Author Archive

አቶ መለሰ ዜናዊ መቶ በመቶ አምባገነን ነበሩ!!!

Sunday, September 16th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ይመራ የነበረው አሁን ኢትዮጵያን በጉልበት የሚያስተዳድረውና እራሱ ላወጣው ህግ እንኩዋን ተገዚ መሆን የተሳነው የወያኔ ህወሀት ኢህአዴግ ቡድን ከሁሉም የባሰውንና በታሪኩ አይቶ የማያውቀውን ከፍተኛና አስከፊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ምስቅልቅሎች ምክንያት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጎሳ ፆታ ቃቅንቃ እድሜ ሀይማኖት ሳይል በከፍተኛ ሁኔታ ህዝቡ ሀገራዊ ስሜት እንዳይኖረው በሀገሩ ላይ የባእድነት ስሜት እንዲሰማው ይባስ ብሎም ሀገሩን ጥሎ እንዲሰደዱ አስገድዶዋቸዋል:: አምባገነኑና ፋሽስታዊው የወያኔ ቡድን በመለስ ዜናዊ በመመራት ላለፉት 21 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጉልበት: እጅግ በጣም ሁዋላ ቀርና የህዝብን ጥቅም ይማያስጠብቅ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም; የአገር የማፈራረስና የኢትዮጵያዊንትን ታሪክና ባህልን የማጥፋትና ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብና የሀገር ሀብት መዝረፋን መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ እየፈጸም ይገኛል::ህዝቡን በጥመንጃ በማስፈራራትና ከታች የተዘረዘሩትን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመከልከል የባንዳንትና የሌብነት ተግባሩን በመፈፅም ላይ ይገኛል::

ህዝቦችን በዘር: በብሄር: በቋንቋ: በሀይማኖት: በቀለም: ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት:: እርስ በእርስ እንዳይስማሙ: አብረው እንዳይኖሩ: አንድንት እንዳይፈጥሩ: በህብረት ማህበራዊና ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹን እንዳይፈቱ: የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብቱ በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ: ከእያንዳንዱ ብሄረሰብና ሀይማኖቶች ለሆዳቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ቆንጥሮ እምነትህ ቀቀንቀህ ባህልህ ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ::

በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ(እራሱ ባወጣውና በማያከብረው ህገመንግስት) መብቶችን፧የመናገር:የመፃፍ:የመሰብሰብ:በቡድን የመደራጀት:ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የመግለፅ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን: የፈለገውን እምነት መከተልና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ወይንም በመሸራረፍና ለጥቂት የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች እና በጥቅም ለተወዳጁዋቸው ብቻ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ::

ታዋቂና ለወደፊት ለአምባገነኑና ለፋሽስቱ ለወያኔ ቡድን የስልጣን ቆይታ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውንና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ታማኝነት ያላቸውንና አላቸው ብሎ የሚጠረጥራቸውን የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን: አባላቶችን: ደጋፊዎችን: ምሁሮችን: መምህራኖችን: ጋዜጠኞችን: ዘፋኞችን: ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት: በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም: አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ: የት እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ: መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና የባንዳነት ተልኮውን መወጣት::

ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰባዊ መብት:በመልካም አስተዳደር:በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ:: ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ (ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ) ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ በተጨማሪም በከፍተኛ ወጪ በማፍሰስ ከሀገር ውጨ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚያስተላልፉዋቸውን ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ማፈንና ከነዚህም ድርጅቶች ጋር የሚሰሩትን ግለሰቦች ኮተት የሆነ የውሸት ክሶች በመደርደር በአሸባሪነት እየከሰሰ ህዝቡ መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም አድርጎዋል::

የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ በመስጥትን በመሸጥ አሳልፎ መስጠት; እኛ ብቅርጽና በመጠን የምናውቃትን ታሪካዊ ኢትዮጵያን ማጥፋት; ህዝቡም በሀገሩ ላይ ስለ መሬት እንዳይጥይቅ በጠመንጃ ማስፈራራት; ምንም እንደማያመጣ በጥጋብና በስድብ ንቀቱን መግለፅ::

ሌላው በአቶ መለስ ይመራ የነበረው የወያኔ ቡድን ለሁለት አስርት አመታት እየታተረ የቆየው የኢትዮጵያን የ3000 አመት ታሪክ መካድ: አሳፋሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ: ታሪክን መበረዝ: የፈጠራ ታሪክ መፍጠር:: የኢትዮጵያን ህዝብ ባህል: ስብእና: ዕምነት: ኩራት: ማንነት: ብሄራዊ እሴቱን: አንድነቱንና ብሄራዊ መገለጫዎቹን ማጥፋት:: የኢትዮጵያን ታራክ የወያኔን ታሪክ ብቻ አድርጎ በካድሬዎቹና ለሆዳቸው ባደሩ ተራ ግለሰቦች ገንዘብ ከፍሎ ማፃፍ:: ልክ እንደ ውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ: ማጥላላት: ማናናቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ የቅጥረኝነቱን ተግባር ፈፅሙዋል አሁንም እየፈፅመ ይገኛል::

በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች የሌብነት ተግባራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፈፅም ወንበዴ ዘራፊ ድርጅት ማቋቋምና ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ: ማደህየት: ማስራብ: የበዪ ተመልካች ማድረግ:: በዘመናዊ ቤት መኖር: የብዙ ቤቶች ባለቤት መሆን: ዘመናዊ መኪናዎችን መቀያየር: በመቶ ሚሊዮኖች የሚጨርስ ህንፃና ፋብሪካዎች መገንባት ለወያኔ ብቻ የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ማግበስበስ:: በጣም የከፋው ደግሞ ከሀገርና ከህዝብ የሚዘረፈው ከፍተኛ ሀብቶች ከኢትዮጵያ ማሸሽና በተለያዩ የውጭ ሀገር ባንኮች መደበቅ ይህም ሳያንስ በባእዳን ሀገር በቢሊየን የሚቆጥሩ ዶላሮችን አውጥቶ ህንፃ መገንባትን እንደ ጀብደኝነት ቆጥረውታል:: የሀገሪቱን አንጡራ ሀብቶች ማእድናትንና የሰው ሀይል ጉልበትንና እጅግ በጣም ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን እርካሽ በሆነ ገንዘብ ለባእዳን አሳልፎ በመሸጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገሩ ላይ የበዪ ተመልካች እንዲሆን ተደርጎዋል::

የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ: በማህበራዊ: በፖለቲካ: በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ ለማድረግ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት: ፈቃድ መከልከል: ባለቤቶቹን ማስፈራራት: ማሰር: ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማፍሰስ ሞገዳቸውን ማፈን:: በቅርቡ እንደተመለከትነው በቀድሞው የወያኔው መሪ በነበሩት በመለስ ዜናዊ መታመምና መሞት የወያኔ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ምን ያህል ህዝቡን ሲያደናብሩበት እንደነበረ አስተውለናል::

ሰሞኑን ከአቶ መለሰ ዜናዊ ህልፈት በሁዋላ የወያኔን የስልጣን እድሜ ለማራዘም ሲባል የእድሜልክ ስራቸውን ምንም እንከን እንደሌለው ልክ መልአክት አድርጎ ማቅረቡ በጣም የሚያስገርምና የሚያስቅ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። በሽፍትነት በውንብድነትና በገዳይነት በዘራፊነት በቅጥረኝነት እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሳችሁበትን ግፍና በደል ሳያንስ ህብረተሰቡን እስካሁን ካቀጣጠለው ሁሉንም አቀፍ (ሰላማዊና ኢ-ሰላማዊ) የሆነ የነፃነት ትግል ለማዘናጋት ካልሆነ በስተቀር ላለፉ ሀያ አንድ አመታት ያየነውና የተገነዘብነው ግብርዎ የግል ባህሪዎ ለህግ የበላይነትን ለማስፈን ያለዎት ቁርጠኝነት: ያመጡት ሰላም ብልፅግና ዲሞክራሲ የመፃፍ የመናገር በአደባባይ ተቃውሞ ማካሄድ የመሰብሰብ መብቶችን ባጠቃላይ ለመልካም አስተዳደርና ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እንደግብአት የሚጠቅሙትን የመገናኛ ብዙሀን መስፋፋት: የተቃዋሚ ታርቲዎች መጎልበት: የህዝብ በማህበራዊ ጉዳዮች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ: ሶስቱ የስልጣን አካላት ከፓርቲ እጅ ንክኪ ነፃ መሆን በነዚ ሁሉ መመዘኛዎች ጠቅላይ ሚንስቴሩና ፓርቲያቸው ሲፈተሹ ምንም ሚዛን የሚደፋ ስራዎች አልሰሩም ወይንም ሆን ብለው ለመስራት አልፈለጉም::

መለስ ዜናዊ እየተከተለ የነበረው የድህነት ማጥፋት ፖሊሲና እስትራቴጂ ላለፉት 21 አመታት ተጨባጭ የሆነ ለወጥ ማምጣት አልቻለም:: ለዚህም ውጤት አለመገኝት ዋነኛ መንስኤዎቹ የሀገሪታን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ፖሊሲና እስትራቴጂ ፤ያስፈፃሚው አካላቶች የችሎታ ማነስ ፤ የህዝብ አሰራሮችን ከፓርቲ አሰራር ለይቶ አለማስኬድና፤ ስር የሰደደ ሙስና ናቸው፡፡ የኢትዮጰያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክሰ ኤጀንሲ በ2003 ዓ.ም ባወጣው መረጃ መሰረት በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በከተሞች ያለው የስራ አጥነት በመቶኛ 18 እንደሆነ ያሳያል፡፡ ድህነትም ከዛሬ አምስት አመት ከነበረበት 39% ወደ 29.6% ዝቅ እንዳለ የመንግስት መረጃዎች ያሳዩናል፡፡ እነዚህ ቁጥሮች አሁንም አገሪቱ ውስጥ አስከፊ ችግሮች እንዳሉ ቢያሳዩንም፤ ትልቁ ጥያቄ ግን እነዚህ መረጃዎች ምን ያህል ልክ ናቸው የሚለው ነው:: ምክንያቱም የወያኔ የዜናና የመረጃ ድርጅቶች የሜያወጡቸው አሀዞች ሀዝቡ በአይኑ ካየውና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ከሚያወጡት እጅግ በጣም የሚራራቅ ነው፡፡ ሌላው ምክንያት የምዕራቡ አለም ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በአመት 3 ቢሊዮን ዶላርና 400 ሺ ቶን የምግብ እህል እርዳታ ለኢትዮጵያ ይለግሳሉ:: እጅግ የሚገርመው የወያኔ ቅጥፈት የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲውና የራሱ ካድሬዎች የፈጠሩትን የኑሮ ውድነት በነጋዴው ህብረተሰብ ላይ ማላክኩ ሲሆን በጣም አሳፋሪው ቅጥፈት ደግሞ የባንክ ብድር እንደፈለጉና በርካሽ የሚወስዱትን ፤ ግብርና መዋጮ ከማይከፍሉትንና ፤ ገበያውን እንደፈለጉ የሚጨፍሩበትን የወያኔን የንግድ ድርጅቶችን እንደምክንያት አለመጥቀሱ ነው ።

ሌላው መለስ ዜናዊ ለለውጥ ዝግጁ አልነበሩም። ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን በህዝብ ድምፅ ሳይሆን በጠመንጃ አስፈራርቶና እርስ በእርስ አባልቶ ለመቆየት ያላቸውን አላማ በገሀድ አሳይተውናል:: ለምሳሌም በተለያየ በከፍተኛ የውሳኔ የሚሰጥባቸው የስልጣን ቦታዎች፤ ለሙስና የተጋለጡ መስሪያቤቶች፤ የህግ ክፍተት ያላቸውና፤ ብዙ የህዝብና የሀገር ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ቦታዎች ላይ መቶ በመቶ በሚያስብል መልኩ በትግራይ ብሄር ተወላጆች ብቻ መያዙ እጅግ ትንሽ የሆኑ የከፍተኛ ስልጣን ቦታዎች በሌሎች የብሄር ተወላጆች ቢያዙም ከአሻንጉሊትነት የዘለለ የመወሰን ስልጣን የላቸውም:: ለምሳሌ በወያኔ መከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች ከሞላ ጎደል በትግራይ ተወላጆችና ለጥቂት ለሆዳቸው ባደሩና ታማኝ የሌሎች ብሄረሰብ ተወላጆች መያዙና የፌደራል ፓሊስን፤ የከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ፤አየር መንገድ፤ በተለያዩ የታክስና የጉምሩክ ገንዘብ መሰበሰቢያ ቦታዎች ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ስልጣን በትግራይ ተወላጆች ከዘጠና በመቶ በላይ የተያዙ ናቸው፧ (በሁሉም የሀገሪቱ ከተሜዎች ላይና የጠረፍ ከተሞች በሚገኙት የጉሙሩክ ኬላዎች ላይ በሙሉ የሚሰሩት የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው)::

ሙስና በኢትዮጵያ ታሪክ አሁን ያለበት ዘግናኝ ደረጃ ደርሶ አያውቅም:: መለስ እንከን የለሽ ብሎ እድሜልኩን የሚፎክርበት ነገር ግን ምንም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያቃተው የልማትና የእድገት ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች ወያኔዎችንና ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩትን አጫፋሪዎቻቸውን ቢሊየነርና ሚሊየነር የሚያደርጉ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ በመካከለኛና በድህነት የኑሮ ደረጃ ይኖር የነበረውን ህዝብ እጅግ ወደከፋ የድህነት አረንቅ ከተውታል:: ይህም በከፍተኛ ሁኔታ አዳዲስ የተራቡ ሌቦችንና በብዛት የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ድሆችንም ፈጥረዋል፡፡ የወያኔ አባላቶች የቀረዑት ፖሊሲና መንግስታዊ አሰራር ሆን ተብሎ እድሜልካቸውን የህዝብና የሀገርን ሀብት እየዘረፉ እንዲኖሩ ተደርጎ ሲሆን በስልጣን በቆዩባቸው ዘመናት ምንም አይነት ህጋዊና ተጠያቂነት ያለው የስራ ባህል ስላላዳበሩ ፤በስልጠናና በዘመናዊ ትምህርት እራሳቸውን ብቁ ስላላደረጉ ከዘረፋ ውጭ ሌላ የህይወታቸውን ማቆያ የማይታያቸው ለሀገርና ለህዝብ ሸክም የሆኑ ዜጎች ሆነዋል፡፡ እንደውም ህዝብን ጉድ ያሰኛ የአንድ ወቅት ከስተት የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድን ባለሀብት ልማታዊ ባለሀብት ብለው በአደባባይ ሸልመው ሲያበቁ በነጋታው ወዲያው ዞር ብለው ያንን ወርቅ የሸለሙትን ግለሰብ ሌባ ነው ያዙልኝ ብለው በአንድ ለናቱ በሆነው የወያኔ ቴሌቢጅን ሲጮሁ ነበር:: ከምርጫ 97 በሃላ የታየው ህጋዊ የመሬት ዘረፋ የወያኔ ሌብነት እርቃኑን የታየበት አጋጣሚ ነበረ::ወያኔ ሌብነት ዋነኛ አላማው እንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ መናገረ ለቀባሪው አረዱት ቢሆንም ቀላሉ መረጃ ግን ላለፉት 21 አመታት አንድም የትግራይ ተወላጅ ወያኔ በሙስና ለፍርድ ቀርቦም ተፈርዶበትም አይተንም ሰምተንም አናውቅም ነገር ግን የሌሎች ብሄር ተወላጅ የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች ባስፈለገ ግዜ ሙሰኛ ተብለው እስርቤት ይገባሉ በሌላ ጊዜ ደግሞ በብሄር ተዋጾ ስም የሞግዚት ስልጣን ይሰጣቸዋል::

በመለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን በሃገራችን በደልና ምሬት እጅግ በዝቷል፤ ስር የሰደደ ሰው ሰራሽ ድህነትና ጉስቁልና ከመቸውም በባሰ በመላው አገሪቱ ተንሰራፍቷል፤ እስርና ሰቆቃ የኢትዮጵያውያን የለት ተለት ከስተቶች ሆነዋል። ህገመንግስቱን በሀይል ለመናድ ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው በማለት የውሸት ክስ ይመሰረትባቸውና በውሸት የተቀነባበረ የሰው የቢዲዮና የፅሁፍ ማስረጃና ምስክር ቀረቦ እስር ቤት መወርወር እንደ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ከተቆጠረ ሰነበተ:: ሰላማዊ ዜጎችን ፤ለነፃነታቸው የሚታገሉትን ግለሰቦችና ቡድኖች፤ ስለ ነፃነት ፍትህና እኩልነት የማፅፉትንና የሚያዜሙትን በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ መዳረጋቸው ዘወትር በወያኔ የመገናኛ ብዙሀን በየቀኑ የምንሰማውና የምናየው ድራማ ሆኖል:: በከተማችን የሚከሰቱ ከባድ ወንጀሎችና ሽብሮች በወያኔ ደህንነቶች ሆን ብለው የተቀነባበሩ መሆናቸውን ዓለም የመሰከረውና ጸሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ላይ እንደዜጋ መንቀሳቀስና በመረጠት ቦታ ህይወት መስርቶ መኖር የማይቻልበት ስርአት ላይ እንገኛለን:: የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ስልጣን በጠመንጃ ሀይል ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የስልጣንና የዘረፋ እድሜውን ለማራዘም በኦርቶዶክስ ሃይማኖትና ቤተርስቲያን ላይና በእስልምና እምነትና አማኞች ላይ በንቀትና በድፍረት የማያቋርጥ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ የሰሞኑ አሳፋሪ ድርጊቶች ናቸው::

እንግዴ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከላይ የተዘረዘሩ ወንጀሎች በሙሉ ላለፉት አርባ አመታት ፈፅመዋልም አስፈፅመዋልም:: ይህንን ሁሉ ወንጀልና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሲፈፅሙ ኖረው እያለ ተዛማጆቻቸው: እሳቸው በፈጠሩት ስርአት የህዝብንና የሃገርን ሃብት የዘረፉ የአየር ላይ ሃብታሞችና የድል አጥቢያ አርበኛ ለመሆን የሚታትሩ ህሊና የሌላቸው ግለሰቦች የተሳሳተና በውሸት የጠቅላይ ሚንስትሩን ያለፍ ታሪካቸውን ለማከም ሲደናበሩ ለማየት ችለናል። አሁን ጠቅላይ ሚንስትራቸው ሞቶም ሁሉም የወያኔ አባላቶች ፧ ደጋፊዎች ፧ በዘር የተዛመዱዋቸውና በስርዐቱ አላግባብ የከበሩ እያሰቡና እየሰሩ ያሉት እንዴት ወያኔ የበላይ ሆኖ እንደሚቀጥል እንጂ እንዴት አገራዊ መግባባት እንደሚፈጠር ፣ የህግ የበላይነት እንደሚሰፍንና ፣ አገሪቱ ካለችበት የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት ቀውስ በምን መልኩ መውጣት እንዳለባት አይደለም::

ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሠቦችም ሆንን የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የወያኔን የማፊያ ስርአት ከጫንቃችን ላይ አስወግደን እኩልነት: ፍትህ: ዲሞክራሲና: እውነተኛ ፌደራላዊ ስርአት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሌላው ግዜ በበለጥ መረባረብ አለብን:: እነዚህን ሁሉ በወያኔ እምባገነንና ዘራፊ ቡድኖች የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊና ኢፍትህአዊ ድርጊቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በኢትዮጵያ ህዝብ የተነሱትን የፍትህ የኩልነትና የነፃነት ትግሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መተባበርና መሳተፍ ይጠበቅብናል::

ወያኔዎች! አገር በውሸት ይፈርሳል እንጂ አይገነባም!

Saturday, August 25th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

የያዝነው አመት የወያኔ በጣም አሳፋሪና ያገጠጠ ውሸትና ቅጥፈት ከመቼውም ጊዜ በላይ ገሃድ የወጣበት ወቅት ነበረ አሁንም እንደቀጠለ ነው:: በወያኔው የፕሮፓጋንዳ ተቁዋም በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቢጅን ድርጅትና በውጭ አገር በሚገኝው አገር ወዳድ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ባደራጁት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቢጅን በመረጃ መረብ የሚጠቀሙ ድህረገፆች ብሎጎች ፓልቶኮች መካከል በመጀመሪያ በመለስ ዜናዊ ጤንነት ዙሪያ ቀጥሎም በህልፈተ ህይወታቸው ዙሪያ ግብ ግብ ተፈጠሮ ነበረ::

በመጀመሪያ የመለስ ዜናዊን መታመም ለህዝብ ይፋ ያደረጉት በስደት የሚኖሩት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግለሰብና በድርጅት ሆነው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በተለይም ራዲዮና ቴሌቢጅንና በጣም በርካታ ድህረ ገፆች የመለስ ዜናዊን መታመም በዘገቡበት ወቅት በወያኔው የፕሮፓጋንዳ ተቁዋም በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቢጅን ድርጅትና በርካታ በወያኔ ደጋፊዎቻቸው የሚተዳደሩ ራዲዮኖች ቴሌቢጅኖችና ድህረ ገፆች ለማስተባበልና ነገሩን ለመደበቅ ሲዘባርቁ ታይተውና ተደምጠው ነበረ:: በተለይም ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናት በመለስ ዜናዊ መታመም ዙሪያ እጅግ የተምታቱ መረጃዎችን አጎረፉ ለምሳሌ “ይህ የኢሳት የፈጠራ ወሬ ነው”, “ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አረብ አገሮችን አይነት አብዮት እንዲነሳ የሚፈልጉ አፍራሽ ሀይሎች የፈጠሩት ወሬ ነው”……………ብለው የተለመደ አይን ያወጣ ቅጥፈታቸውን ደረደሩ:: እናንተ በውጭ የምትገኙ የተለያዩ ራዲዮና ቴሌቢጅንና በጣም በርካታ ድህረ ገፆችን ውሸታሞች ናቹ ብለው ለማሳጣት መለስ ዜናዊን የሚመስል ክስት ግርጥት ያለ ግን እሱን የሚመስል ግለሰብ በወያኔ ቴሌቢጅን ቀርበው ለ 10 ደቂቃ እንዲያወሩ ተደረጉ::

በውጭ የሚትገኙ የተለያዩ ራዲዮና ቴሌቢጅንና በጣም በርካታ ድህረ ገፆች የመለስ ዜናዊን መታመም ባላቸው የመረጃ ምንጮች መሰረት እያጠናከሩ በተደጋጋሚ ለህዝብ ይፋ ማድረጋቸውን ቀጠሉ:: የወያኔ ባለስልጣናትም እየዘባረቁ ባሉበት ወቅት አንድ የአፍሪካ አገር መሪ መለስ ዜናዊ መታመማቸውን አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከአፋቸው አመለጣቸው:: እኚህ የሴናጋል መሪን የወያኔ ባለስልጣኖች ለምን የኢሳት ወሬ ነው እንዳላሉዋቸው በጣም አስገርሞ ነበረ ነገር ግን ቀላል ህመም እንዳጋጠማቸው በቅርቡም ስራ ይጀምራሉ ብለው የተለመደ ውሸታቸውን ቀጠሉ::

የወያኔ ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ ህዝብ ሆድና ጀርባ መሆናቸውን የሚያሳየው ድራማ በጣም ጎልቶ የወጣው የመለስ ዜናዊ ሞት በስደት የሚኖሩት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግለሰብና በድርጅት ሆነው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ከተናገሩ በሁዋላ ነበረ:: የኢትዮጵያውያን ሳተላት ቴሌቢጅን ባገኝው ትክክለኛ መረጃ መሰረት የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር መሞታቸውን አረጋገጠ አሁንም ወያኔዎችና ደጋፊዎቻችው የውሸት መረጃ መሆኑን በግልም በቡድንም ለማስተባበል ተራራ ወጡ ወረዱ:: ሁሉም በመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡ መግለጫዎች እርስ በእርሳቸው የተጠላለፉ የውሸት ፈጠራዎች ነበሩ::ይባስ ብሎም መለስ ዜናዊን ለአዲሱ አመት ይዘው እንደሚቀርቡ ቃል እስከመግባ የደረሰ ነገር ግን ባናመጣውም ምንም አያገባችሁም የሚል መእዕክት ያዘሉ መግለጫዎችና ማስፈራሪያዎች የዝጎደጎዱ::

ከቀናት እሰጣ ገባ በሁዋላ የወያኔ ራዲዮና ቴሌቢጅን መለስ ዜናዊን በተገባልን ቃል መሰረት በአካል ማቅረብ ባይችልም የሞቱን ዜና ለማቅረብ ሞከረ:: ነገር ግን አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ቀድሞ በስደት የሚኖሩት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግለሰብና በድርጅት ሆነው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች የመለስ ዜናዊን መሞት ስለሰማ የኢቲቢ የመርዶ ዜና በወያኔ አፍ ከመነገሩ ሌላ የጠቀመው ነገር የለም:: አንዳንድ ወገኖች ግን የ ኢቲቢ የመርዶ ዜና እጅግ የጠቀመን ነገር ቢኖር ስለ መለስ ዜናዊ መሞት ማውራት ትችላላቹ ተፈቅዶላችዋል ከሚል የዘለለ አይደለም ምክንያቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በስደት የሚኖሩት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግለሰብና በድርጅት ሆነው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ማድመጥና መመልከት ብሎም ከወያኔ ቀድሞ ማሰብና ማውራት በአሸባሪ ህግ ያስከስሳልና::

የወያኔዎችና የመረጃ ተቁዋሞቻቸው አሁንም አይናቸውን በጨው አጥበው የውሸት ድራማቸውን ቀጠሉ:: ያው የሞተ ሰው በባህላችን ክፉ አይባልም አይደል ግን ያልሆነውን ነው አይባልም:: በመለስ ዜናዊ ሞት ያየነው ግን በጣም የፈጠጠ በቅርብ ግዜ ውስጥ የሚያስተዛዝበን ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ የሆነ ነገር ነው:: አሁን አየተካሄደ ባለው የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን የህይወት ታሪክ በተሳሳተ መልኩ እጅግ አጋኖ ማቅረብ በቀጠታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጎዳው እርሳቸውን የወያኔ ባለስልጣናትንና እስከዛሬ በዘርና በጥቅም የተሳሰሪዋቸውን ግለሰቦችና ድርጅቶች መሆኑን ማሰብ ስላቃታቸው ይመስለኛል::

ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናትና በወያኔ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች በተደጋጋሚ እየተነገረች ያለች “መለስ ዜናዊ የጀመረውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ እናስፈፅማለን” እና ተመሳሳይ መልክት ያላቸው መፈክሮች ምን ያህል መንግስት በውሸት እንደተገነባ ያሳያል:: አንድም የመለስ ዜናዊን የግለሰብ አምባገነን አገዛዝ የሚያሳይ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ሁሉም ግለሰቦች የጠቅላ ሚንስትሩ ተሳቢ ሆነው እንዳሳመሙዋቸውና ለመሞታቸው መንስኤ በሚሆን ደረጃ ብቻቸውን አገር ለማሳደግ ይደክሙ እንደነበረ ያሳያል በተጨማሪም ሁሉም የወያኔ ባለስልጣናት ምንም ችሎታና ስልጣን እንዳልነበራቸም ይገልፃል::

ሌላው የወያኔ ባለስልጣናትና የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎቻቸው ሊዋሹን የሞከሩት ነገር ቢኖር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ማዘኑን ነበረ በተለይም አዲስ አበባ የመለስ ዜናዊ አስክሬን የገባ ቀን (ከገባ ቆይታል አልቆየም ሌላ የወያኔ የውሸት ደራማ አለው) ቁጥራቸው በዛ ያሉ የወያኔ አባላት በጥቅምና በዘር የተሳሰሩዋቸው ግለሰቦች ድርጅቶች በወያኔ የውሸት ወሬ የተታለሉና እንደዜጋ ማግኝት ያለባቸውን ጥቅሞች በወያኔ ፍቃድ ብቻ እንደሚያገኙ ተደርገው እንዲያስቡ የተደራጁ ወጣቶች ተገኝተው ነበረ:: ነገር ግን መተኮር ያለበት እውን የአዲስ አበባ ህዝብ መለስ ዜናዊን ስለሚወዱት ነው ወይ አስክሬኑን ለመቀበል የወጡት?? እንደ ኢቲቢ ውሸታምነትና ማን አለብኝነት መለስን ስለሚወዱት ነው ሊሉ ይችላሉ:: ለመሆኑ የአዲስ አበባ ህዝብ መለስን ለተለያዩ ጉዳዮች ከአገር ሲወጣም ሆነ ወደአገር ሲገባ ሸኝቶት ተቀብሎት አይቶትስ ያውቅ ነበረ??

እንደውም በተቃራኒው መለስ ዜናዊ በገባና በወጣ ቁጥር በመንገድ የሚሄድ ፍጥረት ሁሉ (ሰውም እንስሳም) እየተገፈተረ በተገኝው ቀዳዳ እንዲገባ ሲደረግ ቀዳዳ ባልነበረበት ቦታዎች መለስ ዜናዊን እንዳያይ ፊት ወደ ግድግዳ እንዲያደርግ ወይንም ወደሰማይ እንዲያይ እንደጠፈርተኛ የታጠቁ አይናቸውን በሚያጉረጠርጡ ደም የጠማቸው በሚመስሉ ወታደሮች ይገደድ ነበረ:: አሁን የአዲስ አበባ ህዝብ ጭንቅላት የለውም? ነው ወይስ የማስታወስ ችሎታ የለውም? ነው እያላቹ ያላችሁት:: መልሱን ከወያኔዎችና ከፕሮፓጋንዳ መሳሪያቹ ከኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዝን ድርጅት አልጠይቅም በቅርቡ እራሱ የአዲስ አበባ ህዝብ ይነግራችዋል::

የኢትዮጵያ ህዝብ ማየት የፈልግ የነበረው መለስ ዜናዊ በስልጣን ዘመናቸው በነፃነት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ከሚስታቸውና ከልጆቻችው ጋር እንዲዘዋወሩ ነበር:: የወያኔ ባለስልጣናት በጥቅምና በዘር የተሳሰራቹ ግለሰቦችና ቡድኖች በወያኔ የተሳሳተ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሆናቹ የህብረተሰብ ክፍሎች እያደረጋቹ ያላችሁት አስክሬን በመኪና ጭናቹ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እያዞራቹ ህዝብ ይወደው ነበረ ለማለት ከሆነ ሞኞች ናችሁ::
የኢትዮጵያ ህዝብ መለስ ዜናዊን በህይወት እዳለ እንዴት ሊመለከተው ሊወደው ሊጠላው እንደሚችል ይህንን መቅረዐ ምስል ይመልከቱና ይረዱ ESAT The legacy of Meles Zenawi

ወያኔ ፣የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እስከመቼ ባዳ ሆነውብን ይዘልቃሉ

Sunday, July 29th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር ከሞቱ/ከታመሙ ጀምሮ የህወሃትና ወይም ኢህአዴግ( ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማጭበርበር የወጣ ስም መሆኑን እንዳትዘነጉ) ምን ያህል ከአንድ ጎጥ የተውጣጣ የበሰበሰና የተበላሸ የፓርቲና የግለሰቦች ስብስብ እንደሆነ ግልዕ አድርጎልናል:: በጣም አስገራሚው ደግሞ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች/ የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መታመም የኢትዮጵያን ህዝብንም እናንተንም ጋዜጠኞቹን ምንም አያገባችሁም አይመለከታችሁም የግል ጉዳይ ነው በለውን እርፍ አሉት::

የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች/ የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መሞት፣ የሬሳ ሳጥኑ ምን አይነት ነው ፣ መታመም፣ ምን እንዳመማቸው “ካሁን በሁዋላ የሚያሳትም የሚፅፍ የሚያወራ በአሸባሪነት ሊከሰስ እንደሚችል” የሚል ያዘለ መልዖክት አስተላልፈዋል::የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የወያኔ ቃል አቃባይ በረከት ስምዖን የጠቅላይ ሚንስቴሩ መታመም የኢትዮጵያን ህዝብንም እናንተንም ጋዜጠኞቹን ምንም አያገባችሁም አይመለከታችሁም የግል ጉዳይ ነው በለውናል እዚህ ጋር በረከት ስምዖን አንድ እውነት አለው ይህም የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ህዝብ የጠቅላይ ሚንስቴሩን ስልጣን አላገኙም::

ሌላው የመለስ ዜናዊ መሞት/መታመም የት እንዳለ የሚያውቁት ወያኔዎች ብቻ ናቸው ሊያውም ጥቂት አድዋዎች:: ከፍተኛ የደህዴን ፣ የኦህዴድ፣ የብአዴን ብሎም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ብሎ ወያኔ ስም ያወጣላችው ክልሎች ባለስልጣኖች አይደለም የመለስን መሞት/መታመም ይቅርና ትላልቅ ሀገራዊ ውሳኔዎችን የሚሰሙት ልክ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በመጀመሪያ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ ባሉ የህዝብና የግል ሚዲያዎች ሲሆን ከዛም በሁዋላ በወያኔ የሚዲያ ማሰራጫዎች እንደማስተባበያ ሆኖ ሲቀርብ ነው:: በዚሁ ሳልናገር የማላልፈው ከፍተኛ የደህዴን ፣ የኦህዴድ ፣ የብአዴን ብሎም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ብሎ ወያኔ ስም ያወጣላችው ክልሎች ባለስልጣኖች የወያኔውን ጠቅላይ ሚንስቴር መሞት ፣ መታመም እና የወያኔን እርቃኑን መቅረት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ህዝቡ የሚያደርገውን የዲሞክራሲ የፍትህና የኩልነት ትግል እንዲቀላቀሉ እመክራቸዋለው::

ሀወሃት/ኢህአዴግ/ ወያኔ ምንም ድርጅታዊ አሰራር መዋቅር መንፈስ የሌለው የጥቂት በሰፈር የተቡዋደኑ ፣ ለአራት አስርት አመት ያህል አመለካከታቸው መቀየር ያቃታቸው ፣ ጥቂት የሰባዊነት ስሜት በውስጣቸው የሌለ ማፊያ ግለሰቦች ስብስብ እንደሆነ በቀላሉ አስረድተዉናል:: አሁን ልክ እንደጠንቁዋያቸው የሚያዩትና የሚሰግዱለት መሪያቸው መሞት/መታመም በሰፊው ከተነገረ በሁዋላ እንኩዋን የታየባቸው ባህሪ ይሉኝታ የሌላቸው ፣ የሃገር መፍረስ የህዝብ መራብ መቸገር ሳይሆን የወያኔ/የአድዋ አምባገነናዊ ሰልጣን የሚያሳስባቸው የቀን ጅቦች ናቸው:: ወያኔ በህግ መተዳደር የማይፈልግ ፣ የበታችነት መንፈስ ያናወዛቸው ፣ የስግብግብነት ስሜት ደማቸው ውስጥ የሚሮጥባቸው ፣ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ፣ በጠብመንጃ እንጂ በዕውነቶች ዙሪያ መደራደር የማይችሉ ስለመሆናቸው ያለፈው ስራቸው አስገንዝቦናል::

ዲሞክራሲያዊ ስርአት ስም ኢትዮጵያውያንንና የአለምን ህዝብ ያጭበረበሩበት የወያኔን ስልጣንና ጥቅም ብቻ የሚያስከብረው ፧ በአለም ላይ የምርጦች ምርጥ ብለው የሚፎክሩበት ፧ በወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ማሻሻል የሚሞከረው ህገ መንግስታቸው በሁሉም መልኩ ቀዳዳ የበዛበት ነው:: ጠቅላይ ሚንስቴሩን ዘላለማዊ አድርጎ አስቀምጦዋቸዋል :: እነዚህን ቀዳዳዎች ወያኔ እስካሁን ለማሻሻል ለመድፈን አልፈለገም እንደውም ለማጭበርበርና ለማምታታት በሰፊው ሲጠቀምባቸው ተስተውሎዋል ህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብቶቼ ተጥሰዋል ህገ መንግስቱ ይከበር ብሎ ሲጠይቅ ወያኔ ደግሞ ህገ መንግስቱን በሃይል ለመናድ ብሎ ይከሳል :: ላለፉት ሃያ አንድ አመታት ህገመንግስቱ ላይ “መያኔ ብቻ ህገ መንግስቱን መጣስ ይችላል” ተብሎ የተፃፈ ይመስል በየቀኑ መጣስ ብቻ አይደለም እየቀደደው ኖሮዋል ::

የኢትዮጵያን ህዝብ የዋህነት ፣ ታጋሽነት ፣ ጨዋነትና ታዛዝነት ልክ እንደ ፈሪነት፣ ሞኝነትና መሃይምነት ቆጥረውት በጠራራ ዐሃይ በሬ ወለደ ውሸት እየዋሹ ምንም እውነተኛ መረጃ እንዳያገኝ እያፈኑ በጠብመንጃና ኢትዮጵያውያንን እንደፈለጉ እስርቤት በሚያጉሩበት በአራዊት ህጋቸው እያስፈራሩ የወያኔ አምባገነናዊና የአንድ ብሄር የስልጣንና የምጣኔ ሀብት የበላይነት ለማረጋገጥ አቅማቸው የቻለውን ሁሉ እያደረጉ ነው:: አሁን ጠቅላይ ሚንስትራቸው ሞቶም/ታሞም ሁሉም የወያኔ አባላቶች ፧ ደጋፊዎች ፧ በዘር የተዛመዱዋቸውና በስርዐቱ አላግባብ የከበሩ እያሰቡና እየሰሩ ያሉት እንዴት ወያኔ የበላይ ሆኖ እንደሚቀጥል እንጂ እንዴት አገራዊ መግባባት እንደሚፈጠር ፣ የህግ የበላይነት እንደሚሰፍንና ፣ አገሪቱ ካለችበት የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት ቀውስ በምን መልኩ መውጣት እንዳለባት አይደለም::

ወያኔዎች ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በማን አለብኝነት ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማንቃሸሽ መሳደብ ስልጣንን ተገን አድርጎ የሀገርና የህዝብን ሀብት መዝረፍ ለግላቸው ጥቅምና ስልጣን የሀገርንና የህዝብን ጥቅም አሳልፎ መስጠትና የመሳሰሉትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: እነዚህን ሁሉ በወያኔ እምባገነንና ዘራፊ ቡድኖች የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊና ኢፍትህአዊ ድርጊቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በኢትዮጵያ ህዝብ የተነሱትን የፍትህ የኩልነትና የነፃነት ትግሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መተባበርና መሳተፍ ይጠበቅብናል::ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሠቦችም ሆንን የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የሚይዘው የሚጨብጠውን ያጣውን የወያኔን የማፊያ ስርአት እናስወግድ::

ስሙን ቀይሮ ከሚመጣ ወያኔና ከድል አጥቢያ አርበኞች መጠንቀቅ ነው

Tuesday, July 17th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

አምባገነናዊው የወያኔ ገዛዝ የፈጠረው አስከፊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ምስቅልቅሎች ምክንያት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጎሳ ፆታ ቃቅንቃ እድሜ ሀይማኖት ሳይል በከፍተኛ ሁኔታ ህዝቡ ሀገራዊ ስሜት እንዳይኖረው በሀገሩ ላይ የባእድነት ስሜት እንዲሰማው ይባስ ብሎም ሀገሩን ጥሎ እንዲሰደዱ ሆነዋል:: ወያኔ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የፈጠረው አምባገነንዊ የፖለቲካ ሥርዓት በሃገራችን ከፍተኛ ቀውስና የተንሠራፋው ድህነትና ሥራ አጥነት እንዲሰፍን አድርገዋል ህዝቡን በማምለጥ ሠርቶ ለማግኘትና የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ህይወት ለመለወጥ ስደትን ቢሹም ከኢኮኖሚያዊ ፍላጎት በስተጀርባ ወያኔ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የፈጠረው አምባገነንዊ የፖለቲካ ሥርዓት ዋነኛ መንስኤ መሆኑ መዘንጋት የለበትም::

ጠቅላይ ሚንስቴሩ በስልጣን በቆዩባቸው አመታቶች ሆን ብለው ሰምተው እንዳልሰሙ በመምሰል አይተው እንዳላዩ በመምሰል የተለያዩ ወንጀሎችን በኢትዮጵያውያንና በጎረቤት አገሮች ህዝቦች ላይ ሲፈፅሙ ሲያስፈፅሙ ከርመዋል:: ልክ እንደወያኔዎቹ ፍርድ ቤት መለስ ዜናዊ ይከሰስ ቢባል ሊያስጠይቃቸው ከሚችሉ ክሶች መካከል የሃገርን ጥቅም አሳልፎ መስጠት፣ የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት አለመረጋገጥ፣ ለሕዝብ ፍላጎት ተገዢና ተጠያቂ መንግሥት አለመኖር፣ የሕግ የበላይነት አለመከበር፣ የፍትሕ፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት፣ ከወያኔ ካድሬ ውጭ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመሬት ባለቤት እንዳይሆን ማድረግ፣ አስከፊና የተንሰርሳፋ ሙስና ከከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናት እስከ ተራ ካድሬ ድረስ መዘፈቅ …….. ተዘርዝረው የሚያልቁ አይመስለኝም::

መለስ ዜናዊ አይሙቱ እንጂ ቢሞቱ ነብስ ይማር የማልላቸው/የማይባሉበት ዋነኛ ምክንያት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው የስራ ባህል እንዲጠፋ በማድረጉ መሆን አለበት:: በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ሃገር ህዝብ የእድገት ባህልና እምነት መሆን ያለበት ስራና ስራ ብቻ ነው የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ግን ያደረጉት ተቃራኔውንና ሃገር አፍራሽ ተግባር ነው:: የወያኔን ስልጣን የሚያስጠብቅ ሁሉ ሰረቀም ነጠቀም ዘረፈም ገደለም ምንም የማይጠየቅበት ስርዓት ፈጥረዋል ጤናማ የውድድር የስራ እድል እንዳይኖር አድርገዋል በኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ አባል ደጋፊ በመሆን ብቻ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል የተለየ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርገዋል:: በአንድ ወቅት የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር በአንድ ለናቱ ቴሌቢጅናቸው ልማታዊ ባለሃብት ብለው ሲሸልሙ ውለው በሰልስቱ ያንኑ የሸለሙትን ግለሰብ አፋልጉልኝ ያዙልኝ እያሉ ሲቀልዱ ነበረ::

የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር አያድርገውና ሞቱም አልሞቱም ፈለጉም አልፈለጉም መንበረ ስልጣኑን ጥለው መሄድ አለባቸው ልቦና ከሰጣቸው በፈቃደኝነት ካልሆነ ግን…….:: የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ሃያ አንድ አመታት እድል ሰጥቶዋቹ ነበረ ነገር ግን በመጀመሪያም ድርጅት መስርታቹ ጠብመንጃ አንስታቹ ጫካ ስትገቡ የተሳሳተ የፖለቲካ አቅጣጫ ይዛቹ ስለመጣቹ ከሀገርና ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳችሁን ጥቅም ስለምታስቀድሙ ቅን ስላልነበራቹ ህዝባዊ መሰረት ስላልያዛቹ ድሮ ከነበራቹ አመለካከትና ቂመኝነት መቀየር ስላልቻላቹ አሁን በቃችሁኝ እንዳላያቹ ተብላችሁዋል:: የኢትዮጵያ ህዝብ ለውጥ ነፃነት ስልጣን የሃገርን ሃብት በጋራ መጠቀም ሃሳቡን በነፃነት መግለፅ የፈለገውን የፖለቲካ አመለካከት ማራመድ አስፈልጎታል እናንተ በፈቃደኝነት ባተለቁ እንኩዋን በጉልበት አንበርክኮ ያስወርዳችሁዋል::

የወያኔ የኢህአዴግ ስልጣን መልቀቅ ከብዙ ግምገማ በኹዋላ ውሳኔ ላይ የደረሰውና ሊያስወርዳቸው አቅም ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ተበጣጥሰው ያሉት የተቃዋሚ ድርጅቶች አይደሉም:: ብዙዎቹ ተቃዋሚ ድርጅቶች ብዙሃኑን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፉ አይደሉም: የአካሄድ ልዩነት እንጂ የአላማ ልዩነት ባይኖቸውም አብረው መስራት አልቻሉም: ትልቅ ትኩረት የሚሰጡት ድርጅቱ ያለ ለማስመሰል እንጂ እስከ ታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ ወርደው አላማችውን ማስተዋወቅ የአባላቶቻቸውንና የደጋፊዎቻቸውን ቁጥር መጨመር አይደለም: ብዙ ግዜ እርስ በእርስ አቃዋሚ ይሆናሉ ለአባላቶቻቸው ግልፅ የሆነ ድርጅታዊ መዋቀር የላቸውም:: እንደዚህ ያሉ መሰረታዊ ችግሮችን መፍታት ካልቻሉ ህዝቡ እስካሁን መስዋትነት የከፈለበትን ወያኔን ከስልጣን የማባረር ትግል ውጤት አልባ እንዳያደርገው ስጋት አለ::

ለውጥ ፈላጊው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግሉን በተሳካ ሁኔታ ለመጨረስ በህቡዕ ካልተደራጁ ልክ ከዚህ በፊት እንደነበሩት ለውጦች የነመለስ አይነት ጭልፊቶች የድል አጥቢያ አርበኞች መስዋቱን ከንቱ ያደርጉታል:: ህዝቡን በህቡዕ ለማደራጀት ሃላፊነት ያለባቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች የሲቢክ ማህበራት የመረጃ ተቁዋማት ናቸው:: ህዝቡን በህቡዕ ለማደራጀት ሃላፊነት ያለባቸው ድርጅቶች በተቀናጀ መልኩ ለውጥ ፈላጊውን የህብረተሰብ ክፍል የጋራ ጥቅማቸውን በሚያስከብር መልኩ ማሰባሰብና ማወያየት አለባቸው:: የህን የመሳሰሉ መሰረቶች ካሁኑ ካልተሰሩ የትግሉ ውጤት በአንድ በኩል በድል አጥቢያ አርበኞች በሌላው በኩል ወያኔ አጭበርብሮ እራሱን የቀየረ መስሎ (መቸም አይቀየርም) ለመንግስትነት ሊቀርብ ይችላል::

ከወያኔ ጋር የሚሰሩ ድርጅቶችና አባላቶቻቸው ነፃነታቸውን የሚናፍቁ ናቸው

Wednesday, June 27th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

የወያኔ/ኢህአዲግ መንግስት ምንም ህዝብ ህዝብ ሳይሸት ላለፉ ሀያ አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ የይሁንታ ድምፅ አግኝቻለው የበብሄር ብሄረሰብ መብትና እኩልነት አስከብሬያለው እያለ በማምታታትና በማጭበርበር ስልጣኑን የሙጥኝ ብሎዋል:: በሌላው በኩል ደግሞ ህዝቡና ከወያኔ ውጭ ያሉት የኢህአዴግ ካድሬዎችና የአጋር ድርጅቶች አባላቶች በተለያየ ዘዴዎች በመጠቀም አገራዊና ህዝባዊ መሰረትና ውክልና እንደሌለው ለማሳየትና ወያኔ/ኢህአዴግ የአንድን ብሄር ብቻ መብትና ጥቅም የሚታስጠብቅ መሆኑን በማጋለጥ ብቻውን እርቃኑን እንዲቀር እያደረጉት ይገኛሉ::

ከህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዲግ ድርጅቶች (ደህዴን ኦህዴድ ብአዴን) የዛሬ ሀያ አመት በወያኔ ፋብሪካ ሲመሰረቱም ሆነ ካድሬዎቻችው ሲሰበሰቡ ዋነኛ አላማው ህዝባዊ መሰረት እንዳለው በማስመሰል ብዙ መስዋትነት የተከፈለበትን የኢትዮጵያውያንን ትግል የተጠበቀውንና የታለመለትን ውጤት እንዳያመጣ አድርጎ የህዝብን ስልጣን ለመቆናጠጥ ሲባል ነበር:: ለዚህም አላማችው ብዙ ህዝብ የብዛት ያላቸውን ብሄሮች አቅም በማይፈጥሩበት አካሁዋን በወያኔ ስር እንዲደራጁ ማድረግ ነበር ይህንን አድርገውም ይኸው ስልጣናችውን ለሁለት አስርት አመታት እየተንገዳገዱም ቢሆን ቆይተዋል::

ወያኔ ይህንን የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ከሞላ ጎደል በሙሉ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን የስልጣን ክፍፍሎቹን በራሱ በህወሃት ሰዎች እጅ ውስጥ አስገብቶዋል:: እጅግ በጣም ጥቂት የስልጣን መደቦችን ከሌሎች ብሄረሰቦች ለተሰባሰቡ በርቀት መቆጣጠሪያ ለሚጠበቁ የኢሀአዴግ ተብዬ ካድሬዎች ለይምሰል ሰጠ:: ነገር ግን እነዚሁ ከህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዴግ ካድሬዎች (ኦህዴድ ደህዴን ብአዴን) በሀገር ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ምንም አይነት ውሳኔ ሰጭነት ጉልበት የላቸውም:: ኢህአዴግ ለይስሙላና ለማጭብርበር ቀጥቅጦ የሰራቸው ኦህዴድ ደህዴን ብአዴን ክልላችውን ይቅርና አነስተኛ ቀበሌ እንኩዋን በክልላቸው የማስተዳደር ስልጣን እስካሁን አልተሰጣችውም::

ህወሃትና/ኢህአዴግ የስም መቀያየር እንጂ ያው ወያኔ/ህወሃት ማለት ነው እንደውም አንዳንድ ግለሰቦች ኢህአዴግ የወያኔ ክርስትና ስሙ ነው ብለውታል:: መላው የኢትዮጵያ ዝብና ህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዲግ ድርጅቶች አባላቶች (ደህዴን ኦህዴድ ብአዴን) በተለያዩ ጊዜያት የወያኔና የኢህአዴግን አንድነትና ሁለትነትን ግልፅ አድርገውልናል የህወሃትና የኢህአዴግ አንድነት ለኢትዮጵያውያንና ለመላው አለም ከተገለፁበት ክስተቶች መካከል::

፠ ኢህአዴግ ላይ የጠነከረ ተቃውሞ ሲደርስበት በመጀመሪያ የሚጮሁት ህወሃት ወያኔዎች ብቻ ናቸው:: ሚያዚያ 30 ቅንጅትን በጠራው ሰልፍ ላይ አንድ የድርጅቱ አባል ኢህአዴጎችን ወደመጡበት እንመልሳቸዋለን ብለው ነበር ነገር ግን ለዚህ ንግግራችው ወያኔ ህወሃት ብቻውን ነው መልስ ሲሰጥ የነበረው ህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዲግ ድርጅቶች አባላቶች (ደህዴን ኦህዴድ ብአዴን) ምንም አይነት መልስ አልሰጡም እንደውም በንግግሩ የተደሰቱ ይመስሉ ነበረ::

፠ ከህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዲግ ድርጅቶች (ደህዴን ኦህዴድ ብአዴን) ድርጅታዊ ስብሰባዎች ያለ ህወሃት ወያኔ ተሳታፊነት አይካሄዱም በተቃራኒው ግን የህውሃት/ወያኔ ድርጅታዊ ስብስባ ላይ ምንም አይነት ከህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዲግ ድርጅቶች አይሳተፉም::

፠ እስካሁን በወያኔ የስልጣን ዘመን ከህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዲግ ድርጅቶችና አባላቶቻችው (ደህዴን ኦህዴድ ብአዴን) ብቻ ናቸው እንደ ጥፋተኛ ሙሰኛ ልማት አደናፋቂ……..ምናምን ተብለው በህወሃቶች/ወያኔዎች በአደባባይ የሚብጠለጠሉት:: በተቃራኒው ግን አንድም የወያኔ/የህወሃት ድርጅት አባል ከህወሃት ውጭ ባሉ የኢህአዲግ ድርጅቶች (ደህዴን ኦህዴድ ብአዴን) ጥፋተኛ ሙሰኛ ልማት አደናፋቂ ምናምን ተብሎ የተተቸ የለም:: አይደለም ጠመንጃና ስልጣን የያዘውን የወያኔን ድርጅት መተቸት ይቅርና አንድን የድርጅቱን አባል ቆጣ ብሎ መናገር በሀገር ውስጥ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ሁላችንም ያየነውና ያረጋገጥነው ነገር ነው::

፠ በወያኔ/ኢህአዴግ ድርጅታዊ መበስበስና የመልካም አስተዳደር ስርዐት መበላሸት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳስባቸው ኢህአዴግን ለማጭበርበሪያነት የፈጠሩት ህወሃቶች ብቻ ናቸው:: ሌሎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ካድሬዎች ስለድርጅቱ መበስበስም ሆነ መጠንከር የሚያውቁት ከህወሃት ሲነግራቸው ብቻ ነው:: ህወሃት/ወያኔ ድርጅታዊ መበስበስና የመልካም አስተዳደር ስርዐት መበላሸት የሚለካበት አንድና አንድ መመዘኛው መስፈርት የህወሃት/ወያኔ የስልጣንና የምጣኔ ሀብት ባለቤት የማያስደርገው አካሄድ ሲፈጠር ብቻ ነው::

፠ ከፍተኛ የደህዴን የኦህዴድ የብአዴን ብሎም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ብሎ ወያኔ ስም ያወጣላችው ክልሎች ባለስልጣኖች በሀገራዊ ጉዳይ ላይ የተደረጉ ውሳኔዎችም ሆኑ ስምምነቶች ላይ ምንም አይነት የተሳትፎ ድምዕ የላቸውም:: የወሳኝነት ስልጣን ለወያኔና ለወያኔ ብቻ ነው:: ትላልቅ ሀገራዊ ውሳኔዎችን የሚሰሙት ልክ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በወያኔ የሚዲያ ማሰራጫ ነው:: በጣም የሚገርመው ደግሞ በክልሎቻቸው የተፈፅሙትን ድርጊቶች እንኩዋን የሚነገራቸው ወያኔ መረጃዎቹን በሚፈልገው መልኩ ከተጠቀመባችው በሁዋላ በነሱ ልክ እንዲሰፋ አድርጎ ነው::

፠ ከህወሃት ውጭ ያሉት የኢህአዲግና አጋር ድርጅቶች በሚያስተዳድሩዋችው ክልሎች በስተጀርባ ሆነው የሚመሩት የወያኔ ካድሬዎች ናቸው:: ከክልሎች ባለስልጣናት ይልቅ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጭነት ጉልበት ያላቸው በዝቅተኛ የስራ ደረጃ የተቀጠሩ የወያኔ/ህወሃት ካድሬዎች ናቸው::

ከላይ ያየናቸው ተጨባጭ ክስተቶች የሚያረጋግጡልን የህወሃት/ኢህአዴግ በተለያዩ ብሄረሰብ ስም እራሱን ደብቆ የአንድን ብሄር የስልጣንና የጥቅም አስከባሪ ድርጅት መሆኑን ብቻ ነው:: ከአንድ ብሄር ከተውጣጡ ካድሬዎች በስተቀር ምንም የሌሎች ብሄሮች የውሳኔ ተሳትፎ የሌለበት ዘመናዊ ቅኝ ግዛት በሚያስብል ደረጃ ሀገሪቱን እየዘረፍሩና እያስዘረፉ ይገኛሉ :: ከህወሃት/ከወያኔ ውጭ የሆኑት የኢህአዴግ አባላቶች የደህዴን የኦህዴድ የብአዴን ካድሬዎች ብሎም ሌሎች አጋር ድርጅቶች ብሎ ወያኔ ስም ያወጣላችው ክልሎችን የሚያስተዳድሩ የፓርቲ አባላቶች ለጊዜው የሚያገኙት ጥቅም ያስደሰታቸው ቢመስልም ያ ጥቅም ወያኔ ሆን ብሎ ለማባበልና አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ ለመፈዐም አዕምሮዋቸው የማይፈቅድላቸውን ግዳጅ የሚታዘዙበት እንደሆነ ዘግይተው የተረዱ ይመስላሉ:: በአሁኑ ሰዓት ከህወሃት/ወያኔ/ኢህአዴግ ጋር የሚሰሩ ድርጅቶችና አባላቶቻቸው ልክ እንደ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነታቸውን በመናፈቅ ላይ ይገኛሉ::

የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትሩ ብቻ ከስልጣን እንዲወርዱ አይደለም የወያኔ አምባገነናዊና የአንድ ብሄር የስልጣንና የምጣኔ ሀብት የበላይነት ይወገድ ነው

Friday, June 22nd, 2012

ዋለልኝ መኮንን

የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር ከዋሽንግተን ዲሲ በመሰብሰቢያ በአዳራሽ ውስጥ ግምባር ለግንባር በጋዜጠኛ አቶ አበበ ገላው “ነፃነት እንፈልጋለን” ቁጣ አዘል የተቃውሞ ንግግር የሳቸውን የፓርቲያቸውንና የስርአታቸውን የ21 አመት ቅጥፈትና ውንብድና ሳያስቡት በተለያዩ ድጎማዎች የስልጣን እድሜውን በሚያራዝሙለት በሀያላን ሀገሮች መንግስታት ፊት እርቃናቸውን አስቀርቶባቸው :: የነፃነት እንፈልጋለን ጥያቄ የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ፊት ለፊት በግምባር ለማሰማት ከሰማኒያ ሚሊየን በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጡን እያብሰለሰለውና እያረረ መልካም አጋጣሚዎችን በመጠባበቅ ላይ ይገኝ ነበረ, ነገር ግን በአቶ አበበ ገላው ለወያኔው ለጠቅላይ ሚንስቴርና እንደተላላኪ ላገለገላቸው ለሀያላን አገሮች መንግስታት የመጀመሪያና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም አስተላልፎዋል::

ህወሃት ኢሀዲግ 17 አመት ለነፃነት ታግያለው ቢልም ስልጣን ከጨበጠ የታየበት ባህሪ ግን ከነፃነት ጋር በጣም የተቃረነ ነው:: በጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርላማ 99.6 በመቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ድጋፍ አግኝቻለው የሚለው ወያኔ ከምርጫ 97 በሁዋላ ወደፍፁም አምባገነንነት አሸጋግሮ የተለያዩ ጨቃኝና አፋኝ ህጎችን አውጥቶዋል: ሁሉንም በመንግስትና በህዝብ መካከል እንደ ድልድይ የሚያገለግሉትን የሲዚል ተቁዋማትን ህይወት አልባ አድርጎዋቸዋል ሀገራዊ ውሳኔዎች በሙሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብሩ አይደሉም በተቃራኒው የወያኔ የፓርቲ ስልጣንና የአባላቶችን ጥቅም ብቻ የሚያስከብሩ ናቸው:: ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ጭቆናና ተላቆ ነፃነቱን ማወጅ ይፈልጋል::

ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በማን አለብኝነት ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማንቃሸሽ መሳደብ ስልጣንን ተገን አድርጎ የሀገርና የህዝብን ሀብት መዝረፍ ለግላቸው ጥቅምና ስልጣን የሀገርንና የህዝብን ጥቅም አሳልፎ መስጠትና የመሳሰሉትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: ከዚህ በአቶ አበበ ገላው ከተነገራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወያኔዎችና ሌሎችም የጥፋት ተባባሪዎች በአሁኑ ሰአት እራሳቸውን ፈንጂ ላይ እንደቆሙ አድርገው ሊያስቡ ይገባል እንጂ የተለያዩ ተራ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ስህተታችውን ሊደብቁ መሞከሩ አግባብ አይደለም::ምክንያቱም ስህተትን በስህተት ማከም ውጤቱ የደሀ ቀብራራ …… ….የሚባለው ተረት አይነት ይሆናል::

ልክ ከዚህ በፊት እንዳየናቸው አምባገነን አፍሪካዊያን መሪዎች በስልጣን ለመቆየትና የህዝብንና የሀገርን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ የፈፅሙዋቸውና ያስፈፅሙዋችው ኢ-ሰብአዊና ኢ-ፍታዊ ድርጊቶች: የዘር ማጥፋት: የግለሰቦችን ነብስ ማጥፋት ወንጀሎች: ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት በከፍተኛ ሙስና የጠገቡ ባለሀብቶች መሆን: ሀገሪቱዋ እስካሁን በምግብ እራስን ለመቻል ተቀረዑ የተባሉት እስትራቴጂዎች ምንም ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተው በአስር ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን በተደጋጋሚ በከፍተኛ በርሀብ አለንጋ ከመገረፍ አለማዳናቸው: የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ ባለመመለሳቸው ምክንያት በመላው ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ መቀጣጠል ከአቶ አበበ ገላው የነፃነት እንፈልጋለን ቁጣ አዘል ንግግር ጋር በአንድ ላይ ተደማምረው ጠቅላይ ሚንስትሩን ወደ ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ ተዘፍቀዋል:: ሰሞኑን ያየናቸው ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር በተለያዩ በአይን በሚታዩ ምልክቶች እየተገለፁ ይገኛሉ::ለምሳሌ

፨ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከዋሽንግተን ዲሲ መልስ ክፉኛ ታመው ወደ አውሮፓ ለህክምና መሄዳቸው(መታመማቸውን በተለያዩ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ባቁዋቁሙዋቸው የመገናኛ ብዙሀን ባንሰማ ኖሮ የወያኔው ኢሬቴድ ለስብሰባ እንደመጡ አድርጎ ያቀርብ ነበር) :

፨ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተለመደውን ፉከራ ዛቻና ማስፈራሪያ ልክ የግል ንብረታቸው በሚመስለው ኢራቴድ ሳያሰሙ መቆየታቸው(በተለይ ከሰሜን አፍሪካ አገሮች አብዮት ወዲህ የኢትዮጵያን ህዝብ መሳደብ ቀነስ አድርገው ህዝብ ህዝብ ለመሽተት ሞክረው ነበረ ነገር ግን መሳደብ ሱስ ሆኖባቸው አርፈው መቀመጥ አልቻሉም ፊታቸውን ወደ መንግስት ባለስልጣናቶችና ካድሬዎች አዙረው ሌቦች …..ምናምን በማለት የስድብ ሱሳቸውን መወጣት ጀምረው ነበር):

፨ እንደ አንድ የኢትዮጵያን ህዝብ ማስፈራሪያ የሚጠቀሙበትን የወያኔ የ17 አመት የነፃነት ተብዬ ትግላቸውን (ለነገሩ እራሳቸውን ነፃ አውጥተዋል) የሚፎክሩበትን ግንቦት ሀያን እንካን የተለመደውን ሽለላ በአደባባይ አለማሰማታቸው(የግንቦት 20ን ቀን ወያኔ ለስልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ መሳሪያ አድርጎ እየተጠቀሙበት ይገኛል:: ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ጀግና ወያኔ ብቻ እንደሆነና የደርግን ስርአት ብቻቸውን ታግለው ከስልጣን እንዳወረዱ ለማምታታትና ለማስመሰል ይጠቀምባታል: በስልልጣን የሚፎካከሩዋቸውን ሆዳም የኦህዴድ የብአዴንና የደህዴን ካድሬዎችን የስነልቦና ጫና ለማድረግ ይጠቀሙበታል: በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የስነልቦናዊ ጫና ለማድረግ እንዴ ተራራውን ያንቀጠቀጠ ትውልድ (ለነገሩ ሰውን አንቀጠቀጥን አላሉም) አግአዚ ኦፕሬሽን ምናምን የተባሉ በፅሁፍና በፊልም መልክ አዘጋጅተው የዚህን ትውልድ አዕምሮ ለመስለብ ብዙ ደክመዋል: ወያኔን በፍፁም በጠመንጃ ማሸነፍና ከመንግስትነት ስልጣኑ ማስወገድ እንደማይቻል ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ይጠቀሙበታል የደርግን ስርአት ከስልጣን ለማውረድ የትግራይ ህዝብ ብቻ መስያትነት ስለከፈለ አሁን እያደረጉ ያለውን የሀብትና የንብረት ዘረፋ ተገቢ እንደሆነ ለማስረዳት ይጠቀሙበታል):

፨ ሙያቸውን ለሆዳቸው ሲሉ አሳልፈው በሸጡ ጋዜጠኛ ነን ባዮች የማያድን ህክምና መውሰዳቸው(ሰሞኑን ወያኔ አሉኝ የሚላቸውን ሆዳምና አይነ ደረቅ ጋዜጠኛ መሳዮች ሰብስቦ የወያኔውን መሪ ከደረሰባቸው ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር እንዲያገግሙ ለማድረግ ያልቆፈሩት ድንጋይ ያልወጡት ተራራ አልነበረም በጣም የሚገርመው የተሳሳተ መዳኒት ሰተዋቸው የባሰ ህመማቸውንና ችግራቸውን አባብሰውባቸዋል):

፨ የተለመደውን ጠቅላይ ሚንስትሩ “ቢወርዱ ማን እሳቸውን ይተካል” የሚል ይሽሙጥ ወሬ በየጫት ቤትና በየግሮሰሪው አለመብዛት:: የተለመደውን ጠቅላይ ሚንስትሩ “ቢወርዱ ማን እሳቸውን ይተካል” የሚል ይሽሙጥ ወሬ በየጫት ቤትና በየግሮሰሪው አለመብዛት በፊት በፊት ጠቅላይ ሚንስትሩ በየሰፈሩ እሳት የላሱ ወሬ በማራገብ ወደር የማይገኝላቸው በየከተማው በሚገኙ በጫት ቤቶችና በግሮሰሪዎች ወያኔን የሚጠሉ መስለው መረጃ መሰብሰብና ወደህዝቡ መድረስ ያለበትን መልእክት የሚያናፍሱ የወሬ ሜሲ የሆኑ ሆዳሞች ነበሩዋችው እንዚህ ወሬኞች ወያኔና ጠቅላይ ሚንስትራቸው የፖለቲካ ኪሳራ ሲገጥማቸው ከወያኔ ውጭ ለኢትዮጵያ የሚሆን መሪ እንደሌለ ይሰብኩላቸዋል በነዚህ ወሬኞች የሚናደዱት ህዝቡ ብቻ ሳይሆን የመለስ ፓርላማ ውስጥ ሌላውን ብሄር ወክለናል የሚሉትም ሆዳሞች ናቸው

፨ በደረሰባቸው የግንባር ለግንባር ተቃውሞ (ቡጢ) የወያኔና የራሱ ብቻ የሆነው ኢቲቢ የሚይዘውንና የሚጨብጠው ማጣትና::

፨ሜክሲኮ በሚካሄደው በG-20 ስብሰባ ላይ የፊት ገፅታቸው ግርጥት ማለትና ጤነኛ ያለመምሰል የመሳሰሉ የጠቅላይ ሚንስትሩን ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር ወስጥ መሆናቸውን ያሳያል::

የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትሩ ብቻ ከስልጣን እንዲወርዱ አይደለም የወያኔ አምባገነናዊና የአንድ ብሄር የስልጣንና የምጣኔ ሀብት የበላይነት ከስሩ ይወገድ ነው:: ወያኔና ጠቅላይ ሚንስትሩ በተፈጥሮአዊ ግዴታም (በህመም ወይንም በሞት) ሆነ በህዝብ አመዕ መንበረ ስልጣናቸውን መልቀቃችው አይቀርም:: ጠቅላይ ሚንስትሩ ወያኔዎችና ሌሎችም የሌብነት ተባባሪዎች ልብ ሊሉት የሚገባው በቅርብ ግዜ የህዝብን ድምፅ አፍነውና በአለም አደባባይ እራሳቸውን ህዝባቸው እንደሚወዳቸው ሲለፍፉ እንደነበሩት የሰሜን አፍሪካ መሪዎች እራሳችሁን አታታሉ:: እስካሁን እንዳየሁት እንደተፃፈው የህዝብን ጥያቄ በጉልበትና በውሸት ማፈን እንደማይቻል ነው: ወንጀላቹህና ፍርዳቹ ሳይበዛባቹ ከስልጣን አወራረዳቹ ጤናማ እንዲሆን በጥይት እያስፈራራቹህና በወሬ እየዋሻቹ የያዛችሁትን የህዝብ ስልጣን ለራሱ ለህዝቡ መልሱለት::

የተከበሩ የወያኔ ጠቅላይ ምንስቴር የህችን ደብዳቤ በደንብ ለሚሰድቡትና ለሚያዋርዱት ፓርላማዎት ያንብቡላቸው

Tuesday, June 5th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

የተከበሩ የወያኔ ጠቅላይ ምንስቴር የህችን ደብዳቤ በደንብ ለሚሰድቡትና ለሚያዋርዱት ፓርላማዎት ያንብቡላቸው

ላለፉት 21 አመታት የእርሶንና የሎሌዎቾን የውንብድና የህዝብና የሀገር ሀብት ዘረፋ እድሜ ለማራዘም እያሉ ኢትዮጵያዊያንን በተለያዩ ምክንያቶች በመከፋፈልና እርስ በእርሳቸው በማበጣበጥ ሁሉም ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በዲምክራሲያዊ ስርአት ባልው መልኩ ወደ ህዝባዊ ስልጣን እንዳይመጡ ከህዝብ የተዘረፈውን ሀብቶንና ጉልበትዎን ሲያጠፉ ከርመዋል። እስካሁን እርሶና ሎሌዎችዎ በጋራ የፈጠሩዋችው ህዝብን በብሄር: በሀይማኖት: በቋንቋ: በጎጥ: በአናናር ዘይቤው: ከቀድሞ ስርአቶች ጋር በነበራቸው ትስስር ወዘተ መከፋፈልን በመፍጠርና እነዚህም ዘዴዎችዎ ጉልበትዎንና ገንዘብዎን ተጠቅመው ህጋዊ ከለላ እንዲያገኙ አድርገው ወያኔ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ብቻ ኢትዮጵያና ህዝቦቻ በሰላም የሚኖሩ እስኪ መስለን ድረስ አጭበርብራችሁናል ።

እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሳችሁበትን ግፍና በደል ሳያንስ የእርስዎ በተደጋጋሚ በሲቃ የሚናገሩት ስልጣኔን እለቃለው ውሸት አዘል ጩኸት ህብረተሰቡን አሁን ካቀጣጠለው ሁሉንም አቀፍ (ሰላማዊና ኢ-ሰላማዊ) የሆነ የነፃነት ትግል ለማዘናጋት ካልሆነ በስተቀር ላለፉ ሀያ አንድ አመታት ያየነውና የተገነዘብነው ግብርዎ የግል ባህሪዎ ለህግ የበላይነትን ለማስፈን ያለዎት ቁርጠኝነት ያመጡት ሰላም ብልፅግና ዲሞክራሲ የመፃፍ የመናገር በአደባባይ ተቃውሞ ማካሄድ የመሰብሰብ መብቶችን ባጠቃላይ ለመልካም አስተዳደርና ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እንደግብአት የሚጠቅሙትን የመገናኛ ብዙሀን መስፋፋት የተቃዋሚ ታርቲዎች መጎልበት የህዝብ በማህበራዊ ጉዳዮች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ሶስቱ የስልጣን አካላት ከፓርቲ እጅ ንክኪ ነፃ መሆን በነዚ ሁሉ መመዘኛዎች ጠቅላይ ሚንስቴሩና ፓርቲያቸው ሲፈተሹ ምንም ሚዛን የሚደፋ ስራዎች አልሰሩም ወይንም ሆን ብለው ለመስራት አልፈለጉም::

የወያኔ ጠቅላይ ሚንስትሩ የዛቻና የስድብ ሰለባ የሆኑትና ከገዚው የትግሬ ቡድንም ሆነ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋርም ጭምር ሆድና ጀርባ የሆኑት የኢሀዲግ ፓርላማ ውስጥ የሚገኙት የሌሎች ብሄር ተወካይ ነን ባዮች ላይ በተደጋጋሚ በመለስ ዜናዊ የተለያየ አፅያፊ ስድብ ስም ፍረጃ ሲደርስባቸው ከርመዋል:: በጣም የሚያሳፍረው እነዚህ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ ለባርነት ለስደት ለችግር ለፍትህ እጦት ለሀብት ንብረት አገር መሬት አልባ እንዲሆን አሳልፈው ለተራቡ ለጅቦች የሰጡ ስለ ወከላቸው ህዝብ አንገታቸውን ቀና አድርገው አንድም ቀን ሳይናገሩ ሁለት አስርት አመታትን አሳለፉ:: በዚሁ የህዝብ ውክልና እድሜያቸው በአንድ በኩል የኢትዮጵያን ህዝብ ቆመው ሲያዘርፉና ሲዘርፉ በሌላው በኩል የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ ሆነው የመረጣቸውን ህዝብ በማፈንና በማሰቃየትና በማወናበድ ህዝቡ ጠላቱ ወያኔ መሆኑን እንዳያውቅና የተባበረ ክንዱን እንዳያሳርፍበት አድርገውታል::

የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትሩም እነዚሁን የህዝብ ተወካዮች ተብዬዎችን በኢሐዲግ ፓርላማቸው በተደጋጋሚ ከፍ ዝቅ አድርገው እየሰደቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ “አናንተን የበደሉዋችሁ የወከላችሁዋቸው ግለሰቦች ናቸው” ብለው ለመቀላመድ ሲሞክሩ ተስተውለዋል:: የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴርና አጋፋሪዎቻችው የጭቡ ፓርላማቸውን የመሰረቱበት አላማ አንደኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ስርአት አለን ብለው ከእርዳታ ለጋሽ ሀገራት ብዙ ዶላር ለማግኝት ሲሆን ሁለተኛው የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትሩ ህዝቡን የሚያስፈራሩበትና በተወካይ ተብዬዎቹ ላይ የራሱን ወገኖች እንደጠላት እንዲቆጥራቸው መቀስቀሻ መድረክ እስኪመስል ሆኖዋል:: የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔውን ጠቅላይ ሚንስትር እንደ አሳ ሙልጭ ሙልጭ የሚሉትን ባህሪያቸውን ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ስድባቸውን ከመጤፍ አልቆጠረውም:: ምክንያቱም ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በህዝቡ ላይ ለደረሰው የህይወት ምስቅልቅል የዘር መጥፋትና መፅዳት የሀብት የንብረትና መሬት ዘረፋ ዋነኛው ተጠያቂዎች የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴሩ: በዘር የተንዘራዘሩዋቸው: ጦርነት የወለዳቸው ሌቦችና ወክለናችሁዋል ያሉት ለግል ጥቅማቸው ህዝባቸውን አሳልፈው የሸጡትም መሆናቸውን ጠንቅቆ ይረዳል::

ክቡር የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር እስካሁን በቆዩበት የስልጣን ዕድሜዎት ትልልቅ ሹም ሽሮችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል ነገር ግን እስካሁን ያካሄዱት ሹም ሽሮች የኢትዮጵያን ህዝብ መብትና ጥቅም ያስከበሩ አይደሉም:: በተቃራኒው የራሶትን: ለብዙ ዘርዎን ለተንዘራዘሩ: ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ህዝባቸውን አሳልፈው ለባርነት ለሸጡና: በሙስና ለተወዳጁዋቸው ባዕዳኖች ጥቅም ያስከበሩ ናቸው:: በተጨማሪም እስካሁን ያደረጉዋቸው ሹም ሽሮች የተፈለገውን የህግ የበላይነትን ማስፈን: የፍትህ ማጣት: የተንሰራፋ የሀብትና ንብረት ዘረፋ: እርሀብና የተለያዩ የህይወት ምስቅልቅሎችን ማስወገድ አልቻለም:: ስለዚህ ክቡር የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር የእስከዛሬው ሹም ሽርዎ ጉልቻ ቢለዋወጥ….. ስለሆነ የቀረዎት አንድና አንድ አማራጭ እራስዎንና ፓርቲዎትን ከስልጣን መሻር ነው ካልሆነ ግን ልክ እንደ ሰሜን አፍሪካ መሪዎች መጨረሻችሁ ያላማረ እንዳይሆን እፈራለው::

ነፃነት ያጣ ነፃነት ወዳለበት አገር ሲሰደድ ነፃነት አመጣን ያሉት ወያኔዎችም ለምን አብረው ተሰደዱ?

Monday, May 28th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

ላለፉት 21 አመታት በኢትዮጵያ የአገሪቱን ሥልጣን በሙሉ ጠቅልሎ የያዘው የማፊያው የወያኔ አገዛዝ የአንድ ብሄርን የበላይነትን ለማረጋገጥ የስልጣን እድሜውን ለማራዘምና በቡድን ተደራጅተው የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብትና ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ በአገራችንና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ባደረሱት ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የተነሳ ህይወታቸውን ለማዳንና የተሻለ ህይወት ፍለጋ ለማግኝት በብዙ መቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ጥለው በየብስ፤ በምድርና በባህር አያቋረጡ ወደተለያዪ አገራትና አለማት ተሰደዋል አሁንም እየተሰደዱ ይገኛሉ:: የሚሰደደውም የህዝብ ቁጥር ከለት ወደለት እጅግ እየጨመረ እንደመጣ ጉዳዩ ያሳሰባቸው የተለያዩ አለማቀፍ ተቃማት ገልፅዋል::

የኢትዮጵያ ህዝብ በግለሰብና በቡድን ደረጃ ከሚደርስባቸው ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅሎች ለማምለጥና ህይወታቸውን ለማዳን የህይወትና ከፍተኛ የገንዘብ መሰዋትነት ከፍለው ሀገራቸውን የተወለዱባትንና የደጉባትን ቀያቸውን ሀብት ንብረታቸውን ቤተሰቦቻቸውን በግዴታ ጥለው እየሸሹ ይገኛሉ:: ይህንን ሁሉ መስዋትነት ከፍለው ህይወታቸውን ለማትረፍ በድንበር መሸሽ ከሞከሩት ውስጥ ግማሹ በመንገድ ላይ በወያኔ ወታደሮች ይያዛል ግማሹም በምግብና በውሀ እጥረት ህይወቱ ያልፋል ግማሹ ባህር ውስጥ ሰምጦ ይቀራል እጅግ በጣም ጥቂቱ እድል ቀንቶት ከሀገሩ ወጥቶ ለሌላ መከራ ሌላ አገር ይደርሳል (ከሀገር መሰደድ እድለኛ ባያስብልም ህይወትን መቆየት ግን እድለኛ ያስብላል):: ትንሽ የኢኮኖሚ አቅም ያለውና በስደት እጅግ የተዋጣለት ደግሞ አውሮፓና አሜሪካ ይደርሳል::

የህንን ሁሉ በሀገራቸውና በስደት ጉዞ ላይ የሚያጋጥማቸውን መከራ አልፈው በተለያዩ አገራት ከደረሱም በሁዋላ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አምባገነንና ለስደትና ለባርነት መንስኤ የሆናቸውን የወያኔን የማፍያ ቡድን ከስልጣን አስወግዶ ሁሉም ሰው እኩል የሚሆንባት የህግ የበላይነት የሰፈነባት የአመለካከት የመፃፍና የመናገር ነፃነት የተረጋገጠባት የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ የሆነባት ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ መብቶች የሚከበርባትን የጋራ ኢትዮጵያን ለመመስረት በሚደረገው ትግል ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመሳተፍ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ:: ይህንንም ትግል ውጤታማና የተጠናከረ ለማድረግ በተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችና ማህበራዊ ተቃማት ውስጥ በቀጥታ በመሳተፍ በእውቀታቸውና በጉልበታቸው በመርዳት በገንዘብ ማዋጣትና በማሰባሰብ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ:: በአንፃሩ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚደርስባቸው ኢሰብአዊና ኢተፈጥሮአዊ ግፎች አምልጠው በተለያዩ በውጭ አገሮች በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚደርጉት ከፍተኛ የፍትህ የኩልነትና የአገር የማዳን የተጠናከረ ትግል እጅግ በጣም ያሳሰበው የወያኔ የማፊያ ቡድን የህዝብን ትግል ለማጥፋት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል::

የወያኔው ቡድን በመጀመሪያ ያደረገው ልክ እንደነሱ እኩይ ተግባር ካላቸው ከአምባገነን ጎረቤቶቹ አገሮች ጋር ስምምነት ፈጥሮ ምንም አይነት የተቃዋሚ ቡድን መጠለያ እንዳይሰጣጡ መማማል ነበር( እንደውም ለሱዳን መንግስት የወያኔ መሪ መሬት እጅ መንሻ አቅርባል):: የዚህ ስምምነት አባል አገሮች ልክ እንደወያኔ መሪዎች ህዝብን አፍነው የስልጣንና የዘረፋ ዘመናቸውን ለማራዘም የተጠቀሙበት ነው:: ሁለተኛው የወያኔ ቅጥፈት ደግሞ ለምዕራቡ አገሮች ምንም አይነት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፅሙ ኢሰብአዊና ኢተፈጥሮአዊ ድርጊቶች የሉም ብሎ በምዕራቡ አገራት የሚደርጉትን ከፍተኛ የፍትህ የኩልነትና የአገር የማዳን የተጠናከረ ትግል ለማዳፈን መሞከር ነበረ::የምዕራብ አገሮች የወያኔ የማፊያ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈፅማቸውን ኢሰብአዊና ኢተፈጥሮአዊ ድርጊቶች ጠንቅቀው ቢያውቁትም በምስራቅ አፍሪካ ጥሩ ተላላኪያቸው ስለሆነ ከወረቀት ያለፈ እርምጃ ለመውሰድ አልፈለጉም:: ሌላው አሁን ወያኔ እየሞከረው ያለውና በጣም አደገኛውና በጋራ ልንታገለው የሚገባው እንደተኩላ የበግ ለምድ ለብሰው በአውሮፓና አሜሪካ ወያኔ አምባገነን ቡድን ሊፈልጠን ሊቆርጠን ሲል ሸሽተን ነው የመጣነው ብለው የጥገኝነት ጥያቄ አቅርበው ፍቃድ አግኝተው የሚኖሩ ነገር ግን ኢትዮጵያን የሚደርጉትን ከፍተኛ የፍትህ የኩልነትና የአገር የማዳን የተጠናከረ ትግል ለመበታተንና ለማጥፋት የተለመደ የመከፋፈል መሰሪ ስራውን እየሰራ ይገኛል::

አነዚህ ከኢትዮጵያ ህዝብ መሀል የወጡ ጭንቅላታቸው ሆድ የሆነባቸውና አርቆ አስተዋይነት አይምሮ ያጡ የወያኔ አሽከሮችና የአንድ ብሄር የበላይነት ናፋቂዎችና የበታችነት ስሜት ያናወዛቸው ጠባብ ትምክህተኞች በአውሮፓና በአሜሪካ እየተንቀሳቀሱ በወያኔ ፊት እውራሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰባቸው ኢሰብአዊና ኢፍታዊ ግፎችና ጭቆናዎች ካገሩ ከቀየውና ከቤተሰቦቻቸው በግዳጅ ሸሽተው የወጡትንና ለነፃነፃነታቸው የሚታገሉትን በማስፈራራት አሁን እየተደረገ ያለውን የነፃነት የፍትህ የኩልነትና አገር የማዳን እንቅስቃሴ ለማክሸፍና ለማጥፋት ሲሮጡ ተስተውለዋል:: ከዚህም አልፎ ቤተሰቦቻቸውን ማስፈራራት በማሰቃየት አገር ቤት ያለውን ንብረቶቻቸውን በመዝረፍ ሌላ የወያኔ ግዛት እየፈጠሩ ነው:: እነዚህ በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙት ሆድአደሮች ካለማፈራቸው የተነሳ የተለያዩ የወያኔን የስልጣንና የዘረፋ እድሜ የሚያራዝሙ በተቃራኒው ከሀገራቸው በደረሰባቸው ኢሰብአዊና ኢፍታዊ ድርጊት ሸሽተው ያመለጡትንና ለየነፃነት ለፍትህ ለኩልነትና አገር ለማዳን የሚታገሉትን አንገት ማስደፊያና ተስፋ ማስቆረጫ ስራዎች እየሰሩ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን::

አሁን በጋራ ተሰባስበን እነዚህን ጭንቅላታቸው ሆድ የሆነባቸውና አርቆ አስተዋይነት አይምሮ ያጡ የወያኔ አሽከሮችና የአንድ ብሄር የበላይነት ናፋቂዎችና የበታችነት ስሜት ያናወዛቸው ጠባብ ትምክህተኞችን ከስልጣን በጊዜ አስወግደን ሁሉም ሰው እኩል የሚሆንባት የህግ የበላይነት የሰፈነባት የአመለካከት የመፃፍና የመናገር ነፃነት የተረጋገጠባት የሀብት ክፍፍል ሚዛናዊ የሆነባት ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ መብቶች የሚከበርባትን የጋራ ኢትዮጵያን ለመመስረት ካልቻልን እንዳበደ ውሻ የሚቅበዘበዙት ወያኔና ሆድአደሮቹ ሸሽተን ከምንኖርበት ሀገርም እንድንፈራና በነፃነት እንዳንኖር እያደረጉን ይገኛሉ:: እነዚህን በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩና የኢትዮጵያውያንን የፍትህ የኩልነትና የአገር የማዳን ትግል በማስፈራራትና የውሸት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት የማኮላሸት ወንጀል እየፈፅሙ ያሉትን ወያኔዎችና የወያኔ ተላላኪዎችን አጋልጠን ማውጣትና ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ አለብን::

ጠቅላይ ሚንስትሩ አንገታቸው ብቻ ሳይሆን ቅስማቸውም ተሰብሮዋል

Wednesday, May 23rd, 2012

ዋለልኝ መኮንን

ባሳለፍነው ሳምንት በዕለተ አርብ አንድ ጠቅላይ ሚንስትራችንንና ደጋፊዎቻቸውን ያሳፈረ ያናደደና ያስቆጣ በሌላው በኩል ደግሞ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያስደሰተ ክስተት በአሜሪካዋ Washington DC ከተማ ተከስቶ ነበረ:: ይህንን ክስተት የኢትዮጵያ ህዝብ ባገኝው የመረጃ ቴክኖሎጅ በመጠቀም ያየነው ምስል ያነበብነው ፅሁፍ የጠቅላይ ሚንስትራችንን መደንገጥ መሸማቀቅ መቆዘም አንገት መድፋት ከመጠን በላይ አስደስቶናል በተቃራኒው ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ ተንዘራዛሪዎችና ደጋፊዎች እጅግ በጣም እንዴት ተደፈርን እያሉ ሲጮሁ ተስተውለዋል::

የጠቅላይ ሚንስትራችንን መደንገጥ መሸማቀቅ መቆዘም አንገት መድፋት ከመጠን በላይ ያስደሰተው የኢትዮጵያ ህዝብ ደስታውን እየገለፃ ይገኛል:: ብዙሃኖቹ የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ ተስተውለዋል ተደምጠዋል ተሰምተዋል:: ከተሰጡት አስተያየቶች እጅግ ብዙዎቹ አቶ አበበ ገላውን ጅግና አንበሳውን አይጥ አሳከለው ብለው የሚያወድሱ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትራችን ለካ ወንድ የሚመስሉት በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥና በውስጡ በሚቀመጡት ሰዎች ላይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል:: እንደውም አንድ ጉደኛዬ “ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢሰባዊና ኢፍታዊ ስራቸው ከጋኑ ሞልቶ እየፈሰሰ ስነነበረ አንድ ቀን እንደዚ ጉድ እንደሚሰሩ ስለሚያውቁ የታላላቅ ስብሰባ ጉዞዎቻቸው በሙሉ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ነበረ ባለፈው አርብ ግን ሀትሪክ ተሰሩ” አለኝ::ምክንያቱም ላለፉት 21 አመታት አንድም የህዝብ አስተያየትና እርምት ተቀበለው አያውቁም እሳቸው ያሰቡትና የተናገሩት ተቀባይነት ካላገኝ አለም ትገልበጥ የሚሉ ናቸው::

አንዱ አስተያየት ሰጪ ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ አትንኩኝ ባይነትና ለብዙ አመታት በውሸት የገነቡት መንግስት በአቶ አበበ ገላው በቅፅበት ዶግ አመድ ሆነ አለኝ:: በአለሙ ህብረተሰብ ዘንድ ጠቅላይ ሚንስትራችን ታታሪ ታማኝና አስተዋይ መስለው ለመታየት እስካለፈችዋ አርብ ድረስ ያልወጡትና ያልወረዱት ተራራ አልነበረም:: በተለይ እስከመቼ በልመና ህዝቦቻቸውን እንደሚያስተዳድሩ የማያውቁትን ብዙ የአፍሪካ መሪዎችን አፍ በማስከፈት የሚታወቁትና ብሎም በትላልቅ የልመና ስብሰባዎች ላይ የሚወከሉት ጠቅላይ ሚንስትራችን ለ 21 አመታት የገነቡት ግድብ መንገድ ትምህርት ቤት ጤና ጣቢያ ከመዘለፍና ከመተቸት አላዳናቸውም:: ይህ ተቃውሞ በምንም መልኩ ተሰልቶ የሚያሳየስ አሁን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው መንግስት በብዙሀኑ ህዝብ ተቀባይነት ያላግኝ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ህዝቡም ፍትህ ነፃነትና እኩልነት የተጠማ ባገኝው አጋጣሚ ግን እየጮኸ ያለ ጪኸቱም የታፈነ መሆኑን ያሳያል::

ለአየር ከደረሱ አስተያየቶች መካከል ጠቅላይ ሚንስትሩ እስከአሁን ጎበዝ ታማኝና ታታሪ ደጋፊም ሆነ የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይና የሌሎች ተለጣፊ ድርጅቶች አባላቶች የሉዋቸውም ብሎ ያቀረበው ምክንያትም ደጋፊዎቹም ሆኑ የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይና የሌሎች ተለጣፊ ድርጅቶች አባላቶች ድሮ ከነበሩበት አዕምሮአዊ መዳበርና የአመለካከት ደረጃ በስንዝር አለመቀየራቸውና ለመቀየር ጥረት አለማድረጋቸው ነው:: ውሸት ሲበዛ እውነት የሚሆን ስለመሰላቸው አይን ያወጣውን የህገ ወጥ ህይወታቸውን መንግስታዊ አሰራራቸውን በግድ ትክክለኛና ህጋዊ ነው ብሎ ለማሳመን ከመጣር አንድ ቀን ሳይቆጠቡ ላለፉት 21 አመታት እራሳቸውን ከመዋሸት አልፈው የኢትዮጵያን ህዝብና የአለሙን ማህበረሰብ እያወናበዱት የህዝቡን ስልጣን ሀብትና ንብረት በጉልበት ነጥቀውታል ዘርፈውታል::ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲሳሳቱ እያዩ እሰይ አበጀህ እያሉ አገራችንንና ታሪካችንን በጠራራ ዕሀይ አስዘረፉን እነሱም ያሻቸውን ዘረፉ:: እንደውም ከተማችን ውስጥ ሆን ተብሎ የህዝብ ወገንተኝነት አላቸው እንዲባል አነዚህ የህዝብና የሃገር ሀብት የዘረፉ ግዙፍ አቅም የፈጠሩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች ለጠቅላይ ሚንስትሩ አንታዘዝም ወደማለት ደረጃ ደርሰዋል የሚባል ውሸት ልክ ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በየመንደሩ እየተወራ ነው::

ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናትና በሀገርና በህዝብ ሀብት ዘረፋና በጥቅም የተሳሰሩ ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩ ግለሰቦች ቃልቻችን እንዴት ይደፈራል በማለት ቁጣቸውን መቆጣጠር አቅቶአቸዋል:: ሁሉም የወያኔ ባለስልጣናት የተለመደ ቅጥፈታቸውን አሁንም ቀጥለውበት አንዱ አይኔን ግንባር ያድርገው ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ሲል ሌላው ደግሞ የሀያሉ የአሜሪካን መንግስት መሪ ላይም ጫማ ተወርውሮባቸው የለ! ብሎ ጠቅላይ ሚንስትሩና አጫፋሪዎቻችው ላይ የተወረወረውንና የአቶሚክ ቦምብ ያህል ያቆሰላቸውን የአቶ አበበን ተገቢ የሆነ የጀግንንት ስራ ለማጣጣል ሞከር አድርገው ነበረ አልተሳካላቸውም::

በመጀመሪያ የVOA(voice of America) የዜና ዘገባ ብዙ ከሀገር ውጭ መረጃ የማግኝት እድልና አማራጭ ላልነበራቸው ኢትዮጵያውያን ብሎም ትክክለኛውን በጠቅላይ ሚንስትሩ የደረሰውን ክስተት በስልክና በኢንተርኔት መልክት ለሰሙ ሰዎች እጅግ ግራ ያጋባ ነበረ ግራ ከማጋባትም አልፎ በውጭ ሀገር የሚገኙትን እውነተኛና ሚዛናዊ የመረጃ ምንጮቻቸውን እስከመጠራጠር ደርሰው ነበር:: ዘጋቢያቸው በስብሰባው ላይ የተከሰተውን በጠቅላይ ሚንስትሩ የደረሰውን ትክክለኛ ክስተት መዘገብ ከሙያ ግዴታ ሆነ ድርጅቱ ከተቃቃመበት አላማ አንፃር አይን ያወጣ ስህተት ነበረው:: ለምን መደባበቅ እንደፈለገና እውነተኛውን እንዳልዘገበ መልሱን ለራሱ ለዘጋቢውና የህንን አይን ያወጣ ቅጥፈት ለተከታተለና ለታዘበ የኢትዮጵያ ህዝብ ትቼዋለው::አገር ውስጥ ያለችም አንዲት ተንዘራዛሪና ህዝብን እያደነቆረች ያለች ሴቲዮ(Mami) አቶ አበበ ገላውን ለመተቸት ሙከራ ማድረጋን ሰምቼ እንዴት ነደደኝ መሰላቹ:: ሴትየዋ ለነገሩ ያልሞከረችው ስራ የለም ነበረ ስላልተሳካላት ግን በስለላና የህዝብን የአመለካከት አቅጣጫ በማስቀየር የምትተዳደር እንደሆነች ዐሀይ ካሞቀባት ሰነበተ:: እንደዚ አይነት ሰዎች ባለ ሁለት ስለት ቢላ ይባላል ነገም ሌላ ቦታ የሚበላ ካገኙ መለያ መቀየር ብቻ ነው::

እንደውም ጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የመሳቀቅ የመቅበዝበዝና አንገት የመድፋት አደጋ ከደረሰ በሃላ ለያዝ ለገላጋይ ያስቸገሩት አንዳንድ በነፃው የውድድር አለም ውጤታማ መሆን ያልቻሉና ያልተሳካላቸው ዘርዛሮችና ሌሎችም በራስ መተማመን ያቃታቸውና ሆዳቸው አምላካቸው ተሆኑ ግለሰቦች ነበሩ:: እነዚህ ግለሰቦች የህዝብን ድምፅ ለማፈን ለሰሩት ለወደፊቱ በውለታ ከሚያገኙት ጥቅም በተጨማሪ በወያኔ መንግስት ሙሉ ወጪያችው ተሸፍኖላቸው ለወያኔ አባላቶችና ደጋፊዎች ለፖለቲካ ቅስቀሳ የምትጠቅምና አገር ቤት ለሚገኙ ከመንግስት የመረጃ ተቃማት ውጭ ምንም አማራጭ ለሌላቸው ኢትዮጵያውያን ለወሬ ፍጆታ የምትሆን ትንሽ የድጋፍ ሰልፍ ብጤ አዘጋጅተው እንደነበረ በወሬ ደረጃ ተሰምቶአል:: እንደውም አንዱ ምን አለ መሰላቹ መጀመሪያ የወያኔን ማልያ ለብሼ ብሬን ከነከስኩኝ በኻላ መለስን ስቃወም ዋልኩኝ ብሎ ቅሌቱን በአደባባይ አናፈሰው::

በጣም የሚያስቀውና ከስህተታቸው መማር አለመፈለጋቸውን ገሀድ ያወጣባቸው በጉልበት አገርንና ህዝብን እያስተዳደረ ያለው መንግስትና በተጨማሪም ጥቂት የጠቅላይ ሚንስትሩ ደጋፊዎች የህወሀት አባላቶችና የወያኔ ተለጣፊ ድርጅቶች አባላቶች ጠቅላይ ሚንስትሩ የደረሰባቸውን አደጋ ለመሸፋፈን ያደረጉት ጥረት ነበር:: በመጀመሪያ የፈፅሙት ደባ አቶ አበበ ገላው ጠቅላይ ሚንስትሩን ልክ ልካቸውን ሲነግራቸውና አንገታቸውን ሲደፉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ አገር ቤት እንዳይታይ ባደራጁአቸው የመረጃ መረብ ጠላፊ ድርጅቶች እንዲታፈን ማድረግ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ልክ እንደተለመደው በኢትዮጵያ ቴሌቤጅንና ራዲዮ ጠቅላይ ሚንስትሩ የ ስብሰባ በተሳካ ሁሌታ እንደፈፅሙ የሚናገር ተራ የውንብድናና የማጭበርበር ዜና ከኢትዮጵያ ቴሌቤጅንና ራዲዮ ውጭ ሌላ የመረጃ አማራጭ ለሌለው አገር ቤት ላሉት ኢትዮጵያውያን መለፍለፍ ነበረ::

የወያኔ መንግስት በአንድ በኩል የመረጠኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው እያለ በሌላ በኩል የኢትዮጵያን ህዝብ ምንም አይነት ትክክለኛ መረጃና የመረጃ አማራጭ እንዳያገኝ ለማድረግ የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችን በገፍ አስገብቶ ማፈኑንና ማጭበርበሩን ተያይዞታል:: በሀገራችን በአሁኑ ሰአት መንግስትን በአደባባይ መቃወም አይደለም ሌሎች ወገኖቹ ወያኔን ሲቃወሙ መስማትም ማዳመጥም ማንበብም ማየትም በህግ ተከልክሎዋል:: አሁን ወያኔ የቀረው የማፈኛ መንገድ የመረጃ መረብን(Internet) ልክ እንደ ግንቦት 7ና ኦሮሞ ነፃነት ግንባር አሸባሪ ነው ብሎ በህግ ደረጃ በአሻንጉሊቱ ፓርላማ ማኖ አስነክቶ ማፅደቅ ነው::

“ጅግና ይፈጠራል እንጂ አይወለድም” በ G9 ስብሰባ

Saturday, May 19th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

ወንድሞቼ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለሰ ዜናዊ በ21 አመት የአምባገነን የስልጣን እድሜቸው እንደዚህ ያለ ውርደት ሲገጥማቸው አይቼም ሰምቼም አላውቅም:: ከፍተኛ ግፍ:በደል:ጭቆናና ውርደት በሕዝቡ ላይ እያደረሱ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ልክ እንደ ልማት ሰራተኛና ሰላም ወዳድ እራሳቸውን አስመስለው የኢትዮጵያንና የአለምን ማህበረሰብ በውሸት ሲያደነቁሩን ይሀው 21 አመት ሊሞላ ቀናቶች ቀራቸው::

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የስልጣን ዘመናቸው እየረዘመ በመጣ ቁጥር በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈፅሙት የወንጀል መጠንም በአይነቱም ሆነ በይዘቱ እጅግ እየጨመረ ይገኛል ጥቂቶቹን ብናስታውስ
-ህዝቦችን በዘር: በብሄር: በቋንቋ: በሀይማኖት: በቀለም: ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት::

-በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን፧የመናገር:የመፃፍ:የመሰብሰብ:በቡድን የመደራጀት:ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የምግለፅ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን: የፈለገውን እምነት መከተልና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ::

-የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን: አባላቶችን: ደጋፊዎችን: ምሁሮችን: መምህራኖችን: ጋዜጠኞችን: ዘፋኞችን: ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት: በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም: አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ: የት እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ: መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና የባንዳነት ተልኮውን መወጣት::

-ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ:: ህዝቡም መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም ማድረግ::

-የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ በመስጥትን በመሸጥ አሳልፎ መስጠት::

-በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች የሌብነት ተግባራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፈፅም ወንበዴ ዘራፊ ድርጅት ማቋቋምና ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ: ማደህየት: ማስራብ: የበዪ ተመልካች ማድረግ::

-የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ: በማህበራዊ: በፖለቲካ: በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ ለማድረግ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት: ፈቃድ መከልከል: ባለቤቶቹን ማስፈራራት: ማሰር: ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጥት ሞገዳቸውን ማፈን::

እንግዴ እነዚህን ሁሉ ወንጀልና ውሸት የያዘችው እንስራ ሞልታ መፍሰስ ከጀመረች ዘገየች ነገር ግን ልክ እንደ ሌሎቹ የአፍሪካ መሪዎች ጠቅላይ ሚንስትሩም መማር አልፈለጉም ነበርና አንደኛ ደረጃ የውርደት ካባ በ May 18 2012 የG-9(አንዱ አበበ ገላው ነበረ) ስብሰባ ተሸልመዋል:: ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደዚ አይነት ውርደት ይገጥመኛል ብለው እስበው ስልማያውቁ ሲደነግጡና አንገታቸውን ሲደፉ ታይተዋል:: ምክንያቱም ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደዚ አይነት ደፋር ኢትዮጵያዊ እንዳይኖር ለማድረግ ላለፉት 21 አመታት ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያላፈሰሱት መዋለንዋይ ያላንኩዋኩት በር ያልቆፈሩት ጉድጋድ የለም ነገር ግን የተጨቆነን የህዝብ ድምፅ ማስቆም የሚችል ሰዋዊ ፍጥረት እንደሌለ ስለማያውቁ ለማፈን እንሞክራለን ብለው በተደጋጋሚ የውርደት ካባ እየተሸለሙ ይገኛሉ

በአሁን ሰአት ጠቅላይ ሚንስትሩ አስራ አንደኛ ሰአት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ህዝብ ባገኝው አጋጣሚ ሁሉ ሲነግራቸው ቆይቶአል አሁንም ባገኝው አጋጣሚ እየነገራቸው ይገኛል ::ትላንትናም አቶ አበበ ገላው በአለም አቀፉ የ G9 (አንዱ አበበ ገላው ነበረ) ስብሰባ ላይ የተናገሩት በአንድ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል በአምባገነኖች ቀንበር ስር እንዳሉ ሲሆን በሌላ በኩል የአለም አቀፍ እርዳታ ለጋሽ አገሮች የአምባገነኖችን በዜጎቻቸው ላይ የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊና ኢፍታዊ ድርጊቶችና ወንጀሎች መሸፋፈናቸው አስፈላጊ አለመሆኑን ነበር:: በጣም የሚያሳዝነው ግን በህዝብ ትግል ተሸንፈው ተዋርደውና ተጎትተው ከወንበራቸው እንደተጣሉት እንደ ብዙዎች የአፍሪካ መሪዎች የህዝብን የፍትህ የኩልነትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ቸል ማለት አለማድመጥ ይባስ ብሎም አሸባሪ በማለት ህዝብን ሰላማዊ ዜጎችን ፤ለነፃነታቸው የሚታገሉትን ግለሰቦችና ቡድኖች፤ ስለ ነፃነት ፍትህና እኩልነት የሚፅፉትንና የሚያዜሙትን በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለተለያዩ ስቃዮችና እንግልቶች መዳረግ የተለመደ ተግባራቸው ነው::

በኢሀዲግ ፓርላማ ብርቅዬው የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካይ የተናገሩትን( በሁዋላ አልሰማንም አላየንም የለም ተናግረናል) ንግግር ጠቅላይ ሚንስትሩ በደንብ ደጋግመው ሊያጤኑት ይገባ ነበረ ግን ልክ እንደ ሙሃመድ ጋዳፊና ሌሎችም የአፍሪካ መሪዎች በስድብና በንቀት አለፉት አሁን ግን ጌቶቻቸው ፊት ነው የማስጠንቀቂያ ደውል እንዲሰሙ የተደረጉት አሁንም ካልተማሩ …………..

የወያኔ በሃይማኖት ጣልቃ ገብነትና አሞራዎች ጅግራ ሆነው መታየት ቀጥለዋል

Thursday, May 10th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

የወያኔ መንግስት ለስሙ ሀይማኖትና መንግስት ጣልቃ አይገባቡም እያለ ጆሮችንን በየቀኑ ያደነቁረናል ነገር ግን በኦርቶዶክስና በእስልምና እምነት ድርጅቶች ውስጥ በቀጥታ እጁን አስገብቶ በመጀመሪያ ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብርው የኖሩትን ከላይ የተጠቀሱትን የሁለቱን እምነቶች ተከታዮችን ጣልቃ በመግባት እርስ በርሱ እንዲተላለቁ ለማድረግ ብዙ ስራዎች ተሰርተው ነበረ ነገር ግን ህብረተሰቡ ይህ ተግባር የወያኔ አኩይ ስራ እንደነበረ ስለተረዳ በትዝብት ተመልክቶታል:: በሁለተኛ ደረጃ ወያኔ በእምነቶች ውስጥ ጣልቃ መግባቱ ገሀድ የወጣበት በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎችን የፈጣሪን የሚመለክባቸው ሳይሆን የወያኔን ጥቅም ለሚያስከብሩ ከአንድ ብሄር ለተሰበሰቡ ግለሰቦች አስረከበ::

የሰሞኑ የወያኔ ትልቅ ቅሌት ደግሞ በእስልምናም እምነት ውስጥ እያደረገ ያለው ድራማ ነው:: አዲስ የእስልምና እምነት ከውጭ እንዳስመጣ በጉልበትም ካልተቀበላቹ እያለ እያስፈራራ አያሰረ እየገደለ እንደሆነ እያየን ነው:: አንቀበልም ያሉት ደግሞ አሸባሪ እየተባሉ ነው:: የኢትዮጵያ ህዝብ በተደጋጋሚ መንግስት እጁን ከእምነቶቻቸው እንዲያወጣ ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ቢቆይም ይባስ ብሎ ሰሞኑን የወያኔ ዛር የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ እምንት ነፃነት ጥያቄ የሚያነሱትን ህዝቦች ፅረ ሰላም ፅረ ልማት ፅረ ዲሞክራሲና ፖለቲካ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የፖለቲካ አጀንዳ ያላችው ጥቂት ግለሰቦች ናቸው በማለት የመላው ኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ በትእቢትና በንቀት ሲያጣጥሉት አይተናል::

ከትላንት በስቲያ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ለወያኔ ፓርላማ እንደተናገሩት ህዝቡ ስልክ ፌስቡክና የመሳሰሉትን የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች አመፅና ሽብር ለማስነሳት እየተጠቀሙባቸው ነው ሲሉ ተደምጠዋል (ሊበሉዋት የፈለጉዋትን አሞራ ጅግራ ነች ይሉታል ይሄ ነው):: የዚህ ንግግር መልክት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ የነዚ,ለስሙ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት የተባሉት የመገናኛ አውታሮች ቲቪ፣ ሬድዮ፣ ስልክ፣ኢንተርኔት የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ እንዳይሆን እንደሚደረግ በግልፅ ነግረውናል:: በ1997 ምርጫ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ብዙ የምርጫ ቅስቀሳዎችን በሞባይል መልዕክት አካሂድው ከፍተኛ የህዝብ ድምፅ አግኝተው ወያኔን አሸንፈው መንግስት ሌመሰርቱ ቢሞክሩም ወያኔ ስልጣን የጨበጥኩት በጠመንጃ ስለሆነ እናንተም በጠመንጃ ሞክሩ አላቸው:: ተቃዋሚዎቹን የመረጠውም ህዝብ ድምፄ ተሰረቀ ብሎ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በሞባይል መልዕክትና በፌስቡክ በመጠቀም በአጭር ግዜ ውስጥ ተሰባስበዋል:: ነገር ግን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ወዲያውኑ የወሰደው እርምጃ የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት መልዕክት በሞባይል መላላክ እንዳይችል ማድረግ ነበር::

ከዚህ በፊት እንዳየነውየሀገራችንም ሆነ የሌላው አገር አምባገነኖች የህዝብን ጥያቄ መመለስና ቁጣው ማብረድ ሲያቅታቸው እንደዚ ያሉ የመገናኛና የመረጃ ቴክኖሎጂዎችን ማፈንና እርስ በእርሱ መረጃ እንዳይለዋወጥ እድርጎ ትግሉን ማኮላሸት ነው:: እነዚህ የሀገርና የህዝብ ሀብቶች ህብረተሰቡን ማገልገል ሲገባቸው የስርዓቱ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ከመሆን አልፈው ህዝብን ማስፈራሪያ የማፈኛ፣ የማሸበሪያ ከሆኑ ሰነበቱ::

የወያኔ መንግስት ህዝባዊ አመፅ የሚያስነሱ ናቸው በማለት በውሸት በተቀነባበረ ክስ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላቶች ደጋፊዎች የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች በሰብአዊ መብትና በማህበረሰብ ልማት ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የግል ጋዜጣ ባለቤቶችና አምደኞች በየእስር ቤቶቹ እያጎረ ነው። እነዚህ በየማጎሪያ ቤቶቹ የሚገኙትን እስረኞች ቁጥር በእጅጉ ከመጨመሩም በላይ ታስረው በሚገኙበት ቦታ የሚፈጸመው እንግልት እና ስቃይ እጅግ በጣም ተባብሷል::

አሁን የወያኔ አባላቶችና ደጋፊዎች የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያጡበት ሰአት ላይ ይገኛሉ። ትልቁ ችግራቸው እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሱትን ወንጀሎች ኢተፈጥሮአዊና ኢሰብአዊ ድርጊቶች የሀገርና የህዝብ ሀብትና ንብረት ዘረፋ ብሎም የግለሰቦችን የብሄርንና የሀገርን ስምና ታሪክ ማጥፋትና ማበላሸትና የመሳሰሉ የውንብድና ተግባሮቻቸውን እንዴት ማጥፋት እንደሚችሉ የሚቻላቸውን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ነው። ነገር ግን የሄ የመንግስት የሀይል እርምጃ ፉከራ ድንፋታ መደነባበር የህዝባችንን የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ማቆም አያስችለውም::

እኛ ኢትዮጵያውያን ለምንድነው ፍርሀትን የማንፈራው?

Saturday, May 5th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

ወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ህዝብ አመኔታና ይሁንታ ሳያገኝ ላለፉት 21 አመታት አገርና ህዝብን በጠመንጃ ሀይል እያተራመሰና እየዘረፈ ቢቆይም በአሁኑ ሰአት ከወትሮው በተለየ መልኩ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው ኢስባዊና ኢፍታዊ ድርጊቶች ህዝቡ መሸከም ከሚያቅተው በላይ ስለደረሰበት የተለያዩ የፍትህ የኩልነትና የነፃነት ጠያቄዎች ከሁሉም አቅጠጫ ስላመጡበት በከፍተኛ ስጋት እና የመረበሽ መንፈስ ውስጥ ሆኖ ህዝቡን በርሀብ ፤ በማስፈራራት ፤ በእስር ፤ በስቃይ ፤ በስደት ፤ በግድያ፤ በእርስ በእርስ ግጭትና ሁከት እየፈጠረ በጠመንጃ አስገድዶ የባንዳነትና የሌብነት ተግባሩን እየፈፅመ ይገኛል::ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ አስፈራርቶና አጭበርብሮ በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚጠቀምባቸው ብዙ ድብቅና ገሀድ የወጡ እስትራቴጂዎች አሉት::

ትልቁና ዋነኛው የወያኔ የማስፈራርያና የማጭበርበሪያ መሳሪያ ህዝቡን በመረጃ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ማስፈራራት፤ ውሸት የሆነውን የወያኔን የሁለት አሀዝ እድገትን በግድ እንዲዋጡለትና ማድረግና፤ ወያኔ ከስልጣን ከወረደ ኢትዮጵያ ዋጋ እንደሌላት እድርጎ የራሱን ስራዎችና ካድሬዎች ብቻ ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ዋነኛ የወያኔ ሬዲዮና ቴሌቢጅን ተግባራቸው ነው::በወያኔ የሚተዳደሩ ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ የወያኔአዊ አመለካከትና የፓርቲ አቁም ማራመጃ እንጂ ታክስ እየከፈለ መገናኛ ብዙሃን ለገነባው ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠቃሚ መረጃ ማሰማት ይቅርና ማስፈራሪያና ዛቻውንም በተወናበደና በተጭበረበረ መልኩ ብቻ ነው የሚያገኝው:: የኢህአዴግ መንግስት በሀገራችን የሚከሰቱ ማንኛውም ችግሮችንና የችግሮችን መንስኤ በወቅቱ ተረድቶ ስለችግሩ አግባብነት ያላቸውን መረጃዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ባለመቻሉ ወይንም ህዝቡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችንና የችግሮቹን መንስኤ ሆን ተብሎ እንዳያውቅና እንዳይሰማ ስንደረግ ወገኖቻችን ላይ የደረሱትን ችግሮችንና የችግሮቹን መንስኤ አስቀድመን የምንሰማው ከመንግስትና እሱ ከሚያስተዳድራቸው የመረጃ ተቃማት ሳይሆን ከሌሎች በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በፈጠሩቸው የመረጃ ተቀማት እና በአለም አቀፍ የመረጃ ምንጮች ነው፡፡

ሌላ የወያኔ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ዘዴ የኢትዮጵያን ህዝብ በኢኮኖሚ የወያኔ ጥገኛ ማድረግ ነው::ወያኔ እየተከተለ ያለው የድህነት ማጥፋት ፖሊሲና እስትራቴጂ ላለፉት 21 አመታት ተጨባጭ የሆነ ለወጥ ማምጣት አልቻለም ለዚህም ውጤት አለመገኝት ዋነኛ መንስኤዎቹ የሀገሪታን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ፖሊሲና እስትራቴጂ ፤ያስፈፃሚው አካላቶች የችሎታ ማነስ ፤ የህዝብ አሰራሮችን ከፓርቲ አሰራር ለይቶ አለማስኬድና፤ ስር የሰደደ ሙስና ናቸው፡፡ የኢትዮጰያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክሰ ኤጀንሲ በ2003 ዓ.ም ባወጣው መረጃ መሰረት በአሁኑ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ በከተሞች ያለው የስራ አጥነት በመቶኛ 18 እንደሆነ ያሳያል፡፡ ድህነትም ከዛሬ አምስት አመት ከነበረበት 39% ወደ 29.6% ዝቅ እንዳለ የመንግስት መረጃዎች ያሳዩናል፡፡ እነዚህ ቁጥሮች አሁንም አገሪቱ ውስጥ አስከፊ ችግሮች እንዳሉ ቢያሳዩንም፤ ትልቁ ጥያቄ ግን እነዚህ መረጃዎች ምን ያህል ልክ ናቸው የሚለው ነው:: ምክንያቱም የወያኔ የዜናና የመረጃ ድርጅቶች የሜያወጡቸው አሀዞች ሀዝቡ በአይኑ ካየውና የአለም አቀፍ ድርጅቶች ክሚያወጡት እጅግ በጣም የሚራራቅ ነው፡፡ ሌላው ምክንያት የምዕራቡ አለም ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በአመት 3 ቢሊዮን ዶላርና 400 ሺ ቶን የምግብ እህል እርዳታ ለኢትዮጵያ ይለግሳሉ:: እጅግ የሚገርመው የወያኔ ቅጥፈት የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲውና የራሱ ካድሬዎች የፈጠሩትን የኑሮ ውድነት በነጋዴው ህብረተሰብ ላይ ማላክኩ ሲሆን በጣም አሳፋሪው ቅጥፈት ደግሞ የባንክ ብድር እንደፈለጉና በርካሽ የሚወስዱትን ፤ ግብርና መዋጮ ከማይከፍሉትንና ፤ ገበያውን እንደፈለጉ የሚጨፍሩበትን የወያኔን የንግድ ድርጅቶችን እንደምክንያት አለመጥቀሱ ነው ።

ወያኔ ለለውጥ ዝግጁ አለመሆኑንና ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን በህዝብ ድምፅ ሳይሆን በጠመንጃ አስፈራርቶና እርስ በእርስ አባልቶ ለመቆየት ያለውን አላማ በገሀድ አሳይቶናል:: ለምሳሌም በተለያየ በከፍተኛ የውሳኔ የሚሰጥባቸው የስልጣን ቦታዎች፤ ለሙስና የተጋለጡ መስሪያቤቶች፤ የህግ ክፍተት ያላቸውና፤ ብዙ የህዝብ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ቦታዎች ላይ መቶ በመቶ በሚያስብል መልኩ በትግራይ ብሄር ተወላጆች ብቻ መያዙ እጅግ ትንሽ የሆኑ የከፍተኛ ስልጣን ቦታዎች በሌሎች የብሄር ተወላጆች ቢያዙም ከአሻንጉሊትነት የዘለለ የመወሰን ስልጣን የላቸውም:: ለምሳሌ በወያኔ መከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎች ከሞላ ጎደል በትግራይ ተወላጆችና ለጥቂት ለሆዳቸው ባደሩና ታማኝ የሌሎች ብሄረሰብ ተወላጆች መያዙና የፌደራል ፓሊስን፤ የከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ፤አየር መንገድ፤ በተለያዩ የታክስና የጉምሩክ ገንዘብ መሰበሰቢያ ቦታዎች ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ስልጣን በትግራይ ተወላጆች ከዘጠና በመቶ በላይ የተያዙ ናቸው::

ሙስና በኢትዮጵያ ታሪክ አሁን ያለበት ዘግናኝ ደረጃ ደርሶ አያውቅም:: ወያኔ እንከን የለሽ ብሎ እድሜልኩን የሚፎክርበት ነገር ግን ምንም ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያቃተው የልማትና የእድገት ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች ወያኔዎችንና ጥቂት ለሆዳቸው ያደሩትን አጫፋሪዎቻቸውን ቢሊየነርና ሚሊየነር የሚያደርጉ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ በመካከለኛና በድህነት የኑሮ ደረጃ ይኖር የነበረውን ህዝብ እጅግ ወደከፋ የድህነት አረንቅ ከተውታል:: ይህም በከፍተኛ ሁኔታ አዳዲስ የተራቡ ሌቦችንና በብዛት የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ድሆችንም ፈጥረዋል፡፡ የወያኔ አባላቶች የቀረዑት ፖሊሲና መንግስታዊ አሰራር ሆን ተብሎ እድሜልካቸውን የህዝብና የሀገርን ሀብት እየዘረፉ እንዲኖሩ ተደርጎ ሲሆን በስልጣን በቆዩባቸው ዘመናት ምንም አይነት ህጋዊና ተጠያቂነት ያለው የስራ ባህል ስላላዳበሩ ፤በስልጠናና በዘመናዊ ትምህርት እራሳቸውን ብቁ ስላላደረጉ ከዘረፋ ውጭ ሌላ የህይወታቸውን ማቆያ የማይታያቸው ለሀገርና ለህዝብ ሸክም የሆኑ ዜጎች ሆነዋል፡፡ እንደውም ህዝብን ጉድ ያሰኛ የአንድ ወቅት ከስተት የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድን ባለሀብት ልማታዊ ባለሀብት ብለው በአደባባይ ሸልመው ሲያበቁ በነጋታው ወዲያው ዞር ብለው ያንን ወርቅ የሸለሙትን ግለሰብ ሌባ ነው ያዙልኝ ብለው በአንድ ለናቱ በሆነው የወያኔ ቴሌቢጅን ሲጮሁ ነበር:: ከምርጫ 97 በሃላ የታየው ህጋዊ የመሬት ዘረፋ የወያኔ ሌብነት እርቃኑን የታየበት አጋጣሚ ነበረ::ወያኔ ሌብነት ዋነኛ አላማው እንደሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ መናገረ ለቀባሪው አረዱት ቢሆንም ቀላሉ መረጃ ግን ላለፉት 21 አመታት አንድም የትግራይ ተወላጅ ወያኔ በሙስና ለፍርድ ቀርቦም ተፈርዶበትም አይተንም ሰምተንም አናውቅም ነገር ግን የሌሎች ብሄር ተወላጅ የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች ባስፈለገ ግዜ ሙሰኛ ተብለው እስርቤት ይገባሉ በሌላ ጊዜ ደግሞ በብሄር ተዋጾ ስም የሞግዚት ስልጣን ይሰጣቸዋል::

በሃገራችን በደልና ምሬት እጅግ በዝቷል፤ ስር የሰደደ ሰው ሰራሽ ድህነትና ጉስቁልና ከመቸውም በባሰ በመላው አገሪቱ ተንሰራፍቷል፤ እስርና ሰቆቃ የኢትዮጵያውያን የለት ተለት ከስተቶች ሆነዋል። ህገመንግስቱን በሀይል ለመናድ ሲያሴሩ ደርሼባቸዋለው በማለት የውሸት ክስ ይመሰረትባቸውና በውሸት የተቀነባበረ የሰው የቢዲዮና የፅሁፍ ማስረጃና ምስክር ቀረቦ እስር ቤት መወርወር እንደ መደበኛ የህይወት እንቅስቃሴ ከተቆጠረ ሰነበተ:: ሰላማዊ ዜጎችን ፤ለነፃነታቸው የሚታገሉትን ግለሰቦችና ቡድኖች፤ ስለ ነፃነት ፍትህና እኩልነት የማፅፉትንና የሚያዜሙትን በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ መዳረጋቸው ዘወትር በወያኔ የመገናኛ ብዙሀን በየቀኑ የምንሰማውና የምናየው ድራማ ሆኖል:: በከተማችን የሚከሰቱ ከባድ ወንጀሎችና ሽብሮች በወያኔ ደህንነቶች ሆን ብለው የተቀነባበሩ መሆናቸውን ዓለም የመሰከረውና ጸሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ላይ እንደዜጋ መንቀሳቀስና በመረጠት ቦታ ህይወት መስርቶ መኖር የማይቻልበት ስርአት ላይ እንገኛለን:: የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ስልጣን በጠመንጃ ሀይል ከያዘ ጊዜ ጀምሮ የስልጣንና የዘረፋ እድሜውን ለማራዘም በኦርቶዶክስ ሃይማኖትና ቤተርስቲያን ላይና በእስልምና እምነትና አማኞች ላይ በንቀትና በድፍረት የማያቋርጥ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ የሰሞኑ አሳፋሪ ድርጊቶች ናቸው::እነዚህን ሁሉ በወያኔ እምባገነንና ዘራፊ ቡድኖች የሚፈፅሙትን ኢሰብአዊና ኢፍትህአዊ ድርጊቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በኢትዮጵያ ህዝብ የተነሱትን የፍትህ የኩልነትና የነፃነት ትግሎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መተባበርና መሳተፍ ይጠበቅብናል::

አስራ አንደኛው ሰአት ለወያኔ ወይስ ለህዝቡ

Friday, March 16th, 2012

ዋለልኝ መኮንን

ኢትዮጵያ ላለፉት ረጅም አመታት በተለያዩ ጨካኝና አምባገንን መንግስትና የመንግስት ስርአቶች አስተናግዳለች::እነዚህም ስርአቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋትነት ተከፍሉል አሁንም እየተክፈለ ይገኛል:: አሁን ኢትዮጵያን አስተዳድራለው የሚለው የወያኔ ቡድን ከሁሉም የባሰውንና በታሪኩ አይቶ የማያውቀውን ከፍተኛ ግፍ:በደል:ጭቆናና ውርደት በሕዝቡ ላይ እያደረሠበት ይገኛል:: አምባገነኑና ፋሽስታዊው የወያኔ ቡድን ላለፉት 21 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጉልበት: እጅግ በጣም ሁዋላ ቀርና የህዝብን ጥቅም ይማያስጠብቅ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም; የአገር የማፈራረስና የኢትዮጵያዊንትን ታሪክና ባህልን የማጥፋትና ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብና የሀገር ሀብት መዝረፋን መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ እየፈጸም ይገኛል::ህዝቡን በጥመንጃ በማስፈራራትና ከታች የተዘረዘሩትን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመከልከል የባንዳንትና የሌብነት ተግባሩን በመፈፅም ላይ ይገኛል::

-ህዝቦችን በዘር: በብሄር: በቋንቋ: በሀይማኖት: በቀለም: ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት:: እርስ በእርስ እንዳይስማሙ: አብረው እንዳይኖሩ: አንድንት እንዳይፈጥሩ: በህብረት ማህበራዊና ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹን እንዳይፈቱ: የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብቱ በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ: ከእያንዳንዱ ብሄረሰብና ሀይማኖቶች ለሆዳቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ቆንጥሮ እምነትህ ቀቀንቀህ ባህልህ ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ::

-በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን፧የመናገር:የመፃፍ:የመሰብሰብ:በቡድን የመደራጀት:ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የምግለፅ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን: የፈለገውን እምነት መከተልና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ወይንም በመሸራረፍና ለጥቂት የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ብቻ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ::

-ታዋቂና ለወደፊት ለአምባገነኑና ለፋሽስቱ ለወያኔ ቡድን የስልጣን ቆይታ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውንና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ታማኝነት ያላቸውንና አላቸው ብሎ የሚጠረጥራቸውን የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን: አባላቶችን: ደጋፊዎችን: ምሁሮችን: መምህራኖችን: ጋዜጠኞችን: ዘፋኞችን: ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት: በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም: አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ: የት እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ: መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና የባንዳነት ተልኮውን መወጣት::

-ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰባዊ መብት:በመልካም አስተዳደር:በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ:: ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ:: ህዝቡም መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም ማድረግ::

-የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ በመስጥትን በመሸጥ አሳልፎ መስጠት; እኛ ብቅርጽና በመጠን የምናውቃትን ታሪካዊ ኢትዮጵያን ማጥፋት; ህዝቡም በሀገሩ ላይ ስለ መሬት እንዳይጥይቅ በጠመንጃ ማስፈራራት; ምንም እንደማያመጣ በጥጋብና በስድብ ንቀቱን መግለፅ::

-የኢትዮጵያን የ3000 አመት ታሪክ መካድ: አሳፋሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ: ታሪክን መበረዝ: የፈጠራ ታሪክ መፍጠር:: የኢትዮጵያን ህዝብ ባህል: ስብእና: ዕምነት: ኩራት: ማንነት: ብሄራዊ እሴቱን: አንድነቱንና ብሄራዊ መገለጫዎቹን ማጥፋት:: የኢትዮጵያን ታራክ የወያኔን ታሪክ ብቻ አድርጎ በካድሬዎቹና ለሆዳቸው ባደሩ ተራ ግለሰቦች ገንዘብ ከፍሎ ማፃፍ:: ልክ እንደ ውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ: ማጥላላት: ማናናቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ የቅጥረኝነቱን ተግባር እየፈፅመ ይገኛል::

-በብሄርና በጎጥ የተደራጁ ጥቂት የወያኔ ማፊያዎች የሌብነት ተግባራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፈፅም ወንበዴ ዘራፊ ድርጅት ማቋቋምና ህዝቡንና ሀገሪቱን መዝረፍ: ማደህየት: ማስራብ: የበዪ ተመልካች ማድረግ:: በዘመናዊ ቤት መኖር: የብዙ ቤቶች ባለቤት መሆን: ዘመናዊ መኪናዎችን መቀያየር: በመቶ ሚሊዮኖች የሚጨርስ ህንፃና ፋብሪካዎች መገንባት ለወያኔ ብቻ የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ማግበስበስ:: በጣም የከፋው ደግሞ ከሀገርና ከህዝብ የሚዘረፈው ከፍተኛ ሀብቶች ከኢትዮጵያ ማሸሽና በተለያዩ የውጭ ሀገር ባንኮች መደበቅ ይህም ሳያንስ በባእዳን ሀገር በቢሊየን የሚቆጥሩ ዶላሮችን አውጥቶ ህንፃ መገንባትን ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል::

-የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ: በማህበራዊ: በፖለቲካ: በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ ለማድረግ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት: ፈቃድ መከልከል: ባለቤቶቹን ማስፈራራት: ማሰር: ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጥት ሞገዳቸውን ማፈን::

ወያኔ በጠመንጃ ስልጣን ላይ ከተቀመጠ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ መብቶቹን ለማስከበር ያላሰለሰ ትግል እያካሄደ ይገኛል:: ሆኖም እስከ አሁን የተደረገው የትግል መስዋትነት የተፈለገውን ውጥት ማስገኝት አላስቻለም:: ለተፈለገው ውጠት አለመገኝት እንደ ምክንያት ሆነው የተቀመጥት; ብዙና የተለያዩ የትግል ስልቶችን አለመጠቀም: የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች በጋራ ተቀራርቦ አለመስራት: የፓርቲዎቹን አላማና የተለያዩ መረጃዎችን ሰብስቦ ወደ ህዝቡ ለማድረስ የሚያስችል ጠንካራ ተቋም አለመኖር: የአባላቶችና የደጋፊዎች ቁጥር አነስተኛ መሆንና ከአባላቶችና ከደጋፊዎች የሚሠበሠበው ገንዘብ በጣም አነስተኛ መሆን ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው::

የወያኔን ዘረኛና ፋሽስታዊ የአገዛዝ ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከስለጣን ለማስወገድ በመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄዎች ከሁሉም አቅጣጫ እየጎረፈ ይገኛል:: ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሠቦችም ሆንን የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የወያኔን የማፊያ ስርአት ከጫንቃችን ላይ አስወግደን እኩልነት: ፍትህ: ዲሞክራሲና: እውነተኛ ፌደራላዊ ስርአት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሌላው ግዜ በበለጥ መረባረብ አለብን:: የወያኔን ሀገር የማፍረስ የመዝረፍ ታሪክን የማበላሸትና የማጥፋት ተልኮውን አሁን ተባብረን ማስቆም ካልቻልን መስዋቱ ውድመቱ የህዝብና የሃገር ውርደት የከፋ ይሆናል::