2ኛ የፓኪስታን ዜጋ በጋምቤላ ሞተ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ቆስለው ከነበሩት ፓኪስታናዊያን አንዱ ትናንት ሕይወቱ ማለፉን በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሣደር አስታወቁ፡፡

በዚህም መሠረት ጥቃቱ በተፈፀመበት ዕለት የተገደለውን ጨምሮ የሞቱት የፓኪስታን ዜጎች ቁጥር ሁለት ደርሷል፡፡

ቆስሎ የነበረው ፓኪስታናዊ ሕክምና ያገኝ የነበረው በመቱ ሆስፒታል እንደነበር ታውቋል፡፡

በጋምቤላ ክልል በሰፊ የእርሻ ልማት ስራ ላይ ከተሰማራው ሳዑዲ ስታር ዋና ጣቢያ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው ጥቃት የአራት ኢትዮጵያዊያንና የአንድ ፓኪስታናዊ ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።

አራት ፓኪስታናዊያንና አራት ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ተገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ ትናንት ፖኬዲ በምትባል ቀበሌ የመንግሥት ወገን የሆኑ ታጣቂዎች፣ መምህራንና ተማሪዎች ተገድለዋል ሲሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪና በሌላ በኩል ደግሞ የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የሚባለው ቡድን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባዎቹን ያድምጡ

[podcast]http://www.voanews.com/MediaAssets2/amharic/dalet/AMH_sa_ef_gambella-pakistan-killings_05_03_12.Mp3[/podcast]