Author Archive

እሳት ነው ወጣቱ።

Sunday, February 13th, 2011

እሳት ነው ወጣቱ።
ከአቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወ-መንፈሳዊ

እሳት ነው ወጣቱ።

እየለበለበ፤
እያንገበገበ፤
ጠላት ያነደደ፤
ባንዳዎች ያጨደ::
ሐቅ ነው ከጥንቱ፤
አያውቅም ብላችሁ እንዳትጫወቱ፤
ይፋጃል በደሙ እሳት ነው ወጣቱ::
እንኳን ላገራችን፤
ለነፃነታችን፤
ይረ-ሳል መገ ደል?
ይበልጥ በወቸገል??
ስንቱ ጀግና ወድቋል፤
በአጋዚ ሕዝብ አልቋል::
ጅቦች እየመራ፤
ለወገን ሳይራራ፤
ራሱ ጅብ ሁኖ፤
በቅንድብ ሸፍኖ፤
እሱም እየበላ፤
ባዕድ ጅብ ሲያበላ፤
ሃያ ዓመታት ሆነ፤
ደም ከተጀቦነ ::
መለስ ነው “ወቸገል”፤
የሚገል የሚያስገ’ል።
ሌላው ፍርፋሪ ሊጠርግ የተሸጠ፤
ሥልጣን ያራዝማል እያበጣበጠ::
አገር ሁሉን ያውቃል፤
ያን ቀን ይጠብቃል::
ቢሆንም ይጀመር ሌላውም አይቀርም፤
እያንዳንዱን ባንዳ ወጣቱ አይምርም::
እየለበለበ፤
እያንገበገበ፤
ጠላት ያነደደ፤
ባንዳዎች ያጨደ፤
ሐቅ ነው ከጥንቱ፤
አያውቅም ብላችሁ እንዳትጫወቱ፤
ይፋጃል በደሙ እሳት ነው ወጣቱ ::
በግፍ እንደታሰረ፤
ነብስ እየገበረ፤
ደም እንደከፈለ፤
በአምባገነኖቹ እየተገደለ፤
ዛሬም ይታገላል ከሕዝቡ ውስጥ አለ::
ሕዝቡም እያወቀ አምርሮ ተነስቷል፤
ሰበብ ነው የቀረው ትዕግስቱ አብቅቷል::
እናም ነፃነት እንበል፤
ቆርጠን እንታገል፤
ከመለስ ካልጀመርን፤
በግል ካላመረርን፤
ወያኔ ጎናችን መግደል ይቀጥላል፤
መጪው የእኛ ትውልድ:-
ብዙ ደም ይከፍላል::
ግና ዛሬ መለስ፤
የበላው እስኪመለስ፤
እጁ ይያዝ የታል??
ጀግናው መጥቶለታል፤
“ወቸገል”እሱ ነው፤
መግደል የተካነው ::
እናም ይያዝ የታል??
በቃ አልቆለታል::
የሚለበልበው፤
የሚያንገበግበው፤
ፍሞ የሚያነደው፤
ባንዳዎች ያጨደው::
ሰበቡን ጠብቆ፤
የሚገለው አንቆ፤
መጋሙ ሲጀምር፤
ሕዝብ ሲነሳ የምር፤
አይምርም ከጥንቱ፤
አያውቅም ብላችሁ እንዳትጫወቱ፤
ይፋጃል በደሙ እሳት ነው ወጣቱ::

ዝም አይልም ሕዝቡ፤ በቃ ወዮላቸው!

Monday, January 31st, 2011

ከ አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወ-መንፈሳዊ

እንደ ክቡር ደራሲው ከበደ ሚካኤል፦

***”ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት፤
ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት፤
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ፤
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ።”***
ብለው እንደተረጎሙት፤
ይኑር ብዕራቸው ለዘላለም አይሙት።

ሕዝቡ ዝም አይልም ፦በቃ ወዮላቸው!!!

ያጋዚ-ወያኔን
ጠርጎ እስኪፈጃቸው።
ዝም አይልም ሕዝቡ
በቃ ወዮላቸው!!!
እናም፦
እኔም እንደአቅሚቲ ለዘመኑ ብዬው፤
በደም ለታጠቡት ትዕቢተኞች ይሄው።
ኢትዮጵያን ያረዱ የፈጁ ሕፃናትን፤
ሕዝቧን በአደባባይ ገድለው ያስገድሉትን፤
በጊዜ በሥልጣን በገንዘብ ቢ-ገዙ፤
የስጋ-ትል ሆነው ሺህ መግደል ቢያበዙ፤
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ሥርፅ ነው መዘዙ፤
በሞት-ሲቃ ትግል በጣዕር እስኪያዙ።
አይጠፋም እሣቱ የተቀጣጠለው፤
ደሙ “ዋይ!!! ዋይ!!!” ይላል፦
ሲቃ ነው ያጀለው።
እቶን ነው እሣቱ ጠርጎ እስኪፈጃቸው፤
ሲዖል ነች ኢትዮጵያ ለመጨረሻቸው።
ከተሸሸጉበት ሳይጎለጉላቸው፤
በደም እንዳጠቧት እሷም ሳታጥባቸው፤
እንደሲዖል ማንጉግ :-
ሕዝቡ ሳይበላቸው፤
ዝም አይልም ቀልቡ
ያውቀዋል ውስጣቸው።
ዝም አይልም ሕዝቡ
በቃ ወዮላቸው!!!
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው ሥርፅ ነው መዘዙ፤
በሞት-ሲቃ ትግል በጣዕር እስኪያዙ።
ቱኒሲያ ቢነድ
ትግሉ የመን ቢነጉድ
ግብፅ ቢቀጣጠል
ከኤርትርያ ቢዘል
እግዚአብሔርም ሰምቶ ለሕዝቧ ይሰጣል፤
ኢትዮጵያን የነካት የሞት ሞት ይቀጣል።
የኢትዮጵያ አምላክ:-
እንዲያ ሲታገሳቸው፤
ዝም አይልም ሕዝቡ
በቃ ወዮላቸው!!!