አቶ አባዱላ ገመዳ አፈጉባኤ፣ መለስ ዜናዊ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ

አዲስ ነገር | October 4th, 2010

(AddisNegerOnline.com) — በአሁኑ ሰዓት በተወካዬች ምክር ቤት እየተካሄደ ባለው ጉባኤ በኢፌድሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ንግግር የተከፈተ ሲሆን የፕሬዝዳንቱን ንግግር ካደመጠ በኋላ አቶ አባዱላ ገመዳን በአፈ ጉባኤነት አቶ መለስ ዜናዊን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርጦ ለሻይ እረፍት ወጥቷል፡፡

የህዳሴ ሀሳብ በማቅረብ፣ ሀገራችን ባለ ድርብ አሀዝ እድገት ያመጡ ስለሆነ፣ በዓለም አደባባይ ለሀገራቸውና ለአህጉራቸው ኩራት እየሆኑ ስለመጡ ድርጅታችን ኢህአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አገሪቱን እንዲመሩ በድጋሚ መርጧቸዋል ሲሉ የኢህአዴግ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ኀይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

አፈ ጉባኤ አባዱላ በበኩላቸው አንቀፅ ጠቅሰው አቶ መለስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጣቸውን ካበሰሩ በኋላ ቤቱ ከፍተኛ ጭብጨባ ያሰማ ሲሆን አቶ መለስ ራሳቸውም ሲያጨበጭቡ ታይተዋል፡፡ በኋላም እያጨበጨበ ለነበረው ለምክር ቤቱ አባላት ቆም ብለው እጅ ከነሱ በኋላ ቃለ መሀላ ፈፅመዋል፡፡

በእለቱ በአፈ ጉባኤነት የተመረጡት አቶ አባዱላ ተደጋጋሚ ስህተት ሲሰሩ በመቆየታቸው በአዳራሹ የተገኘውን ሁሉ ሲያዝናኑ ነበር፡፡ እርሳቸውም በተሳሳቱ ቁጥር ሲስቁ ታይተዋል፡፡


2 Responses to “አቶ አባዱላ ገመዳ አፈጉባኤ፣ መለስ ዜናዊ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ”

  1. aschalew says:

    aba dula gemeda afe gubae
    aeeeeee

  2. Anonymous says:

    የጉልቻ መቀያየር ወጥ አያጣፍጥም ጃል።

    ወሬውን ትተን በአንድነት እንታገል። መለያየታችን እትዮጵያን ሰው አሳጥቶ ዲንጋዮች ሲለዋወጡባት ይውላሉ። አባካችሁ እንተባበር። ሆዳምነትም ያቁም።



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.