ወያኔ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የቆመ መንግስት አይደለም


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ

ጽሁፉን በ.ፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ወያኔ ለኢትዮጵያ የቆመ መንግስት አይደለም

 ወያኔ ኢህአዲግ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም የቆመ መንግስት አይደለም :: ሀገር ማለት የተለያዩ ብሄሮች ፣ የተለያዪ ጓሳዎች እና የተለያዩ ሃይማኖቶች ያሎቸው ሰዎች መኖሪያ ናት :: እኛም ሀገራችን ብለን የምንጠራት ሀገራችን ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ያላት የተለያዩ ህዝቦች መኖሪያ ሀገር ስትሆን ሕዝቦቾም ለዘመናት በፍቅር፣ በመተሳሳብ ፣ በመከባባር እና በመተባባር አብሮ ሲኖር የነበሩ ህዝቦች እንደነበሩ ከታሪክ መረዳድ እንችላላን::ይችን ሀገራችንን ኢትዮጵያን በተለያዩ ጊዜና ዘመናትም የተለያዩ መንግስታቶች ለዘመናት በመፈራረቅ መርተዋታል

መንግስታቶችም የኢትዮጵያን አንድነት እና ሎአላዊነትን ጠብቀው ህዝቡም ኢትዮጵያዊነቱን ጠብቆ እና አስከብሮ እንዲኖር የበኩላቸውን አስተዋጹ አብርክተው አልፈዋል:: ጀግኖች አባቶቻችንም የኢትዮጵያ ሕዝብም ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሉ ደማቸውን አፍስሰዋል፣ አጥንታቸውን ከስክሰዋል ፣ ህይወታቸውንም መሰዋት አድርገው አሳልፈው ሰተዋል :: ምክንያቱም ኢትዮጵያውነት ኩራት ኢትዮጵያውነት ፍቅር ኢትዮጵያውነት አንድነት መሆኑን ከመሪያቸው ተምረውታልና:: በአሁን ሰአት በስልጣን ላይ ያለው እና የኢትዮጵያን ሕዝብ እየመራው ነው የሚለው የኢህአዴግ ወያኔ መንግስት ወደ ስልጣን ብቅ ካለበት ቀን ጀምሮ ሀገርን በመሸጥ ፣ በመገንጠል እና ሕዝብንም በዘር፣በብሔር፣ በጓሳ እና በቋንቋ በመከፋፈል ኢትዮጵያዊነትን የማጥፋት ርኩስ ተግባሩን እየገፋ ባለበት በእነዚህ አስርት አመታት ውስጥ ግን ኢትዮጵያውነት ኩራት መሆኑ ቀርቶ ውርደድ፣ ስደት መከራ እና ስቃይ መሆኑ እየጨመረ መጥቶል::

በእነዚህ አመታቶች ኢትዮጵያውነት የሀገር ስሜትና ወኔ ከህዝብ ዘንድ የጠፋበት እና ሕዝቡም እንደ ዜጋ መኖር በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል ::በእነዚህ አመታቶች ውስጥ ለሕዝቡና ለኢትዮጲያዊነት ግድ በሌለው በዚህ ሰይጣናዊ እና አረመናዊ አገዛዝ ስር ብዙዎች ታስረዋል፣ ተገለዋል፣ ወላጆች እንዳይወልዱ መካን ተደርገዋል ሕዝቦች ቄያቸውን መሬታቸውንና ሀብት ንብረታቸውን በግፍ ተነጥቀው ለስደት እና ለመከራ ተዳርገዋል፣እናቶች ልጆቻቸው በግፍ ተገሎባቸዋል ይህ ነው የማይባል ብዙ ብዙ ግፍ በሕዝብ ላይ ተፈጽሞል : ከእለት ወደ እለትም ሕዝባችን በሀገሩ ላይ መኖር በማይችልበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል::

ከሰሞኑ እንኮን እንዳየነው የወያኔ ስርአት ባመጠው በዘር እና በጎሳ ፖለቲካ ችግር ምክንያት ድብድባ እና ስቃይ ደርሶባቸው ከምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ የተፈናቀሉ ገበሬዎች አዲስ አበባ ገቡ የሚለወን ዜና  ከድህረ ገጹች ላይ ባነበብኩኝ ጊዜ ውስጤ ምን ያክል በሀዘን እንደተሞላ ልነግራቸው አልችልም እነዚህ ወገኖቻችን አዲስ አበባ በመግባት  በአካባቢው የደረሰባቸውን ችግር በጊዜው ሀገሪቷን እያስተዳደርኩኝ ነው ለሚለው ለወያኔ ባለስልጣኖች ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በመጎዝ ቢያስታውቁም በተገቢው መንገድ አቤቱታቸው ሊሰማ ባለመቻሉ እ ነዚህ ተፈናቃዩቹ “ብንመለስ ሊገድሉን ይችላሉ” በማለት ወደ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ጽ/ቤት በመሂድ ‹‹ፍትህ እንድናገኝ ለኢትዩጵያ ህዝብ ሰቆቃችንን አሰሙልን››በማለት የተማጽኖ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ተመለክተናል፡፡

ዛሬ በየቤቱ በዚህ ጨቋኝ ስርዓት የማይማረር የለም:: የሕዝብም የመኖር ሁኔታ ጥያቄ ውስጥ ነው :: የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ለሕዝብ ምንም የጠቀመው ነገር የለም:: ይልቁንስ በሀገር ሀብት እና ንብረት በማን አለብኝነት እንደፈለጋቸው ሲፈነጥዙ ኖረዋል አሁንም እየኖሩ ይገኛሉ:: መንግስታት ሀገርን ሊያስተዳድሩ እና ሊመሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ የሀገርን ሉአላዊነትን እና የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር ነበር በተቃራኔው ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሕዝቦቿም ለዚህ ባለመታደል መብታቸውን እና ነጻነታቸውን ለመስከበር እንደ ሰው መኖር በሚችሉበት ሁኔታ በነጻነት ለመኖር በመፈለግ በየቀኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሕዝቦች ሀገራቸውን በመልቀቅ ወደተለያዩ ሀገሮች ለስደት ይዳረጋሉ :: በብዛት ወደየ ሃረብ ሀገሩ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን ለተለያየ እንግልት መከራ እና ስቃይ እንዲሁም ለሞት የሚዳረጉ ሲሆን በየቀኑ የብዙዎቹ ህይወት እንደዋዛ ያልፋል::

ነገር ግን ሕዝባችን በየቦታው እና በየአረብ ሀገሩ አሰቃቂ ድብደባ ግፍ እና ግድያ ሲፈጸምበት ሀገርን እየመራው ነው ሕዝብንም እያስተዳደርኩኝ ነው የሚለው የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት አንድም ቀን የዚህ ሕዝብ መከራ እና ችግር ግርፋት  ሰቃይ እና ሞቱ ግድ ሲለው እና ለሕዝቡ አለኝታነቱ ሲቆም አይተን አናውቅም::ስለዚህ የኢህአዲግ መንግስት ለኢትዮጵያም ለኢትትዮጵያ ሕዝብም እስከ አሁንም ምንም የጠቀመው ነገር የለም አሁንም ወደፊትም አይጠቅምም ::ስለዚህ ማንኛችንም ኢትዮጵያኖች ከወያኔ መንግስት ምንም ነገር ልንጠብቅ አይገባም ባይ ነኝ ነገር ግን መብታችንን እና ጥቅማችንን የሚያስከብርልንን መንግስት ለመፍጠር  በመነሳት ለወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ግን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውነትን ሊወክል እንደማይችል ልንነግረው ይገባል ባይ ነኝ:: ለሀገር እና ለሕዝብ ጥቅም ቆሚያለው የሚል መንግስት የሀገርን ሉአላዊነት ሲያስከብር የሕዝብን ደህንነት እና ጥቅም ሲያስከብር ብቻ ነው እንደ መንግስት በሕዝብ ዘንድ ሊታይ የሚችለው በማለት ጹሁፌን ላጠቃል::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ማንኛውም አስተያየት ካሎት [email protected]