Author Archive

አዲስ አማራጭ ማቅረብ የፖለቲካ እድገት ያሳያል

Tuesday, September 25th, 2012

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

መግቢያ፤

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተከታታይ ችግር፤ የስልጣኑ ባለቤት አለመሆኑ ነው። ይህ ሕዝብ፤ ለመብቱ ስኬታማነት፤ ለሃገሩ ክብርና ግዛታዊ አንድነት ያደረገው ትግል፤ የከፈለው ዋጋ፤ ሁላችንም የሚያኮራ ነው። ለስኬታማነቱ ማነቆ የሆነው ሕዝቡ ሳይሆን፤ ለሕዝቡ ቁመናል የምንለው ድሃው ህብረተሰብ ያስተማረን እኛው ነን። ድክመታችንና ጥንካሪያችን ረጋ ብለን መመርመርም ያለብን እኛው ነን። ኋላ ቀር የሆነ ያፖለቲካ ባህል ይዘን ዲሞክራሳዊ ስርአት ለመገንባት አንችልም። ለውጥ የሚያስፈልገን መሆኑን፤ በሃቅ፤ በጥበብ መመርመርና ብሩህ አማራጭና አቅጣጫ ማቀርብ ያለብን እኛው ነን። በእኛ እድሜ፤ ሶስት የመንግስት ለውጦች አይተናል፤ የአጼ ሃይለስላሴ ንጉሳዊ፤ ፌውዳላዊ፤ የመንስቱ ሃይለማሪም ወታደራዊ አምባገነን ሶሻሊዝም፤ መለስ ዜናዊ ይመሩት የነበረውን፤ የጠባብ ብሄርተኛ የአንድ ፓርቲ የበላይነት። አንጻራቸው ይለያይ እንጅ፤ እነዚህ መንግስታት፤ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የማህበረሰብ፤ የስራ እድል፤ የትምህርት፤ የሃይማኖት አድሎና የጥቅም የበላይነት አሳይተዋል። የሃይሉ ሚዛን፤ የጥቅሙ ክብደት ተመሳሳይ ባይሆንም፤ ተከታታይ መንግስታት፤ በሃገራችንና በተራው ህዝብ ላይ ያስከተሉት በደል ክብደት ያለው ነው ለማለት ይቻላል። የተራውን ህብረተሰብ ችግር ሊፈቱት አልቻሉም። የመንግስታቱ የበላዮች፤ የገዥውን ክፍል ያገለግሉ ስለነበር፤ የልዩ፤ ልዩ፤ ህብረተሰብ ክፍሎችን ችግር በጥበብና በዘላቂነት ሊያስወግዱት አልቻሉም። ከህዝብ ድምጽና ስልጣን አንጻር ሲታይ፤ ተከታታይ መንግስታት ጥለውልን ያለፉት ችግር እንጅ መፍትሄ አይደለም።

አሁን፤ ይህ አዙሪኝ የሆነ (Vicious Cycle) ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ ባህል እንዲለወጥ ትንሽ ቀዳዳ ተከፍቷል። ዋናው ጥያቄ፤ ይህን እድል ለመጠቀም ምን ያህል ተለውጠናል፤ ተዘጋጅተናል፤ ምን ያህል ፈቃደኛ ነን፤ ምን ያህል ጥበበኛ ነን? ምን ያህል የሃገርና የሕዝብን ጥቅም ከድርጅትና ከግለሰብ ጥቅም በላይ አስቀድመናል? የሚለው ነው። በእኔ እምነት፤ የአሁኑ እድል ካመለጠን፤ ማንንም ለመውቀስ አንችልም፤ መውቀስ ያለብን እኛኑ ነው።

አንድ የምንጋራው አበይት ጉዳይ ቢኖር፤ የህወሓትን/ኢህአዴግን መንግስት ከሁለቱ የሚለየው ዋና ራእይ፤ “በማይታረቅ፤ የብሄር ልዩነት” የታነጸ መሆኑ ነው። በህገ መንግስቱ አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ የመገንጠል መብትን የተቀበለ የገዥ ፓርቲ የሚለው፤ ከተመቸን አብረን እንኖራለን፤ ካልተመቸን እንገነጥላለን ማለት የኢትዮጵያ ህልውና የተረጋገጠ ሳይሆን፤ የገዥው ፓርቲ እንደፈለገ የሚወስነው ሆኗል ማለት ነው። ማን መብት ሰጠው? የገዥው ፓርቲ፤ ይህን በብሄር ላይ የተመሰረተ ቅርጽ፤ በጦር ሃይል በተረዳ መንገድ ተጠቅሞበታል። አሁንም እንዳለ ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ፤ አምባገነንነትን እንደ ተፍጥሮ ህግ፤ እንደ ሕዝባዊ አገልግሎት አድርገው አለምን ያሳመኑበትን ምክንያት እዚህ አልተችም። አልፏል። መጥቀስ የምፈልገው፤ የማይታረቅ የብሄር ልዩነት፤ የአምባገነን ስርአት ልጅ ነው፤ አደጋው ከፍ ያለ የሚሆነውም ለዚህ ነው። የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት የታላላቅ፤ በተለይ፤ የምእራባዊያንን፤ በቅርቡ ደግሞ፤ የቻይናን አመኔታና ድጋፍ በማግኘቱ፤ አገራችን ያልታየ እድገት (Growth) አስመዝግባለች እየተባለ ይነገራል። በሃይል ማመንጫ ግድብ፤ በመንገድ ስራ፣ በትምህርት ስርጭት፤ በጤና ጣቢያወች ስፋት፤ በህንጻ፤ በከተሞች ስፋት፤ ወዘተ ያሳየው ለውጥ ሊናቅ አይችልም፤ የሚታይ ነው።

ሆኖም፤ እድገቱ አያስደንቅም።የማያስደንቅበት ዋና ምክንያት፤ ከአጼ ሃይለስላሴና ከደርግ መንግስታት ጋር ሲንጻጸር፤ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ከልዩ ልዩ ለጋስ መንግስታት፤ ድርጅቶችና የግል ተቋሞች ቢያንስ US$40 billion አግኝቷል። በስደት ላይ የሚገኘው አሁን ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚገመተው ስደተኛ፤ የእድገቱ ተካፋይ ሁኗል። ቢያንስ፤ በአመት ሶስት ቢሊየን፤ ሰቫት መቶ ሚሊዮን ዶላር ይልካል። ተሳትፎው ጎልቶ የሚታየው በተለይ በፍጆት ስራ፤ በቤት ባለቤትነት፤ በግል ህንጻ፤ በምግብ ተቋሞች፤ በሆቴሎች፤ ወዘተ፤ በቤተሰብ፤ ዘመድና ጓደኛ በመደጎም መስክ ላይ ነው። ይህ በፍጆት ላይ የተመሰረተ እድገት፤ መዋቅራዊ ለውጥ አላመጣም፤ ኢትዮጵያ የባሰውን ጥገኛ ሁናለች። ሕዝቡ፤ በተፈጥሮ ሃብቱ ለማዘዝ ከማይችልበት ደረጀ ላይ ደርሷል። የውጭ አገር እንቬስተሮች፤ ሸክ አላሙዲ፤ ወዘተ፤ በሃገራችን አዛዦች ሁነዋል። ተራው ኢትዮጵያዊ በሃገሩ ድምጽ፤ መብት የለውም።

አለም ባንክ እንደሚገምተው፤ ቢያንስ አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የሚደገፉት ስደተኛው በሚልከው ገንዘብ ነው። ሌሎች በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም፤ የእለት ምግብ የሚያገኙት ለጋስ የሆኑ መንግስታትና ድርጅቶች በሚሰጡት ገንዘብ/ርዳታ ነው። ከሁለቱ መንግስታት ጋር ሲወዳደር፤ የሃይለ ስላሴ መንግስት የእርዳታ ማስረጃ መሰብሰብ (Aid flow data) ከጀመረበት አንስቶ ያገኘው US$150 million፤ ይገመታል። ሳይሰረቅ ከስራ ላይ ዉሏል። የወታደራዊ መንግስት፤ በተለይ ከሶቬት ህብረት ለመሳሪያ መግዣ ያገኘውን ጨምሮ፤ 1974-1991 ከUS$3.4 billion ይገመታል። የህወሓት/ኢህአዴ አንድ አስረኛ መሆኑ ነው። አብዛኛው ለመሳሪያ፤ አገር ለመከላከል የዋለ። ደርግ፤ ከአሜርካ፤ ከእንግሊዝ፤ ከአለም ባንክ ለእድገት የሚሆን ርዳታ አያገኝም ነበር። ከህወሓት/ኢህአዴግ በፊት የነበሩት፤ ሁለቱ የኢትዮጵያ መንግስታት ከእርዳታ የተገኘ ገንዘብ በማሸሺ (Massive Illicit Transfer) አልተከሰሱም። ለመስረቅ፤ ብዙም መፈናፈኛ አልነበራቸውም።

በአንጻሩ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በሙስና፤ በአድሎና ፤ከህግ ውጭ ገንዘብ በማሸሺ በሃገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን ቦታ ይዟል። በአመት፣ ቢያንስ፤ US$ 3 billion ከህግ ውጭ ከሃገር ይወጣል፤ ይሰረቃል። ሙስናና ከህግ ውጭ የገንዘብ ሽሽት ባይኖር፤ ስርአቱ ተሳትፏዊና ፍትሃዊ ቢሆን፤ የኢትዮጵያ የእድገት ደረጃ ከፍ ባለ ነበር። ቢያንስ፤ ሕዝቡ፤ አስተማማኝ የምግብ ዋስትና ያገኝ ነበር። የስራ እድል በብዛት ይከፈት ነበር። የዋጋ ግሽፈት ሊገታ ይችል ነበር፤ ወዘተ። የተገኘው እድገት ዘላቂነትና ፍትሃዊ ሊሆን አልቻለም የምለው ለዚህ ነው። የእድገት ዋና መለኪያው የጥቂት ግለሰቦች ገቢና ኑሮ ተአምራዊ በሆነ ገጽታ ማደግ ሳይሆን፤ የአብዛኛው ህዝብ ኑሮ መሻሻል ሲያሳይ ነው። “የእድገታዊ መንግስት” አመራርና ፖሊሲ ለፍትህ የታሰበ አይደለም። የነፍስ ወከፍ ገቢ ፍጹም ድሃ ከተባሉት እንደ ናይጀር፤ እንደ ዝምባብዌ ካሉት ሊለይ ያልቻለው ለዚህ ነው። ዋናው መለኪያ፤ የአፍሪካ አማካኝ የነፍስ ወከፍ ገቢ US$1,070 ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አሁንም US$365 (በአመት) መሆኑ ነው።

“አስደናቂ እድገት ተጎናጽፋለች” በምትባለው ኢትዮጵያ የገቢ ልዩነት እየሰፋ መሄዱ፤ በድሃና በሃብታም መካከል ያለው የኑሮ ልዩነት አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱ፤ ሊገታ የማይችል የዋጋ ግሸፈት የሰውን ኑሮ መጉዳቱ፤ የወጣቱ እድል ተምሮ መሰደድ ተደጋጋሚ መሆኑ፤ ወዘተ፤ ፖሊሲውና መዋቅሩ የፈጠራቸው፤ ያለለውጥ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ብቻውን ሊፈታቸው የማይችል መሆኑን የሚያሳዩ መለኪያወች ናቸው። “እድገታዊ መንግስት” የተባለው የገዥውን ፓርቲ ባለስልጣኖችና የጥቂት ቤተሰቦችን የኢኮኖሚ የበላይነቱን አስተጋባ እንጅ ዘላቂነትና ፍትሃዊ የሆነ፤ ህይወት ለዋጭ የሆነ እድገትን አልገነባም። ለዚህ የተዛባ የኑሮ ሁኔታ ቀጣይነት አስተዋጾ የሚያደርገው ግልጽነት፤ በህግ የሚተዳደር ውድድር አለመኖሩ ነው። የገበያ ውድድር፤ ያለነጻነት፤ ያለህዝብ ድምጽና ቀጥተኛ ተሳትፎ ሊኖር አይችልም። የሰው ሃይል፤ የተፈጥሮ ሃብት፤ የውጭ እርዳታ፤ የሃገር ውስጥ ገቢ የሚባክነውም ለዚህ ነው። ስርአቱ ለፍትህ፤ ለሰላም፤ ለእርጋታ፤ አብሮና ተቻችሎ ለመኖር ጫና ማድረጉ፤ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ለማጥፋት፤ የሚደረግውን ጥረት ይገታዋል። ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው መላውን የህብረተሰብ ክፍሎች በሃገራቸው ሙሉ ተሳታፊ ማድረግ ብቻ ነው። የገዥው ፓርቲ፤ እነዚህን ችግሮች በከፊልም ቢሆን፤ ቀንሷል ቢባል፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ሃገራችን ከኋላ ቀርነት፤ ከርሃብ፤ ከስደት፤ ከጥገኝነት፤ ከተስፋ መቁረጥ ነጻ ለማድረግ አልቻለም። የፖለቲካ፤ የህብረተሰብ፤ የኢኮኖሚ ምህደሩ (Political, Social and Economic Space) መስፋት ያለበት ለዚህ ነው። የጋራ ችግሮችን በጋራ ለማሰወገድ የሚቻለው፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብቱ ተጠብቆ በሃገሩ ሰርቶ፤ ተከብሮ፤ ተንቀሳቅሶ፤ ኑሮውን ለማሻሻል ሲችል ብቻ ነው።

ሁሉም አለም አቀፍ ዘገባወች የሚያሳዩት፤ ገዡው ፓርቲ የፈጠራቸው የፖሊሲ ችግሮች ለሃገርና ሕዝብ ማነቆ መሆናቸውን ነው። World Economic Forum (2012-2013) ፤ ተቋሞችን፤ አስተዳደርን፤ ህግን፤ ነጻነትን፤ ሙስናና አድሎን፤ የሃብት ሽሽትንና ሌሎች መለኪያወችን ተጠቅሞ ያወጣው ዘገባ ባሳየው መሰረት፤ ኢትዮጵያ ከመቶ አርባ አራት አገሮች መቶ አስራ ስምንተኛ (118th out of 144 countries) ናት። በተለይ በጤና አገልግሎት፤ በትምህርት ጥራት፤ በገብያ ውድድርና ቅልጥፍና፤ በባንክ አገልግሎት፤ በሙስና፤ የሚታየው ዘገባ አሳፋሪ ነው። ዘላቂነትና ፍትሃዊ እድገት ካለ፤ እነዚህ መለኪያወች ከአመት ወደ አመት እየተሻሻሉ በፍጥነት ከሚያድጉ አገሮች ጋር ተወዳዳሪ መሆን ነበረባቸው፤ አይደሉም።
Freedom House ያወጣው Freedom in the World 2012 Index በተለይ፤ የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶች ዘገባ፤ የኢትዮጵያን ኋላ ቀርነት በግልጽ ያሳያል።

የአፈና “ወረርሽኝ” ተቋማዊ ሲሆን፤

ይህ ዘገባ፤ ነጻነት ያላቸውንና የሌላቸውን አገሮች በማወዳደር፤ “ነጻ የሆኑ ህብረተሰቦች ማለት ምንድን ነው” ብሎ ይጠይቃል። ትርጉሙ፤ in societies that are free, “There is open political competition, a climate of respect for civil liberties (and human dignity), significant independent civic life and independent media.” ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያ በፍጹም የለም። የከለከለው ገዥው ፓርቲ ነው። እንዲያውም፤ ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች ነው በተባሉበት ባለፉት አስር አመታት አፈናው እየባሰ እንጅ እየተሻሻለ አልሄደም። ዘገባው ያቀረበውን እንይ። “Five of the ten countries that registered the most significant declines in the Freedom of the World Report over the two-year period (2010-2011) were in Africa: Ethiopia, Gambia, Burundi, Rwanda and Djibouti….Ethiopia continued a decade-long trend of authoritarianism with the government of Prime Minister Meles Zenawi making increased use of anti-terrorism laws against the political opposition and journalists.”

የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነን መንግስት በተለይ፤ በተቃዋሚ ፓርቲወችና በጋዜጠኞች ላይ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ጫና፤ አፈና የሚያደርግበት ለምን ነው? ስልጣኑና የኢኮኖሚ ጥቅሙ እንዳይዛባ ነው። የፖለቲካ ውድድር ካለ፤ ተቃዋሚው አማራጮችን ለሕዝብ ያቀርባል፤ ካቀረበ፤ የመመረጥ እድሉ ከፍ ይላል፤ ምርጫ ዘጠና ሰባት ያሳየው ይህን ነው። የገዥው ፓርቲ የበላዮች ከሁሉም የሚፈሩት ነጻ የሆኑ ጋዜጠኞች እውነቱን ለሕዝብ ያለገደብ ማቅረባቸውን ነው። የሚድያ ቁጥጥር የሚጠቅመው ሕዝቡ እውነቱን በቀጥታ ለማግኘት እንዳይችል በመደረጉ ነው። ከጠበንጃ፤ ከመትረየስ የበለጠ መሳሪያ እውቀትና ያልተበረዘ ዜና ሕዝብ ማግኘቱ ነው። ለዲሞክራሲ ቁልፍ መሳሪያ ነጻ መዲያ መሆኑን የገዥው ፓርቲ የበላዮች ጠንቅቀው ያውቃሉ። የሚገቱት ለዚህ ነው።

ሌላ ቀርቶ፤ የኢትዮጵያን እድገት አድናቂ የሆኑ መንግስታትና አበዳሪ ድርጅቶች ያለውን ጫናና አፈና ያውቁታል፤ በውስጥ ይነጋገሩበታል፤ ያምኑበታል። ጠለቅ ብሎ ያየ ታዛቢ፤ አገር ወዳድ፤ የገዥው ፓርቲ ተራ አባል፤ የጦር ሃይሎች አባል፤ የውጭ ተመልካች፤ ህወሓት/ ኢህአዴግ እነዚህንና ሌሎችን አገራዊ ችግሮች ብቻውን ሊፈታቸው እንደማይችል ይገነዘባል። ችግሮቹ ካልተፈቱ፤ ዘላቂነትና ፍትሃዊ እድገት እንደማይኖርም ያምናሉ። በሁሉም ኢትዮጵያዊያን በኩል የአመለካከት ለውጥ አስፈላጊ የሚሆነው፤ አብሮ ተባብሮ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ሁሉን አቀፍ የሆነ የመንግስት ስርአት መፈጠር ያለበት ለዚህ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ የማይፈልገው፤ እስካሁን እንደነበረው አመራር “በጠላትነት እየተያዩ፤ ሆድና ጀርባ ሁኖ” መኖርን ነው። ለምን? እንኳን በሃገር ደረጃ፤ በቤተሰብ ደረጃም ቢሆን፤ በጠላትንትና በጥላቻ ባህል የጋራ ችግሮችን ለመፍታት አይቻልም። የሌሎች አገሮች ምሳሌ እንደሚያሳየው፤ ፍትሃዊ፤ ሁሉን አቀፍ፤ ለሁሉም አገልጋይ በሆነ የመንግስት ስርአትና አመራር ፓርቲወች በጠላትነት አይተያዩም፤ ጠላትነት የሚመነጨው ዲሞክራሳዊ ስርአትን ከመፍራት ነው። ልዩነትን እንደ ጠላትነት ከመመልከት ልምድ ነው። አድሏዊ መንግስት ለፍትህ የቆመ ተቃዋሚ ሁሉ፤ ጠላት አድርጎ የሚያሳድደው፤ የሚገድለው፤ የሚያስረው፤ ከሰላም፤ከነጻነት፤ ከዲሞክራሲ ይልቅ መረጋጋትን (Permanent Instability and Suspence) ስለሚመርጥ ነው።

አዲስ የለውጥ ምእራፍ፤ አዲስ አቅጣጫ፤ ዛሬ፤

የዚህ አቅርቮት ዋና አላማ፤ የሃገራችን ሁለ ዘርፍ የሆኑ ችግሮች በጋራ ሊፈቱ ይችላሉ የሚል ነው። አገራዊ ችግሮችን በጋራ ለማሰወገድ ከተፈለገ፤ የአንድ ፓርቲ የበላይነት አገዛዝ በአስቸኳ መለወጥ አለበት። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የስልጣኑ ባለቤት መሆን አለበት። መንግስትና መሪወች የሕዝብ ተገዥ፤ የሕዝብ አገልጋይ፤ የህዝብ ድምጽ አዳማጭ መሆን አለባቸው። አዲስ የለውጥ ምእራፍ ማለት እንደዚህ ነው። ለእውነተኛ የዲሞክራሳዊ መንግስት መቋቋም እውቅትና ብልሃት ያለው ሽግግር ማድረግ አሰፈላጊ ነው የሚለውን መሰረተ ሃሳብ ህወሓት/ኢህአዴግና ተቃዋሚ ሃይሎች ከተጋሩ፤ (መጋራት አለባቸው ብየ አምናለሁ)፤ ወደዚህ የሚያደርሱ ቅድመ ሁኔታወችን (Favorable Conditions) መፍጠርና ማመቻቸት የሁሉም፤ በተለይ የገዡ ፓርቲ መሪወች ታሪካዊ ሃላፊነት ነው።ማሰብ ያለባቸው፤ አምባገነናዊ አገዛዝ ከአሁን በኋላ ለገዥውም ፓርቲ የበላዮች አያዋጣም። ሰላም፤ እርጋታ፤ አይኖርም። አንዱ በይ፤ አንዱ ጦም አዳሪ፤ አንዱ በስር ቤት ነዋሪ፤ አንዱ በቤተመግስት ወይንም ቪላ ኗሪ፤ ሆኖ ሰላምና እርጋታ ይኖራል ማለት ዘበት ነው። ለኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት፤ ለመላው ሕዝቧ ሰላም፣ ለፍትህ፤ ለብልጽግና፤ ለእኩልነት፤ ለነጻነት፤ ለከብር፤ ከርሃብ አለንጋ፤ ከጥገኝነትና ከስደት፤ ነጻ ለመሆን፤ ቁመናል የሚሉ መንግስታት፤ ተቋሞችና ግለሰቦች ሊረዱን የሚገባቸው የገንዘብ ወይንም የምግ እርዳታ በመስጠት አይደለም። ፍትህ ካለ የኢትዮጵያ ሕዝብ እራሱን ይችላል፤ አገሩን ዘመናዊ ያደርጋል። ሊረዱን የሚችሉት፤ ህወሓት/ኢህአዴግና ተቃዋሚ ሃይሎች በሙሉ በአስቸኳይ ሁሉን አቀፍ የሆነ፤ ለሰላም፤ ለእርቅ፤ ለፍትህ፤ ለዲሞክራሳዊ ስርአት ሽግግር፤ አገራዊ ስብሰባ እንዲያደርጉ አስተዋጾ በማድረግ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ይህን አዲስም እራፍ ከፋች ሊሆኑ ይችላሉ። ለታሪክ ትተውት የሚያልፉት አስተዋጾ ይህ ነው። ካለፉት ጠቅላይ ሚንስትር የሚለያቸውም ይህ ነው። የእኮኖሚ ተሃድሶ ሊመጣ የሚችለው የፖለቲካና የመንፈው ተሃድሶ ሲኖር ብቻ ነው። አለበለዚያ፤ የዛሬ አምስት አመት፤ አለም አቀፍ ዘገባወች የሚያሳዩት ተመሳሳይ ውጤትን ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ፤ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ የሃገራችን ችግሮች እኛው ተመካከረን፤ እኛው ተደራድረን፤ እኛው ተሰብሰበን፤ እኛው መፍትሄ ለመስጠት እንችላለን የሚል የአስተሳሰብ ውሳኔ ማድረግ አለብን። ይህን ለማድረግ ኢትዮጵያንና መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ማእከል ማድረግ አለብን (Place Ethiopia’s National Inerest and the Interests of all of the Ethiopian People on the Radar Screen and subordinate individual and partisan interest)፤ የቀረው ይከተላል። ይህን ካደረግን በአምስት አመታታ ውስጥ፤ ዛሬ ጋና ነጻ ከተባሉ የአፍሪካ አገሮች ከደረሰችበት ለመድረስ እንችላለን። ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማሪያም ወደዚህ አላማ ለመጓዝ ጥረት ማድረግ አለባቸው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብሯቸው እንደሚቆም አልጠራጠርም።

ሽግግር ሲባል ምን ማለት ነው?

ሁሉን አቀፍ አገራዊ ውይይት አካሂዶ፤ የእርቅ/የዲሞክራሳዊ ስርአት ግንባት ድልድይ የሆነ ጊዜአዊ መንግስት መመስረት ማለት ነው። ይህ በውይይት እንጅ በዛቻ፤ በፉከራ፤ በመለፍለፍ የሚገኝ አይደለም። ለዚህ ለተቀደሰ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሚመኘው አላማ፤ መንፈሳዊ አባቶች፤ የሃገር ሽማግሌወች፤ የታወቁ ምሁራን፤ ወዘተ ድልድይ ሁነው “ተሰብሰቡ፤ ተነጋገሩ፤ አገራችንና ጉራማይሌ ሕዝቧን አስቀድሙ፤ መወነጃጀልን አቁሙ፤ “ታሪክ ያላችሁና ጥበበኛ መሆናችሁን ለአለም ህብረተሰብ አስመስክሩ” ሊሉና የመተማመን ቅድመ ሁኔታን ሊያጠናክሩ ይችላሉ። የድርድር ምርኩዞች፤ አገራዊ አንድነት፤ ሰላም፤ እርቅ፤ ይቅር ባይነት፤ እኩልነት፤ የህግ የበላይነት፤ ነጻ ምርጫ፤ የፖለቲካ ውድድር፤ ዲሞክራሳዊ ስርአት፤ ሰብአዊ መብቶች፤ ሊሆኑ ይችላሉ። ሌሎችን የኢትዮጵያ ሕዝብ በውይይት፤ በምርጫ ሊወስናቸው ይችላል።

ይህን ስል፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ጥቅሙን ወደ ጎን ትቶ፤ ለሰላምና፤ ለእርቅ፤ ለድርድርና ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ግንባታ በሩን በቀላሉ ይከፍታል የሚል “ቅዠት” ውስጥ አልገባም። ጉዞው ቀላል አይሆንም። በመጀመሪያ፤ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች፤ ግለሰቦች፤ ስብስቦች ሁሉ፤ መሰብሰብ፤ መደጋገፍ፤ በአንድ ድምጽ፤ ለአንድ አገራዊና ሕዝባዊ አላማ መቆም አለባቸው። አገር ውስጥ፤ አገር ውጭ የሚባለው ልዩነት መጥፋት አለበት። ይህን ካደረጉ፤ የአለምን ህብረተሰብ፤ በተለይ፤ የደጋፊ መንግስታትን አቋም ሊለውጡ ይችላሉ። ገዥውን ፓርቲ፤ ለድርድር ከሚያስገድዱበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ያለው እድል ከፍ ይላል። ሕዝቡ እንዲደፋፈር ያደርጋል፤ ወጣቱ ትውልድ በብዛት ወደዲሞክራሳዊ ግንባታው፤ ወደ ሰላማዊ አመጹ (Popular, peaceful resistance) እንዲገባ ያበረታታል። የፍርሃትን ባህል ይቀንሳል፤ ወዘተ። ይቻላል ብለን ማሰብ ይረዳል። የገዠውን ፓርቲ ለማሳፈር/ለማጋለጥ ለሚደረገው ትግል አስተዋጾ ያደርጋል። ከውጭ ያለነው አገር ቤት ከሚታገሉ ሃይሎች ጋር የጠነከረ ግንኙነት መፍጠር አለብን፤ የገንዘብ እርዳታ በዘላቂነት መስጠት አለብን።

ያልተሞከረው መሞከር አለበት የምለው ለዚዝ ጭምር ነው። ሆኖም፤ የሰላማዊ አገራዊ ሁሉን አቀፍ ስብሰባና ድርድር ጥሪ፤ ቀላል ይሆናል የሚል ግምት የለኝም። ምኞትና ህልም ሁኖ ሊቀር ይችላል፤ መሞከር አለበት የሚል እምነቴ ግን ጠንካራ ነው። ለዚህ ስኬታማነት ቅድመ ሁኔታወችን ተጠቅሞ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ሊያደርግ የሚገባውን ጥያዌወች ለአለም ሕዝብና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለመሰልቸት፤ ማቅረብ፤ ማስረዳት የተቃዋሚወችና የእያንዳዳችን ሁሉ ሃላፊነት ነው።

ከጦርነት ባህል፤ ወደ እርቅና ድርድር ባህል መራመድ ለሃገራችን ዘላቂነት፤ ለመላው ሕዝቧ፤ ፍትሃዊ/ተሳታፊያዊ እድገት ይጠቅማል። ዘመናዊ የፖለቲካ ባህል ማለትም ይህ ነው። ቂም በቀልነት፤ እብሪተኝነት፤ “እኔ ብቻ ነኝ አዋቂው” ባይነት ካልቆመ የትም አንደርስም።

ቅድመ ሁኔታ ምን ማለት ነው? ምን ያካትታል?

“የምርጫ ዘጠና ሰባት የፖለቲካ መንፈስ” አለ ለማለት የሚያስደፍሩ ምልእክቶች አሉ። ዋናው መለኪያ፤ ሕዝቡ ለዲሞክራሳዊ ለውጥ ያለው ጉጉት ነው። አሁንም አልጠፋም። ለዚህ የቆሙለት በእስር ቤት የሚሰቃዩ፤ በድብቅ የሚሰሩ፤ በውጭ የሚታገሉ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ በነጻነት እንዲሰሩ ከባድ ጫና ቢያደርግም፤ አገር ቤት ሁነው ቀንና ሌሊት የሚታገሉ የሰላማዊ ለውጥ ደጋፊወች፤ ጠበቃወች፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ጋዜጠኞች አሉ። በተለይ ወጣቶች። ቅድመ ሁኔታወች ይመቻቹ ስል፤ መግለጫ የማደርገው ከዚህ በፊት ቅንጅት/ህብረት ያቀረባቸውን ስምንት አንኳር ጥያቄወች ነው። ጥቅማቸው፤ ተገቢነታቸው አልተለወጠም። እነዚህም፤

i) ህወሓት/ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው የምርጫ ቦርድ በአዲስ መልክ ይዋቀር፤ ከገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሆኖ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያለ አድሎ ያገልግል፤
ii) ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲወች፤ የማህረሰብ ድርጅቶች፤ ግለሰቦች መገናኛ ብዙሃን የመጠቀም መብታቸው ይጠበቅ:: የፕሬስ ነጻነት ከስራ ላይ ይዋል፤ የፕሬስ ነጻነት ገደብ የሆነው፤ የሽብርተኝነት ህግ ተብሎ ንጹህ ኢትዮጵያዊያን የሚታሰሩበት ህግ ይወገድ፤
iii) የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ፤
iv) የጦር ሃይሎች በሙሉ፤ በፖለቲካ ውድድር ውስጥ ጣልቃ መግባታቸውን ያቁሙ፤ ከገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሁነው፤ አገራቸውንና መላውን ሕዝብ ያገልግሉ፤
v) የህግ ተቋሞች፤ ፍርድ ቤቶች በሙሉ ከማንም ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሁነው፤ ህብረተሰቡን ያገልግሉ፤
vi) ከገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ የሆነ ኮሚሽን ተቋቁሞ ሁሉንም ግድያወች ይመርምር፤
vii) የፓርላማ አስተዳደር/አሰራር ዲሞክራሳዊና ግልጽነት ባለው መንገድ ይስራ፤
viii) ከላይ ያሉትን ሁሉ የሚያስተናግድ/ የሚዳኝ ከገዥው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ የሆነ ኮሚሽን ይቋቋም የሚሉ ናቸው።

እነዚህን ጥያቄወች ከስራ ላይ ለማዋል እስካሁን በአምባገነኑ መንግስት ያልተደረገ የፖለቲካ ባህል ለውጥ፤ ሂደትና አቀራረጽ አስፈላጊ ነው። በመጀመሪያ፤ ፈቃደኛነት ማሳየት ያለበት ገዥው ፓርቲ ነው። የኢህአዴ መንግስት፤ ኢትዮጵያንና መላውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ማእከልና ተቀዳሚ አድርጎ ፤ ለነገዋ ኢትዮጵያ፤ ለሰላም፤ ለሕዝብ ስልጣን የበላይነት፤ ለእውነተኛ እኩልነት፤ለእርቅ፤ ለመግባባት፤ በውይይት ልዩነቶችን ለመዳኘት መሞከር ታሪካዊ ጥሪ እንደሆን ካየው፤ እንዚህን ቅድመ ሁኔታወች በስራ ይተረጉማል የሚል ግምት አለኝ። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ይህን ለማድረግ ትምህርቱም፤ የስራ ልምዱም፤ ቅንነቱም፤ የአቀራረብ ችሎታውም አላቸው። ፈቃደኛ መሆናቸውን የምናየው ወደፊት ቢሆንም፤ ማበረታታ እንጅ ማነቆ መሆን የለብንም።
ሆኖም፤ ተቃዋሚ ሃይሎች በሙሉ ተባብረው ድምጽ ካላሰሙ፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመሩት መንግስት ወዶ አያደርገውም የሚሉ ብዙ ናቸው። የሃገራችንና የሕዝቧን ታላቅነት የሚያሳይ ይህ መንገድ መሆኑን መቀበለ ግዴታ መሆኑን ለአለም ሕዝብ ማሳሰብ ጠቃሚ የሚሆነው ለዚህ ነው። ውጭ ያለው ተቃዋሚ በቅንነት፤ ባንድነት ከሰራ፤ የአለምን ሕዝብ አስተሳሰብ ለመለወጥ ይችላል። ሰላም፤ እርቅ፤ ይቅር ባይነት፤ ለወደፊቱ ትውልድ ማሰብ፤ የአገርን፤ የህዝብን ችግሮች በጋራ ለማስወገድ መሞከር ያለመድነው ባህል መስሎ ይታያል፡፡ ራስን፤ ጥቅምን ካላስቀደምን በስተቀር፤ ባህሉ አለን። ኢትዮጵያ ለብዙ ሽህ አመታት ክብሯን፤ ነጻነቷን ይዛ የቆየችው ልዩኑነቶችን በማቻቻል፤ አብሮ መኖርን በማጠናከር፤ በጋራ ቁሞ፤ የውጭ ጠላትን በመከላከል ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ ከተከለብን መርዝ አንዱ፤ በዘር መለያየቱ ነው። ወደኋል ዞር ብሎ የመቻቻል ባህልን አድሶ መጠቀም፤ የሃገራችን ሕዝብ ታላቅነት የሚያሳይ እንጅ የድክመት ምልክት አለመሆኑን በተግባር ማሳየት ያለብን እኛው ነን። በዘር ልዩኑት የተበከለ መርዝ ለእኛ ድክመት፤ ለሃገራችን ጥገኝነት፤ ኋላ ቀርነትና ድህነት መሳሪያ መሆኑን ሌላው ሳይቀር አገራችን አንጡራ ሃብቷን፤ የባህር በሯን አሰብን ማጣታችን ብቻ ይመሰክራል። ሁሉን አቀፍ ለውጥ የሚጠቅመው ያለፈውን ስህተት አንዳንደግም፤ ብሩህ የሆነ በር እንድንከፍት ስለሚረዳ ጭምር ነው። አብሮ ተባብሮ የሃግርን ችግሮች ማስወገድ፤ ታላቅ የሆነች፤ በፍጥነት የምታድግ ኢትዮጵያን ይፈጥራል፤ መላውን ሕዝቧን ከድህነት፤ ከስደት ነጻ ያወጣል።

አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር፤ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለዚህ አዲስ ምእራፍ አስተዋጾ እንዲያደርጉ ማበረታታት የሚያስፈልግው ለዚህ ጭምር ነው። በርሳቸው የሚመራው የኢህአዴግ መንግስት ለድርድር ክፍት መሆን የድክመት ምልክት አይደለም፤ ለሃገር፤ ለመላው ሕዝብ የመቆም ምልክት ነው። ለእውነተኛ ዲሞክራሲ፤ ለጭቁን ብሄር/ብሄረሰብ ፍትህ፤ ለነጻነት፤ የመቆም ምልከት ማለት ይህ ነው። በአንጻሩ፤ ለሰላማዊ ድርድር፤ ለእውነተኛ የህዝብ ስልጣን የሚያሸጋግር መንገድ፤ ለፍትህ አለመዘጋጀት የአንድ ፓርቲ አምባገነን አገዛዝ አሁንም ይቀጥል እንደማለት ነው። ይህን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲረዱት፤ ተቃዋሚ ሃይሎች ሁሉ በጋራ፤ ሃየለማሪያም ደሳለኝ፤ ለፍትህ፤ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እስከቆሙ ድረስ፤ አብሯቸው እነደሚቆም ማሰማት ያለበት አሁን ነው።

የመከላከያ ተቋሞች አገራዊ ይሁኑ፤

የኢትዮጵያ የደህንነትና የመከላከያ ሰራዊት የአምባገነን መንግሥት ስርአት ጠባቂና ተከላካይ ሆኖ በ”ጥቁር ቀለም” ታሪክ እንዲፈረጅ መፍቀድ የለበትም። ቃል በገባው የህዝብ አደራ መሰረት፤ የአንድ ፓርቲ የበላይነት ማገልገል ሳይሆን፤ የወገኑን ብሶት በማየት፤ “የጉራማይሌ (Diverse/Mosaic)” ሕዝቡን አለኝታነትና ክብር፤ የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት ብቻ እንዲያስቀድም፤ መመሪያው እንዲያደርግ ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። ዘጠና በመቶ የሚሆነውን ተራ አባል፤ መካከለኛ እዝ፤ ከአንድ ብሄር የተወጣጣው የበላይ እዝ ሊወክለው አይችልም፤ አይገባም፤ ብለን አደራውን እንዲወጣ፤ ሃይሉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጫና እንዳያደርግ፤ ወገኑን እንዳይገድል፤ መቀስቀስ አለብን። ለዚህ፤ የቅርብ ምሳሌ አለ።
ውጣ ውረድ ቢያሳይም፤ የግብጽን የጦር ሃይልና የስለላ ድርጅት ከሶሪያው የሚለየው፤ የህዝብ አመጽ ሲነሳ፤ ታንክ፤ የጦር አውሮፕላን፤ መትረየስ፤ የጠበንጃ አፈሙዝ ወደ ሰላማዊው የግብጽ ህዝብ አላዞረም። ባለማዞሩም፤ የእርስ በእርስ እልቂት ዝቅተኛ ነው፤ የጦር ሃይሉ ከህብረተሰቡ ጎን ቁሟል። አገራዊ እንጅ የገዡ ፓርቲ አገልጋይ አለመሆኑን አስመስክሯል። የኢትዮጵያ የጦር ሃይል የሚያኮራ ታሪክ ሊሰራ ይችላል ብየ የምገምተው፤ የራሱ የሚያኮራ ታሪክ ስላለው፤ አገር ወዳድ ስለሆነ፤ አብዛኛው ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ጠንካራ ስለሆነ፤ ጭምር ነው። የሰላም፤ የእርቅ፤ የነጻነት፤ የፍትህ፤ የዲሞክራሳዊ ስርአት ግንባት፤ የመወያየት፤ አብሮ ችግሮችን የመፍታት ጥሪን እንደሚደግፍ ተስፋ የማደርገው ለዚህ ነው። ጠንካራ ኢትዮጵያ ልትኖር የምትችለው ጠንካራና በነጻነት የሚኖር፤ ያለ አድልወ የሚሰራ፤ ሕዝብ ሲኖር ብቻ፤ ነው የሚለውን እሴት ሊቀበል እንደሚችል መገመት አለብን። ጠንካራ ሕዝብ ያለ ፍትህ፤ ያለ መብት፤ ያለ ክብር፤ ያለ ነጻነት፤ ያለ እኩልነት፤ ሊኖር አይችልም ብለን ለመላው አለም ማስረዳት ያለብን እኛው ነን። ይህን የኢትዮጵያ ጦር ሃይል ያውቃል። ጥሪው ሃይሉን የሚመለከተው ለዚህ ጭምር ነው።

ከለቅሶው ባሻገር እንይ፤

የኢትዮጵያ ሕዝብ አገር አቀፍ በሆነ ሁኔታ፤ ተገዶም ሆነ ፈቅዶ ለመለስ ማልቀሱ በአብዛኛው ሕዝብ ላይ ያለውን ብሶትና ጭንቀት፤ በወጣቱ ላይ የደረሰውን አሳፋሪ የስደት እጣ፤ በፍትህ ላይ ያለውን ተደጋጋሚ (Recurring) ጭነትና አፈና፤ በሃገራችን ላይ የሚታየውንና የሚያንዣበበውን ግልጽ አደጋ ሊበርዘው ወይንም ሊሽፍነው አይችልም።
የመለስን እንደማንኛውም ህያው ከዚህ አለም ማለፍ በሰብእነታቸው አስቦ ማዘን/መቀበል የሰው ፍጥሩ ሁሉ ባህርይ ነው። ሆድ የባሰውም ያለቅሳል። እያዘኑ ያለፈውንና የሚመጣውን ማሰብ አስተዋይነት ነው። ከሚያጠያይቁት ነገሮች አንዱ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ የመለስን “አስከሬን ለምን” ትእይንት አስመሰለው፤ አቀረቡት፤ ሌሎች እንደሚሉት፤ ለምን “አስከሬኑን መነገጃ አስመሰሉት? ለአሁኑና ለተከታታይ ትውልድ ምን መልእክት ለማስተላለፍ ተብሎ ነው? ህወሓት/ኢህአዴግ የቀናት አገር አቀፍ ለቅሶ “ሲያውጅ” የሚያስተላልፈው የአገዛዝ መልክት ስላለው ነውን? ይህ ከሆነ፤ መልእክቱ ምንድን ነው? ለነዚህም ከማውጣት ከማውረድ በላይ መልስ የለኝም። አልፏል። ሆኖም፤ ስብሰቡ፤ “ትእይንቱ” አያስገርምም ብለን ልናልፍ እንችላለን። አንዳዶች እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ ሰሜን ኮሪያን ሁናለች ብለን እንለፈው። ለመለስ ማለፍ ለምን የዚህን ያህል ለቅሶ አስፈለገ ብለን እንለፈው። በደርግም ጊዜ ሰው ተገዶ ተሰልፏል። ንግግሩ፤ ውይይቱ፤ የውጭ መንግስታት ፕሬዝደንቶችና ተወካዮች ለልቅሶው ለምን መጡ፤ መለስን ለምን አሞገሱ፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ፤ ኢትዮጵያዊያን በዘር፤ በሃይማኖት፤ በጾታ፤ በእድሜ፤ በገቢ፤ በኑሮ ሳይገቱ ለምን አለቀሱ፤ በልቅሶው ወቅት ለምን ሕዝቡ የእምቢተኛነት ስሜት አላሰማም፤ የሚለው አይደለም። የዚህ አይነት አስተያየት የትም አያደርሰንም።

በግል ሳየው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋነቱን ደጋግሞ አስምሮበታል፤ እንኳን ለሃያ አመታት አምባገነን ሁኖ የገዛ፤ ለተራ ሰው ያለቅሳል፤ ያዝናል። አንዱም መለያችን ይህ ነው። አብረን ለማልቀስ ከቻልን፤ አብረን የሃገራችን ተጠቃሚወች መሆን መብታችን ነው። ሕዝቡ፤ ኢትዮጵያዊነቱን፤ ሰብእነቱን፤ አስመስክሯል። ሁኔታው ቢፈቅድለት ኖሮ፤ አጼ ሃይለስላሴ ሲያርፉ፤ አገር አቀፍና አለም አቀፍ በሆነ መልኩ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ባለቀሰ ነበር። የሚያሳፍረው፤ የደርግ መንግስት፤ በጊዜአቸው የሚያኮራ ስራ የሰሩትን፤ በአፍሪካና በአለም ከመለስ ዜናዊ በላይ ለሃገራችን እውቅና ከፍ ያለ አስተዋጾ ያደረጉትን መሪ፤ በድብቅ እንዲቀበሩ አደረገ፤ ክብራቸውን በመግፈፍ የኢትዮጵያን ሕዝብ ክብር ገፈፈ። በዚያ ጊዜ የነበሩ እንደሚያስታውሱት፤ በብዙ ሽህ የሚቆጥሩ ኢትዮጵያዊያን በእየቤታቸው አልቅሰዋል። ከዚያ ወዲህ፤ ሁኔታወች አስደናቂ በሆነ መልክ ተለውጠዋል። ከግማሽ በላይ (More than 50 percent of the Ethiopian population of 94 million today) የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው አንድ መሪ ነው፤ መለስ ዜናዊን።

ከንግስት ዘውዲቱ በኋላ፤ (መቶ አመት ሊጠጋ ነው)፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጤና ምክንያት ከዚህ አለም ያለፈ መሪ ሲቀብር የመጀመሪያው መለስ ናቸው። ከሃዘኑ ባሻገር ልብ ብለን ማየት ያለብን፤ መለስ የተለቀሰላቸውና የተቀበሩት እንደ አንድ ብሄር ተወካይ ወይንም እንደ እንደ ትግራይ ተወላጅ ሳይሆን፤ “እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ መሪ፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ” ሆነው ነው። ይህን ስል፤ለሃያ አመታት የሰሩትን በደል፤ እንርሳ፤ ማለቴ አይደልም፤ ቢያንስ በአራት መጽሃፎች ላይ እርሳቸው የመሩት መግንስት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰውን በደል በማስረጃ አቅርቤዋለሁ፤ ሁለቱን መጽሃፎቸን እራሳቸው እንዳነበቡና “እንደተቹብኝ” ተነግሮኛል። ከደጋፊወቻቸው ጋር በይፋ ተከራክሪያለሁ።

ከጠባብ ብሄርተኛነት ወደ ኢትዮጵያዊነት፤

ለተመልካቾች እንቆቅልሽ የሆነው፤ የመለስ ኢትዮጵያዊነት እውቅና ያገኘው ከዚህ አለም ሲሞቱ መሆኑ፤ ነው። አንዱ የምንማረው ትምህርት፤ መለስ በኢትዪጵያዊነታቸው ከኢትዮጵያ መናገሻ ከተማ፤ ከኢትዮጵያ ዋና መታወቂያ ቤተክርስቲያን ከተቀበሩ (ማለትም፤ በአዲስ አበባ)፤ በናቁትና፤ “ጨርቅ ነው” ባሉት ሰንደቅ አላማ” ከተሸፈኑ፤ ህወሓት የተባለው በጠባብ ብሄርተኝነት የተመሰረተው የፖለቲካ ራእይም አብሮ ተቀበረ ማለት ነው። ጠባብ ዘረኝነት ከተቀበረ እልል ብለን መቀበል አለብን። ሌላም አይነት ዘረኝነት እንዳይደገም መከላከል አለብን። ትግራይ፤ አድዋ ቢቀበሩ ኖሮ፤ የአለምና የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ፤ ይደንቀውና ይበሳጭ ነበር የሚል ትርጉም ይሰጥ ነበር። ከዱሮውም እንቃወም የነበረው፤ በብሄር፤ ክልል በተባለ አስተዳደር መደራጀትን ነበር። ለአንድ ብሄር አድልወ ማድረግን ነበር፤ የራስን ብሄር ቡድን ማበልጸግን ነበር። ኢትዮጵያዊነት እስከሞት ድረስ የሚቆይ ሳይሆን፤ ከልጅነት እሰከሞት አብሮ የሚታይ መግለጫ ነው። ከአሁን በኋላ በብሄር መጠራት፤ በብሄር መደራጀት፤ ለብሄር ማሰብ፤ በብሄር መበልጸግ፤ የማይጠቅመው፤ ትርጉም የማይኖረው ለዚህ ነው። በዘር ልዩነት መነገድ በወገንና በሃገር ላይ በደል ሰርቶ እንደማለፍ ነው። መለስ፤ በህይወት በነበሩበት ወቅት፤ “እኔ በብሄሬ ሳይሆን፤ የምኮራው በኢትዮጱያዊነቴ ነው ቢሉ ኖሮ” ታሪካዊ ስራ ሰሩ ለማለት እችል ነበር። አላደረጉም። ሆኖም፤ የቀብራቸው ስነስርአት የለውጥ/የተሃድሶ ምልክት ነው። ወደፊት የምንፈልጋት ኢትዮጵያ፤ ለሁሉም እድል የምትሰጥ፤ ሁሉም የሚኮራባት፤ ሁሉም በፈቃዱ ችሎታ ያላቸውን መሪወቹን የሚመርጥባት፤ አልቅሶ የሚቀብርባት አንድ፤ ፍትሃዊ ሃገር መሆን ይኖርባታል። ከሆነ፤ ሆይ “ብለን እንመርጣለን፤ ወይ አምላክ ብለን” እንቀብራለን ማለት ነው።ነጻነት ማለት ይህ ነው።

ታዛቢወች ለቅሶውን “በአስከሬን መነገድ፤ ምን ትርጉም አለው” የሚሉት ያለፈውና ያሁኑ ምንም ግንኙነት ስለሌለው ነው። መለስ ለኢትዮጵያ ታሪክ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ንቀት ነበራቸው፤ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ንቀት ነበራቸው፤ ለተቃዋሚው ንቀት ነበራቸው፤ ለጋዜጠኞት ንቀት ነበራቸው፤ ለአስተማሪወች ንቀት ነበራቸው። ለራሳቸው ነገድ አድናቆት ነበራቸው። ሰድበው ለሰዳቬ አስተላልፈውናል፤ ሱዛን ራይስ ስትሰደበን፤ ከመለስ የተማረችውን መነሻ አድርጋ ነው፤ ፈጥራ አይደለም። በተለይ፤ ለተቃዋሚው ክፍል ያላትን ንቀት ነው ያቀረበችው። ከመለስ ባገኘችው ግንዛቬና ድምደማ መሰረት ነው የሚሉ ብዙ ታዛቢወች አሉ። እኔ የማሳስበው፤ ታዝበን ከወቀሳ፤ ወደ ኢትዮጵያዊ ለውጥ ማተኮር አለብን የሚል ነው። አለበለዚያ፤ ሙተውም መለስ እንደተፈለገው ከመቃብራቸው የእኛን አስተሳሰብ ይዳኙታል፤ ይገዙናል። እንደዚህ ከሆነ፤ ሁኔታው የሚያመልክተው የእኛን ደካማነት ነው። ማተኮር ያለብን ለወደፊቷ ኢትዮጵያ፤ ለወደፊቱ ትውልድ ነው። ኢትዮጵያዊያን የሚፈልጉት በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ፤ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን አገልጋይ የሆነ መንግስትና መሪ ነው። መጓዝም ያለብን በዚህ በኢትዮጵያዊነት መንገድ፤ ለመላው ኢትዮጵያዊያን አገልጋይ የሆነ ፍትሃዊ ስርአትን ለመገንባት ነው። ቀላል መንገድ አይደለም። የህወሓት/ኢህአዴግ ብዙ ዘርፍ ያለው አገዛዝ መለስ በማለፋቸው አልተለወጠም። በተለይ፤ የቁጥጥር ተቋማት። ቅድመ ሁኔታወች ተስተካክለው፤ ሁሉን የሚያካትት መንገድ ካልተቀየሰ፤ የአምባገነኑ ስርአት እንዳለ ይቆያል፤ አደጋው በዚያው ልክ ያይላል። አደጋው፤ ለህወሓት/ኢህአዴግም ጭምር ነው። ሰላምን የነሳ በሰላም ለመኖር አይችልም። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ይህን ይረዱታል ብየ እገምታለሁ።

ለዚህ ነው፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ አድናቂወች፤ ለኢትዮጵያ እርጋታ፤ ለመላው ሕዝቧ ሰላም፤ ከርሃብ አለንጋ፤ ከስደት፤ ከበሽታ፤ ከጠለላ ማጣት ወዘተ ነጻ መሆን ካሰቡ፤ የስርአቱን ደካማ ጎን ጭምር ማሳየት ይኖርባቸው የነበረው። ለማሳየትም የዲፕሎማቲክ ፕሮቶኮል ካልፈቀደ፣ አድናቆቱን ለዛ፤ ሚዛናዊና እውነተኛነት በተሞላበት፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ “አላዋቂ” በማያደርግበት መልክ ማቅረብ የነበረባቸው።

ተከታታዩ (ክፍል አስራ ሁለት) የአለም ጋዜጠኞች፤ የመንግስታት መሪወች፤ በተለይ፤ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ የተካሄደውንና አሁንም የሚካሄደውን ጫና፤ ግፍና አፈና ለምን አላዩትም፤ ተቃዋሚው ክፍልስ ለዚህ ምን ስትራተጅ አውጥቷል የሚለውን ይዳስሳል።

“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ያሉትን ከስራ ላይ እናውል (አክሎግ ቢራራ)

Wednesday, August 8th, 2012

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

አባቶች እናቶቻችን አያቶቻችን፤ በአጠቃላይ ወገኖቻችን፤ ለእኛ መኩሪያና መታወቂያ የሆነችውን ኢትዮጵያን ለእኛ ከተከታታይ አደጋ መክተው ያቆዩልን በብሄር፤ በሃይማኖት፤ በጾታ፤ በእድሜ፤ ወዘተ ተለያይተው ሳይሆን ለነጻነታቸው፤ ለክብራቸው፤ ለማንነታቸው በመተባበር ታግለው፤ ደማቸውን አፍሰው፤ ህይወታቸውን ሰውተው ነው። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ያሉትን ወርቃማ አባባል በተግባር አሳይተው የተውልንም ለዚህ ነው። ሆኖም፤ የቅርብ ታሪካችን የሚያሳየው የእኛ ትውልድ ለዚህ አባባል ብቁነት አላሳየም፤ አሁንም፤ አብዛኛው፤ በባህርይም ሆነ በአሰራር ገና ብቁነት ለማሳየት እንደ ኤሊ በመጎተት ላይ ነው ለማለት የሚያስገድዱ አመልካቾች አሉ። መመልከት ያለብን ግን ይህን የረጋ የመሰለ አሳሳች ምልክት አይደለም። ከስሩ የሚቭላላውን ከልብ የመሸፈት ምልክት ነው።

በቁጥር ስምንት እንዳሳየሁት፤ ዛሬ ለፍትህ-ርትህ የሚታገለው ተራው ሕዝብ፤ ተማሪው፤ አስተማሪው፤ ወጣቱ ትውልድ ነው። የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖት መሪወችና ተከታዮች በተከታታይ የሚያደርጉት ሰላማዊ ትግል ለዚህ ምልክት ነው። የፖለቲካ ድርጅቶችን፤ የህብረተሰብ ስብስቦችን ቀድመው ሂደዋል። በዚህ ሰላማዊ ትግል ውስጥ ወጣቱ ትውልድ አመልካች ሚና ይጫወታል። እነ አንዷለም አራጌ፤ እነ እስክንድር ነጋና ሌሎች በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ያለውን አፈናና ግፍ ተቋቁመው ለፍትህ፤ ለእውነተኛ እኩልነት፤ ለህግ-የበላይነት፤ ለመላው ሕዝብ ሉአላዊነት፤ ለሃገር አንድነት የሚያደርጉት ሰላማዊ ትግል የቆራጥነት ምልክት ነው። እንደ ተመስገን ደሳለኝ ያሉ ከፍርሃት ነጻ የሆኑ ጋዜጠኞች በአገር ቤት ሆነው ህወሓትን/እሃዴግን በማስረጃ ሲያጋልጡ ለግል ጥቅም ብሎው አይደለም። አፈና፤ ግፍ፤ የእስራት አደጋ፤ ወዘተ አልገታቸውም። እነዚህ አገርና ወገን ወዳዶች ለፍትሃዊ ለውጥ፤ ለወጣቱ ትውልድ፤ በውጭ በስደት ላለን፤ ራሳችን ዲያስፖራ ብለን ለምንጠራው ሁሉ አርአያ ናቸው።

የታመቀ ሃይል ታምቆ አይቀርም፤

የእነዚህ ወጣቶች ትግል የሚያጠነክረው ምልከት፤ የህወሓት አምባ-ገነንነት ዘላቂነት እንደማይኖረው ነው። ዛሬ ጥቂት የሚመስሉት ወጣት ታጋዮች፤ ነገ ብዙ ሚሊዮን እንደሚሆኑ አንጠራጠር። ሌላም ምልክት አለ። እነዚህ ወጣቶች የሚታገሉት ባየር ላይ አይደለም። የሚጋሯት አገር አለች። ይህች አገር ታሪክ ያላት መሆኑን ያውቃሉ። ኢትዮጵያ የሁላችንም መንፈስ ናት። መንፈስ እንደመሆኗ መጠን እነሱና እኛ ካልፈለግን አትጠፋም። እነሱ አትጠፋም ብለው ይታገላሉ፡፡ ቁጥራቸው ይነስ እንጅ በውጭም የእነዚህን አገር ወዳድ፤ ዲሞክራት ታጋዮች አስተሳሰብና እሴቶች የሚጋሩ በአለም ተሰራጭተዋል። በፖለቲካ ድርጅትም ሲታይ፤ አፈናና ግፍ ያገባቸው አገራዊ ድርጅቶች አሉ። በተደጋጋሚ ያሳሰብኩት፤ አሁንም በዚህ ትንተና የማሳስበው፤ ይህን የታመቀ ሃይል ሁሉ ካጎለመስነው፤ ከደገፍነው፤ ካበረታታነው፤ ህወሓት/ኢሃዴግ ሊያቅበው አይችልም።

አንዱን ሲበላው አይቶ ዝም ማለት አያዋጣም፤

ችግሩ፤ ከብሄር፤ ከሃይማኖት፤ ከፖለቲካ እምነት፤ ከጾታ፤ ከእድሜ፤ ከመደብ፤ ካለፈ ታሪክ፤ ከቡድን ባሻገር በማሰብ ተሳስቦ፤ ተባብሮ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የስልጣኑ ባለቤት የሚሆንበትን ብሩህ አቅጣጫ መንደፍና በአንድ ክንድ ከስራ ላይ ከማዋሉ ላይ የተከሰተው ድክመት ነው። ኦሮሞወች የሚሉት ዘላለማዊ ተረት በአርእስቱ ከተጠቀሰው አስተሳሰብ ጋር ተያይዞ ለትንተናየ አጋዥ ስለሆነ፤ አቀርበዋለሁ። “ነጭ፤ ቀይ፤ ጥቁር፤ ዳልቻ፤ ወርቃማ፤ የሆኑ በሬወች አንድ ላይ ሁነው ከጂብ (አውሬ) አደጋ ራሳቸውን ለመከላከል በጋራ ተስማመተው፤ አካላቸውን (ቂጣቸውን) አገጣጠመው፤ ፊታቸውን በያቅጣጫው አዙረው ጠላታቸውን ለመከላከል በመደጋገፍ ለመዋጋት ተስማሙ። አውሬው/ጅቡ ሊበላቸው ሲመጣ፤ በሁሉም አቅጣጫ ያሉት በሬወች ቀንዳቸውን ቀስረው አላስቀርበው አሉ።” ድር አበረ ማለት ይህ ነው።

ጅቡ የበሬወቹን የማይበገር ሰንሰለት በማየት ለመከፋፈል መላ መፍጠር መረጠ። እንዲህ ይላል። “እኔኮ ሌሎቻችሁን አልፈልግም። ነጩ በሬ ብቻ ጎልቶ እየታየኝ ለአይኔ ስላስቸገረኝ፤ እሱን ብቻ ነጥላችሁ አውጡ፤ እናንተን አልፈልጋችሁም” አላቸው። ሞኞች እውነት መስሏቸው ነጥለው ነጩን ያሰወጡታል። ነጩ በሬ የመጀመሪያው መስዋእት ይሆናል። ጅብ አሸነፈ። ይህን በሬ በልቶ ሲጨርስ፤ “ዳልቻው በሬም ከነጩ አይለይም፤ እርሱንም ነጥላችሁ አስወጡልኝ፤ ሌሎችን አልፈልግም” ብሎ ቃል ይገባል። ነጥለው አስወጡት፤ ጅብም ሁለተኛውን በሬ በላ። መጥገብን አያውቅምና ሌላ ለመብላት ተዘጋጀ። የወርቃማው ተራ ይመጣል። በለመደው ዘዴ “ወርቃማው ነጭ ስላለበት ለአይኔ አስቸግሮኛል። አስወጡት፤ ሌሎቻችሁ አታስቡ፤ አልፈልጋችሁም ይላቸዋል።” ደጋግመው የተሞኙት ካለፈው አልተማሩም። አሁንም ከመካከላቸው ወርቃማውን ያስወጣሉ። እንደዚህ ባለ ዘዴ እየለያየ ሁሉንም ጨረሳቸው ይባላል። የእኛም “የከፋፍለህ ግዛው፤ የከፋፍለህ ምታው”ታሪክ ይህን ይመስላል።

ህወሓት/ኢሃዴግ፤ እየመረጠ አማራውን፤ ኦሮሞውን፤ አፋሩን፤ ደቡቡን፤ አኟኩን፤ ትግራዩን፤ ክርስቲያኑን፤ እስላሙን፤ ወዘተ በየምክንያቱ ይገድለዋል፤ ያስረዋል፤ ያስድደዋል፤ ከቀዩ ያስወጣዋል፤ በሰላም ጎን ለጎን የሚኖርውን ሕዝብ እርስ በርሱ ያጣላዋል። በዚህ ሳምንት በቦረናና በጋሪ ህብረተሰቦች መካክል የተካሄደው፤ ለአስራ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ሞት ምክንያት የሆነው፤ የመሬት ይዞታ ግጭት የተፈጠረው ህወሓት በፈጠረው የመሬት ነጠቃና ሰፈራ ፖሊሲ ነው። ይህን የመሳሰሉ ግጭቶች በየአካባቢ ሲካሄዱ ቆይተዋል። መቀጠላቸው አይቀርም።

በኢትዮጵያ ላይ አሁን እየተፈጸመ ያለው “ነጣጥለህ ምታው፤ ነጣጥለህ እሰረው፤ ነጣጥለህ ግደለው፤ ነጣጥለህ አሳደው፤ ነጣጥለህ አክብረው”፤ የበሬወቹንና የጅቡን ተረት ይመስላል። የአገራችን ታሪክ፤ ጥንት የውጭ ጠላቶች (ጅቦች) ሲመጡ የተከተለውዘዴ ልዩነትን ወደ ጎን ትቶ መከታ መሆንን ነበር። ዛሬ፤ የምእራብ አገሮች፤ ቻይና፤ ለጋስ ድርጅቶች፤ ኢንቪስተሮችና ምርጥ የህወሓት ፓርቲ አባላት የኢትዮጱያን ጠንካራነት፤ የህዝቧን በሰላም የመኖር ፍላጎት፤ የወጣቱን ትውልድ ዘላቂነትና ተሳትፏዊ ያለው የእድገት ፍላጎት የማይሹ መሆናቸውን፤ እንዲያውም፤ ወደ ትንንሽ አገሮች በክልል ዙሪያ በመከፋፈል፤ ቀስ በቀስ እንድበታተን የማድረግ ምኞታቸውን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ፤ ህወሓት/ኢሃዴግ በሰላም አብሮ ተሳስቦ የሚኖረውን የክርስቲያንና የእስልምና ተከታይ ህብረተሰብ እርስ በእርሱ እንዲናከስ ሲያደርግ ቆይቷል፤ እየከፋፈለ ወገን በወገኑ ላይ ላይ እንዲነሳ አድርጓል። ይባስ ብሎ፤ ህወሓት የኢትዮጵያን ድሃ ገበሬ በመርዳት፤ አቅሙን በመገንባት ፋንታ፤ ለም መሬቱንና ወንዙን ለውጭ ሃብታሞች ሲነግድ ቆይታያል፡፡ የውጭ ከበርሬወችንና መንግስታትን አላማ አስፈጻሚ አገልጋይ ሆኖ ይገኛል። የዚህ አይነት በዳይ አገዛዝ በታሪካችን ያልታየ ነው።

“የመቶ አመት ታሪክ” ከየት መጣ?

አንባቢው ሊገነዘበው የሚገባ ከታሪካችን ከምንማራቸው አበይት ነገሮች መካከል አንድ ለማስታወሥ እፈለግላለሁ። ባለፈው እንዳመለከትኩት፤ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ፤ የአገራችን ታሪክ አሳጥረው ወደ መቶ አመት ሲለውጡት፤ አላማቸው ግልጽ ነበር። እሳቸው የሚያስቡት ለአጭር ጊዜ ስልጣንና ጥቅማቸው እንጂ፤ ለረጅሙ የአገራችን ጥቅም አለመሆኑን አይተናል። ሆኖም፤ የእርሳቸው ልብ ወለድ ታሪክ ሃቁን አያጠፋውም። ሃቁም፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያኮራ አስተዋጾ በማድረግ፤ አገራችን ከሶስት ሽህ አመታት በላይ እውቅና ሰጥቷታል። መለስ ዜናዊ በተወለዱበት በትግራይ የተደረገውን የጣሊያን ጦርነት፤ ማለትም፤ የአድዋን ድል፤ የሁለተኛውን የፋሽስት የበቀል ወረራ ማየቱ ይበቃቸው ነበር። አዶልፍ ፓርለሳክ የተባሉት የቸክ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ፤ “የሃበሻ ጀብዱ” በተባለው አስደናቂ የምስክር መጽሃፋቸው የመለስን ሃሳብ በለወጠው ነበር።፡ ኢትዮጵያዊያን “እምነትህ ፈረሰ፤ ደንበርህ ተጣሰ” በተባለ ቁጥር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖት፤ ብሄር፤ ጾታ፤ እድሜ ሳይለያቸው በጋራ፤ አገራቸውን ከጠላት ተከላክለው ለተከታታይ ትውልድ አስተላልፈዋል።

ይህን ሲያደርጉ፤ ኢትዮጵያ ከእራሷ ስብጥር ጀግኖች ውጭ ማንም ደርሶላት አያውቅም። ፓርልሳክ ስለ ጣሊያን አሰቃቂ ወረራ እንዳሉት፤ “ኢትዮጵያን ማንም አይረዳትም። ብቻዋን ናት። ….በደበረታቦር (ጎንደር) ብቸኛ አውሮፓዊ መሆኔ ሃዘን ተሰማኝ። ወዲያው ለዚች ለተቀደሰች ሃገር ከነዚህ ምስኪን የገበሬ ወታደሮች ጎን በታላቅ ድፍረትና ጀግንነት በእግዚአብሔር የሚታደሉት ታላቅ ጸጋ መሆኑን ስረዳ ልቤ በደስታ ተሞላች። ከዚህ ቅጽበት ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ሆኛለሁ።” ይህ ፈረንጅ ኢትዮጵያዊ ያደረጉት አስተዋጾ ለእያንዳንዳችን ምሳሌ እነደሚሆን እመኛለሁ። የአሁኑ ትውልድ የሚጠበቅበት ለሰላም፤ ለፍትህ፤ ለሕግ የበላይነት፤ አብሮ ተቻችሎ ድህነትን ለማስወገድ መቀራረብ፤ መቻቻል፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገሩ አዛዥ እንዲሆን ማድረግ ነው።

ከፓርልሳክ የምማረው፤ ዛሬም እንዳለፈው አገርም ውጭም ያሉ ወጣት ታጋዮችና ተቃዋሚወች ለፍትህ የሚታገሉት ማንም ይደርስልናል ብለው ሳይሆን፤ በኢትዮጵያ ህያውነትና መንፈስ ስለሚያምኑ፤ ለመላው የስብጥር (Diverse) ህዝቧ ፍትህ ፍላጎት እውን መሆን ድጋፍ ለመስጠት ስለሚፈልጉ ነው ለማለት ይቻላል። ፓርልሳክ እንዳሉት፤ አሁን ያለው ችግር ካለፈው ይበልጣል እንጂ አይቀልም። በአብዛኛው፤ መላው ሕዝብ የሚሰቃየው በራሱ ወገን ነው። መተባበር የሚያስፈልገው ችግሩ ከመቸውም የበለጠ ከባድ በመሆኑ፤ ብዙ የውስጥና የውጭ ተጠቃሚወች ስላሉ ጭምር ነው። ለጊዜው ሀወሓት/ እሃዴግ የሚረዳው፤ የገንዘብ፤ የመሳሪያና የሌላም ሃይል የሚያገኘው ከውጭና ከእያንዳዳችን ድጎማ ነው። ተቃዋሚ ክፍሎች በአንድ ላይ ከቆሙ፤ በአንድ ድምጽ ለመናገር ከቻሉ ቢያንስ፤ ሶስት ነገሮችን ለማድረግ ይችላሉ፤ አንደኛ፡ አገር ቤት ታፍኖ ላለው እምቅ ተቃዋሚ ብርታት ይሰጡታል፤ ሁለተኛ፤ የገንዘብ፤ የሞራል፤ የሃሳብ ድጋፍ ለመስጠት ይችላሉ፤ ሶስተኛ፤ በውጭ በአንድ ድምጽ የአለምን ህዝብ አስተሳሰብ የመለወጥ እድላቸው ይጠነክራል። መጀመሪይ፤ በስደት ላይ ያለው ህብረተሰብ መደራጀት፤ አብሮ መስራት፤ መተባበር አለበት። በግል/በተናጥል የሚያደርጉት የስልጣን ድርድር የትም አያደርስም። መሰባሰቡና አብሮ መስራቱ፤ ሌላው ስደተኛው በቀጥታም ሆነ በግልጽ ለህወሓት የሚሰጠው ድጋፍ ያቆማል፤ ቢያንስ ይቀንሳል። ተቃዋሚው ክፍል በአንድ ድምጽ ከተናገረ፤ ይህ ለሃያ አንድ አመታት ያገለገለ አገዛዝ መላላቱና መገርሰሱ አይቀርም። የውጭ አገር መንግስታት የተቃዋሚውን ክፍል ሃሳብ ማዳመጥ ይጀምራሉ። አሁን ያለውን ወርቃማ እድል ለመጠቀም ካልቻልን ሌላ ልንገነዘበው የሚገባን ጉዳይ አለ። ህወሓት የሃይል ምንጩን በእየጊዜው ይለዋውጣል።

የህወሓት የገቢ ምንጮች እየተቀየሩ ነው፤

ለምሳሌ፤ ህወሓት አሁን በብዙ ቢሊየን የሚገመት መዋእለንዋይ (investment) በውሃ ግድብ የሃይል ምንጭ ላይ (Hydroelectric Power generation) ፤ በቻይና ድጋፍ የሚያፈሰው ከምእራባዊያን ጥገኝነት ነጻ ለመሆን ነው። ኤሌክትሪክ ለጎረቤት አገሮች በመሽጥ በአመት ብዙ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያገኝ አያጠራጥርም። የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ አራት ጥቅሞች እንደሚኖሩት ከዚህ በፊት በማስረጀ አሳይቻለሁ–ገንዝብ ለማሸሽ፤ ትርፍ የሚያስገኙ ተቋሞችን ለመገንባት፤ የውጭ አገሮችን ድጋፍ ጭብጥ ለማድረግ፤ የገዥውን ፓርቲ የመከላከያ ሃይል ለማጠናከር። ይህ ከሆነ፤ የአበዳሪ ድርጅቶችና ለጋስ የምእራብ አገርች ሚና ይለወጣል ማለት ነው። ጫና የማድረግ ችሎታቸው የበለጠ ዝቅ ይላል። ሆኖም፤ ይህ ለውጥ ለተቃዋሚው ክፍል እድል ይከፍታል። እድሉን ለመጠቀም ከተፈለገ፤ ተቃዋሚ ፓርቲውች ከዘጠና በላይ ሆነው የትም አይደሱም። መሰብሰብ አለባቸው። ተቃዋሚወች፤ የለውጥ አሰፈላጊነት ከዚህ ህወሓት ከሚያደርገው፤ የአገርን ጥሬ ሃብት ተጠቅሞ ታማኞችን ከማክብር፤ የእራስን ደጋፊ ከማጠንከር፤ አምባ ገነንነትን ከማጠናከር ግብ ጋር አብረው ማየት አለባቸው። አለበት። አሁንም፤ ዋናው ተጠቃሚ፤ ማፍያ መሳዩ የህወሓት ምርጥ ቡድን ይሆናል። የመተባበር ሰንሰለት አሁን ካልተጀመረ እየቆየ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

የኦሮሞወች ተረት አንደሚያስተምረን፤ በእኛ (የተማርን ወገኖች ማለቴ ነው) የእራስ መውደድ የተነሳ፤ ህወሓት በመሳሪያ/ጠበንጃና በውጭ ድጋፍ ሃይል ስልጣን የያዘ፤ በእኛ መከፋፈል የበላይነትን ጭብጥ ባደረገው ህወሓት በተባለ የጠባብ ዘር ስያሜ በያዘ ድርጂት ፍጹማዊ ቡድን ነው። ቀርበን ብንመረምረው፤ ህወሓት መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀርቶ፤ የትግራይን ሕዝብ አይወክልም። እርግጥ ነው፤ ስልጣን ከያዘበት ወቅት ጀምሮ፤ ህወሓት፤ አድሏዊ በሆነ መንገድ፤ ከማንኛውም ክልል የበለጠ ባጀት ወደ ትግራይ አፍሷል። የትምርት፤ የጤና፤ የመንገድ፤ የሃይል ማመንጫ፤ የእርሻ፤ የእንዱስትሪ ተቋሞችንና የምርት ዘርፎችን ዘርግቷል። ራሱንና ጥቂት ተጠቃሚወችን አፍርቷል። በአብዛኛው ግን፤ ድሃው የትግራይ ህብረተሰብ፤ በተለይ ወጣቱ ከህወሓት/ኢሃዴግ ዘላቂነትና ፍትሃዊ ያለው ጥቅም አግኝቷል ለማለት አይቻልም። ተጠቃሚወቹ፤ የህወሓት የበላይ አዛዦች መሆናቸውን አመልካች ማስረጃወች አሉ። ሁለት ምሳሌወች። ተመስገን ደሳለኝ “የመለስ አምልኮ” በተባለው በማስረጃ የተደገፈ ጽሁፍ ላይ እንዳሳየው፤ “ማይጨው፤ ሽሬ፤ ሽራሮ፤ አድዋ፤ ተንቤን፤ አዲግራት፤ አክሱም፤ ውቅሮ፤ አዲሮቢ…ሂዱና” ቀርባችሁ መርምሩ። “ምናልባት ባለጸጋ የህወሓት አመራር ታገኙ እነደሆነ እንጂ አርሶ አደሩ እንደኔና እንደናንተ ነው” (እንደ ሌላው ድሃ ኢትዮጱያዊ ማለት ነው)። ቀጥሎም፤ “ የስልጣኔ መጀመሪያ የምትባለውን አክሱምን ተመልከቱ፤ የእነ ኢዛና፤ የእነ ካሌብ አገር….ኢትዮጵያ ነች። የፖለቲካና የንግድ ማእከል የነበርችውስ?” ህወሓት አንድ “ፋኖስ ዲተርጀንት ፋብሪካ የሚባል የሳሙና ፋብሪካ” ከመስራቱ ባሻገር ለአክሱም የድህነት መላቀቂያ ምን አመጣላት ይላል። አብዛኛው የአክሱም ወጣት ኑሮውን የሚያሟላበት ጥንት ከተሰሩት ከሃውልቶች የቱሪስቶች ገቢ ነው። የአክሱም “ብቸኛ ገቢ ቱሪዝም ነው.” ለዚህ ነው፤ ዋልድባን ሆነ፤ የአክሱምን ሃውልቶች፤ ወዘተ እንደ አገራዊ ቅርሶች ጠንቅቆ መያዝ አስፈለጊ የሚሆነው፡፡

የማን ልጅ ይማራል፤ የማን ልጅ ይሰደዳል?

ሁለተኛው ምሳሌ፤ የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣኖች በእቅድ የሚሰሩት የወጣቶች ማጎልመስ (educational investment in youth) ተግባር ሙሉ በሙሉ አድሏዊ ነው። ከተራው የትግራይ ወይንም ሌላድሃ ኢትዮጵያዊ ገበሬ ልጆች እድገትና የወደፊት እድል ሲታይ ቀጭ ነው ለማለት ያስደፍራል። ማን ተጠቃሚ ሆነ? የህወሓት የበላይ ባለስልጣኖች ልጆች ናቸው። ህወሓት የወደፊት መሪወችን፤ ሃብታሞችን፤ እያሰለጠነ ነው ለማለት ይቻላል። የስዮም መስፍንን ምሳሌ ተጠቅሞ “ይድረስ ለኢሃዴግ አመራር አባላት፤ ልጆቻችሁ ቻይና ምን እየሰሩ ነው?” በማለት ተመስገን ደሳለኝ “እናንተ የግንባሩ አባላትና ደጋፊወች! ለመሆኑ አብዛኞቹ የፓርቲያችሁ አመራሮች ምን እያሰቡ እንደሆነ ቀርቶ ምን እያደረጉ እንደሆነ ታውቃላችሁ? ለምሳሌ ስዮም መስፍን፤ ስብሓት ነጋ፤ አባይ ጸሓዪ፤ ክንፈ ገ/መድህን (በህይወት የሌሉ)፤ አርከበ እቁባይ፤ በረከት ሰምኦን፤ አዲሱ ለገሰ…ልጆቻቸው የት ናቸው?…..ካላወቃችሁ እኔ ልንገራችሁ፤ እነዚህ የባለስልጣኖች ልጆች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ፤ የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ከቅርብ አመታት ወዲህ “ወዳጅ” በሆነቻቸው ቻይና ይከታተሉ ዘንድ ተልከዋል….” ድሃው የትግራይና የሌላው ኢትዮጵያ ገበሬ ወይንም መካከለኛ መድብ የለት ጉርስ ለማግኘት ይቸገራል። እነዚህ ምርጥ ተጠቅመው ሲታዩ፤ ማንም ሊጠይቀን አይችልም ብሎው ነው።

ወጣቶች እውነት ወላጆቻቸው በራሳቸው ጥረት ባገኙት ገቢ ሳይሆን የሚደገፉት በኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ገቢ ነው። ጸሃፊው እንዳሳሰበው፤ “ እነዚህ ወላጆች ነጋዴ አይደሉም፤ ወይም ተራ ኢትዮጵያዊ አይደሉም። የሃገሪቱ ፈላጭ ቆራጮች እንጅ።” ልጆቻቸውን ምርጥ እድል የከፈቱላቸው “ፈላጭ ቆራጭነታቸውን” ተጠቅመው፤ ማንም ሊጠይቀን አይችልም ብሎው ነው። የስርአቱ አድሏዊ፤ በደላዊ፤ ዘራፊያዊ መሆን በዚህም ተከስቷል።

የእነዚህን ምርጥ ወጣቶች በድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወጭ በወዳጇ ቻይና ብዙ ሽህ ዶላር እየተከፈለ መማር ስናይ፤ የእነሱ መማር ለምስኪኑ የትግራይ፤ የጋምቤላ፤ የአፋር፤ የኦሮምያ፤ የሶማሌ፤ የጉራጌ፤ የአማራ ወዘተ ድሃ ገበሬ ልጅ፤ በብዙ ሽህ በየወሩ ለሚሰደደድው ወጣት፤ እንደ ተራ ሸቀጥ በእየቀኑ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሚላኩት እህቶቻችን ምን ፋይዳ አለው። የሚደጉመው የወደፊት ገዥወችን መሆኑን ለመጠራጠር አይቻልም። የህወሓት አገዛዝ፤ በተለይ ለድሃው የሚዘገንን የሚሆነው ለዚህም ጭምር ነው።

አፈጣጠሩን ስናይ፤ ልክ እንደ ጣሊያኖች የ “ከፋፍለህ ግዛውን” አገዛዝ አይነት- ለመግዛት፤ ለመማር፤ ሃብት ለመያዝ፤ አመቻች የሆነውን ዘዴ በመጠቀም መጀመሪያ፤ አንድ ብሄርን፤ “መኳንንት፤ መሳፍንት፤ ነፍጠኛ፤ ፌውዳል፤ አህያ፤ ኢሰፓ፤ አድሃሪ” እያለ ህብረተሰቡን ከከፋፈሉ በኋላ፤ በዘርና በቋንቋ–አማራ፤ ኦሮሞ፤ ትግሬ፤ ጉራጌ፤ ሶማሌ፤ አፋር፤ አገው፤ ደቡብ፤ አኟክ፤ ወዘተ እያለ፤ ለያየን። መለያየቱ የእኛ መጥፊያ መሳሪያ እየሆነ ነው። በቋንቋና በዘር፤ በሃይማኖትና በመደለል ሊለያየን የሚሞክረው እንደ በሬወቹና ጅቡ ተረት እያታለለ ሊገዛን፤ “ሊያጠፋን”፤ ሊያደክመን፤ ሊያሳድደን እንጅ ሊያጎለምሰን አይደለም። መከፋፈል ለሙስና፤ ለዘረፋ አመቻች ነው።

ምሳሌ ልስጥ። እኛ ከጋና የባሰ የብሄር/ብሄረሰብ ስርጭት የለንም። እንዲያውም፤ በትብብራችን የተነሳ፤ ሃገራችን ለጋና ሆነ ለመላው የጥቁር ህዝብ መኩሪያና አርአያ፤ የነጻነት አምባ ነበረች። ዛሬ፤ የጋና ህገ መንግስት በብሄር መደራጀትን ከከለከለ ቆይቷል። ጋና፤ የህዝብ ድምጽ የተከበረባት አገር እየሆነች ነው። ጥንታዊቷን ኢትዮጵያን ግን ወደ ኋላ የጎተቷት ህወሃትና መሰል በብሄር የተደራጁ የፖለቲካ መሪወች ናቸው። እነደ ኢትዮጵያዊ አብሮ መኖር፤ መታወቅ ዋጋ እዳይኖረው መደረጉ የዱሮ መታወቂያችንና መከበሪያችን፤ የዛሬ ሃፍረታችን ሆኗል። ስደታችን የዚህ ዋና ምስክር ነው።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ቋንቋችን፤ ቀለማችን፤ ሃይማኖታችን፤ አኗኗራችን ቢለያይም የማያለያዩን ብዙ እሴቶች አሉ። አገራችን የመጀመሬያው ሰው የተፈጠረባት አነደመሆኗ መጠን፤ የሁላችንም የሰው ግንድ አንድ ነው። ደምና አጥንቱ ቢመረመር ሰንሰለቱን ያሳያል። ማንም ኢትዮጵያዊ በአራት አያቱ ያለው የዘር ግንድ አመጣጡ ሲታይ ድብልቅ ነው። ድብልቅነታችን ክብራችን ነው። ባደግሁበት ጎንደር፤ የትግራይ፤ የኦሮሞ፤ የሰላሌ፤ የአገው፤ የጉራጌ፤ የየመን፤ የግብጽ፤ የጣሊያን፤ የአርመን፤ የግሪክ፤ የአይሁድ ወዘተ ተወላጆች ነበሩበት፤ አሁንም እንዳለኡበት አልጠራጠርም። ኢትዮጵያን የሚለያትም ይህ የህዝብ ስብጥር (Diversity) መሆኑን እኔ አልጠራርም። ይህ ስብጥር መኩሪያችን እንጂ መጥፊያችን ሊሆን አይችልም። Black Athena የተባለውን የምርምር ጽሁፍ ብቻ ማንበብ የማንለያይ መሆናችን ያመለክታል። በዘር የተርመሰረተ አስተዳደር የኢትዮጵያን ሕዝብ ከአንድ የሰው ግንድ መፈጠር አይፍቀውም። የህዝብ ቁጥር እያደገ መሄድ ሰንሰለቱን ሊያጠናክረው ይገባል እንጂ፤ ሊሰብረው አይችልም። ከፋፋዮች ቢፈልጉም አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪኩም፤ የወደፊት እድሉም የተሳሰረ መሆኑን ማጤን ለመላው ሕዝብ ጠቃሚ መሆኑን ደጋግሞ ማሳሰስብ ተገቢ ነው። እስካሁን ያሳየው ባህል፤ ጭቆናውና አድሎው መጥፎ ቢሆንም፤ እርስ በእስሩ በዘር ሳቢያ የማይገዳደለው አኩሪ መታወቂው መሆኑን ነው።

የህወሓት/ኢሃዴግ የአገዛዝ ስርአት ከፋፋይ ቢሆንም ያለው የዘር ግንድ ድብልቅ መሆኑ፤ (ማለትም፤ ከሁሉም የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪወች የተወለደና የተመዘዘ)፤ ለውጥ ቢመጣ የእርስ በእርስ መተላለቅ ይመጣል ብሎ መገመት አይቻልም። ሕዝቡ፤ በስር አቱና በስርጭቱ መካከል ያለውን ልዩነት ያውቃል። ሌላው ቀርቶ የኤርትራዊያንን የዘር ስርጭት ብንወስድ፤ አንድም “ንጹህ (ethnically pure) የሚል ለማግኘት ያስቸግራል። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በጻፏቸው ዘገባወች እንኳን፤ የሰራየ፤ የአካለጉዛይና የሃማሴን ህዝብ ከጎንደር የመጣ ነው ብለዋል። ም እራባዊ ቆላማው ምድር ኦሮሞወች ስፍረው የኖሩበት ስለሆነ የኦሮሞ ህብረተሰብ (ዘር) የተቆራኘ መሆኑን ያሳያል።

በአጠቃላይ፤

ይህ የሚያሳየው፤ የትም ብንሄድ፤ ማንኛውንም የዘር ክፍል ብናይ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃገሩን ለመጠበቅ በእየጊዜው “በጦር አበጋዞች” እየዘመተ በአራቱም ማእዘን ሲሰፍር የኖረ፤ እየተዋለደ፤ እየተዛመደ የተቀራረበ በመሆኑ ከሚለያየው ይልቅ የሚያቀራርበው ያይላል። በቋንቋ ወይንም በሃይማኖት ያለው ልዩነት፤ የሚጋራውን ኢትዮጵያዊነት ሊፍቀው የማይችለው ለዚህም ጭምር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ አመጣጡ አንድ መሆኑን ታሪክ ጸሃፊወች ብቻ ሳይሆን፤ መጽሃፍ ቅዱስ፤ ቁራን ደጋግመው በማስረጃ አቅርበውታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ህወሃት አዲስ አድርጎ በፈጠራ በሚጽፋቸው የሃሰት ታሪክና ፕሮፓጋንዳ መደለል የለበትም። መተሳሰቡ፤ መተሳሰሩ፤ አብሮ ለፍትህ፤ ለእውነተኛ እኩልነት፤ ለሃገር አንድነት፤ ለመላው ሕዝብ ሉአላዊነት መታገሉ ለመልካም አገዛዝ በር ይከፍታል። መከፋፈሉ ግን፤ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ታመው ቢቆዩም ባይቆዩም፤ በሌላ ቢተኩም ባይተኩም፤ የህወሓትን የበላይነት አይለወጥም።

የስርአቱ ተጠቃሚወች ጥቅማቸውን ትተው፤ ሊመጣ የሚችለውን የሃላፊነት ጥያቄ ወደ ጎን አድርገው፤ “ኑ፤ አዲስ የሽግግር መንግስት አብረን እንመስርት” አይሉም። የህወሓት የበላዮች፤ የውስጥ ቅራኔወቻቸውን አስወግደው፤ ተቻችለው ያለው አገዛዝ እንዲቀጥል የሚያደርጉ መሆናቸውን አልጠራጠርም። የውጭ መንግስታትም ቢሆን፤ ለራሳቸው ጠቃሚ የሆነ አማራጭ ካላዩ፤ በዘር የተከፋፈለውን የክልል ስርአት፤ በዘር የተመሰረተውን ሕገ መንግስትና አስተዳደር፤ በዘር የተመሰረተውን የስለላና የመከላከያ ተቋም፤ ለውጡ አይሉም። ማነን አይተው? በማን ተማምነው? ጥቅማቸው የሚገለገለው ባለው ወይንም በተመሳሳይ አገዛዝ ነው።

በዘር የተመሰረተው የከፋፍለህ ግዛው፤ የከፋፍለህ ምታው ዘዴ አይበቃ ብሎ፤ አሁን ደግሞ የአገራችን ሕዝብ በሃይማኖት እየበከሉት ነው። መጀመሪያ፤ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እንደፈለጉ አመሱ፤ ህገኛውን ሲኖድ አፈረሱ፤ የበላዮቹን አሳዳደዱ፤ በምትካቸው የፖለቲካ ካድሬወችን ሾሙ፤ የታወቁ ገዳሞችን ማፍረስ ጀመሩ፤ ዋልድባን እንረስ አሉ፤ የማይተኩ ቅርሶች እንዲፈርሱ፤ እንዲሰረቁ አደረጉ፤ ወዘተ። ልክ የበሬወቹንና የአውሬውን ተረት በሚመስል ሁኔታ፤ አሁን ደግሞ በእስልምና ሃይማኖት መሪወችና ተከታዮች ላይ በተከታታይ አስቃቂ አፈና፤ እስራት፤ ማሳደድ እየተካሄደ ነው። በሰላም የሚደረገው የእስልምና ሃይማኖት ሰላማዊ አመጽ (Peaceful Arab Spring type resistance) ከስምንት ወራት በላይ ሲካሄድ ቆይቷል፤ ሊቆም አይችልም። የእስልምና ሆነ የክርስቲያን መሪወችና ተከታዮች ጥያቄ የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ ነው፡፡ ስለሆነም፤ የሌሎች የፍትህ፤ የሰብአዊ መብቶች፤ የህግ የበላይነት፤ የሰላም፤ የመቻቻል ወዘተ ጥያቂወች ዘርፍ ነው። ተቃዋሚወች ሁሉ በየፊናቸውና በጋራ ሊድግፉት ይገባል፡፡የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖት መሪወችና ተከታዮች በመቀራረብ፤ በመተባበር፤ እየሰሩ መሆናቸው ለፍትህ፤ ለዲሞክራሲ፤ ለገር አንድነት፤ ወዘተ የሚደረገውን ትግል ወደ አዲስ ምራፍ እነዳሸጋገሩት ያመለክታል።

ለዚህ ሁሉ አገር ውስጥ ለሚንቀሳቅስና ታፍኖ ላለው የለውጥ ፈላጊ፤ የተሰደደው ግዙፍ ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራ) ምን አስተዋጾ ሊያደርግ ይችላል? በጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ማተኮሩን ከተወ፤ ከፈቀደ፤ ከቆረጠ፤ ከተሰበሰበ፤ አብሮ ከሰራ የገንዘብ፤ የእውቀት፤ የቴክኖሎጅ፤ የዲፕሎማ፤ ወዘተ ሃይሉ ሰፊ ነው። ይህን ሃይል ለሃገርና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትህ ሊጠቀም ይችላል። ሆኖም፤ አገር ቤት ያለውን ተስፋ የሚሰጥ ሁኔታ ለማጎልመስና ለመርዳት፤ በመጀመሪያ በስደት ያለው ግዙፍ ሃይል የበታተነውን ችግር ተቀብሎ፤ ራሱ መፍታት አለበት። ራሱን ማደራጀት፤ ማጎልመስ፤ አብሮ የመስራት፤ የመደጋገፍ፤ በአንድ ድምጽ የመናገር ባህሪና አሰራር ልምዶችን በተግባር ማሳየት ይኖርበታል። ባጭሩ፤ “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” የተባለውን ቅርስ በስራ ማሳየት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ይህን ካላደረገ፤ አገር ውስጥ ላለው ተንቀሳቃሽና እምቅ ሃይል የረባ አስተዋጾ ሊያደርግ አይችልም።

ይቀጥላል
July 30, 2012

የምግብ ዋስትና የኢትዮጵያዊያን መብት ነው

Saturday, June 23rd, 2012

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

በክፍል፡ አምስት፡ ህወሓት፡ ሙሉ፡ በሙሉ፡ የሚቆጣጠረው፡ መንግስት፡ እንዴት፡ አድርጎ፡ ተቋሞችን፡ ወገናዊ፡ እንዳደረገ፤ ሃቭትና፡ ጥሪት፡ ለእራሱና፡ ለደጋፊወቹ፡ እንደሚያካብት፤ የመከላከያ፤ የህግ፤ የውጭ፡ ግንኙነት፤ የጉምሩክ፤ የባንክ፤ የማዘጋጃ፡ ቤት፤ የአስተዳደር፤ የተፈጥሮ፡ ጥሪት፡ አጠቃቀም፤ የስራ፡ ፈቃድ፤ የትምህርት፡ ድርጅቶችን፡ በሙሉ፡ ፖለቲካዊ፤ ዘራዊ፤ እንዳደረገ፡ በማስረጃ፡ አሳይቻለሁ። እድገት፡ አለ፡ ቢባልም፤ የዚህ፡ አይነት፡ አድሏዊ፡ አገዛዝ፡ በምንም፡ መለኪያ፡ ዘላቂነትና፡ ፍትሃዊነት፡ ሊኖረው፡ አይችልም። አሁን፡ ኢትዮጵያ፡ ያለችበት፡ ሁኔታ፡ በልዩ፡ ልዩ፡ ዘርፍ፡ የችግሩን፡ክብደት፤ ስፋት፤ ያሳያል። መንግስት፡ ብቻውን፡ ችግሩን፡ ሊፈታው፡ አይችልም። ህወሓት፡ ያልተገነዝቨውና፡ ሊገነዘቭው፡ የማይፈቅደው፡ አገራዊ፡ ችግሮች፡ ሊፈቱ፡ የሚችሉት፡ ሌሎችን፡ በማቀቭ፤ በማሳደድ፤ በማሰር፤ በመግደል፤ አያገቫችሁም፡ በማለት፡ አይደለም። ችግሮች፡ ሊፈቱ፡ የሚችሉት፡ በአገራዊ፡ አሰራር፡ ስርአት፤ በመላው፡ ህዝብ፡ ተሳትፎ፤ ድምጽ፤ መብት፤ እኩልነት፡ ነው። የስር አቱን፡ ፖሊሲ፡ በመለወጥ፡ ብቻ፡ ነው። የምግብ፡ ዋስትናን፡ ጥያቄ፡ ምሳሌ፡ አድርገን፡ እንይ።

የምግብ፡ ዋስትና፤ ያለ፡ ኢትዮጵያውያን፡ ተሳትፎ፡ አይገኝም፤

በዋሽንግቶንና፡ በካምፕ፡ ዴቪድ፤ በዚህ፡ ሳምንት፡ ደግሞ፡ በሜክሲኯ፡ የተደረጉት፡ የG-8ና፡ የG-20 ስብስብ፡ ያልተገነዘበው፡ የህወሓትን፡ የመጥፎ፡ አገዛዝ፡ ሃቅ፡ ነው። የህዝብን፡ መብቶች፡ የገፈፈ፤ የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመንቀሳቀስ፤ የመምረጥ/መመረጥ፤ ወዘተ፡ መብቶችን፡ ማቀብ፡ ስልቱ፡ የሆነ፡ መሪ፡ ለተራቨ፤ ስራ፡ ላጣ፤ ለሚሰደድ፤ ለሚዋረድ፤ ደንታ፡ የለውም። የዘር፡ ክፍፍልና፡ ጽዳት፤ መሳሪያ፡ የሆነውን፡ የክልል፡ ስር አት፡ ዘላቂነት፡ ለመስጠት፡ የሚሞክረው፡ ለቁጥጥር፡ እንዲያመች፡ነው። የገጠሩን፡ አምራች፡ የሚቆጣጠረው፡ ለማጎልመስ፡ ሳይሆን፤ ስልጣንን፡ ለማቆየት፡ ነው።

የመገናኛ፡ ብዙሃን፡ ቁልፍ፡ የሚሆነው፡ እዚህ፡ ላይ፡ ነው። ህዝብ፡ ለህዝብ፡ እንዲገናኝ፡ ከተፈለገ፡ መገናኛ፡ ብዙሃን፡ሚና፡መጫወት፡ አለበት። እውነቱን፤ በደሉን፤ ሙስናውን፤ አድሎውን፤ ያወቀ፡ ህዝብ፡ ለመብቱ፡ ይታገላል። ማን፡ እንደሚጎዳው፤ ማን፡ እንደሚረዳው፡ ያውቃል። በነጻነት፡ የሚያገለግል፡ የዜና፡ ስርጭት፡ ለመብት፤ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለእውቀት፤ ለመደጋገፍ፤ ለእድገት፤ ለህዝብ፡ አመጽ፤ ለገበያ፡ ስፋት፤ ለድፍረት፡ ቁልፍ፡ነው። በሰሜን፡ አፍሪካ፡ የተካሄደው፡ የህዝብ፡ አመጽና፡ ለውጥ፡ ያለዜና፡ ስርጭት፡ ግብ፡ አይደርስም፡ ነበር። የግብጽ፡ ህዝብ፡ ለመጀመሪያ፡ ጊዜ፡ መሪውን፡ ያለ፡ ተጽኖ፡ ለመምረጥ፡ የቻለው፡ የህዝብ፡ አመጽ፡ ውጤት፡ ነው። ውጤቱ፡ እውን፡ የሆነው፡ በመገናኛ፡ ብዙሃን፡ አጠቃቀም፤ በህዝ፡ ሰንሰለትና፡ አብሮ፡ መነሳት፡ ስልት፡ ጭምር፡ ነው። እኛ፡ ኢትይጵያዊያንም፡ ልምዱ፡ አለን። የጎደለን፡ ድፍረቱ፡ ይመስላል። ለዚህም፡ ነው፤ መለስና፡ ግብረአበሮቻቸው፡ መገናኛ፡ ብዙሃን፡ የሚፈሩት፤ በሙሉ፤ የዘጉት። እነ፡ እስክንድር፡ ነጋ፤ እነ፡ አንዱ አለም፡ አራጌና፡ ሌሎች፡ ነጻ፡ ጋዜጠኞችን፡ እስር፡ ቤት፡ የታጎሩት፤ ሌሎችም፡ ከሃገር፡ እዲወጡ፡ የተገደዱት፡ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለህዝብ፡ ድምጽ፤ ለእውነተኛ፡ ሰላም፡ ስለቆሙ፡ እንጂ፤ ወንጀለኛ፡ ስለሆኑ፡ አይደለም። ሀወሓት፤ ሌላው፡ ቀርቶ፡ በውጭ፡ የምንገኘውን፡ ሁሉ፡ ለማበርከክ፡ ይሞክራል። አንዳንዶቻችን፡ ለፍረሃት፡ ተገዥ፡ የሆነው፡ ለዚህ፡ ነው። ፍርሃቱ፡ በምንም፡ አያዋጣም።

በልቶ፤ ሰርቶ፡ ለማደር፡ ነጻነት፡ ወሳኝ፡ ነው፤

የህዝብ፡ ተሳትፎ፡ የሌለበት፡ እድገት፡ በምንም፡ ፍትሃዊ፡ ሊሆን፡ አይችልም። የ G-8፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ ስብሰባ፡ የተካሄደው፡ እንደዚህ፡ ባለ፡ ሁኔታ፡ ነው። በአሜሪካ፡ የሚገኙ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ይህን፡ አጋጣሚ፡ በመጠቀም፡ እ.አ፡ አ፡ በተከታታይ፡ May 14, 2012 ሁዋይት፡ ሃውስ፡ ሕንጻ፡ ፊት፡ ለፊት፤ ከዚያም፡ በህንድ፡ ኤምባሲ፡ ፊት፡ ለፊት ፤ የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ የሚያኮራ፤ ሁሉም፡ ለመብቱ፤ ለነጻነቱ፤ ለአንድ፡ አገር፤ በአንድ፡ ድምጽ፡ የሚነሳበትን፡ መፈክሮች፡ አንግቮ፡ አጋርና፡ ጠቨቃ፡ ለሌለው፡ ህዝብ፡ ሲሟገት፡ ዉሏል። በ May 18, 2012, ከጥዋቱ፡ ሰቫት፡ ሰአት፡ ተኩል፡ ጀምሮ፡ በሬገን፡ ህንጻ፡ የተካሂደው፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ የኢትዮጵያን፡ ስብጥር፡ ህዝብ፡ ያንጸባረቀ፤ በወጣቶች፡ የተመራ፤ የተቀነባበረ፡ መልእክት፡ ያስተላለፈ፡ ነበር፡ ለማለት፡ እችላለሁ። ከውጭ፡ ያለው፡ ድምጹን፡ ለፕሬዝደንት፡ ኦባማ፤ ለአሜሪካ፡ ህዝብ፤ ለተጠሩ፡ እንግዶች፡አሰማ። አዳራሹ፡ ውስጥ፡ ደግሞ፤ የታወቀው፡ ጋዜጠኛ፤ አቶ፡ አበበ፡ ገላው፡ ታሪክ፡ የመዘገበው፤ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ያከበረው፤ የአሁንና፡ የወደፊት፡ ትውልድ፡ ምሳሌ፡ የሚያደርገው፤ ለፍትህ-ርትእ፡ የቆሙ፡ ሁሉ፡ “አገራችን፡ ሰው፡ አላት” ብለው፡ ሊነሳሱብት፡የሚያስችል፡ መልእክት፡ አስተላለፈ። ቀረብ፡ ብሎ፡ ለሰማው፡ በአዳራሹ፡ ያለው፡ ሁሉ፡ አይኑና፡ ሃሳቡ፡ በሙሉ፤ ከተናጋሪው፡ ላይ፡ ነበር። “መለስ፡ ዜናዊ፡ አምባገነን፡ ነው። እስክንድር፡ ነጋ፡ ይፈታ። የፖለቲካ፡ እስረኞች፡ ይፈቱ። ምግቭ፡ ያለ፡ ነጻነት፡ ዋጋ፡ የለውም። መለስ፡ ሰላማዊ፡ ህዝብ፡ በመግደል፡ ወንጀል፡ ፈጽሟል፡ (ወንጀለኛ፡ ነው)። እኛ፡ የምንፈልገው፡ ነጻነት፤ ነው። ነጻነት፤ ነጻነት፤ ነጻነት.” ጸጥ፡ ብሎ፡ ያዳመጠው፡ ሁሉ፡ በአድናቆት፡ ተቀብሎታል፡ ለማለት፡ እደፍራለሁ። ፕረዝደንት፡ ኦባማ፡ “አመስግናለሁ” ብለው፡ ሲሸኙት፡ ምን፡ ያስቡ፡ እንደነበር፡ ከስራቸው፡ ሲወጡ፡ መግለጻቸው፡ አይቀርም። ለህሊናቸው፡ ምግብ፡ አግኝተዋል።

ሰብእነትን፡ ሲገፉ፤ የእራሳቸውን፡ ብሄረሰቭ፡ “እንቁ፤” አማራውን፡ “ጭራቅ”፡ ብለው፡ የሚሳደቩት፤ ተቃዋሚወቻቸውን፡ ሁሉ፡ የሚያዋርዱት፤ ግለሰቦችን፡ ባልሰሩት፡ ወንጀል፡ ይቅርታ፡ ጠይቁ፡ ብለው፡ እንዲምበረክኩ፡ የሚያስገድዱት፤ ጠቅላይ፡ ሚንስትር፡ መለስ፡ ካሉበት፡ መቀመጫ፡ ሰምጠው፤ ራሳቸውን፤ ወደታች፡ ሲቀረቅሩ፡ የተቀረጸው፡ ሰእል፡ የውርደቱን፡ ክብደትና፡ ቆይነት፡ አሳይቷል። መልክቱ፤ አንድ፡ ግለሰብን፡ በመጥላት፤ በይፋ፡ ማዋረዱ፡ አይመስለኝም። መልክቱ፡ “ነጻነት፤ መብት፤ ፍትህ፤ የህግ፡ የበላይነት፤ እኩልነት፤ የመላው፡ ህዝብ፡ ድምጽና፤ተሳትፎ፡ ይከበር” የሚል፡ ነው። መልክቱ፤ “የአንድ፡ ጠባብ፡ ብሄርተኛ፡ ጠቅላይ፡ ሚኒስትር፡ መሆነወን፡ ያቁሙ፤ መላውን፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ያለ፡ አድሎ፡ ያገልግሉ፤ አድሎወትን፡ ያቁሙ፤ አገራችን፤ “ዘርፎ፡ ለዘራፊ፡ አይዳርጓት” ወዘተ፡ የሚል፡ ነው። ማንም፡ ኢትዮጵያዊ፡ ቢሆን፡ ለኣገሩ፤ ለመላው፡ ህብረተሰብ፤ የቆመን፡ መሪ፡ አያዋርድም። ይህ፡ ቢሆን፡ ውርደቱ፡ ለሁሉም፡ ይሆን፡ ነበር። ጠቅላይ፡ ሚንስትሩ፡ ህወሓትና፡ መንግስቱ፡ “የእነሱ፡ ፓርቲ፤ የእነሱ፡ መንግስት” ተብሎ፡ እንደሜጠራ፡ ያውቃሉ። አብዛኛው፡ ህዝብ፡ ህወሓትንና፡ የሚመራውን፡ መንግስት፡ “የእኔ፡ ፓርቲ፤ የእኔ፡ መንግስት” ናቸው፡ ብሎ፡ አለመቀበሉን፡ ጋሎፕ፡ፓል፡ በማስረጃ፡ አቅርቦታል።

የጠቅላይ፡ ሚንስትሩ፡ በመሪወች፡ ፊት፡ እነደዚህ፡ መጋለጥ፤ መዋረድ (humiliation): የህይወት፡ ሙሉ፡ ለምጽ፡ መሆኑ፡አያጠራጥርም። ይህን፡ ሁኔታ፡ የፈጠሩት፡ እራሳቸው፤ ፓርቲያቸው፤ ደጋፊወቻቸው፤ እንጂ፤ ሌላ፡ ሰው፡ አይደለም። የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ “ጉድ”፡ አልፎም፡ “እሰይ” ማለቱ፡ አልቀረም። በሰአት፡ ወደ፡ ኢትዮጵያ፡የተላለፈው፡ ቪዲዮ፡ ብዙ፡መቶ፡ ሽህ፡ ህዝብ፡ በሞባይል፡ እየተቀባበለ፡ አሰራጭቶቷል። አሁንም፡ እያነጋገረበት፡ ነው። ሲጠቀስ፡ ይኖራል።

ከዚያ፡ ባሻገር፤ ቁም፡ ነገሩ፤ አበበ፡ ገላው፤ እንደ፡ አብዛኞቻችን፡ “ምሁራን”፡ በፍርሃት፡ አልተጠመደም። ለግል፡ ጥቅም፡ አልተገዛም። ታሪካችንና፡ ባህላችን፡ የሚያስተምረን፡ ፍርሃትን፡ ሳይሆን፡ ድፍረትን፤ መከፋፈልን፡ ሳይሆን፡ አብሮ፡ መኖርን፤ እ ራስ፡ ወዳድነትን፡ ሳይሆን፡ አገርን፡ ማስቀደም፤ ነው። ደፍረን፡ መነሳት፡ የነጻነት፡ መለኪያችን፡ ነው። አብዣⶉቻቺን፡ ከእነዚህ፤ መለስ፡ ዜናዊና፡ ታማኝ፡ ቡድናቸው፡ ካዘጋጁልን፡ የፍርሃት፡ ወጥመድ፡ ነጥቀን፡ ብንወጣ፡ ኢያትዮጵያ፡ እንደ፡ ግብጽ፤ እንደ፡ ሊቢያ፤ እነደ፡ ቱኒሲያ፡ ተሳትፏዊ፡ ለውጥን፡ ትቀዳጃለች። ጋዜጠኛው፡ ለአንድ፡ ብሄረሰብ፤ ለአንድ፡ ቡደን፤ ለአንድ፡ ሃይማኖት፡ አልተናገረም። የተናገረው፡ ለኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ በሙሉ፡ ነው። ያሳየን፤ የነጻነት፤ የፍትህ፤ ጥቅም፡ በሳንቲም፡ የሚታሰብ፡ አለመሆኑን፡ ጭምር፡ ነው። ነጻነት፤ በቤት፤ በመሬት፤ በገንዘብ፡ ድጎማ፤ የማይለወጥ፡ መሆኑን፡ ነው። ነጻነት፡ የሌለው፡ ሰው፡ በ እራሱ፡ አይተማመንም። ይፈራል።ይገረፋል፤ ይሰደዳል። በሆዱ፤ ለሆዱ፡ ይገዛል። ለሰብ አዊ፡ መብት፤ ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለሰው፡ ክብር፡ መታገል፡ በዶላር፡ ሊተመን፡ አይችልም። ነጻነት፡ ካለ፡ ያለ፡ አድሎ፡ ለመስራት፤ ለመፍጠር፤ ለመንቀሳቅስ፤ ሃብት፡ ለማግኘት፤ ለመምረጥ፤ ባለ፡ ስልጣኖችን፡ “ሃላፊ፡ ናችሁ፤ አገልጋይ፡ ናችሁ፡” ለማለት፡ ይቻላል። ጠባብ፡ ብሄርተኞችን፤ ሌቦችን፤ ሙስኞችን፤ የንጹህ፡ ደም፡ አፍሳሾችን፤ ለም፡ መሬት፤ ሴቶች፤ ህጻናት፡ እንደ፡ ተራ፡ ሸቀጥ፡ ቸርቻሪወችን፡ በህግ፡ ለመሟገት፤ ደፍሮ፡ ለማጋለጥ፤ ይቻላል።

ለህግ፡ የበላይነት፤ ለፍትህ፤ ለሃገር፤ ለድሃው፡ ህዝብ፤ የቆመ፡ አገር፡ ወዳድ፡ መሪ፡ እንደ፡ ጠቅላይ፡ ሚንስትር፡ መለስ፡ “የመንግስት፡ ሌቦች፡ አሉ። በውጭ፡ ሁለት፡ ቢሊየን፡ ዶላር፡ ያስቀመጡ፡ መኖራቸውን፡ እናውቃለን።” ብዙ፡ ሽህ፡ ቶን፡ ቡና፡ ሲሰረቅ፡ “ማን፡ አንደሰረቀ፤ እናውቃለን። የእኛው፡ እጂ፡ ስላለበት፡ አንከታተለውም” ለማለት፡ አይችልም፤ ህሊናው፡ አይፈቅድም። ከህግ፡ በላይ፡ ነኝ፡ የሚል፡ መሪ፡ ብቻ፡ ነው፡ አይቶ፡ አላየሁም፡ የሚል። ስለሆነም፤ ችግሩን፡ የፈጠረው፡ የህወሓት፡ አገዛዝ፡ ነው። ተጠቃሚው፡ እራሱና፡ ታማኞቹ፡ ናቸው። ሙስናን፡ ስናይ፡ የቻይና፡ ጠበብት፡ አንዳሉት፡ “አሳ፡ የሚገማው፡ ከእራሱ፡ ነው.” የሚለው፡ ለህወሓት፡ አዛዦች፡ አግባብ፡፡አለው። የህወሓት፡ ስር አት፡ የገማው፡ ከቁንጮው፡ ነው።” ጠቅላይ፡ ሚንስትሩ፡ ይህን፡ አያውቁም፡ ብሎ፡ መናገር፡ ቂልነት፡ ነው። የመለስ፡ መንግስት፡ ለፍርድ፡ የሚያቀርበው፡ ዝቅተኛ፡ በሙሰኝነት፡ ተከሳቾን፡ እንጂ፡ “ለገማው፡ ስርአት፡ ተጠያቂ፡ መሆን፡ የሚገባቸውን፡ የመንግስት፤ የፓርቲ፤ ሌቦች፤ የበላይ፡ ባለስልጣኖች፡ አይደለም። ወደ፡ ቤተሰብ፡ ስለሚመራ።

አበበ፡ ገላው፡ ታሪክ፡ በሰራበት፡ ሳምንት፤ May 19, 2012፤ በካምፕ፡ ዴቪድ፤ ከምርጫ፡ ዘጠና፡ ሰባት፡ ወዲህ፡ አስደናቂ፡ የሆነ፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ ተካሂዷል። የሚዲያ፡ ሽፋኑ፡ ከዚህ፡ በፊት፡ ታይቶ፡ የማያውቅ፡ መሆኑን፡ አይቻለሁ። የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ ሰቆቃ፡ ፈረንጆች፡ እንደመዘገቡት፤ “በብዙ፡ መቶ”፤ እኔ፡ እንዳየሁት፤ ከሽህ፡ በላይ፤ የልዩ፡ ልዩ፡ ሃይማኖት፤ የፖለቲካ፤ የማህበራዊ፡ ስብሰብ፤ የወጣትና፡ የሴቶች፡ ተወካዮች፡ ድምቅት፡ ባለው፡ ሑኔታ፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ አካሂደዋል። የሰበሰባቸው፡ አበይት፡ጉዳይ፡ የመለስ፡ ዜናዊ፡ ህወሓት፡ አሰቃቂ፡ ስርአት፡ ነው። ያያዛቸው፡ አበይት፡ ጉዳይ፡ ነጻነት፤ ፍትህ፤ የህግ፡ የበላይነት፤ ሰብአዊ፡ መብት፤ የሰው፡ ክብር፡ ወዘተ፡ መናድ፡ ናቸው። ኢትዮጵያዊያንና፡ ደጋፊወች፡ በደመቀ፡ ሁኔታ፡ ለፍትህ፤ ለነጻነት፡ ሲታገሉ፤ የአሜሪካ፡ ፕሬዝደንት፤ ኦባማ፤ ለ G-8፤ ስለ፡ ምግብ፡ ዋስትና፡ ያቀረቡትን፡ ሃሳብና፡ እቅድ፡ ማጤን፡ አስፈላጊ፡ ነው። በ May 18, 21012: ስብሰባ፡ ላይ፡ እንዲህ፡ አሉ። “ተከታታይ፡ እርሃብ፡ ኢ-ፍትሃዊ፡ ነው። መንግስታት፡ ሁሉ፤ እርሃብን፡ ማጥፋት፡ ተቀዳሚ፡ ተግባራቸው፡ መሆን፡ አለበት። የምግብ፡ ዋስትናን፡ ጭብጥ፡ ማድረግ፡ የጥበባዊ፡ እድገት፡ አመራር፡ መለኪያ፡ ነው። ሰው፡ ክብሩን፡ የሚጎናጸፈው፡ በእርዳታ፡ ሲኖር፡ አይደልም። እራሱን፡ ሲችል፡ ብቻ፡ ነው። ሰውን፡ በምግብ፡ ለመደጎም፡ የምናደርገው፡ እርዳታ፡ ዘላቂ፡ መልስ፡ ሊሆን፡ አይችልም።” ፕሬዝደንቱ፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፤ ምሁራን፤ የእድገት፡ ባለሙያወች፤ ተቋሞች፡ ሲሉት፡ የቆየውን፡ በመቀበላቸው፤ የአሜሪካ፡ የእርዳታ፡ አመራር፡ የተለወጠ፡ ይመስላል። ድጋፉ፡ ትንንሽ፡ ገበሬወችን፤ ድሃውን፤ የአገር፡ ከበርቴውን፡ ለማጎልመስ፡ ይመስላል። እኔ፡ ግን፡ በጀርባ፡ ያለውን፡ አላማና፡ እቅድ፡ እጠራጠራለሁ። የምጠራጠረው፡ የኢትዮጵያን፡ ታናናሽ፡ ገበሬወች፤ የአገራችን፡ ከበርቴወች፡ በዘመናዊ፡ እርሻ፡ ተሳትፎ፡ ለማጠናከር፡ አመራሩ፤ መንግስቱ፡ ከአድሏዊነት፤ ወደ፡ ኢትዮጵያዊነት፡ መለወጥ፡ ይኖርበታል። ኢትዮጵያዊያን፡ የአገራቸው፡ የተፈጥሮ፡ ሃቨት፡ አዛዦች፡ መሆን፡ አለባቸው። መብት፤ ነጻነት፤ ተሳትፎ፡ ከታገደ፡ ኢትዮጵያዊ፡ ተሳትፎ፤ ዘላቂነትና፡ ፍትሃዊ፡ እድገት፡ ሊኖር፡ አይችልም።

ምክንያቱም፤ ከአጼ፡ ሓይለ፡ ስላሴ፡ መንግስት፡ ጀምሮ፤ በተለይ፡ በመለስ፡ መንግስት፤ የአሜሪካ፡ ሰብአዊ፡ ርዳታ፡ ከአስር፡ እስከ፡ አስራ፡ ሶስት፡ ሚሊዮን፡ የሚሆኑ፡ ኢትዮጵያዊያንን፡ በምግብ፡ ድጎማ፡ እንዳይሞቱ፡ ማድረግ፡ ነው። ይህ፡ የጥገኝነት፡ መለኪያ፡ ነው። ታዲያ፤ እስካሁን፡ አመራሩ፡ (Policy) ለምን፡ አልተለወጠም፡ ብሎ፡ መጠየቅ፡ ተገቢ፡ የሚሆነው፡ ለዚህ፡ ነው። ኢትዮጵያ፡ በምግብ፡ እራሷን፡ ከመቻል፡ አልፋ፡ ወደ፡ ውጭ፡ ለመላክ፡ እንደምትችል፡ ማሰረጃወች፡ አሉ። የመሬት፡ ነጠቃንና፡ ቅርሚትን፡ ማየት፡ ብቻ፡ ይበቃል። ድሃው፡ ህዝብ፡ የእድገቱ፡ አጋር፡ ካልሆነ፤ በአመራርና፡ በተግባር፡ ተሳታፌ፡ ካልሆነ፤ ድምጹ፡ ካልተሰማ፤ ነጻነቱና፡ መብቱ፡ ካልተከበረ፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ ሊኖረው፡ አይችልም። የአሜሪካው፡ መሪ፡ ይህን፡ ያውቁታል። ተሳትፎ፡ ከሌለ፡ ፍትህ፡ ሊኖር፡ አይችልም። ዘላቂነት፡ ያለው፡ እድገት፡ ሊኖር፡ አይችልም። ፍትሃዊ፡ እድገት፡ (equitable development)፤ ከአምባ፡ ገነን፡ ስርአት፡ ጋር፡ አብሮ፡ አይሄድም። መለስ፡ ዜናዊ፡ አምባ፡ ገነን፤ በህግ፡ የበላይነት፡ የማያምኑ፡ ከሆኑ፡ (መሆናቸው፡ አያጠራጥርም)፡ መጀመሪያ፤ የፖለቲካው፡ ስርአት፡ መፈታት፡ አለበት፡ ማለት፡ ነው። ፖሊሲና፡ መዋቅሩ፡ ከስር አቱ፡ ጋር፡ የተያያዙ፡ ስለሆነ፡ የመንግስት፡ አመራር፡ ችግር፡ ካልተፈታ፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ ሊገኝ፡ አይችልም። ይህን፤ ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ አልነኩትም፤ ሊነኩትም፡ አይችሉም። መለስ፡ ዜናዊ፡ የአሜሪካን፡ ጥቅም፡እስክ፡ ጠበቁ፡ ድረስ፡ የክብር፡ እንግዳ፡ መሆናቸው፡ይቀጥላል። ሜክሲኮ፡ የተገኙት፡ በዚህ፡ ምክንያት፡ ነው።

ይህን፡ መግቢያ፡ ከሰጡ፡ በኋላ፤ ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ አዲስ፡ እቅድ፡ አለ፡ ያሉት፤ ኢትዮጵያን፤ ጋናን፤ ታንዛንያን፤ ያቀፈ፡ “A New Agriculture Alliance)፡ የእነዚህን፡ አገሮች፡ ጦም፡ አደር፡ አምሳ፡ ሚሊዮን፡ ህዝብ፡ እራሱን፡ ማስቻል፡ የሚል፡ ነው። ለዚህ፡ አላማ፡ ሃብታም፡ አገሮች፡ ሶስት፡ ቢሊዮን፡ ዶላር፡ ወጭ፡ ያደርጋሉ። “ዘላቂነት፡ እንዲኖረው፡ መንግስታት፤ ለጋሽ፡ ድርጅቶች፤ አርባ-አምስት፡ የሚሆኑ፡ የግል፡ ባለ፡ ሃቭቶች፤ ተቋሞች፤ የአካባቪ፡ ስብስቦች፤ ይሳተፉበታል። ከአላማው፡ ላይ፡ ብንስማማም፡ በቤን፡ ሻንጉል፡ ጉሙዝ፤ በደቡብ፤ በአማራ፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ በአፋር፤ በኦሮሚያ፡ በኦሞ፡ ሸለቆ፤ ያሉ፡ የህብረተሰብ፡ ክፍሎች፡ ለጥቅማቸው፡ የቆመ፡ አጋር፡ መንግስት፡ ያስፈልጋቸዋል፡ ማለት፡ ነው። አሁን፤ የላቸውም። አቅማቸው፡ ካልተገነባ፡ (empowerment and engagement): ለጥቅማቸው፡ መቆም፡ ያስቸግራቸዋል። የመንግስት፤ የክልል፤ የአካባቢ፡ ተቋሞች፡ ለቁጥጥር፡ የተሰሩ፡ እንጂ፡ ለአቅም፡ ግንባታ፡ የተመሰረቱ፡ አይደሉም። እውቀቱ፤ መሳሪያው፤ ገንዘቡ፡ ያለው፡ ከግል፡ ባለ፡ ሃብቶች፤ ከውጭ፡ መንግስታት፤ ከአበዳሪወች፡ ጋር፡ እንጂ፡ ከህዝቡ፡ ጋር፡ አይደለም። አቅም፡ ካልተገነባ፤ ዘላቅነትና፡ ፍትሃዊ፡ የሆነ፡ እድገት፡ አሁንም፡ እውን፡ አይሆንም። ለም፡ መሬቱ፤ ለሃብታሞች፤ የምግብ፡ ዋስትናው፤ ለእነሱ፤ የውጭ፡ ምንዛሬው፡ ለህወሓት፡ ይሆናል፡ ማለት፡ ነው። ዋጋ፡ ከፋዩ፡ የአካባቢው፡ ህዝብ፤ የኢትዮጵያ፡ ሸማች፤ ኢትዮጵያ፡ ይሆናሉ፡ ማለት፡ ነው። አዲሱ፡ ውል፡ ከጥቅሙ፡ ጉዳቱ፡ ሊያመዝን፡ ይችላል፡ ለማለት፡ የምደፍረው፡ ውሎች፡ ለገበሬወች፤ ለኢትዮጵያ፡ ሸማቾች፤ ለአገር፡ ከበርቴወች፡ አያመዝኑም፡ በሚል፡ ነው። ነዋሪው፡ ህዝብ፡ በእራሱ፡ ለም፡ መሬትና፡ ወንዝ፡ አዛዥ፡ አይደለም፤ አይሆንም። ጠበቃ፡ የሚሆኑት፤ ማህበራዊ፡ ድርጅቶች፤ ከመንግስት፡ ቁጥጥር፡ ነጻ፡ የሆኑ፡ መገናኛ፡ ብዙሃን፡ ስለሌሉ፡ ለድሃው፡ ህዝብ፡ ጠበቃ፡ አይኖረውም። ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ ባንግላደሽ፤ ሃይቲ፡ የዝቅተኛ፡ አምራቾች፡ ውጤት፡ እጥፍ፡ አድጓል፡ ያሉት፡ ትክክል፡ ነው። በቬትናምም፡ እንደዚሁ። ነገር፡ ግን፡ እነዚህ፡ አገሮች፡ በን ኡስ፡ ብሄርተኛ፡ ቡድን፡ አይመሩም። በባንግላደሽ፡ ዘመናዊ፡ የመገናኛ፡ ስርጭት፡ አለም፡ ያደነቀው፡ ነው። በኢትዮጵያ፤ ህወሓት፡ መገናኛ፡ ብዙሃንን፡ ለመቆጣጠሪያ፤ ለማጥፋት፡ እንጂ፡ ለማጎልመሻ፡ አይፈቅድም። ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ የኢትዮጵያን፡ ድሃ፤ ዝቅተኛ፡ አምራች (smallholder): ለማጎልመስ፡ ከፈለጉ፡ መለስ፡ ዜናዊ፡ መገናኛ፡ ብዙሃንን፡ ነጻ፡ እንዲያደርጉ፡ መማጸን፤ የመሬት፡ ይዞታ፡ እንዲሻሻል፡መምከር፤ እርዳታ፡ ሁሉ፡ ለአቅም፡ ግንባታ፡ እንዲውል፡ ማድረግ፡ አለባቸው። ካልሆነ፤ ከስባዊ፡ አገልግሎት፡ ውጭ፡ እርዳታ፡ እንዳይስጥ፤ መሞከር፡ ወቅታዊ፡ ነው። እርድታ፡ ጎጂ፡ መሆን፡ የለበትም።

አለበለዚያ፤ ኢትዮጵያ፡ ያለ ውጭ፡ ድጋፍ፡ ሕዝቧን፡ ልትመግብ፡ አትችልም። መጋቪ፡ ግን፡ ለመሆን፡ ትችላለች። እንደ፡ ገና፡ ለማሣሰብ፡ የምፈለገው፤ በቅርቡ፡ ጠቅላይ፡ ሚንስተር፡ መለስ፡ ከታወቁት፡ ሃብታምና፡ ለጋስ፡ ቢል፡ ጌትስ፡ ጋር፡ ስለ፡ ዝቅተኛ፡ 15 ሚሊዮን፡ የኢትዮጵያ፡ አምራቾች፡ አቅም፡ የማጎልመስ፡ ጉዳይ፡ የተነጋገሩትና፡ የእርሻ፡ ምርትን፡ ለማሳደግ፡ የተዋዋሉት፤ ሃያ፡ አንድ፡ አመት፡ ሙሉ፡ ሊፈቱት፡ ያልቻሉትን፤ አሁን፡ ደግሞ፤ ካሩቱሪና፡ ሳውዲ፡ ስታር፡ ሊያሟሉት፡ የማይችሉትን፤ በእርሻ፡ ልማት፡ ላይ፡ የተመሰረተ፡ ልማት፡ ውጤት፡ አለማስገኘቱ፡ የምግብ፡ ዋስትና፡ በውጭ፡ ኢንቬሰተሮች፡ ይገኛል፡ ብሎ፡ አዲስ፡ መንገድ፡ የመሻት፡ዘዴ፡ ብቻ፡ ነው። ቢል፡ ጌትስ፡ በቀጥታ፡ አምራቹን፡ ካጎለመሱ፡ ውጤት፡ ይገኛል። በሰፋፊ፡ የንግድ፡ እርሻ፡ ላይ፡ የተሰማሩት፡ የውጭና፡ የውስጥ፡ ተጠቃሚወች፤ የገዡ፡ ቡድን፤ ምርጥ፡ የትግራይ፡ አዲስ፡ ሃብታሞች፤ በግብዣ፡ የመጡ፡ ትርፍ፡ ፈላጊ፡ የውጭ፡ አገሮች፡ የፓርቲው፡ አባል፡ግለሰቦችና፡ መንግስታት፡ ርሃብን፡ ሊያስወግዱ፡ የማይችሉ፡ መሆናቸውን፡ አንጠራጠር። የሚሰሩት፡ ለትርፍ፡ የሚያመርቱት፡ ለውጭ፡ ገቨያ፡ ነው። Guardian, Human Rights Watch, Suvival International, Friends of the Earth, Oakland Institute የደረሱበት፡ ዘገቫ፤ ድምዳሜ፡ ይህ፡ ነው።

እነዚሃና፡ ሌሎች፡ እንዳሳዩት፤ ሁሉም፡ የተሰማሩት፡ ለትርፍ፡ እንጂ፡ ድህነትና፡ ርሃብን፡ ለማስወገድ፡ አይደለም። የመሬት፡ ነጠቃና፡ ቅርሚት፡ ጉዳት፡ በሁሉም፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ላይ፡ እነደሚሆን፡ ብዙ፡ ምርምሮች፡ ያሳያሉ። የመንግስትና፡ የግል፡ ትብብር፡ ችግሩን፡ ሊያስወግደው፡ አይችልም። መንግስት፡ የችግሩ፡ አካል፡ ስለሆነ። የውጭ፡ ሃብታሞች፡ ሚና፡ የፖሊሲና፡ መዋቅራዊ፡ ማነቆወችን፤ መለወጥ፡ አይችልም። ለአለም፡ ገቨያ፡ የምግቭ፡ ዋስትና፡ ማግኘት፤ ትርፍ፡ ማካቨት፡ ነው። ለዚህ፡ ነው፡ ፖሊሲው፡ መለወጥ፡ ያለበት። ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ ይህን፡ ዋጋ፡ አልሰጡትም። በአጭሩ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ በራሳቸው፡ አገርና፡ በራሳቸው፡ የተፈጥሮ፡ ሃብት፡ ላይ፡ አዛዥነታቸው፡ ማክተሙ፡ ለአገራችን፡ ነጻነት፤ አንድነት፤ ለሕቧ፡ ሉአላዊነት፡ አደገኛ፡ ነው። ይህን፡ አንቆ፡ የያዘ፡ የአገዛዝ፡ ስር አት፤ ለመለወጥ፡ የሚችለው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ እንጂ፡ የሃያል፡ መንግስታት፡ ከመለስ፡ ጋር፡ ድርድር፡ አይደለም። እኛ፡ ለማድረግ፡ የምንችለው፡ ድምጽ፡ ማሰማት፤ የመለስ፡ መንግስት፡ ፖሊሲውን፡ እዲለወጥ፡ ማጋለጥ። ካልለወጠ፡ ለአለም፡ፍርድ፡ ማቅረብ። ችግሩ፡ የገባቸውን፡ የአሜሪካ፡ ምክር፡ ቤት፡ አባላት፡ ጠበቃ፡ እንዲሆኑ፡ ቀርቦ፡ ማነጋገር፤ አብሮ፡ መስራት፡ ወዘተ፤ ናቸው።

ፕሬዝደንት፡ ኦባማ፡ በቅርብ፡ አንድ፡ አለም፡ አቀፍ፡ ተቋም፡ ሰለ፡ ኢትዮጵያ፤ የተፈጥሮ፡ ሃቭት፡ አጠቃቅም፡ ያቀረበውን፡ ዘገባ፡ ያዩት፡ አይመስልም። “በአሁኑ፡ ወቅት፡ ከኢትዮጵያውያን፡ ይልቅ፡ የውጭ፡ ባለሃብቶች፡ እና ባለስልጣኖች፡ የበለጠ ሃይልና፡ ስልጣን፡ አላችው፡” የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ በሃገሩ፡ ምንም፡ ሃይልና፡ ዽምጽ፡ የለውም። ተሳትፎ፡ የለውም። ይህ፡ ስርአቱ፡ ያመጣው፡ ማነቆ፡ ነው። የውጭ፡ አገር፡ ባለሃብቶችና፡ ጥቂት፡ የህወሓት፡ ታማኞች፡ የኢትይጵያን፡ የእድገት፡ መሰረቶች፡ ቢይዙ፤ ስርአቱን ስለሚረዳው፡ የገዡ፡ ፓርቲ፡ አለቆች፡ ኢትዮጵያዊያን፡ በራሳችው፡ አገር፡ ቢናቁ፤ ቢያፍሩ፤ ቢሳደዱ፤ ታዛዥና፡ አጎብዳጂ፡ ቢሆኑ፤ እህቶቻችን፡ በአረብ፡ አገሮች፡ ቢዋረዱ፤ ቢራቡ፤ ምንም አይሰማቸውም። ስር አቱን፡ ስለሚጠቅም። ለዚህ፡ ነው፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ከድህነት፤ ከርሃብ፤ ከጥገኝነት፡ ሊያወጣት፡ የሚችል፡ ስር አት፡ አይደለም፡ ለማለት፡ የሚቻለው። የለም፡ የእርሻ፡ ሃብት፡ እና ወንዝ፣ ማእድን፡ እና የኢኮኖሚ አውታሮች፡ ቀስ በቀስ፡ ከአገርና፡ ከኢትዮጵያዊያን፡ እጂ፡ ወደ ፈረንጆች፡ እና፡ ጥቂት፡ የትግራይ ምርጥ፡ ተወላጆች፡ ሲተላለፉ፡ ዝም፡ ብለን፡ ማየት፡ በታሪክ፡ ያስጠይቃል፡ ለማለት፡ የምደፍረው። ሃብት፤ ጥሪት፤ ተሳትፎ፤ የመወስን፡ እድል፡ የሌለው፡ ሕዝብ፤ ድሃ ነው። በሃገሩ፡ ሊኮራ፡ አይችልም። ስለማያዝብት። ከገንዘብ፡ ድህነት፡ የባሰ፡ የመንፈስ፡ ድህነቱ፡ ያጠቃዋል። 76 በመቶ፡ የሆነው፡ የተማረ፡ ክፍል፤ ልሰደድ፤ ይሻለኛል፡ የሚለው፡ አገሩን፡ ጠልቶ፡ ሳይሆን፡ በሃገሩ፡ ሰርቶ፤ ኮርቶ፤ ተከብሮ፡ ለመኖር፡ ስለማይችል፡ ብቻ፡ ነው።

ስደት፡ እጣችን፡ ሆኗል። የአብዛኛው፡ ወጣት፡ ትውልድ፡ ድህ፡ ሁኖ፡ የመቆየት፡ እድሉ፡ ከፍ፡ እያለ፡ እንጂ፡ እየቀነሰ፡ የሚሂየድ፡ አይመስልም። ድህ፡ ሕዝብ፡ መከታ፡ የለውም፡፡ በሰላም፡ ተኝቶ፡ አያድርም። ሆዱ፡ ሞልቶ፡ አያድርም። መብቱን፡ ለማስከበር፡ አቅም፡ አይኖረውም። ህወሃት፡ ለም፡ የተፈጥሮ፡ ሃብት፤ ዉሃ፤ ማእድን፡ ፋብሪካ፡ ከኢትዮጵያዊያን፡ እና፡ ከአገር፡ ወደ፡ እራሱ፡ ተቋሞችና፡ ወደ፡ ደጋፊዎች፤ ወደ፡ ውጭ፡ ባለ፡ ሃብቶች፡ ሲያዘዘዋውር፡ የሚስራውን፡ ያውቃል። ይህ የሃብት፡ ዝውውር፡ ድጋፍን፡ ከኢንቭስተሮች፡ ያመጣለታል። ገንዝቭ፡ እንደልብ፡ ለማሸሽ፡ ያመቻል። ይህን፡ እንደ፡ ድል፡ ይቆጥረዋል። ቁጥጥርና፡ ዝውውር፡ ጣምራዊ፡ ናቸው፤ ይደጋገፋሉ። ከገንዘብ ጥቅሙ፡ ያላነሰ፡ የዲፕሎማሲ፡ ጥቅሙ፡ ከፍ፡ ያለ፡ ነው።

ወደ፡ ውስጥም፡ ብናይ፡ ይህ፡ ስርአትት፡ በራሱ ብቻ፡ የሚሺከረከር፡ አይደለም። ብዙ፡ ደጋፊወችን፡ በጥቅም፤ በጉቦ፤ በማስፈራራት፡ ያቀፈ፡ ነው። ስለዚህ፡ ስርአቱን፤ ከግለሰብ፡ ባሻገር፤ በሙሉ፡ ማየት፡ ይገባል። ተጠቃሚወችን፡ ባይሰበስብ፡ ኖሮ፡ እስክ፡ አሁን፡ ባልቆየም ነበር፡፡ በየቦታው፤ በየሕብረተሰቡ፡ ለእርሱ፡ አገልጋይና፡ አጎብዳጅ፡ የሆኑ፡ ደጋፊወችንና፡ እዝ፡ አስፈጻሚወችን፡ በጥቅም በመሳብ፤ በመደለል፤ በማስፈራራት፡ ወዘተ፤ ሰፋ፡ ያለ፡ ድርጂታዊ፡ አቅም፡ አለው። ሖኖም፤ በግብጽ፤ በሊብያ፤ በቱኒሲያ፤ በየመን፤ አሁን፡ በሶሪያ፡ እንደምናየው፡ በጥቅምና፡ በማስፈራራት፡ የተደራጀ፤ በጎሳ፤ በጠባብ፡ ቡድን፡ የተበከለ፡ ድርጂት፡ “የእምቧይ፡ ካብ፡” ነው። ሕዝብ፡ ከተነሳ፡ በቀላሉ፡ ይናዳል። ይህን፡ በመከፋፈል፡ የተዘረጋ፡ ስልት፡ እራሱ፡ የፈጠረው፡ ነው፡ ለማለት፡ አይቻልም። ከበፊቶቹ፡ የቀዳው፡ መጥፎ፡ ልምድ፡ አለ። በንጉሱ፡ ሆነ፡ በደርግ፡ ዘመናት፡ ከሁሉም፡ የህብረተስብ፡ ክፍሎች፡ የተመለመሉ፡ የስርአት፡ አገልጋዮች ነበሩ። በእነዚህ፡ ስራቶች፡ በደል፡ እና፡ አድሎ፡ አልነበረም ፡ ማለት፡ አይቻልም።

የአሁኑን፡ስርአት፡ የሚለየው፡ ዋናው፡ መለኪያ፡ መነሻው፤ ሂደቱ፡ እና፡ አሰራሩ፡ ሁሉ በዘር፤ ለዘር መሆኑ፤ ለጥቂት፡ ቡደን፡ መሆኑ፡ ነው። የዘር፡ ስርአት፡ አደጋ፡ ሁለ፡ ዘርፍ፤ ሁለ፡ ገብ፡ መሆኑን፡ እናያለን። ይህን፡ ለማድረግ፡ እየመረጠ፡ አለሁልህ፤ ይላል። ‘ድጋፍ፡ ከሰጠህ፡ ትበላለህ፤ ትኖራለህ፤ ትሰራልህ፤ ትማራለህ፤ መሬት፡ ትመራለህ፤ አላስርህም፤ አልገድልህም፤ ካልሰጠህ፡ ወዮልህ’፡ የሚል፡ ነው።የሰውን፡ ስነልቦና፡ ገምቶ፡ “ለከፋፍለህ ግዛው፤ ለፍርሃት፡ ዳርጎናል።

መገንዘቭ፡ የሚገባን፤ ተባባሪነት፤ አብሮ፡ ለአንድ፡ አገራዊ፤ በህዝብ፡ የበላይነት፡ ሊመሰረት፡ የሚገባ፡ ዲሞክራሳዊ፡ አላማ፡ መቆምን፤ ሃይማኖት፤ ጾታ፤ እድሜ፤ ጥቃቅን፤ የዱሮ፡ ታሪክ፡ ልዩነት፡ ሊገታው፡ አይችልም። ለነጻነት፤ ለእኩለነት፤ ለህግ፡ የበላይነት፤ ለፍትህ፡ ለኢትዮጵያ፡ አንድነት፤ ለመላው፡ ህዝቧ፡ ሉአላዊይነት፡ ከቆምን፤ ከህዝብ፡ ጎን፡ ከተሰለፍን፡ ምንም፡ የሚያግደን፡ ሃይል፡ አይኖርም። የሚያግደን፡ ህወሓት፡ ላጠመደልን፡ ማነቆ፤ በተለይ፤ ለፍርሃት፡ አጎብዳጅና፡ ተገዥ፡ መሆናችን፡ ነው። የሚያግደን፡ ለመሰብሰብ፤ ለመደጋገፍ፤ አብሮ፡ ለመስራት፤ ሃይላችን፤ ገንዘባችን፤ እውቀታችን፤ ወዘተ፡ ለአንድ፡ አገራዊ፤ አላማ፡ ለማዋል፡ ፈቃደኛነት፡ ማጣት፤ አገር፡ ሳይኖር፤ ለስልጣን፤ ለግል፡ ዝና፤ ለቡደን፡ መገዛት፡ ጭምር፡ ናቸው። ይህ፡ ባህል፤ አስተሳሰብ፡ መለወጥ፡ አለበት።

ለጎሳዊ ስነ-ልቦና አናጎብድድ (አክሎግ ቢራራ)

Friday, May 11th, 2012

የታሪክ ተጠያቂዎች ሁነናል (ክፍል ሶስት)
PLF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አክሎግ፡ ቢራራ (ዶር)

ይህ፡ በተከታታይ፡ የማቀርበው፡ ሁለ-አቀፍ፡ ትንተና፡ ሶስተኛ፡ ክፍል፤ ካለፉት፡ ሁለት፡ ትንተናወች፡ ለየት፡ ይላል። የሚለይበትም፡ ዋና፡ ምክንያት፤ ባለፉት፡ እንዳስቀመጥኩት፤ የህወሃት፡ ጠባብ፡ ብሄርተኛ፡ ቡድን፡ ፍልስፍና፡ መሰረት፡ መነሻው፡ ባለፉት፡ መቶ፡ አመታት፡ የአማራ፡ ብሄር፡ ህብረተሰብ፡ “ጨቋኝ፤ ነብሰ-ገዳይ፤ ነፍጠኛ፤ የተጠላ፤ ዘራፊ፤ ቅኝ-ገዥ”፤ በሚሉ፡ በመርዝ፡ የተቀባ፡ የዘር፡ መለያ፡የስነ-ልቦና፡ ጦርነት፡ ማካሄዱና፡ በተለይ፡ አብዛኛውን፡ ሃሁ፡ የቆጠረውን፡ ክፍል፤ በዚህ፡ መሰረት፡ በሌለው፡ ክስ፡ተስቦና፡ ተበክሎ፤ እራሱን፡ እንዲጠራጠር፤ በእራሱ፡ እንዳይተማመን፤ ማንነቱን፡ እንዲከዳ፤ በአጎብዳጅነት፡ እንዲኖር፤ ፈሪና፡ አሞት፡ የሌለው፡ እንዲሆን፤ እርስ፡ በእርሱ፡እንዲከፋፈል፡ ማድረጉ፡ ከባድ፡ ሸክም፡ ሆኖ፡ ቆይቷል። ይህን፡ ሸክም፡ ማስወገድ፡ ያለብን፡ እኛ፡ እንጂ፡ህብረተሰባዊ፡ ምሰሷችን፡(the pillars of community and affinity)፤ ታጥቆ፤ እያናጋው፡ ያለ፤ ህወሃትና፡ደጋፊወቹ፡ ሊሆኑ፡ አይችልም።

የህወሃት፡ ፈጣሪወች፤ ህዝብን፡ ከህዝብ፡ ጋር፤ ሃይማኖትን፡ ከሃይማኖት፡ጋር፡ ካላጋጩ፤ ሰውን፡ለጥቅም፡ ፍላጎት፡ ካልሳቩ፤ ተቃዋሚ፡ የሆነውን፡ ካላሳደዱ/ካላሰሩና፡ ሁሉ፡በፍርሃት፡ በእራሱ፡ ላይ፡ ያለውን፡ እምነት፡ ካላስካዱ፤ በስልጣን፡ እንደማይቆዩ፤ ለጠባብ፡ አዲስ፡ “ከኪራይ-የሚገኝ፡ ሃብት፡ ፈላጊወች (new rent-seekers)፤ ጋር፡ በጥቅም፡ ተደጋግፈው፡ ሃብት፡ እነደማያካብቱ፡ያውቁታል። ጽንሰ-ሃሳቡን፡ ከውጭ፡ ቀድተው፡ ስራ፡ላይ፡ ያዋሉት፡ የበላዮች፤ የአማራ፡ ህብረተሰብእ፡ ለትግራይ፡ ብሄረሰብ፡ “አጥፊና፡ አቆርቋዥ” መሆኑን፡ ቀስ፤ በቀስና፡ በዘዴ፤ እኛንና፡ ሌሎችን፡ አሳምነው፡ የፖለቲካ፤ የባህል፤ የኢኮኖሚ፤ ወዘተ፡ ስልጣንና፡ አቅም፡ ከአማራውና፡ ከሌሎች፡ ነጥቀው፡ ወደ፡ ትግራይ፡ ጠባብ፡ ቡድን፡ በዘዴ፡ ማሸጋገሩን፡ በተናጥል፤ ማለትም፤ ከእኛ፡ ባህርይና፡ አሰራር፡ ለይተን፡ መመልከት፡ አንችልም፡ እላለሁ። ምክኒያቱም፤ ውሸት፡ በህወሃት፡ ተደጋግሞ፡ ከተነገረ፡ እውነት፤ እውነት፡ ይሸታል። ይህን፡ ውሸት፡ ህወሃትና፡ ደጋፊወቹ፡ ብቻ፡ ሊያሰራጩት፡ አይችሉም። ለምሳሌ፤ ሌላውን፡ ለማሳመን፡ የተቀነባበረ፡ ፕሮፓጋንዳ፡ ደጋግመው፡ ማስተጋባት፡ አለባቸው። የኢትዮጵያ፡ ምጣኔ፡ ሃብት፤ በድርብ፡ አያደገ፡ ፍትሃዊ፡ ውጤት፡ አሳይቷል፡ የሚለውን፡ እንይ።

በዚህ፡ ሳምንት፡ በአሜሪካ፡ ድምጽ፡ ሬዲዮ፡ ተጋብዠ፡ ከአንድ፡ በ ኢትዮጲያ፡ ከሚኖሩ፡ ባለሙያ፡ ጋር፡ “ፍትሃዊ፡ እድገት፡(equitable growth) አለ፡ ብለው፤ በአንድ፡ የአለም፡ አቀፍ፡ ስብሰባ፡ ላይ፤ ጠቅላይ፡ ሚኒስትር፡ መለስ፡ ስለተናገሩት፡ ያደረግነውን፡ ክርክር፡ ለአንባቢ፡ አቀርባለሁ። እኒህ፡ ባለሙያ፤ ጠቅላይ፡ ሚኒስትሩን፡ ደግፈው፡ የኢትዮጵያ፡ በአመት፤ አስራ፡ አንድ፡ በመቶ፡ እድገት፡ ያሳየው፡ እኮኖሚ፡ (ምጣኔ፡ ሃብት)፤ “ፍትሃዊ” መሆኑ፡ የሚታየው፡ “የገጠሩ፡ሰማንያ፡ አምስት፡ በመቶ፡ የሚሆነው፡ ገበሬ፡ ሕዝብ” በአገራችን፡ “ያልታየ፡ የኑሮ፡ መሻሻልን፡አስመስክሯል፤ ይህን፡ ባይናችን፡ እያየነው፡ ነው፡” ያሉት፡ ነው። ተናጋሪው፡ ይህን፡ ማቅረባቸው፡ አላስገረመኝም፤ ስርአቱን፡ ከደገፉ፡ ተጻራሪ፡ ሃሳብ፡ ለማቅረብ፡ አይችሉም። መብታቸውን፡ አከብራለሁ። እኔ፡ የማየው፤ ከአብዛኛው፡ ድሃ፡ ህዝብ፡ ድህነት፤ በምግብ-የዋጋ፡ ግፍሸት፡ ከሚሰቃየው፡ ኢትዮጵያዊ፤ በ፡ 2012 “የህጻናት፡ መድህን፡ (Save the Children)፤ ባወጣው፡ “ከ20 አገሮች፡ ኢትዮጵያ፡ አስራ-ሰባተኛ፡ በመሆን፡ ለህጻናት፡ ሲኦል፡ ናት፡” ከሚለው፡ አንንጻር፡ ነው። ለተወሰኑማ፡ ዛሬ፡ ኢትዮጵያ፡ ገነት፡ መሆኗ፡ ምንም፡ አያጠያይቅም። ያስደነቀኝ፡ እንደዚህ፡ ያለ፡ተራ፡የፈጠራ፡ ወሬ፡ በኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ላይ፡ ሲካኄድ፡ ሌሎቻችን፡ (አብዛኛወቻችን፡ ማለቴ፡ ነው)፤ በያለንበት፡ አለማስተባበላችን፡ ነው። እንዲያውም፤ ከእውነት፡ የራቀ፡ አነጋገር፡ በተደጋጋሚ፡ እየተነገረ፡ ብዙወቻችን፡ “በሬ፡ ወለደ” የሚሰኘው፡ የእድገት፡ መጠን፡ እውነት፡ ይመስለናል። ማንኛውም፡ በሃቅ፡ የቀረቨ፡ ዘገቫ፡ የሚያሳየው፤ እንኳን፡ ፍትሃዊ፡ እድገት፡ ሊኖር፤ ምስኪንነት፤ ድህነት፤ እርሃብ፤ የሰውና፤ የገንዘቭ”፤ ፍልሰት፤ (destitution, poverty, hunger, human and financial capital flight): በተባባሰ፡ ህኔታ፡ ስፋትና፡ ጥልቀት፡ እያሳዩ፡ ነው። በቅርቡ፤ ቢል፡ ጌተስ፡ እንዳሉት፡ “በድህነትና፡ እርሃብ፡ የተነሳ፤ አብዛኛው፡የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ከአለም፡ አገሮች፡ በበለጠ፡ ደረጃ፤ የምግብ፡ እርዳታ፡ የሚያስፈሊጋት፡ አገር፡ ውስጥ፡ ይኖራል.” እድገት፡ ፍትሃዊ፡ ለመሆን፡ የሚችለው፡ ጥቂት፡ ሃብታሞች፡ ሚሊየነር፤ ቢሊየነር፡ ስለሆኑ፡ ሳይሆን፡ አብዛኛው፡ የኢትዮጵያ፡ ድሃ፡ ሕዝብ፡ የእድገቱ፡ ተካፋይ፡ ሲሆን፡ ነው። የነፍ፡ ወከፍ፡ እያደገ፡ ስሄድ፡ ነው። የዚህም፡ መለኪያ፡ ቢያንስ፤ አንድ፡ ዜጋ፤ በቀን፡ ሶስት፡ ምግብ፡ በልቶ፡ ሲያድር፤ ልጁን፡ ሲያስተምር፤ ጤናው፡ ሲጠበቅ፤ የተሻለ፡ መጠለያ፡ሲኖረው፤ ንጹህ፡ ውሃ፡ ለመጠጣት፡ ሲችል፡ የተማረው፡ ልጁ፡ ያለ፡ አድሎ፡ ስራ፡ ለመያዝ፡ ሲችል/ስትችል፤ ወጣቶች፡ በአገራቸው፡ እድል፡ ሲኖራቸው፡ ወዘተ፡ ነው።

ሰለሆነም፤ ከጠቅላይ፡ ሚንስትሩና፡ ከታዛዦቻቸው፡ ውጭ፡ እድገት፡ “ፍትያዊ፡ ለመሆኑ፡ምንም፡ ማስረጃ፡ የለም። እድገት፡ መኖሩን፡ ግን፡ እኔም፡ አልክድም። ዋናው፡ ጥያቄው፡ እድገቱ፡ ማንን፡ እየጠቀመ፡ ነው፡ የሚለው፡ ነው። በአመት፡ አስራ፡ አነድ፡ በመቶ፡ የሚለው፡ ግን፡ መንግስት፡ የፈጠረው፤ በነጻ፡ ታዛቢወች፡ ያልተመረመረ፡ መሆኑን፡ ለማመልከት፡ እገደዳለሁ። ኢትዮጵያ፡ እንዴት፡ ከቻይና፤ ከህንድ፤ ከቬትናም፡ ከብራዚል፤ ከጋና፤ ወዘት፡ የላቀ፡ አመት፡ በአመት፡ እድገት፡ ልታሳይ፡ እንደቻለች፡ የሚያስረዳኝ፡ አላገኝሁም። የገጠሩ፡ ህዝብ፡ ኑሮ፡ አስደናቂ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ መዋቅራዊ፡ ለውጥ፡ የሚያሳይና፡ ህይወት፡ ለዋጭ፡ ኑሮ፡ መኖር፡ ጀምሯል፡ የሚያስብል፡ አለመሆኑን፤ ቢል፡ ጌትስ፡ ባሉት፡ የመለስኩት፡ ይመስለኛል። በርሻ፡ እረድፍ፡ የአለም፡ ባንክ፡ ባለሙያወች፡ ያጠኑት፡ የሚያሳየው፡ “የኢትዮጵያ፡ መንግስት፡ በሚለው፡ መሰረት፡ የእርሻ፡ ውጤቷ፡ አመት፤ ከአመት፡ ካደገ፡ በዚህ፡አለም፡ ያልታየ፡ ማንም፡ ያልደረሰበት፡ የአርንጓዴ፡ ለውጥ፡ ተቀናጂታለች፡ ማለት፡ ነው” ብለው፡ ባለፈፍው፡ አመት፡ የደመደሙት፤ የመንግስትን፡ የፈጠራ፡ ወሬ፡ ያመለክታል። ስለዚህ፤ ፍትሃዊ፡ እድገት፡ አለ፡ የምንል፡ ሁሉ፡ የፈጠራው፡ወሬ፡ ተባባሪ፡ እንዳንሆን፡ እሰጋለሁ። የስነ-ልቦና፡ መለወጫ፡ ዘዴ፡ ስለሆነ። ህወሃት፡ የሚለውን፡ ሁሉ፡ እንደ፡እውነት፡ ከተቀበልን፤ ለአብዛኛውን፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ አሰቃቂ፡ ኑሮ፡ ክብደት፡ አንሰጠውም፡ ማለት፡ ነው።

ቁም፡ ነገሩ፡ ግን፤ በህወሃት፡ ላይ፡ ብቻ፡ የማተኮር፡ ስነ-ልቦና፤ አገራችንና፡ ከዘጠና፡ ሚሊዮን፡ በላይ፡ የሆነውን፡ ሕዝቧን፡ ያደረሰባቸውን፡ ፈተና፡ ሙሉ፤ በሙሉ፡ አያሳይም። በጥቅሉ፡ ብናየው፡ አራት፡ ነጥብ፡ አምስት፡ ሚሊዮን፡ የሚሆን፡ የትግራይ፡ ህብረተሰብ፡ ወካይ፡ ነኝ፡ የሚለው፡ ህወሃት፡ ስልጣኑንና፡ ጥቅሙን፡ ሊያረጋግጥ፡ የቻለው፡ በእራሱ፡ ሃይል፡ ብቻ፡ አይደለም። ዋናው፡ የስልጣኑ፡ ምሰሶ፡ አድርጎ፡ የሚጠቀምበት፡ የሌሎቻችንን፡ ስነ-ልቦና፡ በመቨረዝ፤ በመስለቭ፤ በማዳከም፤ እርስ፡ በእርሳችን፡ እንድንጣላ፡ በማድረግ፤ በመከፋፍል፤ በጥቅም፤ ለጥቅም፤ ለስልጣን፡ እንድንገዛ፡ በመሳብ፤ በፍርሀት፡ ተጠምደን፡ ማንነታችን፡ እንድንክድና፡ ደፍረን፡ ለፍትህ፤ ለእርትህ፡ እንዳንቆም፡ በማድረግ፤ እንዳንደራጂ፡ የመከፋፈያ፡ ዘዴወችን፡ በያለንበት፡ በመዘርጋት፡ ጭምር፡ ነው። የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ የመዘገበው፡ በዘጠና፡ ሰባቱ፡ ምርጫ፡ ላይም፡ ያሳየው፡ በዘር፡ መለያየትን፡ ሳይሆን፡ በኢትዮጵያዊነት፡ ለአግሩና፡ ለመብቱ፡ የሚቆም፡ መሆኑን፡ ነው። ሰላማዊይ፡ ወገኑን፡ መግደል፡ ልምዱ፤ ባህሉ፤ አለመሆኑን፤ ነው።

የህወያትን፡ የተቀነባበረ፡ የስነ-ልቦና፤ ፕሮፓጋንዳና፡ እቅድ፡ መንሰኤና፡ ያስከተለውን፡ አስከፊ፡ ውጤት፡ በሚገባ፡ ለመረዳት፡ የሚቻለው፡ ከኢትዮጵያ፡ ተማሪወች፡ እንቅስቃሴና፡ ከተከተለው፡ ክፍፍል፤ እ.አ.አ. ከ 1960s ወዲህ፡ ስር፡ በመስደድ፡ ላይ፡ ያለውን፤ ጥቂቶቻችን፡ ይህ፡ በዘር፡ ልዩነትና፡ ጥላቻ፡ ላይ፡ የተመሰረተ፡ ጉዞ፡ ለማንም፡ አያዋጣም፤ አገራችን፡ ይጎዳታል፤ ሕዝቧ፡ በድህነት፡ አዙሪኝ (cycle): እንዲጠመድ፡ ያደርገዋል፡ ብለን፡ ስንከራከርበት፡ የቆየነውን፤ መተኪያ፡ የማይገኝላቸውን፡ ብዙ፡ መቶ-ሽህ፡ የሚሆኑ፤ ከሁሉም፡ ብሄር፤ ብሄረሰብና፡ ህዝብ፡ ክፍሎች፡ የተወጣጡ፤አገር፡ ወዳድ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ለሃገር፤ ለወግን፡ ብለው፡ መስዋእት፡ የከፈሉበትን፤ አሁንም፡ የሚከፍሉበትን፤ በጎሳ፡ የማይታረቅ፡ ልዩነቶች፡ ላይ፡ማር፡ ቀብቶ፡ ያዘጋጀልንን፤ የከፋፍለህ፡ ግዛው፡ የፍልስፍና፡ ጉዞ፡ ጠለቅ፡ ብሎ፡ በመመርመርና፡ በመረዳት፡ የሚገኝ፡ ሃቅ፡ ነው። ይህን፡ ለታሪክ፡ እተወዋለሁ። ዙሮ፡ ማንንም፡ ለመኮነን፤ ለመውቀስ፡ ሳይሆን፡ የስነ-ልቦና፡ ጦርነቱ፡ እኛን፡ ያደከመንና፡ ያከፋፈለን፡ መሆኑን፤ አሁን፡ የተጀመረ፡ አለመሆኑን፤ ይህን፡ ጎጅ፡ የፖለቲካ፡ ባህል፡ ማቆም፡ እንዳለብን፡ ለማመልከት፡ ብቻ፡ ነው።

ሀወሃት፡ አሁን፤ ከስራ፡ ላይ፡ አውሎት፡ የምናየው፡ “የብሄሮች፡ የማይታረቅ፡” ፍልስፍና፡ መሰረት፤ የአማራው፡ ህብረተሰብ፡ ሆነ፡ ተብሎ፡ በተለይ፤ በትግራይ፡ ህብረተሰብና፡ በሌሎች፡ እንዲጠላ፤ አማራው፡ እራሱን፡ እንዲጠራጠር፤ እርስ፡ በእርሱ፡ እንዲጣላና፡ እንዳይተባበር፤ በተከሰሰበት፡ አምኖ፤ አጎብዳጅ፡ እንዲሆን፤ ቀስ፡በቀስ፡ በኢትዮጵያ፡ የፖለቲካ፤ የባህል፤ የኢኮኖሚ፡ ዘርፎች፡ ሁሉ፡ አቅም፡ ያለው፡ ተወዳዳሪ፡ ሆኖ፡ እንዳይሳተፍ፤ ታሪክና፡ አስተዋጾውን፡ ሁሉ፡ እንዲያፍርበት፤ አንዳይቀበል፤ ቢቻል፡ የተማረው፡ ክፍል፡ በሙሉ፤ አገር፡ ለቆ፡ በስደት፡ እንዲኖር፡ ለማድረግ፡ ነው። ካልተቻለ፡ ደግሞ፡ ጸጥ፤ ለበጥ፡ ብሎ፤ አንገቱን፡ ሰብሮ፤ ማንነቱን፡ ክዶ፤ ተነስ፤ ውጣ፡ ሲባል፤ መብት፡ እንደሌለው፡ እዲወጣ፤ ህሊናው፡ ተበርዞ፤ እርስ፡ በእርሱ፡ ተናክሶ፤ አዲሱን፡ ስርአት፡ እንዲቀበል፡ ነበር፤ አሁንም፡ ነው። ይህ፡ ስልት፡ በአንጻሩ፡ የጣሊያን፡ ቅኝ፡ ገዦች፡ ያስተናገዱት፡ የከፋፍለህ፡ ግዛው፡ ስልት፤ የደቡብ፡ አፍሪካ፡ አፓርታይድ፡(Apartheid) የመሰለ፡ ስልት፡ መሆኑን፡ ብዙ፡ ማስረጃወች፡ መዝግበውታል።
በቅርቡ፡ አቶ፡ ገብረመድህን፡ አራአያ፡ ጠቅላይ፡ ሚንስትር፡ መለስ፡ “አማራ፡ ዋና፡ ጠላታችን፡ ነው። ይህን፡ ህብረተሰብ፡ ከስሩ፡ ማጥፋት፡ አለብን፡” ያሉት፡ ማስረጃ፡ ነው። ጠቅላይ፡ ሚኒስትሩ፡ ይህን፡ ያሉበትን፡ ዋና፡ ምክንያት፡ ብዙ፡ የውጭ፡ አገር፡ ባለሙያወች (Paul Collier/ethnic civil war; Bill Easterly, Ethiopian poverty; Michela Wrong, ethnic-based corruption and illicit outflow, etc)፤ ልይ፡ ልዩ፡ ተቋሞች (Human Rights Watch, Amnesty International, Oakland Institute, Survival International, ec)፤ የኢትዮጵያ፡ ምሁራን፤ ተመልካቾች፤ የስባዊ፡ መብት፡ ተቛሞች፡ አስረድተዋል። እኔም፡ በተከታታይ፡ ከዘጠና፡ ሰቫት፡ ምርጫ፡ በኋላ፡ ባቀርብኳቸው፡ አራት፡ መጽሃፎች፤ በተለይ፡ በ “Waves: endemic poverty that globalization can’t tackle–በተባለው፡ ላይ፡ ከብዙ፡ ዓቅጣጫ፤ በብዙ፡ ማስረጃ፡ አስቀምጨዋለሁ።

ህዝብ፡ የማይሳተፍበት፡ እድገት፡ ፍትሃዊ፡ ሊሆን፡ አይችልም፡

እነዚህና፡ ሌሎች፡ ጥናቶች፡ የሚያመለክቱት፡ ማንኛውም፡ የክልልና፡ ጠባብ፡ ብሄርተኛ፡ ስርአት፡ፍትህ/እርትህ፡ የሌለበት፤ በህግ-የበላይነት፡ የማይዳኝ፤ የህዝብ፡ ድምጽና፡ተሳትፎ፡ የሌለበት፤ የውስጥ፡ ውድድር፡ የተከለከለበት፡ ወይንም፡ አድሏዊ፡ ሆነበት፤ ግልጽነት፡ የሌለበት፡ ነው። ስለሆነም፤ እድገቱ፤ ዘላቂነትና፡ ፍትሃዊነት፡ ያለው፡ ሊሆን፡ አይችልም። ዘረኛው፡ ቡድን፤ ማን፡ ሃብታም፡ እንደሚሆን፤ ማን፡ የስራና፧ የትምህርት፡ እድል፡ እንድሚኖረው፤ ማን፡ የከተማ/የገጥር፡ መሬት፡ እንደሚያገኝ፤ ማን፡ የስራ፡ ፈቃድ፡ እንደሚሰጠው፤ ማን፡ ከፍተኛ፡ ቀረጥ፡ እንደሚከፍል፤ የማን፡ ገቪ፡ ከፍ፤ የማን፡ ዝቅ፡ እንደሚል፡ ይወስናል። ይህ፡ ስርአት፤ የሚጎዳው፡ አንድ፡ ብሄረሰብ፡ ሳይሆን፡ አብዛኛውን፡ የኢትዮጵያ፡ ድሃ፡ ህዝብ፡ ነው። ስርአቱ፡ ካልተለወጠ፡ ሁሉም፡ ይጎዳል። ጥቂት፡ ሰወች፡ ብቻ፡ ስልጣንና፡ ሃብት፡ ያካብታሉ።

ዋናው፡ ለማመልከት፡ የምፈልገው፤ ሁላችን፤ ልናጤነው፡ የሚገባን፤ ከህወሃት፡ የመነጨውን፡ የስርአት፡ ችግር፡ ከሁሉ፡ አቅጣጫ፡ ስናየው፡ ፍትያዊ፡ አይደለም፤ ሊሆንም፡ አይችልም። ይህን፡ ከተረዳን፤ ችግሩን፡ ደጋግመን፡ ብናኝክ፤ ቀን፡ ቀን፡ ከሌት፡ ብናወጣ፡ ብናወርድ፡ ቀጣይ፡ ሁኖ፡ የሚታየው፡ ክፍተት፡ የእኛው፡ ድርጂታዊ/አመራራዊ (organizational and leadership crisis)፤ መሆኑ፡ አያጠራጥም። ግፉን፡ እናያለን፡ የምንል፡ ሁሉ፡ በሚያስማሙን፡ የአገርና፡ የመላው፡ ህዝብ፡ ጉዳዮች፡ ላይ፡ ተነስተን፡ እቅድን፡ ወደ፡ ተግባር፡ ለመተርጎም፡ እንቅፋት፡ የሆኑትን፤ በተቃዋሚው፡ ዘርፍ፡ ተዘርግተው፡ ያሉትን፡ ማነቆወች፡ በግልጽ፡ ተወያይተን፡ መፍትሄ፡የምንፈልግበት፡ አሁን፡ ነው። እራሳችን፡ የምንፈጥራቸውን፡ ችግሮች፡ እስካላየን፡ ድረስ፡ የትም፡ አንደርስም። ለምሳሌ፤ ብናውቀውም፡ ባናውቀውም፤ ብንቀበለወም፤ ባንቀበለውም፤ አንዳንድ፡ በፖለቲካና፡ ማህረሰብ፡ ስብስቦች፡ ውስጥ፡ የሚገኙ፡ ግለሰቦች፡ ሌላውን፡ ያለ፡ ምንም፡ ማስረጃ፡ ስም፡ ማጥፋት፤ መወንጀል፤ መኮነን፤ ማስጠላት፤ ተግባራቸው፡ ሲሆን፡ የማይረዱት፡ ይህ፡ ባህሪይ፡ ህወሃትን፡ ደጋፊ፡ መሆኑን፡ ነው።

የእነዚህን፡ አይነት፡ ባህሪይ፡ በቀጥታ፡ መከላከል፡ የሁላችንም፡ ተግባር፡ ሲሆን፤ አብዛኛውን፡ ጊዜ፡ ሰው፡ ይቀየማል፡ ብለን፡ እናልፋለን። የፈጠራ፡ ወሬ፡ ሰምተን፡ ሳንናገር፡ ዝም፡ እንላለን። እውነት፡ ስለመናገር፡ አንድ፡ ፈላስፋ፡ ሲናገሩ፡ “ስለ፡ እራስህ/እራሽ፡ እውነት፡ ለመናገር፡ ካልቻልክ/ካልቻልሽ፤ ስለ፡ ሌላ፡ ሰው፡ ለመናገር፡ አትችልም/አትችይም፡” የተባለው፡ ሙሉ፡ በሙሉ፡ እውነትነት፡ አለው። የዘመኑ፡ ምሁር፡ ትውልድ፡ ስለ-እራሱ፡ እውነት፡ ከመናገር፡ ይልቅ፡ ስለ፡ ሌላው፤ ስለሚቃወመው፡ “ሃጢያት/መጥፎነት፡ ፈጥሮ፡ መናገር፡ ይቀለዋል። ይህ፡ልምድ፡ የጥላቻ፡ ምልክት፡ ነው። መቀቨል፡ ያለብን፤ ከየትም፡ አቅጣጫ፡ ቢመጣ፤ የፈጠራ፡ ወሬ፤ የጥላቻ፡ ፖሊቲካ፤ ስም፡ ማጥፋት፤ ለእውነት፡ ቀጥ፡ ብሎ፡ አለመቆም፡ የንጹህን፡ ሰው፡ ክብር፡ የግፋል፤ አመኔታን፡ አያጠናክርም። እንዲይውም፤ ደጋፊ፡ የሆነን፡ ግለሰብ፡ ከተሳታፊነት፡ ያባርራል፤ ተመልካች፡ የሆነን፡ “ፖለቲካ፡ ኮረንቲ፡ነው”፡ ብሎ፡ ወደ-መሃል፡ ሰፋሪነት፡ ይመራል። በተቃዋሚው፡ ክፍል፡ ደጋግግሜ፡ ለብዙ፡ ጊዜ፡ ያየሁት፡ ሌላው፤ ልንፈታው፡ የሚገባን፡ ችግር፡ ውይይት፡ በቁም፡ ነገሩ፤ በሃሳቡ፤ በችግሩ፡ ላይ፡ ትኩረት፡ መስጠት፡ ሳይሆን፡ በግለሰቡ፡ ላይ፤ በአለፈው፡ ታሪኩ፡ ላይ፡ የምናደርገው፡ ትኩረት፡ ጎጂ፡ መሆኑ፡፡ነው። ይህ፡ ባህሪይ፡ አገራችን፡ እየጎዳት፡ ነው። ግለሰብ፡ ከሃሳብ፡ አለመለየት፡ ኋላ፡ ቀር፡ አመለካከት፡ ነው። ለገንቢ፡ ለውጥ፡ ማነቆ፡ ነው። ጥላቻን፡ የሚፈጥር፡ መሆኑን፡ ደጋግመን፡ አይተናል።

ይህ፡የሽሙጥ፡ አይነት፡ ባህሪይ፡ ለገንቢ-ለውጥ፤ አብሮ፡ ለመስራት፡ እንቅፋት፡ ሁኗል። ሁለቱንም፡ ጎጂ፡ ባህሪወች፡ ለመለወጥና፡ ለሃያ፡ አንደኛው፡ መቶ፡ ክፍለ-ዘመን፡ የሃገር፡ እድገት፡ አስተዋጾ፡ ለማድረግ፡ ከፈለግን፤ የእኛን፡ ድፍረት፤ ፈቃደኛነት፡ እንጂ፤ የህወሃት፡ ፈቃድ፡ አይጠይቁም። አነኝህን፡ የመሳሰሉ፡ የባህሪይ፤ የአስተሳሰብና፡ የስነ-ልቦና፡ ሁኔታወች፡ አለመለወጥ፤ ያለውን፡ የተማረ፡ የሰው፡ ሃይል፡ በታትነውታል። ለአገራዊና፤ ለወገናዊ፡ ገንቢ፡አስተዋጾ፡ እውን፡ መሆን፡ ማነቆ፡ ሁነዋል። የባሰውን፤ ስም፡ማጥፋት፤ ያለ-ማስረጃ፡ ሰውን፡ መክሰስ፤ አንድ፡ ግለሰብ፡ አቅዋሙን፡ ሲለውጥ፡ መጠራጠር፤ ወዘተ፡ የአገራችን፡ ተወዳዳሪ፡ የማይኖርለት፡የሰውና፡ የእውቅና፡ሃይል፡ በታትነውታል፤ ለመጠቀም፡ ማንቆ፡ ሆነዋል። ተቃዋሚ፡ ነን፡ እያልን፤ ህወሃትን፡ በመዋሸት፡ እየከሰስን፤ እየኮነን፤ እኛ፡ ከዋሽን፡ ልዩነቱ፡ የት፡ ላይ፡ እንደሆነ፡ መጠየቅ፡ አለብን። ተስማምተን፡ አገርና፡ ህዝብ፡ ለመርዳት፡ ከፈለግን፡ ተባብረን፡መስራት፡ አለብን። አብረን፡ ለመስራት፡ ሃቀኛ፡ መሆን፡ የሞራል፡ ግዴታችን፡ ንው።

ይህን፡ በደንብ፡ የተረዱት፤ የኢትዮጵያን፡ የጥንትና፡ ዘመናዊ፡ ታሪክ/ሂደት፡ የሚያውቁት፡ የኢትዮጵያ፡ ወዳጂ፡ አሜሪካዊ፡ ሊቅ፤ ፕሮፌሰር፡ ዶናልድ፡ ለቪን፡ የተናገሩት፡ በአእምሮየ፡ ውስጥ፡ ጸንቷል። አንድ፡ ኢትዮጵያዊ፡ ተማሪ፡ የጠየቃቸውን፡ በማስታወስና፡ በመጥቀስ፡ እንዲህ፡ ይላሉ፡፡ “ለመሆኑ፤ ኢትዮጵያዊያን፡ በጋራ፡ ሁነው፡ አንድ፡ አገራዊ፡ ችግር፡ የሚፈቱበት፡ ጊዜ፡ መቸ፡ ነው።” ይህን፡ አባባል፡ በሙሉ፡ እጋራለሁ። እኔ፡ በተወለድኩበትና፡ ባደግኩበት፡ ክፍል፤ ጎንደር፤ የሚነገር፡ ቀልድ፡ መሳይ፡ ቁም፡ ነገር፡ ላስቀምጥ። ጎንደሬወች፡ በያለሉበት፡ ታታሬ፡ መሆናቸውን፡ የተመለከተ፡ አንድ፡ ታዛቢ፤ እንዲህ፡ ይላል። “አንድ፡ ጎንደሬ፡ የአንድ፡ ሽህ፡ ሰው፡ ስራ፡ ለመስራት፡ ይችላል። ሆኖም፤ ሽህ፡ ጎንደሬወች፡ አንድ፡ ቤት፡ አብረው፤ ተባብረው፡ ለመስራት፡ አይችሉም።” ጎንደሬወች፡ ሆኑ፡ ሌሎች፡ ዛሬ፡ የተስማሙበትን፡ ነገ፡ “ያፈርሱታል.” ተባብረው፤ የተቃጠለ፡ ቤት፡ አያጠፉም። ከማዳን፡ ይልቅ፡ ለማጥፋት፡ የሚደረገው፡ባህል፡ያይላል፡ ለማለት፡ የሚያስደፍሩ፡ ብዙ፡ ሁኔታወች፡ ይታያሉ። የሚያስፈራው፡ ይህ፡ አባባል፡ አገራዊ፡ መሆኑ፡ ነው። ይህ፡ ሁሉ፡ ተደማምሮ፡ የሚረዳው፡ ህወሃትን፡ ነው።

የታሪክ፡ ተጠያቂ፡ ከሚያደርጉን፡ ምክንያቶች፡ መካከል፡ ከተወሰነች፡ ገቢው፤ ቀረጥ፡ ከፍሎ፡ ላስተማረን፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ዛሬ፤ እኛ፡ የህብረተሰብ፡ “ምርጦች፤ (political and social elites)” ፤ በምናሳየው፡ባህሪና፡ ተግባር፡ የተነሳ፤ ተባብረን፡ ለአንድ፡ አላማ፡ ቆመን፡ የህዝብን፡ ውለታ፡ ለመክፈል፡ አልቻልነም። ህወሃት፡ እፎይ፡ ይላል፤ አብዛኛው፡የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ “የድርጂት/የመሪ፡ ያለህ፤ የተማሩት፡ የት፡ አሉ፤ የት፡ ገቡ፡” ብሎ፡ የጠይቃል። ነጥቡ፤ ለአላማ፡ አንድነት፡ ዛሬ፡ ተቻችለን፡ ካልተነሳን፤ መቸ፡ ነው፡ የምንደርስለት፡ የሚለውን፡ በህሊናችን፡ እንድናብላላ፡ ያስገድደናል። ይህን፡ ወሳኝ፡ ጥያቄ፡ ካልመለስን፡ የታሪክ፡ መፋረጃ፡ መሆናችን፡ አይቀርም።

በአጠቃላይ፡ ሲታይ፤ የእርስ-በእርስ፡ ክስ፤ የእርስ-በእርስ፡ መዘላለፍ፤ የእርስ-በእርስ፡ መጠላለፍ፤ ስም፡ማጥፋት፡ ወዘተ፤ ሌላው፡ (ቢያንስ፡ ከህወሃት፡ ችግር፡ ጋር፡ የሚወዳደር)፡ ቅጥ፡ ያጣ፤ በግልጽ፡ የማንነጋገርበት፡ የሰነ-ልቦና፤የባህሪይ፤ የእሴት፤ የአመለካከት፡ ችግር፡ ሁለተኛው፡ ከእራሳችን፡ የመነጨ፡ ማነቆ፡ ሁኗል፡ በማለት፡ ባቀርበው፡ ከሃቁ፡ የወጣሁ፡ አይመስለኝም። ይህ፡ እራሳችን፡ መፍታት፡ ያለብን፡ ችግር፡ ነው።

ስለሆነም፤ ችግሩን፡ በሁለት፡ ዘርፍ፡ ማስቀመጥና፡ መፍትሄ፡ መፈለግ፡ የያንዳዳችን፡ ሃላፊነት፡ ሆኗል። የችግሩ፡ መፍትሄ፡ ፈላጊወች፡ ካልሆን፤ የችግሩ፡ አጋሮች፡ መሆናችን፡ አይቀርም። ሁኔታው፡ ከቀጠለ፡ ተጠቃሚው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ሳይሆን፡ ህወሃት፡ ነው።

የችግሮች፡ ሁለት፡ መልክ፤

አንድ፡

የጠባብ-ዘረኝነት፡ ስርአት፡ ያመጣውን፡ ጣጣ፡ በሚገባ፡ ለማስቀመጥ፡ ከተፈለገ፡ ቢያንስ፡ ከሁለት፡ አንጻር፡ መመርመር፡ ተገቢ፡ ነው። አብዛኛው፡ የተቃዋሚ፡ ዘርፍ፡ ያደረገውና፡ አሁንም፡ የሚያደርገው፡ ሃይሉን፤ እውቀቱን፤ ስብስቡንና፤ ውይይቱን፡ ከህውሃት፡ ጠባብ፡ ቡድን፡ ችግር፡ ላይ፡ ማፍሰስ፡ ነው፡ ለማለት፡ ይቻላል። ችግሩን፡ ሚዛናዊ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ በማስረጃ፡ እየደገፉ፡ ማስቀመጥ፡ ተገቢ፡ መሆኑን፡ ባቀርብኳቸው፡ ትንተናወች፡ ሁሉ፡ አሳይቻለሁ። የእራሳችን፡ ድክመት፡ አያይዘን፡ ሳናጤን፡ በህወሃት፡ በደል፡ ማተኮራችን፡ ለመገንዘብ፤ የሚጻፈውንና፡ የሚነገረውን፡ ብቻ፡ ማየት፡ ይበቃል። ህወሃት፡ ለአሰበው፡ ‘የኢትዮጵያ፡ ተቃዋሚ፡ ሃይሎች፡ በምንም፡ አይስማሙም፤ እርስ፡ በእርስ፡ መጠላለፍ፡ ልምዳቸው፡ ስለሆነ፡ እየገባሁ፡ መከፋፈል፡ እችላለሁ’ ብሎ፡ ከስራ፡ ላይ፡ ላዋለው፡ እቅድ፡ የተጠቀመባቸውን፡ መሰረተ፡ ሃሳቦችና፡ ዘዴወች፡ ስንመለከት፡ ይህ፡ ዘዴ፡ ምን፡ ያህል፡ አገራችንና፡ ህብረተስቡን፡ እንደጎዳው፡ እናያለን። ከዚህ፡ አዙሪኝ፡ ችግር፡ ለመውጣት፡ በመጀመሪያ፡ የአስተሳሰብ፤ የአሰራር፤ የአወቃቅር፤ የአመራር፡ ለውጠች፡ ለማድረግ፡ ፈቃደኛ፡ ብቻ፡ ሳይሆን፡ ዝግጁና፡ ብቁ፡ መሆን፡ ያስፈልጋል።

ህወሃት፡ በኢትዮጵያዊነት፡ ፋንታ፡ የጎሳ፡ ስነ፡ ልቦና፡ (psychological make-up and mindset)፡ በኢትዮጵያዊያን፡ ልብ፡ እንዲቀረጽ፡ ማድረጉ፡ ለክፍፍል፡ ፖለቲካ፤ ዋና፡ መሳሪያ፡ ሆኗል። “ብሄር፤ ብሄረሰብና፡ ህዝቦች፡ በምንም፡ ሊታረቁ፡ አይችልም፤ መገንጠል፡ መብታቸው፡ ነው” የሚለውን፡ የፖለቲካ፡ አመራር፡ በ አንቀጽ፡ 39፤ አስገብቶ፡ ድጋፍ፡ ሰጭ፡ መሪወችን፤ ደጋፊወችን፡ መመልመል፤ ህዝቡና፡ አገሪቱ፡ ገደብ፡ ከሌለው፡ ርጋታ፡ የለሽ፡ ወጥመድ፤ (permanent suspense) ውስጥ፡ እንዲገቡ፡ ማድረጉ፡ ለአንድ፡ አላማ፡ ላለሞቆማችን፡ አስተዋጾ፡ እያደረገ፡ ቆይቷል። የሚያሳየው፡ ተቃዋሚው፡ የሚመራው፡በእራሱ፤ ወይንም፡ በኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ አጀንዳ፡ ሳይሆን፡ በህወሃት፡ አጀንዳ፡ ነው፡ ያሰኛል። ህወሃት፡ ይህን፡ ዘዴ፡ ስራ፡ ላይ፡ ሲያውለው፡ የአብዛኞቻችን፡ ደካማነት፤ መከፋፈል፤ የመጠራጠር፡ ባህል፤ ለስሜት፤ ለጉራ፤ ለግለኝነት፤ ለጥቅም፤ ወዘተ፡ በቀላሉ፡ የመውደቅ፡ ዝንባሌን፡ በደንብ፡ ስላጤነ፡ ነው። በእኛ፡ ላይ፡ የስነልቦና፡ ሰለባ፡ ከተካሄደ፡ የተቃዋሚው፡ ክፍል፡ እየደከመ፡ ይሄዳል፤ በረባ-ባረባው፡ ይከፋፋል።ጉልበቱን፤ እውቀቱን፤ ገንዘቡን፡ የሚያጠፋው፡ በመከላከል፡ ላይ፡ እንጂ፡ በማሸነፍ፡ ላይ፡ ያልሆነው፡ ለዚህ፡ ነው። እስከ፡ አሁን፡ የሚታየው፡ ህወሃት፤ ያለ፡ ብዙ፡ ወጭ፤ የተቃዋሚው፡ ክፍል፡ ተሳስቦ፤ እንደ፡ ሰንሰለት፡ ተያይዞ፡ በአንድ፡ አላማ፡ አይቆምም፡ የሚል፡ ስሌቱ፡ እኛ፡ በምናወራውና፡ በምናደርገው፡ ሲሳካለት፡ ቆይቷል፤ አሁንም፡ ያው፡ ነው። ማሻማት፡ የሌለባቸው፡ ምሳሌወች፡ ልስጥ።

የክርስትና፡ ሃይማኖት፡ አመራርንና፡ ተከታዮችን፡ ብንወስድ፤ ህወሃት፡ መከፋፈልን፡ ለመጠቀም፡ ገደቭ፡ እንደሌለው፡ ያሳየናል። የክርስትና፡ ሃይማኖት፡ ተከታዮች፡ የምናመልከው፡ አንድ፡ “ታቦት፤ አንድ፡ አምላክ” ነው፡ ካልን፤ ቢያንስ፡ የ 1,700 አመታት፡ ታሪክ፡ ያላት፡ የኢትዮጵያ፡ ኦርቶዶክስ፡ ቤተክርስቲያን፡ መሰብሰቢያችን፤ መታወቂያችን፤ የመንፈስ፡ ምሽጋችን፡ እንጂ፡ የጠባብ፡ ብሄርተኞች፡ መከፋፈያ፡ ቤት፡ መሆን፡ የለባትም፡ ነበር። ስለሆነም፡ በዚህ፡ እራሳችን፡ ልንጠብቀውና፡ ልንከባበከው፡ በምንችል፡ ታሪካዊ፡ ተቋም፡ ውስጥ፡ የሚካሄደው፡ ክፍፍል፡ ከየት፡ እንደመጣ፡ አውቀን፡ መፍትሄ፡ መሻት፡ የህወሃትን፡ ፈቃድ፡ አይጠይቅም። ተቋሙን፡ መጠበቅ፡ ለፍትሃዊ፡ ስርአት፡ እውን፡ መሆን፤ ለኢትዮጵያ፡ ዘላቂነት፤ ለኢትዮጵያዊያን፡ ክብር፤ ለማንነታችን፡ አስፈላጊ፡ ስለሆነ። ይህ፡ የህወሃትን፡ ፈቃድ፡ አይጠይቅም።

የተቋማት፡ አድሏዊ ፡ሚና፡

በአንድ፡ የዘረኛ፡ ክልል፡ ቡድን፡ ፍላጎትና፡ ጥቅም፡ የሚመራ፤ በስልጣንና፡ የኢኮኖሚ፡ ጥቅም፡የተሳሰረ፤ የተቆላለፈ፤ እርስ፡ በእርሱ፡ የሚረዳዳ፤ ተቋሞቹን፡ ሁሉ፡ (የአመራር፣ የመከላከያ፤ የስለላ፤ የፌደራል፡ ፖሊስ፤ የውጭ፡ ጉዳይ፤ የባንክ፤ የገንዝ፤ የመሬት፡ ይዞታ፤ ሌሎች፡ የተፈጥሮ፡ ሃብት፡ ዘርፎች፡ አስተዳደርና፡ ስርጭት፤ የውጭ፡ እርዳታ)፡ ሙሉ፡ በሙሉ፡ የበላይነት፡ ወደ፡ እራሱ፡ ደጋፊወቹና፡ ፓርቲው፡ ተቆጣጣሪነት፡ ያዛወረው፡ ሌላው፡ አጎብዳጅና፡ ጥገኛ፡ እንዲሆን፡ በማሰብና፡ በማድረግ፡ ነው። ለዚህ፡ ዘዴ፡ እንዲጠቅ፡ ተብሎ፡ ህወሃት፤ የትግራይን፡ ክልል፡ ከሌላው፡ ለይቶ፤ ከመጠን፡ በላይ፤ ግልጽ፡ አድሏዊነት፡በሚያሳይ፡ መልኩ፡ ፈርጂ፡ የሌለው፡ መዋእለ፡ ንዋይ፡ (financial and material investments): ከማእከላዊ፡ መንግስት፡ እየወሰደ፡ ለመሰረተ፡ ልማት፤ ለፍጆት፡ እቃ፡ ማምረቻ፤ ለስራ፡ እድል፡ ማስፋፊያ፤ ለጥቂቶች፡ መክበሪያ፡ ወዘተ፡ ብዙ፡ ቢሊየን፡ ብር፡ አፍስሷል፤ አሁንም፡ ያፈሳል። ህወሃት፡ ይህን፡ ሲያደርግ፡ ዋጋ፡ የሚከፍሉት፡ ሁለት፡ የህብረተስብ፡ ክፍሎች፡ ናቸው። አንዱ፤ ቀረጥ፡ ከፋይ፡ የሆነው፡ አብዛኛው፡ የኢትዮጵያ፡ ድሃ፡ ሕዝብ፡ ሲሆን፤ ሌላው፡ በአድሎ፡ እድገት፡ አገኘ፡ የሚባለው፡ የትግራይ፡ ህብረተሰብ፡ ነው። ለዚህ፡ ህብረተሰብ፡ ጎጂ፡ የሚሆነው፡ ቀረጥ፡ ከፋዩ፡ አብዛኛው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ አድሎውን፡ ሙሉ፡ በሙሉ፡ ስለሚያውቅ፡ ሊረሳው፡ አይችልም። የትግራይ፡ ወጣቶች፡ የትምህርት፤ የስራ፡ የመሾም፡ እድል፡ ሲያገኙ፡ ሌላው፡ እንዴት፡ ይህ፡ ሊሆን፡ ቻለ፡ ብሎ፡ መጠየቁ፡ የማይቅር፡ ነው። ስርአቱ፡ ፍትሃዊ፡ ስርጭትን፡ ለማምጣት፡ አለመቻሉን፡ ህዝቡ፡ በግልጽ፡ እያየው፡ ነው። ስለሆነም፡ የትግራይ፡ ህብረተሰብ፡ ይህን፡ የአጭር፡ ጊዜ፤ ከፖለቲካና፡ ከጠባብ፡ ዘረኝነት፤ ከዘር፡ ጥላቻ፡ የመጣ፡ ጥቅም፡ መቃወም፡ አለበት። ወደፊት፡ የሚያመጣውን፡ አደጋ፡ ማየት፡ ለዚህ፡ ይጠቅማል።

አድሎ፡ ስላለ፡ በጀምላ፡ መወንጀል፡ ይቁም፡

ይህ፡ የህወሃት፡ ሙሉ፡ የፖለቲካና፡ የኢኮኖሚ፡ የበላይነት፡ ቢያንስ፡ ሁለት፡ ያልተጠበቁ፡ ሁኔታወችን፡ ያሳያል። በአንድ፡ በኩል፡ ሌላ፡ መግቢያ፡ ቀዳዳ፡ስለሌለ፡ ብዙ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ወደዱም፡ ጠሉም፡ መሬት፤ ቤት፤ ፋብሪካ፤ ተቋም፤ ሌላም፡ ሃብት፡ ለመያዝና፡ ለማቋቋም፡ ከህወሃት፡ ባለስልጣኖች፡ ፈቃድ፡ ማግኘት፡ ግዴታ፡ ሁኖባቸዋል። በሃገራቸው፡ ይህን፡ ስላደረጉ፡ መወንጀል፡ አለባቸው፡ የሚል፡ ግምት፡ የለኝም። ኢላማው፡ ስርአቱን፡ ለመለወጥ፡ እንጂ፡ ማንንም፡ ለመኮነን፤ ለማውገዝ፤ ለመወንጀል፡ መሆን፡ የለበትም። ጎሳ፡ መኮነን፤መወንጀል፡ የህወሃት፡ ጠባብ፡ ቡድን፡ እሴት፡ እንጂ፡ የአብዛኛው፡ ኢትዮጵያዊ፡ እሴትና፡ ልምድ፡ አይደለም። የአማራ፤ የትግራይ፤ የኦሮሞ፤ የጉራጌ፤ የአኗክ፤ ወዘተ፡ ባህልና፡ ልምድ፡ አይደለም። ሁለተኛው፡ ነጥብ፤ ህወሃት፡ ሆነ፡ ብሎ፤ ትግራይን፡ እንደምሽግ፡ ለመጠቀም፤ ህብረተሰቡን፡ ከሌሎች፡ ወገኖቹ፡ ጋር፡ እንዲጣላ፡ ለማድረግ፡ ያቀደውን፡ ስልት፡ አይተን፡ መላውን፡ የትግራይ፡ ህብረተሰብ፡ የጠባቡ፡ ቡድን፡ አጋር፡ ነህ፡ ማለቱ፡ ህወሃት፡ ካጠመደው፡ ወጥመድ፡ መግባትና፡ ጠባቡን፡ ቡድን፡ የሌለ፡ ክብር፡ መስጠት፡ ነው። ይህን፡ ስል፡ በሁለቱም፡ ጎራ፡ ያሉ፡ ግለሰቦች፡ ለጥቅም፡ ብቻ፡ ብለው፡ ህሊናቸውን፡ አልሸጡም፡ ማለቴ፡ አይደለም። ባጠቃላይ፡ ሲታይ፡ ግን፡ በጀምላ፡ ማንንም፡ ክፍል፡ መኮነን፤ መዝለፍ፤ ማዋረድ፤ መወንጀል፡ ወደ፡ ተፈለገው፡ ብሩህ፡ አላማ፡ ሊወስደን፡ አይችልም። ይህ፡ የመወነጃጀል፡ ባህል፡ በሙሉ፡ እንዲቆም፡ ሁላችንም፡ ጥረት፡ የምናደርግበት፡ ጊዜ፡ አሁን፡ ነው።

የሰብአዊ፡ መብቶች፡ መገፈፍ፡ በ ጎሳ፡ መለየቱ፡ ያዘገንናል፡

ከላይ፡ የጠቀስኳቸውንና፡ ሌሎች፡ የአስተሳሰብ፡ ለውጦች፡ (redirection) ከስራ፡ ላይ፡ ለማዋል፡ እራሱን፡ መርጦ፡ የስልጣን፡ ቁንጮ፡ የያዘው፡ ብሄርተኛ፡ ቡድን፤ ህወሃት፤ እኛን፡ በግልጽ፡ ሆነ፡ በምስጢር፡ ለመያዝና፡ ለመሳብ፡ አጎልማሽ፡ ሁኔታወችን፡ (enabling conditions) አስቀድሞ፡ መፍጠሩን፡ ማጤን፡ያስፈልጋል። አጎልማሽ፡ ሁኔታወችን፡ ፈጥሮ፡ እኛን፡ የእራሱ፡ አጀንዳ፡ ተከታዮች፡ ማድረጉ፡ ጥንካሬውን፡ ያሳያል። ለምን፡ ብንል፤ እያወቅንም፡ ሆነ፡ ሳናውቅ፡ ብዙወቻችን፡ ባዘጋጀልን፡ የጥላቻ፡ መርዝ፡ ተዘፍቀናል፤ ለመውጣት፡ ሲያዳግተን፡ እንታያለን። ለምሳሌ፤ በቅርቡ፡ የአማራ፡ ህብረተሰብ፡ ክፍል፡ ሆነ፡ ተብሎ፡ (deliberate ethnic cleansing and dispossession) ‘የተፈረደበት፡’ ህብረተሰብ፤ እንደከብት፤ በጀምላ፡ ከጉራ፡ ፈርዳ፤ ደቡብ፡ ክልል፡ ኢሰባዊ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ ተገዶ፡ ለስደት፡ ሲዳረግ፡ ስንት፡ የፖሊቲካና፡ የማህበራዊ፡ ድርጂቶች፤ የታወቁ፡ ግለሰቦችና፡ መሪወች፡ የማያሻማ፤ የሚያስተማምን፤ የሚያቀራርብ፤ ህዝብን፡ ከህዝብ፡ ጋር፡ በሰላም፡ እንዲኖር፡ የሚረዳ፡ አቋም፡ እንደወሰዱ፡ አይተናል። የሰባዊ፡ መብቶች፡ መገፈፍ፡ በዘር፤ በጾታ፤ በሃይማኖት፤ በእርዮት፤ በእድሜ፡ አይለዩም። የአማራ፡ ህብረተሰብን፡ የምንለይ፡ መሆናችን፡ መለኪያው፤ ድምጻችን፡ ባለማሰማት፤ ህወሃት፡ ከሚያደርገው፡ የዘር፡ ልዩነት፡ ፍልስፍና፡ ጋር፡ ከመቆም፡ ምንም፡ ለመለየት፡ አለመቻሉ፡ (indistinguishable)፡ መሆኑ፡ ነው። በፍትህ፤ በእርትእ፤ በህግ-የበላይነትና፡ በሰብአዊ፡ መብቶች፡ ማመን፡ ማለት፡ ማንንም፡ ኢትዮጵያዊ፡ ከሌላው፡ ሳይለዩ፡ ድምጽ፡ ማሰማት፤ አቋም፡ መውሰድ፤ መታደግ፡ ማለት፡ ነው።

ሰባ፡ ስምንት፡ ሽህ፡ ህዝብ፡ በአንድ፡ ጊዜ፤ ከአንድ፡ ቦታ፤ ከአንድ፡ ብሄረሰብ፤ በቋንቋው፡ ተለይቶ፡ ከማሳው፡ ተፈነቅሏል። አንዲት፡ እናት፡ ልጂ፡ ወልዳ፡ በወለደችበት፡ ሌሊት፡ ከቤቷ፡ ተገዳ፡ ወጥታለች። እርጉዝ፡ ሴቶች፡ ለጤናቸው፡ በሚያሰጋ፡ ሁኔታ፡ እንደ፡ ተራ፡ ወንጀለኛ፡ ክብራቸው፡ ተገፎ፡ ቤታቸውን፡ ለቀው፡ እስር፡ ቤት፡ ገብተዋል። ህጻናት፤ ወጣቶች፤ እናቶች፤ እሰከ፡ ሰማኒያ፡ ዘጠኝ፡ አመት፡ የሆናቸው፡ አዛውንቶች፡ ለእስር፡ቤት፡ ተዳርገዋል። ሰላማዊ፡ ገበሬወች፡ ከእርሻ፡ መሬታቸው፡ ከሰብላቸው፤ ከአትክልታቸው፤ ከኑሯቸው፡ ተገደው፡ ህየወታቸው፡ ወደ፡ አስጊ፡ ደረጀ፡ ተለውጧል። እነዚህ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ሁሉ፤ ከቤታቸው፤ ከሃብታቸው፤ ከንብረታቸው፡ ተገደው፡ ሲሰደዱ፤ ሲታሰሩ፤ የሚገፈፉት፡ ሃብት፡ ብቻ፡ አይደለም።

ሰው፡ ለምኖም፡ ቢሆን፡ ያድራል። አሰቃቂው፡ ግን፡ ከክብራቸው፤ ከማእረጋቸው፤ ከማንነታቸውን፤ ከሰብእነታቸውን፡ ጭምር፡ መሆኑ፡ ነው። በአማራው፡ ሆነ፤ በአፋር፤ በኦጋዴን፤ በኦሞ፡ ሸለቆ፤ በጋምቤላ፤ በኦሮሚያ፤ ለሚካሔደው፡ ማንኛውም፤ የሰብእነት፤ የክብር፤ የማንነት፡ ገፈፋ፡ (recurring violations of human dignity and human rights)፤ ለገጠማቸውና፡ ለሚገጥማቸው፡ ሁሉ፡ ያለ-አድሎ፤ በግልጽ፡ መቃወም፡ አዲሱ፡ መለኪያችን፡ (criteria) መሆን፡ አለበት። ድምጽ፡ ሳያሰሙ፤ አቋም፡ ሳይወስዱ፡ እንዲሁ፡ ህወሃትን፡ መኮነን፡ በቂ፡ ሊሆን፡ አይችልም። በመኮነን፤ በመወንጀል፤ ስም፡ በማጥፋት፡ ለውጥ፡ ለማምጣት፡ ቢቻል፡ ኖሮ፡ ህወሃት፡ እስካሁን፡ በስልጣን፡ ላይ፡ አይቆይም፡ ነበር። የዘጠና፡ ሰባቱ፡ ምርጫ፡ የሚያሰተምረን፡ በመወነጃጀል፤ ለስልጣን፡ በመወዳደር፤ በመካካድ፡ ባህል፡ የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ አመኔታ፡ አጥተናል። ልዩ፡ ልዩ፡ መልኪያወች፡ የሚያሳዩት፤ ከህዝቡ፡ ጋር፡ የሚቆምበት፡ “ስድሳ፡ ስድስት፤ ስድሳ፡ ስድስትን” የሚሸትና፡ የሚመስል፡ ጊዜ፡ እያየን፡ ነው። ይህን፡ እድል፡ በጥበብ፡ ለመጠቀም፡ የህወሃትን፡ ፈቃድ፡ አይጠይቅም።

ይህን፡ ግንዛቤ፡ ለማቅረብ፡ ያስቻሉኝ፡ ምልክቶችና፡ ምክንያቶች፡ እነሆ። በመሬት፡ ነጠቃና፡ በህዝብ፡ መፈናቀል፡ የተነሳ፡ የጋምቤላ፡ ህብረተሰብ፡ እራሱን፤ ክብሩን፤ ጥቅሙን፡ ለማስከበር፤ በህይወቱ፡ መስዋእት፡ እየከፈለ፡ ነው። የኦጋዴን፡ ህብረተሰብ፡ አሁንም፡ ለመብቱ፡ እየሞተ፤ ዋጋ፡ እየከፈለ፡ ለመብቱ፡ ይታገላል። የአፋር፡ ህብረተሰብም፡ እንደዚሁ። የኦሮሞ፡ ህብረተስብ፡ በህይወቱ፡ ዋጋ፡ ሲከፍል፡ ቆይቷል፤ አሁንም፡ እየከፈለ፡ ነው። በስሜን፡ ኢትዮጵያ፡ የጎንደር፡ ክፍለ፡ ሃገር፡ ህዝብ፡ የህዋሃት፡ መንግስት፡ የውስጥና፡ የውጭ፡ የመሬት፡ ነጠቃ–ለሱዳን፡ መንግስት፡ በምስጢር፡ ለም፡ መሬት፤ ደንና፡ ወንዞች፡ ከህግ፡ ውጭ፤ ህዝቡን፡ ሳያማክር፡ የሚያደርገውን፡ አገርና፡ ደንበር፡ ለዋጭ፡ ተግባር፡ ሲቃወም፡ መቆየቱን፡ ታሪክ፡ ይመስክራል። ከጥቅም፡ ላይ፡ ያልዋለ፡ ሰፊ፡ መሬት፡ አለ፡ የሚለው፡ ህወሃት፤ የጥንት፡ ቅርስ፡ የሆነውን፤ ለተከታታይ፡ ትውልድ፡ መታወቂያና፡ መኩሪያ፤ መተኪያ፡ የማይገኝለትን፡ የዋልድባ፡ ገዳም፡ ለም፡ መሬት፡ ለስኳር፡ ፋብሪካ፡ በሚል፡ ሲያርሰው፡ ህብረተሰቡ፡ በህይወቱ፡ ዋጋ፡ ለመክፈል፡ መዘጋጀቱን፡ እያሳየ፡ ይገኛል። ይህ፡ ጥሪት፡ የጎንደሬ፡ አማራ፡ ብቻ፡ አለመሆኑን፡ አውቆ፡ አብሮ፡ መሰለፍ፡ የህወሃትን፡ ፈቃድ፡ አይጠይቅም። ሌላው፤ የኢትዮጵያ፡ ገበሬ፡ መሬት፡ ጠቦት፡ ሊለማ፡ የሚችልውን፡ ለም፡ መሬትና፡ ደጋፊውን፡ ወንዝ፡ በብዛት፡ ሆነ፡ ብሎ፡ 36 አገሮችን፤ 8,000 የውጭ፡ ግለሰብ፡ ሃብታሞችን፡ ለም፡ ጋብዞ፡ ሲያቀራምት፤ ይታያል። ይህ፡ ከእርሻ፡ መሬት፡ ጋር፡ የተያያዘ፡ አዲስ፡ የቅኝ፡ ገዦች፡ ግብዣ (colonization by invitation) መላውን፡ ህዝብ፡ እንዳሳሰበው፡ ምልክቶች፡ አሉ። ይህን፡ እያደረገ፡ ዙሮ፡ ዋልድባን፡ ለስኳር፡ ማምረቻ፡ አርሳለሁ፡ ማለቱ፡ የሚያሳየው፡ የፖለቲካ፡ እቅዱን፡ እንጂ፡ ለጎንደር፤ ወይንም፡ ለመላው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ እድገትና፡ ደህንነት፡ መቆሙን፡ አይደለም። ጉዳቱ፡ ለጎንደር፡ ህዝብ፡ ብቻ፡ ሳይሆን፡ ለመላውን፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፤ በተለይ፡ የክርስትና፡ ሃይማኖት፡ ተከታይ፡ ለሆነው፡ ነው፡ ለማለት፡ ያስችላል፡፡ ስለሆነም፡ አብዛኛውን፡ የሃይማኖት፡ ተከታይ፡ ሁሉ፡ አስቆጥቶታል፤ አስነስቶታል። እኔ፡ እንደማየው፡ ዋልድባ፡ የሚፈለገው፡ የጎንደርን፡ ህብረተሰብ፡ ኑሮ፡ ለማሻሻል፡ ሳይሆን፡ ይህን፡ የመንፈሳዊ፡ ማማና፡ ለም፡ መሬቱን፡ ወደ፡ ትግራይ፡ ለመጠቅለል፡ ነው። የጎንደር፡ ህዝብ፡ ይህን፡ ሴራ፡ አውቆ፡ ትግሉን፡ ቀጥሏል። ስለሆነም፡ ለማንኛውም፡ የህብረተሰብ፡ ክፍል፡ ትግል፡ ሊሰጠው፡ የሚገባ፡ ድጋፍ፡ ለዚህም፡ ህብረተሰብ፡ ክፍል፡ መሰጠት፡ አለበት።

ሌላው፡ ማንም፡ ሊክደው፡ የማይችል፡ የኑሮ፡ ውድነትና፡ የዋጋ፡ ግፍሸት፡ በየቀኑ፡ ማደግ፤ የነፍስ፡ ወከፍ፡ የገቢ፡ አለማደግ፤ የሃብትና፡ የኑሮ፡ ሁኔታ፡ በሚያሰቅቅ፡ ደረጃ፡ መራራቅ (gross income inequality) የሰብአዊ፡ መብቶች፡ መገፈፍ፤ ሁኔታው፡ ያስመረረው፡ አስተማሪ፡ የሰላም፡ ተቃውሞውን፡ አገር፡ አቀፍ፡ በሆነ፡ ደረጃ፡ ማቅረቡ፡ የአደባባይ፡ ምስጢር፡ ናቸው። በአጼ፡ ሃይለ፡ ስላሴ፡ ዘመነ፡ መንግስት፡ የአብዮት፡ ቀስቃሽ፡ ሆኖ፡ አገራችን፡ ለለውጥ፡ ያሸጋገራት፡ ዋናው፡ የህብረተሰብ፡ ክፍል፡ የአስተማሪወች፡ ተሳትፎ፡ ነው፡ ብል፡ አልሳሳትም። የእስልምና፡ ሃይማኖት፡ ተከታዮች፡ ህወሃት፡ በእምነት፡ ውስጥ፡ ገብቶ፡ የሚያደርገውን፡ ብጥብጥና፡ መከፋፈል፤ ሃይማኖትን፡ ለፖለቲካ፡ ስልጣን፡ መሳሪያ፡ ማድረግ፡ ተቃውመው፡ ከዘጠና፡ ሰባት፡ ወዲህ፡ ታይቶ፡ የማያውቅ፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ አድርገዋል።ብዙ፡ ሰላማዊ፡ ሰወች፡ ሙተዋል። ይህን፡ ሰላማዊ፡ ሰልፍ፡ የክርስትና፡ ሃይማኖት፡ ተከታዮች፡ እንደሚደግፉት፡ ይነገራል። ተስፋ፡ የሚሰጠው፡ እነዚህ፡ አንጋፋ፡ የሃይማኖት፡ ዘርፎች፡ ከጥንት፡ ጀምሮ፡ በሰላም፤ በመከባበር፤ የቆየውን፡ የኢትዮጵያዊነት፡ እሴት፡ ከስራ፡ ላይ፡ እያዋሉ፡ መሆናቸው፡ ነው። ይህ፡ የመተባበር፡ ሰላማዊ፡ ትግል፡ ከቀጠለ፡ ትኩረቱ፡ ከዋናው፡ የህወሃት፡ ከፋፋይ፡ ስርአት፡ ላይ፡ እንጂ፡ ከህዝብ፡ ክፍፍል፡ ላይ፡ አይሆንም፡ የሚል፡ ግምት፡ አለኝ። የታሪክ፡ ሃላፊነት፡ የሚጠይቀው፡ ይህን፡ ተባብሮ፡ አገርን፡ ከአደጋ፡ መከላከል፤ የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ በሙሉ፡ በሰላም፤ ከድህነት፤ ከእርሃብ፤ ከስደት፤ ከኋላ፡ ቀርነት፡ ነጻ፡ የሚሆንበት፡ ድልድይ፡ በየፊናችን፡ ማመቻቸትና፡ መገንባት፡ ብቻ፡ ነው።

በሌላ፡ በኩል፡ የምገነዘበው፡ በየቦታው፡ የምናየው፡ ይህ፡ ሁሉ፡ ያልተቀነባበረ፡ የሰላማዊ፡ ህዝብ፡ እንቅስቃሴ፡ አገር-ቤት፡ ሲካሄድ፡ በውጭ፡ ሆነ፡ በውስጥ፡ ያሉ፡ የፖለቲካና፡ የማህበራዊ፡ ስብስብስቦች፡ የማቀነባበር፤ የአቅጣጫ፡ መስጠት፤ የገንዘብ፤ የሃሳብ፤ የዲፕሎማቲክ፤ የሞራል፤ ድጋፍ፡ የመስጠት፡ ሚናቸው፡ አለመታየቱ፡ ለምን፡ ይሆን፡ የሚለውን፡ ነው። ከላይ፡ እንዳሳየሁት፤ ህወሃት፡ የፈጠረልን፡ የስነ-ሊቦና፡ ወጥመድ፡ ማነቆ፡ መሆኑ፡ አያጠራጥርም። መረዳት፡ ያለብን፤ አገር- ቤት፡ ለሚካሄደው፡ ሰላማዊ፡ የፍትህ፤የእርትህ፡ ትግል፡ ድጋፍ፡ የመስጠት፤ ያለመስጠት፡ አዛዡ፡ ህወሃት፡ አይደለም፤ ሊሆንም፡ አይችልም። የፖለቲካ፡ ሆነ፡ የማህበራዊ፡ እንቅስቃሴወች፡ ሁሉ፡ በህወሃት፡ አጀንዳ፡ አንመራም፡ ብለው፡ ካመኑ፡ ልዩ፡ ልዩ፡ እድሎችን፡ የመጠቀም፤ የማያያዝ፤ የመሰብሰብ፤ የማገናኘት፤ የማቀናጀት፤ (connecting the dots) አበይት፡ ተግባራቸው፡ መሆኑን፡ የመረዳት፡ ሃላፊነት፡ አለባቸው። አገር-ቤትም፡ ሆነ፡ ውጭ፡ የሚገኙ፡ የተቃዋሚ፡ ሃይሎች፡ ይህን፡ የተቀደሰ፡ ተግባር፡ ከስራ፡ ላይ፡ ለማዋል፡ በቅተው፡ ካልተነሱ፡ የታሪክ፡ ተጠያቂወች፡ ይሆናሉ፡ ለማለት፡ የምደፍረው፡ ለዚሁ፡ ነው።

በአጠቃላይ፤ ኢትዮጵያና፡ መላው፡ ሕዝቧ፡ የሚስፈልጋቸው፤ ከድህነት፤ ከእርሃብ፤ ከስደት፤ ከጥገኝነት፤ ከሃፍረት፤ ከፍርሃት፤ ከአድሎና፡ ከሙስና፤ ከማንኛውም፡ ዘርኝነት፡ ወዘተ፡ ነጻ፡ የሚያወጣቸው፤ በነጻ፡ ምርጫ፤ በህግ፡ የበላይነት፤ በእኩልነት፤ በመተሳሰብና፡ በመፈላለግ፤ በጋራ፡ ጥቅም፤ በጋራ፡ አገር፤ እሴቶችና፡ መሰረተ-ሃሳቦች፡ ላይ፡ የተመሰረተ፡ የፍትሃዊነትን፡ ምንነት፡ በሁሉ፡ ዘርፍ፡ እውን፡ የሚያደርግ፡ የፖለቲካ፡ አማራጭ፡ ጭብጥ፡ ማድረግ፡ ነው። ይህን፡ ለማመቻቸትና፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ የእራሱ፡ እድል፡ ወሳኝ፡ እንዲሆን፡ ያልተቆጠቨ፡ ድጋፍ፡ መስጠት፡ የህወሃት፡ አለቆች፡ ፈቃድ፡ አይጠይቅም።

በዚህ፡አጭር፡ ትንተና፡ እንዳሳየሁት፡ ለዚህ፡ ተስፋ፡ አስተዋጾ፡ ለማድረግ፡ በመጀመሪያ፡ እያንዳንዳችን፡ ካለፈው፡ ከመራራ፡ ፖለቲካ፤ ከቂም፡ በቀልነት፤ ከሃሜት፤ ከአሉባልታ፤ ከፍርሃት፡ ባህል፡ በተቻለ፡ መጠን፡ እራሳችን፡ ነጻ፡ ማውጣት፡ አለብን። ህወሃት፡ በቀባን፡ ወይንም፡ እራሳችን፡ በፈጠርነው፡ የጥላቻ፡ መርዝ፤ የሃሜት፤ የእርስ፡ በእርስ፡ መጠላለፍ፤ የጉራ፡ ወዘተ፡ ባህል፡ ተዘፍቀን፡ ለአሁኑና፡ ለወደፊቱ፡ ትውልድ፡ አርአያ፡ ለመሆን፡ እንችልም። ለዲሞክራሲ፡ ስርአት፡ አስተዋጾ፡ ለማድረግ፡ እራሳችን፡ ዲሞክራሲን፡ ከስራ፡ ላይ፡ ማዋል፡ አለብን። አለበለዚያ፡ ጸረ-ዲሞክራሲ፡ ከምንለው፡ ከህወሃት፡ የምንለይበት፡ መሰረት፡ ሊኖረን፡ አይችልም።
ይቀጥላል…

የታሪክ ተጠያቂዎች ሁነናል (አክሎግ ቢራራ)

Friday, April 20th, 2012

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

የህወሃትን ፡ አስከፊ ፡ አገዛዝ፡ ስናማርር፡ ሃያ፡ አንድ፡ አመታት፡ ቆይተናል። ይህ፡ የጠባብ፡ ዘረኛ፡ቡድን፡ ክተጠነሰሰበት፡ ወቅት፡ ጀምሮ፡ ሆነ፡ ብሎ፡ የሚያደርገውን፣ ሰላማዊ፡ ሕዝብ፡ ማሰቃየት፤ ሰብነት፡መግፈፍ፤ ማሳደድ፤ መግደል፤ከአገር፡ ማስወጣት፤ ማን፡ ገዥ፤ ማን፡ ተገዥ፡ እንደሆነ፡ ማሳመን፡ ሞክሩል። ማንን፡ ማጥቃት እንዳለበትም፡ ደንግጓል። ብዙ፡ በማስረጃ፡ የተደግፉ፡ ጽሁፎች፡ እንዳሳዩት፤ በተለይ፡ ኢላማ፡ አድርጎ፡ የተነሳው፡ የአማራው፡ ህብረተሰብ፡ ሰብነትና፡ ክብር፡ እንዲገፈፍ፤ በራሱ፡ ባህልና፡ ታሪከ፡ እንዲያፍር፡ ማድረግ፤ ራሱን፡ እንዲጠላና፡ አግብዳጅ፡ እንዲሆን፡ ማስገደድ፤ አስተዋጾው፡ ቀፎ፡ ነው፡ ብሎ፡ እንዲቀበልና፡ ራሱን፡ እንዲጠራጠር፡ ማሳመን፤ “የሕዝቦች፡ እስር፡ ቢት፡” ተብላ፡ በህወሃትና፡ በተመሳሳይ፡ ጠባብ፡ ዘረኛ፡ ክፍሎች፡ የምትጠራውን፡ ኢትዮጵያን፡ የአማራ፡ ህብረተሰብ፡ ለጭቆናና፡ ለዘረፋ፡ እንደዳረጋት፡ በማሳመን፡ የሞራል፡ ክስ፡ በአማራ፡ ህብረተስብ፡ ላይ፡ ለማቅረብ፡ መሞከር፤ ለዚህም፡ይህ፡ ህብረተሰብ፡ ሃላፊነትና፡ ተጠያቂነት፡ እንዳለበት፡ ለማሳመን፡ መጣር፤ ቀስ፡ በቀስ፡ ከሃብቱ፤ ከማሳውና፡ ከንብረቱ፤ ከሃገሩና፡ ከወገኖቹ፡ እየወጣ፡ ቁጥሩ፡ እንዲቀንስና፡ ለስደት፡ እንዲዳረግ፡ ለማድረግ፡ መጣር፡ ወዘተ፡ ናቸው። አሁን፡ በጉራ፡ ፈርዳ፤ የደቡብ፡ ክልል፡ ወስጥ፡ በሰላማዊ፡ ህጻናት፤ እናቶች፤ አባቶችና፡ በማሳቸው፡ የግብርና፡ ምዋያ፡ የሚተዳደሩ፡ የአማርኛ፡ ተናጋሪ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ላይ የሚያካሂደው፡ ኢስባዊ፡ መፈንቀልና፡ ለዘር፡ ጽዳት፡ ዳራጊ፡ ተግባር፡ ታሪክ፡ እየመዘገበው፡ ያለው፤ የህወሃት፡ ዋና፡ ዋና፡ መሪዮች፡ በህግ፡ የሚያስጠይቅ፡ ወንጀል፡ ነው።

ይህ፡ የኢትዮጵያ፡ ህብረተሰብ፡ አካል፡ ለዚህ፡ አሰቃቂ፡ የመፈንቀልና፡ የዘር፡ ማጽዳት፡ ድርጊት፡ ኢላማ፡ የሆነበት፡ ዋና፡ ምክንያት፡ ወንጀል፡ ስለሰራ፡ ሳይሆን፤ ለኢትዮጵያ፡ የተሰበጣጠረ፤ ጎን፡ ለጎን፡ አብሮ፡ በሰላምና፡ በመከባበር፡ ለሚኖር፡ ህብረተሰብ፡ ድልድይ፡ ስለሆነ፤ ለኢትዮጵያ፡ አንድነትና፡ ሏአላዊነት፡ ምሰሶ፡ ሆኖ፡ ስላገለገል፡ ነው። ከጅምሩ፤ የህወሃት፡ የዘር፡ ፖለቲካ፡ ፈጣሪወች፡ በኢትዮጵያ፡ “የማይታረቁ፡ ልዩነቶች” አሉ፡ በሚለው፡ “የከፋፍለህ፡ ግዛው፤” የፖለቲካ፡ አደረጃጀት፡ ስልት፡ የተጠቀሙትና፡ በዚህ፡ ላይ፡ የተመሰረተ፡ የክልል፡ ስራትን፡ ከስራ፡ ላይ ያዋሉት፡ ሕዝብ፡ ከሕዝብ፡ ጋር፡ ለማጋጨት፡ እንጂ፡ ለተጎዱ፡ የኢትዮጵያ፡ ህብረተስብ፡ ክፍሎች፡ በማሰብ፡ አይደለም። ለኢትዮጵያ፡ ሏላዊነትና፡ ለመላው፡ ሕዝቧ፡ ፍትሃዊ፤ ዲሞክራሳዊና፡ በእኩልነት፡ ላይ፡ የቆመ፡ አማራጭ፡ እውን፡ መሆን፤ የአማራው፡ ህብረተሰብ፡ ተመሳሳይ፡ ፍላጎት፡ ካላቸው፡ አጋሮቹ፡ ጋር፡ ሆኖ፡ አስተዋጾውን፡ እንደሚያደርግ፡ ስለሚታወቅ፡ ጭምር፡ ነው። በህወሃት፡ አለቆች፡ ግምት፡ ይህን፡ አብሮ፡ ተቻችሎ፡ የመኖር፡ እስየት፡ ለመከላከል፡ የአማራ፡ ሕዝብ፡ በተክታታይ፡ ያስመሰከረውን፡ ድልድይነት፡ መስበር፡ ይገባል፡ የሚል፡ ነው። ስለሆነም፡ የአማራ፡ ህብረተሰብን፡ አሰቃቂ፡ በሆነ፡ መንገድ፡ ከኑሮው፤ ከማሳው፤ ከሃብቱ፤ ከስራውና፡ ካለበት፡ ቦታ፡ ሁሉ፤ በሰላም፤ በክብርና፡ በርጋታ፡ እንዳይኖር፡ ማድረግ፡ የአማራ፡ ህብረተሰብ፡ ብቸኛ፡ ችግር፡ ነው፡ ማለቱ፡ አያዋጣም። የኢትዮጵያና፡ የኢትዮጵያዊያን፡ ፈታኝና፡ ወሳኝ፡ ችግር፡ ነው።

ስለ፡ ሆነም፤ እስክ፡ አሁን፡ በሚገባ፡ ያልመረመርነው፡ አበይት፡ ነገር ቢኖር፡ የዘረኝነት፡ አደጋውን፡ የምንቀበል፤ስራቱን፡ የምንቃወም፤ የሕዝባችን፡ ስቃይና፡ መከራ፡ በየቀኑ፡ የምናይ፤ ይሀ፡ ስብነትን፡ የተፈታተነ፡ ሰቆቃ፡ ከራሳችን፡ ድክመት፡ ጋር፡ የተያያዘ፡ መሆኑን፡ ጭምር፡ ነው። የኢትዮጵያ፡ ታሪክ፡ ተከልሶ፡ በውሸት፡ ሲጻፍ፡ ዝም፡ አልን። ህብረ-ብሂራዊ፡ ስራት፡ ቀስ፡ በቀስ፡ ሲናድ፡ ዝም፡ አልን። የሃገር፡ ሏላውይነት፡ እየተቦረቦረ፡ ሲናይ፡ ችላ፡ አልን። ምትክ፡ የማይገኝላቸው፡ አገራዊ፡ ተቋሞች፡ እየተናዱ፡ ስናይ፡ ድምጻቺን፡ ጠፋ። ለም፡ ማሳወች፡ ለውጭ፡ መንግስታትና፡ ድርጂቶች፤ ለምርጥ፡ ግለሰቦች፤ በጂምላ፡ ሲስጡ፡ ድምጽ፡ ሳነሰማ፡ ቆየን። መንፈሳዊ፡ አባቶቻችን፡ የሚጠቀሙበት፤ መተኪያ፡ የማይገኝለት፡ ምድርና፡ ደን፤ ተከታታይ፡ መንግስታት፡ ያከበሩት፡ የዋልድባ፡ ገዳም፡ ለህወሃት፡ ደጋፊ፡ ድርጂቶችና፡ ታማኞች፡ ለስኳር፡ ማምረቻና፡ ፋብሪካ፡ ሲቆፈር፡ እያየን፡ አንዳንዶቻችን፡ ድምጽ፡ ስናሰማ፡ ብዙወቻችን፡ የቁም፡ ተመልካች፡ሆነን፡ ቆይተናል። የአማራ፡ ሕዝብ፡ ልክ፡ ለእርሱ፡ ብቻ፡ በመጣ፡ የወረርሽኝ፡ በሽታ፡ እዳለቀ፡ ሁሉ፡ ቁጥሩ፡ እንደቀነሰ፡ ወይንም፡ በፈቃዱ፡ ማንነቱን፡ እንደለወጠ፡ ተደርጎ፡ በሚያስደነግጥና፡ በሚያናድድ፡ ደረጃ፡ ቁጥሩ፡ ከ፫፬፡ ሚሊዮን፡ ወደ፡ ፩፯ ሚልዮን፡ እየቀነሰ፡ እያየን፡ ዝም፡ ብለናል። ይህ፡ ህዝብ፡ ቁጥሩ፡ የቀነሰው፡ ወደ፡ ጨረቃ፡ ስለተጓዘ፡ እንዳልሆነ፡ እውቅ፡ ነው። ታድያ፡ የት፡ ደረሰ፡ ለማለት፡ ይቻላል። ከአማራ፡ ክልል፡ ውጭ፡ ይኖር፡ የነበረው፡ የአማርኛ፡ ተናጋሪ፡ ወይንም፡ ህወሃት፡ “አማራ፡ እንጂ፡ ኢትዮጵያዊ፡” አይደለህም፡ ብሎ፡ የደነገገበት፡ ሕዝብ፡ ሆነ፡ ተብሎ፡ ማንነቱን፡ እንዲለውጥ፤ ቀስ፡ በቀስ፡ የመጥፋት፡ እድሉ፡ ጠለቅ፡ እንዲል፡ ለማስገደደ፡ መሆን፡ አለበት። አለበለዚያ፡ በ፪፩ኛው፡ መቶ፡ ክፍለ፡ ዘመን፡ የዚህ፡ አይነት፡ የሰብነት፡ ገፈፋ፡ ባልተካሃደ፡ ነበር።

የህወሃት፡ መሪ፡ አላማ፡ የአማራ፡ ቁጥር፡ ሲቀንስ፡ የሚያስከትለው፡ የኣማራው፡ አቅምና፡ ጉልበት፤ ያለው፡ አገር፡ አቀፍ፡ ሚና፡ ይለወጣል፡ የሚል፡ ነው። ቀስ፡ በቀስ፡ የአማራው፡ ሕዝብ፡ ቁጥር፡ ወደ፡ ነኡሰነት፡ ይቀየራል፡ የሚል፡ ዘገባ፡ ስላለም፡ ነው። የሚያሰጋው፡ ቢቻል፡ ህልውናው፡ ጭራሽ፡ እንዲጠፋ፡ መሆኑ፡ ነው። ሆኖም፤ ህወሃት፡ ቢወድም፡ ባይወድም፡ አመራሩ፡ ሊለውጠው፡ የማይችለው፡ ሃቅ፡ ግን፡ ይህን፡ ይመስላል። አማርኛ፡ ተናጋሪወች፡ የአማራ፡ ህብረተሰብ፡ አባላት፡ ብቻ፡ አይደሉም። በአሁኑ፡ ወቅት፤ ቢያንስ፡ ከ፱፻ ሚሊዮን፡ ሕዝብ፡ ፸ ሚሊዮን፡ የሚሆነው፡ አማርኛ፡ ተናጋሪ፡ ነው። ቢያንስ፡ ፶ በመቶ፡ የኢትዮጵያ፡ ህዝብ፡ ድብልቅ፡ ነው። አንደ፡ አማራ፡ ህብረተሰብ፡ ክሁሉ፡ ህብረተስብ፡ ጋር፡ አብሮ፡ የሚኖር፤ የሚጋባ፤ የተደበላለቀ፡ አለ፡ ለማለት፡ አስቸጋሪ፡ ነው። የህወሃት፡ ጠባብ፡ ዘረኛ፡ ቡድን፡ ይህን፡ ሃቅ፡ በምንም፡ ሊቀይረው፡ አይችልም። ሆኖም፡ አማርኛ፡ ተናጋሪው፡ በያለበት፡ የራሱን፡ ህልውና፡ የመጠበቅ፡ ስልት፡ መሻት፡ አለበት፡ የሚለው፡ አስተሳሰብ፡ የወቅቱ፡ አንገብጋቢ፡ ጉዳይ፡ መሆኑ፡ አያጠራጥርም፤ አያከራክርም።

ይህ፡ መረጃ፡ እንዳለ፡ ሆኖ፡ አሁንም፡ የምናየው፡ ተከታታይ፡ ድክመት፡ የእኛው፡ ነው። የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ብዙ፡ የወል፡ እሲየቶች፡ እንዳሉት፡ ከተቀበልን፡ ከሚያራርቁን፡ ንኡስ፡ ነገሮች፡ ላይ፡ ማተኮራችን፡ ለዚህ፡ በዳይ፡ ስራት፡ ምርኮኛ፡ መሆናችን፡ ያሳያል። ተስማምተን፡ ለመስራት፡ ካልቻልን፤ ይህ፡ አሰቃቂ፡ ስራት፡ ይቀጥላል። ጥሩው፡ ነገር፤ በአሁኑ፡ ወቅት፡ የራሳችን፡ ድክመት፡ ለወገኖቻችን፡ ሆነ ለአገራችን፡ አስከፊ ጉዳት፡ ማምጣቱን፡ ከልባችን፡ ለማመን፡ ሙከራ፡ የምናደርግ፡ እየበዛን፡ ሂደናል። ይህ፡ ጥሩ፡ ጅመራ፡ ነው። ግን፡ በቂ፡ አይደለም። ብዙ፡ ስራወች፡ ከፊታችን፡ ይጠብቁናል። አሁንም፡ ካሉ፡ ችግሮቻችን፡ መካከል፡ የለውጥን፡ ጠቃሚነት፡ በሚገባ፡ አለማስቀመጥ፤ አለመተማመን፤ ለጥቅም፡ መገዛት፤ እውነትን፡ በድፍረትና፡ በጨዋነት፡ አለማሳየት፤ ራስ፡ወዳድነት፤ፍርሃትና፡ መከፋፈል፡ ይገኙበታል።

የህወሃት፡ መንግስት፡ ዞሮ፡ዞሮ፡ የአንድ፡ ክልል፤ እንዲያውም፡ የአንድ፡ መንደር፡ የበላይነት፡ መንግስት፡ መሆኑን፡ አሁን፡ ሳይሆን ስልጣን ከያዘበት፡ ጀምሮ፡ እንዳሰመረበት፡ ብናውቅም፤ ለዚህ፡ ችግር፡ መፍቻ፡ ተባብረን፡ ለመስራት፡ የተነሳን፡ ጥቂቶች፡ ነን። ይህን፡ ድክመት፡ አለመገንዘብ፡ ቂልነት፡ ወይንም፡ አውቆ፡ የስራቱ፡ ተባባሪ፡ መሆን፡ ነው። የችግሩን፡ ክብደት፡ በሚገባ፡ የማመዛዘኑን፡ ጥበብ፡ ካላወቅን፡ መፍትህየ፡ ለመጠቆም፡ አንችልም፤ የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ ለመርዳት፤ ታሪክ፡ ያላትን፤ ለጥቁር፡ ህዝቦች፡ ሁሉ፡ አራያ፡ የነበርችውን፡ ኢትዮጵያን፡ ካለችበት፡ ፈተና፡ ለማዳን፡ አንችልም። ልዩነቶችን፡ ወደ፡ ጎን፡ አድርገን፡ በመተባበር፡ ከሰራን፡ ግን፡ ምንም፡ ሃይል፡ አያግደንም። የአረብ፡ አገሮች፡ በሕዝብ፡ የተመሩ፡ ለውጦች፡ የሚያሳዩን፡ አቅጣጫ፡ ይህን፡ ነው። እኛም፡ የራሳችን፡ ልምድ፡ አለን። ምርጫው፡ የእኛው፡ ነው።

አንዱ፡ መረዳት፡ ያለብን፤ ይህ፡ ነው። ገንቢ፡ ለውጥ፡ ለማምጣት፡ የሚቻለው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ለመነሳት፡ ሲወስንና፡ ተባብሮ፡ ለፍትህ፤ ለርትእ፤ ለእኩልነት፤ ለሰላም፤ ለዲሞክራሲ፤ ለህግ፡ የበላይነት፡ ወዘተ፡ ሲነሳ፡ ብቻ፡ ነው። የመነሳት፡ ልምድ፡ አለው። ለመነሳት፡ እንደሚፈልግ፡ ብዙ፡ ምልክቶች፡ አሉ። ውጭ፤ ያለን፡ ለአገርና፡ ለሕዝብ፡ ሰብአዊ፡ መብት፡ የቆምን፡ ተረዳድተን፡ ለአገርና፡ ለሕዝብ፡ በማንኛውም፡ መንገድ፡ የማያቋርጥ፡ ድጋፍ፡ መስጠት፡ ግዲታችን፡ የሚሆነው፡ ለዚህ፡ ነው። ይህን፡ ለማድረግ፡ የሚጎድለን፡ ገንዘብና፡ እውቀት፡ ሳይሆን፡ ፈቃደኛነትና፡ ቁርጠኝነት፡ ነው።

ህወሃት፡ ያጠመደልንን፡ ወጥመድ፤ የብዙ፡ ማህበረ፡ ሰብን፡ አገር፡ በዘር፡ መከፋፈል፡ ችላ ብለን፤ ካለንበት፡ ደረጃ፡ ደርስናል። ይህ በራሳችን፡ ድክመት፤ በራሳችን፡ መበታተን፤ በራሳችን፡ እርስ፡በእርስ መኮራረፍ፤ በራሳችን አገር ሳይኖረን፡ ከፖለቲካ ዉድድር፡ ላይ፡ ማተኮር፤ በራሳችን ራስ ወዳድነት፤ በራሳችን፡ ትእቢት/ጉራ፤ በራሳችን ፍርሃት እና በራሳችን፡ ስንፍና፤ ህወሃት፡ ባጠመደልን፡ ወጥመድ፡ ገብተን፡ እርስ፡ በእርስ ሰንጣላ፡ ወገኖቻቺን፡ የመሪ ያለህ፤ የድርጅት ያለህ፤ እያሉ ነው። ህወሃት፡ እየነጣጠለ፡ ሲመታን፡ አደጋው፡ እኛጋ፡ እስከሚደርስ፡ የምንጠብቅ፡ ብዙ፡ ነን። ምንም፡ እንኳን፡ ኢትዮጵያ፡ በምንም፡ ትጠፋለች፡ ብየ፡ ባላምንም፤ አሁን፡ ከዱሮው፡ በመረረ፡ አገር፡ የማጣት፡ እድላችን ያመዝናል፡ የሚለው፡ ትንተና፡ ቁም፡ነገር፡ እንዳለው፡ እጋራለሁ። ኢትዮጵያ፡ የሱማልያ፤ የርዋንዳ፤ የላበሪያ፤ የኮንጎ፡ ኪንሻሳ፡ አይነት፡ እድል፡ ሊገጥማት፡ ይችላል፡ ብሎ፡ ለአላማ፡ አንድነት፡ መሰብሰብ፡ ከማንኛውም፡ ወቅት፡ የበለጠ፡ አስፈላጊ፡ ነው። የመጀመሪያው፡ መሰረተ፡ እምነት፡ የኢትዮጵያ፡ መንፈስ፡ በምንም፡ አይናጋም፤ ኢትዮጵያ፡ የምትባል፡ አገር፡ አገራችን፡ ናት፤ ታሪካችን፡ የአንድ፡ ነገድ፤ ወይንም፡ የአንድ፡ ዘር፤ ወይንም፡ የአንድ፡ ሃይማኖት፡ ብቻ፡ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ፡ የጋራችን፡ ናት፤ተባብረን፡ መድረስ፡ የሁላችን፡ ሃላፊነት፡ ነው፡ ማለት፡ ስንችል፡ ብዙ፡ ነገሮች፡ መልክ፡ እንደሚይዙ፡ ማመንታት፡ የለብንም። ይህ፡ ሊሆን፡ የሚችለው፡ እኛ፤ በተለይ፤ ተማርን፡ የምንለው፡ የድሃ፡ ህዝብ፡ በረከት፡ ውጥየቶች፡ እንደገና፡ ለመማር፡ ፈቃደኛ፡ ሆነን፡ በዘር፡ የተቀባና፡ የተመረዘ፡ የፖለቲካና፡ የስነልቦና፡ ፍልስፍና፡ ስናስወግድ፡ ነው።

ራሳችን፡ ሳንለውጥ፡ ለማንም፡ የለውጥ፡ ሃዋርያ፡ ለመሆን፡ አንችልም። ስራቱ፡ ባስቀመጠልን፡ መርዝ፡ አዙሪት፡ ታውከን፡ ለውጥ፡ አናመጣም። እንዲያውም፡ ራሳችን፡ ካልለወጥን፡ የችግሩ፡ አካል፡ እንሆናለን። በቋንቋ፡ ብቻ፡ ተለያይተን፡ መላው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ የደማላትን፤ የሰው፡ ፍጥረት፡ መነሻ፡ የሆነችውን፡ አኩሪ፡ አገር፡ ብናጣ፡ ውርደቱ፡ የሁላችን፡ ነው። ህወሃት፡ ቋንቋን፡ እንደ፡ ማነቆና መለያያ፡ አድርጎ፡ ለመሳርያ፡ የሚጠቀምበት፡ የተቆላለፈውን፡ ህብረተስብ፡ ለመበታተን፡ ነው። ተቆላላፊነት፤ አብሮ፡ በሰላም፡ መኖር፤በጋራ፡ አገርን፡ መጠበቅ፤ ዘላቂነትና፡ ፍትህ፡ ያለበት፡ ስራት. መሻት፡ ከጥሩ፡ እስየቶቻቺን፡ መካከል፡ ተቀዳሚነት፡ አላቸው። ህወሃት፡ ይህን፡ ህብረ፡ ብሂየራዊ፡ የተስፋ፡ ቅርስ፡ እየናደው፡ ነው።

ለዚህ፡ አስተሳሰብ፡ ዋና፡ የመደምደሚያ ምክንያት፡ ፈላጭ፡ ቆራጭ፡ የሆነው፡ የመለስ፡ መንግስት የራሱን ህገ መንግስት ፣ አንቀጽ፡ ፫፪ን፡ ሙሉ በሙሉ ጥሶ፡ የዘር ማጥፋት ፡ ኢላማውን፡በተባባሰ፡ ሁንየታ፡ በአማራ ሕዝብ፡ ላይ መዘርጋቱ ፡ አዲስ፡ መለኪያ፡ ስለሆነ፡ ነው። ህግ፡ በማይከበርበት፡ አገር፡ በሰላም፡ ለመኖር፤ ኑሮን፡ ለማሻሻል፤ለማደግ፤ ንብረት፡ ለማፍራት፡ አይቻልም። አሁን፡ የምናየው፡ ኢትዮጵያዊነት፤ የማንኛውም፡ ኢትዮጵያ፡ ተወላጅ፡ መብት፡ ሳይሆን፡ ህወሃት፡ እንደፈለገ፡ የሚሰጠው፤ አንደፈለገ፡ የሚነጥቀው፡ ሁኗል። ማንም፡ በኑሮው፤ በማሳው፤ በሃብቱ፤ በሰብነቱ፡ ሊመካ፡ ከማይችልበት፡ ደረጃ፡ ላይ፡ ደርሰናል። ማንም፡ በአገሩ፡ ሊኖር፡ አይችልም። ማንኛውም፡ መብት፡ ከመቅጽበት፡ ሊወሰድ፡ እንደሚችል፡ ደጋግመን፡ አይተናል። የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመንቀሳቀስ፡ ወዘተ፡ መብቶች፡ ሁሉ፡ እንደ፡ ችሮታ፡ በህወሃት፡ የሚሰጡ፤ እንደቅጣት፡ የሚነሱ፡ ሆነዋል። የሕዝብን፡ ሰቆቃ፡ ከህገ፡ መንግስቱ፡ አንጻር፡ ብናየው፡ ይህኑ፡ ጸረ፡ ፍትህ፤ ጸረ፡ እርትእ፤ ጸረ፡ ርጋታ፤ ጸረ፡ ኢትዮጵያዊነት፤ ጸረ፡ዘላቂነትና፡ ጸረ፡ተሳትፊያዊነት፡ እድገት፡ ነው። ሰው፡ በሃገሩ፤ ሃብት፡ ለመያዝ፤ ለመኖር፤ ለመንቀሳቀስ፤ ማሳ፡ ኑሮት፡ ለማረስ፤ ራሱን፡ ለማሻሻል፡ ካልቻለ፡ ዚየግነቱ፡ የት፡ ላይ፡ ሊሆን፡ እንደሚችል፡ ለማወቅ፡ አይቻልም። የበላይ፡ አዛዦችን፡ ባህርይና፡ ተግባር፡ የሚያሳይ፡ ሰእል፡ ከፊታችን፡ ተደቅኖ፡ የሚታይ፡ ለዚህ፡ ነው። የህግ፡ መከበር፡ ለሰላምና፡ ርጋት፤ ለእኩልነትና፡ እድገት፤ ለዚግነት፤ ለአገራችን፡ ተክታታይነት፡ ቁልፍ፡ነው። ይህ፡ ርጋታና፡ ዘላቂነት፡ የአማራ፡ ሆነ፡ ልዩ፡ ልዩ፡ የህብረተሰብ፡ ክፍሎች፡ በተለያየ፡ ወቅት፡ በህይወታቸው፡ ዋጋ፡ እየከፈሉበት፡ ነው። በታሪካችንም፡ በህይወታቸው፡ ዋጋ፡ ከፍለውበታል።

ህጉ፡ ምን ፡ ይላል?

ህጉ፡ የሚለውን፡ አይቶ ማነው፡ ወንጀለኛ፡ ብሎ፡ ማመዛዝን የሁላቺንም፡ አጣዳፊ፡ ተግባርና፡ ሃላፊነት ነው። “ማንም ፡ ኢትዮጵያዊ፡ ወይንም ፡ በህግ፡ በኢትዮጵያ፡ የሚኖር፡ ሁሉ በአገሩ፡ ለመንቀሳቀስና፡ ለመኖር መብቱ ነው፡” የሚለው ህግ ማን በዚህ፡ ህግ፡ ለመጠቀም፤ ማን፡ ለመኖር፤ ማን ላለመኖር እንደሚችል በተግባር፡ እየመሰከረ ነው። የአማራ፡ ሕዝብ፡ የዚህ፡ መብት፡ ተሳታፊ፡ አይደለህም እየተባለ፡ ነው። የዚህ፡ ህብረተስብ፡ አገዳ፤ በሃይል፡ መሰደድ፤ መፈንቀል፤ ከማሳው፡ መወገድ፡ ወዘተ፡ ከፖለቲካ፡ የበላይነትና፡ ከተፈጥሮ፡ ሃብት፡ ቁጥጥር፡ ጋር፡ የተያያዘ፡ መሆኑ፡ ብዙ፡ ማስረጃ፡ አለ። አይጋ ፡የተባለው፡ የህወሃት (ድረ፡ ገጽ)፡ እና፡ በአዲስ፡ አበባ፡ ነዋሪ፡ የሆነች፡ የፓርቲው፡ ደጋፊ፡ ወይዘሪት፡ ሚሚ ሰብሃቱ፡ ያሉትን፡ ስናይ፡ ነገሩ፡ አስክፊ፡ ደረጃ ፡ ላይ መድረሱንና፡ ፕሮፓጋንዳ፡ እንደ፡ እውነት፡ የሚነገር፡ መሆኑን፡ ያሰምርልናል። ሁለቱም፡ የፖለቲካ፡ እንጅ፡ የህግ ምንነትን፡ ለማሳየት፡ አልሞከሩም፤ አልፈለጉም። አብዛኛው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ የሚለው፤ በአሁኑ፡ ወቅት፤ ያለምንም፡ ገደብ፤ የትም፡ ቦታ፡ ለመኖር፤ ለመስራት፤ ለመግዛት፤ ቦታና፡ ማሳ፡ ለመመራት፤ ስራ፡ ለማግኘት፡ የከፍተኛ፡ ትምህርት፡ እድል፡ ለማግኘትና፡ ሃብት ለመያዝ የሚችሉ፡ የፓርቲው፡ ባለስልጣኖችና፡ ከፍተኛ፡ አባላት፤ ሁነኛ፡ ደጋፊወች፤ ምርጥ፡ የትግራይ፡ ተወላጆች፤ የውጭ፡ ባለሃብቶች፡ ብቻ፡ ናችው።ሁላችንም፡ እዚህ፡ ግንዛቢየ፡ ላይ፡ብንደርስ፡ አያስደንቅም። ለዚህ፡ የህዝብ፡ አስተሳሰብ፡ ዋና፡ ምክንያት፡ የሆነው፡ ስራቱ፡ በይፋ፡ የሚያደርገው፡ አይን፡ ያወጣ፡ በበላይ፡ ባለስልታኖች፡ ብልግና፤ በህወሃት፡ ወገናዊ፡ አድሎና፡ ዘረፋ፡ ነዉ፡፡ ሑለቱም፡ ከላይ፡ የተጠቀሱት፡ ደጋፊወች፡ ያሉት እንዲህ ነው።

ካሉበት፡ ተገደው፡ የወጡት፤ ሰብነታቸውን፡ ህወሃት፡ የገፈፈው፡ አማራዎች “ከህግ ዉጭ፡ ባልተፈቀደላቸው፡ ቦታ፡ ሰለሚኖሩ” ነው፤ ይላል። እነሱ፡ በሃገራቸው፡ “ህገ፡ወጥ፡” ናቸው፡ ማለት፡ ነው።እዚህ፡ ላይ፡ ብቻ፡ የሚያጠያይቀው፡ የአማራ፡ ህብረተሰብ፤ ህገ-ወጥ፡ ከሆነ፡ የትግራይ፡ተወላጆችን፡ ከትግራይ፡ ውጭ፡ ለመኖር፤ ለመስራት፤ የከተማ፡ ቦታና፡ ማሳ፡ የትም፡ ክልል፡ ውስጥ፡ ለመያዝ፤ ሃብት፡ለማከማቸት፤ የትም፡ ቦታ፡ ለመነገድ፡ ወዘተ፡ ማን፡ ህጋዊ፡ አደረጋቸው፡ ብሎ፡ አንድ፡ ሰው፡ ቢጠይቅ፡ መልሱ፡ እንቆቅልሽ፡ ነው። አጋላጭ፡ ነው። ከዚህ፡ ላይ፡ ታሪክ፡ የሚመዘግበው፡ የኢትዮጵያዊነት፡ መለኪያ፡ ጋዚየጣዊ፡ መግጫ፡ ከሰጡት፡ የፖለቲካ፡ ድርጅቶች፡ መካከል፡ አንዱ፡ የኢትዮጵያን፡ በእኩልነት፡ የተመሰረተ፡ አንድነት፡ የሚደግፍ፡ የኦነግ፡ ከፍል፡ በዚህ፡ ወር፡ አጋማሽ፡ ላይ፡ “ህወሃት፡ በሰላማዊ፡ የአማራ፡ ህብረተሰብ፡ ላይ፡ የሚያደርገው፡ ኢሰባዊ፡ መፈንቀል፤ ያለ፡ አግባብ፡ በሃይል፡ ከማሳና፡ ኑሮ፡ አስገድዶ፡ ማስወጣት፡ ወንጀል፡ ነው” ያለው፡ እንከን፡ የለውም። በተለይ፡ ይህ፡ ድርጊት፡ በህጻናት፤ በአናቶች፤ በአባቶች፤ በማሳ፡ የግብርና፡ ስራ፡ የተሰማሩ፡ ኢትዮጵያዊያን፡ ላይ፡ የሚደረገው፡ ዘመቻ፡ ህዝብን፡ ከህዝብ፡ ጋር፡ ለማጋጨት፤ እርስ፡ በእርስ፡ ለማጣላት፤ ብሎም፡ የህወሃትን፡ የፖለቲካና፡ የተፈጥሮ፡ ሃብት፡ የበላይነት፡ ለቡድኑ፡ ለማስተላለፍ፡ ስለፈለገ፡ ነው፡ የሚለው፡ አግባብ፡ አለው። የሰውን፡ ስሚት፡ በመቀስቀስ፤ የኢትዮጵያን፡ ህዝብ፡ እርስ፡ በእርስ፡ ከማጣላት፡ ባሻገር፡ ለማንኛውም፡ ህብረተሰብ፡ ክፍል፡ አይበጅም። የኦነግ፡ መግለጫ፡ የህወሃት፡ ደጋፊዎወችን፡ ሁሉ፡ ያጋልጣል። ሆኖም፡ የኢትዮጵያን፡ ሕዝብ፡ ያቀራርባል። ተቻችሎ፡ ሰላምን፤ የሕዝብ፡ መብትን፤ በእኩልነት፡ አዲስ፡ የትግል፡ምራፍ፡ ለመክፈት፡ ያመቻቻል፤ በር፡ ይከፍታል።

አይጋ፡ በተለይ ያለው፡ የሚዘገንን፡ አባባል፡ “የአማራው ሕዝብ የአካባቢውን፡ ነዋሪወች፡ አንጡራ፡ የተፈጥሮ፡ ሃብት ወስደ። ይህ፡ ማራቆትና፡ እና፡ ማደህየትን ያመጣል።” የትም፡ ሃገር፤ ማንኛውም፡ የሃገር፡ ተወላጅ፡ በዚግነቱ፡ አገሩ፡ ውስጥ፡ ሰርቶ፡ መኖር፡ የአካባቢ፡ ህዝብ፡ ይጎዳል፡ ሲባል፡ የመጀመሪያ፡ መሆኑ፡ ነው። በአሁኑ፡ ወቅት፡ ለሙሉ፡ ዘረፋ፤ ሙስና፤ ያለ፡ አግባብ፡ በአመት፡ ከ፫፡ ቢሊዮን፡ ዶላር፡ በላይ፡ ወይንም፡ ከአምሳ፡ አምስት፡ ቢሊዮን፡ የኢትዮጵያ፡ ብር፡ በላይ፡ ከአገር፡ ህገ-ወጥ፡ በሆነ፡ መልክ፡ የሚያሸሽ፡ ማን፡ እንደሆነ፡ የውጭ፡ አገር፡ ዘገባወች፡ ያሳያሉ። እነዚህ፡ የስራቱ፡ አዲስ፡ ተጠቃሚወች፡ በአንድ፡ በኩል፡ የትም፡ ለመኖር፤ የትም፡ ሃብት፡ ለማካበት፤ የትም፡ ለመንቀሳቀስ፤ የትም፡ የተፈጥሮ፡ ሃበት፡ ለመያዝ፤ የትም፡ ለመዝረፍና፡ እቃና፡ ገንዘብ፡ እንደልብ፡ ለማሸሽ፡ ወዘተ፡ ይችላሉ። የፖለቲካ፡ የበላይነት፡ ለስርቆት፤ ለአድሎ፤ገንዘብ፡ ለማሸሽ፤ ወዘተ፡ እየረዳ፡ እናየዋለን።

በአሁኑ፡ ወቅት፡ አዲስ፡ አበባ፡ ቦልየ፡ ሰፈር፡ የምርጥ፡ ትግራይ፡ መኮንኖች፡ በርካታ፡ ሰማይ፡ ጠቀስ፡ ፎቆች፤ ግምታቸው፡ እያንዳንዳቸው፡ ክ45 እስክ 90 ሚሊዮን፡ ብር፡ (ክባንክ፡ የመጣ)፡ የሚሆን፡ ስለተደረደሩበት፡ ይህን፡ አካባቢው፡ ሕዝቡ፡ “ክልል፡ አንድ” ብሎታል። ይህ፡ ስም፡ የትግራይ፡ ክልል፡ መሆኑን፡ አንባቢው፡ ይረዳዋል፡፡ የህወሃት፡ ደጋፊወች፡ የማይቀበሉት፡ የስልጣንና፡ የሃብት፡ ክምችት፡ መብት፡ ለትግራይ፡ ገዢ፡ ቡድንና፡ ታማኝ፡ ደጋፊወች፡ ብቻ፡ ነው፡ የሚለውን፡ የህወሃትን፡ የግል፡ ፍልስፍናና አመራር፡ ነው። በዚህ፡ ፍልስፍና፡ መሰረት፡ ይህ፡ ቡድን፡ ስልጣን፡ ላይ፡ ለመቆየት፤ ሃብት፤ ለማካበት፡ የግድ፡ ተወዳዳሪ፡ የሆኑ፡ ወይንም፡ ሊቀናቀኑ፡ ይችላሉ፡ የሚላቸውን፡ ሁሉ፡ ማቀበ፡ ወይንም፡ ማስወገድ፡ አለበት። ቁልፍ፡ የሆኑ፡ የተቋም፡ መሪወችን፡ ከደሞዛቸው፡ በላይ፤ ግልጽና፡ አሳፋሪ፡ በሆነ፡ መልክ፡ የፍጆት፤ የቅንጦት፡ አኗኗር፡ እንዲኖሩ፡ ያደርጋል። የህወሃት፡ ጀነራሎች፡ ታላላቅ፡ ፎቆች፡ ለመግዛትና፡ ወይንም፡ ለመገንባት፡ የቻሉት፡ በዚህ፡ “ደግፈኝ፡ እደግፍሃለሁ” በሚል፡ የስልጣን፡ ማቆያ፡ ስልት፡ ነው። ደጋፊወች፡ ለመቀበል፡ የማይፈቅዱት፡ ግን፡ አማራ፡ ሆነ፤ ኦሮሞ፤ አፋር፡ ሆነ፤ ሶማሊ፡ወዘተ፡ በሃገሩ፡ ያለ፡ ገደብ፡ ሊወዳደር፤ የግል፡ ሃብት፡ ለማቋቋም፡ አይችልም። የህወሃት፡ አመራር፡ ፈቃድና፡ ታማኝነት፡ ያስፈልገዋል። ጥቅሙ፡ መታየትና፡ መገምገም፡ አለበት። ማንኛውም፡ ማስረጃ፡ የሚያሳየው፡ የተዘረጋው፡ የኢኮኖሚ፡ የበላይነት፡ ፍጹም፡ የትግራይ፡ ምርጥ፡ ቡድንና፡ ታማኝ፡ ደጋፊወቹ፡ መሆኑን፡ ነው። ይህ፡ ሊሆን፡ የቻለው፡ የፖለቲካውና፡ የኢኮኖሚው፡ ዘርፎች፡ የተቆላለፉ፡ በመሆናቸው፤ ተወዳዳሪነት፡ ባለመኖሩ፤ ባለመፈቀዱ፤ ክልክል፡ በመሆኑ፡ ነው። በብዙ፡ የአፍሪካ፡ አገሮች፡ በታሪክ፡ እንደታየው፡ ሁሉ፤ የፖለቲካ፡ ስልጣን፡ መያዝ፡ ለሃብት፡ ክምችት፡ ቁልፍ፡ ነው። ለሙስና፡ አስፈላጊ፡ ነው። የኢትዮጵያን፡ ለየት፡ የሚያደርጉት፡ ብዙ፡ ምክንያቶች፡ አሉ። ጥቂቶቹ።

የህወሃት፡ ምርጥ፡ ቡድን፡ የሃብት፡ ክምችት፡ በቃኝን፡ አያውቅም። ይሉኝታን፡ አያውቅም። ይቅር፡ ባይነትን፡ አያውቅም። የሰው፡ ልጅ/የግለሰብ፡ መብትን፡ አያውቅም። በህግ፡ የመዳኘትን፡ ምንነት፡ አያውቅም፤ አይቀበልም። በህግ፡ የበላይነት፡ አያምንም። አብሮ፡ መኖርን፡ ይፈራል። የሚያውቀው፡ ዋና፡ እምነት፡ ፍጹም፡ የጠባብ፡ በዘርና፡ በጠባብ፡ ቡድን፡ የተደራጀ፡ የበላይነትን፡ ብቻ፡ ነው። የተፈጥሮ፡ ሃብትን፡ ሙሉ፡ ቁጥጥር፡ ማየት፡ ለዚህ፡ ይጠቅማል፡፡

የኦክላንድ ተቋም (ኦክላንድ፡ ኢንስቲቱት) ያለውን፡ ማየት፡ በቂ ነው። በጋምቢየላ ብቻ 75 በመቶ የሚሆነው፡ ለውስጥ፡ ባለሃብቶች፡ የተስጠው፡ ማሳ (ለም፡ የእርሻ፡ ቦታ) ለትግራይ ተወላጆች፡ መሆኑን፡ መዝግቧል። በኢኮኖሚው፡ ዘርፍ፡ የሚታየው፤ ይህንን፡ የሚመስል፡ ፍጹም፡ የበላይ፡ ቁጥጥር፡ የውጭ፡ ታዛቢወችን፡ ለብዙ፤ አመታት፡ ሲያነጋግር፡ ቆይቷል። “ትግራይ የግላችን፡ ኢትዮጵያ የጋራቺን” የሚለው፡ የኢትዮጵያዊያን፡ ከዚህ፡ የበላይነት፡ የመነጨ፡ ነው። ለምርጥ፡ የትግራይ አዲስ ሃብታሞች፡ አገልጋይ፡ እስከሆነ፡ ድረስ፡ ማንኛውም፡ የስራ፡ ዘርፍ፡ ህጋዊነት አለው። ቡድኑ፡ እንደፈለገ፡ አገር፡ ሊቸረችር፤ ይችላል። ግድያም፡ ሊያደረግ፡ ይችላል። የራሱ፡ ታማኝ፡ ደጋፊ፡ ካልሆነ፡አንድ፡ ሰው፡ ህገወጥ፡ ነህ፡ ለማለት፡ ይችላል። ህጉን፡ ጠምዝዞ፡ ለማሰር፡ ይችላል። አዙሮ፡ ሰው፡ ባልፈጸመው፡ ወንጀል፡ “ይቅርታ፡ ጠይቅ/ጠይቂ” ለማለት፡ ይችላል። ባጭሩ፤ በኢትዮጵያ፡ መኖር/አለመኖር፡ በዚህ፡ መነጽር፡ የሚታይ፡ እየሆነ፡ ሂዷል። እዚህ፡ ላይ፡ ማስተዋል፡ ያለብን፡ እበይት፡ ነገር፡ አለ።

የመለስ፡ መንግስት፡ ሕጉን፡ ሲጠመዝዝ፡ ድርጊቱ፡ አብዛኞቹ፡ የአለም፡ መንግስታት፡ ከተቀበሏቸው፡ የህግ፤ የሚዛናዊ፡ እድገት፡ መስፈርቶችና፡ የሰባዊ፡ መብት፡ መለኪያወች፡ እጅግ፡ የተራራቀ፡ ነው። ለምን፡ እንደተራራቀ፡ እናውቃለን። የብድር፡ ለጋሾች፡ ህገ፡ መንግስቱ፡ ሲጣስ፡ ለምን፡ ዝም፡ እንዳሉ፡ እናውቃለን። በውድድር፡ እናምናለን፡ የሚሉ፡ ለጋስ፡ መንግስታትና፡ አበዳሪ፡ ድርጅቶች፤ በተለይ፡ አለም፡ ባንክ፡ ለምን፡ በድፍረት፡ ውድድር፡ አልባ፡ ስለሆነ፡የኢኮኖሚ፡ አመራር፡ እንድማይናገሩ፡ እናያለን። ምክንያቱ፡ ይህ፡ ነው። የራሳቸው፡ ጥቅም፡ እስካልተነካ፡ ድረስ፤ አንድን፡ አገር፡ “ስይጣን” ወይንም፡ “ዝንጀሮ” ቢገዛ፡ ግድ፡ የላቸውም። የአፍሪካ፡ አንድነት፡ ድርጅት፡ ሆነ፡ የተባበሩ፡ መንግስታት፡ የሰባዊ፡ መብት፡ ድርጅት፡ የህወሃትን፡ ኢሰባዊ፡ ድርጊቶች፡ ተጠያቂ፡ መሆን፤ የሚመለከታቸው፡ ባለስልጣኖች፡ እነማን፡ እንደሆኑ፡ ያውቃሉ። ዝም፡ ብለው፡ የሚመለከቱበት፡ ዋና፡ ምክንያት፡ እኛ፡ በመካከላችን፡ያለው፡ በአንድ፡ ድምጽ፡ ለመናገር፡ አለመቻል፤ ለኢትዮጵያና፡ ለመላው፡ ሕብረተሰብ፡ መብቶችና፡ ጥቅም፡ አብረን፡ ለመቆም፡ አለመደራጀት፡ ናቸው። ይህ፤ ባስቸኳይ፡ መፈታት፡ አለበት። የጎሳና፡ የቋንቋ፡ ስራትና፡ አስተዳደር፡ በምንም፡ ሰላምና፡ ፍትሃዊ፡ እድገት፡ አያመጣም። እንደ፡ አለም፡ ባንክ፡ የውስጥ፡ ዘገባ፤ “የህዝብ፡ ተሳትፎ፡ የሊለበት፡ የልማት፡ አመራር፡ ድህነትን፡ አያጠፋም፤ የአብዛኛውን፡ ኑሮ፡ አያሻሽልም።” እንኳን፡ ለቀረው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ኑሮ፡ መሻሻል፡ ቀርቶ፡ ለኢሃደግ፡ ሰፊ፡ አባላትም፡ አያዋጣም፡ ማለት፡ ነው።

በአጭሩ፤ ከላይ፡ የቀረበው፡ እንደሚያሳየው፡ ለጥቅምና፡ ለፖለቲካ፡ ፍጹማዊ፡ የበላይነት፡ የቆመው፡ የኢሃደግ፡ ስራት፤ በተለይም፡ ህወሃት፡ በበላይነት፡ የሚመራው፡ መንግስት፤ ለሃገር፡ ዘላቂ፡ ጥቅም፤ ለሏአላዊነትና፡ ለነጻነት፤ ለመላው፡ የኢትዮጵያ፡ ሕዝብ፡ ሰላም፤ ለሰው፡ ክብር፤ ለሰብነት፤ ለአብሮ፡ መኖር፤ ለሰባዊ፡ መብት፡ ለሁሉም፡ እድገት፤ ለጋራ፡ ብልጽግና፤ ለፍትህ፡ ወዘተ፡ ደንታ፡ የለውም። በተግባር፡ የሚያሳየው፡ ሊኖረው፡ እነደማይችል፡ ነው። ለዚህ፡ ጨለማ፡ ለሚመስል፡ የህወሃት፡ አገዛዝ፡ በደል፡ ጥልቀት፡ ያላቸውን፤ በማስረጃ፡ የተደገፉ፡ ሃሳቦችና፡ አማራጮች፡ በተከታታይ፡ አቀርባለሁ።

ክፍል፡ ሁለት፡ ይቀጥላል
ሚያዝያ፡ ፲/፪ዖ፬