አባ ፋኑኤል አዲስ ተክል ናቸው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ታላቁ የዘመናችን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አርበኛ የሆኑት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በተለያዩ የቤተክርስቲያናችን አንገብጋቢና አሳሳቢ ጉዳዩች ላይ ጥልቀት ያላቸው፣ በጥንቃቄ የተመረመሩና በመረጃ የተደገፉ የተለያዩ ሐይማኖታዊና ሀገራዊ ጽሁፎችን ለአንባቢያን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በዚህም መሠረት በቅርቡ ከስልጣነ ክህነታቸው የተገፈፉትና የተወገዙት አቶ ታደሰ ሲሳይን አስመልክቶ “አቡነ ፋኑኤል” በመባል የሚጠሩት አባ መላኩ ጌታነህ ስላወጡት መግለጫ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ “አባ ፋኑኤል አዲስ ተክል ናቸው” በሚል ርዕስ የሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ከዚህ ጋር አያይዘን አቅርበናል።

አባ መላኩ በአቶ ታደሰ ሲሳይ ላይ ስለተላለፈው ውግዘትና ክህነታቸው ስለተገፈፈበት ምክንያት ምንም ሳይናገሩ፣ ውግዘቱን በቆራጥነትና በትክክለኛ ክርስትና ዕምነታቸው ኃላፊነቱን ወሰደው ያስተላለፉትን ካህናት ለማጣጣል ያደረጉት የከሸፈ ሙከራ ምን ከምን አብረህ አዝግም እንደሚባለውና እሳቸውም የተሸከሙት ህጸጽና ከክህነት የሚያስወጣ ስነምግባር ሊኖርባቸው እንደሚችል አመላካች ነው።

“በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ነው፤ በምድርም የፈታኽው በሰማይ የተፈታ ነው” የሚል ሥልጣን የተሰጠውና የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም የሚፈትት ካህን እንኳንስ የዝሙትን ያህል አስከፊ ኃጢአት ፈጽሞ ሊቀደስ ይቅርና ከማንም ሰው ጋር  ተራ ጠብ ቢጣላና ቢቀያየም እንኳ ከተጣላው ሰው ጋር ሳይታረቅ አይቀድስ የሚለውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የማዕዘን ራስ የሆነ ህግ ጥሰውና  ንቀው ማንም አይጠይቀኝም ብለው በእብሪትና በማን አለብኝነት ለረዥም ዓመታት ቤተመቅደስ ሲያርክሱ የነበሩትን አቶ ታደሰ ሲሳይን መክሮና ወቅሶ ከክህነታቸው እንዲወገዱና ንስሃ እንዲገቡ ማድረግ ሲገባ፣ አባ መላኩ በተገላቢጦሹ ለአቶ ታደሰ ሲሳይ ጥብቅና መቆማቸው ለምዕመናን እጅግ የሚያሳዝንና የሚያንገበግብ ጉዳይ ነው።

አቶ ታደሰ ሲሳይ በፈጸሙት ዝሙት ምክንያት ትዳሩ የተፈታበትና ልጆቹ የተበተኑበት ወንድም እንባውን ለፈጣሪው እየረጨ ይገኛል። አባ መላኩ ይህን ከፍተኛ በደልና ግፍ  የደረሰበትን ወንድም አቤቱታ ሰምተው አስፈላጊውን ቤተክርስቲያናዊ ውሳኔ በመስጠት ለተበዳዩ ፍትህና ዳኝነትን እንዲሁም በሐመረ ኖህ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ለሚገለገሉ ምዕመናን አቶ ታደሰ ሲሳይ በሰሩት የቤተክርስቲያን ህግ ጥሰት የተወገዙና ክህነታቸው የተሰረዘባቸው በመሆኑ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት በማስወገድ ሌላ ንጹህ ካህን እንዲመደብ ማድረግ ይገባቸው ነበር። ሆኖም አባ መላኩ ትዳሩ ለተበተነበት ወንድም የሰጡት ምላሽ በዓለማዊ ፍርድ ቤት “ሚስቴን ተነጥቄያለሁ” ብሎ ክስ እንዲመሠርት እንዲሁም በዝሙት የተጨማለቁትን አቶ ታደሰ ሲሳይን  የማደናገሪያ የምንኩስና ስም አስለጥፈው የበፊቱ ሳያንስ ያሁኑ እንዲብስ አቶ ታደሰ ሲሳይን ቤተክርስቲያን ማርከሳቸውንና የቤተክርስቲያን ህግ መደፍጠጣቸውን እንዲቀጥሉበት እያሽሞነሞኗቸውና እየተባበሯቸው ይገኛሉ።

አባ መላኩ ይህንን በማድረጋቸው ምን ያህል ህዝበ ክርስቲያኑን እንደናቁትና አንዳዋረዱት ለማሳየት ይቻላል። ለማንኛውም እራሱ አስረጅ የሆነውን የቀሲስ አስተርአየ ጽጌን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። አባ-ፋኑኤል-አዲስ-ተክል