ሰፈሬ ሽሮሜዳ እንጦጦ ኪዳነ ምህረት አቅራቢያ እንደመሆኑ መጠን በርካታ ግዜ በአጋንንት የተለከፉ ፀበልተኛ ወገኖች “ትለቃለህ አትለቅም” በሚለው አስገምጋሚ የአስጠማቂው ቁጣ ሁልግዜም መልሳቸው ከተረበሸ ድምፅ የሚፈልቅ “እለቃለሁ!” የሚል ሲቃ እንደነበር አይቻለሁ። ችግሩ ግን ብዙ ግዜ “እለቃለሁ” ካሉ በኋላም በነጋታው “አብሬያት አድጌ፣ አብሬው ከርሜ” ለማን ትቼው እለቃለሁ” ብለው ድጋሚ ያገረሻሉ። አሁንም አስጠማቂው “አንተ ክፉ መናጢ ትለቃለህ አትለቅም…!?” ሙግታቸውን ይጀምራሉ። መስቀል እና ፀበል ለአጋንቱ ፀር ናቸውና “እለቃለሁ እለቃለሁ…” እያለ ይለፈልፋል። ምሱን ተናግሮ ቀምሶ ጨርሶ እስኪለቅ ድረስ ግን “እለቃለሁ” ስላለ ብቻ አይታመንም!
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዘንድሮም “እለቃለሁ!” እያሉ ነው። በእርሳቸው ፍቅር የተለከፍን እኛ፤ “ያለ እርስዎ በሳል አመራር ችግር እና ጉስቁልና ያበስለናልና እባክዎ ይሄንን አሳብ ወደ አዕምሮዎ አያምጡት!” ብለን ብንመክርም፤ ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አያስጎምጁን!” እያሏቸው ይገኛሉ።
በተደጋጋሚ እንዳየነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አስለፍላፊያቸው ብዙ ነው። ከዚህ በፊት በፓርላማ ውስጥ፤ ከዛም በተለያዩ የውጪ ሃገር ጋዜጠኞች “ትለቃለህ አትለቅም!” የሚሉ አስለፍላፊዎች አጋጥመዋቸዋል። ያው የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትራችንም ደንብ ነውና፣ ስርአቱ ነውና “እለቃለሁ!” እያሉ በተደጋጋሚ ለፍልፈዋል። ነገር ግን አለቀቁም።
እኔ የምለው ግን ክቡርነታቸው በርካታ ግዜ “ለቃለሁ” እያሉ ሲተዉት፣ “ለቃለሁ” ሲሉ ሲተዉት ሰዉ ንግግራቸውን አጓጉል ከእርኩስ መንፈስ ጋር እያዛመደባቸው እኮ ነው…!
በነገራችን ላይ ከላይ ያለውን የኪዳነምህረት ፀበል ትዝታዬን ያመጣሁት እንደው ነገር ለማሳመር ብቻ ብዬ አይደለም። በቅርቡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንድ የውጪ ሀገር ጋዜጠኛ “ትለቃለህ አትለቅም?” ብሎ ሲጠይቃቸው “እለቃለሁ!” ብለው በመናገራቸው (“እለቃለሁ” ብለው ሲለፈልፉ…” ልላቸው ነበር! ይቅርታ ከላይም “ለፈለፉ” የሚል ቃል ካለ ከፀበልተኞቹ ጋር ተምታተውብኝ ነውና በጅምላው ይቅርታ ጠይቄ እቀጥላለሁ)
እና ታድያ ጋዜጠኛው በጠየቃቸው ጊዜ “እለቃለሁ!” ብለው ሲመልሱ አንዱ ወዳጄ “አፈር ስሆን ‘ምስህ’ ምንድነው? በለህ ጠይቃቸው እና ያሉትን አቅርበን ቀምሰው በደንብ ይልቀቁን ሁሌ “ለቀኩ እያሉ አያስጎምጁን!” ብሎ የተናገረውን አስታውሼ ነው።
እኔ የምለው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስልጣን መልቀቅ ከአጋንንት መልቀቅ ጋር ማመሳሰል ፍትሃዊ ንፅፅር ነው ትላላችሁ…!?

አቤ
ቀልድህ እንዴት ደስ ይላል::
ለዛ ያለውና ቁም ነገር የተሞላ ነው::
“ዝንቱ ዘመድ ኢይወጽዕ ዘእንበለ በጾም ወበጸሎት” ብሎአል ጌታችን
ትርጉም
“ይህ አብሮ የኖረ ወዳጅ ጋኔን በጾምና በጸሎት በስተቀር አየወጣም”
ማለት ነው::
ስለዚህ ምሱ ጾምና ጸሎት ነው እላለሁ::
የማርክሰዘም አጋንነንት ስለአለባችው እሱ ደግሞ በጎንደር በ አርባአራቱ አደባራት ካልተገዘተ አይለቃችዉም
ለላው ደግሞ እንዳየከሰሱ ዋስተና የስታችወና የመን አገር ይሂዱ እና ሰለ ሳባወያን ወደ እትዮፕያ አሰፋፈር ያማሩ ከዝያማ የትራይን ህዚብ ያውቃሉ
Ergoraw Reply:
June 1st, 2012 at 2:39 pm
የሀማ ራስችውን እንዲያውቁ ይረዳችው ይሆናል ሰውም ይሆናሉ
Dawit Reply:
June 3rd, 2012 at 11:37 am
very true mark.Lenin,Stalin are all Jew. All To take over people freedom. If you look at the so called tigray state flag the yellow and red are exactly the communist state colors. Communism is a secret monopoly strategy to control every thing!Look at the world today corporations are merging as one, The banks fund wars,May of the world wars are fought because it brought big profit for bankers! Let’s wake up people! We don’t want slavery! Communism is the an ideal system for international robbers,colonizers,organized crime syndicates!
ምሱ 7 ጎራሽ ማካሮፍ ሽጉጥ ይመስለኛል:: ኢጎዉ ከቤተመንግስት አስወጥቶ ስለማያኖረዉ ለብስጭቱ ቀን ቢሆነዉ ብዬ ነዉ::
ፍሪዳ በኪራይ ዘትግራይ Reply:
June 2nd, 2012 at 12:04 pm
ይመችህ ወንድሜ-እንደ ስምህ ጥንቅሽ ሀሳብ! እኔ እንኳን ከነነፍሱ ሞቶም ባገኘው በጎራዴ ከአስራ ሁለት ብበልተው ቅሥስ አይለኝም!
አቤ እግዜር ይባርክህ: በጣም ቅመም የሆነች ጽሁፍ: የሚገርመው አንጀቴም ርሶ ጥርሴም ፈገግ ብሏል!
amazing article !!!!!
You are the Best!
ምሱ አንድነትና እምቢታ ነው አበ
Thanks Abe the Tokichaw.
ሰውየው ስታስበው ዝምብሎ ይለቃል? የሚሆን አደለም ቢሆን እንኩዋን ምሱ ያው የታውቀ ነው {ይሰው ደም} ነው እና የነ እስክንደር ነጋን የነ አንዱዋለም አራጊን ደም ቢጎነጭ እንኩዋን አይለቅም
Meless went leave before his wife and his family make some business destructing and selling Ethiopian Airlines, you will see it soon!!!!!!!!!!!!!!!
Abe! Is there a ‘dislike’ button to your article?
አቤ:
ሰሞኑን ባህርዳር የሰማሁትን አስታወስከኝ::
“‘ይህ ግድብ ሳያልቅ እንዴት እለቃለሁ?’ እንዳይለን ብቻ! እኛ እንደምንም ብለን እንጨርሰዋለን” ማለት ጀምሯል አሉ የባህርዳር ሰው::
ቀሪውን የዛሬ 3 ዓመት ተመልሰን እናወጋዋለን:: እስክዛ ድረስ የራሳችንን ሥራ መሥራት ነው::
አቤ ተባረክ ሰውየው ምሴ የሰማይ ጥግ አፈር ነው እንዳይለን ብቻ
Melese has a big agenda for us! many more conspiracy will come from his criminal organization Off-course he has a thousands of books people say he is educated, the first leader to wear tree piece of suit, western style. Gobez Information is Not Knowledge! True Knowledge is having common sense and character. From Now On His Name Should be ደነዝ መለስ.