መንግስት እንደ ቼልሲ ዘግቶ መጫወትን ለምን መረጠ!?


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ባለፈው ግዜ ቼልሲ ከባርሴሎና ጋር ሲጫወት በሩን ጥርቅም አድርጎ በፓስዋርድ ነበር የዘጋው። ለምን ዘጋ ያልን እንደሆነ በርካታ ምክንያቶችን መደርደር እንችላለን። ከእኛ ይልቅ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ኤርሚያስ የሆነ ነገር ብሎ እንደሆነ እንፈልግ እና እንመልከት። ምንም ካላለም ከቀጣዩ የዋንጫ ጨዋታ ጋር አያይዞ ዘርዘር ያለ አጥጋቢ ምክንያቶች እንደሚነግረን ተስፋ እናድርግ።

ትላንት አንድ ፈረንጅ ወዳጃችን፤ “ብሎጌ በተደጋጋሚ ተዘጋ ብዬ ዋይ ዋይ” ማለቴን ወሬ ሰምቶ ደውሎልኝ ነበር። እኔም ስለሁኔታው አስረዳሁት። “ብታምነም ባታምንም አስራ አንድ ግዜ ብሎጌ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ተዘግቷል፤ ከዛም አልፎ ተርፎ አንዳንድ አክቲቭ የሆኑ ልጆች ፌስ ቡክ አካውንት ሁሉ እየተዘጋባቸው ድጋሚ እየከፈቱ ነው።” ብዬ ማቃጠር፤ ከዛልዎ ፈረንጁ ወዳጃችን በእንግሊዘኛ ተገርሞ ተገርሞ ተገርሞ ሲያበቃ ለመሆኑ “መንግስት ለምንድነው በዚህ ግዜ እንዲህ የሚያደርገው? ምርጫ እንኳ ቢኖር ድምፅ እንዳያሳጡኝ ብሎ ነው ይባላል? አሁን ግን ምን ሆኖ ነው…?” አለኝ። ለዚህ መልስ የለኝም። ስለዚህ እኔ ራሴ ይህንን ጥያቄ ልጠይቅ… መንግስት እንደ ቼልሲ ዘግቶ መጫወት ለምን ፈለገ?

ወሬዬን ልቀጥል ነበር ሳስበው ሁልግዜ እኔ ብቻ ሳወራ “ያንተ ወሬ ብቻ አላልቅ አለ!” እንዳይሉኝ ሰጋሁና ለምን መድረኩን ለአንባቢ ወዳጆቻችን አልተወውም አልኩ “እርስዎም ይሞክሩት” ብንለውም ይሆናል። እንደሚያውቁት ወይም ደግሞ ማወቅ እንደሚገባዎ  መንግስታችን የተለያዩ ዌብ ሳይቶችን ጥርቅም አድርጎ ዘግቷል። ለምን…? እባክዎን ወዳጄ ይሳተፉ… መንግስት ዘግቶ መጫወትን ለምን መረጠ…? እንደ “ሙዳችን” ፈቃድ መልስዎን ከፌስቡኩም ከብሎጉም ሰብሰብ አድርጌ ሌላ ጨዋታ ይወጣው ይሆናል።