Author Archive

የህወኃት ጉዞ የርስ በርስ የመበላላት ታሪክ ነው – ከትእዝብት አድማሱ

Wednesday, February 20th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” – በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

Monday, February 18th, 2013

ለማንበብ እዚህን ይጫኑ

የካቲት 1966 39ኛ ዓመት መታሰቢያና እና ያ ትውልድ ተቋም

Wednesday, February 13th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ለቅሶ ሳቅ – ሳቅ ለቅሶ አሥራደው (ከፈረንሳይ)

Wednesday, February 13th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

መምህሩ እንደ እረኛ ተማሪው እንደ መንጋ! ታደለ መኩሪያ

Wednesday, January 9th, 2013

እንዲህ ያለ ዘመን ፣ዘመነ ጋንድያ፤
ሰው እንዴት ይሆናል፣ ከርሞ እንዳ ጥጃ፤

በሃገራችን ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ይገለፃል። ይህንንም ለማስቆም በትምህርቱ ዓመት መጀመሪያ ላይ የተመዘገቡትን ተማሪዎች ቁጥር መምህራን ተረክበው በዓመቱ መጨረሻ ማስረከብ እንዳለባቸው ለመፍትሔነት ቀርቧል። መምህራንም የደረጃ እድገት፣ የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት የተረከቧቸውን ተማሪዎች ቁጥር ሳይቀነሱ ማስረከብ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህን ዓይነት ቁጥጥር በሰሜን ኮሪያ ‘labor Camp’ እሥር ቤቶች መሰል ጣቢያዎች በተቋቋሙ ትምሀርት ቤቶች የሚሠራበት መመሪያ ነው። ይህ ዓይነት መመሪያ በማስተማርና በመማር ሥራው ላይ አደጋ አለው። መምህራን ከቀለም አባትነታቸው ይልቅ ያለተማሪው ፍላጎት ተቆጣጣሪዎች ያደርጋቸዋል።በሰባዐዊ መብት ገፋፊት ያስፈርጃቸዋል።ተማሪዎችም ቢሆኑ መብታቸውን የገፈፈውን መምህር ለብቀላ ለወያኔ እንዲሰልሉት መንገድ ይከፍታል። ይህ ድርጊት በሰሜን ኮሪያ እየተሠራበት ነው። ለግንዛቤ ያህል በአንድ ወቅት የሰባዐዊ መብት ተከራካሪ ተማኝ በየነ መለስ ዜናዊ ከመሞቱ ሰምንት ወር ቀደም ብሎ እንዲህ ብሎ ነበር፤ ‘ጠቅላይ ሚስትር መለስ ዜናዊ ቢሞት፣ እንደሰሜን ኮሪያን ሕዝብ ለኬሚን ሱንግ አስገድደው እንዳስለቀሱት፤ መለስ ቢሞት ወያኔ መላውን የኢትየጵያን ሕዝብ ያስለቅሱታል’ ያለው ትንቢተ ደረሰ። ይህ አሁን ወያኔ ትምህርትን አስመልክቶ እያደራ ያለው ድር የዘርና የጎሣው ክፍፍል ሌላው አካል ነው።
አንዳንድ በውጭ የሚኖሩ በጎ አሳቢ ‘wishful thinkers’ መሰል ምሁራን እኛ ስለፖለቲካው አያገባንም፣ ግን ስለትምህርት እድገት ምርምር አድርገን የትምህርቱ ሥራ ግቡን እንዲመታ አስተዋጾ እናደርጋለን ሲሉ ይደመጣሉ። ‘ለሥጋው ጾመኛ ነኝ፣ ከመረቁ ሰጡኝ’ አባባል ይመስላል። ‘እንኳን አቺን የዝንብ ጠንጋራ አናውቃለን’ ይላል የሃገሬ ስው! የወያኔ ፖለቲካ ያልገባበትና ሊቆጣጠረው የማይፈልገው መሥሪያ ቤት ወይም የሥራ መስክ የቱ ነው? ሕዝብን እርስ በርሱ ማናከሱ አንሶት በትምህርቱ መስክ አዲስ ደባ አቅዷል። መምሀሩም ተማሪውም በአንድነት እንቢኝ ማለት ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ ቀደም የትምህርቱን ሥራ አስመልክቶ በድህረ ገጾች ሁለት መጣጣፎች አድርጌ ነበር።’ በድንቁርና ላይ ወሮሸባ እንበል’ እና ‘መምህሩም ያስተምር ተማሪውም ይማር’ የሚሉ ነበሩ። ጠቅላላ ይዘታቸው የትምሀርቱን ሥራ አስመልክቶ በባለቤትነት ሕበረተሰቡ መምከር እንዳለበት ጦቁሜለሁ። የትምህርቱ ሥራና የፖለቲካው ሥራ ለየቅል መሆናቸውን ለማሳየት ሞክሬለሁ፤ ዜጎች የሚጎዳቸውን ከሚጠቅማቸው ለይተው የሕይወታቸው መመሪያ ለመንደፍ ትምህርት አማራጭ የሌለው መሣሪያ እንደሆነም ገልጫለሁ። ልጆቻቸው ተኮትኩተው የሚያድጉበትን ሥረዓተ ትምህርት ለመቅረጽ ሐሣብን በነፃነት መግለጽ ቅድሚያ የሌለው ቅድሚያ መሆኑን ጠቁሜአለሁ። የዓለም ሕብረተሰብም ይህንን አውቆ የማወቅና የማሳወቅ መብት ፍጹም ያልተገደበ ነው። በእኛ ሃገር የሕብረተሰቡ አካል የሆኑት መምህራንና ተማሪዎች ሐሣባቸውን ሲገልጹ ሲታሰሩና ሲገደሉ ነው ያየነው።

የወያኔ መንግሥት የትምህርት ሥራው ማሽቆልቆሉንና የተማሪው ለትምሀርት ያለው ፍላጎት እየቀነሰ መምጣቱን አሌ የሚለው አይደለም። ምክንያቱንም አያውቀውም ማለት አይቻልም። ለተማሪው የመማር ፍላጎት ማጣት የትምህርት ሥራው ውጤት ማሽቆልቆል መምህራንና ተማሪዎችን ተጠያቂ ማድረግ ቂልነት ነው። ሐቁን ግን ሰው ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ነው። ለተማሪው ትምሀርት ማቋረጥ ሆነ ለትምህርቱ ማሽቆልቆል ተጠያቂው በመሣሪያና በስለላ ኃይሉ ጉልበቱን አፈርጥም በማያውቀው የትምህርቱ ሥራ ላይ የሚቦራጨቀው ወያኔ ብቻ ነው።

ስለመገናኛ ብዙሃን ለትምሀርቱ ሥራ የቱን ያህል አስተዋጾ እንደላቸው ባለፈው ጹሑፌ ጦቅሜ ነበር። ከሃገር ቤት በኢ ሜ ል የደረሱኝ መልክቶች ‘አንተ የደላህ ነህ ሙቅ ታኝካለህ’ መሰል ነበሩ። ሌላው ቀርቶ እንደቀድሞ ዓመታት ተማሪዎቹን የሚያቃቁ ተግባሮች ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ አይተዩም፤ ሌላው ቀርቶ በትምህርት ቤቶች መጫወቻ ኳስ የለም ፣ ተማሪውም ሆነ አስተማሪው ኳስ የሚጫወቱባቸውን ትጥቅ ማሟላት አይችሉም፤ ተማሪ በጠኔ የሚወድቅበተ ሃገር እኮ ነው ያለን እያሉ ኢ ሜ ል አድርገወልኛል።መጫወቻ ሜዳዎች ቁሻሻ ለብሰዋል፣ የድራማ፣ የክርክር፡ የሰፓርት ውድድር የሳይንስ ፣ የዛፍ ተከላ፣ የወላጅ ቀን፣ሁሉም የሉም። ዩኒቭርሲቲ ተከፈተ እንጂ አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ተገነባ ሲባል የሰማ አለ? የቀድሞቹስ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች መቀመጫ አላቸው። አንደንድ ትምህርት ቤቶች ተንደው ሕፃናት ዳስ በመሰሉ ቤቶች ውስጥ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ አሉ፤ በዙዎቹ አቋርጠው ይሄዳሉ። በኦሮሚያ ኦቢዲዎ አስተዳደር ስንት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገነቡ? የነበሩት ፈርሰው እንደሆን እንጂ አንድም አልተሠራም።

ሕብረተሰቦች በቋንቋቸው እንዲማሩ ተደርገዋል ተብሏል። በቂ መጽሐፍቶች በተባለው ቋንቋ ጥራታቸውን ጠብቀው ቀርበዋል? የሕብረተሰቡን ፍላጎትስ የሚያጸባርቁ ናቸው? ይህን ሆድ ይፍጀው። ቋንቋችን ተከበረ ባሕላችን ታወቀ የሚሉት አፍቃሪ ወያኔዎች፤ ሐቁ ልጆቻቸውን ትልልቅ ከተማዎች ልከው የሚያስተምሩ ናቸው። ያውም በሚያወግዙት ቋንቋ፤ የሚወክሉትን ሕዝብ ግን ባልተሟላ የትምህርት መሣሪያና ባልተጠና ሥረዓት ትምህርት ያደነቁሩታል። ተማሪው ትምህርቱን ቢያቋርጥ እንዴት ይፈረድበታል? መምህሩስ እንዴት ማስቆም ይቻለዋል?
ዛሬ ተማሪን እንደመንጋ መምህሩንም እንደ እረኛ በሆነበት አካባቢ የመማርና የማስተማር ጣምና ለዛ የሌለው መራራ ነው። የዕውቀት ገበታ ሊሆን አይችልም።
ሃገርንና ራሱን የፈጠረ ሕዝብ የሚበጀውን ከራሱ በላይ የሚያውቅለት የለም እና ማንነቱ ከመጥፋቱ በፊት ከዕንቅልፉ መነሣት አለበት። መምህሩንና ተማሪውን ተጠያቂ ማድረግ ከሐላፊነት ከመሸሽ ሌላ የሚፈይደው ነገር የለም።
ዓምላክ ኢትዮጵያን ይታደጋት!

በደብረማርቆስ ከተማ አንድ ኢትዮጵያዊ ላይ ራሱን አቃጥሎ ሞተ

Friday, March 2nd, 2012

“ታጠቅ ህሉፍ የተባለ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሰራተኛ በደረሰበት አስተዳደራዊ በደል በሰውነቱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ በደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ ራሱን አቃጥሎ መሞቱን” የዓይን እማኞች ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ የአካባቢ ነዋሪዎች እንደሚሉት “በደብረማርቆስ ከተማ ልዩ ቦታው አብማ 04 ቀበሌ በአቶ ጫኔ ቤት ውስጥ ተከራይቶ ይኖር የነበረው ታጠቅ ህሉፍ ራሱን አቃጥሎ ገሏል” ብለዋል፡፡

በአካባቢው የነበሩ የዓይን ምስክሮች እንደሚሉት “ታጠቅ ህሉፍ መኖሪያ አካባቢው ሄዶ በልብሱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ እሳት ከለኮሰ በኋላ ወደ መነሐሪያ አቅጣጫ እየተጓዘ ድምጹን ከፍ አድርጐ ይናገር ነበር” ሲሉ ክስተቱን ያብራራሉ፡፡ ሂደቱን የተከታተሉት እንደሚሉት “ምን ሆነህ ነው? ለምን ራስህን አቃጠልክ?” ብለው እሳቱን ሊያጠፉለት ሲሞክሩ “ልታድኑኝ አትሞክሩ፡፡ መሞት አለብኝ፡፡ የትግራይ ልጆች የታገሉት እንዲህ ዓይነት ሥርዓት እንዲመሠረት አልነበረም፡ ፡ በህይወት ኖሬ እንዲህ ያለ ሥርዓት ማየት አልፈልግም፡፡ በዚች አገር ዲሞክራሲና ነፃነት የለም፡፡ ሠርቶ መኖርም አልተቻለም፡፡ በደረሰብኝ ጥቃት ራሴን መግደል ስለአለብኝ ነው፡፡ ወደፊት ሁላችሁም ትሞታላችሁ፡፡” እያለ ይናገር ነበር ብለዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት “በደረሰብኝ ጥቃት ራሴን መስዋዕት አድርጌአለሁ፡፡ እያለ ድምጹን ከፍ አድርጐ እየተናገረ ሲሄድ ልብሱ ተቃጥሎ አልቆ ሥጋው እየተቆራረጠ ወደ እግሩ ሲወድቅ በአሰቃቂ ሁኔታ ይታይ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት አንድ ነጭ ቲዮታ መኪና መጥታ ከጫነቺው በኋላ በመከላከያ ወታደሮች ታጅቦ ወደ ደብረማርቆስ ከተማ ሆስፒታል ገብቷል፡፡

ሆስፒታል ከገባ በኋላ ከሚያክመው ሐኪም በስተቀር ማንም ሰው እንዳያገኘው ተደርጐ ለሁለት ቀን ሆስፒታሉ በመከላከያ ወታደሮች
ሲጠበቅ ቆይቶ በሦስተኛው ቀን ህይወቱ በማለፉ ወላጅ አባቱ ከትግራይ ተጠርተው አስከሬኑን ወስደዋል” ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

ስማቸው እንደይጠቀስ የፈለጉ የሥራ ባልደረቦቹ ነን የሚሉ ግለሰቦች እንደሚሉት “የደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ከሞያው ዲስፕሊን ውጪ
አድርጓል፡፡ ይህውም አንደኛ ታጠቅ ህሉፍ ተቃጥሎ ሆስፒታል ሲገባ የህክምና ካርድ ሳይወጣለት እንዲታከም አድርገዋል፡፡ ጓደኞቹና ማንኛውም ሰው እንዳያየው ከልክለዋል፡፡ ህክምናው ከአቅማቸው በላይ ከሆነ እንኳን ሪፈር ማለት ነበረባቸው፡ ፡ የህክምና ውጤት ሲየጠቁ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም፡፡ በመሆኑም የገቡትን የክምና ቃል ኪዳን ያልጠበቁ፣ የሞያውን ሥነ ምግባር ያላከበሩ ስለሆነ በህግ መጠየቅ አለባቸው” ይላሉ፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመው መቼ ነው? በማለት ለጠየቅናቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ድርጊቱ የተፈጠመው ታህሳስ 4 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ በ11 ሰዓት ሲሆን ወዲያውኑ ሆስፒታል ገብቶ ታህሣሥ 6 ቀን 2004 ዓ.ም ህይወቱ ሊያልፍ ችሎአል፡፡ ከዚያም አባቱ ተጠርተው አስከሬኑን ትግራይ ወስደው ቀብረውታል” በማለት ይመልሳሉ፡፡ እስከዛሬ ለምን ተደበቀ? ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ ሲመልሱ “መረጃውን ማንም
እንዳያገኘው በአካባቢው ከባድ ማስጠንቀቂያ በመስጠቱ ሰው ሁሉ ዝም ማለትን መረጠ፡ ፡ በአካባቢው ዜጐች ሁሉ በሥጋት የሚኖሩበት
አካባቢ ነው፡፡ ሳል እንኳን ብትስል ትርጉም ሠጥተው ለከፍተኛ ችግር የሚያጋልጡ ኃላፊዎች ያለበት አካባቢ ነው፡፡” ሲሉ መልሰዋል፡፡
የደብረማርቆስ ሆስፒታል ኃላፊዎችን ስለ ጉዳዩ መረጃ እንዲሰጡን ብንጠይቅም “እኔን አይመለከትም፡፡ የደረሰኝ መረጃ የለም፡፡ እኔ ስለማላውቅ ሌላውን አነጋግሩ” እያሉ ከጉዳዩ በመሸሻቸው ዜናውን ከዚህ በተሸለ ለመዘገብ አልቻልንም፡፡

“ታጠቅ ህሉፍ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት መካኒክ ሹፌር ሲሆን ጠይም ወፈር ያለ የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪ የነበረ መሆኑ ታውቋል፡
፡ ታጠቅ ህሉፍ ከ27-32 ዓመት ዕድሜ የሚገመት የወጣት ጐልማሳ እንደሆነ፤ በተፈጥሮው ትክክለኛ ያልሆነ ነገር ሲመለከት ሁል ጊዜም የማይደግፍ የዘረኝነትና የቡድተኝነት ስሜት የማይንፀባረቅበት እንደነበረ” በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡

“ከዚህ አስተሳሰቡ በአብዛኛው ከኃላፊዎቹ ጋር ይጋጭ እንደነበርና፡፡ የአለቆቹን ውሳኔ ይቃወም ስለነበረ፡፡ በተለያየ ጊዜ አስተዳደራዊ ጥቃት
ይደረግበት ነበር” ሲሉ በቅሬታ ይገልጹታል፡፡

ወገኔን ታዘብኩት… ትዝብቴ ለሚሰደዱ! (ሶሎሞን አ.)

Thursday, February 23rd, 2012
ኢትዮጵያዊ ተዋዶ፣ ተዋልዶና ተዛምዶ ኖሯል ለዘላለምም ይኖራል! እንዳትሰደድ የሚለውን የወዳጅ ዘመድ ምክር ችላ ብለህ ብትሰደድ ከሁሉ በላይ ሕውሓትን አስደስተህ አንተም ይብዛም ይነስም ችግር ውስጥ ለመባዘን ተዘጋጅ። ከዲያስፖራው ወገን ጋዜጠኛ ወይ ባለጠጋ ካልሆንክ ስለተሰደድክ እምቢልታ አይነፋልህም፣ ነጋሪት አይጎሰምልህም። በስደትህ ምክንያት ስለአገርህ የዲሞክራሲና የነፃነት ዝቅጠት አይነገርም፣ አይወራም ወይም አይፃፍም። እንደዘበት በአንድ ውድቅት ሻንጣህን አንጠልጥለህ ትወጣለህ። ባንተ መሰደድ ምክንያት ስለተደሰተው መንግስትህ፣ ስለተዳከመው ትግል፣ ስለፈረሰው ትዳርህ፣ ስለተበተነው ንግድህ፣ ስለተቋረጠው እቁብህ፣ ስላልተከፈለው እድርህ፣ ስለተጓጎለው ማህበርህ በቅርብ ከምታውቃቸው ሰዎች ውጪ ማንም አያውቅልህም ያንተን መከራ ማንም አያግዝህም። አንድ ኢትዮጵያዊ ተሰደደ አልተሰደደ ምን ለውጥ ሊያመጣ አይነት የዲያስፖራ ፖለቲካ አፉን ከፍቶ ይጠብቅኃል። ወዴትኛውም የምድር አቅጣጫ ብትሰደድ፤ ባገር ልጅ የተቋቋሙ እጅግ ብዙ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶችን ታገኛለህ፣ ካገር ከወገን ተለይቶ ብዙ በመኖር ምክንያት ብዙ ነገር የዘነጉ አንተም የዘነጋኃቸውን ጨምሮ። ካገር ከወገን ተለይቶ ብዙ በመኖር ኢትዮጵያዊ ወዛቸውን ያሟጠጡ በርካታ ወገኖችህን ታገኛለህ። በወያኔ እጅ መርዘም ምክንያት በነፃነት ምድር ላይ ነፃ ያልወጡ በርካታ ወገኖችህን ትቀላቀላለህ። በፖለቲካ ምክንያት ተሰደድኩ ግን ደግሞ ፖለቲካ አያገባኝም የሚሉ እጅግ ብዙ ሰርቶ አደር ቢጤዎችህን ትተዋወቃለህ። በቋንቋህ የሚናገር፣ በባሕልህ የሚያስብ፣ እንጀራ በበርበሬ አዘውትሮ የሚመገብ ትንሽ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግመህ መኖር ትጀምራለህ። እንዲህም ሆኖ ግን በጥቂት አገር ወዳድ ወገኖችህ ሞቅ ያለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በዲያስፖራው ውስጥ መኖሩን ትመለከታለህ። ይህ የዲያስፖራው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያለ አገርቤት አይደምቅም እስከምትል ድረስ አብሮ ሲሞቅና ሲከስም ለማየት ተዘጋጅ። ምንም እንኳን መምረጥም መመረጥም የሚችላው ሕዝብ አገር ቤት ቢኖርም በኢትዮጵያ ውስጥ አንጻራዊ ለውጥ ለማምጣት ለሚታገሉ ማናቸውም የፖለቲካ ድርጅቶች የዲያስፖራው ሚና ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። ይህንንም ለመረዳት የሚከተሉትን ጥቂት እውነታዎች በአንድ አቅጣጫ የነበረውን እንቅስቃሴ ብቻ እየጠቀስኩ ላስታውስህ። በምርጫ 97 ወቅት ለምርጫው የተለየ ገፅታን ያላበሱት ሁለት ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ኃይሎች ሕብረት እና ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲዎች ነበሩ። የ97 ምርጫ ሊደርስ ወራቶች ሲቀሩት ከተመሰረተው ከቅንጅት በፊት ከፍተኛ ድጋፍ የነበረው ሕብረቱ የተመሰረተው በዲያስፖራው ሆድ ውስጥ ነበር። ነገር ግን ከምርጫው ቡኃላ በተነሳው ወደ ፓርላማ የመግባትና አለመግባት ውዝግብ ምክንያት ሕብረቱ በተነፈገው የዲያስፖራ ድጋፍ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዲገባ ተገዶ ነበር። የቅንጅቱ የአገር ውስጥ እንቅስቃሴ በጉልህ ፍሬ ማፍራት የጀመረው ምርጫ 97 ሁለት ወራት የሚጠጋ ጊዜ ሲቀሩት ዶ/ር ብርሃኑ ወደ አሜሪካ አቅንተው ስለቅንጅቱ አጠቃላይ ገለፃ አድርገው ባሰባሰቡት ድጋፍ ነበር። በዚህም በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ባገር ውስጥ ያለውን ሚና ትገነዘባለህ። ቅንጅት ሲሰነጣጠቅ የክፍፍሉ መንስዔ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ቅንጅት አለምዓቀፍ መሆኑን ካልረሳህ ዲያስፖራው ለአገርቤት ፖለቲካ ያለውን ወሳኝነት ትገነዘባለህ። ምንም እንኳን የመያድ ሕግ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተረቆ በስራ ላይ ቢውልም እነዚህን ከመንግስት ቁጥጥር ነፃ የሆኑ ድርጅቶችን በመምራትና አብሮ በመስራት አገሪቱ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከታተል የዲያስፖራው ድርሻ ከፍተኛ ነበር። ከሚያዚያ 30 1997 ወዲህ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገህ አገራዊ ስሜትህን ድምፅህን አሰምተህ እንደማታውቅ ግልፅ ነው። ስትሰደድ ከሚገጥሙህ ጥቂት ጥሩ ነገሮች ውስጥ አንዱ የሰልፍ ናፍቆትህን እዚህ ለመወጣት መቻልህ ነው። አገርቤት የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ሲታሰሩ፣ ገዜጠኞች ሲታሰሩ፣ መሬታችን ሲቸበቸብ፣ የተለያዩ የህብረተሰቡ አካላት በመንግስት በደል ሲደርስባቸው የታፈነውን የአገር ውስጥ ጩኅት የሚያሰሙት በውጭው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም በውጭ መንግስታት ፊት የዲሞክራሲን ጭምብል አጥልቆ ለአመታት ሲሞካሽ የነበረውን የመለስ መንግስት ማንነቱ እንዲገለፅ የተሳካም ያልተሳካም ተቃውሞ በማሰማት ዲያስፖራው አገሪቱ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ ጥሯል። ስለዚህ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የዲያስፖራው ሚና የማይናቅ ቢሆንም አሁን የሚጠብቅህ የዲያስፖራው የማይጨበጥ ችግር ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እያሰለቸ ይገኛል። ይህንንም ስለተሰደድክ እንደልብ ከምታገኛቸው የመገናኛ አውታሮች ትገነዘባለህ። ባገርቤት ኢቲቪና ጥቂት የሬድዮ ጣቢያዎች በሕውሓት ተይዘው ያሻቸውን እንደፈለጉ ይናገራሉ ስለሆነም ህፃናትና ወጣቶች ውሸትን፣ ዘለፋንና ስድብን እየተማሩ እውነትን ሳይሰሙ እያደጉ ይገኛሉ። ወደዚህ ከመጣህ ነገሩ ለየት ይልና ለሶስት የተከፈለ ቡድን ያጋጥምኃል። የምታውቀውን አይነት ዘለፋና ስድብ ካማረህ የመጀመሪያውን ቡድን ኢቲቪንና ኢቲቪን የመሰሉ ጥቂት ድረ-ገጾችን ፈልገህ መክፈት ትችላለህ፣ ከዚህ በጣም በትንሹ ለየት ያለ ስድብ ከፈለክ ሁለተኛውን ቡድን ማለትም የተወሰኑ የፖለቲካ ሃይሎች የሚያሥተደድሯቸውን ድረ-ገጾችን ከፍተህ መዳሰስ ይጠበቅብኃል። ሶስተኞቹ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን የሚያከብሩ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ያላቸው ሲሆኑ በተለያየ ቋንቋ የሚፅፉ ናቸው። የመጀመሪያዎቹ ስለምታውቃቸው ላይገርምህ ይችላል ሁለተኞቹ ግን ከተቃዋሚ ወገን ሆነውና ያደረ ስማቸውን ይዘው የሚንገታገቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ሲሆኑ የተፈጠሩበትን ነገር አለም ዘንግተው የተሳካለት የመሰላቸውን ቢጤያቸውን ሲሰድቡ፣ የገዛ ጓደኞቻቸውንና ሻል ያሉ ፖለቲከኞችሕን ሲዘልፉ፣ ከግለሰብና ከነጋዴ ጋር ሲነታረኩ፣ ኢሳትንና በሥነምግባር የሚመሩ ድረ-ገጾችን ሲያብጠለጥሉ ታነባለህ። ኢሳት ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ገጸ-በረከት ነው። ዲሞክራሲና መልካም አስተደደር በሰፈነበት አገር ላይ እንደኢሳት አይነት የሚዲያ ተቋማት እንደአራተኛ የመንግስት ተቋም ተቆጥረው አገልግሎት ሲሰጡ ይታያል። እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ነፃ ተቋማት ባልተፈጠሩባት አገር ደግሞ ኢሳትን የመሰሉ ተቋማት እንደሁለተኛ መንግስት ያገለግላሉ። የመንግስት ተቋማት የሚባሉት ማለትም ሕግ አውጭ፣ ሕግ ተርጓሚና ሕግ አስፈፃሚ ሲሆኑ ሁሉም ከአራት ኪሎ በሚከፋፈልባት ኢትዮጵያ ላይ ኢሳት የሕዝብን ጩኸት ለማሰማት ብቸኛው አማራጭ ነው ድርጅቱም እያደረገ ያለው ይሕንኑ ነው። ሙያዊ ስነምግባራቸውን በጠበቁ በጥቂት ብርቱ ጋዜጠኞች አማካኝነት የሕዝብ ብሶት ወደሕዝብ እንዲደርስ ማድረግ፣ ለማንም ሳይወግኑ ግን አገርን የሚያጠፉትን ማጋለጥ፣ የተበላሸውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲስተካከል ለማገዝ የመንግስትን የተሳሳተ መንገድ መተቸት(መንግስት ብቻ አጥፊና አልሚ በመሖኑ ምክንያት)፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ መጠየቅ፣ ብሄራዊ እርቅ እንዲኖር መሻት፣ አንድነትን መስበክ ፣ ስለአገሪቱ ያለውን እውነታ መዘገብ ከኢሳት እስካሁን ያየነው ሂደት ነው። በበኩሌ በጣት የሚቆጠሩት ኢሳቶች የሚሰሩትን አይቼ ተገርሜአለሁ። የገዘፉ ውሸቶችን ለመዋሸት ብዙ አቅም እንደሚጠይቅ ለማወቅ ከፈለግህ ኢቲቪን ከኢሳት ማወዳደር ብቻ ይጠበቅብሃል። ከኢቲቪ በገዘፈ ሕንፃ፣ በገዘፈ በጀት፣ በበርካታ የሰው ሃይል በየቀኑ ውሸትን ትሰማለህ። ኢሳት ግን ኢምንት ሆነው እኛን እልፎችን ከቤታችን ተቀምጠን ያለምንም ልፋትና ብርበራ ስለአገራችን እውነተኛና በቂ መረጃ እንዲኖረን ያደረገ የሚዲያ ተቋም ነው። እየተዋረደ ያለውን የኢትዮጵያዊነት ስብእና ለመጠገን ድርጅቱ የሚያደርገውን ጥረት፣ እየጠፋች ያለችውን አገር ለመታደግ የሚያደርገውን ትግል፣ በየስርቻው በኃፍረት ማቅ ለብሰው ያጎነበሱትን ወገኖች ቀና እንዲሉ የሚያደርገው ትጋት፣ ኢትዮጵያ የወላድ መካን አለመሆኗን ልጆቿን ከያሉበት እያወጣ ለማስተዋወቅ የሚሄድበትን መንገድ ለተመለከተ ቅን ሰው ኢሳትን ለጥፋት የተቋቋመ ድርጅት ለማለት መድፈሩ ያስገርምኃል። ኢሳት ነፃና ገለልተኛ ነው፣ ይህ ማለት ደግሞ ኢሳት የሚደግፈው የፖለቲካ ድርጅት የለም ማለት ነው እንጂ የተበላሸን አገራዊ ችግር አይተችም ማለት አይመስለኝም፣ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በኢሳት አይቀርቡም ማለት አይመስለኝም። ኢትዮጵያዊነትን ማጉላት፣ አንድነትን መስበክ፣ ነፃነትን መሻትና ማኃላፊነትን ለመወጣት ጥረት ማድረግ ከኢሳት የምታያቸው እሴቶች ናቸው። በሚገርም ሁኔታ ይሕንን በጥቂት ኢትዮጵያዊነት በሚሰማቸው ወገኖችህ የተመሰረተ አንድ ምርጥ ስጦታ ከራዲዮ ሚሊ ኮሊንስ የሚያመሳስሉ ሰዎች ብቅ ብለውልኃል። እስቲ ስለዚህ ራዲዮ ጣቢያ ላስታውስህና ስለኢሳት ከነገርኩህ ጋር እያዛመድክ ተዝናና። ሚሊ ኮሊንስ የሩዋንዳ ሬድዮ ጣቢያ ነው፤ ሚሊ ኮሊንስ ሲተረጉሙት የሺህ ትራሮች ምድር ማለት ነው አሉ። በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ወቅት ሁቱዎች በቱትሲና በለዘብተኛ ሁቱዎች ላይ ላደረሱት ጭፍጨፋ ሚሊ ኮሊንስ የተባለው ሬድዮ ያሰራጨው መርዘኛ ቅስቀሳ ባጠቃላይ ካለቀው ሕዝብ 10%ቱን ወይም ወደ 45 ሺ ለሚጠጋው ሞት ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። አቶ መለስ በምርጫ 2002 ከመደረጉ ከሶስት ወራቶች በፊት የአሜሪካ ሬድዮ ጣቢያን በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ወቅት አሰቃቂው ጭፍጨፋ እንዲቀጣጠል ምክንያት ከሆነው ከሚሊ ኮሊንስ ሬድዮ ጋር አመሳስለውት ነበር። በወቅቱ የቪኦኤን የአዘጋገብ ስልት ኮንነው ሊሸብቡት እየተዘጋጁ መሆናቸውን መለስ አስታውቀው ነበር። ታዲያ ይሕን ንፅፅር ምን ትለዋለህ? “ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል” ነበር የሚሉት አሮጊቷ የልጅነት ጎረቤቴ? ሴት ስለሆኑ በወንድ መተረት ይወዱ ነበር። ወሬ መጠረቅ ይችሉበታል፤ ያውም በተረትና ምሳሌ እያዋዙ፣ በታሪክ እያስደገፉ። ያኔ አንድ ትልቅ ቤት ውስጥ ለብቻቸው ይኖሩ ነበር። ዘወትር የሚቀመጡባት አንድ የጠፍር ወንበር ነበረቻቸው። ሲቀመጡ ቤቱንም ውጭውንም ለመቆጣጠር እንዲመቻቸው አድርገው አይን የሆነ ቦታ ላይ ነው። ወሬ እንዲያመልጣቸው ስለማይፈልጉ አብዛኛውን ጊዜያቸውን በዚች በርጩማ ላይ ተቀምጠው ወደ ውጭ እያዩ ይውላሉ። አላፊ አግዳሚውን ሲታዘቡ። ድምፃቸው ስለሚያምርና ከሩቅ ስለሚሰማ የሚሰሩ ሰዎችን ሲያርሙ፣ የሚጫወቱ ልጆችን ሲቆጡ፣ በሚልከሰከሱ እንሣትን ሲዝናኑ፣ የሚያውቁትንም የማያውቁትንም ዛሃርምስኬ ሲሉ ይውሉ ነበር። አሮጊቷ ከሁለት አስርት አመታት በፊት ነበር ይህን አይነት ያአኗኗር ስልት ይከተሉ የነበረው ነገር ግን ይህ የኑሮ ሂደት ተቀይሯል ብለህ ካሰብክ መሳሳትህን እነግርሃለሁ። ልክ ካገርህ ስትወጣ የሚቀበልህ ዲያስፖራ ከጥቂቶቹ በስተቀር ያሮጊቷን በርጩማ በተሽከርካሪ ወንበር ቀይሮ፣ ከፊቱ ኮምፒውተሩን ገርግዶ፣ ማይኩን ከጆሮው ደንቅሮ የጥቂቶችን የስራ ውጤት ሲያመክን፣ ጥሩ የሰራን ሲቆጣ፣ በቀልድና በቧልት ሲዝናና፣ የወሬ ሱሱን ከፌስ ቡክ ወደ ፓልቶክ ወደ ስካይፒ ካንዱ ወዳንዱ እየዘለለ ሲዘላብድና ሲያናሽር ታያለህ ። በተደላደለ ሶፋ ላይ ተቀምጦ የርቀት መቆጣጠሪያውን ከጁ ላይ አጣብቆ ከቻናል ወደቻናል እየዘለለ አገር ወገኑን የረሳ፣ ስልክ ከጆሮው ሳያወርድ ለምግብና ለፅዳት እንኳ ጊዜ ያጠረው፣ አገር አገር የሚሉትን ጥቂቶችን ሲያነቅፍ ስታይ ኢትዮጵያዊው ወገንህ ካገር ወጥቶ ሳይቀየር መገልገያ እቃው ብቻ እንደተቀየረ ትታዘባለህ። አንዳንድ ፍረጃዎችና ክሶች ከምን ተነስተው እንደሚደመጡ ባይገባህም ስራ ማጣት ወይም ልምድ እንዲመስሉህ ትገደዳለህ። በመሰረቱ የኢትዮጵያን ታሪክ በቁንጽል መዘርዘርና ቁንፅል ታሪኳንም የፖለቲካው ግንድ ለማድረግ መድከም የራድዮኑን ግብር መድገም ነው። አሉባልታን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማጠንጠኛ አስመስሎ ማቅረብ ራዲዮ ሚለ ኮሊንስን መሆን ነው። ታሪክን በመርዝ እየለወሱ ማቅረብና ፖለቲካውን ወደ ዘር ፖለቲካ እንዲዞር መርዳት ምን ሊፈጥር እንደሚችል መገመት ከባድ አይደለም ስለሆነም እንዲህ የሚያደርጉትን ግለሰቦችና ድርጅቶች ከራዲዮ ሚሊ ኮሊንስ ጋር ማነፃፀር ያባት ነው። ነገር ግን ኢሳትና ተሰዳቢዎቹ ድረ-ገጾች እርስ በርሱ የተከባበረ ኢትዮጵያዊን ለመፍጠር እንጂ የዘር ፖለቲካን ሲያራግቡ አልታዩም። ከምን ተነስተው ለመሳደብ እንደደፈሩ ግርም ይልሃል። የሚገርምህ ደግሞ ካለማወቅ ነው እንዳትል አብዛኞቹ ተምረዋል። መማር ማወቅ ነው፣ እውቀት አይንን ይከፍታል፣ ለህሊና ብርሃን ይሆናል። እውቀት ለእውነት አሳልፎ ይሰጣል። እውነትን በተከፈተ አይን ማየት ደግሞ ለነፃነት እንጂ ለማላከክ አይተጋም። እውነቱን ማየት ካቃታቸው ውሸትን፣ ስድብንና ፍረጃን ግን ማስወገድ ነበረባቸው። አንዳንዴ በምድራዊ እውቀት ጨቅላነት ምክንያት ሰው እምነቱን ወይም አምላኩን እንደማጣቀሻ ሊጠቀም ይችላል። ሃይማኖትና ሳይንስ ጠላቶች አይደሉም። ምድር ሁለቱንም ተጠቅማባቸዋለች፣ ሁለቱንም ትፈልጋቸዋለች። ኢሳት የሕዝባችንን መከራ አይተው በተነሱ በጥቂቶች እርዳታ እየተደገፈ ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ እየተጋ ያለ የቴለቪዥን ተቋም ነው። ዞምቢዎቹ እንደ ራዲዮ ሚሊ ኮሊንስ! በስድብ ባላምንም ክፉ ሰው እንዳለ ግን እውነት ነው። ኢትዮጵያን የዞምቢ ምድር ያደረጓት ክፉ ሰዎች እንዳሉም ግልፅ ነው። ክፉ ሰው ለተሸከማት ጠባብ ሆድ እልፎችን ይበድላል፣ እፍኝ ለማትሞላ እድሜው ሚሊዮኖችን ያጎሳቁላል፣ ወንዝ ለማይሻገር እውቅናው ሕዝቦችን ይዘልፋል፣ የተሰጠውን ፀጋ ለጥፋት ያውለዋል፣ ለሰይጣን ያልታሰበ ክፋት ያስባል። በንደዚህ አይነት ሰዎች ምክንያት ለመነገር የሚከብዱ ታሪኮች ተፈፅመዋል፤ ንፁሓን ተጨፍጭፈዋል፣ ሕዝቦች ተሰደዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ሕፃናት ታርደዋል፣ መንደሮች ጋይተዋል፣ ተራሮች በሰው ልጅ ሬሳ ተሞልተዋል፣ ወንዞች በሰው ልጅ ደም ቀልተዋል። ይህንን የመከራ ምድር የሚፈጥሩትን ክፉ ሰዎች ያዩ አባቶቻችን አምላክን “በእለተ አርብ ግን በከንቱ ውለሃል”ይሉታል። ይሕን ያሉበት ምክንያት እለተ አርብ አምላክ ለሰው ልጅ ሲል ስለተሰቀለ አይደለም ወይም የስራ መጨረሻም ሆኖ አይደለም ወይም ከሌሎቹ ቀኖች አርብ የተለየ ሆኖም አይደለም። ሃያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረት የፈጠረ አምላክ በዕለተ አርብ በፍጥረታት ሁሉ የሰለጠነውን ሰውን ስለፈጠረ ነበር። በዚህ እለት እግዜሩ ሁሉን ውብ አድርጎ ፈጥሮ የፍጥረት መጨረሻ ላይ ለእረፍት እየተዘጋጀ ሰውን ፈጠረ። ይሕን በክፋትና በተንኮል የተሞላ ፍጡር ፈጠርክብን ሲሉ ነው በከንቱ ውለኃል ብለው አምላካችንን የደፈሩት። በደፈናው ሰውን ፈጠርክብን ይበሉ እንጂ ሁሉንም ሰው ማለታቸው አይመስለኝም። ክፉውን፣ ተንኮለኛውን፣ ዘረኛውን፣ ጎሰኛውንና ሰው በሰላም እንዳይኖር የሚያደርገውን ለማለት ነበር። ታዲያ ይህን አባባልና ኢትዮጵያችንን ካሰብክ አንዳንድ ነገሮችን ራስህን መጠየቅህ አይቀርም። እንዲህ እያልክ፤ ቋንቋን እያንሻፈፉ በመተርጎም ሕዝብን ከሕዝብ ሊያቀያይሙ የሚሞክሩት የተወለዱ እለት ይሆን አምላክ የተወቀሰው? የሃሜት ማስታወሻቸውን እንደደገኛ ድርሰት ደጉሰው የተንኮል እንክርዳዳቸውን በየዋሓን ላይ የሚዘሩት የተፈጠሩ እለት ይሆን አምላክ በከንቱ የዋለው? በብሔሮች ላይ የመጨቆንን፣ የመሸነፍን፣ የውርደትን የፈጠራ ታሪክ ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ የሚተርኩና ይህንኑ ውሸታቸውን በሥነጽሁፍ እያስዋቡ ማቅረብና ለቂም በቀል ማነሳሳትን የእለት ግብራቸው አድርገው የሚያሴሩት የተዘሩ እለት ይሆን ፈጣሪ የተሳሳተው? እያልክ መቀጠልህ አይቀርም። እንዲህም ብለህ የዚህን አይነት ሰዎች ወዴት እንዳሉ ለማወቅ ትጋት ወይም ምርምር አያስፈልግህም። ጣትህንም ወደነሱ ብትጠቁም ማንም ተሳሳትክ አይልህም። ለማንኛውም እንደማያዋጣ እየታወቀ ቅዱሱን ማርከስ ይዋል ይደር እንጂ ከፀፀት አያድንም። እንደዚህ አይነት ስሌቶችን ትተን የምንታገለውን ክፉ ባለጋራ በጋራ ብንገጥመው ለሁላችንም መልካም ይሆናል። ከሁሉ በላይ በድኅነት ለሚማቅቀው ወገናችን(የተሻለ ይኖራል የሚባለው አብዛኛው የአዲስ አባባ ሕዝብ ለብቻው እያወራ ይሄዳል አሉ፤ ገበሬው ደግሞ ራሱን እያጠፋልህ ይገኛል)፣ በየአገሩ ለሚደፈሩት እናትና እቶቻችን (ሸዋዬ ሞላ በሳት ተለብልባ የወገን ያለህ እያለች 3 ወራትን በቁስል እየተንገበገበች ኖራ የደረሰላት ባእድ ነበር)፣ በየበረኃውና በየባሕሩ ለሚያልቀው ኢትዮጵያዊ(በየመንገዱ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሆዳቸው እየተቀደደ ይበረበራል፣ ጉበት ኩላሊታቸው ይዘረፋል)፣ መጠጊያ አጥተው ለሚሸጡት ሕፃናት (የሚቀምሱት ያጡ የሰፈርሕ ሕጻናት በምግብ እየተታለሉ ይደፈራሉ ያውም በግብረሰዶማውያን)፣ የሚደርስላቸው አጥተው በየእስር ቤቱ ለሚንገላቱ ወገኖች(ወንድሟንና እናቷን ለማብላት በአረብ አገር የምትንከራተትን አንዲት ኢትዮጵያዊትን ቆንጆ በግፍ የገደለ ሳይጠየቅ ይባስ ብሎ አስከሬኗን እንኳን የሚቀበል መንግስት ሲጠፋ)፣ ከርስት ከጉልታቸው በጉልበት ለሚፈናቀሉትና ለውጭ ባለኃብት ለሚሰጠው መሬታችን (….) ስንል አንዋሽ። የዘር ማጥፋቱን፣ ከሱማሊያና ከኤርትራ ጋር የነበረውን ጦርነት እያልን ብንቀጥል የበደል ጥግ መድረስ ይቸግረናል። ይህን ግፍ አስቀምጠን መሰዳደብን ምን አመጣው? እስካሁን ይህ ተፈፅሞብናል ካሁን ቡኃላስ ምን እስኪመጣ ነው የማንተባበረው? በሬድዮ ሚሊ ኮሊንስ ስንከራከር ወገናችንስ የሚደርስበት ከዚያ ያነስ ይሆን? ካልሆነም ጡረታ መውጣትና ለተስፋዎቻችን መንገዱን መልቀቅ እንዲህ ብሎ ከመዝፈን ያድናል። ይብላኝ ለወገኔ፣ እኔስ ደርሷል ቀኔ፣ አገሬን ገድያት፣ ሳያምርብኝ ልሞት፣ እንዳፈርኩ በስደት፣ በምድሬ ሳልዘራ ሳላፈራ ራሴን፣ ባውድማው ሳልወቃ ሳልሰበስብ ሰብሌን፣ ቀና ሳልል ሞትኩኝ፣ እንደተዋረድኩኝ፣ ፕሮፌሰር ዶክተር ደራሲ መምህር አንቱታው ትምርቱ ከፀፀት ከቁጭት ከሞት ላያድነኝ። ለዚህ ተፅእኖ ፈጣሪ ዲያስፖራ ልቡና ይስጥልን እያልክ መፀለይ አትርሳ!የሚከተለውንም ሊንክ ተጫን! http://ethsat.com/Main/esat_recurring_monthly_donation.html ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ሶሎሞን አ. negasi08@gmail.com

የ«መለስ ዜናዊ ማጀራት መቺ» አቶ ናትናዔል ወደ ታሰሩበት ተወሰደ

Saturday, February 18th, 2012

(አቡጊዳ) – ከአምስት ቀናት በፊት በቃሊት እሥር ቤት ሃላፊዎች ቤት ትእዛዝ፣ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዱዋለም አራጌ ላይ፣ ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ የፈጸመዉ ኢብሳ አስፋዉ የተባለ ግለሰብ፣ ሶስት መቶ እስረኞች በሚገኙበት የቃሊት እሥር ቤት ዞን እንደተሸጋገረ ፣ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

ከነዚህ ሶስት መቶ ሰዎች መካከል፣ መሰረት በሌለዉ የሽብር ተግባር የተከሰሰዉ፣ ሌላዉ የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል፣ አቶ ናትናኤል መኮንን የሚገኝ ሲሆን፣ ደብዳቢዉ በአቶ ናትናኤል ላይ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ፍርሃት እንዳላቸው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት የደረሰን ዜና አክሎ ያትታል።

አቶ መለስ ዜናዊ በቅርቡ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር ፣ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለመታረቅና ለመስማማት ፍላግት እንዳለባዉ በገለጹበት አፋቸው፣ የአንድነት ፓርቲን ጨምሮ በመድረክ አመራር አባላት ላይ ጠረቤዛ እየደበደቡ ዛቻ መሰንዘራቸው ይታወሳል።

በአቶ አንዱዋለም ላይ የደረሰዉ፣ በአቶ ናትናዔልና ሌሎች ላይ ሊደርስ የሚችለው አሳዛኝ የድብደባና የቶርቸር ድርጊቶች፣ ምን ያህል በኢትዮጵያ፣ ለስብእና ደንታ የሌላቸው ፣ ጨካኝ ግለሰቦች እየገዟት እንደሆነ የሚያሳይ መሆኑን የገለጹት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ በአቶ አንዱዋለም ላይ ድብደባ የፈጸመዉንና ዛሬ ወደ አቶ ናትናኤል የተላከዉን ግለሰብ፣ « በአቶ መለስ የተላከ፣ የአቶ መለስ ማጀራት መቺ» ብለዉታል።

ግቡን የሳተ ቀስት

Thursday, January 26th, 2012

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በወለጋ ዩኒቨርስቲ በተፈጠረ ረብሻ 2 ተማሪዎች ሞቱ

Wednesday, January 11th, 2012

(አቡጊዳ) — ለቀምት ከተማ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርስቲ በተፈጠረ ግጭት ሁለት የሕግ ተማሪዎች ሞተው ከትላንት በስቲያ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መፈፀሙን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ አንድ የውስጥ አዋቂ እደሚሉት ከሆነ ደግሞ “ተማሪዎቹ የሞቱት በምግብ መመረዝ ነው” ይላሉ፡፡

የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት ሲራጅና ከማል የተባሉ ሁለቱ የሕግ ተማሪዎች መሞታቸውንና ከትላንት በስቲያ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው
የተፈፀመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ዩኒቨርስቲው በተደጋጋሚ ደውለን ይመለከታቸዋል የተባሉትን ኃላፊዎች ለማነጋገር ጥረት ብናደርግም ስልካቸው ስለማይነሳ የተጣራ መረጃ ማግኘት አልቻልንም፡፡ ሆኖም ግን አንድ ስሜ እንዲጠቀስ አልፈልግም ያሉ ግለሰብ እንዳሉት “በእርግጥ ልጆቹ ሞተዋል፡፡ የሞቱት ግን በግጭት ሳይሆን “በምግብ መመረዝ ነው” በማለት ግጭቱን አስተባብለዋል፡፡
ምንጭ

ከሳሞራ የኑስ ጋር የማይስማሙ ጄነራሎች ተባረሩ !

Wednesday, December 28th, 2011

አገር ዉስጥ የሚታተመዉን ካፒታል ኢትዮጵያ የተሰኘዉን የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ጠቅሰን፣ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መኮንኖች ስራቸዉን እንዲለቁ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚጠቁመዉ ከስራ እንዲሰናበቱ ከተደረጉት መኮንኖች መካከል ጄነራል ሳሞራ የኑስ እና ከርሳቸው ጋር ቅርበት ያላቸዉ ሞኮንኖች እንዳልተነኩ ለማወቅ ችለናል።

ለአቶ መለስ ዜናዊ በጣም ታማኝ የነበሩትና በቅርቡ ግን ከጄነራል ሳሞራ የኑስ ጋር ለመስማማት ችግር የነበራቸዉ ጄነራል ዮሐንስ ገብረ መስቀልን ጨምሮ በርካታ መኮንኖች እንዲሰናበቱ የተደረገ ሲሆን፣ በቅርቡ የሌተና ጀነራልነት ማእርግ የተሰጣቸዉም እውቁ የኦሮሞ ጀነራል፣ ባጫ ደበሌም ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።

መኮንኖችን በዚህ ሁኔታ የማሰናበቱ ሂደት፣ የመከላካያ ሰራዊቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ ባንጸባረቀ መልኩ እንዲዋቀር ለማድረግ የታሰብ ሳይሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአንድ ቤተሰብን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚቆም እንዲሆን ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። “ጦሩን ለማሻሻል፣ አሁን ያሉትን በአዳዲስ ኦፊሰሮችን ለመተካት ታስቦ ከሆነ፣ እነ ሳሞራ የኑስ መልቀቅ ነበረባቸዉ” ያሉን ያነጋገርናቸዉ የፖለቲካ ተንታኝ በጦር ኃይሉ ዉስጥ ሊነሳ የሚችልን ተቃዉሞ ለማፈን ሆን ተብሎ የተደረገ ድርጊት እንደሆነ ይናገራሉ።

በተለይም በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት በተለየ ሁኔታ፣ የትግራይ ሕዝብ ለሰላምና ለዲሞክራሲ የሚደረገዉን ትግል መቀላቀሉ፣ ገዢዉ ፓርቲ በዘጠና ሰባት የትግራይ ተወላጆችን ከሌላዉ ሕዝብ ለማጣላትና ለማራራቅ የተጠቀመበትን የዘር ካርድ መጫወት እንዳልቻለ የገለጹት እኝሁ ተንታኝ “የትግራይ ተወላጆች በብዛት በመኮንንነት ያሉበት የጦር ኃይል ፣ እንደ ዘጠና ሰባቱ ከሳሞራና ከመለስ ጎን ተሰልፎ በሕዝቡ ላይ የተመኮስ አዝማሚያዉ በጣም የወረደ ነዉ። በመሆኑም በጦሩ ላይ ብዙ እምነት ስሌላቸዉ ነዉ እያደረጉ ያሉትን የሚያደርጉት” ሲሉም አስየያየታቸዉን አክሎእዉ ሰጥቷል።

በምርጫ 2002 ወቅት አረጋዊ ገብረ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ የመድረክ አባላትን ደጋፊዎች መገደላቸዉና መታሰራቸዉ ይታወቃል። በቅርቡም በመቀሌ አካባቢ በሺሆች የሚቆጠሩ የትግራይ ነዋሪዎች በግፍ ከቤታቸው እንዲባረሩ በሰፊ ተዝግቧል።

‘ውዳሴ’ ወ በረከት

Wednesday, December 21st, 2011

አቶ በረከት ስምዖን መጽሀፍ አሳተመ ሊያስመረቅም ነው የሚል ዜና ከወደ ሸገር ሰማንና ተደመምን ። እ ህ ህ ም አልን። የአረም እርሻን ያስታውሷል ! የደርጉ ካሳዬ አራጋው በዘመነ ደርግ መገባደጃ የሆነ መጽሀፍ ጽፈው ነበር እናም እቀድሞው ወመዘክር አግኝቼ ሳነበው ለአማርኛ አስተማሪዬ አዘንኩላቸው ፤ ለካንስ በእነ ካሳዬ አንጻር እርሳቸው ሊቅ ነበሩና ! ዛሬ ደግሞ ምስጋና ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን ይሁንና የወረቀት ዋጋ አልቀመስ ብሎ ምንቸቶቹ ደራሲያኖቻችን ብዕሮቻቸውን አግተው ጋኖች ደግሞ ‘ይጽፉ’ ያዙ ።

ለማንኛውም ዜናውን እንደሰማሁ ወደ አዕምሮዬ የመጡ አንዳንድ ጉዳዮችን ላንሳ። መጀመሪያ የጋዳፊ አረንጓዴ መጽሀፍ እፊቴ ድቅን አለ። ጋዳፊ ሊቢያን አመጽ ወጥሮ እየለበለባት መጽሀፋቸውን አንግበው እራሳቸው የተበተቡትን ስንክሳር ያነበንቡ ነበር ። አቶ በረከት እልም ያሉ እልህኛ ሰው እንደሆኑ ብዙ ሰው ያውቃል ይህ እልሃቸው እንደ ጋዳፊ የራሳቸውን የፓለቲካ ፈሊጥ እንደ ጽሁፍ በመጽሀፍ ቢጤ እንዲደራርቱት የማያደርግበት ምክንያት የለውምና ለወዳጆቻቸውም እንደው ቁም ነገር ቢገኝበት ብለን ለምናነበውም ኤጭ እንዳያሰኝ እፈራለሁ። ለዚህ ማሳያ በምርጫ 97 የፓለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ጊዜ አቶ በረከት ሲያቀርቡዋቸው የነበሩ ሀሳቦችን መለስ ይበሉና ያስታውሱ። ፓርቲው የከሰረባቸውንና በህዝብ ተአማኒነት ያጣባቸውን የዲሞራሲና ሰብአዊ መብት ችግሮች እርሳቸው እንደ ስኬት አድርገው ጣታቸውን ቀስረው ይሟገቱባቸው ነበር። እዋናው ችግር ያለው አቶ በረከት እንዚያን ለ15 ዓመታት በቲቪ ሲያስነበንቡዋቸው የነበሩ ድሎች ህዝቡ ‘ቁጩ’ እንደሆነ ማወቁ እርሳችው ደግሞ የፓለቲካ ድርሰታቸውን የእውነቶች ሁሉ እውነት አድርገው ማመናቸው ነበር። ከሁሉም ከሁሉም እንደየ አቅሚቲ በሎሌዎቻቸው በስሱ ስትበተን የነበረችው ‘በረከት መጽሀፍ ትራሱ’ ማሞካሻ በችኮና ደረቅ የመከራከሪያ ዘይቤአቸው ገደል መግባቷ ነው ፤ ቡግናዎች ከእኛ ቀድመው ይህን አውቀው ይሆን ምርጫውን በዜሮ የሸኙዋቸው?
በረከት መጽሀፉን ጻፈ አስመረቀም መባሉን ስንሰማ ዋናው አስደማሚው ጉዳይ እንዴት አድርጎ የሞራልን የግብረ ገብነትን (እንጥፍጣፊም ከቀረ እነርሱ ዘንድ ) ነገር አስታረቀው የሚለው ነው። እነ አቶ በረከት በስልጣን በቆዩበት አመታት የተባ ብዕር አለው ብለው የሚያስቡትንና ህዝባዊውን አስተሳሰብ ይገዛል ብለው የፈሩትን ሁሉ ከፈርኦን ቅናት በላቀ የብቀላ ስሜት ሲያስሩ፤ አንዳንዱን ሲገድሉ የተቀረውን ከሀገር ሲገፉ ነው የኖሩት አሁንም ያሉት። መጽሀፍ የሚጽፍ ሰው ደግሞ በሀሳብ ተሟግቶ የሚያሸንፍ ያም ባይቻል የሚሞክር አይነት ሰው ነው እንበል። እንዲህ የዳጎሰ መጽሀፍ የከተቡ ሰው ይህን ሁሉ አመት ተኝተው ኖሯል ብ ዕረኞችን በጉልበት ሲፋለሙ የነበሩት ወይስ የብዕር አድባር ስትለግም የጉልበቱ አማራጭ እግንባር ላይ ተሰድሮ ቆይቶ? ቀድሞውኑስ ይሄ የብዕረኛነት አቅም ከነበረ ጉልበትን ምን አመጣው? ከያዙት የመንግስት ስልጣን አኳያ የመጻፊያ ሜዳው አድማስ የሚገድበው አይነት አልነበረም አዲስ ዘመኑም ፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጋዜጣም፤ ሪፓርተርም አምድ አይነፍጉም ነበር።( በነገራችን ላይ የሀሳብ እጥረት አስቸጋሪ ጉዳይ ነው ። ህወሃት ነጻ ጋዜጦችን በራሳቸው መንገድ ሊሞግታቸው ሞክሮ የራሱን ነጭ ለባሽ ነጻ ጋዜጦች ሞክሮ አልሆነለትም፤ ኔሽን ጋዜጣን ያስታውሱ።) ለማንኛውም ለአቶ በረከትን በሞራል አንጻር መሞገት ተቃዋሚ ወጣቶችን በአልሞ ተኳሽ አስገድለው ሲያበቁ ‘ባንክ ሲዘርፉ ነው የተገደሉት’ የሚለውን ሙታንን እንኳን ሰላም የሚነሳ ክሳቸውን ላስተዋለ እጅግም አስፈላጊ ስላልሆነ እዚሁ እንተወው።

ምናልባትም የአቶ በረከት የዛሬው ጸሀፊነት እስብዕናቸው ውስጥ የሚርመሰመሰውን አጉል ቅናትም ያሳይ ይሆናል። በብዙ በጉልበተኛ መንግስታት ስር ባደሩ ህዝቦች ታሪኮች ይሄ ክስተት የተለመደ ነው። ፓለቲከኞች በኪነ ጥበብ ይሁን አርክቴክቸር፤ ስነ ጽሁፍ ይሁን የተፈጥሮ ሳይንስ ሕዝብን ያስደመሙ ባለሙያዎች ላይ ከፓለቲካ ባላንጣዎቻቸው ያላነሰ ጥላቻ ያድርባቸዋል። የናይጄሪያ የቀድሞ ጉልበተኛ ሳኒ አባቻን ያስታውሱ ፤ አለም ደግማ የማትወልደውን ጸሃፊውን ኬን ሳሮ ዊዋን በአገር ክህደት ወንጅሎ ለእርድ ለማድረስ ሁለት ወራት አልወሰደበትም። አንዳንድ አምባገነኖች ደግሞ ብዕርን ከመፍራታቸው የተነሳ በስደት ባህር ማዶ ያሉ ጸሃፊዎችን ሁሉ ሳይቀር ጸጥ የሚያሰኙባቸውን መንገዶች ሁሉ መቆፈራቸው አልቀረም። ለነገሩ የእኛ ሰዎችስ ከ ‘ ህዳሴ’ ግድብ በተረፈ ፈራንካ ትንሹንም ትልቁንም ኢትዮጵያ ተኮር ድረ ገጽ ለሐገር ውስጥ አንባቢ እንዳይደርስ ያምቁበት የለ? ታሪክን ወደ ኋላ ለመረመረ የአቶ በረከት ጸሃፊነት የሮማኒያውን ቻውቼስኩና ሚስቱን ‘ምርጥ ሰዓሊነት’ ፤ የሳዳምን የጢግሪስ ወንዝ ‘ ስነ ግጥሞች’ እንዲሁም አፈር ይቅለላቸውን ( ለነገሩ እመሬት አይቀበሩም ለካ የሙታን ቤተ መንግስት ውስጥ ነው ከነግርማ ሞገሳቸው አረፍ የሚሉት አፈር ይቅለላቸውን አልቦ ሊያደርጉብን) የቅርቡን የሰሜን ኮሪያውን ኪም ጆን ኢል በፊልም ፤ ዲዛይንና ጎልፍ ሳይቀር ‘ከአለም አንደኝነት’ አስበን ፈገግ ማለታችን አይቀርም። ደግመን እንበለውና ጉልበተኞች የያዙት አይጥማቸውም ሌሎች ጋር ያለው የፈጠራ ችሎታ በተለይም ሕዝባዊ ተቀባይነት ነው አንጀታቸውን የሚያደብነው።

‘ የሁለት ምርጫዎች ወግ’ አስቂኝ ተቃርኖን ከእነርዕሱ ይዞ ብቅ ብሏል። ህወሃት ምርጫን ‘የሚያሸንፍበት’ መንገድ የቸገረው ይመስል የወጉ መነሻም መድረሻም ምርጫን ማሸነፍ መሆኑ 99.6% የሸንጎ ወንበር ለያዘ ፓርቲ ዛሬም ድረስ የሚከነክነው እረፍት የነሳው ነገር እንዳለ ያሳያል ። የሆነ ጉልበተኛ ቆንጅየ ሚስቱን በጉልበቱ አስግብሮዋት ሲያበቃ ‘ የምትወደኝ ቢሆን ኖሮ ምን አይነት ትዳር ይሆን ነበር ?’ አይነት የውስጡን ሮሮ ! ( አንዳንዴ እንደ መንግስት ሰዎች ፓለቲካን ለማስረዳት እኛም ትዳርን እንደምሳሌ መጠቀም ይልመድብን እንጂ) ህወሃት የቅርቦቹንም ይሁን ከዚያም በፊት ተደረጉ የተባሉትን ምርጫዎች እንዴት ‘እንዳሸነፈባቸው’ ጥቅሙ እምብዛም ይሆናል እንጂ የሀሰት የምርጫ ካርዶችን በፎርጅድ ኮሮጆዎች እጃቸው እስኪዝል ሌሊቱን ሙሉ ሲሞሉ ያደሩ የወጣት ሊግ አባላትን፤ እውነተኛ የምርጫ ኮሮጆዎችን ከምርጫ ጣቢያ የዘረፉና ያጓጓዙ የፓሊስ አባላትና የመንግስት ተቀጣሪ ሾፌሮችን ሳይቀር በአስረጅነት አቅርቦ በአምስት ደቂቃ ቃለ ምልልስ ገደል ማግባት ይቻላል። እንዲያውም ለህወሃት እንደ ፓርቲ ለአቶ በረከትም እንደ መንግስት ሹመኛ የምርጫ አሸናፊነታቸው ‘ሂደቱ’ ላይ መተኛታቸው ለተቃዋሚዎቻቸውም ለደጋፊዎቻቸውም ከ 97ቱ ድንጋጤና ብርክና ትራውማ እስከ አሁንም እንዳላገገሙ ነው የሚያሳየው። ፓርቲው የሚያስፈልገው ከህዝብ ጋር የሚያስታርቀው ቢቻል ፓለቲካዊ ርዕዮት ካልሆነም መለስ ከፓርቲ ሰዎቻቸው ጋር ሲጋጩ እንዳደረጉት ማምለጫ አይነት ‘ ተሃድሶ’ ምናምን የሚል ከዚህም ከዚያም ማደናገሪያ ሀሳብ ይዘው ብቅ ቢሉ የሚመረጥ ይሆናል።

ከሁሉ ከሁሉ ደግም የዚህን ርዕዮት ትንተና ጠቃሚነት ከአቶ በረከት ተክለ ስብዕናም ጋር የሚያገኛኘው ሌላም ቸል ሊባል የማይገባ ጉዳይ ነበር እርሳቸው ወይ በአቅም ማነስ ቸል ካላሉት በቀር። አፍቃሪ ህወሃቶች ከቦናፓቲዝም ጨዋታ በኋላና የድርጅቱ ‘ጭንቅላቶች’ ከፓርቲው ተገለሉ ብለው ካዘኑ ወዲህ ፓርቲው ምላስ ብቻ ሆነ ሀሳብ ጠፋበትን ስላበዙ አቶ በረከት ሚዛኑን ለመድፋት ይታትራሉ የሚልም ግምት ነበር ። ደግሞም ተቃዋሚዎች የአቶ መለስ ‘ጎብልስ’ የሚል ትልቅ ሹመት እንደሰጧቸውም ማስታወስ ተገቢ ነው። እሹመት ስፍራ ከነሙሉ ማዕረጉና ጥቅማ ጥቅሙ መገኘትን ለአቶ በረከት አንመክርም ይመክሩን ይሆን እንጂ ። ለማንኛውም እንደው የፓርቲው ልሂቃን ሁሉ አርትኦት ካደረጉበት አይቀር ሕዝብ የተሳለቀበትን እነርሱም ያፈሩባቸውን የምርጫ ተውኔቶች የመጽሀፍ መነሻም መድረሻም አድርጎ ማቅረቡ ያ ቤት አሁንም የአዲስ ሀሳብ እጥረት እንዳለበት ከማሳየት ያለፈ ፋይዳ የለውም።
መጽሀፉን አላነበብነውም እናም ከርዕሱ ባሻገር እውስጡ ምን ተብሎ ይሆን? ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በአንድ ወቅት አበክረው የሕገ መንግስቱን ባለቤቶች (መቼም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማይባል ግልጽ ነው) የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያወጣልን ? ሲሉ እንደሞገቱት እኛም ውድ አንባቢዎች ይሄ መጽሀፍ የተጻፈበትን ወረቀት ምንዳ እንኳን ይመጥን ይሆን ስንል ከወዲሁ መጠየቃችን አይቀርም። በተለይም የተጻፈበት አላማ አንድ ቦታ ተቸንክሮ የቀረውን የህወሃት ፓለቲካ የውይይት ነፍስ ይዘራበት ይሆን አልያስ እነዚያኑ ላለፉት ሰላሳና አርባ አመታት ከዚያም ከዚህ የተለጣጠፈውን ዶግማ ሲጋቱ የነበሩት የፓርቲ አባላትና ያልታደለውን ሕዝብ መልሶ የሚያሰለችና የሚያታክት ውሃ ወቀጣ ይሆንን? ይህን ጽሁፍ ስጽፍ አንድ የሰማሁት ጨዋታ ትዝ አለኝ። ስዊዘርላንድ ሀገር ውስጥ የሚገኙ ኤርትራውያን አንድ ወቅት ላይ የሀገራቸውን ‘የናጽነት’ በዓል ሲያከበሩ እሐገራቸው ያለውን ግፍና መከራ በዚያውም ባህላቸውን ያደንቅ ዘንድ የፍትህ ሚኒስትሩን በእንግድነት ይጋብዛሉ አሉ። የሚነገረውም ተነግሮ የተለመደው የሙዚቃ ክፍለ ጊዜ ላይ ከበሮአቸውን እየደለቁ ክባቸውን ፈጥረው በእሽክርክሪት እስክስታቸውን ያስነኩታል። የፍትህ ሚኒስትሩ ጸረ ስደተኛ ኖሮ የመጣበትን ጉዳይ ትቶ “ እንዲህ አንድ ቦታ እየዞራችሁ የምትሽከረከሩትን በአንድ ቀጥተኛ መስመር ብታደርጉት አስመራ ትገቡ ነበር” ብሎአቸው አረፈው። ሰው የሚያየው ማየት የሚፈልገውን ነው የሚባለው ይሄው ነው። እኛም አቶ በረከትን እንዲሁ እንጠይቃቸው ። መጽሀፋቸው ያው የፈጀውን የቸከ የዘረኝነት ፓለቲካ ደግመው በለመዱት እሽክርክሪት እየዞሩ ይሉት ፤ የለመዱትን መወድስ ህወሃት ይደግሙበት ይሆን ወይንስ ከምሽጋቸው ወጥተው የማይደፈረውን የሀሳብ ሙግት ፈራ ተባ እያሉም ይሆን ይቀላቀላሉ?

የኋላኛውን መንገድ መርጠው ከሆነ መቸም ከአቶ በረከት እንደ ስማቸው ትልቅ በረከት ተገኘ ማለት ነው። ብረትን መጣል የመሰለ ጀግንነት የለምና። ታዲያ ይሄ መንገድ በአዲስ ዘመንና በአኬልዳማ እንደተለመደው የውሃ መንገድ እንደማይሆን እርሳቸውም አይስቱትም። ሀሳብን በጽሁፍ ማቅረብ የጠራ የንድፈ ሀሳብ ትንተና አቅምን ይህንን ላልደፈረም ፓለቲካዊ ታሪክ አይነት ጽሁፍ ለሚከትብ ደግሞ እውነት ከእርሱ ዘንድ ሲቻል ከነቃጭሏ ካልሆነም በርከት ብላ በተጨባጭ ልትኖር ይገባታል። እንደ አለመታደል ሆኖ የሐገር ቤቶቹ ገዢዎቻችን ከሁሉቱም ሆኖላቸው አያውቅም። ባለፉት ሃያ አመታት የገዚው ቡድን አባላት ወደ መድረክ ለመምጣትና ሀሳብን ለመግለጽ ባለግርማ ሞገስ ሙሉ ልብስ እንጂ ሀሳብ የሚያስፈልግ መስሎ አይታያቸውም ነበር። በ1997 የምርጫ ክርክር ወቅት ይህንን ሁላችንም ይህን ታዝበናል። በረከትም መጣ ዋልዋ ፤የፊት ለፊትን ክርክር ተሽኮርምመው ያለፉትም አቶ መለስ ሳይቀሩ ፓለቲካን በወቅቱ የተቀላቀሉትን አንዳንድ የትርፍ ጊዜ ፓለቲከኞችን ሳይቀር መሞገት ተስኖአቸው ነበር።

ይሄ አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ፤ እኔ ነኝ የማውቀው እናንተ አታውቁም አንድ ታሪክ አስታወሰኝ። ተማሪዎች ሳለን በጋራ በምንጋራው መኝታ ክፍላችን ( ዶርሚተሪ) ፍራሻችንን እመሬት አንጥፈን እናጠናለን። የፈተና ወቅት ሳይሆን አይቀርም ኮሽ የሚልም ነገር አልነበረም። ነገር ግን ሁላችንንም ከንባባችን የሚያስደነብረን የሆነ ጠንካራ የበር መበርገድ ድምጽ ሰማንና ቀና አልን። ለካንስ ጎረቤታችን ያለው ክፍል ውስጥ የሚኖር አይነ ስውር ተማሪ አልኮል ቤጤ ቀማምሶ ኖሮ በእንቅልፍ መሀል ወደ መጸዳጃ ቤት ደርሶ ሲመለስ እመኝታ ክፍሉ የገባ መስሎት ወደ እኛው ክፍል እርቃኑን እየገባ ኖሯል! እኛ እንደተደመምን ነገር ከምላሱ የማያጣው የናዝሬቱ ጓደኛችን ምን አለው ‘ ስማ የእኔ ወንድም አንተ ባታየንም እኛ የማናይህ መሰለህ ወይ እርቃንህን የመጣኽው ? ’ እርሱም ሳቀ እኛም ልባችን እስኪፈርስ ስቀን በገጠመኙ ፋታ ወሰድን። የእኛ ባለስልጣኖች እርቃናቸውን እንደቆሙ እኛ የማናውቅ ይመስላቸዋል ለዚህም የቀድሞውም የአሁኑም ድርሳናቶቻቸው ይህንን ይመሰክራሉ።

አቶ መለስ ዛሬ በህልማቸው የመጣውን ሁሉ ‘ የሻዕቢያ ተላላኪ’ ሲሉ አንዴ በሸንጎአቸው አንዴ በፍርድ ቤቶቻቸው ሊከሱ ከጥቂት አመታት በፊት የኤርትራን የነጸነት ጥያቄ የተረዱበትን መንገድ መጽሀፍ ባሉት ድርሳናቸው ታሪክንም ፤እውነትንም፤ ፓለቲካንም ደገፍ ሳይሉ እንዳሻቸው ጭረዋል። የአቶ በረከትም የምርጫ 97 ሮሮ ለዳመጠ አሁንም በመጽሀፋቸው አሉት እንደተባለው “ ለተቃዋሚዎች ያን ሁሉ ድምጽ የሰጣቸው ነፋስ ነው” ይላሉ ያለ አንዳች ሀፍረት። በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የህዝብ ድምጽን ንፋስም ያምጣው ሱናሚ ውጤቱን ከመቀበል የዘለለ ክርክር የእነማን እንደሆነ አለም ያውቀዋል። ታዲያስ እንዲህ እንዲህ አይነቱ ሀሳብ ላይ ለዘመናት ተኝቶ ማላዘን ሕዝብን መናቅ ራስንም ማስገመት አይሆንምን? ለነገሩ ነፋስ የተባለው ሕዝብ አንድ ቀን አውሎ ነፋስ የሆነ እንደሆነ ጋዳፊ ጭንቅ በወጠራቸው ጊዜ ለከበቡዋቸው ደመ ቁጡ ወጣቶች ያነሱትን ጥያቄ ያስነሳል “ የምታደርጉትን ታውቃላችሁን?” አሉ ተባለ ። እርሳቸው 42 አመታት የሚያደርጉትን ሳያውቁ እነዚያ ወጣቶች በዚያች ቅጽበት የሚያደርጉትን እንዲያውቁ መጠበቅ የዋህነት ነው። እኛም ቤት ይሄው አንድ ቀን መሆኑ አይቀርም። ያኔ ገዢዎቻችንን ምን ሲሉ ይጠይቁ ይሆን?
ቸር እንሰንብት
samson11 @me.com

“ስልታችን እየሰራ ነዉ ፤ በሰላማዊ ትግል ላይ ያለንን ጠንካራ አቋም እናድስ” አቶ ስዬ በአንድነት ጉባዔ ካደረጉት ንግግር

Sunday, December 11th, 2011

የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስቴር የነበሩት፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን የአንድነት ፓርቲ ያደረገዉን የጠቅላላ ጉባዔ በሳካይፒ የተካፈሉ ሲሆን ፣ ድርጅታቸዉ በፈታኝና ከባድ ሁኔታ ዉስጥም እያለ አሁን ያለበት ደረጅ መድረሱ በጣም የሚያስደስት እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ስዬ ገዢዉ፣ ፓርቲ ከጦር በላይ የሚፈራዉ የሰላማዊ ትግል እንደሆነ በማስመር፣ የሰላማዊ ትግሉ ከመቼዉም በላይ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን፣ በተለይም የነ አቶ አንዱዋለም መታሰር የቀሰቀሰዉ ከፍተኛ የትግል ስሜትን በመጥቀስና ገዢዉ ፓርቲ ጠንካራ ታጋዮችን ማሰሩን ቢቀጥልም፣ ትግሉ የበለጠ ይጠናከራል እንጂ እንደማያቆም አስረድተዋል።

አቶ ስዬ ያደረጉትን ሙሉ ንግግር እንደሚከተለዉ አቅርበነዋል፡

የተከበራችሁ የአንድነት ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች

ጤና ይስጥልኝ እንደምን ከረማችሁ፡፡ እንኳን ለሁለተኛው መደበኛ የፓርቲያችን ጉባኤ አደረሳችሁ፤ አደረሰን በማለት የከበረ ስላምታየን አቀርባለሁ፡፡

ጉባኤው እንደወትሮውም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑ ቢታወቅም አሁንም እንደወትሮው በተሳካ ሁኔታ ተከናውኖ አንድነት ፓርቲንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግልን አንድ እርምጃ ወደፊት እንደሚወስደው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

አንድነትን በግልጽ በታወቁ ግቦች፤ ፖሊሲዎች፤ስትራተጂና ስልቶች የሚመራ የምር ፓርቲ እናድርገው ብለን በዚሁ መሰረት መንቀሳቀስን ከጀመርን ቆይቶአል፡፡ ይህ መንገድ ቀላል እንዳልሆነ አስቀድመን ተገንዝበነዋል፡፡ በአንድ በኩል ከእኛ ብዙ ጥረትና ብዙ ምክክርን ይጠይቃል በሌላ በኩል ደግሞ ገዢው ፓርቲ በእኛ ላይ ብዙ እንዲያተኩርና እኛን የምር እንዲወስደን ያደርገዋል፡፡ እየሆነ ያለውም ይህንኑ ነው፡፡

እነ አቶ አንዱአለም እነ አቶ እስክንድር ከታሰሩ ወዲህ በርካታ ዜጎች ‹‹እኔ አንዱአለም ነኝ›› ‹‹እኔ እስክንድር ነኝ›› በማለት የታሰሩት ወገኖቻቸው የጀመሩትን የሰላማዊ ትግል መንገድ ለማስቀጠል ቃል ሲገቡ ተደምጠዋል፡፡ በዚህ መልእክት ውስጥ ሁለት ቁምነገሮች እናገኛለን፡፡ የመጀመርያው አንዱአለም ይፈታ፤ እስክንድር ይፈታ፤ ናትናኤል ይፈታ ማለት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግም ትግሉ አይቆምም እነሱ ቢታሰሩም እኛ እናስቀጥለዋለን ብሎ በግልጽ ማወጅን ያመለክታል፡፡ ይህ ቃል የአንድነቶች ቃል እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም፡፡ ቃሉ የአንድነቶች ቃል ብቻ ሆኖ እንዲቀር ግን አይጠበቅም፡፡ የመላ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወጣቶች ቃል መሆን አለበት፡፡ ይህንን እውን በማድረግ ረገድ ይህ ጉባኤ መነሻ ይሆናል ብየም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ክቡራትና ክቡራን

አንድነት የተመሰረተው በኢትዮጵያ አሁንም ለአገራችን ትክክለኛው የትግል ስልት ሰላማዊ የትግል ስልት ነው፤ መንገዱ አስቸጋሪ ቢሆንም አሁንም በሰላማዊ መንገድ ታግሎ በኢትዮጵያ ዴሞክራስያዊ ሽግግርን እውን ማድረግ ይቻላል በሚሉ ወገኖች መሆኑ ይታወቃል፡፡ አቶ አንዱአለምን ጨምሮ ቆየት ብሎ አንድነትን የተቀላቀልነው ወገኖችም አንድነትን የተቀላቀልነው ከዚህ እምነት በመነሳት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይህ መሆኑ እየታወቀ ከዚህ በፊት ወይዘሪት ብርቱካንን አሁን ደግሞ አቶ አንዱአለምን የመሳሰሉ የፓርቲውን ቁልፍ የአመራር አባላትን ለእስርና ለእንግልት መዳረጉን ተያይዞታል፡፡ ድርጊቱን ለመሸፈን የተለያየ ስምና ምክንያት ቢሰጠውም ሁሉም እርምጃዎች የሚያመለክቱት የአገራችን ገዢዎች ሰላማዊ ትግልን ከጦርና ከፈንጂ በላይ የሚፈሩት መሆኑን ነው፡፡ አንድነት እነሱ በማይችሉበት መንገድ መምጣቱ እጅጉን ያስጨነቃቸው መሆኑን ነው፡፡ ስልታችን እየሰራ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ጊዜ በያዝነው አካሄድ ላይ አንዳችም ጥርጣሬ ሊኖረን አይገባም፡፡ ይልቁንሰ ይህ ጉባኤ በሰላማዊ ትግል ላይ ያለንን የጸና አቋም የምናድስበት፤ ስልቱ ይበልጥ ጥልቀት አግኝቶ የሚቀጥልበትን መንገድ የምንመክርበት አጋጣሚ ይሆናል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ክቡራትና ክቡራን ጉባኤተኞች

በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ላይ መሆኔ ታውቁ ይሆናል፡፡ ሰሞኑ የመጀመርያው መንፈቅ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተናዎች ወቅትም ነው፤ ቅዝቃዜውም የሚጀምርበት ወቅትም ነው፡፡ ጉባኤው ወደ አገሬ ለመምጣትም ከብርዱ ለማምለጥም አጋጣሚ ይፈጥርልኛል ብየ ጠብቄ ነበር፡፡ መምጣት ባልችልም ጉባኤው እንዲሳካ እመኛለሁ፤ የታሰሩት ወገኖቼንም ሁሌ አስባቸዋለሁ፡፡

ከታላቅ አክብሮት ጋራ

ስየ አብርሃ ሐጎስ

ቦስትን፤ ሃገረ አሜሪካ

(አቡጊዳ)

ዶ/ር ነጋሶ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሆኑ

Sunday, December 11th, 2011

(አቡጊዳ) – የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ እሁድ ታህሳስ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባዔዉን አጠናቀቀ። ለሚቀጥሉት አመታት ድርጅቱን በሊቀመንበርነት የሚመሩትን እንዲሁም የድርጅቱ የላእላይ ምክር ቤት አባላትን ጠቅላላ ጉባዔዉ የመረጠ ሲሆን ስብሰባዉ በተሳሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

የድርጅቱ ሊቀመንበር ለመሆን ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶር ንጋት አስፋዉ እንዲሁም ከአንድነት ፓርቲ ጋር የተዋሃደዉ የብርሃን ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ፣ ለእጩነት ቀርበዉ እንደነበረ መዘገባችን ይታወሳል።

ከስብሰባዉ በፊት ዶር ንጋት እራሳቸዉን ከእጩነት በማንሳታቸዉ፣ ፉክክሩ በዶር ነጋሶና በኢንጂነር ዘለቀ መካከል ብቻ እንደነበረ የደረሰን ዘገባ አክሎ ያትታል።

ከጠለቀ ዉይይትና ዲሞክራሲያው ክርክሮች በኋላ የጠቅላላ ጉባዔዉ አባላት፣ ዶር ነጋሶ፣ አሁን የያዙትን ሃላፊነት እንዲቀጥሉና የፓርቲዉ ሊቀመንበር ሆነዉ እንዲቀጥሉ በአብላጫ ድምጽ ወሰኗል። የብዙ አባላትን ድምጽና ድጋፍ ያገኙት ኢንጂነር ዘለቀም፣ ያሸነፉት ዶር ነጋሶ ሳይሆኑ ያሸነፈዉ ዲሞክራሲ እንደሆነ በመግለጽ ፣ የጠቅላላ ጉባዔዉን ዉሳኔ በጸጋ እንደሚቀበሉ፣ ከዶር ነጋሶም ጋር ተያይዘዉ በመስራት፣ ፓርቲዉ የቆሞለትን አላማ ከግቡ ለማድረስ የድርሻቸዉን እንደሚወጡ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

ጠቅላላ ጉባኤዉ የድርጅቱን ሊቀመንበር ከመምረጥ ባሻገር፣ የላእላይ ምክር ቤት አባላትን የመረጠ ሲሆን የድርጅቱ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ በላይ፣ የድርጅቱ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ ዳዊት አስራደ፣ የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች የምክር ቤቱ አባላት እንደሆኑም ለማወቅ ችለናል።

ለሊቀመንበርነት እጩ ተወዳደሪ ሆነዉ ቀርበዉ የነበሩት ዶር ንጋትንና ኢንጂነር ዘለቀን እንዲሁም በእሥር የሚገኙት አቶ አንዱዋለም አራጌንና አቶ ናትናዔል መኮንንን በሌሉበት፣ እንዲሁም ከአሜሪካ አገር ሆነዉ በስካፕይፒ ስብሰባዉ የተካፈሉትን የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስቴር አቶ ስዬ አብርሃን የምክር ቤቱ አባላት እንዲሆኑ ጉባዔዉ መርጧቸዋል።

ከቀድሞ የአመራር አባላት መካከል ዶር ኃይሉ አራያ ፣ አቶ አስራት ጣሴ በድጋሚ የምክር ቤቱ አባል እንዲሆኑ የተመረጡ ሲሆን፣ የድርጅቱ አንጋፋ መሪ የነበሩት ኢንጂነር ግዛቸዉ የምክር ቤቱ አባል እንዳልሆኑም ለማወቅ ችለናል። ኢንጂነር ግዛቸዉ፣ ወጣቶች ወደ ድርጅቱ አመራርነት መምጣት አለባቸው በሚል እነ አቶ አንድዋለም አራጌን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ወደ አማራር እንዲመጡ ያደረጉ ሲሆን፣ ከብርሃን ፓርቲ ጋር ዉህደት እንዲመሰረት፣ ኢትዮጵያዉያን በዘር ሳይከፋፈሉ ለአንዲት ኢትዮጵያ በጋራ መስራት ይቻል ዘንድ የአንድነት ፓርቲ በመድረክ ዉስጥ እንዲሰራ ቁልፍ ሚና ተጫዉተዋል።

ዛሬ በተደረገዉ ጉባዔ የታሰሩ የአንድነት አመራር አባላት ቤተሰቦች፣ የመድረክ አባል ድርጅቶች አመራር አባላት ፣ ዲፕሎማቶች እንደተገኙም ለማወቅ ችለናል። የመድረክ አመራር አባላት በተለይም የአንድነት ፓርቲን የብርሃን ፓርቲ መዋሃዳቸዉን እንደ ትልቅ ስኬት በመግልጽ መድረክም ከግንባርነት ወደ ዉህደት መገስገስ እንዳለበት ገልጸዋል።

የድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሆኑ የተመረጡት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ካቢኔያቸዉን (የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን) የሚሰየሙ ሲሆን፣ የተሰየሙት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአብላጫ ድምጽ የምክር ቤቱን ድጋፍ ካላገኙ ተቀባይነት እንደማይኖራቸዉ የድርጅቱ ሕገ ደንብ ይገጻል።የምክር ቤት አባላት ያልሆኑ የድርጅቱ አባላት፣ በሊቀመንበሩ ከተሰየሙና በምክር ቤቱ ተቀባይነት ካገኙ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሊሆኑ እንደሚችሉም የድርጅት ሕገ ደንብ ይገልጻል።

ለተሰብሳቢዉ በሳካይፒ ንግግር ያደረጉት የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶ ሊቀመንበር አቶ አሎግ ልመንህ ፣ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአገር ቤት የሚደረገዉ ትግል ለመደገፍ ቆርጠው መነሳታቸውን በመግልጽ፣ በተለይም በድርጅቱ ሊቀመንበር የሚመረጠዉና በምክር ቤቱ የሚጸድቀዉ የስራ አፈጻሚ ኮሚቴ በርካታ ወጣቶችን ያቀፈ እንዲሚሆን ያላቸዉን ተስፋ ገልጸዋል።

በውሸት ምላስ ሃገር ሲታመስ በታደለ መኩሪያ

Sunday, December 11th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ ዋሽንግተን ዲሲ

Monday, November 28th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አቶ ደበበ እሸቱ ከእስር ተፈቱ

Sunday, November 13th, 2011

ለማንበብ እዚሕ ይጫኑ

የታሪክ ጎማ እየከነፈ ነው በታሪኩ አባዳማ

Wednesday, November 9th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በሲያትል ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ

Wednesday, October 26th, 2011

ለማንበብ እዚሕ ይጫኑ

አንድ የአንድነት ፓርቲ አባል በድብደባ ተገደሉ

Monday, October 24th, 2011

(አቡጊዳ) — ያለፈዉ ሐሙስ፣ የአቶ መለስ ዜናዊን የፓርላማ ንግግር ካዳመጡ በኋላ፣ በየቦታዉ ያሉ ካድሬዎችና የገዢው ፓርቲ ቅጥረኞች በሰላማዊና ሕገ መንግስቱን እያከበሩ የሚንቀሳቀሱ የመድረክ አባል ድርጅቶችን፣ “ሽብርተኞች ናቸዉ” በሚል የፖሮፖጋንዳ ዘመቻ የከፈቱ ሲሆን፣ የመድረክ አባላትን በየቀበሌዉና በየወረዳዉ የማስፈራራት፣ የማሰር፣ የመግደል ፣ የማወክ ዘመቻቸዉን እንዳጧጧፉ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

በደቡብ ጎንደር በመምህርነት ያገለግሉ የነበሩ፣ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባልና ደጋፊ የነበሩት፣ አቶ ሙሳ ኢብራሁም፣ ጥቅምት ስምንት ቀን 2004 ዓ.ም በኢሕአዴግ ታጣቂዎች ተደብድበዉ መሞታቸዉን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አክሎ ያትታል።

የአንድነት ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ምክር ቤት አባል የሆኑት ሻምበል የሺዋስ ይሁን፣ ጥቅምት ስድስት ቀን በፌዴራል ፖሊሲ ተይዘዉ ከተወሰዱ በኋላ የት እንደደረሱ ማወቅ እንዳልተቻለም የደረሰን ዜና ያመለክትል። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አቶ ሃብታሙ አያሌዉና ዘመዲያ አገዘ የተባሉ፣ በምስራቅ ጎጃም ነዋሪ የሆኑ የአንድነት ደጋፊ፣ ሰኔ ሃያ አምስት ቀን 2003 ዓ.ም በወረዳዉ ፖሊስ ተይዘው ከተወሰዱ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸዉ የት እንዳሉ ለማወቅ እንዳልቻሉ ዜናዉ አክሎ ይገልጻል።

ሐምሌ 13 ቀን 2003 ዓ.ም አሁንም በምስራቅ ጎጃም የሚገኝ የወረዳ ፍርድ ቤት፣ በአቶ አያል ጌታነህ ላይ ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ፣ ለአንድ አመት ከሕብረ ተሰቡ ጋር እንዳይገናኙ የወሰነ ሲሆን ፣ አቶ አያል ጌታነህ በአሁኑ ወቅት በፍርሃትና በትልቅ ወከባ ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ችለናል።

ከጎጆምና ከጎንደር ወደ ሰሜን አለፍ ስንል፣ በትግራይም፣ ዜጎች በብዛት እየታሰሩ እንደሆነም ለማረጋገጥ ችለናል። የመድረክን አላማ የያዘ ወረቀት ለህዝብ ሲያሰራጩ የነበሩት የአረና አባል፣ አቶ አያሌዉ በየነ በሽሬ ተይዘዉ የታሰሩ ሲሆን፣ መምህር ጎይቶም ጸጋዬ የአረና አባል ስለሆኑ ከስራቸዉ ተባረዋል።

አቶ አማረ ተወልደ የተባሉ የአረና አባል፣ እርሳቸዉም በሁመራ የመድረክን አላማ ወረቀት ለሕዝብ ሲያሰራጩ በአማራዉ ክልል ፖሊሶች ተይዘዉ፣ “አረናዎች በትግራይ እንጂ በአማራዉ ክልል መንቀሳቀስ አይችሉም” በሚል ለበርካታ ቀናት እንደታሰሩ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል።

ላለፉት ሶስት ወራት ገዢዉ ፓርቲ ሽብርተኖች ናቸው እያለ ኦሮሚያን የአማራዉን የትግራይ ክልል ጨምሮ በመላዉ አገሪቷ ግዛቶች ከፍተኛ የሆነ ዜጎችን የማወክ ተግባር እየፈጸመ ሲሆን፣ አቶ አንዱዋለም አርጌ፣ አቶ እስክንደር ነጋን ጨመሮ እጅግ በጣም ብዛት ያላቸዉ ሰላማዊ ዜጎች እንዳሰረ የሚታወቅ ነዉ።

ላለፉት ሶስት ወራት የታሰሩ ዜጎችን ስም ዝርዝር በስፋት የያዘ ሪፖርት በቅርቡ ለአንባቢያን ይፋ እንደምናደርግ በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንሞክራለን።

ትጮሃለህ ወይስ ትሞታለህ?

Wednesday, October 5th, 2011

በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

እንደ ላስኪት እየተወጠሩና እየተለጠጡ ቀዳሚና ትክክለኛ ትርጉማቸውን እየለቀቁና እየሳቱ በሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ እንዲሁም ሕገ መንግሥታዊ መብቶች ሳይቀር በመጣስ ዜጎች እያሸማቀቁ ከሚገኙ የበላይነትና የራስ ጥቅም ማዕከል ያደረገ ፖሊሲ የሚያራምድ ሀገራትና መንግሥታት ተቀናቃኞቻቸውን ድባቅ ለመምታት ከፈጠራቸው ቋንቋዎች መካከል “አሸባሪ” (ሽብር። ሽብርተኛ) የሚለውን ቃል ተጠቃሽ ነው፣

ቋንቋው ከቋንቋነቱ አልፎ ሁነኛ ፖለቲካዊ ድምጽ አልባ ገዳይ መሳሪያ በመሆን ሲያገለግልም እሄው አሥር ዓመታት አስቆጥረዋል፣ ዓለማችን አሁን የምትገኝበትን ገጽታ በማላበስ ረገድም “በአሸባሪዎችና” በኃያላን መንግሥታት የተከፈተውን ጦርነት የጎላ ሚና ተጫውተዋል፣ ኪዚህም አልፎ በራስ መተማመን ማጣት ከሚፈጥረው ፍርሃትና ውዥንብር ለማምለጥ “ፀረ-ሽብርተኝነት” በሚል ስም ሕግና ደንብ አርቀቀህ ተቀናቃኞችህን የውሃ ሽታ ማድረግ ከተያያዙት ሕዝባቸውንና ሀገራቸውን በግምት ከሚመሩ ሃገራት መካከልም ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀዳሚ ሰለባ ለመሆንዋ የሚያጠያይቅ አይደለም፣

እውነቱ- በሥልጣን ላይ የሚገኘውን የኢህአዴግ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር በትረ ሥልጣን ጨብጠው ሕዝባቸውንና ሀገራቸውን አቆራምተው አራቁተው ካለፉ ገዢዎች መካከል የባሰ አመጸኛ ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ሀገር የሚያደርገው ነገር ቢኖር መሰሬ ማንነቱንና አፋኝ አንባገነናዊ ሥርዓቱን በሕግ የተደጎሰ ለዘብተኛ ሰይጣን መሆኑ ነው፣

ለመግቢያዬ ይህን ያክል ካልኩ ዘንድ ወደ ዋና ርዕሰ ጉዳዬ ስመለስ በአንዳንድ ምክንያቶች የሕትመት ሥራውን የተጓተተብኝ በመጽሐፍ ሥራ ላይ ተይዜ ለጥቂት ወራት ከጠፋሁ በኃላ በዛሬው ዕለት ብቅ እል ዘንድ የተገደድኩበት ምክንያት በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ በተለይ ንጹሐን ዜጎችን በተመለከተ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ረገጣ መልኩን ለውጦ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ በመምጣቱና እንዲሁም ደግሞ ገዢው ፓርቲ ሕግን ሽፋን በማድረግ ዜጎችን ከማሸማቀቅ አልፎ ለእስርና ለከፋ እንግልት መዳረግ ሥራዬ ብሎ የተያያዘው ኃላፊነት የጎደልው ሥርዓት አላባ ቡድን ሰለባ የሆኑት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና እንዲሁም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ወደ እስር መውረድን ተከትሎ በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሆነ በውጭው ዓለም የተጠለሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ምላሽ ለመቃኘት በተጨማሪም ሁኔታዎችን በማስመልከት ግላዊ አመለካክቴን ለመሰንዘር ነው፣

በተለይ በውጭ የሚኖረው ዳያስፖራ ያነሳን እንደሆነ ከወትረው በበለጠ መልኩ ድምጹ የሚሰማው በአምስት አመት አንድ ጊዜ የምትመጣውን የምርጫ ወቅትና ተለይተው የሚታውቁ የፖለቲካ መሪዎችና ግለሰቦች በገዢው ፓርቲ ወደ እስር ሲወርዱ፦ ይህን ተከትሎ ደግሞ የሚፈጠረው ሞቅታ ለሁላችን ግልጽ ይመስለኛል፣ ያም ሆነ ይህ ግን ሰዎቻችን በታሰሩ ቁጥር አድራጊውና ተደራጊው ከሚገኙበት መልከዓ ምድር ውጭ ሆነህ ይፈቱ! ይፈቱ! ብሎ ጮኸት በሳይንሱ ተሰማርተው በሳል ተሞክሮአቸውን ከሚያካፍሉን ሊቃውንት እይታ አንፃር ሲታይ/ሲመዘን ፈይዳው ድካም ብቻ ሆኖ ሲገኝ ትጮሃለህ ወይስ ትሞታለህ? ለማለት ግድ ብሎኛል፣

በፖለቲካው አለም ሁለት የሚመሳሰሉ ዳሩ ግን የተለያዩ ገጽታዎች አሉ፣ አንዱ በየዋኁ ማኅበረሰብ ዘንድ ስምና ዝና ለማትረፍ ለግል ጥቅም ባንዴራ ታጥቀው ሆ! በማለት የሚያስብሉ፤ ከሀገር ሀገር ከሰፈር ሰፈር ሽርጉድ በማለትም በዜጎች ደም ስር ላይ ሰርጸው ለመግባት የሚተጉ ሲሆኑ ሌላው ደግሞ ስለ ሕዝብ ስለ ሀገርና ስለ ትውልዳቸው ራሳቸውውን ክደው ። ቤተ ዘመዶቻቸውን ትተውና ጥለው ያመኑበት ዕላማ ከገባበት በመግባት መስዋዕትነት በመሆንና በመክፈል በትውልዳቸው ላይ ሰማያት ላይ የተንጣለለው የጨለማ መጋረጃ በመቅደድ ብርሃን የሚሲጡ ናቸው፣ እኒህዎቹ በሕዝቡ ዘንድ እምብዛም ታዋቂዎች አይደሉም በቁጥርም በጣት የሚቆጠሩ እጅግ ጥቂቶች ናቸው፣ ያም ሆነ ይህ ግን ሕዝብ የሚሆነውን ለይቶ የማወቅ ግዴታ እንዳለበት ነው፣

ትጮሃለህ ወይስ ትሞታለህ? ምን አስባለህ በማለት በቅንነት ጥያቃቸውን ለሚያነሱ ወገኖች ቀዳሚ ምላሼ በመታሰር መፈታትን እንጂ በአፍአ ጩኸት የሚወልቅ ሰንሰለት የለምና፣ አንድም የተፈቱ (ላቅ ያለ አመለካከት ያላቸው። የበራላቸው) ሰዎች ሲታሰሩ የታሰሩትን (ብዙሐኑን) ያስፈታሉና፣ ሌላው እንዴት ጩኸት የሚፈጥረው ነገር አለው እንጂ ለሚሉም መጽሐፍ ቅዱስ የኢያሪኮ ግንብ በጩኸት ፈረሰ ሲል ከአፋቸው በሚወጣ ድምጽ ሳይሆን ከአምላካቸው የመጣላቸውን ድምጽ ሳያቅማሙ በመታዘዝ ሞኝነት የሚመስለውን ነገር የህይወት መግቢያና መውጪያ በሆነ በልባቸው ይቅር የኢያሪኮን ግንብ የዓይን ቅንድብ ያንቀሳቅስ ዘንድ በማይቻለው ጩኸት እስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ይቻለዋል፤ እግዚአብሔር ይችላል፤ ለእሱ አንዳች የሚሳነው ነገር የለም፤ ፍጥረት ሁሉ ለእርሱ ይታዛዛሉ፤ ጉልበት ሁሉ ለስሙ ይንበረከል! በሚለውን እምነት ጢም ብሎ በሞላ ልብ ፊት የሰው እጅ የገነባው ግንብ መቆም ስላልተቻለው ሊፈር ችለዋል፣ ይህ ደግሞ ታሪክ ሳይሆን እውነት ነው!! እውነቱነቱን ለማረጋገጥ ደግሞ ሥነ-ጽሑፍን ለማጥናት ደፋ ቀና ማለት ሳይሆን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ማመንታት ለገባህ እውነት በመኖር (መኖር ሲጀምሩ) እውነቱነቱን ማረጋገጥ ይችላሉ፣

ጥያቄው- የትኛው ሕዝብና ሀገር የተጎናጸፈው፤ ያለው፤ ያገኘውና የሚያጣጥመው ነጻነት ለመቋስ ነው ይህ ሁሉ … አሜሪካውያን? እንግዲህ መንገዱ አጭር ነው! አሜሪካም ሆነች አሜሪካውያን የሚታወቁበት ገንዘባችን ለማድረግ ከተፈለገ ያለፉበትን ማለፍ፤ እነሱን መምሰል ነው፣ ይህ ትውልድ (አሜሪካውያን) ዛሬስ በቃን! እስከ መቼ ድረስ! ሲል ግንባሩና ደረቱ ተመቶ የወደቀ አባት እንጂ በሁለት ሃሳብ ላይ ተይዞ ሲመነታ ጀርባው ጥይት በስቶት ሲንደፋደፍ አንጀቱ ተዘርግፎ የሞተ አባት የላቸውም፣

ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች” (የዮሐንስ ወንጌል 12፦24) ሲል እንዳስተማረውም አንድ ተክል እንዲገኝ ከተፈለገ ዘሩ በዘርነቱ መሞት እንዳልበት ሁሉ ማለት በመሞት ሕይወት ማግኘት በዕፅዋት አለም የማይታበል ሐቅ ከሆነ ነጻነት እንደ ሰማይ ከዋክብት የራቀበት ከኢትዮጵያዊ ዜጋስ ምን ይጠበቃል ያልን እንደሆነም በጩኸት ፈንታ የታሰሩትን እኛን ለማስፈታት እስከ ሆነ ድረስ እነሱን ለመምሰል ራሳችንን ማዘጋጀት እንደሚገባን ልባችን አይስተውም፣

በፖለቲካው ዓለም ይሄ በትርፍ ሰዓት የሚጮክ ዓይነት ጩኸት ከቁም ቅዥት የተለየ ትርጉም/አንድምታ የለውም፣ አፍ የመጣለት ሲናገር ሳይሆን ልብ የቆረጠለት ዕለት (ሁለት ሞት የለምና) ድል የአንተ ይሆናል፣ ቅድሳት መጻህፍትም ሆኑ ሌሎች የታሪክ መዛግብት የሚለግሱልን የጥበብ ምክርም ሆነ ከውስጣቸው የምናገኘው የተፈተነ ምስክርነትም ይህ ነው፣

ከዚህ ሁሉ ማብራርያ በኋላ አንባቢን ይፈቱ ብሎ ጩኸት ምን ማለት ነው? በማለት ጥያቄን ብሰንዝር በ ”ባህሪው” እንዲሁ ዓይነት ሰው ካልሆነ በስተቀር የሚከፋ ሰው ያለ አይመስለኝም፣ ምንነው ቢሉ? እነዚህ ሰዎች አይደለም መታሰር በእኛ ሞት በኢትዮጵያ ምድርና ሕዝብ የሚመጣው ለውጥ ካለ በህይወቴ ልትመጣ ያለኸውን ሳትዘገይ ና ና ይህ ባርነት ያደከመው ሕዝብ ይረፍ! በማለት ስራቸውን ያለ አንዳች ስጋትና ፍራቻ ዜግነታዊና ሀገራዊ ግዴታቸውን ሲወጡ የነበሩ ሰዎች በመሆናቸው እንጂ አይ ብንታሰርም መውጣታችን አይቀርም የተባበሩት መንግሥታት። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች። ስቴት ዲፓርትመንት። ኢምንስት ኢንተርናሽናል። በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያውያን ዜጎች … በሚጮኹት ጩኸት በሚፈጥሩት ዲፕሎማስያዊ ተጽእኖና በሌሎች ምክንያቶች የኢህአዴግ መንግሥት ወዶ ሳይሆን ሳይወድ ይፈታል/እፈታላለሁ በማለት የግብር ይውጣ ስራ በመስራት ወደ ውህኒ እንዳልተወረወሩ ባለ ሙሉ እምነትም ነኝ እና፣ እስር ማለት ምን እንደሚመስልና ምን ማለት እንደሆነ ከአንድም ሁለት ጊዜ አውቀዋለሁና፣

እንግዲህ እዚህ ላይ ማወቅ የሚገባን ነገር ቢኖር እንደዚህ ዓይነት ለትውልዳቸው የተሰጡ ሰዎች ከማናችንም ቢሆን ጭብጫባና በስማቸው ቲ-ሸርት አሰርተን እንድንለብሳቸው የሚፈልጉ አይነት ሰዎች ሳይሆኑ እነዚህ ሰዎች ከእኛ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር እንቅስቃሴያቸውን ማለት ስለ ፍትህ። ዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር መስፈን እንዲሁም ዜጎች በሕግ ፊት በእኩልነት የሚታዩበትና የሕግ የበላይነት የሚታይበት ሁኔታ ለማየትና ለመፍጠር በተጨማሪም የዜጎች የመናገር። የመሰባሰብ። ሃሳብህን በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማስከበር ባደረጉትና በሚያደርጉት ትግል ካመንን የጫማቸውን ምልክት እያነፈለፍን እንድንከተላቸው ብቻ ነው፣ እኛን ሲመሩ ከታሰሩ እኛ የእነሱ እነሱ የእኛ መሆናቸውን የምንገልጸው በጩኸት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ ነው፣ ያን ጊዜ ለዓመታት የተገነባ ሴረኛ ሥርዓት ከሥር መሰረቱ ቦቅሰህ ለመጣል የአንዲት ሌት ስራ ብቻ ይሆናል።

በተረፈ አሁንም ወደድንም ጠላንም በኢትዮጵያውን እጅና እግር ላይ የተጠፈረውን ሰንሰለት የሚወድቀው በውል ባለየለት ጩኸት ሳይሆን እግዚአብሔር ፊቱን ወደ ሕዝቡ ሲመልስ/ለድሃና ምስኪን ሕዝብ ሲራራ በዘመናት መካከል በሚሰጠን አንድ ጊዜ ፈጽመው ትኩር ብለው ከተመለከቱ ያዩትን የራሳቸውን ሳይደርጉ የማይመለሱና ለምንም ነገር የማይንበረከኩ ፊታቸው እንደ አንበሳ ኮቴአቸው እንደ ሺህ የፈረስ ድምጽ ጠላቶቻቸውን የሚያርበደብዱ የልጅ የማያባራ ለቅሶና እንባ፤ የእናት ልመናና ምህጽንታ ወደኃላ በማይመልሳቸው። ሆድ በማይብስባቸው ግለሰቦች በሚከፍሉት የእምነት ዋጋና ውጤት ነው፣ ለዚህ ደግሞ ምንም ማስተዣዘኛ አያስፈልገውም፣ ያመነ ከዚህም አልፎ ላመነበትም እምነት የቆመ ሰው አይደለም እስር ሰባት እጥፍ በሚንቀለቀል እሳት ቢወረወርም ይሁንታው ነው፣

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም ሆነ የሌሎች ወገኖቻችን ከእስር መፈታት ሳይሆን የኢህአዴግ አደራሾች የሚሰነጣጥቀው ዜጎች በአንድ ልብና ሃሳብ የእነዚህ የቁርጥ ቀን ሰዎች አሰር ተከትለው/ተከትለን እስከ መጨረሻ ደቂቃ ድረስ ወገባቸንን ሸጥ አድርገን በመታጠቅ መክፈል የሚገባንን ዋጋ ለመክፈል በጽናት ሰላማዊ ትግሉን በማፋፋምና በመቆም ነው፣ ይህን ስናደርግ የማይቀርለት መሆኑን ሲገነዘቡ ሌሎች የውጭ ኃይሎች ከጎናችን መቆማቸው የማይቀር ይሆናል፣ ፖለቲካ ይሉት ይህን ይመስላልና!!

በመጨረሻ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ቀጣይ እርምጃ “ለእናንተ ለምትጮኹ በደንብ ትጮኹ ዘንድ ድምጽ ማጉልያ ያስፈልጋቸዋል” በማለት ክፍያውን በተወካዮቹ አመካኝነት ፍጽመው ቅርባችን ከሚገኙ ስቶሮች የታዘዘልንን መሣሪያ እንወስድ ዘንድ ማውጫ ወረቀት እንዳይልኩልን ነው የምፈራው፣ ከዚህ ባሻገር ግላዊ አመለካከቴን የማይዋጥለት ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ጽሑፉን በማስመልከት የመስለውን የማለት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን ስገልጽ በአክብሮት ነው፣

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com
October 3, 2011

አዘራፊና ዘራፊ ሲበላ ባለ አገር ይቀላውጣል

Wednesday, October 5th, 2011

አሥራዳው (ከፈረንሳይ)

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አይጥ ለሞትዋ የድመት አፌንጫ ታሸታለች! ገብረመድህን አርአያ

Tuesday, October 4th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ለዘግናኙ የመኪና ኣደጋው እልቂት ተጠያቂው ማን ነው?

Monday, October 3rd, 2011

ሰሙኑን የመስቀል ዋዜማ ህዝብ በኣሉን ለማክበር ሽርጉድ እያለ ነበር። በዕለተ ሰኞ ከሰባት ሰኣት በኋላ ኣስደንጋጭ የወሬ ንፋስ መንፈስ ጀመረ። ወሬውም የህወሓት የባህል ቡድን በኣንድ ኣሮጌ ኣውቶብስ ተሳፍረው ወደ ሱዳን ሲጓዙ ሩቅ ሳይሄዱ ከመቀሌ በስተደቡብ 200ኪሎሜትር ርቀት ላይ በቆቦ ኣከባቢ ተገልብጠው ብዙ ኣርቲስቶች እንደሞቱና ብዙዎቹም እንደቆሰሉ ይወራል።

የወሬው ፍንጭ መቀሌ እንደደረሰ ሰዎች ካለወትሮው በየመንገዱ፣ በየንግድ ቤቱና በየሻሂ ቤቱ ሦስትና ከዚያ በላይ እየሆኑ ቁጭት የሚነበብበት ዝምታ እንዲሁም በመንሸኳሸክ ሲነጋገሩ ይታይ ነበር። ቆይቶ ከ10 ሰዓት በኋላ ግን በግልጽ መሰማት ተጀመረ፤ በህወሓትና በመንግስት መገናኛ ብዙሃንም ህዝቡ ከሰማ በኋላ ይሰራጭ ጀመር። ኣደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች በሄሊኮፕተር ወደ ኣሉላ ኣባ ነጋ ኣውሮፕላን ማረፍያ ማመላለስ ጀመሩ። ቁስሎኞቹ ወደ ዓይደር ሆስፒታል ሲገቡ በኣደጋው የሞቱት ደግሞ እየመጡ ናቸው ተብሎ ተወራ፤ የት እንደሚያርፉ ግን ኣልታወቀም። ህዝቡ ግን ከየኣቅጣጫው እየተመመ ወደ ህወሓት ባህል ቡድን ጽፈት ቤትና ወደ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ጽፈት ቤት ተጓዘ። ወደየጽፈት ቤቱ የሚጓዘው ህዝብ ፊት የሚነበበው ሃዘንና ቁጭት ካልሆነ በማሃከላቸው ንግግር የሚባል የለም ነበር።

ግን ደግሞ ለማን መሆኑ የማይታወቅ በየግሉ “ስስታሞች! ሌቦች! ለኣውሮፕላን ክራይ እንዳይከፍሉ ብርቅዬ ወገኖቻችን ኣስጨረሱዋቸው። 26ን ሰዎች እኮ 3 ኮብራዎች ይበቁዋቸው ነበር! ለራሳቸውማ ቢሆን ለኣንድ ሰው ኣንድ ኣውሮፕላን እያንቀሳቀሱ ኣይደለም እንዴ ይላሉ። ይህንን ኣባባል ህዝቡ፣ ነጋዴው፣ መንግስት ሰራተኞችና የህወሓት ኣባል ኣንድ ያደረገ ንግግር ነበር። በኣደጋው የሞቱት የህዝብ ወገኖች በቦታው ሳይደርሱ መሸ ። ህዝቡ ግን እነሱ እስኪገቡ ድረስ እያለቀሰ በፖሊስ ኦርኬስትራ ጽ/ቤትና በፖሊስ ኮሚሽን ጽ/ቤት ኣከባቢ ወደ ሚላኖ ሆቴል ኣከባቢ ሞልቶታል ። በማሃል የክለሉ ባለስልጣናት እነ ኣባይ ወልዱና ቴድሮስ ሓጎስ መጡና ሬሳውም ደረሰ ። በግዜው ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ ማልቀስ ጀመሩ። እዛ ኣጠገባቸው የነበሩ ሴትና ወንደ ወጣቶች ግን ለቀሰውን ትተው ኣስመሳዮች ማን ያምናቸዋል ማታ ማታ ለኣንድ ጠርሙስ ብሉ ለበል ዊስኪ (blue level whiskey) ከ6 እስከ 10 ሺ ብር ኣፍስሳችሁ ስትጠጡ ሳታፍሩ ይባስ ብሎ መጠጣቹ እንዳይጎድልባቹ ወንድሞቻችንና እህቶቻቹ በኣሮጌ መኪና ልካቹ ኣስገልብጣቹ ስታበቁ ኣሁን ማልቀሳቹ ለማስመሰል ነው እንጂ ማን ያምናቸዋል ይላሉ። ግዜው ጨልሞ ስለነበር የኣምቡላንስ መብራት ካልሆነ ምንም ኣይታይም ። የወጣቶቹ ንግግርም በድምጽ እንደሆነ እንጂ ፊታቸው ኣይታይም ነበር በዚህ ምክንያትም በተለይ ከወጣቶች መጥፎ መጥፎ ስድቦች ይደመጥ ነበር ። ኣዎ ወጣቶቹ ኣንድ ያመረሩት ነገር ኣለ እንጂ እንዲህ የህወሓት ባለስልጣናት ፊት ለፊት ተሰድበው ኣያቁም ነበር ምክንያቱ የሰደባቸው ካለ ኣይቀጡ ቅጣት ይጠብቀዋልና ነው።
ኣስከሬኖቹ ወደ ዓይደር ሆስፒታል ተወሰዱ። እዛም ብዙ ህዝብ ነበር የጠበቃቸው:: በክልሉ መሪዎችና በፖሊስ ሓላፊዎችም ላይ በግልጽ የስድብ መዓት ይወርድ ነበር። በወቅቱ በሁሉም ቦታዎች ነበርን። ከኔ ጋር ኣብረውኝ የነበሩ ሁለት ነባር ታጋዮች ለሞቱት የኪነት ቡድን ኣባላት ለኣንኣንደቹ ጎረቤትና በጣም ኣድናቂዎቻቸው ናቸው።
እኔም ለነባር የኪነት ቡድኑ ኣባላት በመመልመል እስከማሰልጠን ልዩ እንክብካቤ ኣድርጌ ስለኣሳደኩዋቸው እንደ ልጆቼ እማያቸው ስለሆንኩ ሁኔታው ስስማ ማመን አቅቶኝ ህልም ወይም ቅዠት ሁነብኛል። የኪነት ቡድን አባላት ለመኪና አደጋ ተጋልጠዋል፤ ከተገለበጡትም ወድያውኑ የሞቱት ብርሃነ ጋኖ፣ ለተመስቀልና ሃንደበት እንደ ሞቱ ሰማሁ። እንደሰማሁ ወድያውኑ መንገድ ይዤ ወደ ማሃል ከተማው ተጓዝኩ። ታክሲዎች ነበሩ ገንዘብም ቢሆን ነበረኝ ግን በእግሬ እጓዛሎህ ኣልናገርም ጸሓይ ነው 3 ኪሎሜትር እንደ ተጓዝኩ ኣሁንም ታክሲዎች ይተላለፋሉ እኔም ብሆን እጓዛሎህ ሳይታወቀኝ የኪነት ብዱኑ ጽፈት ቤት ጋር ደረስኩ። በቦታውም የሟች ቤተሰቦች በሌሉበት በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ ተሰብስቦ ሁሉም ያለቅሳል። እኔም ተቀላቀልኩ። ህዝብም በሁሉም ኣቅጣጫ ይመጣል።ከላይ እንደገለጽኩት ሁሉም ንዴትና ሓዘን በፊቱ ይነበባል። እኔም ከኣምስት ሰዎች ጋር ሁኜ ወደ ሚላኖ ሆቴል ደረስኩ ምክንያቱ የኣስከሬን ማረፍያ እዛው ነው ስላሉኝ። በሚላኖ ሆቴልና በትግራይ ክልል ፖሊስ ኮምሽን በኪነት ቡድኑ ጽፈት ቤት ላይ የነበረው ሁኔታ እዛውም ተመሳሳይ መንፈስ ኣለ። ዓይደር ሆስፒታልም ሄድን። በሺ የሚቆጠረውን ህዝብ ስሜቱ ተመሳሳይ ነው። ከዓይደር በጨለማ ተነስቼ ወደ ቤቴ ለመሄድ ታክሲ ላገኝ ኣልቻልኩም። ለዚህም በእግሬ ወደ ከተማ ተጓዝኩ። ኣብረውኝ ወደ ከተማ የሚጓዙ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ሁላችንም ኣንነጋገርም። ለየብቻችን ግን ንዴት የወለደው ብቻችን እንነጋገር ነበር። በንደዚህ ሁኔታ ሁነን መሃል ከተማ ገባን። በከተማውም መቀሌ እንደ ሁሉ ግዜዋ ኣይደለችም። ምክንያቱም ሁሉም ህዝብ አዝኗል። በየመጠጥና ሻሂ ቤት እንዲሁም ንግድ ቤቶች የሃዘን ሙዚቃ ይሰማል። ጸጥ ረጭ ብሎም ያደምጣል። ይህ መንፈስ ባለፉት ኣመታት ብዙ ታዋቂ ነባር ታጋዮችና ባለስልጣኖች፣ ታዋቂ ነዋሪ ግለሰቦች ሞተዋል። እንደዚህ ኣይነት ኣስደንጋጭ ሁኔታ ግን ኣልታየም። እንደ ገለጽኩት ታዋቂ ሰዎችንና ባለስልጣኖች ሲሞቱ በቀበሌና በየመስራቤቱ ተነግሮዋቸው የማይመጣ ብዙ ሰው ነው። በነዚህ ብርቅየ ኣርቲስቶች ኣደጋ ግን ከህጻን እስከ ሽማግሌ ራሱ ተነሳስቶ ኣስገራሚ የሆነ ትእይንት ኣሳየ። ግዜው መሸና ቤቴ ገብቸ ተኛሁ፤ ይሁን እንጂ እንቅልፍ ባኣይኔ ሊዞር ኣልቻለም። በዚህ ግዜ እኔም ማሰብ ጀመርኩ። የሮብን የቀብር በስነስርኣቱ ትእይንት ሳላይ ለኣደጋ ሰለባ የሆኑ የነበረው ኣቀባበል ኣሳሰበኝ። ለምን የመቀሌ ህዝብ በተለየ ለነዚህ ሚስኪን የህዝብ ልጆች ደነገጠና ተቆረቆረ የሚል ጥያቄ ኣነሳሁ። ብዙ የህወሓት ታጋይና ባለስልጣንም እነሱም በመቀሌ 20 ዓመት ተቀምጠዋል። ለምን እነሱ በተለየ ተወዳጅ ሆኑ የሚል ጥያቄ ደግሜ ኣነሳሁ። የያንዳንዱን ኣርቲስት የ20 ዓመት ጉዞም ገመገምኩ።ምክንያቱም እኔም ስለምወዳቸው ሁሉ ግዜ በሚሰሩበት ጽፈት ቤታቸው ሳልፍ ሰላምታ እንለዋወጥ ነበርን። ሻሂም ይጋብዙኝና ኣብረንም እንጫወት ነበርን። የምንጫወተውም ስላለፈው የትግል ግዜ፣ ስለ ጎስቋላ ኑሮዋቸው፣ መኖርያ ቤት የሌላቸው መሆኑን፣ ንሮኣቸው የተጎሳቆለ መሆኑንና በረሃ ከነበረ ሂወታቸው የተሻለ ኑሮ እንደ ሌላቸው እኔም ኣውቃለሁ እነሱም ያጫውቱኛል። እኔ የዓረና ኣባል በመሆኔ የሚደብቁኝ ነገር ኣልነበረም። እንዳውም እንደ ኣባት ቆጥረው ሁሉም ነገር ሳይሸማቀቁ ያጫውቱኝ ነበር። እንግዲህ እነሱ ይህን የሚያደርጉት ከዓረና ኣባል ኣብረህ ነበርክ ኣብረህም ትጫወታለህ በሚል ህዝብ ተሸማቅቆ እንዲርቅ በሚደረግበት ሁኔታ ነው እነዲህ እየቀረቡ የሚያጫውቱኝ።

እነዚህ ሰዎች 20 ዓመት በመቀሌ ተቀምጠው ምንም እንኳ በማህበር (በእጣ) ቤት ደርሶዋቸው መስራት የጀመሩ ቢኖሩም ኣብዛኛዎቹ ግን በቤት ኪራይ የሚኖሩ ናቸው። የነበረቻቸው የወር ደሞዝ ይቅርና ቤት ሊሰሩባት፣ ቤተሰብ ሊያግዙባት ለራሳቸውም ኣትበቃቀም ነበር። ለዚህ ኣብነት የብርሃነ ጋኖና የለተመስቀል እናቶች ፊት ያየ ሰው ራሱ ምስክር ነው። ሌላ ግን ከመቀሌ ህዝብ በኣጠቃላይም በትግራይ ህዝብ ፍቅር እንደ ነበራቸውና ራሳቸው ዝቅ ኣድርገው ሰው ኣክባሪ እንደነበሩ በህሊናዬ ማሰላሰል ጀመርኩ።

በሌላ በኩል በትግሉ ወቅት የነበራቸው የስራ ድርሻ ህወሓት የደርግ ስርዓት ደምስሶ ወደ ስልጣን እንዲወጣ የነዚህ ብርቅየ ኣርቲስቶች ቡድን የነበራቸው ወሳኝ ሚና ፈጽሞ ተወዳዳሪ የሌለው በስራቸው ውጤት ሲገመት በሻለቆች፣ ብርጌዶችና፣ ክፍለጦሮችና ኮሮች የማይገመት ትልቅ ስራ ሰርተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የህወሓት ካድሬዎች ብዙ ዓመታት ፖለቲካዊ ስራ ሰርተው ህዝብን ኣንቅተው ኣደራጅተው ወደ ትጥቅ ትግል ማስዘመት ያቃታቸው እነኚህ የህወሓት ኣርቲስቶች ግን ለኣንድ ወይም ሁለት ወር ወደ ህዝብ ገብተው የህዝብን ውስጣዊ ሁኔታና ስሜት በማወቅ በመዝሙር፣ ዘፈን፣ በድራማና ትያትር ወዘተ ኣድርገው በመቀስቀስ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የገጠርና የከተማ ወጣቶች ወደ ወታሃደራዊ ማሰልጠኛ ገብተው ሰልጥነው በየጦር ግንባር እንዲዘምት የማድረግ ኣቅማቸው ከፍተኛ እንደነበር በቅርብ እማውቀው ስለነበረ የነዚህ ሰዎች ትዝታ ጭንቅላቴን ረብሾት ኣደረ። ለነባር ሰራዊትም ለውግያ እንዲዘጋጅ ማነሳሳት በድህረ ውግያም ለማጽናናትና ኣእምሮን ለማደስ ትልቅ መሳርያ እንደነበሩ በወታሃደራዊ ፖለቲካዊ ማሰልጠኛዎች ለሰልጣኞች ከሚሰጣቸው ትምህርት ተስማሚ የሆኑ ቅስቀሳ በማድረግ በውጭም በኣገር ውስጥም ለሚኖረው ህዝብ ወደ ትግል እንዲዘምት በማድረግ ትልቅ ሚና እንደነበራቸው በህዝብ እጅጉን ተወዳጅ ያደረጋቸው ስለነበር ያ በትግል ወቅት ከህዝብ የተሰጣቸው ፍቅር ከደርግ ውድቀት በኋላም በመቀሌ ይሁን በሌሎች የክልሉ ዞኖችና በሌላ ክልሎች በነበራቸው ጭዋነት የተሞላበት ኣቀራረብ የፈጠረው ነው የሚል እምነት ያዝኩና የህዝቡ ሰልፍና የነበረው ሃዘን እነኚህ ሰዎች ባህርያቸው በህብረተሰብ ታማኝነትን ኣሰርጸው ስላለፉ ነው የሚል ስሜት ያዝኩኝ። ሰኞ መሽቶ ሲነጋ የመቀሌ ኖዋሪና የመንግስት ሰራተኞች፣ የግል ድርጅት ሰራተኞች በሁሉም የሚታይ በሃዘን ምክንያት ሲነጋገርም ስለብርቅየዎቹ ኣርቲስቶች እልቂት ነው። ሰኞ ቀንን ሙሉ በሁሉም ቦታ መቀሌ በተቃውሞ ሓሜት ተንጣ ዋለች። ከሓሜቶቹም

1. ከመቀሌ ካርቱም ከ3400 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ጉዞ ሲደረግ በኣየር ወይም በኮብራ መኪና ለምን ኣልሄዱም? ይህም በገንዘብ ሲለካ ከ100 ሺ ብር ኣይበልጥም።
2. በኣውቶብስ ከሆነስ ምን ኣይነት ኣውቶብስ? ምን ኣይነት ሹፌር? ብትበላሽ ጥገና ወይም ቅያሪ መኪና የኪነቶቹ ጤንነት የመጎሳቆል ጉዳይ ሂደው ምን ዓይነት ተጽኖ ይነሮዋል የሚል ለምን ኣልታሰበበትም
3. ኪነቶቹ የተከራዩዋት ኣውቶብስ በሰላም ባስ ኣክስዮን ማህበር ለብዙ ዓመታት ኣገልገላ ኣርጅታ ተብላ የተሸጠች ሹፌርዋም ያልታወቀ ለረካሽ ገንዘብ ብለው ለምን ተኮናተሩ? እንደዚህ ዓይነት ስራ የሰሩ ሰዎች መጠየቅ ኣለባቸው
4. ለምን የሰላም አውቶቡስ ኣልተከራዩም ? ከሰላም አውቶቡስ ጋርም ኮንትራት ጠይቀው ውድ ሆኖብናል ብለው እንደተውት ተብሎም ይወራል። በመሆኑም በነዚህ ሰዎች እልቂት ተጠያቂ ሰው መኖር ኣለበት። የሚል ማጉረምረምና ስድቦች ማክሰኞ ስታስተናግድ ዋለች።
የኔ እምነትም ህዝቡ ከላይ ካነሳቸው ጥያቄዎች ጋር ነው የምስማማው። ከመቀሌ ካርቱም ቢያንስ ደርሶ መልስ 3400 ኪሎ ሜትር ነው። ከዛ የሚቀጥሉ ከሆነም ይጨምራል። ታድያ እንዴት ቢያጠኑት ነው ጉዘው? እነኚህ ኣርቲስቶች በሺዎች የሚቆጠር ኪሎሜትር ርቀት በመኪና ተጉዘው ደክመውና በሙቀት ተቃጥለው ምን ሊሰሩ ነው የሚል ጥያቄ በትክክል በመሪዎች መነሳት ነበረበት። ሌላም እነዚህ ሰዎች የትግራይ ህዝብ ሃብትና የብዙ ኣሴት ማህደር ናቸው። ከሁሉም ኣደጋ ሊጠነቀቁላቸውና ሊንከበከብዋቸው ይገባ ነበር። ለባጀት ቁጠባ ከተባለ በዚህ ክልል ያለው የገንዘብ ኣጠቃቀም ኣባካኝ መሆኑና ለብዙ ግብዣና ቅንጦት እንደሚውል ህዝብም የህወሓት ኣባላቶቹም ራሳቸው መሪዎቹም ያውቁታል። ለምን ለዚህች ትንሽ የ26 ሰዎች 100.000 የማይፈጅ በጀት ወደ ሱዳን ደርሶ መልስ ስንት ነው ለኣንድ ሰው 10 ሺ ቢሆንም በጠቅላላ ቢያወጡ 260.000 ብር ነው። ይህ ገንዘብ ለነዚህ ብርቅየ ወንድሞቻችን ቢከፈል ምን ጉዳት ይነሮዋል? ባለ ስልጣኖች በመቀሌ ከተማ ብሉ ለበል ዊስኪ ለኣንድ ማታ ከ6ሺ እስከ 8ሺ ገዝተው የሚጠጡ የማያሰቡ ባለ ስልጣናትም ኣሉ።

እነ ጋኖና እነ ሃንደበት እኮ ከነ ሱራፊኤል፣ መሰረት ስቡሕ (ጠርጣራው)፣ ተወልደ ጅቡቲ፣ ገብረጻድቅ፣ ሙሉጌታ ኣብረሃ (ወዲ ሰርጀንቲ)፣ ሙላው፣ እያሱ በርሄ፣ ወዲ ሰቦቃ፣ ምሕረት፣ ቀለም ማንጁስ፣ ነጻነት (እጅጋዮህ ዮውሃንስ)፣ ብርሃነ ጎበዛይና ብዙ ኣየነ ወዘተ ከላይ እንደጠቀሰኩት እንደ ሺዎች ካድሬዎች፣ ኮሮችና ክፍለጦሮች እንደሚሰሩት ሁሉ የማይተናነስ ሰራ ሰርተው ደርግን በመደምሰስ የነበራቸው ሚና እጀጉን ከፍተኛና የተከበሩ ነበሩ። ስለዚህ የነዚህ ሰዎች ሞት አግዚኣብሄር የፈቀደው እደሜያቸው ስለደረሰ ነው ተብሎ መታለፍ የለበትም። በነዚህ የታየው የጥንቃቄ ጉድለት ብዙ ህጻን ሽማግሌ ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ገድለዋል ወይም ወደ ኣደጋ ጥለዋል። ብዙ ሞያዎችና ልምድ ለትውልድ ሳያሳልፉ በእንዳ ገብሪኤል ተቀብረዋል። በ21ኛው ክፍለዘመን ሰውና ሙያው በጣም ውድ ነው።
ሌላም እነኚህ የኪነት ኣባላት ወደ ሱዳን ሊጓዙ ሲታቀድ ኣሁን እንደተረዳሁት በፌደራል፣ በክልልና በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ታውቀው ኣገር ከኣገር ተስማምተው ኣገር ወክለው የሚሄዱ ናቸው። ለምን ፕሮተኮላቸው ጠብቀው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዝግጅት ተደርጎላቸው ኣልተጓዙም? ጥያቄው ለትግራይ ክልል ባለስልጣኖች ብቻ የሚተው ኣይደለም። ይህ ጉዳይ ለትግራይ ህዝብ ያበሳጨውና እንዲቃወም ያደረገው ይህም ጭምር ነው። በኔ እምነት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ድርጅቶችና ሚኒስቴሮችም ተጠያቂ መሆን ኣለባቸው የሚል እምነት ኣለኝ።
ሌላ ለነዚህ ኣገር ወክለው እየሄዱ ያሉ የኣርቲስት ቡድን የጉዞ ዋስትና፣ ፓስፖርቱ፣ እዚያው ሂደው የሚያርፉበት እየኣንድ ኣንዱን በጀት፣ ለጤንነታቸው፣ ሓኪም የኣገሩ ኣየር ጠባይ ወዘተ ተጠንቶ መፈጸም ነበረበት። ግን እሚያሳዝነው እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ነገሮች ማሟላትስ ይቅር ስለ ኣንድ ኣሮጌ ኣውቶብስም ሊያጠኑ ኣልቻሉም። ከላይ እንደገለጽኩት ሦስት የተመቹ ኮብራዎችም ይበቁዋቸው ነበር ግን ኣልተደረገም። የሚገርመው በኣሁኑ ግዜ ኮብራ ቅመምና በርበሬ ልትገዛ በመርካቶና በክልል ከተሞች ነው ስትሽለኮለክ የምትታየው። ግለ ሰቦችኮ ከሁለት ሦስት ኮብራዎች በላይ ያሰማራሉ። ችግሩ ግን የህወሓት/ኢህኣዴግ ባለስልጣኖች ህዝብ መስታዎት ነውና ህዝብ ይታዘበናል የሚል ኣሰተሳሰብ ከጭንቀላታቸው ከፋቁት ብዙ ኣመታትን ኣስቆጥረዋል።

የቀብሩ ዋዜማ በመቀሌ ከተማ ህዝብ የነበረው ተመልክተናል። ሮብ (የመስቀል) ቀንስ ከጥዋት እስከ ማታ አንዴት ኣለፈች? ትእይንቱ ምን ነበር?
ዕለተ ሮብ ከጥዋት እሰከ ማታ የነበረው ትእይንት
ማክሰኞ መሽቶ ሲነጋ ሮብ 17 መስከረም የተፈጥሮ ዑደት ነውና ተረከበቻት። ይህቺ ቀን ድሮ የመቀሌ ነዋሪ ህዝብ የመስቀል በዓል ለማክበር ጥዋት ተነስቶ ወደ ሰውሒ ንጉስ የመስቀልና ጥምቀት የሚከበርበት ሜዳ ዳሜራ ለመሳተፍ ያለችው ልብስ ለብሶ ሲጓዝ ይታይባት ነበር። የዘንድሮ መስቀል ግን ወደ መስቀል ዳሜራ እንደ መሄድ ፈንታ ጉዞው በሰውሒ ንጉስ ኣጠገብ ወደ ሚገኘው የህወሓት ባህል (ፖሊስ ኦርኬስትራ) ጽ/ቤት እንደ ገመድ ተሳስሮ እያለቀሰ እንደጎርፍ ተመመ። የነዛ ጀግኖች ኣርቲስቶቻችን ኣስከሬንም እዛው መጥቶ ሙሉ ስርዓተ ፍትሓት ሲደረግላቸው ኣረፈደ።
የተከበራቹ ኣንባብያን! ባለፉት 20 ዓመታት ታዋቂ ግለሰቦች ሲሞቱ ወይም የፖለቲካ ባዓሎች ሲከበሩና ስብሰባ ሲደረግ በየቀበሌውና በየወረዳው ትእዛዝ እየተሰጠ ተሰለፉ! ቅበሩ! ተሰብሰቡ! እየተባለ ሰው በግድ ነበር የሚወጣው። በየመስሪያ ቤቱም በትእዛዝ ነው የሚወጣው። የሚወጣው ህዝብም በጣም ኣነስተኛ ነው። እስካሁን ያየናቸው ሰልፎችና ቀብሮች ህወሓት/ኢህኣዴግ እንዲሁ ሳይሰለች በ1984ዓ.ም የየካቲት የህወሓት የምስረታ በዓል ቀበሌ፣ ሲከበር፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ዋዜማና ከድል በኋላ የተደረጉ ሰልፎች ብዙ ይባሉ ነበር ያም በግድ በቀበሌና በወረዳ ተጎትጉቶ። የነዚህ ብርቅየ ጀግኖች ኣርቲስቶቻችን ቀብር ግን የመቀሌ ከተማ የቀጠና፣ ወረዳ መሪዎችና ካድሬዎች ስራ ያስፈታቸው ክስተት ሁኖ ታየ። የመቀሌ ህዝብ ግን ራሱ ኣምኖበት ብቻ ሳይሆን ያ ጉዳይ ዘግናኝና ኣሰደንጋጭ፣ ያለ ጥናት የተሰራ፣ እነዛ ኪነቶች በህዝብ ኣይንና ልብ ገብተው ተወዳጅ በመኖራቸውና በስርኣቱም ተሰሩት ስራ ግምት ሳይሰጠው በዝቅተኛ ኑሮና ድህነት ውስጥ የነበሩ በመሆናቸው ቆጭቶት ማንም ሰው ና ውጣ ሳይለው ከመቀሌና ኣከባቢዋ፣ ከዞኖችና ወረዳዎች ቁርስ ሳይበላ በየኣከባቢው የመስቀል ዳሜራ ሳያከብር ሰውሒ ንጉስና የመቀሌ ጎደናዎች በሙሉ በህዝብ ተጥለቀለቁ። ኣስከሬኑ ገና ሳይነሳ ህዝቡ ተሰልፎ ስርዓተ ፍትሓቱ እየተገባደደ ነው። ሰው ሁሉ በለቅሶ እያረረ እምባውም እየፈሰሰ ኣሳዛኝ ገጽታ ይታይ ነበር።

ሰኣቱ ከተባለለት 3 ሰዓት እያለፈ ነው። ምክንያቱም የህወሓት ባለስልጣኖችና ሌሎች ቀባሪዎች ከኣዲስ ኣበባ እየመጡ ነው ተባለና ቆይተው በቦይንግ ተጭነው ብዙ ሰዎች መጡ። ብዛት ያላቸው የህወሓት ባለስልጣኖችም በተሰለፈው የህዝብ ማሃል ሰንጥቀው ገቡ። ግራና ቀኝ የነበረው የህዝብ ሰልፍ ሓሜትና ጥላቻ እንዲሁም ስድብ ከህዝቡ ፊት ያነቡ ስለነበረ ኣንገታቸው ደፍተው ኣንጠርምመው ኣስከሬኑ ወደ ኣለበት ገቡ። ቆየት ብለው ከህዝቡ ጋር ተፋፍነው ለመጓዝ ጠልተው ነው መሰል ወይም ሌላ ምክንያት ይኖራቸዋል ኣይታወቅም ተመልሰው ኣሁንም ወጡ። ሲመለሱ ሓሜት ቀርቶ ስድብም ነበር። ግን እነሱ ሰምተው እንዳልሰሙ ሄዱ። የኣገር መከላከያ ሰራዊት እጅጉን በብዛት ነበረ። መከላከያው ሰራዊቱ ሓዘን እንደተሰማው ከፊቱ ይታያል።

ሌላ የሟች ቤተሰቦች ከተምቤን፣ ከቆቦ፣ አላማጣ (ራያ) ከኣክሱም፣ ከሸራሮ በብዙ ኣውቶብሶች ሞልተው መጡ። ብዙ ሳይቆዩም ኣስከሬኑ ጉዞ ቀጠለ። መንገዶቹ ጠበቡ፣ ሰው ተጨናነቀ። የከተማው መንገዶች ሁሉ በተጓዥ ሞሉ። ወደየሰማእታት ሓወልት በሁሉም ጎደናዎች ተከፋፍሎ ተጓዘ። የሰማእታቱ ግቢ ከመጣው ህዝብ 1 ከመቶም መያዝ ኣልቻለምና ህዝቡ ወደ እንዳገብሪኤል ጫካ ኣልፎ ለመቆየት ተጓዘ። ያም ቦታ ህዝቡ ሊይዘው ኣልቻለም። በሁሉም ጎዳናዎች በጠራራ ጸሓይ ቆመ። በሓወልት የነበረ የኣስከሬን ሽኝት ስነ ስርዓት ረዘመ። ህዝብም በጸሓይ ደከመ። የአቡነ ጳውለስ ንግግር ኣዳመጥንና ቀጥሎም የክልል መሪያችን ኣቶ ኣባይ ወልዱና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድህንነት ኣማካሪው ኣቶ ጸጋይ በርሄ መግለጫ ሲሰጡ ብዙ ህዝብ ተበሳጭቶ ከነበረበት እየፈረሰ ወጥቶ ወደ እንዳ ገብሪኤል ሄደ። ኣንድ ኣንድ ሰዎችም ጮክ ብለው በመናገር ኣስመሳዮች ኣታጭበርብሩን ራሳችሁ ገድላችሁ ስታበቁ ቀብሩን ወደ ፖለቲካ ማራመጃነት ቀይራችሁ ኣታጭበርብሩን ሲሉ በኣከባቢው የነበሩ የህወሓት መሪዎች ደንግጠ0ው ሁሉም ኣንገታቸው ደፉ። በግዜው ከኣጠገባቸው ብዙ ካድሬዎች ነበሩ። ለነዛ ሲሳደቡ ለነበሩ እውነታቸው ነው የሚሉ ነበሩ። ሲቪል ለባሽ ደህንነትም ነበሩ። ህዝቡ ግን ፍርሓት ኣልነበረውም ድህንነትም ሰምተው እንዳልሰሙ ክትትላቸውን እየቀጠሉ ከህዝብ ኣብረው ማማት ጀመሩ። በሌላ ስራም ይህን ባህል ቢያዳብሩት ኣይከፋም።

ሌላ የነበረው ስድብ ለፖለቲካ ፍጆታ ነው የመጣችሁ እንጂ ኣዝናቹ ልትቀብሩ ኣልመጣቹሁም። ሓቀኞች ብትሆኑ ለገንዘብ ሳትሳሱ ወጪ ብታወጡና በኣውሮፕላን ቢሄዱ ልጆቻችን ኣይጠፉም ነበር ስስታሞች ናችሁ። ለቦይንግ ኣውሮፕላንና ለሄልኮፕተርና ለኣበላቱ ለሆቴል በኣጠቃላይ ለቀብር ማስፈጸምያ ስንት ሚልዮን ብር ጠፋ የሚል ንግግር ሁሉም ቀባሪ ህዝብ ነው የሚናገረው ህጻናትም ጭምር። ሌላ ቀርቶ በኤፍ ኤም መቀሌና ኤፍ ኤም ፋና ህዝቡ በስልክ እየደወለ ወንድሞቻችን በኣሮጌ መኪና ደፋቹሃቸው፤ መንግስት ካለ እነሱን በዚይ መንገድ ያሰማሩ ሰዎች ይጠይቁልን። ለኣንድ ሰው ኣውሮፕላንና ሄልኮፕተር እያንቀሳቀሳችሁ ለነዚህ ኣንድ ኣውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር ለምን ኣልመደባችሁም። ለዘር ማንዘራችሁ በሚልዮኖች እየከፈላቹህ እያሳከማቹሁና እያስተማራችሁ ለነዚህ ብርቅየ ልጆች ከትግራይ ካርቱም ድረስ ያውም ለመንግስት ተልእከሎ ሊፈጽሙ የኣውሮፕላን መጓጓዣ መመደብ ለምን ተሳናችሁ? የሚሉ ኣስተያየቶች ይሰነዘሩ ነበር። በቀብሩ ስነስርዓት የ10 ዓመት ዕድሜ ህጻናት ሳይቀሩ ነበሩ። ሌላ ቀርቶ ወጣት ሴት ልጆች ወደ ቀብር መሄድ የቅርብ ዘመድ ካልሆኑ በስተቀር ወደ ቀብር ወጥተው ኣያውቁም ነበር። በኣርቲስቶቹ ቀብር ግን የሚበዛው ወጣት ሴቶችና ወንዶች ነበሩ።

የኣርቲስቶቹ ቀብር ኣንድ ኣንድ ሰዎች ተቃውሞ ሰልፍ ነው ወይስ ተራ ቀብር እያሉ ጥያቄ የሚያነሱ ብዝዎች ናቸው። በኔ በኩልም ይህ ጉዳይ ቀብርም ተቃውሞ ሰልፍም ነው የሚል እምነት ኣለኝ። ምክናያቱም
1. ህዝብ በምሬት ኣዝነዋል። ለምን? የሚወዳቸው ልጆቹ በመቀሌ ከተማ እየተቀበሩ ነውና በተጨማሪም እነዚህ ኣርቲስቶች በህብረተሰቡ ውስጥ በሁሉም ኢኮኖምያዊ÷ ማህበራዊና ባህላዊ ችግሮችና ሁኔታዎች እንዲሁም በሃዘንም በደስታም ተሳታፊ ስለነበሩ ነው።
2. ተቃውሞም ነው። ምክንያቱም ለምን በኣውሮፕላን ኣልሄዱም? ለምን እንክብካቤ ኣልተደረገላቸውም? ድሆች ከሆንም ለመሪዎችና የት ነበሩ ለማይባሉ ካድሬዎች እንክብካቤ ይደረጋል። በኣጠቃላይም ህወሓት ለፍተውና ተዋግተው ኣካላቸው ጎድለው ወደ ስልጣን ያመጡዋቸው ታጋዮች እንክብካቤ ኣያደርግም። ኣሁን መጥተው ያሉ መሪዎችም በህዝብ ተቃውሞ ስላለ ለፖለቲካ ፍጆታ ነው የመጡ የሚል ተቃውሞ ነው። በሌላ በኩል በዚህ ከተማ ከባድ የኑሮ ውድነት፤ ስራ ኣጥነት፤ የውሃ ችግር፣ የሙስናና ብልሹ ኣስተዳደር ስላለ ተጨማሪ ስሜትም ስላለው ነው። እዚህ ላይ በቀብሩ ስነ ስርዓት ለነበሩ መሪዎች ትልቅ ቅጣት ነው ያጋጠማቸው። ህወሓቶች ግን ሁሌ ከጥፋታቸው ኣይማሩምና ለዚህ የህዝብ ጥያቄና ቁጭት ለማለሳለስ በቀብሩ ስነስርዓት ማግስት በየቀበሌው ካድሬዎችን በመሰብሰብ ሁሌ እንደተለመደው ባህሪያቸው ችግሮቻቸውን በሌላ ኣካል መለጠፍ ይህም ለዓረና ትግራይ እነዚህ ነፍጠኞችና የነፍጠኛ ኣሽከሮች ኣርቲስቶቹ ለምን በኣውሮፕላን ኣልተላኩም እያሉ በሚያናፍሱት ወሬ ህዝብ እያደናገሩ ነው ስለዚህ በትግራይ ህዝብ ንፋስ አንዳይገባ ተጠንቀቁ እያሉ ያስፈራራሉ።

ኣስከሬኑ ወደ መቃብሩ ደረሰ
ሁሉም ቀባሪ ወደ ኣስከሬን ማረፍያ ጉድጓድ ተጠግቶ ከበበው። ሴቶቹም ወደ መቃብር ኣከባቢ መጡ በህጉ ሴት መጠጋት የተከለከለ ነው። ኣሁን ግን እጅግ ብዙ ወጣት ሴቶች ከወንዱ ተደባልቀው ወደ መቃብሩ መጡ። ሴቶች ልቀቁ ሲባሉ ኣንለቅም ኣሉ። ከፊታቸውም ከባድ ቁጣ ይነበብ ነበር።

የህወሓት መሪዎች ወደ መቃብሩ ኣበባ ሊያስቀምጡ ሲመጡ ከወጣቶች ይወርድ የነበረ ስድብ ከተራራ እንደሚወርድ የድንጋይ ናዳ ይመስል ነበረ። ይህ ምን ያሳያል? ለህወሓት መሪዎች የማስጠንቀቅያ ቢጫ ካርድ ነው ከልብ ካዳመጡት።
የቀብር ስነ ስረኣቱ ህዘቡ ከ12 ሰዓት ጥዋት እስከ 7ሰዓት ከ30 ጸሓይ መታኝ ውሃ ጠማኝ ራበኝ ደከመኝ ብሎ ሳይሰለቸው በህዝብ ሓዘንና ንዴት ተፈጸመ። እዚህ ላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ያለ ምንም ኣስገዳጅ ይህን ያህል ቁጥር ያውም ካሁን በፊት ታይቶና ተሰምቶ በማያውቅ መንገድ ተገባደደ።

የቀብሩ ስነ ስርዓት ከተገባደደ በኋላ ምክንያቱ ባልታወቀ ጥዋት ያልነበሩ ብዙ ፌደራል ፖሊሶች ወደ መቃብሩ ባለስልጣኖች ወደ ኣሉበት መጡ። ህዝቡ ምንም ደንታ ሳይሰጣቸው መንገዶች ጠበውት ለማለፍ ተቸግሮ በየኣቅጣጫው በየቤቱ ሄደ። ባለ ስልጣኖቹም በብዙ ወታሃደሮች ታጅበው ተጓዙ። ወደ ማሃል ከተማ ስንመለስ ሁሉም ሴቶች የኩታቸውን ጥለት ወደ ላይ ኣድርገው ለብሰው በተለያየ ስራቸውን ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ። ለምን ሆነ የሚል ጥያቄ እነኚህ ኣርቲስቶች ራሳቸው በበጎ ተግባራቸው በህብረተሰቡ ተወዳጅነት ስለፈጠሩ ነው።

ከቀብር በኋላ ህዝቡ ምን ይላል?
ሁሉም ሰው ከወጣት እስከ ሽማግሌ የነዚህ ሰዎች መጥፋት ተጠያቂዎች መኖር ኣለባቸው የሚል ጥያቄ ኣለ። እነዚህ ኣርቲስቶች ለጉዞ ተነሱ ሲባሉ እንደነ ሃንደበት ያሉ ለምን በኣውሮፕላን ኣንሄድም? ወደ ሱዳን በመኪና ጉዞ ለጤናችንም ጥሩ ኣይደለም፣ ለኣደጋም ተጋላጭነት ኣለው፣ ምክንያቱም ከኣሁን በፊት ወደ ሱዳን ተጉዘን ብዙ ችግር ኣጋጥሞናል የሚል ሓሳብ ቢሰጡም መሪዎቹ ግን ለኣውሮፕላን የሚሆን በጀት የለንም እንዳሉዋቸው ህዝቡ ይናገራል።
ገብሩ ፋኖ የሚባል ኣርቲስት ግን ፍጹም ጠንክሮ በመቃወም ያ የመኪና ለትራንስፖርት የተመደበ በጀት ስጡኝና የራሴን ጨምሬ በኣውሮፕላን ልሂድ ካልበለዚያ በመኪና ኣልሄድም ብሎ እንደቀረ ህዝብ ኣውቀዋል። ይህም በህዝቡ መጥፎ ስሜት ፈጥረዋል።

በሌላ በኩል እነኚህ ኣርቲስቶች ለሰላም ባስ ኣክስዮን ማህበር ኣውቶብስ ኩንትራት ጠይቀው እንደ ነበሩና ዋጋው ውድ በመሆኑ ባጀት የለንም ብለው መልስ የሰጡዋቸው ህዝብ ስላወቀው ሓዘኑንና ንዴቱ ኣባባሰው። ግን እነዚህ ባለ ስልጣኖች ለምን እስከዚህ ድረስ ሳሱ? በትግራይ ክልል በብዙ ሚልዮን ብር በሙስና ይመዘበራል። ሌላ በማስፈጸም ኣቅም ማነስና በላሸቀ ኣስተዳደራቸው ምክንያት ከ2003 ዓ/ም የክልሉ 3.1 ቢልዮን በጀት የ በጀቱ 30% የሚይዝ (930 ሚልዮን) ብር ወደ ማእከላዊ መንግስት ፈሰስ ሁኖ የለም እንዴ? ሌሎች የህወሓት ድርጅቶች በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ኣለ ኣይደለ? እነዚህ ሰዎች ለምን ከሕይወት ይልቅ ገንዘብ ለማካበት ይሳሳሉ? ለገንዘብ እኮ ሰው ነው የሚያመጣው። ኣሁን ሊሄዱበት ታስቦ በነበረው የሱዳኑ ፌስቲቫል ቢያንስ ለጉዞዋቸው ሊሸፍን የሚችል ሽልማት አያጡም ነበር። ግን የሆነውን ሆነዋልና የሚጠየቁ ይጠየቁ። ኣሁን ቤተሰቦቻቸውና ልጆቻቸው የወደፊት እጣ ፈንታቸው ምን ይሁን?

በኔ እምነት የህዝብም ስሜትና ፍላጎት ሊሆን የሚችል እነዚህ ኣርቲስቶች ከበረሃ እንደገቡ የራሳቸው የልጆቻቸውና ቤተ ሰቦቻቸውም በኣኗኗራቸው ምንም ለውጥ የላቸውም። ኣብዛኛዎቹ እስከ ኣሁን የራሳቸው መጠለያ የላቸውም። ጥቂቶቹ ቦታ ኣግኝተው ሊሰሩት ያልቻሉ ናቸው። በነበረች የወታደር ደሞዝም ይቅርና መጠለያ ለመስራት ንሮዋቸው ለመግፋትም ኣታስችልም። የነዚህ የሙታን ልጆች ልትሰጣቸው የምትችል የጥሮታ ኣበል ናት እሷም ትርጉም ያላት ኣይደለችም።
የኔ ኣስተያየት የህወሓት/ኢህኣዴግ መሪዎች በትክክል ኣዝነው ከሆነ ጃኬት ሻርፕና ኮፍያ ለብሰው በኣውሮፕላን ተጉዘው በሓዘን መገኘቱ ጥሩ ነገር ነው። ግን ይህንን በቂ ኣይደለም። ያለፈው ወንጀል እንዳለ ሁኖ መታሰብና መተግበር ያለበት የነዚህ ጀግና ኣርቲስት ልጆችና ቤተሰቦች መጠለያ፣ ምግብ፣ ውኃ፣ ህክምናና ትምህርት የሚያገኙበትን ዕድል ቢያፈላልጉላቸው ሁሉም ዜጋም ለነዚህ ሰዎች እጁ ከመዘርጋት እንደማይቆጠብ ተስፋ ኣለኝ። የህወሓት መሪዎችም የሚሰበሰብ ገንዘብ እንዳይባክን በህዝብና በሟች ቤተሰቦች እንዲሁም በሌሎች ድርጅቶች ኣንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ ገንዘብ ተሰብስቦ ለዘለቄታ ህጻናት ልጆቻቸውም ለመጻኢ ዕድላቸው ቢታሰብላቸውና ቢሰራላቸው ለህወሓት/ኢህኣዴግ ለህዝብም ለመንግስትም መልካም ነገር ይፈጥራል። የሚሰበሰበው ገንዘብ ግን ጥብቅ ቁጥጥርና ግልጽነት እንዲሁም ተጠያቂነት ባለበት ማንም ድርጅትና ግለ ሰብ እጁ በማያስገባበት መፈጸም ኣለበት። ከኣሁን በፊት የነ ሓየሎምና ሌሎች የተሰዉ ታጋዮች ከሰራዊትም ከህዝብም ብዙ ሚልዮን ብር ተሰብስቦላቸው ነበር። ብዙ ሓሜት ኣለ። የነዚህም እንደዛ እንዳይሆን ከሓሜት የጸዳ መሆን ኣለበት። በነዚህ ሰዎች ስምሪት ተሳታፊ የነበሩ ባለ ስልጣኖችም ኣስፈላጊውን እርምት ቢሰጣቸው የህዝብን ቁጣ ሊያበርድ ይችላል።

ክብርና ሞጎስ ምንም ሳያልፍላቸው ለተሰዉ የህዝብ ልጆችና ኣርቲስቶች!
ለቤተሰቦቻቸው ደግሞ ብርታትና መፅናናትን እመኛለሁ!

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
October 3, 3022

በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ከአቶ ስዬ አብረሃ ጋር በቦስተን

Saturday, September 17th, 2011

የቦስትን አንድነት የድጋፍ ድርጅት በውቅታዊ ህገራዊ ጉዳዮች ላይ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማወያየት የውይይት ፎረም አዘጋጅታል
Date: Sunday Sept. 18, 2011
Time: 3:00PM
Place: 402 Rindge Ave. Community Rm.
Cambridge, MA

ተጋባዥ እንግዳ አቶ ስዬ አብራሃ
ለበለጠ፡መረጃ፡617 461 4992

አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋ ታሰሩ

Wednesday, September 14th, 2011

(UDJ) — ዛሬ ከቀኑ አሰር ሰዓት (10፡00) አከባቢ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አንዱዓለም አራጌ በአገዛዙ የደህንነት ሰዎች ታስሮዋል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም ተይዞዋል፡፡ አንዱዓለምና እስክንድር ከሌሎች ሁለት የአንድት ፓርቲ አባለት ጋር ከቀኑ 8፡30 ገደማ ጀምሮ አንድነት ፓርቲ አከባቢ በሚገኝ ካፍቴሪያ አከባቢ እሰከ 9፡30 ገደማ አብሮ ሲጫዎቱ ነበር፡፡

አንድነት ፓርቲ የራሱን ስትራቴጂ ነድፎ፣ በጠራ የትግል አቅጣጫና በከፍተኛ የትግል ሞራል በመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ ትግሉም የራሱ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ትግሉ አምባገነኖች ሊቀለበሱት ወደማይችሉበት ደረጃ በተቻለ ፍጥነት ማድረስ ያስፈልጋል፡፡

ለዚህም አንድነት በጀመረው የሠላማዊ ትግል መንገድ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ለነፃነትና ለዴሞክራሲ ለሚደረገው ትግል፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በህብረት በመነሳት በሀገራችን አምባገነንነት ለአንዴና ለመጨረሺያ ጊዜ እንዲያበቃ መታገል ያስፈልጋል፡፡

የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ድብደባ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተወሰነ

Wednesday, August 31st, 2011

(ፍኖት) — የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ድብደባ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተወሰነ።

“በሽብርተኝነት” ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮና ርዕዮት ዓለሙን ታስረው በሚገኙበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ጠይቀናቸው ነበር፡፡ ተጠርጥረው በታሰሩበት ። “የሽብርተኛ ድርጊት” ስለተባለዉ የሚያውቁት ነገር መኖር አለመኖሩን ጠይቀናቸው ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ውብእሸት ሲመልስ “የቀረበልኝ ጥያቄ በተደጋጋሚ የብተና ፖለቲካ አያልክ ትጽፋለህ፡፡ በታኙ ማን ነው፡፡ ብተና የሚፈልገው ማነው? መንግሥት ኮሚኒኬሽን ሰርገህ ለመግባት የፈለክበት ምክንያት ምንድነው? ውጭ አገር ከሚገኝ አንድ ሚዲያ ጋር ለምን ትገኛለህ? የሚሉ ናቸው፡፡ “ሽብርተኝነት” የሚለውና “ንብረት ሊያወድም” ነበር፡፡” የሚለውን የሰማሁት በሚዲያ” ነው ሲል መልሷል፡፡

ጋዜጠኛ ውብእሸት /እየሳቀ/ “ከቤቴ ለምርመራ የተወሰዱት መጽሐፍት እነ ተክለጻዲቅ መኩሪያ የጻፉትን የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡ በዚህ ላይ የእኔ ጥፋቱ አልገባኝም፡፡ እየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል የሚያሳይ የስቅለት ፊልምና እና ልጄ ሁለተኛ ዓመት ልደቱን አክብሮ ድክ ድክ ሲል የተቀረጸ ፊልም ለምርመራ ብለው ከቤቴ ወስደዋል፡፡ ምናልባት እየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል እጅህ አለበት፡፡ ልጅህም በሽብርተኝነት ይጠረጠራል አንዳይሉኝ እሰጋለሁ፡፡” ሲል በለሆሣስ ገልጾታል፡፡

በመጨረሻም ጋዜጠኛ ውብሸት “የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉደዮች ጽ/ቤት ሠራተኛ ይቀጠላል በመባሉ የትምህርት ማስረጃና የሥራ ልምዴን ከማመልከቻ ጋር አስገብቼ ነበር፡፡ ሳይሳካ በመቅረቱ ቀርቷል፡፡ እኔ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሥራ የመወዳደርና የመቀጠር መብት አለኝ ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ዛሬ ወንጀል ሆኖ ለምን መስረግ ፈለክ ተብሎ በምርመራ ወቅት መጠቀሱ አሳዝኖኛል፡፡ በእስር ላይ እያለሁ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞብኛል፡፡ የግራ ጆሮዬ ከፍተኛ ህመም ይሰማኛል፡፡ በትክክልም አይሰማም” ሲል በሐዘኔታ ገልጾታል፡፡

በኖርዌይ የኢትዮጲያውያን ስደተኞች ሪፖርት

Monday, August 15th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ርዮት አለሙ በሕመም ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ!

Saturday, August 13th, 2011

(ፍኖት) – «በሽብርተኝነት ተጠርጥራ.» በፌደራል ወንጀል ምርመራ በእስር ላይ የምትገኘው ጋዜጠኛና መምህርት ርዮት ዓለሙ በህመም ላይ እንደምትገኝ ወላጅ አባቷ አቶ ዓለሙ ጐቢቦ ለፍኖት ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገለጹ፡፡ አቶ ዓለሙ እንዳሉት ርዮት በህመም ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ መድኃኒት ገዝተዉ እንዳስገቡላትም ገልጸዋል።። ሰውነቷ በህመም መጐሳቀሉንና ሐሳቧም በእጅጉ ከመበታተኑም በላይ ከዚህ በፊት ያልነበረባት የመዘንጋት ባህርዬ የተፈጠረባት መሆኑን የገለጹት አባቷ «ጤንነቷ በጣም አሳስቦናል..» በማለት ጭንቀታቸዉን ገልፀዋል፡፡

ርዮተ ዓለሙ በቋንቋ መምህርነትና በትያትርና ሥነ ጥበብ ሁለት የመጀመሪያ ዲግሪዎች ያላት ሲሆን በ2004 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኢትዮጵያ ሁለተኛ ዲግሪዋን /ማስተርስ/ ለመማር ተመዝግባ እንደነበር ከቤተሰቦቿ መረዳት ተችሏል፡፡

ርዮት ዓለሙ እናቷንና እህቷን የምታስተዳድር ሲሆን በመታሰሯ ምክንያት ደሞዟ መቋረጡን ከቤተሰቦቿ የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የፎነት ለነጻነት እትም ሁለት በሙሉ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የታሰሩ ጋዜጠኞችና የፓርቲ መሪዎች በድጋሚ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸዉ

Monday, August 8th, 2011

(ፎኖት) — ሽብርተኝነት” ተጠርጥረው በፌደራል ወንጀል ምርመራ ታስረው የሚገኙት የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ም/ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዮት ዓለሙ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ/ኢብአፓ/ ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚሐብሄርና የኢብአፓ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ደጀኔ ተፈራ ፓሊስ የምርመራ ጊዜን አለጣናከኩም በማለት በመጠየቁ በድጋሚ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተስጥቶታል፡፡

ባለፈው ሐምሌ 11 ቀን 2003ዓ.ም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት ውብሼት ታዬ፣ ዘሪሁን ገ/እግዚሐብሄር ደጀኔ ተፈራ በቀረቡበት ወቅት ችሎቱን ለመከታተል በርካታ ጋዜጠኞች የእስረኛ ቤተሰቦችና ወዳጆቻቸው በሥፍራው ተገኝተው ነበር፡፡

ሆኖም ግን እስረኞቹን ማነጋገርም ሆነ ችሎት ለመግባት አልተፈቀደም፡፡ እስረኞቹ ከችሎት በሚወጡበት ወቅት ጋዜጠኛ ውብሼት ታዬ ለጓደኞቹና ለቤተሰቦቹ “አይዞችሁ ልበወለድ ነው” በማለት ሲናገር ተደምጧል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የአቶ ዘሪሁን ገ/እግዚሐብሄር ልጅ የሆነችው ሊዲያ ዘሪሁን ለዝግጅት ክፍላችን እንዳላቸው አባቴ እስር ቤት ለመጠየቅ በሄድንበት ጊዜ “አይዟችሁ ፍ/ቤቱ ስቀርብ በነጻ እንደሚለቀኝ እርግጠኛ ነኝ”በማለት ለቤተሰብ ሲናገር በስፍራው የነበረ መርማሪ ፖሊስ “ስለ ቤተሰብና ማህበራዊ ጉዳይ እንጂ ይህንን መናገር አትችልም” ብሎ ከልክሎታል” በማለት ገልጻለች፡፡

ሐምሌ 13 ቀን 2003ዓ.ም በ8 ሰዓት ፍ/ቤት ትቀርባለች ተብላ የነበረችው ርዮት ዓለሙ በዚሁ ዕለት ከሰዓት በፊት ጥዋት ችሎት ቀርባ ተመሳሳይ ቀጠሮ እንደተሰጣት መረዳት ተችሏል፡፡ ውብሼት ታዬ በሐዳር ጋዜጣ፣ በነጋድራስ ጋዜጣ፣ በመሰናዘሪያ ጋዜጣ፣ በጐግል ጋዜጣና በአውራምባ ታይምስ ጋዜጦች ላይ የሠራ ጋዜጠኛ ሲሆን ርዮት ዓለሙ በኤፍኤም ሬዲዮ 96.3፣ በአዲስ ፕሬስ ጋዜጣ ላይ በጋዜጠኝነት ከመስራቷም በላይ በቼንጅ መጽሔት እና በፍትህ ጋዜጣ ላይ በአመዳኝነት የሠራች ጋዜጠኛ ናት፡፡

የፍኖት የመጀምሪያዉ እትም ጋዜጣን በሙሉ በፒ.ዲ.ዔፍ ለማንበበ ከዚህ ይጫኑ

“መቼ ይሆን የምናርፈው?”: የኦጋዴን ረሃብና ጭፍጨፋ

Sunday, July 24th, 2011

ላለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያና በሕዝቦቿ ላይ የተካሄደው ክህደትና ፖለቲካዊ ሸፍጥ ያደረሰው ማህበራዊና ሰብዓዊ ቀውስ ሞልቶ ፈሷል፡፡ ዜጎች ደረጃ ወጥቶላቸው ይረገጣሉ፤የሁላችንም አገር ለከሃዲዎችና ላገልጋዮቻቸው ገነት፣ ለሌሎች ገሃነብ ተደርጋ የስቃይና የመከራ ምድር ሆናለች፡፡ አቶ መለስ ፖለቲካቸውና ፖሊሲዎቻቸው ሁሉ አገርና ህዝብን አዘቅት እያወረደ ለመሆኑ ማስረጃ የሚደረደርበት ወቅት አልፏል፡፡ አሁን ወቅቱ አቶ መለስና በውሸት ላይ የተመሰረተውን አገዛዛቸውን ለመገላገል የምንተጋበትና በተጓዳኝ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመመስረት የምንረባረብበት ወቅት ነው።
የአቶ መለስ አገዛዝ ልዩ መገለጫ ውሸት፣ በውሸት ላይ የተመረኮዘ ባዶ ሪፖርትና የወረቀት ላይ እድገት እንደሆነ ዓለምዓቀፍ ተቋማትና የሚያውቋቸው ሁሉ እየመሰከሩ ነው፡፡ ከማንም በላይ የችግሩ ሰለባ የሆነው እኛ ማረጋገጫ ነን፤ይፋ የወጣው ድርቅና ጠኔም ምስክር ነው
የጋራ ንቅናቄያችን ባገራችን ረሃብ እያሰቃያቸው ላሉት ወገኖቻችን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ የሚያደርገው የአቶ መለስን አገዛዝ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በኦጋዴን ህዝብ ላይ በዝግ የተፈፀመው ጭፍጨፋና ከቦታ ቦታ እንዳይዛወሩ ተከበው በቁም ጠኔ ያለቁ ንፁሃን ወንድሞቻችን ጉዳይ የህሊና ረፍት የሚነሳ በመሆኑ የሁሉም ዜጎች ትብብር እንደሚያስፈልግ ለማሳሰብ ይህንን የጥሪ መግለጫ አውጥተናል፡፡

አንድ ዕድሜያቸውን በውሸት የጨረሱ አዛውንት ነበሩ። ከውሸታቸው ብዛት የተጠሉና የተናቁ ከመሆናቸው በላይ ሰው ሁሉ ስለሚሸሻቸው ቤተሰቦቻቸው ያፍሩባቸ ነበር። እኚህ አዛውንት በሚሰሩበት መስሪያ ቤትም ወሬ ፈጥረው በማጣላት ይታወቃሉ። ቤተዘመድ ያፋጃሉ፤ ጎረቤት ዱላ ያማዝዛሉ፤ ትዳር ያፈርሳሉ፡፡ እሳቸው የለኮሱት ፀብ መዘዙ ሁሉን ስለሚያዳርስ በተግባራቸው የተማረሩ ሁሉ “ከዚህ ሽማግሌ እንዴት እንገላገል ይሆን” እያሉ የመገላገያቸውን ቀን ሲጠባበቁ አንድ ቀን አዛውንቱ በሰው መገደላቸው ተሰማ።

በአዛውንቱ ሞት የደስታ መግለጫ ተበተነ። ሁሉም “ተገላገልን” ተባባሉ። በሩቅ ያሉ በአዛውንቱ ላይ ካላቸው ጥላቻ ብዛት “አርቃችሁ ቅበሩት” የሚል መልዕክት አስተላለፉ። ሁሉም ደስታውን እየገለፀ የቀብር ስነስርዓት ደረሰ። በቀብር ስነስርዓቱ ላይ አንድ ችግር ተፈጠረ። የአዛውንቱን የህይወት ታሪክ የሚያዘጋጅና የሚያነብ ዘመድም ሆነ ጎረቤት ጠፋ። “አዛውንቱ በህይወት ዘመናቸው የፈፀሙት ምን መልካም ታሪክ አላቸው?” በማለት ጎረቤቶቻቸው ሲሳለቁ፣ የቤተሰቡን ችግር የተረዱ አንድ ቄስ “እኔ አስቀድሜ አዘጋጅቻለሁ፣ እኔው አነበዋለሁ” አሉና መፍትሄ ተገኘ።
የውሸታሙ አዛውንት አንድ መስመር የህይወት ታሪክ “አቶ እገሌ ሞቱ፣ ቤተሰቦቻቸውም አረፉ፣ እኛም አረፍን፣ እሳቸውም አረፉ’’ የሚል ስላቅ ሆነ። ቄሱ አስቀድመው ያዘጋጁት የአዛውንቱ የሕይወት ታሪክ ቀብራቸው ከተከናወነ በዃላ የመጥፎ ሰዎች መጨረሻ የሚገለፅበት መዘባበቻ ሆነ።
አቶ መለስ የበረሃውን ትግል ከተቀላቀሉ ጀምሮ የሚታወቁት በውሸታምነታቸው ነው።የቅርብ ባልደረባቸው የነበሩት አቶ ገ/መድህን ያዬህ የአቶ መለስን ውሸታምነት ሲገልፁ “መለስ ድንጋይ አንስቶ ዳቦ ነው ብሎ ከተናገረ ድንጋዩን ዳቦ ያደርገዋል’’ በማለት ነበር። የትግል ባልደረቦቻቸው ምስክርነትና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት ሃያ ዓመታት በተግባር ያረጋገጡት ነገር ቢኖር አቶ መለስ የውሸት አባት መሆናቸውን ነው።
አዎ! በውሸትና በሕዝባዊ ትግል ውስጥ በተቀነባበረ ስውር ደባ የበርካቶች ህይወት ተገበረ።ህዝባዊ ታጋዮችና አታጋዮች ሃሰተኛ ምላስ ባለው መሰሪ ፖለቲከኛ ተበልተው ትግሉ፣ የትግሉ ሰማዕታትና የትግሉ ዓላማ ሙት ሆነ። በዚሁ ሳቢያ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ በሀፍረት አለንጋ እንዲገረፉ፣ ማንነታቸው እንዲደበዝዝና አገራዊ ማንነታቸ እንዲጠፋ ሆነ። ይህም አልበቃ ብሎ ኢትዮጵያን ንብረቷን በመዝረፍና በማዘረፍ ህዝቦቿ ልጅ ልጆቻቸው ሳይቀር በባርነት ተላልፈው እንዲሰጡ የተወሰነባቸው ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም።

ዛሬ ባገራችን በአቶ መለስ የሚመራው አገዛዝ እስካሁንም በሥልጣን የቆየው እንዳሻው የአገራችንን ህዝብና ዓለም አቀፉን ኅብረተሰብ እያወናበደ ሲሆን፣ በስልጣን በቆየበት ሃያ ዓመታት ያተረፍነው ነገር ቢኖር ውርደት፣ የሀብት ዝርፊያ፣ የርስ በርስ ግጭት፣ ድህነት፣ በዘር ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ፖለቲካ ሲሆን በተለይም ሲሸፋፈን ቆይቶ ይፋ የሆነው የወገኖቻችን እጅግ አሳሳቢ የርሃብ አደጋ በየዘርፉ ካጋጠሙት ቀውሶች ጋር ተዳምሮ የአቶ መለስ የሃያ ዓመት ውሸትን መሰረት ያደረገ አገዛዝ ድምር ውጤት ውድቀት መሆኑን ያረጋገጠ ሆኗል።በተጨማሪም በስውርና በግልፅ የሚካሄውን ኢትዮጵያን የመበታተንና ህዝቦቿን የማዋረዱ ተግባር ልክና ገደቡ አልፎ የማንቋቋመው ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላክታል። ታዲያ መቼ ነው “እኛም አረፍን የምንለው?”

አገራችን ያለችበት ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከረረ መሄዱ በእጅጉ አሳሳቢ በመሆኑና የተሸሸገውን ቁጥር ሳይጨምር ራሱ ህወሃት/ኢህአዴግ እንዳመነው ከ5ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለከፋ ርሃብ መጋለጡ አስደንጋጭና አሳፋሪ መርዶ ሆኖብናል። ችግሩ የስርዓቱ በሽታ የወለደው መሆኑ ደግሞ ውስጣችንን በጅጉ ያቃጥለዋል፤ ሀዘናችንንም ድርብ ያደርገዋል።ለዚህም ነው ዛሬ ሁሉም ወገኖች ለፍትህና ለርትዕ መነሳት አለባቸው በማለት ይህንን ጥሪ ለማስተላለፍ የወሰነው።

በእፉኚት እባብ በሚመሰለው የመለስ ፖለቲካ የተጠመቁ ካድሬዎች ለመለስ ኃይል ሆነው ብሄራዊ ማንነታችንን፣ ብሄራዊ ጥቅማችንን፣ ብሄራዊ አንድነታችንንና ጠላትን የሚያስደነግጠው አብሮነታችን ተገፏል። ሀብታችን ተዘርፏል። እየተዘረፈም ነው። ቁም ነገር በሌለው ጦርነት ተማግደናል። በኢትዮጵያውያን የመከላከያ ኃይሎች ደም የሚገኘው ዶላርና የፖለቲካ ቁማር ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተማገድንም ነው። በብሄር ፖለቲካ መርዝ የተለወሰው የመለስ አገዛዝ እርስ በእርስ ወንድማማች ህዝቦችን አጫርሷል፤ እያጨረሰም ነው ። በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች የጅምላ ጭፍጨፋ ተከናውኗል። ምን ቀረ?

በጋምቤላ፣ በደቡብ ክልል፣ በኦጋዴን፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተፈፀመው ጭፍጨፋ አልበቃ ብሎ ወገኖቻችን በመለስ የፖሊሲ ስህተት በከፋ ድርቅ እየተገረፉ፣ መሬታቸው ግን ለባዕዳን እየተቸበቸበ ነው። ለመለስ ከኢትዮጵያዊያን ይልቅ የህንድና የቻይና ዜጎች በልጠዋል። የቱርክና የጅቡቲ ከበርቴዎች ክብር ተሰጥቷቸዋል። በኑሮ ውድነት ድፍን የአገራችን ህዝብ ኑሮ ተናግቷል። ጥቂቶች እየበሉ አብዛኞች ተርበዋል። በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ ያልቻሉ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ እየወደቁ ነው።

ኢኮኖሚው በተወሰኑ ቡድኖች ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎ አብዛኞች ራሳቸውንና ልጅ ልጆቻቸውን ለባርነት አሳልፈው እንዲሰጡ እየተደረገ ነው። ጥቂቶች እየተንደላቀቁ አብዛኞች የበይ ተመልካች እንዲሆኑ ተፈርዶባቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ስቃይና መከራ እየጠነከረ፣ እየከፋና እየከረረ ያለበት ፈታኝ ወቅት ላይ ነን። በመሆኑም በየትኛውም ደረጃና አይነት የፖለቲካ ትግል የተሰማራችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች፣ በዋናነት ባስቀመጥነው የወቅቱ የረሃብ አጀንዳና የኦጋዴን ወንድሞቻችን ላይ የደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ ገሃድ እንዲወጣ ትብብራችሁን እንድታደርጉ እንጠይቃለን። በጥሪያችን መሰረት የሚፈጠረው መረባረብ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ ጅማሮ የሚያመለክት እንደሚሆንም አንጠራጠርም።
የሕዝብ አንደበትና ተሟጋች የሆኑ የነፃ ፕሬስ ውጤቶችን ወደ መቃብር በማውረድ፣ ነፃ ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣ አገር ጥለው እንዲሰደዱ በማድረግ፣ በምትካቸው ህወሃት/ኢህአዴግ ሰራሽ ፕሬሶችና ቅምጥ ጋዜጠኞች ተወልደው የመለስን አገዛዝ በማቀንቀን በአገርና በህዝብ ላይ ክህደት እየፈፀሙ ይገኛሉ። ይህ ህዝብና አገር ላይ የሚፈፀም ክህደት የሚያከትምበትና የስርዓቱ መሪዎች ለፍርድ የሚቀርቡበት ጊዜ መቃረቡን በመረዳት ሳይመሽ በአርአያነት እንደሚጠቀሱት ጥቂት ፕሬሶችና ጋዜጠኞች የዜግነት ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለን እናምናለን።
አድር ባይ ብእርና ለጥቅም የተገዛ ጋዜጠኛነት እንዲያበቃ በጅምላ በተጨፈጨፉት፣ የረሃብ አለንጋ በሚገርፋቸው፣ በግፍ አገዛዝ በታሰሩትና በመለስ ስውር አጀንዳ እየፈራረሰችና እየተዘረፈች ባለችው አገራችን ስም ድምፃችንን እናሰማለን። ለልጅ ልጅ እንዲተላለፍ ታስቦ በመለስ ስውር አላማ ለኢትዮጵያ የተወጠነውን ሴራ በማክሸፍ አዲሲቷን ኢትዮጵያ በመመስረቱ ትግል ውስጥ የመሪነት ሚና የምትጫወቱበት ወቅት ላይ ናችሁና!
የኪነት ባለሙያዎች የህዝብ ስቃይና የአገር ውድቀት ከሚያስጨንቃቸው በላይ ህሊናቸውንና ስብዕናቸውን በንዋይ ሸጠው፣ ለሆዳቸው ተገዝተው ለመለስ ዜናዊ በመርዝ የተለወሰ ፖለቲካ በማጎብደድ ይቅር ሊባል የማይችል የአጫፋሪነት ተግባር ላይ ተሰልፈዋል።ይህ ሁሉ አልበቃ ብሏቸው አቶ መለስን ሸላሚና አመስጋኝ ሆነው ታማኝ አሽከርነታቸውን ሲያረጋግጡ ከማየት በላይ የሚያሳዝን የሞራል ግሽበት ይኖራል ብለን አናስብም። ውስን የኪነት ባለሙያዎችና ፀሐፍቶች ከሚያበረክቱት የትግል ስሜት የተሞላ ተግባር ውጪ አብዛኞች አገርና ህዝብ ሊረሳው በማይችለው የተጠያቂነት ጥፋት ውስጥ ተዘፍቀዋልና በጊዜ ህዝባዊነታቸውን እንዲያሳዩ እንመክራለን። በሌሎች አገሮች የኪነት ባለሙያዎችና ፀሐፍቶች እንደሚያደርጉት በግፍ ለተጨፈጨፉ፣ በረሃብ ለሚረግፉ፣ በነፃነት ጥማት ለሚሰቃዩ፣ ፍትህ ለተራቡ አንደበት እንዲሆኑ እንማፀናለን።

የአገራችን ምሁራኖችም ብትሆኑ ዝምታን መምረጣችሁ ከተጠያቂነት አያድናችሁምና የዜግነት ድርሻቸውን እየተወጡ ካሉት በጣት የሚቆጠሩ ባልደረቦቻችሁ ባልተናነሰ አገራችን እያመራችበት ካለችበት የውድቀትና የአፈና ስርዓት ነፃ የምትወጣበትን መንገድ ማፈላለግ ግዴታችሁ መሆኑን አበክረን እናሳስባለን። እናንተም እያንዳንዱ ዜጋ ነፃ የሚሆንባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ ስትመሠረት ተሳታፊ ሁኑ እንላለን።

የአገራችን ወጣቶች ያላችሁበት የፈተና ጊዜ ያለፈቃዳችሁ የተጫነባችሁ፣ የችግሩ ግንባር ቀደም ተጠቂዎች ብትሆኑም በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ የምትጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነውና እንደወትሮው ሁሉ ወደፊት በምትረከቡዋት አገራችን ላይ እየተከናወነ ያለውን ስውርና ገሃድ ሴራ ተቃወሙ። በወገኖቻችሁ ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ አውግዙ።

የሐይማኖት አባቶችና መሪዎች እንደ እምነታችሁ የሚጠበቅባችሁን ከማድረግ ያገዳችሁን ምክንያት መዘርዘሩ ባያስፈልገንም ዝምታን መምረጣችሁ በምታመልኩትና በምታገለግሉት አምላክ ከቶውንም የሚወደድ አንዳልሆነ በዚህ አጋጣሚ እንጠቁማለን።

የዓለም መንግስታት፣ የአፍሪካ ህብረት አገሮች፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና የፍትህ ተሟጋቾች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ሁሉ አቀፍ የመገናኛ አውታሮች ወዘተ በኦጋዴን ንፁሃን ዜጎች ላይ በአሸባሪዎች ስም የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ ገሀድ እንዲወጣ የበኩላችሁን ታደርጉ ዘንድ እናሳስባለን። በተለይም ለጋሽ አገራት ለድሃ ህዝቦች የምትሰጡት ርዳታ ድሃ ህዝቦችን በጅምላ ለመጨፍጨፍ ተግባር እየዋለ፣ እየተዘረፈ መሆኑን እያወቃችሁ፣በራሳችሁ አጣሪዎች ሪፖርት እየቀረበላችሁ ዝምታን የመረጣችሁበት አግባብ የተዛባ ነውና ለኦጋዴን ህዝብ ጩኸት ጆሮ ስጡ። በኦጋዴን የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ በገለልተኛ አካላት እንዲጣራ ጫና በማድረግ ተባበሩ።

የመግለጫችን አንኳር ጉዳይ የወቅቱ አሳሳቢ ድርቅና የኦጋዴን ጉዳይ እንመለስ፤በ2006-2007 በኦጋዴን የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በርካታ መረጃ አሰባስበናል። በወቅቱ የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ታጣቂዎችን ለመደምሰስ በሚል ህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ ብረት አንጋች ሃይል የወሰደው አስከፊና ሰብአዊነት የጎደለው ጭፍጨፋ በጥቂቱ ይህን ይመስላል።

1. በሶማሌ ክልል ተሰማርተው የነበሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የዓለም አቀፉን ቀይ መስቀልን ጨምሮ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደረገ። ውሳኔው በግብረ ሰናይ ድርጅቶቹ በኩል ቅሬታ ቢያስነሳም አቶ መለስ አቋሜን አልቀይርም አሉ።
2. በአካባቢው የሚፈፀመውን ኢሰብአዊ ድርጊት የሚታዘቡ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከአባቢው ከወጡ በኋላ ኦጋዴን በታጠቁ ሃይሎችና በከባድ መሳሪያ እንዲከበብ ተደረገ።ቀደም ሲል አሸባሪን ለመከላከል በሚል በአካባቢው በተተከሉ የርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች አማካይነት የኦጋዴን አርብቶ አደር ነዋሪዎች መስቀለኛ ወጥመድ ውስጥ እንዲገቡ ተደረገ።
3. ኦጋዴን ሙሉ በሙሉ ከተከበበ በኋላ ወደ ጅቡቲ፣ኬንያና ሶማሊያ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ። በተመሳሳይ ከጅጅጋ የሚወጣና ወደ ጅጅጋ የሚገባ ማንኛውም ዓይነት ሸቀጥ እንዳይንቀሳቀስ ተደረገ። በጅጅጋ የሸቀጦች ዋጋ ናረ። ስኳርና ፓስታ በኮንትሮባንድ እንኳን የማይገኙበት ሁኔታ ተፈጠረ፤ ኑሮም ጋለ። ነዋሪዎች ስጋት ላይ ወደቁ።ይህንን የሚያደርጉት ወንበዴዎች ናቸው በሚል የመለስ ካድሬዎች ቅስቀሳ አካሄዱ።
4. ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት የኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር።በተፈጥሮዋቸው አንድ ቀበሌ መኖር የማይችሉ አርብቶ አደሮች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብአዊ ቀውስ ደረሰ?

ከወራት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ሰሞኑን የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ሚስጥር ይወጣብኛል ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም።

ኦጋዴን በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ተድበስብሶ ቢከርምም ዛሬ በሶማሊያ የተከሰተውን አስፈሪ ርሃብ ተከትሎ ይፋ መሆን ጀምሯል። ድርጅታችን በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ክልል፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተፈፀሙትን ጭፍጨፋዎች በመቃወም እንዳደረገው ሁሉ በኦጋዴን የተፈፀመው ጭፍጨፋ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ነው። የኦጋዴን ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመሆኑ ይህ መግለጫ የሚደርሳችሁ አካላት በሙሉ ድርጊቱን በመቃወም አግባብ ያለው ተፅዕኖ በማድረግ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረክ ትግላችሁን እንድትቀጥሉ አጥብቀን እናሳስባለን።

በኦሮሚያ፣በአማራ፣በትግራይ፣በደቡብ፣በአፋር፣በድሬዳዋ፣በኦጋዴንወዘተየተከሰተው አስደንጋጭ ረሃብ ይፋ የሆነው መለስ አገራችንን ‹‹ወደ መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገሮች አሳድጋለሁ፣ከንግዲህ የእህል እጥረት አያሰጋንም፣የእህል እጥረት ካጋጠመንም ከኪሳችን አውጥተን እንገዛለን›› በማለት ፀሐይ የሞቀው ውሸት ከዋሹ በወራት አድሜ ውስጥ መሆኑ፣የአገራችን ኢኮኖሚ በሁለት አኻዝ አድጓል፣ባገሪቱ የሚመረተው ሰብል በሚሊዮን ኩንታል ጨምሯል ወዘተ የሚል የፈጠራ ሪፖርት በተደጋጋሚ በሚቀርብበት ወቅት ላይ መሆኑ፣የመለስን በቅጥፈት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ከማሳየቱም በላይ ወደፊትም መሻሻል ሊታይ እንደማይችል ያረጋገጠ ክስተት ሆኖ አግኝተነዋል።ስለዚህም “መለስም አረፉ፣ እኛም አረፍን፣ የሚነግዱበት ህዝብም አረፈ” የምንልበትን ጊዜ በማፋጠን አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ የምንመሰርትበትን መንገድ እንድናመቻች ከላይ ለዘረዘርናቸው አካላትና ለመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ወደ ፖለቲካው መስመር ከገቡ በኋላ በመተጣጠፍ፣ ነባር ፖለቲከኞችን በመብላት የህወሓት ፊት አውራሪ ለመሆን የበቁት መለስ፣የቀደመውን የትግል መስመር አስተው ኢትዮጵያን በመበታተን፣ፖለቲካዊ ፋይዳዋን በማመናመን፣የህዝቦቿን ክብር በሃፍረትና በድህነት በማዋረድ፣የቀደሙትን ሰማዕታትና የትግሉን ዓላማ ሙት ያደረጉ በመሆናቸው መለስና ግብርአበሮቻቸው ለተራቡት ህዝቦች የሚላከውን ርዳታ በአግባቡ ያደርሳሉ የሚል እምነት እንደሌለንም ከወዲሁ ለመግለፅ እንወዳለን።
ከትግል ራስን ማሸሽ ለነጻነት የሚደረገውን ትግል ያራዝመዋል። በአዲሲቷ ኢትዮጵያ በሌሎች ትግል ተጠቃሚ የመሆን አስተሳሰብ ቦታ የለውም። በነፃነት ውስጥ የሚፈጠሩ ዜጎች የሚኖሩባት፣ሁሉም ዜጎች ነፃ የሆኑባት አገር ለመመስረት ለሚቀርብ የትግል ጥሪ ምላሽ መስጠት ራስን ነፃ የማውጣት ያህል ነው!!

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ
*******************************************************************************************************************
ለዚህ ደብዳቤ ምላሽም ሆነ ለተጨማሪ መረጃዳይሬክተሩን ለአቶ ኦባንግ ሜቶ (obang@solidaritymovement.org) በመጻፍ ወይም ድረገጻችንን (www.solidaritymovement.org) በመጎብኘት ለመረዳት ይችላሉ፡፡

በመቀሌ ከተማ ከ5000 በላይ የሆኑ ሰላማዊ ሰልፈኞች በፌደራል ፖሊስ ተበተኑ

Wednesday, April 20th, 2011

እነዚህ ሰልፈኞች ሰልፍ ለመውጣት የተገደዱበት ምክንያት ለአራት ዓመታት ያህል የኖርባቸው ቤቶች አስተዳደሩ እስከ ሚያዚያ 17/2003 ዓ/ም ድረስ እንዲያፈርሱ ካልሆነ ቤቶቹ በመንግስት ዶዘር እንደሚፈርሱ የሚገልፅ ደብዳቤ በየቤቱ በመለጠፉ ነው፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የሚኖሩባቸው ወደ ሶስት የሚሆኑ መንደሮች የራሳቸው ቤተክርስቲያን ሁሉ ያላቸው ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ባንዴራ፤ ታቦትና መስቀል የያዙ ቄሳውስት ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ሰልፈኞቹ ዛሬ ሚያዚያ 13/2003 ዓ/ም በመቀሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ ደቡብ ቀበሌ “ማይ አንበሳ” እየተባለ ከሚጠራው አከባቢ ከጧቱ አስራ ሁለት ሰዓት የጀመረው ሰላማዊ ሰልፉ በመጀመሪያ ወደ አከባቢው ንዑስ ወረዳ ወይም ቀበሌ ያመራ ሲሆን ከአስተዳደሩ አጥጋቢ መልስ ሊያገኙ ባለቻላቸው ሰልፎኞቹ ወደ መቀሌ የክልሉ ፅሕፈት ቤት ለማምራት ተገዷል፡፡ ነገር ግን በጉዞ ላይ ሳሉ ከቀኑ 9:30 ብረት በታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ከተከበቡ በኋላ “ከዚህ ማለፍ አትችሉም ወደ መሀል ከተማም አትገቡም እርምጃ እንወስድባቸዋለን” በማለት ካስራሩዋቸው በኋላ ወደየቤታችሁ ሂዱ በማለት ኃይል እንዲበተኑ አድርጓል፡፡

ሰልፉን በካሜራ ሲቀርፅ የነበረው የጥሕሎ መፅሔት አዘጋጅ ወጣት ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ እና ሌላ በግል በራሱ ተነሳሽነት በቪድዮ ካሜራ ሲቀርፅ የነበረ ወጣት በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ተወስዷል፡፡ እነዚህ ወጣቶች የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡

ሰልፈኞቹ አስተዳደሩ ቤቶቹ ስሰሩ ለዓመታት ያህል ምንም ሳይ ቆይቶ ዛሬ አፍርሱ ማለቱ አግባብ ያለመሆኑን ጠቅሰው አሁንም መልስ የማያገኙ ሌላ ሰልፍ ለማድረግ ሀሳብ አላቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት አንድ ቤት ለመስራት ያለው መከራ ከባድ መሆኑን ያወሱት እነዚህ ሰልፈኞች “ከቤታችን መፍረስ በፊት እኛን መግደል አለባቸው እንጂ እኛ በህይወት እያለን ቤታችንን አይፈርስም፡፡” ብለዋል፡፡

በመቀሌ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነት በመስፋፈቱ፤ የንግድ መዛባትና የህንፃ መሳሪያዎች ስሚንቶ ጨምሮ በገዥው ፓርቲ ድርጅቶች በመኖፐል የተያዙ በመሆናቸው ህዝቡ በቀላሉ ሊያገኛቸው ባለመቻሉ ከፍተኛ የሆነ ምሬትና ቁጣ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡

የወያኔ ትራንስፎርሜሽንና ሲያትል

Sunday, April 17th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የመለስ ዜናዊ መልእክተኞች ስብሰባ በዳላስ

Friday, April 8th, 2011

ቅዳሜ አፕሪል 9 ቀን 2011 በዳላስ ከተማ የመለስ ዜናዊ መልእክተኞች ስብሰባ ለማድረግ ሕዝብ ጠርተዋል። ይህ የሕወሐት/ኢሕአዴግ መልእክተኛ ቡድን አላማው የኢትዮጵያውያንን አንድነት የተቃዋሚውን ሊመጣ የሚችል ትብብር ለማናጋት ታስቦ የተሰራ በመሆኑ፤ ይህን መሰሪ አላማ በውጭ በነጻነት የምንኖር ሁሉ ልንቃወም ይገባል። በመሆኑም በዳላስ ነዋሪ የሆንን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በዚህ ስብሰባ ተቃውሞ ስልፍ ስለምናደርግ እንድትተባበሩ ጥሪያችን ይድረሳችሁ።

በቴክሳስ፡ ሒውስተን፣ ኦስተን ከተሞች የምትኖሩ ወገኖቻችን ቅዳሜ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ተካፋይ እንድትሆኑ። እንዲሁም በኦክላሆማ፣ በአርካንሳስ፣ በሉዚያንና እና በቴነሲ ላላችሁ ጥሪ እናደርጋለን። በርሐብ በሚታወቅ ሕዝብ ስልጣናቸውን ለማቆየት ከፍተኛ ወጭ ተደርጎላቸው የመጡ የመለስ ልዑካንን አሳፍረን ልንመልሳቸው ይገባል።

የተቃውሞ ቦታ Marriott hotel 14901 Dallas Parkway. በተጨማሪ ሆቴሉን ለመደወልና የወንጀለኞች አስተናጋጅ መሆኑን ለመንቀፍ በዚህ መደወል ይቻላል 972-661-2800

የኢሃድግ ልኡካን በሰሜን አሜሪካ የኢንቨስትመንት ጥሪና በኢትዮጲያ የነጋዴው ስቃይ

Wednesday, March 30th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የአምባገነኖች የመጨረሻ ቀናትና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ

Friday, March 25th, 2011

ምዕራቡ ዓለም በዋናነነት በሁለት ዋና ምሰሶዎች ላይ የተመረኮዙ መርሆዎችን በማራመድ ከኮሚኒዝም ጋር የተያያዘውን ትንቅንቅ በድል ለማጠናቀቅ ትልሙን ጣለ፡፡ ሁሉን አቀፍ ፀረ-ኮሚኒዝም ጦር መስበቅ እና የተጠናከረችና የፈረጠመች እስራኤልን በመኮከለኛው መስራቅ ማደላደል፡፡ እነዚህ ሁለት ምሰሶዎች ላይ በመመርኮዝ ኮሚኒዝምን የሚያወግዙና የእስራኤልን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥሉ አምባገነኖች ሁሉ በዓለም ዙሪያ በሕዝባቸው ላይ ለሚያደርሱት ምሬትና ዋይታ ኬላው ከፍ ብሉ ተነሳላቸው፡፡ በኋላ ላይ በፀረ-ሽብር ዘመቻው ተባባሪ ለሆኑ አምባገነኖችም ይኸው ቡራኬ ተቸራቸው፡፡ ከምዕራቡ ዓለም ከፍ ሲል ከጠቀስናቸው ሦስት ጥቅሞች ጋር የሚጋጩ ሁሉ ግን በቀጥታና በእጅ አዙር የሰይፋቸው ሰለባ ሆኑ፡፡ ሃፍረትን የማያውቁት የአሜሪካ እና ሌሎች በርካታ የምዕራቡ ዓለም አገራት ተከታታይ መሪዎች ለተራ ጥቅሞች ሳይቀር በአራቱም ማዕዘናት አምባገነኖችን በማወደስ፣ አይተው እንዳላዩ በማለፍና አልፈው ተርፈውም የንፁሃንን ደም ለማፍሰስ የሚረዱ መሳሪያዎችን በመሸለም ለአምባገነኖች ማርገዳቸውን ቀጠሉበት፡፡ ይህን በመሠለው ተግባራቸው በየአገሮቻቸው እውን አድርገናል የሚሉትን የሕዝብ ልዕልና ጭቃ ውስጥ ጥለው እረገጡት፡፡ መገለጫቸውም ተራ ጥቅም ማሳደድ ብቻ ሆነ፡፡ ነገር ግን ውሎ አድሮ ሲጋልቧቸው የነበሩት ስናሮች እነርሱንም ከመርገጥና ለጥቅሞቻቸውም ደንቃራ ከመሆን አልዳኑም፡፡

የምዕራቡ ዓለም ይህን በመሠለው በራሱ መርሆዎችና በስብዕና ላይ በፈፀመው ደባና ክህደት፣ በዓለም ላይ በነበሩ ልዩ ልዩ የፖለቲካ መባዘቆች ለዘመናት ሕዝብን ያንገሸገሹ ሥርዓቶች በሕዝባዊ አቢዮቶች ሲመነገሉ ሌሎች በጎደሎ ስብእናቸው የሚታወቁ፣ ወገኖቻቸውን እንደ ሳር የሚያጭዱ የሕዝብን ዋይታ እንደ የሙዚቃ ጥዑም ዜማ የሚቆጥሩ መረን አምባገነኖች ዓለማችንን መናሃሪያ አደረጓት፡፡ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅና የግፍ ቋት በሆነችው አፍሪካችን፡፡

በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሕዝብ ለዓስርተ-ዓመታት ከራሱ አብራክ በወጡ አምባገነኖች ሰይፍ በገፍ ተበላ፡፡ አሁንም ተደራጅቶ እራሱን መከላከል በማይችልበት ሁኔታ በትውልድ ቀየው በልጆቹ ፊት ይደበደባል፡፡ አልታረም እንዳለ ልጅ በአርጩሜ ይገረፋል፡፡ ባሎች ሚስቶቻቸውን ይነጠቃሉ፡፡ ሚስቶች ባሎቻቸውን በግፍ እስከ ዝንተ-ዓለም ይሰናበታሉ፡፡ በማያባራ ዋይታና በማይጠፋ የሃዘን ረመጥ እየተበሉ በችጋር የሙት ልጆችን ያሳድጋሉ፡፡ ይህን ከመሠለው የሕይወት አውድ ውስጥ ያልተላቀቀው ሕዝብ ይኸም አነሰህ ተብሎ በሚሊዬን የሚቆጠሩ አፋኝ ደህንነቶችና አልሞ ገዳይ ፖሊሶች የብረት መረብ ዘርግተው ጮክ ብሎ እንኳን በአደባባይ ሊቃወም ይቅርና ጮክ ብሎ እንዳያለቅስ ገደብ ጥለውበታል፡፡ ለቅሶውንም፣ ርሃቡንም ቁዘማውንም በዚያችው በጠባብ ማጀቱ በሩን ዘግቶ ይወጣል፡፡ ለአያሌ ዓመታት፡፡ በጭቆና ቀንበር ሥር ሕዝባቸውን የሚያማቅቁ አገሮች ያሏቸው ‹ሕገ-መንግሥቶች› ከብዙዎቹ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከሰፈነባቸው ሃገሮች ቢልቁ እንጅ የሚያንሱ አይደሉም፡፡ ይሁን እንጅ ቃላት ሥጋ ለብሰው ሕዝብን ከጅምላ እስር፣ ርሸና፣ ችጋር፣ አይን ካወጣ ዘረፋና አድልኦ በአጠቃላይ ፍትህን ሞቶ ከመቀበር ሊታደጉ አልቻሉም፡፡ ሕገ-መንግሥት ማለት የአጤዎች ቃል ሆነ፡፡ ለዛውም ቃለ-መርገም፣ ቃለ-ውርደት፣ ቃለ-ውድቀትና ቃለ አጠቃላይ ጥፋት፡፡

የሕዝብ ጫንቃ ይህን ሁሉ ጉድ ቢሸከምም ስንክሳሩ በቀላሉ የሚቋጭ አልሆነም፡፡ በተለይም በአረብ አገሮች እንደተስተዋለው በአንድ ወቅት የሕዝብ ብሶት ወለደን ያሉን አምባገነኖች የተኳቸውን መሪዎች ስብዕና መላበስ ጀመሩ፡፡ ስዩመ-ፈጣሪ ለመሆን ተንደረደሩ፡፡ ልጆቻቸውን ለአልጋ ወራሽነት አጩ፡፡ የእኛው ‹መሪ› ደግሞ ባለቤታቸውን ከአጠገባቸው በመሻጥ በተግባር አልጋ ወራሽ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ‹ከዓምስት ሚሊዬኑ› መሃል መንጥቀው ከደመና በላይ ቁብ አረጓቸው፡፡ እንደ ቢን አሊ መሆናቸው ነው፡፡

በዚህም አልበቃ፡፡ ሕዝብ ሰብዓዊ ክብሩን ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ቁሱንም በገፍ ተነጠቀ፡፡ ሀገርና ሕዝብ በአምባገነኖች ካዝና ውስጥ የሚቆጠሩ ቁሶች ሆኑ፡፡ በዓለማችን በታታሪነታቸው ከዚያም በሚመነጨው ባለፀግነታቸው የሚታወቁት ሃብታሞች ከእነዚህ ዘራፊዎች ተርታ በሀብት መጠን ሊሰለፉ የሚችሉበት አንዳች አቅም አጡ፡፡ በጣም የሚያስደምመው ግን እንደዚህ እንደቁስ የሚቆጥሩትና የላቡን ፍሬ የሚነጥቁትን ሕዝብ እንደሚያፈቅራቸው ደጋግሞም ኮንትራት እንደሚያሰፈርማቸው አምባገነኖቹ ይነግሩናል፡፡ ሲያስፈርማቸውም ከለግስና ጋር ነው፡፡ በግብጽ 95%
‹ድምፁን በመስጠት ሲሆን አቶ በረከት እንዳሉት ለ3ዐ ዓመታት ልማት ባላያት ግብጽ ይኸን ያህል ሕዝብ ሙባረክን ከወደደ የኢትዮጵያን ሕዝብ በማያባራ የእድገት ግስጋሴ የሚያነጉዱትን አቶ መለስን 99.6% ሰጥቶ ኮንትራት እንዳስፈረማቸው መከራከር ምክንያታዊ ለማስመሰል ሳይቀል አይቀርም፡፡ ደግሞስ ለአቢዮታዊ ደሞክራቶች አቢዩታዊ ውሽትስ ምን ይገዳቸዋል? በሌሎቹም የአረብና የአፍሪካ አገሮች የሆነው ይኸው ነው፡፡ የምርጫ ተውኔት፣ የምርጫ ፌዝ፡፡

የእነዚህ አገሮች ሌላው ሁነኛ መገለጫቸው የጫጨ የሲቪል ማህበረሰብ፣ የታፈነና የተመናተለ የግል መገናኛ አውታር፣ ከተሰመረላቸው መስመር እንዳያልፉ በደህንነት ወከባ የዛሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከሥርዓቶቹ ጋር የተቆራኙ የኃይማኖት ተቋማት ናቸው፡፡ ሌሎችም አያሌ መገለጫወቻቸውን ማንሳት ይቻላል፡፡ የሚመሳሰሉበትን ብቻ ሳይሆን የሚለያዩባቸውን ልዩ አገራዊ ክንዋኔዎችንና ገጽታዎች ማውሳት ይቻላል፡፡ ነገር ግን በዚህ አጭር ጽሁፍ ይህንን መሰሉ ዝርዝር ውስጥ መግባት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

አምባገነኖች በሕዝብ ሁለንተና ላይ መቀለድን ሥራዬ ብለው ሲቀጥሉ፣ አዝጋሚም ቢሆን ሕዝብ ያጎበጠውን የጭቆናና የአፈና መርግ ከላዩ ለማውረድ ሥራውን ቀጥሏል፡፡ በተለይም ከእውቀት ማዕድ በቅጡ የተቋደሰ ነገር ግን አምባገነኖች ከሚዘርፉት ጥሪት ላቡን አፍስሶ እንኳን መሳተፍ የማይችል ወጣት መበራከት፣ የጭቆናው መስፋፋትና ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የባጀ የሕዝብ ብሶት ክዳኑን መግፋት መጀመር፣ ለቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና የማህበራዊ- መረብ (Social-networking) መስፋፋት፣ ዴሞክራሲና እውነተኛ የሕዝብ መንግሥት መምረጥ ምን ማለት እንደሆነ በማያሳስት መንገድ ሕዝብ መማር መቻሉ፣ ይኸም ፍርሃትን ለመስበር፣ ተስፋን ለመሰነቅ የማይናቅ ሚና መጫወቱን ልብ ማለት ይቻላል፡፡ በቀደሙ አቢዬቶች ወቅት ተስፋው በቀላሉ ሲሞት፣ ሕልሙ ሲጨናገፍ፣ ፍርሃት በአፈ-ሙዝ አስገዳጅነት በላዩ እንደሰፈረ ሁሉ፣ ከምናቡ ባይጠፋም፣ ጠባሳው ባይሰረዝም ተንገዋሎ እንደሚሄድ ሕዝብ በውል ተረዳ፡፡ ከቶውንስ በሞትና በህይወት መካከል ልዩነቱ ለጠፋበት፣ ለተራበ፣ ለተጠማና ስብእናውን ለተቀማ ሕዝብ ፍርሃት ምን ማለት ነው? ምኑ ምን እንዳይሆን ነው የሚፈራው? እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው ሕዝብ ፍርሃትን አንኮታኩቶ በመጣል ሰብአዊ ክብሩን፣ ሀገሩንና ተስፋውን ከአምባገነኖች መዳፍ ለመንጠቅ ከተንቀሳቀሰ ወራት ተቆጠሩ፡፡ አምባገነኖችም ተራ በተራ ጽዋውን ለባለሳምንቱ እያስረከቡ ከሕዝብ ጫንቃ በሕዝብ ብርቱና የማይናወጽ ትግል እየተሸኙ ነው፡፡ አቶ መለስ እንዳሉት #ሕዝብ ከመሪዎቹ የተሻለ ነው$ና እነርሱ ያስጎነጩትን የግፍ ጽዋ አላስጎነጫቸውም፡፡ ከጫንቃው ላይ ግን አስፈንጥሯቸዋል፡፡ ገናም ያስፈነጥራቸዋል፡፡ አምባገነን መሪዎች መቼም ጥሩ የተውኔት ሰዎች ናቸውና ተውኔቱን ግን ቀጥለዋል፡፡

ቢደላን ኑሮ ትወናው እጅጉን እንድንስቅ ይረዳን ነበር፡፡ ነገር ግን የተሸከምነው መከራ የመሳቅ ኃይላችንንም ነስቶናል፡፡ ምዕራቡ ዓለም የአምባገነኖችን ተውኔት በሙዚቃ አቀነባብሮ ፈገግ እያለ ነው፡፡ እነሱ ቢስቁ ያምርባቸዋል፡፡ ግፉን ሁሉ አባቶቻቸው ከላያቸው አውርደውላቸዋል፡፡ እኛም ዛሬ ዋጋ መክፈል ታሪካዊ ግዴታችን ነው፡፡ ልንወጣው የማንችለው እዳ ግን አይደለም፡፡ ወደ መጀሪያው ሃሳቤ ልመለስ፡፡ ስለአንባገነኖች ተውኔት፡፡ ያለምንም ማጋነን ሁሉም አምባገነኖች የእኛዎቹን ጨምሮ ብርክ እንደያዛቸው መረዳት አዳጋች አይሆንም፡፡ የቢን አሊ ቢቀር በሚሊዬን የሚቆጠር ደህንነትና ፖሊስ የነበራቸው ሙባረክ አጠገባቸው ዘፍ ሲሉ አቶ መለስ ቢደነግጡ ምን ይገርማል? በሙባረክ መገንደስ ብዙ ሰው ቢደሰትም ክስተቱ የሕልም ያህል ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

የማያባራው የአምባገነኖች ተውኔት ብዙ አሳይቶናል፡፡ ሙባረክ ለ18 ቀናት ብዙ መቶዎችን በመግደልና አያሌዎችን በማቁሰል የግብጽን ሕዝብ ጽናት ተፈታተኑት፡፡ ሲያሰኛቸውም በዘመናዊነቷ የሚነገርላትን የካይሮን ከተማ ግመል የጋለቡ ደህንነቶቻቸውን በማዝመት ሠላማዊውን ትግል ለማኮላሽት ክተት አወጁ፡፡ ነገር ግን የግብጽ ወጣቶች ሞትን ባሸነፈው ፅኑ ሠላማዊ ትግላቸው አመከኑባቸው፡፡ ሙባረክ ደጋግመው ተውነዋል፡፡ ደጋግመን በኢትዮጵያችን እንደምንሰማው ሙባረክ አንድ ለእናቱ የግብጽ ዋልታ እና ማገር ነኝ አሉ፡፡ እርሳቸው ከሌሉ ግብጽ ውሃ እንደሚባላት፡፡ 7ዐ ቢሊዬኑንስ ማን ይዘርፋታል ብለው ሳይጨነቁላት የቀሩ አይመስልም፡፡ ወይ እንደ እኛ #ጠቅላይ ሚኒስትር በ64ዐዐ ብር ደመወዝ በችጋር ቢቆራመዱ በተሻላቸው ነበር፡፡ ሙባረክ እስከመጨረሻዋ ሰዓት የግብጽ ሕዝብ ኮንትራት እንዳስፈረማቸው፣ ሕገ-መንግሥቱ የሕዝብ በመሆኑ በሕይወት እያሉ እንዲጣስ እንደማይፈቅዱ ከፍ ብሎ የሚሰማ ቀረርቶ ሲያሰሙ ነበር፡፡ የግብጽ ሕዝብ ግን በታሪኩ ለመጀሪያ ጊዜ እውነተኛ ሕዝበ-ውሳኔ በማድረግ የእኔ የሚለውን ህገ-መንግሥትን እያፀደቀ ነው፡፡ ከሙባረክ ማግስት፡፡

ሊቀ-ጠበብቱ አቶ መለስም ካድሬዎቻቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ እግር ከወርች አስረው የዘረፉትን የ99.6% ተውኔታ ቸውን ሕዝብ የሰጣቸው ኮንትራት አድርገው ተጨፈኑና ላሞኛችሁ ይሉናል፡፡ የሙባረክ አይነት ክርክር ልብ ከማድረቅ ባለፈ ምንም እንዳልፈየደ እያወቁ፡፡ ካስፈለገ ነገ ሌላ ማለት ይቻላል ብለው ነው? ወይንስ የተላበሱት ገፀ-ባህሪ ግድ ብሎዎት?

የሌሎቹን አገሮች ጉዳይ እንተወውና አገራችን ላይ እናተኩር፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከግብፁ ሠላማዊ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ጀምሮ አንፃራዊ በሆነ መልኩ ጥሩ ሽፋን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ዋና ዋና ከተሞች አካባቢ እንኳን ለምንገኝ የአረብ ዲሽ ምስጋና ይግባውና ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የፕሮፓጋንዳ እሩምታ ነፃ ከወጣን ሰነባበትን፡፡ ስሌቱ ሌላ እንደሆነ መገመት ቢቻልም ነፃ ላልወጣው ወገናችን ቲኒሽ ፈንጠቅ ማድረጉ አይከፋም፡፡ ዝም ቢሉ ሕዝባዊ እንቅስቃሴው በኢትዮጵያ ይቀሰቀሳል ብለው እንደፈሩ ሊያሳብቅባቸው ሆነ፡፡ ይልቅስ እግረ መንገዳቸውን እራሳቸውን ከሌሎች እምባገነኖች እለይባቸዋለሁ የሚሏቸውን መላምቶች እያፈላለጉ የፃድቅነት መንገዳቸውን በቴሌቪዥናቸው ቀጠሉ፡፡ መሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ተፈጥሮ ቢሆን ኑሮ ግን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቸኩ ፕሮፓጋንዳዎች ተቀንሰው የህዝብን ድምፅ ማሠማት በጀመረ ነበር፡፡

ውሎ ሳያድር ተወዳዳሪ እንደሌለው የሚነገርለት ጭንቅላት መላምቱን አፈለቀ፡፡ አቶ በረከት በካፒታል ጋዜጣ ለ3ዐ ዓመታት እድገት ታይቶ በማይታወቅባቸው አገራት ሕዝባዊ እንቅስቃሴው እንደተቀጣጠለ ነገሩን፡፡ አክለውም በእርሳቸውና በአቶ መለስ መዳፍ ሥር ባለቸው ኢትዮጵያውያ ግን ይኸ ፈጽሞ እንደማይሳካ ምኞታቸውን አበሰሩን፡፡ ምክንያቱንም ሲቀጥሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የእድገት ማማ ላይ ወጥቶ እየተምነሸነሸ በመሆኑ ከዚህ ድሎቱ ሊያላቀቀው የሚሻን አንዳች ኃይል እንደማይሻ በተለመደ አቢዬታዊ አነጋገራቸው ነገሩን፡፡ ልጅ ቢሮጥ አባቱን አይቀድምምና የእድገቱን ባቡር እያምዘገዘጉት ያሉት ሰው ከመፍትሔ ጋር በአንጡራ ሀብታቸው በኢ.ቲ.ቪ ብቅ አሉ፡፡ ተጠየቁ፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የማይከሰተው ሕዝቡ በነፃ ምርጫ ውክልና የሰጣቸው በመሆኑ ኮንትራቱንም አክብሮ እንደሚሰራ ነገሩን፡፡ ይህን ይበሉ እንጂ አሁን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከሚታይባቸው የሰሜን አፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የከፋ የኢኮኖሚ ድቀትና ፍፁም አፋኝ የሆነ የፖለቲካ ሥርዓት እየመሩ መሆናቸውን ለአፍታም ሊዘነጉት አይችሉም፡፡ ግራ መጋባት ይታይባቸዋል፡፡ ሕዝቡን ይተውትና ለምርጫ ዘረፋ በስራ ሸንግለው የሰበሰቧቸው አባላት በተለይም የወጣት ማህበራት እንዳይተዘቡዎት፡፡ ለነገሩ የወጣት ማህበራት አባላት ታሪካዊ ግዳጃቸውን ተወጥተው የባህር ላይ ኩበት በመሆናቸው ከጎነዎት እንደሌሉ አይዘነጉትም፡፡ አሁን ባደረጉት የማሞያ ምርጫ ደግሞ ሰዎች በማያውቁት በሌሉበት ‹ተመርጠው› መመረጣቸውን ጎረቤቶቻቸው እያበሰሯቸው ነው፡፡ ይኸን በመሰለ ሁኔታ ስለምን ኮንትራት ነው የሚያወሩት? ማነው ምስክረዎ? ለዚሁ ዓላማዎ ያቋቋሙት ጥላዎ የሆነው ምርጫ ቦርድ ወይንስ የአውሮፓ ሕብረት? ከዚህ ወዲያ ምን ተውኔት ይመጣል? ከዚህ ወዲያ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዴት ሊዋረድ ይችላል? ድምፁን የተነጠቀና አንደበቱን በግፍ የተሸበበ ሕዝብ መቼም ምንም አይልም ተብሎ ያልሰጠውን ኮንትራት መፈረሙ ይነገረዋል፡፡ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ አይደል! ከአምባገነኖች መገለጫዎች አንዱ ይኸው ነው፡፡ ለሕዝብ ሥር የሰደደ ንቀት፡፡ ድሮውንም ሕዝብን ባይንቁ አምባገነን ባልሆኑ ነበር፡፡ ከሆኑ ደግሞ ንቀታቸውን በዚህ መልኩ ቢገልፁ አይገርምም፡፡ አንዳንዴ ምን አልባት የስለላ መዋቅራቸውና ካድሬዎቸቸው በሚሰጧቸው የተሳሳተ መረጃ ምክንያት ይሆን ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን አራት ኪሎ ተቀምጠው አንገታቸው ሥር ያሉትን እጅግ ችምችም ብለው ተደጋግፈው የቆሙ የፊትበርን ጉረኖዎችና የሚኖርባቸውን የሕዝብ ብዛት እያዩ፣ ሕፃናት በገፍ በልመና አፋቸውን የሚፈቱባቸውን የአዲስ አበባ ጎዳናዎች እያዩ፣ አዛውንቶች በየፌርማታው ሲያጣጥሩና በየጥጉ ወድቀው ቁርና ሃሩር የሚፈራረቅባቸውን ኢትዮጵያውያን ድንገት ሳያማትሩ ቀርተው አይደለም ስለ ልማት የሚነግሩን፡፡ የኮንትራቱም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ተራ ውሸት፣ አይን ያወጣ የሕዝብ ንቀት ነው፡፡

ሲጀምር አቶ መለስ ካሳለፏቸው 2ዐ ዓመታት እድገት አስመዘገብኩ የሚሉት በ7ቱ ነው፡፡ ቢሞቱ 13ቱን ዓመታት ማንሳትም አይፈልጉም፡፡ ማስረጃቸውም የእርሳቸው የማዕከላዊ ስታስቲክ ባለስልጣን ነው፡፡ ከዚያም ከዘለለ ካድሬዎቻቸው ናቸው፡፡ ካድሬ ደግሞ ምን አይነት ቁጥር እንደሚያቀርብ ግልጽ ነው፡፡ መረጃ እንዴት እንደሚሰበሰብ ጠጋ ብሎ ለሚያውቅ ሰው ይቅርና በሩቁ ያሉትም አጥኝዎች የመረጃዎቹን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ማስገባታቸው አልቀረም፡፡ እነ አቶ መለሰ ግን የበሬ ወለደ የኢኮኖሚ ዕድገት ለጊዜውም ቢሆን ሕዝብን ለማዘናጋት ይበጃል እስካሉ ድረስ ይቀጥላሉ፡፡ የመሬት ይዞታው አልተቀየረም፡፡ የተቀየረ ነገር ካለ የህዝብ ቁጥር ነው፡፡ አሻቅቧል፡፡ መሬት ከተከፋፈለ በኋላ ወደ 14 ሚሊዬን
ለአቅመ አዳምና ሄዋን የደረሱ ኢትዮጵያውያን በወላጆቻቸውና በአያቶቻቸው ይጦራሉ፡፡ በችጋር እቶን ይበላሉ፡፡ ለእነ አቶ መለስ ይኸ እድገት ነው፡፡ ስለኢኮኖሚያዊው መስፈንጠር በሚያወራው ድርሰታቸውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከሚመረተው 94% ገደማ ለፍጆታነት እንደሚውል ተቀምጧል፡፡ በየትኛው ተረፈ ምርት ላይ ተመርኩዞ ኢኮኖሚው እንደሚስፈነጠር አቶ መለስ ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ አቶ ሶፊያን እንኳን ሊረዱት አይችሉም፡፡ ሃቀኛ የሙያ ሰው ከሆኑ፡፡ ከአዲስ አበባ ነዋሪ ወደ 5ዐ% ገደማ ሥራ አጥ ነው፡፡ ይኸም ለአቶ መለስ ዕድገት ነው፡፡ በዚህም ዕድገት ምክንያት ደግሞ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ አይከሰትም፡፡ ትንታኔ የአቶ መለስ፡፡ ሕፃናትን ሻይ ለማጠጣት የብር ስኳር ፍለጋ ከሱቅ ሱቅ በአዲስ አበባ መንከራተት የተለመደ ሆኗል፡፡ ፈልጎ ማጣትም እንዲሁ፡፡ ይሁን እንጂ ይኸም ዕድገት ነው፡፡ በሥራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት የትራንስፖርት ዋጋ ሰማይ ቢነካም በእድገቱ ምክንያት ሰው ክብሩ ወድቆ በሀይገር እንደችቦ ታስሮ ሲሄድ ማየት በኢትዮጵያዊነት ላይ ተስፋ መቁረጥን ሊጋብዝ ይችላል፡፡ ይኸም ለእርሳቸው ዕድገት ነው፡፡ ይኸንም ትራንስፖርት በግፊያ እንኳን ማግኘት ያልቻለው ሕዝብ ረጅሙን ጉዞ ከመቅረት መዘግየት ይሻላል ብሎ እንደ ሲራራ ነጋዴ ይነጉዳል፡፡ ይኸ ከተማ አዲስ አበባ ወይንስ ሞቃዲሾ ብሎ መጠየቅ የማይጠበቅ አይደለም፡፡

በችጋር የሚቆራመደውን የገጠሩን ሕዝብ እንተወው፡፡ ለመሆኑ ከተሜው እንዴት ነው የሚኖረው? እንደ እቶ መለስ ተረት ላውራ፡፡ ልጁ አባቱን አስማት የሚያሳይ ሰው ት/ቤት ስለሚመጣ መግቢያ ስጠኝ ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ አባትየው ሲመልስ እኔ አባትህ እያለሁልህ በ4ዐዐ ብር 7 ቤተሰብ አብልቼ አስተምሬ ሁሉን ችዬ የማኖር አስማተኛ እኔ ያለሁ የምን ሌላ አስማተኛ ያስፈልጋል አለ፡፡ ሁኔታው ከዚህም እጅግ የከፋ ነው፡፡ ይኸም ሆኖ ለአቶ መለስ እድገት ሞልቶ ተርፏል፡፡ ኢህአዴግ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ያሉ የጥራጥሬ እና ሌሎች ፍጆታዎችን ዋጋ በማስታወሻ ይመዘግቡ፡፡ እንዲሁም አሁን ያሉበትን ይመዝግቡ፡፡ በቲኒሹ 5ዐዐ% የዋጋ ጭማሪ በብዙዎቹ ላይ ማስተዋል ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ችጋርና ጭቆና አጉብጠውታል፡፡ ይሄ ግን ለእነ አቶ መለስ አይታያቸውም፡፡ ቢታያቸውም ማመን፣ ቢያምኑም መናገር አይፈልጉም፡፡ አዳዲስ ቃላት እየፈጠሩ ሕዝብን የተስፋ ሙልሙል ማስገመጥ እንጂ፡፡ ከዚያም ሲያልፍ ልዩ ልዩ በዓላትን መፍጠር ነው፡፡ ዳንኪራ ማስረገጥ፡፡ ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ ያከበራቸው በዓላት ቁጥር ከፈጠራቸው ሥራዎች እኩል ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ ሕዝቡን በምን ያደንዝዙት?

ሌላም የማደንዘዣ ትንግርት ማስተዋል ይቻላል፡፡ የአውሮፓ እግር ኳስና የወጣቶች የፍቅር ሁኔታ በሬዲዬ፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ያለ አይመስልም፡፡ ከጥዋቱ 1 ሰዓት እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ሲያሰኘው አደገኛ ቦዘኔ፣ ሲያሰኘው ባንክ ሰብሮ ለመግባት የሚከጀል እያለ የሚፈርጀውን ሲያሰኘውም ለእነ ቡጥሮስ ጋሊ ክብር ግዳይ የሚጥለውን ወጣት ከዚህ በዘለለ በጫት እና በአደንዛዥ እጽ ቢደነዝዝ ሰርግና ምላሹ ነው፡፡ ለምን ብሎ ለሚጠይቅ የግብጽ አይነት ገድል እንዳይሰራ ከፍተኛ ስጋት ስላለው ነው፡፡

የኢህአዴግ የማማለያ ሰነድ እንደሚያሳየው ከተሜነት ባለፉት 2ዐ ዓመታት አቅሙን አሟጦ ሊስፋፋ የቻለው 2% ብቻ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ኢህአዴግ የሳት አደጋ ማጥፊያ መኪና ያላቸው ከተሞች ከአዲስ አበባ ውጭ ይኸ ብሎ መንገር አይቻለውም፡፡ የጤናው ክፍል አደገ ተመነደገ በሚባልበት አገር የትኛው የመንግሥት ሆስፒታል ኤም.አር.አይ ይቅርና ሲቲ ስካን እንዳለው አቶ መለስ ሊነግሩን አቅም የላቸውም፡፡ ከተሜነት በገደምዳሜ መሆኑ ነው፡፡ ግን በደፈናው ስለኢኮኖሚው ማደግ አውርተው አይጠግቡም፡፡ ስራቸውን የሚወዱት እንዲሁ በዘፈቀደ መናገር ስለሚችሉ ይሆናል፡፡ ከ2ዐ ዓመት በኋላም የማይሰለች ድንቅ ሥራ፡፡ እንደጓዶቻቸው ከረጅም አመት ግልጋሎት በኋላ እንኳን የማይደክሙ እና የማይሰለቹ ድንቅ ፍጡር፡፡

በአጠቃላይ በሚከፍለው ግብረ እየተራበ የሚያበላቸውን፣ እየታረዘ የሚያለብሳቸውን፣ የእሳት አደጋ መኪና ሳይኖረው በኮብራ የሚያንፏልላቸውንና እንደግዑዝ በየታዛው ወድቆ እነርሱን በሰገነት የሚያኖረውን ኢትዮጵያዊ ጨርሶ መናቅ ከነውርም በላይ ነው፡፡ አይናቸው በንዋይ እና በስልጣን ግርዶሽ ተከልሏል፡፡ ንቀታቸውም ከፍተኛ ስለመሆኑ ብዙ አያነጋግረም፡፡ እነ አቶ መለስ በሚናኙበት አዲስ ዘመን ስማቸውን አንዴ ቶፊቅ ሌላ ጊዜ ሌላ በማለት የአምባገነን ትንተናቸውን ያስኮምኩምናል፡፡ በአፋቸው በኢትዮጵያ ሊከሰት አይችልም ይበሉ እንጂ በልባማቸው ግን የሚሉትን አያምኑም፡፡ ለዚህም ነው እንደለመዱት የኦሪት ፍየል ፍለጋውን ከወዲሁ የተያያዙት፡፡ በሌሎች አገሮች ሕዝብ ያለመሪ እና ተመሪ ምን አይነት ሚና እንደተጫወተ እያዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በተቃዋሚዎች ካልተመራ በራሱ ምንም ማድረግ እንደማይችል ይነግሩናል፡፡ አክለው ደግሞ አቶ መለስ
ሕዝብ ከመሪዎቹ የላቀ ስለመሆኑ ይነግሩናል፡፡ የሚሉትን ካመኑበት የኢትዮጵያ ሕዝብስ ለምን መሪዎቹን ይጠብቃል? ይኸ አይን ያወጣ ንቀት ነው፡፡ በሌላ ወገን ለገበያ ፍጆታ በማይቀርበው ትንታኔያቸው ኢትዮጵያም ውስጥ ሊከሰት እንደሚችል ያምናሉ፡፡ ስለዚህ ጥርሳቸውን ነቅለው ያደጉበትን ሴራቸውን ተግባራዊ ለማድረግ መደላድል እየፈጠሩ መሆኑ ነው፡፡ በዘመቻ አዲስ ዘመን፡፡ እንደለመዱት መሳሪያ እሰው ቤት በማስቀመጥ፣ ቦንብ አውቶብስ ውስጥ አሊያም ግንብ ስር በማኖር እነከሌ የመሩት ዘመቻ በረቂቁ ደህነነቶቻው አንደከሸፈ ይነግሩናል፡፡ እንዲህ ነው የ‹ሕዝብ ደህንነት› ሕዝቡም አደጋው በቁጥጥር ሥር በመዋሉ እንዲረጋጋ ይነገረዋል፡፡ ይኸ የተለመደ የማፍያ ታክቲካቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ የማይመጥን አመራር ከኢህአዴግ ወዲያ ከወዴት ይምጣ? አሁን ግን ነገሩ ሁሉ ለየቅል መሆኑን ልብ ቢሉ መልካም ነው፡፡

አቢዮታውያን ሆነው እንደቀሩ ሁሉ አሁንም የቀደመ ትወናቸውን የሙጥኝ ማለት የመረጡ ይመስላል፡፡ ይኸ ግን የማይማሩ ወይንም ሁልጊዜም ከማደናቆር ውጭ ከስህተታቸው ሊታረሙ እንደማይችሉ ማሳያ ነው፡፡ ነገር ግን ያልተቀየሩት እነርሱ እንጂ ዓለም እየተቀየረ ነው፡፡ ለጥቅሞቻቸው ሲሉ የንፁሃንን ደም አይተው እንዳላዩ ያልፉ የነበሩ አገሮች ከአምባገነኖች ጋር በመዶለት ለዓለም ሠላምም ሆነ ብልጽግና ሊያመጡ እንደማይችሉ ገብቷቸዋል፡፡ ሕዝቡም እየተለወጠ ነው፡፡ ሕዝብ በፍርሃት እርሃብና ጭቆናን ከመከናነነብ ፍርሃቱን አሸንፎ የክብር ሞት መሞትን መርጧል፡፡ ግብጽ ትመስክር፡፡ ሌሎችም፡፡ ስለዚህ ይልቅስ እራሳችሁን የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄ በአግባቡ መመለስን አስለምዱት፡፡ ይኸን ጊዜ ያምርባችኋል፡፡ ሕዝብ በመደለያ በአለቀ ሰዓት ቢመለስ ኑሮ በሳውዲ ወጭ እንዲሆን የታዘዘው 38 ቢሊዬን ዶላር በረዳው ነበር፡፡ ሕዝብን በመሸንገያ ዝም ማሰኘት እንደማይቻል ብዙ የማይሞቱ ምስክሮችን ማቅረብ ይቻላል፡፡

ያ አይሆንም፡፡ ሕዝብ ለነፃነቱና ለክብሩ የሚሰጠውን ዋጋ በገንዘብ ለመተመን ባይሞከር፡፡ የኢህአዴግን አስተሳሰብ ተቀብለው አሊያም ተገደው የኢህአዴግ አባላት የሆኑም አሁን ያለውን ልዩ ሁኔታ በጽሞና እንደሚረዱት እገምታለሁ፡፡ እነርሱም ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ችግሩም ዘልቆ እንደሚሰማቸው መገመት ይቻላል፡፡ በግብጽና በቱኒዚያ የነበሩ በሚሊዬኖች የሚቆጠሩ የገዥ ፓርቲዎች አባላትም ዞሮ ዞሮ ከወገናቸው ጋር መቆማቸውን በተግባር አይተናል፡፡ ከጥቂቶች በስተቀር፡፡ ደህንነቱና ፖሊሱም ቢሆን እንዲሁ፡፡ የመንንም ሌሎችንም ማከል ይቻላል፡፡ መልእክቴ ግልጽ ነው፡፡ ኢህአዴግ ማደናገሩንና ፌዙን ትቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄዎች በአስቸኳይ ይመልስ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ያነሰም ከዚህ የበዛም አይፈልግም፡፡ በአሁኑ ሰዓት፡፡

እነ አቶ መለስ ይኸን መንገድ ካልመረጡ፤ አቶ በረከት በአንድ ወቀት እንዳሉት ይኸ ድርጅት ብዙ ፈተናዎችን በአሸናፊነት የተወጣ ድርጅት ነው እያሉ በየዋህ ዘላለማዊ ጀብደኝነታቸው ባይቀጥሉ ይመከራል፡፡ ኢህአዴግ ለ2ዐ ዓመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት የአውተበተው የልዩነት መረብ በማንም ሳይሆን በራሱ በኢትዮጵያ ሕዝብ ተበጣጥሷል፡፡ አሁን በምናያቸው የሰሜን አፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሕዝብ አንድነት ብቻ ሳይሆን የዓላማ አንድነትም ምን ያህል ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ መረዳት ይገባል፡፡ የኢህአዴግ መሪዎች አሁንም ከደመናው ካልወረዱ የኢትዮጵያን ሕዝብ በመከፋፈል የልዩነት ግንቦች መሆንን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ ያለፉት 2ዐ ዓመታት፣ ቀደምት የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክም በተለይም ደግሞ አሁን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር እየተፈጠረ ያለው የኢትዮጵያውን መሰባሰብ ለዚህ የህልም ሩጫቸው ፍቱን ማርከሻ ነው፡፡ አቶ መለስ የጭቆና ቀንበረዎን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በአስቸኳይ ያንሱ፡፡ እርስዎም በአስቸኳይ ነፃ ይውጡ፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ እንዴት ቀልድ ጨምራል ጃል!

Monday, March 14th, 2011

በቤቴ ኢቲቪ አይከፈትም፡፡ ከወያኔ ጋር ንክኪ ያለው ሬዲዮም እንዲሁ፡፡ ትክክል እንዳልሆንኩ ይገባኛል፡፡ ምን ላድርግ? ስለሚያመኝ እኮ ነው፤ ወድጄን መሰላችሁ? ይህቺን አልፎ አልፎ የምሞነጫጭራትን ነገር እንካEን የማቀራስመው ባብዛኛው በስማ በለው ከማገኘውና ከውጭ ሚዲያዎች ከምከታተለው ነው፡፡ ይሁንና እኔ አልሰማም ብልም ሰው እያመጣ ሳልወድ በግዴ ይነግረኛል፡፡ እምቢ አልል ነገር ከሰው ጋር ነው የምውል፡፡

ጋደኞቼ እየተናደዱ ትናንት ማታ ‹እገሌ እንዲህ አለ፤ እገሊት እንዲህ አለች› ሲሉ ስለምሰማ አንዳንዴ እቤቴ አለማዳመጤን ሳስበው አልሸሹም ዘወር አሉ ዓይነት ነገር ይሆንብኛል፡፡ ጠበል ሄጄ ትግስቱን እንዲሰጠኝ ልለማመን ይሆን? በእስካሁኑ ሁኔታየ ከቤተሰቤ ጋር የሽንብራ ቆሬ ወይም የጉንዲት አሊያም የሰገሌ ጦርነት ይከፈታታል እንጂ እንዴት ተደርጎ ኢቲቪ በገዛ ቤቴ ይከፈታል? እንደዱሮዋ ሶቪየት ኀብረት ብንሆን ምን ይውጠን ነበር ብዬ ሳስብ ደግሞ ጭንቅ ይለኛል፡፡ የወያኔ ጆሮ ይደፈንና በዚያች ሀገር – በቀድሞው ቀፍዳጅ የሶሻሊስት ሥርዓት ዘመን – ካገራቸው የዜና ማዕከላት በስተቀር የሌላ ሀገር ሚዲያ እንዲያዳምጡ በፍጡም አይፈቀድላቸውም ነበር ይባላል፡፡ የምታስታውሱ ካላችሁ እነዚህ አውሮፓዎችና አሜሪካዎች የዚያችን የሶሻሊስት ሀገር ሕዝብ ልብ ለማሸፈት የተለያዩ ዘመቻዎችን ያካሂዱ ነበር፡፡ ከነዚያ ዘመቻዎቻቸው መካከል አንዱ ‹ሬዲዮ ፍሪ ዩሮፕ› የሚል የሬዲዮ ጣቢያ ከፍተው በኃይለኛ ሞገድ በድፍን ሶቪየት ኅብረት ሊደመጥ የሚችል ፀረ ሶሻሊዝምና ኮሚውኒዝም ቅሰቀሳ ማካሄድ ዋናው ፀረ – ኀበረተሰባዊነት(ሶሻሊዝም) ተግባራቸው ነበረ፡፡ ከዚህ ‹ሕዝብን በራዥ› ጠንቅ ሕዝባቸውን ‹ለመታደግ› ሶቪየቶች ምን ያደርጉ ነበር መሰላችሁ ታዲያ – ማንም ሰው ወደቤቱ ገብቶ መብራት ሊያበራ እስዊቹን ሲነካ የራሱን ሀገር ሬዲዮም አብሮ እንዲከፍት ተደርጎ የድምጽ መጨመሪያና መቀነሻ በሌለው ሁኔታ መብራቱንም እስካላጠፋውና በጨለማ መደናበር እስካልፈለገ ድረስ አጥፍቶ እስኪተኛ የሀገሩን ሬዲዮ ብቻ እንዲኮመኩም የሚያስችል ማብሪያ ማጥፊያ በየቤቱ ተገጠመ አሉ፡፡ አሉ ነው እንግዲህ፡፡ በአሉ ክስና ወቀሳ የለም፡፡ ሌላ ሬዲዮም ሆነ ቲቪ እንዲኖረው አይፈቀድም ነበር አሉ፡፡ ሰውዬው ሲፈልግ በሻማና በጡዋፍ ወይም በኩራዝና በፋኖስ ይቀመጣታል እንጂ መብራት ካበራ የግዱን ያዳምጣታል፡፡ የሚያስደስተው ግን – ይህ ታሪክ እውነትም ይሁን ውሸት – ያ ጊዜ ማለፉ ነው፡፡ የኛ ብቻ አለ እንጂ እየተንቀራፈፈ፡፡ በነገራችን ላይ ይህን ታሪክ ከጨዋታነት አስበልጬ ባላየው ደስ ይለኛል፡፡

አሁን በኛ ሀገር ግና ተመስገን ነው በጥባጭ የቤተሰብ አባላት አንዴ ገመና ሌላ ጊዜ ካEስ ጨዋታ ወይም የእሁድ መዝናኛ 120 ፕሮግራም እያሉ ይጠምሱናል እንጂ የወያኔን ትውከትና ቅርሻት ላለማዳመጥ – ይቅርታ ሌላ መጣኝ ቃል ስላጣሁ ነውና በአሳቻ ሰዓት አንቡልኝ ይቺን ሐረግ – ቲቪያችንን ከነአካቴው መጠርቀም ወይም በዲሽ የፈለግነውን የውጭ ቻናል ማየት በምንችልበት ሁኔታ ላይ መገኘታችን እፎይታን ሰጥቶናል፡፡ እንደራሽያዎቹ ቤት፣ መብራት ስናበራ አብሮ የሚከፈት ቲቪና ሬዲዮ ቢኖረን ምን ይውጠን ነበር? ጉድ እኮ ነው!

ሰሞኑን መሌ መሊሻ ቀደዳዋን በስፋት ይዛዋለች፡፡ እንደሱዋ በለስ የቀናው የሀገር ‹መሪ› መቼም በዓለም ታይቶ የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ከፍ ሲል እንደተናገርኩት በቤቴ ኢቲቪ አይከፈትም ብያለሁ፡፡ ልክፈት ቢሉ እንኩዋን የወያኔን ንዴት በነሱ ላይ ነው የምወጣው፡፡ ምን ቁርጥ አድርÕቸው? ወደፊት ንስሃ ገብቼ ኃጢያቴን አወርዳለሁ እንጂ አሁን እበደልካEቸው እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ መቼም ‹ሰው ነኝና› ብላEልና ዘፋኙ የይቅርታ ዘመን ሲመጣ ይቅር ይሉኝ ይሆናል፡፡ እናም ዛሬ ማታ ለአቡየ ጠበል ጠዲቅ ጎረቤት ሄጄ መሌን እንደማርካቶ ጣቃ ሲቀረደድ በዚያው በፈረደበት ‹ቲቪያችን› አየሁት፡፡ እሰው ቤት በንግድነት ተጠርቶ ሄዶ ቲቪ ዝጉ አይባል! ደግሞስ ማን ማንን ያውቃል? በከንቱ ጭዳ ልሁን? አጅሬን ምን እንደነካው አላውቅም ይህን ሰሞን በትግርኛም ባማርኛም ‹ጋዜጣዊ መግለጫ› መስጠት አብዝቶኣል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫዎቹ ግን እንደወትሮው ሁሉ በተወሰኑ ‹ጋዜጠኞች› ጠያቂነት የሚካሄዱና መልስ ሊሰጣቸው የሚፈለጉ አስቀድመው የተጠኑ ጥያቄዎች ላይ የሚያተኮሩ መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡

በቀደም ዕለት የትግርኛው ጠያቂ (አንድ ብቻ ነው) ‹ የኤርትራ ሕዝብ ከሰሜን አፍሪካው ሕዝባዊ አመጽ ምን ሊማር ይችላል? ብሎ ለጠየቀው ሲመልስ ‹ አንደኛ … ሁለተኛ የኤርትራ ሕዝብ በላዩ ላይ የተጫነበት መንግሥት የአራዊት መንግሥት ስለሆነ በሕዝባዊ ተቃውሞ ከሥልጣን ሊያወርደው የሚችልበትን ትምህርት ቀስሞኣል፡፡ ሦስተኛ …› ብሎ የመለሰው ከኅሊናየ ለምንጊዜውም አይጠፋም፡፡ ‹ይሉሽን ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ› እንዳይባል መለስ የሚሠራውን በሚገባ ያውቃል፤ ግን የገባበት ዕዳ ከባድ ስለሆነና ተፈጥሮውም ውሸታም በመሆኑ ሁሉንም እውነት ከመሸምጠጥ ሌላ ምንም አማራጭ የለውም፡፡ መለስ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው #ፀሐይ በምዕራብ ወጥታ በምሥራቅ ትገባለች፤ ነጭና ነጭ ሲቀላቀል ጥቁር ይሆናል፤ ሁለትና ሁለት ሲደመር አሥራ አንድ ነው፤ ሰው ሲራብ ይጠግባል፤ ሀገር ስትጠፋ ትበለጽጋለች – ትለማለች፤ … $ ቢል ለመናገሩ እንጂ ለመታመኑ ሃሳቡ አይበላውም፡፡ ምን ዓይነት ድፍን ቅል እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ከርሱ ይልቅ ይህን ተፈጥሮውን እያወቁ ብዙ ሰዎች ከርሱ ሥር ሉጥ ሉጥ ማለታቸው በእጅጉ ይገርመናል፡፡ ‹አብሽ ልዋጩን አያጣም› የሚባለው ለካንስ ለዚህ ነው? የሚገርም ፍጡር እኮ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳንሆን – ለማየት ያብቃችሁ – ወደፊት የሰው ልጅ በአጠቃላይ የሚያፍርበት የሚሌኒየሙ አባ ስጠው አደገኛ ውሸታም ነው፡፡ አደገኛነቱም እንደኔ በየጥጋጥጉ የሚወሸከት ሳይሆን የመንግሥትን ትልቁን ሥልጣን ይዞ በ80 ሚሊዮን ሕዝብ ሕይወት ላይ የሚያፌዝና የሚቀልድ ወናፍና ማንዘርዘሪያ ወንፊት መሆኑ ነው፡፡ የተራ ዜጋ ውሸታምነት ዕዳው ቀላል ነው፡፡ በሱ የሥልጣን ቦታ ላይ ሆኖ ይህን ያህል ቅድ በርሜል መሆን ግን ለጊዜው ክፉኛ ያሳዝናል፡፡ ለወደፊቱ ግን ይህ ሰው መቼም ቢሆን መሞቱ አይቀርምና በድኑ ለሁነኛ የሥነ ሕይወት ተመራማሪዎች ተሰጥቶ አንጎሉ ከምን እንደተሠራ መፈተሸ ይኖርበታል፡፡ በበኩሌ እርግጠኛ ነኝ የዚህ ሰው አንጎል የሰው ብቻ ሳይሆን የሆነ የባዕድ ነገር ቅልቅል ሳይኖርበት የሚቀር አይመስለኝም፡፡

እንዲያ ባይሆን ኖሮ፤ #የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ኢሕአዴግን በመምረጡና በፈለገው የምርጫ ሰዓት በዝረራ ሊጥለው እንደሚችል ስለሚረዳ የሰሜን አፍሪካው የተቃውሞ ሕዝባዊ አመጽ ኢትዮጵያን አያሰጋትም፡፡ የኛ ሥጋት የገባነውን ኮንትራት በገባነው ቃል መሠረት ማከናውናችን ነው፡፡ … እርግጥ የኤርትራ መንግሥት አዲስ አበባን ባግዳድ ለማድረግ ሤራ እየሸረበ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ይህን ህልሙን እውን ለማድረግም አንዳንድ ተቃዋሚዎችን ለመጠቀም እንደሚሞክር ፍንጮች እየታዩ ነው፡፡ ይህንን ተንካEሽ ድርጊቱን ደግሞ 80 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሶ ጨብጠው አይጠብቁትም፡፡ ኢሕአዴግና ሕዝቡ እጅና Õንት ሆነው የጀመሩትን ዴሞክራሲያዊ የልማት እንቅስቃሴ ሊያጨናግፍባቸው የሚመጣባቸውን ማንኛውንም ኃይል በብርቱ ክንዳቸው ይመልሱታል፡፡ ሕዝባዊ አመጽና ተቃውሞ አምባገነን መንግሥታትን እንጂ በዴሞክራሲ አግባብ ሥልጣን ላይ የወጡ እንደ ኢሕአዴግ ያሉ መንግሥታት የራስ ምታት ሊሆን አይችልም፡፡ …$ (እፍፍፍ… ደከመኝ እባካችሁ!) ብቻ – ልድገመው – እንዲያ ባይሀን ኖሮ እንዲህ በጥቅስ ውስጥ እንደተቀመጠው ያለ ከበረዶና ከአመዳይ የነጣ ነጭ ውሸት ያለ አንዳች ሀፍረት አይናገርም ነበር፡፡ ስለዚህ መለስ በሽተኛ ለመሆኑ ከዚህ በላይ ማስረጃ ሊቀርብ አይችልም፡፡ በመሠረቱ አምባገነንነት በራሱ እልም ያለ የበሽታዎች ሁሉ ቁንጮ በሽታና ፈውስም የማይገኝለት ትልቁ ደዌ ነው፡፡
yinegal3@gmail.com

ይድረስ ለአንድ የሀገሬ ወታደር! አቢይ አፈወርቅ

Tuesday, March 8th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የፍቅር ኪሳራ የጠብ ትርፍ የለውም በነጻነት ዘገየ

Sunday, March 6th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በለንደን ማክሰኞ ማርች 8 2011

Wednesday, March 2nd, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በሚስጥር መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚጠቅሙ ቀላል ዘዴዎች

Monday, February 28th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የመለስ ከስልጣን መውረጃ ቀን ሲቃረብ

Monday, February 28th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የንባይ ካብ በበዛብህ ትግስቱ

Saturday, February 12th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ታሰረ

Friday, February 11th, 2011

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በፒያሳ ከሚገኝ፡የኢንተርኔት ካፌ ሲወጡ ብዛት ባላቸዉ የፌደራል ፖሊሲ ታጣቂዎች መያዛቸዉን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና ያመለክታል። የፌደራል ፖሊስ ታጣቂዎች ምንም አይነት የፍርድ ቤት መጥሪያም ሆነ ፍቃድ በእጃቸዉ ያልነበረ ሲሆን አቶ እስክንድርን በቀጥታ በፌደራል ፖሊሲ ጽ/ቤት ነበር የወሰዷቸዉ።

በፌዴራል ፖሊሲ ጽ/ቤት እንደደረሱ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር፣ ቁጣ በተሞላበት ሁኔታ እንዳነጋገሯቸዉ የደረሰን ዜና አክሎ ይገልጻል። «በቱኒዚያና በግብጽ እየሆነ ያለዉ በኢትዮጵያም እንዲነሳ አመጽ እያነሳሳህ ነህ። አንድ ነገር ቢፈጠር መጀመሪያ ተጠያቂ የምናደርገርዉ አንተን ነዉ» በማለት ጠንካራ ዛቻና ቁጣ እንደሰነዘሩባቸውም ለማወቅ ችለናል።

በቅርቡ አገር ዉስጥ በሚታተም ጋዜጣ «በቱኒዚያና በግብጽ የሚታየዉ በኢትዮጵያ እንዳይከሰት ምን መደረግ ያለበት ይመስልዎታል ?» ለሚለዉ ጥያቄ ፣ «በሕገ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ምርጫ መጥራት፣ፓርላማን ማፍረስ ይችላል። በመሆኑም አሁን ያለዉን ፓርላማ ፈርሶ ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንደገና አዲስ ምርጫ ቢደረግ፣ የፖለቲካ መረጋጋት ስለሚያመጣ በግብጽ የታየዉ ላይታይ ይችላል» የሚል መልስ በመመለሳቸውና በቅርቡ በተለያዩ ድህረ ገጾች የቀድሞ የኢታ ማጆር ሹም የነበሩትን ጄነራል ጻድቃንን በማንሳት በጻፉት ጽሁፍ፣ ባለስልጣናቱ እንደተናደዱ የሚገልጸዉ የደረሰን ዘገባ፣ የፖሊሱ ሃላፊ የጄነራል ጻድቃን ፎቶ ያለበትን የአቶ እስክንድር ጽሑፍ ቅጂዎች በእጃቸዉ ይዘዉ እንደነበረም ይገልጻል።

«ምን አድርግ ነዉ የምትሉኝ ? መጻፌን ላቁም ወይ ?» ብለዉ አቶ እስክንድር ሲጠይቁ፣ የፖሊስ ሃላፊዉ «እርሱን አላልንህም፤ መጻፍ ትችላለህ። ነገር ግን መስመር አልፈሃል። በእጃችን ብዙ መረጃዎች ከወዲሁ ይዘናል። አንድ ነገር ቢሆን አንለቅህም» የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት።

የፖሊስ ሃላፊዉ ሕዝቡ እንደ ግብጽ ቢነሳ፣ አገዛዙ የሕዝቡን ግፊት መመከት እንደሚችል ሳይገልጹም አላለፉም። «ኢሕአዴግ ማንኛዉም ነገር ያከሽፋል፤ ይቆጣጠራልም» ነበር ያሉት።

አቶ እስክንድር በዚህ ሳምንት ለአንባቢያን ሊያቀርቡት ያዘጋጁትን ጽሁፍ ጨምሮ በርካታ በእጃቸዉ የነበሩ ወረቀቶች የተወሰዱባቸዉ ሲሆን ፣ የዛሬዉ ክስተት ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ቃሊቲ በግፍና በጭካኔ ከመወሰዷ በፊት ፌደራል ፖሊስ በርሷ ላይ ሲያደርግ የነበረዉን ዛቻና ወከባ የሚያስታወስ እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።

በግብጽና በቱኒዚያ የተፈጠረዉ ሁኔታ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያንን ዉስጥ ዉስጡን እያነጋገረ ሲሆን በአቶ እስክድንር ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ገዢዉ ፓርቲ ዉስጥ ድንጋጤና መረበሽ እንደፈጠረ የሚያሳይ እንደሆነም በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ይናገራሉ። «የምንሰማቸዉ ዜናዎች ለመለስ ዜናዊ ደስ የሚያሰኙ አይደሉም። አስተዋይ ቢሆን ኖሮ ከሕዝብ ጋር ተጣልቶ የትም እንደማይደረስ ከሙባረክና ከቤን አሊ ይማር ነበር። እነ መለስ እስክንድርን አስሮ ከማስፈራራት ይልቅ የመከራቸዉን ምክር ያደምጡ ነበር።» ሲሉም አስተያየት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ወጣት እንደፈንጂ ቦምብ

Friday, February 11th, 2011

ከዶ/ር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በህልምአለኝ

በአትዮጵያ ውስጥ በመታየት ላይ ያለው ሁኔታ ወጣቱ የመፈንጃ ጊዜውን እንደሚቆጥር ፈንጂ መሆኑን ያመላክታል፡፡የወጣቱ በሁለንተናዊ ፍርሃትና መሳቀቅ ውስጥ መሆን፤ተስፋ ማጣት፤በሃገሪቱ ላይ እያቆለቆለ በሚሄደው የኢኮኖሚ ውድቀት፤በሚተገበረው የኤኮኖሚ ቀውስ፤ እና የፖለቲካውና የሃገሪቱ እድገት መጨንገፍ ዋነኛ መረጋገጫዎች ናቸው፡፡ የወጣቱ የነጻነትና የለውጥ ጥመኛነቱ የሚታይ ሃቅ ነው፡፡ ጥያቄው ደግሞ ወጣቱ ይህን የሚመኘውንና ለማምጣት የሚጥርለትን ለውጥ ተገፍቶ በሚገባበት ማስገደድ አለያስ በሚወደውና በቆመለት ሰላማዊ መንገድ ነው የሚያመጣው? በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተስፋ መቁረጥና በራእያቸው መጨፍለቅ ያዘኑና በኢትዮጵያቸው ብርሃን ማየት ማሰብ የተከለከሉት ወጣቶች ግራ ተጋብተው በእግሮቻቸው ጣቶች ድምጽ ለመስጠትም እየዳዳቸው ነው፡፡ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ሃገራቸውን ሳይሆን በሃገራቸው ላይ የተጫነውን የግፍ ገዢ፤በመጥላትና ከሃገርና ከወገን በመነጠል ከደቡብ አፍሪካ እስከ ሰሜን አሜሪካ፤ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ሩቅ ምስራቅ ድረስ ስደተኞች ሆነዋል፡፡

በ1935 ዓ/ም እ አ አ አዶልፍ ሂትለር ለፓርቲው መደበኛ ስብሰባ ባደረገው ንግግር ላይ ‹‹ወጣቱን ንብረቱ ያደረገ ብቻ የነገው ባለቤት መሆን የሚችለው›› ነበር ያለው፡፡ ወጣቱን በናዚ ስሜትና ጠበል አጥምቆ የናዚን ፍልስፍና በዓለም ላይ እንዲረጩት ለማድረግ፡፡ ሆኖም ግን ወጣቱን በራሳቸው ቅርጽ ለመለወጥና አእምሮው የተሰለበ ወጣት በመፍጠር ቅዠታቸውን እውነት ላማድረግ ነው የአምባገነኖችና የፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ምኞትና ዓላማ

ሶቭየቶችም ወጣት ኮምሶሞልስን ፈጥረው በፓርቲያቸው ውስጥ በማካተትና በማጨንገፍ ሕዝቡን ለመግዛት ያደረጉት ዘዴም ነበር፡፡የቻይናው ማኦም ወጣቱን በሰፊው በማንቀሳቀስ በ1960ዎቹ ቀዩን ጦር በመፍጠር ‹‹ዘለዓለማዊ አብዮት››የሚል ራዕይ ፈጠረ፡፡የቀዩ ጦር ተግባርም የባሕል አብዮቱን ተግባራዊ ማድረግ ነበር፡፡

በሃገራችን ኢትዮጵያም የዘውዱ አገዛዝ ከተገረሰሰ በኋላ በተፈጠረውና ለ17 ዓመታት በገዛው የደርግ ስርአት ወቅት፤ወጣቱን የወታደራዊው ጁንታና የሲሻሊስት አብዮት አካል ለማድረግ ብዙ ጥረት ተደርጎ ነበር፡፡ይሄ የፍቅር ጎዳና ግን ብዙም ሳይቆይ በደርግ የጭካኔ ቀይ ሽብር በሺህ የሚቆጠረው ወጣት ከቤቱ እየታደነ፤ ከጎዳና ላይ እየታፈነ በመጨፍጨፉ ያ የፍቅር ጎዳና ደም በደም ያውም የነገው ተተኪ ትውልድ በአብላጫው የተጨፈጨፈበት ሆኖ ተደመደመ፡፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲታወስና ሲነገር የሚኖር የሟች ቤተሰቦች ልጆቻቸው የተገደሉበትን ጥይት ዋጋ እየከፈሉ አስከሬን እንዲወስዱ የሚያዝ መመርያ የወታደራዊው ደርግ የበላይ የሆነው መንግስቱ ሃይለማርያም አወጣ፡፡

በንብረተነት የሚያዙት ‹‹ባሮች ብቻ›› ናቸው

አሁን ደግሞ ፈላጭ ቆራጭ የሆነው አምባገነኑ ገዢ መለስ ዜናዊ በተራው የኢትዮጵያን ወጣት በንብረትነት ለመቆጣጠርና የግሉ በማድረግ የዘመናት ባለስልጣን ሆኖ የመቆየት ህልሙን ማስፈጸሚያ ለማድረግ የማይሆነውን ጉዞ ጀምሮታል፡፡ የመለስ እቅድና ቅዠት ግልጽ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ብልህ ወጣቶች በመምረጥና በመመልመል የተፈተኑና የነጠሩ በማለት ለአገልጋይነት ለማዋል ነው፡፡ለመማር፤ስራ ለመያዝ፤የጤና ዋስትና ለማግኘት፤በሰብአዊ አገልግሎት ተግባራት ተሳታፊ ለመሆን የፓርቲው ታማኝ አባል መሆን ወሳኝና አማራጭ የማይደረግለትግዴታ ነው በማለት አወጀ፡፡ ወጣቱ ያለው አማራጭም ህሊናውን ሸጦ የተባለውን መቀበል ሆነ፡፡ ይህን ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነው ግን ያለው አማራጭ በችግር አለንጋ እየተገረፈ በችጋር መቆላትና ከሰብአዊነት ውጭ ሆኖ የዜግነት መብቱን መገፈፍ ነው፡፡ የገዢው ፓርቲ አባል ያልሆኑም ከሚኖሩበት ቀበሌ መብታቸው የሆነውን የስራ መፈለጊያ የድጋፍ ደብዳቤ ማግኘትና ሌላም የመኖር መብቱ የሆነውን ሁሉ ይከለከላል፡፡ አዳዲስ ተመራቂ የሆኑትን የኮሌጅ ተማሪዎችም የፓርቲው አባላት ለማድረግ ወጥሮ መያዣ ሰንሰለት መለስ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡በ2008 እና 2009 የትምህርት ዘመናት ትምህርታቸውን የጨረሱትን የኮሌጅ ምሩቃን የትምህርት ማስረጃቸውን እንዳይወስዱ በማድረግ ሥራ ማግኘታቸውንና መጀመራቸውን ሲያረጋግጡና የተማሩበትን ለመክፈል መቻላቸው ሲታወቅ እንዲወስዱ የሚያግድ ህግ ደነገገ፡፡ ይህ ህግ ግን በገዢው ፓርቲ አባላት ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

የአንድን ሕዝብ ወጣት አካል ‹‹በንብረትነት›› መያዝ ከአልባንያ እስከዝምባብዌ ላሉ አምባገነን ገዢ እርኩስ ባሀሪያቸው ነው፡ወጣትን እንደንብረት መያዝና መገልገያ ማድረግ ከባርያው ስርአት ጋር የተያያዘ የአምባገነኖች ባህሪ ነው፡፡አምነባ ገነኖች አስተዳዳሪዎች ሳይሆኑ ገዢዎች የሚባትም በዚህ የተነሳ ነው፡፡የባርያው ተግባር ጌታውን ማገልገል ብቻ ነው፡፡ጌታው የባርያውን ጉልበትና ሰውነት ይቆጣጠረዋል እንጂ ህሊናውን ጨርሶ አይገዛውም ስለዚህም አሳዳሪው የባርያውን ህሊና በማላሸቅ የጌታው መጠቀሚያነቱን ለማረጋገጥ ስብእናውን አላሽቆ፤ ህሊናውን አዘናግቶ፤ጌታው የሚያስበለት፤ ጌታው የሚያቅድለት ሆኖ እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ይህንንም ለማረጋገጥ አሳዳሪው ባርያውን አቅመቢስ፤ተስፋ ቢስ እና ከርታታ ያደርገዋል፡፡

ወጣቱን-በንብረትነት ወይስ ወጣቱን- በኪራይ

መለስ ባለፈው ምርጫ ተቀዳጀሁ ያለውን የ99.6 በመቶ ምርጫ ፌሽታ ሲያከብር ባደረገው የካፈርኩ አይመልሰኝ ንግግሩ ላይ ‹‹በመካሄድ ላይ ባለው የልማት እንቅስቃሴ ውጤት ተጠቃሚ በሆነውና በተግባር ሊቀላቀልና ተጠቃሚ ለመሆን በወሰነው የኢትዮጵያ ወጣት እጅጉን ኮርተናል፡፡ምስጋናችን በማቅረብ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ላደረጉልን አበረታች ድጋፍ ሁሉ ሰላምታችንን ተቀበሉን እንላለን ሲሉ ምን ማለት እንዳሰቡ ሲሰላ በ2009 በተደረገው ዓመታዊው የወጣቶች ስብሰባ ላይ የተደረገው ንግግር በግልጽ ያስረዳል፡፡አስቀድሞ በተዘጋጀው ዘዴ፤ በሰፊው አዳራሽ ውስጥ በጸጥታ ለተዋጠውና በር ላይ የታደለውን የህወሃት ፓርቲ ኮፊያ ያጠለቀውን በርካታ ወጣት የኢትዮጵያ ወጣቶች ወኪል የሆኑ በማስመሰል መለስ ስብሰቡን ለምን እንደተሰበሰበ በግልጽ ያላወቀውን ወጣት ለፓርቲ አባልነት መመልመያ እቅዳቸውን አስቀድመው ነድፈው ዘረጉለት፡፡ ላለፉት ሶስት ዓመታት ወጣቱን ወደ ፓርቲ አመራር ለማምጣትና ለስልጣን ለማብቃት ያላሰለሰ ጥረት ሲደረግ እንደነበርና ለዚህም የሚያስፈልጉትን ጠንካራ ወጣቶች ምልመላ እንደተካሄደና ከ 30 000 ያላነሱ ወጣቶች እንደተመለመሉ፤ እነዚህም ምርጦች አስፈላጊው ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ በአውራጃ በወረዳና በቀበሌ በስራ በመፈተን ነጥረው የወጡት ወደ ከፍተኛ የስልጣን ደረጃ እንደሚሸጋገሩ በማስረዳት የተሰበሰቡትን ወጣት ወንዶች በ2010 በሚደረገው ነጻና ሰላማዊ ምርጫም እያንዳንዳቸው ሊመዘኑበት የሚችሉትን የድጋፍ አስተዋጽኦ የሚያሳዩበት ወቅትም እንደሆነ አስረዱ፡፡በተጨማሪም ከአመራሩ ጋር በቅርብ በመስራት ለዚህ የምርጫ እንቅስቃሴ ችግር ነው ብለው የሚያስቡትንም ለአመራሮች በማሳወቅ ተጨማሪ ተግባር ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ለወጣቶቹ አስገነዘቡ፡፡

የዚህ የወጣቶች ስብሰባ ዋናው ምክንያት ወጣቱን በራሱ ህሊና ማሰብ እንዳይችልና ለአገዛዙ አሻንጉሊት በመሆን ሁን ያሉትን የሚሆን፤ አድርግ ያሉትን የሚያደርግ፤ ፈጽም ያሉትን ያላአንዳች ጥያቄ የሚያከናውን ስብእናውን ጨርሶ የዘነጋ ፍጡር ለማድረግና ቀጣዩ ዘመንም በወጣቱ ስብእና ማጣት የህወሃት የግል መፈንጫ እንዲሆን የታቀደ ነው፡፡ ወጣቶቹም የፓርቲው ሃቀኛ ተአማኒ ሆነው በመለስና አገልጋዮቻቸው ቅርጽ የተሰሩ ተደረጉ፡፡

አደጋ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ወጣት

እዚህ ላይ ስለ ኢትዮጵያ ወጣት ማንሳቴ ነቁጥር ተሰፍሮ የተቀረጸውን ከ15-24 ያለውን የእድሜ ገደብ መነሻ በማድረግ አይደለም፡፡በአፍሪካ የኢኮኖሚና በየሃገሩ ካለው እውነታ በመነሳት ከ30 በታች ያለውን መሰረት በማድረግ እንጂ፡፡

የኢትዮጵያ ሕገመንግሠት አንቀጽ 36 ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ሕጻናት በጤና፤ ትምህርትና የኑሮ ዋስትና በርካታ መብቶችን በስፋት ይደነግጋል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የህጸናት ስታስቲክ ግን እጅጉን አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው፡፡ከ18 ዓመት የእድሜ ገደብ በታች ያለው የሕዝብ ቁጥር 41 ሚሊዮን ወይም ከጠቅላላው የሕዝብ ቁጥር ግማሽ ሲሆን የዩኒሴፍ ዘገባ እንደሚያስረዳው ግን ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች በሆኑት በህጻናት ላይ የሚደርሰው ከግማሽ በላይ የሚሆነው የሞት አደጋ በምግብ እጦት አለያም የተመጣጠነ ምግብ አለማግኘት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ኢትዮጵያ በግምት ከ5 ሚሊዮን ያላነሱ እናትና አባት አልባ ሕጻናት ሞግዚት ናት፡፡ይህም ከጠቅላላው ሕጻናት 15 በመቶ መሆኑ ነው፡፡ከ800 000 የማያንሱት ደግሞ ወላጆቻቸውን ያጡት በኤይድስ ጠንቅ ሲሆን እነዚሁ ህጻናትም ካሉበት ሁኔታ በመነሳት ለማንኛውም አደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ያለእድሜ ወደ ስራ መግባት፤ባልተጠበቀ የወሲብ ተግባር ከመጠቃታቸውም ባሻገር በቂ ትምህርት አይገኙም፤ የሰብአዊ መብት ጥበቃና እንክብካቤም የላቸውም፡፡በከተሞች ያለው የወጣት ሥራአጥ ቁጥር 70 በመቶ እንደሆነ ይገመታል፤ወደ 85 በመቶ የሚሆነው ወጣት የሚኖረው በገጠር ሲሆን፤ በተለይ በሴቶች ላይና በገጠር ላለው ወጣት የትምህርት ደረጃው በጣም ያዘቀዘቀ ነው፡፡የሴቶቹ ወጣቶች ያለእድሜያቸው ለጋብቻ ይዳረጋሉ፤ ለምሳሌ በአማራው ክልል ከ45 በመቶ በላይ የሆኑት ጋብቻቸውን እንዲፈጥሙ የሚደረጉት በ15 ዓመት የእድሜ ክልል ነው፡፡

በሌላ ጎን፤2.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናት የአካል ጉዳተኞች ሲሆኑ ከመንግስት በኩል የሚደረግላቸው ድጋፍ እጅግ አባሳ ነው፡፡ ከሚያድርባቸው የተመሰቃቀለ ጫና የተነሳ ወጣቶቹ ተስፋ በመቁረጥ ወደ አደገኛ አዝማሚያ ይገባሉ፡፡ የጎጂ እጽ ተጠቃሚ ይሆናሉ፤ ይጠጣሉ፤ያጨሳሉ፤ ወደ ወንጀል ይገባሉ፤ ያለ፤ተጠበቀ የወሲብ ግንኚነት ይፈጽማሉ፤በዚህም የተለያየ በወሲብ በሚተላለፍ በሽታ ኤችአይቪን ጨምሮ ይለከፋሉ፡፡ የሕጻናት የንግድ ዝውውር በስፋት ይካሄዳል፤ በማደጎ ስም ምን አይነት ወንጀል እየተፈጸመ እንደሆነ በዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን በተደጋጋሚ ተወስቷል፡፡

ለመፈንዳት ያቆበቆበው የኢትዮጵያ ወጣት

ውጥንቅጡ የወጣው የኢትዮጵያ ወጣት ሁኔታ ጊዜው እንደተቃረበ ፈንጂ ነው፡፡በሃገሪቱ ውስጥ የሚታየው የኤኮኖሚ ውድቀት፤ ሥራ አጥነት፤ የፖለቲካው ጨቋኝነት፤ የኑሮ ውድነት፤ የገዢው ፓርቲ ከፋፍለህ ግዛ መመርያ፤ ወጣቱን የራሱ አዛዥ እንዳይሆን ያለበት እዝ፤ እነዚህ ሁሉ ለፍንዳታው ሰበብ ናቸው፡፡ ወጣቱ ከዚህ ለመላቀቅና በሃገሩ ላይ እንደዜጋ በነጻነትና በሰለም ለመኖር ለውጥ ያፈልጋል፡፡ጥያቄው ግን ለውጥን እንዴት ሊያመጣ ይችላል ነው፡፡ በተለመደው የጉልበት መንገድ ወይስ በሰለጠነው ሰላማዊ መንገድ? በሌላ በኩል ደግሞ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት፤ በሃገራችን ላይ ያለውን ግፍና መከራ፤ ሰላም እጦት፤ተስፋ ቢስነት፤ በማየትና ራእይ በማጣት የሚወዷትን ሃገራቸውን፤ የሚያፈቅሩትን ቤተሰባቸውን እየጣሉ በመሰባሰብ ፈንታ በየሃገሩ እየተበተኑ ናቸው፡፡ዛሬ ከደቡብ አፍሪከ እስከ ሰሜን አሜሪካ ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ሩቅ ምስራቅ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የማይገኙበት ሃገር የለም፡፡ስለዚህም ለውጥ መጥቶ የተበተነው ሁሉ ተሰባስቦ ሃገሩን በልማትና በእድገት መገንባት አማራጭ ያማይደረግለት ተግባር ነው፡፡ ለዚህ ደሞ አሰባሳቢና መሪ ያስፈልገዋል፡፡

ለወጣቱ ምን አይነት መሪ?

መመለስ ያለበት አንኳርና ወሳኝ ጥያቄ!

አሁን በሃገራችን በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲ ነን ብለው በመንቀሳቀስም፤ በማዝገምም፤ በመኝታም ላይ ያሉ አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በሃቅ ለትግል ቆመው ግን ፍርሃትና ጥርጣሬ ያደረባቸው፤አለያም ትንሽ ትንሽ ተቃዋሚ ብዙ ብዙ ደጋፊ በመሆን ጊዜውን መግፋት የሚሉ፤በጎኑ ደግሞ መስለን ከጉልበተኛው ጋር ተሸጉጠን ሲያስፈልግ እዚህ ካለዚያም እዚያ እያልን ቀኑን መግፋት ብለው ያሾለቁ፤እስከዘለቄታው በተቃዋሚነት ብቻ ክፍም ዝቅም ሳንል መቆየት ያሉ፤ዋናውን ጠላት ትተው ምሩን መንገድ አሳዩን ያላቸውን ሕዝብ እንግዛህ ዝም በል እኛ እናውቅለሃለን በማለት ዓላማቸውን ስተው ሕዘቡን ረስተው ያሉ፤ዕድሜያቸውን በሙሉ በአመራር ላይ ተቀምጠው ጊዜው እያለፈ አዲስና የሰለጠነ የትግል ስልት ሲመጣ ያን መቀበል እያቃታቸው አመራሩን የሚጥኝ ብለው ለውጥ ሳያመጡ ሳይለወጡ ለመኖር የሚመኙ እና በራካታ አይነቶች እንደመኖራቸው ከመሃላቸው አንዳንድ አፈትልከው ወቅቱን ተገንዝበው ለለውጥ በቆራጥነት የሚቆሙ ብቅ ይላሉ፡፡ሁለቱን አይነቶች በአንድ ላይ አዋህዶ መጓዝ እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ያለፈው ወይም ጊዜው ያለፈበት ለአዲሱ ተተኪ ትውልድ ሊያስረክብ የግድ ነው ስለዚህም ለወጣቱ የራሱ የሆነና እንደሱ የሚያስብ፤እንደወጣቱ ፈጣን አመለካከት ያለው፤ሃሳብን ተቀብሎ በማስተናገድ አባላቱንና አብረውት ያሉትን አመራሮች በማበረታታት አብሮ የሚጓዝ መሪ ነው የሚያስፈልጋቸው፡፡

የግብጽ የቁርጥ ቀን ልጆችና መጨረሻቸው !ሾተል – ከባህረ ሰላጤ

Thursday, February 10th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አፍሪካ ተነሽ በጌታቸው አበራ

Thursday, February 10th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ወንድም የኢትዮጲያ ወታደር በጌታቸው ጋረድ

Wednesday, February 9th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ማንን እንመን ለወሣኙ የነፃነት ትግል ? በሎሚተራተራ

Wednesday, February 9th, 2011

መቼም ዘንድሮ የማንስማው፤ የማናየው ጉደ የለምና ከሃያ አመት በኋላም መሪነን ተብዬዎች ሕዝብን አቅጣጫ ማሥያዝ አቅቷቸው በጥርጣሬና በግራ መጋባት እንደገና ወደ ኋላ እንድናፈገፍግና የተቀጣጠለው የነፃነት ትግል እንዲዳፈን ጥረት ማድረግ በርግጥ ተገቢ ነው?። ሕዝብም እምነት በማጣትና በጥርጣሬ ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሆነ ግን እንድትረዱ ያስፈልጋል።

ለምን ሕዝብ በመሪዎቸ ላይ እምነት አጣ ? ቢባለ እንደሚከተለው ነው።

እንጂነር ሃይሉ ሻዎልና Dር ብርሃኑ ነጋ የግንቦቱን 97 (2005) ምርጫ ውጤታማ ማድረግ ሲችሉ ከመሰሎቻቸው ጋራ ባለመግባባትና ወሣኝ አቆም መውሰድ ባለማቻል ምክነያት ሕዝብ የወያኔን ጉሮሮ አንቆ ሊያወርደው ከደረስ በኋላ አከሸፉት፤ አስከሽፉት። “ወያኔ አጭበርብሮቸው ወይስ አስፈራርቷቸው ምን እንደሚባል ሕዝብ ይፍረደው”። ግን የፖሎቲካ መሪ ናቸው ይህን እንዳትረሱ? ።

ትግሉ ግን አሁንም በሕዝብ እጅ ላይ እንደወደቀ መሪነን ተብዬዎቸ ጠንቅቀው ሊረዱ ያስፈልጋል።

በመጨረሻም ኢንጀነር ሃይሉ ሻዎል ማጎንበሱን መረጡ ። እነ Dር ብረሃኑም ወደ አሜሪካ ማራቶን አደርገው ተሳትፈው በማያውቁበት ሽልማትም ባላገኙበት በማራቶን አሜሪካ ገቡ። ምስኪኖ ብርቱካንም ቆራጥነቷን በጀግንነት ካሣየች በኋላ አይዞሸ የተባለችበት የትግል አጋሮቾን አቋም ስታይ እንደ መከላከያ መሣሪያ እንደተጠቀሙባት ስለገባት ከእስር በኋላ አዎ ሚስጥሩ ገብቶኛል መጀመሪያውንም ስህተት ነው የስራሁት ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ስህተት አልሰራም በሚል ፈርማ ከ እስርም ከትግሉም ጨዋታ ወጣች።

ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላም የሃገር ጉዳይ በመሪ አጣሁ ባይነት እንደማይቀር የገባው ሕዝብ ትግሉን ቀጠለ።

ይህ በዚህ እንዳለ የቱኒዝና የ ግብጹ ትግል እንቅስቃሴ የ ሕዝብን የተዳፈነ እሣት ቀስቅሦት የነፃነት ትግሉ ችቦ መቀጣጠል በጀመረ ማግሥት እነ Dር ብርሃኑ እትዮጵያዊ አይደለንም፤ ካሉትና እራሣቸውን (OLF) እና (ONLF) ብለው ከጠሩት ጋራ ድርድር አድርገን ተስማምተናል። በጋራም ወያኔን ለመጣል አብረን መስራት እንችላለን። በሚል ሃሳብ “በ ኢሳት ቴሌቪዥን” ኢንተርቪው አደርጉ። ሳይውል ሳያድርም ስልፍ ከ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ ቀይ ባንዲራ ይዘው ወጡ።

እረንጎዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራችን በሌላ ቀይ ባንዲራ ታጅቦ መፈክሩ ቀለጠ ። የተለያዩ የምዕራባዊ አገሮችም ይሄ ባንዲራ የማነው ? ይሄኛውስ ? እያሉ በግራ መጋባት እየሣቁ አለፉ። ጥቂት የዋህ ኢትዮጵያዊያኖች አንድ እርምጃ ተራምደናል አሉ። በርካታዎች ግራ በመጋባት እራሳቸውን ነቅንቀው አዘኑ። በቅርቡ ወረሃዊውን ድጎማዬን ለማድረግ ወደአገርቤት ደውዬ ኖሮ በቅጡም ስላምታ ሳንለዋወጥ ውርጅብኙ ቀጠለና ፤ምነው አረንጎዴውና ቢጫው ቀዩ ባንዲራችን መሃል በተደነቀረው ኮከብ ተበሣጭተን ሣናባራ ምንድነው እየተደረገ ያለው በሚል ንዴታቸው ገነፈለ። ቀጠሉናም ስሞኑን በየ ቦታው የዳይስፖራውን የፖሎቲካ የስልፍ ትዕይንት ጉዳይ ነው በእሳት በምትሉት የ ቲቪ እስቴሽናችሁ እያየን የምንስቀው ሲለኝ ወንድሜ በብስጭት፤ ተወኝ እባክህ ብዬ ብዙም ሳላወራው ስልኩን ዘጋሁ።

እንደገና ወድኋላ ትግሉ እንዲሄድ የሚደረገበት ምክነያት ግን ምን ሊሆን እንደሚችል ፍርጥ አርጎ ማንም ሊናገር አልቻለም። ኢትዮጵያዊነት ለድርድር መቅረብ የለበትም ብሎ የሚከራከረው “ናሺናሊስት” ( ግትር አክራሪ አማራ) እየተባለ የሚፈረጅበት ምክነያት ግን በጣም የሚያሣዝን ነው። ገሚሱ ትክክል ነው ይላል። ገሚሱ ጥፋት ነው የተሰራው ይላል። ኢትዮጵያዊነት ለድርድር የሚቀርብበት ምክነያት ለምን ይሆን? ብሎ መጠየቅ ግን ተገቢ ነው ባይ ነኝ። በታሪክ ታፍራና ተከብራ በ አባቷቻችን ደምና አጥንት የቆየችን አገር ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ከሚል አካል ጋራ አብሮ መቆሙ በርግጥ አስፈላጊ ነው? ። ወይስ መቅደም ያለበት አዎ እትዮጵያዊነታችንን ተቀብለናል ሌላው ችግራችን ግን ኢትዮጵያን ከ ወራሪው ወያኔ መንጋጋ ካለቀቅን በኋላ በጋራ ልናስተካክል እንችላለን በሚል ተግባብቶ የ ኢትዮጵያን ባንዲራ ይዞ አብሮ መቆም ?።

ይሄን እነ Dር ብርሃኑ ይመልሱት። እንደ እኔ እምነት ከ ወንድሞቻችን ጋራ ለምን ድርድር ተደርገ አይደለም ጥያቄው። ሆኖም ወያኔም ኢትዮጵያን እየጠላ ባንዲራችንንም ጨርቅ ነው እያለ አይደለም እንዴ?። ሕዝብንም እያፈነና እያስረ መከራ ስለሚያሣየን መስለኝ ትግላችን ፤ ታዲያ የነ (OLF) ጉዳይ በምን ሂሣብ ስሌት ነው እትዮጵያዊ አይደለንም ብለው ባደባባይ እየነገሩን አብረው መሰለፋቸው? መሪዎች ተብዬዎችስ የወያኔ መጠቀሚያ ሊያደርጉን ? ወይስ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው በሚል ቸልተኝነትና አፍራሽነት ከነፃነት በኋላ ሌላ ልንወጣ ወደማንችልበት አዘቅት ውስጥ ሊከቱን ? ወይስ በርግጥ ሊያስማሙን ? ምን ይመስላችኋል? ።

አቶ ሌንጮስ ኢትዮጵያዊነትን አምኖ ከህዝብ ጋር በመቆም ችግር አለኝ ቢባልም እንኳን ከነፃነት በኋላ በ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በጋራ መፍትሄ ማምጣቱ አይበጅም ይላሉ? በስተርጅና እንዲህ ያለ የ አፍራሽ ተልዕኮ ማራመድ ተገቢ ነው? ማንስ ይቀበለኝል ብለው ነው? እርሦ እራሦት ይመልሱ።

በመጨረሻም የ ኢትዮጵያ ሕዝብ ከየት እንደመጣ የት እንዳለና ወዴትም መሄድ እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። አሁንም ማን ይምራኝ ከማ ጋር ልቁም የሚለውን የሚወስን እሱ እራሱ ነው። የተጀመረውንም የነፃነት ትግል እራሱ አቀጣጥሎ እራሱ መሪ ፈጥሮ በድል ይወጣዋል። መሪ ነን ያላችሁ በሕዝብ መነጽር ውስጥ ነው ያላችሁትና እራሳችሁን አስተካክላችሁ ሳይመሽ በጠዋቱ ከሕዝብ ጋር መቆም ትችሉ ዘንድ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ
እላለሁ።

የተጀመረው የነፃነት ትግል በሕዝብ የበላይነት የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፊት አስቀድሞ በድል አድራጊነት ይወጣዋል!።

በቸር ይግጠመን
ሎሚተራተራ !

ሂድ እንግዲህ! በረክትም ከሃገር ጠቅልሎ ኮበለለ

Tuesday, February 8th, 2011

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ