ርዕሱ በነጠላ “አንተ” እንደማለት የተገለጸው የፕትርክና ስልጣን የሚያመላክት እንጅ አባ ጳውሎስ ስብእና ላይ ያነጣጠረ የመዘንጠል ወይንም ደግሞ አረጋዊን የማቃለል እንዳልሆነ አንባቢ ይረዳልኝ ዘንድ እጠይቃለሁ። መልካም ንባብ!
በዚህ ርዕስ ውድቀትን የሚያበሰር፣ ሰላምንና መርጋጋትን እንደ ሰማይ ከዋክብት የሚያርቅ በፈንታው ሁከትንና የሽብር ድርጊት የሚያሰፈን፣ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ውድቀት በሚጠባበቁ ልሂቃን ከብዙ ዓመታት በፊት የታቀደውን ዕቅድ ተግባራዊነት የሚያረጋግጥ፣ ወንጌላውያንም በማሳደድ ወንጀለኞች ለመሾም የተላለፈውን ውሳኔና የሚያስከትለውን ውድቀትና ድቀት አንስተን በጥልቀት እንዳስሳለን። በወርሐ ግንቦት 15/2004 የተጠናቀቀውን የሲኖዶስ ስብሰባ ባስተላለፈው ባለ አስር ነጥብ የአቋም መግለጫ በተለይ በተራ ቁጥር ስድስት የሰፈረውን ይኸውም ራሱን “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት ስለሚጠራ አጽራረ ቤ/ያን በተመለከተ የተላለፈውን ጊዜያዊ ውሳኔ ይሆናል። ህዳሴን በተለከተ ለተላለፈው ውሳኔ ቀደም ሲል በዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ “ህዳሴና መነኩሴ ለማንም ለምንም አይበጁም!”[1] በሚል ርዕስ ቀደም ሲል ለንባብ የበቃውን ከግርጌ የተቀመጠውን “ሊንክ” ተጭነው ያንብቡ።
“የዔሊም ልጆች ምናምንቴዎችነበሩ፤ እግዚአብሔርንምአያውቁምነበር፤ የካህናትም ልማድ በሕዝቡ ዘንድ እንዲህ ነበረ፤ ሰው ሁሉ መሥዋዕት ሲያቀርብ ሥጋው በተቀቀለ ጊዜ የካህኑ ሎሌ ይመጣ ነበር፥ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበረ፤ ወደ ድስቱም ወይም ወደ ምንቸቱ ወይም ወደ አፍላሉ ወይም ወደ ቶፋው ይሰድድው ነበር፤ ሜንጦውም ያወጣውን ሁሉ ካህኑ ለእርሱ ይወስደው ነበር። ወደዚያም በመጡት በእስራኤላውያን ላይ በሴሎ እንዲህ ያደርጉ ነበር፤ ደግሞም ስቡን ሳያቃጥሉ የካህኑ ሎሌ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው። ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ ይለው ነበር፤ ሰውዮውም አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት ኋላም ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ትወስዳለህ ቢለው፥ እርሱ አይሆንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፤ እንቢም ብትል በግድ እወስደዋለሁ ይለው ነበር ሰዎቹም የእግዚአብሔርን ቍርባን ይንቁ ነበርና የጎበዛዝቱ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበረች። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2: 12
አፍኒን እና ፊንሐስ (“ማህበረ ቅዱሳን”):
- የእግዚአብሔርን ህግ በመናቅ ቅድሚያ መሰጠትና መቅረብ የሚገባውን የእግዚአብሔር መስዋዕት ትተው ቅድሚያውን ለራሳቸው ይሰጡ እንደ ነበር፣ 1ኛ ሳሙ. 2: 16-17
- የመስዋአቱን ስርኣት ያስተጔጉሉ እንደ ነበር፡
- በመገናኛው ድንኳን ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋር የክብሩ ዙፋን ባለበት በእግዚአብሔር ማደሪያ ውስጥ ያመነዝሩ እንደ ነበር፡
- አስፀያፊ የከነዓናውያን የቤተ ጣዖት ዓይነት አምልኮ ይፈጽሙ እንደነበር:
- እንዲሁም የዔሊ ልጆች ምግባረ ብልሽዎች ከመሆናቸው በተጨማሪም ሌቦች እንደነበሩ ነው። (ቁ. 17)
ይህ ሁሉ የዔሊ ልጆች አስነዋሪ ድርጊታቸው በዋናነት የሚያመላተው ነግር ቢኖር አንድና አንድ ነው ይኸውም በእግዚአብሔር ላይ ያሳዩት ድፍረትና ልክ ያጣ ጣሪያ የነካ ብልግና ነበር። “ምናምንቴ” ማለት በቁም ሲተረጎም እግዚአብሔር የማይፈራ፣ እግዚአብሔርን የማያውቅና የማያምን አጉራዘለል ማለት ነው። ታድያ በዚህ ሁሉ ዓይኑ ያፈጠጠና ልክ ያጣ የሃጢአት መዓት ኤሌ ልጆቹን ለመቅጣት ከአገልግሎታቸውንም ለማገድ ያደረገው ጥረት አለመኖሩ ነው። ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ድምጽ ወዲ ዔሊ እንዲህ ሲል መጣ “ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን አከበርክ? … ክንድህን የአባትህን ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል” ክንድ ስልጣን/ጉልበት/ሐይል ነው የሚያመላክተውና ይህ ሁሉ እንደሚወስድበት ነው የሚናገረው። ለምን?
ü ዔሊ የቤቱ አባወራ/የቤተሰቡ መሪ፣ የበላይ አስተዳዳሪ ነው።
ü ዔሊ በሕዝቡም ሆነ በቤቱ ከእግዚአብሔር ሙሉ የሆነ ሐላፊነትና ስልጣን የተሰጠው ሰውም ነበርና።
በአጭሩ በዔሊ ላይ የነደደች የእግዚአብሔር ቁጣ ዋና ምክንያት፣
ü አንደኛ: እግዚአብሔር ባዘነበትና በተቆጣበት ጉዳይ ላይ ዔሊ በህጉ መሰረት በልጆችሁ እርንጃ ካለመውሰዱና ሐላፊነቱም በአግባቡ ካለመወጣቱ የተነሳ:
ü ሁለትኛ: የልጆቹ የጥፋት አገልግሎት ከወትሮ በበለጠ እየገፉበት በሄዱ ቁጥር ሁኔታዎች የትንም ያህል ቢከፉ ዔሊ ለጠራው፣ ለሾመውና ለቀባው እግዚአብሔር ባለመቅናቱ የተነሳ የሚከተለው ዓይነት ክብር የሌለው ሞት ሞተዋል።
“ዔሊም የጩኸቱን ድምፅ በሰማ ጊዜ ይህ ጫጫታ ምንድር ነው? አለ ሰውዮውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው ዔሊም የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበረ፤ ዓይኖቹም ማየት እስኪሳናቸው ድረስ ፈዝዘው ነበር ሰውዮውም ዔሊን ከሰልፍ የመጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰልፍ ኮበለልሁ አለ እርሱም ልጄ ሆይ፥ ነገሩሳ እንዴት ሆነ? አለው ወሬኛውም መልሶ እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ደግሞ በሕዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖአል፥ ሁለቱም ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም ታቦት ተማርካለች አለ። ሰውዮውም ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ ዔሊ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸምግሎ ደንግዞም ነበርና አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።” ዔሊ አንገቱ ተሰብሮ የሞተበት ምክንያት በዘጸአት 13: 13 ላይ “የአህያውን በኵር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ፤ የሰውንም በኵር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ።” በሚለው የእግዚአብሔር ሕግ መሰረት ነው።
ከራስ ጠጉራቸው እስከ እግራቸው ጥፍር በርኩሰት የተከደኑ ከዔሊ ልጆች የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው ከሕዝቡ ጋር በመውጣታቸው እስራኤል ተበተነ፣ በፍልስጥኤማውያን ፊትም ተመቱ፣ ብዙ ሕዝብም ሞተ፣ ከምንም በላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከች። የባልዋና የአማትዋ ሞት የተደራረበባት የፊንሐስ ሚስትም “የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከች ስለአማትውና ስለባሏም ክብር ከእስራኤል ለቀቀ ስትል የህፃኑ ስም ኢካቦድ ብላ ጠራችው። እርስዋም የእግዚብሔር ታቦት ተማርካለችና ክብር ከእስራኤል ለቀቀ አለች።” (1ኛ ሳሙ. 4: 19-22)
ዛሬም የተሰማ ያለው ድምጽ ይሄ ነው። ኢካቦድ ከመሰደድ ይልቅ ማሳደድን ለመረጠ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ! የሚል። አንድ ሃላፊነት የተጣለበት ባለ ሙሉ ስልጣን ዔሊ የተባለ ሊቀ ካህን የተጣለበትን ከባድ ሃላፊነት በአግባቡ አለመወጣት ይኸውም በማንኛውም ዓይነት የቤተ-መቅደስ አገልግሎት ላይ ተሰማርተው መቆም የማይገባቸው ነውር እንደ ሽልማት የተጎናጸፉ አፍኒን እና ፊንሐስ ከአግልግሎት ማገድና ማስወገድ ሲገባው ሊቀ ካህን ዔሊ ይህንን ባለመድረጉ ከፍ ስንል የተመለከትናቸው አራት ዓበይት ጥፋቶችን ኪሳራዎች በእስራኤል ሕዝብ እንዳስከተለ ዛሬም አባ ጳውሎስ አመኑበትም አላመኑበትም በሁኔታዎች ጫና ተገፋፍተው ባስተላለፉት ውሳኔ ሰደዱ ከቤተ-ክርስቲያኒቱ አልፎ በመላ ሀገሪቱ የሚያስከትለውን ዋይታ ግልጽና ግልጽ ነው። የዔሊ ውሳኔ በሕይወቱ መጨረሻ ለከፋ ውድቀት እንዳደረሰው አባ ሆይ! የእርስዎም መጨረሻ ከዚህ የተለየ አይሆንም። አባ ሆይ! በቀራንዮ የፈሰሰውን ደም ያላማከለና ገሸሸም ያደረገ መሰሪዎች የሸረቡትን ጸረ ወንጌልና በክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ላይ የተቃጣውን አንቀጽ እንደ ራስዎ ቃል ሲያነበንቡት መጀመሪያውኑ ሰላምዎትን ነስቶ ዕረፍት እንደሚያሳጥትዎት እንዴት ዘነጉት? ካደረጉት ዘንዳም ከሞት በፊት ውድቀት ይቀድሞታል! ስል በተሰበረ ልብ ነው።
“ሳሙኤልም ሳኦልን አለው በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፥ አሁንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ስማ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ አማሌቅበመንገድእየተቃወመያደረገበትንእበቀላለሁ። አሁንም ሄደህ አማሌቅንምታ፥ ያላቸውንምሁሉፈጽመህአጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንናሴቱንብላቴናውንናሕፃኑንበሬውንናበጉንግመሉንናአህያውንግደል። ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብጽ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው። የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ለአጋግ፥ ለተመረጡትም በጎችና በሬዎች ለሰቡትም ጥጆችና ጠቦቶች፥ ለመልካሞቹም ሁሉ ራሩላቸው፥ ፈጽሞ ሊያጠፉአቸውም አልወደዱም፤ ነገር ግን ምናምንቴንና የተናቀውን ሁሉ ፈጽመው አጠፉት። የእግዚአብሔርም ቃል። ሳኦል እኔ ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ተጸጸትሁ ብሎ ወደ ሳሙኤል መጣ። ሳሙኤልም ተቈጣ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ ሳሙኤልም በነጋው ሳኦልን ለመገናኘት ማለደ። ሳኦልም ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ የመታሰቢያ ዓምድ ባቆመ ጊዜ ዞሮ አለፈ፥ ወደ ጌልገላም ወረደ የሚል ወሬ ለሳሙኤል ደረሰለት።
ሳሙኤልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦልም። አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክህ ሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ አለው። ሳሙኤልም ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ምንድር ነው? አለ። ሳኦልም ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ መልካሞቹን በጎችና በሬዎች አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አምጥተዋቸዋል፤ የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው። ሳሙኤልም ሳኦልን። ቆይ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ አለው፤ እርሱም። ተናገር አለው። ሳሙኤልም አለ። በዓይንህ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ። እግዚአብሔርም። ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ። ለምርኮ ሳስተህ ለምን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህም? ለምንስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረግህ? ሳኦልም ሳሙኤልን የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቻለሁ፥ እግዚአብሔርም በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ፤ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጥቻለሁ፥ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ። ሕዝቡ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችንና በሬዎችን ከምርኮው ወሰዱ አለው። ሳሙኤልም በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል። ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ። ሳኦልም ሳሙኤልን። ሕዝቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላቸውንም ስለ ሰማሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና የአንተን ቃል በመተላለፍ በድያለሁ። አሁንም፥ እባክህ፥ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፥ ለእግዚአብሔርም እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ አለው። ሳሙኤልም ሳኦልን የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም አለው። ሳሙኤልም ሊሄድ ዘወር ባለ ጊዜ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ ተቀደደም ሳሙኤልም እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀደዳት፥ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጣት፤ የእስራኤል ኃይል እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትምም አለው።” (1ኛ ሳሙ. 15: 1- 29)
ይህ ምዕራፍ ሳኦል በእግዚአብሔር ፊት መናቁን የሚያሳይ ክፍል ነው። የመናቁም ምክንያት ሳኦል አማሌቃውያን (ማህበረ ቅዱሳን”) ፈጽሞ እንዲያጠፋቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን ትዕዛዝ አንደታዘዘው አለመፈጸሙ/አለማድረጉ ነበር። በዋናነት ይህ ያላደረገበትም ምክንያት የከበቡትን ወፋፍራም አማካሪዎቹና ሕዝቡን ፍርቶ በሁኔታዎች ላይ ትገፋፍቶ የወሰነውን ውሳኔ ነበር። ታድያ የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲያሻሽለው ሳይሆን “ያላቸውንምሁሉፈጽመህአጥፋ” የሚለውን በተሰጠው ሃላፊነት ቃል በቃል ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ታማኝነቱን ማሳየትና መግለጥ ሲገባው መልካም የሚመስል ዳሩ ግን ትክክል ያልሆነውን ስራ በመስራት በራሱ ላይ ውድቀትን እንደጠራ ነው የምንመለከተው።
አማሌቅ (“ማህበረ ቅዱሳን”) ማን ነው?
አማሌቅ ማለት በኔጌብና በሲና ምድር ይኖሩ የነበሩ ከኤሳው ዘንድ የሆኑ የምድረ በዳ ሰዎች ሲሆኑ እግዚአብሔር ያገለግለው ዘንድ ከግብጽ ምድር በድንቅና በተአምራት ከባርነት የታደገውን ህዝብ (እስራኤላውያንን) የተቃወሙ አመጸኞች ነበሩ። በተመሳሳይ “ማህበረ ቅዱሳን” ማለት በ1980 ዓም በወቅቱ የሽዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የካህናት ማሠልጠኛ የበላይ ጠባቂ በነበሩበት በብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ አማካኝነት የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ተምሬአለሁ በማለት ታሪኩን ለማያውቅ የዋህ የሚያደናግር በቀድሞ መጠሪያ ስሙ አጠቃላይ ጉባኤ በማለት የሚታወቅ ፓትሪያሪክ ብጹእ አቡነ ቲዎፍሎስ ጨምሮ በብዙሐን የቤ/ያን መምህራንና ሊቃውንት ነፍስ ተጠያቄ የሆነው ነፍሰ ገዳይ ድርጅት ነው። “ማኅበረ-ቅዱሳን” በሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያው ስር ህጋዊ እውቅና አግኝቻለሁ፣ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችን ለማከናወን ብቃትና ቅድስና አለኝ፣ ወጣቶችን በአባቶች እግር ስር እተካለሁ፣ ወጣቶችን በገንዘባቸው በዕውቀታቸው በጉልበታቸው ቤተ-ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አመቻቻለሁ፣ የቤተ-ክርስቲያኗን ሊቃውንት ዝናና ክብር እጠብቃለሁ በሚል ቁልምጫ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን “ሉዓላዊነት”፣ የአባቶችን ክብር፣ የወጣቶችን መልክና አስተሳሰብ፣ የህጻናት የእርስ በእርስ ፍቅር እንደ- ገና ኳስ በማተረማመስ እርስ በርስ እንዲካሰሱ እንዲተፋፈሩ በማድረግ ቤተ-ክርስቲያን የአርምሞና የተደሞ ስፍራ ያደረገ አገር በቀል አሸባሪም ነው። “ማህበረ ቅዱሳን” ማለት ዕቅድ አውጥቶ ፕላን ነድፎና በጀት በጅቶ በማኅሌት፣ በኪዳን፣ በስግደት ያደሩትን አባቶችን ለህዝቡ ትምህርት ለመስጠት እንቅልፋቸውንና ጊዜአቸውን ሰውተው መዝሙር በማጥናት ያደሩትን ወጣቶችን፣ ተቃቅፈው ያደሩትን ባለ ትዳሮችን ለማተረማመስ፣ ለመክሰስና ጥላቻ ለመዝራት በሰዎች ዓይን ዘንድ እውቅና “ያገኘና/የተሰጠው” ሕጋዊ ሽፍታም ነው።
በአንዳንድ ጥንታውያን መጻህፍት በቁጥር 15 ላይ “ሕዝቡ” የሚለውን ቃል “ሰራዊቱ ከአመሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው ምርጥ ምርጡን በጎችና በሬዎች ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መስዋዕት እንዲሆኑ ሳይገደሉ የተዋአቸው ናቸው” በማለት ተጽፈዋል። ታድያ አባም ቢሆኑ ሃላፊነቱን ካራስዎትን አውርደው ያደረጉትን ያደርጉ ዘንድ ለገፋፋዎት ወደ ሲኖዶሱ አባላት ለማስታከክ ቢሞክሩም ቃሉ በማያሻማ መልኩ የሚለው ይህንኑ ነው።
የሚያሳዝነው ሳኦል እግዚአብሔር አማሌቅን ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ የታዘዘውን ትእዛዝ በሙላት አለመፈጸሙ ብቻ ሳይሆን በ2ኛ ሳሙ. ምዕ. 1 ተጽፎ እንደምናገኘው የሳኦል ነፍስ ያለፈችው በአንድ ተራ አማሌቃዊ እጅ መሆንዋን ነው። በቁ. 11 “ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ይዘው ቀደዱ። በሰይፍም ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን ለእግዚአብሔርም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፥ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።” እንዲል አባ ሆይ! ተገድዶውም ሆነ እጅዎትን ተጠምዝዘው የወሰኑትን ውሳኔ በመቀመጫዎት ላይ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳውን አጥፊና አውዳሚ ፈንጅ የጠመዱ ያክል ይቁጠሩ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ላሳስቦት እወዳለሁ።
የሳኦል ሁኔታዎችን ያማከላ በአንጻሩ ደግሞ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ወደ ጎን ያገለለ ውሳኔ በቀሪው ዘመኑ ፍርሃት፡ ጭንቀትንና ውጥረትን እንዳስከተለበት ሁሉ አባ ሆይ! ደቂቀ አማሌቅ “ማህበረ ቅዱሳን” ሾመውና ደግፈው (ባይደግፉትም ተገፍተው ባስተላለፉት ውሳኔ ብቻ) በህልምዎትም ሆነ በውንዎት የሰላም እንቅልፍ እተኛለሁ ብለው እንዳያስቡት። ሳኦል ባለመታዘዙ የሁከት መንፈስ እንደገባበትና ከዚህም የተነሳ በየ ተንቋይ ቤቱ መንከባለል ዳዊትንም ለመግደል እንቅልፍ እንዳጣ ሁሉ ይህንንም የእርስዎ ዕጣ ፈንታ ይሆናል።
በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት የሞላበት ሃጢአትና ርኩሰት በመፈጸም የሚታወቀው፣ ወንጌልን የሚቃወሙ ወንጀለኞች!፣ እርማቸውን ያልቆረጡ ነውረኞች፣ ያለ ክስ ምህረትንና ርህራሄን የማያውቁ ወንጌል ያላለፈባቸው አጥፍቶ ጠፊዎችና ደም የተጠሙ ዛሮች፣ ሰላምንና ዕርቅን የሚያርቁ ሁከተኞች፣ ሽንፈት የተከናነቡ ሽብርተኞች፣ መለያየት ጽብንና ጥላቻን የሚደላቸው ጽንፈኞች ሾመውማ እንዴት ይመችዎታል? ምንም አይመችዎትም! እንደው ቃዬልም እግዚአብሔርን አለው እንዲል ወንድሙን አቤል የገደለ ቃዬል በእግዚአብሔር ፊት በመውጣት “ኃጢአቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት እነሆ ዛሬ ከምድር ፊት አሳደድኸኝ ከፊትህም እሰወራለሁ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል” (ዘፍ. 4፥ 13-14) እንዲል አባ ሆይ! ዛሬስ ያስተላለፉት ውሳኔ፣ ያሰሙት ድምጽ፣ የበደሉት በደልና የፈጸሙት ስህተት በሰው ላይ ሳይሆን በምድር ክበብ ላይ በተቀመጠው በእግዚአብሔር ላይ ነውና ትልቅ ቅጣት በራስዎ ላይ ጠርተዋል። በሁኔታዎች ጫና ላይ ተመርኩዘው ለወሰዱት እርምጃም ሁሉ ሃላፊነቱ ይወስዳሉና ያገኝዎትን ሁሉ ይገድልዎታል! ምን ነው ቢሉ ድልና ጉልበት ያለው በሰዎች ቁጥር ብዛት ሳይሆን ከእውነትና ከጽድቅ ሰፈር ነውና።
በክፉ ላይ እንዳልተኛ አንቃኝ!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America
May 26, 2012

Please come to the point! or don’t waste your time!
Deakon Mulugeta( Mulusidib). Business as usual again. Your article is full of insult and scolds as usual. You and your protestant financed traitors were conspiring to convert Orthodox church to protestant. Mahibere Kidusan was the one who stopped your demonic mission. The Synod was fully convinced with all the evidence presented by Mahibere kidusan . Eventually you and members of the demonic plot were excommunicated. That is why you hate the church fathers and Mahibere kidusan in particular. you are still echoing the same sermon now and then. Everybody knows about you, your plan to convert the church to protestantism and no wonder if you are insulting everyone who is pro Church and its original teaching.
Keep on doing your demonic heresy, Mahibere kidusan will knock your head as usual. One by one the enemies of the church are being punished and evicted from the church.
For the time being i invite you to watch this link
http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=8AnBlMKPBUw#!
የየጁ ደብተራ ቅኔ ሲያጥረው ፉከራ ገባ እንዲሉ የተከበሩ ዲያቆን የሚያደርጉት መዘላበድ በጣም የበዛና ሌላ ሴራ ያለው ይመስላል የግል የዘኬና የዝና ጠብ ካሎት እዚያው ተጠያየቁ ያለያ ጥቅስ እያስታከኩ የተቋምን ስም ማጉደፍ ያውም ያለ በቂ ማስረጃ አግባብ አይደለም ጌታው መጻፍ ካለቦት ነብሰ ገዳዩና ዘረኛውን ታጋይ ጻውሎስ (አባ ዲያቢሎስን)እና አባ መላኩን (አባ ምላጭ) የሚያጋልጥና የሚያወግዝ ጽሑፍ ያዘጋጁ ያለያ በባዶ ቃላት መዘላበዱ አይሰራም ለማህበረ ቅዱሳን የመለስና የተላላኪዎቹ ይበቃዋል ማህበሩ መተቸት ካለበትም አሁን ወቅቱ አይደለም የትኛው አባት አለና ለውስ ደግሞ ወጣቶች የሚተቹት በአጠቃላይ ስለዚህ ስራ ፈት የደብተራ እንቶፈንቶ ብዙ ማለት ባልፈልግም ለዚህ ዌብ ሳይት አዘጋጅ ላስተላልፍ የምፈልገው መልእክት እንዲህ አይነት የግል ችግር ያለባቸው በቀለኞች ማላገጫ እንዳይሆን ማድረግ ተገቢ ነው
በበታችነት ስነ ልቦና የሚማቅቀው የውሸት አባት የጥፋት ጌታ ጭራቁና ሰው በላውና ሕገ አራዊቱ መለስ ዜናዊ ከነጠነባ አስተሳሰቡና ከነድኩማን ስብስቡ ሕዝባችንን በልቶ ማደር እንኳ እስኪሳነው አየዘረፈና ሃገር እየሸጠ ለሃገር መሪነት ይቅርና ለእድር ሊቀመንበርነት የማያበቃው የአመለካከት ዝቅጠትና በትንባሆና በጫት ሱስ የተጠመደ ዋልጌ ተራ የመርካቶ ቁጭራ መምሕራኑን በችሎታ እጥረት ሙስሊሙን በአክራሪነት ለመክሰስ ሲሞክር ትንሽ እንኳ አያፍርም የሕዝብን ደም በዋንጫ እንዳልጠጣ አጭበርባሪ ‘ወገኖቼ ይሄንን ከትግራይ ጀምሮ እስከ አዲስ አበባ በዜጎች ስቃይ እየነገደ የደለበ ደም መጣጭ ጭራቅ ዝም ከተባለ ገና በቁም ያለነውን ብቻ ሳይሆን በመቃብር ያሉትን ጭምር በድን የማይምር በላይሰብ አውሬ በመሆኑ የተከፈለው ተከፍሎ ያለቀው አልቆ ይህን ጥንብ አንሳ ማሶገድ ብቻ ነው ብቸኛው አማራጭ እንዴ ጎበዝ የሊብያ ሕዝብ እኮ ቢያንስ እንደኛ በርሃብ እንዲያልቅ አልተፈረደበትም ስለዚህም ረሓብና ችግር ሳይጨርሰን ይህን አውሬ እናስወግደው
ለማህበረ ቅዱሳን ያዘጋጁት ጥቅስ ለዚህ አይነቱ በላያሰብ አውሬ ያድርጉት ያልበላንን አይከኩልን
ዲያቆን ስለዚህ አራዊትና ስለ ሙስሊምና ክርስቲያን የቆየ የፍቅር የአንድነት በታሪክና ጥቅስ የታገዘ ጽሁፍ የሚችሉ ከሆነ ያዘጋጁ አለያ አይዘላብዱ
አትነሳም ወይ የዕምነት ነጻነትህ
አልተዋረደም ወይ!
#ወደ ጌታህ መንገድ፣ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል)፣ ጥራ፤ በዚያችም እርሷ መልካምበሆነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፤ ጌታህ እርሱ ከመንገደ የተሳሳተውን ሰው አዋቂ ነው፤ እርሱም ቅን የሆኑትን ሰዎች አዋቂ ነው፡፡$ (ቁርዓን 6፡125)
ውሸትን የሚቀጣጥፉት፣ እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነሱ ብቻ ናቸው፡፡$ (ቁርዓን16፡105)
#እንግዲያውስ ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ። በቃላችንም ቢሆን በመልእክታችን የተማራችሁትን ትውፊት ያዙ$ 1ተሰ.2:15
#ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን፤ ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ$ 2ጢሞ.2:2
ለወጉ የሰው በላውና ሃገር ሻጩ መለሰ ዜናዊ የሚመራው አገዛዝ አያሌ የገበሬ ልጆች ለመብት ለነጻነት ሲሉ በከፈሉት የሕይወት መስዋዕትነት ተረማምዶ አወጣሁት ባለው ህገ መንግስት ምዕራፍ 2 አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 3 እና ምዕራፍ 3 አንቀጽ 27 መሠረት መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባና የዜጎች የእምነት ነጻነትን እንደሚያከብር በግልጽ ቢያስቀምጥም ገና ስልጣነ መንበሩን ከተቆጣጠረ እለት ጀምሮ የሃይማኖት ተቋማትን በመዳፈር በተለይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በሙስሊም ኢትጽያውያን የዕምነት መሪዎች ከህገ ሃይማኖትና ከምዕመናን ፈቃድና እውቅና ውጪ የራሱን ተወካዮች በግድ በማስመረጥ በቀጥታ የዕምነት ተቋሞቹን በፖለቲካ መዋቅሩ ስር በማድረግ በሃገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የእምነት ነጻነት በመዳፈር ላይ ይገኛል።
የወያኔ አገዛዝ ከዚህም በላይ ሃይማኖትን በሃይማኖት ላይ በማነሳሳት በስውር ሴራ በመወጠን ለብዙ ዜጎች ሞት ስደትና ለቤተክርስቲያናት እና ለቤተ መስጊድ መቃጠል ምክንያት በመሆን ለሺህ ዘመናት በሰላምና በፍቅር በኖረው ሕዝባችን ላይ መለያየትን በማንገስ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም በየግዜው በተላላኪዎቹ አማካኝነት ሲያካሂድ የቆየው ሠይጣናዊ ተንኮል አልበቃ ብሎት በዓሁኑ ወቅት የጥፋት ሴራውን አጠናክሮ በመቀጠል በሁለቱ ታላላቅ የዕምነት ተቋማት ላይ የከፈተው ዘመቻ ተባብሶ በመቀጠሉ በተለይ በሙስሊም ወንድሞቻችን የዕምነት ነጻነታቸውን ለማስጠበቅ የጀመሩት ሰላማዊ ትግል ተጠናክሮ መቀጠሉና ያሳዩት ጽናት በእጅጉ የሚደነቅ ከመሆኑም በላይ ለክርስቲያን ወገናቸው አርያነትም ጭምር በመፍጠሩ ሃይማኖቱን በቅጥረኞች የተደፈረው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመን በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞውን ማሰማት ጀምሯል።
የመለስ ሕወሐት ቋንጃ ቆራጭ የአጋዚ ነብሰ በላ ጦር የዕምነት ስርዐቱን ለማከናወንና በአንዋር መስኪድ በጸሎት ላይ በነበረው የሙስሊም ምዕመናን ላይ በከፈተው ተኩስ ለዜጎች ሞትና መቁሰል ምክንያት ሆኖ የቆየው የዕምነት ነጻነት ጥያቄ ተገቢውን መፍትሔ ሳያገኝ በመቆየቱ መላው የሙስሊም ሕብረተሰብ ድጋፍ የተሰጠውና ጥያቄዎቹን በሰላማዊና በሕጋዊ ሁኔታ ከሚመለከተው መንግስታዊም ሆነ መጅሊስን እየመራ ከዐለው ሕገ ወጥ አመራር ጋር በመነጋገር የሙስሊሙን ምዕመን ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ሁኔታዎች በማመቻቸት የሃይማኖት መሪዎቹን ያለማንም ጣልቃገብነት በነፃነት እንዲመርጥና ነባሩን የሙስሊሙን አስተምህሮ ለመበረዝ ድጋፍ እየተሰጠው ያለው የሃይማኖት ብረዛና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ አህበሽ የተባለ አዲስ የእምነት አስተሳሰብ ለመጫን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባኤ መጅሊስ መሪዎች መሳሪያነት ሰፊ ዘመቻ እያደረገ ያለው አግባብ ያልሆነ ድርጊት እንዲገታለት የላካቸውን ወኪሎቹን በማስፈራራትና በማዋከብ ሂደቱን ወደአላስፈላጊ ሁኔታ ለመክተት እየገፋ ያለው የወያኔ ቡድን ከድርጊቱ እንዲቆጠብና ከእምነቶቻችን ላይ እጁን እንዲያነሳ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ሆኖ ድምጹን ማሰማት ይኖርበታል ።
ይህው በሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ግፊያና ለሃያ አመታት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የወያኔ ቅጥረኛ በሆኑት አባ ጻውሎስ አዝማችነት ሲፈጸም የቀየው ሕግ አልባና ኢ ሐይማኖታዊ ተግባር ቢዘረዝሩት የማያልቅ ለዕምነቱ ተከታዮች አይደለም ላልሆነው እንኳ እጅግ የሚሰቀጥጥ አሳፋሪ አድራጎት በባሰ መልኩ ቀጥሎ ዛሬ እጅግ ወደ ከፋ ደረጃ ተሸጋግሮ ለሺህ ዘመናት ተከብረውና ተጠብቀው የኖሩትን በተለያዩ ክፍለ ሐገራት ያሉትን ገዳማት ሁን ተብሎ በሚካሄድ በሚመስለው የጥፋት ዘመቻ ንብረታቸው እንዲዘረፍና በእሳት እንዲወድሙ በማድረግ በአሁኑ ወቅት በዝቋላና በአሰቦት ያሉት ገዳማት በእሳት ቋያ ሲለበለቡ ከመንግስትም ሆነ የቤተክርስቲያኗ የበላይ አካል የሆነው ሲኖዶስ ዕርዳት መነፈጋቸው ሳያንስ የሃይማኖቱ መሪዎች ቸልተኝነትና የማህበረ ምዕመናኑ ዝምታን በፍርሐት የቆጠረው እብሪተኛው የመለስ አገዛዝ የዋልድባ ገዳም ንብረት በሆነው አካባቢ ለውጭ ባለሃብቶች ለስኳር ልማት የሸንኮራ አገዳ ለመትከል በሚል የመነኮሳቱን አጽም በዶዘር እየነቀለ በማንዐለብኝነት የሚያደርገውን የግፍ ድርጊት አገዛዙ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለው ንቀት ምን ያህል እንደሆነ ከማሳየቱም በላይ ሁላችንም ተጋግዘን በምንችለውና በማንኛውም መንገድ ታግለን መብታችንን ለማስከበር ለመነሳት ካልቆረጥን በስተቀር ከዚህ በላይ የቀረው እንደ ጥንታዊው የባሪያ አሳዳሪ ስርዐተ ማህበር በቁማችን መሸጥ ብቻ ስለሆነ ለመብትና ነጻነታችንና ለሃይማኖታዊ ስርዐታችን መከበር የሚያስፈልገውን ዋጋ ለመክፈል መቁረጥ ይኖራል አለያ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ የሚለው ተረት መፈጸሚያ መሆን ነው።
እኛ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢዎች ለወገናችን መግለጽ የፈለግነው በዚህች አጭር መጣጥፍ በዕምነት ተቋሞቻችን ላይ የደረሰውን በደል ለመዘርዘር እንችላለን ብለን ሳይሆን በዘር በቋንቋ በብሔርና በሃይማኖትን እንድነጣጠል ሠፊ ዘመቻ ከተካሄደና ለየራሳችን ብቻ እንድናስብ ከተደረገ በኋላ ይህው ዛሬ በተመሳሳይ ወቅት ሃገራችን ለባዕዳን እየተቸበቸበች በሃይማኖታዊ ነፃነታችንና እጃቸውን ከተው የፈለጉትን ለማድረግ እንዲደፍሩን ያስቻላቸው ተነጣጥለን በመገኘታችን በመሆኑ ይህ ይበቃ ዘንድ የተለያየ ብሔረሰብ አባላት እና የተለያየ ሃይማኖት ተከታይ ብንሆንም በአብሮ አደግነታችንና ያተረፍነው ወንድማማችነት ሁሉን ነገር ለመገምገም በመቻላችን የደረስንበት የጋራ ግንዛቤ ለወገናችን ለማካፈልና ከኛ በእውቀትም በእድሜም የሚልቁ ታላላቆቻችን ይህን ዐርዓያ አድርገው ከመለያየት ይልቅ በጋራ ቆመን የጋራ ጠላታችንን መመከት እንድንችል እንዲረዱና በይበልጥም በሕዝባችን ላይ የተደገሰውን የእርስበርስ በሃይማኖትና በጎሳ አሳበው ለማጫረስ በወያኔ አገዛዝ እየተሸረበ ያለውን ሴራ ለማክሸፍ ድርና ማግ ሆኖ የያዘን ኢትዮጵያዊነታችን ማጠናከር ከመቼውም ግዜ በላይ ለሕልውናችን አስፈላጊ የሆነበት ግዜ ላይ መድረሳችን ግንዛቤ ሊሰጠው እንዲገባ ለመጠቆምና ዘርና ሓይማኖት ሳይለየን የጋራ ጠላታችንን ለመታገልና ሃገራችንን ለመጠበቅና እንድንነሳ የአብሮነት ጥሪ ለማድረግ ነው።
አላህ ሰላምና ፍቅሩን ይስጠን! እግዚያብሔር ለእውነት ዘብ እንድንቆም ወኔውን ያድለን!
Do not bring spritual issue to this political page
ውሾቹ ይጮሃሉ: ግመሎችም ይጋዛሉ:: ሙሉጊታ እግዚአብሂር የሰጠህን እድል ብትጠቀም ምን አለ:: አርፈህ ብትማር እንዲህ ያለም ስህተት አትሰራም:: ማህበር ቅዱሳን ለ20 አመት ተፈትኖ እዚህ የደርሰ ነው:: የኢትዮጵያ ህዝብም ቢተክርስቲያና ያለችበትን ችግር ተመልክቶ አደራ ሰጥቶታል:: የተሰጠውን አደራ መጠበቅ የማህበሩ ስራ ነው:: እውነትንም ሰለያዘ ይቀጥላል:: እባክህ ወንድሚ ወደ ልብህ ተመለስ ንሳህም ግባ:: የሰላምንም ድምጽ ትሰማታላህ::
Why people take the respected title ’Diacon’ to publicize themselves; shame on you man. You are a disgrace
Dear Elias,
I indeed acknowledge your effort for sharing value information. I thought you read every article before posting. If you do that and also you see the article from this guy wins your favor to be disclosed to your reader, that is so embarrassing. I do accept people can do and write whatsoever they feel, but they need to have their own religious blog not on what you have.
This guy is not orthodox. He is deliberately insulting us. I DO NOT suggest you to post article with religious topics that is different stuff.
For the Mulugata, Please I strongly suggest you to read bible not only reading but also understanding well not from your interest point of view but from the writers point of view. For the reader Please do see this guy as ETOC.
ተሀድሶ እና ነጭ አህያ ሁለቱ አንድ ናቸው: በደረሱበት አመድ ላይ ከመንከባለል ያለፈ ነገር አያስቡም: ጌታውንም የሚያስብበት እድል የለውም:: አየ ዲያቆን ተብየ ለአቶም ብቁ አይደለህ::ማእረጉ ስለማይመጥንህ አትጻፈው:: ቀሽም::
ዽ/ን ሙሉጌታ በአብዛኛው ጽሁፎችህ በተለይ ቅዱስ ነኝ ብሎ እራሱን ስለኮፈሰው መርዛማ ድርጅት ያለህን አቅዋም ባብዛኛው እጋራዋለሁ:; ይህ ድርጅት ለወደፊቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ትልቅ አደጋ ነው:; ግን ህዳሴ ስለሚለው ሳይሆን “መነኩሴ ለማንም አይበጅም” የምትለውን መናፍቃዊ የምትመስል ቃል ነፍሴ አልወደዳትምና ጽሁፉን እንደገና በሌላ ርእስ ብታወጣው መልካም ይመስለኛል
gegemaw Mulugeta Metah zarem? I never ever seen a stupid person like in my life. You nare loser and you are the dog that barks after the comel! How come on the world a person is taking about the same shit for his enire life? O my God ! Is that True Elias you are DIVIDER and undercover agent for Shabya?
ዪህ ሰሃፊ በኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች ተወግዞ የተባረረ ነው.በመናፍቅነቱ እና በተሳሳተ አካሂዱ እንዲሁም አይምሮ የታመመ በመሆኑ የሚያድርገዉንና የሚጽፈውን እንኩዋን ሰው መረዳት እስክማይችል ዽረስ ማንነቱን መረዳት ትችላላችሁ. መነው አገረህ በመታህ አንተ የዳቢሎስ ዲቃላ እኒ ሴቱዋም አልምርህም. ትሮቴስታንት መሆንህን ለህዝብ አሳውቅና የራስህን ሃይማኖት ሲበክ. እድሜ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት መስሃፍ ቅዱስን አስተምራሃለች የበላህበትን እጅ ነካሽ ልትሆን. ማህበረቅዱሳን ደሞ ባንተ አፍና ሊፊለፋ አይተፉም. ስንዴው ከእንክርዳዱ የሚለይበት እሩቅ አይሆንም.ጊዚህን ተብቅ!!!
ራስክን መርምር ወንድም ማን እንድሆንክ አውቀንሃል
Dear mulugeta u are anti tewahedo we know u very well u are a dead dog go to hell we know very well MK more than u and u r tahedso protestant u go and service to tahdeso never & ever u can’t be tewahedo. U a stupid ediet person don’t call by diakon shit u like a prostitute never write in this blog for our religions
Oh my God this man has not have any relative who can take him to Hospital! He is really mad. Dear readers have you seen people with mental problem around holy water. They simply talk. it is grammatically completely wrong and no coherence of ideas. His writing has no any substance beyond that even he has no the gut to know whether his writing has a connection with what he wants to describe. pls help him by talking to Hospital
“Great minds discuss ideas; Average minds discuss events; Small minds discuss people.” -Eleanor Roosevelt
ራስህን ዲያቆን ብለህ የበግ ለምድ ለብሰህ የመጣህ። የዘበዘብከው ነገር ውስጥ አንድም ውሃ ሚቆጥር ነገር የለውም። ራስህንን መርምር ዝምብለህ አትዘላብድ።