በጥላሁን ገሰሰ ስም እየነገደ ያለው ሰው ምነው ተው ባይ አጣ?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጽሁፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። በጥላሁን ገሰሰ ስም እየነገደ ያለው ሰው

በዲሲና አካባቢዋ በወያኔ ስውር ተልዕኮ ተሰጥቶት እያወናበደ ስለሚገኘው መስፍን በዙ ስለተባለው ግለሰብ ከዓመት ገደማ በፊት በተለያዩ ድረገጾች  “በጥላሁን ገሰሰ ስም እየነገደ ያለው ሰው ምነው ተው ባይ አጣ?” በሚል ርዕስ የተለቀቀው ጽሁፍ  ግለሰቡ “ካፈርኩ አይመልሰኝ” ብሎ፣ እኩይ ተግባሩን ከመተው ይልቅ አጠናክሮ ስለቀጠለበት በድጋሚ አውጥተነዋል። መስፍን በዙ በተለይ ክህነታቸውን የተገፈፉት አቶ ታደሰ ሲላይ ጋር በግብረአበርነት በመቆም እጅግ አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊት በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ ጥቆማዎች ደርሰውናል።  መስፍን በዙ በሃሰት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ነኝ እያለ ቢለፈልፍም፣ በወያኔና ተላላኪዎቹ ቤተክርስቲያኒቷ ላይ የደረሱትን ለምሳሌ የዋልድባ ገዳም ውስጥ ለዘመናት ተከብሮ የቆየ የመናንያንና መነኮሳት መካነ-መቃብር በግሬደር ሲታረስና ሲጠረግ እንዲሁም መነኮሳትና መናንያን ከዘመናት ከኖሩበት ገዳም ሲባረሩ፣ የአሰቦትና የዝቋላ ገዳማት በእሳት ሆን ተብሎ ሲጋዩ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የተንሰራፋው ዘረኝነት፣ ጉቦኝነትና የስነምግባር ጉድለት  ቤተክርስቲያኗንና ምዕመናኗን ከፍተኛ ችግሮች ውስጥ ዘፍቆ በሚገኝበት ጊዜ ውስጥ አካሂዳለው በሚለው ቴሌቪዥንም ሆነ ሬዲዮ አንዲት ነገር ትንፍሽ ሳይል የቀደሞው ቀሲስ ታደሰ ሲሳይ ስልጣነ ክህነታቸውን ሲገፈፉ ጋሻ ጃግሬ በመሆን በውግዘት ለተለዩት ግለሰብ የማወናበድና የማደናገር ወንጀል እየሰራላቸው ይገኛል።

መስፍን በዙ ጋዜጠኛ ነኝ በማለት እያታለለ  ኢትዮጵያዊያን በወያኔ ላያ ተቃውሞ በሚያደርጉበት ቦታ ሁሉ ካሜራ ተሸክሞ በመገኘት ለወያኔ ወሬ አየለቃቀመ እንደሚያቀብል ተደርሶበታል። ይህ ግለሰብ አበበ ገላው ለመጨረሻ ጊዜ  መለስ ዜናዊን ዋሽንግተን ዲሲ መጥቶ በነበረበት ጊዜ በዓለም መሪዎች ፊት በተቃወመውና ማንነቱን ባጋለጠበት ወቅት “መለስ ዜናዊ በአበበ ገላው ተቃውሞ ምክንያት አንገቱን አልደፋም፣  ተቃውሞውም ምንም አልመሰለውም፣ ደክሞት እያንቀላፋ ነበር፤ ወዘተ…” አያለ ከእውነታው የራቀ የቅጥፈት ቪዲዮ አዘጋጅቶ በድረገጽ በማውጣት ህወሃቶችን ጉርሻ እንዲሰጡት ሲለማመጥ የነበረ ዓይኑን በጨው ያጠበ እፍረተቢስና ይሉኝታ የሌለው ልክስክስ ግለሰብ ነው። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይመልከቱ።  http://ecadforum.com/articles/the-bankrupt-propagandist/