በአንድነት ፓርቲ ላይ ደጋፊ ነን ከሚሉ የተወረወሩትን ድንጋይዎች ቆም ብሎ ማጤን ተገቢ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አሳቤ አበበ (ከቶሮንቶ)

ሰሞኑን በአንድነትና መ.ኢ.አ.ድ መካከል ተጀምሮ ለነበረው ውህደት በወያኔ የተከሰቱ መሰናክሎች ሳያንሱ በአሜሪካ ከሚገኙ ደጋፊ ነን ከሚሉ አቶ ግርማ ካሳና አልዩ ተበጀ እንዲሁም እዚያው ኢትዮጵያ ባሉት ዶ/ር ያዕቆብ ሐይለማርያም በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላይ የተወረወሩትን የማፍረሻ ድንጋይዎች ቆም ብሎ መመልከትና ማጤኑ ተገቢ ይሆናል።

በመጀመሪያ አቶ ግርማ ካሳ ደጋፊ እንደመሆኔ ሲሉ አስቀድመው የድጋፍ ደረጃቸው ካለበት ማለፍ እንደማይችል በተሳነው ህሊና የተጻፈውና የተላለፈው ማሳሰቢያ በሰለጠነና ህግ በሚከበርበት ሃገር እንደሚኖር ያሰበና ያወቀ ብእረኛ የሚፈነጥቀው አልነበረም።

በተመሳሳይ ዶ/ር ያዕቆብ ሀ/ማርያም ቀድሞ በርቱካን ከተወቸው ብለው ከመሰሎቻቸው ጋር ድርጅቱን ጥለው የሄዱ ግለሰብ አሁን ለአንድነት አባሎች መታሠርን እንደማስፈራሪያ አድርገው ጠቀሙም አልጠቀሙም በብዙሃኑ የተመረጡትን ግለሰብ በማብጠልጠልና፡ ጥላሸት በመቀባት፡ ለማስፈራራት ነውር ሥራ ሰርተዋል። ዶ/ር ያዕቆብን ነፋሱ ወዴት እያወዛወዛቸው እንደሆነ መረዳት አስቸጋሪ አይሆንም። ዶ/ር ያዕቆብ ሰሞኑን ባወጡት የአንድነትን ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ግዛቸውን የኮነነ ጽሁፍና በትግሉ ውስጥ የታሠሩርትን ሁሉ ተሳትፎም እንዳይኖራቸውና ሌሎችንም ከትግሉ እንዲርቁ የሚያደርግ ተንኮል ለበስ የሆነ የማስፈራሪያ ጽሁፋቸው ”አዛኝ ቅቤ አንጓች” እንዲሉ ዓይነት አፍራሽ እንጅ ገንቢና ጠቃሚ አልነበረም።ቅን የሆነ ልቦና ያለው ሰው ኢንጅነሩ ወደ ምርጫው ከመግባታቸው በፊት ምክሩን በአካልም ሆነ በሌላ መገናኛ መሠንዘር ጭዋነትና ጠቃሚም ነበር!! ከዚያ ባለፈ ግን በድርጅቱ ላይ የደፈጣ በደል ነው የፈጸመት።

እንደዚሁም በከፋ መልኩ ያለማቋረጥ የመከፋፈል ጽሁፎቹ ያላባሩት የአሜሪካው የድጋፍ ድርጅት አካል ነኝ ባዩ አቶ አልዩ ተበጀ ከደጋፊ ወይም ከድጋፍ ድርጅት የማይገባን ተግባር ሲወረውር መክረሙ ብዙዎችን ያሳዘነና ያስገረም ነው። አቶ አልዩ ኢንጅነሮቹን እሱ ከሚጠረጥረው በበለጠ ብዙዎቻችን እሱን እንድንጠረጥር አድርጎናል። ብልሹ አሉባልታዎቹን በጽሁፍ ሲያሠራጭ የተጠቀመው የአንድነትንና፡ የመ.ኢ.አ.ድን ማህተም በማሳዘል ነበር።የድርጅቶቹ ማህተም ከእነሱ ሌላ የድጋፍ ድርጅቶች ልንጠቀም አይገባም አያስችልንምም! የሁለቱን ማህተም ያዘለው ጽሁፉም የሚያወራው አሉባልታ ነበር። አሉባልታው የሚጎዳው አንድነትን እንጅ ኢንጅነሩን አይደለም። እንዲያውም ኢንጅነሩን እልክ ያስይዛል እንጅ ሊያቀራርብና ቀና ልቦና እንዲመጣ አያዘጋጃቸውም። አቶ አልዩ የአንድነት ደጋፊ ነኝ ባይ ሲሆን ውህደታቸው ያልተጠናቀቀና የመፍረስን አሉባልታም እያወራን የመ.ኢ.አ.ድንና የአንድነትን ማህተም ሊያሠፍር እንዴት ያስችለዋል? ይህ ሆን ተብሎ የአንድነትን ጥንካሬ ቄጠማ ለማድረግ ታስቦ የተፈጸመና እየተፈጸመ ያለ በደጋፊ ስም ያደፈጠ ሰው የሚተገብረው ድርጊት ነው።ይህንን የአሜሪካው ይድጋፍ ድርጅት ቸል ሊለው የማይገባ ተግባር መሆኑም መጤን አለበት።

በዚች ጽሁፌ የአንድነት ስድስት የአመራር አባሎች “ትግል እልክ አስጨራሽ” መሆኑን ዘንግተው ለአንድ ሰው ብለው የትግሉን ሜዳ ጥለው ትልቁን የውህደት ጅምርና አፍንጫቸው ሥር የተጠጋውን ምርጫ በትነው በኢንጅነሮቹ አመካኝተው ውሃ እንደነካው ጨው ቀልጠው ክሆነ ጥንካሬ ማጣት እንጅ የኢንጅነሩ የበላይነት ሊያንበረክካቸው ችሎ አይደለም። ለራሳችው ታሪክም የሚያምር ስዕል አልተውም!! በውጭ ያለነው አብዛኞቻችሁን የምናውቀው በፎተግራፍ ነው ስለዚህ በውጭ በደጋፊ ስም ባለን ወገኖችና ኢትዮጵያም የአንድነትን መጠንከርና ያባላቶቹን መጎልበት ለማይፈልጉ ደስ እንዲላቸው ማድረግ በታሪክ ተወቃሽ ያደርጋል።ለዚህም ነበር ጀግናው ሐብታሙ አያሌው በመፈክሩ ”አሜሪካ ሆናችሁ አትንገሩን” ያለው። አለ ምክንያት አልነበረም!! ዛሬ የአቶ አልዩ አሉባልታ የሌሎቹም አፍራሽ ተልእኮ ተተግብሮ ከሆነ አንዱዓለም አራጌና፡ ሃብታሙ አያሌው ሁለት ጊዜ እንደታሠሩ የሚሠማቸው።

አንድነቶች መከፋፈላቸው ሠርቶባቸው ከሆነ ራሳቸውን ጠልቀው እንዲመረምሩ፡ከሟርት ካለፉም ተግባሮቻቸው ከህዝብና ከድርጅቱም ለተቀበሉት ትልቅ አደራና ሃላፊነትሲባል ፍላጎትን እያስሸነፉ ለብዙሃኑ የመገዛትንና የድርጅቱንም ስምና ዝና የሚያስከብሩ ተግባሮችን ለማከናወንና ለሌሎችም አርአያ ሆኖ የመገኘትን ምሳሌነት እንዲኖራቸው ያሻል፡፡ራሳቸውን ያገለሉ ካሉም ከትግል ውስጥ እንደነበሩ ሳያውቁት ነበር የቆዩት ያስብላል።ያ ተከስቶ ዝም ብሎ የተመለከተ ስብስብና ደስተኛ የሚሆን መሪም የመሪነትና ሃላፊነትን የመሸከም ብቃት አለው ሊባል ከቶ አያስችልም ራሱን መዞ ማውጣት አለበት!! ስለዚህ ለመሪነት ህሊናን ከእልክ ማጽዳት፡ ይቅርታንና መከባበርን ከውስጣችን አለማጣት፡ክፋትና ተንኮል የመገልገያ ሙያ አድርገን አለመያዝ አብሮ ለመሥራት እጅግ ጠቃሚና ጉልበትም ይሆናሉ።ያ ካልሆነ ከወያኔ ምን ይለየናል? ህዝቡንም ቀናና ዘወር ብሎ የሚታይበት አንገት አይኖርም።