ይህን ከመፃፌ በፊት አልጀዚራ እያየሁ ነበር። ያሲር አረፋት የተገደለው (…he might have been poisoned with polonium, a rare radioactive isotope. ) ተመርዞ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁም ወሬ አወጁ። ልብሱና የጥርስ ብሩሹን ስዊዘርላንድ ላይ በመመርመር የተገኘውን ውጤት ዋቢ በማድረግ፣ አራፋት 2004 ላይ ተመርዞ ተገድሎ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። ሞቶ ከተቀበረ ከስምንት አመታት በሁዋላ ይህ ምስጢር ተገኘ። በጎ ነው። እውነት ከተቀበረችበት ብቅ ማለቷ በርግጥም በጎ ነው። ጊዜው ሲደርስ ጆንጋራንግ እንዴት እንደተገደለም እንሰማ ይሆናል።
ቴሌቪዥኑን አጥፍቼ ወደ መኝታዬ ሳመራ ስለ አለማየሁ አቶምሳ አስታወስኩ። በተመሳሳይ ተመርዞ መታመሙና ከዛሬ ነገ ህይወቱ ታልፋለች እየተባለ ባንኮክ ህክምና ላይ እንደሚገኝ አውቃለሁ። ለመሆኑ አለማየሁን ማን መረዘው? ለምን አላማ?
የዚህን ምስጢር ከእለታት አንድ ቀን እንሰማዋለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በዚህ ባለንበት ዘመን አስቸጋሪ ሰዎችን የማስወገጃው ቀዳሚ ዘዴ ምረዛ እየሆነ በመሄዱ፣ በጣም አሳሳቢ ሆኖአል። በተለይም እስርቤት ያሉ የነፃነት ታጋዮች፣ ራሳቸውን የሚከላከሉበት እድል በጣም ጠባብ በመሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል።
አለማየሁን በቅርብ አውቀው ነበር። ከኦህዴድ አመራር አባላት የተለየ ነበር። ዋናው ተወዳጅ ባህርይው የአንጎሉን መናገር መቻሉ ነበር። ታዛዥ እና እጁ በደም የተጨማለቀ አለመሆኑም ይታወቃል። ወደ ኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነት ከመሳቡ በፊት ከአመራር አነባላቱ ጋር እየተጋጨ፣ ገለል ተደርጎ ቆይቶአል። የግጭቱ ምክንያት ሙስናን መቃወሙና ማህበራዊ ፍትህ መጠየቁ ነበር። በዚህ ምክንያት በኦነግነት ተፈርጆ በአይነቁራኛ ሲጠበቅ ኖሮአል። በኦነግነት የሚጠረጠር የነበረን ግለሰብ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ለምን እንዳደረጉ ገርሞን ሳንጨርስ፣ መመረዙ ተነገረን።
“ማን መረዘው? ለምን?” ለሚሉት ጥያቄዎች ያልተረጋገጠ ሹክሹክታ እንጂ ምንም መረጃ የለም። በምረዛው በሰፊው የሚታሙት ግለሰቦችም ተጠርተው አልተጠየቁም፣ ስራቸው ላይ ናቸው። አባዱላ እና ሙክታር የድርጊቱ ፈፃሚዎች ስለመሆናቸው ተብሎ ተብሎ ያለቀለት ነው። የወያኔ መንግስትም በጉዳዩ ላይ ትንፍሽ ብሎ አያውቅም። አባዱላ ስልጣኑን በመነጠቁ፣ ሙክታር ደግሞ የአለማየሁን ቦታ በመመኘቱ በርግጥ ይህን ሊፈፅሙ ይችላሉ? ወይስ በእነርሱ ሰም ድርጊቱን የፈፀመ ሌላ ጥልማሞት አለ? አለማየሁ ማገገም ከቻለ ፍንጭ ይሰጠን ይሆናል። እግዚሃር ይማረው!

Why always u consentrate in a person!
You know anything is possible when you have this kind of people in the government. All I am saying is let God save those people who are prisoned, and let us keep on fighting until we get rid of them. Long live Ethiopia
ተስፋየ ጽሁፍህ ይስማማኛል ግን አልፎ አልፎ እዚህ ባይቀርቡ ጥሩ ነበሩ የምላቸው ነገሮች ታቀርባለህ ::
በተለይ ፍርድ ቤት ብቻ ቢነሱ የሚጠቅሙ ጉዳዮች(ለምሳለ የአባዱላ ና ሙክታር ስም ማንሳቱ )እዚህ አስፈላጊ አይመስለኝም ::
የግዜ ጉዳይ እንጂ ስልጣን ላይ ያሉ ወንጀለኞች አንድ ቀን መጠየቃቸው ስለማይቀር የመረጃ ብክነት ይመስለኛል (እውነት ከሆነ)::
በተባ ብእርህ የሚያከራክሩና አመራማሪ ነገሮችን (ጠቓሚም ጭምር )ጽሁፎችን ከአንተ እንጠብቃለን ::
በተረፈ መልካም ጊዜ ለአንተም ለኛም እመኛለሁ
ንባብ መድሃኒት ነኝ ክዲሲ
የተስፋዬ ገ/አብ ወሬ አሁንስ ሰለቸ::
FA9999 Reply:
July 6th, 2012 at 4:38 pm
ከወያኔ ETV 100% ይሻላል እውነት ነው ሚያወራው::
ደግሞ ጀመረህ? አንተ እርትራዊ አይድለክም እንዴ? ምን አገባክ በኢትዮጵያችን ነገር? በቃ እንደ እርጎ ዝንብ ጥልቅ ነው ያንተ ነገር:: የሱዳንንም የፍልጽጤምን ቦለቲካ ትዘባርቃለክ!
FA9999 Reply:
July 6th, 2012 at 4:27 pm
ምን አልክ አንተ? ማን ነው ኤርትራዊ ያደረገው? ተወልዶ ያደገው የኖረው ቢሾፍቱ ነው የሚሞተውም የሚቀበረውም ቢሾፍቱ ነው::
ጽሁፍህን ተመልከተው አንተም ኢትዮጵያዊ ተብለሀል መጀመሪያ ስለራስህ በደንብ እወቅ::
Who will care and read your post? You are just one of those anti-Ethiopian agent and Bandit shabia like Meles, Bereket and Esayas. I want to tell you that you can fool someone once and not twice. I read the post that you post about Bereket and Menelikes-daughter and it tells me how much are posinous snake to bite Ethiopia-and thus you are those Yenat Tute Korach and Banda
ተስፋየ በትውልድ ኢርትራዊ ቢሆንስ? ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ ያደገ ኢትዮጵያውነትን የመረጠ ዘጋ ነው. በረከት ስምኦን ኢርትራዊ አይደለም አንዴ? ስንት የወያነ ባለስልጣናት ኧርትራዊያን አንዳሉ ለማንም ኢትዪጵያዊ ሚስጥር እይደለም.መለስ ቢሆንስ ከየት ነው? ተስፋየን ቤእርትራውነት ከመፈረጅ በፊት ኢትዮጵያን እየረገጥዋት ያሉት ኢትዮጵያውያን /ዘግነት በትውልድ ሃረግ ከሆነ/ ያልሆኑት ሰውች መጀመርያ መባረር አለባቸው.ተስፋየ ሃቅኛ ጸሃፊ መሆኑ ማንም ዘጋ ያውቃል.
keep writing man the truth shall priveil.
Dear Medhanit, you have raised a gerat point and I couldn’t agree more. This kind of accusations needs to be supported by concret evidences. On the flip side of it, Tesfay’s clear intention is to provide tips for concerned Ethiopians in order to expose many unsolved crimes.
The orchestrated killings of Obbo Derarra Kefene, Ato Assefa Maru, and many more are prime examples that required to have a clear investigation. But do we have an independent court system? is the question. Till then, let us focus on gathering our tangable evidences for the long awaited final judgement day!
Cheers!
Berisso.
Brother have u read what ‘alemayew’ wrote on feteh? Now we are bewilder what is writing about u! We need urgent answer. Whether in ur blog or whichever.
አቶ ተስፋዬ : ከአስመሪኖ የወለድካት ልጅ ሰላም ነች? ባለፈው አስመራ በትግርኛ ኢንተርቢው ስትሰጥ ያልካቸው ነገሮች ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለኤርትራ ብታስብ ተገቢ አይመስልህም?
Astelabhe.
እና ምን ይጠበስ
ተስፋየ ጥሩ ጸሐፊ ነህ:: ስትዋሽ ደግሞ ጥሩ ውሸታም ነህ:: አያዋዛህ መዋሸት ትችልበታለህ:: አጅ አጅ ከሚለው ጥሬ ፖለቲካ ያንተ ልብ ወለድ ያዝናናኛል::ኤርትራዊነትህ ለምንድነው አንድ ቀን አንኩዋን አንስተሃት የማታውቅ:: አስመራ መሽገህ መክረምህ የማይታወቅ መስሎህ ነው::የምፈራው ግን አንድ ቀን አዳልጦህ ኦሮሞ ነኝ አንዳትል ነው::
Man, if you are brave enough, tell us the killing of Assefa maru , Gebrezgiaber(gaym) and others in broad day light in the street of addis.
ተሰፋዬ ምንም ስለማታውቀው ነገር በጻፍክ ቁጥር ስዎች ስላንተ ማንንት እንዲያውቁ እያደረክ ነው:: ስለአለማየሁ የጻፍክው እስክዛሬ የነበሩትን በሙሉ እንድጠራጠር አድርጎኛል:: በመጀመሪያ አለማየሁ ያለው ቻይና ነው:: ሁለተኛ አለማየሁ ካገገመ ላልከው ከታመመ በሃላ ሶስቴ አገሩ ለስብሰባ ገብቶ
እንደወጣ ይታወቃል::አለማየሁ ውጭ አገር ብዙ ዘመዶች ስላሉት ሊነግሩህ ይችላሉ: እኔን ጨምሮ::
እባክህን የምትጽፈው ነገር ከሌለህ ያልሆነ ውሸት ከመጫር ሌሎች የሚጽፉትን ማንበብ ይሻልሃል::
አወ በማያገባህ ትገባለህ አንተ አርትራውይ ነህ ምን አገባህ በኢትዮፕያ ጉዳይ አያገባህም በቃ በቃ
ምነው ተስፋየ ላይ ተረባረባችሁበት? አንዲ ከ አስመራው አንዲ ከ ኦሮሞው ቀላቀላችሁት {ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም}የሚባለውን የሃገሪን ተረት አስታወሳችሁኝ
ገናለገና ሚስጥር ያወታል ብላችሁ እንዲህ መዝረክረክ ደግ አደለም
Oh,this illiterate man come again. I really do not want to see his bullshit so called article.It is like a devil written it, and he is a devil too.
ዘመንህን ያለ ስራህ አየገባህ አንዱን ከሌላው በማጋጨት የምትኖር የተረገመ አኣምሮ ያለህ የአርመን ክልሰ ነሀ!!
በየሳምንቱ አንዳንድ ጽሁፍ ብታወጣ ደስ ይለኛል. ወያኒዎችም ያብዳሉ, ለነገሩ ምን ቀራቸው, አብደዋል ቂቂቂቂ…….
Tesfay g/ebab!! We Oromos already knew that u r an EPLF(SHABIA) agent. U’ve tried to manupulate us to serve ur secret mission; just saying many things about the sufferings of oromo as if u & ur masters really care. Bzw don’t u remember as Isayas/ eplf strongly opposed olf not to librate oromiya? So who will believe u damn horse of devil! TOKKUUMAA 4EVER! We orömos know ourselves what is really happening to us! Dont try 2drive us on ur own dirty way, just we already identified best map to freedom!
ተስፋዪ ሁል ግዜ የሚጽፈው ለወያኔ ጥቅም ነው:: እነሱን ሴቭ ለማድርግ:: የኢትዮጵያን ታሪክ ለማጉደፍ:: የራሱ ወገኖች አሉት…ወያኔ ሆነው ግን ለሻቢያ የሚወግኑ….በሁለት ቢላዋ የሚበሉ:: እንደ እሱ ማለት ነው::
ስለዚህ አንዱን እያዋጋ…አንዱን እየጠቀመ…እርስ በርሳችው እያሻኮተ…ሚስጥር አዋቂ መስሎ የውሽት መረጃ እየሰጠ… የሚፈለገውን ቡድን በጎን እየደገፈ ስራውን ይሰራል…ሚስኪኑ ያገሬ አንባቢ ደግሞ ጥሩ ብእር አለው እያለ የሱንና የመሰሪ እላማውን መርዝ ይጋታል…ሲፈልግ ታሪክ አዋቂ…ሚስጥር አዋቂ…ጠላት…አንዳንዴ ተበዳይ…ሃገር ወዳድ…ናፋቂ…አንደ እሥሥት እየተቀያየረ የልቡን ያደርጋል…በርግጥም እውነት ትዘገያለች እንጂ አንድ ቀን ትገለጣለች::
ሃገር ሲረጋጋ አላማውን ሲከውን ወደ ”እናት ሃገሩ…” ገብቶ የሚለውን እንሰማ ይሆናል::
መልካሙን ሁሉ ለድሃዋ ሃገሬ!!!