Author Archive

ዱላ መመከት ያቃተው አማራ

Tuesday, May 14th, 2013

ይኸነው አንተሁነኝ

ህወሓት ሀገራችንን በገልበቱ መግዛት ከጀመረበት ግንቦት 1983 ዓ/ም ጀምሮ ለቁጥር የሚያታክቱ ለመስማት የሚያስጨንቁ ብዙ ቁም ስቅሎችን ፈጽሟል። የራሱን የህወሓትን ፓርላማ አንቀጽ 39ን በመመርኮዝ ራስን የመቻል ጥያቄ አቅርባችኋል ወይም ልታቀርቡ አስባችኋል በሚል ሰበብ ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ የስቃይ ዘመናትን አሳልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል

Tuesday, May 14th, 2013

ፍቅር ለይኩን

በቅርቡ ሙስጠፋ አል ላባድ የተባለ ሊባኖሳዊ ፖለቲከኛና ጸሐፊ Egypt is Battling Ethiopia over the Nile Water በሚል ርዕስ አንድ መጽሐፍ አሳትሞ አውጥቷል። ይህን የአል ላባድን መጽሐፍ "አስ ሳፊር" የተባለ የሊባኖስ ዕለታዊውና ተነባቢ የዐረብኛ ጋዜጣ የመጽሐፉን አጭር ዳሰሳ በፊት ለፊት ገጹ ይዞ ወጥቶ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ"ኢሕአዴግ ደጋፊዎች" መልካም እንቅስቃሴ

Tuesday, May 14th, 2013

ግርማ ካሳ

በዳያስፖራ ቀንደኛ የኢሕአዴግ ደጋፊና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች አስተባባሪ የሚባሉት፣ የሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍል ዋና አድሚን፣ አቶ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) ከአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አደመጥኩ። አባ መላ ጠንካራ ትችት በኢሕአዴግ ላይ ሰንዝረዋል። ይሄም ብዙዎችን ሳያስገርም አልቀረም። "አባ መላ፣ አራዳ ነው፤ ወያኔ ሊወድቅ ሲል ፍሬቻ አብሮቶ ታጠፈ" ያሉም አሉ። ፡) ፡) እኔ ግን ብዙ አላስገረመኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተገፊዎች የባህሪ ለውጥ አምጡ እንጂ!

Tuesday, May 14th, 2013

ገለታው ዘለቀ

ልትታተም ካሰበች አንዲት ልቦለድ ጽሁፍ ላይ አንድ የምናብ ሰው ከተገረመበት ነገር ተነስተን አጭር መልእክት ለማቀበል እንሞክራለን። ይህ የምናብ ሰው ወደ አንድ ሃገር ይሄድና በዚያ በአንድ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ ናሽናል ጂኦግራፊ የተሰኘውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያያል። በወቅቱ ይተላለፍ የነበረው ፕሮግራም የዱር እንስሶች ኑሮ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን ለማስወገድ የታሰበ መድረክ ተዘጋጀ

Monday, May 13th, 2013

በ17 ዓመቷ ራሷን ያጠፋችው ወጣት ቤተሰቦች ልምድ ያካፍላሉ!

“በእኔ ቤተሰብ የደረሰ ልብ የሚሰብር ሀዘን በሌሎች ወገኖቼ ላይ ደርሶ ማየት አልፈልግም” (የኤደን ወላጅ አባት)

‘ልጄን እንደ ንግስት ነበር ያሳደኳት፤ የዚህ ሀገር ልጅ ምኑም አይታወቅም”  የኤደን እናት ወ/ሮ በለጡ

ደራሲ ሐምራዊት ተስፋ በውይይቱ ላይ ትናገራለች!

የአማንዳ ቶድ ወላጅ እናት በውይይቱ ተካፋይ ናቸው!

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 5ቀን 2005 .. May 13, 2012)ባለፈው መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በቫንኩቨር ካናዳ ህይወቷን ያጣችው የ17 ዓመት ታዳጊ ወጣት ኤደን ዘውዱ ቤተሰቦች በራሳቸው ቤተሰብ የደረሰ ሀዘን በሌሎች ወገኖች ላይ እንዳይደርስ ለማንቃት ተግተው እንደሚሰሩ አስታወቁ። በኖርዝ አሜሪካ ልጆችን ለማሳደግ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካተተ መጽሐፍ የጻፉት ደራሲ ሐምራዊት ተስፋም ተጋባዥ መሆናቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ ህወሓት ያልከበደው ኢትዮጵያዊ ማነው?

Thursday, May 9th, 2013

ይኸነው አንተሁነኝ

ሌቱ መሽቶ ይነጋል፤ ሳምንታት ወራት ዓመታት በፍጥነት መንጎዳቸውን አላቋረጡም፤ ክረምትና በጋ ይፈራረቃሉ፤ ወቅቶችም ማንም ሳይረብሻቸው ጊዜያቸውን ጠብቀው እያለፉ ነው፤ አፍጣጭ ገላማጭ ያለባቸውም ማዘዣ ጣቢያቸው ከእኛ አይደለምና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሆሳዕና "ማክበር" – በቀራንዮ "መስቀል"

Saturday, May 4th, 2013

ኤፍሬም እሸቴ

ታላቁ የክርስቲያኖች ጾም፣ ዐቢይ ጾም እነሆ የመጨረሻው "ሰሙነ ሕማማት"/ስቅለት ላይ ደረሰ። ለእምነቱ ተከታዮች የአጽዋማት ሁሉ በኩር እና ዋነኛ (ዐቢይ) እንደመሆኑ ከምንም በዓል በላይ በታላቅ መንፈሳዊ ስሜት የሚከበር ነው። የእምነቱ ተከታይ ላልሆነውም ወገን ቢሆን የሚኖረው ባህላዊ አንድምታ ከፍ ያለ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ታሪኩን በደረቅ ንባብ ለሚመለከተውም ቢሆን ከዕለት-ተዕለት ሕይወቱ ጋር ሊያስነጻጽረው የሚችለው ብዙ ቁም ነገር እንደሚያገኝበት ጥርጥር የለኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርጫ የለም እንጂ ምርጫማ ቢኖር …!

Saturday, May 4th, 2013

ፍቅር ለይኩን
የዛሬው ጽሑፌን በምርጫ ዙሪያ ካጋጠመኝ ትንሽ ቆየት ካለ ገጠመኜ ልጀምር። በደቡብ አፍሪካዊቷ ቢዝነስ ከተማ ጆሐንስበርግ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ የሆኑ ካህን፣ አባትና አገልጋይ የሆኑ በ60ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙ አንድ አዛውንት አባት አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጎዳና ተዳዳሪው የወታደራዊ ደህንነትና መረጃ መኮንን ኮሎኔል ካሣሁን ትርፌ

Tuesday, April 30th, 2013

የጎዳና ተዳዳሪው የወታደራዊ ደህንነትና መረጃ መኮንን ኮሎኔል ካሣሁን ትርፌ

ፍቅር ለይኩን

እንደ አለመታደል ሆኖ ከቅርብ የታሪካችን ዘመን እንኳን ብንነሳ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ የሆነ፣ ብሔራዊ ስሜት ያለው፣ ጠንካራ የሆነ ሕዝባዊ መሠረት ያለው የመከላከያ ኃይል ለመፍጠር እየተደረገ የነበረውና አሁንም እያየነው ያለው ሙከራ መንግሥት በተለዋወጠ ቁጥር ሂደቱ እየተገታ ከዚህ ደርሰናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አባይ ለሕዝብ ወይስ አባይ ለኢሕአዴግ?

Tuesday, April 30th, 2013

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም Dr. Tewodros Adhanom

ግርማ ካሳ

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ በርካታ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ በተለያዩ የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር፣ ለአባይ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሞክረዋል። ነገር ግን በበርካታ ከተሞች፣ ከዚህ በፊት ከነበረው በተለየ ሁኔታ፣ ጠንካራ ተቃውሞ የደረሰባቸው ሲሆን፣ አንዳንድ ከተሞችም፣ ተቃዋሚዎች ስብሰባውን ሙሉ ለሙሉ እስከመቆጣጠር የደረሱበት ሁኔታም እንደነበረም ታዝበናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"መሪ አጣን" እያሉ ማላዘን ይቁም!

Tuesday, April 30th, 2013

መሪነት እና የመሪነት ወለፈንዲዎች

ታደሰ ብሩ

መግቢያ

ማኅበራዊ ለውጥንና እድገትን የሚመለከቱ ዓላማዎች በአንድ ወይም በጥቂት ሰዎች ጥረት የሚሳኩ አይደሉም። እነዚህ ትላልቅ ዓላማዎች እንዲሳኩ የብዙ ሰዎች የተባበረ ጥረት ያስፈልጋል። በርካታ ሰዎችን ለእንዲህ ዓይነቶቹ ግዙፍ ዓላማዎች ማነሳሳትና እና ማስተባበር ነው መሪነት (Leadership) የሚባለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ …

Monday, April 29th, 2013

ተመስገን ደሳለኝ

(ክፍል ፩)

ያለ ወቅቱ በደረሰ ዝናብ እየራሰች ያለችው አዲስ አበባ ዛሬም ከመለስ መንፈስ ተፅእኖ ነፃ አልወጣችም፤ ጣራና ግድግዳዎቿ እንዲህ በምስሉ እና በድርጅቱ አርማ መዥጎርጎሯን ያስተዋለ አንድ ቀልደኛ የባህር ማዶ ወዳጄ "እኔ ከሀገሬ ከወጣሁ በኋላ የኢህአዴግ ዋና ከተማ ሆነች እንዴ?" ብሎ ፈገግ አሰኝቶኛል። በእርግጥ ይህችን ቀልድ ስንፍቃት የምናገኘው ቁም ነገር፦ ከተማዋ በመለስ ውርስ ድንዛዜ ላይ መሆኗ፣ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ…

Monday, April 29th, 2013

(ከተመስገንደሳለኝ)

 (ክፍል)

ያለወቅቱ በደረሰ ዝናብ እየራሰች ያለችው አዲስ አበባ ዛሬም ከመለስ መንፈስ ተፅእኖ ነፃአልወጣችም፤ ጣራና ግድግዳዎቿ እንዲህ በምስሉ እና በድርጅቱ አርማ መዥጎርጎሯን ያስተዋለ አንድ ቀልደኛ የባህርማዶ ወዳጄ ‹‹እኔ ከሀገሬ ከወጣሁ በኋላ የኢህአዴግ ዋናከተማ ሆነች እንዴ?›› ብሎ ፈገግ አሰኝቶኛል። በእርግጥ ይህችን ቀልድ ስንፍቃት የምናገኘው ቁም ነገር፡- ከተማዋ በመለስ ውርስ ድንዛዜ ላይ መሆኗ፣ አስተዳደሯም ያለቅድመ-ዝግጅት ‹‹አፍርሼ ካልሰራሁሽ›› በሚሉ ካድሬዎች ጫጫታና ሩጫ ልቧን እያጠፋት እንደሆነ፣ አንድ ፓርቲ ተመራጭ፣ አስመራጭ፣ ታዛቢ መሆኑን እና የመሳሰሉትን ነው፡፡ የአቶ መለስ ሞትም ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ ስርዓቱን እያንገጫገጨው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"እያንዳንዱ ዜጋ ከራሱ ጋር ይነጋገር" አርቲስት ታማኝ በየነ

Monday, April 29th, 2013

ታምሩ ገዳ

በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ ይቆም ዘንድ እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን አሰተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚገባው እና ከራሱ ጋር መነጋገር እንዳለበት ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዘረፋ ውሎ በእንዳማርያም

Monday, April 29th, 2013

(ገብረመድህን አርአያ)

ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት። ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል፣ ይፎክራል፣ ይሸመጥጣል፣ ያቀረሻል፣ በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል። ብዙም አልደነቀኝም። ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል፣ ታሪክ አውድመዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግጭቱን ማን ለኮሰው?

Monday, April 29th, 2013

(ከእየሩሳሌም አርአያ)

ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ… አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈ ቁልቁል ወርዶ ..ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ።… በዚህ ቅፅበት አንዲት ነጭ ቶዮታ ፒካፕ (ታርጋ የሌላት ወይም ያለጠፈች) ከሱማሌ ተራ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈች ከመጣች በኋላ < በላይ ተክሉ ኬክ> ቤትን አለፍ ብላ ቆመች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

99 ቀናት በአዲስ አበባ

Tuesday, April 23rd, 2013

ጋዜጠኛው ኤን. ማንጄላ (N. Mandela) በኢትዮጵያ

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

በታኅሣሥ አጋማሽ 1954 ዓ.ም በግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱ ጥሪ ተደረገለትና በጥር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ገባ። ይህ ሰው በሦስት ወራት ከአንድ ሳምንት (በ98 ቀናት) ቆይታው ወቅት እጅግ የተጣበበ መርሐ ግብር እንደነበረበት ያስታውቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሲያትል ለኢሳት 50ሺህ ዶላር ተሰበሰበ

Monday, April 22nd, 2013

የጋዜጠኞቹ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙና ውብሸት ታዬ ምስል 33ሺህ ዶላር በጨረታ ተወስዷል

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዚያ 14ቀን 2005 .. April 22, 2013)፦ ትላንት ምሽት በሲያትል ከተማ የኢሳትን ሶስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ታማኝ በየነ እና አቶ መንሱር ኑር በክብር እንግድነት የተገኙበት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት ላይ 50ሺህ የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ደሳለኝ ደበረኝ ደሳለኝ

Wednesday, April 17th, 2013

አባጅፋር

ፊት ላይ ያሉት ቀዳዶች የተበጁት ለመተንፍሰ፣ ለመብላት፣ ለመናገርና ለመናፈጥ ነው። እንዳስፈላጊነታቸው እንጠቀመባቸዋለን። በዚህም ምክንያት ሰውየው ተናገሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የግፍ ጽዋ ሲበዛ አያቀረሽም እንዴ?

Wednesday, April 17th, 2013

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

ዋናው የኢትዮጵያ ህዝብ ችግርና መፍትሄ ያልተገኘለት ነገር፤ የህውሀት ገዢ ቡድን፤ አሁን አለማችን ካለችበት የስልጣኔና የአስተሳሰብ እድገት ደረጃ እጅግ ወደ ኋላ በቀረ እምነትና ፍልስፍና ላይ ተጣብቀው በመቅረታቸው፤ የሁሉ ነገር መፍትሄ ጉልበት ብቻ ነው፤ ጡንቻ ብቻ፤ ጡንቻን አፈርጥሞ መገኘት ብቻ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ደሞዝ፣ መንጃ ፈቃድና ንግግር

Wednesday, April 17th, 2013

ወ/ሮ አዜብ መስፍን Azeb Mesfinአባ ጅፋር

ሰው ይናገራል። ፍሬ ነገር የሆነ፤ ገለባ የሆነ ነገር ይናገራል። ገለባብም ጥቅም አለው። ከብት ይመግባል። ከብቶችም ሆዳቸው ይሞላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍለጋ

Tuesday, April 16th, 2013

ተሾመ ገብረስላሴ Teshome Gebreselasseተሾመ ገብረስላሴ

በቅድሚያ ስለራሴ ልንገርህ። አለመኖርን አላውቀውም ላውቀውም አልጓጓም። በመኖር ቤተ-መቅደስ ውስጥ ነኝ። መኖርን እቀድሳለሁ። መኖርን አሞካሻለሁ። እንዳንተው ስለመኖር አዜማለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነገም አንድ የሚያደርገን ቅመም ምን ይሆን?

Tuesday, April 16th, 2013

ይኸነው አንተሁነኝ

የዚህ ጽሁፍ መነሻ ሰሞኑን የህወሓት ደጋፊ የሆኑ ራዲዮኖች ጋዜጦች ድረ ገጾችና መወያያ ክፍሎች ከአማራው ወገናችን መፈናቀል ጋር በተያያዘ እያሉት ያለው ፍጹም ሚዛን የጎደለው ሀዘኔታ ያልዳሰሰው ከዚያም ሲከፋ ጭካኔ የተሞላበት ንግግር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከማግለል ማሳተፍ ይቅደም

Tuesday, April 16th, 2013

አዋሽ አዳል

ሰሞኑን በአንድ ድረገጽ ላይ "የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ?" በሚል ርዕስ ከልጅ ተክሌ የፃፈውን ካየሁ በሁዋላ ፀሐፊውን በልቤ ወቅሼ አለፍኩት። በነጋታው በሌላ ድረገፅ ላይ ሌላ ርዕስ ይዞ፣ ትንሽ ተቀይሮ አየሁት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኢትዮጵያ መንግሥት ከኢትዮጵያ የተላከ ደብዳቤ

Tuesday, April 16th, 2013

ወ/ሮ አዜብ መስፍን Azeb Mesfinታረቀኝ ሙጬ

የአሁኑን ዘመነ መንሱት አያድርገውና በዱሮ ጊዜ ሰዎች የሚሠነዝሩት ምክር አድማጭ አገኘም አላገኘም መካሪን የሚጎዳ ነገር እንደማይከተል ለመጠቆም "አፍ ወድቆ አይሰበርም" ይባል ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው?

Monday, April 15th, 2013

ገብረመድህንአርአያ (ፐርዝ-አውስትራሊያ)

ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በትግል በረሃበነበርንበት ወቅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (....) በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ላይ ሲከተል የነበረውን አቋሙን ተቀብሮ ከነበረበት ጉድጓድ አውጥቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነማንናቸው የሚለውን ታሪካቸውን እና የተፈጸመውን ጸረ-እምነት ግፍ በአጭሩ ለማሳወቅነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ?

Saturday, April 13th, 2013

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ - ካናዳ)

1-       ጽሁፍ ካላበሳጨ ወይ ካላስጨበጨበ አይመቸኝም። ላለፉት ጥቂት ሳምንታት የሚያበሳጭ ወይ የሚያስጨፍር ርእስ ስጠብቅ ሳልጽፍ ቆየሁ። የኢትዮጵያውያን፤ በተለይም የአማርኛ ተናጋሪዎች ከቤንሻንጉል መባረር በራሱ በቂ አናዳጅና አሳዛኝ ክስተት በመሆኑ፤ እንዲሁም ሌሎች ስለጻፉበት እሱ ላይ ብዙ አልደክምም። ስለዚህ ሌላ አናዳጅ ርእስ ናፈቅኩ። ባለፈው ሰኞ፤ ከአድካሚው ውሎዬ እረፍት ለመውሰድ ወደኢሳት ድረ-ገጽ አመራሁ። የደንቡን አድርሼ ከኢሳት ድረገጽ ወጥቼ ለመሄድ ጣቴን ጠቅ ለማድረቅ ስንቀለቀል፤ በአይኔ የቀኝ ጠርዝ፤ በኢሳት ድረገጽ የግራ ማእዘን ላይ፤ ስድስት ሰባት ወንዶች የተደረዱበት ምስል አየሁና ተመለስኩኝ። አንዳንዶቹ የተለመዱ ፊቶች ናቸው። “ሲሳይ አጌና፤ ታማኝ በየነ፤ ሻምበል በላይነህ፤ ሄኖክ የሺጥላ ...” ከኢሳት ጋር በተያያዘ አንዳንዶቹ አዳዲስ ናቸው። የኢሳት ሶስተኛ አመት ዝግጅትን ለማድመቅ የተመረጡ እንግዶች ናቸው። የሚያበሳጭም ባይሆን፤ እነሆ የሚያወያይ ርእስ ተደግሶልኝ አየሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ – ፮

Friday, April 12th, 2013

ጽዮን ግርማ Tsion Girmaጽዮን ግርማ
ምስክርን የማውቀው ኢትዮጵያ ነው፤ ዛሬ አገኘኹት። በእናቱ ጫንቃ ላይ የነበረው ያ ሁሉ አይበገሬነት ጠፍቶ በፋርመርስ ሥጋ ቤት አንገቱን ደፍቶ ሥጋ ቆራጭ ኾኗል። ምስክር የወጣበት የውስጠኛው ክፍል የገባው ሥጋ ተስተካክሎ እየተቆራረጠ ለገበያ የሚዘጋጅበትና የሥጋ ዘሮቹን ተከትለው የሚመጡትን ቆሻሻዎች ማጽዳት ነው። ምስክር በቆምንበት የተሻለ ኑሮ እየመራ ስለመኾኑ አጠር አጠር አድርጎ ነገረኝ፤ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትግል … ሽንፈት፤ … ድል፤ ሽንፈት …

Thursday, April 11th, 2013

ተመስገን ደሳለኝ

ከምሽቱ አንድ ሰአት አልፏል፤ የእጅ ስልኬ ደጋግሞ ቢጮኽም ትኩረት አልሰጠሁትም። ከጥቂት ሰከንዶች ፋታ በኋላ የቢሮዬ ስልክ ጮኸ፤ አነሳሁት። ለካስ እንዲህ በአንዱ አልመልስ ስላት፣ በሌላው እያፈራረቀች የምትደውለው ዕድሜዋ ወደ ሰባ እየተጠጋ ያለው አሮጊቷ እናቴ ኖራለች፦

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሁለት ወር ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ተሰደዋል

Thursday, April 11th, 2013
  • የመን ውስጥ ምላሱ የተቆረጠውን ሀፊዝ ጨምሮ 25 ኢትዮጵያዊያን ሆስፒታል ገብተዋል
  • ዮርዳኖስን መኪና ላይ አስረው መሬት ለመሬት ጎተቷት፣ (ሚሚ) ተደፈረች ... ቃለምልልስ

ግሩም ተ/ሀይማኖት

የመን ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው በደል ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቷዋል። በጅቡቲ አድርገው ቀይ ባህርን ተሻግረው ወደ የመን የሚገቡትን ኢትዮጵያዊያንን በማገት 1000 እና 1500 የሳዑዲ አረቢያ ሪያል እና ከዛም በላይ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲያስልኩ የሚያደርጉ አፋኞች መኖራችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ መግለጼ ይታወሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አፈወርቆች

Thursday, April 11th, 2013

ዶ/ር ከበደ ሚካኤል Dr. Kebede Michaelኤፍሬም እሸቴ

ከሰሞኑ "ፋኖስና ብርጭቆ" የምትባለውን የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤልን ግጥም በፌስቡክ ገጼ ላይ ለጥፌ ነበር። "ስንቶቻችሁ ይህንን የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤልን ግጥም ታስታውሣላችሁ? በልጅነቱ ይህንን በቃሉ ይወጣ የነበረ አሁንም ያልረሣ ካለ እነሆ ካንገቴ ዝቅ ብዬ አክብሮቴን ልግለጽ" ከሚል ማስታወሻ ጋር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቤንች ማጂ አማርኛ ተናጋሪዎችን ማፈናቀል ዳግም ተጀመረ

Thursday, April 11th, 2013

(ፍኖተ ነፃነት ቁ. 71፣ መጋቢት 29 ቀን 2005)፦ በደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሜኒት ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብና አርፋጅ ቀበሌ ነዋሪዎች በካከል ከ350 በላይ የአማርኛ ተናጋሪ ዜጎች ተፈናቅለው በወረዳው አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትግል… ሽንፈት፤… ድል፤ ሽንፈት…

Wednesday, April 10th, 2013

 (ተመስገንደሳለኝ)

ከምሽቱ አንድ ሰአት አልፏል፤ የእጅ ስል ኬደጋግሞ ቢጮኽም ትኩረት አልሰጠሁትም። ከጥቂት ሰከንዶች ፋታ በኋላ የቢሮዬ ስልክጮኸ፤ አነሳሁት። ለካስ እንዲህ በአንዱ አልመልስስላት፣ በሌላው እያፈራረቀች የምትደውለው ዕድሜዋ ወደ ሰባ እየተጠጋ ያለው አሮጊቷ እናቴ ኖራለች፡-

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዳምጠው ወያኔ/ኢሕአዴግና አፈና በኢትዮጵያ

Friday, April 5th, 2013

/መስፍንወልደማርያም

 

በቀልድ ልጀምር፤ አንድጮሌ የአስመራ ልጅ የእኔ ተማሪ ነበር፤ አንድ ጊዜ የጂኦግራፊ ክፍል ተማሪዎች አንድ ጃፓናዊ አስተማሪ ለመሸኘት ግብዣ አድርገው ነበር፤ በግብዣው ላይ የጠቀስሁት ነገረኛ የአስመራ ልጅ (የአስመራ ልጅ የምለው ላርቀው ፈልጌ እንዳ ይመስላችሁ፤) በአስተማሪዎች ላይ ቀልድ ያሰማነበረ፤ ስለኔ ሲናገር፤መስፍን ወልደማርያም የቢሮውን በር ሁል ጊዜ ክፍት አድርጎ የሚቀመጠው ለምንድን ነው? ይልና እሱው ሲመልስ፣

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዞምቢዎቹ እየመጡ ነው!

Friday, April 5th, 2013

ተመስገንደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ሐምሌ11 ቀን.. በታተመችው ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ ወዳጄ መስፍን ነጋሽ ‹‹ዞምቢዎቹ›› በሚል ርዕስ ዛሬም ድረስ ከህሊናዬ ያልጠፋ ድንቅ ጽሁፍ አስነብቦን ነበር( የዚህ ፅሁፍ ሃሳብም ከዚሁ የተናጠቀነው)፡፡ ይኸ ከሆነ ድፍን ሶስት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ ቀርቶታል፡፡ ‹‹አዲስ ነገር››ወደታሪክነት ከተቀየረች ሁለት ዓመት አልፏታል፡፡ ለምን? …ዞምቢዎቹ ድልስለነሷት፤ እንዴት? ማንም ዞምቢዎቹን ድል አድርጎ ስለማያውቅ፡፡ ዞምቢ ምንድርነው? ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ እንዲህ ገልጿቸዋል፡-

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራው መከራ ላገሩ ስለሠራ

Thursday, April 4th, 2013

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ
እንሁን ቀና ሰው፣ እውነት እንናገር፣
ለእውነት ጥብቅና፣ ሃቁን አስቀድመን፣
ፖለቲካን ወዲያ፣ ትንሽ አቆይተን፣
እስቲ እንተባበር ሃሰት ላይ አድመን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነገን የተሻለ ቀን ለማድረግ፤ ዛሬ ነው መነሳት፤

Friday, March 29th, 2013

ሉሉ ከበደ(ጋዜጠኛና ደራሲ)

ይድረስ ለሀገሬ ወጣቶች

ከዘር ማንነታችን በፊት ሰብአዊ ሰውነታችን፤ ከጎጠኝነታችን በፊት ኢትዮጵያዊነታችን፤ ከሸፍጥ፤ ከተንኮል፤ ከመሰሪነታንችን በፊት ቅንነታችን፤ ከፍርሀታችን በፊት ድፍረታችን፤ እርስ በርስ ከመጠራጠራችን በፊት መተማመናችን፤ ከመፍረክረካችን በፊት በጽናት መቆማችን፤ ከልዩነታችን በፊት አንድነታችን፤ ወያኔ ዛሬ ኢትዮጵያውያንን ከከተተበት መቀመቅ ውስጥ የሚያወጣን ብቸኛ መፍትሄ ከላይ የደረደርኩት ነገር ብቻ የመስለኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልካም መሪ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው?!

Thursday, March 28th, 2013

ታምሩ ገዳ

አቡነ ፍራንሲስ በሕዝብ መሃል በመኪና ሲያልፉ ሕፃን ልጅ ተቀብለው ሲስሙ

በየትኛውም የእድገት ደረጃ ይሁን የፖለቲካ አመለካከት ወይም የሃይማኖት ስርአት ውስጥ ለሚገኝ ማህበረሰብ ሁነኛ መሪ ማግኘት ከእድሎች ሁሉ ትልቁ እድል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። አይደለምም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ

Wednesday, March 27th, 2013

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

ማንም በዕድሜው ብዛት አያስጠራም ስሙን
በጥቂቱም ዕድሜው ይሠራል ሐውልቱን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘጠኝ ቦላሌ …

Wednesday, March 27th, 2013

ይኸነው አንተሁነኝ

የክህደት ቁልቁለት አሉ ታላቁ ምሁር!!! የክህደት ውርስ የበቀል ዛር እያስጎራ፣ የሚሆነውንም የማይሆነውንም እያስቀባጠረ ሃያ አንድ ዓመት እያንደረደረ ወርውሮ እዚህ ያደረሰው ህወሓት ስለመድረሱ እንጅ ወደ ፊት ስለሚሆነው ወይም ስለሚያደርገው ከግምት በላይ የሚያውቀው ነገር ያለ አይመስልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ – ፭

Wednesday, March 27th, 2013

ጽዮን ግርማ

ዋሽንግተን ዲሲ Washington DC

"... እንዴት አድርጌ ደመወዜን እኮ አልሰጠችኝም፤ ቆይ ዛሬ ቆይ ነገ እያለች ይኸው እስከ አሁን ታጉላላኛለች። ማታ ማታ በገባች ቁጥር እስከሚበቃት እነግራታለኁ፤ እርሷ መቼ ሰበብ ታጣለች። ቢጨንቀኝ ላገናኘኝ ልጅ ደውዬ ነገርኁት፤ ይብሱኑ እርሱም እኔም ያበደርኋትን አልከፈለችኝም አለኝ። ወይ አሜሪካ! ጉዷን አየኁላት።" መቼም መመረሯ መግለጫ የለውም። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቋንቋ የህወሓት የጥፋት ሚዛን እና የመጭው ዘመን የኢትዮጵያዊያን ስጋት

Wednesday, March 20th, 2013

ይኸነው አንተሁነኝ

ልቃቂት ነው ሂዎት፤ በእንዝርት ላይ እንደሚሽከረከረው የጥጥ ንድፍ ዘለላ እየተጠማዘዘ እየተሽመለመለ፣ እየጠበቀና እየላላ፣ እየተወጠረና እየረገበ የሚጠመጠም የሂዎት አንጓ። ያንዱ ሂዎት ዘርፍ በሌላው መሰረት ላይ እየተመጠነና እየተደረበ የሚከወን ኩነት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ – ፬

Wednesday, March 20th, 2013

130319usa-tsi-article-04-pic-02ጽዮን ግርማ

... አባ "አንድ ሰው ጨመርሽልና" አሏት ከትውውቃችን አስቀድሞ አብረው እንዳዩን። "ኧረ ተመላሽ ናት አባ፤ ለሥራ ነው የመጣችው" አለቻቸው። "ትዳር መሥርተሻል?" ጠየቁኝ። "አዎን አባ ቆይቻለኹ" አልኋቸው። ሣቅ አሉና "እኔ ደግሞ ገና ከሩቁ ሳይሽ ልድርሽ እያሰብኹ ነበር፤" አሉኝ ሐሳባቸው ያለመሳካቱ የፈጠረባቸውን ስሜት በፈገግታቸው እየሸፈኑ። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የክሽፈት እንጉርጉሮ፣ ታሪክ ላይ ተሸንቅሮ!

Tuesday, March 19th, 2013

መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክካሣሁን ዓለሙ

"አንድ ሰው በአደባባይ ሲናገርም ሆነ ጽሑፍ አሳትሞ ሲያሰራጭ ራሱን አጋልጦአል፤ የተናገረው ወይም የጻፈው መቶ በመቶ ያህል በራሱ ጉዳይ ላይ ብቻ ከሆነ፣ የመተቸት ወይም ሐሳብ የመስጠት ግደታ የለብንም፤ ነገር ግን የተናገረው ወይም የጻፈው በአገርና በሕዝብ ጉዳይ ላይ ከሆነ፣ የዚያ አገር ዜጋ ሁሉ በጉዳዩ ውስጥ የመሳተፍና ሐሳቡን በሙሉ ነጻነት የመስጠት መብት አለው።"

(ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም፣ መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ፣ ገጽ78-79)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ – ፫

Monday, March 18th, 2013

ሬኖ-ኔቫዳ

ጽዮን ግርማ

... ፀጉሯን በፋሽን የተቆረጠች፣ ቀጭን ዝንጥ ያለች ልጅ ቦርሳዋን በአንድ እጇ አስገብታ በአንድ እጇ የስታር ባክስ ቡናዋን እንደያዘች ከአሳንሳሩ ወጣች። የፋሽን ትርኢት በምታሳይ ሞዴል አረማመድ በሽቶዋ አውዳን፣ ማስቲካዋን እያላመጠች በአጠገባችን እልፍ አለች። ከሴቶች ማጌጫ የቀራት ነገር አለ ማለት አይቻልም። እኔ "ልጅቷ" አልኳት እንጂ እሷ እንኳን "ልጁ" ነበረች። በጣም ተገርሜ "ወንድ ነው አይደል?" ስል ወ/ሮ ሐረገወይንን ጠየቅኋት። "አዎ፤ ወንድ ነው፣ ግን ደግሞ ሚስት ነው" አለችኝ። መጸየፏ ከፊቷ ያስታውቃል። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፋሽስቱ ግራዚያኒን ሐውልት መሠራት ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ በአ.አ. ታሰሩ

Sunday, March 17th, 2013

”ይህ የጤንነት አይመስለኝም!” ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም Dr Yakob HailemariamEthiopia Zare (እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. March 17, 2013)፦ የፋሽስቱን ግራዚያኒ ሐውልት በጣሊያን ሀገር በመሠራት ላይ መሆኑን በመቃወም በአዲስ አበባ ሰልፍ ለማድረግ የወጡ ከ35 በላይ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ። ከእነዚህም ውስጥ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ይልቃል ጌትነት ጨምሮ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አመራር አባላት በዛሬው ዕለት ታስረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ – ፪

Sunday, March 17th, 2013

ፒንክ ፖኒ የራቁት ጭፈራ ቤት (አትላንታ - ጆርጅያ) Pink Pony

ጽዮን ግርማ

... በርካቶች ሥራ ፍለጋ በሚሰደዱባት የዓለም ቁንጮ በሆነችው ሀገረ አሜሪካ፣ ገላቸውን ለሽያጭ ላቀረቡት ወጣት እንስቶችስ "አይ የእንጀራ ነገር" ስል ደረቴን ልድቃላቸው ይሆን? ጉዳዩ የእንጀራ አይመስልም፤ እናም ደረት የመድቃቱ ነገር አስፈላጊ አልመሰለኝም። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ

Sunday, March 17th, 2013

መልክአ ኢትዮጵያ - ፪

ፒንክ ፖኒ የራቁት ጭፈራ ቤት (አትላንታ - ጆርጅያ) Pink Pony

ጽዮን ግርማ

... በርካቶች ሥራ ፍለጋ በሚሰደዱባት የዓለም ቁንጮ በሆነችው ሀገረ አሜሪካ፣ ገላቸውን ለሽያጭ ላቀረቡት ወጣት እንስቶችስ "አይ የእንጀራ ነገር" ስል ደረቴን ልድቃላቸው ይሆን? ጉዳዩ የእንጀራ አይመስልም፤ እናም ደረት የመድቃቱ ነገር አስፈላጊ አልመሰለኝም። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ከእኔ ልጅ ጋር ሐረር ከተማ ውስጥ አራት ሰው በፓሊስ ነዳጅ እየተደፋበት በእሳት ተቃጥሎ ሞቷል"

Sunday, March 17th, 2013

ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ W/o Ethiopia Yelemaወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ (ከሐረር የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸው የተባረሩ አዛውንት)

ፍኖተ ነፃነት (መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም.)፦ "ልጄ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ተደርጋ፣ ቤቴን ተነጥቄና ንብረቴ ወድሞ ከሐረር ተባረርኩ" ሲሉ አንዲት የ67 አመት ባልቴት በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ ፩

Sunday, March 17th, 2013

ጽዮን ግርማ Tsion Girmaጽዮን ግርማ

የሚሳሳሙት ደንበኞቻቸው ወንድ እና ሴት ብቻ አይደሉም። አንዳንዴ ወንድና ወንድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሴትና ሴት ሊሆኑ ይችላሉ። በዲሲ፣ በሳንፍራንሲስኮ፣ በቺካጐ እና በአትላንታ ጉብኝቴ ወንድ ለወንድ እና ሴት ለሴት ሲሳሳሙ በዐይኔ ተመልክቻለሁ። ድርጊቱን ማየት እንደመስማት እና ማውራቱ ቀላል አይደለም። ለእንደኔ ዓይነቷ ሊብራል ነኝ ባይ እንኳን መሣቀቁ ነፍስን ከሥጋ ያላቅቃል። ግን ደግሞ ያየሁትን ጽፌ ለማስነበብ ጓጉቼ ስለምጓዝ እየተሳቀቅኹም ቢሆን እንዲህ ያሉትን ቦታዎች ጐብኝቻለሁ። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...