የቴዲ አፍሮ አዲሱ ዜማ “በሰባ ደረጃ”


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አበበ ቶላ

የቴዲ አፍሮ አዲሱ ዜማ “በሰባ ደረጃ” በዋዛ የምንለቀው አይመስልም። ”ቴዲ ያስተፈስህ ልበ-ሰብ” እያሉ ደጋግመው የሚሰሙት እንጂ ይገጥመዋል አይገልጸውም። እያንዳንዱን ስንኝ ድጋሚ ሲሰሙት ”ፓ!” ብለው እየተደንቁ ድጋሚ እያጠነጠኑ የሚያዳምጡት ገራሚ ዜማ ነው። የፌስቡኳም መግቢያስ ለምን ትቅርባችሁ…

ሰባ ደረጃን የእኛ ሰፈር ልጆች መጀመሪያ የተዋወቅናት ”ጋዝ ግዙ” ተብለን ስንላክ፣ ከዛ ቀጥሎ ደግሞ የእንቁጣጣሽ አበባ ”ፎርም” ለመግዛት ራስ መኮንን ሰፈር ልጆች ጋ ስንመጣ ነበር። ከዛ በኋላ ስንጎረምስ ደግሞ ጋሽ አበራ ሞላ አካባቢውን ”ፏ” አድርጎልን ራስ መኮንን መናፈሻ ውስጥ በዛፍ ተከልለን ቁጭ ብለን እየተናፈስን፤ ”እያንዳንድሽ በፒያሳ ያለፍሽ አይቼሻለሁ” እያልን አላፊ አግዳሚውን ስንታዘብ ያው ሰባ ደረጃ ማለት እርሷ አይደለች እንዴ ከዛም ለአቅመ መስሪያ ቤት ስንደርስ የትራንስፖርት ”ሲጠበሸን’ (መጠበሽ ማለት በአራዳ ብሄረሰብ ቋንቋ ማጣት፣ መቸገር ማለት ነው።) እና የጠበሸን ጊዜ እንደምንም ፒያሳ እንደርስና የፒያሳን ቆነጃጅት እያደነቅን እና ዎክ እየበላን ካዘገምን በኋላ ወደቤታችን የምንቀየሰው በሰባ ደረጃ በኩል ነበር። በዚህ ሁሉ መሃል እናንተ ያጣኋችሁ ሰፈሩን ባሰብኩ ቁጥር ከአይኔ ላይ እንደሆናችሁ ማን በነገራችሁ። መልካም ድመጣ! ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ