የኦታዋ ሁሉ-አቀፍ ጉባኤ ሪፖርት

EthiopianReview.com | June 2nd, 2012

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ መመስረትን አስመልክቶ ከግንቦት 10 እስከ 13 ቀን 2004 (ሜይ 18-21 2012) በካናዳ ዋና ከተማ የተደረገው ጉባኤ መግለጫ። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


5 Responses to “የኦታዋ ሁሉ-አቀፍ ጉባኤ ሪፖርት”

  1. pessimist says:

    How fruitful it will be, is remain to be seen.

  2. G/M Haile says:

    Good news.
    Wishing the best of all Ethiopian and Ethiopia.

  3. misikir says:

    በኦታዋ ከተማ ውስጥ ለአራት ቀናት የተካሄደውን ለጋራ ግንባር ምሥረታ ጉባኤ ለመሳተፍ በመቻሌ ዕድለኛ ነኝ እላለሁ።በዚህ ጉባኤ ላይ ዱሮ ሲጋደሉና ሲጋጩ የነበሩት ድርጅቶች ተቀራርበው በሰከነና በበሰለ አመለካከት ከድርጅት ሥልጣን እምነትና አቋም ይበልጥ የአገርን ጉዳይ በማስቀደም ኢትዮጵያን ከገጠማት አስጊ የመበታተን አደጋ ለማውጣት በሚቻልበት ትግል ለመተባበር በአንድ ላይ ለመቆም የጋራ አካል የፈጠሩበት ልዩ ጉባኤ ነው።ይህን ጉባኤ ልዩ የሚያደርገው ሌላው ነገር ደግሞ እንዳለፉት ጊዜዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ በዝግ የሚስማሙበት ሳይሆን በሂደቱ ውስጥ የተለያዩ የሲቪክ ማህበራትና የአገራቸው ጉዳይ የሚያሳስባቸው አያሌ ግለሰቦች በመሳተፋቸውና ወሳኝ ሚና በመጫወታቸው ነው።ለአመራሩም ከተመረጡት መካከል አብዛኛዎቹ ከነዚህ መካከል የተገኙት ናቸው።
    ይህን ጉባኤ ለማዘጋጀት ለ22 ወራት ጥልቀት ያለው ዝግጅትና ውይይት ተካሂዷል።በዝግጅቱ ውስጥ አብረው እንዲሳተፉ ለተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ለሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ለታዋቂ ግለሰቦች ተደጋጋሚ ጥሪ ተደርጎላቸው ነበር።አሉ ለተባሉት ሁሉ ጥሪው ተላልፏል።አንዳንዶቹ የዓላማ ልዩነት የለንም አብረን እንቆማለን ብለው ቃል ቢገቡም በየምክንያቱ በተግባር ሳይገልጹት ቀርተዋል። አንዳንዶቹ ስለሰላም፣አንድነትና ሰብዓዊ መብት፣ስለአገር አንድነት እየሰበኩ በመድረኩ ላይ ተገኙ ሲባሉ እንደ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮኦጵያ፣ኢሕአፓ፣ጥምረት፣ክተት…ወዘተ ወገቤን ያሉ አልጠፉም።ይባስ ብለውም ለቀረበላቸው የደብዳቤ መልዕክትና ጥሪ በጨዋ ደንብ መልስ አልሰጡም።እነዚህ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ነገ ሥልጣን ላይ ቢቀመጡ የሕዝቡን ጥያቄ ሊያዳምጡና መልስ ሊሰጡ መቻል አለመቻላቸውን ያሳዩበት ትእቢት ይሁን ድክመት በመሆኑ ወደዝርዝሩ ለመግባት አልሻም።እንደምገምተው ግን ይህን በመሰለው የህብረት ሥራ ውስጥ ቢሳተፉ የድርጅትና የግል ሥልጣናቸው የሚዋጥባቸው ስለሚመስላቸው ወይም የቆሙለት ዓላማ ለኢትዮጵያ አንድነት መርሆና ዓላማ ጋር የማይስማማ ስለመሰላቸው ነው ለማለት የሚያስችል ግንዛቤ ሳያድርብኝ አልቀረም፤አንዳንዶቹ በተለይም ከግንቦት ሰባት በኩል በጉባኤው አዘጋጆች ላይ የሚሠነዘረው ምክንያት አንድነትን ስለምታስቀድሙ ሌሎቹን ሊያርቅ ይችላልና ለእኛ አሠራር እንቅፋት ይፈጥርብናል የሚል ትችት ነው።ለመሆኑ በኢትዮጵያ አንድነት የማያምን ድርጅትም ሆነ ዜጋ ኢትዮጵያዊ ነው ለማለት ያስችላል?ይህ በእኔ ብቻ ሳይሆን በሌሎቹም ዘንድ የሚነሳ ጥያቄ ነው።የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ በወያኔ አገርን የመሰባበሩ አድማና ተንኮል ስለሆነ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው እላለሁ። ለሥልጣን መታገል የሚቻለው አገር ሲኖር ነው። በሌላው በኩልም የዜና አቅራቢ ተቋማት ያሳዩትን ድክመት ሳላነሳ አላልፍም።የኢትዮጵያን ጉዳይ እያነሱ በጽሁፍ በቃላት የሚያሰራጩ የዜና አውታሮች ፣የቴሌቪዥን፣የራዲዮ፣የድረገጽ ተቋማት በጉባኤው ላይ ተገኝተው ስለስብሰባው እንዲዘግቡና ለሕዝብ እንዲገልጹ በተደጋጋሚ በቃልና በጽሁፍ ተጠይቀው ነበር።እንደሚታወቀው አንድ የዜና አቅራቢ ተቋም እሱ እራሱ ወሬና ዜና እየፈለገ ማቅረብ ሙያው ያስገድደዋል።እስኪጠራና እስኪጋበዝ ድረስ አይጠብቅም።በእኛ የዜና ተቋማት አሠራር ላይ ግን የተለየና ወገናዊነትን የሚያንጸባርቅ ነው።የምንጮህለትና የሚጮሁለት የነጻ ፕሬስ ሕግና አሠራር ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ባለመግለጻቸው ትዝብት ላይ ሳይጥላቸው አይቀርም።የሕዝብ ዓይንና ጆሮ ነን ማለት በቃል ብቻ የሚለፈፍ አዋጅ አይደለም።ከተጋበዙት መካከል ኢትዮጵያን ሪቪው፣አዲስ ድምጽና ቪኦኤ ሰፊ ዘገባ ሲያቀርቡ የኢትዮጵያን ሪቪው ዋና አዘጋጅ አቶ ኤልያስ ክፍሌና የአዲስ ድምጽ አዘጋጅ አቶ አበበ በለው በአካል ተገኝተው ስብሰባውን በመሳተፍ ለመዘገብ ችለዋል።ሌሎቹ ግን ለቀረበላቸው ጥሪ መሳተፍ ቀርቶ አጥጋቢ መልስ አልሰጡም።በዚህም የተነሳ ለማንና ለምን እንደቆሙ የህዝብ ጥያቄና ጥርጣሬ በመነሳት ላይ ነው።በጉባኤው ላይ ላለመገኘት የወሰኑበት ምክንያት ጉባኤው ያመነባቸውን ፣ሕዝብ የሚያነሳቸውንና የሚፈልጋቸውን የመመሪያ አምስት ነጥቦች በመቃወም ይሁን በሌላ ምክንያት ድርጅቶቹና በዜና ማሰራጫው አውታሮች የተሰለፉት ሁሉ ማብራሪያ መስጠት ይኖርባቸዋል።ይሰጣሉም ብዬ እገምታለሁ።ከአሁን በዃላ ተሸፋፍኖ መጓዝ አይቻልም።ማን የትና ለምን እንደቆመ ሕዝቡ ማወቅ ይኖርበታል። ሰልፉም መለየት አለበት፤ “አሸፋፍነው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ”ነውና

  4. T.Goshu says:

    Dear commentator Misikir and all other genuinely concerned fellow Ethiopians,

    I strongly believe and argue that the efforts being made by individuals or groupings (political or civic) are so desirable and encouraging. I do not think any concerned feloow Ethiopian with his or her right mind is against this way of thinking and attitude. It is from this basic principle and conviction that the Otawa Conference and its performance should be taken as a very great step . It desreves due appreciation !!

    However, I strongly argue that the way it intended to approach and reach those who may have different views and approaches about how to deal with those individuals and groupings who/which have reasonable but managable doubt about the ‘ unity and terrtorial integrity of the country” sounds irrational and unproductive as far as our efforts are to go beyond our outdated ( no way unless someone accepts my way) political and cultural attitude. I do not know with whom we should engage if we decide not to go extra mile and talk with those who have different political views and intentions ? I strongly believe that unless we have a courage to have an inclusive engagement , the very backward political culture we have come across for many centuries ,and particularly since the 1970s will take us nowhere.

  5. malebo says:

    በተደጋጋሚ የሚታወቀው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርዽቶች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት የሚያምኑበት የዲሞክራሲ መሰረታዊ ባህሪ መሆኑን አያወቁት ለዘመናት አርስበርስ ሲፋለሙ ለዘመናት የውድ ወገኖችን ህይወት አየሰዋ የፋሽስቶችን አድሚ ሲያራዝምና የህዝብንናትውልድ አልቂት አያራዘመ ነው.
    የዚህም ጉባኤ ትልቁ ግድፈት ይህ በመሆኑ ለላውን ከመቃወም ጉድለታችሁን መመርመር ይሽአላል:



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.