የወያኔ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ24 ተከሳሾች ላይ ከ8 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እሥራት ፈረደ

VOA | July 13th, 2012

ችሎቱ እንደተሰየመ ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም ባዘዘው መሠረት ተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ ሃሳባቸውን በጽሑፍ ማቅረባቸውን ገልጿል።

አስከትሎም እንያንዳንዱ ተከሣሽ በቀረበበት ክሥ መሠረት ጥፋተኛ ሰለተባለ ያስከትላል ያለውን ቅጣት ዘርዝሯል። እንደክሡ ማመልከቻ ቅደም ተከተል አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ፋሲል የኔዓለም የዕድሜ ልክ ፅኑ እሥራት ተፈርዶባቸዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ ቅጣት የተጣለባቸው አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ ሲሆኑ የሃያ አምስት ዓመት ፅኑ እሥራት ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ዘጋቢአችን መለስካቸው አምሃ ሌሎቹም ተከሳሾች የተቀጡበትን ዓመታት ዝርዝር እንዲሁም ቤተሰቦችና የፖለቲካ መሪዎች ስለፍርድ ቤቱ ውሣኔ የሰጡትን መልስ አካቶ ያጠናቀረውን ዘገባ ያድምጡ።




One Response to “የወያኔ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ24 ተከሳሾች ላይ ከ8 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እሥራት ፈረደ”

  1. terbu says:

    መቼም ቢሆን ለሁሉም ነገር ማለቂያና ማብቂያ አለውና የነዚህ የወንበዴዎችም ነገር ከመጠናቀቂያው ላይ የደረስ ይመሰላል:: ለኔ ግን ታላቁ ሰጋት እነሱን ተክቶ ስላም ፍትህና እኩልነትን ሊያውጅና ከዘመናት ስቆቃችን ሊያሳርፈን የሚችል ህይል አዘጋጅተናል ወይ>? ሁሉም ከሰልጣን ወንበር ላይ ቁጢጥ ብሎ ተራውን ሊረግጥ ከሆነ ግን ካሁኑ በጥብቅ ያስብበት! በቃ ሲባል በቃ ነው !የታስሩም ይፈታሉ ለኛም እረፍት ይሁንልን! አሜን!!!



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.