መለስ ዜናዊን የሚያወግዝ ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ተካሄደ

EthiopianReview.com | May 24th, 2012

መለስ ዜናዊን የሚያወግዝ ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ተካሄደ

ለባዕዳን በተላላኪነት የሚያገለግለው አምባገነኑና ፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ በዛሬው ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደበት። ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥው በሮናልድ ሬገን ዓለም ዓቀፍ የንግድ ማዕከል ህንጻ ፊት ለፊት በመገኘት መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ በመፈጸም ላይ የሚገኘውን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ፣ የዲሞክራሲያዊ መብቶች አፈና እንዲሁም የአገሪቱን ለም መሬቶች ዜጎችን በጉልበት በማፈናቀል ለውጭ አገር ባለሃብቶች መቸብቸብን በከፍተኛ ስሜትና ቁጭት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። በዚህ ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ ላይ የኢትዮጵያን ይዘዋቸው ከነበሩት መፈክሮችና መልዕክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

  • መለስ ዜናዊ የጦር ወንጀለኛ ስለሆነ ለፍርድ ይቅረብ
  • መለስ ዜናዊ አምባገነነና ፈላጭ ቆራጭ ነው
  • መለስ ዜናዊ ከ 20 ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ የሚገኝ አምባገነን ነው
  • መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ለም መሬቶች እየሸጠ  ነው
  • መለስ ዜናዊ የዘር ማጽዳት በመፈጸም ላይ የሚገኝ ወንጀለኛ ነው
  • መለስ ዜናዊ በሃይማኖቶች ጉዳይ ጣልቃ በመግባት እየበጠበጠ ነው

በዚህ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ መነሳሳትና የአንድነት ስሜት የተጠናከረና ህዝናባዊ ቁጣ የተላበሰ ትዕይንተ ሕዝብ ላይ ኢትዮጵያዊያን፤ ሙስሊም- ክርስቲያን፣ ወንድ- ሴት፣ ትልቅ-ትንሽ፣ ሳይሉ የሁሉም የአገሪቷ ዜጎች ተሳትፈውበታል። ሰልፉ የተካሄደው በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በሚገኘት በርካታ የፌዴራሉ መንግስት ፣ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ፣ የኮርፖሬት ቢሮዎችና ሌሎችም መስሪያ ቤቶች በሚገኙበት መንገድ ላይ በመሆኑና በርካታ ቁጥር ያላቸውን ተመልካቾችን ቀልብ የሳበ እንደነበረ ታውቋል።በመንገድ ላይ ለሚጓጓዙት እግረኞች የተዘጋጁ ጽሁፎች የታደሉ ከመሆኑም በላይ በርካታ አማሪካዊያንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የመለስ ዜናዊን በደም የተጨማለቀ አስከፊ አገዛዝ ማንነትን እንዲገነዘቡ አስችሏቸዋል።

ከዚህም ሌላ በሰለሞን ቅንድቡ  (ሰለሞን ተካልኝ) አሸርጋጅነት በጣት የሚቆጠሩ የህወሃት ጥቅመኞች የዲሲ ፖሊስ ከህዝብ ዕይታ ደብቆ በሰጣቸው ስርቻ ውስጥ ሲንጫጩና ሲያላዝኑ እንደነበር ታውቋል። በተለይ ከሃዲው ሰለሞን ቅንድቡ ከተቃዋሚነት ወደ መለስ አወዳሽነት በመቀየር “ከሰውነት ወደ ውሻነት ተለውጦ በበላበት የሚጮህ  ውሻ ሆነ” እያሉ አንዳንድ ተሰላፊዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል። በመጨረሻም ሰልፈኛው በነገው ዕለት በካምፕ ዴቪድ፣ ሜሪላንድ በተጠናከረ ሁኔታ ተመሳሳይ ተቃውሞ ለማሰማት ቀጠሮ ይዞ ወደየመጣበት ሂዷል።




We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.