መለስ ዜናዊ የ80 ሚልዮን ብር ቤት እየተገነባለት ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በዘካሪያስ ስንታየሁ | ሪፖርተር

ለመለስ ዜናዊ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ዘመናዊ ቤት በአራት ኪሎ የምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ እየተገነባላቸው ነው፡፡ አዲስ የሚገነባው ቤት እርሳቸውን የሚጐበኙ እንግዶች የሚያርፉባቸውን የእንግዳ መቀበያ ቤቶችን ያካትታል፡፡

ኢሕአዴግ የደርግን አገዛዝ በ1983 ዓ.ም ከሥልጣን ካስወገደ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከነቤተሰባቸው በታላቁ የሚኒሊክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተሰብም የዛሬ ሦስት ዓመት እዚያው ግቢ ውስጥ ወደተሠራው ባለ አንድ ፎቅ ቤት ተዛውሯል፡፡ ይህንን ባለአንድ ፎቅ ቤት የሠራው ቫርኔሮ ኮንስትራክሽን የተባለው የአገር ውስጥ ሥራ ተቋራጭ ኩባንያ ነው፡፡ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤትን ፕሮጀክት በበላይነት የሚቆጣጠሩት ባለቤታቸው ወይዘሮ አዜብ መስፍን ሲሆኑ፣ ግንባታውንም የሚያከናውነው ቫርኔሮ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት በያዝነው የበጀት ዓመት ለግንባታ 14,207,800 ብር የጠየቀ ቢሆንም፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግን ያፀደቀለት 6,318,000 ብር ነው፡፡ በተጨማሪም የቤተ መንግሥት አስተዳደር እንግዳ ማረፊያን ለመገንባት 29,594,000 ብር ቢጠይቅም፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግን 3,796,000 ብር ብቻ ነበር ያፀደቀው፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱ ቤት የሚገነባው ከእነዚህ ሁለት ተቋማት የሚገኘው ገንዘብ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

አዲሱና ዘመናዊው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የታላቁ ቤተ መንግሥት ግቢም በአስደናቂ ሁኔታ ወደ አረንጓዴነት እየተለወጠ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡