Archive for the ‘Amharic’ Category
Wednesday, May 22nd, 2013

ከሎሚ ተራተራ
እነደምን ከርማችሁ ወዳጆች ? እኔ አምላክ ይክበር ይመሰገን ደህና ነኝ። ሰሞኑን ከወደ ትውልድ አገር የመጡን አዛውንት እንኳን ደህና መጡ፤ የሰሜን አሚሪካ አየርሰ እንዴት ተቀበሎት ለማለት ወደ ጎረቤት ቤት፤ ጎራ ብዪ ነበርና፤ አረፍ እንዳልኩ አንድ ቀደም ብሎ ባለሁበት ከተማ ለጥቂት ወራት በርቀት ዝቅ ብለው እጅ በመንሳት የሃገሬን ተናፋቂ ባህል የሚያሰታውሱኝና እጀግም የማከብራቸውን አባት ድምጥ ሰማሁ።
እንድምነ ዋላችሁ አሉ አቶ በልሁ፤ ድምጣቸውን ያለወትሮዎቸው ለዘብ አድረገው፤ ;;’’’’’ እግዚአብሒር ይመሰገን”’ እንደምን ዋልክ በልሁ ግባ፣ ምነው ? ምን አዲሰ ነገር ሰማህ ደግሞ ድምጥህ ያለወትሮው ለዘብ ብሏል አሉ አቶ ታከለ፤ የዛሪን አያረገወና ልጆቻቸውን ለማየት ወደ ሰሜን አሜሪካ ከመጡ ወዲህ ቀረ እንጂ ድሮማ ሰው ሁሉ የሚጠራቸው “ አልሞ ተኳሸ” እያለ ነበር አሉ።
አቶ በልሁና አቶ ታከለ ለረጅም ግዜ ወዳጆች ከመሆናቸውም ሌላ በወቅቱ የሀገራችን ጉዳይ ዙሪያ ዘወትር በቁጭት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ካላቸው ሃገራዊ ፍቀር በመነሳት መደረግ ሰለሚገባው የሃገር ጉዳይ ፤ በተለይም እንዴት አንድነታቸንን መገንባት እንደሚገባን አበክረው ከሚናገሩት የአካባቢያቸን የሰሜን አሜሪካ አዛውንቷች ዋናዎቹ ናቸው።
ወዲያዉ እግራቸው እንደገባ ወንበርም ላይ ሳይቀመጡ አዬ…; ተወኝ እባክህ…..ሲሉ የሰሙትን ለማጫወት ጀመሩ።, እኔም ኖር;……. በዪ እጅ ከነሳሁ በሗላ ጆሮዪን ሰጥቼ ማዳመጥ ቀጠልኩ፣…… ይገርምሃል ሰሞኑን በዚህ በ “ቡል” ቶክ…ነው.. ”ፓል”ቶክ,,….የሚባል…. የመወያያ መደረክ….. አዪ……ለነገሩ እኔ ይሔንን የመወያያ መድረክ ሳይሆን….”የወሬ ቋት” ነው የምለው። አሉና… ቀጠሉ.. አንድ “አባ…መላ….የሚባል….የ..ወያኔዎቹ አፈቀላጤ.. ሚሰጥር አጋለጠ።……የወያኔን..የግፍ ሰራ መደበቅ (መሸፈን) ደከመኝ..ብሎ ተቃውሞ ሲያሰማ ዋለ። ብዙም ሚሰጥር የማወቀው አለ ብሏል..’…. እያለልሕ …..አዳሜ ተሰበሰቦ ….”ውይ መላ ነሸ አሉ ወይ መላ አባ መላ እያለልህ” ከበሮ፤ ይደልቃል።
ሲሉ ከልቤ ሳቅኩና፤ ፈጠን በዪ ማጋለጡ፣ መልካም አይደለምወይ ብዪ ? ጠየቀኳቸው? ሲመልሱ….እሱማ..መልካም..ነው። አሰገራሚዉ ነገር እኮ አራት ቀን ሙሉ..እንደውም አምሰተኛው ቀን ይኸው መጣ ተሰበሰቦ ማዳነቅ ምን ይሰራል? የተገኝወን መረጃ ሰበሰቦ ተግባራዊ ሰራ ላይ ማተኮር ነው የሚበጀው።
ብለው ሲሉ. በዚሁ ቃላቸው ተሰማምቼ እቸኩል ሰለነበር የሚጣፍጠውን ጫዋታ ገና በእፍታው፤ ትቼ በሉ ደህና ይዋሉ ብዪ ተሰናብቼ ወጣሁና፤ እቤቴ እሰክደርሰ” ወይ መላ ነሸ አሉ ወይ መላ አባ መላ” አሉ አቶ በልሁ፤ እያልኩ እያሰላሰልኩ እቤቴ ደርሰኩና ይቺን ለመጫጫር በቃሁ እላችኸላሁ።
ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነው “ወይ መላ ነሸ አሉ፣ ወይ መላ አባ መላ” እያሉ ከበሮ መደልቅ; አባታችን አቶ በልሁ እንዳሉት አይጠቅመንምና መላው ዳይሰፖራውን ይታሰብበት እያለኩ፤ ከዚህ የሚከተለውን ይበጀናል ያልኩትን ብትጠቀምም ባትጠቅምም መፍትሄ ነው። ብዪ ሰለማምን ጀባ እላለሁ።
ዳይሰፖራው ማተኮር የሚገባው፦
1ኛ) በተገኝው ማንኛውም ይጠቅማል የተባሉትን ኢንፎረሜሸኖች በማሰባሰብና በማጠናከር ላልሰማውና ላልተረዳው፣ የህበረተሰብ ክፈል እነዲደርሰ ማደረግና ለውጤቱም ተግቶ መሰራት።
2ኛ) ከማንኛወም አይነት የጥላቻና የ መጎነታተል ወይም የመናናቅ የ ትግል ሰልት መራቅና ወቅታዊና አንገብጋቢው በሆነው የሃገራችን ቸግርላይ በማተኮር ሳንሰልችና ሳንታክት እያንዳንዳችን የድርሻችንን በቅንነትና በኢትዮጲያዊ ጨዋነት ማበርከት።
3ኛ) በወቅታዊው የሃገራቸን የፖሎቲካ፣ የ ኢኮኖሚም ሆነ የመሃበራዊ ችግሮቻችንን እና መፍትሄዎቻቸውንም ጭምር ባለሞያ ወንድሞቻችንንም ሆነ እህቷቻችንን በመጋበዝ ህብረተሰባችን ሰለወቀታዊው የሃገር ችግርና መፍትሄው ማወያየት።
4ኛ) የፖሎቲካ ድረጀቶችም የኔ የፖሎቲካ ፐሮገራም ነው ለወቀታዊው የሃገራችን ችግር ብቸኛ መፍትሄ የሚሆንው። ከሚል አሰተሳሰብ ወጥተን የጋራ የሆነወን የገጠመንን የሃገር ችግር በጋራ አፋጣኝ መፍትሄ ለማምጣት በመቻቻል፤ ተግቶ በጋራ በመሰራት አገር ወሰጥ ላሉት ለፖሎቲካ ድረጅቶች መልካም ኢትዮጲያዊ ሰሜትን በሁሉም መሰክ በመተግበር አጋርንትን በተገበር ማሳየት።
5ኛ) ከሁሉም በላይ ለምናልመውና ለማይቀረው የህዝብ የሃግር ባለቤትነት እያነዳንዱ ዜጋ ድርሻዪ ምንድነው ? በማለትና ለተግባራዊነቱም እውቀቱንም፤ ጉልበቱንም፤ ገንዘቡንም ህይወቱንም ሳይቅር ለመሰዋት የተዘጋጀ መሆን እንዳለበት ማረጋገጥ ነው።
ይህንን ካልተረዳና ለተግባራዊነቱም ካልተዘጋጀን በሰተቀር ቀደም ብዪ በመግቢያዪ ላይ እንደገለጥኩተ ትርፉ አቶ በልሁ እናዳሉት”…
ሆይ… መላ… ነሸ… አሉ… ሆይ,,.. መላ… አባ… መላ…
ነውና… እነዲህ አይነቱን… ባዶ… ከበሮ… ከመደለቅ… ያውጣን! አሜን!!!
በተመሳሳይ መጣጥፍ እሰክንገናኛ ደህና ሁኑ በቸር ይግጠመን! ችርም ያሰማን!
ከሎሚ ተራ ተራ
Wednesday, May-22-13
አሰተያየትዎን/ነቀፊታዎንም ቢሆን: mwl200825@yahoo.com
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 22nd, 2013
ቅዱስ ዳዊት እናንተ የሰው ልጆች እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ በማለት ለንስሐ ስፍራ ሳይኖራቸው ሐሰትን ፀንሰው አመፃን የወለዱትን ሰዎች የገሠጸበትን የቅዱስ መጽሐፍን ኃይለ ቃል መነሻችን ያደረግነው አለምክንያት አይደለም ።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 22nd, 2013
ከዘካሪያስ አሳዬ
አንድ መልካም እድል ሲገኝ በዚያ ዕድል ቀዳሚ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያንቀዠቅዥ ልክፍት አለ። የዚህ ልክፍት መጠሪያም ‹‹አድር ባይነት›› (Opportunism) ይባላል።መልካም አጋጣሚ ወይም ዕድል (Opportunity) ሲገኝ በዚያች ለመጠቀም ያለምንም ይሉኝታ መሽቀዳደም፤በስተኋላ ሊከሰት የሚችለውን ጎጂ ውጤት እያወቁም ቢሆን ‹‹እንደ አመጣጡ እመልሰዋለሁ›› በሚል ድፍረት
መግባት፣ ከየት አመጣ? እንዴት አገኘ? በምን ዘዴእዚህ ደረሰ? የሚሉ የህዝቡ ምን ይላል ጥያቄዎችን ወደ
ጎን አሽቀንጥሮ ጥሎ ጥቅም ፍለጋ ሲል ብቻ ለመሰል አለቆቹ እየተሽቆጠቆጠና የእሱ ቢጤዎችን እያሰባሰበ
የሚንቀሳቀስበት አሰራር አድርባይነት ነው። ሰውሸንኮራ አገዳ አይደለም፤ እየተመጠጠ አይታይም። ከላይ
ስታየው የሚጣፍጥ የመሰለህ አገዳ ገዝተህ ስትቀምሰው ሊጎመዝዝህ ይችላል። የአድርባይም ጉዳይ እንዲሁ ነው።አድርባይነት የተገኘውን መልካም አጋጣሚ ሁሉየግል ጥቅምና አላማን ለማስቀደም የሚደረግ የፖለቲካ
አቋምን ያመለክታል። ጥቅም የሚያስገኝ እስከሆነ ድረስ ማንኛውንም አቋም ለማራመድ (ለመደገፍ) ቆርጦ
መነሳትን፣ ለግምገማም ሆነ ለህጋዊ ተጠያቂነት ንቀት ማሳየትን፣ የህዝብን ውክልናና ስልጣን አሳንሶ ማየትን፣
አይንን በጨው አጥቦ ለጥቅም ሲሉ ብቻ የድርጅቱን ራዕይመመሪያና ደንቦችን የህዝብን ትዝብትና ሃይማኖትንጭምር ጨፈላልቆ ለመሄድ ያለንን ውስጣዊ የጠባይ(የባህርይ) ዝግጁነት የሚያሳይ ክፉ አመለካከት ነው።አድርባይ ሰው በድርጅቱ የፖለቲካ አቋምአያምንም። ያመነ የሚመስለውና ከእሱ በላይ ተቆርቋሪ የሌለ እስኪመስል ድረስ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ለመሪዎቹ(አለቆቹ) ፍቅር ያለው ይመስል የሚሽቆጠቆጠው ያቺን ያሰባትን ጥቅም በእጁ እስኪያስገባና ተጨማሪ ጥቅምለማግኘት የሚያስችል እድል (አጋጣሚ) Opportunity እስካለ ድረስ ብቻ ነው። ‹‹የራስ ጥቅምን መፈለግና ለዚህም ተግቶ መንቀሳቀስ ምን ችግር አለው?›› የሚልጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ሁላችንም የምንሰራው ለመጠቀም
ነው። ራሳችንንና ቤተሰባችንን ለማስተዳደር ሰው የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው። መሬት፣ መኪና፣
ቤት፣ ኢንቨስትመንት፣ አካውንት፣ ደህና ዕቁብ ጥሩዕድር ቢኖረንና የጣፈጠ በልተን ያማረ ለብሰን ብንኖር
አንጠላም። ይህ ደግሞ ኃላፊነት በሚሰማውና በእውቀትና በጉልበት ተሳትፎ ተሰርቶ የሚገኝ ሲሆን ደስ ይላል።እንደ ምርጫና ወዘተ… በመሳሰሉት አጋጣሚዎች በተገኘእድል ከህዝብ በተሰጠ አደራ የራስን ጥቅም ለማስቀደም የሚደረግ የፖለቲካ እሽቅድድም ግን አያዋጣም።አድርባይነት በፓርቲና በመንግስት ተቋማት ኃላፊዎችና ሠራተኞች አማካይነት ሲፈፀም ከፍተኛ ችግር ያስከትላል።ታማኝነት (Loyalty)… ግልፅነት (transparency)…ምስጢር ጠባቂነት (Confidentiality)… ሀቀኝነት(Honesty) ተጠያቂነት (Accountability) አለማዳላት(Impartiality)…ምላሽ ሰጪነት (Responsiveness)አርአያ መሆን (Exemplary) የህዝብ ጥቅም (Public
Interest) ወዘተ… የሚባሉት መሰረታዊና ስትራቴጂክ የዕድገት እሴቶቻችን በሙሉ ጥንጣን እንደበላው የበረሃዛፍ ውስጥ ውስጡን እየተቦረቦሩ ያልቁና ራዕያችንን ገንድሰው ይጥሉብናል። ከዚያ ኋላማ ‹‹የማን ቤት ጠፍቶየማን ሊበጅ… የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ›› እያልን እርስ በርስ ከመጨካከንና ከመተራረድ በቀር የሚተርፈን ነገር የለም።ይህ ማለት ደግሞ ሰዎችን ስንጠረጥራቸውእንኑር፣ ወይም በየጆሯቸው ስር መረጃ እናቁምባቸው፣ስህተታቸውን የሚያሳብቅ ቃጭል እናንጠልጥልላቸው ማለት አይደለም። ወደንና ፈቅደን እንደሰው መጠን አገናዝበን የመረጥናቸው ወኪሎቻችንና አገልጋዮቻችን ስለሆኑ አዲሶቹ በአድርባይነት በሽታ እንዳይለከፉና የተለከፉትም ከዚህ የአድርባይነት አስተሳሰብ እንዲወጡ በተቻለን አቅም እንርዳቸው፣ እናግዛቸው ማለት ብቻነው። አድርባይነት የስብዕና (Personality) ምስክርነው። የአመለካከት ችግር ነው። የሰዎች ስብዕናና አመለካከት የሚቀረፀው ደግሞ አንደወጡበት ቤተሰብና እንደ አደጉበት ማህበረሰብ ነው። ሌብነትን ከሚፀየፍ ቤተሰብና ማህበረሰብ የተገኘ ልጅ ሌብነት ውስጥ ሊገባ አይችልም። ወይም የመግባት እድሉ በጣም ጠባብ ነው።ስለዚህ የሰውዬውን ቤተሰብና ያደገበትን ማህበረሰብ ዳራ ማወቅ ይጠቅማል። አድርባይነትን ከሚያስፋፉ ባህርያት አንዱ ስኬታማ የመሆን ጥማት ነው።ከሌሎች ሰዎች ተሽሎ የመገኘት፣ የማሸነፍ፣ በውጤት፣በዝና በሀብት በልጦ የመገኘት (‹‹ወንዳታ›› የመባል)ውስጣዊ ፍላጎት ነው። ይህን ፍላጎት ለማርካት (ከግብለማድረስ) ሰውዬው ስልጣኑንና የተገኘውን መልካም አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም እስከየትኛውም ጫፍ ድረስ ይጓዛል። ከድርጅቱ (ከፓርቲው) እና ከሚሰራበት ተቋም መርሆዎች ጋር ፈጽሞና ፈጽሞ የማይጣጣሙ ዘዴዎችን(አሰራሮችን) እየተጠቀመና ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቀ
ይሟሟታል። ይህ ደግሞ ለአድርባይነት ይዳርገዋል።ለአድርባይነት ከሚዳርጉ ምክንያቶች ሌላኛው የሰው ልጅያለው የስጋት (ስጋታምነት) ተፈጥሮ ነው። ለትንሹም ለትልቁም መስጋት ይወዳል። በሰላም አገር ‹‹ይገመግሙኝይሆን? ከደረጃ ዝቅ ያደርጉኝ ይሆን?… ይጠረጥሩኝይሆን?… ከቤተሰቤ ወደራቀ ቦታ ያዛውሩኝ ይሆን?ያባርሩኝ ይሆን?… ዕድገት ይከለክሉኝ ይሆን? እያለይጨናነቃል። ከዚያች ከያዛት ቦታ ቢለቅ ወይም ከዚያመስሪያ ቤት ቢወጣ ሰማይ የሚደፋበት ይመስለዋል።በራስ መተማመኑ ብን ብሎ ይጠፋበታል። ስለዚህ ህዝብ የጣለበትን አደራና ተቋሙ የሰጠውን ኃላፊነት እርግፍ አድርጎ ትቶ የጥቅመኛ አለቃው ሽቁጥቁጥ አሽከር(ባሪያ) ሆኖ ያርፈዋል። ‹‹ቢጭኑት አጋሰስ፤ ቢጋልቡት ፈረስ›› ይሆንና ሀሳብ አመንጭነትና ተነሳሽነት የጎደለው አስመሳይ ተራማጅ ሆኖ ይቀራል። ለድርጅቱም (ለተቋሙ)
ሳይጠቅም ህዝቡ የጣለበትን አደራ ሳይፈጽም የትውልድ መዛበቻና የዘመን መሳለቂያ ሆኖ ያርፈዋል። ሌላው ጉዳይ ደግሞ አድርባይነት የሚያስገኘውን ጥቅም (pay off) ከፍአድርጎ የማሰብ አመለካከት ነው። ድርጅቱ ቢያባርረኝ፣ህዝቡ ቢታዘበኝ፣ ህግ ያለውን ቢለኝ አድርባይ ሆኜ አንድ ዝግ ከዘጋሁ ይካካስልኛል። የተቀጣሁትን ሁሉ ያህል ብቀጣ በአድርባይነቴ ባገኘሁት ጥቅም አጥበዋለሁ።ጉድ አንድ ሰሞን ነው። የኛ ሰው እንደሁ ማውራት ልማዱ ነው፤ ስለዚህ ያለውን ይበል… በዚህ ላይ ደግሞ የሚኮንነኝ ሰው የመኖሩን ያህል የሚደግፈኝ ሰውም አለ። ያሉትን ቢሉ ምን ያመጣሉ… ለዚያውስ ለየትኛው ህግ ነው? አንድ ሚሊዮን ዘግተህ ሁለት ዓመት ታስረህ ለምትወጣው ምን ችግር አለ። ሁለት ዓመት እንደሁነገ ናት.. እያሉ የሚያበረታቱ ሞልተዋል። ሌላው ጉዳይ አድርባይነት ‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ›› በሚለው መርህ
መሰረት የሚመራ በመሆኑ ጥሩ ውጤት የተገኘ ጊዜ ነጥቡን ለራስ እየወሰዱ መጥፎ ውጤት በተመዘገበና
ጉዳት በደረሰ ጊዜ ኪሳራውን በሌሎች ላይ ማላከክ(Shifting the costs, blame and disadvantages toothers) የሚቻልበት አሰራር በመኖሩና ይህም በሰዎች አመለካከት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር መሆኑ ነው። ሌላውን ተጠያቂ ማድረግ ጣትን በሌላው ላይመቀሰር ሁል ጊዜም ቀላል ስራ ነው። ለችግሮች ውጫዊ ምክንያት መስጠት ቀላል ነው። የአድርባይነትን ጠባይ ከሚያበረታቱ ነገሮች መካከል መነሳት ያለበት የሰውዬው ወይም የዚያ ቡድን የስልጣን መጠን ነው። ስልጣን ሲባል
ሁሌም ለሙስና ይጋብዛል። ፍፁማዊ ስልጣን ደግሞ ለፍፁማዊ ሙስና አይን ላወጣ አድርባይነት ይዳርጋል።
(All power corrupts, and absolute power corruptsabsolutely) ሰውዬው ከፍ ያለ ስልጣን ያለው ከሆነ ተቆጣጣሪ ስለሌለበት ያገኘውን መልካም አጋጣሚ ሁሉ ለግል ጥቅሙ የሚያውልበት ሰፊ እድል አለው። ስለዚህ አድርባይ ይሆናል። ለአድርባይነት መኖር በር የሚከፍተው
ሌላኛው አመለካከት ደግሞ ‹‹እኔ ባላደርገው ሌላው ያደርገዋል… ስለዚህ ለምን እኔ አላደርገውም›› የሚለው አመለካከት ነው። ሌላው መጥቶ አጋጣሚውን ለራሱ ጥቅም የሚያውለው ከሆነ እኔስ እጄ ባለው አጋጣሚ ብጠቀም ሃጢአቴ እምኑላይ ነው ብሎ ያስባል።የበላይ አለቆቹንም ያያል። ሁሉም በአድርባይነት
በሽታ የተለከፉ ይሆኑበታል። ያላቸውን ቤት፣ መሬት፣መኪና፣ ኢንቨስትመንት… የአኗኗር ሁኔታ ሲመለከት
እኔስ ከማን አንሳለሁ ይላል።እነሱ ምን ተደረጉ ይላል። ለእነሱ ያልሰራ ህግ ለእሱም እንደማይሰራ ያምናል። ይገባበታል፤ በመጨረሻም ከእነሱ ጋር ተለቃቅሞ ይገባታል። እስከዚያው ድረስ ግን ጥቅም ነውና ይሟሟትበታል። አድርባዩ በበዛበት ድርጅት ውስጥ ሆኖ አድርባይ አልሆንም ማለት ይከብዳል።ሁሉም አብዶ ጨርቁን በጣለበት ሀገር ልብስ ለብሶ የሚሄድ ሰው ከተገኘ ዋናው እብድ የሚባለው እሱ
ይሆናል። የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ የሚለውም የአድርባዮች መገለጫ ነው። ሰዎችን አድርባይ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው ሌላው ምክንያት የመረጃ፣ የእውቀት፣የግንዛቤ እጥረት ነው። ሰዎቹ በአድርባይ ጠባያቸው የተነሳ በፓርቲውና በመንግስት ስራ ላይ፣ በህዝብ ላይ፣ በሀገርላይ በመጨረሻም በራሳቸውና በቤተሰባቸው ህይወት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ካልተረዱ አድርባይ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። አንዳንዶች በዚህ ረገድ ማግኘት ያለባቸውን መረጃና ግንዛቤ እንዳያገኙ ወይም የተዛባመረጃ ሆን ተብሎ እንዲያገኙ deliberate disinformation የሚደረጉበት ሁኔታ አለ። ሌሎች ደግሞ አድርባይነት
በሚያስከትለው መዘዝ ላይ መረጃውና ግንዛቤው እያላቸው ሆን ብለው ራሳቸውን የሚያታልሉና በአጉል ድፍረት በልቼ (ተጠቅሜ) የመጣው ይምጣ ብለው የሚገቡ ፈጣጦች አሉ። ሲሾሙ ካልበሉ ሲሻሩ እንዳይቆጫቸው።ከዚህ በላይ ያነሳናቸው በአድርባዩ ሰውዬ በራሱ አማካይነት ተኮትኩተው ስለሚፋፉ የአድርባይነት ባህርያት ነው። ለእነዚህ ተከታታይ ስልጠና ያስፈልጋል።የአመለካከት ለውጥ፣ የግንዛቤ ዕድገት እንዲያመጡ ማድረግ ያስፈልጋል። ካደጉበት የ‹‹እንብላው›› ብሂል የሚወጡበትን እድል ጥልቅ በሆነ ስነአዕምሯዊ ስልጠናና ክትትል ከውስጣቸው ለመንቀል መስራት ያስፈልጋል። ማስተማር
ያስፈልጋል። በሌላ በኩል ደግሞ ተቋማት ራሳቸው ሰዎችን ወደ አድርባይነት ለመገፋፋት የሚያመቻቹበት
ሁኔታ አለ። አንዳንድ ድርጅቶች የአድርባይነት ጠባይ የማያስተናግድ በግልፅ የተቀመጠ ውልፍጥ የማያደርግ
ህግና ደንብ አላቸው። ሰውዬው ምን ቢያደርግ ምን እንደሚደርስበት በግልጽ ተቀምጧል። ይህ ይነገረዋል።
በጽሑፍም ይሰጠዋል። አድርባይ ሆነው የተገኙ ሰዎችንም የሚቆጠቁጥ ቅጣት ይጥሉባቸዋል። በስልጣን ላይ ሳሉባገኙት አጋጣሚ ያከማቹትን ሀብት እንዲያጡ፣ ለበርካታ ዓመታት በእስር እንዲቀጡ፣ ባዶ እጃቸውን እንደመጡባዶ እጃቸውን እንዲወጡ የሚያደርግ የፍትህ አሰራርም አላቸው። ሌሎች ድርጅቶች እንዲህ አይነት በግልፅ የተቀመጠ ህግ ስለሌላቸው የሚደርስባቸው ቅጣትም ከበሉት ገንዘብና ከተቀራመቱት ጥቅም አንፃር ሲታይ በእጅጉ አናሳ በመሆኑ ጓዶችን ሲያዩ እየተሽቆጠቆጡ፣ ዞርሲሉ ምላሳቸውን እያወጡ፣ በህዝብ ላይ እያላገጡ፣ ሰለሄመለሄ እየዋጡና ሙቅ ተበሪድ አማርጠው እየጨለጡ እንዲኖሩ እድል ይሰጣቸዋል። ከተቋማት አንፃር ሲታይ በርካታ ለአድርባይነት የሚገፋፉ አመቺ ሁኔታዎች አሉ።ሁሉንም ዘርዝረን አንችልም። አንድ ቦታ ላይ ማቆም አለብን። የሙስና የኪራይ ሰብሳቢነት የብልሹ አስተደደር
እናቱም አባቱም አድርባይነት (Opportunism) ነው።ልንዋጋውና ልንታገለው ይገባል። ‹‹አድርባይነት››የተባለውን ጽንሰ ሀሳብ በግልጽና በጥልቀት በተለያዩ አደረጃጀቶቻችን አማካይነት ልንገነዘበው ይገባል። በእከክልኝ ልከክልህ በአባልነት ስም እየተሳሳቡ ጥሩ ጥሩውን ውጤት
ወደራሳቸው እየሳቡና ጥፋት ሲገኝ በሌላው ላይ እያሳበቡ፣ምንም ሳይሰሩ እየደለቡ እንዲኖሩ መፍቀድ የለብንም።ይህን መታገል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ኃላፊነትብቻ ነው።ምክንያቱም ወያኔ‹‹አድርባይነት›› ሙያው ስለሆነ እንዲያውም በዋናነት የህብረተሰቡ የራሱ ኃላፊነት ነው። ከየት አመጣችሁ ብሎ መጠየቅ
አለበት፤ ድምፁን መንፈግና በምርጫ ካረዱ መቅጣት አለበት ከደሃ ትከሻው ልናስፈነጥረውና አሽንቀጥሮ መጣል አለበት።ታዲያ ይኽሁላ የምናየው የገዥው መንግስት ባህሪያት አይደሉምን?ለማንኛውም መልካሙን ሁላ ለህዝባችን ይስጥልን!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ከዘካሪያስ አሳዬ
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 22nd, 2013
በሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር
በአዲስ አበባ የሚገኙ የጥቁር ገበያ ባለድርሻዎች በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ነጋዴዎች ከሙስና ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በመታሰራቸው በተፈጠረ መደናገጥ መነሻ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ እያጋጠማቸው መሆኑን ገልፀው፣ የዶላር ምንዛሪ በታሪኩ የሰላሳ ሳንቲም ቅናሽ አሳይቷል።
የከፍተኛ ባለስልጣናቱ በወንጀል የመጠርጠር ዜና ከመሰማቱ በፊት ሃያ ብር ከአርባ ሳንቲም የነበረው የዶላር ምንዛሪ ወደ ሃያ ብር ከአስር ሳንቲም በሳምንት ውስጥ ቀንሷል። በዚህ ቅናሽ ውስጥ አስደንጋጭ የሆነው ክስተት በማንኛውም አይነት ምንዛሪ መጠን ዶላር ወደላይ ሲጨምር ሆነ ሲቀንስ በሰላሳ ሳንቲም የልዩነት ምንዛሪ ውስጥ ወድቆ አለማወቁ መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃዎች ያሳያሉ። በሙስና ከተጠረጠሩ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ጋር በተያያዘ ይህ ልዩነት መፈጠሩ አብዛኛው የጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሪ ባለድርሻ አካላትን ማስደንገጡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቁመዋል።
ባለፉት አራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ የዶላር እጥረት በሀገሪቷ ሲከሰት የጥቁር ገበያ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን ቢገለጽም፣ ከመንግስት እና ከግል ባንኮች ሰራተኞች የገጠማቸው ችግር ግን እጅግ ፈታኝ እንደነበር አስረድተዋል። ይህም ሲባል፣ ለአንድ የአሜሪካን ዶላር ከአንድ ብር እስከ አንድ ብር ከሃምሳ ሳንቲም የባንኩ ደንበኞች ክፍያ እየፈጸሙ ከፍተኛ መጠን ያለው የዶላር ምንዛሪ ከባንኮቹ ማግኘትን በአማራጭነት በመውሰዳቸው ወደ እኛ ከመምጣት ባንኮንችን ተመራጭ ያደርጉ ነበር። ሆኖም ከፍተኛ መጠን ዶላር የማይፈልጉ ደንበኞች በወቅቱ ስለነበሯቸው ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውንም አልሸሸጉም።
በአሁን ሰዓት ከመንግስት ኪራይ ሰብሳቢ የተለያዩ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች ወደ እነሱ ይፈስ የነበረው የኢትዮጵያ ብር ለዶላር ምንዛሪ ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበረው ከመሆኑ አንፃር አሁን የተፈጠረው ድንጋጤ በከፍተኛ ሁኔታ የጥቁር ገበያውን የዶላር ምንዛሪ ይጐዳዋል። የተፈጠረው ድንጋጤ ግለሰቦችን ሳይቀሩ ማሸማቀቁን ያነጋገርናቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አረጋግጠዋል። በስፍራው የተገኙት መረጃዎችም የሚያሳዩት ከመንግስት ከፍተኛ ኪራይ ሰብሳቢ ባለስልጣናት ሰንሰለት ይፈስ የነበረው የኢትዮጵያ ብር ለጊዜ ተቀዛቅዟል። ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ የጥቁር ገበያው አደጋ ውስጥ መውደቁ አይቀርም የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልፀዋል።
ለምን የኢትዮጵያ ብር ወደ ጥቁር ገበያ ይላካል?
በሙስና ውስጥ የተዘፈቁ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተባባሪ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት ከሕግ አግባብ ውጪ የሚያገኙትን የኢትዮጵያ ብር በአዲስ አበባ ጥቁር ገበያ ውስጥ በዘረጉት ሰንሰለት ወደ አሜሪካ ዶላር ለውጠው ወደ ውጭ ሀገር እንዲወጣ በማድረግ ተጠቃሚ በመሆናቸው መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በተለይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዚህ መልኩ የሰበሰቡትን የአሜሪካ ዶላር በተሰጣቸው ያለመፈተሸ መብት በመጠቀም እና በገቢዎችና ጉምሩክ በዘረጉት የኪራይ ሰብሳቢ ሰንሰለቶች አማካይ ወደ ውጭ ይዘውት የሚወጡበት አሰራር ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የሰበሰቡትን የአሜሪካ ዶላር በሳምሶናዊት ቦርሳቸው ውስጥ በመጨመር እና ቦርሳውን ላይ ያለመፈተሽ መብት የሚያጎናጽፋቸውን ልጣፍ በመለጠፍ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ዶላሩን ይዘው የሚወጡበት ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ ሊጠቀሙበት ይችላሉ ሲሉ ግምታቸውን ተናግረዋል።
በአስረጅነት ግምታቸውን ሲያስቀምጡ የገቢዎችና ጉምሩክ ምክትል ዋና ዳሬክተር የነበሩት አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት የተገኘው 26ሺ የአሜሪካ ዶላር እና 19ሺ ዩሮ የአውሮፓ ሕብረት የመገበያያ ገንዘብ በዚህ መልኩ የተሰበሰቡ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ግምት ገልፀዋል። አያይዘውም አንድ ግለሰብ ከ200 የአሜሪካ ዶለር ምንዛሪ ውጪ ይዞ መገኘት እንደማይችል በኢትዮጵያ ሕግ መስፈሩንም አስታውሰዋል። እንዲሁም በአቶ አስመላሽ ወ/ማሪያም መኖሪያ ቤት የተገኘውም አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወደ ዶላር ለመቀየር የተቀመጠ ገንዘብ ሊሆን እንደሚችል ከጥቁር ገበያ ያገኘነው ግምታዊ መረጃ ያሳያል።
ይህን መሰል ተግባር መፈጸም ትርጉሙ ብዙ ሊሆን ይችላል። በተለይ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት መኖሩ እያወቀ የኢትዮጵያን ብር በዶላር እየመነዘረ ወደ ውጭ ሀገር በማስወጣት ተግባር ላይ ከተሰማራ እንደሀገር ትልቅ በደል መሆኑን መገንዘብ ሮኬት ሳይንስ አይሆንም። በዚህ መልኩ የተሰማሩ የመንግስት ባለስልጣናት በወፍ በረር ሲታይ፣ ዶላር ማሸሽ ቢመስልም በተግባር ግን ሲመነዘር የኢትዮጵያ መንግስትን እና ሥርዓቱን ቀስ በቀስ እየሸራረፉ ሊጨርሱት መዘጋጀታቸውን የሚያሳይ ነው። የፓርቲ ሹመኞቹን የመንግስትን ስርዓት ለዘረጋው ገዥ ፓርቲ ቢተውም፣ ተግባራቸው ግን ሕገ መንግስቱን በጠራራ ፀሐይ እየበጣጠሱት ስለመሆኑ አስረጂ አያስፈልገውም።
የገንዘብ ምንጩ ስትራቴጂ
እ.ኤ.አ. የሴፕቴምበር 11 ቀን 2001 የአሜሪካኑን የሽብር ጥቃት ተከትሎ ትንሹ ቡሽ ሴፕቴምበር 20 ቀን 2001 “WAR ON TERROR” በሚል መጠሪያ ዓለም ውስጥ የሚገኙ አሸባሪዎችን ለመደምሰስ ያስችላል በሚል አዲስ ስትራቴጂ ይዘው ብቅ አሉ። ቡሽ ቀጠል አድርገው በአሸባሪዎች ላይ የምንከፍተው ዘመቻ ‘የመስቀል ጦርነት’ ነው በማለት ለዓለም ሕዝብ በይፋ ተናገሩ።
ቡሽ ብዙም ሩቅ ሳይጓዙ በአደባባይ “የመስቀል ጦርነት” የሚለውን ቃል ተገቢ አይደለም፤ ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር አወዛጋቢ ፍቺ ያመጣል በማለት በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጦርነቱን የምንጀምረው በአልቃይዳ እና በእሱ የሽብር መረብ ከተያያዙ አሸባሪዎች ጋር ነው ሲሉ አቋማቸውን በግልፅ አስቀመጡ። ዓለም ከአሜሪካ ጎን ቆመ። ቡሽም፣ ‘ወይ ከእኛ ወይም ከእነሱ’ ጋር መሆንን ምረጡ ብለው ለዓለም ዓቀፉ ሕብረተሰብ ጥሪ አቀረቡ። ዓለምም በወቅቱ በጐ ምላሽ ሰጣቸው። ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። ኦሳማ ቢላደን ግን ከአስር ዓመት በኋላ ተገድሏል።
እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ቁምነገር፤ እንደቡሽ የመጀመሪያ አቀራረብ ቢሆን የተቀደሰውን የእስልምና እምነት ከሽብር ተግባር ጋር ጨፍልቆ ለማየት ያለመ ነበር። ሆኖም ቡሽ ፈጥነው አባባላቸው ስህተት መሆኑን አርመው በይፋ ይቅርታ ጠየቁ። ስለዚህም ነገሮች ለያይቶ ማየት እንጂ በአንድ ቅርጫት ውስጥ ወርውሮ አንድ መለያ መስጠት ተገቢ አለመሆኑ ከዚህ መረዳት ይቻላል።
በተነፃፃሪነት ሲታይ ደግሞ ገቢዎችና ጉምሩክ በቀድሞ ከፍተኛ አመራሮቹ በኩል የኢትዮጵያ ነጋዴዎችን በተለይ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙትን ነጋዴዎች በግብር ስም ሁሉም ነጋዴ ግብር አጭበርባሪ ኪራይ ሰብሳቢ በማድረግ ሽብር “TERROR ON TAX” በነጋዴው ላይ ረጩ። ነጋዴውም ግብር መክፈሉን ሳይሆን ለኪራይ ሰብሳቢ ወይም ለግብር አጭበርባሪ ታፔላን ላለመጋለጥ በሚል ብቻ የገቢዎችና ጉምሩክ ከፍተኛ ሃላፊዎች ተገዢ መሆኑ አረጋገጠ። በመጨረሻም በተፈበረከው የሽበር ማዕቀፍ ውስጥ ነጋዴው ወደቀ። ፍርሃት፣ ስጋት መለያው ሆነ።
ከዚህ በኋላ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮቹ ጋር ተባብሮ መስራት የኪራይ ሰብሳቢዎች የህግ የበላይነትን ማረጋገጫ አድርጎ ተቀበለው። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው መንግስት ከፍተኛውን የሙስና ወንጀል በራሱ መንገድ ደረሰበት እንጂ በአደባባይ በመውጣጥ ለማጋለጥ የደፈረ ታዋቂ ባለሃብት አንድም አልነበረም። በሕግ የማይነኩ በሚመስሉ የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣናት ጋር ሲራኮቱ የነበሩ ታዋቂ የከተማችን ባለሃብቶች ሕግ በራቸው ደጃፍ ሲመጣ ሌላ የፖለቲካ ዓላማ ያለው ተግባር እንጂ ሙስና አይመስለንም ሲሉ በአደባባይ በዘረጉት የኪራይ ሰብሳቢዎች የሙስና ሰንሰለት በመጠቀም ከተማውን እያሟሟቁ ይገኛሉ። እውነቱ ግን ሌላ ሆኖ ነው እየታየ ያለው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በባሕርዳር በተደረገ የኢሕአዴግ 9ኛው ጉባኤ ላይ ከተጋበዙ ባለሃብቶች መካከል አንዱ የከተማችን ባለሃብት ለጉባኤው ያቀረበው ጥያቄ አጠቃላይ መንፈሱ ሲታይ “የኪራይ ሰብሳቢ” መሰረታዊ ይዘት በመቀየር ወደ ‘ሽብር’ መለወጡን አመላካች ነው። ባለሃብቱ ጉባኤውን የጠየቀው እንዲህ ሲል ነበር፣ “የኪራይ ሰብሳቢ ፍቺው በጣም የተለጠጠ ነው። በትክክልም ምን እንደሆነ እንኳን ለመረዳት አዳጋች ነው። በጅምላ ሁሉም ነጋዴ በገባበት ቢሮ ውስጥ ኪራይ ሰብሳቢ እየተባለ ይሸማቀቃል። እኔ እራሴ አሁን ኪራይ ሰብሳቢ በሚባለው ፍቺ ኪራይ ሰብሳቢ ልሁን፣ አልሁን ማረጋገጥ እንኳን አልችልም” ሲል በነጋዴው ላይ የተለቀቀውን ሽብር ለጉባኤው አስረድቷል።
ቡሽም በጅምላ የሚካሄደው ጦርነት የመስቀል ጦርነት ነበር ያሉት። እሳቸው ግን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ከንግዱ ማሕበረሰብ ጋር የበለጠ በመቀራረብ ለኪራይ ሰብሳቢዎች የተጋለጠውን የንግዱን ሕብረተሰብ ከሌላው ጤነኛ የንግዱ ሕብረተሰብ መለየት አለበት። ሁሉም ነጋዴ የኪራይ ሰብሳቢዎች መጠቀሚያም ተባባሪም ሊሆን ስለማይችል ነው። ንግድም ዓለምን የለወጠ የተከበረ ተግባር ከመሆኑ አንፃር መንግስት ከዚህ በፊትም ሲያደርገው እንደነበረው አሁንም አጋርነቱን ማሳየት ይጠበቅበታል። ስለዚህም መሰረታዊ የመንግስትን የገቢዎችና ጉምሩክ ፖሊሲን “በሽብር”፣ “በፍርሃት” ቆፈን ቀይረው ለራሳቸው ጥቅም ያደሩ የመንግስት ባለስልጣናት በፈጠሩት የተሳሳተ የኪራይ ሰብሳቢ ፍቺም በተቻለ ፍጥነት ለንግዱ ማሕበረሰብ መሰረታዊ ዕሳቤውን ማቅረብ ያስፈልጋል። በአንድ ቅርጫት ውስጥ የተቀመጠው የንግዱ ማሕበረሰብ ስምም ተገቢውን ስፍራ ሊያገኝ ይገባል። በመንግስትም በበኩሉ ኪራይ ሰብሳቢዎችን መያዙ ምርጫው ሳይሆን ግዴታው መሆኑን ግንዛቤ መውሰዱም ይጠቅማል። በተረፈ መንግስትና ጤናማው የንግዱ ማሕበረሰብ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጸች መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር በመሆኑ ብዙ ማለት አይቻልም።¾(ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 402 ረቡዕ ግንቦት 14/2005)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 22nd, 2013
በፀጋው መላኩ
አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሰሞኑን የየሀገራቱን የኢኮኖሚ አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት እ.ኤ.አ በ2014 የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ወደ 5 ነጥብ 5 የሚወርድ መሆኑን አስታወቀ።
የገንዘብ ድርጅቱ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያም ሆነ አፈፃጸም ከመንግስት ጋር የሚለያይ ሲሆን የኢትዮጵያን መንግስት የባለሁለት አሀዝ እድገትን ባለአንድ አሀዝ እድገት መሆኑን ሲገልፅ ቆይቷል። እ.ኤ.አ በ2011/12 የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሁለት አሀዝ እድገትን የሚያስመዘግብ መሆኑን በገለፀበት ወቅት የገንዘብ ድርጅቱ በበኩሉ እድገቱ ሰባት በመቶ እንደሚሆን በትንበያው ያስቀመጠበት ሁኔታ ነበር።
የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባለፈው የካቲት ወር በለቀቀው መረጃ የኢኮኖሚ እድገቱን ቀመር ለመስራት ቀደም ሲል ሲጠቀምበት የነበረውን ብሄራዊ የአካውንቲግ ሲስተም በተሻሻለ የሂሳብ ስሌት እንዲቀየር መደረጉን በመግለፅ ብሔራዊውን የኢኮኖሚ እድገት መጠን ወደ 8 ነጥብ 5 በመቶ ያወረደበት ሁኔታ ነበር። በዚህም ወቅት የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የ6 ነጥብ 5 በመቶ እድገትና የኢትዮጵያ መንግስት የእድገት ቀመር ቢቀራረብም ሰሞኑን የወጣው የገንዘብ ድርጅቱ የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ደግሞ የቀጣዩን ዓመት እድገት ወደ 5 ነጥብ 5 በመቶ አውርዶታል። የኢትዮጵያ መንግስት ለተከታታይ ዓመታት የባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት ሲያስመዘገብ መቆየቱን ሲገልፅ የቆየ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ነዳጅ አምራች ካልሆኑ ሀገራት መካከል ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ ነው ተብሎ ሲጠቀስ ቆይቷል።n
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የሜይ 22 ዕትም
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 22nd, 2013
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በጉባኤው
ዋዜማ ላይ እየተወዛገበ ነው
‘‘የማህበሩ አመራር በኪራይ ሰብሳቢነት ተዘፍቋል’’
ከማህበሩ የታገዱ የም/ቤት አባላት
‘‘በኪራይ ሰብሳቢነት የተዘፈቁት የታገዱት አመራሮች ናቸው’’
የማህበሩ አመራር
በዘሪሁን ሙሉጌታ

የአዲስ አበባ ከተማ ገጽታ
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ከግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ የአመራር ምርጫ ያካሂዳል። ማህበሩ ጉባኤ ከማካሄዱ በፊት ወደ 15 የማህበሩ ም/ቤት አመራር አባላትን ማገዱን ተከትሎ ከታገዱት አባላት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።
70 አባላት ካሉት የማህበሩ ም/ቤት መካከል ወደ 23 የሚሆኑ አባላት አለአግባብ ‘‘ተባረናል’’ ሲሉ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅት ማህበሩን እየመራ ያለው የአመራር አካል በኪራይ ሰብሳቢነት መዘፈቁንም አመልክተዋል። በቅርቡ ለሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤም 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የተጋነነ ገንዘብ መመደቡንም ገልፀዋል። የተመደበውም ገንዘብ በአብዛኛው ‘‘ለተሃድሶ’’ ወይም ለመዝናናት የሚውል ከመሆኑም በላይ የገንዘብ አሰባሰብ ሂደቱም ግልፅነት የጎደለው እንደሆነም ተናግረዋል።
ማህበሩ ጉባኤውን ለማካሄድ የጠየቀውን 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ከአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞች፣ ከአዲስ አበባ ገቢዎችና መንገዶች ባለስልጣን እና ከሌሎች መንግስታዊ ተቋማት የሚሰበሰብ እንደሆነም አመልክተዋል።
በማህበሩ አመራር አለአግባብ ታግደናል የሚሉት እነዚሁ ወጣት አመራሮች በተጨማሪ እንደገለፁት የጉባኤው መሪ ቃል (ሞቶ) ‘‘የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመለስን ራዕይ እናሳካለን’’ የሚል መሆኑ ማህበሩ ነፃነት የሌለውና በኢህአዴግ ካድሬዎች የሚሽከረከር መሆኑን ማረጋገጫ ነው ብለዋል።
‘‘አለአግባብ ተባረናል’’ የሚሉት ወጣት አመራሮች የተባረሩበት ምክንያት በማህበሩ አካባቢ ኪራይ ሰብሳቢነት መስፈኑን በማጋለጣቸው፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በሕገ-መንግስታዊ መብታቸው መሠረት በሌላ ነፃ ማህበር ውስጥ አባል በመሆናቸው ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል።
ማህበሩ ለስሙ 80 ሺህ አባላት እንዳሉት ቢነገርም በትክክል የማህበሩን ስራ የሚያከናውኑ ከሁለት ሺህ እንደማይበልጡ ነው ቅሬታ አቅራቢዎቹ የገለፁት። የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወጣት ዮሐንስ ጣሰው ማህበሩን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም በኢህአዴግ ካድሬዎች ተፅዕኖ እንደሚደረግበትም ቅሬታ አቅራቢዎቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በማህበሩ አመራር ላይ በተነሱ ቅሬታዎች ላይ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወጣት ዮሃንስን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ያደረግን ቢሆንም ከስራ መብዛት ጋር በተያያዘ ልናገኘው አልቻልንም። ሆኖም የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ወጣት መድሃኔ መለሰ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፀው ከአንድ ሳምንት በፊት ስብሰባ ተካሂዶ እንደነበር እና 15 የማህበሩ የም/ቤት አባላት ለጊዜው መታገዳቸውን አምኗል። በማህበሩ ሕገ-ደንብ መሠረት የአመራር አባላት የሚባረሩት በጠቅላላ ጉባኤው መሠረት እንደሆነ አስታውቋል። 15ቱ የአመራር አባላት የታገዱት ከክፍለ ከተማ በመጣ ግምገማ መሠረት እየሰሩ አለመሆኑ በተጨባጭ ማስረጃ በመረጋገጡ ከክፍለ ከተሞች ለአስፈፃሚው በመጣ የግምገማ ሪፖርት መሆኑን አመልክቷል። ሦስቱ የአመራር አባላት ደግሞ በገዛ ፈቃዳቸው ከምክር ቤቱ እራሳቸውን በማግለል ሲሆን፤ የቀሩት አምስቱ ደግሞ ከሀገር በመውጣታቸው እንደሆነም ገልጿል።
ለጉባኤው የወጣው የገንዘብ መጠን በተመለከተ ወጣት መድሃኔ ተጠይቆ ትክክለኛው የገንዘብ መጠን 1 ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ሳይሆን አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ብር መሆኑን፤ ከዝግጅት ጋር በተያያዘም ጠቅላላ ጉባኤው መካሄድ ከነበረበት ጊዜ መዘግየቱን በመጪው ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ የወረዳ ም/ቤት ጉባኤዎች ከተካሄዱ በኋላ በሳምንቱ ደግሞ በከተማ ደረጃ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚካሄም አመልክቷል።
ለጉባኤው ወጪ የተደረገው የገንዘብ መጠን በ116 ወረዳዎች ውስጥ ለሚካሄድ ጉባኤ በመሆኑ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን የጠቀሰው ወጣት መድሃኔ በ116 ወረዳዎች ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ የተጠቀሰው ገንዘብ ቢያንስ እንጂ አይበዛም ብሏል።
ማህበሩ በመተዳደሪያ ደንቡ የገንዘብ ምንጩ በመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚደገፉ በመሆኑ ከመንግስታዊ አካላት በአይነት መደገፉ ወይም ስፖንሰር መደረጉ ችግር የለውም፤ የሚለው ወጣት መድሃኔ ገንዘቡ ለተሃድሶ (ለመዝናናት) ይውላል መባሉ በተጨባጭ እቅድ ላይ የሌለ ነገር ነው ሲል አስተባብሏል። ከመንግስት አካላት በገንዘብ ከሚሰጠው ድጋፍ በበለጠ በቲሸርት፣ በኮፍያና በአዳራሽ መልክ የሚደረጉ ድጋፎች እንጂ በካሽ አለመሆኑን አያይዞ ገልጿል።
የማህበሩ የአባላት ብዛት በተመለከተ ቀደም ሲል 80 ሺህ አባላት አሉት ይባል እንደነበር የጠቀሰው ወጣት መድሃኔ፤ ነገር ግን በተደረገው የማጥራት ስራ በአሁኑ ወቅት በማህበሩ እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት የሚሳተፉ የአባላት ቁጥር 32ሺህ መሆኑንም አስረድቷል።
የጉባኤው መሪ ቃል በተመለከተ ‘‘በመለስ ሌጋሲ የወጣቱን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን’’ መባሉ ከማህበሩ ነፃነት አንፃር ስላለው ፋይዳም ተጠይቆ፤ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አስተዳደር ወቅት ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፓኬጆች በመቀረፃቸው፣ በህገ-መንግስቱ ወጣቱ በነፃ በመደራጀቱና ወጣቱ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅተው ተጠቃሚ መሆናቸውን መነሻ በማድረግ የተወሰነ ነው ሲል መልሷል።
በማህበሩ ስም ከሚከራዩ ተቋማት ገቢ ጋር በተያያዘ ምዝበራ ስለመኖሩም ወጣት መድሃኔ ተጠይቆ ከአመራሩ ይልቅ በም/ቤቱ ከታገዱ ወጣቶች ላይ ይሄ ችግር መኖሩን ከታገዱበት ሦስት ምክንያቶች መካከል የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር አንዱ እንደሆነ በመግለፅ በአንፃሩ ማህበሩ አመራሩን የሚቆጣጠርበት ስርዓት መቀየሱን፤ በአሁኑ ሰዓት ሦስት የአመራር አባላት ከኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ጋር በተያያዘ በፍርድ ቤት ተከሰው ጉዳያቸው በሕግ መያዙን በመጥቀስ አመራሩ ኪራይ ሰብሳቢነት እየተዋጋ መሆኑን አመልክቷል።
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በ1990 ዓ.ም የተቋቋመ ማህበር መሆኑ ይታወቃል።n
(ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ሜይ 22 ዕትም)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 22nd, 2013
(ፍኖተ ነፃነት) የአያት አክሲዮን ማህበር፣ በስራአስኪያጁ አቶ አያሌው ተሰማና በሌሎች ማህበሩ አመራሮች ላይ ላይ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተመሠረቱባቸው ክሶች ጥፋተኛ በመባላቸው ዛሬ በልደታ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት በእስርና ከፍተኛ በገንዘብ እንደተቀጡ የፍኖተ ነፃነት የፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
የፍኖተ ነፃነትየፍርድ ቤት ዘጋቢ እንዳስታወቀው የልደታ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት አያት አክሲዮን ማኅበር 90 ሚሊዮን ብር፣ የአያት አክሲዮን የማኅበሩ መስራችና ከፍተኛ ባለድርሻ እንዲሁም ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ 12 ዓመት እስራት እና 3.2 ሚሊዮን ብር ቅጣት፣ ዶ/ር መሐሪ መኮንን 12 ዓመት ፅኑ እስራት እና 436,646 ብር ቅጣት፣ አቶ ጌታቸው አጎናፍር 10 ዓመት ፅኑ እስራት እና 411,969.60 ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡ የአያት አክሲዮን የማኅበሩ መስራችና ከፍተኛ ባለድርሻ እንዲሁም ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ እና ሌሎች ታዋቂ ነጋዴዎች ላይ ክስ በማቀናበርና በየሚዲያው ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶገብረዋህድ ገ/ጊዮርጊስ በሙስና ተጠርጥረው በቅርቡ መታሰራቸው ያስታውቃል፡፡
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013
ከያሬድ አይቼህ ፤ ሜይ 20፥2013

Ato Birhanu Damte (Aba mela)
የፓልቷኩ አባ-መላ ሰሞኑን ገኗል። መግነኑ አልከፋኝም … ይግነን … ለሁሉም ጊዜ አለውና። ግን አባ-መላን ብዙ ጊዜ አዳምጨዋለሁና የአባ-መላን ነገር መዳሰስ ፈለኩ። ሰሞኑን አባ-መላ ገዢውን ፓርቲ መተቸት ጀምሯል። ይህንን የሰሙ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በጣም ፈንጥዘዋል ፡ እኔ አልፈነጠዝኩም። ለምን?
አባ-መላ የሚናገረውን ነገር በየሳምንቱ ፡ አንዳንዴ አልፎ አልፎም ቢሆን ፡ አዳምጨዋለሁ። አባ-መላ የሚያረገውን የሚያረግው ለአንድ አበይት ምክንያት ብቻ ነው፦ የግል ጥቅም። አባ-መላ ሌላ ንዑስ ምክንያት የለውም። የሚያደርገው ፡ የሚናገረው ፡ የሚተነፍሰው ፡ የሚስቀው ፡ የሚያለቅሰው … ወዘተ … ለግል ጥቅሙ ነው (ለግል ጥቅሙ መቆሙ መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም ፡ ያ ምርጫው ነው)።
በ2008 እ.አ.አ. አባ-መላ ክፍል ውስጥ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው (“addis_ababa_1”? በሚል መጠሪያ ስም ሚሳተፍ) ክፍሉ ውስጥ በተነሳ ቅራኔ ምክንያት የክፍሉን ሚስጥር በተቃዋሚ ክፍሎች ውስጥ ገብቶ ሲናገር ሰምቻለው። ከተናገረው ሚስጥር አንዱ ፡ ቃል በቃል ባላስታውስም ፡ አባ-መላ ከሚድሯክ ወይም ከሼህ መሃመድ አልሙዲ በአመት $50,000 ዶላር እንደሚከፈለው ነው። ይሄ ነገር የአባ-መላን ባህሪ እና የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ትኩሳት ለመረዳት ወሳኝ መረጃ ሆኖ አገኝቼዋለሁ።
አባ-መላ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከሚድሯክ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። የሚድሯክ ጥቅም ሲከበር ፡ አባ-መላ ለኢህአዴግ እስክስታ ይወርዳል። የድርጅቱ ጥቅም ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስል ፡ አባ-መላ ደረቱን ይመታል።
አባ-መላ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆኖ አያቅም። አባ-መላ የሚድሯክን ገጽታ የሚያሽሞነሙን ፡ የደርግ ስርዓት ያፈራው ፡ አንደበተ ምላጭ ፡ የሚያደርገውን የሚያቅ ፡ ፕሮፓጋንዲስት ነው።
ታዲያ ምነው ሰሞኑን የፓልቷክ ተቃዋሚ ክፍሎች ባዶ ሆነው የሲቪሊቲ ክፍል ሞልቶ የፈሰሰው? ተቃዋሚ ባካችሁን በአባ-መላ አትበሉ። አባ-መላ ሚያደረገው ሁሉ ለአገራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙና ለሚያገለግለው ድርጅት ጥቅም ብቻ ብሎ መሆኑን እንገንዘብ።
ሚድሯክ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የከፈተና ፡ አያሌ ካፒታል ያፈሰሰ ድርጅት በመሆኑ ድርጅታዊ ገጽታውንና ጥቅሙን መንከባከቡ ተገቢና የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሚድሯክ እና በኢህአዴግ መካከል ሆነን ልንፈጭ ነውና ፡ በአባ-መላ የፓለቲካ ስልት እንዳንበላ ጠንቀቅ እንበል።
አባ-መላንም ሆነ ሌሎች ገዢው ፓርቲን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ሰዎችን ተስገብግበን ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጨመር የለብንም። በጊዜ ውስጥ ሊፈተኑ ፡ አመኔታችንን ቀስበቀስ ሊያገኙ ይገባል እንጂ ተንሰፍስፈን መርዝ ይሁን መድሃኒት እንደያዙ ሳናቅ አንቀበላቸው።
ወቅቱ የህወሃት/ኢህአዴግ መጨረሻ ወቅት ነውና የሚደናበሩትን የገዢውን ፓርቲ በላተኞች ለጥቅማችን እንጠቀምባቸው እንጂ እነሱ አይጠቀሙበን።
_ _ _ _ _ _
ጸሃፊውን ለማበረታታት ፡ ለመውቀስና ለማስፈራራት በዚህ ይጻፉ፦ yared_to_the_point@yahoo.com
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013
ከይገርማል ታሪኩ
(የመጨረሻ ክፍል)
የአባጃሌው ልጅ ሀይሌ ከፊታቸው ጥንቃቄ የሚጠይቅ ስራ ይጠብቃቸዋል:: መዐሕድ ድርጅቴ ነው: ቤቴ ነው ብሎ የተቀበለውን አባል አሳምኖ ወደመኢአድ ማሰባሰብ ቀላል ነገር አይሆንም:: ወያኔ መራሹ መንግስት የትጥቅ ትግል ለማካሄድ ሲንቀሳቀሱ ይዣቸዋለሁ ያላቸው በርካታ ሰዎች ከፕሮፌሰር አስራት ወ/የስ ጋር በእስር ላይ ናቸው:: የእስረኞች ቤተሰቦች: ዘመድ አዝማዶች እንዲሁም መላው አባላት መስዋእትነት የተከፈለበት ድርጅት ሲፈርስ ምላሻቸው ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም:: ጊዜ ወርቅ ነው:: ማንኛውም ነገር በትክክለኛው ወቅት ያለእንከን መፈጸም ይኖርበታል:: የወያኔና አንጋቾቹ የፈጠራ ወሬ የየዋሆችን ልብ ሊፈትን ይችላል:: የፖለቲካ ፓርቲወችም ቢሆኑ እንዳሸን ነው የሚፈሉት:: ጊዜ ከተሰጠ አይደለም የተራው አባል የየወረዳ አስተባባሪወችንም በነበሩበት ማግኘት ይከብዳል:: ጥቃትን ለመመከት ሁሉም የየመሰለውን አማራጭ ሊከተል ይችላል:: መፍጠን ይኖርባቸዋል::
ጠ/ ሚኒስትሩ “ለስልጣን የበቃነው ጀርባችንን በእሳት አስገርፈን ነው” ብለው ያሉት ሀሰትነት የለውም:: ደርግ ከስልጣን የወደቀው እንዲህ በቀላሉ አልነበረም:: የትግራይ ወጣቶችን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያዊ ደርግን ለመጣል እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ አድርጓል:: በትግሉ ወቅት ይህ ነው የማይባል ንብረት ወድሟል:: ከሁሉም በላይ የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል:: ነገር ግን ደርግን ለመጣል በተደረገው ትንቅንቅ መስዋእት የሆኑት ኢትዮጵያውያን ለትግል የተነሱት ወያኔ የሚያዝ የሚናዝዝበትን አምባገነን ስርአት ለመመስረት አልነበረም- የአምባገነኑን ስርአት አፍርሰው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በሚያስከብር ስርአት ለመተካት እንጅ:: ወያኔ ግን የህዝብ ልጆች በመስዋእትነታቸው ያስገኙትን ድል ለራሱ በሚመች መልኩ አዘጋጀው:: ለተሰውት የህዝብ ልጆች ካሳ የሚገባኝ እኔ ነኝ ብሎ ድርቅ አለ:: በርግጥ ወያኔ ደረቅ ብቻም አይደለም- ብልጥም ነው::
የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሞቱም ሆነ እንዲጠነክሩ አይፈለግም:: ተቀናቃኝ ፓርቲወች አሉ መባሉ የገዥውን ፓርቲ መልካም ገጽታ በአንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል:: የዴሞክራሲ ስርአት አንዱ መገለጫ ከገዥው ፓርቲ ሌላ የተደራጁ ተፎካካሪ ፓርቲወች መኖር ነው:: ታማኝ የሆኑ ፓርቲዎች ከመንግስት ልዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይችላል:: ታማኝ ፓርቲዎች ታማኝ ተቃዋሚ ያላቸው ናቸው:: ታማኝ ተቃዋሚ በሆነ ባልሆነው መንግስትን አይጐንጥም: የሰጡትን በጸጋ ይቀበላል:: ሕዝብንና መንግስትን ለመነጠል አይሞክርም:: በዚህ ስሌት መሰረት መኢአድም ሆነ ሌላ ፓርቲ ቢመሰረት ችግር የለውም:: ችግር የሚሆነው ፓርቲዎች ገንነው መውጣት ከጀመሩ ነው:: ሕዝብ የሚደግፋቸው ፓርቲዎች ቀይ መስመርን የተሻገሩ ናቸው:: ቀይ መስመር ማለት ኢሕአዴግ ለተቃዋሚዎች ያስቀመጠው የመንቀሳቀሻ ዳራ ነው:: ቀይ መስመሩን አይደለም ማለፍ መንካት ቀይ ካርድ ያሰጣል:: ቀይ ካርድ ያየ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከጨዋታ ውጭ ይሆናል:: በጥፋትም ይቀጣበታል:: ኢህአዴግ በወረቀት ላይ ያሰፈራቸው የፖለቲካ: የኢኰኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፖሊሲዎች በትክክል በስራ ላይ ቢውሉ ህልውናው ሊያከትም እንደሚችል ያውቀዋል:: የነጻና የገለልተኛ ማህበራዊና ዴሞክራሲያዊ ተቋሞች መኖር ለህልውናው ጸር ናቸው:: ትክክለኛ ምርጫ ቢካሄድ እንደማይመረጥ ይረዳል:: መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማይደግፈው እንዲያውም እንደሚጠላው ያውቃል:: ስልጣኑን ከለቀቀ ደግሞ በስልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ለሰራቸው ወንጀሎች ሁሉ መጠየቅ ይመጣል:: ባለስልጣናቱ ያላግባብ ያከማቹት ንብረት ሊወረስ ይችላል:: ስልጣን ከሌለ አይደለም ሀብት ንብረትን ህልውናንስ እንዴት ማስጠበቅ ይቻላል? ተተኪው መንግስት ያለፈውን ሁሉ ይቅር ብሎ የያዙትን ይዘው ከስልጣን ብቻ ገለል እንዲሉ ስለመፍቀዱ ምን ማረጋገጫ ይኖራል? ስለዚህ ወረቀት ላይ ያለው ለተመልካች ፍጆታ የሚውል ነው:: በስራ ላይ የሚውለው በስውር የሚተላለፈው የውስጥ መመሪያ ነው:: ወረቀት ላይ የሰፈረውንና በተግባር እየታየ ያለውን አለመጣጣም የተመለከተ “እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል?” ብሎ ቢጠይቅ መልሱ ቀላል ነው:: “ፖሊሲወቻችን እንከን የላቸውም:: ዴሞክራት ናቸው የሚባሉ ሀገሮችን በጎ ተሞክሮወች ሁሉ ያካተቱ ናቸው:: ችግሩ የአፈጻጸም ነው:: አፈጻጸምን ለማሻሻል አቅምን ማሳደግ የግድ ይላል:: እና ለአቅም ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እጃችሁን ዘርጉ” የሚል መልስ ይሰጥና ሌላ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ይሰራል:: የመናገር: የመሰብሰብ: ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ: የመምረጥ: ወዘተ መብቶች በወረቀት ላይ ያሉ እንጅ በተግባር የሚተረጎሙ አይደሉም:: እኒህን በወረቀት ላይ የተጻፉ መብቶች ለመጠቀም የሞከረ ማንኛውም አካል ቀይ መስመሩን የተሻገረ ነው::
መኢአድ ዳዴ ማለት እስኪጀምር ድረስ ከመንግስት ምንም አይነት ጥቃት ሊሰነዘርበት እንደማይችል የተረዱት ሀይሌ ካለምንም ስጋት እንደበፊቱ ሁሉ ጎንደርንና ጎጃምን ከዳር ዳር አዳረሷቸው:: በመኪና የሚኬደውን በመኪና: ለፈረስ የተመቸውን በፈረስ ካልሆነም በእግር:: “ግዴላችሁም እኔ ያጠፋኋችሁ ልሁን” ይላሉ ሻለቃ ያገነገኑ ሰዎች ሲያጋጥሟቸው:: ባርኔጣቸውን ከጭንቅላታቸው ላይ አንስተው ፍጹም ትህትና በተመላበት አኳኋን “ጤና ይስጥልኝ ጌታየ” ብለው ሲቀርቡ አይሆንም ብሎ ገፍቷቸው ሊሄድ የሚችል ሰው አይገኝም:: ቀልቡን ሰብሰብ አድርጎ ያዳምጣቸዋል:: በዚህ መልክ ቀደም ሲል የመዐሕድ አባል የነበሩትን ሁሉ ወደመኢአድ አስገቧቸው:: የየወረዳ ኮሚቴዎችንም አጠናከሩ::
’የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲወች ግንባር’ ለመፍጠር የተደረጉት ብዙ ሙከራወች ገንዘብ: ጉልበትና ጊዜ በልተው ሳይሳኩ ቀርተዋል:: በሀገር ውስጥ ከኦብኮና ከደቡብ ሕዝቦች ጋር ተመስርቶ የነበረው ህብረት ብዙ መሄድ ሳይችል ቀርቶ ፈርሷል:: በውጭ ሀገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ያካተተው የተቃዋሚ ሀይሎች ህብረትም ቢሆን አባል ፓርቲዎችን ሰብስቦ ይዞ መቀጠል አልቻለም:: ኢዴፓና መኢአድ ተከታትለው ከህብረት ጋር ተፋተናል ሲሉ አውጀው የየራሳቸውን መንገድ ተከተሉ:: በመሰባሰባቸው ተስፋ አሳድሮ የነበረው ሕዝብ ተስፋው ጫጨ:: ሻለቃ ከህዝብ ጋር ተመሳስለው ኗሪ በመሆናቸው የህዝቡን ስሜት ይከታተላሉ:: ይህ የፓርቲወች ህብረት መፍረስ መሰራት እርሳቸውንም አበሳጭቷቸዋል:: “እንዲያው ምን ይሻላል? የልጅ ጨዋታ አደረጉትኮ” ይላሉ ከመሰሎቻቸው ጋር ሲያወጉ:: እንዲህ እንዲህ ሲል ቆይቶ በአራት ፓርቲዎች (መኢአድ: ኢዴፓ: ቀስተደመና: ኢዴሊ) ጥምረት ቅንጅት ተመሰረተ::
የቅንጅት መመስረት በየአካባቢው ይደረጉ የነበሩትን የፓርቲዎች የጎንዮሽ ሽኩቻ አስታገሰ:: ባህርዳር ጽ/ቤት የከፈቱት መኢአድና ኢዴፓ መድህን መጠላለፋቸውን ትተው በአንድነት ቆመዋል:: ቀደም ባሉት ጊዚያት አንዱ የሌላውን ጽ/ቤት ረግጦ አያውቅም ነበር:: አሁን ሁኔታው ተለውጧል:: ሁለቱም ጽ/ቤቶች የጋራ አገልግሎት እየሰጡ ነው:: ኢዴፓዎች ድንቅ ድንቅ ሰዎች አሏቸው:: ጥሩ ሀሳብ ማመንጨት: በሳል አመራር መስጠት የሚችሉ ሰዎችን ያካተተ ስብስብ ነው ኢዴፓ:: መኢአድ በአደረጃጀት ከኢዴፓ በእጅጉ ይበልጣል:: በሻለቃ ሀይለየሱስ ሀላፊነት ስር የሆነው ባህርዳር ልዩ ዞንና ምእራብ ጐጃም ዞን እስከቀበሌ ድረስ ተደራጅቷል:: በየአንዳንዱ የገጠር ቀበሌ አምስት አምስት አባላት ያሏቸው አመራር ሰጪ ኰሚቴዎች ተቋቁመዋል:: የባህር ዳር የመኢአድ ወኒያምና ቆራጥ አባላት ኢዴፓዎችን ወደዋቸዋል:: በመሀል የነበረው የመፈራራትና የመጠራጠር ስሜት አሁን የለም:: አንድ ላይ ተሰብስበው ይመክራሉ: መክረውም በጋራ ይወስናሉ::
የቅንጅት አመራር ከገዥው ፓርቲ ጋር የሚያደርጋቸው ክርክሮች የሁሉንም ቀልብ ስቧል:: አርሶ አደሩ ሳይቀር ክርክሩን ለመከታተል ሬዲዮ ገዝቶ ጆሮው ላይ ለጥፎ ይውላል:: የሰላ አንደበትና የበሰለ ትችት የኢሐዴግን ተከራካሪዎች ያንተፋትፍ ይዟል:: ፖለቲካው ነፍስ እየዘራ ነው:: ባሕር ዳሮች የበለጠ ተነቃቅተዋል:: አሁንም ባሕርዳሮች እንደማእከል እያገለገሉ ነው:: ከየዞኖች በሚመጡ ችግሮች ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል:: የቅንጅት ኮሚቴው ለችግሮች መፍትሄ ፍለጋ ከፖሊስና ከአስተዳደር ጋር ውይይት ያደርጋል:: መፍትሄ ግን የለም:: ያም ሆነ ይህ ቅንጅት በያንዳንዱ ልብ ውስጥ ቦታ ይዟል:: ትልቅ ስኬት! የቅንጅት የምርጫ ምልክት የሆነው ሁለት ጣት የሰላምታ መለዋወጫ ሆኗል:: መቸም ፌስታ ነው:: እስካሁን ስር የሰደደ ችግር አይታይም::
የኢትዮጵያ አርሶ አደር የመላው ኢትዮጵያን ሕዝብ ከ80%-85% ያህል ይሆናል:: ኢሕአዴግ የትግል አጋሬ ነው የሚለው አርሶ አደሩን ነው:: አርሶ አደሩ የሚኖረው በገጠር ነው:: ስለዚህ ቢያንስ 80% የፓርላማ ወንበር እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ሆኗል:: ቢሆንም እኒህ መአተኛ ቅንጅቶች ወደገበሬው መጠጋት የለባቸውም:: መርዛቸው እንዲህ በቀላሉ የሚነቀል አይሆንም:: ስለዚህ ባህርዳሮች ወደገጠር ተጉዘው አርሶ አደሩን እንዳያሰባስቡ ሆደ ሰፊው ብአዴን መንገዶችን ሁሉ ጥርቅም አድርጐ ዘጋ::
አርሶ አደሩ ተሰባስቦ የሚገኝበት የእረፍት ጊዜ የደብሩ ታቦት የሚከበርበት ቀን ነው:: ለምሳሌ አዴት ታቦቱ መድሀኔአለም ከሆነ አዴቶች የወሩን 27ኛ ቀን ስራ ፈትተው ያከብሩታል:: በእለቱ ቤተክርስቲያን ሄዶ ማስቀደስ: የታመመን መጠየቅ: የተጣላን ማስታረቅ: ዘመድ ወዳጅን መጐብኘት ነው ዋናው ስራ:: ሌላውም ቢሆን እንዲሁ የየራሱን የበአል ቀን በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የሚያሳልፈው:: ይህች ቀን አርሶደሩ ቤተክርስቲያን ተሰባስቦ የሚገኝባት ናት:: ቅንጅቶች ይህችን ቀን እንደሚጠብቁ ግልጽ ነው:: የየደብሩ ታቦት ከሚውልበት ቀን የተሻለ አይገኝምና ወደዚያው ይገሰግሳሉ:: ታዲያ ይህን የሚያውቁት ብአዴኖች እለቷን በተለያየ ፕሮግራም (ጤና: ጸጥታ: ልማት ወዘተ) ወጥረው ይይዛሉ:: ባሕር ዳሮች አርሶ አደሩን አሰባስበው የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ለማስተዋወቅ አልተቻላቸውም:: ከወር አንዲት የበአል ቀን ጠብቀው ተጉዘው ሲደርሱ ፖሊሶች ቀድመው ቦታው ላይ ተገኝተው ’ቤተክርስቲያን ውስጥ የፖለቲካ ስራ መስራት አይቻልም’ በማለት ይከለክሏቸዋል:: ከቤተ ክርስቲያን መልስ ገበሬው ምሳውን እንኳ መብላት አልፈቀድለት ብሎ እስከ ምሽት ድረስ በስብሰባ ይጠረነፋል:: ይህ ቀደም ሲል ያልነበረ ልምድ የተፈጠረው ቅንጅቶች ገበሬውን እንዳያገኙትና እንዳይበክሉት በሚል ነው:: “ቀደም ብለን የያዝነው ፕሮግራም ስለሆነ በእኛ ፕሮግራም ማንም የፖለቲካ ስራ እንዲሰራ አንፈቅድም:: ከፈለጋችሁ በሌላ ቀን ልትጠሩ ትችላላችሁ” እየተባሉ ቅንጅቶች ድካም ብቻ አትርፈው መመለስ ጀመሩ:: ይህንን የተገነዘቡት ሻለቃ አንድ ብልሀት ዘየዱ:: ሀይሌ የማንንም ሀሳብ አይንቁም:: “ከአንድ ራስ ሁለት ይበልጣል: ለእኔ ያልታየኝ ለአንተ ሊታይህ ይችላል” የሚሉት ሀይሌ የሁሉንም ሀሳብ ካዳመጡ በኋላ “ሁሉም የነርሱ ነው:: በየቦታው ሄደን አቤት ብንልም መፍትሄ ልናገኝ አልቻልንም:: በየገጠሩ ለፍተን ሰውን እንዳናገኝ ስለተከለከልን ካለምንም ውጤት ደክመን እየተመለስን ነው:: አርሶ አደሩ እንዳይከዳቸው በጣም ሰግተዋል:: ፈርተውናል:: እንግዲህ አንድ የሚታየኝ አማራጭ አለ: የቤት ለቤት ቅስቀሳ” ሲሉ ተናገሩ:: ይህ ሀሳብ መተኪያ የሌለው ነው ተብሎ በመታመኑ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እንዲካሄድ ተወሰነ:: የየቀበሌው ኮሚቴ አባላት የዚህን ስራ ሀላፊነት ወሰዱ:: በዚህ መሰረት የቤት ለቤት ቅስቀሳው ተጀመረ:: የየቀበሌው ኮሚቴ አባላት ከቤት ቤት እየዞሩ ግንዛቤ ማስጨበጥ ቀጠሉ:: “እናንተ ቅንጅትን እንድትመርጡ የምንፈልገው በምርጫው ቀን በምርጫ ወረቀቱ ላይ ብቻ ነው:: ከዚያ ውጭ እነርሱ የሚሏችሁን ሁሉ እሽ በሏቸው:: ተሰብሰቡ ሲሏችሁ እሽ: ማንን ነው የምትመርጡ ሲሏችሁ እናንተን በሏቸው:: ማን ማንን እንደመረጠ የሚያሳይ መሳሪያ ተክለናል የሚሉት ውሸታቸውን ነው:: እንዲህ አይነት መሳሪያ የለም” እያሉ አስጠኗቸው::
በከተሞች አካባቢ የሚደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በአንጻራዊነት በእጅጉ የተሻለ ነው:: ቅንጅቶች የምርጫ ምልክታቸውን የያዘ ቲሸርት አሰርተው ለብሰዋል:: ትግሉ ኢሕአዴግን በሰላማዊ መንገድ ከስልጣን ለማስወገድ ነው:: አለበለዚያ መብቶች የሚከበሩባት: ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመስረት አይቻልም:: ኢሕአዴግን ከመንበረ ስልጣኑ ለማንሳት አብዛኛውን የፓርላማ መቀመጫ ማሸነፍ የግድ ይላል:: ስለዚህ የእኔ የእኔ ብሎ ነገር የለም:: ቅስቀሳው መካሄድ ያለበት በጋራ ነው:: በጋራ ወጪ መኪና መከራየት: የቅስቀሳ ወረቀቶችን ማባዛት: ሁሉንም- በጋራ መከወን:: ሕዝቡ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ከቅንጅቶች ጐን መቆሙን በግብር እያሳየ ነው:: ጽ/ቤቶች በሰው ተጣበቡ:: ማን ማን እንደሆነ አይታወቅም:: ሁሉም ይወጣል ይገባል: ይሰራል:: አንዳንዶች ስጋት ገብቷቸዋል:: ይህንን እድል ተጠቅሞ ብአዴን ብዙ ነገር ሊያበላሽ ይችላል:: ሻለቃ እንዳባት ይገስጻሉ: ይመክራሉ:: “ቢመጡ እኛ ምን ቸገረን:: በድብቅ የምንሰራው ስራ የለን! ሚስጥር ባይኖርባቸውም ጥንቃቄ የሚጠይቁ አንዳንድ ሰነዶቻችንን ከእይታ አርቀናቸዋል:: እዚህ ያለው ጽ/ቤቱና መገልገያ እቃወች ብቻ ናቸው:: የሚያስፈራን ምንም ነገር የለም:: እንዲያውም እንግዶችን መቀበል ያለብን በትህትና ነው:: አያችሁ በአንድ ሰው ብልጫ አንድ ወንበር ይገኛል: በአንድ ወንበር ብልጫ ደግሞ ገዢ ፓርቲነት:: ያላወቅነው ሰው ሁሉ ጠላታችን ነው ብለን ፊት የምንነሳው ከሆነ ምናልባት ያ ሰው በእውነት ሊያግዘን የመጣ ሰው ቢሆን ሊሸሸን ማለትም አንድ ድምጽ ሊያሳጣን ይችላል” በማለት የአባላትን የጎፈነነ ስሜት ገፈፉ:: ጥድፊያ ነው:: ሁሉም ይሰራል:: ቅንጅቶች ሰርግ የሚደግሱ መሰሉ:: ከሁሉ ከሁሉ ባህር ዳር የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ አስገራሚ ነበር:: የባሕርዳር ኗሪ ለስብሰባው ንቅል ብሎ ወጥቷል:: የፖሊና የፔዳ ተማሪወች ቀድመው ስቴዲዮም ደርሰዋል:: የባሕርዳር ስታዲዮም የቅንጅትን እድምተኛ ሰብስቦ መያዝ ባለመቻሉ አካባቢው ሳይቀር በሕዝብ ተጨናንቋል:: እለቱ የጥምቀት በአል የሚከበርበት እንጅ ስብሰባ የሚደረግበት አይመስልም:: ከአዲስ አበባ የቅንጅት አመራር ተወካዮች ተገኝተዋል:: የመድረክ መሪው ሰላማዊ መፈክሮችን ያሰማል:: በዚህ ወቅት አንድ ለየት ያለ ነገር ተከሰተ:: “አንድ በኢትዮጵያ ባንዲራ ያጌጠች መኪና ክላክስ እያሰማችና ከሰው ጋር እየተጋፋች በቀስታ ወደስታዲዮሙ ዘለቀች:: በመኪናዋ ላይ ያሉት ሰዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው መፈክር ያሰማሉ:: የመድረክ መሪው ጩኸት በተቀላቀለበት መንፈስ ደስታውን ገለጸ:: “በጭብጨባ ተቀበሏቸው” አለ:: ስታዲዮሙ በጩኸትና በፉጨት ድብልቅልቁ ወጣ:: በዚያች መኪና የመጡት ሰዎች የሙገር አግሮ ኢንዱስትሪ ሰራተኞች ነበሩ:: ስብሰባው ከታሰበው በላይ በደመቀ ሁኔታ በስኬት ተጠናቀቀ:: በበነጋታው ጠዋት የሙገር አግሮ ኢንዱስትሪ ባለቤት የሬዲዮ ቃለመጠይቅ እየተደረገላቸው ነበር:: “ቅንጅት መኪናችንን አስገድዶ በመውሰድ ለቅስቀሳ ተጠቀመባት” ብለው እርፍ አሉ:: ምን ያድርጉ? ተይዘዋል ማለት ነው:: የእውነት ዴሞክራሲ አለ መስሏቸው መብታቸውን ተጠቅመው ድጋፋቸውን የሰጡት አግሮ ኢንዱስትሪዎች በወያኔ ተስፈኞች ጥርስ ውስጥ ገቡ::
የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች በየጽ/ቤቶች እየተገኙ እየተደረገ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ይከታተላሉ: አስተባባሪወችን ይጠይቃሉ:: በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ኦሪያል ብራዚል በጣና ሆቴል የቅንጅትና የህብረት ተወካዮችን አግኝተው አነጋግረዋል:: ሁለቱ ድርጅቶች እያከናወኗቸው ያሉትን ተግባራት: በገዥው ፓርቲ እየደረሱብን ነው ያሏቸውን ችግሮች ገልጸው እኛን ለማፈን ከበላይ አካል ተዘጋጅቶ በተዋረድ እስከቀበሌ ድረስ እንዲሰራበት የተላለፈ የውስጥ መመሪያ ነው በማለት ሰነድ አስረክበዋል:: አሜሪካም ሆነች ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች ግንባራቸውን ኮስተር አድርገው ወያኔን “ዋ!” ብለው ከእኩይ ተግባሩ እንዲታቀብላቸው ሊያስፈራሩላቸው አሻፈረኝ ካለም አርጩሜ ቆርጠው ሾጥ ሾጥ አድርገው ሊያስተካክሉላቸው እንደማይችሉ ያውቃሉ:: ግን ተግባሩ መገለጽ ስላለበትና ለፎርማሊቲም ያህል መሆን ስለሚገባው ተደረገ:: በወያኔ እኩይ ተግባር አንጀቱ ያረረ ሁሉም ነው: የራሱ አባላት ጭምር:: ስለዚህ የወያኔን ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ሰነዶችን ማግኘት ከባድ አልነበረም::
አይደርስ የለምና የምርጫው እለት ግንቦት 7 1997 ደረሰ:: ሁሉም በጠዋት ተነስቶ ስፍራ ስፍራውን ይዟል:: የቅንጅት ጽ/ቤት በጣም በጠዋት እንዲከፈት በተወሰነው መሰረት ጽ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰሩ የተመደቡት ሰዎች በጠዋት ተገኝተው ስራቸውን ማከናወን ጀምረዋል:: ሪፖርት ይቀበላሉ: ሪፖርት ያደርጋሉ:: በምርጫ ጣቢያወች በታዛቢነት የተመደቡት የቅንጅት ሰዎች ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷቸው ተሸኝተዋል:: “ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ በፊት የምርጫ ኮሮጆው ባዶ መሆኑን አረጋግጡ: ብአዴኖች ሊያበራግጓችሁ ስለሚሞክሩ በምንም መልኩ ሳትደናገጡ በትእግስት ማጠናቀቅ አለባችሁ:: መራጩ ህዝብ ላይ የሚደረገውን ወከባ ተጋፈጡ:: የሚስጥር ድምጽ መስጫው አካባቢ የኢሕአዴግ ሰዎችን እንቅስቃሴ ተከታተሉ: የድምጽ ቆጠራው እንደተጠናቀቀ የምርጫ ጣቢያው ማህተም ያረፈበት ውጤት ተቀብላችሁ በፍጥነት ወደጽ/ቤት እንድትመለሱ —” ተብለው ተመክረው ነው ቀድመው በየምድብ ቦታቸው እንዲገኙ የተደረጉት:: በሌላ በኩል ከኗሪው ጋር ተመሳስለው በምርጫ ጣቢያወች አካባቢ የሚደረጉ ሁኔታወችን እየተከታተሉ በስልክ ጽ/ቤት ላሉት ሰዎች እንዲያስተላልፉ የተመደቡት ሰዎች በንቃትና በጥንቃቄ ግዳጃቸውን እየተወጡ ነው:: ሁሉም ነገር አሪፍ ነው:: ኢሕአዴግ በምእራብ ጐጃሞች ላይ ተደጋጋሚ የፍተሻ ተኩስ አካሂዶ ችግር የለም ብሎ ደምድሟል:: በወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት የፍተሻ ተኩስ ማለት አንድ ጠላት ሊኖርበት ይችላል ተብሎ የተጠረጠረ አካባቢ ላይ የሚደረግ የሩምታ ተኩስና አሰሳ ነው:: ተኩስ በተደረገበት አካባቢ ጠላት ካለ የአጸፋ ተኩስ ይከፍታል:: ምእራብ ጐጃሞች ይህን የፍተሻ ተኩስ አልፈውታል:: በየስብሰባው ላይ እየተገኙ የገዥው ፓርቲ አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል:: ደረሱብን ብለው ያሏቸውን ችግሮች አሰምተው በሚቀጥሉት አምስት የስልጣን ዘመናቸው ችግሮቻቸው እንደሚቀረፉላቸው በብአዴኖች ቃል ተገብቶላቸዋል:: የየተሰበሰቡበት የውሎ አበል ተከፍሏቸው ተቀብለዋል:: በየስብሰባው ማብቂያ ላይ የቀረበውን ድግስ በደስታ ተጋብዘው ተመራርቀዋል:: ቅንጅት ጸረ ልማት ድርጅት እንደሆነ ተነግሯቸው ልክ ነው ብለው ቅንጅትን አውግዘው ፈክረዋል:: ስለዚህ ብአዴኖች በምእራብ ጐጃም ላይ ስጋት የለባቸውም:: ሙሉ ሀይላቸውን እነርሱን በሚነቅፉና አስተማማኝነታቸው በሚያጠራጥር ዞኖች ላይ ብቻ ማሳረፍ እንዳለባቸው አምነዋል:: እና ለምእራብ ጎጃም የየምርጫ ጣቢያ አስመራጮች የተለየ መመሪያ አልተላለፈም::
የምርጫው እለት ማታ መላው የባሕርዳር ህዝብ እንቅልፍ በአይኑ አልዞረም:: በንቃት ይጠብቃል:: መብራት አሁንም አሁንም ይቋረጣል:: “ሌባ ሌባ” ሲል ሕዝቡ ይጮሀል:: ብአዴኖች ወያኔ የሚሆነውን የሚሆኑ: አድርጉ የሚባሉትን የሚያደርጉ ሮቦቶች ናቸው ብሎ ስለሚያምን ሁሌም ይጠራጠራቸዋል:: መብራት የሚያጠፉ ቀድመው ባዘጋጁት የተሞላ የምርጫ ኮሮጆ ሕዝብ ድምጽ የሰጠበትን ኮረጆ ለመቀየር ነው ብሎ ይጠረጥራል:: እና መብራት ሲጠፋ “ሌባ ሌባ” እያለ ግር ብሎ ወደየምርጫ ጣቢያዎች ይተማል:: አንዳንድ ባለመኪኖች የመኪናዎቻቸውን የፊት መብራቶች ወደምርጫው ቦታ ቦገግ አድርገው በማብራት ሌብነቱን ለመከላከል ይጥራሉ:: በጥበቃ ብዛት ሕዝቡ ተሰላችቶ ወደየቤቱ እንዲመለስ ይመስላል ጊዜን በአግባቡ አለመጠቀም ይታያል:: እሁድ በጠዋት ወረፋ ይዞ ቀድሞ መርጦ ወደጉዳዩ ለመሰማራት ያሰበው ሕዝብ ወረፋው አልደርስ ብሎ እስከእኩለ ሌሊት ድረስ ተጉላላ:: ቢሆንም ሁሉም በእልህ: በጽናትና በትእግስት የፍላጎቱን አሳካ- መረጠ::
ሻለቃ ልጃቸውን እንደሚድሩ አባት በደስታ ብዛት የሚይዙትን የሚጨብጡትን አሳጥቷቸዋል:: ይህን ይዘው ያን ይጥላሉ:: ወዲያ ሄድው ወዲህ ይመለሳሉ:: ሳያስቡት ብድግ ይሉና ተመልሰው ቁጭ ይላሉ:: እርሳቸው የሚወዳደሩበት የምርጫ ክልል መራጭ ወገኖቻቸው አይዞህ ብለዋቸዋል:: ደራወች ጥለው አይጥሏቸውም:: ምእራብ ጐጃም በርሳቸው የተደራጀ በመሆኑ በአሸናፊነት እንደሚወጡ ሙሉ እምነት አላቸው::
ሰኞ እለት ከጠዋት ጀምሮ የቅንጅት የምርጫ ታዛቢወች እየተንጠባጠቡ ወደቅንጅት ጽ/ቤቶች መምጣት ጀመሩ:: የየምርጫ ጣቢያው ማህተም ያለበት የድምጽ ውጤት በእጃቸው ይዘዋል:: የቅንጅት አስተባባሪወች የየምርጫ ክልሎችን አሸናፊ ለማወቅ ከየምርጫ ጣቢያወች የመጡትን ውጤቶች መደመር ቀጠሉ:: ለማመን ይከብዳል:: ምእራብ ጐጃም ላይ መቶ በመቶ (100%) ቅንጅት አሸንፏል:: ቅንጅቶች ብዙ አይነት ስሜት እየተሰማቸው ነው:: ደስታ: ስጋት: ፍርሀት:: ደስታቸው:- የትግላቸው ፍሬ መልካም ከመሆኑ የመጣ ነው:: ስጋታቸው:- ምእራብ ጐጃም ላይ የተገኘው ውጤት በሌሎች ዞኖችና ክልሎች ያልተገኘ እንደሆነ ከሚል የመነጨ ነው:: ፍርሀታቸው:- ሕዝብ በድምጹ የጣለው መንግስት ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል ካለማወቃቸው የተነሳ ነው:: ምናልባት ምክንያት ፈጥረው በድርጅቱና በአባላቱ ላይ የጥፋት ስራ ቢሰሩስ? ሕዝቡንስ ይበቀሉት ይሆን? ወይስ ምን?
ሻለቃ ወታደር በመሆናቸው ጠርጣራ ናቸው:: በተለይ ወያኔ ከቶውንም ሊታመን የማይችል ድርጅት ነው:: ብአዴኖች ደግሞ የራሳቸው ህሊና የላቸውም:: አስፈራራ ሲባሉ የሚያስፈራሩ: ደብድቡ ሲባሉ ሙልጭ አድርገው የሚገርፉ: እሰሩ ሲሏቸው የሚያስሩ: ግደሉ ሲባሉ የሚገድሉ ናቸው:: ለእነርሱ ሕዝብ: ሞራል: ምናምን ቦታ የላቸውም:: ስለዚህ ወያኔ ሱርፍ ብሎበት ‘ለየታዛቢወች የሰጣችኋቸውን የውጤት መግለጫ ሰነዶች በአስቸኳይ ቀሙ’ ካላቸው እሳት ጐርሰው እሳት ለብሰው እንደሚመጡባቸው ያውቃሉ:: አሁንም ፍጥነት ያስፈልጋል:: የውጤት መግለጫ ሰነዶችን ሰብስቦ ማራቅ::
የምእራብ ጐጃም አርሶ አደር ታሪክ ሰራ:: እንዲህ ያለ ውጤት በየትኛውም የሀገሪቱ የየክልል ዞኖች አልታየም:: ሻለቃ በምእራብ ጎጃም ኮርተዋል:: ቃሉን የማያጥፍ: ለእውነት የቆመ: የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ስብስብ ሲሉ ያሞካሻሉ:: ወያኔ ደግሞ ‘ጐጃም በከፋ ሁኔታ አጠቃን:: ጉድ ሰራን:: ጐጃምና ተልባ እያደረ ሸርተት ነው የሚባለው ተረት ሀሰት መስሎን ነበር’ ሳይል አይቀርም:: ጐጃም በፍርሀትና በጥቅም ቃሉን አይለውጥም:: በነጻነት ለመወሰን እድሉን ሲያገኝ ሁሌም ከእውነት ጐን የሚሰለፍ ባለማተብ ሕዝብ ነው:: ’ውሻ በበላበት ይጮሀል’ የጎጃሞች መለያ አይደለም::
ቅንጅት በበርካታ የምርጫ ክልሎች ተጭበርብረናል ባለበት ወቅት አያልቅበት ወያኔም “ካላችሁስ ኧረ እኔም ተጭበርብሬአለሁ” ብሎ ቀረበ:: ይሉኝታና ሀፍረት አልፈጠረበትም:: ለነገሩ ይሉኝታና ሀፍረት የፋራ ነው: ወያኔ ደግሞ አራዳ:: ቅንጅት ቅሬታ ካቀረበባቸው የምርጫ ክልሎች በዳግም ምርጫው አንድም ሳያገኝ ቀረ:: ወያኔዎች ተጭበርብረናል ብለው ቅሬታ ያቀረቡባቸውን ቦታወች አስመለሱ:: እንዲህ ናቸው ወያኔዎች:- ታግለው የሚጥሉ: አባረው የሚይዙ: ሮጠው የሚያመልጡ: ተናግረው የሚያሳምኑ: ተከራክረው የሚረቱ:: እና ሁሉም ሆነ:: በዳግም ምርጫው ምእራብ ጐጃም በድምጹ አስከብሮት የነበረውን አንድ ወንበር አጣ:: ም/አፈ ጉባኤ ሽታየ ምናለ በዳግም ምርጫው በክንዳሙ ወያኔ እገዛ አንድ የፓርላማ ወንበር ከህዝብ ነጠቁ::
-ጐጃም በመጀመሪያወች የወያኔ የግዛት አመታት በተጭበረበረ ገንዘብ ምርቱን ተነጥቋል::
-በ1989 ዓ.ም አካባቢ የጐጃም ሕዝብ ‘የደበቅኸው መሳሪያ አለ’ ተብሎ ታስሯል: ተገርፏል: ተገድሏል::
-ከምርጫው በኋላ ኢሕአዴግ የአማራ ክልልን እንደተሸነፈ አምኖ ሊለቅ ነው የሚል ወሬ ባ/ዳሮች ዘንድ ደረሰ:: ቀጥሎ “እስከቀበሌ ድረስ የሚዘልቅ የክልሉን መንግስት መዋቅር ሰርታችሁ በቶሎ አቅርቡ:: ከዘገየን ቅንጅት ሊያስተዳድር አልቻለም ብለው ተመልሰው ሊወስዱብን ይችላሉ” የሚል መልእክት ከቅንጅት ላእላይ ምክር ቤት መጣ በመባሉ: ኮሚቴ ተቋቁሞ ኰሚቴው የክልሉን መንግስት አስተዳደራዊ መዋቅር ሰርቶ ሰነዱ ፋክስ ተደርጐ ነበር:: ፋክስ የተደረገው ጊዮን ሆቴል በሚገኘው የፋክስ ሜሽን ነበር:: ፋክሱ ለቅንጅት ላእላይ ምክር ቤት መድረስ አለመድረሱ አልተረጋገጠም:: ብአዴኖች ግን እንዴት እንዳገኙት ሳይታወቅ ኮፒው ደርሷቸዋል:: እና በሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያስቀመጡትን ሁሉ ሰብስበው አሰሩ:: እስረኞች ሌሊት ሌሊት በሽፍን መኪና ወደመሸንቲ መንገድ እየተወሰዱ ጫካ ውስጥ ተገረፉ::
-በጥቅምት 1998 የባሕርዳር ኗሪዎች በጥይት ተደበደቡ::
-በሚኒሊክ ጊዜ በደል ተፈጽሞብናል በሚል በአሁኑ ዘመን ያለውን አማራ ለመበቀል ያላፈረው ወያኔ የትናንቱን የምእራብ ጐጃም ጥቃት እንዴት ሊረሳው ይችላል? እና ጐጃሞች ዛሬም በሰበብ አስባቡ እየተሳደዱ ነው::
ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ በሀላፊነታቸው ስር የተቀመጡትን ባ/ዳር ልዩ ዞንና ምእራብ ጎጃም ዞንን እድሜና ተሞክሮ ባጐናጸፋቸው ዘዴ ተጠቅመው ከሁሉም አባላት ጋር አሸንፈዋል:: የድሉ ባለቤትና የትግሉ አራማጅ የነበሩትን መላው የቅንጅት ቤተሰቦች: መላው የባህርዳርና የምእራብ ጎጃም እንዲሁም የራሳቸውን መራጭ የደራ ህዝብ ከልባቸው የክብር መዝገብ ላይ አስፍረዋል:: የቅንጅት አባላትም ሻለቃን በክብር ያስቧቸዋል::
አማሮች ዛሬም ሁነኛ ሰው ያስፈልጋቸዋል::
ረጅም እድሜ ለሻለቃ (ሻቃ) ሀይለየሱስ እጅጉ!
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013
በሰሎሞን ተሰማ ጂ. semnaworeq.blogspot.com

ለብዙዎች “ሙስና” የሚለው ቃል በ1989 ዓ.ም ወዲህ የተፈጠረ ሃይለ-ቃል ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ ቃሉ ግዕዝ ነው፡፡ ትርጉሙም፣“ጥፋት” ማለት ነው፡፡ በአማረኛም የኖረ ሕዝባዊ ግጥም/አባባል አለ፤ እንዲህ የሚል ነው፡፡ “የከንሯ ለዛ፣ የጉንጯ ሙስና፤
“ዐርብ ሮብ ያስክዳል፣ እንኳን ዐሙስንና፡፡” ይላል -
አዝማሪም፡፡ በዚህ አገባብም መሠረት “ሙስና” የሚለው ቃል ትርጉም “ፈራሹ፣ ረጋፊው-መልኳ፣ ውበቷ እንዳጠፋ ገፋፋኝ” ለማለትና ለማሳበብ ነው የፈለገው (ደስታ ተክለ ወልድ፣ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት፣ 1962 ዓ.ም፣ ገጽ-822)፡፡
በቅርቡ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችን ሰብስበው በ2006 ዓ.ም የበጀት ዓመት፣ አንድ መቶ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ እንሰበስባለን” እያሉ ይዝቱ የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታና አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ በዚህ የብር ጮማና የንዋይ ብርንዶ ውስጥ ተቀምጠው የተጣለባቸውን ኃላፊነትና ታማኝነት ቢዘነጉት ምን ያስደንቃል? ኧረ! ጨርሶ በኢትዮጵያ ብር አንገበያይም ብለው፣ በአሜሪካን ዶላርና በእንግሊዝ ፓውንድ ወይም በስዊዝ ፍራንክ ብቻ እንጠቀም ቢሉ ምን ያስገርማል? (ጥፋቱን ሙሉ ለሙሉ እነርሱ ላይ ማላከኩ ተገቢም፤ ትክክልም አይደለም፡፡ እና የማነው? በወቅቱ የእርምት ርምጃ ያልወሰደባቸው አካል ነዋ!፡፡)
በርእሴ ላይ ንዑስ-ርእስ አድርጌ የተጠቀምኩበት ሌላው ነጥብ “ማረ በላዎች” የሚለው ሃረግ ነው፡፡ ሆን ብዬ ነው፡፡ “ሙሰኞች” የሚለውን ቃል ለመጠቀምም ሆነ ለማለት ቀፈፌሽን ስለያዘኝ ነው፡፡ የዘመኑ አላዋቂ ባለስልጣኖችና የእነርሱን ቃል እንደገደል ማሚቶ የሚደግሙት ሎሌዎቻቸው እንደፈለጋቸው ይበሉት እንጂ፣ “ሙሰኞች” የሚል የግዕዝም ሆነ የዐማረኛ አገባብ የለም፡፡ “ሙሰኞች” ማለት ራሱ “ሙሰኝነት” ነው፡፡ ስለሆነም፣ በአማረኛዬ እንዳልሞስን በማሰብ “ማረ በላዎች” የሚለውን የራሴን ሃረግ መርጫለሁ፡፡ ቃሉ፣ የደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላት (በገጽ-804 ላይ) እንደሚፈታው ከሆነ የሚከተለውን ትርጉም አለው፤ “ማረ በላ” ማለት ይላሉ፣ “ጠጉራም፣ ጥፍራም፣ ነጭና ጥቁር፣ ዐጪር ቁመት ያለው አውሬ ነው፣ ማር የሚበላ አውሬ” ማለት ነው ሲሉም ይገልፁታል፡፡ “ቀይ ማር የሚበላ የቆላ ጉንዳንም” ማለት ነው ሲሉ ይገልጹታል፡፡ “ጉንዳን”ም ተባለ “ዐጪር ቁመት ያለው አውሬ” ለምንነጋገርበት ረእሰ-ጉዳይ ገላጭና ተስማሚ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ስለሆነም፣ ተጠቅሜበታለሁ፡፡ ያልደከሙበትን የሚወስዱና የሚዘርፉ ሁሉ፣ “ገፊ-ማረ በላዎች” ናቸው፡፡
ሙስናና ማረ በላነት በኢትዮጵያ የኖረ ተግባር ነው፡፡ ስሙን እየቀያየረ “ሙስና” የሚለው የዐማረኛ ቃል ከመሆኑ በፊት የተለያየ ስያሜ ነበረው፡፡ በነገሥታቱ ዘመን “እጅ-መንሻ” ወይም “መተያያ” እየተባለ ይታወቅ ነበር፡፡ በዘመነ ደርግ ደግሞ “ብዝበዛና ምዝበራ” የሚል ትርጉም ተሰጥቶት ሲንከባለል ከቆየ በኋላ፣ በ1975 ዓ.ም ገደማ “ጉቦ” የሚል ታርጋ ተለጥፎበት በ1976 ዓ.ም “የሠርቶ አደሩ ቁጥጥር ኮሚቴ” የሚባል የአሁኑ “የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን” የመንፈስ አባት በዐዋጅ ተቋቋመ፡፡ ወያኔ/ኢህአዲግ አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ ሰሞንም የዛሬው “ሙስና” ደርግ ያወጣለትን “ጉቦ” የሚል ስሙን እንደያዘ ነበር፡፡ በነሐሴ 2/1983 ዓ.ም አቶ አሰፋ ደስታ የተባሉት የከፍተኛ 13፣ ቀበሌ 10 “የሰላምና መረጋጋት ኮሚቴ ሊቀመንበር” አንዲት አደጋ ካደረሰች ተሸከርካሪ ሹፌር ላይ ሃምሳ (50.00) የኢትዮጵያ ብር “ጉቦ” የተቀበሉትን የቀበሌው ሰላምና መረጋጋት አባላት አሳፍሰው፣ አሳስረዋቸው እንደነበር አዲስ ዘመን ዘገባ ያወሳል (ገጽ-1)፡፡
የወያኔ/ኢህአዲግ ታጋዮችና ተጋዳላዮች በ1984 እና በ1985 ዓ.ም በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱም እየሄዱ “የደርግ/ኢሠፓ አባላት” ናቸው ብለው የጠረጠሯቸውን ሰዎች ከሥራ ለማባረር ይጠቀሙበት የነበረው የስም ማጥፊያና ከሥራ ማስወገጃ አጀንዳቸው፣ “ያላግባብ የሕዝብ ሃብት የዘረፉ” የሚለው ነበር፡፡ (ያኔ፣ የሕዝብ ሀብት ዘረፉ ይባሉ የነበሩትና በወያኔ/ኢሕአዲግ አባላት ይባረሩ የነበሩት “ደርግ/ኢሠፓዎች ቢበዛ ሠላሳ ሺህ ብር ቪላ ቤት የሠሩ፣ ወይም ደግሞ ባለሦስት ክፍል ዛኒጋባ የቀለሱት “ሚስኪኖች” ነበሩ፡፡) ዛሬ ታሪኩ ተቀይሯል፡፡ ከባለአምስት ፎቅ ሕንፃ በታች ያለው ሹም ካለ “ፋራና ፈዛዛ” ብቻ ነው፡፡
በጥቅምት 14 ቀን 1989 ዓ.ም “አቶ ታምራት ላይኔ ከመከላከያ ሚኒስትርነቱና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱም ሲወገድ፣” የጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ጽ/ቤት የሰጠው መግለጫ እንደሚለው ከሆነ፣ “አቶ ታምራት በምግባረ-ብልሹነት ተወወግዷል” ነው፡፡ “ጥይት ያላንበረከከውን ታጋይ፣ ስኳር አንበረከከውም!” ተብሎ ነበር (አዲስ ዘመን፣ ጥቅምት 15/1989 ዓ.ም፣ ገጽ-1)፡፡ ከወራት በኋላ፣ አቶ ታምራትና ወይዘሮ ሻዲያ ሀሰን ከነግብረ-አበሮቻቸው ተከሰው ፍርድ ቤት ሲቀርቡም፣ የተከሰሱበት ወንጀል “ያላግባብ ሃብት በማጋበስ” የሚል ነበር፡፡ በዚሁ ወንጀልም መሠረት፣ አቶ ታምራት ላይኔ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ወሰነበት ተባለ፡፡ (“ተባለ” የምለው ሆን ብዬ ነው፡፡) አቶ ታምራት እስሩን ሳይጨርስ በ2000 ዓ.ም (በቅንጅት ታሳሪዎች ግርግርና በነፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ተለማማጭነት ተፈታ፡፡ በቅርቡ ደግሞ ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ፣ በስዊዝ ባንክ አስቀምጦት የነበረው ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተመልሷል፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት፣ በታኅሣሥ ወር 1989 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አቶ መለሰ ዜናዊና የገመናኛ ብዙኃኖቻቸው “ሙስና” የሚለውን ቃል ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ጀመሩ፡፡ “ሙስና” እና “የፀረ-ሙስና ኮሚሽን” የሚባሉት ቃላት ሕግ ተረቆላቸው፣ ጽሕፈት ቤት ከፍተው፣ “ኮሚሽነርም” የሚባል ሹም ታውቆላቸው መቀፍደድና ማስቀፍደድ ተከተለ፡፡ “ሙስና ሰበብ በቁጥጥር ስር” መዋል የተጀመረው በግንቦት 16/1993 ዓ.ም ነው፡፡ ለማቋቋም የሚያስችለው ውይይት በግንቦት 10/1993 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተካሂዶ፣ ሳምንት ሳይሞላው በግንቦት 16/1993 ዓ.ም ሕግ ሆኖ ፀደቀ፡፡ ወቅቱ በጥድፊያ የተሞላና “የሕወሀት/ወያኔ ስንጠቃ በመቐሌና በሂልት አዲስ አበባ በይፋ የታወቀበት ጊዜ ነበር፡፡ ወያኔ ለሁለት መከፈሉም አርግጥ ነበር፡፡ ይሄንን ሕግ ከሚያረቁትም ሰዎች መካከል የዛሬው የገቢዎችና ጉምሩክ አቃቤ ሕግ አቶ እሸቱ ወልደ ሰንበት ነበረበት፡፡ መቀሌና ባህር ዳር ላይ ምቹ ሆቴሎችን ይዘው “የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና” ሕጉን ማርቀቅ ጀመሩ፡፡(አቶ እሸቱ በ1999 ዓ.ም እንደነገረኝ ከሆነ፣ ሕጉ ባስቸኳይ የተረቀቀው በአቶ ወረደወልድ ወልዴ ትዕዛዝ ሲሆን፣ በአቶ መለሰ ዜናዊ ቀጭን መመሪያም እንደተከወነ ነግሮኛል፡፡ በዚህም መሠረት፣ ሕጉ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተረቀቀና ወዲያው ጸደቀ፡፡ በግንቦት 19/1993 ዓ.ም የፍትሕ ሚኒስትሩና የፀረ-ሙስና ኮሚሽነሯ ወይዘሮ እንወይ ገብረ መድህን፣ “ሕዝቡ የሙስና ወንጀልን ያለፍርሃት እንዲያጋልጥ” ጥሪ ካቀረቡ በኋላ፣ “የፀረ-ሙስና ሕጉ በቂ ጥበቃ” የሚያደርግለትም መሆኑን መግለጽ ጀመሩ፡፡ ከሁለት ቀናትም በኋላ የሙስናው ቲያትር (ገቢር አንድ) መጋረጃው ተገልጦ መታየት ጀመረ፡፡
በዕለተ ዐርብ ግንቦት 21/1993 ዓ.ም፣ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ “ከፍተኛ የሙስና ሴራ ውስጥ እንደሚገኙ በተጠረጠሩት ባለሥልጣነትና ነጋዴዎች ላይ ርምጃ ወሰድኩ” ሲል ለፈፈ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያም በበኩሉ፣ በሙስና ወንጀል ተጠርጣሪ የሆኑትን የመንግሥታዊ ተቋማት ኃላፊዎችና ነጋዴዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለጸ፡፡ በዚህም መሠረት፣ አቶ ስየ አብርሃ (ባለስልጣን)፣ አቶ አሰፋ አብርሃ (ባለሥልጣን)፣ አቶ ምህረትአብ አብርሃ (ነጋዴ)፣ አቶ ፍስሃ አብርሃ-ነጋዴ(አራቱን ወንድማማቾች) እና አቶ ቢተው በለይን፣ አቶ ኃይሉ ለገሠን፣ አቶ ሙሉጌታ ገብረ መድህንን፣ አቶ በለጠ አለማየሁን፣ አቶ ብርሃነ ጂጆን፣ አቶ ሶፊያ ኢብራሂምን (እነዚህ ሁሉ በአንድ ወቅት ስንቱን የሚያንጰረጵሩ የወያኔ ሹማምንት ነበሩ) በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡
ከነጋዴዎቹም መካከል አቶ ምንውዬለት አጥናፉና አቶ አበባው ደስታ (የስታር ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤቶች)፣ አቶ ወርቁ መግራ፣ አቶ አበባው ገላዬ፣ አቶ አስናቀ ጀምበሬ፣ ወ/ሮ አጀብነሽ ሳምሶን፣ ወ/ሮ የሺሃረግ ዘውዴ፣ ሚ/ር ገራርድ ማይክል ሞላይን እና ሌሎችም ነበሩ፡፡ አርብ ማታ በዜና ማሰራጫዎች ተነግሮ፣ ቅዳሜና እሑድን ተራው ሕዝብ እንዲሰልቀው አደረጉት፡፡ ሰኞ፣ ግንቦት 24/1993 ዓ.ም ደግሞ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ማክሰኞ ግንቦት 25/1993 ዓ.ም ደግሞ ኮሚሽነሯ ወ/ሮ እነወይ ገብረ መድህን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድረስ ሄደው “የፀረ-ሙስና ምንጠራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል” ተናገሩ (አዲስ ዘመን፣ ግንቦት 17፣ 18፣ 22፣ 25፣ አና 27 ቀን 1993 ዓ.ም፣ ገጽ-1 ላይ ማግኘት ይቻላል)፡፡ የአሁኑም ክስተት፣ ትዕይነተ-ቲያትር ወሙስና (ገቢር ሁለት) እንደማለት ይመስላል፡፡
በሰኔ 1/1993 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ስየ አብርሃ፣ በመሃል ዳኛዋ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ ውሳኔ መሠረት በዋስ እንዲለቀቁ ተደረገ፡፡ በዚያው ዕለትም፣ የፌዴራል ፖሊስ የምርመራ ማስተባበሪያ ዋና ክፍል የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጥሶ ተከሳሹን አቶ ስየ አብርሃን በድጋሚ አሠራቸው (አዲስ ዘመን፣ ሰኔ 2/1993 ዓ.ም፣ ገጽ-1 እና 5)፡፡ ይህንኑ የአቶ ስየ አብርሃንና የፌዴራል ፖሊስን ግብግብ ተከትሎ በተፈጠረው ውዝግብ የተነሳ፣ በወቅቱ የፍትሕ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ወረደወልድ ወልዴ ተከሰው በሁለት ዓመታት “የፈተና ጊዜ ገደብ” ፍርድ ተጣለባቸው፡፡ ጉዳዩ ከከፍተኛው ፍርድ ቤት አልፎም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ተወስዶ ነበር፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ከብቶ ነበር፡፡ በሰኔ 16/1993 ዓ.ም ኮሚሽነሯ ወ/ሮ እንይ በመገናኛ ብዙኃን ቀርበው (አይናቸውን በጨው አጥበው) እንዲህ አሉ፤ “መንግሥት ባለፉት ሰባት ዓመታት ውሰጥ ሙስናን መዋጋት ሁኔታዎችን ሲያመቻች መቆየቱን” ገልጸው ሲያበቁ፣ “በሙስና ወንጀል የተጠረጠረና የተያዘ ሰው፣ የዋስትና መብት የለውም፤” አሉ፡፡ “ምክንያቱም፣” አሉ ኮሚሽነሯ፣ “ምክንያቱም፣ ተጠርጣሪው የዋስትና መብቱ ከተከበረለት፣ ተጠርጣሪው ሊያመልጥ ስለሚችል ነው፤” ሲሉ አከሉበት፡፡
አስከትለውም፣ “በሙስና የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት እዳይኖረው የሚከለክል ሕግ መረቀቁንና በቅርብም ሥራ ላይ ይውላል፤” ሲሉ ነበር ያለባበሱት (አዲስ ዘመን፣ ሰኔ 17/1993 ዓ.ም፣ ገጽ-1)፡፡
የአሁኖቹም ተጠርጣሪዎችና የታሰሩበት ዕለት፣ የፍርድ ቤት አቀራረባቸው፣ እንዲሁም ተከሳሾቹ እያሰሙት ያለው አቤቱታ በ1993 ዓ.ም አቶ ስየ አብርሃና ባለቤታቸው እንዲሁም ሦስት ወንሞቻቸው ያሰሙት ከነበረው እምብዛም ልዩነት የለውም፡፡ (ቀንቀሎ ስልቻ፤ ስልቻም ቀንቀሎ ነው፡፡) ይሄንን አባባል ይበልጥ የሚያጠናክረው የናዝሬት ጉምሩክ ኃላፊ የተባሉት የአቶ ተመስጌን ጉልላትን “በጋንቤላ በኩል ወደ ደቡብ/ሱዳን ሊሸሹ ሲሉ ተያዙ!” የሚለውን ዜና በሐምሌ 12/1993 ዓ.ም ከወጣው የአቶ ሳሚ ዩሱፍ አኳኋን ጋር ካስተያዩት ነው፡፡ በወቅቱ አቶ ሳሚ በርካታ ብርና ዶላር ይዘው በሶማሊያ በኩል አድርገው ጂቡቲ ከገቡ በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ ገልጾ ነበር፡፡ የአቶ ሳሚ ዩሱፍ ወንጀል እጅግ አስደንጋጭ ነበር፡፡ (ልክ የሌ/ኮሎኔል ሃይማኖት 61 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ሰነድ ይዛ ልታሸሽ ስትል ያዝናት እንደሚለው ዜና፣ የአቶ ሳሚም ወንጀል ለሰሚውም የሚቀፍ ነበር፡፡) አቶ ሳሚ ቤሳ-ቢስቲን ሳይኖረው/ሳያሲዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 22 ሚሊዮን ብር በሕገወጥ መንገድ ከተበደረ በኋላ፣ (ያን ጊዜ፣ “የስኳር ድጋፍ ሰጪ” ከሚባለው ተቋም) “156,000 ኩንታል ስኳር ያለጨረታ ገዝቶ አየር-ባየር ከሸጠ በኋላ ዕዳውንም ሳይመልስ በሶማሊያ በኩል ሊኮበልል ሲል ተያዘ፤” የሚል ነበር (አዲስ ዘመን፣ ሐምሌ 12/1993 ዓ.ም፣ ገጽ-1)፡፡ ዛሬም፣ አቶ ተመስገን የሚኮበልሉበት አቅጣጫ ተቀየረ እንጂ ኩብለላን ነው የመረጡት፡፡ ከሕግ ፊት ሸሽተው እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡
እና፣ አቶ ሳሚ ዩሱፍም ሆኑ አቶ ተመስጌን ጉልላት ከምንድነው የሸሹት? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፡፡ በቀጥታ ወደ መልሱ ከመግባቴ በፊት፣ በግንቦት 4/2005 የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣን ሳነብ ያገኘሁትን መረጃ ላካፍላችሁ፡፡ እንዲህ ይላል፤ “እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት ላለፉት ሦስት ዓመታት ክትትልና ምርመራ ሲደረግባቸው እንደነበረ የታወቀ ሲሆን፣ ከመያዛቸው ሁለት ቀናት በፊት በመቀሌ ከተማ ከሙስና ጋር በተያያዘ ጠንከር ያለ ውይይት መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ ስብሰባም በኋላ ጥንቃቄ በተሞላበት እንቅስቃሴ” ማረ በላዎቹን በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል” -ይላል (ገጽ-37)፡፡ ትልቁ ቁምነገር ያለው የተሰመረበት ንዑስ ዐረፍተ ነገር ላይ ነው፡፡ በፌዴራል መንግሥቱ ዋና ከተማ የሚደረጉ ስብሰባዎችም ሆኑ ውይይቶች “ፍሬ-ከርስኪ” እንደሆኑና የመቀሌቹ ስብሰባዎችና ውይይቶች ግን “መሬት ጠብ የማይሉ” እንደሆኑ ያሳብቃል፡፡ በርግጥም ይህ ለምን ተደረገ ብሎ መመርመር ያስፈልጋል፡፡
የመቀሌዎቹ፣ በ1993 ዓ.ም በእነአቶ ስየ አብርሃም ላይ የእስር ትዕዛዙን የወሰኑት ከዚያው ከመቀሌ ነበር፡፡ አዲስ አበባ በወቅቱ ምቹ አልነበረችም፡፡ ከሚያዝያ 3-7/1993 ዓ.ም ድረስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አመጽና፣ አመጹንም ተከትሎ የነበረው ዝርፊያና ግድያ፤ እንዲሁም የደሕንነትና ኢምግሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ክንፈ ገብረ መድኅን በግንቦት 4/1993 ዓ.ም በመኮንኖች ክበብ መገደል (ወዘተርፈ) አዲስ አበባን የማትታመን ሥፍራ አድርጓት ነበር፡፡ ምርጦቹ ሕወሀቶች መቀሌ ላይ ተሰብስበው፣ “የአቦይ አብረሃ ልጆችና ግብረ-አበሮቻቸው ይታሰሩ!” ቢሉ አያስደንቅም ነበር፡፡ ምክንያቱም፣ ከአዲስ አበባ ይልቅ “መቐለይ” ለሕወሀት ምቹ የቁጥጥር ዞን ስለሆነች ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ስንቱ የእህት ድርጅት አባል ስለላና ብሰሳ እንደሚያደርግባቸው ስለሚያውቁም ነው መቐለይን የመረጡት (በተለይ ብአዴን)፡፡ ታዲያ “አሁን፣ በ2005 ዓ.ም ሚያዝያ ማለቂያና በግንቦት ልደታ ዋዜማስ መቀሌ ላይ ተሰብስቦ መወሰንን ምን ይሉታል?” የምትሉ እንደማትጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ አሁንም ቢሆን፣ አዲስ አበባ ውስጥ ሕዝቡ ባለፈው የቀበሌና የወረዳ/ክፍለ ከተማ ምርጫ እንደታየው ከሆነ ለወያኔ/ኢሕአዲግ ያለውን ስሜት በግልጽ አሳይቷል፡፡” ስለዚህም፣ ከፍተኛው ያገር ገዳይ መቐለይ ላይ ሸብ-ረብ ተደረገ፡፡
ሌላም ምክንያት አለው፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተርን ሪፖርት ተከትሎ “ውስጣዊ ሴራዎች/Ineternal Conspirencies) መካሄደ ላይ ነበሩ፡፡ በ116 የፌደራል መንግሥቱ ተቋማት ውስጥ በተደረገው የኦዲት ምርመራ መሠረት፣ በ84 መ/ቤቶች ከ5.2 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ የጥሬ ገንዘብ ውዝፍ ተገኝቷል፡፡ ይህንን ገንዘብ ደግሞ በየመሥሪያ ቤቱ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዋና መምሪያ ኃላፊዎች ሆነው እንዳሻቸው የሚያደርጉት የሕወሀት/ወያኔ አባላት ናቸው፡፡ ሰንደቅ ጋዜጣ በሚያዝያ 23/2005 ዓ.ም እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ ችግሩ በይብጥ የሚጎላው በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ነው፡፡ 3.2 ቢሊዮን ብሩ ደብዛው የጠፋው በዚሁ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ምናልባትም ደግሞ ከፍተኛዎቹን የጦር መኮንኖች የሚያነካካ ነው፡፡ ብዙዎቹ፣ በማረ በላነት ይታማሉ፡፡ በአንደ በጀት አመት ግን ይኼንን ያህል ገንዘብ ተመዝብሮ አያውቅም፡፡ ምናልባትም፣ አቶ መለሰ ዜናዊ ታመሙ (ሞቱ) የሚል የተምታታ ዘገባ በነበረበት የሰኔ/2004 ማለቂያ ላይ በስልጣናቸን አንቀጥልም በሚል ተስፋ-መቁረጥ ውስጥ የነበሩ አመራሮች ካቅማቸው በላይ አሽሽተዋል፡፡ ይሄንን ደግሞ የብአዴን መሪዎች በሚገባ አውቀውታል፡፡ ማወቃችንንም ያወቅነው በ11ኛው የኢሕአዲግ ጉባኤ ወቅት የአቶ በረከት ስምኦንንና የአቶ አዲሱ ለገሠን ቀና-ቀና ማለት አብጠርጥረን ስላየነው ነው፡፡
በዋናው ኦዲተር ሪፖርት አማካኝነት የብአዴን ሰዎች ራት ለመሆን የተዘጋጁት ሕወሀቶች ከጊ ጋር ሩጫ ጀመሩ፡፡ መቀሌ ላይ መሽገው ሁለት አባላቶቻቸውን “መናጆ” አድርገው በርካታ የብአዴን አባላትን ባላቸው የደሕንነትና የፀጥታ ዕዝ ሰንሰለት ተጠቅመው በቁጥጥር ሥር አዋሉት፡፡ እራት ሊያደርጋቸው ያሰበውን ብአዴንን፣ ሀሪፍ ምሳ አደረጉት፡፡ ብዘዎቹ የብዐዴን ሰዎች ሲታሰሩ “ችግር ይፈጥሩ ይሆናል የተባሉትም የፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሀነ ኃይሉ፣ ሐሙስ ተወካዮች ምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርታቸውን ከቀረቡ በኋላ ከኃላፊነታቸው መታገዳቸውን አወቁት፡፡ ይህንንም ለማድረግ መቐለይ ላይ መሽጎ የነበረው “የትግራይ ሪፐብሊካን ፓርቲ” አመራር፣ የደሕነትና የፀጥታ ኃላፊዎችን ማዘዙ ብቻ በቂው እንደነበረ አልተጠራጠረም፡፡ በዕለተ አርብ፣ ግንቦት 2/2005 ዓ.ም መጋረጃው ተገልጦ “የሙስናው ወንጀልም ጉዳይ” ለሕዝቡ በሰበር-ዜናነት ተነገረው፡፡ (ሕዝቡ ግን የሚገርም ምላሽ ነበር የሰጠው፡፡ የፕሪሜር ሊጉና የሰውለሰው ድራማ ሲያልቅባቸው ጊዜ፣ “የሙስና ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ” የሚል ድራማ ሊያሳዩን ይፈልጋሉን? ሲል ተዘባበተባቸው፡፡ (ጎበዝ፣ ቸር እንሰንብት!)
በሳምናታዊው የአዲስጉዳይ መጽሔት ቅጽ 7፣ ቁ. 164 ላይ፤ በግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም (ገጽ 22-3) የወጣ ነው::
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013
የመፅሐፉ ርዕስ፡- Tower in the Sky (የሰማይ ላይ ግንብ)
ደራሲ፡- ህይወት ተፈራ
አሳታሚ፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ
የገፅ ብዛት፡- 437
የታተመበት ዘመን፡- እ.አ.አ. 2012
የመሸጫ ዋጋ፡- 74ብር
በሰለሞን ኃይለማርያም
ይህንን መፅሐፍ ሳነብ በልጅነቴ በአንድ ዕለት ሰንበት እናቴ እጄን ይዛ ወደ ቤ/ክርስቲያን ስትወስደኝ የተመለከትኩትን ልክ እንደፊልም ወደኋላ ወስዶ እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡
Download (PDF, 134KB)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013
የቀዩ መስመር ሰላባዎች?
By Goolgule.com
May 20, 2013

መለስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከተሰጡት አስተያየቶችና ትንቢቶች መካከል ቀዳሚው የመለስ ሞት ለህወሃት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ መሆኑ ነበር። በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ ዲፕሎማት “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህ እንደሚከሰት ቁልጭ አድርገው ተናግረው ነበር።
መለስ አፍነው የያዟቸው የፖለቲካ ችግሮች ጊዜያቸውን እየጠበቁ የሚፈነዱና በመጨረሻም ፓርቲውን እንደሚፈረካክሰው የተገለጸው በየደረጃ የሚፈነዱት ችግሮች እየበረከቱ በመሄዳቸው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው ችግሮች የእርስ በርስ መበላላት ደረጃ እንደሚያደርሱ በርካታ ወገኖችና መገናኛዎች ጎልጉልን ጨምሮ አመላክተዋል። አሁን አሁን ትንቢቱ የፍጻሜው ጅማሬ ላይ እንደሚገኝ የሚናገሩም አሉ።
የፖለቲካ አቋም ልዩነት ሳይኖር የአስተሳሰብ ልዩነት ማራመድ በህወሃት ዘንድ አይቻልም። ከተሞከረም ክህደት ነው፤ መፈንቅለ መንግስት የማካሄድ ያህል ነው። የርዕዮተ ዓለም ለውጥ የማቀጣጠል ያህል ያስፈርጃል። ሽብርተኛ ያስብላል። ከቶውንም ተቀባይነት ስለሌለው ድንበር ተበጅቶለታል። ድንበሩም “ቀይ መስመር” በመባል ይታወቃል። የ”ቀይ መስመር” ሃሳብ አመንጪና ደራሲ አቶ መለስ ናቸው። “በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ” በሚል የምጸት ስም የሚጠሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም ይህንን የቀይ መስመር ጽንሰ ሃሳብ ለንግግር ያህል ይጠቀሙበታል።
ቀይ መስመር የሚሰመርበት በውል ተለይቶ የተቀመጠ ውስን ጊዜ የለውም። መስመሩ ሁሌም አለ። ሁሉም ቆመውበታል። ከልምድ እንደሚታየው በህወሃት ህመም ኢህአዴግ ሲያተኩሰው በድንገት መስመሩ በደማቁ እንዲቀባ ይደረጋል። መስመሩ የሚቀባበት ደማቅ ቀለም የሚቀዳው አቶ መለስ አፈር ሳይልሱ “በስብሰናል” ሲሉ ከሰየሙት የኢህአዴግ የ”ማበስበሻ” ባህር ውስጥ ነው።
በኢህአዴግ የ”ማበስበሻ” ባህር ውስጥ ያልተነከረ የለም። በዚህ ባህር ውስጥ ሆነው የሚንቦጫረቁት ተቆጥረው አይሰፈሩም። አዲስ አበባ በአራቱም ማዕዘን፣ በክልልና በክልል ዋና ዋና ከተሞች፣ እንዲሁም በተለያዩ አገራት የሚሰነፍጠው የባህሩ “ግልማት” የዜጎችን የመኖር ህልውና ከተፈታተነ ቆይቷል።
በባህሩ ውስጥ በመርከብ ሆነው በጀልባ የሚቀዝፉትን የሚመለከቱ አሉ። ጀልባ የሚቀዝፉት ጌቶቻቸውንና “ልዕልቷን” እያዩ ሽታውን በለመዱት ባህር ውስጥ ይምነሸነሻሉ። በዛው ባህር ውስጥ በደረታቸው እየዋኙና እየተንቦጫረቁ ግብር የሚያስገቡ አሉ። “ዲጂታል” የሚባሉትና “ምስለኔዎቹ” ደሞ የማበስበሻውን “መረቅ የማቅለሚያ ማዕድን” ይዘው አራት ኪሎ የባህሩ አናትና ማማ ላይ ሆነው ሁሉንም ይመራሉ። የባህሩን የመጫወቻ ህግ የሚበላቸውና ከበሰበሰው ባህር ወደ እቶን የሚወረወሩት “የቀይ መስመር ሰለባዎች ” ይለያሉ። ለይተው ሲጨርሱ ለባህሩ ካፒቴን የፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያቀብሉታል። በዚሁ ሂደት ይቀጥላል። አዲስ ነገር የለም። ሊኖርም አይችልም። ይህ መነሻ ነው። ወደ ጉዳዩ እናምራ።
የሰሞኑ ወግ – ኢህአዴግ አመረረ ወይስ ቀለደ?
ሰሞኑን ኢህአዴግ “ሙስና ላይ ዘመትኩ። በህዝብ ጥቆማና ትብበር ሙስና የተንሰራፋበትን ተቋም አበራየሁት። የህዝብ ትብብር አይለየኝ …” በማለት የፍርድ ቤት አሰራርና ህጋዊ የፍርድ አካሄድ እያስኮመኮመ የሚያውጀው አዋጅ ያስገረማቸው ክፍሎች “እንዴት እንመን? እንዴት እንቀበል? ማን ያልተነካካ አለ?” እያሉ ነው። ከተለያዩ አቅጣጫ “ኢህአዴግ አመረረ ወይስ ቀለደ” በሚል ክርክርም እያስነሳ ነው።
የፌዴራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ፓርላማ ቀርበው “ጥናቱ የተጀመረው በአቶ መለስ ትዕዛዝ ከዓመት ከአስር ወር በፊት ነበር” በማለት ምስክርነታቸውን የሰጡበት ዘመቻ አቶ መለስ በህይወት እያሉ ያልተጠናቀቀው በድንገት በመታመማቸው፣ ከዛም በመሞታቸው፣ ከዛም በላይ የሽግግር ወቅት በመሆኑ እንደሆነ አስረድተዋል። መለስ ሲሞቱ ሃይለማርያም ሙስና ላይ ዘመቱ በሚል ስባሪ ታሪክ እንዳያተርፉ፣ ከዚያም አልፎ ዘመቻው የፖለቲካ ልዩነቱ የፈጠረው “የአራግፍ፣ የመንጥር ዘመቻ” እንዳይመስል አቶ አሊ መለስን የዘመቻው “አባትና ባለታሪክ” አድርገው እንዲያቀርቡ መታዘዛቸው ዘመቻው የተለመደው የኢህአዴግ ቀልድ እንደሆነ አመላካች ስለመሆኑ በስፋት አስተያየት የሚሰነዘርበት ጉዳይ ነው።
ምንም ሆነ ምንም ኢህአዴግ ለጀመረው የሙስና ዘመቻ ሊመሰገን ይገባዋል የሚሉ ወገኖች ዘመቻው እንደ ሰደድ እሳት ተያይዞ የሚነድ ስለመሆኑ ሲናገሩ ይሰማል። የኢህአዴግ ደቀ መዝሙር በመሆን የሚታወቁ ድርጅታቸው “የመለስ ቦናፓርቲ” የተሃድሶ ዘመን ተመልሶ እንደመጣ፣ የዚህ ተሃድሶ ፊት አውራሪ ደግሞ እጩ ጠ/ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እንደሆኑ በኩራት እየተናገሩ ነው።
ከደህንነቱ ራዳር የተሰወረ አለ?
በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የማናቸውም ባለሃብቶችና ባለስልጣናት እለታዊና አጠቃላይ የክትትል መረጃ ተመዝግቦ የተቀመጠ ነው። ዋናው ደህንነት የማበስበሻው ባህር ቁልፍ እጁ ላይ ነው። ሲፈለግ ከዋናው ባህር መዝገብ የሚፈልጋቸው ነቅሶ በስሩ ላላው የኢኮኖሚ ደህንነት ዘርፍ ያቀብላል። ለስራው ቅርብ የነበሩና በቅርቡ አገር ለቀው ናይሮቢ የሚገኙ እንዳሉት በዚሁ አሰራር መሰረት አሁን የታሰሩት ሰዎች ሪፖርት ተጠናቆ የቀረበው የዛሬ አምስት ወር ግድም ነው።
ደህንነቱ ማን ከማን ጋር እንደሚሰራ፣ የትኞቹ ባለስልጣናት ከየትኛው “ባለሃብት” ጋር አብረው እንደሚሰሩ፣ በየትኛው ወገኖቻቸውና ዘመዶቻቸው ስም እንደሚነግዱ፣ የኤክስፖርትና ኢምፖርት ስራ እንደሚሰሩ፣ ያለ ማስያዣ ብድር እንደሚፈቅዱና እንዲፈቀድ መመሪያ የሚሰጡ፣ ወዘተ ሙሉ መረጃ እንዳለው የሚጠቁሙት እኚሁ ሰው “ሙስና ከግል፣ ከድርጅትና ከተቋማት አልፎ በመንግስት ደረጃ የተዘረጋ ነውና ማን ማንን ይወነጅላል?” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። አያይዘውም “አገራችን ውስጥ ሙስና በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በመንግስት ደረጃ የተቋቋመ ነው” ብለዋል።
ሌሎችም እንደሚሉት ሙስናው ሊደበቅ በማይችል ደረጃ አገሪቱን እንደ ወባ ወረርሽኝ ሲያጥለቀልቃት፣ በየአቅጣጫው ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር ህዝብን ሲያንገሸግሸው ለምን ዝምታ ተመረጠ? የሚለው አንኳር ጉዳይ ብዙ ከመላምትነት የዘለሉ ምክንያቶች እየቀረቡበት ነው። በተለያዩ ደረጃ የኢህአዴግን የመበስበስና የእድገት ደረጃ የማሟጠጥ ጉዳይ አንተርሰው አስተያየት የሚሰጡ ቅድሚያ አጀንዳ የሚያደርጓቸው አቶ መለስን ነው።
መለስ ዝምታን ለምን መረጡ?
እርሳቸው ምን ያህል ተዋናይ እንደሆኑ አሃዝ ጠቅሶ መናገር ባይቻልም አቶ መለስ አገሪቱ በሙስና መንቀዟን እያወቁ ዝም ማለታቸው ከተባባሪነት እንደማያሸሻቸው ስምምነት አለ። በፓርላማ፤ ከነጋዴዎችና ከኢንቨስትመንት ማህበረሰብ ጋርና ከተለያዩ አካላት ጋር ሲነጋገሩ ሙስናን አስመልክቶ አስገራሚ ዲስኩር ሲያሰሙ ኖረው ያለፉት አቶ መለስ፣ ሙስናን ተሸክመው የኖሩት በፍርሃቻ እንደሆነ የአብዛኞች ማጠቃለያ ነው። አቶ መለስ ሙስናን እንደ ስልት በመጠቀም በዙሪያቸው ያሉትን “በማበስበስ” እንዳሻቸው ይነዱዋቸዋል።
በሙስና የተጨማለቁና በሙስናው ባህር ውስጥ የሚዋኙትን ባለስልጣናት፣ ካድሬዎች፣ ባለሃብቶች፣ የጊዜው ሰዎችና ዘመዶቻቸው ቢታወቁም አቶ መለስ በመፈክር አብረዋቸው ለመኖር የወሰኑትና በዚያው ይህችን ዓለም ባላሰቡበት መንገድ የተለዩት በጡረታና “ያለህን ብላ” በሚል አካባቢያቸውን ለማጽዳት የሞከሩት ሙስናው ውስን አድራሻና መንደር ስለሌለው ነው። ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘና መለስ የፈሩት ሙስና እንዴት ተደፈረ?
መለስ በህይወት እያሉ ሙስናውን ዝም አሉ የሚሉትን ክፍሎች አጥብቀው የሚቃወሙ ቡድኖች ደግሞ “አቶ መለስ የሙስናው አውራ ናቸው። በመንግስት ደረጃ ለተገነባው የሙስና መንደር ፊታውራሪና ይለፍ ሰጪ ናቸው” ሲሉ ይከራከራሉ። የሙስናውን አዝመራ የዘሩ፣ ኮትኩተው ያለመለሙት፣ መጨረሻ ላይም ባህር አዘጋጅተው የማበስበሻ አረንቋ የተከሉት አቶ መለስ በመሆናቸው ርምጃ ለመውሰድ እንደማይቻላቸው፣ ርምጃ ልውሰድ ቢሉም ሁሉም ስለተበከሉ “በአገሪቱ የጦር አዛዥ፣ የፖሊስ አለቃ፣ የደህንነት ሹም፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ፓርላማ፣ ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ፣ ከንቲባ፣ መሃንዲስ፣ ሆስፒታል … የሚቀር ስለማይኖር በቅድሚያ በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅ ይገባል” ሲሉ የሙስናውን አደገኛነትና መንግስታዊ መዋቅር ያለው ስለመሆኑ ይከራከራሉ።
ለማስረጃ ከሚያነሱት መከራከሪያ መካከል “ዋናው የሙስና ሻርክ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት ባለሃብትና በሳቸው መዋቅር ውስጥ ሆነው ከተራ ወንጀል እስከ አገር አቀፍና ድንበር ዘለል ዝርፊያ የሚፈጽሙ “ማፍያዎች”፣ በፌስታል ብር የሚያቀባብሉ ምስለኔዎች፣ የባለስልጣናትን ሚስቶችና ዘመዶች በንግድ ተቋሞቻቸው በመሰግሰግ የአገሪቱን ህግና ህገመንግስት እንዳሻቸው የሚጋልቡ ማጅራት መቺዎች፣ የአገሪቱን ባንኮችና የንግድ ስርዓት በማዛባት ሰርተው የሚበሉ ዜጎችን አሟምተው የጨረሱ፣ የራሳቸው ፖሊስና የደኅንነት ሃይል በመገንባት እንደ መንግስት ያቆጠቆጡ ወዘተ በህዝብ ይታወቃሉ። እኒህ ክፍሎች የአቶ መለስን ኮሪዶርና ማረፊያ ቤት ሲመላለሱበት መለስ ዝም ማለታቸው ከምን የመነጨ ሊሆን ይችላል? የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ መልሱ አንድ ነው። እሳቸውም፣ ባለቤታቸውም፣ ዘመዶቻቸውም፣ ወገኖቻቸውም፣ የትልቁ “የማበስበሻው ባህር” አባል በመሆናቸው ነው። ከዚያም በላይ ደግሞ ልንካው ካሉ የመገንደስ አደጋ ስለሚከተል ነው። በሌላ አነጋገር ከስር እስከ አናት በተለያየ ደረጃ በህገወጥ የበለጸጉና የትንንሽ መንግስታት መሪዎች የሆኑ ስለበዙ አቶ መለስም ሆኑ እሳቸው የሚመሩት ህወሃት መራሹ አስተዳደር የመከልበስ አደጋ እንዳያጋጥመው በመፍራት እንደሆነ ከውስጥም ከውጪም በስፋት የሚታመንበት እውነታ ነው።
ደብረጽዮን “የጎበዝ አለቃ”!!
መለስ ሲያልፉ ሃላፊነቱን ጠቅልለው የተረከቡት መለስ በመተካካት ሰበብ ያዘጋጇቸው ሰዎች ናቸው። ከነዚህ አዲስ አመራሮች መካከል ዶ/ር ደብረጽዮን ዋናው መሃንዲስ ናቸው። መለስ የፈሩትን ጉድ እሳቸው እንዴት ደፈሩት ለሚለው የሰሞኑ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች ዶ/ር ደብረጽዮንን ከፊት ለፊት ያስቀምጣሉ።
ከደህንነት መዋቅር ቁንጮ ላይ እንዳሉና መለስ ከሞቱ በኋላ ህወሃት ፊትለፊት ያወጣቸው ደብረጽዮን ከዋናው ስራቸው በተጨማሪ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ክላስተር የሚመሩ ናቸው። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት እንደ እሳቸው ፍላጎት ቢሆን አሁን የተወሰደው ርምጃ ከአምስት ወር በፊት መከናወን የነበረበት ጉዳይ ነበር።
አሁን በቁጥጥር ስር የነበሩት ሰዎች ከአምስት ወር በፊት በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ይታወቅ እንደነበር የሚናገሩት የደህንነት ሰዎች “ከመለስ ህልፈት በኋላ በተፈጠረው የሃይል ክፍፍል አሸናፊ ሆነው የወጡት ክፍሎች ቅርንጫፍ መቆራረጥ ጀመሩ እንጂ ርምጃው የጸረ ሙስና ዘመቻ አይደለም” ባይ ናቸው። የእነ በረከት ስምዓንና የወ/ሮ አዜብን ቡድን በመጻረር በመለስ ሞት ማግስት ዘመቻ የጀመሩት ቡድኖች ከሙስናው ባህር ውስጥ ተጨልፈው ወደ እቶን ውስጥ እንዲጣሉ ሲወሰን ደረጃ ተዘጋጅቶ እንደሆነ አንዳንድ መረጃዎች ያመለክታሉ።
መለስ አፍነው የያዙት የህወሃት “የመበስበስ” ችግር ገሃድ ከሆነ በኋላ አቶ ስብሃት ነጋ ግንባር ሆነው የወጡ ቢሆንም ለምን ታለፉ? የሚል ጥያቄ ስለመነሳቱ አስተያየታቸውን የሚሰጡት እኒሁ የደህንነት ሰዎች እንደሚሉት “አሁን የተጀመረው ኦፕሬሽን አሸናፊዎቹ ሃይሎች ጉልበታቸውን የሚያሳዩበትና የተጻራሪውን ቅርንጫፍ በመቆራረጥ ዋናውን ግንዶች ማድረቅና ለማገዶ የማዘጋጀት የታሰበ ነው” ዘመቻው በቀጣይነት በጡረታ ስም የሚያስወግዳቸው አውራ ሃይሎች እንዳሉት የሚናገሩት ክፍሎች አቶ አርከበ እቁባይና አምባሳደር ብርሃነ ገ/ ክርስቶስ በዚህ የማጥራት ቀመር ውስጥ እንዳሉበት ይጠቁማሉ።
ወ/ሮ አዜብ መስፍንና አቶ በረከት ስምዖን ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ጀምረው የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ ምንም ዓይነት ርምጃ እንደማይወሰድባቸው ያመለከቱት ውስጥ አዋቂዎች “ስብሃት ግን ቅርንጫፎቻቸው በሙሉ ተመልምለው ብቻቸውን ይቀራሉ። በመጨረሻም እንዲደርቁ ይደረጋል” ሲሉ ስለ ስሌቱ የሚያውቁትን ይናገራሉ።
“አቶ ስብሃት ላይ ርምጃ ከተወሰደ የባህሩ ዋና ተዋናዮች በሙሉ ርቃናቸውን ይቀራሉ። ሁሉም መረጃዎች ከወጡ ህወሃት ራሱ ባሰመረው የሞት መስመር ላይ ግንባር ቀደም ተሰላፊ እንዲሆን ያደርገዋል” የሚሉት የመረጃው ሰዎች፣ ለጊዜው አሸናፊ የሆኑት ክፍሎች የተነፈሱ ቢመስላቸውም ውስጥ ውስጡን የጋመ ጉዳይ ስለመኖሩም አመልክተዋል።
የሙስና ፋይል!! የህወሃት ፓናዶል!!
የፌዴራል የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከበቂ በላይ ጥቆማ እንደሚደርሰው፣ በሚደርሰው ጥቆማ መሰረት የማጣራት ስራ ባከናወነባቸው ተቋማት ላይ ርምጃ ለመውሰድ ሲጠይቅ ማዕቀብ እንደሚደረግበት ሰራተኞቹ ውስጥ ውስጡን የሚነጋገሩበት ጉዳይ ነው። ከደህንነት ጋር በቁርኝት የሚሰራው ይህ ተቋም ሳንጃ የሚሰጠው ህወሃት ሲታመም ነው። ኢህአዴግ ውስጥ ግለት ሲጨምር ሳንጃው ድንበር ተበጅቶ ይታዘዛል። ሰሞኑን የሆነውና ከዚህ ቀደም የተደረጉት ሁሉ የዚሁ አሰራር ነጻብራቆች ናቸው።
“ቴሌ በሙስና ገልምቷል” ከተባለና ዋናው ተፈላጊዎች እንዲሸሹ ከተደረገ ከአራት ዓመት በኋላ ኮሚሽኑ “ሳንጃህን ካፎቱ አውጣው ተባለ” መባሉን የሚያስታውሱ ክፍሎች፣ በህወሃት ክፍፍል ወቅት በአንድ ጀንበር የተሰራውን የማራገፍ ድራማ ያጣቅሳሉ። አሁን በቅርቡ ኦህዴድ ውስጥ የህወሃትን የበላይነት ለመሸርሸር በተነሱ ወጣት አመራሮች ላይ ሙስናን ተንተርሶ የተወሰደውን የማጥራት ዘመቻ ያክላሉ። አሁንም በተመሳሳይ ሰሞኑን የተወሰደውን ርምጃ ከዚሁ ከኖረው የህወሃት “የመበላላት” ታሪክ ጋር የሚያገናኙት ክፍሎች፣ በግልጽ አሁን አሸናፊ ሆኖ ከወጣው ቡድን ቁንጮና “ልዕልት” ጋር አብረው የሚሰሩ ግለሰብና፣ ባለስልጣን መታሰራቸው ቢድበሰበስም የክስ ሂደቱ እየጠና ሲሄድ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አሁን ለመገመት የሚችግር እንደሚሆን ይናገራሉ።
ህወሃት በተለይም ተሹለክልከው መሪ የሆኑት አቶ መለስ ከበረሃ ጀምሮ ተቀናቃኞችን እንዴት ይበሉዋቸው እንደነበር ያጋለጡት የቀድሞው የህወሃት የገንዘብ ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መድህን አርአያ የሃሳብ ልዩነት አስመልክቶ ውይይት ተደርጎ መስማማት ባለመቻሉ በጣም ሲመሽ “አሁን እንረፍ፣ እንተኛ” ከተባለ በኋላ በተኙበት በዛው እንዲቀሩ የተደረጉ ስለመኖራቸው ተናገረው እንደነበር በማስታወስ “የአሁኑ ህወሃት ውሳኔውን ተቋማዊ ለማስመሰል። ተቋሙም በህግ፣ በፍርድ ቤት ችሎት፣ በዳኞችና ራሱ መርማሪ፣ ራሱ ከሳሽ በሆነው የፌዴራል የጸረ ሙስና ኮሚሽን የሚመራ በማስመሰል መበላላቱን “ዲጂታል” አድርጎ እየሰራበት ይገኛል።
ለማጠቃለል
የድሃ ልጆች ቦዘኔ ተብለው ሲታሰሩ አገሪቱ ውስጥ የተዛባ ነገር አልነበረም። በፖለቲካ አመለካከታቸው ዜጎች እስር ቤት ሲጣሉ ህግ የተከበረ ነበር። ንጹሃኖች በፈጠራ ወንጀል ሲገረፉና በስቃይ ሲዘለዘሉ ፍትህ አልጎደለም ነበር። እናት በችግር ልጇን ለገበያ ዝሙት ስትልክ ሃፍረት አልነበረም። በዝርፊያ ገንዘብ አዲስ አበባ በህንጻ ስታብድ አግባብነት አይታይም ነበር። ህዝብ በኑሮ ግለት ሌማቱ ሲደርቅና ገንዳ ላይ ምግብ ፍለጋ ህጻናት ሲባትቱ ችግር ሆኖ አይቆጠርም ነበር። አለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎች እንደ ከብት በየአቅጣጫው ሲታጎሩ የፍትህ ስርዓቱ አልተዛባም ነበር … ሰሞኑን እስር ቤት የተወረወሩት አቶ ገብረዋህድ ፍርድ ቤት ቀርበው ስለ ባለቤታቸውና ልጃቸው ሲናገሩ “አገሪቱ ምን እየሆነች ነው” አሉ። ከኮብራ ወርደው ወህኒ ቤት ሲገቡ የአገሪቱ የፍትህ ስርዓትና የህግ የበላይነት እንደ ደቀቀ ታያቸው። የባለቤታቸው ከስርዓት ውጪ መታሰር አንገበገባቸው። የልጃቸው መታሰር አቃጠላቸው። ሌሎች ምን ይበሉ? የፕሮፌሰር አስራት ቤተሰቦችና ወዳጆች ምን ይበሉ? የእስክንድር ነጋ ልጅና ባለቤት ምን ይናገሩ? የነበቀለ ገርባ፣ የነ ኦልባና ለሊሳ፣ የነ ሌሊሴ ወዳጆ በኦሮሞነታቸው ብቻ ለስቃይ የተዳረጉና የመከራው ተካፋይ የሆኑት ቤተሰቦቻቸው ይህን ያህል ዓመት ችግሩን እንዴት ተሸከሙት?
የአቶ መለስ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የቅርብ ባልደረባና የስራ አጋር የሆኑት የአቶ ገ/ዋህድ ባለቤትና ልጃቸው መታሰር ጥፋት ከሌለባቸው የሚደገፍ ባይሆንም ለሌሎች ባለስልጣናትና የህወሃት አለቅላቂዎች ታላቅ ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነ በተለያዩ የማህበራዊ ድረአውዶች መነጋገሪያ ሆኗል።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013

ከሊሊ ሞገስ
ፈርጉሰን የነገሱበት ሀሙስ
ያ ታሪካዊ ሀሙስ ነበር፡፡ በጠዋቱ ከሰፋፊዎቹ እስከ ታብሎይዶቹ፣ ከቢዝነስ ጋዜጦች የከረረ ፖለቲካ እስከሚያስተናግዱት ድረስ የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ፎቶግራፍ ማተም ግዴታ የሆነባቸው ይመስላል፡፡ ትልልቆቹ ከፊት ገፆቻቸው አልፈው ልክ 25 ዓመታትን ኖሮ በሞት እንደተለየ ሁሉ እንጎቻ የሚያካክለውን የአሰልጣኙን ምስል ‹‹ከ1986-2013›› የሚል ጉልህ ርዕስ አስከትለውበት አትመዋል፡፡
በወሲብ ቅሌቶች፣ በወንጀልና በዝነኞች የግል ህይወት ብርበራ የሚታወቀው ዘ ሰን እንኳን በሽፋን ገፁ ላይ በሜንጦ የተንጠለጠለ የፀጉር ማድረቂያ ማሽን በማተም የአንጋፋውን ስኮትላንዳዊ የሚያንቧርቅ ቁጡ ባህሪይ ዘመን ማብቃቱን ለመግለፅ ሞክሯል፡፡ ዘ ሰን በየዕለቱ በገፅ 3 ላይ በከፊል ራቁት የሚታዩ ቆነጃጅትን ምስል ማተሙ የአስርት ዓመታት ልማዱ ነበር፡፡ ሐሙስ ጠዋት ግን አማላዮ ሞዴሎች ለሰር አሌክስ ቦታውን ለቀው ወደ ገፅ 9 ሄደዋል፡፡
ዘ ታይምስ የተሰኘው የተከበረ ጋዜጣ ባለ 12 ገፅ ተጨማሪ መፅሔት ለአንባቢዎቹ ያቀረበ ሲሆን ‹‹እግርኳስን የቀየረው ሰው›› በሚል ሙሉ ለሙሉ ለፈርጉሰን አውሎታል፡፡ ቴሌግራፍ እንዲሁ በ16 ገፁ የአሰልጣኙን የዩናይትድ ቆይታ ስኬት፣ ውዝግብና የኃላፊነት ፍፃሜ ተርኳል፡፡ 20 ገፆቹን ሙሉ ለእርሳቸው ያበረከተው ጋርዲያን ‹‹ሰር አሌክስ›› የሚለውን የዩናይትድን ታላቅ ሰው የክብር መጠሪያ ብቻ በትልቁ በርዕስነት መፃፉን መርጧል፡፡ ጋርዲያን የፈርጉሰን ምስል የሰፈረበትን ቲሸርት በ20 ፓውንድ ለገበያ አቅርቧል፡፡ ሁሉም ጋዜጦች የሰር አሌክስን የኋላ ህይወት ለመተረክ ፊታቸውን ወደ ግላስጎው አዙረዋል፡፡ የስኬታቸውን መነሻ ስረ መሰረት ለማግኘት ገና በ16 ዓመታቸው ከትምህርት ቤት የተለዩት፣ በወደብ ሰራተኛነት ያሳለፉትና በወጣትነታቸው ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጨዋች እስኪሆኑ ድረስ የመንደር ሱቅ ጠባቂ ስለነበሩት ፈርጉሰን ፅፈዋል፡፡ የሚያስፈራና ቁጡ ባህሪይ እንዳላቸው ሁሉም ተስማምተውበታል፡፡ ፈርጉሰን ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሲመጡ ክለቡ በ31 ሚሊዮን ፓውንድ ገና መሸጡ ነበር፡፡ ከአሰልጣኝነታቸው የመልቀቃቸውን ዜና ይፋ ሲያደርጉ ግን የ2.2 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ይዟል፡፡ ይህን አስደናቂ ስኬት የስነ ፅሑፍ ጥበብ በወለዳቸው ገለፃዎች ያልዳሰሰ የለም፡፡ የሊጉ ጨዋታዎች ሊጠናቀቁ ሲቃረቡ ጠቋሚ ጣታቸውን ሰዓታቸው ላይ አሳርፈው የመስመር ዳኞችን የሚሞግቱት፣ አገጫቸው የሚሰነጠቅ እስኪመስል ማስቲካ የሚያኝኩትና ሲሳካም ሁለት እጆቻቸውን ወደ ላይ አንስተው በመፈንጠዝ ረዳቶቻቸውን የሚያቅፉት ባለሙሉ ልብስ አዛውንት ከፕሪሚየር ሊጉ ምስል መታጣታቸው በሀዘን ተገልጿል፡፡
ሰር አሌክስ ለሚዲያውም ‹‹አምባገነን›› የሆኑባቸው ጊዜያት አሉት፡፡ ምቾት የማይሰጧቸውን ጥያቄዎች ያቀረቡ ጋዜጠኞችን ከእርሳቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች አግደዋል፡፡ ልጃቸው ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የሚያስጠረጥር የቢዝነስ ስራ ሰርቷል ሲል ከዘገበው ቢቢሲ ጋር ለረጅም ጊዜ ተቃቅረው ቃለ ምልልስ ከልክለው ኖረዋል፡፡ ለረጅም ዓመታት ‹‹ጡረታ የሚወጡት መቼ ይሆን?›› ሲሉ የጠየቁት ጋዜጠኞች ጥያቄያቸው በድንገት መልስ ሲያገኝ የፈርጉሰንን ደካማ ጎን ከመግለፅ ይልቅ በሰውዬው ዋጋ የማይተመን ስኬት ላይ አነጣጥረዋል፡፡
ከእንግሊዝ ውጭ እግርኳስን ከዕለታት አንድ ቀን የሚያስታውሱት የአሜሪካ ጋዜጦች እንኳን የታላቁን የስፖርት ሰው ጡረታ ዜና በፊት ገፆቻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ የእግርኳስ ፍቅር እምብዛም በሆነባት ሀገር ቁጥር 1 የሆነው ጋዜጣ ኒውዮርክ ታይምስ እንኳን አልዘነጋቸውም፡፡ በተለያዩ አህጉራት የሚታተመው ፋይናንሺያል ታይምስ የፈርጉሰንን የ27 ዓመታት አገዛዝ ውጤታማነት አብራርቷል፡፡ ከኒውዮርክ ማንሃተን እስከ ሆንግ ኮንግ የመልቀቃቸው ዜና ጉልበት ነበረው፡፡ በእውቁ የአሜሪካ መጽሔት ኒውዮርከር ላይ የሀገሬው ሰው ‹‹ሶከር›› ስለሚለው እግርኳስ የተፃፈ ሀገር ማግኘት ብርቅ ነገር ቢሆንም የፈርጉሰን ዜና ግን አብይ ርዕስ ሆኖበታል፡፡ የፍሎሪዳዎቹ ቢሊየነሮች የግሌዘር ቤተሰቦች ማንቸስተር ዩናይትድን በገቡበት ወቅት ከፈርጉሰን ጋር ቃለ ምልልስ ለመስራት ወደ ኦልድትራፎርድ የተጓዘው የመጸሔቱ ዘጋቢ ከአሰልጣኙ ጋር ያሳለፉትን የጥያቄና መልስ ጊዜ ማስታወሻውን ጽፏል፡፡ ‹‹በእንግድነት መቀበያው ክፍል ከተጨዋቾቻቸው ጋር ሲያወሩ አየኋቸው፡፡ ቱታ ለብሰው የፕላስቲክ ውሃ ይዘዋል፡፡ ወደ እኔ መጥተው በቃለ ምልልሱ ክፍል ቁጭ ስንል ግን ሰውየው ብልህ መሆናቸውን ተረዳሁ፡፡ በዘርፉ ብዙ እውቀት ተሞልተዋል፡፡ ሰማያዊው አይናቸው ግን ቆዳን በስቶ የሚገባ ሰቅጣጭ እይታ አለው፡፡ ጥያቄዬን ከመመለሳቸው በፊት ጥቂት ትንፋሽ ወሰዱ፡፡ ዝምታቸው ፍርሃት ይለቃል፡፡ ‹ከሰፈሬ መጥተህ ለምን ነገር ትፈልገኛለህ? ይህ የእኔ ግዛት ነው› የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ ይመስላል፡፡ ዙሪያዬን ተመለከትኩ የወለቀ ጫማ አልነበረም፡፡››
የኒውዮርክ ዘጋቢ ለቃለ ምልልስ ከፈርጉሰን ጋር የተፋጠጠበት ወቅት የአሰልጣኙና የዴቪድ ቤካም ውዝግብ ወሬ ያልተሳበት ጊዜ ነበር፡፡ በንዴት የጦፉት ፈርጊ የመጫወቻ ጫማ ወርውረው የዴቪድ ቤካምን ቅንድብ ሰንጥቀው የተጫዋቹ ቁስል ስፌት አስፈልጎት እንደነበር ይታወሳል፡፡
የጋዜጠኛው ቃለ ምልልስ ርዕሰ ጉዳይ ግሌዘር የገጠማቸውን የደጋፊዎች ተቃውሞ የተመለከተ ነበር፡፡ ፈርጉሰን የአሜሪካውያኑን ባለሀብቶች በመደገፋቸው የማይናቅ ቁጥር ባላቸው የዩናይትድ ደጋፊዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥረዋል፡፡ ሰውዬው የተገኙበትን የሰራተኛ መደብ አስተሳሰብ አዋርደዋል በሚል ተተችተዋል፡፡ ሶሻሊስት አመለካከታቸውን ሳይቀር ተቃርነዋል ቢባልም እስከ መጨረሻው ድረስ ከአሜሪካውያኑ ጎን ቆመዋል፡፡ ፈርጉሰን አይሳሳቱም ብለው የሚያምኑቱ ተቃውሟቸውን ጋብ አድርገዋል፡፡
ሰር አሌክስ በዚህ ፈተና ብቻ አላለፉም፡፡ በማንቸስተር ዩናይትድ አለቃነት የቆዩባቸው ዓመታት አሮጌውንና ዘመናዊውን ጊዜ ያገናኙ ናቸው፡፡ ከሳተላይት አብዮት እስከ ክፍያ ቴሌቪዥን ድረስ ከሀገር ውስጥ ተፅዕኖ እስከ ዓለም አቀፍ ዝና ድረስ ተመልክተዋል፡፡ ማንቸስተር ዩናይትድን በጠጪዎች ከተሞላ ክለብነት አንስተው በኒውዮርክ ስቶክ ኦክስቴንጅ ድረስ እስከደረሰ ግዙፍ ተቋምነት ድረስ አሳድገውታል፡፡ በዚህ ሂደት የአካዳሚ ሰልጣኝ ህፃናትን ወደ ኮከብነት ከፍ አድርገዋል፡፡ የዲሲፕሊን መመሪያቸውን የጣሱ ተጨዋቾችን ለመቆጣጠር በውድቅት ሌሊት እሰከ ንጋት ሊቆይ የታሰበ የተጨዋቾች ፓርቲን በርግደው ገብተዋል፡፡ በቡድናቸው ውስጥ ጥብቅ የአመጋገብ ስርዓት አስርፀዋል፡፡ የአካል ብቃት ባለሙያዎችን ቀጥረዋል፡፡ ዘመናዊነቱ ተነግሮ የማያልቅ የልምምድ ማዕከል አቋቁመዋል፡፡ የፖሊሲያቸውን ቀይ መስመር ለተላለፉት የመውጫ በሩን አሳይተዋል፡፡
በዝና ልባቸው ያበጠ ቱጃር ተጨዋቾችን ፀጥ ለጥ አድርጎ በመግዛት ለውጤት ማሰለፍ እንደሚቻል የፈርጉሰን ዘመን ተሞክሮ ያረጋግጣል፡፡ ከራቪያ ቢሊየነሮች እስከ ባህረ ሰላጤው ከበርቴዎች ድረስ የፈርጉሰንን የውጤታማነት ጉዞ ሊገቱ ሞክረዋል፡፡ ሃብታሞቹ የፈርጊን የፕሪሚየር ሊግ ዘውድ ነቀነቁት እንጂ እሰከወዲያኛው አላወረዱትም፡፡ ሰር አሌክስ ግን የሌሎችን ዘውድ መገርሰስ ይችሉበታል፡፡ የ45 ዓመቱ ፈርጉሰን በአዲስ ሹመኛነት ወደ ኦልድትራፎርድ ሲመጡ የሊቨርፑል ኃያልነት ጣሪያ የነካ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የሊቨርፑል ኃያልነት የኋላ ታሪክ ነው፡፡ ‹‹የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ካልሆንክ በስተቀር ፈርጉሰን የሚወደዱ ሰው አይደሉም›› ይላል በሊድስ ከተማ ተወልዶ ያደገ አንድ ጋዜጠኛ፡፡ ስለምን አይነት ጥላቻ እያወራ መሆኑ ይግባችሁ፡፡ ‹‹አንዳንድ ጊዜ በብስጭት ያሳብዱኛል፡፡ በተለይ በጨዋታዎች ማገባደጃ ላይ ከወንበራቸው ተነስተው ከዳኞች ጋር ሲጨቃጨቁ ጨርቄን ሊያስጥሉኝ ምንም አይቀራቸውም፡፡ ነገር ግን በምስጢር የፈርጉሰን አድናቂ ነኝ፡፡ ለእርሳቸው በቂም የታጀበ ክብር አለኝ››
ሰር ማት በዝቢም እንዲሁ ነበሩ፡፡ በተጋጣሚ ደጋፊዎች የማይወደዱና በ1960ዎቹ ማንቸስተር ዩናይትድን ለተደራራቢ ክብር ያበቁ ታላቅ አሰልጣኝ ናቸው፡፡ በአውሮፕላን አደጋ በርካታ ተጨዋቾቻቸውን በሞት መነጠቃቸው ከአውሮፓ ሻምፒዮንነት አላገዳቸውም፡፡ ሰር ማት እና ሰር አሌክስ ስኮትላንዳዊ ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት እውቁ ጂኪው መጽሔት ለፈርጉሰን ይህን ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር፡፡
‹‹የስኮትላንድ ምዕራባዊ ግዛት በርካታ ታላላቅ አሰልጣኞችን የሚያፈራው ለምንድን ነው?››
ፈርጉሰን መለሱ፡፡
‹‹ግላስኮአዊያንና የምዕራብ ስኮትላንድ ሰዎች በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ያደጉ ናቸው፡፡ እርጥብ፣ ቀዝቃዛ እና ምህረት የለሽ ብርድ አለው፡፡ አንድ የፌብርዋሪ ጠዋት በፍራንሴብራ ወደብ ተገኝተህ ታውቃለህ?›› ፈርጉሰን ጥያቄያቸውን በጥያቄ መለሱ፡፡ ልጅነታቸውን ያሳለፉበት የመርከብ ፋብሪካ የሚገኝበትን የባህር ዳርቻ መጠቆማቸው ነበር፡፡ በቦታው የብረት ቅዝቃዜ ጣቶችን እንደ እሳት የሚያቃጥል መሆኑን ለጋዜጠኛው ነገሩት፡፡ ‹‹ስትኖርበት ትወደው ይሆናል፡፡ ነገር ግን አስቸጋሪው አየር ያንተን የግል ባህሪይ የመለወጥ አቅም አለው›› ሲሉ መልሳቸውን ቀጠሉ፡፡ ጠያቂውም ዝም አላለም፡፡
‹‹ታዲያ አየሩ ለሰዎቹ ምን የሚሰጣቸው የተለየ ነገር አለ?››
የፈርጉሰን አጭርና ግልፅ መልስ ለቃለ ምልልሱ ማሳረጊያ አበጀለት ‹‹ትጋት!››
በዚህ አስገራሚው ሐሙስ ማንቸስተር ዩናይትድ ፈርጉሰንን በሌላ ስኮትላንዳዊ መተካቱን አስታውቋል፡፡ ዴቪድ ሞዬስን፡፡ የዩናዩትድ ደጋፊዎች ሞዬስ በደም ስራቸው ውስጥ ‹‹ብረት›› እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡ ሽግግሩ አጭርና ያልታሰበ ነበር፡፡ የቀድሞው ፈርጉሰን በወጡበት በር፣ የመጪው ጊዜ ሞዬስ ገብተውበታል፡፡
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013
ራስምታትን የማያውቀው ሰው የለም ለማለት ያስደፍራል፡፡ በህክምና ከጭንቅላት የሚነሳ ማንኛውም ህመም (የአይንና ጆሮ ህመምን ሳይጨምር) እንዲሁም ከኋላ በኩል ካለው የአንገት ክፍል መነሻ የሚነሳ ህመም፣ የራስምታት ይባላል፡፡ የራስምታት በራሱ በሽታ ሊሆን ይችላል፡፡ የበርካታ በሽታዎች ምልክት ሆኖም ይከሰታል፡፡ አንዳንዴ የራስ ምታት የገዳይ በሽታዎች ምልክት የሚሆንበት አጋጣሚዎች አሉ፡፡ የራስምታት በራሱ በሽታ ሲሆን፣ ሶስት አይነት መልክ ይኖረዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በህብረተሰባችን በብዛት የሚታወቀው ሚግሬይን የሚባለው የራስምታት ነው፡፡ ሌሎቹ (tension headache) እና (Cluster headache) ይባላሉ፡፡
ከሶስቱ የራስምታት ዓይነቶች (tension headache) ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ በብዛት ይታያል፡፡
ሚግሬይን የራስምታት (migraine headache) ከ (tension headache) በመቀጠል ከፍተኛ ስርጭት አለው፡፡ ይህኛው የራስምታት አይነት ህፃናትንና አዋቂዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ከጉርምስና ወቅት በፊት ሁለቱም ፆታዎች እኩል በዚህ ህመም እንደሚጠቁ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከዚህ ዕድሜ በኋላ ግን በአብዛኛው ሲጠቁ የሚታዩት ሴቶች ናቸው፡፡ ከጠቅላላው ህብረተሰብ፣ ከወንዶች 16 በመቶ፣ ከሴቶች ደግሞ 18 በመቶ የሚሆኑት ይህ አይነት የራስምታት ይታያባቸዋል፡፡
ክላስተር የራስምታት (cluster headache) የሚባለው ስርጭቱ በጣም አነስተኛ (0.1 በመቶ) ሲሆን፣ 85 በመቶ የችግሩ ተጠቂዎች ወንዶች ናቸው፡፡
ሚግሬይን፣ ስር ሰደድ የሆነ የራስምታት አይነት ሲሆን በዘር የሚተላለፍበት እድልም አለ፡፡ የራስምታቱ የሚያናጋ እና የመውቀጥ አይነት ከፍተኛ የህመም ስሜት ይፈጥራል፡፡ ይህ አይነቱ የራስምታት በአብዛኛው በአንድ የጭንቅላት ክፍል ላይ ይበረታል፡፡ አንዳንዴ በግንባር አካባቢ፣ ሌላ ጊዜ በአይን ዙሪያ እንዲሁም በአንገት ጀርባ አካባቢ የህመም ስሜቱ ይፈጠራል፡፡ በአብዛኛው ሕመሙ የጭንቅላትን ቀኝ ወይም ግራ ክፍል የሚያጠቃ ሲሆን፣ ሁለቱንም የጭንቅላት ክፍል የሚያጠቃበት እድል አነስተኛ (ከጠቅላላው 1/3ኛው) ነው፡፡ ህመሙ አንዴ በቀኝ ቆይቶ በግራ የጭንቅላት ክፍል መፈራረቁ በተለይ የሚለይበት ፀባይ ሲሆን፣ በአንድ በኩል ብቻ ከቆየ (ከተደጋገመ) ከሚግሬይን የራስምታት ውጪ የሆኑ በሽታዎች (ለምሳሌ የጭንቅላት ዕጢ) መጠርጠር ይበጃል፡፡ የሚግሬይን የራስምታት የአካል እንቅስቃሴ ሲኖር (ለምሳሌ ደረጃ መውጣት) የሚቀሰቀስ አይነት ነው፡፡ ከየራስምታቱ ጋር ማቅለሽለሽና ማስመለስ፣ ተቅማጥ፣ የፊት አመድ መምሰል (መንጣት)፣ የእጅ እግር መቀዝቀዝ እንዲሁም በብርሃንና በድምፅ በቀላሉ የመረበሽ ምልክቶች ይታያሉ፡፡ በዚህ የተነሳ ሚግሬይን የራስምታት ያለባቸው ሰዎች ብርሃንና ድምፅ ሽሽት በጨለማና ረጭ ባለ ቦታ መሆንን ተጠቂዎችና ቤተሰቦቻቸው ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክቶቹ ሲታዩ፣ የራስምታቱ ሊጀምር እንደሆነ በሚገባ ያውቃሉ፡፡
ሃያ በመቶ በሚሆኑ የበሽታው ተጠቂዎች ደግሞ ከራስምታቱ ትንሽ አስቀድሞ የሚከሰት እንዲሁም አንዳንዴ ከራስምታቱ ጋር አብሮ የሚቀጥል (aura) የሚባል ምልክት ያሳያሉ፡፡ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ደግሞ ምልክቶቹ (aura) ከራስምታቱ ውጪ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እነኚህ ምልክቶች ከዕይታ ማዕከል ጀምሮ ወደ ውጪ የሚሄድ የተለያየ ቀለማት ያለው ብልጭታ፣ በእይታ ክልል ውስጥ ማየት የማይቻልበት ክብ ስፍራ መፈጠር ናቸው፡፡ ቀላል የሚባለው (aura) ምልክቶች፣ በአንዱ እጅ ላይ፣ በአፍና አፍንጫ አካባቢ፣ የራስምታቱ በተፈጠረበት የጭንቅላት ጎን የመጠቅጠቅ ስሜት መኖር ናቸው፡፡ የሚግሬይን የራስምታት ተጠቂ፣ ህመሙ ከተወው በኋላ ለሃያ አራት ሰዓታት ያክል የአቅም ማጣት፣ በድምፅና ብርሃን የመረበሽ ምልክቶች ያሳያል፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳንድ የህመሙ ተጠቂዎች፣ ህመማቸው ሊያገረሽም ይችላል፡፡
ክላስተር የራስምታት (cluster headache)፣ በአንድ ሳምንት ወይም ወር ላይ ተጠቂውን በተደጋጋሚ አጥቅቶ፣ ከዚያ የወራት ወይም ዓመታት እረፍት ሰጥቶ እንደገና በመምጣት ይታወቃል፡፡ (cluster headache) ሲከሰት በቀን ሁለት ጊዜ ተጠቂውን የሚያሰቃይ ሲሆን፣ አንዴ የተከሰተው ህመም ከሰላሳ ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ቆይቶ ይጠፋል፡፡ ህመሙ በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት በመምጣት ይለያል፡፡ ተጠቂውን ከእንቅልፍ የሚቀሰቀስበት ሁኔታም የተለመደ ነው፡፡ እጅግ ሰቅጣጭ አይነት ሲሆን፣ አንዱ አይን አካባቢ ወይም ከአይን ጀርባ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ አንዳንድ የበሽታው ተጠቂዎች፣ ህመሙን ‹‹አይኔ ውስጥ እሳት ተቀምጧል›› በማለት ይገልፁታል፡፡ የተጠቃው አይን ይቀላል፣ ያነባል፡፡ ህመም በተፈጠረበት የጭንቅላት ጎን (ወይም አይን) ያለው የአፍንጫ ክፍል (ቀዳዳ) ይታፈናል፣ እንዲሁም ንፍጥ ይወጣዋል፡፡ የዚህኛው አይነት የራስምታት ተጠቂዎች፣ ከሚግሬይን የራስምታት ተጠቂዎች በተቃራኒው ይቅበዘበዛሉ፣ ከወዲህ ወዲያ ይራወጣሉ፤ ጭንቅላታቸውን ከግድግዳ ጋር ያጋጩታል፡፡
የራስምታት በራሱ ጊዜ ሲከሰት (የበሽታ ምልክት ካልሆነ) ምክንያቱ የአንጎል የደም ስሮች መስፋትና በዚሁ የተነሳ በአንጎል ውስጥ በደም ስሮች አካባቢ ያሉ የነርቭ ስሮች፣ ከሰፉት የደም ስሮች በብዛት በሚወጡ ኬሚካሎች መለብለባቸው ነው፡፡ ይህ የነርቮች መቆጣት ነው እንግዲህ የራስምታት የሚባለው፡፡ እንደ ሜግሬይን ያሉ የራስምታት አይነቶች ከራስምታት ውጪ በሆኑ በተለያዩ ምልክቶች፣ ለምሳሌ ማስመለስ እና ማቅለቀሽለሽ የመታጀባቸው ምስጢር ደግሞ የራስምታቱ ጠቅላላውን የነርቭ ስርዓት ማወክ መቻሉ ነው፡፡ ለምሳሌ ሚግሬይን የራስምታት የሰውነትን (sympathetic nervous system) ያውካል፡፡ ይህ የነርቭ ስርዓት ሲነቃቃ (ሲታወክ) ደግሞ በስሩ ያሉ የሰውነት ስርዓቶች (ለምሳሌ የምግብ መፍጨት ስርዓት) ይታወካል፡፡ ለዚህም ነው ከሚግሬይን የራስ ምታት ጋር ብዙ አይነት የጤና መቃወስ ምልክቶች የሚታዩት፡፡
የበሽታ ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረውን የራስምታት የሚያመጡ የተለያዩ ምክንቶች አሉ፡፡ በጭንቅላት ላይ ደረሰ አደጋ፣ በአንጎል ውስጥ የሚፈጠር ብግነት፣ የአንጎል ደም ስሮች ውስጥ የሚከሰት ጓጓላ፣ የአንጎል የደም ስሮች መለጠጥ፣ መሳሳትና መፈንዳት፣ በድንገት ከፍተኛ ደረጃ የሚደርስ የደም ግፊት፣ የጭንቅላት ላይ የደም ስሮች መብገን፣ በአይን ውስጥ ድንገት የፈሳሽ ግፊት መጨመር (ግላውኮማ)፣ በተደጋጋሚ ለካርቦን ሞኖክሳይድ ጋዝ መጋለጥ፣ የፓርኪንስንስ በሽታ፣ ጭንቀትንና ደም ግፊትን ለማከም የሚውሉ አንዳንድ መድሃኒቶች፣ ያለ ሐኪም የሚታዘዙ የራስ ምታት መድሃኒቶችን ያለ አግባብ መጠቀም፣ አንዳንድ የልብ ህመሞች (cardiac ischemia)፣ የአንጎል ውስጥ እጢ፣ ማጅራት ገትር፣ የመሳሰሉት ሁኔታዎች የራስ ምታት ያመጣሉ፡፡ የበሽታ ምልክት ተደርጎ የሚታየው የራስምታት፣ ለህይወት አስጊ የሆኑ እንደ የአንጎል እጢ፣ ማጅራት ገትር፣ በአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ ችግሮች ጠቋሚ ሊሆን ሲችል፣ ቀላል የሚባሉ ችግሮች እንደ ቡና ሱስ የማሳሉትንም ሊያሳይ ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን የበሽታ ምልክት የሆነው የራስምታትና ራሱ እንደ በሽታ የሚቆጠረው የራስምታት (migraine, clusture, tension) ተቀላቅለው በአንድ ሰው ላይ የሚታዩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ለምሳሌ (tension headache) ወይም በበሽታ ምክንያት የሚመጡ የራስምታት የሚግሬይን የራስምታትን ሊቀሰቅሱ ብሎም አብረው ሊታዩ ይችላሉ፡፡
የራስምታት አይነቶችን ለመለየት እንዲሁም የበሽታ ምልክት ይሁን ወይስ በራሱ በሽታ፣ ለመለየት የሚደረጉ የተለያዩ ምርመራዎች አሉ፡፡ በተለይ በበሽታ ምክንያት የሚታየውን የራስምታት መንስኤ ለማወቅ እንደ (MRI, CT scan) የማሳሰሉት መሳሪያዎች ወሳኝ ሲሆኑ፣ የደም ምርመራ ማድረግም ለራስምታቱ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ችግሮችን (የማጅራት ገትርን ጨምሮ) ለመለየት ያስችላል፡፡ የራስምታትን መንስኤ በተለያዩ መሳሪያዎችና የላብራቶሪ ምርመራዎች መለየት ቢቻልም ሐኪም የሚያደርገው የአካል ምርመራና ከበሽታው የሚወሰደው መረጃ ግን በሽታውን ለመለየት ምትክ የለሽ ነው፡፡
የራስ ምታት እንዴት ይታከማል?
በሌሎች በሽታዎች የተነሳ የሚመጣውን የራስምታት ለማከም፣ በመጀመሪያ የራስምታቱ መንስኤ የግድ መለየት ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የራስምታቱን ነጥሎ ማከም መሞከር ግን ስኬታማ ካለመሆኑም በላይ፣ መንስኤዎቹ ስር እንዲሰዱ ጊዜ ይሰጣል፡፡ የራስምታት በራሱ እንደ በሽታ ከሆነ ግን የተለያዩ ህክምናዎች የራስምታቱን ብቻ ለማጥፋት ይሰጣሉ፡፡
የሚግሬይን የራስምታትን ለማከም፣ እንደ የራስምታቱ ክብደት የተለያዩ መድሃኒቶች ይሰጣሉ፡፡ ቀለል ላለ የሚግሬይን የራስምታት፣ ያለ ሐኪም ትእዛዝ የሚወሰዱ እንደ ፓራሲታሞል፣ አስፕሪን፣ ዳይክሎፊናክ፣ ኢንደሜታሲን፣ አይቡፕሮፊን የመሳሰሉ መድሃኒቶችን መውሰድ ይቻላል፡፡ ቢሆንም ህፃናት እና በአስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ልጆች አስፕሪን ባይወስዱ ይመረጣል፡፡ የጨጓራ በሽተኞችም ከፓራሲታሞል ውጪ ያሉትን የህመም ማስታገሻዎች ከመውሰዳቸው በፊት ሐኪማቸውን ማማከር ይገባቸዋል፡፡ የጉበትና የኩላሊት ህመምተኞችም የራስምታት መድሃኒቶችን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መጠቀም የለባቸውም፡፡
ከበድ ላለ ሚግሬይን እንደ ergotamine ያሉ መድሃኒቶች ተመራጭ ናቸው፡፡ የሚግሬይንን የራስምታት የሚቀሰቅሱ የተለያዩ ሁኔታዎች ለምሳሌ፣ ጭንቀት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ፆም፣ አብረቅራቂ ነገሮችን መመልከት፣ አንዳንድ ሽታዎች፣ የሲጋራ ጭስ፣ አልኮል መውሰድ፣ ቸኮሌት፣ ቡና ወዘተ… ማስወገድ ህመሙ አስቀድሞ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡ የዚህ ህመም ተጠቂ ህመሙን የሚቀስቅስበት ምን ሁኔታ ወይም ነገር እንደሆነ ለይቶ በማወቅ ቀስቃሹን ነገር ወይም ሁኔታ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡
ክላስተር የራስምታት ለማከም የተለያዩ ህክምናዎች አሉ፡፡
አንዴ የጀመረውን ህመም ለማስቆም መቶ በመቶ የሆነ የኦክስጅን ጋዝ ከ8-10 ሊትር በደቂቃ ለዚሁ በተዘጋጀ ማስክ አማካይነት ከ10-15 በመተንፈስ፣ ጎን ለጎንም የ(triptan) ወይም (ergot) ዝርያ መድሃኒቶች መውሰድ ፍቱን ነው፡፡ ይህን አይነቱን የራስምታት አስቀድሞ ለመከላከል የ(calcium blocker) ዝርያ መድሃኒቶችን መውሰድ ይቻላል፡፡
(tension headache)ን ለማከም፣ ለቀላል ሚግሬይን የተጠቀሱትን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ መድሃኒቶች መጠቀም ይቻላል፡፡
ከቀላሉ ጉንፋን እስከ ወባ እንዲሁም እስከ ጭንቅላት እጢ ያሉ በሽታዎች ምልክት ሊሆን፣ እንዲሁም በራሱ እንደ በሽታ ሊከሰት የሚችለው የራስምታት አፈጣጠርና ህክምና ይህንን ይመስላል፡፡ S
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 21st, 2013
ከኤፍሬም እሸቴ
የሰሞኑ ትልቁ አገርኛ ዜና (ቢያንስ በዳያስጶራው ዓይን) የመንግሥት ባለሥልጣናት በሙስና ምክንያት መያዝና መታሰር እንዲሁም የባሕር ዳሩ ሰላማዊ ሰዎች ግድያ ጉዳይ ነው። አገር ቤት የማይነበቡት ድረ ገጾችና የጡመራ መድረኮች (ብሎጎች)፣ የአካባቢ ሬዲዮኖችና ማኅበራዊ ድረ ገጾች (ለምሳሌ ፌስቡክና ትዊተር) የሚያወሩት ስለዚሁ ነው።
አጀንዳ አንድ
የባሕር ዳሩ ግድያ ከወንጀልነቱ በላይ ትልቅ መወያያ ሆኖ የሰነበተው የገዳዩ ማንነት ጉዳይ ነው። ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ አባል መሆኑ የተለያዩ መላምቶችን፣ ግምቶችን፣ ትርጉሞችን እያሰጠ ሁሉም በፈለገው መልክ እንዲተችበት ዕድል ሰጥቶ ሰንብቷል። የፖለቲካ ልዩነቶች ብቻ ሳይሆኑ የብሔረሰብ ማንነቶችም እየተነሡ “ገዳዩ ከዚህ ብሔረሰብ ነው፤ ከዚያ ብሔረሰብ ነው” በሚል ጥሩም መጥፎም አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። መንግሥትን እና መሠረቱን የሚደግፉት በአንድ በኩል፣ ተቃዋሚዎቹ እና በተለይም የዘር-ፖለቲካን አምርረን እንቃወማለን የሚሉት በሌላ በኩል የሐሳብ ጥይቶች ሲያስወነጭፉ ነበር።
ዝግ እና መተንፈሻ የሌለው ማኅበረሰብ እና ነጻ ማኅበረሰብ ተመሳሳይ አደጋዎችን የሚያስተናግድበት መንገድ እንዴት እንደሚራራቅ ጥሩ ማሳያ ሆኖልኛል። ዝግ እና መተንፈሻ የሌለው ማኅበረሰብ የሌለው ያልኩት ነጻ ሚዲያ የሌለበትን የኛን አገር መሆኑ ግልጽ ነው። ነጻ ማኅበረሰብ ያልኩት ነጻ ሚዲያዎች ያሉበትን እንደሆነው ሁሉ።
Christopher Jordan Dorner የተባለ የሎስ አንጀለስ ከተማ ፖሊስ እና የቀድሞ የጦር ሠራዊት ባልደረባ በሥራ ቦታው በገጠመው አለመግባባት ሰበብ አራት ሰዎችን ገድሎ ለሳምንት ያህል አካባቢውን ሲያሸብር ቆይቶ በመጨረሻ ራሱን እንዳጠፋ መቸም ሳትሰሙ አልቀራችሁም። ከጥር 26 – የካቲት 5/2005 ዓ.ም ድረስ አካባቢውን አሸብሮት ነበር። የታጠቀ ነው። ፖሊስ ብቻ ሳይሆን ወታደርም ነው። የሰለጠነ። በጠላት ላይ ማዞር ያለበትን ጠመንጃ ወደራሱ ዜጎች ሲያዞር እንዴት እንደሚዘገንን መገመት ይቻላል።
ግለሰቡ የሥራ ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ ተሰወረ። ሐሰሳ ተጀመረ። ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን ይሰጡ ነበር። ቀንም ሌሊትም ሲፈለግ ቆየና በሰዎች ጥቆማ ያለበት ተደረሰ። ከዚያም ራሱን አጠፋ። በቃ። ጉዳዩ በዚሁ አበቃ። ስለ ሰውየው ማንኛውንም ዓይነት ማብራሪያ ለሚፈልግ ሰው መረጃዎቹ በስፋት አሉ። ማነው? የት ተወለደ? አደገ? መቼ ወደ ጦሩ ተቀላቀለ? እንዴት ከዚያ ወጥቶ ፖሊስ ለመሆን በቃ? ከባልደረቦቹ ጋር ለምን ተጣላ? ለምን ወደዚህ ዓይነት ወንጀል ሊገባ ቻለ? ወዘተ።
ባሕር ዳርስ? ባሕር ዳር ላይ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ብዙ ሰዎችን ገደለ። ከዚያ … ውዥንብር። ግማሹ 12 ሰው ተገደለ ይላል፣ ሌላው ደግሞ 18 ያደርሰዋል። ሰውየው ማን ነው? መቼ ፖሊስ ሆነ? ለምን ወደ መግደሉ ሊገባ ቻለ? ግድያውን በአጭሩ ማስቆም አይቻልም ነበር ወይ?
ችግሩ ምንድር ነው? ሚዲያ የለም፤ የግል ጋዜጣና ቴሌቪዥን የለም፣ የመንግሥቱም ቢሆን ለዚህ ዓይነቱ ነገር ዝግ ነው። … ነጻ ሚዲያ ሲጠፋና ትክክለኛ መረጃ ሲታጣ በመካከል ምን ይነግሣል? ግምት፣ ውሸት፣ ሽብር፣ ጥርጣሬ። ቢያንስ በዳያስጶራው ሚዲያዎች እና በማኅበራዊ ድረ ገጾች የነበረው እንደዚያ ነው። (‘ዳያስጶራ ልማዱ ነው’ ካልተባለ በስተቀር)።
እንዲህ ዓይነቱ አደጋ ሲከሰት የመጀመሪያው እንዳልሆነ የሚናገሩ ሰዎች አጋጥመውኛል። ሌላም ቦታ የተከሰተ ከነበረ ሊቀጥል እንደማይችል መተማመኛ ማግኘት ይከብዳል። አዕምሯቸው የተቃወሰ መሣሪያ የያዙ ሰዎች መኖር የየትኛውም አገር ችግር ይመስለኛል። ችግሩ ተመሳሳይ ከሆነ መፍትሔውም ከሌላ ትምህርት ሊወሰድበት የሚችል ነው ማለት ነው። በባሕር ዳሩ ጉዳይ እንዳየኹት ግን ዜጎችም ይሁኑ የመንግሥት ሰዎች ነገሮቹን የተመለከቱበት አቅጣጫ ከተለመደው ከዚያው አሰልቺ የአገራችን የዘር-ፖለቲካ አንጻር ብቻ መሆኑ ያሳፍራል።
ለምሳሌ የብዙ ሰው ጥያቄ የ“ፌዴራል ፖሊስ” አባል ከሆነ፣ እነዚህ ፖሊሶች ደግሞ የሰውን ሰብዓዊ መብት በመግፈፋቸው እንጂ ሰላም በማስከበራቸው የሚታወቁ ካልሆነ፣ ግድያው ከተለመደው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አንጻር እንጂ ከወንጀልነቱ አንጻር የተሰጠው ግምት አናሳ ነበር። እንዲያውም ሆን ተብሎ የተፈጠረ የመንግሥት የማሳሳቻ ዘዴ ሆኖም ተተችቶበታል።
አጀንዳ ሁለት
በተመሳሳይ መልኩ የሰሞኑ ትልቅ አጀንዳ የሙስናው እና በሙስናው ምክንያት የተባረሩት ጎምቱ ባለሥልጣኖች ጉዳይ ነው። የባሕር ዳሩን ማስቀደሜ ከምንም ነገር በላይ ክቡሩን የሰው ሕይወትን መጥፋት የተመለከተው ዋነኛ በመሆኑ ነው። በተጨማሪም እንዲህ ዞር ያለበት “ቱቀማ” ሰው ተነሥቶ በየመንገዱ ሲገድል ቢያንስ በእኛ አገር የተለመደ ስላልሆነ ነው። (ቱቀማ (ኦሮምኛ)= ንክ (አማርኛ))።
ግንባራቸው የማይፈታው ብርሃን ኃይሉ በአቅም ማነሥ (የጉልበት ሥራ መሰለ አይደል?) ከሥልጣናቸው ሲባረሩ መልከ መልካሙ አቶ መላኩ ፈንታ (በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር)፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገብረ ዋሕድ ወልደ ጊዮርጊስና የባለሥልጣኑ ዋና ዓቃቤ ሕግ አቶ እሸቱ ወልደሰማያት በፀረ ሙስና ኮሚሽንና በብሔራዊ መረጃ ማዕከል ሰዎች መታሠራቸው ተነግሯል። በሙስና ምክንያት፤ ስኳሯ ላይ ተገኝተው ነው ተብሏል። በዝርዝር ምን እንደሆነና ምን እንደተደረገ የአደባባይ ምሥጢር ስለሆነ ደግሞ ማተቱ አንባቢን ማድከም፣ ቦታ ማበላሸት ነው። ጥያቄው እኛ ዜጎች ዜናውን እንዴት ነው የተቀበልነው የሚለው ላይ ነው።
በሙስና ምክንያት ተይዘው ከታሠሩት ከአቶ ታምራት ላይኔ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ መንግሥት በሙስና አሰርኳቸው የሚላቸውን ሰዎች የታሰሩበት ምክንያት በርግጥም ሙስና ነው ብሎ የሚቀበል ብዙ ሰው አይደለም። ታምራት ላይኔም ሆኑ ስዬ አብርሃና ቤተሰቦቻቸው ብሎም እነ መላኩ ፈንታ ሙስና ውስጥ አልገቡም ብሎ የሚከራከር እንደሌለው ሁሉ ዋነኛ የመታሰራቸው ሰበቡ ግን ሙስናው ነው የሚል አይገኝም። በሙስና መታሰር ቢኖር እነ እንትና መቅደም አልነበረባቸውም ተብሎ ስም መጥራት ሲጀመር በአሳሪዎችና በታሳሪዎቹ መካከል ልዩነት ይጠፋል።
በሙስና ሰበብ ከማሰር የደርጉ “የፍየል ወጠጤ” ዘፈን ይሻላል?
ለመናገር ከመፍራት ካልሆነ በስተቀር የኢሕአዴግ መንግሥት ተቃዋሚዎቹን የማስወገጃ ዘዴ ሕጋዊ የሚመስሉ ሕገወጥ ተግባሮች ናቸው። ለምሳሌ በሙስናና በአሸባሪነት ስም ወህኒ ማውረድ። ደርግ ምን ያደርግ ነበር ብንል የማይፈልጋቸውን ሰዎች “የፍየል ወጠጤ” የሚለውን ልብ ነቅናቂ ዘፈን አስቀድሞ ከዚያ በግልጽ ይገድል፤ ያስር ነበር። ሙስና የዘመናችን የፍየል ወጠጤ ናት ማለት ነው? ከሆነ አይቀር አንድኛውኑ የፍየል ወጠጤው ይሻላል። ከጀርባ ከመመታት እያወቁት ከፊት ለፊት መመታት።
“ኮንስፒረሲ ቲዮሪ” የሚወድ ባህል መፍጠር፣
እውነተኛው ምክንያት ሆኖ ለሰበቡ ግን ሌላ ነገር መፍጠር ቀስ በቀስ አዲስ ልማድ እየሆነ ነው። በሙስና ስም የፖለቲካ ልዩነትን ማስተንፈስ ሲለመድ ነገ በትክክሉ ሙስና የፈጸሙ ሰዎች ለወንጀላቸው ሐዘኔታ የሚሰማው ሰው እንዲያገኙ መንገዱ ይመቻችላቸዋል። በርግጥም ሙሰኞቹን ከፖለቲካ መብት ተከራካሪዎች ለይቶ መመልከት ይከብዳል።
አሸባሪ የሚባለውን ቃልና ሐሳብ በዚሁ አገባብ ልንመለከተው እንችላለን። የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው፣ መብታቸውን የጠየቁ ሰዎች ‘አሸባሪዎች” ሲባሉ ትክክለኞቹን ከአሸባሪው መለየት ከባድ ይሆናል። በዚህ መምታታት ውስጥ የሚያድጉ ልጆች ምን ዓይነት መረዳት ይዘው እንደሚያድጉ ፈጣሪ ይወቀው።
ተኩላ ሳይመጣበት ለቀልድ “ኡኡኡ ድረሱልኝ፣ ተኩላ በጎቼን ፈጀ” ያለው እረኛ ታሪክ አይመጣባችሁም? ለቀልድ ያለው እውነት ሲሆን ረዳት ያጣው ልጅ ታሪክ። ዛሬ ሙሰኛ እና አሸባሪ የተባሉት ነጻ ሆነው እውነተኞቹ ሙሰኞችና አሸባሪዎች መያዝና ለፍርድ መቅረብ ሲጀምሩ ይኼ መንግሥት እንዴት ተአማኒነት ይኖረዋል? አልቅሶ ቢነግረንም አናምነውም ያኔ። በየራሳችን የኢሕአዴግ “ኮንስፒረሲ” እንደሆነ ስለምንገምት።
ለጥቂት ጥቅም ትልቁን አጥር መናድ
የፍየል ወጠጤው ይሻላል ስል የመግደል ጥሩ ኖሮት አይደለም። የደርጉ እንስሳዊ የጭካኔ በሽታ ከዚያው ዘመን ወደ ሌሎች ዘመኖች የማይተላለፍ ስለሆነ እንጂ። ሕግን የተንኮል ማከናወኛ ስናደርጋት ግን በሽታው በዚያ የማይቀር ተላላፊ እናደርገዋለን። በአገራችን ሕጋዊ ተቋማት ስም የሚፈጸሙ ተንኮሎች ተላላፊ በሽታ ይሆናሉ።
በግብጽ ሆስኒ ሙባረክ ወርደው መሐመድ ሙርሲ ቢመጡም የፖሊሱ ችካኔ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ጭካኔ ያልተሻሻለው ለምንድነው? ሕጋዊ ተቋማቱ ሕገወጥነትን ስለተለማመዱና የተላላፊው በሽታ ተጠቂዎች ስለሆኑ ነው። ኢሕአዴግ ጊዜያዊ ድል ለማግኘት ትልልቅ አጥሮችን መናድን ሕጋዊ አድርጎታል። ዛሬ የተናዱትን የሕግ፣ የባህልና የሥነ ምግባር አጥሮች ዳግም መገንባት ቀላል አይሆንም። በጥቂት ዓመታት እንደተናዱት ማደሱም እንዲሁ በጥቂት ዓመታት የሚሳካ ላይሆን ይችላል። … ነገ ያስፈራል።
የመንግሥት ርምጃዎች ትክክል መሆን አለመሆናቸውን ማን ባጣራልን?
ከዚህ ችግር ልንተርፍ የምንችለው እና መንግሥትም ቢሆን የሚናገረው ነገር በርግጥም እውነት እንዳለው ሊያጣራለት የሚችለው እውነታ-አንጣሪ (Fact-checker ለሚለው የሚለውን ነው የተረጎምኩት) ሚዲያው እና መያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ነበሩ። ከእነርሱ ጋር ደግሞ ዓይንና ናጫ፣ እሳትና ጭድ ሆነ። በደርግ ዘመን እንኳን ከመጥፋት የተረፉ መያዶች ከኢሕአዴግ ግን አልተረፉም። እነርሱን ባጠፋ መጠን ራሱን እየጎዳ መሆኑ ከቀን ቀን ግልጽ እየሆነ ነው። ስለ ሀገር እና ስለ መጪው ትውልድ ሲባል ኢሕአዴግ ያፈረሰውን መገንባት መጀመር አለበት። መንገዱንና ሕንጻውን መገንባት ብቻ አገር መገንባት አይሆንም። መንገዱና ሕንጻው ለኢትዮጵያዊው ይገነባለታል እንጂ እኛ ዜጎቹ ለመንገዱና ለሕንጻው አንኖርም። አለበለዚያ አዲስ ነገር በተከሰተ ቁጥር የራሳችንን መላ ምት እየሰጠን “ሕልምና የኛ አገር ፖለቲካ እንደፈቺው” ሆኖ ይቀራል።
ይቆየን፣ ያቆየን
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Monday, May 20th, 2013
ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ ካናዳ)
1. እስኪ ደግሞ ትንሽ ልረብሽ። ጽሁፍ ተሸፋፍነው የተቀመጡ ሀሳቦችን ካልገለባበጠ፤ ያንቀላፉትንም ካልረበሸ አይመቸኝም።
2. አንዳንድ ጠንካራ ምሳሌያዊ አባባሎች በአንድ ሀይማኖት ውስጥ ቢነገሩም፤ መልእክታቸውን የሀይማኖት ድንበር አይወስነውም። ጠቀሜታቸውን ሳይንስና ስልጣኔም አይሽረውም። በአሸዋላይና በአለት ላይ ስለሚገነባ ቤት ጽናት ልዩነት ቅዱስ መጽሀፍ የተናገረውን መጥቀስ ይቻላል። ቃልበቃል አላስታውሰውም፤ ግን እምነታችን በጠንካራና በማይናወጽ አለት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ በፈተናና በጥርጣሬ፤ እንዲሁም በጽናት እጥረት እንዳይበረዝ ሲያስጠነቀቅ፤ መጽሀፍ ቅዱስ “በአለት ላይ የታነጸ ቤት በአሸዋ ላይ እንደ ተገነባ ቤት ንፋስና ወጀብ አያናወጠውም” አይነት ነገር ይላል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Monday, May 20th, 2013
ግርማ ካሳ
(muziky68@yahoo.com)
ሜይ 20 ቀን 2013
አገር ዉስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም፣ በአፍሪካ ሕብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አውጇል። ከግንቦት 15 እስከ 17 ባሉት ቀናት ደግሞ፣ ኢትዮጵያዉያን ጥቁር አልባሳት በመልበስ፣ አገዛዙ በሚያራምዳቸውን ጎጂ ተግባራት ላይ፣ ያላቸውን ተቃዉሞ እንዲገልጹ ጥሪ አስተላልፏል።
ፓርቲዉ በቅርቡ የተመሰረተ፣ ብዙ አገር አቀፍ መዋቅር ገና ያልዘረጋ፣ ተስፋ የሚሰጥና በወጣቶች የተሞላ ለጋ ፓርቲ ነዉ። ጥሪዉ ከቀረበ ገና ሶስት ሳምንት ብቻ እንደመሆኑም፣ ምን ያህል አስቀድሞ ሕዝቡን በማደራጀት አንጻር በቂ ዝግጅት እንደተደረገ ፣ ጥሪው በይፋ ለሕዝብ ከመተላለፉ በፊትም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር (እነርሱም ዝግጅት እንዲያደርጉ) ምን ያህል ዉይይት እንደተካሄደ አላውቅም። በመሆኑም በግንቦት 17 ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመተንበይ አስቸጋሪ ነዉ።
እንደዚያም ሆኖ ግን፣ ከወዲሁ በርካታ ድሎችን ተመዝግበዋል ባይ ነኝ። የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት፣ ይሄን ጥሪ ሲያቀርቡ፣ ምን ያህል ድፍረትና ጀግንነት እንዳላቸው ለማረጋገጥ ችለዋል። ሊታሰሩ፣ ሊደበደቡ፣ ሊገደሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ። እነርሱ መካከል ያሉ፣ ብዙዎቹ ኢንጂነሮች፣ ጠበቃዎች ..ናቸው። የገዢው ፓርቲን ተቀላቅለው፣ የስርዓቱ ተጠቃሚዎች መሆን የሚችሉ ናቸው። ነገር ግን ኢትዮጵያንና ሕዝባቸውን አስቀድመዉ፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለዲሞክራሲና ለሕግ የበላይነት በመቆም፣ ከፊት በመቅደም፣ ትግል ምን ማለት እንደሆነ እያሳዩን ነዉ።
በዚህም ምክንያት፣ በፈታኝና ትእግስት አስጨራሽ ሁኔታ ዉስጥ ተኩኖም፣ አገር ቤት የሚደረገዉን የሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ መግለጫ ከማዉጣትና ገዢው ፓርቲን ከማውገዝ ያለፈ፣ አንድ ምእራፍ ወደፊት እንዲሄድ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አድርጓል። አንድ በሉ።
ለበርካታ አመታት የዳያስፖራዉ ትኩረት አዲስ አበባ ሳይሆን አስመራ ነበር። አገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን ምንም እንደማይሰሩ፣ መስራት ቢፈልጉም መስራት እንደማይችሉ፣ አገር ቤት የሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል «ቅዠት» እንደሆነ ነበር የሚነገረን። ነገር ግን በቅርቡ በተለያዩ ሜዲያዎች እንዳነበብነው፣ እንደ ኢሕአፓ-ዴሞክራሲያዊና የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤት ያሉ አንጋፋ በዉጭ አገር ያሉ ድርጅቶች፣ የሰማያዊ ፓርቲ ላቀረበው ጥሪ ያላቸውን ኢትዮጵያዊና ወቅታዊ አጋርነት ገልጸዋል። በተለያዩ የፓልቶክ ክፍሎች፣ በኢሳት፣ በራዲዮኖች፣ በድህር ገጾች የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ትልቅ ትኩረት ስቦ ውይይትን ጭሯል። ይሄ ሁሉ እንግዲህ የሚያሳየዉ ዳያስፖራው ትኩረቱን አገር ቤት ወደሚደረገው የሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንዲያዞር ማድረጉን ነዉ።
በዉጭ የሚገኘው ወገን ብዙ ሊረዳ፣ ብዙ ሊደግፍ፣ ትልቅም ሚና ሊጫወት የሚችል ነዉ። ይህ ኃይል አገር ቤት ካለው ኃይል ተነጥሎ፣ አገር ቤት ከሚደረገዉ ትግል እራሱን ለይቶ መቆየቱ ብዙ ጉዳት በትግሉ ላይ አምጥቷል። አገዛዙን በእጅጉ ጠቅሟል። በሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ምክንያት፣ አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ለመደገፍ ፣ በዳያስፖራ የሚደረገዉን እንቅሳሴ ማየታችን በራሱ ትልቅ ድል ነው። ብዙዎቻችንን አስደስቶናል። በመካከላችን የነበረዉን መከፋፈል አስወግዶ ከዚህ በፊት በቅንጅት ጊዜ እንደነበረው፣ በአንድነት እንድንሰማራ የማድረግ ትልቅ ኃይል አለዉ። ሁለት በሉ።
በድርጅታዊ መዋቅርና በአባላት ብዛት ከሰማያዊ ፓርቲ እጅግ የላቁ እንደ አንድነት ፓርቲ ያሉ በአገር ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አሉ። እነዚህ ድርጅቶች ተመሳሳይ አላማ እንዳላቸው፣ በዚያም ረገድ ሁሉንም አስተባብረው፣ የተጠናና የተደራጀ የሰላማዊ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ለማድረግ እቅድ እንዳወጡ እንሰማለን። የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፣ በነዚህ ድርጅቶች ዉስጥ በእቅድና በጥናት ደረጃ የተቀመጡ እቅዶች ወደ ተግባራዊነት እንዲሄዱ የሚያበረታታና አሉታዊ አስተዋጾ የሚኖረው ሆኖ ነዉ ያገኘሁት። ሶስት በሉ።
የሰማያዊ ፓርቲን ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን አስከትሎ ገዢዉ ፓርቲ እጅግ በጣም በርካታ ወታደሮች አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳስገባ እየተዘገበ ነዉ። «ከሕዝብ ሊነሳብኝ የሚችለዉን ዉጥረት እንዴት አድርጌ ነዉ የማከሽፈው?» በሚል አገዛዙ ውጥረት ላይ ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ። እንግዲህ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፣ ከወዲሁ ለአገዛዙ ትልቅ መልእክት እንዲደርሰው እያደረገ ነዉ። መልእክቱም «ዝም ብለን አንቀመጥም። ለመብታችን፣ ለነጻነታችን እንሞታለን። ከአሁን በኋላ አንፈራችሁም» የሚል ነዉ። ይሄም በራሱ ትልቅ ዉጤት ነዉ። አራት በሉ።
ሁለት ነገር ብዬ ላቁም። የመጀመሪያዉ ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበዉ ጥሪ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ቢያቀርበዉም፣ ጉዳዩ ሁላችንምም የሚመለከት እንደሆነ ነው። ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት አለብን። በኢሜል፣ በስልክ፣ በኢንተርኔት፣ በቫይበር …ለምናውቃቸው በሙሉ ጥሪ እናስተላልፍ። ሰማያዊዎች ለመታሰር ተዘጋጅተዋል። እኛ ቢያንስ 5፣ 10፣ 20 አገር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዉያንን ጥቁር አልባሳት እንዲለብሱ ማበረታት ሊያቅተን አይገባም። እንረባረብ። «አይ እኔ የማደርገዉ ምን ለዉጥ አያመጣም» በጭራሽ አንበል። ግድ የለም ማድረግ የምንችላትን ትንሿን እናድርግ።
ሁለተኛው ነጥብ፣ ይሄ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የመጀመሪያዉ እንጂ የመጨረሻዉ እንደማይሆን ነዉ። ከአሁኑ የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ትምህርት ተወስዶ፣ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት ፓርቲ፣ መኢአድ፣ አረና ትግራይ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ..የመሳሰሉ አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች በአንድ በኩል፣ እንደ ኢህአፓ-ዴ፣ የሽግግር ምክር ምክር ቤት፣ ሸንጎ ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የመሳሰሉ በሌላ በኩል ሆነው፣ ትግሉን በማቀናጀት፣ አገረ ሰፊ፣ ተከታታይ፣ የተቀናጀ፣ በዲፕሎማሲና በሕዝብ ግንኙነት የተደገፈ፣ የተጠና፣ ሰላማዊ የእምቢተኘት ዘመቻዎች መደረግ አለባቸው፤ ይደረጋሉምም። አብረን ተያይዘን እስከሰራን ድረስ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማሸነፋችን አይቀርም።
ሰላማዊ እንቅስቃሴ ማድረጉ የዜጎች ሙሉ አለም አቀፋዊ መብት ነዉ። አሁን ያለው ገዢው ፓርቲ የሚመጻደቅበት ግን እራሱ የማያካብረው ሕገ መንግስት ሁሉ ሳይቀር፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ሙሉ መብትን ይደነግጋል። በመሆኑም አንዳንድ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲን እንቅስቅሴ ሊያጣጥሉት ይችላሉ። ጸረ-ልማት፣ ሽብርተኘንት፣ ጽረ-ሕገ መንግስታዊ፣ አመጽ ቀስቃሽ ወዘተ የሚሉ ክሶችን ሊሰነዝሩ ይችላሉ። ነገር ግን ይሄን በማድረጋቸው የሚነገሩን ነገር ቢኖር ዘመናዊ ፖለቲካ ያልገባቸው፣ የኋላ ቀር የጫካ ፖለቲካ የሚያራምዱና በራሳቸው የማይተማመኑ መሆናቸውን ነዉ።
ተቃውሟችን በልማት ላይ አይደለም። ተቃዉሟችን በአባይ ግድብ ላይ አይደለም። ኢሕአዴግን እንደ ድርጅት አንቃወምም። የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ኢሕአዴግን የመደገፍ፣ በኢሕአዴግ ፖሊሲ ዙሪያ የመንቀሳቀስና የመደራጀት ሙሉ መብታቸው እንደሆነ እናምናለን። እንደዉም ኢሕአዴግን ከሚደግፉ ፣ ኢሕአዴግ በመልካም አስተዳደርና በደሞክራሲ ረገድ እንዲያሻሻል ከሚፈልጉ ጋር መነጋገር ያስፈልጋል እንላለን። (እንደዉም እንደታዘብነዉ በርካታ የኢሕ፤አዴግ ደጋፊዎች በይፋ የሚደግፉትን ድርጅት እየጠየቁ ያሉበት ወቅት ነዉ)
ነገር ግን የአገዛዙ ባለስልጣናት ሌላዉን የመርገጥ፣ የማሰር፣ የማንገላታት ፣ የማፈናቀልና የመግደል ስልጣን የላቸውም። በዚህ ረግድ የሚፈጽሙትንም እኩይ ተግባራት «ያቁሙ» ብለን ነዉ ተቃዉሞ የምናሰማዉ።
የምንቃወመው፣ ለሕንዶችን ለአረቦች መሬት እየተሰጠ፣ ዜጎችንን ከዚህ ዘር ናቸው በሚል፣ ከቅያቸው በማፈናቀል የሚደረግን አሳዛኝና ጨካኝ የዘር ማጥራት ወንጀልን ነዉ።
የምንቃወመው፣ ድሃዉ ሕዝባችን፣ ታንቆ ከአመት ወደ አመት፣ ለአባይ ገንዘብ እንዲከፍል እየተደረገ፣ ቢሊዮን ዶላሮች ከአገር ቤት መዘረፋቸውን፣ በቱባ የአገዛዙ ጀነራሎችና ባለስልጣናት፣ በአደባባይ ኬት እንዳመጡት በማይታወቅ ገንዘብ የሚሰሩት ፎቆችንና የሚያንቀሳቀሱ ቢዝነሶችን ነዉ።
የምንቃወመው ዜጎች በአገራችን ብእር ስላነሱ ብቻ፣ ወይም «በሃይማኖት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ አይገባ» በማለታቸው፣ ሽብርተኞች እየተባሉ በግፍ መታሰራቸውን ነዉ።
እንግዲህ መብቴ ተረገጠ የሚል ኢትዮጵያዊ ካለ ፣ ይነሳ። መብቱንም ያስከብር።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Monday, May 20th, 2013

በሁለት መንታ መንገድ ላይ የሚገኘው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Monday, May 20th, 2013
እንደመግቢያ፤ አሸዋና አለት
1. እስኪ ደግሞ ትንሽ ልረብሽ። ጽሁፍ ተሸፋፍነው የተቀመጡ ሀሳቦችን ካልገለባበጠ፤ ያንቀላፉትንም ካልረበሸ አይመቸኝም።
2. አንዳንድ ጠንካራ ምሳሌያዊ አባባሎች በአንድ ሀይማኖት ውስጥ ቢነገሩም፤ መልእክታቸውን የሀይማኖት ድንበር አይወስነውም። ጠቀሜታቸውን ሳይንስና ስልጣኔም አይሽረውም። በአሸዋ ላይና በአለት ላይ ስለሚገነባ ቤት ጽናት ልዩነት ቅዱስ መጽሀፍ የተናገረውን መጥቀስ ይቻላል። ቃል በቃል አላስታውሰውም፤ ግን እምነታችን በጠንካራና በማይናወጽ አለት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ በፈተናና በጥርጣሬ፤ እንዲሁም በጽናት እጥረት እንዳይበረዝ ሲያስጠነቀቅ፤ መጽሀፍ ቅዱስ “በአለት ላይ የታነጸ ቤት በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት ንፋስና ወጀብ አያናወጠውም” አይነት ነገር ይላል።
3. ከዚያ የኛ “ትግል” ትዝ አለኝ። የኛ “ትግል”፤ ትግል ካለን፤ በአሸዋ ላይ የታነጸውን ቤት መስሎ ይታየኛል። በአህያ ቆዳ የተሰራ አይነት ቤት፤ ጅብ በጮኸ ቁጥር የሚንቀጠቀጥ። ዛሬ ስለዚያ ነው የምጽፈው። ስለዚያም ብቻም አይደለም፤ እኛንና ጠላቶቻችንን ስለሚለያዩን ወይም አንድ ስለሚያደርጉን ነገሮች እጠቅሳለሁ።
4. ለምሳሌ፤ ጠላቶቻችን ርኩስ መሆናቸው፤ እኛም የነሱን ርኩሰት ነቅሰን ማውጣታችን፤ እኛን ደርሶ ጻድቅ አያደርገንም። አንዳንዶች እነደዚያ የሆንን ሊመስላቸው ይችላል። ለምሳሌ ግንቦት ሰባት ወይንም መድረክ፤ ኢዴፓ ወይንም ኢህአፓ የኢህአዴግን ጉድ አጋለጡ ማለት እነዚህን ድርጅቶች በርግጠኝነት ከኢህአዴግ የተለዩ ያደርጋቸው ይሆናል እንጂ ያለቅድመ ሁኔታ የተሻሉ አያደርጋቸውም። ኢሳትም ለኛ ግሩም ሆነ ማለት፤ በርግጠኝነት ከኢቲቪ ይለየዋል እንጂ፤ ያለአንዳች ቅድመሁኔታ ከኢቲቪ የተሻለ ያደርገዋል ማለት አይደለም። (ይሄ፤ ለምሳሌ ያህል ነው እንጂ፤ ኢሳትንና ኢቲቪን አላወዳድራቸውም፤ ስለዚህ አንዳንዶቻችን ይቺን ሀረግ መዘን ወደ መደምደሚያ እንዳንከንፍ ወይም በኢሳት ላይ የተነሳሁ አይነት አድርገን እንዳንተረጉመው)። በአጠቃላይ፤ ከጠላቶቻችን የተሻልን ክፉዎች ልንሆን እንችላለን፤ ነገር ግን ተራችንን የምንጠብቅ መጥፎዎችም ልንሆን እንችላለን ነው ሁለተኛው ነጥቤ። እንጂ፤ የኢህአዴግን ክፋት ስላጋለጥንና ስለተቃወምን ብቻ የተሻልን ነን ማለት አይደለም። ባለፈው ሰሞን እንደቀልድ በወረወርኩት ጽሁፍ የመጣው ጣጣ ያንን ያሳያል። እኛም ከጠላቶቻችን የተሻልን ላንሆን እንደምንችል ይጠቁማል።
እንደማስታወሻ፡ ካለፈው የቀጠለ
5. ለማስታወስ ያህል፤ ያለፈው ጽሁፌ ሁለት ሀሳቦች ብቻ ናቸው ያሉት። አንደኛ፤ በህዝብ ዘንድ እየተወደደ እየታወቀ ተደማጭነት እያገኘ የመጣው ኢሳት የሚያደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ፤ በህዝብ ዘንድ አሉታዊም አዎንታዊም ውጤት ስለሚያመጣ፤ ጥንቃቄ ያድርግ የሚል ነው። ለምሳሌ፤ ከስድስት ከተሞች ውስጥ በአምስቱ ላይ የአንድ ሀይማኖት ብቻ ተወካዮችን መጋበዝ ብልህነት የጎደለው አካሄድ ነው የሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ፤ ከኢሳት ጊዜያዊ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅትም ባሻገር፤ ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን የምንመለከትበት ቋሚ መንገድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል የሚል ነው። ከዚያ ባሻገር ግን የመንግስትና ሀይማኖትን መለያየት በተመለከተ የቅንጦት የሚመስል ነገር ግን አስፈላጊ የሆነ ውይይት ለመጫር ነው ጽሁፉ ሙከራ ያደረገው።
6. የተሰጡትን ምላሾች ሁሉ ለማንበብ ግዜ አላገኘሁም፤ የተወሰኑትን ግን አለፍ አለፍ ብዬ ተመልክቻቸዋለሁ። አብዛኞቹ ስድቦች ናቸው። ብዙዎቹ አስተያየቶች ደግሞ አስፈግገውኛል። ከጨዋዎቹ ተቺዎቼ ውስጥ አባዛኞቹ ያተኮሩት “ይሄንን አደባባይ ይዘህ ባትወጣ ይሻል ነበር” የሚል ሲሆን፤ በጣም ጥቂት ጨዋዎች ደግሞ “እንዴት ኢሳትን ትነካለህ? ትደፍራለህስ?” የሚሉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ። እንደትልቅ ድፍረት፤ ራስን ከገደል ጫፍ እንደመወርወር፤ ራስን እንደማጥፋትም የቆጠሩትም አሉ። አንዳንዶች ደግሞ ግጭት የተፈጠረ፤ “የከዳሁ” ሁሉ የመሰላቸው አሉ።
7. ካለፈው የፖለቲካ ልምዳችን እንደምናውቀው፤ ሰው ካልተቀየመ ወይንም ካላኮረፈ ወይንም ካልከዳ ራሱንና የራሴ የሚለውን ስለማይተች፤ የበሰሉ፤ የተማሩ፤ በዚህ በምእራቡ ዓለም ለረጅም ግዜ ኖረው የሀሳብን በነጻነትና ያለፍርሀት መግለጽ ፋይዳ ተረድተዋል የተባሉት ሁሉ ያልጠበቅኩትን ተግሳጽ ሰንዝረዋል። በእውነቱ አንድን ጽሁፍ ብቻ መሰረት አድርገን፤ እዚህ ሁሉ ስጋትና ተግሳጽ ውስጥ መግባታችን የሚያሳየው፤ “ጸረ-ኢህአዴጉም ጎራ (የኛ ጎራ ማለት ነው)፤ መንግስት በሚማቅቅበት፤ “ከመንጋው የተለየ ሀሳብን የማስተናገድ ባህል እጦት እንደሚሰቃይ ነው።” ይሄ አደገኛ ነው። እነሆ ቃና ቀይሬ እንደ ንጉስ ላስረዳ ነው።
የትችት ትችት ትችት
8. ባለፈው ሰሞን ወዳጃችን ልጅ ተከሌ ማለፊያ ግሩም ጽሁፍ አንደጻፈ ሰማን። ጽሁፉም ተነበበልን። አሰላሰልነውም። አንዳንድ ሰዎች ለጽሁፉና ለጸሀፊው የሰጡት ምላሽ አላስደሰተንም። ቢሆንም አልገረመንም። ያንዳንዶቹ የተጻፈም ያልተጻፈም ምላሽ ግን አሳስቦናል። የልጅ ተክሌን ሀሳብ ከመተቸትና ከመበለት ይልቅ፤ ልጅ ተክሌን ወደመንቀፍና ወደማጠየፍ አዘንብለዋል። የጽሁፉን ፍሬ ነገር ሳይሆን የጸሀፊው ቁመትና ውፍረት ወርድና ክብደት ላይ የሚወያይ መብዛቱ አጅግ አሳስቦናል። ሀሳቡን ተችተው አስተያየት ለመስጠት የፈቀዱትም ቢሆኑ፤ ያተኮሩት፤ “የራስ ተቋም በአደባባይ አይተችም፤ ለጠላት ደስ ይለዋል፤ ንፋስም ይገባልና” የሚል አይነት ስሜት ይጎላበታል። አንዳንዶች ከቶም የጸሀፊውን ነገር የተገነዘቡ አይመስልም።
9. ቀድሞ ነገር፤ ልጅ ተክሌ የአገራችንንና የህዝባችንን ጥቅም የሚነካ ጽፉህ ይጽፋል፤ አገራችንን የሚጎዳ መንገድ ይሄዳል ብለን አንሰጋም። ይሄ እምነታችን ጥንትም ነበረ፤ አሁንም አለ። በርግጥ ልጅ ተክሌ ብዙም ባልተለመደ መልኩ አፈሙዙን፤ ወደወገን/ወደራሱ ማዞሩ ለብዙዎች ግርታን ቢፈጥር አይደንቀንም። ይሁን እንጂ፤ አንደኛ ልጅ ተክሌ ይሄን ሲያደርጉ የመጀመሪያው አይደለም። ሁለተኛ፤ የኛ የሆነውንና በኛ ምድር ላይ የተተከለውን ልጅ ተክሌ ከሀሳቡ አልፈን እሱን መጠራጠራችን በጎ ሆኖ አላገኘነውም። ስህተትም ነው። ይሄ ጽኑ የተለየ ሀሳብን የመፍራት ደዌም ነው። እስከመቼ የተለየ ሀሳብን እንሸሻለን? እስከመቼስ በራሳችን ድጋፍና ሰልፍ ጫጫታ ተውጠን እንኖራለን የሚል ጥያቄም ፈጥሮብናል? አንዳንዴ ወጣ ብሎ ማየት ያሻል።
የሀሳብ ነውር የለውም፡ የድርጊት እንጂ
10. የተለየ ሀሳብን መፍራት የለብንም። መጋፈጥ እንጂ። ሰው ነፍስ ካወቀ፤ የሀሳብ ነውር የለውም። የሀሳብ ጸያፍም የለውም። የሀሳብ ወንጀልም የለውም። ስለማይናገረው እንጂ ማንስ በጭንቅላቱ የሚያስበውን፤ በልቡም የሚመኘውን እንደምን እናውቀዋለን? ማንም ሰው፤ እንወያይበት፤ እናስበበት፤ እናድግበትም ዘንድ፤ ስህተትም ከሆነ እንዲታረምና እንዳይደገምም ብሎ ባደባባይ በስሙ በጻፈው ጽሁፍ ሲሆን ሲሆን ሊሸለም እንጂ ሊጎሸም አይገባውም። በርግጥ ልጅ ተክሌ ሲጎሸምና ሲዘለዘል የኖረ ወዳጃችን ስለሆነ፤ በአመታት ትችትና ነቀፋ የደነደነው ቆዳው በዚህ ይሰነጠቃል ብለን ከቶም አንሰጋም። የሰዎቻችን ከተለመደው የተለየ ሀሳብን ለማስተናገድ የመፍራትና የመቅፈፍ ነገር ግን ረብሾናል።
11. ደግሞስ በዚህ በምእራብ የነጻነት አጥቢያ የምንኖር ሰዎች ስለምን ትችትን እንፈራለን። ስንት ነገርስ እንፍራ? ስንት ነገርስ ያሸብረን? ኤደን ባህረሰላጤንና ሳህል በረሀን፤ አባይንና ጎጀብን ተሻግረን ተሰደን፤ በንጽጽርም ቢሆን የተሻለ ነጻነት ካለበት ዓለም መጥተንም፤ የተለየ ሀሳብን የመፍራት ሰቀቀን ይከተለን? እንግዲያውስ እላችሁዋለሁ፤ ነጻነታችንና ዴሞክራሲያችን በአለት ላይ እንጂ በአሸዋ ላይ መገንባት እንደሌለበት ህዝባችን ሊያውቀው ይገባዋል። “ይሄን ሀሳብ አንሸራሽር፤ ይሄንን ሀሳብ ግን ከቶም አታንሳው” የሚል ማእቀብና ምክር፤ በአገራችን እንዲሰፍን የምንመኘው ዴሞክራሲና ነጻነት ጸር ነው። ይሄ እስክንድር የታሰረለት፤ ርእዮትም የታጎረችበት፤ ሲሳይም የተሰደደበት ራእይ አይደለም። ደግሞስ፤ ይሄንን የሚፈቅደውስ ማነው? ህሊናችን አይደለምን? ከህሊናችን በላይ የተሻለ ከልካይስ፤ ፈቃጅስ ከወዴት ይገኛል?
12. ለዚህ ነው እኛ ሰው ህሊና ይስጥህ ሲባል እንጂ ልቡና ይስጥህ ሲባል የማይረዳኝ። ህሊና ያለው ሰው ደግሞ ህሊናው የፈቀደውን እንዲናገር፤ ህሊናውን የደረሰበትን ግኝት እንዲመሰክር ልናበረታታው ይገባል እንጂ፤ ልናከላክለው አይገባም። ካልሆነም ደግሞ የጸሀፊውን ሰብእናውን ሳይሆን ሀሳቡን ልንመትረው፤ እይታውን ልንተቸው፤ አመለካከቱን ልንተረክከው እንችላለን። እንጂ የጸሀፊውን ሰብእና ለማጥቃትና ጸሀፊውን ትልቅ ሀጢያት እንደፈጸመ በማነጣጠር የምንናገረውም የምንጽፈውም እኛ የታገልንለትንና ለህዝባችን ልናወርሰው የምንምለውንና የኛን ህልም የሚያንጸባርቅ አይደለም።
የማይጠየቅ ተቋም፤ የማይተች እውቅና
13. ወዳጃችን ልጅ ተክሌ ከዚህ ቀደምም ብዙዎቻችን የምንሸሻቸውን ሀሳቦች ለመናገር የሚጀግን፤ ብዞዎቻችን የምናፍራቸውን ሀሳቦች ለመጻፍ የሚተጋ የስደት ወዳጃችን ነው። ባለፈው ጽሁፍ ያነሳውም ሀሳብ፤ ምንም የሚጣል የለበትም ብለን ባንመሰክርም፤ በራሱ የሚተማመንንና በአለት ላይ የተገነባ ዴሞክራሲን ለመገንባት የሚተጋን ቡድን የሚያስደነግጥ ነገር አላገኘንበትም። ያለበለዚያማ በሚጻፈውና በሚወራው ጠላታችን መደንገጡ፤ የሚናገሩና የሚጽፉትንም ወደእስር ማጋዙ ስህተት አይደለም ማለት ነው። እኛ መንግስትነትን አጥተን በተለዩ ሀሳቦች መንሸራሸር ይሄን ያህል ከበረገግን፤ የመንግስትነትን ስልጣን የያዘው አካል በተቺ ሀሳቦች መንሸራሸር ቢጨነቅና መንገደኛውን ሁሉ ቢያስር ምን ያስደንቃል?
14. በርግጥ፤ ወዳጃችን ልጅ ተክሌ በሰዎች ዘንድ ታምኖ የተነገረውን ምስጢር ያባከነ፤ ወይንም እሱ ለድርጅቶች ባለው ቀረቤታ ያገኘውን መረጃ የተጠቀመ ባሪያችን ቢሆን እኛም ይከፋን ነበር። አንለቀውምም። ለጥፋቱ እንቀጣው ነበር። ይሁን እንጂ ልጅ ተክሌ የተጠቀመው መረጃ ሁሉ አደባባይ በህዝብ ዘንድ በግልጽ ያለ እንጂ፤ የተተቸው ተቋም ጋር በሚሰራበት ግዜ ያገኘው መረጃ አይደለም። ደግሞስ የማይተች እውቅና፤ የማይጠየቅ ተቋም ለመመስረት ነው እንዴ የምንታገለው? እንግዲያውስ ያለፉትን አስር አመታት ብቻ ብንገመግም፤ ትልቁ የጎዳንና እንዳናንሰራራ ቀስፎ የያዘን ጥፋት የምንክባቸውን ለመተቸት፤ የምንቆልላቸውን ለመጠየቅ አለመድፈራችን፤ “ዝም በሉ፡ ጠላት እንዳይሰማ፡ በቃ ይሁንላቸው ይደረግላቸው” የሚለው የተለማማጭነትና የሰቀቀን ባህርይ ነው።
አደባባይ ወይስ ወደጓዳ?
15. በልጅ ተክሌ ላይ ከተሰነዘሩት ትችቶች መካከል፤ “ትችቱ ለምን በአደባባይ ሆነ? ውስጥ ለውስጥ አይሻልም ነበር ወይ” የሚሉት ጥያቄ-ተኮር ትችቶች መልካም እንደሆኑ ይሰማናል። የኛም ሀሳብ ይኸው ነው። ይሁን እንጂ፤ ያ አንድ መንገድ ነው። ብቸኛው መንገድ አይደለም። ልጅ ተክሌም የተከተለውን መንገድ ለመከተሉ ጥሩ ምክንያት ይኖረዋል። ልጅ ተክሌ እንዲህ ያለውን ትችት ይዞ ወደአምባ ሲወጣ፤ ግራ ቀኙን አላየም፤ በቅጡም አላሰላም ለማለት አንደፍርም። መጠየቅ ያለብንን በአደባባይ ባለመጠየቃችን፤ መናገር ያለብን በአደባባይ በግዜ ባለመናገራችን ምክንያት እነሆ ቅንጅት እንደብጉንጅ ውስጥ ውስጡን አብጦ፤ በመጨረሻ አይፈርጡ አፈራረጥ ፈረጠ። ከቅንጅት ቁስል እስካሁንም አላገገምንም። እንደልደቱ አያሌው ያሉ እስካሁንም ያልተካናቸውን ትንታግ ፖለቲከኞች አጣን። (በዚህ ሀሳብ ብቻ የምንበሳጭ እንኖራለን፤ ይሁን እንጂ ልጅ ተክሌ “ልደቱ ናፈቀኝ” የሚል ጽሁፍ እየጻፈ እንደሆነ ጠቁሞናልና ከዚህ ለሰላውም ትችት እንዘጋጅ)።
16. በመሰረቱ በአደባባይ የሚነሱና ውስጥ ለውስጥ የሚነገሩ ሀሳቦች ውጤታቸው አንድ አይደለም። በአደባባይ የሚነገር ነገር ትኩረት ይሰጠዋል። ሰዎች ይወያዩበታል። ተወቃሾችና ተከሳሾች ካሉም ለወደፊቱ ያርሙታል። ተጠያቂ አካልም ወደፊት እጋለጣለሁ ሲል አግባብ ካልሆነ ስራ ይታቀባል። ውስጥ ለውስጥ የሚደረጉ አስተያየቶችና እርማቶች ከስራ ላይ ይልቅ ወደ ቆሻሻ ቅርጫት እንደሚዶሉ የልጅ ተክሌ ምስክርነት አያሻንም። እንጂ፤ የጋዜጠኞቹ ትጋትና ፍጋት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በየአካባቢው የሚገኙ የኢሳት ደጋፊዎች አስተዳደራዊ ምሬትና ስሞታ ቢጻፍ፤ “ይሄ ድርጅት እስካሁንስ እንደምን ቆመ?” ያሰኛል። “ወደፊትስ ይቆማልን?” የሚለውም ጥያቄ የሰይጣን ጆሮ አይስማው በማለት ብቻ የሚጠፋ አይደለም። እንደ ኢሳት ያለ ህዝባዊና ተስፋ የተጣለበት ተቋም እንዲያድግ የአደባባይ ውይይት፤ የግንባር ትችት፤ የፊት ለፊት እርማት ያስፈልገዋል። የምንፈልገው ተቋም በአደይና በጸደይ (የሰዎች ስም ናቸው) ላይ የቆመ ሳይሆን በአለት ላይ የተተከለ መሆን ነው ያለበት። እስካሁንም ሰዎች መካብ እንጂ ድርጅቶች/ተቋማት መገንባት አልቻልንምና።
በአደባባይ የሚሰራ በአደባባይ ይጠየቃል
17. ደግሞስ ኢሳት በአደባባይ የሚሰራ የአደባባይ መገናኛ ብዙሀን እንጂ የህቡእ ጋዜጣ አይደለም። ሰለዚህ ኢሳት ለሚሰራው የአደባባይ ስራ በአደባባይ መጠየቅ አለበት። ለምሳሌ ባለፈው ሳምንት “የእንወያይ፡” ዝግጅታቸው ላይ ወዳጃችን ፋሲል የኔዓለምና አፈቀወርቅ አግደው ያንጸባረቁትን ሀሳብ በአደባባይ እንጂ በውስጥ ተቹ ማለት ስህተት ነው። ምክንያቱም እነሱ ስህተት ቢሆንም ባይሆንም ሀሳባቸውን በአደባባይ የማንጸባረቅ እድል ሲያገኙ፤ የነሱን ሀሳብ የሚቃወመው ሰው ግን በውስጣዊ አስተያየት ብቻ መወሰኑ፤ የነፋሲልን ሀሳብ የሰሙት ሰዎች፤ የተለየውን ሀሳብ እንዳያዳምጡ እድል መንፈግ ነው። ይሄ ኢሳት የቆመለት ኢሳት የቆመበትም መሰረት አይደለም።
18. የሰማያዊ ፓርቲ በመጪው የአፍሪካ አንድነት/ህብረት 50ኛ አመት ምስረታ በዓል ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል። ከአገራችን ያላግባብ የተነቀልን ተቃዋሚዎች ነን የምንል ሰዎችም ድርጅቶችም፤ እንዲህ ያለውን ሰልፍ፤ ጠሪዎቹ ለምንም ዓላማ ይጥሩት “በርቱ ግፉበት፤ ብቻ እንዲህ ብታደርጉት መልካም ነው፤ ይሄንንም ብታክሉበት ሸጋ ነው” ማለት ነው ያለብን። እንጂ ዓላማቸውን ሙሉ በሙሉ ማራከስ፤ አግባብ አይደለም። ልጅ ፋሲል ግን የሰዎቹ የሰልፍ ጥሪ ሀቀኛ መሆኑን እንደሚጠራጠርና እንዲያውም ትኩረት ለማግኘት ያደረጉት አይነት ጥሪ እንደሆነ ነው የተናገረው። ያ ብቻም አይደለም፤ ይሄ አይነቱ ሰልፍ ቢደረግም እንኳን፤ ስርአቱን በምእራባዊያን ዘንድ ሰልፍና ተቃውሞ ፈቃጅ ሊያስመስለወም ይችላል የሚል ፍራቻ አንጸባርቋል። በርግጥ ልጅ ፋሲል ሀሳቡን የሰጠው በግሉ እንደሆነ ቢናገርም፤ እሱ የኢሳት ዋና ማኔጂንግ ኤዲተር እንደመሆኑ መጠን አንድን ነገር ተናግሮ በግሌ ነው የተናገርኩት በማለት ብቻ ሊያመልጥ፤ ኢሳትንም ነጻ ሊያደርገው አይችልም።
19. በሀላፊነት ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ ይሄንን በግሌ ነው ያልኩት የድርጅቱ አቋም አይደለም የሚል ብልሀት ይጠቀማሉ። ልጅ ፋሲል በአስተያየቱ ላይ ከዚህ ቀደም ኢሳት የሰራቸውን ተመሳሳይ የሰልፍ ጥሪ ዘገባዎች እንደምሳሌ አቅርቧል። ከተቀመጠበት የሀላፊነት ወንበር አንጻርም የሚሰነዝረው እያንዳንዱ ሀሳብ የኢሳት ሊመስል፤ ሊሆንም እንደሚችል መረዳት አለበት። እንዲህ ያለውን በአደባባይ የተነገረ ሀሳብ መተቸት ያለብን፤ ኢሳት አንዳንዴ ፈንገጥ ያለ ሀሳብ አይመቸውም እንጂ ሲሆን ሲሆን በራሱ በኢሳት ላይ፤ ያለበለዚያ ግን በተገኘው መድረክ ነው። የለም እንቶኔን አትንኩ የሚለው አስተያየት፤ ለራሱ ለእንቶኔም አይበጅም።
ለነገሩ የኛ ችግር፡
20. ለነገሩ በስደት የምንገኝ ድርጅቶችና ተቃዋሚ ግለሰቦች፤ በአገር ቤት የኛን ስደትና ሚና የሚቀንስ፤ የኛን መኖር ምክንያት የሚያሳጣ እንቅስቃሴ የሚጀምር ሲመስለን፤ ያንን እንቅስቃሴ ለማጣጣልና ለማራከስ እንፈጥናለን። ይሄ እኛም በስደት ወደኬንያ ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ፤ ላለፉት 12 አመታት በኢህአፓም በመኢሶንም፤ በቅርቡ ደግሞ በነግንቦት ሰባትም በነከበደም በነገመቹም ላይ ያስተዋልነው በሽታ ነው። ልክ የዛሬ አስራሁለት አመት ተሰደን ወደናይሮቢ ስንገባ የተቀበሉን ደግ ድርጅቶች ከነገሩንና እስካሁንም ከትውስታችን ካልወጣው ነጥብ አንዱና ዋንኛው “አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች መኖር፤ በምእራባዊያን ዘንድ፤ አገር ቤት ዴሞክራሲ ያለ ያስመስላል” የሚል ነጥብ ነው። እነሆ ታሪክ ራሱን እንዳይደግምና፤ እኛ ከአመታት በፊት እንከሰሰስበት የነበርነውን፤ ማለትም የአገርቤቱ እንዲህ ነው የሚለውን ክስ፤ እኛም በተራችን እንዳንደግም መጠንቀቅ አለብን። ከፖለቲካ ወንጀሎች ሁሉ የከፋው ሌሎችን የከሰስንበትን ጥፋት ወይም በሌሎች በስህተት የተከሰስንበትን ጥፋት እኛ ስንፈጽም ነው።
21. ይቀጥላል።
እኛው ነን፤ ግንቦት ልደታ፤ 2005፤ ተረንቶ፤ ከናዳ
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Monday, May 20th, 2013
ከያሬድ አይቼህ ፤ ሜይ 20፥2013
የፓልቷኩ አባ-መላ ሰሞኑን ገኗል። መግነኑ አልከፋኝም … ይግነን … ለሁሉም ጊዜ አለውና። ግን አባ-መላን ብዙ ጊዜ አዳምጨዋለሁና የአባ-መላን ነገር መዳሰስ ፈለኩ። ሰሞኑን አባ-መላ ገዢውን ፓርቲ መተቸት ጀምሯል። ይህንን የሰሙ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በጣም ፈንጥዘዋል ፡ እኔ አልፈነጠዝኩም። ለምን?
አባ-መላ የሚናገረውን ነገር በየሳምንቱ ፡ አንዳንዴ አልፎ አልፎም ቢሆን ፡ አዳምጨዋለሁ። አባ-መላ የሚያረገውን የሚያረግው ለአንድ አበይት ምክንያት ብቻ ነው፦ የግል ጥቅም። አባ-መላ ሌላ ንዑስ ምክንያት የለውም። የሚያደርገው ፡ የሚናገረው ፡ የሚተነፍሰው ፡ የሚስቀው ፡ የሚያለቅሰው … ወዘተ … ለግል ጥቅሙ ነው (ለግል ጥቅሙ መቆሙ መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም ፡ ያ ምርጫው ነው)።
በ2008 እ.አ.አ. አባ-መላ ክፍል ውስጥ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው (“addis_ababa_1”? በሚል መጠሪያ ስም ሚሳተፍ) ክፍሉ ውስጥ በተነሳ ቅራኔ ምክንያት የክፍሉን ሚስጥር በተቃዋሚ ክፍሎች ውስጥ ገብቶ ሲናገር ሰምቻለው። ከተናገረው ሚስጥር አንዱ ፡ ቃል በቃል ባላስታውስም ፡ አባ-መላ ከሚድሯክ ወይም ከሼህ መሃመድ አልሙዲ በአመት $50,000 ዶላር እንደሚከፈለው ነው። ይሄ ነገር የአባ-መላን ባህሪ እና የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ትኩሳት ለመረዳት ወሳኝ መረጃ ሆኖ አገኝቼዋለሁ።
አባ-መላ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከሚድሯክ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። የሚድሯክ ጥቅም ሲከበር ፡ አባ-መላ ለኢህአዴግ እስክስታ ይወርዳል። የድርጅቱ ጥቅም ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስል ፡ አባ-መላ ደረቱን ይመታል።
አባ-መላ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆኖ አያቅም። አባ-መላ የሚድሯክን ገጽታ የሚያሽሞነሙን ፡ የደርግ ስርዓት ያፈራው ፡ አንደበተ ምላጭ ፡ የሚያደርገውን የሚያቅ ፡ ፕሮፓጋንዲስት ነው።
ታዲያ ምነው ሰሞኑን የፓልቷክ ተቃዋሚ ክፍሎች ባዶ ሆነው የሲቪሊቲ ክፍል ሞልቶ የፈሰሰው? ተቃዋሚ ባካችሁን በአባ-መላ አትበሉ። አባ-መላ ሚያደረገው ሁሉ ለአገራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙና ለሚያገለግለው ድርጅት ጥቅም ብቻ ብሎ መሆኑን እንገንዘብ።
ሚድሯክ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የከፈተና ፡ አያሌ ካፒታል ያፈሰሰ ድርጅት በመሆኑ ድርጅታዊ ገጽታውንና ጥቅሙን መንከባከቡ ተገቢና የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሚድሯክ እና በኢህአዴግ መካከል ሆነን ልንፈጭ ነውና ፡ በአባ-መላ የፓለቲካ ስልት እንዳንበላ ጠንቀቅ እንበል።
አባ-መላንም ሆነ ሌሎች ገዢው ፓርቲን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ሰዎችን ተስገብግበን ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጨመር የለብንም። በጊዜ ውስጥ ሊፈተኑ ፡ አመኔታችንን ቀስበቀስ ሊያገኙ ይገባል እንጂ ተንሰፍስፈን መርዝ ይሁን መድሃኒት እንደያዙ ሳናቅ አንቀበላቸው።
ወቅቱ የህወሃት/ኢህአዴግ መጨረሻ ወቅት ነውና የሚደናበሩትን የገዢውን ፓርቲ በላተኞች ለጥቅማችን እንጠቀምባቸው እንጂ እነሱ አይጠቀሙበን።
_ _ _ _ _ _
ጸሃፊውን ለማበረታታት ፡ ለመውቀስና ለማስፈራራት በዚህ ይጻፉ፦ yared_to_the_point@yahoo.com
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Monday, May 20th, 2013

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ግንቦት 11 ቀን 2005 ፕሮግራም
<<አቶ መለስ አንገታቸውን የደፉበት ቀን ቢያንስ ድምጻችንን ያሰማንበት ቀን ነው።ብዙ ሰዎች በየዓመቱ ሊከበር ይገባል ይላሉ።በስርዓቱ ውስጥ የሚታየው የስልጣን ሽኩቻ ተጠናክሮ ይቀጥላል።አውራው አምባገነን ከሞቱ በሁዋላ አንዱ ገኖ ለመውጣት የሚያደርገው ነው።ሁሉም ቦታው ለኔ ይገባል በሚል ግብ ግባቸው አንዱ አንዱን መክሰሱ አንደኛው ወገን በአሸናፊነት እስኪወጣ ቀጣይ ነው። ወደፊትም አንዱ አንዱን ሲያስር አንዱ ሌላውን ሲከስ እናያለን ።ስርዓቱ ደካማ ነው።የምናየውም የጥንካሬ ምልክት አይደለም...>> ጋዜጠኛ አበበ ገላው አቶ መለስን አንገት ያስደፋበትን የተቃውሞ ድምጹ አንደኛ ዓመትን አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ
<< አማራን ለማጥፋት የተጀመረው አሁን በጉራ ፈርዳና በቤንሻንጉል ብቻ አይደለም ።በ1993 ዓመተ ምህረት 15 ሺህ አማራዎች ከወለጋ ተፈናቅለዋል። አማራ ራሱን መከላከል አለበት እሾህን በእሾህ እሳትን በእሳት ነው...>>
አቶ ተክሌ የሻው የሞረሽ ወገኔ ሊቀ መንበር ለህብር ከሰጡት የመጀመሪያ ክፍል ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ)
የድምጻችን ይሰማ ጉባዔ በአትላንታ (ቆይታ ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር)
ሌሎች ቃለ መጠይቆችም አሉን
ዜናዎቻችን
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የቡና ላኪዎች ሰንጠረዥ የነበራት ደረጃን ተነጠቀች
በቬጋስ ለአባይ ቦንድ ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው የታሰበውን ያህል ባለመሰብሰቡ በስርዓቱ ሰዎች ላይ ቅሬታ ፈጠረ
የሎስ አንጀለሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቆንስላ ተወካይ ሙስናን መቆጣጠር አልቻልንም ማለታቸው ተሰማ
በቬጋስ ኢትዮጵያዊውን የታክሲ አሽከርካሪ ተኩሳ የገደለችው የቀድሞ የአሜሪካ ወታደር ተፈረደባት
በሙስና ክስ የተያዙት ባለስልጣንያለመከሰስ መበቴ ተጥሷል ሲሉ ተናገሩ
የወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተመንግስት አልወጣም ማለትን ዜና የዘገበው ጋዜጠኛ መረጃውን እንዲገልጽ ተጠየቀ
በኢትዮ ኬኔያ ድንበር ላይ ውጥረቱ አይሏል ታጣቂዎች 3ሰዎችን ገደሉ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Monday, May 20th, 2013

የቅዱስ ጊየርጊስ ክለብ ደጋፊ የሆኑ ሙሽሮችም በሥፍራው ተገኝተው ድጋፍ መስጠታቸው የዕለቱን ጨዋታ አይረሴና ደማቅ አድርጎታል፣
ከይርጋ አበበ
ትናንት በአሥር ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽንስ ዋንጫ ጨዋታ የኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የግብጹን ኢ.ኤን. ፒ.ፒ. አይ ( Enginering and Petrolium Processing Industry) ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሉን አመቻቸ።
ከሁለት ሳምንት በፊት በግብጹ ኃያል ክለብ ዛማሌክ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባገባ በሚል ሕግ ከአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር የተሰናበተው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሌላኛው የአህጉራዊ ውድድር የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሌላውን የግብጹን ክለብ በሜዳውና በደጋፊዎቹ ፊት ሁለት ለባዶ በማሸነፍ በዛማሌክ የደረሰበትን የውጤት ማጣት ፀፀት መመለስ ችሏል።
ጨዋታው በተጀመረ በአምስተኛው ደቂቃ ሽመልስ በቀለ ከያሬድ ዝናቡ የተሻገረችለትን ኳስ ከኢ.ኤን.ፒ. ፒ.አይ ተከላካዮች ሾልኮ በመግባት የጊዮርጊሶችን የመጀመሪያ ግብ አስቆጠረ። ሽመልስ ያስቆጠራት ግብ ባለፉት አራት ተከታታይ የክለቡ ጨዋታዎች ሦስተኛ ግቡ ሆና ተመዝግባለታለች። ትንሹ ልጅ ግብ ከማስቆጠሩም በላይ በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ ነበር ያመሸው።
ከዚች ግብ መቆጠር በኋላ ይበልጥ ተጭነው የተጫወቱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በተጋጣሚዎቻቸው የግብ ክልል በተደጋጋሚ ሲመላለሱ ቢታዩም በ26ኛው ደቂቃ ተከላካዩ አበባው ቡጣቆ ሁለተኛዋን ግብ እስካስቆጠረበት ደቂቃ ድረስ ኳስና መረብ ማገናኘት አልቻሉም ነበር። ወጣቱ አጥቂ ዮናታን ብርሃኔ ከማዕዘን ያሻገረለትን ኳስ ከአስራ ስምንት ክልል ውጪ ወደ ግቡ መስመር አክርሮ በመምታት አበባው ቡጣቆ ሁለተኛዋንና የጨዋታውን የመጨረሻ ግብ ማስቆጠር ቻለ።
ሁለት ወጣት የክለቡ ደጋፊዎች በዕለቱ በስታዲየም የጋብቻ ሥነ-ሥርዓታቸውን በመፈፀም ለክለቡ ያላቸውን ፍቅር በገለጹበት ጨዋታ፣ ፈረሰኞቹ ብዙ ግብ መሆን የሚችሉ ኳሶችን ሲያመክኑ አምሽተዋል። በተለይ ሁለተኛዋ ግብ ከተቆጠረች ሦስት ደቂቃ በኋላ አማካዩ ዊሊያምስ አክርሮ የመታትና የኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አዩ ግብ ጠባቂ የመለሰበት ኳስ ተመልካቾችን ያስቆጨች ነበረች፡፡
ከዕረፍት በኋላ ተዳክመው ያመሹት ኢትዮጵያውያኑ በግብጻውያን አቻዎቻቸው የጨዋታ ብልጫ የተወሠደባቸው ሲሆን እንግዳው ቡድንም ሁለት ያለቀላቸው የግብ ዕድሎችን ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል።
ከሰባት ዓመት በፊት ሁለቱ ክለቦች በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተገናኝተው ካይሮ ላይ ዜሮ ለዜሮ ሲለያዩ በአዲስ አበባ ቢኒያም አሰፋ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋ ይታወሳል።
የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ የመልስ ጨዋታ ከሁለት ሳምንት በኋላ በግብጿ ዋና ከተማ ካይሮ ላይ ይደረጋል።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Sunday, May 19th, 2013

ከይርጋ አበበ
የአውሮፓ ሊጎች የውስጥ ውድድሮች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከሚጠበቁት ታላቅ የእግር ኳስ ዜናዎች መካከል ክለቦች የሚያደርጉት የተጫዋቾች ዝውውር አንዱ ነው። ውጤት ፊቱን ያዞረባቸው ታሪካቸውን ለመቀየር ውጤት እና እድል አብራቸው የከረመች ደግሞ ክብራቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ክለባችንን እና ኪሳችንን ይመጥናሉ ያሏቸውን ተጫዋቾች ወደ ክለባቸው ለማዘዋወር ይንቀሳቀሳሉ። ለዛሬ ርዕሰ ጉዳያችን ምንጭ የሆኑን የእንግሊዞቹ ዘሰን፣ ዘኢንዲፔንደንት፣ ቢቢሲ እና የስፔኑ አስ ጋዜጦች የዝውውር መስኮቱን ሊያደምቁ ይችላሉ ያሏቸውን ተጫዋቾች ያስነበቡ ሲሆን እኛም ለአንባቢያን በሚመች መልኩ አዘጋጅተንላችኋል።
1. ዋይኒ ማርክ ሩኒ
እንግሊዛዊው አጥቂ በክለቡ እያሳለፈ ያለውን ሁኔታ ያልወደደው ሲሆን ከቀድሞው አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ጋር የፈጠረው አለመግባባት ወደ ውጪ እንዲመለከት ያደርገዋል ተብሎ ይታሰባል። የዋዛን ሁኔታ በቅርብ ርቀት የሚከታተሉት የፈረንሳይ ሻምፒዮኖቹ ፓሪሴንት ጄርሜኖዎች እንግሊዛዊውን ወደ ክለባቸው ወስደው ከዝላታን ኢብራሞቪች ጋር ለማጣመር ፍላጎታቸውን መደበቅ ተስኗቸው ካሁኑ የማንቸስተርን በር ማንኳኳት ጀምረዋል። ሌሎቹ የልጁ ፈላጊ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ስፔናውያኑ ግዙፎቹ ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ ናቸው።
2.ኔይማር
ብራዚላዊው ወጣት ከባርሴሎና ጋር ቅድመ ስምምነት ላይ ደርሷል ቢባልም ሌላኛው የስፔን ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ የተጫዋቹ ፈላጊ መሆኑን በመግለፅ ወደ ጨረታው ገብቷል። እንደ ስፔኑ አስ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ የፍሎሬንቲኖ ፔሬዙ ክለብ ኔይማርን ከባላንጣቸው እጅ ላይ በመንጠቅ ለብራዚሉ ክለብ ለዝውውር የሰባ ሚሊዮን ፓውንድ ቼክ ይዘው መፈተን ጀምረዋል። ኔይማር የማድሪድን ጥያቄ ተቀብሎ ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው የሚሄድ ከሆነ ከሀገሩ ልጆች ካካ እና ማርሴሎ ደማቅ አቀባበል እንደሚጠብቀው ተጫዋቾቹ በመናገር ላይ ናቸው። የብራዚላዊው ለማድሪድ መፈረም ማድሪድ በመሐል ሜዳ ላይ የኳስ ፈጣሪ ተጫዋች እጥረቱን ይቀርፍለታል ተብሎ ይታሰባል።
3.ጃክ ዌልሸር

ይህ የሚሆን ይመስላችኋል?
የአርሰናሉ ታዳጊ ከለንደኑ ክለብ ይለቃል ተብሎ ባይታሰብም አዲሱ የባየር ሙኒክ አሰልጣኝ ጆሴፕ ጋርዲዮላ ተደጋጋሚ ጥያቄዎቹን ይዞ ወደ እንግሊዙ ክለብ መመላለሱ የጃክ ቀጣይ ክለብ ባየር ሙኒክ ሊሆን ይችላል ሲል ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል። አርሰን ቬንገር የቀጣዩ የውድድር ዓመት የክለባቸው አምበል ያደርጉታል ተብሎ የሚጠበቀው እንግሊዛዊው ወጣት የእኔና የአርሴናል ጋብቻ በቀላሉ አይፈርስም ብሎ መናገሩ ምናልባት ለጋርዲዮላ ፈተና ሊሆንበት ይችላል። ጋርዲዮላ ተሳክቶለት ጃክን ወደ ክለቡ ካዘዋወረ ትልቅ ዝውውር ይሆንለታል።
4.ካሪም ቤንዜማ
አሌክስ ፈርጉሰንን ተክተው ወደ ኦልድትራፎርድ የተዘዋወሩት ስኮትላንዳዊው ዴቪድ ሞይስ በቀጣዩ የውድድር ዓመት በክለባቸው ሊመለከቱት የሚፈልጉት ተጫዋች ቢኖር በሳንቲያጎ ቤርናባው ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳነውን ካሪም ቤንዜማ ነው። ይህንን ፈረንሳያዊ ወደ ማንቸስተር አምጥተው የእግር ኳስ ህይወቱን ሊታደጉለት ይፈልጋሉ። ለስፔኑ ክለብ የ30ሚሊዮን ፓውንድ ቼክ ይዘው የቀረቡት ሞይስ ቤንዜማን ወደ ማንቸስተር ማዘዋወር ከቻሉ አስፈሪ የአጥቂ መስመር መገንባት እንደሚችሉ ዘኢንዲፔንደንት በዘገባው ጠቅሷል። ዘገባው የካሪም ዝውውር የዝውውር ገበያውን ያደምቃል ያስባለውም የልጁ ብቃት መሆኑን ጨምሮ አመልክቷል።
5.ማሩዋን ፌይላኒ
ፌይላኒን በኤቨርተን ጠንቅቀው የሚያቁት ዴቪድ ሞይስ ወደ ኦልድትራፎርድ አብሯቸው እንዲጓዝ ይፈልጋሉ። ላለፉት ጥቂት ዓመታት ማንቸስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን ሲገናኙ በቀያይ ሰይጣኖቹ ላይ የበላይነቱን ሲወስድ የነበረው ቤልጄማዊ ጉልበተኛ የቀድሞ አሰልጣኙን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ላንክሻዬር ዝውውር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የግሌዘር ቤተሰቦች ቤልጄማዊውን ሁለገብ ተጫዋች ወደ ክለባቸው ለማዘዋወር የ24 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ መፈፀም እንዳለባቸው የተነገራቸው ሲሆን፤ ዴቪድ ሞይስም ግድ የለም በእኔ ይሁንባችሁ ማሩዋንን ለማግኘት የፈለገውን መስዋዕትነት መክፈል አለብን ሲሉ ለአዲሶቹ ቀጣሪዎቻቸው ተናግረዋል ሲል ጋዜጣው ዘግቧል።
6.ሌይተን ቤይንስ
የቀድሞው የዊጋን አትሌቲክ የግራ መስመር ተከላካይ ላለፉት ሁለት ዓመታት የፈርጉሰንን ትኩረት መሳብ የቻለ ተጫዋች ነበር። በማጥቃት ላይ የተመሰረተ መከላከልን የሚመርጠው እንግሊዛዊ በአርሴናል፣ ቼልሲ፣ ባየር ሙኒክ እና ባርሴሎና ቢፈለግም የቀድሞ አሠልጣኙን ተከትሎ ቀዩን ማሊያ ይለብሳል የሚለው ግምት የበዛ ሆኗል። የ15 ሚሊዮን ፓውንድ የወጣለት ቢሆንም እድሜው እንደሚፈልገው እንዳይጫወት ያደረገውን ፓትሪስ ኢቭራን ለመተካት ብቸኛው ተጫዋች መሆኑን የተረዱት የማን ዩናይትድ ኃላፊዎች የገንዘቡን ነገር ተውት ብቻ ልጁን ስጡን በማለት የመርሲሳይዱን ክለብ መወትወት ጀምረዋል።
7. ክርስቲያን ኤሪክሰን
ቤልጂየማዊው የ21 ዓመት ወጣት አጥቂ በሊቨርፑል በጥብቅ ይፈለጋል። ወጣቱ ቤልጂየማዊ ግን የሀገሩ ልጆች በብዛት የሚገኙበትን ፕሪሚየር ሊግ ችላ ብሎ ወደ ቡንደስሊጋው መዘዋወርን መርጧል። ከውድድር ዓመቱ መጠናቀቅ በኋላ ፖላንዳዊውን ግብ አዳኝ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ የማጣት ስጋት የተጋረጠባቸው ቦሩሲያ ዶርትመንዶች የክርስቲያን ኤሪክሰን ማረፊያ ለመሆን ተቃርበዋል። ማሪዮ ጉትዝን ለባባሪያኑ ባየር ሙኒክ አሳልፈው የሰጡትና ሌዋንዶውስኪንም ላለማጣታቸው ዋስትና የሌላቸው ጀርመናውያኑ ኤሪክሰንን ከአያክስ አምስተርዳም ለመግዛት ከሊቨርፑል ከባድ ፈተና ቢጠብቃቸውም የልጁ ምርጫ በመሆናቸው የዝውውር መስኮቱ እንደተከፈተ ወደ ክለባቸው ያዘዋውሩታል ተብሎ ይጠበቃል።
8. ፊል ጃግዬልካ
በአርሴናሉ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር በጥብቅ የሚፈለገው የ30 ዓመቱ ጃግዬልካ ዴቪድ ሞይስን ተከትሎ ከመርሲሳይዱ ክለብ የሚለቅ ተጫዋች ይሆናል ሲል ዘሰን ጋዜጣ አስነብቧል። የአስር ሚሊዮን ዋጋ የተቆረጠለት ቢሆንም ሪዮ ፈርዲናንድን የሚያጣው እና የኒማኒያ ቪዲችን የተሟላ አገልግሎት ማግኘት የማይችለው ማንቸስተር ዩናይትድ የሰላሳ ዓመቱን ተከላካይ ለማዘዋወር ፍላጎቱን በአዲሱ አሰልጣኙ በኩል ገልጿል። እንግሊዛዊው የኤቨርተን ሁለተኛ አምበል ወደ ዩናይትድ የሚያደርገው ዝውውር የተጫዋቾችን የዝውውር ገበያ ከሚያደምቁ ተጫዋቾች አንዱ ይሆናል ሲል ጋዜጣው ጨምሮ ገልጿል።
9. ጋሪ ሁፐር
በሴልቲክ ስኬታማ የውድድር ዘመን ያሳለፈውን የ25 ዓመት ወጣት ለማግኘት ከፕሪሚየር ሊጉ የወረዱት የኪው ፒ አር አሰልጣኝ ሃሪ ሬድናፕ ፍላጎት እንዳላቸው ዘኢንዲፔንደንት ገልጿል። የገንዘብ ችግር የሌለበት ኪው ፒ አር የውል ዘመኑ ሊጠናቀቅ የ6 ወር እድሜ ብቻ የሚቀረውን አጥቂ ለማዘዋወር 2ነጥብ 4 ሚሊዮን ፓውንድ የመደቡ ሲሆን ተጫዋቹን በተጠቀሰው ዋጋ አዘዋውረው በሻምፒዮን ሺፑ ያጫውቱታል ተብሎ አይጠበቅም። ነገር ግን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሃያ ዘጠኝ ግቦችን ለስኮትላንዱ ክለብ ያስቆጠረውን እንግሊዛዊ በፕሪሚየር ሊጉ የሚወዳደሩ ክለቦች ሊያዘዋውሩት እንደሚችሉ ይጠበቃል። ልጁ ካለው ችሎታ አንጻር የዝውውር መስኮቱን ያደምቃሉ ተብለው ከሚጠበቁት ተጫዋቾች አንዱ ሊሆን ችሏል።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Sunday, May 19th, 2013

በሁለት መንታ መንገድ ላይ የሚገኘው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ
(ከአዘጋጁ፡ በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን ስናቀርብ ቆይተናል። በደብረሰላም ቤ/ክ ጉዳይ በሚኒሶታ የሚኖሩ ተቆርቋሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕምናን የሚያደርሱን ጽሁፍ አሁንም እንድቀጠለ ነው። በኢሜይል፣ ፕሪንት ተደርገው በሚበተኑ ወረቅቶች፣ በራድዮ፣ በቴሌኮንፍረንስ የሚደረጉ ውይይቶችም እንደቀጠሉ ነው። አሁንም ድምጻችሁ እንዲሰማ የምትፈልጉ ከየትኛውም ወገን የቆማችሁ ካላችሁ ዘ-ሐበሻ የሚደርሳትን የሕዝብ አስተያየት ከማድረስ ወደኋላ እንደማትል በድጋሚ ለማስታወስ እንወዳለን። ለዛሬው ደግሞ ደረሰ ገብረጊዮርጊስ የተባሉ አማኝ በፓወር ፖይንት ሰርተው ያደረሱንን አስተያየት ወደ PDF በመገልበጥ ለአንባቢ በሚስማማ መልኩ አስተናግደናል። )
ከደረሰ ገብረጊዮርጊስ (ሚኒሶታ)
Download (PDF, 592KB)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Sunday, May 19th, 2013

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
በአላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት፣ በረከት ስምኦን ከጀርባ የሚመሩት እና በአንድ ኤርትራዊ የሚዘጋጀው ጋዜጣ አለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር ሲሞክር መታየቱን ተከትሎ ምስጢሩን የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጉዳዩን አጋለጡ። « ሰንደቅ» የተባለውና በነፃ ፕሬስ ስም የሚያደናግረው ጋዜጣ ፍሬው አበበ በተባለ ዋና አዘጋጅነት እንዲሁም በኤርትራዊው ፋኑኤል ክንፉ ምክትል ዋና አዘጋጅነት የሚሰናዳ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሲሆን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በውድ ዋጋ ቢሮ ተከራይቶ እንደሚሰራ ያስታወቁት ምንጮቹ አያይዘውም ፍሬው አበበ ከዚህ ቀደም የብአዴን ልሳን በሆነው « ማህቶት» ጋዜጣ ላይ ይሰራ እንደነበረና ከብአዴን አመራር አባላትም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠዋል። በፓርቲው ልሳን ለመስራት ደግሞ የድርጅቱ አባል መሆን ግድ እንደሚል የጠቆሙት ምንጮቹ “ጋዜጠኛ” ፍሬው የፓርቲው አባል እንደሆነና በነበረው ታማኝነት በበረከት ስሞን ተመርጦ አሁን ባለበት ጋዜጣ እንዲሰማራ መደረጉን አስታውቀዋል። በተጨማሪ «የኢትዮጲያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር» ተብሎ በሚጠራውና የገዢው ፓርቲ ተለጣፊ በሆነው “ማህበር” ጋዜጠኛ ፍሬው የቦርድ አባል ሲሆን፣ ይህ ማህበር በሃገሪቱ ነፃ ፕሬስ እንዳይኖር ቀን ከሌሊት የሚተጋ ነው ሲሉ ምንጮቹ በመግለፅ ተከታዩን ማስረጃ ያቀርባሉ። « ማህበር ተብዬው በሚሚ ስብሃቱ ሬዲዮ በኩል « እነእስክንድር ነጋ አሸባሪ ናቸው» ብሎ ተከራክሯል፤ «አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ» ጋዜጦች ሲዘጉ «ከስረው ነው» በማለት የሽመልስ ከማልን መግለጫ የሚያጠናከር መግለጫ በማውጣት ከመንግስት ወግኖ ተሟግቷል፤ እንዲሁም በተመስገን ደሰላኝ ይዘጋጁ የነበሩት «ፍትህ፣አዲስ ታይምስና ልዕልና» ጋዜጦች በነበረከት ቀጭን ትእዛዝ እንዲዘጉ ሲደረግም የነፍሬው ማህበር ተመሳሳይ አቋም በማራመድ መከራከሩን በዋቢነት የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ በአጠቃለይ ጋዜጠኛ ሲታሰር፣ ሲንገላታና ሲሰደድ ልክ መንግስት ተቀጥላ እየፈጠረ ለመወንጀል እንደሚሞክረው ሁሉ ይህም ማህበር ተመሳሳይ አካሄድ የሚከተል ፀረ-ፕሬስ ስብስብ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ተለጣፊ ማህበር ሊቀመንበር አንተነህ አብርሃም እንደሆነ የጠቆሙት ምንጮቹ የአንተነህ ታላቅ ወንድም አማኑኤል አብርሃ ሲባል የደኢህዴን/ኢህአዴግ ማ/ኮሚቴ አባል መሆኑን አጋልጠዋል።
በሌላም በኩል ምክትል የጋዜጣው አዘጋጅ ኤርትራዊው ፋኑኤል አንድ ሰሞን በኢቲቪ የህትመት ዳሰሳ ላይ ቀርቦ « የኢህአዴግ ደጋፊ ነኝ » ሲል በይፋ መናገሩን ያስታወሱት ምንጮቹ የስርአቱን ትክክለኛነት በመግለፅና በመከራከር የገዢው ፓርቲ «ቋሚ ጠበቃ» ሆኖ መታዩትን ጨምረው ገልፀዋል። (ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ የነበረው አቤ ቶክቻው « የኢቲቪ አምደኛ» ሲል በወቅቱ ተሳልቆበታል)..
ምንጮቹ ከጋዜጣው ጋር በተያያዘ ሲቀጥሉ ይህን አሉ፤ የነፃ ፕሬስ ህልውና በአገሪቱ ጨርሶ እንዲጠፋ በተደረገበት ተጨባጭ እውነታ፣ የህትመት ዋጋ ጣራ በነካበት ሁኔታ ..«ሰንደቅ» የተባለው ጋዜጣ የሚያሳትመው ሁለት ሺህ ኮፒ ብቻ መሆኑ፣ ማስታወቂያ የሌለው መሆኑ፣ በተጨማሪ በሃገሪቱ ውድ በሚባለው ብርሃነ ሰላም ማ/ቤት መታተሙ እንዲሁም አዘጋጆቹ ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመሆኑ ምስጢር ሼህ አላሙዲ መሆናቸውን ያስገነዝባሉ። በዚህን ያክል ኮፒ ትርፍ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ መሆኑን ያመለከቱት ምንጮቹ፣ አላሙዲ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉና ጋዜጣውም በየሳምንቱ ሼኹን ከፍ-ከፍ አድርገው የሚያሳዩና ድርጅቶቻቸውን የተመለከቱ ዜናዎች እያተሙ የማውጣታቸው ምስጢሩ ከገንዘብ ድጋፉ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።
በዚሁ ጋዜጣ ላይ በረከት የሚፈልጉትና « ህዝብ ዘንድ መድረስ አለበት» የሚሏቸውን ምስጢራዊ ጉዳዮች ለሁለቱ የጋዜጣው አዘጋጆች የስራ መመሪያ ጭምር ከመስጠት ባለፈ በረከትና ሽመልስ በተለያዩ የብእር ስሞች ፖለቲካዊ ነክ ፅሁፎች እንደሚያወጡ፣ የሚፈልጉትን መረጃ እንደሚያስተላልፉ፣ ምንጮቹ አጋልጠዋል። እንዲህ ሲሉም ያብራራሉ፥ « የእነአበበ በለውና እስክንድር ነጋ ንብረት እንዲወረስ የተለያዩ የብእር ስሞች (ሽመልስና በረከት) በመጠቀም በጋዜጣው ቅስቀሳ ሲካሄድ ከቀየ በኋላ በመጨረሻ በዋና ክስነት ከቀረበው ውጭ «የንብረት ክስ» በሚል ሌላ ክስ ተመስርቶ የንብረት ውርሱ ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ። መንግስት የሰጠውን ግዳጅ በመወጣት፣ ነፃ ፕሬስን ሽፋን አድርጎ የተሰማራው ሰንደቅ ጋዜጣ ከጀርባ ያነገበው «አላማ» እንዲሁም አካሄድ በህዝብ ዘንድ ጥርጣሬ በማስከተሉ የጋዜጣው የኮፒ መጠን ላለፉት አመታት ሊያድግ እንዳልቻ አስታውቀዋል። በተለይ የጋዜጣው ዋና <አላማ> ተቃዋሚዎችን በአለ በሌለ ጉልበቱ ጨፍልቆ በመምታት በይፋ እንደሚታወቅ አመላክተዋል።
ለዚህም ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጠረውን ሁኔታ በአስረጅነት ይጠቅሳሉ ምንጮቹ፤ አብዛኛው አገር ቤት ያሉ ምሁራን አድፍጠው ባሉበት ተጨባጭ ሁኔታ ገዢውን ፓርቲ በአደባባይ ከሚቃወሙና የተለያዩ የመሟገቻ ሃሳቦችን ከሚያቀርቡ በጣት የሚቆጠሩ ምሁራን አንዱ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ነው በማለት ይገልፃሉ። ጋዜጣው « ዶ/ር ዳኛቸው የመኢአድ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከኢ/ር ሃይሉ ጋር መምከራቸውን» በማስቀደም አያያዞም « የብአዴን አባል ነበሩ» ሲል በተቃዋሚ ክፍሎችና በህብረተሰቡ ዘንድ ጥርጣሬን ለመጫር መሞከሩን የገለፁት ምንጮቹ በረከት ስሞኦን ያጠናቀሩት ዘገባ መሆኑን አጋልጠዋል። ይህ ዘገባ ጨርሶ ከእውነት የራቀ መሆኑን የሚገልፅ ማስተባበያ ዶ/ር ዳኛቸው በጋዜጣው እንዲወጣ ከማድረጋቸው ባሻገር በፌስቡክ ባሰፈሩት መልእክት « እኔ የብአዴን አባል ብሆን ኖሮ ወረቀት በታኝ ሆኜ የምቀር ይመስላችኋል?. አባል ሆኜ ድምፄ ሳይሰማ የእነ ህላዌና በረከት ስምኦን ወረቀት በታኝ ሆኜ ልቀር አልችልም!» ብለዋል።
ምንጮቹ በማጠቃለያ ያነሱት፥ ፍሬው አበበ «ተከሰሰ» ተብሎ የተራገበውን ሲሆን፣ ከስምንት ወር በፊት የተዘገበን እና አዜብ በግልፅ ከቤተ መንግስት እንደማይለቁ በተነገረለት፣ሚሚ ስብሃቱ ሳይቀር ጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያምን የሚያኮስሥና በአንፃሩ ለአዜብ የወገነ ዲስኩር ማሰማቷና እርሷ ምንም ሳትባል «ጋዜጠኛው ተከሰሰ » የተባለው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት ለመሳብ በነበረከት የተቀናበረ « ድራማ» ነው ሲሊ ያጣጥሉታል። ምክንያቱም ሁለት ነው፤ ቀዳሚው በኢትዮጲያ ነፃ ፕሬስ አለ የሚል ስእል በመስጠት እገረመንገዱን <ፍትህ አለ> በሚል እነእስክንድር ነጋ እንዲፈቱ የሚቀርበውን አለም አቀፍ ጥያቄ አቅጣጫ ለማስለወጥ ብሎም «በእነእስክንድር የተሰጠው ውሳኔ በነፃ የህፍትህ አካላት የተወሰነ ነው» ለማለት እንደሆነ ምንጮቹ ያስረዳሉ።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Sunday, May 19th, 2013

ያለንበት ጊዜ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆን ትረጉመ-ቢስ የሆነበት ደረጃ ላይ እየደረሰ እንዳይሆን የሚያሰጋበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያዊነታቸው ሊከበርላቸው የሚገባውን የዜግነት መብት እየተነፈጉ ነው። መንግሥት የዜጎችን መብት ማስከበር ተስኖታል። ይህንን አስመልክቶ የኢሮብ መብት ተማጓች ማህበር (ኢ.መ.ተ.ማ) ተደጋጋሚ እሮሮዎችን ሲያሰማ የቆየ ቢሆንም አድማጭ ጆሮ ተነፍጎት ቆይቷል።
ከአንድ መቶ በላይ የኢሮብ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን በሻዓቢያ ታግተው ከተወሰዱ ይኸው አሥራ ሶስት ዓመት ሊሞላ አንድ ወር ቀርቶታል። ኢ.መ.ተ.ማ የነዚህ ዜጎች እጣ ፈንታ እንዲጠይቅ እንዲሁም የኢሮብ ሕዝብና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ለሺ ዓመቶች የኖሩበት መሬታቸው ለኤርትራ መከለሉን በተመለከተ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም፤ መንግሥት ጆሮ ደባ ልበስ ብሎ መቀመጥን መርጧል። ቀጥሎም በ2003 ዓ.ም ሻዓቢያ እንደገና በወርቅ ማምረት ላይ ተሠማርተው የነበሩ ከ260 በላይ ኢትዮጵያዊያን የትግራይ ተወላጆችን ከምእራብ ትግራይ ጠልፎ በመውሰድ ድኳቸው አጥፍቷል። ሆኖም፤ መንግሥት የነዚህን ዜጎች ደህንነት ለማረጋገጥና የሚገኙበት ሁኔታን ለማጣራት የወሰደው አንዳችም እርምጃ የለም። በተቃራኒው፤ አንዳንድ የኢህአዴግ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ኃይሎች በክስተቶቹ መንግሥት የመረጠውን ዝምታ በማውገዝ የአቋም መግለጫዎችን አውጥቷል። በውጭ ዜጎች መጠለፍ ወታደራዊ እርምጃ እስከመውስደ የተሯሯጠ መንግሥት ታግተው ደብዛቸው ስለጠፉ ዜጎቹ ምንም ዓይነት የሀላፊነት ስሜት አላሳየም የወሰደው እርምጃም የለም።
ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን የማፈናቀል አባዜ እጅግ አስከፊና ዘግናኝ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል። መፈናቀሉ መልከ ብዙ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። ለም የእርሻ መሬቶችን ለህንድና ለዓረብ ባለሀብቶች በስመ-ኢኒቨስትመንት ለመስጠት በሰበብ አስባቡ ከኖሩበት ቀዬ የሚፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር እጅጉን ተበራክቷል። የከተማ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሰበብ አስባቡ ያለምንም ቅድመ ዝግጅት በዓቅማቸው ቀልሰው ለዓመታት ከኖሩበት ቀዬ በማፈናቀል፤ ያለ ምንም ካሳ ቤቶቻቸውን በማፍረስ ሕጻናት፤ ነብሰ-ጡሮች፤ አሮጊት እናቶች፤ ሽማግሌ አባቶችና አቅመ ደካሞች ለሜዳ ኑሮ መዳረጋቸውን ታዝበናል። በተቃራኒው፤ መቐለ ውስጥ እንደታዘብነው ቤት እንዳይሠራባቸው በሕግ የተከለከሉና ለመናፈሻና ለደን እንዲጠበቁ በከተማው አስተዳዳሪዎች የተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሥርዓቱ ባለሥልጣናትና የሥርዓቱ ታማኞች ሕግ ተላልፈው ፎቆችና ቪላዎችን ሲያሰሩ፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የተሰሩ ናቸውና መፍረስ አለባቸው ብሎ የሚያፈርስ ቀርቶ፤ ሕግ ተላልፋቹሀል ብሎ የሚናገር ባለሥልጣንን ለመስማት አልታደልንም። ይህ በመቐለ የተከሰተው ዓይነት አሠራር በሌሎች አከባቢዎችም ተፈፅሞ ሊሆን ይቻላል። ሆኖም ለጊዜው መቐለ ላይ የተጣሰ ሕግ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥም እንደተጣሰ ለማመሳከር የሚያስችል ጭብጥ ስለሌለን በዚሁ ልናልፈው መርጠናል። እነዚህ ከላይ ያነሳናቸው ጭብጦች ላይ ተመርኵዘን በመከሰት ላይ ያለውን ህዝብን የማፈናቀል ተግባር አስፈላጊ ሆኖ እንኳ ቢገኝ ብቁ ቅድመ ዘግጅት ተደርጎ እንዲካሄድ የማድረግ ሓላፊነት ለመሸከም የሚችል መንግሥት እንደሌለን የሚያመላክት ሆኖ እናገኘዋለን። በየጊዜው በሻዓቢያ እየታገቱ ለሚወሰዱና ደብዛቸው ለጠፋ ዜጎች መቆም ያቃተው መንግሥት እንዳለን ከታዘብንም ሰነባብተናል።
አሁን ይህንን አጭር መግለጫ ለማውጣት ያስገደደን እጅግ አስደንጋጭና በዓይነቱም ለየት ያለ ኢትዮጵያዊያንን ለዓመታት ከኖሩበት መሬት የዘር ሐረጋቸው እየተመረጠ አፈናቅሎ የማባረር ኢትዮጳዊነትን የሚፈታተን ተግባር ሲፈጸም መታዘባችን ነው። ከዚህ በፊት ኢትዮጵያውያን ዘራቸው እየተጠና ከጉራ ፈርዳ ተፈናቅለው መባረራቸውን ሰምተናል አንብበናል። ያንን ስንሰማና ስለዛ ስናነብ እጅጉን የደነገጥን ቢሆንም፤ አገዛዙ ከዚህ ስሕተት ተምሯል የሚል ግምት አሳድረን ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ግን ተመሳሳይ ስሕተት እንደገና በተመሳሳይ መልኩ ተደግሞ ተከስቷል። አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ከበንሻንጉል ጉምዝ ፍጹም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ እንዲባረሩ ተደርጓል። በዚህም፤ የኢህአዴግ መንግሥት በጉራፈርዳ የፈጸመውን ኢሰብአዊ ግፍ ከመድገም ወደ ኋላ እንደማይል በሚገባ እንድንረዳ አስችሎናል። ስለሆነም፤ ሁኔታው እጅጉን አሳስቦናል። ኢትዮጵያዊያን በዘር ሐረጋቸው ምክንያት ከተወሰነላቸው ክልል ውጭ መኖር የማይችሉበት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት ሲቀጥል ታዝበናል። ይህ ዛሬ በአማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ዘግናኝና አሳፋሪ የማፈናቀል ተግባር፤ ነገ በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ ላለመቀጠሉ ምንም ዓይንት ዋስተና የለም። ይህ በእንዲህ ከቀጠለ ደግሞ ኢትዮዽያና ኢትዮዽያዊነት ምን ትርጉም ሊኖረው እንደሚችል ህሊና ያለው እያንዳንዱ ኢትዮዽያዊ ቆም ብሎ ራሱን መመርመር ይኖርበታል ብሎ መኢተማ ያምናል። በመሆኑም፤ በሥልጣን ላይ ያለው አገዛዝ፤ ኢትዮጵያዊያንን ከቅያቸው የማፈናቀል ተግባር እንዲያቆም ኢትዮጵያዊያን ተባብረን የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል። የኢህአዴግ አገዛዝም፤ ህዝብን የማፈናቀል ተግባር የሚያስከትለው መዘዝ ምን ያህል አስከፊና አውዳሚ ሊሆን እንደሚችል በወጉ ለመገንዘብ ያለመፈለግን እልህ ማቆም ይጠበቅበታል። ካልሆነ ግን በሂደት ላገሪቱም ሆነ ለራሱ ለኢህአዴግ አላስፈላጊ ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል በወቅቱ ቢገነዘበው የተሻለ ይሆናል።
ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለጉ በፈለጉበት ቦታ ተዘዋውረው ሠርተው ሀብት ለማፍራት፤ ወልደው ከብደው ለመክበርና በገዛ አገራቸው ውስጥ ያለምንም መሳቀቅና መፍራት የመኖር ሕገ-መንግሥታዊ ዋስትና ከሌላቸው ኢትዮጵያ የምትባል አገርና ኢትዮጵያዊ የሚባል ዜጋ ሊኖር ይችላል ብሎ ለማሰብ የሚቻል አይሆንም። ይህ ማለት ግን መንግሥት በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖረውን የመሬት ይዞታ መልክ ለማስያዝ የሚረዳ ፖሊሲ መንደፍ የለበትም ለማለት እንዳልሆነ ግልጽ ሊሆን ይገባል። ለደን ልማት፤ ለመናፈሻ፤ ለዱር አራዊት፤ ለእርሻ፤ ለኢንዳስትሪ፤ ለመኖርያ፤ …….ወዘተ የሚሆኑ ቦታዎች ተለይተው አይከለሉ ለማለት አይደለም። መከለል አለባቸው። አሠራራችንም ሆነ የአመራረት ዘየቤያችን ዘመናዊ ማድረግ ላይ ተቃውሞ የለንም ብቻ ሳይሆን የምንደግፈው ጉዳይ ይሆናል። ሆኖም፤ የድሀው ህዝባችን ኑሮ በማያመሰቃቅልና ዜጎችን በማይለያይ መልኩ በጥናትና በጊዜ እየተለየ መከናወን አለበት ብለን እናምናለን። የማናምነውና ፍጹም የማንቀበለው ጉዳይ ቢኖር ግን የተለያዩ የክልል ትናንሽ ንጉሶችን በመፍጠር ኢትዮጵያዊንን ከኛ ዘር ስላልተወለዳችሁ፤ ይህ ክልል የነ እገሌ ዘሮች የትውልድ ክልል ስለሆነ ወይም ስላልሆነ ከሌላ ቦታ የመጣቹህ ወይም ከሌላ ዘር፤ ወገን የሆናቹህ በዚህ ክልል፤ መንደር፤ ሰፈር…ወዘተ መኖር አትችሉም የሚለው አካሄድ ኢትዮጵያዊነትን የሚንድ አደጋ አለው ብለን በጽኑ እናምናለን። አንድ ኢትዮጵያዊ በአንድ ክልል ውስጥ መጥቶ መኖር ሲጀምር፤ መኖርያውን በሚቀይስበት ጊዜ የመፍቀድም ሆነ የመከልከል ሥልጣን በሕግ የተሰጠው ኣካል ሲከለክልም ሆነ ሲፈቅድ የተገልጋዩን የዘር ሐረግ መስፈርት እንዳይጠቀም በሕግ መከልከል ይኖርበታል እንላለን። አንድ ኢትዮጵያዊ በተወሰነ ቦታ ላይ የተወሰነ ሥራ ለማከናወን ሲፈልግ፤ ያ ቦታ እንዲሰጠው ለመፍቀድም ሆነ ላለመፍቀድ አስቀድሞ በተቀመጠው ፕላን መሠረት በሚቀመጥ መስፈርት እንጂ ግለሰቦች በዘፈቀደ በሚዘውሩት መስፈርት ሊሆን ፈጽሞ አይገባም። ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ዘርና ወገን እየተለየ ኢትዮጵያዊያንን ማፈናቀል እየገፋ ሲሄድ ማቆምያ ድንበር ሊበጅለት የማይቻልበት ደረጃ ሊደርስ እንደምችል መታወቅ አለበት። የዚህ ድምር ውጤት በጋራ መልማትና ማደግ ሳይሆን ተያይዞ መጥፋትን እንደሚያስከትል መጠርጠር የለበትም። የኢትዮጵያ ህዝብ በየክልሉና በየመንደሩ ተከልሎ እንዲኖር የተወሰነ ዕለት እንደዚህ ዓይነት ችግር እንደሚከተል በግልጽ የሚታወቅ እንደመሆኑ መጠን፤ የሚያስከትለውን ችግር ለመረዳት የሚከብድ አልነበረም። በመሆኑም፤ አሁን እያየነው ያለ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ መፈናቀል እንዲከሰት ሆን ተብሎ የታቀደ ፀረ አንድነትና ኢትዮዽያዊነት ተግባር መሆኑም ግልጽ ነው።
በየክልላችን ተወስነን እንድንኖር የተደረገ ዕለት አብሮና ተማምኖ የአገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር የሚቆም ብሔራዊ ሠራዊት አይኖረንም። ለይስሙላ የሚቋቋም ብሔራዊ መከላከያ ኃይል ሊኖረን ይችል ይሆናል። ያ ግን መለዮ የለበሱ ሰዎች ስብስብ እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሠራዊት ሊሆን አይችልም። በኢትዮጵያዊነት ብሔራዊ ስሜት ተኮትኵቶ፤ የችግሯን ገፈት አብሮ ለመቅሰም አብሮ የመሰለፉን ያህል ከጥቅምዋም አብሮ እኩል ለመቋደስ የማይችል ወታደር ብሔራዊ ወታደር ሊሆን አይችልም። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ በቅራኔ በተወጠረ ቀጠና ውስጥ ላሉ አገሮች ቀርቶ አንጻራዊ ሰላም አላቸው በሚባሉ አገሮች ውስጥም ቢሆን ተቀባይነት የለውም። የሠራዊቱን ጉዳይ አነሳን እንጂ በየመስኩ ብንዘረዝረው ሊያስከትለው የሚችለው ውድቀት የት የሌለ ጥፋት እንደሚሆን ለመገመት የሚከብድ አይደለም። በመሆኑም፤ አሁን አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ መጀመርያ በኢትዮጵያዊ ወገንተኝነታችን እንዲሁም ሰው በመሆናችን እጅጉን አሳዝኖናል። በመሆኑም፤ ይህንን አስነዋሪ ተግባር እያወገዝን የነዚህ ዜጎች ጉዳይ ከግብር ይውጣ አሠራር በዘለለ ወደ ተፈናቀሉበት ቀዬ ተመልሰው እንዲኖሩ እንዲደረግና ለደረሰባቸው የአካል፤ የንብረትና የሥነ-አእምሮ ድቀት ተገቢ ካሳ እንዲያገኙ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ከዚህም በተጨማሪ፤ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለኢፈዴሪ ፓርላማ በሰጡት መግለጫ ተግባሩን ማውገዛቸው የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም፤ ማውገዝ ብቻውን የሚፈለገው ውጤት ሊያስጨብጠን እንደማይችልና የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ዓለም አቀፉ ማህበረ-ሰብ በቀላሉ የሚቀበሉትና የሚጃጃሉበት እንደማይሆን ይረዱታል ብለን እንገምታለን። ስለሆነም፤ ኢትዮጵያዊያን በዜግነታቸው ተማምነው ሕጋዊ ዋስትና እንዳላቸው እርግጠ ኛ እንዲሆኑና አገራችን በዓለም አቀፉ ህብረተ-ሰብ የተሰጣትን ገጽታ ወደ በጎነት ለመቀየር ይቻል ዘንድ ባስቸኳይ ሕጋዊ የእርምት እርምጃ መወሰድ ይኖርበታል። በኢ.መ.ተ.ማ እይታ ይህ ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት “የተወሰኑ ኪራይ ሰብሳቢ የወረዳ አስተዳዳሪዎች” የፈጸሙት ነው የሚለው አባባል በአመክንዮ ሊደገፍ የሚችል አይደለም። ቢያንስ ከፍተኛ የፈደራል የመንግሥት ባለሥልጣኖች በወንጀሉ ውስጥ አለመሳተፋቸው በእርግጠኝነት ከታወቀ፤ በጥልቀት ሊመረመር የሚገባው የሕግ ሕፀፅ መኖር አለበት። ካልሆነ ግን ማንም የወረዳ አስተዳዳሪ ከባዶ ተነስቶ ይህን ያህል ህዝብ የማባረር ሥልጣን ይኖሯል ብሎ ለማሰብ እጅጉን ይከብዳል። ስለሆንም፤ ችግሩን ከሥሩ በማጥራት በነዚህ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አስከፊ በደል በማያዳግም መንገድ እልባት እንዲያገኝና ኢትዮጵያዊነት ከመጠውለግ ድኖ እንዲያብብ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ አንዲታገል አጥብቀን እንጠይቃለን።
ኢትዮጵያዊነት በኢትዮዽያዊያን የጋራ ትግል ይለመልማል!!!
የኢሮብ መብት ተማጓች ማኅበር (ኢ.መ.ተ.ማ)
ግንቦት 2005 ዓ.ም
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Sunday, May 19th, 2013
እንግዲህ ይህ ከሆነ አመቱ ሆነ አይደለ… ቅዳሜም ቅዳሜ፣ እሁድም እሁድ ነው እና ምናልባት ካልተገናኘን… እንዳንረሳው፤ ከወዲሁ ቀኑን እንደሚከተለው እንዘክረው… (በቅንፍም ኤድያ እነ እንትናዬ ደግሞ ሊበሳጩብኝ ነው… (በሌላ ቅንፍ እንግዲህ ይቻሉት እኛ ስንቱን ችለነው የለ…))
በመጀመሪያም፤
ብስጭቴ
እኔ እኮ የምለው ሰው አይኑ እያየ የሰራውን ስራ እያወቀ ወደ አሜሪካ ለዛውም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይሄዳል እንዴ!? እውነቱን ለመናገር እኔ አቶ መለስ ዜናዊን ብሆን ኖሮ ዲቪ እንኳ ቢደርሰኝ ሀገር ይቀየርልኝ እላለሁ እንጂ አሜሪካ አልሄድም። እነ ቻይና ባሉበት አለም እነ ሰሜን ኮሪያ በሚኖሩበት ምድር ሰው እንዴት ወደ አሜሪካ ይሄዳል? (ይቅርታ ሰው በሚል የተጠቀሱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ነው)
ዋናው ወሬ፤
የሆነው ሆኖ ትላንት በዋሽንግተኑ ስብሰባ አቶ መለስ ዜናዊ ሲመጡ ከውጪ ያለውን የተቃውሞ ድምፅ በመከራ አልፈው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደግሞ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተሰብሳቢው ፊት፤ ከውጪ ያለው ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ፣ እንዲሁም አዲሳባ ያለው ህዝብ ደግሞ በሰላማዊ ዝምታ በሆዱ ምን እያላቸው እንደሆነ ነጥብ ነጥቡን ነግሯቸዋል። እንደው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውብኝ እንጂ “እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ድረስ ነግሯቸዋል!” ብል የበለጠ ይገልፀዋል መሰል!
የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድርጊት ከዚህ በፊት ጆርጅ ቡሽ ላይ ጫማ ከወረወረው ጋዜጠኛ ጋር የሚቀራረብ ይመስላል። እንደውም በቪዲዮ እንዳየኋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የደረሰው የቅስም ስብራት “በጫማ መመታት በስንት ጣዕሙ!” ያሰኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በስፍራው የተገኙት በባራክ ኦባማ ጋባዥነት ከቡድን ስምንት ሀገሮች ጋር ስብሰባ ሊቀመጡ እንደሆነ ባለፈው ግዜ አውርተናል፤ ከቡድን ስምንቱ ስብሰባ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ታድያ “ግሎባል አግሪካልቸር ኤንድ ፉድ ሴኪዩሪቲ” በተባለው ስብሰባ ላይ ቁጭ ብለው እንደተለመደው ፐርሰንታቸውን እየጠቀሱ ሳለ ድንገት አበበ ገላው፤ “መለስ ዜናዊ…” ብሎ ሲጠራ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን “የደነገጡት መደንገጥ… ከአንድ ታጋይ የሚጠበቅ አይደለም” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ። እኔም እንዳየሁት ጆሯቸውን ማመን አቅቷቸው “የድርጅቴን ብቅል እየፈጨሁ ነው…” ብለው ሊያልፉት የከጀሉ ሁሉ መስሎኝ ነበር።
ብቻ በጣም ክው ማለታቸውን ፊታቸው አሳበቀባቸው። ከዛ እንደምንም ተረጋግተው…“ሰበንቲ….ፐርሰንት” ብለው ንግግራቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድምፅ ከመጀመሪያው ከፍ ብሎ “መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር…” ማለቱን ቀጠለ አሁን ትንፋሽም ቃልም አጠራቸው። አስተያየታቸው “ምነው ዛሬ እግሬን በሰበረው!?” የሚሉ ይመስላሉ። ግን እንደምንም ብለው ለመቀጠል ሞከሩ። ድምፃቸውን ከአበበ ድምፅ ከፍ ለማድረግ እየጣሩ “ሰበንቲ…ፐርሰንት” አልቻሉም። “ምን ላይ ነበር ያቆምኩት…?” ለማለት የፈለጉ ይመስላሉ ባልንጀሮቻቸውን ቃኘት ቃኘት አደረጉ። እነርሱቴ “ራስህ ተወጣው!” ሳይሏቸው አይቀሩም… አበበ ቀጥሏል። “መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር….” አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኛ በላይ ድምፅ ላሳር በሚመስል መልኩ ከአበበ በላይ ጮክ ብለው እና ድፍረታቸውን አሰባስበው፤ “ሰበንቲ ፐርሰንት ኦፍ ዘ ፖፕሌሽን ኢን አፍሪካ….” አሉ። ብሽሽቅ ነው የሚመስለው እንጂ የንግግራቸው አካል አይመስልም!
ድጋሚ አቋረጡ አበበ ግን የሚያቋርጥ አይመስልም በእንግሊዝ አፍ “እስክንድር ነጋ እና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ ምግብ ያለ ነፃነት ዋጋ የለውም! መለስ ዜናዊ አምባ ገነን ነው!” ብሎ እንቅጩን ነገራቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁና ቁና ሲተነፍሱ ኮምፒውተሬን አልፎ ሁሉ ይሰማ ነበር። በሆዴ “ይበልዎት አይሂዱ አላልኮትም ነበር!?” ብልም እውነቱን ለመናገር ግን አንጀቴን በልተውታል።
አቶ መለስ ከትላንትናው የበለጠ ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸው ጭምጭምታ ሰምቻለሁ። ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው ካምፕ ዴቪድ ድረስ ህዝቡን ለማመላለስ የተሰናዱ አውቶቡሶች መኖራቸውን የደረሰኝ ጭምጭምታ ያስረዳል።
እኔማ የሚሰማኝ አጣሁ እንጂ ቀድሞውኑም ይሄ ስብሰባ ይቅርብዎ ብዬ ነበር። ይሄን ግዜ እርሳቸውም በሆዳቸው “ምነው ምነው ምነው በቀረብኝ” የሚለውን ሙዚቃ ሊያዜሙ እንደሚችሉ እጠረጥራለሁ። ምንም ጠቅላይሚኒስትር ቢሆኑ ሰው አይደሉ እንዴ…!? ምክሬን ባለመስማታቸው መፀፀት ካልቻሉ እውነትም ሰውየው ጠቅላይ ሚኒስትር እንጂ ሰው አይደሉም ማለት ነው!
ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቅስም ስብራት የሰማ አንድ ወዳጄ “ይሄኔ ጥሩ አዝማሪ ቢገኝ ይቺን ግጥም በል እስቲ ተቀበል ብሎ ማቀበል ነበር” ብሎኛል…
“አፄ መለስ ዜና እጅግ ተዋረዱ
ምግብ ብለው መጥተው አንጀት በልተው ሄዱ
አንተ አበበ ገላው እንደምን ቻልካቸው
መለስ ቀለስ ሲሉ ጎንበስ አረካቸው”
(አረ ጎበዝ ዜማ ፈልጉና ይችን ነገር ነጠላ ዜማ አደርገን እንልቀቃት በስንት ግዜ የተገኘ የግጥም አዚምን እንጠቀምበት እንጂ!)
በነገራችን ላይ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ አቶ መለስ አዲሳባ ሲገቡ ወይ በጭፈራ ሞቅ ደመቅ አድርገን ካልተቀበልናቸው ወይ ደግሞ ለጥ ብለን ተኝተን ካልጠበቅናቸው በብስጭት ሊጨርሱን ይችላሉ ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም
ኦባማ ግን አራዳ መሆናቸው ነው ሰውየውን ጠርተው ልክ ልካቸውን የሚያስነግሯቸው!? የምር ሽምቅቅ አደረጓቸውኮ! (እኔ ልሸማቀቅ… ልላቸው ነበር አሁንማ አንዴ ጀምረውታል… ይወጡት እንግዲህ!)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Sunday, May 19th, 2013
መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2005
እንግዲህ ኢሳት በነገረኛነትም ሆነ በጠመንጃ-ያዥነት በኩል ከሎሌነት ጠባይ ጋር የተያያዘውን ኢትዮጵያውያን ያለንን አጉል ባህል ሁሉ እየነቀስን እየጣልን በዘመናዊና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ መሠረት ለመጣል ዋና መሣሪያ ሊሆነን ይችላል ብሎ ማመን መነሻ ይሆናል፤ ይህ እምነት ከሌለ የእምቧይ ካብ ነው፤ ይህ እምነት ራስን ማጽዳትንም ይጠይቃል።
ማክሸፍ እንደምንችልበት ከማመን እንጀምር፤ ስለዚህም ኢሳት ሊከሽፍ የሚችልበትን እያንዳንዱን መንገድ ማጥናትና በቅድሚያ ፈውሱን ማዘጋጀት የሚጠቅም ይመስለኛል፤ ይህንን ጉዳይ በትጋት ለመከታተል የኢሳትን አማራጭ የማይገኝለት የአገር ጥቅም በእውነትና በትክክል መገንዘብ ያሻል፤ ዘመን-አመጣሽ ነገር ብቻ አድርጎ መመልከቱ ለወረት ይዳርገዋል፤ ወረትን ማክሸፍ ቀላል ነው፤ ከከሸፈ በኋላ እንዲያንሰራራ ለማድረግ በጣም ከባድ ሥራን ይጠይቃል፤ ስለዚህ ከወዲሁ ኢሳት ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲተከል የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ዘለቄታ እንዲኖረው ማረጋገጫ ይሆናል።
የኢሳት መክሸፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል፤ አንፈራጥጠው ከላይ ቤት እታች ቤት እየቀላወጡ አካላቸውን፣ አእምሮአቸውንና መንፈሳቸውን የሚያባልጉ ሰዎችን ያበራክታል፤ የድብቅብቆሽ ዓለምን እየፈጠሩ የጠራውን ከደፈረሰው፣ የጸዳውን ከአደፈው፣ ሳይለዩ ለሚያወሩት ደካሞች ሜዳውን ያሰፋላቸዋል፤ የወያኔ/ኢሕአዴግን ፍርሃት ወደመርበድበድ ይለውጠዋል፤ የጦርነት ጥሩምባ ለሚነፉትም ሜዳውን እያሳየ የቀረርቶ በር ይከፍትላቸዋል፤ ይህ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምንና ስምምነትን፣ እድገትንና ብልጽግናን፣ ኩራትንና ክብርን አያስገኝም።
ንስሐ ለመግባት ወኔ ለሌላቸው፣ በሠሩት ጥፋት አገርን ወይም ወገንን በመበደላቸው ዛሬም ለመኩራራት ለሚፈልጉት፣ አርበኛውንና ባንዳውን ባንድ ሚዛን አስቀምጠው ለሚተቹት፣ የኢትዮጵያውያንን ሰውነት አራክሰው ጊዜያዊ ጥቅማቸውን ለሚያከማቹ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን በተንኮል እየመነዘሩ የሥልጣን መሰላል ለሚያበጁ ሁሉ ፊት-ለፊት ቆሞ ለሚጋፈጣቸው ኢሳት መድረክ ይሆናል፤ የኢሳት ዋና ጥቅሙ እዚህ ላይ ነው፤ ይህንን ተግባር ለመፈጸም ኢሳት የኢትዮጵያ፤ ኢሳት የኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲሆን መንገዱን እንጥረግ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በባለቤትነት የሚመራውና የሚያካሂደው እናድርገው፤ ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢሳት ላይ ያለው መብት ነው ከተባለ፣ ግዴታውንም አብሮ መቀበል ሳይታለም የተፈታ ይሆናል፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሁሉ ግዴታውን በቃል ኪዳን መቋጨት ከቻለ ኢሳት ከቀፈፋና ለመክሸፍ ይድናል።
የእኔ ምኞት ኢሳት በኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳን ተገንብቶ በሕገ ኀልዮት እየተመራ አዲስ ዓላማ፣ አዲስ የአሠራር ዘዴ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ጉድለቶችን ሁሉ አውቆ በጥንቃቄ እየነቀሰ አዲስ የመተማመንና የመተባበር ባህል ይፈጥራል የሚል ነው፤ (እኔ ቃል ኪዳን የምለው ሁለት ቁም-ነገሮችን የያዘ ነው፤ በአንድ በኩል እውነትን አለመፍራት (ወይም በጥሩ መልኩ ለእውነት መቆም፣) በሌላ በኩል ለአንድ የጋራ ዓላማ የራስን ግዴታ ሳያስተጓጕሉ ለመወጣት በቆራጥነት መቆም፤ ስንት ልጆች አሉህ ተብሎ ሲጠየቅ ሁለት ወይም ሦስት እያለ አጥር ላይ ተንጠልጥሎ የሚመልስ ለቃል ኪዳን አይበቃም፤) ከሩቅ እንደማየው ጥቂት ሰዎች ኢሳትን በቃል ኪዳን ተይዘው ሲጥሩ አብዛኛው ደግሞ በአጋጣሚ እንደተመቸውና እንደፈለገ የተቻለውን የሚያደርግ ምንም ዓይነት ቃል ኪዳን የሌለው ነው፤ ከተሳሳትሁ ደስ ይለኛል፤ አስተያየቴ ትክክል ከሆነ ኢሳት አይዘልቅም፤ መክሸፍ ዕጣ-ፋንታው ይሆናል።
ዓላማውን ሳይመታ እንዳይከሽፍ ኢሳት በቃል ኪዳን መታሰር አለበት፤ እንዴት? ቢባል፣ አንድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በአማካይ በወር አሥር ዶላር ለመስጠት ቃል ኪዳን ቢገቡና የየዓመቱን ግዴታቸውን በአንዴ ቢወጡ፣ በወር አሥር ሚልዮን ዶላር (በዓመት አንድ መቶ ሃያ ሚልዮን ዶላር) ኢሳትን ኢትዮጵያዊነትን የሚያስከብር የሰላምና የፍቅር፣ የብልጽግናና የተስፋ መድረክ ሊያደርገው ይችል ነበር፤ አብዛኛዎቹ ችሎታው ያላቸው ኢትዮጵያውያን ለኢሳት የሚገቡት ቃል ኪዳን ለጥሬ ሥጋና ለመጠጥ የገቡትን ቃል ኪዳን ካላሸነፈ ታማኝ በየነን በያገሩ እየላከ በሚያደርገው ዓመታዊ ቀፈፋ ኢሳት ይገነባል ብዬ ለማመን ያሰቸግረኛል፤ በኢሰመጉ አይቼዋለሁ።
ቀፈፋ ወይም ልመና አንዱና ዋናው የባህል ሕመም ነው፤ እያንዳንዳችን ከዚህ ሕመም ለመዳን በራሳችን ላይ መዝመት የሚያስፈልገን ይመስለኛል፤ በተለይ በአገር ጉዳይ፣ በወገን ጉዳይ ማን ነው ለማኝ? ተለማኙስ ማን ነው? ስለአገሩና ስለወገኑ ችግር የማያውቅ አለ? ለማወቅ የማይፈልግ ይኖራል እንጂ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ችግር ገሀድ ነው፤ በአስከፊ መልኩ ለመረዳት የሚፈልግ በመረረ ቋንቋ የተጻፈውን የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ሀገሬ ገበናሽ (ክፍል አንድ፣ ክፍል ሁለትና ክፍል ሦስትን) ያንብብ። አንብቦ ካላለቀሰ፣ አልቅሶ ‹‹ምን ላድርግ!›› የሚል ቁርጠኛነት ያላደረበት በዓመት አንድ ጊዜ በታማኝ ቀፈፋ አገሩንና ወገኑን መርዳት አይችልም፤ እምነቱ ካለ፣ ስሜቱ ካለ በገንዘብ የሚደረግ ማናቸውም እርዳታ የመጨረሻው፣ መናኛው ነው፤ መናኛ የሚያደርገው የገንዘቡ መብዛት ወይም ማነስ አይደለም፤ ለአገርና ለወገን ከዚያ በጣም የበለጠ የሚከፈል ዋጋ በመኖሩ ነው፤ አያቶቻችንና ቅምአያቶቻችን የከፈሉት ዋጋ በገንዘብ አይመነዘርም፤ እነሱ በሕይወታቸው ያስገኙልንንና እኛ በገንዘብ የሸጥነውን ኩራትና ክብር በገንዘብ ብቻ አናስመልሰውም፤ ቃል ኪዳን እንግባ!
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Saturday, May 18th, 2013

ከተክሌ የሻው
በዘመነ ቅኝ አገዛዝ፣ በአውሮፓውያን ቅኝ ገዥ ኃይሎች ያልተገዛች፣እንዲያውም የቅኝ ገዥዎችን ቅስም በመስበር ነፃነቷንና ማንነቷን አስከብራ የኖረች ብቸኛ አገር ኢትዮጵያ መሆኗን የዓለም ታሪክ የሚያውቀው ብቻ ሳይሆን፣የሚደነቅበት ጭምር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዘመነ ቅኝ አገዛዝ ቀደም ባሉት ዓመታትም የግዛት ማስፋፋት ዓላማን ተከትለው ኢትዮጵያን በተፅዕኖዋቸው ሥር ለማድረግ የተነሱ ወራሪና ተስፋፊ ኃይሎችን ማለትም ፡-
• ከ1521 እስከ 1535 በቱርኮች ሁለንተናዊ ትብብር ብቻ ሳይሆን፣ በቀጥተኛ የጦር መሣሪያና የሰለጠነ ወታደር ለግራኝ መሐመድ በማቅረብ አገሪቱን በቱርኮች አገዛዝ ሥር ለማዋል የተደረገውን እልህ አስጨራሽ ጦርነት፣
• በ1571 የቱርኮችን ቀጥተኛ ወረራ ድሆኖ ላይ፣
• በ1824፣ በ1826፣ በ1829፣ በ1830፣ በ1832፣ ግብፆችን በተደጋጋሚ በባሕረ-ነጋሽ እና በትግራይ ሜዳና ሸንተረሮች ላይ፣
• በ1867 እና በ1868 ግብፆችን ጉንዳጉንዲትና ጉራዕ ላይ፣
• በ1877 ድርቡሾችን ኩንፊት ላይ፤ የወራሪዎችና የተስፋፊዎችን አከርካሪ በመስበር አይደፈሬዎቹ አባቶቻችን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን አስከብረው ለትውልድ በኩራት ማሸጋገራቸውን እናውቃል፡፡ ዓለምም በዚህ አኩሪ የማንነት ተጋድሎ ኢትዮጵያውያንን ሲያደንቅና ሲያከብር መኖሩ ሐቅ ነው፡፡(ተክሌ የሻው፣2003፡16)
በኋላም በዘመነ ቅኝ አገዛዝ ጀግኖች አባቶቻችን በ1896 ጣሊያንን አምባላጌ፣ መቀሌና ዐድዋ ላይ፣ ከ1928 እስከ 1933 የጣሊያንን ፋሽስት ጦር በኢትዮጵያ ዱር ገደሎች ባካሄደው ተከታታይ የነፃነትና ማንነትን የማስከበር ጦርነት፣ በዚህም በከፈሉት ወድር የለሽ ሁለንተናዊ መስዋዕትነት አገራችን የቅኝ ገዥዎች ፍላጎት ተሸካሚ እንዳትሆንና ማንነቷን አስከብራ እንድትዘልቅ ሆኗል፡፡ ይህ የነፃነትና ማንነትን አስጠብቆ የመዝለቅ ተጋድሎ አገራችን ኢትዮጵያ “የነፃነት ምሽግ” የተሰኘ ውድ ስም እንድታተርፍ አድርጓታል፡፡ ይህን የነፃነት ምሽግነቷን በተመለከተ በ17ኛው ምዕተ ዓመት የኖረው ፖርቹጋላዊው የታሪክ ሊቅ ሉዊስ ኡሬታ ሐበሻ የሚለውን ቃል በአረብኛ፣በቱርክ፣ እና በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ትርጉሙ የባዕድ ንጉሥ ግዛት የማታውቅ ነፃና ራስ ገዝ ማለት ነው፤ኢትዮጵያ የምትባለውም ልክ እንደምነግራችሁ ናት፤(ሚሊዮን ነቅንቅ 1993፡13) በማለት የነፃነት ምሽግነቷን መስክሮላታል፡፡
ይህን ተከታታነት ጠብቆ የዘለቀን የነፃነት ምሽግነት የናይጀሪያ መሪ የነበሩት ናምዲ አዚክዊ “ኢትዮጵያ በዓለም ገጽ ከጠፉ የጥቁር ግዛቶች የተረፈች ብቸኛ የተስፋ ችቦ ነች፡፡ የአፍሪካውን አባቶችና አያቶች በዚህ አህጉር አቋቁመውት ለነበረው ሥርዓተ-መንግሥት ሀውልት ነች፡፡ ጓደኞቿ አገሮችና ወራሾቻቸው ከፖለቲካ ታሪክ ገጽ ከተሰረዙ በኋላ ፣ኢትዮጵያ በነፃነት መቆየቷ እጅግ የሚያስደንቅ ነው” (ሚሊዮን ነቅንቅ፣ 1993፡14) በማለት የአባቶቻችን የነፃነት ተጋድሎ አኩሪ ብቻ ሳይሆን፣ ለጥቁሮች ማንነት ምሳሌ መሆኗን ገልጠውታል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ጆርጅ ኤድመንድ ሄይንስ የተባሉ ጥቁር አሜሪካዊ የኢትዮጵያን በነፃነት ተጠብቆ መዝለቅ እንዲህ በማለት ገልጸውታየመል፡፡ “ኩሩዋና ነፃዋ ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ደም ላላቸው ጥቁሮች የነፃነት፣የራስ መቻል፣ከዘመናዊ ሥልጣኔ መልካም መልካሙን የመቅሰምና የንቃተ-ኅሊና ምልክት ሆናለች፡፡”( ሚሊዮን ነቅንቅ፣1993፡15) ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ኢትዮጵያ፣ ከቅኝ ገዥዎች ነፃ የወጡ የአፍሪካ አገሮች የባንዲራዎቻቸውን ቀለሞች አረናጓዴ፣ ብጫና ቀይ ቀለማት ያደረጉት፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት( የአፍሪካ ኅብረት) እና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽ/ቤቶች አዲስ አበባ ላይ የተመሠረቱትና ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና ለመባል ያበቃት ነፃተቷን ጠብቃ በማቆየት ለአፍሪካ የነፃነት ተጋዮች ባበረከተችው የቁሳቁስና የሞራል ድጋፍ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ያለፈ መልካምሙና አኩሪው ታሪካችን ነው፡፡
ቅኝ ገዥ ኃይሎች የቅኝ ግዛት ዓላማቸውን ያስፋፉት በቀጥተኛ የኃይል ወረራና ጦርነት ብቻ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እንዳውም አብዛኛዎቹን አገሮች በቅኝ ግዛታቸው ቀንበር ሥር ያዋሉዋቸው፣ የየአካባቢውን የጎሣና የነገድ መሪዎችን በመናኛ ጥቅማ-ጥቅሞች በመደለል መሬቶችን በመግዛት የራሳቸው በማድረግ፣ሃይመኖታቸውን በማስቀየርና በአገር አሳሽነት ስም በመግባት የየአገሮቹን ባህል፣ቋንቋና ታሪክ በማጥናት ሥልጣኔን እናስፋፋለን በሚል ሽፋን ማንነታቸውን አስጥለው የሌላቸውንና ከእነርሱም ጋር ሊዋሐድ የማይችል ማንነትን እንዲላበሱ በማድረግ እንደሆነ የቅኝ አገዛዝ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ለዚህ አባባል ታማኒነት የቀድሞው የኬንያ መሪና የኬንያ የነፃነት አባት የሚባሉት ጆሞ ኬንያታ “ማኦ ማኦ” በተሰኘው የነፃነት እንቅስቃሴ ወቅት የተናገሩትን መጥቅሱ ተገቢ ነው፡፡ “እንግሊዞች ወደ አገራችን ሲመጡ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው መጡ፤ እነርሱም ዐይናችን ጨፍነን፣ አንገታችን ደፍተን እንድንጸልይ አስተማሩን፣አንገታችን ደፍተን ዐይናችን ጨፍነን ከጸለይን በኋላ ፣ዐይናችን ገልጠን አንገታችን ስናቀና፣ መጽሐፍ ቅዱሱ የኛ፣መሬቱ የነርሱ ሆኖ አገኘነው፡፡” ሲሉ የተናገሩት ቅኝ ገዥዎች በምን መልክ ሕዝቦችን ቅኝ ተገዥ እንዳደረጓቸው በተጨባጭ ያስረዳል፡፡ አገላለጹ ዕውነኛውን የአፍሪካን የቅኝ አያያዝ ስልት በሚገባ ያሳያል፡፡
በርካታ ቁጥር ያላቸው የአፍሪካ አገሮች በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር የወደቁት ከፍሲል ጆሞ ኬንያታ በገለጡትና የጎሣ መሪዎቹ በሸጡት መሬት ላይ በመቆናጠጥ ይዞታቸውን በልዩ ልዩ መንገዶች በማስፋት ነው፡፡ በእኛም ታሪክ ጣሊያን ኤርትራን ለ50 ዓመታት በቅኝ ግዛት እንዲይዛትና ለተከታታዮቹ የዐድዋና የአምስቱ አመታት የአርበኝነት ትግል የዳረገን ፣ሡልጣን ኢብራሂም የተባለው የአፋር ባላባት አሰብን ለጣሊያን የቅኝ ገዥ አስፋፊ ቡድን በመሸጡና ቅኝ ገዥው ኃይል መላዋ ኢትዮጵያን በቁጥጥሩ ሥር ሊያውልበት የሚችልበትን መንገድ ያመቻቸ መቆናጠጫ መሬት በማግኘቱ እንደሆነ በግልጽ ይታወቃል፡፡
በሌላም በኩል ኢትዮጵያውያን ከፍ ሲል በተጠቀሱት በቀጥታ ወረራ ቅኝ ተገዥ ሊያደርጓቸው የቃጡትን ኃይሎች ድል ነስተው የመለሷቸውን ያህል፣በሃማኖት፣ በአገር አሳሽነትና በሥልጣኔ አስፋፊነት ስም የፍላጎታቸው ተገዥዎች ሊያደርጓቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው የመጡ አስመሳይ ወንጌላውያንን፣ አባቶቻችን “ መጽሐፍ ቅዱሱም ሊቃውንቱም በአገራችን አሉ፤ ከእናንተ የምንሻው የዕደጥበብ ሙያተኞችን ነው፤” በማለት መልሰዋቸዋል፡፡ ይኸም ብቻ አይደለም፡፡ የክርስቶስን መወለድና መጠመቅ ያልሰሙትንና ሊሰሙም ያልፈለጉትን የአሕዛብ አገር ትታችሁ ከዚህ ምን ልትሠሩ መጣችሁ/የሚሉ አፋጣጭ ጥያቄዎችን በማቅረብ ለአስመሳይ ወንጌላውያኑ ከንቱ ስብከት ኅሊናቸውን ቀርቶ ጆሮአቸውን ባለመስጠት ወደመጡበት እንዲመለሱ ማድረጋቸው ግልጽ ነው፡፡ በአገር አሳሽነትና በሥልጣኔ አስፋፊነት ስም የገቡትንም አገሪቱ ካሏት የከበሩ ነገሮች የተመረጡትን በገጸ-በረከትነት በመስጠት፣ የአገራቸውን አፈር ግን ከምንም በላይ የሚወዱትና በማንም ሊወሰድ እንደማይችል ለማሳየት በጫማቸው አፈር ይዘው እንዳይሄዱ እግራቸውን አሳጥበው እንደሸኙዋቸው ታሪካችን ያስረዳናል፡፡ እነዚህንና መሰል አባቶቻችን ለነፃነትና ማንነትን አስጠብቆ ለመዝለቅ ያደረጓቸው ተጋድሎዎች ከአካላዊና ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ተጠብቀን ፣ማንነታችንና ነፃነታችን አረጋግጠን እንደንቆይ እንዳደረጉን እንረዳለን፡፡ ይህ የታሪካችን እጅግ መልካሙ፣አስደናቂውና አንፀባራቂው ምዕራፍ ነው፡፡ ታሪኩ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን፣ መላውን የጥቁር ዘር ያኮራና ያስመካ ነው፡፡
ከዚህ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህን የነፃነት ምሳሌነትና የኢትዮጵያዊነት ምንነት መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቻቸውን ምን ያህል ጠብቀው ይዘዋቸዋል? የቱንስ ያህል አዳብረዋቸዋል? ጉዞ አቸው ወደ ፊት ነው ወይስ ወደ ኋላ? የሚሉት ናቸው፡፡ ለነዚህ ጥያቄዎች ተገቢ መልሶች ለመስጠት በአምስት ኣመቱ የአርበኝነት የተጋደሎ ዘመን የነበረውን የሕዝቡን አመለካከትና ከድል በኋላ የተፈጠረውን ትውልድ አመለካከት የተቀረጸባቸውን ነባራዊና ኅሊናዊ ሁኔታዎች በቅጡ ማገናዘብ ይጠይቃል፡፡ ለተነሱት ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ለማግኘት ዕውነት እንደሚባለው ኢትዮጵያውያን የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች ሆነናል? የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ መመለስ አለብን፡፡ አጭሩ መልስ አዎ! ኢትዮጵያውያን የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች ሆነናል የሚል ነው፡፡ ከዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ግን በምን በምን ምክንያቶች ለኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት እንድንዳረግ ያደረጉንን መሠረታዊ ምክንያቶች ማባራራቱ ብዥታ የሌለበት ግንዛቤ እንድንጨብጥ ይረዳናል፡፡
1. ከድል በኋላ የመንግሥቱ ቢሮክራሲ በስደተኛውና በባንዳው ቡድን ጥምር ጥምረት መዋቀር፤
ማንም የአርበኝነት ትግሉን ዘመን ታሪክ በአግባቡ የተከታተለ ሰው ሊረዳው እንደሚችል፣ያ ወቅት ኢትዮጵያውያን ከሦስት የተከፈሉበት ነበር፡፡ አርበኛ፣ስደተኛና ባንዳ፡፡ አርበኞቹ እንደጥንት አባቶቻቸው እምነታቸውን ያልለወጡ፣ማንነታቸወን ያልካዱ፣በዕለታዊ ጥቅማ-ጥቅሞች ባንዲራቸውንና አገራቸውን ያልካዱ፣ ሃይማኖታቸውን ያልለወጡ፣ኢትዮጵያ ወይ ሞቴ ብለው በቁርጠኝነት የቆሙና ነፃነታችንን ተጋድለው ያረጋገጡልን ናቸው፡፡ ከነዚህ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል ራስ አበበ አረጋይ፣ ደጃዝማች ደረሱ ዱኬ፣ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር፣ ራስ አሞራው ዉብነህ፣ደዝማች በላይ ዘለቀ፣ደጃዝማች ታደሰ ይማም፣ፊታውራሪ ሽፈራው ጌታሁን፣ደጃዝማች አድማሱ ብሩ፣ደጃዝማች ወንደወሰን ካሣ፣ደጃዝማች አበራ ካሣ፣ ራስ ሙሉጌታ ይገዙ፣ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ፣ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ብጹዕ አቡነ ሚካኤል እና አያሌ ስማቸው ተዘርዝሮ የማያልቅ፣ግን ስለተጋድሎአቸው ምንም ያልተባለላቸው ዕውነተኛ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል፡፡
ስደተኞች የሚባሉት በጠላት ከመገዛት መሰደድን የመረጡና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ ወጥተው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ኑረው፣ ከድል በኋላ ቀድመው ካገር የወጡትን ንጉሠ ነገሥቱን ተከትለው የገቡ ናቸው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የንጉሠ ነገሥቱ ቤተሰቦች፣መሣፍንቱና መኳንንቱ ማለትም ፡-
1. ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፣
2. ልዑል አልጋወራሽ አስፋው ወሰን ኃይለሥላሴ፣
3. ልዕልት ወለተ-እስራኤል ሥዩም የአልጋወራሹ ባለቤት (ከልጆቻቸው ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴና ከእግጋየሁ አስፋወሰን ጋር)
4. ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሴ ከአምሰት ልጆቻቸው ጋር፣
5. ልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ የሐረር መሥፍን፣
6. ልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ፣
7. ልዑል ሣህለሥላሴ ኃይለሥላሴ፣
8. ብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ፣
9. ልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ ፣
10. ወይዘሮ ጽጌ-ማርያም በሻህ የልዑል ራስ ካሣ ባለቤት፣ከሁለት ልጆቻቸው ጋር፣
11. ልዕልት የሻሽ ወርቅ ይልማ ፣
12. ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣
13. ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ፣
14. አቶ መኮንን ሀብተ ወልድ፣
15. አቶ አክሊሉ ሀብተወልድ፣
16. ደጃዝማች ከበደ ተሰማ፣
17. ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ፣
18. ልጅ አበበ አርኣያ፣
19. አባ ሓና ጅማ፣
20. ደጃዝማች ነሲቡ ዘማኔል፣
21. ደጃዝማች መኮንን እንዳልካቸው፣
22. ደጃዝማች አበበ ዳምጠው፣
23. ደጃዝማች ዐምደ ሚካኤል፣
24. ፊታውራሪ ታፈሰ ሀብተሚካኤል
25. ፊታውራሪ ተሰማ ባንቴ ፣ ወዘተ ያካተተ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡(ገብረወልድ እንድዳ ወርቅ 2000፣105-106)
ባንደው በቁጥሩ ከሁሉም ከፍተኛ የሆነ፣ ሁለመናውን ለጣሊያን ፍላጎት ያስገዛ፣የአንድነታችንና የማንነታችን አውራ ጠላት የነበረው ነው፡፡ ስም ከነበራቸው ታላላቅ ሰዎች ከሚባሉት ሁለንተናቸውን ለጣሊያን ሰጥተው ማንነታችን በእጅጉ ከጎዱት ባንዳዎች መካከል ለአብነት፣ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት፣ራስ ሥዩም መንገሻ፣ደጃዝማች አያሌው ብሩ፣ደጃዝማች ኃይለሥላሴ ጉግሳ፣አቶ አምደ ሚካኤል ደሳለኝ፣አቶ አድማሱ ረታ፣አቶ ለማ ወልደ ገብርኤል፣አቶ ተፈሪ ሻውል፣ አቶ ገብረ ወልድ እንግዳ ወርቅ፣ብላት ዳዊት እቁበ እግዚእ፣ደጃዝማች አስፍሃ ወልደ ሚካኤል፣ጄኔራል መኮንን ደነቀ፣አቶ ብርሃኑ ድንቄ፣ሻለቃ አሰፋ ለማ፣ሼክ አል ሆጆሌ፣ሡልጣን መሐመድ ሃንፋሪ፣ ደጃዝማች ሆሣዕና ጆቴ፣ ደጃዝማች ዮሐንስ ጆቴ፣ሡልጣን አብዱላሂ ጂፋር፣ሡልጣን አባ ጆቢር አብዱላሂ፣ ራስ ጌታቸው ናደው፣ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረየሱስ፣አቶ ይልማ ዴሬሳ፣ብላታ አየለ ገብሬ፣ነጋድራስ ወዳጆ አሊ፣አቡነ አብርሃ፣አቡነ ይስሐቅ ( ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደ-ማርያም፣2005፣16) ደጃዝማች እጅጉ አያሌው፣ ፊታውራሪ ነገደ ዘገዬ እና አያሌ ሆድ አደር ባንዳዎች ወዘተ ይገኙበታል፡፡ ልብ በሉ! እነዚህ ሰዎች ቀደም ሲል የአገርና የሕዝብ ሚስጢሮችን ለጣሊያን በመንገር የማንነታችን አሻራዎች እንዲወድሙ ያደረጉ፣አርበኞች የሚወጡ የሚገቡበትን በመሰለል ያስገደሉ፣ ያሳሰሩ፣የአገርና የሕዝብ ሀብት ያዘረፉ፣ማንነታችን ጥላሸት የቀቡ ፣ ሕዝቡ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ክዶ ጣሊናዊ ማንነትን እንዲላበስ ኅሊናዊ ጫና ሲያሳድሩ የነበሩ የአገርና የትውልድ አውራ ጠላቶች ናቸው፡፡
ከዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ቁምነገር አለ፡፡ ባንዳዎች ወደውና ፈቅደው ነፃነታቸውንና መብታቸውን ለቅኝ ገዥው ኃይል የሰጡ ናቸው፡፡ ማንነታቸውን ክደው የቅኝ ገዥውን ሁለንተናዊ ማንነት ለመላበስ የጣሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ከወራሪው ኃይል በላይ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጠላቶች ናቸው፡፡ የባንዳው ኃይል፣ለፋሽስቱ ቢሮክራሲ በመረጃ አቅርቦት፣በተላላኪነት፣በሹፌርነት፣ በዘበኝነት፣በቤት ውስጥ አሽከርነት፣በአስተርጓሚነት በመሳሰሉት ሥራዎች ተሰማርቶ ይሠራ የነበር ስለነበር፣ የማንበብና የመጻፍ፣ልምድና ችሎታ እንዲያዳብር አድርጎታል፡፡ እግረ መንገዱንም ከአማርኛና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች በተጨማሪ የቅኝ ገዥ ቋንቋዎችን የማንበብና የመጻፍ ዕውቀት እንዲጨብጥ ሆኗል፡፡ ይህም የዘመናዊ ቢሮክራሲን አሠራር እንዲለማመድ በር የከፈተለት መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ስደተኛው ቡድን ተሰዶ በኖረባቸው አገሮች የዘመናዊ ቢሮክራሲን አሠራርና ሌሎች ቋንቋዎችን በተለይም እንግሊዝኛና ፈረንሣይኛን ቋንቋዎች እንዲውቅ ሁኔታዎች ግድ እንዳሉት እንረዳለን፡፡
ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ቢሮክራሲ ሲዋቀር፣ ላገር የሠሩ ሰዎች መሾም መሸለም ሲገባቸው፣በአገር ላይ የሠሩት ከሐዲዎቹና ባንዳዎቹ ተሹዋሚና ተሸላሚ ሆኑ፡፡ወሳኝ ለሆኑት ሕግ የማውጣት፣ሕግ የመተርጎምና የወጡትን ሕጎች የማስፈጸም ኃላፊነቶችን የሚረከቡ ሰዎች መመዘኛ ለኢትዮጵያዊነት ያለ ታማኝነት፣ በነፃነት ትግሉ ዘመን የተከፈለ መስዋዕትነት ሳይሆን፣ ከዘመናዊ ቢሮክራሲ ጋር ያለው ቁርኝት፣የውጭ አገር ቋንቋና የጽሕፈት ችሎታ ሆነው ቀረቡ፡፡ በዚህም የተነሳ ስደተኛውና ባንዳው ቡድን የአንበሣ ድርሻውን ወሰደ፡፡ የነፃነት ታጋዩና ዕውነተኛው ኢትዮጵዊ የበለል ተጣለ፡፡ ይህ ድርጊት ያሳዘናቸው አርበኞችም ደርጊቱን እንዲህ ሲሉ ገለጡት፡፡
አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ፤
ዳር ድንበር ጠብቀን ባቆየናት አገር፣
ውጤቱ ተረፈን ባፍንጫ መናገር፤
ይህ ስደተኛና ባንዳ ቡድን የቀሰመው ዕውቀት ከኢትዮጵያዊነት ዕሴቶች ፣ማንነት፣ባህል፣ቋንቋ፣ሃይማኖትና አጠቃላይ ሁለንተናዊ መስተጋብር ጋር ምንም ዓይነት ቁርኝት የሌለው ስለነበር የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከማንነት የሚያፋታ እንጂ፣ማንነትን የሚያዳብር ባለመሆኑ ትውልዱን ቀስ በቀስ ወደ ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ቦይ አንኮልኩሎ እንዳስገባው እናያለን፡፡ ወሳኝ የመንግሥት መዋቅሮች በባንዳዎችና በስደተኞች መያዝ፣ ባንዳነትና አገር ክዳት ወንጀል መሆኑ ቀርቶ እንደመልካም ሥራ እንዲታይ አስገደደ፡፡ ይህም በተተኪው ትውልድ አመለካካት ላይ አርበኝነት፣ለማንነት መቆምና መታግለ እርባናቢስ እንደሆነ፣በኅብረተሰቡ ውስጥ ክብርና ሞገስ የማያስቸር፣ በአንፃሩ ከሐዲነትና ባንዳነት አሹአሚና አሸላሚ መሆኑን በተጨባጭ እንዲያይ በማድረጉ ኅሊናውን ለቅኝ ተገዥነት ማመቻቸት እንዳለበት በአገሪቱ የሚካሄዱት ድርጊቶች ጠጣር ዕውነት ሆነው ታዩት፡፡በአገሪቱና በሕዝቡ አንጡራ ሀብት ወንጀለኞችና ባንዳዎች እንደፈለጉ ሲናኙበት፣ ቤተሰባቸውን ሲያስተምሩበት፣ ልጆቻቸውን ለቀጣዩ ትውልድ ገዥነት ሲያሰለጥኑበት፣ አርበኛው የበይ ተመልካች መሆኑንን በገሐድ አየ፡፡ የአርበኛው ልጆች በአባቶቻቸው ተጋድሎ የሚያፍሩ እንጂ፣ የሚመኩና የሚኮሩ እንዳይሆን ተመለከተ፡፡ ባንዳነት ማሳፈሩ ቀርቶ መኩሪያ ሆነ፡፡ አርበኝነትና አገር ወዳድነት አዋራጅና የደህነት መገለጫ ሆኖ ታዬ፡፡ ይህ ሁኔታ ትውልዱ ባንዳነትን እንደተገቢ ተግባር እንዲቆጥረው ገሐዳዊ ምሳሌ ሆኖ ቀረበ፡፡ ውጤቱም ከድል በኋላ የተዋቀረው የንጉሠ ነገሥቱ አስተዳደራዊ መዋቅርና በመዋቅሩ የተካተቱ ሰዎች ማንነት ተከታዩን ትውልድ የኅሊና ቅኝ ተገዥነትን እንዲለማመድ አመቻቸው፡፡
2. የትምህርት ፖሊስ በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ አለመመሥረት፣
በስደተኛውና በባንዳ የተዋቀረው የንጉሠ ነገሥቱ ቢሮክራሲያዊ አስተዳደር የቀየሰው የትምህርት ፖሊሲ ትውልዱ በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ላይ ተመሥርቶ፣ በሂሳብ ዕውቀት ላይ መሠረቱን የጣለ፣ለምርምርና አዳዲስ ቴክኖሎጂን አፍላቂ በሚሆንበት መልኩ እንዲሆን አላደረገም፡፡ የትምህርት ፖሊሲው ትውልዱን ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ፈጽሞ የሚያፋታ፣የራሱን ማንነት እየናቀ የሌሎችን አድናቂና ተከታይ በሚያደርግ መልኩ የተቀየሰ ነበር፡፡ ሥርዓተ ትምህርቱ ለፈረንሣና ለእንግሊዝኛ ቋንቋዎች፣እንዲሁም ለማኅበራዊ ሣይንሶች ልዩ ትኩረት የሰጠና ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህልና ለዘመናት ይዛው ከመጣችው አሠራር ጋር የማይገናኝ ስለነበር፣ ትውልዱ ውጭ አምላኪና የራሱን ማንነት ሳያውቀው ቀስበቀስ እያወለቀ እንዲጥል ሠፊ በር ከፈተለት፡፡ ይህም በመሆኑ፣ “የዐዳም ቋንቋ እንደሆነ የሚነገርለት፣እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደተነጋገረበት ብዙ” የሚባልለት የግዕዝ ቋንቋ ከትምህርት ቤትና ከመንግሥት ብቻ ሳይሆን በቤተክረስቲያንም አገልግሎት ሊሰጥበት ከማይቻልበት ደረጃ ተደሷል፡፡ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣ባህል፣ሥነ-ምግባርና አመለካከት በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ባለመካተቱ ፣ወጣቱ ትውልድ የእርሱ የሆነውን ወርቁን ነገር እየጣለ፣ የርሱ ያልሆነውን ኩበቱን ሙጭጭ ብሎ እንዲያዝ ተነገረው፡፡የኢትዮጵያዊነት ልዩ መታወቂያ የሆነው የጽሑፍ ቋንቋ አማርኛ ቀስበቀስ ከትምህርት መገናኛነቱ እንዲወጣ ተደረ ፡፡ የትምህርቱ ይዘት የኢትዮጵያን ባህል፣ታሪክ፣መልከዐ-ምድር፣ቋንቋ፣ ሥነ-ልቦና፣የሕዝብ አደረጃጀትና የአጠቃላይ ማኅበራዊ ግንኙነት ምንነትን ፈጽሞ ግንዛቤ ያስገባ አልነበረም፡፡
የታሪክ ትምህርት ስለግሪክ፣ስለአውሮፓ፣ስለሮም ፣ስለሜሶፖታሚያ፣ስለግብፅ፣ ወዘተ እንጂ፣ ስለኛው ረጅምና አኩሪ ታሪክቻችን፣ስለአርበኞቻችን ማንነትና ተጋድሎ የሚያወሱ ትምህርቶች ለትውልዱ አይሰጡም ነበር፡፡አባቶቻችን ከፖራቹጋሎች፣ከቱርኮች፣ከመሐዲስቶች፣ከግብፆች፣ ከጣሊያኖችና ከአውሮፓ ኃያላን ጋር ስላደረጉት የነፃነትና ማንነትን የማስከበር ተጋድሎ፣የተጋድሎው መሪ ተዋንያን ማንነት ትውልዱ እነዲያወቅ አልተደረገም፡፡ የነካሌብን፣የነኢዛናን፣የነላሊበላን፣ የነዘርዐ-ያዕቆብ፣የነሠርጸድንግል፣የነዐምደ-ጽዮን፣የነልብነድንግል፣የነገላውዲዮስ፣የነቴዎድሮስ፤የነዮሐንስና የነምኒልክ ወዘተ ፖለቲካዊና ወታደራዊ የአመራር ጥበብና ችሎታ፣የነገብርዬ፣የነአሉላ አባነጋ፣የነሀብተጊዮርጊስ ዲነግዲ፣የነገበየሁ ተክሌ የነኮሎኔል አቢሳ አጋ የጦር ሥልትን ዲፕሎማሲያዊ ጥበብ ወዘተ ታሪክ ትውልዱ በቅጡ እንዲያውቀውና እንዲመካበት አልተደረገም፡፡ እንኳን ያን ጊዜ ዛሬም የለም፡፡
የመልከዐ-ምድሩ(ጂኦግራፊ) ትምህርት ስለዓለምና አሕጉሮች እንጂ ፣ስለኢትዮጵያ ወንዞችና ተራሮች፣ ማዕድን፣የውኃ ሀብት፣ የአየር ጠባይ፣የእንስሳት ሀብት፣የመንግሥት ኃላፊነትና ግዴታ፣የሕዝብ መብትና ግዴታ፣ ወዘተ በየደረጃው የሚሰጡ አልነበረም፡፡ የትምህርቱ አጠቃላይ ዓላማ ወደ ውጭ የሚያይ እንጂ፣ ወደ ውስጥ ማሳየት የማይችል ስለነበር፣ትውልዱ ወደ ውጭ እንጂ ወደ ውስጥ እንዲመለከት አላስቻለውም፡፡ ወደ ውጭ መመልከት ደግም፣ማንነትን ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ሌላ ማንነትን ለመላበስ የሚያመቻች በገዛ ፈቃድ ለቅኝ ተገዥነት ራስን ማመቻቸት እንደሆነ በተጨባጭ እያን ነው፡፡ በትምህርቱ ውስጥ የሚካተቱት የመልካም ነገሮች ማመላከቻዎች ኢትዮጵያዊ አለመሆን፣ትውልዱ የራሱ የሆነ፣የተሻለ ነገር እንዳለው ሊገነዘብ ባለመቻሉ፣በተነገረው ምሳሌና ማነፃፀሪያ መሠረት አሻግሮ እንዲመለከት ግድ አለው፡፡ በመሆኑም የ1960 ዎቹ ለውጥ ናፋቂ የነበረው ትውልድ የሽምቅ ውጊያን ከቴዎድሮስ ፣ከምኒልክ፣ከዮሐንስ ከነአሉላ፣ገብርዬ አቢሳ አጋነ፣ አበበ አረጋይ ወዘተ ለመቅሰም ባለመቻሉ የተከተለው የማኦን፣የሆቺሚንንና የቼጉቬራን የሽምቅ ውጊያ ስልት ነበር፡፡ የዘመረውም “ፋኖ ተሰማራ ፣እንደነ ሆቺሚን እንደቼጉቬራ” ሲል ነበር፡፡ የአገሩን ፋኖዎች ልዩ ዕውቀትና ችሎታቸውን ባለማወቁ በቃል በተነገረውና ተጽፎ ባገኛቸው በውጭዎቹ ሰዎች ማንነት ተከታይ ለማፍራት ቀሰቀሰባቸው፡፡ይህም ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት ራሱን እንዲያመቻች እንዳደረገው መገንዘብ ይቻላል፡
በሌላ በኩል፣ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጪ የሚላኩት ፣ ወጥ በሆነ መንገድ ላገሪቱ የሚያስፈልጓትን ሙያተኞች ከራሷ ፍላጎት አኳያ በምትፈልገው የዕውቀት መሥክ የሚሰለጥኑ አልነበሩም፡፡ የሚሰለጥኑት በየግለሰቦቹ ፍላጎትና የትምህርቱን ዕድል በፈቀደው መንግሥት ፕሮግራም መሠረት እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህም በመሆኑ፣ሰልጣኞቹ የሚሰለጥኑት ከአገራቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ግንኙነት በሌላቸው፣የትምህርቱን ዕድል በሰጡ አገሮቸ የትምህርት ፖሊሲ ላይ የተመሠረቱና ከነዚያ አገሮች ታሪክና ባህል፣እንዲሁም ሊደርሱበት ወደ አለሙት ግብ ሊያመራ በሚችል መልኩ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ሠልጣኞቹ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ ተመሳሳይ የፖሊሲ አቅጣጫ ለመንደፍም ሆነ ለማስተማር ግብቡ አልነበሩም፡፡ ፈረንሣይ፣ምዕራብ ጀርመን፣እንግሊዝ፣አሜሪካ፣ሶቭዬት ኅብረት፣ምሥራቅ ጀርመን፣ቼኮዝሎቫኪያ፣ቡልጋሪያ፣ሀንጋሪ፣ዩጎዝላቪያ፣ጣሊያን፣ ወዘተ የተማሩት ለየቅል ቆሙ፡፡ ልዩነታቸው በተማሩበት አገር ብቻ ሣይሆን፣በተማሩበት ተቋምና በተማሩት የትምህርት ዓይነት ጭምር ሆነ፡፡ ይህ ልዩነት ደግሞ እንደ ኢትዮጵያዊነት፣ከኢትዮጵያዊነት ዕሴቶች ተነስቶ፣ኢትዮጵያ ጠቀም ወደ ሆነ አስተሳሰብ ለማምራት መንገዱን ዘጋው፡፡ ከዚህ ላይ ርዕዮተዓለማዊ ልዩነት ተርከፍክፎበት ከድል በኋላ ቀለም የቆጠረው ትውልድ ኢትዮጵያን በየራሱ ፍላጎት በመሳል፣ “እኔ ለኢትዮጵያ የተሻለ አስባለሁ፣ከእኔ ውጭ ያሉት ትክክል አይደሉም” ብለው እንዲያስቡና እርስ በራሱ እንዲጠፋፋ መንገዱን አመቻቸ፡፡ የመጠፋፋቱ ግብግብ በከፋ መልኩ መቀጠል ትውልዱ የእርሱነቱ መታወቂያ የሆነች አገሩን እየሸሸ በመገደድና በመውደድ ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት ራሱን እንደዳረገ በገሀድ እያየን ነው፡፡
3. የአዲስ ገብ ሃይማኖቶች መሥፋፋት፣
ማንም የኢትዮጵያን ሕዝብ ታሪክ የመረመረ ሰው ሊገነዘበው እንደሚችል፣የሕዝቡ መሠረታዊ ሃይማኖቶች፣ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፣ሱኒ እስልምና፣አይሁድና ባህላዊ እምነቶች ናቸው፡፡ እንዚህ ሃይማኖቶች አንዱ በሌላው ውስጥ ያለ በመሆኑ፣ኢትዮጵያዊ ማንነትን ፣የአገርና የቤተሰብ ፍቅር፣ነፃነትና አልበገርም ባነይነት፣ በኢትዮጵያዊነት መመካትና መኩራት ልዩ ዕሴቶቻቸው አድርገው የተቀበሉና ለነርሱም ዳብሮ መቀጠል የየእምነቶቹ ተከታዮች አይከፍሉ መስዋዕትነት በጋራ እየከፈሉ የኖሩ መሆኑ ግልጥ ነው፡፡
ከድል ኋላ “ሃይማኖት የግል ነው፣ አገር የጋራ ነው “ በሚለው የንጉሠ ነገሥቱ የሃይማኖት ፖሊሲ ምክንያት በርካታ አዳዲስ ሃይማኖቶች ወደ አገራችን እንዲገቡ ሠፊ በር ከፈቱ፡፡ ቀደም ሲል ገብተው የነበሩትም ተልዕኮአቸውን ያላንዳች ሥጋት እንዲወጡ ሁኔታዎች የበለጠ ተመቻቸላቸው፡፡ “ገንፎ ሲያምርበት ተንከባሎ ከቅቤ ማሰሮ ይገባል” እንደሚባለው ሆኖ፣ ቀደም ሲል በሃይማኖት፣በአገር አሳሽነት፣በመሬት ግዥና በቀጥታ ወረራ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለማድረግ ያልቻሉ ኃይሎች ፣ ሕዝቡ ወዶና ፈቅዶ የኅሊና ቅኝ ተገዥ የሚሆንበት መንገድ በስፋት ተከፈተላቸው፡፡ ንጉሠ-ነገሥቱ ኢትዮጵዊነትን መጠበቅ የሚያስችል ስልት ሳይነድፉ፣ በሃይመኖት ነፃነት ስም ትውልዱ ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት የሚመቻችበትን መንገድ በስፋት ከፈቱ፡፡ በመሆኑም በርካታ የሃይማኖት ድርጅቶች ወደ አገራችን ገቡ፡፡
አዲስ ገቦቹ ሃይማኖቶች ቀደም ሲል ቅኝ ግዛትን ለማስፋፋት በአፍሪካና በእስያ የተሠማሩ ስለነበሩ የተጠናከ መዋቅር፣በከፍተኛ የመረጃና የሰው ኃይል የተደራጁ ከመሆናቸውም በላይ፣ የቅኝ ገዥ ኃይሎች መዋዕለ ንዋይ በገፍ የሚጎርፍላቸው በመሆኑ ነባሮቹ ኢትዮጵያዊ ሃይማኖቶች ከሚሰጡት መንፈሳዊና ሥጋዊ አገልግሎቶች በላይ ለሕዝቡ በስፋት መስጠት ጀመሩ፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው በሙዚቃ ፣በጭብጨባና በዳንስ የታጀበ በመሆኑ የአድማጮችን ኅሊና በቀላሉ ሳበ፡፡ ከመንፈሳዊ ትምህርቱ፣ዝማሬውና ሽብሸባው በተጓዳኝ፣ የአውሮፓን ታሪክና ስልጣኔ፣ ሕዝቡ የደረሰበትን የዕደገት ደረጃ የሚያሳዩ ፊልሞችን በብዛት አሰራጩ፡፡ ኢትጵያውያንን የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች የሚያደርጉበትን ሁነኛ መሣሪያ የሆነውን የዘመናዊ ትምህርትን ከሃይማኖት ጋር አቀላቅለው የሚያስተምሩበትን የትምህርት ሥርዓት ዘረጉ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በነፃና አልፎ አልፎም በተመጣጣኝ ክፍያ የሕክምና አገልግሎት መሥጠት ጀመሩ፡፡ ዘወትር እሑድ የዕለት ምግብ አጥተው ለሚራቡ ሰዎች የምግብ ፕሮግራም ዘርግተው መመገብ የዘወትር ተግባራቸው አድርገው ያዙት፡፡ የዓመት ልብስ ለሌላቸው የአውሮፓና የአሜሪካ ልባሾችን እየሰበሰቡ በነፃ በማደል እርቃናቸውን እንዲከልሉ አደረጉ፡፡ “ይህም የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል” እንዲሉ ሆኖ፣የበርካታ ሰዎችን ኅሊና እንዲገዙ አስቻላቸው፡፡
ነባሮቹ ሃይማኖቶች አማኙ የሚከተላቸው በመወለድ እንጂ፣በመማር ካለመሆኑም ሌላ፣ሃማኖቶቹ እንዲስፋፉ የሚያስችል የአደረጃጃት፣የሰው፣ የገንዘብና በዕወቀት ላይ የተመሠረተ የመረጃ ፍሰትና ልውውጥ አቅም የሌላቸው በመሆኑ ፣ከአዲስ ገቢዎቹ ሃማኖቶች ጋር ከታሪክ ርዝመት አንፃር ሲመዘን አቻ ለመሆነ ቀርቶ ለመከተል እንኳ እንዳልቻሉ ሁኔታዎች ያሳሉ፡፡
የአዲስ ገብ ሃይማኖቶቹ መሠረታዊ ተልዕኮ ሕዝቡ የኢትዮጵያዊነት ማንነቱ መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቹን ቀስ በቀስ በፈቃዱ አውልቆ ጥሎ የአውሮፓዊ ማንነትን ጥብቆ እንዲያጠልቅ በመሆኑ፣ባቋቋሙዋቸው ትምህርት ቤቶች የተማሩትንና ብሩኅ አዕምሮ ያላቸውን በስኮላር ሽፕ መልክ ወደ አውሮፓና አሜሪካ በመላክ አውሮፓዊና አሜሪካዊ አስተሳሰብና አመለካከል አዳብረውና ይዘው እንዲመለሱና መልስው ወገናቸውን በነርሱ ሥር እንዲሰለፍ እንዲያደርጉ አደራጁዋቸው፡፡ ”እስ በሱ ሥጋን በኩበት ጠበሱ” እንዲሉ፣መልሰው የገዛ ወገኖቻቸውን የራሳቸውን ማንነት ትተው ሌላ ማንነትን እንዲላበሱ እንዲሰብኩና እንዲያስተምሩ አደረጉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በከፈቱዋቸው የጤና ጣቢያዎች የቀጠሩዋቸውን ሰዎች ወደ ውጭ በመላክ ህክምናን ከሃይማኖት ዕውቀት ጋር አጣምረው የሚሠሩ ሰባኪና ሐኪሞችን በብዛት አሰለጠኑ፡፡ በዚህ የተጠናከረ ሂደት የደቡብ፣የምዕራብ፣የደቡብ ምዕራብና የመሀል ኢትዮጵያ ነዋሪ ነባር ሃይማኖቱን እየተዎ የአዲስ ገብ ሃይማኖቶች ተከታይ ሆነ፡፡ ይህም ያለጥርጥር ኢትጵያዊው ኅሊናውን ለቅኝ ተገዥነት ወዶ እንዲያመቻች እንዳደረገው መገንዘብ ይቻላል፡፡ የተግንጣይ ብሔርተኞች ድርጅቶች መሪዎች ተኮትኩተው ያደጉት በነዚህ የአዲስ ገብ ሃይማኖቶች ባቋቋሟቸው ትምህርት ቤቶች መሆኑን ልብ ስንል፣እነዚህ ሃይማኖቶች የቱን ያህል ሕዝቡን ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት እንዳመቻቹት እንረዳለን፡፡
4. የኢትዮጵያ አብዮት ያስከተለው የኅሊና ስብራት፣
ሚሽነሪዎቹ በቂ ተከታይ ማግኘታቸውን ካረጋገጡ በኋላ፣ሕዝቡ በኅሊና ቅኝ ተገዥነት ሥር ወዶና ፈቅዶ ለዘመናት መኖር የሚችለው የትኞቹን ተቋሞች ብናፈርስ ነው/ እንዚህን መዋቅሮችስ እንዴት እናፈርሳለን/ በሚል ጥናት ላይ ተሰማሩ፡፡ በዚህ ጥናታቸውም የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መሠረትና ምሰሶ የሆኑ ተቋሞችን ምንነት ለይተው በማወቅ ተቋሞቹ ሊፈርሱባቸው የሚችሉባቸውን መንገዶች የሚያሳዩ መጽሐፍትን በጥናትና ምርምር ስም ለዓለም አሰራጩ፡፡ የሃይማኖት ተከታዮቻቸውም እንዚህን በኢትዮጵያ መሠረታዊ ጠላቶች ማር ቀብተው ያዘጋጁዋቸውን በርዞች እንደ ደረቅ ሐቅ በመውሰድ ያላንዳች ማመዛዘንና አድሮ እየው ጥያቄ ዋጡዋቸው፡፡
ሚሽነሪዎቹ ባደረጉት ጥናት የኢትዮጵያዊነት መሠረት የሆኑት ተቋሞች “የሥልጣን ምንጭና የአንድነት ምልክት የሆነ ዘውዳዊ ሥርዓት፣የዘውዳዊ ሥርዓቱ ርዕዮተ-ዓለማዊ ክንድ የሆነ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት እና ራሱን በቋንቋ ትስስር ያላደራጀ፣ በመሠረታዊ አደረጀደጀት ደረጃ በአጥቢያ ቤተ እምነቶች ዙሪያ የሚደራጅ፤ከፍ ሲል በአስተዳደራዊ ክልሎቸ ማንነቱን የሚገልጥ፣በሠፊዋ ኢትዮጵያ በበቂ መጠን ተሰራጭቶ የሚኖርና በኢትዮጵያዊነት በጽኑ የሚያምን፣በተፈጥሮው ተዋጊና የአገር ዘብ የሆነ ዐማራ የተሰኘ ነገድ እንደሆኑ ተረዱ፡፡ ኢትዮጵያዊነት ብሔርተኝነትም ሲባል የዐማረው እንጂ፣የሌሎችን ነገዶች የሚጨምር አይለም፣ኢትዮጵያዊነት በሌሎች ላይ ዐማራው የጫነባቸው ዕዳ ነው ሲሉም ጨመሩበት፡፡” እነዚህ ተቋሞች ካልጠፉ ወይም በሕዝቡ ላይ የሚያሳድሩት ሁለንተናዊ ተፅዕኖ ካልተወገደ ኢትዮጵያን በውጭ ኃይሎች ሥር ለማዋል እንደማቻል እርግጠኛ ሆኑ፡፡
ተከታዩ ሥራቸው እንዚህን ተቋሞች እንዴት ማጥፋት ይቻላል? በሚለው ዙሪያ ወጥሮ መሥራት ነበር፡፡ ባደረጉት ጥረትም የነርሱን ዓላማ የሚጋሩ ብቻ ሳይሆን፣ብዙ ማይል ርቀው የኢትዮጵያን የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ በመቶ ዓመት የገደቡ ብሔርተኛ ግለሰቦችንና በሚሽነሪ ትምህርት ቤቶች በፀረ ኢትዮጵያነት ተኮተረኩተው ያደጉ በርካታ ሰዎችን አገኙ፡፡ እንዚህን ግለሰቦች በተለያዩ መሰባሰቢያ መድረኮች ስም እንዲደራጁና የሰው ኃይል እንዲያሰባስቡ፤ፍላጎታቸውን በየጸሎት ቤቱና ባመቻቸው አጋጣሚ ሁሉ እንዲያሰራጩ አበረታቱ፡፡የኦነግ መሠረት የሆነው የሜጫና ቱሉማ ማኅበር የተመሠረተው በዚህ መልክ ሲሆን፣ የኦነግ መሪዎችም ወለጋ ጊንቢ አውራጃ ውስጥ በተከፈተ የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮችና ተማሪዎች በነበሩ ግለሰቦች መሆኑን ስንገነዘብ የአዲስ ገብ ሃማኖቶች ተልዕኮ ምን እንደነበር በቅጡ ልንገነዘብ እንችልለን፡፡ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ድርጅት የተመሠረተውም በትግራይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበር ስም እንደሆነ ይታወቃል፡፡የወያኔ መሥራቾችም በዐድዋ አውራጃ ተወላጆች መያዝ ፣ ዐድዋ ከተማ ውስጥ ከነበረ የሚሽነሪ ትምህርት ቤት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ እንደነበር እንረዳለን፡፡ ከሁሉም በላይ መያዝ ያለበት መሠረታዊ ጉዳይ የብሔረሰብ ጥያቄ አንስተው የተደራጁ ብሔርተኛ ሰዎች የባንዳ ልጆች መሆናቸው ነው፡፡ሚሽነሪዎቹ በዚህ መልክ አደራጅተው ኢትዮጵያን ለመናድ በሚጥሩበት ወቅት ፣ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ከ1960ዎቹ መባቻ ጀምሮ ማርክሳዊ-ሌኒናዊ ርዕዮተዓለምን በተቀበሉ ቡድኖች አቀንቃኝነት የሚያራምዱት የፍትሕና የዲሞክራሲ ጥያቄ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ጊዜ ነበር፡፡ በሁለቱ ወገኖች እንቅስቃሴ የሚፈልጉትን ሳያሟሉ ወይም ሳያገኙ ፣ የየካቲት 1966ዓ.ም ሕዝባዊ አብዮት በድንገት በሕዝብ ብሶት ፈነዳ፡፡
የሕዝቡን ቁጣና ብሶት መሠረታዊ ምክንያቶች በቅጡ ለይቶና አውቆ፣ ሕዝባዊው አብዮቱ በኢትዮጵያዊነት ማንነት ላይ መሠረቱን ጥሎ ወደ ፊት መጓዝ የሚችልበነትን መንገድ የሚያመቻችና የሚመራ ሕዝባዊ ኃይል በወሳኝነት መልኩ ሳይወጣ የፈነዳው አብዮት፣ቅኝ ገዥ ኃይሎቹ ባላሰቡትና ባልጠበቁት ፍጥነት የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ፣ የአንድነትና የሥልጣን ምንጭ የነበረው ዘውዳዊ ሥርዓት በራሱ ዐወቅን ባይ ልጆች እንዲወድም ተደረገ፡፡ የቅኝ አገዛዝ ተልዕኮን አንግበው በሃይማኖት ስም ወደ አገራችን የገቡ ሰዎች የመጀመሪያ ዓላማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሳካለቸው፡፡ ተያይዞም የኢትዮጵያዊነት መሠረታዊ ተቋምና የዘውዳዊ ሥርዓቱ ርዕዮተ ዓለማዊ ክንድና የበርካታው ሕዝብ መንፈሳዊ መሪ የነበረው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በመንግሥትና በሕዝብ ውስጥ የነበረውን ከፍተኛ ኃላፊነት አሳጣ፡፡ ቀሪው ተግባር እምብዛም አድካሚ የማይሆንባቸው የቁልቁለት መንገድ የሆነው፣ሌሎችን ብሔረሰቦች በዐማራው ላይ በጠላትነት ማስነሳትና እርስ በርሳቸው በማበጣበጥ የወል ዕሴቶቻቸውን በራሳቸው በማሳጣት፣ የቅኝ ገዥዎችን ማንነት እንዲላበሱ የማድረጉ ነው፡፡
ለዚህ ተግባርም ትውልዱ ምቹ ሆኖ ቀረበላቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ዐማራው ራሱን ለእርድ አመቻችቶ ቀረበ፡፡ ሌሎቹ በአዲስ ገብ ሃይማኖቶች ተኮትኩተው ያደጉ የሌሎች ነገድ አባል ልጆች ዐማራውን በጠላትነትና በቅኝ ገዥነት ፈርጀው እንደሚመለከቱትና ሊያጠፉት በዝግጅት ላይ ያሉ መሆናቸውን የዐማራው ቀለም ቀመስ ትውልድ አልተረዳም፡፡ ቀደም ሲል ኤርትራን ለመገንጠል የተደራጀው የጀብሃ እና የሻዕቢያ ቡድኖች ፀረ-ዐማራ መሆናቸውን ፈጽሞ የተገነዘበ አልነበረም፤ ይህ ብዥታ ዛሬም የጠራ አይደልም፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ኦሮሞን እገነጥላለሁ የሚል ቡድን በመካከሉ ያቆጠቆጠ መሆኑን የዐማራው ነገድ ምሁራን ልብ አላሉም፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ሕዝባዊ አብዮቱን ለመምራት በተነሳ የሥልጣን ጥያቄ ኢትዮጵያውያን አግባቢ መልስ ላይ ለመድረስ አልቻሉም፡፡ ሁሉ ባፈተተው ተጓዘ፡፡ በጉዞው በርካታ ፀረ-ዐማራና ፀረ- ኢትዮጵያ የሆኑ ድርጅቶች በቅኝ ገዥዎች ፍላጎት ላይ ተመሥርተው ተደራጁ፡፡ ነባሮቹ ጀብሓና ሻዕቢያ፣ሕወሓት፣ ኦነግ፣እስላሚያ ኦሮሞያ፣የኦጋዴን ነፃ አውጭ፣የአፋር፣የጉራጌ የከምባታ፣የወላይታ፣ የሲዳማ፣ ወዘተ እንደ አሸን ፈሉ፡፡ በሌላ በኩል ኅብረ-ብሔራው ድርጅቶች እንደ መኢሶን፣ኢሕአፓ፣ኢዲኅ፣ወዝሊግ፣አብዮታዊ ሰደድ፣ማሌሪድ፣ኢጭአት፣ የመሳሰሉት ተፈጠሩ፡፡ጉዞው ግን ቀላል አልሆነም፡፡ ብዙ ሕይዎትን የጠየቀ፣ማንነትን በእጅጉ የሚፈታተን፣ መወለድን የሚያስጠላ ሆነ፡፡ በዚህ ጉዞው ውስጥም የውጭ ድጋፍ በማግኘት የበላይነትን እናገኛልን በሚል ስሌት ኢትዮጵያውያን ራሳችን ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት አመቻቸን፡፡ የጉዞው ክፋት ያስከተለው ተስፋ መቁረጥ የናቅነውንና አባቶቻችን ድል ነስተው የመለሱትን ቅኝ ገዥ ኃይል ለምነንና ደጅ ጠንተን ቅኝ ተገዥ ለመሆን ስደትን እንድነመርጥ አደረገን፡፡ ይህ አጠቃላይ ሁኔታም ኢትዮጵያውያን ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት እንድንዳረግ አድርጎናል፡፡
በሌላ በኩል፣በአገሪቱ የተለያየ ዓላማና ግብ ይዘው፣በብሔርና በኅብረ-ብሔር ስም የተደራጁ የፖለቲካ ድርጅቶች የጠላትነት ደረጃውንና ስሙን ይለዋውጡት እንጂ፣ሁሉም የዐማራውን ነገድ “በገዥ መደብና በጨቋኝ ብሔርነት” በመፈረጅ የጥፋት ክንዳቸውን አነሱበት፡፡ በነገዱ ላይ በእርዳ ተራዳ ከደረሰበት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅምና መብት ነጠቃ በተጨማሪ፣በኢትዮጵያ ምድር ሠርቶ የመኖር መብቱን እንዲነጠቅ ሆነ፡፡ ስልታዊ በሆነ መንገድ በተከፈተበት የዘር ማጽዳት ዘመቻም ባለፉት የወያኔ አገዛዝ 2.4 ሚሊዮን ሕዝብ የደረሰበት አለመታወቁን የራሱ የወያኔ ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ባለሥልጣን ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህም ቅኝ ገዥዎች ኢትዮጵያን በፈለጉት መንገድ በቁጥጥራቸው ሥር ለማዋል እንቅፋት ሆነውብናል ያሏቸውን ተቋሞች “እሾህን በሾህ “ እንዲሉ ራሳችን፣እራሳችንን እንድናጠፋና የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች እንድንሆን እንዳደረጉን እያየን ነው፡፡ በዚህ ራስን በራስ የማጥቃት ሂደት ውስጥ ከዐማራ ነገድ ውጭ ያሉ ምሁራን በዘር ተደራጅተው የዘራችን አውራ ጠላት ነው ብለው በፈረጁት የዐማራ ነገድ ላይ የጥፋት ክንዳቸውን ሲያነሱ፣የዐማራው ነገድ ምሁራን ራሱን አደራጅቶ ዘሩን ከጥፋት ለመከላከል ካለማሰቡም ሌላ፣የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አባል በመሆን በራሱ ነገድ ላይ የጥፋቱ ተባባሪ ሆኖ ይታያል፡፡ ለአብነት ያህል በኅብረ ብሔራዊ ድርጅቶች ውስጥ ተደራጅተው የነበሩት የዐማራው ምሁራን የገዥ መደብ ነው ብለው በፈረጁት ዐማራ ላይ ያለፍርድ ሂደት አያሌ ዐማሮች ንብረታቸውንና ሕያዎታቸውን እንዲያጡ አድርገዋል፤ ተባብረዋል፡፡ ይህ ነው እንግዲህ “እስ በሱ ሥጋን በኩበት ጠበሱ” የሚያሰኘው፡፡
5. የኅሊና ቅኝ ተገዥነት የሚገልጽባቸው መልኮች፣
የቅኝ ገዥነት መሠረታዊ ግብ የቅኝ ተገዢውን ቋንቋ፣ባህል፣ሃይማኖት፣ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት፣ተቋሞች፣አጠቃላይ ሁለንተናዊ ማንነትን ማስለወጥና የቅኝ ገዥውን ቋንቋ፣ባህል፣ሃይማኖት፣ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት፣ተቋሞችና ማንነት መተካት ነው፡፡ይህም በሁለት መልኩ ተግባራዊ እንደሚሆን የቅኝ አገዛዝ ታሪክ ያስተምረናል፡፡ እነዚህም አካል እና ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ናቸው፡፡ አካላዊ ቅኝ ተገዥነት ከአቅም በላይ በሆኑ አስገዳጅ ምክንያቶች፣ ቅኝ ተገዥ ወገኖች፣ በቅኝ ገዥው ኃይል ሁለንተናዊ ፍላጎት ቁጥጥር ሥር የሚውሉበት ሁኔታ ነው፡፡ አካላዊ ቅኝ ተገዥነት በእንስሳና በሰዎች መካከል ባለግንኙነት መመሰል ይቻላል፡፡ ቅኝ ተገዥው ለአገልጋይነት፣ቅኝ ገዥው ለተገልጋይነት የተፈጠሩ ዓይነት ሆነው የሚታዩበት ነው፡፡ ይህ ግንኙነት በውዴታ፣ወይም በተፈጥሮ ሕግ የተገዛ ባለመሆኑ፣ በቅኝ ተገዥው ኅሊና ውስጥ ምንጊዜም የማይጠፋ፣ጊዜና አጋጣሚን የሚጠብቅ የታመቀ አመጽ የቋጠረ ነው፡፡ አመጹ በራሱ ወይም በተከታዩ ትውልድ ለመቀስቀስ የሚያስችልና ለተቀሰቀሰው አመጽም የሞራል፣ የተፈጥሮና የሰው ሠራሽ ሕግ ጊዜ የማይሽረው ድጋፍ ያለው ነው፡፡ ስለሆነም አካላዊ ቅኝ ተገዥነት የሁለንተናዊ አቅም ማጣት ወይም ማነስ የሚያስከትለው በመሆኑ ቅኝ ተገዥው ማንነቱን ከውስጡ አያጠፋም፡፡ የእርሱነቱ መገለጫዎችን በልዩ ልዩ ዘዴዎች ለትውልዱ ያስተላልፋል፤በሚስጢር ይጠብቃል፡፡ የቅኝ ገዥዎች የሆኑ ማናቸውንም ነገሮች በውስጡ ይጠላቸዋል፤ይጠየፋቸዋል፤ይንቃቸዋል፡፡
ለምሳሌ ሕንዶች ከመቶ አምሳ ዓመታት ያላነሰ በእንግሊዞች ተገዝተዋል፡፡ ባህላቸውን፣ቋንቋቸውን፣እምነታቸውን እንዲለውጡ አያሌ ማስገደጃዎች ጭነውባቸው እንደነበርም ይታወቃል፡፡ ሆኖም፣ ሕንዶች የተጣለባቸውን ጫና ተቋቁመው፣ባሕላቸውን፣ቋንቋቸውንና ሃይማኖታቸውን አስጠብቀው ለነፃነት በቅተዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እስራኤላውያን ከሁለት ሺህ ዓመታት በላይ በኃይል አገራቸውን ተገደው በዓለም አገሮች እንደጨው ተዘርው ሲኖሩ፣ ቋንቋቸውንና ሃይማኖታቸውን በሰው አገር አሰጠብቀው አገር ለመመሥረት ችለዋል፡፡ በሌሎች በቅኝ ግዛት ቀንበር ሥር የነበሩ አገሮችም የምናየው ተመሳሳይ ነው፡፡ከዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን መሠረታዊ ጉዳይ የትኛውም ዓይነት ቅኝ አገዛዝ ግቡ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው፣ የቅኝ ተገዥዎችን ባህል፣ሃይማኖት፣ቋንቋ፣ታሪክና አጠቃላይ ማንነትን አስጥሎ፣ የቅኝ ገዥውን ሁለንተናዊ ማንነት እንዲላበስ ማድረግ መሆኑን ነው፡፡
በአንፃሩ ኅላናዊ ቅኝ ተገዥነት በተለያዩ ምክንያቶች ሰዎች በቡድን ወይም በተናጠል የራሳቸውን ማንነት በገዛ ፈቃዳቸው በመተው የሌሎችን ማንነት መላበስ ነው፡፡ የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ራስን በራስ ሰቅሎ በመግደል ይመሰላል፡፡ ራሱን ሰቅሎ የሞተሰው በክርስቲያን ሃይማኖት ፍታት አይፈታም፤ ነፍሱም እንደማትማር የሃይማኖቱ ሕግ ያስተምራል፡፡ ይህም ማለት ራስን በራስ መስቀል የሞራል፣ የተፈጥሮና የሰው ሠራሽ ሕጎች ድጋፍ የለውም ማለት ነው፡፡ በተመሣሣይ መልኩ፣ራሱን ወዶ ለቅኝ ተገዥነት ያቀረበና የተገዛ ሰው በውስጡ በራሱ ቁጭት የለውም፤ ወዶ ውርደትን የተቀበለ በመሆኑ፣ውርደቱ አይሰማውም፣ባለመሰማቱም ነፃ ለመውጣት አያስብም፤ ቢያስብም የሞራል፣የሰው ሠራሽና የተፈጥሮ ሕጎች ድጋፍ አይኖረውም፡፡ የሚገፋፋው ውስጣዊ ምክንያት የሌለው በመሆኑም፤ለተከታዩ ትውልድ የሚያቀብለው ነገር ስለሌለው ትውልዱ የወላጆቹን ይዞ እንዲቀጥል ይገደዳል፡፡ ስለሆነም የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ከአካላዊ ቅኝ ተገዥነት እጅግ የከፋ ነው፡፡ የከፋ የሚሆነው ወዶ የተቀበለው በመሆኑ፣መውጫ ቀዳዳ የሌለው መሆኑና ቅኝ የተገዛላቸው ፣ቅኝ በመገዛቱ የሚንቁት እንጂ፣የሚያከብሩት አለመሆኑን አለመገንዘቡ ነው፡፡ በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ የአካላዊና የኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ምንነት በመጠኑም ካየን፣ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት የሚገለጥባቸው መልኮች ምን እንደሆኑ ማየቱ፣የኅሊናን ቅኝ ተገዥነት በተጨባጭ በእኛ ሁኔታ ለማየት ያስችለናል፡፡
ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት በሚከተሉት መልኮች ራሱን ይገልጻል፡፡
(1) በባህል፣ (2) በስም፣ (3) በቋንቋ፣ (4) አገርን በመጥላት፣ (5) በስደት፣
1. ባህል፡- ባህል የሰው ልጅ በማምረት፣በማከፋፈልና በመጠቀም ሂደት ውስጥ፣ ሰዎች ከሰዎች እና ሰዎች ከተፈጥሮ ጋር በሚፈጥሩት መስተጋብር ተገቢና ትክክል ነው ብለው በተደጋጋሚ በግልና በቡድን የሚፈጽሙት ተግባር ነው፡፡ አመራረት፣አመጋገብ፣በዐላት አከባበር፣ሰላምታ አሰጣጥ፣አለባበስ፣ደስታና መከራ የሚገለጽባቸው መንገዶች( ዘዴዎች) ፣የጋብቻ ሥርዓት፣ ምግብ አዘገጃጀት፣የአመጋገብ ሥርዓት፣ወዘት ባህል የሚገለጽባቸው ናቸው፡፡
ከነዚህ የባህል መከሰቻ መልኮች ውስጥ ኢትዮጵያውያን ብዙም ያለወጥነውና አጥብቀን የያዝነው የምግብ አዘገጃጀታችን፣ አመጋገባችንና ሃይማኖታዊ የበዐል አከባበር ሥርዐታችን ነው፡፡ አለባበሳችን በአብዛኛው የምዕራባዊው አለባበስ ባህል የተጫነው ነው ፡፡ ካባ፣በርኖስ፣ተነፋነፍ፣ባት ተሁለትና ወንጨሬ ሱሪዎች፣ጋቢ፣አግድሞሽ፣ኩታና ነጠላ ፣ዙሪያ ገብ እና ኋላ ግማሽ እዳይት ቀሚስና ጎዳ፣ጀበርባሬ ኩታ፣ባለጃኖ ጋቢ ወዘት ለወግ በተወሰኑ ሰዎች ካልሆነ ሕዝቡ የኔ ብሎ የያዛቸው አለባበሶች ከሆኑ ዘመን አስቆጥረዋል፡፡ በገና እና በትንሣዔ በአሎች ይደረጉ የነበሩ የአማትና የአማች መገናኛ ዝግጅቶችና በውስጡ ይከናወኑ የነበሩ ሥርዐቶች ፈጽሞ ተረስተዋል፡፡
በገና የክስቶስን መወለድ የደስታ ስሜት መግለጫ በወጣቶች መካከል ይደረግ የነበረ የገና ጨዋታ፣ ዛሬ እንኳን ስለጨዋታው ፣ስለመኖሩም የሚያውቁ መኖራቸውም አጠራጣሪ ነው፡፡ እንደ ዳቢሎስ ተመስሎ በገና ሰሞን በአዋቂዎችና በጎልማሶች ይጨወት የነበረ “ኃይሚሎ” የተሰኘ የጉግስ ጨዋታ ከተረሳ ዘመን የለውም፡፡ በዚሁ ሰሞን ይዘወተር የነበረው የፈረስ ጉግስ ጨዋታ ከጠፋ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡
በፍልሰታ ታዳጊ ወጣቶች ተሰባስበው ሆያ ሆየ እያሉ እየዘፈኑ በሚሰበስቡት ገንዘብና እህል የመስቀል ዕለት ደግሰው የአካባቢውን ሰው የሚመግቡበት፣ ከኅብረተሰቡ ይቸራቸው የነበረ የእደጉ ተመንደጉ ምርቃት፣ ደመራው ከተቃጠለ በኋላ፣በፍሙ በስሎ የሚበላው እርምጦ ዛሬ የለም፡፡ ሴት ወጣቶች በቋግሜ ሳምንት አሸንድየ ታጥቀው፣ አሻንድዬ አበባዬ እያሉ ወቅትን መሠረት አድርጎ ይጨወት የነበር የጨዋታ ባህል ዛሬ በድሮው መልኩ በስፋት አይታይም፡፡ እነዚህና የመሳሰሉት አንዳንዶቹ በምዕራባውያኑ ሲተኩ ሌሎቹ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከሕዝቡ አእምሮ ውስጥ ተሰርዘዋል፡፡ ገና ጨዋታ በእግር ኳስ የተተካ ይመስላል፡፡ ኃይሚሎ፣ጦር ውርወራ ለኢትዮጵያውያን አዲስም እንግዳም ባይሆንም፣ በዳርትና በጦር ውርወራ የተተካ ይመስላል፡፡ የአማትና የአማች ግንኙነት ሌላ መልክ ይዟል፡፡ አማት ፣ምራት፣አይት፣አማች፣አገቡኝ፣ ዋርሳ የሚሉት ቃላት ራሳቸው በአማትና በአማች ግንኙነት መላላት የተነሳ ትርጉማቸው ከማይታወቅበት ደረጃ ተደርሷል፡፡ የምዕራባውያኑ ግንኙነት የበላይነቱን በመያዙ የእኛ ማንነት መገለጫ ተረሳ፤ ወይም ተጣለ፡፡ የጋብቻ ሥርዓታችን በእጅጉ ተለውጧል፡፡ በለቅሶ ጊዜ እንደ ሟቹ ማንነት ይደረጉ የነበሩ ፉከራዎችና ቀረርቶዎች ዛሬ አይደመጡም፡፡ ይህም ኅሊና የራሱን እየተወ የሌሎችን እየያዘ መምጣቱን አመልካች ነው ፡፡ የኅሊና ቅኝ ተገዥነት የሚባለው ይኸነው፡፡
2. ስም፡- ስም መጠሪያ ፣መታወቂያ ነው፡፡ እያንዳንዱ ነገር ከሌላው የሚለይበት የወል፣የጥቅልና የተጸውዖ ስሞች አሉት፡፡ ስሞችም የሚወጡት በዘፈቀደ ሳይሆን፣ ስም አውጨዎቹ በኖሩበት ማኅበረሰብ ባህል፣ቋንቋና እምነት ጋር ተያይዞ የሚሰጥ ነው፡፡( ከዚህ ላይ ስም ስንል ልዩ ትኩረት የምንሰጠው የሰው መሆኑን እናስተውል፡፡) ስለሆነም የአንድ ሰው ስም በወላጆቹ ፈቃድና ውሳኔ የሚሰጥ ነው፡፡ ውሳኔው መሠረት የሚያደርገውም ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ባህልን፣እምነትንና ስም የሚወጣለት ሰው በተወለደበት ወቅት በአካባቢው በተፈጠሩ ሁኔታዎች ላይ ተመርኮዞ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ከዐማራ ነገድ የተወለደ ወይም የተወለደች ሰው፣አበበ፣አበበች፣ላቀው፣ላቀች፣በላቸው፣በላይነሽ፣አስፋው-ወሰን፣ወሰን-የለሽ፣ ወርቁ፣ወርቂቱ (ወርቅነሽ)፣በላቸው ፣በላይነሽ፣አግርደው፣አግርጅው፣አስካበ፣አስካበች፣ፀጋው፣ፀጋነሽ፣ ብሬ፣ ብሪቱ፣ ወዘተ እያሉ ስም ይሰጧቸዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚወጡ ስሞች የአባትየውን ፍላጎት በሚገልጥ መልኩ፣የልጅና የአባት ስም ባንድነት ሲጠሩ የተለየ ትርጉም በሚሰጥ መልኩ ይሰይሟቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ሰውበሰው ደረጀ፣ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ፣ቁምነገር ገበየሁ፣በዓለምላይ ገበየሁ፣ኃይለሥላሴ ቀለጠ፣ ወገን በለጠ፣ አማላጅ በለጠ፣ወዘተ፣ እነዚህ ስሞች የኢትዮጵያዊነት
በተለይም የዐማራ ነገድ ማንነት መገለጫዎች እንደሆኑ በቀጥታ ከስማቸው መረዳት ይቻላል፡፡
ይሁን እንጂ ቀለም ቀመሱ ትውልድ በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም፣ አዲስ ሃይማኖት በመቀበል፣የስም አጠራሩን ለውጭ አገር ሰዎች በቀላሉ አይገባም በሚሉና በመሳሰሉ ምክንያቶች በቤተሰብ የተሰጣቸውን ስም ሆነ እነርሱ ለወለዷቸው ልጆች ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ስሞች ሲሰጡ መታየቱ እግዳ ነገር አይደለም፡፡ ሊያ፣ሚኩ፣ሚሚ፣ሣራ፣ማይክ፣አቤነዘር፣ሌላም ሌላም ሕዝቡ የሚያውቃቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር ምንም ዓይነት ግንኑነት የሌላቸው ስሞች እንሰማልን፤እናውቃለን፡፡ ይህ የራስን ዕንቁ ወርውሮ የሌሎችን ነሃስ መሰብሰብ ከመሆኑም በላይ፣ ራስን ለኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነትን ወዶ ማሰለፍ ነው፡፡ ሌሎቹን ሁሉ ለትዝብት ትተን ሣራ የሚለውን ስም እንደኛ(እንደ ኢትዮጵያዊ) ሆነን እንሰብ፡፡
ማንም መጽሐፍ ቅዱስን የሚከታተል ሰው ሣራ የሚለው ስም እንግዳ ነገር አይሆንበትም፡፡ “የአባታችን” የአብርሃም ባለቤት መሆኑዋን ይረዳል፡፡ ይህ ስም በእበራይስጥ ቋንቋ ትርጉሙ “እናት” እንደማለት ይመስለኛል፡፡ የእብራይስጥን ቋንቋና ባህል ለሚያውቅ ሰውና በዚያ ባህል ለኖረ ስሙ ወርቅ ነው፡፡ የኢትዮጵያዊ ባህልና ቋንቋ ባለቤት ለሆነ ሰው ደግሞ ይህ ስም እንኳን የልጅ መጠሪያ ሊያደርጉት ሊናገሩት የሚከብድ ትርጉም ያለው ነው፡፡ እግዚአብሔር ያሳያችሁ! “ሣራ ነጋ” ብሎ ስም የሚያወጣ ሰው ለልጁ መጠሪያ ሳይሆን መሰደቢያ ነው የሰጣት፡፡ የቋንቋው ሥርዓትና የሕዝቡ ባሕል ከሚፈቅዱት ውጭ የተሰጡ ስሞች የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ስሜት የፈጠራቸው ስሞች መሆናቸውን መጠራጠር አይቻልም፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያዊው በተለይም ዐማራው ማንነቱን ፈቅዶና ወዶ እያወለቀ እየጣለ የሌሎችን ማንነት እያጠለቀ መሆኑ ጉልሁ ማመላከቻ ለልጆቹ የሚያወጣላቸው ስሞች ናቸው፡፡
በአማርኛ ቋንቋ ሥርዓት ውስጥ በተጸውዖ ስም ላይ እየተደረቡ የሚገቡ ለሁለቱም ፆታዎች የሚያገለግሉ ድርብ ስሞች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ድርብ ስሞች የማዕረግ፣የአክብሮትና የተዘምዶ ስሞች ይባላሉ፡፡ የማዕረግ ስሞች በቤተ እምነቶች ወይም በቤተ መንግሥት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ምሳሌ፡- ቤተእምነት፣ እጨጌ፣ጳጳስ፣ቆጶስ፣መላዕ-ከፀሐይ፣ግራ ጌታ፣ ሸህ፤ወዘተ፣፣ ቤተ መንግሥት፣አጼ፣እቴጌ፣ንጉሥ፣ራስ፣ቢትወደድ፣ደጃዝማች፣ፊታውራሪ፣ቀኛዝማች፣ግራዝማች፣ብላታ፤ እነዚህ ስሞች ግለሰቦች ለአገራቸው ባበረከቱት ተግባር፣ባሳዩት አርዓያነት ያለው ሥራ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካለት ተመርምሮ የሚሰጡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ስሞቹ የክብር መጠሪያዎች በመሆናቸው ሌሎች የዚያ ስም ባለቤት ለመሆን የተሻለ ተግባር እንዲፈጽሙ አነቃቂ እንደነበሩ ግልጽ ነው፡፡ በመንግሥት ደረጃ የሚሰጡት የማዕረግ ስሞች በአብዛኛው አገርን ከጠላት በመከላከል ሂደት ውስጥ በተጫወቱት ሚናና በሰላም ጊዜም በአስተዳደር፣ በልማትና መሰል ተግባሮች አርኣያነት ያለው ተግባር ለተወጡ ግለሰቦች ነው፡፡ የቤተ እምነቶቹ ስሞች የሚሰጡት በሃይማኖቱ መንፈሳዊ ዕውቀት ላይ ተመሥርቶ በዚያ ተግባር ላይ ያበረከቱት አስተዋጽዖ ተመዝኖ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ዛሬ በምንገኝበት ነባራዊ ሁኔታ የቤተ እምነቶቹ ስሞች በአገልግሎት ላይ ሲገኙ፣ ከመንግሥት በኩል የሚሰጡት ስሞች እንደ አድኃሪና ኋላ ቀር ነገር ተቆጥረው ተወግዘው የተወረወሩ ሆነዋል፡፡ ማዕረግተኞቹም በማረጋቸው ያፈሩ ይመስላል፣ ሊጠሩበት አይሹም፡፡ ለምሳሌ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ከዚህ ስማቸው ይልቅ “ታጋይ” የሚለው እንደሚመቻቸው ሲናገሩ የተደመጠበት ጊዜ አለ፡፡ “ታጋይ” መንገሻን ለዚህ ያበቃቸው የማዕረግ ስሙን ያገኙት በግል ባስመዘገቡት የመልካም አርኣያነት ተግባር ሳይሆን፣ከንጉሡ ጋር በመጋባታቸውና ከአጼ ዮሐንስም እወለዳለሁ ስለሚሉ፣በነዚህ ሁለት ምክንያቶች ያገኙት በመሆኑ ለስሙ ክብደት ከመስጠት ይልቅ አሳፍሯቸዋል ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ግራዘመም አመለካከት አቀንቃኝ የሆነው ትውልድ ማዕረጎቹን የተረዳበት አቅጣጫ ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ባፈነገጠ መልኩ መሆኑ መዕረጎቹ የገዥና የተገዥ፣የአዛዥና የታዣዥ፣ የሀብታምና የድሀ ግንኙነት መገላጫዎች አድርጎ በመመልከቱ ትውልዱ ስሞቹን በጭፍን አወገዛቸው፡፡ ማዕረግተኞቹም አብዛኛዎቹ በአብዮቱ በግራ ቀኙ ኃይሎች ተመቱ፡፡ የቀሩትም እንደ ራስ መንገሻ ያሉት ዘመኑን ለመምሰል ሌላ ዘመነኛ ስም መረጡ፡፡ ትውልዱ ኅሊናው በቅኝ ተገዥነት ስሜት ሳያወቀው ባይገዛ ኖሮ፣ስሞቹ በልዩ ልዩ መስኮች አርኣያነት ያለው ተግባር ላከናወኑ ሰዎች መጠሪያ እንዲሆን ይፈቅድ ነበር፡፡ይህም ኢትዮጵያዊነትን ማድመቅ እንጂ ማፍዘዝ አይሆንም ነበር፡፡ እንግሊዞች ንጉሣዊ አመራርን አሻሻሉት፣ሕዝቡ በሚፈልገው ደረጃ አሳደጉት እንጂ፣ፈጽሞ አላወደሙትም፡፡ በዚህም የተነሳ “ሰር” የሚለውን የማዕረግ ስም ዛሬም በልዩ ልዩ መስኮች ለሰው ልጅ ጠቃሚ ሥራዎችን ለሠሩ ሰዎች መጠሪያና መከበሪያ እንዲሆን እያደረጉት ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን የራስን ማጥፋት፣የራስ ያልሆነን መካብና ማድመቅ በመሆኑ ሥራችን፣ እነዚህን አገራችን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ስትገለገልባቸው የነበሩ የማዕረግ ስሞች እንዲጠፉ ፈርደንባቸዋል፡፡ ይህም ውጭ አምላኪነት ነው፡፡ ውጭ አምላኪነት ደግሞ ፈቅዶና ወዶ ቅኝ ተገዥነትን መለማመድ ነው፡፡
የተዘምዶ ስሞች የምንላቸው ልጆች ለወላጆቻቸው፣ታናናሾች ለታላላቅ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው የሚሰጡዋቸው እንዲሁም በዕድሜ ታናሽ የሆኑ ሰዎች ታላላቆቻቸውን የሚጠሩባቸው ስሞች ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ ልጆች ወላጆቻቸውን አባባ፣አባበይ፣ እማማ፣ እማመይ፣ታላላቆቻቸውን አይወይ፣ክንዴ፣ጋሻዬ፣መከታዬ፣ወንድም-ዓለም፣እዋዋ፣ወንድም-ጥላ፣ወንድም-ጋሼ፣ እታበባ፣እታለም፣እትሸት፣እንጎቻዬ፣እባባ እገሌ፣ጋሼ እገሌ ፣አይዋ እገሌ፣እማማ እገሊት፣እታታ እገሊት ወዘተ እያሉ መጥራት የቋንቋው ሥርዓትም ሆነ የሕዝቡ መልካም ባህል ነበር፡፡ በሌላም በኩል ወንዶች ለአቅመ አዳም፣ሴቶች ለአቅመ ሔዋን ከደረሱ በኋላ የሚጠሩበት የማዕረግ ስም አላቸው፡፡ ወንዶች “አቶ” ሲባሉ ሴቶች “ወይዘሮ” ላገባች፣ “ወይዘሪት” ላላገባች እያሉ መጠራት እንዳለባቸው ባህሉና ሥርዓቱ ያዛል፡፡
እነዚህ ስሞች ከማዕረግ መገለጫቸው በተጨማሪ በጠሪውና በተጠሪው በካከል እጅግ የቀረበ የሥጋ ዝምድና ያላቸው መሆኑን ከማመልከቱም በላይ፣ ባለማዕረግ ስሙ ታላቅ፣ በማዕረግ ስም ጠሪው ታናሽ መሆናቸውን ላድማጭ ግልጽ በሆነ መንገድ ያስረዳሉ፡፡ ከዝምድና መገለጫ ውጭ ያሉት የአክብሮት ስሞች በአክብሮት ስም ጠሪው በዕድሜ ታናሽ፣ ተጠሪው ታላቅ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ይህ እንዴት ያለ የኢትዮጵያዊነት ልዩና ውብ መታወቂያ ነበር፡፡ ዳሩ ምንያደርጋል/ እነዚህ እንኳን ውጪ ተወልደው ባደጉ፣ በአገር ቤት በተወለዱትና ባደጉት ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በተወለደው ትውልድ ያላዳች አስገዳች ውጫዊ ኃይል በራስ ፍጹም ፈቃድ ስሞቹን ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ተድርጓል፡፡ አባትና እናትን እንደ ጓደኛ በስማቸው መጥራት እንደስልጣኔ ተቆጥሯል፡፡ አለያም እንደምዕራባዊኑ “ዳድ” ፣”ማም” ማለት የተዘወተረ ሆኗል፡፡ የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ማለት ሌላ ምንም ሳይሆን፣የራስን ጥሩ ነገር ትቶ የሌሎችን ባህል፤እምነትና ማንነትን መላበስ ነው፡፡ ወላጆቹን በባህላችን የአክብሮት ስሞች የማይጠራ፣ታላላቅ ወንድሞቹንና እህቶቹን በኢትዮጵያዊ የአክብሮት ስም የማይጠራ ከማንነቱ የተፋታ ነው፡፡ ተጠሪዎችም በባህላችን የሚመጥናቸውን የማዕረግ ስም ነጥለው የሚጠሩዋቸውን ልጆቻቸውንም ሆነ ወንድም እህቶቻቸውን አዎንታዊ መልስ ከሰጡ የመጀመሪያዎቹ ባህል ጣሾችና ሥርዓት አፍራሾች መሆናቸውን ሊረዱት ይገባል፡፡ ለሁሉም ቀለም ቀመሱ ትውልድ ከኢትዮጵያዊነት ጨዋነት፣ባህልና ማንነት ራሱን እያፋታ የመጣ መሆኑ ባህላችን የሚገኝበት ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ ደግሞ የኅሊናዊ ቅኝ ተገዝነት መገለጫ ነው፡፡
3. ቋንቋ፡- ቋንቋ መግባቢያ፣ሀሳብ መግለጫና መለዋወጫ የሆነ የድምፅ ሥርዓት ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የተለያዩ ሕዝቦች የተለያዩ የድምፅ ሥርዓት የሚከተሉ ቋንቋዎች አሏቸው፡፡ ቋንቋ አዳጊም ጠፊም ነው፡፡ ቋንቋ የሚጠፋው በሥራ ላይ የሚያውለው ማኅበረሰብ በልዩ ልዩ ምክንያቶች አልገለገልበት ሲል ነው፡፡ ቋንቋ ዳባሪ የሚሆነውም የቋንቋው ባለቤት የሆነው ሕዝብ የኢኮኖሚ ደረጃ ማደግና ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የሚፈመሠርተው ግንኙነት ሲሠፋ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት በዓለማችን ላይ የጠፉ ቋንቋዎች የመኖራቸውን ያህል፣የዳበሩም እንዳሉም እንረዳለን፡፡ ዳበሩ ከምንላቸው ቋንቋዎች ውስጥ እንግሊዝኛ የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘ ነው፡፡ ጠፉ ከሚባሉት ውስጥ ላቲን አንዱ ነው፡፡በአገራችን ከጠፉ ቋንቋዎች ውስጥ ጋፋትኛ የመጀመሪያው ነው ፡፡ አንፃራዊ በሆነ መልኩ አድጓል ወይም ዳብሯል ከሚባሉት ውስጥ አማርኛ አንዱ ነው፡፡
አማርኛ ቋንቋ አድጓል ስንል በሚጠበቅበት ደረጃ እያደገነው ወይም አድጓል ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ቋንቋው በጽሑፍ ሥራ ላይ ከዋለ ከ320 ዓ.ም ጀምሮ ካስቆጠረው ዘመን አንፃር ሲመዘን ወደ ኋላ እንጂ፣ወደ ፊት ሄደ የሚባል አይደለም፡፡ ይኸም ሆኖ፣ትውልዱ በተጠናወተው ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት ስሜት ሳቢያ፣ አባቶቻችን ባቆዩልን መልኩ እንኳ ለልጆቻችን ለማስረከብ ከማንችልበት ደረጃ ላይ ነን፡፡ ቋንቋ ባህል በመሆኑ የሚከተላቸው የራሱ የሆኑ መንገዶችና ሥርዓቶች አሉት፡፡ ለምሳሌ በአማርኛ ቋንቋ ሰዎች ሰላምታ ሲለዋወጡ የሚከተሉት ሥርዓት አለ፡፡ ሰላምት ሰጪው ጤና ይስጥልኝ እንዴት አደራችሁ? ዋላች? አመሻችሁ ፣ሲል፣ ሰላምታ ተቀባዩ ወይም መላሹ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ ፣ደህና ነን ሲል መመለስ እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ይህ በዛሬው ትውልድ እንደነውር የሚቆጠር ሆኖ፣የሰላምታው ዘይቤ የምዕራባውያኑን መንገድ ተከትሏል፡፡ እዴት አደርክ? አደራችሁ ሲባል መልሱ ደህና ወይም መልሶ እንዴት አደርክ የሚል ነው ፡፡ ይህ የራስን ውብ ነገር መጣል ነው፡፡ በንግግር ወቅት በአማርኛ ጀምሮ በአማርኛ መጨረስ የሚታሰብ አልሆነም፡፡ በመሀሉ እንግሊዝኛ፣ፈረንሣይኛ፣ዐረብኛ፣ ወዘተ ጣልቃ ማግባት የዐዋቂነት ምልክት እንደሆነ መቆጠር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ በሌላም በኩል የአማርኛ እናት ግዕዝ መሆኑ እየታወቀ ግዕዝን እንድንማር ባለመደረጉ፣እኛም ራሳችን ለማስተማርና ለመማር ባለመትጋታችን ዘመኑ ለሚፈጥራቸው አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠሪያ የሚሆኑ ቃሎች ከአማርኛ ስናጣ፣አማርኛን መውቀስና የውጭ ቋንቋዎችን ማግነን የራስን ካለማወቅ የተፈጠረን ችግር፣የቋንቋው ችግር አድርጎ ማቅረብ የራስን ከመናቅ የመነጨ ውጭ አደርነት ስሜት የፈጠረው መሆኑን መጠራጠር አይቻልም፡፡
ትውልዱ ግራ ዘመም ርዕዮት በመከተሉ ሳቢያ፣የተለያዩ ግንኙነቶች መገለጫ የሆኑ ስያሜዎቸን “ ገዥ መደቦች ወይም ብሔረሰቦች” እንዳዎጡዋቸው በመቁጠር ከንግግር ዘይቤ ውጭ እንዲሆኑ ሆኗል፡፡ ምሳሌ “አዝማሪ”፤ ይህ ቃል ትርጉሙ አዘመረ አመሰገነ የሚል ሲሆን፣ትርጉሙን በሚገባ ካለማወቅ የሙያ ማንቋሸሻ እንደሆነ ተቆጥሮ “ አርቲስት” በሚል የውጭ ቃል እንዲተካ ተደርጓ፡፡በምዕራቡ አገር ጢሰኛ፣ገባር የሚሉት ቃሎች ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ቤቶችን ፣መሬቶችን የሚከራዩ ሰዎች የሚጠሩበት የተከራይና አከራይ ግንኙነት መገለጫዎች በመሆን በሥራ ላይ ውለው እናያለን፡፡ እነዚህ ቃሎች በኢትዮጵያችን የጭቆና መገለጫዎች እንደሆኑ ተቆጥረው ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰል ሌሎችም እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ቋንቋው እንዳያድግ ፍላጎት ባላቸው ክፍሎች ስልታዊ በሆነ መንገድ የአማርኛ ቋንቋ እንዲጠፋ የሚሠራው የቤት ሥራ ቀላል አይደለም፡፡ ዛሬ ወያኔ በዘረጋው የትምህርት ፖሊሲ በተዘጋጁ የማስተማሪያ መጽሐፍቶች ፊደሎች ካለቦታቸው ከመግባታቸው በላይ ፣ቃሎቹን በሚገባ የሚገልጹ የግዕዝና የአመርኛ ቃሎች እያሉ ሆን ተብሎ እንግሊዝኛ ወይም ትግርኛ ቃሎች ከአማርኛ ጋር እንዲዳቀሉ ተደርጓል፡፡
አባቶቻችን ስድስት ሀ፣ሃ፣ ሐ፣ሓ ፣ኀ ፣ኃ፣ሁለት ሰ ፣ ሠ ፣ሁለት ጸ፣ ፀ ፣አራት አ፣ኣ፣ ዐ፣ዓ ፣ ፊደሎች ድምፅ የቀረጹት የተለያየ ድምፅና ትርጉም ያላቸው መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡ ለምሳሌ ሀብት፣ሃብት፣ ሐብት፣ሓብት፣ኀብት፣ኃብት ተብለው በተገቢው ድምፅ የተገለጠውን ምረጥ ብንባል ትክክለኛው መልስ በሀሌታው “ሀ” የተጻፈው ነው፡፡ የቀሩት በድምፅና በትርጉም የተለያዩ ናቸው፡፡ ሐመር፣ሐረግ ሕዝብ፣ የሚሉት ቃሎች በሌሎች የሀ ድምፅ እንዳላቸው በሚታወቁት ፊደሎች ቢጻፉ ፍጹም ስሕተት ነው፡፡ ሠራ፣ሥራ፣ንጉሥ፣ ንግሥት ወዘተ የሚሉ ቃሎች በሌላ ሰ ድምፅ ባላቸው በሚመስሉ ፊደሎች ብንጽፋቸው ስሕትት ነው፡፡ ኃይል፣ኃይሉ፣ኅብረት፣ማኅበር፣ ቤሎች የሀ ድምጽ ያላቸው ፊደሎች ቢጻፉ ስሕተት ነው፡፡ በአጠቃላይ ለፊደሎቻችን የሚወክላቸውን ድምፅ በሚገባ አለማወቅ በማይወክሉበት ቦታ ፊደሎችን እያስገባን የቋንቋውን ሥርዓትና አጠቃቀም ከማዛባት አልፎ እያጠፋነው መሆኑን ትውልዱ የተገነዘበ አይመስልም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሀ፣ ሃ ፣ሐ፣ ሓ፣ ኀ፣ ኃ፣ ኻ ፣ህ፣ ሕ፣ ኅ፣ ኽ ፣ ወ ፣ዎ፣ ዉ ፣ ው፣ ዪ ፣ይ ቸ፣ ቼ፣አ፣ ኣ ፣ ዐ፣ዓ፣ ሸ፣ ሼ ፣ ዠ ፣ዤ፣ጀ ፣ ጄ፣ጨ ፣ጬ ወዘተ የሚሉትን ድምፆች ልዩነት በሚገባ ባለማወቅ በማይወከወሉበት ቦታ እያስገባናቸው የቋንቋው ሥርዓት እንዲፋለስ እየተደረገ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህም ሂዶ ሂዶ መዳረሻው ራስን ለቅኝ ተገዥነት ማመቻቸት መሆኑ የተገለጠልን አይመስልም፡፡ የአማርኛን ቋንቋ ድምፆች በሚገባ ለማወቅ ባለመቻላችን፣ ልናውቅም ጥረት ባለማድረጋችን ፊደሎች እንደበዙና አንዳንዶቹም የተደጋገሙ ናቸው በማለት ምትክ የሌላቸውን ቅርሶቻችን እንዲጠፉ እያደረግን ነው፡፡ ቃሎች በሚመጥኑአቸው ድምፆች ፊደሎች አለመጻፍ የድምፅ ልዩነት ብቻ ሳይሆን፣የትርጉምም ለውጥ አላቸው፡፡ በሌላም በኩል ተገቢዎቹን ፊደሎች እንዲጠፉ ፈረድንባቸው ማለት ነው፡፡ ይህም የራስን መጣል፣የሌሎችን ማንጠልጠል ነው፡፡
በቋንቋ ረገድ የራሳችን እየጣልን የኛ ያልሆነን የማንጠልጠላችን ሁኔታ ጎልቶ የሚታየው በሕፃንነታቸው ከአገር የወጡና ውጭ የተወለዱ ልጆች የወላጆቻቸውን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንዲያውቁ አለመደረጉ ነው፡፡ ዛሬ በምዕራቡ ዓለም ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ እንደሚኖር ይታወቃል፡፡ ከተሰዳጁ ኢትዮጵያዊም ውስጥ በርካታውን ቁጥር የያዘው የዐማራው ነገድ እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ይህን ያህል ቁጥር ያለው ሕዝብ ልጆቹን የማንነታቸው ቋሚ መገለጫ የሆነውን ቋንቋቸውን እዲያውቁ ሲያደርግ አይስተዋልም፡፡ ልጆች የወላጆቻቸውን ቋንቋ ባለማወቃቸው፣ወላጆችም ልጆቻቸው የሚያውቁትን የነርሱ ያልሆነ ቋንቋ ስለማያውቁ በቤት ውስጥ የመግባባት ችግር እንዳለ ጎልቶ መነገር ጀምሯል፡፡ ወላጆች ላሉበት አካባቢና ቋንቋ ባይተዋሮች በመሆናቸው የልጆቻቸውን ቤት ሥራ ተከታትሎ ለማሠራት ባለመቻላቸው ወላጅና ተወላጅ “ፈረንጅና አበሻ” ለመባባል በቅተዋል፡፡ ከዚህ የባሰ ውርደትና ሞት የት አለ?
ልጆቻችን የአገራቸውን ቋንቋ እንዲያውቁ አለመደረጉም ወጥተው እንዲቀሩ፣ከማንነታቸው እንዲፋቱ፣ከኅሊና ቅኝ ተገዥነት በባሰ የማንነት ቀውስ ውስጥ እንዲገቡ እየተደረገው መሆኑ በውል የተጤነ አይመስልም፡፡ በዓለም ላይ እንደጨው ተዘርተው ከሁለት ሺህ ዘመን በላይ የኖሩት እስራኤላውያን ቋንቋቸውንና ሃይማኖታቸውን ፈጽሞ አላጠፉም፡፡ እንዳውም በስደት ዓለም አዳበሩት፡፡ ዐማራው ምን እንደነካው አይታወቅም ከእሱነቱ አልፎ፣ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣የጥቁር ሕዝብ መመኪያ የሆነውን የአፍሪካ ብቸኛ የጽሁፍ ቋንቋ ባለቤት የሆነውን የዐማርኛ ቋንቋ እንደዘበት ተመልክቶ እዲጠፋ የፈረደበት ይመስላል፡፡ “ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ፣ ባለዕዳ አይቀበለውም” ነውና እኛ ለልጆቻችን ለማውረስ የተጠየፍነውን ቋንቋ ማን ሊወርስልን፣ሊያሳድግልንና ሊያዳብርልን እንሻለን? ለአማርኛ ከዐማራው ነገድ ሌላ ማን ባለቤት እንዲሆን ይጠበቃል? ቋንቋችን ለመጠበቅና ለማዳበር አለመትጋታችን የኅሊና ቅኝ ተገዥነታችን ያሳደረብን ተፅዕኖ መሆኑን መጠራጠር አይቻልም፡፡
4. አገር የመጥላት ስሜት እየጎለበተ መምጣት፡- ማንም ሰው አገሩን ይወዳል፡፡ ይህ አጠቃላይ አገላለጽ ነው፡፡ አገራቸውን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚጠሉ መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ካለባት የመልካም አስተዳደር ዕጦት በላይ፣ ታዳጊ አገር በመሆኗ ለዜጎቿ የዕለት ተዕለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በብዛትና በጥራት የምታቀርብ አይደለችም፡፡ የየብስ፣የባሕርና የአየር መጓጓዣ እንደፈለጉት አይገኝም፡፡ ቴሌቪዥን፣ማቀዝቀዣ( ፍሪጂ)፣አውቶሞቢል፣ የቤት ውስጥ መጸዳጃ፣ ሶፋ፣ ወንበር ጠረጴዛ፣ የአካል ንጽሕና መጠበቂያ ሙቅና ቀዝቃዛ ውኃ በቤት ውስጥ መኖር ለሰው ልጆች እንደመሠረታዊ አስፈላጊ ነገሮች የሚታዩ ሳይሆን፣ የሀብት መገለጫ፣ያላቸው ሰዎች ብቻ ሆነው የሚታዩ በመሆኑ ለአብዛኛው ሰው እንደቅንጦት የሚታዩ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ “ተድራ ብትመለስ የውኃው መንገድ ጠፋት” ዓይነት የሆነባቸው ሰዎች አውሮፓና አሜሪካ ደርሰው ወይም ኑረው ሲመለሱ በውጭ ያዩትን የመገናኛና የአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በፈለጉት መጠን አለማግኘት አገራቸውን ጠልተው እንዲመለሱ ይሆናሉ፡፡ ከሁሉም በላይ ወደ ገጠር ጎራ ካሉ አቧራው፣ቁንጫው፣ትኋኑና የመንገዱ ውጣውረድ በሚፈጥርባቸው የተለየ ስሜት የተነሳ ዳግም ወደ አገራቸው ላለመመለስ ምለው የሚመጡ አያሌዎች እንደሆኑ በየአጋጣሚው የምንሰማው ሐቅ ነው፡፡ ይህ ማለት ሁለመናቸው ለውጭው ኑሮ የተገዛ መሆኑን ያሳይል፡፡ ሁኔታውን ለመለወጥ ከእኔ ምን ይጠበቃል ብሎ የተሻለ ነገር ለመሥራት፣ቴከኖሎጂ ለማሸጋገር በመትጋት፣ የራስን ድርሻ ተወጥቶ አገርን ሌሎች ከደረሱበት ደረጃ ለማድረስ የሚቻለውን ሁሉ በግልና በተናጠል ከመሥራት ይልቅ፣ የራስን ጠልቶ አያሳየኝ ብሎ ምሎ መመለስ ምን ይባላል/ይህን አቋምና አመለካከት የኅሊና ቅኝ ተገዥነት ካልሆነ ሌላ ምን ልንለው እንችላለን፡፡
5. ስደት ናፋቂነት፡- “ሞት በእንቅልፍ ይለመዳል” እነዲሉ ሆኖብን፣ኢትዮጵያውያን በመሣሪያ ኃይል የፖለቲካ ሥልጣን በጨበጡ ቡድኖች በተከታታይ በተፈጸመብንና በሚፈጸምብን የአፈናና ረገጣ አገዛዞች ስደትን የሞት ያህል እየተለማመድነው መጥተና ፡፡ በግልጽ እነደሚታወቀው፣ አንድ ሰው ከተወለደበትና ካደገበት አካባቢ የሚሰደደው ለሕይዎቱ ቀጣይነት አስጊ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ነው፡፡ እነዚህ የሕይዎት አስጊ ሁኔታዎች ከፖለቲካ አቋም፣ከሃይማኖት፣ከነገድና ከኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ መንገድ ልዩነቶች ሲፈጠሩና አለመግባባት ላይ ሲደረስ እንደሆነ ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድርቅ፣በአንበጣ ወረራ፣ በመሬት መንሸራተትና በጦርነት ምክንያቶች በሚፈጠሩ ችግሮች ሳቢያ፣ የሰሜኑ ወደ ደቡብ፣የደቡቡ ወደ ሰሜን፣የምሥራቁ ወደ ምዕራብ፣የምዕራቡ ወደ ምሥራቅ በመፍለስ እንደኖረና ይህም ለአንድነቱ መሠረት ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ የአገር ውስጥ ፍልሰት የባህል፣የቋንቋና የሃይማኖት መወራረስን በመፍጠር ሕዝቡ የአካባቢያዊ ልዩነቶችን ግድግዳ በመሰባበር፣ኢትዮጵያዊ የሆነ የወል ማንነትን እንዲገነባ እንዳደረገው ግልጽ ነው፡፡ በግልጽ ለመገንዘብ እንደሚቻለው፣የአገር ቤቱ ፍልሰት፣የጠነከረ ኢኮኖሚያዊ አስተሳሰብ፣ ሃይማኖት፣ባህልና ቋንቋ ያላቸው በሄዱበት አካባቢ ነዋሪ ላይ ተፅዕኖ ማሳደራቸው አይዘነጋም፡፡ ተፅዕኖው ሰጥቶ መቀበልን መሠረት ያደረገ ስለነበር የነገዶች ልዩ መታወቂያ የሆነው ቋንቋቸው ተጠብቆ እንዲዘልቅ ሆኗል፡፡
እስከቅርብ ዘመን ድረስ አገርን ጥሎ ወደ ባዕድ አገር መሰደድ ለኢትዮጵያዊያን የሚታሰብ አልነበረም፡፡ ትውልዱ የስደትን ሕይዎት እየተለማመደው የመጣው ከአምስቱ ዓመት የአርበኝነት ትግል ዘመን ጀምሮ ነው፡፡ የስደትንም ሕይዎት ለትውልዱ ያስተማሩት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከነቤተሰባቸው መሣፍንቱንና መኳንንት የሚባሉትን ይዘው አውሮፓ መግባትና መኖር ጋር ተያያዞ ነው፡፡ “እንደንጉሡ አጎንብሱ” ወይም “ግዝ እንደንጉሡ አውድማ እንደ አግማሱ” ይሉ ሆኖ፣ ከዚንያ ዘመን ጀምሮ ትውልዱ ስደትን የሕይዎት ማቆያ አማራጭ መንገድ አድርጎ ወሰደው፡፡ በማከታተልም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ.ኤ.አ 1948 የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችን ባጸደቀበት ወቅት አንድ ሰው ወይም ቡድን በዘሩ፣በሃይማኖቱ እና በሚያራምደው የፖለቲካ አቋም የተነሳ፣መሳደድ፣መታሰርና መገደል የሚደርስበት መሆኑ ከታወቀና ይህም ከተረጋገጠ ወደ ሁለተኛ አገር ሂዶ የመኖር መብት እንዳለው ያወጣው ሕግ የስደተኝነትን መንፈስ በሕዝቦች ላይ እንዳሳደረ እንገነዘባለን፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት ከንጉሠ ነገሥቱ የመጨረሻዎቹ ሁለት ዐሥረተ ዓመታት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን “የመደብና የብሔር ጭቆና” ተፈጽሞብናል፣ለዲሞክራሲ ቆመናል የሚሉ ወገኖች በአገዛዙ ሊፈጸምብን ይችላል የሚሉትን እስራትና እንግልት በመፍራት መሰደዳቸው ይታወቃል፡፡
በዘመነ አብዮት ትውልዱ በየፊናው ተደራጅቶ ባካሄደው የፖለቲካ ሥልጣን ሽሚያ በርካታ ዜጎች ለሞትና ለእስራት መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡ አገዛዙ በሥልጣን ተቃዋሚዎቹና በተገንጣይ ቡድኖች ላይ በወሰደው መራር ርምጃ አያሌ ሰዎች ስደትን እንዲመርጡ እንዳደረጋቸው ግልጽ ነው፡፡ ስደቱ በተከታዩም ብሔርተኛው አገዛዝ በከፋ መልኩ ቀጠለ፡፡ በዘመን ደርግና በዘመነ ወያኔ የሕዝቡ ስደት መሠረት ያደረገው በሚከተለው ፖለቲካዊ አቋም፣ሃይማኖት፣ዘር ወዘተ ከሚመነጭ ግድያና አስራት ፍራቻ ብቻ አይደለም፡፡ የተሻለ ሕይዎት ለመኖር ከመነጨ ፍላጎትም ስደትን የመረጠው ወገን ቁጥር በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ የዚህ ፍላጎት ምንጩም የአገሪቱ ሰላም አስተማማኝ አለመሆን፣ የሥራ ዋስትን አለማግኘት፣የግል ሀብት ተገቢ የሆነ ሕጋዊ ጥበቃ አለማግኘት፣ሥራ በችሎታ ሳይሆን፣ በፖለቲካ ሽርክናና በዘር ላይ መመሥረት ወዘተ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ፣ ፖለቲካዊ ሁኔታውን መነሻ በማድረግ በልዩ ልዩ መንገዶች ሕዝቡ መሰደድን ሥራዬ ብሎ ተያያዘው፡፡ ለዚህም ዋናው ተጠቃሽ ምክንያት ቀድመው የተሰደዱ ሰዎች የግልና የቤተሰብ ሕይዎት በአገር ቤት ከሚኖሩ ጥሩ ነዋሪ ከሚባሉ ሰዎች የተሻለ ሆኖ መገኘት ነው፡፡ በሁለተኛና በሦስተኛ አገር ጥገኝነት ለመጠየቅም ባገር ቤት ያለው የዘር ፖለቲካና በሕዝቡ ላይ የሚፈጸሙ ኢ-ሰባዊ ድርጊቶች ተባብሰው መቀጠል ከፖለቲካ ጋር ምንም ዓነት ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች ለሚያቀርቡት “የመብታችን ተገፈፍን ጥያቄ” ተቀባይነት እንዲኖረው አስገደደ፡፡ ስለሆነም በዓለም አቀፍ ሕጉ መሠረት ወደ ፈለገው አገር መግባት ያቃተው ተሰዳጅ ወገን፣ከኢትዮጵያ ኬንያ፣ ከኬንያ ታንዛኒያ፣ከታንዛኒያ ሞዛምቢክ፣ ከሞዛምቢክ ደቡብ አፍሪካ፣ከደቡብ አፍሪካ ብራዚል፣ ከብረዚል ሜክሲኮ፣ከሜክሲኮ ዩ፣ኤስ.ኤ እያለ አያሌ ፈተናዎችንና ውጣውረዶችን አልፈው የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር ቀላል አለመሆኑ በጉልህ እየታየ ነው፡፡ በዚህ ውጣ ውረድ በሞላበት አስቸጋሪ የስደት ጉዞ በአራዊቶች ተበልተው፣በወባ ተነድፈው፣በልዩ ልዩ በሽታዎች ተይዘው ምኞታቸው ሳይሳካ ለሕልፈተ ሕይዎት የሚዳረጉት ቁጥር የት እየለሌ እንደሆነ በጉዞ ቀንቷቸው ከተመኙት አገር የደረሱ ሰዎች የሚናገሩት ነው፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ከግብፅና ከሶማሊያ ተነስተው ወደ እስራኤልና የመን፣ ከሊቢያ ወደ ጣሊያንና ግሪክ ለመግባት የሚጥሩ፣ ኢትዮጵያኖች በባሕር ላይ በሚያደርጉት ጉዞ ፣ ጉዞው ሕጋዊ ካለመሆኑ የተነሳ ከሚደርስባቸው የመጓጓዣ ጫና፣ እንግልትና መሳቀቅ በላይ የሚጓጓዡበት ጀልባ እየሰጠመና እየተገለበጠ የዓሣ ቀለብ የሚሆኑት አያሌዎች እንደሆኑ፣ የዓለም ብዡኃን መገናኛ መሣሪያዎች ዘወትር ለሕዝብ ጆሮ የሚያደርሱት ዜና ነው፡፡ በሌላ በኩል መንግሥት ነኝ ባዩ ሕፃናትና ወጣት ሴቶችን ለባርነት የሚሸጥ ድርጅት አቋቁሞ ሕዝቡን ለባርነት፣ለኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት አመቻችቶታል፡፡ ወደ ዐረቡ ዓለም በአገራቸው ሠርተው የመኖር ዕድሉን አጥተው በግልና በመንግሥት የሚሄዱት ሴቶች እህቶቻችን ቁጥር እጅግ ብዙ ነው፡፡ እነዚህ እህቶቻችን በዐረቡ ዓለም የሚገቡት ስማቸውን ለውጠው፣ሃይማኖታቸውን በልባቸው ይዘው፣በአፋቸው ግን ቀይረው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህስ በላይ የኅሊና ቅኝ ተገዥነት በምን ይገለጣል?
እኛ ኢትዮጵያውያን ለኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት እጃችን የሰጠን መሆኑ ማሳያው፣በሚደርሰብን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተፅዕኖች ባስከተለብን ሁለንተናዊ ጫና ብቻ የተሰደድን አለመሆኑን ስንገነዘብ ነው፡፡ እነዚህ ጫናዎች የደረሱባቸው ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነትን ወደው ወይም ፈቅደው ሳይሆን፣ ተገደው፣ ከቁጥጥራቸው ውጭ በሆነ ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑን ስለሚገነዘቡ፣ቅኝ ተገዥነቱ በኅሊናቸው ውስጥ ቦታ አይኖረውም፡፡ በመሆኑም የማንነታቸው መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቻቸውን የኔ ብለው ይጠብቋቸዋል፤ይንከባከቧቸውል፤ያስተዋውቋቸዋልም፡፡ በሌሎች ምክንያቶች ማለትም በኢኮኖሚ ጥቅሞችና ለተሻለ ሕይዎት ሲሉ የተሰደዱ ግን ፣ቀድመው ውጪ ያዩ በመሆኑ የነርሱነት መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቻቸውን ፈጥነው ከኅሊናቸው መፋቅ ብቻ ሳይሆን፣ በጥላቻና በንቀት ስለሚመለከቷቸው ያፍሩባቸዋል፤ አይገለገሉባቸውም፤እንዲታወቁም አይፈልጉም፡፡ ከሁሉም በላይ ወላጆች በፈለጉ ጊዜ ከፈለጉት አገር ለመውጣትና ለመግባት እንዲያም ሲል ለመኖር የሚፈልጉ ሰዎች፣ በአገራቸው ምንም ዓይነት የመኖር ችግር ሳይገጥማቸው ሚስቶቻቸው ሊወልዱ ጥቂት ሳምንታት ሲቀራቸው፣ አሜሪካ፣ካናዳ፣ጀርመን ወይም ሌላ አገር ሂደው እንዲወልዱና ሕፃናቱ የዚያ አገር ዜግነት እንዲኖራቸው የማድረጉ ተግባር በስፋት የሚታይ ነው፡፡ የእነዚህ ሰዎች ኅሊናዊ ቅኝ ተገዥነት መጠኑን ያለፈ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነት ያላቸው ስሜትና እምነት ባንዳዊ ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የተሻለ ገቢ ካላቸው ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ልጆቻቸው የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ያላቸው አይደሉም፡፡ ይህም ሕዝቡ ትናንት በዘመነ ቅኝ አገዛዝ ወቅት በአካል ቅኝ ያልተገዛው ኢትዮጵያዊ በሚከተሉት ሁለት ተያያዥና ተደጋጋፊ ምክንያቶች ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት እንደተዳረገ እናያለን፡፡
አንድ ሕዝብ ትውልድ አገሩን ትቶ ወደማያውቀው አገር የሚሰደደው ሁለት ተያያዥና ተደጋጋፊ የሆኑ ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡፡ የመጀመሪያው በአገሩ በሰላም ሠርቶ የመኖር ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማኅበራዊና ባህላዊ መብተና ነፃነቶቹን ሲገፈፍና ሲነጠቅ፣ በሕይዎት ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ሲጣበብበት ነው፡፡ ሁለተኛው ከአገሩ ወጥቶ ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ መኖሩ አስተማማኝ ሲሆን ናቸው፡፡ እነዚህም ከውስጥ አስወጪ ገፊ ኃይል እና ከውጪ ተቀባይ ሳቢ ኃይል መኖር ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ ላለፉት 50 እና 60 ዓመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ሕዝቡን በነበረ መልኩ እንዲኖር የፈቀደ አልሆነም፡፡ ትውልዱ በፖለቲካዊ ፍልስፍና፣በነገድ፣ በሃይማኖት፣በሥልጣን አያያዝ ተከፋፍሎ አገሪቱን የብጥብጥ ምድር አደረጋት፡፡ ሥልጣን የያዙ ቡድኖች ተቀናቃኛችን ነው ያሉትን ግለሰብና ቡድን ያላንዳች ርኅራኄ ገደሉ፣አሰሩ፣አሰቃዩ፤ የፖለቲካ ትርምሱ ማኅበራዊ ሰላምን በእጅጉ በማመሱ፣በሰላም ወጥቶ ለመግባት፣ሠርቶ ለማምረት፣ወልዶ ለመሳም፣አሳድጎ ለመዳር አላስቻለም፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በስፋትና በተከታታይ መታየት ሕዝቡን አማራጭ የመኖሪያ አካባቢን እንዲያማትር ግድ አለው፡፡ ባደረገው የአማራጪ መኖሪያ ፍለጋም ለማስተማር ቀይ ሳንቲም ሳያወጡ በተማረ የሰው ጉልበት ያልተማረ ሰው ሊሠራቸው የሚችሉ ሥራዎችን በጥራት፣በቅልጥፍናና ሥጋት በሚፈጥረው ጥንቃቄ ኃላፊነቱን የሚወጣ ፣ያወቀ፣ግን በርካሽ የጉልበት ዋጋ ጥራት ያለው ሥራ የሚሠራ የሰው ኃይል የሚፈልጉ አገሮች ቁጥር መበራከት፤(አሜሪካ፣ካናዳ፣አውትራሊያ፣ጀርመን፣ኖርዌ፣ስውዲን) የኢትዮጵያዊነት ብሔርተኝነትን ለማጥፋት የረጅም ጊዜ ዕቅድ የነበራቸው አገሮች የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ትውልዱን ከኢትዮጵያዊነት ስሜትና እምነት ለማፋታት ባለቸው የቆየ ዓላማ መሠረት፣ ስደት ፈላጊዎችን በገፍ የመቀበል ፍላጎት አሳዩ፡፡ ይህም የሕይዎት ማቆያ ፣የተሻለ ኑሮ መምራት አማራጪ ይፈልግ ለነበረው ሰው እንደመልካም አጋጣሚ ቆጥሮ የተቸገረውም ያልተቸገረውም ለስደት ተሰለፈ፡፡ ፣ስደትንም አማራጭ የሌለው ተመራጭ አድርጎ እንዲይዘው አደረገው፡፡ በነዚህ የውስጥና የውጪ ሁኔታዎች ተሟልተው መገኘት ኢትዮጵያዊው የተሻለ ኑሮና ሰላም የነበራቸው ሁሉ ቋሚ ንብረቶቻቸውን በአልባሌ ዋጋ እየሸጡ ተሰደዱ፡፡ ምዕራባውያኑ በተለይም ዩ.ኤስ.ኤ በራሱ ፍላጎት የሚሰደደው ሕዝብ የሚፈልገውን ያህል የተማረ የሰው ኃይል ሊያስገኝላት ባለመቻሉ፣ዲ.ቪ የሚል ፕሮግራም በመዘርጋት አያሌ የሦስተኛው ዓለም ሕዝቦችን የተማረ የሰው ኃይል መሳቡ ይታወቃል፡፡ በዚህ ፕሮግራም የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ይህም ወዶና ፈቅዶ ራስን ለኅሊና ቅኝ ተገዥነት ማዋል አለመሆኑን በምን መልክ ማሳመን ይቻላል?
በዚያም አልን በዚህ እኛ ኢትዮጵያውያን በአካል ቅኝ ሳንገዛ፣የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች መሆናችንን ልናስተባብልበት የምንችልበት ማስረጃ የለም፡፡ የሚያዋጣው የኅሊና ቅኝ ተገዥዎች አልሆንም ብሎ በመሸምጠጥ ሳይሆን፣ለዚህ የዳረጉንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ዐውቀን ከነዚያ ሁኔታዎች ልንወጣ የምንችልባቸውን መንገዶች ማመቻቸት ነው፡፡ እንደ ነገድ ሳይሆን፣እንደ አገር በአንድነት ማሰብና በአንድነት መቆም ስንችል ነው፡፡ የተጫነንን ከማንነት የመፋታት አባዜ ከላያችን ላይ አራግፈን ጥለን አኩሪው ማንነታችን ስንላበስ ነው፡፡ ታሪካችን ፣ባህላችን፣ቋንቋችን፣ በአጠቃላይ እኛነታችን ዐውቀን ለማንነታችን ዳብሮ መቀጥል ስንቆም፣ለዚህም ተገቢ የሆነውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ስንሆን ብቻ ነው፡፡
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Saturday, May 18th, 2013
ፈረንጆች ታይታኒክ የተባለችውን ግዙፍ መርከብ የገለበጠውን ዓይነት ከባሕር በታች የተደበቀ ግግር በረዶ ‘ለአንዳንድ የማይታዩ ነገር ግን ግዙፍ የሆኑ’ ችግሮች ተምሳሌት አድርገው ይጠቀሙበታል።ከባሕሩ ውስጥ ብቅ ብሎ የሚታየው የበረዶ ጫፍ ሲያዩት ትንሽ ስለሚመስል ብዙዎችን ያሳስታል-ከሥሩ ያለውን ተራራ የሚያህል ግዙፍ የበረዶ ግግር ለመገመት አያስችልምና።ለዚህም ነው አንዳንድ ተገልጦ ያልታየ ነገር ግን በትንሹ ብቅ ያለ ችግርን “this is only the tip of the iceberg” (ይህ የግግር በረዶው ጫፍ ብቻ ነው) በማለት የሚገልጹት-ከሥሩ ቢታይ ሥር የሰደደና ሰፊ ነው ለማለት።
ሰሞኑን ከተራ ደላሎችና ትራንዚተሮች አንሥቶ እስከ ቱጃር ባለሀብቶችና ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ድረስ የተዳረሰው የሙስና ቅሌት የብዙው ዜጋ የመወያያ ርእስ ሆኖ ሰንብቷል።ይህ የሰሞኑ ክስተት ብቻውን ግን የመጨረሻ ውጤት አይደለም።ይልቅስ ከባሕር በታች ገዝፎ እንደተደበቀው የግግሩ በረዶ ጫፍ ጥቂቱ ማሳያ ነው እንጂ።
መንግሥት ለረጅም ዘመን ሙስናን የመዋጋት ቁርጠኝነትም ቢያሳይም በዚያው ልክ ግን ችግሩ በአገራችን አሳሳቢ ደረጃ ላይ አልደረሰም ሲል ኖሯል። አንዳንድ መረጃዎች ብቅ ሲሉም ችግሩ እንደሚወራው አይደለም፣ የተጋነነ ነው ሲል ተደምጧል። ይህን ሲል ቢቆይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የሙስናን አፈጻጸም ረቂቅነትን እያባከነ ያለውን የሕዝብና የሀገር ንብረት ሲያስተውል ግን አሳሳቢነቱን አምኖ ለመቀበል ተገድዷል፡:
በአገራችን እየተስፋፋ የመጣውን ሙስና በተመለከተ ከመንግሥት አስቀድሞ የነቃው ሕዝቡ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሙሰኞችን በተመለከተ ሕዝቡ “በማስረጃ ካልሆነ” እየተባለ ሐሳቡን የሚገልጽበት መድረክ ባያገኝም እርስ በርሱ መወያየቱ ግን አልቀረም፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፍጥነት ወደላይ እየተተኮሰ የመጣውን የአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት አኗኗር በመመልከትም ሆነ ያካበቱትን ንብረት በመታዘብ ከጥርጣሬ ያለፈ ግንዛቤ ይዞ ነበር፡፡ ቢያንስ እነዚህ ሰዎች ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብና ሀብት ማካበታቸውን መጠርጠር ችሏልና።
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እስከ አሁን ድረስ በሙስና ባሕር ውስጥ ሲዋኙ የቆዩትን ትንንሾቹን ዓሣዎች እንጂ ዓሣ ነባሪዎቹን ለመያዝ ድፍረቱም፣ ፍላጎቱም አቅሙም የለውም እየተባለ ሲታማ ቆይቷል፡፡ በተለያዩ መድረኮችም ተጠይቋል። ለምሳሌም ኮሚሽኑ ባለፈው ማክሰኞ የሰሞኑን ሙስና በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ይኸው ጥያቄ ለኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን ተነሥቶላቸው ነበር። “እኛ ከግለሰቦች ጋር ሳይሆን ከወንጀሉ ጋር ነው ጉዳያችን። ሙስና ከፈጸመ ማንንም አንተውም። ሁሉንም ጥፋተኞች ለሕግ እናቀርባለን” ብለዋል።
ያም ሆኖ ‘የመንግሥትን ሌቦች’ በተፈለገው ሁኔታ ወደፍርድ አደባባይ ቶሎ ቶሎ ብቅ ሲሉ አይተናቸው አናውቅም። አንዳንድ ጊዜ ስለመንግሥት ሌቦች በመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ መሰግሰግና አለአግባብ መበልፀግ አልፎ አልፎ በራሱ በመንግሥት ከሚነገረው ውጪ እነዚህ ‘ሌባ’ የተባሉት ሰዎች የት እንዳሉና የተነከሩበት የሙስና ባሕር ስፋትና ጥልቀትስ ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአብዛኛው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ባሉ በመንግሥት መሥሪያ ቤት ሹሞች የሚፈፀሙትን የሙስና ድርጊቶች ተከታትሎ በማጋለጥና አጥፊዎች በማስቀጣት ረገድ የማይናቅ ሥራ ቢሠራም ትልልቆቹን ዓሣዎች ግን በተደጋጋሚ ጊዜ ሳይደፍራቸው ቆይቶ ነበር፡፡
አሁን ፀረ ሙስና ኮሚሽን የጀመረው ሙሰኞችን ወደሕግ የማቅረብ አካሄድ ይበልጥ ይግፋበት የሚያሰኝ ተግባር ነው፡፡ ለዚህ የኮሚሽኑ እርምጃም ከመቀመጫችን ተነሥተን ተገቢውን ክብርና አድናቆት እንሰጣለን፡፡ ሙስናን መዋጋት የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጎች ሓላፊነት መሆኑን በመረዳት ለኮሚሽኑ ሥራ መቃናት የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ በስም ያልተገለጹ ዜጎችም በአድናቆት እናጨበጭባለን። ይህን በምንናገርበት አንደበታችንም እግረ መንገዳችንን እርማት የሚያሻውን የኮሚሽኑን አካሔድ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡
አንደኛ ነገር ኮሚሽኑ በአንድ መንግሥት መሥሪያ ቤትና በተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን በተመረጡ ተቋሞች ላይ ጊዜ ወስዶ ተመሳሳይ መረጃ የመሰብሰብ ሥራውን ካጠናቀቀ በኋላ ውጤቱን በአንድ ላይ ይፋ ቢያደርግ የተሻለ ይሆን ነበር እንላለን፡፡ አሁን እንዳደረገው በአንድ ቦታ ላይ ማተኮሩ ለሌሎች የማንቂያ ደወል ሊሆናቸው ይችላል፡፡ በዚህም መረጃዎችን ለመደበቅ፣ ምስክሮች ሊሆኑ የሚችሉትን የዶክመንትና የሰው ማስረጃዎችን ደብዛ ለማጥፋት እንዲሁም በሙስና የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት በተለያዩ ዘዴዎች ለማሸሽ ጊዜ ያገኛሉ ማለት ነው፡፡
አሁን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በፍርድ ቤት እልባት እስኪያገኝ ድረስ የሕዝቡም የኮሚሽኑም ትኩረት በእነሱ ላይ ይውልና ያልተጋለጡ ባለሥልጣናት ከሚታዩበት የግግር በረዶው ጫፍ ተነሥተው ወደ ጥልቁ ባሕር ለመግባትና ለመሰወር አመቺ ሁኔታ ሊፈጠርላቸው ይችላል፡፡ ሁለት ዓመት ፈጀ የተባለው ክትትል እነዚህን 24 ሰዎች ብቻ ለመያዝ ከሆነ በርግጠኝነት ዘግይቷል። ክስ ከተመሰረተበት የሙስና ጉዳይ ተነካኪነት አንጻር ሲታይ ሌሎችም ባሕሩ የደበቃቸው ብዙዎች መኖራቸው አይቀርም።
ያም ሆኖ አሁን የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ የግግሩ በረዶ ጫፍ በባሕሩ ተሸፍኖ ሳይጠፋ በፊት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ በሌላ አባባል የአንድ ሰሞን የሚዲያ ግርግር ከመሆን አልፎ ተከታታይ መሆን ይጠበቅበታል ማለት ነው፡፡
ሁለተኛው ጉዳይ ኮሚሽኑ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሀብት ምዝገባ ውጤት ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ብሎ ቃል ከገባ ረዘም ያለ ጊዜ ቢሆንም ይህ እስከ አሁን ባለመፈፀሙ የትኛው የመንግሥት ባለሥልጣን ምን ያህል ሀብት እንዳለው በሕዝቡ ዘንድ ሳይታወቅ ቆይቷል፡፡ ይህ የ30ሺህ ሰዎችን ሀብት መዝግቤያለሁ የሚለው የኮሚሽኑ ድክመት ነው። የባለሥልጣናት ሀብት በጊዜ ቢታወቅ ኖሮ ከሚታወቀው አቅማቸው በላይ ሲያካብቱ ሕዝብ አይቶ ዝም አይልም ነበር።
ሌላው ኮሚሽኑ የግሉን ዘርፍ ‘አያገባኝም’ ብሎ መተዉ አግባብ አይደለም እንላለን። እስከ አሁን ድረስ በሙስና ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተከሰሱት የግል ባለሀብቶች ናቸው። ከየት እንዳመጡት ሳይታወቅ ድንገት ጣሪያ ላይ የሚወጡት የግል ባለሀብቶች ጀርባ ካልተጠና ወደፊትም ባለሥልጣናትን ማባለጋቸው፣ ሙስናውም ተጠናክሮ መቀጠሉ አይቀርም።
የሆነው ሆኖ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እስካሁን የሠራው ሥራ የሚያስመሰግነው ነው። የራሱን አቃቤ ሕግ በሙስና ከመክሰስ አንሥቶ ‘የመንግሥት ሌቦችን’ ጥሩ እያየ ነው። አሁንም የመንግሥት ባለሥልጣናትን ሀብት በፍጥነት ለሕዝቡ ያሳውቅ፡፡ ካሁን በኋላም ጥረቱን በማጠናከር ከሕዝቡም ከሚዲያው ጋር ይበልጥ በመተባበር በሙስና ላይ የተጀመረውንና ጠብ…ጠብ የሚለውን ካፊያ ዘመቻ ወደ ጎርፍ ይለውጥ! ከግግር በረዶው ጫፍ ላይ የሚታዩትንም ሆነ ከባሕሩ ሥር የተደበቁትን ተጠርጣሪዎች ለማጋለጥና ለፍርድ ለማቅረብ ይበልጥ በተቀናጀ ሁኔታ ይነሳ! የሙስናውን ዛፍ ከቅርንጫፉ ብቻ ሳይሆን ከሥሩ ይቁረጥ!!
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Saturday, May 18th, 2013
(ዘ-ሐበሻ) በሕዝብ ዘንድ “ልማታዊ አርቲስት” በሚል የመሽሟጠጫ ስያሜ ከሚጠሩት አርቲስቶች መካከል የቀድሞው የደርግ ወታደርና የአሁኑ የወያኔ ስርዓት ዋነኛ አቀንቃኝ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፤ ለመንግስት በሚያደርጋቸው የአጎብዳጅነት ተግባራት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ የቶክ ሾው ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ የዓየር ሰዓት ተፈቅዶላት ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደጠቆሙት አርቲስቱ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ ያቀርበው የነበረው ቶክ ሾው ውለታው ተዘንግቶ እንዲታገድ ተደርጓል።
“ግራና ቀኝ” የሚል ቶክ ሾው ከሌላኛው ‘ልማታዊ’አርቲስት ሽመልስ በቀለ ጋር ላለፉት 6 ወራት ሲያቀርብ የቆየው የደርጉ ወታደር ሰራዊት ፍቅሬ ይህን የዓየር ሰዓት ያገኘው ለመንግስት ባለው ታማኝነት እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ድንገት ያቀርበው የነበረው ፕሮግራም በወያኔ ካድሬዎች በሚመራው ኢቲቪ እንዲታገድ መዳረጉ አስተተያየት ሰጪዎችን “ፍቅር አለቀ ወይ?” የሚሉ ግምቶችን እንዲሰጡ በር ከፍቶላቸዋል።
የአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት ከተሰማ በኋላ አርቲስቶች ጥቁር በጥቁር ለብሰው “ባለ ራዕዩን መሪ” እንዲቀብሩ በማስተባበር እንዲሁም ጥቁር በጥቁር አንለብስም ያሉና ለቅሶ አንደርስም ያሉ አርቲስቶችን “ሲያስጠቁር” (ለመንግስት በማቃጠር) ነበር እየተባለ የሚተቸው አርቲስቱ 6 ወር በቴሌቭዥን ያቀረበው “ግራና ቀኝ” ቶክ ሾው እንዲታገድ የተደረገው “አዝናኝ ፕሮግራም” አይደለም በሚል ምክንያት ነው ተብሏል። ይህ እገዳ እስከመቼ ሊቀጥል እንደሚችል እንደማያውቁ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከባለፈው እሁድ ጀምሮ መታየት አቁሟል ብለዋል።
ኢቲቪ ወትሮም አዝናኝ ፕሮግራም አቅርቦ የት ያውቅና ሲሉ የሚተቹ አስተያየት ሰጪዎች አዝናኝ ፕሮግራም አይደለም በሚል ቶክ ሾው እንዲታገድ መደረጉ በቂ ምክንያት አይደለም በሚል ከእገዳው በስተጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ይገምታሉ። በተለይም እንደሪፖርተርን ያሉ አፍቃሬ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ያሉ ጋዜጦች “በአቶ መለስ ስም መነገድ ይቁም” በሚል በረዥሙ ሲተቹ የከረሙት እንደሠራዊት ያሉትን ሆዳም አርቲስቶች ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች የኢቲቪ ካድሬ መሬዎች የሰራዊትን ማንነት በግልጽ ተረድተው ይሆናል ያገዱት ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
በዚህ ዜና ዙሪያ ዘ-ሐበሻ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬን ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በቅርቡም በአስገድዶ መድፈር አቤቱታ እንደቀረበበት መዘገቡ ይታወሳል።
የአስገድዶ መድፈር አቤቱታውን ዜና ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለግንዛቤ ደግሞ የታገደውን የሰራዊት ፍቅሬ ሾው አቅርበናል።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Saturday, May 18th, 2013

ከአሰግድ ተስፋዬ
የተወዳጁ እግር ኳስ ስፖርት « ፈጣሪ » እንደሆነች የሚነገርላት ነገር ግን በዓለም አቀፍ ውድድሮች ብዙም ውጤታማ መሆን ያልቻለው እንግሊዝ በተለያዩ ወቅቶች ምርጥ እግር ኳሰኞችን አፍርታለች።
ከነዚህ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች ኮከቦች መካከል ላለፉት ሃያ ዓመታት በስፖርቱ በስኬታማነት ያሳለፈው ዴቪድ ቤካምና ከልጅነት እስከ እውቀቱ የመርሲሳይዱን ክለብ መለያ ብቻ የለበሰው ጂሚ ካራገርን ፣ ዋይኔ ሩኒን ፣ ማይክል ኦዌንና ሌሎች ተጫዋቾችን መጥቀስ ይቻላል።
ከእነዚህ ተጫዋቾች መካከል በስፖርቱ ባስመዘገበው ስኬት ግንባር ቀደም የሆነው ዴቪድ ቤካምና የሊቨርፑሉ ጂሚ ካራገር « ጫማ መስቀላቸውን» ገልጸዋል። የማንችስተር ዩናይትዱ የተከላካይ መስመር ተሰላፊው ሪዮ ፈርዲናንድ ደግሞ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
እነዚህ ጉዳዮች የመገናኛ ብዙኃን ሰሞነኛ መሪ ዜና ቢሆኑም ልዩ ትኩረት ያገኘው የዴቪድ ቤካም ጫማ መስቀል ጉዳይ ነው።
አንጋፋውና ውጤታማው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ የነበሩት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ካሳደጓቸውና « ፈርጊ ቤቢስ » እየተባሉ ይታወቁ ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ዴቪድ ቤካም ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በ115 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል። ለአሳዳጊው ማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ ደግሞ 394 ጨዋታዎችን አድርጓል።
የ38 ዓመቱ ቤካም « ቀያይ ሰይጣኖች » በመባል ከሚታወቀው ማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ጋር ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችንና የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በምስራቃዊ ለንደን የተወለደው የመሐል ሜዳ ተጫዋቹ ቤካም ከአሳዳጊው ክለብ ከተለያየ በኋላ ለስፔኑ ኃያል ሪያል ማድሪድ ፣ በአሜሪካ ሜጀር ሶከር ሊግ ተሳታፊ ለሆነው ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ፣ለጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ፣ በመጨረሻ ደግሞ ለፈረንሳዩ ሻምፒዮና ፓሪስ ሴንት ጄርሜን እግር ኳስ ክለቦች ተጫውቷል። ተጫዋቹ በጨዋታ ዘመኑ ከዩናይትድ ጋር ያነሳቸውን ዋንጫዎች ጨምሮ በጠቅላላው 19 ዋንጫዎችን አንስቷል።
ዴቪድ ቤካም በአራት የተለያዩ ሊጎች ከተለያዩ ክለቦች ጋር ዋንጫ በማንሳት ብቸኛው እንግሊዛዊ ተጫዋችም ነው።
ዴቪድ ቤካም ቀያይ ሰይጣኖቹን በተለ ማማጅነት የተቀላቀለው በአውሮፓውያኑ 1991 ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ለዋናው ቡድን ተሰልፎ የመጫወት እድል አግኝቷል። ከአንድ ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን የፕሮፌሽናል ተጫዋችነት ኮንትራት ፈርሟል። በኦልድ ትራፎርድ በነበረው ቆይታ ያሳየው ምርጥ ብቃቱ ዓለም አቀፍ እውቅና አስገኝቶለታል። ይህንን እውቅናውን ተከትሎም ታላላቅ ተጫዋቾችን በመሰብሰብ የሚታወቀውን የስፔኑን ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሎ በአውሮፓውያኑ 2003 የላ ሊጋውን ዋንጫ አንስቷል።
ከስፔኑ ኃያል ወደ አሜሪካው ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ ተዛውሮ ተጫውቷል። በዚህ ክለብ በነበረው ቆይታ በውሰት ለጣሊያኑ ኤሲ ሚላን ተሰልፎ የመጫወት እድል አግኝቷል። ወደክለቡ ኤልኤ ጋላክሲ ተመልሶ ዋንጫ ካነሳ በኋላ ለፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጄርሜን ፈርሞ ተጫውቷል። እንዲሁም ዋንጫ ካነሳ በኋላ ጫማ መስቀሉን ይፋ አድርጓል።
ቤካም በሦስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ግብ በማስቆጠር ብቸኛው እንግሊዛዊ ተጫዋች ከመሆኑም በላይ በአውሮፓ ዋንጫ ለግብ የሚሆኑ በርካታ ኳሶችን በማቀበል በታሪክ ሁለተኛው ተጫዋች ነው።
«ለልጅነት ክለቤ ማንችስተር ዩናይትድ ተጫውቼ ዋንጫዎችን አንስቻለሁ። ለአገሬም ከአንድ መቶ በላይ ጨዋታዎችን ከማድረጌም በላይ በአምበልነት መርቻለሁ ። ለታላላቅ ክለቦች ተጫውቻለሁ። ይህ ለእኔ ከስኬትም በላይ ነው» ብሏል ስንብቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫው።
«በእግር ኳስ ተጫዋችነት ሕይወቴ ካከና ወንኳቸው ተግባራት ከምኮራባቸው ነገሮች አንዱ አገሬን በአምበልነት መምራት መቻሌ ነው። የሦስቱን አናብስት መለያ በመልበሴ ከታላላቆቹ ተጫዋቾች ተርታ ከመመደቤም በተጨማሪ አገራቸውን ለሚወዱ ደጋፊዎችም የኩራት ምንጭ ሆኛለሁ። በዚህም እድለኛ ነኝ » ብሏል።
ሰዎች ሜዳ ሲገባ ያለውን ሁሉ እንደሚሰጥ ጠንካራ እግር ኳሰኛ እንዲያየኝ እፈልጋለሁ ያለው ቤካም በተጫዋችንት ሕይወቱ የረዱትን ሁሉ አመስግኗል።
የእንግሊዝ ዋና ከተማ የ2012 ኦሊምፒክ የአዘጋጅነት እድል እንድታገኝና እድሉን ካገኘች በኋላም በዝግጅቱ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገውን የቤካምን ከእግር ኳስ ዓለም መገለል አስመልክቶ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች አድናቆታቸውን ለተጫዋቹ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።
ሰሞኑን ራሳቸውን ከእግር ኳስ ተጫዋችነት ማግለላቸውን ካስታወቁት መካከል የሊቨርፑሉ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ጂሚ ካራገር ይገኝበታል። የ35 ዓመቱ ካራገር ክለቡ ሊቨርፑል እሁድ ከኩዊንስ ፓርክ ሬንጀርስ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ ላይ ከተሳተፈ በኋላ ነው ሙሉ ለሙሉ ከጨዋታ ዓለም የሚገለለው።
ካራገር በእግር ኳስ ተጫዋችነት በሊቨርፑል ባሳለፋቸው 16 ዓመታት ሁለት የኤፍኤ ፣ ሦስት የሊግ ፣ሁለት የኮሙኒቲ ሽልድና አንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ቢያነሳም አንድም ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሳያነሳ ከኳስ ተጫዋችነት መገለሉ እንደሚቆጨው ተናግሯል።
« የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ
አላገኘሁም።ይህ ከፍተኛ ቁጭት ውስጥ እንድገባ አድርጎኛል » ብሏል።
ሊቨርፑል 732 ጨዋታዎችን ያደረገው ካራገር ለክለቡ በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ ሁለተኛው ተጫዋች መሆን ችሏል።ለሊቨርፑል በርካታ ጨዋታዎችን በማድረግ ቀዳሚ የሆነው ያን ካላጋን ሲሆን ተጫዋቹ 857 ጊዜ የመርሲሳይዱን ክለብ መለያ አድርጎ ተጫውቷል።
በቴሌቪዥን የእግር ኳስ ተንታኝ ሆኖ ለመስራት ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ካራገር « ጫማውን የመስቀል » ውሳኔ ላይ የደረሰው ከ12 ወራት በፊት እንደነበረም ገልጿል።
እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብ የተከላካይ መስመር ተሰላፊ ሪዮ ፈርዲናንድ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።
ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን 81 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተው የ38 ዓመቱ ፈርዲናንድ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ለማግለሉ በምክንያትነት የጠቀሰው ትኩረቱን ለክለቡ ለማድረግ በመፈለጉ መሆኑን ተናግሯል። እነዚህ ተጫዋቾች ጉዳይ የሰሞኑ የዓለም የመገናኛ ብዙኃን የፊት ገጽ ዜናና መነጋገሪያ ሆነውሰንብተዋል።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Saturday, May 18th, 2013
ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
የአቶ መለስን መሞት መንግስት ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም. ይፋ አደረገ። መንግስት ጥር 17 ቀን 2005 ዓ.ም. የመለስ ራዕይ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ህዝብ በሃዘን መግለጹን የሚያብራራ እና መታሰቢያ ተቋም የሚመሰረት ህግ አወጀ። የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ተቋም የገቢ ምንጭ የግል ለጋሾች፣ ገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞች፣ የኢትዮጵያ መንግስት እና ሌሎች ምንጮች እንደሚሆኑ አዋጁ ጨምሮ አብራራ። መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ደግሞ ህውሃት ‘የመታሰቢያ ተቋም መስራች ጉባኤ’ ተብሎ የሚጠራ ሌላ ድራማ በማዘጋጀት የኢትዮጵያ ህዝብ በአቶ መለስ ራዕይ ፍቅር መጠመዱን እና ይኽን ፍቅሩን በሃዘን መግለጹን የተለያዩ ተናጋሪዎች በጉባኤው እንዲያብራሩ አደረገ። የመታሰቢያ ተቋሙ ግቦች እና ተዛማጅ ጉዳዮችም ተነገሩ። በድርጅታዊ የሚስጢር አሰራር ቀደም ብሎ የተመረጡ የቦርድ አባላት በጉባኤው ላይ አንደ አዲስ ተመረጡ። ወ/ሮ አዜብም ፕሬዘዳንት ተደርጋ ተመረጠች። ‘መለስ እንደተሰዋ ሁሉ እኛም እስከምንሰዋ ድረስ ለመስራት ቃል እንገባለን‘ የሚል የደርግ አይነት መፈክር በማሰማት ምርጫውን መቀበሏን ገለጸች። ይኽ ድራማ የታየው በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ይሁንና አዜብ መስፍን በጉባኤው ላይ ‘እንደ መለስ እስከምንሰዋ ድረስ እንሰራለን’ ስትል ‘እስክንሞት ድረስ አምባገነናዊ አገዛዛችን ይቀጥላል’ ማለቷ ይመስላል። አምስት ነጥቦች አነሳለሁ።
Download (PDF, 107KB)
ክፍል 1ን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ክፍል 2ን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Saturday, May 18th, 2013
ዘጋቢ በየነ መስፍን ከጀርመን
እ.ኤ.አ በሜይ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን በርሊን ከተማ የኢትዮጵያውያን የፖለቲካና ሲቪክ ማህበር አባላት አንድነት ድርጅት (ኢ.ፕ.ኮ.) በጠራው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ350 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ፓርቲ /ኢሕአፓ/፣የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት /ሞረሽ/ እና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አመራር እና አባላትም በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል።

መነሻውን ”ቬንደርሸር ማርክት አንድ” /Werderscher Markt 1/ ከሚባለው የከተማው ክፍል በማድረግ በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ባንድራ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ቻንስለር አንጌላ ሜርክል ጽ/ቤት አድርጓል።
”በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገው የዘር ማጥራት ዘመቻ ይቁም!”
”የህሊና እስረኞች ይፈቱ!”
”የሃይማኖት ነፃነት ይከበር!”
”ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ!”
”የጀርመን መንግስትና የአውሮፓ ህብረት ለአፋኙ የወያኔ አገዛዝ የሚያደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ ያቁሙ!”
”ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር!” የሚሉ መፈክሮች በሰፊው የተደመጡ ሲሆን ከአንድ ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ ተሰላፊው በመጀመሪያ በጀርመን ፓርላማ /Bundestag/ ፊት ለፊት በኋላም በጀርመን ቻንስለር ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ የተለያዩ መፈክሮችን ያሰማ ሲሆን ከአንድ ወር በፊት በኢ.ፕ.ኮ. አማካኝነት በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን የዘር ማጥራት ወንጀል የሚቃወሙ ቁጥራቸው ከሶስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ጀርመናውያንን ፊርማ የያዘውን ሰነድ ለቻንስለሯ ጽ/ቤት ገቢ የተደረገ ሲሆን የኢ.ፕ.ኮ. ሊቀ መንበር፣እንዲሁም የኢሕአፓ ተወካይ፣የሞረሽ እና የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተወካዮች አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ይህ ከሶስት ሰዓት በላይ የፈጀ የተቃውሞ ሰልፍ በሠላምና በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Saturday, May 18th, 2013

(ዘ-ሐበሻ) በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ “የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችና ተቋማት” የውድቀት አደጋ አንዣቦባቸዋል ሲል ስጋቱን ገለጸ። ማህበሩ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “በመምህራን ላይ የሚታየው የ እውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመሙላት አጫጭር ስልጠናዎችንና የክረምት ኮርሶች ቢሰጡም የትምህርቱ ጥራት ዋነኛ መመዘኛ መስፈርት የፖለቲካ ታማኝነት የሚለው ስንኩል የወያኔ አስተሳሰብ ገኖ በመውጣቱ በርካታ ልምድ ያላቸው መምህራን ሥራቸውን እያለቀቁ መሄዳቸው የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ተቋማት በአሁኑ ጊዜ ይበልጥ ተዳክመዋል” ብሏል።
Download (PDF, 621KB)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Friday, May 17th, 2013
ዘ-ሐበሻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ እንዳያጠምቁ መታገዳቸውን መዘገቧ ይታወሳል። ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው ደግሞ አዲስ አበባ የሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት የአጥማቂውን እግድ እንዳጸና ገልጿል። በአነጋጋሪነታቸው የቀጠሉት መምህር ግርማ እንዳያጠምቁ መታገዳቸው ከተሰማ በኋላ ም ዕመናን የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።
ጠ/ቤተክህነቱ ግንቦት 2 ቀን 2005 ለ:-
- ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
- ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ ልዩ ጽ/ቤት
- ለአስተዳደር መምሪያ
- ለሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
- ለምሥራቅ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
- ለፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት
- ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
- ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት
- ለአ/አ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
- ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
- ለአ/አ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ
- ለቂርቆስ ክ/ከ ፍትሕ ጽ/ቤት
ግልባጭ አድርጎ በጻፈው የእግዳ ማጽኛ ደብዳቤ ላይ መምህሩን “አጥማቂ ነኝ ባይ” ሲል ገልጿቸዋል። ደብዳቤውን እንደወረደ ያንብቡት።
ጉዳዩ፡- በአስቸኳይ አጥማቂ መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ጉ/ጽ/ቤት በቁጥር 339/ቀ/አ/ቤ/ክ በ28/8/2005 ዓ.ም የተሰጠው እገዳ መ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት ያጸናው ስለመኾኑ ይመለከታል፤
መ/ር ግርማ ወንድሙ ሰባኬ ወንጌልና አጥማቂ ነኝ፤ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት በሕገ ወጥ መንገድ እስከ አሁን ድረስ በደብሩ እያጠመቁ ይገኛሉ፡፡
ይኹንና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከ1993 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ በየወቅቱ በሕገ ወጥ መንገድ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት ሕዝበ ክርስቲያኑን በየደብሩ ቅጽር ግቢ በማሰባሰብ የሚያጠምቁትን በተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ከቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና ሥርዐት ውጭ በሚፈጸም ስብከትና ጥምቀት፤
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሳይፈቅዱ የሚሰጥ የወንጌልና ጥምቀት አገልግሎት መስጠትን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ቢኾንም በሥርዐተ አልበኝነት በተለያዩ ቦታዎች የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሲጣስ ይታያል፡፡
በመኾኑም መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚፈጽሙት ሕገ ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና የወንጌል አገልግሎት መኾኑን እየገለጽን የእምነታችን ተከታይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከዚህ እግድ ጋራ በተያያዘ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥመው የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ጥብቅ ክትትል በማድረግ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ እያሳሰብን የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላትም የቤተ ክርስቲያኒቱን ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን::
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Thursday, May 16th, 2013
ከይገርማል ታሪኩ
ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ መዐሕድን ሲቀላቀሉ ድርጅቱ በአማራው ክልል እግሩን አልሰደደም ነበር:: ችግሩ ፋታ የሚሰጥ አይደለም:: አማሮች ካለአለሁ ባይ: ካለአይዟችሁ ባይ እየተጨፈጨፉ ነው:: በቀልን ሰንቆ ከበረሀ የተነሳውና ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ በእጁ ያደረገው ወያኔ ሀላፊነት በጎደለው የጭካኔ ተግባር በአማራው ህዝብ ላይ ሽብር ነዛ- ሞት አወጀ:: መዐሕድን በሁለት እግሩ እንዲቆም ለማድረግ በሰውሀይል ማጠናከር ያስፈልጋል:: ህዝብን የማደራጀትና የማንቃት ስራ ገንዘብ ያስፈልገዋል:: የወገን ጩኸት ያባነናቸው አማሮች በከተሞች አካባቢ በቁጭት ድርጅቱን ለማጠናከር ደፋ ቀና ማለት ጀመሩ::
ብዙሀኑ ገበሬ ምን እየተደረገ እንደሆነ እንኳ አያውቅም:: መንግስት ይመጣል መንግስት ይሄዳል:: “ሽህ ቢታለብ ያው በገሌ” እንዳለችው ድመት ማንም መጣ ማን ያው አርሶ አደር ነውና ሁሉም የእለት ጉርሱን የአመት ልብሱን ያሟላ ዘንድ ደፋ ቀና ይላል:: ሌሊት ወጥቶ ሌሊት ይገባል:: ጠብ ለማይል ኑሮ ነጋ ጠባ ደፋ ቀና እንዳለ ይኖራል:: ወሬ የሚያዳምጥበት ጊዜ የለውም:: ብቻ ይሰራል- ሰርቶ ከሚያገኘው ይገብራል:: ገበሬው የሚፈቀደው የግብር ጊዜ ወይም የተለየ መዋጮ እንዲያደርግ ሲፈለግ: አሊያም ለውትድርና:: ከዚያ ውጭ የት ወደቀ የሚለው የለም:: እርሱም የቤቱን ገበና ለመሸፈን ላይ ታች ከማለት ውጪ ስለፖለቲካ የሚያውቀው ነገር የለውም:: መንግስት- አስተዳዳሪ: የህዝብን ሰላም የሀገርን ዳር ድንበር አስጠባቂ: መሰረት ልማት (መንገድ: አስኳላ ትምህርት: የጤና ተቋም…) አስፋፊ መሆኑን ያውቃል:: የመንግስት ዘር መኖሩን ግን አያውቅም:: አንዱን ህዝብ ጎድቶ ሌላውን ለመጥቀም እንደሚያልምም አያውቅም:: በርግጥ በዘር ወይም በቀረቤታ የሚሰሩ ባለስልጣኖች እንደነበሩ: አሁንም እንደማይጠፉ ያውቃል:: የማያውቀው ነገር ቢኖር መንግስት ለአንዱ ወላጅ አባት ለሌላው ደግሞ የእንጀራ አባት መሆን ስለመቻሉ ነው::
ከተሜው የገበሬውን ያህል ለፖለቲካ ሩቅ አይደለም:: ለሚዲያወች የተሻለ ቀረቤታ ስላለው ምን እየተካሄደ እንዳለ መጠነኛም ቢሆን ግንዛቤው አለው:: ስለዚህ ይህንን የህብረተሰብ ክፍል ማደራጀት ብዙም አይከብድም:: ግን እንዴት? ሰላምና መረጋጋት ብሎ መንግስት ያደራጃቸውና የኮር አባል ተብለው የሚታወቁት ምልምል ካድሬወች ህዝቡን ሰላሙን ነሱት:: በኮር አባላት ስብሰባ ላይ የመጀመሪያው ክፍል ኢንፎርሜሽን ማቀበል ነው:: ስለዚህ የኮር አባላቱ አይደለም የሚወራውን የሚበላውንና የሚጠጣውን ሳይቀር እያነሱ እገሌ እንዲህ አለ: እገሊት ከገሊት ቤት ቡና ጠጣች በማለት በየተሰጣቸው ቀጠና ያዩትንና የሰሙትን እያጋነኑ ያቀርቡ ጀመር:: ኢንፎርሜሽን ያላመጣ የኮር አባል ስለሚገመገም ግምገማውን ለማለፍ አይደለም የታየውና የተሰማው ያልታየና ያልተደረገው ሁሉ በንጹሀን ላይ መወራት ጀመረ:: የኮር አባላቱ በግላጭ አይታወቁ ስለነበር አንዱ አንዱን ማመን እየከበደው መጣ:: ፍርሀትና ጥርጣሬ ነገሰ:: የመንግስትን ፖሊሲ ይነቅፋሉ የተባሉ ሰዎች የተነፈሱት ሳይቀር እየተነገራቸው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ምክርና ማስፈራሪ ይሰጣቸው ጀመር:: ምክርና ማስጠንቀቂያውን የጣሱ ሰዎች ሰርቀው ሊያመልጡ ሲሉ ተገደሉ: ወይም መጠጥ ቤት በተነሳ ግጭት ክፉኛ ተደብድበው ሞቱ: ወይም ባላንጣ ጊዜ ጠብቆ ገደላቸው እየተባሉ ተወገዱ:: የደርግ የቀይ ሽብር በድብቅ መተግበር ጀመረ:: ይህን ዘመን ለማለፍ ከተሜው ኮረንቲና ፖለቲካን በሩቁ አለ::
ድርጅት ለመመስረት የሚደረገው ትግል ግን በምንም መልኩ ሊደናቀፍ አይችልም:: መከፈል የሚያስፈልገው መስዋእትነት ተከፍሎ መዐሕድ እውን መሆን አለበት:: ድርጅቱ ስር እስኪሰድ ድረስ ለየት ያለ አካሄድ መከተል እንደሚገባ በመታመኑ በአንዳንድ አካባቢ ዱሮ በኢሕአፓ ጊዜ በነበረው የአደረጃጀት ስርአት መሰረት እምነት የሚጣልባቸውን በተለይ ደግሞ በዚህ መንግስት ደስተኛ ያልሆኑትን ሰዎች ሁለትና ሶስት በአንድ ላይ በማደራጀት ግንዛቤ ማስጨበጥና የአባልነት ፎርም ማስሞላት ተጀመረ:: በዚህ መልክ ውስጥ ውስጡን መዐሕድ ስር መስደድ ጀመረ:: በርግጥ የመጣውን ሁሉ በጸጋ ለመቀበል የግንባር ስጋ ሆነው ፈጥጠው የወጡ በርካታ ሰዎች ነበሩ:: መዐሕድ የሰላም ታጋይ ድርጅት ነው:: ሰላማዊ ትግል ማለት ቅሬታን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለጽ ማለት ነው:: ቅሬታ መፍትሄ ካላስገኘ ትግሉ በመንፈስና በአካል እስከመሸፈት ያደርሳል:: ይህም ማለት ከሀይል ርምጃ በመለስ ያሉትን ሁሉ መጠቀም: እምቢ አልታዘዝም አላደርግም በማለት ተቃውሞን መግለጽን ያጠቃልላል:: አዎ! ሰላማዊ ትግል ማለት ከመንግስት በኩል የሚሰነዘረውን ማንኛውም ጥቃት በሰላም መቀበል ማለት ነው:: ሳያቆስሉና ሳይገድሉ እየቆሰሉና እየሞቱ ማሸነፍ ማለት ነው:: ይህ የትግል ባህሪ በለየላቸው የወያኔ አይነት አምባገነን መንግስታት ዘንድ በእጅጉ ጎጅ ነው:: የህዝብ እምቢ ማለት አያስደነግጣቸውም:: ራሳቸውን መለስ ብለው ለመመርመር አያስችላቸውም:: ይልቁኑ በተደፈርኩ መንፈስ ያወራጫቸዋል:: ለበቀል ጦራቸውን ይሰብቁና ያገኙትን ሁሉ ማጥቃት ይጀምራሉ:: በዚህ መልኩ ሰላማዊ ትግል መስዋእትነቱን ያከፋዋል:: ኋላቀር በሆኑ አምባገነኖች በሚመሯቸው አገሮች ዘንድ ሰላማዊ ትግል የሽምቅ ውጊያ ያህል ያስቀጣል:: ሰላማዊ ታጋይ ማለት ለመንግስት አመራር አልመችም የሚል አጉራ ዘለል ነውና የሸማቂውን ያህል ይቀጣል:: አምባገነኖች አይደለም የተቃወማቸውን ኮከባቸው ያልፈቀደውን ሰው ሁሉ ቢገሉ ይችላሉ:: ወያኔወች ደግሞ ሰላማዊ ታጋይ ያውም የአማራ ማየት ቀርቶ መስማትም አይፈልጉም:: ሆኖም በአግባቡ ከተጠቀሙበት ሰላማዊ ትግል በአጭር ጊዜ ውጤታማ ያደርጋል:: ውጤታማነት ከጠንካራ አደረጃጀትና ከበሳል አመራር ውጭ አይገኝም:: መዐሕድ አመሰራረቱ ለፖለቲካ የስልጣን ፉክክር አይደለም:: አላማው በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጭቆናና ግድያ ለአለም መንግስታትና ለሰብአዊ ድርጅቶች ለማሰማት ነው:: ግን ሁሉም ትግል ያስፈልገዋል:: በዚህ ሂደት ወያኔ መራሹ መንግስት መውደቅ ከቻለ እሰየው ነው- በደምና በአጥንት የሚያምኑት እኩዮች ከጠፉ አማራውን ለይቶ የሚያሳድድ አይኖርም ማለት ነው:: ከዚያ በኋላ ለኢትዮጵያ የሚበጅ የህዝብ አስተዳደር ለመመስረት ተፎካካሪ ሆኖ መቅረብ ይቻላል:: ለሁሉም የህዝብን መንፈስ መማረክ የሚያስችል ሁለንተናዊ ብቃት መጎናጸፍ ያስፈልጋል::
የልጆች ማስፈራሪያ “አባ ዳውሎ” ተብሎ ይጠራል:: አባ ዳውሎን አይቶ የሚያውቅ ልጅ የለም:: ግን አባ ዳውሎን ይፈራል:: ሲያለቅስ የነበረን ልጅ “አባ ዳውሎ መጣብህ” ካሉት ልቅሶውን ይውጣል:: ሻእቢያና ወያኔ ደግሞ ብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን የሚያስፈራሩት “አማራ መጣልህ” ብለው ነው:: በሻእቢያና በወያኔ የተሰበከ የዋህ ይህንን ተቀብሎ አስተጋብቷል:: በኤርትራ እናቶች ልጆቻቸው ሲያስቸግሯቸው “አማራ መጣልህ” ይሏቸው ነበር:: አማራ አፉ እንደአዞ አፍ 180 ዲግሪ የሚዘረጋ ጆሮው እንደዝሆን የሰፋ: አስፈሪ የሆነ ፍጡር እንደሆነ ተደርጎ እየተነገራቸው ያደጉት ልጆች ታዲያ አማራ መጣብህ ሲባሉ ቱር ብለው የትም ይጠፋሉ- እናቶችም ከህጻናቱ ብጥበጣ ተንፈስ ይላሉ:: ይህ በኤርትራ የልጆች ማስፈራሪያ የነበረው አማራ አሁን ከልጆች አልፎ የብሄር ብሄረሰቦች ማስፈራሪያ ሆኗል:: “ነፍጠኛ” የአማራ ተለዋጭ ስም ነው:: እና ነፍጠኞች ከተባለ አማሮች ማለት ነው:: “ነፍጠኞች የብሄር ብሄረሰቦች ጠላቶች ናቸው- ኢትዮጵያ ደግሞ እስር ቤታቸው:: ነፍጠኞች አንገታቸውን ቀና ሊያደርጉ አይገባም:: አንገታቸውን ቀና ካደረጉ መሬትህን ይወስዳሉ: ነጻነትህን ይነጥቃሉ” ነቅተህ ጠብቅ ተብለው ይቀሰቀሳሉ:: የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አማሮችን ጠንቅቀው ያውቋቸዋል:: አማሮች በያሉበት ላባቸውን አንጠፍጥፈው ሰርተው የሚኖሩ እንደሆኑ አሳምረው ያውቃሉ:: አሁን አማራ ክልል ተብሎ በሚታወቀው ክልል የሚኖሩ አማሮችም ቢሆኑ የእግር ጫማ እንኳ የሌላቸው ለፍቶ አዳሪወች መሆናቸውን ይረዳሉ:: አማሮች ጠላቶቻችሁ ናቸው ሲባሉ ግራ ተጋብተዋል:: የትኞች አማሮች ናቸው የእኛ ጠላቶች ብለው መጠየቅ አይችሉም:: እንዲህ ያለ ሰው “የነፍጠኛ ሎሌ” ሊባል ይችላል:: አማሮች በየቦታው ሲታደኑ ብሄር ብሄረሰቦች ውስጣቸው በሀዘን ተኮማትሯል:: በየቦታው ተበትነው ባሉት አማሮች ላይ ጥቃት ለመፈጸም በወያኔና በአጋሮቹ ከተዘጋጁት ገዳይ ስኳዶች ግን ሊታደጓቸው አልቻሉም:: እና የብሄር ብሄረሰቦች አባ ዳውሎ (አማራ) ዘሩ እንዳይጠፋ ተደራጅቶ ድምጽን ከፍ አድርጎ መጮህ: ቀሪውን ወንድም ኢትዮጵያዊ ሀቁን ማስጨበጥና የትግል አጋር ማድረግ ያስፈልጋል::
ሻለቃ ሀይለየሱስ በባህርዳር ልዩ ዞንና በምእራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል:: አባላትን መመልመል: ማደራጀት: የአባላት መዋጮ ማሰባሰብና ቢሮ መክፈት ይኖርባቸዋል:: ሰው የመቅረብ ልዩ ችሎታቸው ወሳኝ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት ረድቷቸዋል:: በጥቂት ወራቶች ውስጥ ምእራብ ጎጃምን እስከቀበሌ ድረስ ወርደው ማደራጀት ቻሉ:: ቢሮወች በበርካታ የወረዳ ከተሞች ተከፈቱ:: ቀስ በቀስ የህቡእ እንቅስቃሴው ገሀድ መውጣት ጀመረ:: የባህር ዳር ቢሮ በማእከልነት ያገለግል ጀመር:: ምንም እንኳ ሀይለየሱስ የምእራብ ጎጃምና የባህርዳር ልዩ ዞን አስተባባሪ ቢሆኑም በክልሉ ዋና ከተማ ተቀማጭ ስለሆኑ የአማራውን ችግር ከየዞኖች እየተቀበሉ ለበላይ የማሳወቅ ስራ በመስራት: መግለጫ በማውጣትና ህዝባዊ ስብሰባወችን በማካሄድ ግዙፍ ስራ ሰርተዋል:: በሰሜን ጎንደር: በደቡብ ጎንደር: በአዊና በምስራቅ ጎጃም ዞኖች ከአቶ አባይነህ ብርሀኑ ጋር በመሆን የዞን አስተባባሪወችን መልምለዋል- ቢሮወችን ከፍተዋል::
የት ይደርሳሉ ብለው በንቀት ይመለከቷቸው የነበሩ የየደረጃው የወያኔ አንጋቾች ህዝቡ ቀስ በቀስ ከእጃቸው እያፈተለከ ወደ መዐሕድ እቅፍ መሰባሰቡን ሲያዩ መበራገግ ጀመሩ:: በሻለቃ ላይ ፈተናወች በዙ:: መጀመሪያ ምክር ቢጤ ተሰጣቸው:: “ምንህ ተነካ- ለምን አርፈህ አትቀመጥም” ተባሉ:: ቀጠሉ የወያኔ ተስፈኞች- ” ብታርፍ ይሻልሀል:: አሊያ አወዳደቅህ ይከፋል” አሏቸው:: አልገባቸውም እንጅ ሀይለየሱስ አይደለም ለዛቻ ለጥይትም አይንበረከኩ:: ይህን ትግል ሲቀላቀሉ ብዙ ነገር ሊደርስባቸው እንደሚችል ተረድተው ነው የወሰኑት:: እና ሀይለየሱስ ይበልጥ ቀበቷቸውን ጠበቅ አድርገው ህዝብ የማደራጀቱን ስራ ገፉበት:: ፖሊሶችና የደህንነት ሀይሎች በየሄዱበት ይከታተሏቸዋል:: ሻለቃ ክፉ አይወጣቸውም:: ብቻ “እንዲያው ልፉ ብሏችሁ እኮ ነው” ይላሉ: ምንም ስህተት እንደማይገኝባቸው ለመግለጽ::
“ማሸማቀቅ” የወያኔ አንዱ የትግል ስልት ነው:: አንድ ሰው ከሚፈጽመው ተግባር እንዲታቀብ ለማድረግ ሲፈለግ በስብሰባ ላይ የማስደንገጥ: በፖሊስና በደህንነት ክትትል የማስበርገግ ድርጊት ነው- ማሸማቀቅ:: ይህ ግን ሀይለየሱስ ዘንድ ሊሰራ አልቻለም:: ራሳቸው ሀይለየሱስም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው በሌሉበት ቤታቸው በተደጋጋሚ ተፈትሿል:: ምን ይገኝባቸዋል? ምንም:: እርሳቸው እንደሆኑ የሰላም አርበኛ::
ወያኔ መዐሕድን ለማጥቃት ሲንቀሳቀስ ብአዴኖች ግዳይ ጥለው ሊሾሙ ሊሸለሙ ተቁነጠነጡ:: በወቅቱ የተከሰቱ ችግሮች ሁሉ የመዐሕድ አፍራሽ እንቅስቃሴ ውጤቶች ተደርገው በመንግስት ሜዲያወች ይናፈሱ ጀመር:: መዐሕድ “ካለወቅቱ የመጣው ዝናብ በእኛ እንዳይሳበብ እየሰጋን ነው” ሲል ወያኔ እየፈጠረበት ያለውን ልብ ወለድ ክስ ነቀፈ:: ወያኔ ግን ሰቅጠጥም አላለ:: ይባስ ብሎ በፈጠራ ክስ የድርጅቱን መስራችና የአማራ ጠበቃ የነበሩትን ፕሮፌሰር አስራት ወ/የስን አሰረ:: የወያኔ አላማ መሪው ከጨዋታ ውጪ ከሆነ ተከታዩ ይበተናል የሚል የተሳሳተ አላማ ነበር:: ያ ዱሮ ቀረ:: ዱሮ የጦር መሪ ሲሞት ሰራዊቱ ትጥቁን ይፈታ ነበር አሉ:: “ንጉስህ ወይም መሪህ ተማርኳልና እጅህን ስጥ” ተብሎ ይለፈፋል:: በቃ በዚያው ጦርነቱ ያበቃል:: ያ ጊዜ አሁን አይደለም:: ሰላማዊ ፍልሚያው ይበልጥ ተጧጡፏል:: አባላት ይመዘገባሉ: ቢሮወች ይከፈታሉ: የፖለቲካ ትምህርት ይሰጣል::
የመዐሕድ ጩኸት ፍሬ አሳየ:: አማሮችን በአማራነታቸው ብቻ ሰብስቦ መግደል ጋብ አለ:: ስለዚህ አሁን መዐሕድ ከአማራው አልፎ ለመላው ኢትዮጵያዊ ሊቆም የግድ ይላል የሚሉ ወገኖች ተበራከቱ:: እውነት ነው:: መጀመሪያምኮ ቢሆን መዐሕድ የተመሰረተው አማራ ተኮር የሆነ ግድያ በመስፋፋቱ ብቻ ነው:: ይህ ችግር ተንፈስ ካለ የሚቀጥለው ተግባር በኢትዮጵያ ላይ በጉልበቱ ነግሦ በዘርና በቋንቋ ህዝቡን እየከፋፈለ ያለውን ጸረ ህዝብና ጸረ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ አሽቀንሮ መጣል ይሆናል:: ይህ ውጤት ሊመጣ የሚችለው መላው ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ ተሰባስበው ለአንድ አላማ መሰለፍ ሲችሉ ብቻ ነው:: መዐሕድ ግቡን አሳክቷል:: ቀጣዩ ትግል ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚያሳትፍ ድርጅት መስርቶ በዚያው የሚካሄድ ይሆናል:: በዚህ መልኩ መኢአድ ተመሰረተ::
ሻለቃ ሀይለየሱስ እጅጉ ኢትዮጵያዊ ወታደር ነበሩ:: ሲያደሙና ሲደሙ የነበሩት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ነው:: ሀገራቸው ኢትዮጵያ ህዝባቸውም ኢትዮጵያውያን ናቸው:: ቀዳሚ አላማቸውን ከመዐሕድ ጋር ያሳኩት ሀይለየሱስ ለቀጣይ ግዳጅ ከመኢአድ ጋር ተሰለፉ::
ይቀጥላል
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Thursday, May 16th, 2013
እስክንድር አሰፋ
ከኖርዌይ

ባለ ራእዩ የወያኔ መንግስት ባልታወቀ ወይም ሆን ተብሎ በተሰራ የቴክኔክ ብልሽት በዚህ ሰሞን በአባላትና ጀሌዎቹ ላይ ለ22 አመታት ታይቶ በማይታወቅ የሙስና ቅሌት ሰበብ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እያጎሯቸው ይገኛል። የሚገርመው ደጋፊዎቻቸው ከሐገር ቤት እስከ ዲያስፖራው ብዙ ሲለፈልፉላቸው ይሰማ ነበር ልማታዊ መንግስታችን፤ ልማታዊ ሚኒስትሮቻችን ፤ ልማታዊው መሪያችን በማለት ከሰብአዊ መብት ጥበቃ በፊት መንገድ ስራና የአፓርታማ ግንባታ ይቅደም በማለት መቆሚያና መቀመጫ አሳጥተውን ነበር አሁን ምን ይውጣቸው ይሆን? እንደ ለመዱት ልማታዊ ሙስና ነው ብለው እንዳያስደነግጡን እንፈራለን።
haገራችንን ኢትዮጵያን ወያኔ /ኢህአዴግ ከተቆጣጠራት ጊዜ ጀምሮ ማለትም እ.ኤ.አ ከ1991 ዓ.ም ሐገሪቷንና ህዝቧን በመሳሪያ አግቶ በዘር በሃይማኖት ከፋፍለው እንዲሁም ከቁጥጥር ውጪ በሆነ የሰብአዊ መብት እረገጣ እና የኢኮኖሚ ቀውስ አድርሰውባታል አሁንም እያደረሱባትም ይገኛሉ።
ዝባችንም ከተወለደበት እና ካደገበት ቀዬው ሰላምን ፍለጋና ኑሮውን ለመምራት ሲል እግሬ አውጪኝ በማለት ወደ ማያውቅበት ሐገር ለመኖር ሲሰደድ፤ በየበረሐው ሲደበደብ፤ እንዲሁም ሲገደል እና በህይወት እያለ ሰውነቱ እየተቀደደ የውስጥ አካሉ ሲሸጥ እያየንና እየሰማንም ነው።
ይህ ሁሉ በደል እና ስቃይ በህዝባችን እየደረሰ ባለበት ጊዜ ስልጣኑን ተቆጣጥረው ያሉት የወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት እኛ እናውቅላችኋለን፤ እናስተዳድራችኋለን በማለት የባለ እራዩን የዘረኛውንና የገንጣዩን መለስ ዜናዊ አመራር አላማ ለማስፈጸም እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን በማለት በህግ ላይ ህግ በማውጣት ህዝቡ ቀና ብሎ እንዳያያቸው በተበላሸና በከረፋ የህግ የበላይነት
ስም ህዝቡን በማፈን፤ ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ነገር ግን በአሸባሪነት ስም የታሰሩ ጋዜጠኞች፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የእምነት ስርዓታችንንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን ምርጫ እምነታችን በሚፈቅደው መንገድ ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ዜጎችን በአሸባሪነት በመወንጀልና በመክሰስ እንዲሁም በዋልድባ ገዳም አባቶቻችንን በማሳደድና በመዝረፍ ሲያሰቃዩ እነሱ ግን በቅሌትና በሙስና የሀገሪቷን ሃብት እና ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል እንዲሁም የሀገሪቷን ጥሬ ሃብትና ንብረት ወደ ውጪ በማሽሽ በውጪ በሚገኙ ዘመዶቻቸው ስምና የነሱ ተባባሪ ወዳጅ መንግስታት ሐገሮች ባንክ ውስጥ በማስቀመጥ ሐገራችንን ኢትዮጵያን በአለም ታይቶ በማይታወቅ የኑሮ እድገት የኋልዮሽ እሽቅድምድም ውስጥ በማስገባት ለከፋ ችግር አጋልጠዋታል።
እውነት አሁን ወያኔ/ኢህአዴግ ሀገራችንን ኢትዮጵያ ይህን ሁሉ አመታት ከግብረ አበሮቹና ከጀሌዎቹ ጋር በመተባበር ሲያደማትና ሲበዘብዛት ቆይቶ አሁን በሙስና ቅሌት ያዝኳቸው በማለት ግብረ አበሮቹን በገሃድ ያጋለጠበትና አሳዶ ወደ ወይኒ የወረወረበትን ምክንያት እውነት ለሐገራች ተቆርቋሪነቱን ለማሳየት ይሆን ? ወይስ የማናውቀው መፍረክረክ ተፈጠረባቸው ? ይህንን ጥያቄ እሱ እራሱ ባለጉዳዩ ይመልሰው ወይም እነሱ እንደ ጀመሩት እራስ በራሳቸው ተበላልተው ያልቁልናል ብለን ዝም ብለን እንመልከት?
እኔ እንደማስበው ወያኔ/ኢህአዴግ በአሁን ሰአት እያረጀ የመጣ ትልቅ የግራር ዛፍ ነው ብዬ አምናለሁ ምክንያቱም ስርአቱ ውስጥ የመፍረክረክ ሁኔታና የመበስበስ ባህሪይ ማሳየቱ ከውስጡ ያሉት ሞተር የነበሩት እራሳቸውን ወደ ማግለል ደረጃ ላይ ደርሰው እያየናቸው ነው ስለዚህ የበሰበሰውን ስርአት በደንብ እንዲበሰብስ አድርጎ የመጣል ሐላፊነት ያለብን ይመስለኛል ለዛም ዋና መፍትሄ የሚሆነው ስርአቱን ፊት ለፊት እና በተለያየ መንገድ የሚታገሉትን ድርጅቶችን ሆነ ግለሰቦችን አንድ በማድረግ ልዩ ነታችንን ትተን በአንድነት መፋለም ያስፈልጋል ብዬ አምናለው ያለ በለዚያ ስርአቱ በሰበሰ አረጀ እራሱ ይወድቃል ብለን ቁጭ ብለን የምንጠብቅ ከሆነ እራሳችን በስብሰን ከዚህ በበለጠ በከፋ አገዛዝ እንደምንገዛ ጥርጥር የለኝም።
መልክት ለወያኔ ደጋፊዎች
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የወያኔን ስርአት የምትደግፉ ወገኑቻችን በአሁን ሰአት አለማችን በቴክኖሎጂ አድጋ አንድ ሆናለች የትም ሆናችሁ የትም ስለ ሃገራችሁም ሆነ ስለምትፈልጉት ነገር ቤት ቁጭ ብላችሁ ማየትም መስማትም ትችላላችሁ ስለዚህ ማሳሰብ የምፈልገው ነገር ሐገራችን ኢትዮጵያ ከየት ወዴት እንደምትሄድ እና በስርአቱ ውስጥ ምን ያህል እንዝላልነትና ሐላፊነት የጎደለው አገዛዝ እንዳለ ለናተም የተደበቀ ነገር ያለ አይመስለኝም እድሜ ለቴክኖሎጂ የለፈውን እንተወውና አሁን በቅርቡም በመገናኛ ቦዙሃን እንደሚደመጠው በሐገራች ላይ ምን ያህል ምዝበራና ዘረፋ እየተካሄደባትና ኢ ሰብአዊ ድርጊት በህዝባችን ላይ እየደረሰ እንደሆን ለናተ መንገር ለቀባሪው አረዱት ማለት ነው ስለዚህ ጠንቅቃችሁ ታቁታላችሁ ። እግዚአብሄር በሰጣችሁ ጭንቅላት በመጠቀም ወደ ሰውኛ አስተሳሰብ ተመልሳችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ከጭቁኑ ኢትዮጵያዊ ጋር ጎን ለጎን በመቆም በአፓርታይድ አገዛዝ ስር የወደቀችውን ሐገራችንን ነጻ ለማውጣት እንታገል በማለት ወንድማዊ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
መረጃ ለማግኘትም ሆነ ለግንዛቤ ሰሞኑን ከወጡት ዜናዎች መካከል በጥቂቱ
ቸር ያሰማን
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች
ድል ለኢትዮጵያ ሞት ለወያኔ
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Thursday, May 16th, 2013
ድምጻዊት አበበች ደራራ ከዚህ አለም በሞት መለየቷን የተለያዩ ድረ ገፆች እየዘገቡ ነው፡፡ ማለዳ ታይምስ ድረ ገፅ ድምጻዊት አበበች ደራራ በስደት አለም እስራኤል አገር ውስጥ በቴል አቪቭ ከተማ ኑሮዋን ካደረገችበት ጊዜ ጀምሮ በጤና መታወክ ለብዙ ጊዜ ስትሰቃይ መክረሟን ገልጾ በዛሬው እለት ህይወቷ ማለፉን እና የቀብር ስነስራቷ በእዚያው በቴል አቪቭ እንደሚፈጸም ጠቁሞአል።
በተለይም ባሳልፍነው ስድስት ወራት ህመሟ በከፍተኛ ሁኔታ ላይ እንደነበር በተለያዩ ሚዲያዎች ከመገለጹም በላይ ለህክምና እርዳታ የሚሆናትን ገንዘብ እንዲሰባሰብ በተለያዩ አገራት ላይ እንዲከናወን መጠየቁ ይታወሳል ።ሆኖም ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ ሲደረግ እንዳልታየ የሚታወቅ ነው ። አበበች ደራራ በራስ ቴአትር ሃገረሰብ የተሰኘ ቡደን በተቋቋመበት ወቅት ከነ ነዋይ ደበበ ጋር በመሆን በማቋቋም ስራዋን በከፍተኛ ደረጃ የጀመረች ድንቅ አርቲስት ነበርች በተለይም በመድረክ ላይ እንቅስቃሴዋ የሰውን ቀልብ ትስባለች እየተባለ የምትወደሰው ድምጻዊት ደራራ የራስ ቴአትር አምባሳደር ትባልም እንደነበር ያገኘነው ፋይል ይጠቁማል።በቴአትር ቤቶች ውስጥ በመድረቅ የሙዚቃ ስራን በመስራት ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈች ሲሆን ጥቂት የማይባሉ ሙዚቃዎችንም በካሴት አሳትማ ልህዝብ አቅርባለች ከነዚህም መካከል በሉ እንጂ ፣ተው ማነህ፣ገላዬ ፣ሰው በፍቅር ታሞ የተባሉት ጥቂቶቹ ናቸው።
አበበች ደራራ በሕመም ተይዛ ለበርካታ ወቅት በአልጋ ላይ ከመቆየቷም ባሻገር ጨርሶ ከሰዎች ጋር ግንኙነት አቋርጣ በሽታዋን ለብቻዋ ስታስታምም እንደነበረች በቅርብ የሚያውቋት ይናገራሉ፡፡
የአበበች ደራራ አስከሬን በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 3.00PM ላይ ወደ ቀብር በወዳጅ ዘመዶች ታጅቦ በመሄድ ሥርአተ ቀብርዋም እንደሚከናወን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። (ምንጭ፡ ሸገር ትሪብዩን)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Thursday, May 16th, 2013
ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ብ/ም/ቤት ባደረገው ስብሰባ ላይ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአንድነት/መድረክ የፖለቲካ ግንኙነት እና የጋራ እንቅስቃሴ ከመቀናጀት እስከ ግንባር ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ላይ የተዘጋጀውን ሰነድ ገምግሞ አፅድቋል፡፡ ሰነዱም ለመድረክና ለመድረክ አባል ፓርቲዎች እንዲሰጥ፣ አባላትና ደጋፊዎች እንዲያውቁት እንዲሁም ለህዝቡና ለመገናኛ ብዙሃን እንዲሰራጭ በተባለው ውሳኔ መሰረት እነሆ ሰነዱን አያይዘናል፡፡
ትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Thursday, May 16th, 2013
ከመሐመድ አሊ መሐመድ (ጋዜጠኛ)
እስኪ በትዝታ ፈረስ ሽምጥ እንጋልብና የምርጫ 97ን ሂደት እንደዋዛ እንዳስሰው፡፡ ምርጫ 97 ሲነሳ ከትውስታ ማህደራችን ጎላ ብሎ የሚወጣው የሚያዚያ 30 ትዕይንተ ህዝብ ነው፡፡ ለነገሩማ ያ ታሪካዊ ዕለት እንዴት ይረሳል? ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመሩ መንገዶች ሁሉ በለውጥ መንፈስ በተሞላ የህዝብ ጎርፍ የተጥለቀለቁበት፣ ያለማንም ቀስቃሽ ህዝብ ለመብቱና ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሆ! ብሎ የወጣበት፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ብቃት ያረጋገጠበት፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ዓለምን ያስደመመበት ያ ታሪካዊ ዕለት እንዴት ይረሳል?
ሚያዚያ 30ን ስናስታውስ አንድ ክስተትም አብሮ ይታወሳል፡፡ “ዴሞክራሲን እናወድስ” በሚል መሪ ቃል መስቀል አደባባይና ዙሪያ ገባውን ባጨናነቀው ህዝብ መሐል አንድት ፒክ-ኣፕ መኪና ወደ አደባባዩ እምብርት ዘለቀች፡፡ በመኪናዋ ላይ በኢትዮጵያ ባንዲራ ደምቆ የለውጥ ሀዋርያነቱን የሚያውጅ ሰው ነበር፡፡ ህዝቡም ያን የለውጥ ሀዋርያ በፍቅርና በስስት ስሜት እጁን ለመንካት ይረባረብ ነበር፡፡ እሱም እጆቹን በማውለብለብ አፀፋና ምስጋናውን ይገልፅ ነበር፡፡ በወቅቱ ስለዚያ የለውጥ ሃዋርያ አንዳች አሉታዊ አስተያየት መስጠት ትልቅ ዋጋ ያስከፍል ነበር፡፡
ከምርጫው በኋላም ያ የለውጥ ሀዋርያ በድርጅቱ ጽ/ቤት ታገተ ተብሎ ህዝቡ በፆም በፀሎት ተጠመደ፡፡ በርካቶች ባገኙት ሚዲያና መንገድ ሁሉ እገታው የፈጠረባቸውን ስሜት በእንባና ሲቃ ሲገልፁ ተደመጡ፡፡ ግና በዚች ምድር ቋሚ ነገር የለምና ያ የለውጥ ሀዋርያ ተብሎ የተወደሰ ሰው ብዙም ሳይቆይ በካሀዲነት ተፈረጀ፡፡ ያ ሰው ማን እንደሆነ ግር የሚለው ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያለገደብ የተሞገሰና የተወገዘ! ግን ለምን?
ስለልደቱ አያሌው ብዙ ተብሏል፡፡ እኔ የተባለውን ሁሉ አልጋራም፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የስልጣን ጉጉት እንዳላቸው አውቃለሁ፡፡ ቢሆንም የፖለቲካ ትግል የመጨረሻ ግቡ ሥልጣን ይዞ ዓላማን ማስፈፀም በመሆኑ የሥልጣን ጥማት እንደነውር ሊታይ የሚገባው አይመስለኝም፡፡ ነውር የሚሆነው ዴሞክራሲያዊ ባልሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ ሲባል የቆሙለትን ዓላማ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማስፈን በሚደረግ ትግል ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ባልሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ መሞከር የትግሉን ዓላማ ምን ያህል ሊጎዳው እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡
ከዚህ አንፃር አቶ ልደቱ በተለያየ ጊዜ ከሥልጣን ሽኩቻ ጋር በተያያዘ ትግሉን የሚጎዱ አፍራሽ እርምጃዎች ወስደዋል፡፡ አቶ ልደቱ በቀድሞው መዐህድ (የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት) አመራርና በወጣቶች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ ድርጅቱን ለቀው ሲወጡ የወሰዱት እርምጃ የድርጅቱን ገፅታ ከማጠልሸቱም በላይ በትግሉም ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት አድርሷል፡፡ በኋላም ኢዴፓ ከተቋቋመ በኋላ በፓርቲው መሥራች አባላት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት አቶ ልደቱ ተቀናቃኞቻቸውን ለማስወገድ የተከተሉት መንገድ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መቆማቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነበር፡፡ በወቅቱ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን የፖለቲካ ሰብዕና ለመግደል/ሽባ ለማድረግ (character assassination/paralization) በእሳቸው ላይ ሲደርስ ያወገዙትን አሉባልታ የመንዛትና ስም የማጥፋት ስልት መከተላቸው አይዘነጋም፡፡
አቶ ልደቱ የራሳቸው ምክንያት ቢኖራቸውም ፓርቲያቸው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በነበረው የትግልና የትብብር ግንኙነቶች ላይም የሚወስዷቸው አቋሞች እንደዚሁ ትግሉን የሚጎዱ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ በተለይም በ1997 ዓ.ም በተፈጠረው #ቅንጅት$ ውስጥ አቶ ልደቱ ሲያሳዩት የነበረው ልታይ ልታይ ባይነትና አጉል #ብልጣብልጥነት$ በተቃውሞው ጎራ ውስጥ በዓይነ-ቁራኛ እንዲታዩ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ ቅንጅት በ1997 ምርጫ ሂደት በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ድምፅ ካገኘ በኋላ ወደ ውህደት ሲያመራ የልደቱን የሥልጣን ፍላጎት ባለማርካቱ በእልህ ተነሳስተው የወሰዱት እርምጃ ታላቅ ታሪካዊ ስህተት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ አቶ ልደቱ ለወሰዱት እርምጃ ምክንያት ቢኖራቸውም እርምጃውን የወሰዱበት ጊዜና መንገድ ከህዝብ እንዲነጠሉ በማድረግ ብዙ ፖለቲካዊ ዋጋ አስከፍሏቸዋል፡፡
አቶ ልደቱ ለቅንጅት መፍረስ ምክንያት አለመሆናቸውን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉም በቀላሉ ሊሳካላቸው አልቻለም፡፡ የእሳቸው መከራከሪያ ቅንጅትን አንድ ልደቱ የሚያፈርሰው ከሆነ ከጅምሩም ቅንጅት የሚባል ጠንካራ ኃይል አልነበረም የሚል ነው፡፡ በእርግጥም ይህ ክርክር በደምሳሳው ሲታይ እውነትነት ያለው ይመስላል፡፡ ነገር ግን አቶ ልደቱ በውህደት ስምምነቱ ላይ መሐተም ለማሳረፍ አሻፈረኝ በማለታቸው የኢህአዴግ መንግሥት ያቋቋመው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅንጅትን የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለመከልከል ምክንያት አግኝቷል፡፡ አቶ ልደቱና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የወሰዱት እርምጃ ቀደም ብሎ የተቀነባበረ ይሁን በድንገት የተፈጠረ ግጥምጥሞሽ ሊያስረዱን የሚችሉት አቶ ልደቱ ብቻ ናቸው፡፡
አቶ ልደቱ ቅንጅት ከፈረሰ በኋላ #ሦስተኛ አማራጭ$ በሚል ያመጡት የፖለቲካ ፈሊጥ ብዙዎችን ግራ ያጋባና እሳቸውንም ለባሰ የፖለቲካ ክስረት የዳረገ ነው፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አማካይ ቦታ/#ሦስተኛ አማራጭ$ እንደሚያስፈልግ ቢታመንም ይህን አቋም ለማራመድ በወቅቱ አቶ ልደቱ ትክክለኛው ሰው ነበሩ ለማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የ1997 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው ውጥረት የቅንጅት መሪዎች ለእስር እስከተዳረጉበት ጊዜ ድረስ በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚዎች መካከል ለነበረው የተካረረ ግንኙነት አቶ ልደቱ ዋነኛው ተጠያቂ ናቸው፡፡
ስለሆነም #የጭፍን ተቃውሞ$ ፖለቲካን ለማውገዝ/ከማውገዛቸው በፊት አቋማቸውን የቀየሩበትን አሳማኝ ምክንያት ማቅረብና ቀደም ሲል ሲያራምዱት በነበረው የተካረረ አቋም ሳቢያ ለደረሰው ጥፋት ሁሉ ኃላፊነት መውሰድና ይቅርታ መጠየቅ ነበረባቸው፡፡ ይህን ሳያደርጉ ድንገት ተነስተው #ሦስተኛ አማራጭ$ በማለታቸውና የተቃውሞውን ጎራ ተጠያቂ በማድረጋቸው ህዝብ ሊያምናቸው አልቻለም፡፡ ይልቁንም ከገዥው ፓርቲ ጋር ለመሞዳሞድ እንደፈጠሩት ሥልት ተቆጥሮ በካሃዲነት አስፈርጇቸዋል፡፡ አቶ ልደቱ በተሳሳተ ስሌት በእጃቸው ውስጥ የነበረውን መልካም ዕድል ካጡ በኋላ ተስፋ ሳይቆርጡ ቢፍጨረጨሩም እንደዋዛ ያመለጣቸውን ዕድል በቀላሉ መልሰው እጃቸው ውስጥ ሊያስገቡት አልቻሉም፡፡
ይህም ሆኖ ግን አቶ ልደቱ አያሌው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሁነኛ ሥፍራ ያላቸውና የሚገባቸውም ሰው ናቸው፡፡ ወደተደራጀ የፖለቲካ ትግል ከገቡ ጀምሮ ያላቸውን ጊዜና አቅም አሟጥጠው ተጠቅመዋል፡፡ በተለይ የ97 ምርጫ ቅስቀሳ በእሳቸው ጫንቃ ላይ ያረፈ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በምርጫ ቅስቀሳው በአንድ በኩል የገዥውን ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች አንገት ሲያስደፉ በሌላ በኩል የተቃውሞውን ጎራ ደጋፊዎች አንጀት ያርሱ ነበር፡፡
አቶ ልደቱ በትግሉ ውስጥ ያላቸው ቆይታ በአንፃራዊነት አጭር ሊባል የሚችል ቢሆንም ያካበቱት ልምድና እውቀት ቀላል የማይባል ነው፡፡ በእኔ እይታ አቶ ልደቱ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ደርዝ ባለው መንገድ ለመገምገምና ለመተንተን ብቃት ካላቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን ተርታ የሚሰለፉ ናቸው፡፡ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው አቶ ልደቱ የተቃዋሚ መሪዎችን ቁጥር በአንድ የሚያሳድጉ ሳይሆኑ በኢትየጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትርጉም ያለው ሚና መጫወት የሚችሉ ሰው ናቸው፡፡ በእርግጥ አቶ ልደቱ የሚጫወቱት ሚና እንደየሰው አተያይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የ1997 ምርጫን ተከትሎ አቶ ልደቱን የገጠማቸው ከህዝብ የመነጠል ፈተናና ፈተናውን በአሸናፊነት ለመወጣት ተስፋ ሳይቆርጡ ያደረጉት ጥረትም ስለሰብዕናቸው የሚነግረን ቁም ነገር አለ፡፡
አንዳንድ ሰዎች #ልደቱ ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ዳግም ላይመለስ የውድቀት ጽዋውን ተጎንጭቷል$ ሲሉ በኩራት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን የልደቱ ከህዝብ መነጠል ለተቃውሞው ጎራ ውድቀት እንጅ በኩራት የሚገለፅ ስኬት አይደለም፡፡ የአንዳንዶቻችን በልደቱ ውድቀት መደሰት ከተራ ምቀኝነት ያለፈ ትርጉም ላይኖረው ይችላል፡፡ ልደቱ ሰው ነውና ተሳሳተ፡፡ የሚሳሳተው ደግሞ የሚሰራ እንጅ ከዳር ቆሞ የሚታዘብ አይደለም፡፡
በነገራችን ላይ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የቅንጅት መሪዎች ከእስር ከተፈቱ በኋላ የፈፀሙት ስህተት በምንም መመዘኛ ልደቱ ከፈፀመው ስህተት የሚያንስ አይደለም፡፡ ዱሮም ቢሆን ልደቱ የወሰደው እርምጃ የቅንጅትን ውድቀት አፋጠነው እንጅ ውሎ አድሮ ቅንጅትን ከመፈረካከስ የሚታደገው ኃይል አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የቅንጅት አፈጣጠርም ሆነ የሰው ኃይል ጥንቅር ረጅም ርቀት መጓዝ የሚያስችለው አልነበረም፡፡
እንደአለመታደል ሆኖ በቅንጅት ጥላ ሥር የተሰባሰቡት ሰዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ መተያየት የማይፈልጉና አንዱ ሌላውን ጠልፎ ለመጣል የሚያደቡ ወይም በየጓዳ ጎድጓዳው የሚያሴሩ ስለመሆናቸው መሪዎቹ ከእስር በተፈቱ ማግሥት እውነቱ ገሀድ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ለቅንጅት መፍረስ ልደቱን ብቻ ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ሁላችንም ድርሻ ድርሻችንን መውሰድ ይኖርብናል፡፡ እኔ የድርሻዬን ለማንሳት ዝግጁ ነኝ፡፡ ያ ታሪካዊ ሂደት “ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን” በሚል ብሂል ተሸፋፍኖ መቅረት ያለበት አይመስለኝም፡፡ በግልፅ ልንነጋገርበትና ልንማርበት ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ስለተቃውሞው ፖለቲካ መፃኢ ዕድል መነጋገር ካለብን ደግሞ #አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ$ እንዲሉ መሆን የለበትም፡፡
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 15th, 2013
መንደርደሪያ
አገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ በተለይም ከአንደኛው እስከ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ህዝቧ
አምልኮ ፈጣሪውን የሚከተልና የሃገሩን ፤ የወገኑን ክብር ሳያስደፍር የኖረ ታላቅ ህዝብ መሆኑን ያስመሰከረ እንደሆነ ታሪክ ይመሰክራል ። ክ7ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በዓለም ላይ ክፍተኛ የእድገት ደረጃውን ጠብቆ ሃገሩ በዓለም ዙሪያ እንድትታወቅ ያደረገ ህዝብ ለመሆኑ ቛሚ ምስክር የሆኑት ታሪካው ህንጻዎቹ ምስክሮች ናቸው።
ለሃገራችው የትውልድ ዓርዓያ ሆነው ያለፉት አባቶቻችንም በክብር ዘውትር በጠላቶች ሲከበሩና ሲፈሩ የኖሩ ለመሆኑ በተደጋጋሚ ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የታሪክ ህያው ምስክር ነው ። ይህች ሃገር ለመላው የጥቁር ዘር ኩራት ሆና በጠላትነት የፈረጁዋት ጠላቶቿን ደግሞ እንደ እሳት የፈጀች ታላቅና ውድ ሃገር ነች።ይህች ሃገር ለምን እንደሊሎቹ የአውሮፓውያን ሃገራት ለምን በሥልጣኔ ወደፊት እንዳልገፋች ኢትዮጵያውያን ስንጠይቅ መልሱ ምን ይሆን?
Download (PDF, 691KB)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 15th, 2013
ፍሬው አበበ

ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ
ሰኞ ዕለት ከሰዓት በኋላ የተንቀሳቃሽ ስልኬ አንጫረረ፡፡ ሳነሳው ለስላሳ የሴት ድምጽ ፍሬው መሆኔን ማረጋገጫ ጠይቃኝ ስታበቃ የቀድሞ ማዕከላዊ ስለምፈለግ ደረስ ብዬ መምጣት እችል እንደሆን በፍጹም ትህትና ጠየቀቺኝ፡፡ በዕለቱ እንደማይመቸኝ፤ ዕረቡ ጠዋት ግን መገኘት እንደምችል ለደዋዬ ነግሬ ሰልኩን ዘጋሁ፡፡ እንግዲህ በፕሬስ ክስ ጉዳይ ለፖሊስ ቃሌን ስሰጥ ይኸኛው ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ ከቀድሞዎቹ ሶስት ክሶች አንዱ የስም ማጥፋት ሲሆኑ ሌላኛው በተሰረዘ ፈቃድ ሰርታችሃል፣ ሌላው ደግሞ ያለፈቃድ ጋዜጣ ታትማላችሁ የሚል ነበር፡፡ በአጋጣሚ ሁለቱ የቀድሞ ክሶች ከፖሊስ ያላለፉ ሲሆን አንደኛው ማለትም የኒቲ የኒቨርሲቲ ያሳትመው የነበረው “ኤቢቢአይ ዊክሊ” የተባለው ጋዜጣ በተሰረዘ ፈቃድ ሰርታችሃል በሚል ክስ ከተመሰረተባቸው 14 ያህል ሰራተኞች አንዱ ሆኜ አንድ ዓመት ተኩል ጊዜያት ያህል ፍ/ቤት ከተመላለስኩ በኋላ እኔን ጨምሮ 13 ተከሳሾችን ፍ/ቤቱ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ ይሰናበቱ ሲል ውሳኔ በመስጠቱ ነጻ መሆን ችያለሁ፡፡ (እዚህ ምድብ ውስጥ የአዲስ ነገሩ አብርሃም በጊዜው ይገኝበት ነበር)
ዛሬ ረቡዕ በጠዋት ማልጄ በመነሳት ቁርስ ቀማምሼ ወደተጠራሁበት የቀድሞ ማዕከላዊ ፖሊስ 3፡15 ሰዓት ላይ ደረስኩ፡፡ ማልጄ መነሳቴ ወድጄ አልነበረም፤የሄድኩበትን የምርመራ ጣጣ ከምሳ በፊት ባጠናቅቅ በሚል ጉጉት ነበር ፤አልሆነም እንጂ፡፡ መርማሪዬ ትሁት ሴት ፖሊስ መሆኑዋ ጭንቀቴን ለጊዜውም ቢሆን እንድረሳ ረድቶኛል፡፡ ያው የተለመደውን አሰልቺ ቅጽ መሙላት ግን የግድ ነበር፡፡ ሙሉ ስም፣አድራሻ፣የእናት ሙሉ ስም፣የአባት ሙሉ ስም፣የትውልድ ቦታ፣ የትውልድ ቦታ አድራሻ፣ብሔር፣የባለቤቴ ስም፣አድራሻ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ስም፣የት/ቤቱ አድራሻ፣የተማርኩበት ጊዜ፤የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስም፣አድራሻ፣ የተማርኩበት ጊዜ፣ የከፍተኛ ትምህርት የተማርኩበት ዩኒቨርሲቲ ስም፣አድራሻ፣የተማርኩበት ጊዜ፣የቀድሞ መ/ቤት ስም፣የነበረኝ ኃላፊነት፣የነበረኝ ደመወዝ መጠን፣ የአሁን መ/ቤት ስም፣ያለኝ ኃላፊነት፣ያለኝ የደመወዝ መጠን፣ የጋብቻ ሁኔታ፣የልጆች ብዛት፣ዕድሜያቸው፣አጠቃላይ ክሱ እና በክሱ ላይ ያለኝ ምላሽ፣ የተጠረጠርኩበትን መፈጸም አለመፈጸሜን (የእምነት ክህደት ቃል) ወዘተ….እጅግ አድካሚ ዶሴ ተሞላና ጨረስኩ ስል አሻራና ፎቶግራፍ መነሳት የግድ ነው ተባልኩ፡፡ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሰጥቻለሁ ብልም ሰሚ አልነበረም፡፡ እዚያም የእያንዳንዱ ጣት አሻራ(የግራ የቀኝ) ፣ ፎቶ ፊትፊት በግራና ቀኝ መነሳት ግድ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ግን በፕሬስ ተፈጸመ ተብሎ በአንድ ሰው በቀረበ አቤቱታ መነሻነት ገና ለገና ተጠርጣሪ ነው የተባለው ፕሬስ ዋናአዘጋጅ የመጀመሪያዋ ቀላል ፈተና መሆኑ ነው፡፡
ፖሊስ ቃል ከመስጠቴ በፊት ሁለት ጥያቄዎች እንዲመለሱልኝ ለመርማሪዬ ጥያቄ አቀረብኩኝ፡፡ አንዱ የተከሰስኩበት ጉዳይ እና ከሳሼ ማን እንደሆነ ነበር፡፡ የተከሰስኩበት ጉዳይ በቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተመንግስት አለመውጣታቸውን ጠቅሰህ ጽፈሃል፣በዚህ ስም አጥፍተሃል የሚል ይዘት ያለው መሆኑ ተነገረኝ፡፡ ዜናው የተሰራው በአበሻ አቆጣጠር መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ.ም ሲሆን በጠቅላው ወደስምንት ወር ገደማ ሆኖታል፡፡

ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ
የዜናው ይዘትም በአጭሩ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ከቤተመንግስት አለመውጣታቸውን በአንድ በኩል በሌላ በኩል በወቅቱ ከተሾሙ 19 ቀናት የሞላቸው ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መኖሪያ ቤታቸው ከሚገኝበት ሳር ቤት አካባቢ በየዕለቱ ትራፊክ እያዘጉ በመውጣትና በመግባት ላይ መሆናቸው፣ የአካባቢውን ህብረተሰብ የመንቀሳቀስ ነጻነት ላይ ችግር መፍጠሩን፣ለደህንነታቸውም ቢሆን አስጊ መሆኑን፣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተመንግስቱን እንዲለቁ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ባልታወቀ ምክንያት ፍቃደኛ አለመሆናቸውን የሚያትት ነበር፡፡ ዜናውን ስንሰራው በትልቁ ታሳቢ ያደረግነውና እንደጋዜጠኛ ሙያዊ ነጻነታችን ተወጥተኛል ብለን የምናስበው የጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስራቸውን ማከናወን በምንም መልኩ ተቀባይነት ያልነበረውና ደህንነታቸውንም በእጅጉ ለአደጋ ያጋለጠ የመሆኑ ጉዳይ ነበር፡፡ የዚህ ዜና መውጣት በአገር ውስጥና በውጪ መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ በመቆየቱ ወ/ሮ አዜብ በክብር ወደተዘጋጀላቸው ቦታ እንዲዛወሩ፣አቶ ኃ/ማርያምም ወደቤተመንግስት እንዲገቡ በማድረግ ረገድ ሁለቱንም ወገኖችን የጠቀመ ውጤት አስገኝቷል ብለን እናምናለን፡፡ በዚህ ዜና መሸለም እንጂ መጉላላትና ክስ ይቀርብብናል ብለን አስበንም አናውቅም፡፡
ሌላው መርማሪዬን የጠየኳት ጉዳይ ከሳሼ ማን ነው የሚል ነበር፡፡ ይህን ጥያቄ በቀጥታ ለመመለስ አልፈለገችም፡፡ምናልባትም አለቆችዋ እንዳትነግር አስጠንቅቀዋት ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ግን እንደተከሳሽ ቃሌን ለመስጠት ቢያንስ ከሳሼ ማን እንደሆነ የማወቅ መብቴ ሳይከበርልኝ ቀርቷል፡፡ በድፍኑ “ከሳሽ ፖሊስም ሊሆን ይችላል” ተብዬአለሁ፡፡ በስም ማጥፋት ክስ ጉዳይ ግለሰብ ከሆነ ራሱ በሚያቀርበው አቤቱታ፣የመንግስት ሹመኛ ከሆነ በዓቃቤ ሕግ በኩል ክስ ሊቀርብ እንደሚችል ያለውን ድንጋጌ አንስቶ መከራከር እዚህ ቦታ ላይ ዋጋ አልነበረውም፡፡ ያም ሆነ ይህ ከሳሼን የማወቅ መብቴ ተከልክዬ እነሆ ቃሌን ለመስጠት በቃሁ፡፡
በዚህ ሁኔታ ጠዋት 3፡15 ገደማ የቀድሞ ማዕካዊ የገባሁ የአምስት ሺ ብር ዋስ እስካቀርብ ድረስ የቁም አስረኛ ሆኜ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ገደማ ግቢውን ለቅቄ ወጥቻለሁ፡፡
ፍሬው አበበ
የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 15th, 2013

Federation Council and Regional Government
ለፌደረሽን ምክር ቤት ህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ
እንደሚታወቀው እኛ ባለፈዉ አመት ከመጋቢት እስከ ሰኔ 2004 ዓም ድረስ ከመኖሪያ ቀያችን ከደቡብ ኢትዮጵያ ስንባረር የነበርን ዜጎች ነን:: የመባርርና የመገፋታችን ጉዳይ ግን እስከ አሁን 2005 ዓም ድረስ ቀጥሎአል:: በቅርቡም የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከልዩ ልዩ ቦታዎች በህገወጥ መንገድ እየተፈናቀልን ስላለነዉ አማሮች በፓርላማ ተጠይቀዉ ሲመልሱ ማንኛዉም ዜጋ በየትኛዉም የኢትዮጵያ ክልል የመኖር ህገ መንግስታዊ መብት እናዳለዉ ገልጸዉ በእኛ ላይ እየተወሰድ ያለዉ እርምጃ ግን ጸረ ህገ መንግስት መሆኑን አስረግጠዉ ተናገረዋል::
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 15th, 2013
‘‘አያያዛችን ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም’’
ተጠርጣሪዎች
*‘‘እስካሁን ተከሳሽ የሚባል የለም፤ እነዚህ ሰዎች ተጠርጣሪዎች ናቸው’’
ፍርድ ቤቱ
*‘‘በሚዲያ የሚተላለፈው ሪፖርት በቤተሰቦቻችን ላይ ጫና እየፈጠረ ነው’’
ተጠርጣሪዎች
በአሸናፊ ደምሴ

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች ማጣራት እያካሄዱባቸው የሚገኙት 24 ግለሰቦች የዋስትና መብታቸውን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ውሳኔ ተሰጣቸው።
በትናንትናው ዕለት የኮሚሽኑ መርማሪ በሦስት ክሶች ከፋፍሎ ክስ የመሰረተባቸው 24 ተጠርጣሪዎች በፍርድ ቤቱ የተገኙ ሲሆን፤ ከትናንት በስቲያ በነበረው የቃል ክርክር ወቅት ተነስቶ የነበረውን የዋስትና ጥያቄ ምላሽ ተሰጥቶበታል። በዚህም የፌዴራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ከምክር ቤት አባልነታቸው መታገዳቸውን የሚያስረዳ ደብዳቤ ሊቀርብ ይገባል ያለው ፍርድ ቤቱ፤ ይህንንም ለማጣራት ለግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በመሆኑም በአንደኛ ክስና በሁለተኛ ክስ ስር የተዘረዘሩት ተጠርጣሪዎች በሙሉ ለግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም የምርመራው ፈቃድ ፀንቶባቸው የተቀጠሩ ሲሆን፤ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ በናዝሬት ጉምሩክ ባልደረቦች ስር የተጠረጠሩት ግለሰቦች ለግንቦት 9 ተቀጥረዋል።
በፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች በናዝሬት ጉምሩክ ባልደረቦች ላይ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ያልተገባ ሀብት አግኝተዋል ሲል ክሱን የዘረዘረ ሲሆን፤ ከስድስቱ ተጠርጣሪ መካከል ሁለቱ ብቻ ጠበቆቻቸውን ማግኘታቸውን በመጥቀስ ቀሪዎቹ ከጠበቆች ጋር እንዳልተገናኙ በመግለፅ ለፍርድ ቤቱ ያስረዱ በመሆናቸው፤ ፍርድ ቤቱም ከጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙና ሀሳባቸውን አደራጅተው እንዲቀርቡ በማለት ለግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ከትላንት በስቲያ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተጠርጣሪዎቹ ለምን ከጠበቆች ጋር አልተገናኙም ለሚለው የፍርድ ቤቱ ጥያቄ በተሰጠው ምላሽ፤ በማረሚያ ቤት የሚገኙ ሰዎች ረቡዕና አርብ ብቻ በጠበቆቻቸው ጋር የሚገናኙበት አሰራር መኖሩ ተብራርቷል። በዚህም ላይ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጠው በመጠየቅ ለግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤት ከቀረቡት ተጠርጣሪዎች መካከል አብዛኞቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጉዳያቸውን ያስረዱ ሲሆን፤ ስለተከሰስንበት ወንጀል በቅጡ የምናውቀው ነገር የለም። አያያዛችን ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም። ሰሞኑን በሚዲያ እየተነገረ ያለው ነገር ትክክል ያልሆነና የቤተሰቦቻችንን አንገት ያስደፋ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ‘‘በምንም መልኩ ቢሆን እስካሁን ተከሳሽ የሚባል ነገር የለም፤ እነዚህ ሰዎች ተጠርጣሪዎች ናቸው’’ ሲል ዐቃቤ ሕግ ክስ ባልመሰረተበት ሁኔታ ተጠርጣሪዎቹ በተሳሳተ ስም መጠራት የለባቸውም ብሏል።
በኮሚሽኑ መርማሪዎች ሁለተኛ ክስ ስር የፌዴራሉ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ ባለቤታቸው ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋዬ እና እህታቸው ወ/ሮ ንግስት ተስፋዬን ከነልጅዋ እንዲሁም ሌሎች በድምሩ 12 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች የቀረቡ ሲሆን፤ የተጠረጠሩበት ወንጀልም ወደሀገር ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለን ሲሚንቶ እንዲገባ በማድረግ፣ በኮንትሮባንድ የተሰማሩ ሰዎችን በማገዝ፣ ከተጠርጣሪዎችም መካከል የሁለቱን ክስ የሚደግፉ ሠነዶችን ማሸሽ በሚሉ ወንጀሎች እጠይቃቸዋለሁ ይላል።
አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ በጠበቃቸው አማካኝነት እንዳስረዱት ‘‘ቤተሰቤ ተበትኗል፤ ልጄ ለትምህርት የሚገለገልበት ላፕቶፕ ተወስዶበታል። ባለቤቴንም ህጉን ባልተከተለ መንገድ ልብስ አስወልቀው ጭምር ፈትሸዋታል፤ ልታሸሽ ነበር ተብሎ የተያዘውም ካርታ ፎቶ ኮፒው መሆኑንና ዋናው በፌዴራሉ ሥነ-ምግባና ፀረ-ሙስና መርማሪዎች እጅ እንደሚገኝም ጭምር አስረድተዋል።
በሌላም በኩል ተጠርጣሪዎቹም በማረሚያ ቤት የተቀበላቸው አያያዝ መልካም አለመሆኑን በመጥቀስ ለፍርድ ቤቱ ያስረዱ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎቹ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የፌዴራሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መርማሪ ቡድን በሙስና ተጠርጥረው ጉዳያቸውን ለፍርድ ለማቅረብ በተሰናዳባቸው 24 ግለሰቦች ላይ ሦስት ክሶችን የመሰረተ ሲሆን፤ በ1ኛ ክስ ስር በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ውስጥ የሚገኙት 7 ተጠርጣሪዎች አቶ እሸቱ ወ/ሰማያት፣ አቶ መርክነህ አለማየሁ፣ አቶ አስመላሽ ወ/ማርያም፣ አቶ ከተማ ከበደ፣ አቶ ስማቸው ከበደ እና ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ይገኙበታል። እነዚህ ቀረጥና ታክስን በማጭበርበርና አራጣ በማበደር የተከሰሱ ግለሰቦች እንዲቋረጥ በማድረግ ወንጀል ተከሰዋል።
በሁለተኛው የክስ ዝርዝር ውስጥ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ አቶ በላቸው በየነ፣ አቶ ጥሩነህ በርታ፣ አቶ ተስፋዬ አበበ፣ አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር፣ አቶ ምህረተአብ ካሳ፣ አቶ ሙሌ ጋሻው፣ አቶ አሞኘ ታገለ፣ ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋዬ፣ አቶ ሀብቶም ገብረመድህን እና ወ/ሮ ንግስቲ ተስፋዬን ጨምሮ በመጨረሻ የተቀላቀሉትን 12ኛ ተከሳሽ አቶ ተወልደ ብስራትን ያጠቃልላል። በዚህም ክስ ስር ተጠርጣሪዎቹ ፈፀሙት የተባለው ወንጀል ወደሀገር ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለን ሲሚንቶ እንዲገባ በማድረግ፣ በኮንትሮባንድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በማገዝ፣ ከተጠርጣሪዎች መካከል የሁለቱን ክስ የሚደግፍ ሰነድ ለማሸሽ ጭምር የሚል ይገኝበታል።
በሦስተኛ ክስነት የተጠቀሰው የናዝሬት ጉምሩክ ባለስልጣናትን የሚመለከት ሲሆን፤ በዚህም ስር አቶ መሃመድ ኢሳን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች የተዘረዘሩ ሲሆን፤ እነሱም አቶ ሰመረ ንጉሴ፣ አቶ ዘሪሁን ዘውዴ፣ ወ/ሮ ማርሸት ተስፋዬ፣ አቶ ሙሉቀን ተስፋዬ እና አቶ ዳኜ ስንሻው ይገኙበታል። የተጠረጠሩበት የወንጀል ክስም በኮንትሮባንድ የተለያዩ ዕቃዎች ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግና ያልተገባ ሀብትን ማካበት የሚሉት ይጠቀሳሉ።
በትናንትናው ዕለት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ለመከታተል ከተገኘው በመቶዎች የሚቆጠር ሕዝብ መካከል ወደ ችሎት መግባት የቻለው ጥቂቱ ሲሆን፤ በአዳራሹ ጠባብነት ምክንያት በተለይም ጋዜጠኞች ቦታ ሊያገኙ አለመቻላቸው ትኩረትን ስቦ ነበር። አንዳንድ የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦችም ችሎቱ በሰፊ አዳራሽ ቢካሄድ የተሻለ ይሆን እንደነበር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።n (ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ሜይ 15 2013 ዕትም)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 15th, 2013
· ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ የታሰበው ከአቶ መለስ ህልፈት በፊት ነው
· ተጨማሪ እርምጃ እንደሚወሰድ ኮሚሽነሩ ፍንጭ ሰጥተዋል
· በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተወሰደው እርምጃ ታስቦበት እንጂ
በግርግር አይደለም ብለዋል
በዘሪሁን ሙሉጌታ

የፌዴራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዓሊ ሱሌይማን ሰሞኑን በድንገት በቁጥጥር ስር በዋሉት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ባለሀብቶችን በተመለከተ በጥንቃቄ የተሞላ መግለጫ ሰጡ።
በመግለጫው ላይ በርካታ ጋዜጠኞች ተገኝተው ለኮሚሽነሩ በርካታ ጥያቄዎች ለማቅረብ ቢፈልጉም ጋዜጣዊ መግለጫው በአጭሩ እንዲከናወን ተደርጓል። በዚሁ ጥንቃቄ በተደረገበት መግለጫ ላይ ኮሚሽነር ዓሊ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ጥናትና ክትትል ሲደረግ የቆየው ከሁለት ዓመት በፊት አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ወቅት መሆኑን አረጋግጠዋል። ኮሚሽኑ በቀጣይም እርምጃ እንደሚወስድ ፍንጭ የሰጡ ሲሆን በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተወሰደው እርምጃ ታስቦበት እንጂ “በቱማታ” አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።
ችግሩ የቆየ ከሆነ አሁን ለምን እርምጃ ተወሰደ ተብለው የተጠየቁት ኮሚሽነሩ ሲመልሱ፤ “ጠመንጃ የያዘ ሰው “ኮሽ” ባለ ቁጥር አይተኩስም” እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ጉዳዮች ነበሩ። ከነዚህም ውስጥ ደግሞ የዜጎችን ሕገ-መንግስታዊ መብት ሳይነካ በቂ ማስረጃ መሰብሰብ በማስፈለጉ ነው” ብለዋል። ሙስናም ቀጣይ ትግል በመሆኑ እርምጃው ዘግይቷል ሊባል አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል። በሌሎችም መስሪያቤቶች ክትትሉ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
“ትልልቅ የመንግስት ኃላፊዎችን መያዝ ድፍረቱ ከዬት ተገኘ?” ለሚለው የጋዜጠኞች ጥያቄ ኮሚሽነሩ ሲመልሱ ከዚህ በፊትም ትላልቅ የመንግስት ኃላፊዎች ክስ ሲመሰርት መቆየቱን ጠቅሰው የኮሚሽኑ ትኩረት ወንጀሉ ላይ እንጂ ግለሰቦቹ ላይ አለመሆኑን ተናግረዋል።
በቂ ማስረጃ ካላችሁ ለምን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ አስፈለጋችሁ ለተባሉት ኮሚሽነሩ ሲመልሱ ይዞ ለመመርመር የሚያበቃ ማስረጃ እና ለፍርድ ቤት አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ የተለያዩ በመሆኑ ነው ብለዋል።
የተጠርጣሪዎቹን ልጆች (ተማሪዎች) ለምን ያዛችሁ ለሚለው ጥያቄም የማውቀው ነገር የለም ብለዋል። ምርመራውም በተጠርጣሪዎቹ ላይ ብቻ እንደሆነ ገልፀዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ለምን አሰራችሁ? ተብለው ኮሚሽነሩ ቢጠየቁም ያለመከሰስ መብት ሊነሳ ይችላል በሚል ብዙም ግልፅ ያልሆነ መልስ ሰጥተዋል።
ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ የባለሥልጣናት የሐብት ምዝገባው አግዟችኋል ወይ ለተባሉት “አግዞናል” በሚል አጭር መልስ ሰጥተዋል። ወደፊትም በግብር ጉዳይ ላይ ኮሚሽኑ ያተኩራል ብለዋል። እርምጃው የፖለቲካ ጉዳይ ስለመሆኑም ተጠይቀው በሀገራችን ብቻ ባይሆን በሌሎች አገሮችም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ሲያዙ ጉዳዩ “ፖለቲካ ነው” መባሉ አይቀርም። ወደፊት የፖለቲካ ኬዝ እንዳልሆነ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ እናሳያለን በማለት በአጭሩ መልሰዋል።
ከሀገር ውጪ ስለኮበለለ ሀብትም ተጠይቀው ለጊዜው አስፈላጊ አይደለም። ነገር ግን በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ተጋግዘን እንሰራለን ሲሉ መልሰዋል።¾ (ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ዕትም)
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 15th, 2013
ከይርጋ አበበ
26 : 38 በስታዲየሙ የተሰቀለው የውጤት ማሳያ ኤሌክትሮኒክስ ሰሌዳ የፈርጉሰንን ከኦልድ ትራፎርድ መለዬት በማስመልከት ያስነበበው ጽሑፍ ነው ።ለዚህ ጽሑፌ ርዕስ ያደረኩት ይህ ቁጥር አሰልጣኙ በክለቡ የቆዩባቸውን ዓመታት እና ያገኟቸውን ዋንጫዎች ብዛት ለመግለፅ የተጠቀሙበት ገለፃ ነው።
በሃያ ስድስት ዓመታት የተገኙ ሰላሳ ስምንት ዋንጫዎችን ወደ ክለቡ የዋንጫ መደርደሪያ ማምጣት የቻሉት ሰር አሌክስ ፣ከጨዋታው በኋላ በስታዲየሙ ለታደሙት የክለቡ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ንግግር አድርገዋል ። በንግግራቸውም እስካሁን በክለቡ ለነበራቸው ቆይታ የተደረገላቸውን እንክብካቤ አድንቀዋል ፤ለክለቡ ውጤት ቀጣይነት ሲባል ለሳቸው የተደረገው ለተተኪው አሰልጣኝም እንዲደረግላቸው ደጋፊዎቹን ተማጽነዋል። ተጫዋቾቹም ለለበሱት ማሊያ ፍቅር እንዲኖራቸው እና ለክለባቸው ውጤት ማማር ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ህዳር ወር መጨረሻ ላይ ማሰልጠን የጀመሩትን ክለብ ለመሰናበት ጫፍ ላይ የደረሱት አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በማንቸስተር የመጨረሻ ዓመት ቆይታቸው የመጨረሻ ዋንጫቸውን በኦልድ ትራፎርድ ያደረጉትን የመጨረሻ ጨዋታ የዌልሱን ክለብ ሁለት ለባዶ በማሸነፍ መጨረሻቸውን አሳምረው ለመውጣት በቅተዋል። በታላቁ ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም በልዩ ትዕይንት የተጀመረውና ከሰባ ሺ በላይ ቀያይ ባንዲራዎች አሸብርቆ በከፍተኛ ድጋፍ የታጀበው የእሁድ ምሽቱ ጨዋታ ከሰር አሌክስ በተጨማሪ አንጋፋውን ፖል ስኮልስንም ለሁለተኛ ጊዜ ለመሸኘት የተመቸ አጋጣሚ ነበር። የሰቀለውን ጫማ በሰር አሌክስ ልመና አውርዶ በማጥለቅ ለቀያይ ሰይጣኖቹ ከፍተኛ አገልግሎትን መስጠት የቻለው ፖል ስኮልስ ከአሰልጣኙ ጋር በክብር ለመሸኘት ችሏል።
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በቁጥሮች
2ፈርጊ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ማግኘት የቻሉት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ብዛት
5 በፈርጉሰን የሰለጠኑቡድኖች ብዛት ሲሆን፡ ኢስት ስቲርሊንግ፣ ሴይንት ሜሪ፣ አበርዲን፣ የስኮትላንድ ብሄራዊ ቡድን እና ማንቸስተር ዩናይትድ
6 በተጫዋችነት ዘመናቸው ሰር አሌክ የተጫወቱባቸው ክለቦች፡ ኩይን ፓርክ፣ ሴይንት ጆንስተን፣ ደንፈርምሊን፣ ፋልክሪክ እና አይር የተባሉ የስኮትላንድ ክለቦች
9 የሰባ አንድ ዓመቱ የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ያገኟቸው የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎች ቁጥር አምስቱን በማን ዩናይትድ አራቱን በአበርዲን
26 ስኮትላንዳዊው አዛውንት በኦልድ ትራፎርዱ ክለብ የነበራቸው ቆይታ በዓመት፡- ይህንን ያህል ዓመት ማንቸስተር ዩናይትድን ያሰለጠነ አሰልጣኝ የለም።
38 የእንግሊዙ ክለብ ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በሰር አሌክስ ፈርጉሰን አሰልጣኝነት ያገኛቸው ዋንጫዎች ብዛት፡- ይህንን ያህል የዋንጫ ብዛት መደርደሪያው ላይ የሰቀለ አሰልጣኝ ሲቪው ላይ የተፃፈለት አሰልጣኝ ከሰር አሌክስ ውጪ ማንም የለም።
104 ሰር አሌክስ በሃያ ስድስት ዓመታት ቀዩን ማሊያ ለማልበስ ወደ ክለባቸው ያስመጧቸው ተጫዋቾች፡- ለመጨረሻ ጊዜ ያስፈረሙት ትውልደ አይቮሪኮስታዊው ክሪስቶፎር ዛሃ ሲሆን ባለፈው ጃንዋሪ ወር በተከፈተው የተጫዋቾች ዝውውር በ15ሚሊዮን ፓውንድ ገዝተው ለአሳዳጊ ክለቡ በውሰት ሰጥተውታል። በፈርጊ ተገዝቶ ለፈርጉሰን ቡድን መጫወት ያልቻለ ተጫዋች።
170 ውጤታማው አሰልጣኝ በተጫዋችነት ዘመኑ ለተሰለፈባቸው ክለቦች ያስቆጠሩት ግብ ድምር፡- ፈርጊ ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ወደ ማንቸስተር ካዘዋወሯቸው 104 ተጫዋቾች ውስጥ የሚበዛውን ቁጥር የሚይዙት አጥቂዎች መሆናቸው አሰልጣኙ ውጤታማ የአጥቂ መስመር ተጫዋች እንደነበሩ ማሳያ ነው ሲሉ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።
370 ቁምጣና ማሊያ ለብሰው ወደ ሜዳ የገቡበት የጨዋታ ብዛት፡- ለስድስት ክለቦች በአጠቃላይ መሰለፍ የቻሉት የጨዋታ ብዛት 370 ብቻ ሲሆን በነዚህ ጨዋታዎች 170 ግቦችን ማስቆጠር መቻላቸው እውነተኛ የጎል ማሽን ነበሩ ያስብላል።
1499 ማንቸስተር ዩናይትድን እየመሩ ወደሜዳ የገቡባቸው ጨዋታዎች፡- ከሳምንት በኋላ 1500ኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን፡- እስካሁን ግን 1499 ጨዋታዎችን አድርገው 895ቱን ማሸነፍ ችለዋል።
የፈርጉሰን ምርጥ አስራ አንድ
የእንግሊዙ ዘ ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ የሃያ ስድስት ዓመት የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ምርጥ 11 ፈራሚዎች እንዲመረጡ በበተነው መጠይቅ መሰረት የአብላጫውን ድምፅ ያገኙትን አስራ አንድ ተጫዋቾች እንዲህ እናቀርባቸዋለን።
1. ፒተር ሺማይክል ምርጡ የፈርጊ ግብ ጠባቂ
2. ጋሪ ኔቭል ዝምተኛው ጀግና
3. ፓትሪስ ኢቭራ የፈርጉሰንን ክፍተት የደፈነ ምርጥ የኋላ መስመር ተጫዋች
4. ያፕ ስታም ደፋር እና አይደክሜ ሆላንዳዊ
አማካይ መስመር
5 . ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ውዱ ተጫዋች የፈርጊ ምርጥ ፖርቹጋላዊ ፈራሚ
6 . ሪያን ጊግስ የአንድ ክለብ ማሊያ ብቻ ገላው የለመደው ዌልሳዊ ምርጥ ባለ ግራ እግር
7 . ሮይ ኪን አየርላንዳዊው ጉልበተኛ በማንቸስተር አሻራው የማይተካ ሚና ነበረው
8. ፖል ስኮልስ ምርጡ እንግሊዛዊ ለፈርጉሰን ቡድን ያልከፈለው አልነበረም
የአጥቂ መስመር
10. ዋይኒ ማርክ ሩኒ በማንቸስተር ያለው ቆይታ ያልተረጋገጠው የኤቨርተን አካዳሚ ፍሬ ከምርጦቹ የፈርጊ ፈራሚዎች አንዱ ለመሆን ጊዜ አለፈጀበትም
11. ኤሪክ ካንቶና የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ የሆነበት ፈረንሳዊ አመለ ብልሹ ከ1995-98 የማንቸስተር ዩናይትድ ውጤት ግምባር ቀደም ተጠቃሽ ነበር።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Wednesday, May 15th, 2013
ከኢየሩሳሌም አርአያ
በሕወሐት የተፈጠረው የቀውስ ማእበል አድማሱን እየለጠጠ መሔዱን ተከትሎ «ታማኝ» ሆነው በሙስና ሲያገለግሉ የቆዩትን ጭምር እየበላ እንደሚገኝ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በቀዳሚነት የሚያነሱት በጉምሩክ ቁልፍ ስልጣን የነበረውን የሕወሐት አባል ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስን ሲሆን እንዴትና በማን ወደስልጣን እንደመጣ እንዲሁም ምን-ምን ተግባራት ይፈፅምና ያስፈፅም እንደነበረ ምንጮቹ ሂደቱን እንደሚከተለው ይገልፁታል።
ገ/ዋህድ በ1993ዓ.ም ፓርቲው ለሁለት መሰንጠቁን ተከትሎ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ተደረገ። ከጉምሩክ ሃላፊነት በተጨማሪ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተርነት ስልጣን እንዲጨብጥ የተደረገው በአቶ መለስ በተለይ በአዜብ ይሁንታ ጭምር እንደነበረ ምንጮቹ ይጠቁማሉ። ገ/ዋህድ ለዚህ ስልጣን የበቃው ለአቶ መለስ ቡድን በከፈለው መስዋእትነት ሲሆን በክፍፍሉ ማግስት የሙስና ዘመቻ ተከፍቶ እነአባተ ኪሾና ሌሎች እስር ቤት እንዲገቡ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከመስጠት አንስቶ ራሱ ክስ አዘጋጅ፣ምስክርና ፈራጅ..በመሆን የላቀ ሚና መጫወቱን ያስታውሳሉ። በዚህ ተግባሩ የበለጠ ታማኝነቱን በማሳየቱ ከአዜብ በሚሰጠው ቀጥታ ትእዛዝ ሙስናውን ማከናወን መቀጠሉን ምንጮቹ አያያዘው ይጠቁማሉ። በ10ሺህ ቶን የሚገመት ቡና ከአዜብ በተቀበለው ትእዛዝ በህገወጥ መንገድ ከአገር ተዘርፎ የተሸጠበትና ጉዳዩም በፓርላማ ተነስቶ በጠ/ሚ/ሩ «የሌቦቹን እጅ እንቆርጣለን» የሚል አስቂኝ ምላሽ መሰጠቱን ያስታውሳሉ። በተጨማሪ በጉምሩክ ለረጅም አመት በመምሪያ ሃላፊነት ሽፋን የተቀመጠውና የቢሮውን የበላይ ሃላፊዎች በጥብቅ ከመቆጣጠር ጀምሮ እያንዳንዱን የሙስና ተግባር ከጀርባ ሆኖ የሚያስፈፅመው የአዜብ የቅርብ ስጋ ዘመድ ፍትሃነገስት ክንደያ እንደሚጠቀስና ግለሰቡ ቀረጥ ያልተከፈለባቸው 500 ሳተላይት ዲሾች እንዲገቡና በአዜብ በበላይነት ይመራ ለነበረው የዘረፋ ቡድን ለሰባት አመታት በየወሩ 20ሚሊዮን ከቴሌ በህገወጥ መንገድ እንዲዘረፍ ያደረገና በኋላም ከነገ/ዋህድ ጋር ሆኖ በርካታ ሙስናዎችን በዋናነት በማስፈፀም እንደሚጠቀስ ያመለክታሉ።
በሌላም በኩል የገ/ዋህድ ባለቤት ኰ/ል ሃይማኖት ስትጠቀስ ከሕወሐት አንጋፋ ሴት ታጋዮች አንዷ ናት፤ ከጡረታ ጋር በተያያዘ ከመከላከያ በመልቀቅ በአዜብ የበላይነት በሚመራው የሴቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቢሮ መስራት ቀጠለች። ለዚህ ቢሮ ከአሜሪካ መንግስት ብቻ በአመት እስከ 240ሚሊዮን ዶላር ይለገሳል። ገንዘቡ ለሚመለከታቸው ወገኖች ሳይሆን የሚውለው የነአዜብ ኪስ ማደለቢያ ሆኖ እንደሚዘረፍ ያመለከቱት ምንጮች ይህም ጉዳይ በፓርላማ ለቀድሞ ጠ/ሚ/ር ተነስቶ « ከእንግዲህ ቁጥጥር እናደርጋለን» የሚል የተድበሰበሰ ምላሽ እንድተሰጠ ያስታውሳሉ። ባልና ሚስቱን በተለያየ ወጥመድ በማስገባት የሙስና ጋሻ-ጃግሬ አድርገው የቆዩት አዜብ እንዲሁም ሌሎቹ ቱባ ባለስልጣናት መጠነ-ሰፊ ዘረፋና ሙስና ጉዳይ ሳይነካ ግልገሎቹን ብቻ (ያውም በአስፈፃሚነት ራሳቸው የመደቧቸውን) ተጠያቂ ማድረግ ተራ ድራማ ነው ሲሉ ምንጮቹ ያጣጥሉታል። በማስረጃነትም፥ 400 ሚሊዮን ብር ለ«ራዲሰን ሆቴል ግንባታ» በሚል ሽፋን በመፍቀድ 150ሚሊዮን ኪሳቸው ከከተቱትና በርካታ ብድሮችን በመፍቀድ (የስጋ ዘመዶቻቸውን ደላላ በማድረግ…) በሙስና የደለቡት አባይ ፀሃዬ ጨምሮ፣ የበታች ሙሰኞች ላይ <ምስክር> ሆነው የቀረቡትና ከአዜብ ጋር በሙስና የሰከሩት አባዱላ ገመዳ፣ የተለያዩ ድርጅቶች ባለቤት ስብሃት ነጋ፣ የቱጃሩን የቢሊዮን ብድር በግል ከመፍቀድ አንስቶ የታዋቂ ባለሃብቶች <ቀኝ እጅ> የሆኑትና ሚስታቸውን ጭምር በሙስና ያሰማሩት በረከት ስምኦን፣ ሶፍያን አህመድ፣ እንዲሁም ቪላዎችን ከ8 እስከ 10 ሚሊዮን ብር ወጪ በማስገንባትና በማከራየት የአገር ሃብት የሚዘርፉ ሁሉም የገዢው ትላልቅ ባለስልጣናት የሙስና ጉዳይ በዋቢነት ይጠቅሳሉ። ባጠቃላይ የስርአቱ ቁንጮዎች የሚያናቁራቸው የገዛ ጥቅምን ከማስጠበቅና አንዱ ጎራ ከሌላው በልጦ በሙስና የሚከብርበትን መንገድ ለማመቻቸት ብሎም ሌላኛውን በመጨፍለቅ ስልጣኑን ከነታማኝ ተከታዮቹ አስጠብቆ የሚቀጥልበትን ብቻ እንደሚያልም የጠቆሙት ምንጮቹ፣ ስርአቱ የአስተዳደር፣የፖለቲካ፣ የፖሊሲ…ወዘተ ልዩነት እንደሌለበት ያሰምሩበታል።
ሌላው ዘብጥያ የወረዱት ባለሃብት አቶ ነጋ ገ/እግዚያብሄር ናቸው፤ የአቶ ነጋ ባለቤት የቀድሞ የሜጋ ኪነጥበብ ሃላፊ እቁባይ በርሄ እህት ናት። ከጥቂት ወራት በፊት ከሙስና ጋር በተያያዘ አስገራሚ ፍርድ የተሰጠውና ጥፋተኛ ተብሎ የተለቀቀው እቁባይ ያንን አይን ያወጣ «ፍርድ» እንዲያገኝ የተደረገው ከአዜብ በተሰጠ ቀጭን ትእዛዝ ነው ያሉት ምንጮቹ ይህ ሊሆን የቻለው አዜብ ከአቶ ነጋ ጋር ባላቸው የቢዝነስ ትስሥር ጭምር መሆኑን አያይዘው ይገልፃሉ። (ሌላም አሳፋሪ ቁርኝት ቢኖራቸውም ለጊዜው ማለፍ ይመረጣል)…
በሌላም በኩል የስዬ አብርሃ ወንድም ምህረተአብ አብርሃ እንዲሁም አይነስውሩ አስመላሽ ወ/ስላሴ ይጠቀሳሉ፤ ምህረተአብ ከስዬ ጋር ተፈርዶበት የተለቀቀው ከአምስት አመት በፊት ሲሆን አሁን ደግሞ ከነገ/ዋህድ ክስ ጋር በተያያዘ አብሮ እንዲቀላቀል ተደርጎዋል።…. አይነስውሩ አስመላሽ (በቅፅል ስማቸው አባይ ነብሶ) በፓርላማ የሕግ ጉዳይ ቢሮን ሲመሩ የቆዩ ናቸው፤ በሕወሐት ክፍፍል ጊዜ እያለቀሱ ፓርቲው እንዳይፈርስ ሲማፀኑ እንደነበር ያስታወሱት ምንጮቹ በተለይ በአንድ ቀን ተፅፎ እንዲወጣ የተደረገውንና አንድ ሰው ለማጥቃት ሲባል ብቻ አዋጅ ሆኖ እንዲፀድቅ የተደረገውን ዋስትና የሚከለክል ሕግ ካረቀቁት አንዱ እንደሆኑ ይገልፃሉ። የአስመላሽ ባለቤት በጠ/ሚ/ሩ ቢሮ ተመድባ በፀሓፊነት የቆየችና በተለይ «ሚስጥራዊ» የሚባሉ ዶክመንቶችንና የአቶ መለስ ፅሁፎችን (በብእር ስም ይወጡ የነበሩትን ጭምር) በመተየብ በታማኝነት ስታገለግል እንደቆየች አመልክተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ጄኔራሎችና የበታች ከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከጥቂት ወራት በፊት ለመጠቆም እንደተሞከረው የሚባረሩ ጄኔራሎች እንዳሉ መገለፁ ይታወሳል። በዚህ መሰረት ከአዜብ ጋር የከረረ ፀብ ውስጥ የገቡት ጄ/ል ታደሰ ወረደን ጨምሮ ሶስት የሕወሐትና ሁለት የብአዴን ጄ/ሎች በሳሞራ ውሳኔ መባረራቸውን ምንጮች ገልፀዋል። በቅርቡ የተጀመረውና « የመለስን ራዕይ እናስፈፅማለን» በሚል መሪ አጀንዳ የቀጠለው ግምገማ ተጨማሪ የመከላከያ የጦር አዛዦችንና የበታች መኮንኖችን ለማባረር ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ማጠናቀቁ ታውቋል። በሳሞራ የተወሰነው ሌላው ጉዳይ ለመከላከያ ከሩሲያ የመጡ የመሳሪያ ባለሙያዎች በተለያዩ ቦታዎች እንዲመደቡ መደረጉ ሲታወቅ ይህም የሆነው « አገሪቱ ውስጥ ችግር ከተፈጠረ ልንቋቋም አንችልም » በማለት ሳሞራ ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸውና ከአየር ሃይል አንስቶ ያለው ወታደራዊ ክፍል እምነት ሊጣልበት ባለመቻሉ እንደሆነ ምንጮቹ አስረድተዋል። የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነቱ ስልጣን የጠ/ሚ/ሩ እንደሆነ ሕገ መንግስቱ ቢደነግግም ነገር ግን ለአቶ ሃ/ማርያም ይህ ስልጣን እንዳልተሰጣቸው፣ ጄ/ሎች ሲባረሩ ከእርሳቸው እውቅና ውጭ እንደሆነ፣ ውሳኔው በሳሞራ እንደሚከናወን ምንጮቹ አስረድተዋል።
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »
Tuesday, May 14th, 2013
Tags: addis ababa, Amharic, business, economy, election, Ethiopia, Ethiopians, export, health, immigration, import/export, market, money transfer, politics, scholarship
Posted in Amharic | No Comments »