የባለሥልጣናቱ መግለጫ የመለስ ዜናዊን ሕመም ክብደት ያሳያል (VOA)

VOA | July 19th, 2012

ዴቪድ ሺን አሁን ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣናት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃኪም ረዘም ያለ የህመም ፈቃድ እንዲወስዱ መክረዋቸዋል፥ ሲሻላቸዉ ወደ ሥራ ይመለሣሉ ማለታቸው የጤና ችግሩ ከባድ መሆኑን ያመለክታል፤ ህመሙ ከባድ ባይሆን ኖሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥራ የሚመለሱበትን ቁርጥ ያለ ቀን ያሣውቁ ነበር ብለዋል ሺን፡፡

አምባሳደር ዴቪድ ሺን ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መንግሥት ጋር ለረጅም ጊዜ በቅርበት የሠሩ በመሆናቸው በዚህ ትኩረት በሚስብ ጊዜ ውስጥ ውስጡን በመንግሥት ውስጥ ምን እንደሚካሄድ ግምታቸውን ሲጠየቁ ባለፈው ግንቦት ለሃያዎቹ ከበርቴ ሃገሮች ጉባዔ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. በተገኙበት ጊዜ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሆነው እንዳገኙዋቸውና ያኔ ምንም የጤና መቃወስ ምልክት እንዳላዩባቸው፣ ይልቁንስ በጣም ጤናማ ይመስሉ እንደነበረ ጠቁመዋል።

ነገር ግን አቶ መለስ አሁን መወያያ ለሆነው የጤናቸው ጉዳይ ፍንጭ የሚሰጡ አንድ ሁለት አስተያየቶች ጣል አድርገው ነበር ብለዋል። ከዚያ አስተያየታቸው እንደተረዱትም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ስለህመማቸው አስቀድመው ሳያውቁ እንዳልቀሩና ተተኪ መንግሥት አቅደዋል የሚል ግምታቸውን አጋርተዋል። ዝርዝሩን ከዘገባው ያድምጡ።

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )



 

 

 

 


3 Responses to “የባለሥልጣናቱ መግለጫ የመለስ ዜናዊን ሕመም ክብደት ያሳያል (VOA)”

  1. Anonymous says:

    I so happy to hear this news of the dictator meles

  2. simon says:

    አምባሳደር ሽን አቶ መለስ አሁን መወያያ ለሆነው የጤናቸው ጉዳይ ፍንጭ የሚሰጡ አንድ ሁለት አስተያየቶች ጣል አድርገው ነበር ብለዋል። ነገር ግን እነዚያን ቃላት ቢጥቅሱልን መልካም ነበር ለኛም ጥሩ ጠቋሚ ነጥቦች በሆኑ ነበር፡፡ ለማንኛውም ለትንታኒያቸውና ለጥቆማው አምባሳደር ሽንን እማመሰግናቸዋለን፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ መለስ ተመልሰው ወደ ስልጣን አለመመለሳቸው መልካም ዜና ነው፡ የተቃዋሚወች ዝምታ ግን አስፈሪ ነው፡ “መለስ ከመጠን ያለፈ የሚዲያ ሽፋን ተሰጠው” ከንግዲህ ወደ ተግባር ቢገባ መልካም ነው: መለስን እያነሱ እሱን መውቀስ ትናንትን አይመልስም ቢያንስ ነገን ብሩህ ተስፋ ለመሙላት የተግባር እንቅስቃሲ ነው: እናም የፖለቲካ መሪዎች እባካችሁ ትግሉን አቅጣጫ አሲዙት: ህዝቡ የናንተን እስትንፋስ ይጠብቃል:
    ቸር እንሰንብት



We would like to hear your opinion.
Join Ethiopian Review's forum and post
your comments. Click here to join us.
If you are already a member, click here.

You must be logged in to post a comment.