“በረከታችሁም” ሆነ ውግዘታችሁ ማንንም አያድንም አይገድልምም! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል | June 11th, 2012

በትናንቱ ዕለት በምዕራቡ ዓለም የሰዓት አቆጣጠር ከለሊቱ 12: 00 (pm) ይሆናል (በሀገር ቤት የሰዓት አቆጣጠር ማለዳ መሆኑ ነው) ወደ አገር ቤት ስልክ መትቼ ነበር። የረጅም ዘመን ትውውቅና ወዳጅነት አለን ከትውውቅም ያለፈ የአባትነትና የልጅነት ያክል የጠበቀ ግኑኝነት ካለን አንድ የዕድሜ ባለፀጋ፣ የመጻህፍት አዋቂ፣ የሲኖዶስ አባልም የሆኑት አባት (ሊቀ- ጳጳስ) በስልክ ተገናኝተን “አውግተን” ነበር። ስልክ የመደወሌ ምክንያት ለሰላምታ ነው። መንፈስን የሚያሳርፍ መንፈሳዊ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላም “ጨወታ ጨወታን ያመጣዋል” እንደሚባለው አገልግሎት በተመለከተ አንዳንድ ነገሮች ስናነሳ ያመራነው ወደ ቤተ-ክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ነበር። አንስተን ከተነጋገርንባቸው ዓበይት ቁምነገሮች መካከል እጅግ የገረመኝና ያሳዘነኝ በመጨረሻው ዕለት በመጨረሻዋ ሰዓት በጥቂት የሲኖዶሱ አባላት ተከሰተ ሲሉ ዝቅ ባለ ድምጽና በስብራት ያወሱልኝኝ በጥቂቱ ለንባብ በሚያመች መልኩ ላካፍላችሁ ወደድኩ።

በዋናነት እኚህ ሊቀ ጳጳስ “ተዉ! እንዲህ ያለ ስህተት መስራቱ አስፈላጊ አይደለም። እየሆነ ያለውም አግባብነት የለውም ደግሞም በታሪክ የሚያስጠይቅ ውርደት እፈጸምን ነው ያለነው። … እዚህ የተሰባሰብን ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሁላችን ሴራው ሳይገባን ቀርቶም አይደለም ታድያ ግን ነገም በቀረን በእኛ ላይ መነሳታቸው የማይቀር ጥቂቶችን ለማሰደሰት ሲባል ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን ጥሰን በገዛ ልጆቻችንን እየገፋን ነው ያለነው … ።” በማለት ድምጻቸውን ካሰሙ ጥቂቶች መካከል አንድ ናቸው።

ቀደም ስል በመግቢያዬ እንደገለጽኩት በመሃከላችን ካለው እጅግ የጠበቀ ግኑኝነትና መቀራረብ የተነሳ በደረቁ ካነሳሁላቸው ጥያቄዎች መካከል ግንቦት 15/2012 ዓ.ም ሲኖዶሱ ያወጣውን የአቋም መግለጫ ቁ. 10 ላይ በሰፈረው “ውግዘቱን” በተመለከተ ያቀረብኩላቸው ጥያቄ የሚከተለውን ነበር “ … በመሰረቱ እናንተስ ብትሆኑ ከዚህ ቀደም ስታወግዙ ተወጋዦቹ ደግሞ ተመልሰው አውግዘውል ውግዘቱም እስከ አሁን እንደጸና ነው ታድያ እንዲህ ባለ ሁኔታ የማውገዝ ስልጣን አላችሁ ወይ? ስል ነበር ጥያቄን ያቀረብኩላቸው። ያገኘሁት መልስ “አይ አንተ ደግሞ … እስቲ ተው … ይህንሳ አታንሳው” በማለት ነበር ቁምነገራቸውን በውስጠ ወይራ ያስጨበጡኝ። እኔም ነገሩ ስለገባኝ ምን ለማለት ፈልገው ነው ለማለት አልደፈርኩም። ባይሆን ግን እዚህ ላይ ለአንባቢያንና ለአማኞች አንድ አንኳር ነጥብ ግልጽ ለማድረግ እወዳለሁ ይኸውም አውጋዡ ይመለከታል። እንደው ከዚህ ቀደም ስታወግዙ ተወጋዦቹ አካላትም በበኩላቸው ውግዘታችሁን ውድቅ በማድረግ ተመልሰው እንዳወገዛችሁ ውግዘቱም እስከ አሁን እንደጸና እናንተም ሆናችሁ ሌላውን የእምነቱ ተከታይ የሚያውቀው እውነት ነው ታድያ እንዲህ ባለ ሁኔታ የማውገዝ ስልጣን አላችሁ ወይ?

ውግዘት እንደሚሰራ ከታመነበት አስቀድሞ የተወገዛችሁ ወጊድ ተብላችሁ የተለያችሁም እናንተው ራሳችሁ አይደላችሁም ወይ? ታድያ ውግዘት ይሰራል ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ መጀመሪያውኑ ውግዘቱ እናንተው ራሳችሁ አቅም እንዳሳጣችሁ እንዴት ዘነጋችሁ? ማን ቢፈታችሁስ ነው ደግሞ ዛሬ ሌላውን ለማውገዝ የተነሳችሁ? እንግዲህ ያሰራችሁም እስኪፈታችሁ ድረስ በተፈቱ ላይ አንዳች ስልጣን የላችሁም! ከዚህ በተረፈ ደግሞ መንጫጫታችሁ ለአፍታ፣ መልሶ መላልሶ የሚደመጥ የወይን ጠጅ ዓይነቱ ሳይሆን እንደ መብረቅ ብልጭ ብሎ የሚጠፋውን የከረመም እንደሆነ ለጤና ጠንቅ የሆኑትን እንደ ዝንብ ያሉትን ነፍሳት የሚሰበስብ የወተት ዓይነት ዘፈን ነው የሚሆነው። ቀለል ባለ አማርኛ እንደ መሰሪው ማህበር “ማህበረ ቅዱሳን” ያለ ድብቅ ዓላማ ያለው በግርግር እንጀራውን የሚጋግር ከማስደሰት አልፎ የእናንተ “አውግዘናል” ማለት አንዳች የሚያመጣው ለውጥም ሆነ የሚፈይደው ፋይዳ የለውም።

እንደው ለመሆኑስ እንዴት ነው አንድ ሰው÷

v  ሊለካ የማይችል ፍቅር

v  ሊሞት የማይችል ሕይወት

v  ሊደመሰስ የማይችል ጽድቅ

v  ሊረበሽ የማይችል ሰላም

v  ሊታወክ የማይችል እረፍት

v  ሊጠፋ የማይችል ደስታ

v  ሊያሳዝን የማይችል ተስፋ

v  ሊቀንስ የማይችል ክብር

v  ሊጨልም የማይችል ብርሃን

v  ሊደክም የማይችል ብርታት

v  ሊረክስ የማይችል ቅድስና

v  ሊያልቅ የማይችል በረከት

v  ሊሻር የማይችል ጥበብ የሰጠንና የሆነልን ጥንት የነበረ ዛሬም ለዘልአለምም ያው/ህያው የሆነውን የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ኢየሱስ ሰበከ መሰከረ ጻፈ ተናገረ ተብሎ ያለ አንዳች ጭብጥና ሙግት በጭፍንና በግርግር “ይወገዝ!” ተብሎ የሚወገዘው? በመሰረቱ ውግዘት የሚገባውም ሆነ የሚያስወግዝ ድርጊት ልብ ተብለዋል? እንግዲህ ይህን ያደረገ፣ የፈጸመና ያስፈጸመ፣ የተባበረ በቅባቶችሁ ላይ እጁን ያኖረና የተማማለ ሁሉ ደም በእጁ ስይፍም በቤቱ እንደሆነ ልብ ይበል።

አንድ መንፈሳዊ ስልጣን የሌለውና ለመንፈሳዊ ስልጣንም የማይገዛ ስመ መንፈሳዊ የመናፍስትና የሙታን ጠሪ ስብስብ አንድ መንፈሳዊ የወንጌል አገልጋይ የማውገዝም ሆነ የመለየት ስልጣን የለውም። አቅም ያንሰዋል! ሃይል ያለው ስራ ለመስራት በጥቂቱም ቢሆን ሃይል ይስፈልጋል። ይህ ማለት በሌላ አገላለጽ ስጋ የስጋን ስራ ከመስራት በዘለለ በመንፈሳዊ ዓለም ላይ አሁንም በድጋሜ እጽፈዋለሁ አንዳች ስልጣን የለውም። እንደውም የሚመከረው በሰላም ዲቃላዎቻችሁን እንድታሳድጉ ነው። ለማስመሰል በገፋችሁበት ቁጥር የከፋውን እውነት ሊመጣ እንደሚችልም ደማችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት።

ሌላ የደነቀኝ ነገር በጉባኤው መሃከል “ወደ ውግዘቱ ከመቸኮላችን በፊት መምህራኖቹ ተጠርተው ይምጡና ቃላቸውን አድምጠን ውሳኔያችን እናስተላልፍ” ሲሉ አንዳንድ የሲኖዶሱ አባላት ያሰሙትን ድምጽ በመቃወም ተጎንብሰው ምድር እየዘበጡ ኡ! ኡ! ብለው የጮኹ “ሊቃ ነጳጳሳት” ነበሩ የሚል ነው። እዚህ ላይ የደነቀኝ ሌላ ሳይሆን እንደው እንደ ጅረት ውሃ ቃሉ ሲተረተር የባሳን ላሞች የሚያስደነብራቸው፣ የሚያንቀጠቅጣቸው፣ የሚያስጮኸቸውና የሚያንፈራግጣቸው ብሎም አራፋ የሚያስደፍቃቸው ነገር ስላልገባኝ ነው። ከቅድሳት መጻህፍት መረዳት እንደሚቻለው ቃል ሲሰማ የሚጮኸው መንፈሳዊ ሰው በቆመበትም መቆምም ሆነ መቀመጥ የማይችለው አጋንንትና ሰራዊቱ እንደሆነ ነው የሚያስተምሩን። ታድያ ተሳስተዋል የተባሉ መምህራን ስህተታቸውን ለማረጋገጥ ቃል ከአፋቸው እንስማ ሲባል ይህን ሁሉ ትእይንት የፈጠሩ ከማን ወገን ቢሆኑ ነው? እንግዲህ ለዚህ ነው ንጽህና ቢኖር ኖሮ አርባና ሃምሳ ሰው መሰባሰቡ ባላስፈለገ ነበር የምለው። ስህተት የተገኘበት ለቤተ-ክርስቲያንም ሆነ ለአማኞች መንፈሳዊ ጤናና አንድነት ጠንቅ ሆኖ የተገኘውን ለማውገዝና ከህብረቱም ለመለየት የአንድ ከነውር የራቀ መንፈሳዊ ሰው ቃል በቂ ነው። ምን ነው? ቢሉ ከቃሉ ጋር እግዚአብሔር ይቆማልና።  ታድያ÷

ü  ለራስዋ ያልተፈወሰች ነፍስ ስለ ፈውስ:

ü  ለራስዋ ያልዳነች ነፍስ ስለ መዳን

ü  ለራስዋ ያልተቀደሰች ነፍስ ስለ ቅድስና

ü  ለራስዋ ከባርነት ቀንበር ያልተላቀቅች ነፍስ ስለ ነጻነት

ü  ለራስዋ ከእስራት ያልወጣች ነፍስ ስለ መፈታት፣ ፈውስ፣ መዳን፣ ቅድስናና፣ ነጻነት የሚጋደለውንና የቆመውን የወንጌል ባለ አደራ ፊት ለፊት መቆምም ሆነ መቀመጥ አይቻላትምና በርቁ “አውገዘናል” መባሉ ምኑ ይደንቃል? እንግዲህ ጥጉ ይህን ታደርጉ ዘንድ ስልጣኑ ብቻ ሳይሆን የሞራል ብቃቱም እንደሌላችሁ ነው በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ የምወደው።

ለእናንተ መዳን በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ወንድሞች የጠራው ባሪያውን በማይተውና በማይረሳ ጌታ ደስ ይበላችሁ። እየሆነ ባለ ነገርም የማናችሁም ልብ አይውረድ ይልቁንስ እንዲህ ባለ ጊዜ የቆሬ ልጆች መዝሙር[1] ከአንደበታችሁ አይታጣ። መጽሐፍ ስለ ዳዊት “ዳዊት እጅግ ተጨነቀ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ” (1ኛ ሳሙ. 30: 6) እንዲል ወንድሞች ሆይ! ልባችሁ ሃይልን በሚሰጥ በእግዚአብሔር ይበርታ ደስም ይበላችሁ።

አሁንም ደግሜ ይህን እላለሁ: እናንተ በብዙ ወከባና እንግልት የምትገኙ ወገኖች ሆይ! በመከራችሁ ብዛት ደስታችሁን የሚበዛበት የሐሴት፣ በለቅሶ ፈንታም የደስታ እንባ የምታነቡበት ዕለት በደጅ ነው። ዕለቱ ምን ይመስላል? ስትሉ የጠየቃችሁኝም እንደሆነ በዚያን ዘመን በይግባኝ ሳይሆን (የተላለፈብኝ ውሳኔ እኔ ቀርቤ ሳልጠየቅ ነው፣ ይህን ያደረገም እገሌ ነው) ተብሎ ተሟግተህም በመርታት ሳይሆን በፍለጋ ያለ አንተ ይህን ሕዝብ ይሰበስብ፣ ያስተምር፣ ይመራና ይመግብ ዘንድ የሚቻለው ማንም የለም፤ የእግዚአብሔር እጅ  መንፈሱም ከአንተ ጋር ናትና እባክህ ወደ እኛ ተመለስ በእኛ ላይም ሁሉ አለቃ መሪም ሁነን እባክህ” ተብለህ በፊታቸው ተሻግረህ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ታገለግላለህ (መሳ. 11÷1- 11)።

ይብላኝ የንጹሐን ህይወት ለማበላሸት፣ ደም ለማፍሰስና ነፍስ ለመግደል ራሳችሁን የሾማችሁና የተሸሟችሁ ቅጥረኞች እንጅ መጽሐፍ “መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።”  እንዲል ጳውሎስ አለን ሲል በታላቅ ደስታ በሙላትና በድፍረት የሚተርከው አዳኝ፣ ከስሞችም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ኢየሱስ ታዳጊህ ነው። ነውረኛሞች “ይወገዙ” ቢባል በአመንዝራነታቸው፣ በሌብነታቸውና በብልሹ ስነ – ምግባራቸው ግርፋት/ቅጣት የሚገባቸው ማፈርም የሚገባቸው ብዙዎች አሉና ስለ ስሙ መገፋታችሁን ክብራችሁ ስለሆነ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ። እንዲህ ባለ ደስታም የሚገኘውን ሐዘን የሌለበት በረከትና ድል ብዙዎቻችን ምስክር ነን።

ወንድሞች ሆይ!

v  ወንጌል የተጠማ:

v  የሰው ክብር የሚያውቅ:

v  የምስራች የሚያወሩትን መልካም እግሮችን እንደ ዓይኑ ብሌን የሚንከባከብ:

v  ከዚህ ሁሉ ተጋድሎአችሁም በኋላ ዘርተህ የሚበቅልበት የሚታረስ ልብ አሳልፎ እስኪሰጥችሁ፤ በአንጻሩ ደግሞ ያስጨነቃችሁ፣ ያሳደዳችሁ፣ የገፋችሁና የተሳለቀባችሁም ጠላት ዓይኑ እያየ ጆሮውኑም እየሰማ በከበረ ስፍራ ላይ ከፍ ከፍ እስኪያደርጋችሁ ድረስ የእግዚአብሔር የትድግና ቀን ሳትናወጹ በጽናት ባስቀመጣችሁ ቦታ ላይ ጸንትችሁ መልካም ውጊያን ከመዋጋት እጃችሁን አትጠፉ። በክርስቶስ ኢየሱስ የተስፋ ቃል ጸንታችሁ መቆም ይቻላችሁ ዘንድም ዘወትር ስለ እናንተ በእግዚአብሔር ፊት እተጋለሁ። የምናምነውና የተከተልነው እግዚአብሔር ጻዲቅ አምላክ ነው! በጽድቅና በእውነት ለሚያገለግሉትም እንደ እግዚአብሔር ያለ ታማኝ አምላክ የለም! ውለታውም የሙት ባሪያው አጥንት ቆጥሮ ትውልድን በበረከት የሚሞላ አምላክ ነው።

 

እግዚአብሔር ያዳናቸው ከጠላቶች እጅ የታደጋቸው ይናገሩ!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

yetdgnayalehe@gmail.com

United States of America

June 10, 2012


[1] “አምላካችን መጠጊያችን ሃይላችን ባገኘን በታላቅ መከራ ረዳታችን ነው ስለዚህም ምድር ብትናወጥ ውኖች ቢናወጡ ተራሮች ቢናወጡ አህዛብ ቢናወጡ የእግዚ አብሔር ማደሪያ ግን እግዚ አብሔር በመካከሏ ነውና አትናወጥም እግዚአብሔር ፈጥኖ ይረዳታል።” መዝ (46) 1-7 


13 Responses to ““በረከታችሁም” ሆነ ውግዘታችሁ ማንንም አያድንም አይገድልምም! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል”

  1. Tazaby says:

    አንተ ግራ የገባህ የዲያቢሎስ ባሪያ!! ላንተ መልስ መስጠት ዲያቢሎስ ጋር መነጋገር ነው:; በውስጥህ ብስጭትና ምቀኝነት የተሞላብህ አርኩስ ነገር ነህ በቃ!!!!!!!

  2. Dawit says:

    አየህ ሙሉጌታ መናፍቅ ማውገዝ ድሮም ያባቶች ባህል ነው:: አርዮስ : መቅዶንዮስ ወዘተ:: የቤተክርስታያንን ትምህርት የማይከተል ሁሉ ከቤተክርስትያን ተለይቶ ይወገዛል:: ተሃድሶን በተመለከተ ውግዘት የተጀመረው አሁን አይደለም:: በ1990 ራሳቸውን የተሀድሶ መነኮሳት ህብረት ይሉ የነበሩት እነ አባ ብ እሴ : አባ ዮናስ ወዘተ ተወግዘዋል:: አሁንም በቅርቡ እየተወገዙ ነው:: አንተ እንደምትለው ያወግዟቸው አባቶች ማስተዋል የተሳናቸው ወይም የማያመዛዝኑ ሆነው አይደለም ያወገዙአቸው:: የቀረበባቸው መረጃ አሳማኝ ስለሆነ ነው:: እስቲ በሰከነ ህሊና ሆነህ አሰበው:: ሲኖዶስ እኮ ከሀምሳ በላይ የቤተክርስቲያኒቱ ምሁራን እና አረጋውያን አባቶች እኮ ናቸው የተሰበሰቡት:: ዝም ብለው ልጆቻቸውን አይለዩም:: የድፍረትህ ብዛት ሲኖዶሱን ምን ብለህ እንደሰደብከው ድጋሚ ላስነብብህ
    “ስመ መንፈሳዊ የመናፍስትና የሙታን ጠሪ ስብስብ አንድ መንፈሳዊ የወንጌል አገልጋይ የማውገዝም ሆነ የመለየት ስልጣን የለውም። አቅም ያንሰዋል! ሃይል ያለው ስራ ለመስራት በጥቂቱም ቢሆን ሃይል ይስፈልጋል።’
    አየህ ላንተ ሲኖዶስ ማለት ሙታን ጠሪ ነው:: አቅም የሌለው ነው:: ሀይል የሌለው ነው:: ለዚህ እኮ ነው ውግዘት ያሰፈለጋችሁ:: ባለጌዎች::አንተ ማነህና ነው ያን ሁሉ ሊቃነ ጳጳሳት እንደዛ ብለህ የምትሳደበው:: በመሰረቱ አንተም ተወግዘህ ከቤተክርስትያን እንደተለየህ ታውቀዋለህ:: ከቤተክርስትያን ስትለይም ቅዱሳን አስፈላጊውን መረጃ አቅርቦብህ ነው:: ውግዘት ማለት ደግሞ ለስይጣን ተላልፎ መሰጠት ነው:: እንዲህ አባቶችን የሚያሳድብህም ያ ክፉ መንፈስ ነው:: አንተ ራስህ ስለቅዱሳን አባቶችና የቤተ ክርስትያን የቁርጥ ቀን ልጆች ስትጽፍ እንዲህ የሚያንዘፈዝግህና የሚያንቀጠቅጥህ ለምንድነው::እስኪ ራስህ እየው:: ከቻልክ ተጠመቅ:: ቅዱሳንን የሚያስዘልፍህ ጋኔን ይርቅልህ ይሆናል::

  3. teklu says:

    በኢትዮጵያ ያሉት የማውገዝ ስልጣን የላችውም አስቀድመው ታስረዋል;; ውግዘቱም እስከ አሁን እንደጸና ያሰራችውም እስኪፈታችው ድረስ በተፈቱ ላይ አንዳች ስልጣን የላችውም;; ስልጣናችው ተይዛለች ቤተ/ክርስትያንንስ ለሁለት የከፈላት ጉዳይስ ምንሆነና;;

  4. Anonymous says:

    You shameless Diakon, now you have told us by whose side you stand. Today I came to know that you stand with the Devil patriarch paulos and those who are destroying and dividing our ethiopian orthodox church being inside and living only up to their stomach. What a shame. Crazy Mulugeta, what is your ultimate goal???????????????????? We will remove dictator zenawi, paulos and other insects like you away from our church and country. Poor mulugeta, even a kid can easily understand what you are barking for. When the synod in ethiopia make a historic decision to continue dialogue with the legitimate synod abroad and seriously condemn devil paulos and his arrogant kids recently, you bark like a dog here. Shame on you though you are shameless and already crazy man with a false title. Why don’t you write on how and why arrogants like zenawi and leba paulos should be removed from power??????????????????????????? I don’t think you are not aware of scandals committed by the so called patriach paulos and butcher zenawi. You hold a title diakon, right? Then how you dare to tell lies instead of the truth? Now, ethiopians around the world are aware of insects like you and cannot be easily misled by such confusing articles from already confused person. Pray unto God to get your conscience back. You are on the wrong side of history and you will be ashamed of yourself when ethiopians get their freedom back.

    Bene lay Teshager Reply:

    Dear anonymous, you are entitled to write you mind and this wouldn’t be bad and should not ascribed to be so by any standard. But, to be judgmental and call some one ” devil” would be ironically unacceptable,by any spiritual standard unless it is the evil one. Doesn’t the holy bible teach not to be judgmental? whatever a person does, s/he will be the one who is to be doomed for the sin.Never take that stand if you are honestly working for the common good. Fight not the person, hate not the person but their idea and come up with a persuasive and inspirational argument. This, not only buy you followers as you can get your idea across the board ,but also it is a great tool towards achieving the intended goal.
    Look you are calling others devil …crazy and all names, then how are you trying to bring justice to that church, community or group ,what ever denomination it may be. Is it not it self contradictory to speak about conscience when you consider human beings, that God has created in his own image, Insects ?
    Do you think it is spiritual , the holy one, to speak about God denying his authority? It is Him and only Him who has the power to judge and it is ungodly to address your issues this way.

    I agree with you that Ethiopians and every one under oppression in whichever corner of the world need freedom and liberation but those who are the courage to bring freedom need to assume a neutral ground about peoples way of thinking , peoples identity, beliefs and values as the nation is so diverse in this aspect.

  5. emmu says:

    ወይ አቶ ሙሉጌታ ለየልህ አይደል::

    በመጀመርያ ዲያቆን እያልክ ማታለልህን አቁም:: ተወግዘህ ከቤተክርስትያን የተለህ ለት ዲቁናህም አብሮ ተይዟል.::
    በመቀጠል ልነግርህ የምፈልገው ዛሬ ማንነትህን በደንብ እንዳሳወቅክ ነው:: በመጀመርያ ችግሬ ከማህበረ ቅዱሳን ነው ስትል ነበር:: አሁን ደግሞ ወደ ሊቃነ ጳጳሳቱ ዞርክ:: ማን ቀረህ::
    ሰው ቤተ ክርስትያን የሚሄደው በረከት ለማግኘትና ሰይጣንን ለመቃወም ነው:: አንተ ግን ሊቃነ ጳጳሳቱ በረከትም አይሰጡ ውግዘታቸውም ፍታታቸውም አይሰራም እያልከን ነው:: ታድያ በረከት ለማግኘት የት እንሂድልህ:: ማን ቀድሶ ያቁርበን:: ማን ያጥምቀን:: መናፍቃን ካምፕ:: ልትለን የፈለከው የመጨረሻ ግብህም ይሄ ነበር::

    አየህ የመጽሀፍ ቅዱስ የመጀመርያ ትምህርት አባትህንና እናትህን አክብር ነበር:: አንተ ደግሞ ተቃራኒውን እያስተማርከን ነው:: ይሄ ደግሞ ያባትህ የስይጣን መርዝ ነው:: አባ ጳውሎስ በቤተክርስትያን ላይ እያደረሱ ያለው ችግር ይታወቃል:: ግን ስንት ደጋግ አባቶች ሲኖዶሱ ውስጥ አሉ መሰለህ:: እነሱ ባይኖሩ ኖሮ አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስትያኗን ምን ሊያደርጓት እንደሚችሉ አይገባህም:: እንዳንተ አገር ጥለው ከመውጣት እዛው ሲኖዶስ ውስጥ ሆነው እየታገሉ ነው:: እነዚህን ነው ” መናፍስት ጠሪ የዲቃላ አባት እያልክ የምት ሰድባቸው:: አንድ ቀን ለስድብህ ሁሉ ባምላካቸው ፊት ፍርድን ትቀበላታለህ::

    ባንተ ቤት ኢየሱስን መስበክ ማለት ” ኢየሱስ ” እያሉ መጨፈር ነው:: እንዲህ ካልተባለ ክርስቶስ አልተሰበከም ማለት ነው:: ትንሽ እውቀትህ እኮ ነው እንዲህ የሚያደርግህ:: ለማንኛውም ግን የቤተክርስትያን መሰረቷም ጉልላቷም ክርስቶስ ነው:: ጸሎታችን አግዚኦ መሀርነ ክርስቶስ ነው:: አንግታችን ላይ መስቀል የምናስረውም ክርስቶስን ሁሌ እንድናስብ ነው:: የቤተክርስትያን ጉልላቷም መስቀል የሆነው ለዛ ነው:: ማንም ምእመን ከርቀት የጉልላቱን መስቀል እያየ ጌታን እንዲያስብ:: ቄሱም ሲያሳልም መስቀል ይዞ ነው:: ቅዳሴውም የክርስቶስን ስጋ ወደሙ ለመፈተት ነው:: በጠዋት የሚደርሰው ኪዳንም ክርስቶስንን ለማመስገን ነው:: ሌላው ቀርቶ ንዋየ ቅድሳቱ ራሳቸው ክርስቶስን የሚሰብኩ ናቸው:: አንተ ግን የተወገዙት ክርስቶስን ስለሰበኩ ነው ትለናለህ:: እስኪ የጻፍካትን ላስታውስህ::እንዲህ ይላል
    “ያው የሆነውን የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ኢየሱስ ሰበከ መሰከረ ጻፈ ተናገረ ተብሎ ያለ አንዳች ጭብጥና ሙግት በጭፍንና በግርግር “ይወገዝ!” ተብሎ የሚወገዘው?”
    አንተ ደፋር ባለጌ ካባትህ ከዲያቢሎስ ስለሆንክ ቤተ ክርስትያንን አባቶችን ትሳደባለህ:: የፍርድ ቀን ታለቅሳታለህ::

  6. AREYA says:

    ባለፈው ላንተ አይደለም ላንባቢያን ተናግሪያለሁ፡፡ እሱማ ምን ልቦና ህሊና ሀፍረት ኖሮት፡፡ ይህ የአምሮ በሽተኛ ነውስላችሁ ባባሌ ያልተደሰታችሁ ትኖራላሁ፡፡ ዛሬ ግን ልጅ የማይሸነግል የተለመደውን ቅዘቱን ስታነቡ የበለጠ ግልጥ ይሆንላችሁአል፡፡ማን ጋር ይሆን የደወለ አቡነ ፋኑኤል ዘንድ ወይስ ኣባ ጳውሎስ? በአጣሪ ኮሚቴ ተጠንቶ ከአርባ ባላይ ጳጳሳት (ሲኖደስ) አምነውበት የተስማሙበትን ጉዳይ ስህተ መሆኑን ለመንገር ይሞክራል፡፡ ዳግሞ በዚሁ ብሎግ ላይ ያሉ ከአሁን በፊት የቃዣቸው ቅዠት ወደ ኃላ አስታውሱአቸው “ማህበረ ቅዱስን” የሚል ልፍላፋ ተገኛላችሁ፡፡ ምነው ፀበል ቦታ ከማህበሩ ልጆች አስጠማቂዎቸ ነበሩት እንዴ? እንዳ አሁኑ ሳይለይለት፡፡ነገም ይህን የተለመደ ልፍለፋውን እጠብቃላሁ፡፡ካለቀቀው ይህተያዡ:: ይህ ብሎግ የሚለጥፈውን ግን ያውቀዋል ወይንስ… አልገባኝም በምትለጥፉአቸው ጦማርች የናንተም ማንነት ይመዘናል አስቡበት! ከለዚያ ግን ብሎጋችሁ ቅዠት የሚስተናገድበት እና ቅዠታሞች የሚጎበኙት መሆኑ የማይቀር ይሆናል፡፡ ላንተ የሰጠሁት ሀሳብ የለም ደግም እንደ ለመደከው እኔ እንዲከተባልሁ ብለህ እግዚአብሐርን በማይፈራ ሰውን በማያፍር በህሊና በማይመዘን ከንቱ ቅዠት ፁሁፍህ እንእንዲ ከተባልሁ ….በሉት እያልህ እንዳትዘባርቅ

  7. Eshete says:

    አቶ ዲያቆን ሰሞኑን አረፍ ብለህ ነበር ደግሞ መጣህ! በነገራችን ላይ የጻፍከውን አላነበብኩትም ግን እባክህ ይቅርብህ ሂድ እዛው አይጋ-ፎረም ላይ

  8. tazabi says:

    This so called “Diakon” is mentally disturbed. I never understood what he is talking about except he is biting everything like mad dog. “Abesku Geberku”

  9. Brook says:

    Soon I will have a blog that teaches my people but never allow such a nonsense articles that abuse our fathers. If he is a true hero why he flee?, why didn’t fight being there?, The smart man wants to live joyfully on the blood of others.
    As to me they have done great job,
    Alias, I know you don’t like my comment and you will not allow it for public, you do your business by annoying people posting the idea of mad dogs. You think your self a democrat. The true democrats are very responsible for the well being of the people. Now what you are doing is so annoying. sadly I learnt that you are the best well known grand son of Kebede michael, the person whom I love for ever. but sorry you have lost our true manner.
    The true democracy teaches responsibility.
    Please please please, can you follow your grand pa? the wise man always learns from others before he damage himself or others, so don’t only follow just your feelings and senses. You should cross checked with reality.
    Consider the manner of a kid that is grown with great family with all best guide lines for his future, grown on a street who has no any idea about human value and grown from a remote area almost alone closed to be wild,….it is hard to expect the same behavior from all of them. So you are treating all of us on the same mood.
    You are trying just on the American mood. But as to my understanding you didn’t get their style though you lived for long time. there are a lot reservations when democracy is causing a mess of their people.

  10. Anonymous says:

    Mulugeta Just shutup ur mouse.

  11. Kumar says:

    “ዘንዶው ቅዱሳንን ይሳደብበት ዘንድ አፍ ተሰጠው…..” ለመሆኑ “ዲያቆን” የሚለውን ማዕርግ ከየት አገኘኸው?

  12. Anonymous says:

    አንተ ሙሉ ሳትሆን ጎዶሎ አንደሆንክ አውቅሁ::ዘንዶዉ ስድብን አንጂ ክብርን አያዉቅምና:: በዲያብሎስ ፈረስ ሆንሀ አባቶቸን የምትሳደብ ከአግዚአብሓር ክሚግኝ በረከት ይልቅ ውጭ ባሉ መናፍቃን ገንዘብ በረከት ይግኝኣል ብለህ ይምታምን ፍጥረት መሆንህን አወቅሁ:: አምላክ ልቦናህን ይመልስ::አምን::



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.