የወያኔ ወሮበላ ዲፕሎማሲያዊነት፣


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩ በጠረጴዛ ውይይት እና የሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካ በመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትና በማድረግ በንጹሀን ዜጎች ደም ላይ ተረማምዶ የጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞ ከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በኃይል በህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘው የሽፍታ ቡድን የበላይነት የሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት አምባገነን እና አረመኒያዊ ስብስብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስገልጽ ቆይቻለሁ፡፡ ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊ አስተዳደር ከሆነ የወሮበላ አገዛዝ መንግስት ደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እና ለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያ ቡድን ነው፡፡ 

በዚህች ትችቴ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እያራመደ ያለውን የሀገር ውስጥ የዲፕሎማሲ ፖሊሲ ለመቃኘት አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ትኩረት በማድረግ ለመዳሰስ የምሞክረው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የተባለው የወሮበላ ስብስብ ቡድን በማራመድ ላይ ያለውን ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ፖሊሲን ለመቃኘት ነው፡፡ በቅርቡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ አረመኒያዊ እና ግልብ መንፈስ የተጠናወተው አንድ የጦር መሳሪያ ታጥቆ ኢትዮጵያውያን/ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ተኩሶ ለመግደል በርካታ ጥይቶችን ሲተኩስ የነበረውን እና ለግድያ ሀራራው ሳይሳካለት የቀረውን የወያኔ ወኪል ለመግለጽ የወሮበላ ዲፕሎማሲ እና የወሮበላ ዲፕሎማት የሚሉትን ቃላት እጠቀማለሁ፡፡ 

እንደ ሬውተርስ የዜና ወኪል አገላለጽባለጠመንጃው ሰውእየተባለ ይጠራ የነበረው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንደጅብራ ተገትሮ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ለማቅረብ ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ በሄዱት በንጹሀን ኢትዮጵያዊያን/ ዜጎች ላይ ሲተኩስ የነበረው በስም ሰሎሞን ታደሰ ገብረስላሴ የተባለው የወያኔ ባለሙሉ ስልጣን የደህንነት አታሼ ነበር፡፡ .. ሴፕቴምበር 29/2014 የተደረገው የሰሎሞን ገብረስላሴ አስደንጋጩ እና አሳፋሪው የእሩምታ ተኩስ ጉዳይ በዓለም አቀፉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ በክብር እና ሞገስ ሳይሆን በቅሌት እና በውርደት፣ በጥበበኛነት እና በምሁርነት ሳይሆን በጅላጅልነት እና በደንቆሮነት፣ በታጋሽነት እና በአርቆ አስተዋይነት ሳይሆን በግልፍተኝነት እና በቅርብ አሳቢነት ሲታወስ ይኖራል፡፡ 

እንደ ሬውተርስ የዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነየዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ቃል አቀባይ ከቀኑ 1215 ሰዓት በሰሜናዊ ምዕራብ ዋሺንግተን . በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተኩስ እንደተሰማ ፖሊስ በስፍራው በመገኘት ተኳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ እስር ቤት ልኮታል፡፡ የዓይን እማኞች እንደገለጹት ከሆነ የጥይት ተኩሱ የተከናወነው ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ በተጠጉ ጊዜ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ብለዋል…“ 

“የወያኔን ኤምባሲ መውረር” 

በሰላማዊ ተቃዋሚዎች የተወሰዱ በርካታ የቪዲዮ ክሊፖች እንደሚያስረዱት እና የኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን/ኢሳት አገልግሎት እንዳመለከተው በቅርቡ በኢትዮጵያ በኦጋዴን እና በጋምቤላ ክልሎች በወያኔ ገዥ አካል ታጣቂዎች በንጹሀን ዜጎች ላይ የተወሰደውን አረመኒያዊ ጭፍጨፋ እና ግድያ በማስመልከት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ተቃውሟቸውን ለመግለጽ እና የወያኔው አምባሳደር ከሆኑት ከአቶ ግርማ ብሩ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ የፊት ለፊት ውይይት ለማድረግ በሄዱት የሰላማዊ ተቃዋሚ ቡድን ግለሰቦች ጥያቄ ማቅረብ ምክንያት ነበር፡፡ 

አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ ከወሰደው የቪዲዮ ክሊፕ እንደሚታየው ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በመጀመሪያ ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ ለመግባት ሲያደርጉ የነበረውን ሁኔታ በግልጽ ያመለክታል፡፡ የተወሰደው የቪዲዮ ምስል የተሰባሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በኤምባሲው ቅጥር ግቢ በመግባት በግቢው ውስጥ ባለ መቀመጫ ቦታ ላይ የደረሱ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ የኤምባሲው ሰራተኞች ለደህንነት ተብሎ ከታጠረው መስታወት በስተጀርባ ሆነው በመመልከት ላይ ነበሩ፡፡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች አምባሳደሩን ማነጋጋር እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ በርካታዎቹ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ጩኸት በማሰማት መፈክሮችን ያስተጋቡ ነበር፡፡ ከመካከላቸው አንዱ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ይህ የወያኔ ኤምባሲ እንጂ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አይደለም፡፡ሌላኛው ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረበ፣ከአቶ ግርማ ብሩ (ከወያኔው አምባሳደር) ጋር ለመነጋገር እንፈልጋለን፡፡ ከእርሳቸው ጋር ስለኦጋዴን፣ ጋምቤላ እና ስለአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ መወያየት እንፈልጋለን፡፡ሌሎች ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ደግሞ የአንዳርጋቸው ጽጌ (ከጥቂት ወራት በፊት በወያኔ ገዥ አካል ከየመን ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ ከተወሰዱት የግንቦት 7 የአመራር አባል) ምስል ያለበትን ቲሸርት በመልበስ እርሳቸው ከእስር እንዲፈቱ ሲጠይቁ ነበር፡፡ ሌላ አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ ደግሞ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣እስክንድር ነጋ (በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው እና  በወያኔ ገዥ አካል 18ዓመታት እስራት ተበይኖበት በአሁኑ ጊዜ ቃሊቲ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት በመማቀቅ ላይ የሚገኘው) ጋዜጠኛ ይፈታሌላው ማንነቱ በውል ያልታወቀ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህ በማለት ጨኸት ሲያሰማ ነበር፣በጎሳ ክፍፍል አገዛዝ ታመናል፣ እናም ሰልችቶናልበግልጽ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣በእንደዚህ ያለ ወሮበላ አገዛዝ እስከ መቸ ድረስ ነው ስንገዛ የምንኖረው? እኛ ታመናል፣ እናም በዘራፊዎች እና በወሮበሎች መገዛት ሰልችቶናል!“    

በኢሳት የተወሰደ የቪዲዮ ምስል እንደሚያሳየው ሁሉም ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዙት ነገሮች ሁሉ ከኤምባሲው ቅጥር ግቢ የተከናወኑ መሆናቸውን ነው፡፡ ከአራት ሰላማዊ አመጸኞች መካከል አንደኛው የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ የያዘ ሲሆን ጥቁር ልብስ ወደ ለበሰው እና መሳሪያ ወደታጠቀው ገብረስላሴ የሚባል የኤምባሲው አታሼ ሲቀርብ ያሳያል፡፡ ወዲያውኑም ገብረስላሴ በማነጣጠር ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች አቅጣጫ መተኮስ ጀመረ፡፡ ሆኖም ግን ዒላማውን ስቷል፡፡ ሰላማዊ አመጸኞች ያለምንም ፍርሀት ወደ ገብረስላሴ መቅረብ ጀመሩ፡፡ ማንነቱ በውል ያልታወቀ አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ እንዲህ በማለት ድምጹን ከፍ በማድረግ በድጋሜ ጩኸቱን ማሰማት ጀመረ፣እኛ ወንጀለኞች አይደለንም፣ ግርማ ብሩን ጥሩልን፣ ከእርሳቸው ጋር ለመነጋገር እንፈልጋለን፡፡ሌላው ሰላማዊ ተቃዋሚ ገብረስላሴን በድፍረት እንዲህ ይለው ነበር፣ወደ ፊት ቀጥል፡፡ ተኩስ!“ በዚህን ጊዜ ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በማነጣጠር እነርሱን ስሜታዊ እንዲሆኑ በመገፋፋት ወደ ኤምባሲው ዋና ህንጻ በመግባት የሽሽት ሙከራ ማድረግ ጀመረ፡፡ በዚህ ሂደት ላይም ገብረስላሴ ሽጉጡን ወደ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በመደገን በተደጋጋሚ ለማስፈራራት ሞከረ፡፡ በመጨረሻም ጥይቶቹን በሙሉ ተኩሶ ስለጨረሰ ሽጉጡ ጥይት አልባ በመሆን የባዶ ሽጉጥ ድምጽ ሲያቃጭል ይሰማ ጀመር፡፡ ባለመሳሪያው እብሪተኛ ደንቆሮ ወደ ኤምባሲው ህንጻ ዘልቆ በመግባት አስተማማኝ ጥበቃ ባለበት ለእንግዶች ጊዚያዊ ማረፊያ ወደተዘጋጀው ወደ ሰራተኞች አካባቢ በመሸሽ ሄደ፡፡ በመጨረሻም አንድ ሰላማዊ ተቃዋሚ ወደ ባንዲራ መስቀያ ቦታው በመሄድ በመሀከሉ ላይ የኮከብ ምልክት ያለበትን የወያኔን ባንዲራ ከተሰቀለበት በማውረድ በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ በመተካት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ሲሰቅል ታየ፡፡ በመጨረሻም ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ ዘልቀው በመግባት ወደ ጊዚያዊ ማረፊያ ቦታው በመሄድ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ መጮህ ጀመሩ፣ነጻነት ነጻነት…“ በማለት፡፡ 

ለተለያዩ ድርጅቶች የሚሰራው የምርመራ ጋዜጠኛ እና ዕውቁ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተሟጋች የሆነው አበበ ገላው ከሌላ ምንጭ ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቧል፣በዩኤስ አቃቤ ሕግ በዋሺንግቶን ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ቢል ሚለር በገብረስላሴ ላይ በመግደል ሙከራ እና ታጥቆም በመገኘቱ ምክንያት ለህግ ቢቀርብ እስከ 30 ዓመታት በእስራት ሊያስቀጣ የሚችል የክስ መጥሪያ ወጥቶበታልብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካ መንግስት መምሪያ ቃል አቀፈባይ የሆኑት ጀን ፔንሳኪ የወያኔ ገዥ አካል የተኳሹን የገብረስላሴን ያለመከሰስ መብት ለማንሳት እና ለህግ እንዲቀርብ ለማድረግ ፈቃደኛ ያለመሆኑን መግለጹን በማስመለከት እንዲህ ብለው ነበር፣ለኤምባሲው የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆኗል፣ እናም በአሁኑ ጊዜ የወንጀል ተጠርጣሪው ግለሰብ አገር ለቅቆ ወጥቷል፡፡“        

አስቀያሚውን የጫካ ትዝታ በዋሺንግተን . መተግበር? 

እስከ አሁን ድረስ በዋሺንግተን . የዲፕሎማሲ ታሪክ የወያኔዲፕሎማሲበሰላማዊ መንገድ ጥያቂያቸውን ባቀረቡ ዜጎች ላይ መሳሪያ አውጥቶ በመተኮስ ማስተናገድ የዴሞክራሲ አባት በሆነችው አሜሪካ ውስጥ ካሉ በየትኛውም ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በታሪክ ያልተሞከረ የመጀመሪያው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ሰሎሞን ገብረስላሴ አነጣጥሮ ተኳሽ ነውን? ጫካ ውስጥ በነበረበት ወቅት ከደርግ ጋር ሲያካሂደው የነበረው የዚያ ጦርነት አስቀያሚ ትዝታ ድንገት ብልጭ ብሎበት ይሆን እንዴ? ሰሎሞን ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት በተሰባሰቡ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ በየትኛውም የዲፕሎማሲያዊ ተቋም ላይ ተሞክሮ ያልታወቀውን ስልጣኔ የጎደለውን የደንቆሮዎች ድርጊት በመናፈቅ ተኩስ ከፍቶ ወገኖቻችንን ለመጨረስ መሞከሩ በእውነት በጫካ በነበረበት ጊዜ ወያኔን ሲቃወሙ የነበሩትን ወገኖቻችንን ሁሉ ሲጨርስ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ያንን እኩይ ምግባር የዓለም የዴሞክራሲ ተምሳሌት በሆነችው አሜሪካ እምብርት ዋሺንገተን .. ላይ ልምዱን ለማስታወስ ያህል ሲነሽጠው የክለሳ ስራ መስራቱ ይሆን እንዴ? ‘ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባእንዲሉ!

ገብረስላሴ የፈጸመው እኩይ ድርጊት በስነልቦና ሳይንስ ትምህርት ተመራማሪዎችአስቀያሚ ትዝታበመባል የሚታወቀውን ከአዕምሮ ጋር ተቆራኝቶ የሚኖረውን እና ሳይታሰብ እና በድንገት ቅጽበታዊ በሆነ መልኩ በአንድ ምክንያታዊም ሆነ ኢምክንያታዊ ክስተት በሚፈጸምበት ጊዜ ላይ ግንፍል ብሎ በመውጣት ወደ ድርጊት ከሚሸጋገር ስነልቦናዊ ድርጊት ጋር ይመሳሰላል፡፡ ከዚህ አንጻር ገብረስላሴ ያልታጠቁ ሰላማዊ አመጸኞችን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ አካባቢ በተመለከተ ጊዜ በአዕምሮ ስነልቦናው ውስጥ ተቀርጾ የተነበበው በከፍተኛ ወኔ እና ከባድ መሳሪዎችን ታጥቆ በመምጣት የእርሱን የአማጺ ቡድን ወያኔን ለመውጋት የመጣ ሰራዊት መስሎ ነው የታየው፡፡ በግልብ አዕምሮው ውስጥ ተጽፎ የሚታየው ይኸው ነው፡፡ ሌላ በጎ ነገር በቡድንም ሆን በግል ያልለመዱትን እና ያላዩትን ነገር ለሰሎሞን ገብረስላሴ ከየትኛው ተሞክሮው ተቀምሮ በአዕምሮው ጓዳ ውስጥ አድሮ ሊከሰት ይችላል ተብሎ ይታሰባል? ጀግናው ገብረስላሴ ያንን የመሰለ ድርጊት በሚጽምበት በዚያን ጊዜ የሀገሮች መስተጋብር ማስፈጸሚያ የሆነውን ኤምባሲን የሚጠብቅ መስሎ አልታየውም፡፡ ይልቁንም በአዕምሮው ላይ ተቀርጾ የኖረው እና አሁንም ያለው የወያኔን የመሬት ውስጥ ምሽግ ጫካ በነበረበት ጊዜ ከጠላት ለመከላከል የሚያደርገውን ቅጽበታዊ እርምጃ መውሰድን ነው የሚያስታውሰው፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በድል አድራጊነት በሚመስል መልኩ ሽጉጡን እያወዛወዘ በዲፕሎማት ወግ ጥቁር ሱፉን ገድግዶ ለብሶ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩስ በታላቋ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ በከፍተኛ ደረጃ የውጭ አገር የዲፕሎማት ሰው መቀመጫ ወንበር ላይ መሆኑን ፍጹም በሆነ መልኩ እረስቶታል፡፡ አይ ጫካ መኖር! የጫካ አስተሳሰብ እኮ በጫካው ውስጥ ያሸነፈ ይኑር የሚለውን የአራዊት አስተሳሰብን የተላበሰ ሆኖ ይገኛል፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በጫካ ህይወቱ ጊዜ ጠላትን ለመከላከል እና አለቆቹን ጠላት ከሚያደርሰው ጥቃት ለመጠበቅ ከአዛዦቹ ይሰጥ የነበረውን ትዕዛዝ ተቀብሎ ይተገብር ወደነበረበት የወያኔ አማጺ ቡድን እግረኛ ተዋጊነት ስራው ተመለሰ እንጅ ዘመናዊ አስተሳሰብ እና የትምህርት ክህሎት ከሚጠይቀው ዲፕሎማትነት ጋር ትውውቅም ሆነ ዝምድና የሌለው መሆኑን በሚገባ ተግብሮ እና አስመስክሮ ወደ አገሩ ሳይሆን ወደ መፈንጫው ተመልሷል፡፡ 

ሰሎሞን ገብረስላሴ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ተልዕኮ እና የውጭ ዲፕሎማት የኗሪነት ፖሊሲ እና ህግ ጥበቃ ምን እንደሆነ እና ምን እንደሚመስል የማያውቀው መሆኑ በግልጽ ይነበባል፡፡ አሜሪካ በውጭ የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ከማንኛውም የጠላት ጥቃት ለመከላከል ፈጣን የሆኑ የባህር ኃይል ሰራዊቷን በማሰማራት ጥበቃ እንደምታደርገው ሳይሆን በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የሚገኙትን የዲፕሎማሲ ፋሲሊቲዎችን ጥበቃ በሚመለከት ግን ኃላፊነቱ የወደቀው በአሜሪካ የመንግስት መምሪያ፣ በደህንነት አገልግሎቱ እና በአካባቢ የፖሊስ ወኪሎች የጋራ ጥረት ላይ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የዋሺንግቶን ከተማ ፖሊስ ለዲፕሎማሲያዊ ፋሲሊቲዎች ደህንነት ሲባል የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ለጥበቃው በተለይም ዘብ ለተወሰኑ ፋሲሊቲዎች ወይም ደግሞ ለደህንነት ጉዳይ ሲባል እየተዘዋወሩ የሚጠብቁ ዘቦችን በመመደብ እና የፖሊስ ምልክት ያለባቸውን ተሽከርካሪዎች በማሰማራት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ መረጃ የማይሰጠው የደህንነት አገልግሎቱ መስሪያ ቤት በዋሺንግትን . አካባቢ ላሉ የዲፕሎማሲያዊ ተቋማት ተገቢ የሆነ ጥበቃ ይሰጣል፡፡ ይህ የደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት በዲፕሎማቱ ማህበረሰብ እና በዲፕሎማቶች ፋሲሊቲዎች ላይ ሊፈጸም የታሰበ አስተማማኝ አደጋ መኖሩን ሲያረጋግጥ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡ 

ያለመከሰስ መብት የተጎናጸፉት ዲፕሎማቶች በማንኛውም መልኩ የጦር መሳሪያን በመጠቀም ሌሎችን ሰላማዊ በሆነ መልክ ተቃውሟቸውን በሚገልጹ ያልታጠቁ ወገኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር፣ ዲፕሎማቶች በእራሳቸው ሀገር በሌሎች ወገኖች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲባል የጦር መሳሪያ ደብቆ መገኘት፣ ወይም ደግሞ በድብቅ መሳሪዎችን በማከማቸት በዩናይትድ ስቴትስ ወይም በዩናይትድ ስቴትስ በሚኖሩ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን በሚያካሂዱ ዲፕሎማቶች ላይ ጥቃት መሰንዘርን የሚፈቅድ ህግ፣ ፖሊሲ ወይም ደግሞ ልምድ በፍጹም የለም፡፡ ዲፕሎማቶች አለመግባባቶችን እና ውዝግቦችን በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የቃላትጥይቶችንይጠቀማሉ እንጅ እንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ እየተገበረው እንደነበረው ቁጥር 38 የካሊበር ሽጉጦችን አይጠቀሙም፡፡ ወዲ ገብረስላሴ በኤምባሲ ቅጥር ግቢ አካባቢ መሳሪያ በመተኮስ ያልታጠቁ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ለመግደል በተደጋጋሚ ባደረገው የግድያ ሙከራ በዋሺንግተን . የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ ህሊና ቢስ እና የሞራል ስብዕናን የጣሰ የወንጀል ድርጊት ሆኖ ሲታወስ ይኖራል፡፡ ይህ አስነዋሪ የወንጀል ድርጊት ወደፊት ለሚመጡት አስርት ዓመታት የወሮበላ የዲፕሎማሲ እኩይ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የሚያግዙ ለዓለም አቀፍ የህግ እና የዲፕሎማሲ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የማስተማሪያ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት ታላቅ እገዛን ያደርጋል፡፡    

ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀው አትችልም፣ 

የዲፕሎማት ሰዎች ተቀራርቦ በመነጋገር፣ ስምምነት በማድረግ እና በመቻቻል (አብዛኛውን ጊዜ በማታለል) ባለመግባባት የሚከሰቱ ውዝግቦችን ለመፍታት ይፈልጋሉ፡፡ የወሮበላ ዲፕሎማቶች ሁሉንም ችግሮች እና ከዚእነዚህ ክሶች ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ውዝግቦችን በመግደል፣ በመደብደብ ወደ ዘብጥያ በመወርወር እና የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን እና ጠላቶቻቸውን በማሰቃየት ይፈታሉ፡፡ ዲፕሎማሲበመንግስታት ተወካዮች መካከል የሚደረጉ ስምምቶችን ለማምጣት የሚያገለግል ትምህርት እና የተግባር ተሞክሮ ነው፡፡ወሮበላ ዲፕሎማት ሰሎሞን ገብረስላሴ የዲፕሎማት ትምህርቱን ያገኘው እና የቀሰመው ኢንላይ ከሚባለው ተረታዊ የዲፕለማት ትምህርት ቤት ነው፡፡ሁሉም ዲፕሎማሲ በማንኛውም መንገድ ቢሆን የጦርነት ቀጣይነት ነው፡፡ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ በዲፕሎማቲክ ያለመከሰስ መብትን መደበቂያ ምሽግ በማድረግ ለአስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የዘለቀውን አከፊውን የወያኔን የጫካ ጦርነት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማምጣት ፈለገ፡፡ 

የሰለጠኑ ወሮበላ ዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብታቸው ተጠብቆ የሚመረጡት እና የሚላኩት እጅግ አናሳ በሆነ አጋጣሚ ነው፡፡ አብዛኞቹ አገሮች ወደ ሌላ አገር የሚያሰማሯቸውን ዲፕሎማቶች የሚመርጧቸው በመንግስት መስሪ ቤቶች ከሚመድቧቸው በከፍተኛ ደረጃ ካሉ ሰዎች መካከል ነው፡፡ አብዛኞቹ የሚመረጡት ዲፕሎማቶችም በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት የቀሰሙ፣ ሰፊ ልምድ ያካበቱ እና ጠለቅ ያለ የፖለቲካ እውቀት ያላቸውን ዜጎች ነው፡፡ ብዙ አገሮችም የዲፕሎማት ሰዎቻቸውን ሾመው ወደመደቧቸው አገሮች ከመላካቸው በፊት ሙያዊ የሆነ እና ከሙያው ጋር አግባብነት ያለው ስልጠና በማዘጋጀት እንዲሰለጥኑ ያደርጋሉ፡፡ 

እጅግ በጣም ውሱን ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሀገር ቢሆን እንደ ወዲ ሰሎሞን ገብረስላሴ ያለውን ተራ ማይም ደንቆሮ መርጦ እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ባለች አገር ላይ ዲፕሎማት ብሎ አይልክም፡፡ በዲፕሎማቲክ መስኩ በጣም ቀልጣፎች ያልሆኑ አገሮች እንኳ ለዲፕሎማሲ ተልዕኮ የመለመሏቸውን ሰዎች ወደየሀገሮች ከመላካቸው በፊት ስለዲፕሎማሲ ስራ ሰልጠና ይሰጧቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት በየጊዜው ከሚለዋወጠው ዓለም አቀፍ ሁኔታ ጋር አብረው ለመሄድ እንዲችሉ እገዛ ያደርግላቸዋል፡፡ የሚሰጠው ስልጠናም በትክክለኛው መንገድ በዲፕሎማሲ ስራ እና ተግባር ላይ ትኩረት ያደረገ እንጅ ስለጦርነት ስልት እውቀት ወይም ዜጎችን በአገራቸው እንዴት መግደል እንደሚችሉ ለማሰልጠን አይደለም፡፡ ለምሳሌም ያህል አዘረባጃን የእራሷ የሆነየዲፕሎማሲ አካዳሚአላት፡፡ ቡልጋሪያም የግሏ የሆነ የዲፕሎማሲ ማሰልጠኛ ተቋም አላት፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ጋና ኮፊ አናን የሰላም ጥበቃ ስልጠና ማዕከል/Kofi Annan Peace Keeping Training Center የሚባል የዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ ተቋም አላት፡፡ በሌላ በኩልም የግል የዲፕሎማቶች ማሰልጠኛ ዩኒቨርስቲዎች ማለትም እንደ Tuft University’s Fletcher School of Law and Diplomacy እና ሌሎች ተቋማትም ከዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ጋር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶች አሉ፡፡ 

ሊታምን በማይችል መልኩ የሚያስደንቀው እና የሚገርመው ነገር በአጠቃላይ የወያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራር በዲፕሎማሲ የሙያ ዘርፎች ላይ የሰለጠነ ወይም ደግሞ በዚህ ሙያ ላይ በቂ ልምድ ያለው ዲፕሎማት የለውም፡፡ ለምሳሌ ያህል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበላይ ቁንጮ የሆነው ሰው የዲፕሎማሲ ሙያ ስልጠናም ሆነ ልምድ የላቸውም፡፡ ምንም፣ ባዶ! የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድኃኖም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከአስመራ ዩኒቨርስቲ በስነ ሕይወት/Biology የትምህርት መስክ ነው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በማስተር ኦፍ ሳይንስ Immunology of Infectious Diሰዓሰስ በሚል ከሎንዶን ዩኒቨርስቲ ያገኙ ሲሆን የፒኤች ዲግሪያቸውን ደግሞ በህብረተሰብ ጤና/Community Health የትምህርት መስክ በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ከኖቲንግሀም ዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል፡፡ ለጤና ሚኒስትርነት ተሾመው ነበር፡፡ በአንድ ጀንበር ምሽት ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ እራሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገኙት፡፡ (እርግጠኛ ነኝ በአንድ ጀንበር ምሽት ደግሞ እራሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገኙታል)፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መወጣጫነት የመጀመሪያ ደረጃ እና ለሚጠብቃቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመታቸው ለይስሙላም ቢሆን ለማሟሻነት ቢጠቅም በሚል እኩይ ስሌት የተቀነባበረ ነው፡፡ እርግጥ ነው አምባገነንነት እና ወሮበላነት በተንሰራፋባት የመጨረሻ ደኃ ሀገር ለዲፕሎማትነት መስፈርቱ ዘር እና ታማኝነት እንጅ ትምህርት እና ልምድ ምን ፋይዳ ይኖረዋል! (ሟቹ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ስለሚኒስትሮቹ አሿሿም የትምህርት ብቃት ማነስ ጉዳይ በቴሌቪዥን ጥያቄ በቀረበላቸው ጊዜታማኝነት እንጅ ማይም ይሁኑበማለት የሰጡትን አስገራሚ እና ፈጣጣ የስላቅ መልስ ልብ ይሏል፡፡) 

ጉድ እኮ ነው ጎበዝ እንዴት አንድ ምንም ዓይነት የዲፕሎማትነት ልምድ እና በመስኩም አስፈላጊ የሆነው ትምህርት ሳይኖረው ወይም ደግሞ ምንም መነሻ መሰረት ሳይኖረው እንዲሁም በአምበሳደርነት (ስለዓለም አቀፍ ህግ እና ዲፕሎማሲ ፍጹም ባይተዋር የሆነ [ከኢትዮጵያ እሳት ወደ ሳውዲ አረቢያ እረመጥ] በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ትችት ይመልከቱ)   እንኳ ሳይሰራ በድንገት እና ቅጽበታዊ በሆነ ሁኔታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነትን ያህል ከባድ ኃላፊነት የሚጠይቅ የሚኒስትርነት ቦታን ይይዛል? 

ለዚህ መልሱ ግልጽ እና አጭር ነው፡፡ አድኃኖም በዘር ሀረጋቸው ብቻ እና ብቻ ነው የወያኔ የከፍተኛ ዲፕሎማት ስልጣን የተሰጣቸው፡፡ በእርግጥ ይኸ ጉዳይ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ ምን ዓይነት የትምህርት ማስረጃ እና ብቃት አቅርቦ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው? መለስ በርቀት የትምህርት ፕሮግራም በተልዕኮ ከእንግሊዝ ሀገር በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የመጀመሪያ ዲግሪውን አገኘ፡፡ ለሁለተኛ ዲግሪውም ከኢራስመስ ዩኒቨርስቲ የዓለም ብቸኛው ታላቅ አዋቂ ነኝ አያለ ሲፎከርበት የነበረውን የልማት ምጣኔ ሀብት/Development Economics የመመረቂያ ጽሁፉን ማጠናቀቅ ያልቻለ ሰው  ነበር፡፡ 

ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ለወሮበላ ዲፕሎማት ልዩ ስልጠና እየተሰጠ በብቃት ላይ ሳይሆን በዘር እና በታማኝነት ላይ ትኩረት በማድረግ የሚኸድበት ስልት እውነተኛውን የዲፕሎማሲ ስራ አካሄድ እንዲበላሽ አድርጎታል፡፡ ለአፍሪካውያን/ የወሮበላ ዲፕሎማቶች ማሰልኛ ተቋም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከአፍሪከ ህብረት የለማኞች አዳራሽ፣ ለአፍሪካ አምባገነኖች እና ወሮበሎች መሰብሰቢያ ከተሰራው አዳራሽ ፊት ለፊት በቅርብ ርቀት ላይ ይገነባል የሚል ግምት አለኝ፡፡ የሚያስገርም ጉዳይ ይሆናል፡፡ 

ከእውነታዎች ጋር ፊት ለፊት መጋፈጥ አለብን፡፡ አሳማን የከንፈር ቀለም መቀባት ይቻላል ቆንጆ ለማስመሰል፣ ሆኖም ግን ከዕለቱ መጨረሻ ያው ዓሳማ ዓሳማ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ እንደ ሰለሞን ገብረስላሴ፣ ግርማ ብሩ ወይም ቴዎድሮሰ አድኃኖም እና ሌሎች በርካታዎቹ ብሪፍ ኬዝ/ቦርሳ እና የይሰሙላ ክብር መስጠት ይቻላል፡፡ በቀኑ መጨረሻም እራሳቸው እራሳቸውን ሆነው ያገኙታል፡፡ ወሮበላ ዘራፊዎች!

መንግስታዊ አገዛዝ ከወሮበላ (የጫካ አገዛዝ ጋር) ሲነጻጸር፣ 

የወያኔን አገዛዝ የወሮበላ አገዛዝ ነው በማለት በምገልጽበት ጊዜ ከምንም በመነሳት በጥላቻ  ወይም ደግሞ ለቡድኑ ክብር ካለመስጠት አይደለም፡፡ አንዲሁም መለስ ዜናዊንየአፍሪካ የለማኞች አለቃነው በማለት ስገልጽ እራሱ በሚጠቀምባቸው ቃላት ላይ መሰረት አድርጌ ነው፡፡ የእራሴን ቃላት እና ሀረጎች እርሱ ከሚሰራቸው እውነታዎች በመነሳት ነው የምርጣቸው፡፡ 

የወያኔ አለቆች በምንም ዓይነት መልኩ ከወሮበላነት (የጫካ) አገዛዝ ወደ መንግስታዊ አስተዳደር በፍጹም ሽግግር አያደርጉም፡፡ በጫካው ዘመናቸው ወጣት በነበሩበት ጊዜ የነበራቸው ልምድ የምሁርነት አስተሳሰባቸውን፣ የሞራል ስብዕናቸውን እና የማህበራዊ ልማት እይታቸውን በጫካው የቅኝት አስተሳሰብ ብቻ እንዲወሰን አድርጎታል፣ ሸፍኖት ቀርቷል፡፡ ከዚያ አልፎ አንዳንዶቹ ዘመናዊ እና ላቅ ያለ የአካዳሚ ትምህርት የማግኘት ዕድል ያገኙ አባላቱ እንኳ ስልጣን ከያዙ በኋላ በተመሳሳይ መልኩ ድሮ ወደነበሩበት የአስተሳሰብ አድማስ በመመለስ የአስተሳሰብ ግልብነት እና የሞራል ዝቅጠትን እና ባዶነትን አንጸባርቀዋል፡፡ 

የወጣትነት የመጀመሪያዎቹን ዓመታት በጫካ ውስጥ አማጺ ሆኖ ከማሳለፍ አንጻር ለመቀየር የማያስችል እና ቋሚ የሆነ የተቸከለ አስተሳሰብን ይፈጥራል፡፡ በአካዳሚክ ዓለሙ ያሉም ሰዎች ይህን ሲመለከቱቱ  የአማጺያንን የጫካ ህይወት መኖር ያልረሱት እና በአዕምሯቸው ላይ የማይለቅ ችካል ስለሆነ ሆብስየመሆን ሁኔታእንዳለው በአእምሯቸው ላይ በጫካ አስተሳሰብ የተቃኘ አንዳች የሆነ ነገር አንደሚፈጠር ነው።  የእንግሊዝ ፈላስፋ የነበሩት ቶማስ ሆብስ የሰለጠነ መንግስት በሌለበት ጊዜእያንዳንዱ ሰው ከሌላው ሰው ጋር በጦርነት ይኖራልበማለት የሙግት ጭብጣቸውን አቅርበው ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ ህይወት በመሆን የተፈጥሮ ህግ ላይብቸኛ፣ ደኃ፣ በጭካኔ የተሞላ፣ አውሬአዊ እና ኋላቀርነት አስተሳሰብን የተላበሰ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ ሆብስ የመሆን ሁኔታ እዳሉት ለአስርት እና ግማሽ ዓመታት በአማጺነት በጫካ ሲኖሩ የነበሩት የወያኔ አማጺ አመራሮች ከጫካ ህይወታቸው ወጥተው ስልጣንን በኃይል ነጥቀው በስልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡ እና የሰለጠነ መንግስታዊ መዋቅር መሪዎች ከሆኑ በኋላ በእርግጠኝነት ሊሆን የሚችለው ምንድን ነው? በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ሲመሩበት የነበረውን የመሆን ሁኔታ እርግፍ አድርገው ትተው የወሮበላነትን መንግስታዊ አገዛዝ በሰለጠነ መንግስታዊ አስተዳደር እንዲቀየር በማድረግ የህግ የበላይነትን በማስፈን እውነተኛ ሽግግርን ሊያመጡ እና ህዝቡን በሚፈልገው መልክ ማስተዳደር ይችላሉን? 

አጋጣሚ ሆኖ ከእነርሱ አባባል ታምራዊ ሀረጎች በመዋስእድገት እና ትራንስፎርሜሽንለማምጣት የምሁራዊ እና የሞራል ብቃቱ ሳይኖራቸው ቀርቷል፡፡ ለወያኔ አለቆች በሰለጠነ ማህበረሰብ ውስጥ ገብቶ አብሮ መኖር አሁን ብዙ ገንዘብ እና ሀብት ከመዝረፍ በስተቀር ለእነርሱ ህይወት በጫካ ውስጥ ይኖሩበት እንደነበረው ዓይነት ቀጣይነት ያለው ነው፣ ምንም ዓይነት ልዩነት የለውም፡፡ በእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስ ምንም ዓይነት የተቀየረ ነገር የለም፡፡ 23 ዓመታት በስልጣን እርካብ ላይ ተፈናጥጠው ከቆዩ በኋላ ምንም ዓይነት የተማሩት ቁም ነገር የለም፡፡ አሁንም ቢሆን በጫካ በነበሩበት ጊዜ ሲያራምዱት የነበረውን ሚስጥራዊ የፖለቲካ ፍልስፍና በህዝቡ ላይ በመጫን ለመቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ የተጠያቂነት እና የግልጽነት ባህሪን አያራምዱም ነበር፣ አሁንም ቢሆን አንድን ታላቅ አገር በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ስርዓት ባለው መልኩ ተጠያቂነት እና ግልጽነትን በተላበሰ ሁኔታ መምራት ሲችሉ ይህንን መተግበር ተስኗቸዋል፡፡ በጫካ ውስጥ ሆነው ከደርግ ወታደራዊ አምባገነን ጋር ትግል ሲያደርጉ በነበሩበት ወቅት ውሳኔ ሰጭነት በጥቂት የወያኔው መሪዎች ብቻ እና ብቻ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት እነዚህ ጥቂት አመራሮች ይመሩት በነበረው ሰራዊት እና በአጠቃላይ በቁጥጥራቸው ስር አድርገውት በነበረው ህዝብ ላይ ጥሬ የሆነ አስተሳሰብን፣ ጭካኔ የተሞላበት ኃይልን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ሰላማዊ አማጺያንን እና የሰላ ትችት ያቀርቡባቸው በነበሩት ወገኖች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መውሰድ ጀመሩ፡፡ ከእነርሱ ሀሳብ ጋር ስምምነት የማያደርጉ ዜጎችን ማግለል፣ እንደ ሰላይነት በመቁጠር መግደል እና ማጥፋት ጀመሩ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መንግስታዊ ስልጣንን ከተቆናጠጡ በኋላም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና ሌሎችንም ለስልጣናቸው አስጊ ናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን ወገኖች ማዋከብ፣ ማሰር፣ መግደል እና ከሀገር እንዲወጡ ማድረግን ስራየ ብለው መተግበር ጀመሩ፡፡ ከእራሳቸው መካከል በሀሳብ በመለያየታቸው የተገነጠሉትን ተስፈንጣሪ ቡድኖች  ርህራሄ በሌለው መልኩ አስወገዷቸው፣ አዋረዷቸው! 

በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ስልጣንን፣ ገንዘብን በመዝረፍ እራስን እንደማበልጸጊያ፣ የፖለቲካ የበላይነት እና ማስፈራራትን እንደ መሳሪያ በመቁጠር ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔ አገዛዝ በሙስና የበከተ እና የሙስናው በሽታ በኢትዮጵያ አካል ላይ እንደ ነቀርሳ እየተሰራጨ መሆኑን ሙስናን በኢትዮጵያ መመርመር/Diagnosing Corruption in Ethiopia በሚል ርዕስ  የዓለም ባንክ አዘጋጅቶ ባወጣው በባለ550 ገጽ ዘገባው ላይ በግልጽ አስፍሮታል፡፡ ወያኔ በጫካ በነበረበት ጊዜ አመራር ላይ መሆን ማለት የእራስን ስብዕና መትከል የነበረ ሲሆን አሁንም ቢሆን በአሁኑ ጊዜ በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ በእርሱ ደቀመዝሙሮች እንደ ትንሹ አምላክ ያህል ይመለክ ነበር፡፡ የእነርሱ ከጫካ አገዛዝ ወደ መንግስታዊ አስተዳደር ያደረጉት ሽግግር የአንድ ሰው፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነት የነበረውን የደርግ አገዛዝ በማስወገድ በአንድ ሰው፣ በአንድ ፓርቲ የወያኔ አገዛዝ ተኩት፡፡ የወያኔ አመራሮች በደርግ አገዛዝ ላይ ያደረጉት ለውጥ አለ ከተባለለወያኔ ጥሩ የሆነው ነገር ሁሉ ለኢትዮጵያ ህዝብም ጥሩ ነውየማለታቸው አምባገናናዊ አመለካከታቸው ብቻ ነው! 

ከወሮበላነት/ከጫካ አገዛዝ ወደሰለጠነ መንግስታዊ አስተዳደር የሚደረግ እውነተኛ ሽግግር የፍልስፍና እና የፖሊሲ ሁለቱንም ነገሮች ስርነቀል በሆነ መልኩ መቀየርን ይጠይቃል፡፡ ይኸ ግን ባዶ ተስፋ ሆኖ ቀርቷል፡፡ በተደጋጋሚ ጊዜ እንደምለው የወያኔ አመራሮች ትክክለኛ መንግስታዊ መዋቅርን ይመሰርታሉ ወይም ደግሞ ትክክለኛ መንግስታዊ ስርዓትን ያራምዳሉ ማለት ሰይጣን ከመጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሰ ያስተምራል እንደማለት ነው፡፡ 

ዴሞክራሲያዊ የመንግስት አስተዳደር መሰረታዊ የሆኑትን መርሆዎች ማለትም የህግ የበላይነት፣ የስልጣን ክፍፍልን፣ የቁጥጥር እና የኃይል ሚዛንን እና ህገመንግስታዊ የአስተዳደር ሂደትን በመተግበር በእውነታ ላይ የተመሰረተ ትችትን በትክክል ለተከናወኑ ስራዎች ደግሞ አድናቆት መስጠት እና መግባባትን ይጠይቃል፡፡ የወያኔ ወሮበላ አመራሮች ለእንደዚህ ዓይነቶቹ ጉዳዮች እጅግ በጣም አነስተኛ የሆኑ ልምዶች ወይም ደግሞ የተግባር ተሞክሮ ጭራሹንም የላቸውም፡፡ በዚህም መሰረት ማንም ቢሆን እነዚህ የወሮበላ ስብስብ አመራሮች በፖለቲካ ህይወታቸው ውስጥ ያልነበራቸውን እና በተሞክሮም የማያውቁትን ተጠያቂነትን እና ግልጸኝነትን ሊያሰፍን የሚያስችል የፖለቲካ ስርዓት ለህዝቡ ማስፈን እና መተግበር ይችላሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩባቸው ጊዚያት ምንም ዓይነት ነጻ ምርጫ አካሂደው አያውቁም፣ በመሆኑም .. 2005 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በዝረራ በተሸነፉበት ወቅት ተአምር የሆነ ያህል ተገርመው ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ታላቅ ትምህርትን ቀስመዋል፡፡ .. 2010 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ 99.6 በመቶ የድምጽ ውጤት በማምጣት (በመዝረፍ አላልኩም) ድል ተቀዳጅተናል፡፡ በጫካ በነበሩባቸው ጊዚያት የሚናገሯቸው ቃላት እራሳቸው ህግ ነበሩ፣ ስለ የህግ የበላይነት ምንም ዓይነት ሀሳብ አልነበራቸውም፡፡ አንድ ጊዜ ስልጣንን ከጨበጡ በኋላ የእነርሱ ቃል እራሱ ህግ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በእራሳቸው ስልጣን ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፣ ይቀጣሉ፡፡ በጫካ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ እነርሱ እራሳቸው ዳኛ፣ ችሎት እና አስፈጸሚ ነበሩ፡፡ በስልጣን ላይ ባሉበት ጊዜ በጫካ ላይ ከነበሩበት ጊዜ የተለየ ነገር የላቸውም፣ ልዩነት አለ ከተባለም በጫካው ጊዜ ይፈጽሙት ያልነበረ አሁን ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር መዋቅርን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶችን በማቋቋም እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ውሳኔው እንዲሰጥ ማድረግ ነው፡፡ በጫካ ውስጥ በፍርሃት እና በበቀል ነው የኖሩት፣ እናም የሲቪል ነጻነቶች እና የእነዚህ ነጻነቶች አተገባበር ለእነርሱ ባዕድ ናቸው፣ ፈጽሞ አይተዋወቁምና፡፡ በአሁኑ ጊዜም ህዝቡ በድንገተኛ መሬት አንቀጥቅጥ አመጽ ያስወግደናል በሚል ፍርሀት ውሰጥ ተቀርቅረው ሌት ቀን ሲባንኑ ይውላሉ፡፡ እናም የሲቪል ነጻነቶች እና መብቶች ቅንጦት የሆኑ ነገሮች ሲሆኑ እነዚህ ቅንጦት የሆኑ ነገሮችም ለእኛ ሳለይሆን ለምዕራባውያን ሰዎች ብቻ የተተው እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ሆኖም ግን እነርሱ፣ የእነርሱ ደቀመዝሙሮች እና ደጋፊዎቻቸው ለሚሰሯቸው ወንጀሎች እና የሲቪል ወንጀሎች ሳይቀር ያለመከሰስ መብትን በመጠቀም የተለያዩ ወንጀሎችን እየፈጸሙ እራሳቸውን በማስደሰት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጭሩ ከዚህ የእኩይ አስተሳሰብ ባለቤት ከሆነው የወሮበላ ቡድን ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን የተላበሰ ስርዓት በኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን የሚያስችለል መንግስታዊ መዋቅር መጠበቅ ከባዶ ተስፋ የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡   

ሰላማዊ ሰልፈኞችን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንዴት? 

በአንድ ታትሞ በወጣ ዘገባ እንደቀረበው የወያኔ አገዛዝ .. ሴፕቴምበር 29/2014 በዋሽንግተን . በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉ ወገኖቻችን ላይ ክስ ለመመስረት እንደሚንቀሳቀስ አሳውቋል፡፡ ዲና ሙፍቲ የተባሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፣የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ገብተው ጸረ መንግስት የሆኑ መፈክሮችን እያሰሙ የኢትዮጵያን ባንዲራ በማውረድ ሁከት በፈጠሩት ሰዎች ላይ የኤምባሲውን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እና በአጥፊዎች ላይ ክስ መመስረት እንዳለበት ይጠበቃል፡፡በሌላ በኩል የወጣ ዘገባም እንደጠቆመው ሰላማዊ ሰልፈኞች በአዲስ አበባ በሚገኘው የዩናይትስ ስቴትስ ኤምባሲ በመሄድሰላማዊ ሰልፈኞች ለህግ መቅረብ አለባቸውየሚል ጥያቄ ያቀረቡ መሆናቸውን አሳውቋል፡፡በቪዲዮ ክሊፑ ላይ እንደሚታየው ሰላማዊ ሰልፈኞች የኢትዮጵያን ብሄር ብሀረሶቦች የሚወክለውን ባንዲራ በማውረድ የጥንቱን እና የነጻነታችን አርማ ሆኖ ሲያገለግል የቆየውን አረንጓዴ፣ ቀይ እና ብጫ ቀለም ያለበትን የህዝቦች ነባር ባንዲራ በክብር ወደነበረበት ቦታው መለሱት፣ አከበሩት እንጂ አላዋረዱትም፡፡  ሰላማዊ ሰልፉ በወያኔ አገዛዝ የተቀነባበረ የመድረክ ላይ ተውኔት ነው፡፡   

ሙፍቲ፣ ቴዎድስ አድሀኖም እና ሌሎች የወያኔ ደናቁርት ምን መመኘት እንዳለባቸው ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

መጀመሪያ፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ጥፋተኛ ለማድረግ በሚደረገው የውንጀላ ብያኔ ላይ ግልጽ መሆን አለበት፡፡ በአሜሪካ አገር የፌዴራል ወይም የኮሎምቢያ ወረዳ ግዛት ወንጀል ስርዓት ኮድ ላይሻጥር ለመስራትየሚል የወንጀል ጥቅስ አይታወቅም፡፡ ምናባዊ የሆነ የወንጀል ክስ በመፈብረክ ክስ እንዲመሰረት ቢያስቡ እና ህዝቡን ለማሳመን ጥረት ቢያደርጉ የእነርሱ የአስተሳሰብ አድማስ በምን ያህል ጥልቀት እንደወረደ እና ስለአሜሪካ ህግ ያላቸውን ድንቁርና የሚያመላክት ነው፡፡ (በእንደዚህ ዓይነት ፍጹም ድንቁርና የተጠናወታቸው ፍጡሮችኢትዮጵያ የምትመራመሆኗን ስመለከት በጣም ተሸማቀቅሁ፣ አዘንሁም!) 

ሁለተኛ፡ የወያኔ ደናቁርት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አገር ማንኛውንም ዓይነት ባንዲራ የኮከብ እና ነጠብጣብ ምልክት ያለባትን የአሜሪካን ባንዲራም ቢሆን ማውረድ ወይም ማዋረድ ወንጀል አለመሆኑን ሊያውቁ ይገባል፡፡ .. 1989 በቴክሳስ ግዛት ጆንሰን የዩኤስ አሜሪካንን ባንዲራ .. 1984 የሬፐብሊካን ብሄራዊ ጉበኤ በዳህላስ፣ በቴክሳስ) ባቃጠለበት ወቅት ጀስቲስ ዊሊያም ብሪናን በአጠቃላይ ሀሳብ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስፍረው ነበር፣በሀሳብ መለያየትን የማስተናገድ መብት ማረጋገጥ የአሜሪካ የመጀመሪያው የህግ ነጻነት ማሻሻያችን የመሰረት ድንጋይ ነው፣ መንግስት በዜጎቹ መካከል አንድነትን የሚያጠፋ ነገር በመፈብረክ የዘፈቀደ ትዕዛዝ በመስጠት ተግባራዊ ማድረግ አይችልም፡፡ይላል፡፡ ስለሆነም አንድ ዓይነት ባህሪ እና መርህ ያለው መንግስት የአንድነት መገለጫ የሆነውን ምልክት በመጣስ ከዚያ መርህ ጋር የሚጣረስ ትዕዛዝን ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡ በቀላል አነጋገር እንኳንስ ይህንን በሸፍጥ የተዘጋጀ የብሄር ብሄረሰቦች የሸፍጥ ባንዲራ ከተሰቀለበት ማዕዘን ማውረድ ይቅርና ጥንታዊውን እና የተከበረውን ያሜሪካ ባንዲራም በእሳት ማቃጠል ህገመንግስታዊ መብት ነው፡፡ 

ሦሰተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ መንግስት በጋዜጦች እና በድረ ገጾች የሚለቀቅ የዲፕሎማሲ ስራን እንደማይሰራ የወያኔ አገዛዝ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ እነዚህ ደናቁርት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የሚፈልጉትን ነገር እንዲያደርግላቸው ከተፈለገ በመጀመሪያ ደረጃ የፕሮቶኮል ስነስርዓትን ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ከውጭ መንግስታት የዲፕሎማቶች የተቃውሞ ጥያቄ ሲቀርብለት የውጭ መንግስታቱ የሚፈልጉትን ለማግኘት ሲፈልጉ እነዚህ ቅሬታ ለማቅረብ የሚፈልጉ መንግስታት መከተል ያለባቸውን ህጎች እና የአካሄድ ስነስርዓቶች በመከተል እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚችል በጣም ዝርዝር በሆነ መልኩ አስቀምጧል፡፡ የወያኔ ደናቁርት በቀጣይነት የሚደርስባቸውን ውርደት እና መሸማቀቅ ለማስቀረት በማሰብ ለእነርሱ ወገናዊነት እገዛን ለማድረግ የዩኤስ አሜሪካንን የመንግስት መምሪያ የውጭ ጉዳይ ሰነድ ቮሊዩም 5 የእጅ መጽሐፍ ቁጥር 1 እንዲመለከቱ እጋብዛለሁ፡፡ (በነገራችን ላይ ስለዲፕሎማቶች ያለመከሰስ መብት መነሳት ጉዳይን በማስመልከት ጥያቄ አቅርባችሁልኝ ለነበራችሁ አንባቢዎቸ በግንባር በመገኘት ምላሽ ባለመስጠቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን ለዚህ ስራ ይጠቅማችኋል በሚል እሳቤ “Diplomatic and Consular Immunity: Guidance for Law Enforcement and Judicial Authorities“ በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን በመረጃ የበለጸገ ሰነድ እንድታነቡት እጋብዛለሁ፡፡ 

አራተኛ፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤቶች እንደ ወያኔው የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች ሳይሆኑ ተከላካዮች የተሟላ ህገመንግስታዊ መብት ያላቸው እና አስገድዶ ቃል ያለመቀበልን፣ ያለመደብደብ እና በሰውነት ላይ የሚፈጸሙ የጥቃት ማስረጃዎችን ጭምር በማካተት አዘጋጅቶ ያስቀመጠ መሆኑን የወያኔ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ የወያኔ ደናቁርት እነዚህን የነጻነት ታጋይ ወገኖቻችንን በህግ ፊት አስቀርበው ለማስቀጣት ከልብ ፈልገው ከሆነ በዚህ በአሜሪካ የህግ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን እና የታጨቁትን ህጎች በሙሉ ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

አምስተኛ፡  የህግ ስርዓት ቢኖር ኖሮ ግርማ ብሩ እና ሌሎች የኤምባሲው ሰራተኞች እንዳደረጉት ሁሉ ገብረስላሴም በታላቁ የፍርድ ቤት ችሎት ቀርቦ ቃሉን መስጠት እና የማስተባበያ ማስረጃ መስጠት የነበረበት መሆኑን የወያኔ ደናቁርት ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ በችሎት ፊት ቴዎድሮሰ አድሃኖም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረቦቻቸው ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ቃል መስጠት የጽሁፍ ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ተከላካይ በግርማ ብሩ፣ በገብረስላሴ፣ በአድሃኖም እና በሌሎች ቀሪ ሰዎች ላይ መስቀልኛ ጥያቄዎችን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በመስቀለኛ ጥያቄዎች ሲጠበሱ ምነው ጫካ ገብተን ደርግን በተዋጋን በለው ሳይመኙ አይቀሩም። 

ስድስት፡ ሶሎሞን ገብረስላሴ በጣም አስቸጋሪ ፈተና ሊያጋጥመው እንደሚችል መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ማስረጃ ለመስጠት ወደአሜሪካ የሚመለስ ከሆነ የዲፕሎማት ያለመከሰስ መብት እንደሌለው ማወቅ ይኖርበታል፡፡ በጣም ከባድ በሆነ ወንጀል ክስ ምክንያት ምንም አይነት አስተያየት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አቃቤ ህግ በኩል አያገኝም። ያለመከሰስ መብቱ እንደማይሰራ እና ክስ ተመስርቶበት ወደ ፍትህ አካል ከመቅረብ እንደማያመልጥ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ገብረስላሴ አንድ ጊዜ በዩኤስ አሜሪካ ከተገኘ እና ያለመከሰስ መብቱ ተነስቶ ጉዳዩ ፍርድ ቤት የሚታይ ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት ችሎት ከመቅረቡ በፊት ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር ውሎ ካለምንም ዋስትና በቀጥታ ወደ ዘብጥያ ሊወርድ እንደሚችል ሊገነዘብ ይገባል፡፡

ሶሎሞን ገብረስላሴ እና የወያኔ አለቆቹ ከፍተኛ የሆነ የሲቪል ህግ ያለበትን እና አስከ አሁን ድረስ በህይወታቸው አይተውት በማያውቁት የፍትህ ችሎት ላይ ይገለገላሉ የሚል ከጥርጣሬ የዘለለ እምነት አለኝ፡፡ በገብረስላሴ ድርጊት ምክንያት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ይደርስ የነበረውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት የወያኔ ኤምባሲ እና ገዥ አካል ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል የረዥም ጊዜ የፍርድ ሂደት ሊኖር ይችላል፡፡ በዩኤስ አሜሪካ በሲቪል ጉዳዮች ላይ የሚታየው እና የሚሰጠው ብይን የመረጃ መለኪያ መስፈርቱነ ባገናዘበ መልኩ በአብዛኛው በሚቀርቡት ማስረጃዎች ላይ መሰረት ተደርጎ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት ከባድ አይደለም፡፡ 

አብዛኞቹ አገሮች የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለማድረግ ስምምነት አድርገው ዲፕሎማት ልከው በመተባበር ከሚሰሩባት ሀገር ላይ የተላከው ዲፕሎማት ወንጀል ሰርቶ ከዚያች ሀገር በመሸሽ አምልጦ ወደ ሀገሩ የመጣን ዲፕሎማት በሀገራቸው ህግ መሰረት የሚቀጡ መሆኑን ማስተዋል አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሶሎሞን ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ባሉት የወያኔ አለቆቹ ቅጣት ሊጣልበት እንደማይችል ጥርጥር የለውም፡፡ ይልቁንም የወያኔን ኤምባሲ ከጠላት ለመከላከል ባደረገው ጀግንነት በወሮበላ ጓደኞቹ የበለጠ እንደሚወደስ እና ጀግና እንደሚባል መገመት ይቻላል፡፡ 

አገሮች እነርሱን በውጭ አገር ሄዶ ሊወክላቸው የሚችለውን ዲፕሎማት ለመምረጥ በአገሪቱ ካሉት የመንግስት ሰራተኞች መካከል በደረጃው እና በትምህርት ዝግጅቱ እና ብቃቱ ላይ በመመስረት እንዴት እንደሚመርጡ እና ለምንም የማይሆን የወሮበላ ዲፕሎማት ለምን መርጠው እንደማይልኩ የእራሳቸው የሆነ ምክንያት አላቸው፡፡ እነዚህ የመንግስት ሰራተኞች በዲፕሎማትነት ተወክለው ሲሄዱ ምን መስራት እንደሚጠበቅባቸው እና የሄዱበትን ሀገር ህጎች እና ደንቦች ማክበር ብቻም ሳይሆን የእራሳቸውን አገር ክብር ሊያዋርዱ ከሚችሉ ነገሮች እራስን ንጹህ በማድረግ በጥንቃቄ መራመድ እና በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ህዝቡ የእራሱን ፍርድ መስጠት እንዲችል መሰረት እንዲያዝ ዕድሉን መስጠት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

ዲፕሎማቶች ወንጀለኛ ከሆኑ የወሮበላ አፋኝ ስርዓቱ ታማኝ ሎሌዎች የሚመረጡ ከሆነ ገብረስላሴ የሰራውን የመሰለ እኩይ ምግባር የተንጸባረቀበት ዓይነት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ስለሆነም ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀው አትችልም። 

ገብረስላሴ በመግደል ሙከራ ምክንያት የተባረረ መሆኑ እውነት ነው፡፡ ሆኖም ግን ህጉ ብቻ ነው እርሱን ነጻ ሊያደርገው የሚችለው፡፡ በአገሮች መካከል ሊኖር የሚገባውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት በማስመልከት 1961 የቬና ስምምነት አንቀጽ 31 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፣አንድ የዲፕሎማት ወኪል የሆነ ሰው ከሚቀበለው አገር የወንጀለኛ ህግ ያለመከሰስ መብቱን ተጎናጽፏልይላል፡፡ ወደድንም ጠላንም የህግ የበላይነት ማለት ሌላ ሳይሆን እንደዚህ ነው፡፡ 

አንደው በነገራችን ላይ….

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በሶማሌ ሚሊሻዎች ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል አስጠነቀቀ 

.. ኦክቶበር 15/2014 ሬውተርስ የተባለው የዜና አገልግሎት የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የሚስጠንቂያ መግለጫ ሰጥቷል በሚል የሚከተለውን ዘገባ አስነብቧል፣በቦሌ በሚገኙ የምግብ ቤቶች፣ ሆቴሎች፣ ቡና ቤቶች፣ የእምነት ቦታዎች፣ የገበያ አዳራሾች እና ታላላቅ የመገበያያ ቦታዎች ሌላ ማስታወቂያ እስካልተሰጠ ድረስ የአሜሪካ ዜጎች እንዳይደርሱ መራቅ አለባቸው ምክንያቱም እነዚህ ቦታዎች ሊከሰቱ በሚችሉ በአሸባሪ ቡድኖች የጥቃት ኢላማ ውስጥ ናቸውይላል፡፡ ሬውተርስ በተጨማሪም እንዲህ የሚል ጥቆማ ሰንዝሯል፣የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ባለፈው ዓመት መጫረሻ አካባቢ አልሻባብ በአዲስ አበባ ከተማ ጥቃት ለመሰንዘር የአውጠነጠነው አስከፊ የሆነ የአጥፍቶ መጥፋት የሽብር አደጋ እንዳለ መረጃ ከደረሰው በኋላ የደህንነት ኃይሉ በተጠንቀቅ ላይ መሆኑንጠቁሞ ነበር፡፡  

ይቅርታ አርጉለኝና ይኸ አስደንጋጭ ዜና ከተሰማ በኋላ የወያኔ ገዥ አካል እንደገና ሶማሊያን ለመውረር እያደረገ ያለው ዝግጅት አለ ማለት ነውነው? እብደት ወይስ ብልሀት!? የዩኤስ ኤምባሲ ማስታወቂያ ኢትዮጵያ እንደገና ሶማሊያን እንድትወር የቀረበ ሀሳብን የመሞከረያ/መገምገሚያ የዳግም ወረራ ወሬ ማናፈሻ ዘዴ ነውን? ዓላማው ይህ ከሆነ ሁሉም ነገር ሁሉ ፍጹም ውድቀት መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ 

ፕሬዚዳንት ኦባማ ባለፈው ሴፕቴምበር 23/2014 ከወያኔ ባለስልጣን ጋር በመሆን ከመጠን ያለፈ ክብካቤ ሲያደርጉ መታየታቸው እና በቪዲዮ ክሊፕ መለቀቁ ስለታሰበው ወረራ በትክክል እንድጠረጥር አድጎኛል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል፣ “…እኛ [ከወያኔ የልኡካን ቡድን አባላት ጋር] ሰላም ማስከበር እና በሰላማዊ መንገድ የግጭት አፈታትን በሚመለከት አሰራሮቻችንን በማሻሻል እንዴት ውጤታማ በሆነ መልኩ መፍታት እንዳለብን ተወያይተናል፡፡ ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ከዓለም ከማንኛውም ሀገር የተሻለች ትሆናለችሰላምን ከማስከበር አንጻር ከብዙዎቹ አንዷ ናት፣ በጣም መጥፎ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ እና ግጭትን በማስወገድ ረገድ ከዓለም ውጤታማ የሆነ የውጊያ ኃይል ያላት ናት…“ በቅርብ ጊዜ የተደረገው ማስታወቂያ የማይቀር የአሸባሪዎች ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል እና ሌላኛው ጫማ የወደቀ መሆኑን የሚያመላክት ነገር ነውን? 

ወደ ኋላ መለስ በማለት .. 2006 አጋማሽ መለስ ዜናዊ በሶማሊያ ህዝብ ላይ ሙሉ አስደንጋጭ እና አስከፊ የጦርነት ጥሪ ከማስተላለፉ እና ታንኮቹ የሞቃዲሾን ከተማ ከመውረራቸው እና ከመርመርመርሳቸው ሁለት ወራት ቀደም ብሎ አልሻባብ እና ጂሀዲስቶች በኢትዮያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየተባለ ብዙ ዲስኩሮች ተደርገው ነበር፡፡ .. 2006 “ጂሀዲስቶች እየመጡ ነው/Jihadists are coming“ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡ ጦርነቱ ከመካሄዱ በፊት ይደረግ የነበረው የፕሮፓጋንዳ ስራ በጣም የሚያስደንቅ ነበር፡፡ .. ዴሴምበር 14/2006 የዩኤስ አሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች የቀድሞ እረዳት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ጃንዳይ ፍሬዘር እንዲህ የሚል ውንጀላ ሰጥተው ነበር፣የዲፕሎማቲክ እና የደህንነት ባለስልጣኖች የእስልምና ህብረት ተዋጊዎች ከሌላው ወገን እገዛ ለማግኘት እና ከእነርሱ ጎን መሰለፍ እንዲችሉ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉየሚል ውንጀላ አሰምተው ነበር፡፡ .. ዴሴምበር 27/2006 በስተሰሜን በኩል 90 ማይሎች ርቀት ላይ የምትገኘውን ሰትራቴጂካዊ የሆነችውን የጆሀርን ከተማ ከተቆጣጠሩ በኋላ የመለስ ዜናዊ ተዋጊ ኃይሎች ወደ ሞቃዲሾ የሚያቃርበውን በረሀ መውረር ጀምረው ነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ የእስላማዊ ህብረት ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይተጨባጭነት ያለው የደህንነት አደጋ ደቅነዋልበማለት የወረራውን አስፈላጊነት እና ፍትሀዊነት አጸደቀች፡፡ ይህንን ጉዳይ በማስመልከት የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ቃልአቀባይ የነበሩት ጎንዛሎ ጋሌጎስ እንዲህ ብለው ነበር፣ኢትዮጵያ በሶማሊያ እየተደረገ ባለው የመሻሻል እድገት ላይ በቅን ልቦና ላይ የተመሰረተ የደህንነት ስጋት ተደቅኖ እንዳለ እና ህጋዊ እውቅና ያለው የሶማሊያ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት በጠየቀው እርዳታ መሰረት ኢትዮጵያ ድጋፏን እየሰጠች ነው፡፡ 

ሶማሊያን የመውረር ዕቅድ በተግባር ለማዋል እየተሰራ ስለመሆኑ የማውቀው ነገር የለም፡፡ እውነት ለመናገር ይህ አካሄድ አሁንም ቢሆን የሚፈይደው ነገር ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡ .. ኦክቶበር 8/2008 “በሶማሊያ የመለስ ዜናዊ የሰላም አስከባሪነት ሸፍጥ ፍጻሜ/The End of Pax Zenawi in Somalia” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስነብቤ ነበር፣እውነተኛው ጉዳይ ሲታይ ሶማሌዎች በመለስ ዜናዊ ወይም በሌላ በማንም ግለሰብ ወይም ቡድን በኃይል በሚደረግ ተጽዕኖ ሰላም ማምጣት አይችሉም ፍላጎትም  የላቸውም፡፡ ሶማሊዎች እና ሶማሊዎች ብቻ ናቸው የእራሳቸውን ችግሮች መፍታት የሚችሉት፣ እናም ይህንን በሚጻረር መልኩ የሚደረጉ ጣልቃገብነቶች ሁሉ አንድም የለየላቸው ውሸቶች ናቸው፣ አለያም ደግሞ ምንም ባለማወቅ የሚደረግ አሳዘኝ የሆነ የዋህነት ነው፡፡ 

ወሮበላን ዲፕሎማት ልታደርገው ትችላለህ ሆኖም ግን ወሮበላነቱን ከዲፕሎማትነቱን ልታላቀቀው አትችልም።  

 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ጥቅምት 12 ቀን 2007 .