ተመስገን ደሳለኝ 4 ወር ወይም 2 ሺህ ብር፤ አበበ ቀስቶ ደግሞ 8 ወር ተፈረደባቸው

አቤ ቶኪቻው | April 30th, 2012

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመሰገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በምታወጣቸው ፅሁፎች በፍርድ ሂደቱ ላይ ጣልቃ ገብተሃል  ተብሎ ተከሶ እንደነበር ይታወሳል።

ተመስገን “የተከሰሱኩት አለ አግባበብ ነው ነው” በሚል ተከራክሮ ፅሁፉ ተከሳሾች የሰጡት መሆኑን አስረድቶ ነበር። ይህንንም ለማረጋገጥ አቃቤ ህግ አበበ ቀስቶ (ክንፈሚካኤል ደበበን) ለምስክርነት ጠርቶት የነበረ ሲሆን መስካሪውም “በፅሁፉ መጠየቅ ካለብኝ የምጠየቀው እኔ ነኝ። ሃሳቤን በፍርድ ቤት ለመግለፅ ባለመቻሌ ጋዜጣ ላይ እንዲወጣ አድርጌያለሁ!” ብሎ ምስክርነቱን ሰጥቶ ነበር።

በዚህም ዛሬ ሚያዝያ 22/2004 ዓ.ም ድጋሚ ቀጠሮ ይዞ የነበረው ፍርድ ቤት በተመስገን ደሳለኝ ላይ አራት ወር እስር ወይም ሁለት ሺህ ብር እንዲሁም በአበበ ቀስቶ ላይ ወደፊት ከሚፈረድበት ላይ የሚጨመር ስምንት ወር እስራት ተፈርዶባቸዋል።

በአሁኑ ሰዓት ተመስገን በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን ከባንክ የሁለት ሺህ ብር ሲፒዮ ጓደኞቹ አሰርተው እስኪመጡለት ድረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ተመስገን ሲፒኦው ለዛሬ ካልደረሰለት ነገ የስራ ቀን ባለመሆኑ ዛሬ እና ነገን እስር ቤት ለማደር ሳይገደድ አይቀርም ሲሉ ወሬውን ያቀበሉኝ ወዳጆቼ ስጋታቸውን ገልፀውልኛል!


One Response to “ተመስገን ደሳለኝ 4 ወር ወይም 2 ሺህ ብር፤ አበበ ቀስቶ ደግሞ 8 ወር ተፈረደባቸው”

  1. fish says:

    መችም የሚሰሩትን አያውቁም ደሞ ቫት አለበት ወይስ ያለቫት ? አጃኢብ !!!Atarteh kefel.
    They need sebeb.Abbe, my advise for Temesgen is to Forget and focus forward.That is how you
    should react.



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.