የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል

VOA | June 4th, 2012

(VOA) — በተደጋጋሚ የዘገብንበት ርዕሰ-ጉዳይ ነው፣ ዋልግድባ ገዳም። በዚህ ገዳም ላይ ደረሱ ከተባሉት አንዳንዶቹን ለመጥቀስ ለስኳር ፋብሪካ ፕሮዤክትና ለሸንኮራ-አገዳ ልማት ቦታው እየታረሰ ነው፤ የአበው መካነ-መቃብር እየተቆፈረ አስከሬናቸው በመውጣት ላይ ይገኛል፣ አያሌ አብያተ-ክርስቲያናት ሊፈርሱ በዕቅድ ተይዘዋል፣ የገዳሙ ንብረት የሆነ በርካታ ገንዘብ ባልታወቁ ታጣቂዎች ተዘረፈ፣ ብዙ ኲንታል የእጣን ምርት ባልታወቁ ሰዎች ተቃጠለ፤ እናም ይህን አባቶች «በደል» ያሉትን በዝርዝር ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የሚገልጹ መነኮሳት አደን፣ ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው ነው የሚሉ ይገኙባቸዋል።

የተባለው ልማት በእርግጥም በዕቅድ ላይ መሆኑን መንግትም ሆነ ጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ ያምናሉ። መንግሥት፣ «ልማቱ ከገዳሙ ብዙ እርቅት ላይ ስለሆነ አይነካውም» ሲል፣ ወደ ስፍራው የተላኩት የጠቅላይ ቤተ-ክህነቱ የዐይን ምስክሮችም ይህንኑ አረጋግጠው፣ «ቤተ-ክህነት የመንግስቱን የልማት ዕቅድ ትደግፋለች” ብለዋል።

የገዳሙ ይዞታ እንዳይነካ ጥያቄ የሚያቀርበው ሕዝብ በአካባቢው ብቻ አልተወሰነም። «ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመ ዓለማቀፍ ኰሚቴ» የተሰኘው ስብስብ የየአካባቢው ተጠሪዎች ለቪኦኤ እንደገለጹት፣ ዛሬ አንድ ዓለማቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄደ ላይ ነው። ሰሜን አሜሪካ ውስጥ ቶሮንቶ-ካናዳ፣ ሎስ-አንጀለስ-ላኪፎርኒያ፣ ኒው-ዮርክና ዋሽንግተን ዲሲ። አውሮፓ ደግሞ ጀርመን፣ ብሪታንያ፣ ብራስልስና አውስትሬሊያ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።

ዛሬ ማለዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተነስቶ ወደ ውጪ ጉዳይ መሥራ ቤት የተጓዘውን የዋሽንግተኑን ሰልፍ ተከታትለን ነበር።

በዚህ ሰልፍ ላይ የክርስትና እምነት ተከታይ ብቻ አይደለም የተገኙት። ሌሎችም በኢትዮጵያውነታቸው ተገኝተዋል።

ከዋሽንግተን ሌላም በሎስ-አንጀለስና በቶሮንቶ ካናዳም ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዶ ነበርና ተወካዮቹን በስልክ አነጋግረናል።

ከዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የተወከሉት ባለሥጣን Ms Lora, ሙሉ ስማቸውን ማግኘት አልተቻለም፤ የሰልፈኛውን ደብዳቤ ተቀብለው ጉዳዩን እንደሚያጤኑትና ተገቢ ነው የሚሉትን ምላሽ በጽሑፍ እንደሚሰጡ ለሕዝቡ ገልጸዋል።

በተለይም ባለፈው ሐሙስ ሰቋር ውስጥ፣ በማግስቱ ዐርብ ደግሞ ገሪማ ላይ ስብሰባ ተካሂዷል። የሐሙሱ፣ እራሱ ሕዝቡ ተጠራርቶ የተሰባሰበበት ሲሆን የዐርቡ ደግሞ ባለሥልጣናት የገዳሙን አሥር ያህል መነኮሳት ጠርተው የሰበሰቡት እንደነበር ተገልጾልናል። በዚህኛውም ሆነ ዛሬ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ከዚያው ከአካባቢው ባለስልጣናት መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ይሁንና ግድቡም ሆነ ልማቱ ገዳሙን እንደማይነካ መንግሥት ገልጧል።

ሙሉውን ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ፡

Play below

 

2 Responses to “የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል”

  1. Tazabe says:

    Give me a break how can you belive Melese the butcher. Once a lair always a lair. He is digging and scattering the skeletons of the Monks and says he is not touching Waldeba. please do not waste you precious time. Victory for our beloved Monks and have the strength to stay the course. I am tired and disgusted of this ethnocentric unbeleiving band ye band lig.

  2. ሰለሞን ረታ says:

    ያከበሩትን ያከብራቸዋል የናቁትን . . .
    የወያኔ አገዛዝ ወደአገዛዝ በመጣበት አኳሓን ካልሆነ ሌላ የሚገባው አይመስልም። ስለዲሞክራሲ ያወራል ግን በተቃራኒ የመፃፍ የመናገር የመምረጥ የመመረጥ የመሳሰሉትን መብቶችን በሚገባ መጠን ለማክበር ግን አልቻለም ። ስለዕድገት ያወራል ግን ፍትሐዊና የሕዝቡን ኑሮ የሚለውጥ
    ዕድገት አይታይም ። በሕገመንግስቱ መንግስትና ሀይማኖት ለየብቻ ናቸው መንግስትም በሃይማኖት
    ጉዳይ ጣልቃ አይገባም/ እነሱ እንደሚሉት / ግን በተግባር እንደታየውና እያየን እንዳለው ጣልቃ
    መግባት አልፈው መጅሊሱንም ቤተክህነቱንም በራሳቸው ሰዎች ሞልተውታል። ፈጣሪን ማምለኪያ
    ቦታ መሆኑን እስክንጠራጠር ድረስ መፍንጪያቸው አድርገውታል። እግዚአብሔር ቸር ነው መሐሪ ነው
    ግን ያከበሩትን ያከብራቸዋል ያላከበሩትን ይንቃቸዋል።
    ለምርጫ ሰሞን ካልሆነ በስተቀር ለባህልና ለታሪክ ግድ የሌለው ኢሕአዴግ የመነኮሳቱንና የምዕመኑን
    አቤቱታ በመናቅ ኣንዲሁም እንደለመደው በመሸንገል የታላቁን የዋልድባ ገዳምን ይዞታ የማፈራረሱን ነገር
    ተያይዞታል። ሕዝብ መርጦኛል እያለ መረጠኝ ሊሚለው ሕዝብ ግን ጥያቄውን ሲመልስለት አይታይም።
    በተለያየ ሰላማዊ የተቃውሞ መንገዶች ተቃውማችንን ገልፅናል። በሰልፍ በፅሁፉች በስብሰባዎች በሌሎችም
    መንገዶች ጥያቄያችንንም አቅርበናል ስም ወጣልን እንጂ ገዳሙን አላድነውም። ለታሪካችንና ለቅርሶቻችን
    ግድ የላቸውም። ጮህን ጮህን ጮህን ግን አልሰሙንም ። ወገኖቼ መፍትሄው ምንድነው እስከመቼ ነው
    ዝም የምንለው ? እስከመቼ?



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.