ለወያኔ ጥቃት የኤርትራ መንግስት ምላሽ

ዶይቸ ቬለ | March 16th, 2012

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ለተሰነዘረባት ጥቃት አፀፋ ለመመለስ እንደማትሻ አመለከተች። የሐገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት መግለጫ መንግስታቸዉ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ጥቃት የሰነዘረዉ ከዩናይትድ ስቴትስና ከተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤት ድጋፍ ሳያገኝ ነዉ ብሎ እንደማያምንም አስታዉቀዋል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የሐገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ የጦርነትን አስከፊነት የማያዉቅ ወደጦርነት ያምራ እንጂ ኤርትራ ይበቃታል፤ ለትንኮሳዉ ምልሽ አትሰጥም ብለዋል። ኢትዮጵያ የጥቃት ርምጃ ኤርትራ ላይ መሰንዘሯን መግለጿ ሁለቱ አገሮች ዳግም ወደሌላ ጦርነት ሊገቡ ይሆን ወይ የሚለዉን ስጋት አስነስቷል። ፈረንሳይ ሁለቱም ሐገሮች ለዉይይት እንዲቀመጡ ስትጠይቅ፤ ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ አደብ እንዲገዙ ተማፅናለች። ጣሊያንም እንዲሁ ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸዉ የተካረረዉን ዉጥረት እንዲያረግቡ አሳስባለች። የአውሮፓው ኅብረት የውጭ ፖለቲካ ኀላፊ ወ/ሮ ካትሪን ኤሽተንም ተመሳሳይ መልእክት ነው በመግለጫቸው ላይ ያስተላለፉት። የአፍሪቃዉን ቀንድ ፖለቲካ የሚከታተሉ ተንታኞች በበኩላቸዉ ለኢትዮጵያ ጥቃት ኤርትራ ወታደራዊ አፀፋ ላትመልስ ትችላለች ባይ ናቸዉ።

ያዳምጡ
* ለኢትዮጵያ ጥቃት የኤርትራ ምላሽ
* የኢትዮ ኤርትራ ግጭት በተንታኞች እይታ
* የአውሮፓው ኅብረትና የኢትዮ-ኤርትራ ውዝግብ


7 Responses to “ለወያኔ ጥቃት የኤርትራ መንግስት ምላሽ”

  1. selam says:

    መለስ ወያኔ ምን ንካው ይህ ቀላል ነበር ስልጣንና የሃገር ሃብት በኩልነት ማካፈል ሰብአዊ መብትን ማክበር የወያኔ ንብረትን የኢትዮጵያ አድርጎ በሰላም መኖር ሲቻል አንዴ ሱማሌ አንዴ ኤርትራ መርጥ ጥቅሙ ምን ሊሆን ነው ይገርማል ባሁኑ ሰአት የወያኔ ፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ነው ያለው በዚ ቢል በዛ ምንም ሰሚ እያጣ ስለመጣ ጭንቀት ፈጥሮበት የሚያደርገውንም ሚያውቀው አልመሰለኝም መቼም እስኪ እንየው ጉድ ሳይፈላ መስከረም አይጠባም ይባል የለ ::

  2. Berhane says:

    የወያነ ጭንቀት ጣራ ላይ የደረሰ ይመስላል መለስ የነ አመሪካን ትኣዛዝ በተግባር ለመተርጎም ላይ ታች ኣያለ ለመሆኑ በቂ መረጃዎች አሉ ኣነሱም በሶማልያ መግባትና መውጣት መየቀኑ ቅጀትና ዉሸት የሚያስፈሩትን በጅምላ ማሰር ኣየተመለከትን ነው ያለነው የሚገርመው ግን ለሰው መብት ኣንጠብቃለን የሚሉት አፋቸውን ይዘው ድምጽ ከመስጠት ዝምታን መርጠዋል ኢትዮጵያ መረትዋ ሲቸረቸር ህዝቡ ከቦታው ሲፈናቀል ከበርተዎች በተዘዋዋሪ ቅኝ ግዛት ሲፈጥሩ የኢትዮጵያ ህዝብ በቅርብም ይሁን በሩቁ መብቱን ለመጠበቅ መነሳቱ የማይቀር ለመሆኑ ካለፈው የመንግስቱም የሃይለስላሰ ስርአት መማር ኣንችላለን መለስም ይህን ተቃዉሞ ለመጠምዘዝ የተጠቀመበት ዘደ እርትራን አጠቃሁ ይለን ጀምሮዋል ኣነ መለስ ለት ተቀን ቢለፉፉ መላላጥ ነው ትርፉ የምስራቅ አፍርቃ ህዝቦች ከጦርነት ትርፍ ሳይሆን ኣልቂትና ኪሳራ መሆኑን ስለሚያውቁ የውያነን መዝሙር ለመድገም ኣንደማይፈልጉ መመልከት ኣንችላለን አፍሪካውያን በየአገርቸው በሰላምና በጉርብትና በመቻቻልና በመስማማት በመኖር ክድህነትና ከችግር ለመውጣት ኣንደመለስ ያሉትን አገልጋዮች መመንጠር ይኖርበታል
    ሰላምና መከባበር ለምስራቅ አፍሪቃ ህዝቦች

  3. Anonymous says:

    ስላም ይሁን ለኢትዮጵያ እና ኢርትሪ ህዝብ በየጊዝየው እየተፊሪረቀ የሚመጣው ፖለቲካ ህዝቡን ለጊዜው ቢለያየውም በደም በታሪክ በባህል የተሳስረ የተዋለደ አንድ ኅዝብ ነው። ለዚህ ምስክርነት አያሰፈልግም ብዙ ኢትዬጵያውያን እና ኢርትሪዉያን አገር አፍቃሪዎች ለዚሀ አላማ አላማ አልፈዋል። ታሪካቸው በወያኔ እና ሳእብያ ተዳፍኖ አይቀርም። ህጉስ

  4. erkihun says:

    This is a strong message for those who stand against Ethiopia, Tamagne, Elias ane Esat the mercinaries camuflaged soldiers of Eritrea. Ethiopia will shine on the eastern corner and horn of Africa. Her enemy will turn arround like they put black rag on their face todays ago.

  5. Anonymous says:

    ena betam yemigermnge tentangoch ye eritrean akim mananasachew new. enga Eritrawian torneten bedenbe adrgen enawkatalen selzihem ahune woyane/agame eyadrege yalew metenakos metfiaw endemihone lenargagetlachu enwedalen

  6. Law and Justice says:

    “Those who rush to aggression are those who do not know what the life of people means,” Eritrean (Shaebia’s more appropriately) Information Minister Ali Abdu told the BBC.
    How about reminding this so called minister of his master’s act of starting up a war just a little more than a decade ago? Was he playing games with “the lives of goats and camels”?
    Or does the life of those butchered tourists and their guides don’t count as life?
    How about the life of those you guys “summarily execute” at numerous hideous prisons like “Adi Abeito”, and “Wi’a”? Is it an abstract concept with no life?
    How about those more than 400 innocents whom you guys summarily executed at around “Me’etir” and labeled as “muslim fundamentalists”? They didn’t qualify as “living and with life”?
    How about your very nature of aggressiveness and aggression that left the whole region brutalized, and destroyed the lives of hundreds of thousands?
    You think you are immune?
    Your dirty and bloodied hands were immersed in Sudan, Ethiopia, Djibouti and Yemen. Now, time is up. Those culprit hands would be served justice, and cut-off in their act, and left there to rot for learning purposes!

  7. Ethiopia says:

    ኤርትራ: ኤትዮፕያን: ለማደናቅፍ: ብዙ: ትሰራለች:: ኤርትራ: አቅምዋን: አውቃ: አርፋ: ካልተቀመተች: የምትከፍለው: ዋጋ: ብዙ: ዪሆናል:: ኤትዮፒያ: በአንደ: ጊዘ: ኤርትራን: ድምትማትዋን: ማትፋት: ትችህላልች:: ያሁኑ: ሲልታን: ላይ: የተቀመተው: ወያነ: ጊን: ለኤትዮፕያ: አስቦ: ሳይሆነ: ለርሱ: የፖለቲካ: ችህዋታ: ነው: እርትራን: ደበደብኩ: የሚለው: ሁለቱ: አንድ: ናችህወና::
    ታላቅዋ: ኤትሂኦፒአ: ጊን: መነሳትዋ: አይቀሪም: ያነ: ተላትዋ: ሁሉ: ሚን:ኢንድሚወተው: ያስብበት::
    ኤትዮፒያ: ለዘላለም: ቲኖራለች::
    ዎያነ: ኢና: ኤርትራ: ዪወድማሉ::



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.