የቪድዮ ምስል ከፋይል
Author Archive
ባህርዳር ከተማ የጅንአድ እየተቃጠለ ነው
Tuesday, May 21st, 2013በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ
Tuesday, May 21st, 2013ከያሬድ አይቼህ ፤ ሜይ 20፥2013
የፓልቷኩ አባ-መላ ሰሞኑን ገኗል። መግነኑ አልከፋኝም … ይግነን … ለሁሉም ጊዜ አለውና። ግን አባ-መላን ብዙ ጊዜ አዳምጨዋለሁና የአባ-መላን ነገር መዳሰስ ፈለኩ። ሰሞኑን አባ-መላ ገዢውን ፓርቲ መተቸት ጀምሯል። ይህንን የሰሙ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በጣም ፈንጥዘዋል ፡ እኔ አልፈነጠዝኩም። ለምን?
አባ-መላ የሚናገረውን ነገር በየሳምንቱ ፡ አንዳንዴ አልፎ አልፎም ቢሆን ፡ አዳምጨዋለሁ። አባ-መላ የሚያረገውን የሚያረግው ለአንድ አበይት ምክንያት ብቻ ነው፦ የግል ጥቅም። አባ-መላ ሌላ ንዑስ ምክንያት የለውም። የሚያደርገው ፡ የሚናገረው ፡ የሚተነፍሰው ፡ የሚስቀው ፡ የሚያለቅሰው … ወዘተ … ለግል ጥቅሙ ነው (ለግል ጥቅሙ መቆሙ መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም ፡ ያ ምርጫው ነው)።
በ2008 እ.አ.አ. አባ-መላ ክፍል ውስጥ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው (“addis_ababa_1”? በሚል መጠሪያ ስም ሚሳተፍ) ክፍሉ ውስጥ በተነሳ ቅራኔ ምክንያት የክፍሉን ሚስጥር በተቃዋሚ ክፍሎች ውስጥ ገብቶ ሲናገር ሰምቻለው። ከተናገረው ሚስጥር አንዱ ፡ ቃል በቃል ባላስታውስም ፡ አባ-መላ ከሚድሯክ ወይም ከሼህ መሃመድ አልሙዲ በአመት $50,000 ዶላር እንደሚከፈለው ነው። ይሄ ነገር የአባ-መላን ባህሪ እና የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ትኩሳት ለመረዳት ወሳኝ መረጃ ሆኖ አገኝቼዋለሁ።
አባ-መላ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከሚድሯክ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። የሚድሯክ ጥቅም ሲከበር ፡ አባ-መላ ለኢህአዴግ እስክስታ ይወርዳል። የድርጅቱ ጥቅም ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስል ፡ አባ-መላ ደረቱን ይመታል።
አባ-መላ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆኖ አያቅም። አባ-መላ የሚድሯክን ገጽታ የሚያሽሞነሙን ፡ የደርግ ስርዓት ያፈራው ፡ አንደበተ ምላጭ ፡ የሚያደርገውን የሚያቅ ፡ ፕሮፓጋንዲስት ነው።
ታዲያ ምነው ሰሞኑን የፓልቷክ ተቃዋሚ ክፍሎች ባዶ ሆነው የሲቪሊቲ ክፍል ሞልቶ የፈሰሰው? ተቃዋሚ ባካችሁን በአባ-መላ አትበሉ። አባ-መላ ሚያደረገው ሁሉ ለአገራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙና ለሚያገለግለው ድርጅት ጥቅም ብቻ ብሎ መሆኑን እንገንዘብ።
ሚድሯክ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የከፈተና ፡ አያሌ ካፒታል ያፈሰሰ ድርጅት በመሆኑ ድርጅታዊ ገጽታውንና ጥቅሙን መንከባከቡ ተገቢና የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሚድሯክ እና በኢህአዴግ መካከል ሆነን ልንፈጭ ነውና ፡ በአባ-መላ የፓለቲካ ስልት እንዳንበላ ጠንቀቅ እንበል።
አባ-መላንም ሆነ ሌሎች ገዢው ፓርቲን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ሰዎችን ተስገብግበን ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጨመር የለብንም። በጊዜ ውስጥ ሊፈተኑ ፡ አመኔታችንን ቀስበቀስ ሊያገኙ ይገባል እንጂ ተንሰፍስፈን መርዝ ይሁን መድሃኒት እንደያዙ ሳናቅ አንቀበላቸው።
ወቅቱ የህወሃት/ኢህአዴግ መጨረሻ ወቅት ነውና የሚደናበሩትን የገዢውን ፓርቲ በላተኞች ለጥቅማችን እንጠቀምባቸው እንጂ እነሱ አይጠቀሙበን።
_ _ _ _ _ _
ጸሃፊውን ለማበረታታት ፡ ለመውቀስና ለማስፈራራት በዚህ ይጻፉ፦ yared_to_the_point@yahoo.com
ሰውየው (የመጨረሻ ክፍል) ከይገርማል ታሪኩ
Tuesday, May 21st, 2013
ከይገርማል ታሪኩ
(የመጨረሻ ክፍል)
የአባጃሌው ልጅ ሀይሌ ከፊታቸው ጥንቃቄ የሚጠይቅ ስራ ይጠብቃቸዋል:: መዐሕድ ድርጅቴ ነው: ቤቴ ነው ብሎ የተቀበለውን አባል አሳምኖ ወደመኢአድ ማሰባሰብ ቀላል ነገር አይሆንም:: ወያኔ መራሹ መንግስት የትጥቅ ትግል ለማካሄድ ሲንቀሳቀሱ ይዣቸዋለሁ ያላቸው በርካታ ሰዎች ከፕሮፌሰር አስራት ወ/የስ ጋር በእስር ላይ ናቸው:: የእስረኞች ቤተሰቦች: ዘመድ አዝማዶች እንዲሁም መላው አባላት መስዋእትነት የተከፈለበት ድርጅት ሲፈርስ ምላሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም:: ጊዜ ወርቅ ነው:: ማንኛውም ነገር በትክክለኛው ወቅት ያለእንከን መፈጸም ይኖርበታል:: የወያኔና አንጋቾቹ የፈጠራ ወሬ የየዋሆችን ልብ ሊፈትን ይችላል:: የፖለቲካ ፓርቲወችም ቢሆኑ እንዳሸን ነው የሚፈሉት:: ጊዜ ከተሰጠ አይደለም የተራው አባል የየወረዳ አስተባባሪወችንም በነበሩበት ማግኘት ይከብዳል:: ጥቃትን ለመመከት ሁሉም የየመሰለውን አማራጭ ሊከተል ይችላል:: መፍጠን ይኖርባቸዋል::
ጠ/ ሚኒስትሩ “ለስልጣን የበቃነው ጀርባችንን በእሳት አስገርፈን ነው” ብለው ያሉት ሀሰትነት የለውም:: ደርግ ከስልጣን የወደቀው እንዲህ በቀላሉ አልነበረም:: የትግራይ ወጣቶችን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያዊ ደርግን ለመጣል እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ አድርጓል:: በትግሉ ወቅት ይህ ነው የማይባል ንብረት ወድሟል:: ከሁሉም በላይ የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል:: ነገር ግን ደርግን ለመጣል በተደረገው ትንቅንቅ መስዋእት የሆኑት ኢትዮጵያውያን ለትግል የተነሱት ወያኔ የሚያዝ የሚናዝዝበትን አምባገነን ስርአት ለመመስረት አልነበረም- የአምባገነኑን ስርአት አፍርሰው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በሚያስከብር ስርአት ለመተካት እንጅ:: ወያኔ ግን የህዝብ ልጆች በመስዋእትነታቸው ያስገኙትን ድል ለራሱ በሚመች መልኩ አዘጋጀው:: ለተሰውት የህዝብ ልጆች ካሳ የሚገባኝ እኔ ነኝ ብሎ ድርቅ አለ:: በርግጥ ወያኔ ደረቅ ብቻም አይደለም- ብልጥም ነው::
የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሞቱም ሆነ እንዲጠነክሩ አይፈለግም:: ተቀናቃኝ ፓርቲወች አሉ መባሉ የገዥውን ፓርቲ መልካም ገጽታ በአንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል:: የዴሞክራሲ ስርአት አንዱ መገለጫ ከገዥው ፓርቲ ሌላ የተደራጁ ተፎካካሪ ፓርቲወች መኖር ነው:: ታማኝ የሆኑ ፓርቲዎች ከመንግስት ልዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይችላል:: ታማኝ ፓርቲዎች ታማኝ ተቃዋሚ ያላቸው ናቸው:: ታማኝ ተቃዋሚ በሆነ ባልሆነው መንግስትን አይጐንጥም: የሰጡትን በጸጋ ይቀበላል:: ሕዝብንና መንግስትን ለመነጠል አይሞክርም:: በዚህ ስሌት መሰረት መኢአድም ሆነ ሌላ ፓርቲ ቢመሰረት ችግር የለውም:: ችግር የሚሆነው ፓርቲዎች ገንነው መውጣት ከጀመሩ ነው:: ሕዝብ የሚደግፋቸው ፓርቲዎች ቀይ መስመርን የተሻገሩ ናቸው:: ቀይ መስመር ማለት ኢሕአዴግ ለተቃዋሚዎች ያስቀመጠው የመንቀሳቀሻ ዳራ ነው:: ቀይ መስመሩን አይደለም ማለፍ መንካት ቀይ ካርድ ያሰጣል:: ቀይ ካርድ ያየ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከጨዋታ ውጭ ይሆናል:: በጥፋትም ይቀጣበታል:: ኢህአዴግ በወረቀት ላይ ያሰፈራቸው የፖለቲካ: የኢኰኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፖሊሲዎች በትክክል በስራ ላይ ቢውሉ ህልውናው ሊያከትም እንደሚችል ያውቀዋል:: የነጻና የገለልተኛ ማህበራዊና ዴሞክራሲያዊ ተቋሞች መኖር ለህልውናው ጸር ናቸው:: ትክክለኛ ምርጫ ቢካሄድ እንደማይመረጥ ይረዳል:: መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማይደግፈው እንዲያውም እንደሚጠላው ያውቃል:: ስልጣኑን ከለቀቀ ደግሞ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ለሰራቸው ወንጀሎች ሁሉ መጠየቅ ይመጣል:: ባለስልጣናቱ ያላግባብ ያከማቹት ንብረት ሊወረስ ይችላል:: ስልጣን ከሌለ አይደለም ሀብት ንብረትን ህልውናንስ እንዴት ማስጠበቅ ይቻላል? ተተኪው መንግስት ያለፈውን ሁሉ ይቅር ብሎ የያዙትን ይዘው ከስልጣን ብቻ ገለል እንዲሉ ስለመፍቀዱ ምን ማረጋገጫ ይኖራል? ስለዚህ ወረቀት ላይ ያለው ለተመልካች ፍጆታ የሚውል ነው:: በስራ ላይ የሚውለው በስውር የሚተላለፈው የውስጥ መመሪያ ነው:: ወረቀት ላይ የሰፈረውንና በተግባር እየታየ ያለውን አለመጣጣም የተመለከተ “እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል?” ብሎ ቢጠይቅ መልሱ ቀላል ነው:: “ፖሊሲወቻችን እንከን የላቸውም:: ዴሞክራት ናቸው የሚባሉ ሀገሮችን በጎ ተሞክሮወች ሁሉ ያካተቱ ናቸው:: ችግሩ የአፈጻጸም ነው:: አፈጻጸምን ለማሻሻል አቅምን ማሳደግ የግድ ይላል:: እና ለአቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እጃችሁን ዘርጉ” የሚል መልስ ይሰጥና ሌላ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ይሰራል:: የመናገር: የመሰብሰብ: ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ: የመምረጥ: ወዘተ መብቶች በወረቀት ላይ ያሉ እንጅ በተግባር የሚተረጎሙ አይደሉም:: እኒህን በወረቀት ላይ የተጻፉ መብቶች ለመጠቀም የሞከረ ማንኛውም አካል ቀይ መስመሩን የተሻገረ ነው::
መኢአድ ዳዴ ማለት እስኪጀምር ድረስ ከመንግስት ምንም አይነት ጥቃት ሊሰነዘርበት እንደማይችል የተረዱት ሀይሌ ካለምንም ስጋት እንደበፊቱ ሁሉ ጎንደርንና ጎጃምን ከዳር ዳር አዳረሷቸው:: በመኪና የሚኬደውን በመኪና: ለፈረስ የተመቸውን በፈረስ ካልሆነም በእግር:: “ግዴላችሁም እኔ ያጠፋኋችሁ ልሁን” ይላሉ ሻለቃ ያገነገኑ ሰዎች ሲያጋጥሟቸው:: ባርኔጣቸውን ከጭንቅላታቸው ላይ አንስተው ፍጹም ትህትና በተመላበት አኳኋን “ጤና ይስጥልኝ ጌታየ” ብለው ሲቀርቡ አይሆንም ብሎ ገፍቷቸው ሊሄድ የሚችል ሰው አይገኝም:: ቀልቡን ሰብሰብ አድርጎ ያዳምጣቸዋል:: በዚህ መልክ ቀደም ሲል የመዐሕድ አባል የነበሩትን ሁሉ ወደመኢአድ አስገቧቸው:: የየወረዳ ኮሚቴዎችንም አጠናከሩ::
’የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲወች ግንባር’ ለመፍጠር የተደረጉት ብዙ ሙከራወች ገንዘብ: ጉልበትና ጊዜ በልተው ሳይሳኩ ቀርተዋል:: በሀገር ውስጥ ከኦብኮና ከደቡብ ሕዝቦች ጋር ተመስርቶ የነበረው ህብረት ብዙ መሄድ ሳይችል ቀርቶ ፈርሷል:: በውጭ ሀገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያካተተው የተቃዋሚ ሀይሎች ህብረትም ቢሆን አባል ፓርቲዎችን ሰብስቦ ይዞ መቀጠል አልቻለም:: ኢዴፓና መኢአድ ተከታትለው ከህብረት ጋር ተፋተናል ሲሉ አውጀው የየራሳቸውን መንገድ ተከተሉ:: በመሰባሰባቸው ተስፋ አሳድሮ የነበረው ሕዝብ ተስፋው ጫጨ:: ሻለቃ ከህዝብ ጋር ተመሳስለው ኗሪ በመሆናቸው የህዝቡን ስሜት ይከታተላሉ:: ይህ የፓርቲወች ህብረት መፍረስ መሰራት እርሳቸውንም አበሳጭቷቸዋል:: “እንዲያው ምን ይሻላል? የልጅ ጨዋታ አደረጉትኮ” ይላሉ ከመሰሎቻቸው ጋር ሲያወጉ:: እንዲህ እንዲህ ሲል ቆይቶ በአራት ፓርቲዎች (መኢአድ: ኢዴፓ: ቀስተደመና: ኢዴሊ) ጥምረት ቅንጅት ተመሰረተ::
የቅንጅት መመስረት በየአካባቢው ይደረጉ የነበሩትን የፓርቲዎች የጎንዮሽ ሽኩቻ አስታገሰ:: ባህርዳር ጽ/ቤት የከፈቱት መኢአድና ኢዴፓ መድህን መጠላለፋቸውን ትተው በአንድነት ቆመዋል:: ቀደም ባሉት ጊዚያት አንዱ የሌላውን ጽ/ቤት ረግጦ አያውቅም ነበር:: አሁን ሁኔታው ተለውጧል:: ሁለቱም ጽ/ቤቶች የጋራ አገልግሎት እየሰጡ ነው:: ኢዴፓዎች ድንቅ ድንቅ ሰዎች አሏቸው:: ጥሩ ሀሳብ ማመንጨት: በሳል አመራር መስጠት የሚችሉ ሰዎችን ያካተተ ስብስብ ነው ኢዴፓ:: መኢአድ በአደረጃጀት ከኢዴፓ በእጅጉ ይበልጣል:: በሻለቃ ሀይለየሱስ ሀላፊነት ስር የሆነው ባህርዳር ልዩ ዞንና ምእራብ ጐጃም ዞን እስከቀበሌ ድረስ ተደራጅቷል:: በየአንዳንዱ የገጠር ቀበሌ አምስት አምስት አባላት ያሏቸው አመራር ሰጪ ኰሚቴዎች ተቋቁመዋል:: የባህር ዳር የመኢአድ ወኒያምና ቆራጥ አባላት ኢዴፓዎችን ወደዋቸዋል:: በመሀል የነበረው የመፈራራትና የመጠራጠር ስሜት አሁን የለም:: አንድ ላይ ተሰብስበው ይመክራሉ: መክረውም በጋራ ይወስናሉ::
የቅንጅት አመራር ከገዥው ፓርቲ ጋር የሚያደርጋቸው ክርክሮች የሁሉንም ቀልብ ስቧል:: አርሶ አደሩ ሳይቀር ክርክሩን ለመከታተል ሬዲዮ ገዝቶ ጆሮው ላይ ለጥፎ ይውላል:: የሰላ አንደበትና የበሰለ ትችት የኢሐዴግን ተከራካሪዎች ያንተፋትፍ ይዟል:: ፖለቲካው ነፍስ እየዘራ ነው:: ባሕር ዳሮች የበለጠ ተነቃቅተዋል:: አሁንም ባሕርዳሮች እንደማእከል እያገለገሉ ነው:: ከየዞኖች በሚመጡ ችግሮች ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል:: የቅንጅት ኮሚቴው ለችግሮች መፍትሄ ፍለጋ ከፖሊስና ከአስተዳደር ጋር ውይይት ያደርጋል:: መፍትሄ ግን የለም:: ያም ሆነ ይህ ቅንጅት በያንዳንዱ ልብ ውስጥ ቦታ ይዟል:: ትልቅ ስኬት! የቅንጅት የምርጫ ምልክት የሆነው ሁለት ጣት የሰላምታ መለዋወጫ ሆኗል:: መቸም ፌስታ ነው:: እስካሁን ስር የሰደደ ችግር አይታይም::
የኢትዮጵያ አርሶ አደር የመላው ኢትዮጵያን ሕዝብ ከ80%-85% ያህል ይሆናል:: ኢሕአዴግ የትግል አጋሬ ነው የሚለው አርሶ አደሩን ነው:: አርሶ አደሩ የሚኖረው በገጠር ነው:: ስለዚህ ቢያንስ 80% የፓርላማ ወንበር እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ሆኗል:: ቢሆንም እኒህ መአተኛ ቅንጅቶች ወደገበሬው መጠጋት የለባቸውም:: መርዛቸው እንዲህ በቀላሉ የሚነቀል አይሆንም:: ስለዚህ ባህርዳሮች ወደገጠር ተጉዘው አርሶ አደሩን እንዳያሰባስቡ ሆደ ሰፊው ብአዴን መንገዶችን ሁሉ ጥርቅም አድርጐ ዘጋ::
አርሶ አደሩ ተሰባስቦ የሚገኝበት የእረፍት ጊዜ የደብሩ ታቦት የሚከበርበት ቀን ነው:: ለምሳሌ አዴት ታቦቱ መድሀኔአለም ከሆነ አዴቶች የወሩን 27ኛ ቀን ስራ ፈትተው ያከብሩታል:: በእለቱ ቤተክርስቲያን ሄዶ ማስቀደስ: የታመመን መጠየቅ: የተጣላን ማስታረቅ: ዘመድ ወዳጅን መጐብኘት ነው ዋናው ስራ:: ሌላውም ቢሆን እንዲሁ የየራሱን የበአል ቀን በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የሚያሳልፈው:: ይህች ቀን አርሶደሩ ቤተክርስቲያን ተሰባስቦ የሚገኝባት ናት:: ቅንጅቶች ይህችን ቀን እንደሚጠብቁ ግልጽ ነው:: የየደብሩ ታቦት ከሚውልበት ቀን የተሻለ አይገኝምና ወደዚያው ይገሰግሳሉ:: ታዲያ ይህን የሚያውቁት ብአዴኖች እለቷን በተለያየ ፕሮግራም (ጤና: ጸጥታ: ልማት ወዘተ) ወጥረው ይይዛሉ:: ባሕር ዳሮች አርሶ አደሩን አሰባስበው የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ለማስተዋወቅ አልተቻላቸውም:: ከወር አንዲት የበአል ቀን ጠብቀው ተጉዘው ሲደርሱ ፖሊሶች ቀድመው ቦታው ላይ ተገኝተው ’ቤተክርስቲያን ውስጥ የፖለቲካ ስራ መስራት አይቻልም’ በማለት ይከለክሏቸዋል:: ከቤተ ክርስቲያን መልስ ገበሬው ምሳውን እንኳ መብላት አልፈቀድለት ብሎ እስከ ምሽት ድረስ በስብሰባ ይጠረነፋል:: ይህ ቀደም ሲል ያልነበረ ልምድ የተፈጠረው ቅንጅቶች ገበሬውን እንዳያገኙትና እንዳይበክሉት በሚል ነው:: “ቀደም ብለን የያዝነው ፕሮግራም ስለሆነ በእኛ ፕሮግራም ማንም የፖለቲካ ስራ እንዲሰራ አንፈቅድም:: ከፈለጋችሁ በሌላ ቀን ልትጠሩ ትችላላችሁ” እየተባሉ ቅንጅቶች ድካም ብቻ አትርፈው መመለስ ጀመሩ:: ይህንን የተገነዘቡት ሻለቃ አንድ ብልሀት ዘየዱ:: ሀይሌ የማንንም ሀሳብ አይንቁም:: “ከአንድ ራስ ሁለት ይበልጣል: ለእኔ ያልታየኝ ለአንተ ሊታይህ ይችላል” የሚሉት ሀይሌ የሁሉንም ሀሳብ ካዳመጡ በኋላ “ሁሉም የነርሱ ነው:: በየቦታው ሄደን አቤት ብንልም መፍትሄ ልናገኝ አልቻልንም:: በየገጠሩ ለፍተን ሰውን እንዳናገኝ ስለተከለከልን ካለምንም ውጤት ደክመን እየተመለስን ነው:: አርሶ አደሩ እንዳይከዳቸው በጣም ሰግተዋል:: ፈርተውናል:: እንግዲህ አንድ የሚታየኝ አማራጭ አለ: የቤት ለቤት ቅስቀሳ” ሲሉ ተናገሩ:: ይህ ሀሳብ መተኪያ የሌለው ነው ተብሎ በመታመኑ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እንዲካሄድ ተወሰነ:: የየቀበሌው ኮሚቴ አባላት የዚህን ስራ ሀላፊነት ወሰዱ:: በዚህ መሰረት የቤት ለቤት ቅስቀሳው ተጀመረ:: የየቀበሌው ኮሚቴ አባላት ከቤት ቤት እየዞሩ ግንዛቤ ማስጨበጥ ቀጠሉ:: “እናንተ ቅንጅትን እንድትመርጡ የምንፈልገው በምርጫው ቀን በምርጫ ወረቀቱ ላይ ብቻ ነው:: ከዚያ ውጭ እነርሱ የሚሏችሁን ሁሉ እሽ በሏቸው:: ተሰብሰቡ ሲሏችሁ እሽ: ማንን ነው የምትመርጡ ሲሏችሁ እናንተን በሏቸው:: ማን ማንን እንደመረጠ የሚያሳይ መሳሪያ ተክለናል የሚሉት ውሸታቸውን ነው:: እንዲህ አይነት መሳሪያ የለም” እያሉ አስጠኗቸው::
በከተሞች አካባቢ የሚደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በአንጻራዊነት በእጅጉ የተሻለ ነው:: ቅንጅቶች የምርጫ ምልክታቸውን የያዘ ቲሸርት አሰርተው ለብሰዋል:: ትግሉ ኢሕአዴግን በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን ለማስወገድ ነው:: አለበለዚያ መብቶች የሚከበሩባት: ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመስረት አይቻልም:: ኢሕአዴግን ከመንበረ ስልጣኑ ለማንሳት አብዛኛውን የፓርላማ መቀመጫ ማሸነፍ የግድ ይላል:: ስለዚህ የእኔ የእኔ ብሎ ነገር የለም:: ቅስቀሳው መካሄድ ያለበት በጋራ ነው:: በጋራ ወጪ መኪና መከራየት: የቅስቀሳ ወረቀቶችን ማባዛት: ሁሉንም- በጋራ መከወን:: ሕዝቡ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ከቅንጅቶች ጐን መቆሙን በግብር እያሳየ ነው:: ጽ/ቤቶች በሰው ተጣበቡ:: ማን ማን እንደሆነ አይታወቅም:: ሁሉም ይወጣል ይገባል: ይሰራል:: አንዳንዶች ስጋት ገብቷቸዋል:: ይህንን እድል ተጠቅሞ ብአዴን ብዙ ነገር ሊያበላሽ ይችላል:: ሻለቃ እንዳባት ይገስጻሉ: ይመክራሉ:: “ቢመጡ እኛ ምን ቸገረን:: በድብቅ የምንሰራው ስራ የለን! ሚስጥር ባይኖርባቸውም ጥንቃቄ የሚጠይቁ አንዳንድ ሰነዶቻችንን ከእይታ አርቀናቸዋል:: እዚህ ያለው ጽ/ቤቱና መገልገያ እቃወች ብቻ ናቸው:: የሚያስፈራን ምንም ነገር የለም:: እንዲያውም እንግዶችን መቀበል ያለብን በትህትና ነው:: አያችሁ በአንድ ሰው ብልጫ አንድ ወንበር ይገኛል: በአንድ ወንበር ብልጫ ደግሞ ገዢ ፓርቲነት:: ያላወቅነው ሰው ሁሉ ጠላታችን ነው ብለን ፊት የምንነሳው ከሆነ ምናልባት ያ ሰው በእውነት ሊያግዘን የመጣ ሰው ቢሆን ሊሸሸን ማለትም አንድ ድምጽ ሊያሳጣን ይችላል” በማለት የአባላትን የጎፈነነ ስሜት ገፈፉ:: ጥድፊያ ነው:: ሁሉም ይሰራል:: ቅንጅቶች ሰርግ የሚደግሱ መሰሉ:: ከሁሉ ከሁሉ ባህር ዳር የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ አስገራሚ ነበር:: የባሕርዳር ኗሪ ለስብሰባው ንቅል ብሎ ወጥቷል:: የፖሊና የፔዳ ተማሪወች ቀድመው ስቴዲዮም ደርሰዋል:: የባሕርዳር ስታዲዮም የቅንጅትን እድምተኛ ሰብስቦ መያዝ ባለመቻሉ አካባቢው ሳይቀር በሕዝብ ተጨናንቋል:: እለቱ የጥምቀት በአል የሚከበርበት እንጅ ስብሰባ የሚደረግበት አይመስልም:: ከአዲስ አበባ የቅንጅት አመራር ተወካዮች ተገኝተዋል:: የመድረክ መሪው ሰላማዊ መፈክሮችን ያሰማል:: በዚህ ወቅት አንድ ለየት ያለ ነገር ተከሰተ:: “አንድ በኢትዮጵያ ባንዲራ ያጌጠች መኪና ክላክስ እያሰማችና ከሰው ጋር እየተጋፋች በቀስታ ወደስታዲዮሙ ዘለቀች:: በመኪናዋ ላይ ያሉት ሰዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መፈክር ያሰማሉ:: የመድረክ መሪው ጩኸት በተቀላቀለበት መንፈስ ደስታውን ገለጸ:: “በጭብጨባ ተቀበሏቸው” አለ:: ስታዲዮሙ በጩኸትና በፉጨት ድብልቅልቁ ወጣ:: በዚያች መኪና የመጡት ሰዎች የሙገር አግሮ ኢንዱስትሪ ሰራተኞች ነበሩ:: ስብሰባው ከታሰበው በላይ በደመቀ ሁኔታ በስኬት ተጠናቀቀ:: በበነጋታው ጠዋት የሙገር አግሮ ኢንዱስትሪ ባለቤት የሬዲዮ ቃለመጠይቅ እየተደረገላቸው ነበር:: “ቅንጅት መኪናችንን አስገድዶ በመውሰድ ለቅስቀሳ ተጠቀመባት” ብለው እርፍ አሉ:: ምን ያድርጉ? ተይዘዋል ማለት ነው:: የእውነት ዴሞክራሲ አለ መስሏቸው መብታቸውን ተጠቅመው ድጋፋቸውን የሰጡት አግሮ ኢንዱስትሪዎች በወያኔ ተስፈኞች ጥርስ ውስጥ ገቡ::
የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች በየጽ/ቤቶች እየተገኙ እየተደረገ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ይከታተላሉ: አስተባባሪወችን ይጠይቃሉ:: በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ኦሪያል ብራዚል በጣና ሆቴል የቅንጅትና የህብረት ተወካዮችን አግኝተው አነጋግረዋል:: ሁለቱ ድርጅቶች እያከናወኗቸው ያሉትን ተግባራት: በገዥው ፓርቲ እየደረሱብን ነው ያሏቸውን ችግሮች ገልጸው እኛን ለማፈን ከበላይ አካል ተዘጋጅቶ በተዋረድ እስከቀበሌ ድረስ እንዲሰራበት የተላለፈ የውስጥ መመሪያ ነው በማለት ሰነድ አስረክበዋል:: አሜሪካም ሆነች ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ግንባራቸውን ኮስተር አድርገው ወያኔን “ዋ!” ብለው ከእኩይ ተግባሩ እንዲታቀብላቸው ሊያስፈራሩላቸው አሻፈረኝ ካለም አርጩሜ ቆርጠው ሾጥ ሾጥ አድርገው ሊያስተካክሉላቸው እንደማይችሉ ያውቃሉ:: ግን ተግባሩ መገለጽ ስላለበትና ለፎርማሊቲም ያህል መሆን ስለሚገባው ተደረገ:: በወያኔ እኩይ ተግባር አንጀቱ ያረረ ሁሉም ነው: የራሱ አባላት ጭምር:: ስለዚህ የወያኔን ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ሰነዶችን ማግኘት ከባድ አልነበረም::
አይደርስ የለምና የምርጫው እለት ግንቦት 7 1997 ደረሰ:: ሁሉም በጠዋት ተነስቶ ስፍራ ስፍራውን ይዟል:: የቅንጅት ጽ/ቤት በጣም በጠዋት እንዲከፈት በተወሰነው መሰረት ጽ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰሩ የተመደቡት ሰዎች በጠዋት ተገኝተው ስራቸውን ማከናወን ጀምረዋል:: ሪፖርት ይቀበላሉ: ሪፖርት ያደርጋሉ:: በምርጫ ጣቢያወች በታዛቢነት የተመደቡት የቅንጅት ሰዎች ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷቸው ተሸኝተዋል:: “ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ በፊት የምርጫ ኮሮጆው ባዶ መሆኑን አረጋግጡ: ብአዴኖች ሊያበራግጓችሁ ስለሚሞክሩ በምንም መልኩ ሳትደናገጡ በትእግስት ማጠናቀቅ አለባችሁ:: መራጩ ህዝብ ላይ የሚደረገውን ወከባ ተጋፈጡ:: የሚስጥር ድምጽ መስጫው አካባቢ የኢሕአዴግ ሰዎችን እንቅስቃሴ ተከታተሉ: የድምጽ ቆጠራው እንደተጠናቀቀ የምርጫ ጣቢያው ማህተም ያረፈበት ውጤት ተቀብላችሁ በፍጥነት ወደጽ/ቤት እንድትመለሱ —” ተብለው ተመክረው ነው ቀድመው በየምድብ ቦታቸው እንዲገኙ የተደረጉት:: በሌላ በኩል ከኗሪው ጋር ተመሳስለው በምርጫ ጣቢያወች አካባቢ የሚደረጉ ሁኔታወችን እየተከታተሉ በስልክ ጽ/ቤት ላሉት ሰዎች እንዲያስተላልፉ የተመደቡት ሰዎች በንቃትና በጥንቃቄ ግዳጃቸውን እየተወጡ ነው:: ሁሉም ነገር አሪፍ ነው:: ኢሕአዴግ በምእራብ ጐጃሞች ላይ ተደጋጋሚ የፍተሻ ተኩስ አካሂዶ ችግር የለም ብሎ ደምድሟል:: በወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት የፍተሻ ተኩስ ማለት አንድ ጠላት ሊኖርበት ይችላል ተብሎ የተጠረጠረ አካባቢ ላይ የሚደረግ የሩምታ ተኩስና አሰሳ ነው:: ተኩስ በተደረገበት አካባቢ ጠላት ካለ የአጸፋ ተኩስ ይከፍታል:: ምእራብ ጐጃሞች ይህን የፍተሻ ተኩስ አልፈውታል:: በየስብሰባው ላይ እየተገኙ የገዥው ፓርቲ አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል:: ደረሱብን ብለው ያሏቸውን ችግሮች አሰምተው በሚቀጥሉት አምስት የስልጣን ዘመናቸው ችግሮቻቸው እንደሚቀረፉላቸው በብአዴኖች ቃል ተገብቶላቸዋል:: የየተሰበሰቡበት የውሎ አበል ተከፍሏቸው ተቀብለዋል:: በየስብሰባው ማብቂያ ላይ የቀረበውን ድግስ በደስታ ተጋብዘው ተመራርቀዋል:: ቅንጅት ጸረ ልማት ድርጅት እንደሆነ ተነግሯቸው ልክ ነው ብለው ቅንጅትን አውግዘው ፈክረዋል:: ስለዚህ ብአዴኖች በምእራብ ጐጃም ላይ ስጋት የለባቸውም:: ሙሉ ሀይላቸውን እነርሱን በሚነቅፉና አስተማማኝነታቸው በሚያጠራጥር ዞኖች ላይ ብቻ ማሳረፍ እንዳለባቸው አምነዋል:: እና ለምእራብ ጎጃም የየምርጫ ጣቢያ አስመራጮች የተለየ መመሪያ አልተላለፈም::
የምርጫው እለት ማታ መላው የባሕርዳር ህዝብ እንቅልፍ በአይኑ አልዞረም:: በንቃት ይጠብቃል:: መብራት አሁንም አሁንም ይቋረጣል:: “ሌባ ሌባ” ሲል ሕዝቡ ይጮሀል:: ብአዴኖች ወያኔ የሚሆነውን የሚሆኑ: አድርጉ የሚባሉትን የሚያደርጉ ሮቦቶች ናቸው ብሎ ስለሚያምን ሁሌም ይጠራጠራቸዋል:: መብራት የሚያጠፉ ቀድመው ባዘጋጁት የተሞላ የምርጫ ኮሮጆ ሕዝብ ድምጽ የሰጠበትን ኮረጆ ለመቀየር ነው ብሎ ይጠረጥራል:: እና መብራት ሲጠፋ “ሌባ ሌባ” እያለ ግር ብሎ ወደየምርጫ ጣቢያዎች ይተማል:: አንዳንድ ባለመኪኖች የመኪናዎቻቸውን የፊት መብራቶች ወደምርጫው ቦታ ቦገግ አድርገው በማብራት ሌብነቱን ለመከላከል ይጥራሉ:: በጥበቃ ብዛት ሕዝቡ ተሰላችቶ ወደየቤቱ እንዲመለስ ይመስላል ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም ይታያል:: እሁድ በጠዋት ወረፋ ይዞ ቀድሞ መርጦ ወደጉዳዩ ለመሰማራት ያሰበው ሕዝብ ወረፋው አልደርስ ብሎ እስከእኩለ ሌሊት ድረስ ተጉላላ:: ቢሆንም ሁሉም በእልህ: በጽናትና በትእግስት የፍላጎቱን አሳካ- መረጠ::
ሻለቃ ልጃቸውን እንደሚድሩ አባት በደስታ ብዛት የሚይዙትን የሚጨብጡትን አሳጥቷቸዋል:: ይህን ይዘው ያን ይጥላሉ:: ወዲያ ሄድው ወዲህ ይመለሳሉ:: ሳያስቡት ብድግ ይሉና ተመልሰው ቁጭ ይላሉ:: እርሳቸው የሚወዳደሩበት የምርጫ ክልል መራጭ ወገኖቻቸው አይዞህ ብለዋቸዋል:: ደራወች ጥለው አይጥሏቸውም:: ምእራብ ጐጃም በርሳቸው የተደራጀ በመሆኑ በአሸናፊነት እንደሚወጡ ሙሉ እምነት አላቸው::
ሰኞ እለት ከጠዋት ጀምሮ የቅንጅት የምርጫ ታዛቢወች እየተንጠባጠቡ ወደቅንጅት ጽ/ቤቶች መምጣት ጀመሩ:: የየምርጫ ጣቢያው ማህተም ያለበት የድምጽ ውጤት በእጃቸው ይዘዋል:: የቅንጅት አስተባባሪወች የየምርጫ ክልሎችን አሸናፊ ለማወቅ ከየምርጫ ጣቢያወች የመጡትን ውጤቶች መደመር ቀጠሉ:: ለማመን ይከብዳል:: ምእራብ ጐጃም ላይ መቶ በመቶ (100%) ቅንጅት አሸንፏል:: ቅንጅቶች ብዙ አይነት ስሜት እየተሰማቸው ነው:: ደስታ: ስጋት: ፍርሀት:: ደስታቸው:- የትግላቸው ፍሬ መልካም ከመሆኑ የመጣ ነው:: ስጋታቸው:- ምእራብ ጐጃም ላይ የተገኘው ውጤት በሌሎች ዞኖችና ክልሎች ያልተገኘ እንደሆነ ከሚል የመነጨ ነው:: ፍርሀታቸው:- ሕዝብ በድምጹ የጣለው መንግስት ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል ካለማወቃቸው የተነሳ ነው:: ምናልባት ምክንያት ፈጥረው በድርጅቱና በአባላቱ ላይ የጥፋት ስራ ቢሰሩስ? ሕዝቡንስ ይበቀሉት ይሆን? ወይስ ምን?
ሻለቃ ወታደር በመሆናቸው ጠርጣራ ናቸው:: በተለይ ወያኔ ከቶውንም ሊታመን የማይችል ድርጅት ነው:: ብአዴኖች ደግሞ የራሳቸው ህሊና የላቸውም:: አስፈራራ ሲባሉ የሚያስፈራሩ: ደብድቡ ሲባሉ ሙልጭ አድርገው የሚገርፉ: እሰሩ ሲሏቸው የሚያስሩ: ግደሉ ሲባሉ የሚገድሉ ናቸው:: ለእነርሱ ሕዝብ: ሞራል: ምናምን ቦታ የላቸውም:: ስለዚህ ወያኔ ሱርፍ ብሎበት ‘ለየታዛቢወች የሰጣችኋቸውን የውጤት መግለጫ ሰነዶች በአስቸኳይ ቀሙ’ ካላቸው እሳት ጐርሰው እሳት ለብሰው እንደሚመጡባቸው ያውቃሉ:: አሁንም ፍጥነት ያስፈልጋል:: የውጤት መግለጫ ሰነዶችን ሰብስቦ ማራቅ::
የምእራብ ጐጃም አርሶ አደር ታሪክ ሰራ:: እንዲህ ያለ ውጤት በየትኛውም የሀገሪቱ የየክልል ዞኖች አልታየም:: ሻለቃ በምእራብ ጎጃም ኮርተዋል:: ቃሉን የማያጥፍ: ለእውነት የቆመ: የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ስብስብ ሲሉ ያሞካሻሉ:: ወያኔ ደግሞ ‘ጐጃም በከፋ ሁኔታ አጠቃን:: ጉድ ሰራን:: ጐጃምና ተልባ እያደረ ሸርተት ነው የሚባለው ተረት ሀሰት መስሎን ነበር’ ሳይል አይቀርም:: ጐጃም በፍርሀትና በጥቅም ቃሉን አይለውጥም:: በነጻነት ለመወሰን እድሉን ሲያገኝ ሁሌም ከእውነት ጐን የሚሰለፍ ባለማተብ ሕዝብ ነው:: ’ውሻ በበላበት ይጮሀል’ የጎጃሞች መለያ አይደለም::
ቅንጅት በበርካታ የምርጫ ክልሎች ተጭበርብረናል ባለበት ወቅት አያልቅበት ወያኔም “ካላችሁስ ኧረ እኔም ተጭበርብሬአለሁ” ብሎ ቀረበ:: ይሉኝታና ሀፍረት አልፈጠረበትም:: ለነገሩ ይሉኝታና ሀፍረት የፋራ ነው: ወያኔ ደግሞ አራዳ:: ቅንጅት ቅሬታ ካቀረበባቸው የምርጫ ክልሎች በዳግም ምርጫው አንድም ሳያገኝ ቀረ:: ወያኔዎች ተጭበርብረናል ብለው ቅሬታ ያቀረቡባቸውን ቦታወች አስመለሱ:: እንዲህ ናቸው ወያኔዎች:- ታግለው የሚጥሉ: አባረው የሚይዙ: ሮጠው የሚያመልጡ: ተናግረው የሚያሳምኑ: ተከራክረው የሚረቱ:: እና ሁሉም ሆነ:: በዳግም ምርጫው ምእራብ ጐጃም በድምጹ አስከብሮት የነበረውን አንድ ወንበር አጣ:: ም/አፈ ጉባኤ ሽታየ ምናለ በዳግም ምርጫው በክንዳሙ ወያኔ እገዛ አንድ የፓርላማ ወንበር ከህዝብ ነጠቁ::
-ጐጃም በመጀመሪያወች የወያኔ የግዛት አመታት በተጭበረበረ ገንዘብ ምርቱን ተነጥቋል::
-በ1989 ዓ.ም አካባቢ የጐጃም ሕዝብ ‘የደበቅኸው መሳሪያ አለ’ ተብሎ ታስሯል: ተገርፏል: ተገድሏል::
-ከምርጫው በኋላ ኢሕአዴግ የአማራ ክልልን እንደተሸነፈ አምኖ ሊለቅ ነው የሚል ወሬ ባ/ዳሮች ዘንድ ደረሰ:: ቀጥሎ “እስከቀበሌ ድረስ የሚዘልቅ የክልሉን መንግስት መዋቅር ሰርታችሁ በቶሎ አቅርቡ:: ከዘገየን ቅንጅት ሊያስተዳድር አልቻለም ብለው ተመልሰው ሊወስዱብን ይችላሉ” የሚል መልእክት ከቅንጅት ላእላይ ምክር ቤት መጣ በመባሉ: ኮሚቴ ተቋቁሞ ኰሚቴው የክልሉን መንግስት አስተዳደራዊ መዋቅር ሰርቶ ሰነዱ ፋክስ ተደርጐ ነበር:: ፋክስ የተደረገው ጊዮን ሆቴል በሚገኘው የፋክስ ሜሽን ነበር:: ፋክሱ ለቅንጅት ላእላይ ምክር ቤት መድረስ አለመድረሱ አልተረጋገጠም:: ብአዴኖች ግን እንዴት እንዳገኙት ሳይታወቅ ኮፒው ደርሷቸዋል:: እና በሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያስቀመጡትን ሁሉ ሰብስበው አሰሩ:: እስረኞች ሌሊት ሌሊት በሽፍን መኪና ወደመሸንቲ መንገድ እየተወሰዱ ጫካ ውስጥ ተገረፉ::
-በጥቅምት 1998 የባሕርዳር ኗሪዎች በጥይት ተደበደቡ::
-በሚኒሊክ ጊዜ በደል ተፈጽሞብናል በሚል በአሁኑ ዘመን ያለውን አማራ ለመበቀል ያላፈረው ወያኔ የትናንቱን የምእራብ ጐጃም ጥቃት እንዴት ሊረሳው ይችላል? እና ጐጃሞች ዛሬም በሰበብ አስባቡ እየተሳደዱ ነው::
ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ በሀላፊነታቸው ስር የተቀመጡትን ባ/ዳር ልዩ ዞንና ምእራብ ጎጃም ዞንን እድሜና ተሞክሮ ባጐናጸፋቸው ዘዴ ተጠቅመው ከሁሉም አባላት ጋር አሸንፈዋል:: የድሉ ባለቤትና የትግሉ አራማጅ የነበሩትን መላው የቅንጅት ቤተሰቦች: መላው የባህርዳርና የምእራብ ጎጃም እንዲሁም የራሳቸውን መራጭ የደራ ህዝብ ከልባቸው የክብር መዝገብ ላይ አስፍረዋል:: የቅንጅት አባላትም ሻለቃን በክብር ያስቧቸዋል::
አማሮች ዛሬም ሁነኛ ሰው ያስፈልጋቸዋል::
ረጅም እድሜ ለሻለቃ (ሻቃ) ሀይለየሱስ እጅጉ!
የሙስናው አስር ምስጢር! (ማረ በላዎቹ ርስ-በርስ ተበላሉ!)
Tuesday, May 21st, 2013
ለብዙዎች “ሙስና” የሚለው ቃል በ1989 ዓ.ም ወዲህ የተፈጠረ ሃይለ-ቃል ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ ቃሉ ግዕዝ ነው፡፡ ትርጉሙም፣“ጥፋት” ማለት ነው፡፡ በአማረኛም የኖረ ሕዝባዊ ግጥም/አባባል አለ፤ እንዲህ የሚል ነው፡፡ “የከንሯ ለዛ፣ የጉንጯ ሙስና፤Tower in the Sky (የሰማይ ላይ ግንብ) – የመጽሐፍ ግምገማ
Tuesday, May 21st, 2013የህወሃት ማበስበሱ ቁማርና የደኅንነቱ ሚና-የቀዩ መስመር ሰላባዎች?
Tuesday, May 21st, 2013የቀዩ መስመር ሰላባዎች?
By Goolgule.com
May 20, 2013
መለስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከተሰጡት አስተያየቶችና ትንቢቶች መካከል ቀዳሚው የመለስ ሞት ለህወሃት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ መሆኑ ነበር። በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ ዲፕሎማት “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህ እንደሚከሰት ቁልጭ አድርገው ተናግረው ነበር።
መለስ አፍነው የያዟቸው የፖለቲካ ችግሮች ጊዜያቸውን እየጠበቁ የሚፈነዱና በመጨረሻም ፓርቲውን እንደሚፈረካክሰው የተገለጸው በየደረጃ የሚፈነዱት ችግሮች እየበረከቱ በመሄዳቸው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው ችግሮች የእርስ በርስ መበላላት ደረጃ እንደሚያደርሱ በርካታ ወገኖችና መገናኛዎች ጎልጉልን ጨምሮ አመላክተዋል። አሁን አሁን ትንቢቱ የፍጻሜው ጅማሬ ላይ እንደሚገኝ የሚናገሩም አሉ።
የፖለቲካ አቋም ልዩነት ሳይኖር የአስተሳሰብ ልዩነት ማራመድ በህወሃት ዘንድ አይቻልም። ከተሞከረም ክህደት ነው፤ መፈንቅለ መንግስት የማካሄድ ያህል ነው። የርዕዮተ ዓለም ለውጥ የማቀጣጠል ያህል ያስፈርጃል። ሽብርተኛ ያስብላል። ከቶውንም ተቀባይነት ስለሌለው ድንበር ተበጅቶለታል። ድንበሩም “ቀይ መስመር” በመባል ይታወቃል። የ”ቀይ መስመር” ሃሳብ አመንጪና ደራሲ አቶ መለስ ናቸው። “በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ” በሚል የምጸት ስም የሚጠሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም ይህንን የቀይ መስመር ጽንሰ ሃሳብ ለንግግር ያህል ይጠቀሙበታል።
ቀይ መስመር የሚሰመርበት በውል ተለይቶ የተቀመጠ ውስን ጊዜ የለውም። መስመሩ ሁሌም አለ። ሁሉም ቆመውበታል። ከልምድ እንደሚታየው በህወሃት ህመም ኢህአዴግ ሲያተኩሰው በድንገት መስመሩ በደማቁ እንዲቀባ ይደረጋል። መስመሩ የሚቀባበት ደማቅ ቀለም የሚቀዳው አቶ መለስ አፈር ሳይልሱ “በስብሰናል” ሲሉ ከሰየሙት የኢህአዴግ የ”ማበስበሻ” ባህር ውስጥ ነው።
በኢህአዴግ የ”ማበስበሻ” ባህር ውስጥ ያልተነከረ የለም። በዚህ ባህር ውስጥ ሆነው የሚንቦጫረቁት ተቆጥረው አይሰፈሩም። አዲስ አበባ በአራቱም ማዕዘን፣ በክልልና በክልል ዋና ዋና ከተሞች፣ እንዲሁም በተለያዩ አገራት የሚሰነፍጠው የባህሩ “ግልማት” የዜጎችን የመኖር ህልውና ከተፈታተነ ቆይቷል።
በባህሩ ውስጥ በመርከብ ሆነው በጀልባ የሚቀዝፉትን የሚመለከቱ አሉ። ጀልባ የሚቀዝፉት ጌቶቻቸውንና “ልዕልቷን” እያዩ ሽታውን በለመዱት ባህር ውስጥ ይምነሸነሻሉ። በዛው ባህር ውስጥ በደረታቸው እየዋኙና እየተንቦጫረቁ ግብር የሚያስገቡ አሉ። “ዲጂታል” የሚባሉትና “ምስለኔዎቹ” ደሞ የማበስበሻውን “መረቅ የማቅለሚያ ማዕድን” ይዘው አራት ኪሎ የባህሩ አናትና ማማ ላይ ሆነው ሁሉንም ይመራሉ። የባህሩን የመጫወቻ ህግ የሚበላቸውና ከበሰበሰው ባህር ወደ እቶን የሚወረወሩት “የቀይ መስመር ሰለባዎች ” ይለያሉ። ለይተው ሲጨርሱ ለባህሩ ካፒቴን የፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያቀብሉታል። በዚሁ ሂደት ይቀጥላል። አዲስ ነገር የለም። ሊኖርም አይችልም። ይህ መነሻ ነው። ወደ ጉዳዩ እናምራ።
የሰሞኑ ወግ – ኢህአዴግ አመረረ ወይስ ቀለደ?
ሰሞኑን ኢህአዴግ “ሙስና ላይ ዘመትኩ። በህዝብ ጥቆማና ትብበር ሙስና የተንሰራፋበትን ተቋም አበራየሁት። የህዝብ ትብብር አይለየኝ …” በማለት የፍርድ ቤት አሰራርና ህጋዊ የፍርድ አካሄድ እያስኮመኮመ የሚያውጀው አዋጅ ያስገረማቸው ክፍሎች “እንዴት እንመን? እንዴት እንቀበል? ማን ያልተነካካ አለ?” እያሉ ነው። ከተለያዩ አቅጣጫ “ኢህአዴግ አመረረ ወይስ ቀለደ” በሚል ክርክርም እያስነሳ ነው።
የፌዴራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ፓርላማ ቀርበው “ጥናቱ የተጀመረው በአቶ መለስ ትዕዛዝ ከዓመት ከአስር ወር በፊት ነበር” በማለት ምስክርነታቸውን የሰጡበት ዘመቻ አቶ መለስ በህይወት እያሉ ያልተጠናቀቀው በድንገት በመታመማቸው፣ ከዛም በመሞታቸው፣ ከዛም በላይ የሽግግር ወቅት በመሆኑ እንደሆነ አስረድተዋል። መለስ ሲሞቱ ሃይለማርያም ሙስና ላይ ዘመቱ በሚል ስባሪ ታሪክ እንዳያተርፉ፣ ከዚያም አልፎ ዘመቻው የፖለቲካ ልዩነቱ የፈጠረው “የአራግፍ፣ የመንጥር ዘመቻ” እንዳይመስል አቶ አሊ መለስን የዘመቻው “አባትና ባለታሪክ” አድርገው እንዲያቀርቡ መታዘዛቸው ዘመቻው የተለመደው የኢህአዴግ ቀልድ እንደሆነ አመላካች ስለመሆኑ በስፋት አስተያየት የሚሰነዘርበት ጉዳይ ነው።
ምንም ሆነ ምንም ኢህአዴግ ለጀመረው የሙስና ዘመቻ ሊመሰገን ይገባዋል የሚሉ ወገኖች ዘመቻው እንደ ሰደድ እሳት ተያይዞ የሚነድ ስለመሆኑ ሲናገሩ ይሰማል። የኢህአዴግ ደቀ መዝሙር በመሆን የሚታወቁ ድርጅታቸው “የመለስ ቦናፓርቲ” የተሃድሶ ዘመን ተመልሶ እንደመጣ፣ የዚህ ተሃድሶ ፊት አውራሪ ደግሞ እጩ ጠ/ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እንደሆኑ በኩራት እየተናገሩ ነው።
ከደህንነቱ ራዳር የተሰወረ አለ?
በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የማናቸውም ባለሃብቶችና ባለስልጣናት እለታዊና አጠቃላይ የክትትል መረጃ ተመዝግቦ የተቀመጠ ነው። ዋናው ደህንነት የማበስበሻው ባህር ቁልፍ እጁ ላይ ነው። ሲፈለግ ከዋናው ባህር መዝገብ የሚፈልጋቸው ነቅሶ በስሩ ላላው የኢኮኖሚ ደህንነት ዘርፍ ያቀብላል። ለስራው ቅርብ የነበሩና በቅርቡ አገር ለቀው ናይሮቢ የሚገኙ እንዳሉት በዚሁ አሰራር መሰረት አሁን የታሰሩት ሰዎች ሪፖርት ተጠናቆ የቀረበው የዛሬ አምስት ወር ግድም ነው።
ደህንነቱ ማን ከማን ጋር እንደሚሰራ፣ የትኞቹ ባለስልጣናት ከየትኛው “ባለሃብት” ጋር አብረው እንደሚሰሩ፣ በየትኛው ወገኖቻቸውና ዘመዶቻቸው ስም እንደሚነግዱ፣ የኤክስፖርትና ኢምፖርት ስራ እንደሚሰሩ፣ ያለ ማስያዣ ብድር እንደሚፈቅዱና እንዲፈቀድ መመሪያ የሚሰጡ፣ ወዘተ ሙሉ መረጃ እንዳለው የሚጠቁሙት እኚሁ ሰው “ሙስና ከግል፣ ከድርጅትና ከተቋማት አልፎ በመንግስት ደረጃ የተዘረጋ ነውና ማን ማንን ይወነጅላል?” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። አያይዘውም “አገራችን ውስጥ ሙስና በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በመንግስት ደረጃ የተቋቋመ ነው” ብለዋል።
ሌሎችም እንደሚሉት ሙስናው ሊደበቅ በማይችል ደረጃ አገሪቱን እንደ ወባ ወረርሽኝ ሲያጥለቀልቃት፣ በየአቅጣጫው ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር ህዝብን ሲያንገሸግሸው ለምን ዝምታ ተመረጠ? የሚለው አንኳር ጉዳይ ብዙ ከመላምትነት የዘለሉ ምክንያቶች እየቀረቡበት ነው። በተለያዩ ደረጃ የኢህአዴግን የመበስበስና የእድገት ደረጃ የማሟጠጥ ጉዳይ አንተርሰው አስተያየት የሚሰጡ ቅድሚያ አጀንዳ የሚያደርጓቸው አቶ መለስን ነው።
መለስ ዝምታን ለምን መረጡ?
እርሳቸው ምን ያህል ተዋናይ እንደሆኑ አሃዝ ጠቅሶ መናገር ባይቻልም አቶ መለስ አገሪቱ በሙስና መንቀዟን እያወቁ ዝም ማለታቸው ከተባባሪነት እንደማያሸሻቸው ስምምነት አለ። በፓርላማ፤ ከነጋዴዎችና ከኢንቨስትመንት ማህበረሰብ ጋርና ከተለያዩ አካላት ጋር ሲነጋገሩ ሙስናን አስመልክቶ አስገራሚ ዲስኩር ሲያሰሙ ኖረው ያለፉት አቶ መለስ፣ ሙስናን ተሸክመው የኖሩት በፍርሃቻ እንደሆነ የአብዛኞች ማጠቃለያ ነው። አቶ መለስ ሙስናን እንደ ስልት በመጠቀም በዙሪያቸው ያሉትን “በማበስበስ” እንዳሻቸው ይነዱዋቸዋል።
በሙስና የተጨማለቁና በሙስናው ባህር ውስጥ የሚዋኙትን ባለስልጣናት፣ ካድሬዎች፣ ባለሃብቶች፣ የጊዜው ሰዎችና ዘመዶቻቸው ቢታወቁም አቶ መለስ በመፈክር አብረዋቸው ለመኖር የወሰኑትና በዚያው ይህችን ዓለም ባላሰቡበት መንገድ የተለዩት በጡረታና “ያለህን ብላ” በሚል አካባቢያቸውን ለማጽዳት የሞከሩት ሙስናው ውስን አድራሻና መንደር ስለሌለው ነው። ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘና መለስ የፈሩት ሙስና እንዴት ተደፈረ?
መለስ በህይወት እያሉ ሙስናውን ዝም አሉ የሚሉትን ክፍሎች አጥብቀው የሚቃወሙ ቡድኖች ደግሞ “አቶ መለስ የሙስናው አውራ ናቸው። በመንግስት ደረጃ ለተገነባው የሙስና መንደር ፊታውራሪና ይለፍ ሰጪ ናቸው” ሲሉ ይከራከራሉ። የሙስናውን አዝመራ የዘሩ፣ ኮትኩተው ያለመለሙት፣ መጨረሻ ላይም ባህር አዘጋጅተው የማበስበሻ አረንቋ የተከሉት አቶ መለስ በመሆናቸው ርምጃ ለመውሰድ እንደማይቻላቸው፣ ርምጃ ልውሰድ ቢሉም ሁሉም ስለተበከሉ “በአገሪቱ የጦር አዛዥ፣ የፖሊስ አለቃ፣ የደህንነት ሹም፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ፓርላማ፣ ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ፣ ከንቲባ፣ መሃንዲስ፣ ሆስፒታል … የሚቀር ስለማይኖር በቅድሚያ በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅ ይገባል” ሲሉ የሙስናውን አደገኛነትና መንግስታዊ መዋቅር ያለው ስለመሆኑ ይከራከራሉ።
ለማስረጃ ከሚያነሱት መከራከሪያ መካከል “ዋናው የሙስና ሻርክ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት ባለሃብትና በሳቸው መዋቅር ውስጥ ሆነው ከተራ ወንጀል እስከ አገር አቀፍና ድንበር ዘለል ዝርፊያ የሚፈጽሙ “ማፍያዎች”፣ በፌስታል ብር የሚያቀባብሉ ምስለኔዎች፣ የባለስልጣናትን ሚስቶችና ዘመዶች በንግድ ተቋሞቻቸው በመሰግሰግ የአገሪቱን ህግና ህገመንግስት እንዳሻቸው የሚጋልቡ ማጅራት መቺዎች፣ የአገሪቱን ባንኮችና የንግድ ስርዓት በማዛባት ሰርተው የሚበሉ ዜጎችን አሟምተው የጨረሱ፣ የራሳቸው ፖሊስና የደኅንነት ሃይል በመገንባት እንደ መንግስት ያቆጠቆጡ ወዘተ በህዝብ ይታወቃሉ። እኒህ ክፍሎች የአቶ መለስን ኮሪዶርና ማረፊያ ቤት ሲመላለሱበት መለስ ዝም ማለታቸው ከምን የመነጨ ሊሆን ይችላል? የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ መልሱ አንድ ነው። እሳቸውም፣ ባለቤታቸውም፣ ዘመዶቻቸውም፣ ወገኖቻቸውም፣ የትልቁ “የማበስበሻው ባህር” አባል በመሆናቸው ነው። ከዚያም በላይ ደግሞ ልንካው ካሉ የመገንደስ አደጋ ስለሚከተል ነው። በሌላ አነጋገር ከስር እስከ አናት በተለያየ ደረጃ በህገወጥ የበለጸጉና የትንንሽ መንግስታት መሪዎች የሆኑ ስለበዙ አቶ መለስም ሆኑ እሳቸው የሚመሩት ህወሃት መራሹ አስተዳደር የመከልበስ አደጋ እንዳያጋጥመው በመፍራት እንደሆነ ከውስጥም ከውጪም በስፋት የሚታመንበት እውነታ ነው።
ደብረጽዮን “የጎበዝ አለቃ”!!
መለስ ሲያልፉ ሃላፊነቱን ጠቅልለው የተረከቡት መለስ በመተካካት ሰበብ ያዘጋጇቸው ሰዎች ናቸው። ከነዚህ አዲስ አመራሮች መካከል ዶ/ር ደብረጽዮን ዋናው መሃንዲስ ናቸው። መለስ የፈሩትን ጉድ እሳቸው እንዴት ደፈሩት ለሚለው የሰሞኑ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች ዶ/ር ደብረጽዮንን ከፊት ለፊት ያስቀምጣሉ።
ከደህንነት መዋቅር ቁንጮ ላይ እንዳሉና መለስ ከሞቱ በኋላ ህወሃት ፊትለፊት ያወጣቸው ደብረጽዮን ከዋናው ስራቸው በተጨማሪ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ክላስተር የሚመሩ ናቸው። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት እንደ እሳቸው ፍላጎት ቢሆን አሁን የተወሰደው ርምጃ ከአምስት ወር በፊት መከናወን የነበረበት ጉዳይ ነበር።
አሁን በቁጥጥር ስር የነበሩት ሰዎች ከአምስት ወር በፊት በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ይታወቅ እንደነበር የሚናገሩት የደህንነት ሰዎች “ከመለስ ህልፈት በኋላ በተፈጠረው የሃይል ክፍፍል አሸናፊ ሆነው የወጡት ክፍሎች ቅርንጫፍ መቆራረጥ ጀመሩ እንጂ ርምጃው የጸረ ሙስና ዘመቻ አይደለም” ባይ ናቸው። የእነ በረከት ስምዓንና የወ/ሮ አዜብን ቡድን በመጻረር በመለስ ሞት ማግስት ዘመቻ የጀመሩት ቡድኖች ከሙስናው ባህር ውስጥ ተጨልፈው ወደ እቶን ውስጥ እንዲጣሉ ሲወሰን ደረጃ ተዘጋጅቶ እንደሆነ አንዳንድ መረጃዎች ያመለክታሉ።
መለስ አፍነው የያዙት የህወሃት “የመበስበስ” ችግር ገሃድ ከሆነ በኋላ አቶ ስብሃት ነጋ ግንባር ሆነው የወጡ ቢሆንም ለምን ታለፉ? የሚል ጥያቄ ስለመነሳቱ አስተያየታቸውን የሚሰጡት እኒሁ የደህንነት ሰዎች እንደሚሉት “አሁን የተጀመረው ኦፕሬሽን አሸናፊዎቹ ሃይሎች ጉልበታቸውን የሚያሳዩበትና የተጻራሪውን ቅርንጫፍ በመቆራረጥ ዋናውን ግንዶች ማድረቅና ለማገዶ የማዘጋጀት የታሰበ ነው” ዘመቻው በቀጣይነት በጡረታ ስም የሚያስወግዳቸው አውራ ሃይሎች እንዳሉት የሚናገሩት ክፍሎች አቶ አርከበ እቁባይና አምባሳደር ብርሃነ ገ/ ክርስቶስ በዚህ የማጥራት ቀመር ውስጥ እንዳሉበት ይጠቁማሉ።
ወ/ሮ አዜብ መስፍንና አቶ በረከት ስምዖን ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ጀምረው የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ ምንም ዓይነት ርምጃ እንደማይወሰድባቸው ያመለከቱት ውስጥ አዋቂዎች “ስብሃት ግን ቅርንጫፎቻቸው በሙሉ ተመልምለው ብቻቸውን ይቀራሉ። በመጨረሻም እንዲደርቁ ይደረጋል” ሲሉ ስለ ስሌቱ የሚያውቁትን ይናገራሉ።
“አቶ ስብሃት ላይ ርምጃ ከተወሰደ የባህሩ ዋና ተዋናዮች በሙሉ ርቃናቸውን ይቀራሉ። ሁሉም መረጃዎች ከወጡ ህወሃት ራሱ ባሰመረው የሞት መስመር ላይ ግንባር ቀደም ተሰላፊ እንዲሆን ያደርገዋል” የሚሉት የመረጃው ሰዎች፣ ለጊዜው አሸናፊ የሆኑት ክፍሎች የተነፈሱ ቢመስላቸውም ውስጥ ውስጡን የጋመ ጉዳይ ስለመኖሩም አመልክተዋል።
የሙስና ፋይል!! የህወሃት ፓናዶል!!
የፌዴራል የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከበቂ በላይ ጥቆማ እንደሚደርሰው፣ በሚደርሰው ጥቆማ መሰረት የማጣራት ስራ ባከናወነባቸው ተቋማት ላይ ርምጃ ለመውሰድ ሲጠይቅ ማዕቀብ እንደሚደረግበት ሰራተኞቹ ውስጥ ውስጡን የሚነጋገሩበት ጉዳይ ነው። ከደህንነት ጋር በቁርኝት የሚሰራው ይህ ተቋም ሳንጃ የሚሰጠው ህወሃት ሲታመም ነው። ኢህአዴግ ውስጥ ግለት ሲጨምር ሳንጃው ድንበር ተበጅቶ ይታዘዛል። ሰሞኑን የሆነውና ከዚህ ቀደም የተደረጉት ሁሉ የዚሁ አሰራር ነጻብራቆች ናቸው።
“ቴሌ በሙስና ገልምቷል” ከተባለና ዋናው ተፈላጊዎች እንዲሸሹ ከተደረገ ከአራት ዓመት በኋላ ኮሚሽኑ “ሳንጃህን ካፎቱ አውጣው ተባለ” መባሉን የሚያስታውሱ ክፍሎች፣ በህወሃት ክፍፍል ወቅት በአንድ ጀንበር የተሰራውን የማራገፍ ድራማ ያጣቅሳሉ። አሁን በቅርቡ ኦህዴድ ውስጥ የህወሃትን የበላይነት ለመሸርሸር በተነሱ ወጣት አመራሮች ላይ ሙስናን ተንተርሶ የተወሰደውን የማጥራት ዘመቻ ያክላሉ። አሁንም በተመሳሳይ ሰሞኑን የተወሰደውን ርምጃ ከዚሁ ከኖረው የህወሃት “የመበላላት” ታሪክ ጋር የሚያገናኙት ክፍሎች፣ በግልጽ አሁን አሸናፊ ሆኖ ከወጣው ቡድን ቁንጮና “ልዕልት” ጋር አብረው የሚሰሩ ግለሰብና፣ ባለስልጣን መታሰራቸው ቢድበሰበስም የክስ ሂደቱ እየጠና ሲሄድ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አሁን ለመገመት የሚችግር እንደሚሆን ይናገራሉ።
ህወሃት በተለይም ተሹለክልከው መሪ የሆኑት አቶ መለስ ከበረሃ ጀምሮ ተቀናቃኞችን እንዴት ይበሉዋቸው እንደነበር ያጋለጡት የቀድሞው የህወሃት የገንዘብ ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መድህን አርአያ የሃሳብ ልዩነት አስመልክቶ ውይይት ተደርጎ መስማማት ባለመቻሉ በጣም ሲመሽ “አሁን እንረፍ፣ እንተኛ” ከተባለ በኋላ በተኙበት በዛው እንዲቀሩ የተደረጉ ስለመኖራቸው ተናገረው እንደነበር በማስታወስ “የአሁኑ ህወሃት ውሳኔውን ተቋማዊ ለማስመሰል። ተቋሙም በህግ፣ በፍርድ ቤት ችሎት፣ በዳኞችና ራሱ መርማሪ፣ ራሱ ከሳሽ በሆነው የፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን የሚመራ በማስመሰል መበላላቱን “ዲጂታል” አድርጎ እየሰራበት ይገኛል።
ለማጠቃለል
የድሃ ልጆች ቦዘኔ ተብለው ሲታሰሩ አገሪቱ ውስጥ የተዛባ ነገር አልነበረም። በፖለቲካ አመለካከታቸው ዜጎች እስር ቤት ሲጣሉ ህግ የተከበረ ነበር። ንጹሃኖች በፈጠራ ወንጀል ሲገረፉና በስቃይ ሲዘለዘሉ ፍትህ አልጎደለም ነበር። እናት በችግር ልጇን ለገበያ ዝሙት ስትልክ ሃፍረት አልነበረም። በዝርፊያ ገንዘብ አዲስ አበባ በህንጻ ስታብድ አግባብነት አይታይም ነበር። ህዝብ በኑሮ ግለት ሌማቱ ሲደርቅና ገንዳ ላይ ምግብ ፍለጋ ህጻናት ሲባትቱ ችግር ሆኖ አይቆጠርም ነበር። አለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎች እንደ ከብት በየአቅጣጫው ሲታጎሩ የፍትህ ስርዓቱ አልተዛባም ነበር … ሰሞኑን እስር ቤት የተወረወሩት አቶ ገብረዋህድ ፍርድ ቤት ቀርበው ስለ ባለቤታቸውና ልጃቸው ሲናገሩ “አገሪቱ ምን እየሆነች ነው” አሉ። ከኮብራ ወርደው ወህኒ ቤት ሲገቡ የአገሪቱ የፍትህ ስርዓትና የህግ የበላይነት እንደ ደቀቀ ታያቸው። የባለቤታቸው ከስርዓት ውጪ መታሰር አንገበገባቸው። የልጃቸው መታሰር አቃጠላቸው። ሌሎች ምን ይበሉ? የፕሮፌሰር አስራት ቤተሰቦችና ወዳጆች ምን ይበሉ? የእስክንድር ነጋ ልጅና ባለቤት ምን ይናገሩ? የነበቀለ ገርባ፣ የነ ኦልባና ለሊሳ፣ የነ ሌሊሴ ወዳጆ በኦሮሞነታቸው ብቻ ለስቃይ የተዳረጉና የመከራው ተካፋይ የሆኑት ቤተሰቦቻቸው ይህን ያህል ዓመት ችግሩን እንዴት ተሸከሙት?
የአቶ መለስ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የቅርብ ባልደረባና የስራ አጋር የሆኑት የአቶ ገ/ዋህድ ባለቤትና ልጃቸው መታሰር ጥፋት ከሌለባቸው የሚደገፍ ባይሆንም ለሌሎች ባለስልጣናትና የህወሃት አለቅላቂዎች ታላቅ ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ በተለያዩ የማህበራዊ ድረአውዶች መነጋገሪያ ሆኗል።
Sport: ከመንደር ሱቅ ጠባቂነት እስከ የአለም ምርጥ አሰልጣኝነት
Tuesday, May 21st, 2013
ከሊሊ ሞገስ
ፈርጉሰን የነገሱበት ሀሙስ
ያ ታሪካዊ ሀሙስ ነበር፡፡ በጠዋቱ ከሰፋፊዎቹ እስከ ታብሎይዶቹ፣ ከቢዝነስ ጋዜጦች የከረረ ፖለቲካ እስከሚያስተናግዱት ድረስ የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ፎቶግራፍ ማተም ግዴታ የሆነባቸው ይመስላል፡፡ ትልልቆቹ ከፊት ገፆቻቸው አልፈው ልክ 25 ዓመታትን ኖሮ በሞት እንደተለየ ሁሉ እንጎቻ የሚያካክለውን የአሰልጣኙን ምስል ‹‹ከ1986-2013›› የሚል ጉልህ ርዕስ አስከትለውበት አትመዋል፡፡
በወሲብ ቅሌቶች፣ በወንጀልና በዝነኞች የግል ህይወት ብርበራ የሚታወቀው ዘ ሰን እንኳን በሽፋን ገፁ ላይ በሜንጦ የተንጠለጠለ የፀጉር ማድረቂያ ማሽን በማተም የአንጋፋውን ስኮትላንዳዊ የሚያንቧርቅ ቁጡ ባህሪይ ዘመን ማብቃቱን ለመግለፅ ሞክሯል፡፡ ዘ ሰን በየዕለቱ በገፅ 3 ላይ በከፊል ራቁት የሚታዩ ቆነጃጅትን ምስል ማተሙ የአስርት ዓመታት ልማዱ ነበር፡፡ ሐሙስ ጠዋት ግን አማላዮ ሞዴሎች ለሰር አሌክስ ቦታውን ለቀው ወደ ገፅ 9 ሄደዋል፡፡
ዘ ታይምስ የተሰኘው የተከበረ ጋዜጣ ባለ 12 ገፅ ተጨማሪ መፅሔት ለአንባቢዎቹ ያቀረበ ሲሆን ‹‹እግርኳስን የቀየረው ሰው›› በሚል ሙሉ ለሙሉ ለፈርጉሰን አውሎታል፡፡ ቴሌግራፍ እንዲሁ በ16 ገፁ የአሰልጣኙን የዩናይትድ ቆይታ ስኬት፣ ውዝግብና የኃላፊነት ፍፃሜ ተርኳል፡፡ 20 ገፆቹን ሙሉ ለእርሳቸው ያበረከተው ጋርዲያን ‹‹ሰር አሌክስ›› የሚለውን የዩናይትድን ታላቅ ሰው የክብር መጠሪያ ብቻ በትልቁ በርዕስነት መፃፉን መርጧል፡፡ ጋርዲያን የፈርጉሰን ምስል የሰፈረበትን ቲሸርት በ20 ፓውንድ ለገበያ አቅርቧል፡፡ ሁሉም ጋዜጦች የሰር አሌክስን የኋላ ህይወት ለመተረክ ፊታቸውን ወደ ግላስጎው አዙረዋል፡፡ የስኬታቸውን መነሻ ስረ መሰረት ለማግኘት ገና በ16 ዓመታቸው ከትምህርት ቤት የተለዩት፣ በወደብ ሰራተኛነት ያሳለፉትና በወጣትነታቸው ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጨዋች እስኪሆኑ ድረስ የመንደር ሱቅ ጠባቂ ስለነበሩት ፈርጉሰን ፅፈዋል፡፡ የሚያስፈራና ቁጡ ባህሪይ እንዳላቸው ሁሉም ተስማምተውበታል፡፡ ፈርጉሰን ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሲመጡ ክለቡ በ31 ሚሊዮን ፓውንድ ገና መሸጡ ነበር፡፡ ከአሰልጣኝነታቸው የመልቀቃቸውን ዜና ይፋ ሲያደርጉ ግን የ2.2 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ይዟል፡፡ ይህን አስደናቂ ስኬት የስነ ፅሑፍ ጥበብ በወለዳቸው ገለፃዎች ያልዳሰሰ የለም፡፡ የሊጉ ጨዋታዎች ሊጠናቀቁ ሲቃረቡ ጠቋሚ ጣታቸውን ሰዓታቸው ላይ አሳርፈው የመስመር ዳኞችን የሚሞግቱት፣ አገጫቸው የሚሰነጠቅ እስኪመስል ማስቲካ የሚያኝኩትና ሲሳካም ሁለት እጆቻቸውን ወደ ላይ አንስተው በመፈንጠዝ ረዳቶቻቸውን የሚያቅፉት ባለሙሉ ልብስ አዛውንት ከፕሪሚየር ሊጉ ምስል መታጣታቸው በሀዘን ተገልጿል፡፡
ሰር አሌክስ ለሚዲያውም ‹‹አምባገነን›› የሆኑባቸው ጊዜያት አሉት፡፡ ምቾት የማይሰጧቸውን ጥያቄዎች ያቀረቡ ጋዜጠኞችን ከእርሳቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች አግደዋል፡፡ ልጃቸው ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የሚያስጠረጥር የቢዝነስ ስራ ሰርቷል ሲል ከዘገበው ቢቢሲ ጋር ለረጅም ጊዜ ተቃቅረው ቃለ ምልልስ ከልክለው ኖረዋል፡፡ ለረጅም ዓመታት ‹‹ጡረታ የሚወጡት መቼ ይሆን?›› ሲሉ የጠየቁት ጋዜጠኞች ጥያቄያቸው በድንገት መልስ ሲያገኝ የፈርጉሰንን ደካማ ጎን ከመግለፅ ይልቅ በሰውዬው ዋጋ የማይተመን ስኬት ላይ አነጣጥረዋል፡፡
ከእንግሊዝ ውጭ እግርኳስን ከዕለታት አንድ ቀን የሚያስታውሱት የአሜሪካ ጋዜጦች እንኳን የታላቁን የስፖርት ሰው ጡረታ ዜና በፊት ገፆቻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ የእግርኳስ ፍቅር እምብዛም በሆነባት ሀገር ቁጥር 1 የሆነው ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ እንኳን አልዘነጋቸውም፡፡ በተለያዩ አህጉራት የሚታተመው ፋይናንሺያል ታይምስ የፈርጉሰንን የ27 ዓመታት አገዛዝ ውጤታማነት አብራርቷል፡፡ ከኒውዮርክ ማንሃተን እስከ ሆንግ ኮንግ የመልቀቃቸው ዜና ጉልበት ነበረው፡፡ በእውቁ የአሜሪካ መጽሔት ኒውዮርከር ላይ የሀገሬው ሰው ‹‹ሶከር›› ስለሚለው እግርኳስ የተፃፈ ሀገር ማግኘት ብርቅ ነገር ቢሆንም የፈርጉሰን ዜና ግን አብይ ርዕስ ሆኖበታል፡፡ የፍሎሪዳዎቹ ቢሊየነሮች የግሌዘር ቤተሰቦች ማንቸስተር ዩናይትድን በገቡበት ወቅት ከፈርጉሰን ጋር ቃለ ምልልስ ለመስራት ወደ ኦልድትራፎርድ የተጓዘው የመጸሔቱ ዘጋቢ ከአሰልጣኙ ጋር ያሳለፉትን የጥያቄና መልስ ጊዜ ማስታወሻውን ጽፏል፡፡ ‹‹በእንግድነት መቀበያው ክፍል ከተጨዋቾቻቸው ጋር ሲያወሩ አየኋቸው፡፡ ቱታ ለብሰው የፕላስቲክ ውሃ ይዘዋል፡፡ ወደ እኔ መጥተው በቃለ ምልልሱ ክፍል ቁጭ ስንል ግን ሰውየው ብልህ መሆናቸውን ተረዳሁ፡፡ በዘርፉ ብዙ እውቀት ተሞልተዋል፡፡ ሰማያዊው አይናቸው ግን ቆዳን በስቶ የሚገባ ሰቅጣጭ እይታ አለው፡፡ ጥያቄዬን ከመመለሳቸው በፊት ጥቂት ትንፋሽ ወሰዱ፡፡ ዝምታቸው ፍርሃት ይለቃል፡፡ ‹ከሰፈሬ መጥተህ ለምን ነገር ትፈልገኛለህ? ይህ የእኔ ግዛት ነው› የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ ይመስላል፡፡ ዙሪያዬን ተመለከትኩ የወለቀ ጫማ አልነበረም፡፡››
የኒውዮርክ ዘጋቢ ለቃለ ምልልስ ከፈርጉሰን ጋር የተፋጠጠበት ወቅት የአሰልጣኙና የዴቪድ ቤካም ውዝግብ ወሬ ያልተሳበት ጊዜ ነበር፡፡ በንዴት የጦፉት ፈርጊ የመጫወቻ ጫማ ወርውረው የዴቪድ ቤካምን ቅንድብ ሰንጥቀው የተጫዋቹ ቁስል ስፌት አስፈልጎት እንደነበር ይታወሳል፡፡
የጋዜጠኛው ቃለ ምልልስ ርዕሰ ጉዳይ ግሌዘር የገጠማቸውን የደጋፊዎች ተቃውሞ የተመለከተ ነበር፡፡ ፈርጉሰን የአሜሪካውያኑን ባለሀብቶች በመደገፋቸው የማይናቅ ቁጥር ባላቸው የዩናይትድ ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥረዋል፡፡ ሰውዬው የተገኙበትን የሰራተኛ መደብ አስተሳሰብ አዋርደዋል በሚል ተተችተዋል፡፡ ሶሻሊስት አመለካከታቸውን ሳይቀር ተቃርነዋል ቢባልም እስከ መጨረሻው ድረስ ከአሜሪካውያኑ ጎን ቆመዋል፡፡ ፈርጉሰን አይሳሳቱም ብለው የሚያምኑቱ ተቃውሟቸውን ጋብ አድርገዋል፡፡
ሰር አሌክስ በዚህ ፈተና ብቻ አላለፉም፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ አለቃነት የቆዩባቸው ዓመታት አሮጌውንና ዘመናዊውን ጊዜ ያገናኙ ናቸው፡፡ ከሳተላይት አብዮት እስከ ክፍያ ቴሌቪዥን ድረስ ከሀገር ውስጥ ተፅዕኖ እስከ ዓለም አቀፍ ዝና ድረስ ተመልክተዋል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድን በጠጪዎች ከተሞላ ክለብነት አንስተው በኒውዮርክ ስቶክ ኦክስቴንጅ ድረስ እስከደረሰ ግዙፍ ተቋምነት ድረስ አሳድገውታል፡፡ በዚህ ሂደት የአካዳሚ ሰልጣኝ ህፃናትን ወደ ኮከብነት ከፍ አድርገዋል፡፡ የዲሲፕሊን መመሪያቸውን የጣሱ ተጨዋቾችን ለመቆጣጠር በውድቅት ሌሊት እሰከ ንጋት ሊቆይ የታሰበ የተጨዋቾች ፓርቲን በርግደው ገብተዋል፡፡ በቡድናቸው ውስጥ ጥብቅ የአመጋገብ ስርዓት አስርፀዋል፡፡ የአካል ብቃት ባለሙያዎችን ቀጥረዋል፡፡ ዘመናዊነቱ ተነግሮ የማያልቅ የልምምድ ማዕከል አቋቁመዋል፡፡ የፖሊሲያቸውን ቀይ መስመር ለተላለፉት የመውጫ በሩን አሳይተዋል፡፡
በዝና ልባቸው ያበጠ ቱጃር ተጨዋቾችን ፀጥ ለጥ አድርጎ በመግዛት ለውጤት ማሰለፍ እንደሚቻል የፈርጉሰን ዘመን ተሞክሮ ያረጋግጣል፡፡ ከራቪያ ቢሊየነሮች እስከ ባህረ ሰላጤው ከበርቴዎች ድረስ የፈርጉሰንን የውጤታማነት ጉዞ ሊገቱ ሞክረዋል፡፡ ሃብታሞቹ የፈርጊን የፕሪሚየር ሊግ ዘውድ ነቀነቁት እንጂ እሰከወዲያኛው አላወረዱትም፡፡ ሰር አሌክስ ግን የሌሎችን ዘውድ መገርሰስ ይችሉበታል፡፡ የ45 ዓመቱ ፈርጉሰን በአዲስ ሹመኛነት ወደ ኦልድትራፎርድ ሲመጡ የሊቨርፑል ኃያልነት ጣሪያ የነካ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የሊቨርፑል ኃያልነት የኋላ ታሪክ ነው፡፡ ‹‹የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ካልሆንክ በስተቀር ፈርጉሰን የሚወደዱ ሰው አይደሉም›› ይላል በሊድስ ከተማ ተወልዶ ያደገ አንድ ጋዜጠኛ፡፡ ስለምን አይነት ጥላቻ እያወራ መሆኑ ይግባችሁ፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ በብስጭት ያሳብዱኛል፡፡ በተለይ በጨዋታዎች ማገባደጃ ላይ ከወንበራቸው ተነስተው ከዳኞች ጋር ሲጨቃጨቁ ጨርቄን ሊያስጥሉኝ ምንም አይቀራቸውም፡፡ ነገር ግን በምስጢር የፈርጉሰን አድናቂ ነኝ፡፡ ለእርሳቸው በቂም የታጀበ ክብር አለኝ››
ሰር ማት በዝቢም እንዲሁ ነበሩ፡፡ በተጋጣሚ ደጋፊዎች የማይወደዱና በ1960ዎቹ ማንቸስተር ዩናይትድን ለተደራራቢ ክብር ያበቁ ታላቅ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ በአውሮፕላን አደጋ በርካታ ተጨዋቾቻቸውን በሞት መነጠቃቸው ከአውሮፓ ሻምፒዮንነት አላገዳቸውም፡፡ ሰር ማት እና ሰር አሌክስ ስኮትላንዳዊ ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት እውቁ ጂኪው መጽሔት ለፈርጉሰን ይህን ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር፡፡
‹‹የስኮትላንድ ምዕራባዊ ግዛት በርካታ ታላላቅ አሰልጣኞችን የሚያፈራው ለምንድን ነው?››
ፈርጉሰን መለሱ፡፡
‹‹ግላስኮአዊያንና የምዕራብ ስኮትላንድ ሰዎች በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ያደጉ ናቸው፡፡ እርጥብ፣ ቀዝቃዛ እና ምህረት የለሽ ብርድ አለው፡፡ አንድ የፌብርዋሪ ጠዋት በፍራንሴብራ ወደብ ተገኝተህ ታውቃለህ?›› ፈርጉሰን ጥያቄያቸውን በጥያቄ መለሱ፡፡ ልጅነታቸውን ያሳለፉበት የመርከብ ፋብሪካ የሚገኝበትን የባህር ዳርቻ መጠቆማቸው ነበር፡፡ በቦታው የብረት ቅዝቃዜ ጣቶችን እንደ እሳት የሚያቃጥል መሆኑን ለጋዜጠኛው ነገሩት፡፡ ‹‹ስትኖርበት ትወደው ይሆናል፡፡ ነገር ግን አስቸጋሪው አየር ያንተን የግል ባህሪይ የመለወጥ አቅም አለው›› ሲሉ መልሳቸውን ቀጠሉ፡፡ ጠያቂውም ዝም አላለም፡፡
‹‹ታዲያ አየሩ ለሰዎቹ ምን የሚሰጣቸው የተለየ ነገር አለ?››
የፈርጉሰን አጭርና ግልፅ መልስ ለቃለ ምልልሱ ማሳረጊያ አበጀለት ‹‹ትጋት!››
በዚህ አስገራሚው ሐሙስ ማንቸስተር ዩናይትድ ፈርጉሰንን በሌላ ስኮትላንዳዊ መተካቱን አስታውቋል፡፡ ዴቪድ ሞዬስን፡፡ የዩናዩትድ ደጋፊዎች ሞዬስ በደም ስራቸው ውስጥ ‹‹ብረት›› እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡ ሽግግሩ አጭርና ያልታሰበ ነበር፡፡ የቀድሞው ፈርጉሰን በወጡበት በር፣ የመጪው ጊዜ ሞዬስ ገብተውበታል፡፡
Health: ራስ ምታት! ዓይነቶቹ፤ ምልክቶቹና ህክምናው
Tuesday, May 21st, 2013
ራስምታትን የማያውቀው ሰው የለም ለማለት ያስደፍራል፡፡ በህክምና ከጭንቅላት የሚነሳ ማንኛውም ህመም (የአይንና ጆሮ ህመምን ሳይጨምር) እንዲሁም ከኋላ በኩል ካለው የአንገት ክፍል መነሻ የሚነሳ ህመም፣ የራስምታት ይባላል፡፡ የራስምታት በራሱ በሽታ ሊሆን ይችላል፡፡ የበርካታ በሽታዎች ምልክት ሆኖም ይከሰታል፡፡ አንዳንዴ የራስ ምታት የገዳይ በሽታዎች ምልክት የሚሆንበት አጋጣሚዎች አሉ፡፡ የራስምታት በራሱ በሽታ ሲሆን፣ ሶስት አይነት መልክ ይኖረዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በህብረተሰባችን በብዛት የሚታወቀው ሚግሬይን የሚባለው የራስምታት ነው፡፡ ሌሎቹ (tension headache) እና (Cluster headache) ይባላሉ፡፡
ከሶስቱ የራስምታት ዓይነቶች (tension headache) ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ በብዛት ይታያል፡፡
ሚግሬይን የራስምታት (migraine headache) ከ (tension headache) በመቀጠል ከፍተኛ ስርጭት አለው፡፡ ይህኛው የራስምታት አይነት ህፃናትንና አዋቂዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ከጉርምስና ወቅት በፊት ሁለቱም ፆታዎች እኩል በዚህ ህመም እንደሚጠቁ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከዚህ ዕድሜ በኋላ ግን በአብዛኛው ሲጠቁ የሚታዩት ሴቶች ናቸው፡፡ ከጠቅላላው ህብረተሰብ፣ ከወንዶች 16 በመቶ፣ ከሴቶች ደግሞ 18 በመቶ የሚሆኑት ይህ አይነት የራስምታት ይታያባቸዋል፡፡
ክላስተር የራስምታት (cluster headache) የሚባለው ስርጭቱ በጣም አነስተኛ (0.1 በመቶ) ሲሆን፣ 85 በመቶ የችግሩ ተጠቂዎች ወንዶች ናቸው፡፡
ሚግሬይን፣ ስር ሰደድ የሆነ የራስምታት አይነት ሲሆን በዘር የሚተላለፍበት እድልም አለ፡፡ የራስምታቱ የሚያናጋ እና የመውቀጥ አይነት ከፍተኛ የህመም ስሜት ይፈጥራል፡፡ ይህ አይነቱ የራስምታት በአብዛኛው በአንድ የጭንቅላት ክፍል ላይ ይበረታል፡፡ አንዳንዴ በግንባር አካባቢ፣ ሌላ ጊዜ በአይን ዙሪያ እንዲሁም በአንገት ጀርባ አካባቢ የህመም ስሜቱ ይፈጠራል፡፡ በአብዛኛው ሕመሙ የጭንቅላትን ቀኝ ወይም ግራ ክፍል የሚያጠቃ ሲሆን፣ ሁለቱንም የጭንቅላት ክፍል የሚያጠቃበት እድል አነስተኛ (ከጠቅላላው 1/3ኛው) ነው፡፡ ህመሙ አንዴ በቀኝ ቆይቶ በግራ የጭንቅላት ክፍል መፈራረቁ በተለይ የሚለይበት ፀባይ ሲሆን፣ በአንድ በኩል ብቻ ከቆየ (ከተደጋገመ) ከሚግሬይን የራስምታት ውጪ የሆኑ በሽታዎች (ለምሳሌ የጭንቅላት ዕጢ) መጠርጠር ይበጃል፡፡ የሚግሬይን የራስምታት የአካል እንቅስቃሴ ሲኖር (ለምሳሌ ደረጃ መውጣት) የሚቀሰቀስ አይነት ነው፡፡ ከየራስምታቱ ጋር ማቅለሽለሽና ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ የፊት አመድ መምሰል (መንጣት)፣ የእጅ እግር መቀዝቀዝ እንዲሁም በብርሃንና በድምፅ በቀላሉ የመረበሽ ምልክቶች ይታያሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ሚግሬይን የራስምታት ያለባቸው ሰዎች ብርሃንና ድምፅ ሽሽት በጨለማና ረጭ ባለ ቦታ መሆንን ተጠቂዎችና ቤተሰቦቻቸው ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክቶቹ ሲታዩ፣ የራስምታቱ ሊጀምር እንደሆነ በሚገባ ያውቃሉ፡፡
ሃያ በመቶ በሚሆኑ የበሽታው ተጠቂዎች ደግሞ ከራስምታቱ ትንሽ አስቀድሞ የሚከሰት እንዲሁም አንዳንዴ ከራስምታቱ ጋር አብሮ የሚቀጥል (aura) የሚባል ምልክት ያሳያሉ፡፡ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ደግሞ ምልክቶቹ (aura) ከራስምታቱ ውጪ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነኚህ ምልክቶች ከዕይታ ማዕከል ጀምሮ ወደ ውጪ የሚሄድ የተለያየ ቀለማት ያለው ብልጭታ፣ በእይታ ክልል ውስጥ ማየት የማይቻልበት ክብ ስፍራ መፈጠር ናቸው፡፡ ቀላል የሚባለው (aura) ምልክቶች፣ በአንዱ እጅ ላይ፣ በአፍና አፍንጫ አካባቢ፣ የራስምታቱ በተፈጠረበት የጭንቅላት ጎን የመጠቅጠቅ ስሜት መኖር ናቸው፡፡ የሚግሬይን የራስምታት ተጠቂ፣ ህመሙ ከተወው በኋላ ለሃያ አራት ሰዓታት ያክል የአቅም ማጣት፣ በድምፅና ብርሃን የመረበሽ ምልክቶች ያሳያል፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳንድ የህመሙ ተጠቂዎች፣ ህመማቸው ሊያገረሽም ይችላል፡፡
ክላስተር የራስምታት (cluster headache)፣ በአንድ ሳምንት ወይም ወር ላይ ተጠቂውን በተደጋጋሚ አጥቅቶ፣ ከዚያ የወራት ወይም ዓመታት እረፍት ሰጥቶ እንደገና በመምጣት ይታወቃል፡፡ (cluster headache) ሲከሰት በቀን ሁለት ጊዜ ተጠቂውን የሚያሰቃይ ሲሆን፣ አንዴ የተከሰተው ህመም ከሰላሳ ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ቆይቶ ይጠፋል፡፡ ህመሙ በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት በመምጣት ይለያል፡፡ ተጠቂውን ከእንቅልፍ የሚቀሰቀስበት ሁኔታም የተለመደ ነው፡፡ እጅግ ሰቅጣጭ አይነት ሲሆን፣ አንዱ አይን አካባቢ ወይም ከአይን ጀርባ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ አንዳንድ የበሽታው ተጠቂዎች፣ ህመሙን ‹‹አይኔ ውስጥ እሳት ተቀምጧል›› በማለት ይገልፁታል፡፡ የተጠቃው አይን ይቀላል፣ ያነባል፡፡ ህመም በተፈጠረበት የጭንቅላት ጎን (ወይም አይን) ያለው የአፍንጫ ክፍል (ቀዳዳ) ይታፈናል፣ እንዲሁም ንፍጥ ይወጣዋል፡፡ የዚህኛው አይነት የራስምታት ተጠቂዎች፣ ከሚግሬይን የራስምታት ተጠቂዎች በተቃራኒው ይቅበዘበዛሉ፣ ከወዲህ ወዲያ ይራወጣሉ፤ ጭንቅላታቸውን ከግድግዳ ጋር ያጋጩታል፡፡
የራስምታት በራሱ ጊዜ ሲከሰት (የበሽታ ምልክት ካልሆነ) ምክንያቱ የአንጎል የደም ስሮች መስፋትና በዚሁ የተነሳ በአንጎል ውስጥ በደም ስሮች አካባቢ ያሉ የነርቭ ስሮች፣ ከሰፉት የደም ስሮች በብዛት በሚወጡ ኬሚካሎች መለብለባቸው ነው፡፡ ይህ የነርቮች መቆጣት ነው እንግዲህ የራስምታት የሚባለው፡፡ እንደ ሜግሬይን ያሉ የራስምታት አይነቶች ከራስምታት ውጪ በሆኑ በተለያዩ ምልክቶች፣ ለምሳሌ ማስመለስ እና ማቅለቀሽለሽ የመታጀባቸው ምስጢር ደግሞ የራስምታቱ ጠቅላላውን የነርቭ ስርዓት ማወክ መቻሉ ነው፡፡ ለምሳሌ ሚግሬይን የራስምታት የሰውነትን (sympathetic nervous system) ያውካል፡፡ ይህ የነርቭ ስርዓት ሲነቃቃ (ሲታወክ) ደግሞ በስሩ ያሉ የሰውነት ስርዓቶች (ለምሳሌ የምግብ መፍጨት ስርዓት) ይታወካል፡፡ ለዚህም ነው ከሚግሬይን የራስ ምታት ጋር ብዙ አይነት የጤና መቃወስ ምልክቶች የሚታዩት፡፡
የበሽታ ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረውን የራስምታት የሚያመጡ የተለያዩ ምክንቶች አሉ፡፡ በጭንቅላት ላይ ደረሰ አደጋ፣ በአንጎል ውስጥ የሚፈጠር ብግነት፣ የአንጎል ደም ስሮች ውስጥ የሚከሰት ጓጓላ፣ የአንጎል የደም ስሮች መለጠጥ፣ መሳሳትና መፈንዳት፣ በድንገት ከፍተኛ ደረጃ የሚደርስ የደም ግፊት፣ የጭንቅላት ላይ የደም ስሮች መብገን፣ በአይን ውስጥ ድንገት የፈሳሽ ግፊት መጨመር (ግላውኮማ)፣ በተደጋጋሚ ለካርቦን ሞኖክሳይድ ጋዝ መጋለጥ፣ የፓርኪንስንስ በሽታ፣ ጭንቀትንና ደም ግፊትን ለማከም የሚውሉ አንዳንድ መድሃኒቶች፣ ያለ ሐኪም የሚታዘዙ የራስ ምታት መድሃኒቶችን ያለ አግባብ መጠቀም፣ አንዳንድ የልብ ህመሞች (cardiac ischemia)፣ የአንጎል ውስጥ እጢ፣ ማጅራት ገትር፣ የመሳሰሉት ሁኔታዎች የራስ ምታት ያመጣሉ፡፡ የበሽታ ምልክት ተደርጎ የሚታየው የራስምታት፣ ለህይወት አስጊ የሆኑ እንደ የአንጎል እጢ፣ ማጅራት ገትር፣ በአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ ችግሮች ጠቋሚ ሊሆን ሲችል፣ ቀላል የሚባሉ ችግሮች እንደ ቡና ሱስ የማሳሉትንም ሊያሳይ ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን የበሽታ ምልክት የሆነው የራስምታትና ራሱ እንደ በሽታ የሚቆጠረው የራስምታት (migraine, clusture, tension) ተቀላቅለው በአንድ ሰው ላይ የሚታዩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለምሳሌ (tension headache) ወይም በበሽታ ምክንያት የሚመጡ የራስምታት የሚግሬይን የራስምታትን ሊቀሰቅሱ ብሎም አብረው ሊታዩ ይችላሉ፡፡
የራስምታት አይነቶችን ለመለየት እንዲሁም የበሽታ ምልክት ይሁን ወይስ በራሱ በሽታ፣ ለመለየት የሚደረጉ የተለያዩ ምርመራዎች አሉ፡፡ በተለይ በበሽታ ምክንያት የሚታየውን የራስምታት መንስኤ ለማወቅ እንደ (MRI, CT scan) የማሳሰሉት መሳሪያዎች ወሳኝ ሲሆኑ፣ የደም ምርመራ ማድረግም ለራስምታቱ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ችግሮችን (የማጅራት ገትርን ጨምሮ) ለመለየት ያስችላል፡፡ የራስምታትን መንስኤ በተለያዩ መሳሪያዎችና የላብራቶሪ ምርመራዎች መለየት ቢቻልም ሐኪም የሚያደርገው የአካል ምርመራና ከበሽታው የሚወሰደው መረጃ ግን በሽታውን ለመለየት ምትክ የለሽ ነው፡፡
የራስ ምታት እንዴት ይታከማል?
በሌሎች በሽታዎች የተነሳ የሚመጣውን የራስምታት ለማከም፣ በመጀመሪያ የራስምታቱ መንስኤ የግድ መለየት ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የራስምታቱን ነጥሎ ማከም መሞከር ግን ስኬታማ ካለመሆኑም በላይ፣ መንስኤዎቹ ስር እንዲሰዱ ጊዜ ይሰጣል፡፡ የራስምታት በራሱ እንደ በሽታ ከሆነ ግን የተለያዩ ህክምናዎች የራስምታቱን ብቻ ለማጥፋት ይሰጣሉ፡፡
የሚግሬይን የራስምታትን ለማከም፣ እንደ የራስምታቱ ክብደት የተለያዩ መድሃኒቶች ይሰጣሉ፡፡ ቀለል ላለ የሚግሬይን የራስምታት፣ ያለ ሐኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ እንደ ፓራሲታሞል፣ አስፕሪን፣ ዳይክሎፊናክ፣ ኢንደሜታሲን፣ አይቡፕሮፊን የመሳሰሉ መድሃኒቶችን መውሰድ ይቻላል፡፡ ቢሆንም ህፃናት እና በአስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች አስፕሪን ባይወስዱ ይመረጣል፡፡ የጨጓራ በሽተኞችም ከፓራሲታሞል ውጪ ያሉትን የህመም ማስታገሻዎች ከመውሰዳቸው በፊት ሐኪማቸውን ማማከር ይገባቸዋል፡፡ የጉበትና የኩላሊት ህመምተኞችም የራስምታት መድሃኒቶችን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መጠቀም የለባቸውም፡፡
ከበድ ላለ ሚግሬይን እንደ ergotamine ያሉ መድሃኒቶች ተመራጭ ናቸው፡፡ የሚግሬይንን የራስምታት የሚቀሰቅሱ የተለያዩ ሁኔታዎች ለምሳሌ፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ፆም፣ አብረቅራቂ ነገሮችን መመልከት፣ አንዳንድ ሽታዎች፣ የሲጋራ ጭስ፣ አልኮል መውሰድ፣ ቸኮሌት፣ ቡና ወዘተ… ማስወገድ ህመሙ አስቀድሞ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ የዚህ ህመም ተጠቂ ህመሙን የሚቀስቅስበት ምን ሁኔታ ወይም ነገር እንደሆነ ለይቶ በማወቅ ቀስቃሹን ነገር ወይም ሁኔታ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡
ክላስተር የራስምታት ለማከም የተለያዩ ህክምናዎች አሉ፡፡
አንዴ የጀመረውን ህመም ለማስቆም መቶ በመቶ የሆነ የኦክስጅን ጋዝ ከ8-10 ሊትር በደቂቃ ለዚሁ በተዘጋጀ ማስክ አማካይነት ከ10-15 በመተንፈስ፣ ጎን ለጎንም የ(triptan) ወይም (ergot) ዝርያ መድሃኒቶች መውሰድ ፍቱን ነው፡፡ ይህን አይነቱን የራስምታት አስቀድሞ ለመከላከል የ(calcium blocker) ዝርያ መድሃኒቶችን መውሰድ ይቻላል፡፡
(tension headache)ን ለማከም፣ ለቀላል ሚግሬይን የተጠቀሱትን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ መድሃኒቶች መጠቀም ይቻላል፡፡
ከቀላሉ ጉንፋን እስከ ወባ እንዲሁም እስከ ጭንቅላት እጢ ያሉ በሽታዎች ምልክት ሊሆን፣ እንዲሁም በራሱ እንደ በሽታ ሊከሰት የሚችለው የራስምታት አፈጣጠርና ህክምና ይህንን ይመስላል፡፡ S
ሕልምና የኢትዮጵያ ፖለቲካ በተቃራኒው ይተረጎማል
Tuesday, May 21st, 2013ከኤፍሬም እሸቴ
የሰሞኑ ትልቁ አገርኛ ዜና (ቢያንስ በዳያስጶራው ዓይን) የመንግሥት ባለሥልጣናት በሙስና ምክንያት መያዝና መታሰር እንዲሁም የባሕር ዳሩ ሰላማዊ ሰዎች ግድያ ጉዳይ ነው። አገር ቤት የማይነበቡት ድረ ገጾችና የጡመራ መድረኮች (ብሎጎች)፣ የአካባቢ ሬዲዮኖችና ማኅበራዊ ድረ ገጾች (ለምሳሌ ፌስቡክና ትዊተር) የሚያወሩት ስለዚሁ ነው።
አጀንዳ አንድ
የባሕር ዳሩ ግድያ ከወንጀልነቱ በላይ ትልቅ መወያያ ሆኖ የሰነበተው የገዳዩ ማንነት ጉዳይ ነው። ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ አባል መሆኑ የተለያዩ መላምቶችን፣ ግምቶችን፣ ትርጉሞችን እያሰጠ ሁሉም በፈለገው መልክ እንዲተችበት ዕድል ሰጥቶ ሰንብቷል። የፖለቲካ ልዩነቶች ብቻ ሳይሆኑ የብሔረሰብ ማንነቶችም እየተነሡ “ገዳዩ ከዚህ ብሔረሰብ ነው፤ ከዚያ ብሔረሰብ ነው” በሚል ጥሩም መጥፎም አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። መንግሥትን እና መሠረቱን የሚደግፉት በአንድ በኩል፣ ተቃዋሚዎቹ እና በተለይም የዘር-ፖለቲካን አምርረን እንቃወማለን የሚሉት በሌላ በኩል የሐሳብ ጥይቶች ሲያስወነጭፉ ነበር።
ዝግ እና መተንፈሻ የሌለው ማኅበረሰብ እና ነጻ ማኅበረሰብ ተመሳሳይ አደጋዎችን የሚያስተናግድበት መንገድ እንዴት እንደሚራራቅ ጥሩ ማሳያ ሆኖልኛል። ዝግ እና መተንፈሻ የሌለው ማኅበረሰብ የሌለው ያልኩት ነጻ ሚዲያ የሌለበትን የኛን አገር መሆኑ ግልጽ ነው። ነጻ ማኅበረሰብ ያልኩት ነጻ ሚዲያዎች ያሉበትን እንደሆነው ሁሉ።
Christopher Jordan Dorner የተባለ የሎስ አንጀለስ ከተማ ፖሊስ እና የቀድሞ የጦር ሠራዊት ባልደረባ በሥራ ቦታው በገጠመው አለመግባባት ሰበብ አራት ሰዎችን ገድሎ ለሳምንት ያህል አካባቢውን ሲያሸብር ቆይቶ በመጨረሻ ራሱን እንዳጠፋ መቸም ሳትሰሙ አልቀራችሁም። ከጥር 26 – የካቲት 5/2005 ዓ.ም ድረስ አካባቢውን አሸብሮት ነበር። የታጠቀ ነው። ፖሊስ ብቻ ሳይሆን ወታደርም ነው። የሰለጠነ። በጠላት ላይ ማዞር ያለበትን ጠመንጃ ወደራሱ ዜጎች ሲያዞር እንዴት እንደሚዘገንን መገመት ይቻላል።
ግለሰቡ የሥራ ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ ተሰወረ። ሐሰሳ ተጀመረ። ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን ይሰጡ ነበር። ቀንም ሌሊትም ሲፈለግ ቆየና በሰዎች ጥቆማ ያለበት ተደረሰ። ከዚያም ራሱን አጠፋ። በቃ። ጉዳዩ በዚሁ አበቃ። ስለ ሰውየው ማንኛውንም ዓይነት ማብራሪያ ለሚፈልግ ሰው መረጃዎቹ በስፋት አሉ። ማነው? የት ተወለደ? አደገ? መቼ ወደ ጦሩ ተቀላቀለ? እንዴት ከዚያ ወጥቶ ፖሊስ ለመሆን በቃ? ከባልደረቦቹ ጋር ለምን ተጣላ? ለምን ወደዚህ ዓይነት ወንጀል ሊገባ ቻለ? ወዘተ።
ባሕር ዳርስ? ባሕር ዳር ላይ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ብዙ ሰዎችን ገደለ። ከዚያ … ውዥንብር። ግማሹ 12 ሰው ተገደለ ይላል፣ ሌላው ደግሞ 18 ያደርሰዋል። ሰውየው ማን ነው? መቼ ፖሊስ ሆነ? ለምን ወደ መግደሉ ሊገባ ቻለ? ግድያውን በአጭሩ ማስቆም አይቻልም ነበር ወይ?
ችግሩ ምንድር ነው? ሚዲያ የለም፤ የግል ጋዜጣና ቴሌቪዥን የለም፣ የመንግሥቱም ቢሆን ለዚህ ዓይነቱ ነገር ዝግ ነው። … ነጻ ሚዲያ ሲጠፋና ትክክለኛ መረጃ ሲታጣ በመካከል ምን ይነግሣል? ግምት፣ ውሸት፣ ሽብር፣ ጥርጣሬ። ቢያንስ በዳያስጶራው ሚዲያዎች እና በማኅበራዊ ድረ ገጾች የነበረው እንደዚያ ነው። (‘ዳያስጶራ ልማዱ ነው’ ካልተባለ በስተቀር)።
እንዲህ ዓይነቱ አደጋ ሲከሰት የመጀመሪያው እንዳልሆነ የሚናገሩ ሰዎች አጋጥመውኛል። ሌላም ቦታ የተከሰተ ከነበረ ሊቀጥል እንደማይችል መተማመኛ ማግኘት ይከብዳል። አዕምሯቸው የተቃወሰ መሣሪያ የያዙ ሰዎች መኖር የየትኛውም አገር ችግር ይመስለኛል። ችግሩ ተመሳሳይ ከሆነ መፍትሔውም ከሌላ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል ነው ማለት ነው። በባሕር ዳሩ ጉዳይ እንዳየኹት ግን ዜጎችም ይሁኑ የመንግሥት ሰዎች ነገሮቹን የተመለከቱበት አቅጣጫ ከተለመደው ከዚያው አሰልቺ የአገራችን የዘር-ፖለቲካ አንጻር ብቻ መሆኑ ያሳፍራል።
ለምሳሌ የብዙ ሰው ጥያቄ የ“ፌዴራል ፖሊስ” አባል ከሆነ፣ እነዚህ ፖሊሶች ደግሞ የሰውን ሰብዓዊ መብት በመግፈፋቸው እንጂ ሰላም በማስከበራቸው የሚታወቁ ካልሆነ፣ ግድያው ከተለመደው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አንጻር እንጂ ከወንጀልነቱ አንጻር የተሰጠው ግምት አናሳ ነበር። እንዲያውም ሆን ተብሎ የተፈጠረ የመንግሥት የማሳሳቻ ዘዴ ሆኖም ተተችቶበታል።
አጀንዳ ሁለት
በተመሳሳይ መልኩ የሰሞኑ ትልቅ አጀንዳ የሙስናው እና በሙስናው ምክንያት የተባረሩት ጎምቱ ባለሥልጣኖች ጉዳይ ነው። የባሕር ዳሩን ማስቀደሜ ከምንም ነገር በላይ ክቡሩን የሰው ሕይወትን መጥፋት የተመለከተው ዋነኛ በመሆኑ ነው። በተጨማሪም እንዲህ ዞር ያለበት “ቱቀማ” ሰው ተነሥቶ በየመንገዱ ሲገድል ቢያንስ በእኛ አገር የተለመደ ስላልሆነ ነው። (ቱቀማ (ኦሮምኛ)= ንክ (አማርኛ))።
ግንባራቸው የማይፈታው ብርሃን ኃይሉ በአቅም ማነሥ (የጉልበት ሥራ መሰለ አይደል?) ከሥልጣናቸው ሲባረሩ መልከ መልካሙ አቶ መላኩ ፈንታ (በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር)፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገብረ ዋሕድ ወልደ ጊዮርጊስና የባለሥልጣኑ ዋና ዓቃቤ ሕግ አቶ እሸቱ ወልደሰማያት በፀረ ሙስና ኮሚሽንና በብሔራዊ መረጃ ማዕከል ሰዎች መታሠራቸው ተነግሯል። በሙስና ምክንያት፤ ስኳሯ ላይ ተገኝተው ነው ተብሏል። በዝርዝር ምን እንደሆነና ምን እንደተደረገ የአደባባይ ምሥጢር ስለሆነ ደግሞ ማተቱ አንባቢን ማድከም፣ ቦታ ማበላሸት ነው። ጥያቄው እኛ ዜጎች ዜናውን እንዴት ነው የተቀበልነው የሚለው ላይ ነው።
በሙስና ምክንያት ተይዘው ከታሠሩት ከአቶ ታምራት ላይኔ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ መንግሥት በሙስና አሰርኳቸው የሚላቸውን ሰዎች የታሰሩበት ምክንያት በርግጥም ሙስና ነው ብሎ የሚቀበል ብዙ ሰው አይደለም። ታምራት ላይኔም ሆኑ ስዬ አብርሃና ቤተሰቦቻቸው ብሎም እነ መላኩ ፈንታ ሙስና ውስጥ አልገቡም ብሎ የሚከራከር እንደሌለው ሁሉ ዋነኛ የመታሰራቸው ሰበቡ ግን ሙስናው ነው የሚል አይገኝም። በሙስና መታሰር ቢኖር እነ እንትና መቅደም አልነበረባቸውም ተብሎ ስም መጥራት ሲጀመር በአሳሪዎችና በታሳሪዎቹ መካከል ልዩነት ይጠፋል።
በሙስና ሰበብ ከማሰር የደርጉ “የፍየል ወጠጤ” ዘፈን ይሻላል?
ለመናገር ከመፍራት ካልሆነ በስተቀር የኢሕአዴግ መንግሥት ተቃዋሚዎቹን የማስወገጃ ዘዴ ሕጋዊ የሚመስሉ ሕገወጥ ተግባሮች ናቸው። ለምሳሌ በሙስናና በአሸባሪነት ስም ወህኒ ማውረድ። ደርግ ምን ያደርግ ነበር ብንል የማይፈልጋቸውን ሰዎች “የፍየል ወጠጤ” የሚለውን ልብ ነቅናቂ ዘፈን አስቀድሞ ከዚያ በግልጽ ይገድል፤ ያስር ነበር። ሙስና የዘመናችን የፍየል ወጠጤ ናት ማለት ነው? ከሆነ አይቀር አንድኛውኑ የፍየል ወጠጤው ይሻላል። ከጀርባ ከመመታት እያወቁት ከፊት ለፊት መመታት።
“ኮንስፒረሲ ቲዮሪ” የሚወድ ባህል መፍጠር፣
እውነተኛው ምክንያት ሆኖ ለሰበቡ ግን ሌላ ነገር መፍጠር ቀስ በቀስ አዲስ ልማድ እየሆነ ነው። በሙስና ስም የፖለቲካ ልዩነትን ማስተንፈስ ሲለመድ ነገ በትክክሉ ሙስና የፈጸሙ ሰዎች ለወንጀላቸው ሐዘኔታ የሚሰማው ሰው እንዲያገኙ መንገዱ ይመቻችላቸዋል። በርግጥም ሙሰኞቹን ከፖለቲካ መብት ተከራካሪዎች ለይቶ መመልከት ይከብዳል።
አሸባሪ የሚባለውን ቃልና ሐሳብ በዚሁ አገባብ ልንመለከተው እንችላለን። የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው፣ መብታቸውን የጠየቁ ሰዎች ‘አሸባሪዎች” ሲባሉ ትክክለኞቹን ከአሸባሪው መለየት ከባድ ይሆናል። በዚህ መምታታት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች ምን ዓይነት መረዳት ይዘው እንደሚያድጉ ፈጣሪ ይወቀው።
ተኩላ ሳይመጣበት ለቀልድ “ኡኡኡ ድረሱልኝ፣ ተኩላ በጎቼን ፈጀ” ያለው እረኛ ታሪክ አይመጣባችሁም? ለቀልድ ያለው እውነት ሲሆን ረዳት ያጣው ልጅ ታሪክ። ዛሬ ሙሰኛ እና አሸባሪ የተባሉት ነጻ ሆነው እውነተኞቹ ሙሰኞችና አሸባሪዎች መያዝና ለፍርድ መቅረብ ሲጀምሩ ይኼ መንግሥት እንዴት ተአማኒነት ይኖረዋል? አልቅሶ ቢነግረንም አናምነውም ያኔ። በየራሳችን የኢሕአዴግ “ኮንስፒረሲ” እንደሆነ ስለምንገምት።
ለጥቂት ጥቅም ትልቁን አጥር መናድ
የፍየል ወጠጤው ይሻላል ስል የመግደል ጥሩ ኖሮት አይደለም። የደርጉ እንስሳዊ የጭካኔ በሽታ ከዚያው ዘመን ወደ ሌሎች ዘመኖች የማይተላለፍ ስለሆነ እንጂ። ሕግን የተንኮል ማከናወኛ ስናደርጋት ግን በሽታው በዚያ የማይቀር ተላላፊ እናደርገዋለን። በአገራችን ሕጋዊ ተቋማት ስም የሚፈጸሙ ተንኮሎች ተላላፊ በሽታ ይሆናሉ።
በግብጽ ሆስኒ ሙባረክ ወርደው መሐመድ ሙርሲ ቢመጡም የፖሊሱ ችካኔ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ጭካኔ ያልተሻሻለው ለምንድነው? ሕጋዊ ተቋማቱ ሕገወጥነትን ስለተለማመዱና የተላላፊው በሽታ ተጠቂዎች ስለሆኑ ነው። ኢሕአዴግ ጊዜያዊ ድል ለማግኘት ትልልቅ አጥሮችን መናድን ሕጋዊ አድርጎታል። ዛሬ የተናዱትን የሕግ፣ የባህልና የሥነ ምግባር አጥሮች ዳግም መገንባት ቀላል አይሆንም። በጥቂት ዓመታት እንደተናዱት ማደሱም እንዲሁ በጥቂት ዓመታት የሚሳካ ላይሆን ይችላል። … ነገ ያስፈራል።
የመንግሥት ርምጃዎች ትክክል መሆን አለመሆናቸውን ማን ባጣራልን?
ከዚህ ችግር ልንተርፍ የምንችለው እና መንግሥትም ቢሆን የሚናገረው ነገር በርግጥም እውነት እንዳለው ሊያጣራለት የሚችለው እውነታ-አንጣሪ (Fact-checker ለሚለው የሚለውን ነው የተረጎምኩት) ሚዲያው እና መያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ነበሩ። ከእነርሱ ጋር ደግሞ ዓይንና ናጫ፣ እሳትና ጭድ ሆነ። በደርግ ዘመን እንኳን ከመጥፋት የተረፉ መያዶች ከኢሕአዴግ ግን አልተረፉም። እነርሱን ባጠፋ መጠን ራሱን እየጎዳ መሆኑ ከቀን ቀን ግልጽ እየሆነ ነው። ስለ ሀገር እና ስለ መጪው ትውልድ ሲባል ኢሕአዴግ ያፈረሰውን መገንባት መጀመር አለበት። መንገዱንና ሕንጻውን መገንባት ብቻ አገር መገንባት አይሆንም። መንገዱና ሕንጻው ለኢትዮጵያዊው ይገነባለታል እንጂ እኛ ዜጎቹ ለመንገዱና ለሕንጻው አንኖርም። አለበለዚያ አዲስ ነገር በተከሰተ ቁጥር የራሳችንን መላ ምት እየሰጠን “ሕልምና የኛ አገር ፖለቲካ እንደፈቺው” ሆኖ ይቀራል።
ይቆየን፣ ያቆየን
የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ከወዲሁ ያስመዘገባቸው ድሎች – ግርማ ካሳ
Monday, May 20th, 2013ግርማ ካሳ
(muziky68@yahoo.com)
ሜይ 20 ቀን 2013
አገር ዉስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም፣ በአፍሪካ ሕብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አውጇል። ከግንቦት 15 እስከ 17 ባሉት ቀናት ደግሞ፣ ኢትዮጵያዉያን ጥቁር አልባሳት በመልበስ፣ አገዛዙ በሚያራምዳቸውን ጎጂ ተግባራት ላይ፣ ያላቸውን ተቃዉሞ እንዲገልጹ ጥሪ አስተላልፏል።
ፓርቲዉ በቅርቡ የተመሰረተ፣ ብዙ አገር አቀፍ መዋቅር ገና ያልዘረጋ፣ ተስፋ የሚሰጥና በወጣቶች የተሞላ ለጋ ፓርቲ ነዉ። ጥሪዉ ከቀረበ ገና ሶስት ሳምንት ብቻ እንደመሆኑም፣ ምን ያህል አስቀድሞ ሕዝቡን በማደራጀት አንጻር በቂ ዝግጅት እንደተደረገ ፣ ጥሪው በይፋ ለሕዝብ ከመተላለፉ በፊትም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር (እነርሱም ዝግጅት እንዲያደርጉ) ምን ያህል ዉይይት እንደተካሄደ አላውቅም። በመሆኑም በግንቦት 17 ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመተንበይ አስቸጋሪ ነዉ።
እንደዚያም ሆኖ ግን፣ ከወዲሁ በርካታ ድሎችን ተመዝግበዋል ባይ ነኝ። የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ ይሄን ጥሪ ሲያቀርቡ፣ ምን ያህል ድፍረትና ጀግንነት እንዳላቸው ለማረጋገጥ ችለዋል። ሊታሰሩ፣ ሊደበደቡ፣ ሊገደሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ። እነርሱ መካከል ያሉ፣ ብዙዎቹ ኢንጂነሮች፣ ጠበቃዎች ..ናቸው። የገዢው ፓርቲን ተቀላቅለው፣ የስርዓቱ ተጠቃሚዎች መሆን የሚችሉ ናቸው። ነገር ግን ኢትዮጵያንና ሕዝባቸውን አስቀድመዉ፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለዲሞክራሲና ለሕግ የበላይነት በመቆም፣ ከፊት በመቅደም፣ ትግል ምን ማለት እንደሆነ እያሳዩን ነዉ።
በዚህም ምክንያት፣ በፈታኝና ትእግስት አስጨራሽ ሁኔታ ዉስጥ ተኩኖም፣ አገር ቤት የሚደረገዉን የሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ መግለጫ ከማዉጣትና ገዢው ፓርቲን ከማውገዝ ያለፈ፣ አንድ ምእራፍ ወደፊት እንዲሄድ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አድርጓል። አንድ በሉ።
ለበርካታ አመታት የዳያስፖራዉ ትኩረት አዲስ አበባ ሳይሆን አስመራ ነበር። አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን ምንም እንደማይሰሩ፣ መስራት ቢፈልጉም መስራት እንደማይችሉ፣ አገር ቤት የሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል «ቅዠት» እንደሆነ ነበር የሚነገረን። ነገር ግን በቅርቡ በተለያዩ ሜዲያዎች እንዳነበብነው፣ እንደ ኢሕአፓ-ዴሞክራሲያዊና የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤት ያሉ አንጋፋ በዉጭ አገር ያሉ ድርጅቶች፣ የሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ጥሪ ያላቸውን ኢትዮጵያዊና ወቅታዊ አጋርነት ገልጸዋል። በተለያዩ የፓልቶክ ክፍሎች፣ በኢሳት፣ በራዲዮኖች፣ በድህር ገጾች የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ትልቅ ትኩረት ስቦ ውይይትን ጭሯል። ይሄ ሁሉ እንግዲህ የሚያሳየዉ ዳያስፖራው ትኩረቱን አገር ቤት ወደሚደረገው የሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንዲያዞር ማድረጉን ነዉ።
በዉጭ የሚገኘው ወገን ብዙ ሊረዳ፣ ብዙ ሊደግፍ፣ ትልቅም ሚና ሊጫወት የሚችል ነዉ። ይህ ኃይል አገር ቤት ካለው ኃይል ተነጥሎ፣ አገር ቤት ከሚደረገዉ ትግል እራሱን ለይቶ መቆየቱ ብዙ ጉዳት በትግሉ ላይ አምጥቷል። አገዛዙን በእጅጉ ጠቅሟል። በሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ምክንያት፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ለመደገፍ ፣ በዳያስፖራ የሚደረገዉን እንቅሳሴ ማየታችን በራሱ ትልቅ ድል ነው። ብዙዎቻችንን አስደስቶናል። በመካከላችን የነበረዉን መከፋፈል አስወግዶ ከዚህ በፊት በቅንጅት ጊዜ እንደነበረው፣ በአንድነት እንድንሰማራ የማድረግ ትልቅ ኃይል አለዉ። ሁለት በሉ።
በድርጅታዊ መዋቅርና በአባላት ብዛት ከሰማያዊ ፓርቲ እጅግ የላቁ እንደ አንድነት ፓርቲ ያሉ በአገር ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አሉ። እነዚህ ድርጅቶች ተመሳሳይ አላማ እንዳላቸው፣ በዚያም ረገድ ሁሉንም አስተባብረው፣ የተጠናና የተደራጀ የሰላማዊ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ለማድረግ እቅድ እንዳወጡ እንሰማለን። የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፣ በነዚህ ድርጅቶች ዉስጥ በእቅድና በጥናት ደረጃ የተቀመጡ እቅዶች ወደ ተግባራዊነት እንዲሄዱ የሚያበረታታና አሉታዊ አስተዋጾ የሚኖረው ሆኖ ነዉ ያገኘሁት። ሶስት በሉ።
የሰማያዊ ፓርቲን ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን አስከትሎ ገዢዉ ፓርቲ እጅግ በጣም በርካታ ወታደሮች አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳስገባ እየተዘገበ ነዉ። «ከሕዝብ ሊነሳብኝ የሚችለዉን ዉጥረት እንዴት አድርጌ ነዉ የማከሽፈው?» በሚል አገዛዙ ውጥረት ላይ ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ። እንግዲህ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፣ ከወዲሁ ለአገዛዙ ትልቅ መልእክት እንዲደርሰው እያደረገ ነዉ። መልእክቱም «ዝም ብለን አንቀመጥም። ለመብታችን፣ ለነጻነታችን እንሞታለን። ከአሁን በኋላ አንፈራችሁም» የሚል ነዉ። ይሄም በራሱ ትልቅ ዉጤት ነዉ። አራት በሉ።
ሁለት ነገር ብዬ ላቁም። የመጀመሪያዉ ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበዉ ጥሪ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ቢያቀርበዉም፣ ጉዳዩ ሁላችንምም የሚመለከት እንደሆነ ነው። ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት አለብን። በኢሜል፣ በስልክ፣ በኢንተርኔት፣ በቫይበር …ለምናውቃቸው በሙሉ ጥሪ እናስተላልፍ። ሰማያዊዎች ለመታሰር ተዘጋጅተዋል። እኛ ቢያንስ 5፣ 10፣ 20 አገር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዉያንን ጥቁር አልባሳት እንዲለብሱ ማበረታት ሊያቅተን አይገባም። እንረባረብ። «አይ እኔ የማደርገዉ ምን ለዉጥ አያመጣም» በጭራሽ አንበል። ግድ የለም ማድረግ የምንችላትን ትንሿን እናድርግ።
ሁለተኛው ነጥብ፣ ይሄ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የመጀመሪያዉ እንጂ የመጨረሻዉ እንደማይሆን ነዉ። ከአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ትምህርት ተወስዶ፣ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ አረና ትግራይ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ..የመሳሰሉ አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች በአንድ በኩል፣ እንደ ኢህአፓ-ዴ፣ የሽግግር ምክር ምክር ቤት፣ ሸንጎ ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የመሳሰሉ በሌላ በኩል ሆነው፣ ትግሉን በማቀናጀት፣ አገረ ሰፊ፣ ተከታታይ፣ የተቀናጀ፣ በዲፕሎማሲና በሕዝብ ግንኙነት የተደገፈ፣ የተጠና፣ ሰላማዊ የእምቢተኘት ዘመቻዎች መደረግ አለባቸው፤ ይደረጋሉምም። አብረን ተያይዘን እስከሰራን ድረስ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማሸነፋችን አይቀርም።
ሰላማዊ እንቅስቃሴ ማድረጉ የዜጎች ሙሉ አለም አቀፋዊ መብት ነዉ። አሁን ያለው ገዢው ፓርቲ የሚመጻደቅበት ግን እራሱ የማያካብረው ሕገ መንግስት ሁሉ ሳይቀር፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙሉ መብትን ይደነግጋል። በመሆኑም አንዳንድ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲን እንቅስቅሴ ሊያጣጥሉት ይችላሉ። ጸረ-ልማት፣ ሽብርተኘንት፣ ጽረ-ሕገ መንግስታዊ፣ አመጽ ቀስቃሽ ወዘተ የሚሉ ክሶችን ሊሰነዝሩ ይችላሉ። ነገር ግን ይሄን በማድረጋቸው የሚነገሩን ነገር ቢኖር ዘመናዊ ፖለቲካ ያልገባቸው፣ የኋላ ቀር የጫካ ፖለቲካ የሚያራምዱና በራሳቸው የማይተማመኑ መሆናቸውን ነዉ።
ተቃውሟችን በልማት ላይ አይደለም። ተቃዉሟችን በአባይ ግድብ ላይ አይደለም። ኢሕአዴግን እንደ ድርጅት አንቃወምም። የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ኢሕአዴግን የመደገፍ፣ በኢሕአዴግ ፖሊሲ ዙሪያ የመንቀሳቀስና የመደራጀት ሙሉ መብታቸው እንደሆነ እናምናለን። እንደዉም ኢሕአዴግን ከሚደግፉ ፣ ኢሕአዴግ በመልካም አስተዳደርና በደሞክራሲ ረገድ እንዲያሻሻል ከሚፈልጉ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል እንላለን። (እንደዉም እንደታዘብነዉ በርካታ የኢሕ፤አዴግ ደጋፊዎች በይፋ የሚደግፉትን ድርጅት እየጠየቁ ያሉበት ወቅት ነዉ)
ነገር ግን የአገዛዙ ባለስልጣናት ሌላዉን የመርገጥ፣ የማሰር፣ የማንገላታት ፣ የማፈናቀልና የመግደል ስልጣን የላቸውም። በዚህ ረግድ የሚፈጽሙትንም እኩይ ተግባራት «ያቁሙ» ብለን ነዉ ተቃዉሞ የምናሰማዉ።
የምንቃወመው፣ ለሕንዶችን ለአረቦች መሬት እየተሰጠ፣ ዜጎችንን ከዚህ ዘር ናቸው በሚል፣ ከቅያቸው በማፈናቀል የሚደረግን አሳዛኝና ጨካኝ የዘር ማጥራት ወንጀልን ነዉ።
የምንቃወመው፣ ድሃዉ ሕዝባችን፣ ታንቆ ከአመት ወደ አመት፣ ለአባይ ገንዘብ እንዲከፍል እየተደረገ፣ ቢሊዮን ዶላሮች ከአገር ቤት መዘረፋቸውን፣ በቱባ የአገዛዙ ጀነራሎችና ባለስልጣናት፣ በአደባባይ ኬት እንዳመጡት በማይታወቅ ገንዘብ የሚሰሩት ፎቆችንና የሚያንቀሳቀሱ ቢዝነሶችን ነዉ።
የምንቃወመው ዜጎች በአገራችን ብእር ስላነሱ ብቻ፣ ወይም «በሃይማኖት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ አይገባ» በማለታቸው፣ ሽብርተኞች እየተባሉ በግፍ መታሰራቸውን ነዉ።
እንግዲህ መብቴ ተረገጠ የሚል ኢትዮጵያዊ ካለ ፣ ይነሳ። መብቱንም ያስከብር።
የሚኒሶታውን ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ በማስመልከት በKfai Radio የተሰጡ የሕዝብ አስተያየቶች
Monday, May 20th, 2013የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ – (ከተክለሚካኤል አበበ)
Monday, May 20th, 2013እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት
1. እስኪ ደግሞ ትንሽ ልረብሽ። ጽሁፍ ተሸፋፍነው የተቀመጡ ሀሳቦችን ካልገለባበጠ፤ ያንቀላፉትንም ካልረበሸ አይመቸኝም።
2. አንዳንድ ጠንካራ ምሳሌያዊ አባባሎች በአንድ ሀይማኖት ውስጥ ቢነገሩም፤ መልእክታቸውን የሀይማኖት ድንበር አይወስነውም። ጠቀሜታቸውን ሳይንስና ስልጣኔም አይሽረውም። በአሸዋ ላይና በአለት ላይ ስለሚገነባ ቤት ጽናት ልዩነት ቅዱስ መጽሀፍ የተናገረውን መጥቀስ ይቻላል። ቃል በቃል አላስታውሰውም፤ ግን እምነታችን በጠንካራና በማይናወጽ አለት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ በፈተናና በጥርጣሬ፤ እንዲሁም በጽናት እጥረት እንዳይበረዝ ሲያስጠነቀቅ፤ መጽሀፍ ቅዱስ “በአለት ላይ የታነጸ ቤት በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት ንፋስና ወጀብ አያናወጠውም” አይነት ነገር ይላል።
3. ከዚያ የኛ “ትግል” ትዝ አለኝ። የኛ “ትግል”፤ ትግል ካለን፤ በአሸዋ ላይ የታነጸውን ቤት መስሎ ይታየኛል። በአህያ ቆዳ የተሰራ አይነት ቤት፤ ጅብ በጮኸ ቁጥር የሚንቀጠቀጥ። ዛሬ ስለዚያ ነው የምጽፈው። ስለዚያም ብቻም አይደለም፤ እኛንና ጠላቶቻችንን ስለሚለያዩን ወይም አንድ ስለሚያደርጉን ነገሮች እጠቅሳለሁ።
4. ለምሳሌ፤ ጠላቶቻችን ርኩስ መሆናቸው፤ እኛም የነሱን ርኩሰት ነቅሰን ማውጣታችን፤ እኛን ደርሶ ጻድቅ አያደርገንም። አንዳንዶች እነደዚያ የሆንን ሊመስላቸው ይችላል። ለምሳሌ ግንቦት ሰባት ወይንም መድረክ፤ ኢዴፓ ወይንም ኢህአፓ የኢህአዴግን ጉድ አጋለጡ ማለት እነዚህን ድርጅቶች በርግጠኝነት ከኢህአዴግ የተለዩ ያደርጋቸው ይሆናል እንጂ ያለቅድመ ሁኔታ የተሻሉ አያደርጋቸውም። ኢሳትም ለኛ ግሩም ሆነ ማለት፤ በርግጠኝነት ከኢቲቪ ይለየዋል እንጂ፤ ያለአንዳች ቅድመሁኔታ ከኢቲቪ የተሻለ ያደርገዋል ማለት አይደለም። (ይሄ፤ ለምሳሌ ያህል ነው እንጂ፤ ኢሳትንና ኢቲቪን አላወዳድራቸውም፤ ስለዚህ አንዳንዶቻችን ይቺን ሀረግ መዘን ወደ መደምደሚያ እንዳንከንፍ ወይም በኢሳት ላይ የተነሳሁ አይነት አድርገን እንዳንተረጉመው)። በአጠቃላይ፤ ከጠላቶቻችን የተሻልን ክፉዎች ልንሆን እንችላለን፤ ነገር ግን ተራችንን የምንጠብቅ መጥፎዎችም ልንሆን እንችላለን ነው ሁለተኛው ነጥቤ። እንጂ፤ የኢህአዴግን ክፋት ስላጋለጥንና ስለተቃወምን ብቻ የተሻልን ነን ማለት አይደለም። ባለፈው ሰሞን እንደቀልድ በወረወርኩት ጽሁፍ የመጣው ጣጣ ያንን ያሳያል። እኛም ከጠላቶቻችን የተሻልን ላንሆን እንደምንችል ይጠቁማል።
እንደማስታወሻ፡ ካለፈው የቀጠለ
5. ለማስታወስ ያህል፤ ያለፈው ጽሁፌ ሁለት ሀሳቦች ብቻ ናቸው ያሉት። አንደኛ፤ በህዝብ ዘንድ እየተወደደ እየታወቀ ተደማጭነት እያገኘ የመጣው ኢሳት የሚያደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፤ በህዝብ ዘንድ አሉታዊም አዎንታዊም ውጤት ስለሚያመጣ፤ ጥንቃቄ ያድርግ የሚል ነው። ለምሳሌ፤ ከስድስት ከተሞች ውስጥ በአምስቱ ላይ የአንድ ሀይማኖት ብቻ ተወካዮችን መጋበዝ ብልህነት የጎደለው አካሄድ ነው የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ፤ ከኢሳት ጊዜያዊ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅትም ባሻገር፤ ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን የምንመለከትበት ቋሚ መንገድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል የሚል ነው። ከዚያ ባሻገር ግን የመንግስትና ሀይማኖትን መለያየት በተመለከተ የቅንጦት የሚመስል ነገር ግን አስፈላጊ የሆነ ውይይት ለመጫር ነው ጽሁፉ ሙከራ ያደረገው።
6. የተሰጡትን ምላሾች ሁሉ ለማንበብ ግዜ አላገኘሁም፤ የተወሰኑትን ግን አለፍ አለፍ ብዬ ተመልክቻቸዋለሁ። አብዛኞቹ ስድቦች ናቸው። ብዙዎቹ አስተያየቶች ደግሞ አስፈግገውኛል። ከጨዋዎቹ ተቺዎቼ ውስጥ አባዛኞቹ ያተኮሩት “ይሄንን አደባባይ ይዘህ ባትወጣ ይሻል ነበር” የሚል ሲሆን፤ በጣም ጥቂት ጨዋዎች ደግሞ “እንዴት ኢሳትን ትነካለህ? ትደፍራለህስ?” የሚሉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። እንደትልቅ ድፍረት፤ ራስን ከገደል ጫፍ እንደመወርወር፤ ራስን እንደማጥፋትም የቆጠሩትም አሉ። አንዳንዶች ደግሞ ግጭት የተፈጠረ፤ “የከዳሁ” ሁሉ የመሰላቸው አሉ።
7. ካለፈው የፖለቲካ ልምዳችን እንደምናውቀው፤ ሰው ካልተቀየመ ወይንም ካላኮረፈ ወይንም ካልከዳ ራሱንና የራሴ የሚለውን ስለማይተች፤ የበሰሉ፤ የተማሩ፤ በዚህ በምእራቡ ዓለም ለረጅም ግዜ ኖረው የሀሳብን በነጻነትና ያለፍርሀት መግለጽ ፋይዳ ተረድተዋል የተባሉት ሁሉ ያልጠበቅኩትን ተግሳጽ ሰንዝረዋል። በእውነቱ አንድን ጽሁፍ ብቻ መሰረት አድርገን፤ እዚህ ሁሉ ስጋትና ተግሳጽ ውስጥ መግባታችን የሚያሳየው፤ “ጸረ-ኢህአዴጉም ጎራ (የኛ ጎራ ማለት ነው)፤ መንግስት በሚማቅቅበት፤ “ከመንጋው የተለየ ሀሳብን የማስተናገድ ባህል እጦት እንደሚሰቃይ ነው።” ይሄ አደገኛ ነው። እነሆ ቃና ቀይሬ እንደ ንጉስ ላስረዳ ነው።
የትችት ትችት ትችት
8. ባለፈው ሰሞን ወዳጃችን ልጅ ተከሌ ማለፊያ ግሩም ጽሁፍ አንደጻፈ ሰማን። ጽሁፉም ተነበበልን። አሰላሰልነውም። አንዳንድ ሰዎች ለጽሁፉና ለጸሀፊው የሰጡት ምላሽ አላስደሰተንም። ቢሆንም አልገረመንም። ያንዳንዶቹ የተጻፈም ያልተጻፈም ምላሽ ግን አሳስቦናል። የልጅ ተክሌን ሀሳብ ከመተቸትና ከመበለት ይልቅ፤ ልጅ ተክሌን ወደመንቀፍና ወደማጠየፍ አዘንብለዋል። የጽሁፉን ፍሬ ነገር ሳይሆን የጸሀፊው ቁመትና ውፍረት ወርድና ክብደት ላይ የሚወያይ መብዛቱ አጅግ አሳስቦናል። ሀሳቡን ተችተው አስተያየት ለመስጠት የፈቀዱትም ቢሆኑ፤ ያተኮሩት፤ “የራስ ተቋም በአደባባይ አይተችም፤ ለጠላት ደስ ይለዋል፤ ንፋስም ይገባልና” የሚል አይነት ስሜት ይጎላበታል። አንዳንዶች ከቶም የጸሀፊውን ነገር የተገነዘቡ አይመስልም።
9. ቀድሞ ነገር፤ ልጅ ተክሌ የአገራችንንና የህዝባችንን ጥቅም የሚነካ ጽፉህ ይጽፋል፤ አገራችንን የሚጎዳ መንገድ ይሄዳል ብለን አንሰጋም። ይሄ እምነታችን ጥንትም ነበረ፤ አሁንም አለ። በርግጥ ልጅ ተክሌ ብዙም ባልተለመደ መልኩ አፈሙዙን፤ ወደወገን/ወደራሱ ማዞሩ ለብዙዎች ግርታን ቢፈጥር አይደንቀንም። ይሁን እንጂ፤ አንደኛ ልጅ ተክሌ ይሄን ሲያደርጉ የመጀመሪያው አይደለም። ሁለተኛ፤ የኛ የሆነውንና በኛ ምድር ላይ የተተከለውን ልጅ ተክሌ ከሀሳቡ አልፈን እሱን መጠራጠራችን በጎ ሆኖ አላገኘነውም። ስህተትም ነው። ይሄ ጽኑ የተለየ ሀሳብን የመፍራት ደዌም ነው። እስከመቼ የተለየ ሀሳብን እንሸሻለን? እስከመቼስ በራሳችን ድጋፍና ሰልፍ ጫጫታ ተውጠን እንኖራለን የሚል ጥያቄም ፈጥሮብናል? አንዳንዴ ወጣ ብሎ ማየት ያሻል።
የሀሳብ ነውር የለውም፡ የድርጊት እንጂ
10. የተለየ ሀሳብን መፍራት የለብንም። መጋፈጥ እንጂ። ሰው ነፍስ ካወቀ፤ የሀሳብ ነውር የለውም። የሀሳብ ጸያፍም የለውም። የሀሳብ ወንጀልም የለውም። ስለማይናገረው እንጂ ማንስ በጭንቅላቱ የሚያስበውን፤ በልቡም የሚመኘውን እንደምን እናውቀዋለን? ማንም ሰው፤ እንወያይበት፤ እናስበበት፤ እናድግበትም ዘንድ፤ ስህተትም ከሆነ እንዲታረምና እንዳይደገምም ብሎ ባደባባይ በስሙ በጻፈው ጽሁፍ ሲሆን ሲሆን ሊሸለም እንጂ ሊጎሸም አይገባውም። በርግጥ ልጅ ተክሌ ሲጎሸምና ሲዘለዘል የኖረ ወዳጃችን ስለሆነ፤ በአመታት ትችትና ነቀፋ የደነደነው ቆዳው በዚህ ይሰነጠቃል ብለን ከቶም አንሰጋም። የሰዎቻችን ከተለመደው የተለየ ሀሳብን ለማስተናገድ የመፍራትና የመቅፈፍ ነገር ግን ረብሾናል።
11. ደግሞስ በዚህ በምእራብ የነጻነት አጥቢያ የምንኖር ሰዎች ስለምን ትችትን እንፈራለን። ስንት ነገርስ እንፍራ? ስንት ነገርስ ያሸብረን? ኤደን ባህረሰላጤንና ሳህል በረሀን፤ አባይንና ጎጀብን ተሻግረን ተሰደን፤ በንጽጽርም ቢሆን የተሻለ ነጻነት ካለበት ዓለም መጥተንም፤ የተለየ ሀሳብን የመፍራት ሰቀቀን ይከተለን? እንግዲያውስ እላችሁዋለሁ፤ ነጻነታችንና ዴሞክራሲያችን በአለት ላይ እንጂ በአሸዋ ላይ መገንባት እንደሌለበት ህዝባችን ሊያውቀው ይገባዋል። “ይሄን ሀሳብ አንሸራሽር፤ ይሄንን ሀሳብ ግን ከቶም አታንሳው” የሚል ማእቀብና ምክር፤ በአገራችን እንዲሰፍን የምንመኘው ዴሞክራሲና ነጻነት ጸር ነው። ይሄ እስክንድር የታሰረለት፤ ርእዮትም የታጎረችበት፤ ሲሳይም የተሰደደበት ራእይ አይደለም። ደግሞስ፤ ይሄንን የሚፈቅደውስ ማነው? ህሊናችን አይደለምን? ከህሊናችን በላይ የተሻለ ከልካይስ፤ ፈቃጅስ ከወዴት ይገኛል?
12. ለዚህ ነው እኛ ሰው ህሊና ይስጥህ ሲባል እንጂ ልቡና ይስጥህ ሲባል የማይረዳኝ። ህሊና ያለው ሰው ደግሞ ህሊናው የፈቀደውን እንዲናገር፤ ህሊናውን የደረሰበትን ግኝት እንዲመሰክር ልናበረታታው ይገባል እንጂ፤ ልናከላክለው አይገባም። ካልሆነም ደግሞ የጸሀፊውን ሰብእናውን ሳይሆን ሀሳቡን ልንመትረው፤ እይታውን ልንተቸው፤ አመለካከቱን ልንተረክከው እንችላለን። እንጂ የጸሀፊውን ሰብእና ለማጥቃትና ጸሀፊውን ትልቅ ሀጢያት እንደፈጸመ በማነጣጠር የምንናገረውም የምንጽፈውም እኛ የታገልንለትንና ለህዝባችን ልናወርሰው የምንምለውንና የኛን ህልም የሚያንጸባርቅ አይደለም።
የማይጠየቅ ተቋም፤ የማይተች እውቅና
13. ወዳጃችን ልጅ ተክሌ ከዚህ ቀደምም ብዙዎቻችን የምንሸሻቸውን ሀሳቦች ለመናገር የሚጀግን፤ ብዞዎቻችን የምናፍራቸውን ሀሳቦች ለመጻፍ የሚተጋ የስደት ወዳጃችን ነው። ባለፈው ጽሁፍ ያነሳውም ሀሳብ፤ ምንም የሚጣል የለበትም ብለን ባንመሰክርም፤ በራሱ የሚተማመንንና በአለት ላይ የተገነባ ዴሞክራሲን ለመገንባት የሚተጋን ቡድን የሚያስደነግጥ ነገር አላገኘንበትም። ያለበለዚያማ በሚጻፈውና በሚወራው ጠላታችን መደንገጡ፤ የሚናገሩና የሚጽፉትንም ወደእስር ማጋዙ ስህተት አይደለም ማለት ነው። እኛ መንግስትነትን አጥተን በተለዩ ሀሳቦች መንሸራሸር ይሄን ያህል ከበረገግን፤ የመንግስትነትን ስልጣን የያዘው አካል በተቺ ሀሳቦች መንሸራሸር ቢጨነቅና መንገደኛውን ሁሉ ቢያስር ምን ያስደንቃል?
14. በርግጥ፤ ወዳጃችን ልጅ ተክሌ በሰዎች ዘንድ ታምኖ የተነገረውን ምስጢር ያባከነ፤ ወይንም እሱ ለድርጅቶች ባለው ቀረቤታ ያገኘውን መረጃ የተጠቀመ ባሪያችን ቢሆን እኛም ይከፋን ነበር። አንለቀውምም። ለጥፋቱ እንቀጣው ነበር። ይሁን እንጂ ልጅ ተክሌ የተጠቀመው መረጃ ሁሉ አደባባይ በህዝብ ዘንድ በግልጽ ያለ እንጂ፤ የተተቸው ተቋም ጋር በሚሰራበት ግዜ ያገኘው መረጃ አይደለም። ደግሞስ የማይተች እውቅና፤ የማይጠየቅ ተቋም ለመመስረት ነው እንዴ የምንታገለው? እንግዲያውስ ያለፉትን አስር አመታት ብቻ ብንገመግም፤ ትልቁ የጎዳንና እንዳናንሰራራ ቀስፎ የያዘን ጥፋት የምንክባቸውን ለመተቸት፤ የምንቆልላቸውን ለመጠየቅ አለመድፈራችን፤ “ዝም በሉ፡ ጠላት እንዳይሰማ፡ በቃ ይሁንላቸው ይደረግላቸው” የሚለው የተለማማጭነትና የሰቀቀን ባህርይ ነው።
አደባባይ ወይስ ወደጓዳ?
15. በልጅ ተክሌ ላይ ከተሰነዘሩት ትችቶች መካከል፤ “ትችቱ ለምን በአደባባይ ሆነ? ውስጥ ለውስጥ አይሻልም ነበር ወይ” የሚሉት ጥያቄ-ተኮር ትችቶች መልካም እንደሆኑ ይሰማናል። የኛም ሀሳብ ይኸው ነው። ይሁን እንጂ፤ ያ አንድ መንገድ ነው። ብቸኛው መንገድ አይደለም። ልጅ ተክሌም የተከተለውን መንገድ ለመከተሉ ጥሩ ምክንያት ይኖረዋል። ልጅ ተክሌ እንዲህ ያለውን ትችት ይዞ ወደአምባ ሲወጣ፤ ግራ ቀኙን አላየም፤ በቅጡም አላሰላም ለማለት አንደፍርም። መጠየቅ ያለብንን በአደባባይ ባለመጠየቃችን፤ መናገር ያለብን በአደባባይ በግዜ ባለመናገራችን ምክንያት እነሆ ቅንጅት እንደብጉንጅ ውስጥ ውስጡን አብጦ፤ በመጨረሻ አይፈርጡ አፈራረጥ ፈረጠ። ከቅንጅት ቁስል እስካሁንም አላገገምንም። እንደልደቱ አያሌው ያሉ እስካሁንም ያልተካናቸውን ትንታግ ፖለቲከኞች አጣን። (በዚህ ሀሳብ ብቻ የምንበሳጭ እንኖራለን፤ ይሁን እንጂ ልጅ ተክሌ “ልደቱ ናፈቀኝ” የሚል ጽሁፍ እየጻፈ እንደሆነ ጠቁሞናልና ከዚህ ለሰላውም ትችት እንዘጋጅ)።
16. በመሰረቱ በአደባባይ የሚነሱና ውስጥ ለውስጥ የሚነገሩ ሀሳቦች ውጤታቸው አንድ አይደለም። በአደባባይ የሚነገር ነገር ትኩረት ይሰጠዋል። ሰዎች ይወያዩበታል። ተወቃሾችና ተከሳሾች ካሉም ለወደፊቱ ያርሙታል። ተጠያቂ አካልም ወደፊት እጋለጣለሁ ሲል አግባብ ካልሆነ ስራ ይታቀባል። ውስጥ ለውስጥ የሚደረጉ አስተያየቶችና እርማቶች ከስራ ላይ ይልቅ ወደ ቆሻሻ ቅርጫት እንደሚዶሉ የልጅ ተክሌ ምስክርነት አያሻንም። እንጂ፤ የጋዜጠኞቹ ትጋትና ፍጋት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በየአካባቢው የሚገኙ የኢሳት ደጋፊዎች አስተዳደራዊ ምሬትና ስሞታ ቢጻፍ፤ “ይሄ ድርጅት እስካሁንስ እንደምን ቆመ?” ያሰኛል። “ወደፊትስ ይቆማልን?” የሚለውም ጥያቄ የሰይጣን ጆሮ አይስማው በማለት ብቻ የሚጠፋ አይደለም። እንደ ኢሳት ያለ ህዝባዊና ተስፋ የተጣለበት ተቋም እንዲያድግ የአደባባይ ውይይት፤ የግንባር ትችት፤ የፊት ለፊት እርማት ያስፈልገዋል። የምንፈልገው ተቋም በአደይና በጸደይ (የሰዎች ስም ናቸው) ላይ የቆመ ሳይሆን በአለት ላይ የተተከለ መሆን ነው ያለበት። እስካሁንም ሰዎች መካብ እንጂ ድርጅቶች/ተቋማት መገንባት አልቻልንምና።
በአደባባይ የሚሰራ በአደባባይ ይጠየቃል
17. ደግሞስ ኢሳት በአደባባይ የሚሰራ የአደባባይ መገናኛ ብዙሀን እንጂ የህቡእ ጋዜጣ አይደለም። ሰለዚህ ኢሳት ለሚሰራው የአደባባይ ስራ በአደባባይ መጠየቅ አለበት። ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት “የእንወያይ፡” ዝግጅታቸው ላይ ወዳጃችን ፋሲል የኔዓለምና አፈቀወርቅ አግደው ያንጸባረቁትን ሀሳብ በአደባባይ እንጂ በውስጥ ተቹ ማለት ስህተት ነው። ምክንያቱም እነሱ ስህተት ቢሆንም ባይሆንም ሀሳባቸውን በአደባባይ የማንጸባረቅ እድል ሲያገኙ፤ የነሱን ሀሳብ የሚቃወመው ሰው ግን በውስጣዊ አስተያየት ብቻ መወሰኑ፤ የነፋሲልን ሀሳብ የሰሙት ሰዎች፤ የተለየውን ሀሳብ እንዳያዳምጡ እድል መንፈግ ነው። ይሄ ኢሳት የቆመለት ኢሳት የቆመበትም መሰረት አይደለም።
18. የሰማያዊ ፓርቲ በመጪው የአፍሪካ አንድነት/ህብረት 50ኛ አመት ምስረታ በዓል ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል። ከአገራችን ያላግባብ የተነቀልን ተቃዋሚዎች ነን የምንል ሰዎችም ድርጅቶችም፤ እንዲህ ያለውን ሰልፍ፤ ጠሪዎቹ ለምንም ዓላማ ይጥሩት “በርቱ ግፉበት፤ ብቻ እንዲህ ብታደርጉት መልካም ነው፤ ይሄንንም ብታክሉበት ሸጋ ነው” ማለት ነው ያለብን። እንጂ ዓላማቸውን ሙሉ በሙሉ ማራከስ፤ አግባብ አይደለም። ልጅ ፋሲል ግን የሰዎቹ የሰልፍ ጥሪ ሀቀኛ መሆኑን እንደሚጠራጠርና እንዲያውም ትኩረት ለማግኘት ያደረጉት አይነት ጥሪ እንደሆነ ነው የተናገረው። ያ ብቻም አይደለም፤ ይሄ አይነቱ ሰልፍ ቢደረግም እንኳን፤ ስርአቱን በምእራባዊያን ዘንድ ሰልፍና ተቃውሞ ፈቃጅ ሊያስመስለወም ይችላል የሚል ፍራቻ አንጸባርቋል። በርግጥ ልጅ ፋሲል ሀሳቡን የሰጠው በግሉ እንደሆነ ቢናገርም፤ እሱ የኢሳት ዋና ማኔጂንግ ኤዲተር እንደመሆኑ መጠን አንድን ነገር ተናግሮ በግሌ ነው የተናገርኩት በማለት ብቻ ሊያመልጥ፤ ኢሳትንም ነጻ ሊያደርገው አይችልም።
19. በሀላፊነት ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ ይሄንን በግሌ ነው ያልኩት የድርጅቱ አቋም አይደለም የሚል ብልሀት ይጠቀማሉ። ልጅ ፋሲል በአስተያየቱ ላይ ከዚህ ቀደም ኢሳት የሰራቸውን ተመሳሳይ የሰልፍ ጥሪ ዘገባዎች እንደምሳሌ አቅርቧል። ከተቀመጠበት የሀላፊነት ወንበር አንጻርም የሚሰነዝረው እያንዳንዱ ሀሳብ የኢሳት ሊመስል፤ ሊሆንም እንደሚችል መረዳት አለበት። እንዲህ ያለውን በአደባባይ የተነገረ ሀሳብ መተቸት ያለብን፤ ኢሳት አንዳንዴ ፈንገጥ ያለ ሀሳብ አይመቸውም እንጂ ሲሆን ሲሆን በራሱ በኢሳት ላይ፤ ያለበለዚያ ግን በተገኘው መድረክ ነው። የለም እንቶኔን አትንኩ የሚለው አስተያየት፤ ለራሱ ለእንቶኔም አይበጅም።
ለነገሩ የኛ ችግር፡
20. ለነገሩ በስደት የምንገኝ ድርጅቶችና ተቃዋሚ ግለሰቦች፤ በአገር ቤት የኛን ስደትና ሚና የሚቀንስ፤ የኛን መኖር ምክንያት የሚያሳጣ እንቅስቃሴ የሚጀምር ሲመስለን፤ ያንን እንቅስቃሴ ለማጣጣልና ለማራከስ እንፈጥናለን። ይሄ እኛም በስደት ወደኬንያ ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ፤ ላለፉት 12 አመታት በኢህአፓም በመኢሶንም፤ በቅርቡ ደግሞ በነግንቦት ሰባትም በነከበደም በነገመቹም ላይ ያስተዋልነው በሽታ ነው። ልክ የዛሬ አስራሁለት አመት ተሰደን ወደናይሮቢ ስንገባ የተቀበሉን ደግ ድርጅቶች ከነገሩንና እስካሁንም ከትውስታችን ካልወጣው ነጥብ አንዱና ዋንኛው “አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች መኖር፤ በምእራባዊያን ዘንድ፤ አገር ቤት ዴሞክራሲ ያለ ያስመስላል” የሚል ነጥብ ነው። እነሆ ታሪክ ራሱን እንዳይደግምና፤ እኛ ከአመታት በፊት እንከሰሰስበት የነበርነውን፤ ማለትም የአገርቤቱ እንዲህ ነው የሚለውን ክስ፤ እኛም በተራችን እንዳንደግም መጠንቀቅ አለብን። ከፖለቲካ ወንጀሎች ሁሉ የከፋው ሌሎችን የከሰስንበትን ጥፋት ወይም በሌሎች በስህተት የተከሰስንበትን ጥፋት እኛ ስንፈጽም ነው።
21. ይቀጥላል።
እኛው ነን፤ ግንቦት ልደታ፤ 2005፤ ተረንቶ፤ ከናዳ
በላተኛው አባ-መላ
Monday, May 20th, 2013የፓልቷኩ አባ-መላ ሰሞኑን ገኗል። መግነኑ አልከፋኝም … ይግነን … ለሁሉም ጊዜ አለውና። ግን አባ-መላን ብዙ ጊዜ አዳምጨዋለሁና የአባ-መላን ነገር መዳሰስ ፈለኩ። ሰሞኑን አባ-መላ ገዢውን ፓርቲ መተቸት ጀምሯል። ይህንን የሰሙ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በጣም ፈንጥዘዋል ፡ እኔ አልፈነጠዝኩም። ለምን?
አባ-መላ የሚናገረውን ነገር በየሳምንቱ ፡ አንዳንዴ አልፎ አልፎም ቢሆን ፡ አዳምጨዋለሁ። አባ-መላ የሚያረገውን የሚያረግው ለአንድ አበይት ምክንያት ብቻ ነው፦ የግል ጥቅም። አባ-መላ ሌላ ንዑስ ምክንያት የለውም። የሚያደርገው ፡ የሚናገረው ፡ የሚተነፍሰው ፡ የሚስቀው ፡ የሚያለቅሰው … ወዘተ … ለግል ጥቅሙ ነው (ለግል ጥቅሙ መቆሙ መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም ፡ ያ ምርጫው ነው)።
በ2008 እ.አ.አ. አባ-መላ ክፍል ውስጥ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው (“addis_ababa_1”? በሚል መጠሪያ ስም ሚሳተፍ) ክፍሉ ውስጥ በተነሳ ቅራኔ ምክንያት የክፍሉን ሚስጥር በተቃዋሚ ክፍሎች ውስጥ ገብቶ ሲናገር ሰምቻለው። ከተናገረው ሚስጥር አንዱ ፡ ቃል በቃል ባላስታውስም ፡ አባ-መላ ከሚድሯክ ወይም ከሼህ መሃመድ አልሙዲ በአመት $50,000 ዶላር እንደሚከፈለው ነው። ይሄ ነገር የአባ-መላን ባህሪ እና የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ትኩሳት ለመረዳት ወሳኝ መረጃ ሆኖ አገኝቼዋለሁ።
አባ-መላ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከሚድሯክ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። የሚድሯክ ጥቅም ሲከበር ፡ አባ-መላ ለኢህአዴግ እስክስታ ይወርዳል። የድርጅቱ ጥቅም ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስል ፡ አባ-መላ ደረቱን ይመታል።
አባ-መላ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆኖ አያቅም። አባ-መላ የሚድሯክን ገጽታ የሚያሽሞነሙን ፡ የደርግ ስርዓት ያፈራው ፡ አንደበተ ምላጭ ፡ የሚያደርገውን የሚያቅ ፡ ፕሮፓጋንዲስት ነው።
ታዲያ ምነው ሰሞኑን የፓልቷክ ተቃዋሚ ክፍሎች ባዶ ሆነው የሲቪሊቲ ክፍል ሞልቶ የፈሰሰው? ተቃዋሚ ባካችሁን በአባ-መላ አትበሉ። አባ-መላ ሚያደረገው ሁሉ ለአገራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙና ለሚያገለግለው ድርጅት ጥቅም ብቻ ብሎ መሆኑን እንገንዘብ።
ሚድሯክ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የከፈተና ፡ አያሌ ካፒታል ያፈሰሰ ድርጅት በመሆኑ ድርጅታዊ ገጽታውንና ጥቅሙን መንከባከቡ ተገቢና የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሚድሯክ እና በኢህአዴግ መካከል ሆነን ልንፈጭ ነውና ፡ በአባ-መላ የፓለቲካ ስልት እንዳንበላ ጠንቀቅ እንበል።
አባ-መላንም ሆነ ሌሎች ገዢው ፓርቲን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ሰዎችን ተስገብግበን ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጨመር የለብንም። በጊዜ ውስጥ ሊፈተኑ ፡ አመኔታችንን ቀስበቀስ ሊያገኙ ይገባል እንጂ ተንሰፍስፈን መርዝ ይሁን መድሃኒት እንደያዙ ሳናቅ አንቀበላቸው።
ወቅቱ የህወሃት/ኢህአዴግ መጨረሻ ወቅት ነውና የሚደናበሩትን የገዢውን ፓርቲ በላተኞች ለጥቅማችን እንጠቀምባቸው እንጂ እነሱ አይጠቀሙበን።
_ _ _ _ _ _
ጸሃፊውን ለማበረታታት ፡ ለመውቀስና ለማስፈራራት በዚህ ይጻፉ፦ yared_to_the_point@yahoo.com
Hiber Radio: ኢትዮጵያ በአፍሪካ የቡና ላኪዎች ሰንጠረዥ የነበራት ደረጃን ተነጠቀች
Monday, May 20th, 2013<<አቶ መለስ አንገታቸውን የደፉበት ቀን ቢያንስ ድምጻችንን ያሰማንበት ቀን ነው።ብዙ ሰዎች በየዓመቱ ሊከበር ይገባል ይላሉ።በስርዓቱ ውስጥ የሚታየው የስልጣን ሽኩቻ ተጠናክሮ ይቀጥላል።አውራው አምባገነን ከሞቱ በሁዋላ አንዱ ገኖ ለመውጣት የሚያደርገው ነው።ሁሉም ቦታው ለኔ ይገባል በሚል ግብ ግባቸው አንዱ አንዱን መክሰሱ አንደኛው ወገን በአሸናፊነት እስኪወጣ ቀጣይ ነው። ወደፊትም አንዱ አንዱን ሲያስር አንዱ ሌላውን ሲከስ እናያለን ።ስርዓቱ ደካማ ነው።የምናየውም የጥንካሬ ምልክት አይደለም...>> ጋዜጠኛ አበበ ገላው አቶ መለስን አንገት ያስደፋበትን የተቃውሞ ድምጹ አንደኛ ዓመትን አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ
<< አማራን ለማጥፋት የተጀመረው አሁን በጉራ ፈርዳና በቤንሻንጉል ብቻ አይደለም ።በ1993 ዓመተ ምህረት 15 ሺህ አማራዎች ከወለጋ ተፈናቅለዋል። አማራ ራሱን መከላከል አለበት እሾህን በእሾህ እሳትን በእሳት ነው...>>
አቶ ተክሌ የሻው የሞረሽ ወገኔ ሊቀ መንበር ለህብር ከሰጡት የመጀመሪያ ክፍል ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)
የድምጻችን ይሰማ ጉባዔ በአትላንታ (ቆይታ ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር)
ሌሎች ቃለ መጠይቆችም አሉን
ዜናዎቻችን
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የቡና ላኪዎች ሰንጠረዥ የነበራት ደረጃን ተነጠቀች
በቬጋስ ለአባይ ቦንድ ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው የታሰበውን ያህል ባለመሰብሰቡ በስርዓቱ ሰዎች ላይ ቅሬታ ፈጠረ
የሎስ አንጀለሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቆንስላ ተወካይ ሙስናን መቆጣጠር አልቻልንም ማለታቸው ተሰማ
በቬጋስ ኢትዮጵያዊውን የታክሲ አሽከርካሪ ተኩሳ የገደለችው የቀድሞ የአሜሪካ ወታደር ተፈረደባት
በሙስና ክስ የተያዙት ባለስልጣንያለመከሰስ መበቴ ተጥሷል ሲሉ ተናገሩ
የወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተመንግስት አልወጣም ማለትን ዜና የዘገበው ጋዜጠኛ መረጃውን እንዲገልጽ ተጠየቀ
በኢትዮ ኬኔያ ድንበር ላይ ውጥረቱ አይሏል ታጣቂዎች 3ሰዎችን ገደሉ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን
ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸነፈ
Monday, May 20th, 2013ከይርጋ አበበ
ትናንት በአሥር ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽንስ ዋንጫ ጨዋታ የኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የግብጹን ኢ.ኤን. ፒ.ፒ. አይ ( Enginering and Petrolium Processing Industry) ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሉን አመቻቸ።
ከሁለት ሳምንት በፊት በግብጹ ኃያል ክለብ ዛማሌክ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባገባ በሚል ሕግ ከአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የተሰናበተው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሌላኛው የአህጉራዊ ውድድር የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሌላውን የግብጹን ክለብ በሜዳውና በደጋፊዎቹ ፊት ሁለት ለባዶ በማሸነፍ በዛማሌክ የደረሰበትን የውጤት ማጣት ፀፀት መመለስ ችሏል።
ጨዋታው በተጀመረ በአምስተኛው ደቂቃ ሽመልስ በቀለ ከያሬድ ዝናቡ የተሻገረችለትን ኳስ ከኢ.ኤን.ፒ. ፒ.አይ ተከላካዮች ሾልኮ በመግባት የጊዮርጊሶችን የመጀመሪያ ግብ አስቆጠረ። ሽመልስ ያስቆጠራት ግብ ባለፉት አራት ተከታታይ የክለቡ ጨዋታዎች ሦስተኛ ግቡ ሆና ተመዝግባለታለች። ትንሹ ልጅ ግብ ከማስቆጠሩም በላይ በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ ነበር ያመሸው።
ከዚች ግብ መቆጠር በኋላ ይበልጥ ተጭነው የተጫወቱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በተጋጣሚዎቻቸው የግብ ክልል በተደጋጋሚ ሲመላለሱ ቢታዩም በ26ኛው ደቂቃ ተከላካዩ አበባው ቡጣቆ ሁለተኛዋን ግብ እስካስቆጠረበት ደቂቃ ድረስ ኳስና መረብ ማገናኘት አልቻሉም ነበር። ወጣቱ አጥቂ ዮናታን ብርሃኔ ከማዕዘን ያሻገረለትን ኳስ ከአስራ ስምንት ክልል ውጪ ወደ ግቡ መስመር አክርሮ በመምታት አበባው ቡጣቆ ሁለተኛዋንና የጨዋታውን የመጨረሻ ግብ ማስቆጠር ቻለ።
ሁለት ወጣት የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ በስታዲየም የጋብቻ ሥነ-ሥርዓታቸውን በመፈፀም ለክለቡ ያላቸውን ፍቅር በገለጹበት ጨዋታ፣ ፈረሰኞቹ ብዙ ግብ መሆን የሚችሉ ኳሶችን ሲያመክኑ አምሽተዋል። በተለይ ሁለተኛዋ ግብ ከተቆጠረች ሦስት ደቂቃ በኋላ አማካዩ ዊሊያምስ አክርሮ የመታትና የኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አዩ ግብ ጠባቂ የመለሰበት ኳስ ተመልካቾችን ያስቆጨች ነበረች፡፡
ከዕረፍት በኋላ ተዳክመው ያመሹት ኢትዮጵያውያኑ በግብጻውያን አቻዎቻቸው የጨዋታ ብልጫ የተወሠደባቸው ሲሆን እንግዳው ቡድንም ሁለት ያለቀላቸው የግብ ዕድሎችን ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል።
ከሰባት ዓመት በፊት ሁለቱ ክለቦች በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተገናኝተው ካይሮ ላይ ዜሮ ለዜሮ ሲለያዩ በአዲስ አበባ ቢኒያም አሰፋ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋ ይታወሳል።
የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ የመልስ ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኋላ በግብጿ ዋና ከተማ ካይሮ ላይ ይደረጋል።
የዘንድሮውን የአውሮፓ እግርኳስን በዝውውር ሊያደምቁ የሚችሉ 9 ተጫዋቾች
Sunday, May 19th, 2013
ከይርጋ አበበ
የአውሮፓ ሊጎች የውስጥ ውድድሮች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከሚጠበቁት ታላቅ የእግር ኳስ ዜናዎች መካከል ክለቦች የሚያደርጉት የተጫዋቾች ዝውውር አንዱ ነው። ውጤት ፊቱን ያዞረባቸው ታሪካቸውን ለመቀየር ውጤት እና እድል አብራቸው የከረመች ደግሞ ክብራቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ክለባችንን እና ኪሳችንን ይመጥናሉ ያሏቸውን ተጫዋቾች ወደ ክለባቸው ለማዘዋወር ይንቀሳቀሳሉ። ለዛሬ ርዕሰ ጉዳያችን ምንጭ የሆኑን የእንግሊዞቹ ዘሰን፣ ዘኢንዲፔንደንት፣ ቢቢሲ እና የስፔኑ አስ ጋዜጦች የዝውውር መስኮቱን ሊያደምቁ ይችላሉ ያሏቸውን ተጫዋቾች ያስነበቡ ሲሆን እኛም ለአንባቢያን በሚመች መልኩ አዘጋጅተንላችኋል።
1. ዋይኒ ማርክ ሩኒ
እንግሊዛዊው አጥቂ በክለቡ እያሳለፈ ያለውን ሁኔታ ያልወደደው ሲሆን ከቀድሞው አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር የፈጠረው አለመግባባት ወደ ውጪ እንዲመለከት ያደርገዋል ተብሎ ይታሰባል። የዋዛን ሁኔታ በቅርብ ርቀት የሚከታተሉት የፈረንሳይ ሻምፒዮኖቹ ፓሪሴንት ጄርሜኖዎች እንግሊዛዊውን ወደ ክለባቸው ወስደው ከዝላታን ኢብራሞቪች ጋር ለማጣመር ፍላጎታቸውን መደበቅ ተስኗቸው ካሁኑ የማንቸስተርን በር ማንኳኳት ጀምረዋል። ሌሎቹ የልጁ ፈላጊ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ስፔናውያኑ ግዙፎቹ ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ ናቸው።
2.ኔይማር
ብራዚላዊው ወጣት ከባርሴሎና ጋር ቅድመ ስምምነት ላይ ደርሷል ቢባልም ሌላኛው የስፔን ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ የተጫዋቹ ፈላጊ መሆኑን በመግለፅ ወደ ጨረታው ገብቷል። እንደ ስፔኑ አስ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ የፍሎሬንቲኖ ፔሬዙ ክለብ ኔይማርን ከባላንጣቸው እጅ ላይ በመንጠቅ ለብራዚሉ ክለብ ለዝውውር የሰባ ሚሊዮን ፓውንድ ቼክ ይዘው መፈተን ጀምረዋል። ኔይማር የማድሪድን ጥያቄ ተቀብሎ ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው የሚሄድ ከሆነ ከሀገሩ ልጆች ካካ እና ማርሴሎ ደማቅ አቀባበል እንደሚጠብቀው ተጫዋቾቹ በመናገር ላይ ናቸው። የብራዚላዊው ለማድሪድ መፈረም ማድሪድ በመሐል ሜዳ ላይ የኳስ ፈጣሪ ተጫዋች እጥረቱን ይቀርፍለታል ተብሎ ይታሰባል።
3.ጃክ ዌልሸር
4.ካሪም ቤንዜማ
አሌክስ ፈርጉሰንን ተክተው ወደ ኦልድትራፎርድ የተዘዋወሩት ስኮትላንዳዊው ዴቪድ ሞይስ በቀጣዩ የውድድር ዓመት በክለባቸው ሊመለከቱት የሚፈልጉት ተጫዋች ቢኖር በሳንቲያጎ ቤርናባው ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳነውን ካሪም ቤንዜማ ነው። ይህንን ፈረንሳያዊ ወደ ማንቸስተር አምጥተው የእግር ኳስ ህይወቱን ሊታደጉለት ይፈልጋሉ። ለስፔኑ ክለብ የ30ሚሊዮን ፓውንድ ቼክ ይዘው የቀረቡት ሞይስ ቤንዜማን ወደ ማንቸስተር ማዘዋወር ከቻሉ አስፈሪ የአጥቂ መስመር መገንባት እንደሚችሉ ዘኢንዲፔንደንት በዘገባው ጠቅሷል። ዘገባው የካሪም ዝውውር የዝውውር ገበያውን ያደምቃል ያስባለውም የልጁ ብቃት መሆኑን ጨምሮ አመልክቷል።
5.ማሩዋን ፌይላኒ
ፌይላኒን በኤቨርተን ጠንቅቀው የሚያቁት ዴቪድ ሞይስ ወደ ኦልድትራፎርድ አብሯቸው እንዲጓዝ ይፈልጋሉ። ላለፉት ጥቂት ዓመታት ማንቸስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን ሲገናኙ በቀያይ ሰይጣኖቹ ላይ የበላይነቱን ሲወስድ የነበረው ቤልጄማዊ ጉልበተኛ የቀድሞ አሰልጣኙን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ላንክሻዬር ዝውውር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የግሌዘር ቤተሰቦች ቤልጄማዊውን ሁለገብ ተጫዋች ወደ ክለባቸው ለማዘዋወር የ24 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ መፈፀም እንዳለባቸው የተነገራቸው ሲሆን፤ ዴቪድ ሞይስም ግድ የለም በእኔ ይሁንባችሁ ማሩዋንን ለማግኘት የፈለገውን መስዋዕትነት መክፈል አለብን ሲሉ ለአዲሶቹ ቀጣሪዎቻቸው ተናግረዋል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል።
6.ሌይተን ቤይንስ
የቀድሞው የዊጋን አትሌቲክ የግራ መስመር ተከላካይ ላለፉት ሁለት ዓመታት የፈርጉሰንን ትኩረት መሳብ የቻለ ተጫዋች ነበር። በማጥቃት ላይ የተመሰረተ መከላከልን የሚመርጠው እንግሊዛዊ በአርሴናል፣ ቼልሲ፣ ባየር ሙኒክ እና ባርሴሎና ቢፈለግም የቀድሞ አሠልጣኙን ተከትሎ ቀዩን ማሊያ ይለብሳል የሚለው ግምት የበዛ ሆኗል። የ15 ሚሊዮን ፓውንድ የወጣለት ቢሆንም እድሜው እንደሚፈልገው እንዳይጫወት ያደረገውን ፓትሪስ ኢቭራን ለመተካት ብቸኛው ተጫዋች መሆኑን የተረዱት የማን ዩናይትድ ኃላፊዎች የገንዘቡን ነገር ተውት ብቻ ልጁን ስጡን በማለት የመርሲሳይዱን ክለብ መወትወት ጀምረዋል።
7. ክርስቲያን ኤሪክሰን
ቤልጂየማዊው የ21 ዓመት ወጣት አጥቂ በሊቨርፑል በጥብቅ ይፈለጋል። ወጣቱ ቤልጂየማዊ ግን የሀገሩ ልጆች በብዛት የሚገኙበትን ፕሪሚየር ሊግ ችላ ብሎ ወደ ቡንደስሊጋው መዘዋወርን መርጧል። ከውድድር ዓመቱ መጠናቀቅ በኋላ ፖላንዳዊውን ግብ አዳኝ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ የማጣት ስጋት የተጋረጠባቸው ቦሩሲያ ዶርትመንዶች የክርስቲያን ኤሪክሰን ማረፊያ ለመሆን ተቃርበዋል። ማሪዮ ጉትዝን ለባባሪያኑ ባየር ሙኒክ አሳልፈው የሰጡትና ሌዋንዶውስኪንም ላለማጣታቸው ዋስትና የሌላቸው ጀርመናውያኑ ኤሪክሰንን ከአያክስ አምስተርዳም ለመግዛት ከሊቨርፑል ከባድ ፈተና ቢጠብቃቸውም የልጁ ምርጫ በመሆናቸው የዝውውር መስኮቱ እንደተከፈተ ወደ ክለባቸው ያዘዋውሩታል ተብሎ ይጠበቃል።
8. ፊል ጃግዬልካ
በአርሴናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር በጥብቅ የሚፈለገው የ30 ዓመቱ ጃግዬልካ ዴቪድ ሞይስን ተከትሎ ከመርሲሳይዱ ክለብ የሚለቅ ተጫዋች ይሆናል ሲል ዘሰን ጋዜጣ አስነብቧል። የአስር ሚሊዮን ዋጋ የተቆረጠለት ቢሆንም ሪዮ ፈርዲናንድን የሚያጣው እና የኒማኒያ ቪዲችን የተሟላ አገልግሎት ማግኘት የማይችለው ማንቸስተር ዩናይትድ የሰላሳ ዓመቱን ተከላካይ ለማዘዋወር ፍላጎቱን በአዲሱ አሰልጣኙ በኩል ገልጿል። እንግሊዛዊው የኤቨርተን ሁለተኛ አምበል ወደ ዩናይትድ የሚያደርገው ዝውውር የተጫዋቾችን የዝውውር ገበያ ከሚያደምቁ ተጫዋቾች አንዱ ይሆናል ሲል ጋዜጣው ጨምሮ ገልጿል።
9. ጋሪ ሁፐር
በሴልቲክ ስኬታማ የውድድር ዘመን ያሳለፈውን የ25 ዓመት ወጣት ለማግኘት ከፕሪሚየር ሊጉ የወረዱት የኪው ፒ አር አሰልጣኝ ሃሪ ሬድናፕ ፍላጎት እንዳላቸው ዘኢንዲፔንደንት ገልጿል። የገንዘብ ችግር የሌለበት ኪው ፒ አር የውል ዘመኑ ሊጠናቀቅ የ6 ወር እድሜ ብቻ የሚቀረውን አጥቂ ለማዘዋወር 2ነጥብ 4 ሚሊዮን ፓውንድ የመደቡ ሲሆን ተጫዋቹን በተጠቀሰው ዋጋ አዘዋውረው በሻምፒዮን ሺፑ ያጫውቱታል ተብሎ አይጠበቅም። ነገር ግን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሃያ ዘጠኝ ግቦችን ለስኮትላንዱ ክለብ ያስቆጠረውን እንግሊዛዊ በፕሪሚየር ሊጉ የሚወዳደሩ ክለቦች ሊያዘዋውሩት እንደሚችሉ ይጠበቃል። ልጁ ካለው ችሎታ አንጻር የዝውውር መስኮቱን ያደምቃሉ ተብለው ከሚጠበቁት ተጫዋቾች አንዱ ሊሆን ችሏል።
የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ሁለቱ ሲኖዶሶች እስከሚታረቁ በገልተኛነቱ ሊቆይ ይገባል
Sunday, May 19th, 2013ከደረሰ ገብረጊዮርጊስ (ሚኒሶታ)
የበረከትና አላሙዲ ልሳን (ከኢየሩሳሌም አረአያ)
Sunday, May 19th, 2013በአላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት፣ በረከት ስምኦን ከጀርባ የሚመሩት እና በአንድ ኤርትራዊ የሚዘጋጀው ጋዜጣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር ሲሞክር መታየቱን ተከትሎ ምስጢሩን የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጉዳዩን አጋለጡ። « ሰንደቅ» የተባለውና በነፃ ፕሬስ ስም የሚያደናግረው ጋዜጣ ፍሬው አበበ በተባለ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በኤርትራዊው ፋኑኤል ክንፉ ምክትል ዋና አዘጋጅነት የሚሰናዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሲሆን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በውድ ዋጋ ቢሮ ተከራይቶ እንደሚሰራ ያስታወቁት ምንጮቹ አያይዘውም ፍሬው አበበ ከዚህ ቀደም የብአዴን ልሳን በሆነው « ማህቶት» ጋዜጣ ላይ ይሰራ እንደነበረና ከብአዴን አመራር አባላትም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል። በፓርቲው ልሳን ለመስራት ደግሞ የድርጅቱ አባል መሆን ግድ እንደሚል የጠቆሙት ምንጮቹ “ጋዜጠኛ” ፍሬው የፓርቲው አባል እንደሆነና በነበረው ታማኝነት በበረከት ስሞን ተመርጦ አሁን ባለበት ጋዜጣ እንዲሰማራ መደረጉን አስታውቀዋል። በተጨማሪ «የኢትዮጲያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር» ተብሎ በሚጠራውና የገዢው ፓርቲ ተለጣፊ በሆነው “ማህበር” ጋዜጠኛ ፍሬው የቦርድ አባል ሲሆን፣ ይህ ማህበር በሃገሪቱ ነፃ ፕሬስ እንዳይኖር ቀን ከሌሊት የሚተጋ ነው ሲሉ ምንጮቹ በመግለፅ ተከታዩን ማስረጃ ያቀርባሉ። « ማህበር ተብዬው በሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ በኩል « እነእስክንድር ነጋ አሸባሪ ናቸው» ብሎ ተከራክሯል፤ «አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ» ጋዜጦች ሲዘጉ «ከስረው ነው» በማለት የሽመልስ ከማልን መግለጫ የሚያጠናከር መግለጫ በማውጣት ከመንግስት ወግኖ ተሟግቷል፤ እንዲሁም በተመስገን ደሰላኝ ይዘጋጁ የነበሩት «ፍትህ፣አዲስ ታይምስና ልዕልና» ጋዜጦች በነበረከት ቀጭን ትእዛዝ እንዲዘጉ ሲደረግም የነፍሬው ማህበር ተመሳሳይ አቋም በማራመድ መከራከሩን በዋቢነት የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ በአጠቃለይ ጋዜጠኛ ሲታሰር፣ ሲንገላታና ሲሰደድ ልክ መንግስት ተቀጥላ እየፈጠረ ለመወንጀል እንደሚሞክረው ሁሉ ይህም ማህበር ተመሳሳይ አካሄድ የሚከተል ፀረ-ፕሬስ ስብስብ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ተለጣፊ ማህበር ሊቀመንበር አንተነህ አብርሃም እንደሆነ የጠቆሙት ምንጮቹ የአንተነህ ታላቅ ወንድም አማኑኤል አብርሃ ሲባል የደኢህዴን/ኢህአዴግ ማ/ኮሚቴ አባል መሆኑን አጋልጠዋል።
በሌላም በኩል ምክትል የጋዜጣው አዘጋጅ ኤርትራዊው ፋኑኤል አንድ ሰሞን በኢቲቪ የህትመት ዳሰሳ ላይ ቀርቦ « የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ » ሲል በይፋ መናገሩን ያስታወሱት ምንጮቹ የስርአቱን ትክክለኛነት በመግለፅና በመከራከር የገዢው ፓርቲ «ቋሚ ጠበቃ» ሆኖ መታዩትን ጨምረው ገልፀዋል። (ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው አቤ ቶክቻው « የኢቲቪ አምደኛ» ሲል በወቅቱ ተሳልቆበታል)..
ምንጮቹ ከጋዜጣው ጋር በተያያዘ ሲቀጥሉ ይህን አሉ፤ የነፃ ፕሬስ ህልውና በአገሪቱ ጨርሶ እንዲጠፋ በተደረገበት ተጨባጭ እውነታ፣ የህትመት ዋጋ ጣራ በነካበት ሁኔታ ..«ሰንደቅ» የተባለው ጋዜጣ የሚያሳትመው ሁለት ሺህ ኮፒ ብቻ መሆኑ፣ ማስታወቂያ የሌለው መሆኑ፣ በተጨማሪ በሃገሪቱ ውድ በሚባለው ብርሃነ ሰላም ማ/ቤት መታተሙ እንዲሁም አዘጋጆቹ ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመሆኑ ምስጢር ሼህ አላሙዲ መሆናቸውን ያስገነዝባሉ። በዚህን ያክል ኮፒ ትርፍ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮቹ፣ አላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉና ጋዜጣውም በየሳምንቱ ሼኹን ከፍ-ከፍ አድርገው የሚያሳዩና ድርጅቶቻቸውን የተመለከቱ ዜናዎች እያተሙ የማውጣታቸው ምስጢሩ ከገንዘብ ድጋፉ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።
በዚሁ ጋዜጣ ላይ በረከት የሚፈልጉትና « ህዝብ ዘንድ መድረስ አለበት» የሚሏቸውን ምስጢራዊ ጉዳዮች ለሁለቱ የጋዜጣው አዘጋጆች የስራ መመሪያ ጭምር ከመስጠት ባለፈ በረከትና ሽመልስ በተለያዩ የብእር ስሞች ፖለቲካዊ ነክ ፅሁፎች እንደሚያወጡ፣ የሚፈልጉትን መረጃ እንደሚያስተላልፉ፣ ምንጮቹ አጋልጠዋል። እንዲህ ሲሉም ያብራራሉ፥ « የእነአበበ በለውና እስክንድር ነጋ ንብረት እንዲወረስ የተለያዩ የብእር ስሞች (ሽመልስና በረከት) በመጠቀም በጋዜጣው ቅስቀሳ ሲካሄድ ከቀየ በኋላ በመጨረሻ በዋና ክስነት ከቀረበው ውጭ «የንብረት ክስ» በሚል ሌላ ክስ ተመስርቶ የንብረት ውርሱ ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ። መንግስት የሰጠውን ግዳጅ በመወጣት፣ ነፃ ፕሬስን ሽፋን አድርጎ የተሰማራው ሰንደቅ ጋዜጣ ከጀርባ ያነገበው «አላማ» እንዲሁም አካሄድ በህዝብ ዘንድ ጥርጣሬ በማስከተሉ የጋዜጣው የኮፒ መጠን ላለፉት አመታት ሊያድግ እንዳልቻ አስታውቀዋል። በተለይ የጋዜጣው ዋና <አላማ> ተቃዋሚዎችን በአለ በሌለ ጉልበቱ ጨፍልቆ በመምታት በይፋ እንደሚታወቅ አመላክተዋል።
ለዚህም ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረውን ሁኔታ በአስረጅነት ይጠቅሳሉ ምንጮቹ፤ አብዛኛው አገር ቤት ያሉ ምሁራን አድፍጠው ባሉበት ተጨባጭ ሁኔታ ገዢውን ፓርቲ በአደባባይ ከሚቃወሙና የተለያዩ የመሟገቻ ሃሳቦችን ከሚያቀርቡ በጣት የሚቆጠሩ ምሁራን አንዱ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ነው በማለት ይገልፃሉ። ጋዜጣው « ዶ/ር ዳኛቸው የመኢአድ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከኢ/ር ሃይሉ ጋር መምከራቸውን» በማስቀደም አያያዞም « የብአዴን አባል ነበሩ» ሲል በተቃዋሚ ክፍሎችና በህብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬን ለመጫር መሞከሩን የገለፁት ምንጮቹ በረከት ስሞኦን ያጠናቀሩት ዘገባ መሆኑን አጋልጠዋል። ይህ ዘገባ ጨርሶ ከእውነት የራቀ መሆኑን የሚገልፅ ማስተባበያ ዶ/ር ዳኛቸው በጋዜጣው እንዲወጣ ከማድረጋቸው ባሻገር በፌስቡክ ባሰፈሩት መልእክት « እኔ የብአዴን አባል ብሆን ኖሮ ወረቀት በታኝ ሆኜ የምቀር ይመስላችኋል?. አባል ሆኜ ድምፄ ሳይሰማ የእነ ህላዌና በረከት ስምኦን ወረቀት በታኝ ሆኜ ልቀር አልችልም!» ብለዋል።
ምንጮቹ በማጠቃለያ ያነሱት፥ ፍሬው አበበ «ተከሰሰ» ተብሎ የተራገበውን ሲሆን፣ ከስምንት ወር በፊት የተዘገበን እና አዜብ በግልፅ ከቤተ መንግስት እንደማይለቁ በተነገረለት፣ሚሚ ስብሃቱ ሳይቀር ጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያምን የሚያኮስሥና በአንፃሩ ለአዜብ የወገነ ዲስኩር ማሰማቷና እርሷ ምንም ሳትባል «ጋዜጠኛው ተከሰሰ » የተባለው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት ለመሳብ በነበረከት የተቀናበረ « ድራማ» ነው ሲሊ ያጣጥሉታል። ምክንያቱም ሁለት ነው፤ ቀዳሚው በኢትዮጲያ ነፃ ፕሬስ አለ የሚል ስእል በመስጠት እገረመንገዱን <ፍትህ አለ> በሚል እነእስክንድር ነጋ እንዲፈቱ የሚቀርበውን አለም አቀፍ ጥያቄ አቅጣጫ ለማስለወጥ ብሎም «በእነእስክንድር የተሰጠው ውሳኔ በነፃ የህፍትህ አካላት የተወሰነ ነው» ለማለት እንደሆነ ምንጮቹ ያስረዳሉ።
ኢትዮጵያዊነት እያበበ ነው ወይስ እየጠወለገ?
Sunday, May 19th, 2013ያለንበት ጊዜ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆን ትረጉመ-ቢስ የሆነበት ደረጃ ላይ እየደረሰ እንዳይሆን የሚያሰጋበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያዊነታቸው ሊከበርላቸው የሚገባውን የዜግነት መብት እየተነፈጉ ነው። መንግሥት የዜጎችን መብት ማስከበር ተስኖታል። ይህንን አስመልክቶ የኢሮብ መብት ተማጓች ማህበር (ኢ.መ.ተ.ማ) ተደጋጋሚ እሮሮዎችን ሲያሰማ የቆየ ቢሆንም አድማጭ ጆሮ ተነፍጎት ቆይቷል።
ከአንድ መቶ በላይ የኢሮብ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን በሻዓቢያ ታግተው ከተወሰዱ ይኸው አሥራ ሶስት ዓመት ሊሞላ አንድ ወር ቀርቶታል። ኢ.መ.ተ.ማ የነዚህ ዜጎች እጣ ፈንታ እንዲጠይቅ እንዲሁም የኢሮብ ሕዝብና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ለሺ ዓመቶች የኖሩበት መሬታቸው ለኤርትራ መከለሉን በተመለከተ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም፤ መንግሥት ጆሮ ደባ ልበስ ብሎ መቀመጥን መርጧል። ቀጥሎም በ2003 ዓ.ም ሻዓቢያ እንደገና በወርቅ ማምረት ላይ ተሠማርተው የነበሩ ከ260 በላይ ኢትዮጵያዊያን የትግራይ ተወላጆችን ከምእራብ ትግራይ ጠልፎ በመውሰድ ድኳቸው አጥፍቷል። ሆኖም፤ መንግሥት የነዚህን ዜጎች ደህንነት ለማረጋገጥና የሚገኙበት ሁኔታን ለማጣራት የወሰደው አንዳችም እርምጃ የለም። በተቃራኒው፤ አንዳንድ የኢህአዴግ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ኃይሎች በክስተቶቹ መንግሥት የመረጠውን ዝምታ በማውገዝ የአቋም መግለጫዎችን አውጥቷል። በውጭ ዜጎች መጠለፍ ወታደራዊ እርምጃ እስከመውስደ የተሯሯጠ መንግሥት ታግተው ደብዛቸው ስለጠፉ ዜጎቹ ምንም ዓይነት የሀላፊነት ስሜት አላሳየም የወሰደው እርምጃም የለም።
ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን የማፈናቀል አባዜ እጅግ አስከፊና ዘግናኝ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል። መፈናቀሉ መልከ ብዙ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። ለም የእርሻ መሬቶችን ለህንድና ለዓረብ ባለሀብቶች በስመ-ኢኒቨስትመንት ለመስጠት በሰበብ አስባቡ ከኖሩበት ቀዬ የሚፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር እጅጉን ተበራክቷል። የከተማ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሰበብ አስባቡ ያለምንም ቅድመ ዝግጅት በዓቅማቸው ቀልሰው ለዓመታት ከኖሩበት ቀዬ በማፈናቀል፤ ያለ ምንም ካሳ ቤቶቻቸውን በማፍረስ ሕጻናት፤ ነብሰ-ጡሮች፤ አሮጊት እናቶች፤ ሽማግሌ አባቶችና አቅመ ደካሞች ለሜዳ ኑሮ መዳረጋቸውን ታዝበናል። በተቃራኒው፤ መቐለ ውስጥ እንደታዘብነው ቤት እንዳይሠራባቸው በሕግ የተከለከሉና ለመናፈሻና ለደን እንዲጠበቁ በከተማው አስተዳዳሪዎች የተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሥርዓቱ ባለሥልጣናትና የሥርዓቱ ታማኞች ሕግ ተላልፈው ፎቆችና ቪላዎችን ሲያሰሩ፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የተሰሩ ናቸውና መፍረስ አለባቸው ብሎ የሚያፈርስ ቀርቶ፤ ሕግ ተላልፋቹሀል ብሎ የሚናገር ባለሥልጣንን ለመስማት አልታደልንም። ይህ በመቐለ የተከሰተው ዓይነት አሠራር በሌሎች አከባቢዎችም ተፈፅሞ ሊሆን ይቻላል። ሆኖም ለጊዜው መቐለ ላይ የተጣሰ ሕግ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥም እንደተጣሰ ለማመሳከር የሚያስችል ጭብጥ ስለሌለን በዚሁ ልናልፈው መርጠናል። እነዚህ ከላይ ያነሳናቸው ጭብጦች ላይ ተመርኵዘን በመከሰት ላይ ያለውን ህዝብን የማፈናቀል ተግባር አስፈላጊ ሆኖ እንኳ ቢገኝ ብቁ ቅድመ ዘግጅት ተደርጎ እንዲካሄድ የማድረግ ሓላፊነት ለመሸከም የሚችል መንግሥት እንደሌለን የሚያመላክት ሆኖ እናገኘዋለን። በየጊዜው በሻዓቢያ እየታገቱ ለሚወሰዱና ደብዛቸው ለጠፋ ዜጎች መቆም ያቃተው መንግሥት እንዳለን ከታዘብንም ሰነባብተናል።
አሁን ይህንን አጭር መግለጫ ለማውጣት ያስገደደን እጅግ አስደንጋጭና በዓይነቱም ለየት ያለ ኢትዮጵያዊያንን ለዓመታት ከኖሩበት መሬት የዘር ሐረጋቸው እየተመረጠ አፈናቅሎ የማባረር ኢትዮጳዊነትን የሚፈታተን ተግባር ሲፈጸም መታዘባችን ነው። ከዚህ በፊት ኢትዮጵያውያን ዘራቸው እየተጠና ከጉራ ፈርዳ ተፈናቅለው መባረራቸውን ሰምተናል አንብበናል። ያንን ስንሰማና ስለዛ ስናነብ እጅጉን የደነገጥን ቢሆንም፤ አገዛዙ ከዚህ ስሕተት ተምሯል የሚል ግምት አሳድረን ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ግን ተመሳሳይ ስሕተት እንደገና በተመሳሳይ መልኩ ተደግሞ ተከስቷል። አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ከበንሻንጉል ጉምዝ ፍጹም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ እንዲባረሩ ተደርጓል። በዚህም፤ የኢህአዴግ መንግሥት በጉራፈርዳ የፈጸመውን ኢሰብአዊ ግፍ ከመድገም ወደ ኋላ እንደማይል በሚገባ እንድንረዳ አስችሎናል። ስለሆነም፤ ሁኔታው እጅጉን አሳስቦናል። ኢትዮጵያዊያን በዘር ሐረጋቸው ምክንያት ከተወሰነላቸው ክልል ውጭ መኖር የማይችሉበት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት ሲቀጥል ታዝበናል። ይህ ዛሬ በአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝና አሳፋሪ የማፈናቀል ተግባር፤ ነገ በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ ላለመቀጠሉ ምንም ዓይንት ዋስተና የለም። ይህ በእንዲህ ከቀጠለ ደግሞ ኢትዮዽያና ኢትዮዽያዊነት ምን ትርጉም ሊኖረው እንደሚችል ህሊና ያለው እያንዳንዱ ኢትዮዽያዊ ቆም ብሎ ራሱን መመርመር ይኖርበታል ብሎ መኢተማ ያምናል። በመሆኑም፤ በሥልጣን ላይ ያለው አገዛዝ፤ ኢትዮጵያዊያንን ከቅያቸው የማፈናቀል ተግባር እንዲያቆም ኢትዮጵያዊያን ተባብረን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። የኢህአዴግ አገዛዝም፤ ህዝብን የማፈናቀል ተግባር የሚያስከትለው መዘዝ ምን ያህል አስከፊና አውዳሚ ሊሆን እንደሚችል በወጉ ለመገንዘብ ያለመፈለግን እልህ ማቆም ይጠበቅበታል። ካልሆነ ግን በሂደት ላገሪቱም ሆነ ለራሱ ለኢህአዴግ አላስፈላጊ ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል በወቅቱ ቢገነዘበው የተሻለ ይሆናል።
ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለጉ በፈለጉበት ቦታ ተዘዋውረው ሠርተው ሀብት ለማፍራት፤ ወልደው ከብደው ለመክበርና በገዛ አገራቸው ውስጥ ያለምንም መሳቀቅና መፍራት የመኖር ሕገ-መንግሥታዊ ዋስትና ከሌላቸው ኢትዮጵያ የምትባል አገርና ኢትዮጵያዊ የሚባል ዜጋ ሊኖር ይችላል ብሎ ለማሰብ የሚቻል አይሆንም። ይህ ማለት ግን መንግሥት በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖረውን የመሬት ይዞታ መልክ ለማስያዝ የሚረዳ ፖሊሲ መንደፍ የለበትም ለማለት እንዳልሆነ ግልጽ ሊሆን ይገባል። ለደን ልማት፤ ለመናፈሻ፤ ለዱር አራዊት፤ ለእርሻ፤ ለኢንዳስትሪ፤ ለመኖርያ፤ …….ወዘተ የሚሆኑ ቦታዎች ተለይተው አይከለሉ ለማለት አይደለም። መከለል አለባቸው። አሠራራችንም ሆነ የአመራረት ዘየቤያችን ዘመናዊ ማድረግ ላይ ተቃውሞ የለንም ብቻ ሳይሆን የምንደግፈው ጉዳይ ይሆናል። ሆኖም፤ የድሀው ህዝባችን ኑሮ በማያመሰቃቅልና ዜጎችን በማይለያይ መልኩ በጥናትና በጊዜ እየተለየ መከናወን አለበት ብለን እናምናለን። የማናምነውና ፍጹም የማንቀበለው ጉዳይ ቢኖር ግን የተለያዩ የክልል ትናንሽ ንጉሶችን በመፍጠር ኢትዮጵያዊንን ከኛ ዘር ስላልተወለዳችሁ፤ ይህ ክልል የነ እገሌ ዘሮች የትውልድ ክልል ስለሆነ ወይም ስላልሆነ ከሌላ ቦታ የመጣቹህ ወይም ከሌላ ዘር፤ ወገን የሆናቹህ በዚህ ክልል፤ መንደር፤ ሰፈር…ወዘተ መኖር አትችሉም የሚለው አካሄድ ኢትዮጵያዊነትን የሚንድ አደጋ አለው ብለን በጽኑ እናምናለን። አንድ ኢትዮጵያዊ በአንድ ክልል ውስጥ መጥቶ መኖር ሲጀምር፤ መኖርያውን በሚቀይስበት ጊዜ የመፍቀድም ሆነ የመከልከል ሥልጣን በሕግ የተሰጠው ኣካል ሲከለክልም ሆነ ሲፈቅድ የተገልጋዩን የዘር ሐረግ መስፈርት እንዳይጠቀም በሕግ መከልከል ይኖርበታል እንላለን። አንድ ኢትዮጵያዊ በተወሰነ ቦታ ላይ የተወሰነ ሥራ ለማከናወን ሲፈልግ፤ ያ ቦታ እንዲሰጠው ለመፍቀድም ሆነ ላለመፍቀድ አስቀድሞ በተቀመጠው ፕላን መሠረት በሚቀመጥ መስፈርት እንጂ ግለሰቦች በዘፈቀደ በሚዘውሩት መስፈርት ሊሆን ፈጽሞ አይገባም። ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ዘርና ወገን እየተለየ ኢትዮጵያዊያንን ማፈናቀል እየገፋ ሲሄድ ማቆምያ ድንበር ሊበጅለት የማይቻልበት ደረጃ ሊደርስ እንደምችል መታወቅ አለበት። የዚህ ድምር ውጤት በጋራ መልማትና ማደግ ሳይሆን ተያይዞ መጥፋትን እንደሚያስከትል መጠርጠር የለበትም። የኢትዮጵያ ህዝብ በየክልሉና በየመንደሩ ተከልሎ እንዲኖር የተወሰነ ዕለት እንደዚህ ዓይነት ችግር እንደሚከተል በግልጽ የሚታወቅ እንደመሆኑ መጠን፤ የሚያስከትለውን ችግር ለመረዳት የሚከብድ አልነበረም። በመሆኑም፤ አሁን እያየነው ያለ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ መፈናቀል እንዲከሰት ሆን ተብሎ የታቀደ ፀረ አንድነትና ኢትዮዽያዊነት ተግባር መሆኑም ግልጽ ነው።
በየክልላችን ተወስነን እንድንኖር የተደረገ ዕለት አብሮና ተማምኖ የአገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር የሚቆም ብሔራዊ ሠራዊት አይኖረንም። ለይስሙላ የሚቋቋም ብሔራዊ መከላከያ ኃይል ሊኖረን ይችል ይሆናል። ያ ግን መለዮ የለበሱ ሰዎች ስብስብ እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሠራዊት ሊሆን አይችልም። በኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜት ተኮትኵቶ፤ የችግሯን ገፈት አብሮ ለመቅሰም አብሮ የመሰለፉን ያህል ከጥቅምዋም አብሮ እኩል ለመቋደስ የማይችል ወታደር ብሔራዊ ወታደር ሊሆን አይችልም። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ በቅራኔ በተወጠረ ቀጠና ውስጥ ላሉ አገሮች ቀርቶ አንጻራዊ ሰላም አላቸው በሚባሉ አገሮች ውስጥም ቢሆን ተቀባይነት የለውም። የሠራዊቱን ጉዳይ አነሳን እንጂ በየመስኩ ብንዘረዝረው ሊያስከትለው የሚችለው ውድቀት የት የሌለ ጥፋት እንደሚሆን ለመገመት የሚከብድ አይደለም። በመሆኑም፤ አሁን አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ መጀመርያ በኢትዮጵያዊ ወገንተኝነታችን እንዲሁም ሰው በመሆናችን እጅጉን አሳዝኖናል። በመሆኑም፤ ይህንን አስነዋሪ ተግባር እያወገዝን የነዚህ ዜጎች ጉዳይ ከግብር ይውጣ አሠራር በዘለለ ወደ ተፈናቀሉበት ቀዬ ተመልሰው እንዲኖሩ እንዲደረግና ለደረሰባቸው የአካል፤ የንብረትና የሥነ-አእምሮ ድቀት ተገቢ ካሳ እንዲያገኙ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ከዚህም በተጨማሪ፤ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለኢፈዴሪ ፓርላማ በሰጡት መግለጫ ተግባሩን ማውገዛቸው የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም፤ ማውገዝ ብቻውን የሚፈለገው ውጤት ሊያስጨብጠን እንደማይችልና የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ዓለም አቀፉ ማህበረ-ሰብ በቀላሉ የሚቀበሉትና የሚጃጃሉበት እንደማይሆን ይረዱታል ብለን እንገምታለን። ስለሆነም፤ ኢትዮጵያዊያን በዜግነታቸው ተማምነው ሕጋዊ ዋስትና እንዳላቸው እርግጠ ኛ እንዲሆኑና አገራችን በዓለም አቀፉ ህብረተ-ሰብ የተሰጣትን ገጽታ ወደ በጎነት ለመቀየር ይቻል ዘንድ ባስቸኳይ ሕጋዊ የእርምት እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል። በኢ.መ.ተ.ማ እይታ ይህ ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት “የተወሰኑ ኪራይ ሰብሳቢ የወረዳ አስተዳዳሪዎች” የፈጸሙት ነው የሚለው አባባል በአመክንዮ ሊደገፍ የሚችል አይደለም። ቢያንስ ከፍተኛ የፈደራል የመንግሥት ባለሥልጣኖች በወንጀሉ ውስጥ አለመሳተፋቸው በእርግጠኝነት ከታወቀ፤ በጥልቀት ሊመረመር የሚገባው የሕግ ሕፀፅ መኖር አለበት። ካልሆነ ግን ማንም የወረዳ አስተዳዳሪ ከባዶ ተነስቶ ይህን ያህል ህዝብ የማባረር ሥልጣን ይኖሯል ብሎ ለማሰብ እጅጉን ይከብዳል። ስለሆንም፤ ችግሩን ከሥሩ በማጥራት በነዚህ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አስከፊ በደል በማያዳግም መንገድ እልባት እንዲያገኝና ኢትዮጵያዊነት ከመጠውለግ ድኖ እንዲያብብ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ አንዲታገል አጥብቀን እንጠይቃለን።
ኢትዮጵያዊነት በኢትዮዽያዊያን የጋራ ትግል ይለመልማል!!!
የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር (ኢ.መ.ተ.ማ)
ግንቦት 2005 ዓ.ም
ታሪክን የኋሊት፤ የአቶ መለስ ድንጋጤ! (አቤ ቶኪቻው)
Sunday, May 19th, 2013እንግዲህ ይህ ከሆነ አመቱ ሆነ አይደለ… ቅዳሜም ቅዳሜ፣ እሁድም እሁድ ነው እና ምናልባት ካልተገናኘን… እንዳንረሳው፤ ከወዲሁ ቀኑን እንደሚከተለው እንዘክረው… (በቅንፍም ኤድያ እነ እንትናዬ ደግሞ ሊበሳጩብኝ ነው… (በሌላ ቅንፍ እንግዲህ ይቻሉት እኛ ስንቱን ችለነው የለ…))
በመጀመሪያም፤
ብስጭቴ
እኔ እኮ የምለው ሰው አይኑ እያየ የሰራውን ስራ እያወቀ ወደ አሜሪካ ለዛውም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይሄዳል እንዴ!? እውነቱን ለመናገር እኔ አቶ መለስ ዜናዊን ብሆን ኖሮ ዲቪ እንኳ ቢደርሰኝ ሀገር ይቀየርልኝ እላለሁ እንጂ አሜሪካ አልሄድም። እነ ቻይና ባሉበት አለም እነ ሰሜን ኮሪያ በሚኖሩበት ምድር ሰው እንዴት ወደ አሜሪካ ይሄዳል? (ይቅርታ ሰው በሚል የተጠቀሱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ነው)
ዋናው ወሬ፤
የሆነው ሆኖ ትላንት በዋሽንግተኑ ስብሰባ አቶ መለስ ዜናዊ ሲመጡ ከውጪ ያለውን የተቃውሞ ድምፅ በመከራ አልፈው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደግሞ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተሰብሳቢው ፊት፤ ከውጪ ያለው ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ፣ እንዲሁም አዲሳባ ያለው ህዝብ ደግሞ በሰላማዊ ዝምታ በሆዱ ምን እያላቸው እንደሆነ ነጥብ ነጥቡን ነግሯቸዋል። እንደው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውብኝ እንጂ “እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ድረስ ነግሯቸዋል!” ብል የበለጠ ይገልፀዋል መሰል!
የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድርጊት ከዚህ በፊት ጆርጅ ቡሽ ላይ ጫማ ከወረወረው ጋዜጠኛ ጋር የሚቀራረብ ይመስላል። እንደውም በቪዲዮ እንዳየኋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የደረሰው የቅስም ስብራት “በጫማ መመታት በስንት ጣዕሙ!” ያሰኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በስፍራው የተገኙት በባራክ ኦባማ ጋባዥነት ከቡድን ስምንት ሀገሮች ጋር ስብሰባ ሊቀመጡ እንደሆነ ባለፈው ግዜ አውርተናል፤ ከቡድን ስምንቱ ስብሰባ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ታድያ “ግሎባል አግሪካልቸር ኤንድ ፉድ ሴኪዩሪቲ” በተባለው ስብሰባ ላይ ቁጭ ብለው እንደተለመደው ፐርሰንታቸውን እየጠቀሱ ሳለ ድንገት አበበ ገላው፤ “መለስ ዜናዊ…” ብሎ ሲጠራ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን “የደነገጡት መደንገጥ… ከአንድ ታጋይ የሚጠበቅ አይደለም” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ። እኔም እንዳየሁት ጆሯቸውን ማመን አቅቷቸው “የድርጅቴን ብቅል እየፈጨሁ ነው…” ብለው ሊያልፉት የከጀሉ ሁሉ መስሎኝ ነበር።
ብቻ በጣም ክው ማለታቸውን ፊታቸው አሳበቀባቸው። ከዛ እንደምንም ተረጋግተው…“ሰበንቲ….ፐርሰንት” ብለው ንግግራቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድምፅ ከመጀመሪያው ከፍ ብሎ “መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር…” ማለቱን ቀጠለ አሁን ትንፋሽም ቃልም አጠራቸው። አስተያየታቸው “ምነው ዛሬ እግሬን በሰበረው!?” የሚሉ ይመስላሉ። ግን እንደምንም ብለው ለመቀጠል ሞከሩ። ድምፃቸውን ከአበበ ድምፅ ከፍ ለማድረግ እየጣሩ “ሰበንቲ…ፐርሰንት” አልቻሉም። “ምን ላይ ነበር ያቆምኩት…?” ለማለት የፈለጉ ይመስላሉ ባልንጀሮቻቸውን ቃኘት ቃኘት አደረጉ። እነርሱቴ “ራስህ ተወጣው!” ሳይሏቸው አይቀሩም… አበበ ቀጥሏል። “መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር….” አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኛ በላይ ድምፅ ላሳር በሚመስል መልኩ ከአበበ በላይ ጮክ ብለው እና ድፍረታቸውን አሰባስበው፤ “ሰበንቲ ፐርሰንት ኦፍ ዘ ፖፕሌሽን ኢን አፍሪካ….” አሉ። ብሽሽቅ ነው የሚመስለው እንጂ የንግግራቸው አካል አይመስልም!
ድጋሚ አቋረጡ አበበ ግን የሚያቋርጥ አይመስልም በእንግሊዝ አፍ “እስክንድር ነጋ እና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ ምግብ ያለ ነፃነት ዋጋ የለውም! መለስ ዜናዊ አምባ ገነን ነው!” ብሎ እንቅጩን ነገራቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁና ቁና ሲተነፍሱ ኮምፒውተሬን አልፎ ሁሉ ይሰማ ነበር። በሆዴ “ይበልዎት አይሂዱ አላልኮትም ነበር!?” ብልም እውነቱን ለመናገር ግን አንጀቴን በልተውታል።
አቶ መለስ ከትላንትናው የበለጠ ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸው ጭምጭምታ ሰምቻለሁ። ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው ካምፕ ዴቪድ ድረስ ህዝቡን ለማመላለስ የተሰናዱ አውቶቡሶች መኖራቸውን የደረሰኝ ጭምጭምታ ያስረዳል።
እኔማ የሚሰማኝ አጣሁ እንጂ ቀድሞውኑም ይሄ ስብሰባ ይቅርብዎ ብዬ ነበር። ይሄን ግዜ እርሳቸውም በሆዳቸው “ምነው ምነው ምነው በቀረብኝ” የሚለውን ሙዚቃ ሊያዜሙ እንደሚችሉ እጠረጥራለሁ። ምንም ጠቅላይሚኒስትር ቢሆኑ ሰው አይደሉ እንዴ…!? ምክሬን ባለመስማታቸው መፀፀት ካልቻሉ እውነትም ሰውየው ጠቅላይ ሚኒስትር እንጂ ሰው አይደሉም ማለት ነው!
ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቅስም ስብራት የሰማ አንድ ወዳጄ “ይሄኔ ጥሩ አዝማሪ ቢገኝ ይቺን ግጥም በል እስቲ ተቀበል ብሎ ማቀበል ነበር” ብሎኛል…
“አፄ መለስ ዜና እጅግ ተዋረዱ
ምግብ ብለው መጥተው አንጀት በልተው ሄዱ
አንተ አበበ ገላው እንደምን ቻልካቸው
መለስ ቀለስ ሲሉ ጎንበስ አረካቸው”
(አረ ጎበዝ ዜማ ፈልጉና ይችን ነገር ነጠላ ዜማ አደርገን እንልቀቃት በስንት ግዜ የተገኘ የግጥም አዚምን እንጠቀምበት እንጂ!)
በነገራችን ላይ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ አቶ መለስ አዲሳባ ሲገቡ ወይ በጭፈራ ሞቅ ደመቅ አድርገን ካልተቀበልናቸው ወይ ደግሞ ለጥ ብለን ተኝተን ካልጠበቅናቸው በብስጭት ሊጨርሱን ይችላሉ ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም
ኦባማ ግን አራዳ መሆናቸው ነው ሰውየውን ጠርተው ልክ ልካቸውን የሚያስነግሯቸው!? የምር ሽምቅቅ አደረጓቸውኮ! (እኔ ልሸማቀቅ… ልላቸው ነበር አሁንማ አንዴ ጀምረውታል… ይወጡት እንግዲህ!)
ስድስት:- ቃል ኪዳን፤ ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ (ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)
Sunday, May 19th, 2013መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2005
እንግዲህ ኢሳት በነገረኛነትም ሆነ በጠመንጃ-ያዥነት በኩል ከሎሌነት ጠባይ ጋር የተያያዘውን ኢትዮጵያውያን ያለንን አጉል ባህል ሁሉ እየነቀስን እየጣልን በዘመናዊና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ መሠረት ለመጣል ዋና መሣሪያ ሊሆነን ይችላል ብሎ ማመን መነሻ ይሆናል፤ ይህ እምነት ከሌለ የእምቧይ ካብ ነው፤ ይህ እምነት ራስን ማጽዳትንም ይጠይቃል።
ማክሸፍ እንደምንችልበት ከማመን እንጀምር፤ ስለዚህም ኢሳት ሊከሽፍ የሚችልበትን እያንዳንዱን መንገድ ማጥናትና በቅድሚያ ፈውሱን ማዘጋጀት የሚጠቅም ይመስለኛል፤ ይህንን ጉዳይ በትጋት ለመከታተል የኢሳትን አማራጭ የማይገኝለት የአገር ጥቅም በእውነትና በትክክል መገንዘብ ያሻል፤ ዘመን-አመጣሽ ነገር ብቻ አድርጎ መመልከቱ ለወረት ይዳርገዋል፤ ወረትን ማክሸፍ ቀላል ነው፤ ከከሸፈ በኋላ እንዲያንሰራራ ለማድረግ በጣም ከባድ ሥራን ይጠይቃል፤ ስለዚህ ከወዲሁ ኢሳት ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲተከል የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ዘለቄታ እንዲኖረው ማረጋገጫ ይሆናል።
የኢሳት መክሸፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል፤ አንፈራጥጠው ከላይ ቤት እታች ቤት እየቀላወጡ አካላቸውን፣ አእምሮአቸውንና መንፈሳቸውን የሚያባልጉ ሰዎችን ያበራክታል፤ የድብቅብቆሽ ዓለምን እየፈጠሩ የጠራውን ከደፈረሰው፣ የጸዳውን ከአደፈው፣ ሳይለዩ ለሚያወሩት ደካሞች ሜዳውን ያሰፋላቸዋል፤ የወያኔ/ኢሕአዴግን ፍርሃት ወደመርበድበድ ይለውጠዋል፤ የጦርነት ጥሩምባ ለሚነፉትም ሜዳውን እያሳየ የቀረርቶ በር ይከፍትላቸዋል፤ ይህ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምንና ስምምነትን፣ እድገትንና ብልጽግናን፣ ኩራትንና ክብርን አያስገኝም።
ንስሐ ለመግባት ወኔ ለሌላቸው፣ በሠሩት ጥፋት አገርን ወይም ወገንን በመበደላቸው ዛሬም ለመኩራራት ለሚፈልጉት፣ አርበኛውንና ባንዳውን ባንድ ሚዛን አስቀምጠው ለሚተቹት፣ የኢትዮጵያውያንን ሰውነት አራክሰው ጊዜያዊ ጥቅማቸውን ለሚያከማቹ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን በተንኮል እየመነዘሩ የሥልጣን መሰላል ለሚያበጁ ሁሉ ፊት-ለፊት ቆሞ ለሚጋፈጣቸው ኢሳት መድረክ ይሆናል፤ የኢሳት ዋና ጥቅሙ እዚህ ላይ ነው፤ ይህንን ተግባር ለመፈጸም ኢሳት የኢትዮጵያ፤ ኢሳት የኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲሆን መንገዱን እንጥረግ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በባለቤትነት የሚመራውና የሚያካሂደው እናድርገው፤ ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢሳት ላይ ያለው መብት ነው ከተባለ፣ ግዴታውንም አብሮ መቀበል ሳይታለም የተፈታ ይሆናል፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሁሉ ግዴታውን በቃል ኪዳን መቋጨት ከቻለ ኢሳት ከቀፈፋና ለመክሸፍ ይድናል።
የእኔ ምኞት ኢሳት በኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳን ተገንብቶ በሕገ ኀልዮት እየተመራ አዲስ ዓላማ፣ አዲስ የአሠራር ዘዴ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ጉድለቶችን ሁሉ አውቆ በጥንቃቄ እየነቀሰ አዲስ የመተማመንና የመተባበር ባህል ይፈጥራል የሚል ነው፤ (እኔ ቃል ኪዳን የምለው ሁለት ቁም-ነገሮችን የያዘ ነው፤ በአንድ በኩል እውነትን አለመፍራት (ወይም በጥሩ መልኩ ለእውነት መቆም፣) በሌላ በኩል ለአንድ የጋራ ዓላማ የራስን ግዴታ ሳያስተጓጕሉ ለመወጣት በቆራጥነት መቆም፤ ስንት ልጆች አሉህ ተብሎ ሲጠየቅ ሁለት ወይም ሦስት እያለ አጥር ላይ ተንጠልጥሎ የሚመልስ ለቃል ኪዳን አይበቃም፤) ከሩቅ እንደማየው ጥቂት ሰዎች ኢሳትን በቃል ኪዳን ተይዘው ሲጥሩ አብዛኛው ደግሞ በአጋጣሚ እንደተመቸውና እንደፈለገ የተቻለውን የሚያደርግ ምንም ዓይነት ቃል ኪዳን የሌለው ነው፤ ከተሳሳትሁ ደስ ይለኛል፤ አስተያየቴ ትክክል ከሆነ ኢሳት አይዘልቅም፤ መክሸፍ ዕጣ-ፋንታው ይሆናል።
ዓላማውን ሳይመታ እንዳይከሽፍ ኢሳት በቃል ኪዳን መታሰር አለበት፤ እንዴት? ቢባል፣ አንድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በአማካይ በወር አሥር ዶላር ለመስጠት ቃል ኪዳን ቢገቡና የየዓመቱን ግዴታቸውን በአንዴ ቢወጡ፣ በወር አሥር ሚልዮን ዶላር (በዓመት አንድ መቶ ሃያ ሚልዮን ዶላር) ኢሳትን ኢትዮጵያዊነትን የሚያስከብር የሰላምና የፍቅር፣ የብልጽግናና የተስፋ መድረክ ሊያደርገው ይችል ነበር፤ አብዛኛዎቹ ችሎታው ያላቸው ኢትዮጵያውያን ለኢሳት የሚገቡት ቃል ኪዳን ለጥሬ ሥጋና ለመጠጥ የገቡትን ቃል ኪዳን ካላሸነፈ ታማኝ በየነን በያገሩ እየላከ በሚያደርገው ዓመታዊ ቀፈፋ ኢሳት ይገነባል ብዬ ለማመን ያሰቸግረኛል፤ በኢሰመጉ አይቼዋለሁ።
ቀፈፋ ወይም ልመና አንዱና ዋናው የባህል ሕመም ነው፤ እያንዳንዳችን ከዚህ ሕመም ለመዳን በራሳችን ላይ መዝመት የሚያስፈልገን ይመስለኛል፤ በተለይ በአገር ጉዳይ፣ በወገን ጉዳይ ማን ነው ለማኝ? ተለማኙስ ማን ነው? ስለአገሩና ስለወገኑ ችግር የማያውቅ አለ? ለማወቅ የማይፈልግ ይኖራል እንጂ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ችግር ገሀድ ነው፤ በአስከፊ መልኩ ለመረዳት የሚፈልግ በመረረ ቋንቋ የተጻፈውን የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ሀገሬ ገበናሽ (ክፍል አንድ፣ ክፍል ሁለትና ክፍል ሦስትን) ያንብብ። አንብቦ ካላለቀሰ፣ አልቅሶ ‹‹ምን ላድርግ!›› የሚል ቁርጠኛነት ያላደረበት በዓመት አንድ ጊዜ በታማኝ ቀፈፋ አገሩንና ወገኑን መርዳት አይችልም፤ እምነቱ ካለ፣ ስሜቱ ካለ በገንዘብ የሚደረግ ማናቸውም እርዳታ የመጨረሻው፣ መናኛው ነው፤ መናኛ የሚያደርገው የገንዘቡ መብዛት ወይም ማነስ አይደለም፤ ለአገርና ለወገን ከዚያ በጣም የበለጠ የሚከፈል ዋጋ በመኖሩ ነው፤ አያቶቻችንና ቅምአያቶቻችን የከፈሉት ዋጋ በገንዘብ አይመነዘርም፤ እነሱ በሕይወታቸው ያስገኙልንንና እኛ በገንዘብ የሸጥነውን ኩራትና ክብር በገንዘብ ብቻ አናስመልሰውም፤ ቃል ኪዳን እንግባ!
በአካል ቅኝ ሳንገዛ፣ ለምን የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች ሆን? – ከተክሌ የሻው
Saturday, May 18th, 2013በዘመነ ቅኝ አገዛዝ፣ በአውሮፓውያን ቅኝ ገዥ ኃይሎች ያልተገዛች፣እንዲያውም የቅኝ ገዥዎችን ቅስም በመስበር ነፃነቷንና ማንነቷን አስከብራ የኖረች ብቸኛ አገር ኢትዮጵያ መሆኗን የዓለም ታሪክ የሚያውቀው ብቻ ሳይሆን፣የሚደነቅበት ጭምር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዘመነ ቅኝ አገዛዝ ቀደም ባሉት ዓመታትም የግዛት ማስፋፋት ዓላማን ተከትለው ኢትዮጵያን በተፅዕኖዋቸው ሥር ለማድረግ የተነሱ ወራሪና ተስፋፊ ኃይሎችን ማለትም ፡-
• ከ1521 እስከ 1535 በቱርኮች ሁለንተናዊ ትብብር ብቻ ሳይሆን፣ በቀጥተኛ የጦር መሣሪያና የሰለጠነ ወታደር ለግራኝ መሐመድ በማቅረብ አገሪቱን በቱርኮች አገዛዝ ሥር ለማዋል የተደረገውን እልህ አስጨራሽ ጦርነት፣
• በ1571 የቱርኮችን ቀጥተኛ ወረራ ድሆኖ ላይ፣
• በ1824፣ በ1826፣ በ1829፣ በ1830፣ በ1832፣ ግብፆችን በተደጋጋሚ በባሕረ-ነጋሽ እና በትግራይ ሜዳና ሸንተረሮች ላይ፣
• በ1867 እና በ1868 ግብፆችን ጉንዳጉንዲትና ጉራዕ ላይ፣
• በ1877 ድርቡሾችን ኩንፊት ላይ፤ የወራሪዎችና የተስፋፊዎችን አከርካሪ በመስበር አይደፈሬዎቹ አባቶቻችን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን አስከብረው ለትውልድ በኩራት ማሸጋገራቸውን እናውቃል፡፡ ዓለምም በዚህ አኩሪ የማንነት ተጋድሎ ኢትዮጵያውያንን ሲያደንቅና ሲያከብር መኖሩ ሐቅ ነው፡፡(ተክሌ የሻው፣2003፡16)
በኋላም በዘመነ ቅኝ አገዛዝ ጀግኖች አባቶቻችን በ1896 ጣሊያንን አምባላጌ፣ መቀሌና ዐድዋ ላይ፣ ከ1928 እስከ 1933 የጣሊያንን ፋሽስት ጦር በኢትዮጵያ ዱር ገደሎች ባካሄደው ተከታታይ የነፃነትና ማንነትን የማስከበር ጦርነት፣ በዚህም በከፈሉት ወድር የለሽ ሁለንተናዊ መስዋዕትነት አገራችን የቅኝ ገዥዎች ፍላጎት ተሸካሚ እንዳትሆንና ማንነቷን አስከብራ እንድትዘልቅ ሆኗል፡፡ ይህ የነፃነትና ማንነትን አስጠብቆ የመዝለቅ ተጋድሎ አገራችን ኢትዮጵያ “የነፃነት ምሽግ” የተሰኘ ውድ ስም እንድታተርፍ አድርጓታል፡፡ ይህን የነፃነት ምሽግነቷን በተመለከተ በ17ኛው ምዕተ ዓመት የኖረው ፖርቹጋላዊው የታሪክ ሊቅ ሉዊስ ኡሬታ ሐበሻ የሚለውን ቃል በአረብኛ፣በቱርክ፣ እና በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ትርጉሙ የባዕድ ንጉሥ ግዛት የማታውቅ ነፃና ራስ ገዝ ማለት ነው፤ኢትዮጵያ የምትባለውም ልክ እንደምነግራችሁ ናት፤(ሚሊዮን ነቅንቅ 1993፡13) በማለት የነፃነት ምሽግነቷን መስክሮላታል፡፡
ይህን ተከታታነት ጠብቆ የዘለቀን የነፃነት ምሽግነት የናይጀሪያ መሪ የነበሩት ናምዲ አዚክዊ “ኢትዮጵያ በዓለም ገጽ ከጠፉ የጥቁር ግዛቶች የተረፈች ብቸኛ የተስፋ ችቦ ነች፡፡ የአፍሪካውን አባቶችና አያቶች በዚህ አህጉር አቋቁመውት ለነበረው ሥርዓተ-መንግሥት ሀውልት ነች፡፡ ጓደኞቿ አገሮችና ወራሾቻቸው ከፖለቲካ ታሪክ ገጽ ከተሰረዙ በኋላ ፣ኢትዮጵያ በነፃነት መቆየቷ እጅግ የሚያስደንቅ ነው” (ሚሊዮን ነቅንቅ፣ 1993፡14) በማለት የአባቶቻችን የነፃነት ተጋድሎ አኩሪ ብቻ ሳይሆን፣ ለጥቁሮች ማንነት ምሳሌ መሆኗን ገልጠውታል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ጆርጅ ኤድመንድ ሄይንስ የተባሉ ጥቁር አሜሪካዊ የኢትዮጵያን በነፃነት ተጠብቆ መዝለቅ እንዲህ በማለት ገልጸውታየመል፡፡ “ኩሩዋና ነፃዋ ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ደም ላላቸው ጥቁሮች የነፃነት፣የራስ መቻል፣ከዘመናዊ ሥልጣኔ መልካም መልካሙን የመቅሰምና የንቃተ-ኅሊና ምልክት ሆናለች፡፡”( ሚሊዮን ነቅንቅ፣1993፡15) ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ኢትዮጵያ፣ ከቅኝ ገዥዎች ነፃ የወጡ የአፍሪካ አገሮች የባንዲራዎቻቸውን ቀለሞች አረናጓዴ፣ ብጫና ቀይ ቀለማት ያደረጉት፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት( የአፍሪካ ኅብረት) እና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽ/ቤቶች አዲስ አበባ ላይ የተመሠረቱትና ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና ለመባል ያበቃት ነፃተቷን ጠብቃ በማቆየት ለአፍሪካ የነፃነት ተጋዮች ባበረከተችው የቁሳቁስና የሞራል ድጋፍ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ያለፈ መልካምሙና አኩሪው ታሪካችን ነው፡፡
ቅኝ ገዥ ኃይሎች የቅኝ ግዛት ዓላማቸውን ያስፋፉት በቀጥተኛ የኃይል ወረራና ጦርነት ብቻ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እንዳውም አብዛኛዎቹን አገሮች በቅኝ ግዛታቸው ቀንበር ሥር ያዋሉዋቸው፣ የየአካባቢውን የጎሣና የነገድ መሪዎችን በመናኛ ጥቅማ-ጥቅሞች በመደለል መሬቶችን በመግዛት የራሳቸው በማድረግ፣ሃይመኖታቸውን በማስቀየርና በአገር አሳሽነት ስም በመግባት የየአገሮቹን ባህል፣ቋንቋና ታሪክ በማጥናት ሥልጣኔን እናስፋፋለን በሚል ሽፋን ማንነታቸውን አስጥለው የሌላቸውንና ከእነርሱም ጋር ሊዋሐድ የማይችል ማንነትን እንዲላበሱ በማድረግ እንደሆነ የቅኝ አገዛዝ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ለዚህ አባባል ታማኒነት የቀድሞው የኬንያ መሪና የኬንያ የነፃነት አባት የሚባሉት ጆሞ ኬንያታ “ማኦ ማኦ” በተሰኘው የነፃነት እንቅስቃሴ ወቅት የተናገሩትን መጥቅሱ ተገቢ ነው፡፡ “እንግሊዞች ወደ አገራችን ሲመጡ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው መጡ፤ እነርሱም ዐይናችን ጨፍነን፣ አንገታችን ደፍተን እንድንጸልይ አስተማሩን፣አንገታችን ደፍተን ዐይናችን ጨፍነን ከጸለይን በኋላ ፣ዐይናችን ገልጠን አንገታችን ስናቀና፣ መጽሐፍ ቅዱሱ የኛ፣መሬቱ የነርሱ ሆኖ አገኘነው፡፡” ሲሉ የተናገሩት ቅኝ ገዥዎች በምን መልክ ሕዝቦችን ቅኝ ተገዥ እንዳደረጓቸው በተጨባጭ ያስረዳል፡፡ አገላለጹ ዕውነኛውን የአፍሪካን የቅኝ አያያዝ ስልት በሚገባ ያሳያል፡፡
በርካታ ቁጥር ያላቸው የአፍሪካ አገሮች በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር የወደቁት ከፍሲል ጆሞ ኬንያታ በገለጡትና የጎሣ መሪዎቹ በሸጡት መሬት ላይ በመቆናጠጥ ይዞታቸውን በልዩ ልዩ መንገዶች በማስፋት ነው፡፡ በእኛም ታሪክ ጣሊያን ኤርትራን ለ50 ዓመታት በቅኝ ግዛት እንዲይዛትና ለተከታታዮቹ የዐድዋና የአምስቱ አመታት የአርበኝነት ትግል የዳረገን ፣ሡልጣን ኢብራሂም የተባለው የአፋር ባላባት አሰብን ለጣሊያን የቅኝ ገዥ አስፋፊ ቡድን በመሸጡና ቅኝ ገዥው ኃይል መላዋ ኢትዮጵያን በቁጥጥሩ ሥር ሊያውልበት የሚችልበትን መንገድ ያመቻቸ መቆናጠጫ መሬት በማግኘቱ እንደሆነ በግልጽ ይታወቃል፡፡
በሌላም በኩል ኢትዮጵያውያን ከፍ ሲል በተጠቀሱት በቀጥታ ወረራ ቅኝ ተገዥ ሊያደርጓቸው የቃጡትን ኃይሎች ድል ነስተው የመለሷቸውን ያህል፣በሃማኖት፣ በአገር አሳሽነትና በሥልጣኔ አስፋፊነት ስም የፍላጎታቸው ተገዥዎች ሊያደርጓቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው የመጡ አስመሳይ ወንጌላውያንን፣ አባቶቻችን “ መጽሐፍ ቅዱሱም ሊቃውንቱም በአገራችን አሉ፤ ከእናንተ የምንሻው የዕደጥበብ ሙያተኞችን ነው፤” በማለት መልሰዋቸዋል፡፡ ይኸም ብቻ አይደለም፡፡ የክርስቶስን መወለድና መጠመቅ ያልሰሙትንና ሊሰሙም ያልፈለጉትን የአሕዛብ አገር ትታችሁ ከዚህ ምን ልትሠሩ መጣችሁ/የሚሉ አፋጣጭ ጥያቄዎችን በማቅረብ ለአስመሳይ ወንጌላውያኑ ከንቱ ስብከት ኅሊናቸውን ቀርቶ ጆሮአቸውን ባለመስጠት ወደመጡበት እንዲመለሱ ማድረጋቸው ግልጽ ነው፡፡ በአገር አሳሽነትና በሥልጣኔ አስፋፊነት ስም የገቡትንም አገሪቱ ካሏት የከበሩ ነገሮች የተመረጡትን በገጸ-በረከትነት በመስጠት፣ የአገራቸውን አፈር ግን ከምንም በላይ የሚወዱትና በማንም ሊወሰድ እንደማይችል ለማሳየት በጫማቸው አፈር ይዘው እንዳይሄዱ እግራቸውን አሳጥበው እንደሸኙዋቸው ታሪካችን ያስረዳናል፡፡ እነዚህንና መሰል አባቶቻችን ለነፃነትና ማንነትን አስጠብቆ ለመዝለቅ ያደረጓቸው ተጋድሎዎች ከአካላዊና ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ተጠብቀን ፣ማንነታችንና ነፃነታችን አረጋግጠን እንደንቆይ እንዳደረጉን እንረዳለን፡፡ ይህ የታሪካችን እጅግ መልካሙ፣አስደናቂውና አንፀባራቂው ምዕራፍ ነው፡፡ ታሪኩ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን፣ መላውን የጥቁር ዘር ያኮራና ያስመካ ነው፡፡
ከዚህ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህን የነፃነት ምሳሌነትና የኢትዮጵያዊነት ምንነት መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቻቸውን ምን ያህል ጠብቀው ይዘዋቸዋል? የቱንስ ያህል አዳብረዋቸዋል? ጉዞ አቸው ወደ ፊት ነው ወይስ ወደ ኋላ? የሚሉት ናቸው፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎች ተገቢ መልሶች ለመስጠት በአምስት ኣመቱ የአርበኝነት የተጋደሎ ዘመን የነበረውን የሕዝቡን አመለካከትና ከድል በኋላ የተፈጠረውን ትውልድ አመለካከት የተቀረጸባቸውን ነባራዊና ኅሊናዊ ሁኔታዎች በቅጡ ማገናዘብ ይጠይቃል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ለማግኘት ዕውነት እንደሚባለው ኢትዮጵያውያን የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች ሆነናል? የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ መመለስ አለብን፡፡ አጭሩ መልስ አዎ! ኢትዮጵያውያን የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች ሆነናል የሚል ነው፡፡ ከዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ግን በምን በምን ምክንያቶች ለኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት እንድንዳረግ ያደረጉንን መሠረታዊ ምክንያቶች ማባራራቱ ብዥታ የሌለበት ግንዛቤ እንድንጨብጥ ይረዳናል፡፡
1. ከድል በኋላ የመንግሥቱ ቢሮክራሲ በስደተኛውና በባንዳው ቡድን ጥምር ጥምረት መዋቀር፤
ማንም የአርበኝነት ትግሉን ዘመን ታሪክ በአግባቡ የተከታተለ ሰው ሊረዳው እንደሚችል፣ያ ወቅት ኢትዮጵያውያን ከሦስት የተከፈሉበት ነበር፡፡ አርበኛ፣ስደተኛና ባንዳ፡፡ አርበኞቹ እንደጥንት አባቶቻቸው እምነታቸውን ያልለወጡ፣ማንነታቸወን ያልካዱ፣በዕለታዊ ጥቅማ-ጥቅሞች ባንዲራቸውንና አገራቸውን ያልካዱ፣ ሃይማኖታቸውን ያልለወጡ፣ኢትዮጵያ ወይ ሞቴ ብለው በቁርጠኝነት የቆሙና ነፃነታችንን ተጋድለው ያረጋገጡልን ናቸው፡፡ ከነዚህ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል ራስ አበበ አረጋይ፣ ደጃዝማች ደረሱ ዱኬ፣ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር፣ ራስ አሞራው ዉብነህ፣ደዝማች በላይ ዘለቀ፣ደጃዝማች ታደሰ ይማም፣ፊታውራሪ ሽፈራው ጌታሁን፣ደጃዝማች አድማሱ ብሩ፣ደጃዝማች ወንደወሰን ካሣ፣ደጃዝማች አበራ ካሣ፣ ራስ ሙሉጌታ ይገዙ፣ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ፣ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ብጹዕ አቡነ ሚካኤል እና አያሌ ስማቸው ተዘርዝሮ የማያልቅ፣ግን ስለተጋድሎአቸው ምንም ያልተባለላቸው ዕውነተኛ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል፡፡
ስደተኞች የሚባሉት በጠላት ከመገዛት መሰደድን የመረጡና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ ወጥተው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ኑረው፣ ከድል በኋላ ቀድመው ካገር የወጡትን ንጉሠ ነገሥቱን ተከትለው የገቡ ናቸው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የንጉሠ ነገሥቱ ቤተሰቦች፣መሣፍንቱና መኳንንቱ ማለትም ፡-
1. ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፣
2. ልዑል አልጋወራሽ አስፋው ወሰን ኃይለሥላሴ፣
3. ልዕልት ወለተ-እስራኤል ሥዩም የአልጋወራሹ ባለቤት (ከልጆቻቸው ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴና ከእግጋየሁ አስፋወሰን ጋር)
4. ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሴ ከአምሰት ልጆቻቸው ጋር፣
5. ልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ የሐረር መሥፍን፣
6. ልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ፣
7. ልዑል ሣህለሥላሴ ኃይለሥላሴ፣
8. ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ፣
9. ልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ ፣
10. ወይዘሮ ጽጌ-ማርያም በሻህ የልዑል ራስ ካሣ ባለቤት፣ከሁለት ልጆቻቸው ጋር፣
11. ልዕልት የሻሽ ወርቅ ይልማ ፣
12. ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣
13. ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣
14. አቶ መኮንን ሀብተ ወልድ፣
15. አቶ አክሊሉ ሀብተወልድ፣
16. ደጃዝማች ከበደ ተሰማ፣
17. ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ፣
18. ልጅ አበበ አርኣያ፣
19. አባ ሓና ጅማ፣
20. ደጃዝማች ነሲቡ ዘማኔል፣
21. ደጃዝማች መኮንን እንዳልካቸው፣
22. ደጃዝማች አበበ ዳምጠው፣
23. ደጃዝማች ዐምደ ሚካኤል፣
24. ፊታውራሪ ታፈሰ ሀብተሚካኤል
25. ፊታውራሪ ተሰማ ባንቴ ፣ ወዘተ ያካተተ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡(ገብረወልድ እንድዳ ወርቅ 2000፣105-106)
ባንደው በቁጥሩ ከሁሉም ከፍተኛ የሆነ፣ ሁለመናውን ለጣሊያን ፍላጎት ያስገዛ፣የአንድነታችንና የማንነታችን አውራ ጠላት የነበረው ነው፡፡ ስም ከነበራቸው ታላላቅ ሰዎች ከሚባሉት ሁለንተናቸውን ለጣሊያን ሰጥተው ማንነታችን በእጅጉ ከጎዱት ባንዳዎች መካከል ለአብነት፣ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት፣ራስ ሥዩም መንገሻ፣ደጃዝማች አያሌው ብሩ፣ደጃዝማች ኃይለሥላሴ ጉግሳ፣አቶ አምደ ሚካኤል ደሳለኝ፣አቶ አድማሱ ረታ፣አቶ ለማ ወልደ ገብርኤል፣አቶ ተፈሪ ሻውል፣ አቶ ገብረ ወልድ እንግዳ ወርቅ፣ብላት ዳዊት እቁበ እግዚእ፣ደጃዝማች አስፍሃ ወልደ ሚካኤል፣ጄኔራል መኮንን ደነቀ፣አቶ ብርሃኑ ድንቄ፣ሻለቃ አሰፋ ለማ፣ሼክ አል ሆጆሌ፣ሡልጣን መሐመድ ሃንፋሪ፣ ደጃዝማች ሆሣዕና ጆቴ፣ ደጃዝማች ዮሐንስ ጆቴ፣ሡልጣን አብዱላሂ ጂፋር፣ሡልጣን አባ ጆቢር አብዱላሂ፣ ራስ ጌታቸው ናደው፣ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ፣አቶ ይልማ ዴሬሳ፣ብላታ አየለ ገብሬ፣ነጋድራስ ወዳጆ አሊ፣አቡነ አብርሃ፣አቡነ ይስሐቅ ( ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደ-ማርያም፣2005፣16) ደጃዝማች እጅጉ አያሌው፣ ፊታውራሪ ነገደ ዘገዬ እና አያሌ ሆድ አደር ባንዳዎች ወዘተ ይገኙበታል፡፡ ልብ በሉ! እነዚህ ሰዎች ቀደም ሲል የአገርና የሕዝብ ሚስጢሮችን ለጣሊያን በመንገር የማንነታችን አሻራዎች እንዲወድሙ ያደረጉ፣አርበኞች የሚወጡ የሚገቡበትን በመሰለል ያስገደሉ፣ ያሳሰሩ፣የአገርና የሕዝብ ሀብት ያዘረፉ፣ማንነታችን ጥላሸት የቀቡ ፣ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ክዶ ጣሊናዊ ማንነትን እንዲላበስ ኅሊናዊ ጫና ሲያሳድሩ የነበሩ የአገርና የትውልድ አውራ ጠላቶች ናቸው፡፡
ከዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ቁምነገር አለ፡፡ ባንዳዎች ወደውና ፈቅደው ነፃነታቸውንና መብታቸውን ለቅኝ ገዥው ኃይል የሰጡ ናቸው፡፡ ማንነታቸውን ክደው የቅኝ ገዥውን ሁለንተናዊ ማንነት ለመላበስ የጣሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ከወራሪው ኃይል በላይ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ናቸው፡፡ የባንዳው ኃይል፣ለፋሽስቱ ቢሮክራሲ በመረጃ አቅርቦት፣በተላላኪነት፣በሹፌርነት፣ በዘበኝነት፣በቤት ውስጥ አሽከርነት፣በአስተርጓሚነት በመሳሰሉት ሥራዎች ተሰማርቶ ይሠራ የነበር ስለነበር፣ የማንበብና የመጻፍ፣ልምድና ችሎታ እንዲያዳብር አድርጎታል፡፡ እግረ መንገዱንም ከአማርኛና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች በተጨማሪ የቅኝ ገዥ ቋንቋዎችን የማንበብና የመጻፍ ዕውቀት እንዲጨብጥ ሆኗል፡፡ ይህም የዘመናዊ ቢሮክራሲን አሠራር እንዲለማመድ በር የከፈተለት መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ስደተኛው ቡድን ተሰዶ በኖረባቸው አገሮች የዘመናዊ ቢሮክራሲን አሠራርና ሌሎች ቋንቋዎችን በተለይም እንግሊዝኛና ፈረንሣይኛን ቋንቋዎች እንዲውቅ ሁኔታዎች ግድ እንዳሉት እንረዳለን፡፡
ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ቢሮክራሲ ሲዋቀር፣ ላገር የሠሩ ሰዎች መሾም መሸለም ሲገባቸው፣በአገር ላይ የሠሩት ከሐዲዎቹና ባንዳዎቹ ተሹዋሚና ተሸላሚ ሆኑ፡፡ወሳኝ ለሆኑት ሕግ የማውጣት፣ሕግ የመተርጎምና የወጡትን ሕጎች የማስፈጸም ኃላፊነቶችን የሚረከቡ ሰዎች መመዘኛ ለኢትዮጵያዊነት ያለ ታማኝነት፣ በነፃነት ትግሉ ዘመን የተከፈለ መስዋዕትነት ሳይሆን፣ ከዘመናዊ ቢሮክራሲ ጋር ያለው ቁርኝት፣የውጭ አገር ቋንቋና የጽሕፈት ችሎታ ሆነው ቀረቡ፡፡ በዚህም የተነሳ ስደተኛውና ባንዳው ቡድን የአንበሣ ድርሻውን ወሰደ፡፡ የነፃነት ታጋዩና ዕውነተኛው ኢትዮጵዊ የበለል ተጣለ፡፡ ይህ ድርጊት ያሳዘናቸው አርበኞችም ደርጊቱን እንዲህ ሲሉ ገለጡት፡፡
አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ፤
ዳር ድንበር ጠብቀን ባቆየናት አገር፣
ውጤቱ ተረፈን ባፍንጫ መናገር፤
ይህ ስደተኛና ባንዳ ቡድን የቀሰመው ዕውቀት ከኢትዮጵያዊነት ዕሴቶች ፣ማንነት፣ባህል፣ቋንቋ፣ሃይማኖትና አጠቃላይ ሁለንተናዊ መስተጋብር ጋር ምንም ዓይነት ቁርኝት የሌለው ስለነበር የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከማንነት የሚያፋታ እንጂ፣ማንነትን የሚያዳብር ባለመሆኑ ትውልዱን ቀስ በቀስ ወደ ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ቦይ አንኮልኩሎ እንዳስገባው እናያለን፡፡ ወሳኝ የመንግሥት መዋቅሮች በባንዳዎችና በስደተኞች መያዝ፣ ባንዳነትና አገር ክዳት ወንጀል መሆኑ ቀርቶ እንደመልካም ሥራ እንዲታይ አስገደደ፡፡ ይህም በተተኪው ትውልድ አመለካካት ላይ አርበኝነት፣ለማንነት መቆምና መታግለ እርባናቢስ እንደሆነ፣በኅብረተሰቡ ውስጥ ክብርና ሞገስ የማያስቸር፣ በአንፃሩ ከሐዲነትና ባንዳነት አሹአሚና አሸላሚ መሆኑን በተጨባጭ እንዲያይ በማድረጉ ኅሊናውን ለቅኝ ተገዥነት ማመቻቸት እንዳለበት በአገሪቱ የሚካሄዱት ድርጊቶች ጠጣር ዕውነት ሆነው ታዩት፡፡በአገሪቱና በሕዝቡ አንጡራ ሀብት ወንጀለኞችና ባንዳዎች እንደፈለጉ ሲናኙበት፣ ቤተሰባቸውን ሲያስተምሩበት፣ ልጆቻቸውን ለቀጣዩ ትውልድ ገዥነት ሲያሰለጥኑበት፣ አርበኛው የበይ ተመልካች መሆኑንን በገሐድ አየ፡፡ የአርበኛው ልጆች በአባቶቻቸው ተጋድሎ የሚያፍሩ እንጂ፣ የሚመኩና የሚኮሩ እንዳይሆን ተመለከተ፡፡ ባንዳነት ማሳፈሩ ቀርቶ መኩሪያ ሆነ፡፡ አርበኝነትና አገር ወዳድነት አዋራጅና የደህነት መገለጫ ሆኖ ታዬ፡፡ ይህ ሁኔታ ትውልዱ ባንዳነትን እንደተገቢ ተግባር እንዲቆጥረው ገሐዳዊ ምሳሌ ሆኖ ቀረበ፡፡ ውጤቱም ከድል በኋላ የተዋቀረው የንጉሠ ነገሥቱ አስተዳደራዊ መዋቅርና በመዋቅሩ የተካተቱ ሰዎች ማንነት ተከታዩን ትውልድ የኅሊና ቅኝ ተገዥነትን እንዲለማመድ አመቻቸው፡፡
2. የትምህርት ፖሊስ በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ አለመመሥረት፣
በስደተኛውና በባንዳ የተዋቀረው የንጉሠ ነገሥቱ ቢሮክራሲያዊ አስተዳደር የቀየሰው የትምህርት ፖሊሲ ትውልዱ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ላይ ተመሥርቶ፣ በሂሳብ ዕውቀት ላይ መሠረቱን የጣለ፣ለምርምርና አዳዲስ ቴክኖሎጂን አፍላቂ በሚሆንበት መልኩ እንዲሆን አላደረገም፡፡ የትምህርት ፖሊሲው ትውልዱን ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ፈጽሞ የሚያፋታ፣የራሱን ማንነት እየናቀ የሌሎችን አድናቂና ተከታይ በሚያደርግ መልኩ የተቀየሰ ነበር፡፡ ሥርዓተ ትምህርቱ ለፈረንሣና ለእንግሊዝኛ ቋንቋዎች፣እንዲሁም ለማኅበራዊ ሣይንሶች ልዩ ትኩረት የሰጠና ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ለዘመናት ይዛው ከመጣችው አሠራር ጋር የማይገናኝ ስለነበር፣ ትውልዱ ውጭ አምላኪና የራሱን ማንነት ሳያውቀው ቀስበቀስ እያወለቀ እንዲጥል ሠፊ በር ከፈተለት፡፡ ይህም በመሆኑ፣ “የዐዳም ቋንቋ እንደሆነ የሚነገርለት፣እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደተነጋገረበት ብዙ” የሚባልለት የግዕዝ ቋንቋ ከትምህርት ቤትና ከመንግሥት ብቻ ሳይሆን በቤተክረስቲያንም አገልግሎት ሊሰጥበት ከማይቻልበት ደረጃ ተደሷል፡፡ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣ባህል፣ሥነ-ምግባርና አመለካከት በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ባለመካተቱ ፣ወጣቱ ትውልድ የእርሱ የሆነውን ወርቁን ነገር እየጣለ፣ የርሱ ያልሆነውን ኩበቱን ሙጭጭ ብሎ እንዲያዝ ተነገረው፡፡የኢትዮጵያዊነት ልዩ መታወቂያ የሆነው የጽሑፍ ቋንቋ አማርኛ ቀስበቀስ ከትምህርት መገናኛነቱ እንዲወጣ ተደረ ፡፡ የትምህርቱ ይዘት የኢትዮጵያን ባህል፣ታሪክ፣መልከዐ-ምድር፣ቋንቋ፣ ሥነ-ልቦና፣የሕዝብ አደረጃጀትና የአጠቃላይ ማኅበራዊ ግንኙነት ምንነትን ፈጽሞ ግንዛቤ ያስገባ አልነበረም፡፡
የታሪክ ትምህርት ስለግሪክ፣ስለአውሮፓ፣ስለሮም ፣ስለሜሶፖታሚያ፣ስለግብፅ፣ ወዘተ እንጂ፣ ስለኛው ረጅምና አኩሪ ታሪክቻችን፣ስለአርበኞቻችን ማንነትና ተጋድሎ የሚያወሱ ትምህርቶች ለትውልዱ አይሰጡም ነበር፡፡አባቶቻችን ከፖራቹጋሎች፣ከቱርኮች፣ከመሐዲስቶች፣ከግብፆች፣ ከጣሊያኖችና ከአውሮፓ ኃያላን ጋር ስላደረጉት የነፃነትና ማንነትን የማስከበር ተጋድሎ፣የተጋድሎው መሪ ተዋንያን ማንነት ትውልዱ እነዲያወቅ አልተደረገም፡፡ የነካሌብን፣የነኢዛናን፣የነላሊበላን፣ የነዘርዐ-ያዕቆብ፣የነሠርጸድንግል፣የነዐምደ-ጽዮን፣የነልብነድንግል፣የነገላውዲዮስ፣የነቴዎድሮስ፤የነዮሐንስና የነምኒልክ ወዘተ ፖለቲካዊና ወታደራዊ የአመራር ጥበብና ችሎታ፣የነገብርዬ፣የነአሉላ አባነጋ፣የነሀብተጊዮርጊስ ዲነግዲ፣የነገበየሁ ተክሌ የነኮሎኔል አቢሳ አጋ የጦር ሥልትን ዲፕሎማሲያዊ ጥበብ ወዘተ ታሪክ ትውልዱ በቅጡ እንዲያውቀውና እንዲመካበት አልተደረገም፡፡ እንኳን ያን ጊዜ ዛሬም የለም፡፡
የመልከዐ-ምድሩ(ጂኦግራፊ) ትምህርት ስለዓለምና አሕጉሮች እንጂ ፣ስለኢትዮጵያ ወንዞችና ተራሮች፣ ማዕድን፣የውኃ ሀብት፣ የአየር ጠባይ፣የእንስሳት ሀብት፣የመንግሥት ኃላፊነትና ግዴታ፣የሕዝብ መብትና ግዴታ፣ ወዘተ በየደረጃው የሚሰጡ አልነበረም፡፡ የትምህርቱ አጠቃላይ ዓላማ ወደ ውጭ የሚያይ እንጂ፣ ወደ ውስጥ ማሳየት የማይችል ስለነበር፣ትውልዱ ወደ ውጭ እንጂ ወደ ውስጥ እንዲመለከት አላስቻለውም፡፡ ወደ ውጭ መመልከት ደግም፣ማንነትን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ሌላ ማንነትን ለመላበስ የሚያመቻች በገዛ ፈቃድ ለቅኝ ተገዥነት ራስን ማመቻቸት እንደሆነ በተጨባጭ እያን ነው፡፡ በትምህርቱ ውስጥ የሚካተቱት የመልካም ነገሮች ማመላከቻዎች ኢትዮጵያዊ አለመሆን፣ትውልዱ የራሱ የሆነ፣የተሻለ ነገር እንዳለው ሊገነዘብ ባለመቻሉ፣በተነገረው ምሳሌና ማነፃፀሪያ መሠረት አሻግሮ እንዲመለከት ግድ አለው፡፡ በመሆኑም የ1960 ዎቹ ለውጥ ናፋቂ የነበረው ትውልድ የሽምቅ ውጊያን ከቴዎድሮስ ፣ከምኒልክ፣ከዮሐንስ ከነአሉላ፣ገብርዬ አቢሳ አጋነ፣ አበበ አረጋይ ወዘተ ለመቅሰም ባለመቻሉ የተከተለው የማኦን፣የሆቺሚንንና የቼጉቬራን የሽምቅ ውጊያ ስልት ነበር፡፡ የዘመረውም “ፋኖ ተሰማራ ፣እንደነ ሆቺሚን እንደቼጉቬራ” ሲል ነበር፡፡ የአገሩን ፋኖዎች ልዩ ዕውቀትና ችሎታቸውን ባለማወቁ በቃል በተነገረውና ተጽፎ ባገኛቸው በውጭዎቹ ሰዎች ማንነት ተከታይ ለማፍራት ቀሰቀሰባቸው፡፡ይህም ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት ራሱን እንዲያመቻች እንዳደረገው መገንዘብ ይቻላል፡
በሌላ በኩል፣ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጪ የሚላኩት ፣ ወጥ በሆነ መንገድ ላገሪቱ የሚያስፈልጓትን ሙያተኞች ከራሷ ፍላጎት አኳያ በምትፈልገው የዕውቀት መሥክ የሚሰለጥኑ አልነበሩም፡፡ የሚሰለጥኑት በየግለሰቦቹ ፍላጎትና የትምህርቱን ዕድል በፈቀደው መንግሥት ፕሮግራም መሠረት እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህም በመሆኑ፣ሰልጣኞቹ የሚሰለጥኑት ከአገራቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ግንኙነት በሌላቸው፣የትምህርቱን ዕድል በሰጡ አገሮቸ የትምህርት ፖሊሲ ላይ የተመሠረቱና ከነዚያ አገሮች ታሪክና ባህል፣እንዲሁም ሊደርሱበት ወደ አለሙት ግብ ሊያመራ በሚችል መልኩ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ሠልጣኞቹ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ ተመሳሳይ የፖሊሲ አቅጣጫ ለመንደፍም ሆነ ለማስተማር ግብቡ አልነበሩም፡፡ ፈረንሣይ፣ምዕራብ ጀርመን፣እንግሊዝ፣አሜሪካ፣ሶቭዬት ኅብረት፣ምሥራቅ ጀርመን፣ቼኮዝሎቫኪያ፣ቡልጋሪያ፣ሀንጋሪ፣ዩጎዝላቪያ፣ጣሊያን፣ ወዘተ የተማሩት ለየቅል ቆሙ፡፡ ልዩነታቸው በተማሩበት አገር ብቻ ሣይሆን፣በተማሩበት ተቋምና በተማሩት የትምህርት ዓይነት ጭምር ሆነ፡፡ ይህ ልዩነት ደግሞ እንደ ኢትዮጵያዊነት፣ከኢትዮጵያዊነት ዕሴቶች ተነስቶ፣ኢትዮጵያ ጠቀም ወደ ሆነ አስተሳሰብ ለማምራት መንገዱን ዘጋው፡፡ ከዚህ ላይ ርዕዮተዓለማዊ ልዩነት ተርከፍክፎበት ከድል በኋላ ቀለም የቆጠረው ትውልድ ኢትዮጵያን በየራሱ ፍላጎት በመሳል፣ “እኔ ለኢትዮጵያ የተሻለ አስባለሁ፣ከእኔ ውጭ ያሉት ትክክል አይደሉም” ብለው እንዲያስቡና እርስ በራሱ እንዲጠፋፋ መንገዱን አመቻቸ፡፡ የመጠፋፋቱ ግብግብ በከፋ መልኩ መቀጠል ትውልዱ የእርሱነቱ መታወቂያ የሆነች አገሩን እየሸሸ በመገደድና በመውደድ ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት ራሱን እንደዳረገ በገሀድ እያየን ነው፡፡
3. የአዲስ ገብ ሃይማኖቶች መሥፋፋት፣
ማንም የኢትዮጵያን ሕዝብ ታሪክ የመረመረ ሰው ሊገነዘበው እንደሚችል፣የሕዝቡ መሠረታዊ ሃይማኖቶች፣ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፣ሱኒ እስልምና፣አይሁድና ባህላዊ እምነቶች ናቸው፡፡ እንዚህ ሃይማኖቶች አንዱ በሌላው ውስጥ ያለ በመሆኑ፣ኢትዮጵያዊ ማንነትን ፣የአገርና የቤተሰብ ፍቅር፣ነፃነትና አልበገርም ባነይነት፣ በኢትዮጵያዊነት መመካትና መኩራት ልዩ ዕሴቶቻቸው አድርገው የተቀበሉና ለነርሱም ዳብሮ መቀጠል የየእምነቶቹ ተከታዮች አይከፍሉ መስዋዕትነት በጋራ እየከፈሉ የኖሩ መሆኑ ግልጥ ነው፡፡
ከድል ኋላ “ሃይማኖት የግል ነው፣ አገር የጋራ ነው “ በሚለው የንጉሠ ነገሥቱ የሃይማኖት ፖሊሲ ምክንያት በርካታ አዳዲስ ሃይማኖቶች ወደ አገራችን እንዲገቡ ሠፊ በር ከፈቱ፡፡ ቀደም ሲል ገብተው የነበሩትም ተልዕኮአቸውን ያላንዳች ሥጋት እንዲወጡ ሁኔታዎች የበለጠ ተመቻቸላቸው፡፡ “ገንፎ ሲያምርበት ተንከባሎ ከቅቤ ማሰሮ ይገባል” እንደሚባለው ሆኖ፣ ቀደም ሲል በሃይማኖት፣በአገር አሳሽነት፣በመሬት ግዥና በቀጥታ ወረራ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለማድረግ ያልቻሉ ኃይሎች ፣ ሕዝቡ ወዶና ፈቅዶ የኅሊና ቅኝ ተገዥ የሚሆንበት መንገድ በስፋት ተከፈተላቸው፡፡ ንጉሠ-ነገሥቱ ኢትዮጵዊነትን መጠበቅ የሚያስችል ስልት ሳይነድፉ፣ በሃይመኖት ነፃነት ስም ትውልዱ ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት የሚመቻችበትን መንገድ በስፋት ከፈቱ፡፡ በመሆኑም በርካታ የሃይማኖት ድርጅቶች ወደ አገራችን ገቡ፡፡
አዲስ ገቦቹ ሃይማኖቶች ቀደም ሲል ቅኝ ግዛትን ለማስፋፋት በአፍሪካና በእስያ የተሠማሩ ስለነበሩ የተጠናከ መዋቅር፣በከፍተኛ የመረጃና የሰው ኃይል የተደራጁ ከመሆናቸውም በላይ፣ የቅኝ ገዥ ኃይሎች መዋዕለ ንዋይ በገፍ የሚጎርፍላቸው በመሆኑ ነባሮቹ ኢትዮጵያዊ ሃይማኖቶች ከሚሰጡት መንፈሳዊና ሥጋዊ አገልግሎቶች በላይ ለሕዝቡ በስፋት መስጠት ጀመሩ፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው በሙዚቃ ፣በጭብጨባና በዳንስ የታጀበ በመሆኑ የአድማጮችን ኅሊና በቀላሉ ሳበ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቱ፣ዝማሬውና ሽብሸባው በተጓዳኝ፣ የአውሮፓን ታሪክና ስልጣኔ፣ ሕዝቡ የደረሰበትን የዕደገት ደረጃ የሚያሳዩ ፊልሞችን በብዛት አሰራጩ፡፡ ኢትጵያውያንን የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች የሚያደርጉበትን ሁነኛ መሣሪያ የሆነውን የዘመናዊ ትምህርትን ከሃይማኖት ጋር አቀላቅለው የሚያስተምሩበትን የትምህርት ሥርዓት ዘረጉ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በነፃና አልፎ አልፎም በተመጣጣኝ ክፍያ የሕክምና አገልግሎት መሥጠት ጀመሩ፡፡ ዘወትር እሑድ የዕለት ምግብ አጥተው ለሚራቡ ሰዎች የምግብ ፕሮግራም ዘርግተው መመገብ የዘወትር ተግባራቸው አድርገው ያዙት፡፡ የዓመት ልብስ ለሌላቸው የአውሮፓና የአሜሪካ ልባሾችን እየሰበሰቡ በነፃ በማደል እርቃናቸውን እንዲከልሉ አደረጉ፡፡ “ይህም የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል” እንዲሉ ሆኖ፣የበርካታ ሰዎችን ኅሊና እንዲገዙ አስቻላቸው፡፡
ነባሮቹ ሃይማኖቶች አማኙ የሚከተላቸው በመወለድ እንጂ፣በመማር ካለመሆኑም ሌላ፣ሃማኖቶቹ እንዲስፋፉ የሚያስችል የአደረጃጃት፣የሰው፣ የገንዘብና በዕወቀት ላይ የተመሠረተ የመረጃ ፍሰትና ልውውጥ አቅም የሌላቸው በመሆኑ ፣ከአዲስ ገቢዎቹ ሃማኖቶች ጋር ከታሪክ ርዝመት አንፃር ሲመዘን አቻ ለመሆነ ቀርቶ ለመከተል እንኳ እንዳልቻሉ ሁኔታዎች ያሳሉ፡፡
የአዲስ ገብ ሃይማኖቶቹ መሠረታዊ ተልዕኮ ሕዝቡ የኢትዮጵያዊነት ማንነቱ መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቹን ቀስ በቀስ በፈቃዱ አውልቆ ጥሎ የአውሮፓዊ ማንነትን ጥብቆ እንዲያጠልቅ በመሆኑ፣ባቋቋሙዋቸው ትምህርት ቤቶች የተማሩትንና ብሩኅ አዕምሮ ያላቸውን በስኮላር ሽፕ መልክ ወደ አውሮፓና አሜሪካ በመላክ አውሮፓዊና አሜሪካዊ አስተሳሰብና አመለካከል አዳብረውና ይዘው እንዲመለሱና መልስው ወገናቸውን በነርሱ ሥር እንዲሰለፍ እንዲያደርጉ አደራጁዋቸው፡፡ ”እስ በሱ ሥጋን በኩበት ጠበሱ” እንዲሉ፣መልሰው የገዛ ወገኖቻቸውን የራሳቸውን ማንነት ትተው ሌላ ማንነትን እንዲላበሱ እንዲሰብኩና እንዲያስተምሩ አደረጉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በከፈቱዋቸው የጤና ጣቢያዎች የቀጠሩዋቸውን ሰዎች ወደ ውጭ በመላክ ህክምናን ከሃይማኖት ዕውቀት ጋር አጣምረው የሚሠሩ ሰባኪና ሐኪሞችን በብዛት አሰለጠኑ፡፡ በዚህ የተጠናከረ ሂደት የደቡብ፣የምዕራብ፣የደቡብ ምዕራብና የመሀል ኢትዮጵያ ነዋሪ ነባር ሃይማኖቱን እየተዎ የአዲስ ገብ ሃይማኖቶች ተከታይ ሆነ፡፡ ይህም ያለጥርጥር ኢትጵያዊው ኅሊናውን ለቅኝ ተገዥነት ወዶ እንዲያመቻች እንዳደረገው መገንዘብ ይቻላል፡፡ የተግንጣይ ብሔርተኞች ድርጅቶች መሪዎች ተኮትኩተው ያደጉት በነዚህ የአዲስ ገብ ሃይማኖቶች ባቋቋሟቸው ትምህርት ቤቶች መሆኑን ልብ ስንል፣እነዚህ ሃይማኖቶች የቱን ያህል ሕዝቡን ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት እንዳመቻቹት እንረዳለን፡፡
4. የኢትዮጵያ አብዮት ያስከተለው የኅሊና ስብራት፣
ሚሽነሪዎቹ በቂ ተከታይ ማግኘታቸውን ካረጋገጡ በኋላ፣ሕዝቡ በኅሊና ቅኝ ተገዥነት ሥር ወዶና ፈቅዶ ለዘመናት መኖር የሚችለው የትኞቹን ተቋሞች ብናፈርስ ነው/ እንዚህን መዋቅሮችስ እንዴት እናፈርሳለን/ በሚል ጥናት ላይ ተሰማሩ፡፡ በዚህ ጥናታቸውም የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መሠረትና ምሰሶ የሆኑ ተቋሞችን ምንነት ለይተው በማወቅ ተቋሞቹ ሊፈርሱባቸው የሚችሉባቸውን መንገዶች የሚያሳዩ መጽሐፍትን በጥናትና ምርምር ስም ለዓለም አሰራጩ፡፡ የሃይማኖት ተከታዮቻቸውም እንዚህን በኢትዮጵያ መሠረታዊ ጠላቶች ማር ቀብተው ያዘጋጁዋቸውን በርዞች እንደ ደረቅ ሐቅ በመውሰድ ያላንዳች ማመዛዘንና አድሮ እየው ጥያቄ ዋጡዋቸው፡፡
ሚሽነሪዎቹ ባደረጉት ጥናት የኢትዮጵያዊነት መሠረት የሆኑት ተቋሞች “የሥልጣን ምንጭና የአንድነት ምልክት የሆነ ዘውዳዊ ሥርዓት፣የዘውዳዊ ሥርዓቱ ርዕዮተ-ዓለማዊ ክንድ የሆነ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት እና ራሱን በቋንቋ ትስስር ያላደራጀ፣ በመሠረታዊ አደረጀደጀት ደረጃ በአጥቢያ ቤተ እምነቶች ዙሪያ የሚደራጅ፤ከፍ ሲል በአስተዳደራዊ ክልሎቸ ማንነቱን የሚገልጥ፣በሠፊዋ ኢትዮጵያ በበቂ መጠን ተሰራጭቶ የሚኖርና በኢትዮጵያዊነት በጽኑ የሚያምን፣በተፈጥሮው ተዋጊና የአገር ዘብ የሆነ ዐማራ የተሰኘ ነገድ እንደሆኑ ተረዱ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ብሔርተኝነትም ሲባል የዐማረው እንጂ፣የሌሎችን ነገዶች የሚጨምር አይለም፣ኢትዮጵያዊነት በሌሎች ላይ ዐማራው የጫነባቸው ዕዳ ነው ሲሉም ጨመሩበት፡፡” እነዚህ ተቋሞች ካልጠፉ ወይም በሕዝቡ ላይ የሚያሳድሩት ሁለንተናዊ ተፅዕኖ ካልተወገደ ኢትዮጵያን በውጭ ኃይሎች ሥር ለማዋል እንደማቻል እርግጠኛ ሆኑ፡፡
ተከታዩ ሥራቸው እንዚህን ተቋሞች እንዴት ማጥፋት ይቻላል? በሚለው ዙሪያ ወጥሮ መሥራት ነበር፡፡ ባደረጉት ጥረትም የነርሱን ዓላማ የሚጋሩ ብቻ ሳይሆን፣ብዙ ማይል ርቀው የኢትዮጵያን የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ በመቶ ዓመት የገደቡ ብሔርተኛ ግለሰቦችንና በሚሽነሪ ትምህርት ቤቶች በፀረ ኢትዮጵያነት ተኮተረኩተው ያደጉ በርካታ ሰዎችን አገኙ፡፡ እንዚህን ግለሰቦች በተለያዩ መሰባሰቢያ መድረኮች ስም እንዲደራጁና የሰው ኃይል እንዲያሰባስቡ፤ፍላጎታቸውን በየጸሎት ቤቱና ባመቻቸው አጋጣሚ ሁሉ እንዲያሰራጩ አበረታቱ፡፡የኦነግ መሠረት የሆነው የሜጫና ቱሉማ ማኅበር የተመሠረተው በዚህ መልክ ሲሆን፣ የኦነግ መሪዎችም ወለጋ ጊንቢ አውራጃ ውስጥ በተከፈተ የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮችና ተማሪዎች በነበሩ ግለሰቦች መሆኑን ስንገነዘብ የአዲስ ገብ ሃማኖቶች ተልዕኮ ምን እንደነበር በቅጡ ልንገነዘብ እንችልለን፡፡ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ድርጅት የተመሠረተውም በትግራይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበር ስም እንደሆነ ይታወቃል፡፡የወያኔ መሥራቾችም በዐድዋ አውራጃ ተወላጆች መያዝ ፣ ዐድዋ ከተማ ውስጥ ከነበረ የሚሽነሪ ትምህርት ቤት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ እንደነበር እንረዳለን፡፡ ከሁሉም በላይ መያዝ ያለበት መሠረታዊ ጉዳይ የብሔረሰብ ጥያቄ አንስተው የተደራጁ ብሔርተኛ ሰዎች የባንዳ ልጆች መሆናቸው ነው፡፡ሚሽነሪዎቹ በዚህ መልክ አደራጅተው ኢትዮጵያን ለመናድ በሚጥሩበት ወቅት ፣ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ከ1960ዎቹ መባቻ ጀምሮ ማርክሳዊ-ሌኒናዊ ርዕዮተዓለምን በተቀበሉ ቡድኖች አቀንቃኝነት የሚያራምዱት የፍትሕና የዲሞክራሲ ጥያቄ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ጊዜ ነበር፡፡ በሁለቱ ወገኖች እንቅስቃሴ የሚፈልጉትን ሳያሟሉ ወይም ሳያገኙ ፣ የየካቲት 1966ዓ.ም ሕዝባዊ አብዮት በድንገት በሕዝብ ብሶት ፈነዳ፡፡
የሕዝቡን ቁጣና ብሶት መሠረታዊ ምክንያቶች በቅጡ ለይቶና አውቆ፣ ሕዝባዊው አብዮቱ በኢትዮጵያዊነት ማንነት ላይ መሠረቱን ጥሎ ወደ ፊት መጓዝ የሚችልበነትን መንገድ የሚያመቻችና የሚመራ ሕዝባዊ ኃይል በወሳኝነት መልኩ ሳይወጣ የፈነዳው አብዮት፣ቅኝ ገዥ ኃይሎቹ ባላሰቡትና ባልጠበቁት ፍጥነት የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ፣ የአንድነትና የሥልጣን ምንጭ የነበረው ዘውዳዊ ሥርዓት በራሱ ዐወቅን ባይ ልጆች እንዲወድም ተደረገ፡፡ የቅኝ አገዛዝ ተልዕኮን አንግበው በሃይማኖት ስም ወደ አገራችን የገቡ ሰዎች የመጀመሪያ ዓላማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሳካለቸው፡፡ ተያይዞም የኢትዮጵያዊነት መሠረታዊ ተቋምና የዘውዳዊ ሥርዓቱ ርዕዮተ ዓለማዊ ክንድና የበርካታው ሕዝብ መንፈሳዊ መሪ የነበረው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በመንግሥትና በሕዝብ ውስጥ የነበረውን ከፍተኛ ኃላፊነት አሳጣ፡፡ ቀሪው ተግባር እምብዛም አድካሚ የማይሆንባቸው የቁልቁለት መንገድ የሆነው፣ሌሎችን ብሔረሰቦች በዐማራው ላይ በጠላትነት ማስነሳትና እርስ በርሳቸው በማበጣበጥ የወል ዕሴቶቻቸውን በራሳቸው በማሳጣት፣ የቅኝ ገዥዎችን ማንነት እንዲላበሱ የማድረጉ ነው፡፡
ለዚህ ተግባርም ትውልዱ ምቹ ሆኖ ቀረበላቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ዐማራው ራሱን ለእርድ አመቻችቶ ቀረበ፡፡ ሌሎቹ በአዲስ ገብ ሃይማኖቶች ተኮትኩተው ያደጉ የሌሎች ነገድ አባል ልጆች ዐማራውን በጠላትነትና በቅኝ ገዥነት ፈርጀው እንደሚመለከቱትና ሊያጠፉት በዝግጅት ላይ ያሉ መሆናቸውን የዐማራው ቀለም ቀመስ ትውልድ አልተረዳም፡፡ ቀደም ሲል ኤርትራን ለመገንጠል የተደራጀው የጀብሃ እና የሻዕቢያ ቡድኖች ፀረ-ዐማራ መሆናቸውን ፈጽሞ የተገነዘበ አልነበረም፤ ይህ ብዥታ ዛሬም የጠራ አይደልም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ኦሮሞን እገነጥላለሁ የሚል ቡድን በመካከሉ ያቆጠቆጠ መሆኑን የዐማራው ነገድ ምሁራን ልብ አላሉም፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ሕዝባዊ አብዮቱን ለመምራት በተነሳ የሥልጣን ጥያቄ ኢትዮጵያውያን አግባቢ መልስ ላይ ለመድረስ አልቻሉም፡፡ ሁሉ ባፈተተው ተጓዘ፡፡ በጉዞው በርካታ ፀረ-ዐማራና ፀረ- ኢትዮጵያ የሆኑ ድርጅቶች በቅኝ ገዥዎች ፍላጎት ላይ ተመሥርተው ተደራጁ፡፡ ነባሮቹ ጀብሓና ሻዕቢያ፣ሕወሓት፣ ኦነግ፣እስላሚያ ኦሮሞያ፣የኦጋዴን ነፃ አውጭ፣የአፋር፣የጉራጌ የከምባታ፣የወላይታ፣ የሲዳማ፣ ወዘተ እንደ አሸን ፈሉ፡፡ በሌላ በኩል ኅብረ-ብሔራው ድርጅቶች እንደ መኢሶን፣ኢሕአፓ፣ኢዲኅ፣ወዝሊግ፣አብዮታዊ ሰደድ፣ማሌሪድ፣ኢጭአት፣ የመሳሰሉት ተፈጠሩ፡፡ጉዞው ግን ቀላል አልሆነም፡፡ ብዙ ሕይዎትን የጠየቀ፣ማንነትን በእጅጉ የሚፈታተን፣ መወለድን የሚያስጠላ ሆነ፡፡ በዚህ ጉዞው ውስጥም የውጭ ድጋፍ በማግኘት የበላይነትን እናገኛልን በሚል ስሌት ኢትዮጵያውያን ራሳችን ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት አመቻቸን፡፡ የጉዞው ክፋት ያስከተለው ተስፋ መቁረጥ የናቅነውንና አባቶቻችን ድል ነስተው የመለሱትን ቅኝ ገዥ ኃይል ለምነንና ደጅ ጠንተን ቅኝ ተገዥ ለመሆን ስደትን እንድነመርጥ አደረገን፡፡ ይህ አጠቃላይ ሁኔታም ኢትዮጵያውያን ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት እንድንዳረግ አድርጎናል፡፡
በሌላ በኩል፣በአገሪቱ የተለያየ ዓላማና ግብ ይዘው፣በብሔርና በኅብረ-ብሔር ስም የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች የጠላትነት ደረጃውንና ስሙን ይለዋውጡት እንጂ፣ሁሉም የዐማራውን ነገድ “በገዥ መደብና በጨቋኝ ብሔርነት” በመፈረጅ የጥፋት ክንዳቸውን አነሱበት፡፡ በነገዱ ላይ በእርዳ ተራዳ ከደረሰበት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅምና መብት ነጠቃ በተጨማሪ፣በኢትዮጵያ ምድር ሠርቶ የመኖር መብቱን እንዲነጠቅ ሆነ፡፡ ስልታዊ በሆነ መንገድ በተከፈተበት የዘር ማጽዳት ዘመቻም ባለፉት የወያኔ አገዛዝ 2.4 ሚሊዮን ሕዝብ የደረሰበት አለመታወቁን የራሱ የወያኔ ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ባለሥልጣን ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህም ቅኝ ገዥዎች ኢትዮጵያን በፈለጉት መንገድ በቁጥጥራቸው ሥር ለማዋል እንቅፋት ሆነውብናል ያሏቸውን ተቋሞች “እሾህን በሾህ “ እንዲሉ ራሳችን፣እራሳችንን እንድናጠፋና የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች እንድንሆን እንዳደረጉን እያየን ነው፡፡ በዚህ ራስን በራስ የማጥቃት ሂደት ውስጥ ከዐማራ ነገድ ውጭ ያሉ ምሁራን በዘር ተደራጅተው የዘራችን አውራ ጠላት ነው ብለው በፈረጁት የዐማራ ነገድ ላይ የጥፋት ክንዳቸውን ሲያነሱ፣የዐማራው ነገድ ምሁራን ራሱን አደራጅቶ ዘሩን ከጥፋት ለመከላከል ካለማሰቡም ሌላ፣የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አባል በመሆን በራሱ ነገድ ላይ የጥፋቱ ተባባሪ ሆኖ ይታያል፡፡ ለአብነት ያህል በኅብረ ብሔራዊ ድርጅቶች ውስጥ ተደራጅተው የነበሩት የዐማራው ምሁራን የገዥ መደብ ነው ብለው በፈረጁት ዐማራ ላይ ያለፍርድ ሂደት አያሌ ዐማሮች ንብረታቸውንና ሕያዎታቸውን እንዲያጡ አድርገዋል፤ ተባብረዋል፡፡ ይህ ነው እንግዲህ “እስ በሱ ሥጋን በኩበት ጠበሱ” የሚያሰኘው፡፡
5. የኅሊና ቅኝ ተገዥነት የሚገልጽባቸው መልኮች፣
የቅኝ ገዥነት መሠረታዊ ግብ የቅኝ ተገዢውን ቋንቋ፣ባህል፣ሃይማኖት፣ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት፣ተቋሞች፣አጠቃላይ ሁለንተናዊ ማንነትን ማስለወጥና የቅኝ ገዥውን ቋንቋ፣ባህል፣ሃይማኖት፣ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት፣ተቋሞችና ማንነት መተካት ነው፡፡ይህም በሁለት መልኩ ተግባራዊ እንደሚሆን የቅኝ አገዛዝ ታሪክ ያስተምረናል፡፡ እነዚህም አካል እና ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ናቸው፡፡ አካላዊ ቅኝ ተገዥነት ከአቅም በላይ በሆኑ አስገዳጅ ምክንያቶች፣ ቅኝ ተገዥ ወገኖች፣ በቅኝ ገዥው ኃይል ሁለንተናዊ ፍላጎት ቁጥጥር ሥር የሚውሉበት ሁኔታ ነው፡፡ አካላዊ ቅኝ ተገዥነት በእንስሳና በሰዎች መካከል ባለግንኙነት መመሰል ይቻላል፡፡ ቅኝ ተገዥው ለአገልጋይነት፣ቅኝ ገዥው ለተገልጋይነት የተፈጠሩ ዓይነት ሆነው የሚታዩበት ነው፡፡ ይህ ግንኙነት በውዴታ፣ወይም በተፈጥሮ ሕግ የተገዛ ባለመሆኑ፣ በቅኝ ተገዥው ኅሊና ውስጥ ምንጊዜም የማይጠፋ፣ጊዜና አጋጣሚን የሚጠብቅ የታመቀ አመጽ የቋጠረ ነው፡፡ አመጹ በራሱ ወይም በተከታዩ ትውልድ ለመቀስቀስ የሚያስችልና ለተቀሰቀሰው አመጽም የሞራል፣ የተፈጥሮና የሰው ሠራሽ ሕግ ጊዜ የማይሽረው ድጋፍ ያለው ነው፡፡ ስለሆነም አካላዊ ቅኝ ተገዥነት የሁለንተናዊ አቅም ማጣት ወይም ማነስ የሚያስከትለው በመሆኑ ቅኝ ተገዥው ማንነቱን ከውስጡ አያጠፋም፡፡ የእርሱነቱ መገለጫዎችን በልዩ ልዩ ዘዴዎች ለትውልዱ ያስተላልፋል፤በሚስጢር ይጠብቃል፡፡ የቅኝ ገዥዎች የሆኑ ማናቸውንም ነገሮች በውስጡ ይጠላቸዋል፤ይጠየፋቸዋል፤ይንቃቸዋል፡፡
ለምሳሌ ሕንዶች ከመቶ አምሳ ዓመታት ያላነሰ በእንግሊዞች ተገዝተዋል፡፡ ባህላቸውን፣ቋንቋቸውን፣እምነታቸውን እንዲለውጡ አያሌ ማስገደጃዎች ጭነውባቸው እንደነበርም ይታወቃል፡፡ ሆኖም፣ ሕንዶች የተጣለባቸውን ጫና ተቋቁመው፣ባሕላቸውን፣ቋንቋቸውንና ሃይማኖታቸውን አስጠብቀው ለነፃነት በቅተዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እስራኤላውያን ከሁለት ሺህ ዓመታት በላይ በኃይል አገራቸውን ተገደው በዓለም አገሮች እንደጨው ተዘርው ሲኖሩ፣ ቋንቋቸውንና ሃይማኖታቸውን በሰው አገር አሰጠብቀው አገር ለመመሥረት ችለዋል፡፡ በሌሎች በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር የነበሩ አገሮችም የምናየው ተመሳሳይ ነው፡፡ከዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን መሠረታዊ ጉዳይ የትኛውም ዓይነት ቅኝ አገዛዝ ግቡ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው፣ የቅኝ ተገዥዎችን ባህል፣ሃይማኖት፣ቋንቋ፣ታሪክና አጠቃላይ ማንነትን አስጥሎ፣ የቅኝ ገዥውን ሁለንተናዊ ማንነት እንዲላበስ ማድረግ መሆኑን ነው፡፡
በአንፃሩ ኅላናዊ ቅኝ ተገዥነት በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች በቡድን ወይም በተናጠል የራሳቸውን ማንነት በገዛ ፈቃዳቸው በመተው የሌሎችን ማንነት መላበስ ነው፡፡ የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ራስን በራስ ሰቅሎ በመግደል ይመሰላል፡፡ ራሱን ሰቅሎ የሞተሰው በክርስቲያን ሃይማኖት ፍታት አይፈታም፤ ነፍሱም እንደማትማር የሃይማኖቱ ሕግ ያስተምራል፡፡ ይህም ማለት ራስን በራስ መስቀል የሞራል፣ የተፈጥሮና የሰው ሠራሽ ሕጎች ድጋፍ የለውም ማለት ነው፡፡ በተመሣሣይ መልኩ፣ራሱን ወዶ ለቅኝ ተገዥነት ያቀረበና የተገዛ ሰው በውስጡ በራሱ ቁጭት የለውም፤ ወዶ ውርደትን የተቀበለ በመሆኑ፣ውርደቱ አይሰማውም፣ባለመሰማቱም ነፃ ለመውጣት አያስብም፤ ቢያስብም የሞራል፣የሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ሕጎች ድጋፍ አይኖረውም፡፡ የሚገፋፋው ውስጣዊ ምክንያት የሌለው በመሆኑም፤ለተከታዩ ትውልድ የሚያቀብለው ነገር ስለሌለው ትውልዱ የወላጆቹን ይዞ እንዲቀጥል ይገደዳል፡፡ ስለሆነም የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ከአካላዊ ቅኝ ተገዥነት እጅግ የከፋ ነው፡፡ የከፋ የሚሆነው ወዶ የተቀበለው በመሆኑ፣መውጫ ቀዳዳ የሌለው መሆኑና ቅኝ የተገዛላቸው ፣ቅኝ በመገዛቱ የሚንቁት እንጂ፣የሚያከብሩት አለመሆኑን አለመገንዘቡ ነው፡፡ በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ የአካላዊና የኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ምንነት በመጠኑም ካየን፣ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት የሚገለጥባቸው መልኮች ምን እንደሆኑ ማየቱ፣የኅሊናን ቅኝ ተገዥነት በተጨባጭ በእኛ ሁኔታ ለማየት ያስችለናል፡፡
ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት በሚከተሉት መልኮች ራሱን ይገልጻል፡፡
(1) በባህል፣ (2) በስም፣ (3) በቋንቋ፣ (4) አገርን በመጥላት፣ (5) በስደት፣
1. ባህል፡- ባህል የሰው ልጅ በማምረት፣በማከፋፈልና በመጠቀም ሂደት ውስጥ፣ ሰዎች ከሰዎች እና ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር በሚፈጥሩት መስተጋብር ተገቢና ትክክል ነው ብለው በተደጋጋሚ በግልና በቡድን የሚፈጽሙት ተግባር ነው፡፡ አመራረት፣አመጋገብ፣በዐላት አከባበር፣ሰላምታ አሰጣጥ፣አለባበስ፣ደስታና መከራ የሚገለጽባቸው መንገዶች( ዘዴዎች) ፣የጋብቻ ሥርዓት፣ ምግብ አዘገጃጀት፣የአመጋገብ ሥርዓት፣ወዘት ባህል የሚገለጽባቸው ናቸው፡፡
ከነዚህ የባህል መከሰቻ መልኮች ውስጥ ኢትዮጵያውያን ብዙም ያለወጥነውና አጥብቀን የያዝነው የምግብ አዘገጃጀታችን፣ አመጋገባችንና ሃይማኖታዊ የበዐል አከባበር ሥርዐታችን ነው፡፡ አለባበሳችን በአብዛኛው የምዕራባዊው አለባበስ ባህል የተጫነው ነው ፡፡ ካባ፣በርኖስ፣ተነፋነፍ፣ባት ተሁለትና ወንጨሬ ሱሪዎች፣ጋቢ፣አግድሞሽ፣ኩታና ነጠላ ፣ዙሪያ ገብ እና ኋላ ግማሽ እዳይት ቀሚስና ጎዳ፣ጀበርባሬ ኩታ፣ባለጃኖ ጋቢ ወዘት ለወግ በተወሰኑ ሰዎች ካልሆነ ሕዝቡ የኔ ብሎ የያዛቸው አለባበሶች ከሆኑ ዘመን አስቆጥረዋል፡፡ በገና እና በትንሣዔ በአሎች ይደረጉ የነበሩ የአማትና የአማች መገናኛ ዝግጅቶችና በውስጡ ይከናወኑ የነበሩ ሥርዐቶች ፈጽሞ ተረስተዋል፡፡
በገና የክስቶስን መወለድ የደስታ ስሜት መግለጫ በወጣቶች መካከል ይደረግ የነበረ የገና ጨዋታ፣ ዛሬ እንኳን ስለጨዋታው ፣ስለመኖሩም የሚያውቁ መኖራቸውም አጠራጣሪ ነው፡፡ እንደ ዳቢሎስ ተመስሎ በገና ሰሞን በአዋቂዎችና በጎልማሶች ይጨወት የነበረ “ኃይሚሎ” የተሰኘ የጉግስ ጨዋታ ከተረሳ ዘመን የለውም፡፡ በዚሁ ሰሞን ይዘወተር የነበረው የፈረስ ጉግስ ጨዋታ ከጠፋ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡
በፍልሰታ ታዳጊ ወጣቶች ተሰባስበው ሆያ ሆየ እያሉ እየዘፈኑ በሚሰበስቡት ገንዘብና እህል የመስቀል ዕለት ደግሰው የአካባቢውን ሰው የሚመግቡበት፣ ከኅብረተሰቡ ይቸራቸው የነበረ የእደጉ ተመንደጉ ምርቃት፣ ደመራው ከተቃጠለ በኋላ፣በፍሙ በስሎ የሚበላው እርምጦ ዛሬ የለም፡፡ ሴት ወጣቶች በቋግሜ ሳምንት አሸንድየ ታጥቀው፣ አሻንድዬ አበባዬ እያሉ ወቅትን መሠረት አድርጎ ይጨወት የነበር የጨዋታ ባህል ዛሬ በድሮው መልኩ በስፋት አይታይም፡፡ እነዚህና የመሳሰሉት አንዳንዶቹ በምዕራባውያኑ ሲተኩ ሌሎቹ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከሕዝቡ አእምሮ ውስጥ ተሰርዘዋል፡፡ ገና ጨዋታ በእግር ኳስ የተተካ ይመስላል፡፡ ኃይሚሎ፣ጦር ውርወራ ለኢትዮጵያውያን አዲስም እንግዳም ባይሆንም፣ በዳርትና በጦር ውርወራ የተተካ ይመስላል፡፡ የአማትና የአማች ግንኙነት ሌላ መልክ ይዟል፡፡ አማት ፣ምራት፣አይት፣አማች፣አገቡኝ፣ ዋርሳ የሚሉት ቃላት ራሳቸው በአማትና በአማች ግንኙነት መላላት የተነሳ ትርጉማቸው ከማይታወቅበት ደረጃ ተደርሷል፡፡ የምዕራባውያኑ ግንኙነት የበላይነቱን በመያዙ የእኛ ማንነት መገለጫ ተረሳ፤ ወይም ተጣለ፡፡ የጋብቻ ሥርዓታችን በእጅጉ ተለውጧል፡፡ በለቅሶ ጊዜ እንደ ሟቹ ማንነት ይደረጉ የነበሩ ፉከራዎችና ቀረርቶዎች ዛሬ አይደመጡም፡፡ ይህም ኅሊና የራሱን እየተወ የሌሎችን እየያዘ መምጣቱን አመልካች ነው ፡፡ የኅሊና ቅኝ ተገዥነት የሚባለው ይኸነው፡፡
2. ስም፡- ስም መጠሪያ ፣መታወቂያ ነው፡፡ እያንዳንዱ ነገር ከሌላው የሚለይበት የወል፣የጥቅልና የተጸውዖ ስሞች አሉት፡፡ ስሞችም የሚወጡት በዘፈቀደ ሳይሆን፣ ስም አውጨዎቹ በኖሩበት ማኅበረሰብ ባህል፣ቋንቋና እምነት ጋር ተያይዞ የሚሰጥ ነው፡፡( ከዚህ ላይ ስም ስንል ልዩ ትኩረት የምንሰጠው የሰው መሆኑን እናስተውል፡፡) ስለሆነም የአንድ ሰው ስም በወላጆቹ ፈቃድና ውሳኔ የሚሰጥ ነው፡፡ ውሳኔው መሠረት የሚያደርገውም ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ባህልን፣እምነትንና ስም የሚወጣለት ሰው በተወለደበት ወቅት በአካባቢው በተፈጠሩ ሁኔታዎች ላይ ተመርኮዞ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከዐማራ ነገድ የተወለደ ወይም የተወለደች ሰው፣አበበ፣አበበች፣ላቀው፣ላቀች፣በላቸው፣በላይነሽ፣አስፋው-ወሰን፣ወሰን-የለሽ፣ ወርቁ፣ወርቂቱ (ወርቅነሽ)፣በላቸው ፣በላይነሽ፣አግርደው፣አግርጅው፣አስካበ፣አስካበች፣ፀጋው፣ፀጋነሽ፣ ብሬ፣ ብሪቱ፣ ወዘተ እያሉ ስም ይሰጧቸዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚወጡ ስሞች የአባትየውን ፍላጎት በሚገልጥ መልኩ፣የልጅና የአባት ስም ባንድነት ሲጠሩ የተለየ ትርጉም በሚሰጥ መልኩ ይሰይሟቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ሰውበሰው ደረጀ፣ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ፣ቁምነገር ገበየሁ፣በዓለምላይ ገበየሁ፣ኃይለሥላሴ ቀለጠ፣ ወገን በለጠ፣ አማላጅ በለጠ፣ወዘተ፣ እነዚህ ስሞች የኢትዮጵያዊነት
በተለይም የዐማራ ነገድ ማንነት መገለጫዎች እንደሆኑ በቀጥታ ከስማቸው መረዳት ይቻላል፡፡
ይሁን እንጂ ቀለም ቀመሱ ትውልድ በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም፣ አዲስ ሃይማኖት በመቀበል፣የስም አጠራሩን ለውጭ አገር ሰዎች በቀላሉ አይገባም በሚሉና በመሳሰሉ ምክንያቶች በቤተሰብ የተሰጣቸውን ስም ሆነ እነርሱ ለወለዷቸው ልጆች ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ስሞች ሲሰጡ መታየቱ እግዳ ነገር አይደለም፡፡ ሊያ፣ሚኩ፣ሚሚ፣ሣራ፣ማይክ፣አቤነዘር፣ሌላም ሌላም ሕዝቡ የሚያውቃቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር ምንም ዓይነት ግንኑነት የሌላቸው ስሞች እንሰማልን፤እናውቃለን፡፡ ይህ የራስን ዕንቁ ወርውሮ የሌሎችን ነሃስ መሰብሰብ ከመሆኑም በላይ፣ ራስን ለኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነትን ወዶ ማሰለፍ ነው፡፡ ሌሎቹን ሁሉ ለትዝብት ትተን ሣራ የሚለውን ስም እንደኛ(እንደ ኢትዮጵያዊ) ሆነን እንሰብ፡፡
ማንም መጽሐፍ ቅዱስን የሚከታተል ሰው ሣራ የሚለው ስም እንግዳ ነገር አይሆንበትም፡፡ “የአባታችን” የአብርሃም ባለቤት መሆኑዋን ይረዳል፡፡ ይህ ስም በእበራይስጥ ቋንቋ ትርጉሙ “እናት” እንደማለት ይመስለኛል፡፡ የእብራይስጥን ቋንቋና ባህል ለሚያውቅ ሰውና በዚያ ባህል ለኖረ ስሙ ወርቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያዊ ባህልና ቋንቋ ባለቤት ለሆነ ሰው ደግሞ ይህ ስም እንኳን የልጅ መጠሪያ ሊያደርጉት ሊናገሩት የሚከብድ ትርጉም ያለው ነው፡፡ እግዚአብሔር ያሳያችሁ! “ሣራ ነጋ” ብሎ ስም የሚያወጣ ሰው ለልጁ መጠሪያ ሳይሆን መሰደቢያ ነው የሰጣት፡፡ የቋንቋው ሥርዓትና የሕዝቡ ባሕል ከሚፈቅዱት ውጭ የተሰጡ ስሞች የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ስሜት የፈጠራቸው ስሞች መሆናቸውን መጠራጠር አይቻልም፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያዊው በተለይም ዐማራው ማንነቱን ፈቅዶና ወዶ እያወለቀ እየጣለ የሌሎችን ማንነት እያጠለቀ መሆኑ ጉልሁ ማመላከቻ ለልጆቹ የሚያወጣላቸው ስሞች ናቸው፡፡
በአማርኛ ቋንቋ ሥርዓት ውስጥ በተጸውዖ ስም ላይ እየተደረቡ የሚገቡ ለሁለቱም ፆታዎች የሚያገለግሉ ድርብ ስሞች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ድርብ ስሞች የማዕረግ፣የአክብሮትና የተዘምዶ ስሞች ይባላሉ፡፡ የማዕረግ ስሞች በቤተ እምነቶች ወይም በቤተ መንግሥት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ምሳሌ፡- ቤተእምነት፣ እጨጌ፣ጳጳስ፣ቆጶስ፣መላዕ-ከፀሐይ፣ግራ ጌታ፣ ሸህ፤ወዘተ፣፣ ቤተ መንግሥት፣አጼ፣እቴጌ፣ንጉሥ፣ራስ፣ቢትወደድ፣ደጃዝማች፣ፊታውራሪ፣ቀኛዝማች፣ግራዝማች፣ብላታ፤ እነዚህ ስሞች ግለሰቦች ለአገራቸው ባበረከቱት ተግባር፣ባሳዩት አርዓያነት ያለው ሥራ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካለት ተመርምሮ የሚሰጡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ስሞቹ የክብር መጠሪያዎች በመሆናቸው ሌሎች የዚያ ስም ባለቤት ለመሆን የተሻለ ተግባር እንዲፈጽሙ አነቃቂ እንደነበሩ ግልጽ ነው፡፡ በመንግሥት ደረጃ የሚሰጡት የማዕረግ ስሞች በአብዛኛው አገርን ከጠላት በመከላከል ሂደት ውስጥ በተጫወቱት ሚናና በሰላም ጊዜም በአስተዳደር፣ በልማትና መሰል ተግባሮች አርኣያነት ያለው ተግባር ለተወጡ ግለሰቦች ነው፡፡ የቤተ እምነቶቹ ስሞች የሚሰጡት በሃይማኖቱ መንፈሳዊ ዕውቀት ላይ ተመሥርቶ በዚያ ተግባር ላይ ያበረከቱት አስተዋጽዖ ተመዝኖ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ዛሬ በምንገኝበት ነባራዊ ሁኔታ የቤተ እምነቶቹ ስሞች በአገልግሎት ላይ ሲገኙ፣ ከመንግሥት በኩል የሚሰጡት ስሞች እንደ አድኃሪና ኋላ ቀር ነገር ተቆጥረው ተወግዘው የተወረወሩ ሆነዋል፡፡ ማዕረግተኞቹም በማረጋቸው ያፈሩ ይመስላል፣ ሊጠሩበት አይሹም፡፡ ለምሳሌ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ከዚህ ስማቸው ይልቅ “ታጋይ” የሚለው እንደሚመቻቸው ሲናገሩ የተደመጠበት ጊዜ አለ፡፡ “ታጋይ” መንገሻን ለዚህ ያበቃቸው የማዕረግ ስሙን ያገኙት በግል ባስመዘገቡት የመልካም አርኣያነት ተግባር ሳይሆን፣ከንጉሡ ጋር በመጋባታቸውና ከአጼ ዮሐንስም እወለዳለሁ ስለሚሉ፣በነዚህ ሁለት ምክንያቶች ያገኙት በመሆኑ ለስሙ ክብደት ከመስጠት ይልቅ አሳፍሯቸዋል ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ግራዘመም አመለካከት አቀንቃኝ የሆነው ትውልድ ማዕረጎቹን የተረዳበት አቅጣጫ ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ባፈነገጠ መልኩ መሆኑ መዕረጎቹ የገዥና የተገዥ፣የአዛዥና የታዣዥ፣ የሀብታምና የድሀ ግንኙነት መገላጫዎች አድርጎ በመመልከቱ ትውልዱ ስሞቹን በጭፍን አወገዛቸው፡፡ ማዕረግተኞቹም አብዛኛዎቹ በአብዮቱ በግራ ቀኙ ኃይሎች ተመቱ፡፡ የቀሩትም እንደ ራስ መንገሻ ያሉት ዘመኑን ለመምሰል ሌላ ዘመነኛ ስም መረጡ፡፡ ትውልዱ ኅሊናው በቅኝ ተገዥነት ስሜት ሳያወቀው ባይገዛ ኖሮ፣ስሞቹ በልዩ ልዩ መስኮች አርኣያነት ያለው ተግባር ላከናወኑ ሰዎች መጠሪያ እንዲሆን ይፈቅድ ነበር፡፡ይህም ኢትዮጵያዊነትን ማድመቅ እንጂ ማፍዘዝ አይሆንም ነበር፡፡ እንግሊዞች ንጉሣዊ አመራርን አሻሻሉት፣ሕዝቡ በሚፈልገው ደረጃ አሳደጉት እንጂ፣ፈጽሞ አላወደሙትም፡፡ በዚህም የተነሳ “ሰር” የሚለውን የማዕረግ ስም ዛሬም በልዩ ልዩ መስኮች ለሰው ልጅ ጠቃሚ ሥራዎችን ለሠሩ ሰዎች መጠሪያና መከበሪያ እንዲሆን እያደረጉት ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን የራስን ማጥፋት፣የራስ ያልሆነን መካብና ማድመቅ በመሆኑ ሥራችን፣ እነዚህን አገራችን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ስትገለገልባቸው የነበሩ የማዕረግ ስሞች እንዲጠፉ ፈርደንባቸዋል፡፡ ይህም ውጭ አምላኪነት ነው፡፡ ውጭ አምላኪነት ደግሞ ፈቅዶና ወዶ ቅኝ ተገዥነትን መለማመድ ነው፡፡
የተዘምዶ ስሞች የምንላቸው ልጆች ለወላጆቻቸው፣ታናናሾች ለታላላቅ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው የሚሰጡዋቸው እንዲሁም በዕድሜ ታናሽ የሆኑ ሰዎች ታላላቆቻቸውን የሚጠሩባቸው ስሞች ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ ልጆች ወላጆቻቸውን አባባ፣አባበይ፣ እማማ፣ እማመይ፣ታላላቆቻቸውን አይወይ፣ክንዴ፣ጋሻዬ፣መከታዬ፣ወንድም-ዓለም፣እዋዋ፣ወንድም-ጥላ፣ወንድም-ጋሼ፣ እታበባ፣እታለም፣እትሸት፣እንጎቻዬ፣እባባ እገሌ፣ጋሼ እገሌ ፣አይዋ እገሌ፣እማማ እገሊት፣እታታ እገሊት ወዘተ እያሉ መጥራት የቋንቋው ሥርዓትም ሆነ የሕዝቡ መልካም ባህል ነበር፡፡ በሌላም በኩል ወንዶች ለአቅመ አዳም፣ሴቶች ለአቅመ ሔዋን ከደረሱ በኋላ የሚጠሩበት የማዕረግ ስም አላቸው፡፡ ወንዶች “አቶ” ሲባሉ ሴቶች “ወይዘሮ” ላገባች፣ “ወይዘሪት” ላላገባች እያሉ መጠራት እንዳለባቸው ባህሉና ሥርዓቱ ያዛል፡፡
እነዚህ ስሞች ከማዕረግ መገለጫቸው በተጨማሪ በጠሪውና በተጠሪው በካከል እጅግ የቀረበ የሥጋ ዝምድና ያላቸው መሆኑን ከማመልከቱም በላይ፣ ባለማዕረግ ስሙ ታላቅ፣ በማዕረግ ስም ጠሪው ታናሽ መሆናቸውን ላድማጭ ግልጽ በሆነ መንገድ ያስረዳሉ፡፡ ከዝምድና መገለጫ ውጭ ያሉት የአክብሮት ስሞች በአክብሮት ስም ጠሪው በዕድሜ ታናሽ፣ ተጠሪው ታላቅ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ይህ እንዴት ያለ የኢትዮጵያዊነት ልዩና ውብ መታወቂያ ነበር፡፡ ዳሩ ምንያደርጋል/ እነዚህ እንኳን ውጪ ተወልደው ባደጉ፣ በአገር ቤት በተወለዱትና ባደጉት ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በተወለደው ትውልድ ያላዳች አስገዳች ውጫዊ ኃይል በራስ ፍጹም ፈቃድ ስሞቹን ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ተድርጓል፡፡ አባትና እናትን እንደ ጓደኛ በስማቸው መጥራት እንደስልጣኔ ተቆጥሯል፡፡ አለያም እንደምዕራባዊኑ “ዳድ” ፣”ማም” ማለት የተዘወተረ ሆኗል፡፡ የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ማለት ሌላ ምንም ሳይሆን፣የራስን ጥሩ ነገር ትቶ የሌሎችን ባህል፤እምነትና ማንነትን መላበስ ነው፡፡ ወላጆቹን በባህላችን የአክብሮት ስሞች የማይጠራ፣ታላላቅ ወንድሞቹንና እህቶቹን በኢትዮጵያዊ የአክብሮት ስም የማይጠራ ከማንነቱ የተፋታ ነው፡፡ ተጠሪዎችም በባህላችን የሚመጥናቸውን የማዕረግ ስም ነጥለው የሚጠሩዋቸውን ልጆቻቸውንም ሆነ ወንድም እህቶቻቸውን አዎንታዊ መልስ ከሰጡ የመጀመሪያዎቹ ባህል ጣሾችና ሥርዓት አፍራሾች መሆናቸውን ሊረዱት ይገባል፡፡ ለሁሉም ቀለም ቀመሱ ትውልድ ከኢትዮጵያዊነት ጨዋነት፣ባህልና ማንነት ራሱን እያፋታ የመጣ መሆኑ ባህላችን የሚገኝበት ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ ደግሞ የኅሊናዊ ቅኝ ተገዝነት መገለጫ ነው፡፡
3. ቋንቋ፡- ቋንቋ መግባቢያ፣ሀሳብ መግለጫና መለዋወጫ የሆነ የድምፅ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የተለያዩ ሕዝቦች የተለያዩ የድምፅ ሥርዓት የሚከተሉ ቋንቋዎች አሏቸው፡፡ ቋንቋ አዳጊም ጠፊም ነው፡፡ ቋንቋ የሚጠፋው በሥራ ላይ የሚያውለው ማኅበረሰብ በልዩ ልዩ ምክንያቶች አልገለገልበት ሲል ነው፡፡ ቋንቋ ዳባሪ የሚሆነውም የቋንቋው ባለቤት የሆነው ሕዝብ የኢኮኖሚ ደረጃ ማደግና ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የሚፈመሠርተው ግንኙነት ሲሠፋ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት በዓለማችን ላይ የጠፉ ቋንቋዎች የመኖራቸውን ያህል፣የዳበሩም እንዳሉም እንረዳለን፡፡ ዳበሩ ከምንላቸው ቋንቋዎች ውስጥ እንግሊዝኛ የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ ነው፡፡ ጠፉ ከሚባሉት ውስጥ ላቲን አንዱ ነው፡፡በአገራችን ከጠፉ ቋንቋዎች ውስጥ ጋፋትኛ የመጀመሪያው ነው ፡፡ አንፃራዊ በሆነ መልኩ አድጓል ወይም ዳብሯል ከሚባሉት ውስጥ አማርኛ አንዱ ነው፡፡
አማርኛ ቋንቋ አድጓል ስንል በሚጠበቅበት ደረጃ እያደገነው ወይም አድጓል ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ቋንቋው በጽሑፍ ሥራ ላይ ከዋለ ከ320 ዓ.ም ጀምሮ ካስቆጠረው ዘመን አንፃር ሲመዘን ወደ ኋላ እንጂ፣ወደ ፊት ሄደ የሚባል አይደለም፡፡ ይኸም ሆኖ፣ትውልዱ በተጠናወተው ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ስሜት ሳቢያ፣ አባቶቻችን ባቆዩልን መልኩ እንኳ ለልጆቻችን ለማስረከብ ከማንችልበት ደረጃ ላይ ነን፡፡ ቋንቋ ባህል በመሆኑ የሚከተላቸው የራሱ የሆኑ መንገዶችና ሥርዓቶች አሉት፡፡ ለምሳሌ በአማርኛ ቋንቋ ሰዎች ሰላምታ ሲለዋወጡ የሚከተሉት ሥርዓት አለ፡፡ ሰላምት ሰጪው ጤና ይስጥልኝ እንዴት አደራችሁ? ዋላች? አመሻችሁ ፣ሲል፣ ሰላምታ ተቀባዩ ወይም መላሹ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ ፣ደህና ነን ሲል መመለስ እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ይህ በዛሬው ትውልድ እንደነውር የሚቆጠር ሆኖ፣የሰላምታው ዘይቤ የምዕራባውያኑን መንገድ ተከትሏል፡፡ እዴት አደርክ? አደራችሁ ሲባል መልሱ ደህና ወይም መልሶ እንዴት አደርክ የሚል ነው ፡፡ ይህ የራስን ውብ ነገር መጣል ነው፡፡ በንግግር ወቅት በአማርኛ ጀምሮ በአማርኛ መጨረስ የሚታሰብ አልሆነም፡፡ በመሀሉ እንግሊዝኛ፣ፈረንሣይኛ፣ዐረብኛ፣ ወዘተ ጣልቃ ማግባት የዐዋቂነት ምልክት እንደሆነ መቆጠር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ በሌላም በኩል የአማርኛ እናት ግዕዝ መሆኑ እየታወቀ ግዕዝን እንድንማር ባለመደረጉ፣እኛም ራሳችን ለማስተማርና ለመማር ባለመትጋታችን ዘመኑ ለሚፈጥራቸው አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠሪያ የሚሆኑ ቃሎች ከአማርኛ ስናጣ፣አማርኛን መውቀስና የውጭ ቋንቋዎችን ማግነን የራስን ካለማወቅ የተፈጠረን ችግር፣የቋንቋው ችግር አድርጎ ማቅረብ የራስን ከመናቅ የመነጨ ውጭ አደርነት ስሜት የፈጠረው መሆኑን መጠራጠር አይቻልም፡፡
ትውልዱ ግራ ዘመም ርዕዮት በመከተሉ ሳቢያ፣የተለያዩ ግንኙነቶች መገለጫ የሆኑ ስያሜዎቸን “ ገዥ መደቦች ወይም ብሔረሰቦች” እንዳዎጡዋቸው በመቁጠር ከንግግር ዘይቤ ውጭ እንዲሆኑ ሆኗል፡፡ ምሳሌ “አዝማሪ”፤ ይህ ቃል ትርጉሙ አዘመረ አመሰገነ የሚል ሲሆን፣ትርጉሙን በሚገባ ካለማወቅ የሙያ ማንቋሸሻ እንደሆነ ተቆጥሮ “ አርቲስት” በሚል የውጭ ቃል እንዲተካ ተደርጓ፡፡በምዕራቡ አገር ጢሰኛ፣ገባር የሚሉት ቃሎች ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ቤቶችን ፣መሬቶችን የሚከራዩ ሰዎች የሚጠሩበት የተከራይና አከራይ ግንኙነት መገለጫዎች በመሆን በሥራ ላይ ውለው እናያለን፡፡ እነዚህ ቃሎች በኢትዮጵያችን የጭቆና መገለጫዎች እንደሆኑ ተቆጥረው ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰል ሌሎችም እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ቋንቋው እንዳያድግ ፍላጎት ባላቸው ክፍሎች ስልታዊ በሆነ መንገድ የአማርኛ ቋንቋ እንዲጠፋ የሚሠራው የቤት ሥራ ቀላል አይደለም፡፡ ዛሬ ወያኔ በዘረጋው የትምህርት ፖሊሲ በተዘጋጁ የማስተማሪያ መጽሐፍቶች ፊደሎች ካለቦታቸው ከመግባታቸው በላይ ፣ቃሎቹን በሚገባ የሚገልጹ የግዕዝና የአመርኛ ቃሎች እያሉ ሆን ተብሎ እንግሊዝኛ ወይም ትግርኛ ቃሎች ከአማርኛ ጋር እንዲዳቀሉ ተደርጓል፡፡
አባቶቻችን ስድስት ሀ፣ሃ፣ ሐ፣ሓ ፣ኀ ፣ኃ፣ሁለት ሰ ፣ ሠ ፣ሁለት ጸ፣ ፀ ፣አራት አ፣ኣ፣ ዐ፣ዓ ፣ ፊደሎች ድምፅ የቀረጹት የተለያየ ድምፅና ትርጉም ያላቸው መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡ ለምሳሌ ሀብት፣ሃብት፣ ሐብት፣ሓብት፣ኀብት፣ኃብት ተብለው በተገቢው ድምፅ የተገለጠውን ምረጥ ብንባል ትክክለኛው መልስ በሀሌታው “ሀ” የተጻፈው ነው፡፡ የቀሩት በድምፅና በትርጉም የተለያዩ ናቸው፡፡ ሐመር፣ሐረግ ሕዝብ፣ የሚሉት ቃሎች በሌሎች የሀ ድምፅ እንዳላቸው በሚታወቁት ፊደሎች ቢጻፉ ፍጹም ስሕተት ነው፡፡ ሠራ፣ሥራ፣ንጉሥ፣ ንግሥት ወዘተ የሚሉ ቃሎች በሌላ ሰ ድምፅ ባላቸው በሚመስሉ ፊደሎች ብንጽፋቸው ስሕትት ነው፡፡ ኃይል፣ኃይሉ፣ኅብረት፣ማኅበር፣ ቤሎች የሀ ድምጽ ያላቸው ፊደሎች ቢጻፉ ስሕተት ነው፡፡ በአጠቃላይ ለፊደሎቻችን የሚወክላቸውን ድምፅ በሚገባ አለማወቅ በማይወክሉበት ቦታ ፊደሎችን እያስገባን የቋንቋውን ሥርዓትና አጠቃቀም ከማዛባት አልፎ እያጠፋነው መሆኑን ትውልዱ የተገነዘበ አይመስልም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሀ፣ ሃ ፣ሐ፣ ሓ፣ ኀ፣ ኃ፣ ኻ ፣ህ፣ ሕ፣ ኅ፣ ኽ ፣ ወ ፣ዎ፣ ዉ ፣ ው፣ ዪ ፣ይ ቸ፣ ቼ፣አ፣ ኣ ፣ ዐ፣ዓ፣ ሸ፣ ሼ ፣ ዠ ፣ዤ፣ጀ ፣ ጄ፣ጨ ፣ጬ ወዘተ የሚሉትን ድምፆች ልዩነት በሚገባ ባለማወቅ በማይወከወሉበት ቦታ እያስገባናቸው የቋንቋው ሥርዓት እንዲፋለስ እየተደረገ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህም ሂዶ ሂዶ መዳረሻው ራስን ለቅኝ ተገዥነት ማመቻቸት መሆኑ የተገለጠልን አይመስልም፡፡ የአማርኛን ቋንቋ ድምፆች በሚገባ ለማወቅ ባለመቻላችን፣ ልናውቅም ጥረት ባለማድረጋችን ፊደሎች እንደበዙና አንዳንዶቹም የተደጋገሙ ናቸው በማለት ምትክ የሌላቸውን ቅርሶቻችን እንዲጠፉ እያደረግን ነው፡፡ ቃሎች በሚመጥኑአቸው ድምፆች ፊደሎች አለመጻፍ የድምፅ ልዩነት ብቻ ሳይሆን፣የትርጉምም ለውጥ አላቸው፡፡ በሌላም በኩል ተገቢዎቹን ፊደሎች እንዲጠፉ ፈረድንባቸው ማለት ነው፡፡ ይህም የራስን መጣል፣የሌሎችን ማንጠልጠል ነው፡፡
በቋንቋ ረገድ የራሳችን እየጣልን የኛ ያልሆነን የማንጠልጠላችን ሁኔታ ጎልቶ የሚታየው በሕፃንነታቸው ከአገር የወጡና ውጭ የተወለዱ ልጆች የወላጆቻቸውን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንዲያውቁ አለመደረጉ ነው፡፡ ዛሬ በምዕራቡ ዓለም ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ እንደሚኖር ይታወቃል፡፡ ከተሰዳጁ ኢትዮጵያዊም ውስጥ በርካታውን ቁጥር የያዘው የዐማራው ነገድ እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ሕዝብ ልጆቹን የማንነታቸው ቋሚ መገለጫ የሆነውን ቋንቋቸውን እዲያውቁ ሲያደርግ አይስተዋልም፡፡ ልጆች የወላጆቻቸውን ቋንቋ ባለማወቃቸው፣ወላጆችም ልጆቻቸው የሚያውቁትን የነርሱ ያልሆነ ቋንቋ ስለማያውቁ በቤት ውስጥ የመግባባት ችግር እንዳለ ጎልቶ መነገር ጀምሯል፡፡ ወላጆች ላሉበት አካባቢና ቋንቋ ባይተዋሮች በመሆናቸው የልጆቻቸውን ቤት ሥራ ተከታትሎ ለማሠራት ባለመቻላቸው ወላጅና ተወላጅ “ፈረንጅና አበሻ” ለመባባል በቅተዋል፡፡ ከዚህ የባሰ ውርደትና ሞት የት አለ?
ልጆቻችን የአገራቸውን ቋንቋ እንዲያውቁ አለመደረጉም ወጥተው እንዲቀሩ፣ከማንነታቸው እንዲፋቱ፣ከኅሊና ቅኝ ተገዥነት በባሰ የማንነት ቀውስ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረገው መሆኑ በውል የተጤነ አይመስልም፡፡ በዓለም ላይ እንደጨው ተዘርተው ከሁለት ሺህ ዘመን በላይ የኖሩት እስራኤላውያን ቋንቋቸውንና ሃይማኖታቸውን ፈጽሞ አላጠፉም፡፡ እንዳውም በስደት ዓለም አዳበሩት፡፡ ዐማራው ምን እንደነካው አይታወቅም ከእሱነቱ አልፎ፣ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣የጥቁር ሕዝብ መመኪያ የሆነውን የአፍሪካ ብቸኛ የጽሁፍ ቋንቋ ባለቤት የሆነውን የዐማርኛ ቋንቋ እንደዘበት ተመልክቶ እዲጠፋ የፈረደበት ይመስላል፡፡ “ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ፣ ባለዕዳ አይቀበለውም” ነውና እኛ ለልጆቻችን ለማውረስ የተጠየፍነውን ቋንቋ ማን ሊወርስልን፣ሊያሳድግልንና ሊያዳብርልን እንሻለን? ለአማርኛ ከዐማራው ነገድ ሌላ ማን ባለቤት እንዲሆን ይጠበቃል? ቋንቋችን ለመጠበቅና ለማዳበር አለመትጋታችን የኅሊና ቅኝ ተገዥነታችን ያሳደረብን ተፅዕኖ መሆኑን መጠራጠር አይቻልም፡፡
4. አገር የመጥላት ስሜት እየጎለበተ መምጣት፡- ማንም ሰው አገሩን ይወዳል፡፡ ይህ አጠቃላይ አገላለጽ ነው፡፡ አገራቸውን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚጠሉ መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ካለባት የመልካም አስተዳደር ዕጦት በላይ፣ ታዳጊ አገር በመሆኗ ለዜጎቿ የዕለት ተዕለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በብዛትና በጥራት የምታቀርብ አይደለችም፡፡ የየብስ፣የባሕርና የአየር መጓጓዣ እንደፈለጉት አይገኝም፡፡ ቴሌቪዥን፣ማቀዝቀዣ( ፍሪጂ)፣አውቶሞቢል፣ የቤት ውስጥ መጸዳጃ፣ ሶፋ፣ ወንበር ጠረጴዛ፣ የአካል ንጽሕና መጠበቂያ ሙቅና ቀዝቃዛ ውኃ በቤት ውስጥ መኖር ለሰው ልጆች እንደመሠረታዊ አስፈላጊ ነገሮች የሚታዩ ሳይሆን፣ የሀብት መገለጫ፣ያላቸው ሰዎች ብቻ ሆነው የሚታዩ በመሆኑ ለአብዛኛው ሰው እንደቅንጦት የሚታዩ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ “ተድራ ብትመለስ የውኃው መንገድ ጠፋት” ዓይነት የሆነባቸው ሰዎች አውሮፓና አሜሪካ ደርሰው ወይም ኑረው ሲመለሱ በውጭ ያዩትን የመገናኛና የአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በፈለጉት መጠን አለማግኘት አገራቸውን ጠልተው እንዲመለሱ ይሆናሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ወደ ገጠር ጎራ ካሉ አቧራው፣ቁንጫው፣ትኋኑና የመንገዱ ውጣውረድ በሚፈጥርባቸው የተለየ ስሜት የተነሳ ዳግም ወደ አገራቸው ላለመመለስ ምለው የሚመጡ አያሌዎች እንደሆኑ በየአጋጣሚው የምንሰማው ሐቅ ነው፡፡ ይህ ማለት ሁለመናቸው ለውጭው ኑሮ የተገዛ መሆኑን ያሳይል፡፡ ሁኔታውን ለመለወጥ ከእኔ ምን ይጠበቃል ብሎ የተሻለ ነገር ለመሥራት፣ቴከኖሎጂ ለማሸጋገር በመትጋት፣ የራስን ድርሻ ተወጥቶ አገርን ሌሎች ከደረሱበት ደረጃ ለማድረስ የሚቻለውን ሁሉ በግልና በተናጠል ከመሥራት ይልቅ፣ የራስን ጠልቶ አያሳየኝ ብሎ ምሎ መመለስ ምን ይባላል/ይህን አቋምና አመለካከት የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ካልሆነ ሌላ ምን ልንለው እንችላለን፡፡
5. ስደት ናፋቂነት፡- “ሞት በእንቅልፍ ይለመዳል” እነዲሉ ሆኖብን፣ኢትዮጵያውያን በመሣሪያ ኃይል የፖለቲካ ሥልጣን በጨበጡ ቡድኖች በተከታታይ በተፈጸመብንና በሚፈጸምብን የአፈናና ረገጣ አገዛዞች ስደትን የሞት ያህል እየተለማመድነው መጥተና ፡፡ በግልጽ እነደሚታወቀው፣ አንድ ሰው ከተወለደበትና ካደገበት አካባቢ የሚሰደደው ለሕይዎቱ ቀጣይነት አስጊ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ነው፡፡ እነዚህ የሕይዎት አስጊ ሁኔታዎች ከፖለቲካ አቋም፣ከሃይማኖት፣ከነገድና ከኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ መንገድ ልዩነቶች ሲፈጠሩና አለመግባባት ላይ ሲደረስ እንደሆነ ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድርቅ፣በአንበጣ ወረራ፣ በመሬት መንሸራተትና በጦርነት ምክንያቶች በሚፈጠሩ ችግሮች ሳቢያ፣ የሰሜኑ ወደ ደቡብ፣የደቡቡ ወደ ሰሜን፣የምሥራቁ ወደ ምዕራብ፣የምዕራቡ ወደ ምሥራቅ በመፍለስ እንደኖረና ይህም ለአንድነቱ መሠረት ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ የአገር ውስጥ ፍልሰት የባህል፣የቋንቋና የሃይማኖት መወራረስን በመፍጠር ሕዝቡ የአካባቢያዊ ልዩነቶችን ግድግዳ በመሰባበር፣ኢትዮጵያዊ የሆነ የወል ማንነትን እንዲገነባ እንዳደረገው ግልጽ ነው፡፡ በግልጽ ለመገንዘብ እንደሚቻለው፣የአገር ቤቱ ፍልሰት፣የጠነከረ ኢኮኖሚያዊ አስተሳሰብ፣ ሃይማኖት፣ባህልና ቋንቋ ያላቸው በሄዱበት አካባቢ ነዋሪ ላይ ተፅዕኖ ማሳደራቸው አይዘነጋም፡፡ ተፅዕኖው ሰጥቶ መቀበልን መሠረት ያደረገ ስለነበር የነገዶች ልዩ መታወቂያ የሆነው ቋንቋቸው ተጠብቆ እንዲዘልቅ ሆኗል፡፡
እስከቅርብ ዘመን ድረስ አገርን ጥሎ ወደ ባዕድ አገር መሰደድ ለኢትዮጵያዊያን የሚታሰብ አልነበረም፡፡ ትውልዱ የስደትን ሕይዎት እየተለማመደው የመጣው ከአምስቱ ዓመት የአርበኝነት ትግል ዘመን ጀምሮ ነው፡፡ የስደትንም ሕይዎት ለትውልዱ ያስተማሩት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከነቤተሰባቸው መሣፍንቱንና መኳንንት የሚባሉትን ይዘው አውሮፓ መግባትና መኖር ጋር ተያያዞ ነው፡፡ “እንደንጉሡ አጎንብሱ” ወይም “ግዝ እንደንጉሡ አውድማ እንደ አግማሱ” ይሉ ሆኖ፣ ከዚንያ ዘመን ጀምሮ ትውልዱ ስደትን የሕይዎት ማቆያ አማራጭ መንገድ አድርጎ ወሰደው፡፡ በማከታተልም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ.ኤ.አ 1948 የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን ባጸደቀበት ወቅት አንድ ሰው ወይም ቡድን በዘሩ፣በሃይማኖቱ እና በሚያራምደው የፖለቲካ አቋም የተነሳ፣መሳደድ፣መታሰርና መገደል የሚደርስበት መሆኑ ከታወቀና ይህም ከተረጋገጠ ወደ ሁለተኛ አገር ሂዶ የመኖር መብት እንዳለው ያወጣው ሕግ የስደተኝነትን መንፈስ በሕዝቦች ላይ እንዳሳደረ እንገነዘባለን፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት ከንጉሠ ነገሥቱ የመጨረሻዎቹ ሁለት ዐሥረተ ዓመታት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን “የመደብና የብሔር ጭቆና” ተፈጽሞብናል፣ለዲሞክራሲ ቆመናል የሚሉ ወገኖች በአገዛዙ ሊፈጸምብን ይችላል የሚሉትን እስራትና እንግልት በመፍራት መሰደዳቸው ይታወቃል፡፡
በዘመነ አብዮት ትውልዱ በየፊናው ተደራጅቶ ባካሄደው የፖለቲካ ሥልጣን ሽሚያ በርካታ ዜጎች ለሞትና ለእስራት መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡ አገዛዙ በሥልጣን ተቃዋሚዎቹና በተገንጣይ ቡድኖች ላይ በወሰደው መራር ርምጃ አያሌ ሰዎች ስደትን እንዲመርጡ እንዳደረጋቸው ግልጽ ነው፡፡ ስደቱ በተከታዩም ብሔርተኛው አገዛዝ በከፋ መልኩ ቀጠለ፡፡ በዘመን ደርግና በዘመነ ወያኔ የሕዝቡ ስደት መሠረት ያደረገው በሚከተለው ፖለቲካዊ አቋም፣ሃይማኖት፣ዘር ወዘተ ከሚመነጭ ግድያና አስራት ፍራቻ ብቻ አይደለም፡፡ የተሻለ ሕይዎት ለመኖር ከመነጨ ፍላጎትም ስደትን የመረጠው ወገን ቁጥር በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ የዚህ ፍላጎት ምንጩም የአገሪቱ ሰላም አስተማማኝ አለመሆን፣ የሥራ ዋስትን አለማግኘት፣የግል ሀብት ተገቢ የሆነ ሕጋዊ ጥበቃ አለማግኘት፣ሥራ በችሎታ ሳይሆን፣ በፖለቲካ ሽርክናና በዘር ላይ መመሥረት ወዘተ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ፣ ፖለቲካዊ ሁኔታውን መነሻ በማድረግ በልዩ ልዩ መንገዶች ሕዝቡ መሰደድን ሥራዬ ብሎ ተያያዘው፡፡ ለዚህም ዋናው ተጠቃሽ ምክንያት ቀድመው የተሰደዱ ሰዎች የግልና የቤተሰብ ሕይዎት በአገር ቤት ከሚኖሩ ጥሩ ነዋሪ ከሚባሉ ሰዎች የተሻለ ሆኖ መገኘት ነው፡፡ በሁለተኛና በሦስተኛ አገር ጥገኝነት ለመጠየቅም ባገር ቤት ያለው የዘር ፖለቲካና በሕዝቡ ላይ የሚፈጸሙ ኢ-ሰባዊ ድርጊቶች ተባብሰው መቀጠል ከፖለቲካ ጋር ምንም ዓነት ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች ለሚያቀርቡት “የመብታችን ተገፈፍን ጥያቄ” ተቀባይነት እንዲኖረው አስገደደ፡፡ ስለሆነም በዓለም አቀፍ ሕጉ መሠረት ወደ ፈለገው አገር መግባት ያቃተው ተሰዳጅ ወገን፣ከኢትዮጵያ ኬንያ፣ ከኬንያ ታንዛኒያ፣ከታንዛኒያ ሞዛምቢክ፣ ከሞዛምቢክ ደቡብ አፍሪካ፣ከደቡብ አፍሪካ ብራዚል፣ ከብረዚል ሜክሲኮ፣ከሜክሲኮ ዩ፣ኤስ.ኤ እያለ አያሌ ፈተናዎችንና ውጣውረዶችን አልፈው የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር ቀላል አለመሆኑ በጉልህ እየታየ ነው፡፡ በዚህ ውጣ ውረድ በሞላበት አስቸጋሪ የስደት ጉዞ በአራዊቶች ተበልተው፣በወባ ተነድፈው፣በልዩ ልዩ በሽታዎች ተይዘው ምኞታቸው ሳይሳካ ለሕልፈተ ሕይዎት የሚዳረጉት ቁጥር የት እየለሌ እንደሆነ በጉዞ ቀንቷቸው ከተመኙት አገር የደረሱ ሰዎች የሚናገሩት ነው፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ከግብፅና ከሶማሊያ ተነስተው ወደ እስራኤልና የመን፣ ከሊቢያ ወደ ጣሊያንና ግሪክ ለመግባት የሚጥሩ፣ ኢትዮጵያኖች በባሕር ላይ በሚያደርጉት ጉዞ ፣ ጉዞው ሕጋዊ ካለመሆኑ የተነሳ ከሚደርስባቸው የመጓጓዣ ጫና፣ እንግልትና መሳቀቅ በላይ የሚጓጓዡበት ጀልባ እየሰጠመና እየተገለበጠ የዓሣ ቀለብ የሚሆኑት አያሌዎች እንደሆኑ፣ የዓለም ብዡኃን መገናኛ መሣሪያዎች ዘወትር ለሕዝብ ጆሮ የሚያደርሱት ዜና ነው፡፡ በሌላ በኩል መንግሥት ነኝ ባዩ ሕፃናትና ወጣት ሴቶችን ለባርነት የሚሸጥ ድርጅት አቋቁሞ ሕዝቡን ለባርነት፣ለኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት አመቻችቶታል፡፡ ወደ ዐረቡ ዓለም በአገራቸው ሠርተው የመኖር ዕድሉን አጥተው በግልና በመንግሥት የሚሄዱት ሴቶች እህቶቻችን ቁጥር እጅግ ብዙ ነው፡፡ እነዚህ እህቶቻችን በዐረቡ ዓለም የሚገቡት ስማቸውን ለውጠው፣ሃይማኖታቸውን በልባቸው ይዘው፣በአፋቸው ግን ቀይረው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህስ በላይ የኅሊና ቅኝ ተገዥነት በምን ይገለጣል?
እኛ ኢትዮጵያውያን ለኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት እጃችን የሰጠን መሆኑ ማሳያው፣በሚደርሰብን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖች ባስከተለብን ሁለንተናዊ ጫና ብቻ የተሰደድን አለመሆኑን ስንገነዘብ ነው፡፡ እነዚህ ጫናዎች የደረሱባቸው ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነትን ወደው ወይም ፈቅደው ሳይሆን፣ ተገደው፣ ከቁጥጥራቸው ውጭ በሆነ ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑን ስለሚገነዘቡ፣ቅኝ ተገዥነቱ በኅሊናቸው ውስጥ ቦታ አይኖረውም፡፡ በመሆኑም የማንነታቸው መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቻቸውን የኔ ብለው ይጠብቋቸዋል፤ይንከባከቧቸውል፤ያስተዋውቋቸዋልም፡፡ በሌሎች ምክንያቶች ማለትም በኢኮኖሚ ጥቅሞችና ለተሻለ ሕይዎት ሲሉ የተሰደዱ ግን ፣ቀድመው ውጪ ያዩ በመሆኑ የነርሱነት መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቻቸውን ፈጥነው ከኅሊናቸው መፋቅ ብቻ ሳይሆን፣ በጥላቻና በንቀት ስለሚመለከቷቸው ያፍሩባቸዋል፤ አይገለገሉባቸውም፤እንዲታወቁም አይፈልጉም፡፡ ከሁሉም በላይ ወላጆች በፈለጉ ጊዜ ከፈለጉት አገር ለመውጣትና ለመግባት እንዲያም ሲል ለመኖር የሚፈልጉ ሰዎች፣ በአገራቸው ምንም ዓይነት የመኖር ችግር ሳይገጥማቸው ሚስቶቻቸው ሊወልዱ ጥቂት ሳምንታት ሲቀራቸው፣ አሜሪካ፣ካናዳ፣ጀርመን ወይም ሌላ አገር ሂደው እንዲወልዱና ሕፃናቱ የዚያ አገር ዜግነት እንዲኖራቸው የማድረጉ ተግባር በስፋት የሚታይ ነው፡፡ የእነዚህ ሰዎች ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት መጠኑን ያለፈ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነት ያላቸው ስሜትና እምነት ባንዳዊ ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የተሻለ ገቢ ካላቸው ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ልጆቻቸው የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ያላቸው አይደሉም፡፡ ይህም ሕዝቡ ትናንት በዘመነ ቅኝ አገዛዝ ወቅት በአካል ቅኝ ያልተገዛው ኢትዮጵያዊ በሚከተሉት ሁለት ተያያዥና ተደጋጋፊ ምክንያቶች ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት እንደተዳረገ እናያለን፡፡
አንድ ሕዝብ ትውልድ አገሩን ትቶ ወደማያውቀው አገር የሚሰደደው ሁለት ተያያዥና ተደጋጋፊ የሆኑ ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡፡ የመጀመሪያው በአገሩ በሰላም ሠርቶ የመኖር ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማኅበራዊና ባህላዊ መብተና ነፃነቶቹን ሲገፈፍና ሲነጠቅ፣ በሕይዎት ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ሲጣበብበት ነው፡፡ ሁለተኛው ከአገሩ ወጥቶ ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ መኖሩ አስተማማኝ ሲሆን ናቸው፡፡ እነዚህም ከውስጥ አስወጪ ገፊ ኃይል እና ከውጪ ተቀባይ ሳቢ ኃይል መኖር ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ሕዝቡን በነበረ መልኩ እንዲኖር የፈቀደ አልሆነም፡፡ ትውልዱ በፖለቲካዊ ፍልስፍና፣በነገድ፣ በሃይማኖት፣በሥልጣን አያያዝ ተከፋፍሎ አገሪቱን የብጥብጥ ምድር አደረጋት፡፡ ሥልጣን የያዙ ቡድኖች ተቀናቃኛችን ነው ያሉትን ግለሰብና ቡድን ያላንዳች ርኅራኄ ገደሉ፣አሰሩ፣አሰቃዩ፤ የፖለቲካ ትርምሱ ማኅበራዊ ሰላምን በእጅጉ በማመሱ፣በሰላም ወጥቶ ለመግባት፣ሠርቶ ለማምረት፣ወልዶ ለመሳም፣አሳድጎ ለመዳር አላስቻለም፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በስፋትና በተከታታይ መታየት ሕዝቡን አማራጭ የመኖሪያ አካባቢን እንዲያማትር ግድ አለው፡፡ ባደረገው የአማራጪ መኖሪያ ፍለጋም ለማስተማር ቀይ ሳንቲም ሳያወጡ በተማረ የሰው ጉልበት ያልተማረ ሰው ሊሠራቸው የሚችሉ ሥራዎችን በጥራት፣በቅልጥፍናና ሥጋት በሚፈጥረው ጥንቃቄ ኃላፊነቱን የሚወጣ ፣ያወቀ፣ግን በርካሽ የጉልበት ዋጋ ጥራት ያለው ሥራ የሚሠራ የሰው ኃይል የሚፈልጉ አገሮች ቁጥር መበራከት፤(አሜሪካ፣ካናዳ፣አውትራሊያ፣ጀርመን፣ኖርዌ፣ስውዲን) የኢትዮጵያዊነት ብሔርተኝነትን ለማጥፋት የረጅም ጊዜ ዕቅድ የነበራቸው አገሮች የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ትውልዱን ከኢትዮጵያዊነት ስሜትና እምነት ለማፋታት ባለቸው የቆየ ዓላማ መሠረት፣ ስደት ፈላጊዎችን በገፍ የመቀበል ፍላጎት አሳዩ፡፡ ይህም የሕይዎት ማቆያ ፣የተሻለ ኑሮ መምራት አማራጪ ይፈልግ ለነበረው ሰው እንደመልካም አጋጣሚ ቆጥሮ የተቸገረውም ያልተቸገረውም ለስደት ተሰለፈ፡፡ ፣ስደትንም አማራጭ የሌለው ተመራጭ አድርጎ እንዲይዘው አደረገው፡፡ በነዚህ የውስጥና የውጪ ሁኔታዎች ተሟልተው መገኘት ኢትዮጵያዊው የተሻለ ኑሮና ሰላም የነበራቸው ሁሉ ቋሚ ንብረቶቻቸውን በአልባሌ ዋጋ እየሸጡ ተሰደዱ፡፡ ምዕራባውያኑ በተለይም ዩ.ኤስ.ኤ በራሱ ፍላጎት የሚሰደደው ሕዝብ የሚፈልገውን ያህል የተማረ የሰው ኃይል ሊያስገኝላት ባለመቻሉ፣ዲ.ቪ የሚል ፕሮግራም በመዘርጋት አያሌ የሦስተኛው ዓለም ሕዝቦችን የተማረ የሰው ኃይል መሳቡ ይታወቃል፡፡ በዚህ ፕሮግራም የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ይህም ወዶና ፈቅዶ ራስን ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት ማዋል አለመሆኑን በምን መልክ ማሳመን ይቻላል?
በዚያም አልን በዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን በአካል ቅኝ ሳንገዛ፣የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች መሆናችንን ልናስተባብልበት የምንችልበት ማስረጃ የለም፡፡ የሚያዋጣው የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች አልሆንም ብሎ በመሸምጠጥ ሳይሆን፣ለዚህ የዳረጉንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ዐውቀን ከነዚያ ሁኔታዎች ልንወጣ የምንችልባቸውን መንገዶች ማመቻቸት ነው፡፡ እንደ ነገድ ሳይሆን፣እንደ አገር በአንድነት ማሰብና በአንድነት መቆም ስንችል ነው፡፡ የተጫነንን ከማንነት የመፋታት አባዜ ከላያችን ላይ አራግፈን ጥለን አኩሪው ማንነታችን ስንላበስ ነው፡፡ ታሪካችን ፣ባህላችን፣ቋንቋችን፣ በአጠቃላይ እኛነታችን ዐውቀን ለማንነታችን ዳብሮ መቀጥል ስንቆም፣ለዚህም ተገቢ የሆነውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ስንሆን ብቻ ነው፡፡
የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ርዕሠ አንቀጽ፡ የሙስናን ዛፍ ለማድረቅ ቅርንጫፉን ብቻ መቁረጥ በቂ አይሆንም
Saturday, May 18th, 2013
ፈረንጆች ታይታኒክ የተባለችውን ግዙፍ መርከብ የገለበጠውን ዓይነት ከባሕር በታች የተደበቀ ግግር በረዶ ‘ለአንዳንድ የማይታዩ ነገር ግን ግዙፍ የሆኑ’ ችግሮች ተምሳሌት አድርገው ይጠቀሙበታል።ከባሕሩ ውስጥ ብቅ ብሎ የሚታየው የበረዶ ጫፍ ሲያዩት ትንሽ ስለሚመስል ብዙዎችን ያሳስታል-ከሥሩ ያለውን ተራራ የሚያህል ግዙፍ የበረዶ ግግር ለመገመት አያስችልምና።ለዚህም ነው አንዳንድ ተገልጦ ያልታየ ነገር ግን በትንሹ ብቅ ያለ ችግርን “this is only the tip of the iceberg” (ይህ የግግር በረዶው ጫፍ ብቻ ነው) በማለት የሚገልጹት-ከሥሩ ቢታይ ሥር የሰደደና ሰፊ ነው ለማለት።
ሰሞኑን ከተራ ደላሎችና ትራንዚተሮች አንሥቶ እስከ ቱጃር ባለሀብቶችና ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ድረስ የተዳረሰው የሙስና ቅሌት የብዙው ዜጋ የመወያያ ርእስ ሆኖ ሰንብቷል።ይህ የሰሞኑ ክስተት ብቻውን ግን የመጨረሻ ውጤት አይደለም።ይልቅስ ከባሕር በታች ገዝፎ እንደተደበቀው የግግሩ በረዶ ጫፍ ጥቂቱ ማሳያ ነው እንጂ።
መንግሥት ለረጅም ዘመን ሙስናን የመዋጋት ቁርጠኝነትም ቢያሳይም በዚያው ልክ ግን ችግሩ በአገራችን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አልደረሰም ሲል ኖሯል። አንዳንድ መረጃዎች ብቅ ሲሉም ችግሩ እንደሚወራው አይደለም፣ የተጋነነ ነው ሲል ተደምጧል። ይህን ሲል ቢቆይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የሙስናን አፈጻጸም ረቂቅነትን እያባከነ ያለውን የሕዝብና የሀገር ንብረት ሲያስተውል ግን አሳሳቢነቱን አምኖ ለመቀበል ተገድዷል፡:
በአገራችን እየተስፋፋ የመጣውን ሙስና በተመለከተ ከመንግሥት አስቀድሞ የነቃው ሕዝቡ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሙሰኞችን በተመለከተ ሕዝቡ “በማስረጃ ካልሆነ” እየተባለ ሐሳቡን የሚገልጽበት መድረክ ባያገኝም እርስ በርሱ መወያየቱ ግን አልቀረም፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፍጥነት ወደላይ እየተተኮሰ የመጣውን የአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት አኗኗር በመመልከትም ሆነ ያካበቱትን ንብረት በመታዘብ ከጥርጣሬ ያለፈ ግንዛቤ ይዞ ነበር፡፡ ቢያንስ እነዚህ ሰዎች ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብና ሀብት ማካበታቸውን መጠርጠር ችሏልና።
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እስከ አሁን ድረስ በሙስና ባሕር ውስጥ ሲዋኙ የቆዩትን ትንንሾቹን ዓሣዎች እንጂ ዓሣ ነባሪዎቹን ለመያዝ ድፍረቱም፣ ፍላጎቱም አቅሙም የለውም እየተባለ ሲታማ ቆይቷል፡፡ በተለያዩ መድረኮችም ተጠይቋል። ለምሳሌም ኮሚሽኑ ባለፈው ማክሰኞ የሰሞኑን ሙስና በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ይኸው ጥያቄ ለኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን ተነሥቶላቸው ነበር። “እኛ ከግለሰቦች ጋር ሳይሆን ከወንጀሉ ጋር ነው ጉዳያችን። ሙስና ከፈጸመ ማንንም አንተውም። ሁሉንም ጥፋተኞች ለሕግ እናቀርባለን” ብለዋል።
ያም ሆኖ ‘የመንግሥትን ሌቦች’ በተፈለገው ሁኔታ ወደፍርድ አደባባይ ቶሎ ቶሎ ብቅ ሲሉ አይተናቸው አናውቅም። አንዳንድ ጊዜ ስለመንግሥት ሌቦች በመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ መሰግሰግና አለአግባብ መበልፀግ አልፎ አልፎ በራሱ በመንግሥት ከሚነገረው ውጪ እነዚህ ‘ሌባ’ የተባሉት ሰዎች የት እንዳሉና የተነከሩበት የሙስና ባሕር ስፋትና ጥልቀትስ ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአብዛኛው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ባሉ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ሹሞች የሚፈፀሙትን የሙስና ድርጊቶች ተከታትሎ በማጋለጥና አጥፊዎች በማስቀጣት ረገድ የማይናቅ ሥራ ቢሠራም ትልልቆቹን ዓሣዎች ግን በተደጋጋሚ ጊዜ ሳይደፍራቸው ቆይቶ ነበር፡፡
አሁን ፀረ ሙስና ኮሚሽን የጀመረው ሙሰኞችን ወደሕግ የማቅረብ አካሄድ ይበልጥ ይግፋበት የሚያሰኝ ተግባር ነው፡፡ ለዚህ የኮሚሽኑ እርምጃም ከመቀመጫችን ተነሥተን ተገቢውን ክብርና አድናቆት እንሰጣለን፡፡ ሙስናን መዋጋት የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጎች ሓላፊነት መሆኑን በመረዳት ለኮሚሽኑ ሥራ መቃናት የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ በስም ያልተገለጹ ዜጎችም በአድናቆት እናጨበጭባለን። ይህን በምንናገርበት አንደበታችንም እግረ መንገዳችንን እርማት የሚያሻውን የኮሚሽኑን አካሔድ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
አንደኛ ነገር ኮሚሽኑ በአንድ መንግሥት መሥሪያ ቤትና በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን በተመረጡ ተቋሞች ላይ ጊዜ ወስዶ ተመሳሳይ መረጃ የመሰብሰብ ሥራውን ካጠናቀቀ በኋላ ውጤቱን በአንድ ላይ ይፋ ቢያደርግ የተሻለ ይሆን ነበር እንላለን፡፡ አሁን እንዳደረገው በአንድ ቦታ ላይ ማተኮሩ ለሌሎች የማንቂያ ደወል ሊሆናቸው ይችላል፡፡ በዚህም መረጃዎችን ለመደበቅ፣ ምስክሮች ሊሆኑ የሚችሉትን የዶክመንትና የሰው ማስረጃዎችን ደብዛ ለማጥፋት እንዲሁም በሙስና የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት በተለያዩ ዘዴዎች ለማሸሽ ጊዜ ያገኛሉ ማለት ነው፡፡
አሁን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በፍርድ ቤት እልባት እስኪያገኝ ድረስ የሕዝቡም የኮሚሽኑም ትኩረት በእነሱ ላይ ይውልና ያልተጋለጡ ባለሥልጣናት ከሚታዩበት የግግር በረዶው ጫፍ ተነሥተው ወደ ጥልቁ ባሕር ለመግባትና ለመሰወር አመቺ ሁኔታ ሊፈጠርላቸው ይችላል፡፡ ሁለት ዓመት ፈጀ የተባለው ክትትል እነዚህን 24 ሰዎች ብቻ ለመያዝ ከሆነ በርግጠኝነት ዘግይቷል። ክስ ከተመሰረተበት የሙስና ጉዳይ ተነካኪነት አንጻር ሲታይ ሌሎችም ባሕሩ የደበቃቸው ብዙዎች መኖራቸው አይቀርም።
ያም ሆኖ አሁን የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ የግግሩ በረዶ ጫፍ በባሕሩ ተሸፍኖ ሳይጠፋ በፊት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ በሌላ አባባል የአንድ ሰሞን የሚዲያ ግርግር ከመሆን አልፎ ተከታታይ መሆን ይጠበቅበታል ማለት ነው፡፡
ሁለተኛው ጉዳይ ኮሚሽኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሀብት ምዝገባ ውጤት ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ብሎ ቃል ከገባ ረዘም ያለ ጊዜ ቢሆንም ይህ እስከ አሁን ባለመፈፀሙ የትኛው የመንግሥት ባለሥልጣን ምን ያህል ሀብት እንዳለው በሕዝቡ ዘንድ ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡ ይህ የ30ሺህ ሰዎችን ሀብት መዝግቤያለሁ የሚለው የኮሚሽኑ ድክመት ነው። የባለሥልጣናት ሀብት በጊዜ ቢታወቅ ኖሮ ከሚታወቀው አቅማቸው በላይ ሲያካብቱ ሕዝብ አይቶ ዝም አይልም ነበር።
ሌላው ኮሚሽኑ የግሉን ዘርፍ ‘አያገባኝም’ ብሎ መተዉ አግባብ አይደለም እንላለን። እስከ አሁን ድረስ በሙስና ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተከሰሱት የግል ባለሀብቶች ናቸው። ከየት እንዳመጡት ሳይታወቅ ድንገት ጣሪያ ላይ የሚወጡት የግል ባለሀብቶች ጀርባ ካልተጠና ወደፊትም ባለሥልጣናትን ማባለጋቸው፣ ሙስናውም ተጠናክሮ መቀጠሉ አይቀርም።
የሆነው ሆኖ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እስካሁን የሠራው ሥራ የሚያስመሰግነው ነው። የራሱን አቃቤ ሕግ በሙስና ከመክሰስ አንሥቶ ‘የመንግሥት ሌቦችን’ ጥሩ እያየ ነው። አሁንም የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሀብት በፍጥነት ለሕዝቡ ያሳውቅ፡፡ ካሁን በኋላም ጥረቱን በማጠናከር ከሕዝቡም ከሚዲያው ጋር ይበልጥ በመተባበር በሙስና ላይ የተጀመረውንና ጠብ…ጠብ የሚለውን ካፊያ ዘመቻ ወደ ጎርፍ ይለውጥ! ከግግር በረዶው ጫፍ ላይ የሚታዩትንም ሆነ ከባሕሩ ሥር የተደበቁትን ተጠርጣሪዎች ለማጋለጥና ለፍርድ ለማቅረብ ይበልጥ በተቀናጀ ሁኔታ ይነሳ! የሙስናውን ዛፍ ከቅርንጫፉ ብቻ ሳይሆን ከሥሩ ይቁረጥ!!
የ’ልማታዊው አርቲስት’ ሠራዊት ፍቅሬ የኢቲቪ ፕሮግራም ታገደ
Saturday, May 18th, 2013
(ዘ-ሐበሻ) በሕዝብ ዘንድ “ልማታዊ አርቲስት” በሚል የመሽሟጠጫ ስያሜ ከሚጠሩት አርቲስቶች መካከል የቀድሞው የደርግ ወታደርና የአሁኑ የወያኔ ስርዓት ዋነኛ አቀንቃኝ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፤ ለመንግስት በሚያደርጋቸው የአጎብዳጅነት ተግባራት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ የቶክ ሾው ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ የዓየር ሰዓት ተፈቅዶላት ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደጠቆሙት አርቲስቱ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ ያቀርበው የነበረው ቶክ ሾው ውለታው ተዘንግቶ እንዲታገድ ተደርጓል።
“ግራና ቀኝ” የሚል ቶክ ሾው ከሌላኛው ‘ልማታዊ’አርቲስት ሽመልስ በቀለ ጋር ላለፉት 6 ወራት ሲያቀርብ የቆየው የደርጉ ወታደር ሰራዊት ፍቅሬ ይህን የዓየር ሰዓት ያገኘው ለመንግስት ባለው ታማኝነት እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ድንገት ያቀርበው የነበረው ፕሮግራም በወያኔ ካድሬዎች በሚመራው ኢቲቪ እንዲታገድ መዳረጉ አስተተያየት ሰጪዎችን “ፍቅር አለቀ ወይ?” የሚሉ ግምቶችን እንዲሰጡ በር ከፍቶላቸዋል።
የአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት ከተሰማ በኋላ አርቲስቶች ጥቁር በጥቁር ለብሰው “ባለ ራዕዩን መሪ” እንዲቀብሩ በማስተባበር እንዲሁም ጥቁር በጥቁር አንለብስም ያሉና ለቅሶ አንደርስም ያሉ አርቲስቶችን “ሲያስጠቁር” (ለመንግስት በማቃጠር) ነበር እየተባለ የሚተቸው አርቲስቱ 6 ወር በቴሌቭዥን ያቀረበው “ግራና ቀኝ” ቶክ ሾው እንዲታገድ የተደረገው “አዝናኝ ፕሮግራም” አይደለም በሚል ምክንያት ነው ተብሏል። ይህ እገዳ እስከመቼ ሊቀጥል እንደሚችል እንደማያውቁ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከባለፈው እሁድ ጀምሮ መታየት አቁሟል ብለዋል።
ኢቲቪ ወትሮም አዝናኝ ፕሮግራም አቅርቦ የት ያውቅና ሲሉ የሚተቹ አስተያየት ሰጪዎች አዝናኝ ፕሮግራም አይደለም በሚል ቶክ ሾው እንዲታገድ መደረጉ በቂ ምክንያት አይደለም በሚል ከእገዳው በስተጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ይገምታሉ። በተለይም እንደሪፖርተርን ያሉ አፍቃሬ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ያሉ ጋዜጦች “በአቶ መለስ ስም መነገድ ይቁም” በሚል በረዥሙ ሲተቹ የከረሙት እንደሠራዊት ያሉትን ሆዳም አርቲስቶች ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች የኢቲቪ ካድሬ መሬዎች የሰራዊትን ማንነት በግልጽ ተረድተው ይሆናል ያገዱት ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
በዚህ ዜና ዙሪያ ዘ-ሐበሻ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬን ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በቅርቡም በአስገድዶ መድፈር አቤቱታ እንደቀረበበት መዘገቡ ይታወሳል።
የአስገድዶ መድፈር አቤቱታውን ዜና ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለግንዛቤ ደግሞ የታገደውን የሰራዊት ፍቅሬ ሾው አቅርበናል።
Sport: የቤካም እና የካራገር “ጫማ ሰቀላ” የእንግሊዛውያኑ ብቻ ሳይሆን የኛም ወሬ ሆኗል
Saturday, May 18th, 2013
ከአሰግድ ተስፋዬ
የተወዳጁ እግር ኳስ ስፖርት « ፈጣሪ » እንደሆነች የሚነገርላት ነገር ግን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ብዙም ውጤታማ መሆን ያልቻለው እንግሊዝ በተለያዩ ወቅቶች ምርጥ እግር ኳሰኞችን አፍርታለች።
ከነዚህ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች ኮከቦች መካከል ላለፉት ሃያ ዓመታት በስፖርቱ በስኬታማነት ያሳለፈው ዴቪድ ቤካምና ከልጅነት እስከ እውቀቱ የመርሲሳይዱን ክለብ መለያ ብቻ የለበሰው ጂሚ ካራገርን ፣ ዋይኔ ሩኒን ፣ ማይክል ኦዌንና ሌሎች ተጫዋቾችን መጥቀስ ይቻላል።
ከእነዚህ ተጫዋቾች መካከል በስፖርቱ ባስመዘገበው ስኬት ግንባር ቀደም የሆነው ዴቪድ ቤካምና የሊቨርፑሉ ጂሚ ካራገር « ጫማ መስቀላቸውን» ገልጸዋል። የማንችስተር ዩናይትዱ የተከላካይ መስመር ተሰላፊው ሪዮ ፈርዲናንድ ደግሞ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
እነዚህ ጉዳዮች የመገናኛ ብዙኃን ሰሞነኛ መሪ ዜና ቢሆኑም ልዩ ትኩረት ያገኘው የዴቪድ ቤካም ጫማ መስቀል ጉዳይ ነው።
አንጋፋውና ውጤታማው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ የነበሩት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ካሳደጓቸውና « ፈርጊ ቤቢስ » እየተባሉ ይታወቁ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ዴቪድ ቤካም ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በ115 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል። ለአሳዳጊው ማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ ደግሞ 394 ጨዋታዎችን አድርጓል።
የ38 ዓመቱ ቤካም « ቀያይ ሰይጣኖች » በመባል ከሚታወቀው ማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ጋር ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችንና የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በምስራቃዊ ለንደን የተወለደው የመሐል ሜዳ ተጫዋቹ ቤካም ከአሳዳጊው ክለብ ከተለያየ በኋላ ለስፔኑ ኃያል ሪያል ማድሪድ ፣ በአሜሪካ ሜጀር ሶከር ሊግ ተሳታፊ ለሆነው ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ፣ለጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ፣ በመጨረሻ ደግሞ ለፈረንሳዩ ሻምፒዮና ፓሪስ ሴንት ጄርሜን እግር ኳስ ክለቦች ተጫውቷል። ተጫዋቹ በጨዋታ ዘመኑ ከዩናይትድ ጋር ያነሳቸውን ዋንጫዎች ጨምሮ በጠቅላላው 19 ዋንጫዎችን አንስቷል።
ዴቪድ ቤካም በአራት የተለያዩ ሊጎች ከተለያዩ ክለቦች ጋር ዋንጫ በማንሳት ብቸኛው እንግሊዛዊ ተጫዋችም ነው።
ዴቪድ ቤካም ቀያይ ሰይጣኖቹን በተለ ማማጅነት የተቀላቀለው በአውሮፓውያኑ 1991 ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ለዋናው ቡድን ተሰልፎ የመጫወት እድል አግኝቷል። ከአንድ ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን የፕሮፌሽናል ተጫዋችነት ኮንትራት ፈርሟል። በኦልድ ትራፎርድ በነበረው ቆይታ ያሳየው ምርጥ ብቃቱ ዓለም አቀፍ እውቅና አስገኝቶለታል። ይህንን እውቅናውን ተከትሎም ታላላቅ ተጫዋቾችን በመሰብሰብ የሚታወቀውን የስፔኑን ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሎ በአውሮፓውያኑ 2003 የላ ሊጋውን ዋንጫ አንስቷል።
ከስፔኑ ኃያል ወደ አሜሪካው ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ ተዛውሮ ተጫውቷል። በዚህ ክለብ በነበረው ቆይታ በውሰት ለጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ተሰልፎ የመጫወት እድል አግኝቷል። ወደክለቡ ኤልኤ ጋላክሲ ተመልሶ ዋንጫ ካነሳ በኋላ ለፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጄርሜን ፈርሞ ተጫውቷል። እንዲሁም ዋንጫ ካነሳ በኋላ ጫማ መስቀሉን ይፋ አድርጓል።
ቤካም በሦስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር ብቸኛው እንግሊዛዊ ተጫዋች ከመሆኑም በላይ በአውሮፓ ዋንጫ ለግብ የሚሆኑ በርካታ ኳሶችን በማቀበል በታሪክ ሁለተኛው ተጫዋች ነው።
«ለልጅነት ክለቤ ማንችስተር ዩናይትድ ተጫውቼ ዋንጫዎችን አንስቻለሁ። ለአገሬም ከአንድ መቶ በላይ ጨዋታዎችን ከማድረጌም በላይ በአምበልነት መርቻለሁ ። ለታላላቅ ክለቦች ተጫውቻለሁ። ይህ ለእኔ ከስኬትም በላይ ነው» ብሏል ስንብቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫው።
«በእግር ኳስ ተጫዋችነት ሕይወቴ ካከና ወንኳቸው ተግባራት ከምኮራባቸው ነገሮች አንዱ አገሬን በአምበልነት መምራት መቻሌ ነው። የሦስቱን አናብስት መለያ በመልበሴ ከታላላቆቹ ተጫዋቾች ተርታ ከመመደቤም በተጨማሪ አገራቸውን ለሚወዱ ደጋፊዎችም የኩራት ምንጭ ሆኛለሁ። በዚህም እድለኛ ነኝ » ብሏል።
ሰዎች ሜዳ ሲገባ ያለውን ሁሉ እንደሚሰጥ ጠንካራ እግር ኳሰኛ እንዲያየኝ እፈልጋለሁ ያለው ቤካም በተጫዋችንት ሕይወቱ የረዱትን ሁሉ አመስግኗል።
የእንግሊዝ ዋና ከተማ የ2012 ኦሊምፒክ የአዘጋጅነት እድል እንድታገኝና እድሉን ካገኘች በኋላም በዝግጅቱ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገውን የቤካምን ከእግር ኳስ ዓለም መገለል አስመልክቶ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች አድናቆታቸውን ለተጫዋቹ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
ሰሞኑን ራሳቸውን ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ማግለላቸውን ካስታወቁት መካከል የሊቨርፑሉ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ጂሚ ካራገር ይገኝበታል። የ35 ዓመቱ ካራገር ክለቡ ሊቨርፑል እሁድ ከኩዊንስ ፓርክ ሬንጀርስ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ ላይ ከተሳተፈ በኋላ ነው ሙሉ ለሙሉ ከጨዋታ ዓለም የሚገለለው።
ካራገር በእግር ኳስ ተጫዋችነት በሊቨርፑል ባሳለፋቸው 16 ዓመታት ሁለት የኤፍኤ ፣ ሦስት የሊግ ፣ሁለት የኮሙኒቲ ሽልድና አንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ቢያነሳም አንድም ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሳያነሳ ከኳስ ተጫዋችነት መገለሉ እንደሚቆጨው ተናግሯል።
« የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ
አላገኘሁም።ይህ ከፍተኛ ቁጭት ውስጥ እንድገባ አድርጎኛል » ብሏል።
ሊቨርፑል 732 ጨዋታዎችን ያደረገው ካራገር ለክለቡ በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ ሁለተኛው ተጫዋች መሆን ችሏል።ለሊቨርፑል በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ ቀዳሚ የሆነው ያን ካላጋን ሲሆን ተጫዋቹ 857 ጊዜ የመርሲሳይዱን ክለብ መለያ አድርጎ ተጫውቷል።
በቴሌቪዥን የእግር ኳስ ተንታኝ ሆኖ ለመስራት ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ካራገር « ጫማውን የመስቀል » ውሳኔ ላይ የደረሰው ከ12 ወራት በፊት እንደነበረም ገልጿል።
እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ የተከላካይ መስመር ተሰላፊ ሪዮ ፈርዲናንድ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን 81 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተው የ38 ዓመቱ ፈርዲናንድ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ለማግለሉ በምክንያትነት የጠቀሰው ትኩረቱን ለክለቡ ለማድረግ በመፈለጉ መሆኑን ተናግሯል። እነዚህ ተጫዋቾች ጉዳይ የሰሞኑ የዓለም የመገናኛ ብዙኃን የፊት ገጽ ዜናና መነጋገሪያ ሆነውሰንብተዋል።
የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) – ክፍል 3 ከ 3
Saturday, May 18th, 2013
ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
የአቶ መለስን መሞት መንግስት ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም. ይፋ አደረገ። መንግስት ጥር 17 ቀን 2005 ዓ.ም. የመለስ ራዕይ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ በሃዘን መግለጹን የሚያብራራ እና መታሰቢያ ተቋም የሚመሰረት ህግ አወጀ። የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ተቋም የገቢ ምንጭ የግል ለጋሾች፣ ገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞች፣ የኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች ምንጮች እንደሚሆኑ አዋጁ ጨምሮ አብራራ። መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ደግሞ ህውሃት ‘የመታሰቢያ ተቋም መስራች ጉባኤ’ ተብሎ የሚጠራ ሌላ ድራማ በማዘጋጀት የኢትዮጵያ ህዝብ በአቶ መለስ ራዕይ ፍቅር መጠመዱን እና ይኽን ፍቅሩን በሃዘን መግለጹን የተለያዩ ተናጋሪዎች በጉባኤው እንዲያብራሩ አደረገ። የመታሰቢያ ተቋሙ ግቦች እና ተዛማጅ ጉዳዮችም ተነገሩ። በድርጅታዊ የሚስጢር አሰራር ቀደም ብሎ የተመረጡ የቦርድ አባላት በጉባኤው ላይ አንደ አዲስ ተመረጡ። ወ/ሮ አዜብም ፕሬዘዳንት ተደርጋ ተመረጠች። ‘መለስ እንደተሰዋ ሁሉ እኛም እስከምንሰዋ ድረስ ለመስራት ቃል እንገባለን‘ የሚል የደርግ አይነት መፈክር በማሰማት ምርጫውን መቀበሏን ገለጸች። ይኽ ድራማ የታየው በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ይሁንና አዜብ መስፍን በጉባኤው ላይ ‘እንደ መለስ እስከምንሰዋ ድረስ እንሰራለን’ ስትል ‘እስክንሞት ድረስ አምባገነናዊ አገዛዛችን ይቀጥላል’ ማለቷ ይመስላል። አምስት ነጥቦች አነሳለሁ።
ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በጀርመን በርሊን ከተማ ተካሄደ
Saturday, May 18th, 2013ዘጋቢ በየነ መስፍን ከጀርመን
እ.ኤ.አ በሜይ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን በርሊን ከተማ የኢትዮጵያውያን የፖለቲካና ሲቪክ ማህበር አባላት አንድነት ድርጅት (ኢ.ፕ.ኮ.) በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ350 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ፓርቲ /ኢሕአፓ/፣የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት /ሞረሽ/ እና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አመራር እና አባላትም በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል።

መነሻውን ”ቬንደርሸር ማርክት አንድ” /Werderscher Markt 1/ ከሚባለው የከተማው ክፍል በማድረግ በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ባንድራ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ቻንስለር አንጌላ ሜርክል ጽ/ቤት አድርጓል።
”በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገው የዘር ማጥራት ዘመቻ ይቁም!”
”የህሊና እስረኞች ይፈቱ!”
”የሃይማኖት ነፃነት ይከበር!”
”ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ!”
”የጀርመን መንግስትና የአውሮፓ ህብረት ለአፋኙ የወያኔ አገዛዝ የሚያደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ ያቁሙ!”
”ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር!” የሚሉ መፈክሮች በሰፊው የተደመጡ ሲሆን ከአንድ ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ ተሰላፊው በመጀመሪያ በጀርመን ፓርላማ /Bundestag/ ፊት ለፊት በኋላም በጀርመን ቻንስለር ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ የተለያዩ መፈክሮችን ያሰማ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በኢ.ፕ.ኮ. አማካኝነት በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን የዘር ማጥራት ወንጀል የሚቃወሙ ቁጥራቸው ከሶስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ጀርመናውያንን ፊርማ የያዘውን ሰነድ ለቻንስለሯ ጽ/ቤት ገቢ የተደረገ ሲሆን የኢ.ፕ.ኮ. ሊቀ መንበር፣እንዲሁም የኢሕአፓ ተወካይ፣የሞረሽ እና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተወካዮች አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ይህ ከሶስት ሰዓት በላይ የፈጀ የተቃውሞ ሰልፍ በሠላምና በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል።
የመምህራን ማኅበር በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ተቋማት መዳከም ዙሪያ ስጋቱን የሚገልጽ መግለጫ አወጣ
Saturday, May 18th, 2013
(ዘ-ሐበሻ) በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ “የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችና ተቋማት” የውድቀት አደጋ አንዣቦባቸዋል ሲል ስጋቱን ገለጸ። ማህበሩ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “በመምህራን ላይ የሚታየው የ እውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመሙላት አጫጭር ስልጠናዎችንና የክረምት ኮርሶች ቢሰጡም የትምህርቱ ጥራት ዋነኛ መመዘኛ መስፈርት የፖለቲካ ታማኝነት የሚለው ስንኩል የወያኔ አስተሳሰብ ገኖ በመውጣቱ በርካታ ልምድ ያላቸው መምህራን ሥራቸውን እያለቀቁ መሄዳቸው የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ተቋማት በአሁኑ ጊዜ ይበልጥ ተዳክመዋል” ብሏል።
ጠ/ቤተ ክህነት የመምህር ግርማ ወንድሙን እገዳ አጸና
Friday, May 17th, 2013
ዘ-ሐበሻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ እንዳያጠምቁ መታገዳቸውን መዘገቧ ይታወሳል። ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው ደግሞ አዲስ አበባ የሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት የአጥማቂውን እግድ እንዳጸና ገልጿል። በአነጋጋሪነታቸው የቀጠሉት መምህር ግርማ እንዳያጠምቁ መታገዳቸው ከተሰማ በኋላ ም ዕመናን የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።
ጠ/ቤተክህነቱ ግንቦት 2 ቀን 2005 ለ:-
- ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
- ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ ልዩ ጽ/ቤት
- ለአስተዳደር መምሪያ
- ለሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
- ለምሥራቅ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
- ለፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት
- ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
- ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት
- ለአ/አ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
- ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
- ለአ/አ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ
- ለቂርቆስ ክ/ከ ፍትሕ ጽ/ቤት
ግልባጭ አድርጎ በጻፈው የእግዳ ማጽኛ ደብዳቤ ላይ መምህሩን “አጥማቂ ነኝ ባይ” ሲል ገልጿቸዋል። ደብዳቤውን እንደወረደ ያንብቡት።
ጉዳዩ፡- በአስቸኳይ አጥማቂ መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ጉ/ጽ/ቤት በቁጥር 339/ቀ/አ/ቤ/ክ በ28/8/2005 ዓ.ም የተሰጠው እገዳ መ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት ያጸናው ስለመኾኑ ይመለከታል፤
መ/ር ግርማ ወንድሙ ሰባኬ ወንጌልና አጥማቂ ነኝ፤ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት በሕገ ወጥ መንገድ እስከ አሁን ድረስ በደብሩ እያጠመቁ ይገኛሉ፡፡
ይኹንና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከ1993 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ በየወቅቱ በሕገ ወጥ መንገድ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት ሕዝበ ክርስቲያኑን በየደብሩ ቅጽር ግቢ በማሰባሰብ የሚያጠምቁትን በተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ከቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና ሥርዐት ውጭ በሚፈጸም ስብከትና ጥምቀት፤
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሳይፈቅዱ የሚሰጥ የወንጌልና ጥምቀት አገልግሎት መስጠትን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ቢኾንም በሥርዐተ አልበኝነት በተለያዩ ቦታዎች የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሲጣስ ይታያል፡፡
በመኾኑም መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚፈጽሙት ሕገ ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና የወንጌል አገልግሎት መኾኑን እየገለጽን የእምነታችን ተከታይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከዚህ እግድ ጋራ በተያያዘ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥመው የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ጥብቅ ክትትል በማድረግ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ እያሳሰብን የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላትም የቤተ ክርስቲያኒቱን ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን::
ሰውየው (ክፍልሁለት) ከይገርማል ታሪኩ
Thursday, May 16th, 2013
ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ መዐሕድን ሲቀላቀሉ ድርጅቱ በአማራው ክልል እግሩን አልሰደደም ነበር:: ችግሩ ፋታ የሚሰጥ አይደለም:: አማሮች ካለአለሁ ባይ: ካለአይዟችሁ ባይ እየተጨፈጨፉ ነው:: በቀልን ሰንቆ ከበረሀ የተነሳውና ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ በእጁ ያደረገው ወያኔ ሀላፊነት በጎደለው የጭካኔ ተግባር በአማራው ህዝብ ላይ ሽብር ነዛ- ሞት አወጀ:: መዐሕድን በሁለት እግሩ እንዲቆም ለማድረግ በሰውሀይል ማጠናከር ያስፈልጋል:: ህዝብን የማደራጀትና የማንቃት ስራ ገንዘብ ያስፈልገዋል:: የወገን ጩኸት ያባነናቸው አማሮች በከተሞች አካባቢ በቁጭት ድርጅቱን ለማጠናከር ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ::
ብዙሀኑ ገበሬ ምን እየተደረገ እንደሆነ እንኳ አያውቅም:: መንግስት ይመጣል መንግስት ይሄዳል:: “ሽህ ቢታለብ ያው በገሌ” እንዳለችው ድመት ማንም መጣ ማን ያው አርሶ አደር ነውና ሁሉም የእለት ጉርሱን የአመት ልብሱን ያሟላ ዘንድ ደፋ ቀና ይላል:: ሌሊት ወጥቶ ሌሊት ይገባል:: ጠብ ለማይል ኑሮ ነጋ ጠባ ደፋ ቀና እንዳለ ይኖራል:: ወሬ የሚያዳምጥበት ጊዜ የለውም:: ብቻ ይሰራል- ሰርቶ ከሚያገኘው ይገብራል:: ገበሬው የሚፈቀደው የግብር ጊዜ ወይም የተለየ መዋጮ እንዲያደርግ ሲፈለግ: አሊያም ለውትድርና:: ከዚያ ውጭ የት ወደቀ የሚለው የለም:: እርሱም የቤቱን ገበና ለመሸፈን ላይ ታች ከማለት ውጪ ስለፖለቲካ የሚያውቀው ነገር የለውም:: መንግስት- አስተዳዳሪ: የህዝብን ሰላም የሀገርን ዳር ድንበር አስጠባቂ: መሰረት ልማት (መንገድ: አስኳላ ትምህርት: የጤና ተቋም…) አስፋፊ መሆኑን ያውቃል:: የመንግስት ዘር መኖሩን ግን አያውቅም:: አንዱን ህዝብ ጎድቶ ሌላውን ለመጥቀም እንደሚያልምም አያውቅም:: በርግጥ በዘር ወይም በቀረቤታ የሚሰሩ ባለስልጣኖች እንደነበሩ: አሁንም እንደማይጠፉ ያውቃል:: የማያውቀው ነገር ቢኖር መንግስት ለአንዱ ወላጅ አባት ለሌላው ደግሞ የእንጀራ አባት መሆን ስለመቻሉ ነው::
ከተሜው የገበሬውን ያህል ለፖለቲካ ሩቅ አይደለም:: ለሚዲያወች የተሻለ ቀረቤታ ስላለው ምን እየተካሄደ እንዳለ መጠነኛም ቢሆን ግንዛቤው አለው:: ስለዚህ ይህንን የህብረተሰብ ክፍል ማደራጀት ብዙም አይከብድም:: ግን እንዴት? ሰላምና መረጋጋት ብሎ መንግስት ያደራጃቸውና የኮር አባል ተብለው የሚታወቁት ምልምል ካድሬወች ህዝቡን ሰላሙን ነሱት:: በኮር አባላት ስብሰባ ላይ የመጀመሪያው ክፍል ኢንፎርሜሽን ማቀበል ነው:: ስለዚህ የኮር አባላቱ አይደለም የሚወራውን የሚበላውንና የሚጠጣውን ሳይቀር እያነሱ እገሌ እንዲህ አለ: እገሊት ከገሊት ቤት ቡና ጠጣች በማለት በየተሰጣቸው ቀጠና ያዩትንና የሰሙትን እያጋነኑ ያቀርቡ ጀመር:: ኢንፎርሜሽን ያላመጣ የኮር አባል ስለሚገመገም ግምገማውን ለማለፍ አይደለም የታየውና የተሰማው ያልታየና ያልተደረገው ሁሉ በንጹሀን ላይ መወራት ጀመረ:: የኮር አባላቱ በግላጭ አይታወቁ ስለነበር አንዱ አንዱን ማመን እየከበደው መጣ:: ፍርሀትና ጥርጣሬ ነገሰ:: የመንግስትን ፖሊሲ ይነቅፋሉ የተባሉ ሰዎች የተነፈሱት ሳይቀር እየተነገራቸው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ምክርና ማስፈራሪ ይሰጣቸው ጀመር:: ምክርና ማስጠንቀቂያውን የጣሱ ሰዎች ሰርቀው ሊያመልጡ ሲሉ ተገደሉ: ወይም መጠጥ ቤት በተነሳ ግጭት ክፉኛ ተደብድበው ሞቱ: ወይም ባላንጣ ጊዜ ጠብቆ ገደላቸው እየተባሉ ተወገዱ:: የደርግ የቀይ ሽብር በድብቅ መተግበር ጀመረ:: ይህን ዘመን ለማለፍ ከተሜው ኮረንቲና ፖለቲካን በሩቁ አለ::
ድርጅት ለመመስረት የሚደረገው ትግል ግን በምንም መልኩ ሊደናቀፍ አይችልም:: መከፈል የሚያስፈልገው መስዋእትነት ተከፍሎ መዐሕድ እውን መሆን አለበት:: ድርጅቱ ስር እስኪሰድ ድረስ ለየት ያለ አካሄድ መከተል እንደሚገባ በመታመኑ በአንዳንድ አካባቢ ዱሮ በኢሕአፓ ጊዜ በነበረው የአደረጃጀት ስርአት መሰረት እምነት የሚጣልባቸውን በተለይ ደግሞ በዚህ መንግስት ደስተኛ ያልሆኑትን ሰዎች ሁለትና ሶስት በአንድ ላይ በማደራጀት ግንዛቤ ማስጨበጥና የአባልነት ፎርም ማስሞላት ተጀመረ:: በዚህ መልክ ውስጥ ውስጡን መዐሕድ ስር መስደድ ጀመረ:: በርግጥ የመጣውን ሁሉ በጸጋ ለመቀበል የግንባር ስጋ ሆነው ፈጥጠው የወጡ በርካታ ሰዎች ነበሩ:: መዐሕድ የሰላም ታጋይ ድርጅት ነው:: ሰላማዊ ትግል ማለት ቅሬታን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለጽ ማለት ነው:: ቅሬታ መፍትሄ ካላስገኘ ትግሉ በመንፈስና በአካል እስከመሸፈት ያደርሳል:: ይህም ማለት ከሀይል ርምጃ በመለስ ያሉትን ሁሉ መጠቀም: እምቢ አልታዘዝም አላደርግም በማለት ተቃውሞን መግለጽን ያጠቃልላል:: አዎ! ሰላማዊ ትግል ማለት ከመንግስት በኩል የሚሰነዘረውን ማንኛውም ጥቃት በሰላም መቀበል ማለት ነው:: ሳያቆስሉና ሳይገድሉ እየቆሰሉና እየሞቱ ማሸነፍ ማለት ነው:: ይህ የትግል ባህሪ በለየላቸው የወያኔ አይነት አምባገነን መንግስታት ዘንድ በእጅጉ ጎጅ ነው:: የህዝብ እምቢ ማለት አያስደነግጣቸውም:: ራሳቸውን መለስ ብለው ለመመርመር አያስችላቸውም:: ይልቁኑ በተደፈርኩ መንፈስ ያወራጫቸዋል:: ለበቀል ጦራቸውን ይሰብቁና ያገኙትን ሁሉ ማጥቃት ይጀምራሉ:: በዚህ መልኩ ሰላማዊ ትግል መስዋእትነቱን ያከፋዋል:: ኋላቀር በሆኑ አምባገነኖች በሚመሯቸው አገሮች ዘንድ ሰላማዊ ትግል የሽምቅ ውጊያ ያህል ያስቀጣል:: ሰላማዊ ታጋይ ማለት ለመንግስት አመራር አልመችም የሚል አጉራ ዘለል ነውና የሸማቂውን ያህል ይቀጣል:: አምባገነኖች አይደለም የተቃወማቸውን ኮከባቸው ያልፈቀደውን ሰው ሁሉ ቢገሉ ይችላሉ:: ወያኔወች ደግሞ ሰላማዊ ታጋይ ያውም የአማራ ማየት ቀርቶ መስማትም አይፈልጉም:: ሆኖም በአግባቡ ከተጠቀሙበት ሰላማዊ ትግል በአጭር ጊዜ ውጤታማ ያደርጋል:: ውጤታማነት ከጠንካራ አደረጃጀትና ከበሳል አመራር ውጭ አይገኝም:: መዐሕድ አመሰራረቱ ለፖለቲካ የስልጣን ፉክክር አይደለም:: አላማው በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጭቆናና ግድያ ለአለም መንግስታትና ለሰብአዊ ድርጅቶች ለማሰማት ነው:: ግን ሁሉም ትግል ያስፈልገዋል:: በዚህ ሂደት ወያኔ መራሹ መንግስት መውደቅ ከቻለ እሰየው ነው- በደምና በአጥንት የሚያምኑት እኩዮች ከጠፉ አማራውን ለይቶ የሚያሳድድ አይኖርም ማለት ነው:: ከዚያ በኋላ ለኢትዮጵያ የሚበጅ የህዝብ አስተዳደር ለመመስረት ተፎካካሪ ሆኖ መቅረብ ይቻላል:: ለሁሉም የህዝብን መንፈስ መማረክ የሚያስችል ሁለንተናዊ ብቃት መጎናጸፍ ያስፈልጋል::
የልጆች ማስፈራሪያ “አባ ዳውሎ” ተብሎ ይጠራል:: አባ ዳውሎን አይቶ የሚያውቅ ልጅ የለም:: ግን አባ ዳውሎን ይፈራል:: ሲያለቅስ የነበረን ልጅ “አባ ዳውሎ መጣብህ” ካሉት ልቅሶውን ይውጣል:: ሻእቢያና ወያኔ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን የሚያስፈራሩት “አማራ መጣልህ” ብለው ነው:: በሻእቢያና በወያኔ የተሰበከ የዋህ ይህንን ተቀብሎ አስተጋብቷል:: በኤርትራ እናቶች ልጆቻቸው ሲያስቸግሯቸው “አማራ መጣልህ” ይሏቸው ነበር:: አማራ አፉ እንደአዞ አፍ 180 ዲግሪ የሚዘረጋ ጆሮው እንደዝሆን የሰፋ: አስፈሪ የሆነ ፍጡር እንደሆነ ተደርጎ እየተነገራቸው ያደጉት ልጆች ታዲያ አማራ መጣብህ ሲባሉ ቱር ብለው የትም ይጠፋሉ- እናቶችም ከህጻናቱ ብጥበጣ ተንፈስ ይላሉ:: ይህ በኤርትራ የልጆች ማስፈራሪያ የነበረው አማራ አሁን ከልጆች አልፎ የብሄር ብሄረሰቦች ማስፈራሪያ ሆኗል:: “ነፍጠኛ” የአማራ ተለዋጭ ስም ነው:: እና ነፍጠኞች ከተባለ አማሮች ማለት ነው:: “ነፍጠኞች የብሄር ብሄረሰቦች ጠላቶች ናቸው- ኢትዮጵያ ደግሞ እስር ቤታቸው:: ነፍጠኞች አንገታቸውን ቀና ሊያደርጉ አይገባም:: አንገታቸውን ቀና ካደረጉ መሬትህን ይወስዳሉ: ነጻነትህን ይነጥቃሉ” ነቅተህ ጠብቅ ተብለው ይቀሰቀሳሉ:: የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አማሮችን ጠንቅቀው ያውቋቸዋል:: አማሮች በያሉበት ላባቸውን አንጠፍጥፈው ሰርተው የሚኖሩ እንደሆኑ አሳምረው ያውቃሉ:: አሁን አማራ ክልል ተብሎ በሚታወቀው ክልል የሚኖሩ አማሮችም ቢሆኑ የእግር ጫማ እንኳ የሌላቸው ለፍቶ አዳሪወች መሆናቸውን ይረዳሉ:: አማሮች ጠላቶቻችሁ ናቸው ሲባሉ ግራ ተጋብተዋል:: የትኞች አማሮች ናቸው የእኛ ጠላቶች ብለው መጠየቅ አይችሉም:: እንዲህ ያለ ሰው “የነፍጠኛ ሎሌ” ሊባል ይችላል:: አማሮች በየቦታው ሲታደኑ ብሄር ብሄረሰቦች ውስጣቸው በሀዘን ተኮማትሯል:: በየቦታው ተበትነው ባሉት አማሮች ላይ ጥቃት ለመፈጸም በወያኔና በአጋሮቹ ከተዘጋጁት ገዳይ ስኳዶች ግን ሊታደጓቸው አልቻሉም:: እና የብሄር ብሄረሰቦች አባ ዳውሎ (አማራ) ዘሩ እንዳይጠፋ ተደራጅቶ ድምጽን ከፍ አድርጎ መጮህ: ቀሪውን ወንድም ኢትዮጵያዊ ሀቁን ማስጨበጥና የትግል አጋር ማድረግ ያስፈልጋል::
ሻለቃ ሀይለየሱስ በባህርዳር ልዩ ዞንና በምእራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል:: አባላትን መመልመል: ማደራጀት: የአባላት መዋጮ ማሰባሰብና ቢሮ መክፈት ይኖርባቸዋል:: ሰው የመቅረብ ልዩ ችሎታቸው ወሳኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት ረድቷቸዋል:: በጥቂት ወራቶች ውስጥ ምእራብ ጎጃምን እስከቀበሌ ድረስ ወርደው ማደራጀት ቻሉ:: ቢሮወች በበርካታ የወረዳ ከተሞች ተከፈቱ:: ቀስ በቀስ የህቡእ እንቅስቃሴው ገሀድ መውጣት ጀመረ:: የባህር ዳር ቢሮ በማእከልነት ያገለግል ጀመር:: ምንም እንኳ ሀይለየሱስ የምእራብ ጎጃምና የባህርዳር ልዩ ዞን አስተባባሪ ቢሆኑም በክልሉ ዋና ከተማ ተቀማጭ ስለሆኑ የአማራውን ችግር ከየዞኖች እየተቀበሉ ለበላይ የማሳወቅ ስራ በመስራት: መግለጫ በማውጣትና ህዝባዊ ስብሰባወችን በማካሄድ ግዙፍ ስራ ሰርተዋል:: በሰሜን ጎንደር: በደቡብ ጎንደር: በአዊና በምስራቅ ጎጃም ዞኖች ከአቶ አባይነህ ብርሀኑ ጋር በመሆን የዞን አስተባባሪወችን መልምለዋል- ቢሮወችን ከፍተዋል::
የት ይደርሳሉ ብለው በንቀት ይመለከቷቸው የነበሩ የየደረጃው የወያኔ አንጋቾች ህዝቡ ቀስ በቀስ ከእጃቸው እያፈተለከ ወደ መዐሕድ እቅፍ መሰባሰቡን ሲያዩ መበራገግ ጀመሩ:: በሻለቃ ላይ ፈተናወች በዙ:: መጀመሪያ ምክር ቢጤ ተሰጣቸው:: “ምንህ ተነካ- ለምን አርፈህ አትቀመጥም” ተባሉ:: ቀጠሉ የወያኔ ተስፈኞች- ” ብታርፍ ይሻልሀል:: አሊያ አወዳደቅህ ይከፋል” አሏቸው:: አልገባቸውም እንጅ ሀይለየሱስ አይደለም ለዛቻ ለጥይትም አይንበረከኩ:: ይህን ትግል ሲቀላቀሉ ብዙ ነገር ሊደርስባቸው እንደሚችል ተረድተው ነው የወሰኑት:: እና ሀይለየሱስ ይበልጥ ቀበቷቸውን ጠበቅ አድርገው ህዝብ የማደራጀቱን ስራ ገፉበት:: ፖሊሶችና የደህንነት ሀይሎች በየሄዱበት ይከታተሏቸዋል:: ሻለቃ ክፉ አይወጣቸውም:: ብቻ “እንዲያው ልፉ ብሏችሁ እኮ ነው” ይላሉ: ምንም ስህተት እንደማይገኝባቸው ለመግለጽ::
“ማሸማቀቅ” የወያኔ አንዱ የትግል ስልት ነው:: አንድ ሰው ከሚፈጽመው ተግባር እንዲታቀብ ለማድረግ ሲፈለግ በስብሰባ ላይ የማስደንገጥ: በፖሊስና በደህንነት ክትትል የማስበርገግ ድርጊት ነው- ማሸማቀቅ:: ይህ ግን ሀይለየሱስ ዘንድ ሊሰራ አልቻለም:: ራሳቸው ሀይለየሱስም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው በሌሉበት ቤታቸው በተደጋጋሚ ተፈትሿል:: ምን ይገኝባቸዋል? ምንም:: እርሳቸው እንደሆኑ የሰላም አርበኛ::
ወያኔ መዐሕድን ለማጥቃት ሲንቀሳቀስ ብአዴኖች ግዳይ ጥለው ሊሾሙ ሊሸለሙ ተቁነጠነጡ:: በወቅቱ የተከሰቱ ችግሮች ሁሉ የመዐሕድ አፍራሽ እንቅስቃሴ ውጤቶች ተደርገው በመንግስት ሜዲያወች ይናፈሱ ጀመር:: መዐሕድ “ካለወቅቱ የመጣው ዝናብ በእኛ እንዳይሳበብ እየሰጋን ነው” ሲል ወያኔ እየፈጠረበት ያለውን ልብ ወለድ ክስ ነቀፈ:: ወያኔ ግን ሰቅጠጥም አላለ:: ይባስ ብሎ በፈጠራ ክስ የድርጅቱን መስራችና የአማራ ጠበቃ የነበሩትን ፕሮፌሰር አስራት ወ/የስን አሰረ:: የወያኔ አላማ መሪው ከጨዋታ ውጪ ከሆነ ተከታዩ ይበተናል የሚል የተሳሳተ አላማ ነበር:: ያ ዱሮ ቀረ:: ዱሮ የጦር መሪ ሲሞት ሰራዊቱ ትጥቁን ይፈታ ነበር አሉ:: “ንጉስህ ወይም መሪህ ተማርኳልና እጅህን ስጥ” ተብሎ ይለፈፋል:: በቃ በዚያው ጦርነቱ ያበቃል:: ያ ጊዜ አሁን አይደለም:: ሰላማዊ ፍልሚያው ይበልጥ ተጧጡፏል:: አባላት ይመዘገባሉ: ቢሮወች ይከፈታሉ: የፖለቲካ ትምህርት ይሰጣል::
የመዐሕድ ጩኸት ፍሬ አሳየ:: አማሮችን በአማራነታቸው ብቻ ሰብስቦ መግደል ጋብ አለ:: ስለዚህ አሁን መዐሕድ ከአማራው አልፎ ለመላው ኢትዮጵያዊ ሊቆም የግድ ይላል የሚሉ ወገኖች ተበራከቱ:: እውነት ነው:: መጀመሪያምኮ ቢሆን መዐሕድ የተመሰረተው አማራ ተኮር የሆነ ግድያ በመስፋፋቱ ብቻ ነው:: ይህ ችግር ተንፈስ ካለ የሚቀጥለው ተግባር በኢትዮጵያ ላይ በጉልበቱ ነግሦ በዘርና በቋንቋ ህዝቡን እየከፋፈለ ያለውን ጸረ ህዝብና ጸረ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ አሽቀንሮ መጣል ይሆናል:: ይህ ውጤት ሊመጣ የሚችለው መላው ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ ተሰባስበው ለአንድ አላማ መሰለፍ ሲችሉ ብቻ ነው:: መዐሕድ ግቡን አሳክቷል:: ቀጣዩ ትግል ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚያሳትፍ ድርጅት መስርቶ በዚያው የሚካሄድ ይሆናል:: በዚህ መልኩ መኢአድ ተመሰረተ::
ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ ኢትዮጵያዊ ወታደር ነበሩ:: ሲያደሙና ሲደሙ የነበሩት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ነው:: ሀገራቸው ኢትዮጵያ ህዝባቸውም ኢትዮጵያውያን ናቸው:: ቀዳሚ አላማቸውን ከመዐሕድ ጋር ያሳኩት ሀይለየሱስ ለቀጣይ ግዳጅ ከመኢአድ ጋር ተሰለፉ::
ይቀጥላል
ባለ ራእዩ ወያኔ/ኢህአዴግ በሙስና ቅሌት እራሱን አጋለጠ
Thursday, May 16th, 2013እስክንድር አሰፋ
ከኖርዌይ
ባለ ራእዩ የወያኔ መንግስት ባልታወቀ ወይም ሆን ተብሎ በተሰራ የቴክኔክ ብልሽት በዚህ ሰሞን በአባላትና ጀሌዎቹ ላይ ለ22 አመታት ታይቶ በማይታወቅ የሙስና ቅሌት ሰበብ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እያጎሯቸው ይገኛል። የሚገርመው ደጋፊዎቻቸው ከሐገር ቤት እስከ ዲያስፖራው ብዙ ሲለፈልፉላቸው ይሰማ ነበር ልማታዊ መንግስታችን፤ ልማታዊ ሚኒስትሮቻችን ፤ ልማታዊው መሪያችን በማለት ከሰብአዊ መብት ጥበቃ በፊት መንገድ ስራና የአፓርታማ ግንባታ ይቅደም በማለት መቆሚያና መቀመጫ አሳጥተውን ነበር አሁን ምን ይውጣቸው ይሆን? እንደ ለመዱት ልማታዊ ሙስና ነው ብለው እንዳያስደነግጡን እንፈራለን።ስም ህዝቡን በማፈን፤ ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ነገር ግን በአሸባሪነት ስም የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የእምነት ስርዓታችንንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን ምርጫ እምነታችን በሚፈቅደው መንገድ ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ዜጎችን በአሸባሪነት በመወንጀልና በመክሰስ እንዲሁም በዋልድባ ገዳም አባቶቻችንን በማሳደድና በመዝረፍ ሲያሰቃዩ እነሱ ግን በቅሌትና በሙስና የሀገሪቷን ሃብት እና ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል እንዲሁም የሀገሪቷን ጥሬ ሃብትና ንብረት ወደ ውጪ በማሽሽ በውጪ በሚገኙ ዘመዶቻቸው ስምና የነሱ ተባባሪ ወዳጅ መንግስታት ሐገሮች ባንክ ውስጥ በማስቀመጥ ሐገራችንን ኢትዮጵያን በአለም ታይቶ በማይታወቅ የኑሮ እድገት የኋልዮሽ እሽቅድምድም ውስጥ በማስገባት ለከፋ ችግር አጋልጠዋታል።
ድምጻዊት አበበች ደራራ አረፈች
Thursday, May 16th, 2013
ድምጻዊት አበበች ደራራ ከዚህ አለም በሞት መለየቷን የተለያዩ ድረ ገፆች እየዘገቡ ነው፡፡ ማለዳ ታይምስ ድረ ገፅ ድምጻዊት አበበች ደራራ በስደት አለም እስራኤል አገር ውስጥ በቴል አቪቭ ከተማ ኑሮዋን ካደረገችበት ጊዜ ጀምሮ በጤና መታወክ ለብዙ ጊዜ ስትሰቃይ መክረሟን ገልጾ በዛሬው እለት ህይወቷ ማለፉን እና የቀብር ስነስራቷ በእዚያው በቴል አቪቭ እንደሚፈጸም ጠቁሞአል።
በተለይም ባሳልፍነው ስድስት ወራት ህመሟ በከፍተኛ ሁኔታ ላይ እንደነበር በተለያዩ ሚዲያዎች ከመገለጹም በላይ ለህክምና እርዳታ የሚሆናትን ገንዘብ እንዲሰባሰብ በተለያዩ አገራት ላይ እንዲከናወን መጠየቁ ይታወሳል ።ሆኖም ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ ሲደረግ እንዳልታየ የሚታወቅ ነው ። አበበች ደራራ በራስ ቴአትር ሃገረሰብ የተሰኘ ቡደን በተቋቋመበት ወቅት ከነ ነዋይ ደበበ ጋር በመሆን በማቋቋም ስራዋን በከፍተኛ ደረጃ የጀመረች ድንቅ አርቲስት ነበርች በተለይም በመድረክ ላይ እንቅስቃሴዋ የሰውን ቀልብ ትስባለች እየተባለ የምትወደሰው ድምጻዊት ደራራ የራስ ቴአትር አምባሳደር ትባልም እንደነበር ያገኘነው ፋይል ይጠቁማል።በቴአትር ቤቶች ውስጥ በመድረቅ የሙዚቃ ስራን በመስራት ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈች ሲሆን ጥቂት የማይባሉ ሙዚቃዎችንም በካሴት አሳትማ ልህዝብ አቅርባለች ከነዚህም መካከል በሉ እንጂ ፣ተው ማነህ፣ገላዬ ፣ሰው በፍቅር ታሞ የተባሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
አበበች ደራራ በሕመም ተይዛ ለበርካታ ወቅት በአልጋ ላይ ከመቆየቷም ባሻገር ጨርሶ ከሰዎች ጋር ግንኙነት አቋርጣ በሽታዋን ለብቻዋ ስታስታምም እንደነበረች በቅርብ የሚያውቋት ይናገራሉ፡፡
የአበበች ደራራ አስከሬን በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 3.00PM ላይ ወደ ቀብር በወዳጅ ዘመዶች ታጅቦ በመሄድ ሥርአተ ቀብርዋም እንደሚከናወን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። (ምንጭ፡ ሸገር ትሪብዩን)
የአንድነት/መድረክ የፖለቲካ ግንኙነት እና የጋራ እንቅስቃሴ ከመቀናጀት እስከ ግንባር ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ግምገማ
Thursday, May 16th, 2013
ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ብ/ም/ቤት ባደረገው ስብሰባ ላይ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአንድነት/መድረክ የፖለቲካ ግንኙነት እና የጋራ እንቅስቃሴ ከመቀናጀት እስከ ግንባር ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ የተዘጋጀውን ሰነድ ገምግሞ አፅድቋል፡፡ ሰነዱም ለመድረክና ለመድረክ አባል ፓርቲዎች እንዲሰጥ፣ አባላትና ደጋፊዎች እንዲያውቁት እንዲሁም ለህዝቡና ለመገናኛ ብዙሃን እንዲሰራጭ በተባለው ውሳኔ መሰረት እነሆ ሰነዱን አያይዘናል፡፡
ትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት
በምርጫ 97 የትዝታ ማህደር ውስጥ የልደቱ ቦታ
Thursday, May 16th, 2013ከመሐመድ አሊ መሐመድ (ጋዜጠኛ)
እስኪ በትዝታ ፈረስ ሽምጥ እንጋልብና የምርጫ 97ን ሂደት እንደዋዛ እንዳስሰው፡፡ ምርጫ 97 ሲነሳ ከትውስታ ማህደራችን ጎላ ብሎ የሚወጣው የሚያዚያ 30 ትዕይንተ ህዝብ ነው፡፡ ለነገሩማ ያ ታሪካዊ ዕለት እንዴት ይረሳል? ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመሩ መንገዶች ሁሉ በለውጥ መንፈስ በተሞላ የህዝብ ጎርፍ የተጥለቀለቁበት፣ ያለማንም ቀስቃሽ ህዝብ ለመብቱና ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሆ! ብሎ የወጣበት፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ብቃት ያረጋገጠበት፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ዓለምን ያስደመመበት ያ ታሪካዊ ዕለት እንዴት ይረሳል?
ሚያዚያ 30ን ስናስታውስ አንድ ክስተትም አብሮ ይታወሳል፡፡ “ዴሞክራሲን እናወድስ” በሚል መሪ ቃል መስቀል አደባባይና ዙሪያ ገባውን ባጨናነቀው ህዝብ መሐል አንድት ፒክ-ኣፕ መኪና ወደ አደባባዩ እምብርት ዘለቀች፡፡ በመኪናዋ ላይ በኢትዮጵያ ባንዲራ ደምቆ የለውጥ ሀዋርያነቱን የሚያውጅ ሰው ነበር፡፡ ህዝቡም ያን የለውጥ ሀዋርያ በፍቅርና በስስት ስሜት እጁን ለመንካት ይረባረብ ነበር፡፡ እሱም እጆቹን በማውለብለብ አፀፋና ምስጋናውን ይገልፅ ነበር፡፡ በወቅቱ ስለዚያ የለውጥ ሃዋርያ አንዳች አሉታዊ አስተያየት መስጠት ትልቅ ዋጋ ያስከፍል ነበር፡፡
ከምርጫው በኋላም ያ የለውጥ ሀዋርያ በድርጅቱ ጽ/ቤት ታገተ ተብሎ ህዝቡ በፆም በፀሎት ተጠመደ፡፡ በርካቶች ባገኙት ሚዲያና መንገድ ሁሉ እገታው የፈጠረባቸውን ስሜት በእንባና ሲቃ ሲገልፁ ተደመጡ፡፡ ግና በዚች ምድር ቋሚ ነገር የለምና ያ የለውጥ ሀዋርያ ተብሎ የተወደሰ ሰው ብዙም ሳይቆይ በካሀዲነት ተፈረጀ፡፡ ያ ሰው ማን እንደሆነ ግር የሚለው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያለገደብ የተሞገሰና የተወገዘ! ግን ለምን?
ስለልደቱ አያሌው ብዙ ተብሏል፡፡ እኔ የተባለውን ሁሉ አልጋራም፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የስልጣን ጉጉት እንዳላቸው አውቃለሁ፡፡ ቢሆንም የፖለቲካ ትግል የመጨረሻ ግቡ ሥልጣን ይዞ ዓላማን ማስፈፀም በመሆኑ የሥልጣን ጥማት እንደነውር ሊታይ የሚገባው አይመስለኝም፡፡ ነውር የሚሆነው ዴሞክራሲያዊ ባልሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ ሲባል የቆሙለትን ዓላማ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማስፈን በሚደረግ ትግል ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ባልሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ መሞከር የትግሉን ዓላማ ምን ያህል ሊጎዳው እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡
ከዚህ አንፃር አቶ ልደቱ በተለያየ ጊዜ ከሥልጣን ሽኩቻ ጋር በተያያዘ ትግሉን የሚጎዱ አፍራሽ እርምጃዎች ወስደዋል፡፡ አቶ ልደቱ በቀድሞው መዐህድ (የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት) አመራርና በወጣቶች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ ድርጅቱን ለቀው ሲወጡ የወሰዱት እርምጃ የድርጅቱን ገፅታ ከማጠልሸቱም በላይ በትግሉም ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት አድርሷል፡፡ በኋላም ኢዴፓ ከተቋቋመ በኋላ በፓርቲው መሥራች አባላት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት አቶ ልደቱ ተቀናቃኞቻቸውን ለማስወገድ የተከተሉት መንገድ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መቆማቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነበር፡፡ በወቅቱ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን የፖለቲካ ሰብዕና ለመግደል/ሽባ ለማድረግ (character assassination/paralization) በእሳቸው ላይ ሲደርስ ያወገዙትን አሉባልታ የመንዛትና ስም የማጥፋት ስልት መከተላቸው አይዘነጋም፡፡
አቶ ልደቱ የራሳቸው ምክንያት ቢኖራቸውም ፓርቲያቸው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በነበረው የትግልና የትብብር ግንኙነቶች ላይም የሚወስዷቸው አቋሞች እንደዚሁ ትግሉን የሚጎዱ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ በተለይም በ1997 ዓ.ም በተፈጠረው #ቅንጅት$ ውስጥ አቶ ልደቱ ሲያሳዩት የነበረው ልታይ ልታይ ባይነትና አጉል #ብልጣብልጥነት$ በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በዓይነ-ቁራኛ እንዲታዩ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ ቅንጅት በ1997 ምርጫ ሂደት በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ድምፅ ካገኘ በኋላ ወደ ውህደት ሲያመራ የልደቱን የሥልጣን ፍላጎት ባለማርካቱ በእልህ ተነሳስተው የወሰዱት እርምጃ ታላቅ ታሪካዊ ስህተት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ አቶ ልደቱ ለወሰዱት እርምጃ ምክንያት ቢኖራቸውም እርምጃውን የወሰዱበት ጊዜና መንገድ ከህዝብ እንዲነጠሉ በማድረግ ብዙ ፖለቲካዊ ዋጋ አስከፍሏቸዋል፡፡
አቶ ልደቱ ለቅንጅት መፍረስ ምክንያት አለመሆናቸውን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉም በቀላሉ ሊሳካላቸው አልቻለም፡፡ የእሳቸው መከራከሪያ ቅንጅትን አንድ ልደቱ የሚያፈርሰው ከሆነ ከጅምሩም ቅንጅት የሚባል ጠንካራ ኃይል አልነበረም የሚል ነው፡፡ በእርግጥም ይህ ክርክር በደምሳሳው ሲታይ እውነትነት ያለው ይመስላል፡፡ ነገር ግን አቶ ልደቱ በውህደት ስምምነቱ ላይ መሐተም ለማሳረፍ አሻፈረኝ በማለታቸው የኢህአዴግ መንግሥት ያቋቋመው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅንጅትን የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለመከልከል ምክንያት አግኝቷል፡፡ አቶ ልደቱና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የወሰዱት እርምጃ ቀደም ብሎ የተቀነባበረ ይሁን በድንገት የተፈጠረ ግጥምጥሞሽ ሊያስረዱን የሚችሉት አቶ ልደቱ ብቻ ናቸው፡፡
አቶ ልደቱ ቅንጅት ከፈረሰ በኋላ #ሦስተኛ አማራጭ$ በሚል ያመጡት የፖለቲካ ፈሊጥ ብዙዎችን ግራ ያጋባና እሳቸውንም ለባሰ የፖለቲካ ክስረት የዳረገ ነው፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አማካይ ቦታ/#ሦስተኛ አማራጭ$ እንደሚያስፈልግ ቢታመንም ይህን አቋም ለማራመድ በወቅቱ አቶ ልደቱ ትክክለኛው ሰው ነበሩ ለማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የ1997 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው ውጥረት የቅንጅት መሪዎች ለእስር እስከተዳረጉበት ጊዜ ድረስ በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚዎች መካከል ለነበረው የተካረረ ግንኙነት አቶ ልደቱ ዋነኛው ተጠያቂ ናቸው፡፡
ስለሆነም #የጭፍን ተቃውሞ$ ፖለቲካን ለማውገዝ/ከማውገዛቸው በፊት አቋማቸውን የቀየሩበትን አሳማኝ ምክንያት ማቅረብና ቀደም ሲል ሲያራምዱት በነበረው የተካረረ አቋም ሳቢያ ለደረሰው ጥፋት ሁሉ ኃላፊነት መውሰድና ይቅርታ መጠየቅ ነበረባቸው፡፡ ይህን ሳያደርጉ ድንገት ተነስተው #ሦስተኛ አማራጭ$ በማለታቸውና የተቃውሞውን ጎራ ተጠያቂ በማድረጋቸው ህዝብ ሊያምናቸው አልቻለም፡፡ ይልቁንም ከገዥው ፓርቲ ጋር ለመሞዳሞድ እንደፈጠሩት ሥልት ተቆጥሮ በካሃዲነት አስፈርጇቸዋል፡፡ አቶ ልደቱ በተሳሳተ ስሌት በእጃቸው ውስጥ የነበረውን መልካም ዕድል ካጡ በኋላ ተስፋ ሳይቆርጡ ቢፍጨረጨሩም እንደዋዛ ያመለጣቸውን ዕድል በቀላሉ መልሰው እጃቸው ውስጥ ሊያስገቡት አልቻሉም፡፡
ይህም ሆኖ ግን አቶ ልደቱ አያሌው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሁነኛ ሥፍራ ያላቸውና የሚገባቸውም ሰው ናቸው፡፡ ወደተደራጀ የፖለቲካ ትግል ከገቡ ጀምሮ ያላቸውን ጊዜና አቅም አሟጥጠው ተጠቅመዋል፡፡ በተለይ የ97 ምርጫ ቅስቀሳ በእሳቸው ጫንቃ ላይ ያረፈ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በምርጫ ቅስቀሳው በአንድ በኩል የገዥውን ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች አንገት ሲያስደፉ በሌላ በኩል የተቃውሞውን ጎራ ደጋፊዎች አንጀት ያርሱ ነበር፡፡
አቶ ልደቱ በትግሉ ውስጥ ያላቸው ቆይታ በአንፃራዊነት አጭር ሊባል የሚችል ቢሆንም ያካበቱት ልምድና እውቀት ቀላል የማይባል ነው፡፡ በእኔ እይታ አቶ ልደቱ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ደርዝ ባለው መንገድ ለመገምገምና ለመተንተን ብቃት ካላቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን ተርታ የሚሰለፉ ናቸው፡፡ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው አቶ ልደቱ የተቃዋሚ መሪዎችን ቁጥር በአንድ የሚያሳድጉ ሳይሆኑ በኢትየጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትርጉም ያለው ሚና መጫወት የሚችሉ ሰው ናቸው፡፡ በእርግጥ አቶ ልደቱ የሚጫወቱት ሚና እንደየሰው አተያይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የ1997 ምርጫን ተከትሎ አቶ ልደቱን የገጠማቸው ከህዝብ የመነጠል ፈተናና ፈተናውን በአሸናፊነት ለመወጣት ተስፋ ሳይቆርጡ ያደረጉት ጥረትም ስለሰብዕናቸው የሚነግረን ቁም ነገር አለ፡፡
አንዳንድ ሰዎች #ልደቱ ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ዳግም ላይመለስ የውድቀት ጽዋውን ተጎንጭቷል$ ሲሉ በኩራት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን የልደቱ ከህዝብ መነጠል ለተቃውሞው ጎራ ውድቀት እንጅ በኩራት የሚገለፅ ስኬት አይደለም፡፡ የአንዳንዶቻችን በልደቱ ውድቀት መደሰት ከተራ ምቀኝነት ያለፈ ትርጉም ላይኖረው ይችላል፡፡ ልደቱ ሰው ነውና ተሳሳተ፡፡ የሚሳሳተው ደግሞ የሚሰራ እንጅ ከዳር ቆሞ የሚታዘብ አይደለም፡፡
በነገራችን ላይ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የቅንጅት መሪዎች ከእስር ከተፈቱ በኋላ የፈፀሙት ስህተት በምንም መመዘኛ ልደቱ ከፈፀመው ስህተት የሚያንስ አይደለም፡፡ ዱሮም ቢሆን ልደቱ የወሰደው እርምጃ የቅንጅትን ውድቀት አፋጠነው እንጅ ውሎ አድሮ ቅንጅትን ከመፈረካከስ የሚታደገው ኃይል አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የቅንጅት አፈጣጠርም ሆነ የሰው ኃይል ጥንቅር ረጅም ርቀት መጓዝ የሚያስችለው አልነበረም፡፡
እንደአለመታደል ሆኖ በቅንጅት ጥላ ሥር የተሰባሰቡት ሰዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ መተያየት የማይፈልጉና አንዱ ሌላውን ጠልፎ ለመጣል የሚያደቡ ወይም በየጓዳ ጎድጓዳው የሚያሴሩ ስለመሆናቸው መሪዎቹ ከእስር በተፈቱ ማግሥት እውነቱ ገሀድ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ለቅንጅት መፍረስ ልደቱን ብቻ ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ሁላችንም ድርሻ ድርሻችንን መውሰድ ይኖርብናል፡፡ እኔ የድርሻዬን ለማንሳት ዝግጁ ነኝ፡፡ ያ ታሪካዊ ሂደት “ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን” በሚል ብሂል ተሸፋፍኖ መቅረት ያለበት አይመስለኝም፡፡ በግልፅ ልንነጋገርበትና ልንማርበት ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ስለተቃውሞው ፖለቲካ መፃኢ ዕድል መነጋገር ካለብን ደግሞ #አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ$ እንዲሉ መሆን የለበትም፡፡
የዓለም ህዝብ ሥጋትና በዚሁ ሥጋት ውስጥ ተተብትባ የተያዘችው ኢትዮጵያ
Wednesday, May 15th, 2013አገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ በተለይም ከአንደኛው እስከ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ህዝቧ
አምልኮ ፈጣሪውን የሚከተልና የሃገሩን ፤ የወገኑን ክብር ሳያስደፍር የኖረ ታላቅ ህዝብ መሆኑን ያስመሰከረ እንደሆነ ታሪክ ይመሰክራል ። ክ7ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በዓለም ላይ ክፍተኛ የእድገት ደረጃውን ጠብቆ ሃገሩ በዓለም ዙሪያ እንድትታወቅ ያደረገ ህዝብ ለመሆኑ ቛሚ ምስክር የሆኑት ታሪካው ህንጻዎቹ ምስክሮች ናቸው።
ለሃገራችው የትውልድ ዓርዓያ ሆነው ያለፉት አባቶቻችንም በክብር ዘውትር በጠላቶች ሲከበሩና ሲፈሩ የኖሩ ለመሆኑ በተደጋጋሚ ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የታሪክ ህያው ምስክር ነው ። ይህች ሃገር ለመላው የጥቁር ዘር ኩራት ሆና በጠላትነት የፈረጁዋት ጠላቶቿን ደግሞ እንደ እሳት የፈጀች ታላቅና ውድ ሃገር ነች።ይህች ሃገር ለምን እንደሊሎቹ የአውሮፓውያን ሃገራት ለምን በሥልጣኔ ወደፊት እንዳልገፋች ኢትዮጵያውያን ስንጠይቅ መልሱ ምን ይሆን?
5 ሰዓታትን በቀድሞ ማዕከላዊ ፖሊስ (ፍሬው አበበ በአዜብ መስፍን ክስ ከተመረመረ በኋላ የፃፈው)
Wednesday, May 15th, 2013ፍሬው አበበ
የዜናው ይዘትም በአጭሩ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተመንግስት አለመውጣታቸውን በአንድ በኩል በሌላ በኩል በወቅቱ ከተሾሙ 19 ቀናት የሞላቸው ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መኖሪያ ቤታቸው ከሚገኝበት ሳር ቤት አካባቢ በየዕለቱ ትራፊክ እያዘጉ በመውጣትና በመግባት ላይ መሆናቸው፣ የአካባቢውን ህብረተሰብ የመንቀሳቀስ ነጻነት ላይ ችግር መፍጠሩን፣ለደህንነታቸውም ቢሆን አስጊ መሆኑን፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን እንዲለቁ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ባልታወቀ ምክንያት ፍቃደኛ አለመሆናቸውን የሚያትት ነበር፡፡ ዜናውን ስንሰራው በትልቁ ታሳቢ ያደረግነውና እንደጋዜጠኛ ሙያዊ ነጻነታችን ተወጥተኛል ብለን የምናስበው የጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስራቸውን ማከናወን በምንም መልኩ ተቀባይነት ያልነበረውና ደህንነታቸውንም በእጅጉ ለአደጋ ያጋለጠ የመሆኑ ጉዳይ ነበር፡፡ የዚህ ዜና መውጣት በአገር ውስጥና በውጪ መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ በመቆየቱ ወ/ሮ አዜብ በክብር ወደተዘጋጀላቸው ቦታ እንዲዛወሩ፣አቶ ኃ/ማርያምም ወደቤተመንግስት እንዲገቡ በማድረግ ረገድ ሁለቱንም ወገኖችን የጠቀመ ውጤት አስገኝቷል ብለን እናምናለን፡፡ በዚህ ዜና መሸለም እንጂ መጉላላትና ክስ ይቀርብብናል ብለን አስበንም አናውቅም፡፡
ለፌደረሽን ምክር ቤት ህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ – ጉዳዩ፤ ህገመንግሰትዊ የመብት ጥሰት ስለተካሄደብን የቀረበ አቤቱታ
Wednesday, May 15th, 2013ለፌደረሽን ምክር ቤት ህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ
እንደሚታወቀው እኛ ባለፈዉ አመት ከመጋቢት እስከ ሰኔ 2004 ዓም ድረስ ከመኖሪያ ቀያችን ከደቡብ ኢትዮጵያ ስንባረር የነበርን ዜጎች ነን:: የመባርርና የመገፋታችን ጉዳይ ግን እስከ አሁን 2005 ዓም ድረስ ቀጥሎአል:: በቅርቡም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከልዩ ልዩ ቦታዎች በህገወጥ መንገድ እየተፈናቀልን ስላለነዉ አማሮች በፓርላማ ተጠይቀዉ ሲመልሱ ማንኛዉም ዜጋ በየትኛዉም የኢትዮጵያ ክልል የመኖር ህገ መንግስታዊ መብት እናዳለዉ ገልጸዉ በእኛ ላይ እየተወሰድ ያለዉ እርምጃ ግን ጸረ ህገ መንግስት መሆኑን አስረግጠዉ ተናገረዋል::
የቀረበውን አቤቱታ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩት ‘‘አያያዛችን ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም’’ አሉ (የፍርድ ቤት ውሎ)
Wednesday, May 15th, 2013
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች ማጣራት እያካሄዱባቸው የሚገኙት 24 ግለሰቦች የዋስትና መብታቸውን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ውሳኔ ተሰጣቸው።የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በተጠርጣሪዎቹ ላይ በጥንቃቄ የታጀበ መግለጫ ሰጠ
Wednesday, May 15th, 2013
የፌዴራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን ሰሞኑን በድንገት በቁጥጥር ስር በዋሉት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ባለሀብቶችን በተመለከተ በጥንቃቄ የተሞላ መግለጫ ሰጡ።ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በቁጥሮች
Wednesday, May 15th, 2013ከይርጋ አበበ
26 : 38 በስታዲየሙ የተሰቀለው የውጤት ማሳያ ኤሌክትሮኒክስ ሰሌዳ የፈርጉሰንን ከኦልድ ትራፎርድ መለዬት በማስመልከት ያስነበበው ጽሑፍ ነው ።ለዚህ ጽሑፌ ርዕስ ያደረኩት ይህ ቁጥር አሰልጣኙ በክለቡ የቆዩባቸውን ዓመታት እና ያገኟቸውን ዋንጫዎች ብዛት ለመግለፅ የተጠቀሙበት ገለፃ ነው።
በሃያ ስድስት ዓመታት የተገኙ ሰላሳ ስምንት ዋንጫዎችን ወደ ክለቡ የዋንጫ መደርደሪያ ማምጣት የቻሉት ሰር አሌክስ ፣ከጨዋታው በኋላ በስታዲየሙ ለታደሙት የክለቡ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ንግግር አድርገዋል ። በንግግራቸውም እስካሁን በክለቡ ለነበራቸው ቆይታ የተደረገላቸውን እንክብካቤ አድንቀዋል ፤ለክለቡ ውጤት ቀጣይነት ሲባል ለሳቸው የተደረገው ለተተኪው አሰልጣኝም እንዲደረግላቸው ደጋፊዎቹን ተማጽነዋል። ተጫዋቾቹም ለለበሱት ማሊያ ፍቅር እንዲኖራቸው እና ለክለባቸው ውጤት ማማር ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ህዳር ወር መጨረሻ ላይ ማሰልጠን የጀመሩትን ክለብ ለመሰናበት ጫፍ ላይ የደረሱት አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በማንቸስተር የመጨረሻ ዓመት ቆይታቸው የመጨረሻ ዋንጫቸውን በኦልድ ትራፎርድ ያደረጉትን የመጨረሻ ጨዋታ የዌልሱን ክለብ ሁለት ለባዶ በማሸነፍ መጨረሻቸውን አሳምረው ለመውጣት በቅተዋል። በታላቁ ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም በልዩ ትዕይንት የተጀመረውና ከሰባ ሺ በላይ ቀያይ ባንዲራዎች አሸብርቆ በከፍተኛ ድጋፍ የታጀበው የእሁድ ምሽቱ ጨዋታ ከሰር አሌክስ በተጨማሪ አንጋፋውን ፖል ስኮልስንም ለሁለተኛ ጊዜ ለመሸኘት የተመቸ አጋጣሚ ነበር። የሰቀለውን ጫማ በሰር አሌክስ ልመና አውርዶ በማጥለቅ ለቀያይ ሰይጣኖቹ ከፍተኛ አገልግሎትን መስጠት የቻለው ፖል ስኮልስ ከአሰልጣኙ ጋር በክብር ለመሸኘት ችሏል።
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በቁጥሮች
2ፈርጊ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ማግኘት የቻሉት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ብዛት
5 በፈርጉሰን የሰለጠኑቡድኖች ብዛት ሲሆን፡ ኢስት ስቲርሊንግ፣ ሴይንት ሜሪ፣ አበርዲን፣ የስኮትላንድ ብሄራዊ ቡድን እና ማንቸስተር ዩናይትድ
6 በተጫዋችነት ዘመናቸው ሰር አሌክ የተጫወቱባቸው ክለቦች፡ ኩይን ፓርክ፣ ሴይንት ጆንስተን፣ ደንፈርምሊን፣ ፋልክሪክ እና አይር የተባሉ የስኮትላንድ ክለቦች
9 የሰባ አንድ ዓመቱ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ያገኟቸው የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎች ቁጥር አምስቱን በማን ዩናይትድ አራቱን በአበርዲን
26 ስኮትላንዳዊው አዛውንት በኦልድ ትራፎርዱ ክለብ የነበራቸው ቆይታ በዓመት፡- ይህንን ያህል ዓመት ማንቸስተር ዩናይትድን ያሰለጠነ አሰልጣኝ የለም።
38 የእንግሊዙ ክለብ ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በሰር አሌክስ ፈርጉሰን አሰልጣኝነት ያገኛቸው ዋንጫዎች ብዛት፡- ይህንን ያህል የዋንጫ ብዛት መደርደሪያው ላይ የሰቀለ አሰልጣኝ ሲቪው ላይ የተፃፈለት አሰልጣኝ ከሰር አሌክስ ውጪ ማንም የለም።
104 ሰር አሌክስ በሃያ ስድስት ዓመታት ቀዩን ማሊያ ለማልበስ ወደ ክለባቸው ያስመጧቸው ተጫዋቾች፡- ለመጨረሻ ጊዜ ያስፈረሙት ትውልደ አይቮሪኮስታዊው ክሪስቶፎር ዛሃ ሲሆን ባለፈው ጃንዋሪ ወር በተከፈተው የተጫዋቾች ዝውውር በ15ሚሊዮን ፓውንድ ገዝተው ለአሳዳጊ ክለቡ በውሰት ሰጥተውታል። በፈርጊ ተገዝቶ ለፈርጉሰን ቡድን መጫወት ያልቻለ ተጫዋች።
170 ውጤታማው አሰልጣኝ በተጫዋችነት ዘመኑ ለተሰለፈባቸው ክለቦች ያስቆጠሩት ግብ ድምር፡- ፈርጊ ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ወደ ማንቸስተር ካዘዋወሯቸው 104 ተጫዋቾች ውስጥ የሚበዛውን ቁጥር የሚይዙት አጥቂዎች መሆናቸው አሰልጣኙ ውጤታማ የአጥቂ መስመር ተጫዋች እንደነበሩ ማሳያ ነው ሲሉ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።
370 ቁምጣና ማሊያ ለብሰው ወደ ሜዳ የገቡበት የጨዋታ ብዛት፡- ለስድስት ክለቦች በአጠቃላይ መሰለፍ የቻሉት የጨዋታ ብዛት 370 ብቻ ሲሆን በነዚህ ጨዋታዎች 170 ግቦችን ማስቆጠር መቻላቸው እውነተኛ የጎል ማሽን ነበሩ ያስብላል።
1499 ማንቸስተር ዩናይትድን እየመሩ ወደሜዳ የገቡባቸው ጨዋታዎች፡- ከሳምንት በኋላ 1500ኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፡- እስካሁን ግን 1499 ጨዋታዎችን አድርገው 895ቱን ማሸነፍ ችለዋል።
የፈርጉሰን ምርጥ አስራ አንድ
የእንግሊዙ ዘ ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ የሃያ ስድስት ዓመት የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ምርጥ 11 ፈራሚዎች እንዲመረጡ በበተነው መጠይቅ መሰረት የአብላጫውን ድምፅ ያገኙትን አስራ አንድ ተጫዋቾች እንዲህ እናቀርባቸዋለን።
1. ፒተር ሺማይክል ምርጡ የፈርጊ ግብ ጠባቂ
2. ጋሪ ኔቭል ዝምተኛው ጀግና
3. ፓትሪስ ኢቭራ የፈርጉሰንን ክፍተት የደፈነ ምርጥ የኋላ መስመር ተጫዋች
4. ያፕ ስታም ደፋር እና አይደክሜ ሆላንዳዊ
አማካይ መስመር
5 . ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ውዱ ተጫዋች የፈርጊ ምርጥ ፖርቹጋላዊ ፈራሚ
6 . ሪያን ጊግስ የአንድ ክለብ ማሊያ ብቻ ገላው የለመደው ዌልሳዊ ምርጥ ባለ ግራ እግር
7 . ሮይ ኪን አየርላንዳዊው ጉልበተኛ በማንቸስተር አሻራው የማይተካ ሚና ነበረው
8. ፖል ስኮልስ ምርጡ እንግሊዛዊ ለፈርጉሰን ቡድን ያልከፈለው አልነበረም
የአጥቂ መስመር
10. ዋይኒ ማርክ ሩኒ በማንቸስተር ያለው ቆይታ ያልተረጋገጠው የኤቨርተን አካዳሚ ፍሬ ከምርጦቹ የፈርጊ ፈራሚዎች አንዱ ለመሆን ጊዜ አለፈጀበትም
11. ኤሪክ ካንቶና የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ የሆነበት ፈረንሳዊ አመለ ብልሹ ከ1995-98 የማንቸስተር ዩናይትድ ውጤት ግምባር ቀደም ተጠቃሽ ነበር።
ከሙስናው በስተጀርባ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
Wednesday, May 15th, 2013ከኢየሩሳሌም አርአያ
በሕወሐት የተፈጠረው የቀውስ ማእበል አድማሱን እየለጠጠ መሔዱን ተከትሎ «ታማኝ» ሆነው በሙስና ሲያገለግሉ የቆዩትን ጭምር እየበላ እንደሚገኝ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በቀዳሚነት የሚያነሱት በጉምሩክ ቁልፍ ስልጣን የነበረውን የሕወሐት አባል ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስን ሲሆን እንዴትና በማን ወደስልጣን እንደመጣ እንዲሁም ምን-ምን ተግባራት ይፈፅምና ያስፈፅም እንደነበረ ምንጮቹ ሂደቱን እንደሚከተለው ይገልፁታል።
ገ/ዋህድ በ1993ዓ.ም ፓርቲው ለሁለት መሰንጠቁን ተከትሎ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ተደረገ። ከጉምሩክ ሃላፊነት በተጨማሪ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተርነት ስልጣን እንዲጨብጥ የተደረገው በአቶ መለስ በተለይ በአዜብ ይሁንታ ጭምር እንደነበረ ምንጮቹ ይጠቁማሉ። ገ/ዋህድ ለዚህ ስልጣን የበቃው ለአቶ መለስ ቡድን በከፈለው መስዋእትነት ሲሆን በክፍፍሉ ማግስት የሙስና ዘመቻ ተከፍቶ እነአባተ ኪሾና ሌሎች እስር ቤት እንዲገቡ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከመስጠት አንስቶ ራሱ ክስ አዘጋጅ፣ምስክርና ፈራጅ..በመሆን የላቀ ሚና መጫወቱን ያስታውሳሉ። በዚህ ተግባሩ የበለጠ ታማኝነቱን በማሳየቱ ከአዜብ በሚሰጠው ቀጥታ ትእዛዝ ሙስናውን ማከናወን መቀጠሉን ምንጮቹ አያያዘው ይጠቁማሉ። በ10ሺህ ቶን የሚገመት ቡና ከአዜብ በተቀበለው ትእዛዝ በህገወጥ መንገድ ከአገር ተዘርፎ የተሸጠበትና ጉዳዩም በፓርላማ ተነስቶ በጠ/ሚ/ሩ «የሌቦቹን እጅ እንቆርጣለን» የሚል አስቂኝ ምላሽ መሰጠቱን ያስታውሳሉ። በተጨማሪ በጉምሩክ ለረጅም አመት በመምሪያ ሃላፊነት ሽፋን የተቀመጠውና የቢሮውን የበላይ ሃላፊዎች በጥብቅ ከመቆጣጠር ጀምሮ እያንዳንዱን የሙስና ተግባር ከጀርባ ሆኖ የሚያስፈፅመው የአዜብ የቅርብ ስጋ ዘመድ ፍትሃነገስት ክንደያ እንደሚጠቀስና ግለሰቡ ቀረጥ ያልተከፈለባቸው 500 ሳተላይት ዲሾች እንዲገቡና በአዜብ በበላይነት ይመራ ለነበረው የዘረፋ ቡድን ለሰባት አመታት በየወሩ 20ሚሊዮን ከቴሌ በህገወጥ መንገድ እንዲዘረፍ ያደረገና በኋላም ከነገ/ዋህድ ጋር ሆኖ በርካታ ሙስናዎችን በዋናነት በማስፈፀም እንደሚጠቀስ ያመለክታሉ።
በሌላም በኩል የገ/ዋህድ ባለቤት ኰ/ል ሃይማኖት ስትጠቀስ ከሕወሐት አንጋፋ ሴት ታጋዮች አንዷ ናት፤ ከጡረታ ጋር በተያያዘ ከመከላከያ በመልቀቅ በአዜብ የበላይነት በሚመራው የሴቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቢሮ መስራት ቀጠለች። ለዚህ ቢሮ ከአሜሪካ መንግስት ብቻ በአመት እስከ 240ሚሊዮን ዶላር ይለገሳል። ገንዘቡ ለሚመለከታቸው ወገኖች ሳይሆን የሚውለው የነአዜብ ኪስ ማደለቢያ ሆኖ እንደሚዘረፍ ያመለከቱት ምንጮች ይህም ጉዳይ በፓርላማ ለቀድሞ ጠ/ሚ/ር ተነስቶ « ከእንግዲህ ቁጥጥር እናደርጋለን» የሚል የተድበሰበሰ ምላሽ እንድተሰጠ ያስታውሳሉ። ባልና ሚስቱን በተለያየ ወጥመድ በማስገባት የሙስና ጋሻ-ጃግሬ አድርገው የቆዩት አዜብ እንዲሁም ሌሎቹ ቱባ ባለስልጣናት መጠነ-ሰፊ ዘረፋና ሙስና ጉዳይ ሳይነካ ግልገሎቹን ብቻ (ያውም በአስፈፃሚነት ራሳቸው የመደቧቸውን) ተጠያቂ ማድረግ ተራ ድራማ ነው ሲሉ ምንጮቹ ያጣጥሉታል። በማስረጃነትም፥ 400 ሚሊዮን ብር ለ«ራዲሰን ሆቴል ግንባታ» በሚል ሽፋን በመፍቀድ 150ሚሊዮን ኪሳቸው ከከተቱትና በርካታ ብድሮችን በመፍቀድ (የስጋ ዘመዶቻቸውን ደላላ በማድረግ…) በሙስና የደለቡት አባይ ፀሃዬ ጨምሮ፣ የበታች ሙሰኞች ላይ <ምስክር> ሆነው የቀረቡትና ከአዜብ ጋር በሙስና የሰከሩት አባዱላ ገመዳ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ባለቤት ስብሃት ነጋ፣ የቱጃሩን የቢሊዮን ብድር በግል ከመፍቀድ አንስቶ የታዋቂ ባለሃብቶች <ቀኝ እጅ> የሆኑትና ሚስታቸውን ጭምር በሙስና ያሰማሩት በረከት ስምኦን፣ ሶፍያን አህመድ፣ እንዲሁም ቪላዎችን ከ8 እስከ 10 ሚሊዮን ብር ወጪ በማስገንባትና በማከራየት የአገር ሃብት የሚዘርፉ ሁሉም የገዢው ትላልቅ ባለስልጣናት የሙስና ጉዳይ በዋቢነት ይጠቅሳሉ። ባጠቃላይ የስርአቱ ቁንጮዎች የሚያናቁራቸው የገዛ ጥቅምን ከማስጠበቅና አንዱ ጎራ ከሌላው በልጦ በሙስና የሚከብርበትን መንገድ ለማመቻቸት ብሎም ሌላኛውን በመጨፍለቅ ስልጣኑን ከነታማኝ ተከታዮቹ አስጠብቆ የሚቀጥልበትን ብቻ እንደሚያልም የጠቆሙት ምንጮቹ፣ ስርአቱ የአስተዳደር፣የፖለቲካ፣ የፖሊሲ…ወዘተ ልዩነት እንደሌለበት ያሰምሩበታል።
ሌላው ዘብጥያ የወረዱት ባለሃብት አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ናቸው፤ የአቶ ነጋ ባለቤት የቀድሞ የሜጋ ኪነጥበብ ሃላፊ እቁባይ በርሄ እህት ናት። ከጥቂት ወራት በፊት ከሙስና ጋር በተያያዘ አስገራሚ ፍርድ የተሰጠውና ጥፋተኛ ተብሎ የተለቀቀው እቁባይ ያንን አይን ያወጣ «ፍርድ» እንዲያገኝ የተደረገው ከአዜብ በተሰጠ ቀጭን ትእዛዝ ነው ያሉት ምንጮቹ ይህ ሊሆን የቻለው አዜብ ከአቶ ነጋ ጋር ባላቸው የቢዝነስ ትስሥር ጭምር መሆኑን አያይዘው ይገልፃሉ። (ሌላም አሳፋሪ ቁርኝት ቢኖራቸውም ለጊዜው ማለፍ ይመረጣል)…
በሌላም በኩል የስዬ አብርሃ ወንድም ምህረተአብ አብርሃ እንዲሁም አይነስውሩ አስመላሽ ወ/ስላሴ ይጠቀሳሉ፤ ምህረተአብ ከስዬ ጋር ተፈርዶበት የተለቀቀው ከአምስት አመት በፊት ሲሆን አሁን ደግሞ ከነገ/ዋህድ ክስ ጋር በተያያዘ አብሮ እንዲቀላቀል ተደርጎዋል።…. አይነስውሩ አስመላሽ (በቅፅል ስማቸው አባይ ነብሶ) በፓርላማ የሕግ ጉዳይ ቢሮን ሲመሩ የቆዩ ናቸው፤ በሕወሐት ክፍፍል ጊዜ እያለቀሱ ፓርቲው እንዳይፈርስ ሲማፀኑ እንደነበር ያስታወሱት ምንጮቹ በተለይ በአንድ ቀን ተፅፎ እንዲወጣ የተደረገውንና አንድ ሰው ለማጥቃት ሲባል ብቻ አዋጅ ሆኖ እንዲፀድቅ የተደረገውን ዋስትና የሚከለክል ሕግ ካረቀቁት አንዱ እንደሆኑ ይገልፃሉ። የአስመላሽ ባለቤት በጠ/ሚ/ሩ ቢሮ ተመድባ በፀሓፊነት የቆየችና በተለይ «ሚስጥራዊ» የሚባሉ ዶክመንቶችንና የአቶ መለስ ፅሁፎችን (በብእር ስም ይወጡ የነበሩትን ጭምር) በመተየብ በታማኝነት ስታገለግል እንደቆየች አመልክተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ጄኔራሎችና የበታች ከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከጥቂት ወራት በፊት ለመጠቆም እንደተሞከረው የሚባረሩ ጄኔራሎች እንዳሉ መገለፁ ይታወሳል። በዚህ መሰረት ከአዜብ ጋር የከረረ ፀብ ውስጥ የገቡት ጄ/ል ታደሰ ወረደን ጨምሮ ሶስት የሕወሐትና ሁለት የብአዴን ጄ/ሎች በሳሞራ ውሳኔ መባረራቸውን ምንጮች ገልፀዋል። በቅርቡ የተጀመረውና « የመለስን ራዕይ እናስፈፅማለን» በሚል መሪ አጀንዳ የቀጠለው ግምገማ ተጨማሪ የመከላከያ የጦር አዛዦችንና የበታች መኮንኖችን ለማባረር ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ማጠናቀቁ ታውቋል። በሳሞራ የተወሰነው ሌላው ጉዳይ ለመከላከያ ከሩሲያ የመጡ የመሳሪያ ባለሙያዎች በተለያዩ ቦታዎች እንዲመደቡ መደረጉ ሲታወቅ ይህም የሆነው « አገሪቱ ውስጥ ችግር ከተፈጠረ ልንቋቋም አንችልም » በማለት ሳሞራ ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸውና ከአየር ሃይል አንስቶ ያለው ወታደራዊ ክፍል እምነት ሊጣልበት ባለመቻሉ እንደሆነ ምንጮቹ አስረድተዋል። የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነቱ ስልጣን የጠ/ሚ/ሩ እንደሆነ ሕገ መንግስቱ ቢደነግግም ነገር ግን ለአቶ ሃ/ማርያም ይህ ስልጣን እንዳልተሰጣቸው፣ ጄ/ሎች ሲባረሩ ከእርሳቸው እውቅና ውጭ እንደሆነ፣ ውሳኔው በሳሞራ እንደሚከናወን ምንጮቹ አስረድተዋል።
“በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያ” ጥናት ትርጉም (117 ገጾች – ጥብቅ ምስጢር)
Tuesday, May 14th, 2013“በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያ” ጥናት ትርጉም ይፋ ሆነ (ሊያነቡት የሚገባ)
Tuesday, May 14th, 2013
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ግንቦት 5፣ 2005ዓም
በኢንቨስትመንት ስም የአገር ሃብትና ትውልድን እየበላ ስላለው የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ የኦክላንድ ተቋምና ድርጅታችን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ዘገባ ይፋ ሆነ። የጋራ ንቅናቄያችን ዋና ዳይሬክተር ጥናቱ በትክክለኛ ጭብጥ ላይ ተመስርቶ እንዲዘጋጅ ለህይወታቸው ሳይሳሱ መረጃ በመስጠት ለተባበሩ ዜጎች “ታላቅ ክብር ይሁንላችሁ። አሁን አትታወቁም። ግን ከቶውንም አትረሱም። ክብር ለማትታወቁት ግን ለማትረሱት የአገር ጀግኖች” በማለት ምስጋና አቅርበዋል።
ኢህአዴግን በደፈናው መቃወምን ዓላማው ያላደረገው ይህ ጥናታዊ ዘገባ ዜጎችን ካደጉበት፣ ከኖሩበት፣ ከቀያቸው፣ ከህልውናቸው፣ ከርስታቸው፣ ወዘተ ያለ አንዳች ውይይት፣ ምክክርና ንግግር በማፈናቀል ለውጪ ኩባንያዎችና ለራሱ ለባለጠመንጃው አገዛዝ ሰዎችና ባለሟሎች መሬት ማከፋፈሉን በማስረጃ ያሳያል። የራሱ የኢህአዴግ አካላትም በሪፖርቱ ውስጥ በአግባቡ ድምጻቸው ተካትቷል። የሚጠቀሙባቸው አዋጆችና ህጎችም አልተዘለሉም።
“የውጪ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥ መግባታቸው ለቴክኖሎጂ ዝውውር፣ በአገሪቱ ያለውን የምግብ እጥረት ለማስወገድ ይረዳል” የሚሉ ምክንያቶች እያቀረበ ያለው ኢህአዴግ በተግባር ሲፈተሽ ተግባሩና ዓላማው ምን እንደሆነ የሚያመለክተው ጥናቱ የስርዓቱ ሰለባዎች፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢንቨስተሮች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የቅርብ ምስክሮች፣ የተለያዩ ከዓለምአቀፍ ተቋማት የተገኙ መረጃዎች፣ አገዛዙ ራሱ ይፋ ያደረጋቸው መረጃዎችና ለጥናቱ አስፈላጊ የተባሉ አኻዞች የተካተቱበት በመሆኑ እውነታውን ህዝብና ማናቸውም ወገኖች እውነቱን ለመረዳት ያስችላቸዋል ተብሎ በጉልህ ታምኖበታል።
በምሳሌ ለማሳያነት የተጠቀሰው የሳዑዲ ስታር ኩባንያ የሚያመርተውን ሩዝ ደብረዘይት በገነባው ተቋሙ አማካይነት ሩዙን የመለየትና ለኤክስፖርት የማዘጋጀት ስራ ይሰራል። የተመረጠውና መለኪያውን የሚያሟላው ሩዝ ኤክስፖርት የሚደረግ ሲሆን፣ ደቃቃውና በሚሊሜትር ተለክቶ ለኤክስፖርት ደረጃ የማይበቃው አገር ቤት እንዲቀር ይደረጋል። ከዚህ አንጻር እንኳ ቢታይ የመሬት ኢንቨስትመንት የተባለው ዓለም ጠንቅቆ ለሚያውቀው የአገራችን የምግብ እጥረት ችግር መፍትሄ ሊሆን አይችልም። በጥናቱ ዝርዝር ጉዳዩ አለ።
ኢህአዴግ በፖለቲካው ውድማ ላይ ቆሞ የሚያወራውና በተግባር የሚሆነውን እውነት ከሰለባዎቹ አንደበት በመቅዳት ሊስተባበል በማይችልበት ደረጃ ያቀረበው ጥናት፣ ዜጎች ከቀያቸው ከመፈናቀላቸው በፊት ምክክርና የስነልቦና ዘግጅት እንዲደረግ ጊዜ እንደሚሰጥ በህግ የተደነገገ ስለመሆኑ፣ ነግር ግን እውነታው የተገላቢጦሽ መሆኑንን ጥናቱ በማስረጃ ያትታል። ዜጎች ነገ ስለሚሆነው እንኳ ሊያውቁ በማይችሉበት ደረጃ ማለዳ ካረፉበት ሲነቁ ዶዘር ማሳቸውን፣ የጓሮ አትክልታቸውን፣ የኑሯቸው መሰረት የሆነውን ደናቸውን፣ ቤታቸውን ሲጠርግ እንደሚያዩ እነዚሁ መከረኞች ለህይወታቸው ሳይሳሱ መናገራቸውን ጥናቱ ትኩረት ሰጥቶ አቅርቦታል።
የመሬት ካሳ እንኳ ባግባቡ የማያገኙት ወገኖች በራሳቸው አንደበት፣ በግብር የደረሰባቸውንና ከፊት ለፊታቸው ያለውን አደጋ አስመልክቶ በዝርዝር ሚዛናዊ በማድረግ ያቀረበው ጥናት ኢህአዴግ ለማስተባበል ከፈለገ በዜናና በተራ ጩኸት ሳይሆን በመረጃ የተደገፈ፣ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ ሚዛናዊ ሪፖርት ካቀረበ ብቻ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) በማስተባበያነት እንደሚቀበለው አስቀድሞ ለመግለጽ ይወዳል።
በአገርና በግለሰብ ደረጃ መረጃ ለማዳረስ፣ በተመሳሳይ ኢህአዴግ የሚያሰራጨውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ማጋለጥ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቱን ማሳየት፣ የተሳሳተውን ፖሊሲ ማስቀየር ዋናው የጥናቱ ዓላማ ነው። በጥናቱ በቀረበው ጭብጥ መሰረት የዓለም ባንክ፣ ወዳጅ አገሮች፣ አበዳሪ አገሮች ፖሊሲ አውጪዎች ወዘተ አካሄዳቸውን እንዲመረምሩ ለማስቻል ሰፊ ስራ የተሰራ መሆኑንን በዚህ አጋጣሚ እንጠቁማለን። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተለያዩ የውጪና የአገር ውስጥ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ሰፊ ስራ የተሰራ ቢሆንም፣ በዋናነት የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ምን እየተሰራ እንደሆነ ሲረዳ ትግሉን ማቅለል፤ ውጤቱንም ማቅረብ ይቻላል የሚል እምነት አለን።
በዚህና በሌሎችም ተዛማጅ ምክንያቶች በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት፣ ረዥም ጊዜ ተወስዶ የተሰራው የትርጉም ሰራ ሰውን የሚያክል ክቡር ፍጥረት ከማደሪያው እንዲወጣ ተደርጎ እንዴት ወደ ጉድጓድ እንደሚወረወር ለመጪው ትውልድ በታሪክነት፣ አሁን ላለነው በመረጃነት፣ ከሁሉም በላይ ከጩኸትና ከመረጃ አልባ ክስ የምናገኘው ጥቅም አለመኖሩን በመረዳት አቋቋምን ለማስተካከል ይረዳል፣ ታላቅ ምሳሌም ይሆናል ብለን እናምናለን።
ጥናቱን በማሰራጨትና ዜጎች እጅ እንዲደርስ በማድረጉ በኩል የሁሉም ወገኖች ያልተቆጠበ ጥረት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን። በዚህ አጋጣሚ እናወጣዋለን ብለን ካሰብንበት ጊዜ በማለፍ ተጨማሪ ሳምንታት በማዘግየታችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ በአገራችን ካለው የመረጃ አፈና አኳያ የጥናቱ መጠን ሰብሰብና አጠር ባለ መጠን በኢሜይል እንደሚሰራጭ ሆኖ በአዲስ መልክ ሲቀናበር ተጨማሪ ሳምንታትን መውሰዱ የግድ ሆኗል፡፡
የጋራ ንቅናቄያችን ጽሁፉን የማሰራጨቱ ስራ በጨዋነት፣ ለጽሁፉ ባለቤቶች (ለእንግሊዝኛው የኦክላንድ ተቋም ለአማርኛው ደግሞ አኢጋን) አስፈላጊውን እውቅና በመስጠት እንዲሆን በዚህ አጋጣሚ አበክረን እንሳስባለን። ከመሬት ነጠቃ በላይ የከፋ ወንጀል የለም። ዜጎችን በምድራቸው ወደ ባርነት የሚያሸጋግረው የመሬት ነጠቃ የአገሪቱን ሃብትና ንብረት እየበላ ነው። ይህንን ወደር የሌለው ወንጀል ለማጋለጥ፣ ለመታገል፣ ለመቃወምም ሆነ ተዛማጅነት ያላቸው ተግባራት ለማከናወን ለሚፈልጉ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ይረዳ ዘንድ (Land Grab – http://landgrabsmne.wordpress.com) የሚባል ብሎግ እንዲሁም በፌስቡክ Land Grab/መሬት ነጠቃ መከፈቱን ለማሳወቅ እንወዳለን። በቅርቡ የሚሻሻለው ይህ ብሎግና የፌስቡክ ገጽ ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ ሁሉም ዓይነት ማስረጃዎች የሚታተሙበት ስለሚሆን መረጃ ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ መልካም አጋጣሚ ይሆናል።
በኢሜይል ለማግኘት የሚፈልጉ በሙሉ በሚከተለው አድራሻ (media@solidaritymovement.org) ቢጠይቁን በቀጥታ የምንልክ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡
በመጨረሻም የጋራ ንቅናቄያችን ዋና ዳይሬክተር ለተርጓሚው ከሁሉም በላይ ግን የስርዓቱ ላንቃ ስር ሆነው የህይወት ዋጋ በመክፈል መረጃ ለሰጡት ወገኖች የአክብሮት ምስጋና አቅርበዋል። አቶ ኦባንግ በመልዕክታቸው “በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችሁዋልና ክብር ይሁንላችሁ” ብለዋል፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ግብረኃይል
*********************************************************************************************************
ለዚህ ደብዳቤ ምላሽም ሆነ ለተጨማሪ መረጃ ዋና ዳይሬክተሩን ለሚዲያ ክፍሉ (media@solidaritymovement.org) በመጻፍ ወይም ድረገጻችንን (www.solidaritymovement.org) በመጎብኘት ለመረዳት ይችላሉ፡፡
ቃለምልልስ የሶማሊያውን ክልል ፕሬዚዳንት ምስጢራዊ ቪድዮዎችን ለአደባባይ ካበቃው አብዱላሂ ሁሴን ጋር
Tuesday, May 14th, 2013አቡነ ማቲያስና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል
Tuesday, May 14th, 2013ጸሐፊው በፍቅር ለይኩን (በሪፖረተር ጋዜጣ እንዲወጣ ካደረጉ በኋላ ለዘ-ሐበሻም እንደላኩት)
በቅርቡ ሙስጠፋ አል ላባድ የተባለ ሊባኖሳዊ ፖለቲከኛና ጸሐፊ Egypt is Battling Ethiopia over the Nile Water በሚል ርዕስ አንድ መጽሐፍ አሳትሞ አውጥቷል፡፡ ይህን የአል ላባድን መጽሐፍ ‹‹አስ ሳፊር›› የተባለ የሊባኖስ ዕለታዊውና ተነባቢ የዐረብኛ ጋዜጣ የመጽሐፉን አጭር ዳሰሳ በፊት ለፊት ገጹ ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡ ራኒ ጌሃ የተባለ ጋዜጠኛም የሊባኖሱን ‹‹አስ ሳፊር›› ጋዜጣ ዳሰሳ Egypt and Ethiopia Heading Toward a War Over Water በሚል ርዕስ በእንግሊዘኛ አሳትሞ ወሬውን ለዓለም መገናኛ ብዙኃን አድርሶታል፡፡
ሊባኖሳዊው ጸሐፊ በመጽሐፉ ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ ያላትን ጥንታዊና ሺሕ ዘመናትን ያስቆጠር፣ ታሪካዊና ሕጋዊ የሆነ ልዑላዊ መብቷን በመጋፋት ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው ግዙፍ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ እየገነባች ነው በማለት የተለመደውን ውግዘትና ማስፈራራት የተንጸባረቀበት የሚመስል እሳቤውን በመጽሐፉ በሰፊው አካቶታል፡፡
ጸሐፊው ይህ ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ያለችው ግዙፍ ግድብ ‹‹በግብፃውያን ጉሮሮ ላይ የመቆም ያህል ነው፡፡›› ሲል በቁጣና በእልኽ ስሜት ውስጥ የገባ በሚመስል ሁናቴ ነው የገለጸው፡፡ ይኽም ይላል ሙስጠፋ አል ላባድ 97.5 በመቶ በረሃማ ለሆነችው ግብፅ፣ ዓለምን እጹብ ድንቅ ላሰኘው ለግዙፍ ሥልጣኔዋ፣ ወርቃማ ለሆነው ታሪኳ፣ ክብርና ኩራቷ እንዲሁም 90 ሚሊዮን የሚሆነው የግብፅ ሕዝብ ሁለተናዊ ሕይወት ቁልፍ በሆነው በዚህ ታሪካዊ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችው የኃይል ግንባታ ለግብፃውያን አስጊ መሆኑን ነው የገለጸው ላባድ በመጽሐፉ ውስጥ፡፡
ይኸው ጸሐፊ ግብፅ፣ ሱዳንና ብሪታኒያ የተዋዋሉትን የ1950 ስምምነት በማንሣት ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ያላትን መብት ማንም ሊጋፋው የማይችል ታሪካዊና ሕጋዊ መብቷን መሆኑን አስረግጦ ሊያስረዳንም ሞክሯል፡፡
ላባድ በተጨማሪም የታችኛዎቹ የተፋሰሱ አገራት የሆኑት ግብፅና ሱዳን በተናጠል ከእንግሊዝ ጋር ያደረጉትን ስምምነት ሕጋዊ እውቅና በመስጠት ይደግፋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ በላይኛዎቹ ተፋሰስ አገራት በኢትዮጵያ አስተባባሪነት በናይል ወንዝ ላይ ፍትሐዊ የሆነ የውኃ አጠቃቀም እንዲኖር ያደረጉትን የኢንተቤውን ስምምነት በማንሣት ኢትዮጵያ በላይኛዎቹ ተፋሰስ አገራት መካከል ያደረገችውን ስምምነት በተመለከተ ሲናገር ‹‹ኢትዮጵያ ግብፅን በጉልበት ለማስፈረም አትችልም፤›› ሲል ይደመድማል፡፡
ይህ ስምምነትና ይላል ላባድ ግብፅ እስከሌለችበትና እስካልተስማማች ድረስ ዋጋ የሌለው ወረቀት ላይ ብቻ ፉከራ ነው የሚል አንድምታ የተንጸበራቀበት አቋሙን ለመግለፅ ሞክሯል በዚሁ መጽሐፉ፡፡
ሙስጠፋ አል ላባድ ግብፅ ወይም ግብፃውያን ዘወትር የማያንቀላፉ፣ ንቁ የሆነና በተጠንቀቅ የቆሙ ሁለት ዓይኖች አሏት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ትልቁና ዋንኛው ዓይኗ ሁሌም በዓባይና በዓባይ ዙሪ ላይ እንደተተከለ ነው፡፡ ሌላኛው ዓይኗ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅና በባሕረ ሰላጤው እንደሚያማትር ጽንፈኝነት የተጫነው በሚመስል አገላለጽ ሊያስረዳን ይዳደዋል፡፡
እናም ሙስጠፋ ግብፅና ግብፃውያን በዓባይ ዙሪያ ላይ ምን ያህል ስሱና ቀልድ የማያውቁ መሆናቸውንም ሊነግረን ይሞክራል፡፡ ይኸው ሊባኖሳዊ ጸሐፊ ኢትዮጵያ ይህን ያህል ግዙፍ የሆነና በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው የኤሌክትሪክ ማመንጫ ኃይል ለመገንባት ያነሳሳት ምክንያቶች በማለት ስድስት ዐበይት ምክንያቶቹን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ይተነትናል፡፡ ወደእነዛ የሙስጠፋ አል ላባድ ትንታኔዎች ለመግባት አልሻም፡፡
ነገር ግን ሊባኖሳዊው ጸሐፊ ሙስጠፋ አል ላባድ በዚህ መጽሐፉ ውስጥ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ግዙፍ ግንባታና ይኽን ተከትሎም ከናይል ተፋሰስ አገራት በዋነኝነት ደግሞ ከግብፅ ጋር የገባችበትን ፍጥጫና የጀመረችውን ውይይት/ድርድር ፈር ለማስያዝ ግብፅ ምን ዓይነት ውሳኔ ልትወስድ እንደምትችል የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው ይለናል፡፡
ነገር ግን ይላል ሙስጠፋ ማብራሪያውን ሲቀጥል ግብፅ ለወደፊቱ የምትወስደውን እርምጃ ምንም ይሁን ምን የምናየው ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን ግብፅ ይህን ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ግዙፋ ግንባታ ለማስቆም መውሰድ ካለባት እርምጃ መከካል ብሎ በግንባር ቀደምትነት ከጠቀሳቸው ምክንያቶቹ መካከል ሲጠቅስም፡-
ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ያላትን ‹‹የማይለወጥና የማይሻር›› ታሪካዊ፣ ሕጋዊና ሉዓላዊ የሆነ ጥቅሟን ለማስከበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሺሕ ዘመናት እናት በሆነችው በግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን በኩል ከፍተኛ የሆነ ጫና ማሳደር የምትችልበትን አማራጭ ማየት ይገባታል በማለት አበክሮ ይገልጻል፡፡
ሙስጠፋ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ልማት በግብፃውያን ሕልውና ላይ የመፍረድ ያህል ነው ብሎ ለሚሟገትላት ግብፅ ለዚህ የሞት ሽረት ጥያቄ ያለ ምንም ልዩነት ሁሉም ግብፃዊ ሊነሣ እንደሚገባው ይወተውታል፡፡ እናም በዚህ የሞት ሽረት ዲፕሎማሲያዊ ትግል ግብፅና ግብፃውያን ያላቸው ተስፋ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኩል ብቻ እንደሆነ ለግብፅና ለግብፃውያኑ አበክሮና አስረግጦ ገልጧል፡፡
በእርግጥ ግብፃውያን በሃይማኖት ወዳጃቸው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኩል የተቻላቸውን ያህል ጥረት ሊያደርጉ እንደሚችሉ እርግጥ ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነን ባለፈው ወርኻ ክረምት የግብፅ ሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባልና አዲሱ የግብፅ ፕሬዝዳንት የሆኑት መሀመድ ሙርሲ ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ወደ መዲናችን አዲስ አበባ መጥተው በነበሩበት ጊዜ ከነፍሰ ሔር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን በይፋ ከመገናኛ ብዙኃን አይተናል፣ አድምጠናል፡፡
ይህ የመሀመድ ሙርሲ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያደረጉት ጉብኝትና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ እንደ አንዳንድ ተንታኞች ሁለት ዐበይት ምክንያቶች ሊኖረው እንደሚችል ተገልጾ ነበር በወቅቱ፡፡
የመጀመሪያው በሁለቱ አገራት ማለትም በግብጽ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያንና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኩል ለሺሕ ዘመናት ለዘለቀው ታሪካዊ ግንኙነት ክብርና እውቅና መስጠት ሲሆን፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ጥንታዊና ታሪካዊ የሆነ የሁለቱ አገራትና አብያተ ክርስቲያናትን ግንኙነት አስታኮ በጥንታውያኑ ኢትዮጵያውያን ነገሥታት ዘመን በኢትዮጵያ በኩል በእናት ቤተ ክርስቲያናቸው በግብጽ ኮፕቲክ ክርስቲያን ወንድሞቻቸው ላይ ይደረስ ለነበረው በደልና ግፍ እንደማስፈራሪያ ሆኖ በቆየውና ለግብፃውያን ሕልውና መሠረት በሆነው በዓባይ ወንዝ ላይ የተንጠለጠለ እንደሆነ ነው፡፡
ምናልባትም ሌላኛው ምክንያት በዘመነ ሆስኒ ሙባረክ አንፃራዊ በሆነ መልኩ የተረጋጋ ሕይወት አላቸው የሚሉት ግብፃውያኑ ክርስቲያኖች የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ ባልተጠበቀ ሁናቴ ወደ ግብፅ ፖለቲካ ማማ ላይ መውጣቱ በግብፃውያኑ ክርስቲያኖች ላይ ምንም ዓይነት የተለየ ጫና፣ ግፍና መከራ እንደማይደርስባቸው ዋስትና ወይም ማረጋገጫ የመስጠት ዓይነት እንደሆነ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡
ይሁን እንጂ የመሀመድ ሙርሲ ጉብኝትና ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ያደረጉት ውይይት ዐቢይ አጀንዳ ግን የዓባይ ውኃ ጉዳይ መሆኑን ለመናገር ነቢይ ወይም ወልይ መሆን የሚያስፈልገው ነገር አይመስለኝም፡፡ እናም መሀመድ ሙርሲ ወደ ስልጣን በመጡ ማግሥት በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ሰበብ ይህን የግብፅንና የግብፃውያንን ቁልፍ አጀንዳ፣ የዓባይን ጉዳይ ከግብፅ ጋር ቆየና ታሪካዊ ግንኙነት ባላት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጠረጴዛ ላይ ማስቀመጣቸው፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የአደራ መልእክትና ትልቅ የቤት ሥራ መስጠታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
ይህን ከላይ በአጭሩ ለመግለጽ በሞከርኩት የሙስጠፋ አል ላባድ መጽሐፍ ውስጥ ግብፅና ግብፃውያን በዓባይ ውኃ ላይ ለመደራደር ያላቸው ተስፋ ‹‹በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲየን በኩል ብቻ ነው፡፡›› የሚል አንድምታ ያለው ምክሩና ከሰሞኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባትና መንፈሳዊ መሪ የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ባስተላለፉት ቃለ ቡራኬ ስለ ዓባይ ውኃ ጉዳይ ያነሡት ቁም ነገር ለዚህ አጭር መጣጥፍ መነሻ ሆነኝ፡፡
በመላው በክርስትና ሃይማኖት አማኞች ዘንድ ባለፈው ሳምንት የተከበረውን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል አስመልክተው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ለሚገኙ መንፈሳዊ ልጆቻቸው ቡራኬና ቃለ በረከት አስተላልፈው ነበር፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ ባስተላለፉት በዚህ በቃለ በረከታቸውና በቡራኬያቸውም፡- ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የዘመናት እንቆቅልሽ ሆኖ በቆየ በአንድ ወቅታዊ፣ አንገብጋቢና እጅግ ወሳኝ በሆነ አገራዊ አጀንዳ ላይ ፍጹም አዎንታዊነት፣ የድልና በእግዚአብሔር አምላካችን ኃይል ሁሉ ይቻለናል የሚል እምነትና ጽናት በተንጸባረቀበት በሚመስል፣ በትንሣኤው በዓል ‹‹የእንኳን አደረሳችሁ!›› የመልካም ምኞት መግለጫቸው ለኢትዮጵያውያን ሁሉ አንድ ዐቢይ የሆነ መልእክትን አስተላልፈዋል፡፡
ይኸውም ኢትዮጵያ አገራችን በእግዚአብሔር ከአምላኳ በተቸራት በጥንታዊውና በታሪካዊ ወንዟ በዓባይ ላይ የጀመረችው ታላቁ የሕዳሴው ግድብ ያለ ምንም ጥርጥር በድል ተጠናቆ፣ ለፍሬ በቅቶ፣ ‹‹ከዓባይን ልጅ ውኃ ጠማው›› ተረት ወጥተን ከዓባይ በረከት ጠጥተን የምንረካበት መልካምና ብሩኅ ዘመንን ኢትዮጵያውያን ሁሉ በዓይናቸው እንደሚያዩት ቅዱስነታቸው ያላቸውን ጽኑና የማያወላውል ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ቅዱስነታቸው በዚህ መልእክታቸውም ለሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባለበትና በተሰማራበት የሥራ መስክ ሁሉ በአገር ፍቅር ስሜት፣ በአንድነትና ጠንካራ የሥራ መንፈስ የበኩሉን እገዛና ርብርብም እንዲያደረግም ነው ያሳሰቡት፡፡
የቅዱስ ፓትርያርኩ ይሄ መልእክታቸው በአንዳንዶች ዘንድ እምብዛም የተወደደላቸው አይመስልም፡፡ እንደውም እነዚሁ ይህ የፓትርያርኩ መልእክት ያላስደሰታቸው በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውን ወገኖቻችን ይህች በመንግሥት ተቀንብባ ለፓትርያርኩ አንደበት ለሕዝብ ይደርስ ዘንድ የተላላፈች ‹‹ኢህአዴጋዊ›› መልእክት ናት በማለት የሰላ ትችታቸውን ሰንዝረዋል፡፡
እርሳቸው የሃይማኖት አባት ናቸው እንጂ የመንግሥት አፈ ቀላጤ አይደሉም፡፡ እናም በዚህ በትንሣኤው በዓል ላይ ማስተላለፍ የሚገባቸው መልእክት እኛ የሰው ልጆች ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሥኤ ስለተጎናጸፍነው ነጻነት፣ ድል፣ በረከትና የዘላለም ሕይወት እንጂ ስለ መንግሥት የፖለቲካ አጀንዳ መሆን አልነበረበትም በማለት ቅሬታቸውን በጓዳም በይፋም ሲገልጹ ተሰምተዋል፡፡
በበኩሌ ግን ከትንሣኤው ኃይልና ተስፋ፣ መንፈሳዊነት ተቀዳሚና ዋና አጀንዳነት ባሻገር ይህ በዓባይ ወንዝ ላይ የተጀመረውን የታላቁን የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በማስመልከት ቅዱስ ፓትርያርኩ 40 ሚሊዮን ለሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ምእመኖቻቸው ያስተላለፉት መልእክት የመንግሥት ፖለቲካዊ አጀንዳ ነው የሚያስብለው ምክንያት ብዙም አይዋጥልኝም፡፡
አገራችን ከድህነት፣ ከልመና፣ ከራብ፣ ከስደት፣ ከተመጽዋችነት… ወዘተ የምትወጣበትና እኛም ሕዝቦቿም ለጥ ብለን ከተኛንበት የስንፍና ፍራሽ ላይ አቅንቶ የሚቀሰቅሰን ሁለተናዊ የሆነ የትንሣኤው አዋጅ መለከት በብርቱ እንደሚያስፈልገን ጥያቄ የለውም፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ ዕለት ለአገራችንም ሆነ ለሕዝባችን ሁለተናዊ የሆነ ትንሣኤ እንደሚያሰፈልገው ማወጅ የአንድ መንፈሳዊ አባት ተግባርና ኃላፊነት እንደሆነ ነው አጥብቄ የማምነው፡፡
ብሔራዊ ጥቅማችን፣ የአገራችንን ነፃነት፣ ልዑላዊነትና አንድነት በተመለከተ ቤተ ክርስቲያናችን እንደ ትላንትናው ሁሉ በቃልም በተግባርም የነበራትን ወሳኝ ሚናና ተሣትፎ በተመለከተ ዛሬም ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ማሰማቷ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ትላንትና ያደረገችው፣ ዛሬም ልታደርገው የሚገባና ወደፊትም አጽንታ ልትቀጥልበት የሚገባው መልካም የሆነ ክርስቲያናዊ ባህል ነው የሚመስለኝ፡፡
ስለሆነም የዓባይ ጉዳይ በማንም ይነሳ በማንም አንድ የማምንበት እውነት ግን አለ፡፡ ይኸውም የዓባይ ጉዳይ ብሔራዊ አጀንዳችን፣ የሁላችንም ጉዳይ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡ በአንድ የታሪክ ወቅት ታይተው የሚያልፉ የአንድ መንግሥት ወይም የአንድ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ ዓባይና የዓባይ ጉዳይ ዘርን፣ ጎሳን፣ ሃይማኖትን ሳይለይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ አንገብጋቢ ጉዳይ እንጂ፡፡
በዓባይ ጉዳይ ላይ ንጉሡ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ፣ በርካታ ኢትዮጵውያን ምሁራንና ዲፕሎማቶች ያደረጉት በርካታ የሆኑ ጥረቶችና ልፋቶች ነበሩ፡፡ የደርግ መንግሥት እንዲሁ የበኩሉን ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፣ ለፍቷል፡፡ ዛሬ እነዚህ መንግሥታት አልፈው ታሪክ ሆነዋል፡፡ ኢትዮጵያችን ግን ዛሬም አለች፣ ወደፊትም ትኖራለች፡፡ ዓባይ ወንዛችንም ትላንትና ነበር፣ ዛሬም አለ፣ ወደፊትም ይኖራል፡፡
የኢህአዴግ መንግሥትም በለስ ቀንቶት ይህ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ሁሉ የዘመናት እንቆቅልሽ የሆነውን ዓባይን ጉዳይ ከወረቀት አጀንዳነት ወደ መሬት በማውረድ በታሪካችን በአፍሪካ ትልቅ የሆነውን ሕዳሴውን ግድብ እውን ለማድረግ የበኩሉን ተግባራዊ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ኢህአዴግም እንደ ትላንትናዎቹ የኃ/ሥላሴና የደርግ መንግሥታት ያልፋል፣ አንድ ቀን እንደ ሸማም ተጠቅልሎ በታሪክ ማኅፀን ውስጥ በተራው ይገባል፡፡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውን ግን ዛሬም፣ ሁሌም ይኖራሉ!!
ከጥንት ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ ነበረች፣ ዓባይም ነበር፡፡ ኢህአዴግ ገና ሳይታሰብ፣ ሳይጸነስና ሳይኖርም በፊት ዓባይ ይፈስ ነበር፣ ዛሬም በፊታችን እየፈሰሰ አለ፣ ወደፊትም ሲፈስ ይኖራል፡፡ መንግሥት ዓባይን በየትኛውም መልኩ ቢሆን የራሱን ፖለቲካዊ አጀንዳ ማስፈጸሚያ፣ ዕድሜ ማራዘሚያና ጊዜያዊ የፖለቲካዊ ትርፍ ማጋበሻ አደረገውም አላደረገውም ዓባይን በማልማት ረገድ ግን ከአሁን ወዲያ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ወደኋላ የምንመለስበት ጉዳይ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ለምን ቢባል የዓባይ ጉዳይ በእኛ ዘመን የህልውናችን፣ የመኖርና ያለ መኖር ጥያቄ ሆኖ ከፊታችን ተድቅኗልና፡፡
ስለሆነም በዓባይ ወንዝ ላይ የሚካሄድ ማንኛውንም ዓይነት ልማትን በተመለከተ የሃይማኖት አባቶቻችንም ሆኑ ባለ ሥልጣኖቻችን ከሚነግሩን በላይ በተግባር አንደበት፣ በፍቅርና በአንድነት መንፈስ እጅ ለእጅ ተያይዘን ልንወጣው የሚገባን ታላቅ የሆነ የቤት ሥራ ገና ከፊታችን እንዳለን ነው የሚሰማኝ፡፡
በዚህ ረገድ ደግሞ ከዓባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ ታላቅ የሆነ ታሪካዊ ሚና የነበራትና ያላት ጥንታዊቷና ሐዋርያዊቷ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፣ መንፈሳዊ አባቶችቻንና መሪዎቻችን እንዲሁም እኛ ክርስቲያኖች ሌላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለ ምንም ልዩነት በማስተባበር ገና በተግባር ልንወጣው የሚገባ ትልቅ የቤት ሥራ በፊታቸው ተደቅኖ እንዳለ ይሰማኛል፡፡
ይህ አጭር መጣጥፍም ቤተ ክርስቲያናችን፣ መንፈሳዊ አባቶቻችንና መሪዎቻችን እንዲሁም እኛንም ጨምሮ ዓባይ ወንዛችንን በተመለከተ ከቃል ባለፈ በተግባር ልንወጣው የሚገባ ትልቅ የቤት ሥራ ከፊታችን ተዘርግቶ እንዳለ በቅንነት መንፈስ ለማሳሰብ ነው፡፡ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያናችን በቀደመ ታሪክ ዘመኗ የዓባይ ወንዝን በተመለከተ የነበራትን ወሳኝ ሚና ከታሪክ ማሕደር በመፈተሸና አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማያያዝ የበኩሌንና የተሰማኝና ጥቂት ነገር ለማለት ነው ብዕሬን ያነሳሁት፡፡
ግብፃውያኑ በመንፈሳዊነት ስም ባቀነባበሩት፣ የፈጠራ ተረት ተረት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለ1600 ዘመናት በግብፃውያኑ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የባርነት ቀንበር ውስጥ ወድቃ ስትማቅቅ እንደነበር የታሪክ መዛግብቶቻችን ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ሐቅም የቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ አጥኚዎችና የሥነ መለኮት ምሁራኖቿም ሳይቀሩ የሚመስክሩት ነው፡፡
እነዚህ በአፍሪካና በመላው ዓለም ባለፉት ሺሕ ዓመታቶች ባስመዘገቡት ድንቅና ኃያል ሥልጣኔያቸው የተነሣ በዓለም መድረክ እንደ ብርቅ የሚታዩ ጥንታዊ የሆኑ ሁለቱ አገራት፣ ኢትዮጵያና ግብፅ ለዘመናት የሰው ዘር ታሪክ፣ ቅርስና ታላቅ ሥልጣኔ አሻራ ማሳያ የሆኑ ታላላቅ አገራት መሆናቸው በሰፊው ሲጠቀስ ቆይቷል፣ አሁንም ይጠቀሳሉ፡፡
ለእነዚህ አገራት ታሪክ፣ ታላቅ ሥልጣኔና ዕድገት መነሻና እምብርት ደግሞ የዓባይ ወንዝ እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡ ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍም፡- ‹‹ስለ ዔደን ገነት ሲያትት የዔደን ገነትን ከከበቡትና ከሚያጠጡት ወንዞች መካከል አንዱ የዓባይ ወይም የግዮን ወንዝ መሆኑን በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ የዘፍጥረት ጸሐፊ የሆነው እስራኤላዊው ነቢይ ሙሴ ይኽው የዓባይ ወንዝም ኢትዮጵያን መሬት ሁሉ እንደሚከብ ይናገራል፡፡››
በክርስቲያኖች ቅዱስ መጽሐፍ ዘንድም ሆነ በእስልምና ሃይማኖት ቅዱሳን መጻሕፍት የከበረ ስምና ዝና ያላት ኢትዮጵያ ገና ከፍጥረት ማግሥት ጀምሮ የራሷን መንግስት አቋቁማ የምትኖር፣ ኃያላ፣ ባለ ታሪክና ልዑላዊት አገር እንደነበረች ይመሰክራሉ፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ የዓለማችን ታላቅ የሆኑ የአይሁድ፣ የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖቶች ማእከል እንደሆነችም ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያ የታሪክ፣ የሃይማኖትና የሥልጣኔ ማእከል መሆኗ ብቻ ሣይሆን ከኢትዮጵያ ምድር ፈልቆ ሱዳንና ግብፅን አቋርጦ ወደ ሜድትራኒያን ባሕር የሚገባው የዓባይ ወንዝ አያሌ ዘመናትን ላስቆጠረው ለግብፃውያኑ አፍሪካዊው ሥልጣኔ፣ መነሻና መሠረት እንደነበር የታሪክና የአንትሮፖሎጂ ምሁራን አስረግጠው ጽፈዋል፡፡
ከእነዚህም ምሁራን መካከል አፍሪካውያኑ ስመ ጥር፣ እውቅ ምሁራንና የታሪክ ተመራማሪዎች የሆኑት ሼክ አንታዲዮፕና ኢቫን ኢቫን ሰርቲማ በጥናታቸው፡- ‹‹ግብፅ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ የመንፈስ ልጅ›› እንደሆነች ባሳተሙት በዳጎስ ጥናታቸው በግልጽ ጽፈዋል፡፡
ኢትዮጵያንና ግብፅን ከሚያስተሳስሩ ዋና ጉዳዮች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ታሪካዊው የዓባይ ወንዝ ነው፡፡ ዛሬ ዓለም ጉድ የሚሰኝበት የግብፃውያኑ ታሪክ፣ ቅርስና ታላቅ ሥልጣኔ መሠረቱ የዓባይ ወንዝ ነው፡፡ እነዛ ዓለምን ጉድ ያሰኙና በየቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ቱሪስቶችን ቀልብና ዓይን የሚቆጣጠሩ የግብፅ ፒራሚዶች የተገነቡት የዓባይ ወንዝ ዳርቻን ተከትለው ነው፡፡
ግብፅና ግብፃውያን ከዓባይ ውጪ የሚኖሩት ሕይወት፣ የሚተርኩት ታሪክ፣ ዓለም ሁሉ የሚያየው፣ የሚያደነቅውና ጉድ ጉድ የሚሉለት አንዳንችም ሥልጣኔም ሆነ ቅርስ የላቸውም፡፡ ዓባይ ለግብፅና ለግብፃውያን ሁሉን በሁሉ ነው ብንል ብዙም ከእውነታው የራቅን አይመስለኝም፡፡ ለዚህም ይመስለኛል በተለምዶ ‹‹ታሪክ አባት›› ተብሎ የሚጠራው ጥንታዊው ታሪክ ጸሐፊ ግሪካዊው ሄሮዱተስ Egypt is the gift of Nile ሲል በአጭር ቃል ግብፅን የገለጻት፡፡
እናም ኢትዮጵያና ግብፅ ለዘመናት ተሳሰረው የቆዩበት እትብት የዓባይ ወንዝ መሆኑን ማንኛችንም ብንሆን እንስተዋለን ብዬ አልገምትም፡፡ ይህ በዓባይ ወንዝ አማካኝነት የተፈጠው የሁለቱ አገራት ታሪካዊ ትስስር የክርስትና ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ መግባት በኋላ ደግሞ ሌላ የሃይማኖትና የታሪክ የቃል ኪዳን ውልን ፈጠረ፡፡ ከ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በኋላ የኢትዮጵያ የስልጣኔ ልጅ ናት ተብላ የተጠቀሰችው ግብፅ ዳግም ለኢትዮጵያውያን የመንፈስ እናት ሆና በታሪክ መድረክ ብቅ አለች፡፡
ይህ ግብፃውያን በሃይማኖት ስም ከኢትዮጵያ ጋር የተሳሰሩበት የእናትነትና የልጅነት መንፈስ የፈጠረውን ወይም ያመጣውን መንፈሳዊ ፋይዳና ጥቅም፣ እንዲሁም ያሰከተለውን መንፈሳዊና አሥተዳደራዊ ቀውስና ውጥንቅጥ ለመተንተን የዚህ ጽሑፍ ዓላማ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ እዚህ ጋር ሳይነሳ ሊታለፍ የማይገባው ነጥብ ቢኖር፡- ግብፃውያን በሃይማኖት ስም በኢትዮጵያ ላይ የጫኑት ከባድ ቀንበርና ብርቱ ክንድ ከጊዜ በኋላ መልኩን ቀይሮ ወደ ፍፁም አምባገናነዊነትና ቅኝ ግዛትነት ተቀይሮ እንደነበር ሁላችንም ቢሆን ልንዘነጋው አይገባንም፡፡
በወርቅ፣ በእንቁ፣ በከበሩ ስጦታዎች ጋጋታ ወደ ኢትዮጵያ ይመጡ የነበሩት በጣት ከሚቆጠሩት ግብፃውያን ጳጳሳት በስተቀር የሚበዙት ከስምና ከምልክትነት ባለፈ (Puppet Fathers) ይሄ ነው የሚባል ሥራ እንዳልነበራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ አጥኚዎች በግልጽ ይናገራሉ፡፡
በተለይም ደግሞ ግብፅ ሙሉ በሙሉ በሙስሊም ወራሪዎች እጅ ከወደቀችበት ዘመን ጀምሮ ግብፃውያኑ ገዢዎች በጳጳሳቱ በኩል ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የሆነ አጀንዳቸውን ለማስፈጸም በተቀነባበረና በረቀቀ ሴራ እንዲያም ሲል በኋላኛው ዘመን በጦር ኃይል አጀንዳቸውን ለማስፈጸም ወደኋላ እንዳላሉ የታሪክ ድርሳናቶቻችን በሚገባ ያስረዳሉ፡፡
ግብፃውያኑ ኢትዮጵያ አንድ ቀን የዓባይን ወንዝ ልትገድብ ትችላለች የሚለው ስጋታቸው ቀን ከሌሊት እረፍት ስለማይሰጣቸው ዓባይን በዓይነ ቁራኛ ነበር የሚከታተሉት፡፡ እናም ኢትዮጵውያኑ በዓባይ ወንዝ ላይ ያላቸውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ይቃኙ ዘንድ ሁለት ሼኼዎችን ጳጳስ አድርገው በተለያዩት ጊዜያት በቃፊርነት ወደ ኢትዮጵያ ምድር ልከው እንደነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ይህን የግብፃውያኑን አሣፋሪ ቅሌት በታሪክ ድርሳናት ውስጥ አስፍረውታል፡፡
በኢትዮጵያ በኩልም የዓባይ ወንዝ ለአናሳዎቹ ግብፃውያን ክርስቲያኖች የመደረደሪያና ለግብፃውያኑ ገዢዎች ማስፈራሪያ መሣሪያም በመሆን ያገለገለበት በርካታ ጊዜያቶች ነበሩ፤ በተለይም ደግሞ በዛግዌ ስርወ መንግሥትና በመካከለኛው ዘመን ታሪካችን፡፡
በእነዚህ ሁለት ጥንታዊ እና የታላቅ ሥልጣኔ ባለቤቶች በሆኑ ሀገራት መካከል በየጊዜው ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ይነሳ የነበረው የዓባይ ውኃ ጉዳይ ነበር፡፡ እናም በዛግዌ እና በመካከለኛው የኢትዮጵያ የታሪክ ዘመን ወደ ግብፅ የሚፈሰው የዓባይ ውኃ መጠን በቀነሰ ቁጥር ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ መነሳቱን ከታሪካችን እንረዳለን፡፡
የግብፅ ነገሥታት አልፎ አልፎ የዓባይ ወንዝ በምንጩ አካባቢ በሚደርስ ድርቅ ምክንያት የፍሳሹ መጠን የሚቀንስ መሆኑን ባለመጠርጠር፣ የኢትዮጵያውያን ውኃን የዘጉት ወይም ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲፈስ ያደረጉት እየመሰላቸው፣ ውኃውን ለማስለቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ነገሥታት ዘንድ በየጊዜው መልእክተኛ ይልኩ ነበር፡፡
ለምሳሌ ታሪክ ጸሐፊው የዓረብ ተወላጅ አል ማኪን ድርጊቱ ከሆነበት ከሁለት መቶ ዓመት በኋላ ሲጽፍ በፋቲሚድ ሥርወ መንግሥት በሡልጣን አቡ ታምሊን አል ሙስታንዚር የአገዛዝ ዘመን (1036-1094) ግብፅ የሚደርሰው የውኃ ብዛት በ1089-1090 አካባቢ ቀነሰ፡፡ በዚህ የተነሳ ሡልጣኑ ወዲያውኑ የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ሚካኤልን ከፍ ያለ ገጸ በረከት አስይዞ ኢትዮጵያውያን የተቋረጠውን የዓባይን ወንዝ እንዲለቁ ለመለመን ወደ ኢትዮጵያ እንደላካቸው አትቷል፡፡
አል ማኪን ጉዞውም በ1092 እና በ1094 ዓ.ም ማሃል ባለው ጊዜ ውስጥ ነበር በማለት፤ የኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት የነበረው ይምርሃነ ክርስቶስ አንድ ኮረብታ እንዲፈርስ ባዘዘ ጊዜ የውኃው መጠን በአንድ ሌሊት ሦስት ጫማ ከፍ ብሎ አደረ ሲል በመጽሐፉ በሰፊው ተርኮአል፡፡
በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የግብፅ ማምሉክ ሡልጣን አል ናሲር ሙሀመድ ኢብን ቃላኡን በርካታ አብያተ ክርስቲያናት የማፍረሱና ክርስቲያን የሆኑ ዜጎቹን በጽኑ የማሰቃየቱ ዜና ወደ ኢትዮጵያ ደርሶ ከፍ ያለ የኀዘን ስሜት መፍጠሩን አል ማቅሪዝ የተባለው የሞሮኮ ተወላጅ ታሪክ ጸሐፊ በወቅቱ ዘግቦአል፡፡
በታሪኩ ውስጥ ስሙ ባይጠቀስም ከ1380-1409 ዓ.ም የነገሠው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዳዊት አንድ የልዑካን ቡድን ወደ ግብፅ ልኮ የዓባይን ወንዝ ፍሳሽ ወደ ሌላ አቅጣጫ በማዞር የግብፅን ሕዝብ በራብ ለመፍጀት እንደሚችል ለግብፁ መሪ በብርቱ ማስጠንቀቂያ ገልፆለት እንደነበር ጽፎአል፡፡
ኢብን ፋድል አል አልዑማሪ የተባለ አንድ የግብፅ ቤተ መንግሥት ባለሟልና ጸሐፊ ‹‹ማሳሊክ አል አብሳር ፊ ማምሊክ አል አምሳር›› ቀጥታ ትርጉሙ ‹‹የነገሥታት ምድር ቅኝት›› በሚል ርዕስ በዘመኑ ያስተዋለውን የተለያየ ነገር ጽፎ ነበር፡፡ በዚህ መጽሐፉ ሀበሾች (ኢትዮጵያውያን) ወደ ግብፅ የሚፈሰውን ዓባይን እንደሚቆጣጠሩና ለግብፅ ሡልጣን ከበሬታ ሲሉ ብቻ ውኃው እንደተለመደው ወደዚያ እንዲፈስ የሚፈቅዱ መሆናቸውን ይናገራሉ ሲልም ገልጾአል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከግብፃውያኑ መንፈሳዊ ባርነትና ፖለቲካዊ ሴራ ትላቀቅ ዘንድ የኢትዮጵ መንፈሳዊ አባቶችና ንጉሡ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከ1600 ዓመታት መራር የግብፃውያን ቀንበር ተላቃ የራሷን መንፈሳዊ መሪ ካገኘች አምሳ ዓመታት ያህል ተቆጥረዋል፡፡ ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከግብፃውያን አገዛዝ ብትላቀቅም ሁለቱን አገራትን በሚያስተሳስራቸው በዓባይ ጉዳይ ላይ አሁንም ድረስ ግብፃውያኑ ክርትስቲያኖች ሆኑ ሙስሊሞች ያላቸው አቋም በዓባይ ላይ ለምን ሲባል ጥያቄ ታነሳላችሁ የሚል ዓይነት ጠንካራና ግትር ነው፡፡
ግብፃውያኑ ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ ያላትን የመጠቀም መብት በተመለከተ ሲነሳ ሁሌም ዓይናቸው ደም ነው የሚለብሰው፣ ይህ ቅናታቸውና ቅንነት የጎደለው ጭፍንነታቸው ከዓባይ አልፎም ኢየሩሳሌም ድረስ ሣይቀር እንኳን ተሻግሮ በኢትዮጵያውኑ ጥንታዊ ይዞታ በሆነው በዴር ሱልጣን ገዳም ላይ ያሳረፈውን ብርቱ ጥላቻና ክንድ አይተናል፣ ታዝበናልም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ምናልባት በሌላ ጊዜ ሰፋ አድርጌ እጽፍ ይሆናል፡፡
ግብፃውያኑ እንቀድሞው ዘመን በመንፈሳዊነት ስም ኢትዮጵያንም ሆነ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ዳግም በቅኝ ገዢነት መንፈስ ይዘው ዓላማቸውን ለማስፈጸም ምንም ዓይነት ዕድል እንደሌላቸው ካወቁ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የዓባይ ውኃን በተመለከተ ኢትዮጵያ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብቷ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ እንደሆነ ግብፅና ግብፃውያን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተረዱት መጥተዋል፡፡ እንደቀደመው ዘመን በማስፈራራትና በዲፕሎማሲያዊ ጫና የዓባይን ውኃ ከመጠቀም የሚከለክሉበት ምክንያት እንደሌላቸውም እርግጥ ሆኗል፡፡
አሁን አሁን ከግብጽ እየወጡ ያሉ መረጃዎችና ዜናዎች እንደሚያሳዩትና በቅርቡ ፕሬዝዳንት ሙርሲም እንዳረጋገጡት፡- ‹‹ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታካሂደው ልማት ግብፅንና የተቀሩት የተፋሰሱን አገሮች እስካልጎዳ ድረስ ደስተኞች ነን፡፡ ከጎናችሁም እንቆማለን ሲሉ እየተደመጡ ነው፡፡›› ይህ ከልብና ከቅንነት የመነጨ ከሆነ መልካም የሚባል እርምጃ እንደሆነም የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብም እየገለጹ ናቸው፡፡
ሕዝባችን ለዘመናት ከተጣበው ድህነት፣ የመከራ፣ ሰቆቃና የስደት ሕይወት ተላቆ በአገሩና በሕዝቡ መካከል ተረጋግቶና እፎይ ብሎ መኖር እንዲችል ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ መልካም አስተዳር፣ ልማት … ወዘተ በጣሙን አስፈላጊ ናቸው፡፡
መንፈሳዊ ተቋማትና መሪዎቻቸው በአገራችን ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትሕ፣ መልካም አስተዳደር፣ ዕድገትና ብልጽግና እንዲሰፍን የራሳቸው የሆነ ከፍተኛ ድርሻና ተሣትፎ አላቸው፡፡ በቅርቡም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑት ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ በዓባይ ወንዝ ላይ ስለተጀመረው ልማት፣ በዴር ሱልጣን ገዳማት ጉዳይና እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኒቱ የተንሰራፋውን ሙሰናና ሙሰኞችን በተመለከተ ያስተላለፉት መልእክት ብዙዎችን ደስ አሰኝቷል፡፡
የቅዱስነታቸው ይህ ቃል ከቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ብፁዓን አባቶቻች ጋር በመተባበር ተግባራዊ ሆኖ የምናይበትን ጊዜ መንፈሳዊ ልጆቻቸው በታላቅ ጉጉት እንጠብቃለን፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስለተንሰራፋው ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የሞራል ዝቅጠትና ውድቀት፣ እንዲሁም የመንፈሳዊነት ሕይወት መታጣት ብዙ የተባለለት ያረጀና ያፈጀ ጉዳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ችግሩን ከማውራት በስተቀር ይህን ነው ተብሎ ሊነሣ የሚችል ተግባራዊ እርምጃ እስካሁን አልተወሰደም፡፡
እንዲሁም ቅዱስ ፓትርያርኩ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ያጣበቡትን ነጋዴዎችና ዘራፊዎች ያለ ምንም ቅደም ሁኔታ በማስወጣት መንፈሳዊና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰዱና፣ በተጨማሪም የተሠጣቸውን መንፈሳዊ የሆነ ኃላፊነት ዘንግተው ፍጹም መንፈሳዊ ባልሆነ አካሄድ በሥጋዊና በዓለማዊ ምኞት ተጠልፈው፣ ያልደከሙበትንና ያለፉበትን ሀብትና ገንዘብ የማከማቸት ሥራ ውስጥ ተዘፈቁ የቤተ ክርስቲያኒቱን ኃላፊዎች ተገቢውን ሥርዓት እንዲይዙ እንደሚያደርጉ ያስተላለፉት መልእክት በእውነት ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ በመንፈሳዊ ቅንአትና ቆራጥነትና እንዲሁም ባላቸው ከፍተኛ መንፈሳዊ ኃላፊነትና እረኝነት በቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ አገልጋዮችና ተከታዮቿ መካከል ለአገርና ለወገን የሚቆረቆር፣ የተሠጠውን ግዴታውንና ኃላፊነቱን በታማኝነት የሚወጣ፣ በወንጌል የእውነት ቃል የታነጸ መልካም ዜጋና ትውልድ ለመፍጠር ከቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ አባቶች ጋር የበኩላቸውን ጥረት በማድረግ ተወዳጅና ተከባሪ አባት እንዲሆኑልን እመኝላችኋለሁ፡፡
በተጨማሪም ቅዱስ ፓትርያርኩ የዓባይን ውኃ በፍትሐዊነት የመጠቀም መብታችንን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከግብፅ ጋር የነበራትንና አሁንም ያላትን የረጅም ዘመን ግንኙነትና እንዲሁም ታሪካዊ ትስስር ከግምት ውስጥ በማስገባት የጀመሩትን እንቅስቃሴ ይቀጥሉበታል የሚል ጽኑ ተስፋ አለኝ፡፡
ከግብፃውያን ጋር ለረጅም ጊዜያት አተካራ በገባንበትም በዴር ሱልጣን ገዳማችን ጉዳይን በተመለከተም ፓትርያርኩ በኢየሩሳሌም ለረጅም ዓመታት በመቆየታቸው ያለውን ሃይማኖታዊ ሆነ ፖለቲካዊ ችግሩን በሚገባ ያውቁታልና ቅዱስ ሲኖዶስንና መንፈሳዊ ልጆቻቸውን በማስተባበር ሰፊ የሆነ ሥራን ሊሠሩ እንደሚችሉ መንፈሳዊ ልጆቻቸው ተስፋ እናደርጋለን፡፡
በቀጣይ ጽሑፌ በዴር ሱልጣን ገዳም ዙሪያ ያለውን ታሪክና የግብፃውያኑን ሴራ ከወቅታዊው የዴር ሱልጣን ገዳም ጉዳይ ጋር አያይዤ ለመጻፍ ከወዲሁ ቃል በመግባት ልሰናበት፡፡
ሰላም! ሻሎም!
ቱጃሮቹ የማን.ሲቲ ባለቤቶች ሮቤርቶ ማንቺኒን አሰናበቱ፤ ማን ሊተካቸው ይችላል?
Tuesday, May 14th, 2013ጣሊያናዊው ሮቤርቶ ማንቺኒ በዱባይ ባለሀብቶች የሚመራውን ማንችስተር ሲቲን ከአርባ አራት አመታት በኋላ ሻምፒዮን ባደረጉ በአመታቸው ከክለቡ አሰልጣኝነት ተሰናብተዋል።
ማንችስተር ሲቲ እግር ኳስ ክለብ በይፋዊ ድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ አሰልጣኙ በአመቱ እንዲያሳኩ ከተቀመጡላቸው ግቦች መካከል አብዛኛዎቹን ማሳካት አልቻሉም ፤ በዚህም ምክንያትነት ከኃላፊነታቸው ተሰናብተዋል ብሏል።
አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ማንችስተር ሲቲን በቀጣዩ አመት በሚካሄደው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ መሆን የሚያስችለውን እድል እንዲያገኝ ቢረዱትም ከተቀመጡላቸው ግቦች መካከል አብዛኛዎቹን አለማሳካታቸው ለስንብታቸው መንስኤ መሆኑን ክለቡ አስታውቋል።
በውድድር አመቱ ክለቡ የቀሩትን ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችና በአሜሪካ የሚያደርገውን ዝግጅት ምክትላቸው ብሪያን ኪድ እንደሚመሩም በመግለጫው ይፋ አድርጓል።
የክለቡን የአሰልጣኝነት ኃላፊነት ይረከባሉ ተብለው ከሚጠበቁት ታላላቅ አሰልጣኞች መካከል ቺሊያዊው የስፔኑ ማላጋ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ ግንባር ቀደሙ መሆናቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።የስፔኑን ኃያል ሪያል ማድሪድን በአውሮፓውያኑ 2010 በአሰልጣኝነት የመሩት የ59 አመቱ ፔሌግሪኒ ባለፈው እሁድ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
ማንችስተር ሲቲ እግር ኳስ ክለብ የአሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒን ስንብት ይፋ ባደረገበት መግለጫው አሰልጣኙ ክለቡን በኃላፊነት ከተረከቡ ከአውሮፓውያኑ 2009 ጀምሮ ለሰሩት ስራ ምስጋና አቅርቧል።
«ሮቤርቶ ያስመዘገቧቸው ውጤቶች ማንታቸውን ይገልጻሉ ። ከክለባችን ደጋፊዎች ታላቅ ፍቅርና አክብሮት ማግኘት ችለዋል ። ለክለባችን ቃል በገቡት መሠረት ውጤት አስገኝተውልናል። ከእርሳቸው ጋር መለያየት ከባድ ቢሆንም በዚህ የውድድር አመት ያስመዘገቡት ውጤት ሲመረመር በአመቱ ለማሳካት ከተቀመጠላቸው ግብ አንጻር ዝቅተኛ ሆኖ በመገኘቱ እንዲሰናበቱ ተወስኗል » ብለዋል የክለቡ ሊቀመንበር ካልዱን አል ሙባራክ በመግለጫቸው ።
የ48 አመቱ ጣሊያናዊ ሮቤርቶ ማንቺኒ በአውሮፓውያኑ 2009 ማርክ ሂውዝን ተክተው ክለቡን በኃላፊነት ከተረከቡ በኋላ ማንችስተር ሲቲን የኤፍኤና የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባለቤት ማድረግ ችለዋል።
በዚህ የውድድር አመት ግን ክለቡ ከሻምፒዮኑ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሰፊ የነጥብ ልዩነት ያለው መሆኑ፣ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር በጊዜ መሰናበቱና በኤፍኤ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በዊጋን አትሌቲክ ተሸንፎ ዋንጫ ማጣቱ የአሰልጣኙን ስንብት እንዳፋጠነው ይገመታል።
ዜና ዘ-ትግራይ (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)
Tuesday, May 14th, 2013አንድ፡ አድዋ
በትግራይ አድዋ ወረዳ የሚገኙ ሦስት የአልመዳ ፋብሪካዎች (አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ አልመዳ ልብስ ስፌት ፋብሪካና (አልመዳ) ሳባ እምነበረድ ፋብሪካ) የኬሚካል ቆሻሻ (Chemical Residue) የሚጠራቀምበት ከመሬት በታች የሚገኝ ጋን ፈንድቶ ወደ ላይ በመተኮሱ የአከባቢ ብክለት አስከትሏል። ይህንን የቆሻሻ ኬሚካል ማጠራቀምያና ማጣርያ ፍንዳታ አደገኛና መርዘኛ ሽቶ በመፍጠሩ በአከባቢው (እስከ አስር ኪሜ ራዲያስ ድረስ) የዉሃና የአየር ብክለት አስከትሎ በሰዎችና እንስሳት የመታመም ምልክቶች እየታዩ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ የፋብሪካዎቹ ሰራተኞች (ከ 500-600 የሚደርሱ) ችግሩ ተቋቁመው እንዲሰሩ ስለ ተገደዱ የጤና ችግር እንዳያስከትልባቸው በመስጋት ለትግራይ ክልል መንግስትና ለትእምት ሓላፊዎች አቤት ያሉ ሲሆን እስካሁን ግን መልስ አላገኙም። መንግስት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ተማፅነዋል።
ሁለት፡ ታሕታይ ማይጨው
በትግራይ ክልል፡ ማእከላዊ ዞን፣ ታሕታይ ማይጨው ወረዳ (ከሁለት ሳምንት በፊት ነው) የመንግስት ሰራተኞች ከህወሓት ሓላፊዎች ጋር አለመግባባት ፈጥሯል። በወረዳው ወደ 650 የሚሆኑ አስተማሪዎች፣ 420 የግብርና ሰራተኞች፣ ከ300-350 የጤና ሰራተኞችና ከ550 በላይ የወረዳው የመንግስት አስተዳደር ሰራተኞች የኢኮኖሚ ጥያቄ አስነስተዋል። እነኚህ ሰራተኞች የወር ደመወዛቸው አነስተኛ ሁኖ ሲያበቃ (ግብር ሲቆረጥበት የባሰ እንደሚያንስ ነው) ተጨማሪ ወጪ ስለበዛባቸው መኖር አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ገልፀዋል።
ደመወዛቸው አነስተኛ፤ ከዚህ የመንግስት (የማይቀረውን) ግብር ይቆረጣል፣ የህወሓት የአባልነት መዋጮ ይቆረጣል፣ የትግራይ ልማት ማህበር (TDA) ይቆረጣል፣ የአባይ ግድብ ይቆረጣል፣ (የቀይ መስቀል የሚቆረጥባቸውም አሉ) ወዘተ … ። በቃ መቁረጥ ነው። ተጣርቶ እጃቸው የሚገባ በጣም ትንሽ ብር ነው። በትንሽ ብር (ከንሮ ውድነቱ ጋር ተደምሮ) ህይወት ለነሱ መከራ ሁናለች።
ችግራቸው ለዞኑ አስተዳደር ለማስረዳት ሞክረዋል። ‘ወጪ በዝቶብናል’ አሉ። አስተዳዳሪውም ‘የመንግስት ትእዛዝ ነው’ አለ። እንሱም ‘ቢያንስ የህወሓት አባልነት መዋጮ ይቀነስልን’ አሉ። አስተዳዳሪውም ‘ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የህወሓት አባል መሆን አለበት፤ አለበለዝያ ግን ከስራው ይባረራል’ ብሎ አስፈራራቸው። አሁን ተስፋ በመቁረጥ ላይ ናቸው።
ሦስት፥ ሽሬ
በሽሬ አከባቢ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር መኖሩ ለማወቅ ችያለሁ። ከሩቅ ቦታ የሚመጣው የጉድጓድ ውሃ (ንፁህ ያልሆነ ውሃ) በብዙ ብር ይገዛል። አብዛኞቹ የሽሬ ሆስፒታል ታካሚዎች በውሃ ወለድ በሽታዎች የሚሰቃዩ መሆናቸው መረጃ ደርሶኛል። በአከባቢው ከዓመታት በፊት በእስራኤላውን ባለሙያዎች የተጠና የውሃ ቁፋሮ ተደርጎ እንደነበርና በሙስና ምክንያት ውጤታማ ሳይሆን ቀርቶ እስካሁን ድረስ የዉሃ ችግሩ እንዳለ ነው።
አራት፡ የትግራይ መንግስት ፕላን
የትግራይ መንግስት በግብርና ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት የመስኖ እርሻ ለማስፋፋት ብዙ ዉሃ ለማቆር የሚያግዙ ቁፋሮዎች አከናውነዋል። ብዙ የዉሃ ጉድጓዶች ተቆፈሩ። ውሃ ተጠራቀመ። አርሶ አደሮች በዓመት ሁለቴ ማፍራት እንዲችሉ ምርጥ ዘርና መዳበርያ (fertilizer) በብድር እንዲወስዱ ተገደዱ (ካልወሰዳቹ መሬታቹ ለሌላ ሰው አሳልፈን እንሰጠዋለን በሚል)። አርሶ አደሮቹ ተበድረው ወሰዱ። ተጠቀሙበት። እህሉ ሳይደርስ የቁፋሮውን ውሃ ደረቀ። ፍሬ ሳይሰጥ ቀረ። ብድሩ ግን አለ። ከሰኔ ወር በፊት ብድሩ መመለስ አለባቸው። ከየት አምጥተው ይከፍሉታል? አርሶ አደሮቹ ተጨናንቋል።
አንድ ነገር ሲተገበር መጀመርያ በጥናት የተደገፈ መሆን አለበት።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ የሰማያዊ ፓርቲን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ደገፈ
Tuesday, May 14th, 2013
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 2005 ዓም የአፍሪካ ህብረት የወርቅኢዮቤልዮ በአል በሚከበርበት ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ተከትሎ ”የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ያለው የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ “ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው የጠቀሳቸው አራት ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ መልስ እንዲያገኙ ከሚታገልላቸው ዋና ዋና የህዝብ ጥያቄዎች መካከል ውስጥ የሚገኙና ዘረኛው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በዘረጋው የጭቆናና የግፍ መረብ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በግዴለሽነት በግልፅ በአደባባይ ከሚፈፅመው ስቃይ ፣ መከራና ፣ እንግልት ጥቂቶቹ በመሆናቸው ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበው ወቅታዊና ተገቢ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን ሙሉ ለሙሉ የተቀበለው መሆኑን በአፅንዎት ይገልፃል::” ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ።
ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ህዝባዊ በመሆኑ ፤ በዚህ ዘረኛ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከልክ ያለፈ ጭቆና ፣ ረገጣና ፣ እንግልት ደርሶብኛል የምትሉ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ፣ በምንወዳት ሃገራችን ለህዝብ የሚበጅ ቀና ለውጥን የምትመኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ፤ እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማትና ፣ የሲቪክ ማህበራት ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና የህዝብ አደራ በጫንቃችሁ እንደተሸከማችሁ በመገንዘብ ፤ የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ ተልኮ መፈፀም ታሪካዊ ግዴታችሁ መሆኑን በመረዳት ፤ ከሰማያዊ ፓርቲ ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ጎን እንድትቆሙ ሲል በጥብቅ እያሳሰበ ፤ ሃገራዊ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል:: የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ብሏል።
ሰውየው – ክፍል 1
Tuesday, May 14th, 2013ሰውየው
መካከለኛ ቁመና አላቸው: ሰውነታቸው ሞላ ደልደል ያለ ወንዳወንድ:: እድሜአቸው ወደ 70 አመት የሚጠጋ ቢሆንም የሰውነት አቋማቸውና ጥንካሪያቸው ሲታይ ሀምሳም የደፈኑ አይመስሉም:: የእግር መንገድ ይወዳሉ:: በውትድርና ያሳለፉት ዘመን ጥንካሪያቸው ላይ አሻራውን አሳርፏል:: እና አሁንምንቁ: ቀልጣፋ: ደፋርና ጠንካራ ናቸው:: ለሽርሽር ብሎ አብሯቸው የወጣን ሰው በላብ እስኪጠነፍር ድረስ ያሽከረክሩታል:: ደከመኝን ብዙም አያውቁም:: ቁጥብ አንደበት አላቸው:: በቁም ነገር ጊዜ ቁምነገር መናገር በቀልድ ጊዜም መቀለድ ይችላሉ:: ቁምነገራቸው ከመሬት ጠብ አይልም:: ጨዋታቸውአይጠገብም:: ካገኙት ጋር ሁሉ አፍ የሚካፈቱ ግን አይደሉም:: ከማን ጋር መዋልና ምን መስራት እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ:: ውለታ መዋል ይችላሉ:: ለተቸገረ ደራሽ: አሳቢና ተቆርቋሪ ናቸው:: ቤታቸው የሄደን እንግዳ ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዳሉ:: ሰው በልቶ የጠገበ አይመስላቸውም:: አንድነገር ብቻ አይወዱም “ጥቃት”:: ጥቃትን ከምንም በላይ: ከራሱ ከሞትም ቢሆን አብልጠው ይጠላሉ:: ያላግባብ ጥቃት የፈጸመባቸውን ሰው ልኩን ሳያሳዩ አይለቁም:: ያም ሆኖ አጥቂው ጥፋቱን አውቆ ይቅርታ ከጠየቃቸው ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገው ወደቀድሞው ለስላሳ ማንነታቸው ይመለሳሉ::የቤተክርስቲያን ሰው ስለሆኑ ይቅርታን የእግዚአብሄር መቅረቢያ መንገድ አድርገው ይወስዳሉ:: “ሽህ ጊዜ ኧረ ከዚያም በእጅጉ ለሚበልጥ ጊዜ ጥፋት እያጠፋን: ከፈቃዱ እየወጣን: በእብሪትና በትእቢት ስንት በደል ከፈጸምን በኋላ ‘በመጥፎ ስራችን ተጸጽተናል ማረን’ ብለን እግዚአብሔርን ይቅርታስንጠይቀው ይቅርታ ያደርግልናል አይደል? ይቅርታ እየለመንንና ይቅርታ እየተደረገልን እያለ በድያለሁና ይቅርታ አድርጉልኝ ብሎ የሚመጣን ሰው አይ አይሆንም ብለን እንዴት ልንገፋው እንችላለን:: ይቅርታ ካላደረግን ይቅርታን መጠየቅ የለብንም:: ይቅርታ የእግዚአብሔር ነው” ይላሉ ከዚህ ጋርየተያያዘ ጉዳይ ሲነሳ ከሰሙ::
ወደውትድርናው የገቡት በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት ነው: በ1950ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ:: ትውልዳቸው ከደህና ቤተሰብ ቢሆንም አስተዳደጋቸው ግን እንደማንኛውም ተራ ኢትዮጵያዊ ነው:: ማንኛውም ህጻን ሆኖ ያደገውን ሆነው ነው ያደጉት:: ትምህርት ቤት ገብተው ተምረዋል:: ወጣትነትሁሉን አስፈሪ ነገር ለመድፈር ያስችላል:: ውትድርና ቀላል ነገር አይደለም:: ጨዋታው ከህይወት ጋር የተያያዘ ነው:: በዚያን ጊዜ የነበረ ወታደር ደረቱን ለጦር ግንባሩን ለጥይት ለመስጠት የቆረጠ እንደባህታዊ በየበረሀው በቀበሮ ጉድጓድ ለመኖር: ራሱን አሳልፎ አገርንና ህዝብን ከጥቃት ለመከላከል የተሰለፈነበር:: ኢትዮጵያ ሀገራችን የጠላት ችግር የለባትም:: ከአሁኑ የሶማሊያ ክልል አልፎ እስከ አዋሽ አርባ ድረስ ያለውን መሬት ከኢትዮጵያ በሀይል ነጥቆ ታላቋን የሶማሊያ ግዛት ለመመስረት ያለመው የዚአድባሬ መንግስት: ኤርትራን ከኢትዮጵያ አስገንጥለው የአረቡ ዓለም አካል ለማድረግ በግብጽፊታውራሪነት የተሰለፉት የአረብ ሀገሮች: የኢትዮጵያን ሰላምና እድገት የማይፈልጉት ሁሉ ጀብሀንና ሌሎች ሀገር በቀል አፍራሽ ሀይሎችን አሰልፈው ዙሪያ ገባውን የሚያቆስሉበት ዘመን ነበር:: ያኔ ነው ሰውየው ይህን ራስን ለመሰዋእትነት አሳልፎ በመስጠት ሀገርንና ህዝብን ለመታደግ የሚል አላማአንግበው ወደ ውትድርና የገቡት::
እኒህ ሰው ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ ይባላሉ:: ብዙ የሀገር አውራወች ከበቀሉበት ደቡብ ጎንደር ነው ትውልዳቸው:: የያኔው የ1950ዎቹ ወጣት ሀይለየሱስ ፈጣንና ቀልጣፋ ነበሩ:: በልጅነታቸው ከእኩዮቻቸው ጋር ሲጫወቱ ሮጦ የሚቀድማቸው: ታግሎ የሚጥላቸው አልነበረም:: ሽንፈትን አይወዱም: እናይታገላሉ ታግለውም ያሸንፋሉ:: በዚያን ወቅት የነበረው ይህ ለጥቃት ያለመንበርከክ ስሜት: ከራሳቸው አልፈው ለህዝብና ለሀገር እንዲሰለፉ አስገደዳቸውና ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደውትድርናው ገቡ:: በተራ ውትድርና ለአመታት ካገለገሉ በኋላ ለምክትል መቶ አለቅነት ተወዳድረው ከጓደኞቻቸውየተሻለ ውጤት አምጥተው በማለፋቸው ሆለታ የመኮንኖች ማሰልጠኛ ተቋም ገብተው በምክትል መቶ አለቅነት ተመረቁ::
የምክትል መቶ አለቅነት ማእረግ ካገኙ በኋላ በተለያዩ የጦር አውድማወች ከጓድ መሪነት እስከሻምበል አዛዥነት አገልግለዋል:: ያን ያገጠጠ የኤርትራ ተራራ እንደዝንጀሮ እየቧጠጡ በመውጣት ሻቢያንና ጀብሀን እያሳደዱ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተዋል:: ወታደሮቻቸው በበሰለ አመራራቸውና ወታደራዊስልታቸው ያደንቋቸዋል:: ለሀገርና ለወገን ባላቸው ፍቅር ያከብሯቸዋል: በጀግንነታቸው ይመኩባቸዋል:: ዘመድ ወዳጆቻቸው እንዲሁም ጓደኞቻቸው ይኮሩባቸዋል:: የኤርትራን ደጋና ቆላ መሬቶች ጀብሀንና ሻቢያን ሲያሳድዱ ረጋግጠውታል:: ከተሰነይ እስከናቅፋ: ከአከለጉዘይ እስከምጽዋ ቆንጥሩንእየመነጠሩ አሜካላውን እየጠረጉ: ረሀብና ጥምን ተቋቁመው ድካም ሳያዝላቸው ተመላልሰውበታል:: በተደጋጋሚ በደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ምክንያት በምድር ጦር መምሪያ ውስጥ እንዲሰሩ ሲደረግ ደስተኛ አልነበሩም:: እኒያ በኤርትራ መሬቶች ከጠላት ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቁ ጥለውየሚወድቁት የትግል አጋሮቻቸው ሁኔታ በምናባቸው እየታያቸው ወደዚያው ሂድ ሂድ የሚል ስሜት ይተናነቃቸዋል:: ግን ምንም ማድረግ አልቻሉም: የበላይ ውሳኔ ነዋ!
የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ጸር የሆነው ወያኔ መራሹ ኢህአዴግ ስልጣን ሲቆጣጠር ሻለቃ ሀይለየሱስ ለተሀድሶ ከጓደኞቻቸው ጋር ወደጦላይ ተወሰዱ:: በጦላይ ቆይታቸው ብዙ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊቶች አይተዋል:: በአንድ ወቅት አንቱ ተብሎ ይፈራና ይከበር የነበረ የጦር መሪ ባልሰለጠነ የዘር ሰራዊትከፍ ዝቅ ሲደረግ ማየትና መስማት ከምንም በላይ ያማል:: እንዳይቻል የለምና ይህም ታለፈና ሀይለየሱስ ከማጎሪያ ካምፑ ተሰናብተው ወያኔ ባስቀመጠው የእድሜ ገደብ ተጠቅመው የጡረታ መብታቸውን አስከብረው ኑሯቸውን ከአዲስ አበባ ወደባህርዳር አዙረው ቤት ሰርተው ልጆቻቸውን እያሳደጉመኖር ጀመሩ:: ወቅቱ እንዲህ እንዳሁኑ አልከፋም ነበርና ሻለቃው በጡረታ በሚያገኙት 400 ብር የማይሞላ ገንዘብ ልጆቻቸውን ለማሳደግ ብዙም አልቸገራቸውም::
ይህ በእንዲህ እንዳለ የወያኔ የጫካ ፖሊሲ በከፋ መልኩ መተግበር ጀመረ:: “አማራ የትግራይ ጠላት ነው:: አማራ መጥፋት አለበት” ብለው ወያኔዎች በመተዳደሪያ ደንባቸው ያስቀመጡትን ፖሊሲ በተግባር መተርጎም ጀመሩ:: አማሮች ቡና ለቅመው: እህል ሰብስበው: ወይም በማንኛውም የጉልበት ስራተሰማርተው ያገኟትን ጥሪት ለዘመመ ጎጇቸው ማቃኛ ለኑሮ መደጎሚያ ለማድረግ እግር ወደመራቸው አሊያም ስራ ይገኛል ብለው ተስፋ ወደአደረጉበት አካባቢ እንደሄዱ ሳይመለሱ በዚያው ወድቀው ቀሩ:: ነፍጠኛ መጣብህ እየተባሉ ብሄር ብሄረሰቦች እየተቀሰቀሱ በየአካባቢው አማሮች እየታደኑእንዲገደሉ ተደረገ:: አንገታቸው ተቆረጠ ሆዳቸው በሳንጃና በገጀራ ተቀደደ:: በደህናው ጊዜ ሁሉም አገሬ ብለው ከቦታ ቦታ መርጠው ለጤናቸው ወይም ለስራቸው የሚስማማ ነው ብለው ባመኑበት የሀገሪቱ ክፍል ካካባቢው ህዝብ ጋር ተዋልደውና ተስማምተው የኖሩት አማሮችና የአማራ ዝርያያለባቸው ሰዎች ሁሉ ይህ ቀረ የማይባል ግፍ ተፈጸመባቸው:: ም/ጠ/ ሚኒስትር የነበረው ታምራት ላይኔ በጅጅጋ ተገኝቶ ‘እዚህ ያሉት አማሮች ሊገዟችሁ: ሊዘርፏችሁ: ሊገድሏችሁ የመጡ ናቸው:: ለምን ዝም ብላችሁ ታይዋቸዋላችሁ:: ዱላው በእጃችሁ ጠላቶቻችሁ በደጃችሁ’ አይነት ንግግር አደረገናየአማሮችን የስቃይ ደረጃ በእጅጉ አናረው:: በአሶሳ: በወተር: በበደኖ (የየአካባቢውን ሰለባ እግዜር ይቁጠረው) አማሮች ከነነፍሳቸው በገደል ተጣሉ: እንደበግ ታረዱ:: አዛውንቶች: ህጻናት: ወንዶች ሴቶች: ሁሉም ተረሸኑ:: አማራነት ብቻውን ለሞት ዳረገ:: አቅም ያገኙ ሀብት ንብረታቸውን ሳይይዙነፍሳቸውን ለማትረፍ የተወለዱበትና ያደጉበትን: ሀብት ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበረበትን አካባቢ ጥለው ባዶ እጃቸውን ተሰደዱ:: ‘አማሮች ወደመጡበት ሲመለሱ ምንም ነገር እንዳያንጠለጥሉ:: ባዶ እጃቸውን ነው የመጡት: መመለስ ያለባቸውም ባዶ እጃቸውን ነው:: ቤታቸውን: ድርጅታቸውንእንዳትገዟቸው:: ምን ያደርጉታል:: ይዘውት አይሄዱ ተብሎ በየሰፈር ተሿሚወች እንዲለፈፍ ተደረገና አማሮች ባዶ እጃቸውን ‘በለው በለው’ እየተባሉ የወደቁት ወድቀው የተረፉት እንዲሰደዱ ተደረገ::
ኢትዮጵያ የምትባለዋ ሀገር ታሪክና ስም የሚያንገሸግሻቸው ወያኔወች ኢትዮጵያን ለማጥፋት በቅድሚያ አማራውን ማጥፋት ብለው ወስነው የጥፋት ዘመቻውን አጧጧፉት:: አማሮች በየቦታው የጣእር ድምጽ አሰሙ:: በረጅም ዘመን የሞት የሽረት ትንቅንቅ ያቆያትን: በጥቁሮች ታሪክ ያልታየ ገድል ፈጽሞ ከነጮች ጋር ድንበር ተካሎ በደምና በአጥንቱ መሰረት የገነባትን ኢትዮጵያን ያወረሰ ኩሩ ኢትዮጵያዊ እየታደነ ታረደ:: ለደርቡሾች: ለግብጾች: ለቱርኮች: ለሶማሊያወች: ለጣሊያኖችና ለእንግሊዞች ያልታጠፈ ክንድ በገዛ ልጆቹ ዛለ:: የወራት የእግር መንገድ እየተጓዘ ደረቅ ዳቦቆሎና እንጎቻ እየገመጠ በዚያመንገድ ባልነበረበት ዘመን እባቡ እየነደፈው: ወባው እየጣለው: የዱር አውሬው እያጠቃው: ይኸ ሁሉ የሚያጎድልበት ሳይበግረው ረሀብና ጥሙን ችሎ በጦር በጎራዴ ከዳር ዳር እየዞረ: የሀገር ትርጉም ቀደም ብሎ ገብቶት ‘እኔ ለሀገሬ’ ብሎ ከጠላት ጋር ተናንቆ በደምና በአጥንቱ አስከብሮ ባቆያት ኢትዮጵያላይ የተቀመጡ የጊዜው ሰዎች የዚያን አንበሳ ኢትዮጵያዊ ልጆች እየለቀሙ በመፍጀት ውለታውን ከፈሉ:: ከኢትዮጵያዊነት ደረጃው ዝቅ ብሎ የማያውቀው አማራ ሀገሬ እንዳለ የሀገር ትርጉም ባልገባቸው ርጉም ልጆቹ ሀገሩን አጣ:: ‘የአማራው ሀገር የት ይሆን?’ ሲልም ጠየቀ:: አማራ ተብለው በብአዴን ስርየተሰባሰቡ ከንቱወች ‘ከክልላቸው የወጡት አማሮች ጉዳይ አይመለከተንም’ አሉ:: በዚህ ጊዜ ነበር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ የሚወተውተውን አማራ ‘እስቲ መጀመሪያ ለራሳችን እንሁን- እያጠፉንኮ ነው’ በሚል መልክ እንደራጅ ብለው ጥቂት መሰሎቻቸውን ይዘውመዐሕድን የመሰረቱ::
ሻለቃ ሐይለየሱስ እጅጉ ጡረታ የወጡት ከትግል አይደለም:: በዚያም ላይ እየተጠቃ ያለው ወገናቸውና በደም እየታጠበች ያለች ሀገራቸው ጉዳይ ሰላም ነስቷቸዋል:: እናም የወያኔን ወደስልጣን መምጣት ተከትሎ ጠበንጃቸውን የሰቀሉት ሻለቃ ጠበንጃቸውን አውርደው ና ወልውለው በሚያውቁበትናወያኔን በሚገባው መንገድ ሊያነጋግሩ አልፈቀዱም:: የአለም ሁኔታ ለእንደዚህ አይነት ትግል አመች አይደለም:: ወያኔና ሻእቢያ ደርግን አሸንፈው ስልጣን እንዳልነጠቁ አሳምረው ያውቃሉ:: ‘ኢምፔሪያሊዝም ይውደም’ እያሉ የሰው ምስል ቀርጸው በእሳት ሲያቃጥሉ የነበሩትን ደርጎች ለመበቀል: በምትኩምየራሷን ተላላኪወች ለማንገስ አሜሪካ በነደፈችው መርሀ ግብር መሰረት የጦር ጀኔራሎች እንዳያዋጉ በተለያየ ነገር በመደለል ውጊያውን እንዳበላሹትና ሁሉም ነገር በወያኔና በሻእቢያ የበላይነት እንዲደመደም እንዳደረጉ ያውቃሉ:: የኢትዮጵያ ጦር ‘ይህንን ቦታ አጥቅተህ ያዝ’ ይባላል:: ጦሩ የተባለውን ቦታአጥቅቶ ሲይዝ ምክንያቱን በማያውቀው ሁኔታ ወደኋላ አፈግፍግ ይባልና እንደገና ሌላ ትእዛዝ ይመጣበታል:: በዚህም ምክንያት በስንት መስዋእትነት የያዘውን ምሽግ እንደቀላል ነገር ለቆ እንዲመለስ ይደረጋል:: ብዙም ሳይቆይ ‘ተለዋጭ ትእዛዝ’ ተብሎ አጥቅተህ ይዘኸው የነበረውን ምሽግ በአፋጣኝመልሰህ በእጅህ አድርግ ይባላል:: ይህ ሲሆን ግን የሻእቢያ ጦር በውጊያ ተሸንፎ ለቆት የነበረውን ምሽግ ቀድሞ እንዲገባበት ተደርጎ ነው:: ከጠላት ማስለቀቁን እንጅ ተመልሶ በጠላት እጅ መውደቁን ያልጠረጠረው የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደምሽጉ ሲመለስ የመሸገው የጠላት ጦር በሩምታ ተኩስ ይቀበለዋል-በዚህ አይነት የተበላሸ አመራር የሰራዊቱን የውጊያ ፍላጎት አሟጠው አጠፉት:: ይህን ሀይለየሱስ ጠንቅቀው ያውቃሉ:: ሶሻሊስት ርእዮተአለምን ይከተሉ የነበሩ ሀገሮች ሁሉ እጣ ፈንታ ይኸው ሆኗል:: የሶቭየት ህብረትን መፈራረስ ተከትሎ ‘ኢምፔሪያሊዝም ይውደም’ እያሉ ኢምፔሪያሊዝምን ይወክላልብለው ሆዱ የተንዘረጠጠ: ጥርሱ ያገጠጠ: የዶላር ምልክት በተነፋ ሆዱ ላይ የተለጠፈበት የካርቶን ስእል እየሰሩ ሲያቃጥሉና ኢምፔሪያሊዝምን ያጠፉ ያህል በደስታ ሲቃ በእሳቱ ዙሪያ ክብ እየሰሩ ሲጨፍሩ የነበሩትን ሶሻሊስቶች አሜሪካ በአካል ተበቀለቻቸው- ብትንትናቸውን አወጣቻቸው- ሀገራቸውንጭምር:: የኢትዮጵያም ታሪክ ያው ይህንን የተከተለ ነው:: ይህ ለሀይለየሱስ እንግዳ ነገር አይደለም:: ሶሻሊዝም እንደስርአት ካከተመ በኋላ ሁሉም ነገር በአሜሪካ በጎ ፈቃድ ስር ወደቀ:: ወዲያ ወዲህ ማለት አልተቻለም:: ችግር አለብኝ የሚል ወገን ሁሉ በሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካና የአውሮፓ ሀገሮችኤምባሲወች ባሉባቸው ከተሞች ‘እግዚኦ’ ብሎ በደልን ማሰማት ብቸኛ አማራጭ ሆነ:: በስሜት ተነሳስቶ ‘ዘራፍ’ ብሎ ጫካ የሚገባ ሰው ቢኖርም ትርጉም የለውም:: የያዘውን ጥይት አስጨርሰው ካስተኮሱ በኋላ በዱላ አባሮ መያዝ ይቻላል:: ውጊያ ለመጀመር የሎጀስቲክስ ተከታታይ አቅርቦት: የስልጠናናየቴክኒክ እርዳታ: የመረጃና የነጻ መሬት መኖር ወሳኝ ነው:: ያንን ማግኘት እጅግ ከባድ ነው:: አንደኛ ወያኔ ማንኛውንም የኢትዮጵያ ጥቅም አሳልፎ በመስጠት ከበፊት የኢትዮጵያ መሪወች ሁሉ በተለየ ለጎረቤት ሀገሮች ተመችቷል:: ሁለተኛ ወያኔ የአሜሪካ ተላላኪ በመሆኑ ሁለንተናዊ ድጋፍ ይደረግለታል-መረጃን ጨምሮ:: ስለዚህ የተሻለው መንገድ በደልን በእግዚኦታ ማሰማት ነው:: ይህንን የተረዱት ሻለቃ የአማራውን ጩኸት ለመጮህ መዐሕድን ተቀላቀሉ::
ይቀጥላል
Hiber Radio: የስዬ አብርሃ ወንድም ዳግም በሙስና ታሰረ
Monday, May 13th, 2013የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ግንቦት 4 ቀን 2005 ፕሮግራም
<<አቶ መለስ ግፈኛ መሪ ነበር።የዚህ ግፈኛ ልደቱ ሊከበርለት አይገባም ብለን ተቃውመናል።የአማራው፣የጋምቤላው፣የአፋሩ መፈናቀል የዚህ ሁሉ ቀውስ መነሻው መለስ ዜናዊ ነው።ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅም ሽማግሌነኝ ሲል ቆይቶ ከስርዓቱ ጋር ያለውን ወዳጅነት ልደቱን ኤምባሲ ሊያከብር ሲመጣ አግኝተነዋል። ይሄ ሰው ገለልተኛ ሽማግሌ አይደለም ።ወገንተኛ ነው ተቃውመነዋል. . .>> አቶ መስፍን (በዲሲ የአቶ መለስን ልደት ሊከበር አይገባም ያለውን ተቃውሞ ካስተባበረው ግብረ ሀይል አስተባባሪዎች አንዱ ለህብር ከሰጡት)
<<እኔ ትግሬ አይደለሁም ወልቃይት ሰሜን ጎንደር ነኝ።ወልቃይት ትግሬ የተባለው በወያኔ ዘመን በግድ ነው።ወያኔ ሲወገድ የወልቃይት ትግሬነት ያበቃል። እዚህ የመጣሁት መለስ ዜናዊ የተወለደበት ቀን የተረገመ ነው ሊዘከር አይገባም ብዬ ነው...>> ከሰልፈኞቹ አንዱ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<<ተስፋ አልቆርጥም !>> ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቃሊቲ የጻፈው ደብዳቤን ተርጉመን ይዘናል
<<የግራዚያኒን ሐውልት መሰራት የሚደግፉት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር በቅሌት ስልጣን ለቀዋል።አሁን አዲስ ስልጣን ላይ የወጡት ግራዚያኒን የሚቃወሙ ናቸው።መታሰቢያው በቆመበት አውራጃ የተሾሙት አዲስ ሰውም ግራዚያኒን ይቃወማሉ ይሄ ለእኛ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ሐውልቱ እንዲፈርስ ወይ ስሙ እንዲቀየር መታሰቢያ እንዳይኖረው የምናደርገው ተቃውሞ ሰሚ እያገኘ ነው።የአውሮፓ ሕብረት ለላክንለት ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቶናል ...>>
አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ዓለም አቀፍ ተቃውሞ የሚያስተባብረው ግብረ ሀይል ቦርድ ም/ሰብሳቢ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
ሌሎች ቃለ መጠይቆች አሉን
ዜናዎቻችን-
– የስዬ አብርሃ ወንድምን ጨምሮ ከሙስና ጋር በተያያዝ የተጠረጠሩ 16 ከፍትኛ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ታሰሩ
- አገሪቱ በእስር አመታታ ውስጥ ከ11 ቤሌዮን ዶላር በላይ አጥታለች
- ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሙስና ተጠርጥረው ስለታሰሩት እንዳይጽፍ በደህንነቶች ማስጠንቀቂያ ተሰጠው
- ለአጼ ሀይለስላሴ ሐውልት ሊቆም ይገባል ሲሉ ፕ/ር ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎች የፈረሙበት ጥያቄ ለሀይለማሪያም ደሳለኝ ቀረበ
- ለአቶ መለስ ልደት ሊከበር አይገባም ያሉ ኢትዮጵያውያን ዋሽንግተን ኤምባሲ ፊት ለፊት ተቃውኦ አደረጉ
* ፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ ልደቱን ለማክበር ከመጡ የስርዓቱ ደጋፊዎች መካከል ነበሩ
- አቶ ሃይልማሪያም ደሳልኝ የፍትህ ሜኔስትራችውን አባረሩ እርምጃው ከአማራ ተወላጆች የዘር ማጽዳት ዘመቻ ጋር ያያዙት ወገኖች አሉ
- በኢትዮ ኬኒያ ድንበር ላይ በተቀሰቀሰ የጎሳዎች ግጭት 8 ሰዎች ሞቱ
- በቬጋስ በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ የፍሪያስ አሽከርካሪዎች ለገቨርነሩ ድምጻቸውን ለማሰማት
ሌሎችም ዜናዎች አሉን




















