ዜና ቤተክርስቲያን የታደሰ ሲሳይ “ገበና መሸፈኛ የበለስ ቅጠል” አባ መላኩ ጌታነህ (“ፋኑኤል”) ከድጡ ወደማጡ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አባመላኩ ወደምንኩስና አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት ልብስ ሰፊ እንደነበሩ ይታወቃል። ምን አነሳስቷቸውና በምንስ ምክንያት በአንድ ጀምበር ወደ ምንኩስናና ብሎም ወደክህነት እንደገቡ የሚያውቁት እሳቸው ብቻ ነው። ስለእሳቸው በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ብድግ ብለው ተነስተው ከተሰወሩ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምንኩስና ቆብ ጭነው ወደ ሰፈራቸው እንደተመለሱና ምንም ዓይነት የገዳም ኑሮ፣ ሥርዓቱና ሥነምግባሩ ያልነካቸው፤ የከተማ ጩሉሌ ወይም በዘመኑ ቋንቋ “አራዳ” እንደሆኑ ነው። አባ መላኩ በልብስ ሰፊነት ይተዳደሩ በነበሩበት ጊዜ የተቀደደ ልብስን ይሰፉ እንደነበረና አዲስ ጨርቅ ወይም ጣቃ ቀደው ይሰፉም እንደነበር አራሳቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል። የተቀደደን መጥቀም፣ የተቦጨቀን መጣፍ ወይም የተዛነፈውን ማስተካከል የማንኛውም ልብስ ሰፊ ተግባሩ መሆኑ አይዘነጋም። ታዲያ አባ መላኩ ከልብስ ሰፊነት ሙያ ይዘውት ወደ ቤተክህነት የመጡት መቅደዱን፣ መሸርከቱንና መጉመዱን ብቻ ነው። አሁን ግን የሚቀዱት ሐይማኖትን፣ የሚሸረክቱት ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እንዲሁም የሚጎምዱት ደግሞ የምዕመናንን ሕሊናና አመለካከት ነው። ለነገሩስ “ግም ለግም አብረህ አዝግም” እንደሚባለው አባ መላኩ ክህነቱ የተሰረዘበትን የዝሙት ቀበኛውን ታደሰ ሲሳይን ቢሸፍኑና ጋሻ ጃግሬ ቢሆን ምን ይገርማል? ሁለቱም በግብራቸውና በባህሪያቸው ተመሳሳይ  መሰሪዎችና አታላዮች በመሆናቸው ነው።

አባ መላኩ በሹመትና በስልጣን ሰክረው፣ የተናገሩን ቃል አጥፈው፣ የተፉትን ልሰው በፊት አውግዘዋቸው ከነበሩት ከቀደሞው አባ ገብረመድህን (አቡነ ጳውሎስ) ጋር  ህሊናቸውን ሸጠው መቀላቀላቸው፤ የደለበ ስጋ እንጂ ህሊና እንደሌላቸው በገሃድ “መላኩ በመላኩ” ላይ የመሰከሩበትን፣ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ መሆናቸውንና ቀላማጅነታቸውንና አታላይነታቸውን የሚያረጋግጠውን እራሳቸው አባ መላኩ የተናገሩትን ከዚህ በታች አዳምጠው የራስዎን ፍርድ ይስጡ። በዚህም መሠረት ከሰባት ዓመት ገደማ በፊት በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚሰራጨው ነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ ላይ አባ መላኩን አስመልክቶ የቀረበ መርሃግብር ለግንዛቤ እንዲረዳ እንዳለ እዚህ ላይ አቅርበነዋል። (አባ መላኩ ይህንን የተናገሩት ከዛሬ 17 ዓመት ገደማ በፊት ነው)።

አባ መላኩ በወዶገብነት ተመልሰው ለወያኔና ለአባ ገብረመድህን (አቡነ ጳውሎስ) እጅ ከመስጠታቸው በፊት በስደት ለሚኖረው ሕዝብ በሃሰት ይናገሩ የነበረው በዝርዝር ሰፍሯል። አባ መላኩ በዚህ ንግግራቸው ላይ በመጀመሪያ እንዴት ከኢትዮጵያ ውጭ እንደተላኩና በምንስ ሁኔታ ወደ አሜሪካን አገር እንደመጡ በራሳቸው አንደበት ተናግረዋል።  ከተናገሯቸው ውስጥ ዋና ዋናውን ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

“…አቡነ ጳውሎስን ከሚቃወሟቸው የቤተክርስቲያን ልጆች አንዱ ነኝ…”

  “….ስደተኝነት ጥገኝነት እንዲሰጠኝ ጠይቄ አሁን የምኖረው በስደተኝነት

     እንደሆነ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ…”

 “… ለቤተክርስቲያንና ለሃገር እንደቆሙት ካህናት እኔም አንዱ ተቃዋሚ

     መሆኔ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ…”

  “…እኔም እኝህን ሰው (አባ ገብረመድህን) እግዚያብሔርን ትተው ዛሬ

   የመንግስት አገልጋይ በመሆናቸው እኔም ከሚያወግዟቸው ክፍል አንዱ

  እኔ መሆኔ በዚህ አጋጣሚ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ።…”

 ከሁሉም በላይ በጣም የሚገርመው፣ የሚያሳዝነውና የሚያስተዛዝበው ንግግራቸው ላይ ከመጽሃፍ ቅዱስ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 6 ቁጥር 2 ጠቅሰው የተናገሩት ነው። ይኽውም “….የእግዚያብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል የሚገባን አይደለም….”  ይህ ከ17  ዓመታት በፊት የጠቀሱት የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል ዛሬ እራሳቸው ላይ እየመሰከረባቸው ይገኛል።  እሳቸው ናቸው በአሁን ጊዜ ለማዕድና ለሥልጣን በመቆም የኢትዮጵያን ህዝብ እግር ከወርች ጠርንፈው በሽዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን እየጨፈጨፉ፣ እያፈናቀሉ፣ እያሰደዱና እያሰቃዩ ለሚገኙት ለወያኔዎቹ ለነ ስብሐት ነጋና አባይ ጸሐዬ መሳሪያ የሆኑት። አባ መላኩ ጌታነህ የጀመሩትን የማወናበድና የማምታታት ተልዕኮ አጠናክረው ቀጥለውበታል። እራሱ አስረጅ የሆነውን በሬዲዮ የተላለፈውን መርሃ ግብር ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ። አባ መላኩ