ለአለም ደቻሳ የሚደረግ መታሰቢያ እና የፍትህ ጥያቄዎች

ዶይቸ ቬለ | March 23rd, 2012

ወደ ሊባኖስ በቤት ሰራተኝነት ሄዳ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቷ የጠፋው የአለም የሞት ምክንያት? የፍትህ ጥያቄ? የሌሎች እህቶቻችን እጣ? ሌላም ሌላም ጥያቄዎች በውጪም ይሁን በአገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በአሁኑ ሰዓት በሰፊው የሚያነጋግር ጉዳይ ነው። በርካታ ወጣት ኢትዮጵያውያን ወደ አረብ አገሮች ለስራ ይሄዳሉ። አንዳንዶችን ጥሩ ሌሎችን መጥፎ ዕድል ይገጥማቸዋል። በቶሮንቶ ካናዳ እና በቦስተን ዩናይትድ እስቴትስ ከአለም ደቻሳ ህልፈት በኋላ በመካሄድ ላይ ስላሉ እንቅስቃሴዎች በጎ ፍቃደኞች ገልፀውልናል። ይህን መሰል አሳዛኝ አሟሟቶች መድረሳቸው ከዚህ ቀደምም በተለያዩ አጋጣሚዎች ተሰምተዋል።ያም ሆኖ አሁንም በርካታ ወጣቶች የወደፊት እድላቸውን ለማቃናት ወደ አረብ አገር መሄድን እንደ አንድ አማራጭ ያያሉ። ከነዚህም አንዷ አባይነሽ ግርማ ነች። ለአራት አመት ያህል ቤሩት ቆይታ በቅርቡ ወደ ሀገሯ ተመልሳለች። ወጣቷ ተሞክሮዋን አካፍላናለች። ዝርዝሩን ከዘገባው ማድመጥ ይችላሉ። ያዳምጡ


3 Responses to “ለአለም ደቻሳ የሚደረግ መታሰቢያ እና የፍትህ ጥያቄዎች”

  1. በጊዜው በቀለ ጃለታ says:

    ለአለም ደቻሳ 3/16/2012 በጊዜው በቀለ ጃለታ ሜኖሰታ
    ይች አለም ጠፋች
    የደቻስዋ ጉብል ተገፋች
    የኢትዮጲያ ኦርኮማዋ ተወገደች
    ተለማምጣ በነነች
    ተንሰቅስቃ ተነነች
    በከብት አገር ተወልዳ
    ከአራዊት ጋር ተለማምዳ
    ከእንስሶች መንደር ተወግዳ
    እንቆቅልሻ ይች አለም
    የት እንደገባች አናውቅም
    ፀሀይ በቃ አታገኝም
    ጨለመባት የኛው ኑሮ፤የዚህ አለም
    ተንከራታ ሳትደሰት
    ተነቅላ ከዕትብቷ መሬት
    ከሰፊው አፈር ግባት
    ወገኖቸ ሳይጠይቋት
    አዘገመች ወደ አቀበት
    የሊባኖስ ፍሬ ቅስፈት
    ነጎደች ወደ ማይደረስበት
    ሥር ሰደደች ወዲያው ጠወለገች የኛ አትክልት
    ከአድማስ ማዶ ሰው ካለባት
    ከቅዱሳን ከአዕላፍት
    ከንጹሓን ከመላዕክት
    ልትኖር ይሆን በአንድነት
    ይሆን ይሆን ይች እመቤት
    ወይስ…..
    የእሳ ምኞት
    የእሳ ቅዠት
    የህልም እዣት
    ከአገር ማዶ ባሻገር
    ወይ አልኖረች በኛው ሸገር
    ልመናዋ ለመጥፋት ነው ላለመኖር
    ወደ ምርጡ ለመንደርደር
    ከእንባችን ጋር ትዘክር
    የእሳ አይደለም፤ የኛው ነው ይህ ተዝካር

    በቁም ቁመታችን
    ህያው ሳለ ቁመናችን
    ያሳየናል፤ይታየናል መሞታችን
    በቁልቅለት መውረዳችን
    መልክ ማግኛ፤ መስታውት ነው ምሥላችን
    ተከተፈ ወገናችን
    ሥለያዘን ጠላታችን
    ሄደችብን ውዳችን
    የስቃዩ ፤ መመሳሰል አንድነቱ
    እዚያም እዚህ፤ተመሳሳይ በሁለቱ
    ስለገባት ከጥንቱ፤ ከጥዋቱ
    መመለሱን፤ ጠላችው የኑሮው ክፋቱ
    ሁሉን ጣለች የኛ ቢፍቱ
    እነ ጊፍቲ ፤ እነ ቡልቶ፤ እነ ጉልቱ
    ተዋረዱ ሆኑ ገልቱ
    እንግዲህ፤ እነሱም ሀሁ ይበሉ ይንገላቱ
    ለመኖር ይዋቱ
    ይታገሉ ከእንስሳቱ
    ከልምዳችን ከእንግልቱ
    አትበሏቸው ኑሩ በርቱ፤ ምናለበት አውሬዎቹ ቢሞቱ
    የሰው ዘሮች እንዲኖሩ እንዲፈቱ!

  2. korokonch says:

    ግተም ተዎና ገንዘበ ላኩ

    forget poem ,forget hateta collect money and send it for her family.She had a debt
    please collect money and cover her dettes–bederochon..she is dead what the use? you said

    she run from her country because of Miser ,help her family, her children
    say also to Tamagne Beyene to be one of you

  3. k doro manekia says:

    we are human .We live we dye. all we die. but help her children

    stop ወረ



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.