Author Archive

በአዲስ አበባ የፍተሻና የዝርፊያ አቤቱታ

Wednesday, February 20th, 2013

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ልዩ አካባቢዎች “በሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ያነጣጠረ የቤት ለቤት ፍተሻና ዘረፋ እየተካሄደ ነው” የሚል ጥቆማ በደረሰን መሠረት ሁኔታውን ለማጣራት ሞክረናል። በጥቆማው መሠረት በሌሊት ፍተሻ የተሠማሩት ሰዎች ማንነታቸውን እንደሚደብቁና የጥቃቱ ሰለባዎች ደግሞ፥ በየካና ቦሌ ክፍለ ከተሞች፥ በኮልፌ ቀራንዮ፥ ቤቴልና አካባቢው ሠፈሮች የሚኖሩ ሙስሊሞች ናቸው።

ሙስሊሞቹ ይህ በዘመቻ መልክ እየተፈፀመብን ነው ያሉት የቤት ፍተሻና ዝርፊያ በእርግጥ እየተካሄደ ነወይ? ከሆነስ ለምንና ባሁኑ ወቅት ይካሄዳል?
እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎች ይዘን ማምሻውን የጥቃቱ ሰለባ ሆነናል ወደሚሉ ሰዎችና ፖሊስ ደውለን ነበር።

ሰሎሞን ክፍሌ ነው ዘገባውን ያጠናቀረው፤ ያዳምጡት

አንጋፋው የሙዚቃ ሠው ተስፋዬ ለማ አረፈ

Tuesday, February 5th, 2013

«ከአርባ ስድስት ዓመታት በፊት የአሜሪካ የሰላም ጓድ ሆኜ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዝኩበት ጊዜ በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ስማረክ የተዋወቅኩት ተሥፋዬ ለማ ለኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ከፍተኛ አስተዋጽ ያደረገ ሰው ነው።» ቻርልስ ሳተን።

በአንዳንዶች የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ አባት የሚል የቁልምጫ ሥም የተሰጠው እውቁ ሙዚቃ ሰው ተሥፋዬ ለማ ባለፈው ሃሙስ ለሊት፥ ለአርብ አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ተሥፋዬ ለማ «ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ፤» በሚል ይታወቅ የነበረው የቀድሞውን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፥ የዛሬውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ሙዚቃ ባንድ በመራባቸው ዓመታት፥ የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ በአጠቃላይ የኅብረተሰቡንም ሆነ የሌሎች ተቀባይነትና ተሰሚነት ማስገኘት ባስቻሉ ሥራዎቹ ይወደሳል።

ተሥፋዬ ለማ ከኦርኬስትራ ኢትዮጵያ በኋላም በተለያዩ የሙዚቃ ተቋማት ባከናወናቸው ሥራዎቹ፥ ባፈራቸው ታዋቂ ድምጻውያን እና እንዲሁም ጥላሁን ገሰሰን ጨምሮ ለገናና ድምጻውያን በጻፋቸው የሙዚቃ ድርሰቶቹም ይታወቃል።

ተስፋዬ፥ የህክምና ክትትልና እገዛ ከሚያገኝበት የአዛውንቶች መኖሪያ ሳለ የደረሰውን በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ታሪክ ላይ ያተኮረ ዳጎስ ያሉ ገጾች ያሉት መጽሃፍ ለማሳተም ጥረት በማድረግ ላይ ሳለ ነው፥ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

የአንጋፋውን የሙዚቃ ሠው ተሥፋዬ ለማን ህይወትና ሥራ ለመዘከር የተሰናዱትን ቅንብሮች ከዚህ ያድምጡ።

ቆይታ ከሁለገቧ አርቲስት ዓለም ጸሃይ ወዳጆና ከአርቲስት ዓለማየሁ ገብረህይወት ጋር

Play below

 

ቆይታ ከተሥፋዬ ለማ የእድሜ ልክ ወዳጅ፥ Charles Sutton ጋር

Play below

 

ሃሣብን በመግለፅ ነፃነት ኢትዮጵያ 137ኛ፣ ኤርትራ የመጨረሻ፣ ሶማሊያ በዓለም እጅግ አደገኛ ሆኑ

Thursday, January 31st, 2013

ኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕጓን በጋዜጠኞች ላይ አስከፊ በሆነ መንገድ ስለምትጠቀም የጋዜጠኞች አያያዝ ደረጃዋ ቀደም ሲል ከነበረችበት በአሥር መውረዱን ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ድርጅት አስታወቀ፡፡ ዛሬ በወጣው የድርጅቱ ሠንጠረዥ ኤርትራ ከ179 ሃገሮች 179ኛ ሆናለች፡፡ ባለፈው የአውሮፓ ዓመት ብቻ 18 ጋዜጠኞች የተገደሉባት ሶማሊያ በዓለም እጅግ አደገኛዋ ተባለች፡፡ አምብሯዝ ፒየር – የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የአፍሪካ ዴስክ ኃላፊ

Play below

 
ሃሣብን በነፃነት በመግለፅ እና በፕሬስ ነፃነት በኩል ምሥራቅ አፍሪካ በተለይ የአፍሪካ ቀንድ ከአጠቃላዩ አህጉር እጅግ አሳሳቢው መሆኑን በምኅፃር አርኤስኤፍ ወይም ራፖርቶር ሣን ፍሮንቲዬ ወይም ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ዋና ፅሕፈት ቤቱ ፓሪስ-ፈረንሣይ የሚገኘው ዓለምአቀፍ ቡድን የአፍሪካ ዴስክ ኃላፊ አምብሯዝ ፒየር ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ቡድኑ ዛሬ ባወጣው የአውሮፓ 2013 ዓመት የፕሬስ ነፃነት ሠንጠረዡ ላይ አርትራ የመጨረሻዋ መሆኗን የገለፁት አምብሯዝ ፒየር “…አንድም የግል ፕሬስ የሌለባት፣ በአፍሪካ ትልቋ የጋዜጠኞች እሥር ቤት…” ሲሉ ጠርተዋታል፡፡

ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም ከሽብር ፈጠራ ጋር በተያያዘ አሥራቸው የነበሩ ሁለት ስዊድናዊያን ጋዜጠኞችን ባለፈው መስከረም መልቀቋ እንደ በጎ ዜና ቢሰማም ለሃገሪቱ ጋዜጠኞች ግን ሁኔታው አሁንም ከባድ መሆኑን አምብሯዝ ገልፀዋል፡፡

“… በዚህች ሃገር ውስጥ ያለው ችግር ባለሥልጣናቱ ፀረ-ሽብር ሕጉን የሚጠቀሙበት የመረጃ ነፃነትን ለመገደብ ጉዳይ ነው…” ብለዋል አምብሯዝ ፒየር ስለኢትዮጵያ በሰጡት መግለጫ፡፡

የፍትኋ ርዕዮት ዓለሙ፣ የአውራምባ ታይምሱ ውብሸት ታየ፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ከሶማሊያ ይዘው የወሰዷቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ኤርትራዊያን ጋዜጠኞች ሳልህ ኢድሪስ ጋማ እና ተስፋልደት ኪዳኔ ተስፋዝጊ፣ እንዲሁም ሃሣቡን በኢንተርኔት የሚገልፀው ብሎገኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ በኢትዮጵያ እሥር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የሪፖርተር ሳን ፍሮንቲዬ የአፍሪካ ዴስክ ኃላፊው አምብሯዝ ፒየር አመልክተዋል፡፡

የኤርትራው ወታደሮች አመፅ – ነገሩ ምንድነው? ሰዎቹስ እንዴት ናቸው? ወደፊትስ?

Tuesday, January 22nd, 2013

VOA – ወደ አንድ መቶ የሚሆኑ የኤርትራ ወታደሮች ሰሞኑን ባካሄዱት አመፅ የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ይዘውት ውለዋል፡፡ ምሽት ላይ ለቅቀው ወጥተዋል፡፡ ነገሩ ምንድነው? ሰዎቹስ እንዴት ናቸው? ወደፊትስ?

በአሁኑ ሰዓት ያለውን ሁኔታ ለማወቅ «ኤርትራዊያን» የተሰኘ መጽሐፍ ደራሲና በድንበር-የለሽ ጋዜጠኞች ቡድን የቀድሞው የፕሬስ ነፃነት ዳይሬክተር፣ ፍሪላንስ ጋዜጠኛ ሌኦናር ቪንሶንን የቪኦኤ የአፍሪቃ ቀንድ ክፍል ኃላፊ ፒተር ሃይንላይን አነጋግሯል።

ሌኦናር ቪንሶን በኤርትራ ጉዳይ ላይ ላለፉት አራት ዓመታት ጥናቶችን እያካሄደ ይገኛል፡፡

ፒተር ለቪንሶን ያቀረበው የመጀመሪያው ጥያቄ ወደ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ሄደው መሥሪያ ቤቱን ተቆጣጥረው የነበሩት ሰዎች አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነበር፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ

ሙስሊሞች ‘ድምፃችን ይሰማ’ ሲሉ የአንድ ዓመት መታሰቢያ አደረጉ

Sunday, January 20th, 2013

“ድምፃችን ይሰማ” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ አባላት ለመንግሥት ጥያቄ ያቀረቡበትን አንደኛ ዓመት በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሰሞኑን አስበዋል፡፡
ዕለቱን ዓርብ ጥር 10 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባና በሌሎም አካባቢዎች በተከናወኑ ሥርዓቶች ማሰባቸው ታውቋል፡፡

“ሠላማዊው ትግላችን የተጀመረበት አንደኛ ዓመት ነው” በሚል ሰሞኑንም በተለያዩ ከተሞች ውስጥ የሚስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት የተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶችን ማካሄዳቸውን ከአዲስ አበባ ከሐረርና በደሴ ከተሞች ያነጋገርናቸው ምዕመናን አመልክተዋል፡፡

አዲስ አበባ ላይ ምዕመናኑ ያለፈውን ሣምንት ያሣለፉት እሥር ቤት የሚገኙትንና ቤተሰቦቻቸውን በመጠየቅ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

ሐረር ከተማ ውስጥ “365 ቀናት ለሃይማኖት ነፃነት” በሚል ርዕስ የተሠናዳ ሥነ-ሥርዓት በኢማን አራተኛ መስጊድ ከተከናወነ በኋላ በተፈጠረ ሁኔታ መካከል አንድ በዚያ ሲያልፍ የነበረ ሕፃን በጥይት ተመትቶ መሞቱንና እናቱም መቁሰሏን የሚናገር ጥቆማና ዜና ደርሶናል፡፡ ሰሞኑንም የሐረሪ ፖሊስ ሁለት ወጣቶችን ከአዲስ አበባ ይዞ መውሰዱና ማሠሩም ተሰምቷል፡፡

ሁኔታውን ከሐረሪ ፖሊስ ለማጣራት ብዙ ሙከራዎችን ብናደርግም የሐረሪ ፖሊስ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ ወይም ዝግጁ ሣይሆን ቀርቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በደሴው ሸዋበር መስጊድም እንዲሁ የተቃውሞ ሥነ-ሥርዓት መካሄዱንና አማኒያንና ኢማሞችን ጨምሮ የታሠሩም ሰዎች መኖራቸውን የሚናገር ጥቆማ ሰምተናል፡፡

ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ደሴ ፖሊስ ደውለን በቢሯቸው ያገኘናቸው ሳጅን ቸርነት ተፈጠሩ የተባሉት ሁኔታዎች ሁሉ “ያልነበሩ ናቸው” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የደሴ ከተማ የአስተዳደርና የፀጥታ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ በላይ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ችግር መኖሩን እርግጥ ነው ብለው “አክራሪዎች ናቸው” ያሏቸው ሰዎች ኢማሞችን እንደሚጋፉ፣ የሶላትና የፀሎት ሥርዓቶችን እንደሚረብሹና መናገሪያዎችን እንደሚገነጣጥሉ፣ “ከመካከላቸው ነው” ያሉትም አንድ ሰው ሌላ ሰው በጩቤ ወግቶ ጉዳዩ በሕግ የተያዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጥያቄአቸውን ለመንግሥት ያቀረቡት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ትግላቸው ሰላማዊ መሆኑን በየአጋጣሚው ይናገራሉ፡፡

በዋሽንግተን ዲሲና በአካባቢው ያሉ ሙስሊሞችና ደጋፊዎች የሚካፈሉበትን የፊታችን ጥር 18 ወይም ጃንዋሪ 26 የሚካሄድ አንድ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን ፈርስት ሂጅራ የሚባለው ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚገኝ ተቋም አስታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ሙስሊሞች ዓርብ ጥር 10 ቀን የዋለውን የከተራ በዓል ምክንያት በማድረግ “…ዕለቱ የክርስቲያን ወገኖቻችን በዓል በመሆኑ አንዋር መስጂድ አቅራቢያ በሚገኙ ቤተክርስቲያኖች ሊኖር የሚችለውን ዝግጅት ታሣቢ በማድረግ በአዲስ አበባ ፕሮግራሙ በኑር (በኒ) መስጂድ የሚከናወን ሲሆን በየክልሎችም አመቺ በሆኑ መስጂዶች ላይ ይከናወናል፡፡” የሚል መልዕክት ቀደም ሲል በትነው የፀሎቱንና “ድምፃችንን እናሰማለን” ያሉበትን ቦታ ለውጠዋል፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

የርዕዮት ዓለሙ ይግባኝ ውድቅ መደረጉን ዓለምአቀፍ ድርጅቶች አወገዙ

Tuesday, January 8th, 2013

VOA – በጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ላይ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማፅናቱ ያሣዘናቸው መሆኑን ዓለምአቀፉ የሴቶች የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት – IWMF እና ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ድርጅት CPJ አስታውቀዋል፡፡

IWMF መግለጫውን በይፋ አውጥቶ ያሠራጨ ሲሆን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኤሊሣ ሊዝ ሙኞዝ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት ጉዳይ ድርጅታቸውን በእጅጉ የሚያሠጋው መሆኑን አመልክተዋል፡፡

“ርዕዮት ለጋዜጠኝነት ነፃነት ያላትን ድፍረት፣ ቁርጠኝነትና ጥንካሬ እናደንቃለን፡፡ ቀደም ፀሰል የተላለፈባት ፍርድ በመፅናቱ ማዘናችንን እንገልፃለን፡፡ ይህ ለእርሷ ሕይወት ብቻ ሣይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሣብን በነፃነት ለመግለፅ ነፃነትም ጭምር አሣዛኝ ቀን ነው፡፡ ለሌሎች በእሥር ላይ ለሚገኙ ጋዜጠኞችም የሚሰማንን መቆርቆር እንገልፃለን” ብለዋል ዳይሬክተሯ፡፡

ዓለምአቀፉ የሴቶች የመገናኛ ብዙኃን ባወጣው ይፋ መግለጫው ኢትዮጵያ ውስጥ እሥር ቤት ውስጥ ባሉ ጋዜጠኞች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ፣ በፕሬስ ነፃነት አያያዟ በዓለም እጅግ ጨቋኝ ከሚባሉ ሃገሮች ተርታ መመደቧን አስታውሶ ባለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዘመን በአፍሪካ ውስጥ ከኤርትራ በስተቀር ሌላ ማንም ሃገር በማይስተካከለው ሁኔታ ጋዜጠኞችን ማሠሩን አመልክቷል፡፡

“የሚወቅሱትን ድምፆች ለማፈን በአደናጋሪው የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕግ መንግሥቱ በተደጋጋሚ መጠቀሙ እጅግ አሣሣቢ ነው” ያለው ይኸው መግለጫ ርዕዮት በሰኔ 2003 ዓ.ም (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ከተያዘች ወዲህ ለብዙ ወራት ያለ ክሥ መታሠሯን እና በኋላም ተግባሯ ሙሉ በሙሉ የጋዜጠኛ ሥራ ሆኖ ሣለ በሽብር ፈጠራ መከሰሷን ዘርዝሯል፡፡

“ባለፈው ነሐሴ በከፊል በተሣካው ይግባኝ በርዕዮት ላይ ቀድሞ የተላለፈው የ14 ዓመት እሥራት ፍርድ ወደ አምስት ዓመት እንዲቀንስ ቢደረግም እስከአሁን የቆየችባቸው 19 ወራት እያንዳንዷ ቀን ወይም ወደፊት በእሥር የምትቆይባቸው 41 ወራት እያንዳንዷ ቀን የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሬስ ነፃነትን ዋጋ እንዳረዳ የምትጎተጉት ማስተወሻ ነች” ብሏል መግለጫው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ ውሣኔውን እንደሚቃወምና እንደሚያወግዝ የአፍሪካ የአድቮኬሲ አስተባባሪ መሐመድ ኬይታ አስታውቋል፡፡

“ያሣዝናል – አለ ኬይታ – ኢትዮጵያ ውስጥ ለሕግ የበላይነት መከበር ቀኑ የኀዘን ቀን ነው፡፡ ምክንያቱም በርዕዮት ዓለሙ ላይ የተመሠረተቱት የሽብር ፈጠራ ክሦች በማስረጃ ለማስደገፍ የቀረቡት ፍፁም አስቂኝ ናቸው፡፡ እነዚህን ክሦች ፈትሸናቸዋል፡፡ የተከሠሠችው በጋዜጠኝነት ላከናወነቻቸው ሥራዎች ነው፡፡ እነዚህ ተቀባይነት ያላቸውና ሕጋዊም መረጃን የመሰብሰብና የማሠራጨት ሥራዎቿ መንግሥትን የሚወቅሱ ናቸው፣ የተቃዋሚ ቡድኖችን እንቅስቃሴ በተመለከተም ዘግባለች፡፡ ይህ መንግሥቱን የሚተቹ የግርግዳ ላይ ፅሁፍ ሣይቀር እንደማስረጃ የቀረበበት ክስ አስገራሚ ነው፡፡” ብሎታል፡፡

በክሦቹ ላይ የተጠቀሱት ጭብጦች በማንም ነፃ ወገን እንደሽብር ፈጠራ አድራጎት ማረጋገጫ አለማግኘታቸውን ወይም አለመደገፋቸውን የሲፒጄው አስተባባሪ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የታየው “የፍትሕ መጨናገፍ ነው” ብሎታል፡፡

ሃገሪቱ ለሽብር ፈጠራ አድራጎት የተጋለጠች መሆኗንና መንግሥቷም የበረታ የሽብር ፈጠራ እንቅስቃሴዎች ሥጋት እንዳለበት ሲፒጄ እንደሚገነዘብ ሞሐመድ ኬይታ አመልክቶ “የጋዜጠኝነት ሥራቸውን በሚያከናውኑ ባለሙያዎች ላይ የሽብር ፈጠራ ክሥ እየመሠረተ ሽብር ፈጠራን ከእውነተኛው መገለጫው እያሣሣተና ክብደቱንም እያቀለለው ነው” ብሏል፡፡

“በዚህ አድራጎቱ ርዕዮትና ባልደረቦቿ ዓለምአቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ እያደረገና የመናገር ነፃነትን ለማፈን እያደረገ ያለውን ተግባር እያጋለጠ ዋጋውን እራሱ ይከፍላል” ብሏል የሲፒጄው የአፍሪካ አድቮኬሲ አስተባባሪ ሞሐመድ ኬይታ፡፡

ርዕዮት ዓለሙ የዓለምአቀፉ የሴቶች ሚድያ ድርጅት የ2012 ዓ.ም በጋዜጠኝነት ላሣየችው ድፍረት እና የዚሁ የ2012 ዓ.ም የሄልማን/ሃሜት ሽልማቶች ተሸላሚ መሆኗ ይታወቃል፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የፊታችን አርብ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ

Wednesday, September 19th, 2012

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ። ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ሃይለማሪያም ደሳለኝ እስካሁንም በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን የሚጠሩት በዚሁ ማእረግ ነው። በተለይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩበት ቀን ጀምሮ ሀገሪቷን የመምራት ሃላፊነት ተረክበዋል ቢባልም የመጠሪያቸው ነገር አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

ቃለ መሃላ ፈጽመው ሙሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑትም ፓርላማው በመደበኛው ጊዜው በሚያደርገው ስብሰባ እንደሆነ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል። አቶ ሃይለማሪያም ፓርላማ ቀርበው ቃለ መሃላ እንዲፈጽሙ የማድረጉ ጉዳይ አስቸኳይ እንዳልሆነም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የተገለጸው በተደጋጋሚ ነው። ባለፉት ሁለት ቀናት ግን ያልተጠበቀና ድንገተኛ ጥሪ ለፓርላማ አባላት ተላልፎአል። እናም የፊታችን አርብ በሚያደርገው አስቸኳይ ስብስባ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃለ መሃላውን እንደሚፈጽሙ ይጠበቃል።
ስነስርዓቱ በድንገት እንዲከናወን የተወሰነውም የፊታችን ማክሰኞ በሚከፈተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ አገሪቱን ወክለው እንዲገኙ መሆኑ ተጠቁሞአል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኢህአዴግ አራት አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በሊቀመንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተፈጠረውን የስልጣን ክፍተት ለመድፈን ምርጫ አካሂዷል። በዚሁ ፓርቲ ውስጥ የአቶ መለስ ዜናዊ ምክትል የነበሩት አቶ አባይ ወልዱ ሊቀመንበር፣ የኮሚኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል።
የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።

ኃይለማርያም ደሣለኝ ማን ናቸው?

Tuesday, September 18th, 2012

ምክር ቤቱ የሚሰበሰው በመደበኛ የመክፈቻ ጊዜው፣ ማለትም በመስከረም መጨረሻ እንደሆነ ሲገለፅ የቆየና የመንግሥት የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር በረከት ስምዖን ባለፈው ቅዳሜ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፓርላማውን በአስቸኳይ መሰብሰብ አስፈላጊ እንዳልሆነ ገልፀው እንደነበረ የሚታወስ ቢሆንም ይህ ሃሣብ ግን ትናንት ተቀይሮ ስብሰባው በአስቸኳይ እንዲጠራ ስለተወሰነበት ምክንያት የተሰጠ ማብራሪያ የለም፡፡

ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ የኢሕአዴግን ምክር ቤት ሙሉ ድጋፍ ያገኙት አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ “ለኃላፊነቱ በቂ ዝግጅት ያላቸውና መልካም ሰብዕናም የተላበሱ ናቸው” ሲሉ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡

ለመሆኑ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ማን ናቸው? የትምህርት፣ የሥራና የቤተሰባቸውን ጨምሮ የግል ሕይወታቸውን የእስክንድር ፍሬው ዘገባ ይዳስሣል፡፡

የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን መለስካቸው አመሃ ደግሞ በዚሁ በአዲሶቹ የኢሕአዴግና የኢትዮጵያም መሪዎች ላይ አንድ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ስሜት ለመቃኘት ሞክሯል።

በኢህአዴግ ማዕከላዊ ምክር ቤት ስብሰባ የግንባሩና የአገሪቱ መሪዎች ይመርጣሉ።

Thursday, September 13th, 2012

በኢህአዴግ ማዕከላዊ ምክር ቤት የመሪዎች ምርጫ ሂደት፤ በወቅቱ የአገሪቱ መሪ ማንነትና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የተካሄደ ቃለ ምልልስ።

የኢህአዴግ ማዕከላዊ ምክር ቤት በያዝነው ሳምንት መገባደጂያ በሚያካሂደው ስብሰባ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የፓርቲውን ሊቀመንበርና የአገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊን የሚተካ መሪ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በማእከላዊ ምክር ቤቱ ስብሰባና የምርጫ ሂደት፤ እንዲሁም ብዙዎችን ሲያነጋግር በሰነበተው በአገሪቱ ኅገ መንግስታዊ ድንጋጌ መሠረት አቶ መለስን በተጠባባቂ ጠቅላይ ሚንስትርነት የተኩት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በመንግስት ብዙኃን መገናኛዎች በምክትል ጠቅላይ ሚንስርነት መጠራትና ሌሎች ተዛማች ርዕሶች ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዲሬክተር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ነው።

ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች አልተፈቱም (VOA)

Monday, September 10th, 2012

የኢትዮጵያ መንግሥት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ፥ ሁለቱን ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ጨምሮ 1,923 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ አስታውቀዋል። በሽብርተኝነት ተከሰው የታሠሩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ጉዳይ ግን ለይቅርታ ቦርዱ አለመቅረቡን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ኢሕአዴግና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦታ ጉዳይ

Wednesday, September 5th, 2012

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢህአዴግ/ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሣኔዎችን አሣልፎ ማክሰኞ፤ ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም ማምሻውን ተጠናቅቋል። ስብሰባው በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኋላ ባሁኑ ወቅት «ሀገሪቱን እየመራ ያለው ማነው?» ለሚለው እጅግ አንገብጋቢ ጥያቄ በቂ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ትላንት ማታ ባሣለፋቸው ውሣኔዎች ላይ ግን ይህን አስመልክቶ በግልፅ እና በማያሻማ ቋንቋ የተገለፀ ነገር የለም።

የተባለው፥ “… የግንባሩን ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀ መንበር የመሰየም ጉዳይ የግንባሩ ምክር ቤት ሥልጣን በመሆኑ በመስከረም 2005 የመጀመሪያ ሣምንት በሚካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ እንዲፈፀም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ወስኗል …” ነው።

«ዲሞክራሲ በተግባር ፕሮግራም» ይህንኑ መነሻ ያደረገ ዝግጅት አለው። ሰሎሞን ክፍሌ የሕገ መንግሥት ባለሙያ ጋብዞ አወያይቷል።

ዝግጅቱን ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሽግግር ምክርቤት ኣመራር ከVOA ኣዲሱ ኣበበ ጋር

Tuesday, August 7th, 2012

ከኣቶ ስለሺ ጥላሁንና ከዶ/ር ፍስሓ እሸቱ ጋር በሁለት ክፍሎች የተዘጋጀውን ውይይት ያድምጡ፡

ክፍል ሁለትን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ፡

መለስ ዜናዊ ሥልጣን ላይ ያለመኖር አንድምታ ዙሪያ ትንታኔ (VOA)

Thursday, July 26th, 2012

የተለያዩ ምንጮች የጤና ይዞታቸውን አስመልክተው የሚያቀርቧቸው መረጃዎች መለያየትና ይፋ ተጨባጭ መረጃ ያለመኖር የአቶ መለስን ወደ አገር መሪነት መንበር መመለስም ሆነ የአገሪቱን አመራርና ቀጣይ ሁኔታ ይበልጥ አነጋጋሪ አድርጎታል።

ይሄንኑ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ተንታኝ ጋብዘናል። ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገ/ማርያም በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ክፍለ ግዛት የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የኅግ ባለ ሞያ ናቸው።

ፕሮግራሙን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ፡

በአቶ መለስ ሕመም ላይ የህወሓት መሥራቹ አቶ ግደይ ዘርዓጽዮን አስተያየት

Thursday, July 19th, 2012

አቶ ግደይ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ውስጥ ለ12 ዓመታት ከቆዩ በኋላ በአ.ዘ.አ. በ1987 ዓ.ም. «በፖለቲካና ሌሎች» ሲሉ በገለጿቸው ምክንያቶች ከድርጅቱና ከሃገርም ወጥተው ባሁኑ ወቅት በተቃዋሚነት በልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ላይ መሰለፋቸውን ያስረዳሉ።

በተለይ አሁን በቅርቡ በተመሠረተው ሸንጎ ውስጥ በዋና ፀሐፊነት ያገለግላሉ።

ዝርዝሩን ከቃለምልልሱ ያድምጡ።

የባለሥልጣናቱ መግለጫ የመለስ ዜናዊን ሕመም ክብደት ያሳያል (VOA)

Thursday, July 19th, 2012

ዴቪድ ሺን አሁን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣናት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃኪም ረዘም ያለ የህመም ፈቃድ እንዲወስዱ መክረዋቸዋል፥ ሲሻላቸዉ ወደ ሥራ ይመለሣሉ ማለታቸው የጤና ችግሩ ከባድ መሆኑን ያመለክታል፤ ህመሙ ከባድ ባይሆን ኖሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥራ የሚመለሱበትን ቁርጥ ያለ ቀን ያሣውቁ ነበር ብለዋል ሺን፡፡

አምባሳደር ዴቪድ ሺን ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሥት ጋር ለረጅም ጊዜ በቅርበት የሠሩ በመሆናቸው በዚህ ትኩረት በሚስብ ጊዜ ውስጥ ውስጡን በመንግሥት ውስጥ ምን እንደሚካሄድ ግምታቸውን ሲጠየቁ ባለፈው ግንቦት ለሃያዎቹ ከበርቴ ሃገሮች ጉባዔ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. በተገኙበት ጊዜ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሆነው እንዳገኙዋቸውና ያኔ ምንም የጤና መቃወስ ምልክት እንዳላዩባቸው፣ ይልቁንስ በጣም ጤናማ ይመስሉ እንደነበረ ጠቁመዋል።

ነገር ግን አቶ መለስ አሁን መወያያ ለሆነው የጤናቸው ጉዳይ ፍንጭ የሚሰጡ አንድ ሁለት አስተያየቶች ጣል አድርገው ነበር ብለዋል። ከዚያ አስተያየታቸው እንደተረዱትም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ስለህመማቸው አስቀድመው ሳያውቁ እንዳልቀሩና ተተኪ መንግሥት አቅደዋል የሚል ግምታቸውን አጋርተዋል። ዝርዝሩን ከዘገባው ያድምጡ።

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )



 

 

 

 

መለስ በቅርቡ እንደሚመለሱ አቶ ስብሃት ነጋ አስታወቁ (VOA)

Wednesday, July 18th, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጤንነት ሁኔታ አስጊ እንዳልሆነና በሚቆጠሩ ቀናት ውስጥም ወደሥራቸው እንደሚመለሱ ከሕወሓት መሥራቶችና አንጋፋ መሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ስብሃት ነጋ ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡ ያዳምጡ

በአዲስ አበባ አወሊያ መስጊድ ፖሊስና ሙስሊሞች ተጋጩ፣ ከ100 በላይ ቆሰሉ (VOA)

Saturday, July 14th, 2012

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን በማስተናገድ ላይ በምትገኘው አዲስ አበባ ትናንት ማምሻውን ፖሊስና በአወሊያ መስጊድ አቅራቢያ የተሰባሰቡ ሰዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ከመቶ በላይ መታሰራቸውንና መቁሰላቸውን፤ የእስልምና ኮሚቴው ገለጸ።

የኮሚቴውን ቃል አቀባይ አህመዲን ጀበል ጠቅሶ የብሉምበርግ የዜና አውታር እንደዘገበውና፤ የዝግጅት ክፍላችን ያናገራቸው የአይን ምስክሮችና አንዳንድ የኢንተርኔት ፎቶዎች እንደሚያሳዩት፤ ግጭቱ ጥይት፣ ቆመጥ፣ ድንጋይና አስለቃሽ ጋዝ የተተኮሰበት ነው። በዚህ ግጭት አንድ ሰው ሳይገደል እንዳልቀረ ኮሚቴው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚንስትር ድዔታ አቶ ሽመልስ ከማል ለብሉምበርግ የዜና አውታር፤ በግጭቱ 72 ሰዎች መታሰራቸውንና ስድስት የፖሊስ ባልደረባዎችን ጨምሮ 10 ሰላማዊ ሰዎች የቆሰሉበት መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

አቶ ሽመልስ አክለውም በአወሊያ ት/ቤትና መስጊድ አቅራቢያ መንገድ በመዝጋት የፖለቲካ መፈክር ያሰሙ የነበሩትን ሰዎች ፖሊስ በአስለቃሽ ጋዝ መበተኑን ተናግረዋል። ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጥይት አለመተኮሱን አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።

በአወሊያ መስጊድ የተሰባሰቡ ሰዎችን ወክለው ለብሉምበርግ የዜና አውታር መግለጫ የሰጡት አህመዲን ጀበል ፖሊስ በአወሊያ መስጊድ ተሰባሰበው በሰላይ የተቀመጡ ሙስሊሞች ላይ አጥር ጥሶ በመግባት፣ ጥቃት ማድረሱን ተናግረዋል።

“በሩን ሰብረው ገብተው በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ተኩስ ከፈቱ” ብለዋል አቶ አህመዲን።

በኢትዮጵያ መንግስትና በእልምና ምክር ቤቱና ደጋፊዎቹ መካከል ግጭቱ የተባባሰው፤ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ እየገባ ነው በሚል በምክር ቤቱ በተነሳ ቅሬታ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት የሃይማኖት ጉዳዮችን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ይተው፤ መሪዎቻችንን እራሳችን እንምረጥ ይላል፤ ምክር ቤቱ።

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ምክር ቤቱ በውስጡ የፖለቲካ ተልእኮ ያላቸውና ኢትዮጵያን በእስላማዊ ህግ የምትመራ አገር የማድረግ ጽንፍ የረገጠ አክራሪነት ያለባቸው አካላትን አካቷል ሲል ወንጅሏል።

ይሄ አስተያየት የተሰማው በሚያዝያ ወር በአርሲ አሳሳ ከተማ ውስጥ አንድ የእስልምና አባት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ይመራሉ በሚል በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተቀሰቀሰ ግጭት 4 ሰዎች ከተገደሉና በርካቶች ከታሰሩ በኋላ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል በአዲስ አበባ ትናንት ማምሻውን የተቀሰቀሰው ግጭት መብረዱንና ሁኔታው በቁጥጥር ስር መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መሪዎችን በምታስተናግድበት ወቅት አንዳንድ ሃይሎች ብጥብጥ ለመፍጠር እየጣሩ ናቸው በለዋል አቶ ሽመልስ ከማል።

ዝርዝር ዘገባው ያዳምጡ፣

Play below

 

የወያኔ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ24 ተከሳሾች ላይ ከ8 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እሥራት ፈረደ

Friday, July 13th, 2012

ችሎቱ እንደተሰየመ ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም ባዘዘው መሠረት ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ ሃሳባቸውን በጽሑፍ ማቅረባቸውን ገልጿል።

አስከትሎም እንያንዳንዱ ተከሣሽ በቀረበበት ክሥ መሠረት ጥፋተኛ ሰለተባለ ያስከትላል ያለውን ቅጣት ዘርዝሯል። እንደክሡ ማመልከቻ ቅደም ተከተል አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ፋሲል የኔዓለም የዕድሜ ልክ ፅኑ እሥራት ተፈርዶባቸዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ ቅጣት የተጣለባቸው አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ ሲሆኑ የሃያ አምስት ዓመት ፅኑ እሥራት ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ዘጋቢአችን መለስካቸው አምሃ ሌሎቹም ተከሳሾች የተቀጡበትን ዓመታት ዝርዝር እንዲሁም ቤተሰቦችና የፖለቲካ መሪዎች ስለፍርድ ቤቱ ውሣኔ የሰጡትን መልስ አካቶ ያጠናቀረውን ዘገባ ያድምጡ።



የእሁዱን የሕዝበ ሙስሊም ስብሰባ ወያኔ ሕገወጥ ነው አለ

Friday, July 13th, 2012

ሐይማይኖትን ሽፋን ያደረጉ አንዳንድ ወገኖች የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ በሚካሄድበት ቀን የተከለከለና ሕገወጥ ስብሰባ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው ሲል ፌደራል ፖሊስ አስጠንቅቋል፡፡

በሌላ በኩል ግን በአዲስ አበባ መስጊዶች የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ወይም ሰደቃ ለማድረግ ዕሁድ ሐምሌ ስምንት ቀን የተያዘው የሙስሊም አማኒያን ፕሮግራም ሠላማዊ ነው፤ የሐይማኖት ጉዳይ ነው፤ በታሰበው መሠረት ይካሄዳል ሲሉ የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ከሚል ሸምሱ ለቪኦኤ አመልክተዋል፡፡

የመንግሥትን ማስጠንቀቂያ የሚመለከተውን ዘገባና ከአቶ ከሚል ሸምሱ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለምልልስ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ፡፡

በሳውዲ አረቢያ ያለ ፍርድ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ሥቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጸ

Monday, June 25th, 2012

ለበርካታ ወራት በሳውዲ አረቢያ ያለፍርድ የታሰሩ ከሰላሳ በላይ ኢትዮጵያዉያን የክርስትና እምነት ተከታዮችን ለማስፈታት የታለመ ሰላማዊ ሰልፍ በዛሬው ዕለት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ተካሄዷል።

ከዋሽንግተኑ የሳውዲ ኤምባሲ ደጃፍ ለሦሥተኛ ጊዜ የተካሄደውን ሰልፍ የጠሩት በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዓለም ዙሪያ በአማንያን ላይ የሚፈጸሙ በደሎችን ለመዋጋት የቆመ አንድ መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገ የሰብዓዊ መብት ድርጅት በመተባበር ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ እዚያው ሳውዲ ዐረቢያ ውስጥ ባሉ በርካታ እስር ቤቶች ውስጥ «ያለ ፍትሃዊና በቂ የፍርድ ሂደት እአማቀቅን ነን፤ ስቃዩን ተሸክመናል፤» የሚሉ በእስር ቤቶች ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ብሶታቸውን ገልጸውልናል።

የዘገባዎቹን ሙሉ ዝርዝር ቀጥሎ ያድምጡ፤

Play below

 

ባድመ ከተማ አቅራቢያ ከባድ የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ ምስክሮች ገለጹ (VOA)

Friday, June 8th, 2012

በኢትዮጵያና ኤርትራ ሰሜን ምእራብ ድንበር ባድመ ከተማ አካባቢ የተኩስ ድምጽ መስማታቸውንና ቁስለኞች በሃኪም ቤት ሲታከሙ መመልከታቸውን አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎችና፤ በአካባቢው አባላት እንዳላቸው የሚናገሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ።

ከሳምንት በፊት ኤርትራ 21ኛ የነጻነት ቀኗን ባከበረችበት እለት የኢትዮጵያ ጦር ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት ማካሄዱን የኢትዮጵያ የመከላከያ ምንስቴር ምንጮችን ጠቅሶ የሪፖርተር ጋዜጣ የዘገበ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ማብቂያ ደግሞ በባድመ የሚገኝ አንድ ት/ቤት መቃጠሉን ጋዜጣውና ቪኦኤ ያነጋገራቸው የአይን ምስክሮች ገልጸዋል። በከተማው አንድ አውቶብስ መቃጠሉም ተዘግቧል።

በኢትዮጵያና ኤርትራ ሰሜን ምእራብ ድንበር ባድመ ከተማ አካባቢ አዲ ኮከብና አዲ ድዓሮ ቀበሌዎች እንዲሁም በባድመ ከተማ አቅራቢያ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በምሽት የከባድ መሳሪያ ተኩስ፤ እንዲሁም የነፍስ ወከፍ ጥይት ድምጽ እንደተሰማ አንድ የአካባቢው ሰው ለዝግጅት ክፍላችን ያዩትን ገልዋል።

የአይን ምስክሩ የተኩስ ድምጽ መስማታቸውንና ቁስለኞች በሃኪም ቤት ሲታከሙ መመልከታቸውን ለቪኦኤ ገልጸዋል።

ሳምንታዊው የሪፖርተር ጋዜጣ የመከላከያ የውስጥ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ ጦር ባለፈው ሳምንት ድንበር ተሻግሮ የሰነዘረው ጥቃት፤ አንድ ብርጌድ የኤርትራ ጦር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ነው ብሏል።። በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ባይታወቀም ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናትን ጨምሮ ወታደሮች የተማረኩበት እንደሆነ ተጠቅሷል። በኢትዮጵያ በኩል የደረሰው ጉዳት አልተገለጸም።

ከዚህ ጥቃት በኋላ በተከታታይ የሚሰሙ የተኩስ ድምጾች እንዳሉ ምስክሩ ለቪኦኤ የገለጹ ሲሆን በባድመ ከተማ የሚገኝ አንድ ት/ቤት በከባድ መሳሪያ ተመቶ መቃጠሉን ገልጸዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ከአዲስ አበባ የተሰጠ መግለጫ የለም። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር አቶ አሊ አብዱ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ “በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቢያለሁ” ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባዮችን ለማግኘት ያደረግንው ጥረት አልተሳካም።

የታህታይ አዲ አቦ አስተዳዳሪ ለአከ ገ/እግዝሄር ከባድመ ከተማ ሆነው ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት መግለጫ፤ በባድም ከተማ የተቃጠለ ትምህርት ቤትም ሆነ አውቶብስ የለም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት ድንበር ተሻግሮ በኤርትራ ጦር ላይ ጥቃት ሰንዝሯል በሚሉ ዘገባዎች እንዳነበቡ ገልጸው። በአካባቢው የሰሙት የተኩስ ወይም የውጊያ ድምጽ እንዳልነበረ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል።

የድንበር ተሻጋሪ ጥቃቶች ሁለቱን አገሮች በሚያዋስነው ሰፊ የ1ሽህ 500 ኪ.ሜ ድንበር አልፎ አልፎ ይከሰታል። በቅርብ ጊዚያት በአፋር በኩል በጎብኝዎች በሚዘወተር ስፍራ የደረሰውን ጥቃት የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ለሚሰለጥኑ ታጣቂዎች ኃላፊነቱን ሲሰጥ፤ ኤርትራ አስተባብላለች።

በቅርብ ጊዚያት ደግሞ በምእራብ በኩል በተከዜ ወንዝ ዙሪያ አነስተኛ የወርቅ ማእድን አውጭዎች መታፈናቸውን መንግስትና ተቃዋሚዎች ይገልጻሉ። አረና ትግራይ የተቃዋሚ ፓርቲ እንደሚለው ከ259 በላይ ሰዎች በኤርትራ መንግስት ታፍነው ተወስደዋል።

የአረና ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት፤ ባለፈው ሳምንት ተካሄደ ስለተባለው የድንበር ተሻጋሪ ጥቃትና ስለ አፈናው የሚያውቁትን ለቪኦኤ ሲናገሩ

“ስለግጭቱ፣ ሻቢያ (የኤርትራ መንግስት) ጋር ስለሚደረገው ውጊያ ዝርዝር ነገር ያወቅንው ነገር የለም። አንዳንድ ሰዎች በአካባቢው የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማና የተኩስ ልውውጥ እንዳለ ይናገራሉ” ብለዋል።

የዚህን ዘገባ ዝርዝርና የዓይን ምስክሮች የተናገሩትን ከዚህ በድምጽ ዘገባው ያድምጡ።

Play below

 

ኦብነግ ጅጅጋ አጠገብ “ከ50 በላይ የወያኔ ወታደሮችን ገደልኩ” አለ

Monday, June 4th, 2012

(VOA) — ግንባሩ ጥቃቱን የፈፀመው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ደበች ሕሪሶ በተባለ አካባቢ ባለፈው ዕሁድ ግንቦት 19 አድርሰውታል ላለው ጥቃት በወሰደው የበቀል እርምጃ ነው፡፡
ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር በጠቅላላው ስድስት መኮንኖችን ጨምሮ 168 ወታደሮችን መግደሉን መግለጫው አክሎ ጠቁሟል፡፡

ባለፈው ዕሁድ የመከላከያ ሠራዊቱ አድርሶታል ሲል ኦብነግ በሚያሰማው ክስ 18 ሠላማዊ ሰዎችን መግደሉንና ከ15 በላይ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የግንባሩ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ገልፀዋል፡፡

ተዋጊዎቻቸው እንደወሰዱት በተናገሩት የበቀልና እስረኞችንም የማስፈታት እርምጃ ሁለት መኪኖችን ማቃጠላቸውን፣ የተለያዩ መሣሪያዎችና የመገናኛ ሬዲዮኖችን መማረካቸውን፣ ብርቆት ከተማንም ለ15 ሰዓታት ተቆጣጥረው መቆየታቸውንና ለወታደራዊ ስትራተጂ ሲባል ለቅቀው መውጣታቸውን አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በተጠቀሰው ውጊያ ውስጥ መሣተፋቸውን የተናገሩትና “ለሕዝቡ አገልግሎት የተሠራ የውኃ መሣቢያ ሊያወድሙ የመጡ ወንበዴዎችን ከአካባቢው አባርረናል” ያሉት ሻለቃ ሙክታር ሼኽ ሞሐመድ የሚባሉ የክልሉ ልዩ ፖሊስ አዛዥ በግጭቱ ወቅት 35 የኦብነግ ተዋጊዎችን መግደላቸውንና አሥር መማረካቸውን ለሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት ክፍላችን አስታውቀዋል፡፡

ቀደም ሲልም የክልሉ ልዩ ፖሊስ አሥር ሲቪሎችን ራቅዳ በተባለች ቀበሌና በአካባቢዋ ገድሏል፤ ዘፈፋ አካሂዷል፤ የከፉ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችንም ፈፅሟል ሲሉ ሂዩማን ራይትስ ዋች የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ስለሰጡት መግለጫ የተጠየቁት ሻለቃ ሙኽታር ሼክ ሞሐመድ መግለጫው “አንዳችም መሠረት የሌለውና የተለመደ የሂዩማን ራይትስ ዋች ፕሮፓጋንዳ ነው” ብለውታል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

Play below

 

የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል

Monday, June 4th, 2012

(VOA) — በተደጋጋሚ የዘገብንበት ርዕሰ-ጉዳይ ነው፣ ዋልግድባ ገዳም። በዚህ ገዳም ላይ ደረሱ ከተባሉት አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ለስኳር ፋብሪካ ፕሮዤክትና ለሸንኮራ-አገዳ ልማት ቦታው እየታረሰ ነው፤ የአበው መካነ-መቃብር እየተቆፈረ አስከሬናቸው በመውጣት ላይ ይገኛል፣ አያሌ አብያተ-ክርስቲያናት ሊፈርሱ በዕቅድ ተይዘዋል፣ የገዳሙ ንብረት የሆነ በርካታ ገንዘብ ባልታወቁ ታጣቂዎች ተዘረፈ፣ ብዙ ኲንታል የእጣን ምርት ባልታወቁ ሰዎች ተቃጠለ፤ እናም ይህን አባቶች «በደል» ያሉትን በዝርዝር ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚገልጹ መነኮሳት አደን፣ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ነው የሚሉ ይገኙባቸዋል።

የተባለው ልማት በእርግጥም በዕቅድ ላይ መሆኑን መንግትም ሆነ ጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ ያምናሉ። መንግሥት፣ «ልማቱ ከገዳሙ ብዙ እርቅት ላይ ስለሆነ አይነካውም» ሲል፣ ወደ ስፍራው የተላኩት የጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ የዐይን ምስክሮችም ይህንኑ አረጋግጠው፣ «ቤተ-ክህነት የመንግስቱን የልማት ዕቅድ ትደግፋለች” ብለዋል።

የገዳሙ ይዞታ እንዳይነካ ጥያቄ የሚያቀርበው ሕዝብ በአካባቢው ብቻ አልተወሰነም። «ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመ ዓለማቀፍ ኰሚቴ» የተሰኘው ስብስብ የየአካባቢው ተጠሪዎች ለቪኦኤ እንደገለጹት፣ ዛሬ አንድ ዓለማቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄደ ላይ ነው። ሰሜን አሜሪካ ውስጥ ቶሮንቶ-ካናዳ፣ ሎስ-አንጀለስ-ላኪፎርኒያ፣ ኒው-ዮርክና ዋሽንግተን ዲሲ። አውሮፓ ደግሞ ጀርመን፣ ብሪታንያ፣ ብራስልስና አውስትሬሊያ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።

ዛሬ ማለዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተነስቶ ወደ ውጪ ጉዳይ መሥራ ቤት የተጓዘውን የዋሽንግተኑን ሰልፍ ተከታትለን ነበር።

በዚህ ሰልፍ ላይ የክርስትና እምነት ተከታይ ብቻ አይደለም የተገኙት። ሌሎችም በኢትዮጵያውነታቸው ተገኝተዋል።

ከዋሽንግተን ሌላም በሎስ-አንጀለስና በቶሮንቶ ካናዳም ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዶ ነበርና ተወካዮቹን በስልክ አነጋግረናል።

ከዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተወከሉት ባለሥጣን Ms Lora, ሙሉ ስማቸውን ማግኘት አልተቻለም፤ የሰልፈኛውን ደብዳቤ ተቀብለው ጉዳዩን እንደሚያጤኑትና ተገቢ ነው የሚሉትን ምላሽ በጽሑፍ እንደሚሰጡ ለሕዝቡ ገልጸዋል።

በተለይም ባለፈው ሐሙስ ሰቋር ውስጥ፣ በማግስቱ ዐርብ ደግሞ ገሪማ ላይ ስብሰባ ተካሂዷል። የሐሙሱ፣ እራሱ ሕዝቡ ተጠራርቶ የተሰባሰበበት ሲሆን የዐርቡ ደግሞ ባለሥልጣናት የገዳሙን አሥር ያህል መነኮሳት ጠርተው የሰበሰቡት እንደነበር ተገልጾልናል። በዚህኛውም ሆነ ዛሬ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ከዚያው ከአካባቢው ባለስልጣናት መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ይሁንና ግድቡም ሆነ ልማቱ ገዳሙን እንደማይነካ መንግሥት ገልጧል።

ሙሉውን ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ፡

Play below

 

የእሁድ ጠዋት ራዲዮው ተወዳጅ ድምጽ አረፈ

Monday, May 28th, 2012

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሬዲዮ የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ባለ ልዩ ግርማ ድምጽና አቀናባሪ ታደሰ ሙልነህ ባለፈው ረቡዕ ለሃሙስ አጥቢያ ነው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየው።

የዕውቁን የራዲዮ ሰው ታደሰ ሙልነህን ህይወትና ሥራ በራዲዮ መጽሄት እንዘከራለን።

ከሁለት ዓመታት በፊት ከታደሰ ጋር ከነበረን ቆይታ የተወሰደ ድምጽና እንዲሁም ከወዳጅና የቀድሞ የሞያ ጓደኞቹ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ቀጥሎ ያድምጡ።

ፒተር ሃይንላይን እና አስተርጓሚው ስመኝሽ የቆየ ከእሥር ተለቀቁ

Saturday, May 26th, 2012

የአሜሪካ ድምፅ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ፒተር ሃይንላይን እና አስተርጓሚው ስመኝሽ የቆየ ዛሬ ከእሥር ተለቅቀዋል፡፡ ዝርዝሩ ዘግየት ብሎ ይወጣል፡፡

በኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት ይዞታና የገቢ ተጠቃሚነት ዙሪያ ክርክር (VOA)

Sunday, May 6th, 2012

«ፍትሃዊ የገቢ ክፍፍል፤» የምሽቱ ክርክር የሚያነጣጥርበት ጭብጥ ነው።
በኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ ዓመታት በተከታታይ ከአሥራ አንድ ነጥብ በመቶ በላይ የሆነ የምጣኔ ሃብት መዘገቡን የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ ሲገልጥ መቆየቱ ይታወቃል።

ተዘገበ የተባለውን ዕድገትና ያመጣውን ለውጥ አስመልክቶ ታዲያ የሁለት ወገን ውዝግቦች መሰማታቸው አልቀረም።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አዲስ አበባ ውስጥ በተከፈተ አንድ ዓለም አቀፍ የኅብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባሰሙት ንግግር፥ የተባለው ዕድገት ያስገኘው ጥቅም «ፍትሃዊ የገቢ ክፍፍል፤» አምጥቷል፤ ብለዋል።

እሰጥ አገባ ይህንኑ የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር መነሻ በማድረግ የሁለት ወገን ዕይታ የተስተናገደበት ክርክር ይዞ ቀርቧል።

የክርክሩን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤

Play below

 

ለአርሲ ግጭት ተጠያቂው ማን ነው? (VOA)

Sunday, May 6th, 2012

በምእራብ አርሲ አሳሳ ከተማ ለአራት ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነውን  ፖሊስና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት ሃላፊነት ማን እንደሚወስድ እያወዛገበ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ሽፋን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲመሩ የነበሩ አንድ የአሳሳ ከተማ ነዋሪን የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ሲያውሉ፤ ግብረ አበሮቹ በፈጠሩት ሁከት በሰው ላይና በንብረት ጥፋት ደርሷል ብሏል።

በስፍራው የነበሩ የአይን ምስክሮች ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው፤ ለምን እንደሚታሰር፤ ከታሰረም መብቱ ተጠብቆ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያመራ፤ ወይም የአካባቢው ማህበረሰብ ለህግ እንዲያቀርብ በጠይቁ ጊዜ ፖሊሶች ሁኔታውን ባለመቀበል ሰውየውን ሲያስሩ፤ ማህበረሰቡ በቁጣ ድንጋይ መወርወር መጀመሩን ይገልጻሉ። ለዚህ ቁጣ የፖሊስ አጸፋዊ ምላሽ ጥይት በቀጥታ ውደ ሰዎች መተኮስ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ሰዎች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል።

ከኦሮሚያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮማንደር አበበ ለገሰና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ

Play below

 

2ኛ የፓኪስታን ዜጋ በጋምቤላ ሞተ

Thursday, May 3rd, 2012

በጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ቆስለው ከነበሩት ፓኪስታናዊያን አንዱ ትናንት ሕይወቱ ማለፉን በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሣደር አስታወቁ፡፡

በዚህም መሠረት ጥቃቱ በተፈፀመበት ዕለት የተገደለውን ጨምሮ የሞቱት የፓኪስታን ዜጎች ቁጥር ሁለት ደርሷል፡፡

ቆስሎ የነበረው ፓኪስታናዊ ሕክምና ያገኝ የነበረው በመቱ ሆስፒታል እንደነበር ታውቋል፡፡

በጋምቤላ ክልል በሰፊ የእርሻ ልማት ስራ ላይ ከተሰማራው ሳዑዲ ስታር ዋና ጣቢያ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው ጥቃት የአራት ኢትዮጵያዊያንና የአንድ ፓኪስታናዊ ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።

አራት ፓኪስታናዊያንና አራት ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ተገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ ትናንት ፖኬዲ በምትባል ቀበሌ የመንግሥት ወገን የሆኑ ታጣቂዎች፣ መምህራንና ተማሪዎች ተገድለዋል ሲሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪና በሌላ በኩል ደግሞ የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የሚባለው ቡድን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባዎቹን ያድምጡ

Play below

 

በአዲስ አበባ የፓኪስታን አምባሣደር ስለጋምቤላው ጥቃት ተናገሩ

Wednesday, May 2nd, 2012

በጋምቤላ ክልል አንድ ፓኪስታናዊና አራት ኢትዮጵያዊያንን የገደለው ጥቃት “በፓኪስታንና ዜጎቿ ላይ ያነጣጠረ አይደለም” ሲሉ በኢትዮጵያ የአገሪቱ አምባሣደር ኡላም ዳስ ተጊር ገለፁ።

በሌላ በኩል ደግሞ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚባል ድርጅት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ከትናንት በስተያ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተገደለው ፓኪስታናዊ አንድ ሣይሆን አራት መሆናቸውን ገልፀው እንደነበር ይታወሣል፡፡

በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሣደር ዛሬ በሰጡን መግለጫ ላይ የተቀናበረውን ዘገባ እና መግለጫውን መነሻ በማድረግ አቶ ኡባንግ ሜቶ የሰጡንን ቃለምልልስ ያዳምጡ፡፡

Play below

 

በጋምቤላ የታጣቂዎች ጥቃት አራት ኢትዮጵያዊያንና አንድ የፓኪስታን ዜጋ ተገደሉ

Tuesday, May 1st, 2012

በጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች ትናንት ማምሻውን በፈፀሙት ጥቃት አራት ኢትዮጵያዊያንና አንድ የፓኪስታን ዜጋ መገደላቸው ተገለፀ፡፡

የክልሉን ፖሊስ የጠቀሱት የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንዳሉት አራት ኢትዮጵያዊያንና አራት ፓኪስታናዊያን ደግሞ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ተገደሉ የተባሉት ፓኪስታናዊያን ቁጥር አንድ ሣይሆን አራት መሆናቸውንና በአጠቃላይ የሞቱት ሰዎች ቁጥር አሥራአንድ መድረሱን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተባለ ድርጅት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ያድምጡ፡፡

Play below

 

በአርሲ በፖሊስና በህዝቡ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 4 ሰዎች ተገደሉ (VOA)

Monday, April 30th, 2012
በምእራብ አርሲ ዞን አሳሳ ከተማ የዓርብ ጸሎት አድርሰው ከመስጊድ በሚመለሱ ሰዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያስ 4 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ሽፋን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲመሩ የነበሩ አንድ የአሳሳ ከተማ ነዋሪን የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ሲያውሉ፤ ግብረ አበሮቹ በፈጠሩት ሁከት በሰው ላይና በንብረት ጥፋት ደርሷል ብሏል። በስፍራው የነበሩ የአይን ምስክሮች ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው፤ ለምን እንደሚታሰር፤ ከታሰረም መብቱ ተጠብቆ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያመራ፤ ወይም የአካባቢው ማህበረሰብ ለህግ እንዲያቀርብ በጠይቁ ጊዜ ፖሊሶች ሁኔታውን ባለመቀበል ሰውየውን ሲያስሩ፤ ማህበረሰቡ በቁጣ ድንጋይ መወርወር መጀመሩን ይገልጻሉ። ለዚህ ቁጣ የፖሊስ አጸፋዊ ምላሽ ጥይት በቀጥታ ውደ ሰዎች መተኮስ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ሰዎች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ አዛዥ አቶ ደበሌ አዱኛ የእስልምና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የጅሃድ ጦርነት ሲቀሰቅስ የነበረ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ፤ ጥቂት ግብረ አበሮቹ በፈጠሩት ሁከት 4 ሰዎች መገደላቸውንና 10 ፖሊስ መቁሰሉን አቶ ደበሌ የመንግስቱ ልሳን ለሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ከሰላማዊ ሰዎች የቆሰለውን ቁጥር ይፋ አላደረጉም። “ይሄ ቡድን የሚያራምደው ሃይማኖት አይደለም፤ በሃይማኖት ሽፋን ድብቅ የፖለቲክ አጀንዳ ያለው ነው። ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ያረጋገጠውም የግለሰቦቹ አላማ ይች አገር የተያያዘችውን የልማትና የእድገት ጉዞ ማደናቀፍ ነው” ብለዋል። አቶ ደበሌ አክለውም በአሳሳ በተቀሰቀሰው ሁከት የህዝብ አገልግሎቶች ማለትም የስልክና የፖስታ ቤት ህንጻዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል ያላቸውን ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጸዋል። የመንግስቱን ቃልና የአሳሳ ከተማ ነዋሪዎችን የምስክርነት ቃል በዚህ ዘገባ ያዳምጡ [podcast]http://media.voanews.com/audio/amh_arsi_killings.Mp3[/podcast]

በኑሮ ውድነት ላይ የመለስ ዜናዊ ማብራሪና የባለሙያዎች ትንተና

Tuesday, April 24th, 2012

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያው የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ቀርቦ በሰጠው የአገሪቱ ሁኔታ መግለጫ፤ በምጣኔ ሃብት ዙሪያ ያተኮረው ንግግሩ በዋጋ ንረት ላይ ነበር።

የገንዘብ ዋጋ ማጣት ወይንም ግሽበት መንስዔዎችን ከዚህ ቀደም በነበሩ የፓርላማ ንግግሩ ዘርዝሮ፤ ለኢትዮጵያ የግሽበት መንስዔ ግን የሚበዛው በገበያ ስርዓቱና ከውጭ በሚመጣ የዋጋ ጭማሪ መሆኑን ሲያሰምርበት የቆየው መለስ፤ በዘንድሮው ንግግሩ በባለሙያዎች አስተያያት “በግልጽ ችግሮቹን ያመኑበት” ንግግር ነው። የመለስ ንግግር ላይ በመመርኮዝ የኢኮኖሚክስ መምህር ፕሮፌሰር ሰይድ ሃሰንንና የካርኒጊ ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ሽመልስ መኮንን ጋር ያደረግንውን ውይይት ያዳምጡ

Play below

 

የሺፈራው ሽጉጤ “ርካሽ ፕሮፓጋንዳ”

Friday, April 13th, 2012

(VOA) — የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሰጠው መግለጫ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ባለሥልጣናት በተፈናቀሉት ዜጎች ጉዳይ የያዙትን አቋም መነሻ ያደረገ ይመስላል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የተፈናቀለ ሰው እንደሌለ ነው የገለፁት።

“ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎች ቤንቺ ማጂ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ እንደሠፈሩ ነው፤ አልተፈናቀሉም፤ ውሸት ነው” ብለዋል። “የመጡበት ሁኔታ ትክክል ስላልነበረ አካባቢውን ለቅቀው መውጣት የነበረባቸው” ያሏቸው “አንድ ሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰዎች ንብረት በማፍራታቸው ከጉራ ፈርዳ እንዳይፈናቀሉ ተደርጓል” ብለዋል።

“በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የሠፈሩ ነባሮች ግን ከህዝቡ ጋር ተዋድደውና ተከባብረው ኑሯቸውን ቀጥለዋል፤ የአማራ ብሔር ተወላጆች ከደቡብ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል የሚለው ዜና ውሽት ነው” ብለዋል።

በመኢአድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አበበ የተነበበው የድርጅቱ መግለጫ ግን የፕሬዚደንቱን አስተያየት አውግዟል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የተናገሩትን “ርካሽ ፕሮፓጋንዳ አሣዛኝና አሣፋሪ ሆኖ አግኝተነዋል” ብለዋል።

“ፕሬዚዳንቱ ፀሐይ የሞቀውን እውነት ለመሸፈን ሲሉ ከክልሉ የተፈናቀለ የለም ማለታቸው ኢሰብአዊ ኢዴሞክራሲያዊና የዜጎችን ክብር የነካና ያዋረደ ነው” ብለዋል።

“መንግሥት በሕዝብ ላይ ለደረሰ ስቃይ ጆሮና ዐይን ሰጥቶ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ በተራ ፕሮፓጋንዳ መጠመዱን ያሣያል” ብለዋል።

ከጉራ ፈርዳ የሚፈናቀሉ ብሔረ አማራ ገበሬዎች ቁጥር ከነቤተሰባቸው ወደ ሰባ ስምንት ሺህ እንደሚደርስ መኢአድ ጠቁሟል።

እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ መግለጫዉን ተከታትሏል፤ አዲሱ አበበም ከዋሽንግተን ቢሯችን ወደ ተፈናቃዮች ስልክ ደውሎ የሰሞኑን ሁኔታ ዘግቧል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያድምጡ።

Play below

 

ዕውቁ የኪነ ጥበብ ሰው አፈወርቅ ተክሌ አረፉ

Thursday, April 12th, 2012

በመላው ዓለም ታዋቂነትና ከፍተኛ ከበሬታን ያገኙት ኢትዮጵያዊው የስነ ጥበብ ሰው ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ትላንት ማምሻውን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ ተከታዩን አጠናቅሯል።

Play below

 

ወያኔ በሸንኮራ እርሻ ሳቢያ የአፋርን ህዝብ እያፈናቀለ መሆኑ ተገለጸ

Monday, April 9th, 2012

የአፋር ሰብዓዊ መብቶች ድርጅት በአፋር ክልል ውስጥ ይስተዋላል የሚለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አስመልክቶ ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ማውጣቱን ሰሞኑን በበተነው የፕሬስ መግለጫ አስታውቋል፡፡

መግለጫው ሲጀምር “ለሃገር ውስጥና ለውጭ መገናኛ ብዙኃን ዝግ በሆነው በአፋር ክልል ውስጥ ብዙ የጭካኔ አድራጎቶችና የመብቶች ረገጣዎች” እንደሚካሄዱ፣ እነዚህ በአፋር ሲቪሎች ላይ ይፈፀማሉ ያላቸው “በደሎች ሳይገለጡና ሳይዘገብባቸው” እንደሚቀሩም አመልክቷል፡፡

“ምንም እንኳ በቅርቡ በኤርታአሌ አካባቢ የውጭ ሃገር ጎብኚዎች መገደላቸውና መጠለፋቸው የዓለምን ትኩረት ወደክልሉ ቢስብም መንግሥት በዞን ሁለት ሲቪሎች ላይ እያካሄደ ያለው የበቀል እርምጃና ወከባ ግን ብዙም ትኩረት አልተሰጠውም” ይላል የሰብዓም መብቶች ድርጅቱ መግለጫ፡፡
በዞን ሁለት የጅምላ እሥራት እየተካሄደ መሆኑን፣ ሠራተኞች ተቃዋሚዎችን ትደግፋላችሁ እየተባሉ ከሥራ እንደሚባረሩ ይኸው መግለጫ ጠቁሟል፡፡
በአዋሽ ሸለቆ ላይ በተዘረጉትና በሁለት ግድቦች ውኃ በሚጠጡት የሸንኮራ አገዳ ሰፋፊ እርሻዎች ሣቢያ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ሰው እየተፈናቀለ መሆኑ በመግለጫው ላይ ከሠፈሩ ሌሎችም ክሦች መካከል ይገኛል፡፡

ቪኦኤ በስልክ ያነጋገራቸው በአፋር ክልል በተባሉት አካባቢዎች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቱ የተጠቀሱትን ክሦች የሚያጠናክሩ ሲሆን ለቪኦኤ ጥያቄዎች መልስ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ አቶ አሊ አብደላ አሊ የተባሉትን አቤቱታዎች አስተባብለዋል፡፡
ዝርዝሩን ከቅንብሩ ያዳምጡ፡፡

Play below

 

በደቡብ ክልል የተፈናቀሉ አማራ አርሶ አደሮች ጉዳይ እያነጋገረ ነው

Friday, April 6th, 2012

በቅርቡ ከደቡብ ክልል ልዩ ሥሙ አባ ፈርዳ ከተባለው አካባቢው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች የዛሬ ይዞታና ክልሉ የወሰደው እርምጃ፤ እንዲሁም የህጉ ዕይታ ይፈተሻል።

ባሁኑ ወቅት እዚያው በሥፍራው የሚገኙ አርሶ አደሮች፥ አንድ ሁለቱን ጨምሮ ጉዳዩን የሚከታተለው የተቃዋሚው መኢአድ አንድ ተጠሪና የክልሉ ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ሰብሳቢ ተጠይቀዋል።

Play below

 

የአዲስ አበባ መምህራን ወደስራ ተመለሱ

Thursday, April 5th, 2012

በቅርቡ ይፋ የተደረገውን የመምህራን ደመወዝ እርከን ጭማሪ “በቂ አይደለም በማለት” በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሚገኙ አንዳንድ ት/ቤቶች፤ የተደረገው የስራ ማቆም እርምጃ አብቅቶ፤ መምህራን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰዋል።

ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ መምህራን፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን ቀጥለው፤  በጎን ጥያቂያቸውን በግልና በህብረት ተደራጅተው እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል። እየተደረገብን ያለው ጫና ጥያቂያችን ሳይመለስ ስራ እንድንጀምር አድርጎናል ሲሉ አንዳንድ መምህራን ተናግረዋል።

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች፤ በተለይ በአማራ ክልል አንዳንድ ወረዳዎችም አንዳንድ ት/ቤቶች የስራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር። በሰሜን ጎንደር ደምቢያ ዞን የሚገኙ በ6 ት/ቤቶች ለቀናት የዘለቀ የስራ ማቆም አድማ ተካሂዶ ነበር።

በተመሳሳይ መልኩ ስራቸውን እየሰሩ ጥያቄያቸውን ለመንግስት አካላት አቤት ለማለት ወስነው መምህራኑ ወደስራቸው ከተመለሱ ሳምንታት ተቆጥረዋል። ሆኖም 6 መምህራን ከስራቸው ታግደዋል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ መምህራን ከሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች የደመወዝ ክፍያ ጋር የተመጣጠነና ወጥ ያልሆነው የደመወዝ እርከን ተገቢ አይደለም በማለት ከትምህርት ምንስቴርና ከሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣናት ጋር ውይይትና ድርድር ከጀመሩ ቆይተዋል።

በተለይ በደመወዝ እርከን ማስተካከያ ጥያቂያቸው ላይ እስከ ጥር 30 ምላሽ ለማግኘት ሲጠብቁ የነበረ ቢሆንም፤ በጉዳዩ ላይ በቂ ምላሽ አልተሰጠም ብለው እንደሚያምኑ መምህራኑ ይገልጻሉ።

የኢትዮጵያ መንግስትም በቅርቡ የመምህራንን ህይወት ይለውጣል ያለውን የደመወዝ ጭማሪ እንደየደረጃው ከ69 -140 ብር የደረጃ ማስተካከያ አድርጓል።

ከኑሮ ውድነቱ ጋር የተስተካከለና መሰረታዊ የምግብና የመጠለያ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ደመወዝ ይገባናል፤ ጥያቂያችን ተሰሚነት ያግኝ ሲሉ አንዳንድ ት/ቤቶች የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ ቢሆንም፤ ከዘገባችን እንደተረዳንው፤ አሁን በመላ አገሪቱ የመማር ማስተማር ሂደቱ ለጊዜው ቀጥሏል፤

በደምቢያ ወረዳ መምህራን ወደ ስራ ገበታቸው ሲመለሱ፤ 6 አስተማሪዎች ከስራቸው ታግደዋል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣናት አቤቱታችንን ይስሙን፤ ድምጻችንን የምናሰማው በሰላማዊ መልኩ ሆኖ ሳለ፤ የወረዳና ቀበሌ ባለስልጣናት የሚያደርሱብንን ወከባ፣ የስራ ማገጃዎችና ክሶች እንቃወማለን ይላሉ ስማቸውን ያልጠቀሱ አንድ መምህር።

ከስራ የታገዱት መምህራን፤ እስካሁን ደመወዛቸው አለመቋረጡን ገልጸው፤ ወደ ስራ ገበታቸው ተመልሰው ጥያቂያቸውን እንደሌሎች የሙያ ባልደረቦቻቸው በማህበራቸው በኩል ጥያቄ ማቅረብ እንደሚፈልጉ ነው የገለጹት።

ሆኖም የወረዳና የቀበሌ ባለስልጣናት ያለምንም አይነት የፍትህ ሂደት፤ የወላጆችና መምህራን ህብረት፤ እንዲሁም በፓርቲ ባለስልጣናት ተሰባስበው  ባስቻሉት ችሎት የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርበው፤ መምህራኑን ጥፋተኛ ብለዋቸዋል።

ያዳምጡ
ክፍል 1

Play below

 
ክፍል 2

Play below

 

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁኔታ

Monday, April 2nd, 2012

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ለወራት ሲማጸኑ ከነበሩበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽ/ቤት ደጃፍ በኃይል ወደተለያዩ አካባቢዎች መጋዛቸውን የስደተኞቹ ተወካዮች አስታወቁ።

የኃይል እርምጃውን ማምለጣቸውን የተናገሩ ስደተኞች እንዳመለከቱት፥ የየመን ፖሊስ ኃይል ነው፥ በስደተኞች ጽ/ቤት ተመዝግበው ለበርካታ ዓመታት በዚያች አገር የኖሩትን ጨምሮ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩትን እነኚህን ስደተኞች በከፍተኛ የኅዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እያሳፈረ በብዙ መቶ ኪሎሜትሮች ወደ ራቁ አካባቢዎች ያጓጓዘው።

Play below

 

እሥልምና በኢትዮጵያና የሰሞኑ ውዝግብ

Sunday, April 1st, 2012
በቅርቡ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሙስሊም ትምህርት ቤት አወሊያን ያስተዳድር የነበረው ድርጅት አክራሪነትንና ጥላቻን ያስተምር ስለነበር እንዲባረር ተደርጓል ማለታቸውና በአወሊያ ጉዳዮች ዙሪያ የተቋቋመው ኮሚቴ ተጠሪ ደግሞ ሚኒስትሩ ለተናገሩት ማስረጃ የለም ማለታቸውን ዘግበናል። መንግሥት አህባሽ የተባለው የእስልምና ዘርፍ ትምህርት ላይ እንዲውል እያደረገ ነው፤ ይህን የሚደግፉና የሚነቅፉ የሃይማኖቱ ተከታዮች አሉ። ለምን? አህባሽ ቀድሞ አብዛኛው ህዝበ ሙስሊም ከሚከተለው ዕምነት በምን ይለያል? ወሃቢያ የሚባለውስ የዕምነት ዘርፍ ምንድነው? እነዚህና ሌሎችም ተዛማጅ ጥያቄዎችን አድማጮች ለሃይማኖቱ ምሁራን አንስተዋል፡፡ በጥያቄዎ መልስ ዝግጅት ቀርበው መልስ ለአድማጮች ጥያቄዎች መልስ የሰጡልን አቶ አደም ከሚል ከኢትዮጵያ፣ ኢማም ሼህ ሣላህዲን ከአትላንታ - ዩናይትድ ስቴትስ ናቸው፡፡ ቅንብሩን ያዳምጡ፡፡ [podcast]http://www.voanews.com/MediaAssets2/amharic/dalet/AMH_sa_tb_muslim_awolia_adem_salahadin_03_31_12.Mp3[/podcast]

የእነአቶ አንዱአለም የሽብር ክስ ችሎት 3ኛ ቀን ውሎ

Wednesday, March 28th, 2012

አምስተኛ ተከሣሽ ክንፈሚካኤል ደበበ በአንደኛ ተከሣሽ በአቶ አንዱዓለም አራጌ በችሎቱ ላይ ተገኝቶ የነበረው ሌላው ዘጋቢያችን ፒተር ሃይንላይን ባጠናቀረው ሌላ ዘገባ ደግሞ እስክንድር ነጋ ለችሎቱ ባሰማው ቃል “የሕሊና እሥረኛ ነኝ” ማለቱንና መንግሥትን በኃይል ለመጣል አሲረሃል ተብሎ የቀረበበትን ክሥ ማስተባበሉን፤ የፍርድ ቤቱን ብይን አስመልክቶም ታሪክ እንደሚፈርድ ማሳሰቡን አመልክቷል፡፡

እስክንድር ለሃያ ደቂቃ ያህል ለችሎቱ በሰጠው ቃል እንደዐረብ አብዮት ዓይነት ንቅናቄ ኢትዮጵያ ውስጥም መሠረት ሊኖረው እንደሚችል መፃፉንና ለሰላማዊ ትግል መጥራቱን ያመነው እስክንድር ለሁከት ወይም ሕገመንግሥቱን በኃልይ ለመጣል ለሚያነሣሣ አድራጎት አለመቀስቀሱን ተናግሯል፡፡

በዚሁ የችሎቱ የመጀመሪያ ዕለት የቀረቡት የመጀመሪያው ተከሣሽ አቶ አንዱዓለም አራጌ ክሦቹ ሁሉ የተመሠረቱት በሃሰት ላይ ተመርኩዘው መሆኑን መናገራቸው ተዘግቧል፡፡

በችሎቱ ላይ ዋና ምስክር ሆነው የቀረቡት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ተከላካዮቹ የፖለቲካ ለውጥ እንዲመጣ ይንቀሣቀሱ የነበሩት በሕጋዊ መንገድ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

ተከላካዮቹ “የሽብር አድራጎት ለመጠንሰስ ያሴሩ ነበር” ሲል አቃቤ ሕግ ቀደም ሲል እንደማስረጃ ያቀረበባቸው የተቀረፁ ድምፆች የተጫጫሩና ለመስማት አዳጋች የሆኑ የስልክ ንግግር ቅጂዎች እንደነበሩ ፒተር በዘባው ላይ ጠቁሟል፡፡

የሰብዓዊ መብቶችና ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት ተሟጋች ቡድኖች የኢትዮጵያውን ፀረ-ሽብር ሕግ የሃገሪቱን ሕገመንግሥት የሚረግጥና የፖለቲካ ነፃነትን የሚያግድ ነው ሲሉ አንደሚነቅፉት ይታወቃል፡፡

እስክንድርም በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት ሕጉ ተቃውሞን ለመገደብ የታሰበ ነው ሲል በኢንተርኔት ባወጣው ፅሁፍ ተችቶት ነበር፡፡

የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ ከእስክንድር ጋር ታሥራ የነበረችው ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል ዛሬ ለቪኦኤ በሰጠችው ቃል እስክንድር “የግንቦት ሰባት አባል ነህ” መባሉ እንደሚያሣዝነውና የሚናገረው የግንቦት ሰባት አባል አለመሆኑንና ጋዜጠኛ መሆኑን እንደሆነ አመልክታለች፡፡

እስክንድርና አቶ አንዱዓለም ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ከታሠሩና በኋላም በምህረት ከተለቀቁ 130 ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ሰዎች መካከል ይገኙ ነበር፡፡

ባለፈው መስከረም አዲሱ ፀረ-ሽብር ሕግ ተግባራዊ እንደሆነ ከሌሎች ስድስት ተከሣሾች ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸውና አብዛኞቻቸው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች 18 ሰዎች የግንቦት ሰባት ደጋፊዎች ናችሁ ተብለው በሌሉበት መከሰሳቸው ይታወቃል፡፡

የአሁኖቹ ተከሣሾች ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ከተበየነ የሞት ፍርድ ሊጠብቃቸው እንደሚችል የሕግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

Play below

 

ተከሳሾች ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት ወያኔ እንዳሰቃያቸው ተናገሩ

Tuesday, March 27th, 2012

በእነ አቶ አንዱዓለም አራጌ የክሥ መዝገብ የቀረቡ ተከሣሾች መከላከያቸውን ማሰማት ቀጥለዋል። አንዳንዶቹ ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት ለወራት መታሰራቸውንና የማሰቃየት ተግባር እንደተፈጸመባቸው ለችሎቱ ገልፀዋል።

Play below

 

የእነ አቶ አንዱዓለም አራጌ መከላከያ ምሥክሮች ተደመጡ

Tuesday, March 27th, 2012

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ እነ አቶ አንዱዓለም አራጌን መከላከያ ምሥክሮች መስማት ጀመረ። ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዱዓለም ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረተ ቢስ ነዉ አለ። ፍርድ ቤቱ እስካሁን ዉሳኔ አልሰጠም።

ዘገባውን ያዳምጡ

Play below

 

በዋልድባ ጉዳይ የኢትዮጵያዊያን ሠልፍ በዋሽንግተን

Monday, March 26th, 2012

ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የተሰባሰቡ ወጣት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ያስተባበሩት ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተካሂዷል።

Play below

 

መምህራን ወደሥራ እንዲመለሱ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

Monday, March 26th, 2012

ለአንድ መቶ አምስት መምህራን አንድ መቶ አምስት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎችን የለጠፈው የኮከበ ፅባህ ሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አድማ የመቱት መምህራን ዛሬ ሥራ ካልጀመሩ እንደሚባረሩና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል።

በተፈጠረው ሕገ ወጥ ተግባር በሀገር፣ በሕዝብና በተቋም ላይ የሚደርሰው ሰብዓዊና ቁሣዊ ሃብት ውድመት በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑም ያስጠነቅቃል።

መምህራኑ ዛሬ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ የጠየቀው ደብዳቤ ይህ ካልሆነ ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ ተቆጥሮ ተገቢው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ያሳስባል።

የሌሎች ትምህርት ቤቶች መምህራንም ተመሳሳይ የሥራ ማቆም አድማ መትተዋል።

የከፍተኛ አሥራ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የደራርቱ ቱሉ መሰናዶ ትምህርት ቤት፣ አዲስ ብርሃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እንደ ኮከበ ፅባህ ሁሉ ሥራ ያለመጀመራቸውን ምንጮች ገልፀዋል።

ለከፍተኛ አሥራ ሁለትና አዲስ ብርሃን መምህራን ተመሣሣይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሷል።

በየካቲት አሥራ ሁለት ወይም በቀድሞ አጠራሩ በመነን ሁለተኛኛ መሰናዶ ትምህርት ቤትም ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ትምህርት ተስተጓጉሏል።

የመምህራኑ የተቃውሞ መነሻ ተደረገ የተባለውን የደመወዝ ጭማሪ አስመልክቶ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሰሞኑን በቴሌቪዢን የተሰጠ መግለጫ ነው።

ጭማሪውን ይፋ ያደረጉት ባለሥልጣናት የተጠቀሙበት አገላለፅ በራሱ ለተቃውሞው ምክንያት አስተዋጽዖ ማድረጉን አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ መምህር ለቪኦኤ ገልፀዋል።

“የመምህሩን ህይወት በከፍተኛ ደረጃ የሚለውጥ፣ ኑሮን የሚያሻሽል የመምህራንን ፍልሰት የሚያስቆም የቀደመውን የሙያውን ማዕረግ የሚመልስ” በማለት ክበው የተናገሩት ከደሞዝ ጭማሪው መጠን ጋር የማይጣጣምና ይልቁንም በመጋነኑ ምክንያት በመምህሩ ላይ በኪራይ ቤት ጭማሪና በመሳሰሉት ችግር የፈጠረ ነው ብለዋል።

መፍትሔ የሚሆነውም መንግሥት የጭማሪውን መጠን በግልፅ ተናግሮ መምህሩን ይቅርታ መጠየቅ ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያድምጡ።

Play below

 

ዋልድባ ገዳምና የስኳር ፕሮጀክት

Saturday, March 24th, 2012

የዋልድባ ገዳም ይዞታዎች የሆኑ አካባቢዎችን «መንግሥት ለልማት ሊያውል ነው፤ በተለይም የስኳር ፋብሪካ ሊያቋቁምበት ነው» የሚል መረጃ ስለደረሰን ሁኔታውን ለማጣራት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰዎች ከቦታው አጋግረናል። በዚሁ መሠረት ሁለት ፕሮግራሞችን ስናቀርብ የመንግሥትን ወገን አላገኘንም ነበር። ባለፈው ረቡዕ ግን ከዚያው ከአካባቢው የማይፀብሪ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሣይ መረሳ መልስ ሰጡንና የሁለት አባቶችን አስተያየት አካትተን አቅርበነዋል። በዚህ ዝግጅት ባለፈው ረቡዕ የላለፈውን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢው አዲሱ አበበ ከአንዳንድ ተጨማሪ ማብራሪያዎች ጋር አጣምሮታል።

Play below

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀበቶ እያጠበኩ ነው አለ

Friday, March 23rd, 2012

«ኢትዮጵያ በጋዜጦች» የተሰኘው ሳምንታዊ  ፕሮግራማችን

-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀበቶ ማጥበቅ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለጸ

-ኢትዮጵያ በኤርትራ ግዛት ላይ ስለወሰደችው እርምጃ

-በአለም ደቻሳ አሟሟት ላይ ሙሉ ምርምመራ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ጠየቀች የሚሉትን ርእሶች

ይዞ ቀርቧል።

Play below

 

የዝቋላ ገዳም እሳት – መለስካቸው አምኃ (VOA)

Friday, March 23rd, 2012

ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምሥራቅ 15 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ የሚገኘው ዝቋላ ተራራ በአቦዬ ገብረመንፈስ ቅዱስ ስም የቆመው ጥንታዊ ገዳም የሚገኝበት ሥፍራ ነው፡፡ በተራራው ላይ ያለው ገዳም መቃጠል የጀመረው መጋቢት ስምንት 2004 ዓ.ም መሆኑን አንድ እማኝ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡ ቃጠሎው ስፋት ያለውን የአካባቢውን ደን ማቃጠሉን እማኙ አመልክተው እሳቱ ወደገዳሙና በአካባቢውም ወዳለው ፀበል መቃረቡንም ጠቁመዋል፡፡ ስለቃጠሎው መንስዔ እኒሁ እማኝም ሆኑ ሌሎች የአካባቢው ሰዎች እንደማያውቁ ገልፀው ከተራራው ግርጌ ግን አክሳዮች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ከመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

Play below

 

ጋዜጠኝነት፤ ለውጥና ተጠያቂነት

Thursday, March 22nd, 2012

«ለማህበረሰብ ለውጥ የጋዜጠኞች አዎንታዊ ሚና ምን ሊሆን ይገባል?» በሚል ርዕስ በቅርቡ በዚህ ዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደን አንድ የውይይት መድረክ ተንተርሶ የተቀናበረ ዝግጅት ነው። የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎቹ፥ የኢንተርኔት ድረ ገጽ ጸሃፊና አሰናጅ፥ እንዲሁም የጋዜጣና የራዲዮ ፕሮግራሞችን አዘጋጅተው ይበልጡን ለኢትዮጵያዊው ማኅበረሰብ በማቅረብ የሚታወቁ ጋዜጠኞች ናቸው።

የውይይት ሥነ ሥርዓቱን የተከታተለው አሉላ ከበደ ከተወያዮቹ አራቱን ጋብዞ አነጋግሯል።

የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ለማዳመጥ ቀጥሎ ያለውን ይጫኑ።

Play below

 

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሶሪያ

Thursday, March 22nd, 2012

የፕሬዝዳንት ባሽር አላሳድን አስተዳደር በተቃወሙ ዜጎቿ ላይ ያልተቋረጠ የኃይል ጥቃት በከፈተችው ሶሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወገኖቿን ለመርዳት የምትንቀሳቀስ አንዲት በስደት ላይ የምትገኝ ወጣት ናት ባለ ታሪኳ።

የዘገባውን ዝርዝር ለመስማት የሚቀጥለውን ይጫኑ

Play below

 

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ተሽመድምደዋል ሲል አምነስቲ አሳሰበ

Tuesday, March 20th, 2012

በኢትዮጵያ በተግባር ላይ የዋለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣው አዋጅ፤ የሰብዓዊ መብት ስራዎችን አከርካሪ ሰብሯል ይላል፤ የመብት ተሟጋች ቡድኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል።

ድርጅቱ በዚህ ሳምንት ይፋ ባደረገው አዲስ የሁኔታ አጣሪ ዘገባ፤ በኢትዮጵያ የሴቶች፣ የህጻናት፣ የቡድንና የግለሰብ መብት ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች፤ አገልግሎቶቻቸውን እንዲዘጉና እንዲገድቡ ተገደዋል ይላል።

ከሶስት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ በተግባር ላይ የዋለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣው አዋጅ፤ በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ስራዎች አስተጓጉሏል፤ አልፎም አንዳንድ ድርጅቶች ስራቸውን እንዲያቋርጡ አድርጓል ይላል የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ሪፖርት።

“በጣም በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ስማቸውንና ስራቸውን ለመቀየር ተገደዋል። ስራቸውን “ልማታዊ” ተብሎ በተቀየሰላቸው መንገድ ብቻ እንዲያተኩሩ ሆነዋል” ይላሉ የአምነስቲ የአፍሪካ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሚሸል ጋጋሪ። “በሰብዓዊ መብት ስራቸው ለመቀጠል ያሰቡ ጥቂት ድርጅቶች፤ የገንዘብ ድጋፍ ስለማያገኙ አገልግሎቶቻቸውን እያቆሙ ነው።”

ካጋሪ አክለውም በዚህ ጥናት ላይ በቅርበት ክትትል የተደረገባቸው ሁለት ትላልቅ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በባንክ የሚገኘው ገንዘባቸው እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል፤ ስራቸውም ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ከመቶ የማይሞላ ነው ይላሉ።

በ1987ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በአንድ ወቅት ከ17ሽህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊ ሴቶች ነጻ የህግ ምክርና ድጋፍ ይሰጥ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ማህበሩ ለስራው ያገኘው የነበረው የገንዘብ ድጋፍ በመንጠፉ፤ ስራውን በበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ወስኖ የተመጠነ አገልግሎት ለመስጠት ተገዷል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናሏ ሚሸል ካጋሪ የኢትዮጵያ መንግስት ይሄንን ህግ ከማውጣቱ በፊት፤ በግለሰብና በቡድን ማለትም የሴቶች መብት፣ የህጻናት ጉዳይ፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ የአራጋዊያንና ሌሎች የማህበረሰቡ አካላትን ይዞታ ለማሻሻል በሚሰሩ ድርጅቶች ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽዕኖ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በህብረት አስታውቆ እንደነበር ያወሳሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ግን በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠውን የዜጎች የመደራጀት መብት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሕግ ውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ለአገሪቱ ዜጎች የሚሰጡትን ሚና የሚያሳልጥ ህግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን በህጉ መድቅም አስቀምጦ በፓርላማ አጽድቆታል።