Author Archive

የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የምንል መልካም አጋጣሚው አሁን ነው

Sunday, May 13th, 2012

ገረመው አራጋው

በአገራችን ኢትዮጵያ አምባገነኑ የመለስ ስርዓት በስልጣን ላይ በቆየባቸው ባልፉት 20 ዓመታት ውስጥ  ኢሰብአዊ ኢዲሞክራሲያውዊ ኢፍታዊ ድርጊቶችን ሲፈፅምብን ቆይተናል::  ስርዓቱ ግን አንድም ጊዜ ከድርጊቱ ለመታቀብ አልሞከረም እኛም ከዚህ በደልና ጭቆና ለመላቀቅ እንዳንችል የተለያዩ አስፈሪ አዋጆችን መመሪያዎችን ድንጋጌዎችን እያወጠና እራሱ ላወጣው ህገ መንግስት እንካን ሳይገዛ ባደባባይ በተደጋጋሚ በማን አለብኝነት ከህግ በላይ እየሆነ እጅግ በጣም ብዙ ንጹሃን ዜጎችን ያስራል ያዋክባል ታሰቃያል ከሀገር እንዲሰደዱ ያደርጋል ይገላል  ወዘተ::  ህዝቡን በኑሮ ውድነት በመልካማ አስተዳደር እጦት በህግ የበላይነት አለመከበር በሙስና መንሰራፋት በዲሞክራሲያዎ መብቶች ባለመከበር በሚደርስበት በደል ስርዓቱ እጅ እጅ ብሎት  የዝሆን ጎሮ ይስጠኝ በማለት ድርጊቱን በሰፊው እየፈጸመ እያስፈፅመ ይገኛል::

ኢትዮጵያዊያን በሀገራችን ላይ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ባህል እንዲመጣና ከሚደርስብን ስቃይና መከራ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመላቀቅ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ  እጅና ጋንት ሆኖ መታገል የወቅቱ አንገብጋቢ ሁኔታ ሆኖ ተገኝታል::  የኢትዮጵያ ህዝብ እየደረሰበት ካላው በደልና ጭቆና ለመላቀቅ እሱ እራሱ እንጂ ባእዳንም ሆነ የባእዳን ጋሻ ጃግሬዎች አለመሆናቸውን ጠንቅቆ ያውቃል :: ህዝቡም እራሱን ከባርነት ቀንበር ሊያወጠ የሚችለው እራሱ ብቻ እንደሆን በማያሻማ መንገድ አረጋግጦዋል :: የሰብሃዊ መብቶች ተከራካሪ ተቃማት ጩከት እቤቱታ ዘገባና ተማጽኖ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም የፈየደለት ነገር የለም::  ይህንን የአምባገነን ስርዓት ከስልጣን ለማውረድ በሚደረገው የትግል ሂደት ሰላማዊ ትግል አስፈላጊነቱ የማያጠያይቅ ቢሆንም በሰላማዊ ሰልፍ በህዝባዊ አመጽ ካልተደገፈ የራሀብ አድማ የጾም ጸሎት የሻማ ማብራት የመሳሰሉት ተቃዎሞዎች ሁሉ ወደ አርህድ አንቀጥቅጥ ህዝባዊ ቁጣ እስካልተለወጠ ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ይመጣል ብሎ ማሰብ የህልም እንጀራ ይሆናል:: ከእንግዲህ ወዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ የትግሉ አቅጣጫ አላማና ግብ የወያኔን አረመኔ ስርዓት ከስልጠን ማስወገድ መሆኑን ሊረዳው ይገባል::

ከአሁን በሃላ ወያኔን በምርጫ ሂደትና በሰላም ብቻ ታግለን ከስልጠን እናስወግደዋለን ብሎ ማሰብ የዋህነት ብቻ ሳይሆን ሞኝነትም ጭምር ነው::  ይህንን እውነታ ያልተገነዘቡ ግን በሰላማዊ ትግል ስርዓቱን እንቀለብሳለን ብለው የሚያምኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢያንስ የትግሉ እንቅፋቶች እንዳይሆኑ ከፍተኛ  ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል:: ይህንን እያወቁ ለወያኔ ከለላ እየሰጡ ወይንም ተለጣፊ እየሆኑ የህዝብን ትግል ለማምከን ጋሬጣ የሚሆኑት ክፍሎች የወያኔ አባሪ ተባባሪ እንደሆኑ ጠንቅቀው ሊያውቁት ይገባል:: በዚሁ ስር ነቀል የትግል እንቅስቃሴ ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ዋና ጠላት መሆኑን ተረድተው ይህንን  የእናት ቱት ነካሽ የሆነውን አረመኔ ስርዓት ለመጠል ማንኛውንም መሰዋትነት ለመክፈል ታግለው ህዝቡን ለማታገል የተዘጋጁ ሊሆኑ ይገባል::  አገራችን እረጅም ጊዜ ታሪክ ወያኔን የመሰለ የወገን ጠላት አጋጥሞት እንደማያውቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል::  ይህንን ዘረኛ ቡድንና የወገን ጠላት አስፈላጊው መስዋትነት ተከፍሎ ከስልጠን ከማስወገድ በስተቀር ሌላ አማራጭ የሌለ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቃል::

ዛሬ በዲሞክራሲ አደጉ የምንላቸው ምዕራባዊያን መለስን በምስራቅ አፍሪካ እንደ ተላላኪና ጉዳይ አስፈፃሚ ስለሚጠቀሙበት ብሎም ምንም አይነት የዲሞክራሲ ስርአት ያልገነቡት ቻይናና ህንድ ለተፈጥሮ ሀብት እንደልባቸው መዝረፍ እንዲመቻቸው   ከወያኔ ጋር ስለተባበሩ የኢትዮጵያ ህዝብ በአምባገነኑ መለስና ለሆዳቸው ባደሩ ቡችሎች እየደረሰበት ያለውን ስቃይና መከራ እንግልት ከራሱ ከኢትዮጵያ ህዝብ በስተቀር ሊረዳው  የቻለ የውጭ ሃይል አልተገኝም::   ምዕራብያዊያንም ሆኑ ሌሎች ቡድኖች ለራሳቸው ዘላቂ ጥቅም ብቻ ሲባል ወያኔን እንደ መሳሪያ በመጠቀም ለኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ስቃይና መከራ አባሪ ተባባሪ ሆነዋል ህዝባችንም ስቃይና በደሉን ሰሚ አጥቶ ወደ ፈጣሪው አቤቱታውን በማሰማት ላይ ይገኛል::

በአሁኑ ወቅት የወያኔን ዘረኛና ፋሽስታዊ የአገዛዝ ስርአት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከስለጣን ለማስወገድ በመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የእኩልነትና የፍትህ ጥያቄዎች ከሁሉም አቅጣጫ እየጎረፈ ይገኛል::  ማንኛችንም የሀገሬ ሠላምና ደህንንት ይመለከተናል የምንል ግለሠቦችም ሆንን የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በጋራ ተሰባስበን የተቀጣጠለውንና እየተፋፋመ የመጣውን ታላቅ የህዝብ አመፅ በሁለንተናዊ የትግል እስትራቴጂ እንዲታገዝ አድርጎ የወያኔን የማፊያ ስርአት ከጫንቃችን ላይ አስወግደን እኩልነት: ፍትህ: ዲሞክራሲና: እውነተኛ ፌደራላዊ ስርአት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ከሌላው ግዜ በበለጥ መረባረብ አለብን::

ጸረ አማራነት አንድ ቀን ጸረ ህዝብነት ይሆናል!

Friday, May 11th, 2012

ገረመው አራጋው

የጎሳ ግጭትና እልቂት ዛሬ ዛሬ ጆሮአችን እንዲያም ሲል አይናችን እየለመደ መጣና እንደሌላው ጊዜ ብዙም የሚሰቀጥጥና የሚያስፈራ ወሬ አይደለም ዛሬ ካለንበት ጊዜ ላይ የደረስነው ባለፉት አያ አመታት በተለያይ የአገራችን ክፍሎች የብሄር ግጭትና የዜጎች ከመኖሪያ ቦታቸው መፈናቀል እየሰማንና እያየን ነው የመከራ ጊዜ እረጅም ነው ይባላል ግን ደግሞ ከዚያም በላይ ሃያ አመት አጭር ጊዜ አይደለም የኢትዮያ ህዝብ ከሞትና ከእቂት ከስደትና ክፍረሃት ጋር መኖሩን በግድ እየተለማመድን ነው ማለት ይቻላል ዛሬ በሀገራችን ላይ ሌላው ቀርቶ ለሰልፍ የወጣና ለምርጫ የተነሳን ህዝብ በጥይት ማስፈራራት ማሰር መደብደብ ማሰቃየትና መግደል  አዲስ ነገር አይደለም ሞትንና እልቂትን ሁሉም ከልጅ እስከ አዋቂ እየቀመሰ ነው::

ብዙ ሰው እንዲሁ በተለምዶና  ለአፍ ብቻ ካልሆነ በስተቀር ዛሬ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚነሱትን  ግጭቶችና  ግድያዎችን ማን እንደፈጠረውና እንዳቀነባበረው መጠየቁን  ትታል የትም ይሁን የት በጎሳዎች መካከል የሚቀጣጠለው ሁከትና ግጭት በእነማን ፍላጎትና  ግፊት እንደሚካሄድ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቀዋል በስልጠን ላይ ያለው አምባገነን የወያኔ ስርዓት ጫካ ገባሁ ሲል ጀምሮ ትግሌ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ነው ካለ ከዘረኛ ቡድን ሌላ ባይጠበቅም አምባገነኑ የመለስ ስርአት የአማራውን ህዝብ  ለማጥፋት ገና ከደደቢት የጀመረውን ዘመቻ ቀስ በቀስ እየፈፅመና እያስፈፅመ መሆኑን ፅሀይ የሞቀው ሀቅ ከሆነ ሰነበተ::

ወያኔ ወደስልጣን  በጠመንጃ ሀይል ከመጣ ጀምሮ የአማራን ህዝብ ማንነትና ታሪኩን ለማጥፋት የላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቶአል አሁንም አጠናክሮ ቀጥሎበታል ለምሳሌ ወያኔ ወደስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸሙት ወንጀሎች;

አማራው ህዝብ ለብዙ ዘመናት ያስተዳድራቸው የነበሩትን  የጎንደርንና የወሎን ሰፋፊና ለም  መሬቶችን ወደፊት ታላቅዋን  ትግራይ ለመመስረት   ወደ እራሱ ግዛት ያጠቃለለው ወያኔ የአማራውን ህዝብ ከለም መሬቱ አፈናቅሎ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጥገኛ እንዲሆኑ እንዲራቡ  እንዲሰደዱም አድርጎአል ይህ በዚህ ሳያንሰው ማንም የክልሉ ነዋሪ ሳያውቅና ሳይሰማ  የአማራን መሬት ለሱዳን አስረካቦል የአካባቢው ነዋሪዎች በባእድና በወያኔ ወታደሮች አስጨፍጭፋል::

በአማራው ላይ ጥቃት የተጀመረው ዛሬ ሳይሆን ከፋሽስት ኢጠሊያ ወርራ ግዜ ጀምሮ እንደነበር ታሪክ ይመሰክራል ይህንንም የባንዳነት ተግባር ወያኔ ጠመንጃ ካነሳ ጊዜ ጀምሮ በትግል ወቅትም ሆነ መንግስት ከሆነ በሃላ በግልጽና በስውር ከአፍራሽ የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን አያሌ ጥቃቶችን በዚህ ህዝብ ላይ ሲያካሂዱበት እንደነበር  የትናንት ትዝታችን ነው   ሆን ተብሎና በተቀነባበረ መልኩ በአርባጉጉ በምስራቅ ወለጋ በበደኖ በአረካ ወዘተ አያሌ አማሮችን ጨፍጭፋል አስጨፍጭፋል እንዚህም  የዘር ማጥፋት ድርጊቶች ክተፈጸሙ በሁዋላ የወያኔ መንግስት እንድም ግለሰብ ለፍርድ አለማቅረቡ እራሱ ወያኔ የድርጊቱ ዋነኛ ተዋናይ እንደነበረ ያረጋግጣል::

ዘሩና ታሪኩ እንዲጠፋ በወያኔ የተወሰነበት የአማራው ህዝብ እንደ ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት አባባል በራሱና በታሪኩ የሚተማመን አትንኩኝ ባይ ለነጻነቱ ለህልውናው ለህይማኖቱና ለሀገሩ ዳርድንበር ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ማች በመሆኑ ነው ለማያባራ ጥቃት የተዳረገው ወያኔ ወደ ሰልጠን ከመጠበት ጊዜ ጀምሮ አማራውን ነፍጠኛ በማለት ከሌላው ጎሳ ጋር ተፋቅሮ ተጋቤቶ ተዋልዶና ተዋህዶ ከኖረበት ቀየው በግፍ ሲያባርሩት እንደነበር ከሞት የተረፉት ተፈናቃዮች ምስክር ናቸው በተለይ በሽግግሩ ዘመን በአማራው ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ታሪክ ምን ግዜም ሲያስታውሰው ይኖራል ::

በጣም የሚገርመው በአንድ ወቅት አምባገነኑ መለስ የአማራውን ህዝብ እንዳያንሰራራ አድርገን አዳክመነዋል እስክታውንና ተረቱን ይዞ ይኑር ማለቱ አይዘነጋም ይህንኑ የአለቃቸውን ቃል እንደየገደል ማሚቱ  የሚያስትጋቡ አንድ  የወያኔ ጀነራልና  ጦር መሪ የሆኑት ግለሰብ በአንድ  ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር  በታጋዮች የህይወት መስዋትነት በተከፈለ አካላቸውን ባጡ በትግራይ ልጆች ደም እኮ ነው ደርግን ከፍተኛ መሰዋትነት ከፍለን ከስልጣኑ አውርደነዋል አማራውንም ደግሞ እንዳያንሰራራ አድርገን አጥፍተነዋል ማለታቸውን እናስታውሳለን::

የወያኔ ድበቅ አጀንዳ አሁን ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይ በቤንች ማጂ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ እራሱ ባወጣው ህገ መንግስት ውስጥ ዜጎች በፈለጉት ክልል የመኖርና ሀብት የማፍራት መብታቸውን በመጣስ  እጅግ ቁጥራቸው የበዛ የአማራ ብሄር ወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመ ይገኛል በደሉን እያስፈጸመ ያለው የአምባገነኑ የመለስ ሰርዓት በሚሰጠው መመሪያና ትህዛዝ ከክልሉ መስተዳድር ጀምሮ እስከ ወረዳ ባሉ ተላላኪዎቹ በተቀናጀ አሰራር ነው ከማፈናቀሉ ተግባር ጋር በተያያዘ የወቅቱ ትልቅ ጥያቄ የደቡብ ክልል አስተዳደር ቀደም ሲል ሆነ አሁን በተለይ የአማራ ብሐር ተወላጆችን ለበርካታ አመታት ከኖሩበት እያፈናቀለና ወደመጡበት እየመለሰ ያለው ለምንድ ነው? ለአማራ ህዝብ መብትና ጥቅም የቆምኩነኝ የሚለው አሻንጉሊቱ ብአዴንስ የክልሉ ዜጎች መፈናቀልን በመደገፍ በዝምታ የተቀበለው ለምንድን ነው?

አማራውን ከፌደራል መንግስት ስልጣን የማራቁ  ድብቅ ተልኮ ወያኔ ስልጠን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ሲያከናውነው የነበረ ረቂቁ ሴራ ለማሳካት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም ነገር ግን ሊሳካለት አልቻለም  ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ትልቅ የህዝብ ብዛት ያላቸውን አማራንና ኦሮሞን ህዝቦች በማጋጨት እድሜአቸውን ለማርዘም ያሴሩት ሴራ ሲከሽፍባቸው ዛሬ ደግሞ ተጋብቶ ተዋልዶ ተከባብሮና ተስማምቶ በሰላም የሚኖረውን የደቡብ ኢትዮጵያ ነዋሪዎችን ሰላም በማደፍረስ ወቅታዊውን የመምህራን ጥያቄ :የህዝብ የኑሮ ውድነት: የሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብት መከበር ጥያቄ አቅጠጫ ለማስቀየር የተጠቀመበት እኩይ ተግባር መሆኑን  የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቀዋል::

በአማራ ህዝብ ላይ ጥላቻን መሰረት አድርገው በመካሄድ ላይ ያሉ ማንነቱንና ታሪኩን የማጥፋት ዘመቻ በአሁኑ ወቅት በጣም ተባብሰው ቀጥለዋል አማራው እንደ ህዝብ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ጭቆናና መከራ ሁሉ ተጠያቂ ተብሎ ሲወገዝ ቆይታል ገዝው ሁሉ አማራ ተባለ እንጂ ፓለቲካቸው ለሰፊው የአማራ ህዝብ የፈየደው ብዙ አልነበረም የአማራ ህዝብ ሰፊ ነው በኢትዮጵያነቱ አምኖ ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመሆን ታሪክ የሰራም ህዝብ ነው አምባገነኑ የመንግስት ስርዓት ይህንን እውነታ ወደጎን  በመተው የአማራን ህዝብ ማስጨፍና ማፈናቀልን ለጥቃት  ማጋለጡን ቀጥሎበታል ብዙሃኑ የአማራ ህዝብ  በማያወላዳ መልኩ ለአገር አንድነት የቆመ ነው ይህ የኢትዮጵያዊነት ስሜቱ እንደ ሀጥያትና ወንጀል ተቆጥሮበት ከተወገዘ ደግሞ እራሱን ለማዳንና መከላከል የግድ ይሆንበታል አማራን ያህል ሰፊ ህዝብ አግልሎና አውግዞ ልማት አካሂዳለው ማለት ዘበት መሆኑን አምባገነኑ የመለስ ስርአት ጠንቅቆ እንዲያውቀው ይገባል::

 

ጥቃታችን ከፋና እኛንም አስከፋን

Tuesday, May 1st, 2012

ከገረመው አራጋው

ሀገራችን ኢትዮጰያ በአሁኑ ሰአት እጅግ በከፋ ሥራ አጥነት፣እየጨመረ የሄደ የእኩልነት ፍትህ መታጣትና: ሥር የሰደደ ድህነት በከፍተኝ ሁኔታ አለመረጋጋት ፈጥሮባታል ለዚህም ዋነኝ ተጥያቂ መለስና ግብረአበሮቹ ናቸው::  ከአንደበታቸው የስድብ ቃላትን በማዝነብ ለዘለዓለም የበላይ ሆነው የሚኖሩ የመስላቸው እነዚህ አምባገነን; ፋሽስታዊው; በዘርና; በትንሽ መንደር የተደራጀው የወያኔ ቡድን ላለፉት 21 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጉልበት: እጅግ በጣም ሁዋላ ቀርና የህዝብን ጥቅም ይማያስጠብቅ የአገዛዝ ስርአት በመጫን የስልጣን ዕድሜውን ማራዘም; የአገር የማፈራረስና የኢትዮጵያዊንትን ታሪክና ባህልን የማጥፋትና ተልኮውን መፈጸም እና የህዝብና የሀገር ሀብት መዝረፋን መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ እየፈጸም ይገኛል::ህዝቡን በጥመንጃና በአራዊት ህግ በማስፈራራትና ከታች የተዘረዘሩትን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመከልከል የባንዳንትና የሌብነት ተግባሩን በመፈፅም ላይ ይገኛል::

የወያኔ የሞኝ እድሜ ማራዘሚያው እስትራቴጂ ህዝቦችን በዘር  በብሄር በቋንቋ  በሀይማኖት በቀለም  ብሎም በጎጥ እንዲለያዩ ማድረግና ክፍተኛ የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳ በህዝቡ ዘንድ ማሰረጨት:: እርስ በእርስ እንዳይስማሙ: አብረው እንዳይኖሩ  አንድንት እንዳይፈጥሩ  በህብረት ማህበራዊና ፖለቲካዊና እኮኖሚያዊ ችግሮቹን በጋራ እንዳይፈቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ጥላቶቹን ለመታገል አቅምና ስምምነት እንዳያጎለብቱ በዘር ፖለቲካ እንዲወጠሩ ማድረግ  ከእያንዳንዱ ብሄረሰብና ሀይማኖቶች ለሆዳቸው ያደሩትን ጥቂት ግለሰቦችን ቆንጥሮ እምነትህ ተጥብቆልሀል ባህልህ ጥቅምህ ተከብሮልሀል ብሎ በህዝብ ላይ መሳለቅ::

ወያኔ እራሱ በማያከብረው ይህን  ከአርቃቂዎቹ በስተቀር ለአብዛኛው ሕዝብ ግልፅ ያልሆኑ ብዙ ነገሮች ያሉበት ሕገ-መንግሥት  የህጎች ሁሉ የበላይ ብሎ በሚጥራው ህገ መንግስቱ ላይ የተፃፉትን  ህጎች ለተወሰኑ ግለሰቦችና ቡድኖች ብቻ ስንዲሰራ ማድረግ በርካታ የህዝብን ተፈጥሮዊና ህገመንግስታዊ መብቶችን  መናገር  የመፃፍ  የመሰብሰብ በቡድን የመደራጀት ሀሳብን በአደባባይ ወጥቶ የምግለፅ: በሀገሩ ላይ የመሬት ባለቤት መሆን  የፈለገውን እምነት መከተልና የመሳሰሉትን በኢትዮጵያ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ወይንም በመሸራረፍና ለጥቂት የወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ብቻ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድረግ::

በኢትዮጰያ ውስጥ የወያኔን የተሳሳተና ከገደብ ያለፈ የጭቆና   አገዛዝ በአደባባይ መቃወም  ስለ ኢትዮጵያዊነት መደራጀት መስበክ መናገርና ማዜም መጻፍ እንደወንጀል የሚቆጥርበት ጊዜ ላይ ተደርሳል:: ሆኖም በአሁን ሰአት ወያኔ መጥነ ሰፊ ዘመቻ እያደረገ ያልው ታዋቂና ለወደፊት ለአምባገነኑና ለፋሽስቱ ለወያኔ ቡድን የስልጣን ቆይታ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውንና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ታማኝነት ያላቸውንና አላቸው ብሎ የሚጠረጥራቸውን የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን  አባላቶችን  ደጋፊዎችን  ምሁሮችን  መምህራኖችን  ጋዜጠኞችን  ዘፋኞችን  ነፃ አሳቢ ዜጎችንና በተለያዩ የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ማስፈራራት:በእስር ማሰቃየት  በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ጉዳት ማድረስ:ንብረታቸውን መውረስ መዝረፍ ማውደም  አስፈራርቶ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድርግ: የት እንደደረሱ እንዳይታወቅ ማድረግ  መግደልና ሌሎችንም የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈፅም ሀገር የማፈራረስ ህዝብንና ሀገርን የማዋረድና የባንዳነት ተልኮውን መወጣት::

ለህዝብ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ለምሳሌ በሰባዊ መብት:በመልካም አስተዳደር:በህግ የበላይነትና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ መጥነኛም ሆነ ጥልቅ ግንዛቤ እንዳያገኝና እንዳይኖረው ተግተው በመስራት ህዝቡ በዲሞክራሲያዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳይኖረው ማድረግ:: ስለ ሰባዊ መብት መልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን ለህዝቡ በማስተማርና በማስረፅ ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች: ነፃ ጋዜጦች: የራዲዮና የቴሌ ፕሮግራሞችን ሆን ብሎ የተለያዩ አፋኝና ሰንካላ ሰላማዊዮቹንና የብዙሀኑን መብት የሚያቀጭጩ የሌቦችንና የጥቂቶችን ቡድኖችን ስልጣን የሚያፋፋ ህጎችንና መመሪያዎችን አውጥቶ ለህዝቡ እንዳይደርሱ ማድርግ:: ህዝቡም መብቶቹን እንዳያውቅና እንዳይጠቅም ማድረግ::

ለውጭ ሀገርዜጎችና ለጥቂት የወያኔ ቡድን አባላት መሬት የማግኘት ያልተገደበ መብት በተሰጠባት ሃገር በገዛ ሃገራቸው ከአንድ ክልል ወደሌላ ክልል በመሄድ  መኖር የጀመሩ ወገኖችን ክልላችሁ ስላይደለ ወደክልላቸው ተመለሱ መባላቸው የወያኔ አገር የማፈራረስ ተልኮው ገሀድ ወጥቶበታል ::የኢትዮጵያን ህዝብ የሀገር የመሬትና የንብረት አልባ አድርጎ የወያኔ አባላት ብቻ የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ማድርግ:: ሀገርንና መሬትን ለባእዳን መሸጥና ለጎረቤት ሀገሮችም ትላልቅ መሬቶችን ቆርሶ በመስጥትን በመሸጥ አሳልፎ መስጠት; እኛ ብቅርጽና በመጠን የምናውቃትን ታሪካዊ ኢትዮጵያን ማጥፋት; ህዝቡም በሀገሩ ላይ ስለ መሬት እንዳይጥይቅ በጠመንጃ ማስፈራራት; ምንም እንደማያመጣ በጥጋብና በስድብ ንቀቱን መግለፅ::

የኢትዮጵያን የ3000 አመት ታሪክ መካድ: አሳፋሪ በሆነ መልኩ ማቅረብ: ታሪክን መበረዝ: የፈጠራ ታሪክ መፍጠር:: የኢትዮጵያን ህዝብ ባህል: ስብእና  ዕምነት  ኩራት  ማንነት  ብሄራዊ እሴቱን  አንድነቱንና ብሄራዊ መገለጫዎቹን ማጥፋት:: የኢትዮጵያን ታራክ የወያኔን ታሪክ ብቻ አድርጎ በካድሬዎቹና ለሆዳቸው ባደሩ ተራ ግለሰቦች ገንዘብ ከፍሎ ማፃፍ ለምሳሌ የአድዋ ጦርነትን ያሸነፉት ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ፣ትግሬዎች ናቸው  ብሎ የሀገርንና የኢትዮጰያን ታሪክ መካድ :: ልክ እንደ ውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ  ማጥላላት  ማናናቅና የመሳሰሉትን አስነዋሪ የቅጥረኝነቱን ተግባር እየፈፅመ ይገኛል::

የኢትዮጵያን ምንም አይንትአማራጭ የመረጃ ምንጭ እንዳያግኝ ማድረግ:: የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዳያገኝና በኢኮኖሚ: በማህበራዊ: በፖለቲካ: በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዳይሆን ማድረግ:: እኔ አውቅልሀለው የምነግርህን ብቻ ተቀበል ብሎ ህዝብን በወያኔ የመረጃ ማሰራጫዎቹ ማደንቆር:: ትክክለኛ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህዝቡ የሚያደርሱትን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመረጃ ተቃማትን የግል ጋዜጣዎችን ራዲዮዎች ቴሌቪዥን እና ድህረ ገዕች መረጃዎችን ለህዝቡ እንዳያደርሱ ለማድረግ አታሚ ድርጅቶችን መዝጋት  ፈቃድ መከልከል  ባለቤቶቹን ማስፈራራት ማሰር: በቁጥር እጅግ ብዙ የሆኑ ጋዜጥኝች የታሪክ ፅሀፊዎች ተኪነጥበብ ሰዎች ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ:: በራዲዮና የቴሌቢጅን የሚሰራጩትን መረጃዎች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጥት ሞገዳቸውን ማፈን::

የመለስና የግብራበሮቹ አደባባይ የወጣው የቅጥፈት ተግባራቸው በይስሙላ ምርጫ አጭበርብሮም ሆነ በመሳሪያ አስገድዶ ስልጣን መጨበጥ፣ ስልጣን  ላይ መቆየት፣ ሃብት ማጋበስ፣ ርዕዩተ ዓለማቸውን ተጠቅመው ህበረተሰቡን ስልጣን ላይ እንዲያቆያቸው አድርገው ማዋቀር ፣ ነፃ ሲቪክ  ድርጅቶች እንዳይኖሩ ወይንም እንዲዳከሙ ማድረግ፣ ነፃ ፕሬስ እንዳይኖር ያሉትም ተዳክመው እራሳቸውን  ሳንሱር ማድረግ እንዲለምዱ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በሚመለከት ደግሞ የተወሰኑትን በገንዘብ ድጎማ ወይንም በፍራቻ ተለጣፊዎቹ እንዲሆኑ ማድረግ ሲሆን ጠንካራ  እና ሃቀኛ በሆኑት ተቃዋሚዎች ላይ ደግሞ የፖለቲካ   እና የገንዘብ ምህዳሩ እንዲጠብባቸው እና እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ ተዳክመው የኢትዮጵያን  ህዝብ  የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለማድረግ ከጀመሩት ሰላማዊ እና ህገ መንግስታዊ ትግል ሜዳ እንዲወጡ ለማድረግ ያልተቋረጠ ጫና ማድረግ ናቸው።

አሁን የተፈጥረው የትግል እንቅስቃሴ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ  ህዝብ  እንዚህን ሁሉ ግፍና በደሎች እያደረሱበት ያሉትን ጥቂት የግለሰብና ቡድኖች ስብስቦችን ከፍተኛ በሆነ የቁጭትና በጀግንንት ወኔ ከሁሉም አቅጣጫ በድርጅትም ተሰብስቦ ሆነ በተናጥል በመሆን የተፈጥሮአዊና ሰብአዊ መብቶቹን ለማስከበር ያላሰለሰ ትግል እያካሄደ ይገኝል:: የኃይማኖት ተቋማት፣ ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ ሴቶች፣ አርሶአደሩ፣ ከተሜው፣ ሰራተኛው፣ ስራ አጡ፣ ነጋዴው፣ ባለሀብቱ እና የመሳሰሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች  በማሳተፍ ከትግሉ የሚጥበቀውን ውጥት በአጭር ግዜ ለማምጥት ሁሉንም የትግል ስልቶች በመጥቀም  ሀገራችንን ከአምባገነኖች መዳፍ ለማውጥት በአንድነት መታገል አማራጭ የሌለው ውሳኔ ሊሆን ይገባል::