Author Archive

በምእራብ ጎጃም ሁለት የወያኔ ሹሞች ተገደሉ

Friday, January 13th, 2012

በአማራ ክልል ሥር በሚገኘው የምዕራብ ጎጃም ዞን በይልማና ዴንሳ ወረዳ በአዴት ከተማ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ ሁለት የወያኔ ሹሞች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት ፖሊሶች እና ሌላ ጄሌ ባለስልጣን ከፉኛ መቁሰላቸውን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ዜና ገለጸ።

እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ባለፈው ረቡዕ ጥር 2 ቀን ለወያኔ በጄሌነት አድረው ህዝባቸውንና አገራቸውን በመበደል ላይ የሚገኙት የወረዳው ባለስልጣናት የጨረቃ ቤቶችን ለማፍረስ በተንቀሳቀሱበት ጊዜ፣ ህዝቡ ቤታችንን አታፈርሱም በማለት አጥብቆ ተቃውሞ ነበር።

መለስ ዜናዊ የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች በሃይል ለመተግበር እንዲያስችለው በየክልሉ አሰልጥኖ ባሰማራቸው አነጣጥሮ ተኳሾች የተማመኑ የወረዳው የወያኔ ጄሌ ባለስልጣናት ግን፤ ለህዝቡ ተቃውሞ የተለመደውን ንቀት በማሳየት ለተቃውሞ የተሰበሰበውን ህዝብ በፖልስ ሃይል ለማባረር በመወሰናቸው ውዝግቡ እየተካረረ ሂዶ ድንጋይ እስከመወራወር እንደደረሰ ተዘግቦአል።

የህዝብ ቁጣ ገንፍሎ ድንጋይ መወራወር መጀመሩ ይበልጥ ያበሳጫቸው የወረዳው ባለስልጣናት አጃቢ ፖልሶች ወደ ህዝብ መተኮስ በመጀመራቸው ከተሰብሳቢው ህዝብ አንዱ በያዘው ዱላ የአንድ ፖልሲ ጠመንጃ በመቀማት የወረዳውን ግብረሀይል ይመራ የነበረውን የወረዳው የኢንዱስትሪ ሀላፊ ይበሉ ደሴን ተኩሶ እንደገደለና አጠገቡ የነበረውን የከተማውን አፈ ጉባኤ እንድሪስን ክፉኛ አንዳቆሰለ ለማወቅ ተችሎአል።

የወያኔ አለቆቻቸው በከፈቱላቸው የሃብት ዘረፋና ሙስና ልባቸው ያበጠው የወረዳው ሹሞች የህዝቡን ተቃውሞ ከምንም ባለመቁጠር በገጠሙት ግብግብ ቤቱ እንዳይፈርስበት ለመከላከል በቆረጠው የአዴት ከተማ ነዋሪ ይህንን የመሰለ ቅጣት መቅመሳቸው መላውን ያካባቢውን ህዝብ እንጀት እንዳራሰና ወሬውም ወዲያው በመላው ወረዳና አካባቢው እንደተሰራጨ የግንቦት 7 ዘጋቢ አረጋግጦአል።

ጀግናው የአዴት ከተማ ነዋሪ በገዛ አገሩ ከሰራው ቤት ሊያፈናቅሉት በተላኩት የወያኔ ጄሌዎች ላይ የተቀዳጀው ይህ ድል ለሌሎች ክልሎችና ከተማ ነዋሪዎች ታላቅ አርአያነት ሊኖረው የሚችል እንደሆነ የዘገበው ዘጋቢያችን ፤ ዱላ የያዘው የአዴት ነዋሪ በዱላው ዱላ ያልነበረው ደግሞ ከፊት ለፊቱ ባገኘው የድንጋይ ናዳ በወያኔ ተላላኪዎች ላይ ባደረሰው ጉዳት ከተገደሉት 2 ሹሞች በተጨማሪ ሁለት ፖልሶችና አብረዋቸው በነበሩ ሌሎች የወረዳው የወያኔ ጄሌዎች ላይ ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ እንዳደረሰባቸው ገልጾአል።

የገዛ ወገኖቻቸውን በማፈንና በማሰቃዬት የመለስ ዜናዊን የሥልጣን እድሜ ለማራዘም በሆዳቸው ተገዝተው ወያኔን እያገለገሉ ያሉ ፖሶች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃም በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ድርሷል ተብሎአል። አብዛኞቹ ቁስለኞች በሞጣ ሆስፒታል ተወስደው እየታከሙ ሲሆን፣ ጉዳት የደረሰባቸው የወያኔ ተላላኪዎች እና ፖሊሶች ደግሞ ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተያይዞ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

በአዴት ከተማ ነዋሪዎችና በወያኔ ተላላኪዎች መካከል የተነሳውን ግጭት ለመቆጣጠር ግጭቱ በተነሳ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ የፌደራል ፖሊስ ተልኮ አካባቢውን የተቆጣጠረ እንደሚገኝና ይህ ዜና እስከተጠናከረበት የዛረው ቀን ድረስ ውጥረቱ እንዳልረገበ ታውቆአል።

አካባቢውን በመቆጣጠር ላይ ያለው የፌደራል ፖሊስ መሳሪያ ቀምተው ባለሥልጣናቱን የገደሉትን ግለሰቦች በማደን ላይ ናቸው የሚለው ዘጋቢያችን ፖሊስ በርካታ ሰዎችን እንዳሰረም አረጋግጦአል። ከሟቾቹ አንዱ የሆነው ይበሉ ደሴ በቅርቡ ከጎንች ቆለላ ቀበሌ ወደ አዴት ከተማ ተዛውሮ የመጣ ሆድ አደር የወያኔ ጀሌ ነው ተብሎአል።

የአዴት ወረዳ ህዝብ በምርጫ 97 ወቅት ሙሉ በሙሉ ቅንጅትን የመረጠ እንደሆነ ይታወሳል።

በአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች የሚያደርጉትን አድማ እንደቀጠሉ ነው

Friday, January 13th, 2012

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን ኢሳት እንደዘገበው ከሳምንት በፊት የተጀመረው የአወሊያ ኮሌጅ ተማሪዎች ተቃውሞ እየከረረ በመሄዱ የወያኔ የጸጥታ ሀይሎች በተማሪዎች ላይ ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ ተጋብተው የኮሌጁን ግቢ ዘግተው ተቀምጠዋል።

መንግሥት ተብዬው አገዛዝ ያሰማራቸው የኮሌጁ ባለሥልጣናት አለአግባብ የትምህርት ይዘቱን በመቀየራቸውና መምህራንን በማባረራቸው የተቆጡት የኮሌጁ ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን ማሰማት ከጀመሩበት ያለፈው ማክሰኞ ጥር 1 ቀን ጀምረው ምግብ እንዳላገኙና ግቢያቸውን ለመልቀቅም ፈቃደኞች እንደልሆኑ የገለጸው ኢሳት የአወልያ ኮሌጅ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በትናንትናው ዕለት ለተለያዩ የእስልምና ተከታዮች የስልክ ጥሪ በማድረግ ለዝሁር ጸሎት እንዲቀላቀሏቸው ጠይቀዋል ተብሎአል።

ኢሳት ተማሪዎቹን ለማግኘት በተደጋጋሚ ስልክ እንደደወለና የተደወለበት ስልኮች “ጥሪ አይቀበልም” የሚል መልስ ከማግኘት ውጭ ሊሳካለት እንዳልቻለ ገልጾአል።

ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም ዘጎችየ በባህልና በቋንቋ ከመለያየት አልፎ ለዘመናት አብሮ የኖረውን ሙሲልም ሃይማኖትን ከክርስቲያን ጋር ለማጋጨት እንደሚንቀሳቀስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ አንዱን ሙስሊም ከሌላው ለማጋጨት አክራሪ የሚል ታርጋ እየለጠፈ በአህባሽ እምነት አራማጆችና ዋህብይ ብሎ በሚጠራቸው ምዕመናን መካከል የጠብና የግጭት ግንብ እየገነባ መሆኑን ደጋግመን መዘገባችን ይታወሳል

ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑን ለቀምት ከተማ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርስቲ ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ ሲራጂ እና ከማል የተባሉ ሁለት የሕግ ተማሪዎች መገደላቸውን ኢሳት ዘግቦአል።

ተማሪዎቹ የተገደሉት በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት እስካሁን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ ውስጥ አዋቂዎች ”ተማሪዎቹ የሞቱት በምግብ መመረዝ ነው”ማለታቸውን ፍኖተ -ነፃነት የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።

የሟች ተማሪዎቹ የቀብር ሥነ ሥርዓት ባለፈው ማክሰኞ ጥር 1 ቀን ተፈጽሟል። ኢሳት ሰለጉዳዩ የዩኒቨርሲቲውን ሀላፊዎች ለማነጋገር በተደጋጋሚ ሞክሮ ፤ሀላፊዎቹ ስልካቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት እንዳልተሳካለት ገልጾአል።

አንድ ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባል፦ የሁለቱ ተማሪዎች መሞት ከምግብ መመረዝ ጋር የተያያዘ ነው በማለት ሁኔታውን ለማስተባበል እንደሞከሩ ገልጾ ተማሪዎቹ የሞቱት በምግብ መመረዝም ይሁን በግቢው ውስጥ ተነስቶ በነበረው ግጭት፤ አገዛዙን ከተጠያቂነት እንደማያድነው የህግ ባለሙያዎች አስተያዬታቸውን መስጠታቸውን ዘግቦአል።

ሰሞኑን በወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎችና በፌዴራል ፖሊሶች መካከል በተፈጠረ ግጭት የመማር ማስተማሩ ሂደት እንደተቋረጠ ኢሳት መዘገቡንም አክሎ ገልጾአል።

ሃሰትን እንድናገር ያስገደደኝ መንግስት ነው ማለት አያዋጣም!!!

Friday, January 6th, 2012

በዘረኛው ቡድን አማካኝነት የአገራችን የሞራል እሴቶች ሆን ተብለው እየተዋረዱ ነው።ድሮ ድሮ “እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር” የሚባል መልካም አባባል ነበረን። ዛሬ ይህን የመሰሉ አባባሎች ከል እንዲለብሱ በመደረጉ እውነትን  የሚናገር በግዞት ተይዞ የመከራ እንጀራ ይበላል የመከራ ውሃም ይጠጣል።

እንደ ንጉስ አክዓብ በዙሪያው ብዙ ሃሰተኛ መማክርትን የሰበሰበው መለስ ዜናዊ የእውነትን ድምጽ የመስማት ልምድ የለውም።ሃሰት የኑሮው መሠረት ነች። ሃሰት አገርን እንደሚሰብር መለስ ጠፍቶት አይደለም በሃስት መሰረት ላይ መቆምን የመረጠው ይልቁንስ አገሪቷን ፈጽሞ ለመሰባበር ካለው እምነት የተነሳ እንጂ። መለስ ዜናዊ የተጠራበት በእውነትና በጽድቅ ላይ የቆመችን አገር ለመፍጠር ሳይሆን በሃሰት ላይ የታነጸች መሠረቷ የሚናወጥ አገርን መፍጠር ነው። መለስ የተጠራበትን ምግባር የቆመለትን ዓላማ እያስፈጸመ በመሆኑ የእርሱ ውሸታምነት አይደንቀንም። እኛን የሚደንቀን የመለስ ዜናዊን ውሸት ለማስፈጸም የሚሸቀዳደሙ ምናምንቴ ግለሰቦች እንደ አሸን መፍላታቸው ነው።

አንዳንዶች ምን እናድርግ ተገደን ወይም ፈርተን ነው እውነት ያልሆነውን የምንናገረው ሲሉ ይደመጣሉ። እውነቱ ግን እውነት ያልሆነውን አለመናገር እምቢ ማለት ሲችሉ ሃሰትን ለመምረጥ ፈቃደኛ መሆናቸው ነው። ሃሰትን አልናገርም፤ ያላየሁትንም አልመሰክርም ለማለት ሰው መሆናቸው ብቻ ያስገድዳቸው ነበር። ሃይማኖታቸው እና ሂሊናቸውም ከእውነት ጋር ብቻ እንዲተባበሩ ይመራቸው ነበር። እነዚህ ግን የውሸትን መንገድ መርጠዋል።ውሸትን በመናገራቸው ዛሬ ሆዳቸውን ሞልተው ለማደር ችለዋል። እንዲህ ያሉቱ ያልሆነውን ሆኗል፤ ያልሰሙትን ሰምተናል፤ ያላዩትን አይተናል ባሉ ቁጥር ብዙ ንጹሃን ዜጎች ለመከራ እንደሚዳረጉ ለማወቅ የሚያንሱ አልነበሩም። ግና ምን ያደርጋል ልባቸው በእግዚአብሄር እምነት ያልጸና፤ሂሊናቸውም በሆዳቸው የተሸነፈ በመሆኑ ከሃሰተኞች ጋር መተባበርን ሙያ አድርገውታል። ይህን ነውራቸውንም “ስማርት” አካሄድ እያሉ ይሞከሻሹበታል። እነርሱ “ስማርት” አካሄድ የሚሉት ነውር ምግባራቸው በወገኖቻቸው ላይ የተፈጸመ ክህደት መሆኑን አበክረን ለማሳወቅ እንወዳለን።

በማንኛውም መንገድ በሃሰት ወገንን ለሚከሱ ቡድኖች የሃሰት መስካሪ ሁኖ መገኘትና ዜጎችን ለመከራ መዳረግ ተቀባይነት ያለው ተግባር አይደለም።ሆድን ለመሙላት ብሎ ያላዩትን እንዳዩ፤ ያልሰሙትን እንደሰሙ አድርጎ  መናገር የሃሰት አባት ለሆነው መለስ ዜናዊ ጀሌና ደጀን መሆኑን እያንዳንዱ ሃሰተኛ ሊረዳው ይገባል። መለስ ሳይፈለግ ሃያ ዓመት በሙሉ በአገራችን ጫንቃ ላይ የተጫነ ጨካኝ ገዢ ነው። ይህን ዘረኛና ዘራፊ ግለሰብ እየዋሹ ለመርዳት መሞከር እውነትን መግደል ሃሰትን ማንገስ ነው።ይህ ደግሞ ከሥነምግባር አኳያ የሰውን ክብርና ማንነት የሚያሳንስ ተግባር ብቻ ሳይሆን እውነት እራሷን ገልጻ ለፈራጅነት እድል በምታገኝበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ በወነጀለኝነት የሚያስጠይቅ ነው። በፈረሃ እግዘአብሄር ለሚኖር የእምነት ሰው ደግሞ ወንጀሉ እላይ እሰማይ ቤት ድረስ የሚዘልቅ እንደሆነ የእምነት መጽሃፍትና አባቶች ያስተምራሉ። በምድራችን ህግ ሳይቀር ነውር ከሆነው የሃሰት ምስክርነት ተግባር ውስጥ አለመዘፈቅ እየተቻለ በዚህ ወይም በዚያ ተገድጄ መለስ ዜናዊ በተቀነባበረ የሃሰት ክስ በዜጎች ላይ ለሚፈጽመው ሰቆቃ መሳሪያ ሆንኩ  ማለት በምንም መልኩ ተቀባይነት ያለውና ይቅርታ ሊያሰጥ የሚችል ተግባር አይሆንም።

ክፉውን እንድሠራ ከሚያስገድዱኝ ሃይሎች የሚያድነኝ ማን ነው? አይባልም። የእምነት ሰዎች ከሆንን ከክፉ ጋር እንዳንተባበር የሚያግደን የእግዚአብሄር መንፈስ አለ። ከእምነት ውጪ ከሆን ደግሞ ሂሊና የሚባል የስብዕናችን ምሶሶ አለ። ከዚያም አለፍ ብሎ “ሰው ምን ይለኛል የሚባል” በማህበረሰባችን ውስጥ ከትውልድ ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ “ይሉኝታ” አለ።እነዚህን ሁሉ አልፎ እውነትን ከል አልብሶ ሃስተን አስጊጦ መናገር ራሱን ሰው ነኝ ብሎ ከሚቆጥር አካል የሚጠበቅ ተግባር አይደለም።

በአገራችን የነጻነት ጎህ የሚቀድበት ዘመን ሩቅ አይደለም። አሁን የጨለመ የሚመስለው ሊነጋ ሲል እንደሆነም መገንዘብ ያስፈልጋል።እነመለስ በዚያች አገር እንዳላጋጡ የሚቆዩ አይደሉም። እጅግ ሲፈራ የነበረው ጋዳፊ ዛሬ የለም። በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ “እንደ ጋዳፊ አይቀርልህም” እያሉ ወጣቶች መጮሃቸውንም ልብ ማለት ያስፈልጋል። ሃስት እድሜው አጭር ነው። የሃሰት አባት የሆነው መለስ ዜናዊና ቡድኑም እድሜያቸው ረዥም አይደለም። እነዝህን በክፋታቸው ጸንተው ለመኖር የሚመኙትን ቡድኖች ታግሎ ከአገሪቷ ጫንቃ ላይ ማባረር የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ነው።ለእነመለስ ውሸት እምቢ ማለት ትክክለኛና የሚያስመሰግን ተግባር ነው። እነርሱ የሚፈጽሙትን ዝሪፊያ መቃወም፤ በዘረኝነት ላይ በተመሰረተ መዋቅር “ከወርቅ ተገኘን” ያሉን የአገሪቷን የፖለቲካ ሥልጣንና የኢኮኖሚ ዘርፎችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረው በገዛ ሃገራችን ባይተዋር ሲያደርጉን እምቢኝ ማለት ለራሱ ተፈጥሮአዊ ማንነት ክብር ከሚሰጥ እያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው።

ድርጅታችን ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ፤ አገራችንን ከል አልብሶ ሊያዋርዳት ቆርጦ የተነሳውን ዘረኛውን የትግራይ ገዢ ጉጅሌ በመፋለም ለሁላችንም እኩል የሆነች አገር ለመመሥረት የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው። አገራችን መለስና ቡድኑ ከፈጠሩት ሕፀፅ እንድትፀዳ ቀንና ማታ እየሰራ ነው። ሁሉንም የሚያስኬዱ መንገዶች እየሄደበት ነው። እኛ እንደ ግንቦት 7 አንግበን የተነሳነውን አላማና ግብ ለማሳካት በዘረጋናቸው መንገዶች ሁሉ ተጉዘን መለስና ግብረአበሮቹ ያሰፈኑትን ፍርሃትና ሽብር በመናድ፤ ፍትህና እኩልነት የነገሰባት፤ የሰው ልጆች በነጻነትና በደስታ የሚኖሩባት፤ የበለጸገችና ሉአላዊነቷ የተጠበቀ አገር ለመመሥረት የሚያስፈልገውን መሰዋዕትነት በቁርጠኝነት ለመክፈል ስንዘጋጅ እያንዳንዱ ዜጋ ባለበት ሆኖ አቅምና ጉልበቱ የፈቀደውን ሁሉ ለዚህ የነጻነት ትግል እገዛ ያውላል የሚል እምነት ይዘን ነው።

የግንቦት 7 ድምጽ ዝግጅት ክፍል ዘረኛው መለስ ዜናዊና ጥቂት ግብረአበሮቹ በወገኖቻችን ላይ እየፈጸሙ ያለውን ሰቆቃ ለማስቆም በብሄር፤ በቋንቋ፤ በሃይማኖት ወይም በፖለቲካ ልዩነት ሳንከፋፈል ሁላችንም በጋራ መነሳት ያለብን ጊዜው አሁን መሆኑን አብክሮ ያሳስባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!!

በጀኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ የወሰደውን አቋም በመደገፍ ግንቦት7ና ጥምረት መግለጫ አወጡ

Friday, January 6th, 2012

በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጥላ ሥር ከሌሎች የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ተባብሮ ለመታገል መወሰኑን ገሃድ ማድረጉን ተከትሎ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከትናንትና በስቲያ መግለጫ አውጥቶአል።

“የጋራ ትግል የጋራ አገር” በሚል ርዕስ ግንቦት7 ባወጣው በዚህ መግለጫ “በኢትዮጵያ የሰፈነውን ዘረኛ አምባገነን ሥርዓት አስወግደን በምትኩ የግልና የወል መብቶች የተከበሩባት፤ ፍትህና እኩልነት የሰፈኑባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በምናደርገው ትግል ውስጥ በጀኔራል ከማል ገልቹየሚመራው ኦነግ አዎንታዊ የሆነ ወሳኝ እርምጃ መውሰዱ “በጋራ ትግል የጋራ ጠላታችንን አስወግደን፤ የጋራ አገራችንን ተባብረን ለመገንባት ወደ ሚያስችለን ምዕራፍ ሊያሸጋግረን ይችላል የሚል እምነት እንዳለው ገልጾአል።

“የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በአንድ ጠንካራ አመራር ሥር ሆኖ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅምና መብት ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱን ዜጎችና ሕዝቦች በሙሉ መብቶችና ጥቅሞች በጋራ ለማስከበር በሚደረገው ትግል ተሳታፊ ቢሆን ኖሮ ሊገኝ የሚችለውን ሕዝባዊና ሃገራዊ ጥቅም ግዙፍ እንደሚሆን ማንም አይስተውም ነበር” ያለው የግንቦት7 መግለጫ፤ የኦሮሞ ምሁራን በተለይ የፖለቲካ ልሂቃኑና ኦነግ በአንድነትና በአንድ ድምጽ እየተናገሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሚያደርገው የጋራ ትግል የኦሮሞን ሕዝብ ታላቅነት የሚመጥን ሃገራዊ የኃላፊነት ሚና እንዲጫወቱ ግንቦት 7 እና በርካታ ወገኖች ሲያደርጉት የቆዩት ጥረት የተፈለገውን ውጤት በተፈለገው ጊዜ ሊያመጣ አለመቻሉ እንዳላስደሰተው አልሸሸገም።

ሁሉም የአገራችን ሃይሎች አንድ ላይ ሆነው የህዝባችንን ስቃይና መከራ እድሜ ለማሳጠር በጋራ እንዲታገሉ ዘወትር የሚወተውተው ግንቦት 7 በዚህ መግለጫው፤ ምንም እንኳ የኦሮሞ ሃይሎችን አንድ ላይ ለማምጣት እስከዛሬ የተደረጉ ጥረቶች ለጊዜው ባይሳኩም በአጭር ጊዜ ይሳካ ዘንድ ሁሉም ወገን አቅም የፈቀደለትን ሁሉ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል የሚል እምነት እንዳለው ገልጾአል።

ጥምረት ለነጻነት፤ ለፍትህና ለ እኩልነትም በበኩሉ፤ በጀኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦነግ ቡድን ከሌሎች የዲሞክራሲ ሃይሎች ጋር ተባብሮ በአገራችን ውስጥ የተንሰራፋውን ኢፍትሃዊነት ታግሎ ለማስወገድ የሚያስችለውን ይህንን ደፋር እርማጃ በመውሰዱ የተሰማውን ደስታና አድናቆት ገልጾ፤ በአገራችንንና በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃ እድሜ ለማሳጠር የሚሹ ሌሎች የኦነግ ሃይሎችም ተመሳሳይ እርምጃ ወስደው የዲሞክራሲ ትግሉን ያጠናክራሉ ብሎ እንደሚያምን አስታውቆአል።

“ሽብርተኛ”፣ “በአኬልዳምኛ” – ለእኩልነት የሚታገል አርበኛ!

Thursday, December 8th, 2011

በደል በዛ!!! ፍትህ በሌለበት አገር መኖር አልችልም!!! በዚህ ሁኔታ መኖር ኑሮ አይባልም!!! ግፍና መከራ እያየሁ መኖር አልችልም!!! እኔ ለእናንተ አርዓያ ለመሆን እሞታለሁ!!! እናንተ ታግላችሁ ነፃ ውጡ!!!

እነዚህ ነበሩ በመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ተማሮ በራሱ ላይ እሳት የለኮሰው የመምህር የኔሰው ገብሬ የመጨረሻ ቃላት። እነዚህ ቃላት በአዕምሮዎቻችን ውስጥ እየጮሁ እረፍት ነስተውናል። እውነትም ግፍና መከራን እየተቀበሉና እያዩ እንዴት መኖር ይቻላል?

የእርምጃው ግዝፈትና የመልዕክቱ ክብደት ነው የየኔሰውን ዜና እረፍት በመላው ኢትዮጵያና ከኢትዮጵያም ውጭ ከመቅጽበት እንዲሠራጭ ያደረገው። መምህር የኔሰው ገብሬ ራሱን በእሳት ማቃጠሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ የደረሰበት የምሬት ደረጃ ገላጭ ነው።  የመለስ ዜናዊ አሽከሮች መምህሩን የአዕምሮ ሕመምተኛ ለማስመሰል መሞከራቸው ዜናውን አባባሰው፤ የመለስ ዜናዊን አረመኔነት አጎላው።

ከመምህር የኔሰው በኋላም እዚያው ዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ውስጥ አንድ ሌላ እጩ መምህር በደረሰበት የአስተዳደር በደል ተማርሮ በትምህርት ቢሮ ግቢ ውስጥ በሚገኝ ዛፍ ላይ ራሱን ሰቅሎ  ለመግደል ሞክሮ የነበረ መሆኑ ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ደወል ነበር።

መምህር የኔሰው ገብሬ ወደ ሁላችንም አዕምሮ የላከውን ይህንን ጠንካራ መልዕክት ለማደብዘዝ ሲሉ ነው የመለስ ዜናዊ ተላላኪዎች “አኬልዳማ” የተሰኘውን ውስጠ-ባዶ ጯሂ ፊልም ያቀነባበሩልን።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለመለስ ዜናዊ ጆሮ ጠቢዎች የማይመች መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ለዚህ ፊልም ምላሽ መስጠት አስፈላጊ አይደለም። መለስ ዜናዊ ንቀት በወጠረው ቁጥር ለሚያሰማቸው የውሸታሙ እረኛ “ቀበሮ  መጣብኝ!!!” ጩኸቶች የኢትዮጵያ ህዝብ  ጆሮ መስጠት ካቆመ ውሎ አድሯል።

ያም ሆኖ ግን “የአኬልማ” አዘጋጆች ባልጠበቋቸው ምክንያቶች የፊልሙ መታየት ጠቀሜታ ያለው ሆኖ ተገኝቷል። እስቲ ከቻሉ ፊልሙን ደግመው በጥሞና ይመልከቱና ለሚከተሉት ጥያቄዎች ምላሽ ይስጡ።

  • ሽብርተኛ ማነው?
  • ሽብርተኛ እንዴት ያለ  ሰው ነው?

በፊልሙ “ሽብርተኛ” ተብለው የሚጠሩ ሰዎች የታወቁና የተከበሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። እነዚህ ዜጎች የሚታወቁት ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለዲሞክራሲ በመቆማቸው ነው። እነዚህ ሰዎች ፍቅርን እንጂ ጥላቻን ሲሰብኩ አልተሰሙም።

ስለዚህም “አኬልዳማ”

“ሽብርተኛ” ማለት የመለስ ዜናዊን ዘረኛ አገዛዝ በመቃወም ለሕዝቦች ነፃነትና እኩልነት የሚታገል ኢትዮጵያዊ ማለት ነው።

የሚል ትርጉም ይሰጣችኋል።

“ሽብርተኛ እንዴት ያለ ሰው ነው?” ለሚለው ጥያቄም የፊልሙ ምላሽ

“ሽብርተኛ” ቅን፣ ትሁትና ህሊናው የሚገዛው ሰው ነው።

የሚል ምላሽ ታገኛላችሁ።

ታድያ “በአኬልዳማ” ትርጉም መሠረት ሽብርተኛ መሆን የማይፈልግ ማነው? በአኬልዳማ ትርጓሜ መሠረት ሽብርተኛ መሆን የማይፈልግ ዘረኛ፣ ሆድ-አደር፣ አድርባይ፣ ብልጣ ብልጥ እና ፈሪ ነው።

የኢትዮጵያ ወጣቶች እና አዛውንቶች፤ ወንዶችና ሴቶች በዘረኞች፣ በሆድ-አደሮች፣ በአድርባዮችና ፣ በብልጣ ብልጦች እና ፈሪዎች የሚደርስባቸውን ወከባ ተቋቁመው በአኬልዳምኛ ሽብርተኛ ሆነው ራሳቸውንና አገራቸውን ነፃ ማውጣታቸው አይቀሬ ነው።

በአኬልዳምኛ “ሽብርተኛ” ማለት አገር ወዳድ፤ ነፃነት ወዳድ፤ ፍትህ  ወዳድ ማለት ነው። በአኬልዳምኛ ሽብርተኛ መሆን ክብር ነው።

ግንቦት 7 : የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በመለስ ዜናዊና ዘረኛ ቡድኑ “ሽብርተኛ” መባል የሕዝባዊነትና የአርበርኝነት ኒሻን እንደሆነ ተረድተን ትግላችንን በበለጠ ጥንካሬና ቁርጠኝነት እንድናፋፍም ጥሪ ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

(ግንቦት 7)

ኃጥዓን በሠለጠኑ ግዜ ህዝብ ያልቀሳል!!!

Thursday, December 8th, 2011

በአገራችን ውስጥ ህዝብ ማልቀሱን አላቆመም። መለስ ዜናዊ የሚመራው ዘረኛና ነውረኛ ቡድን በስልጣን ላይ ከተቆናጠጠ ወዲህ ደግሞ ሮሮው በጥልቀት ልቅሶው በስፋት ቀጥሏል። በኢትዮጵያችን ውስጥ ህዝብ ያዘነበትና የተከፋበት ዘመን እንዲህ እንደ መለስ ዜናዊ ዘመን ያለ አልታየም።የሮሮው ጥልቀት የኔሰው ገበሬን የመሰለ ዜጋ በራሱ ላይ ላምባ አርከፍክፎ እንዲቃጠል አድርጎታል። ይሄ ብዙ ዜጎችን አሳዝኗል።አስለቅሷል።

አዎን በአገራችን ላይ እግዜርን የማያውቁ ክፉ ኃጥዓን ቡድኖች ተነስተል። የእነዚህ ቡድኖች ድርጊትም ህዝብን ከዳር እስከዳር እያስለቀሰ ነው። ክፉ ድርጊታቸውም ድንበር ተሻግሮ የሩቅ ሰዎችን ጭምር እያሳዘነ ነው።

የአንድ አገር ህዝቦች ባንድነት እንዳይቆሙ ተፋቅረውና ተሳስበው እንዳይኖሩ ሆን ብሎ የሚለያዩበትን መንገድ መፍጠር ኃጢዓት ነው። ወንድምን በሃሰት አስመስክሮ በሃሰት አስፈርዶ ስቃያቸውን ማብዛት ኃጢዓት ነው። በኃይማኖት ድርጅቶች መካከል ጠብና ክርክር ተፈጥሮ ደም እንዲፈስ ማድረግ ኃጢዓት ነው። ይህን የመሰሉ ኃጢአቶች በህወት ሲፈጸሙ ከርመዋል። አሁንም እየተፈጸሙ ነው።መለስና ይህ ክፉ ዘረኛ ቡድኑ ስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ እንዲህ ያሉ ኃጢአቶች በአገራችን ላይ ሲፈጸሙ ይኖራሉ።

በዓለማችን ላይ ህዝብ የህዝብ ጠላት የሆነበት ግዜ ታይቶ አይታወቅም። መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ግን አማራ የትግራይ ህዝብ ዋነኛ ጠላት ነው ብለው ጽፈው ለትውልዱ አስቀምጠውለታል። ይህንንም እንዲመስክርላቸው ሃውልት አስቀርጸው አቁመዋል። ኦሮሞ አማራን ሊበቀል የተዘጋጀ እንደሆነ አድርገው ሲሰብኩ ሁለት አስርተ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ይህም እውነት እንደሆነ ለማስመለስ በክፉም በደጉም አብረው በኖሩ አማሮችና ኦሮሞዎች መካከል ብጥብጥ ፈጥረው የብዙ ንጹሃን ደም እንዲፈስ አድርገዋል። እንዲህ በየቦታው አብሮ በኖረ ህዝብ መካከል ጥላቻን እየሰበኩ የዜጎች ደም በከንቱ እንዲፈስ ማድረግ ኃጢዓት ነው።መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ግብራቸው ኃጢዓት ሁኖ አብሮአቸው የከረመ ስለሆነ ክፉ ምግባራቸውን እንደ ጽድቅ እየቆጠሩት በደስታ ሰክረው ይኖራሉ። አገሪቷ እንዲህ ባሉ ቡድኖች በተያዘች ወቅት በእነመለስ ዜናዊ መንገድ አለመሄድ ብጹእነት ነው።

ሌላው ህዝብን የሚያቀያይሙበትና ደም የሚያፋስሱበት መንገድ ኃይማኖት ነው።ሙስሊምና ክርስትያን አብሮ ተፋቅሮና ተከባብሮ የሚኖርባት ጥሩ አገር ኢትዮጵያ ነበረች። መለስና ዘረኛ ቡድኑ ስልጣነ መንበሩን ከተቆናጠጡ በኋላ በሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች መካከል ጠብ ተፈጥሮ ብዙ ደም ፈሷል። ህወሃት በፈጠረው መሰሪ ተንኮል ምክንያት በሃይማኖት ምክንያት ግጭት ተፈጥሮ በጎንደር፤ በወሎ፤ በአዲስ አበባ፤ በጂማና በመሳሰሉት ቦታዎች የብዙ ንጹሃን ደም ፈሷል። መለስ ዜናዊ ግን ራሱ በፈጠረው ግጭት የሚገለውን ገድሎ የሚያስረውን አስሮ ዜጎችን አስለቅሶ ወንበሩን እንደያዘ ቀጥሏል። እንዲህ በወንድማማቾች መካከል ጠብንና ክርክርን መዝራት ክፉ ኃጢዓት ነው። እግዚአብሄር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ ሰባተኛውን ግን ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች። እርሷም በወንድማማች መካከል ጠብን የሚዘራውን ነው።ምሳሌ 6 ቁጥር 19.

በገዛ አገራችን ውስጥ ወንድም ወንድሙን በሃሰት እንዲከስ፤ አንዱ በአንዱ ላይ በሃሰት እንዲመሰክር ሲደረገ የአንድ ትውልድ ዘመን ተቆጠረ።” ነገራችሁ እውነት ከሆነ እውነት ሃሰት ከሆነ ደግሞ ሃሰት ይሁን” የተባለው የታላቁ መጽሃፍ ቃል ክብር እንዳይኖረው ሁኗል። ፍትህን እንዲያስጠብቁ የተሾሙ አቃቤ ህግያን ሆን ብለው ዜጎችን በሃሰት ከሰው በሃሰት አስመስክረው የሞት ፍርድ ሲያስፈርዱ የፍትሁን ሥርዓት በኩኔኔ እየተኩት መሆኑን እንዳይገነዘቡ እዝነ ልቦናቸው በዘረኝነትና በሴሰኝነት በሽታ ደንዝዟል። እንዲህ የፍትሁን ሥርዓት ማዋረድ ለአገራችንም ለትውልዱም አይበጅም ያሉ እውነተኞችና በጽድቅ እንቁም ያሉ የሚዋረዱበት ሃሰተኞችና በክፉ ሥራዎቻቸው የበረቱ የሚሾሙባት የሰው ዘር ምድረ በዳ እንድትሆን እየተደረገች ነው።

መለስና ግብረ አበሮቹ አገራችንን አዋርዶ፤ ድንበሯን አፍርሶ፤ ምድሪቱንም ሸንሽኖ ለባእዳን አሳልፎ ሰጥቶ፤ ፍቅራችንንም አጥፍቶ ዘመኑን ሁሉ ለመኖር ምኞት አለው። እንዲህ ያልተመኘ ክፉ አምባገነን የለም።ጋዳፊ እሰከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለመረዳት አእምሮው ደንዝዞ ነበር። ሆሲኒ ሙባረክም እንዲሁ ብዙ ዘመን አእምሮው ማስተዋል ተስኖት ነበር።መለስ ዜናዊ ከእነዚህ አምባገነኖች ለመማር እምቢ ብሎ የንጹሃንን ደም እንዲሁ በከንቱ እያፈሰሰና ክፉ ሃሳብን እያፈለቀ አገራችንን ልንወጣ ወደምንቸገርበት አዘቅት ውስጥ እየነዳት ነው።

ማንም ኩነኔን የሚጸየፍና ጽድቅን የሚፈልግ መለስ ዜናዊንና ግበረ አበሮቹን በሚችለው ሁሉ መዋጋት አለበት። ግንቦት ሰባትም አገራችን የእውነትና የጽድቅ አውድማ እንድትሆን መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ለፍርድ እስከሚቀርቡ ድረስ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። እነዚህ ኃጥአኖችንም ለመገለበጥ ቆርጦ እየሰራ ነው።

ድል ለኢትዮጵያችን ይሁን !!!!

መለስ ዜናዊ የሚያሸሸው ገንዘብ መጠን 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተጋለጠ

Thursday, December 8th, 2011

በዘረኛው መለስ ዜናዊ የሚመራው የትግራይ ገዢ ጉጂሌ ቁንጮዎች እንደ አውሮጵያዊያኑ ዘመን አቆጣጠር ከ2000 እስከ 2009 ባለው የ9 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ብቻ ከ 11 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከአገር በማሸሽ በውጪ አገር ባንኮች በግል ሂሳባቸው እንዳከማቹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት መርሀግብር ሥር ጥናት ያካሄደው “ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ” የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባወጣው የቅድመ ዳሰሳ ሪፖርት አጋለጠ።

ጥናቱን ባካሄደው ተቋም መረጃ መሠረት፦ በስርቆት፣ በሙስናና በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች የተገኘ ነው የተባለው ይህ ትልቅ መጠን ያለው ገንዘብ፤ መለስ ዜናዊ እራሱ በተገኘበት አለም አቀፍ መድረክ ከዛሬ 6 ወር በፊት ይፋ ከሆነው 8 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ3 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብልጫ ያለው መሆኑም በጥናቱ ተገልጧል። ይህ 3 ቢሊዮን 260 ሚሊዮን ዶላር በአንድ አመት ጊዜ ማለትም የቀድሞው ሪፖርት ባልሸፈነው የ2009 ዓም ብቻ የተዘረፈ መሆኑ ጥናት አድራጊውን ተቋም ሳይቀር አስደንግጦአል።

በአለም በድህነት ከመጨረሻዎቹ አገሮች ተርታ ከሆነቺው አገራችን ተሰርቆ በውጪ አገር ባንኮች የተደበቀው ይህ ገንዘብ ምንጩ፤ ለልማት፤ ለድህነት ቅነሳና ለሰብአዊ እርዳታ ከምዕራባዊያን አገሮች የተገኘ እንደሆነ ሲታወቅ ባለሥልጣናቱ በጫረታ፤ በሙስናና በዘረፋ ገንዘቡን አጭበርብረው በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ሥም ከባህር ማዶ በከፈቱት ባንኮች ያሸሹት እንደሆነም ተገልጾአል።

አሥራ አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ማለት በአገራችን ገንዘብ ሲመነዘር ከ 187 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ሲታወቅ፤ ይህ ደግሞ በምድር ላይ ሊሠራ ወደሚችለው ልማት ቢተረጎም መለስ ዜናዊ ሥልጣን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት 20 አመታት 80 ቢሊዮን ብር በማውጣት 27 ሺ ኪሎሜትር መንገድ ሰርቻለሁ በማለት የሚነዛውን ጉራ ከእጥፍ በላይ በማሳደግ፤ መላውን የአገሪቱን ገጠሮች በአቅራቢያቸው ካለው ትላልቅ ከተሞች ጋር ማገናኘት የሚችል 60 ሺ ኪሎሜትር ርዝመት ያላቸው መንገዶችን መገንባት የሚችል ነበር።

ከዚህም በተጨማሪ የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ያስችል ይሆናል በሚል ስሌት ያለምንም ጥናትና ዕቅድ በህዝብ ላይ የተጫነውን የአባይ ግድብ መዋጮ 54 ቢሊዮን ብር በቀላሉ በመሸፈን በተቀረው 133 ቢሊዮን ብር ፤ ከ4 ሚሊዮን በላይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉትን ወገኖች፤ በአሁኑ ጊዜ በምግብ ለስራ ፕሮግራም የታቀፉትን ከ7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች ጎዳናዎች ላይ ወድቀው በቆሻሻ ገንዳዎች ላይ ምግብ እየለቀሙ የሚኖሩትን ዜጎች ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን እንዲችሉ ለማቋቋም እንደሚያስችል መረጃዎች ያመለክታሉ።

ህብረሰተቡን እያስመረረ ያለው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዬው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረትም እንዲሁ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንስ እንደነበር ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይህንን ጥናት ያካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ተራዲኦ አካል የሆነው ተቋም “የኢትዮጵያ ህዝብ በዝርፊያ የተነሳ ደሙ ሁሉ ተመጥቶ አልቋል፣ ከማለት አልፎ ፣ “ኢትዮጵያዊያኖች ከድህነት ለመውጣት የቱንም ያክል ቢፍጨረጨሩ፣ አሁን በሚታዬው ዝርፊያ ወደ ታች የሚፈስን ወንዝ፣ ወደ ላይ በመዋኘት ለመጨረስ ሙከራ እንደማድረግ ይቆጠራል።” ሲል የመለስ አገዛዝ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ አሰልፋታለሁ እያለ በየጊዜው የሚያውራውን ወሬ ተረት ተረት አድርጎታል።

በሙስና ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ተዘፍቀው ገንዘባቸውን በውጭ አገር ባንኮች በማስቀመጥ ላይ የሚገኙት በአብዛኛው እራሱ መለስ ዜናዊና ባለቤቱ አዜብ መስፍንን ጨምሮ ከፍተኛ ስልጣን የተቆናጠጡ ጥቂት የህወሀት ጄኔራሎችና ባለስልጣናት ናቸው።

አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በቅርቡ ባወጡት ጥናታዊ ጽሁፍ አሁን ይፋ የሆነው ተጨማሪ 3 ነጥብ 26 ቢሊዮን ዶላር ሳይካተት ባለፈው የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ይፋ የሆነው ከኢትዮጵያ የተዘረፈውን 8 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ወደ አገር ቤት ቢመለስ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ የሚዋጣውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ሸፍኖ፣ 90 የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፤ 18 ዩኒቨርሲቲዎች፣ 27 ኮሌጆች፤ 36 ዘመናዊ ሆስፒታሎች፤ 180 ጤና ጣቢያዎች፤ 6 የዘይት ፋብሪካዎች፤ 4 የስሚንቶ ፋብሪካዎች እንዲሁም አራት እጂግ ከፍተኛ የሚባሉ አግሮ ኢንደስትሪዎችን ለማቋቋም ያስችላል።

በትራንስፎርሜሽን እና እድገት ስም የመለስ አገዛዝ ባለፉት 10 አመታት ብቻ ከቻይናና ከህንድ መንግስታት ከ 25 ቢሊዮን ዶላር በላይ መበደሩን ቀደም ተብሎ መዘገቡ ይታወሳል። የመለስ ባለስልጣናት ለሚያካሂዱት ዘረፋ ፣ መጪው ትውልድ ከፍሎ የማይጨርሰው እዳ ውስጥ እየገባ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 10 ዓመታት በሙስና ወደ ውጭ ባንኮች የፈሰሰውን ገንዘብ ለመቆጣጠር ተችሎ ቢሆን ኖሮ ፣ የኢትዮጵያ የዚህ አመት በጀት 300 ቢሊዮን ብር ይደርስ እንደነበር ኢሳት ከባለሙያዎች ያገኘውን ሙያዊ ትንበያ አስደግፎ ዘግቦአል።

እንደኢሳት ዘገባ በከፍተኛ ደረጃ ዝርፊያ ከሚካሄድባቸውና የኦዲት መስሪያቤቶችን የምርመራ ውጤት ለመቀበል ፈቃደኛ ከማይሆኑት መስሪያ ቤቶች መካከል ደግሞ መከላከያ ሚኒስቴር አንዱ ነው።

በሳሞራ የኑስ የሚመራው መከላከያ ሚኒስቴር፣ ለጦር ጀኔራሎችና ለህወሀት ከፍተኛ ባለስልጣናት እቃዎችን ያለቀረጥ እንዲያስገቡ በማድረግ፣ ከፍተኛ ዝርፊያ እንደሚያካሂድ ኢሳት በቅርቡ በሰራው የዶኩመንታሪ ፊልም ማጋለጡ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ጉምሩክ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን፣ መብራት ሀይል እና ዋና ዋና የገንዘብ ምንጭ የሆኑ ተቋማትን የተቆጣጠሩት፣ የህወሀት ባለስልጣናት፣ ከመስሪያ ቤቶች ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየዘረፉ ነው እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። የወያኔ ባለሥልጣናት የለየለት ዘረፋ ላይ የተሰማሩት ከምርጫ 97 ወዲህ ሲሆን፣ አሁንም ድረስ ተጡዋጡፎ መካሄዱን የፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ዘገባ ያመልክታል።

የአለም መንግስታት በአለም እጅግ ደሀ ከሆነችው እና በምጽዋት ከሚያኖሩዋት ኢትዮጵያ፣ ይህን ያክል ገንዘብ መዘረፉን ከሰሙ በሁዋላ የሚያወጡት መግለጫ በጉጉት እየተጠበቀ ነው ተብሎአል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ቱርክ ላይ ዘረኛው መለስ ዜናዊ በተገኘበት ታላቅ አለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ያጋለጠው 8 ነጥብ አራት ቢሊዮን ዶላር ዘረፋን አስመልክቶ ወያኔ ሹሞች እስከዛሬ ቃል እልተነፈሱም።

ሰሞኑን ይፋ የተደረገው ሪፖርት አዘጋጆች ” ኢትዮጵያውያን እዬደሙ ነው በማለት” የዝሪፊያውን አስከፊነት በሪፖርታቸው ላይ አስፍረዋል።

በበረከት ስሞኦን ቁጥጥር ሥር ያለው ብአዴን በግምገማ እየተተራመሰ ነው

Thursday, December 8th, 2011

ዘረኛው መለስ ዜናዊ በበላይነት በሚመራው ህወሃት ሥር ተቀጥያ በመሆን ላላፉት 20 አመታት የህወሃትን ጸረ አማራ ፖሊሲ ሲያስተገብሩና ሲያስፈጽሙ የኖሩ በዚህም የተነሳ የገዛ ወገኖቻቸውን ህዝብ መከራና ሲቃይ ዕድሜ ሲያራዝሙ የቆዩ የብሄረ አማራ ድርጅት የክልልና የዞን አመራርና አባላት በሌላ ዙር ግምገማ እየተተራመሱ መሆኑን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከባህር ዳር ባስተላለፈው ዜና ገለጸ።

በአማራ ክልል ያሉትን አባላት በግምገማ የማተራመሱ ሥራ የተጀመረው ፤ በክልሉ ያሉ ወጣቶች ቁጥሩ እየጨመረ በመጣው የሥራ አጥነትና የኑሮ ውድነት እጅግ እየተማረሩ በአገዛዙ ላይ የሚያሰሙት ግልጽ ተቃውሞ በአደባባይ ላይ መሰማት በመጀመሩ፤ በክልሉ ታምቆ ከኖረው ጸረ ወያኔ ስሜት ጋር ተዳምሮ ባልተጠበቀ ሰዓት ህዝባዊ አመጽ ሊቀሰቅስ ይችላል ተብሎ ስለተሰጋ፤ ነባር የብአዴን አባላትን በሙስናና በዲስፒሊን ሰበብ ከሥራ አሰናብቶ ወጣቶችን ሥራ ለማስያዝ እንቅስቃሴ በመጀመሩ ነው ተብሎአል።

ከበረከት ስሞኦንና ከአዲሱ ለገሰ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው አንዳንድ የክልሉና የዞኑ ብአዴን አመራር አባላት በሙስና የተዘፈቁ መሆናቸው እየታወቀ ለበርካታ አመታት ዝም ሲባሉ እነደነበረ የዘገበው ዘጋቢያችን፤ በሙስና የአስተዳደር በደል ውስጥ እጃቸው ያልገባው በርካታ አባላቱ እንደማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በኑሮ ውድነቱ እየተሰቃዩ በመሆናቸዉ በአገዛዙ ላይ የምር ተቃውሞ እያሰሙ መምጣታቸው አገዛዙ ያልጠበቀው ሌላ እራስ ምታት እንደቀሰቀሰበት ገልጾአል።

የበርካታ አባላቶቹ ልብ መክዳት ያሳሰበው የመለስ ዜናዊ ዘረኛ ቡድን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት እምነት ሊጣልባቸው የማይችሉቱ ተባረው በምትካቸው ትምህርታቸውን ከከፍተኛ ትምህረት ተቋማት ጭምር አጠናቀው ለአመታት ሥራ አጥ ሆነው የተቀመጡት እየተመለመሉ እንዲገቡና የመንግሥት ሥራ እንዲሰጣቸው እንቅስቃሴ በመጀመሩ፤ የእርምጃው ሰለባ በሆኑት ነባር አባላትና ውሳኔውን በሚያስፈጽሙ አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተፈጥሮአል።

በምስራቅ ጎጃም የምርጫ 97 ውጤት ተጭበርብሮአል ተብሎ እንዲጣራ በተወሰነበት ወቅት የዳኝነት ሥልጣኑን በመጠቀም ፍርድቤት የሰጠውን ውሳኔ ገልብጦ ለወያኔ ታማኝነቱን ያስመሰከረውና ለበረከት ስሞኦን ቀረቤታ እንዳለው የሚነገርለት የሺጥላ እምሩ የተባለ፤ በአሁኑ ሰዓት የምስራቅ ጎጃምና የአዛ ዞን የጸረ ሙሲና ኮሚሽን ሃላፊ ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኘው የብአዴን አባል ሰሞኑን በግምገማ ስም ከሃላፊነቱ ተወግዶ በቁም እስር ላይ እንደሚገኝ ዘጋቢያችን አረጋግጦአል።

ይህ በዚህ እንዳለ ወያኔ አገር አቀፉን የመምህራን ማህበር አፍርሶ በምትኩ ታማኝ አባላቶቹ የሚመሩት ማህበር በክልል ደረጃ ካዋቀርበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ክልል መምህራን ማህበር ውስጥ በመንቀሳቀስ የክልሉ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ለመሆን የበቃውን መምህር መንግስቱ አህመዴን፣ ከስልጣን ለማስወገድ ወያኔ ዘመቻ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል።

እንደምንጮቻችን መረጃ ወያኔ መምህሩን ከስልጣኑ ለማስነሳት የፈለገው ናዝሬት ተካሂዶ በነበረው አለማቀፍ የመምህራን ጉባኤ ላይ “የመምህራንን የደሞዝ ጭማሪ፣ የደረጃ እድገትንና የማስተማርና ሀሳብን የመግለጽ መብቶች ፣ ከሁሉም በላይ መምህራን ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ እንዲሆኑ፣ በሰለማዊ ሰልፍ ሳይቀር መብታቸውን እንዲጠይቁ ሊፈቀድላቸው ይገባል” የሚሉ ሀሳቦችን በመሰንዘሩ እንደሆነና እርሱ ያቀረበው ሃሳብ ለውይይት አለመቅረቡ አበሳጭቶት ስብሰባውን ረግጦ በመውጣቱ ነው።

መምህር መንግስቱ አህመዴ የኢህአደግ አባል እንደሆነ ሲታወቅ የመምህራንን መብት መከበርንና የመማር ማስተማር ነጻነትን አስመልክቶ ከአለቆቹ ጋር እየተጋጨ በመምጣቱ በበርካታ መምህራን ዘንድ አድናቆትና ፍቅር ለማተረፍ የበቃ እንደሆነ ይነገርለታል።

በአማራ ክልል የመምህራን ፕሬዝዳንት አቋም ያልተደሰቱ የወያኔ ባለስልጣናት በተለያዩ የወረዳ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው “የማህበሩ ሊቀመንበር የግንቦት7 አባል ነው፤ መምህራን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ እና ከመንግስት ጋር እንዲጋጩ እየቀሰቀሰ ነው” በማለት ግለሰቡን ለማጥቃት ቅስቀሳ እንደጀመሩበት ተያይዞ የደረሰን ዜና አረጋግጦአል።

ሆኖም የክልሉ መምህራን ከሊቀመንበራቸው ጎን በመቆም “የማህበሩ ሊቀመንበር ከስልጣን የሚወገድ ከሆነ፣ መምህራን የራሳቸውን እርምጃ ይወስዳሉ” በማለት በማስጠንቀቃቸው ና በአቋማቸውም በመጽናታቸው አገዛዙ ያሰበውን እርማጃ ለመውሰድ እንደተደናገጠና፣ ነገር ግን ከአገር አቀፉ መምህራን ማህበርም ሆነ ከሌሎች ንኡስ ማህበራት ጋር እንዳይገናኝ እንዳደረገው ታውቆአል።

በአማራ ክልል የብአዴን አባላት መካከል በተነሳው ክፍፍል በቅርቡ መሳሪያ በመማዘዝ እስከመጋደል የደረሱ እንደነበሩና በጎንደር ከ180 በላይ አባላት በፈቃዳቸው ከአባልነት መሰናበታቸውና አብዛኛዎቹ ለድርጅቱ የነበራቸውን ታማኝነትና ታዛዝነት ትተው አገዛዙን በማማረር እንደተጠመዱ መዘገባችን ይታወሳል።

ጋዳፊ ተገደሉ፤ መለስ ይፎክራል፤ ህዝብ ተማሯል!!!

Thursday, November 3rd, 2011

ጥቅምት ወር ሲመጣ … “በግንቦት 7 1997 የሰጠነው የምርጫ ድምፃችን ይቆጠርልን!” በማለታቸው በጥቅምት 1998 ዓ.ም. በአዲስ አበባና ሌሎችም ከተሞች ጎዳናዎች በአጋዚ ጥይት በግፍ  የተገደሉ፤ ለአካል ጉዳት የተዳረጉ፤ የተደበደቡ እና የተጋዙ ወገኖቻችንን በሃዘንና በቁጭት እናስታውሳለን።

ዘንድሮ የጥቅምት 98 ሰማዕታትን በምንዘክርበት ወቅት ሶስት አዳዲስ ኩነቶች ተደራርበው መጥተዋል። እነዚህ ኩነቶች የተለያዩ ቢመስሉም በአንድነት ሲጤኑ እየሄድንበት ያለውን መንገድ የሚያሳዩ በመሆናቸው አዛምደን ልናቀርባቸው ወሰነን።

1. የሊቢያው ጋዳፊ አብዝተው ፎክረው ነበር፤ ግን ተዋርደው ተገደሉ

የሊቢያው ኮሎኔል ሙዓመር ጋዳፊ አብዮተኖችን “አይጦች፣ በረሮች፣ ሃሽሻሞች፣ ዱሪየዎች በመሆናቸው ቤት ለቤት እየሄዳችሁ፣ እያሳደዳችሁ ግደሏቸው!” ሲሉ “ይወደኛል” ለሚሉት ህዝብ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር። ሆኖም ግን ይነሳልኛል ያሉት ህዝብ ተነስቶባቸው በያዝነው ጥቅምት ወር ታሪካቸው በአሳዛኝ አጨራረስ ተደመደመ። ጋዳፊ እጎርፍ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ተያዙ፣ ቆሰሉ፣ ተጎተቱ፣ ተዋረዱ፣ ሞቱ። ልጆቻቸውም ከፊሉ ተገደሉ፤ ሌሎቹ ተሰደዱ። አልጋቸውን ይወርሳል ይባል የነበረው ሰይፍ አል-ኢስላም ሄይግ ለሚገኘው ዓለም ዓቀፍ ችሎት እጁን ለመስጠት እየተደራደረ  ነው የሚል  ወሬ እየነፈሰ ነው።

2. መለስ ዜናዊ አብዝቶ  እየፎከረ ነው

ሰሞኑን ዘረኛው መለስ ዜናዊ እንደ ጋዳፊ ሁሉ በትዕቢት፣ ድንፋታ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ የታጀበ ንግግር አድርጓል። እሱም ልክ እንደጋዳፊ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችን “ጋጠ ወጦችና ወንጀለኞች” እያለ ሁሉም ሰብስቦ ማሰር እንደሚችል ዝቷል። “የሚንጣጡ ጋዜጠኞች” አርፈው እንዲቀመጡም አስጠንቅቋል። መለስ ዜናዊ ልክ እንደ ጋዳፊ ቃላት አይመርጥም። አረንጓዴውን መጽሃፍ ከማገላበጥ በስተቀር ጋዳፊን ለመሆን የቀረው ነገር የለም።

3. የህዝብ ምሬት መገንፈል ጀምሯል

በደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በዳውሮ ዞን የሚገኘው የዋካ ከተማ ህዝብ በአስተዳደር በደል፣ በኑሮ ውድነትና በወረዳ  አከላል መነሻነት ተቃውሞ ቀስቅሷል። የዞኑ ካድሬዎች “በእያንዳንዳችሁ በር ላይ ድንኳን ይተከላል፤ ሞት ይዘራባችኋል!” እያሉ ቢያስፈራሩም ህዝቡ ግን “የመብት ጥያቄዎችን ከመጠየቅ ወደኋላ አንልም” ብሎዓል።  ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፤ ዋካ በፌደራል ፓሊስ ተወራለች።  በአርባ ምንጭም ከወራት በፊት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እስካሁን አልበረደም። በየቦታው ዜጎች እየታሰሩና እየተደበደቡ ቢሆንም ትግሉ ቀጥሏል። በመላ ሃገሪቱ ቁጭትና ምሬት በዝቷል።

የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በሃይማኖት ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ እየገባ ምዕመናንን ለማበጣበጥ የሚያደርገው ጥረት እጅግ መራር የሆነ ተቃውሞን እየፈጠረ ነው። በአሁኑ ሰዓት በተለይ በእስልምና እምነት ውስጥ የሚደረገው ጣልቃ ገብነትና ፍረጃ ሞስሊሙን ማኅበረሰብ በእጅጉ አስቆጥቷል።

ከላይ የሰፈሩት ሶስት ነገሮች – የጋዳፊ የውርደት ሞት፤ የመለስ ዜናዊ ፉከራ እና እየተጠናከረ የመጣው የህዝብ ተቃውሞ – ከጥቅምት 98 ሰማዕታት ዝክር ጋር በአንድነት ሲታዩ  የሚሰጠን አንድ አጠቃላይ ምስል አለ።

በመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ለሃያ ዓመታት ተረግጠናል፤ ተዋርደናል፤ ተገድለናል። በሰላማዊ መንገድ መሪዎቻችንን ለመምረጥ የነበረን ህልም ተከርችሞ መዘጋቱ ካረጋገጥን እነሆ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል። ሰማዕቶቻችንን የተሰውለት ዓላማ እስካሁን እግብ አለመድረሱ ይቆጨናል። ሆኖም ግን ሁኔታዎች እየተቀየሩ ነው።

ከመለስ ዜናዊ በላይ ያቅራሩና የፎከሩ አምባገነኖችም ተገርስሰዋል። ከሃያ አመታት በላይ ተቀጥቅጠው የተገዙ የቱኒዚያ፣ የግብጽና የሊቢያ ህዝቦች ዛሬ ነፃነታቸውን አረጋግጠዋል።

እኛም ዘንድ ፍንጮች እየታዩ  ነው።  “እኔ ምን አቅም አለኝ” የሚባልበት ወቅት አልፏል። የመለስ ዜናዊ የማስፈራሪያ “የፀረ-ሽብር” ህግ መሳለቂያ ሆኗል። “ለነፃነትና ለፍትህ መቆም ‘ሽብርተኛ’ የሚያስብል ከሆነ “እኔም ሽብርተኛ ነኝ” የሚሉ ድምፆች ከየአቅጣጫው እየተሰሙ ነው።  በመለስ “የፀረ-ሽብር” ህግ የተከሰሱ ዜጎች ህዝብ “የነፃነት አርበኞች” እያለ ይጠራቸዋል።

ሁላችንም አንዱዓለም አራጌዎች፣ ሁላችንም እስክንድር ነጋዎች፤ ሁላችንም ደበበ እሸቱዎች፤ ሁላችንም ውብሸት ታዬዎች፣ ሁላችንም ርዕዮት ዓለሙዎች፣ ሁላችንም ስለሺ ሀጎሶች፣ ሁላችንም በቀለ ድሪባዎች፤ ሁላችንም ኦልባና ሌሊሳዎች ነን። አሁን ሁላችንም እስረኞች ነን።  በቅርቡ ግን እስር ቤቶቻችንን ሰብረን ነፃ እንወጣለን!!!

የሚል ድምጽ ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው።

በአርባ ምንጭና በዋካ እንዳየነው የህዝባዊ እምቢተኝነት ፍንጮች እዚህም እዚያም እየታዩ ነው። ዛሬ እነዚህ  የተናጠል እርምጃዎች ቢመስሉም በአፋጣኝ መቀናጀታቸው አይቀርም። በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልግ ዜጋ ሁሉ “የኔ ተሳትፎ ኢምንት ነው” ሳይል በተቻለው ሁሉ ትግሉን የሚያግዝበት ወቅት ላይ ደርሰናል ብሎ  ግንቦት 7  የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያምናል።

ትናንሽ ነውጦች ሲጠራቀሙ ታላቁን ማዕበል አስነስተው ለመለስ ዜናዊ ትዕቢት የመጨረሻውን እልባት ይሰጣሉ ብሎ ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። ማዕበሉ እየመጣ ነው!!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

ከጋዳፊ ውድቀት መለስ ይማር!

Thursday, October 27th, 2011

ሊቢያን ለአርባ ሁለት ዓመታት ቀጥቅጠው የገዙት ኮሎኔል ጋዳፊ በትውልድ መንደራቸው ስርት ውስጥ እጎርፍ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ ተገኙ። እንደተባለው ከሆነ ከወርቅ የተሠራ ሽጉጣቸውን የመጠጣት እድል እንኳን ሳያገኙ በአልባሌ ጥይት ቆሰሉ። “አይጦች፣ በረሮዎች፣ ሃሽሻሞች፣ ዱርየዎች” እያሉ በሰደቧቸው እና የመድፍ ናዳ ሲያወርዱባቸው በነበሩ ወጣት አብዮተኞች ጫማ ተረገጡ፣ ተጎሸሙ። በጥፊ ተመቱ፤ ተዋረዱ። በመኪናም ታስረው ተጎተቱ:: እየጮሁ በአሳዛኝና በአዋራጅ ሁኔታ ህይወታቸው አለፈ።  … እጅግ አሳዛኝና አዋራጅ የሆነ አጨራረስ!!!

ጋዳፊ ስልጣንና ከስልጣን የሚገኝን ጥቅማ ጥቅም በዘመድ አዝማድ በማከፋፈላቸው በእሳቸው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ጦስም ለመላው ቤተ-ዘመዶቻቸው ደርሷል። በአሁኑ ሰዓት የቤተዘመዶቻቸው አባላት አንድም ተገድለዋል፤ አልያም ተሰደዋል።

የተባበሩት መንግሥታት እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የጋዳፊ አሟሟት እንዲመረመር በመፈለጋቸው የእስልምና ሃይማኖት በሚጠይቀው መሠረት በሞቱ ሃያ አራት ሰዓት ውስጥ አልተቀበሩም። ይህም ለቀሪ ቤተሰቦቻቸው ሌላ ሞት ነው።

“ይወደኛል!!! ህይወቱንም ለኔ ሲል አሳልፎ ይሰጣል!!!” ያሉት ህዝብ ግን በጭፈራ ላይ ነው። የጋዳፊ አስከሬን በአልባሌ ምንጣፍ ላይ ተዘርሮ ለሥጋ ማቆያነት ይውል በነበረ የብረት ሣጥን (ኮንተይነር) ውስጥ ለቀናት ተቀምጦ ለእይታ በቅቶአል። በአገዛዝ ዘመናቸው በአካል ቀርበው ሊያዩዋቸው ያልበቁ ሁሉ አስከሬናቸውን በገዛ ዓይኖቻቸው ለማየት ወረፋ ይዘው ታይተዋል። ይህ ወረፋ የተያዘው በሌላ ሃገሮች እንደሚደረገው ለተከበሩ መሪዎች የመጨረሻውን ክብር ለመክፈል የተያዘ ወረፋ አይደለም። የጋዳፊን በውርደት የተሞላ አፈጻጸም ለመመልከት እንጂ።  እንዲያውም የጋዳፊን አስከሬን በማየት ለመደሰት ሲሉ ብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው የመጡ ሰዎችም ነበሩ ተብሏል። የሚስራታ ነዋሪዎች የጋዳፊን አስከሬን በማየት ቢደሰቱም በከተማቸው ውስጥ እንዲቀበሩ ግን አልፈቀዱም።

በሌላው ዓለምም ያለው ስሜት ተመሳሳይ ነው። ምናልባት ብዙዎች ጋዳፊ ህግ ፊት ቀርበው ቢያዩዋቸው ይመርጡ ነበር ይሆናል። ያም ሆኖ  በመሞታቸው አልተከፉም። ዓለም ከተንሰራፉባት አምባነነኖች አንድ ቀንሶላታልና በጋዳፊ ሞት ተደስታለች።

የዛሬ አንድ ዓመት ሊቢያ ውስጥ የነበረው ሁኔታ ዛሬ ካለው ጋር ማስተያየት እንደምን ያለ ከባድ ነገር ነው!? የዛሬ ዓመት ጋዳፊ ሊቢያን ብቻ ሳይሆን መላውን አፍሪቃ እና መካከለኛውን ምሥራቅ የሚያርበደብዱ ብርቱ ሰው ነበሩ። የዛሬ ዓመት ሁሉ በእጃቸው፤ ሁሉ እደጃቸው ነበር። ለስብሰባው አንዱ አገር ጎራ ሲሉ ዓይኖቻቸው እሳት የሚተፉ በሚመስሉ ሆኖም ግን ቆነጃጅት በሆኑ አጃቢዎቻቸው መሃል እንደ አንባሳ ደቦል ይንጎማለሉ ነበር። የዛሬ ዓመት እንኳንስ በአካል ፊት ለፊት፤ በቴሌቪዥን እንኳን ምስላቸውን ማየት የሚያስፈራ ነበር። የዛሬ ዓመትና  ከዚያ በፊት በነበሩ አርባ ዓመታት ሁሉ የጋዳፊ ቃል የፈጣሪ ቃል ያህል ነበር።

ዛሬ ግን ያ ሁሉ ተቀይሯል። ጋዳፊ በተለይ በሊቢያውያን የተናቁ፣ የተዋረዱ፣ የተጠሉ ሰው መሆናቸው ተረጋግጦአል። በአርባ ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ “ገነባሁት” ብለው ይኮሩባቸው ከነበሩ ነገሮች ውስጥ እሳቸውን ተከትሎ ለሚመጣው ትውልድ፣ ህዝብና መንግሥት የሚተላለፍ ነገር የለም። የገነቡት ሁሉ ፈርሷል። “አል ጀምሃሪያ” ወይም “የህዝብ አስተዳደር” ይሉት የነበረው የአገዛዝ መዋቅር ተንዷል። የጋዳፊው “የአብዮታዊ ዲሞክራሲ” መጽሃፍ ማለትም “አረንጓዴው መጽሃፍ” በአደባባይ ተቃጥሏል። በውጭ አገራት በጥሬ ገንዘብና በኢንቬስትመንት መልክ ያስቀመጡት በ120 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚገመት ሃብት እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል። ጋዳፊ ያወደሱት ሁሉ ረክሷል። ጋዳፊ የሰቀሉት ባንዲራ ወርዶ፤ በእሳት ተማግዷል።

ከአርባ ሁለት ዓመታት አገዛዝ በኋላ ሊቢያ እንደገና እንደ አዲስ ሃገር ነፃነቷን አውጃለች። ሊቢያውያን ገና ብዙ ፈተናዎች ይጠብቋቸዋል፤ ቢሆንም ግን የችግሮቻቸውን ሰንኮፍ ነቅለዋል። ለዚህም ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቢያዊያንን “እንኳን ደስ ያላችሁ!” ይላል።

መለስ ዜናዊ ከጋዳፊ ውድቀት ቢማር ለራሱም፣ ለቤተሰቦቹም፣ ለዘመዶቹም ምንኛ በበጀ! መለስ ዜናዊ ሆይ! በውሸትና በጉልበት የቆመ ሥርዓት እንዲህ በጥቂት ወራት ውስጥ ይደረመሳል። በውሸት እና በጉልበት የቆመ ሥርዓት ሲደረመስ ተጠርጎ ከሚጣል ፍርሽራሽ ውጭ ቀሪ ነገር አይኖረውም። ይህንን የምንለው በንድፈ ሃሳብ ደረጃ አይደለም፤ አንተም እኛም በዓይኖቻችን እያየነው ነው።

ግንቦት 7፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊቢያ ላይ እንደረሰው ዓይነት የህይወትና የንብረት መስዋዕትነት ሳይከፈል የሥርዓት ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎ ያምናል። ለዚህ ግን የመለስ ዜናዊና ዘረኛ ቡድኑን ፈቃደኝነት ይጠይቃል። ስለሆነም በመለስ ዜናዊ ዙርያ ያላችሁ ሁሉ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ እንላለን። እብሪት የትም እንደማያደርስ ከጋዳፊ አይተነዋል።

በጋዳፊ ላይ የደረሰው ሁሉ ለመለስና ዘረኛ ቡድኑ ማስጠንቀቂያ ሊሆነው ይገባል። እኛ ነፃነታችንን እናከብራለን፤ እንወዳለን። እኛም እንደ ሊቢያውያን ለነፃነታችን የህይወት ዋጋ ጭምር ለመክፈል ዝግጁዎች ነን። ቆርጠናል፤ አምርረናል። መጨረሻችሁን ማሳመር ወይም ማበላሸት የእናንተ ምርጫ ነው።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ሁላችንም አንዱዓለም አራጌዎች ነን!!!

Thursday, September 22nd, 2011

ዛሬ የምንገኝበት እውነታን አቶ አንዱዓለም አራጌ በመለስ ዜናዊ ችሎት በተናገራቸው ሁለት ዓረፍተ ነገሮች አጠቃሎታል፤ እንዲህ በማለት።

ለመጀመርያና ለመጨረሻ ጊዜ የምለው አለኝ፤ በኢትዮጵያ የተያዘው ነገር የፖለቲካ ተቃውሞ አፈና ስለሆነ ፍርድ ቤቱ እስከ ሞት ድረስ መወሰን ይችላል፡፡ ከዚህ በኋላ ምንም ነገር አልናገርም።

በመለስ ዜናዊ ዘረኛና አፋኝ ህግ መሠረት ህጋዊና ሰላማዊ ትግል በሽብርተኝነት ያስከስሳል። አቶ አንዱዓለም እንዳለውም ለዚህ ችሎት ሃቅን መናገር ፋይዳ የለውም። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደታየው በችሎት ላይ የተቀመጡ “ዳኞች” እንደማንኛውም ሰው “ለፍ/ቤቱ” ውሳኔዎች እንግዶች ናቸው።  ስለሆነም ችሎቱ ላይ ለተቀመጡ ግዑዛን ፍጥረቶች ማብራሪያ መስጠት – ሰሙም አልሰሙም – በሚያነቡት ውሳኔ ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም። በዚሁ ሁሉ ምክንያት እችሎት ተብዬው ውስጥ መከራከር ዋጋ የለውም።

ከዚህ በፊት አንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ  ከሰው የሰማሁት ቀልድ ነው ብለው የሚከተለውን ተናግረው ነበር።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በሦስት ይከፈላል -  ታስረው የተፈቱ፣ የታሰሩ እና ወደፊት የሚታሰሩ

ከላይ የተባለው ቀልድ ነው። እውነታው ግን ሁላችንም የታሰርን መሆናችን ነው። ዛሬ ሁላችንም አንዱዓለም አራጌዎች፣ ሁላችንም እስክንድር ነጋዎች፤ ሁላችንም ደበበ እሸቱዎች፤ ሁላችንም ውብሸት ታዬዎች፣ ሁላችንም ርዕዮት ዓለሙዎች፣ ሁላችንም ስለሺ ሀጎሶች፣ ሁላችንም በቀለ ድሪባዎች፤ ሁላችንም ኦልባና ሌሊሳዎች ነን። ዛሬ እያንዳንዳችን በኢትዮጵያ እርስ ቤቶች ከሚማቅቁ ወገኖቻችን እንደ አንዱ ወይም እንደ አንዷ ነን። ሁላችንም እስረኞች ነን።

ከፊት ለፊታችን የተደቀነውም ጥያቄ እንዲህ የሚል ነው።

ለመሆኑ የታሰርንበትን እስር ቤት ሰብረን ለመውጣት ዝግጁዎች ነን? … …. ወይም በእስር ለመማቀቅ ፈቅደናል?

አሳሪዎቻችን ጥቂቶች መሆናቸውን እናውቃለን። እኛ ታሳሪዎቹ ግን ብዙሃን መሆናችንን የታወቀ ጉዳይ ነው። እንደምን ጥቂቶች ብዙሃንን አስረው እንዲንደላቀቁ እንፈቅዳለን?

የታሰርንበት ወህኒ ቤት የበሰበሰና ገፋ ቢደረግ የሚደረመስ መሆኑን እናውቃለን። የብረት አጥር ይመስሉ የነበሩ የቱኒዚያ፣ የግብጽና የሊቢያ እስር ቤቶችም ተደምሰው ህዝቦቻቸው የነፃነት አየር መተንፈስ መጀመራቸውን አይተናል። እናስ የታሰርንበትን አሮጌ እስር ቤት የመደርመስ አቅም እንዴት እናጣለን?

ቆርጠናል። ሁላችንንም እንደ አቶ አንዱዓለም አራጌ መሮናል። ነፃነት ዋጋ እንደሚያስከፍል እናውቃለን። የነፃነት ዋጋ ህይወትም ሊጨምር እንደሚችል እናውቃለን። ነፃነታችን የሚጠይቀንን ዋጋ ለመክፈል ደግሞ  ዝግጁዎች ነን።

የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ መወገድ ይኖርበታል። የመለስን አገዛዝ በቶሎ  መላቀቅ፤ አዲሲቷን ውብ ኢትዮጵያን በቶሎ ያስገኝልናል።

በ2004 ዓ.ም.  ይህ መልካም አጋጣሚ እንዲያመልጠን አንሻም። በዚህ ዓመት እስር ቤቶቻችንን ሰባብረን በመውጣት የነፃነት አየር መተንፈስ እንፈልጋለን፤ ለዚህም ተነስተናል።

አዎ !!! አሁን ሁላችንም አንዱዓለም አራጌዎች፣ ሁላችንም እስክንድር ነጋዎች፤ ሁላችንም ደበበ እሸቱዎች፤ ሁላችንም ውብሸት ታዬዎች፣ ሁላችንም ርዕዮት ዓለሙዎች፣ ሁላችንም ስለሺ ሀጎሶች፣ ሁላችንም በቀለ ድሪባዎች፤ ሁላችንም ኦልባና ሌሊሳዎች ነን። አሁን ሁላችንም እስረኞች ነን።  በቅርቡ ግን እስር ቤቶቻችንን ሰብረን ነፃ እንወጣለን!!!

ድል ለኢትዮጵያ  ህዝብ!!!

በመለስ ዜናዊ “ሽብርተኛ” መባል የአርበኝነት ሜዳሊያ ሆኗል

Friday, September 16th, 2011

ለገዛ ራስና ለሃገር ነፃነት አርበኛ መሆን በመለስ ዜናዊ እና እሱ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች “ሽብርተኛ” ያስብላል፤ ያስከስሳል፤ ያሳስራል።

አርበኝነት ክብር ነው። አርበኝነት የመልካም ዜግነት ከፍተኛው መገለጫ ነው። አርበኝነት የታላቅ ስብዕና መገለጫ ነው። በመለስ ዜናዊ እና እሱ በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች “ሽብርተኛ” መባል የአንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ወይም ኢትዮጵያዊ ድርጅት አርበኝነት ማሳያ ሆኗል። እናም በመለስ ዜናዊ “ሽብርተኛ” መባልና የሚያኮራና የሚያስደስት ነገር ሆኗል።

መለስ ዜናዊ “ሽብርተኛ” እያለ የሚጠራቸው ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦች-

  1. ዘረኝነትን የሚቃመው፣
  2. ለሰብዓዊ መብቶች ልዕልና ጥብቅና የቆሙ፣
  3. ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና እድገት ብሩህ ራዕይ ያላቸው፣
  4. የህዝብ አመኔታና ፍቅር የተቸራቸው፣ እና
  5. በሙያቸውም የተከበሩ

ዜጎች መሆናቸው በተደጋጋሚ ታይቷል። በመለስ አንደበት “ሽብርተኛ” መባል የአንድን ኢትዮጵያዊ ታላቅነት ማሳያ ሆኗል።

ወጣቶቹ ጋዜጠኛች ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት ዓለሙ በለጋ እድሜዓቸው በመለስ ዜናዊ “ሽብርተኛ” የመባልን ክብር ተቀዳጅተዋል። በመለስ አገዛዝ “ሽብርተኛ” መባላቸው ብቻውን ስለ ውብሸትና ርዕዮት ታላቅነት ብዙ ይናገራል። በርካታ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በውብሸትና ርዕዮት መንፈሳዊ ቅናት አድሮባቸዋል።

አቶ በቀለ ድሪባ፣ አቶ ኦልባና ሌሊሳ እና በርካታ ሌሎች ቆራጥ ኢትዮጵያዊያን ለመለስ ዜናዊ “የሽብርተኝነት”፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ  የአርበኝነት ኒሻን በቅተዋል።

ሰሞኑን ደግሞ አዛውንቱ አርቲስት ደበበ እሸቱ ለዚህ ታላቅ ክብር መብቃቱ መለስ ዜናዊ መስክሮለታል። ይህ ደግሞ  ለአርቲስቱ ቀድሞውኑ በነበረው ክብር ላይ ተጨማሪ ካባ ደርቦለታል።

በድርጅቶችም ቢሆን እንደዚያው ነው።

መለስና አሻንጉሊት ፓርላማው ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችን እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚመዝኑበት መለኪያ አንድ አይደለም። በመለስ ፓርላማ አንድ ኢትዮጵያዊ ድርጅት “በሽብርተኝነት” ተፈረጀ ማለት ድርጅቱ

  1. የመለስን አገዛዝ ስጋት ላይ ጥሎታል፣
  2. በርካታ ተከታዮች አሉት፣ እና
  3. ኢትዮጵያ ውስጥ ይንቀሳቀሳል

ማለት ነው።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለዚህ እውቅና በቅቷል።

ግንቦት 7 አሁን ባገኘው እውቅና ሳይኩራራ መለስ ዜናዊንና መላውን አገዛዙን ከዚህም በላይ አስጨንቆና አስገድዶ ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ ለማውረድ ተግቶ ይሰራል።

የመለስ ዜናዊ “የፀረ-ሽብርተኝነት” አዋጅ የኢትዮጵያን ህዝብ ይበልጥ ያስቆጣል፤ ይበልጥ ያነሳሳል እንጂ ማስፈራራት አይችልም።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ችጋር በቃን!!! ረሃብ በቃን!!! መለስ በቃን!!!

Thursday, July 14th, 2011

በወገኖቻችን ላይ አስከፊ ችጋር መጥቷል። ምሥራቅና ደቡብ ኢትዮጵያን በአስከፊ ሁኔታ እያጠቃ ያለው ጥልቅ መሠረት ያለው ችጋር እንጂ የአንድ ወቅት ረሃብ አይደለም:: ከአሁኑ ሰው በረሃብ መሞት መጀመሩ ከሁለትና ሶስት ወራት በኋላ የሚመጣውን አደጋ ከባድነት መገመት ይሰቀጥጣል።

  • “ከ10% በላይ ተከታታይ እድገት አሳይተናል” የሚለው ዓይን ያወጣ ውሸት፣
  • “ድህነትን ተረት እናደርጋለን” የሚለው ጉረኛ መፈክር፣
  • የመለስ ዜናዊ ጀሌዎች በፎቅና ቪላዎች መንበሽበሽ፣
  • የለም መሬቶች ለቻይናና አረብ ቱጃሮች መታደል፣
  • የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራድዮ “የህዳሴ ብስራቶች”፣
  • ወዘተ …. ወዘተ

ለህዝባችን ቁርስ፣ ምሳና እራት አልሆኑም።

መለስ ዜናዊ እንደለመደው ችግሩን በተፈጥሮ እና በለጋሾች ፈጥኖ አለመድረስ ማላከኩን ተያይዞታል።

  • ለመሆኑ እየተደጋገመ ለሚመጣ ችጋርና ረሃብ ተፈጥሮ ብቻውን በቂ ምክንያት ሆኖ ያውቃልን?
  • ለምንድነው ፍትህና ነፃነት በሰፈነባቸው አገሮች ውስጥ ዝናብ ጠፍቶ የእርሻ ምርት በከፍተኛ መጠን በሚቀንስበት ጊዜ ሰው በረሃብ የማይሞተው?
  • አስከፊ የረሃብ ዜናዎች የሚሰማባቸው አገሮች በሙሉ ነፃነት የታፈነባቸው አገሮች መሆናቸውስ የአጋጣሚ ጉዳይ ነውን?
  • ለምንድነው አንድ ዓይነት ችግር እየተደጋገመብን መላ መፈለግ ያቃተን? “ችግር የመሳካት እናት ናት” የሚለው ብሄል ምነው እኛ ዘንድ አልሰራ አለ?

ችግር የመሳካት እናት የምትሆነው በነፃነት ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ሲኖር ነው። የኢትዮጵያ ገበሬና አርብቶ አደር ነፃነቱ ተገፎ እያለ እንደምን ችጋርን መቋቋሚያ መፍትሄ መፈለግ ይችላል?

ነፃነቱን የተገፈፈ ጭንቅላት ለችግሮች መፍትሄ የማፍለቅ አቅም የለውም። እንዲህ ዓይነቱ ጭንቅላት ችግሮችን ማሸነፍ ሳይሆን ተሸናፊነትን ተቀብሎ ከችግሮች ጋር ተስማምቶና ተወዳጅቶ መኖርን ይመርጣል። ለዚህም ነው የአስተዳደር በደልና ረሃብ ምክንያትና ውጤት ብቻ ሳይሆን እጅና ጓንትም ጭምር የሆኑት። ነፃነት ያለው ህዝብ ረሃብን እንደሚያሸነፍ ተደጋግሞ የታየ ጉዳይ ነው። ለዚህም ነው ረሃብን የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት ውጤት ብቻ አድርጎ ማቅረብ እውነትን መሸፈጥ የሚሆነው። ችጋርና ረሃብ የብልሹ አስተዳደር ውጤቶች ናቸው።

በአገራችን ውስጥ የተንሰራፋው ስር የሰደደ ችጋር፣ አገዛዝ በተቀየረ ቁጥር እየባሰበት የመጣው የብልሹ አስተዳደር ውጤት ነው። አገራችንን የችጋር ቀጠና ካደረጉ የ20 ዓመታት የመለስ ዜናዊ “የሽፍታ ኢኮኖሚ” ፓሊሲ ውጤቶች መካከል አንዳንዱን ለአብነት ያህል መዘርዘር ይቻላል።

  1. በየጊዜው በሚፈነዳዱ ግጭቶች ሳቢያ አርብቶ አደሩ ተረጋግቶ ስለረዥም ጊዜ ህይወቱ ማሰብና መዘጋጀት አልቻለም። ያለፉት ሃያ አመታት በሙሉ የአርብቶ አደሩ ምኞት ነብሱን ማዳን እና የእለት ጉርስን ማግኘት ብቻ እንዲሆን ተደርጓል። ለዘላቂ ልማት የታሰበ ነገር ባለመሆኑ እነሆ የአንድ የዝናብ ወቅት የዝናብ ካፊያ መጥፋትን እንኳን መቋቋሚያ አቅም አጥቷል።
  2. በመለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመን የደን ጭፍጨፋና የመሬት መሸርሸር በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል። አገሪቷ በፍጥነት ወደ ምድረበዳነት እየተቀየረች ነው።
  3. ገበሬና መሬት ተለያይተዋል። አዳዲሶቹ ባለሃብቶች ለፈጣን ኪስ መሙላት እንጂ ለዘለቄታ የአፈር ልማት ፍላጎቱም፣ እውቀቱም የላቸውም። ለም መሬቶች በኢንቨስትመንት ስም በዘመኑ የወያኔ ጉልተኞች በመያዛቸውና እነሱ ደግሞ በተራቸው ለባዕዳን ቱዳሮች እየሸጡ በመሆኑ ባለሃገሩ ጭሰኝነት እንኳን አጥቶ ለቀን ሠራተኝነትና ልመና ተዳርጓል። በዚህም ምክንያት ገበሬው እንኳንስ ትልቁን የአየር መዛባት ትንሿንም የዋጋ ነውጥ መቋቋም እስከማይችልበት ደረጃ ተዳክሟል።
  4. በዘር በተመሰረተ ክልላዊ ድንበር ሳቢያ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው ውስጥ ተዘዋውረው መሥራትና ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከረሃብ መታደግ አልቻሉም። ከአንድ ክልል ወደሌላው ከተሰደደ የአገራችን አርሶ አደር ይልቅ ከቻይና ለመጣ ገበሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የእርሻ መሬት ማግኘት ይቀለዋል። እንዲያውም ኢትዮጵያዊው ገበሬ በዱላና በጥይት ሲባረር፤ የቻይናው ገበሬ ብድርና ማበረታቻዎች ይሰጠዋል።
  5. ፋይዳ ያለው የስነ ህዝብ ፖሊሲ ባለመኖሩ የህዝብ ብዛት አሻቅቧል። የመለስ ዜናዊ የስታትስቲክስ ባለሥልጣን ቁጥራችንን በትክክል ሊነግረን ባይፈልግም እንኳን ረሃብ መብዛታችንን እየነገረን ነው።

በአንፃሩ

  1. የወያኔ ቁንጮዎች ራሳቸውን ባለቢሊዮኖች አድርገዋል። በተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሃግብር (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) ጥናት መሠረት መለስና ሸሪኮቹ 8.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ አስወጥተዋል። ይህ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ወደ 150 ቢሊዮን ብር (ብር 150, 000, 000, 000) ይጠጋል። ይህ ገንዘብ 50, 000 የጤና ጣቢያዎችን ወይም 150, 000 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወይም 214, 285 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን መሠራት ያስችል ነበር። የመለስ ዜናዊ ባለሥልጣኖች በአገር ውስጥ ያካበቡት ሃብት ከላይ ከተጠቀሰው እጅግ በላይ ነው። የጥቂቶች ያለአገባብና ያለቅጥ መክበር እና የብዙሃኑን ህዝብ መደህየት፣ ችጋር ቋሚ ክስተት እንዲሆን አድርጓል።
  2. አገር በቀል እና ዓለም ዓቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የተራበውን ወገናችን ለማዳን በሚረባረቡት በአሁኑ ወቅት የመለስ ዜናዊ አገዛዝ 200 ታንኮችን ለመግዛት 100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጓል። ይህንን ራሱ መለስ ዜናዊ በትዕቢት አረጋግጦልናል። አንድ መቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር ከ 1.7 ቢሊዮን ብር (ብር 1, 700,000,000.00) በላይ ነው። ለታንኮቹ መግዣ በወጣው ገንዘብ 2, 428 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶችን መገንባት ይቻል ነበር። መለስ ዜናዊ ግን የውሃ ጉድጓዶችን ከመገንባት ይልቅ ታንኮችን ገዝቶ መታቀፍን መርጧል።

እነዚህና የመሳሰሉት ጭብጦችን በማንሳት አገራችን ውስጥ የሰፈነው ችጋር የመለስ ዜናዊ ፓሊሲ ታክሎበት እንጂ ተፈጥሮ ብቻውን ያመጣው ችግር አለመሆኑን መረዳት ይቻላል።

ህዝባችን በነፃነት ማሰብ፣ መመራመር፣ መፈተሽ ቢችል ኖሮ ረሃብን ማጥፊያ ብልሃት ማግኘት ባላቃተውም ነበር። ወደፊትም ቢሆን ተፈጥሮ እኛ እንደፈለግናት አትሆንም፤ መተማመኛችን የሰው ልጅ ወሰን የለሽ የፈጠራ ችሎታና ችግሮችን የመፍታት አቅም ነው። ለዚህ ደግሞ ችግሮችን በልጦ መገኘት ያስፈልጋል። የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ ሁሌ ከችግሮች በታች ሆኖ የእሱን ፈቃድ እንዲያሟላ ይፈልጋል፤ ለዚህም ነው ባርነትን ያወጀብን። መለስ ዜናዊን ከሥልጣን ሳናስወግድ ድህነትንና ረሃብ እናስወግዳለን ማለት ዘበት ነው::

በችጋር ለሚጠቃው ወገናችን መድረስ የምንችለው፤ የችጋሩ መሠረታዊ ምክንያት የሆነውን የመለስ ዜናዊን አገዛዝ አስወግደን ፍትህና ነፃነት የሰፈነባትን፤ ፈጠራ የተስፋፋባትን ኢትዮጵያን ስንገነባ ብቻ ነው። ጊዜ የለም …. ረሃብ ጊዜ አይሰጥም ። የወገኖቻቸንን ሕይወት ለመታደግ በአንድነት እንነሳ።

ችጋር አንገፈገፈን፣ ረሃብ በቃን!!! በቃ!!!!!

በቃ!!! ጋዬ!!! ይአከል!!! አሎኒ!!! ዲታህ!!! ወጣንደም!!! በስ!!! ጊዴስ!!!

የኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው ሳባ ኢንጂነሪንግ የአስራ አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር እዳ ያለበት መሆኑ ታወቀ

Thursday, June 30th, 2011

ከህወሃት የንግድ ድርጅቶች አንዱ የሆነው ሳባ ኢንጂነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ወያኔ በመንግሥት ይዞታ ሥር የነበሩትን ንብረቶች ወደ ግል ለማዛወር ባወጣው ደንብ ከአራት አመታት በፊት ከመንግሥት በርካሽ ዋጋ የገዛውን የአዲስ ጡብ ማምረቻ ፋብሪካ ክፊያ ዋጋ እስከዛሬ ባለመፈጸሙ ክስ የቀረበበት መሆኑን ለአገዛዙ ቅርበት ያለዉ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ። እንደ ሪፖርተር ዘገባ ሳባ ኢንጂነሪንግ በገባው ውል መሰረት ክፍያውን በወቅቱ ባለመክፈሉ የ11.4 ሚሊዮን ብር ባለ ዕዳ መሆኑ ታውቋል።

በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የነበሩትን አብዛኛዎቹን የንግድና የማምረቻ ተቋሞች በሽያጭ ስም ወደራሱ የግል ድርጅት ያዞታ ያዛወረው የትግራይ ጉጂሌ በ1999 ዓም አዲስ ጡብ ማምረቻ ፋብሪካ የተባለውን የልማት ድርጅት ለመሸጥ የይስሙላ ጨረታ ያወጣ ሲሆን፣ ሳባ ኢንጂነሪንግ ጨረታውን አሸንፎ ድርጅቱን በ23 ሚሊዮን ብር ለመግዛት በመስማማት ጥቅምት 29 ቀን 1999 ዓ.ም. የግዢ ውል ተፈራርሟል ተብሎ ነበር፡፡ በወቅቱ ሳባ ኢንጂነሪንግ የሽያጩን ዋጋ 35 በመቶ የሆነውን 8,052,000 ብር ብቻ ከፍሎ ፋብሪካውን እንዲረከብ ከተደረገ በኋላ ቀሪውን 14.9 ሚሊዮን ብር በ5 አመት ዉስጥ እንዲከፍል ሁኔታዎች የተመቻቹለት ቢሆንም እስከዛሬ ድረስ ምንም ሳይከፍል መቆየቱን ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል። “ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች” እንደሚባለው ህወሃቶች በርካሽ ዋጋ ወደስማቸው ያዛወሩትን የመንግሥትና የህዝብ ንብረት ላለፉት 4 አመታት ያህል ሰርተውበት ከግዢው ዋጋ በላይ ትርፍ ያጋበሱበት ቢሆንም በዕዳነት ያለባቸውን የህዝብ ገንዘብ ለመክፈል ፍቃደኛ ያለመሆናቸውን ይህ ለህዝብ ይፋ የሆነው ዘገባ አጋልጧል።

የሳባ ኢንጂነሪንግን ሽያጭና ግዢ በሚመለከት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የኩባንያው ሰራተኛ በሰጡት አስተያየት ሻጭና ገዢ የሆነው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ብቻ ሳይሆን በህዝቦቿና በአገሪቱ ሉአላዊነት ላይ የፈለገውን ደባ ሲፈጽም የነበረ ስለሆነ ከ20 አመት አገዛዝ በኋላ ሥልጣናቸው የሚገረሰስ ስለማይመስላቸው ይፈንዱ ብለው ነው እንዲህ አይነት ዜና ወጣ እንጂ ኢፌርት የሚቆጣጠራቸው ድርጅቶች ሁሉ በተመሳሳይ መንገድ መገኘታቸውን ህዝብ መቼ ያጣዋል ብለዋል ።

ኤፈርት በአሁኑ ሰዓት የአገሪቱን አብላጫ የንግድ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር ባለ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ባለሃብት ኩባንያ ሲሆን የፋሽስቱ መለስ ዜናዊ ባለቤት አዜብ መስፍን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የምትመራው ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል።

መደናበር ያመጣው “የሽብርተኝነት” ፍረጃ

Thursday, June 23rd, 2011

የመለስ ዜናዊ አሻንጉሊት ፓርላማ ሰኔ 7 ቀን 2003 ዓ.ም. ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄን (ግንቦት 7)፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን (ኦነግ) እና የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባርን (ኦብነግ) በሽብተኝነት መፈረጁ ተሰምቷል።

ለመሆኑ ፓርላማው በምን ሥልጣኑ ነው ድርጅቶችን የሚፈርጀው? እሱ ራሱ ማን ነውና?

የመለስ ዜናዊ ፓርላማ ለዚህ ፍረጃ መነሻ ያደረገው በ2001 ዓ.ም. የወጣው “የፀረ- ሽብርተኝነት አዋጅ” መሆኑም በፍረጃው ዜና ተነግሯል።

ለመሆኑ “የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ” ምንድነው?

ግንቦት 7፣ በሰኔ 4 ቀን 2001 ዓ.ም ርዕሰ አንቀጽ ቁጥር 56 ላይ እንደገለፀው “የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ” ህገ-አልባነትን ህጋዊ ያደረገ አዋጅ ነው። በዚህ ህገ-ወጥ አዋጅ መነሻነት እና ህገወጥ በሆነ ፓርላማ ውሳኔ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ድርጅቶች “ሽብርተኛ” ተብለው ተፈረጁ ማለት አስቂኝ ነው።

መለስ ዜናዊ እና ቡድኑ በሽብር ተጸንሰው፤ በሽብር ማደጋቸውን እናውቃለን። እነሱ በኢትዮጵያዊያን ደም ተረማምደው፤ ብዙ ድልድዮችን አፍርሰው እና በርካታ ባንኮችን ዘርፈው ምኒሊክ ቤተመንግሥት መድረሳቸውን እናስታውሳለን። እነዚህ እኩይ ኃይሎች ቤተመንግሥት ከገቡም በኋላ ኢትዮጵያዊያንን መግደልና መዝረፋቸውን ቀጥለዋል፤ ከኢትዮጵያ ጫንቃ እስካልወረዱ ድረስ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን መዋረድ መቀጠሉ አይቀርም።

በአንፃሩ ግንቦት 7፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላማዊ ምርጫ መሪዎቹን እንዲመርጥ ቀስቅሰው የግንቦት 97ን ታሪካዊ ድል እንዲመጣ ጥረት ባደረጉ ሰዎች የተጀመረ ንቅናቄ መሆኑ የታወቀ ነው። ግንቦት 7፣ በምርጫ 97 ህዝብ መለስንና ፓርቲውን ባለመምረጡ መጨፍጨፉ፣ መጋዙና መታሰሩ ሳያንስ ለወደፊቱም የሰላማዊ ምርጫ በር ተከርችሞ የተዘጋ በመሆኑ ምክንያት የተፈጠረ ድርጅት ነው። ግንቦት 7፣ የግንቦት 7 ቀን 1997 የተስፋ ብርሃን እና ከማግስቱ ጀምሮ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያጠላው ጭለማ የፈጠሩት መስተጋብር ውጤት ነው።

ግንቦት 7፣ ካልተገደደ በስተቀር ጉልበትን የመጠቀም ፍላጎት የሌለው፤ ከጽንሱ ጀምሮ ሰላማዊና ስልጡን (civic) ድርጅት ነው። ኃይል ለመጠቀም ቢገደድ እንኳን ለሰላማዊ ዜጎች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጥ ህዝባዊ ድርጅት ነው። እስከዛሬም ሰላማዊ ዜጎችን አደጋ ላይ የጣለ እርምጃ ወስዶ አያውቅም፤ ወደፊትም አያደርግም። እንዲህ ዓይነቱን ለህግ ልዕልና የቆመ ሰላምተኛና ህዝባዊ ድርጅትን “ሽብርተኛ” ተብሎ በመለስ ዜናዊና ፓርላማው መፈረጁ በራሱ ምፀት ነው።

ይሁን እንጂ ፍረጃው ከማስገረም ባለፈ በግንቦት 7 ሥራ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ለውጥ የለም። ግንቦት 7 ከሌሎች የኢትዮጵያ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ህዝብን የሥልጣን ባለቤት የማድረግ ትግሉን ይገፋበታል።

ከሽብርተኝነት ፍረጃው ጋር ሰሞኑን እየታዘብናቸው ያሉት የመለስ ዜናዊ መራወጦች በርካታ ናቸው።

ለምሳሌ

  1. ረሃብ ከተሜውን ሳይቀር እያጠቃ ባለበት በአሁኑ ወቅት በ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር 200 ታንኮች ከዩክሬን ተገዝተዋል።
  2. የህዝባችንን ብሄራዊ ስሜት በመቀስቀስ አባይ አዲስ የማዘናጊያና የዘረፋ ፕሮጀክት ሆኗል።
  3. ከፍተኛ ባለሥልጣኖችን በመላክ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያንን መጎነታተል ተጀምሯል።
  4. ሃብታም ነጋዴዎችንና አርቲስቶችን ለማማለል የሚደረገው ስብሰባና ሩጫ ደርቷል።
  5. ድሃውን ነጋዴ ሙሉ በሙሉ ከገበያ ለማስወጣት የሚያስችሉ የንግድ ህጎችና ደንቦች ተረቀው ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ ለማዋል ዝግጁ ሆነዋል።

በጥንቃቄ ያስተዋለ ሰው እነዚህ ሁሉ የተበታተኑ ክስተቶች አለመሆናቸውን ይረዳል። ሁሉም በአንድነት ሲጤኑ መለስ ዜናዊ በብርቱ ስጋት ውስጥ ያለ መሆኑን ያስረዳሉ። መለስን እያቅበጠበው ያለው ደግሞ የሁኔታዎች መሳከር ነው።

በአንድ በኩል መለስ የተሟሟቀ ገበያ ውስጥ ነው። ለም መሬቶቻችንን ለባዕዳን ቱጃሮች በመቸብቸብ በመቶ ቢሊዮኖች ብር የሚቆጠር ሃብት ማሸሽ ችሏል። ይህንን የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሃግብር (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) አረጋግጧል፤ መለስም ፊት ለፊት ሲነገረው አላስተባበለም። ይህን የጦፈ ቢዝነስ መተው አይፈልግም። ስልጣንና ሃብት ጥሞታል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያዊያን በአገዛዙ ተንገሽግሸዋል። በየቦታው የሚሰማው ቃል “በቃ!” የሚል ነው። ኢትዮጵያዊያን “ኑሮ መሮናል፤ አገዛዝ አንገሽግሾናል። እኛም እንደ ጎረቤቶቻችን አምርረን እንነሳ!” እያሉ ነው። የስልጣኑ ማብቂያ መዳረሱ ተሰምቶታል።

ወዳጆቹ የሆኑት ዩ.ኤን.ዲ.ፒ፣ የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ. ኤም. ኤፍ) ውሸቱን ከመጠራጠር አልፈው ማጋለጥ ጀምረዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ሚስ ክሊንተን አዲስ አበባ ውስጥ የተናገሩትም እረፍት የሚነሳው ነገር ነው። ሚስ ክሊተን የመብራት መጥፋት እንኳን ሳይበግራቸው ፊት ለፊት “የአፍሪካ አምባገነኖች መሄጃችሁ ደርሷል” ብለዋቸዋል።

እነዚህን ኩነቶች ሁሉ በአንድ ላይ ስናይ ነው የአሻንጉሊቱ ፓርላማ ውሳኔ እንድምታ የሚገባን። መለስ ስልጣን ጥሞታል፤ ወዳጁም ጠላቱም እየነገረው ያለው ግን በጊዜ እንዲለቅ ነው። ነብሱ ተጨንቃለች።

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው። በጣር ላይ ያለው መለስና የዘረፋ ጓዶቹ በተለያዩ ስሞች ሊጠሩን ይችላሉ፤ እኛ ግን ከዓላማችን ዝንፍ አንልም። የመለስን ዜናዊ አገዛዝ ማብቃትና በምትኩም የህዝብ የሥልጣን ባለቤትነትን በዓይኖቻችን ሳናይ እረፍት አይኖረንም። እኛ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ “በቃን!” ብለናል፤ አንተም አንቺም “እኔም በቃኝ!” ብለህ ተነስ፤ ተነሺ።

በሁሉም ቋንቋዎቻችን መፈክራችን አንድ ነው።

በቃ!!! ጋዬ!!! ይአከል!!! አሎኒ!!! ዲታህ!!! ወጣንደም!!! በስ!!! ጊዴስ!!!

ሃገራቸውን ጥለው በሚሰደዱ ጋዜጠኞች ቁጥር ኢትዮጵያ የቀዳሚነቱን ስፍራ ያዘች

Thursday, June 23rd, 2011

በአህጽሮተ ቃሉ ሲፒጄ በመባል የሚጠራው አለም አቀፉ የጋዜጠኛች መብት ተንከባካቢ ድርጅት በትናንትናው እለት ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንደገለጸው እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከ2001 እስከ 2011 ባለው ጊዜ ውስጥ በዓለማችን አገራቸውን ጥለው ወደ ሌሎች አገሮች በሚሰደዱ ጋዜጠኛች ቁጥር ኢትዮጵያ አንደኛ መሆኗን አስታወቀ።

ስፒጄ የጋዜጠኞችን ስደት አስመልክቶ አገሮችን በደረጃ ሲያስቀምጥ ከኢትዮጵያ 79፤ ከሶልማሊያ 68 ፤ከኢራን 66 ፤ ከኢራቅ 55 ፤ከዚምባብዌ 49፤ ከኤርትራ 47፤ ከሲሪላንካ 25፤ ከኩባ 25 ፤ከኮሎምቢያ 20፤ ከሃይቲ 18፤ ከሩዋንዳ 18 ፤ እንዲሁም ከኡዝቤክስታን 18 ጋዜጠኞች ባለፉት 10 ዓመታት አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን አስታዉቋል።

ሲፒጄ ባወጣው በዚሁ ሪፖርቱ በተለያዩ አገሮች ለጋዜጠኞች ለስደት መዳረግ ዋነ ዋናዎቹ ምክንያቶች የሃይል ጥቃት፤ እስርና እንግልት መሆናቸውን አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም ሲል ሲፒጄ በ2007 ባወጣው መግለጫ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቁጥር አንድ የሚዲያ ጠላት እንደሆነ መግለጹ የሚታወስ ነዉ። ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ የአሜሪካና የጀርምን ድምጽ ሬድዮ ጣቢያዎችን፤ የግንቦት ሰባትንና የሌሎች ተቃዋሚ ደርጅት ሬድዮ ጣቢያዎችንና አንዲሁም በቅርቡ የተቋቋመዉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዢን የአየር ላይ ሞገዶችን በከፍተኛ ዋጋ ከቻይና በተገዛ መሳሪያ እንደሚያፍን ታዉቋል።

ከየመን ህዝባዊ አብዮት ምን እንማራለን?

Thursday, June 9th, 2011

ህዝባዊ አብዮት ከተቀጣጠለባቸው የአረብ አገራት ሁሉ በመልክዓ ምድር አቀማመጥ የየመንን ያህል የሚቀርበን የለም። የኢትዮጵያና የየመን መመሳሰል በመልክዓ ምድር አቀማመጥ ብቻ አይደለም፤ መመሳሰላችን በብዙ ጉዳዮች ነው።

  1. የመን የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የነገሰባት አገር ናት፤ ወይም ነበረች። አሊ አብደላ ሳልህ ለሰላሳ ሶስት ዓመታት ገዝቷታል። ኢትዮጵያም የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ የነገሰባት አገር ናት። መለስ ዜናዊ ለሃያ ዓመታት ገዝቷታል።
  2. የመን በበርካታ ዘውጌ ማኅበረሰቦች (ብሄር፣ ብሄረሰቦች) የተገነባች አገር ስትሆን አሊ አደብላ ሳልህ በተግባር የየመንን ህዝብ እርስ በርሱ እያጋጨና እያስታረቀ ሲገዛ፤ በወሬ ደግሞ ተበታትና የነበረችውን የመን አገናኝቶና አዋድዶ ያቆያት አስመልሎ ሲሰብክ ኖሯል። የኛው ጉድም ኢትዮጵያን ከመበታተን ያዳንናት እኔና ጓደኞቼ ነን ማለቱ ሳያንሰው ለወደፊቱም እኛ ከሌለንም መበታተኗ አይቀሬ ነው እያለ ያስፈራራል።
  3. የመን ከአረብ አገሮች ሁሉ በድህነት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ያለች አገር ናት። ኢትዮጵያም በድህነት ከአፍሪቃ – በዚህም ምክንያት ከዓለም – አገሮች የመጨረሻ ደረጃ ላይ ያለች ናት።የአሊ አብደላ ሳልህ አገዛዝ “ስለፈጣን እድገት” ሲናገር የቆየ ቢሆንም የመን ዜጎቿ በመሃይነትና በበሽታዎች የተጎዱባት እና ኋላ ቀር ባህል የሰፈነባት አገር ናት። የኛዋ ኢትዮጵያዋም የፈጣን እድገት መዝሙር የሚዘመርባት ቢሆንም ዜጎቿ ከየመን በባሰ ሁኔታ በመሃይምነትና በበሽታ እየማቀቁ ያሉባት አገር ናት።
  4. “የመን የአሊ አብድላ ሳሊህ የከሰረ የቤተሰብ ቢዝነስ ነች፤ መንግስቷም ከወደቁ መንግሥታት ተርታ ነው” ተብሏል። ኢትዮጵያም የመለስ ዜናዊና ቡድኑ የግል ሃብት ሆናለች። በመለስ እጅ ያለችው ኢትዮጵያዊ እየተመዘበረች፤ ለአረቦችና ህንዶች እየተሸጠች ከስራለች፤ እየከሰረችም ነው። መለስ የሚጫወትባት ኢትዮጵያችንም ከወደቁ መንግሥታት ተርታ ገብታለች።
  5. የመን ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚው እጅግ በጣም አነስተኛ በመሆኑ በዘመናዊ የመገኛና ዘዴዎች ለአመጽ መጠራራት የማይሞከር እንደሆነ ሲነገር ነበር። በዚህም ምክንያት የአሊ አብደላ ሳልህ ካድሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ገለልተኛ የሆኑ ምሁራንም ሳይቀሩ የቱኒዚያና የግብጹ አይነቱ አብዮት የመን ውስጥ የማይሞከር ነው ሲሉ ነበር። ኢትዮጵያም ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚው ቁጥር እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ተመሳሳይ ህዝባዊ አብዮት የመቀስቀሱ እድል አሳንሰው የሚያዩ በርካቶች ናቸው።
  6. አሊ አብደላ ሳልህ ራሱን የፀረ-ሽብርተኝነት ትግል አጋር አድርጎ በማቅረብ የአሜሪካና የአውሮፓ መንግሥታትን ድጋፍ በሰፊው ሲያገኝ ቆይቷል። የኛው መለስም የአካባቢው ፀረ-ሽብርተኝነት ትግል አጋር ሆኖ በመቅረብ እያጭበረበረ ነው።
  7. ኣሊ ኣብደላ ሳልህ በሰላዮቹና አልሞ ተኳሽ ወታደሮቹ ብዛት ህዝብን በማስፈራራቱ አንዳችም የተቃውሞ እንቅስቃሴ የማይታሰብ መሆኑ ሲወራ ነበር። የኛው መለስም ጆሮጠቢዎችና አጋዚዎችን በብዛት በማሰማራቱ፤ ህዝብም እርስ በርሱ እንዳይተማመን በማድረጉ አብዮት የማይታሰብ ነው የሚሉ አልጠፉም።
  8. የመናዊያን “ጫት አፋቸውን ስለሞላው የተቃውሞ ጩከት ማሰማት አይችሉም” ተብሎ ተቀልዶባቸው ነበር። በኢትዮጵያ ህዝብና ወጣት የትግል ሞራል ላይ የሚሳለቁም ብዙዎች ናቸው።

በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ባለችው የመን ውስጥ ህዝባዊ አብዮት ተቀሰቀሰ። የመናዊያን እንደ ቱኒዚያና ግብጽ የዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን ትኩረት አልሳቡም። አልጀዚራም ቢሆን የየመንን አብዮት እንደግብጽ በተከታታይ አልዘገበም። ይህ ሁሉ ግን የመናዊያንን ተስፋ አላስቆረጠም።

የመናዊያን ከአራት ወራት በላይ የአሊ አብደላ ሳልህን አገዛዝ ተጋፈጡት። በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የህይወትና የአካል መስዋዕትነት ከፍለው እነሆ ዛሬ ለድል ተቃርበዋል።

“እኔ ከሌለሁ አገሪቷ ትበተናለች፤ ስለዚህም በጭራሽ ስልጣኔን አልለቅም” ያለው አሊ አብደላ ሳልህ በባሩድ ፊቱና ጀርባው ተለብልቦ ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል። ለብዙዎች የአሊ አብደላ ሳልህ የስልጣን ዘመን አብቅቷል። ከቁስሉ አገግሞ ወደ የመን ቢመለስ እንኳን የምትጠብቀው እሱ የማያውቃት የመን ናት።

ለመሆኑ እኛ ከየመን ምን እንማራለን?

  • ድህነታችን፣ ኋላቀርነታችን፣ የበርካታ ዘውጌ ማኅበረሰቦች ውጤት መሆናችን ህዝባዊ አብዮቱን ያከብዱት እንደሆነ እንጂ እንዳይነሳ እንደማያደርጉት ከየመን መማር እንችላለን።
  • በጽናት የታገለ ህዝብ ድልን ሳይቀዳጅ ቤቱ እንደማይመለስ ከየመን እንማራለን።
  • በህዝብ መጠላታቸው ፊት ለፊት ሲነገራቸው ለማይገባቸው ለእንደ አሊ አብደላ ሳልህ ዓይነቱ አምባገነኖች ከሰላማዊው ትግል ጎን የጡንቻ አስፈላጊ የቱን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ከየመን እንማራለን።

ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የየመን የነፃነት ታጋዮች ላደረጉት ተጋድሎ ያለውን አድናቆት እየገለጸ ለተቀጃጁት ድል የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላልፋል። ኮርተንባችኋል። በቅርቡ የተሟላ ድል እንደምትቀዳጁ ባለሙሉ ተስፋ ነን።

እኛም በቅርቡ የናንተን መንገድ እንከተላለን። አምባነንነት፣ ረሃብና እርዛት፣ ግፍ እኛም እንደናንተው መሮናል፤ አንገፍግፎናል። እንደናንተው እኛም “በቃ!” ብለናል።

በቃ!!! ጋዬ!!! ይአከል!!! አሎኒ!!! ዲታህ!!! ወጣንደም!!! በስ!!! ጊዴስ!!!

ሃያ የክህደት፣ የውርደት፣ የዘረኛነትና የዘራፊነት አመታት

Thursday, May 26th, 2011

ወያኔ የሚያከብረውን 20ኛ የድል አመት አስመልክቶ ከግንቦት 7 የተሰጠ መግለጫ

ሃያ የክህደት፣ የውርደት፣ የዘረኛነትና  የዘራፊነት አመታት

                                               ግንቦት 18 2003 ዓ.ም

 በደርግና በመንግስቱ ሃይለማሪያም ቦታ ወያኔና መለስ ዜናዊ ከተተኩ 20 አመት ሆነው። ሰሞኑን መለስ ዜናዊ ሃያኛውን የንግስና በአል ለማክበር ከፍተኛ  በጀት መድቦ እየተራወጠ ነው። የፈረደበት ህዝብም በአሉን እንዲያጅብ በየቀበሌውና በየመስመሪያ ቤቱ ቀጭን ትእዛዝ ደርሶታል። ያው መንግስቱና ኢሰፓ ሲያደርጉ እንደነበረው ማለት ነው። ዛሬም እንደ ትናንቱ ህዝብ የሃገሩንና የራሱን አራጆቹ ድግስ እንዲያሞቅና ለዲስኩራቸው እንዲያጨበጨብ እየተደረገ ያለው ሠራተኛው በደሞዙ፤ ሌላው ከቀበሌ በሚያገኘው ስኳር፣ ዘይትና ሌሎችም አግልግሎት በኩል በሚመጣበት ማስፈራሪያ ነው። ክቅርብ ጊዜ  ወዲህ የሃገሪቱ ህዝብ በማንኛውም የህይወት ዘርፍ ያለመለስ ዜናዊ ካድሬዎቹ ሳንባ መተንፈስ እንዳይችል የሚያደረገው ሸምቀቆ እየጠበቀ ሄዷል። ብቸኛው ቀጣሪ፤ ስኳርና ዘይት አከፋፋይ፤ የእድገትና የከፍተኛ ትምርት እድል ደልዳይ፤ ፍትህንና የባንክ ብድርን ፈቃጅ ወያኔ ብቻ በሆነበት ሃገር ህዝብ  ምርጫው ሰልፍ መውጣት፤ ለወያኔ ገንዘብ ማዋጣት፤ ወያኔ የሚያዘውን ሌላም ትእዛዘ መፈጸም ሆኗል። ይህ ግን እውነታውን አይደብቀውም። ከወያኔ የሻምፓኝ፣ የሽቶ፣ የከበሮ፣ የእልልታና የፉከራ ድግስ ጀርባ ያለው የስርአቱ አስከፊ ገጽታና ክርፋት መሸፋፈኛዎቹን ሰብሮ  በአይን መታየቱ በአፍንጫ መሸተቱ አልቀረም።

 ያለፉት ሃያ አመታት ለኢትዮጵያ እንደምን ያሉ አመታት ነበሩ?

  1. ሃያ የወያኔ አመታት ለመጀመሪያ ግዜ በሃገራችን ታሪክ ከአንድ ዘር ብቻ የተሰባሰቡ ጥቂት ግለሰቦች የሃገሪቱን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ስልጣን፤  የሃገሪቱን ሃብት፣ መሬቱንና ማዕድኑ፤ የሃገር ውስጥና የወጭ ሃገር ንግዱን፤ የኮንስትራክሽን፣ የባንክ፣ የኢንሹራንስ፣ የትራንስፖርት፣ የማምረቻና  ማከፋፈያ ስራውን የተቆጣጠሩበት፤ እፍረትና ይሉኝት የለሸ ነውረኛና አደገኛ ስራ የተሰራባቸው አመታት ናቸው።
  2. ያለፉት 20 አመታት ሃገሪቱ በጥቂት ለዘረፋ ስልጣን በያዙ ዘረኞችና አፋኞች እጅ በመወደቋ ታላቅ የተፈጥሮና የሰው ሃብቷንና እንዲሁም ባለፈው 20 አመታት የተገኘው አንጻራዊ ስላም ተጠቅም ድህነትን ረሃብን ስደትን ሀገራዊ ውርደትን ማስቆም የምትችልበትን እጅግ ታላቅ እድል ያባከነችባቸው አመታት ናቸው።
  3. ያለፉት 20 አመታት፣ በየትኛዎቹም ኢትዮጵያ መንግስታዊ ስርአቶች ከቶ ተደርገው የማይታወቁ፤ በሃገራችንና በህዝቧ ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ሃገራዊ ክህደቶች የተፈጸሙባቸው አመታት ናቸው። ኢትዮጵያችን ከዚህች ሃገር ውስጥ በወጡ ልጆቿ ሳይሆን ለሃገሪቱና ለህዝቧ ከፍተኛ ጥላቻ ባላቸው፤ ሃገሪቱንና ህዝቧን መበቀል የግድ የሆነባቸው፤ ቂም አዝለው ስልጣን በያዙ የውጭ ወራሪዎች እጅ የወደቀች እስክትመስል ሃገራዊና ህዝባዊ ክብሯ አጥታ የተዋረደችባቸው አመታት ናቸው።
  4. ያለፉት 20 አመታት በየትኛውም ዘመን ስልጣን ላይ የወጡ ገዥዎች አስበውትና  አድርገውት በማያውቁት ደረጃ የሃገር ሃብትና ቅርስ ስልጣን ላይ ባሉ ጥቂት የትግራይ ገዥ ጉጅሌ አባላት እየተዘረፈ በባእድ ሃገራት የተከማቸበት አመታት ናቸው። እኝህ አመታት የዘረኛው ገዥ ጉጅሌ  አባላት ለዘረፋ እንዲያመቻቸው ያስጠጓቸው የውጭ ሃገራት ዜጎች በሃገራችን ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ  የህዝቡን ለም መሬት፣ ወርቅ ሌላም ማእድን እንዳሻቸው እየዘረፉና የሃገሪቱን ህዝብ ከባርነት ስርአት ባለተናነሰ የጌታና የሎሌ ግንኙነት እንዳሻቸው እያዋረዱ እንዲያሰሩ ስድ የተለቀቁባቸው አመታት ናቸው።
  5. ያለፉት 20 አመታት ዳኝነትና ፍትህ የሚባል ነገር ጭራሽኑ ካገር የጠፋበት፤ ዜጎችና ህዝቦች ተቆጪ በሌላቸው በዘርና በጥቅም በተሳሰሩ የገዢው ጉጅሌ የጦር አዛዦች፣ የደህንነት አባላትና ካድሬዎች እንዳሻቸው የሚረሸኑበት፤ ህዝብ ለሰቆቃና ለእስራት የተዳረገበት፤ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ ሳይቀር የሚሰማውን መናገር እንዳይችል  የስጋትና የፍርሃት ቀንበር ውስጥ የወደቀችባቸው፤ እንዲሁም በዘር ማጥፋትና በሰው ልጆች ላይ እንደተፈጸሙ ተደርገው የሚታዩና በአለምአቀፋዊ ወንጀለኛነት የሚያስጠይቁ ታላላቅ ወንጀሎች በመላው ሃገሪቱ ህዝብ ላይ የተፈጸሙባቸው አመታት ናቸው።

 በጥቅሉ ያለፉት 20 የወያኔ የግዛት አመታት የኢትዮጵያን ውርደት፤ የህዝቧን የድህነት፣ የባርነትና  የሰቆቃ  ህይወት በማየት በሚደሰቱ ጸረ ሃገርና ህዝብ ሃይሎች እጅ ወድቃ አበሳዋን ያየችባቸው አመታት ናቸው።  ግንቦት 20 የተባለውን የዛሬውን የወያኔዎች በአል የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስበው፣ በሃዘን በቁጭትና በንዴት ነው። የወያኔ እድሜ እንዲረዝም ሳይሆን እንዲያጥር በመመኘት፣ በመጸለይ፣ በመደራጀትና በመታገል ነው። የግንቦት7  የፍትህ የነጻነትና  የዴሞክራሲ ንቅናቄ ስሜትም ከህዝብ ስሜት የተለያ አይደለም። ለዚህም ነው በወያኔ የፈንጠዝያ እለት ውደቀታቸው የማይቀር መሆኑን የምናረዳቸው።

 ውድመት ለዘረኛውና ለዘራፊው ጸረ-ሃገርና ጸረ -ህዝብ ጉጅሌ

እርገት ለኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት የእኩልነት የፍትህና የአንድነት ፍላጎት     

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ለ4ኛ ጊዜ የተከራየው ሳታላይት ጃም ተደረገ

Thursday, April 21st, 2011

በዘረኛውና አፋኙ የወያኔ አገዛዝ ተደጋጋሚ አፈና እየተካሄደበት ያለው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ኢሳት ለ4ኛ ጊዜ የሳታላይት ጣቢያ ለመቀየር የተገደደ ቢሆንም በአዲሱ የሳታላይት በአዲሱ ሳታላይት ላይ የተጀመረው ስርጭት ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ ከፍተኛ ጉልበት ባለው የሳታላይት ሞገድ መጥለፊያ መመታቱን ኢሳት አስታወቀ።

 የመለስ ዜናዊ አፋኝ አገዛዝ የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት ለመገደብ በሚያካሁደው አምባገነናዊ እርምጃ በአገር ውስጥ የሚታተሙት ነጻ ጋዜጦችን ፍቃድ በመከልከል፤ ፍቃድ ያገኙትን ደግሞ በማስፈራራት፤ በማወክና የህትመት ዋጋ በመጨመር መንቀሳቀስ እንዳይችሉ እያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከአገር ውጪ ወደ ኢትዮጵያና አካባቢው በሬዲዮና ቴሌቪዥን የሚደረጉ ስርጭቶችን በሙሉ ለማፈን ከፍተኛ የሆነ የአገሪቱን ሃብት እያፈሰሰ እንደሚገኝ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ሳይቀር ስለሰብዓዊ መብት አያያዝ ይፋ በሚያደርግበት አመታዊ ሪፖርቱ ገልጾአል::

ህዝባችን ምንም አይነት ነጻ የሆነ መረጃ እንዳያገኝ እና ከወያኔ የዜና ማሰራጫዎች የሚተላለፉትን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ብቻ እየተጋተ እንዲኖር ለማድረግ ከደሃው ህዝባችን ጉሮሮ በተነጠቀ ገንዘብ ነጻና ገለልተኛ የሆነ መረጃ የሚያስተላልፉትን መገናኛ ብዙሃን የሚያፍን መሳሪያ በውድ ዋጋ ከቻይና እየተገዛ አገልግሎት ላይ መዋል በጀመረበት በዚህን ሰዓት ቁጥሩ ከ3 ሚሊዮን በላይ የሆነው የአገሪቱ ዜጋ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ተገልጾ በአገዛዙ በኩል ለውጪ መንግስታት የልመና ጥሪ ቀርቦአል። ወያኔ በአገሪቱ ውስጥ አስፍኛለሁ ስለሚለው እና በየዕለቱ ዜጎችን የሚያደንቁርባቸው ፍትህ፤ እኩልነት፤ ልማት እና እድገት እውነት በምድራችን ላይ የሚታዩ ቢሆን ኖሮ የሌሎች መገናኛ ብዙሃን መኖር እነመለስ ዜናዊን ይህንን ያህል ሊያስፈራ የሚችልበት ወይም ለልማት እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ሊውል ይችል የነበረ ብዙ ሚሊዮን ብር ወጪ እየተደረገ በቀን አንድ ሰዓት ብቻ ከሚተላለፈው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እስከ በሳምንት 2 ቀን ብቻ የሚተላለፈው የኢህአፓ ሬዲዮ ለመጥለፍ ባላስፈለገ ነበር የሚሉ ብርካታ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።

 ኢሳት ስርጭቱን ወደ አገር ቤት ከጀመረበት ቀን አንስቶ የወያኔ አፈና ለአንድም ቀን እንዳልተለየው የሚናገረው የኢሳት መስራች ቦርድ፤ ለዲሞክራሲ የሚደረገው ትግል ፍሬ እስኪያፈራና በአገራችን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት እስኪረጋገጥ ድርስ ኢሳትን በገንዘብ ወይም በሞገድ ጠለፋ ለማዳከም ወያኔ የሚያደረገውን ማናቸውንም አይነት መሰናክሎች ተቋቁሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ለማገልገል የሚያስችለውን ሁሉ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት በፈረንጆች አቆጣጠር ከአፕሪል 14 ቀን 2011 ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ እና አካባቢዋ ስርጭት እያደረገበት ያለው አዲሱ ሳታላይት አፕስታር (APSTAR) 2 አር በመባል የሚታወቅ እንደሆነና ይህ ጣቢያ ቀደም ሲል ስርጭቱ ይተላለፍበት ከነበረው ታይኮም 5 አጠገብ የሚገኝ ሆኖ በ ሲ ባንድ 76.5 ድግሪ ኢስት ሆርዞንታል፣ ፍርኩዌንሲ 3840 ሜጋ ሄርዝ፣ ሲምቦል ሬት 27500 መሆኑን ን ከኢሳት የተሰጠ መግለጫ ያስረዳል። ኢሳት በውጪ የሚገኝ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በአገር ቤት ላለ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ይህንን አዲሱን ሳታላይት ፍሪኩዌንስ በማሰራጨት እንድትተባበር ጥያቄ አቅርቦአል።

የወያኔን አፈና ለመቋቋም ተብሎ በ8 የተለያዩ አጫጭር እና መካከለኛ ሞገዶች በሳምንት 3 ቀናት ጠዋትና ማታ ወደ አገራችን ስርጭት የሚያደርገውን የግንቦት 7 ድምጽ ሬዲዮን ጨምሮ፤ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ፤ የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ |ዶቼ ቬሌ| ፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሬዲዮ እና የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ሬዲዮም እንዲሁ እጂግ በጣም ብዙ ሚሊዮን ዶላር ወጪ እየተደረገ ከፍተኛ የሆነ የሞገድ ጠለፋ እየተካሄደባቸው በአገር ውስጥ የመሰማት ችሎታቸው ክፉኛ የተጎዳ መሆኑ ታውቋል።

የማጥቃት ዘመቻው ተጀምሯል፤ ሁሉም ለፍልሚያ ይታጠቅ!!!

Thursday, April 14th, 2011

የመለስ ዜናዊ አገዛዝን ለማስወገድ የሚደረገው የተባበረ የማጥቃት ዘመቻ ሚያዝያ 1 ቀን 2003 ዓም በሰሜን አሜሪካ ተጀመረ። የመለስ ዜናዊ ምስለኔዎች ሚያዝያ 1 እና 2 በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች ስለ አምስት ዓመቱ “የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ለመስበክ እንዲሁም “በአባይ ግድብ” እንቁልልጭ ኢትዮጵያዊያንን በማማለል ገንዘብ ለመሰብሰብ ያደረጉት ሙከራ ከሽፎ የህዝባዊ አመጹ ክብሪት ተጫረ። መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያዊያንን ትኩረት ለመሳብ ይረዱኛል ብሎ በከፍተኛ ወጪ ያዘጋጃቸው ስብሰባዎች በተገላቢጦሽ የህዝባዊው አመጹ ጅማሮ ማብሰሪያ ሆኑ።

በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሎስአጀለስ፣ ሚኒያፓሊስ፣ ቶሮንቶ አትላንታ፣ ዴንቨር … የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላትና ምስለኔዎቻቸው ለዓመታት አይተውት የማያውቁት የቁጣ መዓት ወረደባቸው። በአባይ ግድብ ዜና ይጨፍራል ያሉት ህዝብ “በባድመ፣ በምርጫ፣ በእርዳታ እህል ያልታመነ በአባይ ወንዝ ልማት አይታመንም” አላቸው። ቦንድ ለመግዛት ይሸቀዳደማል ብለው ተስፋቸውን የጣሉበት ዲያስፖራ “በላባችን ያገኘንውን ገንዘብ ለስዊዝ ባንክ አንሰጥም” አሏቸው። “አሁንስ መለስ ጀገነ” ይላሉ የተባሉ ሰዎች “የመለስ አገዛዝ በቃ!” አሉ።

ኢትዮጵያዊያን “በቃ!!! ገዬ!!! ይአከል!!! አሎኒ!!! ዲታህ!!! ወጣንደም!!! በስ!!! ጉደስ!!!” ሲሉ በአንድነት ጮኹ፤ ጨፈሩ። ቀድሞ በጋራ ተሰልፈው የጋራ ተቃውሞ በጋራ ለማሰማት ይቸገሩ የነበሩ ወገኖች በአንድነትና በጋራ “የመለስ አገዛዝ በቃን” ሲሉ መስማት ኢትዮጵያዊያን ያኮራ፤ መለስና አሽከሮቹን ግን በእጅጉ ያሸማቀቀ ክስተት ሆነ።

በግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እምነት ሚያዝያ 1 እና 2 በሰሜን አሜሪካና የታዩት የተደራጁ ህዝባዊ ተቃውሞዎች የአገር አቀፉ ህዝባዊው ተቃውሞ መጀመሪያ ናቸው። ከእንግዲህ ድል ሳይጨበጥ ወደ ቤት መመለስ የለም። በጅማሮው እለት የታየው የአንድነትና የእልህ ስሜት ተጠናክሮ ከቀጠለ፤ በውጭ አገራት ያለው ኢትዮጵያዊ በያለበት በዚህ መልክ ከበረታ፤ ነገ ትግሉ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚዘልቅ እና ውጤታማም እንደሚሆን እርግጠኛ መሆን ይቻላል።

ከእንግዲህ የጥቃት ዘመቻችንን ለማፋፋም የወያኔ ሹማምንት ስብሰባ እስኪጠሩ መጠበቅ የለብንም። ከመለስ አገዛዝ ጋር እየነገዱ ያሉ የንግድና የኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን፤ የትምህርት ተቋማትንና ታዋቂ ሰዎችን እያፈላለግን ከመለስ ዜናዊ አምባገነን ሥርዓት ጋር የሚደርጉትን ግንኙነት እንዲያቋርጡ ማስገደድ ይኖርብናል። መለስ ዜናዊና ወንጀለኛ ባልደረባዎቹ ለፍርድ የሚቀርቡበት ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል። ጥቃታችንን በሁሉም መስኮች ማጠናከር ይገባናል። ከእንግዲህ ማፈግፈግ የለም። የጥቃት ዘመቻው ተጀምሯል። ሁሉም ለመጨረሻ ፍልሚያ ይታጠቅ!!!

የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ በቅቶናል፤ አንገሽግሾናል!!!

በቃ!!! ገዬ!!! ይአከል!!! አሎኒ!!! ዲታህ!!! ወጣንደም!!! በስ!!! ጉደስ!!!

በተለያዩ ከተሞች የ«ተነሱ» ጥሪ ወረቀቶች መበተናቸው ቀጥሉአል

Thursday, April 14th, 2011

በኢትዮጵያ ላይ የተጫነው ግፈኛና ዘረኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያዊያን ትከሻ ላይ ተሽቀንጥሮ ይውድቅ ዘንድ ግፊቱና ህዝብንም ለዚሁ ትግል የማያነሳሳ ጥሪ መቅረቡ ተጡዋጡፎ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ባወጣው ዘገባ ገለጸ::

እንደ ኢሳት ዘገባ በአዲስ አበባ ከተማ ከተበተኑት ጽሁፎች ውስጥ አባይ ወንዝን በላያችን ላይ ያለውን የአምባገነንነት ቀምበር ካስወገድን በሁአላ እንሰራዋለን የሚል እንደሚገኝበት ተገልጹአል::

ከበርካታ ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ ቀስቃሽ ወረቀቶች በየግድግዳው እንደሚለጠፉና ሲበተኑም እንደነበር በተደጋጋሚ የተዘገበ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ በቃ የሚሉ ጽሁፎ በየመንገዱ ተበትነው እንደሚገኙ ይህንም ወረቀት ማን እንደበተነ አጋልጡ በመባል ሴተኛ አዳሪዎች እየታሰሩ መሆኑን ኢሳት ምንጮቹን በመጥቀስ ዘግቡአል::

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በተለይም የሰሜን አፍሪቃው ህዝባዊ አብዮት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በሃገር ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ እጂግ እያስፈራውና እያስጨነቀው እንደመጣ ሲዘገብ የቆየ ሲሆን ከዚህ ጭንቀት መውጫ መንገድ አድርጎ እየወሰደ ያለው ርምጃም ንጹሃን ዜጎችን በጂምላ ወደ እስር ቤት ማጎር እንደሆነ በርካታ የዜና አውታሮች የዘገቡት መሆኑ ይታወቃል::

ከስድስት ኪሎ ወደ ጊዮርጊስ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ (አፍንጮ በር ድልድይ) ላይ ሞት ለወያኔ የሚል ጽሁፍ በትላልቅ ፊደላት ተጽፈው እንደነበር መግለጻችን ይታወሳል ፣፡ በራሪ ወረቀት በከተማ ውስጥ የመበተኑ ሥራ ተፋፉሞ በመቀጠል ሰሞኑን በመርካቶ ውስጥ እየተበተነ እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሎአል።

የኦሮሞ ፈዴራሊስት ዋና ጸሃፊ ከ40 በላይ አባላቶቻቸው መታሰራቸውን ገለጹ

Thursday, March 17th, 2011

የወያኔ አገዛዝ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሰሜን አፍሪካው አይነት ህዝባዊ አመጽ ሊነሳብኝ ይችላል  ከሚል ፍርሃት በርካታ ወጣቶችን በሰበብ አስባብ እያሰረ እንደሚገኝ የግንቦት 7 ዘጋቢ ከአዲስ አበባ  በላከልን ሪፖርት ገለጸ።

እንደዘጋቢያችን ሪፖርት አዲስ አበባን ጨምሮ ባሉት ትላልቅ ከተሞች ብዛት ያላቸው የደህነንትና የፈደራል ፖሊስ አባላት ከመመደባቸውም በላይ ወያኔ ባሰማራቸው ፖሊሶችና የደህንነት ሠራተኞች  ካለመተማመን ይመስላል የህወሃት አባላት የሆኑት ታማኝ ወጣቶች ከትግራይ ክልል ተመልምለው  በትላልቅ ከተሞች ውስጥ ተበትኖአል ።

ይህ በዚህ እንዳለ የኦሮሞ ኮንግረስና የኦፌዲን አመራር አባላት በየግል ለኢሳት በሰጡት መረጃ ከ40 በላይ አባላቶቻቸው ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ መታሰራቸውንና አንዳንዶቹ ፍርድ ቤት ቀርበው የቱንዚያን አይነት ህዝባዊ አብዮት ለመቀስቀስ ትንቀሳቀሳላችሁ በሚል ክስ መወንጀላቸውን፤  የተቀሩት ግን የት እንዳሰሩዋቸው እንኳን ለማወቅ እንዳልተቻለ ለመረዳት ተችሎአል። እንደሁለቱ የኦሮሞ ድርጅቶች መረጃ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች ተመሳሳይ ማዋከብና እንግልት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ይህም ወያኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ካለው ተከታታይ የጥቃት  እርምጃ አንዱ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎአል። በሰሜን አፍርካ እና መካከለኛው ምስራቅ እየትካሄደ ያለው ህዝባዊ አብዮት መለስ ዜናዊን ምን ያህል እረፍት እንደነሳው የቱንዚያው አይነት አብዮት ይነሳብናል ብዬ ሳስብ አላድርም በማለት ያደረበትን ስጋት ከፍተኛነት በተዘዋዋሪ ገልጾአል ባለፈው ቅዳሜ ጋዜጣዊ መግለጫው።

የሰሜን አፍሪቃ ህዝባዊ አመፆችና ያገራችን እጣ ፈንታ

Thursday, March 3rd, 2011

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ - እሁድ ፌብሩዋሪ 13፣ 2011 ዓ:ም:: በዳላስ ከተማ ግንቦት ሰባት በጠራው ሀዝባዊ ስብሰባ ላይ የቀረበ ንግግር

ሆሳም ካሊፍ የ50 አመት እድሜ ባለጸጋ የሆነ ግብጻዊ መሃንዲስ ነው:: ጣህሪር አደባባይ ሲዘዋወር ያገኘውን አንድ ምእራባዊ ጋዜጠኛ ተጠግቶ እኛ ከቱኒዝያ ምን እንደተማርን ታውቃለህ? ይለዋል:: የደረሰን መልእክት የሚለው “ራስህን አታቃጥል: ማቃጠል ያለብህ በውስጥህ የሰፈረውን ፍርሃት ነው:: የሚለውን መልእክት ነው” ይለዋል::

የዚህን የጣህሪር አደባባይ ትእይንት የሚመለከት ጋዜጠኛ በአግራሞት ከታዘበው ነገር ዋነኛው በህዝቡ ውስጥ ያየው የመሰረቅ ስሜት ነው:: ይህ የሙባረክ ስርአት የሰረቀባችው የህዝቡን ንብረት ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ ውድ የሆነ ነገር ነው:: የአንድን የግብጽ ትውልድ እጣ ፈንታ ነው የሰረቀባችው ሆኖ የተሰማቸው::

በካይሮ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑ አንድ ምሁር በዚሁ የንጻነት አደባባይ ሲዘዋወሩ ውለው ማታ አሜሪካ ለሚኖር ወዳጃቸው ደውለው ያሉት ደግሞ “ናስር: ሳዳትና ሙባረክ ለ40 ዓመታት በዘረጉት የግፍ የአገዛዝ ስርአት በመንገፍገፍ እነጥፍጥፍ አድርገው ያራገፉብኝን የአገሬን የግብጽን ፍቅር: እነኝህ የጣህሪር አደባባይ ወጣቶች በ 15 ቀናት ውስጥ መለሱልኝ:: አሁን ከነሱ ጋር ሆኘ ብሞትም አይቆጨኝም” ነበር ያለው::

በመጀመሪያ በቱኒዚያ ከዚያም በግብጽ ያየናችው ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ብዙ ጉዶች አያሳየን ነው:: እጅግ በሚዘገንን የአፈና ስርዓት ውስጥ ተወልደው ያደጉ ወጣቶች እምቢ ለመብቴ ብለው ያሳዩት የሚገርም ጀግንነት: ልጇ በእንቅስቃሴው የሞተባት እናት በልጇ መሰዋት የተሰማትን ክብር የገለጸችበትና ሌላው ወንድ ለጇ የሞተው ልጇን አላማ ከዳር እንዲያደርስ ስትማጸን በሰማንበት: አዲሱ የሙባረክ ምክትል ፕሬዜዳንት ሱሌይማን የግብጽ ህዝብ ገና ለዴሞክራሲ አለመብቃቱን ለአለም ህዝብ ያለማፈር ሲነግሩ: ከኛ በላይ ዴሞክራሲ ላሳር ነው ሲሉ የነበሩት የምእራብ መንግስታት በቶኒ ብሌር አማካኝነት ለግብጽ ህዝብ ከነጻነትና ከዴሞክራሲ ይልቅ መረጋጋት የበልጣል: የኛም ጥቅም የሚጠበቀው በሱ ነው ብለው ያለማፈር ሲናገሩ የሰማንበት ጊዜ ነው:: ይህ የብሌር ንግግር እጅጉን ያስከፋው እውቁ የዘመናችን ፈላስፋ እስላቮይ ጂጄክ ይህንን የምእራባውያን የታመቀ የዘረኛነት መገለጫ: “አረቦች ወይንም አፍሪካኖች ለዴሞክራሲ አልበቁም” የሚል የነጻነትን አለም አቀፋዊነት መርህ የሚጋፋ አሳፋሪ ትእይንት ብሎ ተሳልቆ: ግብጾች ለኛ ዴሞክራሲን ያስተማሩበት ክስተት ነው ብሎታል:: ወይዘሮ አና ጎሜዝ በግንቦት 97 ምርጫ ወቅት የህዝቡን የዴሞክራሲ ፍላጎት በምርጫው እለት ለሰአታት ተሰልፎ ዝናብና ሀሩር እየተፈራረቀበት በትእግስት: በሚገርም ዲሲፕሊንና በነቂስ ወጥቶ ሲመርጥ ተመልክተው ያሉትም ይህንንው ነበር ::

ይህንን ተአምራዊ የነጻነት እንቅስቃሴና በወቅታዊ የሃገራችን ፖለቲካ ላይ ያለው እንድምታ ላይ ያለኝን አስተያየት ከማቅረቤ በፊት በዚህ ስብሰባ ላይ ተካፋይ እንድሆን ስለጋበዛችሁኝ ምስጋና ላስቀድም::

ንግግሬን ፈር ለማስያዝ እንደሚከተለው ከፋፍዬ አቀርባለሁ። በመጀመሪያ በሰሜን አፍሪቃና  መካከለኛው  ምሥራቅ እያየነው ባለው ክስተት ምንነት ላይ የራሴን ግንዛቤ አቀርባለሁ። ቀጥዬም ለዚህ ህዝባዊ መነሳሳት አስተዋጽኦ አድርገዋል ብዬ የማምናቸውን ጉዳዮች እያነሳሁ እኔ በገባኝ መንገድ ለመዳሰስ እሞክራለሁ።  ከዚያ ቀጥሎ  እስካሁን ካየነው የምንወስዳቸው ትምህርቶች ላይ አተኩራለሁ። በመጨረሻም ቱኒዚያ ውስጥ ተለኩሶ እየተቀጣጠለ ያለው የነፃነት ችቦ  እኛ አገር እንዲደርስ ማድረግ ይኖርብናል ብዬ የማምናቸውን ነገሮች እነሳለሁ።

ምንድነው እየሆነ ያለው?

ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ መሠረታዊ የሆነ የለውጥ ሂደት ውስጥ ናቸው። “አብዮት” የሚለውን ቃል መጠቀምም እንችላለን። ይህ አብዮት የአካባቢውን ጂኦ-ፓለቲካ ሙሉ በሙሉ ይለውጣል ተብሎ ይገመታል።  አንዳንድ ሰዎች አብዮቱን የሰሜን አፍሪቃና የመካከለኛው ምሥራቅ ክስተት ብቻ  አድርገው ሲወስዱት ይስተዋላል። ይህ ትክክል ስላለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃዎች አሉ። የቱኒዚያው ችቦ ነፀብራቅ በአውሮፓ በአልባኒያና ሰርቪያ፤ በሩቅ ምሥራቅ ደግሞ በኢራቅ ውስጥ በጉልህ ታይተዋል። በዩጋንዳና ናጄሪያም ውስጥ ብልጭታው ታይቷል። የያዝነው የአውሮፓውያን 2011 በሃይማኖትና በዲሞክራሲ ሽፋን ተንሰራፍተው ለተቀመጡ አምባገነኖች በሙሉ የሚመች ዓመት እንደማይሆን መልዕክቱ የተላለፈላቸው ይመስላል። ህዝብ ለአስር ዓመታት የሰማው ባዶ ስብከት የሰለቸው መሆኑ በግልጽ የተናገረበት አጋጣሚ ነው። ይህ ለውጥ የጽንፈኝነት አደጋ ባለባቸው አገሮች ውስጥ በሲቪል መብቶች ዙርያ ያጠነጠነ ንቅናቄ መሆኑ ይበልጥ አጓጊ አድርጎታል።

የሁኔታዎች ፍጥነት እጅግ አስገራሚ ነው። በቱኒዚያ ለሃያ ሶስት ዓመታት የተንሰራፋው አምባገነን በወር ውስጥ ወደቀ። በግብጽ ለ30 ዓመታት የተደላደለውና የኃያላን አገሮች ከፍተኛ ድጋፍ ያለው መንግሥት በ15 ቀናት ውስጥ ተነቀነቀ። በዮርዳኖስ፣ በየመንና አልጄሪያ ውስጥም የመንግሥታቱ ጥርሶች ተነቃነቁ። በአካባቢው ያሉት አምባገነኖች ካቢኔን መፐወዝ፤ ደመወዝ መጨመር፤ ዋጋ መቆጣጠር፤ “በሚቀጥለው ምርጫ አልወዳደርም” እያሉ  ቃል በመግባት ማዕበሉን ለማቀዝቀዝ እየጣሩ ነው። ህዝባዊው ንቅናቄ ግን ይበልጥ ሥር እየሰደደና እየተሰራጨ እንጂ እየበረደ አይደለም።

የየመኑ አሊ አብደላ ሳልህ ገና የቱኒዚያውን ህዝባዊ አብዮት ሲያይ ለእሱም እንደማይቀርለት ተገንዝቦ በሚቀጥለው ምርጫ እንደማይሳተፍ፤ ሥልጣንን በማውረስ እንደማያምን በመግለጽ የወጣቱን አጀንዳ ለመንጠቅ ያደረገው እሽቅድድም አስገራሚ ነው። የሱዳኑ አልበሽርም “ብትፈልጉ በድጋይ ውገሩኝ እንጂ ከአገር አልወጣም” ሲል የአገሩን ወጣቶች “አንጀት ለማራራት” ሞከረ። የኢራቁ አልማለኪም ለሶስተኛ  ጊዜ እንደማይወዳደር ቃል ገባ። ይህ ሁሉ ሆኖ  ግን ቱኒዚያ ላይ የተለኮሰው ችቦ  እየጎመራ  ነው። ሌላው ቀርቶ ፍጹም የተዘጋች አገር በምትመስለው ሳዉዲ ዓረቢያ ውስጥ እንኳን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። በጎረቤታችን በጅቡቲም እየተንተከ ነው:: ይህ አብዮት እያዳረሰ ያለው በሃይማኖት ሰበብ የሲቪል መብቶች በሚረገጥባቸው አገሮች ውስጥም መሆኑ በአይነቱ ልዩ  ያደርገዋል። ይህንን ሁሉ በአንድነት ስናስተውል ነው “ምንድነው እየሆነው ያለው?” የሚለው ጥያቄ መሠረታዊ መሆኑ የምንገነዘበው።

በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በርካታ ጥናቶች እንደሚደረጉ ጥርጥር የለውም። ወደፊት ብዙ ሊጨመሩባቸው የሚገቡ ነገሮች ቢኖርም እስካሁን በአየነው መነሻነት የሚከተሉት ድምዳሜዎች ላይ መድረስ ይቻላል ብዬ አምናለሁ።

  1. ይህ ህዝባዊ አመጽ ያሳየን ነገር የነፃነትና የዲሞክራሲ ፍላጎት ዘርን፣ ባህልንና ሃይማኖትን ተሻጋሪ መሆኑን ነው። ነፃነትና ዲሞክራሲ ለምዕራባዊያን ባህልና ሃይማኖቶች የተመቹ፤ ለሌሎች ባህሎችና ሃይማኖቶች ጋር አብረው የማይሄዱ ተደርጎ ሲወሰድ ቆይቷል። “አረብና አፍሪካዊ ለሆዱ ሲል ቢረገጥ አይከፋውም” የሚል ሃሳብ ብዙ ጊዜ በስውር፤ አንዳንዴም በግልጽ ሲነገር ቆይቷል። የሰሞኑ የሰሜን አፍሪቃ ህዝባዊ አመጾች ይህንን አስተሳሰብ በማያንሰራራ ሁኔታ በታትኖታል።  በተደጋጋሚ በፓሊሶች የሚደርስበት ውርደት ተሸክሞ ከሚኖር ራሱን ያቃጠለው ቱኒዚያዊው ወጣት መሃመድ ቦዛዚ በተግባር የነገረንም ይህንን ነው። እንደ አሜሪካዊ ወይም አውሮፓዊ ወጣት ሁሉ እሱም በራሱ ህይወት ላይ ራሱ የመወሰን መብት ያለው መሆኑን፤ ይህ መብት ከሚገፈፍ አለመኖሩ የሚመርጥ መሆኑን አሳይቶናል። ከካይሮው የጣህሪር አደባባይ ሰልፈኞች ጥያቄ በተለያየ መንገድ ይቅረብ እንጂ ማጠቃለያው “ባርነት በቃን! ውርደት በቃን!!” የሚል ነው።
  2. ሰው ነፃነቱን ሲጎናፀፍ ለራሱ የሚሰጠው ክብር ምን ያህል ከፍ እንደሚል የሰሜን አፍሪካው ንቅናቄ አሳይቶናል። “እኔ ምን አቅም አለኝ” “የመጣውን መቀበል እንጂ ምን ማድረግ እችላለሁ” የሚል ሰው በታህሪር አደባባይ ህዝባዊ ተቃውሞ  ውስጥ ማግኘት አይቻልም። እዚያ የተሰበሰ ሰው በሙሉ “የኔ ተሳትፎ ዋጋ አለው” ብሎ  የሚያምን፤ በመሳተፉም ክብር የሚሰማው ነው። እንዲያው በዚህ ንቅናቄ ውስጥ መሳተፍ ራሱ የክብር መገለጫ ሆኗል። በዚህም ምክንያት ነው በርካታ ግብፃዊያን ከህዝባቸው ጋር ለመራብ እና ለመታገል ክብር ሲሉ  ከአውሮፓና አሜሪካ የተመለሱት። በዚህም ምክንያት ነው ሰልፎቹ የተቃውሞ ሰልፍ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የአንድነት ማሳያ የሆኑት። ሰልፎቹ የደስታና የተስፋ ቦታዎች ሆነዋል። ሠርጋቸውን በታህሪር አደባባይ ያደረጉ ጥንዶችንም ሳይቀር አይተናል።
  3. ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣው የባለቤትነት ስሜት ነው። ወጣቶች የተቃዉሞ ሰልፎችን ለመጥራት እና ራሳቸውን በግንባር ቀደምትነት ለማሰለፍ ከማንም ፈቃድ ይሁን እርዳታ አልጠበቁም። ፓርቲዎች ወይም የታወቁ ሰዎች እንዲመሯቸው አልጠበቁም። ኃያላን መንግሥታት እንዲደግፏቸው አልተለማመጡም። እያንዳንዱ ሰው የራሱን ኃላፊነት ራሱ ወስዷል።  ሰልፈኞች የግብጽ ባለቤቶች እኛ ነን ብለው በማመናቸው እርምጃዎቻቸው ሁሉ ኃላፊነት የተሞላው ነው። የግብጽ ሙዚየም ከዘረፋ የተከላከሉት ራሳቸው ሰልፈኖች ናቸው። ፓሊስ በጠፋ ጊዜ የፀጥታ  አስከባሪዎች የወጡት ከራሱ ከሰልፈኛው ነው። መንገድ የሚጠርጉት እነኝሁ ታጋዮች ናቸው::

በህዝባዊ አመፁ ዋዜማ አገራቱ የነበሩበት ሁኔታ

ቱኒዝያ፣ ግብጽ፣ ዮርዳኖስ፣ የመንና አልጄሪያ ከአረብነት እና እስላም ሃይማኖት በተጨማሪ በርካታ የሚያመስሏቸው የጋራ ባህሪያት አሉዋቸው። አንዳንዶቹን ከዚህ በታች እዘረዝራለሁ።

1.       አምባገንነት፡ በእነዚህ አገሮች ሥልጣን በአንድ ግለሰብ ወይም በአንድ አነስተኛ ቡድን መያዝ የተለመደባቸው ናቸው። ብዙዎች አምባገነኖች ከሃያ ዓመታት በላይ በመንግሥት ሥልጣን ላይ  ቆይተዋል።  እኚህ አምባገነኖች በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት መሪነት መቀየር ካስፈለጋቸው የሚመጠቀሙት ስልት ርስ በርሳቸው መተካካትን ነው። በዚህም ምክንያት ሥልጣን በአንድ ቤተሰብ የተያዘባቸው ነበሩ።

2.      የሴራ ምርጫዎች፡ በእነዚህ አገሮች ሁሉ የሴራ ምርጫ ሲደረግባቸው የቆዩ ናቸው። የሴራ ምርጫ በስልጣን ላይ ያለው ኃይል እንደገና የሚመረጥበት አሊያም በሥልጣን ላይ ያለው አካል በሚፈልጋቸው ሰዎች የሚተካበት ድግስ ነው። እነዚህ አገሮች ተደጋጋሚ የሴራ ምርጫዎችን ማድረጋቸው “ዲሞክራሲ አስፍነናል” ብለው ለመመፃደቅ ረድቷቸዋል። ምዕራባዊያንም እውነተኛ ዲሞክራሲ ከምዕራቡ ዓለም ውጭ የማይሆን ነገር አድርገው ስለሚወስዱት “ሙከራ ማድረጋቸው” እራሱ እንደ ትልቅ ነገር እየቆጠሩት ሲያሞካሹዓቸው ቆይተዋል።

3.      ፀረ-ሽብርተኝነት: እነዚህ አገሮች በፀረ-ሽብር ትግል የአሜሪካና የአውሮፓ  መንግሥታት አገሮች አጋሮች  የሆኑ በዚህም ምክንያት የአሜሪካና የአውሮፓ መንግሥታት እንክብካቤና ጥበቃ ያልተለያቸው ናቸው። በተለይም ሙባረክ የአሜሪካ ሁነኛ ወዳጅ መሆኑ የአሜሪካ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያገኝ የነበረ ከግብጽ ይልቅ ለአሜሪካ ጥቅም የቆመ ሰው ነበር።

4.      የተቃዋሚዎች መዳከም፡ በቱኒዚያና በግብጽ ህዝባዊው ተቃውሞው የፈነዳው የተቃዋሚ ኃይሎች በተዳከሙና በተከፋፈሉበት፤ ህዝብም ውስጥ በከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ በነበረበት ወቅት ነው።

5.      የኑሮ ሁኔታ ማሽቆልቆል: የእነዚህ  አገራት ውስጥ መንግሥታት ስለ ኢኮኖሚ እድገት ሲሰብኩ የቆዩ  ቢሆንም የአብዛኛው ህዝቡ የእለት ተእለት ኑሮ በዋጋ ንረትና በሥራ እድሎች እጦት እያሽቆለቆለ  ሄዷል።

6.      ከፍተኛ  የሃብት መበላለጥ: የአብዛኛው ህዝብ የእለት ተእለት ኑሮ እያሽቆለቆለ የየአገራቱ ገዢዎችና ተባባሪዎቻቸው የተንደላቀቀ  ህይወት፤ ዓይን ያመጣ ዘረፋና ሙስና ሌላው የጋራ ባህሪያቸው ነበር።

ከላይ ከተዘረዘሩት ነጥቦች አንፃር አገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ሁኔታ ስንገመግም በሁሉም ነጥቦች ከሁሉም በባሳ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ስለሆነም የሰሜን አፍሪካን ህዝባዊ አመጽ የቀሰቀሱት ከላይ በተዘረዘሩት ነገሮች  ምክንያት ከሆነ ተመሳሳይ ነገር ኢትዮጵያም ውስጥ የመነሳቱ እድል ከፍተኛ ነው።

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በጎጂ መልኩ የምትለይባቸውን አራት ነጥቦችን ማንሳት ያስፈልጋል።

  1. በሥልጣን ላይ ያለው ቡድን ባህርይ። በአገራችን በሥልጣን ላይ ያለው ገዢ ቡድን ራሱን እንደ አገሪቱ ዜጋ የማያይ፤ ዜጎችም “ወገናችን ነው” ብለው ለመቀበል የሚቸገሩበት ሁኔታ መኖሩ በህዝብና መንግሥት መካከል የፊት ለፊት ግጭት ቢነሳ ወደ ጠቅላላ ውድመት ያመራል የሚል ስጋት በአንዳንድ ሰዎች ውስጥ እንዲኖር አድርጓል፤
  2. የጦር ሠራዊት፣ የፓሊስና  የስለላ ተቋማት ዘረኛ  በሆነ  መንገድ የተደራጁ በመሆናቸው  ህዝቡ በአንድነት እንዳይነሳ እንቅፋት ይሆናሉ፤ ቢነሳም የተቃውሞውን ሲቪል ባህርይ በማሳጣት ዘርን መሠረት ወደ አደረገ  ግጭት ያመራ ይሆናል የሚል ትንተናም የሚሰጡ ሰዎች አሉ፤
  3. በምርጫ 97 ማግሥት በደረሰት አፈናና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መከፋፈል ምክንያት የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ ቆርጧል፤ ህዝቡ ቢነሳሳም ትግሉ በመሪ እጦት መሰናከሉ አይቀርም የሚል ትንተናም ይሰጣል።
  4. በኢትዮጵያ ውስጥ የመረጃ ስርፀት በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ እንደ ቱኒዝያና ግብጽ በTweeter እና Facebook ሰልፉን ማስተባበር አይቻልም የሚል ሃሳብ በተደጋጋሚ ይነሳል።

አራቱም ነጥቦች በተወሰነ መጠን እውነት አላቸው። ሆኖም ግን እነዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባዊ አመጽ እንዳይነሳ ይከላከላሉ ብዬ በበኩሌ  አላምንም።

ከቱኒዚያና ግብጽ ህዝባዊ አመፆች ትምህርት

  1. የወጣቶች ተሳትፎ: በቱኒዚያና ግብጽ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ውስጥ ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል። እንዲያውም ንቅናቄዎቹ ባለቤት ይኑራቸው ቢባል “የወጣቶች ንቅናቄ” ነው መባል የሚችለው። የቱኒዚያና ግብጽ ወጣቶች ወላጆቻቸው ባስቀመጡላቸው ሥርዓት መኖር አልፈለጉም። ወላጆቻቸው ያኖሩላቸው ሥርዓት ባርነት ነበር። እነሱ ሊኖሩበት የሚፈልጉትን ሥርዓት ወላጆቻቸው ሊገነቡላቸው እንዳልቻሉ ተረድተዋል። እናም ለራሳቸው የሚመኙትን ሥርዓት ራሳቸው ለመገንባት ቆርጠው ተነሱ።

ኢትዮጵያም ውስጥ ለለውጥ ሌላ ጎዳና ያለው አይመስለኝም። ያለፉት ትውልዶች መልካም ተግባራትን አከናውነዋል። ሆኖም ጀምረው ያልጨረሷቸው እና ጭራሹን ያልጀመሯቸው በርካታ ነገሮች ለአሁኑ ወጣት ተላልፈዋል። የዛሬው የኢትዮጵያ ወጣት ብዙ እዳ ከወላጆቹ መረከቡ እጅግ የሚያሳዝን ነው። የሆነ ሆኖ ወጣቶቻችን አንድ ቁም ነገር መረዳት ይገባቸዋል – ወላጆቻቸው ለእነሱ የሚመች ሥርዓት አልገነቡም፤ አይገነቡምም። ለራሳቸው የሚሆን ሥርዓት መገንባት ያለባቸው ራሳቸው ናቸው። የቱኒዚያና የግብጽ ወጣቶች ኃላፊነት መወሰድ ሲጀምሩ ነው ጉርምርምታ ወደ አመጽ የተሸጋገረው። ወጣቶች በዚህ ትግል ውስጥ ካልገቡ የሚኖረው ማጉረምረም ብቻ ይሆናል።

  1. ፈጠራ፤ የራሱን ነፃነት ያወጀ ትውልድ የፈጠራ ችሎታው ምን ያህል እንደሚጎለብት በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። በቱኒዚያና ግብጽ ወጣቶች ያለ አንባገነኖች ጣልቃገብነት የሚደራጁበት ነፃነት ስላልነበራቸው ህልሞቻቸውን የሚጋሩባቸው መድረኮች አልነበሯቸውም። የነፃነት መንፈስ በውስጣቸው በሰረፀ ጊዜ ግን ይህ ችግር ህልሞቻቸውን አላጨናገፈውም። ለሌላ ተግባር የተዘጋጁትን Facebook እና Twetter ለዓላማቸው ማስፈፀሚያነት ተጠቀሙባቸው። የሚገርመው ነገር እያጣጣረ ያለው የሙባረክ መንግሥት ኤንተርኔትን የዘጋው ወጣቶቹ በአካል ከተገናኙ በኋላ መሆኑ ነው። ታሂር አደባባይ ማራኪ ያደረገው የወጣቹ ፈጠራ ጭምርም ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የኢንተርኔት ስርጭት አነስተኛ መሆኑ የሚያሰጋቸው ወገኖች እምነታቸው ማረፍ ያለበት በወጣቶች የፈጠራ ችሎታ ነው። ወጣቶች አምርረውና ቆርጠው ከተነሱ እነዚህ ችግሮች የሚወጡባቸው መንገዶች አያጡም። [በምርጫ 97 ዋዜማ በአንድ የገጠር ከተማ የወያኔ ደጋፊዎች ሰልፍ ይወጣሉ። ብዙ የንብ ምልክት የታተመበት ወረቀት በየቤቱ ተበተነ። በዚህ የተናደደው ወጣት የአባቱን አንድ የንብ ቀፎ ከነንቦቹ ተሸክሞ “አርማችን ነው” እያለ ሰልፍ ወጣ። ግርግሩ ንቦቹን ረበሻቸውና ሰልፈኛው በመንደፍ ሰልፉን በተኑት። ነፃነት የሚሰማቸው ወጣቶች የሚያመጡት መፍትሄ ይገርማል]

  1. በራስ የመተማመን ስሜት: ቱኒዚያዊያንና ግብፃዊያን ፍርሃትን ማሸነፍ የቻሉ በራስ የመተማመን ስሜት በመፍጠራቸው ነው። ግብጽ መለዮ ለባሽ ከሆነው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ውጭ 350 000 የሚደርስ ሰላይና ነጭ ለባሽ አላት ተብሎ  ይገመታል። ይህ ሁሉ ሠራዊት ግን አመጹ እንዳይነሳ ማገድ፤ ከተነሳም በኋላ ማፈን አልቻለም። በራስ የመተመመን ስሜት መተሳሰብን፣ መተጋገዝን፣ የጋራ ጥቅምን ማስቀደምን ይፈጥራል።
  2. የሚዲያ ሚና፤ ለእነዚህ ህዝባዊ መነሳሳቶች በመጀመሪያ Facebook እና  Tweeter ቀጥሎ ደግሞ አልጀዚራና CNN የተጫወቱት ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው። ኢትዮጵያዊያን ከዚህ የምንወስደው ትልቅ ትምህርት አለ። ኢትዮጵያ ውስጥ ተመሳሳይ አመጽ ቢነሳ የትኛው ሚዲያ ነው የሚዘግብልን? በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሉት ወገኖቻችንን እርስ በርሳቸው በምን መንገድ ይገናኛሉ። የኢሳትን አይነት ነፃ የሚዲያ ተቋም መኖር ለትግላችን የሚኖረው ፋይዳ አሁን ፍንትው ብሎ ሊታየን ይገባል።
  3. ጽናት፤ በተለይ ግብፃውያን ዓለምን ያስደመመ ጽናት አሳይተዋል። ህዝባዊ እምቢተኝነት ውጤታማ እንዲሆን  በጽናት መታገልን ይጠይቃል። በነገራችን ላይ የሙባረክ ደጋፊዎች በፈረስና ግመል መምጣታቸው ራሱ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ከአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ጋር የመፋለማቸው ገላጭ ይመስላል።
  4. መቻቻል፤ ሰዎች ለትላልቅ ዓላማዎች ሲሰለፉ መለስተኛ ቅራኔዎች ፋይዳ አይኖራቸውም። የነፃነት ትግል ግብፃዊያንን አፋቅሯል። በክርቲያኖች ጥበቃ ሞስሊሞች ሲሰግዱ፤ ለክርስትያኖች ቅዳሴ ሞስሎሞች ከለላ ሲሰጡ ማየት ችለናል። የሁለቱም ሃይማኖቶች ተከታዮች በጋራ በየእምነቶቻቸው ለነፃነት ፀልየዋል።
  5. የምዕራባዊያን ድጋፍ፤ ምዕራባዊያን የዓለም ህዝቦች ነፃነታቸውን ቢቀዳጁ እና ዲሞክራሲን ቢያሰፍኑ ደስተኞች ይሆናሉ። ሆኖም ግን ከሌሎች አገራት ህዝቦች ነፃነት የራሳቸውን ደህንነት ያስቀድማሉ። ይህ የአገሮች ባህርይ ነው። ለነፃነታችን በምናደርገው ትግል የዲሞክራሲያዊ አገሮች ድጋፍ ለማግኘት መሬት ላይ ያለው ሁኔታ መቀየር እንዳለበት ቱኒዚያም ግብጽም አረጋግጠውልናል። መሬት ላይ ያለው ሁኔታ  ሲቀየር ደግሞ ትላንት እሹሹሩ ያሉትን አምባገነን አንስቶ ከማፍረጥ እንደማይመለሱ በመጀመሪያ ከቱኒዚያው ቤን ዓሊ: ከዚያም ከግብጹ ሙባረክ የተማርነው ትልቅ ቁም ነገር ነው። አምባገነኖቹ የዘረፉትን ገንዘብ እንኩዋን እንዳይበሉ ከመቼው በውጭ ያስቀመጡትን ገንዘብ እንዳያወጡ እንደዘጉባቸው አይተናል::
  6. የሲቪክ ድርጅቶች ሚና፤ በጉልህ ባይዘገብም ሲቪክ ማኅበራት ያደረጉት አስተዋጽኦ ፈጽሞ ሊዘነጋ አይገባም። በርካታ የበጎ አድራጎት ማኅበራት እዚያው እሰልፉ ሜዳ  ውስጥ ተፈጥረው ፋፍተዋል።  የጤና ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የኢፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በተደራጀ መንገድ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል። የእነዚህ መጠናከር ማኅበራዊ ትስስርን አጠናክራል። በተጨማሪም ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተማጋቾች በስፋት እንዲቀሳቀሱ የመብትጥሰቶች እንዲመዘገቡ ረድቷል።

ከካይሮ  ወደ አዲስ አበባ

የመብት ረገጣ፣ አፈናና ችጋር ኢትዮጵያ ውስጥ በከፋ ሁኔታ መኖሩ የካይሮው ህዝባዊ አመጽ ወደ ኢትዮጵያ የመዛመት እድሉን ከፍ ያደርገዋል። ኢትዮጵያዊያን ለሰብዓዊና የዜግነት ክብራቸው፣ ለነፃነታቸው፣ ለፍትህና ለተሻለ ህይወት ሲሉ በጋራ መነሳታቸው የማይቀር ነገር ነው። ነገር ግን የአመፃው አነሳስ፣ ፍጥነቱና ጥልቀቱ ከአገር አገር የተለያየ መሆኑ አይቀርም። ስለሆነም ካይሮ ያየነውን ፎቶ ኮፒ አዲስ አበባ ውስጥ አናይ ይሆናል። በሰሜን አፍሪቃ ውስጥ ያየናቸው ህዝባዊ አመጾች በጥንቃቄ ታቅደው የተሰሩ ነገሮች አይደሉም። ሆኖም በመጀመሪያ ሌሎች አገሮች ሰርተው ያሳዩን ነገሮች መኖራቸው እኛን በእጅጉ ይጠቅመናል ብዬ አምናለሁ። ከእነሱ ተምረን፤ ራሳችንን መርምረን የጎደሉንን ለመሙላት እድል አግኝተናል። ይህንን ታሪክ የፈጠረልንን እድል በሚገባ  ለመጠቀም በቶሎ  ልንፈጽማቸው ይገባሉ ብዬ የማስባቸውን ነገሮች ላንሳ።

  1. ኢትዮጵያ በቁጥር ከብዙ እስላማዊ አገሮች የበለጡ ሙስሊም ዜጎች ያሏት አገር ናት፡፡ በሙስሊም ዜጎች ብዛት ኢትዮጵያ ከሳዉዲ አረቢያ፣ ከሱዳን፣ ከአፍጋኒስታንና ከኢራቅ ትበልጣለች፡፡ በዚህም ምክንያት የሙስሊሙን ማኅበረሰብ በስፋት ያላሳተፈ ንቅናቄ ህዝባዊ ሊባል አይችልም፤ ግቡንም አይመታም። የሰሜን አፍሪቃ ሙስሊሞች ለሲቪክ መብቶች መቆም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ያበረታታል ብዬ አምናለሁ። በግብጽ ሞስሊሞችና ክርስቲያኖች በአንድ ላይ መቆማቸው ለኢትዮጵያም ሞስሊሞችና ክርስቲያኖች ትልቅ ትምህርት ነው።

ወያኔ የኦርቶዶክስና የእስላም፤ የእስላምና የፕሮቴስታንት፤ የኦርቶዶክስና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን እያናከሰ እስካሁን እድሜው አራዝሟል። አሁንም መሠሪ በሆኑ መንገዶች በሃይማኖቶች መካከል ያሉት ግኑኝነቶች እንዲሻክሩ እየተደረገ ነው። በግብጽ እንዳየነው ለሰብዓዊ ክብር፣ ለነፃነትና ለእኩልነት የሚደረግ ትግል የሁሉም ሃይማኖቶች አማኞች የጋራ ትግል ነው።

ስለዚህም በተለያዩ ሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል ያለው አላስፈላጊ ንትርክ በአስቸኳይ በማቆም ትኩረታችንን በነፃነት ትግሉ ላይ ማድረግ ይኖርብናል። የተፈጠረው ሁኔታ  ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን የነፃነት ትግልን በስፋት እንዲቀላቀሉ ያደርጋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ ሊያመልጠን የማይገባ ትልቅ እድል ነው።

  1. ዘረኝነት ለሃያ ዓመታት የወያኔ መንግሥት የፓሊሲ ምሰሶ ሆኗል። የወያኔ ዘረኝነትና ኢፍትሃዊነት ፍጹም ዓይን ያውጣ በመሆኑ ህዝባዊ አመጽ ቢነሳ በፍጥነት ወደ ዘር ግጭቶች ሊያመሩ ይችላሉ የሚለው ስጋት ምንም መሠረት የሌለው አይደለም። በዚህም በተጨማሪ ለነፃነት የምንሰጠው ትርጉምም የተለያየ  መሆኑ አንዱ ትልቁ ችግራችን ሆኖ ቆይቷል። በግለሰብ ነፃነት እና በቡድን ነፃነት መነሻነት የተደራጁ ድርጅቶች ተቀራርበው ለመሥራት በመቸገራቸው ሁሉም በወያኔ ለመረገጥ የተመቹ ሆነዋል።

በቱኒዝያና በግብጽ የታየው ህዝባዊ አመጽ አገራችን እንዲደርስ ይህ ሲለያየን የቆየው አጥር ፈርሶ በአንድነት መቆም መቻል አለብን። በብሄርም ይሁን በአገር መደራጀታችን ሳይለያየን ለክብራችን፣ ለነፃነታችንና ለተሻለ ኑሮ በጋራ መቆም አለብን።

ወያኔ ሲወድቅ አገር እንደማይፈርስ ብቻ ሳይሆን የተሻለች አገር እንደምትኖረን ለህዝባችን ማረጋገጫ የምንሰጠው ዛሬ በምናሳየው መግባባት፣ መተጋገዝና መተባበር ጥልቀት ነው።

  1. የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያ እንጂ የወያኔ ሠራዊት አለመሆኑ እንዲገነዘብ ማድረግ አጣዳፊ ተግባር መሆን ይኖርበታል። ሠራዊቱ ከፓለቲካ ገለልተኛ መሆን ይኖርበታል። ይህንን እውን የማድረግ ሥራ አሁን ካሉት የወያኔ አዛዦች ትዕዛዝ አለመቀበልንም ሊያጠቃልል ይችላል። የፓሊስና የደህነቱም ክፍል አባላትም አገራዊ ስሜት እንዲኖራቸው፤ እነሱም የነፃነትን ጣዕም እንዲረዱ የመቀስቀሱ ሥራ ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባዋል።
  2. የፓለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማኅበራት ወያኔን ለመጣል ብቻ ሳይሆን ከዚያ በኋላ የምትኖረዋንም ኢትዮጵያ በጋራ ለመምራት የሚተባበሩ መሆኑን ዛሬውኑ ማሳየት ይኖርባቸዋል። የመንግሥትን ሥልጣን ለመረከብ ብቃት ያላቸው መሆኑን የገዛ ራሳቸውን፣ ሌሎች ድርጅቶችን: ህዝብን እና ሌሎች አገራትን ማሳመን ይጠበቅባቸል።
  3. የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች ከዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች ጋር ያላቸውን ቅርበት ማሻሻል ይኖርባቸዋል። የኤለክትሮኒክስ ፓስታዎች (email)፣ Facebook, Tweeter እና ሌሎችንም የኔትዎርክ ዘዴዎችን መፈተሽ ይኖርብናል።
  4. አስተማማኝ የሚዲያ ተቋማት መኖር እጅግ አስፈላጊ ነገር በመሆኑ ኢሳትን የማጠናከር ተግባር እንደ አገራዊ ሥራ መወሰድ ይኖርበታል።  ከዚህም ሌላ በግልም ሆነ በቡድን የተጀመሩ የሬድዮ ስርጭት አገልግሎቶች የሚቀናጁበት መንገድ ሊፈለግ ይገባዋል።
  5. የወያኔን አፋኝ ሥርዓት በትጥቅ ትግል ለመፋለም የተሰለፉ ኃይሎች ብርታት የካይሮዉን ችቦ አዲስ አበባ ለማድረስ ትልቅ ጉልበት ይሰጣል ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ በስትራቴጄ ምርጫ ልዩነት ምክንያት የሚነሱ ክርክሮች ቆመው ሁሉም አንድ የጋራ ግብን አስበው ሊንቀሳቀሱ ይገባል እላለሁ።
  6. በመጨረሻም ይህ አብዮት ዓለም ዓቀፍ ይዘት ያለው በመሆኑ በትግል ላይ ላሉ በየትም አገር ላሉ ህዝቦች ወገናዊ ድጋፍ መስጠት አስፈላጊ ነው። በተለይ የግብጽ አብዬት ውጤታማ  መሆን ወደፊት ለሚመጡት ወሳኝ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለግብጽ ህዝብ ያለውን ድጋፍ ማሳየት ይኖርብናል እላለሁ። የአካባቢውና የአለም አምባገነኖች ሙባረክን አይዞህ እንደሚሉት ሁሉ እኛም ታጋዮችን አይዞአችሁ ማለት ይጠበቅብናል::

ማጠቃለያ

በሰሜን አፍሪካ ተነስቶ ወደ መላው ዓለም እየተዳረሰ  ያለው አብዮት በአይነቱ አዲስ የሆነና ጥልቅ የሆነ እንድምታ  ያለው ክስተት ነው። የነፃነት ፍላጎትና ዲሞክራሲ የምዕራቡ ባህል አካል አድርጎ  በመውሰድ እኛ ለዲሞክራሱ ያልበቃን አድርጎ ሲመለከት የነበረው አስተሳሰብን ያሳፈረ  ክስተት ነው።

ይህ ክስተት ወደ ኢትዮጵያ ሊደርስ ይችላል፤ ስለሆነም መዘጋጀት ይኖርብናል። ዝግጅቶቻችንን በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች መመደብ  ይቻላል።

  • አንደኛ በውስጣችን ያለውን ልዩነት መቀነስ ይገባናል፤ ቢያንስ የልዩነቶችን ደረጃ መመዘንና ቅደም ተከተል ማውጣት: አውጥተንም በዚያ ቅደም ተክተል መሰረት መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል::
  • ሁለተኛ የሚዲያ አጠቃቀማችን ማሳደግ: ማዘመንና በወሳኘ ቁምነገሮች ላይ ማነጣጠር ይኖርብናል፤
  • ሶስተኛ የተለያዩ  የትግል ስልቶች በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በተግባር ተደጋጋፊ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅብናል።

እነዚህን በጊዜ ከከወንን ይህን እጹብ ድንቅ የሆነ አጋጣሚ ተጠቅመን ስብዕናችንን አስከብረን፣ በሰላምና በፍቅር የምንኖርባት አገር እንድትኖረን ማድረግ እንችላለን። አለበለዚያ ግን ሳንጠቀምበት አለፈ ብለን ከምንቆጭባቸው መልካም አጋጣሚዎች አንዱ ይሆናል። ምርጫው በእጃችን ነው።

መፈክራችን በቃጋዬ ነው::

ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።

የፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ከሃገር ኮበለሉ

Thursday, March 3rd, 2011

የዘረኛውና አምባገነኑ ወያኔ አገዛዝ የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የነበሩት ኮማንደር ደምሳሽ ሃይሉ በወያኔ ዘረኛነት ተማረው ስራቸውንና አገራቸውን ለቀው በስደት እንግሊስ አገር መግባታቸው ታወቀ::

ኮማንደር ደምሳሽ ሃይሉ በግንቦት ሰባት ስም በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከተከሰሱ የአማራ የጦር መኮንኖች ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው ተብለው በወያኔ የደህንነት ሠራተኞች በአይነ ቁራኛ የሚጠበቁ እንደነበሩ ቢታወቅም ከጥቂት የአማራ መኮንኖች ውጪ ሌሎች የሥርዓቱ ታማኞች ናቸው እንዲባሉ ብቻ  የጸረ ሽብርተኝነት ዘመቻ ግብረሃይል ቃል አቀባይ ሆነው ስለግንቦት 7 እስረኞች በሬዲዮና ቴለቪዥን መግለጫ እንዲሰጡ ሲደረግ እንደነበር ይታወሳል።

ኮማንደር ደምሳሽ ሃይሉ የወያኔን አገዛዝ ባገለገሉባቸው በርካታ አመታት የትግራይ ጉጂሌ አባላት የሆኑት የፖሊስ እና የጦር መኮንኖች በሚያሳዩት ዘረኛ አሰራር እጅግ ሲማረሩ እንደቆዩ የሚናገሩ የብ አዴን መረጃ ምንጮቻችን፤ የጸረሽብር ዘመቻ ቃል አቀባይ ሆነው ያገለግሉ በነበረበት ወቅት ሳይቀር በሽብርተኝነት ሥም ስለሚታሠሩም ሆነ ኢላማ ሰለሆኑ ሰዎች ከርሳቸው ይልቅ በማዕረግና በደረጃ ከርሳቸው የበታች የሆኑ የትግራይ ተወላጅ የበለጠ መረጃ ያገኙ እንደነበር ይናገራሉ።

የጎጃም ተወላጅ የሆኑት ኮማንደር ደመላሽ ሃይሉ ወያኔን የተቀላቀሉት በጸረ ደርግ ትግል ወቅት እንደሆነ ይታወቃል። በመለስ ዜናዊ የሚመራው ዘረኝ እና ፋሽስት አገዛዝ በተለይም በአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል በደልን ሲፈጽም እንደቆየ መረጃዎችን በማስደገፍ በተከታታይ ስንዘግብ የቆየን መሆናችን አይዘነጋም:: በተለይም በቅርቡ ከወያኔው አምባገነን አገዛዝ ቃሊቲ እስር ቤት ሾልኮ በወጣ መረጃ ዘረኛው አገዛዝ የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆ ላይ የሚፈጽመው ሰቆቃ በቃላት መግለጽ የሚያስቸግር እና ለሂሊና የሚሰቀጥጥ እንደሆነ ስታወቅ የግንቦት 7 እስረኞች በተባሉት አማራ ተወላጆ ላይ በጣም  ጸያፍ የሆነ ስድብ ከመጠቀም ጀምሮ  ብልት ላይ ጠርሙስ ማነልጠልና የዘር ፍሬንም መቀጥቀጥ የመሳሰሉ ዘግናኝ ተግባራትን እየፈጸመ መሆኑ መጋለጡ አይዘነጋም::

ኮማንደር ደምሳሽ በወያኔ ዘረኝነት ከሚማረሩት በርካቶች አንዱ ሲሆኑ ለምን እና እንዴት ከአገር እንደወጡ ወደፊት መረጃ አጠናክረን የምናቀርብ መሆናችንን ከወዲሁ እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ከቱኒዝያና ግብፅ እኩያዎቻቸው ሊማሯቸው የሚገቡ ቁምነገሮች

Thursday, February 17th, 2011

“በሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አብዮት ከሰሃራ በታች ወደ አሉ የአፍሪቃ አገሮች ይዳረሳል ወይስ አይዳረስም?” በሚል አፍሪካዊያን በየቦታው ክርክሮች ይዘዋል። ቤን ዓሊ ከቱኒዝያ እንደተባረረ ከፊል ግብፃዊያን ግብፅን ከቱኒዝያ የሚለዩዋት ነገሮች ላይ አጽንዖት እየሰጡ “ግብፅ ቱኒዝያ አይደለችምና እዚያ የሆነው እዚህ ሊደገም አይችልም” እያሉ ሲከራከሩ ነበር። እርግጥ ነው ግብፅ ቱኒዝያ አይደለችም፤ ነገር ግን ቱኒዝያ የሆነው እግብፅም ተደገመ። ህዝባዊው ቁጣ ግብፅ ውስጥ አላበቃም። “ትናንት ሙባረክ፤ ዛሬ አብደላ!!!” የሚሉ መፈክሮች በችጋር በተጎዳችው፤ ውስጣዊ አንድነት በሌላት እና በኢንተርኔት ስርጭትም እጅግ ኋላቀር በሆነችው የመን ውስጥ ተፋፍሟል። በአንፃሩ ደግሞ የኑሮም ሆነ የሥራ አጥነት ችግር እጅግም ያላጠቃትን ባህሬንን አልማራትም። ከአመት በፊት በምርጫ ሰበብ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ በጉልበት በታፈነባት ኢራን ውስጥም አዲሱ አብዩት እግሩን አስገብቷል። ባጭሩ ይህ በዓይነቱ አዲስ የሆነው ህዝባዊ ቁጣ እጅግ በተለያዩ የኑሮና የቴክኖሎጂ እድገት ደረጃዎች ላይ ወደአሉ አገሮች ተዳርሷል።

ስለሆነም ኢትዮጵያ ቱኒዝያ ወይም ግብፅ አለመሆኗ ወይም በአንዳንድ አመላካከቶች እነሱን አለመምሰሏ እዚያ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አብዮት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይዘልቅ ይከለክለዋል ማለት አይደለም።   በዚህም ምክንያት “እኛ ዘንድ ይደርሳል፤ አይደርስም?” በሚል ከመከራከር “ከእነዚህ አገራት ህዝባዊ አብዮቶች  የምንማራቸው ቁም ነገሮች ምንድናቸው?” ብሎ መጠየቅና የጎደሉንን አሟልቶ መገኘት ከፍተኛ የሆነ ተግባራዊ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ከቱኒዝያና ግብፅ የእድሜ አቻዎቻቸው በርካታ ነገሮችን መማር ይችላሉ ብለን እናምናለን። በተለይ ደግሞ ወጣቶቻችን የሚከተሉት ነጥቦችን እንዲያጤኑ እንመክራለን።

  1. ድርጅት፤ አምባገነንነት በሰፈነባቸው አገሮች የዘመኑ ወጣቶች  የሚፈጥሯቸው ድርጅቶች ቀድሞ ከምናውቃቸው የድርጅት ዓይነቶች በእጅጉ የተለዩ ናቸው። የቱኒዝያም ሆነ የግብጽ ወጣቶች ራሳቸውን በጥሩ ሁኔታ ያደራጁ ቢሆንም እንኳን ድርጅቶቻችው በልማድ የምናውቃቸው ዓይነት ግትር መዋቅር ያላቸው አይደሉም። ድርጅቶቻቸው በኦፊሴል ያልተመዘገቡ፤ እየታዩ የማይጨበጡ ዓይነት ኢንፎርማል ስብስቦች ናቸው። እነዚህ ስብስቦች የሥራ ቡድኖች በመሆናቸው እንደ ሥራው ብዛትና ማነስ በቀላሉ የሚሰፉና የሚጠቡ ናቸው። እነዚህ የወጣቶች ድርጅቶች በተለያየ ጊዜዓት የተለያዩ ቅርጾችን ይዘዋል። አንዳንዶቹ በአካል የማይተዋወቁ የፌስ ቡክ ጓደኞች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ደግሞ የኳስ አድናቂዎች ናቸው። ቱኒዚያዊያንና ግብፆች በእንዲህ አይነቱ ተጣጣፊ አደረጃጀት የመንግሥት ሰላዮችን ጭንቅላት አዙረዋል። የኢትዮጵያም ወጣቶች ከቱኒዚያና ግብጽ ወጣቶች በመማር ከኢትዮጵያ ባህልና እድገት ጋር ተስማሚ የሆነ ሆኖም ተጣጣፊ የሆነ አደረጃጀት ሊከተሉ ይገባል።
  2. የመረጃ ልውውጥ፤ በወያኔ  ደባ ምክንያት ኢትዮጵያ አገራችን በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እጅግ ወደ ኋላ የቀረች ቢሆንም ወጣቱ ልዩ ልዩ የፈጠራ ዘዴዎችን ተጠቅሞ  የመረጃ መረቡን ማስፋት፤ ዘመናዊውንም ባህላዊውንም የመረጃ ልውውጥ አቀናጅቶ  መጠቀም ይኖርበታል። ለምሳሌ ከውጭ አገር ወደ አገር ቤት የሚተላለፉ ለእውነት ወገንተኛ የሆኑ የፌድዮና የቴሌቪዥን ስርጭቶች በኢትዮጵያ በስፋት እንዲታዩ ዘመቻ በማድረግ የመረጃ አድማስን ማስፋት ይቻላል። ለእነዚህ ሬድዮዎችና  ቴሌቪዥኖች መረጃዎችን በመስጠትም የጠበቀ  ግኑኝነት መፍጠር ይገባል። ወጣቱ የማያልቅ የፈጠራ ክህሎቱን ለመረጃ ልውውጥ ማዋል ይኖርበታል።
  3. መቻቻል፤ ሰዎች ለትላልቅ ዓላማዎች ሲሰለፉ መለስተኛ ቅራኔዎች ፋይዳ አይኖራቸውም። የነፃነት ትግል ግብፃዊያንን አፋቅሯል። በክርስቲያኖች ጥበቃ ሞስሊሞች ሲሰግዱ፤ ለክርስትያኖች ቅዳሴ ሞስሎሞች ከለላ ሲሰጡ ማየት ችለናል። የሁለቱም ሃይማኖቶች ተከታዮች በጋራ በየእምነቶቻቸው ለነፃነት ፀልየዋል። የኢትዮጵያ ወጣቶች ከዚህ ጠቃሚ ትምህርት ሊቀስሙ ይገባል። የነፃነት ትግል ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታና እድሜ  አይለይም። ነፃነት ሰው በሰውነቱ ብቻ ሊያገኘው የሚገባ  ፀጋ ነው። ሆኖም ግን በግብጽ ሙባረክ እንደሞከረው፤ በየመን አሊ አብደላ ሳልህ እንዳደረገው ሁሉ ወያኔም ህዝብን ከህዝብ በጎዳና ለማጣት እና እሱ ገላጋይ ሆኖ ለመግባት መሞከሩ አይቀርም። ወጣቶች ይህን ቀዳዳ በተቻለ መጠን  ማጥበብ ይኖርባቸዋል። ለዚህ አንዱ መፍትሄ የተቃውሞ  ዓላማን ግልጽ ማድረግ ነው። ዳቦ፣ ሥራ፣ ፍትህና ነፃነት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታና እድሜን አይለዩም።
  4. በራስ የመተማመን ስሜት: ቱኒዚያዊያንና ግብፃዊያን ፍርሃትን ማሸነፍ የቻሉ በራስ የመተማመን ስሜት በመፍጠራቸው ነው። ግብፅ መለዮ ለባሽ ከሆነው የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ውጭ 350 000 የሚደርስ ሰላይና ነጭ ለባሽ አላት ተብሎ  ይገመታል። ይህ ሁሉ ሠራዊት ግን አመጹ እንዳይነሳ ማገድ፤ ከተነሳም በኋላ ማፈን አልቻለም። በራስ የመተማመን ስሜት መተሳሰብን፣ መተጋገዝን፣ የጋራ ጥቅምን ማስቀደምን ይፈጥራል። ወጣቱ በራሱ ሲተማመን ከታላላቆቹ “አመራር” መጠበቅ ይተዋል። ያኔ ነው እውነተኛ ህዝባዊ አብዮት ማካሄድ  የሚቻለው።
  5. መብት፣ ክብር እና ባለቤትነት: በቱኒዝያና ግብፅ ሰብዓዊ መብቶች፣ ሰብዓዊና አገራዊ ክብር እና የሃገር ባለቤትነት ጉዳይ በስፋት የተነሱ ፍሬ ሃሳቦች ናቸው። አገራችን በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ዓለምን ትመራለች። አገራችን ፓሊስ የወንዶችን የዘር ፍሬ፤ የሴቶችን ደግሞ ጡት በመቀጥቀጥ የሚደሰትባት አገር ናት። እንዲህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ተግባር የሚፈጸመው ደግሞ  ሩቅ ሳይሆን በዋናው ከተማ  አዲስ አበባ ውስጥም ነው። በአንድ ወቅት የጂኖሳይድ ዎች ፕሬዚዳንት ዶ/ር ግሪጎሪ ስታንተን እንደተናገሩት አገራችን በአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ውስጥ ትገኛለች። በአንድ ትንሽ ቡድን ቅኝ የመገዛትን ያህል አዋራጅ ነገር የለም። ወጣቱ ከዚህ ውርደት ራሱን ነፃ  አውጥቶ የራሱን ክብር ለማስጠበቅ መነሳት ይኖርበታል። ወጣቱ “ኢትዮጵያ የኔ ናት!” ብሎ እንዲነሳም ያስፈልጋል።

የኢትዮጵያ ወጣት እነዚህ አምስት ነገሮች ከሰሜን አፍሪቃ አቻዎቹ መማር አለበት ብለን እናምናለን። ጊዜ የለም። ሁኔታዎች በፍጥነት እየተቀያየሩ ነው። ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣት ለመብቱ፣ ለክብሩና ለሃገሩ ሲል ዛሬውኑ ይነሳ!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!!

የመለስ አገዛዝ በስጋት ተወጥሯል

Friday, February 11th, 2011

(ግንቦት ሰባት) — በሌሎች መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ እቃዎች ላይ የሚጨመረው ዋጋ ንረት ከዕለት ወደ ዕለት ህዝባችንን የኑሮ ውድነቱን መቋቋም ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ሲያደርሰው “የኢኮኖሚያችን ማደግን አመልካች ነው” እያለ ሲያላግጥ የኖረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በቱንዚያ ፈንድቶ አምባገነኖች ያሉበትን አገራት እያዳረሰ ያለውን ህዝባዊ ቁጣ በመፍራት ጊዜያዊ የሽንገላ እርምጃ መውሰዱን እንደቀጠለ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለግንቦት 7 ዘጋቢ ገለጹ። እንደዘጋቢያችን ምንጮች ቀደም ሲል በአለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መለዋወጥ ሽፋን በሰበብ አስባቡ ይጨምር የነበረው የነዳጅ ዋጋ ላለፉት ወራት እንዳይጨምር ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሆነና በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዕጥረት በአብዛኛው የነዳጅ ማደያዎች በመፈጠሩ ነዳጅ ለመሙላት ታይቶ የማይታወቅ ወረፋ በየቦታው እየታየ መሆኑ ታውቆአል።

ዘጋቢያችን ስለሰሞኑ የነዳጅ ወረፋ መራዘም ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት በቱኒዚያ ተቀጣጥሎ እንደሰደድ እሳት በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት እየተዛመተ ያለው የህዝብ አመጽ እንቅልፍ እንደነሳውና ይህም በመሆኑ በቁዋፍ ላይ ባለው ህዝብ ላይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ቢደረግ አመጹ ድንገት ሊፈነዳ ይችላል ከሚል ፍራቻ መሆኑን ገልጸዋል:: ይሁን እንጂ ቀን መቁጠር ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያዊያን ብሶት አንድ ቀን መፈንዳቱ አይቀሬ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎቹ አክለው ገልጸዋል::

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ባስተላለፈልን ሪፖርት የአዲስ አበባ ከተማና በሌሎች ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዘረኛው አገዛዝ የማሙአያ ምርጫ አካሂዱ በማለት ጥያቄ ቢያቀርብም ለጥሪው ማንም ጆሮ ሳይሰጠው እንደቀረ ለማወቅ ተችሎአሎ:: በዚህም ምክንያት የአምባገነኑ ወያኔ ካድሬዎች በየቦታው እየተዘዋወሩ ህብረተሰቡን ማስፈራራት መቀጠላቸውንም ዘጋቢያችን ከስፍራው ባስተላለፈልን ሪፖርት ገልጹአል::

በተያያዜ ዜና ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በተደጋጋሚ እያደረገ ያለው የብር ምንዛሪን አቅም የማውረድ ርምጃ አሁንም የገበያ ዋጋ ግሽበትን እያባበሰ እንደሆነ ብሉምበርግ የዜና አውታር ባወጣው ዘገባ ላይ አሳይትዋል:: እንደ ብሉምበርግ የዜና አውታር የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት በቅርብ ቀን ከደረሰበት የአስራ አራት ነጥብ አምስት በመቶ ወደ አስራ ሰባት ነጥብ ሰባት በመቶ ማሻቀቡን አስታውቁአል:: ከዚሁ ጋር በተያያዘ የምግብ ዋጋ ከነበረበት የዋጋ ውድነት ደረጃ አሁንም የአስራ ሶስት ነጥብ ስድስት በመቶ እንዲሁም የምግብ እህል ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ ደግሞ የሃያ ሶስት ነጥብ ሰባት በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጨምሮ አስታውቁአል::

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ከደረሰበት የተጠራቀመ ጥላቻ የተነሳ ህዝባዊ አመጽ ሊነሳብኝ ይቺላል ብሎ በመስጋት ሸማቹን ህብረተሰብ ለማስደሰት ከአቅርቦት ጋር በፍጹም የማይጣጣም የዋጋ ተመን በቅርቡ እድርጎ እንደነበረ ይህም ዋጋ ማስተካካያ የተደረገባቸውን የፍጆታ ዕቃዎች ከገቢያ ላይ እንዲጠፋ እንዳደረገው ህዝብ በቅሬታ እየተናገረ ነው።

መለስ ዜናዊ በሙኒክ ጀርመን ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ገጠመው

Thursday, February 10th, 2011

እንደፈረንጆች አቆጣጠር ከፈብሪዋሪ 4 እስከ 6 በሙኒክ ከተማ በተደረገው የጸጥታ |ሴኩሪቲ| ስብሰባ ላይ ለመገኘት በጀርመን የልማት ትብብር ሚንስቴር ተጋብዞ የነበረው ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በጀርመንና አካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እንደገጠመው የግንቦት 7 ድምጽ ተባባሪ ዘጋቢ ከሙኒክ ከተማ በላከልን ዜና ለማወቅ ተችሎአል። ቁጥራቸው ወደ 3 ሺ የሚገመት ኢትዮጵያዊያን በነቂስ ወጥተው ባሰሙት የተቃውሞ ሠልፍ፤ መለስ ዜናዊ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ መለስ ዜናዊ አምባገነንና በዜጎቹ ላይ ሰቆቃ የሚፈጽም ነው፤ መለስ ዜናዊ ሌባ ነው ፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ በኦሮሚያና ሌሎች ቦታዎች ለፈጸመው ዘር ማጥፋት ወንጀል ለፍርድ ይቅረብ ወዘተ የሚሉ መፈክሮች ሲስተጋቡ መዋላቸው ተዘግቦአል።

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን ኢሳት በኢትዮጵያዊያኑ የተደረገውን ተቃውሞ በቀጥታ ከስፍራው ለኢትዮጵያዊያን አድማጮቹ ያስተላለፈ ሲሆን በየግላቸው ተቃውሞ ሰልፉን አስተባብረው የወጡ የኦጋዴን እና የኦሮሚያ ነጻነት አቀንቃኞች የኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻቸውን ሠልፍ በመቀላቀል ጸረ መለስ ዜናዊን መፈክር በጋራ ሲያስተጋቡ እንደዋሉ በምስል የተደገፈ ዘገባ እንዳቀረበ ለማወቅ ተችሎአል።

መለስ ዘናዊ ከድህረ ምርጫ 97 ጀምሮ በየሄደበት ታላላቅ ተቃውሞዎች ሲገጥሙት እንደኖሩና በፈረንጆች አቆጣጠር ዲሰምበር 2006 ዓም በብራስል ከተማ ተዘጋጅቶ በነበረው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ከአዳራሹ ዘልቀው የገቡ ኢትዮጵያዊያን መለስ ዜናዊ ለንግግር መድረክ ላይ እንደወጣ የኢራቁ ሳዳም ሁሴንና መለስ ዜናዊ አንድ ናቸው ፍርድ ይገባዋል በማለት መፈክር ማስተጋባት ሲጀምሩ በድንጋጤ ብዛት ለ20 ደቂቃ የተሰጠውን ንግግር ማጠናቀቅ ተስኖት አንዳቋረጠ በመድረክ ላይ ሆኖም እጅና ከንፈሩ ሲንቀጠቀጥ እንደተስተዋለ በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።

በተያያዜ ዜና በአምባገነኑና ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ግፍና በደል እናት ሃገራቸውን ለቀው በስደት ኖርዎይ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የኖርዎይ መንግስት የስደተኝነት ጥያቄአችንን በአግባቡ አላስተናገደም በሚል ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸውን ዘጋቢያችን ከኦስሎ ኖርዎይ ባስተላለፈልን ዘገባ ገለጸ:: ሰልፈኞቹ የወያኔውን አምባገነን አገዛዝ ዘግናኝ ድርጊቶችና ጭፍጨፋዎች የሚገልጹ ፎቶግራፎችን እንዲሁም መፈክሮችንም መያዛቸውም ታውቁአል::

ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በተለይም በኦስሎ ከተማ ባካሄዱት ሰልፍ የአምባገነኑንና ዘረኛውን መለስ ዜናዊ እንዲሁም የበረከት ስም ኦን፣ አዜብ መስፍንና ሌሎችንም የአምባገነኑ ስርአት ቁኝጮዎች ፎቶግራፎቸ ኦስሎ ከሚገኘው የኖርዎይ ፓርላሜንት ጽ ቤት ፊት ለፊ በእሳት ማቃጠላቸው ታውቁአል::

እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ኢትዮጵያዊያኑ በኖርዎይ ያደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ በዋነኛነት በኦስሎ ከተማ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የኖርዎይ ከተሞችም ጭምር መሆኑን ለማወቅ ችለናል:: በኦስሎ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ ሰልፈኞች የተገኙ ሲሆን ሰልፈኞቹ ከፖልኪሶች ጋርም መጋጨታቸው ታውቁአል:: ይሁን እንጂ ከፖሊስ ጋር በተደረገው ግጭት የደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ዘጋቢያችን ጨምሮ ገልጹአል::

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደረሰን ዘገባ ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በኦስሎ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ካካሄዱ በሁአላ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት ከቤተክርስትያኑ አንወጣም ማለታቸውንና የኖርዎይ መንግስት ተገቢዉን መልስ የማይሰጣቸው ከሆነ ጥያቄአቸውን ማቅረብ እንደሚቀጥሉ በመግለጽ የረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ ዘጋቢያችን ባስተላለፈልን ሪፖርት አስታውቁአል::

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ባለው ጥፋት ምክንያት እጂግ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለስደት እንደሚዳረጉ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በስደተኞች ብዛት የቀዳሚነት ስፍራን እየያዘች መምጣቱአን መዘገባችን ይታወሳል::

ለስኬታማ ህዝባዊ አመጽ ልንጠቀምባቸው የሚገቡን ዘዴዎች

Thursday, February 3rd, 2011

የሰሜን አፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ወጣቶች፥ “አገሮቻችን ከዚህ የተሻሉ ናቸው፤ ያለንበት ችጋር፣ ጭቆና እና ውርደት መገለጫችን ሆኖ ሊቀር አይገባውም። እንዲህ ባለ ኋላ ቀርነት ውስጥ እራሳችንን ልናይ አልቻልንም። የተቀረው አለም ህዝብ እርቆ ሄዷል፤ እኛ ምን አንሶብን?” በሚል ጥያቄ፤ ንዴት እና ቆራጥነት ተነሳስተው የነጻነትን እሳት አቀጣጥለዋል።

ቱኒዚያውያን ከአንድ ወራት በፊት ለሃያ ሶስት አመታት የገዛቸውን አምባገነን ካስፈረጠጡት በኋላ፣ የነጻነት መንፈስ እሳት በግብጽ ላይ ወርዶ ለአስርተ አመታት የቆየን ፍርሃት በልቶታል። ቀድሞ አንገታቸውን ዝቅ ያደረጉ ቀና ብለዋል። ትናንት ፖሊስ ጌታ ነው ብለው ያመኑ ድሃ አደጎች የትልቅነትን መንፈስ ተላብሰዋል። የሰለሉ እጆች ጠንክረዋል። የተሰበሩ መንፈሶች ተገጣጥመዋል። የፈረሱ ግንቦች ተጠግነዋል። የጠወለጉት አበቦች ለምልመዋል። ጨለማን ያዩ የነበሩ በተስፋ ተሞልተዋል። ትናንት ሲረገጡ እራሳቸውን ዝቅ አድርገው የተቀበሉ፤ ዛሬ በቀጥቃጦቻቸው ትክክል ቆመው እውነትን በድፍረት የሚናገሩ ሆነዋል።

ለሰላሳ አመታት በአንድ ገዢ በትር ስር የኖሩት ልጆች፣ የነጻነት ጸሃይ ከአድማስ ባሻገር ተደብቃ እንዳትቀር በጩኸታቸው አስገድደዋታል…እሷም ብቅ የምትል ትመስላለች።

ህዝባዊው ሞገድ ግብጽ አላቆመም። የመንም እየተናወጠች ነው። አልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ ዮርዳኖስ፣ እና ጎረቤታችን ሱዳንም እጣ ደርሷቸዋል። በሳውድ አረቢያ እና በጋቦንም መለስተኛ የተቃውሞ ሰልፎች ተስተውለዋል። የአልጄሪያ እና የሶሪያ የዴሞክራሲ ታጋዮች በሚቀጥለው ወር የተሟሟቀ ተቃውሞ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙም ተሰምቷል።

እንግዲህ ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ፤ በተለይም ከስኬታማው የቱኒዚያ ንቅናቄ እና ግብጽን እያንቀጠቀጠ ካለው እንቅስቃሴ በስተጀርባ፤ የሚያስገርሙ የወጣቶች የፈጠራ ሃሳቦች እና ድርጅቶች ተስተውለዋል። ለረዥም አመታት፥ በርካቶች በነዚህ አገራት እንዲህ ያለ ህዝባዊ አመጽ መንግስት ሊጥል አይችልም፤ የመንግስታቱ አፈና ከባድ ነው ብለው ሲያጣጥሉ ቆይተዋል። ያም ደግሞ በተወሰነ ደረጃ እውነት ነው፤ ህዝቡ እነዚህን ሰልፎች ለማካሄድ ብዙ መስዋእትነት እየከፈለ ነው። ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች፥ ይህ የሚካሄደው በአገራችን ቢሆን ኖሮ ከዚህ እጅጉን የከፋ እና በብዙ እጥፍ ያየለ መስዋእትነት እንደሚከፈል ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ፥ በነዚህ በሰሜን አፍሪካ አገራት ከተከሰቱ ህዝባዊ አመጾች የምንማረው አንድ ቁምነገር አለ። ይህም ቁምነገር ለአገራችን ወጣቶችም ቢሆን አስተማሪ ነው። በአጭሩ ሲቀመጥ፥ “ለሁሉ ችግር መፍትሄ ያለው በገዛ እጃችን ውስጥ ነው።” የሚለው ነው። በአሁኑ ሰዓት፥ በኢትዮጵያ ውስጥ የአመጽ ሰልፍ የጠራ ቡድን የለም። ይሁን እንጂ፥ በሰሞኑ ክስተቶች በመገፋፋት፣ ብዙ ወጣቶች ተነሳሽነት እያሳዩ ይገኛሉ።

ስለዚህም የቱኒዚያ እና የግብጽ ወጣቶች፥ ከነፍሰ ገዳይ የመንግስት የደህንነት ሃይሎች እና ፖሊሶች ለማምለጥ እና ስኬታማ አመጽ ለማካሄድ ከተጠቀሙባቸው ዘዴዎች ውስጥ የተወሰኑትን፤ እንዲሁም ሌላ ቦታ የተገኙ ሃሳቦችን ሰብስበን ለማካፈል ወደናል። እንደሚከተለው እናቀርባቸዋለን።

  1. በቱኒዚያ እና በግብጽ ህዝባዊው አመጽ ያለ ከልካይ እንደ ጎርፍ እንዲፈስ ከረዱት ዘዴዎች አንዱ፥ ሰልፈኞቹ በፖሊስ ላይ ያሳዩት ብልጣብልጥነት/ወይም ወጣቶቻችን እንደሚሉት ሽወዳ ነው። የፖሊስ መኪና ሊገባባቸው በማይችሉ ትናንሽ የመንደር መንገዶች ላይ በየሰፈሩ መሰብሰብ እና ሰልፉን እና የአብሮነትን ስሜት ማሟሟቅ፤ የፖሊስ ወይም የደህንነት ሰራተኞች ቁጥር ከህዝብ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ሁልጊዜም ቢሆን ዝቅተኛ መሆኑን መረዳት፤ በተጨማሪም፥ ፖሊሶች ብቻቸውን ወዲያ ወዲህ ለማለት ስለሚፈሩ በቡድን መጓጓዛቸው ሽፋናቸውን እንደሚቀንስባቸው ማወቅ፤ እና የመሳሰሉት ተስተውለዋል።
  2. በቱኒዚያ፥ ሰልፎች የጀመሩት በትናንሽ ከተሞች ነው። ከዛ ቀስ እያሉ ወደ ዋና ከተማው መጡ። ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ፥ የአዲስ አበባ ህዝብ ብቻውን የተጨፈጨፈው ተቃውሞ የተጀመረው እዛ ስለሆነ እና አብዛኛው ፌዴራል ፖሊስ እና በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ የጦሩ አባላት በመዲናይቱ ስለተሰባሰቡ ነው። ተቃውሞ የሚጀመረው በሺሆች በሚቆጠሩት የኢትዮጵያ መንደሮች ቢሆን ግን፥ አገዛዙ ያንን ለመቆጣጠር ሲል ፖሊሶቹን ወደየክፍላተ አገራቱ ይልካል። ያም ሃይሉን ይለጥጥበትና ይዳከማል። አዲስ አበባ ላይ ሃይሉ ከተዳከመ ደግሞ፥ በሚሊዮኖች የሚቆጠረው የከተማይቱ ህዝብ የተቀሩትን የፖሊስ እና የደህንነት ሰራተኞች ተቋቁሞ የአራት ኪሎን ቤተመንግስት እንደ ንብ የማይወርበት እና አምባገነኑን በቁጥጥር ስር የማያውልበት ምንም ምክንያት አይኖርም። አገዛዙ ይህንን ፈርቶ በገጠር የሚከሰቱ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር የጦር ወይም የፌዴራል ፖሊስ ሃይሎችን ካልላከ ደግሞ፣ ያም ይጎዳዋል። ምክንያቱም፥ እያንዳንዱ የገጠር ነዋሪ እየተነሳ የወያኔ ካድሬዎችን፣ ሰላዮችን እና ሚሊሻዎችን በቁጥጥር ስር ሲያውል፤ ቀጥሎ ያለው መንደርም የልብ ልብ እያገኘ ያንኑ ያደርጋል፤ ያም እየተስፋፋ ይሄድና የአገዛዙን ውድቀት ያፋጥነዋል።
  3. ፖሊስን ማዳከም። ሰሞኑን በግብጽ፥ ወጣቶቹ ከፖሊስ ጋር የድመት እና የአይጥ ጫወታ ሲጫወቱ ነበር ይባላል። አንድ የፖሊሶች ቡድን መጥቶ አንድ የወጣቶች ስብስብ በስንት መከራ ሰብሮ እና ወጣቶቹን በተለያየ አቅጣጫ አሯሩጦ እፎይ ከማለቱ፤ በአስር አቅጣጫ የሮጡት ልጆች መንደራቸውን ከማንም በላይ ስለሚያውቁ እንደገና አንድ ቦታ ተሰብስበው ቁጭ ይላሉ። ፖሊስን የማዳከም ጥቅም እራሱን የሚገልጠው ህዝባዊ አመጹ ለቀናት ሲቀጥል ነው። የተዳከመ ፖሊስ ህዝቡን መጋፈጥ ይሳነውና ሰልፉ ከቁጥጥሩ ውጪ ይሆናል፤ የስፋም ይቆርጣል።
  4. የፈረቃ ሰልፍ። የግብጽ የሰልፍ አቀናባሪዎች፤ ህዝቡ በፈረቃ ሰልፍ እንዲወጣ መልክት አስተላለፉ። ማለትም፥ የመጀመሪያው ፈረቃ ለስምንት ሰአታት ሲሰለፍ፣ ሁለተኛው ለቀጣኡ ስምንት ሰዓታት፤ የተቀረው ደግሞ ለቀጣዩ። ህዝቡ ብዙ ሚሊዮን ከመሆኑ የተነሳ፣ እንደዚህ እየተፈራረቀ ሌሊቱን ሙሉ መንገድ ላይ ለመቅረት ይችላል። ፖሊሶች ግን በቁጥር ትንሽ ስለሆኑ፣ እንደዚህ በፈረቃ እንስራ ቢሉ ቁጥራቸው የባሰውኑ ያንሳል። ይህ ፖሊሶቹን ከማዳከሙ በተጨማሪ፤ ሌሊት ላይ በየቤቱ በመዞር የአመጹ መሪዎች ናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን ዜጎች ለማሰር የሚያስፈልጋቸውን ፋታ አይሰጣቸውም።
  5. የታቀደ መበታተን እና ፖሊስን አሳስቶ ህዝቡ ወደሚፈልገው አቅጣጫ መምራት። በአንድ ወቅት በመራቤቴ አካባቢ፣ ህዝብ አምጿል የሚል ወሬ ተሰምቶ፣ ያንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ወደ ከተማዋ የተላኩትን የደህንነት ሰራተኞች፣ ህዝቡ “ሽፍታ! ሽፍታ!” ብሎ እየጮኸ ወደ ጫካ መራቸው ይባላል። እዛ ምን እንደተደረጉ አይታወቅም። ነገር ግን ተመልሰው አልመጡም። ለማንኛውም፥ በተለያየ አቅጣጫ በመበተን እና ፖሊሶች ተከትለው እንዲመጡ በማድረግ፤ ህዝብ የቁጥር አብላጫ ያለው መስሎ ከተሰማው፤ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው ይችላል። ይህኛው ዘዴ፥ ፖሊስ እና ደህንነት ከማዳከም አኳያም ትልቅ ጥቅም አለው።
  6. ብቁ የሆነ የመረጃ መለዋወጫ እና ለህዝብ መልክት ማስተላለፊያ ማግኘቱም ለሰልፎቹ ስኬት ቁልፍ ነበር። ቱኒዚያ እና ግብጽ ከአገራችን ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ የሆነ የኢንተርነት አገልግሎት ሽፋን ያለባቸው አገራት በመሆናቸው ወጣቶች ለመገናኘት እና ሃሳብ ለመለዋወጥ ችግር አልነበረባቸውም። ይሁን እንጂ፥ መንግስታቶቻቸው አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ ያም ተዘጋባቸው። ያ ግን ተቃውሟቸውን አላቆመውም። በሁለቱም አገራት፥ ደርግን የሚቃወሙ ወጣቶች በአገራችን ያደርጉ እንደነበረው፣ ወጣቶች በየግድግዳው ላይ መፈክሮችን በመጻፍ ህዝባቸውን ያበረታቱ እና አምባገነኖቹን ይቃወሙ ነበር።
  7. ሰሞኑን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ፌስቡክ በተባለው የኢንተርነት መገናኛ መረብ ላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ሲካፈሉት አየሁ ብለው አንድ አድማጫችን የላኩልን ዘዴ ደግሞ በብር ላይ ተቃውሞን መጻፍ ነው። ይህ ሃሳብ ከዚህ ቀደም በሌሎች አገራት በስራ ላይ የዋለ ሲሆን፤ ብር እራሱን በራሱ ስለሚያጓጉዝ መልክቶች በፍጥነት እንዲዘዋወሩ ይረዳል።
  8. መልክቶችን የአገዛዙ ሰላዮች ሳያዩ ማዘዋወር በትኩረት ቢታሰብበት ከማንም በላይ ለኢትዮጵያውያን ይቀላል። ከጥቂት አስርተ አመታት በፊት አደን ማደን በህግ ክልክል ነው የተባሉ አባቶቻችን፤ ባጠመዱት ወጥመድ ሲሮጥ መጥቶ የገባላቸውን ድኩላ ደብቀው ወደቤት ለመውሰድ ችግር አልነበረባቸውም። በኬሻ ጠቅልለው አህያ ላይ ይጭኑትና፤ ከላዩ ከሰል ወይም እንጨት ይጭናሉ። ድኩላ ጭኖ ብዙ ኪሎሜትር ሳይነቃበት መሄድ የሚችል ኢትዮጵያዊ ታዲያ፣ ጥቂት መቶ በራሪ ወረቀቶችን ከአዲስ አበባ ደብረብርሃን፤ ወይም ወልቂጤ መውሰድ እያቅተውም።
  9. መረጃን የማከፋፈል ስራን የሚወስዱ ሰዎች ለህዝባዊ አመጽ ቁልፍ ከመሆናቸው የተነሳ፣ የአምባገነናዊ አገዛዞች የደህንነት መዋቅር ዋና ኢላማዎች ናቸው። ስለዚህም በጥንቃቄ መመላለስ አለባቸው። ለምሳሌ፥ በራሪ ወረቀቶችን እያባዙ ማከፋፈሉን በአንድ ማእከላዊ ስፍራ ከመስራት ይልቅ፤ ለተለያዩ እና ለማይተዋወቁ አካላት ማከፋፈሉ ይቀላል።
  10. እራስን መከላከል። አምባገነኖች ሲጠበቡ፤ ሰው ከቅጠል ለይተው አያዩም። አገርንም ከአንድ ብጣሽ ወረቀት አስበልጠው አያዩም። መጨፍጨፍ ያለባቸውን ይጨፈጭፋሉ፤ ማቃጠል ያለባቸውን ሁሉ ያቃጥላሉ። በአንድ አገር ለውጥ የማምጣት ተግባር፤ በተለይም አምባገነናዊ አገዛዝን የማስወገድ ስራ፤ መስዋእትነትን የሚያስከፍል ነው። ከቤትህ ስትወጣም ይህንን አውቀህ ነው። ይሁን እንጂ፥ እስከ ሞት የሚደርስ መስዋእትነት ለነጻነትህ እና ለአገርህ ለመክፈል ዝግጁ ብትሆንም፤ እሞታለሁ ብለህ ግን ከቤትህ አትውጣ። አላማህ ለመኖር፤ ድል ለማድረግ እና ነጻ አየር ለመተንፈስ ይሁን። ውድ የሆንክ የፈጣሪ ልጅ መሆንህን፤ አገርህም ከመኖርህ እንጂ ከመሞትህ እንደማታተርፍ አትርሳ። ስለዚህ እራስህን ከጥቃት መከላከልን ጠንቅቀህ አስበህበት ውጣ።
  11. የመለስ ዜናዊ አገዛዝ፥ ባለፉት አምስት አመታት ሰልፈኞችን መቆጣጠር በሚችልበት መንገድ ላይ ከምእራባውያን መንግስታት ስልጠና አግኝቷል። በርካቶች፥ አገዛዙ ገና ከጅማሬው ግብጽ እና ቱኒዚያ እንዳደረጉት አስለቃሽ ጭስ መርጨት ሳይሆን፣ ጥይት መተኮስ እንደሚጀምር ይገምታሉ። ያ እንዳለ ሆኖ፥ ለይስሙላ ያህል፤ ለፈረንጆቹ፥ “ይኸው የሰጣችሁኝን ጋስ ተጠቅሜበታለሁ” ለማለት፤ ወይም ከተኩሱም አቀላቅሎ አስለቃሽ ጭስ የሚረጭ ከሆነ፤ በኮምጣጤ እና በሎሚ ጭማቂ የተነከሩ ሻሾችን ይዞ ከቤት መውጣት እና ጋሱ መረጨት ሲጀምር ያንን ወደ አይን ማቅረብ ይረዳል ይባላል። ለማንኛውም፥ አፍና አፍንጫ ለመሸፈን፤ እንዲሁም በወገን ላይ አደጋ ቢደርስ ቁስል መሸፈኛ እንዲሆን፤ በተቻለ መጠን ነጠላ እና ሻሽ ይዞ ከቤት በውጣት ይጠቅማል።
  12. ምግብና ውሃ። የትግራዩ ገዢ ቡድን፥ ከዚህ ቀደም ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ጋር ጦርነት በሚያካሄድበት ወቅት፤ ወደ ኦጋዴን የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋት ህዝቡን በረሃብ የመጨረስ “ስልት” ተብዬ ጭካኔ ተጠቅሞ ነበር። አምባገነናዊ አገዛዞች አልገዛ ያላቸውን ህዝብ በማስራብ ይታወቃሉ። አገዛዙ አሁንም ተቃውሞ ቢነሳበት፤ ይህንን ስልት ሊጠቀም ይችላል። ይሁን እንጂ፥ ይህ ኢትዮጵያውያንን የሚያሰጋ ጉዳይ አይደለም። በአገራችን፥ እንኳን በመንደሮች እና በትናንንሽ ከተሞች ይቅርና፤ በመዲናይቱ ውስጥ እንኳ፣ ብዙው ሰው ትንሽም ትሁን ጓሮ እና ግቢ አለው። ይህ ማለት ደግሞ፥ ቲማቲም፣ ካሮት፣ ጎመን፣ ድንች እና የመሳሰሉትን በቀላሉ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ማብቀል ይችላል። እነዚህ አትክልት፤ ያለ እንጀራ በተለያየ መልክ ተዘጋጅተው ሊበሉ ይችላሉ። እንደ ስኳር እና የምግብ ዘይት የመሳሰሉትን ለተወሰነ ጊዜ ማጣት በሰውነት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት የለም። የመጠጥ ውሃ ችግርን ለመቀነስ፤ እያንዳንዱ መንደር በመተባበር ቢሪ/ወይም የውሃ ጉድጓድ መቆፈር ይችላል። የጉድጓድ ዉሃ ብዙውን ጊዜ ለመጠጥነት ንጹህ ቢሆንም፤ በቀላሉ ማጽዳት፣ ወይም አፍልቶ እና አቀዝቅዞ መጠጣት ይችላል። እንግዲህ እነዚህ ከሁሉ አስቀድሞ ሊደረጉ የሚገባ ዝግጅቶች ናቸው።
  13. የአላማ ጥራት እና ጽናት። የምናምጽበትን ምክንያት ጠንቅቀን ማወቅ ከብዙ አደጋ ይጠብቀናል። በራሳችን እና በአገራችን ላይ ጊዜያዊም ሆኔ ዘላቂን ጉዳት ከማድረስ ያተርፈናል። ሰሞኑን በግብጽ፥ ተስፋ የቆረጠው መንግስት የደህንነት ሰራተኞቹ እና ከእስር የተለቀቁ ወንጀለኞች የህዝብ እና የአገር ንብረት እንዲዘርፉ መንገድ ላይ ለቋቸዋል። የዚህ ዘረፋ ሰለባ ከሆኑት ተቋማት እንዱም ከአለም ታሪካዊ ቅርሶች ውስጥ ሶስት አራተኛውን ይዟል የሚባለው የአገሪቱ ሙዚየም ነው። ይህ ሲሆን፤ ሰልፈኞቹ እጅ ለእጅ ተያይዘው በሙዚየሙ ፊት በመቆም ከዘራፊዎቹ ጋር ትልቅ ተጋድሎን በማድረግ የአገራቸውን ሃብት ተከላክለዋል። ይህ ሲሆን፥ ሰልፈኞቹ ዞር ብለው ከዘረፋው በመቀላቀል እራሳቸውን ሊጠቅሙ ይችሉ ነበር። ነገር ግን የወጡበት አላማ ያ እንዳልሆነ፤ ከምንም በላይ ደግሞ የአገርን ሃብት እና ቅርስ መጠበቅ የያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት እንደሆነ ስለተረዱ በርትተው ቆሙ። የትግራዩ ገዢ ቡድን ባለስልጣናት፥ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶች ከአገር እያስወጡ እንደሚሸጡ ከዚህ ቀደም ተወርቷል። በቅርቡ በኢትዮጵያ ህዝባዊ አመጽ ቢከሰት፣ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው የተለያዩ የህዝብ እና የመንግስት ተቋማትን ለማስዘረፍ እንደሚሞክሩ እና በሰልፈኞች ላይ እንደሚያላክኩ ይገመታል። ዝርፊያ በሌለበት ዝርፊያ ተፈጽሟል ብለው እንደሚከሱ ከምርጫ 97 ልምዳችን እናውቃለን። ታዲያ በእንዲህ አይነቱ ወቅት የአገርን ሃብት ሊጠብቅ የሚችለው ዜጋው ብቻ ነውና፤ ለዚህ እንዘጋጅ።
  14. የመለስ ዜናዊ አገዛዝ፥ ከዚህ ቀደም ጭንቀት ውስጥ ሲገባ የዘር እና የሃይማኖት ግጭት እንደሚያነሳሳ ከልምዳችን እናውቃለን። ወደፊትም ቢሆን አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ ያንን ለመቀስቀስ ተዘጋጅቶ እና፤ ያንን ስራ የሚሰሩለትን ሰዎች በዙሪያው ኮልኩሎ እንደሚቀመጥ ጠንቅቀን እናውቃለን። ባለፈው ሳምንት በግብጽ የሆነው ክስተት ከዚህ አኳያ ትልቅ ትምህርት ሊሆነን ይችላል። ሙስሊሞች ወደ ጁማአ ጸሎት ሲገቡ፤ ክርስቲያን ወንድሞቻቸው ውጪ ቆመው ጸሎተኞቹን እና መስጊዶችን እንደሚጠብቁ ቃል ገቡ። እኛም በኢትዮጵያችን እንደዚህ ያለ ፍቅርን እና መተሳሰብን ልናሳይ ይገባናል። ከሁሉ አስቀድመን፤ ባህላችን እና ሃይማኖቶቻችን ስለ ጉርብትና የሚያስተምሩንን አንርሳ። መለስ ዜናዊ የሲቪል ልብስ የለበሱ ቅጥረኞቹን አሰማርቶ በዚህና በዚያ ዘውጌ ማህበረሰብ ላይ፤ በዚህና በዚያ ሃይማኖት አባላይ ላይ ተነሳ እያለ በጆሮህ ቢያንሾካሹክ፤ ጥላቻን የሚያውጆ በራሪ ወረቀቶች በአገዛዙ ሰዎች ተዘጋጅተው ቢበተኑ፤ አንዱንም አትስማ። አንተ የወጣኸው ነጻነትን እና የተሻለ ኑሮን ፍለጋ እንጂ ወገኖችህን ልታጠቃ አይደለም። ስለዚህም፥ በአቋምህ ጽና።
  15. ሰልፈኞች፥ የህዝብ ንብረት እነሱን ለማፈኑ ስራ ጥቅም ላይ ሲውል ሲያዩ፤ ያንን ንብረት እንደ ጠላት ንብረት ያያሉ። ለምሳሌ በግብጽ በርካታ የፖሊስ መኪናዎች ተቃጥለዋል። ህዝቡ ይህን በማድረጉ ወንጀል አልፈጸመም፤ እራሱን የመከላከል መብት ስላለው። ይሁን እንጂ፥ ይህ አምባገነኖች የሚጠቀሙበት ተሽከርካሪ ወይም ህንጻ፤ ዞሮ ዞሮ የኛው ንብረት ነው። ሲቃጠል የሚከፍለው ህዝብ ነው እንጂ አምባገነኑ አይደለም። ታዲያ እንዴት አድርገን እራሳችንን እንከላከል? ላሰበበት ሁልጊዜም ቢሆን የተሻለ አማራጭ አይታጣም። ለምሳሌ፥ ሰሞኑን አንዳንድ ብልጥ የግብጽ ወጣቶች፤ የፖሊስ ተሽከርካሪዎችን በማቃጠል ፈንታ፤ ባትሪዎቻቸውን በማስወገድ እና ከፖሊሶቹ አይን በመሰወር መኪናዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ አድርገዋል። ይህ አንድ ዘዴ ነው።
  16. ድፍረት። እንግዲህ አምባገነናዊ አገዛዞችን ለመገልበጥ፤ በመጀመሪያ ፍርሃትን ማሸነፍ ይገባል። በአመጽ ስራ የሚሳተፉ ሰዎች፤ ብዙ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ፍርሃት እንደሚሰማቸው ይናገራሉ። ነገር ግን የመጀመሪያዋን እርምጃ ከወሰዱ በኋላ፤ ስጋታቸው እየሟሸሸ ይሄድና ጨርሶ ይጠፋል። ስለዚህ፥ ጀግና ሁሉ ከፍጥረቱ ጀምሮ ደፋር ነበር የሚል አመለካከት ከያዝን ተሳስተናል። ድፍረት የሚገኘው በሂደት ነው። እናም የመጀመሪያዋ እርምጃ ወሳኝ ነች።

እንግዲህ፥ እነዚህ የሃሳብ ስብስቦች ያቀረብነው፤ ለችግር ሁሉ መፍትሄ በገዛ እጃችን እንዳለና፤ ለሰው አእምሮ የማሰብ ችሎታ ማቆሚያ እንደሌለው ለማሳሰብ ያህል ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ከቱኒዚያ እና ከግብጽ ወጣቶች በምንም በኩል አያንሱም። ማለቂያ የሌላቸው ግሩም ሃሳቦች ማፍለቅ እንደሚችሉ አንጠራጠርም። ከምንም በላይ ልናስታውሳቸው የምንወደውም ይህንኑ ነው። እንደሚችሉ!

ህዝባዊ አመጽ ከቱኒስ ወደ ካይሮ እና ሰንዓ፤ አዲስ አበባስ?

Sunday, January 30th, 2011

በቱኒዚያ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ እንደ ሰደድ እሳት ወደ አካባቢው አገሮች እየተዛመተ ነው። ወላፈኑ አልጄሪያ፣ ሞሮኮና ሊባኖስን አዳርሶ አልባኒያ ደርሷል። አሁን የእሳቱ ሰደድ ግብጽና የመን ውስጥ በመንቦግቦግ ላይ ይገኛል።

ሰሜን አፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የለውጥ ማዕበል ውስጥ ናቸው። የአምባነኖች ጡንቻ መፈርጠም፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መዳከም ህዝቡን ከትግል እንዲሸሽ አላደረገውም። እንደ ቱኒዚያው መሃመድ ቦዛዚ እንደየመንዋ ታዋኮል ኮርማን ያሉ “እስካሁን በነበርንበት ሥርዓት ከምንቀጥል ህይወታችን ማጣት ይቀለናል” የሚሉ ወጣቶች ተበራክተዋል።

የአንባገነነት መንሰራፋት፤ “በመተካካት” ስም ስርወ-መንግሥት የማቋቋም ህልም፤ የፍትህ እጦት፤ የውሸት ምርጫዎች መብዛት፤ የሰብዓዊ መብቶች መረገጥ፤ የሥራ አጥነት መበራከት፤ የፓሊስ፣ ጦር ሠራዊትና እና “የጆሮ ጠቢዎች” መብዛት፤ የኑሮ መወደድ እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መዳከም ከቱኒዚያም ሆነ ከግብጽ ይልቅ የኢትዮጵያው አምባገነን መለያ ባህርያት ናቸው።

ለውጥ እንደ ወረርሽን የመሰራጨት ኃይል አለው። በአንዱ አገር የተነሳው ተቃውሞ ወደ ጎረቤት ለመዛመት ጊዜ አይፈጅበትም። እናም ቱኒዝያ የተጫረው እሳት በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የሰሜን አፍሪካንና የመካከለኛ ምሥራቅ አገሮችን መንካቱ በጭራሽ የማይቀር ነገር ነው። በእነዚህ አገሮች ሁሉ የሥርዓት ለውጥ ከመጣ አዲስ ጂኦ-ፓለቲካ ይፈጠራል።

ይህ የሰደድ እሳት አዲስ አበባ ሊደርስ ይችላል። ከላይ እንደተገለፀው ኢትዮጵያ ከሰሜን አፍሪካና መካከለኛ ምሥራቅ የምትጋራቸው በርካታ ባህርያት አሉ። በኢትዮጵያውያን እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ በግብጽም በየመንም ከበደረሰው በብዙ እጥፍ ይበልጣል፤ እኛ ዘንድ ያለው ችጋርም እነሱ ዘንድ ካለው ጊዜዓዊ ረሃብ ጋር የሚወዳደር አይደለም። አገራችን በአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ሥር በመሆኗ ህዝባዊ እምቢታን ካረገዘች ቆይቷል። ቅራኔዎች ለመፈንዳት ሰበብ መጠበቅ ከጀመሩ ውሎ አድሯል። ስለሆነም ዛሬ ካይሮና ሰነዓ እያየነው ያለው ህዝባዊ ትዕይንት ነገ አዲስ አበባ ውስጥ ልናየው እንችላለን።

ይህ መልካም ዜና ቢሆንም ሥጋትም አለብን። እኛ ኢትዮጵያውያን ወያኔ የተከለብን ተጨማሪ በሽታ ስላለብን ጥንቃቄዓችን የላቀ መሆን ይኖርበታል። ወያኔ በዘር ያደራጀው ጦር ከህዝብ ጋር ይወግናል ብሎ መጠበቅ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ወያኔ የተከለብን ዘረኝነት እኛንም ጠልፎ እንዳይጥለን ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ እንዲነሳ ይጠይቃል። እኛም ለመብቶቻችን መቆም ግዴታችን ነው ይላል። የነፃነትና የዲሞክራሲ ወገንተኛ የሆን ፓርቲዎች ሁሉ እየተፈጠረ ያለውን ሁኔታ በንቃት እንድንከታተል፤ ተመሳሳይ ሁኔታ በአገራችን ቢከሰት መከተል ስለሚኖርብን ስልቶች እንድንወያይና፤ በጋራም በግንባር ቀደምትነት እንድንቆም ያሳስባል። የወያኔ ዘረኛ አወቃቀር የትግላችንን አቅጣጫ እንዳያስት ሁላችንም በኃላፊነት እንንቀሳቀስ ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የወያኔ የዋጋ ተመን ምንነትና ለምንነት

Thursday, January 27th, 2011

ዶ/ር ታደሰ ብሩ

“ሰባራ ዜና” እንደ “ሰበር ዜና”

ሥጋ በኪሎ 52 ብር እንዲሸጥ ተወሰነ!!!

ይህ ዜና ምን ስሜት ፈጠረባችሁ? እንደምሰማው ከሆነ ዜናው ብዙ ሰዎችን አደናግሯል። አንዳንዶች “የተለመደ የወያኔ ማጭበርበሪያ ነው” በማለት ሲያጣጥሉት፤ ሌሎች ደግሞ “ዘገየ እንጂ መልካም ተግባር ነው” ሲሉ አወድሰውታል።

ለእኔ ዜናው ሰባራና አስቂኝ ነበር። አሁን ይህንን ማስታወሻ ስጽፍም እየሳቅኩ ነው። ያም ሆኖ ግን አንዳንዶች በዚህ ዜና መደሰታቸው ገርሞኛል፤ አስግቶኛልም። “ለካስ እኛ እንዲህ በትንሽና በማይመስል ነገር የምንታለል ነን?” እንድል አድርጎኛል። ይህንን ማስታወሻ እንድጽፍ ያነሳሳኝ አንዱ ምክንያትም ይኸው ስጋት ነው። እንዴት ይኸ ሰባራ ዜና ደህና ነገር ያመጣል ተብሎ ይታሰባል?

“ነገር በምሳሌ …” እንዲሉ አስተያየቴን በምሳሌ ላስረዳ። አማካይ ክብደት ያለው ሠንጋ በሬ 5000 ብር እየተሸጠ ባለበት ሰዓት አንድ መወደድ የፈለገ ሹም “ከዛሬ ጀምሮ የአንድ በሬ ዋጋ 3000 ብር ነው” ብሎ አወጀ እንበል። መቸም በሬዎች ሁሉ እኩል አለመሆናቸው ለመረዳት አይቸግረንም። ሻጩም ገዢውም ይህንን ያውቃሉ። እናም አዋጁ እንደወጣ ሰዎች ምን እንደሚያደርጉ ለመገመት አያዳግትም። ሸማቹ አዋጁ እንደወጣ ተሯሩጦ ትልልቁን በሬ በ3000 ብር ይሸምታል። ይህ መብት ለሻጭ የተነፈገው ካልሆነ በስተቀር ሻጭም የራሱን በሬ በ3000 ብር መግዛት ያዋጣዋል (ይህ እንግዲህ “በሬ የመደበቅ ወንጀል” የማያሳስር ከሆነ ነው)።

ጥቂት እድለኛች ተሯሩጠው ትላልቅ በሬዎችን በርካሽ መግዛት ይችሉ ይሆናል። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ገበያው አዲሱን ሥርዓት ይለምዳል። ትልልቆቹ ተሸጠው ያልቃሉ። ትንንሾቹ ደግሞ ከባለ 3000 ዎቹ በላይ እንዲደልቡ (እንዲወፍሩ) ገበያው አይፈቅድላቸውም። አዋጁ ባይኖር ኖሮ 1000 ብር ያወጣ የነበር ጥጃ ዛሬ 3000 ብር ስለተለጠፈበት ብቻ የሚገዛው ያገኛል ማለት አይደለም (ይህ እንዲሆን ሻጭን ብቻ ሳይሆን ገዢንም ማስገደድ ይጠይቃል)። አዲሱ ሥርዓት ሲለመድ ወደ ገበያ የሚመጡት በሬዎች ድሮም ቢሆን በ3000 ብር ሲሸጡ የነበሩት ዓይነት ብቻ ይሆናሉ። በሌላ አነጋገር በገበያ ውስጥ የምናያቸው በሬዎች እንደፋብሪካ እቃ ተመሳሳይ ይሆናሉ ማለት ነው። ማን ተጎዳ? ከረጅም ጊዜ አኳያ ከታየ ሻጭም ገዢም ሁሉም ተጎጂዎች ናቸው። የገበያ ኢኮኖሚ አንዱ ውበት አማራጮችን ማብዛቱ ነው። ዋጋ ስንወስን የጥራት አማራጮችን እናጠፋለን።

ለመሆኑ ምሳሌዬ ሊሆን የሚችል ነገር ነው? አስቸጋሪነቱ ግልጽ ቢሆንም በጭራሽ አይሆንም ብዬ አልከራከርም። የአላሙዲኑ ኤልፎራ፣ ዶሮዎች ላይ ይህንን ማድረግ ችሏል። በኤልፎራ ዶሮዎች መካከል እጅግም ልዩነት ስለሌለ ገዢዎች ሳይከራከሩ በውስን ዋጋ ይገዛሉ። በዶሮ የሆነው በበሬ ይሆናል?

አንዳንድ ሰዎች የዋጋ ቁጥጥር ያለና ወደፊትም የሚኖር በመሆኑ አዲስ ነገር እንዳልሆነ ይከራከራሉ። እውነታቸውን ነው። ነገር ግን ዝርዝር ውስጥ ገብተው የዋጋ ቁጥጥር መቸ፣ እንዴትና በምን ዓይነት ሸቀጦችና አገልግሎቶች ላይ ሊሆን እንደሚገባው መተንተን አይፈልጉም። በተለይም ደግሞ አሁን ተመን የተደረገባቸውን ሸቀጦች ባህርይ በመተንተን ስለ ተመኖቹ የረዥም ጊዜ ጠቀሜታና ተፈፃሚነት ማብራሪያ ሲሰጡ አላጋጠመኝም። ችግሩ ደግሞ ያለው ዝርዝር ውስጥ ሲገባ ነው። ለኤልፎራ ዶሮዎች የሆነው ለሀረርና ጅማ ሠንጋዎች ላይሆን ይችላል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የገበያ ኢኮኖሚ አይደለምና ለአስተዳደራዊ ዋጋዎች አዲሶች አይደለንም። በአገራችን የመብራት፣ የውሃ፣ የስልክ፣ የፓስታ አገልግሎች …. ዋጋዎች በገበያ ኃይሎች ተወስነው አያውቅም። ሸማች በእነዚህ አገልግሎቶች ዋጋ ላይ ይህ ነው የሚባል ተጽዕኖ የለውም። [በነገራችን ላይ የካ ክፍለ ከተማ ባለው የቴሌ ሂሳብ መቀበያ ቢሮ ውስጥ “ደንበኛ ንጉሥ ነው!!!” የሚል በትላላቅ ፊደላት የተፃፈ ጥቅስ አለ። ንጉሥነት ቀርቶ በቴሌ ዓይን ለሎሌነት እንኳን እንዳልበቃን ምርጫ 97 አሳይቶናል። በዚያ ወቅት መስማት የተሳናቸው ዜጎች SMS እንዳይዘጋ ለምነው ምላሽ አጥተዋል። መብራት ኃይል ሲያሻው “የዘወትር አገልጋያችሁ የሆነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክና መብራት ኃይል .....” እያለ መብራት እንደሚቋረጥ ይነግረናል። በ97 ከሚያዝያ 30 በኋላ ቅንጅት ስብሰባ በጠራባቸው ቦታዎች ሁሉ መብራት ይጠፋ እንደነበርም መረሳት የለበትም። በእንዲህ ዓይነት የተዛባ ሥርዓት ደንበኛ ንጉሥ ሳይሆን ባሪያ ነው።]

ወደ ሰባራው ዜና ልመለስ። እኔ የሥጋ ብልቶችን አላውቅም። ሆኖም ግን “በሥጋዎች” መካከል ያለው ልዩነት በበሬዎች መካከል ካለው ልዩነት የሰፋ እንደሚሆን እገምታለሁ። ሉካንዳ ቤቶች ብዙ የሥጋ ደረጃዎች እንደሚኖራቸው አልጠራጠርም። የክትፎ ሥጋ 90 ብር በነበረበት ጊዜም 52 ብር ይሸጡት የነበረ የሥጋ ዓይነት አይጠፋም። አዲሱ የዋጋ ተመን ከሠራ (ያውም ከሠራ ነው) የምንሸምተውን የሥጋ ጥራት ድሮ 52 ብር ይሸጥ ወደነበረው ደረጃ መውረዱ የማይቀር ነው።

ሌላው አማራጭ ደግሞ እንደ ቴሌ አይነት የመንግሥት ድርጅት አቋቁሞ ሥጋን የመቸርቸርን ኃላፊነት መስጠት ነው። ይህ ደግሞ የሸማቾችን ባርነት ጎትቶ ያመጣል። [በ97 እንደ ቴሌና መብራት ሁሉ የሥጋ እደላ በመንግሥት እጅ ቢሆን ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር?]

ከላይ ስለ ሥጋ የተባለው ሁሉ ሩዝም ላይ ይሰራል። ከሃያ በላይ የሩዝ አይነቶች ኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንዳሉ (ወይም እስከ አዋጁ እለት እንደነበሩ) ተነግሯል። አዲሱ ህግ በትክክል ሥራ ላይ ከዋለ የሩዝ ዓይነቶች ምርጫ “ተረት” ይሆናል።

ስለ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ጥራት

ለሁሉም ነገር የጥራት ደረጃ አለው። የአንድ ሸቀጥ ወይም አገልግሎት እሴት የሚወስነው ደግሞ በጥራት ደረጃው ነው።

“ሩጫ ምን ማለት ነው?” ቢባል “ሩጫ በፍጥነት መራመድ ማለት ነው” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። “ፍጥነት” የጥራት መለኪያ ነው። በዚህ የጥራት መለኪያ የተለያዩ “መራመዶች” እጅግ የተለያዩ ደረጃዎች፤ በዚህም ሳቢያ እጅግ የተለያዩ እሴቶች /values/ አሏቸው። ዘገምተኛው

መራመድ “በጎታታነት” ሲያሰድብ፤ ፈጣኑ መራመድ ደግሞ ዋንጫ ያስገኛል፤ ሚሊዮን ያሸልማል፤ ጀግና ያስብላል። ሁለቱ “መራመዶች” ገበያ ቢወጡ በገበያ ዋጋዎቻቸው መካከል የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ሊኖር ይችላል። በጩኸትና በዘፈን መካከል ያለውም ልዩነትም የጥራት ልዩነት ነው። ጩኸት ሊያሳምም ይችላል፤ ዘፈን ግን ይፈውሳል። እንዲህ ዓይነት በርካታ ምሳሌዎችን መዘርዘር ይቻላል። ጥራት ልፋትን ይጠይቃል። ጥራት ለሥራ ክብር መስጠትን፤ ለሸማች መጨነቅን፤ ቃል ማክበርን ይጠይቃል።

በአገራችን ያለውን የትምህርት (በተለይም የከፍተኛ ትምህርት)፣ የጤና አገልግሎት፣ የመንገዶችንና የከተማ ህንፃዎች አሰራር ላስተዋለ ወያኔ ያለበትን የጥራት ግንዛቤ ጉድለት የቱን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ይገነዘባል። የሰሞኑ የዋጋ ትመናም “ጥራት” የተሰኘው ጽንሰሃሳብ በወያኔ ፓሊሲ አውጪዎች (ፖሊሲ ካልነው ማለት ነው) ጭንቅላት ውስጥ አለመኖሩ ያሳየናል። ስለዚህም ነው በነሱ ጭንቅላት ውስጥ ሥጋ ሁሉ አንድ ዓይነት፤ ሩዝ ሁሉ አንድ ዓይነት፤ ደብተር ሁሉ አንድ ዓይነት፤ ሻይ ቅጠል ሁሉ አንድ ዓይነት ሆኖ የታያቸው።

ስለ “ስግብግብ” ነጋዴዎች

በሰሞኑ ዜና መነሻነት የኢትዮጵያ ነጋዴዎች የተለየ የስግብግነት ባህርይ አላቸው የሚሉ በርካታ አስተያየቶችን አንብቤዓለሁ። ለምን የኛ ነጋዴዎች እንዲህ ዓይነቱን ባህርይ እንዳዳበሩ ለማብራራት የሞከረ ግን አላጋጠመኝም።

የወያኔ ካድሬ በስነምግባር ጉድለት ነጋዴን ሲከስ መስማት የሚገርምም፤ የሚያሳዝንም ነው። ማን ማንን ነው በስነ ምግባር ጉድለት የሚከሰው? ነጋዴውስ ምን እንዲሆን ነው የሚጠበቅበት?

“በገበያ ኢኮኖሚ ነጋዴው የስነ-ምግባር ተገዥ እንዲሆን አይጠብቅበትም። የራሱን ጥቅም የሚያስጠብቅ ነጋዴ መኖር ለገበያ ኢኮኖሚ በቂ ነው” እያለ አጥብቆ የሚከራከር፤ እኔ የሱን ሃሳብ ስለምቃወም “ቢዝነስንና በጎ-አድራጎትን ታምታታለህ” የሚለኝ ጓደኛ ነበረኝ፤ መከራከሩን ተውነው እንጂ አሁን አለ። ለኢኮኖሚክስ ተማሪዎች የእሱን ክርክር መረዳት አዳጋች አይሆንም።

መሠረታዊው የኢኮኖሚክስ ቲዎሪ እንዳለ ሆኖ ቢዝነስ (ቢያንስ እኔ በምረዳው መንገድ) ከፍተኛ ስነምግባር የሚጠይቅ ማኅበራዊ ተግባር ነው ብዬ አምናለሁ። እኔ ከዚህም በላይ እሄዳለሁ። ንግድ (ቢዝነስ) ሰውን ትሁት ያደርጋል ብዬ አምናለሁ። ንግድ ደንበኛን (በዚያው ሰውን) ማክበርን ያስለምዳል። ትዕቢተኛ ሰው ነጋዴ መሆን አይችልም። እንዲህ በማመን የመጀመሪያው ሰው አይደለሁም፤ የመጨረሻም አልሆንም። ሁለት የቆዩ ጥቅሶችን እዚህ ጋር እንዳስገባ ይፈቀድልኝ።

Commerce …softens and polishes the manner of men (1).

It is almost a general rule that wherever manners are gentle, there is commerce; and wherever there is commerce, manners are gentle (2).

ለእኔ ቴሌና መብራት ኃይል ነጋዴዎች አይደሉም ማለትም የቢዝነስ ኮርፓሬሽኖች አይደሉም። ለእኔ አላሙዲንና የወያኔ “ነጋዴዎች” ነጋዴዎች አይደሉም። ስለ ስግብግብ ነጋዴዎች ስናወራ እነማንን ማለታችን እንደሆነ ግልጽ መደረግ አለበት። የምንናገረው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ስለተቆጣጠሩት ሰዎችና ተቋማት ከሆነ ከስማቸው በስተቀር በሃሳቡ ስለምስማማ ይህንን ነጥብ እዚሁ እጨርሳለሁ። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የተቆጣጠሩት የወያኔና የአላማሙዲን ድርጅቶችና ሰዎች መሆናቸው የማያከራክር ጉዳይ ነው። እነሱ ዘራፊዎች እንጂ ነጋዴዎች አይደሉም። እነሱ የቢዝነስ ብቻ ሳይሆን ምንም ዓይነት ስነ- ምግባር የላቸውም። የምንናገረው ስለ ነጋዴዎች ከሆነ ግን የኢትዮጵያ ነጋዴዎች አሁን ተጋንኖ የሚነገረውን ያህል የጎላ የስነ-ምግባር ችግር አለባቸው ብዬ አላምንም።

እርግጥ ነው በመላው ማኅበረሰባችን ውስጥ እየደረሰ ያለው የስነምግባር መሸርሸር ነጋዴውን መንካቱ የማይቀር ነው። ውሸታም ጳጳስ፤ ውሸታምና ፈሪ “ሽማግሌ”፤ ለሞባይል ቀፎ የመንግሥትን በጀት የሚያጭበረብር የፀረ-ሙስና ኮሚሽነር ባለበት አገር “በገዛሁበት ነው የምሸጥልዎ” እያለ ጥቂት ሳንቲሞችን የሚያጭበረብር ባለሱቅ መኖሩ ለምን ይገርመናል? ይህ የሚያመለክተው በስነምግባር ረገድ ብዙ መሥራት እንደሚኖርብን ብቻ ነው። በአንፃራዊ መልኩ ከታየ ግን በስነምግባር ረገድ የንግዱ ማኅበረሰብ ሰርቶ፣ ለፍቶ፣ ጥሮ በራሱ ጉልበትና ላብ ፍሬ የሚያድር፤ ለሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች አርዓያ መሆን የሚችል ነው።

ይሁን እንጂ የወያኔ ሹማምንት ስለነጋዴዎች ስግብግብነት ሲያወሩ የገዛ ራሳቸውን ወይም በየቢሮው የሰገሰጓቸውን ሹሞቻቸውን ወይም በኮንትሮባንድ የተሰማሩትን የጦር መኮንኖቻቸውን እያሰቡ አይደለም። በስግብግብነት እየተወነጀሉ እየተዘጉ ያሉትም የችርቻሮ ሱቆች ናቸው። “ሩዝ ኪሎው በብር 12.50 ገዝተህ ኪሎው በብር 12.50 ሸጠህ አትርፍ” ተብለው ይህን ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበትን ጥበብ ገና ስላላገኙ ስግብግብ ተብለው ብዙ ሱቆች ተዘግተዋል።

ፓሊሲ አውጪዎቹ እና ኢኮኖሚክስ

የወያኔ የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ ደንበኛ በሆኑበት ሆቴል የታዘቡትን “ህገወጥ” የዋጋ አጨማመር በምሳሌነት ተጠቅመው የሰጡት ገለፃ አስቂኝ ነው። እንደሚኒስትሩ ገለፃ የቅቤ ዋጋ መጨመር ቅቤ ባልገባባቸው ምግቦች ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ማምጣት የለበትም (3)

እንደሳቸው አገላለጽ በክትፎ ዋጋ ላይ የሚመጣ ለውጥ በሌሎች የምግብ ዓይነቶች ላይ ምንም ተፅዕኖ የለውም። ሌላ ምሳሌ ብወስድ “በኮካኮላ ላይ የሚመጣ የዋጋ ለውጥ ፒፕሲን ምን አገባው?” እያሉን ነው። ሰውየው ምን ዓይነት ኢኮኖሚክስ እንደተማሩ እግዜር ይወቀው። ገበያ ሸቀጦችን በተለያዩ መንገዶች የሚያያይዝ መሆኑ የአንደኛ ዓመት ኮርስ ነው።

ይህን አፍረን እንለፈው ብንል እንኳን ሌላም ግዙፍ ስህተት አለ። እንደሳቸው ገለፃ ከሆነ የሸቀጦችና አገልግሎቶች የገበያ ዋጋ የሚወሰነው ሸቀጦቹን ወይም አገልግሎቶቹን ለማምረት በወጣው ወጪ ነው። ይህ በግልብ ሲታይ እውነት ቢመስልም በጣም የተሳሳተ ኢኮኖሚክስ ነው። የገበያ ዋጋን በማምረቻ ወጪ ማሰብ አቅርቦት /supply/ ላይ ብቻ ያተኮረ ግማሽ ኢኮኖሚክስ ነው። ኢኮኖሚክሱን ሙሉ ለማድረግ እሸማቹ ኪስ ውስጥ ያለው የገንዘብ ብዛት ማሰብ ይጠይቃል። በሌላ አገላለጽ ፍላጎትን /Demand/ እና የገንዘብ የመግዛት አቅምን እሂሳብ ውስጥ ማስገባት ግድ ነው። የሸቀጦችና አገልግሎቶች የገበያ ዋጋ የሚወስኑት ሸቀጦቹን ለማምረት በወጣው ወጪ ብቻ ሳይሆን በየሰው ኪስ ውስጥ ባለ የወረቀት ገንዘብ ብዛት ጭምርም ነው። ገበያ ውስጥ የወረቀት ገንዘብ እየበተኑ ነጋዴው ዋጋ ጨመረ ብሎ መውቀስ የሚያሳፍር ነው። ለብሄራዊ ባንክ የወረቀት ብተና ገበያ የሚሰጠው ምላሽ በዋጋ ላይ የሚጨመሩ ቁጥሮች መሆኑ እንዴት ሳያውቁ ቀሩ? ይህ የሶስተኛ ዓመት ኮርስ ነው።

የፓሊሲው ቀዳዳዎች

ፓሊሲው ብዙ ቀዳዳዎች እንዳሉት ካሁኑ እየታየ ነው። አንዳንዱን ቶሎ ቶሎ አንስቼ ልለፍ።

  1. ምርጥ ሥጋ መግዛት ከፈለጉ ለወንበር አሊያም ለአዋዜ ብለው ጠቀም ያለ ገንዘብ ይክፈሉ፤
  2. ጥራት ያለው ሩዝ ከፈለጉ ሩዙን ለሚይዙበት ፌስታል ጠቀም ያለ ዋጋ ይክፈሉ፤
  3. ራሳቸው ወያኔዎቹ ጥራት ያለው ሸቀጥ ይፈልጋሉና ሱፐር ማርኬቶች እንደ “ባለኮከብ” ሆቴሎች ተቆጥረው ከተመን ነፃ እንዲሆኑ የቀረበው “አቤቱታ” ተቀባይነት ማግኘቱ አይቀርም እናም አቅሙ ካልዎት የሚፈልጉትን እቃ ሱፐር ማርኬት ሂደው ይግዙ፤
  4. ረሃብ ቀጠሮ የማይሰጥ ስለሆነ “ይታገሱ” ልልዎት አልችልም እንጂ ይኸ ፓሊሲ ከጥቂት ወራት በኋላ ጨርሶ መረሳቱ የማይቀር መሆኑን አይዘንጉ።

እዚህ ላይ አጽንዖት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ታሪፉ ተፈፃሚ እንዲሆን የሌሎች በርካታ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ዋጋ መወሰን እንዳለበት ነው። አለበለዚያ “ቀዳዳው” ብዙ ነው። በተለይም ኪራይና ምንዳ (wage) ካልተስተካከሉ ታሪፉን ለማስፈፀም ምን ያህል እንደሚያዳግት ለማወቅ ከወር በላይ የሚፈጅ አይመስለኝም፤ የእነሱን ዋጋ መወሰን ደግሞ አረንቋ ውስጥ መግባት ነው። የገዛ ራሱን ኪስ ስለሚጎዳበት ወያኔ የኪራይ ዋጋን ለመወሰን የሚሞክር አይመስለኝም።

“ፓሊሲው” ለምን? ለምን አሁን?

በመጨረሻ ላነሳ የምፈልገው ጉዳይ ወያኔ ይህንን ፓሊሲ ለምን ፈለገ? ለምንስ አሁን ፈለገው? የሚሉትን ጉዳዮችን ነው:: ለእነዚህ ጥያቄዎች ፈጣንና አጭር ምላሽ ለመስጠት አራት ነጥቦችን ማንሳት ይበቃል ብዬ አምናለሁ።

  1. ግቡን ያልመታው የብር ምንዛሪ ምጣኔ ቅናሽ “እፍርት” ለመሸፈን፤

የብር ምንዛሬ በድንገት እንዲቀንስ በተደረገ ሰሞን “ቆራጡ” እርምጃ የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚያመነጥቅ ገለፃ ሲሰጥ ነበር። የሚገርመው ልክ እንዳሁኑ የቅቤና ሌጣ ምግቦች ምሳሌ ሁሉ ያኔም የምንዛሪው ለውጥ በገቢ እቃዎች ላይ ካልሆነ በስተቀር ሌሎችን ሸቀጦች አይነካም ተብሎ ነበር። ገበያው አልታዘዝ ስላለ ሰበብ መፈለግ አስፈላጊ ሆነ።2. የትራንስፎርሜሽን መፈክር ባልተጠበቀ ፍጥነት መወየብ ያመጣው መደናገጥ፤

2. ከዚህ በፊት “የመፈክር ኢኮኖሚ” በሚል አጭር ጽሁፍ እንደገለጽኩት የወያኔ ኢኮኖሚ የመፈክር ኢኮኖሚ ነው። የመፈክር ኢኮኖሚ መፈክሩ ሲሰቀል ይሟሟቅና መፈክሩ ሲወይብ እንዘጭ ይላል።

የትናንስፎርሜሽን መፈክር ሳንጠግበው መወየብ ጀመረ። ስለሆነም ካሁኑ እቅዱ ያልተሳካባቸውን ምክንያቶች ማዘጋጀት ያስፈልጋል። አዲሱ ፓሊሲ “ስግብግብ ነጋዴ” የሚባል ምናልባትም “ነፍጠኛን” የሚተካ መደብ ፈጠረ።

3. የቱኒዚያ ክስተት የፈጠረው መረበሽ፤

የቱኒዚያው ሃቅ መለስንና ማፍያ ቤተሰቡን ቢያሸብር ምንም ሊገርመን አይገባም። የንግድ ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ እንደገለጹት “የቱኒዚያው ችግር እዚህ እንዳይደገም” ብለው “የሱሪ በአንገት” ፓሊሲ ነደፉ።

4. አጀንዳ ማቀበል፤

ወያኔ እንደተለመደው አንድ አጀንጃ አቀብሎን እኛ አጀንዳ ላይ ስንራኮት እሱ አገር የመበትን ሥራዉን ያቀላጥፋል።

5. እርስ በርስ ማጋጨት፤

ከሁሉም በላይ ዋነኛው ምክንያት የምለው ይህ ነው። ወያኔ በተገኘው መንገድ ሁሉ ከፋፍሎን እርስ በርስ ሲያጣላን ኖሯል። በዘርና በሃይማኖት የማጣላቱን ሴራ የተመኘውን ያህል ባይሆንም ጥሩ ውጤት አምጥቶለታል። አሁን ደግሞ የሥራ ዘርፍ አንዱ የመከፋፈያ መንገድ ሆኖ ቀርቧል። ወደፊት ደግሞ ምናልባት ወጣትና ጎልማሳ፤ ወንድና ሴት ለያይቶ ያጣላን ይሆናል።

ማሳረጊያ

ወያኔ እስካሁን ከተዋጣለት ነገሮች አንዱ በየጊዜው ኢትዮጵያዊያንን እርስ በእስ ማናከስ መቻሉ ነው። አማራና ኦሮሞ፤ አፋርና ሶማሌ-ኢሳ፤ ስልጤና ጉራጌ፤ አኝዋክና ኑዌር …. እስላምና ኦርቶዶክስ፤ ኦርቶዶክስና ፕሮቶቴስታንት፤ ፕሮቴስታንትና ፕሮቴስታንት፤ ኦርቶዶክስና ኦርቶዶክስ፤ እስላምና እስላም … ወያኔ በተገኘው ስንጥቅ ሁሉ እየገባ እርስ በርስ አናክሶን ተንሰራፍቶ ለመግዛት ችሏል። አሁን ደግሞ የመንግሥት ሠራተኛንና ነጋዴን ለማጣላት ቆርጦ ተነስቷል።

አንዳንድ ሰዎች ወያኔ በፈጠረው የኑሮ ችግር እጅግ በመጎዳታቸው መፍትሄ የተባለ ነገር ሁሉ ቢሞክር “ይሠራ ይሆናል” የሚል ባዶ ተስፋ የሚሳድሩ ሆነዋል። ወያኔ ደግሞ የህዝባችንን ተስፈኛነትና የዋህነት ለራሱ ጥቅም ያውለዋል። ትግላችን ውጤት እንዲያፈራ ወያኔ በሚሄበት መንገድ ሁሉ እየተከታተልን፤ የተንኮል ሴራዎቹን ማጋለጥ መቻል አለብን። ሰባራ ዜናዎችን “ሰበር ዜና” ማለትን መተው መቻል አለብን።

ከዚህም በተጨማሪ በየጊዜው በሚወረወሩልን አጀንዳዎች ሳቢያ ትኩረታችን እንዳይዛባ መጠንቀቅም ይኖርብናል። የኢትዮጵያ ህዝብ በከፋ ድህነት ውስጥ እየማቀቀ፤ ሰብዓዊ ክብሩና ነፃነቱ በዘረኞች ተነጥቆ ኑሮውን በባርነት እየገፋ ባለበት ባሁኑ ሰዓት “የዋጋ ማሻሻያ ኣደረግን” ብሎ ማወጅ አንድም የተቃውሞ ኃይልን ለመከፋፈልና የህዝብን ትግል ለማዳከም የሚደረገውን ደባ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ነጋዴን በህዝብ ጋር ለማጣላት ታቅዶ የተደረገ ስለመሆኑ ለኣፍታም መዘንጋት የለብንም።

***

————————————-

(1) Robertson, William . 1769. Views of the Progress of Society in Europe.

(2) Motesquieu, Charles de. 1949. [1748] Sprits of Law. New York: Hafner.

(3) የሚኒስትር ዴኤታውን ገለፃ በጀንዋሪ 19 ሪፓርተር አማርኛ ጋዜጣ ይመልከቱ

በቦሌ አካባቢ በሚገኝ የአፈና ጣቢያ ንጹሃን አንደሚሰቃዩ ታወቀ

Thursday, December 23rd, 2010

የትግራዩ ገዢ ጉጅሌ በቦሌ አካባቢ ባቋቋመው የሰቆቃ ጣቢያ በርካታ ንጹሃን እየተሰቃዩ እንደሚገኙ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን በላኩት መረጃ አስታውቀዋል።

ዘረኛው አገዛዝ ባለፉት ሃያ አመታት ውስጥ በርካታ የምስጢር እስር ቤቶችን በአገሪቱ ዙሪያ ከፍቶ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎችን እያፈነ ሲያስር እንደነበር ሲነገር ቆይቷል። ሰሞኑን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰ መረጃ እንደሚያመለክተው፥ ከነዚህ እስር ቤቶች ውስጥ አንዱ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አካባቢ ይገኛል።

ይህ ጣቢያ በበብሔራዊ መረጃ እንደሚመራ እና ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ አስራ አንድ ሰራተኞች እንዳሉትም ለማወቅ ተችሏል። እነዚህ ሰራተኞች ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ እና ያለ ፖሊስ መጥሪያ ዜጎችን አፍነው ፊታቸውን በጨርቅ በመሸፈን እና አፋቸውን በፕላስተር በማሸግ፤ ጥቁር መስታወቶች እና ቁጥር 2 ታርጋ ባሏቸው ኮብራ መኪናዎች ወደ እስር ቤቱ እንደሚወስዷቸው መረጃው ያስረዳል።

ወደ አፈና ጣቢያው በደረሱ ግለሰቦች ላይ የተለያዩ የሰቆቃ ተግባራት የሚፈጸሙ ሲሆን፤ የተሰነዘረባቸውን ወንጀል የማይቀበሉት ተገድለው እንደሚቀበሩ እና ያመኑት ወደ ማእከላዊ እስር ቤት እንደሚዘዋወሩ በአገዛዙ የደህንነት ተቋም ውስጥ የሚሰሩ ምንጮች ገልጸዋል። ከሞት ከተረፉት ውስጥ በርካቶች እስካሁን በማእከላዊ እስር ቤት፣ በፌዴራል ማረሚያ ቤት እና በየጦር ካምፖች ውስጥ ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ነው።

ወደዚህ ጣቢያ ተወስደው ለስቃይ ከተዳረጉ ዜጎች ውስጥ ከኬንያ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ እና ከሱዳን ታፍነው የመጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ብዙ እንደሆኑ ከመረጃው ለማወቅ ተችሏል።

ብአዴን እስከመቼ በምርጥ ባርያነት ይፈነጥዛል?

Friday, November 26th, 2010

ባርነት ክፉ ነገር ነው። ለጌታ በመስገድ ብዛት በተገኘ ሙገሳ መፈንጠዝ ደግሞ ከባርነትም የባሰ ነው። ባርያ ዛሬ ነፃ ባይሆንም ወደፊት ነፃ የመውጣት ህልም አለው። በጉልበተኛ ፈንጋይ ነፃነቱን ቢያጣም የህሊና ነፃነቱን ያላስደፈረ ባርያ ለሙሉ ነፃነት መታገሉ የማይቀር ነው። የባርያው ከአሳዳሪው ጋር እኩል የመሆን ህልም ትግሉ ሲሰምር እውን ይሆናል። በባርያነቱ እየፈነጠዘ ያለ ባርያ ግን ነፃ ሰው የመሆን ህልሙንም ጭምር አጥቷል። እንዲህ ዓይነቱ ባርያ በአካልም፤ በመንፈስም ባሪያ ነው። ነፃ ሰው የመሆን እድል የለውም።

አፄ ኃይለሥላሴ፣ በመጀሪያዎቹ አስርታት ዘመነ ንግሥናቸው “የባርነት አስወጋጅ ቢሮ” የሚባል ተቋም ነበራቸው። ይህ ቢሮ ገንዘብ ለጌቶቻቸው እየከፈለ ባሮችን ነፃ ያወጣ ነበር። ታድያ አንዳንድ “ታማኝ” ባሮች እቢሮው ድረስ እየሄዱ ለጌቶቻቸው ገንዘብ ካስገኙ በኋላ ባርነታቸውን ይቀጥሉ እንደነበር ሰነዶች ያስረዳሉ። ነፃ የሚወጡበትን ገንዘብ ለጌታቸው በመስጠት ተጨማሪ ገቢ አስገኝተዋልና ባሮቹ በጌቶቻቸው ይወደሱ እንደነበር መገመት ይቻላል።

እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ዛሬ የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሚገኝበት ሁኔታ ይህንን ይመስላል። ብአዴን፣ የህወሃት ምርጥ ባርያ መሆኑ ሳያንሰው በባርነቱ የሚፈነጥዝ ድርጅት ነው። ብአዴን የጌታውን፣ የህወሃትን ማለትም የመለስን ሙገሳን ለማግኘት የሚሆነውን መታዘብ ህሊናን ያቆስላል።

ሰሞኑን የብአዴን ፈንጠዚያ ወቅት ነው። ጌታው ህወሃት – በአምሳለ መለስ ዜናዊ – ባህርዳር ድረስ ሂዶ አሞግሶታል። “ጎበዝና ታማኝ ባርያ” መሆኑ ነግሮታል። ሠላሳ ሻማ ተለኩሶለት ተፍነቅንቋል። “በ1985 ተወልጄ በ2003 እንዴት ሠላሳ ዓመት ሊሞላኝ ቻለ?” ብሎ መጠየቅ አይቻለውም፤ አይገባውምም። ባርያ የሰጡትን ይቀበላል። በ30 ፋንታ 10 ዓመት ነው ቢሉትም ይቀበላል። “የኢህዴን ታሪክ ለኔ ምኔ ነው?” ብሎ አይመራመርም። መጠየቅ እና መመራመር ለባሮች የተሰጠ ነገር አይደለም። አስፈላጊው ነገር ታማኝ ባርነትን እያረጋገጡ ማብላትና መብላት፣ ማጠጣትና መጠጣት፣ ማስጨፈርና መጨፈር እና ማዘረፍና መዝረፍ ነው። የአሳዳሪው መልካም ፈቃድ ከሌለ እነዚህ ሁሉ እንደማይኖሩ ያውቃልና፤ ብአዴን “እድሉን” እየተጠቀመበት ነው።

በዚህ መሃል የአማራ ህዝብ ይታዘባል፤ ይዘግባል። “ተያንዳንዱ ቤት ስንት ስንት ተዋጣ፤ ተመንግሥትስ ካዝና ስንት ወጣ?” እያለ ገበሬው ይጠይቃል። የብአዴንን ጌቶችና አጃቢዎቻቸውን ለመጠበቅ ከትግራይ ለመጡ ዘቦችና ፊርማቶሪዎች 16 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኗል መባሉ፤ ለከተሞች ማሸብረቂያ አምፖሎችና ጨርቆች 5 ሚሊዮን ብር መውጣቱ፤ ለሚበላና ለሚጠጣ 30 ሚሊዮን መመደቡ፤ እንዲያው ለድግስ ብቻ ወደ 60 ሚሊዮን ብር መውጣቱ እብዙ ድሆች አማሮች ጆሮ ደርሷል። ለድግስ የወጣው ገንዘብ የአማራ ክልል ተማሪዎችን በሞላ የዓመት ደብተርና እርሳስ ይሸፍን እንደነበር በየቤቱ ይጉረመረማል። ብአዴንን ግን ይህ አያሳስበውም። ብአዴን ጌታው ያዘዘውን በመፈጸም የሚደሰት ጥርቅም ነው። “አጉርሰኝ” ሲለው ያጎርሳል፤ “ጉረስ” ሲለው በደስታና በችኮላ ይጎርሳል።

የአማራ ህዝብ ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም። በባዕድ ወረራ ጊዜ ለጣልያን ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። ከዛሬዎቹም በተሻለ በጌቶቻቸው ጣሊያኖች ይሰሙ ነበር። ብአዴን ግን ራሱን ከባንዳነትም አውርዶ ባርነት ደረጃ ላይ የጣለ ከመሆንም አልፎ በባርነቱ የሚደሰት ድርጅት ነው።

ብአዴንን በተመለከተ ግልጽ ያልሆነ ጉዳይ ቢኖር አንድ ነገር ብቻ ነው። “እሱም እስከ መቼ ነው ጌታው በባርያነቱ እንዲፈነጥዝ የሚፈቅድለት?” የሚለው ጥያቄ ነው። ሁኔታዎች እንደሚያመላክቱት በወያኔ ዓይን የብአዴን ዋጋ እያሽቆለቆለ ነው። ሁሉም የይስሙላ ስልጣን ቢሆኑም አስቀድሞ ከአፈጉባዬነት ቀጥሎ ደግሞ ከመለስ ምክትልነት መባረሩ ብአዴን ለወያኔ የማይጠቅም ያረጀ ባርያ እየሆነ የመሆኑ ማሳያዎች ናቸው። ከእንግዲህ ወያኔ ይህን አሮጌ ባርያ የሚያሞካሽበት ምክንያት የለውም። የአሁኑ ቡረቃም የስንብት ይመስላል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ብአዴንን ከአባላቱ ለይቶ ማየት ይሻል። ድርጅቱ ከባንዳም የወረደ ነፃ የመውጣት ተስፋ የሌለው ባርያ ነው። ሆኖም ግን ኅሊና ያላችሁ አባላት ካላችሁ በፍጥነት ራሳችሁን ከዚህ ድርጅት የምታላቅቁበትን አሊያም እውስጡ ሆናችሁ ድርጅቱን የምትገድሉበትን መንገድ መሻት የራሳችሁ ኃላፊነት ነው። እንኳን የብአዴን የወያኔም እድሜ አጭር እንደሆነ እንነግራችኋለን። ልቦና ያላችሁ ወደ ውስጣችሁ ተመልከቱ እንላለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

መለስ ዜናዊ በግብጽ ላይ ያስተላለፈው ማስጠንቀቂያ እራሱን እንደ አገር-ወዳድ ዜጋ ለመቅረጽ የሚያደርገው ሙከራ አካል ነው ተባለ

Thursday, November 25th, 2010

ዘረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ባታስብ ይሻላታል ሲል በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ የሆነ ማስጠንቅቂያ መስጠቱ እራሱን እንደ አገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ ለማስቆጠር ከሚያደርጋቸው ሙከራዎች ውስጥ አንዱ ነው ተብሏል።

ዘረኛው አምባገነን ማክሰኞ እለት ለሬውተርስ የዜና አውታር በሰጠው ቃለ መጠይቅ፥ “ኢትዮጵያን ለመውረር የሞከረ ማንኛውም ሃይል ከሞት ተርፎ ታሪኩን ለመናገር ደርሶ አያውቅም። ግብጾችም ከዛ የተለዩ ሊሆኑ አይችሉም፤ ያንንም የሚያውቁ ይመስለኛል፤” ሲል ደስኩሯል። ግብጽ በበኩሏ ይህ የመለስ ንግግር አስገራሚ እና ያልተጠበቀ እንደሆነ በመግለጽ፤ ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ገልጻለች።

መለስ ዜናዊ በአንድ በኩል ከግብጽ የኢኮኖሚ እርዳታ እየጠየቀ አብሬሽ ቆማለሁ እንደሚል እና በሌላ ጎን ደግሞ ከተቀሩት የአባይ ተፋሰስ አገራት ጋር ሆኖ ግብጽን በማስፈራራት ሁለቱን ጎን ሲጫወት መቆየቱ ይታወቃል። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ድጋፍ ለማግኘት ሲል “የውጭ ጠላት” ዘፈኑን አጠናክሮታል።

የዝግጅት ክፍላችንን ያናገሩ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፤ መለስ ዜናዊ ለግብጽ የሰጠው ማስጠንቀቂያ፣ እራሱን እንደ ኩሩ እና አገር ወዳድ ዜጋ በመቅረጽ፤ ለኢትዮጵያ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ ለመደበቅ እና ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርገው ሙከራ ነው ብለዋል።

ብሩህ ራዕያችንን በተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደግፍ!

Saturday, October 23rd, 2010

ደግ መመኘት መልካም ነገር ነው። የምፈልገውን ነገር ጠንቅቀን ማወቃችን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። መድረሻችንን ማወቅ ያለብን ለጉዞ ከመነሳታችን በፊት ነው። አዎ! ግልጽ የሆነ ራዕይ ያለን መሆኑ ወሳኝ ነገር ነው።

ይሁን እንጂ ራዕይ ወሳኝ ነገር ቢሆንም እንኳን ብቻውን ግን የትም አያደርስም። ልንደርስ የምፈልገውን ቦታ ማወቃችን ጉዞው የሚፈልገውን ፈተና ለማሸነፍ እና ጉዞው የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያበቃ ብርታት ካልሰጠን ከንቱ ነው። መልካምን መመኘት፤ መልካምን ማለም ጥሩ ቢሆንም ምኞት በተግባራዊ እንቅስቃሴ ካልታገዘ ውጤታማ አይሆንም።

እንደባሮች አዋርዶ እየገዛን ያለው ዘረኛው የትግራይ ገዢ ጉጅሌ ተወግዶ ማየት የብዙ ኢትዮጵያዊያን ፍላጎት ነው ብለን እናምናለን። የዜጎች ነፃነት የተከበረባት፤ የህግ የበላይነት የነገሰባት፤ እኩልነት የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ብዙ ኢትዮጵያዊያን የሚጋሩት ራዕይ ነው ብለን እናምናለን። ችጋርና ድህነት ጠፍተው፤ የሌሎች አገሮች ተመፅዋችነታችን አብቅቶ፤ የህጻናትና የመሬት ሸያጭ ተወግዶ፤ በአረብ አገራት የእህቶቻችን የስቃይና ውርደት ኑሮ አብቅቶ ማየት ብዙዎቻችን የምንመኘው ነገር ነው ብለን እናምናለን። ባርነትንና ድህነትን ለመሸሽ ሲሰደዱ በበረሃ ንዳድ የሚያልቁ;፤ ባህር ውስጥ የሚሰምጡ እና በጎረቤት አገራት እስር ቤቶች ውስጥ የሚማቅቁ ዜጎች የሌሏት ኢትዮጵያዊያን ማየት ብዙዎቻችን የምንጋራው ራዕይ ነው ብለን እናምናለን።

እነዚህን መልካም ምኞቶች፤ እነዚህን ውብና ብሩህ ራዕዮችን የሚያሳካው ማነው? እንዴት ነው የሚሳኩት? መቼ ነው የሚሳኩት? እነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ለመልሱ ጣታችንን ሽቅብ ወደ ፈጣሪያችን ወይም ወደ ጎን ወደ ሌላው ወገናችን ከመቀሰራችን በፊት ራሳችንን እንፈትሽ።

ምኞታችን፣ ራዕያችን የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ፈቃደኞች እስካልሆንን ድረስ መመኘታችን ብቻውን የትም አያደርሰንም። የኛ እልህ፤ የኛ የዓላማ ጽናት፤ የኛ ቁርጠኝነት የክፋት ኃይሎች ካላቸው ቁርጠኝነትና ጽናት በላይ እስካልሆነ ድረስ ሠናይ-ግብር ክፋትን ማሸነፍ አይቻለውም።

መልዕክታችን ግልጽ ነው። ፍትህን መናፈቅ፤ በዘረኝነት መንገሸገሽ፤ አምባገነን አገዛዝን አምርሮ መጥላት ጥሩ ነው፤ ግን በቂ አይደለም። በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ የሚቀይረው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው። እያንዳንዳችን በተቀናጀ መንገድ ትናንሽም ብትሆን ጠጠር ከወረወርን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክፋትን ከአገራችን ማስወገድ እንችላለን።

ስለሆነም ለራስዎ፣ ለአገርዎ እና ለወደፊቱ ትውልድ ብሩህ ራዕይ ካለዎት እና ራዕይዎ ተሳክቶ ማየት የሚፈልጉ ከሆነ የሚከተሉትን ይፈጽሙ።

  1. የተደራጀ ትግል ባነሰ ወጪና በአጭር ጊዜ ውጤታማ ያደርጋልና ንቅናቄያችንን ይቀላቀሉ። የእርስዎን ዝግጁነት የሚመጥኑ የአደረጃጀት መዋቅሮችን፣ የትግል ስልቶችን እና የተሳትፎ ዓይነቶችን አዘጋጅተናል።
  2. በማናቸውም ምክንያት ከኛ የሚመርጡት፤ ከኛ በተሻለ የእርስዎን አገራዊ ራዕይ የሚያሳካ ሌላ ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ካለ ይቀላቀሉት።
  3. ግንቦት 7ን እና/ወይም ሌሎች ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶችን በገንዘብዎ፣ በእውቀትዎና በጊዜዎ ይርዱ።
  4. ወያኔ እየሸረበልን ባለ የዘርና የሃይማኖት ቅራኔ ውስጥ እንዳንገባ፤ በኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባት እንዲሰፍን ተግተው ይስሩ። በኢትዮጵያዊያን መካከል በዘርና ሃይማኖት ልዩነት ባለማድረግ አርዓያ ይሁኑ።
  5. በፀረ-ወያኔ ጎራ የተሰለፉ ኃይሎች ተባብረው እንዲቆሙ የበኩልዎን ድርሻ ያበርክቱ። የሌሎች ድርጅቶችን ህመምና ስጋት ለመረዳት ጥረት ያድርጉ። አስታራቂ ይሁኑ።
  6. ከአሉባልታ ነፅተው የተግባር ሰው ይሁኑ። ፓለቲካችንን ከውሸት፣ ከጭፍን ጥላቻ እና ተራ ወሬዎች ለማንፃት ተግተው ይስሩ።
  7. ከወያኔ ድርጅቶች ጋር ፈጽሞ አይነግዱ። እቃዎቻቸውን አይግዙ፤ አገልግሎቶቻቸውን አይጠቀሙ።
  8. በወያኔ ላይ ያለዎትን ተቃውሞ በተገኘው እድል ሁሉ ተጠቅመው ይግለፁ። ተቃውሞዎን በየበዓሉ፣ በየስብሰባው፣ በሩጫዎች፣ በሌሎች የስፖርት ዝግጅቶች ወቅት በጩኸት፣ በፉጨት፣ በየበሩና ግርግዳው በብጥስጣሽ ወረቀቶች በመፃፍ ይግለጹ። “ሞት ለዘረኛው ወያኔ!!! ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!!!” ይሁን መፈክርዎ።
  9. የህሊና እስረኞችን ይዘክሩ፤ ቤተሶቦቻቸውን ይደግፉ።
  10. የግንቦት7 ራድዮና ሳምንታዊ ጋዜጣን ይከታተሉ፤ ለሌሎችም ያሰራጩ። የሰሙትን መረጃ ወይም ዜና ሳይንቁ ለግንቦት 7 ይላኩ።
  11. በማናቸውም መንገድ ወያኔን የሚጠቅም ተግባር አይፈጽሙ። በመሬት ወይም በገንዘብ አይደለሉ። መለስ እያደለ ያለው መሬት የሱ አያቶች ከጣሊያን ጋር አብረው ሊያስወስዱት ሲጥሩ የእርስዎ አያቶች ደማቸውን አፍሰው ያሰረከቡን መሆኑን አይርሱ።
  12. የወያኔን የኢንቬስትመንት ግብዣ አይቀበሉ። የህዝብ መብት ባልተከበረበት፤ የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት፤ ዘረኛነት በነገሰበት ሃገር ውስጥ ራስዎን የገዢው ሎሌ ካላደረጉ በስተቀር በጥረትዎ ያፈሩት ንብረት ባለመብት አለመሆንዎን ይወቁ። ሎሌ ከሆኑ ደግሞ ጊዜዓዊ ተጠቃሚ እንጂ ባለመብት አይደሉም።
  13. ውጭ አገር የሚኖሩ ከሆነ ለቤተሰቦችዎ ገንዘብ ሲልኩ የወያኔ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ማስታገሻ በማይሆን መንገድ ያድርጉት። ኦፊሲያላዊ መንገዶችንም ሆነ ወያኔ በየአገሩ ያደራጃቸው የገንዘብ ማስተላለፊያዎችን አይጠቀሙ።
  14. በአገር ቤት የሚገኙትን ወገኖቻችንን መረጃ ለማስራብ ወያኔ የሚያደርገውን የመገናኛ ብዙሃን አፈና ለመበጣጠስ ጥረት የሚያደረጉ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በገንዘብዎና በእውቀትዎ ይደግፉ::
  15. የዲፕሎማሲው ትግል አካል ይሁኑ። ሰላማዊ ሰልፍ ይውጡ፤ በረሃብ አድማዎች ይሳተፉ።
  16. ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔዎችን እኩይ ተግባራት ከማጋለጥ አይቦዝኑ። ለፓለቲከኞች፣ ለሕዝብ ተወካዮች፣ ለሥራ ባልደረቦችዎ፣ ለክፍል ጓደኞችዎ ዜግነትን ሳይመርጡ የወያኔን ዘረኝነት፣ ጨፍጫፊነት፣ ዘራፊነትና አምባገነንነት ያሳውቁ።
  17. ጠዋት “ዛሬ ለትግሉ የማበረክተው ምንድነው?” ብለው ይጠይቁ፤ ማታ ጠዋት ያሉዋቸውን ፈጽመው እንደሆነ ራስዎን ይፈትሹ።

ዘረኞችና አምባገነኖች ከጫኑብን ዜጋዊና ሃገራዊ ውርደት በአፋጣኝ መገላገግል የምንችለው እነሱ ሊያዋረዱን አምረውና ተግተው እንደሚሰሩ ሁሉ እኛም አምርረንና ተግተን “አትችሉም! አንፈቅድላችሁም!” በሚል እልህና ቁጭት በርትተን ስንሰራ ብቻ መሆኑን ፈጽሞ አይዘንጉ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የግንቦት 7 ራድዮ ፕሮግራም ከግምሽ ሰዓት ወደ አንድ ሰዓት ተረዘመ

Thursday, October 14th, 2010

ማስታወቂያ

የግንቦት 7 ራድዮ የስርጭት ሰዓት ከግምሽ ሰዓት ወደ አንድ ሰዓት ተረዘመ

የግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ  ከጥቅምት 6 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ የሚያስተላልፈውን የሬዲዮ ፕሮግራም ከግማሽ ሰአት ወደ ሙሉ የአንድ ሰዓት ዝግጅት ከፍ በማድረግ ከጠዋቱ 3 እስከ 4 ሰዓትና በድጋሚ ማታ ከ2 እስከ 3 ሰዓት እንደሚያስተላልፍ  በደስታ ይገልጻል። እገረ መንገዱንም  በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የምትገኙ አድማጮቻችን ለዝግጅት የሚረዱንን መረጃዎች ፤ አስተያቶችንና ጥቆማዎችን

በተለመደው ስልክ ቁጥራችን          0044 203 286 9661    ወይም

በኢሜል አድራሻችን                       g7radio@ginbot7.org

እንድትልኩልን በትህትና አንጠይቃለን። መረጃ ሃይል ነው እና ዘረኛው ወያኔ በሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ጭቆና፣ አፈና እና ዘረፋ ባለማቋረጥ በማጋለጡ ሥራ እንድትተባበሩ ወገናዊ ጥሪ ቀርቦሎታል።

የግንቦት 7 ድምጽ ዝግጅት ክፍል

ለአዜብ መስፍን የቀራት የበርበሬ ንግድ ብቻ ነው

Thursday, October 14th, 2010

ከዝግጂት ክፍላችን

“ወደ ውጭ አገራት ስትሄድ እና እንግዶችን ስትቀበል ሚስትህን ከጎንህ የማታኖርበት ምክንያት ምንድን ነው?” ተብሎ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥያቄ የቀረበለት መለስ ዜናዊ፤ “አይ እሷ ዝም ብላ ተራ የቤት ሚስት መሆን አትፈልግም፤ የፓርቲ አባል ከመሆኗ በተጨማሪ የራሷ ንግድ አላት፤ እናም በዛ ላይ መስራት ትፈልጋለች። እሷ የራሷን ንግድ ስትሰራ እኔ ደግሞ የመንግስት ስራዬን ስሰራ እንቆይና ኋላ ላይ ተገናኝተን የጋራ የቤተሰብ ስራችንን እንሰራለን፤” ማለቱን ሰማን።

ወሬው ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ተቀድቶ፣ በነጋድራስ ጋዜጣ ተጠቅሶ፤ በአዲስ ነገር ኦንላይን ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ፤ በኛ ደግሞ መልሶ ጭብጡ ወደ አማርኛ ዞሮ የቀረበ ነውና ሰውየው የተናገረውን ቃል በቃል አልያዝን ይሆናል፤ ጉዳዩ ውስብስብ ስላልሆነ ግን ከተናገረው ጭብጥ ሊርቅ እንደማይችል እርግጠኞች ነን።

እንግዲህ በገዢው ቡድን ቁጥጥር ስር ያሉ የህዝብ መገናኛ ብዙሃን እንዴት እንደሚሰሩ ለምናውቅ፣ መለስ ዜናዊ የተጠየቀውን ጥያቄ ከመጠየቁ በፊት እንዳየው እና ምናልባትም ጥያቄውን ራሱ እንዲጠየቅ የፈለገው እሱው እንደሆነ መገመት እንችላለን። አዲስ ዘመን ጋዜጣ ይህንን ጥያቄ እንዲጠይቀው ለምን እንደፈለገ ወይም እንደፈቀደ አሁን ባናውቅም፤ አዜብም ከባሏ ጋር እየገነነች በመጣችበት ዘመን ስለሷ እንዲወራ መፈለጉ ይገባናል።

እንግዲህ መለስ ዜናዊ እንዳለን አዜብ የራሷ ንግድ አላት፤ እሱን ካወቅነው ቆይተናል። ስብሃት ነጋን አባራ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ትልቅ ድርሻ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ያለውን ኤፈርትን ከመቆጣጠሯ በፊት የሜጋ አሳታሚ ሃላፊ እንደነበረችን እናውቃለን። ነገር ግን በግልጽ ከሚታወቁት የንግድ እንቅስቃሴዎቿ በተጨማሪ ጫት እና እንጀራ ሳይቀር ወደ ውጭ አገራት የመላክ ንግድ በማንቀሳቀስ እንደከበረችም መረጃዎች አሉ። እነዚህን የንግድ እንቅስቃሴዎቿን ከዳር ለማድረስም የመንግስት ተቋማትን እንዳሻት ስታሽከረክር ቆይታለች።

የቤተሰቡ የስራ ክፍፍል ግልጽ ሆኖ የቆየ ይመስላል፤ ባልየው የፖለቲካ ስልጣን ተቆጣጥሮ ጫት የሚያመላልሱላት ጄኔራሎች ያቀርብላታል፤ ከህግ በላይ ሆና የምትነግድበትን መንገድም ይፈጥርላታል። እሷ ከአስመጪ እና ላኪነት እስከ ችርቻሮ ድረስ ገብታ በመነገድ አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ለቤተሰቧ ከቢሊዮን ዶላር በላይ አከማችታለች።

አሁን አሁን ግን የቤተሰቡ ስራ አንድ ላይ ሰብሰብ እያለ ያለ ይመስላል። አዜብ ወደ ፖለቲካው አለም ገፍታ እየገባች ነው። የዛሬ አምስት አመት ፓርላማ በመግባት በንኡስ ኮሚቴ መሪነት ጀምራ፤ አሁን የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆናለች። ዳር ላይ ያሉ የንግድ ስራዎችን ትታም ኤፈርትን ተቆጣጥራለች። ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው እሁድ የዘገበው እና ዛሬ በዜና ክፍለ ጊዜ ያሰማናችሁ መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ፥ መለስ ዜናዊ የአገሪቱ ዋና የስኳር ነጋዴ ለመሆን ትእዛዝ አስተላልፏል።

ጫት ቃሚዎች ሁሉ ከአሁን በኋላ በአረንጓዴው ቅጠል ስኳር ዘገን አድርጋችሁ ወደ አፋችሁ ስትጨምሩ፣ ቅጠሉንም ስኳሩንም የሰጣችሁን እያሰባችሁ ምርቃት ልታደርጉ እንደሚገባ ልብ በሉ። ወጣ ብላችሁ ለበርጫ የምትጠቱት ቢራም ቢሆን የሌላ አይደለም። ሰሜን ኮሪያውያን ለሚያገኙት መፍትሄ ሁሉ ምስጋና የሚገባው ለታላቁ መሪ፣ ለውዱ መሪ፣ ለጄኔራሉ እና ለአባታችን ኪም ጀንግ ነው እያሉ ፎቶግራፉን እጅ እንደሚነሱት፤ በቅርቡ የመለስ ዜናዊን ፎቶግራፍ ጎንበስ እያላችሁ መሳለማችሁ አይቀርም።

ገዢው ቤተሰብ የበርበሬ፣ የሽንኩርት እና የዘይትን ንግድ የተቆጣጠረ እለታ ደግሞ ምድረ ኢትዮጵያዊ የሚቀረው ቅሪት ቢኖር ትንፋሹ ብቻ ነው። የበርበሬ ነገር ከነተሳስ አይቀር አዜብ መስፍን እስካሁን ለምን እንዳላሰበችበት ሊገባን አልቻለም። ጣሊያን ኢትዮጵያን ለአምስት አመታት በተቆጣጠረ ጊዜ ወጥ ውስጥ ጨው አትጨምሩ ብሎ ህዝቡን ሊያሳብድ ምንም አልቀረው ነበር። አሁን ምድረ አበሻ በርበሬ ቢወሰድበት ጤናማ ሆኖ ይቀጥላል?

ወያኔ የማዳበሪያን ንግድ ተቆጣጥሮ አብዛኛውን የኢትዮጵያ ገበሬ መሄጃ ባሳጣበት አስተሳሰቡ ስለ በርበሬ ያላሰበበት ምክንያት በእውነቱ ግልጽ አይደለም። ስሌቱ ቀላል ነው፦ በቃ፥ “የህዝቡን ጤንነት ለማሻሻል ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ከአሁን ጀምሮ በርበሬ መመረት ያለበት ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ነው ሲል መመሪያ አስተላልፏል። ከዚህ በኋላ በርበሬ የሚመረተው ከመንግስት ልዩ ፈቃድ በሚሰጣቸው ፋብሪካዎች ብቻ ነው። ፈቃድ ሳያገኝ በርበሬ ሲያመርት የተገኘ ህገ-መንግስቱን በሃይል ለመናድ በመሞከር ይከሰሳል፤ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ ሞትም ይቀጣል።” የሚል አዋጅ ማውጣት።

ከዛ በኋላ በርበሬ የማምረት ፈቃድ ለኤፈርት መስጠት። ቀጥሎ በርበሬ ለመግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በየቀበሌው እንዲመዘገቡ ትእዛዝ ማስተላለፍ። ያልተመዘገበ በርበሬ አያገኝም። ተመዝግቦ ዘግሞ ጸባዩን ያላሰመረም አይሸጥለትም። ገዢው ጸባዩን ባሳመረ ቁጥር የሚሸጥለት መጠን ከፍ ይላል፤ ባስከፋ ቁጥር ደግሞ እየቀነሰ ሄዶ ምንም እስካለማግኘት ይደርሳል።

የናንተን አናውቅም እንጂ ይሄ ለኛ ጥሩ የንግድ ሃሳብ ይመስለናል። ያለ ምንም ክፍያ ለቀዳማይ ነጋዴዋ ለማስተላለፍም ፈቃደኞች ነን። እንግዲህ በእውነቱ ይህ የተናገርነው ነገር ቀልድ ይምሰል እንጂ፤ የወያኔ አገዛዝ ባለፉት ሃያ አመታት ሲያካሄድ የቆየውን ዘረፋ ሂደት ከሞላ ጎደል የሚገልጽ ነው። ደግሞ እውነቱን በበርበሬ ላይ እንደዚህ ያለ መመሪያ ቢወጣ ሊገርመን አይገባም።

ሰዎቹ ላመኑበት ዘረፋ፣ ሌብነት እና ግድያ ጠንካሮች እና ጨካኞች ናቸው። ጥያቄው፥ እኛ ላመንበት እውነት፣ ፍትህ እና ነፃነት ምን ያህል ጠንካሮች እና ጨካኞች ነን የሚለው ነው።

አምና እንዴት አለፈ፤ ለዘንድሮስ ምን ሰነቅን?

Thursday, September 16th, 2010

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋገረን ይላል።

ያለፈው ዓመት ለኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች የመከራ ዓመት ነበር። በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ጋሻ መሬት ለባዕዳን ተቸብችቧል። ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ከአራት አስርት ዓመታት በፊት “መሬት ላራሹ” የሚል መፈክር አንግበው ሕይወታቸውን የሰውት የኢትዮጵያ መሬት በኢትዮጵያዊያን ጉልተኞች ተይዞ ገበሬው “አርሰህ ሲሶ ገብር” ስለተባለ ነበር። ዛሬ ግን የኢትዮጵያ መሬት በባዕዳን ጉልተኞች ተይዞ ገበሬው ሙሉ በሙሉ ከግብርናው ተነቅሎ “የቀን ሠራተኛ ሁን” እየተባለ ነው። “ከድጡ ወደ ማጡ” የተባለው በኢትዮጵያ አርሶ አደር ላይ ደርሷል።

የኢትዮጵያዊያን ከተሞች የቅኝ ግዛት ከተሞች ሆነዋል። ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው በአደጉ አገሮች እንኳን የማይገኙ የተንጣለሉ ቤቶችና ግቢዎችን ሲገነቡ ድሃው ከደሳሳው ጎጆው እየተፈናቀለ መውደቂያ አጥቷል። ባሳለፍነው ዓመት አዲስ አበባ ከፍተኛ የሃብት መበላለጥ የሚታይባት አፍሪካዊት ከተማ ሆናለች።

ኑሮ እየከፋ ቢሆንም ወያኔን ሕዝቡን በወሬ እንዳጠገበው ነው። “አብዮታዊ ዲሞክራሲ”፣ “ቦናፓርቲዝም”፣ “ጥገኛነት”፣ “ልማታዊነት፣ “ኒዮ ሊበራሊዝም” … እነዚህ ሁሉ የወያኔ ማምታቻ ቃላት ናቸው። 2002 ሲገባደድ ደግሞ “ትራንስፎርሜሽን” የተሰኘ አዲስ ማምታቻ ይዞ መጥቷል። በዚህ አዲስ ማምታቻ ሕዝቡን የተስፋ እንጀራ ይቀልባል።

2002 ያለፈው እስር ቤቶች በነፃነት ታጋዮች እንደተሞሉ ነው። ለራሱ ክብር የሚሰጥ፣ ለነፃነቱ ቀናኒ የሆነ እና ሃገሩን የሚወድ ዜጋ መኖሪያው እስር ቤት የሆነባት አገር ኢትዮጵያ ነች። የዛሬይቷ ኢትዮጵያ በህፃናትና አዛውንት እስረኞች ላይ ሰቆቃ የሚፈፀምባት አገር ናት።

ያለፈው ዓመት የወያኔ ዘረኝነት “ከወርቅ ሕዝብ” ወደ “ወርቅ ጎጥ” ከዚያም ወደ “ወርቅ ቤተሰብ” በመጨረሻም ወደ “ወርቅ ግለሰብ” የዘቀጠበት ዓመት ነበር። የዚህ የቁልቁለት ጉዞ ከዚህ በታች መወረድ እማይችልበት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ በቅርቡ በተደረገው የወያኔ ጉባዬ ውጤት ተረጋግጧል። የአገዛዙ እምብርት የሆነው ወያኔ አመራር በመለስና ስብሃት የሥጋና የጋብቻ ዘመዶች እንዲያዝ ተደርጓል። በአንፃሩ ደግሞ በየክልሉ የተደራጁት ሎሌ ድርጅቶች መሪዎች እንደካርታ ተፐዋውዘው ቦታ እንዲቀያየሩ ተደርጓል። በዚህም የመለስ ዜናዊ ቤተሰብ በህዋህት ውስጥ ሲደላደል በየክልሉ ባሉ ሎሌ ድርጅቶች ውስጥ ያሉት ግንባር ቀደም አገልጋዮች ምቾች እንዳይሰማቸው ተደርጓል። ይህም የዘረኝነት አለንጋ ራሳቸው ወያኔዎችንም ጭምር እየገሸለጣቸው መሆኑን ያሳያል።

2002 መለስ ዜናዊ እንደ ቪኦኤ አይነቱን የውጭ አገራት ዜናዎችን እንደሚያፍን በግልጽ የተናገረበት ዓመት ነው። እውነተኛ መረጃን ነፍጎ በምርኮ የያዘውን ሕዝብ በጨለማ እየነዳ ነው።

ባጭሩ ያለፈው ዓመት የወያኔ ፋሽስትነት ፈጦ የወጣበት፤ ዘረኝነት የሁላችንም የጋራ ጠላት መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ የተረጋገጠበት ዓመት ሆኗል።

ባለፈው ዓመት ለነፃነት በሚደረገው ትግል ጎራም የተፈጠሩ አዳዲስ ክስተቶች አሉ። ከሁሉም በፊት ወያኔ ለሰላማዊ ትግል ያለውን እድል ሙሉ በሙሉ የዘጋ በመሆኑ “ወያኔን በምን መንገድ እንታገለው?” የሚለው ጥያቄ አላስፈላጊ ሆኗል። ከወያኔ በኋላ በምትኖረው ኢትዮጵያ ባህርያትም ላይ ወደ መግባባት እየተሄደ ነው። በተፈለገው መንገድ ባይፈጥንም እንኳን ይህ ሂደት የነፃነት ኃይሎችን አስተባብሯል። ዛሬ ብዙዎች ከወያኔ በኋላ የምትኖረውን በየደረጃው በሕዝብ ነፃ ፈቃድ በተመረጠ መንግሥት የምትመራን ውብ አገር አሻግረው መመልከት ችለዋል። በዚህም ምክንያት በድርጅቶች መካከል የነበረው ሽኩቻ እየቀነሰ፤ ተቀራርቦ የመሥራት ባህል ደግሞ ከእለት ወደ እለት እየጎለበተ መጥቷል። እጅግ ብዙ ቢቀረንም አበረታች ምልክቶች እየታዩ ነው።

በሲቪሉ ማኅበረሰብም ውስጥ “የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል” የሚለው እምነት ከመጎልበትም አልፎ በተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተተረጎመ ነው። የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ጥምረት መፈጠሩ የዚህ ውጤት ነው።

የኢሳት ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) መፈጠርም ኢትዮጵያዊያን በኅብረት ከተነሱ እንደምን ያለ ውጤቶችን ሊያመጡ እንደሚችሉ ያመላከተ ነው።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ያለፈውን የትግል ዘመን ያሳለፈው ድርጅታዊ ብቃቱን በማጎልበት ነበር። ዛሬ ግንቦት 7 በኢትዮጵያም ከኢትዮጵያ ውጪም ጠንካራ ድርጅታዊ መሠረት ተክሏል፤ ከሌሎች የፓለቲካና የሲቪክ ማኅበራት ጋር ያለውንም ግኑኝነት አዳብራል። በቅርቡም ከሁለት ኢትዮጵያዊያን የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር ጥምረት ፈጥሯል።

ከሌሎች ድርጅቶች ጋር መተባበራችን የወያኔን ውድቀት ማፋጠን ብቻ ሳይሆን የወደፊቷን ኢትዮጵያ መሠረት መጣል ነው ብለን በጽኑ እናምናለን።

አዲሱ ዓመት ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች በጋራ ተነስተን ወያኔን የምናርበደብድበት ይሆናል ብለን እናምናለን። ለዚህም ቀንና ለሊት በትጋት እንሰራለን።

2003 ዓም የፍሬዓማ ትግል ዓመት እንዲሆንል እንመኛለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የመለስ ዜናዊን ወደ አሜሪካን ሃገር መጓዝ በመቃወም ሰልፍ ሊደረግ ነው

Thursday, September 16th, 2010

እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2003 ጀምሮ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በየዓመቱ የሚካሄደው የዓለም ሃገራት መሪዎች መድረክ በዚህ ዓመት በሚያደርገው ስብሰባ የዓለማችን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታና ተጸኖው በሚል ርእስ መለስ ዜናዊ ጽሁፍ እንዲያቀርብ መጋበዙን የዩኒቨርሲቲው ድረገጽ አስታውቋል።

በዚህ ዓመታዊ ስብሰባ፥ በዓለማችን ፈታኝ እየሆኑ በመጡ ወቅታዊ የፖለቲካ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ችግሮች ዙሪያ ውይይትና ክርክሮች የሚደረጉ ሲሆን ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የሚገኝበት ስብሰባ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ሮቱንዳ ሎው ሊብራሪ ሴፕቴምበር 22 ቀን 2010 ከ 4 ፒኤም እስከ 5 ፒኤም እንደሆነ ታውቋል።

የዘረኛውን አምባገነን ወደ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ መጋበዝ ተከትሎ በውጭ ሃገራት የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ካሁኑ ከፍተኛ ተቃውሞና ቁጣ በመግለጽ ላይ ያሉ ሲሆን ወደ ዩኒቨሪሲቲው በሚመጣበት ወቅትም የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ እንቅስቃሴ መጀመሩም ታውቋል። በውጭ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲን በተቃውሞ ኢሜይሎች፣ ስልክ ጥሪዎችና ደብዳቤዎች እያጨናነቁ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል። ቀደም ሲል የመለስ ዜናዊን መምጣት ለማስተዋወቅ በድረ-ገጹ ላይ ባኖረው ጽሁፍ መለስ ዜናዊን ያሞገሰው ተቋምም በርካታ ተቃውሞዎችን ከተቀበለ በኋላ ሙገሳውን እንዳስወገደ ለመረዳት ችለናል።

በዚህ አጋጣሚ የግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘረኛና አምባገኑን መለስ ዜናዊን ለመቃወም በሚደረገው ሰልፍ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሳተፉ፤ እንዲሁም በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው ማህበረሰብ የሃገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ እንዲገነዘብ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪውን ያቀርባል።

አዜብ መስፍን የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆና መሾሟ ተዘገበ

Thursday, September 16th, 2010

የዘረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ባለቤት የሆነችው አዜብ መስፍን በህወሃት አስረኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆና መሾሟ ተዘግቧል።

በኢትዮጵያ ስልጣን ተቆጣጥሮ ያለው ቡድን አስኳል የሆነው ህወሃት (ወይም ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) ሐሙስ እለት አስረኛ መደበኛ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ ስምንት የቀድሞ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱንም አሰናብቷል። ከስምንቱ ውስጥ፥ የፓርቲው አባት እና የመለስ ዜናዊ ፖለቲካዊ ሞግዚት እንደሆነ የሚነገርለት ስብሃት ነጋ በእርጅና ስም መልቀቂያ ጠይቋል ሲል የአገዛዙ አንደበት የሆነው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ዘግቧል።

ስብሃት ነጋ ከዚህ ቀደም ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነቱ እንደተወገደ ይታወሳል። ከዛሬ አመት በፊት በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ የአማርኛ ዝግጅት ላይ ለቃለመጠይቅ ቀርቦ ጉዳዩን በሚመለከት ጥያቄ የቀረበለት ስብሃት፣ “በፓርቲው አካባቢ እሱን ያለመፈለግ ሁኔታ” እንዳለ ገልጾ ነበር። ይሁን እንጂ ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች የስብሃት ከቁልፍ የስልጣን መቀመጫዎች መወገድ ከአዜብ መስፍን ጋር ሳይያያዝ እንደማይቀር ይናገራሉ።

የዘረኛው አምባገነን ባለቤት ከተወሰኑ አመታት ወዲህ እየገነነች የመጣች ሲሆን፤ በፓርቲው ውስጥ ከስብሃት ነጋ ጋር በከረረ የግል ሽኩቻ ውስጥ እንደሚገኙ ይነገራል። ስብሃት ነጋ የወያኔ ኩባንያ የሆነውን ኤፈርትን ከማስተዳደር ስራው ሲነሳ አዜብ መስፍን የምክትልነት ካባ ለብሳ ድርጅቱን መቆጣጠርዋ ይታወቃል።

በዚሁ የህወሃት አስረኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ስዩም መስፍን፣ አርከበ እቁባይና አባይ ጸሃዬ ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነታቸው ተነስተዋል። በተያያዘ ዜና፥ የወያኔ ተለጣፊ ፓርቲ የሆነው ብአዴን (ወይም ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) የረዥም ጊዜ የይስሙላ መሪው የነበረውን አዲሱ ለገሰን አስወግዶ በደመቀ መኮንን ተክቶታል። ሌላኛው ተለጣፊ ፓርቲ ኦህዴድ አባ ዱላ ገመዳን አስወግዶ አለማየሁ ቱምሳን በሊቀመንበርነት ተክቶታል።

“የብርትኳን ሳምንት” በፌስቡክ ላይ ታስቦ ሰነበተ

Thursday, September 16th, 2010

ከሃያ ወራት በላይ በግፍ እስር ላይ የምትገኘው የአንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ፌስቡክ በተባለው የግንኙነት መረብ ድረ-ገጽ ላይ በዚህ ሳምንት ታስባ ሰንብታለች።

ሊቀመንበሯን ለማሰብ እንቅስቃሴ የጀመሩት ኢትዮጵያውያን፣ ካለፈው ረቡእ እስከ ዛሬ መስከረም 1 ድረስ በመረቡ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ወዳጆቻቸው በሙሉ ፎቶግራፏን በየገጾቻቸው እንዲያስቀምጡ የሚጋብዝ ዘመቻ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ወ/ት ብርትኳን ከቅንጅት ባልደረባዎቿ ጋር ከእስር ቤት የተፈታችበትን ትክክለኛ ሁኔታ በስዊድን አገር በተደረገ ስብሰባ ላይ በማስረዳቷ እና ያንንም ቃል ለማጠፍ ፈቃደኛ ባለመሆኗ አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በታህሳስ 2001 እንዳሰራት ይታወሳል። ከታሰረችም በኋላ በከፍተኛ ደረጃ ሰብአዊ መብቶቿ ሲጣሱ እንደቆዩ እና፤ እስካሁን ድረስ ከእናቷ እና ከአምስት አመት ልጇ በስተቀር ጠበቃዋ እና ሌሎች ወዳጅ ዘመዶች እንዲጎበኟት እንደማይፈቀድ ይታወቃል።

የውጭ ምንዛሪ ለውጡ እውነተኛ ምክንያቶች እና መውሰድ የሚኖርብን እርምጃዎች

Thursday, September 9th, 2010

(Ginbot 7) — ወያኔ በድንገት የብርን የምንዛሬ ምጣኔ በ20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎ ቀድሞ በ13.62 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘር የነበረው አንድ የአሜሪካ ዶላር በብር 16.35 እንዲመነዘር አዟል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እንደ ወታደራዊ ተቋም በትዕዛዝ የሚመራ በመሆኑ ለምንዛሪው ምክንያት መጠየቅ ያለበት መለስ ዜናዊ እንጂ የባንኩ ገዢ ወይም “ቦርድ” የተባለው ስብስብ አይደለም። የባንኩ ገዢም ሆነ ቦርዱ አስፈፃሚዎች እንጂ ወሳኞች አይደሉም። የገንዘብንም የበጀትንም ፓሊሲዎች የሚቀርፀው ወይም እንደተመቸው የሚጫወትባቸው መለስ ዜናዊ እንደሆነ አገር ያወቀው ጉዳይ ነው። እናም መለስ ዜናዊ ይኸን ድንገተኛ የምንዛሬ ለውጥ ያደገረባቸውን እውነተኛ ምክንያቶችን ማወቅ ይጠቅማል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባደረገው መጠነኛ ምርምር እና ስለወያኔ ባህርይ ካለው እውቀት በመነሳት የውጭ ምንዛሪው ለውጥ እውነተኛ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል።

  1. ፈጣን ዘረፋ – ይህ ከፍተኛ የምንዛሪ ለውጥ ድንገተኛ የሆነው ለተራው ኢትዮጵያዊ እንጂ ለወያኔ ባለሥልጣኖች እንዳልሆነ እኛ በተጨባጭ የደረስንበት ጉዳይ ነው። የምንዛሪው ለውጥ ከመደረጉ ጥቂት ቀናት በፊት ጀምሮ ወያኔ “አሜሪካ ገንዘብዋን ልትቀይር ነው” የሚል ውዥንብር በማስወራት የዋሁ ነጋዴ የያዘውን የውጭ ገንዘብ እንዲቀይር ገፋፋው። የወያኔ ባለሥልጣኖችና ተላላኪዎቻቸው ደግሞ በጎን በስፋት ወደ ገበያ የቀረበውን የውጭ አገር ገንዘብ ሸመቱ። ግዢው ሲጠናቀቅ ትዕዛዙ ተላለፈና በአንድ ጊዜ ሃብታቸው በ20 ከመቶ እንዲያድግ ተደረገ። እንዲህ አይነት መሰሪ ተግባር በዘራፊነታቸው በታወቁ መንግሥታት ዘንድ እንኳን አስፀያፊ ተግባር ነው፤ ለወያኔ ግን ብልህነት ነው።
  2. “ተወዳዳሪነትን ማሳደግ” - ወያኔ ለም መሬት የመሸጥ ፉክክር ውስጥ ገብቷል። ቻይና መንግሥቷ እራሱ ነጋዴ ሆኖ መሬት እየሸመተ ነው። ህንድና ሌሎች አገራት ደግሞ የመሬት ግዢውን እንዲያጧጡፉ የየሃገራቸው ቱጃሮችን እያበረታቱ ነው። አፍቅሮተ-ንዋይ የማስተዋያ አዕምሮዓቸውን የሰለበባቸው የአፍሪቃ አገሮች ገዢዎች “ከእኔ ግዙኝ፤ ከእኔ ግዙኝ” በሚል ፉክክር ውስጥ ገብተዋል። ወያኔ ለባዕዳን ለም መሬትን በሄክታር በአስር ዶላር እየሸጠ ቢሆንም ከዚህም በታች በማውረድ “ተወዳዳሪነቱን” ከፍ ለማድረግ ታጥቆ ተነስቷል። የቡናና የጫት የወጪ ንግድ እና የማዳበሪያና የመድሃኒት የገቢ ንግዶች በምንዛሪ ለውጥ ምክንያት እጅግም እንደማይለወጡ የታወቀ ጉዳይ ነው። ለወያኔ በብር መርከስ ምክንያት የሚፋፋ ንግድ ያለው የመሬት ሽያጭ ብቻ ነው። እናም ወያኔ የብር ምንዛሪ በመቀነስ የኢትዮጵያን ለም መሬት በሳንቲሞች በመቸርቸር ለባህዳን አስረክቦ እማንወጣው ማጥ ውስጥ ሊያስገባን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው።
  3. ከድሃው ወደ ሃብታም የሚጎርፈው የሃብት ፍሰትን ማሳለጥ – አሁን የተደረገው የምንዛሬ ለውጥ ብዙም ጊዜም ሳይወስድ የአገር ውስጥ ዋጋዎችን ማስጨመሩ አይቀርም። በዚህም ምክንያት ለጥቂት ጊዜዓት ጋብ ብሎ የነበረው የዋጋ ግሽበት ይቀሰቀሳል። የዋጋ ግሽበት ደግሞ የወያኔ ጥብቅ ወዳጅ ነው። የዋጋ ግሽበት ድሃው የሚያጠራቅመውን ገንዘብ ስውር በሆነ መንገድ እወያኔ ኪስ ውስጥ ይከትለታል። በዋጋ ግሽበት ምክንያት ሃብቱን በኢትዮጵያ ብር ያስቀመጠ ይከስራል፤ የኢትዮጵያ ብርን የተበደረ ደግሞ ይከብራል። በዛሬዋ ኢትዮጵያችን ውስጥ ሃብት በብር – ለዚያው በትናንሽ ብሮች – የሚያስቀምጠው ድሃው ነጋዴና የመንግሥት ሠራተኛው ነው፤ በሚሊዮኖች የሚበደረው ደግሞ “ልማታዊ ባለሃብት” እየተባለ የሚቆላመጠው ወያኔ፣ የወያኔ ወዳጅ አልያም የወያኔ ወገንተኛ ነው። እናም የሰሞኑ የምንዛሪ ለውጥ ሃብትን ከድሃው ሀገርተኛ ወደ ወያኔው ሃብታም ሲያሸጋግር የነበረው የዋጋ ንረት እንዲቀሰቀስ ታስቦ የተደረገ ነው።
  4. የትላልቅ ቁጥሮች ፍቅር – ወያኔ ትላልቅ ቁጥሮችን ይወዳል፤ ለህልውናው ያስፈልጉታልም። በውሸት የተሞሉ የቁጥር ቁልሎች የእርዳታው ምንጭ ናቸው። የብርን አንፃራዊ ዋጋ በ20 ከመቶ በመቀነስ የ15 በመቶ ዓመታዊ እድገት ህልሙን የማሳካት እቅድ አለው። ከዚህ አንፃር ሲታይ ይህ የምንዛሪ ለውጥ “የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅዱ” አካል ነው። ዋጋዎች ሲጨምሩ ቁጥሮችም ይጨምራሉ። ወረቀት ላይ እስከታየ ድረስ እድሃው ማዕድ ላይ እድገቱ ባይታይም ዓለም ባንክን እምብዛም አይጨንቀውም።

እኛ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ወያኔ በኢትዮጵያዊያንና በኢትዮጵያ ላይ እንዲጨፍር እስከፈቀድንለት ድረስ እንዲህ የረቀቁ የዘረፋ ዓይነቶችን በመፈልሰፍ ማስደመሙን ይቀጥልበታል። የወያኔን የዘረፋ ጥበብን እየተከታተሉ ማጋለጥ ተገቢ ቢሆንም ዋነኛ ሥራችን መሆን ያለበት ግን በሁለገብ ትግል ወያኔን ፊት ለፊት ገጥሞ ማዳከም ብሎም ማስወገድ ነው።

ግንቦት 7 ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደገለፀው ሁሉ በውጭ አገራት የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ባለመሆን ብቻ እንኳን ወያኔን ማስጨነቅ ይችላል። የወያኔ ማባበያዎችን ተቀብለው ሃብታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ያሻገሩ ወገኖች ዛሬ አባብለው በወሰዷቸው ሰዎች ተንኮል የንብረታቸው 20 በመቶ ማሙቷል። ይህ የምንዛሪ ለውጥ የመጨረሻው እንዳማይሆን ከወዲሁ ማስጠንቀቅ እንወዳለን። ወያኔ ጥቅም እስካገኘበት ድረስ ደግሞ ብርን ማዳከሙን ይቀጥልበታል። ወያኔ ለራሱ ካልሆነ በስተቀር ለማንም ደንታ የለውም። ይህን ከልብ ከተረዳን ደግሞ ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ ማትኮር ይኖርብናል።

በግንቦት 7 እምነት ዘላቂው መፍትሄ በተባበረ ክንድ ወያኔን ማስወገድ ነው። ለዚህ ወሳኝ ትግል ሁላችንም በጋራ እንነሳ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የኛ “ትራንስፎርሜሽን ፕላን” ኢትዮጵያን ከዘረኝነት ማጽዳት ነው

Thursday, August 26th, 2010

(Ginbot7.org) — አንድን ነገር ደጋግሞ እየሠራ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ አዕምሮው በትክክል የማይሠራ ሰው ብቻ ነው ይባላል። ወያኔ አዕምሮዓቸው በትክክል መሥራት በማይችል ሰዎች የተሞላ ድርጅት መሆኑ ድርጊቱ ይመሰክራል። ባለፉት አምሳ ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ሲደረግ የቆየው በባዶ ቁጥሮች በተነፋ እቅድ የመኩራራትን “ስልት” ዛሬ እነ ግርማ ብሩ እንደ አዲስ ጥበብ ያስተዋውቁን ይዘዋል። የወያኔ የሰሞኑ ማደንቆሪያ “አዲሱ” የአምስት ዓመት እቅድ “ትራንስፎርሜሽን ፕላን” በመባል ፈረንጅና ስም እንዲኖረው ከመደረጉ በስተቀር በይዘትም ሆነ በቅርጽ ከድሮዎቹ የባሰ እንጂ የተሻለ ነገር የለበትም።

የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እቅድ ታሪክ መለስ ብሎ ለተመለከተ በተመሳሳይነታቸው መገረሙ አይቀርም። ሁሉም ወረቀት ላይ የሚጮኹ ናቸው። ሁሉም የየጊዜው ባለሥልጣኖች ጉራቸውን ነዝተውባቸዋል። ይሁንም እንጂ አንዳቸውም እናሳካለን ያሉትን ግማሹን እንኳን ተግባራዊ አላደረጉም። በተለይም ባለፉት ሠላሳ አመታት እቅዶቹ ብቻ ሳይሆን አቃጆቹም አልተቀየሩም። ለምሳሌ ግርማ ብሩ፣ መኮንን ማንያዘዋል እና ሱፍያን አህመድ የደርግ ማዕከላዊ ፕላን ባለሥልጣናት በነበሩበት ጊዜ በአየር ላይ የተንሳፈፉ እቅዶችን እየነደፉ ስለፈጣን ልማት አይቀሬነት “በደርግኛ” ሲተነትኑ ነበር። ዛሬ ያው የሰለጠኑበትን የውሸት እቅድ “አጠናክረው” “በወያኔኛ” መተንተን ተያይዘውታል። እነዚሁ ሰዎች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ውስጥ ስለመሆኑ ቢያንስ በሶስት የተለያዩ ጊዜያት ተናግረዋል። የመጀመሪያው የደርግን የአስር ዓመት እቅድ ሲያስተዋውቁ የተናገሩት ሲሆን፤ በዘመነ ወያኔ ደግሞ ይኸ ሁለተኛ ጊዜዓቸው ነው። ዘወትር ተግባራዊነቱ የማይታይ “የመዋቅራዊ ለውጥ እቅድ” አጋፋሪዎች ሆነው መቅረታቸው ህሊናቸውን አይኮሰኩሰውም። “እናመጣለን ብላችሁት የነበረው እድገት የታል?” ብሎ የጠየቃቸው ስለሌለ ውሸትን ከመለማመድ አልፈው ከአጥንትና ሥጋቸው ጋር አዋህደውታል። ይብዛም ይነስ ያላቸውን የአካዳሚና የአስተዳደር እውቀት እየቀለበ ለሚጋልባቸው አምባገነን ሁሉ መጠቀሚያ አድርገውታል። እናም አሁን ለበለጠ ውሸት ተበረታተው ቀርበዋል። ከእነዚህ ሰዎች የተሻለ የአድርባይነት ህያው ተምሳሌት ከየት ይገኛል?

አሁን የታወጀው “የትራንስፎርሜሽን እቅድ” በዘፈቀደ ከተሞሉ ቁጥሮች በስተቀር መሬት ባለ ሃቅ ላይ ላለመመሥረቱ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት ማረጋገጥ ይቻላል። “ምን ተደርጎ ነው ኢኮኖሚው በአንድ ጊዜ እንዲህ የሚመነደገው?” የሚለው ጥያቄ መሠረታዊ ነው። ማንም እንደሚረዳው የአገር ኢኮኖሚ በአንድ ምሽት በቅሎ የሚያድር እንጉዳይ አይደለም። ለእንጉዳይም ቢሆን ደመናና ካፊያ ያስፈልገዋል። አሁን እየተነገረን ያለው እድገት ምንጩ እምን ላይ ነው? ይህ ጥያቄ በተደጋጋሚ ተነስቶ መልስ ባለማግኘቱ ወደ ሌሎች ጥያቄዎች እናልፋለን። ወያኔዎች እንዲህ በቀላሉ መመንደግ እንደሚቻል እያወቁ ምነው እስከዛሬ ተንቀረፈፉ? ለምንድነው ባለፈው አምስት ዓመት የታቀደውን ግማሽ ያህል እንኳን ሰብል ያልተሰበሰበው? ከ16. 7 ሚሊዮን ቶን ወደ 38.21 ሚሊዮን ቶን እናሳድጋለን ተብሎ ታቅዶ 18.08 ሚሊዮን ቶን ላይ ሲቆም ማን ተጠየቀ? ለምንድነው የኢንዱስትሪው ድርሻ 16.5 ከመቶ ይሆናል ተብሎ ታቅዶ ድሮ ከነበረበት 13.6 ከመቶ ወደ 13 ከመቶ ያሽቆለቆለው? ባለፉት አምስት ዓመታት ያልሰራው እቅድ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንደሚሠራ በምን ተገመተ? ጥያቄዎቻችን ብዙ ናቸው። የአፋር ክልል አምስት ሚሊዮን ተማሪዎችን አስመዘገበ እያለ ከሚቀደድ የዋሾዎች ቡድን እርባና ያለው ምላሽ ይገኛል ተብሎ ስለማይጠበቅ ጥያቄዎቻችንን እዚሁ ላይ ማብቃቱን መርጠናል።

አንድ ሃቅ ግን አጽንዖት ሊሰጠው ይገባል። ይህም “የአምስት ዓመቱ የትራንስፎርሜሽን ፕላን” የውሸት ክምር መሆኑ ነው። ከውሸትነቱ በተጨማሪ ግን ይህ እቅድ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ የበለጠ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነው። ይህንን በመጠኑም ቢሆን ዘርዘር አድርጎ ማየት ይበጃል።

ወያኔ በዘር የተከፈለች ሁለት ኢትዮጵያዎችን ፈጥሯል። አንደኛዋ ኢትዮጵያ የወያኔዎችና የምስለኔዎቻቸው ነች። ይህች አገር ሃብታምና በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች ያለች ናት። የዚች አገር ዜጎች ቁጥር ከጥቂት መቶ ሺዎች አይበልጥም። ሌላኛዋ ኢትዮጵያ 80 ሚሊዮን ያህል እንሆናለን ተብሎ የምንገመተውን የያዘችው ምስኪኗ እማማ ኢትዮጵያ ናት።

ሃብታሟ ኢትዮጵያ በዓመት 3.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እርዳታ ስለምታገኝ በዓመት 15 በመቶ ማደግ ያንሳታል። እርግጥ ነው እርዳታ የሚመጣው በድሃዋ ኢትዮጵያ ስም ነው። ይሁን እንጂ የሃብታሟ ኢትዮጵያ “ምርጥ” ዜጎች አንዱ በተቋራጭነት፣ ሌላው በእቃ አቅራቢነት፤ አንዱ በደላላነት፣ ሌላው በአስፈፃሚነት ቢሊዮኖቹን ዶላሮች ይከፋፈሉታል። የውጭ እርዳታ እና “በምርጥ ዜጎች” መካከል ያለው የሃብት ክፍፍል እንዲቀጥል መንገዶች መሠራት፤ ግድቦች መገንባት አለባቸው – አለበለዚያማ ምን በምን ሰበብ ሊወሰድ ኖሯል?

በከተሞች አዳዲስ ፎቆችና ቪላዎች መገንባታቸውም እሙን ነው። ሆኖም አሁንም እነዚህ ፎቆችና ቪላዎች የእነማን ናቸው ብሎ መጠየቅ ያሻል። መልሱም ቀላል ነው – ንብረትነታቸው የሃብታሟ ኢትዮጵያ ዜጎች ነው። በድሆች መንደር ውስጥ የዱባይ ህንፃ መንትያዎች ቢገነቡ የመበላለጣችን እንጂ የመልማታችንን መጠን አያመለክቱም።

የሃብታሟ ኢትዮጵያ ዜጎች ሃብት በአገር ውስጥ ብቻ አይደለም ያለው። እነዚሁ ሰዎች በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና በአረብ አገሮች የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን እያከማቹ ነው። አዜብ መስፍን፣ ስብሃት ነጋ፣ ሳሞራ የኑስ፣ ገዛኢ አበራ፣ አርከበ እቁባይ፣ አባይ ፀሃዬ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳ እና መሰሎች በውጭ አገራት ያከማቹት ሃብት በመቶ ሚሊዮኖች የአሜሪካ ዶላሮች የሚገመት ነው።

የአብዛኞቻችን ኢትዮጵያ ግን እያደር እየከሳችና እየገረጣች ነው። የአብዛኞቻችን ኢትዮጵያ በድህነት፣ በበሽታ፣ በማይምነት፣ በፍትህ እጦት ዓለምን ትመራለች። ዜጎቿ አገር ለቀው እንዳይወጡ በር ተዘግቶባቸው የሚገኙ እስረኞችና ግዞተኞች ናቸው። ይህች ኢትዮጵያ በቅራኔዎች ተወጥራ ልትፈነዳ ደርሳለች። የሁለተኛዋ ኢትዮጵያ ዜጎች መሬት በአንደኛ ኢትዮጵያ ዜጎች እየተነጠቁ ገበሬዎች ለቀን ሠራተኝነት እንኳን የወያኔ አባልነት ፎርም በመሙላት ተገዢነታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚገደዱባት አገር ናት።

ታድያ የሶፍያን አህመድና ግርማ ብሩ “የትራንስፎርሜሽን ፕላን” የየትኛዋ ኢትዮጵያ እቅድ ነው? ሃብታሟ ኢትዮጵያ “ትራንስፎርም” ከሆነች ቆይቷል፤ ደግሞ 15 ከመቶ ያንሳታል። የኛዋ ኢትዮጵያ ግን ስለምን እየተነገረ እንደሆነም አይገባትም። እሷ በሰቆቃ፣ በእልህና በቁጭት ተሞልታ ለውጥን በማማጥ ላይ ያለች ናት። ስለ “ኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን” ለመቀለድ ጊዜም ፍላጎትም አቅምም የላትም።

“የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ፕላን” ነፋስ ላይ የቆመ በመሆኑ ከግርግር በስተቀር መሬት ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። ሆኖም ከሌሎች ተመሳሳይ እቅዶች ይኸኛው የከፋ የሚያደርገው በሌሎች አገሮች እርዳታ በትንሹ እንኳን ቢሳካ ጥቂት ዘረኞችን ጠቅሞ አብዛኛዎቻችንን የሚጎዳ መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ ለማናችንም አይበጅም።

ኢትዮጵያ በሁለት ተከፍላ መቆየት አትችልም። “ትራንስፎርም” መደረግ ያለበት እውነታ ይህ ነው:: የኛ ትራንስፎርሜሽን ፕላን ዘረኝነትን በማጥፋት ኢትዮጵያን የሁሉም ዜጎቿ የእኩል አገር ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ይቻላል፤ እናደርገዋለንምም!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ስርአት የለም ሲል ተመጻደቀ

Thursday, August 26th, 2010

የቪኦኤ አዲስ አበባ ዘጋቢ ፒተር ሄንሌይን በኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ሲስተም ስለመኖሩ ላቀረበለት ጥያቄ፤ ውሸት የማይሰለቸው ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አይኔን ግምባር ያርገው በሚል የተለመደ ቅጥፈቱ “እንደጃፓንና ቦትስዋና አንድ ጠንካራ ፓርቲ እንጅ የአንድ ፓርቲ ስርአት የለም” በማለት ተመፃድቋል። በጃፓንም ሆነ ቦትስዋና ለረጂም ጊዜ ስልጣን ላይ የቆዩት ፓርቲዎች በሃገራቸው ውስጥ በሰፊው የህዝብ አመኔታን አግኝተው የህዝብ ድምጽ ማጭበርበር ሳያስፈልጋቸው ወይንም በህዝብ የተመረጡትን መግደል፤ ማሰርና ከሃገር ማሰደድ ሳያስፈልጋቸው ስልጣን ላይ የቆዩ ኡሁን እንጂ እንደ መለስ ዜናዊና ቢጤዎቹ ግለሰቦች ለአስርና ላሃያ ዓመታት በስልጣን ላይ የቆዩበት ወቅት አልተመዘገበም ።

ከዚህም ሌላ የመናገር የመሰብሰብ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን መገደብ ሳያስፈልጋቸው የሃሰት የልማት እድገት ቁጥር ሳይፈበርኩ በአለም ዘንድ ዝናን ያተረፈ መሰራታዊ የእድገት ለሃገራቸው ያስመዘገቡ መሆኑን መለስና ቢጤዎቹ ልብ ብለውት አያውቁም ተብሏል። መለስ ዜናዊ አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ እንዳያልፍ በካድሬዎቹ አማካኝነት ገድቦ ከያዘ በኋላ 99.6% አግኝቻለሁ በማለት በቀድሞ የኮሚዩኒስት ሃገራት በስልጣን ላይ የነበሩ ባለ አንድ ፓርቲ ስራቶች ሲከተሉ የነበሩትን መንገድ ተግባራዊ አድርጓል። ለማወናበድና ለመቅጠፍ በማስረጃነት የሚጠቅሳቸው እንግሊዝ ቦትስዋና ጃፓን አንድም ወቅት በንደዚህ አይነት ውጤት አሸነፍንበት ያሉበት ወቅት እንደሌለ ይታወቃል።

በቪኦኤ ጋዜጠኛ ወያኔ 99.6% አሸንፊያለሁ ስላለው ምርጫ የታዛቢ ቡድን ሪፖርት ተጠይቆ የሰራው ሴራ የተጋለጠበት መለስ ዜናዊ “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ግምገማ ሪፖርት ቢዘገይም አያስጨንቀኝም ከዋናውና ማጠቃለያ ሪፖርታቸው በፊት ያቀረቡልኝ የመጀመሪያ ሪፖርት አያስደስትም እናም እንደ መረጃ ለመያዝም የሚየስደፍር አይደለም ብሏል። የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በመጀመሪያ ግምገማ ሪፖርቱ የ2010ሩን ምርጫ ግልጽነት የጎደለው እና ዓለማቀፋዊ መስፈርቶችን የማያሟላ ነው ማለቱ ይታወሳል።