“መለስ ታመመ” የሚለውን ወሬ ተከትሎ፣ ኮማ ውስጥ መግባቱና መሞቱ እየተነገረ ሰንብቶአል። የወያኔ መንግስት ግን ወሬውን አፍኖ ለመቆየት ተጨናነቀ። መለስ ጀርመን ሃገር ላይ ቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጉ በአንድ ወገን ሲገለፅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ቤልጅየም 10 ቀናት አልጋ ይዞ መሰንበቱ ተሰምቶአል።
“አዲሳባ ገባ” የሚለው ተሰምቶ ሳያበቃ፣ “ብራስልስ ላይ መሆኑ ተረጋገጠ” ተባለ። ወሬዎቹ መልከ ብዙና ውል አልባ ነበሩ። ዞረም ቀረ መለስ ታሞአል። ከመለስ መታመም ጋር በተያያዘ እንዲሞትም ሆነ እንዲፈወስ የሚፀልዩ ተደምጠዋል። ከህይወት ልምድ እንደተረዳሁት ከሆነ፣ አምላክ የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ እጁን ስለማያስገባ የሁለቱንም ወገን ፀሎት የሚሰማ አይመስለኝም። መፍትሄው አበበ ገላው እንዳደረገው፣ እያንዳንዱ ለአላማው መሳካት አንድ ነገር ማድረግ ብቻ ነው።
እርግጥ ነው፣ መለስ በደም ካንሰር እና በአንጎል እጢ ህመም በመሰቃየት ላይ መሆኑ ተረጋግጦአል። በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው፣ ከዚህ በሁዋላ እንደቀድሞው ወደ ቢሮው ገብቶ ስራውን መስራት ይቸገር ይሆናል። እንደሚሰማው ከማንበብና ከመፃፍ እንዲገለል በሃኪም የተመከረው ከስድስት ወራት በፊት ነበር። ዞሮ ዞሮ መለስ በህይወት አለ። እንዲህ በአጭር ጊዜ ለህይወቱ የሚያሰጋው አለመሆኑም ይሰማል። እንደተነገረው ቀዶ ህክምናም አላደረገም። የአንጎል እጢውን በጨረር ሊያክሙት ሲሞክሩ ነበር የከረሙት። ቀዶ ህክምና ለመሞከር ጊዜው ገና መሆኑን ዶክተሮቹ ለመለስ ነግረውታል። ይህን መረጃ እንደ ጥሬ እውነታ በመያዝ ግን ስለ አጠቃላዩ የአካባቢያችን ፖለቲካ አንዳንድ ነጥቦችን
ማንሳት ይቻል ይሆናል።
የመለስን መታመም ተከትሎ በኢህአዴግ የአመራር አባላትና በጄኔራል መኮንኖች መካከል የተፈጠረው መቧደን በጣም አሳሳቢና ለውይይት የሚጋብዝ ሆኖ ሰንብቶአል። አመራር አባላቱ የመለስ እድሜ አጭር መሆኑን በመገመታቸው ለህልውናቸው ሲሉ አይኖቻቸውን ወደ ምኒልክ ቤተመንግስት ልከው ከረሙ። አሁንም በሰራዊትና በሲቪል ባለስልጣናት መካከል የስልጣን ሽኩቻ ስለመኖሩ እየተፃፈ ነው። ኢህአዴግ ቀድሞውንም አንድነት አልነበረውምና ከመለስ መታመም ጋር ድርጅቱ በየአቅጣጫው ሲፈነዳዳ ታይቶአል። የመለስ አልጋ ወራሽ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉ ስሞችም በየሚዲያው እየተገለፀ ቆይቷል። ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ አዜብ መስፍን እና ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ቀዳሚ እጩዎች ሆነዋል።
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ የፃፈውን አይቻለሁ። የግምት ወይም የመረጃ ስህተት አለባቸው። ለአብነት በረከት ስምኦንና አዜብ መስፍን በአንድ ቡድን ውስጥ ሊሰሩ አይችሉም። በሁለቱ መካከል ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ጦርነት ተነስቶ ሰንብቶአል። አዜብ በሚዲያ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ገብታ በረከትን ለማዘዝ ሞክራ ነበር። በረከት በጣም በመበሳጨቱ፣ “አንቺን በዚህ ጉዳይ ውስጥ ምን ያገባሻል? ሚስት ብቻ መሆንሽን ለምን ትረሽዋለሽ?” ይላታል።
በበረከት ልቅ ንግግር እብደት ውስጥ የገባችው አዜብ በሃይለማርያም ደሳለኝ በኩል በረከት ላይ ተፅእኖ ለማድረግ ሞከረች። እዚህ ላይ ግን በረከት ችግር ውስጥ ገባ። ወደደም ጠላ ሃይለማርያም የበላይ አለቃው ነው። መንበርከክ ግን አልቻለም። የብአዴን ምንጮች እንደሚገልፁት፣ በረከት ስምኦን አኩርፎ ወደ እናት ክልሉ ዋና ከተማ ወደ ባህርዳር ኮበለለ። ስራውን ትቶ ባህርዳር አንድ ሳምንት እንደቆየ በአዲሱ ለገሰ ልመና እና ማግባባት ወደ አዲስአበባ ሊመለስ ችሎአል። የመለስን መታመም ተከትሎ በረከት ወላጅ አልባ ልጅ መስሎ ታየ። መለስ ከስራው ገለል ከማለቱ የተፈጠረ ቁጥር አንድ ሽኩቻ ነበር። አዜብ ሃይለማርያም ደሳለኝን መጋለብ መጀመሯ እውነት ነው። እዚህ ላይ ሃይለማርያም ወደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሳበበትን ዋና አላማም ለመረዳት ያሰችላል። ነባር ሚኒስትሮችና ትግሬ ያልሆኑ ታጋዮችን በዚህ መንገድ ከቤተመንግስቱ ለማራቅ ሃይለማርያም መልካም መንገድ ሆኖ ሊያገለግል ይቻለዋል።
የህወሃት ነባር የአመራር አባላት በዚህ ወቅት ይከፋፈላሉ ማለት ግን ለእውነት የቀረበ አይደለም። ከተከፋፈሉ ቤተመንግስት ውስጥ ማን እንደሚገባ ያውቃሉ። የምኒልክን ቤተመንግስት አንድ ጊዜ ከለቀቁ፣ ዳግም እንደማይመለሱባትም ይረዳሉ። ስለዚህ ህወሃት ለአራት ወይም ለሶስት ተከፋፍሎ ትርምስ ውስጥ እንደሚገባ መጠበቅ የዋህነት ነው። ከተመስገን ትንታኔ የምስማማበት የብአዴን ተፎካካሪነት ጉዳይ ነው። በዚህ ወቅት አዲሱ ለገሰ እንደሚገመተው በጡረታ የተገለለ አይደለም። እንደ ጆርጅ ኦርዌል ውሾች ሸሽጎ ያኖራቸው ከፍተኛ መኮንኖች ካሉት ብልህነቱን ማድነቅ ይቻላል። ብአዴን ተሸፋፍኖና ተጠጋግኖ ያደፈጠ ድርጅት ነው። አብዛኞቹ የብአዴን ካድሬዎች ቁጭት ይሰማቸዋል። ህወሃትን የሚገለብጡበት አጋጣሚ ከተገኘ፣ ከመጠቀም አይመለሱም ተብሎ ይታሰባል። በርግጥ ከህወሃት የተሻለ ስርአት መገንባት ይችላሉ ተብሎ ተስፋ አይደረግም። ህላዌና ካሳ ሸሪፎ ከኢህአፓ መንፈስ ጋር አብረው ያሉ እንደመሆናቸው፣ ኢህአፓን
ወደ ጓዳቸው ለመጋበዝ ይሞክሩ ይሆናል። መለስ ዜናዊ ዘግይቶም ሆነ ፈጥኖ በሞት የሚሰናበት ከሆነ የብአዴን አመራር አባላት ከባድ ፈተና ውስጥ ይገባሉ። ምክንያቱም የመለስ ዜናዊ መንግስታዊ ወንበር በሌላ የህወሃት ሰው የሚወረስ ከሆነ፣ ለብአዴን ታሪካዊ ውርደት ይሆንበታል። ብአዴን ለ23 አመታት የኢህአዴግ ምክትልነትን ወንበር ይዞ ቆይቶአል። ከ23 አመታት በሁዋላ ሊቀመንበሩ “በሞት” ቦታውን ሲለቅ፣ ብአዴን ሊቀመንበርነቱን መተካት ካልቻለ ለዘመናት የሚወነጀሉበትን አሽከርነት በማፅደቅ እነርሱም ወደ መቃብራቸው ያመራሉ። በግብፅ የቀበሌ አስተዳደር ውስጥ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ምንጊዜም ምክትልነት ቋሚ ቦታቸው እንደሆነው ሁሉ፣ ብአዴንም ምክትልነትን አምኖ ሳይቀበል
አልቀረም። ከዚህ ውርደት ለመዳን ብአዴን ሁለት አማራጮች አሉት። የመጀመሪያው መለስ እንዳይሞት መፀለይ ሲሆን፣ ሁለተኛው የመለስን ወንበር ለመያዝ ሽምጥ መጋለብ ናቸው።
መለስ የሰራዊቱን ትግርኛ ተናጋሪ አመራር ለሁለት ከፍሎ ሲያስተዳድረው ነበር። በቀጥታ ሳሞራ የኑስ የሰራዊቱ አዛዥ ቢሆንም፣ በጎን ደግሞ ሌላ መዋቅር ዘርግቶ ቆይቶአል። ታደሰ ወረደ እና ወዲ አሸብር የሚባሉት ጄኔራሎች ከሳሞራ እዝ ውጭ ከመለስ ጋር ግንኙነት ነበራቸው። ታደሰ ወረደ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ድፍረቱም ብቃቱም ሊኖረው ይችላል። ወዲ አሸብር እብድ ነው። ምን ሊያደርግ እንደሚችል ከወዲሁ መገመት አይቻልም። የመለስን ልጅ ክርስትና ያነሳው ጄኔራል ወዲ መድህን፣ አቅሙ ባይኖረውም የታዘዘውን የመፈፀም ችግር የለበትም። እነዚህ ሶስት ጄኔራሎች አዜብና ቴዎድሮስ ላይ ሊደርስ የሚችል አደጋ ካለ ለመመከት ተወርዋሪ ሃይል ይዘው የሚጠብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። በተቀረ
የህወሃት ጥቅምና ስልጣን እስካልተነካ ድረስ ሰራዊቱ ወደ ቤተመንግስት ታንክ ለማንቀሳቀስ አይገደድም።
ከመለስ መታመም ጋር ተያይዞ በኢህአዴግ ውስጥ ከብአዴንና ከህወሃት ነባር አመራር አባላት በቀር ለሽኩቻው ብቃት ያለው ሃይል ማየት አይቻልም።
ለመሆኑ በዚህ ወቅት የተቃዋሚ ሃይላት ቦታ የት ነው?
አንዳንድ ተቃዋሚዎች እራሳቸውን ከምርጫ ውጭ በማድረግ፣ “አዜብ ትተካለች፣ የለም ሃይለማርያም ነው” ሲባባሉ ስሰማ ጠጉሬን ማከኬ አልቀረም። በትግርኛ ተናጋሪዎች ቁጥጥር ስር የወደቀው መድረክ ራሱን እንደ አማራጭ በማየት ፈንታ፣ “የሚተካ የተዘጋጀ ሃይል የለም። መጥፎም ቢሆን መንግስት ያስፈልጋል” አይነት ህወሃትን የማዳን አዝማሚያ ያላቸው ይመስላል። “የአንድነት” መሪ ዶክተር ነጋሶ የሚሰማቸው ጠፋ እንጂ እሳቸውም እንደ መለስ ታመዋል። እግዜር ይማራቸው።
“ኢህአፓ ምን እያሉ ይሆን?” በሚል ወደ ድረገፃቸው ገብቼ ነበር። “ኢህአፓ በአዲስ አበባ ወረቀት በተነ” የሚል ዜና ለጥፈዋል። ከ30 አመታት በሁዋላም የትግል ስልት አልቀየሩም። ፌስቡክ እና ኢሜይል በተስፋፋበት
ዘመን ወረቀት መበተን ለምን ያስፈልጋል? በጥንት ዘመን ወረቀት መበተን ያስፈለገው ሌላ አማራጭ ስላልነበረ ነው።
የዶክተር ፍስሃ እሸቱ የሽግግር ምክርቤት፣ “መለስ ሞቶአል፣ አረጋግጠናል” ብለው አውጀዋል። ፊሽ መቼም ችኩል ነው። አዲስ ናቸውና ከልምድ እየተማሩ ይሄዱ ይሆናል። የፖለቲካ ድርጅቶች ለዜና መሽቀዳደም የለባቸውም። ዜና መቅደም የጋዜጠኞች ስራ ነው። እንደ ሽግግር ምክርቤት አቅጣጫ ማሳየት ነው የሚጠበቅባቸው። በመሰረቱ የመለስ መሞት የችግሮች መፍትሄ አይሆንም። ከመለስ መወገድ በሁዋላ ስልጣኑን ህዝብ እንዲቆጣጠር ታክቲክና ስትራቴጂ መንደፍ ያስፈልጋል።
በመጨረሻ የተስፋ አይኖች የሚያርፉት በታጠቁት ሃይሎች ላይ ነው። ኦነግ፣ ግንቦት 7 እና ሌሎችም ሃይሎች ተቀናጅተው አንድ የታጠቀ የጋራ ሃይል ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል። አለመረጋጋት ቢፈጠር የሚያረጋጋ ሃይል ያስፈልጋልና ይህ ለነገ ሊባል የማይገባ ተግባር ይመስለኛል። አንዲህም ሆኖ የሃይል ሚዛኑን ስመረምረው በአስፈሪ ጭጋግ ውስጥ ያለን መስሎ ይሰማኛል። ህወሃት ደክሞታል። የሚገፈትረው ግን አጣ። ተቃዋሚዎችም አልተደራጁም። መንገዱ ወዴት ያደርስ ይሆን? እንደ ፕሮፌሰር መስፍን፣ “እግዜር ያውቃል” ማለት ብቻ ይሆን የቀረን?
በጥንት ዘመን አንድ ጋዜጣ፣ “ማርክ ትዌይን ሞተ” የሚል ዜና አትሞ ነበር። ማርክ ትዌይን ለጋዜጣው በላከው የማስተባበያ ደብዳቤ፣ “ስለኔ መሞት የፃፋችሁትን ዜና አንብቤዋለሁ። ተጋንኖአል።” ብሎ ነበር። ምናልባት መለስ በቴሌቭዥን ብቅ ብሎ፣ ተመሳሳይ ነገር ይነግረን ይሆናል። የሚበጀው ህወሃት እንደ ስርአት ይሞት ዘንድ፣ ታክቲክና ስትራቴጂ ነድፎ መትጋት ብቻ ይመስለኛል።

ተስፍሽ ስለ ፍሽ ያልሽው እስማማለሁ ስለ ሌላው ግን አሁን ስለቸኮልኩ ነገ ጠብቀኝ
impressive analysis. There is always inside daynamic which favors change or status que. Those who want to bring a democratic change need to analayse the situation and stratigize to make it happen.wishful thiking it just that wishful. This is an opportunity both within TPLF who invison a peaceful existance with other Ethiopians under democratic governance. We have to help theme come out if they are there and I would think there are. if not they must separate from other ethiopians and live iin thier Tigy kelil.
Tesfaye Gebreab, Thank you for your excellent analysis of the current situation in Ethiopian politics.
I read both of your books, it was amazing how your reveal the truths about woyane leaders and their Followers, but most of the people don’t like the truths. So, do not give up your struggle.
Yidne from Dallas, TX In the name of Lenin whom died in Badmay front.
I am ashamed of myself reading this thrash ኣርticle!
As to me you are in state of riding blind horse.
አንተን ምን አገባክ እና ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካን የምትፈተፍተው?
በጣም ደስ የሚል እና ለብዙ ተቃዋሚ ድርጚቶች ግንዛቢ ሊሰጥ የሚችል ጽሁፍ!!! እንዲህ ማሰብ ስንችል ነው አገር የሚመራው
Tesfaye I read your article. It is interesting. Your prection and analysis are wonderful;I believe your opinion is based on your previous relation with your former bosses. If your are not responsible for what had been done by woyane, you had played a big roll in their propaganda war. History will judge all. so, you have mentioned the EPRDF collitions,and predicted the fate of the collitions after Meles death. As you have mentioned in your previous books and some articles you present yourself as a true democrat and close to Oromo people even more than former president Negaso Gidada. so, why you did not mention the fate of Oromo or OPDO after Meles. Do you thing Oromo is not significant roll player in Ethiopia politics? or you are going to be like THE HABASHA’S mind; “live alone Oromo, the are nothing more than number.” You mentioned Addisu Legesse is not out of power but he has been hybernated. on the other hand you forget the generals and the significant roll or number of oromo military personnels. Finally, I want to say no matter what there will not be any political deal without Oromo participation. It is a bitter pill to swallow for those who don’t want to hear good about Oromo, but we are far ahead more than our rivals think.
Where were you when there was similar rumors about Esiyas some time ago? You Ertirians always talk and comment and critisize about ethiopia and ethiopian but not Eriteria and eriterians.
Esiayas and Meles are two sides of the same coin.
Excellent and interesting analyses by great man, Tesfaye. Jiraadhu!!!
Nice article Tesfish!
The opposition groups/parties are miles and miles away from where the action is taking place and doing nothing other than talking, writing and forming more and more parties. EPRDF is in the country, working day and night to stay in power. How do you change a system from outside? How do you intend to lead if there is so much disconnect between you i.e., the oposition and the people? For the sake of discussion, let’s say both Meles and his party are gone tomorrow. What makes you think that you elites living in comfort in Europe and America will be welcome to go back an lead?
አንተ ሰው አንዳንዲ ጥሩ ትዘግባለህ አንዳንዲ ደሞ ትቀባጥራለህ እራስህን እንደውስጥ አዋቂ ትመድባለህ በርግጥ አንድ የማይካድ ነገር አለ እሱም ምንድነው ቀንደኝ ወያነ እንደንበርክ ነው ነገሮች ሲስተካከሉና ኢትዮጵያውያን ሲያሸንፉ ለፍርድ ከሚቅርቡት ሰውች አንዱ አንተ ነህ ይህ በንዲህ እንዳለ ሆኖ አንተ በግልጽ ያለህበትን ቦታና ሃገር ሳትናገር ሃገር ውስጥ ከወያኒ ጥይትና የግፍ አገዛዝ ግርፊያና እስራት ጋ እይተጋፉ ባላቸው አቅም ለህዝብ ውነቱን ለማሰማት የሚታገሉ ጋዚጤኝዋችን ለመዝለፍ ያን ቆሻሻና ዘርኝ በእርህን አትቀስር
“የሚበጀው ህወሃት እንደ ስርአት ይሞት ዘንድ፣ ታክቲክና ስትራቴጂ ነድፎ መትጋት ብቻ ይመስለኛል::”
የዛረው ተራኪ, የተላንቱ ዘና ዘጋቢ , ያመናው ባለ ታሪክ እና የፈዲት ሰደተግና ሚን ማውራት አማረህ???
የ ፈተራ ታሪክ አንደን ያልካል. ተዘብት ነው ተርፉ የላል ሰዉ…የብካህ
R u really concerned about ethiopia? Shame on u! every body already knew who u really are- haattu!! Bzw why u & ur master isayas afewerki hate prof Mesfin? Let me guess, b/c he always expose your ‘idiot-hood’
Hi tesfish;
Your analysis is always interesting. Yet, I always see softy conclusions. Why are you always after OLF? Are you EPLF (SHABIYA)?
I said this because I have seen that very asserted in all your literature. You seem to have sympathy for the Oromo’s as you were an eyewitness while your late Ma’ am was exchanging with them. This is the wicked character among majority Eritreans taking advantage of the innocents, as they were doing it over their Ethiopian brothers/sisters for long until the final break up the late 1990′s. I always read your books with deep interest and enthusiasm as you are well informed and witty in your flow, and your articles but I have a hunch that you want to ride the Oromo, with the strategy you have been brought up in your family, especially your Mother as you have exposed it in your own pen within the “gazetegnaw mastawosha”.
Your strategy seems an offshoot of “Shabiya” as they also want to ride the Oromo’s through, OLF, against the rest Ethiopians. This I said because you never say anything on “shabiya” nothing negative on OLF.Isn’t that what ‘Esayas Afoworki is doing? Are you sure your Eritrian blood is not troubling you? Now you began to include Ginbot 7.
Please reread your synthesis and come back with good conclusions. I really appreciate your deep and broad information but according to my evaluation what you lack is good strategy and good conclusions.
Sinziro
This is my strong wish.
Well great country with way back 3000 yrs civilization like Ethiopia should not be driven by just ‘a wish’. May be I say my ‘strong prayer”. Yet, this works among those who believe prayer works in politics matters. Why not? as God has created all and still has business with all. Any ways this is my belief. Just forget no need to worry. What if I change my title to be “my vision for my nation”. May be many will agree to this phrase as it is a contemporary hot cake. Ok! “vision” meaning what I want to see! But who am I after all? Sure a citizen with full right to suggest my ideals very freely as it should be in democratic civil society. My vision for the coming New Ethiopia is very short, clear and down to earth.
I want to see all the politicians from way back the early 1950′s(if they’re still alive) be them from EPUD,EDU,TPLF,EPLF,CUD,etc.. being the next parliamentarians. I really mean it, they deserve that position as representatives of all the Ethiopians, but no other executive power except just ‘a parliamentarian’s power’ for the next five years(2013-2017). This I say because they were involved in the past severe bloodshed and they are all now in either late fifties or their their sixties, there fore they are not fit to bear executive power. Yet I say they still deserve the parliament.
I want to see all the court system be held by professional lawyers who are above 60. yrs old. No need of any sophisticated criteria but their professional excellency with their age will be enough.
I want to see guys in their late thirties and forty’s being the executives(ministers,high rank officials). The criteria should be still professional excellence with competence.
I want to see the constitution that we have, retain its everything except the cessation article 39, and a bit modification on the article on sovereignty of the nation.
I want to see building up on the existing policies, modifying them with a justified process.
Presidential system, every four years election, but no election except implementing my vision for the transitional years 2013-2017. The en-trim president must be Oromo!Not necessarily OLF.
SINZIRO
Bravo tesefish, you gave us real information which are tired by garbag
What don’t you grow up and write a sensible analysis? You are patronising the opposition and insulting weyanes (which I like). It is just a confused article from an Eritrean who is dying to see Ethiopia’s disintegration; just shut up and choke on the money you stole …
ሰላም ላንተ ይሁን ተስፋየ.ጽሕፉ ጥሩ እንከን ያምይውጥለት ነው ብቻ ግስግስ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ(መቸም ጎሕ የኢሓፓ መጽሄት ነበርች ንጉስ ስሞቱ ደርግ በተተካ ወቅት)
መደራዸት ነው ዋናው ሃይል.ቁምነገሩ ሲመዘን ደሞ ውጤቱ አርኪና መራኪ ይሆናል-ልክ ደርግ ከነ ገነራል መንጉስቱና ግርማሜ እንደተማረ የአሁኑ ሃይል ደግሞ ከ 1989 ዸነራሎች ማማር አለባቾው.በትግራይ ወያነ የተበተበተ አንዻ ሆዱ ባዶ ነው ብቻ ደፍረት!!
ተመስገን እንዺ ይቅረታ
አይኖሩም.
ሞት ለቁዱሳኑ
ልእኮዮሁ
አይሆነም..
ትንሳኤ ዩሁን
በሙታኑ
ጽዋ..
ታሪክ የናገራል እኮ..
የሚናገር እንባ..
መስረቱ ነን ፍቅር ይኑር በጛ
ቅሬታ የለነም መለስ ሄዶ
ማን ገባ..
አንድነት አስከለን ደረስ
ለኤትዮጵያ ማማ..
ብስራት ነው….
አቶ ተስፋዬ ገ/ አብ አንተን ስመርምር ነብርኩ ጽሁፎችኽን እክታተል ነብርኩ ለምትፅፋቸው አድንቅኅልሁ አሁንግን አንተ ግልጽ አድርግኽ አውጥታኻል ትክክላኛው የሻቢያ ስላይ የሻቢያ ስላይ እናንተ ያምትሹትን እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ አይስጣት የማትለወጥ ክፉ ስው
በጣም ጥሩ ጹሑፍ ነው::የሥርዓት ለውጥ በአገራችን እንድመጣ መትጋት ዛሬ ነገ የማይባል ነገር ነው::
በጣም ጥሩ አድርጎ ተስፋዪ አስቀምጦታል:: ህዋሃት መውደም አለበት ነገር ግን ማንነው ወንዱ???
አቶ ተስፋዬ ገ/አብ ትክክልኛ ስላይ መሆንህን የሚያሳይ ፅሁፍ ነው ብዙ ያንተን የፃፍካቸውን አይቻልሁ ብጠራጠርም የዛሬው ግን ልዩ ነው
“መለስ የሰራዊቱን ትግርኛ ተናጋሪ አመራር ለሁለት ከፍሎ ሲያስተዳድረው ነበር። በቀጥታ ሳሞራ የኑስ የሰራዊቱ አዛዥ ቢሆንም፣ በጎን ደግሞ ሌላ መዋቅር ዘርግቶ ቆይቶአል። ታደሰ ወረደ እና ወዲ አሸብር የሚባሉት ጄኔራሎች ከሳሞራ እዝ ውጭ ከመለስ ጋር ግንኙነት ነበራቸው። …” would you please tell us in detail ?
እድመ ዪስቲህ ተስፋየ ገብረሃብ! ዮኡ አረ ዎንደርፍኡል ሪይተር! ኢ አም ፋን ኦፍ ዮኡ!!
አቶ ተስፋዬ ገ/አብ ትክክልኛ አሰተያየት ነው ያስቀመተው ::
ጥሩ ጽሁፍ ነው ግን አሁንም ብቀላ አልተውህም:: የፍትህ አዘጋጂ ተመስገን በ ቅፅ 5 ቁጥር 195 አርብ ሰኔ 29 2004 ዓ.ም ላይ አደገኝ ጽሁፍ ስላወጣብህ የ “መረጃ እጥረት” በለህ ቀባጠርህ::ብቀላ ይቅርብሕ ጽሁፍ ግን ጥሩ ነው
ቀላማጅ, ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ሰው ያምነኛል ብለህ ማሰብህ ራሱ ይገርማል
ውብ ትንታኔ ነው:: ትክክለኛውን መንገድ ላይ ቆመህ ሰዎች ቡድኖች በዚያ በኩል እንዲመጡ እያሳየህ ነው:: ብራቮ ተስፍሽ