስት የወጣው ዘገባ “ አዲሱ የምግብ ዋስትናና የተመጣጠነ ምግብ ጥምረት የተረጋጋና ወጥነት ያለው የእርሻ ልማት እድገት በማምጣት 50 ሚሊዮን ለችጋር የተዳረጉትን ነፍሶች፤ከችጋር አውጥቶ በሚቀጥለው 10 ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ገዢዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማድረግና፤ለየሃገራቸው የምግብ ዋስትና ውጤታማ እቅድ በመንደፍና የግሉ ኢንቬስትመንትም ሕብረት ሁኔታዎች በሚያመቹበት ኢንቬስትመንቱ እንዲጨምር የጂ8 ቃልም ተጠብቆ ለአፍሪካ ፈጣንና አቅመ ብዙ የሆነ ዘላቂነት ያለው የእርሻ ልማት ማስገኘት ነው::”

በዓለም ታዋቂ ፤ታላላቅ ህብረ ብሄራዊ የሆኑ በርካታ የምግብ ኩባንያዎች <<እንደ ሽርክናው አካል>> ካርጊል፤ ዱፖንት፤ ሞንሳንቶ፤ ሲንጌንታ ኤጂ የአፍሪካን የእርሻ እድገት ለማገዝ የግሉ ዘርፍ የአፍሪካን የእርሻ ልማት ማገዣ የውል ዴክሌሬሽን>> ፈርመዋል። በ2010 በወጣው የዩ ኤስ ኤይድ መግለጫ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ በገጠሩ ከ10 ውስጥ ስምንቱ 0.93 ሄክታር ይዞታ ላይ ይኖራል።ይሄውም አናሳ የመሬት ይዞታ ለብዙሃኔ ኢትዮጵያውያን እጅጉን አስፈላጊውን ምርት የሚያርቡ ናቸው። አዲሱ ጥምረት ማለትም ካርጊል፤ ዱፖንት፤ ሞንሳንቶ፤ክራፍት፤ዩኒሊቨር፤ሲንጌንታ፤ኤጂ እና ሌሎችም የእርሻ ሕብረብሄራዊዎች አፍሪካን ከችጋር ለመታደግ፤ረሃብን ለመከላከል፤እና ራሳቸውን ለማስቻል የአፍሪካን ለም መሬቶች በሊዝ ይይዛሉ። ታዲያ ትንንሽ ቦታዎች የያዙት አፍሪካውያን የታላላቆቹን ኩባንያዎች የእርሻ ንግድ ሊቁዋቁዋሙት ይቻላቸዋል?

በኢትዮጵያ ወስጥ ያለውን የርሃብና የችጋር ሁኔታ በተመለከተ፤መደበኛ የሆነው የገዢው ፓርቲና ዓለም አቀፍ ረጂዎች ምላሽና መሸሻ መንገዳቸው፤በሃገሪቱ ያለውን እውነታ ችጋር ማር በመቀባት፤አለሳልሰውና አሳስተው፤ (ስር የሰደደ የተመጣጣነ ምግብ እጦት፤<<የምግብ ዋስትና>> ምናምን በማለት ይሸፋፍኑታል። “የአፍሪካ የችጋር ጨዋታ በካምፕ ዴቪድ” የሚለውን የኔን ጦማር ይመልከቱ።) የተፈጥሮ ሃይላትን በመውቀስ ማለቂያ የሌለውን ምጥዋት ማቅረብ። በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ለሚከሰተው ችጋርና የተራቡ ምስኪኖች እልቂት መጥፎ አስተዳደሩ አንድም ጊዜ ተወቃሽ ሆኖ አያውቅም :: ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፉ የምግብ ፕሮግራም (WFP) በኢትዮጵያ ዘገባው በሃገሪቱ ውስጥ <<3.2 ሚሊዮን ዜጎች ለምግብ እጦት ይዳረጋሉ፤ለዚህም (WFP) የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተጨማሪ 183 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለምግብ ዋስትናው ያስፈልገዋል።

የመለስ ዜናዊ የእርሻ ሃላፊ ምትኩ ካሳ የወቅቱን የምግብ ዋስትና እጦት በድርቅ ላይ፤ በዝናቡ መጥፋት፤በዝናቡ ወቅቱን ባለመጠበቁ አሳሰቦትል። “ይህን መሰሉ የመሸሻና ድክመትን የመደበቅ ሰበብ ደግሞ ለእኛ አዲስ ነገር አይደለም። ባለፈው ዓመትም ከኢያም በፊት ተጋፍጠነዋል፤እና እስካሁንም እየተቁዋቁዋምነው ነው። በአሁኑ ጊዜ ሃገሪቱ ይህን ለማሸነፍ በቂ ሪሶርስና ዘዴም አላት::” ይህም ዘዴ ባለፉት በርካታ ዓመታት ሲደረግ እንደነበረው ሁሉ በሙያዊ ልመና ተሰማርቶ ምጥዋት መቅፈፍ ነው። ከወራት ባልበለጠ ጊዜ የአሜሪካን መንግስት ለኢትዮጵያና ለአፍሪቃ ቀንድ ተጨማሪ 200 ሚሊዮን ለችጋሩ ለመርዳት ወስኖአል።በ2011 የአሜሪካን መንግስት በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን ችጋር ለመርዳት $1.1 ቢሊዮን ዶላር ሰብአዊ እርዳታ አድርጉዋል። በ2008 ኢትዮጵያ ከ$3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተመጥውታለች።ይህም ኢትዮጵያን ክፈተኛውን የአፍሪካ የልማት እርዳታ ተቀባይ አድረጉዋታል።በኢትዮጵያ ማለቂያ የሌለው የምጥዋት ችሮታ!

ኢትዮጵያ ማለቂያ የሌለው “”የምግብ ዋስትና እጦት ይገጥማታል’’ ማለት ጠሃይ ነገ ትወጣለች ብሎ እንደመተንበይ ነው። የምግብ ዋስትና እጦት በ2050 በጣም ይገዝፋል።የአሜሪካ ተንባይ ቢሮ በ2050 የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት በሶስት እጥፍ በማደግ 278 ሚሊዮን ይደርሳል የሚለውን አስደንጋጭ ትንበያ አሰምቶናል።ያንንም የሰማው መለስ ዜናዊ በማን አለብኝነቱና በአካኪ ዘራፍ ማን ያለ እኔ ባይነቱ በ2011 በችጋር ላይ ድልን እቀዳጃለሁ በማለት ያውጃል። “እራሳችንን ለመመገብና የተትረፈረፈ ምርት ላመስገኘት የሚያበቃን እቅድ አውጥተናልና በ2015 ከማንም እርዳታ ከየትም ምጥዋት አንሻም”” ይለናል።

በአዲሱ ለምግብና ለተመጣጠነ ምግብ ዋስትና አሜሪካና ሌሎቹ የጂ8 አባላት የአፍሪካን ችጋር ተጎጂዎች ለመርዳትና የአፍሪካን ፈላጭ ቆራጭ የሕዝብ ጠላቶች የሆኑ ገዢዎችን መርዳቱ የሚያስከትለውን የሞራል ውድቀት አልተገነዘቡትም አለያም አውቀውት ደንታ አልሰጡትም። የገጣሚውን ሩድ ያርድ ኪፕሊንግን ቃል በመዋስ፤በአፍሪካ ለተራቡና የችጋር ተጠቂ ለሆኑት ሕዝቦች ማለቂያ የሌለውን ምጥዋት መቸርን የራሳቸው “”ሸክም’’ አድወርገው ተቀብለውታል። ሆኖም ግን አሁን በመካሄድ ላይ ያለው ”አዲሱ የችጋር ጨዋታ” ትንሽ ረቀቅ ያለ ነው።ሕብረብሄራዊ የሆኑትን ዓለም አቀፍ የምግብ ኩባንያዎችአፍሪካን ”ለማዳን” በሚል ስም 1) እነዚህን ትላልቅ የእርሻ ኩባንያዎች የምርታቸውን ገበያ ያጣ ትርፍራፊያቸውን ችጋር ባጠቃቸው የአፍሪካ ሃገራት እንዲያፈሱ 2) በዓለም አቀፉ ገበያ ተፈላጊና እትራፊ የሆኑትን ምርቶች ለማምረትና ለገበያው ላመቅረብ መረ በአፍሪካ ያሉትን በመቶ ሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠሩትን ለም መሬቶች በሊዝ ስም በመቀራመት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ።ይህ አዲሱ ጥምረት ለዘመናት ተረጂነትን ያጎለበተውን ስርአት በመጠበቅ፤ የምግብ እርዳታን ሱስ በአፍሪካ በማደርጀት አፍሪካውያንን አናሳ ገበሬዎች ከይዞታቸው እያፈናቀሉ ና የምርት አቅማቸውን በማዳከም ችጋርን በራሳቸው እንዲቁዋቁዋሙት ማድረግ ነው።

እውነትን ማረጋገጥ

ሊታሰብበት የሚገባው በሂደቱ ውስጥ ካሉት ጥቂቶቹ አሜሪካንን ጨምሮ ወይም ዓለም አቀፉ ሚዲያ “ስለአዲሱ ጥምረት”አንዳችም ትኩረት አለመቸራቸው ነው። ሌላው ቀርቶ እርዳታን የኒያዳርሱት የሰብአዊ መብት ተሙዋጋቾች እንኩዋን እንደመልካም የማስታወቂያና የመቀስቀሻ መንገድ ነው የተመለከቱት።ኦክስፋም ግን አሻፈረኝ ባይ ሆንዋል። ሰበቡም “አዲሱ ጥምረት አዲስም አይደለም፤ደሞም ሃቀኛ ጥምረትም አይደለም” የሚል ነው።ግርግሩ አናሳ ገበሬዎችን በተለይም ሴቶችን ለጉዳት የሚጥል ነው።ጥምረቱ በእቅዱ ሴቶችን ወደ መድረኩ ማምጣት አለበት።” የአክሽን ኤይድ ደግሞ አመራርነት ነበረው። “አዲሱ ጥምረት የግል ሴክተሩን የሚወክል እንደመሆኑ፤ ፕሬዜዳንት ኦባማ እንዳሉት፤ ይህ በጣም አነስተኛ የሆኑትንም የግብርና ዘርፎችን ማካተት አለበት።በአፍሪካ ግብርና ውስጥ ሴቶች ናቸው ቁልፉን ሚና የሚጫወቱት።ማንኛውም የግል ሴክተር ጥምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሲንቀሳቀስ ሴቶችን ማካተቱ ግዴታ ሲሆን፤የአፍሪካን ሲቪል ማሕበረሰብም ማዕከል ሊያደርገው ይገባል::”

ልዩ ትኩረት የሚያስፈልገው ውይይት የተደረገበት የምግብ ዋስትና ነው እንጂ በሰሚቱ የተነጋገሩበት አይደለም። የዩ ኡስ ኤይድ አስተዳዳሪና የውይይቱ መሪ የነበረው ራጂቭ ካህን መለስ ዜናውን ለንግግር ሲጠራው የሚከተለውን በማለት ነበር።

በብዙ ሰዎች ሕሊና ውስጥ ተቀርጦ ያለው የኢትዮጵያ ምስል ከችጋር ጋር የተሳሰረ ነው።ከዚሁ ጋር ደግሞ በሕዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ ባለው እንቅስቃሴና ጠንከር ያለ ኢንቬስትመንት በግብርናው በኩል በማበረታታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ከዘንድሮው ችጋር አድነሃል። አዲስ ጥምረት በምንፈጥርበትም ነአሁኑወቅት ቢሆንም ስለዚህ ጉዳይ ልትነግረን ትፈቀውዳለህ? በግላችን ባደረግነው ውይይት ቃላችንን ጠብቀን የግሉን ዘርፍ ማቀፍ እንዳለብን በሕዝባዊ ኢንቬስትመንት በሕዝባዊ ድርጅቶች መታገዝ ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው ልትነግረን ትችላለህ?

መለስ ሲመልስም:

በአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን በአናሳዎቹ ባለእርሻ ገበሬዎችናበግሉ ሴክተር መሃል የሚደረግ ጥምረት ነው። በዚህም ዋናውን ቦታ የሚይዙት አናሳ መሬት ያላቸው ገበሬዎች 70 በመቶውን (አበበ ገላው መለስ ዜናዊን ዲክቴተር.ፈላጭ ቆራጭ………. በማለት ከንግግሩ አናጠበው) በአፍሪካ ከሕዝቡ 70 በመቶው በትንሽ ይዞታ ላይ የሚያርሱ ናቸው።ስለዚህም እነዚህን ትራነስፎርም በማድረግ የኖሩበትን ከመለወጥ በፊት ምንም አይነት የግብርና ተስፋ በአፍሪካ ሊኖር አይችልም።አሁን ባለንበት ደረጃ የግሉ ሴክተር ሚና አናሳውን የግብርና ባለቤት መደገፍ ነው። የገጠር መንገዶች ጥያቄ አለ፤የውሃ ችግር አለ፤የመስኖ ውሃ አዘረጋግ አለ። ይህ ሁሉ የሕብረተሰቡን አስተዋጥኦ ይፈልጋል። በእርግጥ ብዙ ያስፈልገናል። ከዚሁ ጋር የሕዝቡን ኢንቬስትመንትም እንሻለን። እኛ በአፍሪካ ያለነው አቅማችን የፈቀደውን እያደረግን ነው።እንዳልኩት አብዛኛዎቹ ሀገሮቻችን ከበጀታችን 10 በመቶውን በእርሻ ላይ እያዋልን ነው።ያም ሆኖ ተጉዋዳኞች ያስፈልጉናል። ዛሬ ጠዋት ፕሬዜዳንቱ (ኦባማ) ቃል ስለተገባው 22 ቢልዮኑ አኩዊላ ኢንሽዬቲቭ ሲናገሩ ነበር። ቃል የተገባልንን ገንዘብ ፕሬዜዳንቱ እንዳሉት እንፈልገዋለን። እንዲሁም የዳበሩት ሃገሮች በግብርናው በኩል ሊያደርጉ የሚገባቸው አለ፤ ምክንያቱም ገበሬዎቻችሁን ስትደጉሙ፤የኛ ገበሬዎች ደግሞ በድሆች ገዢዎቻቸው መደጎም ሳይችሉ በእኩል ደረጃ ሊወዳደሩ አይችሉም።ለምሳሌ በአውሮፓ ዩኒየን እያንዳነዱ ላም በቀን $2 ይሄ ደግሞ አንድ አፍሪካዊ ገበሬ በቀን ከሚያገኘው የበለጠ ነው። በመሆኑም ድጎማው የሚተገበርበት መንገድ ቢኖር ከድህነትና ከችጋር ማምለጫ መንገድ ይሆነናል።

መለስ ዜናዊ ”በሕዝባዊ ድርጅቶች ውስጥ ባለው እንቅስቃሴና ጠንከር ያለ ኢንቬስትመንት በግብርናው በኩል በማበረታታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ከዘንድሮው ችጋር አድነሃል…” የሚለው የካሃን ግምት ዝም ብሎ በዘፈቀደ የተሰነዘረ አስተያየት ነበር።ይህም የሚያሳየው ዩ ኤስ ኤይድ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ምንያህል ተአማኒ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ደንታ ቢስ መሆኑን የሚያሳየው።በዩ ኤስ ኤይድ ኦዲት ሪፖርት መሰረት (ማርች 2010, ገጽ 1). ኦዲቱ በዩ ኤስ ኤይድ/ኢትዮጵያ የቀረበው የድርጊት እቅድ እና ዘገባ ተቀባይነት ያለው ይሁን አይሁን የእርሻ ፕሮግራሙ አባላት የተጠቀሰው ውጤት ድጋፍ መስጠት አልቻሉም።በእርግጥም የኦዲት ቡድኑ የዘገባውን ውጤት ትክክለኛነት ከቀረበለት ማረጋገጫ የተባለ ሰነድ ላይ ለማመሳከር ሲሞክር በጥህፈት ቤቱም ሆነ ወይም ተግባሩን በሚያስፈጥሙት ቢሮዎች በኩል ይህን ማድረግ አልተቻለም። ሙሉና ወቅታዊ ድርጊታዊ ዘገባ ሰነድ በሌለበት የማኔጅመንት እቅድ፤ ዩ ኤስ ኤይድ ለመቆጣጠር የሚያስፈልገውን ዋነኛ መሳርያ የግብርናወ ፕሮግራም መተግበሩን ማረጋገጥ ጨርሶ አልተቻለም።

ከሃንና መለስ ዜናዊ ስለ “ሕዝባዊ ኢንቬስትመንት” እና “አነስተኛ መሬት ያለቸው ገበሬዎች” ላሞቹ ወደጋጣው እስኪገቡ ሊያወሩ ቢችሉም፤ ዋናው የነገሩ ቁምነገር ግን ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎቹ አፍሪካዊ ሃገራት፤ በሃገሪቱ ውስጥ በተንሰራፉት ፈላጭ ቆራጭ እኩይ ገዢዎች በሚያወሩት በምግብ እራስን የመቻል አርቲ ቡርቲ፤ ወሬያቸውና ከህበረብሄር ኮርፖሬሽኖች ጋር በሚፈጥሩት የነጋ አልነጋም የ ”ምግብ ዋስትና ማረጋገጫ” አዲስ ጥምረት ጠብ የሚል አንዳች ፋይዳ አይኖርም። በተኩላዎችና በጅቦች መሃል የአንድነት ህብረት ለጋዜል የሚተርፍ አንድም ጠብታ አይኖርም።

ባለፉት ስድስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ መለስ ዜናዊ (ለ99 ዓመታት ሊዝ በሚል) ለህንዶች፤ለቻይናዎች፤ለኮርያዊያን፤እና ለሳውዲ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ልጭ ገበያ እንዲያቀርቡ በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠሩ ለም መሬቶችን በሽርፍራፊ ሳንቲሞች ደረጃ ቸብችቦአል። የመለስ ዜናዊ ገደብ የለሽ አካኪ ዘራፍ ቀረርቶ ከ36 በላይ ከሆኑ ሃገራት ጋር የመሬት ውል ገብቻለሁ በሚል ይጮሃል።እነዚህ መሬቶች ደግሞ አንዳችም መተኪያ አለያም መቁዋቁዋሚያ ትክም ሆነ ካሳ ካልተሰጣቸው አነስተኝ መሬት ያላቸው ገበሬዎች ተነጥቆ ሲሆን የትላልቆቹ ኩባንያዎች ምኞትና የትርፍ ህልማቸው ምርታቸውን ለውጭ ገበያ በዳበረ ትርፍ መሸጥ ነው።

የእርሻ መሬት፤ጨርሶ የመሬት ባለቤት የመሆን መብታቸው በሕግ ተነፍጎ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እነዴት ይቻላታል? በሃገር ውስጥ የምግብ እህልን እያመረቱ ሌላውን ሃገር የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ የአምራቹ ሃገር ሕዝብ ግን መጨረሻ በሌለው ችጋር ሲጠበስ የምግብ ማምረቱ ነገር ምን ትርጉም አለው? ለም መሬቶችዋን ለካሩቱሪ፤ ሳውዲ ስታር፤ ካርጊል wezet በሊዝ ስም ሽያጥ ተካሂዶባት ባለችበት ሁኔታና እነዚህ ግዙፍ የሆኑ ኩባንያዎች ደግሞ ዓላማቸው ምርታቸውን ለትርፋመናነታቸው ማረጋገጫ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ቀደምት ተግባራቸው በሆነበት ሁኔታ ኢትዮጵያ እነዴት ብላ ነው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የምትችለው። 0.93 ሄክታር የሆነች አነስተኛ መሬት ላይ የሚያርሰውስ ገበሬ በምን አቅሙ ነው ከነሱ ጋር ተወዳድሮ ለነፍስ ማቆያው ያህል እንኩዋን የሚያመርተው? ነው ወይስ በችግሩና በታላላቆቹ የምርት ፋበሪካዎች እየተገፋና እየተጨፈለቀ ከጨዋታ ውጪ በመሆን ከአምራችነት ወደ ገዢነት በታላላቆቹ የምርት ፋበሪካዎች እየተገፋና እየተጨፈለቀ ከጨዋታ ውጪ በመሆን ከአምራችነት ወደ ገዢነት ሊዘዋወር ነው? መለስ ዜናዊ

ያላዋቂ ሳሚ ሆኖ ችክክ ብሎ የመሬት ባለቤትነትን በመቃብሬ ላይ በማለት በዓለም አቀፍ አዋቂዎች የተመሰከረለትና የመሬት ባለቤትነት ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ዋነኛ መሳርያ መሆኑን በተለመደው ባህሪው ክዶአል።መለስ በ200 እንዳለው (እስከቅርቡም በዚሁ አቁዋሙ እንዳለ ነው)

አሁን ባለንበት ደረጃ መሬትን በግል ንብረትነት መፍቀድን ለመቀበል አንድም አሳማኝ ምክንያት አላገኘሁም።የህንን ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ ሰበቡ ይህ ነው የሚል ማስረጃም አላየሁም።መሬትን የግል በማድረግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይቻላል የሚልና ገበሬውን ከችግሩ የሚያላቀቀው ይሄው ብቻ መሆኑን በአሳማኝ ሰበብ ብረዳና ገበሬውም ይህን የሚፈቅድ ሆኖ ካገኘሁት የኛም ፖለቲካዊ ፍቃደኛነት ከዚህ የተለየ አይሆንም ነበር።ይሁንና ግን መሬትን የግል በማደረግ አርሶ አደሩ ለ፤ያገኝ የሚችለውንም ሆነ ወደፊትም ይህ በመሆኑ ሊያስከትልበት የሚችለውን ችግር ከወዲሁ በማመዛዘን መሬትን የግል ማድረጉን አንፈቅድም። ወደፊት በኢንዱስትሪው መስክ ላይ ማትኮር እንዳለብን እናምናለን፤እነዚህም አርሶ አደሮች በዚያ መስክ ከእርሻው ውጪ የመቀጠር እድል ማግኘት አለባቸው።

በ2012 “የአፍሪካን አነስተኛ አምራች ገበሬዎች ሕይወት የመለወጥን አስፈላጊነት መለስ ዜናዊ በድፍረት ተናግሮ ነበር። ወይም ”ከአነስተኛው አምራቹን ገበሬ ውጪ በግብርናው መስክ ምንም ተስፋ እንደማይኖር መለስ ዜናዊ ደስኩሮ ነበር።ለኢትዮጵያ ታላቁ ለጋሽ ዩ ኤስ ኤይድ በ2010 ዘገባው (ምናልባትም ካህን ሳያነቡት ያለፉት) የተሳካ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥና፤ የሰመረ የእርሻ ልማት እድገት ሊገኝ የሚችለው 100% ገበሬው የመሬቱ ባለቤት ሲሆን ብቻ ነው። በሃገሪቱ ያለው ሁኔታና የመለስ አካሄድ ግን ገበሬውን ባለበት በመርዳትና የመሬት ባለቤትነት ዋስትና በመስጠት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ፈንታ መሬቱን በሊዝ ስም፤ ኢንቬስተሮች በሚል ሽፋን በመሸጥ ባለመብቱን ከኖረበትና ተወልዶ ካደገበት አለያም ለዓመታት ጎጆ ቀልሶ ከሚኖርበት እያፈናቀለ ለስደትና ለውርደት መዳረግን ነው።

ነጣነት የሌለበት ምግብ ትርጉም አልባ ነው

የኢትዮጵያ የምግብ ተመጥዋችነት ባለፉት 4 አሰርት ዓመታት እንደነበረው ይቀጥላል።የሰብአዊ መብት ዓለም አቀፋዊ ዴክለሬሽን እና የሕጣናት መብት ኮንቬክሽን የማንኛውም ሰበአዊ ፍጡር ምግብ የማግኘት መብት የተጠበቀ ነው ይላል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ገን በሁለት የችጋር መከራዎች ውስጥ ተዘፍቁዋል።የማይፋቅ ረሃብና ጥም የማይቆርጠው የነጣነት ረሃብ፤ ዴሞክራሲ፤የሰብአዊ መብት መከበር ጥማት።ኢትዮጵያዊያን ለዘህ ግፍና መከራ የተዳረጉት ግልጥነት በሌለው፤ ኢሰብአዊ በሆነ፤ አረመኔያዊ አስተዳደር ሳቢያ ነው።

በ2007 የዓለም የምግብ ቀን ላይ የጀርመን ፕሬዜዳንት ሆርስት ኮህለር ከተናገሩት ውስጥ

……. ችጋር ሊያመልጡት የማይችሉት አጋጣሚ ነው። ሆኖም ግን በብልህና በሳል ፖሊሲ ሊወገድ ይችላል። ይህ ደሞ ሊሳካ የሚችለው ያልበለጠጉ ሃገራት መሪዎች ለሕዝቦቻቸው የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥን ቀደምት ተግባራቸው ሲያደርጉ ነው። የዴሞክአሲ ተሳትፎን ለሕዝቡ በመስጠትና ተግባራዊ በማድረግ እርግጠኛ የሆነ የሕዝብን ፍላጎት ማያው አዴ ነው።የሕንዱ ታዋቂና የተከበሩ ሎውሬት አማርቲያ ሴን በተደጋጋሚ እንዳሉት ምርጫ በሌለባቸውና ተቃዋሚም በሌለበት፤ ገዢዎች በሃገራቸው ላይ በሚከሰተው ችጋር የተነሳ ስላጣናችንን እናጣለን ብለው መስጋትን አያውቁም።…መልካም አስተዳደርና እና በሃቅ ሕዝቡን ለማገልገል የቆሙ ተሹዋሚዎች፤ለኢኮኖሚ ፖሊሲው ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ናቸውና የሕዝቡን ስሜትና ፍላጎት በመረዳት ቸጋርን ማጥፋት ይችላሉ።

ከይዞታ መሬቱ ላይ በተፈለገ ሰአትና ባልተጠበቀ ወቅት ሊባረር እንደሚችል በስጋት ውስጥ ያለ የአነስተኛ ምርት ገበሬ እንዴት ብሎ ነው ያለችውን ጥሪት አውጥቶ በእርሻው ላይና በእርሳ መገልገያ መሳርያ ላይ ሊያውል የሚችለው? ማንን እንዴት አምኖ? ለረጂም ተከታታይ ጊዜያት በእርዳታ መኖርን የለመደ ህብረተሰብ መረዳትን ባህሉ ያደርግና ከመስራት ይልቅ እርዳታን መተማመኛ ያደርገዋል። ችጋር እኮ ባልበለጠጉት ሀጋራትም ሆነ በሌሎቹም ምንግዜም የተሳሳተ የፖለቲካ አካሄድ ውጤት ነው።

ምናልባትም ይቺን የልመና ተምሳሌት የሆነችውን አፍሪካ ፕሬዜዳንት ኦባማ በመሰረታዊ በሆነው የዴሞክራሲ ፕሪንስፕል ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ አዲስ ትስስር በመፍጠር ለውጥ ሊያስገኙ ይችሉ ይሆናል። “ምግብን በተመለከተ አፍሪካ ራስዋን የማትችልበት አንድም ሰበብ የለም።በመንደሮች ውስጥ የሚኖሩ የራሴ ቤተሰቦች አሉ።እነሱም ለረሃብ ተጋልጠው አያውቁም።የሚኖሩት ግን ችጋር በገሃድ ባለበት መንደር ውስጥ ነው።” በኢትዮጵያ ላለው ችጋር መፍትሄው የፖለቲካውን መዘውር በትክክለኛው ሁኔታ ለማሽከርከር ፈቃደኛ በመሆንና ዴሞክራሲያዊና ነጣ ምርጫ፤ተጠያቂነት፤ግልጥነት፤ለፖሌቲካው ሰፋ ያለ ክፍት ቦታ በመፍጠር፤ሰብአዊ መብትን በአግባቡ በማክበር ተግባራዊ ማድረግ ነው። ፕሬዜዳንት ኦባማ መለስ ዜናዊንና ሌሎቹንም አፍሪካዊ ገዢዎች “በመንደሩ ውስጥ የሚኖረው ለችጋር የተጋለጠው ሰው፤ችግር ለመፍጠር በቁጣ የነደደ መሆኑን ማሳሰብ አለባቸው።

ኢትዮጵያዊ ጋዘተጠኛ አበበ ገላው፤ በአዳራሹ ውስጥ ሕዝባዊ መከራና ስቃይ ገፋፍቶት በመነሳት ለፈላጭ ቆራጩ ግፈኛው መለስ ዜናዊ ……..””ያለነጣነት ምግብ ትርጉም የለውም” በማለት አሳሰበ። አበበ ገላው ትከከል: አይደለም?

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ:: http://www.ethiopianreview.com/amharic/?author=57

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የመኖር ዋስትና ስለማጣት

Tuesday, May 29th, 2012

ከየእግዜሩ ተሾመ ተፈሪ

የወያኔ/ኢህአዲግ መንግስት በአገሪቱ በዘረጋው ፍትህ የጎደለው የኢኮኖሚ ሥርዓትና የአስተዳደር በደል የተነሳ አፍቃሪ ወያኔ/ኢህአዲግ የሆኑ ግለሰቦች በአንድ ጀምበር ሚሊየነር ሲሆኑ አብዛኛው ህብረተሰብ ግን ወደ ድህነት አዘአቅት ተወርውሮ አይቶት የማያውቀው እጅግ አስከፊ ኑሮ እየገፋ ይገኛል፡፡

የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም ጥረት ከማድረግ በስተቀር ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ደንታ የሌለው የገዢው መንግስት በማናለብኝነት እኔ አውቅልሃለው፣ እኔ የምልህን ብቻ ስማ፣ በምመራህ መንገድ ተከተል በማለት ሰብአዊ መብቱንና ዲሞክራሲያዊ ነፃነቱን ነፍጎታል፣ ለሰው ሰራሽ የከፋ የኑሮ ውድነትም ዳርጎታል፡፡ በዚህም የተነሳ የሀገሪቱ ዜጎች የሰው ሀገር እንዲናፍቁና ለስደት እንዲነሳሱ አድርጓቸዋል፡፡ በኢሚግሬሽን መ/ቤት በየቀኑ የሚታየው ቁጥር ስፍር የሌለው ሰውም የዚህ ችግር ነፀብራቅ ነው፡፡ ከፊሉም በበረሃና በዱር ለመሰደድ ሲሞክር ለወንበዴና ለዱር አውሬ አደጋ እየተጋለጠ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እጅግ አስከፊና አሰቃቂ ነው፡፡ በገጠር የወያኔ/ኢህአዲግ ካድሬዎች የመሬት ሰጪና ነሺ ስለሆኑ ለሙ መሬት የሚሰጠው ለታታሪ ገበሬው ሳይሆን ለፓርቲ አባሎችና ለፖሊቲካ ደጋፊዎች ነው፡፡ ከዚህም በላይ ገዢው መንግስት በገጠር ገበሬውን እኔ የምልህን የማትሰማ፣ የምሰጥህን ትእዛዝ የማትቀበልና የማትፈጽም ከሆነ ከያዝከው የእርሻ መሬት ትለቃለህ እያለ ያስፈራራዋል፡፡ የከፊሉንም ገበሬ መሬት በመንጠቅ ለውጪ ባለሀብት እየሰጠበት ይገኛል፡፡ ይሄን መከራና ስቃይ አልቀበልም ያለ ገበሬ ሚስትና ልጆቹን በገጠር ያለአንዳች ረዳት በመተው ወደ ከተማ በስደት እየፈለሰ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሚስትና ልጆቹ ለችግርና ለረሃብ ተዳርገዋል፡፡ እሱም የከተማው ኑሮ ከምንግዜውም በላይ የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥ የበዛበት ወቅት በመሆኑ ከእነሱ ያልተሸለ ኑሮ እየኖረ ነው፡፡

በከተማ የሚገኘው አብዛናው የመንግስት ሠራተኛ የBPR (Business processing and re-engineering) ፖሊሲ ተጠቂ ነው፡፡ በመሠረቱ የBPR አላማ ለፓርቲ አባል መመልመያና ለኢህአዲግ ለሚያጎበድዱ መሾሚያ ሲሆን የኢህአድግን የተሳሳተ ፖሊሲ ለሚቃወሙ ደግሞ የደረጃ እድገት መከልከያና ከሥራ ማፈናቀያ ዘዴ ነው፡፡ በመሆኑም የመንግስት ሠራተኛው በሰበብ አስባቡ እየተፈረጀ ያለ ምንም ምክንያት ከሥራ ገበታው እየተፈናቀለ ይገኛል፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በዚህ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ላይ ከሥራ ገበታው የተገለለ ሰው የኑሮ ውድነቱን እንዴት አድርጎ መቋቋም ይቻለዋል?

የሥራ አጡ ቁጥር እጅግ በጨመረበት በአሁኑ ወቅት የመንግስት መረጃ ወጣቱ ሥራ ይመርጣል እየተባለ በአዋጅ ይነገርለታል፡፡ የትኛው የሥራ መስክ ተከፍቶ ነው የሚመረጠው? ትንሽ አለ የሚባለውም የኮብል ድንጋይ ስራ ሲሆን ይህንንም የገዢው ፓርቲ ለፖለቲካ ድጋፍ ብሎ ያደራጃቸው ወጣቶች ናቸው እየተጠቀሙበት ያለው፡፡ በአንዳንድ የውጪ ኢንቨስተሮችና የእርዳታ ድርጅቶች የሚከፈቱ የሥራ እድሎችም በመንግስት በኩል ክልከላ ስለሌለ በአብዛኛው ከውጪ በሚገቡ የሌላ ሀገር ዜጎች ተይዞ ይገኛል፡፡

የኢህአዲግ የገዢው ፓርቲ የንግድ ድርጅቶችና ደጋፊዎች በተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ተሰማርተው ቢሮክራሲያዊ እንቅፋት እንዳይገጥማቸው፣ የቀረጥና ግብር ውጣ ውረድ እንዳያስቸግራቸው፣ የካፒታል እንዲሁም የመረጃ እጥረት እንዳይኖርባቸው ሁሉ ነገር ተመቻችቶላቸዋል፡፡ በአንፃሩ የወያኔ/ኢህአዲግ ደጋፊ ያልሆነ የንግዱ ህብረተሰብ በነፃነት ተንቀሳቅሶና ተወዳድሮ እንዳይሰራ ፍታዊ ባልሆነ ግብርና ቀረጥ ጫና፣ ቢሮክራሲያውዊ ውጣ ውረድ፣ የፋይናንስ እጥረትና በጉቦ ወዘተ… ሁለገብ እንቅፋት እንዲገጥመው በማድረግና ተወዳዳሪነቱን በማዳከም ከሥሮ ከገበያው እንዲወጣ ይደረጋል፡፡

የተምሮ ማስተማር የትምህርት ዘርፍም አደጋ ላይ ነው፡፡ የገዢው መንግስት የተሻሉ መምህራንን በሰበብ አስባቡ እያባረረ እውቀት ችሎታና ብቃት የሌላቸውን አፍቃሪ ኢህአዲጎችን በመተካት የትምህርቱን ጥራት አዳክሞት ይገኛል፡፡ ይህ ደግሞ በወደፊቱ የሀገሪቱ እድገት ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተፅእኖ በጣም አደገኛ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በቅርቡ ደግሞ ለኑሮ ውድነት ማስታገሻ አስተማሪዎች ጥቂት ደሞዝ ጭማሪ ጠየቁ በማለት መንግስት በአንዳንድ መምህራኖች ላይ ከሥራ ገበታቸው የማፈቀናል ተግባር እያካሄደ ነው፡፡ በተማሪውና በአስተማሪው መካከል መልካም ግንኙነትም እንዳይኖር መንግስት አስተማሪውን በተማሪው እያሰለለ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ አስተማሪው በነፃነት ማስተማር፣ ተማሪውም ትምህርቱን በሥነ ሥርዓት መከታተል የማይችልበት ደረጃ በመድረሱ ት/ቤት ለስም ብቻ ገብቶ የሚወጣበት ሆኗል፡፡

በኢትዮጵያ ሀገራችን በአሁኑ ጊዜ የኑሮ ውድነትን፣ የትምህርት ጥራት ውድቀትን፣ የሥራ እጥረትንና በአጠቃላይ የአስተዳደር በደልን ተከትሎ ሀገሪቱ እጅግ የከፋ ችግር ላይ ነች፡፡ በዚሁ ላይ ህብረተሰቡ በነፃነት እንዳይንቀሳቀስና ሃሳቡን እንዳይገልፅ በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ጠንካራ የደህንነት/ስለላ ስርአት በመዘርጋትና እንዲሁም በህብረተሰቡ መካከል በገንዘብ በመደለል አንድ ለአምስት ሰዎች የሚል ስውር ሰላዮች በማሰማራት ህብረተሰቡ ከቤቱ በሰላም እንዳይወጣና እንዳይገባ እያወኩት ነው፡፡ ለመብታቸውና ለነፃነታቸው ለመታገል ቀና የሚሉትን ደግሞ አሸባሪዎች፣ የግንቦት 7 አባላት፣ የአርበኞች ግንባር አባላትና ደጋፊዎች በማለት በየፍርድ ቤቱና በየእስር ቤቱ ያለምንም መረጃ እንዲሰቃዩና እንዲታጎሩ እየተደረገ ነው፡፡

አቶ መለስ ዜናዊና መሰሎቻቸው በሀገር ያልታየ አሀዝ በውሸት በመጥቀስ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ እንዳደገችና ወደፊትም እንዲሁ በፍጥነት እያደገች እንደምትሄድ በየጊዜው ይደሰኩሩልናል፡፡ ኢትዮጵያ ግን ለሳቸውና ለመሰሎቻቸው ካልሆነ በስተቀር ለሌላው ህብረተሰብ የችግርና የመከራ ሀገር ሆናለች፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ ከወያኔ ሹማምንቶችና መሰሎቻቸው በስተቀር ሌላው ህብረተሰብ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በሀገሪቱ የመኖር ዋስትናው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ ይገኛል፡፡

መለስ አለምላስ!

Monday, May 28th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

‹‹ነጻነትን›› ብሎ የጮህው ወገን

በሜይ 18 2012 መለስ ዜናዊ በማይዋጥለትና ጨርሶ እስከመቃብሩ ድረስ ሊረሳው የማይችለውን ትምህርት ቀሰመ፡፡በነጻው ሃገር፤ ሃሳብን ያለምንም ገደም መግለጽ በሚቻልበት ነጻ ምድር፤መለስ አፉ ተለጎመ፡፡ ያ ያለገደብ ባሻው መልኩ ስድብና ነቀፌታ፤ ፌዝና ሽሙጥ፤ተራ ክብረ ነክ ቃላት ሲተፋ የነበረው አንደበቱ ታሰረ፡፡ በዋሺንግቶን ከተማ የሚኖረው ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አበበ ገላው፤ በጂ8 ስብሰባ መሃል ስለ አፍሪካ የምግብ ዋስትና ላይ በተካሄደው ውይይት መሃል ብድግ ብሎ አዳራሹን ባናወጠው ድምጽ ሲናገር መለስ ዜናዊ አይኑ ፈጦ ቀረ:: የአበበ ገላው ሃያል ድምጽ አስተጋባ:-

መለስ ዜናዊ አምባ ገነን (ዲክታተር) ነው፤ እስክንድር ነጋ ይፈታ፤የፖለቲካ እስረኞችን ፍታ:: መለስ ዜናዊ ዲክታተር ነህ!፤ሰብአዊ ክብርን እያዋረድክ ሰዎችን ለሞት የምትዳርግ ወንጀለኛ ነህ፡፡ ነጻነታችንን እየተገፈፍን ምግብ አያስፈልገንም፡፡ ከምግብ በፊት ነጻነታችን እንፈልገዋለን፡፡ ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት!

በማለት ወጣቱ ጋዜጠኛ ነጻነትን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጠራ፡፡ በአዳራሹ የነበሩት ተሳታፊ የተከበሩ ሁሉ በአግራሞት ተመለከቱት፡፡ አበበ ገላው ያንን አጭር፤ ንግግር ሲሰጥ ለመለስ ግን ማለቂያ የሌለው የመከራ ቀን ወቅት የሆነበት መብረቃዊ ጥሪ ነበር፡፡

አፍ ዘጊው አፉ ሲዘጋ: መተንፈስ ሲያቅተው:- መለስ ዜናዊ የራሱን መድሃኒት ሲቀምስ

መለስ ዜናዊ ገና ‹‹በአፍሪካ የአስተራረስ ትራንስፎርሜሽኑን›› እያለ ሰበካ ሲጀምር: አበበ ገላው አዳፈነው:: ይህን ለማስረዳት ግን ከ 30 ቃላቶች በላይ መሄድ አልቻለም፡፡ የኢትዮጵያውያን ወኪል የአበበ ገላው ድምጽ ‹‹ምግብ ያለ ነጻነት ዋጋ የለውም፡፡የሚያስፈልገን ነጻነት ነው፡፡ ነጻነት! ነጻነት!›› ሲል: መለስ እንደገና ለሴኮንዶች ያህል ሰመመን ወሰደው፡፡ “ቃል የተገባልንን 22 ሚሊዮን ዶላር እንፈልጋለን፤ይሰጣችኋል የተባልነውን ዶላር አምጡ አለ መለስ:: ምንግዜም እንደሚባለው ዞሮ ተመልሶ ገንዘብ ነው ምኞቱ ገንዘብ ነው ቅዠቱ፡፡ አበበ የማይፈልገውን ስም ግን ሁኔታው አስገድዶት የመለስን ስም ጠራው፡፡ በአዳራሹ ያሉት አይኖች ሁሉ ወደ ተጠራው ሰው አፈጠጡ! ተጠሪው አይኖቹን በልጥጦ በድንጋጤ ወዴት ማየት እንዳለበት የጠፋው ይመስል ተደናገጠ፡፡ መለስ በዚህ የቁም ቅዠት ውስጥ ሆኖ ያኔ ነው አበበ ገላውን በፍርሃት የአየው፡፡ መለስ የተራበውን አንበሳ ውሳኔ ለማወቅ እንደተደናገጠው ገመሬ ዝንጀሮ አይኑ ተጉረጠረጠ፡፡ፈራ! “እንዴ!!!ይሄ አበበ ገላዉ አይደለም እንዴ? ቃሊቲ አስገብቼ ዘግቼበት አልነበረም እንዴ? እንዴት ወጥቶ እንዴትስ እዚህ ደርሶ፤ አሁንስ ምን እያደረገ ነው? ግራ የገባው ግራ ዕይነት ነበር ሁሉ ነገር ለመለስ፡፡ አልደፈርም ብሎ ሲኩራራና በአጫፋሪዎቹም ማን ሊደፍርህ የተባለለት መለስ ዜናዊ ጭራዋ የተቆረጠች አይጥ ሆኖ ተብረከረከ፡፡

መለስ መልሶ ራሱን ለመቆጣጠር በመጣርና የጀመረውን ለመቀጠል በመሞከር ሃሳቡንና የማስመሰያ እቅዱን ከመናገር ይልቅ እንደተበላሽ የሙዚቃ ሸክላ ይደጋግም ጀመር፡፡ ‹‹ሰባ በመቶው…. እእእ የአፍሪካ ሰባ በመቶው ሕዝብ….እ እ…›› ምንም ማድረግ አልቻለም፡፡ ወደ ሰብሳቢው በመመልከት ‹‹እባክህ አድነኝ›› በሚል አመለካከት ያየው ነበር፡፡ ሰብሳቢውም እሱም በነገሩ ተደናግጦና ተገርሞም ነበርና ከአንደበቱ የወጡት ቃላቶች ‹‹ደህንነቶች እባካችሁ እርዳታ›› የሚሉት ብቻ ነበሩ፡፡ለሰባት ሴኮንዶች ያህል ያ አፉ እንዳመጣለትና እንዳሻው ፓርላማ በሚለው ስብስብ ውስጥ ሲደነፋ የኖረው መለስ ጨርሶ ሕሊናው ማሰብና ማሰላሰል በማይችልበት ደረጃ ውስጥ ሰመመን ገዛው፡፡ጭንቅላቱ ተደፋ፤ አገጩ መሬቱን ሊያስስ ደረሰ፤ በፍርድ ፊት ቀርቦ በዳኛው የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ነፍሰ ገዳይ፤ባዶውን ወለል እያየ በውስጡ ‹‹ምን አቅብጦ አመጣኝ እንደሚል በቁጭት ተውጦ፤ በፍርሃት ርዶ፤ በንዴት ከስሎ ዝም አለ:: የቪዲዮ ካሜራው በአቅርቦት ሲያመጣው፤የጭንቀት ትንፋሹ ወጥሮት፤ወደ ማስመለሱ ደረጃ ያደረሰው ይመስል ነበር፡፡ ሸሚዙን አልፎ የሚርገበገበው ደም ስሩ ሊፈነዳ ደርሷል፡፡ የደም መዘዋወሩ ለሴኮንድ ስራውን ያቆመ ይመሰል ነበር፡፡የሰውነቱ መለዋወጥ ሺህ ቃላቶችን ይናገሩ ነበር፡፡ ብቻ የሞት የሽረቱን ያህል በመፍጨርጨር ምንም እንዳልሆነ ለማስመስል በመሞከር ከንፈሩን አድርቆና ተቆጣጠሮ ከመንቀጥቀጥ እየተከላከለ፤ ማጉረምረሙን ቀጠለ፡፡ በሚናገርበት ወቅትም፤እጆቹ ይርገበገቡ፤ጣቶቹ እየተወጠሩ ራሱን መቆጣጠር መቻሉን ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ክፋቱ ግን የዚያ የቆራጥ የሕዝብ አንደበት ድምጽ ውቃቢውን ገፎታልና ጨርሶ ጀግንነቱ ሊታይለት አልቻለም፡፡ በመረዋው ድምጽ ተዳፈነ፡፡

እራሱን እንደነበልባል እሳተ ገሞራ በመቁጠር ‹‹ተቃዋሚዎች ይህን የ2010 ምርጫ ለማደናቀፍ ቢሞክሩ›› በማለት መለስ ዜናዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማስፈራረትና በስልጣኑ በመኩራራት እንደደነፋውና ‹‹ምርጫውን ለማደናቀፍ ካሰቡ፤ በሙሉ ሃይላችን ጨፍልቀን፤እስከዘልአለሙ እንዘጋባቸዋለን›› በማለት የፎከረው ይሄው ሰው ነው:: ዛሬ እንዲህ ምላሱ ያነቀውና ጉሮሮውን የወጠረው፡፡ ዛሬም ቢቻለው አበበን በጥርሱ ሳይቀር ቢቀረጣጥፈውና አጣድፎ ቃሊቲ አስገብቶ ‹‹በሉት›› ቢል ምኞቱ ነበር፡፡ጉረኛው፤ ተኩራሪው፤ጋጠ ወጡ፤ አሽሙረኛው፤መለስ ዜናዊ ተሳዳቢው፤ ዛሬ ምላሱ ተሳሰረ፤መናገር ተሳነው:: ወጣቱን የሕዝብ ተሟጋች ሊቋቋመው ጨርሶ ብቃት አጣ፡፡ ወኔው ተሰለበ፡፡ለፓርላማና ለድርጅት አባሎቹ ጉራ ሲተረትር የኖረው፤ ለሚቀርብለት ቃለ መጠይቅ ብላጣ ብልጥ መልስ የሚሰጠው፤አዋቂና ምሁር ለመምስል የሚኩራራው መለስ ዜናዊ አፉ ተለጉሞ እስቲ ትንፍሽ ትልና እንደተባለ ያህል፤የሚሰነዘርበትን ‹‹ ጨቋኝ ገዢ፤ሰብአዊ መብትን በመጣስ ሰዎችን የምተገል ነህ›› ሲባል ከመስማት ሌላ ምርጫ አጣ፡፡

መቼስ ምን ይደረግ ሃገሩ አሜሪካ ሆነና ከዚህ ሌላ ማድረግ የሚችለውም አልነበረውም፡፡በዚህ በነጻ ሃሳብን የመግለጽ መብት በተከበረበት አሜሪካ፤ ንጉሱን ተራ፤ ተራውን ሰው ንጉስ በሚየደርግበት ሃገር ምን የበል? የሚመረውን ማጣጣም፤ የማይፈልገውን ከመሸከም ባሻገር ምን ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከሌሎቹ ተሳታፊዎች ተርታ ሆኖ ልብስ አልባው ንጉስ ላይ እንደረሰበት አይነት ሁሉም በፍርሃት አፉን በተለጎመበት ሁኔታ ሕጻኑ ልጅ ግን የንጉሱሰን እርቃን መሆን ‹‹ ንጉሱ ልብስ አልለበሱም!›› ብሎ እንዳጋለጠው አይነት መለስም በጀግናና በማይገበር ተሟጋች አንደበት ‹‹መለስ ዜናዊ ፈላጭ ቆራጭ ዲክቴተር ነው” ተብሎ ተጋለጠ፡፡ ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን፤መለስን በምጥና በጭንቀት ሰአቱ አዩት፡፡ ሁል ጊዜ ‹‹አቤት ጌታዬ፤ እሺ ጌታዬ›› የሚሉት አሽቃባጮቹ በሌሉበት፤በአምላኪዎቹ አፋሽ አጊንባሾቹ በሌሉበት፤ለውርደቱና ለእውነተኛው ማንነቱ ተጋለጠ፡፡ ያቺ አጭር 19 ሴኮንድ የዳዊትንና የጎልያድን ታሪክ በድጋሚ አሳየች፡፡ ለታዛቢዎቹና ለጉዳዩ ባለቤቶች ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ለ21 ዓመታት ሲያስር ሲገል ሲያፈናቅል ሲክድ ሃገርን ሲሸጥ የነበረና መላውን ኢትዮጵያዊያን ለጉሞ የኖረው መለስ ዜናዊ በ19 ሴኮንድ የተነጣጠረ ምት ሲለጎም አንደበቱ ጥርቅም ብሎ ተዘጋ፡፡

በነጻ የመናገር መብት ሃይል እና ለሃይልም እውነት ሲነገር

እኔ ለሁሉም ነጻ የመናገር መብት በሚለው ዲክቴተሮችንም ጨምሮ አምናለሁ፡፡ በ2010 ሴብቴምበር ላይ መለስ ኮሎምቢያ ዩኒበርሲትይ ተጋብዞ ለመናገር ከየአቅጣቸው ውግዘት ሲደርስበት እኔ ያን ጊዜም የመለስን የመናገር መብት እንዲከበር ተከራክሬአለሁ፡፡ከዚሁ በተጓዳኝም ተቃዋሚ ሃሳብ ያላቸውም ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲቃወሙ መብታቸዉን እደግፋለሁ፡፡ ምናለበት ሁሉም የየራሱን ይናገርና ፍርዱን ለአድማጫ መተው፡፡ፕሬዜዳንት ኦባማ ንግግር ሲያደርጉ ተቃውሞ ይሰማል፡፡በቅርቡ በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ንግግር ባደረጉበት ወቅት አንድ ተቃዋሚ ተቃውሞውን ሲያሰማ ፕሬዜዳንቱ አልደነገጡም: ከንግግራችዉም ዘነፍ አላሉም: ግራም አልተጋቡም፡፡ ለተቃዋሚውም ያሉት ‹‹ጌታው፤እኔ እዚህ የተገኘሁት እነዚህን ሰዎች ለማነጋገር ነው፡፡አንተ ደሞ የራስህን ስብሰባ ጥራ፡፡ ያንን ሳታደርግ በመናገርህ ግን ብልግናህን አሳየህ፡፡……..የሌሎቹን ስሜት እትንካ ጣልቃም አትግባ፡፡ተግባባን? ሰውዬውም ሁኔታው በአግባቡ ስለገባው በተናገረው አላፈረበትም በሁኔታው ግን ተደናገጠ፡፡ይህም በነጻ የመናገር አካል ነውና፡፡

የሂሰኞች ቪቶ (“heckler’s veto”) ለአሜሪካ ሕገ መንግስት በጣም ወድ የሆነው የፈርስት አሜንድመንት አካል ነው፡፡ምንግዜም መሪዎች ናቸው የሕዝባቸውን አንደበት ሊለጉሙ በስልጣናቸው የሚመኩት፡፡በሂሰኞች ቪቶ ግን ግለሰቦች ባለስልጣኖችንና ጉልበተኞችን ዝም ያሰኙበታል፡፡ መንበሩ ይለዋወጣል፡፡ ማለትም መለስ ዜናዊ በአበበ ገላው ሴንሰር ተደረገ፡፡እቀሙ ቢኖርና ትንሽም ብትሆን ሀቅ በመለስ ውስጥ ኖራ ቢሆን ለአበበ ‹‹ከምግብ በላይ ነጻነትን እንሻለን›› ውንጀላ፤መልስ መስጠት ይችል ነበር፡፡ ለጥቂት ጊዜ ራሱን ካረጋጋ በኋላ ከነጻነታቸው ጀምሮ በርካታ የአፍሪካ ዲካታተሮች ለዓለም ሲሉት እንደኖሩት ሁሉ፤ አቅመቢሶች ብዙሃን፤ መሃይሞች፤የታረዙ፤የታመሙና ለረሃብ የተጋለጡ የፖለቲካ ዴሞክራሲን ለማጣጣም ገና ችሎታው የላቸውም፡፡ ፍላጎታቸው በሆድ ዴሞክራሲ ላይ እንጂ፤የፖለቲካ ዴሞክራሲና የፖለቲካ መብት አይደለም፡፡ አፍሪካውያን በዳቦና ለዳቦ ነው የሚኖሩት፤ለብዙሃኑ አፍሪካውያን፤ ምርጫ፤የፍትህ መብት፤እና ነጻነትፍቺና ትርጉም አልባ ናቸው በማለት መመለስ በቻለ ነበር፡፡

ለየት ባለ መልኩና ክብርና ባጎናጸፈ ሁኔታ ልከበር ይገባኛል በማለት መለስ ያስብ ይሆናል፡፡እንደአፍሪካ መሪነቱ አንቱታ ይገባኛል ይልም ይሆናል፡፡ በዊኪ ሊክስ በኩል ሾልኮ የወጣው ሰነድ እንደሚያስረዳው ከሆነ ሰውዬው መመለክን፤በምእራቡ ዓለምና ከተቻለም ከዲያስፖራው ተቀባይነትና ከበሬታን የሚናፍቅ፤ሕልመኛ ነው ይለዋል፡፡ በምእራቡ ዓለምም የአፍሪካ ልዑል ራስ ሆነ በሚያሸበርቅ የብረት ጡሩር ተውቦ፤ በአፍሪካ ችጋር፤ ድህነት፤ የፍትህ እጦት፤ ላይ ያን የሚያብረቀርቅ ጦሩን ሲሰካበትና አፍሪካን ነጻ ሲያወጣት በሚመስል መልኩ መሳልና መቀረጽን ይጓጓል፡፡የዘመናዊነት ፈጣሪ፤የአዳዲስ ጉዳይ ፈጣሪ፤የትራንስፎሜሽን አውራ በመባል ሊታወቅ ነው ምኞቱ፡፡በተገነቡት መንገዶች፤ለአንጸባራቂዎቹ የገነባቸው ህንጻዎች፤አድረጌያለሁ ለሚለው የትምህርት ስርአት መሻሻል፤ስለትራንስፖርቱ፤ስለጤናና የሃይል ማመንጫው መሃንዲሱ ነኝና ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ይህን ተግባሬን ሊያደንቁልኝና በአመራሬ ስር ሊወድቁ ይገባል ብሎ ይቃዣል፡፡አበበ ገላውን እገድልሃለሁ በማለት ሲደነፋ የነበረው የደህነንት አባልም የተፋው ይህንኑ ነበር፡፡‹‹ኢትዮጵያ እኮ ተለውጣለች፡፡ ወደ ሃገር ገብተህ ለውጡን ስላላየህ ነው፡፡ኢትዮጵያ በጥሩ ሁኔታና በግሩም መሪ ስር ነች፡፡ እንዳንተ አይነቶች ሰዎች ናቸው ከርቀት እየጮሁ ያስቸገሩን››::

ኢትዮጵያ በጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም፡፡ በዓለም ላይ በጥንታዊነቷ፤ ባለታሪክና በነጻነቷ፤ በአፍሪካም በሕዝብ ብዛት በሁለተኛ ደረጃ ላይ በመሆን የምትታወቀው ኢትዮጵያ፤ በድህነትም ቢሆን በዓለም እጅጉን ድሆች ተብለው ከታወቁት ሀገራት ከኒጄር ለጥቃ በሁለተኛ ደረጃ ላይ አለች፡፡ ላለፉት በርካታ አመታት በአሰርት ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ችጋሩን ሊቋቋሙት የበቁት በዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ምጽዋትና ችሮታ ብቻ ነው፡፡በኢትዮጵያ ያለው የመገናኛ ሁኔታ ከእያንዳንዱ መቶ ሰው 5 የእጅ ስልክ የሚያዳርስ ነው፡፡ሕብረተሰቡ በጠቅላላው አንቅሮ የተፋውና ተስፋም የቆረጠበት ደካማና ተልካሻ የሆነ የትምህርት ስርአት የተዘረጋባት ሃገር ኢትዮጵያ ነች፡፡የሕክምና አገልግሎትና የጤና አጠባቁ ጉዳይ ንጽህናን በተመለከተም ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ነች፡፡ይህም ኢትዮጵያን በጤና አጠባበቁ መስፈርት ከ110ሩ የወደቁ ሀገራት መሃል በ109ኛው ተርታ ያሰልፋታል፡፡አንጸባራቂዎቹ ሕንጻዎችና ውድና በጣም ዘመናዊ የሆኑት በየጎዳናው ላይ የሚርመሰመሱት ተሸከርካሪዎች ከላይ ከተገለጹት እውነታዎች አንጸር እንቶ ፈንቶ እርባና ቢስ ያደርጋቸዋል፡፡

አስተምህሮትና የመማርያ ወቅት

በ1798 የአሜሪካን ኮንግሬስ ኤልየን ኤንድ ሴዲሽን አክት (Alien and Sedition Act) በማጽደቅ ማንም በመንግስት ላይ ክብረ ነክ፤አስጸያፊ ጽሁፍ ያወጣ በእስራት የሚቀጣበትን ሕግ ደነገገ፡፡በዚያን ወቅት የነበሩትን ፕሬዜዳንት ጆን አዳምስን በመውቀሳቸውና ሂሳዊ አስጠያየት በማውጣታቸው በርካታ ጋዜጠኞች አስራት ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ለማይረባው ግነትና ወሰን ላጣ አሳፋሪ፤ ሁኔታ፤ ዋጋ ቢስ ከበሬታ ፍለጋና ንፉግነታ የተሞላው በመሆኑ፤ቶማስ ጄፈርሰን ፕሬዜዳንት ሲሆኑ በዚህ አክት መነሾነት የታሰሩትን ሁሉ በነጻ እንዲለቀቁ አደረጉ፡፡በ1787 ቶማስ ጄፈርሰን፡- እኔ መንግሽት የሌለበት ጋዜጣ ወይስ ጋዤጣ የሌለበት መንግስት ብባል መንግስት የሌለበት ጋዜጣን እምርጣለሁ አሉ፡፡

የአሜሪካው ሕገመንግስት ፈርስት አሜንድመንት ለአሜሪካኑ ፕሬዜዳንትም ሆነ አሜሪካን ለሚጎበኝ የአፍሪካ ዲክታቶር ግፈኛ ገዢ ምንም አይነት የማን አለብኝነት ድጋፍ አይሰጥም፡፡በአሜሪካ ግዛት ውስጥ ሂስን ማካሄድ ገደብ ያልተበጀለት ሃሳብን በነጻ የመግለጽ አካል ነው፡፡ግበአሜሪካ፤የፖለቲካ ስልጣን መያዝ መልካም የሕገመንግስቱ አካል ነው፡፡የፖለቲካ መሪዎችም ላይ ሂስ ማድረግ የሕመንግስት መብት መሰረት ነው፡፡ሁሉም የአሜሪካ የፖለቲካ ሰዎች ከምንም በላይ የሚቀበሉት አንድ ሕግ ‹‹ሙቀቱን ካልቻልክ ከማድቤቱ ውጣ››የሚለውን ነው፡፡መለስ ዜናዊም ሊገነዘበውና ሊያዳምጠው የሚገባው ትምህርት ይህ ነው፡፡

መለስ አንድ መረዳት ያለበት ጉዳይ ያልሰጠውን መቀበል እንደማይቻል ነው፡፡ ዘወትር ተጠርጎና ተስተካክሎ እንደሚመቸው ሆኖ ወደሚጠበቀው ፓርላማው በመግባት ይደሰኩራል፤.ይጮሃል ሰውን ያዋርዳል፤ተቃዋሚዎችም ላይ ያሾፋል ያንጓጥጣቸዋል፡፡የዊኪሊክስ መዛግብትም ጠንካራ የሚባሉትን አምባሳደሮች እንኳን፤ያጭበረብራቸዋል፤ይቆጣጠራቸዋል፤ያስፈራራቸዋል፤ይዝትባቸዋል ይላል፡፡በነጻነት መናገር የሚፈቀድበት ሃገር ሲመጣ ደግሞሃሳቡን ብቻ ሳይሆን በአገዛዙ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መበት ጥሰትና ሌሎቹንም የፈላጭ ቆራጭ ባህሪው ያስከተላቸውን ኢሰብአዊ ድርጊቶች ለመከላከልና ራሱን ለማዳን ዝግጁ ሊሆን ይገባዋል፡፡

መለስ ዜናዊ በዓለም መሪዎች ፎረም ላይ ለመናገር በሴብቴምበር 2010 በመጣ ጊዜ የሚከተለውን ሃሳብ ሰንዝሬ ነበር፡፡

መለስ ዜናዊ ወደ ሃገሩ ለመመለስ ወደ አውሮፕላኑ ሲሳፈር፤ በንግግሩ ወቅት ተቃውሞና ሂደቱንም ማቋረጥ ስለገጠመው ስለ ዲያስፖራው በማማረር እያጉረመረመ መመለስ የለበትም፡፡ምናልባትም ሁኔታው በአሜሪካን ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በሃሳብ መጋጭት ሳቢያ የሚከሰተውን ሁኔታ ሊማርበት እንዲችል ያሳየው ይሆናል፡፡ ምናልባትም በመጠኑም ቢሆን ሃሳቦች ቀርበው ተቀባይነት እንደሚያገኙ፤እንደሚወድቁም፤ውይይትና ክርክር በነጣ እንደሚራመዱና ቂምና በቀልም እንደማያዝሉ ተምሮ ያደንቀውና ሁለተኛ ለማሰብም እድሉን ያገኝ ይሆናል፡፡እንጂ እሱ እንደሚያደርገው ገና ተናግረው ሳይጨርሱ አለያም ሃሳባቸውን አጠቃለው ሳይገልጹ ለወህኒ፤ ለግርፋት፤ ለመከራና ሰቆቃ አይዳረጉም፡፡ከጠበበ አእምሮአዊ ሂደትና ከዛገ አስተሳሰብ መላቀቂያው ነጻ የመናገር መብት ነው፡፡በእኔ ግምት መለስ ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት በመቅሰም፤ከአሰቃቂውና ከጨለማው ዓለሙ ወጥቶ፤ሕግ አልባና ጠባብ አስተሳሰቡ ይላቀቃል ብዬ አምናለሁ፡፡‹‹ሠላማዊ ለውጥን ለመቀበል ፍቃደኛነት የሌላቸው፤ለውጥን በግዴታቸው እያንገሸገሻቸው እንዲቀበሉ ይሆናሉ::››

ተስፋ፡፡ የማይሞት ዘልአለማዊ ተስፋ በኢትዮጵያ ሲያብብ፡፡ መለስ በዚህ የአሜሪካው ጉዞው ጠቃሚና ገንቢ ትምህርት ለመቀበል መቻሉን እጠራጠራለሁ፡፡ከታሪክ ግን ሰፋና ጠለቅ ያለ እውቀት እንዲያገኝ ጸሎቴ አይለየውም፡፡ ይሄዉም ‹‹ሠላማዊ ለውጥን አሻፈረን የሚሉ በግፊትና በአመጽ የሚመጣውን ለውጥ አይቀሬ ያደርጉታል::››

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

“ደጀ ሰላም” የማ/ቅዱሳን ናት በሚል ለተስተናገደ ጽሑፍ የተሰጠ ማስረጃዊ ምላሽ

Thursday, May 24th, 2012

ደጀ ሰላም የማ/ቅዱሳን ናት በሚል የተለያዩ የተሐድሶ መናፍቃን ብሎጎች ሲጽፉ ከመቆየታቸውም በላይ ኢትዮጵያን ሪቪው ላይ ጽሑፋቸውን እስከማውጣት ደርሰዋል (ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)። ለብልግናቸው መልስ መስጠት ባይገባንም “ማስረጃ” ብለው ያቀረቡትን ማታለያ ግን ዝም ብለን ልናልፈው አልፈቀድንም… [ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ]

ለኢትዮጵያ ሆቴሎች፣ የሸቀጣሸቀጥ መደብሮችና ለድርጅቶቹ ደንበኞች በሙሉ

Wednesday, May 16th, 2012

[Click here to read in PDF]

በወያኔ/ህወሓት ላይ የሚካሄደዉን የኢኮኖሚ ማእቀብ ለማስተባበር የተቋቋመዉ ግብረ ሃይል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን (media) ያደረጉትን ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማእቀብ ጥሪ መሰረት በማድረግ ነዉ። የዚህ የኢኮኖሚ ማእቀብ ዓላማም የወያኔ አገዛዝን የገቢ ምንጭ ለማድረቅ ነው።

የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ወደውጭ አገር የሚልኳቸው ሸቀጣሸቀጦች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያስገኙለት ነው። ስለዚህ ከኢትዮጵያ የሚመጡ እንጀራ፥ ቢራ፥ ወይን ጠጅና የመሳሰሉት ምርቶች ላይ የኢኮኖሚ ማእቀብ ተጥሏል። እነዚህ የገቢ ምንጮች ወያኔ በሕዝባችን ላይ የሚያደርሰዉን ግፍ እንደሚያጠናክሩ ሁላችንም ተረድተን ሕዝባችንን ለመታደግ ማእቀቡ ላይ እንድንተባበር በአክብሮት እንጠይቃለን።

ህወሓት/ወያኔ የመንግስት ስልጣን በጠመንጃ ሃይል ከጨበጠ ጀምሮ አንድነታችንን ሲሸረሽር፣ ሃገር ሲዘርፍና ሲያዘርፍ ኢትዮጵያውያን እንዳይጠይቁት በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ ሆዳሞቹን ደግሞ በፍርፋሪ እያታለለ ላለፉት 21 ዓመታት ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱን በጠየቀ ቁጥር መልሱ ግድያ፣ ግርፋት፣ የረሃብ ቅጣትና እንዲሁም እንዲሰደድ ማድረግ ነው። ህወሓት/ወያኔ ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን የእርሻ መሬቶቻቸዉን ለአረቦች፣ ለሕንዶች፣ ለቻይናና ዶላር ለሰጠዉ ሁሉ እየቸበቸበ የአገሪቱን ዜጎች የባርነት ቀንበር ስር እያስገባቸዉ ነዉ። ከወያኔዎችና ከቡችሎቻቸዉ በስተቀር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቻችን በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ነዉ።

የዚህን የወያኔ አገር ዘረፋ በዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የሚተዳደሩ ሆቴሎች፥ ምግብ ቤቶችና የሸቀጣሰቀጥ መደብሮች አውቀውም ሆነ ባለማወቅ ተባባሪ በመሆን ሂደት ውስጥ ይገኛሉ። ለዚህም ዋናው ማስረጃ ግሎባል Global Financial Integrity የተባለዉ አለም አቀፍ ድርጅት ከኢትዮጵያ ዉስጥ ከ2000 እስከ 2009 (እአአ) ዓ.ም ድረስ ብቻ በተለያየ መንገድ ከአገር ዉስጥ የወጣዉ ገንዘብ 11.7 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ሪፖርት አድርጓል። በወያኔ ነጋዴዎች አማካኝነት ሸቀጣሸቀጦች ከአገር በወረቀት ብር ተሸምተዉ በዳያስፖራ ለኢትዮጵያዉያን የንግድ ድርጅቶች በማከፋፈል፥ የዳያስፖራ ኢትዮጵያዉያንም እነዚህን ሸቀጦች በመግዛት በአገር ዘረፋ ሂደት ዉስጥ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ መተባበራቸዉ ግልጽ ነዉ። ዜጎቻችን በዚህ ዘረፋ ምክንያት በሚፈጠረዉ የእቃ እጥረት የሲኦል ሕይወት ዉስጥ እየወደቁ፣ የወያኔ ወኪሎች ግን በዉጭ ባንኮቻቸዉ ሃብት እያካበቱና እየተጠናከሩ ነዉ።

ይህ የኢኮኖሚ ማእቀብ የትብብር ጥሪ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ፣ ከኢትዮጵያ የሚመጡ የምግብና የመጠጥ ሸቀጦች፥ በተለይ እንጀራ፥ ቢራ፥ ወይን ጠጅና የመሳሰሉት ምርቶች እየተቀብላችሁ በየመደብራችሁና በየሆቴሎቻችሁ ለሽያጭ የምታቀርቡ ድርጅቶችና ባለቤቶቻቸዉ፣ እነዚህን ሸቀጦች ባለመግዛትና ባለማከፋፈል እንድትተባበሩ በትህትን እንጠይቃለን።

በዲያስፖራ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንም ይህ የማእቀብ ጥሪ የኢትዮጵያን ወገኖቻችን የመታደግ ጥሪ መሆኑን ተረድታችሁ፣ ጥሪው ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ባለመደብርና ባለሆቴል ባለቤት ወዳጆቻችሁ፥ ዘመዶቻችሁ ጥሪውን እንዲያከብሩ እንድትመክሩና፣ እናንተም እነዚህን ሸቀጦች መግዛት እንድታቆሙ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም በአክብሮት እንጠይቃለን።

በህወሓት ላይ ኢኮኖሚ ማዕቀብ ግብረሃይል| Email: boycott.tplf@gmail.com * Tel: 703 828 4821

የኦታዋ፣ ካናዳ ሁሉ አቀፍ ጉባኤ በዚህ ሳምንት ይጀምራል

Wednesday, May 16th, 2012

ቀን May 18 – 21, 2012
ቦታ Ottawa, Canada
መረጃ consult4Eth@gmail.com

የስብሰባው ዓላማና ፕሮግራም (PDF – እዚህ ላይ ይጫኑ)

Addis Dimts Radio interview on the Ottawa Conference. Listen below:

Play below

 

ኢትዮጵያን ከጥፋት ለመታደግ በቁርጠኝነትና በኅብረት እንነሳ

Tuesday, May 15th, 2012

የ“ብሩኅ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” መግለጫ

ኢትዮጵያ እጅግ ረጅም የአገርነትና ተከታታይነት ያለው የመንግሥትነት ታሪክ ካላቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ናት፡፡ የረጅም ዘመን አገርነቷና የተከታታይ በሀወርታዊ መንግሥት ባለቤት መሆኗ፣በጥንታዊ ሥልጣኔ ቅሬቶቿና በራሷ የጽሑፍ ቋንቋ የተገለጸ ነው፡፡ የአክሱም ሀውልት፣የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ታሪካዊ ቦታዎች በአርኪዮሎጂስቶች ጥናትና ምርምር ከምድር ውስጥ ተቆፍረው የተገኙት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፣ ገንዘቦችና ልዩ ልዩ መገልገያ መሣሪያዎች የረጅም ዘመን ታሪኳ ቋሚ ነቃሾች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ረጅም አገራዊና የመንግሥትነት ታሪክ ልዩ የሚያደርገው ተጨብጦ በነበረው ጥንታዊ ሥልጣኔና ተከታታይነቱን በጠበቀ መንግሥትነት መኖር ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱ የብዙ ማኅበረሰቦች አገር መሆኗና፣ ማኅበረሰቦቹ በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ፣ ደስታና መከራን፣ ሰላምና ጦርነትን፣ሰፈራና ስደትን ዕኩል የተጋሩ የጀግኖችና የኩሩ ሕዝብ መታወቂያ በመሆኗ ጭምር ነው፡፡

የአገሪቱና የመንግሥቱ ተከታታይነት፣ የማኅበረሰቡ በሀወርታዊነት፣ እንዲሁ በልዩ ተዓምር ዕውን የሆነ አይደም፡፡ ተስፋፊነትንና ቅኝ ገዥነትን መነሻና መድረሻ አድርገው በተደጋጋሚ ሊወሩን፣ ቅኝ ተገዥ ሊያደርጉን፣ ነፃነታችን ሊገፉ፣ ሃይማኖታችን ሊያስለውጡ፣ ሊነጣጥሉንና ተዋራጅ ሊያደርጉን በተለያዩ ጊዚያት፣ ወራሪና ቅኝ ገዥ ሠራዊት አሰልጥነውና አደራጅተው፣ ባሕር አቋርጠው፣ ድንበር አልፈው የመጡ፣ የፖርቱጋልን፣ የኦቶማን ቱርክን፣ የግብፅንና የጣሊያንን ወራሪዎችና ቅኝ ገዥዎች ፍላጎት፣ ሕዝቡ በየዘመኑ ከነበሩ ንጎሦችና የየአካበቢው ገዥዎች ዙሪያ በመሰለፍ በከፈለው ውድና ምትክየለሽ የሕይወት፣ የአጥንትና የደም ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ የኢትዮጵያ አንድነትና በሀወርታዊነት ለረጅም ተከታታይ ዘመናት ፀንቶ እንዲኖር፣ የኢትዮጵያዊነት መሠረት፣ ቋሚ፣ ምሰሶ፣ ማገርና ጣራ በመሆን አገልግሏል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያውያን መጨረሻ ግቡ ሥልጣንን መቆጣጠር የሆነ፣ መነሻ ምክንያቶቹ ወይም ስበቦቹ ደግሞ፣ አካባቢያዊነት፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ኢኮኖሚ፣ ባህልና ርዕዮተ-ዓለም በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ልዩነቶችን በመምዘዝ በሚፈጠር ግብግብ  አገሪቱ ባላቋረጠ የርስበርስ ጦርነቶች ውስጥ ያለፈችና ያለንም መሆኑ ታሪካችንና የምንገኝበት ነባራዊ ሁኔታ ያስረዳል፡፡ ይህም በመሆኑ የአገራችን ታሪክ በአመዛኙ የጦርነት ታሪክ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ሁለቱ ጦርነቶች ማለትም የውጭ ወራሪዎችንና ቅኝ ገዥ ኃይሎችን የመከላከሉና የውስጥ የሥልጣን ግብግብ ጦርነቶች በታሪካችን ውስጥ ሁለት ጉልህ ተቃራኒ ክስተቶች ጎን ለጎን እንዲጎለብቱ አድርጓል፡፡ የመጀመሪያው ክስተት የማፍረስ ሲሆን፣ ሁለተኛው የመገንባት ባህርይ ነበረው፡፡

የአገራችን የረጅም ዘመን ታሪክና በተለይም፣ ከ1ኛው እስከ 5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ጨብጣው የነበረው የሥልጣኔ ደረጃና የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎች ዛሬ ከምንገኝበት የዕድገትና አጠቃላይ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር፣ ከላይ ከተገለጹት ሁለት ተቃራኒ ክስተቶች የማፍረስ ጎኑ እጅግ የበረታ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ የአገርን ዳር ድንበር፣ የሕዝቡን ነፃነትና ሉዓላዊነት ለመከላከልና ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም በሥልጣን ይገባናል ባዮች የተቀሰቀሱ የርስበርስ ጦርነቶች ተገንብተው የነበሩ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የባህል፣ የማህበራዊ፣ የወታደራዊና የቴክኖሎጂ መፍለቂያ ተቋሞች፣አሠራሮች፣ ግንኙነቶች ወዘተ … እንዳሉ በማውደሙ፣ የዕድገት ተከታታይነት እንዲቋረጥ በማድረግ፣ አገሪቱ የተገነባን በማፍረስና አዲስ መሠረት በመጣል ሽክርክሪት ውስጥ አስገብቶ ዕድገቷ የኋሊት እንዲጓዝ አድርጓል፡፡

ዕድገት የተከታታይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ ፖሊሲዎች ውጤት እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይህ ተከታታይነት ደግሞ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ባህል ውስጥ እንኳን ትናንት ዛሬም በፖለቲከኞች ኅሊና ውስጥ ተገቢ ቦታውን ያገኘ ባለመሆኑ፣ ዕድገት ለኢትዮጵያ በርቀት የሚታይ አድማስ ከመሆን አላለፈም፡፡

በአገራችን ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ጎልተው ከሚታዩት የጦርነት ክስተቶች ሌላኛው ጎን፣ ጦርነቱ ልዩ ልዩ ማኅበረሰቦችን እንዲዋሐዱና አንድ ሕዝብ፣ የወል ታሪክ፣ የጋራ አገር፣ የወል ኢትዮጵያዊ የማንነት ዕሴቶችና ተመሳሳይ ሥነልቦና እንዲመሠርቱና የልዩነት ግድግዳዎችን ደረማምሰው ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንዲሆኑ ያስቻለው የግንባታ ሂደት ነው፡፡

በልዩ ልዩዎቹ ማኅበረሰቦች መካከል የተፈጠረው አንድነት በአመዛኙ በሁሉም የጋራ ፍላጎት ሰጥቶ የመቀበል፣ ወስዶ የመመለስ፣ በተናጠልና በወል እንቅስቃሴዎች፣ በተፈጥሮ ገፊና ሳቢ አስገዳጅ ኃይሎች ግፊት፣በጦርነት፣በጋብቻ፣በስደት፣ በፍልሰት፣ በንግድ፣ በጉዲፈቻ፣ወዘተ..አማካኝነት ተለንቅጦ የተዋሐደ በመሆኑ፣ የተፈጠረውን አንድነት በቀላሉ ለማንተርተር፣ለማንጓለልና ለማበጠር እንዳይቻል አድርጎታል፡፡ ኢትዮጵያ የብዙ ማኅበረሰቦች የአንድነት አገር ናት የሚያሰኛትም ይኸው አንዱን ማኅበረሰብ ከሌላው ነጥሎ በራሱ ለማቆም የሚያስችል፣ የመነጠያ ሁለንተናዊ የማንነት መከሰቻ ሁኔታ የሌለ፣ አገሪቱ የማኅበረሰቦቿ ፍጹም ውሕድ አንድነት የተፈጠረባት ሕዝብ አገር በመሆኗ ነው፡፡

የአገራችን ጥንታዊ ሥልጣኔ፣ ጨብጣው የነበረው ዕድገትና በዓለም ላይ  የነበራት ተደማጭነት፣የያዘችው ጂኦ-ፖለቲካዊ ቦታ፣ ያላት የውኃ ሀብትና የተፈጥሮ ሀብት፣ በአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ላይ የተቀዳጀችው አንጸባሪቂ ድል፣ ለጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች ነፃነት ያበረከተችው የአርኣያነት ተግባር፣በጥቅሉ፣ ኢትዮጵያ ያላት ቁሳዊና ኅሊናዊ ሀብት፣ የመከበሪያ፣ የመታፈሪያ፣ የመደመጫና የተከታታይነት ዕድገት መጨበጫ የሁለንተናዊ ብቃት ቋት በሆነን ነበር፡፡ የሆነው ግን ተቃራኒው ነው፡፡ ተከታታይነትና ወጥነት ያለው ፖለቲካዊ ባህል፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ፖሊሲ አለመኖር፣ በጥንታዊ ሥልጣኔአችን ላይ መሠረት ያደረገ ቴክኖሎጂ ማዳበር አለመቻላችን፣ ያለንን የተፈጥሮ ሀብት አልምተን በጥቅም ላይ አለማዋላችን፣ ያለንን ካፒታል በአግባቡ መጠቀም አለመቻላችን፣ ይህ ሁኔታ ጠላት ገዥ በመሆን የጥቃት ዒላማ እንድንሆንና ለዙሪያ ገብ ችግሮችና ተዋራጅነት ተዳርገናል፡፡

ከሁሉም በላይ ባለፉት አምሳና ስልሳ ዓመታት ትውልዱ ከነባራዊ የወል ኢትዮጵያዊነት ዕሴቶች መውጣት ብቻ ሳይሆን፣ የአገራዊ አንድነት መሠረት የሆኑትን ተቋሞች፣ ዕምነቶች፣ አሠራሮችና ግንኙነቶች ከማጥፋት ባሻገር፣ በልዩነቶች ማለትም፣ በርዕዮተ-ዓለም፣ በቋንቋ፣ የነባሯን ኢትዮጵያ ታሪክ በመቀበልና ባለመቀበል ዙሪያ በመደራጀት አገሪቱን የጦርነት አውድማ በማድረግ ከመኖር ወደ አለመኖር እንድትሸጋገር እይደረጋት ነው፡፡

በተለይ የወያኔ አገዛዝ የሚያራምደው የዘር ፖለቲካ፣ ያደራጀው በልዩነት ላይ የተመሠረተ የመንግሥት ቅርጽ፣ አገሪቱን ወደብ አልባ ማድረጉና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ሥልጣኔና  አገራዊ መሠረት የነበረችውን ባሕረ-ነጋሽ/ምድረ ባሕሪ ማስገንጠሉ፣ ምዕራባዊ የግዛት አካሏን ለሱዳን መሥጠቱ ወዘተ…የአገራችን የጥፋት የቁልቁለት ጉዞ ማመላከቻ ቋሚ ነቃሾች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያውያን ከተጋረጡብን የመበተንና እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለመቀጠል ታላቅ አደጋ በተጨማሪ፣ በልዩ ልዩ የችግር አረንቋ ውስጥ ነን፡፡ ርሀብና ቸነፈር ከሚገመተውና ከሚነገረው በላይ በሕዝቡ ሕይዎት ውስጥ ሥር ሰዷል፡፡ የርሃቡ ክፋትና ስፋት በ1880ዎቹ ተከስቶ ከነበረውና በታሪካችን ከሚታወቀው አሰቃቂ ርሃብ የሚለየው “እናት ልጇን በላች” የሚለው አሳፋሪ፣ አሳዛኝና አስደንጋጭ ዜና አለመሰማቱ ብቻ ነው፡፡

የአገሪቱ ድንግልና ለም መሬቶች ለሳውዲ ዓረቢያ፣ ለሕንድና ለቱርክ ባለሀብቶች ገበሬው እየተፈናቀለ፣ በስጦታ በሚያሰኝ ደረጃ በርካሽ ዋጋ ለ99 ዓመታት እየተሸጠ ነው፡፡ ሆን ተብሎ በሚራገበው የዘር ፖለቲካ የጎሳ ብጥብጥና የሃይማኖት ግጭቶች አገራችን በታሪኳ አይታው ወደማታውቀው የጥፋት ነውጥ ውስጥ ገብታለች፡፡ ሕዝቡ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ሳይሆን፣ሠርቶ የመኖር የዜግነት መብቱን ካጣ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

እነዚህና መሰል ችግሮች የተወሰኑት ካለፉት ዘመናት የወረስናቸው ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ ወያኔ በታሪካዊና ወቅታዊ፣ በነባራዊና ጊዜአዊ፣ በሩቅና በቅርብ ጠላቶቻችን ለዘመናት ሲደግሱልን የነበረውን የጥፋት ተልዕኮ አስፈጻሚ በመሆን የሚያራምደው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፖሊሲዎች ውጤቶች ናቸው፡፡ በግልጽ እንደሚታወቀው የአገራችን ችግሮች ብዙና ውስብስብ ናቸው፡፡ የችግሮቹ ቋት ወይም ቋጠሮ ግን የመልካም አስተዳደር ዕጦት እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡

በሂደት የተንከባለሉትንም ሆነ፣ ወያኔ ሆን ብሎ፣ በፖሊሲ ቀርጾ እያራገባቸው ያሉትን ሁለንተናዊ የአገርና የሕዝብ ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለማስወገድ፣ ብሎም ያለንን ካፒታል በሥርዓትና በአግባቡ ተጠቅመን ድህንትን፣ በሽታን፣ ርሃብንና አጠቃላይ ኋላ ቀርነትን ለማስወገድ ያለው ብቸኛ አማራጭ የሀሳብ፣ የአመለካከት፣ የዓላማና የተግባር አንድነት የሚያስገኝ ድርጅታዊ ኃይል መፍጠር ነው፡፡ ይህም ኃይል ሌላ ምንም ሳሆን፣ ሕዝቡ ዕውነተኛ ፍላጎቱን፣ መሆን የሚሻውን ሊገልጽበት የሚችል፣የችግሮቹ ማስወገጃ፣ የሰላሙ ማስፈኛ፣ የዕድገቱና ብልጽግናው ማስገኛው፣ የነፃነቱና የዕኩልነቱ ማረጋገጫው፣ የሰብአዊ መብቱና የዲሞክራሲያዊ መብቶቹ ማስከበሪያ የሚሆን ሕዝባዊ ኃይል ማለት ነው፡፡

ከአገራችን የፖለቲካ ድርጅቶች ታሪክና ከሕዝቡ ፖለቲካዊ ባህል አንፃር ያለውን አስቸጋሪነት በመመዘን፣ ይህን ዓይነት ባሕሪና ተልዕኮ ያለው ድርጅት እንዴት ዕውን ማድረግ ይቻላል? በዚህ ዓላማ ዙሪያ የተደራጁ በርካታ ድርጅቶች እያሉ፣ ይህ አዲስ የሚመሠረት ድርጅት ካሉትና ከነበሩት በምን ይለያል? አዲሱን ድርጅታችንን ለውጤት የሚበቃ ለማድረግ ምን ዓይነት የአሠራርና የአደረጃጀት ስልት እንከተላለን? የሚሉት ጥያቄዎች መነሳትና ተገቢ የሆነ መልስ ማግኘት ያለባቸው ናቸው፡፡

በዚህ ረገድ “ብሩኅ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄን” መሥራቾች ላለፉት ሦስት ዓመታት በተከታታይ በቡድንና በተናጠል ከላይ በተነሱትና መሰል ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጥያቄዎችና ርዕሶች ዙሪያ ሰፊ ውይይትና ክርክር፣ ጥናትና ምርምር በማድረግ ሕዝባችንን የዘላቂ ድል ባለቤትነና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣

ግቡ፡-

  1. በመሣሪያ ኃይል ሥልጣን ላይ ያለውን የወያኔ መንግሥት ተብዬ፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም፣ የሕዝቡን ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ዳርድንበሯንና የሕዝቡን አንድነት ሆን ብሎ የጎዳ በመሆኑ፣
  2. የሃገራችን፡ የተፈጥሮ፡ ሃብት፡ ዘርፎ፡ ለዘራፊ፡ በመስጠት፡ ህብረተሰቡን፡ ለድህነት፤ ርሃብ፤ የኑሮ፡ ዋጋ፡ ግፍሸት፤ ጥገኝነት፤ ታዛዥነት፤ ስደት፤ የዳረገው፡ በመሆኑ፤
  3. የአገሪቱን ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሕጋዊ የተፈጥሮ በሯን ወዶና ፈቅዶ የሰጠ በመሆኑ፣
  4. የተከተለው የመንግሥት አደረጃጀት ቅርጽና የሚያራምደው፤ የዘር፡ የፖለቲካ፤ ማህበራዊና፤ የኢኮኖሚ፡ አመራር፡ ከጥቅሙ፡ ጉዳቱ፡ ያመዘነ፤ ለጥቂቶች፡ የሃብት፡ ማካበቻ፡ ለአብዛኛው፡ ህብረተሰብ፤ አሰቃቂና፡ ተስፋ፡ የሚአስቆርጥ፡ ሁንየታወች፡ ስለፈጠረ፤ ስራቱ፡ የአገራዊ ክህደት መጸብራቅነቱ፡ ግልጽ፡ እየሆነ፡ በመታየቱና፡ ለመበታተን፡ ያለውን፡ አደጋ፡ ለማቆም፡ ስለማይችል፤ በምትኩ ሕዝቡ በነፃ ኅሊናውና ፍላጎቱ እንዳሻው የሚወስንበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረት እንዳለበት ሙሉ ስምምነት ደርሰናል፡፡

ወደዚህ ግብ ለመቃረብም በስልት ደረጃ መከተል ያለብን፣ በነባሯ ኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት፣የግዛት ክልልና ታሪክ፣በህግ የበላይነትና በነጻ የሕዝብ ተሳትፎ ምርጫ ከሚያምኑ ብሔራዊና ህብረ -ብሔራዊ ንቅናቄዎች፣ ፓርቲዎች፣ ድርጅቶች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ጋር በሚያግበቡንና አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ዙሪያ ተባብሮና ተመካክሮ መሥራት፣ በተቻለ መጠን ልዩነቶችን በውይይትና በምክክር መፍታት እንጂ፣ በጠላትነት ላለመፈራረጅ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን፣ የእንቅስቃሴአችን ሙሉ ትኩረት በወያኔ አገዛዝ ላይ እንጂ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት በሚማስኑ ኃይሎች ዙሪያ እንዳይሆን ሙሉ ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡

በዚህም መሠረት በንቅናቄው መመሥረት አስፈላጊነት፣ በግቡና በስልቱ ዙሪያ ላይ የወል መግባባት ከተደረሰ በኋላ፣ በዚህ ታሪካዊ ወቅት ንቅናቄው እውን እንዲሆን ያስፈለገበት ምክንያቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡

እነዚህም፡-

  1. የሚመራበት የዓለም አመለካከት ከኢትዮጵያዊነት መልካም ዕሴቶች የሚመነጭ፣ አስተዳደራዊ፣ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፖሊሲዎቹ በኢትዮጵያ መልካም ውርሶችና ቅርሶች ላይ እንዲመሠረት ማድረጉ ወይም ለኢትዮጵያዊነት ዕሴቶች ልዩ ትኩረትና ክብር መስጠት መቻሉ፤
  2. የንቅናቄው የአደረጃጀት መርህ፣ ዲሞክራሲያዊ፤ ፍትሃዊ፤ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነትን መሠረት ያደረገና የምንደራጀውም ልዩ በሚያደርጉን ጉዳዮች ዙሪያ ሳይሆን፣ አንድ በሚያደርገን ኢትዮጵያዊነት ዙሪያ መሆኑ፤
  3. ልዩነቶቻችን ፈርጦቻችንና ጌጦቻችን እንጂ፣ መራኮቻና መለያያ መስመሮቻችን አለመሆናቸውን መረዳታችን፤
  4. ኢትዮጵያ የበሀወርታዊ ሕዝብና መንግሥት አገር መሆንና ለረጅም ዘመን የዘለቀ ታሪክ ያላት መሆኑን አምነን፣ ይህ ታሪክ ዘመንና ወቅቱ ከሚጠይቁት ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር እየተጣጣመ ወደላቀ የዕድገት ደረጃ እንዲሸጋገር አስፈላጊ ሁኔታዎችን ማሟላት ያለብን መሆኑን በማመናችን፤
  5. የነባሯ ኢትዮጵያ ታሪክና የማዕከላዊ መንግሥት አመሰራረት ሂደት፣ በዓለም ከታዩት አገሮች አፈጣጠር የሚለየው በቦታ፣ በጊዜና በአድራጊ ግለሰቦች እንጂ፣ በሌሎች መሠረታዊ ሂደቶች የማይለይ፣ በግድ መታለፍ የነበረበት የነባራዊ ሁኔታዎች ውጤት መሆኑን ተገንዝበን፣ ተሠሩ ለሚባሉ ስሕተቶች በታሪክ ዓይን እየተመረመሩ፣ ስሕተቶች ከነበሩ ወደፊት የማይደገሙበትን ሁኔታ በማመቻቸት በመልካም የወል ውርሶቻችን ላይ በመመሥረት የአገሪቱን ልማትና ዕድገት ለማፋጠን የቆምን መሆኑ፤
  6. የኢትዮጵያ መፃዒ ዕድል በልጆቿ አንድነት ላይ የሚወሰን በመሆኑ፣ ይህ አንድነት ደግሞ ያላንዳች ሳንካ ዕውን የሚሆነው ባለፉት ዘመናት በርዕዮተ-ዓለም፣ በዘር፣ በክልል፣በስልጣን ግብ-ግብ፤ በሃይማኖት ወዘተ..ዙሪያና በዓላማ ማስፈጸሚያ ስልቶች ተለያይተው የተዳሙ፣ ፊት የተዟዟሩና አለመግባባት የፈጠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ብሔራዊ እርቅ ሲያወርዱ ስለሆነ፣ ለዚህ ተግባራዊነት ተገትን የምንሠራ መሆኑ፤
  7. የንቅናቄው አባላት የሚመዘኑት በዘራቸው፣ በፆታቸው፣ በሃይማኖታቸው ወይም ባለፈ ታሪካቸው ሳይሆን፣ በኢትዮጵያዊነታቸውና ለኢትዮጵያ አንድነትና ፍትሃዊ እድገት ዳብሮ መቀጠል ከሚያበረክቱት አስተዋጽዖ አንፃር ብቻ መሆኑ፤
  8. የንቅናቄው አባላት የሚቀበሉትና የሚያምኑት፤ የትግሉ መስክ ኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመራ መሆኑ፤
  9. የዲሞክራሲ ዋነኛ መገለጫ ከሆኑት መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ሆኖ፣አማራጮች ቀርበውለት የፈለገውን የመምረጥ መብት ማረጋገጡ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የአማራጭ ሀሳቦችንና አሠራሮችን መኖር ይጠይቃል፡፡ ከዚህ አንፃር፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ ለማዳበርና ዲሞክራሲያዊ መብቱን ተግባራዊ እንዲያደርግ ደጋፊና አማራጭ ሆነን መቅረባችን ናቸው፡፡

“ቆሎን መቆርጠም እንጂ፣ ማሸት አይጨርሰውም” እንደሚባለው፣ የኢትዮጵያን ችግሮች ማስወገድ የሚቻለው ስለችግሯ በማውራት ሳይሆን፣ በመሥራት ነው፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከሦስት ዓመታት በላይ ሲወያይ፣ ሲመክርና ሲከራከር የኖረው ስብስብ የሀሳብና የተግባር መገለጫው የሆነ “ብሩኅ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲዊ ንቅናቄ” የተሰኘ ድርጅት በመመሥረት ከመጋቢት 30 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ይፋ እንቅስቃሴ መጀመራችንን  ለኢትዮጵያ አንድነት ዳብሮ መቀጠል ቁርጠኛ ፍላጎት ላላቸው ኢትዮጵያውያን ስናበስር፣ ከተደራጀን የማንፈታው ችግር እንደሌለ በመተማመን ነው፡፡

“ከፖለቲካ በራቅን ቁጥር በምንበልጣቸው ሰዎች በመገዛት እንቀጣለን” ሲል ታላቁ የማኅበራዊ ሣይንስ ፈላስፋ ፕሌቶ  የተናገረው ዕውነታ፣ ዛሬ በአገራችን በገሀድ እየተፈጸመ ያለ በመሆኑ፣እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከፖለቲካው መድረክ በመራቁ ምክንያት በሚበልጣቸው ሰዎች  በመመራት ከሚፈጸምበት ቅጣት ለመዳን የብሩኅ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲዊ ንቅናቄ ንቁ አባል በመሆን ኢትዮጵያን ከጨርሶ ጥፋት እንድንታደጋት ብሩኅ ኢትዮጵያ አገራዊ ጥሪ ያቀርባል፡፡

ኢትዮጵያን ከጨርሶ ጥፋት እንታደግ!

ኢትዮጵያዊነት ኅብረ ብሔራዊ ማንነታችን ነው!

የብሩኅ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲዊ ንቅናቄ (ብሩኅ ኢትዮጵያ)

የቅዱስ ሲኖዶስ 33ኛው ጉባኤ መግለጫ

Tuesday, May 15th, 2012

ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

“ሲዋን” የተሰኘ አዲስ መጽሃፍ ለንባብ በቃ

Tuesday, May 15th, 2012

በጋዜጠኛ ዳንኤል ገዛኽኝ የተጻፈው “ሲዋን” የተሰኘው አዲስ መጽሃፍ በዩናይትድ ስቴትስ ጆርጂያ አትላንታ ታትሞ ለንባብ በቃ። መጽሃፉ ዋና የታሪኩ ሂደት የሚያጠነጥንበት መስመር ከኢትዮጲያ ሶማሊያ ከዚያም ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረገውን አስቸጋሪ የስደት ጉዞ ታሪክ የሚዳሥ ሲሆን ሙሉ የመጽሃፉ ታሪክ በ እውነተኛ ሂደት ላይ የሚያተኩር መሆኑም ታውቆዋል።

መጽሃፉ 297 ገጾች ያሉት ሲሆን አስከፊውን የአረቢያን ባህር የጀልባ ጉዞ አሰቃቂነት ይተርካል። በሌላ በኩልም ደራሲው ከሃገር በወጣበት የምርጫ 97 ማግስት እና የምርጫ 97 ዋዜማ እውነተኛ ሂደት እና እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ በመረጃ አስደግፎ ትውስታውን የገለጸበት የመጽሃፉም ክፍል የሚዳሰሰው ሌላው የታሪክ ሂደት እንደሆነ ለማወቅ ተችሎዋል።

በሌላ በኩል ምንም እንኩዋን የመጽሃፉ ደራሲ ከመንግስት በተቃጣበት አደጋ ሳቢያ ሃገር ጥሎ ለመሰደድ የበቃበትን ሂደት በታሪኩ ውስጥ ለአንባቢያን ያቅርብ እንጂ ፡ በስደቱ ጎርፍ ውስጥ የሚያልፉ በርካታ ኢትዮጲያውያንን ታሪክ የዳሰሰ እና ለማመን የሚያዳግቱ ግን የመጽሃፉ ደራሲ በአይኑ የተመለከታቸውን የሰባ አንድ ሰአታት የየብስ ላይ ጉዞ እንደዚሁም ዘግናኙን የአርባ አንድ ሰአታት የባህር ላይ ጉዞ ከባለታሪኮቹ አጋጣሚዎች ጋር ለንባብ አብቅቶዋል። በመጽሃፉ ውስጥ ከቀረቡት ታሪኮች ውስጥ በባህር ጉዞ ላይ እያሉ ስለሚሞቱት ስደተኛዎች ፤ እንዲሁም ከኢትዮጲያ የጠረፍ ከተማዎች አንስቶ እስከ ሶማሊያ ድረስ በሰው አዘዋዋሪዎች ዜጎች ላይ የሚደርሰው በተደጋጋሚ በውጪ ሚዲያዎች በግርድፉ የሚቀርቡ ወሬዎች ተተንትነው የቀረቡበትም ሂደት እንዳለ ከመጽሃፉ ለመረዳት ተችሎዋል።

ደራሲው ይህንን መጽሃፍ የጻፈበትን ሂደት እና እውነታ አስመልክቶ መጽሃፉ ለህትመት ከመብቃቱ በፊት መጽሃፉን ለማንበብ የታደሉት ሁለቱ እውቅ ጋዜጠኛዎች እና ጸሃፍት ተስፋዬ ገብረ አብ እና ክንፉ አሰፋ በመጻሃፉ ጀርባ ላይ በሰጡት አስተያየት በታሪኩ መገረማቸውን ጠቅሰው አስተያየታቸውን አቅርበዋል። “ሲዋን” የተሰኘው መጽሃፍ በአሁኑ ወቅት በአትላንታ ታዋቂ ሃበሻ ማርቶች በመሸጥ ላይ ሲሆን እንደዚሁም በላስቬጋስ ፤ በዳላስ ፤ በካሊፎርኒያ ፤ በቺካጎ አውሮፓ ጣሊያን ሮም፤ በፈረንሳይ ፓሪስ በመከፋፈል ላይ ሲሆን በቀጣይም ወደሌሎች የአውሮፓ እና የአሜሪካ ከተማዎች እንደሚሰራጭ ለማወቅ ተችሎዋል። መጽሃፉን ለማግኘት እንዲሁም ለማከፋፈል የሚፈልጉ ክፍሎች በዚህ ስልክ ቁጥር መጠየቅ ይችላሉ።

የስልክ ቁጥር 404 610 6954
Email: daniel_mb1232000@yahoo.com

እርቅ፣ ይቅርታና ብሔራዊ ንስኃ ያስፈልገናል

Monday, May 14th, 2012

በፍቅር ለይኩን

ከዛሬ ወር በፊት አንድ ሰው በጎንደር በደባርቅ ከተማ በአንዲት ቀበሌ ውስጥ ድል ያለ ድግስ ደግሶ ብሉልኝ ጠጡልኝ በማለት የመንደሩን ሰው ሁሉ በደስታና በፈግግታ ተውጦ ቁጭ ብድግ እያለ ያስተናግዳል፡፡ የዚህ ደስታና ድግስ ምክንያቱ ደግሞ ድግሱን ያዘጋጀው ሰው በደርግ ዘመን ጸረ አብዮተኛ ተብሎ ተይዞ ከሌሎች ሰዎች ጋር እግራቸውና እጃቸው በእገረ ሙቅ/በእግር ብረት ተጠፍሮ በአቀርቢያቸው ወደሚገኘው የሊማሊሞ ገደል ውስጥ ሊጣሉ ይወሰዳሉ፤ ወደ ገደሉ እንደደረሱም የወሰዷቸው አብዮታዊ ታጣቂ ጓዶች እያደፉና እያዋረዱ ወደ ገደሉ ያለምንም ርኅራኄ ይወረውሯቸዋል፡፡

የዛሬው የዚህ ድግስ ባለቤትም ወደዚህ ገደል ሲጣል ባላወቀው ተዓምር የፊጥኝ ከታሰረበት እግር ብረት የተነሳ ከአንድ ዛፍ ላይ ይንጠለጠልና ወደ ገደሉ ቁልቁል ከመወረድ ይድናል ግና በዛፉ ላይ ሆኖ ራሱን ማዳን የሚችልበት አማራጭ አልነበረውም፤ ምክንያቱም እግሮቹም ሆኑ እጆቹ የፊጥኝ በእግር ብረት ታስረዋልና ያለው አማራጭ በዛው እንደተንጠለጠለ ሞቱን መጠበቅ ወይም በሆነ ተዓምር ሰዎች ደርሰውለት እንዲያድኑት ተሰፋ ማድረግ ነበር፡፡ ምንም እንኳን በዚህ ጅው ካለ ገደል ቁልቁል ተፈጥፍጦ ከመሞት አሊያም ደግሞ እንደ ውሻ ክራንቻ ጥርስ ከሾሉት የሊማሊሞ ዐለቶች የሞት ፍርድና ከገደሉ በታች ከሚገኙት እንደ ነብርና ጅብ ካሉት አውሬዎች መቦጫጨቅ መትረፉ ለአፍታ እረፍትን ቢሰጠውም እንዲህ በዛፍ ላይ እንደተንጠለጠለ ከሞት ጋር ተፋጦ ምን ያህል ሰዓታትና ቀናት መቆየት እንሚችል ግን እርግጠኛ አልነበረምና ጭንቀቱ በቃላት የሚገለጽ አልነበረም፡፡

ከለሁለት መራር የመከራና የነፍስ ውጭ የነፍስ ግቢ ቀንና ሌሊት በኋላ ሁለት የደባርቅ ሽማግሌዎች በዛ መንገድ ሲያልፉ ያዩታል እናም ቀረብ ሲሉት በሕይወት ያለ የሚንቀሳቀስ ሰው ነው፡፡ ራብና የውሃ ጥም ባደከመውና ባሰለለው ድምፅ እባካችሁ አድኑኝ ይላቸዋል፡፡ እነዛም ሰዎች ከተንጠለጠለበት ዛፍ ላይ አውርደው ከቋጠሩት ስንቅ አቃምሰውና ውኃ አጥተውት ካረጋጉትና ነፍሱን ከመለሱት በኋላ በምንም ምክንያት በዚህ ዛፍ ላይ እንደተንጠለጠለ ይጠይቁታል እርሱም ጸረ አብዮተኛ በሚል ሰበብ ወደ ገደል ሲወረወር በተዓምር በዛፉ ተንጠልጥሎ መትረፉን ይነግራቸዋል፡፡

እነዛም ሰዎች ዥው ባለው የሊማሊሞ ገድል የወደቁ ወጣቶችን እያሰቡ ልባቸው በሐዘን እየደማ ‹‹አይ ኢትዮጵያ ልጆችሽ እንዲህ የገደል፣ የአውሬ፣ የጥይትና የአሞራ ሲሳይ ይሁኑ…!›› በማለት እንባቸውን ወደ ጸባዖት ጢቅ በማድረግ ሐዘናቸውን ወደ አምላክ ካሰሙ በኋላ ወደ ትግራይ መንገድ ይሸኙታል፡፡ ይህም ሰው ከትግራይ ወደ ሱዳን ይገባል ከዛም ወደ አሜሪካ ይሻገራል፡፡ በአሁን ሰዓት የዚህ ታሪክ ባለቤት ሰው በአሜሪካ አገር ትምሕርቱን ተምሮ ኑሮውን በዛ አደላድሎ በዴንቨር ኮሎራዶ በሕክምና ሙያ ላይ ተሰማርቶ የሚኖር ነው፡፡ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ይህን አስገራሚ ታሪኩንና ከሞት የተረፈበትን ቀን ለመዘከር ሲል ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ደባርቅ ይመጣል፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ደግሞ ወደሊማሊሞ ገደል የተጣለበትና በዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ የተረፈበት እለት የተወለደበት ቀን በመሆኑ በሀገሩ በደባርቅ በተወለደበት ቀዬና በወገኖቹ መካከል ሆኖ ሁለቴ የተወለደበትን ቀን በምስጋና ለማሰብ ሲል ነበር ከሀገረ አሜሪካ ወደ ደባርቅ ወደ ትውልድ መንደሩ ከበርካታ ዓመታት በኋላ የተመለሰው፡፡ ይህን አሳዛኝ ታሪክ ደግሞም አስደሳች ዜና የዘገበው በእለተ ሰኞ በማለዳው የፋና ራዲዮ የዘጠና ደቂቃ ፕሮግራም ነው፡፡ ዜናውን ለፋና ያደረሰው ደግሞ የጎንደር ፋና ኤፍ ኤም 98.1 ባልደረባ ነው፡፡

ይህን ዜና በሰኞ ማለዳ በሐዘን በዳመነ መንፈስ ከሰማሁ በኋላ በየጓዳው ስንት ያልተነገሩ እና ያልወጡ ግፎችና በደሎች በኢትዮጵያችን እንዳሉ ተሰማኝ፡፡ እናም በሰማሁት ታሪክ ላይ የተሰማኝን ለማለት ውስጤን አንዳንች ስሜት ገፋፋው እናም ብዕሬን ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ውስጥ ሆኜ አነሳሁ፡፡

በዘመነ ደርግ በዚህ ዓይነት አሰቃቂ ግፍና ሞት የረገፉ የእምዬ ኢትዮጵያ ልጆች ብዙ ሺህ መሆናቸው ብዙዎቻችን የምናውቀው ነው፡፡ በበራቸው ደጃፍ በየመንገዱ በጥይት አረር ረግፈው ደማቸውን እንደ ኤልዛቤል ውሾች የላሱት ወገኖቻችንን ቤት ይቁጠራቸው፡፡ አስክሬናቸው እንኳን በክብር እንዳይርፍ በጥይት በተደፉበት የአውሬና የአሞራ ሲሳይ የሆኑ ወገኖቻችን ስናስብ ዛሬም ልባችን ያዝናል፣ ነፍሳችንም በሐዘን ይመታል፡፡ ዘጠኝ ወር በማሕጸናቸው ዓለም ለተሸከሟቸው እናቶች ልጆቻቸው ለተገደሉበት የጥይት ዋጋ እንዲከፍሉ በተጠየቁበት፣ ቅጥ የለሽ ግፍና ኢሰብአዊነት በነገሰባት እና የምስኪኗ ኢትዮጵያ እናቶች ወላድ ማኅጸናቸውን በረገሙበት፣ በእንባ ጎርፍ በታጠቡበት በዛ ቀውጢ ወቅት፣ ሀገሪቱ በደም በጨቀየችበትና ምድሪቱ አኬልዳማ በሆነችበት፣ በአራቱም ማእዘናት አስፈሪ ጣእረ ሞት በንዣበበበት የእምዬ ኢትዮጵያ የጣእርና የምጥ ወቅት፡-

የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ፣

ልጅሽን አሞራ እንጂ አይቀብረውም ዘመድ፡፡

ተብሎ ሙሾ በተደረደረባት ኢትዮጵያችን በአብዮት ጨካኝ ሰይፍ ወንድ ሴት ወጣት አረጋዊ ሳይባል የሺህዎች ደም በከንቱ በፈሰሰባት አገር በዳይም ተበዳይ ከልብ የሆነ ይቅርታ ሳይጠያየቁና ብሔራዊ እርቅና ምሕረትን ለማውረድ በተገደርንበት ሁናቴ ዛሬም የግፍና የበደል ታሪካችንን እሹሩሩ እያልን ለሌላ በቀል ሌላ ግፍ ተረኞችን የምናስተናግድበት የጉድ ምድር ሆናለች ሀገራችን ኢትዮጵያ፡፡ ዛሬም የብዙ ሺህዎች የግፍ እንባና ደም እንደ አቤል ደም የፍርድ ያለህ፣ የፍትህ ያለ እያሉ ወደ ጸባዖት ጩኸታቸውን እያሰሙ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ግፍ በተፈጸመባት ምስኪን ኢትዮጵያ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዚህ ድርጊት ፈጻሚ የነበሩ ሰዎች በግልፅ በሆነ መንገድ በአደባባይ ይቅርታ የጠየቁበትና ተበዳዮችን ተገቢውን ካሣ ባልካሱበት ሁናቴ አለመኖሩና አንዳንዶችም የሠሩት ነገር ትክክል እንደሆነና ማንም በግፍ የተገደለ ሰው እንደሌለና የተወሰደው እርምጃ ሁሉ አብዮታዊና ፍትሐዊ እንደሆነ ያለ ምንም ኸፍረት እየነገሩንና እየጻፉ ባለበት ሁናቴ ቂም በቀል፣ ግፍ፣ መከራና ጉስቁልና ዛሬም በምድራችን ቀጥሏል፡፡

የዚህ ጹሑፍ ዓላማ ያለፈውን በደልና ግፍ በማውሳት የተገጂዎችን የሐዘን ቁስል እንዲመረቅዝ ለበቀልና ለጥላቻ እንዲነሳሱ ለማድረግ አይደለም፤ ግና ዛሬም በዚህ ድረ ገጽ ላይ ባለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ የደብቡ አፍሪካውን የቁርጥ ቀን ልጅ የይቅርታና የሰላም አባት የማንዴላን እና የትግል አጋሮቻቸውበደቡብ አፍሪካ ያወረዱትን የይቅርታ መንፈስ በማውሳት የደም ሸማን ጸጎናጽፋ ለምትታይ አኬልዳማ ለሆነች ኢትዮጵያችን ከልብ የሆነ ይቅርታና ብሔራዊ ይቅርታን ማወጅ እንደሚያስፈልግ ለመጠቆም ነው፡፡ ዛሬም ለበቀል ሰይፋቸውን የሳሉ እና ለሞት የሚፈላለጉ ሕዝቦች ባሉባት ሀገር የነገ ፍጻሜያችንና ዕጣ ፋንታችን ሲታሰብን ነፍሳችን በጽኑ የምትደክም ይመስለኛል፡፡

አስገራሚው ነገር ይህ ሁሉ ግፍ በተፈጸመባት ግን ደግሞ ክርስትናንና እስልምናን በሰላም ተቀብላ ለሺህ ዘመን ኖራለች ተብሎ በምሳሌነት በምትነሳ ምድር ያ ሁሉ ግፍና በደል ሲፈጸም፣ እንባና ደም በተቀላቀሉበት እምዬ ኢትዮጵያ እርቅ ሰላምና ፍቅር ይውረድ ብለው በአደባባይ የተናገሩ፣ የገሰጹ የሃይማኖት አባቶችንና የአገር ሽማግሌዎችን ትላንትና የት እንደነበሩና ዛሬስ አድራሻቸው የት ነው ብለን እንድንጠይቅ የሚያስገድድ ነው በታሪካችን የሆነው ያየነውና የሰማነው ግፍና በደል፡፡

‹‹አባቶቻችን ሲታጠቡ እስከ ክንድ ከታረቁ ከልብ!›› ይላሉና፤ ይቅርታ፣ እርቅና ሰላም በሕዝቦች፣ በመሪዎች፣ በሃይማኖት ተቋማትና በሃይማኖት አባቶች ሁሉ መካከል ይወርድ ዘንድ ያስፈልጋል፡፡ ብሔራዊ የሆነ የይቅርታ መንፈስም ያሰፈልገናል፡፡ ለዚህ ደግሞ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ ምሁራንና የታሪክ አጥኚዎች፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሕግ ተቋማትና በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተሳታፊ የሚሆኑበት ግልጽ የሆነ በአደባባይ እርቅ፣ ይቅርታና ብሔራዊ ንስኃ ያስፈልገናል፡፡

እግዚአብሔርን ኢትዮጵያን ይባርክ!
ሰላም! ሻሎም!

(fikirbefikir@gmail.com)

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ሰራተኞች አስጠነቀቁ

Friday, May 11th, 2012

(ኢሳት ዜና) – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ሳምንታት ሸኚዎች ወደ ውስጥ ገብተው ዘመዶቻቸውን እንዳይሸኙ ክልከላ መጣሉን በተደጋጋሚ ስንዘግብ ቆይተናል። የአየር መንገድ ሰራተኞች እንደሚሉት መንግስት እግዱን የጣለው የሽብር ጥቃት እንደሚፈጸም መረጃው ስለደረሰው ነው። ይሁን እንጅ አንዳንድ ወገኖች መንግስት ወደ ሳውዳ አረብያ የሚጎርፉትን ወጣት ሴቶች ህዝቡ እንዳያያቸው የተጠቀመበት ስልት ነው ሲሉ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣት ሴቶች በቦሌ አየር ማረፊያ ሲስተናገዱ በፊልም የተደገፈ መረጃ አቅርበዋል። ኢሳት ከአንዳንድ ሰራተኞች ባገኘው ጥቆማ መንግስት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ እንዲሁም የምእርባዊያንን ድጋፍ እንደያዘ ለመቆየት ምናልባትም የተቀናበረ የፈጠራ የሽብር ጥቃት ራሱ አዘጋጅቶ ራሱ ሊፈጽም ይችላል የሚል ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል።

ዘገባው ከተላለፈ በሁዋላ ከፍተኛ የአየር መንገዱ ኢንጂነሮች መንግስት እያቀደ ካለው ድርጊት እንዲቆጠብ እና ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በሚል ሚስጢራዊ መረጃዎችን ለኢሳት ልከዋል። እንደ ከፍተኛ ኢንጂነሮች ጥቆማ በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 21 አመታት አገልግሎት ላይ የዋለውን ቦይንግ 757 – 260 ETAKC አስመስሎ በተሰራ የበረራ ክንፍ በማደስ 100 በመቶ የብቃት ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ተችሎአል። በዚህም መሰረት በቦይንግ 757- 260 ET AKE ላይ ተመሳሳይ ስራ ይሰራል ተብሎ በእቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም ላለፉት 2 ወራት ስራው ሳይጀመር ቆይቷል።

ሰሞኑን የስራ አመራር ሃላፊዎች በጣም ለተወሰኑ ቴክኒሻኖች በዚሁ አውሮፕላን ላይ ያሉ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ እቃዎች በሚስጢር ከአውሮፕላኑ ላይ እንዲነሱ ጥብቅ በሆነ ትእዛዝ ሰጥተዋል። ማኔጂመንቱ ለኢንጂነሮች የሰጠው ምክንያት አውሮፕላኑ የሽብርተኝነት አደጋ ሊፈጸምበት እንደሚችል መረጃ ደርሶናል የሚል ነው። ኢንጂነሮች በበኩላቸው አውሮፕላኑ የሽብር ጥቃት የሚፈጸምበት ከሆነ በሚቀጥለው ሳምንት ስራ እንዲጀምር ለማድረግ ለምን ተፈለገ በማለት ይጠይቃሉ። ኢንጂነሮች እንደሚጠረጥሩት መንግስት በዚያ አውሮፕላን ላይ አንድ የሆነ አደጋ ሊፈጽም ተዘጋጅቷል ። ይሀው የበረራ መርሀ ግብሩን አያይዘው የላኩት የአየር መንገዱ ከፍተኛ ኢንጂነሮች መረጃውን ይፋ ለማውጣት የፈለጉበትን መንገድም ገልጠዋል- ጉዳዩን ለህዝቡ አስቀድሞ በማሳወቅ መንግስት ነገሩ እንደ ታወቀበት አውቆ ከዚህ ድርጊቱ ይቆጠባል የሚል እምነት አለን በማለት ለኢሳት ገልጠዋል።

ጉዳዩን በማስመልከት የኢትዮጵያን አየር መንገድ ባለስልጣናት ለማነጋገር ብንሞክርም ሊሳካልን አልቻለም ይሁን እንጅ አየር መንገዱ አስተያየቱን በማንኛውም ጊዜ ካቀረበ ለማውጣት ዝግጁ ነን። አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአቶ ግርማ ዋቄ አመራር በአፍሪካ ደረጃ ተመራጭ አየር መንገድ ለመሆን መብቃቱ ይታወሳል። አቶ ግርማ ዋቄ በጡረታ እንደተሰናበቱ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን የማኔጅመንቱን ስፍራ የተረከቡ ሲሆን ቀድሞ የቦርዱ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ስዩም መስፍን ደግሞ ስልጣኑን ለአቶ አዲሱ ለገሰ አስረክበዋል።

የሃይማኖቶ አባቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ ጥሪ ያቀርባሉ – ቅዳሜ 5 PM

Friday, May 11th, 2012

በብጹህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዮስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የሚመራው 33ተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 1 እስከ 3 ቀን 2004 (May 9 – 11, 2012) በዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል። ቅዱስ ሲኖዶስ ወቅታዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መመሪያዎችን ይሰጣል፥ እንዲሁም ወቅታዊ የሀገራችን የኢትዮጵያን ሁኔታ ዳስሶና ተወያይቶ ሀገራዊ ጥሪ ለኢትዮጵያውያን ያቀርባል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን ከ11 ሰዓት (May 12 at 5፡00 PM) በዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

ጋዜጣዊ መግለጫውን ለማዳመጥ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት በዚህ ስልክ ይደውሉ፣ 712 432 0075, መግቢያ ኮድ 215-557#