የወያኔ ቆይታ በሎስ አንጅለስ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Ethiopians protest against TPLF junta in Los Angeles August 2014
ሎስ አንጅለስ በወያኔ አምባገነኖችና አጋፋሪዎቻቸው ልትጎበኝ ዝግጅቱ ከታቀደ ቆይቷል። እንዳውም የሃይለማሪያም የክብር ድግሪ መሸለሚያ ወይም መሳለቂያ ልትሆን ታጭታለች።

የወያኔ ሥራ አስፈፃሚዎች እነ ወንድወሰን መስፍን፣ እነአበራ ገብሬ፣ እነፀሃይ ኃይሉና የሮዛሊንድስ ምግብ ቤት ባለቤቶች ወንድማማች ፍቅረና ሞገስ ጌቶቻቸዉን ሊቀበሉ ሽርጉዱን ተያይዘውታል።

የሮዛሊንድስ ምግብ ቤትን ኢትዮያዊያን አንቅረው ከተፉት ዓመታት አልፈዋል። ከወንድማማቾቹ ባለቤቶች አንዱ ሞገስ ወደኢትዮጵያ በመሄድ ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችንን ለሳዉዲ ከበርቴዎች ለዘመናዊ ባርነት የመደለል ሥራ ሲያካሂድ ቆይቶ የእህቶቻችን ጉዳይ ይፋ ወጥቶ ኢትዮጵያዊያን ቁጣቸውን በዓለም ዙሪያ ካሰሙ በኋላ ገበያው በመቀዝቀዙ ተመልሶ በሎስ አንጅለስ UBER ሥራ ላይ መሰማራቱ ተሰምቷል። ወንድሙ ፍቅረ ደግሞ ሕሊናውን ሽጦ ልቡንና ቤቱን ከፍቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠላቶች ሲያስተናግድ የኖረ ስለሆነ የእራት ግብዣ ቢያደርግላቸው አይደንቀንም።

ነፃነት ባለበት አገር እየኖሩ ነፃነት ገፋፊን በፊት ለፊት ለማስተናገድ እራሳቸውን ያዘጋጁ ጥቂት ሕሊና ቢሶች መኖራቸው ቢታወቅም ይልቁንም “ማኖ ነክተው” ሕሊናቸውን በጊዚያዊ ጥቅም የቀየሩ ይበልጥ ያሳፍራሉ። ከእነዚህ አሳፋሪዎች ዋናውን ቦታ በጊዜው የያዘው አሳፋሪ ወንድወሰን መስፍን ነው። በርግጥ የባለታሪኩ የራስ መስፍን ልጅ መሆኑን የዘመኑ ስራዉ እንድንጠራጠር አድርጎናል። ከወያኔ የተሰጠውን ችሮታ አፀፋ ለመመለስ ሽር ጉድ ብሎ ጌቶቹን ዘመናዊ ጉቦ ሰጥቶ መሸኘት ህሊናው የተቀበለው የአገር ክህደት መሆኑን በጊዜው ይረዳል ብለን እንገምታለን። አይ ኢትዮጵያ “የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” ይሏል ይህ ነው።

ታዲያ ሁሉም አይሞላምና እድሜ ለአበበ ገላውና ለመብት ተቆርቋሪ ኢትዮጵያዊያን ለሃይለማርያም ሊሰጥ የነበረው የAzusa Pacific Univesity የክብር ዲግሪ በዩኒቨርሲቲው ፈጣን ዉሳኔ እንዲሰረዝ ተወሰነ። የሃይለማሪያም የሎስ አንጅለስ ጉዞ አፈር በላ። ሁሉም የሚሆነው ለምክንያት ነውና ኢትዮጵያዊያኖችም ከወዲሁ አስበውበት በተጀመረው እንቅስቃሴ ሎስ አንጅለስን፣ ሳንዲያጎን፣ ላስቬጋስንና የሰሜን ካሊፎርኒያን ዋና ዋና ከተሞች ያቀፈ ግብረኃይል ለመቋቋም በቃ።

ሆድ ወደፊት አገር ወደኋላ በሚል መርህ የተሰማሩ ሆድ አደሮችም ለአርብና ለቅዳሜ መዘጋጀት ጀመሩ። ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን ሀሳባቸውን በመፃፋቸው ያለፍርድ ያሰሩ፣ሕዝብ በግፍ የገደሉ፣ ያፈናቀሉ የሕዝብ ጠላቶችን የነፃነት ዋጋ በተከፈለበት አገር እየኖሩ የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃነት የገፈፈውን የወያኔን አገዛዝ ማስተናገድ የነውሮች ሁሉ ነውር ነው።

የሐሙሱ ፕሮግራም መሰረዝ ለወያኔ ተደጋፊዎች የፎቶግራፍ ጊዜ ሰጣቸው። (ተደጋፊዎች ስንል በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ የሆኑትን ማለታችን ነው።)

በማግስቱ ዓርብ August 1st, 2014 የተቃውሞ ሰልፍ መኖሩ ስለተሰማ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚሆን ፎቶግራፍ ለመነሳት ጊዜ ሰጣቸው። አይ ተደጋፊ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማታለያ ፎቶግራፍ ማዘጋጀት…….. ይህ አይነት ማጭበርበር አሁንም አለ እንዴ?… ከኢሳትም በኋላ?…የሕዝብ ጩኸት እንደደወል በቀጥታ እየተሰማ?…. ለነገሩ ትዕዛዝ መፈፀም እንጂ በእራስ ሕሊና መመራት ከእነዚህ አገልጋዮች ሊጠየቅ አይገባም።

የወያኔ Investor ተብዮዎች ከአሜሪካ ነጋዴዎች ለመገናኘት የመጡ የዘመኑ ሰዎች አርብ በጠዋት ወደ ስብሰባው ሲገቡ ድርጊታቸውን ለማጋለጥ በታቀደ ሕዝባዊ ጥሪ ቀድሟቸው የደረሰ ኢትዮጵያዊ እጆቻቸው በደም የተነከሩ የወገኑን ገዳዮች፣ አሳሪዎች፣ አፈናቃዮችና ባንዳዎችን ፊት ለፊት ለማግኘት አፍጥጦ ይጠብቃል። ጩኸቱም የወገንን ጩኸት ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ከሎስ አንጅለስ የንግድ ምክር ቤት በተሰጣቸው የተዛባ መረጃ ተታለው ሊመጡ የሚችሉ የልዩ ልዩ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ድምፃችንን እንዲሰሙና የኢትዮጵያን እውነተኛ ገጽታ እንዲረዱ ለማድረግ የታቀደ ነበር።

ደምፃችንን እየሰሙና መፈክሮችን እያነበቡ ሀሳባቸውን የቀየሩ ባለሀብቶች ጥቂት አልነበሩም። ከዚህም በተጨማሪ በሆቴሉ አርፈው የነበሩ እንግዶች ስናስተላልፍ የነበረውን መልእክት በሚገባ በመረዳታቸው በሆቴሉ ቅሬታቸውን በመግለፅ በዚህ ሆቴል ወደፊት እንደማያርፉ የገለጹን ነበሩ።

በልማት ስም የወገኖቻችንን የባርነት ዘመን ማራዘም በነፃነት ዓለም ከሚኖር ማንኛዉም ነፃነት ወዳጅ የማይጠበቅ ነው።
No human rights, No investment
Invest inhuman rights. Not in human wrongs
Stop funding Dictatorship
Stop Supporting, Aiding, and Investing in Tyranny
Stop Supporting State Sponsored Terrorism.

እነዚህና የመሳሰሉት መፈክሮች እየተሰሙ በጀግናዉ አንዳርጋቸው ጽጌ የተደረሰዉ “ላንቺ ነው ኢትዮጵያ” እየተዘመረ ሳለ የወያኔ ተደጋፊዎች በትልቅ አውቶቡስ ከች አሉ።

አይ መዋረድ የት ይደበቁ በሕዝብ እየተሰደቡ የታሪክ አዘቅትነታቸው በቪዲዮ ተቀርፆ ለትውልድ በሚቀመጥበት ሁኔታ ፍጥጥ ብለዉ መጡ።

ከመጀመሪያው አዉቶቡስ 1…2 … 3 እያሉ እየንተጠባጠቡ መዉረድ ቀጠሉ። ይህን ያህል ተቃዉሞ ያልጠበቁት እንደነበረ ከፊታቸው ይነበባል። 8 ወርደው ሌሎች ይኖራሉ ብለን ብንጠብቅ አልወረዱም። አውቶቡስም ሄደ። አንወርድም ብለው ተመለሱ ወይንስ እነዚህ ብቻ ናቸው?… በእርግጥ ለጥቂት ሰው የ80 ሰው አውቶቡስ ተከራዩ?.. እስቲ እንተወው ወደ ጩኸታችን። ጥቂት ቆይተን ሌላ አውቶቡስ መጣ። ተጠራርተን ሄድን የተለመደውን የሕዝብ መልክት አፍንጫቸዉ ድረስ ለማድረስ ተጠጋን። ወረዱ 1…….3 ቀጠሉ ከ20 የማይበልጡ የቀሩትስ?… እዛዉ ቀርተው ይሆን?… አንዳንዶቹ የቅሌት ፊታቸዉን በያዙት ነገር በመሸፈን ያቺን ደቂቃ እንደምንም አለፏት። ጩኸታችንን እየሰሙ ገቡ።

የበለጠ የሚያበሳጨው እንደ እኛው ነፃነት ፍለጋ ተሰደናል ብለዉ እራሳቸው በነፃነት አገረ እየኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለነፃነት ለሚአደርጉት ትግል ደንቃራ የሆኑ ግለሰቦች፤ ኢትዮጲያንና ኢትዮጵያዊነትን እንደሸቀጥ የሚቆጥሩ፤ ለወገን ስቃይ ቅንጣት ያህል የማይቆረቆሩ የዘመናችን ባንዳዎች ናቸዉ። ስለዚህ ከአሁን በኋላ እነዚህ የዘመኑ ባንዳዎች በእኛ ላይ እየነገዱ የወያኔን የግፍ አገዛዝ እንዲያራዝሙ መፍቀድ የለብንም።

ነፃነት ወዳድ የሆነ ሁሉ እነዚህን በደም ገንዘብ የሰከሩ የወያኔ ይቅርታ ለማኞችን ማግለልና ትብብሩን መንፈግ ይጠበቅበታል።

ይህ በመጀመሪያ ደረጃ የሚደረግ የነፃነት ትግል ጥሪ ነው።

ወደፊት ወደ ሕሊናቸው በጊዜ ያልተመለሱ የወያኔ አጋፋሪዎችን የጠቀለለ ጽሁፍ ይዘን ብቅ እንላለን።
ትውልድን እያጠፉና አገር እየዘረፉ በልማት ስም ማጭበርበር ይብቃ!

ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘላለም ትኑር!