ቤሩት ውስጥ ስትደበደብ በቴሌቭዥን የታየችው ኢትዮጵያዊት ሕይወቷ አለፈ

VOA | March 15th, 2012

ሰሞኑን በዩቱብ በተሰራጨው የቴሌቭዥን ዜና አሠሪዋ ቤሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ደጃፍ በአሰቃቂ ሁኔታ እያንገላታና በግድ እየጎተተ ወደ መኪና ሲያስገባት የታየቸው ዓለም ደቻሳ በትላንትናው ዕለት ሕይወቷ ማለፉ ታወቋል። የቆንስላ ቢሮው ተጠሪ አቶ አሳምነው ደበሌ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጡት፥ የሦስት ልጆች እናት የሆነቸው ዓለም ለህክምና ተወስዳ በነበረበት ሆስፒታል ሌሊቱን ራሷን ሰቅላ ተገኝታለች ብለዋል።

በቤሩት ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ልጅቱን ከአሠሪዋ ጥቃት  ሊስጥላት በተገባ ነበር በማለት ቁጣ ማሰማታቸውን ያካተተውን የዚህን ዘገባ ዝርዝር ቀጥሎ ያድምጡ

Play below

 


We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.