የአላሙዲ አሽከሮች በዲሲ ባዘጋጁት የወያኔ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን እንዳይሳተፉ የቀረበ ጥሪ

EthiopianReview.com | July 3rd, 2012

የአላሙዲ አሽከሮች በዋሽንግተን ዲሲ ባዘጋጁት የወያኔ ፌስቲቫል ላይ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዳይሳተፉ የቀረበ ጥሪ

[PDF]

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ ዝግጅት በዳላስ ቴክሳስ ከጁላይ 1 – 7፥ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሄሪቴጅ በዋሽንግተን ዲሲ ከጁላይ 27 – 29 ይካሄዳሉ። እነዚህን የኢትዮጵያውያን ዝግጅቶች ለማፍረስ ወያኔያዊ ተልዕኮ ያላቸውና በገንዘብ የተገዙ ግለሰቦች ያደረጉት ሙከራ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ተልእኮአቸው ከሽፎ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) የበለጠ ተጠናክሮ፥ ራሱን ከወያኔ ካድሬዎችና ከአላሙዲ አሽከሮች አጽድቶ እየወጣ ይገኛል።

ሆኖም የአላሙዲ አሽከሮች ዛሬም ቢሆን እርኩስ ተልእኮዋቸውን ለመወጣት ከመሞከር አልታቀቡም። በአንጋፋዉ ESFNA ስም ላይ (ONE) በመቀጠል ድርጅቱን ለመከፋፈልና ህብረተሰባችን ውስጥ ውዥንብር ለመፍጠር የሞከሩት እኩይ ተግባር ፍርድቤት ቀርበው እንዲታቀቡ ተደርጓል።

በዚህም ሳያበቃ፣ ሆዳደሮቹ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የስፖርት ማሕበር አንድ (AESAONE) በሚል ስያሜ በዋሽንግተን ዲሲ ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 7 ድረስ የስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጃለሁ ብለው ተነስተዋል። ይህ ዝግጅት በዳላስ ከሚካሄደዉ የESFNA ታላቅ የስፖርትና የባሕል ፌስቲቫል ዝግጅት ቀናት ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን በማድረግ ያሰራጩት የእነሱን መሰሪ ተልእኮ በግልጽ የሚያስረዳ ነው።

ይህ የእነዚህ ጥቂት ሆድ አደሮች ጥርቅም ከአላሙዲ በሚቸራቸዉ ገንዘብ ከርሳቸውን ከመሙላት ባሻገር፤ ከነርሱና ከአላሙዲ ጀርባ የወያኔ አገዛዝ እንዳለበትና ዓላማውም ኢትዮጵያውያንን የመከፋፈል አጀንዳ ቅጥያ መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።

ውድ ወገኖች!

በመስጠም ላይ ያለ ሰው፣ አድኖ ላያድነዉ አረፋም ቢሆን ይጨብጣል እንዲሉ፣ አንዴ በአባይ ስም፣ አሁን ደግሞ በስፖርት ሽፋን የተገመደው ተንኮል ለወያኔ የእግር እሳት የሆነበትን ዳያስፖራ ለማወናበድ የታለመ ነው። ታዲያ ይህን እየተካሄደ ያለውን ሴራ እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ለማክሸፍ ሃገርወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ እንሰለፍ።

በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተመሰረተዉ Boycott TPLF ግብረሃይል ይህን በስፖርት ሽፋን ኢትዮጵያውያንን ለማወናበድና ለመከፋፈል የተዶለተውን ሴራ በጋራ እንድናከሽፍ ጥሪውን ያቀርባል።

በዋሽንግተን ዲሲ የወያኔ መልእክተኞች ትላንት ተቋቋምን ብለው ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥተው አዘጋጀን የሚሉትን ፌስቲቫል ሀገርወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዳትተባበሩ ጥሪ እናደርጋለን። በሚሊዮን ዶላር የተከራዩት ስታዲዮም የሰዓት እላፊ የታወጀበት መንደር ሆኖ ጭር እንዲል እንድናደርገው እንጠይቃለን።

በአንጻሩ ወደ ዳላስ ቴክሳስ በማምራት ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 7 ቀን 2012 ድረስ በሚካሄደው የሁላችንም መገናኛ፣ መዝናኛና የኢትዮጵያዊነት መግለጫ በሆነው 29ኛው በESFNA ፌስቲቫል ላይ በመሳተፍ በዓሉን የደመቀ እንድናደርገው እናሳስባለን።

የወያኔ ሴራ በየፈርጁ ይከሽፋል!
Boycott TPLF ግብረሃይል

Email: boycott.tplf@gmail.com
Tel: 703 828 4821


27 Responses to “የአላሙዲ አሽከሮች በዲሲ ባዘጋጁት የወያኔ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን እንዳይሳተፉ የቀረበ ጥሪ”

  1. አንዋር says:

    እኔ በጣም የሚያሳዝነኝ ሰርተርው መብላት እየቻሉ፣ በደም የተለከረውን የወኔን እንጀራ ለመብላት ደፈቀና የሚሉትን ወገኖች ስመለከት ነው። በተለይ አሜሪካን አገር ብዙዎች ባዶ እጃቸውን ከአገራቸው ተሰደው ገበተው ሚሊየነር የሆኑበት፣ ማንበብ መፃፍ እንኩዋን የማይችሉ የነበሩ ዶክተርና ፕሮፌሰር የሆኑኑበት ከዓለም አገሮች በተለየ ሁኔታ ልዮ ዕድል ያለባት አገር ነች። ታዲያ በዚህች ዕድል የምትሰጥ አገር ውስጥ ተቀምጠው ሰርተው ማድግ ሲችሉ፤ ያልሰሩበትን እንጀራ ለመብላት ያውም በደም የተነከረ ለመብላት የሚንሰፈሰፉን ሰዎች ማፈሪያዎችና ሰነፎች ከማለት ሌላ ስለነሱ ብዙ መናገር አያስፈልግም። እነዚህ ሰው ሆነው በሰውነት በማሰብ ፋንታ እንደ እንስሳ በሆዳቸው ተገዝተዋልና። እንስሶች ናቸው።

    አንዋር
    ከዲሲ

    Anonymous Reply:

    አይ አንዋር ገበሬው

    yenisew Reply:

    አይ እንዋር እንዳንት ማሰብ አልችልም.አንት አሰብና ሃግሪቱን አንድ ደረጃ ከፍ አድርጋት 21 አመት ሙሉ የት ነበርክ.

  2. Alemu says:

    በመጀመሪያ የኣላሙዲ አሽክሮቸ ብሎ መሳደብ ተገቢ አይደለም:: ቀጥሎም አገር ወዳድ መሆናችሁን በምን አውቃለሁ:: የበግ ለምድ ለብሶ ማታለል ይምስላል:: በልማትና በአስፖርት ሳንትባበር አንደት ስልጣን ላይ ብትሆኑ ክዚህ መንግስት የተሻለ ትሰራላችሁ ብየ ለማመን አችላለሁ:: ስለዚሀ ይህ መሰረተ ቢስ ጥሪ ተቀባይነት የለውም:: የህዝብን ንቃተ ህሊና ባትንቁ ጥሩ ይመስለኛል:: ለአገር ላጋራ ጥቅም አየሰራን በማንቀበላቸው ጉዳዮች ተቃውሞ ማቅረብ አንችላለን:ኣንደ አላሙዲ አንቨስት ማድረግ አንችላለን:: ህንዶችና ቻያናዎችም ተፈቅዶላቸው በልማቱ ተሳትፈዋል:: ይህንን አይንት ጠባብና የግል ጥቅም የሚያራምዱ ለአገራችን ምንም አንድማይፈይዱ ጠንቅቀን አናውቃለን::ለአገራችን መበታተንና ለብሀሮች መብት መረገጥ ምክንያት የሆነውን የቀደሞ አስተዳደር አንፈልግም::በስመ ኢትዮጵያ ስም ነግደውብናል:: ባሪያ አድርገው በድንቁርናና በድህነት ለዘመናት ገዝተውናል::አገር ወዳድ ከሆናቸሁ ለአገራችን ጥቅም አብረን አንስራ::

    geremew Reply:

    እሽከሮች ናቸውና በትክክል ነው የተጠሩት:: እንደውም እኔ የምጠራችው ባንዶች ብዬ ነው:: ምክንያቱም እላሙዱ የኢትዮጵያ ጠላትነቱንና የወያኔ እባልነቱን በገዛ እራሱ እንደበት እረጋግጡዋል:: ስለሆነም ለአላሙዱ የሚገዙና በጥፋት ድርጊቱ የሚሳተፉ ማለትም AESAONE በሚል ስም ለሚደረገው ማወናበድ ተባባሪ የሚሆኑ በሙሉ ኢትዮጵያ ነጻ ስትወጣ እንፈራረዳለን:: ፈጣሪ ከኢትዮጵያ እውነተኛ ልጆች ጋር ይሁን::

    sew Reply:

    ስልጣን የህዝብ ነው:: ተወደደም ተጠላም አንድ ቀን ነጻ እንወጣለን

    Aragaw Reply:

    Alemu

    You are Woyane

    Weyane Reply:

    Whether you like it or not, you will be ruled by Weyane for 100 years to come!

    Berhae Reply:

    የመቶ አመት ህልም ስታልሙ ትኖራላችሁ ይልቁንስ ለ ህዝቡ ስርታችሁ
    አመምዋታችሁን አሳምሩ መቶ አመት አንገታችሁ እስኪስበር ስትንክራተቱ
    ትግራይን በረሃ ስውን ድሀ አርጋችሁ እንዳታስቀሩት

  3. T.Goshu says:

    Well, there in no doubt that getting organized , promoting and pursuing one’s objective is one of the fundamental civil or human rights.From this well- justified perspective, we have no any illusion about the what our brothres and sisters are doing – forming their own sport club (” All Ethiopian Sport Asociation -AESA1″) and holding its first “festival”at any time and place they want. So, I do want to make clear that the innocent majority of the Ethioipian dispora in North America and all over the world are not saying that there is something wrong with exerciecing this basic right . To repeat, it is absolutely rediciculous to see those individoals (” leaders of the AESA1″ who are deliverately misinterpreting and misinforming the very clear and straight-forward beliefs and concerns of the innocent majority.
    Having said this introductory part of my remak , let me say few points about the very reason why the innocent majorty strongly challenge and condemn the behavior and actions of those lost ( at least temporariyl) brothers and sisters .
    1) To fail the Ethiopian Diaspora in particular and the people in general, and sell out themselves for the sake of financial tips offered by a tycoon (Al Amaudi) who provided and continue to provide the tyrannical regime which is determined to stay in power by any means including the killing macine with huge financial support is not simply wrong but it is a matter of being partner for terrible political crime. That is why it is safe to say that the very disturbing steps being taken by those very poor and wicked -minded individuals has nothning to do with the question of exerciecing acceptable civil rights. This is a month of June , during which hundreds of innocent fallen Ethiopians are remebered . It is not yet one year since the great teacher,Yenesew Gebre paid the most ultimate sacrifice hopping for the realization of respect for human dignity. At this moment, hundreds and thousands of innocent opposition political party members, activists ,journalists and others who try to express their genuine concerns are paying huge sacrifices for the making our country a place in which all citizens can live in genuine peace and shared prosperity. Again, who is one of the partners in this horrible situation? There is no doubt it is Al Moudi. So, how it is justifiable to argue that selling oneself and become part of this miserable game is the matter of civil rights ?? It is absolutely a very evil-guided bevavior and pracrice. Please ,our lost brothers and sisters, do not cheaply cheat yourself and go down to the very verge of the cliff of self -duhumanization. Please ,do not try to drag other genuine Ethiopians down to your dirty job . I wish I could have any other humble or polite expression ; but there is no any other way except calling the spade spade. That is the way it is!

    2) To those so-called singers ( it is difficult to say artists) such as Kuribachew , Eneye , Madingo and others , I want to say that selling out yourself and dancing your tail waging dances with very cynical and ruthless ruling elites and their cronies at the very expenses of the very lives of the innocent people of Ethiopia and at the very surviaval of the country herself is absolutely inexusable . I hear some honest fellow Ethiopians saying that people like Kuribachew, Eneye ,Madingo and etc. are not expected to undestand or engage in political ideas and activities. Well, it might be true under normal political challenges. But the situation in our country does not require any deep understanding or analysis at all. Any innocent illiterate fellow Ethiopian knows very well and even more than enough about the very ugly political game being played in our country .Because the very ill-guided political ,socio-economic and moral situation is the day-to-day experience . Do not tell me ,Kuribachew that you are going to join the evil -dancing festival because you are in need of some left-over money from a man who have promised to sacrifice what he has including his life for the sake of prolonging the bloody political situation in our beloved country.

    To Eneye Takele , you may join the dance “festival” organized by individuals who have lost their human reasoning and diginity . But you need to know that you are going to be a much more disgrace and disappointment to the very essence of art /culture , and the very cosequence of this will be very painful.

    To “Madingo” (I think you got this big name wrongly) , I want to say that the song you sang or sing about Ethiopia and its flag, and Emporor Tewodros has nothing to do with your ugly tail waging dance with highly parastic political cadres of the tyrannical regime. I advise you to perform or sing about the mastermind of brutal ruling circle like your coleague Solomon Tekalegne ( Kindibu Mamaru), not about greatly patriotic Ethiopians .

    Anyway, millions of genuine Ethiopians will contiune their justified struggle against all odds including your ugly behavior and act.

    The struggle for justice and freedom shall prevail!!

    Altaye Reply:

     ሁሉንም የነዚህን ከጠላት ጋር ማእድ ለመቁዋድስ የተሰለፉ ሆድ አደሮችን ሁኔታ በዝርዝር ስላሳወቁን ምስጋና ይድረስዎት።

  4. Melkamu says:

    ለአላሙዱ አሽከሮች, ቀላዋጮች, ተስፈኞች, ወሬ እመላላሾች, ቅምጦች (ወንዶችንም ሴቶችንም ይመለከታል), ስራ ሳትሰሩ ለብዙ እመታት በርጥባንና በልመና የምትኖሩ በሙሉ እንድ መልእክት እለኝ:: ባለፈው 15 ውስጥ የአበበ ገላውን “ከምግብም በላይ ነጻነት እንሻለን” የሚለውን መልእክት አልሰማችሁም ወይ??? የት ነው የምትኖሩት?? ሆዳችሁን በክብራችሁና በሞራላችሁ የሸጣችሁ ከጋማ ከብት የማትለዩና ጥቅም ካገኛችሁ የተጫናችሁን የምትሸከሙ ከንቱ ፍጥራን ናችሁ:: እኔ የማዝነው ለልጆቻችሁ ነው:: “የዛ የባንዳ ልጅ” እያሰኛችሁ ታኖራቸዋላችሁ:: ተዋርዳችሁ እዋራጆች ናችሁ:: ከጥፋት ለመመለስና ስም ለማደስ ማንኛውም ጊዜ ስለሚቻል ይህችን በኢትዮጵያን ሪቭው የወጣች ርኦሰ እንቀጽ እንብቡ:: ተመለሱ::
    http://www.ethiopianreview.com/amharic/?p=59751

  5. Buta madingo says:

    ሆዳሞች በጭንቅላታችሁ እንጅ በሆዳችሁ አታስቡ ሆድ ለምግብ ጭንቅላት ለማሰብ የተስጠን ነው; ስለዚህ በምጥዋት ሳይሆን በሰራ እንብላ; አይናችሁን ግለጡ

  6. Zenebe M says:

    ብዙዎቻችሁ ምናልባት ሳታውቁ የገባችሁ ልትሆኑ ትችላላችሁ ነገር ግን አሁንም እየተነገራችሁና ወገናችን በርሃብ አለንገ እየተገረፈ ነው; ከመኖሪያው እየተፈናቀለ; የሚበላውና የሚጠጣው አጥቶ የጎዳና ተዳዳሪ በሆነበት በአሁኑ ሰዓት ይህን እየሰማችሁና እያያችሁ; ለወገን ተቆርቁአሪነት ከሌላችሁ; ከላይ እንደተገለጸው ኔከሞትኩ እሳር አይብቀል ካለችሁ አህያ አትሻሉ:: ወገናችን ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ጉርሻ እንጀራ አጥቶ በየቆሻሻ መጣያው ሲዝግን የሚውለው በወያኔ አገዛዝ ምክኒያት ነው:: ይህን ማሰብ አቅቱአችሁ ስግብግብነት በግንዝብ ህሌናችሁን ከሸጣችሁ የአልሐሙዴን አሽከሮች መባል; የወያኒእ እንባ ጠባቂዎች መባል ሲያንሳችሁ ነው:: እየተነገረው የማይሰማ አህያ ወይም በግ ነው::

  7. hagos says:

    ለመሆኑ ከኢትዮፕያ የሚመቱት አርቲስቶች የት ነው የሚሄዱት?

    hagos 2 Reply:

    እንጃላቸው !!! በተለይ እነ ማዲንጎ ባይሆን ኤልያሰ ተባባል ያለው ተመቸኝ እንክፈልህ እና ለዲሲ ስራ ሲሉት ብሩስ ጥሩ ነበረ ከማን ጋር ልበላበት ከማን ጋረ ልዝናናበት ነው ያለው

  8. Tazaby says:

    ሰው ለሆዱ ከተገዛ ክ አንስ ሳ በምን ይለያል በ አላሙዲን ገንዘብ የተገዛችሁ ሁሉ አንስ ሳ ናችሁ በቃ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  9. Bene lay Teshager says:

    Dear Alemu, I definitely agree with you. Every one of us has the right to support or oppose any of the parties and we are entitled to that very democratic right. If we condemn those who have a different view point or stand than we do, then where is the issue of legitimacy and balanced or matured political thinking ? and how can we entertain ideas of different nature and content when we ourselves are complacent ,judgmental or ethnocentric? How can we work for a public good when personal interests are co-opted over the common good ?
    Is it right to slam others because they have different ideas or belong to a certain political group? If so, how are we different from the dictators ? Isn’t this kind of mentality that grows to dictatorship?
    How do we think and expect the other party to love us or be politically just about us when we are wrong ?
    Whose freedom are we speaking about when we are standing against the freedom of others ? Whom are we going to liberate when we are trying to dominate or block others way of thinking?
    If we want to get things right and win public heart , I would say self interest has to be put aside and common interest has to come first. In fact what we think seems right in our own eyes, but it is essential to go deep down and be far sighted and be able to find ourselves in the hearts of others. This is how we can win peoples heart and fix the problems that can affect the lives of the people that we are fighting for. This needs a huge commitment , not a silly act in the public area, a complete detachment from the self ,not a mere hatred over others for who they are and what they like or think…when we stand selfless, that is when we can only say ” we co-opted freedom over food”.
    i am not done yet but …

  10. yagersew says:

    አቤት ያች አገር ያፈራቻቸው ቆሻሾች ! እንደሰው ሳይሆን እንደ እንስሣ ለሆዳቸው የሚኖሩ ከብቶች ! አሜሪካን እየኖሩ እርጥባን ፍለጋ ብትሞቱ ይሻላችሁ
    ነበር ! በወገኖቻችሁ ደም መነገድ ዛሬ አይደለም የጀመራችሁት:: ክርስቶስ ያቺን አገር አንድ ቀን መታደጉ አይቀርም::

  11. YES HR-2003 says:

    There is no TWO ESFNA.
    There is no TWO CUD.
    There is NO more separation.
    Boycott ESFNA-One, which is formed to destroy our EFSNA.
    God Bless Ethiopia!

  12. Dawicho says:

    Listen People This So Called Rich Guy Is Not Your Friend He has big Agenda! Do You Know For Example He Belongs To A secret Society of Sweden! This Guy Is Front man For Western And Arab Investors. What Is a front man? A front man is a stooge,something like a Dummy The real players are Bankers. So What they want from Ethiopia! O Yeah! Her Land, Her Strategic location,e.t.c They are building projects somethings like USA we call ghettos in America a concentration camp in the city! They Will Break our nation economy, currency put their to knees,you already seen form Derg 7 now to TPLF 19 us dollar. Bankers are vampires they will gang up to break any countries they want to control! recent study show only 2 countries are now free from International Centralize Banking System . They Are N. Korea and Iran! Hey People Do Your Home Work አላሙዲ is a Criminal who finance criminal organization in ethiopia. All These criminals need to be arrested along with their fellow dignitary servants! Get The Fear out of your heart people! we are dealing with mass murderers criminal syndicates whom conglomerate to totally enslave the entire population!

  13. Taye says:

    YE ALAMUDI “wushemoch’ nachew !!!!!

  14. Tulu Oda says:

    The day of reckoning with traitors is approaching fast. These traitors will pay the price for their betrayal.

  15. Ibrahim Sulumin says:

    ኣህይ ብቻ ናት ብሆድዋ ይምታስብ እና አንድ ጌዜ የጭረቃ ግዳይ ሆና ትትርፋልች.እዚህ አንድ ነገር አለ ስብሃት ነጋ ከነ ጻህየ ደባልቆ ,ብስራት አማረን ኮለኔል ይትባርክ አማረን ሌሎች ትግራዮች ብሰም ኤርትራውያን አንዴ ድሞ ብስመ ኤትዮጵያ ሆኖ እየነገዱ ነው.በስወደን እነ ታደሰ ግበረግዛብሐር እነ ማኣዛ ግርማይ ወዘተ እንዳሉ ብሁሉ ትግራይ ወያኖዎች ባሉበት መደርክ ወይ እንላቾው.ጠቃቅን እና ደቃቅዎች ናቾው.

  16. Asheber says:

    Unless they’re born ignorant or just became stupid, it’s just as simple as saying, “We don’t buy anything you say or anything you want to organize.” No wonder the big tyrant himself is not welcome here in the US. This isn’t a place where you buy ‘dogs’ with your oil money. Just do your time, and God willing, it will all be over. There will come a point in time when justice will prevail, and all you tyrants will face a haunting truth about the poor lives of all innocent fellow Ethiopians … our blood on your hands.

    Bene lay Teshager Reply:

    Ashe , you said it well . I like when peoples mind is contently and rational. The struggle should be for justice and equality for the poor . Every one will be held accountable for each and every deadly action against the people . It is only a matter of time !

  17. Anonymous says:

    hi gays you all of you live in us.do you what is democracy? damm…….n



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.