የሰማእታቱ ደም ይጮሃል
የኢትዮጵያን ሪቪው ወቅታዊ ርዕሰ አንቀጽ
በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የሰማዕታቱ ደም ይጮሃል፣ የኢትዮጵያን ሪቪው ወቅታዊ ርዕሰ አንቀጽ
ግምቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ መብቱን ተጠቅሞ ወያኔን በምረጫ ያባረረበት፣ተስፋም የሰነቀበት ታሪካዊ ወቅት ነበር። ይሁን እንጂ መለስ ዜናዊ እጅግ ከፈተኛ በሆነ ልዩነት መሸነፉን ሲያውቅ የብዙሃኑን ድምጽ መስረቅና ማጭበርበር ከመረጠ በሁዋላ ድምጻችን ይከበር ብለው ሰልፍ የወጡትን ዜጎች የአጋዚን ነፍሰ ገዳይ ታጣቂዎችን በማሰማራት ንጹሃን ኢትዮጵያዊያንን በጠራራ ጸሃይ ረፈረፈ። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያንን ደግሞ በከባድ ሁኔታ አቁስሎ የተቀሩትን በብዙ ሽህ የሚቆጠሩትን እስር ቤት ወረወራቸው።
መለስ ዜናዊ የአዲስ አበባን፣ የደሴን፣ የአዋሳን፣ የአምቦን፣ የነቀምቴን፣ የድሬዳዋን፣ የአርባምንጭንና የሌሎችም የአገሪቱን ዋና ዋና ከተሞችን በንጹሃን ደም ካጨቀየና የቅንጅት መሪዎችን እስር ቤት ከቆለፈባቸው በኋላ በአጼ ሚኒሊክ ቤተመንግስት ውስጥ ተንሰራፍቶ ተቀምጦ የአጋዚን ነፍሰ በላ ቡድን አባላትን ግብር አውርዶ በአልኮል መጠጦች ይራጭ ነበር።
በአጋዚ ጦር ጭፍጨፋ እናቶቻቸውንና አባቶቻቸውን ያጡ ልጆች፣ ባሎቻቸውን ያጡ ሚስቶች፣ እህቶቻቸውን ያጡ ወንድሞች፣ ሚስቶቻቸውን ያጡ ባሎች፣ወንድሞቻቸውን ያጡ እህቶች፣ ዘመዶች፣ ጓደኞች፣ ጎረቤቶች፣ አሁንም ድረስ እያነቡ ይገኛሉ። በዛን የጭፍጨፋ ወቅት ታክሲ ነጅዎች “የሙታን ደም ከመንገድ እስኪደርቅ ድረስ መኪናችንን አንነዳም! “ ያሉት ሲታወስ አእምሮ ያደነዘዛል። ይህ የያዝነው ወር የሰኔው ጭፍጨፋ የተደረገበት ሁልቆ መሳፍርት የሆኑ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያን በግፍ የረገፉበት ሰባተኛ ዓመት የሚዘከርበት ወቅት ነው ። ይህ በንጹሃን ዜጎች ላይ በወያኔ የደረሰው ጭፍጨፋ በኢትዮጵያዊያን አእምሮ ለዘመናት በከፍተኛ ሀዘንና ብሔራዊ ቁጭት ሲታወስ ይኖራል።
ያለ ህዝብ ይሁንታና ምርጫ የሚገዛው መለስ ዜናዊ አንድ ቀን ህዝባዊ መነሳሳቱ መቀጣጠሉ እንደማይቀር ስለሚያውቅ በመላው ዓለም ውስጥ በማንኛውም አገር ውስጥ ባልታየ መልኩ በግድያ ወይም በአደጋ የሞቱ ሰዎች አስከሬን የሚመረመርባቸው ሆስፒታሎችን በፖሊስ መስሪያቤቱ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሥር አድርጎ የተቃወሙትን ገድሎ ለመቅበር እንዲያመቸው ይህንን የሚያመለክቱ መረጃዎች አፈትልከው እንዳይወጡ ለማፈን ሴራ ሸርቧል። ሆኖም ይዋል ይደር እንጂ መለስ ዜናዊና ግበረአበሮቹ ለሰኔውና ለህዳሩ ጭፍጨፋዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎችም በ21 ዓመት የአፈናና የአምባገነን አገዛዙ ጊዚያት ለፈጸማቸው ወንጀሎች ተይዞ ለፍርድ መቅረቡ ወይም ከህዝብ ጋር በሚያደርገው ጦርነት መጨረሻ አሸናፊ የሚሆነው ሕዝብ ስለሆነ እንደ ሊቢያው ኮሎኔል ጋዳፊ እሱም ላይ ህዝባዊ እርምጃ የሚወሰድበት ጊዜ ቅርብ እንጅ እሩቅ ኣይደለም።

አዎን ብትክክል, መለስ የኢትጵያን ሕዝብ ሲያሸማቅቅ ሲያስርብ ሲያስር ሲያስገድል ህዝቡን ከመሬቱ አፈናቅሎ ለጠገቡ የውጭ ባለ ህብቶች ሲያድል 21 አመት ሙሉ በበቀል ብትሩን ሲያተርምስ አና በዙሪያው ካሉ ነብስ ገዳይ አጨፍሪይዎቹ ጋር ሲቀለድብት ያልገባቸው ነገር የኢትዮጵያ ሕዝብን በጣዱት ምድጃ አነሱንም አንድሚያንጨረጨር ከቶሁኑ አለመረዳታቸው ነው አዝንላቸዋለው በጥፍት ትቢኢት ንቀት አብሪት ልባቸው ደንድኖ ሊመጣባቸው ያልውን መከራ አንዳያዮ ጋርዶባቸዋል ነብስ ገዳዮ መለስ አና አድምተኞቹ ለህዝብ የበላይንት መገዛት ካልቻሉ ነገሩ ሁሉ አንድ ጋዳፈ አይቀርም ጥፊ ነው የሚሆነው አግዛብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
All of Ethiopians will never forget our brothers and sisters who were gunned down by TPLF security forces. The killer and the murderer Meles Zenaw, will be hanged like Sadam Hussien. The question of his hanging is a matter of “when” not “if”. Check out this video.
http://www.youtube.com/watch?v=XYXczlVlLyY
Tewodreos, I agree with you that he will be hanged, but up side down.
Yes, he will be killed by a bullet and hanged up side down like his roll model Mossoloni.
ይኽው ዛሬ የግብጽ ሕዝብ የሙባረክን እገዛዝ እንኮታኩቶ ጥሎ እራሱ ያመነበትን እዲስ ፕሬዝዳንት መርጦእል:: የሚቀጥለው ነጻ የሚወጣው እገር ደግሞ ኢትዮጵያ ነው:: የተጨቆነ ህዝብ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ነጻ መውጣቱ እይቀርም::ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
he shouldn’t be killed he should be hanged and pull his body all over the country.
We will bring Meles and his party to justice for the crimes he commited against thousands of Ethiopians. Meles is Ethiopian Hitler.
Yes he must be hanged upside down and his body should be dragged on the streets of Addis Ababa just like the Italian Fascist invaders on the order of Zenawi’s model Mussolini did toour patriots.
our unity will be the best thing to over throw all TPLF’s bandit group !!
መለስ ዜናዊና ተንዘራዛሪዎቹ የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና አንድነት ከአንድ ብሄር የስልጣንና የጥቅም የበላይነት ጋር አስተሳስረውታል:: ጎበዝ የወያኔን የአፓርታይድ አገዛዝ ስርአት ተባብረን ካላስወገድን የሚደርስብን የስቃይና የግድያ ወንጀሎች ይቀጥላሉ በቅርብ ግዜም አገር እንደማይኖረን ያለፉት 21 አመታት የወያኒን ተሞክሮዎችን ማየት በቂ ነው::