የእስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ
በ.ፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። እስክንድር ነጋ
በብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ ስም የሲኖዶሶች ድርድር
አስመላሽ ገበየሁ
ከደቡብ አፍሪካ
ከውጭው ሲኖዶስ በቁጥር 2087/2012 በ 10/19/2012 ለአዲስ አበባው ሲኖዶስ አቃቤ መንበር ለአቡነ ናትናኤል የተጻፍውን ደብዳቤ አስመልክቶ የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘንና ብስጭት ለመግለጽ ቃላቶች ያጥሩኛል። አባቶቻችን ሰላምታ መለዋወጣቸው ባልከፋ ነበር ሆኖም ወንድማቸውን ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስን መስዋዕት ለማድረግ የተላከውን ደብዳቤ በተለይም “…..ይህንን ከባድ ስራ በምናካሂድበት ጊዜ የአፍራሽነት ተልዕኮ ያላቸው መስለው የሚታዩ ቢኖሩ እርምጃችንን የሚያሰናክሉ ሊሆን አይገባም። ለምሳሌ እንደ ብጽዕ አቡነ መቃሪዮስ ያሉ የሚናገሩትና የሚሰሩት በራሳቸው ፈቃድ እንጅ ሲኖዶሳችንን ወክለው እንዳይደለ ……እኛም የማንደግፈው መሆኑ እንዲታወቅልን…..” ይላል። በጣም ያሳዝናል። ለነገሩ ለዚችው ሆዴ በሬውን አረድኩት የሆነ ነገር ነው።ማለትም በአገራችን ብሂል
“በሬ ሆይ፤ በሬ ሆይ ሞኙ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገድሉን ሳታይ
እልም ካለው ገደል ገብተህ ወደቅህ ወይ?”
ዓይነት የሆነ ደብዳቤ ነው። ያሳዝናል። ዳሩ ግን በስብሃት ነጋና በአባይ ጸሐዬ የሚመራው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ መቼ ዋዛ ሆነና በውጭ ያሉትና “ዕርቅ ሰላም” በሚሉት አባቶች ላይ የስቅላት የሞት ብይን አስተላለፈባቸውና 6ኛ ፓትርያርክ ሾመና አቆብቅበው የነበሩትን ሁሉ አስተነፈሳቸው። እንደ ዮሴፍ ወንድማችውን ለመሸጥ (ለመደራደር) የተፈተለው የድብዳቤ ፈትል ውሃ በላው።
የውጭው ሲኖዶስ አራተኛው ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ትክክለኛው ፓትርያርክ ናቸው። የቤተክርስቲያን ህግ አንድ ፓትርያርክ በህይወት እያለ አሱን አስወግዶ ሌላ ፓትርያርክ መሾም ህገውጥነት ነው ብሎ ጸንቶ በመቆም ለወደፊቱ እንዳይደገም መሠረት የሆኑ ጉዳዮችን ማንሳትና ለጥንታዊቷ ተውህዶ ቤተክርስቲያናችን የነገረ መለኮትና ቀኖና ቤተክርስቲያን መቆም ሲገባው የኋሊት በመሄድ በብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ ማመካኘት ምን ይሉታል? ወይንስ ውስጡን እንደምናውቀው በተሞከረው ድርድር ላይ አባ ጳውሎስ ብጹዕ አቡነ መርቆሪዎስን “ከሥልጣን የለቀቁት በህመም ምክንያት ወደው ነው” ብለው እንደዋሹና እንዲያስዋሹ በጋሻ ጃግሬዎቻችው የተቀነባበረ የስብሐት ነጋና የአባይ ጸሃዬ ሴራ ዓይነት ይሆን? ይህ ደብዳቤ እውነቱን የሳተ ያንቀላፋና ዓላማውን የሳተ ነው።
አቡነ መቃሪዎስን የወነጀለው ዶሴ ማብሪያሪያና ማስተባበያ ያስፈልገዋል። ዛሬ የተዋህዶን ትምህርት ያፋለሱ፣ ታሪክ ያቃወሱ ሰዎችንና መጻህፍቶቻቸውን እንዳንቀበል ሰርቶ ከማሰራትና በውስጣቸው በቤተ ምኩራብ የገበትን የሸቀጥ ሰዎች በክርስቶስ ጅራፍ ከመገሰጽ ይልቅ ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስ እውነትን በመናገር በጽድቅ የጀመሩትን ህይወት “አፍራሽ” ብሎ መደራደር ምን አመጣው? ከዮሴፍ የወንድሞች ሽያጭ በምንስ ይለያል? እንደዚህ ዓይነቱ ከንቱ የማሳጣት ቀላጤ በቤተክርስቲያን ጠንክራ እንድትነሳ ህዝባችንም ነጻ እንዲወጣ የሚያደርግ መንገድ አይደለምና እራሳችንን ከዕርም እናውጣ። ጨካኝ አለቃም አንሁን። “.. ዘይትሃጸብ እምድኃረ ገሠሠ በድነ ወካዕበ ይደግም ገሢሠ ምንተ ይበቁ አዖ….” ሲራክ 31፡30
ማለትም እሬሳ የነካውን ሰው መልሶ ለመንካት እጁን ቢታጠብ መታጠቡ ምን ይጠቅማል? እንዳለው ከገባንበት እርም ሳንወጣ እንደገና ሌላ እርም ውስጥ ለመግባት አንሞክር። ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስን እርም ያልተጫናቸው ከተገፋው ህዝብ ጋር እንዳይቆሙ፣ እንዳያጽናኑ፤ እንዳይሰሩ፣ ለአገራቸውና ለህዝባቸው መከራ በአደባባይ እንዳይጮሁ እንቅፋት ከመሆን ያላለፈ ሚዛን የሌለው ማኒፌስቶ በስብሃት ነጋ መሆኑን አለማስተዋላችን ለዚችው ሆዴ በሬዬን አረድኩት እንደተባለ እውነተኛ አባቶቻችንን በጠላት መሸንገያ አንረድ።
ከዚህ አስጸያፊ አድራጎታችንም እንታቀብ። ይልቁንስ እርሙን ፈልጋችሁ አውጡና ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንንም ለትውልዱም ፈውስ የሚሆነው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው “…አዕትቱ እምላዕእሌክሙ እኩየ…” ክፉን ከመካከላችሁ አውጡት 1ቆሮ 5፡13 ይላል እንጅ እውነትን የሚናገሩትን ከመካከላቸሁ አውጡና መደራደሪያ አድርጉ ወይም ሽጡ አይልም። የዚህ ዓይነቱ ወንድምን አሳልፎ የመስጠት ከውድቀትና ከዕንቅፋት በስተቀር ምንም ሊፈይድ አይችልምና እንጠንቀቅ። መከራው ቢበዛም ለተዋህዶ ቤተክርስቲያን ትንሳዔ በመፈቃቀር፣ በአንድነት ከህዝባችን ጋር እንቁም። እራሳችንን በአስታራቂዎች ስም ከሥልጣን ናፋቂዎች ጉያና ከዕርምና ከተዋህዶ አሳዳጆች አናውጣ።
ብጽዕ አቡነ መቃሪዮስ በየአህጉራቱ ለምንገኝ ምዕመናን ኢትዮጵያዊያን በዚህ ምድር ተልኳችን ፈጽመን ፈጣሪ ወዳዘጋጀልን ቦታ እስክንሄድ የተጉ የእውነተኛ የእረና ምሳሌያችን ናቸውና በግፍ ለታሰሩ ይጮሃሉ፣ እንደበግ ለታረዱት ክርስቲያኖች ይጮሃሉ፣ በመንገላታት ላይ ላሉ ይጮሃሉ፣ ለስደተኞች ይጮሃሉ፣ በተለያየ መከራ ላሉ ይጮሃሉ፣ ለተቆራረጠችውና ወደብ አልባ ለሆነችው ኢትዮጵያይጮሃሉ። መስቀላቸውን ከፍ አድርገው በወገናቸውና በህዝባቸው ላይ ለሚደርሰው ማለቂያ ለሌለው ደባና የተደራረበ ግፍ ይጮሃሉ፣ ያዝናሉም። ለወገን ፍቅር ለቤተክርስቲያን አንድነትና ክብር ቆመው ለተሰው በዓለም ዙሪያ አጽማቸው ለተበተነው በረሃና ከተማ ሳይሉ ጸሎት ያደርጋሉ።
ብጽዕ አቡነ መቃሪዮስ ከተበተነው ስደተኛ ጋር የቆሙ የተወደዱ የቤተክርስቲያናችንና የአገራችን ተወዳጅ ብጹዕ አባት ናቸው። እኝህ አባት ከመንደርተኝነትና ከጎሰኝነት የራቁ ሁሉንም በእኩል አይን የሚያዩና የሚባርኩ ደገኛ አባት ናቸው። ፊታቸው ላይ የሚያዩት የህዝባቸው ሃዘን ያንገበግባቸዋል። በጥቅሉ የእውነተኛ ተዋህዶ አባት የታማኝ ኢትዮጵያዊ ዜግነት መምህር ምሳሌ ናቸው። ዛሬ አገር ማለት ጎጥ፤ ቤተክርስቲያን ማለት ጎጥ፣ ሐይማኖት ማለት ጎጥ፣ ወገን ማለት ጎጥ በሆነበትና ይኽው በሚሰበክበት የሕዝብን ሀብት የግሌ ነው በሚሉ ከንቱ ጎጠኞችና የሥልጣን ጥመኞች የሰነዘሩት ቀላጤ ባዶና መሠረት የሌለው እራሱ በራሱ የቀበረ ተቀባይነት የሌለው ደብዳቤ ነውና ከእንደዚህ አይነቱ የመጠላለፍ ውድቀት እንውጣ።ልብ ያለው ልብ ይበል!
ለጦር ወንጀለኛው ሮዶልፎ ግራዚያኒ ሃውልት መቆሙን የሚቃወም ታላቅ አለማቀፋዊ ትዕይንተ-ሕዝብ በዲሲ ተጠራ
እ.አ.አ. በ1930ዎቹ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንጹሃን ወገኖቻችን ላይ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ለፈጸመው ሮዶልፎ ግራዚያኒ የመታሰሰቢያ ቤተመዘክርና የመናፈሻ ቦታ መሰየሙን የሚቃወም ዓለም ኣቀፍ ሰልፍ ተጠርቷል።
ግራዚያኒ በዓለም አቀፍ ስምምነት የተከለከሉና የተወገዙ የመርዝ ጋዝና ፈሳሽ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአውሮፕላን ላይ በማዝነብ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ላይ የጅምላ እልቂት ፈጽሟል። ግራዚያኒ ከዚህም በተጨማሪ ሊቢያ ውስጥም ከፍተኛ እልቂት እ.አ.አ. በ1920ዎችም ውስጥ ፈጽሟል። በዚህም መሠረት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ለፈጸማቸው የጦር ወንጀሎች 19 ዓመት እስር ተበይኖበት እንደነበር ይታወቃል።
ለዚህ ዓለም በአለም ዓቀፍ ደረጃ “አራጅ” በመባል ለሚጠራው የቢኒቶ ሙሶሊኒ የቀኝ እጅ በመሆን በጦር ሚኒስትርነት ተመድቦ እጅግ ዘግናኝና የሰው ልጅ ይፈጽማቸዋል ተብሎ ለመናገር የሚዘገንኑ ማሳቃያዎችን ለፈጸመው የጦር ወንጀለኛ ለአዶልፎ ግራዚያኒ በደቡባዊ የሮም ከተማ በሚገኝ ቦታ በአገሪቱ ግብር ከፋዮች ወጭ መታሰቢያ ተሰርቶለታል። ይህም የሚያሳየው በአሁን ሰዓት ጣሊያንን በማስተዳደር ላይ ያለው መንግስት ለኢትዮጵያውናንና ለሊቢያውያን ያለውን ንቀትና ጥላቻ ነው። ለምሳሌ ያህል ጀርመን ውስጥ ለአዶልፍ ሂትለርና ለተካታዮቹ መዘክር መስራት ይቅርና ስለናዚዎች በበጎ ሁኔታ ማንሳት እንኳ በህግ የተከለከለና “ውግዝ ከማሪዎስ” የሆነ ተግባር ነው። ይህ ሊደረግ ቢሞከር እንኳ ምን ያህል ዓለማቀፋዊ ትኩረትና ውግዘት በተለይም ከይሁዳዊያን እንደሚያስከትል መገመት አያዳግትም። ለነገሩ ጀርመኖች እንኳን ይህንን ሊያደርጉና ሊያስቡት የሚችሉት ነገር እንኳን አይደለም። ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ እንደሚባለው ጣሊያኖች ይህንን እጅግ የሚያስቆጣ ወንጀል በኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸሙት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ ባንዳና ለአገሪቱ የማይቆረቆር መሆኑ ስለሚያውቁ ነው።
ይህ ዓለማቀፋዊ ሰልፍ የሚካሄደው እ.አ.አ. ማክሰኞ፣ ፌብሪዋሪ 19, 2013 ከጠዋቱ 10 ኤ.ም. ሲሆን ቦታው ዋሽንግተን ዲሲ 3000 Whitehaven Street, N.W. Washington D.C. 20008 በሚገኘው የኢጣሊያ ኢምባሲ ፊትለፊት ነው። ስለዚህ ስልፍ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 301-202-4579 ይደውሉ ወይንም በድረገጽ አድራሻ www.globalallianceforethiopia.org ይጎብኙ። ይህንን ታላቅ ዓለማቀፋዊ ትዕይንተ ህዝብ በተመለከተ የተዘጋጀውን እራሱ አስረጅ የሆነውን በራሪ ወረቀት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ታላቅ አለማቀፋዊ ትዕይንተ ሕዝብ
ስለ ቀኖና ቤተክርስቲያን መከበርና በግፍ የተሰደዱትን ሕጋዊውን ቅዱስ ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው ስለመመለስ ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ። መግለጫውን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ
የተስፋይቱ ምድር ተስፋ እኛ “ወንድማማቾች ነን”
ውድ ኢትዮጵያዊያንና ይሁዲ ወገኖቻችን
እኛ ኢትዮጵያዊ- እስራኤላዊያን ይሁዲዎች በሁሉም ዘርፍ ጠንክረን በብቃት ለመገኘትና በሁሉም አቅጣጫ ያለንን እምቅ ዕውቀትና ኃይል በማስተባበር በአንድነት በመቆም መብታችንን ከማስከበር አልፎ በማናቸውም በአገራችን በእራኤል ባሉ ከፍተኛ የሥራ አመራር መስኮች ላይ ለመሳተፍና ውጤት ለማምጣት በድርጅት መሰባሰብ ወሳኝና የማይታለፍ መሆኑንን ተገንዝበናል። በዚህም መሠረት እነሆ በተስፋይቱ ምድር ተስፋ የሚሆን ኢትዮጵያዊ- እስራኤላዊ ይሁዲዎችን መብት ለማስጠበቅ ብቁ ሆነን በመገኘት መሪ የመሆንን ተስፋ እግዚያብሔር ኃይል አድርገን እርሱ እግዚያብሔርም ያከናውንልናል ብለን በማመን በተስፋይቱ ምድር ተስፋ “እኛ ወንድማማች ነን” የሚለውን ፓርቱ በአገራችን በእስራኤል መስርተን ሌሎች መሰል የእስራኤል ፓርቲዎች ጋር ለመወዳደር እየተንቀሳቀስን መሆኑን እያበሰርን በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን ትብብርና ድጋፋችሁ እንዳይለየን እንጠይቃለን። ይህንን አስመልክቶ የወጣውን ሙሉ መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ወንድማማቾች ነን
በግሩም ተ/ሀይማኖት
የሰው ልጅ ላይ ሊፍጸም የማይገባው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የመን ውስጥ ባሉ የተደራጁ አፋኞች ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ነው፡፡ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን በዓልን በገመድ ታንቀው ሲደበደቡ ከነበሩ እና ከሞት ተርፈው ሰነዓ ከገቡ ልጆች ጋር አሳለፍኩ፡፡ ሰውነታቸው ላይ በድብደባ ያረፈውን ቁስል እያየን አንገታቸው ላይ ገመዱ የከረከራቸው ምልክት ሰቅጥጦን ከሞት እንዴት እንደተረፉ እያወጉን በእንባ ታጅበን አሳለፍን፡፡
በዓልን ለማክበር ሁሌም እንደማደርገው ከሰዓት በኋላ ቤቴ ተሰባስበን ምሳ በልተን እንጨዋወታለን፡፡ ካሊድ ለገሰ የተባለ ጓደኛዬ ስልክ ደወለልኝ እና ከባህር የመጡ ሁለት ልጆች አግኝቼ ነበር ይዣቸው ልምጣ? አለኝ፡፡ ከባህር ከመጡማ ይዘሀቸው ና በዓልን አብረውን ያሳልፉ አልኩት፡፡ እኔ ያሰብኩት ብዙ ተንገላተው ደክመው እና ተርበው ስለሆነ የሚመጡት ለራሳችን ያዘጋጀነውን ተቃምሰው በደስታ አብረውን ይዋሉ ብዬ ነው፡፡ በአብዱል ገዊ ግሩፖች ተይዘው በገመድ ታንቀው የተረፉ ናቸው፡፡ ብዙ ተደብድበዋል…ሲል ካሊድ አከለልኝ፡፡ ደነገጥኩ ከዚህ በፊ እዛ ቦታ ተይዘው፣ ተደብድበው የመጡ ብዙ ልጆች አናግሬያለሁ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ከአንድም ሰው እንኳን በስህተት ጥሩ ነገር አልሰማሁም፡፡ ውስጤ የነበረው በዓል የማክበር ፍላጎት እሳት እንደነካው ላስቲክ ኩምትር ሲል ታወቀኝ፡፡ በበዓሉ ዋዜማ እሁድ ታህሳስ 28 ቀን በነበረኝ ቀጠሮ መሰረት UNHCR ቢሮ ሄጄ ያየኋቸውን ሁለት ኢትዮጵያኖችን እያስታወስኩ ስለ እነሱም አሰላስል ጀመር፡፡ UNHCR ቢሮ ውስጥ ካገኘኋቸው(ካየኋቸው) ሁለት ሴቶች አንደኛዋ ግፋ ቢል ከፍ አድርጌ ብገምታት 16 መት የሚሞላት ልጅ ነች፡፡
ከባህር እንደወረዱ በሚያግቱት ግሩፖች ተይዛ ከደብደባ ብዛት መስማት ትስኗታል፡፡ የቢሮው ሰራተኞች በምን መንገድ ቃለ-ምልልስ እንደሚያደርጉላት ግራ ተጋብተዋል፡፡ መሄድ መራመድ ሁሉ አትችልም፡፡ እግሯን አንፈርክካ ገተት ገተት ትላለች፡፡ ጾታዊ ጥቃት እንደ ደረሰባት ከሁኔታዋ ገመትኩ፡፡ ጆሮዋ ብቻ ሳይሆን ራሷ በድብደባ ችግር ተከስቶባታል፡፡ ፍዝዝ ቅዝዝ…ያለች ናት፡፡ ቁጭ ባለችበት እንቅልፍ ይዟት ጭልጥ ይላል፡፡ ብትት ትልና እንደገና ጭልጥ ትላለች፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሌሊት ራሷን እና ጆሮዋን የተመታችው ሲጠዘጥዛት ስታቃስት፣ ስታለቅስ እንቅልፍ አጥታ ስለምታድር ነው፡፡ ይዛት የመጣችውን ሴት ላናግራት ብሞክርም ኦሮሚኛ ባለመቻሌ በቋንቋ መግባባት አልቻልንም፡፡ ምስጋና ለኡስማን አብዳ ፊቶ አስተርጉሞልኝ ነው ይህን ያህልም የተረዳሁት፡፡ በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት ኡስማን አብዳ ፊቶ ማለት ሚስቱ UNHCR በር ላይ በፖሊሶች ተደብድባ የ5 ወር ጽንስ ማስወረዷን ከነ ህክምና ማስረጃዋ አቅርቤ ነበር፡፡ በቅርቡ አሳትመዋለሁ ብዬ ባሰብኩት መጽሀፍ ውስጥ ከሙሉ ማስረጃው ጋር ታሪኩን አቅርቤዋለሁ፡፡
አሁንም ኡስማን ወደ ሁለተኛዋ ሴት እያሳየኝ ‹‹…እሷ ደግሞ እዛ አግተዋት በነበረ ሰዓት እንደ ፈለጋቸው ሲያደርጓት(ሴትነቷን ሲጠቀሙ) ከርመው አርግዛ ነው የመጣችው፡፡…ይሄው ወልዳ አራስ ነች›› አለኝ፡፡ ይሰቀጥጣል በደላችን በዛ፡፡ እዛ ቦታ ታፍነው እርጎዝ ሆነው እና ወልደው ሳይ ከእሷ ጋር አራተኛዬ ነው፡፡ ኢነተር ሶስ የተባለ በሴቶች ጉዳይ የሚሰራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ በአንድ ቀን 8 ሴቶች ሲመጡ ተደፍረው ህክምና እየተደረገላቸው አይቻለሁ፡፡ ይሄ ሁሉ ለምን ምነው ረሳኸን….ከፈጣዬ ጋር ሙግት ይዤ ስንገታገት የቢሮው ሰራተኛ የሆነው ነቢል የሚሉት መጣ፡፡ ልጅ ይዛ ሲያያት ‹‹ባለፈው ኢንተርቪው ስትገቢ ልጅ የለሽም ነበር አሁን ከየት አመጣሽ? የማነው?..›› ሲል ይጠይቃታል፡፡ ተገዳ ስትደፈር፣ በሴትነቷ ሲጫወቱባት ቆይቶ እርጉዝ እንደነበረች በሰዓቱ መናገሯን ገለፀች፡፡ አሁንም በስቃይ በኦፕሬሽን እንደወለደችው ስትነግረው ሰማሁ፡፡ ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ አልቅሼ ምንም ላደርግላቸው ባለመቻሌ እርጉም ደሀ ኪሴን ረግሜ ቤቴ ገባሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ…..በዓልን በዓል ለማስመሰል ተሰባስበን ሳለ በነገሩኝ ነገር ተረብሼ በዓሉ በዓል አልመስል አለኝ፡፡ ከእነሱ የሰማሁት አሳዛኝ ታሪክ ደግሞ….
የብታጅራ ልጆች ናቸው፡፡ ማህመድ ሁሴን እና ወርቅዬ ይባላሉ፡፡ ቡታጅራ ባለ ደላላ አማካኝነት ነው (ቤተሰቦቻቸው ደላላዎቹን በህግ እንዲፋለሙ በስልክ ተነጋግረናል፡፡) ስምንት ሺህ ብር ከፍለው ለጉዞ የተነሱት፡፡ ደላላዎቹ በቅብብል የሚሰሩ ናቸው፡፡ ከእነሱ ጋር ሌላም የቡታጅራ ሰው አለ፡፡ ያውም የ8 ልጆች አባት፡፡ ይህ ሰው ከሰመራ ተነስቶ ደዋሌ በሚባለው ቦታ አድርጎ ለስምንት ቀን የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ወደ ጅቢቲ የሚኬደውን የእግር መንገድ አቅቶት ሜዳ ላይ ወድቆ ቀረ፡፡ እነሱ ስቃያቸውን አይተው አዩ ከሚባለው የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ተነስተው የየመኗ ሞካ ይደርሳሉ፡፡ መኪና ቆሞ ነው የጠበቃቸው፡፡ ይሄ ደግሞ እኔ በተደጋጋሚ ከሚያዙ ሰዎች እንዳጣራሁት ጀልባ ጫኞቹና አፋኞቹ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ተነጋግረው ከጀልባ ሲወርዱ ይጠብቋቸዋል፡፡ መኪና ላይ ጭነዋቸው ለሶስት ሰዓት አካባቢ ተጓዙ፡፡
በግንብ ከታጠረ ትልቅ ግቢ ውስጥ ከተቷቸው፡፡ ‹‹…ሳዑዲያ የሚቀበላችሁን ሰው ስልክ ቁጥር ስጡን ደውለን 1000 የሳዑዲያ ሪያል ከላኩ ትፈታላችሁ፡፡ ያለበለዚያ አንለቃችሁም…እስከዛው በሰላም የያዛችሁትን ሳንቲም ራሳችሁ አውጡ…›› ይሏቸዋል፡፡ ሁሉም ያለውን በተለያየ ቦታ ደብቋል፡፡ አይገኝብኝም ብሎ ዝም…ስልክ ቁጥር ስጡን ሁሉም ዝም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በተራ ልብሱን እያወለቀ ራቁቱን ፓንት እንኳን ሳይቀር ማስወለቅ ጀመሩ፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ይህን ድርጊት የሚያደርጉት ተቀጥረው የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡ ከተለያየ ብሄር አሉ፡፡ ኦሮሚኛ የሚያስተረጉም አለ፡፡ ትግሪኛ የሚያስተረጉም አለ፡፡ አፋርኛ የሚያሰተረጉም አለ፡፡ ታዲያ ማስተርጎም ብቻ እንዳይመስሎት ስራቸው፡፡ እህል ውሀ የማያሰኝ አጣና ይዘው ፌሮ ብረት ይዘው ወገናቸውን ይቀጠቅጣሉ፡፡ አካል ያጎድላሉ፡፡
እነዚህ ወገናቸውን የሚያሰቃዩትን በተመለከተ ሰሞኑን የተከሰተ ነገር ላነሳ ወደድኩ፡፡ አበጋዝ ይባላል፡፡ ሳዑዲያ ድንበር ላይ ለደላላዎች ተቀጥሮ የሚሰራ ሀይለኛ ገራፊ ነው፡፡ አበጋዝ ትክክለኛ ስሙ አይደለም፡፡ ሁሉም የሚያውቁት በዚህ መጠሪያው ነው፡፡ ብዙዎችን አካል በማጉደል የሚታወቅ ጨካኝ ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ከሳዑዲያ መጥተው የመን ከሚቆዩት ጋር ተደባልቆ ሰነዓ ከተማ ገባ፡፡ ሀሳቡ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ነው፡፡ በሱ ተደብድበው ብዙ ስቃይ የደረሰባቸው ተሰባስበው ኤምባሲ ከሰሱት፡፡ ውሸታቸውን ነው ብሎ ስለካደ ኤምባሲው በነጻ ለቀቀው፡፡ ኢትዮጵያ ድረስ ተከታትለው ልጆቹ ጠቁመው አሳያዙት፡፡ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ አጣርቶ ወህኒ አውርዶታል፡፡ የመን ያለ ኤምባሲ ቸልተኝነቱን አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በጅምሩ እንዲቀጥል አሁንም ጥሪ እናሰማለን፡፡
ወርቅዬ ታሪኩን እያፈሰሰልኝ ነው፡፡ ሰውነቱ ደልደል ያለ ነው፡፡ አብሮት ያለው መሀመድ ደግሞ በተቃራኒው ቢያስነጥስ ድፍት የሚል ለንቋሳ ነገር ነው፡፡ ‹‹…ወንዱንም ሴቱንም መለመላችንን እያስቀሩ ያወለቅነው ልብስ ላይ ስማችንን ጽፈን እንድናስቀምጥ ተደረገ፡፡ ሁላችንንም አንድ ክፍል ውስጥ ነው ያጎሩን፡፡ አስብ ሴቱንም ወንዱንም፡፡ ራቁታችንን እያዩን ይስቁብናል፡፡ (እዚህ ጋር በአንድ ወቅት ቃለ-ምልልስ ያደረኩት ልጅ ያለኝን ላክልበት፡፡ ስንያዝ 16 ሰዎች ነበርን፡፡ ሁለት ሴት 14 ወንዶች፡፡ ሁላችንንም ልብሳችንን ካስወለቁን በኋላ ፊታችንን አዙረን ወደ ግርግዳ እያየን እንድንቆም አደረጉን፡፡ ከዛ ከኋላችን እያዩ እነሱ ሴጋ ይመታሉ፡፡ማለት ራሳቸውን በራሳቸው ያረካሉ፡፡)
‹‹….ልብሳችንን አንድ በአንድ ፈተሹ፡፡ ምንም ሳንቲም ሳያስቀሩልን ወሰዱ፡፡ ስልክ ቁጥር ጽፎ ይዞ ደብቆ ይተገኘ ይገደላል አሉ፡፡ እኔ ይሄ የእህቴ ነው ዱባይ ነች አልኩ፡፡ አንዱንም ሳዑዲያ ያለ ጓደኛዬን ስልክ ሰጠሁ ለመትረፍ ብዬ፡፡ እህቴም ጋር ዱባይ ደወልኩ፡፡ ያላትን ገንዘብ መነሳትህን አላወኩም ኢትዮጵያ ላኩት አለችኝ፡፡ ጓደኛዬም ሳዑዲያ ያለው እሺ እልካለሁ ብሎ በአረቢኛ ካናገራቸው በኋላ ሲደወልለት አላነሳም አለ፡፡ ልብሳችንን ከመለሱልን በኋላ ተጠራሁ እና የተንጠለጠለው ገምድ ውስጥ አንገትህን ክተት ተባልኩኝ፡፡ አማራጭ የለኝም መሳሪያ ይዟል፡፡
ከተትኩ፡፡
ገመዱን ሳቡና አንጠለጠሉኝ፡፡ ትግሪኛ አስተርጓሚው ‹ገና ነው ህይወቱ አልወጣም..› እያለ አቆዩኝ፡፡ በቃ መተንፈስ አቅቶኝ….›› የእሱን ንግግር አቋርጦ መሀመድ ቀጠለ ‹‹ሱባን አላህ..ፍርግጥ ፍርግጥ..አለ፡፡ በቃ እኔማ ሞተ ብዬ አወረዱት የተወሰነ ሰዓት ራሱን አያውቅም ነቃ፡፡…እሱ ሲነቃ ደግሞ እኔን አንጠለጠሉኝ፡፡ ይሄውልህ አንገቴ…››አንገቱ ተከርክሮ ቆስሏል፡፡ ማጅራቱ ላይ ገመዱ የሸመቀቀው ቆዳው ሁሉ ተልጧል፡፡ ምኑን አይተህ አለና ሸሚዙን ወለቅ አደረገው፡፡ ጀርባው የተገረፈበት ተተልትሏል፡፡ ተሰብስበን በዓል እናከብራለን ብለን ተሰብስበን አለቀስን፡፡ ካሊድ ለገሰ(መንግስቱ ለገሰ)፣ ጸሀይ በየነ፣ ሄለን ገብረእግዚአብሄር፣ አስማ ገ/እግዚአብሄር ነብዩ ተስፋዬ ሰብለ ዩሀንስ እና ፉዓድ ነን ትዕይንቱን ለማየት የነበርነው፡፡ በእርግጥ ከዚህ በፊት አይኑ የጠፋ፣ እጅ እግሩ የተሰበረ…ለበርካታ ሆነው ደፍረዋት ሽንቷን መቆጣጠር ያቃታት ሴት…የጡቷን ጫፍ በላይትር ለኩሰው ያቃጠሏት…ራሱን በመዶሻ በርቅሰውት ራሱን የሳተ፣ ብረት አግለው ብልቷን የተኮሷት…አይቻለሁ አናግሬያለሁ፡፡ አሁን ደግሞ አዲስ የሰማሁት በገመድ አንቀው እያሰቃዩ መግደል የበለጠ ሰቅጣጭ ነው፡፡
በመሀመድ ቁስል እና ጠባሳ በማልቀሳችን፣ አይናችን እንባ በማቆሩ ገና ምን አያችሁና የሚል ይመስል ወርቅዬ ትረካውን ቀጠለ፡፡ በተለያየ ጊዜ ስድስቴ ነው የተሰቀልኩት፡፡ አልሞት እያልኳቸው ያወርዱኛል፡፡ በኋላ ላይ ዱላ ይዞ መጣና ግራ ትከሻዬን እስኪ በቃው ወገረኝ፡፡ እጄ ሞተ መሰለኝ ዝልፍልፍ ሲልበት በቀኝ ትከሻዬ ላይ ድብደባውን ቀጠለ፡፡ ቀኙም እጄ ደንዝዞ አልታዘዝህ አለኝ፡፡ በዚህን ጊዜ ጀርባዬ ላይ ይነርተኝ ገባ፡፡ ብጮህ ማን ይድረስልኝ? በመጨረሻ ፌሮ ብረት አንስቶ የጀርባ አጥንቴን ሰበረው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ደገመኝ…›› አሁንም ብዙውን ሰዓት በዝምታ የሚቆዝመው መሀመድ አቋረጠውና ራሱ ጀመረ፡፡ ‹‹እሪሪ.. ብሎ ጮኸ..በቃ ተዝለፍልፎ ወደቀ፡፡በዚህን ጊዜ በለው…በለው የሚለው አማርኛ ትንሽ ትንሽ የሚችለው አረብ እግር ስር ነበርኩ፡፡ እንዲህ ቢመቱኝ እኔማ ሟች ነኝ ብዬ ‹እንዲያው በእናትህ እኔስ እሞታለሁ፡፡ ያለኝን የወንድሜን ስልክ አሰጣለሁ አታስመታኝ ብዬ እግሩን ሳም አደረኩት፡፡ ደገምኩና ምጥጥ አድረጌ እግሩን ሳምኩት፡፡ በዚህ ሰውነት እሞት ነበር፡፡ እዩት እስኪ ሰውነቱን …›› የወርቅዬን ልብስ ገልጦ ጀርባው ላይ በብረት መተው ያሳበጡትን እና መቀመጥ መቆም ያቃተው የተሰበረ እጥንቱን ቦታ አሳየን፡፡ አንገታቸውን ገመድ ውስጥ ከተዋቸው በዛው የሚሞቱትን እንደቀልድ ወረድ አድርገው ወደ አንድ ጥግ ጣል ያደርጓቸዋል፡፡
‹‹እሪሪሪሪ…….›› ብጮህ ወደድኩኝ፡፡ ግን ወደ የት? ለማን? ምን ሰሚ ማን ተከራካሪ አለንና?… አሁን ይብቃ!!!!!!!…….ምሬት የወለደው የብሶት ጩኸቴን ስሙኝ፡፡ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ የወገን ያለህ! ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትሉ ወገኖች ዝም የማይባልበት ሰዓት ላይ ደርሰናል፡፡ እየአንዳንዳችን የየበኩላችንን ልናደርግ ይገባናል፡፡ መንግስት እንዲሰማ ትኩረት እንዲሰጥ ማድረግ የምትችሉ ሁሉ እባካችሁ በርካታ ወገኖች በየቀኑ እያለቁ፣ አካለ ጎዶሎ እየሆኑ፣ መታከሚያ እያጡ በችግር እየተሰቃዩ ነው እባካችሁ…….የየመን ሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን፣ የየመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ማነጋገር የምትችሉ አካሎች እባካችሁ እባካችሁ፡፡ …..መረጃ ለምትፈልጉ ሰዎች ሁሉ ልጆቹን ማቅረብ ብቻ ሳይሆን የማውቀውን ሁሉ በማድረግ እተባበራለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ የምትሉ፣ ኢትዮጵያን እወዳለሁ የምትሉ ሁሉ ደጋግሜ እንደምናገረው ኢትዮጵያ ያለህዝቧ ባዶ መሬቷን አይደለም የምትወዱት፡፡ ህዝቡ እያለቀ ዝም የሚል ሀገር ወዳድነት እምኑ ላይ ነው፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችሽ ይህን ጉድ ዝም ካላችሁ ለየትኛው ህዝብ ነጻነት ነው የምትታገሉት? አሜሪካ ላለው? አውሮፓ ላለው? ለኢንቨስተሩ?….ኪሱን ላደለበው?…ዝም ካላችሁ ድምጽ ማሰማትም ሆነ መፍትሄ መፈለግ ግድ ካልሰጣችሁ ስልጣል ላይ ተቀምጦ ከለው ስርዓት በምን ትሻላላችሁ?….
ያወራነው ሄ ብቻ አይደለም፡፡ በጣም ብዛት ያለው ጉድ ነግረውኛል፡፡ ሰፋ አድርጌ ልመለስበት ወደድኩ፡፡ ከልጆቹ ጋር የማደርገውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ በምስል አስደግፌ ለማቅረብ እሞክራለሁ
ማንን እንመን? ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በማን እጅ ነች?
ሳምሶን መኮንን
ከዳላስ
December 14, 2014
ለሥጋችንና ለነፍሳችን በምሳሌነት የሚጠቅም ስራ ሰርተው ሊያሳዩን ይችላሉ ተብለው የመጨረሻውን የስልጣን ልጓም የጨበጡትን መንፈሳውያንንና ሥጋውያን መሪዎች በዚህ ሰሞን የተናገሩትን ሰማን። የተጻፈውንም አነበብን። መዘርዘር ባያሻም፤ ህዝባዊውን ጥያቄ የሚመለከታቸውና ሀላፊነት ያለባቸው በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ያስተማረቻቸው ሰዎች ለሚሰጡን መልስ መሰረት እንዲሆን ከሞላ ጎደል መጥቀስ የሚያስፈልግ ነው። ጥያቄያችን በተወጋገዙት ሰዎች መካከል የተካሄደውን የሚመለከት ብቻ ባለመሆኑ፤ “የገላጋይ ደም የለውም” የሚለውን የባህል ንግግራችን በመርሳት አስታራቂዎችም ራሳቸውን ለመደበቅ በሽምግልና ላይ መታየት የነበረበትን ሞራል ጥለውታልና እነሱንም ይመለከታል።
፩ኛ በቤተ ክርስቲያናችን መካክል የተነሳው ይህ ውዝግብ በመንግስትና በተቃዋሚዎች መካከል ከተነሳው ውዝግብ እጅግ ውስብስብ ከታሪክ ከአገርና ከማህበራዊ ጉዳይ ባሻገር በጣም አስቸጋሪ የሆኑ እንደ ነገረ መለኮትና የቀኖናን የጣስ የመሳሰሉትን ነገሮች ያዘለ ነው። ይህን የተወሳሰበ ነገር ለመፍታት ምን ልምድ፤ ችሎታ፤ እውቀትና ብቃት አላቸው ? ማነው መልምሎ ያመጣቸው? ሰው ሁሉ ከተበከለበት ከግላዊ ጥቅም ከዝምድናና ከፖለቲካው ምን ያህል የራቁ ናቸው?
፪ኛ ተመርጠውና ወክለው ከመጡ፤ አቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ “ፓትርያርክ መርቆርዮስ ላገራቸው አፈር እንዲበቁ ነው እንጅ ከቀደመው ውሳኔ የተለየ የሚደረግ ነገር ለምን አሉ?
፫ኛ ከበጎ ህሊናና ከገርነት ተነስተው እውነቱን መስክረው ሊሆን የሚገባውን ጠቁመው ያቀረቡትን የኢ.ህ.ዴ.ግ. ፕሬዝደንት ሀሳብ መደገፍ ሲገባቸው፤ ኢሀደግ ተቃውሟል፤ ምን አገባቸው ብለው ለምን ፕሬዝዳንቱን ገሰጿቸው?
፬ኛ የሀገሪቱ ፕሬዝደንትስ በበጎ ፈቃደኞችና በራሳቸው ንጹህና ገር መንፈስ በመነሳሳት የተሰማቸውን በግላቸው መጻፋቸው ትክክል ሆኖ ሳለ፤ ለምን ከመንግስት ጋራ በማገናኘት ቃላቸውን አጠፉት? እንዳንድ አንጋፋ የሀገረ ሽማግሌና ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን አማኝ በግሌ የምመኘው ይህ ነው ማለት ለምን አልቻሉም? ዲሞክራሲ ከተባለ የራሳቸውን ነጻነት ለመጠቀም ምን አገዳቸው? ያሁኑ ጠቅላይ ምኒስቴር ወልደማርያም ብላ ያስጠመቀቻቸው የክብርትና የዋሂቱ ወላጅ እናታቸው እምነት፤ ስንት ቅዱሳን አወገኖቻችን ያለፉበትንንና አሁንም እሳቸው እመርሀለሁ የሚሉት ከ፵፩ ሚሊዮን በላይ ያቀፈው እምነት እንደሚወክል ያውቃሉ። በቤተ ክርስቲያናችን ሲወገዝ በኖረው በሰባልዮስ እምነታቸው በመለካት አበላልጠው ይህ ሁሉ ህዝብ እንዳልዳነና በክርስቶስም ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው አድርገው፤ እናቴ አልዳናችምና እየጸለይኩላት ነው ሲሉ አልፈሩም። አላፈሩም፤ የሃይማኖት እኩልነት እያሉ የምሰብኩትን አላከበሩም። የጠቅላይ ምኒስትሩ እንቅስቃሴ ይህ ሆኖ ሳለ፤ ፕሬዝዳንታችን በማያሳፍረው በታሪካዊው እምነታቸው ቀጥ ብለው ለመቆም ለምን አቃታቸው?
፭ኛ አቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ አቋማቸው ይህ ከነበረ፡ ለምን ልዑካኑ እንዲመጡ ተስማሙ? የፓትርያርክ መርቆርዮስን አካል ለአገራቸው አፈር እንዲሰጡ ለመለመን ነበር?
፮ኛ ስደተኛው ሲኖዶስ አባላት ነን የሚሉት፤ ካወገዙት ሲኖዶድስ ሰብሳቢ የተነገረውንና ከፕሬዝደንቱ የተነገረውን እየሰሙ ምን መነሻ ይዘው ነው ውይይት የጀመሩት?
፯ኛ ግዝቱንስ እንዴት ፈተውት ነው አብረን ቀድሰን አብረንም እስከ መካከል ሄደናል ያሉት? ከአሜሪካ ራዲዮ እንደተነገረው ወፈ ገዝት ናችሁ ለተባለው ጥያቄስ መልሳቸው ምንድነው? የቪ.ኦ.ኤ. ጋዜጠኛ አቶ አዲሱ እውነቱን ስላወጣ ይመሰገናል። በሞራል አንጻር ጋዜጠኛ አቶ አዲሱ የሚከሰስበት፣የሚወቀስበት አንዳች ዘይቤ የለም። ስለቤተክርስቲያኗ የሰዎችን ድምጽ ለህዝቡ አቀረበ። የራሱን ማብራሪያ አልሰጠም። የራሳቸውን የአቡነ ናትናኤልንና የፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊውርጊስን የወኪላችውን ድምጽ ነው ያቀረብው። “ልናስታርቅ ነበር ነገሩን አበላሸብን” ተብሎ በሰንካላን እኩይ መንፈስ ሊተች አይገባውም።ብራቮ አዲሱ! አይ ካላችሁም ሜዳውም ይኽው ነው ውጡና እንስማችሁ። ግን በምን ሞራል…….።
፰ኛ እንደገና አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክነቸውን ተገፈው አባ ዘሊባኖስ በመባል ክህነታቸውን የተቀበለ የተባረከ እንዳይኖር ቃል በተላለፈው ውግዘትም ተካተዋል። እንዲሁም ሌሎችም ሊቃነ ጳጳሳትም አብረው ተወግዘዋል። ይህንን እንዴት ዘለውት ነው? ውግዘቱ ሳይነሳ እንዴትስ አብረው ኪዳን አደረሱ?
ዶክተረ መርዓዊ ተበጀም እድል አያምልጠን በሚል ርእስ ጽፈው ለመላ ኢትዮጵያውያን ባቀረቡት “በአቡነ መርቆ ርዮስ ላይስህተት ካለ እንደ አቡነ መልከ ጼዴቅ በሲኖዶስ ይታይ” በማለታቸው በአቡነ መልከ ጼዴቅ ላይ የተወሰደ ውሳኔ እንዳለ በግልጽ አሳይተዋል። ከዚህ ሁሉ የተደራረበ የውግዘት ሸክም እንዴት ተላቀው ነው? ምንም እንዳልተደረገ አስመስለው ለማለፍ ለምን ሞከሩ? ፓትርያርኩም አባ ዘሊባኖስ ተብለዋል” በነሱ መባረክም አብሮ መሳተፍም የተወገዘ ነው ተብሏል? ይህን ሁሉ እንዴ ተሻግረው ነው የአዲስ አበባውም ሆነ የውጭው ሲኖዶሶች “አብረን በልተናል፤ አብረን ጸልየናል፤ አብረን ውለናል፤ ከግማሽ ጉዞም በላይ ተጉዘናል።” ለማለት የበቁት?
ይህ ከዚህ በላይ የተገለጸው አነጋጋሪና አጠያያቂ ሂደት በቅርቡ ከንሳስ ላይ ተፈጸመ ተብሎ በሰፊው በጽሁፍ እየቀረበ በመላ ዓለም ሲነበብ የነበረውን ታሪክ ዘወር ብለን በማጤን እንድንመለከተው አድርጎናል። በከንሳስ ላይ በተፈጸመው ታሪክ ተዋናይ የነበሩት አሁንም በሁለቱ ሲኖዶሶች ለተከሰተው ችግር ፈች ሆነው ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ያሉት ዶክተር አማረ ተጠያቂነቱ ስለሚመከታቸው ደራርበው የተሸከሙት ዶክተርነታቸው ከቤተ ክርስቲያናችንም ሊቃውንት በላይ እንደሆኑ የሚጠቁመው “ሊቀ ማእምራን” የሚለው ማእረጋቸው ከተማሩት ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና አንጻር ለዚህ መልስ በመስጠት ሊያስተምሩን የተደራረበው ማእራጋቸው ያስገድዳቸዋል።
ከዚህ ቀደም አቡነ ማትያስ ከንሳስ ላይ ሄደው ብዙ አስተማሪ የሆኑ ትምህቶችን የጻፉትን ቀሲስ አስተርአየን ለተወሰነ ጊዜ አግጃለሁ በማለታቸው። ቀሲስም አቡነ ማትያስ የሚከተሉትና ያገዱበት ምክንያት ከኦርቶዶክስ ትምርህትና ቀኖና ውጭ እንደሆነና እንደማይቀበሉት ለህዝቡ “የምነግራችሁ የኦርቶዶድክስ ተዋህዶ እምነትና ትምህርት ሳይሆን ቢገኝ ልገረፍ” በማለት መስክረው ጥለው ወደ ቤታቸው እንደሄዱና፤ ምስክርነታቸውን አምነው የተቀበሉት ምእመናን ባደረጉት ጽናት ባካባቢው ካሉት ኦሬንታልና ምስራቃውያን አብያተ ክርስቲያናት ትብብርና ድጋፍ ቆሙ። ቀሲስ የምእመናን ድጋፍ ካለኝ፤ ካልተሳሳትኩ፤ መላው ኦርቶዶክስም ከደገፈኝ ለምን የራሴን ቤተ ክርስቲያን አልከፍትም ሳይሉ፤ እገዳውን በማክበር በቤተ ክርስቲያናችን ህግ መሰረት የታገድኩበት ምክንያት ተጣርቶ በስህተቴ ንስሀ ገብቼ ወይም አጋጁ አቡነ ማትያስ በስህተታቸው ተቀጥተው እስካልተገለጸ ድረስ ቤተ ክርስቲያን ሊከፍቱ ይቅርና ኪዳን አላደርስም በማለት፤ ዲሲ ላይ ጉባዔ እንዲካሄድ አስደረጉ።
ጉባዔውም “ቀሲስ አልተሳሳቱም። የተሳሳቱት እርሰዎ ነዎት። ስለዚህ በመካከላችን ይገኙና ነገሩን እንፍታው” በማለት በአቡነ ገብርኤል መሪነት ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህን መጋቤ አዕላፍ መክብብን ወደ አቡነ ማትያስ እንደላከና የተከፋፈለው የከንሳስ ህዝብም አንድነቱ እንዳይሻክር ይደረግ” ቢሏቸው አቡነ ማትያስ ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆኑ የሚያሳየው ቃለ ጉባኤ በድረ ገጾች ቀርቦ በሰፊው ተነቧል።
እንኳን ትክክለኛውን ይዘህ በመቆም የደረሰብህን እገዳ ተወውና ከእገዳ አልፎ ሁላችንስ የተወገዘን አይደለም እንዴ ዝም ብለህ ሂደህ ቀድስ እያሉ እነ አቡነ ገብርኤል ቀሲስን ቢገፏቸውም፤ ኪዳን እንዲያነቡ ቢጠየቁም በኔ ላይ የተሰነዘረው እገዳ ተመርምሮ ተጣሮ ልክ መሆኔን ወይም መሳሳቴ ተገልጾልኝ የምቀበለውን ንስሀ ሳልጨርስ ኪዳን አላነብም። የኔ ጥያቄየ እዚህ ድረስም የመጣሁት ሂድና ዝም ብለህ ቀድስ እንድትሉኝ አይደለም። በባህላችን ካህን አይደለም፤ እምነት የሌለው ሰው እንኳ አንድ ኢትዮጵያዊ በፈጠረህ የምታደርገውን አቁም ሲባል ማቆም አለበት ይህም ባህል በህዝባችን መንፈስ ስለተቀረጸ ያን ላለመስበርና በኔና በአቡነ ማትያስ ንግግር ህዝብ ስለተከፈለ ለማጥራት ነውና። ስህተቱ ካልተጣራ ወደ ከንሳስ አልመለስም። በማለታቸው ታይቶ ሁሉ ነገር ተመርምሮ እንዲጣራ ካስደረጉ በኋል የካህናቱ ጉባኤ ያቡነ ማትያስን ስህተት እንዲታረም ለበላይ ገለጸ። በአቡነ ጳውሎስ ለሚመራው የላኩትን ቃላ ጉባኤ ይመለከታቸዋል በማለት በውጭ ላለው ሲኖዶሱም ልከዋል። የከንሳስ ኪዳነ ምህረት የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ይስሀቅ ቀሲስ ትክክል መሆናቸው ገልጸው የከንሳስ ኪዳነ ምህረት ምእመናን እንደነበራችሁ ቀጥሉ” የሚል መልእክት ቢጽፉም “ማርያምን ክደዋል” እያሉ የማህበረ ቅዱ ሳን አባላት አልተቀበሉትም።
የሰንበት ተማሪዎች መከፋፈሉን ስለፈለጉ፤ ከካህናቱ ጉባዔና ካቡነ ይስሀቅ እውቀትና ስልጣንም ርቀው በመሄድ ቀሲስን ማርያምን ክደዋልና አንቀበልም ብለው በማመጻቸው ቀሲስና የተዋህዶ ምዕመናን ከአምስት አመታት በላይ የደከሙበትን ህንጻና የሰበሰሰቡትን ገንዘብ መካፈል ይገባናል ሳይሉ በሰላም አስረክበው ወጡ። ቤተ ክርስቲያንን ወደ ዓለማዊ ዳኛ መውሰድ ክልክል ነው በማለት ያላንዳች ቅሬታ በስህተት ለከሰሷቸው ሰዎች አስረክበው” መድኃኔዓለም በሚል ስም ቤተ ክርስቲያን ጀመሩ። ከዚያም በኋላ እነኝሁ ሰዎች የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን እንዲዘጋ በከተማው የሚያሰራጩትን አሉባልታ እንዲያቆሙ የገሰጻቸው አካል ባለመኖሩና ስለዘመቱባቸው፤ በመካከላችን ተገኝታችሁ አርሙን የሚል ጥያቄ ተመሳሳይ እምነት ወዳላቸው ወደ እነ ፓትርያርክ ሽኖዳ አቀረቡ። ፓትርያርክ ሽኖዳና የቀሩትም ተመሳሳይ እምነት ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት በአካል በመገኘትና በጽሁፍ መሰከሩላቸው።
ከዚያ በኋላ ቀሲስ የተማሩትን ቤተ ክርስቲያን ያስታጠቀቻቸውን ያላንዳች መወላወል በጽሁፍ ማሰራጨት ቀጥለው የከበቧቸውን አሉባልተኞች አፍ መዝጋት ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያናችንን የነገረ መለኮት መሰረታዊ ትምህርት እያነጻጸሩ ጥርት ባለመንገድ አከታትለው በማቅረብ ሁሉን አስተማሩት። እነሆ ዛሬ ለምሳሌነት ለመጠቀስ በቁ። በነቀሲስና በአቡነ ማትያስ መካከል በተነሳው ጉዳይ ቀሲስ የተናገሩትንና የወሰዱት አቋም የደግፈውን ጉባዔ የመሩትና ያስተናገዱ ሊቀ ማእምራን ዶክተር ካህን ዛሬ ደግሞ አስታራቂ በመሆን በሁለቱ ሲኖዶሶች ዋናኛውን ቦታ በመምራት ላይ ናቸው። የተወጋገዙት አባቶች አብረው ሲቀድሱ ምን አሉ? ምንስ ተሰማቸው? ፕሬዝደንቱ የተለያየ ቃል እየተናገሩ ዓቃቤ መንበረ ፓትርያርኩም ልኡካን ከላኩ በኋላ የተናገሩትን እየሰሙ የተወጋገዙትን አፈራርሞ መልቀቅ መልካም ሽምግልናን ያሳያልን? የተጣሉትማ ተጣልተዋል። ዶክተር አማረ ከላይ የተገለጸውን ራሳቸው እንዳካሄዱት እያወቁ እሳቸው በጀመሩት መንገድ ችግሩን መፍታት እንደማይችሉም ግልጽ ሆኖ ሳለ የዶክተር አማረ ላይ ታች ማለት ከተወቃሽነት ለማምለጥ ነው እንዴ?
ህዝቡ ማንን ይመን? የተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በማን እጅ ነች? ስለመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን ያሉ መጻህፍት ምን ይላሉ? ቀሲስ እስካሁን ብዙ ጽፈዋል፤ በጽሑፎዎም ብዙ ሰው ተምሮበታል፤ በሰሞኑ የተካሄደውን ሳይሰሙ የቀሩ አይደሉምና ምን ይሰማወታል? መፍትሄውስ ምንድነው ይላሉ? እስካሁ አዝነው ተበሳጭተው ከገለጿቸው ችግሮች ይህ አሁነ የተከሰተው ችግር ዝቅተኛ ሆኖ በዝምታ ታዝበው የሚያልፉት አይመስልምና አስበውበት ከዚህ በኋላ መደረግ ያለበትን ጭምር በመጠቆ ም ቢገልጹት መልካም ነው። የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት በቅዱስ መንፈስ እየተመሩ ያስቀመጡትን እውነት ማለትም በነገር መለኮት ጥናት ውስጥ ቅዱስ ቁርባን እግዚኦ ተብሎ በቅዳሴ የሚደመደም ነው። ያለ ጾም ፋሲካ፣ ያለፋሲካ ጾም የለም እንደሚባለው ማለትም ሁሉም በዓሎቻችን ጾሞች ናችው፣ ሱባዔዎች ናችው፣ ቅዳሴያችንም የሁሉ ነገር መደምደሚያ ነው። ስለዚ ግዝት ሳይወርድ አብሮ ቅዳሴ ከቶ ሊሆን አይችል። ተደርጎም ከሆነ ሲኖዶሶቹ በይፋ ማብራሪያ እንዲሰጡበት እንጠብቃለን።ለሥጋችሁ መጥቶ ይረፍ ወይም ይውደቅ ከሆነ ሽንገላው አትጨነቁ። ጌታችን መድኃኒትችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመጣ በቅዱስ ሚካኤል መለከት ይነፋል። ሥጋን ከየትም ያመጣል ይሰበስባል። ውጭ ሁን፣ ውስጥም ሁን፣ የትም ሁን ጌታ ሊሰበስብ አዎ ይመጣል። የቀኖና ቤተክርስቲያን ጥሰት፣ ውግዘት እውነትን በትኖ ለመቃብር መሆን የለበትም። ሁለቱም ሲኖዶሶች ልብ በሉ። የማይሰበረው የቤተክርስቲያን ሞራል ነውና አስተውሉ።
የአስታራቂ ኮሚቴ አባላት ነን ከሚሉ አንዳንዶች በዳላስ እንደሰማነው ለማገናኘት እንጂ ለማስታረቅ አይደለም ከሆነ ቤተክርስቲያናችንን አያውቋትም። ለዚህ ነበር እንዴ ማስታረቁን ከጀመሩት በዕድሜ፣ በዕውቀትና በጥበብ ከበሰሉ ኮሚቴዎች እኛ ካህናት ነን በሚል “መፈንቅለ ኮሚቴ” በማድረግ የምትውተረተሩት? (በአንድ ወቅት በኢሳት ቲቪ በጋዜጠኝ አቶ ሲሳይ አጌና የተላለፈውን ይመልከቱ) ይልቁንስ ወደነበሩት ኮሚቴዎች ጋር አብራችሁ ብትራመዱ ሊሰምር ይችላል። ልብ በሉ ቤተክርስቲያናችን የራሷ የሆነ ቋንቋና ሂደት ያላት ከፖለቲካው ሁሉ የረቀቀ፤ ረቂቅ ምህዋር ያላት ነች። እውነት ካልመጣ ለማገናኘት ነው በሚል ሽፋን ከእውነት ውጭ ዕርቅ የለም። አይመጣምም። ነፍሳቸውን ይማርና የሊቀመዘምራን አበባው ይግዛው መቃብር ፖለቲካዊ ማባበያ እንጅ ትጥቅ ማስፈቻ ሆኖ “ስጋችን ከገባ ምን አገባን” መሆን የለበትም። የመሰደዳችሁ ምክንያት ምን ሆነና! እስኪ ንገሩን? ለምን ተሰደዳችሁ? ለምንስ ተወጋገዛችሁ? እሳተ መለኮት ቀልድ ሆነ እንዴ? እንዲያ ከሆነማ ሳትሰደዱ ያማረ፣ ያማር ገዳም እኮ ነበረላችሁ። ትውልዱ ያልተሸራረፈ እውነት ይሻል። እውነት ነው ጊዜዎቹ አሰልችዎች ናቸው፤ አንዳንዶችም በውስጣችሁ ቡርቦራውን ተያይዘውታል። ለሁሉም ግን ጽናት ይሻል።
ሊቀ መዘምራን አበባው ይግዛው አሁን በስልጣን ላይ ካለው ወያኔ-ኢህ አዴግ ጋር የተስማሙበት አንዳችም ማስረጃ የለም። ይልቁንስ በመጀመሪያው የዕርቅ ኮሚቴ ውስጥ ሆነው ግዝቱን አውርዳችሁ ተጨባበጡና ለእርቅ ተቀመጡ ነበር ያሏችሁ በግምባር ቀርበው። የምንታገለው ለመቃብር ወይንስ ለመንፈሳዊ አርበኝነት ነው? መንፈሳዊ አባትነት ሰው ይቀብረኛል ብሎ ሳይሆን በመንፈሳዊ አርበኝነት ማለፍ ነው። ሁላችንም እንሄዳለን፣ እናንቀላፋለን ለዘላለም። በውስጥም በውጭም ያላችሁ ብጹአን አባቶች ከውድቀት መጋረጃ መውጣት አለባችሁ። መንፈሳዊ ታሪክ ስሩ። የቤተክርስቲያን ቀኖና እንደ ልጆች “አየሁሽ፣ አየሁሽ” የድብብቆሽ ጨዋታ ሆነ እንዴ? ይህ ከቶ ሊሆን አይችለም። ጉዳዩ አገር ውስጥ ገበተው ወይንም ውጭ ተገናኝተው ህክምን እየታከሙ አብሮ መብላትና መጠጣት አይደለም። ይህንንማ አህዛብም ያደርጉታል። ጉዳዩ የፈርሰው ቀኖና ቤተክርስቲያን መጠገን (መከበር) ነው።
የአሁኖቹ እናስታርቃለን የሚሉት ኮሚቴዎች በትዕዛዝ ብጹአን አባቶችን አትናገሩ፣ ጭጭ እረጭ በሉ በሉ ብለው በሌላ አንጻር ግን ከአራት ኪሎው መንግስትም ሆነ ከአራት ኪሎው ሲኖዶስ ፓትርያርክ መርቆሪዎስ “ለአገራቸው አፈር ይብቁ በአንዲት ቦት ተወስነው (በግዞት) ይቀመጡ” ብሎ የተዘበራረቀና የተመሰቃቀለ መግለጫ በጽሁፍም በሬዲዮም ሲሰጡ ኮሚቴው አትናገሩ ብሎናል ብለው መልስ አለመስጠት ሕዝቡን ማጃጃል ነውና የሽማግሌ ሊቃውንት ያለህ! ማንን እንመን? ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በማን እጅ ነች?
በዳላስ የተካሄደው የሁለቱ የሲኖዶሶች እርቀ ሰላም ውይይት ያለተጨባጭ ውጤት ተጠናቋል
ሳምሶን መኮንን
ከዳላስ
December 9, 2012
ለፓትርያርክነት ዕጩ ተወዳዳሪ በሆኑት በአቡነ ገሪማ የሚመራው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ መልዕክተኞች ቡድን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ “በመረጡት ቦታ በጸሎት ተወስነው ይቀመጡ፣ ለሀገራቸው አፈር ይብቁ” ሲል በአንጻሩ ደግሞ እውነትን በሚያከብሩት ለታሪክ ምስክርነት እግዚያብሔር ባስቀመጣቸው በብጹዕ አቡነ መልከ ጸዲቅ የሚመራው ህጋዊው በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ መልዕክተኞች በበኩሉ “ወደ እውነቱ ተመልሰን ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ከነሙሉ ማዕረጋቸውና ክብራቸው ወደ ፓትርያርክ መንበራቸው ይመለሱ፣ የተጣሰው (የተሰበረው) ቀኖና ቤተክርስቲያን ይጠገን፣ ለትውልድ ያልተከፋፈለች አንዲት ቤተክርስቲያን እንድናስተላልፍ፣ የታሪክ የትውልድ ተወቃሽ አንሁን” ሲል ሃሳቦች ቀርበው ክርክሩ በርትቶ በዚህ ዋናው ቁም ነገር ነጥብ ላይ ያለምንም ውጤት ተጠናቋል። ባለፈውረቡዕ።
ዳሩ ግን እንደው ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ሆኖ ነገሩ ለአምስት ቀናት ስብሰባው እንዲዘልቅ ተደርጎ ለድጋሚ ስብሰባ ለአራተኛ ዙር ውይይት ለሰላም በር መዘጋት የለበትም በሚል ሰበብ መላውን በሳተ መቋጫ ወደ ሰባት ነጥቦች የሚሆኑ የአቋም መግለጫ ብጤ በማውጣት ተጠናቋል። ይሁን እንጅ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ አዲስ ፓትርያርክ ከሾመ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ካለመገንዘብ ፓትርያርኩ ይመለሱ ብሎ አስረግጦ ታሪካዊ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ “በር ላለመዝጋት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮች ላይ መግለጫ እንዳይጥ” በሚል ተልካሻ ምክንያት የኮሚቴው ሃሳብ በዝርዝር ለህዝብ ሳይገለጽ ለቀጣይ ስብሰባ ተላልፏል። ይህን ስብሰባ ያካሄደው ኮሚቴ ከፍተኛ የአገር ጉዳይ ተሸክሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምዕመናን የልብ ትርታ የሆነ አንገብጋቢ ጉዳይን የተበላሸ የዕድር ስብሰባ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አድርጎታል። በጣም ያሳዝናል። በታሪክም ያስጠይቃል።
በዚህ እግዚያብሔር ባመቻቸው ወሳኝ ጊዜና ወቅት እልባት ካልተገኘ መቼ ሊገኝ ይችላል? ውግዘቱ እያለ አባቶች ተገናኝተው ኪዳን ካደረሱና በጋራ “ቅዱስ” ካሉ፣ ማዕድ ከተቋደሱ፣አብረው ሁሉንም ነገር ከከወኑ ግዝት ማለት ውሉን ስቷል ማለት ነው። እውነትም ወፈ-ግዝት። “በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፣ በምድርም የፈታኽው በሰማይ የተፈታ ይሆናል” የሚለው አምላካዊ ቃል ተረት ተረት ሆኗል ማለት ነው። ግዝቱ ሳይወርድ ማን እየተባባሉ ሊጠራሩ ነው። ወይንስ በመልዕክተኛና በስማ በለው በተለያየ ክፍል ነበር ጉዳዩ የተከናወነው። ጉዳዩ የመብልና የመጠጥ ወይም የግል ጠብ አይደለም። ጉዳዩ እጅግ ከፍተኛና አንገብጋቢ የሆነው የቀኖና ቤተክርስቲያን ጉዳይ መሆኑ ልብ ያለው ልብ ይበል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአጼ ዘርያቆብ ዘመነ መንግስት (1444-1468 ዓ.ም. ) አንስቶ በስራ ላይ የዋለውን የቤተክርስቲያኗ መተዳደሪያ ሕግ የሆነው ፍትሃ ነገስት ላይ ስለ ሹመት አስንቶ አንቀጽ 4 ቁጥር 70 ላይ በግልጽና በማያሻማ ሁኔታ እንደተቀመጠው “ይህች ሹመት በ፩ ዘመንና በ፩ ሀገር ለሁለት ሰዎች ልትሆን አይገባም። ይህ በአንድ ሀገር ከተደረገ ግን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና። ለሚገባቸው ሰዎች በሁለት ሀገሮች ብትሰጥ ልማድ ተገቢ በሚያደርገው አገር አስቀድሞ ለተሾመው ትጽናለት። ይህ በአንዲት ቦታ ቢሆን አስቀድሞ ለተሾመው ትጽና። ይህ በአንድ ጊዜ ቢሆን ከነርሱ አንዱም አንዱ ሊተዋት ይገባል። መራጮችም አስቀድሞ የተሾመውን መምረጥ ይገባቸዋል። ተካክለው ቢገኙ በታቦቱ ፊት ቆመው በዕጣ ይሁን።” በዚህም መሰረት አስቀድመው ለተሾሙት ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ሥስጣናቸውን መልሰው በመስጠት ፋንታ ህገ ወጥ ተግባራቸውን በቤተክርስቲያንና በምዕመናን ላይ ለመጫን እንቅልፍ አጥተው በመራወጥ ላይ የሚገኙት። ይህንን የቤተክርስቲያንችንን የማዕዘን እራስ የሆነ የማይሻር፣ የማይተካ፣ የማይሰረዝ፣ የማይደለዝና ከሰዎች የግል ሥስጣንና ጥቅም ጋር የማይለወጥ ህግ በጫማቸው እረግጠው ነው እነአቡነ ገሪማ ለሹመት በመተራመስ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያላገጡ የሚገኙት።
ገና እርቅ ይመጣል ተብሎ የቤተክርስቲያኗ ስርዓት በድጋሚ ሊጣስ አይገባውም። ሲሆን የሚገባው የተበላሸውንና የተጓደለውን አስተካክሎ ለአንዴና ለመጨረሻ የቤተክርሲቲያኗን አንድነት መገንባት ነበር። በእውሸት ላይ የተመረኮዘ ዕርቅ ቢመጣም ስር ስለሌለው አይጸናም። እውነትንና ጽናትን ለትውልድ ሳይሸራረፍ በተሟላ ሁኔታ ማስተላለፍ ይዋል ይደር የሚባልበት ጉዳይ አይደለም። ከዚህ ውጭ ሁለቱንም ወገኖች ብዙ የሚያራምዳቸው አይሆንም። ነገሮች ይለወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም ነገሮች ብሰው ተገኝተዋል። ከሚሰጡት የሬዲዮ መግለጫዎች እስከ ስብሰባው ፍጻሜ ያለውን መመልከት ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው።
ስለሆነም ለሃያ ዓመታት ቤተክርስቲያንን ሲያናውጥ ለነበረ ችግር ትክክለኛና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ሁሉም ምዕመን የዚህ የዛ ሳይባባል የጋራ ድምጹን ፓትርያኩ እንዲመለሱ በማሰማት ለአንዴና ለመጨረሻ ችግሩ እንዲቀረፍ የበኩሉን የምዕመንነቱንና የዜግነቱን አስተዋኦ ማበርከት ይጠበቅበታል። አባቶችንስ አየናቸው። ትናንት በአባ ጳውሎስ እምቢተኝነት ሲያመካኙ ቆይተው አሁን ደግሞ “እሽ ይመለሱ ብንልም መንግስት አይደግፋቸውም” አሉ። ወያኔ በወኪሉ በፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤ ይመለሱ ብሎ ሲያረጋግጥ የአዲስ አበባው አባቶች ቅዱስ ፓትርያርኩን “ለሃገራችው አፈር ይብቁ በሚሰጣቸው ቦታ ይቀመጡ” ብለው ለራሳቸው መንበሯን እያዩ እየቋመጡ እንቅፋት መሆናቸውን ሕዝብ ጠንቅቆ የተገነዘበ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል። ልቦና ይስጣቸው፣ ለሚያልፍ ቀን ይህችን ታሪካዊት፣ በብዙ መስዋዕትነትና የእግዚያብሔር ቸርነት ተጠብቃና ተከብራ የነበረች ቤተክርስቲያንን አዋርደው ለአዋራጅ ዳርገዋታል። የጊዜ ጉዳይ ነውእንጅ ቤተክርስቲያን የቀደመ ክብሯንና አንድነቷን ስትጉናጸፍ የተዋረዱና የቀለሉ እነሱ መሆናቸውን ታሪክ ሲዘግበው ይኖራል።
በዚህ ግትርና እውነቱን ያላገናዘበ አቋም ምክንያት የዳላሱ የእርቀ ሰላም ውይይት ገንዘብ በማሰባሰብ ለሌላ ቀጣይ ስብሰባ ያለውጤት ተበትኗል። ለቀጣይ አራተኛ የተበላሸ የዕድር ስብሰባ። መግለጫውንና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን አካተን በተከታታይ መረጃዎችን እንደምናወጣ እንገልጻለን። ማንም ወደደም ጠላም ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ያነጻትና ቤተክርስቲያን አንድ መሆኗ አይቀርም። ይህ ሁሉ አልፎ፣ ቸሩ እግዚያብሔር የቤተክርስቲያናችንና የአገራችንን ትንሳዔ ያሳየን።
በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የዕርቅ ውይይት በአሁኑ ጊዜ በዳላስ ከተማ ውስጥ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ይህንን አስመልክቶ ከወያኔ ከፍተኛ ሹማምንት ደብዳቤ መጻፉ ታውቋል። ይህንኑ እራሱ አስረጅ የሆነውን ደብዳቤ ከዚህ በታች ይመልከቱ። ዝርዝር መረጃዎችንና ትንተናዎችን በቅርቡ አናወጣለን።
ስለ እውነት፤ እውነት የት ነው?
የዛሬን አያድርገውና የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውንተኛ ሊቃውንት ስለነገረ መለኮት የሰጡት ምስክርነትና እውነት ጊዜና ታሪክ የማይሽረው ዛሬ አንዳንዶች ሊያስተካክሉትና ሊገለብጡት ቢሞክሩም እውነተኛ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ግን አረጋግጠውት ወንጌል የሚያስከፍለውን የደም ዋጋ እየከፈሉ አልፈዋል። የእነኛን እውነተኛ የተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ኮቴ እየተከተሉ ያሉትም በብዙ መከራና ጭንቅ እውነቱን እየመሰከሩ ይገኛሉ።ሆኖም ዛሬ በተለይ የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የነገረ መለኮትን ትምህርት እያፋለሱ እያንሸራተቱ ወደ ካቶሊክና ፕሮቴስታንት ጉያ ሊከቱ ሲጣደፉ በሚሯሯጡበት ተዋህዶ ፈተናዋ በበዛበት በዚህ አጣብቂኝ ወቅት የተዋህዶን ሊቃውንት ምላሽ የሚሻ ጉዳይ ሆኖ ባለበት በዚህ ወቅት እድሉ ባያመልጠንስ ሲሉ ዶክተር መርዓዊ ተበጀ የፃፉትና በድረገፅ የለጠፉት ፅሁፍ ለዚህ ጽሁፍ የጥያቄ ሃሳብ “ስለእውነት እውነት የት ነው?” በሚል ተጻፈ።
የተከበሩ ዶክተር መርዓዊ ተበጀ መጽፍዎት ጥሩነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ “ፓትርያርክ እያለ፣ ፓትርያርክ አይሾምም” ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 4 ቁጥር 70-78 ጠቅሰው አስቀምጠዋል። ነገር ግን እራስዎን በራስዎ ጠይቀው ህሊናዎት ለምን ያንን ጥያቄ እንደጠየቀ መልሱን ለእርስዎ ትተን “አንተ ለምን ዳር ዳር ትላለህ የሚለኝ ካለ ይሉና በስደት ያሉት ፓትርያርክ በዘመነ ደርግ የፈጸሙት በደል ኖሮ ከመንበረ ፕትርክናቸው የሚያስወርድ በደል ከተገኘባቸው እንደ ብጹዕ አቡነ መልከ ጸዲቅ በቀኖና ቤተክርስትያን ይታይባቸው ባይ ነኝ” ብለዋል። ይገርማል!
የተከበሩ ዶክተር መርዓዊ ለመሆኑ ብጹዕ አቡነ መልከ ጸዲቅ እርስዎ እንዳሉት ከሆነ ምን ብለው ነው የተወገዙት? ጭብጡስ ምንድንነው? ወይንስ አህያ በበላ ዳዋ ተመታ እንዲሉ ሆኖ ነው? ባልተወሰነ ነገር አሉባልታን እስከዛሬ ተሸክሞ እንዴት ወደህዝብ ጭንቅላት ዛሬ ለመላክ በምን ነጥብ (አስተምህሮ) መነሻዎት ምንድን ነው? ከየት መነጨ? ወሬውስ በነማን ተሰራጨ? በየትኛው ሲኖዶስ? መቼ? በምን እርዕስ ተወገዙ? የውግዘቱ ውሳኔና ነጥቦቹስ ምንድን ናቸው?
ነገረ መለኮቱን ህዝብ ማሰልቸት ይሆናል ብለው ለዓመታት እርስዎ ካህኑ ከሸሹና ያልተወገዘን እንደተወገዘ አድርጎ አዛብቶ ማቅረብዎት ከምን አንጻር ነው? እንዴትስ ተሸክመውትስ እሰከዛሬ እያነከሱ ቆሙ? ማንን ለማስደሰት ይሆን? ማንም ሳይጠይቅዎት ዳር ዳር ትላለህ ብለው የራስዎትን ዳር ዳር ማለትዎትን መስክረዋልና ዳኝነቱን ለህሊናዎት ትተን እድል አያምልጠን ብለው እርቅ እንዲፈጸም በሚል ሃሳብ ጀምረው ለእርቅ እንቅፋት በሚሆን ሃሳብ ሲደመድሙት እርቅ እንዳይፈጸም የተወላገደ ሃሳብ ያቀረቡ አይመስልዎትም?
እድሉ አያምልጠን ሲሉ የእግዚአብሔር ሰው የሆኑትን አረጋዊውን አባት ብጹዕ አቡነ መልከ ጸዲቅን በነገር ዝርቅ (ተረት ተረት) ለፍርድ አቀርባለሁ ነው የሚሉን? ወይንስ ሌላ? የነገር መለኮቱ እውነት የት ላይ ነው? ይህ ካልሆነ ስህተት ሲደጋገም ብዬ ሰባት ገጽ ጻፍኩኝ ብለው እንዳሉት ሁሉ ስለነገረ መለኮቱ ምን ይላሉ? ስለምንስ ይህንን መድፈር ተሳነዎት?
በአጠቃላይ ሌሎች ሊቃውንተ ቤተክርስትያን በያላችሁበት፣ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ፣ የሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሎጅ፣ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅና ሌሎችም ይህ አሳሳቢ ጉዳይ የሚመለከታችሁ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ዶክተር መርዓዊ ተበጀ ብጹዕ አቡነ መልከ ጸዲቅ ተወገዙ ያሉበትን ጉዳይ እንዴት ታዩታላችሁ? ስለ እውነት፤ እውነት የት ነው?
ቸር ይግጠመን።
ከእውነቱ ታየ
December 2, 2012
ጽሁፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። “እግዚአብሔር የቀባው”
“እግዚአብሔር የቀባው”
ቀሲስ አስተርአየ
ሕዳር ፳፩ ቀን ፪ሽ፭
Nigatuasteraye@gmail.com
“እግዚአብሔር የቀባው” የምትለውን አነጋገር ብዙ ሰው በተደጋጋሚ ይናገራታል። ከየት መነጨች? ጠቀመች? ወይስ ጎዳች? ሊቃውንቱስ እንዲት ይተረጉሟታል?
ነቢዩ ዳዊት ባንድ ወቅት “እግዚአብሄር በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ” (፩ኛ ሳሙ ፳፮፡ ፲፩) ብሎ ተናግሮ ነበር። በእውነት ይህ ቃል በሥልጣን በተለይም በክህነት አገልግሎት ያሉትን ሰዎች እግዚአብሔር የቀባቸው ናቸውና ቢሳሳቱም “እግዚአብሄር ይቅጣቸው” ብሎ ህዝብ እንዳይናገራቸው፤ እንዳይወቅሳቸውና እንዳይከሳቸው የሚከለክልና የሚያግድ ነውን?
ዳዊት “እግዚአብሄር በቀባው ላይ እጄን አልዘረጋም” ያለው፤ “አማልክተ ኢትህሚ ወለመኮንነ ህዝብከ ኢትበሎ እኪተ“ (ዘፍ ፳፪፡፳፰) ማለትም፦ “መሪህን አትንቀፍ አትተችም” የሚለው ህግ ያለ ምንም ገደብ እንዲጠበቅ አልነበረም። ስልጣኑን ወይም ክህነቱን መጋረጃ አድርጎ የፈለገውን ስህተት በህዝብ ላይ የሚፈጽም ማንም ሰው በዝምታ እንዲታለፍም አልነበረም።
ታሪኩ ባጭሩ እንደዚህ ነው። ሳኦል ዳዊትን አሳዶ ለመግደል ቀንና ሌሊት ይጥር ነበር። ከእለታት አንድ ቀን አቢሳና ዳዊት ሳኦልን እንቅልፍ ጥሎት አገኙት። አቢሳ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ ላይ ጥሎታልና እንደተኛ ባንድ ውግ ብቻ ገድየው ልገላግልህ? ብሎ ዳዊትን ፈቃድ ጠየቀው (ሳሙ ፳፮፡፰)። ዳዊት ግን “ሕያው እግዚአብሄር ይመታዋል። ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል። ወደ ሰልፍ ወርዶ ይገደላል” የሚል የትንቢት ቃል ተናገረ።
ዳዊት እንዳለውም፤ ሳኦል ከሌላ ሰራዊት ጋራ ለመዋጋት በተሰለፈበት ድል ተነስቶ ራሱን በራሱ ገደለ (፩ኛ ሳሙ ፴፩፡፩᎗፲፫)። ዳዊት በሳኦል ላይ እጄን አልዘረጋም ያለው፤ የሳኦልን ስልጣን ከመረከቡ በፊት የሳኦል ህይወት እንዴት እንደሚቆም በእግዚአብሔር መንፈስ አስቀድሞ ስለተረዳ ነበር።
“እግዚአብሄር በቀባው ላይ እጄን አልዘረጋም” ያለው ዳዊት፤ አስመሳዮችና በወሬ የሚተዳደሩ ሰዎች ደፍረው የማይናገሩት፤ የማይታለፍ ሊገለጽ የሚገባ የፈጸመው የተቀደሰ ነገር አለ። ሳኦል ከሌላ አቅጣጫ ከመጣበት ሰራዊት ጋራ ሲዋጋ ተሸንፎ ተስፋ ቆረጠና “በጣላቶቼ እጅ ከመውደቅ ግደለኝ” ብሎ የራሱን ጋሻ ጃግሬ ለመነው። ጋሻ ጃግሬውም አልገደለውም። ሳኦል እራሱን በራሱ ገደለ። ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል ራሱን በገደለበት መንገድ እዜያው ላይ ራሱን ገድሏል” (፩ኛ ሳሙ ፴፩፡፭)። የተፈጸመው ታሪክ ይህ ሆኖ ሳለ፤ ግርግሩን በመጠቀም ሹመት ሽልማት የፈለገ፤ ባካባቢ ሆኖ ይህንን የተመለከተ ወሬኛ፤ ዳዊት ያለምንም ተቀናቃኝ እንደሚነግሥ ተረድቶ፤ ይህን ይዤ ወደ ዳዊት ብቀርብ ጥቅም አገኛለሁ ብሎ በመገመት ያልገደለውን “እኔ ሳኦልን ገደልኩልህ” እያለ ዳዊትን ቀረበው። ዳዊት በከንቱ ውዳሴ ህሊናውን ያላስጎነበሰ፤ በወሬ ሹመትና ሽልማት ለማግኘት የተቅነዘነዘውን ወሬኛ ሰው ለነገር አቀባይነት ይጠቅመኛል ሳይል መቀጣጫ ይሆን ዘንድ በሚመራው ህዝብ ፊት ቀጣው (፪ኛ ሳሙ ፩፡፲፮)። ይህ የዳዊትን ማንነት የሚገልጽና ጊዜ ላነሰው ባለ ስልጣን ነገር በማቀበል ለሚኖሩት ወሬኞች ተግሳጽን ያዘለ ትልቅ ትምህርት ነው።
ጥልቅና ምጡቅ በሆነ ምክንያትና ግንዛቤ “እግዚአብሄር በቀባው ላይ እጂን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሄር ከኔ ያርቅ” (፩ኛ ሳሙ ፳፮፡ ፲፩) ብሎ ዳዊት የተነገረውን ያልተረዱ ብዙ የዋሀን ሰዎች ሸፍጠኞችን ቢቃወሙ የሚቀሰፉ እየመሰላቸው፤ ጳጳስ ሰረቀ፤ ዘረፈ፤ ዋሸ፤ ዘሞተ፤ ወለደ የሚል ነገር ሲሰሙ መቃወማቸው ይቅርና “ኧረ ኧረረረረ መስማቱም ኃጢአት ነው!” ይላሉ። ሸፍጠኞችም ይህንን ጥቅስ እንደ ማስፈራሪያ አድርገው በመጠቀም መጋረጃ አርገውታል። ይህ አይነት መንፈስ ከዳዊት አባባል ጋራ ፈጽሞ የሚገናኝ አይደለም። ሊቃውንቶቻችንም አይቀበሉትም።
የሊቅውንቶቻችን የነ ኔታ አንዳርጌ ግንዛቤ
ከዕለታት አንድቀን አንድ በሰው ፊት የተከበሩ፤ ውስጣቸው ግን የተበላሸ ሰው፡ ውሻ ገደል ከሚባለው ቦታ ላይ ስህተት ፈጸሙ። “ስህተቱ ቢገለጽ እግዚአብሄር የቀባቸውን ክብር መንካት ነውና ዝም በሉ ሰውየውንም ሸፍኗቸው” ተባለ። ሰውየ ግን ይህንን ሽፋን በመጠቀም ወደ ጫጋልና ደብረ ጽጌ እየተዘዋወሩ በስህተቱ ቀጠሉ። በመጽሐፋዊው ቅኔያቸው የተደነቁት የደብረ ሊባኖሱ ገዳም የቅኔ መምህር የነበሩት፤ በኋላ ወደ ተወለዱበት አገር ብቸና ጊዮርጊስ ተመልሰው ያረፉት መሪጌታ አንዳርጌ ካሳ። “ካህን ቢሳሳት እግዚአብሄር የቀባው ነውና አትናገረው” የሚባለው ነገር ወደ ተሳሳተ ባህል ተለውጦ ህዝብ በመጉዳት ላይ መሆኑን በመግለጽ በመጻሕፍት ላይ መስርተው ሙሉ ቤት ዘረፉ። ቅኔው የገዳሙን ሊቃውንት አንቀሳቀሰ። ተመሳሳይ ችግር የነበረባቸው በሳቸው ላይ እያጉረመረሙ ተነሱባቸው።
በዚያው በውሻ ገደል ይኖሩ የነበሩት፡ የስመ ጥሩው የስሬው ቅኔ መምህር የኔታ ጥበቡ ደቀ መዝሙር የነበሩት፡ ሌላው የገዳሙ የቅኔ መምህር የኔታ አምዴ፡ የሳምንቱ የቅኔ ባለተራ ስለነበሩ በእጣነ ሞገር ቅኔያቸው የእለቱን ቅዱስ ካወሱ በኋላ፡ በአሰረ ንጉሡ ላይ የየኔታ አንዳርጌን ቅኔን የሚደግፍ በሊቃውንቱ ፊት ተቀኙ። በብህትውናቸው በቅድስናቸው የሚደነቁ የኔታ ላእከም፤ ግርማ በተሞላበት ድምጻቸው “ይበል” ብለው ከቀመጡበት ብድግ አሉ።
የኔታ አንዳርጌም “ስህተቱ ቢገለጽ እግዚአብሄር የቀባቸውን ክብር መንካት ነውና ዝም በሉ ሰውየውንም ሸፍኑት” እያሉ የሚያስተምሩ ሰዎች የሚቀጥሉና፤ ሕዝቡም ትምህርቱን አምኖ የሚቀበለው ከሆነ፤ ነውር ነው ተብሎ ሊታፈርበት የሚገባው ሁሉ ኃጢአት ባህል ይሆናል። መዋረድና ማፈር የሚገባቸው መልካም እንደሰሩ ሆነው ይሸለሙበታል። የሞራል፤ የስነ ምግባር ሰዎች፤ አንገታቸውን እንዲደፉ፡ እንዲናቁ፡ እንዲዋረዱና እንዲያፍሩ ይደረግበታል ብለው ከሳቸው በፊት የነበሩት አለቃ ንጉሤ የሚባሉት ሊቅም በዚህ ላይ የተቀኙትን ነግረውናል። ቅኔውም እንደሚከተለው ነው።
አይቴኑ ለነውር ብሔረ ሙላዱ፤ በውስተ ኩሉ ብሔር እስመ ከመነግድ ይሄሉ።
ትምህርተ ዝኒ ነገር ከመ ይትግሀድ ለኩሉ።
ኀጥዕ ይሳለቅ ላዕለ ጻድቅ፤ ከመ ዘንጹህ ወሠናይ ባህሉ።
እስመ እንዘ ሠርዌ በውስተ ዓይኑ፤ እምዓይነ ቢጹ ብሩህ አውጽኦተ ሠርዌ ዘያስተዴሉ።
አይሁድሂ ሐዋርያት በጽእለቶሙ ጸአሉ።
አብዳነ ዝንጉአነ ወሐሳውያነ እንዘ ይብሉ።
እስመ እንዘ ብእሴ ጻድቀ ዘሀለዎሙ ይስቅሉ።
ውጹአን እምነ ጽድቅ በጽድቅ ርእሶሙ ተለአሉ።
የቅኔው ይዘት ባጭሩ “አይቴኑ ለነውር ብሔረ ሙላዱ” ነውር ሊታፈርበት ሲገባ እንደሙያ ሆኖ እንደ ቅኔ የሚፈልቀው ኧረ ከየት ነው? እያሉ በመደነቅ ምንጩን ከጠየቁ በኋላ፤ “በውስተ ኩሉ ብሔር እስመ ከመነግድ ይሄሉ” ማለት “አሁንማ አገሩን ሁሉ ወሮት ያደልደረሰበት ምን ቦታ አለና፡ የነውርን መነሻ አጠያየቀኝ” ይሉና፤ “ኀጥዕ ይሳለቅ ላዕለ ጻድቅ፤ ከመ ዘንጹህ ወሠናይ ባህሉ” ማለትም ይህን ነገር ባጭር ካልቀጨነው ማፈር የሚገባው ነውረኛ፤ ንጹህ ባህል እንደሚከተል ሆኖ ደህነኛውን እንደሞኝ እንዳልተማረ በማየት ያጃጅለዋል። ካሉ ባኋላ ቀጠሉን “ውጹአን እምነ ጽድቅ በጽድቅ ርእሶሙ ተለአሉ” በማለት ቅኔውን ደመደሙ። ማለትም፦ ከመስመር የወጡት ነውረኞች በነውራቸው ይኩራራሉ ያልገባው ህዝብም ያከብራቸዋል። ወጣቱም እንደምሳሌ ይወስደውና መመለሻ ከሌለው ሞራል ውድቀት ውስጥ መውደቅ ይመጣል።
የኔታ አንዳርጌ ይህን ያለቃ ንጉሤን ቅኔ አስታውሰው የነገሩን፤ “እግዚአብሄር በቀባው ላይ እጂን አልዘረጋም” የሚለው አነጋገር ህዝቡን አፈዘዘው። ሞራለ ቢሶችንም መረን ለቀቃቸው ብለው በዘረፉት ቅኔ የተነኩ ሁሉ በወቀሷቸው ጊዜ፤ የተሰለፉበት ሙያ እንዳስገደዳቸው ባያደርጉት ግን ከሳቸው በፊት ከነበሩት መምህሮቻቸው የተረከቡትን የሞራል ሃላፊነት ለመወጣት እንዳደረጉት ለማሳየት ነበር።
እኔም ያለቃ ንጉሤንና የመምህሮቼን የየኔታ አንዳርጌንና የነ የኔታ አምዴ ብቃትና ችሎታው ባይኖረኝም። ጳጳሱ ወለደ፤ ከመንግስትና ከነጋዴ ጋራ የጥቅም ተሻሚ ሆነ፤ “ዋልባ የገባ አይወጣ፡ ከል የገባ አይነጣ” እየተባለ ይነገርለት የነበረው መነኩሴ ሁሉ ዋልባን እየለቀቀ ወደ ከተማ በመገስገስ ከህዝብ ጋራ እየተጎራበተ ማህበራዊ ኑሮ ጀመረ ሲባል እሰማለሁ፤ አያለሁም። በሌላ በኩል ደግሞ “እግዚአብሄር በቀባው ላይ መናገር ልክ አይደለም” የሚሉ ሰዎችም ገጥመውኛል። ታዲያ ከመምህሮቼ የሰማሁትን የዘረፉትንም ተቀብየ፤ እራሴ ሙሉ ቤት ቆጥሬ ነግሬበት እንዴት ሳልመሰክር ልለፈው?
ዳዊት በእግዚአብሄር ተመርቶ “እግዚአብሄር በቀባው ላይ እጂን አልዘረጋም” ያለበትንም ምክንያት ተረድቶ የተፈጸመውን ቅዱስ ተግባር፤ ለጥፋት ለኃጢአትና ለበደል መጋረጃ ማድረግ፤ በበደል ላይ በደል፤ በኩነኔ ላይ ኩነኔ፤ መፈጸምና ተያይዞ መጥፋትን የሚያስከትል እንጅ፤ ትህትናን ወይም ጻድቅነትን አያተርፍም። እነ ቅዱስ ጳውሎስም “እግዚአብሄር በቀባው ላይ እጂን አልዘረጋም” የሚለውን በዚህ አይነት ሽባ በሆነ መንፈሰ አልተረጎሙትም። የቅዱስ ጳውሎስን አቋም እንመልከት።
የቅዱስ ጳውሎስ አቋም
ባንድ ወቅት “የእግዚአብሄርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን”(፳፫፡፬_፭)። ብሎ አንድ ያልተረዳ ሰው ለቅዱስ ጳውሎስ ጥያቄ አቀረበ። ቅዱስ ጳውሎስም “ሊቀ ካህን መሆኑን ባላውቅ ነው” ብሎ መለሰለት። ይህንን ለይተው ያልተረዱ ሰዎች፤ “አንድ ጊዜ ካህን ነህ፤ ወይም ሹም ነህ ከተባለ በኋላ፤ ካህንን ወይም ጳጳስን መዝለፍ ትክክል አይደለም” ይላሉ። ይህ የቅዱስ ጳውሎስ ንግግርም ለጥፋተኞች መጋረጃ በመሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከከፍተኛ ጉዳት ላይ ከጣሏት አስተሳሰቦች አንዱ እንደሆነ ለማየት እንሞክር።
ቅዱስ ጳውሎስ “ወኢያድሉ ለገጽ ወኢይንስኡ ሕልያን ፡እስመ ሕልያን ያዐውሮ ለጠቢባን ወያሴስሎ ለቃለ ጽድቅ“(ዘዳ ፲፮፡፲፱) የሚለውን፤ ማለትም፦ ዳኛ መዛኝ እንደሆነ፤ ዳኝነት መመዘን ሲሆን፤ ህግ ደግሞ ሚዛን እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ያውቃል። መማለጃ (ጉቦ) ዳኝነትንና ሚዛናው ፍትሕን ነቃቅሎ በመጣል ህብረተ ሰብን በድቅድቅ ጨለማ የሚጥል እንደሆነ ተምሮ የተረዳ የህግ ምሩቅ ነው። ህግ ተምሮ ማወቁ ብቻ ሳይሆን “እግዚአብሔር ቆመ ውስተ ውስተ ማኅበረ አማልክት። ወይኴንን በምእከለ አማልክት . . . ፍትሑ ለነዳይ.. ወአጽድቁ ግፉዐ ወምስኪን“ መዝ ፹፩፡፩_፬) ማለትም_እግዚአብሔር በፈራጆች መካከል ቆሞ ይፈርዳል። ስለዚህ ለተበደለው ለተገፋው ፍረዱ”ብሎ ዳዊት የተናገረውን ደጋሚ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ፦
ለይቶ ለማያት ህሊናው፤ ትምህርቱና እምነቱ አልፈቅዱለትም። ከእለታት አንድ ቀን በፍርድ አደባባይ ተከሶ ቆመ።
“ወንድሞቼ ሆይ እኔ እስከዚህች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኖሬአለሁ”(የሐዋ ፳፫፡፩) በህግ ፍረዱብኝ እያለ ራሱን ለትክክለኛ ፍርድ አዘጋጅቶ አቀረበ። ዳኛው ሚዛናዊ ፍርዱን ጥሎ፤ ጳውሎስን አፉን በጥፊ እንዲመቱት ሰዎችን አዘዘ(፪)። ጳውሎስ የህግና የሞራል ሰው ስለነበረና ህግ ሲጣስ ሞራል ሲደመሰስ አላስችለው አለ። “አንተ በኖራ የተለሰንክ ግድግዳ! እግዚአብሔር ይምታህ! በህግ ልትፈርድብኝ በህግ ወንበር ላይ ተቀምጠህ ሳለህ፤ ያለ ሕግ እንድመታ እንዴት ታዝዛለህ? (የሐዋ ፳፫) ብሎ ዳኛውን ገሰጸው። አንድ አድርባይ “የእግዚአብሄርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን”(፳፫፡፬_፭)። ብሎ ጳውሎስን በፍርዱ አደባባይ ላይ አፋጦ ያዘው።
“ስሜን በማያምኑ ህብረተ ሰብ መካከል ያንጸባርቅ ዘንድ አገልጋይ እንዲሆነኝ መርጨዋለሁ” (የሐዋ ፱፡ ፲፭) ብሎ ክርስቶስ የመረጠለትን ሐዋርያዊ አገልግሎት በዝምታ፤ በይሉኝታና፤ በፍርሀት ረግጦት ማለፍ ለጳውሎስ ትልቅ ክህደት ሆነበት።
“የእግዚአብሄርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን” ሲባል በመስማት ብቻ፤ ውስጡን ጠልቆ ሳይረዳ ያፈጠጠበትን ግለ ሰብ፤ ዳኛውንና ባደባባይ የተሰበሰውን ህዝብ ለማስተማር ቅዱስ ጳውሎስ እድል አገኘ። ቅዱስ ጳውሎስ ህጉን ከዳኛውና ከግለ ሰቡ ይልቅ የበለጠ እንዲሚያውቅና ለህጉ እንደቆመለት ለመግለጽ ሲል “አማልክተ ኢትህሚ ወለመኮንነ ህዝብከ ኢትበሎ እኪተ“ (ዘፍ ፳፪፡፳፰ ማለትም፦ በህዝብህ አለቃ ላይ ክፉ አትናገር” የሚለውን ከህግ ጠቅሶ “ሊቀ ካህን መሆኑን ባላውቅ ነው” ብሎ የጥብቅና አመላለስ ባደባባይ መለሰ።
የኢትዮጵያው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከዚህ በላይ የተገለጸውን እንዴት እንደሚገነዘቡት ከዚህ በታች እንመልከት። ቅዱስ ጳውሎስ “ሊቀ ካህን መሆኑን ባላውቅ ነው” ያለበት ምክንያት፦
ካህኑና ህጉ አልተዋወቁም። መዛኝነቱንም አላወቀም። ባለማወቁም የህጉን ሚዛንነት ሰበረው። ለቅዱስ ጳውሎስ ይህ በህዝብ ፊት የተፈጸመውን የተደራረበ ስህተት ሳይቃወም ማለፍ መስማማትና ማጽደቅ ስለሆነ ከራሱ ህሊና ጋራ መጋጨት አልፈለገም። “ወንድሞቼ ሆይ እኔ እስከዚህች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ኖሬአለሁ”(የሐዋ ፳፫፡፩) እያለ የመሰከረለትን የራሱን ህሊና መካድ ሆነበት።
ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሄርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን”(፳፫፡፬_፭)። ተብሎ ሲጠየቅ “ሊቀ ካህን መሆኑን ባላውቅ ነው” ብሎ የመለሰው፤ ለተሳሳተው ዳኛና፤ ለስህተት መጠቀሚያ ሆኖ ለቀረበው ህግ እውቅና በመስጠት የራሱን ህሊና እንዳያጎድፍ እንጅ ለተሳሳተው ካህን ወይም ዳኛ ክብር ለመስጠ አይደለም። ምክንያቱም ጳውሎስ “በሕግ ለመፍረድ በህግ ወንበር ላይ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ህግ እመታ ዘንድ ታዝዛለህን”(፫) በማለቱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ እንዲመታ ያዘዘው ካህንና ዳኛ እንደሆነ ያውቃል። ይሁን እንጅ በፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጠው የሚሰራውንና ያለበትን ሀላፊነት ሳያውቅ፤ ያለ ቦታውና ያል አቅሙ ተቀምጦ፤ ያለበትን ቦታና ፍርድን እያረከሰ ስለሆነ የጳውሎስ ሕሊና ሊቀበለው ይቅርና “አንተ በኖራ የተለሰንክ ግድግዳ እግዚአብሔር ይምታህ። በህግ ልትፈርድብኝ በህግ ወንበር ላይ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እንድመታ እንዴት ታዝዘለህ? (የሐዋ ፳፫ ) ብሎ ባደባባይ በህዝብ ፊት ዳኛውን ከዳኝነቱ አውርዶ ጣለው።
ቅዱስ ጳውሎስ ይህን የመሰለ ደካማ ባህርይ ያለውን ሰው እውቅና ሰጥቶ ከሚደርስበት ጊዜአዊ ችግር ከማምለጥ ይልቅ፤ እውቅናውን ነፍጎ የሚደርስበትን ስቃይ መቀበሉን መረጠ” ይላሉ ያብነቱ ጉባኤ ሊቃውንት።
እነዚህን የመሳሰሉ ጥልቅ ግንዛቤና ማስተዋል የሚጠይቁ ነገሮች ተብራርተው ለህዝብ ባለመነገራቸው፤ ላድር ባዮች ወይም ግንዛቤ ለሌላቸው ሰዎች “ሹም ዳኛ(ካህን) እግዚአብሔር የቀባው ወይም በእግዚአብሄር ፈቃድ የተሰየመ ነውና አትናገረው” እንዲሉ ምክንያት ሆኗቸዋል። ለብዙ ዘመን ሲነገሩ በመኖራቸው ወደ ባህል በመለወጥ ለህዝብ መጉጃም ሆነዋል።
ማንም ግለሰብ ይህንን ጥልቅ ግንዛቤ ሳይረዳ “የእግዚአብሄርን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን”(፳፫፡፬_፭) ብሎ የተሳሳተውን ለመጋረድ መሞክር፤ ያለህግ ለተቀመጠ የኖራ ልስን ዳኛ (ካህን) ጀሌ መሆንን ያስከትላል። ይህን የተናገሩ እነ ነቢዩ ዳዊትና እነ ቅዱሳን ጳውሎስ ናቸው። ሲናገሩትም መስዋዕትነትን በሚጠይቁ ጊዜዎች ትምህርት ለመስጠት እንጅ ለሸፍጠኖች ሽፋን ለመስጠ አልነበረም።
እስቲ ቆም ብለን እናስብ! ያስቀመጥነውን ከቦታው ስናጣው ትእግስት የሌለን። ቤታችን ሲዘረፍ፤ ገንዘባችን ሲወሰድ፤ የልብሳችን ጫፍ ስትነካ፡ ባንዲት ሳንቲም ስንበለጥ ለመብታችን የምንታገል ሰዎች ስንሆን፤ ዳኛ የእውነት ሚዛንነቱን ሲሰብር፤ የተቀደሰውን ፍርድ ሲያረክስ፤ ለእምነት ለመንፈሳዊነት ለቅድስና ለሞራል ለታማኝነት ምንጭና መለኪያ ናት በምንላት ቤተ መቅደስ ይህ ሁሉ የሞራል ድቀት ጎርፍ ሲያጥለቀልቅ “እግዚአብሔር የቀባውን መናገር ኃጢአት ነው” እያልን ዝም ማለት ተገቢ ነውን? ለመሆኑ የእግዚአብሄር ቅባት ምንድነው? የእግዚአብሄር ቅባት በዚህ መንገድ የምንጠቀምበት ከሆነ እያረከስነው መሆናችንን አናስተውልምን?
ባለንበት አገር የሚኖረው ህዝብ የሚያደርገውን እንመልከት! ዓለማውያን መሪዎች ሲባልጉ “ለዓለማዊ ህይወታችን ምሳሌ ልትሆኑን አትችሉም” ብለው ሲያባርሯቸው እየተመለከትን ነው። “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም እንደ እኔ ቅዱሳን ሁኑ” የሚለውን ትእዛዝ ለማክበር ከተቀደሰው ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብተው አ፩ዱ አብ ቅዱስ የሚሉ አይደሉም። “ቅዱስ” ብለው ኪዳኑንም የሚመሩ አይደሉም። ይሁን እንጅ ህጸጽ የተገኘባቸውን “እግዚአብሄር ይይላቸው እንጅ እኛ ምን አገባን” ብለው አይሸከሟቸውም።
በዚህ መንገድ የኛን ስንመለከተው ከሁሉም እራቀ። ወንጌሉ የሚነገርበትን ፈረንጆች stage ብለው ከሚጠሩት አብልጠን ቅዱስ ለማድረግ ስንል “አውደ ምህረት” እንላለን። ፈረንጆች መታሰቢያ ያሉትን፤ እኛ “ሥጋውና ደሙ” እንለዋለን። የሚከናወንበትን “ቤተ መቅደስ” ብለን በማክበር ቅዱሳን ሕጻናት እንኳ እንዳይደርሱበት እንከላከላለን። ካህናትን በተፈጥሮ ህግና በወንጌል በተደነገገው ቁዱስ ጋብቻ የተወሰኑና የእግዚአብሄር አይኖች፤ የንስሀ አባቶች ናቸው እንላለን። ፤ ጳጳሶቻችን ሴት የማያዩ ገንዘብ የማይወዱ ዓለምን የናቁ ብጹአን ቅዱሳን ናቸው እንላለን። መነኮሳት በገንዘብና በሴት መከሰስ ይቅርና ከየገዳም መውጣት የለባቸውም የሚል ስርአትም ያለን ሰዎች ስንሆን፤ እንደኛ ይህን ያህል የተደራረበ የቅድስና ስርአት በሌላቸው ላይ ይህን ያህል መዘርክረክ ሳይታይባቸው፤ ለምንድነው በዚህ ዘመን በእኛ ይህን ያህል የተዝረከረከ ነገር የተከሰተው? “እግዚአብሄር በቀባው ላይ እጂን አልዘረጋም” የሚለው የተቀደሰ ቃል በተሳሳተ መንፈስ ሲነገር በመኖሩ አይደለምን? ሌላ ምክናያት አለ?
በቤተ ክህነቱ ላይ ቀጣፊ፡ አታላይ፡ ዋሾ፡ ዘራፊ፡ ከሀዲ፡ አድርባይና ቀላማጅ ተሰብስቦ ሲንጫጫበት “እግዚአብሄር ይውጉዳው እኔ ምን አገባኝ” ብለን ተስማምተንና ተቀብለን ለመኖር እንዴት እንወስናለን? ምን አይነት አዚም ዞረብን? በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን በዋሸንግተን ዲሲ ቅድስት ማርያም የተከሰተውን መልካም ምሳሌ ሳልጠቅሰው አላልፍም።
የተደራረበ ሸፍጡ፡ ቅጥፈቱና ክህደቱ አሰለችቷቸው የዋሸንገትን ቅድስት ማርያም ምእመናን በቅርቡ ያባረሩት ደፍተራ፤ ባንድ ወቅት “እጀን ከአፍአዊ እድፍ ጉድፍ ንጹህ እንዳደረኩ ንጹሀን ሆናችሁ ለመቀበል ባትቀርቡ እኔ ከበደላችሁ ንጹህ ነኝ” (ቅ ገ ፹፫ ቁ ፵፫) የሚለውን ቃል ከተናገረ በኋላ። እንደገና በዚያችው ቅጽበት ገልብጦ “እኛ ካህናቱ ብንሳሳት አትዩን ዝም ብላችሁ የምንነግራችሁን ስሙን” ብሎ ተናገረ ተብሎ፤ በይፋ በተነገረ ጊዜ፤ እንዴት ሰውን ሁሉ እንደ እቃ ቆጠረው? ብሎ ያላዘነ ሰው አልነበረም። ህዝቡ ነቅቶ በሱ ላይ የወሰደው ርምጃ ቢዘገይም፤ በሱና በመሰሎቹ የተወሰደው ርምጃ፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ያሉትን አስመሳይ መነኩሴዎች ጳጳሳትና ካህናት ከያሉበት እየመነጠሩ ለማውጣት ለሚሞክሩ ቅዱስ ሞራል ላላቸው ክርስቲያኖች ቅዱስ ምሳሌ እንደሚሆን በሰፊው ተነገረ። ይህ በየቦታው ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያናችንን ካማስተካከልም አልፈን፤ ኢትዮጵያን ካለችበት ማጥ ማውጣት እንደምንችል አልጠራጠርም።
ሸፍጠኞች የሚጠቀሷት እነሱን የምትደግፍ የምትመስል ምእመናንን የምታስፈራራ አንዲት ሐረግ አለችንና እሷንም አንመልከታት። “አንተሰ ሕዝባዊ አልብከ ሥልጣን ከመ ትኮንኖ ለካህን በእንተ መሥዋዕት አላ ሶበ ትሬእዮ ለካህን ይገብር ከመዝ ጉየይ ኀበ ክልእ መካን ወኢትኮንኖ”(ሃ. አ. ም. ፳፪፡ ፲፪) በማለት ሰለስቱ ምእት የተናገሯት ናት። ይህም ማለት “ክህነቱ የሌለህ አንተ ምእመን ሆይ! ካህኑ የምትነቅፍበትን ነገር ፈጽሞ፤ ለአምልኮት ህሊናህን የሚያውከው ከሆነ፤ የየታዘብከው ካህን በሚቀድስበት ጊዜ እራስህን አግልል እንጅ፤ ስለመስዋዕቱ ክብር ስትል ካህኑን መስዋእቱን በሚያቀርብበት ወቅት አትንቀፈው” ይህ ትእዛዝ የተሰጠው የካህኑ አገልግሎትና የመስዋዕቱ ክብር ተቆላልፎ ግለሰቡ ያየውን ያላዩ በንጹህ ህሊና በተመሰጦ አምልኮት ላይ ላሉ ሰዎች እንቅፋት ላለመሆን ነው። ብዙ ሰው በማስረጃ ያረጋገጠውን ስህተት የጸመውን ካህን ጳጳስ መነኩሴ በዝምድና በጓደኝነትና በመንደር ልጅነት ወይም በድርጅት ምክንያት ጋርደው ማለት አይደለም።
“ከማሽላ አዝመራ ሲያባርሩት፡ ወደ ዘንጋዳ ክምር፤ ከዚያ ሲያባርሩት፤ ወደ ስንዴና ጤፍ ክምር፡ እየዘለለ እንደ እሚያስቸግር የቆላ ዝንጀሮ፤ ካንዱ አገር፡ ወደ ሌላ አገር፤ ካንድ ሰባካ፡ ወደ ሌላ ሰባካ ፤ ካንድ ደብር፡ ወደ ሌላ ደብር እየተዘዋወረ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚያውከውን ዝም በለው፤ ተባበረው፤ ተከተለው፤ ወይም በሀሜት እለፈው ማለት አይደለም። የምነትና የሞራል ሰዎች ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይቃወሙታል።
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አቋም
“እመሰ ወደቅነ ውስተ ግበ ፍትወት፤ ወነበርነ ውስተ ጽልመት ዘግብረ ዓለም። ይደልወነ ናንቃዕዱ ላዕለ ገዓር። ወንስጥጥ ልብሰ ጽልመት ዘየአውደነ ወይከልአነ ነጽሮ”( ተግ ገጽ ፪፻፵፩_፵፪) ማለትም፦ በስግብግብ ባህርይ ፈተና ተጠልፈን ጨለማው ጥቅጥቅ ካለበት ጉድጔድ ብንወድቅ፤ ከወደቅንበት ወጥተን ከጨለማው ለመላቀቅ እንጣር። የጋረደንን የሸፈንን ነገር ሁሉ ሰንጥቀን እንውጣ” እያለ ሸክሙ የከበዳቸውን ሰዎች ቅዱስ ዮሐንስ አበረታታ።
የምዕራቡ ክርስትና ቅዱስ የሚለው፤ በኋላ ተጸጽቶና ንስሀ ገብቶ ብዙ መጻህፍት ጽፎ ያለፈው አውግስቲን የሚባለው፤ ባንድ ወቅት የሮማ መንግስት ባደረሰባቸው መጫን አንገዛም ያሉትን ሰዎች ለማስገዛት ሲል፤ ከፖለቲከኞች ጋራ በማበር በፈጠረው የፖለቲካ ዘዴ “ሰው በውርስ ኃጢአት የተወለደ ስለሆነ መገዛት አለበት” ብሎ በግልጽ ሰበክ። ኦርቶዶክሳዊው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ በተጫናቸው ጭቆና ተንገሽግሸው “በቃን ከላያችን ውረድ” የሚሉትን ድሆች “በኃጢአት ውርስ የመጣባችሁ መርገም ነውና ተገዙ የምትል ከሆነ። አንተና እንዲገዙ የምትሰብክላቸው ሰዎች እንዴት ተወልዳችሁ ወደ ዚህ ዓለም ልትመጡ ቻላችሁ?” በሚል ንግግሩ የገዥዎችንና ያውግስቲንን ቀልብ ገፈፈው። የአውግስቲን ሸፍጥ አንደ አዚም አፍዞት የነበረውን ህዝብ የዮሐንስ ትምህርት ከተኛበት ቀሰቀሰው። የተቀሰቀሰው ህዝብ ዮሐንስን “አፈወርቅ” የሚለውን የክብር ቅጽል አቀዳጀው። ከዚህ ቀደም፦
፩ኛ የዘመናችንን ጳጳሳት ከአርቶዶክስ ትምህርትና ትውፊት ምን ያህል እንደራቁ ለማሳየት “የዘመናችን ጳጳሳት በዮሐንስ አፈወርቅ ዐይን ሲታዩ” ሀምሌ ፲፭ ቀን ፪ሺ ፩ ዓ ም የተጻፈውን ይመልከቱ
፪ኛ የኦርቶዶክሱን ነገረ መለኮት አመሰራረትና ግንዛቤ ከሮማ ካቶሊክና ከፕሮቴስንታንት ለመየት፤ መስከረም ፲፯ ቀን ፪ሺ ፪ ዓም “ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በሮማ ካቶሊክና በፕሮቴስታንት የሚሰጣት አክብሮትና ግንዛቤ” በሚል የተጻፈውን ይመልከቱ።
የተሳሳተና ያለቦታው የተቀመጠ መሪ “እግዚአብሄር የቀባው” ነውና መንቀፍና መተቸት ኃጢአት ነው እያሰኙ የሚኖሩና ይህንንም የሚሰብኩ ሰዎች የሞራል ውድቀት የተጠናወታቸው እንደሆኑ ለማሳየት “የእምነትና የሞራል ግዴት” በሚል ርእስ ማቅረቤ ይታወሳል። “እግዚአብሔር የቀባው” በሚል ርእስ ያዘጋጀኋትን ይህችን ጦማር ያስከተልኩበት ምክንያት፤ ብቃት እውቀትና ሞራል ሳይኖራቸው የተሰየሙትንና ሊሰየሙ በዝግጅት ላይ ያሉትን ሁሉ አለመቃወም ትህትናንና ቅድስናን የሚገልጽ ሳይሆን ከውድቀት እጅግ ወደ ባሰ ውድቀት የሚከት መሆኑን ተገንዝበን የምንከላከልበትን መንገድ እንድንፈልግ ነው።
ማንም እነዚህን ተከታታይ ጦማሮች አንብቦ ከተረዳና፤ ወደፊት አከታትየ የማቀርባቸውን ጦማሮች ካነበበ፤ ለካ እንዲህ ነው እንዴ! ብሎ ባለጌውን አስመሳዩን ቀጣፊውን ጳጳስ ቄስ መነኩሴ፡ ባዲስ ፋሽን እራሱን መምህር እያለ በመሰየም የተነሳውንም መምህሬ እገሌ፤ ወይም ድርጅቴ በማለት ከመከተል ይልቅ ከነሱ አሉባልታ ተላቆ ምጻሕፍት ምን ይላሉ? ወደ ሚለው ደረጃ በመድረስ ለቤተ ክርስቲያናችን ቅድስና ቅድሚያ እንዲሰጥ ዓይኑን ይከፍትለታል። ለመቃወምም የሞራል ድፍረቱ ይዳብርለታል። የማይረቡ የማይጠቅሙ ሰዎች በተቀደሰው መንበር ተሰይመው በተራቸው ግልቢያቸውን እንዳይጀምሩ አሁኑን ተቃውሞውን ማሰማት እንዲችልም ይረዳዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን አካል የሆነ ሁሉ መጽሐፍ እያነበበ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የጉባኤ ሊቃውንት አተረጓጎምና አገላለጽ ተረድቶ ስህተቱን ልይቶ እየገለጸ አታላዩን ሁሉ አንቀበልም ወደሚለው የሞራል ብቃት ካልደረሰ፤ ዶክተረ አረጋዊ በርሄ ገልጸው በመጽሐፋቸው እንዳቀረቡልን፤ አቶ ስብሀት ነጋና ገብረ ኪዳን ደስታ በቤተ ክርስቲያናችን የጫኑብንን መርግ በቀላሉና ባጭር ጊዜ ፈንቅለን ከላያችን የምናስወግደው አይደለም። እንዲያውም አሁን ፓትርያርክ ለመሆን በጩነት ቀረቡ የተባሉት ሰዎች በቤተ ክርስቲያናችን ላያ ተጭነው ሸክሙ እየከበደ የሚሄድ ይመስላል።
ይቆየን
ለሌሎች ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ጦማሮች የሚከተለዉን ድህረ-ገጽ ይመልከቱ::
http://www.medhanialemeotcks.org/
በዲሲ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ጣሊያንና ቫቲካን ኢምባሲዎች ፊትለፊት በመገኘት እ.አ.አ. በ1930ዎቹ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ላይ ጭፍጨፋ ለፈጸመው ሮዶልፎ ግራዚያኒ የመታሰሰቢያ ቤተመዘክርና የመናፈሻ ቦታ መሰየሙን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ግራዚያኒ በዓለም አቀፍ ስምምነት የተከለከሉና የተወገዙ የመርዝ ጋዝና ፈሳሽ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአውሮፕላን ላይ በማዝነብ በብዙ ሽህ ኢትዮጵያውያን ላይ የጅምላ እልቂት ፈጽሟል። ግራዚያኒ ከዚህም በተጨማሪ ሊቢያ ውስጥም ከፍተኛ እልቂት እ.አ.አ. በ1920ዎችም ውስጥ ፈጽሟል። በዚህም መሠረት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ለፈጸማቸው የጦር ወንጀሎች 19 ዓመት እስር ተበይኖበት እንደነበር ይታወቃል።
ለዚህ ዓለም በአለም ዓቀፍ ደረጃ “አራጅ” በመባል ለሚጠራው የቢኒቶ ሙሶሊኒ የቀኝ እጅ በመሆን በጦር ሚኒስትርነት ተመድቦ እጅግ ዘግናኝና የሰው ልጅ ይፈጽማቸዋል ተብሎ ለመናገር የሚዘገንኑ ማሳቃያዎችን ለፈጸመ ው የጦር ወንጀለኛ ለአዶልፎ ግራዚያኒ በደቡባዊ የሮም ከተማ በሚገኝ ቦታ በአገሪቱ ግብር ከፋዮች ወጭ መታሰቢያ ተሰርቶለታል። ይህም የሚያሳየው በአሁን ሰዓት ጣሊያንን በማስተዳደር ላይ ያለው መንግስት ለኢትዮጵያውናንና ለሊቢያውያን ያለውን ንቀትና ጥላቻ ነው። ለምሳሌ ያህል ጀርመን ውስጥ ለአዶልፍ ሂትለርና ለተካታዮቹ መዘክር መስራት ይቅርና ስለናዚዎች በበጎ ሁኔታ ማንሳት እንኳ በህግ የተከለከለና “ውግዝ ከማሪዎስ” የሆነ ተግባር ነው። ሊደረግ ቢሞከር እንኳ ምን ያህል ዓለማቀፋዊ ትኩረትና ውግዘት በተለይም ከይሁዳዊያን እንደሚደርስ መገመት አያዳግትም። ለነገሩ ጀርመኖች እንኳን ይህንን ሊያደርጉና ሊያስቡት የሚችሉት ነገር እንኳን አይደለም። ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ እንደሚባለው ጣሊያኖች ይህንን እጅግ የሚያስቆጣ ወንጀል በኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸሙት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ ባንዳና ለአገሪቱ የማይቆረቆር መሆኑ ስለሚያውቁ ነው። ለዚህም ዋናው ማስረጃ ይህ መዘከር ከተከፈተ በኋላ የወያኔ አገዝዛ ያቀረበው ምንም ዓይነት ተቃውሞ የለም። እንደውም አንድ ሰልፈኛ በስላቅ መልክ ሲናገሩ እንደተደመጡት ወያኔዎች ለጣሊያን መንግስት “እንኳን ሰራችሁ፣ በርቱ” የሚል መልዕክት ሳያስተላልፉ እንደማይቀር መጠርጠር ይገባል ብለዋል።
በሰልፉ ላይ የተነሱ የሚከተሉትን ፎቶግራፎች ይመልከቱ።
ከህጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
መግለጫውን በሙሉ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ ይህንን ይጫኑ። የኢ.ኦ.ተ.ቤ. ህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
ቀራፊ፤ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
አቡነ መርቆሪዮስ የአ/ኦ/ተ/ቤ ሕጋዊ ፓትርያርክ
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ

“ጉልቻ ቢለውጥ ወጥ አያጣፍጥም” የኢትዮጵያን ሪቪው ወቅታዊ ርዕሰ አንቀጽ
በኢትዮጵያ ላይ እንደ አልቅት ተጣብቆ የህዝቡን ደም እየመጠጠ፣ እየገደለ፣ እያሰቃየና የፈለገውን እያደረገ ለሃያ አንድ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ቅጥረኛው፣ ጎሰኛው፣ አምባገነኑና ዘራፊው የህወሃት አገዘዝ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በስልጣን ላይ ቢቆይም ወይም በትረ ስልጣኑን ለሌላ ወያኔ ቢያስተላልፈው፣ አጠቃላዩ የአፈናውና የግፈኛው ሥርዓት ተገርስሶ እስካልወደቀ ደረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያመጣው አንዳችም ለውጥ አይኖርም። ሕወሃቶች ከደደቢት በረሃ ተማምለው የመጡበትን ታላቁንና ለብዙ ዘመናት የኖረውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነቷንና አገራዊ አንድነቷን የማፈራረስና የማዳከም የጥፋት ዓላማቸውን ከሥልጣን እስካልተነቀሉ ድረስ እንደሚቀጥሉበት በሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡበት ጊዜ አንስቶ እየታየ ነው። “ከዝንጅሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ” እንደሚባለው መለስ ዜናዊ በሌላ ወያኔ ቢተካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያመጣው ምንም ዓይነት ለውጥ አይኖርም።
የህወሃት ቡድን ከመነሻው አንስቶ እስከአሁን ድረስ ከአርባ ዓመታት በላይ የሰራበትን ወደፊትም ለመቀጠል በዕቅድ ይዞ የሚንቀሳቀስበትን መሠረታዊ የኢትዮጵያን ብሔራዊና አገራዊ አንድነት የማፈራረስና የማላላት እኩይ ዓላማ ኢትዮጵያዊያን እስካላስቆሙት ድረስ እንደሚቀጥልበት ምንም ዓይነት ብዥታ ሊኖር አይገባም። አንዳንድ የዋሆች የእባቡን የወያኔን ባሕርይ ካለመረዳት እንደሚሉት “መለስ በሌላ ወያኔ ቢተካ የተሻለ ጊዜ ሊመጣ ይችላል” ብለው ሲናገሩ ይደመጣሉ። የወያኔ ድርጅት እንደ ድርጅት አምባገነን፣ ጸረ-ዲምክራሲ፣ አፋኝ፣ ጎሰኛ፣የንጹሃን ደም አፍሳሽና ከሁሉም በላይ ጸረ ኢትዮጵያዊ ነው። ስለሆነም የወያኔን ድርጅት እንደ ድርጅትና ሥርዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጭንቃ ላይ አወርዶ በማፈራረስ በምትኩ ኢትዮጵያዊ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት መተካት እንጅ ወያኔዎችን አንዱን ወያኔ ከሌላው ወያኔ ጋር በማነጻጸር “እከሌ ከእከሌ” ይሻላል እያሉ ከእውነታው የተለየ ጉንጭ አልፋ ወሬ ማናፈስ፣ ወያኔዎችን መጥቀም እንጅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ማለት አይደለም።
በቅርቡ ወያኔመውደቂያው እንደተቃረበ ስላወቀ እንዳበደ ውሻ በመልከፍከፍ ከፍተኛ ትኩረቱን ያደረገው የሃይማኖት ተቋማትን ማጋየትና ማፈራረስ እንዲሁም ምዕመናንን ማበጣበጥ ላይ ነው። ታሪካዊዎቹን የአሰቦትና የዝቋላ ገዳማት ላይ እሳት በመለኮስ እንዲሁም ጥንታዊውንና ተደፍሮ የማያውቀውን የዋልድባ ገዳምን በመድፈር የመንኮሳትን መካነመቃብር በትራክተር በማረስና ቤተመቅደሶችን በማፈራረስ እኩይ ተገባር ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ለማስገባት ወያኔ እንደ ሸቀጥ ከውጭ ባስመጣው “አህባሽ” በሚባለው የተጭበረበር አስትምህሮት ሐይማታቸውን ለመበረዝና ለመከለስ እንዲሁም የሀገር ፍቅራቸውንና አንድነታቸውን ለማናጋት የሚያደርግባቸውን ደባ ለማክሸፍ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር እየከፈሉ ይገኛል። ወያኔ ይህ ብቻ ሳይበቃው ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የሃይማኖታቸውን አስተዳዳሪዎችን እራሳቸው በመስጊዶቻቸው መምረጥ ሲገባቸው ሰርጎ ገብ ካድሬዎችን በማሰማራት ሐይማኖታቸውን በሰላም እንዳያካሂዱ እንቅፋት በመፍጠር ላይ ይገኛል። ሆኖም ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በአንድ ቃልና ድምጽ በሙስሊምነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ወያኔ የሚያደርስባቸውን ግፍና በደል ተጋፍጠው በመመከት ላይ ይገኛሉ። ይህ ሙስሊሞች መብታቸውን ለማስከበር በሰላማዊና ህጋዊ ሁኔታ በማድረግ ላይ ያሉት እንቅስቃሴ ወያኔን በከፍተኛ ሁኔታ ፍርሃትና መርበትበት ውስጥ ጥሎታል። የሙስሊሞች ጥያቄ ወያኔን እንዲህ ሊያንዘፈዝፈውና ሊያወራጨው የቻለው ሙስሊሞች እንደ ሙስሊምነታቸውንና እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው አንድ ሆነው በመነሳታቸውና የወያኔን የጎሳ አጥር ሰበረው በመውጣታቸው ነው። ሙስሊሞች እንደ ኢትዮጵያዊ ሆነው ጥያቄያቸውን በአንድነት ባያቅርቡና በተበታተነ ሁኔታ ቆመው ቢሆን ኖሮ ወያኔ “የኦሮሞ ሙሲሞች እንዲህ አሉ” ወይም “የአፋር ሙስሊሞች እንዲያ አሉ” ወይም የጉራጌ ሙስሊሞች ይህንን ጠየቁ ወዘተ” እያለ እንደለመደው ከፋፍሎ ለመግዛት በሚችልበት ህኔታ ሊያላግጥበትና ለራሱ መጠቀሚያ ሊያደርገው በቻለ ነበር። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በዚህ ተጋድሏቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነትና በጎሳ አለመለያየት ለወያኔ ብቻ ላይሆን ለመላው ዓለምም አረጋገጠዋል።ይህም የትግል ሥልት ለወደፊቱ በተጠናከረና በተቀላጠፈ ሁኔታ ሊቀጠልበት የሚገባ በፍጥነት ውጤት የሚያመጣ የትግል ዘዴ ነው።
ኢትዮጵያውያኖች በሙሉ በአሁኑ ሰዓት ጎሳና ሃይማኖት ሳይለዩ ከወያኔ ጋር ከፍተኛ ትንንቅና ፍልሚያ የገቡበትና የሚደርሳባቸውን ጭቆናና የግፍ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የህይወት መሰዋዕትነትን ጭምር እየከፈሉ የሚገኙበት ወሳኝ ወቅት ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ይህንን በኢትዮጵያዊነት የጀመሩትን አንድነት አጠናክረው በመቀጠል ይህንን የበሰበሰ አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ፤ ከላይ እስከ ታች ድረስ ድረስ በምዝበራ፣ በጉቦና በዝርፊያ የተጨማለቀ የባዕዳን ተላላኪ የወያኔን አገዛዝ አሽቀጥረው የሚጥሉበት ጊዜ ቅርብ እንጅ እሩቅ እንደማይሆን ሳይታለም የተፈታ ነው።
የኢትዮጵያዊነት ቅርስ
በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
(የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር በሰሜን አሜሪካ ለሚያደረገው ፪ኛ ዓመታዊ በዓል የተበረከተ ጦማር)
የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር ለሁለተኛ ጊዜ በማክበር ላይ የሚገኘውን በዓል አስመልክተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በቋጠሮ ድረገጽ ላይ ለንባብ ያበቁትን እጅግ ጠቃሚና ትምህርት ሰጭ ጽሁፍ አቅርበንላችኋል። ምስጋናችን ጽሁፉን ላዘጋጁት ለቀሲስ አስተርአየ ጽጌና በድረገጽ ለለቀቁት ለቋጠሮ ድረገጽ አዘጋጆች ይድረስልን። ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ
የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር ሁለተኛ ክብረ በዓል/ፌስቲቫል በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር ከጁላይ 27 እስከ ጁላይ 29, 2012 ድረስ በጆርጅ ታውን ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሁለተኛውን ክብረ በዓል በደማቅና በተሳካ ሁኔታ አካሄዷል። በዚህ ዝግጅት ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉ ከመሆኑም በላይ በተላይ የልጆች ተሳትፎ እጅግ የጎላ ነበር። በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ዝግጅቶች የቀረቡ ከመሆናቸው በላይ ከብዙ በጥቂቱ የእግር ኳስ ጨዋታ፣ የሩጫ ውድድር፣ የባህል ሙዚቃ፣የመጽሃፍ ምረቃ፣ ይገኙበታል።
የዘንድሮ የክብር እንግዳ ብጹዕ አቡነ መልክጻዲቅ ሲሆኑ አባታዊ የሆነ ምክራቸውንና አበረታች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተለይም በመዝጊያው ዝግጅት ላይ ታዋቂውና ጀግናው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተገኝቶ ታዳሚውን በሙሉ ያነቃነቀ በአፈና አገዛዝ በመማቀቅ ላይ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት እንደሚያስፈልገው ጥሪውን በድጋሚ አቅርቧል። ከዚህም በላይ ታዋቂና አገር ወዳድ ከሆኑት ድምጻዊያን መካከል ሻምበል በላይነህ፣ ጸሃዬ ዮሐንስና አብዱ ኪያር ተገኝተው የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ኩራትን የሚያንጸባርቁ ታላቅ መልዕክት ያላቸውን ዘፈኖቻቸውን ተጫውተዋል። አርቲስት ታማኝ በየነም ተገኝቶ ቀስቃሽ መልዕክት አስተላልፏል።
በዚህ ክብረ በዓል ላይ ኢትዮጵያዊያን እንደዚህ በነቂስ በመውጣት የአገርና የወገን ፍቅር እንጅ አላፊ ጠፊ ገንዘብ እንደማይገዛቸው ለወያኔ/አላሙዲ ተላላኪዎች አስፈላጊ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዲሲው የአላሙዲ ፌስቲቫል ላይ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተረጨ ቢሆንም ዝግጅቱ በተመልካች ድርቅ ተመቶ እንደነበርና ወያኔዎች ለአሳሳች ፖሮፓጋንዳ እንዲያመቻቸው እስቴዲዮሙ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎችን ሰንደቅ አላማ አስይዘው፣ አለክፍያ አስገብተው ሲያስተናግዱና ሲያሽሞነሙኑ እንደነበር ይታወሳል። እዚህ ክብረ በዓል ላይ ግን በዋናነት የተገኙት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ጥቂት ጥሪ የተደረገላቸው ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ እንግዶችም ተገኝተዋል። “ብዙ ከመስማት አንዴ ማየት ይሻላል” እንደሚባለው እራሳቸው አስረጅ የሆኑትን ከዚህ በታች የተለጠፉትን ፎቶግራፎች ይመልከቱ።
እንዴት እኩል ይሙት
ወቅታዊ ግጥም። በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። እንዴት እሉል ይሙት።
ለውጥና ማምከኛ የወያኔ ስልት!
ከዳዊት ዋስይሁን
ለውጥ የተፈጥሮ ህግ ነው። ነገሮች በህዋችን ውስጥ በማያቋርጥ አንቅስቃሴ እና ለውጥ ላይ እንዳሉ ሳይንሱ አረጋግጦታል። አገራችን እና ሕዝቦችዋ ለውጥን ከተራቡና ከናፈቁ አመታት ተቆጠሩ። ከዚህ በፊት ህዝቡ ተስፋ ጥሎባቸው ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሎባቸው የነበሩ የለውጥ ወቅቶች በኛ እንዝላልነትና በገዢዎቻችን ብልጣብልጥነት ከእጃችን ላይ በቀላሉ ሲነጠቁ አስተውለናል። ገዢዎቻችን በጣም ጥንቁቅና የነቁ ስለሆነ እነሱ እጅ የሚደርስ የመረጃ እና የእንቅስቃሴ ትንሽ የለውም፤ ለደረሳቸው መረጃ አፋጣኝ ምላሽ ሲሰጡ ለሚጀመሩ ማናቸውም አይነት የለውጥ እንቅስቃሴዎች በጭካኔ በትር ያኮላሹታል ድጋሚ እንዳያንሰራራ ለሌሎች ትምህርት ይሰጡበታል።
አሁን ግን የሚጠቀምበት ካለ ለለውጡ በከፍተኛ ደረጃ አስተዋጾ የሚያደርግ ፍንጭና ጅማሬ እየታየ ያለው ከዚህ በፊት በሸሩ፣ በተንኮሉ፡ በከፋፋይነቱ ወደር ከሌለው ከህውሓት መንደር ውስጥ ሲሆን፤ ይህም ከዚህ በፊት ከህዝብ ዘንድ ተነስቶ በቶሎ እንደሚታፈነውና ጭላንጭሉን እንደሚያጠፉት ብልጭታ አልሆነም ይልቅስ ከቀን ወደ ቀን ነገሮች ከቁጥጥር ስር እየወጡባቸው እርስ በራሳቸውም እየተሰላለሉና እየተጠባበቁ እንዳለ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ጥበቡ እንግዲህ እዚህ ላይ ነው በወያኔዎች ሰፈር የተፈጠረው ድንገተኛ ያልተጠበቀ አደጋ ወደሚታይ የእርስ በርስ አለመተማመንና መከፋፈል እንደመራቸው በሌላው ወገን ደግሞ በንሮ ውድነት፤ በፍትህና በመልካም አስተዳደር እጦት፤ በእንግልት እንዲሁም በሁሉም ማህበራዊ ዘርፍ የተቆላና የተጠበሰ ማህበረሰባች አፋጣኝ ለውጥ ናፋቂ ሲኖር፤ እንግዲህ የተቃዋሚ መሪዎቻችን የመምራት ምህንድስና ሚስጥሩ የሚፈተነው እነኝህን ሁለት ያፈጠጡ ዋና ግብአቶች አገናኝቶ ለለውጥ ፈላጊው ህዝባችን ጥያቄው ሲመልሱለት ነው።
በወያኔ መሐል በተፈጠረው ክስተት ካለው እሮሮ ጋር ተዳምሮ በህዝብ ዘንድ የለውጥ ናፍቆቱንና ረሃቡን ከመቼውም ጊዜ በላይ አጉልቶታል፣ ከዚህም የተነሳ ተስፋ ሰጭ ጭላንጭሎች ከአራቱም ማእዘን እየታዩ ይገኛሉ። ”አሁን ለውጥ” ”ቀጣይ ሂደት” ”የሚፈጠር ክስተት” ህዝቦችዋ በጉጉት እየጠበቁት ያለው ታላቅ ተስፋዎች ሆነዋል። ውነትም ያለውን ሂደትና ተጨባጭ ሁኔታውን ስንፈትሸው ወደ አንድ ደረጃ እየደረሰን እንዳለ ንፋሱ ይናገራል፣ የለውጥ ደመናዎች የመጨረሻ በረከታቸውን ሊለቁ በተጠንቀቅ እንዳሉ ይመስክራሉ።
እንግዲህ የህዝቡን ወቅታዊ ጥያቄና ናፍቆት የትኛውም የተቃዋሚ መሪና የህዝብ ስቃይ ይሰማኛል የሚል የፖለቲካ ስው አፋጣኝና ታሪካዊ ተጨባጭ ምላሽ ሊሰጥ ይገባዋል።
ስለዚህ ምን ይደረግ?
በመጀመሪያ ደረጃ ወያኔ ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ አፍራሽ ስልቶችን ጠንቅቆ ማጥናት ለያንዳንዱ ማምከኛ ማዘጋጀት መቻል፤ ከነዚህም ውስጥ ማናቸውም ከየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ወሳኝ መረጃዎችን ያለመናቅ፤ በወያኔም ሆነ በህዝቡ አካባቢ ያሉ ክስተቶችን በትእግስትና በጥሞና እየተከታተሉ መፍትሄ የሚሰጠውን መስጠት፤ ክትትል የሚያሻውን መከታተል፤ ተግባር የሚሻውን መተግበር አንዲሁም ለድርጅት ፍጆታ የሚሆነውን እንደየ ፈርጁ እየለዩ እንደ አስፈላጊነታቸው መጠቀም።
ሌላውና ዋናው ወያኔ ለሚጠነስሳቸውን አፍራሽ ተንኮሎች በጥንቃቄ መፍትሄ ማዘጋጀት ከንኝህም ውስጥ በአሁን ሰአት አገር አቀፋዊ አንቅስቃሴ እየሆነ የመጣውን የኢትዮጵያውያን ምስሊሞችን እንቅስቃሴ ወያኔ ሂደቱን ወደ አልተጠበቀና እርሱ ቁማር ሊቆምርበት ትርፍም ሊያገኝበትና እርስበርስ ሊያፋጀን ወደሚችል አቅጣጫ ለማስያዝ የሚያረገውን ያላሰለሰ የፕሮፖጋንዳ ጦርነት ተገንዝቦ በማህበረሰባችን ዘንድ አስፈላጊውን የማንቃትና የማደራጀት ስራ መስራት።
በዚህ ላይ ወያኔ የአቶ መልስ ሁኔታን የሚገልጽ ማናቸውም አይነት መረጃ የማህበረሰቡን የልብ ትርታን የሚጨምርና ለለውጥ የሚያዘጋጅና የርሱ ህልውና ማክተሚያ ነው ብሎ ስለሚያምን፣ ከንደዚህ አይነት መረጃዎች ማህበረሰቡን የማገድ ዘመቻ ስለሚጀምር።
እንዲሁም በአሁን ሰአት በህውሓት ማሃል በተፈጠረው ከፍተኛ ድንጋጤ ከዚህ በፊት ያለማቋረጥ ይደሰኮሩ የነበሩ ልማታዊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻዎች ለጊዜው ጋብ ያሉ ይመስላል፤ ነገር ግን ይህ ክስተት ቀጣይነት ስላምይኖረው እንደውም በተጠናከረ ሁኔታ የፕሮፖጋንዳው ዘመቻ ሊጀመር ስለሚችል እና በማያያዝ ለተከታታይ ማህበረሰቡ ላይ አሰልቺ የሆነውን ልማታዊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በመጠነ ሰፊ ከተለቀቀበት ምንም እንዳልተፈጠረና ሁኔታዎች መስመራቸውን እንደያዙ ማህበረሰቡ አመለካከት ላይ ማስረጽ ይቻላል ብሎ ስለሚያምን።
በማያያዝም የአቶ መለስም ጉዳይ ከዋና ጉዳይነት ወርዶ ተራ ይሆናል፤ እንዲሁም በህውሓት መካከል የተፈጠረው ችግርም መፍትሄ ያገኛል ብሎ ቅስቀሳውን በተጠናከረ ሁኔታ ስለሚሰራ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ታች ላለው ማህበረሰብ የሚያስፈልገውን ትክክለኛው መረጃ በየጊዜው እንዲደርሰው ሁኔታዎችን ማመቻቸት።
ማስገንዘቢያ! ወያኔ ቀውስ በተፈጠረ ሰአት ሁሉ ማህበረሰቡን ከተፈጠረው ሁኔታ የሚያርቅበትና ለራሱ ጊዜ የሚገዛበትን ክስተት ይፈልጋል፣ ለምሳሌ አይዶል ሾው፤ እግር ኳስ፤ የቲቪ ድራማ እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎችን ይጠቀማል።
በተለይ ጁላይ 27፣ 2012 የሚከፈተውን የለንደን ኦሎምፒክ እንደ ትልቅ እድል ነው የሚጠቀምበት። ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ከፍተኛ የመገናኛ ሽፋን በመስጠት እንዲሁም በየአደባባዩ በትላልቅ እስክሪን በነጻ በማሳየትና በህብረተሰቡ መካከል የመወያያ ርእስ እንዲሆን በማድረግ የማህበረሰቡን አስተሳሰብ መስመር ለማስቀየር ከፍተኛ ዘመቻ እንደሚጀምር ይታመናል ስለዚህ በዚህም አካባቢ ምን መሰራት እንዳለበት መዘጋጀት።
ለማጠቃለያ ወቅቱ ጠንካራና ብልህ አመራርን የሚጠይቅበት ጊዜ ነው፤ ጥያቄው ግልጽና ወሳኝ ነው፤ ሕዝቡም የኛን ጥሪ እየጠበቀ ነው፤ ግን እኛ የት ነው ያለነው????
ጁላይ፡ 25/2012
ፀሃፊውን ለማግኘት፦ zoloaba112@yahoo.com
የሰማእታቱ ደም ይጮሃል
የኢትዮጵያን ሪቪው ወቅታዊ ርዕሰ አንቀጽ
በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የሰማዕታቱ ደም ይጮሃል፣ የኢትዮጵያን ሪቪው ወቅታዊ ርዕሰ አንቀጽ
ግምቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ መብቱን ተጠቅሞ ወያኔን በምረጫ ያባረረበት፣ተስፋም የሰነቀበት ታሪካዊ ወቅት ነበር። ይሁን እንጂ መለስ ዜናዊ እጅግ ከፈተኛ በሆነ ልዩነት መሸነፉን ሲያውቅ የብዙሃኑን ድምጽ መስረቅና ማጭበርበር ከመረጠ በሁዋላ ድምጻችን ይከበር ብለው ሰልፍ የወጡትን ዜጎች የአጋዚን ነፍሰ ገዳይ ታጣቂዎችን በማሰማራት ንጹሃን ኢትዮጵያዊያንን በጠራራ ጸሃይ ረፈረፈ። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያንን ደግሞ በከባድ ሁኔታ አቁስሎ የተቀሩትን በብዙ ሽህ የሚቆጠሩትን እስር ቤት ወረወራቸው።
መለስ ዜናዊ የአዲስ አበባን፣ የደሴን፣ የአዋሳን፣ የአምቦን፣ የነቀምቴን፣ የድሬዳዋን፣ የአርባምንጭንና የሌሎችም የአገሪቱን ዋና ዋና ከተሞችን በንጹሃን ደም ካጨቀየና የቅንጅት መሪዎችን እስር ቤት ከቆለፈባቸው በኋላ በአጼ ሚኒሊክ ቤተመንግስት ውስጥ ተንሰራፍቶ ተቀምጦ የአጋዚን ነፍሰ በላ ቡድን አባላትን ግብር አውርዶ በአልኮል መጠጦች ይራጭ ነበር።
በአጋዚ ጦር ጭፍጨፋ እናቶቻቸውንና አባቶቻቸውን ያጡ ልጆች፣ ባሎቻቸውን ያጡ ሚስቶች፣ እህቶቻቸውን ያጡ ወንድሞች፣ ሚስቶቻቸውን ያጡ ባሎች፣ወንድሞቻቸውን ያጡ እህቶች፣ ዘመዶች፣ ጓደኞች፣ ጎረቤቶች፣ አሁንም ድረስ እያነቡ ይገኛሉ። በዛን የጭፍጨፋ ወቅት ታክሲ ነጅዎች “የሙታን ደም ከመንገድ እስኪደርቅ ድረስ መኪናችንን አንነዳም! “ ያሉት ሲታወስ አእምሮ ያደነዘዛል። ይህ የያዝነው ወር የሰኔው ጭፍጨፋ የተደረገበት ሁልቆ መሳፍርት የሆኑ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያን በግፍ የረገፉበት ሰባተኛ ዓመት የሚዘከርበት ወቅት ነው ። ይህ በንጹሃን ዜጎች ላይ በወያኔ የደረሰው ጭፍጨፋ በኢትዮጵያዊያን አእምሮ ለዘመናት በከፍተኛ ሀዘንና ብሔራዊ ቁጭት ሲታወስ ይኖራል።
ያለ ህዝብ ይሁንታና ምርጫ የሚገዛው መለስ ዜናዊ አንድ ቀን ህዝባዊ መነሳሳቱ መቀጣጠሉ እንደማይቀር ስለሚያውቅ በመላው ዓለም ውስጥ በማንኛውም አገር ውስጥ ባልታየ መልኩ በግድያ ወይም በአደጋ የሞቱ ሰዎች አስከሬን የሚመረመርባቸው ሆስፒታሎችን በፖሊስ መስሪያቤቱ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሥር አድርጎ የተቃወሙትን ገድሎ ለመቅበር እንዲያመቸው ይህንን የሚያመለክቱ መረጃዎች አፈትልከው እንዳይወጡ ለማፈን ሴራ ሸርቧል። ሆኖም ይዋል ይደር እንጂ መለስ ዜናዊና ግበረአበሮቹ ለሰኔውና ለህዳሩ ጭፍጨፋዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎችም በ21 ዓመት የአፈናና የአምባገነን አገዛዙ ጊዚያት ለፈጸማቸው ወንጀሎች ተይዞ ለፍርድ መቅረቡ ወይም ከህዝብ ጋር በሚያደርገው ጦርነት መጨረሻ አሸናፊ የሚሆነው ሕዝብ ስለሆነ እንደ ሊቢያው ኮሎኔል ጋዳፊ እሱም ላይ ህዝባዊ እርምጃ የሚወሰድበት ጊዜ ቅርብ እንጅ እሩቅ ኣይደለም።
ህጋዊውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ይቅርታ መጠየቅ አለብን
ከተድላ ጌትነት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ካሳለፈቻቸው ዘመናት ማለት ዘመነ ዮዲት ጉዲት ዘመነ ግራኝ ዘመነ ኢጣሊያ (የአምስቱ አመት ወረራ) የባሰ የመከራ ዘመን መግፋት ከጀመረች ድፍን 20 ዓመት ሆነ።የጉዲትም ሆነ የግራኝ ግልጽ ጠላትነት በመሆኑ አባቶቻችን የቻሉትን ቅርስና ንዋየ ቅድሳት በየዋሻውና በጉድጓድ ውስጥ በመደበቅ ጥቂት የማይባሉ ዘመን ተሻጋሪ ቅርሶችንና መንፈሣዊ እሴቶችን አቆይተውልናል። በዚያ ዘመን የነበረው ግልጽ ጥፋት ለመሸሽም ሆነ ለመደበቅ ዕድል ነበረው የአሁን ዘመን የአገሬ ሰው የወዳጅ ጠላት እንደሚለው አማኝ መስለው ይልቁንም በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከልና ቅርሶችንና መንፈሣዊ ሀብቶችን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ቃል ገብተው የተሾሙ በትልቁና በወሣኙ ቦታ ላይ ሆነው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር የሚመዘብሩ አባ ጳውሎስ የቀደሞ ጠላቶች በግልጽ ሊያጠፉዋት ያልቻሉትን እርሳቸው በስውርና በግልጽ አወደሟት።
የቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመንግሥት የሚቀርበው በፓትርያርኩ በኩል እንደሆነ ግልጽ ነው። ዛሬ መንግሥትን ስለ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይህን አደረግህ ይህን አጠፋህ ማለት አይቻልም። በእርግጥ አስቀድሞ የሚስማማውን መርጦ ማስቀመጡ ባይካድም ሥርዓቱን ጠብቆ ለመንግሥት የቀረበ ጉዳይ የለም። ይህም የሆነው አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ የሌላቸው ሆኖ አይደለም አብያተ ክርስቲያናትም ችገር ሳይገጥማቸው ቀርቶ አይደለም። በተለይም የእስልምና አክራሪ ቡድኖች አብያተ ክርስቲያናትን በየጊዜው ያቃጥላሉ አሁን እየተስራፋ ያለው ሃይማኖት የለሽ ትውልድ ሥልጣን በያዘበት ቦታ ሁሉ ቀደምት የቤተ ክርስቲያናትን ይዞታና ቅርስን መንፈሣዊ እሴቶችን ሁሉ በተቻለ አቅሙ ያጠፋል። ይህን ለመከላከል የሀይማኖት መሪው ግዴታ ነበር ነገር ግን እራሱን አጥፊና አውዳሚ በመሆኑ ጉዳት ደረሰ አልደረሰም ብሎ ሃይማኖቱን ወክሎ እራሱን አጥፊ (አውዳሚ) በመሆኑ ጉዳት ደረሰ አልደረሰም ብሎ ሃይማኖቱን ወክሎ ይጮሀል ልብ በሉ የዋልድባ መታረስ የዝቁዋላ መቃጠል ለአባ ጳውሎስ ደስታ ነበር። ለዘመናት የታወቁ ለአማኙ ሕብረተሰብ ብርቅዬ የሆኑት የገዳማቱ መጻሕፍት ዘመን ተሻጋሪ ታሪካችን ሀይማኖታዊ ዕውነታዎች ባህልና ሥልጣኔን አምቀው የያዙ በታሪክ ምሁራን የእውቀት መሥራቶች ለተመራማሪዎች የጥበብ ምንጮች የሆኑ ቅርሶች ይገኙበታል ምመናን ከቦታ ደርሰው ኃጢአታቸው ይሰረይላቸዋል። ወደነዚህ ቦታዎች የደረሱ ሁሉ የመንፈስ እርካታ ያገኛሉ የለመኑትን የተሳሉትን ሁሉ ያገኙባችዋል::
በአንፃሩ ትልቅ የካውንስሊንግና የህክምና ሆስፒታሎችን ወክለው በዘመን ያልተፈታ እንቆቅልሾችን እየፈቱ ከዘመን በኋላ ላለው ተስፋም ሰንቅ ሆነው ኖረዋል። የነዚህ ገዳማት ችግር ሁሉንም ትውልድ አንቀሳቅሷል። በእግራቸው ተጉዘው እሳቱን ለማጥፋት የደከሙ በቦታው ተገኝተው እያጠፉ ልማደኛው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲዋሽ አይተው አትዋሽ እሳቱ አልጠፋም በማለታቸው እግራቸው በጥይት ተመተው የቆሰሉም አልጠፉም። ይህ ችግር በሀይማኖቱ መሪ አፈቀላጤዎች ውሸት ነው ተብሎ ተነገረ በአይናችን አይተን መናገር እንኳን የማንችልበት ጊዜ ላይ መሆናችን በእርግጥም እየዘነጋነው ነው እንጂ ቆይቷል ፡፡
በእርግጥ እኔ ሳስበው ግን ህጋዊው ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቅሬዎስ ያለስማቸው ስም ሰጥተን ለቤተክርስቲያን አይጠቅሙም ብለን የተባለው ሰምተን ስናረጋግጥ እኛም ዝም አልን። አይደሉም የሚባልበት እድል በይኖርም እንኳን እውነቱን ተናግረን በሞትን ይሻለን ነበር፡፡ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የምእራባውያኑን ትራዲሽን ሳይሆን የቤተክርስቲያኒቱን ስርዓት ህግ ጠብቀው የቆዬ ግን የነበሩበት ዘመን ለመስራት የሚያስችል እድል የሌለበት በመሆኑም ስለቤተክርስቲያን መከራከር አይቻልም ነበር። ያም ሆኖ በጦርነት ቀጠናዎች እንኳን አፅናኝ አባት እየመደቡ እኛ ሐይማኖት እንጂ ፖለቲካ ምን አገባኝ እያሉ ጭንቁን ዘመን በጭንቅ አሳልፈውታል፡፡ በጦርነት የተያዙ ቦታዎች ጥለው ወደ መሀል አገር የመጡ አባቶችን ፡”ከማን ነው ተነጥላችሁ የመጣችሁት ያ እኮ ወገናችሁ፣ ልጃችሁ ነው” ብለው በማለታቸው ቂም ተቋጥሮባቸው መሀል አገሩን ወያኔ ሲቆጣጠረው ከወያኔ ቢሮ ሄደው ፓትርያሪኩ እንዲወርዱ ህዝቡ እዲያምፅ የተለያዩ ቅስቀሳዎች እንዲኖሩ ህዝቡ እንዲያምን ስልት ነደፉ። ወያኔ ውሸቱን እውነት ማድርግ የቆየ ብቸኛ እውቀቱ በመሆኑ ጊዜ ሳይወስድበት የሚባለው ሁሉ አስብሎ እንዲወርዱ ተደረገ ፡፡ ይህ ግፍ ሀሰት ሲነገር ዝም ብለን በማየታችን ቤተክርስቲን በጭንቅ የጠበቁት አባት በወሬ ሰምታችሁ ከጠላችሁ “በግልፅ ጥፋትን ታያላችሁ ዘመናችሁ የሀዘን ይሆናል” ብሎ ፈረደብን መሰል ለዘመናት አነባን። ይችን የታሪክ እውቀት የስልጣኔ አርማ የሆነችውን ቤተክርስቲን ውድቀት በዓይናችን አየን ጠላት ተሳለቀብን። ወዳጆች አፈሩብን እኛም አለቀስን። ዋልድባም ታረሰ አሰቦትም ተቃጠለ።
ይህ ሁሉ ሲሆን ህገወጡ የወያኔው አቡነ ጰውሎስ ለሽርሽር ግብፅ ነበሩ። ህጋዊው ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሬዎስን ማንነት በአኗኗራቸውን መንፈሳዊ ህይወታቸውን ማየት ይቻላል፡፡ ነጋ ከፀሎት መሸ ከፀሎት ከሚተጉ አባቶች ዋነኛ እንደሆኑ ቀርቦ ማጣራት ይቻላል፡፡ አሁን ያለው መንፈሳዊ ህይወታቸው በአንድ ቀን የመጣ አይደለም። አብሮ የኖረ ነው እንጂ ችግሩ እኛ ሳናጣራ ስለምናወራ ሳናውቅ ስለምንጣላ ነው እንጂ መንፈሳዊ ህይወት በአንድ ጀንበር የሚመጣ አይደለም። ትላንትም እንዲህ ነበሩ በእርግጥም ስለአሳዘናቸው አዝነውብናል። ሀዘናቸውም እየጎዳን ስለሆነ ይቅርታ መጠየቁ ለእኛም የህሊና እረፍት ለቤተክርስቲያን እድገት ይሰጣል። መንፈሳዊ አባታችንን ነፃ እንውጣ። እግዚአብሔርም አባ ጳውሎስን በፍርዱ ከዲያቢሎስ አገልጋዮች ጋር ይደምርልን፡፡
አሜን
ተድላ ጌትነት
ባየር፣ ጀርመን
ይህንን ጽሁፍ በ ፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ከታንክ አብራክ የተወለደው ጀግና
የኢትዮጵያን ሪቪው ርዕሰ አንቀጽ
“ከምግብም በላይ ነጻነት እንሻለን!”
ጋዜጠኛ ኣበበ ገላው በሃያላኑ መንግስታት ጉባኤ ፊት “ከምግብም በላይ ነጻነት እንሻለን!” ሲል ተናገረ። በርግጥ ይህ አባባል ለአንዳንድ ሰነፎች ብዙም ትርጉም ላይሰጥ ይችላል። በመሰረቱ ግን ነጻነት አንዱ የእኛ የሰው ልጆች መሰረታዊ ፍላጎት ነው። በተለምዶ የሰው ልጆች ፍላጎቶች ሶስት ናቸው ይባል ነበር። ግን አይደለም አራት ናቸው። ከምግብ፣ ከልብስና ከመጠለያ ጋር ነጻነት አንዱ መሰረታዊ ፍላጎታችን ነው። እንዲያውም የሰው ልጅ ነጻነቱን ከምግብም ሁሉ በላይ ሲሾመው ይታያል። ማን ነው እስቲ ማርና ወተት እየጠጣህ ጮማ እየቆረጥክ ኑሮህን በወህኒ ቤት አድርግ ቢባል እሺ የሚል? ማንም ለዚህ አይመዘገብም። ይልቁን የመንቀሳቀስ፣ የመናገር፣ የመምረጥ መብቱ ተከብሮለት ደረቅ ዳቦውን በነጻነት እየበላ ወይም ቆሎውን እየቆረጠመ በቤቱ ኩርምት ብሎ ቢተኛ ይመርጣል። ይህ የሚያሳየው የሰው ልጅ ለነጻነቱ ታላቅ ክብርና ቦታ እንደሚሰጥ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ አቶ መለስ ዜናዊ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተኮፍሰው ለመዝለቅ የሚያስችላቸውን ቀለብ ለሚቆርጡላቸው ኃያለን መንግስታት ልማታዊ መንግስት የሚያስመስላቸውን ተውኔት ቢሰሩም ሃገራችን ውስጥ ግን ህዝባችን በከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛል። ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆን እንኳ በቂ ዳቦም የለም። ስለሆነም የአቶ መለስ ተውኔት፣ ከተራ ጉንጭ አልፋነት የበለጠ ቦታ የሚሰጠው ቁምነገር አይደለም።
አበበ የገለጸው ይህንን ሃቅ ነው። ነጻነት ያስፈልገናል! ታዲያ፣ ያ…. አበበ የተናገረበት ቅጽበት አቶ መለስን፣ እንደውሻ ጭራ አስቆልፎ፣ አስደንግጦና አዋርዶ በዋሽንግተኑ ኢምባሲያቸው ውስጥ የተደገሰላቸው ግብር ላይ እንዳይገኙ እፍረት ውስጥ ጥሏቸው ወዲያውኑ አስፈርጥጦ ወደ አገር አስመልሷቸዋል። ደቡብ አፍሪካም ውስጥ በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን እንዲሁ አንገታቸውን ደፍተዋል። የአበበን መልዕክት ለወደፊት ትግላችን መፈክር አድርገን በተጠናከረ ሁኔት በአንድነት መንቀሳቀስ ይጠበቅብና። ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ እንኳን አገራችን በምትገኝበት የአፍሪካ አህጉር ለዘመናት ተንሰራፍተው የነበሩ አምባገነኖች በቱኒዚያ፣ በግብጽና በሊቢያ በሕዝባዊ አመጽና መነሳሳት ተገርስሰው ወድቀዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጭቆና በእነዚህ አገሮች ውስጥ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር እጅግ የከፋና የተባባሰ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የወያኔ በትር ያላረፈበት ዜጋና የሕብረተሰብ ክፍል ስለማይገኝ ኢትዮጵያውያን ተባብረን የመለስ ዜናዊን ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ከስልጣን አውርደን በምትኩ ሁሉን ኢትዮጵያዊ የሚያሳትፍ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የምንመሰርትበት ወቅት ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ አሁን ነው እንላለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ክፉን ሥራ እግዚያብሔር ይገልጣል፤
የዐርብ ፍቅረኞችም በትንሳዔው ይወድቃሉ
የተሰወረ የማይታይ፣ የተከደነ የማይገለጥ የለምና ሆኖም እስኪገለጥ ግን የአካልብት ልክፍት የማይቀር ነውና ባለንበት ዘመን በፓትርያርክ በብጹዕ አቡነ መርቆሪዎስ በሚመራው በሕጋዊው ውጭ በሚገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ በገጠመው ወከባ ሁላችንም እራሳችን ባለመመርመር ባለመታደል ዋኖቻችን ለሆኑት በጹአን አባቶቻችን ለልፋታቸው ምስጋና ሳንሰጥ ጭራሽ ከሳሽ ብንሆንባቸውም እግዚያብሔር አምላክ “በውሃ ውስጥ ባለፍክ ጊዜ ካንተ ጋር እሆናለሁ በወንዞችም ውስጥ ባለፍክ ጊዜ አያሰምጥህም፣ በእሳትም ውስጥ በሄድክ ጊዜ አትቃጠልም ነበልባሉም አይፈጅህም” ኢሳ 43፡2 በሚለው ቃል እየተጽናኑ፤ “ብነኖርም ለእግዚያብሔር ብንሞትም ለእግዚያብሔር ነው”ብለው ሳይበገሩ በአንድነት ቆመው ይልቁንም የከዳተኞች ክፋት ለቀኖች ክፋት መስታወት ሆኗቸው ጊዜውን እየዋጁ የያዙትንም አልበተኑም።
ከዳተኞች ግን መንጋውን በመጠበቅ ለተጉት አባቶች አጋዥ ከመሆን ይልቅ የሥጋ ምኞት ለመፈንቅለ ሥልጣን ህሊናን የሸጡበት የተሳከሩ መነኩሴ መሰል አምስቱ ከልቦች የራሳቸው የልክፍት አረር በአባቶች ላልይ ተኩሰው ህዝቡን ለመከፋፈልና የአባቶችንና የምዕመናንን ስም እንበለ ከነቱ በማጉደፍ በየዋሁና የሲኖዶሱ ስብከተ ወንጌል የጅርባ አጥንት በአባ ወልደተንሳዔ ስም በመነገድ ምዕመናን በምዕመናን ላይ በማነሳሳት ዘመቻ ተጠምደዋል። የዚህም ወጤቱ እየታየ ነው። ወንጌል ሰባኪ አባ ወልደ ተንሳዔን እኛን ሲያስተመሩን በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር “ አውጣኝ ያለ ወጣ፣ አባላኝ ያለም በላ፣ ተኝቶ ተገኝቶ አሳማ ተበላ” እንዳሉን ሁሉ ዛሬ በተገላቢጦሽ መሰሪዎቹ አምስቱ ከልቦች እርስዎን ተኝተው ያገኙዎት በሚመስል ሁኔታ በስምዎ ነገደው እርስዎንና ቤተክርስቲያንን ከመብላታቸው በፊት እንደእግዚያብሔር ቃል “አንተ የምትተኛ ተነስ ንቃ ጊዜው መሽቷልና” በርትተው ይጸልዩ። ምናልባትም ተጎድተውም ቢሆን ለቤተክርስቲያኒቷ አንድነት ሲሉ ትልቁን የወንጌል ተራራ ይቅርታን ይድፈሩና መሰሪዎች ኢካቦድ በጨለማ የተከሉትን በይቅርታ በመንቀል ታሪክ ይስሩ። ጊዜው መሽቷል።
በተለይም በኢትዮጵያ በግፍ የለነጻነት የታፈነውን ህዝብ እንደቤተክርስቲያን ቀደምት አባትነታቸው የኢትዮጵያዊውን መከራነ ፍዳ እረፍት ነስቷቸው ገፈኞች ቀንበራቸውን ከሕዝቡ ላይ እንዲያነሱ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በመላው ዓለም አደባባይ ለነጻነት በመጮህ ላይ የሚገኙትን በሁለት ጎን የተሳሉትን የየኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሊቀ ጳጳስና የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ አረጋዊው ብጹዕ አቡነ መልከ ጻዲቅን ለምን ወያኔን አወገዙ፤ ለምን የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያዊያን ናቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ስለሚደርስባቸው በደል ቤተክርስቲያን ትጮሃለች በማለት በመናገራቸው ለምን በዚህ የወያኔን ግፍ አጋለጡ በሚል ዲያቢሎሳዊ ተልዕኮ አባቶችን በድረ ገጾቻቸው በማዋረድ ሴራቸው እየተስተዋለ ነው።
ሆኖም ሊቀ ጳጳሱ ብጽዕ አቡነ መልከ ጻዲቅ እውነት አርነት ያወጣቸው እንደ እግዚያብሔር ቃል በሁለት ጎን የተሳሉ ናቸውና በእምነታቸው ቆመው ከእግዚያብሔር በቀር ማንም በሳቸው ሥልጣን እንደሌለው በማስረገጥ ከተገፉት ጋር የቆሙ አረጋዊ አባት ናቸው። እነዚህ የምግባር ድሆች ከልቦች እንደቃሉ ሳይሆን እንደ ዶላሩ የሚሰብኩበት የመበለቶች ተረት ተረት የሆነ ቀኖና ቤተክርስቲያን ፈርሶ ወይም ተጥሶ በህጸጽ የተሞላው ሁሉ የግድ ቄስ ካልሆነ፣ ክህነት ያልሰጠ የማርያም ጠላት የሚሉና በተግባርም ያሳዩ፤ ከገፊዎች ጋር በመቆም ስብከቱን በሃሰት ፍቅር ያበዱበት በአጠቃላይ በመምህርና በአባ (መነኩሴ) ስም የተነሱ ጥቅመኛ ከልቦች ከቤተ እግዚያብሔር መልካምነት እንዲጠፋ በማድረግ ሕጋዊውን በውጭ የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ በማወክና በመፈታተን ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ አምስቱ አካልብት የእግዚያብሔርን ተግሳጽ የናቁ፣ መስዋዕቱን ያቃለሉ፣ ዋናዎቹን የማያከብሩ ምናልባትም በስደት ስም በሲኖዶሱ የኤሊ ልጆች ሾልከው ገብተው የተሾሙና የመኖሪያ ፍቃድ ማገኛ መጠለያ በማድረግ ንጹሃን አባቶችን በማመስ ተልዕኮ ላይ ተሰማርተዋል። ቀደምት ዋናዎቹ ሲኖዶሱን ይዘው የተሰደዱ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች በነዚህ ከልቦች ተዋርደዋል፣ አይ ጊዜ! ስለዚህ በኢትዮጵያ ያለው ጥፋት ሳይበቃን በነሱም ሆነ በሌሎቻችን በደል የእግዚያብሔር ፍርድ ለወርድ የዳመነ ቢሆንም ይህንን ባለማስተዋል፤ መገሰጽን እንደመናቅና እንደመደፈር ቆጥረው የቆሙ መስሏቸው መውደቃቸውን ስተው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የማዕዘን ራስ የሆኑትን አባቶች ሲዘልፉ ተስተውለዋል።
እግዚያብሔር “ያከበሩኝን አከብራለሁ፤ የናቁኝም ይናቃሉ” ቢልም ካለመስማት ሽማግሌ ማጣት ከእግዚያብሔር ቅጣት አንዱ መሆኑንም ባለመረዳት በሊቀ ጳጳሱ በብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስና በብጹዕ አቡነ ይስሃቅ ሞት መቀጣታችንን አላስተዋሉም። ከዳተኞቹ ጭራሽ በነሱ ስም ንግድ የጀመሩትም ተስተዋል እንጅ ይህ የአምስቱ አካልብት የስመ አባዎችና መምህራን ድፍረትና ማናቸውም የቤተክርስቲያን ነጋዴ የአፍኒንና የፍንአስ ዕጣ ከመሆን አያልፍምን ዕምነታችንን የምንወድ ሁሉ ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስም ቤተእግዚያብሔር የጨካኝ ከልቦች ዋሻና መናከሻ ሊሆን አንፈቅድምና ስደተኛውም ብዙ መስዋዕትነትን የከፈለበት በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለዚህ ከላይ ለተመለከተው ችግር በአስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል።
የሚገርመው አምስቱ ውሾች(ውሾች) እራሳቸው ወያኔ ሆነው አመጣጣቸውንም እያወቁ አንዴ ማህበረ ቅዱሳን፣ አንዴም ደግሞ ወያኔ ገብቶበታል እንዴ እያሉ በሌላ ጊዜ ደግሞ የፖለቲካ ሰዎች ተቆጣጥረውታል፣ ዶክተሮች አላስቀርብ አሉን በማለት በወያኔ ስም በማስፈራራት ሀቁን ለማፈለስና በጽናትና በአንድነት ያሉትን ቀደምትና ዋናዋዎቹን ሊቃነ ጳጳስ አባቶቻችንን ለመከፋፈል በፓትርያርኩ ስም የሚጠቀሙበት የልክፍት አዙሪት አስከፊ ቢሆንም ክብር ገን ከቀደሙት ዋናዎቹ አባቶቻችን አለቀቀችና የእገዚያብሔርን ስራ በመስራት በብርሃን መመላለሳቸውን ቀጥለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ እነዚስ አምስቱ ውሾች ቤተክርስቲያንንም ስደተኛውንም በመናቅ ግፋም ሲል የዋህ ሲያገኙ በማስጨብጨብ የረከሱ የአፍሚንና የፊንአስ ጊዜ ስደተኛ ለማድረግ ከስም አይጠሩ አባታቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም ልክፍታቸውን ቀጥለውበታል። የአድራጎታቸውን አስከፊነት አውቀው እንዲመለሱና ክፉ ስራቸውን እንዲተው በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ካህናትና ምዕመናን የተሰጣቸውን ምክክር አጣጥለውታል። ሆኖም ኢትዮጵያና ቤተክርስቲያን የክብር በሮቻችን በመሆናቸው አሁንም ደግመን እየነገርን ከጥፋት ተመለሱና ኑና እንወቃቀስ እንላለን። ዳሩ ግን አምስቱ ከልቦች ክብር ከራሳቸው የለቀቀ የኑፋቄ ባሮች ናቸውና አባቶችን፣ቤተክርስቲያንና ምዕመናን፣ ለኢትዮጵያ ነጻነት የቆሙትን ዜጎች በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና ህዝቧን የሚያዋርዱ ቡድንተኛ ኢካቦች ናቸውን ማስተዋል ጠፍቶባቸዋል።
እነዚህ አምስቱ አካልብት (ኢካቦድ) ኢትዮጵያን አገርና ህዝብ ፈርሶ እያለ የድረሱልን ጥሪ እየተስተጋባ በየማዕዘናቱ ኃይሉን በጸሎት ከማሰባሰብ ይልቅ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ለህዝቧ ዓይን የሆኑትን በማዋረድ ምንዝርና በሆነው አድመኝነት የነጎዱ እራሳቸው ኩነኔዎች ሆነው ኮናኝ የሆኑበት እራሳቸውን ሳያውቁ ሌላውን በቅዱስ መንፈስ የሚመረመራቸውን እናውቃለ የሚሉ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለምን ጣሳችሁ ሲባሉ፣ ለንስሃ ከመዘጋጀት ይልቅ የህጸጽና የነውር አገልጋይ በመሆን የቡድንተኝነትና የአድመኝነት ቁማር በመጫወት የአገርን፣ የቤተክርስቲያን፣ የአባቶችን ክብርና የምዕመናንን እንድነት በመሸርሸር እንጀራ የበሉበትን ተረከዝ በመንከስ ላይ ይገኛሉ። ከዚህም በላይ ኮቴያቸውን በህጋዊዊ ውጭ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ እያሰሙ ነውና እነዚህ ኢካቦድ በሚያራግፉት የምንደኝነት አባራ ያላወቃቸውንና ያልጠረጠረውን በፓትርያርኩ ስም በመነገድ አንድነቱን ሸርሸረው በጥርጣሬ፣በምንደኝነት በኑፋቄ በመከፋፈል ላይ ናቸው። አምላካችን ለሁሉ አስተዋይ ልቡና ይስጠው።
ባሳለፍናቸው ረዥም ዓመታት ብጹአን አባቶቻችን ለአገርና ለምዕመናን የምትጸለዩ መሆናችሁን በትክክል ብናውቅም፤ ካዛ ባለፈ አፋጣኝ የህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ በመጥራት ወይንም አባቶቻችን እግዚያብሔር በሚያሳያችሁ መንገድ የምዕመናኑን የመንጋችሁን አንድነት ከከልቦችና (ከውሾች) ከኢካቦድ ትታደጉትና ኢካቦድ በጨለማ የሰሩትን በብርሃን ትገልጡትና አንድነታችን ትጠግኑትና ያጠፋም ተጸጸቶ፣ ፍቅር ይሰፍን ዘንድ እየተማጸንን ምዕመናን ከእውነት ያልሆኑት እውነትን እንደማይሰሙ እንደ አባታቸው ሃሰትን ሲናገሩ ከራሳቸውና ከሃሰት አባታቸው ልጅነታቸውን እንዳሳወቁ በመገንዘብ ኢካቦድ (ከልቦች/ውሾች) ላቀዱት በሁከት የመከፋፈልና የግርግር የስም ማጥፋት በሽታቸውን ልክፍት የተነሳ ሰላም እንደሌላቸው አውቀን ሳንገበር በጊዜውም አለጊዜውም በዓለም ዙሪያ ቤተክርስቲያናችንን በመልካም ተጋድሎ በመጠበቅ ከቀደምት ዋናዎቹ አባቶቻችን ድምፅ እንድንሰማ እግዚያብሔር ይርዳን።
ከእግዚያብሔር ሥራ ፊት የኢካቦች ሥራ አይቆምም። የእግዚያብሔር ሰዎች አብረውን አሉና “ስቀሎ ስቀሎ” የአርብ ፍቅረኞች በትንሳዔው ይገለጣሉ። ይበተናሉ። ይወድቃሉ።
እግዚያብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
በውነት እንዳልካቸው
ወያኔ ከፍተኛ ተቃውሞ በዋሽንግተን ውስጥ ደረሰበት
በእብሪትና በማንአለብኝነት የተወጠረው ወያኔ በሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ላይ በማድረግ ላይ የሚገኘውን የመብት ረገጣና ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። በዚሁ ሰልፍ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ዘር፣ ሃይማኖትና ጾታ ሳይለዩ በአንድነት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው የወያኔ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት የተቃውሞ ድምጻቸውን በአንድነት ከፍ አድርገው አሰምተዋል።
በዚህ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውንና በወያኔ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ላይ ያላቸውን ተመሳሳይና ቁርጠኛ አመለካከታቸውን ያሳዩበት መድረክ ነበር። በተለይም መለስ ዜናዊ በቅርቡ የአገሪቱን ሃብት በማባከን ከውጭ ገንዘብ ከፍሎ ያስመጣውን የተጭበረበረ የሃይማኖት አስተምህሮት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ በኃይል ለመጫን የሚያደርገውን ተልካሻ ሙከራ ሰልፈኛው አበክሮ ተቃውሟል።
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ መመስረትን አስመልክቶ ከግንቦት 10 እስከ 13 ቀን 2004 (ሜይ 18-21 2012) በካናዳ ዋና ከተማ የተደረገው ጉባኤ መግለጫ። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። በጨለማ ውስጥ ያለ ሕዝብ ብርሃን ያያል
በጨለማ ያለ ህዝብ ብርሃን ያያል
በኢትዮጵያ ውስጥ በማናቸውም ዕምነት ውስጥ የፖለቲካ ዝናር የታጠቁ፣ ምንደኛ ቃየላዊያን የሰው ልጅ ነጻነት፣ ወደማይፈቅደው የጨለማ ጎዳና ቢያንገላቱትም የራሳቸው የክህደት ፈጠራ እንዳነገቡ ወደ ጥልቁ ወውረዳቸው የማይቀርና በጨለማ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብርሃን የሚያይበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
መሰሪዎቹና የመለያየትና የተንኮል ትምህት ተባባሪዎቻቸውም በንቀትና በማጣጣል “ጨርቅ” ያሏት የጥቁር ሕብቦች የነጻነት ምልክት የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ/ ባንዲራ (አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ) የፍርዷ ቀን ደርሶ በአቶ መለስ ዜናዊና በግብረአበቻቸው ላይ ያ “ወራዳ” ያሉት ሕዝብ የነጻነቱን የጩኽት ድምጽ በዓለም አደባባይ ወራዳነታቸውን አንገታቸውም በመድፋት ራሳቸው አቶ መለስ ዜናዊ ያረጋገጡት እውነታ ነው። ይህንን ይመልከቱ። http://www.youtube.com/watch?v=hUVsq-FDFRE&feature=relmfu
ስለሆነም የኢትዮጵያን የነጻነት እሳት ለመገደብም ሆነ ለማጣጣል የሚዳዱ ቢኖሩ “በቃኝ “ ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ሊያደርግ እንደሚችል የረዥም ዘመናት ታሪኩን ያልተገነዘቡ አሊያም በክህደት የቆሙ ብቻ ናቸው። ይህ በምድረ አሜሪካ በአምባገነኖች ላይ ያስተጋባው የኢትዮጵያ ነጻነት (Freedom) ጩኽት ድምጽ በቅብብሎሽ በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም በሌሎችም የዓለም አገሮች ማስተጋባቱን ቀጥሏል። (እግዚያብሔር ይመስገን)። በመሆኑም ከዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ጩኽት ድምጽ ቅብብሎሽ ተቃራኒ የሆነ አሰራር ይዞ ኢትዮጵያን ልምራ ወይንም ለኢትዮጵያ አውቅላታለሁ የሚል ማናቸውም ቡድን ከጠላት እንጅ ከወዳጅ እንዳልሆነ ሁሉም አገር ወዳድ ልብ ሊለው ይገባል።
የዚህ የነጻነት ጩኽት ቅብብሎሽ በሁሉም መስክ ለኢትዮጵያ ነጻነት በሚጠሩ ማንኛውም ህዝባዊና ሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንቶችና ሰልፎች ወይም ስብስቦች ላይ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ ላይ፣ በአንድ ጥላ ስር የማያሰባስብና የማያሳትፍ፣ እንቅስቃሴና ጥሪ ውጤት አልባ ከመሆኑም በላይ በአገሪቱ ላይ እንደ አልቅት ተጣብቆ ደሟን የሚመጠውን የመለስን አገዛዝ ዕድሜ ማራዘምም ነው የሚሆነው። የአቶ መለስ አምባገነን አገዛዝ የኢትዮጵያዊነትን ብሔራዊ ስሜትና ራዕይ ከትውልድ ጭንቅላት ሰርዞ ሊቆራርጡንና ሊያቆራርጡን ቢዳክሩም ኢትዮጵያዊያን የአንድ እናት ልጆች መሆናችንን ሊገቱት ከቶ አልቻሉም።ይልቁንም ኢትዮጵያ ወይም ነጻነት ብለን አንገታቸውን አስደፍተናቸዋል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ጩኽት ድምጽ ቅብብሎሽ እንደ ሰደድ እሳት በሁሉም ቦታና ጊዜ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ይቀጥላል።
ሀቁን ተረድተው ጥፋቱን ከማረም ይልቅ እርስበርስ እንድንለያይና እንድንበላላ፣ እንድንገዳደልና እንዳንተማመን የሚያደርጉንና የፈጠሩትን ፖሊሲ ለራሳቸው ለአቶ መለስና ለአገዛዛቸው አከናንበን የኢትዮጵያዊ የፍቅር አንድነታችንን የበለጠ ገንብተን በክብር ለማለፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በማናቸውም መስክ ድምጹን እንዲያሰማ በሚደረገው ተግባራዊ ውጤታማ ሥራ በጨለማ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ብርሃን ያያል።
ከመሬት የኢትዮጵያ ህዝብ ንቅናቄ
መለስ ዜናዊን የሚያወግዝ ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ተካሄደ
ለባዕዳን በተላላኪነት የሚያገለግለው አምባገነኑና ፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ በዛሬው ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደበት። ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥው በሮናልድ ሬገን ዓለም ዓቀፍ የንግድ ማዕከል ህንጻ ፊት ለፊት በመገኘት መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ በመፈጸም ላይ የሚገኘውን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ፣ የዲሞክራሲያዊ መብቶች አፈና እንዲሁም የአገሪቱን ለም መሬቶች ዜጎችን በጉልበት በማፈናቀል ለውጭ አገር ባለሃብቶች መቸብቸብን በከፍተኛ ስሜትና ቁጭት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። በዚህ ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ላይ የኢትዮጵያን ይዘዋቸው ከነበሩት መፈክሮችና መልዕክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
በዚህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ መነሳሳትና የአንድነት ስሜት የተጠናከረና ህዝናባዊ ቁጣ የተላበሰ ትዕይንተ ሕዝብ ላይ ኢትዮጵያዊያን፤ ሙስሊም- ክርስቲያን፣ ወንድ- ሴት፣ ትልቅ-ትንሽ፣ ሳይሉ የሁሉም የአገሪቷ ዜጎች ተሳትፈውበታል። ሰልፉ የተካሄደው በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በሚገኘት በርካታ የፌዴራሉ መንግስት ፣ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ፣ የኮርፖሬት ቢሮዎችና ሌሎችም መስሪያ ቤቶች በሚገኙበት መንገድ ላይ በመሆኑና በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተመልካቾችን ቀልብ የሳበ እንደነበረ ታውቋል።በመንገድ ላይ ለሚጓጓዙት እግረኞች የተዘጋጁ ጽሁፎች የታደሉ ከመሆኑም በላይ በርካታ አማሪካዊያንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የመለስ ዜናዊን በደም የተጨማለቀ አስከፊ አገዛዝ ማንነትን እንዲገነዘቡ አስችሏቸዋል።
ከዚህም ሌላ በሰለሞን ቅንድቡ (ሰለሞን ተካልኝ) አሸርጋጅነት በጣት የሚቆጠሩ የህወሃት ጥቅመኞች የዲሲ ፖሊስ ከህዝብ ዕይታ ደብቆ በሰጣቸው ስርቻ ውስጥ ሲንጫጩና ሲያላዝኑ እንደነበር ታውቋል። በተለይ ከሃዲው ሰለሞን ቅንድቡ ከተቃዋሚነት ወደ መለስ አወዳሽነት በመቀየር “ከሰውነት ወደ ውሻነት ተለውጦ በበላበት የሚጮህ ውሻ ሆነ” እያሉ አንዳንድ ተሰላፊዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል። በመጨረሻም ሰልፈኛው በነገው ዕለት በካምፕ ዴቪድ፣ ሜሪላንድ በተጠናከረ ሁኔታ ተመሳሳይ ተቃውሞ ለማሰማት ቀጠሮ ይዞ ወደየመጣበት ሂዷል።
መለስን ለቀቅ ኢትዮጵያን ጠበቅ፡፡ኢትዮጵያን ጠበቅ
ከብሥራት ደረሰ – አዲስ አበባ
ከጦቢያ መጽሔት ቅጽ 10፣ ቁጥር 11/1995 ከገጽ 25 የተወሰደ
አምላኬሰውሥራ
ለወገኑ አሳቢ አገሩን የሚወድ፤
እባክህ አምላኬ ኢትዮጵያ ሰው ትውለድ፡፡
ቁጣህን አብርደው አንጀትህ ይራራ፤
ማህጸኗን ባርከህ እባክህ ሰው ሥራ፡፡
አርግዞ ለመውለድ ዘጠኝ ወር ይረዝማል፤
የዕድገቱም ሂደት በእጅጉ ይርቃል፡፡
ታምርህ ይገለጽ ኢትዮጵያ ሰው ትውለድ፤
ሳይማር ያወቀ ሳይድህ የሚራመድ፤
ስቃይ መከራዋን ፈጥኖ የሚያስወግድ፡፡
መስሚያ ጆሮ ያለው የሕዝቧን እሮሮ፤
አሽንቀጥሮ እሚጥል ጠላቷን ወርውሮ፡፡
አንገቱ የማይዞር መለስ ብሎ እማያይ፤
ማህጸኗን ባርከው ለዳግመኛ እንዳታይ፡፡
የጭቃ እሾህ ደምሳሽ ጀግና ባለፈረስ፤
ሰው ፍጠር አምላኬ ለዛሬ የሚደርስ፡፡
የጠባውን ጡቷን ጨክኖ በመንከስ፤
ድንበሯን በማጠር ከኤርትራ መለስ፤
በጎሣ ከፋፍሎ ዜጎቿን የሚያምስ፤
ማየት አትፈልግም ኢትዮጵያ መሯታል፤
ይህን እሚያውቅላት ሰው ያስፈልጋታል፡፡
ዐይኗ ሊጠፋ ነው ዘወትር በማልቀስ፤
አምላኬ ሰው ፍጠር ዕንባዋን የሚያብስ፡፡
አምላክ ወይ ጥበብህን እባክህ ግለጠው፤
ማለዳ ሰው ሠርተህ ለቀትር አድርሰው፡፡
“ጀግና የወጣበት ዘመኑ እኮ ርቋል፤
አርጅቶ ገርጅፎ ማህጸኗም ደርቋል፡፡”
ተብሎ ሲወራ በጅጉ ታዝናለች፤
ባርከው ማህጸኗን ቆራጥ ሰው ናፍቃለች፡፡
ዘጠኝ ወር ሩቅ ነው እንደዘጠና ዓመት፤
ጭራሽ ፋይዳም የለው “ወፌ ቆመች” ማለት፡፡
አምላኬ ሰው ሥራ ዛሬ እሚታደጋት፡፡
የኢትዮጵያን ሪቪው ርዕሰ አንቀጽ
ቀዳሚው ትውልድ “አፍንጫን ሲመቱት ዓይን ያለቅሳል” ይላል። ይህ ስነ-ቃል ብሃራዊ ስንቅ ሲሆን በአንድ ኣካባቢ ያለ ኢትዮጵያዊ አካል ሲነካ በሌላው በኩል ያለው ወገን ያማል! ብሎ እንዲነሳ ይነሽጣል።
ብዙሃዊት ሃገር ኢትዮጵያ በአራቱም ማእዘናት ያሉት ልጆችዋ ለጋራ ፍትህና እድገት ካልቆሙ ሁልጊዜም እንዲሁ እንዳነከሰች ትኖራለች። ባንድ ጎራ ያለው ባህላዊ ቡድን በባህሉ ወይም በሃይማኖቱ ጥቃት ሲደርስበት ዘራፍ! አፍንጫን ሲነኩት አይን ያለቅሳል ብሎ በሌላው የሃገሪቱ ክፍል ያለው ወገኑ ካልተነሳ የአንድነት ወዙ የቱ ጋር ነው? ኣንድነት ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ወገን እና ሃይማኖት እየለየ ጥቃት ሲፈጸም ሌላው ወገን ለወገን ደራሽ ወገንነቱን በተግባር ሲያሳይ አይደለምን?
ዛሬ የብዙሃዊት ኢትዮጵያ ባህላዊ ቡድኖች አንዴ በባህላዊ ቡድናቸው አንዴ በሃይማኖታቸው ጥቃት ሲደርስባቸው ይታያል። ለአብነት በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ማፈናቀል እንዲሁም በአማራና በአፋር ወንድሞቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃትና በእስልምና ተከታዮችና ዘንድ እየደረሰ ያለው የመንግስት ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በገዳማትና በክርስትና ሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚፈጸመው ግፍ ይጠቀሳሉ።
እነዚህ የባህል ቡድንንና ሃይማኖትን እየለዩና እያነጣጠሩ የሚፈጸሙ ግፎች የኢትዮጵያዊያንን የአንድነት መንፈስ ሊፈትኑ የመጡ ታሪካዊ ክስተቶች ናቸው። በመሆኑም እስልምናው ሲነካ ክርስቲያኑ ፣ ክርስቲያኑ ሲነካ ሙስሊሙ፣ ጋምቤላውና አፋሩ ሲነካ ሌላው ኢትዮጵያዊ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ብድግ ሊል ይገባዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን ግፎችን በትዕግስት በስሎ ጊዜና ሰዓት ለሚጠብቀው ታላቁ ህዝባዊ ንቅናቄ የመነሻ አደባባይ ሊያደርጋቸውና ለሃያ ዓመት የተሸከመውን ትከሻውን ያጎበጠውን ብልሹ አስተዳደር አስፈንጥሮ የሚጥልበትን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የሚያቀጣጥልበት አውድ አድርጎ ሊጠቀምባቸው ይገባል እንላለን።
ድል ለኢትዮጵያችን!!
በእግዚያብሔር ህግ ላይ ድርድር የለም
“………..እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥ ……..” የይሁዳ መልዕክት 1፡12
ሰሞኑን ከእምነቱ ተከታዮች እውቅናና ውክልና ውጭ ለወያኔ ባደሩ “አስታራቂ” ተብየዎች አማካይነት በሚስጢር ፊኒክስ ውስጥ በህጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ሲኖዶስና በህገውጡ የአባ ገብረመድህን “ሲኖዶስ” መካካል ሲካሄድ የነበረው ውይይት ለወያኔ በሚያመች ሁኔታ መደምደሙን ከስፍራው የሚናኙ ወሬዎች ያመለክታሉ። ከሁሉም በላይ የእግዚያብሔር ህግ እንደ ዓለማዊ ህግ በፖለቲካ ድርድርና ሰጥቶ መቀበል እንዲሁም “በእከከኝ ልከክልህ” የሚለወጥና የሚሻር ነገር እንዳልሆነ እየታወቀና “ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም” የሚለውን የወንጌል ቃል ደፍጥጠው በቤተክርስቲያኒቷ ታሪክ እንደ አርዮስ ክህደት የሚቆጠር ከፍተኛ ክህደትና ደባ ፈጽመዋል። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ህግንና ቀኖና ጥሰው በነፍጥ አንጋቾች መንበረ ፓትርያርኩ ላይ የተቆናጠጡት አባ ገብረመድህን ወርደው ንስሃ ይግቡ፣ ትክክለኛው ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው ይመለሱ በማለት ፋንታ የተጭበረበር የፖለቲካ ውሳኔ ማሳለፋቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤተክርስቲናኒቷን አማኞች እንደሚያበሳጭ ይታወቃል።
በአገራችን የተጣላ ሰው ለማስታረቅ እንደምሳሌ ሲነገር የኖረ ብሂልን እዚህ ላይ ማቅረብ ይጠቅማል። ይኽውም አንደ ሰው ሌላው ሰው በድሎት፣ ጎድቶት፣ ገንዘቡን ቀምቶት ከኖረ በኋላ በዳይ ለመታረቅ ቢፈልግ በመጀመሪያ ማድረግ ያለበት የቀማውን ገንዘብ መመለስ፤ ከዚያም ይቅርታ መጠየቅ በመጨረሻም መካስ ናቸው። አባ ገብረመድህን የቀሙትን መንበረ ፓትርያርክነት ሳይመልሱ ምን አይነት እርቅ ነው ሊደረግ የሚችለው? አታራቂዎችስህ ይህ ተራ ጸብ አለመሆኑን እያወቁና የእግዚያብሔር ህግ መጣሱን እየተመለከቱ አለማዊና ፖለቲካዊ መርዛቸውን ለምንድን ነው በየኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ላይ ለመርጨት የሚፈልጉት? በእግዚያብሔር ህግ ላይ ድርድር የለም። ወንጌሉ የሚያስተምረን “ እውነቱን እውነት በሉ፤ ሀሰቱንም ሀሰት በሉ” ነው። እርቅና ሰላም የቤተክርስቲያናችን የማዕዘን እራስ ናቸው። እርቅና ሰለም ግን እውነቱን ይዞ፣ ፈሪሃ እግዚያብሔርን ተመልክቶ እንጅ መካሄድ ያለበት በስልጣን ላይ ያለውን ለማስደሰት የሚደረግ ግን ቤተክርስቲያኒቷን በእጅጉ የሚጎዳና የህዝበ ክርስቲያኑን እምነት የሚያቀጭጭና የሚያጨልም ነው። በቅርቡ በዚህ ርዕስ ላይተጨማሪ ዘገባ ይቀርባል።
የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ኦክቶበር 8 ቀን 2011 አርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ ውስጥ በሚገኘው የመናፈሻና የስፖርት መስክ ላይ ያዘጋጀው የቤተሰብ የሽርሽር ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ። በዚሁ ዝግጅት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ከነልጆቻቸው የተገኙ ሲሆን የመናፈሻ ቦታው በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆ ታዳሚዎችም በተለያዩ የኢትዮጵያ የአገር ባህል አልባሳትን ተጎናጽፈው አምረውና አጊጠው ተገኝተዋል። በዝግጅቱ ላይ የተሟላ የኢትዮጵያ ምግቦችና የፍም ጥብስ የተስተናገደ ሲሆን በተለይም ለልጆች ልዩ ምሳ ቀርቦላቸው የነበረ ከመሆኑም ባላይ ልጆች እርስ በርሳቸው ሲጫወቱና ሲቦርቁ ውለዋል።ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ የቡና ሥርዓት ተካዷል። በዝግጁ ላይ በርካታ የኢትዮጵያ የንግድ ድርጅቶችና ምግብ ቤቶች አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ኢትዮጵያን ሪቪው “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አምባገነን አገዛዝ ማስወገድና መተካት” በሚል ርዕስ ልዩ ህዝባዊ ስብሰባ በዋሽንግተን ከተማ ውስጥ ቅዳሜ, ሴፕተምበር 3, 2011 አዘጋጅቷል። ስብሰባው የመለስ ዜናዊ አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ በምን መንገድ ስለሚወገድበትና በማንስ ስለሚተካበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ይሰጣል። በስብሰባው ላይ ንግግር የሚያደርጉ እንግዶች የስም ዝርዝር በቅርቡ ይፋ ይደረጋል።
ቀን፤ ሴፕተምበር 3, 2011
ቦታ፤ ዋሽንግተን ኢቲካል ሶሳይቲ
አድራሻ፤ 7750 16th Street N.W. Washington D.C. 20012
ሰዓት፤ 5:30 PM
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
Email: ethrev@gmail.com
ስልክ ቁጥር፤ 703-824-4821
በዚህ ዓመት አንጋፋው ኢትዮጵያን ሪቪው የተመሠረተበትን 20ኛ ዓመት በድምቀት ለማክበር በርካታ ተግባሮችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያን ሪቪውን ያለፈውን አኩሪ ታሪክና የወደፊቱን ብሩህ ዕድል የምናሳይበት የተለያዩ ዝግጅቶችን እናቀርባለን።
ኢትዮጵያን ሪቪው ግልጽ ዓላማና ተልዕኮ አለው። በመጀመሪያና በግምባር ቀደምትነት የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚያደርገውን ተጋድሎ የተቀደሰ ዓላማ ያለው መሆኑን ይቀበላል፣ ያከብራል። ኢትዮጵያን ሪቪው ካለፉት 20 ዓመቶች አንስንቶ ሲያደርግ እንደነበረው ለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ሙሉ ድጋፉን በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥልበታል። ለወደፊቱም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዱ መረጃዎችን በማቅረብ የበኩሉን አስተዋጽኦ በትጋትና በንቃት ያበረክታል። “መረጃ ኃይል ነው!” “ህዝብ የማወቅ መብት አለው!” የሚሉ መሪ ቃሎችን አንግቦ ህዝባዊና አገራዊ አገልግሎቱን ይቀጥልበታል። የኢትዮጵያ ህዝብም ከወያኔ አፋኝ አገዛዝ የሚላቀቅበት ጊዜ ቅርብ መሆኑንም በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያን ሪቪው ለመግለጽ ይወዳል።
እዚህ ደረጃ ልንደርስ የቻልነው በአንባቢዎቻችንና በደጋፊዎቻችን ያልተዛነፈ ፍቅርና ድጋፍ እንዲሁም በትጉህ ሰራተኞቻችን የቀንና የሌሊት ሥራ ነው።
የኢትዮጵያን ሪቪው የ 20 ዓመቶች አገልግሎት በልዩ ሥርዓት ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ቅዳሜ July 2, 2011 (እአአ) ስለምናከብር እርስዎ እንዲገኙልን በአክብሮት ጋብዘንዎታል።
ቦታ፤ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኤቲካል ሶሳይቲ
አድራሻ፤ 7750 16th Street NW, Washington DC 20012
የትኬት ዋጋ፤ $50 (ትኬት ከድረ ገጽ ላይ መግዛት ይቻላል። እባክዎ እዚህ ላይ ይጫኑ)
|
|
በዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በሚካሄደው ክብረ በዓል ላይ ለመሳተፍ የማትችሉ ደጋፊዎቻችን፣ ትኬቱን በመግዛት ኢትዮጵያን ሪቪው ለወደፊቱ ላቀዳቸው ተግባሮች ማከናወኛ የሚሆን አስተዋጾ በማበርከት ተሳተፉ።
በወያኔ አፋኝ አገዛዝ ላይ የሚደረገው ብሔራዊ የአርነት ትግል ወሳኝ ደርጃ ላይ ደርሷል
ከግንቦት 20 ቀን 1983 ዓም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለ20 ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ አስከፊ የሆነ አፋኝ አገዛዝ በመጫን፤ በአገሪቷ ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ንጽሃን ዜጎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ በግፍ በመጨፍጨፍ፣ በእስር ቤት በማማቀቅ፣ ለስደት በመዳረግ፣ ንብረታቸውን በመዝረፍ፣ በማንገላታት፣ በማዋከብ እንዲሁም በርካታ ሰቆቃዎችን በመፈጸም ላይ የሚገኘው የወያኔ አገዛዝ ተገርስሶ የሚወድቅበት ጊዜ እውን እየሆነ በመምጣት ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሰሞኑን አምባገነን ገዥዋን ከሥልጣን መንግላ ካባረረችው ከቱኒዚያ ውስጥ ከነበረው ሁኔታ እንዲሁም ግብጽ ውስጥ ከሚገኘው ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ የከፋና የመረረ እንደሆነ በገሃድ የሚታይ ነው። በእነዚህና በሌሎችም በርካታ የአፍሪካና የመካከለኛ ምሥራቅ አገሮች ውስጥ የሚገኙት አገዛዞች የተለመዱ ወይም ተራ አምባገነኖች በመሆናቸው ማንኛውም አምባገነንና ፋላጭ ቆራጭ አገዛዞች የሚፈጽሙትን ግፍና በደል በህዝባቸው ላይ ይፈጽማሉ። ወያኔ ግን ተራ አምባገነን ሳይሆን በቅኝ ገዥነትና በጠላትነት የተቀመጠ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱን ህዝብ በጎሳ በመሸንሸን የጎሳ አፓርታይድ አገዛዝ በአገሪቷ ላይ በመጫን በአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች አንጋችነትና ቀላቢነት ለመንበረ ሥልጣን የበቃ በመሆኑም ጭምር ነው። ይህም ነው የኢትይጵያ ህዝብን ትግል ጣምራ ትግል እንዲሆን የሚያስገድደው። ቀዳሚው ትግል ቅኝ ገዥውን ወያኔን ከሥልጣን ሰገነት ላይ አውርዶ ማንኮታኮት ሲሆን ተከታዩ ደግሞ፣ ለሁሉም ዜጎች የሚሆን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማቋቋም ነው።
ወያኔ በዕለት ዕለት ተግባሩ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ እንዳስመሰከረው አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ ብቻ ሳይሆን የአገሪቷና የህዝቧ ጠላትም ጭምር ነው። በዚህም ምክንያት ነው ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትንንቅ ከአንድ ተራ አምባገነን አገዛዝ ጋር የሚደረግ ዲሞክራሲ የማስፈን ትግል ሳይሆን የብሔራዊ የአርነትና የነጻነት ትግልና የተቀደሰ ዓላማ ያለው ታላቅ ተግባር ነው። ወያኔ የህይወት መስዋዕትነትን በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ለረዥም ዘመናት የከፈሉላትን አገር በወረራ በመያዝ የባርነትና የአፋኝ አገዛዙን በመጫን፤ እንዲሁም ለዘመናት በትደረጉ ጥረቶች የተገነቡትን በሕዝቦች መካከል የዳበሩትን መስተጋብሮች ገዝግዞ ለመበጠስ ያልፈነቀለው ድንጋይ አይገኝም። ወያኔ የገሪቱን ብሔራዊ ሰራዊት በመበተን፣ መንገዶችን ህንጻዎችንና ድልድዮችን በማውደም የአገሪቱን አንጡራ ሃብት የሆኑትን ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ባንኮች፣ የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶችንና ሌሎችንም የአገር ንብረቶችንና ቅርሶችን በመዝረፍ በጠላትነት አገሪቷን ረግጦና አፍኖ በመግዛት ላይ ይገኛል። ይህ አፋኝ ሥርዓት የኢትዮጵያን ህዝብ ከዓለም በመጨረሻው ተርታ በማሰለፍ የመረጃ አቅርቦት እንዳይኖረው ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚተላለፉ የሬዲዮና የቴሌቬዝን አገልግሎቶችን በማፈን፣ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመዝጋት ህዝቡን በኢኮኖሚ አድቅቆ፣ በሥነልቡና አደንዝዞና አሰቃይቶ በመግዛት ላይ ይገኛል።እንዲሁም የአገሪቱን ብርቅዬና ለም መሬቶችን ለባዕዳን በርካሽ በመቸብቸብ የማይጠረቃውን የገንዘብ አኮፋዳውን በመሙላት ላይ ይገኛል።
ሆኖም በተለያየ ጊዜ እደተዘገበው ወያኔ በሕዝብ የተጠላና የተወገዘ በመሆኑ በጣት ከሚቆጠሩት ጥቅም ተጋሪዎችና ፍርፋሬ ለቃሚዎች በስተቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ በ1997 ዓም ብሔራዊ ምርጫ ለዓለም እንዳሳየው ከጫንቃው ላይ አውርዶ ጥሎታል። ወያኔ በሥልጣን ኮርቻ ላይ ተንፈናጦ ለመቆየት የቻለው በባዕዳን እርጥባና አይዞህ ባይነት እንጅ በሌላ ምክንያት ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝህ ከዳር እስከ ዳር በመንቀሳቀስ ለአገሩ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም እርምጃ መውሰድ የሚገባው ታሪካዊ ወቅት ላይ ደርሷል። ከዛሬ 21 ዓመታት ገደማ በፊት የምሥራቅ አውሮፓ ሕዝቦች ለዘመናት ተንሰራፍቶባቸው የነበሩትን አምባገነንሥርዓቶች አንኮታኩተው በምትካቸው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶችን ለመመስረት ችለዋል። ዘንድሮም ይህ የለውጥ ብርሃን በሰሜን አፍሪካ አገሮች ብቻ ሳይወሰን ወደ እኛይቱም ኢትዮጵያ እንደሚፈነጥቅ ሳይታለም የተፈታ ነው። ለሁሉም ጊዜ አለውና!
የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አለእፍረትና አለይሉኝታ በውጭ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ በኢንቨስትመንት ሽፋን ገንዘቡን አምታቶ ለመሞጭለፍና እያባነናቸው የሚገኘው ህዝባዊ አመጽ የመነሳት ስጋት የህዝብን ትኩረት ለማስቀየር ህወሃቶች በትናንትናው ዕለት በብርሃነ ገብረክርስቶስ የሚመራ ልዑክ በዋሽንግተን ከተማ በመላክ የጠሩት ስብሰባ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ተቃውሞ ምክንያት ተሰርዟል። የልዑካኑ ቡድን ለማጭበርበሪያ “የትምህርት ሚኒስቴር” ተብዬው በተላላኪውና በተለጣፊው ደመቀ መኮንን እንደሚመራ ቢገለጽም ዋናው የስብሰባው መሪና የበላይ ተቆጣጣሪው ከወያኔ መስራቾች አንዱ የሆነው ቀንደኛው የመለስ አንጋች ብርሃነ ገብረክርስቶስ እንደሆነ ይታወቃል። በትናንትናው ዕለት በግላጭ እንደታየው ደመቀ መኮንን ንግግር በማድረግ ላይ እንዳለና ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በሚሞክርበት ጊዜ ብርሃነ ገብረክርስቶስ በሁኔታው ስላልተደሰተና ሽንፈቱን መቀበል ስላቃተው የድምጽ ማጉያ ከእጁ በመመንጨቅ፣ ደመቀን እንዳዋረደው በገሃድ ታይቷል። ለነገሩ ወያኔዎች የደመቀን አይነት ለሆዳቸው ያደሩ ሰዎችን ስለማያከብሯቸው እንደውሻ ነው የሚያዩዋቸው። ውሻ ስራው ከበር መጮህ ሲሆን እልፍኝ ልግባ ቢል በእርግጫ እንደሚመታና እንደሚባረር ብርሃነ ገብረክርስቶስም የህወሃትን የበላይነትን በትናንትናው ዕለት ደመቀን በማዋረድና ስዕብናውን በመንካት ህዝብ ፊት አብክቶታል። ሌላው ካድሬ ረደዋን አብደላም አንዳችም ቃል ሳይተነፍስ እንደተለጎመ የጋማ ካብት ልፍለፋና ቅጥፈት የለመደውን ምላሱን በአፉ አጣብቆ ወደመጣበት አቅንቷል።
ብርሃነ ገብረክርስቶስም የዋሽንግተን አምባሳደርነትን እንደእርስት ለብዙ ዓመታት ይዞ ከፍተኛ የኢትዮጵያን ሃብት ሲዘርፍና ለመለስ ዜናዊ የተለያዩ ንብረቶችን ሲያከማችና ከፍተኛ የሃገሪቷን የውጭ ምንዛሪ በመስረቅ የመለስን የውጭ ባንክ ሃሳብ ሲያደልብ ቆይቶ ለተመሳሳይ ዘረፋ ወደ ብራሰልስ ተዛውሮ እንደነበር አይዘነጋም። አሁን ደግሞ በቅርቡ የውሸት ሥልጣን ይዞ ላይ ታች ለሚለው ለሆዳሙ ኃይለማርያም ደሳለኝ አለቃ ሆኖ፤ ነገር ግን ለማጭበርበሪያ በምክትልነት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ እንደተመደበ ይታወቃል።ትናንትና ግን ብርሃነን ቀልብ እርቆት ጭር እንዳለች ዶሮ ሲቁለጨለጭና ሲገለማመጥ የተመለከቱ አንዳንድ ሰዎች “አጠገቡ በመሆን ከውሲባዊ ፍላጎቱ አንስቶ ሁሉን ስራ ስትሰራለት የነበረችው ሰሎሜ ታደሰ አጠገቡ ስለሌለች ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። እነዚሁ ሰዎች እንደተናገሩት የብርሃነ ከሰሎሜ ጋር መዳራት የኢትዮጵያን ህዝብ 5 ሚሊዮን ዶላር አስከፍሏል። የብርሃነ ገብረክርስቶስ የቀድሞ ሚስት ከዛሬ 12 ና 13 ዓመታት ገደማ በፊት ብርሃነን በዝሙት ጉዳይ ክስ መስርታበት ስለረታችው፣ ካሳ እንዲሆናት 5 ሚሊዮን ብር እንደተፈረደላት ይታወቃል። ይህንንም ገንዘብ አፍንጫውን እየተያዘ ግብር የሚያስከፍሉት የኢትዮጵያ ህዝብ ከጉሪሮሮው ነጥሎ ከፍሎታል።
በዚሁ ስብሰባ ላይ በአምባሳደርነት የተቀመጠው የተለጣፊው የኦ.ፒ.ዲ.ዮ. አመራር አባል የሆነው የስሙላ አምባሳደር ግርማ ብሩ ይሁን እንጅ፣ እውነተኛ ሥልጣን ያለው በዋሃደ በላይ ዕጅ እንደሆነ የታወቀ ነው። እንደ ግርማ ብሩ ያሉት ሆዳሞች ደግሞ ሌላ ተስፈኛ ሆዳም ማስከተላቸው ስለማይቀር እርሱም እንዳቅሙ በቅርቡ በወዶ ገብነት የኦሮምን ህዝብ ለወያኔ ሸጦ ፍርፋሪ ስልጣን ፍለጋ በስተርጅና የሚጎናበሰውን ንጉሴ ቢራቱን “የኮሚኒቲ ተወካይ” በሚል የውሸት ታፔላ ለጥፎበት በስብሰባው ላይ አፉን እንዲከፍት አድርጎታል። ንጉሴ ቢራቱ በደረሰበት የግል የኢኮኖሚ ቀውስ በተለይም ገዝቶት የነበረው ቤት ዋጋው ወድቆ የሚከፍለው ስላጣ የዋሽንግተንን የኦሮሞ ማህበረሰብ ገንዘብ መንትፎ ቢወሰድም ሊበቃው ስላልቻለና በታክሲ ስራም “ሌቦች ሊዘርፉኝ” ይችላሉ እያለ በፍርሃት ስለሚንቀጠቀጥና በአግባቡ ስለማይሰራ የረባ ገቢ ስላላገኘ ወደወያኔ ኢምባሲ መልከስከስ ከጀመረ ጥቂት አመታት እየተቆጠሩ ነው። ነገር ነገርን ያነሳዋል እንደሚባለው ቅሌታሙ ንጉሴ ቢራቱ በዘመነ ደርግ ቀንደኛ ካድሬ በመሆን ብዙ ወንጀል የፈጸመና የኢ.ሰ.ፓ.አ.ኮ. አባል በመሆን በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ምክትል ዳይሬክተርነት ከተሾመ በኋላ፣ በወቅቱ ቀንደኛ ካድሬዎች ወደሚላኩበት የኮሚኒስት አገር ወደ ቡልጋሪያ ለትምህርት ተልኮ ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ ወደአሜሪካን አገር በመምጣት “እኔ ኦሮሞ ነኝ፣ ጭቁን ነኝ” በማለት ብዙ ሰዎችን በማታለል የኦሮሞ ኮሚኒቲ በዋሽንግተን ዲሲ ሊቀመንበር በመሆን ለከፍተኛ ሥልጣን ሲቋምጥ ቆይቶ የነበረ ተዋርዶ አዋራጅ የሆነ ግለሰብ ነው። አሁን ደግም ተግልብጦ ለወያኔ በግምባር ቀደምትነት በወሬ አቀባይነትና አለቅላቂነት ተሰማርቷል። ይህ ወራዳ ግለሰብ ብዙ ጊዜ ካንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ወደ ሌላው ሲገለባበጥ የተመለከቱ ሰዎች “ከመገለባበጥ ብዛት አጥንቱ ተሰባብሮ ስላለቀ ነው ሰውነቱ በስጋ ብዛት ተነርቶ የሚታየው” እያሉ ሲያወሩ ተደምጠዋል።
ህወሃት በጣም ሊገባውና ሊቀበለው ያልቻለው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ በሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጠበት ጊዜ አንስቶ እንደ ውጭ ወራሪ እንጅ እንደ ኢትዮጵያ መንግስት ቆጥሮት አያውቅም። ህወሃት የሚለካውና የሚመዘነው ለአምስት አመታት የአገራችንን ህዝብ ሲያርድና ህዝቧን ሲከፋፍል እንደነበረው እንደ ፋሽስቱ ጣሊያን እንጅ እንደ ኢትዮጵያዊ መንግስት አለመሆኑን ነው። ህወሃትን ከጣሊያን ጋር የሚያመሳስለው ተግባሩ እንጅ፣ የበቀለውማ ከእኛይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበር። ሆኖም በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አንጋችነት ለሥልጣን የበቃ ስለሆነና አሁንም ተጠሪነቱ ለነዚሁ ባዕዳን ስለሆነና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለባዕዳን ሳያሰልስ አሳልፎ በመስጠት ላይ ስላለ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጫንቃው ላይ አውርዶ አንኮታኩቶ ሊጥለው አመቺውን ጊዜ እየጠበቀለት ነው የሚገኘው።
ብርሃነ ገብረክርስቶስ ህሊናው በዶላር ብዛት ስለሰከረ በደንብ ማሰብ ስለተሳነው ነው እንጅ ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ ለበርካታ ጊዜ ስብሰባ ጠርቶ እየተዋረደ የሰረዘበት ጊዜ በርካታ ነው። በትናንትናው ዕለት በሃዋርድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ህወሃቶች አስበው የነበረው “በውጭ የሚገኘው ህዝብ ድጋፍ እየሰጠን ስለሆነ በአገር ውስጥ ያላችሁ ተቃዋሚዎች በውጭ ያሉት ለእናንተ ድጋፍ ስለማይሰጧችሁ አመጽ እንዳታስነሱ” ለማለት ነበር። ለዚህም የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ካሜራ የሚቀርጹ ሰዎችን አስመጥቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ በቴሌቭዥን ለማስተላለፍ ነበር። በዚህ አጋጣሚ ከህወሃት ውጭ ያላችሁ ከዚህ የልዕካን ቡድን ጋር አብራችሁ የመጣችሁ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ጊዜው ሳይመሽባችሁ በስደት ካለው ወገናችሁ ጋር እንድትቀላቀሉና እራሳችሁን ከወያኔ ባርነትና ተፅእኖ ነጻ እንድታውጡ እናሳስባችኋለን። ደመቀ መኮንንና ረደዋን አብደላም ብትሆኑ ያስቀየማችሁትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቃችሁ ይህንን እድል ተጠቅማችሁ ወደ ወገናችሁ ብትቀላቀሉ ይሻላችኋል። ጊዜው ሳያልፍ ከዚህ በመስጠም ላይ ካለ መርከብ ላይ እራሳችሁን ፈጥናችሁ ብታድኑ ይሻላችኋል!!!
በትናንቱ ስብሰባ ላይ ለመገኘት የመጓጓዣና የሆቴል ወጭ ተከፍሎላቸው ከተለያዩ የአሜሪካና የካናዳ ከተሞች የመጡት አመዛኞቹ ሰዎች የህወሃት አባላት መሆናቸውን ተመልክተናል። ስብሰባው እዛው ወያኔ ኢምባሲ አስቀድመው ቢያደርጉት ይሻላቸው ነበር።ህወሃቶች በትናንትናው ዕለት የደረሰባቸውን ከፍተኛ ውርደትና እፍረት እንደለመዱት “በደርግ- ኢሰፓዎችና በሻቢያዎች” ላይ አላከዋል። በጣም የሚገርመው ደገሞ ደርግና ሻቢያ ተዛምደው ወያኔንን ሲቃወሙ? ይህ የወያኔ ውሸት እግር አውጥቶ የሚሮጥ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ወያኔዎች ውርደት ከባድ ነገር ስለሆነ መቀበል ስላቃታቸውና ህሊናቸውን ስለሳቱ የሚናገሩትን ነገር አንኳ ትርጉም ይሰጣል የሚለውን ለማመዛዘን አልቻሉም። በየትኛው ጊዜ ነው ደርግና ሻቢያ አብረው የሰሩት??? ይልቅ የደርግንና የኢሰፓን ስም በማንሳት እንደ አህያ የጫናችሁባቸውን የሚሸከሙትን እነ ንጉሴ ቢራቱን አስታስደንግጡ፣ አታሸማቁ። እነ መለስ ዜናዊና ብርሃነ ገብረክርስቶስ የሻቢያ ቅጥረኛነታቸው የሚያረጋግጥው በትናንቱ ስብሰባ “ባድማ የማነው” ተብሎ ብርሃነ ገብረክርስቶስ ሲጠየቅ ምነው አፉ ተቆለፈ??? በመጨረሻም ወያኔዎች ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሲነሱ አሸምቀውበት በነበረው በደደቢት ዋሻ በሚመሰለው በወያኔ ኢምባሲ ስብሰባውን እንቀጥላለን ብለው በከፍተኛ ውርደት፣ ክስረትና ብስጭት ስብሰባውን እንዲሰርዙ ተገደዋል። በዚሁ ርዕስ ላይ ተጨማሪ መረጃ ሰሞኑንን እናወጣለን። የኢትዮጵያ ህዝብ ድል ቅርብ ነው!!!
የኢህአዴግ የኢንቨስትመንት ጥሪ እና ዘረፋው
የኢህአዴግ ልዑካን የፊታችን ሚያዚያ 10 እና 11/2011 በአሜሪካና አውሮፓ ከተሞች በውጭ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ጋር ለመምከር
እንደሚመጡ በይፋ አስታውቀዋል፤የተልእኮው ዋናው አላማው በሰሜን አፍሪካና በአረቡ ኣላም የቀጠለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ እውን
እንዲሆን ዲያስፖራው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማምከን እንዲሁም ወደሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ በስፋት እንዲፈስ ለማድረግ ያለመ ነው፤
** በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደምም በሀገር ቤት ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል፤ውጤቱ ደግሞ ምን እንደነበር
ወዳጆቻችን እና ጉዋደኞቻችን በከፍተኛ ጥረት ያፈሩትን የውጭ ምንዛሪ በሰበብ አስባቡ ተዘርፈው ሕይወታቸው ሲመሳቀል ታዝበናል::
** እንኩዋን ከውጭ ሀገር የሄደው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ በሀገር ቤት በንግዱ ዓለም ዘመናት ያስቆጠሩ በሰበብ አስባብ እየተገፉ የሀገሪቱ
ኢኮኖሚ በገዢው ፓርቲ ኩባንያዎች እና በጥቂት ሸሪኮቻቸው እጅ ወድቐል፤ ባለሀብቱ በግብር፣በአራጣ ወዘተ እየተሳበበ ወደ ወህኒ እየተነዳ፣
የቀረውም እየኮበለለ ይገኛል፤ጥቂት ማይባሉትም ወደ ድህነት ተገፍተዋል፤ጥቂቶችም ራሳቸውን አጥፍተዋል፤የጌታነህ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ዮሃንስ
ጌታነህና የአሴ ማርብል ባለቤት አቶ አስፋው ይርጋ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ሰለባዎች ናቸው፤
** ነጋዴው በሀገሪቱ በሰፈነው የጉልበት አገዛዝ ስጋት ውስጥ በመውደቁ የህልውናው ዋስትና አድርጎ የወሰደው በስልጣን ላይ ላሉት
ገዢዎች እጅ መንሻ ማቅረብ ነው። ስልጠን ላይ ያለው ቡድን አንድ ግዜ ለምርጫ ዘመቻ፣ሌላ ግዜ ደግሞ ለህንጻ ማሰሪያ በሚል የንግዱን
ሕብረተሰብ እያስገበረ ይገኛል፤ ኢሕአዴግ ለ2002 ምርጫ ብቻ 57 ሚሊዮን ብር ከነጋዴው ሰብስቧል፤በዚህ መልክ ነጋዴውን እያራቆተ
እስካለፈው ጥቅምት ከወጪ ቀሪ 100.3 ሚሊዮን ብር ማከማቸቱን በይፋ አስታውቐል፤
** በሀገሪቱ በሪል ስቴት መስክ ቀዳሚ የሆነው የሃያት ሪል ስቴት ባለቤትን ጨምሮ ቁጥራቸው የበዛ ነጋዴዎች በእስር ቤት ናቸው፤ለእስር
የሚሰጠው ምክንያት ታክስ፣ አራጣ የሚል ቢሆንም ፣በኩባንያዎቻቸው የገዢው መደብ ሰዎችን ባለድርሻ እንዲያደርጉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ
የሚመጣበቸውን ጥሪ ባለማስተናገድ እነደሆነም የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ሰፈር የሚነሳ ጉዳይ ነው፤
** ዲያስፖራው የግል መኖሪያ ቤት እንዲሰራ እየተጠየቀ አንዳንዶች ሄደው መስራት የ ቻሉ ቢሆንም ፣በከተማዋ ዳር ከሰሩት ውጭ
ሌሎቹ ለሰሩት ቤት ዋስትና አጥተው ከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቀዋል፤ቦሌ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኦሎምፒያ አካባቢ ግንባታ ፈቃድ ወስደው
በቅርቡ ተሰርተው የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ የነበሩ ዋጋቸው ከ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ እና የዚምቧቤ ኤምባሲን ጨምሮ የውጭ
መንግስታትና ድርጅቶች የተከራዩዋቸው .ቤቶች እንዲፈርሱ ተወስኖባቸዋል።የተወሰነባቸው። በከተማዋ ዳር የሰሩትም ቢሆኑ ከአቅም በላይ በሆነ
ምክንያት ንብረታቸውን ለመሸጥ ለመለወጥ ቢፈልጉ እንኩዋን 80 በመቶ ሰርተው ካላጠናቀቁ መሸጥ እንዳይችሉ ሕገ መንግስቱ የሰጠው የንበረት
ባለቤትነት መብት ተሽሮ በህግ ታግደዋል፤
** አቶ ስብሃት ነጋ በአደባባይ ለቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ተናግረው እናዳረጋገጡት ዛሬ በኢትዮጵያ ትልቁ ኩባንያ የሕወሃቱ
ኤፈርት ነው፤ርሳቸው በትግሉ ዘመን በሰበሰብነው ሀብት ተነሳን ብለው ቢናገሩም ያለምንም መያዣ 1.7 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ወስደዋል፤ወለዱ ብቻው ወደ 300 ሚሊዮን ብር ሲጠጋ ፋይሉ እንዲዘጋና እንዲጠፋ ተደርጉዋል፤የባንኩ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ገዛሀኝ ይልማ
በ1998 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ራሳቸውን ያጠፉበት ን ሁኔታ የቅርብ ምንጮች ከዚህ የኤፈርት ብድር ጋር ያይዙታል፤ቀደም ሲል ከሀገሪቱ
ባንክ የወሰዱትና ያስቀሩት ገንዘብ አልበቃ ብሎአቸው ዛሬም በተጨማሪ እየወሰዱ ለፓርቲያቸው ሬዲዮ ፋና እና ለዋልታ ኢንፎርሜሽን
ማዕከል ሕንጻ ገንብተዋል፤ሌሎች በርካታ ሕንጻዎችም ደርድረዋል፤ በተከራይ በኩል ያለውን ችግር ለመቅረፍ የመንግስት ተቐማት
የነበሩበትን የመንግስት ቤት እየለቀቁ ወደ እነሱ ሕንጻዎች እንዲገቡ አድርገዋል።
** ዛሬ በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያለው ዕውነታ ከዚህም እጅግ የሰፋ በሙስና የተበከለ፤ ከሀብት እና ችሎታም ባሻገር ታማኝነትንና በይበልጥም
የደም መመዘኛን በዋናነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሕሊናን በመሸጥ እንኩዋን የሀገር ባለድርሻ መሆን አይቻልም፤…በአጠቃላይ ሀገራችን በኢኮኖሚው መስክ ብቻ
ሳይሆን በፖለቲካውም መስክ አፈና የነገሰባት፣የሚሊዮኖች ድምጽ የታፈነባት የጨለማ ምደር ሆናለች ፤ሀገራችንን ጭለማ ውስጥ ከተው፣ሕዝብ
አደህይተው እና አራቁተው የተዘፈዘፉብንን ሸክሞች በህዝባዊ እንቅቃሴ ለመጥረግ የተላኩብንን የጭለማ መልክተኞች በማሳፈር በሀገር ቤት ላለው
ወገናችን ብርታት እንሁነው፤ ዘረኝነት ይብቃ !.አምባገነንነት ይብቃ ! ዘረፋ ይብቃ !.ድንቁርናም ይብቃ !
መልዕክታችን
መልዕክታችን ግልጽ ነው። ፍትህን መናፈቅ፤ በዘረኝነት መንገሸገሽ፤ አምባገነን አገዛዝን አምርሮ መጥላት ጥሩ ነው፤ ግን በቂ አይደለም።
በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ የሚቀይረው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው። እያንዳንዳችን በተቀናጀ መንገድ ትናንሽም ብትሆን ጠጠር
ከወረወርን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክፋትን ከአገራችን ማስወገድ እንችላለ።ለራስዎ፣ ለአገርዎ እና ለወደፊቱ ትውልድ ብሩህ ራዕይ ካለዎት
እና ራዕይዎ ተሳክቶ ማየት የሚፈልጉ ከሆነ የሚከተሉትን ይፈጽሙ።
· የወያኔን የኢንቬስትመንት ግብዣ አይቀበሉ። የህዝብ መብት ባልተከበረበት፤ የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት፤ ዘረኛነት በነገሰበት ሃገር ውስጥ
ራስዎን የገዢው ሎሌ ካላደረጉ በስተቀር በጥረትዎ ያፈሩት ንብረትባለመብት አለመሆንዎን ይወቁ። ሎሌ ከሆኑ ደግሞ ጊዜዓዊ ተጠቃሚ
እንጂ ባለመብት አይደሉም።
· ውጭ አገር የሚኖሩ ከሆነ ለቤተሰቦችዎ ገንዘብ ሲልኩ የወያኔ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ማስታገሻ በማይሆን መንገድ ያድርጉት።
ኦፊሲያላዊመንገዶችንም ሆነ ወያኔ በየአገሩ ያደራጃቸው የገንዘብ ማስተላለፊያዎችንአይጠቀሙ።
· በአገር ቤት የሚገኙትን ወገኖቻችንን መረጃ ለማስራብ ወያኔ የሚያደርገውን የመገናኛ ብዙሃን አፈና ለመበጣጠስ ጥረት የሚያደረጉ
የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በገንዘብዎና በእውቀትዎ ይደግፉ::
· የተደራጀ ትግል ባነሰ ወጪና በአጭር ጊዜ ውጤታማ ያደርጋልና ንቅናቄያችንን ይቀላቀሉ። የእርስዎን ዝግጁነት የሚመጥኑ የአደረጃጀት
መዋቅሮችን፣ የትግል ስልቶችን እና የተሳትፎ ዓይነቶችን አዘጋጅተናል። የእርስዎን አገራዊ ራዕይ የሚያሳካ ሌላ ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ
ድርጅት ካለ ይቀላቀሉት።. ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶችን በገንዘብዎ፣በእውቀትዎና በጊዜዎ ይርዱ።በፀረ-ወያኔ ጎራ የተሰለፉ
ኃይሎች ተባብረው እንዲቆሙ የበኩልዎን ድርሻ ያበርክቱ። የሌሎች ድርጅቶችን ህመምና ስጋት ለመረዳት ጥረት ያድርጉ።አስታራቂ
ይሁኑ።
· ወያኔ እየሸረበልን ባለ የዘርና የሃይማኖት ቅራኔ ውስጥ እንዳንገባ፤በኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባት እንዲሰፍን ተግተው ይስሩ።
በኢትዮጵያዊያን መካከል በዘርና ሃይማኖት ልዩነት ባለማድረግ አርዓያ ይሁኑ።
· ከአሉባልታ ነፅተው የተግባር ሰው ይሁኑ። ፓለቲካችንን ከውሸት፣ ከጭፍን ጥላቻ እና ተራ ወሬዎች ለማንፃት ተግተው ይስሩ። ከወያኔ
ድርጅቶች ጋር ፈጽሞ አይነግዱ። እቃዎቻቸውን አይግዙ፤አገልግሎቶቻቸውን አይጠቀሙ።
· በወያኔ ላይ ያለዎትን ተቃውሞ በተገኘው እድል ሁሉ ተጠቅመው ይግለፁ።ተቃውሞዎን በየበዓሉ፣ በየስብሰባው፣ በሩጫዎች፣ በሌሎች
የስፖርት ዝግጅቶች ወቅት በጩኸት፣ በፉጨት፣ በየበሩና ግርግዳው በብጥስጣሽ ወረቀቶች በመፃፍ ይግለጹ። “ሞት ለዘረኛው ወያኔ!!!
ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!!!” ይሁን መፈክርዎ።
· የህሊና እስረኞችን ይዘክሩ፤ ቤተሶቦቻቸውን ይደግፉ።ራድዮና ጋዜጣን ይከታተሉ፤ ለሌሎችም ያሰራጩ። በማናቸውም መንገድ ወያኔን
የሚጠቅም ተግባር አይፈጽሙ። በመሬት ወይም በገንዘብ አይደለሉ። መለስ እያደለ ያለው መሬት የሱ አያቶች ከጣሊያን ጋር አብረው
ሊያስወስዱት ሲጥሩ የእርስዎ አያቶች ደማቸውን አፍሰው ያሰረከቡን መሆኑን አይርሱ
· የዲፕሎማሲው ትግል አካል ይሁኑ። ሰላማዊ ሰልፍ ይውጡ፤ በረሃብአድማዎች ይሳተፉ።ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔዎችን እኩይ
ተግባራት ከማጋለጥ አይቦዝኑ።ለፓለቲከኞች፣ ለሕዝብ ተወካዮች፣ ለሥራ ባልደረቦችዎ፣ ለክፍል ጓደኞችዎዜግነትን ሳይመርጡ የወያኔን
ዘረኝነት፣ ጨፍጫፊነት፣ ዘራፊነትናአምባገነንነት ያሳውቁ።17. ጠዋት “ዛሬ ለትግሉ የማበረክተው ምንድነው?” ብለው ይጠይቁ፤
ማታጠዋት ያሉዋቸውን ፈጽመው እንደሆነ ራስዎን ይፈትሹ።ዘረኞችና አምባገነኖች ከጫኑብን ዜጋዊና ሃገራዊ ውርደት በአፋጣኝ
መገላገግል የምንችለው እነሱ ሊያዋረዱን አምረውና ተግተው እንደሚሰሩ ሁሉ እኛም አምርረንና ተግተን “አትችሉም! አንፈቅድላችሁም!”
በሚል እልህና ቁጭት በርትተን ስንሰራ ብቻ መሆኑን ፈጽሞ አይዘንጉ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Contact: Ethiopians.say.beka@gmail.com
ዓለም አቀፍ የሲቪክ ንቅናቄ ለለውጥ በኢትዮጵያ ሚያዚያ 2003/April 2011
በወያኔ አፋኝ አገዛዝ ላይ የሚደረገው ብሔራዊ የአርነት ትግል ወሳኝ ደርጃ ላይ ደርሷል
ከግንቦት 20 ቀን 1983 ዓም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለ20 ዓመታት በኢትዮጵያ ላይ አስከፊ የሆነ አፋኝ አገዛዝ በመጫን፤ በአገሪቷ ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ንጽሃን ዜጎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ በግፍ በመጨፍጨፍ፣ በእስር ቤት በማማቀቅ፣ ለስደት በመዳረግ፣ ንብረታቸውን በመዝረፍ፣ በማንገላታት፣ በማዋከብ እንዲሁም በርካታ ሰቆቃዎችን በመፈጸም ላይ የሚገኘው የወያኔ አገዛዝ ተገርስሶ የሚወድቅበት ጊዜ እውን እየሆነ በመምጣት ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሰሞኑን አምባገነን ገዥዋን ከሥልጣን መንግላ ካባረረችው ከቱኒዚያ ውስጥ ከነበረው ሁኔታ እንዲሁም ግብጽ ውስጥ ከሚገኘው ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ የከፋና የመረረ እንደሆነ በገሃድ የሚታይ ነው። በእነዚህና በሌሎችም በርካታ የአፍሪካና የመካከለኛ ምሥራቅ አገሮች ውስጥ የሚገኙት አገዛዞች የተለመዱ ወይም ተራ አምባገነኖች በመሆናቸው ማንኛውም አምባገነንና ፋላጭ ቆራጭ አገዛዞች የሚፈጽሙትን ግፍና በደል በህዝባቸው ላይ ይፈጽማሉ። ወያኔ ግን ተራ አምባገነን ሳይሆን በቅኝ ገዥነትና በጠላትነት የተቀመጠ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱን ህዝብ በጎሳ በመሸንሸን የጎሳ አፓርታይድ አገዛዝ በአገሪቷ ላይ በመጫን በአገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች አንጋችነትና ቀላቢነት ለመንበረ ሥልጣን የበቃ በመሆኑም ጭምር ነው። ይህም ነው የኢትይጵያ ህዝብን ትግል ጣምራ ትግል እንዲሆን የሚያስገድደው። ቀዳሚው ትግል ቅኝ ገዥውን ወያኔን ከሥልጣን ሰገነት ላይ አውርዶ ማንኮታኮት ሲሆን ተከታዩ ደግሞ፣ ለሁሉም ዜጎች የሚሆን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማቋቋም ነው።
ወያኔ በዕለት ዕለት ተግባሩ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ እንዳስመሰከረው አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ ብቻ ሳይሆን የአገሪቷና የህዝቧ ጠላትም ጭምር ነው። በዚህም ምክንያት ነው ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትንንቅ ከአንድ ተራ አምባገነን አገዛዝ ጋር የሚደረግ ዲሞክራሲ የማስፈን ትግል ሳይሆን የብሔራዊ የአርነትና የነጻነት ትግልና የተቀደሰ ዓላማ ያለው ታላቅ ተግባር ነው። ወያኔ የህይወት መስዋዕትነትን በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ለረዥም ዘመናት የከፈሉላትን አገር በወረራ በመያዝ የባርነትና የአፋኝ አገዛዙን በመጫን፤ እንዲሁም ለዘመናት በትደረጉ ጥረቶች የተገነቡትን በሕዝቦች መካከል የዳበሩትን መስተጋብሮች ገዝግዞ ለመበጠስ ያልፈነቀለው ድንጋይ አይገኝም። ወያኔ የገሪቱን ብሔራዊ ሰራዊት በመበተን፣ መንገዶችን ህንጻዎችንና ድልድዮችን በማውደም የአገሪቱን አንጡራ ሃብት የሆኑትን ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ባንኮች፣ የመንግሥትና የግል መሥሪያ ቤቶችንና ሌሎችንም የአገር ንብረቶችንና ቅርሶችን በመዝረፍ በጠላትነት አገሪቷን ረግጦና አፍኖ በመግዛት ላይ ይገኛል። ይህ አፋኝ ሥርዓት የኢትዮጵያን ህዝብ ከዓለም በመጨረሻው ተርታ በማሰለፍ የመረጃ አቅርቦት እንዳይኖረው ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚተላለፉ የሬዲዮና የቴሌቬዝን አገልግሎቶችን በማፈን፣ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመዝጋት ህዝቡን በኢኮኖሚ አድቅቆ፣ በሥነልቡና አደንዝዞና አሰቃይቶ በመግዛት ላይ ይገኛል።እንዲሁም የአገሪቱን ብርቅዬና ለም መሬቶችን ለባዕዳን በርካሽ በመቸብቸብ የማይጠረቃውን የገንዘብ አኮፋዳውን በመሙላት ላይ ይገኛል።
ሆኖም በተለያየ ጊዜ እደተዘገበው ወያኔ በሕዝብ የተጠላና የተወገዘ በመሆኑ በጣት ከሚቆጠሩት ጥቅም ተጋሪዎችና ፍርፋሬ ለቃሚዎች በስተቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ በ1997 ዓም ብሔራዊ ምርጫ ለዓለም እንዳሳየው ከጫንቃው ላይ አውርዶ ጥሎታል። ወያኔ በሥልጣን ኮርቻ ላይ ተንፈናጦ ለመቆየት የቻለው በባዕዳን እርጥባና አይዞህ ባይነት እንጅ በሌላ ምክንያት ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝህ ከዳር እስከ ዳር በመንቀሳቀስ ለአገሩ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ጥቅም እርምጃ መውሰድ የሚገባው ታሪካዊ ወቅት ላይ ደርሷል። ከዛሬ 21 ዓመታት ገደማ በፊት የምሥራቅ አውሮፓ ሕዝቦች ለዘመናት ተንሰራፍቶባቸው የነበሩትን አምባገነንሥርዓቶች አንኮታኩተው በምትካቸው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቶችን ለመመስረት ችለዋል። ዘንድሮም ይህ የለውጥ ብርሃን በሰሜን አፍሪካ አገሮች ብቻ ሳይወሰን ወደ እኛይቱም ኢትዮጵያ እንደሚፈነጥቅ ሳይታለም የተፈታ ነው። ለሁሉም ጊዜ አለውና!