የፊላደልፊያው የወያኔ ጆሮ ጠቢ ጸጋዬ አረፈ ተጋለጠ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 

በፊላደልፊያ ከተማ ውስጥ ለበርካታ ዓመታ ኖሬያለሁ። ወደ አሜሪካ እንደመጣሁ ዘመድጋ አርፌ አንዳንድ ጉዳዬቼን ለማስፈጸም በምንቀሳቀስበት ጊዜ በወቅቱ ፊላደልፊያ ውስጥ የኢምግሬሽን ጉዳዬችን በተለይም የፖለቲካ ጥገኝነት ማመልከቻዎችን መጻፍ፣ ሰነዶችን መተርጎምና የተለያዮ ፎርሞችን በመሙላት አገልግሎት የሚሰጠውን ጠበቃ አቶ ጸጋዬ አረፈን ለመተዋወቅ ቻልኩኝ። የፖለቲካ ጥገኝነት ማመልከቻዬን የጻፈልኝ እሱ ሲሆን ክፍያውን በካሽ እንድፈጽምለት በጠየቀኝ መሠረት ከፍየዋከሁ። ለነገሩ በዛን ጊዜ በቼክ ወይም በክሬዲት ካርድ ክፈለኝ ቢለኝ እንኳ ከየት አምጥቼ እከፍለው ነበር? ለአገሩ እንግዳ ለሰው ባዳ ነበርኩኝና።  የፖለቲካ ጥገኝነት ማመልከቻዬ ፋይል ከተደረገ ከተወሰኑ ጊዚያቶች በኋላ ነው ጸጋዬ ጠበቃ ሳይሆን ከህግ ውጭ ማለትም የጥብቅና ትምህርቱና ፈቃዱ ሳይኖረው በማጭበርበር የህግ ሥራ እንደሚሰራ የተረዳሁት። ቁጭቴና ንዴቴ “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኽ” ዓይነት ሆኖብኝ እጄን አጣጥፌ ውጤቴን እጠብቅ ነበር።

በአሁን ጊዜ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በመኖር ላይ እገኛለሁ። ለብዙ ዓመታት ያህል ጸጋዬን አይቸው አላውቅም ነበር። ሆኖም በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የወያኔ ኢምባሲ ውስጥ ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የግድያ ሙከራ በማድረጉ ምክንያት ከአሜሪካ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለተባረረው “ለወዲ ወይኒ” ወይም ሰለሞን ታደሰ ድጋፍ ለመስጠት ሕወሃት የጠራውን ሰልፍ ለመቃወም ስቴት ዲፓርትመት ፊትለፊት ከተገኙት ኢትዮጵያዊያኖች መካከል ተገኝቼ ነበር። ጸጋዬን ካየሁት ብዙ ዓመታት ተቆጥረው ስለነበረና በጣም ስለወፈረና ስለተለወጠብኝ ጠጋ በዬ ለማየት እስክሞክር ድረስ እሱ መሆኑንም አላወኩኝም ነበር። ለካስ ዋና የህወሃት የውስጥ አርበኛና ካድሬ ነበር! እኔ ይህንን ያኔ ባውቅ ኖሮ እንኳንስ የፖለቲካ ጥገኝነት ጉዳዬን ልሰጠው ይቅርና ባለፈበት መንገድም አልሄድም ነበር። የሚገርም እኮ ነው ከአገራችን አባረውን እዚህ ደግም ይከተሉናል እንዴ? በዛን ቀን ጸጋዬ አረፈ ከባንዳው ሰለሞን ተካልኝ (ሰለሞን/ ቅንድቡ) ጋር ዋና የህወሃት ሰልፍ አሸርጋጅና አጋፋሪ ሆኖ አየሁት።

ጸጋዬ “ባንዲራ ተደፈረ” በሚል ማወናበጃ በተግባር ግን “ህወሃት ተጠቃ፣ ተደፈረ” በማለት “የዘሬን ብረሳ ይዘርዝረኝ” ብሎ ሲወራጭና በዜና ማሰራጫም ሲቀባጥር ተመለከትኩት። እዛ ሰልፍ ላይ የተዋወቁት አንድ የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ፊት ፊቴ ቆሞ ስለሚሳደበው ስለ ጸጋዬ አንስቼለት ግርምቴን ስነግረው ላካስ እሱም በደንብ ያውቀው ነበርና ስለሱ ያጫወተኝ በጣም አስደንግጦኛል። ሰውየው እንደነገረኝ ከሆነ ከጸጋዬ ጋር አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚተዋወቁና ጸጋዬ የትያትር ክፍል ውስጥ ተማሪ የነበረ መሆኑንና ወያኔዎች ኢትዮጵያን ከወረሩ በኋላ አሜሪካ እንደላኩትና አሜሪካም ከመጣ በኋላ የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄው ውድቅ ሆኖበት ከአገር ሊባረር ሲል ኦክላሆማ ዩኒቨርስቲ ውስጥ መምህር የሆኑ ፕሮፌሰር ቴድ ቬስታልን ተቋዋሚ በመምሰል አወናብዷቸውና አታሏቸው ኢምግሬሽን ቦርድ አስቀርቧቸው  ወደ ኢትዮጵያ ተገዶ ቢመለስ ሰቆቃና ግድያም በወያኔ እንደሚፈጸምበት ምስክርነት እንዲሰጡለት አስደርጎ አሜሪካ ውስጥ የመኖር መብት አንደተፈቀደለት በዝርዝር አጫወተኝ። ሰውየው ጨምሮ እንደነገረኝ ከሆነ ጸጋዬ የፕለቲካ ጥገኝነት ሊሰጠው የማይገባና አጭበርብሮ የአሜሪካን ዜግነት የወሰደ ሰው መሆኑንም ጠቆመኝ። ሰውየው የኔን የፖለቲካ ጥገኝነት ጉዳይ ጸጋዬ ይዞልኝ እንደነበር ስነግረው “አዬ ትያትር ነው የሰራብህ” ብሎ አሳቀኝ።

ጸጋዬ ይህ ሳይበቃው አለችሎታው በህወሃት ካድሬነቱ ብቻ በንቀትና በድርቅና በማይመለከተው ጉዳይ ማለትም የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ “የፍትህና የዜጎች በህግ ፊት መዳኘት” በሚል ርዕስ  “በእሰጥ አገባ” መርሃግብሩ ላይ እ.አ.አ. ዲሴምበር 5 ቀን 2014 ባካሄደው ክርክር ላይ አቶ እስራኤል ፈይሳ ከሚባሉ ኢትዮጵያ ውስጥ በዳኝነት አገልግሎት ላይ ተሰማርተው የነበሩና የወያኔ መጠቀሚያ አልሆንም ብለው ወያኔን አውግዘው ካናዳ ውስጥ በስደት የሚኖሩ ጨዋ ሰው ጋር ባደረገው ክርክር በዝረራ ተሸንፏል። አቶ እስራኤል ኢትዮጵያ ውስጥ የዳኝነት ነጻነት የለም፣ ዳኝነት የህወሃት መጠቀሚያ መሳሪያ ነው በማለት ከራሳቸው ልምድ በመነሳት ነጥቦችን በዝርዝር በማስቀመጥ የህወሃትን አገዛዝ እርቃኑን አስቀርተውታል። ጸጋዬ ግን “ሃቅ ያንቃል” እንደሚባለው የሚቀላምደው አጥቶ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ስለሌለው ስለአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድቤትና ስለፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ምርጫ በመቀባጠር እራሱን አዋርዶ በአንጻሩም አቶ እስራኤል የተናገሩትን በማመን የመደዴና የተራ ካድሬ ልፍለፋውን ኦቀርሽቷል። በጣም የሚገርመው ግን የኤሜሪካ ድምጽ ራዲዮ፣ በተለይም ታዋቂው ጋዜጠኛ አሉላ አባተ ጸጋዬን መጋበዙ “ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አለ” እንደሚባለው ነው። በተዘጋጀው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሊናገሩ የሚችሉ በርካታ ክህሎቱ ያላቸው ሰዎች እያሉ ይህንን ወናፍና ቆሮቆንዳ መጋበዙ በጣም አስተዛዛቢ ነው።

በመጨረሻም ጸጋዬ በጭፍን ዘረኝነት በመነሳት ሌሎችንም ጸረ ኢትዮጵያ ድርጊቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይገመታል። እኔስ የምለው “ጸጋዬ አረፈ” በሚያደረገው ወራዳ ስራው በቁሙ አረፈ፣ ሞተ ነው የምለው። እራሱ አዘጋጅቶ በድረገጽ ላይ የለጠፈውን ጽሁፍ ይህንን በመጫን ይመልከቱ። http://lnk.splashurl.com/bGb ሌሎችንም የወያኔ የውስጥ አርበኞችና ጆሮጠቢዎች እግር በእግር እየተከታተሉ ማጋለጥ ተገቢ ነው።