Archive for the ‘Amharic’ Category

UTC 16:00 የዓለም ዜና 08.07.2014

Tuesday, July 8th, 2014

Early Edition – ጁላይ 08, 2014

Tuesday, July 8th, 2014

የኢትዮጵያዊያን የዓመቱ ፌስቲቫል ተጠናቀቀ

Monday, July 7th, 2014
      ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ በሳን ሆዜ - ካሊፎርኒያ ሲካሄድ የሰነበተው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና የባሕል ፌስቲቫል ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ተጠናቅቋል፡፡ የዓመቱ የክለቦች ደረጃዎችም ታውቀዋል፡፡ የቨርጂነያ ቡድን በኔልሰን ማንዴላ ስም የተሰየመውን ዋንጫ አሸንፏል፡፡ ለዝርዝሩ የተያያዘውን የአዲሱ አበበን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያዊያን የዓመቱ ፌስቲቫል ተጠናቀቀ – ጁላይ 07, 2014

Monday, July 7th, 2014
Ethiopians in North America, sports and cultural festival

በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ እንግሊዝና ሂዩማን ራይትስ ዋች ተናገሩ – ጁላይ 07, 2014

Monday, July 7th, 2014
Andargachew, HRW, England

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግብፅ ጋር የተሸለ አቅጣጫ ላይ እንደሆኑ ገለፁ – ጁላይ 07, 2014

Monday, July 7th, 2014
Ethipian Parliament alocated next budget  

አቶ አንዳርጋቸው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የሚያሰሙት ቁጣ እንደቀጠለ ነው

Monday, July 7th, 2014

ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አሳልፈው በሰብአዊ መብት ጥሰትና ህዝብን በማሰቃየት በአለም የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ዘወትር ለሚወገዘው ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው መስጠታቸው ያበሳጫቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የነጻነት ትግሉን የምንቀላቀልበትን” መንገዱን ምሩን” በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ ነው።

ለኢሳት ስልኮችን እየደወሉ ቁጣቸውን የሚገልጹት ኢትዮጵያውያኑ ፣ አንዳርጋቸው በነፍሳቸው የከፈሉትን  መስዋትነት እነሱም ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አብዛኞቹ አስተያየት ሰጪዎች ትግሉን ለመቀላቀል መንገዱ እንደጠፈባቸው ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ አመራሩን ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ይጠይቃሉ።

ግንቦት7 ሰኔ 29 ቀን 2006 ዓም ባወጣው መግለጫ  ትግሉ “ሁላችን አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጿል።

አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ልክ እንደሱ ትሁት ሆኖ ግን ቆራጥ፤ ሆደ ሰፊ ሆኖ በዚያው ልክ ደግሞ መራር፤ አስተዋይና ብልህ ሆኖም ተግባር ተኮር መሆን ማለት ነው ብሎአል።

አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ወያኔን ለማስወገድ መደረግ የሚገባውን እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ሰው እንዲሁም ለአገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለት ነው የሚለው የግንቦት 7 መግለጫ፣ አገዛዙ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ካተኮረባቸው ምክንያቶች አንዱ የወያኔን የዘር ፓለቲካና ፕሮፖጋንዳ በሚያመክን መልኩ በተግባር ትግል ውስጥ ካሉ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ እና ሌሎች ዘውግ ተኮር ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ጋር ተግባራዊ ትብብር ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ድረስ ማቀራረብ በመቻሉ መሆኑን ገልጿል።

ንቅናቄው  “አገዛዙን  ለመጣል ትልቁን ድርሻ የሚያበረክተው ሕይወታቸውን ለመስጠት የቆረጡ፡ ከቁም ውርደትና ባርነት ለነጻነትና ለፍትህ ከወያኔ ጋር ጉረሮ ለጉረሮ እየተናነቁ እየጣሉ ለመውደቅ ፤ መስዋእት ለመሆን በወሰኑ ኢትዮጵያዊያን  ወገኖቻችንና  የህዝብ ሃይሎች  የሚያደርጉት ተግባራዊ እንቅስቅሴ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጠይቋል።

በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተቃውሞ ሰልፎችን እያዘጋጁ ነው። በካናዳ ኦታዋ ማክሰኞ  በብሪቲሽ ከፍተኛ ኮሚሽን መንገድ ከ1 ፒም ጀምሮ ይካሄዳል። በነገው እለት በተለያዩ ከቶሞች የሚደረጉት ሰልፎች ዋነኛ አላማቸው ምንድንነው በማለት ካስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑትን አቶ ውሂብ የሽጥላን አነጋገረናቸዋል

ከአሁን በሁዋላ እያንዳንዱ ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊ በዚህ ወሳኝ ወቅት ልዩነትን በማጥበብ በአንድነት ቆሞ የህግ የበላይነትን በሀገራችን ለማስፈን በመፋለም ታማኝነትን ማሳየት ይጠበቅበታል ሲልራዲዮ ነጃሽ አስታወቀ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ሂውማን ራይትስ ወች ገለጸ

Monday, July 7th, 2014

ሰኔ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ ለኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች ተላልፎ መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ማግኘቱን ገልጿል።

የየመን ባለስልጣናት ሰነዓ ከሚገኘው ኤል ራህባ አየር ማረፍያ ላይ እኤአ ጁን 23 ወይም 24 ከእንግሊዝ ኢምባሲ ጋር እንዳይገናኝ አድርገው አቶ አንዳርጋቸውን ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ ልከውታል ሲል ሂውማር ራይተስ ወች አስታውቋል።

የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው የአቶ አንዳርጋቸው ደህንነት እንደሚያሰጋቸው ገልጸው፣ መንግስት ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጠበቆቻቸውና ከእንግሊዝ ኮንሱላር ሰራተኞች ጋር እንዲገናኙ እንዲፈቅድ ጠይቀዋል።

አለም በሙሉ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ በአንክሮ እየተከታተለው መሆኑን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ልብ ሊሉት ይገባል ሲሉ ሌፍኮው ተናግረዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ ደግሞ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን በሃይል ወደ ኢትዮጵያ እንዲወሰዱ መደረጋሸውን  በአገሪቱ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችን ጠቅሶ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እንደሚደርስባቸው የገለጠው አምነስቲ፣ በአቶ አንዳርጋቸውም ላይ ከፍተኛ ስቃይ ሊደርስበት ይችላል ሲል አክሏል።

አምነስቲ አያይዞም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከጎረቤት አገሮች የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር በርካታ ኢትዮጵያውያን ያለፍላጎታቸው ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ስቃይ እንዲደርስባቸው እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

አምነስቲ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው የታሰረበትን ቦታ እንዲያስታውቁ ጠይቋል።

ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ጁላይ 07, 2014

Monday, July 7th, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የጀርመን እና አሜሪካ የስለላ ዉዝግብ

Monday, July 7th, 2014
ጀርመን አንድ ዜጋዋ በሀገሪቱ የስለላ ተቋም ተቀጥሮ ለዩናይትድ ስቴትስ እንደሚሰልል ከደረሰችበት ወዲህ ጉዳዩ የሀገሪቱን ከፍተኛ የፖለቲካ ኃይሎች እያነጋገረ ነዉ። በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለመሰላለልን ስምምነት ለመፈረም ዝግጁ አለመሆኗን ዋሽንግተን ባለፈዉ ሳምንት መገባደጃ ላይ አመልክታለች።

የኬንያዉ የጎሳ ግጭት መንስኤ

Monday, July 7th, 2014
የኬንያ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች መንግሥትን በመንቀፍ ህዝብ ለተቃዉሞ እንዲወጣ ጥሪ ያቀርባሉ። በሀገሪቱ የሚታየዉ የፖለቲካ ልዩነትና መቃቃር፤ የጎሳ ግጭት ቀዉስ አጥልቶበታል። በኬንያ በሚገኙት የተለያዩ ጎሳዎች መካከል የሚታየዉ ቀዉስ እየሰፋ መጥቶአል።

የእስራኤልና ፍልስጤም መበቃቀል

Monday, July 7th, 2014
የዘመነ-ዘመናቱ ፀሎት፤ ድርድር፤ የዲፕሎማሲ ጥረት ብዙዎች ብዙ ጊዜ እንዳሉት«ከልብ እና ፍትሐዊ» ሥላልሆነ---ሠላም የለም።ከልብ የሚደረገዉ ፖለቲካዊ መደባባት፤ ወታደራዊ መገዳደል፤እና መበቃቀል ግን ጥንትም-ድሮም ዘንድሮም አለ።

የአቶ አንዳርጋቸዉ እገታና የመብት ተሟጋቹ ተቋም

Monday, July 7th, 2014
የአዉሮጳ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመን-ርዕሠ ከተማ ሰነዓ አዉሮፕላን ማረፊያ ተይዘዉ ወደ ኢትዮጵያ ተግዘዋል የተባሉትን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ፅጌን ለማስፈታት እንዲጥሩ GESELLSCHAFT FÜR BEDROHTE VÖLKER የተሰኘዉ የጀርመን የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠየቀ።

Early Edition – ጁላይ 07, 2014

Monday, July 7th, 2014

ሰኔ 28,2006 የሙዚቃ ቃና ፐሮግራም( July 05,2014) – ጁላይ 07, 2014

Monday, July 7th, 2014
በዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም በአሜሪካ የቢል ቦርድ ሰንጠረዥ ላይ ከመቶዎቹ ምርጥ ዜማዎች መካከል በዚህ ሳምንት ከአንድኛ እስከ አስረኛ ደረጃ የወጡትን ምርጥ ዜማዎች ያጠቃልላል::

አንዳርጋቸው ጽጌ የሕዳሴው ታጋይ ከቴዎድሮስ ሐይሌ

Monday, July 7th, 2014

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሰበር ዜና – የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ የተፃረረው የፓትርያርኩ የአድባራት አለቆች ዝውውር ቁጣ ቀሰቀሰ፤ አዲሱ የደ/ጽጌ ቅ/ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሕዝቡ ተቃውሞ አቀባበል ሳይደረግላቸው ተመለሱ

Sunday, July 6th, 2014
  • ቋሚ ሲኖዶሱ የካህናቱንና ምእመናኑን አቤቱታ በመቀበልና የፓትርያርኩ ጥያቄ እንዲጣራ በማዘዝ፣ በሓላፊነታቸው እንዲቀጥሉ የወሰነላቸው ውጤታማው የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ ገብረ ጻድቅ፣ ውሳኔውን የሚፃረር የዝውውር ደብዳቤ በአባ ማትያስ ትእዛዝ ተጽፎባቸዋል፡፡
  • የፓትርያርኩን አግባብነት የሌለው ትእዛዝ በመቃወም የደብሩን ሀብት ከአማሳኞች ሰንሰለታዊ ምዝበራ ለመከላከል እንዲሁም የቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ በማስከበር የደብሩን ሰላም ለማስጠበቅ መንፈሳዊነት በተሞላው አኳኋን የሚንቀሳቀሱ የአጥቢያው ካህናት፣ ሠራተኞችና ምእመናን በኃይል ለማስፈራራት ሙከራ እየተደረገ ስለመኾኑ ተመልክቷል፡፡
  • የአጥቢያው ካህናት፣ ሠራተኞችና ምእመናን፡- ውጤታማው አስተዳዳሪ አግባብነት በሌለው የፓትርያርኩ ትእዛዝ መነሣታቸውን በመቃወም ስላቀረቡት አቤቱታ፣ ለቦሌ ክ/ከተማ ካራማራ ንኡስ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝተው ለክፍለ ከተማው አዛዥና ለጸጥታ ሰዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
  • ጥያቄአቸው÷ በሕጋዊ ውሳኔ ተመድበው በሰላማዊ መንገድ እየመሯቸው የሚገኙት ውጤታማው አስተዳዳሪ ስለተነሡበት የፓትርያርኩ ትእዛዝ በማስረጃ የተደገፈ ምላሽ እንዲሰጣቸው መኾኑን አመልካቾቹ ገልጸዋል፡፡
  • ፀረ – የአማሳኞች ሰንሰለታዊ ምዝበራ የኾነውን ሰላማዊ እንቅስቃሴአቸውን ግለሰባዊና ፖለቲካዊ በማስመሰል ከመንግሥት ለማጋጨትና የኃይል ርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚደረግ ግፊት እንዳለ የጠቀሱት የደብሩ ካህናት፣ ሠራተኞችና ምእመናን÷ ‹‹ወደ ፖሊቲካ ይቀይሩብናል፤ እኛ ግን ፖሊቲከኞች አይደለንም›› ብለዋል፡፡
  • የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በሚፃረረው የፓትርያርኩ ትእዛዝ ከሳሪስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ተዛውረው በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የተመደቡት አለቃ፣ ‹‹ወደ ደብሩ መሔድ የሚገባቸው ከሰበካ ጉባኤው አስተዳደር ጋራ አስቀድመው ከተነጋገሩና ከተግባቡ ብቻ እንደኾነ›› በትላንት ዕለት ከፖሊስ ተነግሯቸው እንደነበር ተገልጧል፡፡፡

*                   *                  *

  • የአጥቢያው ካህናት፣ ሠራተኞችና ምእመናን የደብሩን ሰላምና ሀብት ከአማሳኞች የምዝበራ ሰንሰለት ለመጠበቅና የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ ለማስከበር የሚያደርጉት የተቀናጀ ጥረት÷ ከቋሚ ሲኖዶሱ፣ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎችና ከሌሎችም አጥቢያዎች ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገለት ነው፡፡
  • ውጤታማና የብዙኃን ተቀባይነት ያላቸውን አለቆች፣ በጥቅመኝነት በታወረው የአማሳኞች ምክር ማዘዋወርን የመረጡት አባ ማትያስ፣ ቋሚ ሲኖዶሱ ያልተቀበለውን የዝውውር አቋማቸውን በባለሥልጣናት ጉልበት እና በአማሳኞች ተንኰል ለማስፈጸም መንቀሳቅሳቸውን ቀጥለዋል፡፡
  • ፓትርያርኩ÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መሠረት አድርገው ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋራ እየተወያዩ ከመሥራት ይልቅ ‹‹አለቆችን በራሴ ፍላጎት ብቻ የማዘዋወር ሥልጣን ከሌለኝ ፓትርያርክነቴ ምንድን ነው?›› ሲሉ ለባለሥልጣናት አቤቱታ ማቅረባቸው ተጠቁሟል፡፡
  • ለአቋማቸው ተቀባይነት አለማግኘትና ላስከተለው ከፍተኛ ተቃውሞ ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠያቂ ለማድረግ በአማሳኞች አመቻችነት ከሚገናኟቸው ባለሥልጣናት ጋራ መክረዋል፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹‹የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ኾነው አላሠራ አሉኝ፤›› በሚል በማኅበሩ ላይ ጫናቸውን ለማጠናከርም እየተዘጋጁ ነው ተብሏል፡፡

*                   *                  *

St. Urael parish head row02በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ዛሬ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከእሑድ ሰንበት ጸሎተ ቅዳሴ መጠናቀቅ በኋላ የደብሩ ካህናት፣ ሠራተኞች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና በርካታ ምእመናን ውጤታማው የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ ገብረ ጻድቅ ወደ ሌላ ደብር መዛወራቸውን በተመለከተ ተቃውሟቸውን ሰላማዊነት በተሞላው አኳኋን ሲያሰሙ ውለዋል፡፡

በተቃውሞው እንደተገለጸው÷ ከሐምሌ ወር ፳፻፫ ዓ.ም. ጀምሮ ካህናትና ምእመናን በአንድ ቃል በሚመሰክሩለት የተሟላ ክህነታዊ አገልግሎትና ብቃት ያለው አስተዳደራዊ ክህሎት ደብሩን የመሩትና በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ፋይናንሳዊ ሀብቱን ከአማሳኞች የምዝበራ ሰንሰለት ጠብቀው ከፍተኛ የልማት አቅም በመፍጠር መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ ገብረ ጻድቅ እስከ ዛሬ ከታዩት አለቆች ኹሉ ይልቅ ውጤታማ ኾነዋል፡፡

ውጤታማው አስተዳዳሪ፣ ከሰበካ ጉባኤው ጋራ በመተባበር÷ በስብከተ ወንጌል፣ በመልካም አስተዳደር እና በልማት መስኮች ያሳዩት የአገልግሎት ፍሬ በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ጭምር መረጋገጡን በተቃውሞው ተመልክቷል፡፡

ውጤታማው አስተዳዳሪ ዓመት ሳይሞላቸው ለደብሩ በፈጠሩት ከፍተኛ አቅም የያዟቸውን ዕቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ ዕድል ሊሰጣቸው የሚገባ እንጂ የአጥቢያውን ሀብት እንደለመዱት ለመቀራመት ባሰፈሰፉና በፓትርያርኩ ዙሪያ በተሰለፉ አማሳኞች ምክር ሊነሡ እንደማይገባ በብርቱ ተጠይቋል፡፡

በፓትርያርኩ ዙሪያ የተሰለፉ አማሳኞች ከደብሩ ልማደኛ መዝባሪዎች ጋራ ሰንሰለታዊ ግንኙነት በመፍጠር የፈበረኩት ክሥ፣ ባለፈው ረቡዕ፣ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በተካሔደው የቋሚ ሲኖዶሱ ሳምንታዊ ስብሰባ ላይ በፓትርያርኩ አማካይነት እንዲያው በደፈናው ቀርቦ እንደነበር ተገልጧል፡፡

ይኹንና ክሡ አንድም ፓትርያርኩ በደፈናው ተቀበሉኝ ያሉትን የፈጠራ ክሥ በማስረጃ ማስደገፍ ባለመቻላቸው፣ በሌላም በኩል ከፓትርያርኩ የስማ በለው ክሥ ይልቅ የተቋማዊ ለውጥ ጥናቱ አጋር የኾኑት አስተዳዳሪ በስብከተ ወንጌል፣ በመልካም አስተዳደርና በልማት ስላደረጉት ውጤታማ ጥረት በቅርበት የሚያውቀው የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በቃለ ጉባኤ አስደገፎ ከሰጠውና ቅ/ሲኖዶሱ በንባብ ካዳመጠው ምስክርነት ጋራ በቀጥታ የሚፃረር በመኾኑ በተባበረ ድምፅ ውድቅ ተደርጓል፡፡

የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ለቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ መነሻ እንዲኾን በፓትርያርኩ ትእዛዝ ሠርቶ ያቀረበው የዝውውር ቃለ ጉባኤ÷ አጥቢያው ከኹለ ገብ ሕንጻው የኪራይ ውል፣ ከሙዳይ ምጽዋትና ሌሎች በርካታ የገቢ ምንጮቹ በተጭበረበሩ ሰነዶች ከ22 ሚልዮን ብር በተመዘበረበትና ሰላሙ በታወከበት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ከደብረ ነጎድጓድ ቅ/ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ተዛውረው የተመደቡት መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ፣ ደብሩን ከማረጋጋትም በላይ በአጭር ጊዜ በስብከተ ወንጌል፣ በመልካም አስተዳደርና በልማት እንዳስመዘገቡት የዘረዘረው የሥራ ፍሬ የሚያስመሰግን እንጂ ከሓላፊነት የሚያሥነሳ ኾኖ እንዳላገኘው ቋሚ ሲኖዶሱ መወያየቱ ተጠቅሷል፡፡

አቡነ ማትያስ÷ አለቃውን በማንሣትና በቀጣይ በሚካሔደው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ምርጫ አጋጣሚ አስተዳደሩን በመቆጣጠር በጥንቃቄ የተጠበቀውን የአጥቢያውን ቅምጥ ሀብት የመቀራመት ዕቅድ ያላቸው የደብሩ ልማደኛ መዝባሪዎች፣ በዙሪያቸው ከተሰለፉ አማሳኞች ጋራ የሸረቡትን ተንኰል ከመቀበላቸው በፊት በሐሰት ተከሣሹን አስተዳዳሪ በሚገባ አቅርበው ያውቋቸው እንደኾነ በቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ጥያቄ እንደቀረበላቸውም ተዘግቧል፡፡

አለቃው እንዲነሡ በፓትርያርኩ የተያዘው አቋም ተቀባይነት የሚኖረው በበቀልና በጥቅመኝነት ስሜት መቅረቡ የታመነው የአማሳኞች ክሥ ልዩ ሀገረ ስብከቴ ነው ከሚሉት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ከቀረበው የአስተዳዳሪው ዘርፈ ብዙ የውጤታማነት ምስክርነት ጋራ ተነፃፅሮ ሐቀኝነቱ ሲረጋገጥ ብቻ መኾኑን ቋሚ ሲኖዶሱ በውሳኔው አመልክቷል፤ እስከዚያው ድረስ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ለቋሚ ሲኖዶሱ ቀርበው በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ የተመደቡት ውጤታማው አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ ገብረ ጻድቅ በምደባቸው ጸንተው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ በሙሉ ድምፅ መወሰኑ ታውቋል፡፡

ፓትርያርኩ ግን በውሳኔው የተስማሙ መስለው በወጡ ማግሥት፣ አስተዳዳሪው ወደ ሳሪስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን እንዲዛወሩና አዛውንቱ የሳሪስ አለቃም ወደ ደብረ ጽጌ ቅ/ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲሔዱ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፤ ትእዛዙም በልዩ ጽ/ቤታቸው የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ፊርማ ለየአለቆቹ በተከታታይ ቀናት መድረሱ ተገልጧል፡፡

St. Urael parish head row01

ተዋሕዶ ሃይማኖቴ የጥንት ነሽ የናትና አባቴ፤ ማዕተቤን አልበጥስም ትኖራለች ለዘላለም፤ አንመካም በጉልበታችን እግዚአብሔር ነው የኛ ኃይላችን፡፡

ደብዳቤው ለበርካታ የመንግሥት አካላት ግልባጭ መደረጉ የተገለጸ ሲኾን ይህም ፓትርያርኩ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ተደግፎ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋራ እየተወያዩ የተስማሙበትን ውሳኔውን ከማስፈጸም ይልቅ በጥቂት አማሳኞች የክፋት ምክር መመራትንና በባለሥልጣናት ጉልበት መመካትን መምረጣቸውን እንደገፉበት ያጠይቃል ብለዋል፤ ምእመናኑ በተቃውሟቸው፡፡

አኹንም ጥያቄአቸው የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ ማስከበርና አስተዳዳሪው ከሓላፊነታቸው አላግባብ የሚነሡበት ምክንያት ግልጽ እንዲደረግልን ነው የሚሉት አቤቱታ አቅራቢዎች፣ አለቃውን በሥራቸው ከሚያውቋቸውና በውጤታማነታቸው ከሚደግፏቸው በቀር ግለሰባዊ ጉዳይ እንደሌላቸው ገልጸዋል፤ እንቅስቃሴቸው ፀረ ሰላምና ፖለቲካዊ ነው በሚል ከመንግሥት ጋራ ለማጋጨት የሚሰነዘረው ትችትም አገልጋዩና ምእመኑ መብቱን እንዳይጠይቅና እናት ቤተ ክርስቲያኑን እንዳይጠብቅ ለማሸማቀቅ ያለመ የአማሳኞች የተለመደ ተንኰል ነው ብለዋል፡፡

አስተዳዳሪው በማስረጃ ተደግፎ የሚቀርብ ጥፋት ካለባቸው፣ በአማሳኞች የምዝበራ ሰንሰለታዊ አሠራር እንደተለመደው፣ ከደብር ደብር ከማዘዋወር ይልቅ በሓላፊነት ቦታ ከመቀመጥ ታግደው በሕግ መጠየቃቸውን እንደሚመርጡ፣ ይህም በደብሩ መዋቅር በተለያየ የሓላፊነት ደረጃ የመሸጉና በዓይነ ቊራኛ የሚከታተሏቸውን ልማደኛ መዝባሪዎችን ጭምር ማካተት እንደሚኖርበት ለዚኽም በግንባር ቀደምነት እንደሚሰለፉ ተናግረዋል፤ ምእመኑ በየአጥቢያው ምዝበራን ለመዋጋት ከአማሳኞች ጋራ የሚፈጥረውን ግጭት ለመፍታት በሚል እንደፈሊጥ የተያዘው ያለተጠያቂነት የማዘዋወር አሠራርም መታረም እንዳለበት አሳስበዋል – ‹‹ሌላውስ ደብር ቤተ ክርስቲያን አይደለም ወይ? ለዘራፊዎች ለምን ተጨማሪ ዕድል ይሰጣቸዋል?›› በማለትም ይጠይቃሉ፡፡

St. Urael parish head row00ካህናቱ፣ የጽ/ቤት ሠራተኞቹና ምእመናኑ በዛሬው የእሑድ ሰንበት ረፋድ ተቃውሞው የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በሚፃረረው የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ደብዳቤ መነሻነት በተላለፈላቸው ሕገ ወጥ የዝውውር ትእዛዝ ማልደው የመጡትን አረጋዊውን የሳሪስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባትነት አክብሮ ነገር ግን መመደባቸውን ሳይቀበል በጨዋነት መልሷቸዋል፤ የሚከተለውን ማሳሰቢያም ከዐውደ ምሕረቱ ተሰጥቷል – ‹‹ጥያቄአችን ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር የሚል እንጂ የአንድ አለቃ መነሣት አይደለም፤ እርስዎን አባታችንን እናከብርዎታለን፤ ጥያቄአችን በአግባቡ እስኪመለስ ድረስ ግን እንዳይመጡ፡፡››

ከቁጥሩ ብዛት ጋራ መንፈሳዊነትና ሰላማዊነት የታየበት የአገልጋዩና ምእመናኑ የተቀናጀ የተቃውሞ ሥርዓት በደብሩ የተገኙትን ስቭል ለባሽ የጸጥታ ሰዎችና የፖሊስ ኃይሎች ጭምር ያስደመመ ነበር፡፡ ይኹንና ዘግይተው የደረሱ በቁጥር እስከ አርባ የሚገመቱ የፌዴራል ፖሊሶች ሦስቱንም የቤተ ክርስቲያኑን በሮች በመዝጋት ዙሪያውን ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርጉ የክ/ከተማው ኮማንደር ናቸው በተባሉና በደብሩ ውስጥ በስቭል ልብስ በቆዩ አዛዥ ትእዛዝ እንዲመለሱ መደረጋቸው ታውቋል፡፡

በፓትርያርኩ የተመደቡት አስተዳዳሪ በመጡበት አኳኋን ተቀባይ ሳያገኙ መመለሳቸውን ተከትሎ ከሠርሆተ ሕዝብ ከተደረገ በኋላ ሰባት ያህል ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የጽ/ቤት ሠራተኞች፣ የሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእመናን ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ካራማራ ንኡስ ፖሊስ ጣቢያ ተጠርተው መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡

ለሰላም ሲባል አስተዳዳሪው ለዛሬው አቀባበል ከመሔዳቸው በፊት ከሰበካ ጉባኤው ጋራ አስቀድሞ መነጋገርና መግባባት እንደሚጠበቅባቸው ትላንት ማምሻውን ከፖሊስ ማሳሳቢያ ደርሷቸው እንደነበር በንግግሩ ተጠቅሷል፤ የዝውውር ውሳኔው በፓትርያርኩ እንደታዘዘ በመጥቀስ አስተዳዳሪውን እንዲቀበሉ ለማድረግ ከፖሊስ በኩል የተደረገው ሙከራ ግን ትእዛዙ አግባብነት እንደሌለው በሚገልጽና እንቅስቃሴው ተገቢ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ መንፈሳዊነቱንና ሰላማዊነቱን ጠብቆ እንደሚቀጥል በሚያመለክት ማብራሪያ ምላሽ እንደተሰጠበት ታውቋል፡፡


ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ጁላይ 06, 2014

Sunday, July 6th, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ከግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና የመጀመሪያ እርከን ተግባሪዊ የትግል ጥሪ

Sunday, July 6th, 2014

ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!

በየጊዜው እየከረረና እየመረረ የመጣው ትግላችን “ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ወደ ተባለ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ይህ ጽሁፍ የዚህን የትግል ምዕራፍ ምንነትና ይዘት በአጭሩ ያብራራል። በዚህ ጽሁፍ ላይ የሰፈሩት ዓረፍተ ነገሮች ተነበው የሚታለፉ ሳይሆን በተግባር የሚተረጎሙ ሥራዎች ናቸው።

አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ምን ማለት ነው? አንዳርጋቸው ጽጌ ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለእኩልነት በጀግንነት የቆመ፤ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ሲከፍል የነበረና አሁንም እየከፈለ ያለ መሪያችን ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ልክ እንደሱ ትሁት ሆኖም ግን ቆራጥ፤ ሆደ ሰፊ በዚያው ልክ ደግሞ መራር፤ አስተዋይና ብልህ ሆኖም ተግባር ተኮር መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ወያኔን ለማስወገድ መደረግ የሚገባውን እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ ሰው መሆን ማለት ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ለአገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለት ነው።

ወያኔ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ካተኮረባቸው ምክንያቶች አንዱ የወያኔን የዘር ፓለቲካና ፕሮፖጋንዳ በሚያመክን መልኩ በተግባር ትግል ውስጥ ካሉ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ እና ሌሎች ዘውግ ተኮር ድርጅቶች ጋር ንቅናቄዓችን ተግባራዊ ትብብር ማድረግ የሚችሉበት ደረጃ ድረስ ማቀራረብ የቻለ መሪ መሆኑ ነው። ከሁሉም በላይ ለወያኔ የጉሮሮ ቁስል የሆነበት ደግሞ ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ጋር ግንቦት 7 የፈጠረው ጠንካራ ትብብር ነው። በትህዴን ጋር በመሆን አቶ አንዳርጋቸው ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ጀርባ መንጠልጠል እንዳይችል አድርጎታል። እናም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት ከዘረኝነት ፀድቶ መገኘት ማለትም ጭምር ነው። አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ማለት በኢትዮጵያዊያን እኩልነት እና እኩል ባለመብትነት ከልብ ማመን እና ለእኩልነት በጽናት መታገል ማለት ነው።

አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን የግድ የግንቦት 7 አባል መሆንን አይጠየቅም። አንዳርጋቸው ጽጌን ለመሆን ለመልካም ዓላማዎች መሳካት ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀትን እንጂ የግድ ከአንድ ወይም ከሌላ ድርጅት ጋር መወገንን አይሻም። ያም ሆኖ ግን አንዳርጋቸው ጽጌን የሆነ ሰው በጠንካራ ድርጅት የታገዘ ትግል አስፈላጊነት ይረዳል።

በመጨረሻም አንዳርጋቸው ጽጌን መሆን ኦኪሎ ኦኴኝ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ እና እዚህ ዘርዝረን ልንጨርሳቸው የማንችላቸው ጀግኖቻችንን ሁሉ መሆን ማለት ነው።
የ“ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን” ዘመቻ ትኩረቶችን በየጊዜው የምንገልጽ ሲሆን ከነገ ጀምሮ በሥራ ላይ መዋል ያለበት የዓለም ዓቀፍ ዘመቻው የመጀመሪያ እርከን ትኩረቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።
የዘመቻው የመጀመሪያው እርከን ትኩረቶች

ይህ የመጀመሪያ እርከን ሶስት ቦታዎች ላይ ያተኩራል፡- የመን፣ ብርታኒያ እና ወያኔ

የመንን በተመለከተ

የየመን መንግሥት የዓለም ዓቀፍ ህግም ሆነ የየመን የራሷን ህግ በመተላለፍ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል። ከመጀመሪያው ጀምሮ ለየመን መንግሥት የተደረገው ተማጽኖ ሰሚ ጆሮ አላገኘም። እስካሁንም ድረስ የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸውን ማሠሩንና ለወያኔ አሳልፎ መስጠቱን በይፋ አላመነም። እኛ ባለን መረጃ መሠረት በአይሮፕላን ማረፊያው ከማገት ጀምሮ በልዩ በረራ ወደ ኢትዮጵያ እስከ መላክ ድረስ ያለውን የውንብድና ሥራ በየመን በኩል ሆኖ የሠራው ቀጥታ ተጠሪነቱ ለየመን ፕሬዚዳንት የሆነው የስለላ ድርጅት ነው። በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ሊቀለበስ የማይችል እና በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል። የየመን መንግሥትና ሕዝብ ይህን እንዲያውቁት ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው የተግባር እንቅስቃሴ አካል ነው።

የመንን በተመለከተ የሚቀጥለው ሳምንት ዘመቻችን ግብ ቁጣችንን የየመን ፕሬዚዳንት እና የየመን መንግሥት ብቻ ሳይሆን የየመን ሕዝብም እንዲያውቅ ማድረግ ነው። የሚከተሉት ተግባራት ለአብነት ያህል ተጠቅሰዋል።

1.ለየመን ፕሬዚዳንት አዲስ መረር ያለ ደብዳቤ ተጽፎ በፋክስና በኢሜል በየመን መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶችና ኤምባሲዎች አድራሻዎች መላክ። በመልዕክት መጨናነቅ ከሚገባቸው የየመን ተቋማት አንዱ አዲስ አበባ የሚገኘው የየመን ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆናችሁ በዘመቻው የምትሳተፉ ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ እናሳስባለን፤ የኢንተርኔትና የፋክስ መልክቶችን ስትልኩ ራስን ለጉዳት በማያጋልጥ መንገድ መደረግ ይኖርበታል።

2.የየመን ኤምባሲዎችን ሥራ ማወክ በሚችሉ ሰልፎችና ተቃውሞዎች ማጨናነቅ። የፕሬዚዳንቱን ፎቶና የአገሪቱን ባንዲራ ማቃጠል። ይህ በውጭ አገራት ብቻ መደረግ ያለበት ነው።

3.በውጭ አገራት በየከተሞች ለሚገኙ የየመን ኮሚኒቲዎች ደብዳቤ መፃፍና መንግሥታቸውን እንዲቃወሙ መገፋፋት፤ ይህንን ካላደረጉ ግን ከመንግሥታቸው ጎን ተሰልፈው በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እንዳወጁ የምንቆጥረው መሆኑን በማያሻማ መንገድ መንገር፤

4.በየመን አየር መንገድና በማናቸው የየመን የንግድ ድርጅቶችና ቢዝነሶች ላይ እቀባ ማድረግ፤ በቢዝነሶቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ። ይህ ተግባር በኢትዮጵያም ከኢትዮጵያ ውጭም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መተግበር የሚኖርበት አቢይ ተግባር ነው።

5.በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የየመን ቢዝነሶችን መርጦ ምርቶቻቸው እና አገልግሎቶቻቸው እንዲጠሉ ማድረግ። ከእንግዲህ በየመን ገንዘብ የተሠራ ወይም ከየመን የመጣ ብስኩትም ይሁን ሲጃራ የወገናች ደም የነካው እቃ ነው።

ብርታኒያን በተመለከተ

የእንግሊዝ መንግሥት ማድረግ የነበረበትን እና ማድረግ ይችል የነበረውን ሁሉ አድርጓል ብለን አናምንም። እርምጃው ፈጣን አልነበረም፤ አሁንም አይደለም።
ስለሆነም እንግሊዝን በተመለከተ የዘመቻችን ግብ የእንግሊዝ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት በመንፈጉ መክሰስ እና ከአሁን በኋላም ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለውና መሪያችን እንዲያስፈታ መወትወት ነው። የሚከተሉት ተግባራት ለአብነት ተዘርዝረዋል።

1.የእንግሊዝ መንግሥትን በህግ መክሰስ (ይህ በንቅናቄው ጽ/ቤት የሚሠራ ሲሆን ዝርዝሩ ወደፊት ይገለፃል)፤

2.ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ደብዳቤ ጽፎ በፋክስና በኢሜል ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ለኤምባሲዎች በብዛት መላክ። አንዱ ትኩረት የሚደረግበት ኤምባሲ አዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በዘመቻው የሚሳተፉ ወገኖች አስፈላጊው ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

3.በለንደን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደጃፍ፤ በሌሎች አገሮች ደግሞ በእንግሊዝ ኤምባሲዎች ቁጣ የተቀላቀለበት የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄድ።

ወያኔን በተመለከተ

ወያኔን በተመለከተ የሚደረጉ ትግሎች በሙሉ ወያኔን ከስልጣን በማስወገድ ላይ ያነጣጠሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ወያኔን ለመጣል ትልቁን ድርሻ የሚያበረክተው ሕይወታቸውን ለመስጠት የቆረጡ፡ ከቁም ውርደትና ባርነት ለነጻነትና ለፍትህ ከወያኔ ጋር ጉረሮ ለጉረሮ እየተናነቁ እየጣሉ ለመውደቅ ፤ መስዋእት ለመሆን በወሰኑ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንና የህዝብ ሃይሎች የሚያደርጉት ተግባራዊ እንቅስቅሴ ነው ፤ እንቀላቀላቸው።
በተለያዩ ምክንያቶች ወሳኙን ትግል መቀላቀል የማይችሉ ወገኖቻችን በያሉበት ሆነው ከወያኔ የስለላ መረብ ተጠነቅቀው ራሳቸውን በቡድን ያደራጁ፤ ይህንኑ የሚያግዙ ተግባራት ለመፈጸም ራሳቸውን ያዘጋጁ። እነዚህ ተግባራት ወያኔን በገቡበት እየገቡ በማሳፈር ፤እረፍት በመንሳት፤ የፈፀሟቸውን ወንጀሎች በአደባባይ በመናገር እንዲሸማቀቁ በማድረግ፤ ማንነታቸው ለሸሪኮቻቸው ወይም ለሥራ ባልደረቦቻቸው በመንገር ወዳጅ በማሳጣት፣ ንግዶቻቸውን ኩባንያዎቻቸው እንዲከስሩ በማድረግ የፋናንስ አቅማቸው በማዳከም ረገድ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ቀላል እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ከዚህ አኳያ ሊደረጉ ከሚገቡ ተግባራት የሚከተሉት በምሳሌነት ተዘርዝረዋል።

1.በምዕራቡ ዓለም በተለያዩ ሽፋኖች ተሰግስገው ያሉት እና የሚመላለሱ ወንጀለኞች የወያኔ ሹማምንትና ደጋፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ መደራጀትና እንደየሀገሩ ሁኔታ አግባብ ያላቸውን የህግ መሳሪያዎች መጠቀም፤

2.በመላው ዓለም የወያኔ ኤምባሲዎችና የኮንሱላር ጽ/ቤቶች ሥራ መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ መፍጠር፤

3.በመላው ዓለም የወያኔ አባላትና ደጋፊዎችን ከያሉበት (ከሰፈር፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በንግድ የተሰማሩ ..) በማደን ማስነወር፣ ማግለል፣ ማዋረድ፤ ከእነሱ ጋር አንዳችም የንግድም ፡ የሥራ ፤ የማኅበራዊ ትብብርና ግንኙነት አለማድረግ፤ ፊት መንሳት ፤ በሥራዎቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳዎችን ማካሄድ። የወያኔ አባላትንና ደጋፊዎችን በሁሉም ዓይነት ግንኙት ማግለል፡ አለመተባበር በኢትዮጵያም ውስጥ በስፋት በሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል።

4.በማናቸውም የዓለም ክፍል ለሥራ ወይም ለሽርሽር የሚዘዋወሩ ከፍተኛ የወያኔ ሲቪል፣ የወታደራዊና የደህነት ባለሥልጣኖችና የጦር መኮንኖችን እየተከታተሉ ማሸማቀቅ፣ ማስነወር፣ መውጫ መግቢያ ማሳጣት፤ በየትኛውም የዓለም ክፍል ተቀባይነት እንደሌላቸው በሕዝብ ላይ ለፈጸሙት ወንጀሎች ሁሉ የሕዝብ ቁጣ ዒላማ እንዲሆኑ እንደልባቸው መፏላል እንዳይችሉ ማድረግ። በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝብ ራሱ በቡድን አደራጅቶ ለወያኔ ታጣቂዎች ጥቃት ሳያጋልጡ አድብቶና አስልቶ ተመሳሳይ ድርጊቶች መፈፀም

5.የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በወያኔ አገዛዝ የሚመሩ እንዲሁም በወያኔ ኤፈርት ስር ያሉ ኩባንያዎች፤ቢዝነሶች ላይ እቅባ ማድረግ፤ የሸቀጥና የአገልግሎታቸው ተጠቃሚ አለመሆን፤ በእነሱ ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ፤ በልዩ ልዩ መንገዶች ሥራቸውን ማጨናገፍ ማደናቀፍ፤ አሻጥሮችን በተደራጀ መልክ፣ በጥናትና በብልሃት ተግባራዊ ማድረግ። ይህ በኢትዮጵያም በመላው ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተግባሪዊ መደረግ ይኖርበታል።

6.በዌስተር ዩኒየን፣ በመኒ ግራም እንዲሁም በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ በወያኔ ደጋፊዎች በመሠርቷቸው ልዩ ልዩ የገንዘብ ላኪ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ አለመላክ፤ በየአካባቢው አማራጭ የገንዘብ መላኪያ መንገዶችን መፈለግ፤ እነዚህ በሌሉባቸው አካባቢዎች የፈጠራ ችሎታን በመጠቀም ገንዘብ ለዘመድ አዝማድ በወያኔ በኩል ሳይላክ የሚደርስበትን ሁኔታ መፍጠር፤ የወያኔን የፋሽታዊ አገዛዝ አንዱና ዋነኛ ምሰሶ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ የማድረቂያ ዘዴዎችን ሁሉ በመፈለግ ተግባሪዊ በማድርግ የወያኔን በዘረኝነትና በዘረፋ የተገነባ የገንዘብና የኢኮኖሚ አቅም ማዳከም፤ መቦርቦር፤ መናድ።

7.ከወያኔ ጋር የሚሠሩ የውጭ አገር ድርጅቶች ከወያኔ ጋር ያ ያላቸውን ሽርክና እንዲያቋርጡ መወትወት፤ አልሰማ ካሉ በቢዝነሳቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማካሄድ። (የእነዚህን ዝርዝሮች በተከታታይ ይገልጻሉ)

8.የምዕራብ አገራት ዩኒቨርስቲዎች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እንዲመረምሩ ማሳሰብ። በተለይ ደግሞ ሳያስተምሩ ለወያኔ ሹማምንቶች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማስጠንቀቅ፤ ተግባሮቻቸውን ለተማሪዎቻቸው ጭምር መንገር (ለምሳሌ University of Greenwich ከ International Leadership Institute ጋር ያለውን ግኑኝነት እንዲሰርዝ፣ እስከዛሬ የሰጣቸውንም የማስትሬት ዲግሪዎች እንዲመረመር የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፎ በብዛት በፋክስ መላክ፤ ተመሳሳይ ደብዳቤ Open University እና ከወያኔ ጋር ተሻርከው ለሚሠሩ ዩኒቨርስቲና ኮሌጆች መላክ)

9.ይህ ዘመቻ ለጊዜው በወያኔ ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም፣ የሕዝቡን የነፃነትና የፍትህ ጥረት የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ዜጎች በሆኑ ቱጆሮችና ከወያኔ ጋር የተያያዙ የንግድ ቤቶችና ኩባንያዎች የዘመቻው ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ። (ዝርዝራቸውን በተከታታይ እናወጣለን)

በመጨረሻም የወጣቱ የማያልቅ የፈጠራ ችሎታ ከላይ በዝርዝሩ ውስጥ ያልተካተቱ ሆኖም ግን ውጤታማ የሆኑ የተቃውሞ መግለጫ ዘዴዎች ያፈልቃል ብለን እናምናለን። ስለሆነም ዘመቻውን በየአካባቢው በሚገኝ ሀሳብና ፈጠራ ማዳበር ይቻላል። ይህ ዘመቻ ወያኔ ከስልጣን እስኪባረር ድረስ በየጊዜ እየከረረ መሄድ እንዳለበት ታሳቢ አድርጎ መነሳት ይኖርበታል። ስለሆነም በየጊዜው አዳዲስ ነጥቦችን ተግባሪዊ የትግል ስልቶችን እንጨምራለን።
ለመላው የአትዮጵያ ሕዝብ፣ በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሁሉ፣ ለሁሉም የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ሁሉ በኅብረት በጋራ ሆነን፤ ትከሻ ገጥመን ለተግባሪዊ ትግል በቁርጠኝነት እንድንነሳ ጥሪያችንን እናቀርባለን ።

ይህ ዘመቻ ወያኔን ከስልጣን ለማባረር ምድር ላይ ከምናደርገው የመረረ ትግል ጋር ሲቀናጅ የሚፈለገውን ውጤት ስለሚያስገኝ ለነፃነቱ ግድ ያለው ዜጋ ሁሉ በሙሉ ኃይሉና አቅሙ ተሳትፎ እንዲያደርግ ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገራዊ ጥሪ ያቀርባል።

በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ የመንግሥት ተቋማትና ተግዳሮቶቹ

Sunday, July 6th, 2014
የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን መሠረተ ልማት ዘርግቶ በአቅድ መንቀሳቀስ የሚፈለግና የተለመደም ጉዳይ ቢሆንም፣ የሚሠምረውም ሆነ ውጤታማ ሆኖ መገኘት የሚቻለው ፣ ሥራ በየረድፉ በሙያ በሰለጠ የሰው ጉልበት በተቀላጠፈ ሁኔታ ሲከናወን ነው።

ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ጁላይ 05, 2014

Saturday, July 5th, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

UTC 16:00 የዓለም ዜና 05.07.2014

Saturday, July 5th, 2014
የዓለም ዜና

ሙርሲ የተወገዱበት 1ኛ ዓመት

Saturday, July 5th, 2014
በግብፅ የሙሥሊም ወንድማማችነት ማህበር የቀድሞው ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ ከሥልጣን የተወገዱበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ግዙፍ ተቃውሞ ተካሄደ። የሴቶች ዓለም አቀፍ የምክር ቤት መድረክ አባላት ሴቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚያጋጥማቸው የፀጥታ ችግር አንፃር ጠንካራ ርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አስተላለፈ።

የግብፅን ያስደነገጠዉ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

Saturday, July 5th, 2014
የግብፅ መንግሥት በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሬ አደረገ። የሀገሪቱ የዜና አገልግሎት አል- አህራም እንደዘገበው ግብፃዉያን ከዛሬ ጀምሮ በየነዳጅ ማድያው ከ40 እስከ በ80 መቶ ጭማሪ ገንዘብ በማዉጣት ነዳጅ ይሸምታሉ።

አዜብ መስፍን በጠና ታመዋል፤ የአባዱላ ልጅ ሞተ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

Saturday, July 5th, 2014

ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ ከፖለቲካው መድረክ እየተገለሉ የመጡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በጠና መታመማቸውን ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። በስኳር ህመምና በደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት አዜብ መስፍን የሰውነት ክብደታቸው እንደቀነሰና የመጎሳቆል ሁኔታ በገጽታቸው እንደሚታይ የጠቆሙት ምንጮቹ ለስኳር በሽታ በየእለቱ ከሚወስዱት መድሃኒት በተጨማሪ ለደም ግፊትም እንክብሎችን እንደሚወስዱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። አዜብ በመኖሪያቸው አብዛኛውን ቀናት እንደሚያሳልፉ የጠቆሙት ምንጮቹ በፖለቲካው የደረሰባቸው ኪሳራ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸውና ለበሽታ እንደዳረጋቸው አያይዘው ገለጸዋል።

ቦሌ ከሳይ ኬክ ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኘውና አቶ ስዩም መስፍን ለ19ዓመት የኖሩበት እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር ለሁለት አመት የኖሩበት መኖሪያ ቪላ ውስጥ የሚኖሩት አዜብ መስፍን ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ላይ የሚገኘውን የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ለአዜብ በቢሮ መልክ እንደተሰጣቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ቀን ቀን በዚህ ቢሮ ለብቻቸው ያሳልፉ የነበሩት አዜብ መስፍን በጠና ከታመሙ ወዲህ ላለፉት አምስት ሳምንታት ወደዚህ ቢሮ ገብተው እንደማያውቁና በቤታቸው እንደሚያሳልፉ ያስታወቁት ምንጮቹ አክለውም ፓርቲው በሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች መገኘት እንዳቆሙና ለመጨረሻ ጊዜ የተገኙት ከሁለት ወር በፊት ኢህአዴግ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በዚሁ ጉባኤ ከተሰብሳቢው ኋላ ለብቻቸው ተቀምጠው የታዩት አዜብ ምንም ሳይናገሩና አስተያየት ሳይሰጡ ስብሰባውን ከመጨረሳቸው ባሻገር ከስተውና ተጐሳቁለው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰው ከዚያ ወዲህ ህመሙ እየጠናባቸው እንደሄደ አያይዘው ገለፀዋል። አዜብ የባለቤታቸውን ቦታ በመተካት የጠ/ሚ/ርነቱንና ፓርቲውን የመምራት እቅድና ምኞት በተቀናቃኛቸው ስብሃት ነጋ ከከሸፈባቸውና የሚተማመኑባቸው የደህንነት ባለስልጣናትና የፓርቲው ቁልፍ ሰዎች እስር ቤት መወርወርና መባበረር ለከፍተኛ የሞራል ድቀትና ለበሽታ እንደዳረጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል።

አዜብ የኤፈርት ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ተብለው ቢሰየሙም ምንም አይነት የአመራር ሚና እንደሌላቸው የጠቆሙት ምንጮቹ በነስብሃት ተመድበው ተቋሙን ሲመሩ የቆዩት አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ወደ ራዲዮና ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ እንደሆኑና ከርሳቸው በኋላ ደግሞ የአርከበ እቁባይ ታናሽ ወንድም ጌታቸው እቁባይ እየመሩት መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል። ከአዜብ ጋር በተፈጠረ ያለመግባባት ከኤፈርት ለቀው የቆዩት ጌታቸው እቁባይ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ እንዲመለሱ መደረጉን አመልክተዋል። አዜብ ወደ ትግራይ -መቀሌ ከተጓዙ 6 ወር እንዳለፋቸው አክለዋል። በኤፈርት ውስጥ የአዜብ ደጋፊዎች በነስብሃት ተለቅመው መውጣታቸውን ያስታወሱት ምንጮቹ በቅርቡ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር የሚለውን የአዜብ ስልጣን በመግፈፍ ሊያባርሯቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። …ይህ በእንዲህ እንዳለ የአባዱላ ገመዳ ልጅ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ ከዚህ አለም በሞት እንደተለየ ታውቋል። የ26 አመቱ ወጣት ኮሚያስ አባዱላ በጉበት በሽታ ምክንያት ወደ ታይላንድ- ባንኮክ ተልኮ ለአንድ አመት ሲታከም ከቆየ በኋላ ሊድን ባለመቻሉ ከአራት ሳምንት በፊት ህይወቱ አልፏል። በባንኮክ ለአንድ አመት የሆስፒታል ቆይታው ለህክምና ብቻ ከ880ሺህ ዶላር ወጪ እንደተረገለት ታውቋል።

በተመሰሳሳይ ሶስተኛ ታናሽ እህቱ (የአባዱላና ራሄል ልጅ) ከአምስት አመት በፊት በገጠማት የሳንባ፣ የአንጀትና የአእምሮ በሽታ በባንኮክ ሆ/ል ለሁለት አመት ህክምና የተከታተለች ሲሆን፣ ለህክምናው ጠቅላላ የወጣው 2.5ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ከዚህ ቀደም ይፋ በተረገው መረጃ መገለፁ ይታወሳል። ይህ ሁሉ ገንዘብ ከህዝብ የተዘረፈ ለመሆኑ አያጠያይቅም። ይህቺ ናት አገሬ! ..ለማንኛውም የአባዱላ ወንጀል ልጁን አይመለከተውም። ወጣት ኮሚያስ በአባቱ ድርጊት ነፃናነት ስለማይሰማው – በየእለቱ አልኮል ይጠጣና ይበሳጭ እንደነበረ ቅርብ የሆኑ ጓደኞቹ ተናግረዋል። የጉበት በሽታውም መንስኤ ይኸው ነው። ነፍስ ይማር!

የነፃነት ትግልን እስር እገታና ግድያ ከቶውንም ሊገታው አይችልም ዳኛቸው ቢያድግልኝ

Friday, July 4th, 2014

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

አቶ አንዳርጋቸው “ለኢትዮጵያ መንግሥት ተሰጡ” ሲል ግንቦት ሰባት አስታወቀ

Friday, July 4th, 2014
የየመን መንግሥት የግንቦት ሰባትን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷል ሲል ግንቦት ሰባት አስታውቋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው “ለኢትዮጵያ መንግሥት ተሰጡ” ሲል ግንቦት ሰባት አስታወቀ – ጁላይ 04, 2014

Friday, July 4th, 2014
Andargachew extradited to Ethiopia, Ginbot7 says

የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተላልፈው መሰጠታቸውን ተከትሎ ግንቦት 7 የክተት አዋጅ አወጀ

Friday, July 4th, 2014

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ፣ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ባወጣው መግለጫ ፣ “የየመን መንግሥት በህገወጥ መንገድ ያገተብንን የንቅናቀዓችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ” ብሎአል።

“የአገሩን የረዥም ጊዜ ጥቅም ማየት የተሳነው የየመን መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ አምባገኑን ወያኔ መርጦ መሪያችንን ለእርድ አሳልፎ ሰጥቶብናል ፣በዚህም ሳቢያ የየመን መንግሥት ይቅርታ የማያሰጥ ፤ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል” ሲል ግንቦት 7 አስታውቋል።

” የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወዳጅ ጎረቤት ትሁትና ቀና ቢሆንም ጥቃት በሚያደርስበት የቅርብም ሆነ የሩቅ ጎረቤት ላይ ግን ቁጣውን የሚመጥን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ያውቅበታል።” በማለት የሚዘረዝረው የግንቦት 7 መግለጫ፣ “የወያኔ ፋሽስቶች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማሰቃየት ትግላችንን ማቀዝቀዝ እንደማይችሉ ልናረጋግጥላቸው እንወዳለን ።”ብሎአል።
“ወያኔ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በውንብድና ጠልፎ መውሰዱ የትግሉን ሜዳ አስፍቶታል ፤ የትግሉንም ዓይነት አብዝቶታል ። ይህ ደግሞ የወያኔ ፋሽስቶችን ከፍ ያለ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ።” በማለት ድርጅቱ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።
“የፓለቲካ ልዩነት አጥር ሆኖ ሳይከልላችሁ ከገናችን ለቆማችሁት የሲቪክ ማኅበራትና ዜጎች ሁሉ በወገናዊ
ተግባራችሁ ልባችን ተነክቷ ልያለው ግንቦት 7 ፣ ከዚህ በላይ ደግሞ ለቀጣዩ ወሳኝ ፍልሚያም እንደምንቆም እና የወያኔን እድሜ እንደምናሳጥር እምነታችን አጠንክሮልናል” ሲል አክሎአል።
መግለጫው ” ከዛሬ ጀምሮ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳርጋቸውጽጌን ሆኗል” ካለ በሁዋላ፣በአቶ
አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ለደረሰውና ለሚደርሰው ጥቃት እያንዳንዱ የወያኔ ሹም በግል ዋጋ እንደሚከፍል ፣ ሕዝብ ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው ራሱ ወያኔ መሆኑን እንዲሁም በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስር የክተት አዋጅ መታወጁን በመጥቀስ” ህዝቡ ለጥሪው መልስ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የአቶ አንዳርጋቸውን መያዝና ተላልፎ መሰጠት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው

Friday, July 4th, 2014

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዲት እናት ” እኔ ሁለት ልጆች አሉኝ፣  ልጆቼን ዛሬ ብሰጥ ደስ ይለኛል” ሲሉ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ የተሰማቸውን ስሜት በለቅሶ ገልጸዋል።

አንድ ወጣት ደግሞ እርሱና ጓደኞቹ በአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ወደ ትግል ፈጥነው እንዲገቡ እንደሚያደርጋቸው ገልጸዋል።

“ቀድሞ ዘርዘሩን ዘርቷል” በሚል ቅኔ የተቀኙት አንድ ኢትዮጵያ ደግሞ በአንዳርጋቸው መስዋትነት፣ ነጻነታችንን እውን እናደርጋለን ብለዋል

ሌላ ወጣት ደግሞ ” እርሱ ይህን ያክል መስዋትነት ከከፈለ እኛም እሱ የከፈለውን መስዋትነት መክፈል አለብን” ሲል ለመታገል መቁረጡን ገልጿል።

የየመን መንግስት አንዳርጋቸውን አሳልፋ በመስጠቷ ሰውነቴ በፍርሃት ሳይሆን በቁጭት እየተንቀጠቀጠ ነው የሚሉት አንድ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ “እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” ብሎ መነሳት እንዳለበት ገልጸዋል።

ህዝቡ የሚሰጠውን አስተያየት በአድማጮች አስተያየት ክፍለ ጊዜ እናቀርባለን።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ።

Friday, July 4th, 2014

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአንዋር መስጊድ እጅግ በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በተካሄደው ተቃውሞ ፣ መንግስት “መጅሊሱን ለህዘበ ሙስሊሙ እንዲያስረክብ እንዲሁም የታሰሩትን መሪዎች እንዲፈታ” ጠይቀዋል።

“ትግሉ የጽኑዎች ነው፣ ፍትህ ይስፈን፣ የእምነት ቤቶቻችን ይከበሩ፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ የትግላችንን መነሻ እናሳካው የማነፍርበት የትግል መዳረሻችን ነው፣ አፈና ግፍና ማስገደድ ይቁም” የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።

ሙስሊሙ ኢትዮጵያውያን በረመዳን ጾም መግቢያ ጀምሮ ጠንካራ ተቃውሞዎችን እየሰማ ነው።

በሸኮና መዠንገር በተነሳው ግጭት አንድ የልዩ ሃይል አዣዝ ተገድሏል።

Friday, July 4th, 2014

ሰኔ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በርካታ የሌሎች አካባቢ ሰዎች ተፈናቅለው፣ በቴፒ ከተማ ኤግዢቢሽን አዳራሽ ሰፍረዋል። ሰፋሪዎች በምግብ እና በውሃ ችግር ለአደጋ መጋለጣቸው ታውቋል። እስካሁን ከ700 ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ግጭቱ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ ከቁጥጥር ውጭ መውጣቱ ተነግሯል። ልዩ ፖሊስና የወረዳው ፖሊስ፣ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቁት የሸኮና መዠንገር ተዋጊዎች ጋር እየተዋጋ መሆኑ ታውቋል።

ሸኮና መዠንገር መሬታቸው ጻኑ ቀበሌ ለደቡብ ክልል መሰጠቱን ይቃወማሉ ። ባለስልጣኖች ግጭቱ ከአቅማችን በላይ ነውና ለቃችሁ ውጡ እያሉ በአካባቢው ላሉ ሰዎች እየተናገሩ ነው።

 

 

ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ጁላይ 04, 2014

Friday, July 4th, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

አፍሪቃ እና ሶፍትዌር

Friday, July 4th, 2014
በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በኢንተርኔት አማካይነት በቀላሉ የሚገኙ መረጃ እና አገልግሎቶችን ተጠቅሞ እውቀትን እንዴት ማዳበር ይቻላል የሚሉ ጥያቄዎች ከሰኞ እስከ እሮብ በቆየው እና ዶይቸ ቬለ ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን መድረክ የተነሱ ጥያቄዎች ናቸው።

የወለኔ ህዝቦች ጥያቄና አቤቱታ

Friday, July 4th, 2014
ፓርቲው በቅርቡ በሰጠው መግለጫ በአባላቱና በአመራር አካላት እንዲሁም በደጋፊዎቹ ላይ የመብት ጥሰት መፈፀሙንና ኢ ህገ መንግሥታዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውንም አስታውቋል ።

አመፅና ብቀላ በእስራኤል

Friday, July 4th, 2014
የእስራኤል ፖሊስ ኢየሩሳሉም ዉስጥ ከፍልስጤም የተቃዉሞ ሰልፈኞች ጋ መጋጨቱ ተሰማ። ፍልስጤማዉያኑ በፅንፈኛ እስራኤላዉያን ሳይገደል እንዳልቀረ በሚገመተዉ ፍልስጤማዊ ታዳጊ ወጣት ቀብር የተሰባሰቡ እንደሆኑ አሶሲየትድ ፕረስ ከስፍራዉ ዘግቧል።

የጀርመንና የቻይና ልዩ ግንኙነት

Friday, July 4th, 2014
የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በያዝነዉ ሳምንት መጨረሻ ቻይናን ይጎበኛሉ። ሜርክል የጀርመን ከፍተኛ የንግድና ባንክ ባለስልጣናትን አስከትለዉ ለአራት ቀናት በቻይና በሚያደርጉት ጉብኝት ከፕሬዝደንት ሺ ቺ ፒንግና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪጂንግ ጋ ይነጋገራሉ።

040714 ዜና 16:00 UTC

Friday, July 4th, 2014

Early Edition – ጁላይ 04, 2014

Friday, July 4th, 2014

የአፍሪቃ ፖለቲካ በጋዜጠኞቿ ዓይን

Friday, July 4th, 2014
ዶይቸ ቬለ በዚህ ሳምንት ያስተናገደው ሰባተኛው የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መድረክ ትናንት ተጠናቀቀ። በጉባዔው ከ100 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ወደ 2,000 የሚጠጉ የመገናኛ ብዙኃን፣ የፖለቲካ እና የኤኮኖሚው

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተላልፈው ተሰጡ

Friday, July 4th, 2014

“የተፈጠረው ሁናቴ እጅግ ቢያሳዝንም ይህንን አለማቀፍ ህግ የሚጥስ አገዛዝ ለመጣል ሁላችንም ቆርጠን እንድንነሳ ያደርጋል” አቶ ነአምን ዘለቀ

 

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. July 3, 2014)፦ ከዱባይ ወደ አስመራ በመጓዝ ላይ የነበሩትና የመን ውስጥ ሰንዓ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራንዚት የወረዱት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እዛው የመን ታግተው ከቆዩ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው መሰጠታቸው ተረጋገጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን እገታ መፍትሄ አላገኘም

Thursday, July 3rd, 2014

ወደ ኢትዮጵያ እንዳይተላለፉ ስጋቱ አይሏል

ኤርትራዊያኖች የየመን አየር መንገድን እንዳይጠቀሙ ማስተባበር ያስፈልጋል አቶ ዳንኤል ጥላሁን (የህግ ባለሙያ)

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. July 3, 2014)፦ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለጉዞ መሸጋገሪያ የመን ከገቡ ጀምሮ በአገሪቱ ደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸውን አስመልክቶ ኢትዮጵያዊያን ቁጣቸውን እያሰሙ ሲሆን በተለይ የየመን አየር መንገድን በመቃወም ኤርትራዊያን የጉዞ ማእቀብ እንዲያደርጉ አንድ ተቀማጭነቱን ካናዳ ያደረገ የህግ ባለሙያ ጥሪ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“አንዳርጋቸውን ልቀቁ” የሚል እንቅስቃሴ እየታየ ነው – ጁላይ 03, 2014

Thursday, July 3rd, 2014
Ethiopia, Andargachew, ginbot7, habesha.net

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል አንዳርጋቸው በአስቸኳይ እንዲለቀቅ አስጠነቀቀ

Thursday, July 3rd, 2014

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጂ አንድ ግለሰብ አይደለም” በሚል ርእስ ባወጣው ጠንካራ መግለጫ ” የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ  ስህተት  መሆኑን  ዘግይቶም ቢሆን  ተረድቶ የነፃነት ታጋዩን እንዲለቅ” አስጠንቅቋል።  ይህ ባይሆን ግን ይላል የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” አንዳርጋቸው ወያኔ እጅ ውስጥ ከገባ  የትውልዱ  የበቀል ሰይፍ ከዛሬ ጀምሮ ከሰገባው መውጣቱን እንዲያውቁት ” ያስፈልጋል።

“ምንም አይነት ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ መነሻምክንያት ለአቶአንዳርጋቸው በየመን መንግሥት መታገት እናመታሰር ምክንያት ሊሆን እንደማይችል ” በመግለጽ ” የየመን መንግሥት የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይእንዲለቅ ላለፉት ተከታታይ ቀናት የተደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤት አለማስገኘቱን ፣ ከዚህም በመነሳት አቶ አንዳርጋቸው ለዘረኛውእና ከፋፋዩየወያኔ ቡድን ሊሰጥይችላል የሚለው ስጋታችን ቀን በገፋእና ምላሽ በራቀ  ቁጥር እየጨመረ ” ሄዷል ብሏል በመግለጫው።

በግንቦት 7ሕዝባዊ ኃይል በኩል የነፃነት ታጋዩ ለወያኔ ተላልፎመሰጠቱን መቶ በመቶእስከምናረጋግጥበት ቅጽበትታጋዩን የማስለቀቅ ጥረቱ መቀጠል እንዳለበት በጽኑ እናምናለንየሚለው ህዝባዊ ሃይሉ፣ “አንዳርጋቸውን ማሰር ይቻላል፤ምናልባትምበዚህ ቅጽበት ተችሏል፤አንዳርጋቸውንማሰቃየትይቻላል፤ምናልባትም በዚህ ቅጽበት ተችሏል፤አንዳርጋቸውን መግደል ይቻላል።

ሞትን ፈርቶ ወደ ትግል አልገባምናአንዳርጋቸውን በማሰር የአንዳርጋቸውን እንደ እቶን የሚያቃጥል የፍትህ፣የነፃነት፣ የዴሞክራሲናየእኩልነት መንፈስ ግን ለሴኮንዶች እንኳን ማሰር አይቻልም፣   አንዳርጋቸውን በማሰቃየትያን ዘመን ተሻጋሪ የሆነ የትውልዱን መንፈስ የሚገዛ የሁላችንም የምትሆን የጋራ ኢትዮጵያን የመፍጠርንጹህ ራዕዩን ግን ፈጽሞማቁሰል አይቻልም!!!

አንዳርጋቸውን በመግደል ዕንቁ ዓላማውን መግደል ከቶ አይቻልም፤ የታሪክ መዛግብት ገጾች ለዚህ ሃቅ በሚመሰክሩ እውነታዎች የተሞላ ነውና” በማለት የሚያትተው መግለጫ፣  አንዳርጋቸውን በመግደል “ከአባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ እንዳልተፈጠረ  ይቆጠራል፣ልጅ አባቱን ሩጦመቅደም አለበት፣ስለዚህ እናንተ ወጣቶች እኛን ሩጡእናብለጡ ቅደሙን፣ቀናዎች ሁኑ፣ርስ በርስ ተዋደዱ፣ያለፉት ትውልዶች የሰሩትን ስህተት ላለመድገም ታሪክን ከስሩ ተረዱ፣ ያለማወቅ ጠንቅ ከሚያመጣው ጥፋት ለመዳን ሁሌም ለእውቀት ጉጉዎች ሁኑ።

ለማወቅ ጣሩ፣የማይቀረው ሞታችሁ ለፍትህ፣ለዴሞክራሲ እና  ለነፃ ኢትዮጵያ ይሁን” እያለ ላለፉት በርካታ አመታትያስተማራቸውእናየኮተኮታቸው የነፃነት ታጋይ አርበኛ  ወጣቶችን እና እሳት መንፈሳቸውን መግደል አይቻልም:” ሲል ያክላል።

“አንዳርጋቸውንበአንድ ካቴናበማሰር፤ በአንድክፍል ውስጥ በመዝጋት ወይም በአንድ ጥይትበመግደል “መገላገል” የሚቻል አንድ ግለሰብ አይደለም::አንዳርጋቸው ለሽህ ካቴናዎች የማይታጠፉ እጆች፤ ለሽህ ማጎሪያዎች የገዘፈ ገላ፤ ለሽህ ጥይቶች የሰፋ እና ሽህ ጥይቶችን የሚተፋ ግንባር እና ደረት ያለው ብርቱ ታጋይ ነው። አንዳርጋቸው አንድ ግለሰብ አይደለም፤ የማይጨበጥ ጽኑ መንፈስ እንጅ!!!” ሲል ለመሪያቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

አንዳርጋቸውይላል መግለጫው በማስከተል ” ለአርባ አመታት በሚጠጋ የፖለቲካ ሕይወቱ ሁሉ በረሃ የሚወረወረው አፈር ላይ የሚንከባለለው፤ በእሱ እድሜ  በማይታሰብ ሁኔታ እንኳን የበረሃ ሃሩር፣ጥም እና ረሃብ የሚያንገላታው ነገ ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት ወይ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስቴርነት ለመምራት ካለው ሰዋዊ ፍላጎት አይደለም::የሱ ምኞት የሁላችንም የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ማየት ነው!!! አንዳርጋቸው ሁሌ ለሚያልማት ንጽህት ኢትዮጵያ መሥራት የነበረበትን ፈታኝ እና ታሪካዊ ሥራዎች  ቀድሞ  አከናውኗቸዋል::ላለፉት 6 እና 7 ዓመታት ከጥልቅ የፖለቲካ  ተሞክሮው እየቀዳ ለወጣት  ኢትዮጵያውያን በየበረሃው እየዞረ አስተምሯል::

እያማጠ አደራ ብሏል::እያለቀሰ ምኞቱን፣ፍላጎቱን እና ራዕዩን ከውስጡ አውጥቶ መዳፉ ላይ በማስቀመጥ ልቡን ለታዳጊዎች አሳይቷል::ንጹህ ዓላማው ሽህ ባለ ራዕዮችን  ፈጥሯል የተግባር ሰዎችን አምርቷል::የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል አንዳርጋቸው እንደመጥምቁ ዮሃነስ በበረሃ  እየዞረ ሲያስተምር እና  ሲሰብክ ከፈጠረው ንጹህ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ላይ የበቀለ ኃይል ነው:: ”

መግለጫው በመጨረሻም ”  ዛሬ አንዳርጋቸው በአካል አብሮን ላይኖር ይችላል::ነፍሳችን ውስጥ ያሰረፀው ዘላለማዊ መንፈስ ግን እስከመጨረሻ ህቅታችን ድረስ አብሮን ይዘልቃል::አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን አቆማለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ ዓለምን እና ሁኔታዎችን መገንዘብ የማይችል ከራሱ የተጣላ የወያኔ አይነት ቂል ብቻ ነው::አንዳርጋቸውን በማስቆም ትግሉን ማስቆም አይቻልም::መንፈስን ማስቆም ከቶ ማን ይቻለዋል??አንዳርጋቸው እኮ መንፈስነው::

ሁሉም ቦታ፣ሁሉም ጫፍ፣ሁሉም ልብ ውስጥ የሚገኝ እና የሚንሳፈፍ መንፈስ::” ካለ በሁዋላ ” የየመን መንግሥት የፈጸመው ድርጊት እጅግ  ስህተት  መሆኑን  ዘግይቶም ቢሆን  ተረድቶ የነፃነት ታጋያችንን ባስቸኳይ ይለቀው ዘንድ አሁንም ደጋግመን እንጠይቃለን::ይህ ሳይሆን ቀርቶ  ታጋያችን ወያኔ  እጅ ውስጥ ከገባ ግን የትውልዱ  የበቀል ሰይፍ ከዛሬ ጀምሮ ከሰገባው መውጣቱን እንዲያውቁት እንፈልጋለን::ወያኔም ይህ የቂል ድርጊት የነፃነት ታጋዮችን የበለጠ ቁጭትእናየበቀልእርምጃዎች ውስጥ የሚከት መሆኑን አብሮ ሊገነዘበው ይገባል::ለዚህ ቃላችን ታሪክ ምስክር  ይሁንብን::” በማለት መግለጫውን አጠቃሏል።

የየመን መንግስት በአተፐ አንዳርጋቸው ዙሪያ እስካሁን የሰጠመው መግለጫ የለም። ኢሳት የተለያዩ የአገሪቱን ባለስልጣናት ለማነጋገር ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የጸጥታ ሃይሎች መታገታቸውን ተከትሎ የሚሰጡት አስተያየቶች ቀጥለዋል

Thursday, July 3rd, 2014

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመላ አገሪቱ የስልክ መልእክቶችን በመደወል ለአቶ አንዳርጋቸው ጀግንነት ድጋፋቸውን የሚገልጹ፣ በእርሱ መታሰር የኢትዮጵያ ህዝብ የተሰማውን ስሜት የሚገልጹና ስለቀጣዩ ህዝባዊ እርምጃ አስተያየቶችን የሚሰጡ በርካታ የስልክ መልእክቶች ለኢሳት እየደረሱ ነው።

“እድሜየ 50ዎቹ አጋማሽ ነው፣ ከስራ ውየ ስገባ የሰማሁት ዜና አስደንግጦኛል፣ ስሜቴን መቆጣጠርም አልቻልኩም፣ ቤተሰቤን ልጆቼን ትቼ ትግሉን ለመቀላቀል ወስኛለሁ” በማለት የተናገሩት አንድ የመንግስት ሰራተኛ፣ የመን አንዳርጋቸውን መፍታት አለባት ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል።

“አንድ ቴውድሮስን ልናጣ ነው፣ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም እግዚዎ በሉ” ያሉ አንድ ሰው፣ የደሴ እና አካባቢው ህዝብ በዜናው መረበሹን እያለቀ ተናገሯል

“የሮመዳንን ጾም በወጉ መጾም አልቻልኩም፣ አባቴ የሞተ ቀን እንኳን እንደዚህ አላዘንኩም” የሚሉት አንዲት ሙስሊም ኢትዮጵያዊ፣ የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ከሰሙበት ጊዜ ጀምሮ “ሲጾም ውለው አናፈጥርም ያሉ ቤተሰቦች” መኖራቸውንም ገልጸዋል።

ሌላ አስተያየት ሰጪ እናት ደግሞ ” እኛ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች እየኖርን፣ ሁኔታው ይቀየራል ብለን አዲስ ተስፋ ስናደረግ ይህ ነገር በመፈጸሙ በጣም እናዝናለን ” ካሉ በሁዋላ፣ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በሚፈጸመው ነገር ሁሉ ዝም ብለው እንደማያዩ አክለዋል።

“የመኖች እንዲያውቁት የምንፈልገው ኢትዮጵያ ውስጥ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅ የሆነ ህዝብ ያለ መሆኑን ነው” በማለት የገለጸው አንድ ወጣት፣ የመን  በአስቸኳይ እንድትለቀው ጠይቋል። “የመን ያደረገቸው ነገር ህዝቡን ይበልጥ ለትግል የሚያነሳሳ ነው” ያሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ ፣ እርሳቸው በሚኖሩበት አካባቢ ያለው የህዝብ ንዴት ከፍተኛ መሆኑን አክለዋል

የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በአቶ አንዳርጋቸው መታገት ዙሪያ መግለጫ እያወጡ ነው

Thursday, July 3rd, 2014

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአፓ የየመን የጸጥታ ሃይሎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የወሰዱትን እርምጃ በጽኑ አውግዞ፣ የአገሪቱ መንግስት በአስቸኳይ እንዲለቀው ጠይቋል።

አንዳርጋቸው በአምባገነኖች ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ተከሶ ሞት የተፈረደበት በመሆኑ፣ ተላልፎ ቢሰጥ ለከፋ ስቃይና ሞት ሊዳረግ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር አደገኛ የሆነ አሰራር የሚፈጥር በመሆኑ ድርጊቱ በጽኑ ሊኮነን ይገባዋል ሲል ኢህአፓ አሳስቧል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ተነስቶ ድርጊቱን ማውገዝና አቶ አንዳርጋቸው ተላልፎ እንዳይሰጥ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ኢህአፓ አክሎ ገልጿል።

ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚደረገው ትግል እንዲህ አይነት አስከፊ እርምጃዎችን በመውሰድ እንደማይቆም ገዢዎች ሊያውቁት ይገባል ሲል መግለጫውን አጠቃሏል።

ሸንጎ ባወጣም መግለጫ ደግሞ አቶ አንዳርጋቸው ተላልፎ ቢሰጥ ከፍተኛ የሆነ ስቃይ ሊደርስበት እንደሚችል አስጠንቅቆ፣ “ይህአሳልፎየመስጠትጉዳይተግባራዊእንዳይሆንምኢትዮጵያውያንየፖለቲካና ሰብአዊመብትድርጅቶችእንዲሁም፣የየመንእናአለምአቀፍሰብአዊመብት ተሟጋቾችአስቸኻይጥረትእንዲያደርጉ”ጥሪአስተላልፏል።

“በሀገራችን ውስጥ ያለውን ውስብስብ ችግር መፍታት የሚቻለው ግለሰቦችን በማገትና በማሳገት ወይንም ሊያባራ በማይችል የአመጽ አዙሪት ውስጥ በመሽከርከር ሳይሆን በሆደ ሰፊነት በብሄራዊ መግባባት እና እርቅ ሁሉንም ሀይሎች አሳታፊ የሆነ ስርአት በመፍጠር ሊሆን እንደሚገባው” ሸንጎ አክሎ ገልጿል።

በመላው አለም የሽብር ጥቃቶች ሊፈጸሙ ይችላል በሚል ጥበቃዎች ተጠናክረዋል

Thursday, July 3rd, 2014

ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው የሽብር ድርጅቶች ጥቃት ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ ለመሆናቸው አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው አመልክቷል።

ይህን ተከትሎም በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ እና በሌሎችም አገራት አየር መንገዶች ላይ የሚታየው ጥበቃ ተጠናክሯል””

ኡጋንዳም በአየር መንገዷ ላይ ሽብር ሊፈጸም ይችላል በሚል ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገች ነው።

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው? (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ-ማርያም)

Thursday, July 3rd, 2014

ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤ በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ በጣም ሰፊ የሆነ ሀተታ በቴዎድሮስ ዘፈኖች ላይ በማቅረባቸው ምን ያህል አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ አግኝተውበት ይሆን ብዬ አነበብሁት፣ ምንም ለአገር የሚጠቅም ጉዳይ አላገኘሁበትም፤ በዘፈኖቹ ላይ በተደረገው ሂስም ከጋዜጠኞቹ መሀከል የሙዚቃ ሙያ ባለቤት እንዳለ ብጠይቅም ጋዜጣው ባለሙያ እንደሌለውና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሙያ ማማከራቸውን ነገሩኝ፣ ስሙ እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣ ባለሙያ አይባልም፣ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ በዚህ በራሱ በማይተማመን ሰው ምስክርነት ላይ በተመሰረተ ረጅም ነቀፌታ ቴዎድሮስን ደበደቡት።

ሁለተኛው የቴዎድሮስ ጣጣ በመኪና ሰው ገጭቷል ተብሎ መከሰሱ ነው፤ በሌሊት፣ በጨለማ ነው፤ ቴዎድሮስ እንደሚለው «እኔ ወደአገሬ የገባሁት ሰውዬው ሞተ በተባለበት ቀን ማግስት እንደሆነ ቪዛዬ ያረጋግጣል፣» (ነጋድራስ መስከረም 30/2001 ዓ.ም. ) በኋላም ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ እንደነበረ ተነግሮአል፤ በዚሁ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ የሚከተሉት መረጃዎች ተጠቅሰዋል ፦

ቴዎድሮስ ከውጭ የተመለሰው በ22/2/1999 ዓ.ም መሆኑ
ሰውዬው በ 22/1/1999 ሞቶ አስከሬኑ በ22/2/1999 ዓ.ም መመርመሩን የጽሑፍ ማስረጃ፣
ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ በሆስፒታሉ የተገለጸው የምርመራ ቀን እንዲለወጥ መጠየቃቸው፣
ከአሥራ ሦስት ቀኖች በኋላ በተደረገ ምርመራ መኪናው ላይ ምንም ደም አለመገኘቱን፣
ይህ ሁሉ ሆኖ በቴዎድሮስ ላይ ተፈርዶበት ወህኒ ወርዶ ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ ቆይቶአል።

ከዚያ ወዲህ ደግሞ በተቀነባበረ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ፣ በመጀመሪያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በደል ከአለ ግልጽ ሆኖ ቢወጣና ሁላችንም ብናውቀው ጥሩ ነው፤ አለዚያ ግን እየተደራጁ አንድ ግለሰብን ለማጥቃት የሚደረገው እርምጃ የሚወገዝና ልንቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነው፣ አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ይህንን ክፋት አምጠው የወለዱትና ለማሳደግ የሚሞክሩት ሰዎች፤ የማሰብ ችግር ያለባቸውና ክፋታቸው ተመልሶ እነሱኑ የሚያጠቃ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ እንኳን የሌላቸው ናቸው።

ሦስተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የበደሌ ቢራ ፋብሪካ በቴዎድሮስ ዘፈን ለመጠቀም ሲፈልግ፣ የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ነው፤ እንደተገነዘብሁት ቴዎድሮስ ትንሽ በቁንጫ ተሰቃየ እንጂ ክፍያው አልቀረበትም፣ ነገር ግን ቴዎድሮስን አንደሰው፣ እንደኢትዮጵያዊ፣ እንደዘፋኝ የሚያውቁት ሰዎች የሉም፤ ወይም በጨለማዎቹ ሰዎች ተሸንፈዋል፤ ወይም በፍርሃት ቆፈን ደንዝዘዋል! የጨለማ ሰዎቹ ቴዎድሮስ ካለበት አንጠጣውም የተባለው ቢራ ለቴዎድሮስ ወዳጆች እንዴት ጣፈጣቸው?

አራተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የመጣው ሦስተኛውን ጥቃት ለመቋቋምና ለማረም ምንም ዓይነት የማረሚያ እርምጃ ስላልተወሰደ ነው፤ የበደሌ ቢራ ኩባንያ እንዳደረገው ሁሉ የኮካኮላ ኩባንያም ቴዎድሮስ ካሣሁንን ለአሻሻጭነት መረጠ፤ የጨለማዎቹም ሰዎች እንደገና ተነሡ፤ ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤ አሁንም ቁንጫው ትንሽ ምቾቱን ከመቀነሱ በስተቀር ቴዎድሮስ ገንዘቡን አላጣም፤ አሁንም የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።

የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው፤ ስለዚህም ቴዎድሮስን እንደሰው እንዳያዩት እዚያ ገና አልደረሱም፤ እንደኢትዮጲያዊ እንዳያዩት መናፍቃን ናቸው፤ እንደዘፋኝ እንዳያዩት ጆሮአቸው አይሰማም።

በአዲስ ነገር ተጀምሮ እስካሁን አልበርድ ያለው ቴዎድሮስን ነጥሎ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያቱ ምንድን ነው? በጥሞና ሊታይና ሊመረመር የሚገባው በአዲስ ነገር ጋዜጣና በጨለማዎቹ ሰዎች መሀከል ያለ የሚመስለው ድርጅታዊ ግንኙነት ነው፤ የአንድ ግለሰብን ሰብዓዊ መብቶች እየደጋገሙ በመርገጥ አጋጣሚ እየፈለጉ ማጥቃት የሚጎዳው ተረጋጩን ብቻ ሳይሆን ረጋጮቹንና የጋን ወንድሞችንም ነው፤ አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ… ኤርትራ እና የመን ተፋጠዋል (መልእክተ ዜና – በዳዊት ከበደ ወየሳ)

Thursday, July 3rd, 2014

ኤርትራ የየመንን አየር መንገድ እንደምትዘጋ አሳወቀች (ምክንያቱ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ነው)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰና፣ የመን ውስጥ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ታፍኖ መታሰሩ ብሎም አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አለመታወቁ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ትራንዚት እያደረገ በነበረበት ወቅት ነበር በየመን ታጣቂዎች ታፍኖ የተወሰደው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በየቦታው ድምጻቸውን ለማሰማት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ’ነዚያ ሁሉ ድምጾች ግን ጎልቶ የወጣው በኤርትራ በኩል የተላለፈው መግለጫ ነው። ይህን የኤርትራን መግለጫ መሰረት በማድረግ፤ ሌሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የራሳችንን ሃሳብ እንሰጣለን።

ኤርትራ ለየመን በላከችው መልዕክት መሰረት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ካልተፈታ፤ በኤርትራ አየር ላይ የሚሄዱትንም ሆነ፤ ምድር ላይ የሚያርፉት የየመን አውሮፕላኖች የሚታገዱ መሆኑን ገልጿል። ይህ ደግሞ እያደገ ለመጣው የየመን አየር መንገድ ትልቅ ኪሳራን የሚያስከትል ነው። ኤርትራ የጀርመኑን ሉፍታንዛ ካገደች ወዲህ፤ የየመን አየር መንገድ ሉፍታንዛን ተክቶ፤ አስመራ ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት ወደ አውሮፓ የሚሄዱም ሆኑ የሚመጡ አውሮፕላኖች በየመን በኩል አድርገው ማለፍ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። አሁን ኤርትራ የየመን አየር መንገድን እንደሉፍታንዛ የምታገድ ከሆነ፤ የየመን መንግስት የሚያገኘው ከፍተኛ ገቢ ሊቀንስበት ይችላል።

ከዚህ በፊት ባቀረብነው ዘገባ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ አገር ዜግነት ያለው እና የእንግሊዝን ፓስፖርት ይዞ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ስለአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስናወራ፤ የ እንግሊዝንም መንግስት የጉዳዩ ባለቤት ማድረግ ያስፈልጋል። እንግሊዝ ዜጋዋ በየመን ታስሮ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይላክ በአውሮፓ ዲፕሎማሲያዊ ስራ መስራት ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ እና የመን እስረኛን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ቢኖራቸውም፤ የመን የ እንግሊዝ ዜግነት ያለውን ሰው አሳልፋ እንዳትሰጥ በዛቻ ሳይሆን፤ በህጋዊ መንገድ የመንን መሞገት ያስፈልጋል።

ከ እንግሊዝ በተጨማሪ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችም በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡ ማድረግ ሌላው ብልሃት ነው። አሜሪካ ከየመን ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት በመጠቀም አቶ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈታ በየመን የአሜሪካ ኢምባሲ ጥረት እንዲያደርግ ጫና መፍጠር ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት ግንቦት ሰባት የሚያወጣቸው የማስፈራሪያ መግለጫዎች ድምጸታቸውን በማስተካከል እንደአንድ በሳል የፖለቲካ ድርጅት የሚታይ ዲፕሎማሲያዊ ስራ በመስራት ለውጤት መብቃት አለባቸው። በመሆኑም ከማስፈራሪያ መግለጫዎች ይልቅ፤ ከዲፕሎማሲያዊው ዘመቻ ጎን ለጎን… ህጋዊ ጠበቃ በየመን አዘጋጅቶ፤ ጉዳዩ በኢሚግሬሽን እና በዋናው ፍርድ ቤት እንዲታይ በማድረግ፤ ቢያንስ አቶ አንዳርጋቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይላክ ጊዜ መግዛት ይቻላል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ ዜግነት ያለው እንደመሆኑ መጠን ዲፕሎማሲያዊው ዘመቻ በእንግሊዛውያን ጭምር እንዲሰራ፤ ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎች የአገሪቱ ሚዲያዎች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ ተገቢ ነው። የምናወጣቸውም መግለጫዎች በአማርኛ ሳይሆን ሁሉም አገራት በሚረዱት እንግሊዘኛ ቋንቋ ሊሆን ይገባዋል። ከዚያ ውጪ ግን “አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባስቸኳይ ካልተፈታ በኢትዮጵያ እና በየመን ባለስልጣናት ላይ እርምጃ እንወስዳለን” አይነት መግለጫዎች፤ ወያኔ ኢህአዴግ “ግንቦት ሰባት የአሸባሪዎች ድርጅት ነው” የሚለውን አባባል ከማጠናከር ውጪ ብዙም ፋይዳ ላይሰጥ ይችላል።

ይህ ብቻም አይደለም። በማህበራዊ ድረ ገጾች እና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከዚህ በፊት ያደረጓቸው ንግግሮች እየተለጠፉ መሆኑን ታዝበናል። እንዲህ አይነቶቹ… ቀደም ሲል የተደረጉ ንግግሮችን አሁን ለእይታ ማቅረቡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስሩ እንዲጸናባቸው እንጂ፤ እንዲፈቱ ስለማይረዳቸው፤ በዚህ ረገድ ሌላ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በድጋሚ ለማሳሰብ ያህል… ግንቦት ሰባትም የማስፈራሪያ መግለጫዎችን ከማውጣት ይልቅ፤ በሌሎች ዜጎች እየተደረጉ ያለውን ጥረት ማስተባበር እና ዲፕሎማሲያዊ ይዘት እንዲኖራቸው ማድረግ አለበት። ኤርትራ ያደረገችውን ውሳኔ በማድነቅ፤ ሌሎች አገሮችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ማበረታታት ከግንቦት ሰባት አመራሮች የሚጠበቅ ነው።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሌሉበት ሞት የተፈረደባቸው መሆኑን፣ ንብረታቸው በወያኔ ኢህአዴግ መወረሱን፣ ወላጅ አባታቸው እና ቤተሰባቸው በእስር መንገላታቱን አጉልቶ በማውጣት የወያኔ ኢህአዴግን አስከፊ ገጽታ ማሳየት ይቻላል። አሁንም የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ወደ ኢትዮጵያ ብትመልስ በወያኔ ኢህአዴግ ሊደርስባቸው የሚችለውን የግድያ ወንጀል ማሳወቅ እንጂ፤ “አቶ አንዳርጋቸው ካልተፈታ ወዮላቹህ!” የሚለው አይነት ማስፈራሪያ ህሊና ለሌላቸው የሁለቱም አገራት አምባገነን መሪዎች ላይሰራ ይችላል። ህዝብ እና አገር የሚመሩት በእውቀት እና በጥበብ ጭምር በመሆኑ፤ ህጋዊ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመከተል… ነገር ግን በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ አቶ አንዳርጋቸውን የማስፈታቱን ሂደት እንቀጥል – የዛሬው ዜና መልእክታችን ነው።

ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ጁላይ 03, 2014

Thursday, July 3rd, 2014
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች