ዴሞክራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ወይስ የለም? (እርስዎ ምን ይላሉ?)

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ | May 18th, 2012

ዴሞክራሲ ትልቅ ፅንሰ ሐሳብ ነው፡፡ ከዚያም ባሻገር ሆኖም ልክ እንደአብዛኛዎቹ የዓለማችን እውነታዎች ፍፁም ሊሟላ አይችልም፡፡ ነገር ግን ምሁራን ዴሞክራሲን መለኪያ ቅንጣቶችን ያስቀምጡለታል፡፡ በነዚህ ቅንጣቶች እየለኩም ነው ሃገራትን ዴሞክራሲያዊ፣ ከፊል ዴሞክራሲያዊ፣ ፀረ ዴሞክራሲያዊ… እያሉ ሲፈርጁ የምንመለከተው፡፡ እኛስ፣ ኢትዮጵያውያን ራሳችን ዴሞክራሲያችንን መመዘን ብንችል ብላችሁ ተመኝታችሁ አታውቁም፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የማሰቢያ ቋቶች (think tanks) አሁን አሁን ብቅ ብቅ ማለት ቢጀምሩም ብዙዎቹ ደፍረው ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን እያነሱ ጥናት አያደርጉም፡፡  በየዓመቱም እየገመገሙ ‹‹አድገናል፣ ወድቀናል›› አይሉንም፡፡ አገራችን ‹‹በማደግ ላይ ያለች›› በመሆኗ እና ምናልባትም እጅግ ዴሞክራሲያዊ የሆኑ መንግስታት ስታገኝ እንዲህ ዓይነት ተቋማት ወደፊት እየተበራከቱ እንደሚመጡ ተስፋ ማድረግ ብንችልም እስከዚያው ግን እኛ የበኩላችንን ጥረት ብናደርግስ?

ብዙ ጊዜ የሚሞግተኝ ጥያቄ አለ፡፡ (በተለይ ይህንን ጦማር ለማንበብ የታደልነው) ብዙዎቻችን ከተሜዎች ወይም ከተማ ቀመስ ነን፡፡ 80 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የገጠር ነዋሪዎች ናቸው፤ በይነመረብ (Internet) ለነርሱ ቅንጦት ነው፡፡ ለብርሃን ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል እንኳን ለማግኘት አልታደሉምና ማለቴ ነው፡፡ ታዲያ ስለኢትዮጵያ ስናወራ ከራሳችን ስሜት እና ልምድ ተነስተን እንደመሆኑ የብዙሐኑን ስሜት እና እውነት ማንፀባረቃችንን እርግጠኛ መሆን ይቸግረኛል፡፡ እርግጥ ነው፤ ገጠሬው ኢትዮጵያዊ የሚባልለትን ያህል እንዳልበለፀገ እግር ጥሎን ስንሄድ፣ ዘመድ አዝማዶቻችን ሲመጡ እና በሌሎችም አቋራጮች እንገነዘባለን፡፡

ችግሩ
ገጠሬው ኢትዮጵያዊ ለበይነመረብ ብቻ ሳይሆን ለቀለም ትምህርት እና መረጃም ሩቅ ነው፡፡ (ይህ ጥቂት የማይባሉ ከተሜዎችን ያልለቀቀ ነገር ቢሆንም፤) ገጠሬው ግን እስካሁን ‹‹ንጉሥ አይከሰስ›› በሚለው እምነቱ እንደፀና ነው፡፡ የዴሞክራሲ ፅንሰ ሐሳብ እና ፍላጎቱ ዘልቆ ገብቶታል ለማለት የሚያስደፍር እውነት አይታየኝም፡፡

እንዲህ ዓይነቱ እውነት በየትኛውም ዓለም የፀና ነው፡፡ ዕጣ ፈንታ ከውልደታቸው እስከ ዕድገታቸው ነገሮችን የማወቅ ዕድል ያመቻችላቸው ሰዎች አሉ፤ እነዚህ ሰዎች ደግሞ ተፈጥሮ ያመቻቸላቸውን የመልካም አጋጣሚ ብድር መመለስ አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ ተጠቃሚ ዜጎች፣ ጥቅም ለጎደለባቸው መታገል አለባቸው ነው ነገሬ፡፡ ስለዚህ ገጠሬው ያፈራውን እህል ብቻውን እንደማይበላው ሁሉ ከተሜውም ስለዴሞክራሲ ገብቶኛል የሚል ከሆነ የዴሞክራሲን አጀንዳ ጠረጴዛ ላይ ሲያስቀምጥ ለከተሜው ብቻ ሳይሆን ለገጠሬውም ጭምር ነው ማለት ነው፡፡

ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ገጠሬው ስለዴሞክራሲ የሚኖረው ግንዛቤ ከከተሜው ያነሰ ነው የሚል መስማሚያ ላይ መድረስ አወዛጋቢ አይመስለኝም፡፡ እስኪ ደግሞ ኢትዮጵያዊው ከተሜ በአሁኑ ስርዓት ስለሚተገበረው ዴሞክራሲ ምን ይላል የሚል ጉጉት አደረብኝ፡፡ ነገር ግን ከተሜውን ሁሉ ማግኘት አይቻልም፡፡ ስለዚህ የነበረኝ አማራጭ ለበይነመረብ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊያን (ናሙና ከተሜዎች መሆናቸው አያጠራጥርም፤ ነገር ግን ከተሜ ሁሉ በይነመረብ ተጠቃሚ አይደለም፡፡ ቢሆንም በይነመረብ ተጠቃሚዎች ለዓለማዊ መረጃዎች ቅርብ እንደመሆናቸው ስለዴሞክራሲም የሚኖራቸው ግንዛቤ የተሻለ እንደሚሆን በማመን) የመስመር ላይ ቅኝት (online survey) አዘጋጅቼ ውጤቱን ለመተንተን እና በጦማሬ ላይ ለማተም ፈለግኩ፡፡ እነሆ ጥያቄዎቹንም አዘጋጅቼ እዚህአቀረብኩላችሁ፡፡

መጠይቁን ሳዘጋጅ የተጠቀምኩት በርካታ ምሁራን ዴሞክራሲ ይለካባቸዋል ብለው በሚያስቀምጧቸው ቅንጣቶች ነው፡፡ እነዚህም ፍትሐዊ ምርጫ፣ ነፃ ሲቪክ ማሕበረሰብ፣ በነፃ ሐሳብን የመግለፅ መብት፣ የሕግ የበላይነት፣ የብዙሐን መሪነት፣ የግለሰብ ነፃነት እና ሌሎችንም ያካትታሉ፡፡  

ጥያቄዎቹን ከማቅረቤ በርካቶች መሙላት መጀመራቸውን ሪፖርቱ ላይ ተመልክቻለሁ፡፡ አንዳንድ አስተያየቶች እየደረሱኝም ነው፡፡ ጥያቄዎቹ ‹አማካይ› የላቸውም (ጥቁር እና ነጭ ብቻ ናቸው)፣ የተፈለገውን ያህል ብዛት ያለው ሰው ምላሽ መስጠት ሊፈራ ይችላል፣ የዚህ ቃለ መጠይቅ ድምዳሜ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚገነዘቡ የ'አሁኑ'ስርዓት ተጠቃሚ ነን ባዮች ሊፈጥሩት የሚችሉትን ድምዳሜ የማስቀየር ተፅዕኖ የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ስጋቶቹ እና እንደድክመት የተነሱት እና ሊነሱ የሚችሉት ሐሳቦች ተገቢም ትክክልም ናቸው፡፡ ሆኖም የዚህ አነስተኛ ቅኝት ዋና ዓላማ ከድምዳሜውም በላይ ነው፡፡ ስለዴሞክራሲያችን መወያየት መቻል፡፡ ስለዚህ ከላይ ጥያቄዎቹን በመሙላት በበይነመረብ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ስለዴሞክራሲያችን ያለውን አመለካከት ጠቅላላ ምስል ለመገመት ይረዳን ዘንድ መጠይቁንበመሙላት የቻልነውን ያክል እንሞክር፡፡

10 Responses to “ዴሞክራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ወይስ የለም? (እርስዎ ምን ይላሉ?)”

  1. ግሩም says:

    ኤልያስ ምን አይነት ጥያቄ ነው? ምን አይነት መንጋደድ ነው? ልጠይቅ ካልክም ኢትዬጵያችን ህልውናዋ አለ ወይስ አደጋ ላይ ናት ?የሚል ሊሆን ይገባል።

  2. Ababahir says:

    ጥያቄው በራሱ አሳፋሪ ነው፡፡ በቃ አሳፋሪ ብቻ፡፡

  3. Gebreyohannis says:

    ወይ ዲሞክራሲ እሱስ በቀረብን ድሮም አናውቀውም ህዝባችን በልቶ ማደር ቢችል እንዴት ጥሩ ነበር:; ህዝቡ እኮ በርሃብና በችጋር እየተገእፈ ነው ወገን ምን ይሻላል ትላላችሁ

  4. koster says:

    How can there be democracy under fascist Meles Zenawi? Are you joking? Is Eskinder Nega, Andualem Aregie, Reeyot Alemu and several journalists and politicians languishing under fascist Meles reign of terror due to democracy. Are Ethiopians evicted from their own country because of democracy? If there was democracy any Ethiopian should live and work anywhere in Ethiopia. Now it is only Tigrean fascists who can roam around Ethiopians as a master but not other Ethiopians. Let the Ethiopian people judge.

  5. azeb says:

    Can you mention one democratic country under dictatorship? Stupied question.

  6. abulu says:

    This should never be an issue at this critical time when Ethiopians lock horns for freedom from the woyane bondage of slavery.Fail’ure to understand the current prevailing situation,is tantamount to woyanes divertionary tactic.i would have not been wondered if the so called survey conducted by AIGA forum and other woyane mannipulated sites.Pleas dont waste your time .Now the Ethiopians are in bitter survival struggle against the woyane genocidal thugs. Defer the survey until we form a government genuinly run by the people for the people .

  7. Anonymous says:

    le enante melkam neger slemaytayachhu democracy binorm litawqut atchilum

  8. hiwot says:

    ኣዎ በደንብ አለ!

  9. walelgne says:

    አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞ ብቻ ነው ያለው እሱም እጅግ በጣም የተማረረ ብሶቱና ጩኽቱ ያልተሰማ የፈነዳ እለት ግን ልክ የሚያስገባ ታሪካዊና ኩሩ ህዝብ አለ:: ክራሲ ግን ገና አልተወለደም

  10. freeman says:

    Dear writer have you made a research about the knowledge difference between the rural and urban Ethiopians with regard to there socio-political awareness. Do you have a chance to talk with the two groups of people you labeled knowledgeable and unknowledgeable. Do you know or remember where TPLF suffered a lot in the 2005 election. Do you have any idea how the rural Ethiopians monitored the ballot box with no infrastructure of electric power, TV access so and so.
    To make the long story short please stop writing your biased or deluded idea and label the 80% + population of Ethiopians and hide your negligence via accusation of the whole population.

    One thing you are right yes the Ethiopian rural population did not have access to facebook and sat and chat the whole day like you did. But I am confident they are much better or at least as equal aware of their political and democratic rights as the so called people elites (as you called yourself).



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.