ክፉን ሥራ እግዚያብሔር ይገልጣል፤
የዐርብ ፍቅረኞችም በትንሳዔው ይወድቃሉ
የተሰወረ የማይታይ፣ የተከደነ የማይገለጥ የለምና ሆኖም እስኪገለጥ ግን የአካልብት ልክፍት የማይቀር ነውና ባለንበት ዘመን በፓትርያርክ በብጹዕ አቡነ መርቆሪዎስ በሚመራው በሕጋዊው ውጭ በሚገኘው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ በገጠመው ወከባ ሁላችንም እራሳችን ባለመመርመር ባለመታደል ዋኖቻችን ለሆኑት በጹአን አባቶቻችን ለልፋታቸው ምስጋና ሳንሰጥ ጭራሽ ከሳሽ ብንሆንባቸውም እግዚያብሔር አምላክ “በውሃ ውስጥ ባለፍክ ጊዜ ካንተ ጋር እሆናለሁ በወንዞችም ውስጥ ባለፍክ ጊዜ አያሰምጥህም፣ በእሳትም ውስጥ በሄድክ ጊዜ አትቃጠልም ነበልባሉም አይፈጅህም” ኢሳ 43፡2 በሚለው ቃል እየተጽናኑ፤ “ብነኖርም ለእግዚያብሔር ብንሞትም ለእግዚያብሔር ነው”ብለው ሳይበገሩ በአንድነት ቆመው ይልቁንም የከዳተኞች ክፋት ለቀኖች ክፋት መስታወት ሆኗቸው ጊዜውን እየዋጁ የያዙትንም አልበተኑም።
ከዳተኞች ግን መንጋውን በመጠበቅ ለተጉት አባቶች አጋዥ ከመሆን ይልቅ የሥጋ ምኞት ለመፈንቅለ ሥልጣን ህሊናን የሸጡበት የተሳከሩ መነኩሴ መሰል አምስቱ ከልቦች የራሳቸው የልክፍት አረር በአባቶች ላልይ ተኩሰው ህዝቡን ለመከፋፈልና የአባቶችንና የምዕመናንን ስም እንበለ ከነቱ በማጉደፍ በየዋሁና የሲኖዶሱ ስብከተ ወንጌል የጅርባ አጥንት በአባ ወልደተንሳዔ ስም በመነገድ ምዕመናን በምዕመናን ላይ በማነሳሳት ዘመቻ ተጠምደዋል። የዚህም ወጤቱ እየታየ ነው። ወንጌል ሰባኪ አባ ወልደ ተንሳዔን እኛን ሲያስተመሩን በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር “ አውጣኝ ያለ ወጣ፣ አባላኝ ያለም በላ፣ ተኝቶ ተገኝቶ አሳማ ተበላ” እንዳሉን ሁሉ ዛሬ በተገላቢጦሽ መሰሪዎቹ አምስቱ ከልቦች እርስዎን ተኝተው ያገኙዎት በሚመስል ሁኔታ በስምዎ ነገደው እርስዎንና ቤተክርስቲያንን ከመብላታቸው በፊት እንደእግዚያብሔር ቃል “አንተ የምትተኛ ተነስ ንቃ ጊዜው መሽቷልና” በርትተው ይጸልዩ። ምናልባትም ተጎድተውም ቢሆን ለቤተክርስቲያኒቷ አንድነት ሲሉ ትልቁን የወንጌል ተራራ ይቅርታን ይድፈሩና መሰሪዎች ኢካቦድ በጨለማ የተከሉትን በይቅርታ በመንቀል ታሪክ ይስሩ። ጊዜው መሽቷል።
በተለይም በኢትዮጵያ በግፍ የለነጻነት የታፈነውን ህዝብ እንደቤተክርስቲያን ቀደምት አባትነታቸው የኢትዮጵያዊውን መከራነ ፍዳ እረፍት ነስቷቸው ገፈኞች ቀንበራቸውን ከሕዝቡ ላይ እንዲያነሱ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በመላው ዓለም አደባባይ ለነጻነት በመጮህ ላይ የሚገኙትን በሁለት ጎን የተሳሉትን የየኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሊቀ ጳጳስና የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ አረጋዊው ብጹዕ አቡነ መልከ ጻዲቅን ለምን ወያኔን አወገዙ፤ ለምን የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢትዮጵያዊያን ናቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ስለሚደርስባቸው በደል ቤተክርስቲያን ትጮሃለች በማለት በመናገራቸው ለምን በዚህ የወያኔን ግፍ አጋለጡ በሚል ዲያቢሎሳዊ ተልዕኮ አባቶችን በድረ ገጾቻቸው በማዋረድ ሴራቸው እየተስተዋለ ነው።
ሆኖም ሊቀ ጳጳሱ ብጽዕ አቡነ መልከ ጻዲቅ እውነት አርነት ያወጣቸው እንደ እግዚያብሔር ቃል በሁለት ጎን የተሳሉ ናቸውና በእምነታቸው ቆመው ከእግዚያብሔር በቀር ማንም በሳቸው ሥልጣን እንደሌለው በማስረገጥ ከተገፉት ጋር የቆሙ አረጋዊ አባት ናቸው። እነዚህ የምግባር ድሆች ከልቦች እንደቃሉ ሳይሆን እንደ ዶላሩ የሚሰብኩበት የመበለቶች ተረት ተረት የሆነ ቀኖና ቤተክርስቲያን ፈርሶ ወይም ተጥሶ በህጸጽ የተሞላው ሁሉ የግድ ቄስ ካልሆነ፣ ክህነት ያልሰጠ የማርያም ጠላት የሚሉና በተግባርም ያሳዩ፤ ከገፊዎች ጋር በመቆም ስብከቱን በሃሰት ፍቅር ያበዱበት በአጠቃላይ በመምህርና በአባ (መነኩሴ) ስም የተነሱ ጥቅመኛ ከልቦች ከቤተ እግዚያብሔር መልካምነት እንዲጠፋ በማድረግ ሕጋዊውን በውጭ የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ በማወክና በመፈታተን ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ አምስቱ አካልብት የእግዚያብሔርን ተግሳጽ የናቁ፣ መስዋዕቱን ያቃለሉ፣ ዋናዎቹን የማያከብሩ ምናልባትም በስደት ስም በሲኖዶሱ የኤሊ ልጆች ሾልከው ገብተው የተሾሙና የመኖሪያ ፍቃድ ማገኛ መጠለያ በማድረግ ንጹሃን አባቶችን በማመስ ተልዕኮ ላይ ተሰማርተዋል። ቀደምት ዋናዎቹ ሲኖዶሱን ይዘው የተሰደዱ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች በነዚህ ከልቦች ተዋርደዋል፣ አይ ጊዜ! ስለዚህ በኢትዮጵያ ያለው ጥፋት ሳይበቃን በነሱም ሆነ በሌሎቻችን በደል የእግዚያብሔር ፍርድ ለወርድ የዳመነ ቢሆንም ይህንን ባለማስተዋል፤ መገሰጽን እንደመናቅና እንደመደፈር ቆጥረው የቆሙ መስሏቸው መውደቃቸውን ስተው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የማዕዘን ራስ የሆኑትን አባቶች ሲዘልፉ ተስተውለዋል።
እግዚያብሔር “ያከበሩኝን አከብራለሁ፤ የናቁኝም ይናቃሉ” ቢልም ካለመስማት ሽማግሌ ማጣት ከእግዚያብሔር ቅጣት አንዱ መሆኑንም ባለመረዳት በሊቀ ጳጳሱ በብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስና በብጹዕ አቡነ ይስሃቅ ሞት መቀጣታችንን አላስተዋሉም። ከዳተኞቹ ጭራሽ በነሱ ስም ንግድ የጀመሩትም ተስተዋል እንጅ ይህ የአምስቱ አካልብት የስመ አባዎችና መምህራን ድፍረትና ማናቸውም የቤተክርስቲያን ነጋዴ የአፍኒንና የፍንአስ ዕጣ ከመሆን አያልፍምን ዕምነታችንን የምንወድ ሁሉ ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስም ቤተእግዚያብሔር የጨካኝ ከልቦች ዋሻና መናከሻ ሊሆን አንፈቅድምና ስደተኛውም ብዙ መስዋዕትነትን የከፈለበት በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለዚህ ከላይ ለተመለከተው ችግር በአስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል።
የሚገርመው አምስቱ ውሾች(ውሾች) እራሳቸው ወያኔ ሆነው አመጣጣቸውንም እያወቁ አንዴ ማህበረ ቅዱሳን፣ አንዴም ደግሞ ወያኔ ገብቶበታል እንዴ እያሉ በሌላ ጊዜ ደግሞ የፖለቲካ ሰዎች ተቆጣጥረውታል፣ ዶክተሮች አላስቀርብ አሉን በማለት በወያኔ ስም በማስፈራራት ሀቁን ለማፈለስና በጽናትና በአንድነት ያሉትን ቀደምትና ዋናዋዎቹን ሊቃነ ጳጳስ አባቶቻችንን ለመከፋፈል በፓትርያርኩ ስም የሚጠቀሙበት የልክፍት አዙሪት አስከፊ ቢሆንም ክብር ገን ከቀደሙት ዋናዎቹ አባቶቻችን አለቀቀችና የእገዚያብሔርን ስራ በመስራት በብርሃን መመላለሳቸውን ቀጥለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ እነዚስ አምስቱ ውሾች ቤተክርስቲያንንም ስደተኛውንም በመናቅ ግፋም ሲል የዋህ ሲያገኙ በማስጨብጨብ የረከሱ የአፍሚንና የፊንአስ ጊዜ ስደተኛ ለማድረግ ከስም አይጠሩ አባታቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም ልክፍታቸውን ቀጥለውበታል። የአድራጎታቸውን አስከፊነት አውቀው እንዲመለሱና ክፉ ስራቸውን እንዲተው በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ካህናትና ምዕመናን የተሰጣቸውን ምክክር አጣጥለውታል። ሆኖም ኢትዮጵያና ቤተክርስቲያን የክብር በሮቻችን በመሆናቸው አሁንም ደግመን እየነገርን ከጥፋት ተመለሱና ኑና እንወቃቀስ እንላለን። ዳሩ ግን አምስቱ ከልቦች ክብር ከራሳቸው የለቀቀ የኑፋቄ ባሮች ናቸውና አባቶችን፣ቤተክርስቲያንና ምዕመናን፣ ለኢትዮጵያ ነጻነት የቆሙትን ዜጎች በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና ህዝቧን የሚያዋርዱ ቡድንተኛ ኢካቦች ናቸውን ማስተዋል ጠፍቶባቸዋል።
እነዚህ አምስቱ አካልብት (ኢካቦድ) ኢትዮጵያን አገርና ህዝብ ፈርሶ እያለ የድረሱልን ጥሪ እየተስተጋባ በየማዕዘናቱ ኃይሉን በጸሎት ከማሰባሰብ ይልቅ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ለህዝቧ ዓይን የሆኑትን በማዋረድ ምንዝርና በሆነው አድመኝነት የነጎዱ እራሳቸው ኩነኔዎች ሆነው ኮናኝ የሆኑበት እራሳቸውን ሳያውቁ ሌላውን በቅዱስ መንፈስ የሚመረመራቸውን እናውቃለ የሚሉ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለምን ጣሳችሁ ሲባሉ፣ ለንስሃ ከመዘጋጀት ይልቅ የህጸጽና የነውር አገልጋይ በመሆን የቡድንተኝነትና የአድመኝነት ቁማር በመጫወት የአገርን፣ የቤተክርስቲያን፣ የአባቶችን ክብርና የምዕመናንን እንድነት በመሸርሸር እንጀራ የበሉበትን ተረከዝ በመንከስ ላይ ይገኛሉ። ከዚህም በላይ ኮቴያቸውን በህጋዊዊ ውጭ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ እያሰሙ ነውና እነዚህ ኢካቦድ በሚያራግፉት የምንደኝነት አባራ ያላወቃቸውንና ያልጠረጠረውን በፓትርያርኩ ስም በመነገድ አንድነቱን ሸርሸረው በጥርጣሬ፣በምንደኝነት በኑፋቄ በመከፋፈል ላይ ናቸው። አምላካችን ለሁሉ አስተዋይ ልቡና ይስጠው።
ባሳለፍናቸው ረዥም ዓመታት ብጹአን አባቶቻችን ለአገርና ለምዕመናን የምትጸለዩ መሆናችሁን በትክክል ብናውቅም፤ ካዛ ባለፈ አፋጣኝ የህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ በመጥራት ወይንም አባቶቻችን እግዚያብሔር በሚያሳያችሁ መንገድ የምዕመናኑን የመንጋችሁን አንድነት ከከልቦችና (ከውሾች) ከኢካቦድ ትታደጉትና ኢካቦድ በጨለማ የሰሩትን በብርሃን ትገልጡትና አንድነታችን ትጠግኑትና ያጠፋም ተጸጸቶ፣ ፍቅር ይሰፍን ዘንድ እየተማጸንን ምዕመናን ከእውነት ያልሆኑት እውነትን እንደማይሰሙ እንደ አባታቸው ሃሰትን ሲናገሩ ከራሳቸውና ከሃሰት አባታቸው ልጅነታቸውን እንዳሳወቁ በመገንዘብ ኢካቦድ (ከልቦች/ውሾች) ላቀዱት በሁከት የመከፋፈልና የግርግር የስም ማጥፋት በሽታቸውን ልክፍት የተነሳ ሰላም እንደሌላቸው አውቀን ሳንገበር በጊዜውም አለጊዜውም በዓለም ዙሪያ ቤተክርስቲያናችንን በመልካም ተጋድሎ በመጠበቅ ከቀደምት ዋናዎቹ አባቶቻችን ድምፅ እንድንሰማ እግዚያብሔር ይርዳን።
ከእግዚያብሔር ሥራ ፊት የኢካቦች ሥራ አይቆምም። የእግዚያብሔር ሰዎች አብረውን አሉና “ስቀሎ ስቀሎ” የአርብ ፍቅረኞች በትንሳዔው ይገለጣሉ። ይበተናሉ። ይወድቃሉ።
እግዚያብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
በውነት እንዳልካቸው

The author of the above statement has to state who he/she is. If it is a group let us know. We are tired of people who complain.
አንተ ማነህ? አስተያየት ከመስጠትህ በፊት ስምህን አስተዋውቅ::ምናልባት ራስህን መደበቅ ብትፈልግ እንኩአን የሆነ ስም አስቀምጥ እንጂ እንደ ሙት መንፈስ አትንቀሳቀስ:: ደግሞስ ስለምንድነው የምታወራው? በቃላትና ሃረግ ክብደት ሃሳብ ግልጽ ስለማይሆን ሃሳብህን የሚያስረዳልህን አቀራረብ ምረጥ:: ለመሆኑ ስለምን እንደምታወራ አንተስ ታቀዋለህ? ስለምታወራው ነገርስ በቂ መረጃ አለኝ ብለህ ታምናለህ? ይህን እንደማታሙአላ ከጽሁፍ ተብዬህ መረዳት ይቻላል:: ወይም ደግሞ እልም ያልክ እውነትንና እግዚአብሔርን ከካዱ ወገኖች ጋር ወግነሃል; ማለት ነው::የትኛውም ይሁን በዚች አንድ ገጽ ሃሳብ ላይ ያልረገጥከው ቦታ የለም:: ይህ ደግሞ አንተ እብድ እንደሆንክ በግልጽ ያሳያል:: በሰው ላይ ለዚያውም ምንም በማታቀው ጉዳይ ላይ ለመፍረድ ከመነሳትህ በፊት አንደኛ ስለነገሩ በቂ እውቀት ሁለተኛ ሚዛናዊነት ያለው ህሊና ሊኖርህ ይገባል:: እንዲህ ያለ የተሳሳተና አራምባና ቆቦ እየረገጥክ ያቀረብከውን ማደናገርያ ጉዳዩን የሚያቀው ንቆሃል ቢጤዎችህ አጨብጭበውልህ ይሆናል:: እውነት ግን ሚዛኑአን ሳትስት የተደበቀች ስትሆን ሳትጠፋ ትኖራለች:: ባንተ ጽሁፍ ውስጥ ግን እውነት የለችም:: ባንተ ቤት እንግዲህ መቀኘትህ መስሎህ ይሆናል:: አምስቱ አካልብት የምትላቸው ራዕየ ዮሃንስ አምስቱ ውሾች የሚለውን ቅጂ ወስደህ ይመስለኛል:: መጀመርያ መጽሃፍ ቅዱስን አንተ አታርምም እና አካልብት ብለህ አታምታታ:: ሁለተኛ ውሾቹ እነማን እንደሆኑ ሶስቱ ጣቶችህን ወዼት እየጠቆሙ እንደሆነ ብትመለከት ትረዳዋለህ:: ሃሳብህ ከንቱ ስለሆነ ራስህን መደበቅህ ተገቢ ይመስለኛል::
የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ ውስጣቸው ግን ነጣቂዎችና ተኩላዎች ከሆኑ ከሃሰተኞች እራሳችሁን ጠብቁ ብሎ ቅዱስ ወንጌል እንዳስተማረን እንዲሁም ሓዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሆዳቸው አምላካቸው ገንዘብን የሚወዱ ብሎ እንደተናገረው ዛሬ ወንጌልን ሰብኮ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሰዎችን መጥራት ሳይሆን የተያዘው በምን መልኩ ገንዘብ ማግኘት እችላለሁ የሚለው ነው እንደ SHINKIFU አዪነት ዎሮበአላ ክ አምስቱ ክልብ አንዱ ገልቱ;;
አምስቱ ክልቦት እናንተ መንፈሳውያን አልነበራችሁም፡፡ እናንተ ድራማ ስትሠሩ ነውኮ የኖራችሁት፡፡ መድረክ ላይ ወጥታችሁ መንፈሳዊ ድራማ ትሠሩ ነበር፡፡ ልብሳችሁ፣ንግግራችሁ፣የእጅ አጣጣላችሁ፣ ጸሎታችሁ፣ የተዋናይ ነበር ተጋለጣትሁ the author of the article is he put the truth in the light.
ጊዜው ሲደርስ ሁሉም እውነቱን ሲረዳው ደስ ይላል! አሁንም አጥርታችሁ የማታዩ የ5ቱ የውሻው ተከታዮች ለባሰ ውድቀት እንዳትዳርጉ
አባታችን አቡነ መልክጽዲቅ በማስተማር ከአምላካቸው ጋር የተቀያየሙትንና በሰፊው ጎዳና እየነጎዱ ያሉ የክርስቲያን ወገኖችን ለንስሐ እንዲበቁና እንዲመለሱ ከተረት ፈቅ ያለውንና እውነቱን ሳይፈሩ ስለነገራችሁ አትጥሉአችው፤ ይልቁንም መስታዉታችሁ ስለሆነ እውነትን ተመልከቱበት። እራሳችሁንም እዩበት። የንስሐ ፍሬንም አፍሩበት።
ለመሆኑ እናንተ መቼ ነው ስድብ መተላለፍ/ኃጢአት መሆኑን የምትረዱት? መቼስ ነው በመሳታችሁ የሚገስጿችሁን ካማሳደድና ስም ከማጥፋት የምትታቀቡት? የእናንተን የንግድ እሩጫ ያልተቀበለ፣ እናንተን ያላወደሰና የመበልት ተረታችሁን አሜን አሜን ያላለ ሁሉ ሕገ ወጥ እንዴት ነው ሊሆን የሚችለው? በመላው የአሜሪካ ክፍል ወጣቱን ከሽማግሌው፣ ምእመናንን ከካህናት፣ አባቶችን ከልጆች በማበጣበጥ ለክርስትና ቀናዒ መስላችሁ በሕዝቡ ፊት ሽርጉድ ስትሉ ልባዊ ክርስቲያን ትመስላላችሁ። ለመሆኑ የእድሜ እኮሌታቸውን ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ሰንቀው የላመ ሳይበሉ፣ የጣመ ሳይጠጡ፣ ቆሎ ቆርጥመው፣ ደበሎ ለብሰው፣ ከውሻ ተፋልመውና ቁራሽ ለምነው ተምረው አሁን ላሉበት ማዕረግ የደረሱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ከናንተ እኛ እንሻላለን ለቤት ክርስቲያንም እኛ ይበልጥ እንቆረቆራልን እያላችሁ በመታበይ ስትነቅፏቸውና ስታዋርዷቸው የምትኖሩ ያልነቃ ያለ ይመስላችኋል? ነገር ግን በምግባረ ትዕቢት ያደገው እኔነታችሁ ለተግሳጽ አንገቱን ስላደነደነ እንደ ሳጥናኤል መንጸፈ ደይን አውርዶ ሳያንኮታኩት ስለማይለቃቸሁ የእናንተ ማነኛውም ሥራ በናንተ አመለካከት “እንደ ፀሐይ ሲያበራ የሚኖር” ነው ትላላችሁ። በመጽሐፈ ሰሎሞን …አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል… የሚለውን ባትዘነጉት የምትመለሱበትን ልቡናና ከእኔ እኮ እገሌ ይሻላል /ከእኛ እነ አባ ይበልጣሉ የምትሉበትን ማስተዋል ታገኙ ነበር። ለመወጣጫ የረገጣችሁትን የትዕቢት መሰላል ወደነበራችሁበት ስትመለሱ የምትጨብጡበት ውርደት በደጅ እንደ ሆነ ልብ በሉ።ጊዜያቸውን አጥፍተው ሌሊቱን ከቁንጫ/ከተባይ ጋር እየታገሉ ዉዳሴ ማርያምን አዚመው፣ ሰዓታቱን ቆመው፣ ማኅሌቱን አድርሰው፣ ድጓ ጾመ ድጓ አዚመው/ተምረው፣ ዳዊቱን አነባብረው፣ መልክዓ ማርያምን መልክዓ ኢየሱስን ደግመው፤ ክሕነት ተቀብለው ምስጢር አይተው በአገልግሎት ያደጉትን የቅድስት እናት ቤተክርስቲያንን አበው ስትሳደቡ እንዴት አፋችሁን አይዛችሁም? የአማናውያን ቅዱሳንን መዝገብ መርምሩ። “የጽድቃችሁ” ካባ የመረገም ማቅ እንዳይሆን ጠርጥሩ። ጌታ ፈሪሳዉያንን በገሰጸበት በአማናዊ ቃሉ … እናንተ ግመልን የምትውጡ ትንኝን የምታጠሩ… ይላችኋል።
ክርስቶስ ለሁሉም የሰው ዘር ድኅነት ሲል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእመቤታችን ድንግል ወላዲተ አምላክ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በእመቤታችን ሥጋችንን ለብሶ ስለእኛ ስለሰው ልጆች (እናንተንም ይጨምራል) ሲል የተቀበለው መከራ በዓይነ ኅሊናችሁ ይመላለስባችሁ። ሕይወቱ ይኑራችሁ እንጅ! ለማስመሰል በምታነበንቡት የሽንገላ “ወንጌል” ተጠላልፋችሁ እየወደቃችሁ መሆኑን የሚነግሯችሁን ሁሉ የዝሆን ጆሮ ማለት ይብቃችሁ። ከየአቅጣጫው እናንተን የሚቃወም ሲነሳ እንደ ክርስቲያን ጥፋት አጥፍተናል ማለት ነው? ስለዚህ ቆም ብለን እራሳችንን እንመርምር ለምን አትሉም? አለዚያማ እናንተ “የቀደሙት ሓዋርያት” እናንተን የሚተቹና ታረሙ የሚሉ አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካሕናት፣ ምእመናን በሙሉ ደግሞ የቀደሙት አሳዳጆች ጻሕፍት ፈሪሳዊያንና አረማዊያን ናቸው ማለት ነው። ለቤተክርስቲያን ለሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ መከፋፈልና ለውድቀቷ አስተዋጽዖ በውጪው ዓለም የምትዘሩትን እንክርዳድ/መርዝ አቁማችሁ ለንስሐ ተዘጋጁ። አሁን የያዛችሁት ሩጫ ሳውል (ቅዱስ ጳውሎስ) ከመጠራቱ በፊት እግዚአብሔርን እያገለገለ እየመሰለው ይተጋበት የነበረው ሩጫ ስለነበረ ለወንጌል የተለየበት ሰማያዊ መብረቅ ለእናንተ ይወርዳል ብላችሁ አትጠብቁ፤ የሚያነደው ይልቁንም ድንገት ያለንስሐ ወደ አመድ የሚለውጠው ነደ እሳት እንጂ። የመውጊያውን ብረት እየተቃወማችሁ ያለችሁትም እናንተ ስለሆናችሁ ወዮላችሁ። አምስቱ ጭፍሮች ዉሶች;;
እድሜ ለንስሐ ይስጣችሁ!
በ5ቱ ክልቦች የዘመን ፍጻሜ በደረሰብን በእኛ ዘመን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በማን አለብኝነት እየተጣሰ፣ ሕጉን ጠብቀው እንዲያስጠብቁ የተሾሙት ሕግ-ጣሽ፣ ሥርዓት ደምሳሽ ሆነው ያሉበት፣ የቤተ ክርስቲያን ፈርጥ መሆን የሚገባቸው ምዕመናን ቤተ ክርስቲያንን ለግል ዝናና ጥቅም መጠቀሚያ ለማድረግ ደፋ ቀና ለሚሉት ምንደኞች የኋላ ደጀን በመሆን በማወቅም ባለማወቅም ቤተ ክርስቲያንን በማፍረስ ተልእኮ ላይ ሁሉም ተባብሮ ያለበት ጊዜ ሆኖ ስለተሰማኝ ከስሜታዊነት የመነጨ ሀሳብ ነው እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ብዙ ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ድርጊቶች በዙሪያችን እየተፈጸሙ መሆናቸውን ያልተገነዘበ ቢኖር የኅሊና ደጁን ምንም እንዳያስተውል የዘጋ፣ ቤተ ክርስቲያን የፈለገችውን ብትሆን የማይገደው፣ ለቤተ ክርስቲያን ምንም ተቆርቋሪነት የሌለው ብቻ ነው እላለሁ፡
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያኖች አምልኮታቸውን የሚፈጽሙባት የሚቀድሱበት የሚያስቀድሱበት ሥጋወደሙን የሚያቀብሉበት የሚቀበሉበት የአምልኮ ቦታ በመሆኗ ክርስቲያኖች እስካሉ ድረስ ቤተ ክርስቲያን መተከሉ አይቀሬ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለሁሉ ነገር የተዘጋጀ ሥርዓትና ደንብ አላት፡፡ ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደሚተከል በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ አባቶች የወሰኑት ውሳኔ የደነገጉት ድንጋጌ አለ።
፡ ኢትየጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን መለወጥ እንደማይችል በቅዱስ መጽሐፍ የተገለጸ ቢሆንም ዳሩ ግን አንደንዶች ምድረ ኢትዮጵያን ለቀው አትላንቲክን ተሻግረው ምድረ አሜሪካንን ሲረግጡ ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓቱን፣ ፈሪሃ እግዚአብሔሩን አሽቀንጥረው በመወርወር ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን እንኳን መቅረብ እንደማይገባቸው ያምኑ የነበሩት ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን ከፋች ሆነው፣ እንዴት እንደሚቀደስ ምን እንደሚሠራ “ሊቃነ ካህናት” ሆነው ካህኑን ሲመሩ፣ ሲሻኝ ጢስ ወጋኝ እንዲሉ ምክንያት ፈጥረው ከህኑን ሲያባርሩ፣ ከዓላማቸው ጋር የሚተባበረውን ለፈቃዳቸው የሚንበረከከውን ሲቀጥሩ ላስተዋለው ጉድ የሚያሰኝ ነው፡
አንዳንዱ ካህንም የተሾመበትንና ሥልጣነ ክህነት የተቀበለበትን ዓላማ ወደ ጎን ትቶ፣ “እስከ ዛሬ ከበላዬ በነበሩት ተጎድቼ ኖሪያለሁ፣ አሁን ግን ሁሉን ማድረግ ወደምችልበት ዓለም መጥቻለሁ” በማለት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የማይፈቅድለት መሆኑን እያወቀ፣ አንቱ ለመባል፣ ሀብት ለማካበት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን አምዘግዝጎ በመጣል እንደ መሸቀጫ ሱቅ “ቤተ ክርስቲያን” ከፍቶ የግል ጥቅሙን ሊያጋብስ እያስተዋልን ነው፡፡በዚህ በዲሲ…
በኃይል ጩህ አትቆጥብ፣ ድምጽህን እንደመለከት አንሣ” እንደተባለው ነቢይ የተማሩትንና የተረዱትን ላልተማረውና ላላወቀው እንዲያሳውቁ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰባክያነ ወንጌል “ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ” ብለው ቤተ ክርስቲያንን የስብከታቸው ማእከል ማድረግ ሲገባቸው በላያቸው ላይ ያነገሱዋቸውን ሰዎች ፈቃድ በመፈጸም ምንደኛነታቸውን በስውር አይደለም በገሃድ ያለምንም እፍረት እየገለጡ ያሉበት ጊዜ ነው፡፡ እንዲህ ስል እግዚአብሄር የሚያውቃቸው ራሳቸውን ቀብረው ከቤተ ክርስቲያን መድረክ ተገፍትረውም ሆነ ተከልክለው በሚሆነው ነገር ሁሉ እያዘኑ በበዓታቸው ተወስነው ያሉ መኖራቸውን ባለመዘንጋት ነው:: መንጋውን የመጠበቅና የማሰማራት እንዲሁም እውነትን የማስተማር ተልዕኮ ተቀብላችሁ በቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ የቆማችሁ ካህናትና ሰባኪያነ ወንጌል ሃስትን በማቅረብ የምዕመኑን ኅሊና በሀሰተኛ ምላስ በማደንዘዝ የህገወጦችና የጥቅመኞች አጋፋሪነታችሁን ትታችሁ ነገ ፍርድ ከእግዚአብሄር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ እንደሚመጣ ከወዲሁ ተገንዝባችሁ ወደ ኅሊናችሁ በመመለስ ከአፈ ቀላጤነት ወደ ወንጌል አርበኝነት ትለወጡ ዘንድ ምክሬ ነው፡፡
እናንተም ልታስተምሩት ልትመሰክሩት የሚገባውን እውነት ልባችሁ እያወቀ ዳሩ ግን ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ብላችሁ እውነቱን ሰውራችሁ በስራችሁ ያለውን ምእመን ወደ ጥፋት የምትመሩት ከሆነ እግዚአብሄር ሓላፊነታችሁን በአግባቡ ባለመወጣታችሁ የበጎቹን ደም ከእናንተ እንደሚጠይቅ ለእናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛል። ዳሩ ግን ዕውቀት ሳይሆን እምነትና ተግባር ስለሆነ የሚያጸድቀው የእምነትና የተግባር ሰው ሁኑ፡፡ኢካቦድ ሆናችሁ አትቅሩ;;
“ተቀባይ ከሌለ ሌባ አይኖርም” እንደሚባለው ለሕገ ቤተ ክርስቲያን መጣስ የምዕመናንም አስተዋጽኦ እንዳለበት መገንዘብ ያስፈልጋል። በምዕመንነት ደረጃ ቀርቶ በቅስና ደረጃ ያለ እንኳን ቤተ ክርስቲያን ባርኮ እንደማይከፍት እየታወቀ “ማንም ይክፈት ማንም ቤተ ክርስቲያን መኖሩን ብቻ ነው የምንፈልገው፤ ሌላው እኛን አይመለከተንም” የሚል ከአንድ ምዕመን መደመጥ የማይገባውን አስተያየት እየሠጡ ጉዳዩ እንደማይመለከታቸው አድርገው የሚናገሩ እንዲሁም ግብረ በላ በሆኑ ሰባክያን ልቦናቸው የደነደነና የቆሙበት መንገድ ትክክል እንደሆነ አድርገው የሚቆጥሩ እንዲሁም ቤተሰባዊነትን ከሃይማኖት በላይ አድርገው የያዙ ምእመናን የጥፋቱ መሪ ፊት አውራሪ ለሆኑት ወገኖች ተባባሪ ሆኖ መገኘት ችግሩ መፍትሄ እንዳያገኝ አድርጎታል። ከእኔ ይልቅ ሴት ልጁን ወይም ወንድ ልጁን የሚወድ ቢኖር ለእኔ ሊሆን አይችልም እንዳለ ጌታ ምርጫችንን ቤተ ክርስቲያን አድርገን ቤተ ክርስቲያንን ተጣብተዋት ያሉትን መዥገሮች ለመንቀል በቁርጠኝነት መነሳት ያስፈልጋል። ቤተ ሰባዊነት ይሉኝታ ግዴለሽነት እነዚህ ሁሉ አንቀው ይዘውን ተዘልለን ብንቀመጥ የቤተ ክርስቲያን አምላክ አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱን ይታደጋታል። በዚያን ጊዜ ግን እናንተ ወዮታ እንዳለባችሁ እወቁ። ካአምስቱ ክልቦች ተጤንቀቁ;;
“ተቀባይ ከሌለ ሌባ አይኖርም” እንደሚባለው ለሕገ ቤተ ክርስቲያን መጣስ የምዕመናንም አስተዋጽኦ እንዳለበት መገንዘብ ያስፈልጋል። በምዕመንነት ደረጃ ቀርቶ በቅስና ደረጃ ያለ እንኳን ቤተ ክርስቲያን ባርኮ እንደማይከፍት እየታወቀ “ማንም ይክፈት ማንም ቤተ ክርስቲያን መኖሩን ብቻ ነው የምንፈልገው፤ ሌላው እኛን አይመለከተንም” የሚል ከአንድ ምዕመን መደመጥ የማይገባውን አስተያየት እየሠጡ ጉዳዩ እንደማይመለከታቸው አድርገው የሚናገሩ እንዲሁም ግብረ በላ በሆኑ ሰባክያን ልቦናቸው የደነደነና የቆሙበት መንገድ ትክክል እንደሆነ አድርገው የሚቆጥሩ እንዲሁም ቤተሰባዊነትን ከሃይማኖት በላይ አድርገው የያዙ ምእመናን የጥፋቱ መሪ ፊት አውራሪ ለሆኑት ወገኖች አጥር ሆኖ መገኘት ችግሩ መፍትሄ እንዳያገኝ አድርጎታል። ከእኔ ይልቅ ሴት ልጁን ወይም ወንድ ልጁን የሚወድ ቢኖር ለእኔ ሊሆን አይችልም እንዳለ ጌታ ምርጫችንን ቤተ ክርስቲያን አድርገን ቤተ ክርስቲያንን ተጣብተዋት ያሉትን መዥገሮች ለመንቀል በቁርጠኝነት መነሳት ያስፈልጋል። ቤተ ሰባዊነት ይሉኝታ ግዴለሽነት እነዚህ ሁሉ አንቀው ይዘውን ተዘልለን ብንቀመጥ የቤተ ክርስቲያን አምላክ አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያኒቱን ይታደጋታል። በዚያን ጊዜ ግን ወዮታ እንዳለብን እወቁ።
መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ ” …ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። ” ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፫ ፡ ፩ – ፭
ሰለዚህ አገልጋዮች ነን በሚሉት ዘንድ የሚታየው የባህርይ ለውጥ ወይም የሚንጸባረቀው ባህርይ እንግዳ አይደለም። ለማንኛውም ለቤተክርስቲያን ጥቅምና ሥርዓት መጠበቅ የሚሰራ ሰው ወይም አገልጋይ ማግኘት ከባድ ነው። ሁሉም በቤተክርስቲያን ሰበብ የራሱን ትከሻ የሚያሳብጥና የራሱን ጥቅም አስከባሪ ሆነ እንጂ። ጥቂቶች ይኖሩ ይሆናል፤ ካሉም እነርሱን ያብዛልን ባይ ነኝ። ዳሩ ግን ሁሉም የራሱን እንጂ የእግዚአብሔርን የሚሻ ሰው የለምው። አባቶችም በአምስቱ ክልቦች ተዋርደዋል በዚሀም ዋናዉን ጵሁፍ ላክሁ;;
Please expose the five spies and let the mass know who they are.
We have no idea who the five weshoch are. For the reader,things has to be clearly indicated to grasp the message of the article. The other point is whatever wrong they have done,it is not apropriet to call names and insult people,the very thing the writer is accusing the five woshoch with. Having said that,our holy fathers have shown us what courage is. When so many people shut their mouths never daring to say a word against the woyane regime, those holy fathers have openly rised their voices to condemn the horrundous crimes of Meles and his cronies. By thier stedfastness, courage, and determination, they have shown us the way to rise up in unison against the tyrant regime. At their age,they have chosen to leave a country lead by criminals despite the possibility of having a quite life had they chosen to remain in Ethiopia.May God give them long live to return back to a free Ethiopia one day. My special admiration to the learned admirable Archbishop Abune Melkesedek and the courages abune Mekarious. May God give you long live .May God allow me to kiss your cross One day in Addis Abeba.
God bless Ethiopia
እቡነ መልክ ጻዲቅና እቡነ መቃሪዮስ እውነተኞች የምንወዳቸው እባቶቻችን ናቸው:: ወያኔንን በማውገዛቸውና በአገሪቱ ውስጥ ለተበደለ በሙሉ ለክርስቲያኑም ለሙስሊሙም ቤተክርስቲያን መጮህ እንዳለባት በማሳሰባቸው ምክንያት የወያኔ የውስጥ እርበኞች በጣም ተቆጥተዋል፡። አነዚህ አካልብቶች (ሰው በሎች) ክርስቲያን ነን እያሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካስተማራቸው ትምህርቶች አንዱን እንኳ ስራ ላይ የማያውሉ ሲሆኑ ለተበደለ በመጮህ ፋንታ ለበዳዮች የሚከራከሩ፣ ከደሃውና ከተራበው ጎን በመቆም ፋንታ ከነፍሰገዳዮች ማዕድ የሚቋደሱ፣ መንፈሳዊውን ሕይወት ትተው ለዚህ ዓለም ሃብትና ጥቅም ሲንደፋደፉ የሚኖሩ አጋሰሶች የሚጋለጡበት ጊዜ አሁም ነውና ሁላችንም ነቅተን እነዚህን ተባዮች በእፈርሳታ መልክ ነቅለን ማውጣት እለብን:: እነዚህ በየቤተክርስቲያኑ ውስጥ የተሰገሰጉ የውስጥ እርበኞች ኢትዮጵያዊው ለአገሩ እንዳንጮህ እንደበቱን ሸብበውና ሰልፍ እንዳይወጣ በተሳሳተ ትምህርታቸው እግር ከወርች እስረው እነሱ ግን በህዝብ ገንዘብ ተንደላቀው የሚኖሩበት ጊዜ እልፏል:: እቡነ መልክ ጻዲቅና እቡነ መቃሪዎስ የዘመናችን እቡነ ጴጥሮሶች ናቸው:: ድል ለኢትይጵያ ሕዝብ!!!
ለዲሲ ባለ ሱቆች በካድሬዎችና በሊቃውንት መካከል ያለው ልዩነት አስተውሉ ጌታችን “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” እንዳለ
ክክልቦቺ ራቁ;;
ጽድቃቸውም የመንፈስ ቅዱስ ደስታና ሰላም የሌለው ነው (ሮሜ 14፥17)። እንደዚህ ያሉ ክርስቲያኖች በጣም አደገኞች ናቸው ምክንያቱም ክርስቲያኖችን ወደ ስህተት ትምህርት ይመራሉ አዲስ ሱቅ በዲሲ ክፍተው አባቶችህን ይሳደባሉ በሞተ አስክሬን ይነግዳሉ በምንፍቅና ስክረዋል;;በፓትርያርኩ ይነግዳሉ በማያውቁት በማይደግፉት የህዝብ ስልፍ ለመታየት ሞክረዋል:: ህዝቡም ነቅቶ ታዝቦአል::
ጉድ እኮ ነው። የተሐድሶው መሪ ሰሞኑን በኢሳት በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደሱቅ ቤተ ክርስቲያን ሰለሚከፍቱ ሰዎች መልዕክት ሲያስተላልፉ ጥያቄአቸው ስላልተመለሰ ሌላ ቤተክርስቲያን ቢከፍቱ ምን ችግር አለበት ብለው አረፉ። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደሚቋቋም አጥተውት አይመስለኝም። ሆን ብለው በማን አለብኝነት የዋሁን ህዝብ ለማሳሳት ስለፈለጉና እራሳቸውን ትክክል ለማድረግ ሌላውን መኮነን ስላለባቸው ነው። ይህ ነው ክርስትና? ወንድሞቻቸውን በሀሰት መወንጀል? መቸም ህሊና የሚባለው ነገር ጭራሹን ሞቶ ካልሆነ በስተቀር ይህንን እውነት አያጡትም።
የከልቦቹ መንገድ አባቶቻቸውን መሳደብ ቃላቸውን ማናናቅ፣ ትዛዛቸውን አለማክበር ነው። አባትን እየተሳደቡ ትልቅ ሰው መሆን አይቻልም። አባትማ ልጁን መቆጣት፣ መቅጣት የተለመደ ነው፤ ትክክለኛ አካሄድም ነው። በሃይማኖት ስልጣን ያለው አባት የሚናገረው ሊከበር ይገባል። የከነዓን አባት ካም አባቱ ኖህ ወይን ጠጅ ጠጥቶ ራቁቱን መሆኑን እንዳየ ልብስ ማልበስ ሲገባው ለወንድሞቹ ራቁቱን እንዲያዩት ሄዶ በመንገሩ ከነዓንን እንደረገመው መጽሐፍ ጽፎልናል። ከልቦቹ አባቶቻቸው ያጠፉት ነገር የለም። አባቶች እነሱን (ከልቦቹን) አስተምረው ከዚህ ከማድረስ በስተቀር እኛ የምናየው ያጠፉት ነገር የለም። አባቶቻቸውን ከማክበር ይልቅ ማቃለልን፣ በአደባባይ አሻቅቦ ያልሆነ ነገር በመናገር ሌሎችም የስድብ ናዳ እንዲያወርዱ ያደርጋሉ። በየጊዜው በጽሑፍ የሚያወርዱባቸውን/የሚያስወርዱባቸውን የስድብ ናዳም አይተናል። የዘሩትን ዘር መብቀሉን፣ ማደጉን፣ ማፍራቱን ሳይመለከቱ በየቦታሁ “ዘራሁ” ይላሉ። አንድ ማማሰያ ይዘው አሥር ድስት ይጥዳሉ። አንድ ቤተ ክርስቲያን ችግር ተፈጠረ ሲባል ችግሩን መፍታት ሲገባ “ሌላ ክፈቱ” የሚል መመሪያ ይሰጣሉ። በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ ችግር መፍታት ያልቻለ ሰው እንዴት ነው ሰፊ የሆነ መተባበርን፣ መፋቀርን፣ መታገስን፣ አንዱ ለሌላው ማሰብን የሚጠይቀውን የክርስትና ሕይወትና የእግዚአብሔር መንግሥት የሚያመጣው? ስህተትን መቀበል ሐጢያት አይደለም። ስህተትን ተቀብሎ ይቅርታ መጠየቅ ታላቅነት ነው። ይቅርታ ጠይቃችሁ ይቅር ባትባሉ የእናንተ እዳ መሆኑ ይቀራልና ነጻ ወጣችሁ ማለት ነው። ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም፣ ለህዝበ ክርስቲያኑ አንድነት፣ ለእናንተም የህሊና ነፃነት ጥፋታችሁን ጥፋት በሉት። አባቶቻችሁን ከለመታዘዝ ይልቅ አክብራችሁና ታዛችሁ መኖር ብትችሉ እናንተም የሚያከብራችሁ ታገኛላችሁ። ካልሆነ ግን በሰፈራችሁት መስፈሪያ ተሰፈራላችሁ። የዘራነውን እንደምናጭ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን እናንተው በአንደበታችሁ ታስተምራላችሁ። የምትናገሩትን መሆን ካልቻላችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
ስለዚህ በስህተት ላይ ስህተት ለመሥራት ከመሮጥ ለማስተካከል እንታገል። ዛሬ ከልቦች (ውሾች) የሆኑት ነገ ትክክለኛ ሰዎች መሆን ይችላሉ። እግዚአብሔር ሁሉን የመለወጥ ስልጣን አለው። ያልሆነውን ልቦና ወስዶ እርሱን በሚያመልክ ትህትና የተሞላበት ልቦና ሊሰጠን ይችላል። ከልብ (ውሻ) የተባሉትም ወንድሞቻችን ናቸው። ክርስቶስ ለሁላችንም ሞቶልናል። ያንን ተመልክተን ስህተትን ዘወር በል እንበለው። ክርስቶስ እንደተሰቀለ ስህተቱን እንስቀለው። እኛ ነፃ እንድንወጣ ነው የተሰቀለው። ስህተትን አምነን ስንመለስ መጥፎ ሥራን ሰቀልነው ማለት ነው። አዲስ ሰዎችም ሆን ማለት ነው።
ዉድ አባቶህቻቺን አምስቱ ክልቦች ምእመናኑን አያወኩትና ሲኖዶሱንም ሊያፈርሱ እየተንቀሳቀሱ ስለሆነ የስደተኝኣውን የነጽኣነት
ትግል ለመጥኣል በበተክርስትያን ውስጥ እያምታቱ ስለሆነ ” የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። . . .” የሐዋሪያት ሥራ ፳ ፥ ፳፰
ቀደምት አባቶችአችን ፓትርያርክ መርቆሪዎስ; አቡነ መልክ ጻዲቅ አቡነ ኤልያስ; አቡነ ጎርጎሪዎስ;.. ሐዋርያው ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መከረ «ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ። ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር። ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው? ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።» (1ጴጥሮስ 4፡12-1
አምስቱ ውሾች/ ከልቦች/…«ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።» (ማቴዎስ 5፡11-12)።
ስለዚህአ ምስቱ ውሾች/ከልቦች/ አንድነታችሁን ለመገዝገዝ በሲኖዶሱ ውስጥ በጽናትና በአንድነት ያላችሁትን ቀደምትና ዋናዋዎቹን ሊቃነ ጳጳስ አባቶቻችንን ለመከፋፈል ቢያላዝኑም እንደ እግዚአብሔር ቃል በጽናትና በአንድነት በመቆም እያደረጋችሁት ያለውን ተጋድሎ ኮርተንበታል ምስጋንችን ይድረስችሁ;;