ረዥሙ ጉዞ ለአሜሪካ ህዝብ የተሟላ አገራዊ ህብረት


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

እ.ኤ.አ ኤፕሪል 10/1957 ዕድሚያቸው 28 ዓመት የሞላቸው ዶ/ር ማርቲን ሊተር ኪንግ በሴንት ሌውስ ከተማ የነጻነት ሰልፍ ላይ በመገኘት “የዘር ግንኙነት እድገት በሚል ጥያቄ ላይ እውነተኛ ምልከታ” በሚል ርዕስ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ በንግግራቸው ላይ ማርቲን ሉተር ኪንግ የሴንት ሌውስ ትምህርት ቤቶች “ጸጥታቸው እና ክብራቸው በተጠበቀ መልኩ“ በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተደራጁ የነበራቸውን አድናቆት አቅርበው ነበር፡፡ የሴንት ሌውስ ትምህርት ቤት የአገሪቱን የዘር ግንኙነት ለማሻሻል ማስተማር ይችላል ብለውም ነበር፡፡ “አብዛኛው የደቡቡ የአገሪቱ ክፍል እንደ ሴንት ሌውስ ካሉ ከተሞች ትምህርት ሊቀስም የሚችልባቸው በርካታ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ በአንድነት መደራጀት ያለምንም ችግር ጸጥታ እና ሰላማዊነት በሰፈነበት መልኩ ተግባራዊ መሆን ይችላል፡፡“ ሆኖም ግን የማርቲን ሉተር ኪንግ ዋና ዓላማ “በተደጋጋሚ ወደ እርሳቸው የሚመላለሰውን ጥያቄ መጋፈጥ ነበር፡፡ አንዳሉትም “ እናም ይህ ጥያቄ በአገሪቱ ውስጥ ባሉት ሁሉም ወንዶች እና ሴቶች ከንፈሮች ላይ የተንጠለጠለ ነበር፡፡ የዘር ግንኙነት እድገት ጥያቄን አስመልክቶ ሁሉም ህዝቦች ይደነቁ እና ይገረሙ ነበር፡፡ እንዲህ በማለትም ጥያቄ አቅረበው ነበር ፣ “በእርግጠኝነት በዘር ግንኙነት ጉዳይ ላይ መሻሻል ታይቷልን?“

እ.ኤ.አ ማርቲን ሉተር ኪንግ በ1957 ንግግራቸውን ካደረጉ 57 ዓመታት በኋላ ኦገስት 2014 ወደ 21,000 አካባቢ የሚጠጋ የሙት መንፈስ ያረፈባት ከሴንት ሌውስ ወጣ ብላ በምትገኘው የፈርግሰን ከተማ በእራሷ ህዝቦች የዘር ግንኙነት ሳቢያ በመሰቃየት ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ ኦገስት 9/2014 ባዶ አጁን በመንገድ ላይ የሚሄደውን ሚካኤል ብራውን የተባለውን የ18 ዓመት ጥቁር ወጣት ዳረን ዊልሰን የተባለ ነጭ የ28 ዓመት የፈርግሰን ፖሊስ አባል በአሳዛኝ ሁኔታ በጥይት ተኩሶ ገድሎታል፡፡ የብራውን ቤተሰቦች የግል የሬሳ ምርመራ እንዲደረግ ካደረጉ በኋላ የታየው ውጤት ወጣቱ ቢያንስ 6 ጊዜ በጥይት ተደብድቦ የተገደለ መሆኑን ያመላክታል፡፡

ግድያው ለቀናት የዘለቀ ቁጠኛ  ሆኖም ግን ሰላማዊ ተቃውሞን ቀስቅሷል፡፡ ጥቂት ግለሰቦች የአጋጣሚውን ውዥንብር እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም የዘረፋ እና የአውዳሚነት ወንጀሎችን ፈጽመዋል፡፡ በደርዘን የሚቆጠሩት ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የፖሊስ ምላሽ ግን አሳፋሪ እና አሳዛኝ ነበር፡፡ 150 የሚሆኑ ፖሊሶች በአካባቢው ከሚገኝ የህግ አስከባሪ ማዕከል በመነሳት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጋስ በመርጨት እና በመንገዶች ላይ እየተካሄደ ያለውን ሰልፍ ለማጨናገፍ ሞክረዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ እንዲህ እያሉ ይጮሁ ነበር፣ “እጃችን ወደ ላይ ነው! አትተኩሱ!“ የልዩ መሳሪያ እና ስልት ቡድን ከባድ የመከላከያ ብረት ለብሰው ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ለመተናኮል ተዘጋጅተው መንገዱን ወረሩት፡፡ አልሞ ተኳሽ ፖሊሶች በማታ አነጣጥረው በሚያሳዩ መነጸሮች እየተመለከቱ፣ ከከባድ የጦር ተሽከርካሪዎች ጫፍ ላይ በመሆን ኢላማቸውን እያነጣጠሩ ይቃኙ ነበር፡፡ የሚሳውሪ ገዥ የሆኑት ጃይ ኒክሰን ሁኔታውን ለማረጋጋት የሚሳውሪን አውራ ጎዳና ጥበቃ በማጠናከር፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ለብሄራዊ የጥበቃ አባላቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የተመልካች ጥያቄም: “ይህ ድርጊት የተፈጸመው በበፋሉጃ፣ በኢራቅ  ወይስ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በፈርግሰን ከተማ ነው?”  ይህ ታምራዊ ነገር ነው!

የጥቃት ሰለባው እናት የሆኑት ሌስሌይ ስፓደን ሊደረግ የሚገባውን የእራሳቸውን ግምት እንዲህ በማለት አስቀመጡ፣ “ይህንን ሰው [የፖሊስ ኃላፊ] በቁጥጥር ስር ማዋል እና ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ማድረግ መቻል ያ ነው ፍትህ ማለት፡፡“ እ.ኤ.አ ኦገስት 18/2014 የ53 ዓመት ጎልማሳ የሆኑት ፕሬዚዳንት ኦባማ ከብራውን የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ መልኩ በአሜሪካ ውስጥ የዘር ግንኙነትን በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “አስደናቂ የሆነ እድገትን አስመዝግበናል፣ ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን በቂ የሆነ እድገት አስመዝግበናል ለማለት አያስደፍርም፡፡“ አሁንም የማርቲን ሉተር ኪንግን የ1957 ጥያቄ እንደገና ለማጤን “በእርግጠኝነት ተጨባጭነት ያለው እድገት አስመዝግበናልን?“ በወቅቱ የማርቲን ሉተር ኪንግ ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር፣ “ረዥም፣ በጣም ረዥም ጉዞ በማድረግ መጥተናል፣ ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ረዥም፣ በጣም ረዥም መንገድ ይቀረናል፡፡“

እኔ በእውነት በጣም ይደንቀኛል፡፡ በአሜሪካ ውስጥ በእርግጠኝነት “አስደናቂ የሆነ እድገት” አስመዝግበናልን? እውነት ለመናገር “ረዥም መንገድ” ተጉዘን መጥተናልን? ከዘር ግንኙነት ጋር በተያያዘ መልኩ “ትክክለኛ” ወይም ደግሞ “አስደናቂ እድገት” ለማስመዝገብ ምን ያህል እድገት ማስመዝገብ አለብን? ረዥም ጉዞ ለማድረግ ምን ያህል ጉዞ መጓዝ ይኖርብናል? በአሜሪካ እውቀትን የተላበሰ የዘር ግንኙነት እድገት ጉዞ አድርገናል ወይስ ደግሞ ታላቅ የሆነ የልዩ መሳሪያ እና ስልት ምሽግ እድገትን አጠናክረናል? የዘር ግንኙነትን በሚመለከት ረዥሙን መንገድ በተሳሳተ አቅጣጫ ተጉዘነዋልን?

ማርቲን ሉተር ኪንግ በ1957 ንግግራቸው እንዲህ ብለው ነበር፣ “የዘር ግንኙነትን በሚመለከት የእድገት ጥያቄን ያስነሳሉ ተብለው የሚጠበቁ ሶስት መሰረታዊ የሆኑ አመለካከቶች አሉ፡፡“ አንድ ሰው “ፍጹም የብሩህነት አመለካከትን ሊወስድ ይችላል፡፡ የፍጹም ብሩህነት አመለካከት ባለቤት የሆነ ሰው በዘር ግንኙነት ዙሪያ ረዥም ጉዞ በማድረግ መጥተናል በማለት ሊሞግት ይችላል፣ እናም ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በሲቪል መብት አጠባበቅ ዙሪያ አመርቂ የሆኑ ስራዎች ተሰርተዋል፣  ከዚህ አንጻር ያለው ችግር ለመፈታት ተቃርቧል በማለት ድምዳሜ ይሰጣል፡፡ ሁለተኛው አመለካከት “ፍጹም የሆነ ጨለምተኝነትን” የሚያንጸባርቅ ሲሆን በዘር ግንኙነት ዙሪያ በጣም ጥቂት የሆኑ ጥረቶች ብቻ ተከናውነዋል ይላል፡፡ “ፍጹም ጨለምተኛው” “መፍትሄ ከሰጠናቸው ነገሮች ይልቅ በርካታ ቸግሮችን ፈጥረናል” በማለት የክርክር ጭብጡን በማቅረብ በዚህ ዙሪያ እድገት ከማሳየት ይልቅ የኋልዮሽ እርምጃ ተጉዘናል ይላል፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግ ሶስተኛውን አቋም በመያዝ የእራሳቸውን ትንታኔ ይሰጣሉ፡፡ ሶስተኛው አቋም የሁለቱን ተጻራሪ አመለካከቶች ጽንፈኛ አቋም በማስወገድ እውነተኛን ነገር በማውጣት ለማስታረቅ ጥረት ደርጋል፡፡ ስለዚህም እውነተኛውን አመለካከት የያዘው ቡድን ከብሩህ አመለካከት ባለቤት ጋር ማለትም ረዥም በጣም ረዥም ጉዞ በማድረግ መጥተናል ከሚለው አመለካከት ጋር ስምምነት ያደርጋል፡፡ ሆኖም ግን ከፍጹማዊ ጨለምተኝነት ጋር ስምምነት በማድረግ ረዥም በጣም ረዥም ጉዞ በማድረግ መጥተናል ሆኖም ግን ገና የምንጓዘው ረዥም በጣም ረዥም ጉዞ ይቀረናል በማለት ሁለቱን በእኩል ዓይን ለማየት ጥረት ያደርጋል….”

እ.ኤ.አ በ2014 የማርቲን ሉተር ኪንግ “ሶስተኛው አቋም” እስከ አሁንም ድረስ ትክክለኛው አቋም እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በአዕዝርቱ ቦታ ካለው የጌቶች ቤት ጀምሮ እስከ ኋይት ሀውስ ቤት ድረስ ረዥም በጣም ረዥም ጉዞ በማድረግ መጥተናል፡፡ ወደ ቤተመንግስት ለመግባት እና የተወካዮች ምክር ቤት አባልም ተመርጠን ሆነናል፡፡ ጥቂቶቻችን ከከተማ አፓርትመንት ህንጻ በማምለጥ ወደ ከተማ ቤት እና በህንጻ መጨረሻ ላይ ስላለ ምቹ መኖሪያ ቤት ለመግባት እንሽቀዳደማለን፡፡

ሆኖም ግን በእስር ቤቱ ውስጥ ምንድን እየተደረገ ነው? በፍርድ ቤቶች ውስጥስ? በትምህርት ቤቶች ቅጥር ግቢ ውስጥስ?

እ.ኤ.አ በ1957 ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ በማለት የእውነት መሰረቶችን ጣሉ፣ “የቱንም ያህል እድገት ያስመዘገብን ቢሆንም በጥቁሮች ላይ የሚታየው ድህነት በጣም አስደንጋጭ እና አሳሳቢ ነው፡፡ አርባ ሶስት በመቶ የሚሆነው የጥቁር አሜሪካ ቤተሰቦች እስከ አሁንም ድረስ በቀን ከ2,000 ዶላር ያነሰ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው የመሆኑን ጥሬ ሀቅ መቀበል አለብን፡፡ ይህንን እውነታ በአሜሪካ ከሚኖሩ ነጮች ውስጥ 17 በመቶ የሚሆኑት በዓመት ከ2,000 ዶላር ያነሰ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከሚያገኙት ጋር ማነጻጸር ምን ያህል ልዩነት እንዳለ በግልጽ ያመላክታል፡፡ ሃያ አንድ በመቶ የሚሆኑት የጥቁር አሜሪካ ቤተሰቦች በዓመት ከአንድ ሺህ ዶላር ያነሰ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያገኛሉ፡፡ ይህንን አሀዝ ሰባት በመቶ ከሚሸፍኑት በዓመት ከ1,000 ዶላር ያነሰ ከሚያገኙት ነጭ የአሜሪካ ቤተሰቦች ዜጎች ጋር አወዳድሩት፡፡ ሰማንያ ስምንት በመቶ ጥቁር የአሜሪካ ቤተሰቦች በዓመት ከ5,000 ዶላር ያነሰ ነፍስ ወከፍ ገቢ ያገኛሉ፡፡

“ይህንን አሀዝ 60 በመቶ ከሚይዙት በዓመት ከ5,000 ዶላር ያነሰ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከሚያገኙት ነጭ የአሜሪካ ቤተሰቦች ጋር አወዳድሩ፡፡ በሌላ መንገድ ግልጽ ለማድረግ 12 በመቶ የሚሆኑት ጥቁር የአሜሪካ ቤተሰቦች በዓመት 5,000 ዶላር ወይም ከዚህ የበለጠ የነፍስ ወከፍ ገቢ የሚያገኙ ሲሆን 40 በመቶ የሚሆኑት የአሜሪካ ነጭ ቤተሰቦች በዓመት 5,000 ዶላር ወይም የበለጠ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያገኛሉ፡፡ ረዥም በጣም ረዥም ጉዞ ተጉዘናል፣ ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን የኢኮኖሚ እኩልነትን ለማምጣት ገና ረዥም በጣም ረዥም ጉዞ ይቀረናል፡፡”

ማርቲን ሉተር ኪንግ ቢኖሩ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሁለተኛውን አስርት ዓመት የዩኤስ አሜሪካንን የህዝብ ቆጠራ በመገምገም ኩራት የሚሰማቸው አልነበረም፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 27.4 በመቶ የሚሆኑ አፍሪካ – አሜሪካውያን በድህነት አራንቋ በመማቀቅ ላይ የሚኖሩ ሲሆኑ (በግምት በነጮች ላይ የነበረው የድህነት መጠን ደግሞ ሶስት ጊዜ እጥፍ ይሆናል) 39 በመቶ የሚሆኑት የአፍሪካ – አሜሪካውን ልጆች ግን ድሆች ተደርገው ተቆጥረዋል፡፡ እ.ኤ.አ ከ1983 እስከ 2010 ድረስ የነጭ አሜሪካ ቤተሰቦች አማካይ ሀብት ከጥቁር አሜሪካውያን/ት ቤተሰብ ሀብት በ6 እጅ ገደማ ይበልጥ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1963 ለነጭ አሜሪካውያን/ት ቤተሰቦች የስራአጡ ቁጥር 5 በመቶ የነበረ ሲሆን ለጥቁር አሜሪካውን/ት ቤተሰቦች ደግሞ 10.9 በመቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 ለጥቁር አፍሪካውያን/ት ቤተሰቦች የስራአጡ ቁጥር 6.6 በመቶ የነበረ ሲሆን ለነጭ ቤተሰቦች ደግሞ 12.6 በመቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ ከ1963 አስከ 2012 የጥቁሮች አማካይ የስራአጥነት መጠን 11.6 በመቶ ነበር፡፡ እንደ አሜሪካ የስራ ቢሮ አሀዛዊ መረጃ ዘገባ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2013 እድሚያቸው ከ16 – 19 ዓመት ለሆኑት አፍሪካ – አሜሪካውን ወጣቶች የስራአጥነት መጠኑ 393% ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 የነጭ ወጣቶች የስራአጥነት መጠን 12.2 በመቶ ነበረ ሲሆን የጥቁር አሜሪካውን/ት ወጣቶች ደግሞ 24.8 በመቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 52.1 በመቶ የሚሆኑት ጥቁር አፍሪካውያን/ት ልጆች በነጠላ ቤተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን የነጭ አሜሪካውያን/ት ልጆች ደግሞ 19.9 በመቶ ነበሩ፡፡ እንደ ፒው የምርምር ማዕከል ዘገባ ከሆነ   “እ.ኤ.አ በ2010 በአካባቢ፣ በስቴት እና በፌዴራል መስተዳድሮች በእስር ቤት በቀጥጥር ስር የነበሩት የነጭ አሜሪካውያን/ት ብዛት ከ100,000 ውስጥ 678 የነበሩ ሲሆን ጥቁሮቹ ግን 4,347 ነበሩ፡፡ እንደ ፍትህ ቢሮ አሀዛዊ መረጃ እ.ኤ.አ በ2010 ወደ እስር ቤት በመጋዝ መጠን ሲታይ ጥቁር አሜሪካውያን ወንዶች ከነጭ አሜሪካውያን ወንዶች 6 እጅ ብልጫ ነበራቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ1960 የነጭ ወንዶች ወደ እስር ቤት የመጋዝ መጠናቸው ከ100,000 የአሜሪካ ነዋሪዎች ውስጥ 262 የነበረ ሲሆን የጥቁር ወንዶች ደግሞ 1,313 ነበር፡፡ በአሜሪካ ውስጥ ከ18 – 24 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ጥቁር ወንዶች 7.9 በመቶ የሚሆነውን ይሸፍናሉ፣ ሆኖም ግን 2.8 በመቶ ብቻ የሚሆኑት በህዝብ ዩኒቨርስቲዎች በቅድመ ምረቃ ፐሮግራም ትምህርታቸውን ይከታተላሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 በተደረገ አንድ ጥናት ዘገባ መሰረት በፖሊስ ኃላፊዎች፣ በጥበቃ አባላት ወይም እራሳቸውን በሰየሙ ወሮበላዎች ከህግ አግባብ ውጭ ቢያንስ 313 የሚሆኑ አፍሪካ አሜሪካውያን/ት ተገድለዋል፡፡ “ይህም ማለት አንድ ጥቁር ዜጋ በደህንነት ኃላፊዎች በየ28 ሰዓት ልዩነት ይገደል ነበር፡፡“ ጥናቱ እንዳመለከተው ይህ ቁጥር በማነስ የተቆጠረ እንደሆነ ያመላክታል ምክንያቱም በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች በግድያው ወንጀል ለተሳተፉ የፖሊስ አባላት ዘር ምንነት መስፈርት የተመዘገበ መረጃ አልነበረም፡፡ በኒዮርክ ከተማ በተካሄደ ፈጣን ጥናት መሰረት 85 በመቶ የሚሆኑት ተጠርጣሪዎች ጥቁሮች እና ላቲኖች ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን 8 በመቶ ብቻ የሚሆኑት የወንጀል ፈጻሚዎች ነጮች ነበሩ፡፡ በሌላው የአገሪቱ ጫፎች ማለትም በኦክላንድ፣ በካሊፎርኒያ ኤንኤኤሲፒ/NAACP ባወጣው ዘገባ መሰረት ደግሞ እ.ኤ.አ ከ2004 – 2008 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ በከተማ ውስጥ በግድያ ወንጀሉ በተሳተፉት 45 የፖሊስ አባላት ከተገደሉት ሰዎች መካከል 37 የሚሆኑት ጥቁሮች ነበሩ፡፡ አንድም ነጭ አልነበረም፡፡ የተኩሱ አንድ ሶስተኛው ግድያን ያስከተለ ሲሆን ማንም የፖሊስ አባል በሰራው ወንጀል ተጠያቂ አልነበረም፡፡

በጥቁሮች ላይ አድልኦ በመፈጾም ላይ የተመሰረቱት የፍትህ ስርዓቱ ችግሮች የሚከተሉትን ያካትታል፡ በድንገት ማስቆም እና ምርመራ ማካሄድ፣ እንዲሁም ያለበቂ ምክንያት በጥርጣሬ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል፣ ማስፈራራት፣ ከመጠን ያለፈ እና ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ መውሰድ፣ ሙያዊ ያልሆነ ድርጊት መፈጸም፣ የዘር አድልኦ መፈጸም፣ በጥቁር ላይ መኪና መንዳት/ማስኬድ እና ስልጣንን መከታ በማድረግ ሌሎች የመሳሰሉትን የሰብአዊ መብት እረገጣዎች ማካሄድ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የፖሊስ የሰብአዊ መብት እረገጣ የተለያዩ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መሰረት ባላቸው የአፍሪካ- አሜሪካውያን/ት  የህብረተሰብ ከፍሎች ላይ ይፈጸማሉ፡፡ እነዚህ የሰብአዊ መብት እረገጣዎች “በተዋንያን፣ በፕሮፌሽናል ኳስ ተጫዋቾች፣ በኮሌጅ ተማሪዎች እንዲሁም በጥቁር ፖሊሶች ላይ ይፈጸማሉ፡፡” ይህ ወንጀል በፌዴራል አቃብያነህግ ላይም ይፈጸማል፡፡ የአገሪቱ ዋና ማዕከል ክፍል በሆነችው በጆርጅ ዋሽንግተን ከተማ በቅርቡ አንድ ዋና የፌደራል አቃቤ ህግ ከፖሊስ ጋር የገጠመውን ችግር በማስመልከት እንዲህ የሚል አቤቱታ አቅርቦ ነበር፡፡ “ከአክስቴ ልጅ ጋር በመሮጥ ላይ ነበርኩ፡፡ የፖሊስ መኪና አየተነዳ ወደ እኔ መጣ፣ በእኔ ላይም መብራቱን ማብራት ቀጠለ፣ ድምጹን ከፍ እድርጎ በመጮህ “ወዴት ነው የምትሄደው? ቁም! አለኝ፡፡ እንዴ! ሲኒማ ለማየት እየሄድኩ ነው፡፡ አሁን የኃይል ቃል በተቀላቀለበት መልኩ መልስ መስጠት ጀመረ፡፡ እኔም እንደዚሁ ማድረግ ጀመርኩ፡፡ ይህ ወዴት እንደምንሄድ የምንፈልገው አይደለም፡፡ ዝም በል፡፡ በጣም ተናደድኩ እና ከቁጥጥር ውጭ ሆንኩ፡፡ እኔን ባስቆመኝ ጊዜ የፌዴራል አቃቤ ህግ ነበርኩ፡፡ ህጻን ልጅም አልነበርኩም፡፡ የፌዴራል አቃቢ ህግ ነበርኩ፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ ፍትህ መምሪያ የምሰራ ሰራተኛ ነበርኩ፡፡ ስለሆነም እኔው እራሴ ይህንን ከመሰለ አስቸጋሪ ሁኔታ ጋር ተፋጠጥኩ፡፡”

ከህግ አግባብ ውጭ የዘፈቀደ እስራት፣ ሙያዊ ያልሆነ እና ህገወጥ የፖሊስ አስገዳጅነት ትልቅ የከተማው ችግር ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ችግር ከዚያም ባነሰ መልኩ በትናንሽ ከተሞች ተንሰራፍቶ የሚገኝ ችግር ነው፡፡ እንደ ሚሳውሪ ዋና አቃቤ ህግ መስሪያ ቤት ዘገባ የህዝብ ብዛቷ 15,865 በሆነችው ፈርግሰን ከተማ እድሚያቸው ከ16 ዓመታት በላይ የሆኑ 4,632 ጥቁሮች በፈርግሰን ፖሊስ መምሪያ እንዲቆሙ ተደርገዋል፡፡ ይህ አሀዝ በተመሳሳይ መልኩ ከነጮች ጋር ሲነጻጾር የነጮቹ ቁጥር 686 ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2013 የፈርግሰን ፖሊሶች 5,384 ሰዎችን ያስቆሙ ሲሆን 521 የሚሆኑት ደግሞ ከመኪና ትራፊክ ማስቆም ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር ስር  ሲውሉ ከእነዚህ ውስጥ 483ቱ ወይም 93 በመቶው ጥቁሮች የነበሩ ሲሆን ነጮቹ ደግሞ 36 ብቻ ነበሩ፡፡ ፈርግሰን ወደ ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው ህዝቧ (61%) ጥቁር ነው፣ ሆኖም ግን የከተማዋ ከንቲባ፣ ከስድስቱ የከተማዋ ካውንስል አባላት አምስቱ አባላት፣ ከስድስቱ የትምህርት ቤት ቦርድ አመራር አባላት አምስቱ ነጮች ናቸው፡፡ 50 አባላትን ከያዘው የፈርግሰን ፖሊስ ኃይል ውስጥ 3 ብቻ ጥቆሮች ናቸው፡፡ ዋና የፖሊስ ኃላፊው ነጭ ነው፡፡

የዘፈቀደ የህግ አተገባበር በመንገዶች ላይ ብቻ የሚጠናቀቅ አይደለም፡፡ በቀጥታ ወደ ፍርድ ቤቶች እና ወደ አቃብያነ ህግ መስሪያ ቤቶችም ሰተት ብሎ ይገባል፡፡ አንዴ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ጥቁሮች ከነጮች የበለጠ በእስር ቤት የፍርድ ጉዳያቸው ሲታይ ይቆያል፡፡ አብዛኞቹ በፍርድ ቤቱ ህግ መሰረት የሚሄዱ እና የስራ ጫና የበዛባቸው፣ የገንዝብ አቅም የሌላቸው እና የሰራተኛ ኃይልም በሌላቸው ጠበቃዎች ይወከላሉ፡፡ በካሊፎርኒያ አፍሪካ – አሜሪካውያን/ት እና ላቲኖ አሜሪካውያን/ት ተከላካዮች ተመጣጣኝ ባልሆነ መልኩ በባለ ሶስት ነጠብጣብ ህግ ይወከላሉ፡፡ “አፍሪካ – አሜሪካውያን/ት ከጠቅላላው ህዝበ 6.5 በመቶውን ይሸፍናሉ፣ ሆኖም ግን 30 በመቶ ገደማ የሚሆነውን የእስረኛ ብዛት ማለትም 36 በመቶ የሁለተኛ ደረጃ ጠቃጠቆ እና 45 በመቶ የሚሆነውን የሶስተኛ ደረጃ የህግ ጠቃጠቆ ይይዛሉ፡፡”

ከዚህ የሚቀሰመው ትምህርት ግልጽ እና ቀላል ነው፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአንድ የፖሊስ ምርመራ እና የወንጀል ተጠርጣሪ ሰው አያያዝ ጉዳይ ላይ በግልጽ እንደጠቆመው፣ “አንድ መንግስት የእራሱን ህግ ከማክበር እና ከመመልከት ውድቀት የበለጠ በፍጥነት የሚያወድም እና ህልውና የሚያሳጣ ምንም ነገር የለም፡፡“ በህግ የበላይነት ላይ ሸፍጥን ከሚጎነጉኑ እና ህጉን ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ለማስፈጸም የሸፍጥ እጆቻቸውን የደረቀ ጭራሮ አስመስለው ቃልኪዳን ከሚፈጽሙ ቃልአባይ የይስሙላ ህግ አስፈጻሚዎች የአውዳሚነት ባህሪ የበለጠ ምንም ዓይነት ነገር የህግ የበላይነትን ሊደመስሰው የሚችል ነገር የለም ለማለት እችላለሁ፡፡

በረዥሙ መንገድ እንዴት ነው ወደፊት የምንገሰግሰው?

እ.ኤ.አ በ1957 ማርቲን  ሉተር ኪንግ እድገት እንዲመጣ ከተፈለገ በርካታ ነገሮችን ማከናወን አለብን ብለው ነበር፡፡ “የምርጫ ካርድ ድምጾችን ማግኘት መቀጠል አለብን፡፡ የሰዓቱ  ጥያቄ በምርጫ ካርድ አማካይነት የፖለቲካ ስልጣንን መጨበጥ መቻል ነው፡፡“ እንዲህ በማለትም አጽንኦ በመስጠት ተናግረዋል፣ “የምርጫ ካርዶችን በብልሀት እና በአግባቡ የመጠቀም የሞራል ኃላፊነት አለብን፡፡“ በፈርግሰን ከተማ አፍሪካ – አሜሪካውያን/ት ሁለት ሶስተኛውን የህዝብ ቁጥር ያያዙ ቢሆንም እንኳ በማዘጋጃ ቤት ምርጫ ላይ ድምጻቸውን ለመስጠት ብዙም ጥንካሬ አይታይባቸውም ነበር፣ ምክንያቱም ህብረተሰቡ በአብዛኛው “ወጣት፣ ደኃ፣ ተሻጋሪ እና ከአፓርታማ ወደ አፓርታማ ለመንቀሳቀስ በዝግጅት ላይ ያለ ስለሆነ ነው፡፡” እ.ኤ.አ በ2013 በተካሄደው የማዘጋጃ ቤት ምርጫ በሁለቱም በጥቁሮች እና በነጮች የተሰጠው ድምጽ በሚያስገርም ሁኔታ በጣም አናሳ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ነጮች ከጥቁሮች ከአፍሪካ – አሜሪካውያን/ት የበለጠ በሶስት እጥፍ ድምጽ የመስጠት ዝንባሌ አሳይተው ነበር፡፡ ፈርግሰን የማርቲን ሉተር ኪንግን መርህ ለመተግበር አስገዳጅ ጉዳይ የያዘች ማለትም የድምጽ ካርዶችን በመጠቀም የፖለቲካ ስልጣኑን  ለመጨበጥ ሰዓቱ በጥቁሮች እጅ ላይ መሆኑን ያመላክታል፡፡ በፈርግሰን ከተማ የሚገኙ አፍሪካ – አሜሪካውያን/ት የእራሳቸውን መሪዎች ለመምረጥ የሚያስችሉ የድምጽ መስጫ ካርዶች ብቻ አይደሉም ያሏቸው ሆኖም ግን ከሁሉም የበለጠ ያለመምረጥ መብትም አላቸው፡፡ በሚሳውሪ የተሻሻለው ደንብ ምዕራፍ 77 ክፍል 77.650 ስር እንዲህ የሚል አንቀጽ ሰፍሮ ይገኛል፣ “በሶስተኛ ደረጃ ላይ ያለ የምርጫ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ቅሬታዎችን በማሰባሰብ በሰለጠኑ የድምጽ ሰጭዎች አማካይነት ማስወገድ ይቻላል…“ ፈርግሰን “የሶስተኛ ደረጃ ከተማ” ናት፣ እናም ፈርግሰናውያን/ት የማዘጋጃ ቤቱን ምርጫ አስፈጻሚ ኃላፊን የማባረር ህጋዊ መብት አላቸው፡፡ በዚያ ዓይነት መንገድ የማርቲን ሉተር ኪንግን ትምህርት ማስተማር እና ተጠያቂነትን በእራሳቸው አካባቢያዊ መንግስት ላይ ለመጫን ብቻ አይደለም ሆኖም ግን በፈርግሰን ላይ ያለውን አጠቃላይ የፖሊሲ ባህል መቀየር ነው፡፡ የፈርግሰን ህዝብ የድምጽ መስጫ ካርድ ጡንቻዎቻቸውን መለጠጥ ይችላሉን? የሚሳውሪ ግዛት ሴናተር ጃሚላህ ናሽድ ለሴንት ሌውስ ግዛት አቃቤ ህግ ሮበርት ማኩሎች ከሚካኤል ብራውን አደጋ ጉዳይ እራሱን ያዳነበትን መሰረት አሳማኝ ምክንያት ማለትም ፖሊስ የነበሩት የማኩሎች አባት በስራ ላይ እያሉ መገደላቸውን በመጥቀስ በድረ ገጽ ላይ የአቤቱታ ጥሪ አቀረበች፡፡ የ70,000 ሰዎችን ፊርማ ማሰባሰቧን ዘገባ አቀረበች፡፡ የእርሷ የአቤቱታ ማሰባሰብ ስራ ለድምጽ መስጠት ተግባር ከተመዘገቡት ድምጽ ሰጭዎች መካከል 25 በመቶ ያህሉን ማስፈረም ብትችል ኖሮ ከንቲባውን፣ የከተማውን ካውንስል እና የትምህርት ቤት ቦርድ አባላትን ማባረር ትችል ነበር፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ የሚል ምክር ሰጥተዋል፣ “የአገሪቱን ህግ ለማስከበር የፌዴራል መንግስቱ ያለውን ስልጣን ሁሉ እንዲጠቀም ለማሳመን ያለንን ጥረት ሁሉ እንቀጥልበታለን፡፡“ ሆኖም ግን ለፌዴራል ሲቪል መብቶች ህግ እና ከአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት አስገዳጅ ድርጊቶች በኋላ ጀምሮ ነገሮች ሁሉ በግዛቶቹ መብት አጠባበቅ ዙሪያ የተለዩ ይሆኑ ነበር፡፡ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኤሪክ ሆልደር የፈርግሰን ከተማን ጉብኝት ተከትሎ የሚከተለውን አውጀው ነበር፣ “ይህ አቃቤ ህግ እና ይህ የፍትህ መምሪያ የቆሙት ለፈርግሰን ህዝቦች ነው፡፡ የፈርግሰን ከተማ ህዝብ ሂደቱን በሚመሩት በፌዴራል ወኪሎች፣ መርማሪዎች እና አቃብያነ ህጎች ላይ እምነት ሊያድርበት ይገባል፡፡“ በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች እንቅስቃሴ እና የፌዴራል የምርመራ ሀብቶች በጋራ የማርቲን ሉተር ኪንግን ወደፊት ለመገስገስ የውጤታማ ድርጊት ትዕዛዝን ያሟላሉ፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግ እ.ኤ.አ በ1957 ለእውነተኛ እና ለትክክለኛ አመራር ሲባል ህዝቡን ከአረመኔነት ባህሪ በማውጣት ቃልኪዳን ወደ ተከበረባት፣ ነጻነት እና ፍትህ ወደ ሰፈነባት መሬት የማምጣት ቀጥታ የሆነ ፍላጎት አለ ብለው ነበር፡፡ ማሉኪ ተማጽዕኗቸውን ለፖለቲካ አመራሮች ብቻ አልነበረም ያቀረቡት ሆኖም ግን ለሞራል አመራር ሰጭዎች ጭምር እንጅ፡፡ በህብረተሰቡ እና በፍትህ ላይ ፍቅር ያላቸውን እንዲሁም ትህትና ያላቸውን እና ከግል ስግብግብነት የጸዱትን መሪዎች እንፈልጋቸዋለን ብለው ነበር፡፡ ስለማይፈለገው የአመራር ዘይቤ ዓይነት ግልጽ የሆነ ግንዛቤ ነበራቸው፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ለፖለቲካ ስራው ስኬታማነት ብቁ የሆነ ነጭም ሆነ ጥቁር ቀስቃሽ“ መሪዎች እነዚህም መሪዎች በቀላሉ ደምፍላት ውስጥ በመግባት የሚገነፍሉ፣ እና በቀላሉ ስብዕናቸውን ሸጠው ለአሽከርነት ጫንቃቸውን ያላደነደኑ፣ ለህዝብ እይታ እና አፍቅሮ ንዋይ ያላነሆለላቸው፣ እንዲሁም የእነርሱን ግላዊ ፍላጎት ለማሳካት ሲሉ የህዝቡን አጠቃላይ ፍላጎት በማፈን ለግል ፍላጎት እና ጥቅማቸው መስዋዕትነትን የሚከፍሉ መሪዎች አስፈላጊ አይደሉም ብለው ነበር፡፡ ማሉኪ የታዕይታ መሪዎችን በየአጋጣሚው በህዝብ ዘንድ ልታይ ልታይ የሚሉትን፣ ከአፋቸው ፈጣን የሆኑ ነገር ግን የተግባር ደሀ የሆኑ መሪዎች ለምንም ጉዳይ አይፈለጉም ብለው ነበር፡፡

ማሉኪ በአሁኑ ጊዜ ያለውን የእኛን የአመራር ብቃት ማነስ ፣ ማለትም በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ቆሞቀርነት፣ በግዛት ደረጃ ያለውን ስምምነት የለሽ ስርዓት እና በጠባብ ከባቢያዊ አስተዳደር የተንሰራፋውን ቅጥ ያጣ ስርዓት ቢመለከቱ ኖሮ በሀፍረት እራሳቸውን ይዘው ይጮሁ ነበር፡፡ ህዝቡን ከአረመኔነት በማውጣት፣ ነጻነት እና ፍትህ ወደሰፈነባት ወደ ተስፋዋ መሬት ለማምጣት እውነተኛ እና ትክክለኛ አመራር መፈለግ ማለት በጥንታዊቷ የግሪክ ከተማ በጠራራ ጸሐይ በእጅ የፋኖስ መብራት ይዞ በመጓዝ እውነተኛ ሰው ለመፈለግ ከተደረገው ጥረት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ያመላክታል፡፡ የእራሳቸውን መንገድ የሚያውቁ፣ ህዝቡን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ በረዥሙ መንገድ ሊመሩ የሚችሉ ህዝቡን ለነጻነት እና ለፍትህ የሚያበቁ  የተማሩ ብሩህ አስተሳሰብ እና የሞራል ስብዕና ያላቸው የፖለቲካ መሪዎች ከወዴት ሊገኙ ይችላሉ? ኦ! ከህዝቡ ጋር ፍቅር ያላቸው እና ፍትህን የሚያጎናጽፉ ትህትና ያላቸው ወጣት አሜሪካውያን/ት መሪዎች ከወዴት ይገኛሉ?

ማርቲን ሉተር ኪንግ እ.ኤ.አ በ1957 ለህዝቡ የሰላማዊ እንቅስቃሴ እና የድርጊት መርሀ ግብር ጥሪ አስተላልፈው ነበር፡፡ በዚህ የጥሪ ዕለት ወደ ዋሽንግተን በመሄድ ጸሎት ለማድረግ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ውስጥ ላለ ለማንኛውንም ነጻነት ናፋቂ ጥቁር አሜሪካዊ/ት እንዲህ የሚል ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ “እዚያ የምንሄደው ማንንም ለማስፈራራት አይደለም፡፡ እዚያ የምንሄደው እዚያ ምን እደምትሰሩ ለመንገርም አይደለም፡፡ በቀላሉ አነጋገር እዚያ የምንሄደው እስከ አሁን ድረስ ስለተደረገው ነገር አምላክን ለማመስገን እና በሌላው የሽግግር ወቀት ደግሞ ለስኬታማነታችን አምላክ እንዲያግዘን ለመለመን እና አገሪቱ በጥሩ ህሊና ለለውጥ እንድትተጋ ለመማጸን ነው… እኛ የምንታገለው ለእራሳችን ጥቅም ብቻ አይደለም፣ ሆኖም ግን እየታገልን ያለነው ለሀገሪቱ አጠቃላይ ጥቅም ነው፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግ በ2014 በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ለማንኛውም ነጻነት ናፋቂ አሜሪካዊ/ት ለነጻነት፣ ለፍቅር እና ለሰላም ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ያበረታቱ ነበር፡፡ ማንኛውም ነጻነት ናፋቂ አሜሪካዊ/ት ዘርን፣ የቆዳ ቀለምን፣ ኃይማኖት፣ ርዕዮት ዓለም እና እምነት ከግምት ውስጥ ሳይገባ ሁሉም ወደ ስደት ጸሎት እንዲገባ በማድረግ ለአገሪቱ ልዕልና፣ ሲባል ኢፍትሀዊነትን፣ ለማስወገድ ለዚህች አገር ህልውና አንድ ነገር ያደርጉ ነበር፡፡

በዚህች ዓለም ላይ በሰከነ መንፈስ ማሰብ አለብን፣ ኃይልን መጠቀም የለብንም፣

ማርቲን ሉተር ኪንግ እያንዳንዳችን ለእያንዳንችን ትክክለኛ ነገር ማድረግ አለብን በማለት የሚከተለውን ተናግረው ነበር፡፡ “የእኛ የአካሄድ መንገዶች ጥንቃቄ በተሞላበት የሞራል ስብዕና እና ክርስቲያናዊነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን እርግጠኞች እንሁን፡፡ ለበርካታ ዓመታት በህዝቡ ላይ ተንሰራፍቶ የቆየውን ኢፍትሀዊነት እና ጭቆና ስናስታውስ በእርግጠኝነት በጣም ከባድ ነገር ነው፣ ሆኖም ግን በሁኔታው መበሳጨት የለብንም፣ በዚህ መንገድ ችግሮችን መፍታት ስለማይቻል ወደ ጥላቻ ዘመቻ ለመግባት አንሞክር፡፡ ማንም በዚህች አገር ውስጥ የሚኖር ሰው ከስሜታዊነት በጸዳ መልኩ በሰከነ መንፈስ ማሰብ አለበት፡፡ ጥላቻን በጥላቻ መመለስ የሚፈይደው ነገር የለም፣ ይህ ድርጊትም ለማንም አይጠቅምም፣ እንዲያውም ጥላቻ በዓለም ላይ እንዲነግስ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ኃይልን በምንም ዓይነት መንገድ መጠቀም የለብንም፡፡ ምናልባትም አንዳንድ ጊዜ የኃይል ድርጊት ሰለባ ልንሆን እንችላለን፣ ሆኖም ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ኃይልን ለመጠቀም ሸፍጥ መስራት የለብንም፡፡ በምናካሂደው ትግል ውስጥ ኃይልን ለማስወገድ አስተማማኝ ጥረት የማናደርግ ከሆነ ገና ወደዚች ዓለም ያልመጣው ትውልድ ለረዥም እና ጨለምተኛ መራራ ሌሊት እንዲገፋ በማድረግ መጨረሻ ለሌለው እና ትርጉም አልባ ለሆነ ውርስ አውርሰን የምናልፍ ይሆናል፡፡ በምንም ዓይነት ሁኔታ ኃይልን እንደ ትግል መጠቀሚያ ስልት መውሰድ የለብንም፡፡“

ጉዳዩ ስለዘር እና ቀለም አይደለም፣ ይልቁንም ጉዳዩ ሰው በሰው ልጅ ላይ ስለሚያደርሰው ኢሰብአዊነት ድርጊት ነው፣

ኗሪነቱን በኩራት በአሜሪካ እንዳደረገ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ እና እንደ የአሜሪካ የህገመንግስት፣ የፖለቲካ ሳይንቲስት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ባለሙያነቴ በፈርግሰን ከተማ እየተካሄደ ያለው ድርጊት በቀላሉ የዘር እና የቆዳ ቀለም ብቻ ጥያቄ ነው የሚል አምነት የለኝም፡፡ የመንግስታት ስህተቶችን እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በሚመለከት የአስተሳሰብ አድማሴን ከአሜሪካ ውጭ ከፍ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ በፈርግሰን ከተማ እና በሌሎችም በአሜሪካ ግዛቶች የማስተውላቸው ተመሳሳይ አጋጣሚዎች ያለምንም ጥርጥር የዘር ጉዳይ ነው- በሰው ልጆች ዘር ላይ የሚፈጸም ኢሰብአዊነት፡፡

የሰው ልጅ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጽማቸው ኢሰብአዊነት ድርጊቶች በአሜሪካ ላይ ብቻ የሚፈጸሙ ችግሮች ብቻ ተደርገው መወሰድ የለባቸውም፡፡ ይህ በየትም ቦታ ያለ የሰው ልጆች ችግር ነው፡፡ የፖሊስ ጭካኔ በዓለም አቀፍ ኢሰብአዊነት ባህል ላይ መርዛማነትን የተላበሰ ‘ኃይል’ በተባለ እኩይ ድርጊት ላይ ነዳጅ የሚርከፈከፍበት አንድ ጉዳይ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፖሊስ መምሪያዎችን በማቋቋም የአፈና ተግባራትን የሚያካሂድ የሸፍጠኞች ተቋም ነው፡፡ የሰው ልጅ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጽመው ኢሰባዊነት ድርጊት በመጥፎ ድርጊት ተምሳሌነቱ ከሁሉም በላይ ከብዙ ሚሊዮን በፊት የሰው ዘር መፍለቂያ ከሆነችው አሁን ደግሞ የሰብአዊ መብት መቀበሪያ በሆነችው በአፍሪካ ላይ የሚገለጽ መሆኑን ስመለከት ደግሞ በሀፍረት እራሴን በእጆቸ በመያዝ ብስጭቴን ስገልጽ ልቤ ይሰበራል፡፡

እ.ኤ.አ በሜይ 2014 የኢትዮጵያ ገዥው አካል የፖሊስ እና የደህንነት ኃላፊዎች 47 ያልታጠቁ የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎችን ከሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ከአዲስ አበባ በ80 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማ ላይ ገድለዋል፡፡ በተፈጸመው ፍጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰጠው ምላሽ እና ቁጣ አናሳ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ገዳዮችን እና እንዲፈጁ ያሰማራቸውን አካል በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የማጣራት ስራ አልተጀመረም፡፡ እ.ኤ.አ በ2005 የደህንነት እና የፖሊስ ኃይሎች አሁን በህይወት በሌለው በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ቁንጮ በነበረው በአቶ መለስ ዜናዊ ግላዊ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ስር በማዋል 193 ያልታጠቁ ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ በቀን ብርሀን በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ በተኩስ እሩምታ እንዲገደሉ ሲደረግ 761 የሚሆኑት ደግሞ በጽኑ እንዲቆስሉ ተደርገዋል፡፡ እነዚህ 237 የፖሊስ ወሮበላ ገዳዮች በስም ዝርዝር የሚታወቁ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ለፍርድ ለፍትህ አካል አልቀረቡም፡፡ ለእነዚህ የግፍ ሰለባዎች ዓለም አቀፍ ጩኸት እና ለወንጀሉ ተመጣጣኝ ካሳ እንዲሰጥ የቀረበ ጥያቄ የለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የደህንነት፣ የፖሊስ እና የጦር ኃይሎች በኦጋዴን፣ በጋምቤላ እና በሌሎች የአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን ገድለዋል፡፡ የአሜሪካ መንግስት ለዘህ በደም ለተጨማለቀው እና ደም ለጠማው አገዛዝ ዋነኛ የገንዘብ እና የፖለቲካ ድጋፍ ሰጭ ቀንደኛ አጋሩ ነው!

እ.ኤ.አ ኦገስት 2012 የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ 34 በማዕድን ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ዜጎችን ማሪካና በምትባል በሰሜን ምዕራብ የደቡብ አፍሪካ በምትገኝ ግዛት ርህራሄ በጎደለው መልኩ በአረመኒያዊነት በግፍ ገደለ፡፡ በዩቱቤ ቪዲዮ የተለቀቀው እልቂት ከምንጊዜውም በላይ በድረ ገጹ ከተለቀቁት ግድያዎች በላይ አስደንጋጭ እና አስደማሚ ነበር፡፡ የማሪካና ጭፍጨፋ እ.ኤ.አ በ1960 በደቡብ አፍሪካ ሻርፕቪሌ በምትባል ቦታ ላይ በግፈኛው የአፓርታይድ ስርዓት ለተፈጸመው እልቂት ቀሪ ተቀጥላ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በቁስል ላይ እንጨት መስደድ እንደሚባለው የደቡብ አፍሪካው ዋና አቃቤ ህግ ባለስልጣን ከማሪካና እልቂት በተረፉ የማዕድን ሰራተኞች ላይ የግድያ እና ሌሎች ወንጀሎች በማለት ክስ መሰረተ፡፡ በዳርፉር፣ በላይቤሪያ፣ በሴራሊዮን፣ በመካከለኛው አፍሪካ ሬፐብሊክ፣ በማሊ፣ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፐብሊክ እና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ላይ የገዥው አካል የደህንነት እና ፖሊስ ኃይሎች ግድያ እና እልቂትን ሲያዘንቡ የዓለም ህዝብ ፊቱን አዙሮ አላየሁም በማለት ለጉዳዩ ያለውን ደንታቢስነት አሳይቷል፡፡

እኔ እንደተመለከትኩት ከሆነ ችግሩ ምርመራ ያልተካሄደበት የሰው ልጆችን ሰብአዊ መብት ሁሉ የሚያወድም የአእምሮ በሽታ ነው፡፡ ይህም ኃይል ይባላል (የመበሳጨት፣ የንዴት፣ የተስፋ መቁረጥ፣ የተስፋቢስነት፣ የክብር ማጣት፣ የኢፍትሀዊነት፣ ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሀት፣ ድንቁርና፣ ወዘተ የመሳሰሉት እኩይ ምግባራት የመጨረሻ ውጤት ነው)፡፡ ኃይል የነብስ በሽታ ነው፡፡ ኃይል አብዛኛውን የሰው ልጆች ስብዕና በቋሚ የውሸት እምነት ውስጥ የሚያስቀምጥ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ ችግሮቻችንን ሁሉ በመግደል፣ በማሰቃየት፣ የሰው ልጅ መብቶችን በመርገጥ እና ጠላቶችን በመግደል ማጥፋት ይቻላል የሚል እምነት እንዲኖረን የሚያደርግ ነው፡፡

ኃይል ጠብመንጃዎችን አንደናመልክ ያደርገናል፡፡ የጠብመንጃ የበላይነት በተለያዩ ቦታዎች የህግ የበላይነትን ግብዓተ መሬት እያስገባ ነው፡፡ የፖሊስ ኃይላችንን በብረት ለበስ እና ግዙፍ ተሽከርካሪዎች፣ ጠብመንጃዎች፣ የሌሊት መነጽሮች፣ የእጅ ቦንቦች እና ሌሎች መሳሪያዎችን ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ወታደራዊ ክምች ጋር የጦር መሳሪያዎችን በማግኘት ወታደራዊ ኃይላችንን በማጠናከር ላይ እንገኛለን፡፡

ኃይል ጥቃት ፈጻሚዎችን በኃጢያት ስራዎች ላይ የበላይነትን በመቀዳጀት ዓለምን በሙሉ ያሽከረክራል፡፡ ለእዚያ የአዕምሮ በሽታ ፈውስ መድኃኒት እንፈልጋለን ምክንያቱም ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳስተማሩን “ኃይል ማጥፋት የሚፈልገውን ለማጥፋት ያለመ የቁልቁለት መንገድ ነው፡፡ ኃይል ጭራቃዊነትን ለማጥፋት በሚል ሰበብ እራሱን ያባዛል፡፡ ኃይልን በመጠቀም ውሸታምን ሰው መግደል ይቻላል ሆኖም ግን ውሸት እራሱን መግደል ወይም ደግሞ እውነትን ማበልጸግ ከቶውንም አይቻልም፡፡ ኃይልን በመጠቀም ጥላቻ ፈብራኪውን መግደል ይቻላል ሆኖም ግን ጥላቻን እራሱን መግደል አይቻልም፡፡ በእርግጥ ኃይል በእራሱ ብቻ ጥላቻን የመፍጠር ሀይሉ ያነሰ ነው፡፡ ኃይልን በኃይል መመለስ ከዋክብት ያልነበሩበትን ሰማይ የበለጠ በጨለማ እንዲዋጥ በማድረግ የጨለማውን ይዘት የበለጠ በመጨመር ኃይልን ያባዛል፡፡ ስልጣን ከጠብመንጃ አፈሙዝ የሚገኝ ሳይሆን ከህዝቦች ፍላጎት የሚመነጭ ነው፡፡

ፖሊሶች AK-47ን፣ የኡዚን፣ M-16ን እና ለስራው የሚያስፈልጉ ሌሎች መሳሪያዎችን በመጠቀም አደንዛዥ ዕጽ አከፋፋዮችን እና ዋሮበሎችን፣ የባንክ ዘራፊዎችን እና ሌሎች ሃላፊነት የማይሰማቸውን ዘፈቀደዎች መጋፈጣቸውን ማቃለል አይቻልም፡፡ በጥቂት ስህተት ፈጣሪ ፖሊሶች ሰበብ ሁሉንም የፖሊስ አባላት መውቀስ ተገቢ አይደለም፡፡ በአሜሪካ የመኖሪያ ቤቶች እና መንገዶች በመቶዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጠብመንጃዎች ከመኖር አንጻር ፖሊሶች በአንድ ወቅት በሙያቸው ላይ የጠብመንጃ ኃይል ሰለባ በመሆን ለችግር ሊዳረጉ እንደሚችሉ ምክንያታዊ የሆነ ግምት አላቸው፡፡ በአመክንዮ የሚያምኑ ሰዎች ፖሊስ ቀላል የሆነ ስራ እንደሌለው ይስማማሉ፣ ይልቁንም በጣም ፈታኝ የሆነ ስራ እንዳለቸው አይካድም፡፡ ሆኖም ግን ዋናው ቁም ነገር ማንም ፖሊስ ቢሆን እስከ አሁን ድረስ የሰላም ኃላፊነት ቀላል ስራ ነው ብሎ ፊርማውን ያስቀመጠ የለም፣ ምክንያቱም ቀላል ስራ አይደለምና ፡፡ አንዳንደ ሰዎች በሚያድርባቸው ጥላቻ እና ግላዊ ስግብግብነት እኩይ ምግባራትን ለመፈጸም የፖሊስን ሙያ ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ ጥርጥር የለኝም፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ፖሊሶች የፖሊስ ባጅ ለመግደል፣ እና ያዋረዷቸውን ሰዎች መብት ለመደፍጠጥ እንደ ፈቃድ ይጠቀሙበታል፣ ነገር ግን ሰላም በህዝቡ ዘንድ ጣታቸውን በሚቀስሩ ጥቂት ፖሊሶች ጥረት ብቻ የሚመጣ አይደለም፡፡ ማንኛውም የፖሊስ ኃላፊ “ለመከላከል እና ለማገልገል” በሚል መርህ ላይ ተመስርቶ ህይወቱን መግፋት አለበት፡፡

እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዩኤስ አሜሪካ ያለው የፖሊስ ባህል፣ የፖሊስ አካዳሚው ስርዓተ ትምህርት እና አጠቃላይ የፖሊስ ህብረተሰብ አዕምሯዊ ዝግጁነት  የደኃውን ህብረተሰብ  የቆዳ ቀለም በተለይም በከተሞች አካባቢ የሚኖሩትን ህዝቦች፣ የጦርነት ቀጣናዎችን እና ሽብርተኛ ለመሆን የሚችሉትን በልዩ የጥበቃ ቡድን አባላት እና በአልሞ ተኳሾች አስቀድሞ በመዘጋጀት ለመጠበቅ እንዲችል ያበረታታዋል፡፡ ከዚህም አንጻር በሚጠብቁት ህብረተሰብ መካከል የማይኖሩት የፖሊስ ኃይል ኃላፊዎች በፍርሀት እና በጭንቀት ይኖራሉ፡፡ ለደኃ ህዝቦች የፖሊስ ጥበቃ ከማድረግ ይልቅ ህብረተሰቡን መጠበቅ የስልት ችግር ይሆናል፡፡ በቆዳ ቀለም ተለያይቶ መኖር  ወንጀል መሆኑ በህግ እስካልተረጋገጠ ድረስ ወንጀል ሊሆን አይችልም፡፡ እንደስልት አካሄድ ፖሊስ በመጀመሪያ ተኩሶ ይገድላል፡፡ ከዚያም በኋላ ምላሽ መስጠት ይጀምራል፡፡ መልሱም በህብረተሰቡ የፖሊስ ጥበቃ (የህዝብ ደህንነት ችግሮችን ለመፍታት በህብረተሰብ- ፖሊስ አጋርነት) የተፈጸመ እንጂ በተደራጀ የፖሊስ ኃይል የተደረገ አይደለም ይባላል፡፡ መልሱ በአሁኑ ጊዜ በዘር ላይ የተመሰረተውን የፖሊስን ባህል ለማበላሸት እና በሰው ልጆች ክብር እና ጥበቃ ላይ እንዲመሰረት ለማስቻል ነው፡፡ መልሱ በእውነታ ላይ የተመሰረተ (ፍትሀዊ እና የተሟላ ምርመራ) እና እርቀ ሰላም በማውረድ ላይ (ፖሊስ እና ህብረተሰቡን በአንድ መድረክ ላይ አድርጎ ለበርካታ ዓመታት እና አስርት ዓመታት የተከሰቱ ቅሬታዎችን እና ሀሜቶችን ለማስወገድ በመወያየት እንዲሁም ፖሊስ እና ህብረተሰቡ ወደፊት እንዴት ባለ የተቀናጀ እና መግባባት ባለበት ሁኔታ አብረው መጓዝ እንዳለባቸው) የሚያመላክት ዘዴ ነው፡፡ አንድን የፖሊስ አባል ከስሶ በህግ ፊት ማቅረብ ብቻውን በቂ አይደለም፣ ይልቁንም አጠቃላይ የፖሊስ መምሪያው ለህዝቡ ተጠያቂ እንዲሆን ማስቻል ዋናው መልስ ነው፡፡ ለስነ ልቦና ለውጥ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅም ዋናው አብይ ጉዳይ ነው፡፡ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉት ሁሉም የህበረተሰብ አካላት የፖሊስ መምሪያውን የሚቆጣጠሩና እና የሚይዙ እንደሆኑ እንዲሰማቸው ማድረግ እና ፖሊስ ህብረተሰቡን ለመውረር በእራሱ በህብረተሰቡ ላይ በኃይል የተጫነ እንዳልሆነ በህዝቡ ዘንድ ግንዛቤ እንዲያዝ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

ከጠላቶቻችን ጋር ተገናኝተናል፣

ተከታታይነት ያለውን የካርቱን ጨዋታ ባለሙያ የሆነውን የፖጎን አባባል በመዋስ “እኛ ህዝቦች ጠላቶቻችንን አግኝተናል፣ ጠላቶች እኛው እራሳችን ነን“ በሚለው ላይ እምነት አለኝ፡፡ መልስ ልንሰጥባቸው የሚገቡ ጥያቄዎች ግልጽ ናቸው፡፡ በጠላት ላይ ጦርነትን በማወጅ ሰላምን ማምጣት ይቻላልን? ጠላቶቻችንን ማሸነፍ የምንችለው በመውረር እና በማጥቃት ነው ወይስ ደግሞ ቀረብ ብለን እንዲጽናኑ እና ካሳም እንዲያገኙ በማግባባት ነው? ከጠላት ጋር እርቀ ሰላም በማውረድ እና ጓደኛ በማድረግ ነው ሰላም የሚመጣው ወይስ ደግሞ ጠላትን በኃይል አንበርክኮ በማሸነፍ እና የተነገረውን ብቻ እንዲፈጽም በማድረግ?!

እ.ኤ.አ በ2009 በጥቁር ህዝቦች የታሪክ ወር ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፣ “ይህች ሀገር በማሰሮ ውስጥ ተጥዶ በሚፈላ የጎሳ ፖለቲካ እና ዘርን መሰረት ባደረገ ፍልስፍና ላይ እራስን በኩራት ኮፍሶ የነገሮችን ሂደት እንዲቀጥሉ መመልከት ማለት ይህች ሀገር የፈሪዎች እና የቦቅቧቆች አገር እንደሆነች እገነዘባለሁ፣ እምነቴም ይኸው ነው፡፡ አሜሪካውያን/ት አሁንም ቢሆን አሜሪካ የነጻነት መሬት እና የጀግኖች መኖሪያ መሆኗን ማሳየት አለባቸው፡፡ እውነተኛው ጥያቄ ግን የምን ጀግና አሜሪካዊ/ት-ነጩ፣ ጥቁሩ፣ ቡናማው፣ እና ሌሎችም በዚህ መካከል ያሉ- ጠላቶቻቸውን ሲያገኙ በዚህ መልክ ምላሽ የሚሰጡ ናቸው፡፡ ጀግኖች አሜሪካውያን/ት በጠላቶቻቸው ላይ ምን መወሰን እንዳለባቸው የሚወሰነው እንደ ህዝብ እና እንደ ሀገር ለፍትህ በምናደርገው ረዥም ጉዞ ወይም ደግሞ እንደ ተለዋጭ የተቃርኖ ሀሳብ በአምባገነናዊ ጥላቻ፣ ስምምነት ማጣት እና ግጭቶችን በመፈብረክ የለት ከዕለት ተግባር በማድረግ ነው፡፡ ምርጫው ለእያንዳንዱ/ዷ አሜሪካዊ/ት የተተወ ነው፡፡ ምርጫው በእያንዳንዱ/ዷ አሜሪካዊ/ት ፊት ቆሟል፡፡ ጆን. ኤፍ ኬነዲ እ.ኤ.አ በ1963 የሲቪል ማህበረሰብ መብትን በማስመልከት “ለሰላማዊ አብዮት” ጊዜው አሁን ነው“ በማለት የሚከተለውን ንግግር አድርገው ነበር፣

የንዴት እና የጥላቻ እሳቶች በእያንዳንዱ ከተማ ይንቀለቀላሉ፣ የህግ መፍትሄዎች በእጅ በሌሉባቸው በሰሜን፣ በደቡብ፡፡ በዋና ዋና መንገዶች በሰላማዊ ሰልፍ፣ በሰልፍ እይታ እና በተቃውሞ ውጥረት በመፍጠር ፍራቻን በማንገስ እና ለህይወት አደጋን በመጋበዝ የኋልዮሽ ጉዞ ይፈለጋል፡፡ ከዚህ አንጻር እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ በሞራል ስብዕና ቀውስ ውሰጥ ተዘፍቀናል፡፡ ጉዳዩ በጨቋኝ የፖሊስ የጋጋታ እርምጃ ሊቋጭ የሚችል አይደለም፡፡ በመንገዶች ላይ በሚደረግ የተጠናከረ ሰላማዊ ሰልፍ እልባት እንዲያገኝ የሚተው አይደለም፡፡ በይስሙላ እንቅስቃሴዎች እና ንግግሮችም ጸጥ የሚል ጉዳይ አይደለም፡፡ በየግዛታችሁ እና በአካባቢያዊ የህግ ማዕከሎች ከዚህም በላይ በዕለት ከዕለት ህይወታችን ላይ ኮንግረሱ ተጨባጭነት ያለው እርምጃ የሚወስድበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ኃላፊነቱን ወደ ሌሎች ማላከክ በቂ አይደለም፣ ይህ ችግር የአንድ የሀገሪቱ ክፍል ወይም የሌላ አለዚያም ደግሞ የተጋረጡብንን ችግሮች ፊት ለፊት በመጋፈጥ መፍትሄ የሚገኝላቸው እና በቀላሉ የሚፈቱ አይደሉም፡፡ ታላቅ ለውጥ ከእጃችን ላይ ይገኛል፣ እናም የእኛ ተግባር እና ግዴታ ያንን አብዮት ያንን ለውጥ ለሁሉም ዜጋ ሰላማዊ እና ገንቢ በሆነ መልኩ ማካሄድ ነው፡፡ ምንም የማያደርጉ ሀፍረትን እንዲሁም ኃይልን ይጋብዛሉ፡፡ ነገሮችን ድፍረት በተቀላቀለበት መንገድ የሚያደርጉ ደግሞ መብትን እና እውነትን መሰረት ያደርጋሉ፡፡

እድገት ማለትወደ ኋላ ሄዶ ወደፊት መራመድማለት ነው፣

እ.ኤ.አ በ1954 ማሉኪ “ወደ ኋላ ሄዶ ወደፊት መራመድ” በሚል ርዕስ በአል ሞንተጎመሪ ቤተክርስቲያን በዴተር ጎዳና ረዥም እና አድካሚ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የእኛ ትልቁ ችግራችን በሳይንሳዊ ምርምር ልቀታችን ዓለምን በሙሉ አንድ ጎረቤት እንድትሆን አድርገናል፣ ሆኖም ግን በሞራል ስብዕና ልቀታችን ዓለምን ወንድማማች እና እህትማማች ማድረግ ተስኖናል፡፡ እናም በአሁኑ ጊዜ የተደቀነብን ታላቅ አደጋ በአውሮፕላን ጭነን በመቶዎች እና በሺዎች ንጹሀን ዜጎች ላይ እንደ በረዶ የምናዘንበው አቶሚክ ቦምብ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ልንፈራው የሚገባን አቶሚክ ቦምብ በሰዎች ልብ እና አእምሮ ውስጥ የተዳፈነውን እና ከመቅጽበት በመፈንዳት ወደ ጥላቻ የሚሸጋገረውን እንዲሁም አደገኛ ጉዳትን ሊያስከትል የሚችለውን እራስ ወዳድነትን ነው…“ እንዲህ ሲሉም አስጠንቅቀው ነበር፣ “በአሁኑ ጊዜ የእኛ ስልጣኔ ወደፊት የሚራመድ ከሆነ ወደ ኋላ መመለስ አለብን፣ እናም ከዚህ ቀደም ጥለናቸው የመጣናቸውን በጣም ውድ እና አስፈላጊ የሆኑትን የሞራል ስብዕና እሴቶች ፈልገን መያዝ አለብን…“

ምንም በማያጠራጥር መልኩ አሜሪካ በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ እጅግ ተደናቂ የሆነ እድገትን አስመዝግባለች፣ እንዲሁም ደግሞ አመርቂ የሆነ ታላቅ የኢኮኖሚ እድገትን አምጥታለች፡፡ ሆኖም ግን እንዴት እና በምን ዓይነት ሁኔታ ነው እርስ በእርሳችን እንደምንግባባ እና እንደምንፈቃቀር የሚያግዝ የሞራል ስብዕና እድገትን ለማስመዝገብ ትግል ማካሄድ የምንችለው? ከዓለም እጅግ ታላቅ የሆነውን፣ የገንዘብ፣ የሳይንስ፣ የትምህርት እና የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ገንብተናል፡፡ ነገር ግን የወንድሞቻችንን እና የእህቶቻችንን ደህንነት ጠባቂ ለመሆን ገና ረዥም በጣም ረዥም ጉዞ መጓዝን ይጠይቀናል፡፡

በመሬት ላይ ያለ የሰው ልጅ ዘር ሁሉ እራሱን ከእራሱ መጠበቅ አለበት፡፡ እንደዚህም ሆኖ በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ ተስፋ በቆረጠ መልኩ የእራሱን ዘር ለማጥፋት የተዘጋጀ ይመስላል፡፡ የሰው ልጅ ሰብአዊነትን በመላበስ የፍቅር ህይወትን ማጣጣሙን እንጅ እርስ በእርሱ መተላለቁን ማቆም አለበት፣ እናም “ለዘመናት ያከማቻቸውን ጎራዴዎች እና የጦር ፍላጻዎች  ወደ ማረሻ እና የአትክልት ማስተካካያ መሳሪነት መቀየር አለበት፡፡“ እርስ በእርሳችን ጥላሸት እየተቀባባን ሰብአዊነትን ልናራምድ ከቶውንም አንችልም፡፡ ሰብአዊነቱ በተዋረደ ህዝብ ላይ በጣም አናሳ የሆነ የሰብአዊነት መንፈስ ብቻ ነው የሚቀረው፡፡ በሰው ልጅ ዘር ላይ አንድ አሸናፊ ብቻ ነው ሊኖር የሚችለው – ሴት/ወንድ ወይም ደግሞ ሁሉም የሰው ዘሮች ተሸናፊዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሰው ልጅ በሰው ልጅ ላይ የሚያደርገውን ኢሰብአዊነት ድርጊት ለማስቆም ሚሊዮን ያህል የተለያዩ መንገዶችን መፈለግ አለብን፡፡ ሌላው አማራጭ በሮበርት በርነስ የግጥም ስንኞች ላይ እንደሚከተለው ቀርቧል፣

ብዙ እና ስለት ብዙ ጎጂ ካራዎች፣

ከእራሳችን መቅን አጥንት ጋር የተዋሀዱ ማረጃዎች፤

እራሳችንን ብዙ ስለታማ የአረብ ብረቶች አድርገን፤

በጸጸት፣ በጥፋተኝነት  እና ሀፍረት ስሜት ተጀቡነን!

እናም ሰው ቀጥ ብሎ የቆመ የእርሱ ሰማየ ገነት፤

የፍቅር ጣዕም ፈገግታ የልብ ብሩህነት የማይታይበት፤

የሰው ልጅ በሰው ልጅ ላይ የሚያሳየው ኢሰብአዊነት እና ኃይል፤

በሺዎች እና ለቁጥር ለሚያዳግቱ ሀዘኖች ይዳርጋል፡፡

እ.ኤ.አ በ1957 ማርቲን ሉተር ኪንግ ሴንት ሌውስ ስለዘር ግንኙነት አገሪቱን ልታስተምር ትችላለች በማለት ተናግረው ነበር፡፡ እንደዚሁም ደግሞ እ.ኤ.አ በ2014 የፈርግሰን ከተማ ህዝብ ለአሜሪካ ህዝብ በርካታ ነገሮችን ሊያስተምር እንደሚችል ተናግረው ነበር፡፡ የፈርግሰን ህዝብ እጃቸውን አውጥተው አትግደሉን ሲሉ እንዲሁም የፈርግሰን ከተማ ፖሊስ ለፈርግሰን ህዝብ የሰላምታ እጃቸውን ሲዘረጉ ትምኅርቱ  አንደተጀመረ አውቃለሁ፡፡

በስደተኛነት መነጽር አሜሪካንን ስመለከታት የተባበሩት የአሜሪካን ግዛቶችን ብቻ አላይም ፡፡ አያየሁ ያለሁት ለሰብአዊነት የተባበሩ ህዝቦችን ነው፡፡ ሰዎችን ከእያንዳንዱ አገር ማዕዘን እና መሬት ከምትባለዋ ፕላኔት የፖለቲካ እና የኃይማኖት ስቃይን ለማምለጥ ወይም ደግሞ የተሻለ የኢኮኖሚ ዕድል በማግኘት ህይወትን ለመምራት ወደ አሜሪካ በመምጣት ጥገኝነትን ሲጠይቁ አያለሁ፡፡ ከእኔ በፊት እንደነበሩት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጥገኝነትን የሚሹ ዜጎች ሁሉ እኔም “ከተሰባሰቡት ህዝቦች” መካከል “ነጻ አየርን ለመተንፈስ” ወደ አሜሪካ በመምጣት እስከ አሁን እዚሁ እገኛለሁ፡፡

በዓለም ላይ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ከሰብአዊ መብት ጥበቃ ጋር በተያያዘ መልኩ ወደአሜሪካ እጅና አግራቸውን ቆርጠው ሰጠው ቢመጡ አይቀፋቸውም፡፡ በማአሪካ ብዙ ችግሮች አሉብን፣ አጅግ በጣም በርካታ ችግሮች፡፡ ሆኖም ግን ውስብስብ ችግሮቻችንን በኋይት ሀውስ፣ በሴኔቱ ጽ/ቤት፣ በኮንግረሱ አዳራሽ ወይም ደግሞ በዩኤስ ጠቅላይ የንግድ ምክር ቤት አካላት ልንፈታቸው አንችልም፡፡ ለችግሮቻችን መልስ ሊሆኑ የሚችሉት መልሶች ሁሉ በልብ የጓዳ ክፍሎቻችን ታጭቀው ይገኛሉ፡፡ መሰረታዊ የሆኑ እሴቶቻችንን (አብዛኛውን ጊዜ የምንሰብካቸውን ሆኖም ግን ባነሰ መልኩ የምንተገብራቸውን) በመጠቀም እና በዘረኝነት፣ የውጭ ዜጎችን እና ባህላቸውን በመፍራት፣ በዘር እና በኃይማኖት ጽንፈኝነት ላይ እና በሌሎች በልቦቻችን እና በአዕምሯችን ጓዳ ውስጥ ተደብቀው ባሉት እኩይ  ምግባራት ላይ ነጻነትን ማወጅ አለብን፡፡ ከዚያም “እውነተኛይቱን ዓለም ማምጣት” እና “እነዚህ እውነታዎች በእራስ መስካሪ እንዲሆኑ ሁሉም ወንዶች እና ሴቶች እኩል ሆነው ተፈጥረወል…“

እ.ኤ.አ በ1957 ማሉኪ “በእርግጠኝነት እድገትን አስመዝግበናልን?“ የሚል ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡ በ2014 ላይ የእኔ ምላሽ ተከታታይነት ያላቸው በርካታ ጥያቄዎችን ያስከትላል፡ የእድገት ትክክለኛ መለኪያው ምንድን ነው? በኢኮኖሚ እና በፖለቲካው መስክ ምን ያህል ርቀት ተጉዘን መጥተናል ነው ? በልቦቻችን እና በአዕምሮዎቻችን መካከል ያሉትን ክፍተቶች ለማጥበብ ምን ያህል እድገቶች እንደተመዘገቡ መለካት ስንችህል ነው? ጥላቻ በልቦቻችን እና በአዕምሯችን መካከል የፈጠረውን የባህር ሰላጤ ስንገድብ ነው? እውነተኛው የእድገት መለኪያ ከልቦቻችን እስከ አዕምሯችን ድረስ የተዘረጋውን ረዥሙን መንገድ በፍቅር ለማስተሳሰር በተገነቡት ድልድዮች ብዛት ሊለካ አይችልምን? ትክክለኛው የእድገት መለኪያ እንደ አሜሪካ ዜጋ ረዥሙን መንገድ በመጓዝ ምልኡነት የጎደላትን ዓለም የተሟላች እና ለሁሉም የሰው ልጅ ዘር የተመቸች ለማድረግ ከሚደረገው ተነሳሽነት ጋር በማማያያዝ መለካት የለበትምን?

=========

“ ይህንን ጉዳይ ገና ህጻን በነበርኩበት ጊዜ እሰራው ነበር፡፡ በ 90 አመቴ  ይህን አረጋለሁ ብዬ ኣላስብም ነበር ፡፡  ስለሆነም ለድል ለመብቃት አሁኑኑ መነሳት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ሰዎች የ90 ዓመት እድሜ ካስቆጠሩ በኋላ ሊሰሩት አይችሉምና”  ሄዲ ኤፕስተን የ90 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ እና ከናዚ እልቂት በታምር ተርፈው በሴንት ሌውስ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተገኙ አዛዉንት

“እኔ ሰላምን እመርጣለሁ፡፡ ሆኖም ግን ችግር የሚመጣ መሆኑ ከተረጋገጠ እና የማይቀር ከሆነ በእኔ የህይወት ዘመን እንዲመጣ እመኛለሁ፣ በመሆኑም የእኔ ልጆች ያለምንም ችግር በሰላም መኖር ይችሉ ዘንድ::“ ቶማስ ፔን

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ነሐሴ 20 ቀን 2006 ዓ.ም