ቅዱስ ሲኖዶስ: ‹‹እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?›› ሲል ፓትርያርኩን ጠየቃቸው፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተጠሪነት አንቀጽ ላይ የተጀመረው ውይይት በመካረር አደረ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Holy Synod in session

  • አቡነ ማትያስ÷ የሊቃነ ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ተጠሪነት ለፓትርያርኩ በማድረግ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት የኾነውን የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት በፓትርያርኩ የበላይነት ለመተካት ከምልአተ ጉባኤው ጋራ መሟገታቸውን አጠናክረው ውለዋል፡፡
  • የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ያላትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን