የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ታመው ቤልጅየም መዲና ብራስልስ በሚገኝ ሴይንት ሉክ በተባለ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን በኢንተርኔት የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ በአዲስ አበባ በይፋ አለመታየታቸው፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይትም ሆነ ትናንት በተጠናቀቀው የአፍሪቃ ህብረት ጉባዔ ላይ አለመገኘታቸው ብዙ እያነጋገረ ነው። ስለዚሁ ጉዳይ በአዲስ አበባ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም፤ በብራስልስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተያየት ለማግኘት በኢሜይል ብንጠይቅም ዜናው ውሸት እና የተሳሳተ ነው በሚል ያቀረብነውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል። በመሆኑም፡ ብራስልስ የሚገኘው ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በዚያ ሕክምና እያደረጉ ነው ስለመባሉ በበኩሉ የሰማው እንዳለ ጠይቄው ቀጣዩን መልስ ሰጥቶኛል። … [ያዳምጡ]
Play below

ዋናው ትልቁ ቁም ነገር አበበ ገላው በሽታውን ቀስቅሶበት መታመሙና መንገላታቱ ነው እንጂ ለምን ገደል ገብቶ አይታከምም ይሀ ነፍሰ ገዳይ ምንም በሽታ የለበትም የሱ በሽታ እንደውሃ ያፈሰሰው የድሃ ህዝብ ደም ያስከተለበት የመንፈስ መረበሽ ነው
ይህን ያሂል ለአንድ ሰው ኖር ሞተ ሚንዲነው ለዉቱ