Author Archive

ፕሬስደንት ኦባማን ለድጋሜ ምርጫ ለምን አንደምደግፋቸው

Friday, September 14th, 2012

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም

ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

በ2008 ምርጫ ወቅት ዕጩውን ፕሬዜዳንት ኦባማን በደስታ ነበር የደገፍኳቸው? በእርግጠኝነት! ባለፉት አራት ዓመታት ጊዜ ያከናወኑት ሁሉም  ተግባራቸውንስ የምስማማበት ነው? ፈጽሞ! በ2008 የገቡትን ቃላቸውንስ በሙሉ አክብረዋል? እንዲያዉም! በ2012 በፕሬዜዳንት ኦባማ ቅር ተሰኝቻለሁ? በሚገባ! ግን: እኮ አኔ ብቻ ሳይሆን  በ2008 የደገፏቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካኖችም ቅሬታ አላቸው፡፡ በምርጫቸው ወቅት ታሪክ እንደተሰራ ያመኑና መልካሙን ሁሉ የተመኙላቸውም በአሰርት ሚሊዮን የሚቆጠሩም የዓለም ሰዎችም ባለቅሬታዎች ናቸው፡፡

ከሞላ ጎደል የሆነ ቅሬታ ቢኖረኝም ፕሬዜዳንት ኦባማ በድጋሚ እንዲመረጡ እደግፋለሁ:: ምክንያቴም የኣላማዬና የእምነቴ አራማጅ በመሆናቸው ነው:: ፕሬዜዳንት ቢል ክሊነተን ባለፈው ሳምንት በ2012ቱ የዴሞክራቲክ ኮንቬንሽን (ስብሰባ)ንግግራቸው እንዳስቀመጡት፤ በዚህ የ2012 ምርጫ ሁለት ምርጫዎች አሉን፤

“በራስህ ቧጠህ ተወጣውን ከፈለጋችሁ ሪፓብሊካንን ምረጡ፡፡በእኩልነት ሃላፊነትን የምንወጣበትና፤በሚገኘውም ውጤት እኩል የመገልገል እድል ካላችሁና ሁላችንም በአንድነት ያገባናል የምትሉ ከሆነ ድምጻችሁን ለባራክ ኦባማና ለጆ ቢደን ስጡ፡፡ሁሉም የአሜሪካን ዜጋ በምርጫ እንዲሳተፍ፤ የምርጫ ሕግንም አካሄድ መቀየር  አግባብ አይደለም ብላችሁ የምታምኑ ከሆነና የወጣቱን፤ የምስኪኑን ዜጋ፤የአናሳውን ዜጋ ክፍል፤የአካል ጉዳተኞችን መራጮች ቁጥር መቀነስ አገባብ አይደለም የምትሉ ከሆነ ባራክ ኦባማን ደግፉ፡፡ ፕሬዜዳንቱ የአሜሪካንን የሁለንተና ዕድል በጨቅላ እድሜያቸው ወደዚህ የመጡትን ወጣት ስደተኞች ኮሌጅ የመግባት እድል፤ በውትድርናው ተካፋይ መሆንን፤ድምጻችሁን ለባራክ ኦባማ ስጡ፡፡ የአሜሪካ ሕልምና ፍላጎት ጠንክሮ የሚጓዝበትንና በዚህ ውድድር በበዛበት ዓለም፤የአሜሪካ ለሰላም የቆመና የብልጽግና ተቀዳሚ መንግስት እንዲሆንና እንዲቀጥል ካለማችሁ ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ለኦባማ ነው ድምጻችሁን መስጠት ያለባችሁ፡፡

እኔ እድልን በጋራ ሃላፊነትንም በጋራ የሆነ ሀገርን ነው የምመርጠው፡፡ ሁላችንም በአንድ ላይ የሆነ ሕብረተሰብን ነው የምደግፈው፡፡

ወከባው ሪፓብሊካኖች ከዘመናት ውድቀት ትንሳኤ እያደረጉ ነው በማለት ይጮሃል፡፡በ2008 ከነበራችሁበት ሁኔታ አሁን የተሸለ ሁኔታ  ላይ ናችሁ በማለት ይሳለቃሉ::  ሃቁ እራሱ እንዲናገር እንፍቀድለት፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ በ2008 ሥልጣን ሲረከቡ አሜሪካ በወር 750,000 ሥራ አጦች ይፈጠሩባት ነበር፡፡ በፕሬዜዳንት ኦባማ አስተዳደር ግን ከግሉ ክፍለ ኤኮኖሚ 4.5 ሚሊዮን ተፈጥረው ሳለ ከ2011 ጋር ሲመዛዘን ከ2008 ወቅት አንሻልም? በሚገባ እንጂ!

በ2008 የአሜሪካን ኤኮኖሚ በዎል ስትሪት በትሪለዮን ውስጥ አዘቅዝቆ ነበር፡፡ የመኪናው ኢንዱስትሪም እርሙን ሊያወጣ ቀናት ነበር የቀሩት፡፡በ2012 የስቶክ ማርኬት (አክሲዮን) ዋጋው በእጥፉ ጨምሯል፡፡ ሚት ሮምኒ እንዳለውም የመኪናው ኢንደስትሪ አልሞተም ይልቅስ ተፍፉወመ እንጂ፡፡ በ2012 የጄኔራል ሞተርስ ገበያ በ15.5 ከመቶ ከ2011 በተሸለ አሻቀበ፡፡ ጂ ኤምም በ2008 ከነበረበት አዘቅት ወጥቶ 248,750 መኪናዎች ለመሸጥ በቃ፡፡ ይህም ከ2008 ዓም የተሸለና ተስፋ የሚሰጥ መሻሻል ነው፡፡ታዲያ የአሜሪካን የአውቶ ፋበሪካ እንደገና ወደ አንበሳነቱ ተመልሶ ማግሳት አልቻለምን?

ፕሬዜዳንት ኦባማ ሁሉም የሚችለውን ለሁሉም ጠቃሚነት ያለውን የጤና ኢንሹራንስ ዘዴ በፕሬዜዳንታዊ ዘመናቸው ይፋ ከማድረጋቸው ቀደም ብሎ 40 ሚሊዮን አሜሪካውያን የጤና ዋስትና የላቸውም ነበር፡፡ በ2014 አብዛኛው የአሜሪካ ዜጋ አቅማቸውን ያመጣጠነ የጤና ዋስትና ይኖራቸዋል፡፡ የጤና ዋስትና ድርጅቶችም በጤናማውና በበሽተኛው ባለውና በሌለው፤ በሚል ልዩነት ማድረጋቸው ያከተመ ይሆናል፡፡ ወላጆችም ልጆቻቸው 26 እስኪሆናቸው ድረስ በቤተሰባቸው የጤና ዋስትና ውስጥ አካተው ያቆዩዋቸዋል፡፡ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑና የሜዲኬር ተጠቃሚዎችም በመድሃኒቶቻቸው ላይ ቅናሻቸውን ያጣጥማሉ፡፡ እነዚህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ታዲያ በ2008 ከነበሩበት ሁኔታ የተሸለ ደረጃ ላይ አይደሉም? ያለጥርጥር እንጂ!

ከፕሬዜዳንት ኦባማ ሥልጣን መያዝ ቀደም ብሎ ሁሉም በየፈርጁ ተጠቃሚውን፤ከክሬዲት ካርድ እስከ የተማሪዎች መማርያ ብድር ከዚያም አልፎ ተጠቃሚውን ሁሉ ግራ ሲያጋቡትና በጥቃቅን ፅሁፎች በማደናበር፤ሕጋዊ በሚመስሉ አሳሳች መጠቀሚያዎች ሕብረተሰቡን አጃጅለውት ቆይተዋል፡፡ አሁንስ የአሜሪካን ተጠቃሚ ሕብረተሰብ በ2012 ያለው ሁኔታ በ2008 ከነበረው አይሻልም? አያጠያይቅም?

ሴቶች በስራው ዘርፍ 47 በመቶውን (66 ሚሊዮን ሴቶች በስራ ላይ) ይይዛሉ፡፡በብዙ ኢንዱስትሪዎች ሴቶች ከወንዶች ያነሰ ክፍያ ነው የሚደረግላቸው፡፡ ከ2008 በፊት ሴቶች ከወንዶች ባላነሰ መልኩ እንዲከፈላቸው ድምጻቸውን ማሰማት አይችሉም ነበር፡፡ፕሬዜዳንት ኦባማ ሊሊ ሌድቤተር እኩል ክፍያ ህግ ፤ ማንንም የማያገለውን ሴቶችን፤በጾታ ሰበብ እኩል ክፍያን የሚታገድባቸውን፤በቀለም፤ በዘር፤ በሃይማኖት፤በዕድሜ፤ በአከለ ጉዳተኛነት፤የተጎዱትን ሁሉ ያቀፈውን ህግ ፈርመው አጸደቁ፡፡ታዲያ እነዚህ አሜሪካኖች በ2012 ዓ.ም ከ2008 ዓ፤ም ሁኔታቸው አለተሻሻለም? ምንም አያጠራጥርም!

ከጁን 2008 በኋላ አሜሪካ 182,060 ሠራዊት ወደ ኢራቅ ልካለች፡፡ በ2012 ሁሉም የአሜሪካ ተዋጊ ሃይሎች ከኢራቅ ነቅለው ወጥተዋል፡፡በ2014 ደግሞ ሁሉም ተዋጊ ሃይሎች ከአፍጋኒስታን ለቀው ይወጣሉ፡፡ ሬዜዳንት ኦባማም እነዚህ የጦር አባላት ለሚቀጥሩ ድርጅቶች፤ትምህርታቸውን ለመቀጠል ለሚመርጡትም የትምህርት ዕድሉ እንዲሰጣቸውና የመልሶ በነበሩበት ቅድመ ዘመቻ የመቀጠር እድል እንዲያገኙ ይህንንም  ለሚያደርጉት ድርጅቶችና መሰል ተቋማት የታክስ ተጠቃሚነት (ታክስ ክሬዲትስ)፤ እንዲሰጣቸው በፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡በፕሬዜዳንት ኦባማ አስተዳደር ውቅት ዓለም ስለአሜሪካ ያለው አስተያየት ‹‹በመጠኑ መሻሻልን›› አሳይቷል፡፡እነዚህ የጦር አባላትስ በ2008 ከነበሩበት ሁኔታ አሁን በ2012 የተሻሻለ ሁኔታ አይደሉምን? አሜሪካስ እንደሃገር ቀደም ሲል ከነበረችበት ሁኔታ አሁን ከበሬታን አላገኘችምን? በ2008  ከነበረን ጠቅላይ የጦር አዘዥ (ኮማንደር ኢን ቺፍ) አሁን ያለን አይሻልም? እንዴታ!

እርግጥ ሁሉም ነገር በ2008 ከነበረበት ሁኔታ ተሻ ሽሏል ማለት አይደለም፡፡ ኦሳማ ቢን ላደን ከአሁን ይልቅ በ2008 ዓም እርግጥ በተሸለ ሁኔታና ፓኪስታን ከነበረበት ቪላ የሽብር ተግባሩን ተንደላቆ ያ ቀነባብር ነበር፡፡ ከሱም ጋር የሽብር አጋሮቹ ሁሉ በምቾት  ሽብርተኛ ተግባራቸውን ያከናውኑ ነበር፡፡ ሼክ ሳዒድ አል ማስሪ፤(የአልቃዳው 3ተኛ ደረጃ ሃላፊ): አንዋር አል-አውላኪ (የአረቢያን ፔንሰዊላ አልቃይዳ): አቡ ሃፍሲ አልሻሃሪ (በፓኪስታን ኦፐሬሽን የአልቃይዳ ሃላፊ): ከፍተኛ የአልቃይዳ ባለስልጣኖች፤ አብድ አል-ራህማን፤ ኢሊያስ ካሲማሪ፤አማር አልዋ ኢሊ፤ አቡ አል አልሃሪቲ፤ አቡ አዩብ አል መስሪ፤ ሃምዛ አል ጃዊፊ፤ አቡ ኦማር አል ባጋዳዲ፤ አሊ ሳላህ ፋራሃን፤ ሃሩን ፋዙል እና ሳለህ አሊ ሳለህ ብሃን (የምስራቅ አፍሪካ አል ቃይዳ) በተሸለ ሁኔታና ነበሩ፡፡ ሌሎችም በባሊ የማታ ክበብ ለተፈጸመው የቦምን ጥቃትና ሕይወታቸው ላለፈው 180 ሰዎች ተጠያቂ የሆኑት የአልቃይዳ አባላት እና ብዙዎቹ አባላትስ አሁን በ2012 ካሉበት በተሸለ ሁኔታና ነበሩ፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ ተግባራቸውን እንዳልፈጸሙ በመረዳት፤ እና ኤኮኖሚውን በማሻሻል ጥረቱ ገና የሚቀራቸው እንዳለ ይገነዘባሉ፡፡ ባለፉት 4 ዓመታት የተጓዙበትም መንገድ ቀላል እንዳልነበረ የምናውቀው ነው፡፡ በሚቀይሱት መንገድ ላይ ሁሉ ተቃውሞ ነበረባቸው፡፡ ከዓላማቸው ሊያናጥቧቸው ተሞክሯል፤መንገዱን ለመዝጋት ተጥሯል፤ከዚያም አልፎ የሪፓብሊካኑ ቁንጮ ሹም ‹‹አንድና ብቸኛው ታላቁ የፖለቲካ ግባችን፤ ፕሬዜዳንት ኦባማ የአንድ ተርም ፕሬዜዳንት ብቻ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ የኔና በሃገሪቱ ያሉት የሪፓብሊካን ፓርቲ አባላት ብቸኛና ዋና የሆነው የፖለቲካ ተልዕኮ ይሄው ነው፡፡››  ሲሉ በሴኔቱ መድረክ ላይ ተናግረው ነበር፡፡

ፕሬዜዳንት ኦክሊንተን እንዳስተዋሉት፤ ፕሬዜዳንት ኦባማ ‹‹የወረሱት ባዶና የተሰናከለ ኤኮኖሚ ነበር፡፡ያንን የፈራረሰ ኤኮኖሚ ላማዳንና ወደ ነበረበት ለመመለስ ዘመናዊ መሰረት አዋቅረው፤ አስቸጋሪውን ጉዞ ተያያዙት፤ በዚህም ሚዛናዊ ኢኮኖሚ በመንደፍ ብዙ ሚሊዮን አስተማማኝ የሥራ እድል የሚፈጥር አደረጉት፡፡አሁንም መደረግ ያለበት በርካታ ጉዳይ አለ፡፡አዳዲስ ስራዎች መፈጠር አለባቸው፡፡በትምህርቱ ዘርፍ አዳዲስ ኢንቬስትመንቶች መምጣት አለባቸው፡፡የሥራ ስልጠናና አዳዲስ መዋቅሮች መዘርጋትም አስፈላጊ ነው፡፡ያም ሆኖ ግን በበርካታ ዘመናት ሂደት የተፈጠሩትን ችግሮች ሁሉ ፕሬዜዳንት ኦባማ በአንድ ተርም ውስጥ ማጠናቀቅ አይጠበቅባቸውም፡፡”

ፕሬዜዳንት ኦባማ፤ ኢትዮጵያና አፍሪካ

ሁል ጊዜም ፖለቲካዊ ንግግርና ፖለቲካዊ ተግባር ልዩነት አለው፡፡ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካውያን በ2008 ምርጫ ወቅት በፍቅርና በእልህ ለባሮክ ኦባማ መመረጥ ደፋ ቀና ያሉ ደጋፊዎች፤  አሁን የተገባው ቃል አልተከበረም፤ ሁሉም ነገር ለይስሙላ የተባለ ነው በሚል ወቀሳ ይሰነዝራሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ሊደረግ የታሰበውስ የፍትህ የሰብአዊ መብት የዴሞክራሲ ተስፋ ምን አጨለመው በሚል ቅሬታቸውን ያሰማሉ፡፡ የምር ግን ፕሬዜዳንት ኦባማን ግድ የለሽ በመምሰላቸው፤ በጉዳዩ ላይ ቀዝቀዝ በማለታቸው ልንወቅሳቸው ይገባልን?

እውነቱ ገሃድ ሊወጣ የግድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ለዴሞክራሲ፤ ለሰብአዊ መብት እውነታነት፤ፕሬዜዳንት ኦባማ ያደረጉት አለያም ያላደረጉት እኛ ትውልደኢትዮጵያ አሜሪካውያን ካደረግነው ወይም ካላደረግነው ጥረት የተለየ አይደለም፡፡ ይህ ነው አፍጥጦ የሚያየን እውነት መቀበል ያለብን፡፡ የፕሬዜዳንቱ እርምጃ አለያም ያልተወሰደው እርምጃ፤የኛን ተግባር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መስታወት ነው:: ልክ እንደ ፕሬዜዳንቱ አባባል ሁሉ እኛም ለዴሞክራሲ፤ ለመልካም አስተዳደር፤ለሰብአዊ መበት ለኢትዮጵያና ለሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት ያለንን ምኞትና ፍላጎት እንናገራለን እንመኛለን፡፡ ያም ሆኖ ግን ያንን በመተግበሩ ላይ ግን አልተሳካልንም፤ ከሽፎብናል፡፡ፕሬዜዳንት ኦባማ በአሜሪካ ብሔራዊ ፍላጎትና ደህንነት አተኩረው ነበር ያደረጉትም ያላደርጉትም፡፡ እኛ ደሞ በግላችን ችግርና በግላችን ደህንነት ላይ ተወጥረን ነበር ያደረግነዉም ያላደረግነዉም፡፡

በሶማሊያና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በነበረው የአልቃይዳ ችግር የኦባማ አስተዳደር፤ በኢትዮጵያ ያለውን የፍትሕ፤ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት እጦትን ወደ ጎን ብሎት ነበር፡፡ በሶማሊያ ይካሄድ የነበረውን ጦርነት በመለወጥና የድሮን (አሮፒላን) ጣቢያዎች በመዘርጋት አጣዳፊውና የበሰለው ስትራቴጂ ነበር፡፡ በዚህም ሳቢያ የምርጫ ሂደቶች በገዢው መንግስት ሲጨናገፉና የምርጫው ውጤት ሲገለበጥና ተሸናፊውን አሸናፊ ሲያደርጉት፤ የነጻው ጋዜጣ አባላት ለእስር ሲዳረጉ፤ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ለግፍ እስር ሲዳረጉ አሜሪካ በሚያሳፍር መልኩ የአየሁትን አላየሁም የሰማሁትን አልሰማሁምን ዘዴ መረጠ፡፡ በኔ አስተያየት ያ ስህተት ነው፡፡ የአሜሪካ መንግስት በሶማልያ ሲያደርግ የነበረው ሽብርንና ሥብርተኞችን የመዋጋትና የማጥፋት ተግባሩ ጋር የማይተናነሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የታየውና አሁን በመታየት ላይ ያለው የዴሞክራሲ፤የሰብአዊ መብት፤ የመልካም አስተዳደርና የፍትህ ጉድለት በእኩል ደረጃ ሊታዩ ይገባ ነበርና ነው፡፡

አስቲ ደሞ እኛ ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሩካን የሆንነው በሃገራችን ስለፍትሕ፤ ስለሰብአዊ መብት፤ ስለዴሞክራሲ፤ስለመልካም አስተዳደር እጦት ባለፉት አራት ዓመታት ጊዜ ምን አደረግን?

በዚህ ጉዳይ ላይ ከመናገርና ለዚህም ሁኔታ ከመቆምና እነዚህን እሴቶች ተግባራዊነት ለማረጋገጥ አብዛኛዎቻችን ዝምታንና በታዛቢነት ራቅ ማለትን መርጠናል፡፡ አብዛኛዎቻችን በየግላችን የዴምክራሲንና የሰብአዊ መብትን ዋጋ ከፍተኛነት ስንነጋገር ስንመጻደቅ እንደመጣለን፡፡ያም ሆኖ ይህን እምነታችንን በአደባባይ ደፍረን ለመናገር ግን ሃሞታችን ይደክማል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ደፍረን የተናገርን እንደሆነ፤ በኢትዮጵያ ያለው ገዢ መንግስት ቤታችንንና ኢንቬስትመንታችንን ይወስድብናል ብለን እንፈራለን፡፡ ወደ ሃገር ለመግባትም ቪዛ ከመከልከል አልፎ ሃገር ስንገባም ሊያስረን ይቸላል በሚል ፍርሃት ታጥረናል፡፡ በዚህም የግል ጥቅማችንንና ፍላጎታችንን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃገር አቀፍ ጥቅም ፍላጎትና ደህንነት በላይ አድርገን አስቀምጠናል፡፡

ከዚህም የከረሩና መመለስ የሚገባን ሌሎች ጥያቄዎች አሉ፡፡ባለፉት 4 ዓመታት የኦባማ አስተዳደር በሃገራችን ላይ ስላለው የዴሞክራሲ፤ የሰብአዊ መብት፤ የፍትሕ፤ የመልካም አስተዳደር እጦት አስፈላጊውን እንዲያደርግ ምን ውጥረት ፈጠርንበት?

በአስተዳደሩ ድምጻችን እንዲሰማ ተባብረን በአንድነት ቆምን?

የሕገመንግሥታዊ መብታችንን ተጠቅመን በዙህ ጉዳይ ላይ አስተዳደሩ ተጠያቂነቱን አሳወቅነው?

በግልጽና ሃቅን በያዘ መልኩ እኛ የኦባማ አስተዳደር ያደረገው ትክክል አይደለም፤ አስተዳደሩ ቃሉን አላከበረም ለዚህም ብለን ጣታችንን ወደ ፕሬዜዳንት ኦባማ በምንቀስርበት ወቅት የሶስቱን ቀሪ ጣቶቻችንን አቅጣጫ ብንመለከት ወደራሳችን ማመልከታቸውን እንረዳለን፡፡

እርግጥ ፕሬዜዳንት ኦባማ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ስላከናወኑት ሁኔታ ቅሬታ ሊሰማን አግባብ ነው፡፡ የበለጠ ቅር ልንሰኝ የሚገባን ግን፤በራሳችን ጉድ ነው፡፡

ያገጠጠው እውነታ ግን በኢትዮጵያና በአፍሪካ ስላለው የዲክታተራዊ አገዛዝ የፕሬዜዳንት ኦባማ ሃላፊነት አይደለም እርግጥ ስለሁኔታው የሞራል ግዴታ አለባቸው ዲክታተሮችንም ደግፈው አብረዋቸው ሊቆሙ ተገቢ አይደለም፡፡ እንደ ፕሬዜዳንትም የአሜሪካንን ደህንነትና ፍላጎት ማስቀደም ተገቢ ነው፡፡እኛም የራሳችንን ፍላጎትና ደህንነት እንደምናስቀድመው ሁሉ፡፡ ለሁሉም ሚዛን ልናበጅለት ይገባል፡፡ማንም ቢሆን በመስታወት በተገነባ ቤት ውስጥ እየኖረ ድንጋይ ለመወርወር ቀዳሚ ሊሆን አይገባም፡፡

ፕሬዜዳንት ኦባማ ስለሰብአዊ መብት ከምርና ከልባቸው አስፈላጊነቱን ያምናሉ፡፡ ተግባራዊ ማደድረጉ ግን አስቸጋሪ ነው፡፡ባለፈው ስፕሪንግ፤ ሁኔታውን ረጂምና አድካሚ ትግል መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ‹‹የሲቪል ራይት እንቅስቃሴ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ለሴቶች መብት ድምጽ ማግኘትም አስቸጋሪ ነበር፡፡ለሰራተኛው ክፍል መሰረታዊ ጥበቃ ማስገኘትም አስቸጋሪ ነበር፡፡በዓለም ዙርያ ጋንዲም ማንዴላም ያደረጉት ሁሉ አስቸጋሪ ነበር፡፡ጊዜ ይወስዳል፡፡ከአንድ ትርም የበለጠ ጊዜ ይወስዳል፡፡ከአንድ ፕሬዜዳንት የበለጠ ይጠይቃል፡፡ከግለሰብም የበለጠ ሃይል ይፈልጋል፡፡የሚያስፈልገው ዕምነተ ጠንካራ የሆኑ ተራ ዜጎች፤ሃገራችን ወደ ክፍተኛው ጣሪያ ለማድረስ ሳይደክሙና ሳይሰለቹ ተስፋ ሳይቆርጡ የሚቆሙትን ነው፡፡”

ሰብአዊ መብትን በአፍሪካም ሆነ በኢትዮጵያ ለመጠበቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ለኔልሰን ማንዴላ አስቸጋሪ ነበር፤ ለኦባማም አስቸጋሪ ነው፡፡እንደኛ ያሉ ዜጎችን ታግለውና በቆራጥነት ቆመው በኢትዮጵያና በአፍሪካ ለተግባራዊነቱ የሚሟገቱና እውን ለማድረግም የማይታክቱ የዜጎችን  ቆራጥ ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡

ኖቬምበር 6፣ 2012እናስታውስ

በኖቬምበር 6 አንድ ጥያቄ ይጠብቀናል፡፡ ጥያቄው በኢትዮጵያ ስላለው ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት እጦት አይደለም፡፡ ጥያቄው በአሜሪካ ምን አይነት ሕብረተሰብ እንፈልጋለን የሚለው ነው፡፡ ፕሬዜዳንት ክሊንተን እንዳሉት፤ ‹‹ ከፈለግህ ብቻህን ነህና በራስህ ተወጣው››ን ከሆነ ምርጫህ የሪፓብሊካንን ቲኬት ቆርጣችሁ ተጠጋጉ፡፡ የእኩልነትና የጋራ እድልን ለመቅሰም የምትመርጡና የጋራ ሃላፊነትን ለመውሰድ ካሰባችሁና ‹‹በአንድነት እንወጣውን ሕብረተሰባዊ ስብስብ ካሰባችሁ ድምጻችሁን ለባሮክ ኦባማ ስጡ፡፡” በሚለው ሃሳብ እስማማለሁ::

የፕሬዜዳንት ኦባማ ሲናገሩ “የአሜሪካ  ህዝብ ሆይ ይህ ጉዞ ቀላል ይሆናል አላልኩም፤አሁንም ቢሆን አልልም፡፡አዎን፤ መሄጃችን አስቸጋሪ ነው፤ ሆኖም መድረሻችን የተሻለ ነው፡፡ አዎን ጎዳናችን ረጂም ነው ግን በአንድነት እንጓዘዋለን፡፡ ወደኋላ አንመለስም፡፡ ማንንም ወደ ኋላ እንተውም፡፡ተያይዘን በመደጋገፍ አብረን እንዘልቃለን፡፡ከድላችን ጥንካሬ እናመርታለን፤ከስህተታችን እንማራለን፤ ዕይናችንን ግን ባሻገር ባለው ጠፈፍ ላይ እናተኩረዋለን፡፡ደስታ ከኛ ጋር ነውና፡፡እናም የዚህ የተባረከ ሃገር ዜጎች በመሆናችን የተባረክን ነን፡፡”

በኖቬምበር 6 ለባራክ ኦባማና ለጆ ባደን ድምጼን እሰጣለሁ:: ምክንያቱም የዚያ ዕድልን በመካፈል ሃላፊነትን የሚወጣው የአሜሪካ አካል መሆንን ስለምመርጥ ነው፡፡ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማን የምመርጠው ፍጹም ስለሆኑ ሳይሆን ሁሉም ጥቅምን በመካፈል፤ ሃላፊነትን የሚወጣ ፤ የተባበረና የተስማማ የአሜሪካንን ሕብረተሰብ ለመገንባት ቀና አቅጣጫ ስለያዙ ነው፡፡ ‹‹ሁላችንም በአንድ ላይ ለአንድነት የቆምን ነን::››

ፕሬዜዳንት ኦባማ በሚቀጥለው 4 ዓመታት ምን ማድረግ እንደሚገባቸውና  ከማረፋቸው ብዙ ጎዳና መጓዝ እንዳለባቸው ይገነዘባሉ፡፡ ገጣሚው ሮበርት ፍሮስት ቅኔያዊ በሆኑ ቃላቶች እንዳስቀመጠው ‹‹ጥሻው ወበት ፈሶበታል፤ጭለማና ጥልቀት ያለው፡፡ እኔ ደሞ ቃል ለምድር ለሰማይ ብዬ ቃሌን ሰጥቻለሁ፡፡ ስለዚህም ከመተኛቴ ማረፌ በፊት ብዙ ጎዳና ይጠበቅብኛልና፡፡

ፕሬዝዳንት ኦባማ አሁንም የሁሉንም ትውልደ ኢትዮጵያ አሜሪካናውያን ያልተቆጠበ የድምጽ ድጋፍ በኦሃዮ፤ቨርጊኒያ፤ፍሎሪዳ፤ሰሜን ካሎራይና፤ኮልራዶ፤ሚቺጋን፤ኔቫዳ፤ዊስኮንሲን እና በተቀረውም የአሜሪካ ግዛት  ሊያገኜ ይገባል፡፡ ሁለኩንም አንባቢዎቼን ፕሬዜዳንት ባሮክ ኦባማ በድጋሚ ምርጫ ለድል እንዲበቁ እጠይቃለሁ፡፡ አዎን አሁንም ይቻለናል…

የተተረጎመው ከኢንግሊዘኛው ጽሁፍ:  http://open.salon.com/blog/almariam/2012/09/09/why_i_am_supporting_president_obamas_re-election

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

በኢትዮጵያ ወቅቱ ወደፊት መራመጃ ነው

Friday, September 7th, 2012

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም

ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

በኢትዮጵያ ወቅቱ መጥረቢያውን ቀብሮ ወደፊት መራጃ ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት ‹‹ከጠላትህ ጋር ሰላምን መመስረት ከፈለግህ፤ከጠላትህ ጋር አብረህ መስራት አለብህ በዚህን  ጊዜ ጠላትህ አጋርህ ይሆናል፡፡›› እኔ ደግሞ ትንሽ ላክልበትና፤ጠላትህ ወዳጅህና ተባባሪህ ይሆናል፡፡ከታሪክ እንዳየነው፤ ብሔራዊ አሜሪካኖች (አሜሪካን ኢንዲያንስ) በመሃከላቸ ሰላምን ሲፈጥሩ፤መጥረቢያቸውን፤ መቁረጫቸውን በመሬት ውስጥ ይቀብሩታል:: ይህም በመሃላቸው ተነስቶ የነበረውን አለመግባባት መቋጨቱን ማረጋገጫ ነው፡፡ዛሬ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ያንን የጎሳ ክፍፍሉን፤የሃይሞኖት ልዩነቱን፤የሰብአዊ መብት ጥሰትን እርግፍ አድርገው ማጥፋታቸውን ለማረጋገጥ መጥረቢያቸውን መቅበር ይገባቸዋል እላለሁ፡፡ አሁን እጅ ለእጅ ተጨባብጠን፤እርስ በርሳችን ተቃቅፈን፤ሁለንተናችንን ለአዲሲቱ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ፤ የሕግ የበላይነት የተከበረባት ኢትዮጵያ፤ሰብአዊ መብት የተጠበቀባትና ዴሞክራቲክ ስነስራት የተከበሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት መዋል ይገባናል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ በመክፈት ጥላቻንና ቂም በቀልን ወደ ኋላ በመተው የምንቀጥልበት ወቅት ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው መሆን ያለበት፡፡ እራሳችንን ካለፈው የመከራ ሸክምና ካሰረን የሰንሰለት ቋተሮ አላቀን ለትውልድ ሲያመን የነበረውን ቁስል በማከምና በማዳን ከእንግዲህ ፈጽሞ ያለፈውን በማመንዠክ የምንም ሁኔታ እስረኞች ላለመሆን ለመጪው ትውልድ ልናረጋግጥለት የሚገባን ዛሬ ነው፡፡ ማንዴላ ‹‹በእልህ  የጠጡት መርዝ ጠላቴን ይገድልኛል ብሎ እንደማሰብ ነው››  ብለው ነበር፡፡ ማንዴላ የእልህን መርዝ በመጠጣት አይደለም አብዛኛዎቹን ‹‹ከጠላቶቻቸውን››ይበልጥ በመኖር ያሸነፉት::  አሁንም በሕይወት ቆይተው 94ኛውን የዕድሜ ክልላቸውን እያጣጣሙት ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ አካባቢና በዲያስፖራው አካባቢ በርካት እልሆች አሉ፡፡ በአብዛኛዎቹ ውስጥ ለጊዜው ዝም ያሉና ያንቀላፋ በመቁሰልና በሽንፈት የተበለጡ የሚመስላቸው በርካቶች አሉ፡፡ በሌላ ጎን ደግሞ በድል አድራጊነት ተኮፍሰው፤በሌሎች ችግር ጮቤ የሚረግጡና የሚደነፉ አሉ፡፡ ከዚያ ባለፈ ደግሞ ምንም አይመለከተንም በሚል ወደጎን ዞር ብለው የሚኖሩ ይገኛሉ፡፡ ያለፈውን ሁሉ ትቶ  ታሪካዊ ጥላቻን ከውስጥ የማውጫው ቀን አሁን ነው፡፡ ምሬትን ከውስጣችን አውጥተን መጣያው ቀን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡ ተፎካካሪዎቻችንን ወደሰላማዊ አንድነት መጥሪያችን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡ መግባባት መጀመር ያለበት ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ አፋጣኝ የመልካም አስተዳደርንና የዴሞክራሲን እውነታ መገንባት የሚገባን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡

ዛሬ አፋጣኝ መሻሻልን በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ግንባታ ላይ እንጀምር

የቀድሞው ጠቅላይ መኒስትር መለስ ዜናዊ በ2007 ዓም ‹‹ራዕያቸው(ስጦታቸው) ኢትዮጵያን አንቆ ከያዛት የድህነት አረንቋ ማውጣት የሚቻለው በተመቻቸና ቀጣይነት ያለው ልማት ብቻ ሳይሆን በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ግንባታ ነው›› ብለው ነበር፡፡ ከምርና በዕውነት እነዚህን የመለካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ግንባታ ፈጣን መሻሻሎች መጀመር ያለብን ዛሬ ነው፡፡ እነዚህ መሻሻሎችም ፍጥነታቸው ከሁሉም የፖለቲካ እስረኞች መፈታት ጋር መጀመር ያለባቸውና: ጸረ ሽብርተኝነት የሚለውን አዋጅም በማስተካከል የሲቪል ማሕበረሰቡንና ሌሎችንም የሲቪል ማሕበረሰብ አሳሪ ህጎች በማሻሻልና በማስተካከል ለሕግ የበላይነት መከበር መጀመር ያለብን ዛሬ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች መለቀቅ አለባቸው፡፡ሁኔታቸው በአሜሪካን መንግሥት ሰበአዊ መብት ሪፖርት፤በተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ሰብአዊ መበት ተሟጋች ድርጅቶች ዘገባ ውስጥ በገሃድ ተቀምጠው ታይተዋል፡፡ የአሜሪካን ስቴት ዲፓርትመነት የሰብአዊ መብት ሪፖርት (ኤፐሪል 2011) ባሰፈረው እውነታ መሰረት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ወህኒ ቤቶች ያለውን ሕገ ወጥ ግድያ፤ ስቃይ፤ድብደባ፤የታሳሪዎችን አለአግባብ መሰቃየት፤የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በፖሊስ የሚደርስባቸውን ወከባና ግፍ የተሞላው አበሳ፤ በልዩ የፖሊስ ሃይልና ሚሊሺያዎች የሚሰነዘረውን ሕገ ወጥ ድርጊት፤ በወህኒ ቤቶቹ ያለውን ዝቅተኛና መኖር የማያስችል ሁኔታ፤የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችና መልካም አሳቢዎች አለአግባብ በዘፈቀደ መያዝ፤ያለፍርድ ለረጂም ጊዜ በወህኒ ቤት መሰቃየት……..›› በዝርዝር ተዘግቧል፡፡

በ2010 የሁማን ራይትስ ዎች የዓለም አቀፍ ዘገባ ስለ ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያ የፖሊስ ሃይል፤በጦር አባላትና በሌሎችም ተመሳሳይ አባላት፤በደህንነት አባላት በቅጣት መልክ በተቃዋሚ ደጋፊዎችና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ላይ የሚፈጸመው ስቃይና የእስረኞች የአያያዝ ሁኔታ አሳሳቢነትና መከራ የከፋ ከመሆኑም ባሻገር በሚስጣራዊ ማጎሪያዎች፤ በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ በእስር የሚገኙት ንጹሃን ዜጎች ሁኔታ አሳሳቢነቱ በየጊዜው እየከፋ የሚሄድ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የጸረ ቶርቸር(የስቃይ አያያዝ) ኮሚቴ (ኖቬምበር 2010) ዘገባው በፖሊስ አባላት በወህኒ ቤት ሃላፊዎች፤በደህንነት አባላት፤እንዲሁም በወታደራዊው ክፍል አባላት የሚደርሰውን ግፍና መከራ፤በፖለቲካ ተቃዋሚ አባላትና ደጋፊዎች፤በተማሪዎች ላይ፤ሽብርተኞች ተብለው በሚፈረጁ ላይ፤የተቃዋሚ ሃይላት ደጋፊዎች (የኦ ኤነ ኤል ኤፍን) እና የኦ ኤል ኤፍ ተጠርጣሪ ደጋፊዎች የተባሉትን ሁሉ በተለያዩ ቦታ በማጎር የሚደርስባቸውን ስቃይ በአግባቡ በመዘገብ ይፋ አድርጓል፡፡ ማጎሪያዎቹ ከታወቁት ማጎሪያዎች በተጨማሪ፤ ፖሊስ ጣቢያዎች፤ ወታደራዊ ካምፖችና ይፋ ያለሆኑ ቦታዎች ጭምር ዜጎች በግፍ እየታፈኑ እንደሚሰቃዩ ሪፖርቱ ጨምሮ ይፋ አውጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ ምን ያህል እስረኞች እንዳሉ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መበት ተሟጋቾች ሁኔታውን እንዲያዩም ሆነ ታሳሪዎችን እንዲያነጋግሩ አይፈቀድላቸውም፡፡የተለያዩ አካላት ግምታዊ ቁጥር ሲያስቀምጡ፤ ከብዙ መቶዎች እስከ አሰርት ሺዎች እንደሚደርሱ ይገምታሉ፡፡በቅርቡ የወጣው የጄኖሳይድ ዎች ሪፖርት የፖለቲካ እስረኞችን ብዛት በመቶ ሺህ አድርጎ አስቀምጦታል፡፡በየቀኑ የፖለቲካ ሰዎች፤ያለውን መንግስት የሚተቹ፤ተቃዋሚ ሃይላት፤ለእስር በመዳረግ ላይ ናቸው፡፡ባለፉት ዓመታት የኦ ኤፍ ዲ ኤም፤ የኦሮሞ ሕዝቦች ኮንግሬስ፤በፖለቲካ አመለካከታቸው ሳቢያ የተነሳ ቁጥራቸው የበዛ አባላት ለእስር ተዳርገዋል፡፡ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲ ተቃዋሚ አባላት አባሎቻቸው ለእስር እንደተዳረጉ አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ጋዜጠኞች፤የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ቆራጥና አልበገር ባዩን የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሩን አንዱ ዓለም አራጌን፤ዓለም አቀፋዊ ክብርና ሞገስ የተሰጣቸውን እስክንድር ነጋንና ርዕዮት ዓለሙን ኤዲትር ውብሸት ታየን ጨምሮ፤የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች፤የረጅም ዓመታት እስር ተፈርዶባቸዋል፡፡

የመልካም አስተዳርና የዴሞክራሲ አፋጣኝ ግንባታ ጸረ ሽብርተኝነት ተብሎ የተቀመጠውንም አዋጅ ቁ›. 652/2009 በሚገባ  መስተካከል ይገባዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ይሄ ሕግ የፖለቲካ ተቃዋሚ አባላትን ደጋፊዎችን አመራሮችን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ለማገትና ወደ ወህኒ ለመጣል በመሳርያነት ያገለገለ ነው፡፡ ሕጉ በሁሉም ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ተወግዟል፡፡የሁማን ራትስ ዎች ሕጉን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ለማፈን፤በነጻ የመንግስትን ፖሊሲ የሚተቹትን፤የሰብአዊ መበት ተሟጋቾችን ለማስደንገጫና ለማሰርያ መጠቀሚያ ነው በማለት አጣጥሎታል፡፡‹‹የጸረሽብርተኛነት ሕግ የተባለው ሕግ ሳይሆን መንግስት የሚፈራቸውንና ለስልታኔ አደገኞች ናቸው፤ ይቀናቀኑኛል ብሎ የሚያስባቸውን ንጹሃን ዜጎች ዝም ለማሰኛ የተቀረጸ የገዢው መንግስት የብረት መሳርያ ነው ይለዋል፡፡ ማንኛውንም ያለውን መንግስት ሂደትና ተግባር በገምቢ ጎኑም ሆነ መታረም በሚገባው አለያም ሕጸጹን በማንሳት የሚተቸውን በሙሉ ሽብርተኛ በማለት እየኮነነ ለእስር የሚያበቃ ነው ይለዋል፡፡

ይህ ህግ እንደሚለው: ማንኛውንም አይነት ጽሁፍ  ሽብርተኝነትን የሚያበረታታ ከሆነ ለእስር ያስዳርጋል፡፡ ማንኛውም ግለሰብ በሽብርተኝነት ከተጠረጠረ ሰው ጋር የዋለ ወይም ያነጋገረ አለያም የሱን ሃሳብ የደገፈ እራሱም እንደሽብርተኛ ይፈረጃል፡፡ ማንኛውም ሰው በተጠረጠረ ሰው ላይ አዎንታዊ አስተያየቱን ቢያሰፍር አለያም ሕጉ አላግባብ ነው የተተረጎመው በሚል አስተያየቱን ቢሰጥ እሱም ሽብርተኛ ነው ይላል ሕጉ፡፡ማንኛውም ቤተሰብ ጎረቤት ሽብርተኛ ብሎ የጠረጠረውን ወዲያውኑ ለፖሊስ ሳያሳውቅ ቢቀር በ10 ዓመታት እስር ይቀጣል ይላል ሕጉ፡፡ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ከሽብርተኛነት ተጠርጣሪ ጋር ሆነው ከተገኙ ለሽብርተኝነት እንዳሴሩ ተቆጥረው በሽብርተኝነት ይፈረጃሉ ይላል ሕጉ፡፡

በዚህ ጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ መሰረት አንድ ፖሊስ ማንንም የጠረጠረውን ዜጋ ያላንዳች ማስረጃና የፍርድ ቤትም የመያዣ ትዕዛዝ በዘፈቀደ ጠርጥሬዋለሁ፤ መስሎኛል፤ አይነ ውሃው አላማረኝም፤ በሚሉ ነጥቦች ሳቢያ በቁጥጠር ስር ሊያውለውና ለበርካታ ቀናት ሳምንታት ወራት በእስር ስር ሊያቆየው ሕጉ ይደነግግለታል፡፡ በዚህም መሰረት አንድ ፖሊስ የጠረጠረውን ሰው ንብረት፤ቤቱን፤የስልክ ጥሪዎቹን፤የሞባይል ግንኙነቶቹን፤ሬዲዮ፤ ፖስታ፤እና መሳይ ግንኙነቶችን የመጥለፍ የመቅዳት መብት በሕጉ ተደንገጎለታል፡፡ ፖሊስ ማንኛቸውንም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ባለስልጣን፤ባንክን እና የግል ድርጅቶችን፤ወይም ግለሰብን፤ዶኩሜንቶችን እንዲያስረክብ፤ምስክርነት እንዲሰጥ፤ያስገድደዋል፡፡አንድ የሽብር ተጠርጣሪ ያለፍርድ በወህኒ ቤት ለአራት ወራት ሊማቅቅ ደንቡ ያዛል፡፡ማንኛቸውም በመንግስት አቃቤ ሕግ የቀረበ ማስረጃ ሁሉ፤የማይታበል ሃቅ ተብሎ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ እንዲሁም ከተጠርጣሪው ላይ በማሰቃየትና በግርፊያ በድበደባ የተገኘ የ‹‹እምነት›› ቃል ምርጣሪውን በማሰቃየት የተገኘም የግፍ ወለድ ማስረጃም ቢሆን ተቀባይነት ያገኛል ይላል ሕጉ፡፡

ቀደም ብዬ የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ላይ ባሰፈርኩት አስተያየት፤ ሕጉ ዴሞክራሲያዊ የሲቪል ማሕበረሰብን መኖርም ጭምር የሚጻረር መሆኑን ጠቅሼያለሁ፡፡ አለመስማማትም ሽብርተኝነት ነው፡፡ማሰብም ሽብርተኝነት ነው፡፡በለካው አገዛዝ ላይ ስህተቱን መናገርም ሽብርተኝነት ነው፡፡የራስ ሕሊና ባለቤት መሆንም ሽብርተኝነት ነው፡፡ሰላማዊ ተቃውሞም ሽብርተኝነት ነው፡፡እራስን አለመሸጥና በአቋም መጽናትም ሽብርተኝነት ነው፡፡ለሰብአዊ መብትና ለዴሞክራሲ ጥብቅና መቆምም ሽብርተኝነት ነው፡፡ ለሕግ የበላይነት መቆምም ሽብርተኝነት ነው፡፡በሃገር ላይ ለሚሰነዘር ሽብርተኝነትም በሰላማዊ መንገድ መቃወምም ሽብርተኝነት ነው፡፡ማንም ቢሆን ስለሽብርተኝነት በቂ ግንዛቤ ሊኖረው ተገቢ ነው፡፡ኔልሰን ማንዴላ በደቡብ አፍሪካ በነበረው አፓርታይድ አገዛዝ ለ27 ዓመታት ሽብርተኛ ተብለው ነው ወደ ወህኒ የተጣሉት፡፡ ከእስር ሲለቁቅም ‹‹ትላንት ቴሬሪስት (ሽብርተኝ) ተብዬ ነበር፤ ከእስር ስለቀቅ ግን ሀለኩም ወገኖቼ አሳሪዎቼም ጭምር አቅፈውኝ ነበር፡፡ደጋግሜ እናገር እንደነበረው ሁሉ ለነጻነታቸው የሚታገሉ ሁሉ በሃገራቸው መሪዎች ሽብርተኞች ይባላሉ፡፡ እኔም ትላንት ሽብርተኛ ነበርኩ፤ዛሬ ግን ትላንት ሽብርተኛ ብለው በፈረጁኝ ሰዎች እደነቅ አያለሁ ነው ያልኳቸው፡፡ የ‹‹ጸረሽብርተኛ ሕግ›› የሚባለው ‹‹ሕግ›› መወገድ አለበት፡፡

የልግስናና ሕብረተሰብ አዋጅ ቁ. 621 2009 መወገድ አለበት፡፡ይህ ሕግ በመላው የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰበት አዋጅ ነው፡፡ ደንቡ መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በሰብአዊ መበት ጉዳይ እንዳይነቀሳቀሱ፤በጾታ ጥቃት ጥብቅና ላይ መንቀሳቀስን፤በሃይማኖት እኩልነት ጉዳይ፤አለመግባባትን በማስወገድ ሂደትና እንቅስቃሴ፤የፍትሕ ስርአቱን በተመለከተና የምርጫን ጉዳይ ሚዛናዊነትንም አስመልክቶ እንዳይንቀሳቀሱ ያግዳል፡፡ ማንኛውም ሃገር በቀል የእርዳታ ድርጅት ከ10 በመቶ በላይ ድጋፍ ከውጪ አካላት ካገኝ እንደውጪ ድርጅት ይቆጠራል ይላል፡፡ሃገር በቀል የሆኑት የእርዳታ ድርጅቶች ከሃገር ውስጥ ለእንቅስቃሴያቸው በቂ ገንዘብ ማግኘት ስለማይችሉና መንግስትም ለነዚህ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች የገንዘብ ድጎማ የሚያደርጉ ድርጅቶችንም ሆነ ግለሰቦችን በተቃዋሚ ደረጃ ስሚፈርጃቸው፤ ለእንቅስቃሴያቸው የሚሆነውን ገንዘብ ከውጪ ከማግኘት ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡ በአጠቃላይ ሕጉ የሃገር ውስጥም ሆኑ የውጪ መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ለጋሽ ድርጅቶች በብቃትና በነጻነት እንዲሁም የቆሙለትን ዓላማና ተረጂውን ሕዝብም ድጋፉን በበቂ እንዳያገኙ የሚያደርግ ሕግ በመሆኑ ድርጅቶቹን በደፈናውና በአጣቃላይ ሽባ የሚያደርግ ደንብ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳትም ሕጉ ሲታይ በሥራ ላይ ያለውን ሕገመንግስት የሚቃረንና የማያከበር ደንብ ነው፡፡ ይህ ሕግ አብዛኛዎቹን የሕገመንግስቱን ደንቦች፤ሃሳብን በነጻ የመግለጽን መብት በነጻ መሰብሰብን በማሕበር መደራጀትን፤መንፈጉን በርካታ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የተጩበት ጉዳይና ሕግ ነው፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያ በመስቀለኛው ጎዳና ላይ ቆማለች፡፡ አፋጣኝ የዴሞክራሲ እድገት፤መልካም አስተዳደርን፤አስተማማኝ እርምጃዎችን በመጀመር በዴሞክራሲ መንገድ መጓዝ ይገባል፡፡ አለያም የኢትዮጵያ ምርጫው  የኋልዮሽ በመንሸራተት ወደባሰው የጭቆና አምባገነን ስርአት መጓዝ ይሆናል፡፡ ወይም በነጻ ዝላይ መልክ ወደምስቅልቅልና ብጥብጥ ትገባለች፡፡ ምርጫው የእኛ ነው፡፡ ሁላችንም ልንማረው የሚገባን እጅጉን አስፈላጊ ትምህርት አለን፡፡ አሁን በስልጣን ላይ ያሉትም ህሊናቸው ጋር ተገናኝተውና ተስማምተው ለሕሊናቸው ተገዢነትን ማረጋገጥ መቻል አለባቸው፡፡ ‹‹ሰላማዊ የለውጥ አብዮትን የማይቻል የሚያደርጉ ከሆነ፤የግዴታ አብዮትን አይቀሬ ማድረጋቸውን ሊገነዘቡት የግድ ነው፡፡” ሌሎችም ማርቲን ሉተር ኪንግ በአንድ ወቅት ለታዋቂው የጥበብ ሰውና የሰብአዊ መበት ተሟጋች ለሃሪ ቤላፎንቴ ስለዘሮች አንድነት መዋሃድ የተናገሩትና ማስታወስ ይኖርባቸዋል፡፡ ‹‹ፍርሃቴ ሕዝቦቼን በመቃጠል ላይ ቀዳለ ቤት እያወሃድኳቸው ነው፡፡ በዚህ አባባል ማርቲን ሉተር ኪንግ ያሳሰቡት የዘር ልዩነትን በማጥፋት ሂደት ሊከሰት የሚችለውን አለመግባባትና ብጥብጥ ማለታቸው ነበር፡፡ቤላፎንቴም ‹‹ታዲያ ምን ማድረግ ይኖርብናል›› ሲሏቸው፤‹‹እኛ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ልንሆንና ቤቱን ከቃጠሎ ማዳናችን ተገቢ ነው›› በማለት ነበር ኪንግ የመለሱት፡፡‹‹ሁላችንም ኢትዮጵያውያን የእሳት አደጋ ተከላካዮች በመሆን ፈጣኑን እድገትና መልካም አስተዳደር እንዲሁም የዴሞክራሲን እውነታዊነት ጎዳና ማረጋገጥ ያለብን ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው!››

Translated from Ethiopia: Time for Radical Improvements

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

አቶ መለስ እልፈት ስንብት

Wednesday, September 5th, 2012

ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም

ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

ከ275 ሳምንታት በላይ አንድም ሳምንት ሳላቋርጥ ረጃጂሞችና አስረጂዎች የሆኑ አስተያየቶች በመልካምና ጎጂ ጎኑም ጭምር በኢትዮጵያ ላይ ቁንጮ ባለስልጣን በነበረውና ሁለት 10ት ዓመታት ባሳለፈው ሰው ላይ ጽፌያለሁ፡፡መለስ ዜናዊ አልፏል፡፡ የሞቱ መንስኤ ግን በመንግሥት ጥብቅ ሚስጥርነቱ እንደተቆለፈ ነው ያለው፡፡

መለስ ስለፈጸመውና ስላመለጠው ጉዳይ በሕይወት ዘመኑ እያለ በብቃት ያነሳሁት ስለሆነ አሁን ከህልፈቱ በኋላ ብዙም የምለው የለኝም፡፡ ሕልፈተ ሞቱ ያሳዝነኛል፤ ምክንያቱም፤ ጆን ዶን እንዳለው ‹‹የማንም ሰው ሞት ያሳንሰኛል፤ ምክንያቱም እኔም ቁጥሬ ከሰብአዊያን ጋር ነውና ፡፡ሞት ለሁላችንም በእኩል መንገድ መጪ ነው፡፡ሲመጣም ሁላችንንም በእኩል ደረጃ ያስቀምጠናል፡፡›› እንደ ሃቀኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፤የለየለት ፈላጭ ቆራጭ ባለ ስልጣን ቢሞትም ያሳዝነኛል ምክንያቱም በሰብአዊ መብት ጉዳይ፤በፍትሕ ሚዛናዊነት ላይ፤በእኩልነት ላይእና በመሳሰሉት  ላይ ሲጓደሉ ለሙግት በመሰለፌ ነው፡፡

መለስን የምሰናበተው በሃዘን ወይም በክስ ሳይሆን ይልቅስ ያመለጠን እድል በማሰብና የወደፊት ተስፋን በመመኘት ነው፡፡ የወደፊት ኢትዮጵያን ህልውና ግንባር ቀደም በማድረግ ነው፡፡

መለስ ዜናዊ ዕድል ዕጣ ያወጣችለት ሰው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ዕጣ ፈንታ ታሪካዊ ሚና እንዲጫወት መርጦት ነበር፡፡ለ17 ዓመታት ሃገራችንንና ሕዝቦቿን ለግፍና ለመከራ ለስቃይ ዳርጎት የነበረውን ወታደራዊ አገዛዝ ታግሎ ያሸነፈው ጎራ አባል ነበር፡፡ መለስ በድሉ ወቅት ዴሞክራሲን በሃገሪቱ ለማክበርና ልማትን ለመዘርጋት፤ቃል ገበቶ የነበረ ቢሆንም፤ ዓመታት ተቆጥረው ባለፉ ቁጥር የተገባው ቃል መፍረስም እንዲሁ እያለፈና እየተካደ ሄደ፡፡መለስ በዚህ ወቅት ከመልካም ምግባርና ቃል ከማከበር ባህል ጋር ጨርሶ በመለያየት፤የባሰ ጨቋኝ፤ የከፋ ፈላጭ ቆራጭ፤ የለየለት ከፋፋይ፤ ጭርሱን ሃሳብ ላለመቀበልና እኔን ብቻ ስሙኝ የኔን ብቻ ተቀበሉ ማለትን አብሮ ካስወጣው ጨቋኝ አገዛዝ የባሰ የለየለት ደክታተር ሆነ፡፡ በመጨሻው የግዛት ዘመኑ ሃገሪቱን ወደ ፖሊሳዊ አስተዳደር በመለወጥ በሰላዮች የታጠረ መንግስት ፈጥሮ ዘመናዊ  የዋጋው ጣሪያ መጠን ባጣ የቴክኒዮሎጂ ውጤት በመጠቀም፤ሕዝቡን ረገጦ የሃገሪቱን ሃብት አሟጦ በባዶ ካዝና መግዛቱን ቀጠለ፡፡ የፕሬስን ነጣነት አፈነ:: የሲቪል ሶሳዬቲውን ላይፈታ ከረቸመ፤ተቃዋሚዎችን በመላው ተስፋ በማስቆረጥና የትግል ሜዳውን በማጥበብ ብሎም በመዝጋት ሰነከለ፡፡ ፍርሃትና ጥላቻ በሕብረተሰቡ ውስጥ እንዲነግስና መተማመን እንዲጠፋ መረቡን ዘረጋ፡፡ ይህ ደግሞ በከተማዎች ብቻ ሳይሆን በሃገሪቱ ክልሎች በመላው ነበር፡፡ በ1991 ከጫካ ሲመጣ ይዞት የመጣውን የውጊያ ሳንጃውን ወደ አፎቱ ሳይመልስ መለስ መፈራትንና መጠላትን በአንድነት ተላበሰ፡፡ መለስ በተቅናቃኞቹንና ነቃፊዎቹ ያልተወደደና ተቀባይነት የሌለው ሰው ነበር::  ከአጃቢዎቹና በጥቅም ገዝቶ ከሚያሽከረክራቸው ዘንድ ግን መለስ እንደዓምላክ፤ቅዱስ ቅዱስ የሚባል፤ አመራሩ እንከን የለሽ የሆነ፤ የግድያ አፈናና እስራት ትዕዛዙ የተባረከ ነው በማለት ያገዝፉት ነበር፡፡ በመጨረሻውም የግዛት ዘመኑ፤ መለስ በፍጹም አምባገነን ስልጣን የሚገዛ በመሆን በስልጣኑ አለአግባብ የሚጠቀም ጀብደኛ ሆኖ ነበር፡፡ይህንኑ ስልጣኑን ይበልጥ ለማጠንከር ሲዳክር፤ ተወዳዳሪ የሌለው በሌሎችም ሀገራት እንደምሳሌ በመጠቀስ አርአያ ሊሆን የሚችልበት ዕድሉ ጋር ተላለፉ፡፡

ባለፉት 21 ዓመታት ተስፋ ከተጣለበት ዴሞክራሲያዊ አስተዳዳሪ ሊሆን ከመቻል ይልቅ፤ወደለየለት ፈላጭ ቆራጭ ዲክታተርነት የተገለበጠው መለስ ዜናዊ ማን ነበር? በሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ የምንከሰውና የምንወቅሰው፤ወንጀለኛው የሰው ልጅ ጠላት የሚባለው ማነው?  ሲኤን ኤን በቅርቡ እንደገለጸው ባህሪው በሃገራችን የዴሞክራሲን መወለድ ያጨነገፈውና ‹‹ለአፍሪካዊ ፖሊስ ስረአት አገዛዝ›› ተጠያቂ የሆነው ግለሰብ ማነው? ያንን የምስኪኖች ሃገር ለድህነት ሕዝቡን ለስደትና ለመከራ ተጠያቂ ሆኖ የሚነሳውስ እሱ ብቻውን ነውን? ምናልባትም ይህን ጥያቄ እንዴትና በምን ሰበብ ይህ እስከ መለስ ሕልፈት ድረስ ሲሞግተውና ስህተቱን ነቅሶ እያወጣ ያሳየን ሰው አሁን ከሞተ በኋላ ያነሳዋል እንዴት ነው   ሊባል ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ዕውነቱ መነገር ስላለበት ነው፡፡

ላለፉት 21 ዓመታት እኛው ነን መለስን ጉልበት የሰጠነው፡፡ እኛ ፈሪዎች ሆነን ነው እሱን ያጀገነው፡፡የሱ የክፋቱም ሆነ የዘረኝነቱ አበራቾች እኛው ነበርን፡፡ እኛው ነን ለመለስ በርሃባችን፤ በችጋራችን፤ ሰበብ ሆነን በሚሊዮን የሚቆጠረውን ዶላር እንዲያጋብስ ያደረገንውና ብክነቱን ወንጀሉን ኢሰብአዊነቱን እየመዘገብንና እያስመዘገብን፤ የሰብአዊ መብት ጥሰቱን በማስረጃ እያስደገፍን በማቅረብም በየዓመቱ መሳርያዎቹ ነበርን:: እኛ ስል እኛ የመለስ ፓርቲ አባላትና ተባባሪዎች ነን::  የፍትሕ መድረኩን የአዞ ፍርድ ቤት እንዲያደርገውና፤ እንዲያስር እንዲፈታ ከዚያም አልፎ 99.6 በመቶ ድል ገጠመኝ ሲል ሆ ብለን አጨብጭበን ማሕተማችንን በመርገጫ አርጥበን ይሁንታውን የሰጠነው፡፡ እኛው ነን በፖሊስነት በስለላው መረብ በማገልገል፤ በጦሩ ውስጥ በመሰለፍ ንጹሃን ዜጎችን እንዲረሸኑ ምላጭ የሳብን፤ እኛው ነን፡፡ እኛው ምሁራኑ አይደለንም እንዴ  መለስን ብቻውን እንዲሆንበትና እንዳሻው በመሰለው ሲያዝበት ምን አገባን ብለንና ጎመን በጤናን መርጠን ልክ አይደለም ማለትን የፈራነውና ለአላማ መቆምን ችላ ያልነው? በብሩሁ የዴሞክራሲ ጎዳና ለመጓዝ የተጀመረውን የተስፋ መንገድ እኛው ተቃዋሚቆች አይደለንም እንዴ እርስ በርስ በመጣላትና ከሃገርና ከሕዝብ እራሳችንን እና የራሳችን ከፍ ከፍ በማስቀደም በሚሊዮን የሚቆጠረው ደጋፊያችን እንድንመራው ሃላፊነት ሲጥልብን ሸብረክ ብለን ከንቱ ያደረግነው፡፡ እኛ በዲያስፖራው ያለን አይደለንም እንዴ ዝምታን መርጠን ሃለፊነት የጥቂት ብለን የግብር ይውጣ አድርገነው ጩኸቱን አንዳንሰማ ጆሯችንን ደፍነን እንዳንናገርበት አፋችንን ሸብበን፤ ጥቂቱ ሲጮሁና ሲደክሙ ብዙዎችችን ገለል ብለን የሕዝቡን ሞትና ስቃይ ያገለልነው፡፡ እኛ ግለሰቦቹስ አይደለንም እንዴ መለስ እንዳሻው ሲፈነጭ ተው ለማለት ብርታቱንና ፈፍቃደኝነቱን አጥተን ሃገርን ለድህነት ሕዝብን ለችጋር ያጋፈጥነው፡፡ ማንኛችንም ከሃጢአቱ ንጹህ ነን ብለን እጃችንን ማጠብ አይቻለንም፡፡መለስ አውቆ ሲሳሳት ለመናገር ሳንፈልግ ከችሮታው ለመቋደስ መርጠን ላለፉት 21 ዓመታት ዝም ያልነውም በምንም መንገድ ከተጠያቂነት መቼም ይሁን መቼ ልናመልጥ ከቶ አይቻለንም፡፡ ስለዚህም ለተፈጠረውና ለተከናወነው ሁሉ ጣታችንን ወደ መለስ ስንቀስር ሶስታ ጣቶቻችን ወደራሳችን ማመልከታቸውን ልንዘነጋው አይገባንም፡፡

መለስ እጅጉን ሲበዛ እራስ ወዳድ የሆነ የሥላጣን ጥመኛ ነበር:: ያውም የሥልጣንን አንድ ጎን ብቻ ያወቀ፡፡ከእውነት ጋር ጨርሶ ያልተግባባ በመሆኑ እውነተኛ ሃቅ ከሕዝብ ፍቃድ የሚገኝና ሕግንም በተከተለ መንገድ ብቻ የስልጣንን ትግበራ ማካሄድ እንደሚቻል ጨርሶ አላወቀም ነበር፡፡ የመኖርና ያለመኖርን ሃይል በጁ የያዘ  ሆኖ አጠቃቀሙ ላይ ግን ባለመኖር ላይ እንዲያደላ ያደረገ፡፡ ፖሊሱም፤ ዳኛውም፤ከሳሹም፤ አቃቤውም ፍትሁም፤ ፍርዱም፤ ሰቃዩም፤ ሁለመናው እራሱ መለስ ብቻ ነበር፡፡መለስ ባለሙሉ ስልጣንነቱ የማይደፈር የማይገረሰስ ዘልአለማዊ እንደሆነ አድርጎ አሳምኖ አጃጅሎት ነበር፡፡ከዕድል ጋር የነበረውን ታላቅ ቀጠሮ ሳተው፡፡

ባይልለት ነው እንጂ መለስ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት መሪ ሊሆን ይችል ነበር፡፡በታሪክ ያወቅናቸው በርካታዎቹ ዲክታተሮች ታላላቅ መሪዎች ነበሩ፡፡ ታላቅነታቸው የተገኘው በሕዝቦቻቸው ላይ ባሳደሩት ተጽእኖና ክፋት ነው፡፡እንከን የሌላቸው መሪዎች ታላቅነትን የሚያገኙት ሕዝብ ይወዳቸዋልና ነው፡፡ የታላቅነታቸው ምንጭ በልባቸው ግልጽነትና ርህራሄ ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ተወዳዳሪ የሌላቸው እንከን የማይገኝባቸው የተትረፈረፈ የሕዝብ ፍቅር ያላቸው ተወዳጅ  መሪ ናቸው፡፡ ዛሬ ማንዴላ የሰብአዊነት አርማ ሆነው ይታያሉ፡፡ማንዴላን ለዚህ ያበቃቸው  ስብእናቸው፤ የንግግር ችሎታቸው፤የአስተዳደር ብስለታቸውና አመራራቸውም ሳይሆን እሳቤያቸውን ጭንቃቸው የሌት ቀን ጥረታቸው ስለ ሕዝቦች በመሆኑና ስለ ስልጣን አለመጨነቃቸው ነው፡፡ ማንዴላ አንዲት ዘለላ የፍቅር ዘር ከልባቸው አውጥተው የዘር ጥላቻና መለያየት ቂም በቀልን ሊያጠፋ በሚችል መልካም ምግባርና ፈቃደኛነት፤መቻቻልና ትዕግስት ላይ በመትከላቸው ነው፡፡ዓለም በደቡብ አፍሪካ በሚፈሰው የጥቁርና ነጭ ሰዎች ደም መፍሰስ ሲዳላና ሲተርት ማንዴላ ጥቁርና ነጭ ደቡብ አፍሪካውያንን አንድ ላይ በማሰባሰብ፤በእርቀሰላም ጠበል በማጥመቅ አንድነታቸውን መሰረቱላቸው፡፡ ሠላም ብለው ሁሉንም ለሠላም አሰለፉ፡፡ጥላቻን ከስሩ ነቅለው ጣሉና አስጣሉ::

መለስ ከዕድል ጋር ቀጠሮ ነበረው፡፡በማንዴላ ጫማ ውስጥ ሆኖ የእግራቸውን ፈለግ በመከተል ታሪክ ሰርቶ ታሪከኛም ሊሆን ይችል ነበር፡፡ጠንካራና አንድ ግንባር የፈጠሩ ኢትዮጵያንን ማጠናከርና ዕውነት የነበረውን መልሶ ማረጋገጥና የፈረሰውን መገንባት በቻለ ነበር፡፡በብሔር ተራርቀው እንዲተያዩ ያደረጋቸውን መልሶ ለማገኛኘትና ለማዋሃድ ድልድዩን የመስራት አቅም ነበረው፡፡እሱ ግን የዜጎችን መለያየትና በጎሪጥ መተያየታቸውን መረጠ፡፡ይህ ተጋጊጦና ቀለም ተቀባብቶ የተሰራው መንገድ ደግሞ ለሕብረት ሳይሆን በተለያየ እርባና ቢስ ጎዳና የሚያስኬድ ሆነ፡፡ የሚገነባው ድልድይ ሁሉ ድጥ የሞላበት፤ ግድቡም ገደብ የመኮገተው ሆነና ለውጪ ሰዎች የሃገርን መሬት ቆራርሶ መቸርቸርን አስከተለ፡፡ይህም በልማት ስም በቅንጥብጣቢ ሳንቲሞች አሳልፎ የተሰጠና የጠፋ ጠፍ መሬት ሆነ፡፡ መለስ ከዕድል ጋር ኢትዮጵያን በአንድነት ለመገንባት የነበረውን ቀጠሮ አመለጠው፡፡

መለስ ከዕድል ጋር ቀጠሮውን ቢያከብር ኖሮ ምሳሌ ሊሆን የሚገባ መሪ ብቻ ሳይሆን፤በሥራውም ሆነ በውጤቱ ሊጠቀስም ይችል ነበር፡፡ለቁጣ ፈጣን በሰሩ ለነበሩትም ቀና ስሜት ያልነበረው ነበር፡፡ በ2008 ብርቱካን ሚዴቅሳን ሲያስር፤‹‹ብርቱካንን ለመፍታት አንዳችም መግባባት የለም ጨርሶ አራት ነጥብ፡፡ ያለቀ የደቀቀ የሞተ ጉዳይ ነው፡፡›› ብርቱካን አንዳችም ስህተት አልፈጸመችም ነበር፡፡በዓለም አቀፍ እውቅናን ያላቸው ጋዜጠኞች ሰርክ ዓለምና እስክንድር በወህኒ ቤት ለተወለደው ከጊዜው በፊት ለመጣው ልጃቸው የማቆያ መሳርያ ተጠቃሚነትን መከልከል፤ለሰብአዊነት እንደሌለው ጭፍን አመለካከት በገሃድ ያሳያል፡፡ ለአሜሪካን ዲፕሎማቶች ‹‹ ተቃዋሚውን ወገን ባለ በሌለ ሃይላችን እንደቁሳቸዋለን›› በማለት ገደብ የለሽ ፉከራውን ሲያሰማ ዋጋ ቢስነቱን አሳወቀ፡፡ከአካኪ ዘራፍ ይቅር ማለትን በስልጣን ላይ በነበረበት ማሳየቱ የበለጠ ጠቀሜታ ነበረው፡፡ይልቅስ ቂም በቀልን መረጠ፡፡ መለስ የማንዴላን ፈለግ በመከተል፤ ከተቀቃዋሚዎች ጋር በመስራት ጠላቶቸሁን ወዳጅ አድርጎ ሊያሰልፍ በቻለ ነበር፡፡ በዚህም ዕድል ሊፈጥርለት ከሚችለው ቀጠሮ ጋር ተለያየ!

በቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመን፤ በደህነነት፤በግል የኤኮኖሚ ግንባታ፤ በዋስትናም ጭምር የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፍ ለማድረግ በሚያስችል ዕድል ላይ መለስ ቀጠሮ ነበረው፡፡መለስ‹‹በኤኮኖሚ ዕድገትና በዴሞክራሲ በታሪክም በቲዎሪም ቀጥታ ግንኙነት የለም››ብሎ ያምን ነበር፡፡ ሕዘቡ መሰረታዊ መብቱን እየተገፈፈ፤ ወደ ግጭት እየተመራ፤ግጭትንና ጦርነትን እንዲያስብ እየሆነ እንዴት ተደርጎ ነው ዘላቂነት ያለውን እድገት የሚያመጣው፡፡ የሰበአዊነት መሰረቱ ክብሩ ነው፡፡ሆድን መሙላት ላይ ብቻ ያተኮረ ግን አይደለም፡፡እርግጥ የተራበ ሰው ቁጡና ግልፍተኛ ነው፡፡የዚያ የተራበ ሰው ዓላማ ግን ፍርፋሪ ማግኘት ብቻ ሳይሆን የሕሊና ነጻነትና ክብሩንም ማግኘት ነው፡፡

የድሆች ድሀ፤እና የቱጃሮች ቱጃር ከምንም በላይ ከምግብም አስቀድመው ክብራቸውን ይናፍቃሉ፡፡ከእሩብ ምእተ ዓመት በፊት በሃገሪቱ የተከሰተውን ርሃብ በተመለከተ ዘገባ ላመቅረብ በቦታው የተገኘው የምእራቡ ዓለም ጋዜጠኛ እንደዚያ በመሰለ ረሃብና ችጋር ውስጥ ያለው ሕዝብ ለዕደላ ቢሰለፍም ክብሩንና ኩራቱን እንደተላበሰ ነበር እንጂ እንደርሃቡ አስከፊነት በመንሰፍሰፍና በመሽቀዳደም ለዕርዳተው ሲታገሉ አልታዩም፡፡ጋዜጠኛውን ያስገረመው በዚያን ወቅት አንዱ በሌላው ዜጋ ላይ ለሆዱ ሲል አንዱ ሌላውን በመግፋትና በመሽቀዳደም ማየት ባለመቻሉና ይልቅስ በመተሳሰብና በመከባበር አንዱ ሌላውን እያከበረ ማየቱ ነበር፡፡ክብር ደግሞ በተለያየ ገጹ ይገለጻል፡፡የመናገር ነጻነት፤የማሰብ፤በየሃይማኖት የእምነት፤የመሰባሰብ፤ለጉዳቱ አቤት የሚልበት፤ከማንኛውም በበለጠ ደግሞ አንድን መንግሥት ከመፍራት መላቀቅ፡፡ መለስ ግን ሰው በዳቦ ብቻ ይኖራል ብሎ ያምን ነበር፡፡በብቸኝነትም በግምብና በሞርታር አምኖ ኖረ፡፡በዚህም ያን የተስፋና የዕድል ቀጠሮውን ሳተ፡፡

መለስ ይቅር ባይና ታጋሽ አልነበረም፡፡አልፎ አልፎ ለምህረት ፈቃደኝነቱን እንደአስፋጊነት ሲጠቀምበት እንጂ ለይቅር ለእግዜር በሩን ከፍቶት አያውቅም፡፡ የሰጠውንም ምህረት ቢሆን እንደ መልሶ ማጥቂያ ጎራዴ ማርኳችሁ ባላቸው አናት ነላይ በማውለብለብ ነበር፡፡ዘወትርም እንደማራቸው ሁሉ መልሶ ደስ ባለውና ስሜቱ ባነሳሳው ወቅት ወደ ወጡበት ማጎርያ ሊከታቸው እንደሚችል ያሳስብና ይፎክር የነበረ ነው፡፡ከመወያየት ይልቅ ግጭትን፤ከማስማማት ይልቅ የራሱን ፍቃድ በመጫን ያምን ነበር፡፡የምንግዜም ፍላጎቱ በማሸነፍ ላይ ስለነበር ጨዋታው ሁሉ በዜሮ ግጥሚያ ይከተት ነበር፡፡ መለስ ከዕድል ጋር የነበረውን ቀጠሮ አጣው፡፡

መለስ ጨርሶ የሰራውን ስህተት የማያምን ተፈጥሮ ነበረው፡፡ስህተትን በማመንና ከስህተትም መማር እንደሚቻል ተገንዝቦት አያውቅም፡፡በሰራውም ስህተት ይቅርታ በመጠየቅ ስህተቱን በማረም ማስተካከል መቻሉንም ይጠላዋል፡፡በ2005 ዓ/ም ሕይወታቸው ያለፈውን 200 ሰላማዊና መብታቸውን ጠያቂ ዜጎች ሕልፈትና በጥይት ናዳ የቆሰሉት 800 የሚደርሱ ወገኖችን ሁኔታ በተመለከተ ሲጠየቅ የሰጠው አሳዛኝ መልስ‹‹ በመሞታቸው አዝናለሁ ነገር ግን እንዚህ እኮ ሰላማዊ ሰልፈኞች አልነበሩም ሰላማዊ የሆኑ ሰልፈኛች እኮ እጃቸው ቦንብ አይወረውርም፡፡›› ለዚህም መለስ ራሱ ካዋቀርው አጣሪ ኮሚቴ የተሰጠው የምርመራ ውጤት እነዚህ ሰላማዊ ሰልፈኞች አንዳችም የጦር መሳርያ ያልያዙ፤ ባዶ እጃቸውን መብታቸውን ለማስከበር የወጡ ናቸው›› የሚል ነበር፡፡መለስ ሁኔታውነ በተመለከተ ለማስረዳትም ሆነ ሟቾቹን በተመለከተም ለቤተሰቦቻቸው የይቅርታ ስሜት እንኳን አላሳየም፡፡በዚህም የተነሳ ነው እኔ ከወንበር ላይ ያለ መምህርነት ወደ እማይሰለችና የማያቋርጥ የሰብአዊ መበት ተሟጋችነት የተለወጥኩት፡፡

መለስ ዘወትር ልክ ነኝ ብሎ ያስባል ባለሟሎቹንም ያሳምናል፡፡ከስህተቱና ከግድፈቱ መማር እንደሚችል ጨርሶ ተገልጦለት አያውቅም፡፡መለስ አንድ ጊዜ አውቆም ይሁን ድንገት አዳልጦት፤ስህተቱን ያመነበት ወቅት ነበር፡፡አንድ ጋዜጠኛ ስለውጪ ጉዞው የተከሰተውን ተቃውሞ በተመለከተ ሲመልስ፤‹‹በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ስህተት ፈጽመን ይሆናል፡፡ አዝናለሁ፡፡ ምናልባትም ሰበቡ በሃገር ውስጥ ስለምናደርገው እንቅስቃሴ በአግባቡ ስላልገለጥንላቸውና ከማስረዳት ጉድለት የመጣ ነው::›› እዚህም ላይ ከዕድል አጋጣሚ ጋር የነበረውን ቀጥሮ ሳተ፡፡

መለስ የሕግን የበላይነት ቢያከብር ኖሮ የወጣለት መሪ ለመሆን ይችል ነበር፡፡ ደጋግሞ ‹ሕገመንግሥታችን›› እያለ ስለሕግ የበላይነት ቢወተውትም አንድም ቀን ግን ሕገመንግሥቱን አክብሮ ለሕግም የበላይነት እራሱን አስገዝቶ አያውቅም፡፡ስለ ሰብአዊ መብት ጥሰት በዓለም አቀፍ ሕብረተሰቡ እንደወቀሰ፤እራሱ ያወጣውን የሃገሪቱን ሕገ መንግሥት መንግስት የሰብአዊ መበት ዘገባና ሌሎችም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የመለስን መንግሥት ሕጸጽ ነቅሰው በማውጣት ለእርማት ጥሪ ቢያሰሙም የመለስን ጆሮ ማግኘት ግን አልተቻለም፡፡በዚህና በተመሳሳይ ሰበቦች መለስ ከጊዜ አጋጣሚ ዕድል ጋር የነበረውን ቀጠሮ አፋለሰ፡፡

መለስ የተግባር ሰው ነበር፡፡ ተግባርን ግን ከራዕይ ጋር አጋጨው፡፡ስለ ‹‹ኢትዮጵያ እድገት›› ይሰብካል ‹‹አንዳንድ ሰዎች ‹‹ ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ልዕልናዋ›› ሊመልሳት ይፈልጋል ይላሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች የራሱንም አገልጋዮችና አምላኪዎች ጨምሮ ከሃገሪቱ ጋር ያለውን ትስስር ጨርሶ ማወቅ አልቻሉም፡፡በ2007 የሚሌኒየም አከባበር ላይ ‹‹በዚህ በአዲሱ ሚሌኒየም ንጋት ላይ ሃገራችን በዓለም ካሉ ድሃ ሀገሮች ግንባር ቀደምዋ ናት›› ብሎ ነበር፡፡በዚያው ወቅት ሲናገር ከሌላ 1000 ዓመት በኋላ ኢትዮጵያዊያን 4ኛውን ሚሌኒየም ለማክበር ሲሰባሰቡ ሶስተኛው ሚሌኒየም ለኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የጨለማው ወቅት መጨረሻ መጀመርያ ነው ይላሉ ነበር ያለው፡፡የሚያሳዝነው ግን ከሱ በፊት የነበሩት በርካታዎች እንደመለስ ሁሉ ብለው ነበር ግን ሲሳካ አልታየም እንጂ፡፡ በበርሊን ከሸፈባቸው፡፡በሮምም ከአንድ ምእተ ዓመት ተኩል በፊት ሳይሆን ቀረ፡፡ በተሪፖሊና በባግዳድም እንዲሁ፡፡ መንገድ ቢሰሩም፤ግንባታ ቢካሂዱም፤ ግድብ ቢገድቡም፤ ጦር ሰብቀው ጦርነት ቢያካሂዱም ሁሉም ተጠራርገው ወደ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ነው የወደቁት፡፡

ከመጻኢ ዕድል ጋር የኛ ቀጠሮ

እኛ የአሁኑ ዘመን ነዋሪዎች ከመጻኢ ዕድላችን ጋር አዲስ ቀጠሮ አለን፡፡ ቀጠሯችንን ከማክበራችን አስቀድሞ ግና፤መለስ ካተረፈልን ደጋግ ችሮታዎች ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተን መስማማት ኖርብናል፡፡ እውነቱም መለስ የደረጋቸው ተግባራት ሁሉ ብቻውን የፈጸማቸው አለመሆናቸውን ማመን አለብ፡፡ በመለስን ስህተቶች ስህተት ከማለታችን በፊት የራሳችንን ስህተቶችና ድክመቶች ተቀብለን ማመን ይገባናል፡፡ የመለስን ስህተቶች በመኮነን ብቻ የትም አንደርስም፡፡ ያን ማድረግ የሚያመጣው ተመልሶ ወደጠሉት መግባትን ብቻ ነው፡፡ ባለፈው ስህተት ስናመነዥክ የወደፊቱን ሂደታችንን መቃብሩ ውስጥ ሆኖ መለስ እንዲቀይስልን የምንመኝ ነው የሚያደርገን፡፡ ላለፉት 21 ዓመታት የታዩትን ድክመቶች በመንቀስ እያጠራን ወደፊት መሄድን፤ ቁስላችንን ማጥገግ፤ ከፍርሃታችን መላቀቅን፤ቅራኔዎችን ማስታረቅን መማር የግድ ነው፡፡ ታሪክ እያነሱ ጥላቻን ማጫር ዋጋ የለውም፡፡ ፍቅርን ለማነጽ መጣር አለብን፡፡ከየአንዳንዳችን ለእየአንዳንዳችን ፍቅርንና መተሳሰብን መሰጣጣት መማር ይገባናል፡፡አሁን እንግዲህ መለስ የለምና፤ ሁላችንም የማነዴላን ጫማ ተጫምተን፤ አቅማችንን አሰባስበንና አጠናክረን ኢትዮጵያችንን በጠነከረ መሰረት ላይ የሕግ የበላይነትን ለመገንባት መቆም አለብን፡፡ ያለፈ ጥላቻን ማንቆሩ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ አሁን ያለውና የሚቀርብልን ጥያቄ ግልጽ ነው፡፡እኛም ከመጻኢ ዕድላችን ጋር ያለንን ቀጠሮ እናፋልሰው ይሆን?

በዚህ ዓመት መጀመርያ ላይ ‹‹ ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ወደ ዴሞክራሲ  የማይቀረው ሽግግር›› በሚል መነሻ ስጽፍ ነበር፡፡በዚህም ሽግግር ወቅት ሊደረግ ስለሚችለው ሂደት አማራጮችም ጠቃቅሻለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ  የአንድ ሰው የበላይነትና ፈላጭ ቆራጭ ዲክታተሪያዊ አገዛዝ አክትሟል፡፡ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገውን ሽግግር ፍጻሜ ለማድረስ፤ለመጻኢ ዕድላችንም ቀጠሮውን ለማክበር ብሔራዊ የሰላምና የመግባባት ድርድር መጀመር ተገቢ ነው፡፡ ይህንንም ለመጀመር ቅድሚያ ሚሰጠው ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች መፍታትና፤ፕያንንም አሳሪና ተብታቢ የሆነውን ‹‹የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ›› የተባለውን ደግሞ በማየት ቦታውን ማስለቀቅ ግንባር ቀደም ተግባር ሊሆን አማራጭ የለውም፡፡

ወደ መልካም  አስተዳደርና  ዴሞክራሲ ጎዳና

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመለስን ጠንካራና ደካሞ ጎኖች በማንሳት አስተያየቴን ሰጥቻለሁ፡፡ በግሌ ከመለስ ጋር አንዳችም ችግር የለኝም፡፡ተገናኝተን ተዋውቀንም አናውቅም፡፡የሱን ፖለቲካ፤ ሂደት፤ ንግግሮቹን፤ ግን ተከታትያለሁም አጥንቻለሁ፡፡ የኔ ትኩረት ሰበአዊ መብትን ያስቀደመ በመሆኑ በማንኛውም ነገር ከሱ ጋር አለመስማማትን ስመርጥም በቅድሚያ የሰብአዊ መብትን የማክበር ግዴታ መወጣት እንዳለበት ስላመንኩ ነው፡፡ የኔ አንዲት ሰበቤ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት መከበር ነው፡፡ በ2005 በተካሄደው ምርጫ ማግስት  በንጹሃን ዜጎች ላይ መብታቸውን ለማስከበር  ባዶ እጃቸውን ሕገ መንግሥቱን አክብረው በወጡት ላይ በተከሰተው ጭፍጨፋ ሳቢያ ነው በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ላይ ትኩረት አድርጌ መንቀሳቀስ የጀመርኩት፡፡ እኔ ቆራጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነኝ:: ይህም ወንጀል ነው የሚባል ከሆነ እኔም ወንጀለኛ ለመሆን በኩራተ ዝግጁ ነኝ፡፡

መለስ ከመጻኢ ዕድል ጋር እንደጀግና ኖሮ እንደ ጀግና ለማለፍና ሃገሪቱን በመላ መቀበሪያው ለማድረግ ቀጠሮ ነበረው ብዬ አምናለሁ፡፡ የታላላቅ ስራዎቹ ታሪኩና ልእልና በእብነ በረድ ላይ ሳይሆን በሃገሩ ሰዎች በሴቱም በወንዱ ልብ ውስጥ ሊቀረጽለት ይችል ነበር፡፡ እኔ ግን እንደ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የመለስን ልእልና የማስበው በ2005 ዓ/ም ከተፈጠመው ጭፍጨፋ ጋር በማያያዝ፤ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን የፖለቲካ እስረኞች የሚታጎሩበትን ወህኒ ቤት፤ የፖለቲካ መገልገያ የሆኑትን ችሎቶች፤እና የሕግ የበላይነት የተደፈረበትን ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት ነው፡፡

መለስ በ2007 ከአልጀዚራ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ተስፋውንና ሊያደርግ የሚፈቅደውን ግን ጨርሶ ያልተሞከረውንና እንዲሁ በቃለ ምልልስ ብቻ ተሰምቶ የተቋጨውን ሃሳቡን ሰምቼ ነበር፡፡ በዚያ አባባሉ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ከመከራና ከፍትሕ እጦት ከዴሞክራሲ አፈና፤ ተጠያቂነትን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ የተስፋ ብልጭታ እንዳለው ተናግሮ ነበር፡፡ ያ ግን ነበር ብቻ ሆኖ ቀረ እንጂ አንዱም አልተሳካም፡፡ተስፋዬ ነው ብሎ ያነሳቸው ነጥቦች በተግባር ቢተረጎሙ ኖሮ ታላቅ እድገት እናይበት፤ ነጻነት የምናይበት የምንመሰክርበት ራዕይ ነበር፡፡ያ መለስ ያለው የወደፊት ተስፋ አሁን ነው፡፡የሱን ሳይቋጭ የቀረውን ራዕዩን መተግበር ያለብን አሁን ነው፡፡መልካም አስተዳደርንና ዴሞክራሲን በተግባር ማሳየት የሱን ያልተቋጨ ተስፋ ከግብ ማድረስ ነው፡፡ ይህን የመለስን ችሮታ ተተኪ ባለስልጣኖቹ በግልጽ አምነውና ገሃድ አውጥተው የመለስን የአመራር ብቃት የማሳያ መዘክር ሊያደርጉት ተገቢ ነው፡፡ ይህ ፈጣን ለውጥ በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ላይ ተመስርቶ አሁን መጀመር ያለበት ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች በነጻ በመልቀቅና ያንን አሳሪ ሆነውን የሽብርተኝነት አዋጅ በሕግ የበላይነት ላይ በማስተሳሰር ሊሰራ የሚችል እንጂ የቂም መወጫነቱንና የዝም ማሰኛነት ባህሪውን በመለወጥ ማስተካከልን ተግባራቸው ሊያደርጉት ይገባል፡፡ አዲሱ የኢትዮጵያዊያን ዓመት መለወጫ ዳር ላይ በመሆናችን በአዲሱ ዓመት ፈጣን ለውጥን በመልካም አስተዳርና በዴሞክራሲ እውነታ ሂደታችንን እንደ አዲስ መጀመር ይኖርብናል፡፡

ሁለቱን አሰርት ዓመታት የመለስን አገዛዝና የግዛት ዘመኑን ለማክበር ትንሽ በኑሮውም በሕልፈቱም ጀግና የሆነው ሰው ለማለት ብችል ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ወንዱ ም ሴቱም ትልቁም ትንሹም፤እንባቸውን እንደጅረት እያፈሰሱ፤በፈቃደኝነት፤ አንዳችም እዝና ድጎማ ሳይደረግበት፤ የቀበሌ አዋጅ ሳይታከልበት፤ አልቃሽ ሳይቀጠርና ለደረት መምታት አንድ ዋጋ ለእንባ ብቻ ሌላ ዋጋ ሳይተመንለት፤ አልቅሱ ተብሎ ሳይለፈፍበት ሕዝቡ በራሱ ፈቃደኝነት ቢያነባለትና መንገዱ ሁሉ እንባ መራጫ ቢሆን ምን ያህል ደስ ባለኝ ነበር፡፡ያ እንዳይሆን ግን ሞቱንና ቀብሩን የፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ አሁንም በሕይወቱ በነበረ ጊዜ አበጀህ ሲሉትና ሲገፋፉት የነበሩት አሁን ደግሞ ለራሳቸው ጥቅም ማስጠበቂያ አደረጉት፡፡ለመለስ እንደ አንድ አክራሪ ሂስ አቅራቢው ልከፍለው የምችለው ከበሬታ ያን ‹‹ፈጣን ለውጥና መሻሻል በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ግንባታ”  በኢትዮጵያ ሲካሄድ ሳይ ብቻ ነው፡፡

ለአንድ ጋዜጠኛ መለስ በአንድ ወቅት ‹‹ኢትዮጵያዊያን እኔን ዲክታተር ነው የሚሉ ከሆነ ሌሊቱን በሙል እንቅልፍ ሳልተኛ አድራለሁ ግን እርግጠኛ ነኝ ይህን አይሉም›› ብሎ ነበር፤ የሚገርመው ግን፤መለስ ለመጨረሻ ጊዜ ከአንድ ቆራጥ ወጣት ጋዜጠኛ አንደበት የሰማው ቃል ይህንን የተጠራጠረበትንና ሊሸሽገው የሞከረውን እውነታ ነበር፡፡ ‹‹እኔ ያንን አልጠበቅሁምም አላሰብኩም ነበር፡፡ግን ሆነ፡፡በጊዳዩ አልቆጭም፤ሆኖም ግን በጊዜው መጨረሻ ላይ መሆኑና ማረጋገጫውን ማሰማቱ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ::››

ሌሎች ሰዎች መለስን ባለ ራዕይ፤መሪ ታሪክ የማይዘነጋው አፍሪካዊ መሪ፤›› በማለት የሕይወት ታሪኩን አጀግነውና አሰማምረው ይጻፉለት፡፡ እኔ ግን  ሼክስፒር: ከጁሊየስ ቄሳር ጽሁፍ ቃላት ተውሼ በዚያ እሰናበተዋለሁ፡፡

ሰዎች አንዳንድ ጊዜ የራሳቸው መጨረሻ እድል ባለቤቶች ናቸው

ውድ መለስ የኛ ህልውና በከዋክብቶቻችን ላይ አይደለም

በራሳችን እንጂ፤ እኛ ታዛዦች ነን::

ስለዚህ:

ወዳጆች፤ኢትዮያዊን፤የሃገሬ ወንዶችና ሴቶች ጆሯችሁን አውሱኝ

አሁን ወቅቱ መለስን መቅበሪያ እንጂ ማመስገኛው አይደለም

ሰዎች የሰሯቸው እኩይ ተግባራት ከኋላቸው ይቀራሉ

መልካሞቹ ግን ከአጥንቶቻቸው ጋር መቃብር ይወርዳል

ለመለስም እንዲሁ ይሁን::

Translated from:  A Farewell to Meles Zenawi

የሠላም ራዕይ ለኢትዮጵያ

Wednesday, July 25th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ፕሬዜዳንት ኔልሰን ማንዴላ ባለፈው ሳምንት 94 ዓመታቸውን አከበሩ፡፡እግዚአብሔር ረጂም ዕድሜንና ጤናን ይስጣቸው፡፡

ፕሬዜዳንት ማንዴላን የሚያከብሩና የሚያፈቅሩ ሰዎች ‹‹ማዲባ››ብለው ይጠሩዋቸዋል፡፡እሳቸውም የሰብአዊ ፍቅር ተስፋ፤ ትእግስት፤ራዕይ ናቸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ በጭለማው ሰአት ማዲባ ከጭለማ እስር ሲወጡ ፈገግታ ለብሰው፤ በእጃቸው ሻማ ይዘው ሕዝባቸውን አፓርታይድ ከሚባል እስር ቤት ለማውጣት ተዘጋጅተው ነበር፡፡ደቡብ አፍሪካ ሕዝቦቿ ጦር አስልተው ለመጋደል ሲዘጋጁ፤ማዴባ ነሃል ገብተው ‹‹አንተም ተው አንተም ተው›› ብለው እጅ ለእጅ አያይዘው፤ አጨባብጠው፤ ጦራቸውን፤ቀስታቸውን፤ጎራዱያቸውን፤አቅልጠው አዲሲቷን ደብብ አፍሪካ መገንቢያ ብረት እንዲሆን አድርገዋል፡፡ይሄንንም ሲያደርጉ ያሉት ‹‹መቼም፤መቼም ፤መቼም ቢሆን፤ሃገራችን ውስጥ አንዱ አንዱን ቀጥቅጦ ሊገዛ፤ ካሁን በኋላ አይችልም›› ነበር፡፡ የዓለም ሕዝብ በስራቸው ተደንቆ ሲመለከት ማዴባያሉት ‹‹ እኔ እኮ መልአክ አይደለሁም ምናልባት ሙከራ የሚያደርግ ሃጢአተኛ መልአክ ነው ብላችሁ ካላመናችሁ፤በስተቀር፤መላክ ለመሆን የምሞክሩ ሃጥአን የአፍሪካ መሪዎች ብናገኝ እንዴት ደስ ባለን ነበር::››

እኔ ከማዴባ ጋር ሃሳባዊ ንግግር ብዙ ጊዜ አደርጋለሁ፡፡በግንቦት 2011 ላይ በሳምናታዊ ጦማሬ ላይ ስለአንደኛው ንግግሬ ለአንባቢዎቼ አቅርቤ ነበር፡፡ በችኮላ መንፈስ፤ማዴባን እንዲህብዬ ጠየቅኋቸው ‹‹የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጮች ለምን ይሆን የሚደነፉት?›› መልሳቸውም በደቡብ አፍሪካ ላይ የተወሰነ ነበር፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት ‹‹ፈጽሞ ፈጽሞ ፈፅሞ፤ ይህች ውበት የሞላት ሃገራችን፤አንዱ ሌላውን ቀጥቅጦ የሚገዛባት ሃገር አትሆንም›› ነበር ያሉት፡፡ቀጥለውም ‹‹ግን›› አሉ፤‹‹የውቧ ሃገራችን ህልማችን የምትደርስበት ቦታ በይቅርታ ባይነትና በጥሩ ልቦና ስንሄድ ብቻ ነው፡፡››

ሕልምና ቅዠት ስለ ውቧ ኢትዮጵያ

የሰብአዊ ተሟጋችና የምሁር ለሰሚ መናገር እውነትን ለስልጣን ያዦች መከሰትና ወደፊት ካለፈው ይሻላል የሚለውን ተስፋ ይዞ መጓዝ ነው፡፡ እውነተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎት የለውም፡፡ የሰብአዊ መብት ፖለቲካ፤ የሰው ልጅ ክብርና ሞገስ መጠበቅ ፖለቲካ ነው፡፡ ስለ አይዲዎሎጂ አለያም ወገናዊነት ፖለቲካ ወይም የሥልጣን ሽሚያ አይደለም፡፡የሰብአዊ መብት ተሟጋች ስለወደፊት ተስፋ ነው የሚያተኩረው፡፡ ቫክላክ ሃቬል የቼክ ፕሬዜዳንትና ሰብአዊ መብት ተሟጋች ሲናገሩ ‹‹ተስፋ የአእምሮ ግንዛቤ ነው፡፡ በጥልቀት ስናየው ተስፋ የአእምሮ ግንዛቤ ነው፡፡ጠልቀን ስናየው ደግሞ ተስፋ መደሰት ማለት አይደለም፤ተስፋ አንድ ጥሩ ነገርን ማድረግ ነው ብለዋል፡፡አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፤በሚያደርገው ድርጊት ለሚያገኘው ለጥቅም ወይም የገነነ ስም አይደለም፡፡ የፈጠነ የፖለቲካ ለውጥም ይመጣል ብሎ አይደለም፡፡ ሃቫል እንዳሉት አንድ ጥሩ ነገርን ማድረግ፤ ያ ነገር በርግጥ ሁኔተኛ ይሆናል በማለት አይደለም፡፡ ባለፉት ዘመናት ስለ ሰብአዊ መብት በኢትዮጵያ ስጮህ ፈላጭ ቆራጮቹን ስቃወም፤የማደርገው ድርጊት ፈጣን ውጤት ያመጣል ብዬ አይደለም፡፡ወይም በአንድ ሌሊት መዋቅሩ ይለወጣል በማለት አይደለም፡፡ለረጂም ጊዜ ስለ ሰብአዊ መብት የተናገርኩት፤ የጻፍኩት፤የተሟገትኩት መልካም ጥሩ ነገር በመሆኑ ነው፡፡

በቅርብ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ይሆናሉ አይሆኑም የሚሉ ቅዠቶች እየተከሰቱ ነው፡፡ውቢቷ ኢትዮጵያ የት ትደርሳለች የሚል ሕልም በብዛትም አይሰማም፡፡ ሹክሹክታውም ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ ወደ የርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ልትወድቅ ትችላለች የሚሉ አሉ፡፡ ግን በእግዜር አይንም ሆነ በሰው የኢትዮጵያ እድል ከአንድ ሰው እጣ ጋር የታሰረ ሊሆን አይችልም፡፡ ሌሎች ደሞ ስለ መአት እያወሩ፤በንዴትና በማማረር ይበሳጫሉ፡፡ ግን የሚታያቸው ጀንበር የሚጠልቅበትን ስርአት እንጂ ጸሃይ የምትፈነጥቅበትን አዲሱን ቀን፤ለማየት አልተቻላቸውም፡፡እንዲሁም ሌሎች ስለመከፋፈል፤ መበታተን፤መቃቃር፤ሲረበሹ ይደመጣሉ ይታያሉ፡፡ ቤተሰብ በቋንቋ፤በባህልና በሃይማኖት መተሳሰራችንን የዘነጉት ይመስላል፡፡ ሌሊች የሚያስጨንቃቸው፤በአንድ ሰው ጀርባ ላይ የተመሰረተ መንግስት ምን እንደሚደርስበት ነው፡፡ ሁሉም ግን ለሚገምተው፤ ለሚያስበው፤ ለሚመኘው፤ ለሚጨነቀው መልሱ “አረ አለሁ በነፍስ፤ እኔ መለስ” ሊሆን ያችላል፡፡ ግን ይህን ያህል አንድ ሐሙስ ለቀረው መንግስት አስፈላጊና አሳሳቢ ነው?

ይህ ዓመት ሲጀመር ‹‹ኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ›› በሚል ርእስ አንድ መጣጥፍ እያቀረብኩ ነበር፡፡ አንዱ ጦማሬ ላይ፤ እንዳልኩት በፈላጭ ቆራጭና ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ድልድል ላይ ብዙ አታላዮች፤ ወንበዴዎች ሥልጣን ለመስረቅ ይዘጋጃሉና ከባድ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብዬ ነበር፡፡ ባለፈው ወር ደግሞ ቀደም ያለ ሕገመንግስታዊ ንግግር እንጀምር ምክንያቱም የለውጥ ጊዜ እየተከሰተ ነው ብዬ ነበር፡፡በቅርብ ጊዜ የሚታዩ እውነታዎች ከፍተኛ ለውጥ በኢትዮጵያ እንደሚከሰት ነው ሁኔታው የሚያመላክተው፡፡ አንዳንዶች ኢትዮጵያ የምትወድቅበት ሁኔታ ቢያቃዣቸውም እኔን ደግሞ ከባድ ሃሳብ ላይ የጣለኝ የተቃዋሚው ቡድን፤ አንድ ሰው ስለ ኖረና ስላልኖረ የሚያደርጉት ነገር ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የስርአት ለውጥና ሽግግር ሁሌም ክፉኛ አስቸጋሪ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ታሪክ ይህን ይመሰክራል፡፡ ከንጉሳዊ አገዛዝ ወደ ሶሻሊዝም የነበረው ሽግግር በጣም አስከፊ ነበር፡፡ በሶሻሊዝም ስም በሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሶሻሊዝም ወደ ሪቮሊውሽናሪ ዴሞክራሲ ደግሞ አናቂና ሰላቢ መንግስት ይሄው በአፍሪካ ታይቶ የማይታወቅ ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ መንግስት ለ21 ዓመታት ተቀምጧል፡፡ በ1977 የታየው የዴሞክራሲ ብርሃን በአንድ አፍታ ጠፍቷል፡፡ አሁን ሕዝብን እስረኛ ያደረገው ስርአት፤ ጸሃይ እየጠለቀችበት ነው፡፡ የእስረኞቹም ዋና ሹም መጋረጃ ወደ መከናነብ እያመራ ይመስላል፡፡

ሆኖም በሃገሪቱ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እየተከሰተ ነው፡፡አነስተኛ ፍንዳታዎች በየቦታው ይታያሉ፡፡ ያለው ሁኔታ ሕዝቡን አስከፍቶታል፡፡ ሙስናው፤ስልጣን አለአግባብ መጠቀም፤ ያስተዳደር ጉድለት በገሃድ ይታያሉ፡፡ ይህን በአረብ ሃገሮች የሚደረገውን ለውጥ ስንመለከት ያሉት ገዢዎች ከፍ ያለ የሃሳብ ስጋት ሳይደርስባቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡ ሆኖም ቅሉ የጨቋኞቹ ስርአት ምን ይድረስበት አይድረስበት ብዙም አያስጨንቀኝም፡፡ የሚያስጨንቀኝ የተቃዋሚ ቡድኖች ምን እንደሚያደርጉ ነው፡፡እንደተለመደው የተገኘውን እድል ለማጣት ይጥሩ ይሆን? እኔ ብቻ ላሸንፍ ሌላው ይውደቅ ይሉ ይሆን? አንዱ ሌላውን እኔ ከሱ ልብለጥ የሚል ሂደት ይከተሉ ይሆን? ወይስ አንዱ ሌላውን፤ በብልጠት፤ ባሻጥር፤በዘዴ ለማሸነፍ ይሞክሩ ይሆን?

አለዚያስ ከፍ ብለው ይነሱስ ይሆን? አንዱ ሌላውን ይቅርታ ይጠይቅ ይሆን? አብረን ለሃገራችን እንስራ ይሉ ይሆን? ከሁሉም በላይ በወንድምነትና እህትነት እጅ ለእጅ ተጨባብጠው የያዙትን ጦርና ቀስት ወርውረው ኢትዮጵያን ለመገንባት ይዘጋጃሉ ይሆን?፡፡ማዴባ ያሉትን ተቀብለው በስራ ላይ ያውሉ ይሆን? ይሄ ነው የሚያሳስበኝ፡፡ ‹‹ነጻነት ጎህ ቀዳ ስትወጣ ስራችንን በበለጠ አጠናክረን መስራት አለብን፡፡ነጮችንም ያገራችንንም ልጆች አስገብተን ደቡብ አፍሪካን እንዲገነቡ ማድረግ አለብን፡፡ይህ የነጻነት ንቅናቄ የናንተም ነው ልንላቸው ይገባል፡፡›› እናዳሉት ማዴባ!

ሃጢአቱን እንጂ ሃጢአተኛውን አንጥላ

ጋንዲ ሲጽፍ፤የሰው ልጅ ሁለት ባህሪ አለው፡፡ ጥሩ ሲሰራ ማመስገንና ክፉ ሲሰራ ደግሞ መንቀፍ ነው፡፡ ያም ሆኖ የሰውን መጥፎ ስራውን መጥላት እንጂ ሰውዬውን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡ አንዱ ሌላውን በዘሩ፤ በቀለሙ፤በቋንቋው፤በሃይማኖቱ፤ቢጠላው ትርፉ ብዙ ጥላቻ ብቻ ነው፡፡ ማዴባ ሲናገሩ፤‹‹ማናቸውም የሰው ልጅ ሲወለድ ጥላቻ ይዞ አይደለም፡፡ ሰው ጥላቻን ተምሮ ነው ያገኘው፡፡የሰው ልጅ በተመሳሳይ መንገድ ፍቅርንም ሊማር ይችላል፤ ምክንያቱም ፍቅር ከተፈጥሮ ጋር የሚመጣ ጸጋ ነውና!፡፡” ይህም ከሆነ የጥላቻ ትምህርትን አለመማር ይቻላል በቦታው ፍቅርንም በሃገር ማስተማር ይቻላል፡፡

የጋንዲን ትምህርት መማር ተገቢ ነው፡፡ በጥላቻና በክፋት የተሰሩ ነገሮች ስሪታቸው ከመቃብር በላይ ለረጂም ጊዜ ይኖራል፡፡ ክፋትን ተከትለን ክፋትንም ከሰራን ቅዱስ ወንጌል እንደሚለው ‹‹ቤቱን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፤ ሰነፍም ለጠቢብ ተገዢ ይሆናል››ይላል፡፡ ጥፋትንና ተንኮልን ተንኮለኞችንና አጥፊዎችን ከተከተልን እኛም ነፋስን እንወርሳለን፡፡ ነፋሱም ያገራችን መዋቅር ሊገነጣጠል ይችላል ሆኖም ሃጢአቱ ላይ አተኩረን አብረን ኤሎሄ ኤሎሄ ብንል የምንወርሰው ከፈላጭ ቆርጭነት አገዛዝ ዴሞክራሲ፤ ከሰብአዊ መብት ጥሰት፤ሰብአዊ መብት ክብረት፤ከጥላቻ ፍቅርን፤ ከንትርክ ይቅርታን እንወርሳለን፡፡ በስልጣን ቁንጮ የተቀመጡትም ማወቅ ያለባቸው ለውጥ መውጣቱ እንደማይቀር ነው፡፡ ሰላማዊ ለውጥ ሊመጣ ይችላል፤ ብልህ ከሆንን የምንተሳሰብ ከሆንን:: ግን ለውጡ መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡

በኢትዮጵያ አሁን ስንት ሰአት ነው

ቅዱስ ወንጌል እንደሚለው ‹‹ለሁሉም ጊዜ አለው›› ለፍቅር ጊዜ አለው፤ ለጥላቻ ጊዜ አለው፤ለጦርነትም ሆነ ለሰላም ጊዜ አለው፡፡ አሁን ለኢትዮጵያስ ጊዜው ምንድን ነው? …ጊዜው የሰላም ነው፤ጊዜው ከመራራነት ወደ መግባባት የሚለወጥበት ሁነኛው ወቅት ነው፡፡ጥላቻን ጥሎ መፈቃቀርያ ጊዜ ነው፡፡የተስፋ የእምነት የእውነት የመተሳሰብ የመተማመን የእውቀትና የብልጽግና ጊዜ ነው፡፡

ማዴባ ሲናገሩ ‹‹ለአፍሪካ ሕልም አለኝ ይሄውም በሰላም እንድትኖር ነው፡፡ብዙዎቹ አስተዳዳሪዎች አዋቂና ብልሆች ናቸው፡፡ተባብረው ችግርዋን ለፈቱላት ይችላሉ፡፡›› ብለው ሲቀጥሉም‹‹ይህች ዓለም የዴሞክራሲ የሰብአዊ መብት የሚከበርባት መሆን አለባት፡፡ አለም ከችጋር ከድንቁርና፤ የእርስ በርስ ጦርነት ተወግዶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ፤በስቃይ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ከስደት መትረፍ አለባቸው፡፡”

ማዴባ ሁል ጊዜ የመንፈስ ጥንካሬና፤ተስፋ ያሰጡኛል፡፡በ2011 መስከረም ጦማሬ ላይ ስጽፍ እንዳሰፈርኩት ‹‹ኢትዮጵያ በተዘበራረቀ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡ በፈላጭ ቆራጭ መዳፍ ስር ነው ያለችው፡፡ መለስ አንዴዬ ሲናገር እንዳለው፤‹‹እኛን የሚቀናቀን ካለ እናደቀዋለን፤ እንደዱቄት!፡፡” ማናቸውም ዜጋ፤ ማንም ሰው፤እንደዚህ ዓይነት አሰቃቂ አነጋገር የሚነገርባት ቦታ፤ ኢትዮጵያ መሆን የለባትም፡፡ ማናቸውም ዜጋ አለፍርሃት፤ረሃብ ጭቆና ለመኖር የሚቻልባት ሃገር መሆን አለባት፡፡ ይሄንንም ስል በረጂም መንገድ ማዴባ ባጭሩ ደቡብ አፍሪካ በማናቸውም አይነት ካሁን በኋላ አንዱ ወገን ሌላውን በጭቆና ቀጥቅጦ የሚገዛባት ሃገር ልትሆን አትችልም እንዳሉት ነው፡፡

የኢትዮጵያን ሰላም የምመኘው ኢትዮጵያዊያኖች በጎ አሳቢዎች ናቸው በሚለረ እምነት ነው፡፡ ማዴባ በዓለም ላይ ካሉት በጎ አሳቢዎች ሁሉ ግምባር ቀደም ናቸው፡፡ እሳቸውም አንድ ወቅት ላይ ሲናገሩ፤‹‹በህይወቴ የነጭ ጭቆናን ተቃውሜያለሁ፤ የጥቁር ጭቆናን ተቃውሜያለሁ:: ዘወትር የምመኘው ደቡብ አፍሪካ ነጻና በዴሞክራሲ ስርአት እንድትተዳደር ነው፡፡ ለዚህም ምኞቴ በስፋት እታገላለሁ፡፡አስፈላጊ ከሆነም ይህ ተግባራዊ እንዲሆን እራሴን አሳልፌ እሰጣለሁ››ብለው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ምኞታቸው ከፍ ያለ ቢሆንም ሁኔታውንም ይገነዘባሉና፤ ችግራችንን በሰላምና በምክር መፍታት ካልቻልን ቀሪው ምርጫ ሕዝብን ማስጨፍጨፍ አስከፊ ሁኔታ ይሆናል፡፡ ማዴባ ሲናገሩ: “ባሁኑ ጊዜ ችግርን በሰላም ለመፍታት ከአምባ ገነን መንግስት ጋር መጯጯህ ፍሬ ከርስኪ ጉዳይ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡ምናልባት ይህን አስተያየት ተመልሰን ልንመለከተው ይገባል፡፡ለመሆኑ በቂ ጥረት አርገናል ወይ?” በዚሁ መልክ በኢትዮጵያ ንግግር መጀመር፤ ከንቱ ውዳሴ ይሆን? ደጋግሞስ መነጋገር፤ከጨፍጫፊወች ጋር የሰላማዊ መፍትሄ መንገድ መሻት ከንቱ ነው? ………አይመስለኝም፡፡

እንደምናየው ሁሉ የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ፤ አንድ ሁሉ ነገር፤የሚባል ዓምልኮ በወደፊቷ ኢትዮጵያ ተስፋ ያለው ነገር አይደለም፡፡ ከታሪክ መማር ተገቢ ነው፡፡በሶርያ በሊቢያ፤የሆኑ አሳዛኝ ነገሮች ከዚህ መዘዝ የመነጩ ናቸው፡፡

ማዴባ ከአፓርታይድ ጭቆና ወደ ዴሞክራሲ ስርአት መሸጋገር ምን እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል፡፡‹‹ሕዝቡ መጠየቅ መሳተፍ አለበት፡፡ድርድርም ሲደረግ ፊት ለፊት መሆን አለበት፡፡ “የወደፊቷ ደቡብ አፍሪካ፤የምትተዳደረው፤ዘረኝነት በሌለበት መንገድ ነው፡፡ነጮች የሥላጣን ማነቆ ይዘው ያለበት የረጀ ያፈጀ ሁኔታ መጥፋት አለበት” ማዴባ ብለዋል::

በዚህ መሰረት በኢትዮጵያም ቢሆን ሕዝቡ መሳተፍ አለበት፤ የሃገሪቷም የወደፊት ዕጣ ፈንታ በዴሞክራሲያዊ ስርአት በተመረጠ ጎሳና ዘር በማይል መሰረት ላይ መጣል አለበት፡፡ብልጦች አፈጮሌዎችና አወናባጆች ቦታ አይኖራቸውም፡፡

ሥራው ከባድና ፈታኝ ቢሆንም ሁላችንም ልንሳተፍበት የግድ ነው፡፡

ማዴባ ከእስር የወጡ የመጀመርያው እለት የተናገሩት፤ ስለ ሕብረትና መግባባትና መደማመጥ እንጂ፤ በደቡብ አፍሪካ ባለፉት ረጂም ዘመናት ስለተከናወኑት ሂደቶች አልነበረም፡፡‹‹ሕዝባችንን ማስተባበር በአሁኑ ጊዜ ታላቁ ስራችን ነው፡፡ማናቸውም መሪ በግሉ ሊሰራው የሚችለው ጉዳይ አይደለም፡፡ የመሪዎቻችንና የድርጅታችን ምግባር ዴሞክራሲያዊ በሆነ ስርአት፤ ወደፊት መቀጠልን ነው፡፡መረጋገጥ ያለበት ጉዳይ የእንቅስቃሴውን መሪ ሕዝቡ መምረጥ እንዳለበት ነው፡፡›› ነበር ያሉት:: በኢትዮጵያም ቢሆን፤አንድ መሪም ሆነ ድርጅት ማንም፤የሕዝብን አንድነት ሊፈጥር አይችልም፡፡ ስለዚህ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤በስቪክ፤ በሃይማኖት፤ በወጣቶች፤ በሴቶች እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶችና መሪዎች ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡

ማዴባን እንኳን ለ94ኛው የልደታቸው በዓል አደረሳቸው፡፡

ባለፈው ሳምንት አርክ ቢሾፕ ዴዝሞንድ ቱቱ ሲናገሩ፤‹‹ለማዴባ ከምንሰጣቸው ታላቅ ስጦታ ምሳሌያቸውን ስንከተልላቸው ነው›› ብለው ነበር:: ስለዚህ ለማዴባ የማበረክትላቸው ታላቅ ስጦታ ከአሁን በኋላ በእሳቸው ጫማ ፈለግ እንደምከተል ማረጋገጥ ነው፡፡ ማዴባ በቃላቸውም በሥራቸውም በጣም ብርታት ሰጥተውኛል፡፡ እስከ አሁንም ዕውነትን ሥልጣን ለጨበጡ እንድናገር ለኢትዮጵያም መልካም ሕልም እንዳልም ያደረጉኝ እሳቸው ናቸው፡፡ ከአሁን በኋላም በሳቸው ምሳሌ ለማስተማር፤ ለማሳወቅ ወደፊት በጥንካሬ የሚቀጥል ነው፡፡የጉዞዬም አቅጣጫ መልካምነትንና እርቀ ሰላምን የሚዬዝ ነው፡፡የማዴባ መንገድ ጉዞ ወደምንሄድበት ቦታ ያለጥርጥር ያደርሰናል ማለት አይደለም፤ሆኖም ግን ባሁኑ ጊዜ እሳቸው ከቀየሱት መንገድ ውጪ ወደ እርቅና መልካምነት የሚያደርሰን ሌላ መንገድ አይታየኝም፡፡

ምናልባት በዚህ አባባሌ እንደአላዋቂና ተላላ ሊመለከተኝ ይችል ይሆናል፤ ግን በተረጋጋ መሬት ላይ እንደቆምኩ አውቃለሁ፡፡ ከኔም ጋር የሚቆሙ ተመልካቾች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ የማዴባንም መንገድ መከተሌን የሚደግፉ ይኖራሉ፡፡ ቢቻልም ከኔ ጋር የማዴባን ጎዳና አብረው ለመሄድ ፍላጎት ያላቸው ሊኖሩ ይችላሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ ካልሆነም ብቻዬንም ቢሆን ጉዞውን ለመቀጠል መርጫለሁ፡፡ የብቻ ጉዞ ቢደክመኝም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያኖች በሚያዘግሙበት ጎዳና ነጻነታቸውን ክብራቸውን ለማግኘት ከነሱ ኋላ ሆኜ እያነከስኩም ቢሆን እከተላለሁ፡፡ ለማደርገው ጉዞ ግን ከማውገዝም ሆነ ከማወደስ መዘንጋት የሌለበት በጎ አሳቢ ኢትዮጵያዊ መሆኔን ነው፡፡ እንደተባለው ሁሉ ‹‹አንዳንድ ሰዎች ነገር ተመልክተው ለምን ይላሉ፤ እኔ ግን ስላልነበሩ ጉዳዮች እያለምኩ ለምን እላለሁ፡፡›› ስለዚህም የማዴባን የጫማ ፈለግ ተከትለን አንሄድም? ለምን ኢትዮጵያ በሰላም ሆና አናልምም? የአንዳችን ሕልም ከሌላችን ሕልም ስለኢትዮጵያ ሠላምና ብልጽግና ለምንስ አይሆንም? በጎ አሳቢ ኢትዮጵያዊያኖች እንሁን! ለምንስ መሆን ያዳግተናል?

(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::)

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

ኢትዮጵያ የኛ፥ የምጽዋት ምርኮኛ?

Monday, July 9th, 2012

ከፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

የምጽዋት ምርኮኛ

‹‹ቦንዴጅ›› ከንግሊዚኛ ሲተረጎም በውጭ ሃይል በምርኮኝነት መታገት ወይም መያዝ ማለት ነው፡፡ ሕዝቦች ለእዳ ሲዳረጉ ያን ጊዜ የዕዳ ምርኮኛነት ይሆናሉ:: ተገደው አለፈቃድኘት ሲያገለገሉ በባርነት ገበሩ ማለት ነው:: በ1960ው አመታት በፊት አፍሪካ የቅኘ አገዛዝ ምርኮኛ ነበረች:: አፍሪካውያን በባርነት ቀንበር ውስጥ ነበሩ፡፡ አሁንስ ግን አፍሪካ የርዳታ ‹‹ቦንዴጅ›› ምርኮኝነት (ለምሳሌ በዓለምአቀፍ የእርዳታ ምርኮ ዘመን እንደ አዲስ ቃል መጠቀሚያነት) ሆና ትገኛለችን?

የዓለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ደርጅቶችን፤የተባበሩት መንግስታትን የእርዳታ ኤጀንሲን፤ዩ ኤስ ኤይድስን፤የዓለም ባንክንና አይ ኤም ኤፍን ያካተተውን ‹‹ኢንዱስትሪ›› ግራሃም ሃንኮክ ‹‹የችጋራሞች ጌቶች›› በሚለው መጽሃፉ ምንነታቸውንና ማንነታቸውን ከነተግባራቸውና ከሃብታምነት ወይም የጌትነታቸውን መሰረት ቁልጭ አድርጎ አስነብቧል፡፡ደፋር አቀራረቡ ብዙዎችን ‹‹የዓለም አቀፍ መጽዋቾችን›› ቢያበሳጭም ሃቁን መካድና እውነትን መሸሽ የሚቻል አልሆነም፡፡የደራሲው መሰረታዊው ክርክሩ፤ ‹‹የዓለም አቀፍ እርዳታ የጊዜም፤የገንዘብም ብክነት›› ከመሆኑም አልፎ፤ተረጂ ምጽዋተኞችን የሚጎዳ በመሆኑ በአስቸኳይ፤ ሊቆም ይገባል ነው፡፡በ1989 የተመጸወተው 60 ቢሊዮን ዶላር ጉዳቱን ፤ለመድረስ በቂ መሳርያ ከመሆኑም አልፎ እጅጉን ጎጂና በፍላጎታቸው ላይም ጫና የሚፈጥር ማሰርያ ነው፡፡በከፍተኛ ደረጃም ከባቢውን አየር በማይታመን የጥፋት ዘመቻው አብክቶታል፤በተመጽዋቾቹ ላይ ሶምሶማ እየጋለበ የሚጨፍርባቸውን አስከፊ ገዚዎችንም ህጋዊነት እየሰጠ ሕዝቡን ግን በቸልታ በመመልከትና ለጩኸታቸውም ጆሮ በመንፈግ ይቅር የማይባል በደል አድርሶባቸዋል ይላል ሃንኮክ ፡፡

የሃንኮክ አስተያየትና አባባል፤‹‹ዓለም አቀፍ እርዳታ››‹‹በታክስ ስም ከምሰኪኖቹ የሃብታም ሃገር ሰዎች የሚሰበሰበው ገንዘብ፤ ለሃብታሞቹ የድሆች ሃገር የግፍ ገዢዎች እየተመዘዘላቸው ተመልሶ ለክፉ ቀናቸው መቋቋሚያ እንዲሆን ወደ ሃብታም መጽዋቾች ሀገር በወጣበት መንገድ ባይሆንም ተመልሶ ግን በባንክ ይቀመጥላቸዋል፡፡‹‹ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ››እና‹‹ መቆም አይገባውም ምክኛቱም ድሆቹ ችጋራም ተምዋቾች ካለሱ ሊኖሩ አይችሉም›› የሚለው አባባል ጥቂት የዝናብ ጠብታ ታህል እውነትነት እንኳን ቢኖረው እነዚህ በድህነት የችጋር አረንቋ ውስጥ ያሉት ችግርተኞች እርዳተው ከመምጣቱ ከዘመናት ቀደም ብለው ከነበሩበት ሁኔታ ተለውጠው መታየት ነበረባቸው፡፡ያም ሆኖ ከሆነ ምጽዋቱ በአሁኑ ጊዜ መቆምና ማንንም ለጉዳት ሳይዳርግ ከገባበት ሁሉ እንደአመጣጡ ውልቅ ብሎ መሄድ በተገባው ነበር፡፡

ሃንኮክ ሲጽፍ: አስቀያሚው እውነታ ደግሞ የዚህ የምጽዋት ነገር ችግሩ ቀጥተኛ ተረጂዎቹ ሕዝቦች ይህን እርዳታ ይቀንስ ይጨምር፤ማወቅ ቀርቶ ምጽዋት ተብሎ በስማቸው ከሚጎርፈው ገንዘብ ድርሻቸውን ቀርቶ ርዝራዡን ማግኘት ቀርቶ ከረጂው ድጅት ተወካዮች ጋር እንኳን በአጋጣሚም ሆነ በድንገተኛ መገጣጠም ተያተውም አያውቁ፡፡በቢሊዮኖች ዶላር በሚቆጠረው እርዳታ አላስፈላጊ በሆኑ የመጽዋቹ ሃገር ፍብረካዎች ምርት ደረጃው ያዘቀዘቀ ምርታቸውን ከማፍሰስ ባሻገር፤ በረጂዎቹ ብልጣ ብልጥ ደላላዎች፤ አገናኞች፤ኤክስፐርት በሚባሉት፤በአጭበርባሪ ጉዳዩ በሚመለከታቸው የተረጂ ሃገራት ሚኒስትሮች፤አመኔታ በሌላቸው ስራውን አከናዋኞች፤በማይታመኑ አሻሻጭና ደላላዎቻቸው፤በጉቦና በጋጠወጥነት ማግበስባስ፤በፕሬዜዳንቶቹ ራስ ወዳድነትና ንፍገት፤የሕዝብ አሉታ ሳያገኙ በጉልበትና በማን አለብኝነት በስልጣን ጣራ ላይ በተጎለቱ ገዢዎች፤ ስለሃገራቸው ጉዳይ ከሕዝብ ጋር ፈጽሞ ምክክር ማድረግን ከማይፈቅዱ መሪዎች ጋር አገልጋዮቻቸው ጋር ለሕዝብና ለሃገር በተሰነዘረ ችሮታ እነሱ ሕዝብ ነን በማለት እንዲንደላቀቁበትና የገንዘቡን ባለዐጭዳ ሕብረተሰብ እያደኸዩና እያሰሩ፤ እያሰቃዩና እየገደሉት እንዲኖሩ ይፈቅዱላቸዋል፡፡

ሊያሻሽሉትና ሊያስተካከሉት፤ ከፍ በማድረግ ሕዝቡን ከመከራና ሰቆቃ ሊያወጡት ሲገባ እነሱ እነዚህ በጣም ታዋቂና አዛኝ የሚባሉት ዓለም አቀፍ መጽዋቾች ሃገር በቀል የሆኑና ለወገኖቻቸው ተቆርቋሪና አዛኝ መስለው የሚቀጠሩትን በመያዝና በስራው መስክ ቢያሰልፉም እነዚህ ሃገር በቀሎች ግን ከህብረተሰቡ ጋር ተገናኝተው ችግሩን በመቅረፍ ፈንታ፤የቀን ከቀን ግንኙታቸውን ቸል በማለት ሊቀረፍ የሚገባውን ችግር ይብሱን ያሳድጉታል፡፡ ከመጠን በላይነሃ ከተግባራቸው እጅጉን በናረ መልኩ የሚከፈላቸው ምጽዋት ሰጪ ተወካዮች በሃገራቸው በኢንዱስትሪ ማእከል አለያምበንግድ ዘርፍ ተቀጥረው ከሚያገኙት የበለጠ ያገኛሉና፤በተቸሪዎቹ ሕይወትና ሃገር ላይ ምዝበራቸውን ያመቻቻሉ፡፡በትክክለኛው አጠራር ሙያቸው ‹‹ሰብአዊነት›› ቢሆንም የድርጊታቸው ሁኔታ የሚያሳየው ግን‹‹ሽያጭ›› ‹‹ኢንጅነሪንግ›› ሊባል የሚገባው ሲሆን፤በማይወጡትና እውቀቱና ግንዛቤያቸው የሚያተኩረው ወደ ራስ ጥቅም በመሆኑ፤የተሰማሩበትን የዕርዳታ ድርጅት ውጤት በቁጥር ሊሰፈር በሚችል ሚዛን ጨርሶ ማሳየት አይችሉም፡፡እነዚህ እራሳቸውን በቅራቅንቦ የከበቡ አንዳችም ጠቀሜታ ጠብ የማይላቸው ከንቱ የምስኪኖች ሎርዶች የዘመኑ ውዳቂዎች ሆነው ግና ለማንም ተጠያቂነት የሌለባቸው ሆነው ያላቅማቸው ስልጠን የተጫነባቸው ናቸው፡፡

ምጽዋት፡ ምርኮኛ በኢትዮጵያ ‹‹ለግፈኛውና ለጨካኙ›› ይሁንታና እውቅና መስጠት?

በዚህ መጣጥፌ ሃንኮክ ስላነሳው አስተያየት ማንሳቴ ለተቅላላ ግነዛቤ ብቻ አይደለም፡፡ ሃንኮክ አመለካከት ላይ በመመስረት፤በቅርቡ ለኢትዮጵያ ይፋ የሆነውን የአሜሪካንን የ1.54 ቢሊዮን ዶላር ምጽዋት ‹‹የዓለም አቀፉን የምጽዋት ድርጅት›› ስመረምረው ሳወጣና ሳወርደው ለጭፍንና ማን አለብኝ ግፋዊ ገዢዎች እውቅና መስጠት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የዩኤስ ኤይድ ሚሲዮን ዳይረክተር ቶማስ ስታል የ1.5 ቢሊዮን ዳረጎት በተመለከተ እንዳሉት ‹‹ይህ ምጽዋት በሁለቱ ሃገሮች መሃል የነበረውን ግንኙነት በማሳደግ ከረጂ ተረጂነት፤ ወደ ኤኮኖሚ ተባባሪነት ያሳድገዋል›› ነበር ያሉት፡፡‹‹ይህ ታላቅ ስምምነት›› የሚያነጣጥረው በትምህርቱ መስክ፤ጤና፤እርሻ፤መልካም አስተዳደርን በማሳደግ በኩል እያገዘ በተለይም የኢትዮጵያን እድገትና ትራንስ ፎርሜሽን ስትራቴጂ አጋዥ ሃይል ይሆናል፡፡ ከ2011-2012 ድረስ ባለው ጊዜ ለኢትዮጵያ ከአሜሪካ የሚደረገው የምጽዋት መጠን፤ወደ 675 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በማደግ በአራት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ላይ ያተኩራል፡፡ አራተኛው ግብ ደግሞ፤መልካም አስተዳደርን በማሻሻልና በማሳደግ ላይ ያተኮረና በሁሉም ሴክተሮች በኩል ተጠያቂነትንና የግጭቶችን ማስወገጃ ዘዴ ማስተማርያ ይሆናል፡፡ በዚህስ በተነደፈው ግብ የአሜሪካን መንግስት የመለስ ዜናዊን ግፈኛና ጨቋኝ ፈላጭ ቆራጭ ገዢነት እውቅና ይሰጣል?

የዩኤስ ኤይድ ሪፖርት እንደሚለው:

ከሞላ ጎደል ነጻ ማለት በሚቻለውና ኢህአዴግ ተወዳጅነቱን ከመጠን በላይ እርግጠኛ የሆነበትና በምርጫው ወቅት ግን በሚያሳፍር ሁኔታ ድምጽ የተነፈገበትና ለምርጫ ውርደትና የታየውን የዴሞክራሲ ጭላንጭል አውድሞ የጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ያልበሰለ ባህሪ ያሳየበት የ2005 ምርጫ ነበር፡፡ ከዚያው ጋር ተያይዞም የተቃዋሚው ጎራ ተከፋፍለው በመፈረካከሳቸው የኢህአዴግ ገዢ መንግስትም የግዛት ዘመኑን በማራዘም የግፍ አገዛዙንም አዳበረ፡፡ የሲቪል ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ በመቅጨት፤ሚዲያውን ተስፋ በማስቆረጥ፤ የሽብርተኝነት ሕግ በማውጣትና ተግባራዊ በማድረግ መያዝና ማሰርን ስራው አድርጎ መንቀሳቀሱንና አፈናውን ማካሄድ ቀጠለ፡፡ ያወጣውም የሽብርተኝነት ሕጉ እንዳሻው ለማሰር ለማፈንና ለማስፈራራት ተቃዋሚውን ጎራም ቀልቡን አሳጥቶ ዝም ማሰኛ መሳርያው አድርጎ ያለአንዳች ይሉኝታ በሃፈርትና በቅሌት የተመላውን ድርጊቱን ቀጠለ፡፡ በ2010 በተካሄደውም ተወዳዳሪ አልባ የምርጫ ወቅት መራጭም ተመራጭም፤ አስመራጭም አስፈጻሚም፤ሕግ አውጪም ተግባሪም በመሆን ይሉኝታ እንኳን ለስሙ ያህል ያላሳየበትን የምርጫ አታሞ ደልቆ ከማንም ይበልጥ እራሱን በማታለልና፤ ለምን ፤እንዴት የሚል ጥያቄ የማያውቁትን የአቤት ጌታየ እሺ ጌታዬ አባላቱን 99.6 በመቶ አሸነፍን በማለት የፓርላማውን ወንበር በድፍረት ተቆጣጠረው፡፡ ከ2010 ምርጫ በኋላ የታሰሩት የፖለቲካ እስረኛች የተፈቱ ቢሀንም፤የታቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ ገዚው ፓርቲ በመቆጣጠርና የፖለቲካ ሜዳውን በማጥበብ፤የሲሰቪል ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ በማዳከም ፤ በጠበበ የፖለቲካ ሜዳ፤በተደቆሰ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጎራ የግፍ እስር መቀጠል እንዳለ በሆነበት ወቅት በምጽዋት ስም 1.5 ቢሊዮን ዶላር? በአጠቃላይ በ2009 የልማት ድጋፍ ስም 3.8 ቢሊዮን ዶላር?

ዩ ኤስ ኤይድ በዴሞክራሲ ግንባታው፤በአስተዳደር ማሻሻሉ፤በችግር አፈታት ብልሃቱ ላይ ከፌዴራል ጉዳየች ቢሮ ጋር በቅርቡ በመስራት ላይ ነበር፡፡ኡን እንግዲህ የ2010 ምርጫ በማብቃቱ የፖለቲካ ውጥረቱ በመጠኑ ረገብ ማለትን አሳይቷል፤ የሃይለኛ ተቃዋሚ ጎራ አባላትም ተፈትተዋል ቢባልም በሺህ የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አሁንም በእስር ፍዳቸውን በማየት ላይ ናቸው፡፡

በገዢው መንግስት በኩል ታላላቅ መጽዋች ሃገራት ስለ አሳሳቢው የዴሞክራሲ ሁኔታ፤አስተዳደር የተደረገው ውይይት፤ በሚታየው የገዢው ሕግ አልባነት፤የአስተዳደር በደል፤ የሕገመንግስቱ ጥሰት አንዳችም የመግባባትና የተፈለገውን ሕዝባዊ መብት ለማስገኘት አልተቻለም፡፡ የዓለም ባንክ፤ዩ ኤን ዲ ፒ፤ዲ ኤፍ አይ ዲ፤ሲ ዳ(ካናዳ)፤ ዩ ኒ ሴፍ፤ኢ ዩ፤ ሲዳ(ስዊድን)አይር ላንድ፤ጀርመንና ሌሎችም በጥምር ሆነው ያለውን ችግር ለመፍታትና ገዢውን ፓርቲ ወደ ትክክለኛው አካሄድ መምራትና ሕገመንግስቱ በሚያዘው ስርአት ውስጥ ማካተት እንዴት ሆኖ አቃታቸው?

ዩ ኤስ ኤይድ በሚሰጠው የችሮታ ድጋፍ በሁሉም ደረጃ ያሉትን ተቋማት በአጠቃላይ (በተለይም የአካባቢ የፌዴራል ጉዳዮች) በአካባቢ ለሚነሱ ግጭቶች በደህንነት አባላቱ መፍትሄ ማስገኘትን ቸል በማለት፤ችግሮቻችሁን በራሳችሁ ክልል በኩል ፍቱት በሚል የመሸንገያ ዘዴ ‹‹ጉዳት አታድርሱ›› ‹‹አትጎዳዱ›› በሚል የህብረቱ መጽዋች አባላት የተነሱበትን ዓላማ ቸል በማለትና ገዢውን ፓርቲም ላለማስከፋት ሥልጠናውን ዘግተው፤ ሰልጣኞችንና ቀሪውን የሕብረተሰብ አባላት ላበዱ ተናካሽ ውሾች አስረክበው ወጡ፡፡

የመጽዋች ሃገሮች ኢትዮጵያን የችጋር ዋነኛ ሰለባነት በማረጋገጥ በመደጎምና፤ታላቅና በዋናነት ለሃገሪቱና ለሕዝቦቿ አስፈላጊነቱ በተረጋገጠውና ቅድሚያም ሊሰጠው ተገቢ በሆነው የዴሞክራሲ፤ ሰብአዊ መብት ገፈፋን ማስወገድ የሲቪል ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ ገደብ ማሸነፍን፤ በሕገመንግስቱ የተረጋገጠውን ሃሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን ማስከበርን፤ የኢንፎርሜሽን በነጻ የማግኘትን መብት ማስከበርን በተመለከተ ተከፋፍለው ይገኛሉ፡፡እነዚህ የመጽዋች ሃገሮች፤በውስብስብ ማስመሰያ የቃላት ጨዋታ ሁኔታዎችና በሚታየው የገሃዱ የፖለቲካ ጭቆና፤የገዢዎች በኤኮኖሚው በኩል የበላይነትና የሰብአዊ ደራሽ አደጋዎችን በሌላ ጎን በማሰለፍ ችግር ውስጥ ይታያሉ፡፡በዚህ ባለሁለት ስለት ሰይፍ ሁኔታ ወስጥ መጽዋች ሃገራት ቀጥተኛ ባይሆንም የጎንዮሽ የማረሚያ ሃሳብ ማቅረብና እምቢተኛውን የጉልበት አዋቂና ግፍ አድራሽ ለመቅጣትም አቅሙ ቢኖራቸውም ፈቃደኛነቱ ግን ርቋቸዋል፡፡ ምናልባትም ሼክስፒር እንዳለው ከነዚህ አፈ ቅቤ ልበ ጩቤዎች መጠንቀቅን እወቁበት ይመስል ይሆን?

የውድድር ምርጫና ሌሎች የዴሞክራሲ ሂደቶች በሌሉበትና ገዢው መንግስትም የዜጎቹን ፍላጎት ጨርሶ በናቀበትና የባለመብቶቹን ጉዳይ ገደል ይግባ በማለት በቋጨበት ሂደት ላይ፤አንዳችም የፖለቲካ መተንፈሻ ማየት በጣሙን አስቸጋሪ ነው፡፡ አዲሱ የኢትዮጵያ የልማትና እድገት ትራንስፎርሜሽን እቅድ፤ውስን የሆኑ የአስተዳደርን ጥቃቅን እዚህ ግቡ የማይባሉ ጉዳዮችን ለይቶ ያካተተ ነው፡፡ ማለትም ወሳኝ የሆኑና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡትን በንጉሱና ደርግ ዘመን ጠፍተው የነበሩትን ሕዝባዊ እሴቶች አሁን ባለው የአብታዊ ዴሞክራሲያዊ በሌላው ዓለም ተቀባይነት ያጣ የግዛት ስርአት ውስጥ ማግኘት ያቻላል ማለት ከንቱ ውዳሴ ነው፡፡ታዲያ የመለስ ዜናዊ መንግስት ከ21 ዓመታት የፈላጭ ቆራጭ የግፍ አገዛዝ ዘመናት በኋላ ማሳየት ያልፈቀደውን የዴሞክራሲ ስርአት ባለፉት ስርአቶች ወቅት አልነበሩም ለማለት የሚያበቃ ድፍረት ሊኖረው ይችላል? እንዴት ተቀለደ እባካችሁ ብቃት ያለውና ወገናዊ ያልሆነ የፍትህ ስርአት መኖር የግሉን ኢንቬስትመነት አካላትና ግለሰቦችንና መጽዋቾችን የሚያስፈራራ ውሳኔ ውስጥ የሚያሰልፋቸው ሁኔታ ነው፡፡ በሌላ ወገን ደሞ በፖለቲካው ሜዳ ታማኝነታቸውን ያረጋገጡ የንግዱ ተጠቃሚዎች የተቀመጡትን ህጎችና ድንጋጌዎች በምርኩዝ ተስፈንጥረው በመዝለል ግባቸውን ማሳካታቸው ነው፡፡ይህ በገዢው መደብ ስር ያለ ህግም እነዚህን በልዩነት የሚመለከትና ህገወጥነትን የሚተገብር ስርአት አራማጅ መንግስት ውስጥ ሁኔታውን ማየት የለት ተለት ተግባር ነው፡፡ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ለዘብ ያለ ወገናዊነት? ሑኔታው ሁሉ እኮ በገዢው መደብ ፈቃደኝነት ላይ ብቻ የተመሰረተና የሚተገበር እኮ ነው፡፡ ይህ ተሰምቶ ያውቃል?

የኢትዮጵያው/ዩ ኤስ ኤይድም በነጻ የመወዳደርያ መድረክ በሌለበት ሁኔታ አንዳችም የፖሊሲ ፕሮግራም ማከናወን አለመቻሉን ያምናል፡፡በመካሄድ ላይ ያለው የግለሰቦች፤ የውጭ የእርሻው መስክ ኢንቬስተሮች፤ የመሬት ሽሚያ ሁኔታ በሚጨምርበት ሁኔታ ፖሊሲው የመሬትን አጠቃቀም ስርአት ማበጀትንና መፈናቀልን በማስወገድ በኩል የነዋሪውን መብት በመጠበቅና በማክበር ሚዛናዊ አድግትን ያረጋግጣል መባሉስ…………. ለግለሰብ የእርሻው ዘርፍ ኢንቬስተሮች‹‹መሬትን መስጠት››! ተሰምቶ ይታወቃል!

ወዳለፈው 2004፡ ያን መልካም ወቅት እንደነበረው ማስቀመጥ

በ2004 ዩ ኤስ ኤድ ‹‹የምግብን ማጣት ውድቀት አዙሪት መስበር፡ በኢትዮጵያ ችጋርን መከላከል›› አስተዳዳሪው አንድሪው ኤስ ናስቲዮስ ባሰፈረው ዘገባ ውስጥ ከተካተተው በቅንጭቡ የሚከተለው ነበረበት፡

….ኢትዮጵያ በሚታየው የምግብ አቅርቦት ችግረና በችጋሩ ሁኔታ ብቻዋን የቆመች ሃገር አይደለችም፡፡በመሆኑም ብቻዋናም ውጤቱ ዘንድ መድረስ አትችልም፡፡ጎረቤቶቿና የእድገት አጋሮቿ በአንድነት ይህን የችጋሩን ሂደት ማስወገድ፤ የምግብ እጦቱን ሂደት በመቀየር፤ ቀዳኒነት ሊሰጥ የሚገባውን የሕዝቦችን ጤናና የኤኮኖሚ ሁኔታ ማሻሻል፤ ለአሁኑና ለተተኪው ትውልድ አስፈላጊ ቢሆንም ወደዚያ ግብ መድረስ ቀርቶ መጠጋትም አልተቻለም፡፡ይህንንም ሁኔታ በአግባቡ ለመቋቋም የኢትዮጵያን ገዢ መንግስት ፈቃደኝነት፤ቁርጠኝነት፤ለለውጥ መነሳሳትን ይጠይቃል፡፡በኢትዮጵያ ያለው እውነታ አሳማኝና ግልጽ ነው፡፡ከሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች ያነሰ በተለይም ከምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች ጋር ሲወዳደር የወደቀ መሆኑን ያለፉት ዓመታት ያሳያሉ፡፡የዚህ የኢኮኖሚ ውድቀት ሰበቡም ድርቅና የችጋሩ ሁኔታ ሳይሆን በሃገሪቱ ላይ የሚታየው የአስተዳደር ድህነትና እጦት፤ የምግብ አቅርቦት ማነስ ሳይሆን ይልቁንስ ስትከተለው በነበረው ደካማ የኤኮኖሚ ፖሊሲ አነስተኛ በሆነው የኢንቬስትመንት የኤኮኖሚና የእርሻ እድገት፤የሌሎችም ምርቶች መቀነስ ናቸው፡፡ የኤኮኖሚው መውደቅም የሶሻል ደረጃውንም መድከም አባብሶታል፡፡የህ ደሞ ገዢውን መንግስት ስርአት ባለው ሁኔታ መምራት አላስቻለውምና ለችግር መዳረግ አማራጭ የለውም፡፡

በሜይ 2012 የወቅቱ ዩ እስ ኤይድ ዳይረክተርና የጂ8 ሀገራት በዋሽንግቶን የምግብ ዋስትና ስብሰባ ወቅት ለመለስ ዜናዊ በመግቢያ ንግግሩ ላይ፡

……ብዙ ሰዎች ስለኢትዮጵያ ያላቸው አመለካከት በችጋር ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም በተወሰደው የእርሻ ኢንቬስትመንት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በቅርቡ ከተከሰተው የድርቅ ሁኔታ ከችጋር በማዳን ከምግብ ተመጽዋችነትና ከእርዳታ ምግብ ልመና አድነሃቸዋል፡፡ምንም እንኳን አሁንም የግሉን ማህበረሰብ ያካተተ አዲስ የምግብ ዳረጎት ስርአት እየነደፍን ቢሆንም፤ከስብሰባው ውጪ በግል ካነሳነውና አስተያትህን ከሰነዘርክበት ሃሳብ አኳያ በገባነው ቃል ላይ መጽናት ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው ያልከውን ልታካፍለን ትችላለህ?

መለስ ቃል አልወጣውም አንደበቱ ተያዘ ተሳሰረ፡፡

ባለፉት ዘመናት ሁለ፤ ኢትዮጵያ የአሜሪካ እርዳታ የተባለው ሁሉ ተጠቃሚ ነበረች፡፡‹‹የኤኮኖሚ እርዳታ›› ‹‹የልማት እርዳታ›› ‹‹ወታደራዊ እርዳታ›› ‹‹ቴክኒካ፤ እርዳታ›› የድንገተኛ አደጋ እርዳታ›› ‹‹የችግር ማስወገጃ እርዳታ›› ‹‹የሰብአዊ እርዳታ›› እኛ የሌሎችም እርዳታዎች ተጠቃሚ ናት፡፡‹‹የባንድ ኤይድ›› እና ‹‹የላይቭ ኤይድም›› ምጽዋት አካል ነበረች፡፡ ዛሬ ዛሬ ደሞ ኢትዮጵያ ለዘለቄታው ‹‹በቦንድኤይድ›› ተጠፍንጋለች!

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

የነጻ ፕሬስና የዝንጀሮ ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ

Monday, July 2nd, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

እውነት በሃሰት ዲል ሲመታ!

ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትየጵያ ውስጥ ያለውን የፐሬስ ነጻነት ለማስከበር በሚደረገው ግብግብ ውስጥ የትግሉ ደጋፊ በመሆን በርካታ ጦማሮችን ጽፌያለሁ፡፡ በ2009 ባቀረብኩት ርእስ ስር የሰፈረው፤‹‹በኢትዮጵያ ነጻ ፐሬስ አኳያ ያለው የጦርነት ጥበብ›› የሚል ነበር፡፡ በነጻው ፕሬስ ላይ ይዥጎደጎድ የነበረውን የግፍ ጡጫ በተመለከተ ያደረብኝን መገረም ያመላከተም ነበር፡፡ “አንዲት ቢራቢሮን ለመግደል ትልቅ የድንጋይ መፍለጫ መዶሻ ማንሳት! ይሄ ነው እንግዲህ በነጻው ፕሬስ ላይ በ ግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ ገዢ መለስ ዜናዊ አላዋቂ ጦር አዝማችነት አሁን የተሰነዘረው ጥቃት፡፡” በ2007 በጻፍኩት ርእስ ‹‹በዝንጀሮ ፍርድ ቤት የአንኮ ፍርድ›› የሚል ሲሆን ጉድለትን ማረሚያ ሃሳቦችን ላለመቀበልና ግድፈቶችን ለማስተካከል የሚሰነዘርን ሂስ ለማፈን በጥቅም ላይ የዋለውን ትርጉም የለሽ ሂደትና በነጻው ፕሬስ ላይ የተቃጣውን የ “ካፍካዊ” የአፈና ዘዴ የተመለከተ ነበር፡፡ ዝነኛው የፍራነስ ካፍካ የመጽሃፍ ጥራዝ፤ የፍርድ ሂደቱ በፍርዱ ውሳኔ ይጀምራል:: “የሆነ ሰው ስለ ዮሴፍ የፈጠራ ወንጀል ሲያወራ ነበር፡፡ አንድ እለት ጸሃይ ገና ስትፈነጥቅ ያለ አንዳች ወንጀልና ያለምንም የማስረጃ ጠብታ ተያዘ፡፡” ከየጌቶቻቸውን ቅዠት በሚያዳምጡትና በቅዠት በሚመሩት የዕውቀት ድሆች በሆኑ ዳኞች ፊት ለፍትህ ቅረብ ተባለ፡፡የዮሴፍ ጉዳይ ያለቀት መስተጋብር ነበር፡፡ የፍረዱ ሂደት ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ምንነቱ የማይታወቅ ሚስጥር ነበር፡፡ከፍትሕ ወንበሩ በስተጀርባ በድፍረትና በማን አለብኝነት ማሃይምነታቸውን ተከናንበው፤ አሻንጉሊቶቹ ዳኞች ተብዬዎች ተወዝፈዋል፡፡ ዮሴፍ ክሱ ምን፤ ወንጀሉ ምን የት እንዴት የሚለውን ጨርሶ ስለማያውቅና የሚያውቀው ጉዳይ ቢኖር ንጽህናውን ብቻ በመሀኑ እነዚህ አገልጋዮች ላቀረቡት የፈጠራ ውንጀላ መከላከል አልቻለም፡፡ ምኑን ምን ብሎስ ይከላከል፡፡ ሊመሰክሩበት በሽርፍራፊ ጥቅማ ጥቅም ተገዝተው ስብእናቸውን ሸጠው ሊመሰክሩበት የተዘጋጁትን እቃዎች እንኳን መጠየቅ ማወቅም አልተፈቀደለትም፡፡ የዮሴፍ የፍርድ ሂደት በተደጋጋሚ እየተሰረዘ ይቀያየራል፤ ይዘገያል፡፡ ሕግም ሆነ ስርአት በሌለበት የክስ ሂደት ላይ ጠበቃው ጨርሶ ሊረዳው አልቻለም፡፡

በኢትየጵያ ያለው የመለስ ዜናዊ “ካፋካዊ” የዝንጀሮ ችሎት በኢትየጵያ የቅጥፈት የፍርድ ሂደት እንግዲህ የዚህ ተመሳሳይ ነው፡፡መለስ ዜናዊም እንግዲህ በእስክንድር ነጋ፤ርእዮት ዓለሙ፤ውብሸት ታዬ፤የስዊዲን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺብዬና ጆን ፒርሰን፤የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አንዱዓለም እና በሌሎቹም ላይ አገኘሁት በሚለው ድል የተነሳ እንገመሬ ዝንጀሮ ደረቱን ሊመታ ሊጨፍር ይችላል፡፡ የሁዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ እንደሚያሳየው እስካሁን ድረስ በጠረሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት ለእስር የታደረጉት ንጹሃን ቁጥር ወደ 34 ደርሷል፡፡ባለፉት 6 ወራት በኢትዮጵያ 11 ጋዜጠኛች፤በትንሹ 4 ተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች እና 19 ሌለች ለግፍ ወህኒ ተዳርገዋል፡፡

የመለስ ችሎት የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ለመሀኑ አንዳችም ጥርጣሬ የለም፡፡የአሜሪካን መንግስትና ሌሎችም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይህንኑ በአጽንአት ያረጋግጣሉ፡፡‹‹ከፍተኛ ተብለው በሚጠቀሱ ጉዳዮች›› የኢትየጵያ ፍርድቤቶች የአዝጋሚነት ባህሪ አለባቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፍርድ ቤቱ የውንጀላ ተከሳሾች ፋይል ጫና፤በአብዛኛው ደግሞ በፍርድ ስርአቱ ላይ በፈጠሩት አላዋቂ ሳሚ አይነት መሃይምነት የበዛበት ሂደት ስለሚሆንባቸውን እራሳቸው የመሰረቱት የክስ ፋይል እራሳቸውም ሊገባቸው ስለማይችልና ምን እንደሀነ ማወቅ ስለሚሳናቸው ከዚያ ግራ መጋባት ለመውጣት ሲሉ ማስረጃ ለማሰባሰብ በሚል ሰበብ የቀጠሮ ማራዘሚያ ይጠይቃሉ፡፡›› በ2010 የአሜሪካን ስቴት ዲፓርትመንት የየሃገሮች ዘገባ በኢትዮጵያ ስላለው ፍርድቤት ‹‹ሕጉ ነጻ የፍትህ ስርአትን ያዛል፡፡ ምንም እንኳን የሲቪሉ ችለት በተሻለ ነጻነት ቢሰረም፤የወንጀሉ ችሎት ግን እጅጉን ደካማና ስንኩል እንዲሆንና በትእዛዝ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ችግር ሲያጋጥምም ከገዚው መደብ ሃላፊዎች ጋር በሞባይል በመነጋገር የሚፈረድበት የፖለቲካ ውሳኔ ጣልቃ የሚገባበትም ነው::››

በዝንጀሮ ችሎት ላይ የተጣለ ውግዘት

በግፍ ለእስር የታደረጉት ንጹሃን ጋዜጠኞችና ሌሎችም እንዲፈቱ፤ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት (ሂዩማን ራይትስ ዎች) ና ሌሎችም ውገዘታቸውን እያስተላለፉ ነው፡፡የጋዜጠኞች መብት ጠባቂ ኮሚቴ ባስተላለፈው ተቃውሞ፤ “የኢትየጵያ መንግስት እንደገና እንደተለመደ ባህሪው፤ ሕጉን ሂሳዊና ነጻ የሆኑትን ዘጋቢዎች እያፈነ ነው፡፡ የኢትየጵያ መንግስት አሁንም በማስፈራራትና በማሰር አለያም ለስደት ከመዳረግ አልተቆጠበም፡፡ ይህም የኢትዮጵያ መንግስት በጣም ቀላልና ሚዛን ለማይደፋ ሂሳዊ አስተያየት እንኳን የመቀበያ አቅም እንደሌለውና ፈቃደኛነት አልባ መሆኑን ያሳያል፡፡” ይህን መሰሉ የህግ አካሄድ በፍትህ ስርአቱ እንዲቀለድበትና አመኔታ እንዲያጣ፤የሚሰነዘሩት ክሶች ሁሉ የቅዠትና የድንብር ግትር ፈጠራዎች እንደሆኑ በመግለጽ፤ ‹‹ይህ ወቅት በኢትዮጵያ የፍርድ ስርአት የጨለመበት ጊዜ ነው፡፡መንግስት አንድም የተቃውሞ ድምጽ እንዳይሰማ ለማድረግ በሚወስደው የግፍ ውሳኔ መሰረት ሃሳብን በነጻ የመግለጹ ጉዳይ ወደ መቃብር እየወረደ ነው፡፡ የፍርዱ ውሳኔ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፡፡” በኢትየጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ ‹‹የጠንካራና ሰላማዊ ታጋይ ጋዜጠኞች ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ የጸረ ሽብርተኛነት ሕጉ ሕገመንግስቱ ሃሳብን በነጻ ለመግለጽ ከሰጠው ሕገ መንግስታዊ መብት ጋር ለመጣጣሙ ጥረጣሬ እያሳደረብኝ ነው›› ብለዋል፡፡ የአሜሪካኑ ሴኔተር ፓትሪክ ሊሂም ባለፈው ሳምንት ለኮንግሬሽናል ሬኮርድ እንዳስቀመጡት፤ እንደ እስክንድር ነጋ ያሉትን ሰላማዊ ሰዎች በፖለቲካ ጎራ እንዳይነቀሳቀሱና አስተዋጽአ እነዳያደርጉ እያፈናቸውና እያሰራቸውም ነው›› በማለት የፍትሁን መዛባት በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የኢትየጵያ ሽፍንፍኑ የጸረሽብርተኝነት ሕጉ ነጻውን ፕሬስ ለማንና ለመወንጀል የተፈበረከ መሀኑ በሰፊው ሲተችበት የከረመ ነው፡፡ እስክንድር ነጋና የሌለች ጋዜጠኞች ለእስራት መዳረግ የዓለም አቀፍ ሁኔታ በሚፈቅደው መሰረት በመንቀሳቀሳቸውና ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ በመግለጻቸው ነው ለእስራት የተዳረጉት የራሱን ዜጎች ዴመክራሲያዊ መብት መጠቀምን በሚፈራ መንግስት ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት የአሜሪካን ምንግስት አስተዳደር የሚነሱ የሥብር ሁኔታዎችን በማጥፋት በኩል ባለን መግባባት በሚል ለመለስ ዜናዊ እውቅናና ድጋፍ የቸረው ቢሆንም፤ ግንኙነቱን የራሱን ጥቅምና የፖለቲካ ስልጣን ማጠናከሪያ በማድረግ ተጠቅሞበታል ከሽብርተኞች የሚለዩንን ጉዳየች አበክረን መመርመር ይገባናል፡፡በዚህም የሚቸረውን እርዳታ ተቀናቃኝ ሰላማዊ የሕዝብ ወገኖችን ለማፈኛነት እንዳይውል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡

አይበገሬዎቹ እስክንድርና አንዱዓለም!

ከካፍካው ዮሴፍ በተለየ ሁኔታ ‹‹ እንደውሻ›› ሳይሆን እስክንድርና ዓንዱዓለም ወደ መታሰርያ ቦታቸው ሲመለሱ አንበሳ አደን ውሎ በድል እየተከፈሰ እንደሚመለሰው አይነት ነበር አመላለሳቸው፡፡(ከሺ ጅቦች አንድ አንበሳ የላቀ ክብር ይጎናጸፋል፡፡) ቀደም ብለው ከበላይ ገዢ ጌቶቻቸው በሚፈስ የፍርድ ውሳኔ እንደሚጠናቀቅ ተገንዝበዋል፡፡ በመለስ ዜናዊ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ማንም የተከሰሰ ጋዜጠኛም ሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ የክስ መዝገቡ በነጻ የለቀቀው የለም፡፡ መጠርያ ስሙ ከምንም በላይ ገኖ፤ በተጠራ ቁጥር የገዢዎቹን መደብ አባላት የሚያርበደብደው ፤ የኢትየጵያ ፕሬስ ነጻነትም አርማ የሆው እስክንድር ነጋ ለነዚያ እርባና ቢስ ዓላማ ቢሶች መልእክት ነበረው፡፡ ‹‹እኔ ለሰላማዊ ትግል ታግያለሁ፤ ማንንም ግለሰብ ደፍሬ አላውቅም ከክብሩ ዝቅ አድረጌ አላውቅም፤ ምንም ወንጀልም አልፈጸምኩም፡፡ ስለዚህም ከከሳሾቼ በበለጠና እጅጉን በገዘፈ መልኩ ንጹህ ሕሊና አለኝ፡፡ ዝም ሊያሰኙት ሞከሩ››:: በሁልጊዜ ባሕሪው እስክንድር ነጋ ለጉልበተኞቹ እውነትን አሳያቸው፡፡ ‹‹ለፍትህ ልትቀሙ የግድ ነው፤ ሕሊናችን የፈቀደልንን እንድንናገር መብታችን ልትነኩብን አይገባም፤… በነጻ የመናገር መብታችንን ለመገደብ አንዳችም ህጋዊ መብት የላችሁምና፡፡››

በቅርቡ ታዋቂና የተከበሩ እራሳቸው ለግፈኛ ገዢዎች ጡጫና እስር መከራ የተዳረጉ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች የእስክንድርን መፈታት በመጠየቅ፤ ከባድ የሆነ ውግዘት በመሰንዘር፤ ‹‹እስክንድር ነጋን በሽብርተኛነት ፈርጀ ማሰሩ አግባብነትና ተቀባይነት የሌለው ነው››ብለዋል:: ጀግናዬ ስለሆነው እስክንድር ነጋ ባለፈው ኤፕሪል ለክብሩ ጥቂት ቃላቶች አስፍሬ ነበር፡፡

እስክንድር ለየት ያለ ጀግና ነው፡፡ ጀግንነቱን ያረጋገጠው ደግሞ ከእውነትና ከሃሳብ ባልራቀ መሳርያው ነው፡፡ ቅጥፈትን በሃቅ ሰይፍ ይቀነጥሰዋል፡፡እኩይ ሃሳቦችን በመልካም አስተሳሰብ ያሸንፋል፡፡ ይህን ሁሉ ሲያደርግ ትጥቁ የሰላ ብእር ብቻ ነው፡፡ እስክንድር ተስፋ መቁረጥን በብሩህ ተስፋ ይዋጋዋል፤ፍርሃትን በቆራጥነት፤ቁጣን በምክንያታዊነት፤ስድነትን በጨዋነት፤መሃይምነትን በእውቀትና ብልሃት፤ ግልፍተኛነትን በእርጋታ፤ ጭቆናን በመቻቻል፤ጥርጣሬን በመታመን፤ ጭካኔን በርህራሄ ያሸንፋል፡፡››

በየቦታው ለተበተኑት የፕሬስ ታጋየች አርማና ኩራት፤ ጀግና የሆው እስክንድር ነጋ፤ እርባና በሌላቸው እራሳቸውን እንኳን በማያውቁ፤ ከመታዘዝና ትእዛዝ ከመቀበል ውጪ እኔ የሚለው ቃል እንግዳ በሆነባቸው ግብስብሶች ለፍርድ መብቃቱ እዬዬዬዬ የሚያሰኝ ነው፡፡

አንዱአለምም ሽንጡን ገትሮ ተናገረ:

ያሳለፍነው ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰብአዊ ክብሩና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የታገለበት ዘመን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ባለቤት ለመሆን እስካሁን አልታደለም፡፡ እኔም በተፈጠርኩበት በዚህ ዘመን ለራሴ፣ ለልጆቼና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ዴሞክራሲና ነፃነት እንደሚገባን በማመን አቅሜ በፈቀደው መጠን ታግያለሁ፡፡ ይኼን በማድረጌ በማንም ላይ በክፋት አልተነሳሁም፤ ይኼን በማድረጌ ህግ ጥሼ አላውቅም፤ ይኼን በማድረጌ በደሃዋሃገሬ ጥቅም ላይ አልተነሳሁም፤ ይሄን በማድረጌ ፈጣሪዬን፣ የኢትዮጵያን ህዝብም ሆነ ህሊናዬን የሚያሳዝን አንዳች ነገር ፈፅሜያለሁ ብዬ አላምንም፡፡ ፍፁም ሰላምይሰማኛል፡፡ እኔን እዚህ ያቆመኝ የነፃነት ናፍቆት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችም ፍትህን ለምኜ ስነፈግ ይኼ የመጀርያዬ አይደለም፡፡ ከሳሾቼ እንድጠጣውየሚፈልጉትን የግፍ ፅዋ በፀጋ ከመጠጣት ውጪ ባልፈረፀምኩት ወንጀል ማቅለያ የመጠየቅን አማራጭ ህሊናዬ ስላልተወልኝ አዝናለሁ፡፡

መለስ ዜናዊ ደግሞ ደጋግሞ ነጻውን ፕሬስ የሚከሰው የሚደቁሰው ለምንድን ነው?

ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑትንና ተፍጨርጫሪ የሃገሪቱን የነጻውን ፕሬስ አባላት፤መለስ ዜናዊ ወጥቶ ወርዶ አፋሽ አጎንባሽ ሀኖ ለምንድን ነው የሚፈታተናቸው? ለምንስ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ውግዘትስ መስሚያ ጆሮ የደፈነበት ሰበብ ምንድን ነው? በሃገሪቱ ብዙ መዋእለ ንዋይ የሚያስወጡትንና እርባና ቢስ የሀኑትን ጋዜጦች መጽሄቶች፤ሬዲዮና ቴሌቪዥን ይዞና ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትሉ ግን የራሳቸውን ስም እንኳን በአግባቡ መጻፍ የማይችሉ ሁልቆ መሳፍርት የሌላቸውን በቀቀን ጋዜጠኞች የሚያንጋጋው መለስ ዜናዊ ትንሽ ሺወች ቅጂ የሚያወጡትን የነጻውን ፕሬሶች ለምኔ ብሎ ነው ግራ የሚያጋበቸው?

መልሱ በጣም ቀላል አጭርና ግልጽ ነው፡፡ሃቁ! መለስ እውነትን መቀበልም ሆነ እውነት ምን እንደሆነ ጨርሶ አያውቃትምና ነው፡፡ የገዢውን ግፈኛ መንግስት ሙስናውን፤ጭቆናውን፤ችጋሩን፤ጋጠ ወጥነቱን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው የግሉ ነጻ ፕሬሱ ስለሆነ ነው፡፡ ነጻው ፕሬስ እሱነቱንና ማለቂያ የሌለውን ውድቀቱን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው ነጻው ፕሬስ ስለሆነና ያንን መቋቋም ስለማይችል ነው፡፡ የሕብረተሰቡን ትክክለኛ አስተሳሰብና አመለካከት ለመስማትና ሕዝቡ የሚሰነዝረውን አስተያየት አዳምጦ ድክመቱን ለማወቅ ብቃቱም ፈቃደኛነቱም ስለሌለው የእውነት ነጸብራቅ የሆነውን ነጻ ፕሬስ ማድመጥም መስማትም አይችልም አይፈልግም፡፡ ድክመቱን ነቅሰው በማውጣት የሕዝብን ጉዳትና ስሜት በመከታተልና በማወቅ ሲነግሩት ከመስማትና ከማስተካከል ይልቅ ተደፈርኩኝ ባይነትን ዋነኛ የጀግንነት ማስመሰያው አድርጎ መኖርን ይመርጣል፡፡ በአካባቢው ያጎራቸው እርባና ቢሶችም በተናገረ ቁጥር እልታቸውንና ጭብጨባቸውን ስለሚያቀልጡለትና፤ ንግግሩን በመቀባበል ያለ አንዳች ማገናዘብ እየደጋገሙ የማሰልቸት ቱልቱላቸውን በመንዛት ያላንተ ማን አለ በሚሉት የሆድ መሙያ ውሽከታቸው በማሞገስ ያልሆነውን እያደረጉት ወደ ጥፋት ገደል እየገፉት ቢሆንም እሱ ግን ሽንገላቸውን እውነት ብለ እራሱን በማታለል የሚኖር ነውና እውነትን ይፈራታል፤ ከእውነት ጋር ደግሞ የግል ፕሬስ ማህበርተኛ በመሀኑ እሱንም ይጠላዋል ይፈራዋል፡፡

በቅርቡ በአረቡ መንደር በታየው ክስተት መረዳት እንደሚቻለው፤ጨቋኝ ገዢወች ከአሸዋ እንደተሰራ ግንብ ናቸውና በቀላሉ የባህር ወደብ ሲነኩ ፍርክስክሳቸው ይወጣል፡፡ ምንም ያህል ሕዝቡን ቢያስፈራሩትና የነጻውንም ፕሬስ ቢያዋክቡት በመጨረሻው ግን በታላቁ የሕዝብ ውሳኔና መነሳሳት በአቧራ መሰብሰቢያ ተጠራርገው ወደ ታሪካዊ ቀሻሻ መጣያ መወርወራቸው አይቀሬ ነው፡፡

በነጻው ፕሬስ ላይ ወከባውና ጠርነቱ ይቀጥላል...

ወከባውና ጦርነቱ በሃቅ ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ የነጻውን ፕሬስ ማዋከቡ ይቀጥላል፡፡ብቸኛው በሃገር ውስጥ በመንቀሳቀስና ፍንክች ያባ ቢላ ልጅ ባለው በፍትሕ ጋዜጣ ላይ የታወጀው ጦርነት ለወከባው መቀጠል ማስረጃ ነው፡፡ዘመቻው በጣም ዝቅተኛና ተራ አሉባልታዊ ሂደት ያለበት፤ተንኮሉ ተራ ያልተገራ ግልቢያ የሚመስል፤ጸሃፊውም ሆነ አርሞ ይሁንታ የሰጠው ውሸት ያለቀበት ተላላኪ መሆኑ በይፋ ይታያል፡፡ይህን የሚያደርገው የስለላ ቡድንም በፍትሕ ላይ ያነጣጠረውን የውንጀላ ዳር ዳርታ በዚህ መልኩ ማድረጉ ሃገሪቱ በምን አይነት ሰዎች እንደምትጠበቅ የሚያሳይና የሚያሳፍር ነው፡፡የፍትሕ ጋዜጣን ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝን ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት እንዳለው አስመስሎ በማዘጋጀት ወደ ኢሜይሉ መላክ ቢያሳፍርም እነሱ ላኪዎቹ ግን ድል አደረግን ጉድ ሰራነው ብለው እየተጨባበጡ ሳይገባበዙ አይቀሩም፡፡ ያሳዝናል ተራ የውንብድና ተግባር ነውና! ኢሜይሉ በአልሸባብ ሰዎች እንደተዘጋጀና ወደ ተመስገን ሲላክ በሰላዮች ተጠልፎ የተያዘ ለማስመሰል ከንቱ ጥረት ተደርጓል፡፡

እንደሚታወሰው አልሸባብ በሚስጥር በኢትዮጵያ፤በሶማሌላንድ፤በኬንያና ኡጋንዳ የሽብር ቅስቀሳ ስራ እንድሰራ መድበኛል፡፡ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንድችል ከወኪልህ ከአቶ ማሙሽ ፈንቴ ጋር ኤርትራ ውስጥ ተገናኝተን በጋዜጣህ ላይ የፕሮፓጋንዳ ጽሁፎች ለማተም በተደረሰው ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያንና የአሜሪካንን ጥቅም የሚገዱ ጽሁፎች ለማተምም ያንተን ስምምነት አግኝተናል፡፡

ምነው ብትተዉን ጃል!

ይሄ እኮ አዲስ አይደለም ላለፉት በረካታ ዓመታት ያየነው ነው፡፡የመለስ ዉንጀላ ሶስት ደረጃ አለው፡፡መጀመርያ ተቃዋሚ አስደንጋጮቹን ለማሳነስ ይመክራል:: ለጥቆ ይወነጅላል፤ በሶስተኛው ስብእናቸውን ይነጥቃል፡፡ በእስክንድር ነጋ፤ በአንዱዓለም አራጌ፤በዳዊት ከበደ እና በለሎቹም ላይ የፈጸመው ደባ ይህንኑ ነው፡፡አሁን ደሞ ፍትሕ በአንደኛው ደረጃ ላይ ነው፡፡ስም ማጥፋትና ወንጀል ማግበስበስ፤ ተመስገን ደሳለኝና ፍትሕ አሁን በስም ማሳነሱና ማጥፋቱ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡በቅርቡ የገዢው ስርአት ንብረትና አፈ ጉባኤ በሆኑት መገናኛዎች ሁሉ ‹‹አሸባሪዎች፤‹‹ሰርጎ ገቦች›› ‹‹ጠብ ጫሪዎች›› ‹‹የሽብር ሴራ ቀስቃሾች›› ‹‹የውጭ ቀጥረኞች›› ‹‹ሰላዮች›› ሌላም ሌላም በመባል የንባብና የጽሁፍ መማርያ አፍ መፍቻ ይሀናሉ፡፡ ልክ በእስክንድር ነጋና አንዱ ዓለም አራጌ ላይ እንደተፈጸመው ሁሉ ከጥቂት ቀናት በኋላ በመንገድ ላይ ሲያዝ በቪዲየ ይቀረጽና የተመስገን መታገት ይወራል፡፡ (አስክንድር ነጋ በታገተበት ወቅት የነበረውን ዘግናኝና አሳፋሪ የሰላዮች ተግባርና በዚያ በሽብር ወቅት ሕጻን ልጁ ሲያለቅስ እነዚያ ለሰው ክብር፤ ለሕጻናት ርህራሄ የሌላቸው ማፈሪያዎች ሲፈነድቁና ሳቅ በሚመስል ግልፈጣ ሲያጓሩ ያሳዩትን ቪዲዮ ሁሉም ሊያየው ተገቢ ነው፡፡)

ከዚያም የተጀመረው የስብእና ማራከስ ሂደት ይቀጥላል፡፡ማሰቃየቱ፤ ፍርድ ቤት ከመቅረብ አስቀድሞ ዱላው፤ ሕክምና መከልከል፤ ከቤተሰብ ጋር ግንኙነት መከልከል፤ በየቀኑ እስረኛ መዘለፍ፤ ለብቻ ለይተ ማሰርና ሌላም ሌላም የግፍ ጫና ይከተላል፡፡ በመጨረሻም የተመስገን ደሳለኝና የሌለቹም የፍትህ ጋዜጣ ባለሙያዎች የፍርድ ጨዋታ በዝንጀሮዎቹ የፍትህ አደባባይ አምባሳደሮችና የውጭ ዓለም አቀፍ ድርጅተች ወኪሎች፤ የንጹሃን ተከሳሸች ቤተሰቦች በአዳራሹ በሚገኙበት ይቀጥላል፡፡ወዲያውም የፍርዱ ውሳኔ ይነበባል… ጥፋተኛ፤ ጥፋተኛ፤ ጥፋተኛ…15 አመት.. 20 አመት… የሞት ፍርድ…

ሁሉም ነገር ሳያታለም የተፈታ ነው!

ዘመቻው ይከሽፋል፤ ጠርነቱ ግን በአሸናፊነት

ይህ በኢትየጵያ ያለው የነጻው ፕሬስ ያላለቀ ታሪክና በውስጡ የሚገኙት የባለድሎችና የፍትህ አልባዎች እጣ ፈንታ መንታ ስለት ያለው ሰይፍ በመዘዙ ግፈኛ ፈላጭ ቀራጭ ገዢዎችና የተባእራቸውን፤ እርሳሶቻቸውን፤ የኮምፒዩተር መተየቢያ ቦርዳቸውን በአነገቱ ጋዜጠኞች የሕዝብን አመኔታና ፍቅር ይሁንታ ለማግኘት በሚካሄደው ጦርነት ይለያል፡፡ የዚህ ጦርነት ውጤት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ተፈትዋል ብዬም አምናለሁ:: ኤድዋርድ ቡልዌር­-ሌተን በግጥሙ እንዳሰነበበው የመጨረሻው ድል ያላንዳች ጥርጥር የብእር አንጋቢዎቹ ነው፡፡

እነሆ እውነት!

ከሰዎች አገዛዝ በጣሙን የላቀ

ከማንኛውም ሃይል የብእር ሃይል ነው እጅግ የመጠቀ

የአጎብጓቢዎች ድንፋታ ምንም ላይፈይድ

ከጌቶቻቸው አፍ በሚሰነዘር ፍርድ

አይበገሬዎችን ለማንበርከክ ዱካቸውን ለማጥፋት

የማይወጡትን መሞከር የማይቻለውን መመኘት

ምድር ድምጽ አልባ መስላ እየታዘበች

ሰይፉ ይውደቅ ትላለች ብእርም; ሃገርን ታድናለች፡፡

ሆኖም: ታላቁ ጥያቄ ሃገርን ማዳን ወይስ ነጻውን ፕሬስ ማዳን ከሆነ: እኔ ቶማስ ጄፈርሰን እንዳለው ሁሉ ሁለተኛውን እመርጣለሁ፡፡ ‹‹የመንግስታችን መሰረቱ የህብረተሰቡ አመለካከት በመሆኑ፤ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባወም ያንን ማስከበር ነው፡፡መንግስት ያለ ጋዜጣ ይኑረን ወይስ ጋዜጣ ያለመንግስት የሚለው ሃሳብ ቢቀርብልኝ እኔ ሁለተኛውን ለመምረጥ ቅንጣት ታህል ጊዜ አልፈጅም::››

የጠላቶቻችን ተግባርና፤የወዳጆቻችን ዝምታ

ደ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳሉት ‹‹የጠላቶቻችንን ቃሎች ከምናስታውስ ይልቅስ የወዳጆቻችንን ዝምታ እናስበዋለን›› እኔ ደግሞ፤ የጠላቶቻችንን ተግባርና ግፋዊ ድርጊት እያሰብነው ይቅርታንም እንቸራለን የሚያደርጉትን አያውቁትምና፡፡ የሚፈጸመውን ግፍ፤የሕዝብ መብት ገፈፋ፤ የሰብአዊ መብት መጣስን፤የፍትህን እጠትና ሌላውንም ሁሉ እያዩ እነዳላዩ እየሰሙ እንዳልሰሙ በመሆን ጀሯቸውን የጠቀጠቁትን፤ አፋቸውን የለጎሙትን፤ አንደበታቸውን የዘጉትን ወዳጀቻችንን ግን ይቅርታም አልቸር ልረሳውም አልፈቅድም፡፡

በእስር ስር ያሉትን ዘወትር አብረናቸው እንዳለን ከማሳወቅና እንዳልረሳናቸውና እንዳልተውናቸው ከማሳየት የላቀ ምንም ተስፋ የለም፡፡ እስክንድር ነጋ አንዱዓለም አራጌ ርእዮት ዓለሙና ሌሎችም የግፍ ታሳሪወች በጨካኝና ግፈኛ ገዢ ዋሻ ውስጥ ናቸው፡፡ በየእለቱ ነፍሳቸው እንዲሳሳና እንዲንበረከኩ እየተደረጉ ነው፡፡ ይህን ደግሞ አንሰማውም ዋሸው ጥልቅ መዝጊያው ድርብ ነውና፡፡ ድምጻቸው ታፍኗልና ድምጻቸው ልንሆንና ልንጨህላቸው ይገባል፡፡ ያሉበት ቦታ የግፈኛው አገዛዝ የግፍ ዋሻ በትንፋገት የተሞላና ለበሽታ የሚያጋልጥ በመሆኑ ስቃያቸው ሊሰማን ተገቢ ነው፡፡ ስለኢትየጵያ የፐለቲካ እስረኞች ጉረሯችን እስከሰል መጨህ ያለብን ለታይታ ሳይሆን፤ግዴታችን፤ክብራችን፤ትክክልና እውነትም በመሆኑ ነው፡፡ በመጨረሻም፤ የኢትየጵያ ፍጻሜ ሊሆን የሚገባው የግፍ ገዢዎችና ፈላጭ ቀራጮቹ እንደሚያስቡት ግልብነት አይደለም፤ ጭካኔ፤ግፍ፤ኢሰብአዊነት ሳይሆን፤ ያለሃጢአታቸው ለተዘጋባቸው ወገኖቻችን ክብር ስንል በሰብአዊነት፤ በክብር፤በመደማመጥ፤ በመግባባት፤ በአንድነት መሆን አለበት፡፡ለዚህም ነው በአንድ ላይ እጅ ለእጅ በመያያዝ ላለመድከም ለራሳችን ቃል ገብተን፤ጥሪዎችን በማዳመጥ ብቻ ሳይሆን አዳምጦ በመቀላቀል፤ ያለ እረፍት በኢትዮጵያ ያሉትን የፐለቲካ እስረኞች የነጻነት መድረሻ ማፋጠን አለብን፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም የፐለቲካ እስረኞች ይፈቱ!

የእትዮጵያ ነጳ ፕሬስ ነጳ ይሁን!

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

ኢትዮጵያ፡- ሰማይ ተደረመሰ!

Monday, June 25th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ሰማዩ ተደረመሰ!

ብዙዎች አንባቢዎቼ ‹‹ተረት ተረት የመሰረት››ን የመኝታ ተረቶች ምን ያህል እንደምወዳቸው ያውቃሉ፡፡ በቅርቡ በጣም የምወደውን የመኝታ ሰአት ተረት “የፒኖኪዮን ታሪ በአፍሪካ” ጽፌ ነበር፡፡

ለመሆኑ ሰለ ሚጢጢዋ ጫጩት ክፉኛ ዽንጋጤ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?

ይሄዉላችሁ አንድ ቀን ሚጢጢዋ ጫጩት ጓሮ መሬቱን በመጫር ላይ ሳለች፤አንዲት ነገር አናቷ ላይ ዱብ አለባት፡፡‹‹እረገኝ››፤ ‹‹ሰማዩ ተደረመሰ! ቶሎ ሄጄ ለንጉሡ ልናገር፤ አለች፡፡ ሚጢጢዋ ጫጩት ሄኒ ፔኒን እስታገኝ ድረስ ሮጣ ሮጣ ሮጣ፤ ሲታገኛት፤ ምንድን ነው ልብሽ እስኪፈነዳ የሚያሮጥሽ አለቻት:: እንዴ ሄኒ ፔኒ ሰማዩ እኮ እየተደረመሰ ነው:: ታዲያ ለንጉሱ ልነግር ነዋ አለች፡፡ ሚጢጢዋ ጫጩትና ሄኒ ፔኒ ይህንኑ ደግመው ለዳኪ ዳድል፤ ለጉሲ ሉሲ፤ ለተርኪ ለርኪ፤ ለፎክሲ ሎክሲም በእግረ መንገዷ ላይ ሲያገኛቸው ነገረቸው፡፡ ይህን የሰማውም ፎክሲ ዎክሲ ቀበሮ: ታዲያ እኮ እኔ ወደ ንጉስ ቤት የሚያደርሰውን አአቁአራጭ አውቃለሁ ኑ ተከተሉኙ አላችው፡፡ ያ ተንኮለኛ ፎክሲ ዎክሲ ቀበሮ ግን በነዚህ በሚያማምሩ ባለላባዎች ጓደኞች: በመንደላቀቅ ሊቀረጣጥፋቸው ወደ ጉድጓዱ በር ነበር የወስዳቸው፡፡ ተሰባስበው ወደ ፎክሲ ዎክሲ ዋሻ ሊገቡ ሲሉ፤ የንጉሱ የአደን ውሾች ሲጯጯሁ ሰሙ፡፡ ፎክሲ ዎክሲም ይህን ሲሰማ ጉድ እንደፈላበት አውቆ በአቆራራጭ በጫካው ውስጥ በመሹለክለክ የንጉሱ የአደን ውሾች ከኋላው ሲከተሉት መለስ ብሎ ሳያይ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ጠፋ፡፡

የሚጢጢው ጫጩት ታሪክ በኢትዮጵያ ያለውን መንግስት መባነን፤ ቅዠት፤ ፍርሃት፤የሚያሳይ ነው፡፡ ለሕብረተሰቡ መድረስ ያለበትን ዜናና ኢንፎርሜሽን ፈላጭ ቆራጩ ግፈኛው መለስ ዜናዊ ለማፈን በተንቀሳቀሰ ቁጥር ሰማዩ ይደረመስበታል፡፡ በ2010 የአሜሪካን ድምጽን የአማርኘውን ፕሮግራም ለማፈን የማይታመንና የተለመደውን የውሸት ጣቃ በመተርተር ሲወነጅል: ‹‹በተለያየ መንገድ እንደተረዳነው ላለፉት በርካታ ዓመታት የአሜሪካ ድምጽ የአማራኛው ሬዲዮ አሳፋሪ የሆኑትን እንደ ሩዋንዳው ሬዲዮ ሚል ኮሊንስ፤በሚመስል መልኩ አጥፊና አጋጭ የሆነ ጨርሶ የጋዜጠኝነትን ስርአት ያልተከተለ፤ አጥፊ ፕሮፓጋንዳ እንደሚዘራ ተገንዝበናል›› በማለት የአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያን፤የሩዋንዳ እልቂት ሬዲዮ ጣቢያ ለማድረግ ተንደፋድፈዋል፡፡

መለስ ለመላው ዓለም በዓለም እጅጉን አስጊ የሆኑትን ሽብርተኛች አትዮጵያ ውስጥ ይዣለሁ፤ አስሬያለሁ፤አደገኞች የሆኑትን ዎደር የለሽ በነጻ የመጻፍ የ2012 የፔን ተሸላሚውን እስክንድር ነጋን፤ ወጣቷን አይበገሬ ወጣት ጋዜጠኛና የ2012 የ ዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን በጋዤጠኝነት ጥንካሬ ተሸላሚዋን ርዕዮት ዐለሙን፤ እንዲሁም ጀግናውን በመለስ የፍርሃት አስተዳደር የተዘጋው የአውራአምባ ታይምስ ኤዲተር ውብሸት ታዬን ቃሊቲ አስገብቻለሁ በሚል የእብለት ቱልቱላ ደንፍቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካው ሴኔተር ፓትሪክ ሊሂ ባቀረቡት የኮንግሬስ ሬኮርድ ንግግራቸው የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞች በሰላማዊ መንገድ ተግባራቻውን እንዳያከናውኑ አሰቸጋሪ ሁኔታ በመፍጠር እስንድር ነጋን የመሳሰሉት በጋዘተጠኝነት ሙያቸውም በፖለቲካውም ምድር እንዳይነቀሳቀሱ አድርጓቸዋል በማለት ተናግረዋል፡፡

ኢትጵያውያን በሃገራቸው የተነፈጋቸውን በነጻ ኢንፎርሜሽና ከተለያዩ ነጻ ዘጋቢዎችና ሚዲያዎች ማግኘት እንዳይችሉ መለስ በሚቻለው ሁሉ በመሽከርከር በማገድ ላይ ይገኛል፡፡ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች (ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ) እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ መንገስት ማንኛውንም የኢንፎርሜሽን ልውውጥ እንዳይቻልና ኢትዮጵያዊያን ከዓለም ሁኔታ ተነጥለው እንዲኖሩ በማድረግ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሚጢጢ ጫጩቶች እጅግ ከመደናበራቸው የተነሳ፤ ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠሩዋቸው ማተሚያ ቤቶች እንደ ብርሃንና ሰላም ባሉት ማተሚያ ቤቶች የሚታተሙት ጋዜጦች በሙሉ ፖለቲካዊ ምርመራ ሳንሱር እንዲደረግባቸው አድረጓል፡፡ በተቀረጸው የሕትመት ውል ኮንትራት አንቀጽ 10 ስር ‹‹ሕግን የሚጻረሩ ህትመቶችን ስለመከልከል›› በሚለው ውስጥ ማተሚያ ቤቱ ምንም አይነት ሕግን የሚተላለፍ ጉዳይ ያለ መስሎ ከተሰማው ላለማተም መብት አለው፡፡ የመጻፍ ነጻነት የተከበረ ነው በምንም ሁኔታ ሳንሱር አይኖርም የሚለውን የህገመንግስቱን አርቲክል 29ኝን ይጻረራል ብሎል፡፡ ነጻና ገለልተኛ ለሙያው ታማኝ የሆነና በራሱ የህግ ልዕልና የሚመራ ከአገልጋይነት የነጻና ሕዝባዊ የሆነ ዳኛ ብቻ ነው በበቂ ምክንያት ላይ በመንተራስ የሚዲያን ነጻነት ሊገታ የሚችለው፡፡ ያም ሆነ ይህ ለመለስ ዜናዊና ለኩባንያው ስለ ሕገመንግስታዊ ሕግ መናገር ማለት፤ ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ አለያም ውሃ ቢወቅቱት እምቦጭ እንደማለት ከንቱ ድካም ነው፡፡

ድንበር አልባ ጋዜጠኞች እንደሚሉት ብቸኛ የኢንተርኔት ግልጋሎት ሰጪ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም› ቶር የተባለውን ዓለማ አቀፍ የኔት ወርክ አገልግሎትና የተዘጉ ድህረገጾችን በስውር መክፈቻ ለመዝጋትና ለማፈን መሳርያ ገዝቷል:: ቶር እንዳሰባሰበው መረጃም ከማርች እስከ ጁን 2012 ባለው ወቅት በቶር ተጠቃሚ የሆኑትን ግለሰቦች ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ መሃል ከ350 እንደማይበልጡ ዘግቧል፡፡ይህም ያን ያህል ወጪ የወጣው ከ80 ሚሊዮን ህዝብ መሃል ከ400 የሚያንሱ ግለሰቦች በመጠቀማቸው ነው ማለት ነው፡፡ ምን ይሉት አስተሳሰብ ነው ይሄ ወይስ ጭርሱን ገዢው መንግስት በፍርሃት ርዶ የሚያደርገውን ማጣቱ ነው፡፡

ሰማዩ እየተሰነጣጣቀ ነው!

የግል ኮምፒዩተርና የራሳቸው ኢንተርኔት ካላቸው ባሻገር በገጠርም ሀፖነ በከተማው ውስጥ ያሉት ወጣቶች መሃል የስካይፔ እና የሌሎች በኢንተርኔት ስልክ መጠቀሚያ አገልግሎቶች በጣሙን ተወዳጅነት አላቸው፡፡ያም ሆኖ ግን የነዚህ ተጠቃሚዎች ከቁጥር የማይገባ ከመሆኑም ባሻገር የሚገኘውም አገልግሎት ዋስትና የሌለው ብል እንደበላው ጨርቅ የሚቆራረጥና ተስፋ አስቆራጭ አገልግሎት ነው፡፡ የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍል ጥናት እንደሚያሳየው፤በፍሪደም ሃውስ ፍሪደም ኦን ዘ ኢንተርኔት 2011 ላይ ሲያስረዳ ኢንተርኔቱ ከተገኘ በኋላ በአዲስ አበባ ሳይበር ካፌ ውስጥ አንድ መልእክት ከፍቶ ለማንበብ ያውም በብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ስድስት ደቂቃዎች ይወስዳል፡፡በሰብ ሰሃራ አፍሪካ ካሉት ሃገሮች ሁሉ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ የኢነርኔትን መልአክቶች የምትቆጣጠር ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ዪንተርኔት ተጠቃሚው ቁጥር 0.5 በመቶ ከሰማንያ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ መሃል ነው፡፡በዚህም ሁኔታ ከሴራሊዮን ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነች አንደኛ ሴራሊዮን ትሆናለች፡፡ሌላ አብሯቸው የተሰለፈ የዚህ አጸያፊ ተግባር ተሳታፊ አልተገኘም፡፡

ምንም አንኳን ኢትዮጵያ በብዛት የሰው ቁጥር ያለባት ሃገር ብትሆንም፤እርባና ቢስ የሆነ መዋቅር ያላትና መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽንን አገልግሎት በሞኖፖል የያዘበት ሃገር በመሆኗ የዲጂታል ሚዲያውን እድገትና የሕብረተሰቡንም ተጠቃሚነት እንዲያቆለቁል እያደረገው ነው፡፡ በአህጉሩም ካሉት ሀገራት በሙሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች አነስተኛው ቁጥር የሚገኝባት ሀገር ናት፡፡ በአፍሪካ ካሉት ሁሉ ከፍተኛውን የኢንተርኔት መቆጣጠርያ መሳርያ ያስገባችና ለዚያውም ለተሻለ የሃገርና ሕዝብ አገልግሎት የሚችለውን ገንዘብ የሕዝብን መብት ለማፈኛ መጠቀሚያ አድርጎታል፡፡ የነጻ አስተሳሰብ መብት ገፈፋን በይበልጥ በማጠናከር፤የነጻው ፕሬስን በማገድ፤እና በ2005 ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከስር መሰረቱ ምርጫውን ካሸነፉበት ጊዜ አንስቶ የዚህ መሰል አጸያፊ ተግባር ገዚው መንግስት በማከናወን ላይ ነው፡፡

አንድ ዜጋ ስካይፕ የኮምፑተር ስልክ መነጋገሪያን በመጠቀሙ ብቻ መለስ ዜናዊ ለ15 ዓመታት ማሰርን ለምን ፈለገ? ታዛቢዎች እንደሚሉት ይህ የቴሌ የውሸት ቀላማጅ ሕግ፤ በእርባና ቢስ ዲክታተሮች መደናበርና መቅበጥበጥ፤ ንፍገት ጥቅም ፍለጋ የተነሳ ተግባር ነው፡፡ የቢቢሲ የቀድሞ የዜና ዘጋቢ ስትናገር፤ ገዢው መንግስት ይህን የሚያደርግበት ዋነኛው ሰበብ በመንግስት የሚተዳደረው ቴሌኮሙኒኬሽን በዚህ ገዳዳ ሕግ በመጠቀም ሕብረተሰቡን በአቅሙ ስልክ የሚያስደውሉትና ኢንተርኔት ካፌዎች ከስራ ውጭ በማድረግ ለማዘጋትና ብቸኛ አገልግሎት ሰጪነቱን በማረጋገጥ አሁንም ቀድሞም እንደሚያደርግ እጅጉን በናረ ዋጋ ከሕብረተሰቡ አቅም ጋር ባልተመጣጠነ ተመን ንግዱን ለመቀጠል እንዲችል ነው፤ብላለች፡፡ ከዚህ ባለፈም ገዢው መንግስት ባስገባው ብዙ የሃገሪቱ ገንዘብ በፈሰሰበት መቆጣጠርያው ስካይፕ የኮምፑተር ስልክ መነጋገሪያ በቀላሉ ሊጠለፍ ስለማይቻልና አስቸጋሪነቱ ደግሞ የስለላውን ስራ ስለሚያከሽፍበትም ነው፡፡ በዚህ አካሄዱ ገዢው መንገስት ከሕገመንግስቱ መመርያ ውጪ እንደፈለገው በማድረግ የህዝብን መብት ደግሞ ደጋግሞ ለመግፈፍ እንዲያስችለው የወጣው አዋጅ የሚያሳፍርም የሚገርምም ነው፡፡

የቴሌኮም ቀላማጅ ህግ እወጃ 2012

አሁን በስፋት የሚነገርለት የቴሌኮም የቅልመዳ አዋጅ እንደሚናፈሰው ወሬ ሳይሆን አሁን፤ ገና በረቂቅ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ሆኖም ግን ቀድሞ የነበሩትን ህግ ተካ ወይም በነዚያ ላይ ተመስርቶ ወጣ ተባለም በራሱ ወጣ ቢባልም ረቂቅ የሚባል አንድም አዋጅ ለመለስ የማሕተሙ ፓርላማ ቀርቦለት አያውቅምና አሁንም እንደተለመደው ያለቀለትና በመለስ ተፈርሞ ከቀረበ ፓርላማ ተብዬውም አገልግሎቱን ለማረጋገጥ እንደተለመደው እጃቸውን አውጥተው (አውረዱ እስኪባሉ) ያጸድቁታል፡፡ የመለስ ቃል ሕግ ነው፡፡ እርባና የሌለውን ሰብስቦ መለስ እስካቀረበው ድረስ ፓርላማውም ማሕተሙ ነውና በመርገጫ አስነክቶ ማረጋገጫ ያሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህም ይህም የቴሌኮም የውሸት አዋጅ መጽደቁ የታወቀ ነው አለምንም ጥርጥር የተረጋገጠ ነው፡፡ ግን ይህ የቴሌ አዋጅ ምነድን ነው?

አዋጁ በፊት ለፊቱ ስታይ፤በሃገሪቱ ላይ ሲሰራበት የኖረው የቴሌኮም አዋጅና መመርያ ሁሉ በቂ አይደለምና ይህን የቴሌኮም አገልግሎት አዋጅ ማውጣት አስፈልጎታል በሚል እቀድ የተጠነሰሰ “ህግ” ነው፡፡ የቴሌኮም አግልሎቶችም የእጅ ስልኮችን አገልግሎት፤የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት፤ማንኛውንም ማስተላለፍና መቀበል ወይም ግንኙነት መፍጠርን ያጠቃልላል፡፡ ማንኛውም ሰው በመፈብረክ፤ በመገጣጠም፤የመገናኛ መሳርያዎችን ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት፤ከቴሌኮሙኒኬሽን ፍቃድ ውጪ ቢንቀሳቀስ ከ10 እስከ 15 ዓመት በእስራት ይቀጣል፡፡ ማንም ይህን መሰል መሳርያዎች በንብረትነት ይዞም ቢገኝ ከ1 እስከ 4 ዓመት በእስራት መከራውን ይበላል፡፡ ካለፈቃድ ከቴሌኮም እውቅና ውጪ ቢንቀሳቀስ ከ7-15 ዓመት እስራት ይደርስበታል፡፡ የህጉ አርቲክል 6 ማንም የቴሌኮምና መገልገያ በመጠቀም የሽብርተኝነት መልእክት ሲያስተላልፍ ቢገኝ የሸብርተኝነት አዋጁ በሚያዘው መሰረት ከ3 እስከ 8 ዓመት ይታሰራል፡፡….በማለት አንቀጽ በአንቀጽ ደርድሮታል፡፡

ስካይፕን መጠቀም ወንጀል ነው ከተባለና ለእስር የሚያበቃ ከሀነ እኔ ለወገኖቼ ያለኝ ምክር ከውጪው ዓለም ጋር ለመገናኘት ቀድሞ በአያት ቅድመ አያቶቻችን ይደረግ እንደነበረው የጭስ ትነት ምልክትን፤ የአታመና የነጋሪት ጥሪን፤ የፒቶግራም ስእልን፤ የእርግብን መልእክተኛነት ለመጠቀም ማሰልጠንን፤ የሞርስ ኮድን ነጠብጣብ ሳይንስ መማር ነው:: (ግን: እንተወው የሞርስ ኮድን: እሱም የቴሌን ሃይል ስለሚጠቀም፡፡)

እንደሚታየው ከሀነ ይሄም አዋጅ ያው እንደሌሎቹ ቀርጠ ቀጥል ስራ ነው፡፡ (የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ተብሎ ባለፈው እንደወጣው አዋጅ ቁጥር 652/2009) የተገኘውም ከብዙ ሃገራት አዋጆች ነው እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ካሉ (ወየር ፍረውድ እንደሚባለው ሕግ ለማለት ነው፡፡)የቴሌኮም አዋጅ ግን ከማንኛውም ሃገር ህግ ጋር ጨርሰ ሊገናዘብ የማይችልና ብቻውን የሆነ ከየሃገሩ ህጎች ተቀነጫጭቦ የተጣበቀና አላቂ ሳሚ ይሉት አይነት ሁነኛ ሕግ ተብሎ ለማስፈራሪያነት ብቻ ሊወጣ የታሰበ ጭንጋፍ አዋጅ ነው፡፡በአዋጁ ላይ የቴሌኮሙኒክሽን ንብረት ይላል፡፡ ይህም ማላት በጥቅም ላይ የዋለ አለያም ሊውል የታሰበና የታቀደ ለማልት ነው፡፡ በዚህ አዋጅም ስር ማንም የመባይል ቀፎ የያዘ ሰው፤ ወይንም የግል ለገናኛ ዎኪ ተኪ፤አለያም ብዝሃ መጠቀሚያ ያለው ኮምፒዩተር በማይክረሰፍት ዊንደው የተፈበረከ፤ከመገናኛው ሚኒስቴር ሳያስፈቅድ ሲገለገልበት ቢገኝ የሚለው አዋጁን ከጨዋታ ውጪ ያደርገዋል፡፡ሌላው ቀርቶ ልጆቻችን ረጂም ክር ዘርግተው ጫፍና ጫፉ ላይ ጣሳ አድርገውበት እንደስልክ አስመስለው የሚነጋገሩበትም በዚሁ አዋጅ ስር ፤በእስሩ ደንብ ስር ይመደባሉ ማለት ነው፡፡ ፈጽሞ ሕሊና ቢስነት ነው!፡፡

ሕጎች በአግልጋዮች የፓርላማ ማህተም ሲፈጠሩ ማንም ቢሆን ቋሊማው ወይም ሕጉ በኢትዮጵያ የመርገጫ ፓርላማ እንዴት እንደተሰራ ማየት የለበትም፡፡ምናልባት አባባሉ ናር ያለ ሊመስል ይችላል፡፡ እውነቱ ግን ከኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ ሕጎች አይወጡም፤ ይልቁንስ መርገጫ ሆነው ማህተሙን ማሳርፍ ነው የፓርላማው ተግባር፡፡ አስመሳይነት የተሞላበት ክርክር ያውም የሚነሱት ነጥቦች ዋነኛውን እንዳያሰቀይሙ በመዛን ተለክተው ሆኖ ወዲያው ይሁንታው ይሰጣል፡፡ በቃ፡፡ ያንድን ሰው ፈቃድ በመፈጸም ብቻ ሕግ አድርጎ ማውጣት ተገቢነትም ተቀባይነትም የሌለው ነው፡፡ ሼክስፒር እንዳለው “የራሳቸውን ፈቃድና ፍላጎት ሕግ የሚያደርጉ ሁሉ ሕግ አልባዎች ናቸው ፡፡”

አሁን ለመውጣት ተረግዞ ያለው የቴሌ ሕግ ከሕግ አቀራረጽ አንጻር የጨነገፈ ነውና የህግ እንግዴ ልጅ ሊባል ይችላል፡፡ በይዘትም በቅርጽም ሂደቱም ካለፉት የማይለይ ነው፡፡ በፓርላማው ሕግ ተብሎ በሚወጣው ሁሉ በእጅጉ እገረማለሁ፡፡ በቅርቡ ባሰፈርኩት ጽሁፌ ላይ ሰለ ቆርጦ ቀጥል የሽብርተኝነት አዋጅ ፈላጭ ቆራጩ የመለስ ገዢ መንግስት ከሌሎች ሃገሮች ተሞክሮ በመውሰድና በመቅዳት ወይም በመኮረጅ ያጣመርነው ነው ላላው ምላሽ፤ይህን ስሰማ ለተወሰደው ሃፍረት የለሽ ተግባርና ግልብ አነጋገር ሃገሬ ላይ በደረሰው ጉድ በሃዘን ተሸማቅቄ በእፍረት አንሼ መቀመጤን ገልጨ ነበር፡፡ ነገሩ እንደተባለው ሳይሆን ከማንም ሃገር ህግ ጋር የማይገናኝ ቆርጦ የተቀጠለ ኩረጃ ነው፡፡ የዚህ የቴሌኮም አዋጅ አሳፋሪው ጉዳይ ከብዙው መሃል ለምሳሌ ቅጣቱ ከድርጊቱ ጭብጥ ጋር የማይገናኝና ለአተረጓጎምም የማይሆን ነው፡፡ አንድ ሰው በኮምፒዩተር ላይ ባለ ያውም በራሱ ኮምፒዩተር ላይ በቆጠረ በሚከፍልበት ኢንተርኔት በመጠቀሙ ሳቢያ ለምን ተብሎ ነው የ 15 ዓመታት እስር የሚበየነበት፡፡ምን በደለ ምን አጠፋ፡፡ ይህ ክፋትና ተንኮል ብቻ ሳይሆን ምቀኝነትም ሊባል ሲያንሰው ዕብደት ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር የቴሌኮም አዋጅ፤በማንኛውም መመዘኛ ቢሆን ድጋፍ የማያገኝ ማወናበጃ ነው፡፡በሃገሪቱ ያሉት ህገች በመላ በቴሌኮም ላይ የሚፈጸሙትን ደባዎች ለማስታገስ ብቃት የላቸውም ይላል፡፡ ይህ አባባል ግን ድጋፍ የሚሆነው የማስረጃ ብጣሽ እንኳን የለውም፡፡ በነጻ የተካሄደ ጥናትም ሆነ ወይም በገዢውም ትብብር የተደገፈ የኢንተርኔት ማጭበርበር መጠነ ሰፊ መሆኑን የሚያሳይ ብልጭታም የለም፡፡ የሃገርን ደህንነት የሚጎዳ ጉዳይ በዚህ ሳቢያና መሳርያነት መፈጸሙን በተገቢው ማሳመን አልተቻለም ጥናት አልተደረገም፡፡ ሕዝባዊ አስተያየትና ድጋፍም ሆነ የባለሙያ ማረጋገጫ ጨርሶ አልቀረበበትም፡፡ሕጉ ከፍርሃት ውጪ፤ ከመረበሽ ያለፈ አንዳችም ሰበብ የለውም፡፡

ከዚህ የባሰና አስቸኳይ ትኩረትን የሚጠይቅ አሳሳቢ ጉዳይ አለ፡፡ ባለፈው እንደሚታወሰው፤በ2008 በጠራራ ጸሃይ ሰርሳሪ ሌቦች 16 ሚሊዮን ደላር የሚያወጣ የወርቅ ጥርብ ሰርቀው ያለአንዳች ችግር ከባንኩ ቅጥር ሲወጡ ተስተውሏል፡፡ ምንም እንኳን ድርጊቱ የውስጥ አዋቂወች ደባ መሆኑ ቢታወቅና በተወሰኑ ሰዎች ላይ ጣት ቢቀሰርም ምንም የተወሰደ የሕግ እርምጃ አልታየምም አልተሰማም፡፡ በ2007 የመንግስት ሃብት የሀነውን 600 ሚሊየን ደላር ከክልሉ በጅረወንድ ካዝና መሰወሩን ለማ አራጋው ይፋ ሲያደርግም መለስ ዜናዊ አፍንጫን ሲመቱት አይን ያለቅሳል ሆኖበት ለማን ከስራ አሰናብቶ በህዝብ ፊት ክልሉ ካሽ ገንዘቡን ሊያቃጥል ይችላል በማለት የጎዳና ምላሽ ሰጠ፡፡ የዚያ የተቃጠለ ገንዘብ አመድም አልተገኘም፡፡ በፌብሪዋሪ 2011 ለዓለም ገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀው 10000ቶን ቡና ከመጋዘኑ እምጥ ይግባ ስምጥጥ ሳይታወቅ መቅረቱን መለስ ዜናዊ በይፋ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያም ነጋዴዎችን ሰብስቦ በቪዲዮ በተቀረጸ ቃለ መለስ መልእክቱ ‹‹ለአሁኑ ይቅርታ እናደርግላችኋለን ምክንያቱም በዚህ ቡና መሰወር የሁላችንም እጅ ስላለበት አለ፡፡ ሁሉም አይፈራም ጋሜን እየዘፈኑ ቡና ጠጥተው ወደ የመጡበት ተመለሱ፡፡ ባለፈው ዲሴምበር ላይ ፋይናንሻል ግለባል ኢንተግሪቲ ሲዘግብ ኢትየጵያ አነስተኛ የኤኮኖሚ አቅም ያላት ሃገር በ2000 እና በ2009 መሃከል በህገወጥ መንገድ ሃገር እየጣሰ የወጣው 11.7 ቢሊዮን ዶላር፤ ይበላጣል› በማለት ነበር የዘገበው፡፡ እዚህ ላይ ስለሕግ እያለ የሚጣራ እንዳለ እናያለን፡፡ ባለፈው ወር መለስ ‹‹ብሄራዊ ጉዳየችን ስንመከት ዓላማ ያላቸውን ሰዎች ወደ ተራ ሌባነት ሲቀየሩ በማየት ገዢዎችን የሚጋፈጣቸው መተት ምን ይሆን››? በአፍሪካ ስለሚታየው የተራ ማጭበርበር ሁኔታ እስቲ እንመልከትና እኛም እንደመሪነታችን በዚያ ያለንን ድርሻ እናስላ‹‹ አለ:: ታላቅ ጥያቄ ነው›!› የኢትየጵያን ሕዳሴ ሊያመጣ የሚንደረደረው ሰውዬ ይህን ያነሳውን መሪ ጥያቄ መመለስ አይቸግረውም፡፡ለዚህም የተዘጋጀ መልስ ሊኖረው ይገባል፡፡ የጸረ ምዝበራን መታገያ መንገዱን ማስላቱና መተግበሩ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡እነዚህ መዝባሪዎች ሊያዙ የሚችሉበት መንገድ ሊነደፍ ይገባል፡፡ መዝባሪዎቹ በአደራ የተሰጣቸውን የህዝብ ሃብት በየግላቸው ወደ ውጪ ባንክ ሲያሸሹና ሲከለብሩበት፤ የገንዘብ ብክነቱ በሃገሪቱ ላይ የሚያስከትለው ችግር ተመዝኖ መቀጣጠርያ ሊወጣለት ሲገባ ቢመዘን ሚዛን የማይደፋውን የኢንተርኔት ካፌዎችን ለመዝጋት ህግ ማውጣትና ስካይፔን ለመከልከል መሮጡ ትርጉም አልባ አጉል ድንፋታ ነው፡፡

አዋጁ በየትኛውም አቅጣጫ ይተርጎም ቢባል መገናኛወችን ለማፈን፤ ስካይፕን የመሳሰሉ የቴክኖዎሎጂ ውጤተች በመከልከል የነዚህ ተጠቃሚ የሆኑ ሁሉ ደሞ ገዢውን መንግስት ለመጣል የተነሱ ናቸው ብሎ ማሰብ መንገዱን የሳተ አመለካከት ነው፡፡ ይህን ቴክኒዎሎጂ ለመገናኛነት የሚጠቀሙትም በጣት የሚቀጠሩ ናቸው፡፡ በሌላ መልኩ በስካይፕ ሲጠቀሙ የተገኙትን ይያዛሉ ይታሰራሉ በሚል ማስፈራራት ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ውጤትም መጠቀም ለእስራት እንደሚዳርግ ከአዋጁ አስቀድሞ በማስፈራሪያነት አውርቶ ማስወራቱ ለአዋጁ ትግበራ ቅስቀሳ ነው፡፡ ሪፐርተርዊዝ አውት ቦርደርስ እንደዘገበው፤ አዋጁ በጣም የተለጠጠ በመሆኑ ለመቆጣጠርና ፈር ለማስያዝ እጅጉን አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በውስጡ የተካተቱት አንዳንድ ጉዳየጭ የተለባበሱ ናቸው፡፡ በአንቅጽ 6 ስር ያለው ‹‹የሽብርተኝነት መልእክት ማለት ነው?›› በእጅ ስልኮች ላይ የሚገኘው መለስ ዜናዊ ፈላጭ ቀራጭ ዲክቴተር ነው›› የሚለው የጥሪ ማንቂያ (በኢትየጵያ ደሞ ይህ በጣሙን የሚደመጥ የእለት ተእለት ጉዳይ ነው) እና የዚህ ተጠቃሚም ለ15 ዓመታት እስር ሊዳረግ ነው፡፡

የአንድ አዋጅ መንስኤው ነጻነትን ለማረጋገጥና ነጻና ዴሞክራሲያዊ የሆነ ፍትህ ለህዝቡ ለማስገኘት ሊሆን ይገባዋል፡፡

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

ሕብረት በዓምልኮት (ዓምልኮተ ሕብረት)

Monday, June 18th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

አንድ ህዝብ፤ አንድ ሃገር!

ላለፉት ሁለት አሰርት ዓማታት ኢትዮጵያ የሰብአዊ መበት ጥሰት፤ የወንጀል እና ጸረ ተፈጥሮ፤ ድርጊት መታያ ሃገር ሆና ከርማለች፡፡ አሁን ግን የሃይማኖት አባቶች እስላም ክርሰቲያኑ በአንደነት በመቆም ዓምለኮታቸውን ለማስከበር ትግል ጀምረዋል፡፡ የሙስ ሊሙና የክርስትና ሃይማኖት መሪዎቻቸውና ተከታዮቻቸው፤ አንድነት በመሆንና ሕብረት በመፍጠር የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር እጆቻቸው ላለመላቀቅና ሕብር ሆነው ለመኖር ተያየዘው ህሊናዊ አስተሳሰባቸውብ በነጻነት ለመጠቀም እንዲችሉ ውህደታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ይህንንም ለማክሸፍ ጠንካራ ጉልበቱን የተማመነ ሃይል ውህደታቸውን ለማፈራረስና አለመግባባት ለመፍጠር በተንኮል የተሳለ ምላሱን ጎልጉሎ ተጋርጦባቸዋል፡፡በቅርቡም ከማያልቀው የእርግምት አስተሳሰበ የተወለደ ሁለቱን በአንድነት የኖሩና በመሃላቸው እንከን ያለነበረባቸውን ሃይሞኖቶች ለማጋጨት እኩይ ነገር ተጭሮ ነበር፡፡ የገዢው ፓርቲ ቁንጮ ውሸት አይታክቴ ተንኮል ምሳ ራቱ፤ በፈቀደው መንገድ እየጎተተ ለሚመራውና ያሻውን ‹‹አዎን›፤እሺ›› ለሚያሰኘው ፓርላማው እንዲህ ብሎ ውንጀላ አቅርቦ ነበር፡፡

በቅርቡ የጥምቀት በዓል እለት አንድ ሃገር አንድ ሃይማኖት የሚል መፈክር ነበር፡፡ መፈክሩን ያነሱት ደግሞ ጥቂቶች ነበሩ፡፡ እኛ ደሞ አንድ ሃገር አንድ ሃይማኖት የሚል ህገመንግስት የለንም፡፡አንዳንድ በቁጥር አናሳ የሆኑ በኢትዮጵያ የክርስቲያን መንግስት ብቻ እንዲኖር የሚመኙ አሉ፡፡ እነሱም በትምህርት ወደ ህሊናቸው ሊመለሱ ይችላሉ፡፡ ማንም ቢሆን ሳላፊ የሆኑት ሁሉ አልቃይዳ ናቸው ማለት አይችልም፡፡ ይሄ ስህተት ነው፡፡ ግን እርግጥ ሁሉም አልቃይዳዎች ሳላፊስ ናቸው፡፡በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የአልቃይድ ቡድን ተገኝቷል፡፡ የዚህ ቡድን አባላት በሙሉ ሳላፊ ናቸው፡፡ይህ ማለት ግን በኢትዮጵያ ያሉት ሳላፊ በሙሉ አልቃይዳ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ አብዛኛዎቹ አይደሉም፡፡ እነዚህ ሳላፊዎች ግን ትክክለኛውን የማስተማር መንገድ የሳቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሳላፊዎች በኢትዮጵያ አብዛኛው ሕብረተሰብ ሙስሊሞች ናቸው ይላሉ፡፡ ትክክለኛው የሕዝብ ቆጠራ ግን ይህን አያሳይም ይላሉ፡፡ እነሱ እንደሚሉት አባላጫው ቁጥር ሙስሊሞች ስለሆኑ መንግስቱ የሙስሊም መሆን አለበት ነውየሚሉት፡፡ ይህ አመለካከት ደግሞ አሰባስቧል፡፡

በአክራሪነት ላይ፤በጎጠኝነት ላይ፤በሃይማኖቶች ላይ እሳት መጫሩ ማንን ነው የሚጠቅመው?አንድ ሃገር አንድ ሃይሞነት የሚለውንስ የቁራ ጩኸት ማን ነው ከጀርባ ሆኞ የሚያስተጋባው? ከሴብቴምበር 9/11 በኋላስ የአልቃይዳን ተክል ማን ነው የዘራው? አሁን በኢትዮጵያ ያለው ከፍተኛ ችግር የእስልምና መንግስት በሚሉና የክርስቲያን መንግስት በሚሉት መሃል ያለ ግብግብ ነው? ኢትዮጵያን የገጠማት እልህ አስጨራሽ ችግርስ በዴሞክራሲና በፈላጭ ቆራጭ ገዢ መሃል ያለው ልዩነት ነው ወይስ የእስልማናና የክርስትና አክራሪነት ነው? አል ቄይዳስ ለኢትዮጵያ ፈታም ችግር ነው? ወይስ የኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የተጫነው የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ ስርአት ነው? የእስልምና አክራሪነት በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ዋነኛው ችግር ነው? የክርሰቲያን አክራሪነትስ ቢሆን? ኢትዮጵያን ወጥሮ የያዛት ችግርስ አልቃይዳ ነው? ወይስ በሙስና የተዘፈቀውና ብቸኛው የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ቀፍድዶ ያዛት አንድ ሰው አንድ ፓርቲ የሚለው ፈላጭ ቆራጭ ግፋዊ አገዛዝ ነው?

በሃይማኖቶች መሃል ቅራኔዎችን ለመዝራትና ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ለማበጣበጥ የሚደረገው ውጤት አልባ መንደፋደፍ የገዢው ፓርቲ የግፍ አገዛዝ፤ ለፈላጭ ቆራጭ ስርአታቸው እድሜ ማራዘሚያ የሚጠቀሙበት ኤጭ የተባለ ስትራቴያጂቸው በመሆኑ ቁንጮው የሃገር ጦስ መለስ ዜናዊ ይህን እንደፖለቲካ ነበልባል ሊያጫርስ ይችላል በሚል እመነት ነው አሰካክቶ ያቀረበው፡፡ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ስለ አንድ ሃገርና አንድ ሃይሞኖት አይደለም፡፡ ያንን የችግር እሳት ጫሪ የሆነውን አባባል በመጠቀም፤ ታላቁን የሕዝቡን የጉዳይን ሃሳብ ገለል በማድረግና አቅጣጨውን ለማስቀየር ሲል፤ ጭብጡን ከሕገመንግስቱ ሃማኖታዊ ትንታኔ አውጥቶ ሌላ መንገድ ሊያስዬዘው ይጥራል፡፡የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 11 በግልጽና በቀጥታ እንዳስቀመጠው፡- ‹‹የመንግስታዊ ሃይማኖትየለም: መንግስትም በሃይማኖቶች ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖቶችም በመንስት ጣልቃ አይገቡም፡፡ አንቀጽ 27ም ቢሆን አጠናክሮ የሚያስረዳው፤‹‹ሁሉም የነጻነት፤ የአስተሳሰብ እና የሃይማኖት ነጻነት አለው፤ ይህም መብት በራሱ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እምነት ሊኖረው፤ ብግለሰብም በቡድንም በተናጠልም በመሰባሰብም፤በዓምልኮት ቦታዎች እምነቱን ሊያካሂድ፤ ሊያስተምር እንደሚችል በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ማንም የማንንም እምነት ያለፈቃዱ እንዲቀበል ማስገደድ አይችልም፤ይህን ማድረግም የምርጫ ሃይማኖቱን መድፈር ስለሚሆን አይፈቀድም፡፡

‹‹ሃይማኖት የግል ምርጫ ጉዳይ ነው፤ሃገር ደግሞ የጋራ ሃላፊነት ነው››

የታወቁ የሙስሊሙና የክርስቲያኑ መሪዎች፤በሃይማኖታዊና፤የፖለቲካዊ አክራሪነት ላይ ተጋሪ አይሆኑም፡፡በማንኛውም ጊዜ ቢሆን የየትኛውም እምነት መሪ በሃገሪቱ ውስጥ የዚህ ሃይማኖት ተከታይ መንግስት ብሎ ተናግሮ እንደማያውቅ እንጂ ብሏል ለሚባለው መላው የጠፋ የተፈበረከ ውንጀላ ማሰረጃ ማቅበር አይቻልም፡፡ ሃይማኖቶችን ለመከፋፈል የተቀረጸው የሚያሳፍረው ተንኮላዊ ሙከራ በግልጽ የሚታይ ነው፡፡ ማንም ቢሆን የአልቃይዳን የተፈበረከ ኢትዮጵያን መቆጣጠር ቅዠት ማንም አያምንም ወይም ፈንድሜታሊስቶች የኢትዮጵያን መንግስት ለመውረስ ያስባሉ ብሎ አያምንም፡፡ የክርስታናና የሙስሊሙ እምነት ተከታዮች አንድነትና ሕብረት በሃይማኖት ነጻነት ላይ ያላቸው ውህደት ለሌላው ዓለም ምሳሌ ነው፡፡

በቅርቡ በካናዳ ቶሮንቶ፤የሙስሊሙና የክርስታናው ሃይማኖት እምነት ተከታዮች ለውጪ ኢንቬስተሮች የእርሻ ቦታ ለመሸጥ በሚል ሰበብ የቆየውንና የእምነትና የሃገር አውራ የሆነውን የዋልድባ የእምነት ገዳም ከተሰነዘረበት ደባ ለማዳን ጥሪ ለማቅረብ በአንድነት ግንባር ፈጥረው ከውጭ ኢንቬስተሮች የማፈራረስና የማውደም እኩይ ተግባር እንዲድን ጠይቀዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ በአሁኑ ወቅት በዋልድባ ባጠገብ የሚገኘውን ገዳም አፍርሶ ለሸንኮራ አገዳ ማምረቻ እርሻ ለመስጠት በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ካህናት መሰለ እንግዳ በክርስቲያኑና በሙስሊሙ አማኞች መሃል ያለውን ታሪካዊ የጠነከረ ሁኔታ እንደሚከተለው ገልጸውታል፡፡

የሙስሊሙ እምነት ተከታዮች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሃገሪቱን በመጠበቅ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ናቸው፡፡ታሪክ መዝግቦ እንዳስቀመጠው የሙስሊም ሕብረተሰብ አባላት አባቶች የኢትዮጵያን ነጻነት ለማስጠበቅ ከጠላት ጋር ተዋግተዋል፡፡የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን የሚጎዳ ሁኔታ ሲፈጠርም የሙስሊሙ ህብረተሰብ አባላት ወገኖቻችን ከጎናችን ቆመው አብረውን ችግሩን ተጋፍጠዋል፡፡ዛሬም የቶሮንቶ የሚስሊሙ አማኞች መሪ አብረውን ቆመዋል፡፡እንደምታውቁት በአሁኑ ሰአት የሚስሊሙ ሕብረተሰብ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ፈታኝ የሆነ መከራና ችግር ተጋርጦባቸዋል… ሁላችንም በህብረት አብረን እንቆማለን፡፡

የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በመላ፡፡ ከጨለማው ሃይልና አንዳችም ፍሬ ከማያፈረው ጋር ህብረት አትፍጠሩ፤ጥንታዊቷና ታሪካዊዋ ኢትዮጵያ የጥቁሮች ሁሉ ነጻነት አብሳሪዋ ኢትዮጵያ፤በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ታላቃ አደጋ ገጥሟታል፡፡የገዢው ፓርቲ የወያኔ ኢንቫየርሜንታል ፕሮግራም (ለም መሬትን ለውጭ ነጋዴዎች ማከፋፈል) ሃይማኖታችንንና እምነቶቻችንን እያጠፉት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የወያኔ ውጥንቅጥነትና ግርግር ሽብር በኢትዮጵያ ላይ ታላቅ ሃፍረትን እያስከተለባት ነው፡፡ ቀደም ሲል የወዲ ዜናዊና የአባ ገብረመድህን የቤተክህነቱ አስተዳደር ከገዢው ፓርቲ ጋር ግምባር ፈጥረው በቤተክህነቶች ላይ የመቃጠል አደጋ፤እስራት ስቃይ እና በሃይመኖት አባቶች ላይ የግድያ ተግባር እንዲፈፀም አድርገዋል፡፡ የዝቋላ ገዳምንም ለቃጠሎ ዳርገውታል፡፡ አሁን ደግሞ የስኳር ፋበብሪካ በሚል ሰበብ የዋልድባ ገዳምን ለቤተክህነታችን ዋነኛ ቅዱስ ስፍራ የሆነውንና ታሪካዊውን ገዳም ለማፈራረስ አቆብቁበዋል፡፡ ምሁራን የፈለቁበት ስፍራ ነው፡፡ አባቶቻችንም ከአደጋ ለመከላከል ሲሉ ለዋልድባ ቆመው ደማቸውን አፍሰዋል፡፡ ሞተዋል፡፡ በመሆኑም የዋልድባን ነዋሪዎች የንግድ እርሻ ለመጀመር፤ እንዲሁም የአባቶቻችንን ቅሪት በማስቆፈር ማንከራተት ማፈናቀል፤ እጅጉን አሳፋሪና አዋራጅ ተግባር ነው፡: የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ምን ተስባለህ፤ ምን እያየህ ነው፤ የሃይማኖት ገዳማት ሲፈርሱና የአባቶቻችን አጽም ካረፈበት ተቆፍሮ ሲጣል፤የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ሲዋረዱና ሲቃጠሉ የሃይማኖት አባቶች ምን ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡

ሃጂ ሞሃመድ ሰይድ የሃገሪቱን አንድነት በተመለከተ የሁላችንንም ግዴታ እንደሚከተለው አስቀምጠውታል‹‹

… እንደምታውቁት ኢትዮጵያ የተለያየ ሃይማኖት፤ያለባት በተለይም ኦርቶዶክስና ሙስሊሙ፤ለረጂም ዘመን፤የኖረባት፤የተማከለባት የተዋደደባት ሃገር እንደሆነች በታሪክ የተመዘገበ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በኛ እንኳ እድሜ በ50 ዓመት እንደዛሬ ያለ ችግርና መከራ ኢትዮጵያ ደርሶባት አያውቅም፡፡ሃይማኖት የግል ነው፡፡ሃገር ግን የጋራ ነች፡፡ሃገር ከሌለ ሃይመኖት የለም፡፡ሃገር ላይ ነው ሁሉ ነገር የሚገኘው፡፡በአሁኑ ወቅት ላይ ኢትዮጵያ በሃይማኖቷ ጸንታ የኖረችው ሃገር፤ፈራርሳለች፡፡ ሙስሊሙን ከክርስቲያኑ ጋር ለማጣላት፤ረጂም ጊዜ ዘመቻ ተደረገ፡፡ አልተሳካም፡፡ኦሮሞውን ከአማራው ጋራ ለማጋጨት ተጣረ፡፡ አልተሳካም፡፡ አሁን የሃይማኖት መሪዎቹ ቀደም አድርገው ተናግረውታል፤ በኢትዮጵያ ሙስሊም በአሁኑ ወቅት ላይ፤እኛ እምናውቀው በታሪክ ተመዝግቦ፤እስላም ማለት አንድ አይነት ሙስሊም ነው፡፡ የሰውም አይፈልግ አደራ ሚቀበል፤አደራ የሚያደርስ፤እስላም ካበለ፤ ሰማይ ካልዘነበ፤ሃገር ጠፋ ነው፡፡ አደራ ሚሰጠው ዱሮ፤ለወንድሞቻቸው ለሙስሊሙ አደራህን ብሎ ማንኛቸውም ወገን ሁሉ፤ለልጄ ይህንን፤አድርስለት ሲባል፤የማይቀንስ የማይጨምር የነበረውን፤ከሊባኖስ ሌላ የተፈጠረ ሃይሞኖት አምጥተው፤ኢትዮጵያን እያበጣበጧት ነው፡፡

ዛሬ እንደምታውቁት አርብ ነው፡፡አርብ ወደ መስጊድ እንጂ ወደ ስብሰባ ወደ ዓለማዊ ጉዳይ መምጣት ባልተገባኝ ነበረ፡፡የሃገር ጉዳይ ነው፡፡ሃገር ከሌለ፤ሃይማኖትን ማስከበር፤ ለጸሎት የማይመችበት ጊዜ ነው፡፡አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተከብረው የኖሩት፤በሙስሊሙም በክርስቲያኑም ነው እንጂ፤የኢትዮጵያ ቅርስ ነው፡፡ የሃይማኖት መሰረቱ፡፡ ደብር ማለት፤ እንደምናውቀው፤ቅጠል በልተው፤ጥሬ ቆርጥመው፤ውሃ ጠጥተው የሚኖሩባት ሃገር እንጂ፤ለቻይናና ለህንድ ኢትዮጵያ ተሸጣ፤ ሰዉ ዛሬ ያያችሁት እንደሆነ ዳገት እየቆፈረ ቆፍር ተብሎ በራበው አንጀቱ ላይ አካፋና ዶማ ይዞ ሲጭር ያውላል:: በራበው አንጀቱ ላይ አካፋና ዶማ ይዞ ሲጭር ይውላል፤ሲጥር ያመሻል፤ ይሄ ለኢትዮጵያ ትልቅ ውርደት ነው፡፡ሜዳውን ሸጠውታል፤ለሙን መሬት ይዘውታል፤ገንዘቡ ሃገራችን ላይ የለም::

የኢትዮጵያ ትውልድ አለ ወይ በአሁኑ ወቅት? ዩኒቨርሲቲ የገባው ወጣት፤ሞራሉ ወርዶ፤ተነክቶ፤ጫት እያላመጠ፤ሲጃራ እያጨሰ፤ትውልድ እንዲጠፋ አድርገውታል፡፡ እኔ በእውነት፤እንዲህ ያለ አመራር፤እንዲህ ያለ አስተዳደር፤በዓለም ላይ በወገኑ ላይ ፤ በደል የሚያደርስ፤ታሪክ አላነበብኩም፡፡ ስለሆነም፤በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የደረሰውን ችግርና መከራ ለመግለጽ፤ለያንዳንዳችን አንድ ቀን ቢሰጠን አይበቃም፡፡ እንግዲህ ከሃይማኖት ከማጥፋት የበለጠ በደል አለ? የለም፡፡ አለእንዴ? (ብለው ላቀረቡት ጥያቄ ተሰብሳቢው ሕዝቡ በአንድ ቃል የለም ሲል መለሰ) ሃይሞነት ከጠፋ ኢትዮጵያ የለችም ማለት ነው፡፡ ስሟ ብቻ ካርታ ላይ ኢትዮጵያ የሚባል እንጂ፤የውጭ ሃገር እንደሆነ መሬቱን ገዝቶታል፤ገንዘባቸውን አሻግረዋል፤በገንዘባቸው ይጠቀማሉ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን፤ ዘጠኝ ባንዲራ ተተክሎ፤እነሱ የለሉ ለት፤ለዘጠኝ ተከፍለን ስንታኮስና ስንጋደል እንድንኖር፤ በፕሮግራማቸው ላይ ያዘጋጁልን ስለሆነ፤ የሃይሞነት፤ የዘር፤የጎሳ፤ልዩነት ሳናደርግ፤ኢትዮጵያን እንድንታደጋት፤የታሪክ ሃላፊነት አለብን፡፡

ልጆቻችንና የልጅ ልጆቻችን፤እንዲሁ እንደኛ እንደተሰደዱ ሊኖሩ ሃገር እንደናፈቃቸው ትውልዱ መበተኑ ነው፤ እስቴ እንዲያው ቆም ብለን ሌትም ሆነ ቀን ስናስበው፤ያሁኑን አስተዳደር የመሰለ በኢትዮጵያ ላይ ተፈጥሮ ታሪክ አንብባችሁ ወይም ለዚህ የደረሳችሁ ሰዎች አይታችኋል? (ብለው ላነሱት ጥያቄ ተሰብሰዳቢው አላየንም ብሎ መለሰላቸው) ስለዚህ የመፈክር ብቻ ሳይሆን ሙስሊሙም፤ሌላውም ሃይማኖት ተከታይ፤ አቤቱታችንን ለማይናወጠው ለዓምላካችን አቤቱታ ማቅረብ፤ ደግሞ፤ መሰረት መጣል አለብን፡፡ እኔ ለደረስኩበት በኢትዮጵያ ላይ፤ አንበጣ፤ ዘይሪ ተምች የሚባል አውሬ ነበር፤ በዚያን ወቅት ላይ የሃይማኖት መሪዎች ሙስሊሙም ወደ አላህ ዱሮ ዱሮ ዱሮ ይላል ክርስቲያኑም ደግሞ፤ እነዚህኑ ጸሎቶች በቤተክርስቲያንና በየአድባራቱ አድርሷል፡፡ በዚያን ወቅት ላይ ፈረጃ ወይም መልእክት ይተላለፍ ነበር፡፡ ስለዚህ በሃይሞኖታችን ጸንተን፤ ለአንድነታችን ደግሞ ጠንክረን ሃገራችን ኢትዮጵያን፤ እምንጠብቅበት ባለአደራዎች ስለሆንን እውጫ ያለነው፤ ከኢትዮጵያ ክልል ውጭ ያለነው ደሞ ወንድሞቻችን ልጆቻችን በአሁኑ ወቅት ላይ ትውልድ እንዲጠፋ የተደረገ ስለሆነ፤ ሁላችሁም የተቻላችሁን ያህል እርዳታ ማድረግ አለባችሁ፡፡ የገነዘብ ብቻ አይደለም፤ የሞራል ድጋፍ መስጠት አለብን፡፡ መምከር አለብን፤ኡኡ ማለት አለብን፡፡ ከዚህ በኋላ ብዙ ቢናገሩት፤ሚዛኑ ሊሞላ ስላማይችል ንግግሬን እዚህ አቆማለሁ፤ ኢትዮጵያ በሠላም የምትኖርበት፤ ይህ አስተዳደር የሚለወጥበት፤ በአንድነት ሁነን፤ ወደ ዓምላካችን እንለምን እያልኩ ንግግሬን እዚህ ላይ አቆማለሁ፡፡

ብዝሃ ሃይማኖቶች፤ ሃገር አንድ ብቻ!

በኢትዮጵያዊያን መሃል ‹‹ሃይማኖት የግል ምርጫ መሆኑን፤ ሃገር ግና የጋራችን›› መሆኑን ሃጂ ሞሃመድ ሰኢድ በአጽንኦት አስረድተውናል፡ ሊቀ ካህናት መሰለ እንግዳ ሙሲሊማኑና ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ በታሪካቸው ሁሉ በሰላማዊና በመተሳሰብ በመተጋገዝ፤ አብረው እንደኖሩ በ ትክክል ሁኔታ አስገንዝበውናል፡፡በክርስቲያን ወንድሞቻቸው ላይ ችግር ሲጋረጥ ሙስሊማኑ አብረውን ቆመዋል፡፡ አሁን ደግሞ ሁለቱንም ሃይማኖቶችና አማኞቹን የሚፈትን ግዙፍ ችግር መጥቷል፡፡ ችግሩ ደግሞ የፈላጭ ቆራጭ አረመኔያዊ አገዛዝና ስላጣንን አለአግባብ የሚጠቀም ስርአት ውልደት ነው፡፡ጉዳዩ ለሃገርና ለእመነት አሳሳቢና አደገኛ ነው፡፡ችግሩም መፍትሄ ሊያገኝ የሚችለው፤በተለያዩ እምነት ተከታዮች፤ዘሮች፤ቋንቋ ተጠቃሚዎች ኢትዮጵያ ዊያን የጠነከረና የማይፈታ አንድነት ብቻ ነው፡፡ የነዚህ ሁለት ሃይማኖቶች መሪዎች ምሳሌነት፤ ለምእተ ዓመታት ሲካሄድና በተግባርም ሲታይ የኖረውን የሁለቱን ሃይማኖቶች ትስስር በእሳ ላሙና በክርስቲያኑ መሃል የኖረውን መተሳሰብና አንድነትን ነው የሚያሳየን፡፡የበለጠ አንድነታዊ መግባባትን የሚጠይቅ ነው፡፡ያለውን እያዳበረ የጎደለውን በመሙላትና በማስተካከል ሊቀጥል ተገቢነቱን ነው፡፡ይህን ስናደርግ ደግሞ አዲሲቱን ኢትዮጵያችንን ለመቅረጽና የሃይሞኖት ነጻነትም በተግባር የሚረጋገጥበትን ና ማንም ግለሰብ እንደየምርጫው በሚከተለው ሃይማኖት አስተሳሰቡን በነጻ የሚያራምድበትን መንገድ መፍጠር ነው፡፡

የመለያየት ጣጣ ዋጋው

የሃይማኖት አለመግባባት ጣጣ ምን ሊያስከትል እንደሚችል የቅርቡ የናይጄርያ ሁኔታ ሊያስተምረን ይገባል፡፡ በናይጄርያ ውስጥ በተለያየ የህብረተስብ ክፍል ውስጥ ያሉ ሙስሊማኖችና ክርስቲያኖች አላንዳች ችግር በውህደትና በመግባባት አብረው በመኖር ልማዶቻቸውን እየተካፈሉ፤በስራም አብረው በመሰለፍ በሰላም እንደኖሩ ታሪክ ምስክር ነው፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ ግን አንዳንድ መቆራቆሶች እየታዩ ከርመዋል፡፡በአጠቃላይ ግን ሰላማዊ ሕይወት ይመራሉ፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ግን ሰላማዊው ግንኙነት ፈተና ገጥሞታል፡፡አንዳንድ አስተሳሰባቸው የተዛባ ስብስቦች በእምነት ቦታዎች በመስሪያ ቦታዎች በመንግስት ቢሮዎች ላይ አደጋ በመጣል ላይ ተሰማርተዋል፡፡ የንጹህ ዜጎች ህወት ማለፍና የንብረት መውደምም አስከትሏል፡፡ የሙስሊሙና የክርስቲያኑ አማኞች ሁኔታው የሃይማኖቶች ልዩነትና አለመግባባት ሳይሆን በመሬት ይዞታ ላያ ያተኮረ ችግር እንደሆነ ይመሰክራሉ፡፡ ለራሳቸው ጠባብ ግብ ሲሉ ብቻ እሳቤያቸው የጎደለ የፖለቲካ ሰዎች ደጋፊዎች ጉዳዩን የማንነት ጥያቄ በማድረግ ልዩነቱን በማባባስ ይጠቀሙበታል፡፡ መገናኛ ብዙሃኑም ቢሆኑ የሚያስፈሩ ዘገባዎችን ከነዚሁ እርባና ቢስ ደጋፊዎች ጎን በመሰልፍ ዘገባ በማቅረብ በህብረተሰቡ መሃል ፍራቻን መረበሽን አስከትለዋል፡፡ የሙስሊሙ ጥላ ከለላ የሆነው ጃማ አቱ ናስሪ እስላም የተባለው በናይጄርያ የሚገኝ ድርጅት፤41 ሰዎችን አቁስሎ የ3ቱን ሕይወት ያሳለፈውን የቦንብ ጥቃት በመቃወም በቦስና ቢዩ የተፈጸመውን ድርጊት አውግዟል፡፡ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑት ፕሬዜዳንት ጉድላክ ጆናታን በዚህ ሰበብ የሚገኘው የሃገር ጥፋት ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የአስተዳደራቸው ግንዛቤና መግለጫም እንዳሉት “በክርስቲያኑ ሕብረተሰብና በሙስሊሙ ሕብረተሰብ መሃል የጠነከረ ግጭት የለም፡፡ብድር መመላለሻ ሊሆን አይችልም በመልሶ ማጥ ቃት የሚገኝ ጠቀሜታም ሆነ ለጉዳዩ ማብቂያ ማግኘት አይቻልም፡፡አንዱ ያደረገውን አጸፋ መስጠቱስ የት ሊቆም ነው?፡፡ናይጄርያ እንደ ሃገር መቀጠል አለባት፡፡” ኢትዮጵያም እንደ ሃገር መቀጠል አለባት፡፡

የአንድነት ፈተና

ለዘመናት ክርስቲያኖችና ሙስሊማኖች በሰላም አብረው ኖረዋል፡፡ያ እንደሚቀጥልም አያጠራጥርም፡፡ በፈላጭ ቆራጭ አረመኔያዊ ገዢ ግን ሁለቱም ለአደጋ ተጋልጠዋል፡፡ የፖለቲካ ሰዎች የከሸፈባቸውን የእምነት መሪዎች ያሳኩታል፡፡ የክርስቲያኑና የሙስሊሙ ሃይማኖቶች መሪዎች አለመግባባትን በማሰወገድና የመግባቢያና የአንድነት ድልድይ በመፍጠር ታላቅ ወሳኝ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፡፡ በመግባባትን በመከባበር የስራ አንድነትን ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ የመግባባትን፤የመተሳሰብን፤ዘር በመዝራት የጥላቻና እኩይ አስተሳሰብ ዘር ለመርጨት ሌት ተቀን የሚያንቧችሩትን መርዘኞች ሊያሸንፉ ብቃቱ አላቸው፡፡ ሕግን በማረጋገጥና ነጻነታቸውን ለማግኘት እንደሚናፍቁት ሁሉ፤ ሕዝቡ መልካም እንዲያስብና የሞራል ብቃትም እንዲኖረው የሃይማኖት መሪዎች ያስፈልጉታል፡፡ የእምነት አባቶች መንገድን ሲያመላክቱት ሕዝቡም በሕብረት በአንድነት የመግባባትና የመከባበር የመተሳሰብ ድልድይን ይገነባል፡፡

በአሜሪካና በሌሎችም ሃገራት የእምነት ድርጅቶች የተጓደኑ የእምነት ካወንስሎች ይመሰርታሉ፡፡ይህም ካውንስል በተለያዩ አማኞች መሃል መግባባት መተሳሰብና መፋቀር ሊኖር እንዲችል፤ በህብረተሰቡ መሃል ያለውን ችግር ለመቅረፍም አብረው እንዲቆሙ መሳርያ ይሆናል፡፡የተጓደኑ ሃይማኖቶች ካውንስል ከመነጋገርና ከውይይትም ባለፈ የህብረት ስራ በመፍጠር የህዝብ አግልግሎትና በማዋቀር፤ የአካባቢ ችግሮችን በማስወገድ በሃይማኖቶች መሃል ያለውን ልዩነት እያከበረ በቀናው መንገድ ተሳስበውና ልዩነቶቻቸው እንደተጠበቁ ሆነው አብረው ለሃገርና ሕዝብ የሚቆሙበትን መንገድ የሚመራ ነው፡፡ይህን መሰሉ የሃይማኖት ተጓዳኝ ካወንስል በኢትዮጵያ የመያፈጠርበት አንዳችም ምክንያት የለም፡፡

አንድነትን ፈተናው በአግባቡ ሊታይ ተገቢ ነው፡፡‹‹ሃይማኖት የግል ሃገር የጋር ነው›› የሚለውን መርህ በትክክሉ ከተገበርነው የአንድነትን ፈተና በድል አድራጊነት እንወጣዋለን፡፡ ዓላማው የማንኛውም ሃይማኖት አክራሪነት በመወገዝና በመቀዋም ብቻ የሚያበቃ ስለማይሆን ሕብረተሰቡን ማስተማርንና ማንቃትንም ይጠይቃል፡፡በግልጽ እንደሚታየው በኢትዮጵያ ውስጥ፤ ከማንኛቸውም የፖለቲካ መሪዎች በላይ የሃይሞኖት መሪዎች ተቀባይነትና ክብር አላቸው፡፡የፖለቲካ ሰዎች ስለ ሃይመኖቶች መቆራቆስ ሲያነሱ የሃይሞኖት አባቶች ደግሞ መቻቻልን ማስተማር አለባቸው፡፡የኢትዮጵያ ችግር ከቴዎሎጂ ልዩነት የመነጨ አይደለም፡፡የኢትዮጵያ ችግር ምንጩ ቲዎሎጂን በተሳሳተ ትርጉም ሊጠቀሙበት በሚሹ አላዋቂዎች የተነሳ ነው፡፡

‹‹ሃይሞኖት የግል ምርጫ ነው፤ ሃገር ግን ጋራ ነው›::
‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ምን ታስባላችሁ?!ምን ያታያችኋል?፤የሃይማኖት ማምለኪያ ቦታዎቻችን ሲቃጠሉና እምነቶቻችን ሲጠፉና ለአደጋ ሲጋለጡ እያየን ባለንበት ወቅት የሃይማኖት አባቶች ሚና ምነድን ነው?›

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ethiopianreview.com/amharic/?author=57

ኢትዮጵያ፡ ወደ ሕገ መንግስታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና

Monday, June 11th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ 

ላለፉት ጥቂት ወራት  በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ መንግስት ወደ ዴሞክራሲ በሚል ርዕስ ስጽፍ ነበር፡፡ከነዚህ አስተያየቶች በመጨረሻው ጦማር ላይ ስጥፍ “በዴሞክራሲው መሸጋገርያ ድልድይ ላይ ስልጣንን በሚየነፈንፉ ግለሰቦችና ቡድኖች መሃል ግጭትና ግብግብ አይቀሬ ሲሆን፤ተራው የህብረተሰብ ክፍል ስልጣናቸውን በሚያኮላሹትና ለግል መጠቀሚያ በሚያደርጉት ላይና ሥልጣናቸውን የሙጢኝ ባሉት ፈላጭ ቆራጮች ተሰላችቷል መሮታልም፡፡ይህ ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ወደ ዴሞክራሲ በሚደረገው ሥግግር ወቅት የሚፈጠረው ግርግር ስልጣንን ለመጥለፍ ላቆበቆቡት መንገድ ይከፍትላቸዋል፤ ስለዚህም ዴሞክራሲን አስገድዶ በመጥለፍ በዴሞክራሲ ስም መልሰው ያን አረመኔያዊ ፈላጭ ቆራጭ ስርአትን ሊያስቀምጡ እንደሚተጉ አሳስቤ ነበር፡፡” በዚህኛው ጦማሬ ላይ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው ሕገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ሕገመንግስታዊ ‹‹ቅድመ ውይይት›› አስፈላጊነት አተኩራለሁ፡፡ 

ለዴሞክራሲ ሰላማዊው አጥር 

አብዛኛዎቹ የሕብረተሰብ አባላት ከመራር አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ በጣም ፈታኝና ውስብስብ የሆኑ አጥሮች ተጋርጠውባቸዋል፡፡በ1776 አሜሪካ ከግፈኛው የእንግሊዝ ጨቋኝ ስርአት ከተላቀቁ በኋላ፤13ቱ ቅኝ ግዛቶች፤እስከ 1781፤አርቲክል ኦፍ ኮንፌዴሬሽን እስኪፈርሙና ወቅታዊ የሆነ መንግስተ መስርተው ለጊዜው እስኪቀላቀሉ ድረስ በራሳቸው ቆይተው ብሔራዊ መንግስት መሰረቱ፡፡ይህ ሁኔታ ግን አላዋጣም ምክንያቱም ግዛቶቹ ዋነኛ የሚባሉትን የስልጣን ቁልፎች እንደያዙ በመቆየታቸው ግብይትን፤የውጭ ንግድን ስርአትና ሁኔታን በመቆጣጠር መንግሰት ታክስን እንዳየሰበስብ ገደብ ስለጣሉበት ይህንኑ ለማስተካከልና ፈር ለማስያዝ ጦር ማሰለፍ ግድ ሆነ፡፡ ይህንንና ሌሎቹንም ዋነኛ የተባሉትን ችግሮች በመፍታት ለመረጋጋትና ለዴሞክራሲያዊ ሂደት የተማመነ ሁኔታ ያስገኙት አሁን በስራ ላይ ያለውን ሕገ መንግስት በ1787 ከተቀበሉት በኋላ ነው፡፡ 

የቅርብ ሁኔታዎችም ሃገራት ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ በሚያደርጉት ሽግግር፤ ውስብስብ የሆነ ችግር እንደሚጋረጥባቸው ነው፡፡ ‹‹ከአረቦች ስፕሪንግ››ሂደት በኋላ 1 ዓመት ጊዜ ውስጥ የዴሞክራሲ ማዋቀሩ ሂደት በሊቢያ ግብጽ፤ቱኒዝያ፤የመን እና ሌሎችም የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ በጣም አወዛጋቢና ፈታኝ ፈተና ገጥሟቸዋል፡፡በግብጽ፤ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስቱ ወደ ሕገ ምንግስታዊ የሲቪል አስተዳደር እየመራው ነው፡፡የግብጹ ወታደራዊ ስብስብ በግብጽ የሚታየውን የዴሞክራሲ ጫጩት ቅፈቅፍ ቤት በመጠበቅ ላይ ነው፡፡ በርካታ ግብጻዊያንም በግልጽ እንደሚያነሱት ጥያቄ ከሆነ፤ ወታደራዊው ባለአደራ በማለባበስ ሂደቱ ግብጽን ወደ አለፈው የሙባረክ ስርአት ለመመለስ እያቆበቆበ ነወይ ይላሉ፡፡ በቅርቡ በሚካሄደው የምርጫ ሂደት ውስጥ የሙባረክ የመውደቂያው ሰአት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው አህመድ ሻፊክ ለጁን 16-17 ለመጨረሻው ወሳኝ ፍልሚያ ለከተሰለፉት ተወዳዳሪዎች አንዱ ነው፡፡ በታህሪር አደባባይ ከፈነዳው የበቃኝ አብዮት አንስቶ 12000 ግብጻዊያን ለእስር ተዳርገዋል፤ብዙዎችም በወታደራዊው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ በርካታ ስመጥር የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ድርጅቶች ምንግስትን በግድ ለመለወጥ በሚል በሃገሪቱ የአቃቤ ሕግ ቢሮ ተወንልለዋል፡፡ወደ ዲክተቴርሽፕ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ መንሸራተትና የኋልዮሽ ጉዞ? 

በቱኒዝያ ባለፈው ኦክቶበር የተመረጠው የሕገ መንግስት አርቃ ኮሚሽን በአንድ ዓመት ውስጥ ተስፋ የሚያጭር ውጤት እያሳየ ነው፡፡በጣሙን የሚያበረታታው ሂደታቸው ደግሞ የሕገ መንግስት አርቃቂዎቹ በተወሳሰቡ የፖለቲካ ምናምኖች ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ ሥላጣንን በአግባቡ በስራ ላይ የሚያውልና የፈላጭ ቆራጭነትን ስርአት ድጋሚ መከሰት የሚገታ ሕገመንግስት በማርቀቅ ላይ መሆናቸው ነው፡፡ልዩ ል ‹‹ኮሚሽኖች›› በማዋቀር  እነዚህ አርቃቂዎች ምን አይነት ምንግስት በሚለው ምርጫ ላይ በማትኮር (በፓርላሜንታሪና በፕሬዜዳንታዊ) የስልጣኑን ሚዛን በመጠበቅ፤ የፍትህ ስርአቱን ሚዛናዊነት ሕዝባዊነት፤ሥላጣንን በአግባቡ በማከፋፈል ስርአት ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰሩ መሆናቸው ነው፡፡ 

በሊቢያ ያለው የዴሞክራሲ ሂደት ግን እስከዚህም ተስፋ የሚታይበት አይደለም፡፡ በኦገስት 2011 ‹‹ለሽግግር መንገዱ የሕገመንግስት ረቂቅ››(እውነተኛነቱን ማረጋገጥ አልተቻለም) በሊቢያ ውስጥ በሰፊው ይዘዋወር ነበር፡፡ ከምእራብያኑ ሊበራል ዴሞክራሲ ሃገራት ሕገመንግስት ላይ ተቆርጦ የተለጣጠፈ፤ ስለየህግ የበላይነት፤የግለሰብ ሰብአዊ መብቶች፤ ስለመናገር ነጻነት ስለሃይሞነት ነጻነት፤ ስለመድበለ ፓርቲ ያወራል፡፡ ሌሎችም የሕገመንግስት ረቂቆች በመዘዋወር ላይ ናቸው፡፡ባለፈው ማርች 60 አባላት ያሉት የሕገመንግስት አርቃቂ ኮሚቴ ተዋቅሮ የሊቢያን ዋነኛ የሚባሉትን 3 ግዛቶች እንዲወክል ተሰይሞ ነበር፡፡ነገር ግን ሊቢያውያን በጣሙን አጣዳፊና አንገብጋቢ የሆኑ የመረጋጋት ችግሮች አሏት፡፡መደበኛ የሆነ ቋሚ ጦር በሌለበት፤ጋዳፊን ለመጣል በዘፈቀደ ተሰባስበው የነበሩት አማጽያን አሁንም እርስ በርስ በመቆራቆስ ላይ በመሆናቸውና እንቅስቃሴያቸውም ባለመገታቱ ችግር አለባቸው፡፡ጨለማ በጋረደው ሕገመንግስታዊ ማርቀቅ ሂደት ውስጥ ብልጭታ የሚያሳየው የነጻው ስብስቦች የሊቢያ ጠበቆች፤ምሁራን፤ ጁሪስቶች፤መምህራን፤ እና ሌሎችም በትጋት በማርቀቁ ስራ ላይ ናቸው፡፡እንደዚህ የተገነጣጠለ አካሄድ ደግሞ የማርቀቁን ተግባር ለብጥብጥና አለመግባባት እንዲያመራ ያደርገዋል፡፡በዚህም ሰበብ በመጨረሻው ላይ ሰፋ ያለውን የሕብረተሰብ አካል በማንቃት ለክርክርና ለተሳታፊነት በመጋበዝ ሕገመንግስቱ በሊቢያ ሲነደፍ በባለቤትነት ይሰለፋል፡፡ 

ከሌሎች ውድቀትና ስህተት መማር፤  ሕገመንግስትን ለመንደፍ ቅድመ ውይይት በኢትዮጵያ 

ከፈላጭ ቆራጩ አገዛዝ መውደቅ ጋር ከምንም በፊት ዋነኛና መሰረታዊ ሆኖ የሚነሳው ጥያቄ፤ አሁን ስላለው ሕገመንግስት መደረግ ያለበት ጉዳይ ነው፡፡አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገመንግስት የአንድ ፓርቲ የአንድ ግለሰብ ስርአት ማካሄጃ መሳርያ ነው፡፡ሕብረተሰቡን ለመከፋፈል በአንድ ሰው ፍቃድና ‹‹እውቀት›› በዘር ላይ፤በጎጥ፤በክልል፤በወረዳ፤በቋንቋ እና በመሳሰሉት ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በሚካሄደው ሽግግር በጣም ጠንካራ የሆነ የሽግግር ሕገመንግስት አስፈላጊነት የሚጠበቅ ነው፡፡(ወታደራዊው ድርጅት ስልጣንን በግርግር ካልነጠቀ) አሁን ስላለው ሕገመንግስት በአብላጫው የሕብረተሰብ ክፍል ከቅሬታ ያለፈ ስሜት ይታያል፡፡ ሕገመንግስቱ በየወቅቱ በገዢዎቹ ይደፈራል፤የገዢውንና የአገዛዙን ግፈኛና የበደል ሁሉ መጋዘን የሆነውን ግለሰብ ስልጣን ለማጠናከርና ለማቆየት የሚጠቅም ሆኖ ነው ያለው፡፡በ2009  የዓለም አቀፍ የክራይስስ  የሚባለው በተግባሩ እጅጉን ከበሬታ የተቸረው፤ ለተባበሩት መንግስታት፤ ለአውሮፓ ዩኒየን፤ ለዓለም ባንክ በአደገኛ ግጭትና ሊወሰድ ስለሚገባው መፍትሄ አማካሪ የሆነው ቡድን፤በጣም አሳሳቢ የሆነውን ርዕስ አንስቶ ነበር፡፡ 

የኢህአዴግ በዘር ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝም አለመግባባትንና ግጭትን ከማስወገድ ይልቅ በፌዴራል መንግስታት መሃል በመሬት፤በተፈጥሮ ማእድናት፤የግዛት ክልል አያያዝና ከመንግስት በሚሰጥ ዓመታዊ በጀት ላይ ላይ ግጭቶችን አባብሷል፡፡ከዚህ ባለፈም በዘር ላይ የተመሰረተው ፌዴራሊዝም ብሄራዊውን ጥያቄ መመለስ ተስኖታል፡፡የኢህአዴግ የዘር ፖሊሲ የአንዳንድ ወገኖችን ስልጣናቸውን ሲያጎለብት ፤በውይይትና በመነጋገር የተደረሰበት ውሳኔ አይደለም፡፡ ለአማራውና ለብሔራዊ ምሁራን ክፍል የዘር ፌዴራሊዝም የጠነከረ አንድነት ያለው መንግስት ይፈጥራል፡፡እንደ ኦ ኤን ኤል ኤፍ (የኦጋዴን ነጻ አውጪ) እና ኦ ኤል ኤፍ (የኦሮሞ ነጻ አውጪ)የጎሳ ፌዴራሊዝም አርቲፊሻል ነው፡፡ 

ተጠያቂነትና ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም የሰብአዊ መበት መደፈር፤ሙስና፤ ለሽግግር መንግስቱ ሌላ የሽግግር ሕገመንግስቱ መፍትሄ ሊያገኝለት የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ይህ ደግሞ በቅርቡ የዩናይትድ እስቴትስ ባወጣው የሃገራት የሰብአዊ መብት አካሄድ በ2011 ባወጣው ዘገባ ላይ ተቀምጧል: 

የኢህአዴግ (የገዢው ፓርቲ) አባልነት ለአባላቱ የሚያስገኘው የጠቀሜታ መጠን ሰፊ ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ በርካታና መጠነ ሰፊ የሆኑ ስራዎችን ያካሂዳል፤በዚህ ሳቢያም ስራና የስራ ኮንትራት ውሎችን ለአባላቱ ብቻ ይሰጣል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ እንዳነሱት የአካባቢ ባለስልጣናት ፓርቲያቸውን በመተው ወደ ኢህአዴግ ፓርቲ እንዲገቡና መንግስታዊ ድጋፍ ያለውን ማዳበርያ፤የእርዳታ ምግብ ተጠቃሚነትን፤የስራ እድል ማግኘትን፤እድገትን፤ተማሪዎችም በጥሩና ቅርባቸው ወደሆነው ዩኒቨርሲቲ መመደብን፤፤በመጀመርያ ዲግሪም ስራ የማግኘት እድልና ሌሎችም መንግስታዊ የሆኑ እድሎችን ማግኘት እንደሚችሉ ያግባቧቸዋል፡፡ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት የፕራይቬታይዜሽን ትግበራውን አለአግባብ ሲጠቀሙበትና ሲገለገሉበት ይታያሉ፡፡

በሕጉ መሰረት ይግል ንብረቶችን ለመመርመር ሕጋዊ ፈቃድ ማግኘት አለባቸው፤ በተግባር ፖሊሶች ይህን ሕግ ሲጥሱት እንጂ ሲያከብሩት አይታዩም፡፡ መንግስት የሚከፈላቸው አሳባቂዎች በመሰማራት በግለሰቦች ላይ ስለላ እንዲያካሂዱ ያደርጋል፡፡የደህንነት አባላት በመንግስት ለጥያቄ የሚፈለጉትን ቤተሰብ አባላት በማሰርና በማንገላታት ላይ ተሰማርቷል፡፡ ብሄራዊ መንግስታትና እና ሪጂናል መንግስቶች ‹‹የመንደር ምስረታ›› በሚል ጋምቤላ፤ ቤንሻንጉል፤ጉሙዝ፤እና ሶማልያ ክልሎች ውስጥ (እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ) የስለላው አባላት ነዋሪዎችን በመደብደብ (ለሞት የተዳረጉም አሉ) ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በማሰር በማጉላላት በመንደር ምስረታው ላይ ጣያቄ ያነሱትን ዝም ለማሰኘት ሞክረዋል፡፡በዚህም የተነሳ ሌሎቹ የአካባቢው አባላት አለመናገርን መርጠዋል፡፡ሕገ መንግስቱ ሃሳብን በነጻ መግለጽን የመናገር መብትን፤ የፕሬስ ነጻነትን ያወጀ ቢሆንም ገዢው ፓርቲና ልዩ ልዩ መዋቅሮቹ ግን በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው ይከበር እያሉ የሚጮሁለትን ሕገመንግስት ከማንም በባሰ መልኩ እየደፈሩትና እየጣሱት ይገኛሉ፡፡መንግስት አሁንም ጋዜጠኞችን አታሚዎችን ባለንብረቶቹን፤ኤዲተሮቹን በግብታዊ ውሳኔና በይሆናል አለያም ሌሎችን ዝም ለማሰኘት ያስራቸዋል፡፡ በየትምህርትቤቱና በዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቹ በኢህአዴግ መርህ መሰረት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እየታነጹ ነው፡፡  በኢትዮጵያ የፈላጭ ቆራጭን የግፍ አገዛዝ መወድቅ ተከትሎ፤አብዛኛዎቹ የጉዳዩ ባለቤቶች በሽግግሩ ወቅት የሚያገለግል ሕገመንግስት እንዲቀረጽና የሚነሱትን አሳሳቢ ጉዳዮች ሁሉ የሚፈታ እንዲሆን መጠየቃቸው አይቀርም፡፡ በቅርቡ የፈላጭ ቆራጭን አገዛዝ ገርስሶ የጣለው በሰሜን አፍሪካ የተከናወነው ሂደት ለኢትዮጵያ የሚቸረው ትምህርት ካለ ሁሉንም የጉዳዩን አካላት ያካተተ ‹‹ባለ አደራ መንግስት›› መፍጠሩ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በኔ አመለካከት ለዚህ አማራጭ የሚሆነው መጨረሻውን ጊዜ ከመጠበቅና ግብታዊ የሆነ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት አሁኑኑ ውይይቱን(እኔ ቅድመ ውይይት የምለው) መጀመሩ ነው፡፡የተዋጣ የሽግግር ሂደት ለማምጣት እንዲቻልም በፓርቲዎችና በተደራጁ ሃይሎች ላይ የተወሰነ ሳይሆን ከሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ አባላት የታቀፉበት እንዲሆን ማድረጉ ተገቢ ነው፡፡ 

ከዲክታተር የጭቆና አገዛዝ የተላቀቁትን የአረብ ሃገራት የሽግግር ሁኔታ በመመልከት ኢትዮጵያ ብዙ ትምህርት ልትቀስም ትችላለች፡፡ቀዳሚውና ማነኛው ትምህርትም፤ሰፋ ያለና ዘላቂነት ያለው ቀጣይ ውይይት ሕገ ምንግስቱን በማዘጋጀቱ ርእስ ላይ ማካሄዱ ነው፡፡የአዲሲቱ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ቁልፍ ጭብጥ ምን ሊሆን ይገባል?ካለፉት መንግስታት የግዴት የዘርና የጎሳ አደረጃጀት ወጥተን አንድ ወጥ የሆነና የአንድነታችን መገለጫ ወደሆነ ስርአት እንዴት እንደርሳለን? በሕገመንግስቱ አቀራረጽ ላይ ተገቢ የሆነውን የዜግነት ድርሻቸውን ሊወጡ እንዲችሉ ሁሉንም የሕግረተሰብ ክፍሎች ማስተማርና መስገንዘብ የምንችለው እንዴት ነው፡፡ሁከሉም የዴሞክራሲ ተሟጋቾች በአንድነት የሚሰሩበትን መንገድ በማምጣት የሽግግር ሂደቱን ሰላማዊ ማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታስ እንዴት ነው የምንፈጥረው?ውይይትና  ድርድርንስ እንዴት እናካሂዳለን፡፡ 

ከፈላጭ ቆራጭ የአረመኔ አገዛዝ ውድቀት በኋላ የሕገ መንግስት አቀራረጽ 

የቅርቡ ታሪክ እንደሚያሳየው ከሰሜን አፍሪካው የአረብ በቃኝ ባይነት ሕዝባዊና ሰላማዊ አመጽ ኢትዮጵያ የምታገኘው ትምህርት፤ከተለያዩ የጉዳዩ ባለቤቶች የተውጣጡ አባላት የተካተቱበት ‹‹የባለአደራ ምንግስት››መሰየም ነው፡፡ይህ አይነቱ መንግስት ደግሞ የሚመራበትና ስራውን የሚያከናውንበት የሽግግር ወቅት ሕገ መንግስት ያስፈልገዋል፡፡ይህም ዘላቂውንና ዋነኛውን የሃገሪቱን መመርያ ሕገመንግስት ለማርቀቅ ስለሚረዳውን በሂደቱም የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ እንዲያስችለው ነው፡፡በኢትዮጵያ ስላለው ፈላጭ ቆራጭ የድንፋታና የግፍ አገዛዝ መውደቅ ተከትሎ ሌሎች አጋጣሚዎችም ሊታዩ ይችላሉ፤(እንደ ቀጥተኛ የሆነ የወታደራዊ ክፍል ጣልቃ ገብነት) እንደኔ እንደኔ ችግሩን እስኪከሰት ከመጠበቅ ወዲያውኑ ሁሉንም የሚያስማማ ውይይትና ድርድር ማካሄድ፡፡ የሕግ የበላይነትን ማእከል ያደረገ መንግስታዊ ስርአት ይመጣል የሚለውን መላ ምት ኢትዮጵያዊያን በአረቡ ሃገራት ከተካሄደው የዴሞክራሲያው ስርአተ መንግስት ግናባታ መማር የግድ ነው፡፡ በአረኑ ዓለም የበቃኝ ትግል ቅድመ ግንዛቤ ያልተወሰደበት ጉዳይ፤በሽግግሩ ወቅት የሕገመንግስቱን ማርቀቅና መመርመር ሃላፊነት ሊሸከም የሚገባው ማነው የሚለው ነው፡፡ የምእራቡ ዓለማት የሕገመንግስት አነዳደፍ ባለሙያዎች፤ችሎታና ብቃት ያላቸው ምሁራንና ጠበብት፤ የማስተማርያ ዶኩሜንቶች በገፍ፤በመላክ እንከን የለሽ ዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዴት መገንባት ይቻላል ለሚለው እገዛ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡በፓርቲዎች የሚወከሉ ሃገራዊ የጉዳዩ ባለቤቶችእና ድርጅቶችበሽግግር መንግስቱና በደጋፊያቸው ወታደራዊ ክፍል ፈቃደኝነት መሰረት የተካፋይነት ሚና እንዲጫወቱ ይፈቀድላቸዋል፡፡ይህ አካሄድ ግን ሌላውን አብላጫ ቁጥር ያለውን ዜጋ፤የሲቪሉን ማህበረሰብ አካል፤እና ከስርመሰረቱ ያሉትን ዜጎች ድምጻቸው እንዲሰማና የውይይቱ አካል ሊሆኑ እንዲችሉ  አላካተታቸውም፡፡ የዚህ አካሄድ ደግሞ በይበልጥ ባለቤት ያደረገው ምሁሩን ክፍል ብቻ በመሆኑ ተራው የዜጋ ክፍል የኔነትና የይገባኝ ጥያቄው ባለመመለሱ የራሱ አድርጎ አይቀበለውም፡፡ እርግጥ ቴክኒካል የሆኑ ርእሶች ስለሚነሱ የምሁሩ አስፈላጊነት አያጠያይቅም፡፡በአረቡ ዓለም እንደታየው ከሆነ ግን በኮሚቴው የተካተቱት ምሁራንና ሊቃውንት አማራጮችን በመክፈት በሕገመንግስቱ አቀራረጽ ሂደት እጅግም  ጠቀሜታ ያለው ሁኔታ አልፈጠሩም፤ሰፊው ዜጋ ያለተሳተፈበትና ድምጹን በነጻና ዴሞክረሲያዊ በሆነ መንገድ በማሰማት ያልተሳተፈበት የሕገመንግስት አነዳደፍ የብዙሃኑን ፈቃደኝነት የሚያሳይ ሳይሆን የጥቂት አዋቂዎችና ተጠቃሚዎች ፈቃድ የሚያረጋግጥ ነው፡፡የሕገመንግስቱ ማርቀቅ ተግባር ለብዙሃኑ ዜጎች ተሳትፎ መንገድ መክፈት ይገባዋል፡፡ ለዚህ ማሰረጃ የሚሆነውም በአረቡ የበቃኝ ትግል ማግስት የታየው የሲቪል ማህበረሰቡን፤የብዙሃኑን ድርጅቶች፤ሴቶችን፤ ወጣቱን፤ያገለለ ነበር፡፡ሙባረክን መንግሎ ለመጣልና የፈላጭ ቆርጭ ስርአቱን ማክተሚያ በማምጣቱ ትግል ክፍተኛውን ሚና የተጫወቱትና ሕይወታቸውን የሰዉት ወጣቶች አጋር ተፋላሚዎች በማረቀቁ መንደር አለመታየታቸው አየስገርምም? 

ኢትዮጵያ ከአረቡ የሽግግር ሕገመንግስት አቀራረጽ በመነሳት ሌሎች እጅግ አስፈላጊ የሆኑና ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት የምትችላቸው ነጥቦች አሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ድርጅቶች፤መሪዎች፤ምሁራን፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ በአንድነት ስርአት ያለው ፐሮግራም በመንደፍ ህብረተሰቡን ማስተማር፤ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ትምህርት፤ወሳኝና የተዋጣለት የዴሞክራሲያ ስርአተ ማሕበር ለመመስረት የሚረዳ ተግባር ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አሁን ስላለው ሕገመንገስት ጭላንጭሉ የሚታየውን ውይይተ በማዳበርና ይፋ በማውጣት በግልጽና በነጻነት ሕዝቡ እንዲነጋገርበትና ጥቅምና ጉዳቱን በመንቀስ በምትኩ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያበቃ ሕገመንግስት መንደፍ አለባቸው፡፡ሕዝቡን በማስተማሩ ረገድ ተግባብተው፤ለአንድ ግብ በመቆም፤ተስማምተው ሊንቀሳቀሱ የግድ ነው፡፡ 

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

የመለስ ዜናዊ ድንቀኛ ተረቶች

Monday, May 21st, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ በተካሄደው በ‹‹ ዓለም አቀፉ የኤኮኖሚ ስብሰባ ላይ›› የግፍ ገዢው የፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ አርቲ ቡርቲ መነባንብ:

በኔ እምነት በታሪክም ሆነ በቲዎሪ የኤኮኖሚ እድገትና ዴሞክራሲ ቀጥተኛ ግንኙነትም ሆነ ተዛምዶ የላቸውም፡፡ በኔ አመለካከት፤ በኤኮኖሚ እድገት ላይ የሚያስከትለውን ጫና ገሸሽ አድርገን ዴሞክራሲ በራሱ ጥሩ ነገር ነው፡፡በኔ አመለካከት አፍሪካውያን በጣም ስብጥሮች ነን፡፡ ስለዚህም ነው ብዬ አምናለሁ በመሃላችን ያለውን ግንኙነት ሰላማዊ የሚያደርገው፡፡እነዚህን ስብጥር ሰዎች በአንድነት ለማቆየት ያለው አማራጭም ዴሞክራሲ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ስለዚህም ዴሞክራሲን መዘርጋት ይኖርብናል: ግን ለእደገት ብለን አይደለም፡፡ዴሞክራሲን መዘርጋት ያለብን ስብጥር የሆኑትን በአንድነት ለማቆየት እንድንችል ነው፡፡ የኔ አመለካከት ይሄ ነው፡፡ያም ሆኖ ግን በዚህ የምሽት ተረት ተረት፤የእንቅልፍ ማምጫ ተረብ እና የኤኮኖሚን ልማትና ዴሞክራሲን የሚያገናኝ ፈጠራና የውሸት ተረት አላምንም፡፡በታሪክ ይህን የሚያረጋግጥ መሰረት የለም: በኔም አመለካከት ከልማት እድገት ጋር የሚያገናኘው መሰረት የለም፡፡ ይህንን የቅዠት ክርክር ማካሄድ ጨርሶ አያስፈልግም: ምክንያቱም ዴሞክራሲ ብቻውን ቆሞ ብቻውን ሊያበራ ይችላልና፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የኤኮኖሚ ዕድገትን ከዴሞክራሲ ጋር የተገናኘ ነው ብለው ““የቅዠት ተረት ተረት” የተናገሩት ፕሬዜዳንት ኦባማ በ2009 በጋና አክራ ይሄ ነው፡፡

ልማት በመልካም አስተዳደር ላይ ይመሰረታል፡፡ታሪክ ትክክለኛውን ውሳኔ ያመላክተናል፡፡የሕዝቦቻቸውን ፍላጎት የሚያከብሩ፤በሕዝቦች ፈቃደኝነት የሚያስተዳድሩ በሃይልና በማንአለብኝነት ከሚገዙ የበለጠ ልማታዊ የበለጠ የረጉ፤እና የበለጠ ስኬታማ ናቸው፡፡ መሪዎች ራሳቸውን ለማሳበጥና በሃብትም ለመክበር ጥረት የሚያደርጉ ከሆኑ፤ ማንኛውም ሃገር ሃብት ሊኖረው አይችልም፡፡ፍትህ የሕግ የበላይነት በሚጨፈለቅበትና በሙስናና በሌብነት በተመሳቀለ ሃገር ውስጥ ለመኖር የሚመኝ ማንም የለም፡፡ ይህ አይነቱ ሁኔታ ያለበት የዴሞክራሲ ሃገር ሳይሆን የግፍ ሃገር ነው፡፡ያንን የመሰለውን አስከፊ ስርአት መገላገያው ደግሞ አሁን ነው… በ21ኛው ክፍለ ዘመን፤ችሎታ ያላቸው፤ታማኝነት ያላቸው፤እና ግልጽነትን የሚቀበሉ ኢኒስቲቲዩሽኖች ለዚህ ስኬት ቁልፍ ናቸው፡፡—–ጠንካራ ፓርላማ፤ታማኝ የሆነ የፖሊስ ሃይል፤ነጻና ለራሳቸው ሕሊና የሚገዙ የፍትህ ስርአት አባላት፤ነጻና ዴሞክራሲያዊ ፕሬስ፤ ንቁና ልማታዊ የሆነ የግል ዘርፍ፤የሲቪል ማህበረሰብ፡፡ ለዴሞክራሲ ነፍስ የሚዘሩበትና መከታ የሚሆኑት እነዚህ ናቸው፤ ምክንያቱም በሕብረተስቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ አስፈላጊው ይሄው በመሆኑ፡፡…. ታሪክም ከነዚህ የአፍሪካ ጀግኖች ጋር ይቆማል እንጂ ራሳቸውን በሥላጣን ለማክረም ግፍ ከሚሰሩትና ለግለሰብ ፍላጎታቸው አመጽ ከሚያስነሱትና ሕገ መንግስቱን እንዳሻቸው ከሚያመሳቅሉት ጋር አይሰለፍም፡፡አፍሪካ ጡንቸኞች አየስፈልጋትም፤የሚያስፈልጋት የፈረጠሙ ዴሞክራሲያዊ ኢንስቲቲዩሽኖች ነው፡፡አፍሪካ የተሻለና ስፋት ያለው እድገት እንደሚኖራት ጥርጥር የለኝም፡፡

እኔ የምወዳችው ተረቶች

እንደሌላው ሰው እኔም የእንቅልፍ ማምጫ ተረቶች እወዳለሁ፡፡ የምመርጠው ደግሞ “ፒኖኪዮ በአፍሪካ” የተሰኘው፤ ነው:: ከአሻንጉሊትነት ወደ ሰውነት መለወጥ የሚመኘውን ፒኖኪዮ ሰው መሆን ሊችል ይችላል ግን ተአማኒነት ይጠበቅበታል፡፡ ፒኖኪዮ መዋሸት በጣም ይወዳል ያውም ገደብ የሌለው ትላልቅ ውሸት፡፡ፒኖኪዮ በዋሸ ቁጥር አፍንጫው ይረዝማል፡፡

‹‹ፐፍ: ዘ: ማጂክ ድራጎን እና ሕያው የሆኑ ውሸቶች ሃገር›› የተባለዉን ተረት እወደዋለሁ፡፡ ፐፍ: በቤቷ ያለውን ችግር ለመሸሽ የምትፈልገውን ሳንዲ የተባለች ልጅ ሕያው የሆኑ ውሸቶች ሃገር ወሰዳት፡፡ በዚያም ፒኖኪዮንና ጂብ መጣ እያለ በዉሸት የሚያስፈራራውና የሚጮኸውን ልጅ አገኘች:: ከዚያም ሌላ ማንም አይቶ የማያውቀውን ወይን ጠጅማ ላምና: ሮዝማውን ዝሆን አየች፡፡

ጥንታዊውን የኢትዮጵያ ታሪክ ተናጋሪ የኤሶፕን ግብረገባዊ ተረቶችም እወዳቸዋለሁ፡፡ ድሮ ዱሮ አንድ በጎችን ጠልፎ ለመውሰድ ችግር ያለበት ተኩላ ነበር፡፡የችግሩ መነስኤም ጠባቂው ንቁና ጠንቃቃ ስለነበር ነው፡፡አንድ ቀን ቀበሮው የተጣለ የበግ ቆዳ አገኘና ያንን ቆዳ ለብሶ በጎቹን ተመሳስሎ ከመንጋዎቹ ጋር ተደባለቀ፡፡እያደባ አንድ ባንድ በጎቹን በመብላት ላይ እያለ አንድ ቀን እረኛው አወቀበትና ከዚያን ዕለት ጀምሮ ሰርቆ ገድሎ መብላት አልቻሃለም::

ተምሳሌታዊና ድርብ ትርጉም ሰጪዎችንና የተረት አነጋገሮችን እወዳለሁ፡፡ እንደ ጆርጅ ኦርዌል የፖለቲካ ቋንቋ ያዘሉት:: ጀርጅ ሲተርት ፖለቲከኖች: ሃሰትን እንደ እውነት ግድያን የተከበረ ተግባር አድርገው ያቀርባሉ፡፡በዚህም መልኩ ጦርነት ሠላም፤ነጻነትም ባርነት፤መሃይምነት ምሁርነት፤ድህነት ሃብት፤ችጋር የተትረፈረፈ ምግብ፤ የጸሁፍ ቁጥጥርን የፕሬስ ነጻነት፤ግፍን መልካምነት፤ እያሉ ያቀርባሉ፡፡

አዎንና የልጆችን የጨዋታ ግጥምም እወዳለሁ፡-

ሃምፕቲ ዳምፕቲ የተባለ እንቁላል ግድግዳው ላይ ተቀመጠ፤ አወዳደቁም ተአምራዊ ነበር!

ጤናማ ሕብረተስብ፤ ዴሞክሬይዚ እና ንኮቹ ዲክታተሮች

“ብቸኛው ሕዝቦችን በሰላም ለማቆየት ያለው አማራጭ ዴሞክራሲ ነው” ይላል መለስ፡፡ ሃሰት ከሚኖርበት ሃገር አንዳንድ እውነተኛ ታሪኮች፡ እንመልከት-

ፍሪደም ሃውስ የዩናይትድ ስቴትስ ስቴት ዲፖርትመንት

በኤፕሪል 2008 በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ምርጫ ተካሂዶ ነበር፡ፍሪደም ሃውስ እና ፡ ያሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ባደረጉት ዘገባ መሰረት፤የተቃዋሚ ፓርቲ ተፎካካሪ ተመራጮች ከምርጫው በፊት በመንግስት ሃይላት በመንገላታትና ከምርጫው እራሳቸውን እንዲያገሉ በመያዝና መሳደድ ስቃያቸውን ይበሉ ነበር፡፡በዚህም የተነሳ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው ራሳቸውን በማግለል ስለተዉት መንግስትና ፓርቲው ብቻውን ተወዳድሮ ደጋፊዎቹ የምርጫ ተፎካካሪዎች ከፍተኝ ብልጫ አኙ፡፡ ገዢው ፓርቲ ለምርጫ ከቀረቡት ከ3 ሚሊዮን ያላነሱ መቀመጫዎች 99 በመቶውን አሸነፈ፡፡

የዓለም ባንክ (2012)

በሜይ 2010 በተካሄደው ምርጫ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ (ኢፒአርዲኤፍ) እና አጋሮቹ 99.6 በመቶ ምርጫውን በማሸነፍ የተቃዋሚውን ቁጥር በሕዝብ ተወካዮች 547 ወንበር ከ174 ወደ ሁለት አወረደው፡፡ ኢትዮጵያ በሰብ ሰሃራ አፍሪካ ከሚገኙት ሃገራት በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛዋና፤ በዓለም ካሉት ድሃ ሀገራት አንዷ ነች፡፡የኑሮ ደረጃውም ቢሆን በዓለም ካሉት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ካሉትም የባሰች ዝቅተኛ ነች፡፡በዚህም በዓለም 6ተኛ ደረጃ ላይ ያለች ድሃ ሀገር ናት፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል (2009)

የኢትዮጵያ መንግስት ለሃገርም ውስጥ ሆነ ለውጭ ሃገራት እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች፤ አዲስ አሳሪና አፋኝ ሕግ አውጥቶ፤ የሰብአዊ መብትን በመግፈፍ ወንጀለኛ አድርጎል፡፡የበጎ አድራጎትና የማህበራት ሕግ (2009) የተፈጠረበት ዋነኛ መንስኤ፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፤ የሲቪል ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ፤ለመቆጣጠርና እንቅስቃሴያቸውን ለመግታት ታስቦ ነው፡፡ይህንንም በማድረግ መጪውን የ2010ን ምርጫ ከወዲሁ ለራስ ድል ለማዘጋጀትና ተቃዋሚውን ከምርጫ ውጪ ለማድረግና በሰበብ አስባቡ ለመወንጀል እንዲያመች የታሰበ ነው፡፡

ሁማን ራይትስ ዎች (2010)

ኢትዮጵያዊያን በነጻ መናገር፤ ሃሳባቸውን መግለጽ፤የፖለቲካ ስብሰባዎችን ለማዘጋጅት፤የመንግስትን መግለጫዎችና አግባብነት የሌላቸውን አዋጆች ለመቃወምም ሆነ የተለየ ሃሳብ ለማቅረብ፤ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ፤ በነጻ ፕሬስ ሃሳባቸውን ማስፈር ጨርሶ የማይችሉበት የፍርሃትና የጭንቀት ሁኔታ ውስጥ ናቸው፡፡የዴሞክራሲ ቴክኒካል አሰራር ፍሬም ለዘለቄታው ማታለያና የገዢው ፓርቲ የመከላከያ ብረት ግንብ ሆኖ የገዢውን ፓርቲ ፍላጎት ማሟያ ብቻ እንዲሆን የታቀደ ከመሆኑም አልፎ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣኖች ለሚያደርሱት ሕዝባዊ ግፍ ተጠያቂነት የለባቸውም፡፡

የዓለም የፋይናንስ እውነታ ዎል ስትሪት ጆርናል (2011)

ኢትዮጵያ ከ2000 እስከ 2009 ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያየ እኩይ ድርጊት ብክነት 11፣7 ቢሊዮን ዶላር ተመዝብራለች፡፡የኤኮኖሚው አቅም ደካማና የኑሮ ውድነት ሕዝቡን አላላውስ ብሎ ወጥሮ በያዘው ሃገር ላይ እንዲህ አይነት ብክነትና ስርቆት እጅጉን አሳዛኝ ነው፡፡ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድም አውቀው እንዳላወቁ በመሆን ባለስልጣናት ከባለስላጣናት ጋር በመወዳጀት በ2009 ብቻ ከሕግ ውጪ 3.26 ቢሊዮን ዶላር ካለፉት ሁለት ዓመታት በእጥፉ ከሃገር ወጥቷል፡፡

የጋዜጠኞች መብት ጠባቂ ኮሚቴ (2011)

በአፍሪካ ጋዜጠኞችን በማሰር፤ በማሰቃየት፤ በማንገላታት ዝና ካተረፉት ሃገራት መሃል ከኤርትራ ቀጥላ የግፍ ከረጢት በመባል የተመዘገበችው ኢትዮጵያ ነች፡፡ግፉና መከራው እያሰቃያቸው ብዙ የነጻው ፕሬስ አባላት ሃገራቸውን ጥለው ለስደት ተዳርገዋል፡፡ይህም በቁጥር በዓለም ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል፡፡እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ መለስ ግን፤ለኖርዌጂያኑ (Aftenposten) ጋዜጣ‹‹ ለሕግ ልዕልና መከበር ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ ሰብአዊ ምብትንም በአግባቡ እናከብራለን፡፡ሃገራችን የህዝቦቿ የዴሞክራሲ መብት በአግባቡ የተከበረባት ሃገር ነች››በማለት የሌለ ነገር አለ በማለት ይቀላምዳል፡፡

ሁማን ራይትስ ዎች (2011)

የኢትዮጵያ መንግስት ስለ ሽብርተኛነት መከላከል ያወጣውን የይስሙላ አዋጁን ሰላማዊ ሰዎችን ለማሰርና ለማሰቃየት ሊጠቀምበት የፈጠረው ነው፡፡የጸረ ሽብር ሕጉ በራሱ ትልቁ ችግር ነው፡፡ዓለም አቀፉ ሕብርተሰብ በተለይም የአውሮፓ ዩኒየን፤ ዩናይትድ ስቴትስ፤ዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት ይህን ሕግ ለምን ሰላማዊ እንቅስቃሴንና የሰላመዊውን ሕዝብ ድምጽ ለማፈኛነት እንደዘረጋው ሊጠይቁት ተገቢ ነው፡፡

የኮንግሬስማን ዶናልድ ፔይን ዘገባ (2007)

ሰብአዊ መብት 2003 ( ዴሞክራሲና ተጠያቂነት አክት 2007 የተወካዮች ምክር ቤትን ድጋፍ አግኝቶ በኦክቶበር 2 2007 አለፈ) የአገር አስተዳደር ሚኒስቴር የሰብአዊ መብትን በመደገፍ አንድ ማዕከል ፈጥሮ ለሃገር በቀል የሰብአዊ መበት ተሟጋቾች የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርግበትን ዘዴ መቀየስ አለበት፡፡ሕጉ፤የዴሞክራሲን ሂደት በመደገፍ የዴሞክራሲን እውነታ ማጎልበትን ሲደግፍ፤የአሜሪካ መንግስት ሰብአዊ መብትን ለማደርጀት የሚያደርገውን ጥረትና እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የሚያውክ ከሆነ ይህን መሳዩን የሰብአዊ መብት አፈና ለማቆም የሚደረገው እርዳታ ሁሉ ከሰብአዊ መበት መከበር ጋር ተጓዳኝ መሆን እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡የ2005 ውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ፤ ከመንግስት በኩል ያስከተለውን ኢሰብአዊና ጸረ ዴሞክራሲ ተግባር አስመልክቶ የደህንነት ክፍሉን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡

የአሜሪካው ሴኔተር ረስ ፌይንጎልድ እና ፓትሪክ ሌሂ ረቂቀ ህግ 3457 (2008) ላይ አስተያየታቸው

ሚስተር ፌይን ጎልድ፤ – ሚስተር ፕሬዜዳንት፤በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትንና የዴሞክራሲን ረቂቀ ህግ 3457ን ድጋፍ ለማስታወቅ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ፡፡የዚህ ረቂቀ ህግ ዋናው ጥቅም በኢትዮጵያ ውስጥ የፖሊሲውን ግብ ለማረጋገጥና እውነተኛው ዴሞክራሲ ከተጫነበት ጫና ተላቆ ለሕዝቡ ጠቀሜታ የሚውልበትን ነጻ ሂደት ለማረጋገጥ ነው፡፡ ነጻ የሆነ የህግ ስርአትና የሕግ የበላይነት፤የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶች መከበርን፤በነጻው ሚዲያ ላይ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ የተጣለውን አፋኝ ገደብ ማስንሳት፡፡… እየባሰባት በሚሄደው የፖለቲካ ውጥረት ላይ ሰምተን አልሰማንም አይተን አላየንም በማለት ችላ ካልነው፤በግፍ ወደ ወህኒ የሚጣሉትን ንጹሃን ከረሳናቸው፤መንግስታዊ ያልሆኑ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ገደብ ከተጣለባቸውና ስራቸው እንዲዳከም ሲደረግ ችላ ካልን፤በኦጋዴን አስተዳደር ቀደም ሲል በኦሮሚያ፤በአማራው፤በጋምቤላ የተፈጸመውን በቸልታ እንዳለፍነው ሁሉ አሁንም ሰዎች በግፍ ሲገደሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ካልን፤ከተጠያቂነት አናመልጥም………

2010 የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የሜይ 2010 የምርጫ ዘገባ

በአብዛኛው የሃገሪቱ ክልሎች የገዢው ፓርቲና መንግስታዊ እንቅስቃሴዎችና ምርጫው ላይ የነበረው ልዩነት ጨርሶ አይታይም ነበር፡፡ ገዢው ፓርቲ መልሶ መንግስት ነው፡፡የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢ ቡድን፤የመንግስትን መገልገያና ሌሎችም ያና መጠቀሚያ ሲውሉ ተመልክቶ ታዝቧል፡፡ገዢው ፓርቲና አጋር ፓርቲዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ547 መቀመጫዎች 544ቱን አሸነፉ፡፡ በዚህም የምርጫው ሂደት ዓለም አቀፍ ደረጃውን መመዘኛ ማሟላት አቅቶታል፡፡ግልጽነት አልነበረውም እንዲሁም ለሁሉም ምርጫ ተፎካካሪዎች መድሎ የሌለበት ሂደትም አላሳየም፡፡ ለገዢው ፓርቲ በሁሉም መልኩ የወገነ ሁኔታ ነበረው፡፡

የመለስ መልስ፡- ለ2010 ለአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ታዛቢ ኮሚቴ ሪፖርት

የአውሮፓ ዩኒየን የምርጫ ዘገባ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ መወርወር ያለበት ቆሻሻ ነው፡፡ዘገባው ስለእኛ ምርጫ አይደለም፡፡ገዢው ፓርቲ በመፈርጠሙ የተነሳ የአንዳንድ አውሮፓውያን ኒዮ-ሊበራልስ የቅናትና ምቀኝነት ዘገባ ነው፡፡ማንም ወረቀትና ብዕር ያለው የፈለገውን መሞንጨር ይችላል፡፡

ይህ ነው የመለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ያለው ዴሞክራዚ!

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ:: http://www.ethiopianreview.com/amharic/?author=57

በካምፕ ዴቪድ የአፍሪካ የችጋር ትርኢት

Monday, May 14th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ባለፈው ሳምንት የሁዋይት ሀውስ ቤተ መንግስት ቃል አቀባይ ጄይ ካርኒ ፕሬዜዳንት ኦባማ የጋናን፤ የታንዛንያን፤የበኒን ፕሬዜዳንቶችንና መለስ ዜናዊን የስምንቱን የኤኮኖሚ ሃያላን ሃገሮች (G8) ስብሰባ ላይ በካምፕ ዴቪድ ሜሪላንድ በሜይ 19 ስለ ምግብ ዋስትና በሚካሄደው ውይይት ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የአሜሪካን መንግሥት ለዘመናት ለአፍሪካ አህጉር የምግብ እርዳት ሲያደርግ መክረሙ ይታወቃል፡፡ አሁንም በድጋሚ አፍሪካን ‹‹የመረረ የችጋር ወቅት›› ገጥሟታል ይላሉ ፕሬዜዳንት ኦባማ፡፡ ኦክስፋም በበኩሉ ከአሁኑ አስፈላጊው ሁሉ ካልተደረገ በስተቀር በመታየት ላይ ያሉ ጠቋሚ ምልክቶች ሁሉ እጅጉን ዘግናኝ የሆነ መአት እንደሚከተል ያሳያሉ ይላል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት በበኩሉ ባስተላለፈው የድረሱ ጥሪው፤ በሳሄል ምእራብ አፍሪካ ለ800,000 በችጋሩ ለተጎዱት ረሃብተኞች መርጃ የሚሆን 70 ሚለዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግ፤አስቀድሞ ማስጠንቀቂያው መተንበዩን መሰረት አድርጎ ኢትዮጵያና ሶማልያ በጉዳቱ ወደ አዘቀዘቀው ደረጃ እንደሚወርዱም ይፋ አድርጓል፡፡ የዝናቡ አናሳ መሆንም አስፈላጊውን ምርት ስለማያስገኝ የግጦሽ መሬትንም መልሶ ስለማያለማው፤በአጠቃላዩ አካባቢም የውሃ እጦት ሌላው ችግር በመሆኑ የደቡብ ኢትዮጵያውን ክፍል በእጅጉ የሚጎዳና ሕዝቡንም ለመረረ ችጋር ከብቱንም ለእልቂት የሚዳርግ ክፉ ቀን እንደሚመጣ ይተመናል:: ይህ ደሞ በገሃድ እየታየ ያለ በመሆኑ አደጋው ከአደጋዎች ሁሉ የባሰ በሆነ መልኩ ነው፡፡ አንባቢዎቼ እንደሚያስታዉሱት ሁሉ ባለፉት ሁለታ ዓመታትና ከዚያም ባለፈ በኢትዮጵያ ስለሚከሰተው ችጋር በርካታ አስተያየቶችን አስመልክቼ ጽፌ ነበር፡፡

የችጋር ትርኢት በኢትዮጵያ

ባለፉት ዘመናት የነበሩት አሁንም ያሉት የኢትዮጵያ ገዢዎች ስለችጋር መከሰት የራሳቸውን ቸልተኛነት፤ አቅምየለሽነት በመካድ ነጻ በማድረግ በተጠያቂነት ያልወቀሱትና ሃላፊነት ያልሸሹበት ዘዴ የለም፡፡ በ1974 ዓ.ም. ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዲምብልቢይ ይፋ እስኪያደርገው ድረስ ረሃብ የለም ሲሉ ከርመው ነበር፡፡ በዲምብልቢይ ፊልም ሕዝቡ ረሃቡን አየ፤አዘነ፤ አንገቱን ደፍቶ አለቀሰ፡፡ የወገኑ በችጋር መቆላት ቅስሙን ሰበረው፡፡ የቀድሞው የሶሻሊስት ጁንታ መሪ መንግስቱ ሃይለማርያምም በ1984-85 የተከሰተውን ችጋር በድፍረተና በማንአለብኝት ክዶ ሁኔታውን በዓይናቸው ያዩትንና የታዘቡትን ሁሉ ገሸሽ በማደረግ ስችጋሩና እልቂቱ አንስተው ሲጠይቁት በመመጻደቅ ‹‹የምን ችጋር›› ነበር እያለ ያሾፍ ነበር፡፡

መለስ ካለፉት መሰል ገዢዎች ሁሉ የተለየ ብልጣ ብልጥ ነው፡፡ በሃገሪቱ በላይ በሚንሰራፋው የችጋር ወቅት ሁሉ የህዝብ ግንኙነት መሳይ ተግባር ይወጣል፡፡ያለው “የምግብ እጥረት” በሚል ሽፋን በመጠቀም በጣም የጎላውን “ረሃብ” የሚለውን ቃል አይጠቀም እንጂ ከዚያ ባሻገር ምንም አይቀረውም፡፡ ለመለስ በሃገሪቱ ላይ ችጋር የለም፡፡ ያለው የምግብ እጥረት ነው፡፡ የከፋ የተመጣጣነ የምግብ እጦት ነው: ያለው የምግብ ዋስትና ማጣት ነው፤ የምግብ አቅርቦት ችግር ነው፤ እና ሌላም ልላም ይላል መለስ፡፡ እንደሱ የማሳሳቻ ጥምጥም አካሄድ እነዚህ ሁሉ የየእርሻ ዘዴን አጠቃቀም አለማወቅ ያመጣቸው ችግሮች፤የባለስላጣናቱ የእውቀት ድህነት፤ሙስና፤እና የወንጀለኛነት ውጤት ወዘተ አይደሉም ቢልም፤እነዚህ ሁሉ ግን በችጋርና ድርቅ፤በተደጋገመ የዝናብ እጥረት ሳቢያ የሰብል መበላሸት፤የደኖች መጨፍጨፍ፤የመሬት መሸርሸር፤ ከመጠን በከላይ የመሬቱ ምርታማነት ማጣት እና በሌሎችም ሰበቦች የተፈጠሩ ችግሮች ናቸው፡፡ መለስ ባለፈው ጃነዋሪ 2011 ላይ ለሲ ኤን ኤን በሰጠው የቅጥፈት መግለጫ ላይ፡ “ኢትዮጵያ በጣም አሰቃቂ የሆነ የችጋር ወቅት ውስጥ ሆና፤ ሕዝቡም ለችጋር ተጋልጦ ሳለ አንተ በሌላ ሃገር ጉዳይ ጣልቃ ገብ በመሆን ይህን ያህል ገንዘብ እንዴት ታባክናለህ? ለሚለው የሰጠው ዓይን ያወጣ የቅጥፈት ምላሽ፤‹‹ማንኛቸውም ሰብአዊ ድርጅቶች ሊነግሩህ እንደሚችሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ችጋር የለም ድርቅ ቢኖርም እኛ ግን ሕዝባችንን በአግባቡ ልንመግብ እንችላለን…….›› ብሎ አድበስብሶታል::

ዓለም አቀፎቹ የድህነት ቃራሚዎች/ አጎብጓቢዎች (poverty mongers/pimps “PMPs”) የምግብ እጥረትን ለማስረዳት ‹‹ሳይንሳዊ›› መገለጫ ፈጥረውለት፤ መለስ ደግሞ ያንን በሃገሪቱ ላይ ያንሰራፋውን የችጋር መጠንና በሕዝቡ ላይ የሚያደርሰውን እልቂት ለመደበቂያና መሸሸጊያነት እየተጠቀመበት ነው፡፡ እነዚህ ቃራሚ/አጎብጓቢዎች ምንም ያህል የምግብ እጥረት ቢኖርና ገጦ ቢታይም ችጋር የሚለውን መግለጫ እየሸሹትና ሳይንሳዊውን መደባበቂያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ መለስ ደግሞ በዚህ በተፈጠረው መግለጫ ውስጥ በመሸጎጥ ችጋረ የለም ይለናል፡፡ በነሱ ብልጥታዊ ሰበብ ደግሞ ሁኔታው በ‹‹የከፋ የምግብ ዋስትና እጦት›› ጭንቀት፤አጉል ገጠመኞች›… እያሉ ያሾፋሉ፡፡ በአፍሪካ ውስጥ በሳይንሳዊ ማስረጃ እንደተረጋገጠው ችጋር ሊኖር ጨርሶ አይችልም ብለው ሳያምኑበት ሊያሳምኑ ይጥራሉ፡፡ ስለዚህም የዚህ ሁኔታውን አፍኖ በዝምታ የማለፉ አድማና ዱለታ በማጭበርበሪያ ጭንብል በመሸፈን የኢትዮጵያን የችጋር አሰቃቂ መልክ ለመደበቅ ከፍ ያለ ጥረታቸው ነው፡፡

መለስና ከፍተኛ መኮንኖቹ በድርቅ ሳቢያ የተፈጠረውን የምግብ አቅርቦት እጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቆጣጥረን እናሸንፈዋለን ብለው ምለው ተገዝተው ነበር፡፡የሃገሪቱ የድርቅ መከላከያን የአስቀድሞ ጥንቃቄ ሹም ስምኦን መቻሌ፤ መኩራራትና በእርግጠኝነት ‹‹ኢትዮጵያ በቅርቡ የምግብ ዋስትናን ጣረጋግጣለች›› ብሎ ነበር፡፡ ላለፉት በርካታ ዓመታትም መለስ “የሴፍቲ ኔት ፕሮግራም”፤ በምግብ ተረጂነት ላይ መተማመንን ለማስቆም፤ፈላጊውንና አቅራቢውን በማቀራረብና በቂ ምርት በማስገኘት የፕሮግራሙን ስኬታማነት በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ በኦክቶበር 2011 መለስ ለታማኝ የፓርቲው ሰዎች የተለመደ ቅልመዳውን ሲያቀርብ ‹‹ከምግብ ተረጂነት የሚያወጣንንና እራሳችን በበቂ ለመመገብ የሚያስችለንን፤ በ2015 ከምግብ እርዳት ጋር የምንለያይበትን ዘለቄታዊ እቅድ ነድፈናል ብሎ ነበር፡፡ የመለስ የበቂ ምርት ማግኛ ዘዴም፤የሃገሪቱን በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር ለም መሬት ለውጭ ኢንቬስተሮች ለሚላቸው ባዕዳን የተመረጡ የእርሻ ቦታዎችን በሊዝ በመችብቸብና ዓላማቸውም የሃገሪቱ ሕዝብ በችጋር እያለቀ ምርታቸውን ወደ ውጭ ሃገራት ለመሸጥና ለማትረፍ የሆነውን አሰራር ነው፡፡ መለስ የመሬቶችን የህዝብ ሃብት በማድረግ ከተረጂነት መውጫ መንገዱን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ የህዝቡን ባለንብረትነት ፈጽሞ ይቃወማል:: ይህ ደግሞ በየትም ቦታ ታይቶ የማይታወቅ ስርአት ነው፡፡ባለፈው ዓመትም የምግብ አቅርቦት ዋጋ ግሽበት 47.4 በመቶ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

በኢትዮጵያ የምግብ አቅርቦት እንደፖለቲካ መሳርያነት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡ችጋር አዲሱ የተቃዋሚዎች ማጥፊያ፤ ማዳከሚያ ተስፋ ማስቆረጫ መሳርያ በመሆን በማገልገል ላይ ነው፡፡ መለስ ኢትዮጵያውያንን በችጋር ማጥ ውስጥ በመዝፈቅና ሆዳቸውን ባዶ በማድረግ ሕዝቡ አንገቱን እንዲደፋ ሞራሉን እንዲያጣ፤ ጥንካሬው ተሰብሮ አገልጋዩ እንዲሆን፤መንፈሱ እንዲላሽቅና ህሊናው የመከራ ቋት እንዲሆንና ማሰብ እንዲያቅተው በማድረግ ገዢነቱ ተሳክቶለታል፡፡ ሕዝቡም አቅሙን ተገፏል ወኔው ተዳክሟል፡፡ የመለስን አገዛዝ የሚቃወሙ ሁሉ ሰብአዊ የምግብ ተረጂነት መብታቸውን መገፈፍ ብቻ ሳይሆን፤ለስደት በሚዳርገው ዘዴ ስደተኛ በማድረግ፤እነሱነታቸውን በማጣጣልና ተስፋ በማስቆረጥ፤አለያም የያዙትን የእርሻ ማሳቸውን በሰበብ አስባቡ በመቆራረጥና በማሳነስ፤የብድር ተጠቃሚነት መብት እንዳይኖራቸው፤ የማዳበርያና የዘር እህል እንዳያገኙ በማድረግና በሌላም ሌላ ግፍ ማዳከሙ ተሳክቶለታል፡፡ የጋምቤላን ጉዳይ በተመለከተም የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መበት የሚጥሰውን ነዋሪዎች ከያዙትና ካለሙት መሬታቸው ላይ በግዴታ እንዲለቁ በማድረግ አንድ ሙሉ ነዋሪ ቦታውን ሕንዶች በኢንቬስተርነት እንዲነጥቋቸው ተደርጓል፡፡ ከብዙዎቹ ተሟጋቾች መሃል ሁማን ራይትስ ዎች፤ በሰብአዊ የምግብ እርዳታ ፕሮግራሙ ላይ: ሲዘግብ ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት በተከታታይ የምግብ እርዳታውን እንደ ፖለቲካ መጠቀሚያ፤ ተረጂውን ማግለያ፤ ለመቆጣጠርያነት እያዋለው ነው፡፡ የገዢውን ፓርቲ ጨዋታ ለመቀላቀል ፈቃደኛ ካልሆንክ በተገቢው የተቆጣጣሪ የውጭ ታዛቢ ግበረ ሃይል እንዳትታገዝ ሆነህ ከጨዋታው ውጪ ትደረጋለህ፡፡ ስለዚህም የተጠናከረና ወለም ዘለምን የማይቀበል በራሱ ተማምኖ የሚንቀሳቀስና ግድፈቱን ይፋ የሚያወጣ የውጪ ታዛቢ ካለተፈጠረል በስተቀር ይህን ጨቋኝ ኢሰብአዊ የሆነ ገዢ መንግስት ማስተካከል የማይሞከር ነው›› ብልዋል:: በ2011 ላይ በሃገሪቱ ውስጥ ካለው ገዢ ፓርቲ ጋር ተወዳጅተውና ተቀብለው ከሚንቀሳቀሱት ውጪ በፖለቲካ አመለካከት ልዩነታቸው ሳቢያ ከአሜሪካን መንግስት ተችሮ የነበረው 850 ሚሊዮን ዶላር የማግለል ስርጭት በመለስ ፓርቲ ስለተፈጸመው የስርጭት ደባ የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት ለማጣረት ቃል ቢገባም፤‹‹እስካሁን ድረስ ስለጉዳዩ አንድም የወጣ ዘገባ የለም››:: በ2011 የአሜሪካው የምርምር ቢሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በ2050 በመጠን በመግዘፍ ወደ 278 ሚሊዮን ያሻቅባል፤ ብሎል:: በዚህም በሽታ ችጋር ጦርነትና እልቂት ሌላም ሌላም ሰበብ ሕዝቡን ወደ ምግብ አምራችነት ግዳጅ ያሰድገባዋል፡፡ የመለስ ገዢ መንግስት ብሔራዊ የቤተሰብ መምሪያ እቅድ በአግባቡ መዘርጋት ስላልቻለ ወደ ተፈራው ችጋርና ችግር በተፋጠነ ሂደት መግባቱ የማይቀር ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚከሰተው ችጋር 90 በመቶው ሰው ሰራሽ ነው፡፡

የዓለም ባንኩ መሪ ኤኮኖሚስት ዎልፍጋንግ ፌንግለር በኦገስት 17 2011 ላይ እንደ ዓለም አቀፍ የባንክ ሰውነቱ ለአስተያየቱ እጅጉን ታማኝ ነበር፡፡ ሲናገርም፡- ‹‹ በአፍሪካ ቀንድ ያለው የችጋር ጉዳይ ለዋጋ የሚጠየቀው የተጋነነነ ዋጋና በሚፈጠረው የእርስ በእርስ ግጭት የመጣ እንጂ በተፈጥሮ ሳቢያ የተከሰተ አይደለም፡፡ይህ ችግር ሰው ሰራሽ ነው፡፡ድርቅ በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ሁኔታው ወደ ርሃብ እንዲቀየር ያደረገው ግን ዋነኛው ሁኔታ መጥፎ ፖሊሲ መፈጠሩ ነው፡፡በሌላ አገላለጥም በኢትዮጵያ ውስጥ መጥፎና እኩይ አስተዳደርየችጋሩ መንስኤ ነው እንጂ ድርቅና የአካባቢ ዓየር ያመጣው ጣጣ አይደለም፡፡ የኦክስፋም ዓለም አቀፍ ዳይረክተር የሆኑት ፔኒ ላውረንስ፤ኢትዮጵያን ከጎበኙ በኋላ የደረሱበት ድምዳሜ ‹‹ሕብረተሰቡ ለሰብሉ የመስኖ ውሃ ቢኖረው፤የሰብሉ ማጠራቀሚያ ጎተራ በብቃት ቢያገኝ፤እና በቂ ውሃ ከዝናቡ ማቆርያ ቢሰራለት ማንኛቸውንም የሚያጋጥማቸውን ችግር ሁሉ በቀላሉ ሊቋቋሙት ይችላሉ በማለት ዘግበዋል፡፡ የዓለም አገልግሎት የአፍሪካ ኤዲተር የሆኑት የቢቢሲው ማርቲን ፕላውት ሲሉ፤ያሁኑ በገበሬው ላይ የወረደበት ችግር መንስኤ መንግስት መሬቱን የራስህ ነው ግን አታዝበትም አይነት ደንብ በማውጣት ገበሬው ከዚያ እንዳይነቀሳቀስ ለማድረግ ያወጣው ደንብ በመሆኑ ሊነሱ የሚገባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች፤ ሶሻሊዝምን ያወገዘው መንግስት እና ነጻ የገበያ ኤኮኖሚን እተላለሁ የሚል አካል፤ መሬትን በተመለከተ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሊሆን አይችልም በማለት መመጎቱ ለምንድን ነው? ለምበንስ ስርአት ያለው የመስኖ ውሃ እንዲዘረጋ አልታቀደም? የሰብል ማከማቻ ሰፋፊ ቋትስ ለምን የለም? የዝናብ ውሃ መማቆርያስ ለይስሙላ ሳይሆን በወጉ ለምን አልተዘጋጀም? በእርግጥና በእውነት ግን ለኢትዮጵያ መለስ ዜናዊ የምግብ ዋስትና ፖሊሲ አለው?

ለዓመታት በሰብአዊ የእህል ምጥዋት አረንቋ ውስጥ የተዘፈቀችው ኢትዮጶያ በቅርቡ የምግብ ዋስትናን ታረጋግጣለች ብሎ ማሰብ ከቅዠት ውጪ ሊሆን አይችልም፡፡ የመጪው ዐመታት በአፍሪካ ቀንድና በሳህል ሊያጋጥም በሚችለው ችጋርና የረሃብ ሰደድ እጅጉን ያስጨንቃቸዋል፡፡ ባለፈው ወር የአሜሪካን መንግስት ሊከተል የሚችለውን የዝናብ እጥረትና የሚያመጣውን የድርቅ ሁኔታ ለመቋቋምና ሕዝቡን ከችጋር ሞት ለመታደግ ተጨማሪ የ200 ሚሊዮን የምግብ ዕርዳታ ለመቸር ቃል ገብቷል፡፡የአሜሪካን መንግስት ለኢትዮጵያ፤ ኬንያና ሶማልያ የ1.1 ቢሊዮን ዶላር የሰብአዊ ዕርዳታ ሰጪ ነው፡፡

በሜይ 19 ላይ ፕሬዜዳንት ኦባማና የ G8 መሪዎች እንደገና ሊያጤኑት የሚገባቸው 3 መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉ፡፡ማለቂያ የሌለው እርዳታ ለአፍሪካ ቀንድ ሃገራት መስጠቱ የሚያስከትለው የሞራል ድቀት ምን ሊሆን ይችላል? እነዚህን ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ገዢዎች መርዳቱና እነሱ ያንን መተማመኛ በማድረግ ተደላድለው ለግፍ አገዛዝ በእርዳታው ገንዘብ የበለጠ መመቻቸታቸው የረጂዎቹን የሞራል ኪሳራ አያስከትልም? በአፍሪካ ውስጥ በተደጋጋሚ በመከሰት ላይ ያለውንስ የችጋርና የድርቅ መፈራረቅና በተደጋጋሚ መከሰት ዘወትር ሰበቡ የዓየር ለውጥ በመሆን መቀጠሉስ በአፍሪካ ላለው የማይነቀል የምግብ እጥረት አስተዋጽኦ አያደርግም? የ G8 መሪዎች ለመለስ ዜናዊ ሊያቀርቡለት የሚገቡ ሌሎች ጥያቄዎች አሉ፡፡በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር ለም መሬቶቹን ለህንድና ለአረብ ሃገራት የምግብ ዋስትና ማምረቻነት እየሸጠ የራሱን ሕዝብ ወደ ችጋርና ሞት የሚዳርግን ሃገር፤ ዓለም መርዳት ያለበት በምን መመዘኛና ሰበብ ነው? ለምንስ ተብሎ ነው የሚሰጠውን የሰብአዊ የምግብ አቅርቦት መርጃ ለፖለቲካ መጠቀሚያ በማድረግ ተቃዋሚዎቹን ለመጉጃ፤ ለማስደንበርያ፤ ለማስራቢያ፤ ለማፈናቀያ፤ዴሞክራሲን ለመጨፍለቂያ፤ሰብአዊ መብትን ለመድፈሪያ፤ ፍትህን ለማጥፋት መጠቀሚያ ለሚያደርግ ሃገርስ ለምን ተብሎ ነው የሚረዳው?

የ G8 መሪዎች ስለ‹‹ምግብ እጥረት›› መነጋገር ይችላሉ፡፡ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ላለው ችጋር ምላሽ ግን፤በረሃብ በመሰቃየት ላለው ሕዝብ እፍኝ ምጽዋት መቸርና፤ ለፈላጭ ቆራጭ ጨካኝ ገዢዎች የመዝናኛ ወቅትና የነጻ ምሳ አቅርቦት የችግሩ መቅረፊያ ሊሆን አይችልም፡፡ እፍኝ ምጽዋት ችጋርን ከማጥፋት ይልቅ የሞራል ውድቀትን በማስከተል የዘልአለም ተመጽዋችነትን ፍላጎት ያበረታታል፡፡ መለስና መሰለቹ ግፈኛ የአፍሪካ ጨቋኝ ገዢዎች የምግብ እጥረቱን አስመልክቶ ለሕዝቡ ዘላቂ መፍትሔ የማስቀመጥ ሃሳብም ፍላትም የላቸውም:: ምክንያቱም ዓለም ሁል ጊዜ ረሃብን በተመለከተ እንደማይጨክን ስለሚያውቁ ችግሩን እያወቁት አፍነው በመያዝ በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ጩኸታቸውን ማቅለጣቸው የተለመደ ዘዴያቸው ነው፡፡የአሜሪካን መንግስት እነደዓለም ቀደም ሹመኛነቱ ርሃብ በገባበት ሁሉ ደርሶ እርዳታ በመስጠት ተጠቂዎችን ከችጋር ማዳንን የሞራልና ሰብአዊ ግዴታ አድርጎ ያየዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ለዚህ ሁኔታ የሚሰጡትንም የልማት እርዳታ ችሮታ፤ብድርን፤የበጀት ድጋፍ ችሮታውንም ለዴሞክራሲ ማበብና ተግባራዊነቱ፤ የሰብአዊ መብት መከበርና መየበቅ፤የህግ የበላይነትን ማክበርና ለሱም መገዛትን ማረጋገጫ ጉልበትም አድርገው የመያዝ የውዴታ ግዴታ አለባቸው፡፡

በ2010 በተካሄደው የማስመሰያ ምርጫ የመለስ ፓርቲ 99.6 የፓርላማ ወንበሮችን አሸነፍኩ ብሎ ስልጣን መያዙ ይታወሳል፡፡ ባለፉት ዓመታት ውስጥ መለስ ዜናዊ አስገራሚ የኤኮኖሚ እድገት አሳይተናል በሚል የማይጨበጥ ተስፋ ቢስ እድገት ከመፎከር ውጪ እድገቱን ግን ማሳየት ካለመቻሉም ባሻገር፤በሃገሩ ውስጥ ያለውን የምግብ እጥረት ለማሸነፍ እዚህ ግባ የሚባል ስትራቴጂ ማቅረብ አልቻለም፡፡ በሃያ አንድ ዓመታት የመለስ አገዛዝ ውስጥ፤ኢትዮጵያ ከእርዳታ ለማኝነት ሳትላቀቅና በየጊዜው የልመናዋ ቋትም እየበዛ ከመሄድ አልተላቀቀም፡፡ ኢትዮጵያውያን እጅጉን በከፋና መፍትሔ በሌለው የምግብ እጥረት ውስጥ መዘፈቁ፤ከችግሩ ጋር በቀጥታ ሊታይ በሚችል መልኩ የፖለቲካ አሰራር ባለመዘርጋቱ ነው፡፡ የሕንዱ የኤኮኖሚ የኖቤል ሽልማት አሸናፊው አማርቲያ ሴን ርሃብን ለማስወገድ ትክክለኛው መንገድ፤ዴሞክረሲን ሕዝባዊ በማድረግ ሰብአዊ መብትንም በማጠናከር ነው በማለት ያስረዳል፡፡ በዓለም ታሪክ ውስጥ፤ዴሞክራሲ በትክክለኛው መልኩ በሚተገበርበት ቦታ ችጋር ደርሶ አያውቅም፡፡ ምክንያቱም ዴሞክራቲክ አደስተዳዳሪዎች ምርጫቸውን ማሸነፍ ስለአለባቸውና የህዝብንም ሂሳዊ አመለካከት በግላጭ ስለሚቀበሉ ያጋጠማቸውን ችጋርና ድርቅ መቋቋምና አጥጋቢ መፍትሔ የማስገኘት ግዴት ስለአለባቸው ነው፡፡

የሴን ዴሞክራሲያዊው ‹‹የድርቅን አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ አውታሮች” የሉም:: ተቃዋሚ ፓርቲዎች አላአንዳች ሰበብ ይጨፈለቃሉ፤ መሪዎቻቸው ለመከራ ይዳረጋሉ፤ይወነጀላሉ ይታሰራሉ፡፡ ነጻው ፕሬስም ይታፈናል፤ ነጻ ጋዜጠኞችም ገዢውን መንግስትና ሹመኞቹን በሚፈጽሙት ደባና ሙስና በማጋለጣቸውና ገዢዎችም ለሚከተሉት ጭፍን የማንአለብኝ አገዛዝ አስተሳሰባቸውን በመግለጽና ትክክለኛውን መንገድ በማመላከታቸው ለወህኒ ይዳረጋሉ፡፡ ስለችጋሩ እውነታውን ሊዘግቡ አይፈቀድላቸውም፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ድርቅን ለማስወገድ የተቋቋሙት ድርጅቶችም ጭምር አረማመዳቸው ሁሉ ጥንቃቄን ባጠናከረ መልኩ በፍርሃት መሆን እንዳለበት ተረድተዋል፡፡ ህጉ ሀገሬውንም የውጭውንም የእርዳታ ተግባር ፈጻሚውንና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹን በወንጀለኛነት የሚያካትት ሆኗል፡፡ መለስ ዜናዊ አመጣዋለሁ እያለ በማይተገበር የሃሰት የዴሞክራሲ ነጻነት እውነታ በመዋሸት የተካነ ነውና የዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶችን በዚህ መንገድ ሲያታልልና ሲዋሻቸው ኖሯል፡፡ ባለፉት በርካታ ዓመታት ሂደት ውስጥ መለስ ሊመጣ ነው ደርሷል፤ በዝግታ እንደርስበታለን ብለን አቅደን ፈጥነን ደረስንበት የሚለውን የዴሞክራሲ ነጻነት እንኳን ልናየውና አካሉ ልንሆን ቀርቶ በሕልማችን እንኳን ለማየት ተስኖናል፡፡ ይልቁንስ የመለስ አገዛዝ ጭካኔ በየቀኑ ከአቅም በላይ እየሆነ፤ አገዛዙ ሕዝብን ኑሮ እንዲመረው የሚያደርግ፤ ሲጨንቀው በሚያወጣቸው እዛዞችና አዋጆች ግራ መጋባት፤ የተማረው ዲግሪውን ታቅፎ ኮብል ስቶን መጥረብ፤ ያን ኮብል ስቶን ሊጠርበው የሚገባው የተማረው የሚቀመጥበት ወንበር ላይ በድፍረት መጎለትና የመለስን እድሜ መለመንን በየቀኑ እያደገና የሕዝቡም ችግርና ስቃይ በዚያው ልክ ሰበዛ ማየት ግን ተችሏል፡፡

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ምን ሊያደርግ ይገባል?

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሊያደርግ የሚገባው፤አደርጋለሁ በማለት ሲያውጅ የነበረውን ብቻ ነው፡፡ በ2009 ፕሬዜዳንት ኦባማ ጋና: አክራን በጎበኙ ወቅት፤ ሲናገሩ እንዳሉት:-

ልማት ሁል ጊዜ የሚሳካው መልካም አስተዳደር ሲኖር ነው፡፡ ታሪክ ትክክለኛውን ውሳኔ ያቀርባል፡፡የራሳቸውን ሕዝቦች ውሳኔ ሚያከብሩ መንግስታት፤በጉልበትና ማንአለብኝነት የሚገዙ ሳይሆኑ በሕዝባዊ ይሁንታ የሚያስተዳድሩ፤የበለጠ ፍሬያማ፤ የተረጋጉ፤ከፈላጭ ቆራጭና በግፍ ከሚገዙ የበለጠ የተሳካላቸው ናቸው፡፡ የራሳቸውን ምቾትና የግል ሃብታቸውን በማሰቀደም ሃገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚበዘብዙ መሪዎች ሃገር ጨርሶ ለሃገራቸው ጠቀሚ ንብረት አያተርፉም፡፡ ማንም ቢሆን የሕግ የበላይነት ተረግጦ በሙስናና በዘረፋ በሚመራ ሃገር ውስጥ መኖርን አይመኝም፡፡ ይህ አይነቱ ስርአት ዴሞክራሲያዊ ሳይሆን የግፍና የመከራ አገዛዝ ነው፡፡ ያን የመሰለውን የግዛት ዘመን ጨርሶ ለመጣልና ለማስወገድ ወቅቱ አሁን ነው…….. በ21ኛው ክፍል ዘመን ችሎታ ያላቸው፤ ታማኝ የሆኑ፤ለተጠያቂነት የበቁ ኢንስቲቲዩሽኖች የስኬት ማረጋገጫዎች ናቸው—– ጠንካር ምክር ቤቶች፤የሲቪል ማሕበረሰብ አባላት፤ታማኝ የፖሊስ አባላትና የመከላከያ ሃይል፤ ነጣ ይፍትህ ስአት አባላት፤ነጣ የመገናኛ ብዙሃን፤ንቁ የሲቪል ማሕበረሰብ አባላት፤ እነዚህ ናቸው ለዶሞክራሲያዊነት ነፍስ ዘርተው የሚያገለግሉት ምክንያቱም በሕዝቡ የእለት ተእለት ኑሮ ውስጥ አስፈላጊዎቹ መዘውሮች፡፡ …ታሪክ ከነዚህ ጀግና አፍሪካውያን ጎን ይቆማል እንጂ በጉልበትና አላስፈላጊ በሆነ መንገድ ስልጣንን የሙጢኝ የሚሉትና ሕገ መንግስታቸውን ለራሳቸው እንዲሆን በዘፈቀደ ራሳቸውን በስልጣን ለማቆየት በሚለውጡትና በማያከብሩት ጎን አይኖርም፡፡ አፍሪካ ማን አለብን ባዮችንና በጉልበታቸው የሚመኩትን አትፈልግም፡፡ የምትፈልገው ጠንካራና ጉልበታም የሆኑ ድርጅቶች (ኢንስቲቲዩሽኖች) ነው፡፡ በተሻለ አስተዳደር እርግጠኛ ነኝ አፍሪካ ተጨባጭ የሆነ ሰፊ ልማትና የእድገት ራዕይዋን የማሳካት ተስፋዋ እውን ይሆናል፡፡

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ >> http://www.ethiopianreview.com/amharic/?author=57

ለሴራ ሊዮን ፍትሕ! ለኢትዮጵያስ?

Monday, May 7th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

t2ግፍ ጦረኛው ቻርልስ ቴይለር ወደ ወህኒ!

በአራት ዓመታት ውስጥ በ420 የፍርድ ሂደት፤ ቀናት: 115 ምስከሮች ተሰምተው፤ 50,000 ገጾች ያሉት ማስረጃ ተገናዝቦ፤ 1,520 መረጃ ኤግዚህቢቶች ከተመሳከሩ፤ በህውላ ለሴራ ሊዮን በተባበሩት መንግስታት በተቋቋመው ልዩ ችሎት በቀረበበት 11 ዝርዝር ክስ ቻርልስ ቴይለር: የግፍ ጦረኛውና የቀድሞው የላይቤርያ ፕሬዝደንት: ጥፋተኛ ተብሎ ተፈርዶበታል፡፡ በሰብዊ መብት ላይ ባደረሰው ወንጀል፤ ግድያ፤ አስገድዶ መድፈር፤ ሲቪል ማህበረሰቡን አካሉን በማጉደል፤እጅ በመቁረጥ፤ ሕጻናትን በጦር ሜዳ በማሰማራት፤ የፍትወት ባርነት በማካሄድ፤ ከኖቬምበር 30, 1966 እስከ ጃንዋሪ 18, 2002 በሴራ ሊዮን ሽብር በመንዛትና በማስፋፋት ወንጀል ቻርልስ ቴይለር ተበይኖበታል፡፡ በሴራ ሊዮኑ ግጭት 50,000 ዜጎች ለሞት ተዳርገዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ተናግሮል፡፡ ቴይለር በጭካኔ የተሞሉትን አረመኔዎች እነ ፎዲ ሳንኮህ: ሳም ‹‹ቢንቢው›› ቦካሪን: እና ኢሳ ሴሳይን በመርዳቱና በመደገፉ፤ እንደባርያ በቁፋሮው ላይ ተሰማርተው በሚያወጡት የአልማዝ ማዕድን ሽያጭ በሚከፈለው የደም አልማዝ ገንዘብ እቅድ በማውጣት፤ የጦር ስልት በመንደፍ፤ መሣርያ በመስጠት ላደረገው የግፍና የጥፋት ትብብር ነበር የስወነጀለው፡፡ ቴይለር በሚቀጥለው ወር ላይ የፍርድ የስራት ቅጣት ውሳኔው ይሰጠዋል፡፡

በካሳሾች የምስክር ሂደት ላይ በማስረጃ አቀራረብ ከሴ ራሊዮን የጭፍጨፋ ቡድን ጋር ቴይለር የነበረውን ግንኙነት በተመለከተ የነበሩት ማስረጃዎች ጥቂት በመሆናቸው ከሳሽ ችግር ነበረበት፡፡ በማንኛውም ወቅት በአመጽያኑ ግንባር መገኙትን በትክክል የሚያሳይ ምንም ማስረጃ አልነበረም፡፡ ቴይለር ወደሴራ ሊዮን የላካቸው የላይቤርያ ተዋጊዎች በሴራሊዮን ውጊያ አውድ ላይ ለመገኘታቸው ተጨባጭ ማስረጃ አልነበረም:: ከሳሾች ክሳቸውን ለማጠናከርና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ከቴሌፎንና ከሬዲዮ ግንኙነት የተጠለፉ ንግግሮችን፤በቴይለር የደህንነት ቡድን ውስጥ የነበሩት ስዎች ከሰጡት የቃል ማስረጃ እና ሌሎችም ቴይለር ወደ ሴራ ሊዮን መሣርያ ለመላኩ ማስረጃ የሆኑትን በማሰባሰብና ለዚህ ቴይለር (የደም) የአልማዝ ክፍያ እንደተደረገለት የሚያሰይ ተጨባጭ ማሰረጃ ነበር ያቀረቡት፡፡

“የማዘዙን ሃላፊነት” (command responsibility) በተመለከተ ቴይለር ክሱን አልተቀበለም:: ለሴራ ሊዮን የተሰየመው ልዩ ፍርድ ቤት የሚመራበት ደንብ አንቀፅ 6(3) ግን እንደሚከተለው ያዛል “የበላይ ሃላፊው በእዙ ስር ያሉት በሕግ የተከለከለን ወንጀል እንደሚፈጽሙ ድርጊቱን ካወቀ ወይም የሚያውቅበት ሁኔታ ካለ፤ይህንንም ድርጊት እንዳይፈጸም ካላደረገና ፈጣሚዎችንም እንዲቀጡ ካላደረገ፤ ተጠያቂነት: አለበት”ይላል:: ቴይለር የRUF አመጺአን ወንጀል እንደሚፈጽሙ ሰብአዊ መብትን እንደሚደፍሩ ቢያቅም ሙሉ ቁጥጥር እነሱ ላይ እንዳለው በቂ ማስረጃ አልነበረም:: ቴይለር ስለማንኛውም በሴራ ሊዮን ስለተፈጸመው ወንጀልም ሆነ ሰብዊ በደል ጨርሶ እንደማያውቅና ሃላፊነትም እንደማይወስድ ለችሎቱ አስታውቋል፡፡ እራሱን የሠላም መልዕክተኛ በማድረግ ለሰባት ወራት ለራሱ ምስክርነት ቆሞ ሲከራከር ነበር፡፡

የፍርዱ ሂደት ከወጪ አንጸር 250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስወጥቷል፡፡ ይህን ሁሉ ወጪስ ማውጣት ያስፈልግ ነበር? ፍትሕ የተቀመጠለት ዋጋ አለ እንዴ? ተመኑ ስንት ይሆን?

የአፍሪካውያን የጸረ ሰብአዊ መበት ስብስቦች መጠራቀሚያ ሰሌዳ

የዓለም አቀፉ የፍትህ ችሎት (ICC) አሁን በህይወት ላሉትና ላለፉትም የአፍሪካ አውሬ ጨቋኝና ግፈኛ ገዢዎችን ፍርድ ለማቅረብ ይጥራል፡፡ የኮት ዲ ቯሩ የቀድሞ ፕሬዜዳንት ላውረንት ባግቦ፤ የሱዳኑ ፕሬዜዳንት ኦማር አል በሺር፤ (ላለፉት ለሞአመር ጋዳፊ) የመያዣ ማዘዣ አውጥቷል፡፡ ጋብጎ ባስከተለው ግድያ፤አስገድዶ መድፈርእና ሌሎችም የግብረስጋ ግንኙነት ማስገደድ፤ያለፍርድ በመግደልና በሌሎችም የሰብአዊ ጥሰቶችና በምርጫው ወቅት ባስከተለው የሕዝብ እልቂት በዓለም አቀፉ የሄይግ ፍርድ ቤት ፍርዱን ሊቀበልና በቴይለር ወንበር ላይ ሊቀመጥ ግርግር በሌበት ሁኔታ ወደ ዓለም አቀፉ ፍርድቤት አምርቷል፡፡ አልበሽር በዓለም አቀፉ ፍርድቤት የ2009 ማዘዣ ሲሳለቅና ሲዘባበትባቸው፤ ‹‹ንገሯቸው፡፡ለሁሉም ንገሯቸው፤ለአቃቤ ሕጎቹ፤ለችሎቱ አባላት፤እና ለዚህ ፍርድ ቤት ደጋፊዎች በሙሉ ንገሯቸው፤ሁላችሁም ከጫማዬ ስር ናችሁ በሏቸው›› አለ:: (ጊዜው ሲደርስ ግን በሺር በዓለም አቀፉ ግርድ ቤት ጫማ ስር መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡) የተባበሩት መንግሥታት በበሺር አገዛዝ ወቅት 300,000 ሰዎች የገቡበት ጠፍቷል ብልዋል:: ከበሺር ጋር አዳብሎ የተባበሩት መንግሥታት በሌሎችም የሱዳን ዜጎች በእነ ጠበቃውና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ሃላፊው አህመድ ሃሩን፤ በዳርፉር ነጻ አውጪዎች ላይ ከበሺር ጋር የተባበረው የሚሊሺያ መሪ አሊ ኩህሻዬብ፤ ባህር ኢድሪስ አቡ ጋርዳ የነውጠኞች መሪና በሌሎች ሁለት ሱዳናውያን ላይ የመያዣ ትእዛዝ አውጥቷል፡፡

የዓለም አቀፉ የፍትህ ችሎት (ICC) በሰብአዊ ጥሰት በኬንያውያንም ላይ ክስ መስርቷል፡፡ የዝነኛው ኬንያዊ የነጻነት ታጋይና ነጻ አውጪ ጆሞ ኬንያታ ልጅ የገንዘብ ሚኒስትሩ ኡሁሩ ኬንያታ በ2008 በተካሄደው ምርጫ ወቅት በፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪዎቹ በራይላ ኦዲንጋና ሙዋይ ኪባኪ መሃል በተፈጠረው የምርጫ ግጭት ክስ ተመስርቶበት በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ማዘዣ እንደወጣበትና ለፍርድ እንደሚቀርብ ሲሰማ ሥራውን በፍቃዱ ለቋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ከዲሴምበር 2007 እስከ ፌብሪዋሪ 2008 ባለው ጊዜ በተፈጠረው የሳምንታት ግጭት ከ1,200 ሰዎች ያላነሱ እንደሞቱና፤ 600,000ሺ ሰዎች ደግሞ ተገድደው ተፈናቅለዋል፡፡ በዩጋንዳ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ የ‹‹ሎርድ ሬዚዝስታንስ አርሚ› ቁንጮ አመራር አባላት ላይ ጉደኛውን ጆሴፍ ኮኒይን እና ምክትሉን ቪንሰንት ኦቲና ሌሎች ሶስት ከፍተኛ የጦር አዘዦች ላይ ክስ መስርቷል፡፡ በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ የተለያዩ የአመጽ ተካፋዮች የኮንጎ ፖለቲከኞችና የጦር መሪዎች ወታደሮች፤ ቶማስ ሉባንጋን ዳዪሎን፤ ጄን-ፒየር ቤምባ ጎምቦ፤ቦስካ ኒታንጋዳ፤ማቲው ኡንጉዶሎ ቹ እና ሌሎች ሁለት አባላትም ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ በሙአመር ጋዳፊ ልጅ ሳይፍ አል-ኢስላም ላይ፤ በሊቢያው የስለላ መዋቅር ሃላፊው በዚህ ዓመት ማርች ላይ በሞሪታንያ በተያዘው አብዱላህ አል-ሴኑሲ ላይም የመያዣ ማዘዣ አውጥቶባቸዋል፡፡ ሊቢያውያን በሁለቱ ሰዎች ላይ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ወደ ሄይግ እንዲላኩ ያወጣውን ማዘዣ በመቃወም ሁለቱ ሰዎች በሃገራቸው እንዲዳኙ እንዲፈቅድ ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስም ምርመራም አልመሰረተም

በሱዳን፤በኬንያ፤በዩጋንዳ፤በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ፤ በሊቢያ እና በሌሎች አገሮች የሰብአዊ መብት ጣሾችን ወንጀለኞችን እያሰሰ ማዘዣ ሲያወጣባቸው የተባበሩት መንግስታት ሴኪዩሪቲ ካውንስል ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ችላ ብሏቸዋል፡፡ ሰብአዊ ጥሰትንና የጦር ወንጀለኛነትን ድርጊቱን በኢትዮጵያ በተመለከተ፤ በገሃድ የሚያመለክቱ በቂ ማስረጃዎች በዶኩሜንት ተካተው አሉ፡፡

በኢትዮጵያ በ2006 የተፈጸመውን እንዲያጣራ በመለስ ዜናዊ የተዋቀረው አጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ሪፖርት፤ በትንሹ ከሕግ ውጪ በሆነ መልኩ፤ባዶ እጃቸውን መብት ጥየቃ የወጡት 193 ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን፤763 ሰዎች መቁሰላቸውን፤ወደ 30,000 ሺህ የሚጠጉ በ2005 የምርጫ ወቅት ለእስራት መዳረጋቸውን አጣሪ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል፡፡ ኮሚሽኑ እንዲያጣራ የተፈቀደለት በጁን 8 2005 በአዲስ አበባ የነበረውን ሁኔታና እንዲሁም ከኖቬምበር 1 እስከ 10 2005 በሌሎች አካባቢዎች የነበረውን ሁኔታ ነበር የታዘዘው፡፡ አጣሪ ኮሚሽን በሌሎች አካባቢዎች ከሕግ ውጪ የተፈጸሙ ግድያዎችና የመቁሰል አደጋዎች እንዲሁም ለእስር መዳረግን በተመለከተ በቂ ማስረጃ ነበረውና ያ ከቀረበው ጋር ቢጣመር ኖሮ ቁጥሩን ከእጥፍ ባለፈ ባገዘፈው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ግድያ መቁሰል ለእስር መዳረግ የተፈጸመውም መለስ ዜናዊ ጦሩ፤የስለላ መዋቅሩ በራሱ የእዝ ሰንሰልት ስር መሆናቸውን በይፋ ለህዝብ ካሳወቀ በኋላ ነበር፡፡

አጣሪ ኮሚሽኑ እነዚህ ለሞት የተዳረጉት ሰላማዊ ሰዎች በሙሉ ከጦሩና ከስለላ አባላት በተተኮሰና ግንባራቸውንና ደረታቸውን በመመታት የሞቱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ኮሚሽኑ የሰለጠኑ የበቁ ነፍሰ ገዳይ ተኳሾች በጭፍን አነጣጣሪ ቅልጥም ሰባሪነታቸውን በማረጋገጥ ያገኙት ላይ ሁሉ ቃታ እየሳቡ አላስፈላጊ የሆነ ግድያ ፈጽመዋል፡፡ ኮሚሽኑቀ በተጨማሪም ኖቬምበር 3 2005 ሰቀቀናዊ የቃሊቲ ወህኒ ቤት ትርምስ ተነሰትዋል ተብሎ የጥበቃ አባላቱ 1,500 ጥይቶቻቸውን በ15 ደቂቃዎች ውስጥ አርከፍክፈው 17 እስረኛ ገድለው 53ቱን ቁስለኛ አድርገዋል፡፡ ኮሚሽኑ በመረመረው 16,990 ገጽ ማስረጃ ከ1,300 እማኞች ባገኘው ምስክርነት፤ ወራት በፈጀው ምርመራው ይህን እውነታ አረጋግጧል፡፡ በዚህም ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ 237 የፖሊስና የደህንነት አባላት በቀጥታ ተካፋይ እንደነበሩና በመጨረሻም ከነበሩበት ስራ ገለል መደረጋቸውን ኮሚሽኑ ማስረጃ አለ፡፡ በዚህ ተሳትፎ የነበሩት የፖሊስና የደህንነት አባላት ቢረጋገጡም በመለስ ዜናዊ ገዢ መንግስት አንዳቸውም በወንጀለኛነት አልተጠየቁም፤ አልተመረመሩም፤ አልተያዙም፤አልተከሰሱም ለፍርድም አልቀረቡም፡፡

በግድያው ተካፋይ የነበሩ አለያም ግድያውን በትዕዛዝ ያስፈጸሙ፤ ለፈጸሙት የጦር ወንጀል ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ ይህን ወንጀል የሚያውቁና ሊያውቁ የሚገባቸው ቁንጮ ወታደራዊና የሲቪል ባለስልጣኖች እርምጃ በላመውሰዳቸው በእዝ ተዋረድ ስልጣናቸው ሃላፊነቱ ሊለቃቸው አይችልም፡፡ ሂውማን ራይትስ ዋች ሲያብራራ: “በሶማልያ በሰፊው በአጠቃላይ በየመንደሩና በሃገሪቱ ላይ በተካሄደው የዘዴ ጭፍጨፋ ትእዛዝ የሰጡት የኢትዮጵያ ጦር አዘዦች በሲቪሉ ሕብረተሰብ ላይ ለተፈጸመው ግፍ፤ በጦር ወንጀለኛነት ሊጠየቁ ተገቢ ነው፡፡የሶማሌ ሪጂን ለተፈጸመው ስቃይ፤ አስገድዶ መድፈር፤በግዳጅ ማፈናቀል የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል ነውና የኢትዮጵያ መንግሥት ዋነኛው ሃለፊነት አጉዳይ ነውና ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ በነዚህ በተጠቀሱት አስከፊና ዘግናኝ ወነንጀሎች ማንም ሰው በወንጀለኝነት አልተጠየቀም፤በቁጥጥር ስር አልዋለም፤ክስ አልተመሰረተበትም፤ በመለስ መንግስትም ተጠያቂም አልሆነም፡፡

በ2010 ለተባበሩት መንግስታት ኮሚቴ ኤጌንስት ቶርቸር ሲያትት:

አስከፊ የስቃይ ሁኔታዎችንና ሌሎችንም አስከፊ ድርጊቶችን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚፈጸመው ሰብአዊነትን በሚያዋርድ ድርጊት ላይ አቤቱታ አቅርቦ ነበር፡፡ስቃይና ሰብአዊ ያልሆነ ድርጊት በኢትዮጵያ የጦር አባላት፤ ፖሊሶችና በደህንነት አባላት ይፈጸማል፡፡ የሽብርተኛነት ተጠርጠሪዎች፤ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና መንግስት በሚፈራቸው ሁሉ ላይ ከሰብአዊ ውጪ የሆነ መከራ ይፈራረቅባቸዋል፡፡በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙትን የስቃይ የመከራና የግፍ ተግባራትን የሚመሰክሩ ማስረጃዎች ሁማን ራይተስ ዎች ሰብስቦ ማስረጃዎችን አከማችቷል፡፡ በመንግስቱ የደህንነት አባልት የሚፈጸመው ግፍና ስቃይ በአዛዥ ፖሊስ አባላት፤ ከተራው አባል በጣም የረቀቀና የመረረ ነው፡፡በሁማን ራይትስ ዎች ዘገባ መሰረት ወታደራዊ የዕዝ ባለስልጣኖች በነዚህ ግፎች አፈጻጸም ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ማስረጃ አላቸው፡፡

የዓለም አቀፍ የፍትሕ ችሎት ወይስ የዓለም አቀፍ መድልዎ ችሎት?

ለሴራ ሊዮን የተቋቋመው ልዩ ፍርድ ቤት ታሪካዊና የሚደገፍ የሚሆንበት ምክንያት በሰው ልጆች ላይ ባደረሰው የመብት ጥሰትና የጦር ወንጀሎችን ለፍርድ ማቅረቡ ነው፡፡የሚደረስበትም ውሳኔ የአፍሪካን ቅንጡ ገዢዎች ከአረመኔያዊ ተግባራቸው የሚገታና የአፍሪካ የፈላጭ ቆራጭ ገዢዎችም ከተጠያቂነት ነጻ ነን ብለው ማሰብን ጊዜው ያለፈበት ተረት ተረት መሆኑን እንዲገነዘቡ የሚያደርግ እንደሚሆን አያጠያይቅም፡፡ በ2003 ቴይለርን ለፍርድ እንዲቀርብ ክስ የመሰረተበት ዴቪድ ክሬን በጥንቃቄ እንዳሰፈረው ‹‹ይህ በዓለም አካባቢ መሰማት የጀመረው ደወል እስከመጨረሻው ይህን ጣእመኛ ድምጹን ማሰማቱን አያቆምም፡፡ የሃገርህ መሪ ሆነህ የሃገርህን ሕዝብ የምትጨፈጭፍ ከሆነ፤ቀጣዩ በደወሉ ተጠሪው አንተ ነህ፡፡›› የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን የቴይለርን አመለካከት ‹‹ለዓለም ወንጀለኞች ፍትሕ አንድ ትልቅ መሰረት ነው፡፡ በዚህም ለዓለም ዙርያ ማንም ባለስልጣን ቢሆን ከእንግዲህ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ያሳስባል›› ሆኖም ግን የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤትና የተባበሩት መንግሥታት ሴኪውሪቲ ካውንስል በመድልዎ ለሚከናወን አሳፋሪ ድርጊት መዳረግ የለባቸውም፡፡ በሰብአዊ መብት ጥሰትና በሌሎችም ኢሰብአዊ ድርጊቶች በሱዳን፤ ኡጋንዳ.፤ በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ፤በኬንያ፤ፍትሕን እየሰፈኑና ያቂዎችን ለፍትህ እያቀረቡ በኢትዮጵያ በሚደረገውና እየተደረገም ባለው፤ ለእያንዳንዱ ወንጀል ተጨባጭ ማስረጃ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተጠናቅሮ መኖሩን እየሰሙ “ጆሯቸውን መድፈን፤ እያዩ አይናቸውን መጨፈን፣ስለሁኔታው ትንፍሸሽ ላለማለት አፍን መለጎም” ሌላውን ድርጊት ሁሉ የለበጣና ሚዛኑን የሳተ በገደዳው የሚዳኝ ያደርገዋል፡፡ የሰብአዊ መብት ጥሰትን ለረገጡና የጦር ወንጀል ለፈጸሙ የተለያየ የአመለካከት ደረጃ ሊወጣለት አይገባም፡፡ መመዘኛው የምት ጥሰት፤ ፍትህ አልባ ግድያ፤ አስገድዶ መድፈርና በግዳጅ ማፈናቀል ከመሆን ውጪ ሌላ መመዘኛ አልተቀመጠለትም፡፡ጥሩና መጥፎ ተብለው የሚፈረጁ የጦር ወንጀለኞችና የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀለኞች የሉም፡፡ ወንጀለኞች እንጂ፡፡የጦር ወንጀለኞችና የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀለኞች፤ ‹‹ሥብርተኞችን ለመዋጋት›› በሚለው ማስመሰያና ማጭበርበርያ ሕጋቸው ሊጫወቱብንና ሊያሳስቱን ጨርሶ አይችሉም፡፡ ይህን እንደመደበቂያ የሚጠቀሙበት እራሳቸው ሽብርተኞችና ሥብር ፈጣሪዎች ናቸውና፡፡ ለጦረኞችና ለግፈኞች የተዘጋጀ የጭካኔ ቁንጅና ውድድር የለም፡፡ ለሱዳን ኬንያ ኡጋንዳ ለዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ጥሩ ነው ተብሎ የተቀመጠውና ያገለገለው ድንጋጌ ለኢትዮጵያም ጥሩ ሆኖ ሊያገለግል ይገባል፡፡ ተጠናቅሮ ባለው ማስረጃና ዶኩሜንት መሰረት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ከተሰየመበት ከ2002 ጀምሮ በተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችና የሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች ሌላው ቢቀር ምርመራ እንዲካሄድ የማድረግ የአደራ፤የህግና ፤የሞራል ግዴታም አለበት፡፡

በእኢትዮያ የታሰሩ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ: http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

ይድረስ ለተከበረው ኢትዮጵያዊ ጀግና እስክንድር ነጋ!

Monday, April 30th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

አይበገሬው እስክንድር ነጋ!

በሜይ 1 2012 ኢትዮጵያዊው ግንባር ቀደም ጋዜጠኛና የፖለቲካ እስረኛ፤ የመጻፍ ነጻነት ተሟጋች አርበኛ፤ እስክንድር ነጋ፤ ከ1922 ጀምሮ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘውና ለነጻ ፕሬስጥብቅና በመቆምለ ዓለም የጽሁፍ ነጻነት ተነፋጊዎች በመሟገት ላይ ያለው ታዋቂው የአሜሪካ ፔን ፤ ድርጅት ጭቆናንና አፈናን አሻፈረን በማለት በግፈኛ ገዢዎች ወደ ወህኒ ለሚታፈኑ የሚሰጠው ታላቁ ሽልማት ለ እስክንድር ይሰጠዋል፡፡ ይህ ሽልማት፤ከበሬታ የሚሰጠው፤ በአልበገርነትና ለዲክታተሮች ግዛት እምቢ፤አሻፈረን በማለት ከታፈነ የማስመሰያ ነጻነትለእውነትና ለነጻነት በክብር በመቆም በአፋኞቹ ገዢዎች የሚጣለውን ማንኛቸውንም ግፍና መከራ ለመቀበል፤ እራሳቸውን መስዋእት ለማድረግ በቆራጥነት፤ ግፍና መከራውን ለመቀበልየቆሙትን ሃሳብን በነጻ የመግለጥ ተሟጋቾች የሚደፋ የክብር ሽላማት ነው፡፡

እስክንድር በግፍ አገዛዝ ሃገሪቱን ረግጠው በመግዛት ላይ ባሉት በነመለስ አስገዳጅ ባለስልጣኖች ለእስር በመዳረጉ ሽልማቱን በኒውዮርክ በግንባር በመገኘት ሊቀበለው አይችልም፡፡ ሽልመቱ እስክንድር ነጋ ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲና የነጻነት ጀግና መሁኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ከዚህም አልፎ እስክንድር ነጋ ሰብአዊ መብትን ዴሚክራሲን፤ነጻነትን ለሚያከብሩአፍሪካውያን ሁሉ ጀግናቸው ነው፡፡እስክንድር የጭቆና፤የግፈኛ ገዢዎች ጫና አልቀበልም! በማለት የቆመ የነጻነት አርማ ነው፡፡

‹‹ሽብርተኛ›› በመባል ሀጋሪቱን በመግዛት ላይ ባሉ ሽብርተኞች እስክንድር ለእስር ተዳርጓል፡፡ ያም ሆኖ በዓለም ላሉ በርካታ የፕሬስ ነጻነት ጀግኖች፤ ጀግና ነው፡፡ በቅርቡ በዓለም ዙርያ በጭቆናና በአፈና አገዛዝ ለእስራት ተዳርገው የነበሩና ሌሎችም እስክንድርነጋ በግፍ ከታፈነበት ወህኒ እንዲለቀቅ ሙግት ከከፈቱትና ለነጻነቱ ድምጻቸውን ካሰሙት መሃል

የዴይሊ አብዘርቨር (የላይቤርያ ቀደምት ነጻ ጋዜጣ) መስራች ኬነዝ ቤስት፤የሜክሲኮ ግንባር ቀደም ታዋቂና የተከበረች ጋዜጠኛና ደራሲ ሊዲያ ካቾ፤በጄኔራል ፒኖቺ የግፍአገዛዝ ዘመን የቺሊ መሪ ጋዜጣ አናሊሰስ ኤዲትርና በቺሊ ዩኒቨርሲቲ የጆርናሊዚም ፕሮፌሰር፤ በሌባነን የሜይ ቺዳክ ፋውንዴሽን መስራችና ፕሬዜዳንት፤ በቅርቡ ከተቃጣባትየፈንጂ አደጋ ከሞት ለጥቂት የተረፈችው ሜይ ቺዳክ፤በእንግሊዝ የተከበረው ጋዜጠኛና የሰንዴይ ታይምስ ጋዜጣ ኤዲትር ሰር ሃሮልድ ኢቫንስ፤የኢራን ግንባር ቀደም ጋዜጠኛአክባር ጋንጂ፤ የእስራኤል ታዋቂ ነጻ ጋዜጠኛና በጆርዳን የሚገኘው አማንኔት በዓለም የመጀመርያው ዓለም አቀፍ ሬዲዮጣቢያ መስራች ዳውድ ኩታብ፤ ጉዌን ሌስተር፤ዘናሚቢያን ተባለው የናምቢያ ነጻ ጋዜጣ ኤዲተር፤ሬይሞንድ ሉው የነጻው ፕሬስ አበው ተሟጋችና የደቡብ አፍሪካ ጽሁፍ ነጻነትና የጋዜጠኞች እንቅስቃሴ ነጻነት ተከራካሪየደቡብ አፍሪካ የፕሬስ ካውንስል ሊቀመንበር፤ ቬራን ማቲክ በሳይቤርያ የሬዲዮ ቢ92 ተባባሪ መስራችና በ1990 አድልዎና ወገናዊነት ያልነበረው ቀጥተኛ ዘገባ ስታቀርብየነረችው ዘጋቢ፤አዳም ሚቺንክ የፖላንድ ተወዳጅና ከፍተኛ የሽያጭ ቁጥር ያለው የፖላንድ ጋዜጣ ዋና ኤዲተር፤ፍሬድ ሜምቤ፤የ ዛማቢያ ፖስት ጋዜጣ ኤዲተር፤ኒዛር ናዩፍየሲሪያው ትሩዝ(ሃቅ) ጋዜጣ ኤዲተር፤ፓፕ ሳይን የሳዊት አል ዴሞክራሲ ኤዲተርና ለምእራብና ለመካከለኛው አፍሪካ የሬውተር ዘጋቢ፤የዘመናት የኢራን ኤዲተርና ጸሃፊበሻህም ሆነ በቅርቡም ለእስር ተዳርጎ የነበረው ናዲም ሰነር፤ በሕንድ አወዛጋቢ ጋዜጠኛ በመባለክ የሚታወቀውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚጽፈው የደይሊ ኢንዳያኑ አሩንሹሬ፤በፔሩ ኢንቬስትጌቲቭ ጋዜጠኛና ኤዲተር የእለታዊው ሲግሎ ቪየንቲኖ፤ እነዚህ የነጻው ፕሬስ ተሟጋች ነጻ ጋዜጠኞች ለፈላጭ ቆራጩና ግፈኛው ገዢ ለመለስዜናው፤የኢትዮጵያ ግፈኛና ይሉኝታ ቢስ ገዢ መንግስት እስክንድር ነጋን ያለወንጀሉና ሃጢአቱ እውነትን ይዞ ለእውነት ቆሞ ለሕዝብ ፍትህን ዴሞክራሲን ሰብዊ መብትንበመጠየቁ ብቻ ለእስር በማደረጉ ያላቸውን ውግዘት በማሳወቅ፤ በእስክንድርና በሌሎችም ሃዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን ጭፍንና ጊዜው እያለፈበት ያለውን የማን አለብኘነትአገዛዝ ድርጊት የሚቃወሙ መሆናቸውንና መንኛውም ዴሞክራሲያዊ መንግሽት በዜጎቹ ላይ እንዲህ አይነት ደባ እንደማይፈጽም አሳስበው ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡

በሴብቴምበር 2011 ዊሊያም ኢስተርሊ በኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የኤኮኖሚክስ ፕሮፌሰር፤ማርክ ሃምሪክ የዋሽንግተን ናሽናል ፕሬስ ክለብ ፕሬዜዳንት፤ የ ኒው ዮርክ ኦፕን ሶሳየቲፋውንዴሽን ፕሬዜዳንት አሬህ ኒየር፤ኬነዝ ሮዝ የሁማን ራይትስ ዎች ጋዜጠኞችን መብት ለማስጠበቅ ኮሚቴ ኤክሲኪዩቲቭ ዳይረክተር፤እስክንድር ከወህኒ እንዲወጣ የአሜሪካ መንግሥትጣልቃ እንዲገባና ሽብረተኝነትንምይህም ጨርሲ ተቀባይነት እንደሌለው እንዲያስታውቅ ጠይቀው፤ በእርዳታ መልክ ለዚህ ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ መንግስት የሚደረገውም የ600,000,000 ዶላር ችሮታም ለዚህ መለሰል ተግባር መዋል እንደሌለበት እንዲታወቅላቸው አሳስበዋል፡፡

እስክንድር ነጋን ያጀገነው ምንድን ነው?

በተረትና በባህላዊ ወጎች በርካታ የተለያዩ ጀግኖች አሉ፡፡አንዳንዶች በሚያጋጥማቸው አደጋ ወቅት በሚያሳዩት የሞራል ጥናካሬ ይጀግናሉ፤አንዳንዶች ደሞ ለክብራቸውን ለዓላማቸውበመቆማቸው ይጀግናሉ፡፡ እንዲሁም አንዳንዶች ጠላቶቻቸውን በፍልሚያው ሜዳ በመግደላቸው ድል በማሸነፋቸው ጀግና ይባላሉ፤ለፍቅር የተሰዉ ጀግኖችም አሉ፤ዘመናዊና ባህላዊ ጀግኖችም ይታያሉ፤ያልታወቀላቸውም ጀግኖች አሉ፤ደግሞም የድል አጥቢያ ጀግኖችም አሉ፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ ሁሉም የሚጋሩት አንድ ባህሪ አላቸው፡፡መስዋእትነት፤ታማኝነት፤ጥንካሬ፤ቆራጥነት፤ እርግጠኛነት፤ ያለማወላወል እና ሌሎችም ሁኔታዎች፡፡

ከዚህ ሁሉ በተለየ አካሆን ግን እስክንድር ጀግና ነው! እስክንድር እውነትንና ሃሳቦችን ብቻ በመያዝ የሚዋጋ ጀግና ነው፡፡መነሻው ሃሳብ መድረሻው ሃቅ ነው፡፡ መቀላመድን በእውነት ሰይፍ ያነበረክካል፡፡መሰረተ ቢስና መደለያ ማታለያ የሆኑ ሀሳቦችን በሚቻል፤በሚታመን፤ትክክለኛና ሕዝባዊ በሆነ ሃሳብ ይረታዋል፡፡ብእር ብቻ የጨበጠው እስክንድር ነጋ የሚዋጋው በብእሩ ነው፡፡ ጥርጣሬን የሚዋጋው በመታመን፤ጭካኔን በርህራሄና በችሮታ፤ መሃይምነትን በዕውቀት: ጠባብ አስተሳሰብን በትእግስት: ቁጣን በምክንያታዊነት፤ጭቆናን በጥንካሬ ብልግናን በረጋ አንደበት ያሸንፋል፡፡ያንን የጨካኝና የሰው በላ አውሬ መሰል ፊቱን ፊት ለፊት እያየ ለስምንተኛ ጊዜ ልትይዙኝ ልታስሩኝ ትችላላችሁ፤በተዘጋና ብቸኛ በሆነ ጉረኗችሁ ውስጥ ልታስገቡኝ ትችላላችሁ፤ ልትደበድቡኝ ግፍና መከራ ልታደርሱብኝ ልታሰቃዩኝ ትችላላችሁ፤መድረሻ ልታዋክቡኝ ለሃሰት ፍርድም ልታቀርቡኝ ልትወነጅሉኝ ትችላላችሁ፤ በዚያ በስቃይ በታጠረና የግፍ አምባ በሆነው ወህኒያችሁ ያለምግብ ያለህክምና ያለምንም የቤተሰብ ግንኙነት፤ልታፍኑኝ ትችላላችሁ፡፡ ስሜን ለማጥፋት ክብሬን ለማዋረድእኔነቴን ለማጉደፍ፤ ከኔም አልፋችሁ ባለቤቴን ልታስሩ ቤተሰቤን ልታሰቃዩ ትችላላችሁ፡፡ልጄንና ሚስቴን በማዋካብ ኑሮ የገሃነም ያህል እንዱሆንባቸው ማድረግ አያቅታችሁም አውቃለሁ፡፡ያሻችሁን አድርጉ፤የፈላጋችሁትን ፈጽሙ፤ እስኪበቃችሁ በኔና በቤተሰቤ ላይ የግፍና የመከራ ጫና አውርዱብን እንጂ ሕይወቴ እሳከለችና መተንፈስ እስከቻልኩ ድረስይህን የናንተን የጭቆና የግፍ አገዛዝ ተቀብዬ አልኖርም፡፡ ጭካኔያችሁን፤አውሬነታችሁን፤ግፋችሁንማ ጨርሶ ለመቀበል ቀርቶ ላበውም አልሞክርምና እሱን መዋጋት ብቻ ነው ፍላጎቴ: በማለት የሞገተና በጽናት ቆሞ አልበገርም የዕጣ ፈንታዬ ወሳኝ የመንፈሴ አዘዥ እኔ እስክድር ናጋ ነኝ: ያለ ኢትዮጵየዊ ጀግና ነው::

እስክንድር ነጋ፤ የወቅቶች ሁሉ ጀግና

እስክንድር ወኔው የሞላ ነው፡፡ ከሰባት ወራት በፊት ‹‹በፖሊስ ኮሚሽነሩ‹‹ ታዛዦች ተይዞ ወደ ኮሚሽነሩ ቢሮ በመውሰድ በኮሚሽነሩ ግፋዊ አፍ ዝም እንዲል ካልሆነ ደሞ ለእስርእንደሚዳረግ ና በኢንተርኔት ላይ የሰፈራቸው ጽሁፎቹና በተለያየ ወቅት ለተለያዩ መገናኛዎች የሰጣቸው ቃለ መጠይቆች እሳት ጫሪ ናቸው፡፡ ጄኔራል ጻድቃን ጡሩን ይጫናል ብለህ ጽፈሃል፡፡ በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁን ኢህአዴግ ሕገ መንግስቱን ለመጠበቅ ብቃት አለው፡፡አንድ ነገር ቢፈጠር የመጀመርያው ተጠያቂ አንተ ነህና እንመጣብሃለን አለው፡፡እስክንድርም እና መጻፌንና ቃለ መጠይቅ መስጠቴን እንዳቆም ነው የምትነግረኝ? ላለው ሲመልስለት አይደለም አለውና በመቀጠል ግን ኮሚሽነሩ፤ ክልሉን ማለፍህን ነገረንሃልናጥንቃቄ ልታደርግ ይገባል አንተን ለመወንጀል በጃችን በቂ ማስረጃ አለን በማለት የከረረ ማስጠንቀቂያም ማስፈራሪያም ሰነዘረ፡፡ እስክንድር ገን መጻፉን ቀጠለና የፖሊሱ ኮሚሽነር ጋር የነበረውን ቆይታ ሁሉ ያላንዳች ፍራቻ ለሕዝብ አቀረበው፡፡በዚህም አላበቃም እስከመጨረሻው እለት ድረስ ሕጸን ልጁን ከት/ቤት ለመውስድ በመጠበቅ ላይ እንዳለ ያዙት፡፡ ያ ሕጻንም የአባቱን በፖሊስ መያዝ ሲያይ ‹‹አባዬ›› ብሎ ሲጮህ ስቃይን መፈጸምና በውጤቱ መደሰት መሳቅ መንፈቅፈቅ የቀን ተቀን ተግባራቸው የሆነው ለግፈኞች እርካታና ለግዛት ማረዘሚያነት የተሰማሩት ፖሊሶችም በሕጻኑ የድንጋጤ ጩኸት ሳቁ! አሁን እስክንድር ፍርድ በሌለበትና ሳይፈረድበት ወንጀለኛ ተብሎ ውሳኔ ተላልፎበት በባዶ ችሎት ባላጠፋው ጥፋት ባልሰራው ድርጊት፤ በማያምንበት ደባ አሁንም ፍርድ እየጠበቀ ነው፡፡

እስክንድር የሃቅ ሰው ነው፡፡ በሴብቴምበር 2010 መለስ ወደ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በድፍረት ብቅ ባለበትና ሹልክ ብሎ በገባባት ጊዜ አስክንድርና የጋዤጠኝነት ሙያ አቻውየሆነችው ጋዜጠኛ ባለቤቱ ሠርክ ዓለም ፋሲል ለኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ሲ. ቦሊንጀር የመለስን ገደብ የለሽየ ጭካኔና የግፍ አገዛዝ የሚያስረዳ ደብዳቤ ጽፈው ነበር፡፡

እኛ በክህደት ተፈርጀንና ተወንጅለን የታገድን ጋዜጠኞች ነን፡፡መለስ ዜናዊ በተደጋጋሚ በሚያካሂደው የምርጫ ረገጣና ማጭበርበር፤ሳይፈረድብን፤ ትህን ተነፍገን፤ ባዶችሎት ቀርበን ከ16 ወራት በኋላ የተለቀቅን ነን፡፡በዚሁ ወህኒ ቤት ሠርክ ዓለም ፋሲል ካለወቅቷ ለመውለድ ተዳርጋለች እንክብካቤም ተነፍጓታል፡፡

ሕጻኑ ሲወለድ የሰርክዓለም የወህኒ ቤት ሁኔታ በፈጠረው እንግልትና ስቃይ ኪሎዋ እጅጉን ያነሰበት በመሆኑ ይህች ሕጻን በአፍሪካ ካሉት ወህኒ ቤቶች ሁሉ ዝቅተኛ በሆነው ቃሊቲ በዚህ ሁኔታ ለተወለደ ህጸን ህይወቱን ለማቆየት ያለው መፍትሄ የማቆያ ሙቀት(ኢነኩቤተር) መሆኑን ቢያሳውቁም በወህኒ ቤቱ ባለስልጣኖች ተቀባይነትሳያገኝ ቀረ፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ በተአምር ሕጻኑ ጤናማ ሆነ አደገ፡፡….ምንም እንኳን ሃሳቡን የመግለጽ መብቱን ብናከብርም በአገዛዙ የግፍ ቀንበር ስር በመማቀቅላይ ያሉትን ነጻና አንዳችም ወንጀል ያልፈጸሙ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ግፍና በደል ከግምት በማስገባት ይህን መሰሉን ገዢ መንግስት በበላይነት የሚመራውመለስ በዚህ የተከበረ የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ እንኳን መገኘት ስለሚያረክሰው ይህ ሊታሰብበት ተገቢ ነው፡፡

እስክንድር አዛኝና ርህራሄ የተላበሰ ሰው ነው፡፡በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ የሆነችው ብርቱካን ሚዴቅሳ ከታፈነችበት ወህኒ ቤት ስትለቀቅ እስክንድር አነጋግሯት ነበር፡፡ ‹‹ጀግናችን ስለሆንሽ እንኮራብሻለን›› አለኳት! በፊቷ ላይ የቆሰለ ስሜት ታየኝ በውስጧ አንድ የተፋነ ነገር እንዳለና ፈንድቶ ለመውጣት ሲታገላት እንደነበር ያስታውቃል:: ግላው የወዳጅነት ውይይ ት ለማድረግ ሁኔታው አመቺ አልነበረም፡፡ በርካታ ሰዎች ነበሩ፡፡ስለዚህም ተናግሬ ስጨርስ ከዓይን ግንኙነት እንደሸሸች አይነት አንገ ቷን ቀለስ አድርጋ መሬት ላይ አይኖቿን መሬቱ ላይ ተክላ እራሷን በአሉታ ነቀነቀች፡፡ከዚያም እጅግ በለሰለሰ ድምጽ ‹‹አመሰግናለሁ›› አለች፡፡ የተናገርኩት መልሶ ኮረኮረኝ አባባሌ ለማባበልና ብርታት ለመስጠት መስሎ ተሰምቷት ቢሆንም እኔ ግን ከምሬ ነበር ያልኩት፡፡ ለብርቱካን አሁን የሚያስፈልጋት ግን ይሄ አልነበረም በሕይወቷ ካጋጠማት ሁሉ መራራውን ወቅት ያሳለፈች አንዲት ሴት አጠገብ ነበር ያለሁት፤ በውጧ ምሬት ያቋተባት ሴት፡፡ባይሳካላቸውም እድሜያቸውን የገፉና የማይጠግቡት የስልጣን ረሃብ በየእለቱ ግፍ የሚያሰራቸውና ሁሉንም እስካሁን ባይሳካላቸውም ተስፋ ለማስቆረጥ የሚታክቱ ጨካኝና አረመኔ ገዢዎች ለመከራ መዳረግን ሙያቸውን መሳርያቸው ያደረጉ ሰዎች ያደረሱባት ጫና ያብሰለስላታል፡፡አሁን ደግሞ እስክንድር በመለስ የመከራና የግፍ ወህኒ ቤት የብርቱካንን ቦታ ይዟል፡፡

እስክንድር ባህሉንና ከበሬታን የሚያውቅ ሰው ነው፡፡ ‹‹ አቡነ›› ፓውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ‹‹ጳጳስ›› ገና በህይወት እያሉ ግዙፍ የሆነውን ሃውልታቸውን የጵጵስና 18ኛ ዓመታቸውን ሲያከብሩ ባስተከሉበት ወቅት፤ እስክንድር አንድ ጥያቄ አነሳ፡፡

ሃውልት ማቆም በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጨርሶ የተወገዘ ነው ምክንያቱም ያንን ማድረግ ማለት፤ ሰብአዊ ፍጡርን ከቅዱስ መንፈስ አግዝፎ ማሳየት ስለሚሆን መደረግ የለበትም፡፡በኢትዮጵያ ረጂም ታሪክ ያለው የኦርቶዶክስ ቅዱስ መጽሃፍ ከሰብአዊ ፍጡሮች ይልቅ መንፈሳዊ መለኮቶችን አግዝፎ ማሳየት እንደለብን አበክሮ ያስተምራል፡፡ ስለዚህም ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ ላመጡት አቡነ ሠላማ እንኳን ሃውልት አልቆመላቸውም፡፡ ለቤተክህነት ዜማዎችን ላፈለቀው ቅዱስ ያሬድ፤በላስታ እነዚያን የድንጋይ ፍልፍል ቤተክርስቲያናትን ላበረከተው ላሊበላ፤ለኢትዮጵያዊው ታላቅ ቅዱስ ለአቡነ ተክለሃይሞነትም ቢሆን ሃውልት አልቆመላቸውምና ለምን አሁን የኢትዮጵያን የኦርቶዶክስ እምት በሚያጎድፈና በሚያንኳስስ መልኩ ሃውልት ይቆማል፤ ለምንስ የኦርቶዶክስ ባህል ይደፈራል?

እስክንድር በኢትዮጵያ ለግፍና መከራ ለስቃይ ለተዳረጉት ሁሉ ምስክር ነው::

ጭቆናው ይቅርታን የማያውቅ በየዕለቱ እየበዛ የሚሄድ ነው፡፡የምግብ ዋጋና የገንዘቡ አቅም ተዳክሞ የሚሰጠው የግዢ ዋጋ ከሃምሳ በታች ወርዷል፡፡ሥራ አጥነትም ከመቀነስ ይልቅ ፍጥነቱ በመጨመሩ ላይ ነው፡፡ አነስተኛ ስራዎች የሃገሪቱ የጀርባ አጥንት ቢሆንም ውጤት ከማምጣት ይልቅ ለመከራና ለመሸማቀቅ ደርሰዋል፡፡በገዢው ፓርቲ መንደር ጭንቀትና ፍርሃት፤ መርበድበድና ውጥረት ነግሷል፡፡

እስክንድር የተስፋ ድምጽ ነው

……. አመጽን ለማነሳሳት የሚያበቃ ተስፋ እንጂ ጭቆናን የሚሰንቅ አይደለም፡፡ ግብጾችና ሊቢያናውያን ለዘመናት ካጋጠማቸው መከራ የባሰ አጋጥሟቸው አይደለም በ2011 ለአመጽ የተነሳሱት፡፡ ጥቂቶች የበለጠ የነጻነት ሕይወትን ተመኙና ከጫንቃቸው ላይ ግፈኛውን አገዛዝ ከመሰረቱ ነቅለው ለመጣል ግንባር ቀደም ሚና ተጫወቱ፡፡ለዚህ ደሞ የቱኒዚያው ሁኔታ በአካባቢው ሁሉንም ነገር ለወጠው፡፡ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተረጋገጠ…..በሰብ ሰሃራ ሀገሮች ተስፋ ፈነጠቀና የተረፉትም የአካባቢው ግፈኛ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ሊወገዱ እንደሚችሉ የተስፋ ፍንጭ ታየ፡፡የአረቦች መነሳሳት ተስፋ በየበሩ ማነኳኳት ያዘ፡፡በሩን ከፍቶ ለመግባትም ለረጂም ጊዜ አይጠበቅም፡፡ ማንኛው የሰብሰሃራን ፈላጭ ቆራጭ እንደሚገነደስ ማንም አያውቅም፡፡ ሆኖም ግን አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡አንድ ጊዜ መዛመት ጀምሯልና ማንም ሊያግደው አይችልም፡፡ሙባረክ የአረብ ሃገራት ታላቁ ፈላጭ ቆራጭና ለዘመናትም ቀጥቅጦ የገዛው ግንድ መገንደስ ለሌሎች የአረብ ሃገራት የወርቅ ስጦታ እንደሆነው ሁሉ፤ኢትዮጵያም በሰብሰሃራ ትልቁ ግፈኛ ፈላጭ ቆራጭ መገንደስም ለአፍሪካ ሃገራት ሁሉ መነሳሳትና በቃ ማለት የወርቅ ስጦታ ይሆናቸዋል፡፡ ያለ ግብጽ የአረብ ሃገራት ማመጽ አይኖርም ነበር፡፡ ከኢትዮጵያም ውጪ የአፍሪካ የጭቆና በቃኝ መነሳሳት አይታሰብም፡፡

መልዕክተ እስክንድር

የአፍሪካን አህጉር ትልቁን ፈላጭ ቆራጭ ጨካኝ መንግስት በመምራት ላይ ያለው መለስ ዜናዊ ጋዳፊ ከውድቀት ቀድሞ ያደርግ እንደነበረው ብለው ብዙዎች እንደሚገምቱት ሳይሆን አስቀድሞ በጥንቃቄ ሊስብበት ተገቢ ነው፡፡ግድያ ሊቢያናውያንን እንዳስቆጣና እንዳስነሳ ፤ከነሱ በፊትም ቱኒሲያኖችንና ግብጾችን እንዳስቆጣ፤ሊያስከትል የሚችለው መራር ሁኔታ ነው፡፡ ባልተጠበቀ ሁኔታ በድንገት ወጣቱ ለሞት ያለውን ፍርሃት እርግፍ አድርጎ ጣለ፡፡ ሞትን ረሳ፡፡ጋዳፊ በእጽ የደነዘዙ ብቻ ናቸው ሞትን የሚደፍሩት ያለውን በተግርባር በማስተባበል ከፊታቸው የሚታያቸው ተስፋ አመጹን እንዲያቀጣጥሉና ለድል እንዲበቁ አደረጋቸው፡፡

ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ገዢዎችን የሚያሸንፋቸው ተስፋ ብቻ ነው፡ በኢትዮጵያ ተስፋ እንዲያብብ ተስፋ እንሰንቅ::

ምነው ችሎታውና መራቀቁ፤ ብቃቱና የቅኔው ችሎታ በኖረኝና ለእስክንድር ነጋ በውስጤ ታምቆ ያለውን አክብሮት መግለጽ በቻልኩ፤: እስክንድር ነጋ ለዚህ በ2012ቱ ፔን/ ባርባራ ጎልድ ሰሚዝ የጽሁፍ ነጣነት ሽልማት በመብቃቱ ከፍተኛ ደስታዬን ባክብሮት ላስታውቀው እፈልጋለሁ:: ለዚሁም በ1875 ዊሊያም አርነስት ሄኔሊ በጻፈው‹‹ አይበገሬ›› (Invictus) በሚለው ግጥም አክብሮቴን ልግለጽለት፡፡ ይህ ግጥም ነበር የኔልሰን ማንዴላን ተስፋ በአፓርታይድ ወህኒ ቤት ሲያለመልም የነበረው፡፡ አሱ ማለት እኮ ፍጹም የሆነ ተስፋና ጥንካሬ ያለው፤የእያንዳንዱን ሰብአዊ ፍጡር ውስጣዊ የነጻት ስሜት የሚወክል ተስፋ የሰነቀ ነው፡፡

‹‹ጥንካሬ ከጡንቸኝነት የሚገኝ አይደለም፤ ከጠንካራ መንፈስና ልቦና እንጂ›› ጋንዲ

ለእስክንድር ነጋ ነጻነቱ ይመለስለት!
ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮች ለማግኘት እዚህ ይጫኑ

ፍጥረታዊ ፍትሕ ወይስ ዘረኛ ፍርደገምድልነት?

Monday, April 23rd, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ተበዳዩን እንደ ወንጀለኛ!

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የመርገጫ ማህተም የሆነውን ፓርላማ ግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ መለስ ዜናዊ ተገደው ከደቡብ ኢትዮጵያ ‹‹የተፈናቀሉትን›› የአማራዎች (አንዳንዶች‹‹በተንኮል ዘዴ ዘር ማጥፋት›› ብለውታል) በተመለከተ፤ በጉዳዩ ላይ ተቃውሞ ያሰሙትንና ፤ ዜናውን እንዲሰራጭ ያደረጉትን፤ በደፈናው ሃላፊነት የሌላቸው በማለት በማዉገዝና እውነቱን ሸምጥጦ በመካድ ጨርሶ መፈናቀል እንዳልተካሄደ ለማሳመን ሲፈላሰፍ ታይቷል፡፡ መለስ ስለመፈናቀሉ ማሳሳቻውን ማስረጃ ሲያቀርብ አንዳችም መፈናቀል ያልተካሄደ በማስመሰል አንዳንድ ሕገወጥ ከሰሜን ጎጃም የፈለሱ (‹‹ሰፋሪዎች›› ይላቸዋል) ከደቡብ መኖርያቸው የተነሱበት ምክንያት ቦታው የአካባቢ ደንና ፊጥረታዊ ሃብት ጥበቃ ነው ሲል ሊሞግት ሞክሯል፡፡ እንዲያውም ለምን ያሉትንና የጋራነት መታወቂያችን ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት የቆሙትን ድርጅቶች በተመለከተ፤ መለስ በጠራራ ጸሃይ ሲሰብክ:

….. ባለፉት አሰርት ዓመታት በታሪክ አጋጣሚ፤በርካታ ሰዎች፤… ወደ ሰላሳ ሺህ የሚጠጉ ሰፋሪዎች፤ ከሰሜን ጎጃም (የፈለሱ) በቤንጅ ማጂ ዞን (በደቡብ ኢትዮጵያ)ሰፍረዋል፡፡ በጉራ ፈርዳ 24.000 ሰፋሪዎች አሉ፡፡ ቦታው ጫካማ ስለሆነ ብዙ ሰው አይኖርበትም፡፡በተለያየ ሰበብና አጋጣሚ ሁሉም የድርሻውን ያገኛል የሚጎዳ አይኖርም፡፡እነዚህ ህገወጥ ሰፋሪዎች ባልተቀናጀ መልኩ ነው የሰፈሩት፡፡ እነዚህ ህገ ወጥ ሰፋሪዎች በተናጠልና በተመሰቃቀለ መንገድ፤ የአካባቢውንም የዓየር ሁኔታ በሚበክል መልኩነው የሰፈሩት፡፡ይህ ደሞ አጥፊና ጎጂ ነው፡፡

ሰፈራው የአካባቢውን ዓየር ሁኔታ ባገናዘበ፤ የጫካውን መጥፋት ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ታስቦ የተከናወነ አይደለም፡፡ድንግል የሆነው ጫካ መጠበቅ አለበት፡፡ሰፋሪዎቹበቀላሉ ሊለማ የሚችልና አፍሪ ቦታ ነው የፈለጉት፡፡ደን ሆነ አልሆነ ደንታ የላቸውም፡፡ደኑን እየጨፈጨፉ ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ከሰል ያከስላሉ፡፡ በዚህ የተነሳም በርካታየአካባቢ ብክለትና ጉዳት ተፈጽሟል፡፡…… ሰፋሪዎች ወደፈለጉበት ቦታ ሄደው በመስፈር የአካባቢውን ደን በማጥፋት መኖር አይችሉም፡፡ሕገ ወጥ በመሆኑ ሊቆምይገባዋል፡፡ ይህን እውነታ ለማጭበርበር የሚጥሩ ሁሉ ሃላፊነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ ዕውነትን አጥርቶ ማየት ያስፈልጋል፡፡የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብት በእኩል ደረጃሊጠበቅ ይገባል፡፡ አማሮች ተፈናቀሉ ለስደት ተዳረጉ በማለት የሚጮሁት ማንንም የማይጠቅም ቅስቀሳ ነው በማድረግ ላይ ያሉት፡………..

መለስ በቀላሉ ሲያስቀምጠው፤ እነዚህ ‹‹የሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› የአካባቢውን የደን ሁኔታ ያጠፉ ወንጀለኞች ናቸውና ተገደው መነቀልና መሰደድ አለባቸው፤ እንዲያውም በወንጀል ባለመጠየቃቸው እድላቸውን ሊያመሰግኑ ይገባል፡፡

የአፍሪካ የከባቢ ዓየር ዋና ሹም

ስለአካባቢ ዓየር ሲነሳ በአፍሪካ ካሉት ከማንኛቸውም በበለጠ እውቀትና ችሎታ ያለው ሰው ቢፈለግ ከመለስ ሌላ ጨርሶ የት ሊገኝ?! ምንስ ቢሆን የአፍሪካ ዋና የከባቢ ዓየር መኮንን ተብሎ የለም እንዴ! በ2009 መለስ በኮፕንሃገን በተካሄደው ስብሰባ ላይ የአፍሪካዊያንን ተደራዳሪዎች በመምራት ተገኝቶ ነበር፡፡ በዚህ ቦታ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች መገኘት መንስኤውም፤የምእራቡ ዓለም እያጠፋና እያዛባ ያለውን የተፈጥሮ ዓየር፤ ደግሞም የተከተለውን የአየር ለውጥ፤በዓለም የሙቀት ሁኔታው መባባስን፤እና ሌላውንም በተመለከተ የሞራል ካሳና የገነዘብ መቀጫ ለመጠየቅ ነበር ዘራፍ ብሎ የተነሳው፡፡ በዚህም 40 ቢሊዮን ዶላር ካልተፋ ስብሰባውን እንደሚያጨናግፈው ረግጦ እንደሚወጣ ደንፍቶ ነበር፡፡

እኛ በአናሳው የምናቀርበው ስምምነት ተቀባይነት ካጣ፤ ቁጥራችንን በመጠቀም ውሳኔው ውድቅ እንዲሆን እናደርጋለን…….እንዲያውም አካሄዳቸውና ውሳኔያቸውአህጉራችንን አስገድዶ የሚዳፈር ከሆነ ስብሰባውን ረግጠን እንወጣለን፡፡……..ከዚህ ቀደም ይደረግ እንደነበረው የአፍሪካ ፍላጎትና አቋም ሊታፈን አይችልም አይገባምም፡፡……. አፍሪካ፤የአፍሪካ ሕብረት አባላትን ሀገራት የሚወክልና ሙሉ ስልጣን ያለው አንድ ብቸኛ ተደራዳሪ ቡድን ትሰይማለች፤…. ለኔ ዋነኛው ቁልፍ ጉዳይ፤አፍሪካ የዓለምን አየር መዛባት አስመልክቶ በተፈጠረው ጉዳት ልትካስ ተገቢ ነው፡፡ በርካታ ኢኒስቲቲዩሽኖች ይህን በቁጥር ለማስቀመጥ ሞክረው የተለያየ ተመን አስቀምጠዋል፡፡ከዚህ በመነሳትም ማእከላዊው ቀመር በዓመት 40 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል፡፡

ስብሰባው በተጀመረ በማግስቱ ፤ መለስ ከ‹‹አፍሪካ አስገድዶ ደፋሪዎች›› ጋር በ10 ቢሊዮን ዶላር ውለታ ለመፈጸም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ሆነ፡፡ አፍሪካውያን ወንድሞቹንም ጥሬ ብር ከአርቲ ቡርቲ ቃላት ይሻላል በማለት አሳመነ፡፡

……እርግጥ ይሄ የኔ ሃሳብ ምናልባትም ከሕግ አኳያ ለደረሰብን በደልና ጥፋት፤ በልማታችን ላይ ለደረሰብን በደል ሙሉ ካሳ ይገባናል በማለት ሃሳብ ያቀረቡትንአፍሪካውያንን ቅር ሊያሰኝ ይችላል፡፡ የኔ ሃሳብ ቀስ በቀስ ወደ ተነሳንበት ቁጥር ያደርሰናል፡፡ ይህን ፈንድ መቆጣጠርና በዚህም የአስተዳደር ስልጣን ማግኘትና በወሳኝነት መቀመጥ ዋነኛ መሳርያችንና አስተማማኝ የፋይናነስ ፍሰት ማግኛችን ነው፡፡

በኦክቶበር 2011 መለስ በአፍሪካ ኤኮኖሚ ኮንፍራንስ ላይ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር፡-

……..በአህጉራችን ያለው መሬት፤ከመሬቱ መሳሳትና ከማለቁ የተነሳ ዛፎቹ ሁሉ ወድመዋል፤በአፈሩ መሸርሸር፤ለድርቅና ለጎርፍ፤በዓለም ላይ በመከሰት ላይ ባለው የዓየርመዛባት ሳቢያም ከዚህ ቀደም ታይቶ ወደማይታወቅ የጎርፍና የድርቅ ሁኔታ ተዳርገናል፡፡የአርሻዎቻችን መሰረትም እጅጉን አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡

ስለዚህም በመለስ አተማመን ወደ አውሮፓውያን አስገድዶ ደፋሪዎቻችን በመመለስ በድጋሚ ተጨማሪ የገንዘብ ካሳ ማግኘት ይኖርብናል፡፡

በኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊ ፍጥረታዊ ተሰጥኦዎችi ተንከባካቢነት

በአፍሪካ የዓየር ለውጥና የዓለምን የሙቀት ሁኔታ በተመለከተ መለስ ዜናዊ አዋቂ የሚል የለበጣ ስያሜ አግኝቷል፡፡ ይሁንና ግን በኢትዮጵያ ውስጥ በመካ ሄድ ላይ ስለአለው የአካባቢ ብክለት፤በተለይም በኢትዮጵያ የደኖችን መጨፍጨፍና መጥፋት በተመለከተ ግንዛቤ አለውን? የኢትዮጵያ የእርሻ ምርምር ኢኒስቲቲዩት (በሃገሪቱ ያለው ግንባር ቀደም የእርሻ ኢኒስቲቲዩት) ዘገባ እንደሚያመላክተው በ2020 ኢትዮጵያ ጠቅላላ ደኖቿን ታጣለች ብሏል፡፡

ባለፈው የምዕተ ዓመት ለውጥ ላይ የኢትዮጵያ ደን 40 በመቶ ነበር፡፡ በወታደራዊው አገዛዝ ዘመን በ1987 ላይ ወደ 5.5 በመቶ አዘቀዘቀ፡፡ በ2003 ወደ 0.2 ወረደ፡፡የትዮጵያ የእርሻ ምርምር ኢኒስቲቲዩት ኢትዮጵያ በየዓመቱ 200.000 ሄክታር ደን እንደምታጣ ይናገራል፡፡ በ1990 እና በ2005 መሃል ኢትዮጵያ 14.0 በመቶ የደን ሽፋኗን አጥታለች፡፡(2.114.00 ሄክታር) በተጨማሪም 3.6 ከመቶ የዛፍ ተክሎችን አጥተናል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በመጪው 11 ዓመታት ኢትዮጵያ በ2020 ደን አልባ ሃገር ወደመሆኑ ትሸጋገራለች፡፡

በ 2004 የተደረገ ጥናት እንደሚያስረዳው፤ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ሄክታር መሬቷ በደን በቀል ዛፎች የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 7 በመቶው የደን እርሻ ነው፡፡63 በመቶ ገደማው ጫካማው ቦታ ደሞ በኦሮሚያ ክልል ያለ ሲሆን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ደግሞ በ19 በመቶ ተከታይ ሲሆን፤ጋምቤላ 9 በመቶውን ያካትታል፡፡ በጣም የሚያስገርመውታዲያ መለስ ዜናዊ የደን እንክብካቤን አስመልክቶ ትኩረት የሰጠው ለቤንች ማጂ/ ጉራ ፈርዳ መሆኑና፤ በ2012 በእጅጉ መጠን ያጣው ችግር፤ ስርአት አልባ የሆነው የውጪ የንግድሁኔታ በአካባቢው መዳበሩ መሆኑን ነው፡፡ ከዚሁ ጋርም የደኖችን መጨፍጨፍ ሰበብ ያደረገው እንቅስቃሴው በዘር ላይ የተመሰረተ ማሳደድና ነዋሪዎችን በትውልድ ሀረጋቸው ብቻ ለማፈናቀል መወሰኑ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን፤መለስ ለአካባቢ ደህንነት ተቆርቋሪ ለመምሰል ‹‹የሰሜን ጎጃሞችን ሰፋሪዎች›› በማስረጃ የተደገፈ መፈናቀል አወዛጋቢውን ርእስ ለመሸፈንና ከወቀሳና ከትችት ለመዳን በማታለያነት ተጠቀመበት?

መለስ ዜናዊ ስለአካባቢ ዓየር መቆርቆርን፤በሃሳብ መባዘንን ስለደኖች እንክብካቤ መቆጨትን፤ በማስመሰያነት ከመጠቀም ውጪ አንድም የእውነት ፍንጭ የሌለው ነው፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት፤መለስ ዜናዊ በጣም ፍሬያማ የሆኑትን ለም የደን መሬቶች ለሳውዲዎች ለሼሆቹ፤ለህንዶች፤ለቻይናዊያን፤ለኮርያውያኖችና የዶላርን ስም ለጠሩና ቁጥር ለጠቀሱ ሁሉ በሊዝ ስም ሸጦላቸዋል፡፡ እንደ የተከበረው የኦክላንድ ኢኒስቲቲዩት [OI] ግንዛቤ ከ2008 ጀምሮ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ

በትንሹ 3.619.509 ሄክታር መሬት ለውጪ ኢንቬስተሮች (ቁጥሩ ሊበልጥም ይችላል) አስተላልፏል፡፡….የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት በመሬቶች ላይ ስለተከናነው ድርድር ሁሉ በውይይት መግባባት ተደርሶበት ነው፡፡ አንድም የተፈናቀለ ነዋሪየለም፡፡ የተሰጠው መሬትም በጥቅም ያልዋለ ጦም አዳሪ የነበረ ነው በማለት ቀልመድመድ ቢያደርግም የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ግን ከነዋሪዎች ጋር ተካሄደ ስለተባለው ውይይትአንዳችም ማረጋገጫ አላገኘም፡፡ ………..በውሃ አጠቃቀም ላይ አንዳችም ገደብ አልተደረገም፤ በአካባቢው ዓየር ላይ ሊያደርስ ስለሚችለው ብክለት(EIA) ምንም የተወሰደ ጥናት አልነበረም፤ቁጥጥርም አልተደረገም፡፡ ኢንቬስተሮች ውሃን ያላንዳች ገደብ እንዲጠቀሙበት መፍቀድ እጅጉን የሚያስገርምና አሳዛኝ ደንታ ቢስነት ነው፡፡ የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ከኢንቬስተሮች በተደረገት ገለጻ፤ ምንም አይነት ቁጥጥርና ገደብም ስለሌባቸው የአካባቢውን ወንዝ በመገደብ ሊገለገሉበት እንዳቀዱና በአካባቢ የዓየር ቁጥጥርም አንዳችም ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን ገዢው መንግስትና ባለስልጣኖቹ የአካባቢ ዓየር ጥበቃ ይደረጋል በማለት ቢናገሩም ከመንግስት በኩል አንድም የማስረጃ ማሳመኛ ሊያቀርቡ፤ ጥናትና ቁጥጥር ለመኖሩና ለመከበሩም ቢሆን አንድም የመንግስት ባለስልጣን ወይ የየአካባቢው ሹም በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ቦታው ደርሶ እንደማያውቅ ነዋሪዎች ሲመሰክሩ፤ ኢንቬስተሮችም ይህ ሁኔታ ለመከናወኑ አንዳችም ማስረጃ የላቸውም፤ የጠኝውም ሃገር ደግሞ ይህን አይነት ሁኔታ ተካሂዶበት አይውቅም፡፡………… ከአርሻ ይዞታ ላይ መፈናቀል በሰፊው የሚካሄድ የእለት ተእለት ሂደት ነው፤ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮችም ተገቢውን ማካካሻ አልተከፈላቸውም፤ከመኖሪያና እርሻቸው ሲነቀሉም በሌላ አካባቢ የእርሻ ቦታ እንዲፈልጉ በመደረግ በመሆኑ ከሌሎች የአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በቦታ ሰበብ ውጥረት እንዲፈጠር እየተደረገ ነው፡፡

በመጨረሻውም ሼሆቹ፤ሳውዲዎች፤ህንዶች፤ቻይናዊያን፤ ኮርያዎች (ሼሳህቻኮ) ለሙን መሬት በማቃጠል ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማብቀልና ለመክበር የተሰባሰቡትና መሬቱንም በሻጩ መንግስት የተከፋፈሉት ኢንቬስተሮች ሲባሉ፤ ለእለት ጉርስና ቤተሰቡን ለማኖር በማለት ኩራማን በምትሆን መሬት ላይ ኑሮውን ለማሸነፍ የሚጥረው ዜጋ ግን፤ ሕገወጥ ኗሪ (‹‹ሰፋሪ››) ይባላል፡፡ እነዚህ ስብስቦች (ሼሳህቻኮ) ለ‹‹ልማት›› በሚል የማደናገርያ ቃል፤በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር መሬት ለ99 ዓመታት ተሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከሞነርያ ቀያቸው በጉልበት በመፈናቀል የእርሻና የመኖርያ ቦታቸውን ለነዚህ ሼሳህቻኮች እንዲያስረክቡ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ሼሳህቻኮች ከግምት በማይገባ ገንዘብ ያሻቸውን ያህል የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ ሲፈቀድላቸው፤ ኢትዮጵያውያን ግን የባለቤትነት ይዞታቸውን አንዳችም የገንዘብም ሆነ የቦታ ትክ ሳይደረግላቸው እንዲባረሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ሼሳህቻኮ በብርሃን በግላጭ በአክብሮት የደስታ አቀባበል ሲደረግላቸው፤ ዜጎች ግን ጸሃይ ከመጥለቋ በፊት አካባቢውን ጥለው እንዲሰደዱ ይደረጋሉ፡፡ ሼሳህቻኮ የመሬት ባለቤትነት መብት ሲኖራቸው ኢትዮጵያውያን ደግሞ ለመሬት አልባነት ይዳረጋሉ፡፡ ሼሳህቻኮ የነገስታታነት ከበሬታ ሲሰጣቸው፤ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዱላ መባረርን ይቸራሉ፡፡ እንደ ኦክላንድ ኢኒስቲቲዩት ጥናት ከሁሉም በላይ የሚያሳፈረው በ ሼሳህቻኮ እርሻዎች ላይ ለመስራትና ኑሮን ለመታገል የፈቀዱትም ኢትዮጵያውያን በመጤዎቹ እንደ እንስሳ በመቆጠር ለግፍ መዳረጋቸው ነው፡፡

ወደ ሼሳህቻኮ ግዛት እንኳን በደህና መጣችሁ!

‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› ሊያከብሩትና ሊከተሉት የሚገባ የአካባቢ ዓየር ሕግ አለን?

የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› ከይዞታቸው መነቀል አስፈላጊ መሆኑን መለስ ሲያስረዳ፤ ‹‹ሰፋሪዎቹ›› ሕገወጥ፤በዘፈቀደ ቦታውን የያዙ፤ እና የአካባቢ ዓየርንም ደህንነት የሚያበላሹ ናቸው በማለት ይወነጅላቸዋል፡፡ ለመሆኑ የመለስ ገዢ መንግስት፤ሕጋዊነትን የሚጠይቅ፤ ስርአት የተቀመጠለት፤የገጠር አሰፋፈር ደንብ አለው? ለምሳሌ በጉዳዩ ላይ የተቀመጠው ወሳኙ ሕግ፤ ‹‹የገጠር መሬት አስተዳደርና አጣቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/2005›› በእርሻ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ሁሉ፤ መሬትን ያለምንም ገደብ ይፈቅዳል እንጂ አሰፋፈርን በተመለከተ እንዴት መከናወን እንደሚገባው የሚለው አንዳችም ነገር የለም፤ ስለአስተዳደሩም የሚገልጸው ስርአት የለም፡፡ አተገባበሩን በተመለተ ሙሉ መብቱን ሙያው፤ብቃቱ፤ችሎታውም ለሌላቸው ‹‹የአካባቢው ባስልጣናት›› ትቶታል፡፡ በእርግጠኝነት አዋጅ ቁጥር 456 ስለ ደን መሬት ጥበቃ፤አስተዳደር አንዳችም የሚለው ቃል የለውም፡፡በደፈናው የግብር ይውጣ ያህል፤ ደን፣የደን መመናመን፤እና የደን መሬት በማለት ይዘጋዋል፡፡

የተሸሻላና አዋጅ ቁጥር 456ን የተካውም አዋጅ ቁጥር 106/2007 ቢሆን፤ እንዲያው በይሆናል ግምት፤የታወጀ እንጂ ክልሉ የአካባቢ ዓየር ጥበቃ ኤጀንሲ የለውም፡፡ አዋጅ ቁጥር 456ን ተግባራዊ የማድረጉ ሃላፊነት በእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ ስር የተጣለ ሚንቀሳቀሰው ግን የተፈጥሮ ሃብትንና የዱር አራዊትን በመጠበቁ ላይ እንጂ የደን ጥበቃውን በተመለከተ ጨርሶ የተጣለበትን ሃላፊነት አልተረዳውም ወይም ከጉዳይ አላስገባውም፡፡ የመሬት አጠቃቀም ገደብን በተመለከተ በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ድንጋጌ ቁጥር 66/2007 ከጫካማ ቦታዎች ወይም ደኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ግንኙነቱ ከውሃማ ቦታዎችን ከተንሸራታች መሬቶች ጋር ነው፡፡ በደፈናው ብቻ ደኖችን ስለማመናመን ወይም ስመጨፍጨፍና ለእርሻነት ስለማዋል የሚጠቅስ አንዳችም ክልላዊ ሕግ የለም፡፡ እና ታዲያ ‹‹ሰፋሪዎች›› ምን አድርጉ ነው የሚባሉት?

የፌዴራሉ ‹‹የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 542/2007›› ቢሆንም ዝም ብሎ የእቅድ አቅጣጫ ጠቋሚ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡አዋጁ የመንግስትንና የግል ደኖችን ያከብራል ይላል እንጂ፤ደኖች እንዴት ሊለሙ እንደሚችሉ የሚየሳየው አካሄድ አለያም ደግሞ ግለሰቦች በስራው ለመሰማራት ፈቃዱን ከየት እንደሚያገኙ አይገልጽም፡፡ አዋጁ የግል ደኖች አልሚዎችን ግዴታ ሲደረድር ስለመብታቸው ግን ምንም አይልም፡፡ የአዋጁ ብዘው ቦታ የተሞላው ወደፊት ምን ሊደረግ ይገባል በሚል የምኞት እቅድ ላይ ነው፡፡

መለስ የቤንች ማጂ ‹‹ሰፋሪዎች›› ከአስፈላጊው የአካባቢ ዓየር መመርያ አዋጅ ቁጥር 299/2002 ጋር በሚጋጭ ሁኔታ ነው በማለት ሊያሳስት ይሞክራል፡፡ ይህ አዋጅ አስቀድሞ የተባለው ፕሮጄክት ተግባራዊ ከመሆኑ አስቀድሞ ሊጠናና ሊመረመር ይገባዋል፡፡ የዚህ አዋጅ ቁጥር 299 አባባልና አተረጓጎም ‹‹ሰፋሪዎቹ›› የአካባቢን ዓየር ሁኔታ ከሚመለከተው ሕግ ተጠያቂነት ውጪ ናቸው፡፡ከዚያ ይልቅ ለአዋጅ ቁጥር 456 (የገጠር መሬቶች አስተዳደርና ጥቅም) ተገዢ ይሆናሉ፡፡ይህ ሁሉ የሕጋ ቃልና የቴክኒክ አጠራርና አላስፈላጊው ክርክር ሁሉ ይቀርና ጉዳዩ በሙሉ የፖለቲካ ጥያቄና የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ይሆናል፡፡ በጊቤ ግድብ 3 ሂደት ላይ የቀረበው የከባቢ ዓየር አስተያየት በግልጽ የሚያሳየው ሁኔታ የፖለቲካ ጉዳይ ሲሆን የሚያስከትለውን ነው፡፡

የዘር ጥሰት ወይስ የደን እንክብካቤ?

ከደቡብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ/ጉራ ፈርዳ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች በግዴታ መፈናቀላቸው አያጠያይቅም፡፡በአሜሪካ ድምጽ ላይ የተስተናገዱት ቃለ መጠይቆች፤ በግዳጅ መባረራቸውን በግልጽ ያስረዳል፡፡ስለዚህም ቸል የማይባለውንና ሊታለፍ የማይገባውን ጥያቄ ልንጋፈጠው የግድ ነው፡፡ይህ አስገድዶ ከቀዬ ማፈናቀል የዘር ጥላቻ ነው ወይስ የተለመደ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅ ነው? መለስ ዜናዊ ይህን አስገድዶ ማፈናቀልን በተመለከተ ማሳመኛ አድርጎ የሚያቀርበው የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› የተፈናቀሉበት ምክንያት ደኑን በማጥፋታቸውና አሰፋፈራቸውም በተለምዶ እንደሚያደርጉት ስርአት ያጣና ከህግ ውጪ በመሆኑ ነው ሲል፡ የደቡቡ ገዢ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩሉ ደሞ መለስ ስላነሳው ‹‹ሰፋሪዎች›› ስላደረሱት የደን መጨፍጨፍ፤ አንድም ቃል አልወጣውም፡፡ የፈጣሪ ያለህ ታዲያ ማን ሊታመን ነው?

ዘር ማጥፋት እንዲህ ነው ሊባል የሚችል ህጋዊ ትርጉም የለውም፡፡በ1993 የተባበሩት መንግስታት ኮሚሽን ቃሉን ሲተነትነው ‹‹ሆን ተብሎ ታቅዶ ከተወሰነ አካባቢ የተወሰነ ዘር ተወላጆች የሆኑትን በጉልበት፤ በማስፈራራት አፈናቅሎ ቦታውን ለሌሎች ዘሮች ለመስጠት የሚፈጸም›› ይለዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት ሴኪውሪቲ ካውንስል የባለሙያዎች ኮሚሽን ድንጋጌ 780 የዘር ማሳደድን ሲተነትንም በሰብዊ ፍጡሮች ላይ የሚፈጸም ወንጀል በመሆኑ እንደጦር ወንጀል ይቆጠራል ይላል፡፡የተለያዩ ድንጋጌዎችና ትንታኔዎች ወንጀልነቱን በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ ያረጋገጡት ነው፡፡የነዚህም ‹‹ሰፋሪዎች›› መፈናቀል ሆን ተብሎ በተመረጡ ብሄሮች ላይ የተፈጸመ ነዋሪውን የማግለል ደባ መሆን አለመሆኑ በተጠናቀሩት ማስረጃዎች ሊረጋገጥ የሚችል፤ጉዳይ ነው፡፡

ማካካሻ አይገባምን?

‹‹ሰፋሪዎቹ›› የተፈናቀሉት የሃገሪቱን ደን ከጥፋት ለማዳን ነው ተብሎል የሚለውን የመለስ ሰበብ አምነን የምንቀበል ከሆነ፣ የተፈናቀሉትና ርስታቸውን፤ መኖርያ መንደራቸውን፤ ንብረታቸውን ያጡት ከፍ ላለ የሀገር ጥቅም መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ አባባሉ የሚታመን ሆኖ ፤በአዋጅ ቁጥር 456 ‹‹ሰፋሪዎቹ›› መሰረት መብታቸው ሊከበርላቸው የግድ ነው፡፡ በአዋጁ ላይ ‹‹የገጠር መሬት ይዞታው ለሕዝባዊ ጠቀሜታ የተወሰደበት ሰው፤ በነበረበት ቦታ ላይ ባለማውና ባፈራው ሃብት መሰረት ተመጣጣኝ ማካካሻ ሊያገኝ አለያም ተመጣጣኝ የሆነ ትክ ሊሰጠው ይገባል›› ይላል፡: እነዚህ ሰፋሪዎች ግን ለተዘረፉት ቦታ፤ እንስሳትና ንብረት እንዲሁም ላደረጉት የልማት ውጤት አንዳችም ማካካሻ አልተደረገላቸውም፡፡ ጸሃይ ስትጠልቅ በድቅድቅ ጨለማ አካባቢያቸውን ለቀው፤ በጀርባቸው የለበሱትን ጨርቅ ብቻ ይዘው: ሕጻናት ልጆቻቸውን አዝለው እንዲጠፉ ብቻ ነበር የተገደዱት፡፡ ሌላው ቢቀር ከሕጉ አባባል አኳያ ማካካሻ ሊደረግላቸው አይገባም?

እረ የህግ ያለህ! እረ የህግ ያለህ!

የኢትዮጵያ ሽግግር ወደ ዴሞክራሲና የማንነት ፖለቲካ

Monday, April 9th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

በኢትዮጵያ ታሪክ ራሱን ይደጋግመዋል

ባለፈው ሳምንት የአሜሪካን ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ዘገባ ከሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በግዳጅ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉትን በርካታ ኢትዮጵያዊያንን የሚመለከት ነበር፡፡ በዘገባው መሰረት፤ ከዚሁ ከደቡባዊ ክልል በጉራ ፈርዳ በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ በርካታ የአማራ ተወላጆች በአካባባዊ ባለስልጣናት ንብረታቸውን ይዘው በአስቸኳይ ከአካባቢው ለቀው ወደ ‹‹ሞት ወረዳ›› የቀድሞ ቀያቸው እንዲሄዱ ለዳግም ስደት ተዳርገዋል፡፡ ለአሜሪካን ድምጽ በሰጡት የአቤቱታና የሰሚ ያለህ እሪታቸው በአካባባዊ ባለስልጣናት ተጠርተው የእርሻ ቦታቸውን በመልቀቅ፤ ቤተሰባቸውንና ጓዛቸውን ይዘው አካባቢውን ከጸሃይ ጥልቀት በፊት ለቀው እንዲወጡ መመርያ ተሰጥተዋል፡፡ አብዛኛዎቹ እነዚህ ተፈናቃዮች፤ በዚያው ተወልደው ያደጉና ቀሪዎቹ ደግሞ ለዓመታት ኑሯቸውን የመሰረቱ ናቸው፡፡ ስርአት ያጣው የመፈናቀል ዕጣ የደረሰባቸው ቤተሰቦች፤ መኖርያቸውን አላግባብ ይዘነው የነበረ በመሆኑ አሁን በፈቃደኝነት ለአካባቢው መስተዳደር በፈቃደኝነት መልሰናል የሚል የመስተዳድሩን ሰነድ በግድ እንዲፈርሙ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በመቶ የሚቆጠሩ እነዚህ የመከራና የግፍ በደል ተሸካሚ ተፈናቃዮች ና ቤተሰቦቻቸው አካባቢውን በመልቀቅ አቤቱታቸውን ለመለስ ዜናዊ ለማሰማትና የአካባቢው መስተዳድሮች የጣሉባቸውን የመፈናቀል በደል እንዲያስነሳላቸው ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ አቅንተዋል፡፡ ለአቤቱታ አገር ቆርጠው በዜግነት መብታቸው ለመጠቀምና አቤቱታ ለማሰማት ከፓርላማው በር ላይ የተሰበሰቡት አቤት ባዮች፤ አቤቱታቸው በመደመጥ ፈንታ በደህንነት ተከበው ተበድለው እንደበዳይ በመኪና ተጫነው ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡ የመለስ ዜናውም ተወካይ ለአሜሪካን ድምጽ በሰጠችው መግለጫ ስለተባለው ጉዳይ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ጉዳዩን ለማጣራት ግን ሂደት መቀጠሉን ተናግራለች፡፡ በዚህ በኩል ደህነንት ማዘዝ በአሜሪካን ድምጽ በኩል ደሞ ጉዳይ ማጣራት ምን የሚሉት ቅልመዳ ነው? በቅርቡ በአሰርት ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች በአካባቢው ባለስልጣናት ትእዛዝ በጉልበት ከደቡብ ሕዝቦች ማስተዳደር ባንቺ ማጂ ዞን መፈናቀላቸው ይታወቃል፡፡

የሕዝቦች ግዳጃዊ መፈናቀል (<<ሰፈራ>> መንደር ምስረታ›› ‹‹የአካባቢ ለውጥ›› ወ ዘ ተ ር ፈ ………) በኢትዮጵያ አስከፊና ዘግናኝ ታሪክ ያለው ነው፡፡ የመለስ አገዛዝ በመንደር ምስረታ ስም በርካታ ፕሮግራሞችን በማካሄድ፤(ቋሚ የሆነ ከትውልድ ቦታ ንቅለትና ስደት) በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል በጋምቤላ ነዋሪዎችን አፈናቅሎ የሕንድ ስሪት ለሆነው ለካሪቱሪና ለሌሎችም ኢንቬስተሮች በዜጎች ስደት ላይ ያበበ ንግድ ማካሄዱን የመለስ ገዢ መንግሥት ይክዳል፤ የመለስም ከፍተኛ የእርሻ ባለስልጣን ‹‹የስደት እንቅስቃሴ በጋምቤላ ጨርሶ የለም›› ቢልም የዩኒሴፍ የአካባቢ ጥናት ግን የሚከተለውን ይላል

ነዋሪ ዜጎችን ማፈናቀሉ (ከቅድመ ስሪታቸው ማፈናቀል) በጋምቤላ መጠኑን የሳተና ምክንያተዊነቱም የማያሳምን ነው፡፡ በቅርቡም የአኝዋኮች (ሌሎችም በቁጥር አናሳ ዘሮች)ባህል ጨርሶ እንደሚጠፋ አያጠራጥርም፡፡ ባህላዊ ደህንነት፤ራስን መቻልና ራስን ማስተዳደር፤ ለነዚህ ዜጎች መብታቸውና ሊከበርላቸውም የሚገባ የነሱነታቸው መገለጫ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ህጋግትም ጥበቃ ሊደረግላቸው ቢደነገግም በጋምቤላ ግን ትርጉሙ ጠፍቶ የግፍ መንደር እየሆነ ዜጎችም የግፍ ተጠቂ በመሆን ላይ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን የገዛው የደርግ መንግሥት ኢትዮጵያን ከ1970 እስከ 1991 ድረስ ሲገዛ ሠፈራን ለፖለቲካው መጠቀሚያ በማድረግ ሰርቶበታል፡፡ደርግ ህወሃት በያዛቸው መንደሮች የተገደዱ ሠፋሪዎችን በማሰማራት ለወያኔ ድጋፍ ለማሳጣትና ለሚሰነዘርበት ጥቃት መከላከያ አድረጓቸው ነበር፡፡በ1984 ዓም በተከሰተው ችጋር ሳቢያ ደርግ የ1.5 ሚሊዮን የተገዳጅ ሰፋሪዎችን በወያኔ ከተያዙና ለችጋር ከተጋለጡ ሰሜናዊ አካባቢዎች ወደ ደቡብና ደቡባዊ ምእራብ አካባቢዎች አሰፈረ፡፡ በዚህም ጊዜ ደርግ ሰፋሪዎቹ ያለምንም ማስገደድ በፈቃደኝነት ሰፈራውን ተቀላቅለዋል ብሎ ነበር፡፡ በዚሁ የሰፈራ ፕሮግራም በህመምና በችጋር በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖች በሞት ተቀጥፈዋል፡፡ከዚህ መከራ ከከበበው ያልተሟላ ሰፈራ መንድርም ለመሸሽ ጉዞ የጀመሩት ኢትዮጵያዊያን ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተው ለሞት ተዳርገዋል፡፡

የሚያስገርመው ግን የሰሜኖቹ የትላንት ተዋጊዎችና ላለፈው 21 ዓመታት ኢትዮጵያን ለመግዛት የበቁት መለሳዊ ገዢዎች ደርግንና የሰፈራ ፕሮግራሙን ‹‹የማፈኛ አስር ጣቢያ›› (“concentration” camps) በማለት ያወግዝና ያንቋሽሽ ነበር፡፡ እነዚህ ሰፋሪዎች ወደ ትውልድ መንደራቸው ጨርሶ እንደማይመለሱና (እትብታቸው ከተቀብረበት)ከመንደራቸው መለያየታቸውን ያናፍስና ያወግዝ ነበር፡፡ በ2012 ደግሞ እነዚሁ የግዴታ መፈናቀልና ሰፈራ ተቃዋሚ የነበሩት የአሁኖቹ ገዢዎች ዜጎችን ከመኖርያ ቀዬአቸው አስገድዶ ለማፈናቀልና ካለፈው በባሰና ነከፋ መልኩ መድረሻ ለማሳጣት የሚካሄደውን እቅድ ቀዳሚ መሃነዲሶች ሆነው በመንደፍና አዲስና እኩይ ዘዴ በመጠቀም ዜጎችን ያለአግባብ በማፈናቀል ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡ ታሪክ በኢትዮጵያ እራሱን ደግሞ ደግግሞ ያሳያል ማለት ይቻላል፡፡ በአርቲክል 7 (d) የሮም ስታቸር መሰረት የሕዝቦች የዓለም አቀፍ ሕግ ከሚፈቅደው ውጪ በግዴታ ማፈናቀል እንደ ኢሰብአዊ ድርጊት የተመዘገበ ወንጀል ነው፡፡

ክልልና ባንቱስታንነት

ላለፉት በርካታ የግዛት ዓመታት መለስ ዜናዊ ጠብ የማይለውን ‹‹የዘር ፌዴራሊዝምን›› በአንጸባራቂ መጠቅለያ አሳምሮ ለማቅረብ እየጣረ ነው፡፡ የዘር መከፋፈያ አጠራር በመስጠት ኢትዮጵያዊያንን ለያይቶ በፈጠረው የፖለቲካ አጠራር እንደ ከብት በመደልደል፤ ክልል በማለት መድቧል፡፡ (የዚህም ትክክለኛ ትርጉሙ የተከለለ ማለት ሲሆን ቃሉም ታጥሮ የተከለለ ማለትም ነው፡፡ ክልል በአፓርታይድ ዘመን የነበረውን የዘር ልዩነት ባንቱስታኒዝም ለመፈረጅ የተጠቀሙበት ቃልን ይመሳሰላል፡፡የክልላዊነት ፍልስፍና ከደቡብ አፍሪካው ባንቱስታኒዝም ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሁለቱም ፍልስፍናዎች የተወሰኑ ብሄሮችን ለማግለልና በተከለላቸው አካባቢ ብቻ ተገድበው እንዲኖሩ በማድረግ በጊዜ ሂደትም የራሳቸውን ግዛት ለመፍጠር እንዲችሉ ለጥፋት የሚያነሳሳ ሂደት ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ሆን ብሎና በቅድሚያ ሊፈጸምና ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚያስችለውን እኩይ ተግባር በማለም አንቀጽ 39ኝን የመገንጠል መብት የሚፈቅደውን አስቀምጧል፡፡ማለትም ክልሎች ቀስ በቀስ የራሳቸው መንግስትን ለመፍጠር ይበቃሉ፡፡ የባንቱስታንም አመሰራረትና ሂደቱመም ይህንኑ ለመተግበር ነበር፡፡

ከዚህ ባለፈም የሚመሳሉበት በርካታ ሁኔታ አለ፡፡ የባንቱስታን ቀዳሚ ፖሊሲም ጥቁር አፍሪካውያንን የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ከማድረግ ይልቅ የአንድ መንደርና አካባቢ ነዋሪዎች ለማድረግና ደቡብ አፍሪካን የነጮች ግዛት አድርጎ ለማስቀጠል የታቀደ ሴራ ነበር፡፡ በዚህም የፖለቲካ መብታቸውን በማፈንና በመንሳት፤ብሔራዊ መብታቸውን በመንጠቅና በማሳጣት፤ በነጻ በሃገሪቱ መንቀሳቀስን፤ ሰብአዊ መብታቸውን በአጠቃላይ የዜግነታቸውን መብት በመግታት፤ ባንቱስታኒዝም ጥቁር አፍሪካውያንን ነጻነት ነስቶ አገቷቸው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ደቡባዊ ግዛት በመካሄድ ላይ ያለው የአስገድዶ ማፈናቀል ተግባር ባንቱስታኒዝም በደቡብ አፍሪካ የፈጸመውን ኢሰብአዊ ተግባር የሚያከናውን ክልል የሚባል ትርጉም የተሰጠው ነው፡፡ ክልላዊነትም ኢትዮጵያን በዘጠኝ ክልላዊ መንግሥት በሚል ቦታ በዘር ድልድል ቆራርጦ በደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ጥቁር አፍሪካዊያንን አግልሎ ሥላጣኑን እስከዘለቄታው ለማቆየት እንደተጠቀመበት ሁሉ በኢትዮጵያም ለመሰል ግባር ውሏል፡፡ International Crises Group, (a research organization that gives advice to the United Nations, European Union and World Bank):

የህወሃትና የኢህአዴግ አንድ ወቅት ከትግራይ የገጠር ነዋሪ ጋር የነበራቸውን ቅርብ ትስስርና ግንኙነት እርግፍ አድርገው በመተው አሁን ከሕዝቡ ተለይተው በመግዛት ላይ ናቸው፡፡ይህም አናሳ የሁኑት የፖለቲካ ባለስልጣናት የህወሃት ሥራ አስፈጻሚ አባላትና በተለይም ጠቅላይ ሚኒስተሩ ናቸው የሃገሪቱን የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚወስኑት›› በማለት ያረጋግጣል፡፡

የጎሳ ፖለቲካ ካርታ ጨዋታ ያብቃለት

በኦክቶበር 2011 በሳምንታዊ መጣጥፌ ላይ የጨቃኞችና አምባገነኖችና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የመሳርያ ግምጃ ቤት ውስጠ የሚገኘውን የመጨረሻ መሳርያቸውን ከፋፍሎ በግፍ መግዛትን አስመልክቼ ጽፌ ነበር፡፡

ላለፉት በርካታ ዓመታት፤በኢትዮጵያ የሥልጣን ወንበር ላይ የተኮፈሱት ገዢዎች እምነታቸው ወይም ዓላማቸው ‹‹እኛ የሕዝቡ መሪዎች በጣም ጋጠ ወጥ የሆነውን አገዛዝ ለመመስረት…………..›› በግምጃ ቤታቸው ያስቀመጡትን የግፍና የጭካኔ አገዛዛቸውን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ ሕዝቡን በዘርና በብሄር፤ በከተማው፤ በመንደር፤ዝቅ ብሎም በጉርብትና መከፋፈል ችለዋል፡፡ የብሔር ፌዴራሊዝም በሚል የተንኮል ድልድል በአካባቢ ሊገድቧቸው በቅተዋል፡፡ሕብረተሰቡን በቋንቋና በሃይማኖት፤ የኖረ ቁርኝታቸውን ለመበጠስና በሃገር ውስጥና በውጪ ያለውን ኢትዮጵያዊ ለማለያየት ጥረት አድርገዋል፡፡

ባለፈው ጃንዋሪ መጣጥፌ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አንድ እንዲሆኑና ለአንድ ዓላማ በመሰለፍ፤ በገዢዎች የተፈበረከውን ድውይ የሆነ አስተሳሰብ ያዘለውን የዘር የጎሳና የመንደር፤ የሃይሞነትና የብሄር መከፋፈልን አፍርሰን በአንድነት በኢትዮጵያዊነት በመቆም የአንድነት ድልድይ መልሰን በመገንባት ከድህነት ከችጋር ከእርዛት ከመሃይምነት እንድንላቀቅ ጠይቄ ነበር፡፡ ዘወትር የአሜሪካን ሕገመንግሥት መግቢያው ላይ የሰፈረውን ‹‹እኛ የአሜሪካን ሕዝቦች፤ትክክለኛውንና የማይነቃነቃውን አንድነታችንን ለመፍጠር…….››የሚለውን ሳነብ በዚህ ግዙፍ አባባል ልቤ ይሞላል፡፡

የዘር ፖለቲካን ድል በመንሳት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረግ ሽግግር

ከዲክተቴርሽፕ ወደ ዴሞክራሲ በሚደረግ ሽግግር ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያጋጠም የሚችለው ችግር፤በላዕላይ መዋቅሩ የተጋረደው የዘር ፖለቲካና የክልላዊነት ድልድል ነው፡፡አንዳንድ ሰዎች የክልሊዝም ፍልስፍና በሃገሪቱ ውስጥ ብጥብጥን ወቅታዊም ቢሆን፤ያለመረጋጋትን ሁኔታ በሽግግሩ ወቅት ብቻ ሳይሆን፤አንድነትን በማጠናከሩና ወደ ቀድሞው ህዝባዊ አንድነትና መግባባት መመለሱንና የኢትዮጵያን የፖለቲካ ነጻነት ሊሞግት እንደሚችል ይገምታሉ፡፡ በኔ ግምት የዚህ ግብግብ የማንነትን ፖለቲካና የዘር ጣያቄ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር፤ሰብአዊ ክብርን በረጋ መግባባት ለማጎልበት (በዚህም ግጭትንና ሕገወጥነትን በማስወገድ) የሚያስችል ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡

ለኔ ዋነኛውና መሰረታዊው ጉዳይ፤የመለስ ዜናዊ ‹‹የዘር ፖለቲካ የካርታ ጨዋታን›› መጫወቱ ውጤታማ ነው ወይ የሚለው ነው፡፡ ካገሪቱን ቅጥና አመራር ለማሳጣትና የራሱን አንድ ሰው አንድ ፓርቲ አገዛዝ ለመምራት ትክክለኛ ነው ብሎ በማመንና ለሱ እስከተስማማው ድረስ ሃገሪቱንና ሕዝቡን ከምንም ሳይቆጥር በማንአለብኝነት ፈላጭ ቆራጭ ስርአቱ ተጠቅሞበታ ል፡፡ ይህን‹‹የዘር ቁማር መጫወቻ ካርታውን›› ተቀናቃኞቹን ለማንበርከክና ለብስጭት ለመዳረግ፤በሃገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እየናረ ያለውን የኑሮ ውድነት ከሕዝቡ ሃሳብ ለማራቅና ለማረሳሳት፤ (ተቀማጭነቱ በአዲስ አበባ የሆነው አክሴስ ካፒታል የሼር ኩባንያ ባለፈው ዓመት ጥንቅሩ ኢትዮጵያ በዓለም የዋጋ መዋዠቅ 40.6 በመድረስ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች ብሏል) የዘር ክፍፍሉን ጨዋታ ለመለስ ተዉን በመምረጥ እኛ በዜጎች መሃል የዕርቀ ሰላምና የመግባባት የብልጽግና ውህደት በመፍጠሩ ላይ እናትኩር ፡፡

የማንነት መገለጫ ይገነባል፤ዳግምም ተሸሽሎ ይገነባል፤እንደገናም ለተሸለ ይገነባል፡፡ ይህንንም የሚያሳዩና ህብረተሰቡን የሚጠቅሙ በርካታ ሳይንሳዊና ጥናታዊ ጽሁፎች አሉ፡፡ በሌላ መልኩም የብሄር ማንነት እንደማንኛውም ማንነት ተለዋዋጭ ነው፡፡በስደት፤ በጋብቻ፤በትምህርት በመቀላቀል አንድነት በሚመሰረትበት ሁኔታ፤በኤኮኖሚ እድገትና በመሳሰሉት ሊለዋጥ ይችላል ማለት ነው፡፡ብዙ ጊዜ የህብረተሰብና ሕጋዊ ፍትህ በማይኖርበት ወቅት፤ የህግ ልዕልና በእኩልነት በማይኖርበት፤ደካማ አስተዳደር ባለበት፤ዘረኛነት ይጠነክርና ግጭት ሊከሰት ይችላል፡፡ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፤ለምሁራንእና ለሌሎችም ትልቁ ፈተና የዘር ፖለቲካንና ባለፈውም ሆነ በአሁኑ ሁኔታ የተፈጠረውን አለመግባባትና የገዢዎች የመኖር ዋስትና ያሉትን ጥላቻ በማሰወገድ በሰበአዊ መብቶች ላይ በተመሰረተ መግባባት ላይ ማተኮር ነው፡፡ በኔ እምነትም ማንኛውንም ነገር ለሃገርና ለሕዝብ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚቻለው በቅድሚያ ልዩነታችንን በመንቀስ ወደእንድነት የምንመጣበትን ውይይት ለማካሄድ የውይይቱን አካሄድና መግቢያና መውጫውን በመስማማት ፈቃደኛነትን በማስቀደም ብቻ ነው፡፡ለዚህም የሚረዳን በቅድሚያ ዘር የሚለውን ለመነጋገርያ በሚጠቅምና በሚያግባባ ትርጉሙ ላይ መስማማት፡፡

ለማንነት አዲስ ቃል መፍጠር

በኢትዮጵያ ስለተከሰተው የዘረኛነት ሁኔታን በተመለከተ ቀደም ባለው ጊዜ ይህን ሁኔታ ሊያወያይ የሚችል አንድ አዲስ ‹‹ቋንቋ›› እንዲፈጠር ሃሳብና ሊሆን ይገባል በሚልም ሃሳብ አቅርቤ ነበር፡፡ ለጊዜው (ቃሉንም ኒዎሎጊዝምስ ብዬው ነበር) ዋናው እምነቴም ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝና ጭቆና የበለጠ እየደረጁና እየተንሰራፉ የሚሄዱት ሕዝቡ አንድነት ሲያጣና ሲራራቅ፤ በዘርና በጎሳ ተለያይቶ ጎሪጥ ሲተያይ መሆኑን አመላክቼ ነበር፡፡አንድነት የጠንካሬ፤የአብሮነት፤የሰላም እና የእርቀ ሰላም መሰረት ነው፡፡የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ጭራቃዊ ገዢዎች በዘር መከፋፈልን ከፍፍለው ለመግዛት መጠቀሚያ መሳርያቸው አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡

እኔ ዘረኝነትን እንደ አንድ ሳንቲም የአንድነት ሌላው ገጽታ ነው የማየው፡፡የጎሳዎች ስብስብ የብሔራዊ አንድነት ውበትና ቅርጽ ነው፡፡አንድነት የመበታተን አደጋ የማያጋጥመው በብሔረሰቦች መሃል አለመጣጣምና መግባባት ሲጠፋ ነው፡፡ መለስያዊው የዘር አመለካከት ግን ኢትዮጵያን እንደ 9 የተለያዩ ብሔረሰቦች መመልከትና ክልሎች ብሎ ማስቀመጥ ነው፡፡ ክልል የሚለው ቃል በራሱ መታገትን፤ መገደብን፤ መራራቅን አመላካች ነው፡፡መለስም እንደሚያምነውና እንደሚመኘው ኢትዮጵያ የአንድ ሕዝብ ሃገር ሳትሆን በብሔር ብሔረሰቦች ተገጣጥማ ሲያስፈልግ የምትበታተን፤ ሕዝቦቿም አንድ የሚያደርጋቸው ምንም ፋይዳ የሚሞላ ጉዳይ እንደሌላቸው ነው፡፡(ይህ ደሞ ከፋፍሎ ለመግዛት ዋነኛው ሽፋንና መሳርያም ነው) በኛ እምነት ግን ኢትዮጵያውያን ሁሉም በአንድ ጥላ ስር የሚኖሩ፤ በአንድነታቸው የሚያምኑ፤ የሁሉም የሕግ ጥበቃ ከአድልዎ የጸዳና ሚዛናዊ የሆነ፤ኢትዮጵያም በዳበሩና ብዛት ባላቸው ባህሎች ተሳስሮና ተፋቅሮ የኖረ የሚኖርና በመኖርም ላይ ያለ ሕዝብ ሃገር ናት፡፡ ሕዝቡ በሃገሪቱ ዙርያ ገብ ያለ አንዳች ተጽእኖ፤ገደብ በፍቅር በመግባባት በመተሳሰሰብና በመስራት የሚኖሩ ናቸው፡፡

በሁላችንም ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ አዲስ አይነት አንድነት በመፍጠር ነው ከተጫነብን አረመኔያዊ የፈላጭ ቆራጭ የባርነት አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርአት መሸጋገር ያለብን፡፡ይህም የተለየ አንድነት፤የሚቆምበት ዋናው መደብ የሁላችንም የጋያ ፕሮፓጋንዳ ከሆነው ዘረኝነት የበለጠ ዋጋ ያለው ሲሆን ነው፡፡ ሁላችንም ለሰብአዊ ክብር ያለብን ቃልኪዳናዊ ግዴታ ቅጥ ካጣውና መላቢስ ከሆነው የአንድ ዘር ግነትና ጋጠ ወጥነት የበለጠ ዋጋ እንዳለው አምነን መቀበል ነው፡፡ በከፍተኛ መመርያና፤ እምነት ላይ የተመሰረተ ነውና፡፡ አፍሪካዊ በሆነው አባባልና አጠራር ላይ ኔልሰን ማንዴላ እንደሚሉትና የሰውን ልጅ አፈጣጠር በሚያስረዳው መልኩ የአፍሪካን የተለያዩ ዘሮች ዩቡንቱ “Ubuntu” ብለን መጥራት እንችላለን፡፡ ሰው ሰው መሆን የሚችለው ሌሎች ሰብአዊ ፍጡሮች ሲኖሩ ነው፡፡ የሌሎችን ሰዎች ድጋፍና ይሁንታ እስካለገኘን ድረስ አንዳችም ነገር መከወን አንችልም፡፡ዩብዩኒቲ፤ እያንዳንዳችን እንደወንድማማች፤እህትማማች፤አንዳችን ስለአንዳችን ማሰብን መተሳሰብን፤መተማመንን፤ መቻቻልን፤የሞራል ግዴታን የምናከብርበት ነው፡፡ አንዳችን ሌላውን እየለየ በጎጂ ጎኑ በሚያሳየን የተቀባና በሰዎች ተንኮል የተፈበረከ መነጽር ኦሮሞውን ለብቻ ትግሬውን ለብቻ አማራውን ለብቻ፤ ደቡቡን ለብቻ ጉራጌውን ለብቻ፤ በዘር ሸንሽኖ እንደቅርጫ ስጋ የሚያሳየንን መለሳዊ አመለካከት በመምረጥ ጨርሶ ሊሆን አይችልም፡፡ይልቁንስ ሁሉም በአንድ የሚኖርባትን ሃገርና በፍቅርና በመግባባት ተከባብሮ የሞነር ህዝብ፤ፍትህና እኩልነት የጋራቸው የሆኑ ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ መልሰን መገንባት ነው፡፡

ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን የምጠይቀው፤ ለዚህ ልዩ አንድነታችን መቆም እንድንችል ነው፡፡ይህንንም አንድነት እኔ ሁሙኒቲ “humunity”እና ዩዩኒተ “younity” እለዋለሁ፡፡ሁሙኒቲ በዘር ላይ ተመሰረተ አንድነት ዜግነት ሳይሆን በዓለም አቀፍ ህግጋት ሰብአዊ ክብር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ግዴታ ያለበትናነው፡፡ሰብአዊ መብትን፤ ፍትሀን በእኩልነት የሚያስቀምጥ ለሕግ የበላይነት መገዛትን የሚወስን ነው፡፡የማንኛውም የስልጣን መሰረት ሕዝባዊ ይሁንታና በዚህም የተዋቀረው ሕገመንግስት በመመርያነት የሚተገበርበት፤ ተጠያቂነትን፤ ግልጽነትን፤በግዳጅ የሚያስቀምጥም ነው፡፡ እነዚህን ወደ ተግባር መለወጥ ከቻልን የተበዳዮችን መብት በማስጠበቅ፤የሰብአዊ መብት የተነፈጉትን ብናከብርላቸው፤ ምንጊዜም እንዳይጠሱና እንዳየበጣጠሱ፤ገደብ ብናደርግላቸው፤ሕብረተሰቡን ስለነዚህ ቀዳሚ ተግባራት በሚገባ እንዲያውቃቸውና እንዲንከባከባቸው እንዲጠብቃቸው በማስተማር በእውቀት ብናበለጽገው ፤ ወጣቱን ተተኪ ትውልድም ዴሞክራሲያዊ ለሆነ ሁኔታ ብናዘጋጀው፤ሙስናን፤ በስልጣን አለአግባብ በማን አለብኝነት መባለግን፤ በመታገል በዜጎች መሃል የጠበቀና የማይበጠስ አንድነት በመፍጠር አንድነትን በተግባርና በሃቅ ላይ አስቀምጠን የጋራ ንብረታችን ማድረግ እንችላለን፡፡ እነዚህ ውድ የሆኑ ዋጋዎቻቸው የማይተመን ጉዳዮች ከጎደሉብን ግን መለያየትና አለመግባባት ቤታቸውን ይሰሩብናል፡፡

አረመኔ ገዢዎች ጥቃቅን ልዩነቶቹን በማጉላትና በማባዛት ሕዝቡን ይከፋፍሉታል፤ ሕዝቡም በሚገባ ሳያውቀውና ሳያገናዝበው በሚመቱት የመለያየት ከበሮ ድምጽ በመመራት ለዜማቸው ይጨፍራል፡፡ በኔ የሁሙኒቲ “huminity” እምነት ግን የአመለካከት ልዩነት፤እምነት ሊኖር ይችላል፤የአመለካከት ልዩነት ደግሞ የእምነት ልዩነት ሊሆን አይችልም፡፡ዓለምአቀፋዊውን የሰብአዊ መብት ብንመለከት ስለኛ ዘር፤ ዜግነት፤ቋንቋ ሃይማኖት ወይም ሌላ ጉዳይ ሳይሆን፤ የጭቆናንና የክፉአረመኔያዊ ገዢዎችን አስኳል በመንቀል የዴሞክራሲ ስርአትን በመገንባት ለሕግ የበላይነት ተገዢነትን ማዳበር ነው፡፡

የ ዮዩኒቲ “younity” ግንዛቤዬ እኔና እርስዎ ነአንድነትና በቆራጥነት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎችንና ጭቆናቸውን በህብረት ለመታገል መነሳታችን ነው፡ የእምነታችን መመስረቻም፤እያንዳንዳችን ለጭቆና ማበቃትና ለነጻነት በረጂሙ የተሳሰርን የነዚህ ሁኔታዎች መገናኛ ቁልፎች መሆናችን ነው፡፡ ለነጻነት ያለን ፍላጎትም ከአንደንነት ሰንሰነለት ጋር ያቆራኘንና ጭቆናን ለማጥፋት መንገድ ይሆነናል፡፡ ኢትዮጵያዊያን የሆንን ሁሉ የሰብአዊ መብትን መከበር፤ በሚገባ አውቀንና አሳውቀን ልንጠብቀው ይገባናል፡፡የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ህብረተሰቡ አመለካከቱ አንድ እንዲሆንና አዲስ የሁሚኒቴ “huminity” አስተሳሰቡን እንዲያዳብር የማድረግ ሃላፊነት ይጠበቅባቸዋል፡፡የሲቪክ ማህበረሰቦች ለዚሁ ሁሙኒቲ ጥብቅና መቆም፤ምሁራን የዚህን መንገድና ቋንቋ በማስተማር የተለያየ አመለካከት ያላቸውን ማቀራረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ወጣቱ ትውልድም ለቀደምት ትውልድ የሁሙቲን አስፈላጊነት በማስተማር ለአዲስና ለብሩህ ተስፋ ኢትዮጵያ መመስረት ማዘጋጀት አለበት፡፡ ለዘለቄታው አንድነት ማረጋገጫ ደግሞ ማንኛውም ተራው ዜጋ የሁላችንም በሚሆነው ሰብአዊነት ዩብዩኒቲ (ubunity) ቋንቋ መነጋር አለበት፡፡

አፍሪካውያን ቅኝ ገዢውን ስርአት እና አፓርታይድን በጨቋኝ ስርአት ላይ ግንባር ሲፈጥሩ አሸነፉትና ጣሉት፡፡በቅርቡም የግብጽ፤ የቱኒዚያ፤ የሊቢያ፤ ዜጎች ‹በሕብረት ጸንቶ የቆመን ሕዝብ የሚያሸንፈው ሃይል የለም›› የሚለውን በተግባርና በቆራጥነታቸው አረጋግጠዋል፡፡ ሕብረትና አንድነት የማጣት ዋጋው ደግሞ ለመከራ መጋለጥ፤ለብዝበዛ መዳረግ፤ለመለያየት መንገድ መክፈት፤ መሳርያ መሆን ነው፡፡ ምርጫችን ሁልጊዜ ማልቀስ፤ ዘወትር ማውራት፤ በየቦታው ለችግር መጋለጥ፤ በፍርሃት መታሰር ሊሆን ይችላል፡፡ እርስ በርሳችን በመናቆር፤ አንዳችን አንዳችንን በማጥላላት፤ ለጥቅምና ለቁራሽ ስንል ወገንን ማሳለፍ፤ እራሳችንን ለማቆየት ብዙዎችን መክዳት የሚያስከትለው ውጤት ግን መብትን በማጣት ለባርነት መዳረግን ነው፡፡ አለያም ዩብዩኒቲ፤ ሁሙኒቲ፤ እና ዮዩኒቲ የአንድነትን ጎዳና መምረጥ ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእህትማማችነትና በወንድማማችነት መንፈስ መሰባሰብ አለብን፡፡የዘርን የሃይሞነትን፤የቋንቋን እና ሌሎችንም ልዩነታችንን በመቻቻልና በማስወገድ ተቀናጅተን የጥንቱን አንድነታችንን በመከባበርና በመተሳሰብ መመለስ ይኖርብናል

የመለስን የዘር ፖለቲካ ካርታ ለመጫወት ፈቃደኛ መሆን ማለት ለጥፋት ወደሚዳርግ ልዩነት፤የዘር ፖለቲካ፤አለመግባባትና መናቆር፤መዳረግ ነው፡፡በጉራ ፈርዳ፤ በጋምቤላ፤በቤንች ማጂ፤እና በሌሎችም ቦታዎች መለስ ላስከተለውና በሕዝቡ ላይ ስለጫነው የግፍ ቀንበር ደጋግመን ልንረግመውና ልናወግዘው እንችላለን፡፡ ግን ከዚያ ባለፈም ከዘር ፖለቲካ ተገልለን፤ የአንድነታችን የሆነችውን ኢትዮጵያን መገንባት እንችላለን፡፡ ግን እንዴት………?

ከቁጡነት፤ ከጥላቻ፤ ከክፋት የጸዳ አዲስ ብሔራዊ ግንኙነት መፍጠር

አዲስ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ቀጥተኛውና አመቺው መንገድ፤የቆየውንና ጊዜው ያለፈበትን በጥላቻና በጀብደኝነት ላይ ተመስርቶ የነበረውን አንድነት በመተው ነው፡፡የአፍሪካ አንድነት ቋሚ ጸ/ቤት በሜይ 1963 በአዲስ አበባ በተመሰረተበት ወቅት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የአፍሪካ አንድነት ያስፈለገበትን ዋነኛ ምክንያት አስረድተው ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ከግማሽ ምአት በፊት የተሰነዘረው አስተያየት አሁን መልሶ በኢትዮጵያ ላይ እያጉረመረመ ነው፡፡

ስለአፍሪካ አንድ መሆን ስናስብ ስለነጻነት ብቻ ሳይሆን ስለአንድነትም ነው፡፡ይህ አዲስ ፈተና ሲቀርብልን ከአለፈው ትምህርት በመውሰድ ተስፋና መበረታታት ይሰማናል፡፡በመሃላችን ልዩነት እንዳለ አይታበልም፡፡እኛ አፍሪካውያን የተለያየ በሃልን እናስተናግዳለን፡፡……………. እንደ ነጻ ሰዎች የእኛ ጥረታችን አዲስ ግንኙነት ለመፍጠር መጣር ሊሆን ተገቢ ነው፡፡…….ብለው ነበር፡፡

ጎሰኛነትን ወይም ዘረኝነትን በማግለል፤ በግልጽ የጠበቀ አንድነታችንን በማሳወቅና በማረጋገጥ ባጋጠመን እድልና ቦታ ሁሉ የኢትዮጵያዊነት እምቢልታችንን ከፍ አድርገን በማሰማት በኢትዮጵያችን ሰብአዊነትን ባረጋገጠ መልኩ ኢትዮጵየዊነትን መገንባት ነው፡፡ ከጥርጣሬና ከጥላቻ የጸዳ አዲስ አንድነትና ግንኙነት እንገንባ……….

(ይቀጥላል)

ለኢትዮጵያዊያን፤ የጨለመው ስደት በኖርዌይ

Monday, March 26th, 2012

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

በሃገራቸው ባለው ጨካኝና አረመኔያዊ አገዛዝ ሳቢያ፤ገዛዙ በፈጠረው የኑሮ ውድነት፤ የነጻነት እጦት፤በችጋሩ፤ በሙስና፤ አረመኔው መንግሥት ሆን ብሎ፤ አውቆ፤ ፍጥረቱ ለጥፋት ተልእኮው በኢትዮጵያዊያን ላይ ስደትናእንግልትን ማደርጀት ነው፤ በሚፈጽመው የዲያቢሎስ ተግባር ሃገራቸውን ጥለው የተሰደዱት ኢትዮጵያዊያን በሰሜን አፍሪካ፤በመካከለኛው ምስራቅ በሌሎችም የአፍሪካ ሃገራት ለባሰ መከራና ስቃይ እየተዳረጉ ነው፡፡ ኢትዮጵያውስጥ መኖር ሳይሆን ለመኖር ማሰብ እንኳ ችግር ሆኖባቸው ስደትን ቢመርጡም ስደቱም ዳግም እያሰደዳቻው ነው፡፡

ባለፈው ጃንዋሪ በሺህ የሚቆጠሩትን ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞች፤ ወደሰሜን አፍሪካና ወደመካከለኛው ምስራቅ ፍልሰትን፤ ስደትን በተመለከተ ‹‹ኢትዮጵያ፤ ለመካከላኛው ምስራቅ የሽግግር ሰርጥ›› የሚል አንድ ጽሁፍአውጥቼ ነበር፡፡ ተጨባጭ የሆኑ ማረጋገጫ ማስረጃዎች፤በነዚህ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ፤ በደልና ኢሰብአዊ ድርጊትና ‹‹በውል የታሰረ ባርነት›› የሚደርስባቸውን መደፈርና የኤኮኖሚ ጫናና ግፍ በገሃድ ያሳያል፡፡ባለፈው ኦገስት መጨረሻ ላይ የጋዳፊ ልጅ ሚስት የኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛዋ ላይ የፈላ ውሃ በመላ ሰውነቷ ላይ በመገልበጥ እንዳቃጠለቻትና ፊቷ ማንነቷን ማሳየት እስከሚያስቸግር ድረስ አድርሳት እንደነበረ ምስሏንተመልክተናል፤አለያም ሰምተናል (ለቪዲዮ እዚህ ይጫኑ) ፡፡ ሌላዋ ወጣት የቤት ሰራተኛ፤ግፉ ስላንገሸገሻትና ምሬት ስለበዛባት፤የመለስ ዜናዊን አገልጋይ በአንድ ስብሰባ ላይ ፊት ለፊት ተጋፈጠችው(ለቪዲዮ እዚህ ይጫኑ) ፡፡ጥያቄ እያነሳች መልስ እጣ ብላ አፋጠጠችው፡፡‹‹ለምንድን ነው ይሄ መንግሥታችን ስለእኛ ደንታ ቢስ የሆነው?ለምን ስለእኛ ትንሽ እንኳን አያስብም፤ምን ሆናችሁ? መን ገጠማችሁ? ለምን አይለንም? ዓይኖቿ በእንባ ተሞልተው እያነባች ‹‹የታለ ባንዲራችን? አሁንስ በቃ አንገፈገፈኝ ከዚህ በላይ ዝምታ አልችልም››!!!!! (ለቪዲዮ እዚህ ይጫኑ)

ከሁለት ሳምንታት በፊትም ሌላዋ ስደተኛ ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ፤ያድኑኛል፤በችግሬ ይደርሱልኛል፤በዜግነቴ ከጎኔ ቆመው ይሞግቱልኛል፤ አያስነኩኝም ብላ በሞኝነት የዜግነት መብቷ በምታምንባቸውበሌባነን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጃፍ፤ በጎዳና ላይ እንደቆሻሻ እቃ ስትጎተትና ስቃይ ሲደርስባት፤ እየተረገጠችና እየተጠፈጠፈች ፍዳዋን ስትበላ፤ አመኔታዋን የጣለችባቸው የቆንሲላው ባለስላጣን፤የገዢው መንግስትአገልጋዮች፤በየመስኮታቸው ሆነው ከማየት ውጪ ሳይደርሱላት ቀሩ(ለቪዲዮእዚህይጫኑ)በግድና በጉልበት መንገደኛው እንደ ትርኢት ጉዱን እያየ፤ የቆንሲላውም የገዢው ሹሞች ድርሽሳይሉላት፤በጠራራ ጸሃይ ታፍና በመኪና ተወሰደች፡፡ ከቀናት በኋላም፤የሊባኖስ ባለስልጣናት፤ኢትዮጵያዊቷ ዓለም በነበረችበት የስነልቡና ታካሚዎች ሆስፒታል ውስጥ እራሷን መግደሏን ይፋ አደረጉ፡፡ባለፉት ጥቂት ቀናት ኢትዮጵያዊያን የመን ከሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን እርዳታ ለማግኘት በሄዱበት ጊዜ በየመን ፖሊሶች በአደባባይ እንደተደበደቡ ተዘግቦ ነበር፡፡ ከነዚህም ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መሃል 25ቱ ለእስር ሲዳረጉ፤ ሌሎች ደግሞ በየመን ሰብአዊ ምት ጠባቂ ቢሮ ለአቤቱታና ለደህንነታቸው ጥበቃ ለመጠየቅ ቢሄዱ ዳግም በየመን ፖሊስ የዱላ ናዳ ወርዶባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ፤ በሱዳን፤በደቡብ አፍሪካም በሕግ አስከባሪፖሊሶችና በጎዳና የሃገሬው ጉልበተኞች ግፍና መከራ ደርሶባቸዋል፡፡በዓለም ላይ መብታቸውን የተገፈፉና መድረሻ ያጡ፤በሃገራቸውም እንደዜጋ፤ በስደትም እንደ ሰብአዊ ፍጡር ሕልውናቸው ተገፎ ለመከራና ለስቃይ የተዳረጉሕዝቦች ኢትዮጵያዊያኖች ናቸው፡፡

በቅርቡ አዲሱ አሳዛኝና የበደል በደል የሆነው፤የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የግፍ ዜና ደሞ የተሰማው ከኖርዌይ ነው፡፡ሰሞኑን የኒርዌይ መንግስት፤የግዴታ ምልሰት፤(forced deportation) በሚል አዲስ አስገድዶ ወደ መጡበትለመመለስ ባወጣው ደንብ፤ ከመቶ እስከ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ስደተኞችን፤ወደ ኢትዮጵያ ሊመልስ ነው፡፡ እንደሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ዘገባ፤እነዚህ ኢትዮጵየዊያን ስደተኞች ላለፉት በርካታዓመታት በኖርዌይ በስራ ተሰማርተው እንደነበር ያስረዳሉ፡፡እነዚህ ስደተኞች በመጀመርያ ወደ ኖርዌይ ሲገቡ በሃገሩ መንግሥት የስራ ፈቃድ ደብተር በህጋዊ መንገድ ተስጥቷቸው እንደነበርና፤ በኖርዊጂያን ሕብረተሰብ መሃልሠርተው እንዲኖሩ መብት አግኝተው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ስደተኞቹ ኢትዮጵያዊያንም፤የሃገሪቱን ቋንቋ አጥንተው፤ከባሕሉ ጋር ተግባብተውና ተስማምተው በመኖር ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህ ለመከራ የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችመሃልም፤በኖርዌይ የተወለዱና ለበርካታ ዓመታት የስደተኛነት ፍቃድ ጠያቂዎች ማእከል ውስጥ የሚኖሩ 450 ሕጻናት ይገኙበታል፡፡ከሕጻናቱ መሃል በርካታዎቹ ከኖርዌጂያን ቋንቋ ውጪ አያውቁም፤ ሕጻናቱ በሙሉትምህርታቸውን በመከታታል ላይ ያሉ ናቸው፡፡

እነዚህ ስደተኞች በሃገራቸው ያለውን ግፈኛና ጨቋኝ የመለስን ገዢ መንግሥት መከራ ለማምለጥ በጥፍራቸው ቆመው፤እድላቸውን ብቻ ተስፋ በማድረግ እግራቸው እስኪላላጥና፤ችጋር በስቃይ ቆልቷቸው የስደት ዓላማቸውየተሳካላቸው ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹም የመለስን ግፈኛና ዘረኛ፤ ፈላጭ ቆራጭ፤ አምባገነን መንግሥት ተቃዋሚዎች ናቸው ፡፡ በአለፈው ኦክቶበር 2011 በኦስሎ የተካሄደውን የኤነርጂ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ የመለስንበስብሰባው ላይ መገኘት በመቃወም፤በሃገራቸውና በወገናቸው ላይ የሚደርሰውን ግፍ ፈጻሚውና አስፈጻሚው መለስ የተባለ ነቀርሳ መሆኑን በማጋለጥ፤ በኦስሎ ከተማ አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ናቸው (ለቪዲዮእዚህይጫኑ) በኖርዌይ ያለውን ነጸነት፤ የሰብአዊ መብት መከበር፤ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት መሰረተ በማድረግ፤ላለፉት በርካታ ዓመታት በዓለም ዙርያ ያሉ ኢትዮጵያውያን የሚያነሱትን ርእሰ ጉዳይ በመቀላቀል ይሳተፉየነበሩ ቀንደኛ ተቃዋሚዎችና ለሃገርና ለሕዝብ የቆሙ ስደተኞች ናቸው፡፡

‹‹የመግባቢያው ስምምነት ሰነድ››

የዚህ አስገድዶ ወደ መጡበት የግፍና የመከራ፤ ከዚያም አልፎ ለሞት አገዛዝ ወዳለበት መመለስ መሰረቱ፤የመግባቢው ስምምነት ሰነድ (MOU) (መ ስ ሰ) መፈራረም ነው፡፡ይህ ስምምነት የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብትን ድንጋጌበተመለከተ፤ወደ መጡበት መመለስን የሚያመላክተውን አንቀጽ ሰበብ በማድረግ በግፈኛውና ዘረኛው መለስ ዜናዊና፤በኖርዌይ መንግሥት መሃል የተፈረመ ነው፡፡ የስምምነቱ አላማም የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ወደ መጡበትየሚመለሱትን መብት እንዲያከብር ይላል፡፡የምልሰቱንም ሂደት በተመለከተ የኖርዌይ መንግስት አስፈላጊውን ቁጥጥር ማድረግ፤ ድጋፍ መስጠትን፤ለኢትዮጵያ ግፍኛና ፈላጭ ቆራጭ መንግስት እንደሚያደርግ ስምምነት ተደርጓል፡፡በፍቃደኝነት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የተስማሙት በሙሉ ሃገራቸው እንደደረሱ የተወሰነ የገንዘብ መቋቋሚያ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡

በጣም አሳፋሪውና አሳዛኙ ጉዳይ ደግሞ፤በመስማሚያውሰነድ ተለጣፊ ሰነድ (annex) ቁጥር 3 ላይ የሰፈረው ነው፡፡ ‹‹ የኖርዌይ መንግሥት ስለኢያንዳንዱ ተመላሸ ስደተኛ የግል ታሪክ፤ፓስፖርት፤ማንነት (ዘር) የመንጃ ፈቃድ፤ በአዲስ አበባ በሚገኘው የሮያል ኖርዌይ ኤምባሲ ቢሮበኩል ለመለስ ግፈኛ መንግስት የስለላ ድርጅት ቢሮ እንደሚሰጥና ሁሉንም ሂደትና አፈጻጸም በተመለከተም የኖርዌይ ፖሊስና ደህንነት ቢሮ እንደሚከታተል ይገልጻል፡፡ይህም ማለት የእያንዳንዱ ተመላሽ ስደተኛ ማንነትና ተግባርከታወቀ በኋላ ለወህኒ መዳረግንና ግርፊያን፤መከራን ያስከትላል፡፡በዚህም የኖርዌይ መንግሥት ለዘረኛውና አምባገነኑ መለስ የደህንነትና የቁጥጥር ስራ እየሰራለት ነው ማለት ነው፡፡

ስምምነቱ እንደተፈረመ ወዲያው፤የኖርዌይ ዓለምአቀፍ ልማት ሚኒስትር ኤሪክ ሶልሄይም የመለስ ገዢና ግፈኛ ኢሰብአዊ፤ጸረ ዴሞክራሲ፤ ፍትህ አልባ መንግስት 350 ሚሊዮን ክሮነር ዓመታዊ እርዳታ እንደሚመጸወት አስታወቀ፡፡(ይህ ሁኔታ እነደአዲስ ሊያስገርመን አይገባም፡፡ በዘመነ ደርግ ቤተእስራኤሎችን የማጓጓዙ ሂደት ላይ የመንግሽትን ይሁንታ ለማግኘት 35 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ክፍያ ተፈጽሟል፡፡ይህም ስደተኞችን በዘመናዊ የኖርዌጂያዊ ዘዴ የስደተኞችሽያጭ መሆኑ ነው፡ ኖርዌይን ያህል ሰላማዊ ነኝ ብሎ፤ የሰብአዊ መብት ሊከበር እንደሚገባ የሚዘምር መንግሥት፤በሕዝቡ ሳይሆን በግዴለሽ ባለስልጣናት እንዲህአይነት ተግባር መፈጸሙ የሚያሳዝን ነው፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ በርካታ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤የኖርዌይ የተለያዩ የፖለቲካ መሪዎች፤የሃገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ግለሰቦችም ስለ ምልሰቱ የጠነከረ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነድ ወይስ ስደተኞችን ሽያጭ

በቅድሚያ ሊብራራ የሚገባው ጉዳይ አለ፡፡ በማንኛውም የዓለም አቀፍ የሕግ ዘርፍ፤ይህ የመግባቢያ ሰነድ በጭራሽ የስደተኞች በግዳጅ የመመለስ ስምምነት ሰነድ ሊባል አይችልም፡፡በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሰረት፤ የመግባቢያሰነድ በዋናነት ሊጠቀስ የሚችል የሕግ ሰነድ ነው፡፡ይህም ብዙ የስምምነት ሰነዶች አካል(treaty) ሊሆን ስለሚገባ በተባበሩት መንግሥታት ጽ/ቤት ተመዝግቦ እውቅና ሊያገኝ የሚያስፈልገው ነው፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድበሚገባ በሥራ ላይ ከዋለ እንደመደበኛ የስምምነት ሰነድ ሊያገለግል ይችላል፡፡ይህ ሰነድ ዋስትና ነው አይደለም ለሚለውም ዓለም አቀፉ ደንብ በሚጠይቀው መሰረት በሁለቱ ተስማሚዎች መሃል የሚኖር ውለታ ነው፡፡

የኖርዌይ መንግስትና ግፈኛው የመለስ ገዢ ስርአት ውለታ የተግባቡበት ያላዋቂ ሳሚ አይነት ሙንጫሪ እንጂ ሰነድ ነው ለመባል ያላሟላው ግድፈት ስላለበት ሕጋዊ ሰነድ ሊባል አይችልም፡፡የሞራል ልሽቀትን ለመሸፈኛ፤ይህንንምተጠቅሞ ለሰው በላውና ግፈኛው መለስ ዜናዊ ወህኒ ቤቶችና ከፍ ብሎም ጣታቸው የመሳርያቸውን ቃታ ለመሳብ፤ሰብአዊ ፍጠርን ስብእናውን አሳጥቶ ለመግደል፤ጣታቸውን ለሚያሳክካቸው፤ የመግደል ሱሰኞች፤ የመለስአገልጋዮች ለማስረከብ የተነደፈ ነው፡፡

‹‹የመለስ ወህኒ ቤቶች ግፍና በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰው በደል በሰፊው የተነገረለትና የታወቀ ነው›› ሰነዱ በቀድሞው አጠራር ‹‹የጨዋ ሰዎች ስምምነት››(gentlemen’s agreement) አለያም‹‹የሰነድ ልውውጥ›› (exchange of notes) ይባል የነበረው አይነት ነው፡፡(በግምትና በምናልባት ላይ የተመሰረተ ሃሳብ ነው፡፡) ሊሆን ይችላል በሚል ግንዛቤ የተቀረጸ ስለሆነ ጨርሶ ግዴታ አያስገባም፡፡በመለስና በኖርዌይመንግስት መሃል የስደተኞችን ደህንነትና ቀጣይ ሰላማዊ ኑሮን በተመለከተ አንዳችም ዋስትና ያላዘለው ይህ ሰነድ፤የኖርዌይ መንግስት በሃገሩ በሕጋዊ መንገድ ገብተው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ሕግ በሚጠይቀው መሰረት ዛሬ ነገእየተባሉ፤ መልስ በመጠባበቅ ላይ ያሉትን ኢትዮጵያዊያን፤ለመለስ የግፍና የኢሰብአዊ አገዛዝ አሳልፎ በመስጠት ባለፈው በመሃላቸው ለተፈጠረው አለመግባባት ማለዘቢያ ማድረግ ነው፡፡ ሰነዱ አንድ ጊዜ በአውሮፕላን ተጭነውለግፍና ለመከራ ድርጎ ከተራገፉ በኋላ አንዳች መብት ማስከበርያ አለያ የመለስን መንግሥት ለተጠያቂነት የሚያበቃ ቃል የለውም፡፡ የኖርዌይ መንግሥት ከሃገሩ አውጥቶ ለጅብ መንጋ ካስረከበ በኋላ ተበሉ አልተበሉ፤ተነከሱ አልተነከሱ ጠፉ ኖሩ ጉዳዩ አይደለም፡፡ ምናልባት፤ የኖርዌይ መንግሥት ይህን ሰነድ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ሊለው ይችላል፤ቀሪው ዓለም ግን ‹‹ስደተኞችን ለንዋይ›› አለያም ሰብአዊ ፍጡሮችን ለተፈጠረአለመግባባትና ቁርሾ ማለዘቢያ ከማለት ውጪ ምንም ብሎ ሊጠራው አይችልም፡፡

ጠቦቶችን ለቀበሮ መንጋ ማቅረብ

ኔቪል ቻምበርሊን፤ በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ዋዜማ፤ በጀግንነትና በድል አድራጊነት ‹‹ይህ ውል ሁለቱ ሃገሮች ወደ ጦርነት እንዳይገቡና ከጦርነት እንዲርቁ የተፈረመ ነው………ስሙ የሰፈረበት ሰነድ ይሄው፤የኔም ስምአለበት……››ብሎ ተናገረ፡፡ወዲያው ግን የሙኒክ ውለታ ወይም ስምምነት፤ ከተጻፈበት ወረቀት ያነሰ ዋጋ ያለው እንደነበረ ለመገንዘብ ተቻለ፡፡ ሂትለርም በቻምበርሊን የስላቅ ሳቅ ሳቀበት፡፡

የራሱን ሕገ መንግሥት የረገጠና የጨፈለቀ ራሱ ያወጣቸውን ሕግጋት የጣሰ እና የደመሰሰ ፤ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ ያሾፈናያላገጠ፤ በአሰርትሺ የሚቆጠሩ ዜጎችን ለእስርና ለመከራ የዳረገ፤ በምርጫ 99.6 በመቶ አሸነፍኩ ብሎ ከሰውም አልፎ ለራሱ የዋሸ፤ የአጠቃላይ ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን እንቅስቃሴ የገታ፤ጋር መዋዋል ዘበት ነው፡፡ በጣም መጥፎ የሆነ አላዋቂነት ላይ የተመሰረተ ክህደት ነው፡፡አለያም የኖርዌይ መንግሥት ስለ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ደንታቢስ መሆኑንና ለወደፊትም ኖርዌይን ለስደት የሚመኙትን ተስፋ በማስቆረጫነት ለመጠቀም የተዘረጋ መረብ ነው፡፡

ይህንን የመግባቢያ ሰነድየኖርዌጂያን መንግሥት የስደት ተቀባይነት ላጡ ኢትዮጵያዊያን እንደ ‹ሰብአዊ›› እና ‹‹የክብር›› የምልሰት ‹‹ሰብአዊ ቅልቅል››በመጥራቱ መሳቂያና መሳለቂያ ነው የሆነው፡፡የኖርዌይ መንግሥት ረዘም ያለየቅሌት መንገድ ተጉዞ፤ዓለም ይህን የስምምነት ሰነድ ‹‹የሰብአዊነት መልሶ መቀላቀያ›› ቢለውም በመጨረሻው ግን ግፈኛውና ፈላጭ ቆራጩ ዘረኛው መለስ ዜናዊ፤በኖርዌይ መንግስትና ባለስልጣናት ሞኝነትና፤ ባሳዩት የሞኝአመኔታ እንደአምሳያው ሂትለር ፍቅፍቅ ብሎ ይስቅባቸዋል፡፡ ወደ ሃገራቸው በመገደድ የተመለሱትም ኢትዮጵያዊያን በመለስ የማጎርያ ወህኒዎች ተመልካች አጥተው ለተለያዩ መከራና ስቃይ ተዳርገው እምባዎቻቸው አልቀው፤ደም ያጎርፋሉ፡፡ በዚህ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድም የኖርዌይ መንግሥት የእነዚህን ተመልካች ያጡ መከረኛ ኢትዮጵያዊያን በብርና እንቁ ያጌጠ ሰሃን ላይ አድርጎ ለመለስ ዜናዊ የቀበሮ መንጋ በዳረጎት መልክ አቅርቧል፡፡ዕውነታው በምንም መልኩ አጠያያቂ አይደለም፡፡

በኢትዮጵያ ወቅታዊውና ትክክለኛው ሁኔታ፤ በዓለም ላይ ባሉ በአብዛኛዎቹ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና በዓለም ግንባር ቀደም መገናኛዎች የታወቀና የተሰራጨ ነው፡፡ሃቁ ያማይታበልና በአጭሩ በሁማን ራይትስ ዎች የ2012 ስለኢትዮጵያ ሁኔታ የቀረበ ነው፡፡ የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ እንዲህ ብሏል

የኢትዮጵያ መንግሥትና ባለስልጣናት መሰረታዊ የሆነውን ራስን በነጻ የመግለጽ መብትን፤ የዜጎችን የሰላማዊ ሰልፍ መብት እየገደቡት ነው፡፡በ2011 በርካታ ኢትዮጵያዊያን በግፍ ታፍሰው ለእስር ተዳርገዋል፤እስከአሁንድረስም ለግፍ ተዳርገው፤በስቃይና በመከራ በእስር ላይ ናቸው፡፡ክስ ሳይመሰርትባቸው፤በመታሰርና በተለዋጭ ተጨማሪ ቀጠሮ በመጉላላት፤ከጠበቆቻቸ ውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ግንኙነት ተከልክለው፤በተለይሽብርተኛነትን ለመከላከል በወጣው አዋጅ መሰረት፤መብትን እንደፈለጉ መንፈግ በመቻሉ፤በዚያ እየተጠቀሙ ታሳሪዎችን ለግፍ ያበቃሉ፡፡ይህንንም እስከ አራት ወራት ድረስ ለመጠቀም አዋጁ ይፈቅዳል፡፡ በ2009የጸደቀው አዋጅም፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ሃገር በቀል እርዳታ ለጋሽ ድርጅቶችን፤ከ10 በመቶ በላይ የውጭ እርዳታ ማግኘት የሚያግድ በመሆኑ፤ምንም አይነት ጠቃሚ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ አግዷቸዋል፡፡ ሃገር በቀሉምሆነ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጨርሶ ወህኒ ቤቶችን መጎብኘት አይችሉም፡፡በእስራት ላይ የሉትን የፖለቲካ አስረኞችም ይሁን ሌሎች ታሳሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አዳጋች ነው፡፡

በኖርዌይ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ በማንዣበብ ላይ ያለው ተጨባጭ ፍርሃት

ኖርዌይ ስለ ስደተኞች ያላትን ሕግ ለኖርዌይ ሕገደንብና የፍትሕ ስርአት የሚተው ይሆናል፡፡ያም ሆኖ ግን የኖርዌይ የስደተኞች ሕግጋት በ1951 እ አ አ የተደነገገውንና በ ማርች 23 1953 የጸደቀውን፤ በ1967 የተሸሻለውንየስደተኞች መብት መጠበቂያ ዓለም አቀፍ ደንብን ግን ያከበረ ሊሆን ይገባል፡፡

የኮንቬንሽኑ ቁጥር 1 ስደተኛን በተመለከተ ‹‹በተጨባጭ ማስረጃ በዘሩ፤ በሃይማኖቱ፤በብሔሩ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት፤የአንድ ስብስብ አባል በመሆኑ፤ከትውልድ ሃገሩ በመሰደድ በሃገሩ ላይ ሰብአዊ መብቱ የተጠጋውን ስደተኛነው››ይለዋል፡፡›› ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችም ይህን ደንብ አጣቅሰው ነው ክርክራቸውን የሚያቀርቡት፡፡

በኮንቬንሽኑ ቁጥር 33 (1) መሰረት ‹‹በጎሳው፤በሃይማኖቱ፤በብሔሩ፤በፖለቲካ አቋሙ፤ ማንኛቸውም ሃገር ስደተኛውን ለማባረር አለያም ሸሽቶ ወደ ወጣበት ሃገርና ስብእናው ወደሚደፈርበት የአረመኔ ገዢዎች ወደሚገዙበት ሃገሩመልሶ ሊልከው፤እንዲሄድ ሊያስገድደው ጨርሶ አይገባም፡፡›› አስገድዶ ወደመጡበት መመለስን ዓለም አቀፉ ሕጋዊ ተቋምም በጽኑ የሚያወግዘውና የሚቃወመው ተግባር ነው፡፡ ይህ ሲጣስ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችኮሚሽን ጣልቃ ገብነት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ በኖርዌይ የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ጉዳይ ግን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ጣልቃ ገብነት የታሰበበት አይመስልም፡፡

በኖርዌይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዘራቸው፤በሃይሞነታቸው፤በብሔራቸው፤ባላቸው የፖለቲካ አቋም፤ የተነሳ በሕይወታቸው ላይ ሊደርስባቸው የሚችለውን ከፍተኛ ስጋት በተመለከተ ከኮነቬንሽኑ ድንጋጌ በመነሳት ሕጋዊየመብት ጥያቄን ያስነሳል፡፡ ተቀባይ ሀገራት፤አለያም ስደተኞቹ ያሉበት የስደት ሃገር፤ሊያጣራ የሚገባቸው ጉዳዮች በግልጽ በኮነቬንሽኑ ላይ ሰፍረዋል፡፡የሃገራቱ የስደተኞች ሕግ መመርያ የስደተኛውን የትውልድ ሃገር ወቅታዊ ሁኔታማጣራት እንዳለበት ያመለክታል፡፡ማስረጃዎችን የማቅረቡ ግዴታ በስደተኛው ላይ የሚጣል ሲሆን፤የማስረጃው ክብደትና ጥንካሬ በስደት ወቅት ግን ያለምንም ጥርጣሬ የስደተኛውን ፍርሃት እርግጠኛነት ላይሆን እንደሚችልሳይሆን ሊሆን እንደሚችል መቀበልን ይጠይቃል፡፡

የግፈኛውን የመለስ ዜናዊን ተለዋዋጭና እስስታዊ ፤የዲክታተርነት ባሕሪው በየወቅቱ እየባሰ ማደግ መሰረት ባደረገ መልኩ፤ኢትዮጵየዊያን ስደተኞች ላይ ሊደርስባቸው የሚችለውን ስቃይ መከራና ፍዳ፤ ከኢትዮጵያውያን ውጪላሉ በማረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብና ማሳመን አስቸጋሪ ነው፡፡ መለስ ካለራሱ ስልጣንና ጥቅም ውጪ የማየት ችሎታው ስለጠፋበት፤ለውጭ ሰዎችና ለሃገር ውስጥ ሕዝቦች ካባውን መቀያየሩን ያውቅበታል፡፡ ሃሰቱን እውነትለማስመሰልም ከራሱ ጤፍ ከሚቆላ ምላሱ ባለፈ፤ ሌሎችን በመቅጠር ተሟጋቾች እያቆመ፤የውጪውን ዓለም ሲያታልል፤ ሲያስመስል፤የከረመና አሁንም ያለ ነው፡፡ እነዚህ ስደተኞች ሃሳባቸውን ባሉበት ሃገር ላሉ ባለስልጣናትበቋንቋቸው ማስረዳት ባለመቻላቸው፤ ሕጉን ካለማወቅ፤የእያንዳንዱን የድርጊት ቀናት በውል ካለማስታወስ፤ቅደም ተከተልን ካለመገንዘብ የተነሳ በዘገባ አቀራረብ ላይ መመሳቀል ሳቢያ፤ያላሟላና የማያሳምን ለማለት ቀላል ነው፡፡ኮንቬንሽኑ በስደተኞች ጉዳይ ሂደት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን አንዳንድ ድክመቶች በማገናዘብ፤ስደተኛውን በመደገፍ ለውሳኔው ቀናነት መቆምን መሰረት ማድረግ እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡

በኖርዌይ መንግሥት በግዴታ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ በሚደረጉ ስደተኞች ላይ ምን ሊደርስባቸው ይችላል?

የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ይኑርም አይኑርም፤የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደሃገራቸው እንደተመለሱ በግፈኛው ገዢ መንግስት ጫና እንደሚፈጠርባቸው፤ ለእስርና እንግልት እንደሚዳረጉ አያጠያይቅም፡፡ ካላንዳች ጥርጣሬበዚህ የግዳጅ ምልሰታቸው መብት አልባ ይሆናሉ፡፡ ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ መብት አላቸው ቢልም( የኢትየዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 13 (የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን፤ያካትታል፡፡) በፍጹም ሕገመንግስታዊ መብታቸው አይከበርላቸውም፡፡ሃሳብን የመግለጽና የነጻው ፕሬስ በታገደበት ሃገር፤የሚደርስባቸውን በደል አቤት የሚሉበት ጨኸታቸውን የሚያሰሙበት መንገድ አይኖራቸውም፡፡ ፍትህ በተዋረደበትና በዘቀጠበትምድር፤ፍትሕን ያገኙበትና፤ የሚደርስባቸውንም በደል የሚሞግቱበት መንገድ ጨርሶ የማይታሰብ ነው፡፡ የሲቪል ማሕበራት ተቋማት በታፈኑበት፤ማንም ሊቆምላቸው አይችልም፡፡የሕግ የበላይነት በማይተወቅበት፤ፈላጭቆራጭነት በነገሠበት፤ የዘር መድልዎ በተንሰራፋበት፤ አድልዎና ማንአለብኝነት በተዘረጋበት የመለስ ግዛት፤ያለጥያቄ አንድ ባንድ እየታገቱ ለሥቃይና ለመከራ ይጋለጣሉ፡፡ እነዚህ በግዳጅ ለምልሰት የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን፤መብታቸውን የሚያስከብሩበት ምንም ዘዴ የላቸውም፡፡በኢትዮጵያ፤ሕግ እራሱን ከሕግ በላይ አድርጎ በኮፈሰው አንድ ሰው እጅ ነው ያለው፡፡በግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ መለስ እጅ!

መለስ ዜናዊ አካሄዱን ሁሉ፤በተንኮልና በንፉግ ስሌት እያሰላ፤ወደ ተንኮል ማስገቢያ ዘዴዎች ብቻ፤ህልምና ቅዠቱ የሆኑ፤ቆሞም ተቀምጦም ለጥፋት ተግባር የቆመ፤ጉድለተ ብዙ የሆነ ግለ ሰብ ነው፡፡የነዚህ ስደተኞች ዜና ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ከሕዝብ ግንዛቤ እንደሚርቅ ያውቃል፡፡ስለ ደህንነታቸውም ሆነ ስለ ሁኔታቸው የሚከታተል አይኖርም ብሎም ያስባል፡፡የነዚህን ስደተኞች ጉዳይ የሚከታተልና መብታቸውንየሚያስከብርላቸው አንድም ተቋም እንደሌለና፤የነበሩትንም ሰንክሎ እንደአገዳቸው ያውቃል፡፡ መለስ ዜናዊ ጊዜውንና ወቅቱን በእኩይ ሚዛን መርምሮ ያገናዝባል፡፡ማንም ትኩረት በማይሰጥበት ጊዜ፤እነዚህን ተገደው የተመለሱስደተኞች፤አንድ ባንድ እያሳፈነ ለመከራ ይዳርጋቸዋል ያጠፋቸዋል፡፡ያ ነው የመለስ የስምምነት ሰነድ ውጤቱ፡፡በቅድሚያ በእርግጠኛነት መተንበይ እንደሚቻለውም ከአንድ ዓመት በኋላ በጣት የሚቆጠሩ ተመላሽ ስደተኞች ብቻበሕይወት ይተርፋሉ፡፡

የ ኖርዌዩ የመግባቢያ ስነት (MoU) እንደ ኢትዮጵያው ሕገመንግሥት ሁሉ፤ከባዶ ተስፋና፤ ከማይጨበጡና ትርጉም አልባ ከሆኑ ቃላት ውጪ፤ሌላ የሚያስገኘው ጥቅምም ሆነ ቁምነገር የለውም፡፡ በመለስ ዜናዊ ፈላጭ ቆራጭአስተሳሰብና ዙፋን ፊት፤በጣም አናሳ የሆነ ትርጉም ብቻ ነው የሚኖራቸው፡፡ የስደተኞቹ ሕገመንግስታዊ ጥበቃ በቅዠት ላይ እንደተመሰረተው ሁሉ በመግባቢያ ሰነዱም (MoU) ላይ የሰፈረውም አርቲ ቡርቲ እንደዚያው ነው፡፡ይህ ሰነድ(MoU) ወደፊት ታሪክ እንደሚመሰክረው ከብጣሽ መጫርያ ወረቀት የተለየ እንደማይሆን የታወቀ ነው፡፡

ስለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዶ/ፍሪድትዮፍ ናንሰን ምን ያደርጋሉ?

ኖርዌይ በብዙ ታላልቅ ጉዳዮች ትታወቃለች፡፡–በዓለም አቀፍ የኖቤል ሽልማት፤በዓለም አቀፍ የሰላም እና የኦስሎ አኮርድ፡፡በ2007 እ አ አ ኖርዌይ በዓለም በከፍተኛ ደረጃ የሰላማዊነት ክብር ተጎናጽፋ ነበር፡፡በዓለም ዙርያም ላሉ ስደተኞች በምታደርገው ሰብአዊ ድጋፍም ጭምር ትታወቃለች፡፡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ማግስት አንስቶ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል ለተፈናቀሉ፤በሃገራቸው የነበረው አስከፊ ስርአት በዴሞክራሲበመተካቱ፤ሰብአዊ መብቶች በመከበራቸው፤ፍትሕ በአግባቡ መተርጎም በመጀመሩ ወደ ትውልድ ሃገራቸው በፈቃደኝነት ለተመለሱት ድጋፍና እገዛ ችሯል፡፡

የስደተኞችን ጉዳይና ስደተኞችን መርዳት በተመለከተ፤ ለስደተኞች ዘላቂ መፍትሔን በመሻትና ተግባራዊ ማድረግን አስመለክቶ የኖርዌዩን ተመራማሪ፤ሳይንቲስት፤ዲፕሎማት፤ሰብአዊ አገልግሎት ሰጪ፤ ዶር ፍሪድትዮፍ ናንሰንንየሚስተካከል የለም፡፡ዶ/ር ናንሰን፤በ1922 እ አ አ ሃገር አልባ በሆኑ ሰዎች ስም (የ‹‹ናንሰን ፓስፖርት›› በመባል በዓለም አቀፍ ታዋቂ የሆነው ለሃገር አልባ ሰዎች የሚሰጥ መታወቂያ) የዓለም የሠላም ሽልማት ተሸላሚ ለመሆንበቅቷል፡፡የዶር ናንሰን ተግባርና እንቅስቃሴ፤በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሩስያውያን፤ የግሪኮችን የቱርኮችን፤ የአርመናውያንን፤ ሕይወት አድኗል፡፡ በቅርቡም የኖርዌዩ ተወላጅ ኳስ ተጫዋቹ ቢዮርን ሄይደንስቶርም በስደተኞች ሕይወትለውጥ ለማምጣትና ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሲል ዓለምን በቢስኪሌት ዞሯል፡፡ ታዋቂው ኖርዌጂያዊው ደራሲ ያን ኪየርስታድ የኢትዮጵያዊያንን ስደተኞች ጉዳይ አስመልክቶ በሚገባ ገልጾታል፡፡‹‹ከቢሮክራሲያዊ አካሄድ አኳይ የተፈጸው ተግባር ልክ ነው፡፡(ለምልሰት መዳረግ) ያም ሆነ ይህ ግን ለዚህ የግብር ይውጣ ውሳኔና ትግበራ አንድ ቃል ብቻ ነው መገለጫው፡ ያሳፍራል፡፡››

ዶር ናንሰን ስለ መግባቢያ ስምምነቱ (MoU) እንዲያውም ስለ ስደተኞችን በሽያጭ (RfC) ቢያዩ አለያም ቢሰሙ ምን ሊያደረግ እንደሚችሉ ሳስብ ይገርመኛል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀንስ ስቶልተንበርግን አንድ ጥያቄ መጠየቅ ብችል የምላቸው፡ ዶር ናንሰን የእርስዎን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ምን ያደርጉ ነበር? ዶር ናንሰን በጣም እርግጠኛ ነኝ ለኖርዌጂያን ወገኖቻቸው ‹‹የሞራል ቁጣ ሲገደድ›› በሚል ሌላ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ያቀርቡላቸዋል፡፡

እሪ ይበል ወንዙ፤ እሪ ይበል ሃይቁ!

Monday, March 19th, 2012

ከዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ከሶስት ዓመታት ቀደም ብሎ ‹‹እሪ በልልኝ ሃይቁ፤ በተፈጥሮ ላይ የተፈጸመ ወንጀል››በሚል ርዕስ ሳምንታዊ መጣጥፍ አቅርቤ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜው መጣጥፌ ያተኮረው በወቅቱ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ላይ በ50 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኘውና በአንድ ወቅት በጠቃሚ ወንዝነቱ ይታወቅ የነበረውን አሁን ለብክለት የተዳረገውን የቆቃን ሃይቅ ውሃ በመጠጣት፤ለበሽታና ለሞት የተጋለጡትን በአሰርት ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ሕለፈት በተመለከተ ነበር፡፡ በእንግሊዝ ሃገር በሚገኘው የዱርሃም ዩኒቨርስቲ የሚገኙት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ሳይንቲስት የቆቃን ውሃ ከመረመሩ በኋላ፤‹‹በጣም ከፍተኛ የሆነ ‹‹የማይክሮኪሰቲስ ባክቴርያ›› የተከማቸበት መሆኑንና፤ይህም የሰውን ልጅ በከፍተኛ ደረጃ ለጉዳት የሚያጋልጥ እንደሆነ ይፋ አድርገው ነበር፡፡የኔም የሙግቴ መነሻ የሆነው ይህ አገላለጥና ያደረሰው፤ እያደረሰ ያለውና ወደፊትም ሊያደርስ የሚችለው ሕዝባዊ ጉዳት አሳስቦኝና ወገንም አሳዝኖኝ ነበር እሪታ ያሰማሁት፡፡

በቆቃ ሃይቅ ላይ ያጋጠመው እልቂት የችግሩ መንስኤ ብቻ ነው፡፡ኢትዮጵያ የዓየር ብክለት ጥፋት እየደረሰባት ነው፡፡የጫካዎች መውደም፤የአፈር መሸርሸርና በዝናብ መታጠብ፤የሕዝብ ቁጠር መጨመርና የመሬት ሰብል መንሳት፤የዚሁ የዓየር ለውጥ ያመጣቸው መዘዞች ናቸው፡፡የኢትዮጵያ የእርሻ ምርምር ተቋም ኢትዮጵያ በየዓመቱ 200.000 ሄክታር የደን መሬቷን እንደምታጣ አስታውቋል፡፡ምናልባትም ይህ ሂደት ካልተገታ፤ከ 11 ዓመታት በኋላ በ2020 ኢትዮጵያ አጠቃላይ የደን ሃበቷን ታጣለች፡፡

የግቤ ግድብ፤ ግድቡና የተገደቡ ኢትዮጵያዊያን

ልክ በቆቃ ሃይቅ ላይ ለሞት እንደተዳረጉት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፤በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ኦሞ ወንዝ አካባቢ የሚኖሩት ሕዝቦች፤የከባቢ ዓየር ተጎጂ በመሆን ለችጋር መጋለጥ፤ለስደት መዳረግ ሳይሆን፤በሚደርሰው እልቂት ሕዝቡ ከምድረገጽ መጥፋት ሊደርስ ይችላል፡፡ይህ ደግሞ በመላ ምት የተባለ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ወንዞች በመባል የታወቀ ‹‹የአካባቢን ሁኔታ፤የሰበአዊ መብት ጥበቃ ድርጅት፤ተግባሩም ‹‹የአካባቢን ወንዞቸንና የወንዙ ተጠቃሚ የሆኑትን ነዋሪዎች መብት ጠባቂ ድርጅት›› የሰጠው ጥናታዊ መረጃ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

የኦሞ ወንዝ፤በደቡብ ምዕራብ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኬንያዊያን፤የሕይወታቸው መሰረት ነው፡፡አሁን በመሰራት ላይ ያለው የግቤ 3 ግድብ ለነዋሪው ጎጂ በሆነ መልኩ የኦሞን ወንዝን ፍሰት ሁኔታ፤የአካባቢውን ሁኔታ አልፎ፤በዓለም የታወቀውን የወንዝ በረሃ የተባለውን የቱርካናን ሃይቅ ፍሰት ጭምር በአደገኛ ሁኔታ ይለውጠዋል፡፡የታችኛው ኦሞ ሃይቅ በዩኔስኮ የተመዘገበ ታሪካዊ ስፍራ ነው፡፡በአካባቢውም የስምንተ ነገዶች ነዋሪዎች የሆኑ፤ ከ200.000 በላይ አርሶ አደሮች በወንዙና በወንዙ ዳርቻ በመጠቀም እርሻቸውን፤ ለከብቶቻቸውም ግጦሽ በማግኘት ኑሯቸውን ሲመሩ ኖረዋል፡፡አሁን ግን ዕድሜ ለግድብ 3ና ጆሮ እያላቸው ለማይሰሙ፤ አይን እያላቸው ለማያዩ ጭፍን ጨቋኝና ግፈኛ መሪዎች ለእልቂት ተዳርገዋል፡፡

የኦሞ ወንዝና መጋቢ ምንጮቹ የሃይደሮ የመብራት ሃይል ማመንጫነት በመቀየሩ፤ የአካባቢውን ነዋሪ ሕልውና ባላገናዘበን ደንታ ባላስገባ ግፈኛ መልኩ፤ለዓለም አቀፍ አልሚዎች (ኢንቬስተሮች) በመሰጠት ለውጭ ሽያጭ ለሚቀርብ የእርሻ ውጤት ተሰጥተዋል፡፡‹‹ግልገል ግቤ 1››ከዓለም ባንክና ከአውሮፓ ሕብረት የልማት ባንኮች በተገኘ የ300 ሚሊዮን ዶላር ብድር የተገነባ ነው፡፡ከ6 ዓመታት ግንባት በኋላ፤ በ2004 ዓም ሥራውን የጀመረው ግድብ 193 ሜጋ ዋት ያመነጫል፡፡ይህ 63 ስኩየር ኪሎሜትር የፈጀው የግድቡ ይዞታ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩትን 10.000 ነዋሪዎች ለተፈናቃይነት ዳርጓል፡፡ግንባታውን እንደሚያካሂደው ሥራ ተቋራጩ ኢጣልያዊው ሳሊኒ አባባል፤ ‹‹ይህ የግልገል ግቤ1 ተከታይ ነው፡፡ይህ ግድብ ግን እንደሌሎቹ ግድቦች የሃይል ማመንጫ ግድብ ሳይሆን፤ ከግልገል ግቤ የተረፈውን ፍሰት፤በኢፎታ ተራራ ሥር በሚያልፈው የ26 ኪሎሜትር ርዝመት ባለው ቱቦ በመፍሰስ ወደ ኦሞ ወንዝ የሚገባ ነው፡፡ይህንንም ለመገንባት 373 ሚሊዮን ዩሮ ሲፈጅ፤በኢጣልያንና በአውሮፓ የልማት ባንኮች በተሰጠ ብድር የተገነባ ነው፡፡ግልገል ግቤ 3 በታላቅ ግርግርና ሁካታ፤ አሸሸ ገዳሜ በበዛበት የድንፋታ ዝግጅት ፌብሪዋሪ 2010 ሃገሪቱን በመግዛት ላየ ባሉ ገዢዎችና በአጋሮቻቸው ከተመረቀ በኋላ መገርሰሱ ይታወሳል፡፡የአካባቢ ደህንነትና የዓየር ንጽህና ተሟጋቾችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳስባቸው ጊቤ 3 ነው፡፡የኦሞን አካባቢ ተንተርሰው ሕይወታቸውን የሚመሩትን ከ300.000 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ሕይወታቸውን ለከፍተኛ የአካባቢ ብክለት አደጋ ያጋልጣል፡፡ባለሙያዎቹም እንደሚሉት፤ግቤ 3 የወንዙን ስሱ የሆነውን ተፈጥሮ ሊያበላሸው የሚችል መሆኑን አበክረው ያስጠነቅቃሉ፡፡ ሰሚ ካለ!

ጊቤ” የአካባቢ ብክለት ከፍተኛ ቀውስ በመገንባት ላይ

የጊቤ 3 ግንባታ የተጀመረው በ2006 ነው፡፡ የኢትዮጵያ የዓየር ብክለት ጥበቃ ባለስልጣን፤ጊቤ 3ን በተመለከተ ያገኘውን የጥናት ውጤት ይፋ በማድረግ ግንባታውን ፈቅዷል፡፡ዘገባው ዐይና ያወጣ፤ ያፈጠጠ ውሸት፤ቅለመዳ የሆነ የይሁንታ የቅሌት ማሕተም ነው፡፡ ዘገባው ያለአንዳች ይሉኘታና ሃፍረት፤….በግንባታው ሰበብ በጣም መጠነኛ የሆነ የአካባቢ የዓየር ለውጥ ሊከተል ይችላል፤ የግልገል ግቤ ግናባታ አካባቢ ለሰዎች መኖሪያነት ተስማሚ ያልሆነ፤በገዳይ የቢነቢዎች ነፍሳትና የአንቅልፍ በሽታ የሚያስከትሉ ነዳፊ ነፍሳት የሚፈለፈሉበት ነው….. በማለት ለዘመናት ሰዎች በአካባቢው እየኖሩ ሕይወታቸውን ሲመሩ መኖራቸውንም ሊያስክደን ጥሯል፡፡

በ2006 በጊቤ 3 ግድብ አካባቢ የሚኖሩ 253.412…….የእንቅልፍ በሽታ በሚያዙ ነፍሳትና በዳገታማና ቁልቁለት ከባቢው ሁኔታ የተነሳ፤በወደፊቱ ግድብ አካባቢ ነዋሪዎች የሉበትም፡፡ ነዋሪዎች የሚገኙት፤በደጋማው ሥፋራ ከግድቡ ርቆ ባለ ቦታ ላይ ነው………በአናሳው የዝናብ መጠንና በእንቅልፍ በሽታ፤አሲያዦቹ ነፍሳት፤ታይፖኖሶሚያሲስ በሚባለው የከብት በሽታ የተነሳ ለከብቶች ማርቢያም ስለማይሆን በኦሞ ደልደሳላው ስፍራ በጣም አነስተኛ ግብርና ነው የሚካሄደው፡፡አካባቢው በጣም በከፋ መልኩ የወባ ትንኝ ስለሚረባበት በወባ በሽታ ተጠቂዎች በርካታ ናቸው……..ከአካባቢው የተነሱትም ነዋሪዎች ዩኔስኮ ከመዘገበው ክልል የራቁ ነዋሪዎች ናቸው…….አንዳችም ለታሪክ፤ለሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር፤የአካባቢና የታሪክ ምስክርነት ያለው የአርኪዎሎጂ ቅሪት በግንባታው አካባቢ የለም……. በታችኛው ኦሞ በርካታ የከብቶች በሽታ ያለበት ነው፡፡

ይህ በቅጥፈትና በማለባበስ ላይ የተመሰረተው፤ሙያ አልባ የሆነ የአካባቢ ሁኔታ ዘገባ፤ ግንባታው ከተጀመረ ከሁለት ዓመታት በኋላ መውጣቱ ከየአቅጣጫው ውግዘት የደረሰበትና የኢትዮጵያን የአካባቢ ብክለት ጥበቃ ሕግጋት የሚቃረን ነው፡፡ ዘገባውም ከግንባታው መጀመር አስቀድሞ ይፋ ሊደረግ ሲገባው በማን አለብኝነት የሚመራ በመሆኑ፤እንዳሻው ሕግን ጥሶ፤ እውነትን አለባብሶ፤በምርምር መልኩ ሳይሆን በቅጥፈት መልኩ፤ይፋ ሆኗል፡፡የኢትዮጵያ የአካባቢ ብክለት ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ተወልደ ገብረእግኢአብሔር በአካባቢው ላይ የተጋረጠውን አደጋ በማስመልከት፤ጥናታዊ ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የተሰነዘሩትን አደጋዎች፤ያቀረቡትን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሃሳብ በአጠቃላይ በማጥላላት ውድቅ ሲያደርጉ ያላንዳች የጥናት መቃወሚያ ሃሳብ በጭፍንና በድፍረት ተችተዋል፡፡

እነዚህ የዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች ጊቤ 3 የሚገነባበትን ቦታ ከካርታ ውጪ አያወቁትም፡፡እነዚህ ስለጊቤ 3 መገንባት እሪታቸውን የሚያሰሙት ሁሉ ከቦታው በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው የሚገኙ ናቸው፡፡በበኩሌ ጩኸታቸውን ከቁምነገር አልቆጥረውም፡፡ከተቃዋሚዎቹ አንዳቸውም ኢትዮጵያዊ አይደሉም፡፡አንዱ ከኬንያ ሲሆኑ በርካታዎቹ ደግሞ ከአውሮፓ ናቸው፡፡ወደ ስፋረው ሄጃለሁ ያለው አንድ ሰው ነው፡፡ የቢ ቢ ሲ ጋዜጠኛ፡፡እሱ ደግሞ ይህን ሁኔታ በተመለከተ ከአንድ ቀን ባላለፈ ቆይታው ብዙም ሊል የሚችል አይደለም፡፡…….የዚህ የጊቤ መገንባት ተቃውሞ መሰረቱ መሃይምነት ነው፡፡ስለዚህም፤ ይህን ጩኸታቸውን አላስፈላጊ በማለት በቸልታ አልፈዋለሁ፡፡

ነጻ የሆነው የአፍሪካ የማእድን የሥራ ቡድን (ARWG) ከአሜሪካ፤አውሮፓ፤ከምስራቅ አፍሪቃ የተሰባሰቡ ምሁራንና አማካሪዎች፤በተመሳሳይ የግድብ ግንባታና የተፋሰስ ወንዞች ጥናት ያካሄዱና፤ከበቂ ባለፈ ችሎታቸውን ያስመዘገቡ፤ዓለም አቀፍ ተቀባይነትም ያላቸው ጠበብት፤በርካታ ማመሳከሪያዎችና ማስረጃዎች በማጣቀስ ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡አቶ ተወልደ እነዚህን አስተያየት ሰጪዎችና አስተያየቶች ያጣጣሉበት ዋነኛው ምክንያታቸው ልክ እንደ አዘዦቻቸው ለሃገርና ለወገን በአጠቃላይ ለሰብአዊ ፍጡር፤ ጨርሶ ግዴታ የሌላቸው በመሆናቸው እንጂ አምነውበት አለመሆኑን ልባቸው ያውቀዋል፡፡ይህን ካላሉ የመኖር ህልውናቸው ያቆማል፡፡ መባረር፤ መንገዋለል፤ መጣል እጣ ፈንታቸው መሆኑንም ስለሚያውቁና፤አለቆቻቸውን በማስደሰትና ሃቅን በመካድ በሸፍጥ ፈረስ መጋለብን ብቸኛ የመኖራቸው ዋስተሳና አድርገውት ነው፡፡በዚህም ከማንም ይበልጥ ማሃም ያደረጉት እራሳቸውን ብቻ ነው፡፡

በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የቀረበው ዶኩሜንት፤በተሳሳተ መንገድ የተቀረጸና በርካታ ማሳሳቻዎች የተካተቱበት፤አላስፈላጊና ከእውነታ የራቁ ሰንጠረዦች የተሰመሩበት፤ሳይንሳዊ ለማስመሰልና ለማሰኘት ሲባል፤ሁኔታዎች በተጭበረበሩ ቃላት የሰፈሩበት፤ለጋሥና አበዳሪ ድርጅቶችን በማሳመን ገንዘብ ለማጋኛ የተፈጠረ የሃሰት ሰነድ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡

ስለታችኛው ኦሞ ሸለቆ ትክክለኛ የሆነ የአካባቢ ጥናትና ሁኔታ እንደሚያሳየው፤የግቤ 3 መጠናቀቅ፤ኢትዮጵያ፤ኬንያና ሱዳን በወሰን በሚገናኙበት ቦታ ላይ አስከፊና ዘግናኝ የሆኑ አደጋዎች ያስከትላል፡፡….በታችኛው ኦሞ ላይ የሚኖሩት ሕዝቦች ኑሯቸው የተመሰረተው በውሃውና በውሃው ጠርዝ ዙርያ በሚያመርቱት ሰብል ላይ ነው፡፡የምግብ ምርታቸው፤ አሳ ማጥመዳቸው፤የክብቶቻቸው ህልውና ሁሉ የተመሰረተው በኦሞ ወንዝ ላይ ነው፡፡ የግቤ 3 ግንባታ ሲጠናቀቅ ነዋሪው ከፍተኛ የኤኮኖሚ ቀውስ ያጋጥመዋል፡፡ለችጋር፤ለበሽታዎች፤ለሞት ይዳረጋል፡፡

ዩኔስኮ በጁን 2011‹‹ጊቤ 3 የቱርካናን ሃይቅ ስስ የሆነ ተፈጥሮአዊ ሁኔታ በመቀየር ሊያስከትል የሚችለውን አስከፊ ሁኔታ በማስረገጥ ስጋቱን ገልጦና በነዋሪዎች ላይ የሚፈጠረውን አሰቃቂ ኢሰብአዊ ጉዳት በማስረዳት፤የኢትዮጵያ ገዢዎችና ፓርቲያቸው በአሰቸኳይ የግቤ 3ን ግንባታ እንዲያቋርጡ በማሳሰብ፤ግንባታው ህገ ወጥ መሆኑንም፤የሌላን ሃገር ቅርስና ታሪካዊ ተቋም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለአደጋ ማጋለጥ አግባብ እንዳልሆነና፤ተቀባይነትም እንደሌላው አስታውቋል፡፡‹‹ቴሪ ሃታዌይ የዓለም አቀፍ ወንዞች የአፍሪካ ፕሮግራም ዳይረክተር፤በአፍሪካ በመገንባት ላይ ያለው ታላቁና ተወዳዳሪ የሌለው የዘመኑ አጥፊ ግድብ ጊቤ 3 ነው፡፡ ግንባታው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆኑ ነዋሪዎችን ለችጋርና ለግጭት የሚያጋልጥ ግንባታ ነው በማለት ግንባታውን አውግዘዋል፡፡

አምባ ገነኑ ዲካታተር፤የግፍ ማህደር የሆነው፤ለሰብአዊ ፍጡር ደንታ የሌለው፤ግፈኛው መለስ ዜናዊ፤ የጊቤ 3ን ግንባታ በተመለከተ ሲመልስ፤በዘወትር የማጣጣልና የንቀት፤ የማንአለብኝነትና የአካኪ ዘራፍ፤ መኩራራትና ድንፋታ ነው፡፡‹‹እነዚህ የግድቡ መገንባት መቆም አለበት የሚሉ ሁሉ የአፍሪካን ልማት ማየት የማይፈልጉ ናቸው፡፡የነሱን ሀገር ጎብኚ ዜጎች የምናስተናግድ ሙዚያምና ኋላ ቀር ሆነን እንድንኖር የሚሹ ናቸው፡፡››……የመለስ ወኪሎችም ስር ስሩ በመከተል የግንባታውን ሂደት የተቃወሙትን ሁሉ በማጥላላት ውትወታቸውን ተያይዘውታል፡፡ ምእራባውያን ተሟጋቾች በአካባቢ ጥበቃ የሞኖፖል መብት የላቸውም፡፡ወይም በትክክለኛነት ላይ የበላይነት መብት የላቸውም፡፡ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ተሟጋቾች ያልተረጋገጠ መሟገቻ ነው የሚያቀርቡት፡፡››

ሂስ የሚያቀርቡበትን ባልታረመ አነጋገሩ ማጥላላትና ማዋረድ፤ በተራ ስድብና በጋጠ ወጥነት መልስ መስጠት የመለስ ባህሪው ነው፡፡በ2010 በተካሄደው ምርጫ ወቅት መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ አሸነፍኩ ሲልና የድል ከበሮ በመምታት እራሱንና አገልጋዮቹን ሲያታልል፤ የአውሮፓ ሕብረት ምርጫው ዓለም አቀፍ መመዘኛን አላሟላም፤ ባሉበት ውቅት መለስ ሲመልስ፤ ባይመረጥ እንኳን መሪ ነኝ ይላልና፤ለዚያም ለሚለው እንኳን በማይመጥን ተራ የቅሌት ቃል በመጠቀም ‹‹ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ውስጥ መወርወር ያለበት ቆሻሻ ነው፡፡ ዘገባው ስለምርጫው ሂደት ሳይሆን፤የአንዳንድ የገዢውን ፓርቲ ጥንካሬ የማይወዱ አውሮፓውያን ኒዮ ሊበራሎች አስተያየት ነው፡፡ማንም ቀለምና ወረቀት ያለው መጫር ይችላል››…. በማለት ነበር የመለሰው፡፡….ባለፈው ወር ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል ያወጣውን ሰነድ በተመለከተ፤ሰነዱ ነጻውን ፕሬስና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማሰርና ለመለጎም የወጣ ሰንድ ነው በማለታቸው፤መለስ በተለመደ እንዳመጣለት በሚወረወር ያልተገራ ቋንቋው ነበር ያጣጣለው፡፡

በኛ ላይ ሴራ እየተጎነጎነብን ነው፡፡…..ለዚህም ከበስተኋላው ምክንያት አለው፡፡…..ይሄ ሰብአዊ መብት የሚባለው ድርጅት ሃሳቡ የፖለቲካ ፍላጎቱን ለማካሄድ ነው፡፡……ድርጅቱና ወዳጆቹ በተወሰኑ ሃገራት ላይ አስተሳሰባቸውን ለመጫን ይፈልጋሉ፡፡አሁን ዓለም ከሚከተለው እምነት ለየት ያለን አካሄድ አይደግፉም፡፡ስለዚህም ይህ ሴራ እኛን ለማንበርከክና የነሱ ተገዢ ለማድረግ ነው፡፡ስለዚህም የሚሉት ሁሉ ከሰብአዊ መብት ጋር ጨርሶ ግንኙነት የለውም፡፡የጊቤን መገንባት የሚቃወሙ ሁሉ የራሳቸው ፍላጎትና እምነት ያላቸውና፤ያንንም በሀገራት ላይ ለመጫን የሚመኙ ናቸው ማለት ነው፤ በመለስ አስተሳሰብ፡፡በቅሎን ‹‹እናትሽ ማን ነች ቢሏት አባቴ በቅሎ ነው አለች›› እንዲሉ፡፡

የአፍሪካ ግፈኛ ገዢዎችና የአፍሪካ ነጫጭ ዝሆኖች

የአፍሪካ አረመኔ ገዢዎች ትላልቅ ፕሮጄክቶች የመገንባት አባዜ አለባቸው፡፡በአፍሪካ መንግስታዊ ተቋምን እንደግል ንብረትና መጠቀሚያ ማዋል መሰረቱ፤‹‹ትልቅ ሰው›› ሳይሆኑ ለማስመሰያነት የመኮፈሻ በሽታ ነው፡፡ የአፍሪካው ግዙፍ ሰው ዝናን ለመቀዳጀት ትላልቅ ፕሮጄክቶች መንደፍን፤ በዚህም ገናናነትን፤ ዘልአለማዊነትን፤ከሁሉም በላይ ደግሞ ለራሳቸውና ለምንዝሮቻቸው ሃብት ማጋበሺያነት ያውሉታል፡፡ሆኖም ግን እነዚህ ትላልቅ እርባና ቢስ ፕሮጄክቶች በገሃዱ ሲታዩ፤ ‹‹ነጫጭ ዝሆኖች›› ናቸው፡፡(ጠፊና ዋጋቢስ የሆኑ ፕሮጄክቶች ናቸው)፡፡ በአይቮሪ ኮስት በዓለም ታላቁን ቤተመቅደስ ፌሊክስ ሁፌት ቡዋኜ በያማስኩሮ፤የእመቤታችን ገዳም በመባል የሚታወቀውን በ300 ሚሊዮን ዶላር አስገንብተው ነበር፡፡ዛሬ ያ ብዙ ወጪ ያስወጣ ገዳም ባዶውን ቀርቷል፡፡ሞቡቱ፤ በምእራብ ዴሞክራቲክ ኮንጎ (ዛይር) የኢንጋ ግድቦችን በዓለም ታላቁ የሚባለው የውሃ ፏፏቴ ላይ አስገንብቶ ነበር፡፡ በኢንጋ ወንዝ ላይ የተገነቡት ሁለቱ ኢንጋ 1 እና 2 ግድቦች ለሃገር ፍጆታ በጣም ከፍተኛ ሃይል ያመነጫሉ ተብሎ በስፋት ተወርቶለት ነበር፡፡ዛሬ በጣም አነስተኛ የሆነ ሃይል በማመንጨት ላይ አለ፡፡በ1990 መጨረሻ ላይ ጦርነት ሲፈነዳ፤እነዚህን ግድቦች ማስተዳደር ባለመቻሉ እርባና አጥተዋል፡፡በኡጋንዳ የተገነባው ቡጃንጋሊ ግድብ፤በግድቡ አካባቢ በሚገኙ ነዋሪዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ፈጉዳት በማድረስ ነዋሪውን ለመከራ ዳርጓል፡፡በነዋሪዎቹ ላይ ስደትና መንከራተት አስከትሎ እርሻዎቻቸውን በማጥፋት አፈናቀሏቸዋል፡፡የመካከለኛው አፍሪካ ሪፓብሊክ በራሱ ራሱን ያነገሰው ጄን-ቤዴል ቦካሳ፤ሕዝቦች በችጋር እየተቆሉ መኖር ሲያስመርራቸው፤ ለነሱ ትኩረት በመስጠት ፈንታ፤በመቶ ሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር፤ባለ 500 መቶ ክፍሎች ኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል አስገንብቶ ነበር፡፡

የአፍሪካ ግፈኛ ገዢዎች፤ ሕዝቦቻቸው በችጋር ሲያልቁና መኖር ጣር ሲሆንባቸው፤ግድብ ማስገንባትን፤አብረቅራቂ ህንጻዎችን ማስገንባትን ይወዳሉ፡፡ይህን የሚያደርጉት ግላዊ ሃብትን ለማካበት፤መኮፈሳቸውን ለመጨመር፤ተስፋ ያጣ ህልማቸውንና ምኞታቸውን ለማሟላት፤ ድክመታቸውንና ችሎታ ቢስነታቸውን ለመሸፈን የቻሉ እየመሰላቸው ነው፡፡በደም የተጨማለቀ እጃቸውን ያጸዱ እየመሰላቸውና በስልጣን ላይ ለዘለቄታው ለመቆየት የሚያስችላቸው እየመሰላቸው ነው፡፡እርቀኑን የቀረ ግፈኛ የአገዛዝ ማንነታቸውን በማይጨበጥና በማይታይ ልማታዊ እቅድና፤እድገት ለመሸፈን ይሞክራሉ፡፡እነዚህ የግፍ ቋት የሆኑ አረመኔ ገዢዎች፤ ሕዝብ በችጋር ቢያልቅ፤ በምግብ እጦት ቢሰደድና ለሞት ቢዳረግ፤ገሃነም ቢገባ ደንታቸው አይደለም፡፡የአካባቢው ዓየር ቢበላሽ ደንታቸው አይደለም፡፡የነዋሪው ኑሮው ቢቃወስ፤ባህላዊና አርኪዎሎጂያዊው የሃገሪቱ ሃብት ቢወድም የነሱ ጉዳይ አይደለም፡፡ ግፈኛውና ጨካኙ መለስ ዜናዊ ዝናውን ማሳወቅ የሚፈልገው በአፍሪካ ረጂሙን ባለ 240 ሜትር ታላቁን የግቤ 3 ግድብ በመገንባቱ ነው፡፡‹‹‹የአፍሪካ ነቢይ›› በመባል ሊታወቅ ነው ህልሙ፡፡ባለፈው ፌብሪዋሪ 2011 ባለ 245.000 ሄክታር የስኳር እርሻ በታችኛው ኦሞ ለማስገንባት ሲነሳ፤በኩራት በተሞላ እርግጠኛነት ሲያቅራራ ‹‹በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በጣም ግዙፍ የሆነ የመስኖ ልማትና የእርሻ ልማት በዚህ አካባቢ ይኖራል፡፡ ለዚህ ቃሌን እሰጣችኋለሁ፡፡ምንም እንኳን አካባቢው ለስልጣኔ ኋላ ቀር በመባል ቢታወቅም፤የፈጣን ልማታዊ እንቅስቃሴ ተምሳሌት ይሆናል፡፡››

‹‹ለዚህ ፈጣን ልማት›› በሙርሲዎች፤በሱሪዎች፤በቦዲዎች የእርሻና የከብት አርቢዎች የሚከፈለው ዋጋ፤መሰደድ፤ለጥፋት መዳረግ፤ከባህላዊ ኑሮ ጋር መለያየት፤የቀደምት የእርሻ ይዞታን ማጣት፤ለግጭት መዳረግ ነው፡፡››

የበለጠ ሃይልና ጥንካሬ ለኢትዮጵያዊያን፤ ደካማነትና ልፍስፍስነትን ለአረመኔ ገዢዎች

እንደማንኛውም ሃገር ሁሉ ኢትዮጵያም ለሕዝቦችዋ ጥቅም የሚውል የሃይል ማመንጫዋን መገንባትና ማልማት ይገባታል፡፡የረጂም ጊዜ የልማትና የእድገት እቅዷን በማሳካት፤ሕዝቦችዋን ከረሃብና ከኑሮ ውድነት ሰቆቃ ማውጣት ተገቢ ነው፡፡በአሜሪካው የሕዝብ ቁጥር ትንበያ ቢሮ ዘገባ፤የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በ2050 እ አ አ ሶስት እጥፍ በማደግ፤ወደ 280 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይተነብያል፡፡ስለዚህም ሃገሪቱ ለሕዝቦችዋ የበለጠ የሃይል ማመንጫ ፤ለዘለቄታውም የሚበጅ የሃይል ማሳደጊያ ማእድን ያስፈልጋታል፡፡

ጊቤ ግድብ 3 ግን ከላይ የተጠቀሰውን እቅድ ለማስፈጸሚያነት የታቀደ አይደለም፡፡በእቅድ የተነደፈው 1.870 ሜጋዋት ለጅቡቲ፤ ለሱዳን፤ ለኬንያ ለሽያጭ የታለመና በዓመት 300 ሚሊዮን ዩሮ ሊያሰገባ የታቀደ ነው፡፡ይህም ቢሆን ለእርግጠኛነቱ ዋስትና የለውም፡፡ በቅርቡ የወጣው የዓለም አቀፍ ለፋይናነስ ተአማኒነት የተባለው ያወጣው ዘገባ፤በ2000 እና በ2009 መሃል ከሃገሪቱ 19 ቢሊዮን ተመንተፏል፡፡እነዚህ ግቤ 3ን እናለማለን የሚሉት፤ በዚህ ማስረጃነት ግን ማንንም ለማታለል እንደማይችሉ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ‹‹ይሁንላቸው፤ትላንት ተወልደን ይሆናል፤ ዘሬ ማታ ግን አይደለም›› ሞኛቸውን ሌላ አካባቢ ይፈልጉ!

የዛሬዋ አፍሪካ የማይዋጠው እውነት፤ጨቋኝ ገዢዎቿ ከከባቢ ዓየር ብክለት በባሰ ሁኔታ በሃገርና በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት ጭቆናና ግፍ የተሞላበት አገዛዛቸው ነው፡፡እነዚህ አፍሪካዊ ጨቋኝና ግፈኛ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች እያደረሱ ያሉት በደል መጠነ ሰፊ ነው፡፡አፍሪካውያን ለችጋር፤ ለመከራ፤ ለስደትና ለሌሎችም መከራዎች የተዳረጉት በአካባቢው የዓየር ለውጥ በተፈጥሮ ችግር ሳይሆን፤ አቅመቢሶቹና ሕሊናቸው የከዳቸው፤ራስ ወዳድ ገዢዎች ባላቸው ደካማነትና የስልጣን ጥማት የተነሳ ነው፡፡አህጉሪቷ፤ አሁን በቃኝን በማያውቁና፤ አቅማቸውን ባላገናዘቡ፤እኩይ መሪዎች እንደነቀርሳ ባደረባቸው የሥልጣን በሽታ፤ከዓየር መዛባት ከሚያደርሰው ቃጠሎ በበለጠ እየተቃጠለች ነው፡፡…….ሌሎች ዓለማት በዓየር ለውጥ ሳቢያ በተከተለው ንዳድ ሲለበለቡ፤አፍሪካ ደግሞ በመሪ ነን ባዮች የገዢዎች እሳት አራ እየተንጨረጨረች ነው፡፡አውሮፓውያን በማንነታቸው ግልባጭ ማህተም ሲሞናሞኑ፤ አፍሪካ ግን ከመሪዎች የጫማ እርግጫ ግፍ ጫና ለመላቀቅና ነጻነትን ለመተንፈስ እየዳከረች ነው፡፡አሜሪካኖች በጭስ ትነት ሳቢያ ከሚያጋጥመው ስራይ ለመገላገል ሲጥሩ፤አፍሪካውያን ግን የጭቆና አገዛዝ ግፍና መከራ ከሚመረትበት የከሰል ማዕድን ውስጥ ተጠምደው ስቃያቸውን ይቆጥራሉ፡፡አፍሪካ የከባቢ ዓየር ብክለት ለውጥ ተጠቂ ሳትሆን ፤የገዢዎች ለውጥ የትግል ፈተና ለውጥ ውስጥ ናት፡፡

የአካባቢ ዓየር ብክለት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ተወልደ ገብረእግዚአብሔር፤ኢትዮጵያውያን በጥንቃቄ ሊያገናዝቡት የሚገባ አስተያያት ሰንዝሯል፡፡ጊቤን የሚቃወሙት ‹‹ለጊቤ ያላቸው እውቀት ከሺ ኪሎሜትር ርቀት ነው፡፡አባባላቸውን ትኩረት ጨርሶ አልሰጠውም፡፡……ከነዚህ ተቃዋሚዎች አንዳቸውም ኢትዮጵያዊ አይደሉም›› ካለ በኋላ የግድቡ ተቃዋሚዎች ‹‹መሃይሞች›› ናቸው በማለት ደምድሟል፡፡ የተወልደ አባባል ግን ኢትዮጵያውያን ባለመቃወማቸው የተነሳ ሳይሆን የተቃወሙትን ሁሉ አሰባስቦ በሽብርተኝነት በመፈረጅ ወደ ቃሊቲ ለማስገባትና አፋቸውን ለመለጎም ባለመቻሉ ነው፡፡

እውነቱ ግን የመለስ አገዛዝ ስለ ጊቤ 3 ግንባታ ከመጀመሩ አስቀድሞ አንዳችም ቃል ባለመተንፈሱና፤ በጥቂቱ የተተነፈሰውም ቢሆን ሥራው ከተጀመረ በኋላ ስለሂደቱ፤አለያም ዝርዝር ሁኔታ ባለመቅረቡ ነው፡፡በግንባታው ቦታ በኦሞም ካሉት ሃላፊዎችም ጋር ቢሆን፤ ግንባታው በዝምታ ተውጦ ረጂም ሂደት ከተጓዘ በኋላ ነበር፤ድፍንፍን ያለ፤ግልጽነት የጎደለው፤የይስሙላ ንግግር የተከናወነው፡፡የግድቡን መገንባት አስመልክቶ፤ የመናገር መብት በተለጎመበት፤ ነጻው ፕሬስ በታፈነበት፤ውይይትም፤ ሃሳብ ማቅረብም፤ አማራጭ መሰንዘርም ጨርሶ የማይታሰብ ነው፡፡በገዢዎቹ አመለካከት፤ስለ ጊቤ 3 ግድብ ተቃውሞ ማሰማት ከሽብርተኝነትና በሃገር ላይ ከማመጽ ተለይቶ የሚታይ ጉዳይ አይደለም፡፡ መቀመጫው በኦክላንድ ኢንስቲቲዩት የሆነው አሜሪካ በቀል ‹‹ሃሳብ ማመንጫ››(think-tank) የገዢው ባለመሳርያ አገልጋዮች፤ወደኦሞ መንደር እንዴት እንደመጡና(በተለይም፤ቦዲ፤ ሙርሲ፤ሱሪዎችን)ስለስኳር ልማቱ ያላቸውን አስተያየት እንደጠየቋቸው ዘግቧል፡፡ነዋሪዎቹ ግብታዊ ስምምነት እንዲሰነዝሩ ይጠበቅባቸው ነበር፤ያ ሳሰሆን ቢቀር ደግሞ አጸፋው ድብደባ፤ ማጎሳቆልና ለፖሊስ ማሰቃያ (ቲዘር) መዳረግ፤ እንግልትና ማስፈራራት ነበር፡፡

ከጊቤ 3 ግንባታ ተቃዋሚዎች መሃል አንድም ኢትዮጵያዊ የለም፤ በማለት ተወልደ ገብረእግዚአብሔር የሰነዘረው አባባል በኢትዮጵያውያን አጸንኦት ሊሰጠው የሚገባ አባባል ነው፡፡ ተወልደ ማለት የዳዳው ‹‹ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራውን ጨምሮ ስለጉዳዩ ግንዛቤም፤ እውቀቱም የላቸውም፤ ስለግንባታው ምንም ስሜት ስለሌላቸው፤ሌሎች ወገኖች በማያገባቸው እየጮሁ ነው›› ነው፡፡ የአካባቢ ሁኔታን በተመለከተ እርግጥ ነው የሚከላከሉትና ሙግት የሚያሰሙት የሲቪል ማህበረሰብ አባላት ናቸው፡፡‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የሰብአዊ መብት እንቅስቃሴ በገዢው ስርአት በ2009 በወጣው የማፈኛ አዋጅ ጫና ታንቋል፡፡ የእነዚህ ድርጅቶች መታፈን ደግሞ ኢትዮጵያውያን ስለ ሃገራቸው ጉዳይና ስለሚከናወነው ሕገወጥ እንቅስቃሴ፤መሬትን ለውጭ ሰዎች ልማት በሚል ሰበብ መሸጡን እንዳያውቁ አድርጓል፡፡ቢያውቁም አዋጁና ጣጣው አያስተነፍሳቸውም፡፡የጊቤ 3ን ግንባት ቻይናውያን ከግብ ያደርሱታል ተብሎ በገዢው መንደር ቢታመንም፤በኢትዮጵያ በርካታ የአካባቢ ሁኔታዎች ጎጂ ለውጥ በማንዣበብ ላይ ነው፡፡አሁን ኢትዮጵያውያን እነዚህን ጎጂ የአካባቢ ለውጦች በተመለከተ መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በድብቅና ሃቁን በሸፈጠ አካሄድ ስለሚከናወነው የጥፋት ተልእኮ፤ የውጭ የሰብአዊ መበት ተሟጋቾች ላደረጉት እንቅስቃሴ፤ድምጻቸውን ከፍ አድርገው፤ጉዳያችንን ጉዳያቸው አድርገው፤በተለይ በኦሞ ወንዝ አካባቢ ያለውን እኛም የጉዳዩ ባለቤቶች ስውሩን ደባ እንድናውቀው ስለደረጉልን ልናመሰገነሳቸው ይገባል፡፡ያም ሆኖ ግን ታላቁን ጫና አሁንም እነሱ እንዲሸከሙልን ማሰብ የለብንም፡፡ከእነሱ ጋር በመደባለቅና በማገዝ እንዲረዱን መርዳት ይጠበቅብናል፡፡ከዚህም በመነሳት የራሳችንን የአካባቢ ጥበቃ ድርጅት በተለይም በዲየስፖራው በመመስረት የኢትዮጵያ ንጹህና የዳበረ የአካባቢ ሁኔታ ሊጠበቅና ሊንከባከቡት የሚገባ ሃብታችን መሆኑን ልንገነዘብ ተገቢ ነው፡፡ ይህን ሳናደርግ ብንቀር ግን እኛም የኦሞ ወገኖቻችን ላይ በግድቡ ሳቢያ የደረሰው ችጋር፤መሰደድ፤ አልቂት እንደሚደርስብን ሳንጠራጠር መቀበል አለብን፡፡

ለዶናልድ ፔይን የሰብአዊ መብት ችሮታ

Tuesday, March 13th, 2012

ከዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ዶናልድ ፔይን መሪ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ጥሪ፤መሪ የከበሮ ጎሳሚ ነበሩ

ባለፈው ሳምንት ባሰደነገጠን የዶናልድ ፔይን ከመሃላችን መለየት፤ሁሉም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በእጅጉ አዝነናል፡፡ፔይን በአሜሪካ ኮንግሬስ ተወዳዳደሪ የሌላቸው ብቸኛ ጠበቃችን ነበሩ፡፡ድንገተኛ መለየታቸው ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ የነጻነት የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ትግል ማዝገምን ያስከትልብናል፡፡ሆኖም ግን ፔይን ትተውልን የሄዱት የሰብአዊ መብት፤ጥብቅናና ለረጂም ዓመታት በፍትጊያና በትግል ውስጥ የነበረውን ሂደት ነው፡፡አሁን ደሞ የዚህ ፍትጊያ እጣ ፈንታ በኛ ላይ ተጥሏልና፤ ሸክሙ የኛ የሞራል ግዴታችን ነው፡፡ይህንንም ችሮታቸውን አጠናክረን፤ በሰፊው ሙግቱን አቀነባብረን፤የውጤቱን ጊዜ ማፋጠን ግዴታችንም፤አደራም፤ያውም ታላቅ የመብት ተሟጋቹ ጥለውብን ያለፉት አደራ ነው፡፡

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የዶን ፔይንን ሕለፈት መሸከምና ማመን ባቃተው ሕሊናችን ስንጨነቅ ብንሰነብትም፤በሌላ ጎን ደግሞ፤እኛ በዲያስፖራው ያለን ኢትዮጵያውያን በቡድንም ይሁን በተናጠል፤ ጥለውልን ላለፉት ታሪካዊ አደራና ችሮታ፤ምን ልናደርግ እንችላለን በሚለው እሳቤ ላይ ስንቆዝም ነበር፡፡ሁሉም የማይወድቅ ሃሳብ አላቸው፡፡ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነጻ ትምህርት እድል የሚያስገኝ ተቋም እንመስርት፡፡ በስማቸው የሰብአዊ መብት ኮንፍራንስ እናዘጋጅ፡፡ እሳቸው ቆመውለት ለነበረው የእርዳታ ለጋሽ ድርጅት ገንዘብ እናሰባስብ፡፡ በስማቸው የሚሰየም ልዩ በአል እንመስርት፡፡እና ሌሎችም፡፡

እነዚህ ሁሉ እዚህ ቀረሽ የማይባሉ ታላቅ ቁም ነገሮች ናቸው፡፡በኔ አመለካከት ግን፤ለዶናልድ ፔይን ለትግላቸው፤ልፋታቸውና ጥረታቸው ዘልአለማዊነት ልናደርገው የሚገባን ጉዳይ፤ የጀመሩትንና ታላቅ ውጣ ውረድና ጊዜያቸውን የሰዉለትን ዓላማቸውን፤ሳንዘናጋና ቀጠሮ ሳንይዝለት፤አሁኑኑ ተጋባራዊ በማድረጉ፤እንቅስቃሴያችንን በማጠናከር ለውጤት ማብቃት ነው፡፡ ለአፍሪካ የፔይን ታላቅ ችሮታ ለሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ ተግባራዊነት ያካሂዱ የነበረው ጥረት ነው፡፡ለኢትዮጵያም ብቸኛ ስጦታቸውና ያላሰለሰ ጥረታቸው፤የሰብአዊ መብት፤ግልጽነትና ተጠያቂነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአሜሪካ ስርአት ደረጃ እንዲስተካከል ማድረግ ነበር፡፡

በምርጫ ጣቢያቸው በኒው ጄርሲም ሆነ፤በታላቁ አህጉራዊ ወረዳቸው አፍሪካም ውስጥ፤የዶናልድ ፔይን ተግባር፤ ኑሯቸውና የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው፤ሕዝባዊ አገልግሎት ማበርከት ነበር፡፡ በአፍሪካ ድምጻቸው ለታፈነባቸውና ማንነታቸው በጨካኞችና እርባና ቢስ ጀብደኞች ለተደፈረባቸው፤መታወቂያቸው ለተገፈበባቸው ሁሉ፤ድምጽ ለመሆን፤ከቦታ ቦታ፤ከሃገር ሃገር ተዘዋውረዋል፡፡ ለአፍሪካና ለአፍሪካውያን ላደረጉት አስተዋጽኦና ለወጡ ለወረዱበት ፈተና ሁሉ አንዳችም ምስጋናም ሆነ አድናቆትን አልጠበቁም፡፡ ላጋጠማቸው ችግርና ፈተናም አንድም ጊዜ ቅሬታ አላደረባቸውም፤ ይልቁንም በነዚህ አረመኔ ዲክታተሮች የተሰነዘረባቸውን ጥቃት ሁሉ ኢላማውን እንዲስትና እሳቸውም በእውነተኛውና በትክክለኛው የሰው ልጅ ከተፈጥሮ በተሰጠው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ እጦት የሚሰቃዩተን በማገዝና አቤቱታቸውን በማሰማት ሂደት ላይ ነበር ተጠናክረው የኖሩት፡፡

ስለዶናልድ ፔይን ችሮታ ግንዛቤ

ዶናልድ ፔይን፤ማርቲን ሉተር ኪንግ የፍትሕ፤የሰላምና የብልጽግና ግንባር ቀደም ከበሮ ጎሳሚ ሊሏቸው ይችል የነበሩ ሰው ነበሩ፡፡ እኛም ግንባር ቀደም የዴሞክራሲ፤ሰብአዊ መብት፤የአፍሪካ ነጻነት ከበሮ ጎሳሚነታቸውን በሚገባ እናውቃለን፡፡በኢትዮጵያም ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲተገበር መሪ የነጋሪት መቺ ነበሩ፡፡የነጻና እውነተኛ የፍትሕ ስርአት፤የነጻው ፕሬስ ነጻ እንቅስቃሴ መሪ ባለአታሞ ነበሩ፡፡በታወቁና በሚስጥራዊ ቦታ በግፍኞች ታፍነው ለሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ መለቀቅ ግንባር ቀደም ከበሮኛ ነበሩ፡፡ግንባር ቀደም አታሞ ጎሳሚነታቸው፤በአፍሪካ ለረጋና ለሰከነ ሁኔታ፤ ለዴሞክራሲ፤ ለኤኮኖሚ ልማት ነበር፡፡የከበሮ ምታቸው በኢትዮጵያና በአሜሪካ ሕዝቦች መሃል የኖረውን ወዳጅነትና ግንኙነት አጠናክሮ በመቀጠሉ ስርአት ላይ ነበር፡፡ዶናልድ ፔይን በኢትዮጵያ ውስጥ ለተጠያቂነትና ለዴሞክራሲ መተግበር ቀዳሚ የከበሮ መቺ ነበሩ፡፡

በዶናልድ ፔይን ግንዛቤ ላይ መነጋገር ማለት፤ አሜሪካ ለአፍሪካ፤በተለይም ለኢትዮጵያ በገባችው የዴሞክራሲ ግንባታ ቃል ላይ መነጋገር ማለት ነው፡፡ በዲሴምበር 2009፤ የሃገር አስተዳደር ሚኒሰቴርዋ ሂላሪ ክሊንተን፤የአሜሪካን የሰብአዊ መብት ፖሊሲ መሠረት፤በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ ሲያብራሩም፤‹‹የሰብአዊ መብትና የነጻነት እሳቤዎች ከፊል ዓለማችን ውስጥ እንዳለው የለበጣና የይስሙላ መፈክር ሊሆን አይችልም፡፡›› ለጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደሚተንም ውሃ ጠብታ አይሆንም፡፡ ሰብአዊ መብት ዓለማቀፋዊ ነው፡፡ የኢትዮጵያ፤የአፍሪካ፤ የአውሮፓ፤ የአሜሪካ አለያም የሌላው ዓለም ተብሎ የሚደለደል የሰብአዊ መብት አይነትና ቅርጽ የለም፡፡

‹‹ዴሞክራሲ፤ነጻነት፤ሰበአዊ መብት በዓለም ላይ አንድ አይነት ትርጓሜ እያገኙ ናቸውና በምንም መልኩ ቢሆን ማንኛውም ሃገር ላይ፤ በማንኛውም መሪ፤ ትረጓሜያቸው እንዲለወጥና በዲክታተሮች ሊታገዱ ሊፈቀድላቸው አይገባምም፡፡አይቻልምም፡፡የሃገር አስተዳደር ክሊንተን፤ ‹‹የአዲሱ ዓለም ስርአት የሰብአዊ መብቶችን በማስከበር ላይ የተመሰረተ ሊሆን ተገቢ ነው›› በማለት አሳስበዋል፡፡‹‹እነዚህ መብቶች››ቀላልና በቀላሉም ሊተረጎሙ የሚችሉ ናቸው፡፡የንግግር ነጻነት፤ነጻ የመገናኛ ብዙሃን፤ የሃይማኖት ነጻነት፤ የመሰብሰብና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፤ማንኛውም ሰው በሚኖርበት በነጻነት መኖርና አለአግባብ ከመፈተሸ፤ ከመያዝ፤ከመቀጣት ነጻ እንዲሆን፡፡ እነዚህ መመርያዎች ማንም በየትም በሰላም ለመኖር መቻሉን የማረጋገጫ መነሻዎች ናቸው፡፡እነዚህ የማይተረጎሙና ለመረዳት አዳጋች የሆኑም አይደሉም፡፡ይልቅስ ሕይወትን የምንመራበትን መንገድ የሚቀይሱ ናቸው፡፡ በመኖሪያነት ነጻነትን እያደነቅን ነጻ የምንሆንባቸው ናቸው፡፡ ሰዎች በነጻ ምርጫቸው የሚሻላቸውን አስተዳደር የሚመርጡበት የዴሞክራሲ ቁልፋቸው ይህ እድልና መብት ሲኖራቸው ብቻ ነው፡፡

‹‹እነዚህ መብቶች››ቀላልና በቀላሉም ሊተረጎሙ የሚችሉ ናቸው፡፡የንግግር ነጻነት፤ነጻ የመገናኛ ብዙሃን፤ የሃይማኖት ነጻነት፤ የመሰብሰብና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት፤ማንኛውም ሰው በሚኖርበት በነጻነት መኖርና አለአግባብ ከመፈተሸ፤ ከመያዝ፤ከመቀጣት ነጻ እንዲሆን፡፡ እነዚህ መመርያዎች ማንም በየትም በሰላም ለመኖር መቻሉን የማረጋገጫ መነሻዎች ናቸው፡፡እነዚህ የማይተረጎሙና ለመረዳት አዳጋች የሆኑም አይደሉም፡፡ይልቅስ ሕይወትን የምንመራበትን መንገድ የሚቀይሱ ናቸው፡፡ በመኖሪያነት ነጻነትን እያደነቅን ነጻ የምንሆንባቸው ናቸው፡፡

ሰዎች በነጻ ምርጫቸው የሚሻላቸውን አስተዳደር የሚመርጡበት የዴሞክራሲ ቁልፋቸው ይህ እድልና መብት ሲኖራቸው ብቻ ነው፡፡ የሃገር አስተዳደር ሚነስትር ክሊንተን፡- ለኛ የሕዘቡ የመጨረሻ የሃሳባቸው ውሳኔ የሚገኘው ተመራጮች በሚያሰተላልፏቸው መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ከነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ነው፡፡እነዚህ መመርያዎች ለይስሙላ የተቀመጡ ሳይሆኑ፤ሊጠበቁ፤ ልንከላከልላቸውና ልናስተላልፋቸው የሚገቡ ናቸው፡፡በአንዳንድ ሃገሮች‹‹መሪዎች እያወቁ ለመተግበርና ሕዝቦችም እንዲገለገሉባቸው ፍቃደኛ ባለሆኑባቸው ሃገራት፤የአሜሪካ መንግሥት እነዚህን መሰል መሪዎች ጭቆናቸው እንዲያበቃና ሕዝቡ ነጻ እንዲሆን ግፊት ማድረግና፤ ይህን በትክክለኛው ጎዳና ማቃናት ላይ ያሉትን ደግሞ ለመርዳት ዝግጁ ልንሆን ይገባል፡፡ ቆራጥ የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችንም ሕዝቡ ለሚያካሂደው ትግል የሚያደርጉትን ተሳትፎ በመደገፍ፤ማበረታት ዓላማችን ሊሆን ተገቢ ነው፡፡የኦባማ የሰብአዊ መብት ፖሊሲ የሚመራባቸው አራት ቋሚ ምሰሶዎች አሉት፡፡

የመጀመርያው፤ለሰበአዊ መብት መከበር ቁርጠኝነት እኛን ጨምሮ ያለን ቆራጥነት ነው፡፡ሁለተኛው፤የሰብአዊ መብት አጀንዳዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ በትክክለኛነቱና እርግጥኛነቱ በተረጋገጠበት አካሄድ ሊሆን ይገባል፡፡ወደግድግዳው ስንንደረደር ሊገጥመን በሚችለው አስቸጋሪ ሁኔታ ለመወጣት፤ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ሳይሆን፤ችግሩን አስወግደን፤ወደ አለምንበት አቅጣጫ ልናልፍ የምንችልበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ የተመሰረተና፤የሕብረተሰቡን ኑሮ በማሻሻል ላይ ያነጣጠረ ሊሆን ይገባል፡፡ ሶስተኛ፤ በዜጎችና በነዋሪዎች ፍላጎትና ፈቃደኝነት ላይ ለውጥን እንደግፋለን፡፡ የሰብአዊ መብትን የሰብአዊ እውነታ የማድረግ እቅድ የመንግሥታት እቅድ ብቻ ሊሆን አይገባም፡፡የግለሰቦችንና የድርጅቶችን ትብብር የሚጠይቅና በነዋሪዎችና ከድንበር ባሻገር የሚታሰብም፤ የስብእና ክብርን፤ሰብአዊነት ባስተሳሰራቸው መሃል ሊሆን ይገባል፡፡ አራተኛ፤ ተስፋ በሚታይባቸው አካባቢም አዎንታዊ ምላሻችን ሊደርስና፤እንቅስቃሴውም ሊደገፍ ሲገባ፤የሰብአዊ ሕይወትም በሚዛኑ ላይ ተንጠልጥሎ ሲገኝ ሚዛኑ ወደ ተሻለ ኑሮና የሕዝብ ነጻነት እንዲያጋድል የሚቻለንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

ለኦባማ አስተዳደር የሰብአዊ መብት ግዴታውን ማስገንዘብ

የሰበአዊ መብትን በተመለከተ ተጠያቂነት ከቤት መጀመር አለበት፡፡ ‹‹ከራሳችን››፡፡ በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትን ለማበራታት ለመጠበቅ፤ የኦባማ አስተዳደር ምን አድረጓል? በግንቦት 2010 የመለስ ዜናዊ ገዢ መንግሥት 96.6 በመቶ ምርጫ አሸነፍኩ ሲልስ አሜሪካ ምን አደረገች?አሜሪካ መለስ ዜናዊ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲያካሂድ ገሃዳዊ ጫና አድርጓል? በሚታወቅና ሚስጥራዊ በሆኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ያፈናቸውን የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ማድረጉ ላይ አሜሪካ አስቦበታል? የመለስ ዜናዊ የግፍና ጨቋኝ አገዛዝ የነጻውን ፕሬስ እንቅስቃሴ ሲያዳክምና ሲዘጋ፤የአሜሪካ ድምጽን የአማርኛ ድምጽ ፕሮግራም በኤሌክትሮኒክ መሳርያዎች በመታገዝ ሲያፍን የአሜሪካ መንግሥት ምን እርምጃ ወሰደ?

ዘይቤያዊ የሆነ ምላሽ

የሃገር አስተዳደር ክሊንተን፤ ‹‹ሩጫችን ከግንቡ ትይዩ ሲያደርሰን›› እና ጭቆናና የሰብአዊ መብት መረገጥን ሲያሳየን፤ ‹‹በተስፋ መቁረጥ ከማፈግፈግ ይልቅ ዘይቤያዊ ዘዴን በመጠቀም በጭቆና ውስጥ ያሉትን በማገዝ ምላሹን እንሰጣለን፡፡›› በግንቦት 2010 የዓለም የነጻነት ቀን በተከበረበት ጊዜ ፕሬዜዳንት ኦባማ ባደረጉት ንግግራቸው፡- ያለፈው ዓመት በዐለም አቀፍ ደረጃ የነበረው የፕሬስ ነጻነት መጥፎ ነበር፡፡ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታ ሕዝቦች በኢንተርኔት መረጃዎችን በማግኘት፤በእጅ ስልኮች፤እና በሌሎችም የቴክኖውሎጂ መገናኛ ዘዴዎች መጠቀም ሲችሉ እንደ በኢትዮጵያ ያሉ ገዢ መንግሥታት ግን……………ሕዝቡ በእነዚህ የቴክኖውሎጂ ውጤቶች እንዳይጠቀምና መረጃዎችን እንዳያገኝ እያፈኑት ነው፡፡›› አሁን አሁንማ የመለስ ገዢ መንግሥት ከእነዚህ አፈናዎች አልፎ ነጻ ጋዜጦችን መዝጋትና የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራምን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳያዳምጥ እስከማድረግ ደርሷል፡፡በዚህስ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ መንግሥት የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ጭቆናና የነጻው ፕሬስን ሲያፍን ዘይቤያዊ የሆነ ምላሽ ሰጥቷል?

በሕዝቡና በነዋሪው መነሳሳት ለተገኘ ለውጥ ድጋፍ መስጠት

የሃገር አስተዳደር ክሊንተን፡ ‹‹ሰብአዊ መብት›› ‹‹የሰብአቸዊ መበት እውነታ›› ሊሆን የሚችለው ግለሰቦችና ድርጅቶች ከነዋሪዎቸና ከዚያም አልፈው ከድንበር ባሻገር ተዋህደውና ተስማምተው ለመስራት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡ ያ ካልሆነ እውነታ ሊሆን ጨርሶ የማይታሰብ ነው፡፡ በየካቲት 2010 ምክትል የሃገር አስተዳደር የሆኑት ማርያ ኦቴሮ የሲቪል ማሕበረሰብ ሕግ የተባለውን የመለስ ገዢ መንግስት ያወጣውን እወጃ በተመለከተ፤ ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር፡፡ አንድ ዘገባ እንዳመላካተው፤በዚህ ደንብ ሰበብ የተነሳ፤ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር ከ4600 ወደ 1400 በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ አሽቆልቁሏል፡፡ የድርጅቶች አባላት ቁጥርም እንደ ደረሰኝ ጥቆማ በ90 በመቶ ቀንሷል፡፡‹በኢትዮጵያ ‹በዜጎች እና በቆራጥ ዜጎች ግለሰቦችና በተደራጁ ቡድኖች መነሳሳት ላይ የተመሰረቱ››ግልጋሎትና ሕዝባዊ ድጋፍ ሰጪዎች፤ በጨቋኝ ገዢዎች ፈላጭ ቆራጭ መመርያ ብትንትናቸው ሲወጣ የአሜሪካ መንግሥት ምን እርምጃ ወሰደ?

የሚዛኑን ተዳፋት ወደ ተስፋ ሰጪው ወገን እንዲያዘም ማድረግ

የአገር አስተዳደር ክሊንተን እንዳሉት፤የአሜሪካን መንግሥት ተስፋ የሚታይበትን እያገናዘበ፤ከዚያ አቅጣጫና ከሱ ጋር መስራትን ይመርጣል፡፡በግንቦት 2010 የምርጫ ወቅት፤የአሜሪካን መንግሥት የኢትዮጵያን ሁኔታ ወደተሻለ አቅጣጫ ለመውሰድ እድሉ ነበረው፡፡በምርጫው ማግስት የአሜሪካን መንግሥት ጠንካራ መግለጫ አወጣ፡፡ከኢትዮጵያ ጋር ሰፊና ጠንካራ መሰረት ያለው ግንኙነት ቢኖረንም ገዢው መንግሥት በመከተል ላይ ያለውን ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደርን በተመለከት ግን ጥርጣሬያችንን ለመንግሥት ገልጸናል፡፡…….በአሁኑ ምርጫ የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የሚወስደው አቋምና የምርጫው ሂደት የወደፊቱን የአሜሪካንንና የኢትዮጵያን ግንኙነት ይወስናል፡፡…..ይህም በኢትዮጵያ በኩልም ስለግንኙነታችንን ማሰብን ይጨምራል፡፡ከዚህም በመነሳት የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ቀጥተኛ የሆነውን መግለጫ በጥሞና ሊያስተውሉ ተገቢ ነው፡፡…..ከዚህ መንግሥት ጋር ውይይታችንን እንቀጥላለን፤ የዴሞክራሲያዊ ተቋማትም ግንባታ ደረጃዎች እንዳሉትና ጊዜ እንደሚጠይቅ እንገነዘባለን፡፡

ኤች አር 2003 የኢትዮጵያ ዴሞክራሲና ተጠያቂነት አክት፤

Your browser may not support display of this image.የሃገር አስተዳደር ሂላሪ ክሊንተን የአሜሪካንን የሰብአዊ መበት ፖሊሲ በግልጽ ከማስቀመጣቸው ቀደም ብሎ፤ዶናልድ ፔይን፤ከእሳቸውም በፊት የነበሩት የኒው ጀርሲው ኮንግሬስማን ክሪስቶፈር ሰሚዝ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ኤች አር 2003 (በአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት በ2007 አለፈ) በትክክልና በብቃት የኦባማ አስተዳደር ያዋቀራቸውን የሰብአዊ መብት ምሰሶዎች መስፈርት በሚገባ ያካተተ ነው፡፡ በትክክልም በቂ ጥርስ ለሃገር አስተዳደር ሂላሪ ክሊንተን ጠንካራና ብርቱ አባበል የሚሰጥ ነው፡፡የዶን ፔይንን ሕይወትና ክቡር፤የተግባር ችሮታቸውን የምንጠብቅላቸው ፤እራሳችንን በኤች አር 2003 ወስጥ ለተካተቱት መግቢያ ቃላቶቸ እና ለአጠቃላይ ኤች አር 2003 ለተሸከማቸው ግዙፍ መብቶች አፈጻጸም ስንሰለፍና ስንጥር ብቻ ነው፡፡ለማንም ያልወገነው፤ የተከበረውና የኮነግሬስ በተመጻሕፍት የቀኝ እጅ የሆነው የኮንግሪስ የጥናት ማዕከል ሕግ የተቀመጠበት የተግባር ድርጊት፡-

(1) ሰብአዊ መብትን፤ዴሞክራሲን፤የፍትህ አስፈጻሚ አካላትን በነጻነት መንቀሳቀስ፤የነጻውን ፕሬስ ነጻነት፤የፌዴራል ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያን መንግሥት የኤኮኖሚ እድገት (2) በሽብርና ሽብርተኘነት ላይ ያለውን ዓለም አቀፋዊ መከላከልን መተባበር (3) በኢትዮጵያ ያሉትን የፖለቲካ እስረኞችና ሁሉንም የሕሊና እስረኞች የሚፈቱበትን ሁኔታ ማመቻቸት (4) በአካባቢው መረጋጋትን፤ዴሞክራሲን፤የኤኮኖሚ ልማትን ማበረታታት፡፡ (5) ሰበአዊ እርዳታዎችን በተለይም በአጋዴን ክልል ማበረታታት እና (6) በኢትዮጵያና በአሜሪካ መሃል ያለውን የኖረ ወዳጅነት ማጠናከር፡፡

(2) የሰብአዊ መብት ተጠያቂነት በኢትዮጵያ፤ደንቡ በአሜሪካ ኮንግሬስ መቀረጽ የጀመረው የ2005ን ምርጫ ተከትሎ በተከሰተውና በማስረጃ በተደገፈው የ193 ንጹሃን ዜጎች መገደልና፤ከምርጫ በኋላም በተጨፈጨፉት 73 ንጹሃን ዜጎች ምክንያት ነው፡፡በኖቬምበር 2005፤ የኒው ጀርሲው ኮንግሬስማን ክሪስተፈር ስሚዝ፤ የወቅቱ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ ሊቀመንበር፤4423 በመባል የታወቀውን (‹‹ኢትዮጵያ ኮንሶሊዴሽን አክት››) አረቀቁ፡፡

(3) ሕጉ በተጨማሪም የአሜሪካን መንግስትን ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅትን ጠቀሜታ ያካተተ፤የሲቪል ህብረተሰቡን ስብስብ መርጃ የፋይናንስ ድጋፍን፤የነጻ ሰበአዊ መብት ተሟጋቾች መቆጣጠር የሚየስችላቸውን መንገድ፤ለፖለቲከ ድርጅቶች ዴሞክራሲያዊ ችሎታ ማዳበርያ፤የፖሊስና ደህንነት አባላት፤ የግድቦች ግንባታዎች እና የትብብር የደህንነት እንቅስቃሴ ሁሉ ኢትዮጵያ፤ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን ማከበሯ ማረጋገጫ እስኪገኝ ድረስ እንዲታቀብ፡፡ ኤች አር 4423 ወደ ኤች አር 5680 ተሻሻለ፡፡(‹‹በኢትዮጵያ ነጻነት፤ዴሞክራሲ፤ሰብአዊ መብትን ተግባራዊ ለማድረግ የወጣ››) በ2007 ፔይን የአፍሪካን ንኡስ ኮሚቴ ለመምራት በተሰየሙበት ወቅት፤ ድንጋጌው በአዲስ ቁጥራዊ አጠራር ተለወጠ፡፡ኤች አር 2003 ተባለ)እና በኦክቶበር አለፈ፡፡ ይህም ማለት በኦባማ መስተዳደድር እንደመመርያ ሆነው የተዋቀሩትን የአራቱ ምሶዎች ትግበራ በትክክል ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ እንዲሰሩ የሚያደርግ ነው፡፡

ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን የሰብአዊ መብት ድንጋጌ ፖሊሲያቸውን መመርያ ንግግር ሲያጠናቅቁ፤የሰብአዊ መብት ጥበቃን ሂደትና ተግባራዊነት ለማስፈጸም ጠንክሮና ተግቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም፡- ይህ እኛ የምናከናውነው ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ ስለእኛነታችንም እንጂ፡፡አስፈላጊውን ትግልና ቆራጥነት ካላደረግን በስተቀር፤እኛ ነን የምንለውን ልንሆን አንችልም፡፡ በሰብአዊ መብት ማመን ማለት ለተግባራዊነቱ ሁሉ የሚጠይቀውን ለመክፈል ፈቃደኛና ቆራጥ መሆን ማለት ነው፡፡ይህንን መብት በሁሉም ቦታ፤ ለሁሉም ሃገራትና ዜጎች ለማስፈጸም የውዴታ ግዴታ ሰነዱን ስንፈርም፤ይህንንም እውን ለማድረግ ሂደቱ የሚጠይቀውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ፈቃደኛነታችንንም ነው የምንፈርመው፡፡

በኮንግሬስማን ፔይን ሕልፈት የኤች አር 2003ን ሕይወት እንዲያንሰራራ በማድረግ እነዚያን ግዙፍ ቃላቶች የአሜሪካን ሰብአዊ መብት ፖሊሲ በኢትዮጵያና በአፍሪካ በአጠቃላይ እንዲፈጸም ለማድረግ እንችላለን፡፡ወይም በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትን ጉዳይ ጨርሶ እንዲወድም ለማድረግ ትግላችንን በማቆም ዳግም በኢትዮጵያ ስለሰብአዊ መብት ጉዳይ ላለማንሳትና እንዲረሳ ለማድረግ እራሳችንን እናዘጋጃለን፡፡

ከኤች አር 2003 በኋላ ስለተዋቀረው ረቂቅ ሕግ (ቢል)፤ ትግላችን ቀላል አለያም የዋዛ ውጣ ውረድ አይሆንም፡፡ጉዟችን ዳገታማና አስቸጋሪ፤ ፈታኝ ነው፡፡ የትግላችንም ቀና መንገድ በጨቋኞችና ግፈኞች ተገዢ፤ በወር 50.000 የሕዝብ ደም ዶላር በሚከፈለው የ ኬ ጎዳና ተሟጋች ስለተያዘብን በየቀኑ የኮንግሬስን የግራናይት ወለል እየተሳለመና ለገቢ ወጪው ኮንግሬስማን እጅ እየነሳ፤ተቀባይነት ለማግኘት እየጣረ፤ የኢትዮጵያውያንን ሰብአዊ መብት ለማሳፈንና፤ በአረመኔዎች ጥይት ለማስደብደብ፤ በቡጢያቸው ለማስወገር፤ በወህኒ ቤታቸው ለማሳጎር፤ጉብ ቂጥ በማለት ላይ ነውና ትግላችን እንዲህ ቀላል አይሆንም፡፡ስለዚህም ኢትዮጵያውያን በተለይም በአሜሪካ ነዋሪ የሆንን ኢትዮጵያውያን፤ቀላል ምርጫ ቀርቦልናል፡፡ለዚህ ፈታኝና አስቸጋሪ ግን ወሳኝ ፍልሚያ መፈረም፡፡ከባዱን ጫና ለመሸከም ቆርጠን መነሳት፡፡ዶናልድ ፔይን ለኢትዮጵያ የነበራቸውን የሰብአዊ መብትና የዴሞክራሲ ሕልምና ራዕይ፤ምኞትና ፍላጎት እውን ማድረግ፡፡ ሌላው መንገድ ደግሞ ይህን ጅማሮ አቋርጦ የበቃኝ ሽሽት መያያዝ፡፡

ዶን ፔይን ለኢትዮጵያ የገቡትን የማይታጠፍ ቃላቸውን እኛ ኢትዮጵያውያን ዕውን እናድረገው!

ሽግግር ከአምባገነን ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት

Wednesday, March 7th, 2012

ከፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም

(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ማህተመ ጋንዲ በቅድሚያ ታሪካዊ የብረት ግምብ ነበር ለፈላጭ ቆራጮች ያስቀመጡላቸው፡፡ ‹‹አምባ ገነኖች፤ ፈላጭ ቆራጮችና ነፍሰ ገዳዮች፤ ነበሩ፤ ለጥቂት ጊዜ የማይደፈሩ ሆነው ይቆዩና በመጨረሻው ግን መጨፍለቃቸው አይቀሬ ነው፡፡ ዘወትር ስለዚህ ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡››ሲል፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ፤ የጋንዲ ትንቢት እውን ሲሆን፤ የግፈኛ ገዢዎች የድንፋታ ቃላቶችና አካኪ ዘራፍ ፉከራዎች እንደ ዶሚኖ መጫወቻ ጠጠሮች በዐረብ ድንገተኛ እልህ ቁጣ የግፍ በቃን መነሳሳት ሲገረሰስ አየን፡፡የቱኒዚያው ቤን አሊ ከ24 ዓመታት በኋላ የቆመበት የስልጣን መረጋገጫው አዳለጠው፤ የግብጹ ሆስኒ ሙባረክም ከ32 ዓመታት የገዢነት መንበሩ ተወርውሮ እየተገፋ ወደ ፍትሕ አደባባይ ቀረበ፡፡ጋዳፊ አይጦች እንዳላለ እራሱ ከተሸሸገበት የአይጥ ጎሬ ተጎትቶ በአደባባይ ለእይታ ቀርቦ፤እራሱ ባስጠረበው የወርቅ ሽጉጥ ህይወቱ አለፈች፡፡የየመኑ አሊ ሳላህ፤ ለ33 ዓመታት በግፍ ከገዛና በፊቱ ላይ በፈንጂ ፍንጣሪ አጓጉል ሆኖ ከቆሰለ በኋላ አሁን ለመሰደድና ኑሮውን ከመሰሉ መለስ ጋር ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ ለመሰደድ ተገዷል፡፡ (አለማወቅ ሆኖ ነው እንጂ እዚያም ቤት እሳት አለ እንዲሉ በአንድ ቦታ መሰባሰባቸው የጭንቅላታቸው የማሰብ ስፋት ምን ያህል ጠባብ መሆኑን ነው የሚያሳየው) በሺር አል አሳድ አሁን በሲሪያ ሉካንዳ እያካሄደ ቢሆንም፤ እንደፈላጭ ቆራጭ ወንድሞቹ ተራው ሲደርስ በአንድ ረድፍ መቆሙ አይቀሬ ነው፡፡

የሰብ ሰሃራ አፍሪካም ፈላጭ ቆራጮች ሲንሸረተቱና መቀመጫቸውን ሲለቁ ታይተዋል፡፡ ኮተ ዲቩዋሩም ሎራንት ባግቦ ከመኮፈሻው የሽቅርቅር ነጭ ኮሊታው ሸሚዙ ተለያይቶ በቤተመንግሥቱ ከተወሸቀበት ጓዳው ተይዞ በፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግድያ ለፍርድ ለዓለም የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፏል፡፡ የኒጀሩ ማማዱ ታንጃ ሕገመንግሥታዊ የስልጣን ገደብን በመጣስ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ቢፍጨረጨርም የኒጀር ጦር አሽቀንጥሮ አውርዶታል፡፡ የማማዱ ታንጃም ቀንደኛ ተወዳዳ በሕዝባዊ ምርጫ ሥልጣኑን ተረከበ፡፡በቅርቡም፤የሴኔጋሉ መሪ የ85 ዓመቱ አብዱላዬ ዋዴ የሶስተኛ ጊዜ ምርጫ ለማድረግ ለማጭበርበር ሲያቅድ ሕዝባዊ ዐመጽ ተቀጣጥሎበት ምርጫ እንዲካሄድ ሲደረግ አብዱላዬ ዋዴም ለመወዳደር ሞክሮ በቂ ወንበር ሳያገኝ በመቅረቱ በዘዴ ስልጣን ለመያዝ በመንቆራጠጥ ላይ ቢሆንም አሸነፈ ቢባልም ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዲያጋጥመው አያጠራጥርም፡፡

ባለፈው ዓመት በጃንዋሪ 2011 ‹‹ከአፍሪካ ፈላጭ ቆራጮች ውድቀት በኋላ›› በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ አቅርቤ፤ እግረመንገዴንም 3 መሰረታዊ ጥያቄዎች አንስቼ ነበር፡፡ ለመሆኑ በአፍሪካ ያለው የፈላጭ ቆራጮች የጭቃ ስሪት ቤት ሲፈራርስና ከነዚያ ጭቃ ቤቶች በስተጀርባ ያለው የፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ቅዠት ሲፈራርስ አፍሪካ ምን ትሆን ይሆን? የአፍሪካ ጉዳይ ‹‹ጨዋታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ›› ጨዋታ ይሆንና የማይጠገን አወዳደቅ ደርሶባት ዳግም መልሳ መገንባት የማትችል አህጉር ትሆናለች? እነዚያስ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎችና የሕዝብ ደም፤ግፍና ሰቆቃ በጃቸው ላይ ያለባቸው አውሬዎችስ ምን ያጋጥማቸው ይሆን? ለመጨረሻው አንድጥያቄ ዝግጁ መልስ ሲኖረኝ ለሁለቱ ግን አላገኘሁላቸውም፡፡

ሕዝቡ የበቃኝ፤በቃችሁ አታሞውን በነዚያ የገዢዎች ጭቃ ቤት ዙርያ መጎሰም ሲጀምር የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ገዢዎች በእጃቸው ሊገባ የሚችለውን ኮተታቸውን በመሰብሰብ ቅራቅንቧቸውን አክተው፤ ልክ የሌሊት ወፎች ከተቀበሩበት ወጥተው እንደሚበሩት አይነት ሲበሩ ጥቂቶቹ ደሞ በጭቃው ልስን ስንጥቅ ውስጥ ያም ካልሆነ በአቅራቢያ ካሉ መሰል ግፈኛ ገዢዎች መንደር በመደበቅ ፍትሕን የሚሸሹ ስደተኞች ለመሆን ይሞክራሉ፡፡ሌሎች ደሞ እመንጥ ይግቡ ስምጥ በይፋ ሳይነገር የዘረ4ፉትን ሃብታቸውን አዩን አላዩን በሚል ኑሮን ለመቀጠል ይታገላሉ፡፡ እነዚህ ግፈኞች ሃገሪቱን ዘርፈው ለሕዝቡ ባዶ ካዝና ትተውለት በመኮብለላቸው፤ሕዝቡም በትግሉ ካገኘው፤ ከነጻነት ንጋት ጋር በወረሰው ባዶ ኤኮኖሚ፤ መለመላውን በቀረው የባንክ ሳጥን፤በተራቆቱ የገበያ መደርደሪያዎች፤ የግፍና የስቃይ መናሃሪያ በሆኑ የግፍ እስር ቤቶች በታፈኑ እስረኞች፤ለሥልጣን በመቋመጥ በተራቡ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ሽኩቻ የተተራመሰ የፖለቲካ ውጥንቅጥ ይጠብቀዋል፡፡

ኢትዮጵያን ከፍርስራሹ በኋላ ማነው የሚጠግናት?

የግፍና የፈላጭ ቆራጮች የጭቃ ግንብ ሲፈርስ ኢትዮጵያን ምን ይጋጥማታል? ኢትዮጵያ ከውድቀት የማትነሳበት ሁኔታ ያጋጥማትና ተበታትና ትቀራለች?ወይስ ኢትዮጵያ እንደ ሊቢያ፤ ግብጽ፤ ቱኒዚያ፤ ያለ ሁኔታ ውስጥ ትገባለች? ወይስ እንደሲሪ ያለው ሁኔታ? አሁን ነግፍ የሚገዟት ገዢዎች እንደሚሉትና እንደሚያስፈራሩበት የራሳቸው ብቻ የሆነው አስተሳሰብ አይገጥማትም ብሎ ማንም በእርገጥኝነት መናገር አይችልም፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ መበታተን እድሏ ከሆነ ምን ይደረግ፤ ግን አፈጣጠሯና የኢትዮጵያ እውነታ እንደሚታወቀው ከሆነ ግን ለመበታተን የተፈጠረች አይደለችም››

በእርግጠኝነት መባልና መጠበቅ የሚቻለው እውነታ ግን፤በፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ገዢዎች የደቀቀችውን ኢታዮጵያ መልሶ የመገንባትና ጠላቶቿ እንደሚመኙላት ከመሆን የሚያድኗት ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያን የሚሉ ወዳጆቿ ናቸው፡፡እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ፤የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን፤የሲቪሉ ማሕበረሰብ፤እና የነጻው መገናኛ ብዘሃን አባልት፤ የዴሞክራሲ ተሟጋቾች፤የሰብአዊ መብት ታጋዮች፤የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ እና ኢትዮጵያን ያሉ ሁሉ በአንድነት በመተሳሰብና በመግባባት በመሰባሰብ ሃገቱን ከአንድ ሰው አንድ ፓርቲ ግዛት አላቀው በሕግ በታገዘ የመድበለ ፓርቲ ሃገር ሊያደርጓት ይችላሉ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ተጋርጦ የቁም ስቅላቸውን ሲያሳያቸው ከነበረው የግፍ አገዛዝ በመውጣት ለወደፊት የተሸለና ነጻነት የሰፈነባት፤ የዴሞክረሲ መብት ያለባት፤ የፍትሕ የበላይነት የተደነገገባት፤ አንድ ሆነው በአንድነት እየመከሩና እያቀዱ፤ ልዩነታቸውን ተቻችለው፤በግልጽ በመወያየትና ጥበባዊ ሃሳብን በማፍለቅ፤ ለዕውነት በእውነት በመቆም፤በመከባበር፤ያለተጽእኖ በመደራደር፤ ኢትዮጵያን መመስረት ከፈለጉ፤ የሕዝብን ፍላጎት እምነትና ውሳኔ በማክበርና በመቀበል መንቀሳቀስ የግድ ይላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ካወንስል (ኢብሽካ)

በኢትዮጵያ ያለው የፈላጭ ቆራጭ ግፈኛ ገዢዎች ግድግዳ ሲፈራርስ መደረግ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ፤ በቅርቡ መሰረታዊ ዓላማ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ይህን ሁኔታ በሃላፊነት ለመሸከም ፈቅደዋል፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ካወንስል (ኢብሽካ) ከሁሉም አቅጣጫ በተለያየ መስክ ያሉትን ኢትዮጵያውያን ሁሉ በማሰባሰብ፤ ኢትዮጵያን ካለችብት የግፍና የጭቆና ዘረኛ አገዛዝ አውጥቶ፤ወደ ዴሞክራሲያዊትነት ለመለወጥ እንዴት በሚል ነጥብ ላይ ማወያየት አቅዷል፡፡

በግልጽ የተቀመጠው ዓላማውም ‹‹በተለያየ ቦታና ሚና ላሉት ኢትዮጵያውያን የጉዳዩ ባለቤቶች የመልካም ግንኙነትን ፍላጎት ማዳበር፤መግባባትን መገንባት፤ የግንኙ ነትንና የኢንፎርሜሽን ልውውጥን መረብ መዘርጋት›› የሚል ነው፡፡ ኢብሽኮ ከየትኛውምና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ቁርኝት ጨርሶ የለውም፤አሁንም ሆነ ወደፊት መሠረታዊ የሆነ የዴሞክራሲ ሥርአትን ከመዘርጋትና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በመፍጠር፤ የሰብአዊ መብት መከበርን ማረጋገጥ ውጪ ሌላ ተልእኮ የለውም፡፡ ምኞት ዓላማና ግቡም ሁሉንም ያካተተ የዴሞክራሲ ስርአት ተሟጋቾችን በመፍጠር ሃገራችን ነጻ፤ዴሞክራሲያዊ፤ሰላማዊና የዳበረች የለማች እንድትሆን መጣር ብቻ ነው፡፡

ለዚህ ከባድና ሃገር አቀፍ ውጣ ውረድ የበዛበት የነጻነት ራዕይ ከተሰለፉት ግንባር ቀደም ሰዎች አንዱ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ነው፡፡ፍስሃ በትምህርቱና በቴክኒካዊ ትምሕርት ታላቅ እቅድ ያሳካ ወጣት ኢትዮጵያዊ ነው፡፡እ አ አ በ1991 ዓ፤ም ዩኒቲ በመባል የታወቀውን ዩኒቨርሲቲ ዘር ዘርቶ፤ በሃገሪቱ የመጀመርያውና አስፈላጊውን መመዘኛ ሁሉ በማሟላት የመጀመርያውና ትልቁ፤ብቸኛው የግል ዩኒቨርሲቲ ለመሆን የበቃውን ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲን የመሰረተ ነው፡፡ በ2008 ዓ፤ም ለዓመታት በየቀኑ በሚፈጠርበት አዳዲስ ህግጋትና ደንብ ጋር ከመንግሥት ጋር ሲታገልና ውደቅ አልወድቅም ግብ ግብ ሲያካሂድ ቆይቶ የመንግሥት ፍላጎት የግል ተቋማትን ማዳከምና ማጥፋት መሆኑን በመጨረሻው በመገንዘብ፤ እጅግ የሚወደውን፤ጉልበቱን፤ እውቀቱን፤ማንነቱን የሰዋለትን የሚወደውን ዩኒቨርሲቲውን ሽጦ ፍስሓ ለስደት በቃ፡፡(ስለዚህ ጉዳይም በወቅቱ በተደጋጋሚ ጥሁፍ አቅርቤ እንደነበር ሊታወስ ተገቢ ነው፡፡)

ይህን የመሰለውን ውስብስብነት ያለበትን የፖቲካ እንቅስቃሴ ለመምራት ፍስሃ ትክክለኛው ሰው ነው ሊባል አይችል ይሆናል፤በራሱ አንደበት እንደተናገረው ፖለቲካን ከሚሸሹትና እራሳቸውን ከፖለቶካ መስህብ ካገለሉት አንዱ ነበር፡፡እምነቱም ፖለቲካና የንግድ ሥራ አይስማሙም የሚል ነው፡፡ ያም ሆኖ በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ሙስናን፤የአስተዳደር ብልሹነትን፤በሥላጣን አለአግባብ መጠቀምን፤ቢገነዘብም አይቼ አላየሁም፤ሰምቼ አልሰማሁም፤ አልናገርም ማለትን መርጧል፡፡‹‹ምን አገባኝና!›› ወደማለት ከማዘንበልም አልፎ ኢትዮጵያዊነ ቱንም ጠልቶት ነበር፡፡ እየዋለ እያደረ ሲሄድ ግን በየዕለቱ የሚፈጸመውን የሕዝቡን መከራና ግፍ፤በመመልከት፤ እራሱን ከእውነታው በማሸሽ ተመልካች በመሆኑ ‹‹የህሊና ወቀሳቀው›› መቆሚያ መቀመጫ አሳጣው፡፡ በመጨረሻውም በሚያየውና በሚሰማው፤በየቀኑ በሚያዳምጠው ሕዝባዊ ብሶትና ግፍ፤ ገዢው መንግሥት እኔ ያልት ብቻ፤ ሕዝብ ማለት እኔ የምለውን የሚቀበል ብቻ ነው የሚለውን መመልከቱ ስላንገሸገሸውና በተለይም፤ የሕዝቡን አቤቱታ ሰሚ ማጣት በማገናዘብ ምሬቱ ወደ ራሱ ዞረና ‹‹ጥንካሬን ከእውነት፤ እምነትን ከፈጣሪ›› በመቸር፤ለዚህ ሁሉ እኔም ድርሻ ሊኖረኝ ይገባል በሚል እምነት፤ሕዝቡንና ሃገሪቱን ከተጋረጠባት ክፉ፤ ዘረኛ፤ ጀብደኛ፤ሙሰኛ፤ጨካኝ ገዢ ለማላቀቅና፤ ስርአቱን በመለወጥ ሃገሪቱና ሕዝቡ የዴሞክራሲ፤ የሰብአዊ መብት፤ የፍትሕ የበላይነት ባለቤቶች እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ ለመክፈልና ለማድረግ የዜግነትና የሞራል ግዴታ እንዳለበት በይፋ ይናገራል፡፡እንደምርጫና ፍላጎት ግን አሁንም በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ በመሰማራት በርካታ የኢትዮጵያን ወጣቶች የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት እንዲችሉ ማስተማርን ይመርጣል፡፡

ፍስሃ ሲናገርና አለአንዳች ማጋነን፤ በሰከነ አንደበት፤ ግልጽ በሆነ አገላለጡ ከመማረክ የሚያመልጥ የለም፡፡ቃላቶቹ ቀጥተኛና እውነት እንጂ እንደፖለቲከኛ፤ ታስቦባቸው፤ እንዲጽሙ ሆነው ተቀምመቀው የሚወጡ አይደሉም፡፡ እንደወረዱ ወደሰው ደርሰው ግን ያሳምናሉ፡፡ እውነት እውነቱን ብቻ ይናገራል፡፡ ስሜቱን ነው የሚያካፍለው፡፡ሕዝባዊ ንግግሮቹ የጋንዲን ‹‹ሳቲግራሃ››(የሃቅ ሃይል) ያስታውሳል፡፡‹‹መቶ በመቶ እቅዳችን ግቡን እንደሚመታ የምናረጋግጠው በሁለት ምክንያት ነው፡፡ በመጀመርያ የምናደርገው ሁሉ በዕውነት ላይ የተመሰረተ ነው፤ በእግዚአብሔርም እናምናለን፡፡› በፍስሃ ንግሮች ውስጥ ማንዴላዊነትም አለ፡፡ በተደጋጋሚ ‹‹ለሃገሬ የዴሞክራቲክ ለውጥ ለማምጣት እስከቻልኩ ድረስ ከማንም ጋር እሰራለሁ፡፡›› ይላል፡፡ ታላቁ ኔልሰን ማንዴላም ሲያስተምር ‹‹ከጠላትህ ጋር ሰላምን መፍጠር ከፈለግህ፤ ከጠላትህ ጋር መስራት ይኖርብሃል፡፡ ጠላትህም ተባባሪህ ይሆናል›› ነው ያለው፡፡

ፍስሃ፤ኢብሽካ በኢትዮጵያ ያለውን የግፍና የጭቆና መንግሥት አስወግዶ ዴሞክራሲን ለማስፈን እስከተሰለፈ ድረስ፤ ከማንም ጋር፤ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታና ገደብ፤ ለመስራት ፈቃደኛ ነኝ ይለናል፡፡ በተግባር ላይ በሚሰማሩ ሰዎች እምነት አለው፡፡‹‹እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ 1 በመቶ መስዋእትነት ቢከፍል፤በስድስት ወረታ ውስጥ መጠነ ሰፊ ለውጥ እናመጣለን፡፡ የሕዝባዊ አገልጋይነት ፈቃደኝነትና ፍላጎት ልናዳብር ተገቢ ነው፡፡ ለሕዝባዊ አገልግሎ የመሰለፍ ባህል ማዳበር ይገባናል፡፡ ለፖለቲካ ሥላጣን ፍላጎትም ምኞትም የለንም፡ሕልምና ራዕያችንም ይህን የዴሞክራሲያዊ ሽግግር አፋጥነን ተግባራዊ በማድረግ ወደየሙያችን መመለስ ብቻ ነው፡፡››

ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሽግግር

በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሽግግግሩ ፈታኝ ሊሆን ይችላል የማይቻል ግን ጨርሶ አይደለም፡፡ወደ ዴሞክራሲ ሽግገሩ ምን ይመስላል? በኢትዮጵያ የተገነባው የጭቃ ግንብ ሲደረመስና ሚስጥራዊ ድበቃውና ጉዱ ሲጋለጥ፤ ሁለት ዋነኛ ጉዳዮች እርቃነ ስጋቸውን ይጋለጣሉ፡፡ በቅድሚያ ሕዘቡ ብሔራዊ የገንዘብ ጎተራው ባዶ መሆኑንና፤ ሃገሪቱም ወደ አዘቀዘቀ የመዋዕለ ንዋይ ክስረትና ዓለም አቀፍ ውስጥ እንደተዘፈቀች ይረዳሉ፡፡ በሁለተኛ ደረጃም የተጠናከረና መሰረት ያለው የዴሞክራሲ መዋቅር ባለመኖሩ ለተወሰነ ወቅት ያልተረጋጋ ሁኔታና ውጥረትና አለመግባባት ያጋጥማል፡፡ ይህን መሳዩን ሽግግር በተሸለ ለማወቅና መፍትሔም ለማግኘት፤ በኢትዮጵያ፤ በፈላጭ ቆራጭ አገዛዙ መጨረሻና በዴሞክራሲ የብርሃን ፍንጣቂ ጊዜው መሃል ያለውን አሉታዊ ሁኔታ ማጤን ያስፈልጋል፡፡

የከፋፍለህ ግዛ እቅዳቸውን ለማሳካት ኢትዮጵያን በግፍና የበደል ጭቆና በመግዛት ላይ ያሉት፤የወቅቱ ጊዜያዊ፤አረመኔ፤የግፍና የበደል ቋት የሆኑት ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች፤ ሓገራችንን፤ በዘር፤ በጎሳ፤ በመንደር፤ በቀበሌ፤ በጎጥ፤ከፍፍለዋታል፡፡ያ ነው እንግዲህ ለችግር መብቀያና ቁጥቋጦ ሊሆን የሚችለው፡፡ የወረቀት ላይ ነበር በሆነው ደንብና አዋጅ ቀርጸው በፈጠሩት ቃለ አባይ የምርጫ ቦርዳቸው፤ በየቀኑ በሚወጣ ደንብና እገዳ በበዛበት አዋጃቸው፤ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎን ጨርሶ እንዳይንቀሳቀሱና፤ ከአባሎቻቸውም ሆነ ከሌሎች የሕብረተሰቡ ክፍሎች ጋር እንዳይገናኙ የብረት ማነቆ አድርገውባቸዋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እንደ ፍየል በየእለቱ እየታገቱ በእስር እየተንገላቱ ነው፡፡ ቆራጥ የሕዝብ አንቀሳቃሽና የዴሞክረሲ፤ የሰብአዊ መብትና የፍትሕ ተሟጋቾች፤ በሽብርተኛነት እየተፈረጁና የሃሰት ክስና ሰነድ እየተዘጋጀባቸው ለእስር እየተዳረጉ ነው፡፡ ሕዝቡ ያለአንዳች መንስኤ፤ በዘፈቀደ እየተያዘና ለእስር እየተዳረገ በመሆኑ የሕግ የበላይነት እንኳን ሊተገበርና ስሙም አይነሳም፡፡ በሚታወቁና ሚስጥራዊ በሆኑት የገዢው የሰላማዊ ሰዎች ማጎርያ ጣቢያዎች የሚፈጸመው የስቃይ ምርመራና ግፍ ማስረጃ በተደጋጋሚ የቀረበበት ነው፡፡ የግለሰቦች ነጻነት ጨርሶ የማይታሰብ ነው፡፡ ሃሳብን በነጻ መግለጽ አሁን አሁንማ የሽብርተኛነት ማረጋገጫ እየሆነ ነው፡፡ ነጻ የህትመት ውጤቶችም በገዢው ፓርቲበ ቃታና ጡጫ ስር ናቸው፡፡ የእለት ተዕለት ዛቻ፤ ማስፈራራት በጣት የሚቆጠሩትን የህትመት ውጤቶች ባያስጎነብሳቸውም እንዲያቀረቅሩ ለማድረግ እየተሞከረ ነው፡፡ አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉት የኤሌክትሮኒክ ጣቢያዎች፤ ድህረገጾች፤ ኢሜይሎች፤ (እድሜ ለቻይና፤ ጸረ ነጻነት፤ ጸረ ዴሞክራሲ፤ ጸረ ፍትህ፤ጸረ ሰብአዊ መብት መንግሥት ትብብር) ከጥቅም ውጪ ሆነው ተዘግተዋል፡፡ የግል ሚዲያዎችም ጫናው ሲበዛባቸው ተቋርጠዋል አታሚዎቹና ባለቤቶቸሁም እስርና እንግልትን በመሸሽ ሃገር እየጣሉ ለስደት ተዳርገዋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ ድርጅቶችም በአሻንጉሊቱ ፓርላማ እየተወገዙ መብታቸውን ተገፈዋል፤ የሕግ የበላይነትም በይስሙላው ፍተሕ አደባባይ በሚኮፈሱ ሙያ አልባ የገዢው አገልጋዮች ተሞለው ግልጋሎት ሰጪነታቸውም፤ ፍርፋሪ ለሚጥልላቸው ገዢው መደብ ሆኖ አፈናውንና ጭቆናውን ሕጋዊ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ምሉዕ በኩላሄ በሥላጣን ጣሪያው መብትም ለአንድ ግለሰብ ተጠራርጎ በመሰጠቱ ያለ አንዳች ሕገመንግሥታዊ አካሄድና ክትትል፤ ቁጥጥርና ተጠያቂነት እንደፈለገ እንዲጋልብበት ተደርጓል፡፡ ከዚህ መሰሉ አገዛዝ ወደ ዴሞክረሲያዊ አስተዳደር የሚደረግ ሽግግር፤ በገዢዎቹ ላይ ብቻ የሚደረግ የቅርጽ ለውጥና ሂደት ብቻ ሳይሆን፤ሥር ነቀል የሆነ የህብረተሰቡንም ስሜትና የሲቪል ማህበረሰቡንና የሃገሪቱንም የፖለቲካ ባሕልም መለወጥ የግድ ነው፡፡

ከፈላጭ ቆራጭ ሥርአት ወደ ዴሞከራሲያዊ ስርአት ሽግግር፤የሽግግር ወቅት ጉዳይ ብቻ ነው!

የፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች መገርሰስ ብቻ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ልደት ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ከፈላጭ ቆራጭ ፍርስራሽ ውስጥ የዴሞክራሲ ግንብ ሊፈጠር አይችልም፡፡የዴሞክራሲ ውልደት ብዙ ውጣ ውረድና የሕብረት ሥራን ይጠይቃል፡፡ለተፈጠሩትና ሲተገበሩ የነበሩት ችግሮች ሁሉ ጥበባዊ መፍትሔና ዘዴ የስፈልጋቸዋል፡፡ለዚህ ደሞ ቀና ፍላጎትና መልካም አመለካከት ይጠይቃል፡፡ኢትዮጵያን ከተጣለባት የፈላጭ ቆራጭ አረመኔያዊ ችግርና ማነቆ ለማላቀቅና ዴሞክረሲን ለመገንባት ብዙ መስዋእትነት ያስፈልጋል፡፡ይህች በችግርና በመከራ ውስጥ በእርኩስና ንፉግ፤ በእኩይና አረመኔ ገዢዎች መዳፍ ሥር የከረመች ሃገራችን፤ የዶሞክራሲ አካላትና ጠንካራ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የተጠናከረና ህያው የሆነ የሲቪክ ማህበረሰብ ባልተዋቀረበት፤ ነጻ ሆነውበመንቀሳቀስ የዴሞክረሲን ልደትና የአእድገቱን አካሄድ የሚተልሙ የፕሬስ ድርጅቶች በሌሉበት ከዚህ ፍዳ እንድትላቀቅ ለማደረግ የሁሉንም ይሁንታና ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡

በቅርቡ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሽግግር ያካሄዱት ሃገራት ታሪክ እንደሚያሳየው፤የሽገግግር ችግሩ እራሱ የሽግግር ሂደቱ ነው፡፡በዲክታተር ስርአት መውደቅና በዴሞክራሲያዊው ስርአት አመሰራረት መሃል ጠባብ የሆነ የታሪክ ውሳኔን የሚጠይቅ ሂደት ያጋጥማል፡፡ በዚያች ጠባብ የመስኮት ክፍተት በምታህል ሂደት ውስጥ በሽግግሩ ወቅት ከዚያ ከፈራረሰው የፈላጭ ቆራጭ ግፈኛና ዘረኛ ፍርስራሽ ውስጥ የሚፈጠረው፤የሚናፈቀውና የሚመረጠው የዴሞክራሲ ፍሬ ነው ወይስ ያለፈው የክፉ ገዢ አመድ ተለውጦ በሌላ መልክ እራሱ የፈረሰውን ግፈኛ አገዛዝ የሚተካ የባሰ አረመኔ ነው፡፡ በአጭር አነጋገር፤በፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ መፍረስና በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ፤ወሳኙ የሽግግሩ መስኮት ነው፡፡ በባለቤቶቹ መሃል በሚነሳ አላስፈላጊ አፍራሽ ውድድርና ግጭት፤ አመኔታ መጥፋት፤ሁሉም የየራሱን እምነትና ፍላጎት አራማጅ ከመሆን፤ ዴሞክራሲ የሚገነባ ከሆነ ውጤቱ ደካማ፤ ጥቅም የለሽ ነው የሚሆነው፡፡ሽግግሩ በቀና ግልጽና መግባባት ላይ በተመሰረተ ውይይት ላይ ያተኮረ ከሆነ፤የሁሉም ፍላጎት ለሃገርና ለሕዝብ ቢል እራስን ሳይሆን የተደረሰበትን የስምምነት ራዕይ ያገናዘበ፤ ዘላቂ የሃገርን እድገትና ልማት የህብረተሰብን አንድነትና አዲስ ስርአት ማጎልበት ጋር የተዋሃደ ከሆነ፤ዘላቂና አስተማማኝ የዴሞክራሲ ግንባታ ያብባል፡፡

ይህን ሃሳብ በተመለከተ የኢትዮጵያ ታሪክ በቂ ምስክርና ረጋገጫ ነው፡፡በ1991 በተካሄደውና በአሜሪካ አደራዳሪነት በተከናወነው የሽግግር ሂደት ወቅት፤መለስ ዜናዊ በሰላ አንደበቱና በረቀቀ እኩይ አካሄዱ፤ኤሪካንና ሁሉንም ባለጉዳዮችና ባለመብቶች በማጭበርበር በአጭር አሰቀራቸው፡፡በቅርቡ ቃለጠይቅ የተደረገላቸው የአሜሪካው አደራዳሪ ወኪል ኸርማን ኮህን ይፋ እንዳወጡት፡

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ቲ ፒ ኤል አፍ፤ያ በር ላይ ደርሷል፡፡ ስለዚህም ምርጫችን ለስልሶ ማርፍ ቢልና በመረጥነው የአገባብ ዘዴ ጦርነቱ እንዲያበቃና ቀጣይ ጥፋትም እንዳይከሰት ማድረግን ነበር፡፡…….መንግሽቱን ተረከቡ አላልንም፡፡ያልነው አዲስ አበባን ተቆጣጠሩ ነው፡፡አዲስ አበባን በመቆጣጠር የሚያረጋጋ ሃይል ያስፈልግ ነበር፡፡ ከዚያም በእርጋታ የሽግግር ሂደቱን ተግባራዊ በማድረግ አዲስ መንግሥት መመስረት ነበር ፍላጎታችን፡፡ ኮኸን ሲያጠቃልሉ፤ ‹‹ምን ያደርጋል ብዙም ሽግግር አለነበረም፡፡›› ነው ያሉት፡፡

ኮኸን በማከልም፡

ሁሉን ፓርቲዎች በማስተባበርና በማግባባት፤በአንድነት በመቆም እንዲሰሩና አንድ የዶሞክራሲ ይዘት ያለው መንግሠት እንዲመሰርቱ፤ኢትዮጵያና ኤርትራም በአንድ ገንዘብ እንዲጠቀሙ፤የሚል ሃሳብ ይዤ ነበር የጀመርኩት፡፡ ከኔ ሃሳብ ስንዘራ በኋላ ሶስቱ ፓርቲዎች ሌላ አደራዳሪ ሳያስፈልጋቸው ውይይታቸውን መቀጠል ወሰኑ፡፡ወዲያው ወደ አንድ የተለየ ክፍል በግባት የግላቸውን ውይይት ካካሄዱ በኋላ አንድ መግለጫ አወጡ፡፡ መግለጫውም፡- ሁሉን ፓርቲዎች አቀፍ የሆነ አንድ ኮንፍራነስ በአዲስ አበባ ጁላይ 1 እንዲካሄድና በዚያው ወቅትም የሽግግር መንግሥት ለማዋቀር ውይይትና ድርድር እመዲካሄድ ስምምነት ላይ መደረሱን የሚያበስር ነበር፡፡በአንድና አጭር ብቸኛ መግለጫ መለስ የሥግግሩን ሂደት አስገድዶ በመስረቅ ጠቅልሎ ኪሱ ከተተው፡፡ወዲያውም ሥልጣንን የግሉ በማድረግ የፈላጭ ቆራጭ የግፍ አገዛዙን ማስረጽ ቻለ፡፡ለዚህም ነው ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገው የሽግግር ወቅት እጅጉን ፈታኝና አሳሳቢም የሚሆነው፡፡ማንም ግለሰብ ሆነ ፓር፤ ቀጣዩን የዴሞክራሲ ሽግግሩን እንዳይነጥቅ አለያም እንዳያጭበረብርና ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያስኬደው ሁሉም ነቅቶ መጠበቅ ያለበት፡፡የሽግግሩ ሂደት በራሱ ሊተገበር የሚገባውን የ‹‹ዴሞክራሲ›› ምንነት ያሳያል፡፡የተለያዩ የሽግግር ሂደቶችናማካሄድና የተለያዩ ውጤቶች ማግኘት ይቻላል፡፡በዚህም ውጤት ሚዛናዊ የሆነ የባለመብቶቹ ድርሻም ሊሰመር ይችላል፡፡ለምሳሌ የሽግግሩ ሂደት በጎሳ ፖለቲካ ላይ ያተኮረ ከሆነ፤በጎሳዎቹ መሃል በሚበቅል ፉክክርና እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የበላይነት፤የዴሞክራሲው ሂደት ሊቀጭጭና ሊከስም ይችላል፡፡አንዱ ግለሰብ የፖለቲካ መሪ፤አለያም ስብስብ የሽግግር ሂደቱን ለመጥለፍ ከተሳካላት የሚያስከትለው ውጤት አሳዛኝና አሳፋሪ ነው የሚሆነው፡፡

ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርአት ሽግግር ምን ማለት ነው? በኔ አመለካከት፤ ቀላል ነው፡፡ መሰረታዊ በሆነው እሳቤ እጀምራለሁ፡፡በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ በጉልበት፤በሃይል፤በብልጠት፤ወይም በድብብቆሽ ክፉ ምግባር አይገነባም፡፡በአንደ ፓርቲ፤ በአንድ ሰው፤በተወሰኑ አንጃዎች፤በአንድ ብሄር ወይም ጊሳ፤አለያም በአንድ ውሱን በሆኑ የህብረተሰብ ቡድኖች ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ መሰረቱ ሊጣል አይችልም፡፡የአፍ መደለያ ብቻ በሆነ፤አንድነት፤መግባባት፤መፈቃቀር በሚል ሽንገላ ብቻም ሊበቅል አይችልም፡፡ በኢትዮጵያ ዕውነተኛው ዴሞክራሲ ሊያብብና ተግባራዊ ሆኖ ሕዝባዊ ተቀባይነት የሚኖረው፤ከፈላጭ ቆራጭነት የወጣና ሁሉንም አቀፍ የሆነ ስብስብን ያካተተ፤ለውይይት የሚያበቃ፤መደራደርና መከራከር፤ መግባባትና መቻቻል እንዲሁም መተማመን፤ ሃሳብ መለዋወጥ የሚታይበት የነገዋን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ማዕከል ያደረገ ሽግግርና ሂደት ሲኖር ብቻ ነው፡፡

ይህ ምናልባት አስቸጋሪ መስሎ ሊታይ ይችላል፡፡ የኔ ሃሳብ፤የዴሞክራሲ ሽግግር ውጤታማ ሊሆን እንዲችል፤ በጣም ወሳኝና አስፈላጊው ጉዳይ የባለጉዳዮች መብዛትና አንድነት ሳይሆን፤በባለጉዳዮቹ መሃል መተማመንና መግባባት፤ የግቡን መድረሻ በመተማመን ያቀዱትን ወደ ተግባር ለመለወጥ ፈቃደኝነት፤ ለዚህ ዓላማ የጸናና ቆራጥ እምነትና ፍላጎት ያላቸውን፤ምንነቱን አውቀውና ተገንዝበው ለዚህ ጉዳይ ያላሰለሰ ጥረትና ለድካም አይበገሬነት ያላቸውን፤ በግልጽ በመነጋገር አለመግባባትን የሚያስቀሩ ሆነው ከተዋቀሩ ይህ ነው ዋናው መሠረት፡፡‹‹ሁላችንም በአንድ ጀልባ ላይ ነን፡፡የምንቀዝፈውም የግፍ፤ የጭቆና፤ የሙስና፤የመብቶች ገፈፋ ማዕበል ወደሚፈልቅበት አቅጣጫ በመሆኑ፤ወይ አብረን እንዋኛለን ካልሆነም አብረን እንሰምጣለን››ነው ዓላማችን፡፡

የሽግግር መስኮቱ ከተከፈተና ከመከፈቱ አስቀድሞ መደረግ ያለበት ምንድን ነው?ከመሰረቱ እንጀምር፡፡ ምን ዓይነት ‹‹ዴሞክራሲ››ነው የምንፈልገው? በሁለት ገዢዎች የግዛት ዘመን፤‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ተብሎ በተቀረጸ የግፍ ሂደት ጊዜያት አሳልፈናል፡፡ለኢትዮጵያ፤ አሁን ኮንሰቲቴዩሽናል ዴሞክራሲ ተፈላጊና ወቅታዊ ነው?፡፡ የኮንስቲቲዩሽናል ዴምክራሲ አወቃቀርና ንድፈ ሃሳብ፤የመንግሥትን ስልጣንና የፖለቲካ ስልጣንን ለሚመሩ ሃይላቸውን የሚለካ ነው፡፡ሕገ መንግሥቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ ሕግ ሆኖ የተቀረጸ ሲሆን ግለሰብም ሆነ ምንም አይነት ድርጅት አለያም ሃይል ሊያጣምመው፤ በዘፈቀደ ሊቀንሰው፤ ሊጨምር፤ እንዳሻ ሊቀነጣጥቡትም አይችሉም፡፡ ሕገ መንግሥቱ መተዳደርያና መመርያ፤ ሃገርንና ሕዝብን ጠባቂ እንጂ ለመበደያ፤ ለግፍ መፈጸሚያ፤ ለጥቃት ደንብና ስርአት ማውጫ ጨርሶ ሊሆን አይችልም፡፡

የመንግሥት ባለስልጣናት ስልጣናቸው የሚለካውም ሆነ የሚገደበው፤ እነሱም በጥቅም ላይ የሚያውሉት ከሕገመንግስቱ አተረጓጎም አኳያና ከዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ጋር በተደረገው መግባባት ብቻ እንጂ;ከዚያ ውጪ አይፈጸምም፡፡በፌዴራሊዝም አወቃቀር ሥልጣን በማዕከላዊና በክልላዊ መንግስቶች መሃል ተለክቶ ሊከፋፈል ይችላል፡፡(የጎሳ ፌዴራሊዝም ማለት፤ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ለመድብለ ፓርቲ ጨቋኝና አፋኝ እንደሚሆነው ማለት ነው)የፖለቲካ ኢንስቲቲዩቶች፤በተለይም የፍትሕ አካላት፤የላዕላይ መዋቅሩ አካላት ከሆኑ ባለስልጣናት ትእዛዝና ተጠሪነት ነጻ ስለሚሆኑ፤ፍትህንና ለፍትህ አስፈላጊ የሆኑትን መስፈርቶች ያለ ሥልጣን ግፊት ያከናውናሉ፡፡ በኮኒስቲቲዩሽናል ዴሞክራሲ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ የመሸነፍ እድል ይገጥማቸዋል፡፡(በተለይም ሕዝቡን የማዳመጥ ፍላጎት ካጡ መሸነፋቸው አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ መሰል ዴሞክራሲ ማንም 99.6በመቶ ምርጫ ያሸንፋል ማለት ቀልድ ነው፡፡በዚህ አይነት ዴሞክራሲ መንግሽታት ሕዝቦችን ይፈራሉ እንጂ ሕዝቡ መንግሥትን አይፈራውም፡፡በኢትዮጵያ ኮኒስቲቲዩሽናል ዴሞክራሲ ወቅቱ አሁን ነው?

የፈላጭ ቆራጭ (ዲክተተርሺፕ) አገዛዝ በራሱ እስኪፈራርስ መጠበቅ?

አንዳንድ ሰዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጨቋኝ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የጭቃ ግንብ ተፍረክርኮ የሚደረመስበትን ጊዜ ለመወሰን በጣሙን ይጨነቃሉ፡፡ጋዳፊም ሂነ፤ቢን አሊ፤ሙባረክ ወይም ሳሊህ የጭቆና ግዛታቸው ማብቂያና የፈላጭ ቆራጭነታቸው ማክተሚያ መች እንደሆነ ማወቅ መች ሆነላቸውና፡፡እጅግ ውስብስብ የሆነው የደህንነት ሁኔታዎች መሰብሰቢያ ጥርቅምስ የአረቡን ዓለም ለግፍ አገዛዝ በቃኝን መነሳሳት መች ደረሰበት፡፡የጋንዲ የብረት ግንብ ግን አስቀድሞ በእርግጠኝነት አስቀምጠፐታል፡፡ ‹‹ግፈኞች፤ ነፍሰገዳዮችና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ለጊዜው የማይደፈሩ ቢመስሉም መጨረሻቸው ግን አይሆኑ ሆነው መውደቅ መሆኑ አያጠያይቅም፤ ይህን ነው ዘወትር ማሰብ››

የግፈኛ ገዢዎች ውድቀት ቀኑን ጠብቆ መምጣቱ የማየቀር በመሆኑ፤ወቅቱን ማፋጠንም ይጠበቃል፡፡ ይህንን ደግሞ በአካባቢያችን በሚከናወነው የውድቀት ሂደት ማመዛዘን ይቻላል፡፡ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ውስጣቸው ባዶና ደካሞች፤ልፍስፍሶችና ዋዣቂዎች ናቸው፡፡ውስጣዊ ገጽታቸውም በሙስናና በሥልጣናቸው አላግባብ መባለግ የተበከለና የተመረዘ ነው፡፡ የሚፈልጓቸውን የሕብረተሰብ አባላት ልብና ሕሊና ጨርሶ መግዛት ስለማይችሉ፤ ድጋፍ ይሆኑናል ብለው የሚያስቧቸውን ሰዎች ታማኝነታቸውን በማስፈራራት፤በጉልበት በመያዝ፤ ተቃዋሚዎችን በማስደንገጥ፤በማወናበድ ተግባር ላይ ለማሰማራት ይጥራሉ፡፡የአመራራቸውም እምነት ባለማመን ላይ የተመሰረተ ሲሆን የራሳቸውንም ደጋፊዎች በጥርጣሬ አይን ነው የሚመለከቱት፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የግፈኞች አገዛዝ መጨረሻው በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ በተራቡ፤የተጨነቀው ገጠሬና የቀን ሠራተኛው፤ለዓለም አቀፍ የመሬት ዘራፊዎች መሬቱ እየተነጠቀ በሳንቲሞች የተሸጠበት ዜጋ፤የትምህርትና የሥራ እድል በተነፈጉት ቁጥር ስፍር በሌላቸው ወጣት ሴቶችና ወንዶች ኢትዮጵያዊያን፤በቤት እጦት የሚንገላቱት ብዙዎች፤እጅና እግራቸውን ታክስ ካሠራቸው የንግዱ ሕብረተሰብ አባላት፤በጠራራ ጸሃይ መብታቸውን ተገፈው በየእስር ቤቱ በተወረወሩት ኢትዮጵያውያን ዜጎች ገጽ ላይ በጉልህ ይነበባል፡፡ለዚህ መፍትሄውን አምጡ ቢባል፤ዜጎች ክብራቸውን ላለማስደፈር ከምንም በላይ አድርገው ሲያምኑና ለዚህም እጅ ለእጅ ተያይዘው መከላከል ሲጀምሩ ነው መልሱ የሚሆነው፡፡ በአረቦች መነሳሳትም የታየው ይሄው ነው፡፡

በዴሞክራሲያዊ ሽግግር ወቅት የምርጫን የተለመደና የሃሰት ውንብድና ተግባር መጠበቅ

አንዳንድ ሰዎች ከግፍ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ የአስተዳደር ስርአት ሽግግሩ በምርጫ በተአምር ፈላጭ ቆራጮች ሲወድቁ ይከናወናል ብለው ያምናሉ፡፡ማንኛውንም የዴሞክራሲ ጉዳይ በምርጫ ውጤት ላይ ትቶ መጠበቅ አስተማማኝነቱ ያጠራጥራል፡፡በ1991 ሽግግር መለስ ዜናዊም ለኸርማን ኮኸን ነገሮችን ለማስተካከል ምርጫ እንደሚከናወን ከመለስ ዜናዊ ቃል ተገብቶለት እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ሆኖም የ2005ን ምርጫ ሂደትና ውጤት ከተመለከተ በኋላ ኮኸን የመለስ ተቃዋሚ ሆነ፡፡ስለዚህም ሲያስረዳ፤ መለስን በአደባባይ የሚቃወምበትና የሚኮንንበት ምክንያት ‹‹የ2005 ዓ/ም ምርጫ በመሰረቁ ነው፤ በትክል የምርጫው ውጡት በመለሶች ተሰርቋል›› ይላል፡፡‹‹ከ2005 በኋላ በኢትዮጵያ ምርጫ ውጤት መሰረቅ ብቻ ሳይሆን፤ገዢው ፓርቲ ስለድል አድራጊነቱ ሲናገር መቀለጃ ሆኖ ታይቷል፡፡መዘባበቻ ሆኗል፡፡‹‹በ2010 ግንቦት ያገኘነውን 99.6 በመቶ የምርጫ ውጤት ልብ በሉ›› ‹‹በ2008 ዴሞክራሲያችን ያሰገኘልንን የክልሎች ምርጫ ውጤት 3.4 ሚሊዩን መቀመጫዎች ተቃውሞ የቀረበባቸውን መቀመጫዎች መዘንጋት አይገባም››

ኢብሽካ፡ ቁርጥ ቀን!

ግለሰቦችን፤ ስበስቦችን፤ ከስር ጀምሮ ለሚካሄደው የዴሞክራታይዜሽን አስተዋጽኦ የማሰባሰቡ ዓላማ ተስፋ ሰጪና አበረታችም ነው፡፡ግለሰቦችን የሲቪክ ማህበረሰብ አባላትን ተሟጋቾችንና ተንቀሳቃሾችን ለዚሁ ዓላማ ማሰለፉና፤ በስቃይ ላሉት፤ መከላከያ ለሌላቸው መከላከልን፤ የሰውን ልጅ ክብር ወደነበረበት ተፈጥሮአዊ ሁኔታ መመለሱ፤ ድምጻቸው ለታፈነው ድምጽ መሆን ዋጋ የማይተመንለት ታላቅ ተግባር ነው፡፡ ከስር መሰረቱ አንስቶ ከግፈኛ ገዢዎች የፈላጭ ቆራጭ ግዢ ለመላቀቅ የሁሉም መሰለፍ በርካታ ሁኔታዎችን ያስተካክላል፡፡ በወቅቱ ፈተናና ግፍ ተስፋችን ሁሉ ተስፋ ሲያጣ፤ የነገው እምነታችን በዛሬው ግፍ ሲዋጥብን፤ እልህን በእልህ ለማሸነፍ ቆርጠን መነሳት አለብን፡፡ ለዚህም ከየዕለት ተግባራችን 1 በመቶ በኢትዮጵያ ለሚከናወነው የግፈኞች ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ መገርሰሻ ሲውል ሃገራችንን ወደ ዴሞክራሲዊ ስርአተ ማሕበር እናሸጋግራታለን፡፡ ይህ ነው የሁሉም ራዕይ ሊሆን የሚገባው፡፡

የቻይናው ድራጎን (ጭራቅ) እና የአፍሪካ ጅቦች አሸሸ ገዳሜ

Thursday, February 23rd, 2012

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም

(ከአንግሊዘኛ የተተረጎመ)

የቻይናው ደራጎን (ጭራቅ) ከአፍሪካውያን ጅቦች ጋር አሸሸ ገዳሜ ጭፈረውን እያስነካው ነው፡፡ ለዚህ ደራጎን አፍሪካ በምንም መልኩ ተስማሚ ሁኔታ አትፈጥርለትም፡፡ ታሪክ እንደሚያስረዳው በአንድ ወቅት የአፍሪካውያን መኩሪያና መመኪያ የነበረችው ምድር አሁን የጅቦች መሰባሰቢያ ትልቅ ዋሻ ፈጥራ (የአፍሪካ ሕብረት) የጅቦቹ መፈንጪያ መናሃርያ ሆናለች፡፡ለዚህ የጅቦች መገናኛ፤ መዶለቻ፤ መለመኛ፤ ሕዝባዊ ማነቆ መፍተያው ሁሉ ለሚከናወንበት ግንባታ የሚያስፈልገውን ወጪ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተሸፈነው በቻይና ነው፡፡ ሲባልም፤ ይህ ቻይና ለአፍሪካ የሰጠችው የሰው በላዎቹ (ጅቦች) የአፍሪካ መሪዎችልመና መልስ ነው በማለት ጅቦቹ የታላቁን ደራጎን ስጦታ ለማመስገን በተሰበሰቡበት ወቅት የተሰነዘረ አባባል ነው፡፡

ይህ ውብ ግንባታ………ከእንግዲህ የአህጉራችን የሕብረት አባላት የሚሰበሰቡበት ማዕከላዊ ቢሮ ሲሆን፤የተገነባውም በቀድሞው የሃገራችን ዓለም በቃኝ በመባል ይጠራ በነበረው ነፈሰ ገዳዮች፤ ሌቦች፤አስገድዶ ደፋሪዎች፤ፍትህን የሚያዛቡ፤አጭበርባሪዎች፤ወዘተ ይታሰሩበት በነበረበት የወህኒ ቤቱ ፍራሽ ላይ ነው፡፡ ይህ ታላቅና ግዙፍ ሕንጻ የሚያመላክተው የአህጉሪቱ መሪዎች ለዓመታት በሕዝብና በሃገር ላይ ጭነውት ያለው መከራና ስቃይ፤የነዚህ ሰው በላዎች የጅብነት ዘመን ማለቂያውንና እንደፈረሰው የወንጀለኞች ማጎርያ የነሱም የግዛት ዘመን አብቅቶ፤ አህጉሪቱና ሕዝቦችዋ ለዘመናት ከተጫነባቸው ሰቆቃ ነጻ የሚሆኑበት ዘመን መቃረቡን ነው፡፡ ስለዚህም ቻይና ይህን ግንብ ማስገንባቷ ትክክልና ተገቢም ነው፡፡ምክንያቱም ተከታዩ ዘመን የአፍሪካ ትንሳኤ ነውና፡፡ ዘመኑ ያለቀባቸውም በግፍ ሥልጣን ላይ ያለሕዝባዊ ፈቃድ የተጎለቱት መሪዎችም ለፍርድ የሚቀርቡበት ወቅት መዳረሻው በመሆኑ፡፡

ይህን የአፍሪካን ትንሳኤ የሚያመላክት አዳራሽ፤የአፍሪካን ራዕይ የሚጠቁመውን ግንባታ በመገንበታችሁ……… ለቻይና መንግስትና ሕዝብ ከፍተኛ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፤ ይህ ግኑኝነታችንም ዘላቂነት ያለው ሆኖ በየጊዜው እንዲያብብ እንመኛለን ስልም የምናገረው ሁላችንንም በመወክል ነው፡፡

ስለቻይና መንግሥት ችሮታ ምስጋናውና ጫማ መላሱ መጨረሻ አልነበረውም፡፡‹‹ስጦታው›› በአፍሪካና በቻይና መሃል የተገነባውን ወዳጅነት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መሄዱን አመላካች ነው፡፡የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ፕሬዜዳንትና ከ1979 አንስቶ የኤኳቶሪያል ጊኒ ፈላጭ ቆራጭ ፕሬዜዳንት ቴዎድሮ ኦቢያንግ ኢንጉዌማም በባለ 20 ባለመስታወት ፎቅ ላይ ሆነው መጪው በሚገባ ታየይቷቸዋል፤ለዚህም ነው…… የአዲሲቱ አፍሪካ የነገው ነጻ አፍሪካና አፍሪካውያን የብርሃን ፍናጣቂ፤ ለወደፊቷ አፍሪካ የምንፈልገው›› በማለት ሳይገባቸው እውነቱን የተናገሩት፡፡

ደራጎኑም በበኩሉ ተስማምቷል!

‹‹…በቻይናና በአፍሪካ መሃል የቆየ ልማዳዊና ባሕላዊ ግንኙነት አለ፡፡ቻይና ምንጊዜም ቢሆን የአፍሪካ ጥሩ ወዳጅ፤መልካም አገር፤እና ታማኝ ወንድም ነች፡፡ አንድነትና መረደዳት ልማታዊ ድጋፍ በቻይናና በአፍሪካ መሃል የኖረና ወደፊትም ቢሆን ዘለቄታ ያለው እንዲሆን እቅዳችን ነው፡፡ …ሠላም መረጋጋትና ልማት ቅድሚያ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃም አፍሪካውያን ችግራቸውንና አለመግባባታቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ ምርጫቸውን እናከብራለን፡፡ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳይ በራስ ወዳድነት በመነሳትና የራስን ጥቅም በማስቀደም መግባት ችግሩን በመፍታት ፈንታ ይበልጡን ያወሳስበዋል፡፡ ሶስተኛም አፍሪካውያንን በህብረት ጥንካሬያቸውን እንዲያጎለብቱ ድጋፋችን አይለያቸውም፤አራተኛ የአፍሪካን ልማት በማስቀደም የበለጠ ድጋፍ ልናደርግ ተገቢ ነው፡፡ በቻይና አፍሪካ ወዳጅነት ዕድገት ሂደት ውስጥ ጣልቃ አለመግባትንና የየሃገራቱን ልእልና አክብረን በውስጥ ጉዳያቸውም ላላመግባት ውሳኔያችንን እናከብራለን… ለአፍሪካ ከምናደርጋው ድጋፍ ጋር የፖለቲካን ክር እንደማነቆ ጨርሶ አናያይዝም… የአፍሪካንና የቻይና ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርም ከምንም ነጻ የሆነ የ600 ሚሊዮን ብር እርዳታችንን ለአፍሪካ ሕብረት በሚቀጥለው ሶስት ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ እናደርጋለን፡፡››

በአፍሪካ የ‹‹ቻይና ሞዴል››

የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች በቻይና ሞዴል የኤኮኖሚ ልማት በሚለው መርሃ ግብር ላይ የእኔ እቀድም እኔ እቀድምና የቻይና ፍቅር ለእኔ ለእኔ ማለትንና መሽቀዳደምን እንደፈሊጥ ይዘውታል፡፡ የሕዝብን ይሁንታ አግኝቶ የማያውቀውና የኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ገዢው መለስ ዜናዊ የቻይና ሞዴል የሚለውን በመከተል ታማኝነቱን አረጋግጧል፡፡

ሁላችንም ስንመኘውና ስንጓጓለት የነበረው የአፍሪካ ትንሳኤ እውን ለመሆን መንገዱን ጀምሯል፡፡ለዚህም ማስረጃ ሊሆን የሚችል አልኩ ባዮችና ምሁራን በአደባባይ ስለአፍሪካ ዳግም ወደ ቅኝ ግዛትነት መመለስን ሲያውጁ ቢከርሙም አሁን ግን መታቀብ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡ የአህጉራችን ይህ ውብና ድንቅ ሆኖ የታነጸው አዲሱ ማከላችን የአፍሪካ ሕብረት በትግላችን መሀላ በመተግበሩ የአፍሪካን ትንሳኤ አመላካች ነው፡፡

የቻይና ሞዴል ማለት ግን በእርግጠኝነት ምንድን ነው?

የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የቻይና ሞዴል የሚለውን ቃል በግልጽና በትክክል ለማስረዳት ፈቃደኛ ከመሆን ይልቅ፤ እንደ ኮከብ ቆጣሪና መወድስን እንደማያውቀው አጭበርባሪ ጠምጣሚ ከንፈራቸውን በማላወስ ብቻ ያልፉታል፡፡ እነዚህን ፈላጭ ቆራጭ ሰው በላ ጅቦች የማመን ትንሽም ቢሆን ፈቃደኝነቱ ካለን፤‹‹የቻይና ሞዴል አፍሪካን ከተጫናት ድህነትና ችጋር አላቆ፤ የሕዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት አሟልቶና ነጻነቱን አስረክቦ፤በኢኮኖሚና በኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገቱን ለማፋጠን የሚያስችል ነው፡፡››ቻይና የዓለም የኦኖሚ ሃይል ልትሆን የበቃችው፤ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ተወላጆች ኢንቬስተሮች በሯን በመክፈትና ታክስን በመቀነስ፤ አስፈላጊ በሆኑትም ሂደቶች የጋራ አዋ|ጪ በመሆን፤እንዲሁም የጉልበት ሥራን ሰፋ በማድረግ ነው፡፡ይህ ነው ለቻይናና ለአፍሪካ የእኩል በእኩል ሁኔታን ይፈጥራል የሚባለው፡፡

እዚህ ላይ ግን አንድ ማነቆ ተቀምጧል፡፡ ቻይና ይህን እመርታ ልታሳይ የሄደችበት መንገድ እኮ ማንኛውንም ጉዳይ በአንድ ፓርቲ ስርአት ውስጥ ጠፍራ በመያዝና፤ማንኛውንም እንቅስቃሴ፤የሲቪል ማህረሰቡንም፤ ወታደራዊ ተቋማትን፤የደህንነቱን መዋቅር፤በአጠቃላይ ስርአቱ ሥር ያሉትን ሁሉ የመንግሽትን ጥቅምና ፍላጎት፤ ደህንነት ጠባቂዎች በማድረግና ሕዝቡን በማግለል የሕዝቡን የእለት ተእለት እንቅስቃሴና ሃሳቡን የመግለጽ ፍላጉተቱን ሁሉ መቆጣጠርያና የቅድሚያ ማክሸፊያ መዋቅር በመዘርጋት ነው፡፡

ስለ የቻይና ሞዴል ወደ አፍሪካ ስለመምጣቱ ጉዳይስ ቻይና ምን እሳቤ አላት?

‹‹ብዙ እሳቤ የለንም›› ይላሉ በአፍሪካ ጉዳይ ልዩ የቻይና ወኪል የሆኑት ሊዩ ጉጂን በእርግጠኝነት ሲገልጹ ‹‹አሁን እያደረግን ያለነው ልማዳችንን ማካፈል ብቻ ነው፡፡እውነት እላችኋለሁ እመኑኝ ቻይናውያን የፖለቲካ እምነታችንን፣ የአገዛዝ ስርአታችንን፤ ወደ አፍሪካ እንደውለታ ክፍያ ለማስተላለፍ ሃሳብም ሆነ ፍላጎት የለንም፡፡ እኛ ራሳችን ገና ሞዴላችን የዳበረና የተዋጣለት፤ ብቃቱ የተረጋገጠለት የቻይና ሞዴል ነው ብለን አናምንም››

ታዲያ የቻይናውያን መሪዎች እምነታቸው ይህ ከሆነ፤ በአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ሞዴል እያሉ የሚያጨበጭቡለትንና ሰማየ ሰማያት እያወጡ የሚጨፍሩለትን ሞዴል ባለቤቶቹ ገና ያላደገ ያልለማ፤… ነው የሚሉትን ሞዴል ይዘው አሸሸ ገዳሜ የሚያምቧርቁት? ምናልባት እነዚህ ደም መጣጭ የሆኑ የአፍሪካ ዲክታተሮች የቻይና ሞዴል የሚሉትን እንደአይነርግብ መከለያቸው በማድረግ ኢኮኖሚውን ከአፍሪካ ጥገት አላበው ለመጨረስ ማስመሰያ የእድገት መስመር አድርገውት ይሆን?‹‹ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሉ›› እንዲሉ አይነት ነው እንጂ የ‹‹ቻይና ሞዴል›› ያው እንዳለው የአንድ ፓርቲ ስርአትከ1960 የቅኝ ግዛት ማነቆ ወጡበት ጊዜ ጀምሮ የነበረና ያለ ነው፡፡የዩጋንዳው ዩዌሪ ሙሴቪኒ፤የሩዋንዳው ፖውል ካጋሚ፤የ86 ዓመቱ የዝምባዌው ሮበርት ሙጋቤ የግዛት ዘመናቸውን ለማራዘም የተጠቀሙበት ሞዴል ነው አሁንም ተመልሶ የቻይና ሞዴል ተብሎ የሚለፈፈው፡፡ባለፉት የፍቅር ወቅቶች መለስ፤ሙሴቪኒና ካጋሚ (በክሊንተንና በብሌር ይሁንታ በተጫነላቸው ክብረ ዘውድ) ‹‹የአዲሲቱ አፍሪካ አዲስ ትውልድ መሪዎች›› በመባል የግዛት ዘመናቸውን ለማራዘም እንዲችሉ ተብሎ ይጠሩበት ነበር፡፡አሁን ደሞ የምእራቡ ዓለም መልእክተኞችና ጉዳይ ፈጻሚ በመሆን በየተላኩበት ሰብአዊ መብትን በመግፈፍ፤ የሕግን ልዕልና በመድፈር፤ ሰብአዊ መብትን በመጣስ የተልእኮ ክፍያቸውን ግብር ከፋዩ ሕዝብ በማያምንበት ቦታ እንዲውል እየተደረገ ለነዚህ ሰው በላ ፈላጭ ቆራጮች የአገልጋይነታቸውን እየተከፈሉ ነው፡፡ በሌላ በኩሉ ግን ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሁሉ ስለነዚህ አፍሪካውያን አገልጋዮች ተግባር በአግባቡ ከማጋለጥና አለአግባብ ከሕዝብ የሚሰበሰብም ክፍያ መቆም እንዳለበት ትግላቸውን አላቆሙም፡፡የአንድ ሰው ለገዢነት የአንድ ፓርቲ መመሪያነት ተጨፍልቆና አዲስ ስመ ጥምቀት ተሰጥቶት አሁን ‹‹የቻይና ሞዴል›› የሚባለው ቀደም ሲል ክዋሚ ንክሩማህ የሰብ ሰሃራው አፍሪካ መሪ ሞክሮት ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ የከሰፈ ተሞክሮ ነው፡፡ንክሩማህ ልክ እንዳሁኑ ወቅታዊው የቻይና ሞዴል አራጋቢ ብርማ መሳይ ምላስ፤ ንክሩማህም በዚያን ወቅት ኒኦ ኮሎኒያሊስምን (ንክሩማህ የፈጠረው የማስጠያ ቃል) እና ኢምፔሪያሊዝምን አፍሪካን በመበዝበዛቸውና ለድህነት በመዳረጋቸው ይረግምና ያወግዝ ነበር፡፡ የንክሩማህ ፈጣን የኢንደስትሪያላይዜሽን ፕሮጋራም ጋናን ከውጭ ምጸዋትና እርዳታ፤ በሀሃገሪቱ የካካዋ የዓለም ግብይት ላይ ከፍተኛ ውድቀት አድርሶ ነበር፡፡ሌሎችም ተግባራዊ ያደረጋቸው የኤኮኖሚ ልማት እቅዶችም በማያዳግምና ትንሳኤ በሌለው መልካቸው ለውድቀት ተዳረጉ፡፡

በ1966 ዓም በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን በወረደበት ጊዜ ጋና በአፍሪካ ከፍተኛ ሃብታም ከመባል ደረጃ ወርዳ ዝቅተኛ የችጋር ሃገር ሆና ነበር፡፡በተመሳሳይም በአፍሪካ ከፍተኛ የእርሻ ምርት ውጤት ላኪነት አሽቆልቁላ ወደ ከፍተኛ የእርሻ ምርት ውጤት ገዢነት ወርዳለች፡፡የአንድ ሰው አንድ ፓርቲ መኖር እንደብሔር ግጭት አስወጋጅ፤የዘር ግጭት ፈጪ ከመሆን ይልቅ በይበልጥ አጉልቶ ያሳየው የጭግሩ አባባሽና የግጭቶቹ አመንጪና አባባሽ መሆኑን ነው፡፡እንዲያውም ከበርካታ ተሞክሮዎች እንደታየው የዚህ አገዛዝ ዋናው ተግባር እነዚህን ችግሮችና ግጭቶች በመፍጠር በሕብረተሰብ መሃል አለመግባባትና ግጭት ተጠናክረው የሃገሮች የአንድነት ነቀርሳ እንዲሆኑ ማድረግ መሆኑ ታይቷል፡፡ይህ እውነታም በአፍሪካ አህጉር ከሃገር ሃገር እንደ ሰደድ እሳት በመያያዝ ተዳርሶ የሃገሪቱን መኩሪያን ታሪካዊነት የሚመሰክሩትን፤ የውጭ ጎብኚዎችን የሚስቡትን የዱር አራዊት ጭምር ለስደትና ለርሃብ ዳርጓል፡፡ያም ሆኖ ግን የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች፤የወታደራዊ ጁንታ ገዢዎች፤አለ ያሉትን ዘዴያቸውን ሁሉ አንድ ገዢ አንድ ፓርቲ ያለውን ጠቀሜታ ለማሳመን የቱንም ያህል ቢፍጨረጨሩ ውጤቱ ግን ከገሃዱ እውነታ ሊያልፍላቸው አልቻለም፡፡ያም እውነታ ባለብዙ ፓርቲ መሆንን ብቻ ማዋጣቱንና ጠቀሜታው ነው፡፡ አሁን ያሉት ፈላጭ ቆራጭ የአፍሪካ እርባና ቢስ ገዢዎች ደግሞ እንደገና ወደ ኋላ መልሰው አፍሪካን ሊገድል ማነቆ አስሮባት ሲያስጨንቃትና አላላውስ ብሎ እንደግመል ሽንት ወደኋላ ሲጎትታት የኖረውን ስርአት ሊያመጡ ያረጀውንና የአግልግሎት ዘመኑን የጨረሰውን የማይላስ የማይቀመሰውን ጉዳይ በአዲስ ካባ ደርተው ‹‹ምርጡ የቻይና ሞዴል›› ብለው ሊያለብሱን ይዳዳቸዋል፡፡ያንኑ ተዝካሩ የተባላውን አንድ ሰው አንድ ፓርቲ፡፡

የ‹‹ቻይና ሞዴል›› በአፍሪካ ያለው ሁኔታ

መለስ ዜናዊና ሌሎቹ የተባበሩት የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ይህን ገና ‹‹እምቦቀቅላ›› የሆነውን ‹‹ቻይና ሞዴል›› በእውነት መልኩ እየተቀበሉትና እየተከተሉት ነው? የሃገር ውስጥና የውጪ ኢንቬስተሮች በአፍሪካ ሥራቸውን ለማከናወን ነጻ እንቅስቃሴና ትግበራ አላቸው? ባልተብብራሩና ምንነታቸው በግልጽ መረዳት በማይቻል፤ ባቃዣቸው ቁጥር በሚወጡ ደንቦችና መመርያዎች ሳይታሰሩና ለችግር ሳይዳረጉ ይንቀሳቀሳሉ? እውቀት የለሽ የባለስላጣኑ ጃዊሳዎች ሳይጎሽሟቸውና መላ ቅደሱን ሳያጠፉባቸው ድርጅቶቻቸውን ይነራሉ? የነገው አዋጅና ደንብ ምን ይለን ይሆን ብለው ከማሰብ ይልቅ ለገበያው አስፈላጊው፤ ለፈላጊው ጠቃሚው ምን ይሆን ብለው ማቀድስ ይችላሉ? ለመሆነጁ በኢትዮጵያ ካለው ሥራ ውስጥ ስንቱ ነው ለመደራደር በሚያመችና ግልጽ በሆነ መመርያ የታቀፈው የኢንቬስትመንት አካል?የ2011ዱ የዓለም ባንክ ያወጣውና 183 ሃገራትን የፈረጀበት መመዘኛ (The 2011 World Bank Ease of Doing Business Index) በኢትዮጵያ ያሉትን ሁኔታዎች መመዘኛው በአሳዛኝ ደረጃ ላይ ያስቀምጣል፡፡ በአጠቃላይ ግምገማው 11ኛ ያደርጋትና፤

ሥራን ለመጀመር (99) የግንባታ ፈቃድ ለማከናወን (56) የመብራት ተጠቃሚ ለመሆን (93) ንብረትን ለማስመዝገብ (113) ብድር ለማግኘት (150) ኢንቬስተሮችን ጥቅም ማስጠበቅ (122) ታክስ ለመክፈል (40) ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ (157) ውልን ማስከበር (57) አለመግባባትን ለመፍታት (89)

የ‹‹ቻይና ሞዴል›› ለመለስ ዜናዊና ለግብረአበሮቹ ፈላጭ ቆራጮች በስልጣን ለመቆየት የሚያጠልቁት ጭንብላቸው ነው፡፡ ይህንኑ ጭምብል ደሞ በሕዝቡ አመለካከት ላይ አጥልቀው እውነቱን እንዳያውቅ ሊያደርጉታ ይሞክራሉ፡፡ ይህን በማድረግም ግልጥነትና ተጠያቂነት እንዳይኖራቸው፤ተወዳዳሪና ተቀናቃኝ ያሉበት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዳይኖር፤ሕዝቡ የንብረት ባለቤትነት መብት እንዳይኖረውና ሁል ጊዜ የስርአቱ ለማኝና የሃገሩ ባይተዋር እንዲሆን፤ሃሳብን በነጻነት እንዳይገልጽ፤ነጻ ፕሬስ እንዳይኖር፤የፍትህ አካላት ታዛዥነታቸው ለፍትህ ስርአቱ ሳይሆን ለገዢዎች ጥቅም ማስጠበቂያ እንዲሆን የሚያደርጉትን ጸረ ህዝብና ጸረ ሃገር ድርጊታቸውን ለመሸፈን ይጠቀሙበታል፡፡ በዚህ ድርጊታቸው ሕዝቡ የስርአቱ ተገዢና አገልጋይ እንዲሆን፤ ለመቆጣጠርያነት ፖለቲካውን በማነቆነት በማስቀመጥ፤ ኤኮኖሚውን ተብትበው በማሰርና በኪሳቸው በመክተት ሃገሪቱን ለችጋርና ለምድረባዳነት፤ ሕዝቡን ለመከራ ስቃይና ኑሮን ለመጥላት ማድረጊያነት ሆን ብለው ይጠቀሙበታል፡፡የ‹‹ቻይናን ሞዴል›› የኤኮኖሚ ልማትን በመቃዠት ደረጃ እያራገቡ የፖለቲካ ነጻነትን በገሃድ ለመጨፍለቅ የሕዝቡን ዴሚክራሲያዊ ነጻነት መርገጥ ስለሚያስችላቸው ሕዝቡን በዚህ እያማለሉ የሃገሪቱን ብሔራዊ ኤኮኖሚ በግላቸው ይመገምጉታል፤ያደርቁታል፡፡

በቅርቡ፤ፋይናንሻል ግሎባል ኢንተግሪቲ ሲጽፍ፡- ‹‹…ኢትዮጵያዊያን ደማቸው ተመጦ ተመጦ ባዷቸውን እየቀሩ ነው፡፡ከአዘቀጠው የድህነት አረንቋ ለመውጣት ምንም ያህል ቢጠሩና ቢድሁ ዋናቸው ወንዙ ወደሚፈስበት ሳይሆን ወደሚመነጭበት ስለሆነ እስከማዕዜኑ ከዚያ መውጣት ዘበት ነው፡፡›› ይህ ነው እንግዲህ ለኢትዮጵያና ለአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት የ‹‹ቻይና ሞዴል›› የሚባልላቸው፡፡