ግርምት፣ ትዝብት፣ ፍርሃት እና ፀሎት!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አቤ ቶኪቻው

እኔ የምለው ወዳጄ ቅድም ስለ በእውቀቱ ስዩም ጉዞ ሳወራ አብሬው አነሳዋለሁ ብዬ ስደተኛ እንደመሆኔ መጠን ቀልብ አጥቼ የራሳሁት አንድ ጉዳይ አለ… ምን መሰልዎ…!?

ታዋቂዋ ተዋናይ መሰረት መብራቴ ከሀገር ወጥታ አሜሪካ ጥገኝነት ጠየቀች የተባለው እውነት ነው እንዴ!? መቼም ምን ሆና!? ብሎ መጠየቅ አግባበብ አይደለም። ምክንያቱም “ጉዳችንን” መቼ አጣነውና!

መሰረት መብራቴ በቀጥታ ከፖለቲካው ጋር የሚያገናኛት ነገር ባይኖርም ሁሉን ሰብስበው መያዝ የሚፈልጉ ዋና “የሴራ” ሂደት ባለቤቶች መሰረትንም፤ “የኢህአዴግ ንብረት ነሽ አለበለዛ ወዮልሽ!” አይሏትም ለማለት አያስደፍርም።

እውነቱን ለመናገር በአቶ በረከት ስምዖን የመፅሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝቶ፤ “ከመፅሀፉ የተመረጠ አንድ ክፍል አንብብ” መባል እንኳንስ መሰደድ ጫካ መግባትም ያሰኛል። ሰውየው የኢህአዴግ ባለስልጣን ስለሆኑ አይደለም እንዲህ የምለው… “እህ” ይበሉኝማ፤ ባለፈው ጊዜ በጣም የምናከብረው ፍቃዱ ተክለማሪያምን ጨምሮ ሌሎችም “አርቲቶች” የሁለት ሀውልት ወጎች መፅሐፍ ምረቃ ላይ ከመፅሀፉ የተወሰነ ክፍል በዕለቱ ለነበረው ታዳሚ እንዲያነቡ ታዘው ነበር። “ትዕዛዝ አይደለም” የሚለኝ ካለ፤ “የጌቶች ልመና ከትዕዛዝ እኩል ነው” የሚለውን የአበው ንግግር አስታውሳለሁ።

ታድያ በዛ ምረቃ ዕለት አንጋፋው ፍቃዱ ተክለማርያም እያነበበ ሳለ አንድ እንኳ በቅጡ የሚሰማው ሰው አልነበረም። ራሳቸው የአቶ በረከት ስምዖን ሳይቀሩ ውስኪያቸውን እየጨለጡ ወሪያቸውን ሲያቀልጡት ነበር። (ካላመኑኝ “ዩቲዩብ” ይመስክር!) ምስኪን ፍቃዱ ተክለማርያም ግን በሞቅታ ውስጥ ላሉት ባለስልጣኖች ንባቡን ቀጥሏል። በእውነቱ እኔ ፍቃዱን ብሆን ኖሮ የአፄ ቴውድሮስን ሽጉጥ የምመኘው ይሄኔ ነበር! ለአንድ ተዋናይ መድረክ ላይ ስራ አቅርብ ተብሎ አለመሰማትን ያህል ውርደት የትም የለም። በእርግጥ ሰዎቻችንም ቢሆኑ አርቲስቶቹን እጃቸውን እየጠመዘዙ አብራችሁን ኳስ ተራገጡ አብራችሁን መሸታ ጠጡ የሚሉት ወደዋቸው እንዳልሆነ ይታወቃል…! እናስ? የተባለ እንደሆነ አርቲሰቶቹ ያላቸውን የተቃባይነት በረከት ለመቋደስ እንደሆነ ግልፅ ነው።

እናም መሰረት መብራቴም እንዲህ አይነት ተደጋጋሚ እጅ መጠምዘዞች አይደርሱባትም ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ፍሬንዶቼ ሰዎቹ እኮ አምርረዋል።  በዚሁ ሰሞኑን ተመስገን ደሳለኝ ላይ የደረሰውን ማንሳት እንችላለን!

እኔ የምለው ትላንት ፍትህ ጋዜጣን በኢንተርኔት ተመልክቻት ነበር። “ፍትህ እና አልሸባብ ምን አገናኛቸው!” በሚል ርዕስ ተመስገን የፃፈውን ተመልክቼ በጣም ነው የተደነቅሁት። እኔ የምለው ሰዎቻችን ይሄንን ያህል ወርደዋል!? ተዋርደዋል እንዴ…!? አረ ሼ…!

አንዴ… ቆይኝማ ደብዳቤውን ላላያችሁት ወዳጆች  እዚሁ ላይ ላምጣምውና እንየው ድጋሚ እስቲ…

“To Ato Temesgen Desalegne

Chief Editor of Fitih magazine

Ethiopia

It has to be remembered that AlShebab has assigned me secretly to make propagation activities in Ethiopia, Somaliland, Kenya and Uganda. To accomplish the task we have agreed with you through your representative Ato Mamush Sentie in Eritrea to publish propaganda articles against the Ethiopian government, against the interest of the Ethiopian people and the American government. It has to be remembered that we have paid US dollar 24,000 for 30 consecutive editions. Now alshebab has made strategic change to accomplish its tasks. Therefore we need the 14 edition charges US dollar 11,200 dollar to alshebab. We believe that you will return back the money to our organization. If this is not fulfilled on time you will bear a cost on your representative Ato Mamush Sentie and your life according to the rule of the organization.

Alshebab wins

Ahmedin Nasir”

ተመስገን በፅሁፉ ላይ እንደነገረን፤ እኔም በበኩሌ የዚህን ደብዳቤ የእጅ አጣጣል  በፍፁም የአልሸባብ ነው ብሎ ማመን ይከብደኛል። ይህ ኢሜል ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነው የተላከው ብዬ ደፍሬ ለመናገር ባልችልም፤ ከኢትዮጵያን ሄራልድ መሆኑ እንደማይቀር ግን 99.6 % እርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ!

እስቲ አስቡት ተመስገን ደሳለኝ የኢትዮጵያን መንግስት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የአሜሪካንን መንግስት ጥቅም የሚፃረር ፕሮፖጋንዳ ለአልሸባብ ለማተም ሲስማማ…! ምናለበት “የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ” የሚለውን እንኳ ቢያወጡት! ይሄ ግፍ ምናምን የሚባለው ነገር ቀረ እንዴ…!?

ሌላው ይህ “የአልሸባብ” ተወካይ እንደሚለው ከሆነ ተሜ 30 እትሞች ላይ እኛን መንግስታችንን እና አሜሪካንን የሚጎዳ ፕሮፖጋንዳ ሊያወጣ 24 ሺህ ዶላር ተቀብሏል። አንግዲህ አሁን መልስልን የተባለው 11200 ዶላር ነው። ያም ማለት ከግማሽ በላይ ፕሮፖጋንዳውን ተግባራዊ አድርጓል ማለት ነው። እስቲ የትኛው የፍትህ ጋዜጣ ፅሁፍ ነው “አልሸባብዬ የኔ ጌታ አይዞህ በርታ በርታ…!” የሚል ይዘት ያለው!? በበኩሌ ከሀጥያቴ የተነሳም እንደሆነ እንጃ እንዲህ አይነት ፅሁፍ ፍትህ ጋዜጣ ላይ አይቼ አላውቅም! እናንት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ብፁህ የሆናችሁ ትመሩኝ ዘንድ እለምናለሁ!

እርግጥ ነው ፍትህ ጋዜጣ የመንግስትን እንከን ፈልገው ከሚተቹት ጋዜጦች ወገን ናት። እንደውም አውራ ናት ማለት ይቻላል። ይህም የኢትዮጵዩያ ህዝብ ፍላጎት ለመሆኑ ሁላችንም “ቀፈፈኝ” ብለን ስንወጣ፤ እርሱ የመጣው ይምጣ ብሎ በፃፈ ቁጥር የአንባቢው ምላሽ እንዴት እንደሆነ ራሱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኤጀንሲን ጠይቆ መረዳት ይቻላል።

ለማንኛውም ባለፈው ጊዜ የሰማናት ጭምጭምታ እውን ልትሆን ይመስላል። ከዛም በተጨማሪ ሰዎቻችን ከበድ ያሉ ጥቃቶችንም ሰንዝረውብን “አልሸባብ አደረገው!” ሊሉን ይችሉም ይሆናል። በእውነቱ ይሄ ምንም ባልታጠቀ ህዝብ ላይ ጣንያን የተጠቀመው የአውሮፕላን ድብደባ ጋር ይመሳሰላል ብል ምንም ማጋነን አይሆንም… ከሆነም ይሁን…(ደሞ ለማጋነን! ይህው መንግስታችን ስንት ነገር ያደርግ የለም እንዴ!?)  እና በፀሎቱም በጥንቃቄውም መትጋት ያስፈልጋል። የሰማሃት ጭምጭምታ ምንድናት? ብሎ የጠየቀ መልሱን በአዲስ መስመር ያገኘዋል።

መንግስት ተጨማሪ ሰዎችን በአሸባሪነት ክስ ሊጠረንፍ አስቧል አሉ። እዚህ ውስጥ ፍትህ ጋዜጣ ነፃነት ጋዜጣ እና አገር ቤት ያሉ ጦማሪያን ሊኖሩበት እንደሚችሉ ጠርጣሮቹ ጠርጥረዋል።  ስለዚህ ነቃ ብሎ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል ያለ ሁሉ አረማመዱ ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን አደራ ማለት ይገባል። ለቸሩ መድሃኒያለምም አደራ እንላለን!