ጤናይስጥልኝ እንደምን አምሽታችኋል ? ዛሬ ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳው ፣ አዲስ ዘገባ ሊያቀርብልን በዝግጅት ላይ ነበረ ፣ ግን አልሆነም! እጅግ ያሳዝናል! ከዚህ በኋላ ድምፁ በራዲዮ ሊሰማ አይቻልም ። ወጣቱ፤ ጎልማሳው ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳው፤ ትናንት እሁድ፣ ከአዋሳ ወደ አዲስ አበባ ከ 2 ወንድሞቹ ጋር በመመለስ ላይ ሳለ፤ ከዜና ምንጮቻችን እንዳረጋገጥነው፣ ባጋጠመ የመኪና አደጋ ሳቢያ ፤ እርሱና፤ አንደኛው ወንድሙ ህይወታቸው አልፏል። በዚህ ዘግናኝ ህልፈተ ህይወት፣ ቤተሰብ ፤ ቤተዘመድ ፤ ጓደኞች ፣ እኛም የሥራ ባልደረቦቹ እጅግ አዝነናል። ስለሆነም የዛሬውን ሥርጭታችንን፣ ከሞላ ጎደል በአጠቃላይ፤ ለእርሱ መታሰቢያ እንዲሆን አድረገናል። በዚህ በራዲዮ ጣቢያው ማዕከል ከሚገኙ 6 ባልደረቦቹ ጋር የተካሄደው ልዩ ውይይት ፤ ቀጥሎ ይቀርባል።
የታደሰ እንግዳው ኅልፈትና ዶይቸ ቨለ
ዶይቸ ቬለ | July 16th, 20124 Responses to “የታደሰ እንግዳው ኅልፈትና ዶይቸ ቨለ”
We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.
You must be logged in to post a comment.

ክርስቶስ ነብስህን በገነት ያኑራት
ታዴ ነፍስ ይማር. ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ ነበር. ወያኔ ሲያስር ሲፈታው እጁን ያልስጠ ጀግና. ፊት ለፊት እንደተጋፈጣቸው ሳያፈገፍግ ያለፈ ሰው ነው. ሩህሩህና ክፋት የማያውቅ ነበር. ሃገሩ ነጻ ወጥታ ሳያይ በሞት መለየቱ ያበግናል. መጽናናት ለቤተሰቦቹ ይስጣቸው. የታዴ ስራ ህያው ሆኖ ይኖራል.
ኦዲዮ ፋይል አልትያያዝም
በጣም አሳዛኝ ዜና! ሰዎች ስንባል እንደዚ ነን: ነብስ ይማር በታም የምወደው ጋዜጠና ነበር::LEBETESEBOCHU EGZHABHER SINATUN YST